Saturday, May 10, 2014

My Takes on the Ethiopian Dam and the Addis Ababa Master Plan Messay Kebede

May 9/2014

The issue of the so-called “Grand Ethiopian Renaissance Dam” has proven very tricky for all those Ethiopians who oppose the present regime. On the one hand, no Ethiopian wants to see Ethiopia’s right to use the waters of Nile for its own development contested so that any interference from external countries appears as an unacceptable assault on its sovereignty.On the other hand, many Ethiopians are understandably apprehensive of the detrimental ecological and social impacts of such a huge project and are skeptical about its economic benefits, a skepticism based on the failures of the experience of huge dams in other African and non-African countries.

Recently, three eminent Ethiopian scholars, namely, Minga Negash, Mammo Muchie, and my dear friend Seid Hassan wrote an article in which they argue that Ethiopians must engage in a cost-benefit analysis instead of opposing the project based solely on its alleged negative consequences. They find that the dam will provide “valuable economic benefits,” but they also admit that it will have several negative “side-effects.” This admission led them to say that “Ethiopians may legitimately ask questions and raise concerns about the manner in which the Government of Ethiopia is handling the project.” Accordingly, while concerns are legitimate, a simple one-sided opposition is not.

Since the article was obviously written to help Ethiopians resolve the dilemma in which they find themselves, I must confess that I remain as perplex as before. After reading the article, I still wonder whether the opposition to the dam project is really misplaced. Precisely, the cost-benefit analysis that they advocate seems to show an imbalance in favor of cost because even if we concede that the dam will be economically beneficial, the question remains as to who will benefit from the project and at what costs. The three scholars are right when, dismissing the validity of colonial treaties, they defend the sovereign right of Ethiopia to use the waters of the Nile. Unfortunately, the question is not only about sovereignty, it is also about the misuse of the right by a ruling clique whose records in the defense of Ethiopian interests have been so far nil.

It is fair to say that people should not expect anything good coming from a ruling elite that so wholehearted landlocked Ethiopia. Moreover, the fragmented nature of Ethiopian society thanks to the ethnic divisions implemented by the TPLF puts us in no position to antagonize further our enemies. There is no doubt that Egypt will engage in destabilizing policy, short of a military attack, to either stop the construction or makes it very costly for Ethiopia. True, as concerns ecological consequences and social adversities, such as displacements of people, palliatives can be found to mitigate the damages. Nonetheless, can one seriously expect that the ruling elite, assuming that it is capable of such concerns, will take the necessary measures to alleviate the harmful downsides of the dam?

It is also true, as noted by another dear friend, Tecola Hagos, in a recent article, that the existing government was successful in removing the traditional opposition of Sudan. The question is, at what cost? Is the seceding of Ethiopian territories, which happen to be in the Amhara region, the price for the Sudanese support? Who has any idea of the secret deals between the Sudanese and the Ethiopian governments? Clearly, to change the dam into a project in which benefits would outweigh costs, the condition is to have in place a nationalist and democratic, that is, accountable, government.

Last but not least, is the project really economically viable? I am no expert in this matter, but plenty documented studies on the real benefits of grand dams exist that invite caution, if not outright skepticism. Caution is all the more advised since the project originated from the former prime minister whose dictatorial ethos and aspiration to personal grandeur have left Ethiopia in a state of shamble. As pointed out by Alemayehu G. Mariam’s article, dictators are consumed by vanity and the need to justify their rule. As a result, they launch grandiose projects whose purpose is both to flatter their aspiration to grandeur and hide the misery and pettiness of their rule. It is important that we resist the temptation of separating the dam from Meles’s megalomania if only because it gives the reason why alternative proposals that would be less costly and more in tune with the environment and the interests of surrounding people were discarded in favor of the Grand Renaissance Dam. I am not convinced by the argument that economic benefits are dependent on the size of the dam, and not on a smart, efficient, more manageable use of the water.

To the argument of economic benefits, Tecola adds that projects like the grand dam can work as antidotes to the ethnic division of Ethiopia. Projects with a national dimension counter the fragmentation of the country and serve as achievements around which people can rally and repair their torn unity and national identity. As a harsh critic of Meles and his regime, Tecola knows that national projects are not enough to patch up Ethiopian unity. Centuries of common existence did not deter the Tigrean TPLF from advocating and implementing an ethnonationalist agenda. To counter the trend, we need a government that expressly dismantles the institutions created to divide Ethiopia and promotes a national culture that permeates ethnic identities.

That is why Tecola supplements his support to the dam with the argument that “the current Government of Hailemariam Desalegn seems to be engaged in a subtle fight to reverse such disastrous course of national disintegration.” In thus making his support conditional, Tecola joins all those Ethiopians who have serious concerns about the good use of the dam, the only but important difference being that concerned Ethiopians, in which I include myself, are not as optimistic as Tecola in the belief that the actual prime minster has the necessary power to reform the regime. In light of this uncertainty about the reformist agenda of the prime minister, I maintain that it is still reasonable to oppose the construction of the dam.

The upshot of all this is that the mentioned articles, despite their good intention and estimable arguments, do not do the job of appeasing my original concerns. To support the construction of the dam, I require an open debate about the pros and cons and the release of all relevant official and secret documents. By debate I do not mean the defense of the project by the officials of the government, but the presentation of alternative projects. The goal must not be to obtain endorsement, but to allow people to exercise their free and enlightened judgments with no attachment of political significance that would be construed as supporting or opposing the regime. Of course, some such condition amounts to nothing else but a change of government, given that the present regime will never subscribe to an open debate. Anyway, the construction of the dam is on its way so that the time for open debate has already passed. Even so, I reserve the right to oppose a fait accompli if only to show that the dictatorial regime did not fool me a bit.

The second issue I want to deal with is the riots caused by the expansion plan of Addis Ababa into Oromo territory. University students from various towns located in Oromia have expressed their opposition to the expansion plan by engaging in peaceful demonstrations. Undoubtedly, a number of legitimate questions can be raised against the plan, the most important being the utility of such an expansion. Why expand Addis Abba further when already its disparity with other towns is only too wide? Why not use the available resources to expand other towns that badly need to grow? This focus on Addis Ababa seems to be a continuation of the policy of make-believe, so dear to dictatorial regimes. It is more about impressing tourists, foreign visitors, and supporters than implementing a policy of development that really benefits the country as a whole. More importantly, the plan does no more than expand what Addis Ababa has effectively become, namely, the secluded island of exclusive enrichment for the cronies of the regime.

Another legitimate concern has to do with the fate of the Oromo peasants who surround the town. Unsurprisingly, the government insists that the plan promotes the integrated development of Addis Ababa and its surroundings. But seeing the government’s previous records of forced displacement of peasants with no or inadequate compensation in other regions of Ethiopia, there is no reason to suppose that a different fate awaits Oromo peasants. One more time, what matters is not the declared good intention, but the reality of an implementation devoid of established process of accountability. Any more than in the case of the dam, Oromo students have little reason to take at face value what the government is saying or promising.

The irony of the whole case is that the regime is reaping what it has sown. The creation of ethnic regions and their definition as sovereign nations could only backfire at the plan to expand Addis Ababa into a territory considered as the exclusive property of the Oromo. In principle, the invention of nations within the Ethiopian state considerably limits the authority of the central government so that Oromo students are within their rights accorded by the ethnonationalist constitution of the TPLF. The crackdown on the students is just another proof that the TPLF has done nothing but trample its own constitution since it came to power. Accordingly, what is absolutely unacceptable is the violent repression of the students who did nothing but use their recognized right to express their demands in a peaceful way. This savage repression, which caused many deaths, should be emphatically denounced by all Ethiopians.
That said, it must be at the same time clear that the condemnation of repression does not mean the endorsement of ethnic politics and borders. Indeed, from what I have read so far, Oromo students oppose the expansion because it violates the sovereignty of Oromia. For unionists, this is not the right reason and they should say so openly. They must condemn the violation of Oromo students’ right to protest peacefully, but they also must make quite clear that the condemnation is not an approval of killil politics.

I take this opportunity to ask unionists to become more aggressively engaged in favor of Ethiopian unity. It is high time that unionists drop their timid approach to unity in the hope that their timidity will decrease the secessionist tendency of Oromo nationalists. Especially, the Amhara elite must shake off their sense of guilt over the marginalization and mistreatment of Oromo under the previous Amhara dominated regimes. The fall of these regimes, which would not have been possible without the active and multifarious participation of Amhara elites and people, exonerates, so to speak, the Amhara and celebrates their decisive input in the rise of a new Ethiopia in which ethnic groups with their language and characteristics will flourish in conjunction with their Ethiopianness. EPRDF and other ethnonationalist groups present the new Ethiopia as a political reality born against the will of the Amhara when we all know that nothing would have been possible without the primary rise of Amhara students and elites against the imperial regime. Indeed, the time has come to raise the mere defense of Ethiopian unity to the offensive level and this change begins with the work of unifying the unionist base and laying out a clear vision of what the new Ethiopia will be. Our rallying motto should be: unity in diversity versus diversity in disintegration!
Wake Up Unionists!

Friday, May 9, 2014

“የኢትዮጵያ የብሔሮች ጥያቄና መፍትሔዉ” እስክንድር ነጋ(ከቃሊቲ እስር ቤት)

May 9/2014
የዲሞክራሲያዊ መብቶች ጋር ተያይዞ፣ የብሔረሰቦች የእኩልነት መብት በቃልና በፕሮግራም ብቻ ሳይሆን፣ በግብር መታወቅ
አለበት፡፡ የእያንዳንዱም ብሔረሰብ ቋንቋ፣ ባህል፣ ሃይማኖትና ሌሎችም መለያዎች በእኩልነት መታወቅና መከበር አለባቸዉ፡፡
ብሔሮች ሁሉ ትልቅም ሆነ ትንሽ የራሳቸዉን የወደፊት ዕድል የመወሰን መብት መታወቅና በትክክል ከስራ ላይ መዋል አለበት፡፡
ብሔሮች ቋንቋቸዉንና ጠቃሚ የሆኑትን ባህሎቻቸዉን በነፃ እንዲያዳብሩ መደረግ አለበት፡፡ ማንም ሰዉ በዉስጥ አስተዳደራቸዉ
ላይ ጨቋኝ ተፅዕኖ እንዳያደርግ መከላከል አለበት፡፡ ኢትዮጵያን ከብሔሮች እስር ቤትነት ወደ ብሔሮች ማበቢያ ሥፍራ ማድረግ
ያስፈልጋል፡፡ ይቻላልም፡፡ የሕዝቦች አንድነት፣ በሳንጃና በመድፍ በተቋቋመዉ አንድነት ፋንታ፣ በመግባባትና በመፈቃቀድ ላይ
ሊመሠረትና እንደአለት ጸንቶ ሊኖር የሚችለዉ በዚህ መንገድ ብቻ ነዉ፡፡ በንጉሱ እና በደርግ ጊዜ የብሔርን ጥያቄ አንግበዉ
የተነሱ አካላት ሕዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ(ሻቢያ)፣ ሕወሓት እና ኦነግ ነበሩ፡፡ በአሁን ግዜ ግን ነፃ አዉጭ ብሔር የሌለዉ
የደቡብ ክልል ብቻ ነዉ ይህም ሊሆን የቻለዉ እንደሚመስለኝ የጎሳዎች ብዛት እና የመልክአምድራዊ አቀማመጥ ብሎ ነግሮኛል፡፡
አምባገነን ባለበት አገር ላይ የብሔር ጥያቄ የሚያነሱ አካላት እየበዙ እንጅ እያነሱ አይሄዱም፡፡ እንደ ምሳሌ ታላቋን ሩስያ ማንሳት
በቂ ነዉ፡፡ በእስታሊን አምባገነንነት ምክንያት አብዛኞቹ አገሮች ለመገንጠል ምክንያት ሆናቸዋል፡፡ ኢትዮጵያ የዩጎዝላቪያ፣ የራሽያ
እና የሶማሊያ እጣ ፋንታ ሳያጋጥማት እኛ ቀድመን ልናድናት ይገባል፡፡ ይሄም ሊሆን የሚችለዉ በአንድ እና አንድ መንገድ ብቻ
ነዉ፡፡ እሱም በሰላማዊ ትግል ወያኔን ስናስወግድ ብቻ፡፡ከዛም ስራዉ የኛ የጋዜጠኞች እና የፖለቲከኞች ይሆናል፡፡ የብሔር
ፖለቲካ የበሰበሰ እና ያለፈበት መሆኑን ምርጫ 1997 አስተምሮን አልፏል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ኤርትራ እንዳትገነጠል የበኩልን
ድርሻ ቢወጣም በወያኔ እንቢተኝነት በ1984 ዓ.ም ምህረት ህዝቡን አሰሩ፣ ገደሉ አቆሰሉ፡፡ ይህም አልበቃ ብሏቸዉ የኤርትራ
ህዝብን በምርጫ በማወናበድ ምርጫቸዉን አሳኩ፡፡ በየት አገር ነዉ ባርነት ወይስ ነፃነት የሚል ምርጫ የተካሄደባት አገር አለች፡፡

የኤርትራ ህዝብ ግን የጣሊያን እና የእንግሊዝ አስተዳደር አሻፈረኝ ብሎ ወደ እናት አገራቸዉ ለመመለስ የበኩላቸዉን ጥረት
ሲያደርጉ እንደነበር የታሪክ ድርሳናቶች ይናገራሉ፡፡ ሁለት ኤርትራዊያን ግለሰቦችን ማንሳት ያዉም በቂ ነዉ ዘርዐይ ደረስ
ጣሊያኖች በኢትዮጵያ ባንዲራ ላይ ሲቀልዱ በመበሳጨት ጣሊያኖች ላይ ጉዳት አድርሷል፤ አብርሃም ደቦጭ በግራዚያኒ ላይ
ቦምብ በመወርወር የመግደል ሙከራ ያደረገ እና ያቆሰለ፡፡ህዝቡም ሲጠይቅ የነበረዉ ኢትዮጵያዊነት ነዉ፡፡ይህንንም አሳክተዉ
ከ60 ዓመታት በኋላ ተመልሰዋል፡፡ ለዚህ ሁሉ መሳካትም የዉጭ ጉዳይ ሚኒስተር የነበሩት የአክሊሉ ሀብተወልድ ድርሻ ላቅ ያለ
ነበር፡፡

“ኢትዮጵያ ወይም ሞት” በማለት በሀገር ፍቅር ማህበር ስር የተሰለፉ ሀገር ወዳድ ኋይሎች ህዝቡን በማስተባበር በነቂስ ወጥቶ
የኤርትራን ግዛቶች ሲያጥለቀልቅ እንደነበርም ይታወሳል፡፡ ከኢትዮጵያ ጋር አብረዉ ለመኖር የሚፈልጉ ህዝቦች ነበሩ፡፡ ሁሉም
የኤርትራ ህዝብ ለመገንጠል ከሻቢያና ከወኔ ጋር አብረዉ ቁመዋል ማለት ከእዉነት የራቀ ነዉ፡፡ የኤርትራ መገንጠል
ለአስገንጣኞች አካላት ብቻ ነዉ የጠቀመዉ፡፡ ኤርትራ በመገንጠሏ የኤርትራ ህዝብ ምን አገኘ? የኢትዮጵያ ህዝብስ ምን አገኘ?
አሁንም የኤርትራ ህዝብ በጭቆና፣ በርሀብ፣ በስደት እና በበሽታ እያለቀ ነዉ፡፡ መገንጠል እንደማያዋጣ የኛዉ ኤርትራ
አስተምራናለች፡፡

እስክንድር ነጋ የሚፈልገዉ እኩልነትና ነፃነት የሠፈነበት፣ የህዝቦቿ አንድነት ከብረት የጠነከረባትና ብሔረሰቦች ሁሉ ያበቡባት፣
የማንም ተመፅዋች ያልሆነ በራሱ የሚተማመን በማንም ፊት የባታችነት ስሜት ሊኖረዉ የሚችል ህዝብ እንዲይፈጠር ነዉ፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝቦች ትግል የፈጀዉን ጊዜ ቢፈጅምና የፈለገዉን ያህል መሥዋዕትነት ቢጠይቅም፣ ብዙ ችግሮችና መሰናክሎችን
ከፊታችን ቢደቀኑም፤ የዚች ዓይነት ኢትዮጵያ እንድትመሰረት እስከ መጨረሻዉ ለመታገል ቆርጨ ተነስቻለዉ፡፡ የእናት አገራችን
ህልዉና ላያስጠብቅ የሚችለዉ ለ22 ዓመታት ፈላጭ ቆራጭ ጫማ ስር የተረገጠችበት ብሔራዊ ነፃነቿን ክብሯ ተገፍፎ የቆየችበት
ዓመታት ነዉ፡፡ በሁሉም ወገን የሚደረገዉ መሯሯጥና መሰናዶ ሲታይ አበረታታች ነዉ፡፡ ወሳኝ የሆነዉ ፍልሚያ ገና ከፊታችን
እንደሚጠብቀን ምንም ጥርጥር ሊኖረዉ አይችልም፡፡

የግንቦት 7 መስራች እና መሪ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በሚመለከት ከግብፅ መንግስት እርዳታ ተቀብሏል ተብሎ ወሬ እየተናፈሰ መሆን
ስጠይቀዉ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ብርሃኑ የሚያደርገዉ አይመስለኝም ካደረገዉ ግን በጣም አዝኘበታለዉ፡፡ ለምንድን ነዉ
አባቶቻችን የሰሩትን ስህተት የምንደግመዉ፡፡ መኢሶን፣ ኢህአፓ፣ ጀብዐ እና ወያኔ በአንድ ይሁን በሌላ መልኩ የዉጭ እርዳታን
እየተቀበለዉ፡፡ አገራችን እና ህዝቧን ጎርቷል፡፡ ኤርትራን እንድናጣ ሁነናል፡፡ አሁንም መናገር የምፈልገዉ ኢህአዴግን እና
ኢትዮጵያን ለይተን ማዬት አለብን፡፡ ኢህአዴግን የጎዱ እየመሰላቸዉ አገራችንን እያደሟት ነዉ፡፡
ለተቃወሚ ፓርቲዎች እችን መልዕክት አስተላልፏል፡፡

1.የዉጭ ኋይሎች ድጋፍ የዚችን ኩሩና ታሪካዊ አገራችንን ብሔራዊ ክብርና ነፃነት የማይነካ፣ ራስን ለመቻል የምታደርገዉን
ጥረት የሚያግዝ እንጅ የማያደናቅፍ እርዳታ መሆን አለበት፡፡

2. ማንኛዉም ህዝብ በዉጭ እርዳታ ላይ በመተማመን አብዮቱን ከግብ ለማደረስ እችላለሁ ብሎ ካሰበ ራሱን ማታለሉ ብቻ
ሳይሆን አብዮቱንም ብሔራዊ ነፃነቱን ያጣል፡፡ ማንም ህዝብ በተለይም ደግሞ እንደኢትዮጵያ ሕዝቡ ኩሩና ባለታሪክ ሕዝብ ከሆነ
ለገዛ ነፃነቱ፣ ለገዛ ለዉጡ ለገዛ ክብሩ ከሁሉም በፊት መተማመን ያለበት በራሱ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ስለሆነም የዉጭ
እርዳታን በሚመለከት በኩል ብሔራዊ ክብርና ነፃነት እንደዚሁም ከሁሉ በፊት በራስ መተማመን የሚለዉ ዋናዉ መመሪያችን
ይሆኑ፡፡

እስክንድር ነጋ

ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫ ጊዜያቸዉን ማባከን የለባቸዉም የሰማያዊ ፓርቲ እና አንድነት ፓርቲ የሰላማዊ ትግል መንገድ
መቀላቀል አለባቸዉ፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲ “ሰላማዊ ትግሉን(አብዮቱን) እኛ ካልመራነዉ አብዮት አይሆንም” ከሚል አመለካከት
መጀመሪያ መላቀቅ አለባቸዉ፡፡ትግሉን ማንም ይምራዉ ማን ሕዝቡ ለትክክለኛዉ የስልጣን ባለቤት መሆን አለበት፡፡ ዛሬ
የሚወነጃጀሉት ኢህአፓ፣ መኢሶን፣ ማሌሪድ፣ ሰደድ፣ ወዝ ሊግ፣ ሻዕቢያ፣ ህወሓት ይህን የህዝብ መብት ረግጠዉ እና አፍነዉ
በህዝቡ ቦታና ጥያቄ እራሳቸዉን መተካታቸዉ ሲሆን ዋና የህዝቡን የበመደል መነሻ ምክንያት ይህ ነዉ፡፡ በመሆኑም በአንዳንድ
ታዳጊ አገሮች ዉስጥ ሕዝቡን በዙሪያቸዉ አጠቃለዉ ለማሰለፍ አይነት ተግባራዊነት ታላላቅ ሰዎችን የመሰሉ እንኳን ለማፍራት
አልቻለችም፡፡ ከዚህ አኳያ ጋንዲን ያፈራች ህንድ፣ ማኦን ያፈራች ቻይና፣ ማንዴላን ያፈራች ደቡብ አፍሪካ እና ፓትርስ ሉሙባን
ያፈራች ኮንጎ ጋር ሀገራችን በአቻ አትታይም፡፡ እነዚህ ታላላቅ ሰዎች ከሀገራቸዉ አልፈዉ የአለም ሰዎች ሁነዉ ኑረዋል፡፡እየኖሩም
ነዉ፡፡ እንዲያዉም ኢትዮጵያ ዛሬ የጎደላት ነገር ቢኖር እኒእኒህን የመሰሉ ቅን ሰዎችን ማግኘት ነዉ፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ እንኳን
የብሔረሰቦችን የአመለካከት ድንበር አቋርጦ በማለፍ የህዝቦቷን አመኔታ ሊያገኝ የቻለ የፖለቲካ ሰዉ መፍጠር ቀርቶ ለተወለደበት
ብሔረሰብ ለመቆም የቻለ ሀቀኛ የህዝብ ሰዉ መፍጠር አልተቻለም፡፡

በመጨረሻም እስክንድር ልብን በሚማርክ ሁኔታ ስለ ኢትዮጵያ እናት እና አባቶቻችን ለብዙ ዓመታት ታግለዉና ተዋግተዉ
ነፃነታቸዉን ያወጁት፡፡ ስለዚህ ይህ ትዉልድ ጭቆናና ግፍ በቃኝ ብሎ የራሱን መሪዎች ገርስሶ መጣል አለበት፡፡
“እኔ ለዲሞክራሲ ስል ታሰርኩ እንጅ ሌላ ምን ሆንኩኝ ለነፃነት የምከፍለዉ መስዋዕትነት እስከ ሞት ድረስ ነዉ”

እስክንድር ነጋ

“እኔ ከኢትዮጵያ የተሻለ አገር የለኝም የምታሰርባት፣ የምገረፍላት፣ የማለቅስላት፣………. በቃ በአጭሩ እኔ የምሞተዉ በአገሬ
በኢትዮጵያ መሬት ነዉ፡፡ ነፍሴም የምታልፈዉ ሥጋዬም የሚፈርሰዉ በምወዳት አገሬ ኢትዮጵያ ነዉ”

እስክንድር ነጋ

Ethiopian bloggers allege being beaten in detention

May9/2014
Ethiopian bloggers allege being beaten in detention
Addis Ababa (AFP) – Three Ethiopian bloggers appeared in court Thursday with two alleging they had been beaten while in detention, a case that has been condemned internationally as an assault on press freedom.
The three are part of a group of nine bloggers and journalists accused by police of “serious crimes”, with the other six having appeared in court a day earlier. Thursday’s hearing was held in closed session.
None have yet been charged, with police requesting more time to investigate their case.
“The detainees told the presiding judge that they were beaten by the police investigators under their feet and slapped and punched on their faces,” defence lawyer Amha Mekonen told AFP.
But she said the police had denied the claim, saying “no one had touched” the detainees.
On April 25 and 26, six members of the blogging collective Zone Nine and three journalists were arrested by police, with the government saying they were being investigated for “serious crimes”, without elaborating.
The arrests prompted an outcry from rights groups, with the Committee to Protect Journalists (CPJ) calling them “one of the worst crackdowns against free expression” in the country, while Amnesty International said it was part of a “long trend of arrests and harassment of human rights defenders.”
Ethiopia has one of the most closed press environments in the world, the CPJ says, with at least 49 journalists forced into exile — a figure only beaten by Iran and Somalia.
Ethiopia has also been accused of cracking down on independent media and doling out heavy sentences for journalists under controversial anti-terror legislation.
The six who appeared in court Wednesday will next appear on May 17. The three in court Thursday will next appear on May 18.
US Secretary of State John Kerry urged Ethiopia to allow greater freedoms for civil society and journalists, during a visit last week, expressing concern for the group.
UN human rights chief Navi Pillay has condemned the arrests, warning the country is increasingly muzzling freedom of expression under the guise of fighting terrorism.

Thursday, May 8, 2014

ከሃሮማያ ዩኒቨርስቲ የወጡ ተማሪዎች ትምህርት ለመጀመር ድፍረቱ እንደሌላቸው አስታወቁ

May 8/2014

 ኢሳት ዜና :-በድሬዳዋና በሃረር አብያተ ክርስቲያናትና በግለሰቦች ቤት ተጠግተው የሚገኙ ተማሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት በዩኒቨርስቲው ውስጥ የሚታየው ድባብ አስፈሪ መሆን ትምህርት በቶሎ ይጀመራል የሚለውን ተስፋ አጨልሞታል። መንግስት ውጥረቱ መርገቡን በመግለጽ ከግቢ የወጡ ተማሪዎች ተመልሰው እንዲገቡና ትምህርት እንዲጀምሩ ጥሪ ቢያቀርብም፣ አንዳንድ ግቢውን ጎብኝተው የተመለሱ ተማሪዎች ግን ሁኔታው አሁንም አስፈሪ በመሆኑ ትምህርት ለመጀመር ፍላጎት የለንም ብለዋል።
አንድ ተማሪ ” በተማሪዎች መካከል መተማመን በመጥፋቱ ፣ በውጭ ያሉ ተማሪዎች ዶክመንታቸውንና ልብሶቻቸውን ይዘው ወደ አካባቢያቸው ከመመለስ ውጭ የመማር ፍላጎት የላቸውም” ብሎአል።
በሌላ በኩል ደግሞ በኦሮምያ ክልል የህወሃትና የኦህዴድ ካድሬዎች እየነዙት ያለው በአንድ ብሄር ላይ ያነጣጠረ የጥላቻ ዘመቻ ያሰጋቸው አንዳንድ ኢትዮጵያውያን፣ ህዝቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሁሉ እንዲያደርግ እየመከሩ ነው።
በተመሳሳይ ዜናም ሰማያዊ ፓርቲ ” ኢትዮጵያውያንገዥውፓርቲበፈጠረውየከፋፍለህግዛስርዓትሳይወናበዱበዜጎቻችንላይየሚደርሰውንህገወጥእርምጃ ላይ ድምጻቸውንእንዲያሰሙናለስርዓቱመሳሪያከመሆንእንዲቆጠቡ” ጠይቋል።
“የዜጎችንጥያቄበግድያማስቆምአይቻልም” በሚል ርእስ መግለጫ ያወጣው ሰማያዊ ፓርቲ፣ በአሁኑወቅትኢትዮጵያነጻእንዲወጡእገዛያደረገችላቸውንጨምሮአብዛኛዎቹአገራትየህዝብንጥያቄበተገቢውየሚያዳምጡ፣ችግሮችሲኖሩበጠረጴዛዙሪያናበሰከነመልኩመፍታትየሚችልመንግስትመመስረትሲችሉበተቃራኒውበአገራችንስልጣንላይያለውህወሓት/ኢህአዴግግንዜጎችንበኃይልእየገዛ” እንደሚገኝ፣  በቅርቡበአገሪቱየተለያዩክፍሎችየተፈጸሙትንግድያዎችናሌሎችህገወጥእርምጃዎችበምሳሌነትበማንሳት ጠቅሷል።
ፓርቲው  ” የአዲስአበባናበዙሪያዋየሚገኙትከተሞች ‹‹የተቀናጀመሪፕላን ›› አስመልክቶበስርዓቱላይጥርጣሬየገባቸውየዩኒቨርሲቲተማሪዎችያነሱትሰላማዊጥያቄተከትሎበርካታተማሪዎችናነዋሪዎችህይወታቸውንማጣታቸውን ፣ መቁሰላቸውንና መታሰራቸውን፣ ከወራትበፊትበሀረርከተማየተከሰተውንቃጠሎተከትሎምዜጎችላይተመሳሳይእርምጃመወሰዱን፣  በባህርዳርናጎንደርከተሞች ‹‹ህገወጥግንባታነው›› ተብለውያለካሳ፣ቅያሬናበቂጊዜቤታቸውየፈረሰባቸውዜጎችቤታቸውበዚህሁኔታመፍረሱአግባብአለመሆኑንበመግለጻቸውበጥይትመደብደባቸውን፣በተለይምጥያቄያነሳሉተብለውየተፈሩትአባወራዎችእስርቤትውስጥመታጎራቸውን ” አውስቷል።
“ዜጎችጥያቄያችውምንምይሁንምን ‹‹መንግስትነኝ!›› ብሎስልጣንላይየተቀመጠአካልጥያቄያቸውንአዳምጦበሰከነመንገድምላሽወይንምመፍትሄየመስጠትግዴትየነበረበትቢሆንም፣ገዥውፓርቲ ግን ምላሹ  ጥይት ነው” ሲል ኮንኗል።ፓርቲው በመያያዝምገዥውፓርቲየዜጎችንጥያቄበኃይልለማፈንየሚሞክረውለዜጎችመሰረታዊጥያቄንአሟልቶአገርየመምራትብቃትየሌለውከመሆኑአንጻርህዝብሌሎችበርካታጥያቄዎችንያነሳብኛልብሎስለሚሰጋ፣የተነሱትንምጥያቄዎችየመመለስአቅምስለሌለውናምንምአይነትችግርቢኖርምህዝብእያስፈራራለመግዛትካለውአባዜየሚነሳ መሆኑን ጠቅሷል።
         
አገራችንከመቼውምጊዜበላይወደበፖሊስመንግስትነት መለወጡዋን የሚጠቅሰው ሰማያዊ ፓርቲ፣  ኢትዮጵያዜጎችሰላማዊጥያቄያቸውንለመንግስትየማያቀርቡባት፣ጥያቄያቸውንሲያቀርቡምህይወታቸውንየሚያጡባትአገርእንደሆችየሰሞኑአረመኔያዊእርምጃ ማሳያ መሆኑን ገልጿል።

ገዥውፓርቲበኢትዮጵያውያንላይየወሰደውንእርምጃህጋዊለማስመሰልየባንክዘረፋንናህገወጥየቤትግንባታንየመሳሰሉትንምክንያቶችበመጥቀስየተወሰደውንእርምጃህጋዊለማድረግመሞከሩምተጠያቂነትየጎደለውናከምክንያትየራቀበመሆኑ፤እነዚህዜጎችላይየተወሰደውንእርምጃላይለህዝብበቂመረጃእንዲሰጥናተጠያቂነቱንእንዲወስድም አሳስቧል፡፡ዜጎች ህወሓት/ኢህአዴግበፈጠረውየከፋፍለህግዛስርዓትሳይወናበዱበዜጎቻችንላይየሚደርሰውንህገወጥእርምጃላይድምጻቸውንእንዲያሰሙናለስርዓቱመሳሪያከመሆንእንዲቆጠቡእንዲሁምአገርበቀልናዓለምአቀፍየሰብአዊመብትተቋማት፣የሚዲያተቋማት፣የፖለቲካድርጅቶችናሚዲያዎችገዥውፓርቲበህዝብላይእየወሰደውያለውንየኃይልእርምጃእንዲያጋልጡናእንዲቃወሙ፣እያጋለጡናእየተቃወሙያሉትምአጠናክረውእንዲቀጥሉሰማያዊፓርቲጥሪውን አቅርቧል።

Wednesday, May 7, 2014

Ethiopian Bloggers, Journos Court Case Adjourned; Two More Detained At The Scene

May 7/2014
Ethiopian Bloggers, journos court case adjourned; two more detained at the scene
Tesfalem and Zelalem being escorted to the Court today.
Journalist Tesfalem Waldeyes and Blogger Zelalem Kibret escored by armed police in Court today (picture Courtesy of Twitter updates)
The closed trail of three of the six detained members of the bloggers’ collective, Zone 9 and three other journalists that was held today  in the Arada First Instance Court First Bench , Addis Abeba, has been adjourned to May 17, 2014 according to sources who were in the court premises. The three bloggers that appeared before the court today were Atnaf Berahane, Natnael Feleke, Zelalem Kiberet, and 3 journalists; Edom Kassaye, Tesfalem Weldeyes and Asmamaw Hailegorgis. The remaining bloggers; Befekadu Hailu, Mahlet Fantahun and Abel Wabella are expected to appear before the court tomorrow.
Although none of the detainees have officially been charged yet, sources indicated that according to the defendants’ lawyer police is accusing the detainees of “receiving finance & materials from foreign sources, links with terrorism designated Diaspora based groups” and thus asked for more time to conduct investigation as there are “still few others yet at large and are suspected of having links with the detainees”.
According to online updates and witness statements, the detainees looked “frail and tortured” while others felt they looked “strong and full of hope”. Some had waved and smiled to families and friends.
Meanwhile, twitter updates by those that attended the court proceedings show that two more people have been detained outside the Court premises today. Kiya Tsegaye, a lawyer by profession and contributor to print outlets in Addis Abeba was detained at the scene for what witnesses believed  ”taking the photographs of the detainees”. Similarly,  Solomon Seyoum, an editor at Finote Netsanet, the voice of the opposition Party Unity for Democracy and Justice (UDJ), was also arrested by the police.
The male prisoners were handcuffed and were escorted in and out of the court by a number of armed federal police officers.
Follow the #Freezone9bloggers hashtag on Twitter for more updates and reports on the issue.

“የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ጥያቄ ፍትሐዊና ሕጋዊ ነው”

May 7/2014
ሰንደቅ ጋዜጣ
አቶ አባዱላ ገመዳ
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈጉባዔ
በአዲስአበባዙሪያያሉትንበኦሮሚያክልላዊመንግስትውስጥየሚተዳደሩከተሞችንከአዲስአበባጋርበማስተሳሰርበጋራለማልማትየወጣውንየተቀናጀመሪዕቅድ በመቃወም ሰሞኑን በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች የተካሄደው ተቃውሞ ተከትሎ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል። በአዳማ፣ በድሬዳዋ፣ በጅማ፣ በመደወላቡ፣ በአምቦ፣ በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲዎችና በጠቅላላው በ11 ዩኒቨርሲቲዎች የተቀጣጠለው ተቃውሞ መነሻው የአዲስአበባና የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ትግበራ ጉዳይ ነው። ዕቅዱ “የኦሮሚያ ከተሞችን በመቁረስ ወደአዲስአበባ ለማጠቃለል የታቀደ ነው፣ በርካታ ኦሮሞዎች ከቤት ንብረታቸው ሊፈናቀሉ ነው” የሚሉ አስተያየቶች በተለይ በማህበራዊ ድረገጾች በስፋት በመሰራጨታቸው ተማሪዎች ግራ በመጋባት የወሰዱት እርምጃ እንደሆነ ይታመናል። መንግሥታዊ አካላትም በወቅቱ ሕዝቡን በማሳተፍ ስለፕላኑ (ዕቅዱ) በቂና ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይቶችን አለማድረጋቸው ለግጭቱ መነሳት አንድ ምክንያት መሆኑ እየተነገረ ነው።
የመንግሥት ኮምኒኬሸን ጽ/ቤት ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ በመደወላቡ እና በአምቦ ዩኒቨርሲቲዎች ከተቃውሞው ጋር በተያያዘ 10 ሰዎች መሞታቸውን ይፋ ያደረገ ሲሆን በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ እግርኳስ በመመልከት ላይ ባሉ ተማሪዎች ላይ ባልታወቁ ሰዎች በተወረወረ ፈንጂ 70 ያህል ተማሪዎች ሲቆስሉ አንድ ተማሪ መሞቱን አስታውቋል።
ጽ/ቤቱ በዚሁ የመንግሥትም አቋም በገለጸበት መግለጫው በፌዴራልና በክልል የፀጥታ ኃይሎች ትብብር ሁከቱ በተፈጠረባቸው ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ያለውን ሁኔታ ለማረጋጋት መቻሉን ጠቅሶ እስካሁን በተደረገው ማጣራት ከበስተጀርባ በመሆን ሁከቱን በማነሳሳትና በማቀነባበር ተግባር ላይ የተሰማሩት ጥቂት ፀረ ሰላም ኃይሎች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል ብሏል። ከዚሁ ግርግር በስተጀርባ የቆሙትና ከዚህ ቀደም በነበሩ ግጭቶች እጃቸውን ሲያስገቡ የነበሩ የአገር ውስጥና ከአገር ውጭ ያሉ ኃይሎች በሚቆጧጠሯቸው ሚዲያዎች እየታገዙ ይህንን የተማሪዎችን ጥያቄ ለጥፋት ዓላማቸው መጠቀሚያ ለማድረግ መንቀሳቀሳቸውን በመግለጫው አስታውቋል።
በተፈጠረው ሁከት ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸውና ወገኖችና ቤተሰቦቻቸው መንግስት የተሰማውን ሐዘን የገለጸ ሲሆን የጥፋቱ ዋነኛ አንቀሳቃሽ የነበሩትን ተከታትሎ ለፍርድ ለማቅረብ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።
በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉትን በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ውስጥ የሚተዳደሩ ከተሞችን ከአዲስ አበባ ጋር በማስተሳሰር በጋራ ለማልማት የወጣውን የተቀናጀ መሪ ዕቅድ ጋር ተያይዞ በተማሪዎች ስለተነሳው ጥያቄና በመንግሥት ስለተወሰደው እርምጃ የአሜሪካ ድምጽ አማርኛ ክፍል የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈጉባዔ የሆኑትን አቶ አባዱላ ገመዳን ከትላንት በስቲያ አነጋግሯል። እንደሚከተለው ቀርቧል።
ጥያቄ፡- ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ብዙ ሰዎች ሞተዋል። ሰልፉ የተካሄደው ባልታጠቁ ተማሪዎች ነው። በሮቤ፣ በአምቦ፣ በጅማ፣ በነቀምት፣ በመዳወላቡ፣ ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል። መንግሥትም ራሱ ሐሙስ ዕለት ባወጣው መግለጫ እስከ 10 ሰዎች መገደላቸውን አምኗል፣ በዚህ ላይ የሚሰጡን ምላሽ ምንድነው?
አቶ አባዱላ፡- እውነት ነው፤ በኦሮሚያ ክልል ባሉት ዩኒቨርሲቲዎች የተነሳ የተቃውሞ ጥያቄ አለ። ጥያቄው የተነሳው በኦሮሚያና የአዲስ አበባ የጋራ ማስተር ፕላን በሚመለከት የተነሳ የተቃውሞ ጥያቄ ነው። በሁሉም አካባቢ ተማሪዎች ያነሱት ጥያቄ ፍትሃዊና ሕጋዊ ነው። እነዚህን ፍትሃዊና ሕጋዊ ጥያቄ በየአካባቢው ያሉት፣ የዩኒቨርሲቲ አስተዳደርም ሆነ በየአካባቢው ያሉት አስተዳደሮች ለመመለስ ጥረት አድርገዋል። ጉዳዩን በቅርበት ይከታተሉ የነበሩ የመንግሥት ኃላፊዎችም በጉዳዩ ሒደት ላይ ማብራሪያ ለመስጠት ሞክረዋል። ይሁንና አንዳንድ ቦታ ተማሪዎቹ ጠየቁ፣ በቂ መልስ አላገኘንም አሉ። ለበላይ አካልም ጥያቄያቸው እንዲሄድላቸው ጠየቁ፣ ግን ደግሞ ያ-ምላሽ ከመምጣቱ በፊት ነው ሰልፍ ወጡ። እንግዲህ ሰላማዊ ሰልፍ የመውጣት ሕገ-መንግሥታዊ መብት ነው። ይህ በሕገ-መንግስቱ የተቀመጠ ነው። ይሄ እንደተጠበቀ ሆኖ ሠላማዊ ሰልፍ ሲወጣ አስቀድሞ ማሳወቅ እንደሚገባ ይደነግጋል። ይሄ የሚሆነው በአካባቢው ያለ የመንግሥት አስተዳደር ሰልፍ የወጣው ሕዝብ አንድም ጉዳት እንዳይደርስበት ለመከላከል ነው። ሁለተኛ ደግሞ በሌላው ዜጋ ንብረትና ሐብት ጉዳት እንዳይደርስ ለመጠበቅ ነው። እነዚህ ሁለቱ ካልተሟሉ ችግር ሊከሰት እንደሚችል በአገራችንም በሌሎች ዴሞክራሲያዊና ባደጉ አገራትም ይታወቃል። መጀመሪያ ተማሪዎቹ ጥያቄያቸው ፍትሐዊ ሆኖ ሠላማዊ ሰልፉ ሕጉን ተከትሎ ያለማካሄድ ችግር ያጋጠመበትና ሳያሳውቁ በኃይል ስለተወጣ ከተማ ላይ በንብረት ላይ የደረሰ ኪሣራ አለ። ይሄ ወደባሰ ችግር እንዳይሰፋ የፀጥታ ኃይሎች ለመከላከል የወሰዱት እርምጃ አለ። የፀጥታ ኃይሎች አድማ ለመበተን ጢስ እና ውሃ ተጠቅመዋል። ይህን አልፎ ለሕይወት መጥፋትና ለሌሎችም ችግሮች የተከሰቱበት ሁኔታ አለ።
ጥያቄ፡- የተማሪዎቹ ጥያቄ ፍትሐዊና ሕጋዊ ነው ብለዋል። ሠላማዊ ሰልፍ ደግሞ በሕገመንግሥቱ የተቀመጠ መብት ነው ብለዋል። ሠላማዊ ሰልፍ ማድረግ የሚፈልግ ለመንግሥት አካላት ማሳወቅ ነው ብለዋል። ነገር ግን የታጠቁ ኃይሎች ልጆቹ ላይ ተኩስ እንደከፈቱና በዚህም ምክንያት የማይተካ ሕይወት እንደተሰዋ ነው የሚነገረው። ጥያቄያቸው ትክክለኛ እስከሆነ ድረስ ለዚህ ግድያ ምን መልስ ይሰጡናል?
አቶ አባዱላ፡- በመጀመሪያ ይህ መምጣት የሌለበት ነው። ሕይወትም ንብረትም መጥፋት በጣም የሚያሳዝን ነው። መንግሥትም ሐዘኑን ገልጿል። እኔም በቦታው ደርሼ አይቻለሁ፣ አዝኛለሁ። መሆን የማይገባው ጉዳይ ነው። በቦታው በኃይል ለመመለስ ወይም በጥይት ለመመለስ አይደለም ዝግጅቱ። አንድ ምሳሌ ለማንሳት ልሞክር። የአድማ በታኝ የፌዴራል ፖሊስ በቦታው የደረሰው ብዙ ተሽከርካሪዎችና ንብረት ከተቃጠለ በኋላ ማታ ላይ ነው። ማምሻውን 11 ሰዓትና ከዚያ በኋላ ነው የደረሰው። ቃጠሎው እየሰፋ ሲሄድ ነው፣ የክልሉ መንግሥት ይሄ ነገር የከፋ ሕይወት ሊያጠፋ ስለሚችል የሚቆጣጠር ኃይል መግባት አለበት ብሎ ለፌዴራል መንግሥት ጥያቄ አቅርቧል።
ጥያቄ፡- ተማሪዎቹ መኪናዎችን ሲያቃጥሉ ነበር ነው የሚሉኝ?
አቶ አባዱላ፡- እንግዲህ በአምቦ ከተማ ቀደም ሲል ሠላማዊ ሰልፍ ሲወጣ ማሳወቅ ይገባል ያልነው ባመፈፀሙ፣ ቅድመ ዝግጅት ባለመደረጉ፣ ተማሪዎቹ በግቢያቸው ውስጥ የመጨረሻውን ዝግጅት አድርገው የወጡ ቢሆንም፤ ከውጪ ግን ተማሪዎችን የተቀላቀለ ብዙ ኃይል አለ። የዘረፋ ፍላጎት ያለው፣ የማውደም ፍላጎት ያለው ኃይል ተቀላቅሏል። ከተቀላቀለ በኋላ ለምሳሌ በአምቦ አበበች መታፈሪያ የሚባል ሆቴል ተዘርፏል። ሆቴል ውስጥ የነበሩት የቱሪሰት መኪናዎች ተቃጥለዋል። እንደዚህም የኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ ተቃጥሏል። የምዕራብ ሸዋ ፍ/ቤት ዶክመንቶችና ፍ/ቤቱ ራሱ ተቃጥሏል። እንዲያውም ተማሪዎች ናቸው ለማለት የማያስችለው ከጥበቃ ኃይሎች ትጥቅ በመቀበል ወደተኩስ የተገባበት ሁኔታ ነበር። ይሄ ነገር ሄዶ ሄዶ ብዙ ሕይወት፣ ብዙ ንብረት እንደሚያወድም ይታወቃል። መንግሥት ይህን የመቆጣጠር ኃላፊነት አለበት።

“ሰልፉ የተካሄደው በእኛ ትዕግስትና ጥንካሬ እንጂ በመንግሥት አልተፈለገም” ”

May 7/2014
የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚታዩ የማኅበራዊ አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች ላይ ያተኮረ “የእሪታ ቀን” በሚል ሰላማዊ ሰልፍ አካሂዷል። ሰላማዊ ሰልፉ ከተከናወነ በኋላ የፓርቲውን ሊቀመንበር ኢንጂነር ግዛቸው ሺፈራውን አነጋግረናቸዋል።
ሰንደቅ፡- ባለፈው እሁድ (ሚያዚያ 26 ቀን 2006 ዓ.ም) የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ምን ያህል የተሳካ ነበር?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- ሰልፉ እንዳይካሄድ ከነበረው ከፍተኛ የሆነ እንቅስቃሴ አንፃር ከፍተኛና ስኬታማ ሰላማዊ ሰልፍ ነበር።
ሰንደቅ፡- ሕብረተሰብ ውስጥ አለ ካላችሁት ችግር አንፃር እንደምትጠብቁት በቂ የሆነ ሕብረተሰብ በሰላማዊ ሰልፉ ወጥቷል የሚል እምነት አላችሁ?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- ካለው ሁኔታ አንፃር አዎ። አንደኛ ለመቀስቀስ ዕድል አልሰጡንም። የሰላማዊ ሰልፉን እውቅና ያገኘነው በእኛ ትዕግስት እንጂ እውቅናውን መስጠት አልፈለጉም። ከሕግ ውጪ በሆነ መልኩ ሰልፉን ለማካሄድ ማንም ሰው መፈረም ቢችልም አመራሩ ካልፈረመ እውቅና አልሰጥም አሉ። ሶስት የፓርቲ አመራሮች ሄደው ፈረሙ። እኔ በአጋጣሚ በማኅበራዊ ጉዳይ ሀዘን ላይ ስለነበርኩ እሱም ካልመጣ በመባሉ ከሶስቱ አመራሮች በተጨማሪ እኔ አራተኛ እንድፈርም ተደርጓል። በእርግጥ የእኔ መፈረም ችግር አይመስለኝም። ነገር ግን ህግ የማክበር ጉዳይ አይደለም። ጊዜ የማጣበብ ጉዳይ ነው። ከዚህ ጎንለጎን ለቅስቀሳ የወጡ አባሎቻችንን አሰሩብን። እውቅና ያለው ሰልፍ መሆኑን እያወቁ አባሎቻችንን አሰሩ። ለምሳሌ የፓርቲያችን የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘካሪያስ የማነብርሃን፣ የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ነብዩ ኃይሉ ታስሯል። እንደዚሁም ዘላአለም የአዲስ አበባ ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ታስሯል። ከዚህ አንፃር ስታየው ሰላማዊ ሰልፉ ስኬታማ ነበር።
ሰንደቅ፡- የሰማያዊ ፓርቲ አባላት አጋርነታችሁን በሰልፉ ላይ ለመግለፅ ሙከራ ቢያደርጉም መከልከላቸውን ገልፀዋልና ለምን ተከለከሉ?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- ማንም ሰው አልተከለከለም። በእርግጥ እኔን አላገኙም። ነገር ግን በኋላ ሳጣራ ማንም ኢትዮጵያዊ በዚያ ሰልፍ መሳተፍ የእኛ ፍላጎት ነው። ነገር ግን እንደሰማሁት የእነሱን (የሰማያዊ ፓርቲ ማለታቸው) ቲሸርት የራሳቸውን አርማ ይዘው ለመካፈል ሞክረዋል የሚል ነው። እነሱ ሰልፍ ባካሄዱ ጊዜ የእኛ አባሎች የእነርሱን አርማና መፈክር ይዘው ነው የተሳተፉት። እና እነሱ የሰማያዊ ፓርቲን በአንድነት ሰልፍ ለማስተዋወቅ ሙከራ ያደረጉ ይመስላል። በእኛ አባላት በኩል ሰልፉ የአንድነት ፓርቲ መሆኑን በመግለፅ መፈክሩም፣ አካሄዱም በአንድነት ፓርቲ የሚመራ መሆኑ ተነግሮአቸዋል። ይሄ ደግሞ ትክክል ነው። በእኛ በኩል ሁሉም መፈክር ላይ ማህተም አድርገናል። ከዚያ ውጪ ያለው መፈክር እኛን እንደማይወክል ቀደም ብለን ሰርተናል። ባጅም አድለናል። እና ሰልፉ የሌላ ፓርቲ ማስታወቂያ ወይም መፈክር ማቅረቢያ አይደለም። በተጠየቅ (logic) ብታየውም ሁሉም የሰልፉ አካሄድ የአንድነት መሆኑን ለማስገንዘብ ነው።
ሰንደቅ፡- በሁለቱ ፓርቲዎች መካከል እንደተቋምም ሆነ እንደ ግለሰብ ያለው ግንኙነት ጤናማ ነው?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- እኔ እንደማስበው ይሄ ለጥያቄ የሚቀርብ አይመስለኝም። በእኛ በኩል በራሳችን ትዕግስት ሁሉንም ፓርቲ የምናየው በእኩልነት ነው። ከሁሉም ፓርቲ ጋር በጋራ ለመስራት በራችንን ከፍተናል። ከዚያም አልፎ የእኛ አላማ ፓርቲዎች ተዋህደው አንድ ጠንካራ ፓርቲ መፍጠር ነው። እንግዲህ እነሱ በዚህ ላይ ይስማሙ አይስማሙ እነሱን መጠየቁ ይሻላል። አንድነት ግን ከሁሉም ፓርቲ አብሮ ለመስራት እስከውህደት ምንጊዜም ዝግጁ ነው። 
ሰንደቅ፡- ባለፈው እሁድ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል ቀጣይ አቅጣጫችሁ ምንድነው?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- እሁድ እለት የተካሄደው ሰልፍ እራሱን የቻለ የአዲስ አበባ የፓርቲው መዋቅር ያዘጋጀው ነው። ይህንን እንደ ትልቅ መዋቅር ነው የምናየው። ከአዲስ አበባ ውጪም በሲዳማ እና በምስራቅ ጎጃም እንዲሁም በአዳማ ይኖረናል። እነዚህ አካላት በራሳቸው አየጠነከሩ የአቅም ግንባታ እንዲያደርጉ በማድረግ እንዲቀጥሉ ነው። ለምሳሌ በደራሼ ጊዶሌ ከተማ በተመሳሳይ እሁድ እለት ሰልፍ ተካሂዷል። ወዲዚያው አንድ የስራ አስፈፃሚ አመራርና የቀጠና አስተባባሪ ልከናል። ወደፊትም ዞኖቹ የራሳቸውን አቅም ገንብተው የማዕከል የፖለቲካ አቅም ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ ይካሄዳል። ከዚህ ጎንለጎን የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ አሁን ለመሬትና ለፍትህ እየተካሄደ ነው። በቀጣይ ደግሞ በሶስተኛው ፌዝ “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነትና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ” መርሀግብር ይኖረናል። ከሰኔ 30 በኋላ የሚጀመር ይሆናል። ይህም ፖለቲካውን ከአንድነት ወደ ሕዝብ የማውረድ እንቅስቃሴ ነው። ከዚህ ጎንለጎን በስትራቴጂው ዘርፍ አማራጭ ፖሊሲዎች የማዘጋጀት፣ የምርጫ ማኒፌስቶ፣ የምርጫ ስትራቴጂ ማዘጋጀትና የአማራጭ ፖሊሲ ትውውቅ ውይይቶች ይካሄዳሉ። በዚህም በአዳራሽ ስብሰባ የተለያዩ ምሁራን በተገኙበት የሚደረግ ይሆናል።
ሰንደቅ፡- ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር የመዋሃዱ ጉዳይ ያበቃለት ጉዳይ ሆኗል ማለት ይቻላል?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- ያበቃለት ነገር የሚባል ነገር የለም። በእኛ በኩል ለውህደት ሙሉ በሙሉ ስትራቴጂካዊ በሆነ መንገድ አንድ ጠንካራ አብይ ብሔራዊ ፓርቲ መፈጠር አለበት ብለን እናምናለን። ውህደትን እንደ ጠንካራ ግብ ስለያዝነው ምንጊዜም ቢሆን የምንቀጥልበት ጉዳይ ነው።
ሰንደቅ፡- በአሁኑ ወቅት የተለያዩ ሰላማዊ ሰልፎች ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ከመሆኑ አንፃር የፖለቲካ ምህዳሩ በምን ደረጃ ላይ ነው ትላላችሁ?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- የፖለቲካ ምህዳሩ በእጅጉ እንደተዘጋ ነው። ሰልፍ ማካሄድ ወደማንችልበት ደረጃ ነው የደረስነው። የትናንትናውን ሰልፍ ለማካሄድ አንድ ወር ፈጅቶብናል። የሰልፍ እውቅና ማግኘት አስቸጋሪ ስለሆነ ለፖለቲካ ምህዳሩ አለመስፋት ዋነኛ ምሳሌ ነው። ሕዝባዊ ስብሰባ አዲስ አበባ ውስጥ ለማካሄድ አስበን አዳራሽ አጥተናል። የአዲስ አበባ አስተዳደር የሁላችንም አስተዳዳሪ እንደመሆኑ መጠን ፍትሃዊ አገልግሎት መስጠት ካልቻለ በሕገ-መንግስቱ መሰረት ለሰልፍ አንድ ወር መፍጀት የለበትም። እኛም ታግሰን ሁኔታውን አክብረን እውቅና ሲሰጠን ማየት የፖለቲካ ምህዳሩ መስፋቱን አያሳይም። አሁንም ከሁለት ወር በፊት የጀመርነው የአዳራሽ ስብሰባ በአዳራሽ እጦት ማካሄድ አልቻልንም።
ሰንደቅ፡- ቀደም ሲል ሰላማዊ ሰልፍ ስታደርጉ አይታይም፤ አሁን ግን ወደ አደባባይ የመውጣቱ ሁኔታ ከመታየቱ አንጻር በፖለቲካ ምህዳር መስፋት በኩል የተሻሻለ ነገር አለ ብለው የሚያምኑ አካላት አሉና እርስዎስ ምን ይላሉ?
     ኢንጂነር ግዛቸው፡- አንተ ማየት ያለብህ ሂደቱን ነው። ሰልፉን በነፃነት እያካሄድን አይደለም። እውቅና ለማግኘት አንድ ወር እየፈጀብህ ምህዳሩ ሰፍቷል ማለት አይቻልም። ሰልፉ በእኛ ትእግስትና ጥንካሬ እንጂ በመንግስት በኩል አልተፈለገም። ሰልፍ ስናካሂድ ብዙ ሰዎች ይታሰራሉ እና ሰልፉ መካሄዱ አይደለም ዋና አላማው፤ ሂደቱ ላይ አሁንም ነፃ አይደለንም። ሂደቱ ላይ አሁንም አፈና ይካሄድብናል። የማስፈራራት ዘመቻው ከፍተኛ ነው። ሚዲያው ሙሉበሙሉ የኢህአዴግ ፕሮፓጋንዳ ማስተላለፊያ ሆኗል። እኛን አያስተናግደንም። የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ሰልፉን እንደምናካሂድ ማስታወቂያ አዘጋጅተን ሄደን ተከልክለናል። የፍትህ አካላት አካባቢም ችግር አለ። የእኛ አባላት በመኪና ስለቀሰቀሱ ለአስር ቀናት ፖሊስ አሰራቸው። ሕግ አስከባሪውም በሕገ-መንግስቱ መሰረት እየሰራ አይደለም። ነፃ የሲቪል ማህበረሰብ የለም። ያሉትም የኢህአዴግን ቡራኬ ያገኙ ናቸው። እና ከድሮው በጣም ተዘግቷል። ሚዲያው ሚዛናዊ መሆን ሲገባው በእኛ ላይ ፕሮፓጋንዳ ያደርጋል እና ደምረው ስታየው በእጅጉ እየተዘጋ ነው።

የኃይለማርያም ደሳለኝ ቁልቁለቶች

May 7/2014
ከጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ


በ2005 ዓ.ም መጀመሪያ አቶ ኃይለማርያም “ጠቅላይ ሚኒስትር” ተደርጎ በኢህአዴግ ሲሾም፤ በፓርቲው ውስጥ አክራሪ ብሔርተኛ የአመራር አባላት ከመኖራቸው አኳያ፤ መቼም ቢሆን “ራሱን ችሎ ይቆማል” ብሎ መጠበቁ ተምኔት እንደሆነ በርካታ የፖለቲካ ተንታኞች መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ይህ ኃይል እንኳን እንደ ኃይለማርያም ላለ የድል አጥቢያ መሪ ቀርቶ፣ ከድርጅቱ ምስረታ ጀምሮ እስከ ምኒሊክ ቤተ-መንግስትም ድረስ ታላቅ የተጋድሎ ታሪክ ለነበረው አቶ መለስም ቢሆን ክፍተት ካገኘ አለመመለሱን የ93ቱ ሣልሳዊ ህንፍሽፍሽ በግልፅ አሳይቶ ማለፉ አይዘነጋም፡፡ በተጨማሪም ራሱ መለስ ዜናዊ በድህረ ምርጫ 97 የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ ዘብጥያ ወርደው የነበሩትን የቅንጅት አመራሮች “ከእስር እንዲፈቱ ብፈልግም አክራሪው ኃይል ተቃወመኝ” ማለቱን ዊክሊክስ የተሰኘው የመረጃ መረብ የአሜሪካ አምባሳደርን ጠቅሶ ይፋ ማድረጉ ይህንኑ ያስረግጣል፡፡ የአምባሳደሩ መረጃ የተጋነነ፤ አሊያም “ተጋግሮ የቀረበለት ነው” ሊባል ቢችል እንኳ “ጭስ በሌለበት…” እንዲሉ፤ በግንባሩ ውስጥ አክራሪ ኃይል ለመኖሩ በጠቋሚነት ሊወሰድ ይችላል፡፡Continue Reading –>

Tuesday, May 6, 2014

ዛሬ በኦሮሚያ ክልል በደምቢዶሎ ከተማ ሕዝብ ላነሳው ጥያቄ የመንግስት ምላሽ ጥይት ሆነ፤ ውጥረቱ ቀጥሏል

May 6/2014
የአንዲት ሴት ልጅ ሕይወት እንደጠፋ ተነግሯል

(ዘ-ሐበሻ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን አዲሱን ማስተር ፕላን በመቃወም በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ትምህርት ተቋሞች ውስጥ የተነሳው ተቃውሞ እየተቀጣጠለ በተለያዩ ከተሞች እየተዛመተ ሲሆን በዛሬው ዕለት በደምቢዶሎ ከተማ በተደረገ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የመንግስት ወታደሮች የሃይል እርምጃ መውሰዳቸውን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ከስፍራው ዘገቡ።

እንደምንጮቻችን ዘገባ ከሆነ ደምቢዶሎ ከተማ የመንግስት ወታደሮች በሰልፈኞች ላይ የጥይት እሩምታ ያወረዱ ሲሆን ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ወገኖች መጎዳታቸውንና የህክምና መስጫ ጣቢያዎችም በቁስለኞች መጨናነቃቸውን እንደምንጮቻችን ዘገባ ከሆነ ደምቢዶሎ ከተማ የመንግስት ወታደሮች በሰልፈኞች ላይ የጥይት እሩምታ ያወረዱ ሲሆን ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ወገኖች መጎዳታቸውንና የህክምና መስጫ ጣቢያዎችም በቁስለኞች መጨናነቃቸውን

ዘጋቢዎቻችን ገልጸዋል። በዛሬው ተቃውሞ ምን ያህል ሰዎች እንደሞቱ ምንጮቻችን ያደረሱን መረጃ ባይኖርም ከሌሎች ወገኖች
ባገኘነው መረጃ የአንዲት ለጊዜው ስሟና ማንነቷ ያልታወቀ ሴት ልጅ ሕይወት ጠፍቷል።

ከአዲስ አበባ 650 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ደምቢዶሎ ከተማ ያለው ውጥረት ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ
አልበረደም።

ዘ-ሐበሻ ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሷት ትመለሳለች።
ይህ በእንዲህ እንዳለ መንግስት “አዲስ አበባን እና የኦሮሚያ ልዩ ዞንን በልማት ለማስተሳሰር የተዘጋጀው የጋራ ማስተር ፕላን ልዩ
ዞኑን ብሎም አጠቃላይ የኦሮሚያን ክልል የበለጠ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው” ሲል ገለጸ። መንግስት በምእራብ ሸዋ ዞን የዞኑ
ነዋሪዎችና የመንግስት ተወካዮች ጋር አካሄድኩት ባለው ውይይት “በውይይቱ በዞኑ የተወሰኑ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረውን
ሁከትና ብጥብጥ ተከትሎ በጠፋው የሰው ህይወትና የንብረት ውድመትን አውግዘዋል” ሲል በሚቆጣጠራቸው ሚድያዎች በኩል
ዜናውን አሰምቷል። ይህን ውይይት የመሩት ውይይቱን የመሩት አፈጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር
ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ሪፎርም ክላስተር አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር ወይዘሮ አስቴር ማሞ “ማስተር ፕላኑ
የኦሮሚያን ልዩ ዞንና የክልሉን ተጠቃሚነት የበለጠ የሚያረጋግጥ ነው” ሲሉ መናገራቸውን የመንግስት ሚድያዎች ዘግበዋል።

የአንድነትን ሰልፍ አስመልክቶ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች በየክፍለ ከተማው የሚገኙ የ2ኛ ደረጃ ርዕሰ መምህራንን ሰብስበው መመሪያ ሰጧቸው

May 6/2014
gk2
መጋቢት 27 ቀን 2006 ዓ.ም ጠዋት በአዲስ አበባ የሚገኙ የ2ኛ ደረጃ ርዕሰ መምህራንን የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ሰብስበው እሁድ ዕለት በተደረገው የአንድነት ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የተገኙ መምህራንን ፈትሸው እንዲያወጡና እንዲያጋልጡ የሚል መመሪያ የተሰጣቸው ሲሆን ተማሪዎችን ሰብስበው የኔት ወርክ ችግር እስከ ሰኔ 30 ድረስ እንደሚፈታ ከዚያ በኋላ ምንም ዓይነት ችግር እንደማይኖር ሌሎቹ ችግሮች ግን እንደሚቀጥሉ ለወላጆቻቸው እንዲያስረዱ እንዲደረግ ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸው ስብሰባው ተጠናቋል፡፡
በተያያዘ ዜና እሁድ በደማቅ ሁኔታ የተጠናቀቀው ሰላማዊ ሰልፍ ያስደነገጣቸው ደህንነቶችና ካድሬዎች በሰልፉ ላይ የተገኙ ነዋሪዎች ቤት በመሄድ በማስፈራራት ላይ እንደሚገኙ ለፍኖተ ነፃነት ገለጹ፡፡

Ethiopia: Brutal Crackdown on Protests

Security Forces Fire On, Beat Students Protesting Plan to Expand Capital Boundaries 
Human Rights Watch 

May 6, 2014

Image

Nairobi, May 5, 2014) – Ethiopian security forces should cease using excessive force against students peacefully protesting plans to extend the boundaries of the capital, Addis Ababa, Human Rights Watch said today. The authorities should immediately release students and others arbitrarily arrested during the protests and investigate and hold accountable security officials who are responsible for abuses.

On May 6, 2014, the government will appear before the United Nations Human Rights Council in Geneva for the country’s Universal Periodic Review of its human rights record.

“Students have concerns about the fate of farmers and others on land the government wants to move inside Addis Ababa,” said Leslie Lefkow, deputy Africa director at Human Rights Watch. “Rather than having its security forces attack peaceful protesters, the government should sit down and discuss the students’ grievances.”

Since April 25, students have demonstrated throughout Oromia Regional State to protest the government’s plan to substantially expand the municipal boundaries of Addis Ababa, which the students feel would threaten communities currently under regional jurisdiction. Security forces have responded by shooting at and beating peaceful protesters in Ambo, Nekemte, Jimma, and other towns with unconfirmed reports from witnesses of dozens of casualties.

Protests began at universities in Ambo and other large towns throughout Oromia, and spread to smaller communities throughout the region. Witnesses said security forces fired live ammunition at peaceful protesters in Ambo on April 30. Official government statements put the number of dead in Ambo at eight, but various credible local sources put the death toll much higher. Since the events in Ambo, the security forces have allegedly used excessive force against protesters throughout the region, resulting in further casualties. Ethiopian authorities have said there has been widespread looting and destruction of property during the protests.
The protests erupted over the release in April of the proposed Addis Ababa Integrated Development Master Plan, which outlines plans for Addis Ababa’s municipal expansion. Under the proposed plan, Addis Ababa’s municipal boundary would be expanded substantially to include more than 15 communities in Oromia. This land would fall under the jurisdiction of the Addis Ababa City Administration and would no longer be managed by Oromia Regional State. Demonstrators have expressed concern about the displacement of Oromo farmers and residents on the affected land.

Ethiopia is experiencing an economic boom and the government has ambitious plans for further economic growth. This boom has resulted in a growing middle class in Addis Ababa and an increased demand for residential, commercial, and industrial properties. There has not been meaningful consultation with impacted communities during the early stages of this expansion into the surrounding countryside, raising concerns about the risk of inadequate compensation and due process protections to displaced farmers and residents.

Oromia is the largest of Ethiopia’s nine regions and is inhabited largely by ethnic Oromos. The Oromos are Ethiopia’s largest ethnic group and have historically felt marginalized and discriminated against by successive Ethiopian governments. The city of Addis Ababa is surrounded on all sides by the Oromia region.

Given very tight restrictions on independent media and human rights monitoring in Ethiopia, it is difficult to corroborate the government crackdown in Oromia. There is little independent media in Oromia to monitor these events, and foreign journalists who have attempted to reach demonstrations have been turned away or detained.

Ethiopia has one of the most repressive media environments in the world. Numerous journalists are in prison, independent media outlets are regularly closed down, and many journalists have fled the country.

Underscoring the repressive situation, the government on April 25 and 26 arbitrarily arrested nine bloggers and journalists in Addis Ababa. They remain in detention without charge. In addition, the Charities and Societies Proclamation, enacted in 2009, has severely curtailed the ability of independent human rights organizations to investigate and report on human rights abuses like the recent events in Oromia.

“The government should not be able to escape accountability for abuses in Oromo because it has muzzled the media and human rights groups,” Lefkow said.

Since Ethiopia’s last Universal Periodic Review in 2009 its human rights record has taken a significant downturn, with the authorities showing increasing intolerance of any criticism of the government and further restrictions on the rights to freedom of expression and association. The recent crackdown in Oromia highlights the risks protesters face and the inability of the media and human rights groups to report on important events.

Ethiopian authorities should abide by the UN Basic Principles on the Use of Force and Firearms by Law Enforcement Officials, which provide that all security forces shall, as far as possible, apply nonviolent means before resorting to force. Whenever the lawful use of force is unavoidable, the authorities must use restraint and act in proportion to the seriousness of the offense. Law enforcement officials should not use firearms against people “except in self-defense or defense of others against the imminent threat of death or serious injury.”

“Ethiopia’s heavy handed reaction to the Oromo protests is the latest example of the government’s ruthless response to any criticism of its policies,” Lefkow said. “UN member countries should tell Ethiopia that responding with excessive force against protesters is unacceptable and needs to stop.”

የጎሳ ፖለቲካ አራማጆች የሚጠቀሙበት የፖለቲካ ፎርሙላ

May 6/2014
horse-riding-adventure-ethiopia


ፎርሙላ (ቀመር)
አንድ የጎሳ ፖለቲካ ማለት በመጀመርያ ቤተሰብህን የተለዩ ፍጥረት እንደሆኑ መስበክ መጀመር ማለት ነው። እነርሱ የተለዩ መሆናቸውን በደንብ ማሰብ ሲጀምሩልህ ደግሞ በመቀጠል የሰፈርህን እና የወንዝህን ሰዎች ልዩ መሆናቸውን በሚገባ መስበክ ነው። የሰፈርህን ሰዎች ልዩ እና የተለዩ መሆናቸውን ስትነግር ግን የአንተ ቤተሰብ ጋር እንደማይደርሱ ግን ደግሞ ከቤተሰብህ ዝቅ ባለ መልክ የተለዩ መሆናቸውን ወትውታቸው። በመጨረሻ አንተ የቤተሰብህም ሆነ የሰፈርህ ብቸኛ አለቃ መሆንህን ትነግራቸውና ከሰፈርህ ማዶ ያሉ ሰዎች ደግሞ እርኩስ፣ የተለዩ፣ ጥንትም አባቶችን ሲበድሉ እንደነበሩ የሆነ ያልሆነ ተረታ ተረት እየነገርክ ተራራ የሚያህል ጥላቻ እንዲያድርባቸው አድርግ።

ፎርሙላ (ቀመር) ሁለት 

ከእዚህ በኃላ በሰፈርህ ሰዎች እና ማዶ ባሉ ሰፈር ሰዎች መካከል በአንተ የጦር አበጋዝነት ጦርነት እንዲከፈት አድርግ። ጦርነቱን ልትከፍት ስትል ትልቅ ችግር ሊገጥምህ ይችላል። ለምሳሌ ለዘመናት በክፉም  ሆነ በደግ አብረው የኖሩ ሰዎች ናቸው እና ከአንተ ሰፈርም ሆነ ከማዶ ሰፈር ያሉ የበሰሉ ሽማግሌዎች ወይንም አስታራቂዎች ነገሩን እንዳያበርዱብህ ተጠንቀቅ። ”የፍቅር ዘመቻ” ብሎ በሰፈርህ መካከል ዘፈን ልዝፈን፣ ፍቅርን ልዝራ፣ ብሎ የሚነሳ ሀገር የወደደው ዘፋኝ ካለ ቀድመህ በቻልከው ነገር በማማሰያም ሆነ በብረት ምጣድ ደብድበህ አባረው። የስም ማጥፋት ናዳ ልቀቅበት። ዘፋኝ እና የሃይማኖት ሰዎች አንድ ናቸው። ሁለቱም ዓለም አንድ ነው፣ ምናምን እያሉ አላማህን ያደናቅፉብሃል። ‘ቀንድ ቀንዳቸውን’ በላቸው። ከሃይማኖት በፍቅር የተሰበሰቡ ማሕበራት ካሉም እግር ከእግር እየተከታተልክ አድክማቸው። ከቻልክ ዝጋቸው።
የሃይማኖት እና የኪነት ሰዎች ብቻ አይደሉም የዓላማህ ጠላቶች ጋዜጠኞች፣ ብሎገሮች ሁሉ ቀድመው የሰፈርህን ሰዎች ከማዶ ሰፈር ሰዎች ጋር አብረው እንዲኖሩ ሊሰብኩ ይችላሉ እና ፈጥነህ ከእየቤታቸው ፖሊስ ልከህ ልቀማቸው! ያዛቸው! ማዕከላዊ ወስደህ አጉራቸው! ነግሬሃለሁ ጉድህን ይዘከዝኩታል። በሰፈርህ እና በማዶ ሰፈር መካከል ልታጋጭ ያሰብከውን ጉድ ሁሉ ለሀገር ይነዙልሃል። ይህ ብቻ አይደለም ቤተሰብህ ከሰፈርህ ሰው የተለየ አለመሆኑን፣ አንተም በቤተሰብህ እና በሰፈርህ ሰዎች ላይ መንገስ እንደማይገባህ፣ ሌላ ‘በሰፈርህ እና በማዶ ሰፈር ሰዎች መካከል ልዩነት የለም በፍቅር እንኑር’ የሚል ሰው መንገስ አለበት ብለው ለሕዝቡ ይነግሩብሃል። እናም ፍጠን! እሰራቸው!ልክህን አሳያቸው!።

ፎርሙላ (ቀመር) ሶስት 

ይህንን ሁሉ ከጨረስክ በኃላ አንተ እና ቤተሰብህ ጥንቱንም የተለያችሁ ፍጥረቶች መሆናችሁን በተለይ አዲስ ለሚወለዱት ልጆች እየሰበክ በሰፈርህ ሰዎች እና በማዶ ሰፈር ሰዎች መካከል  እረጋ ብለህ ቡናህን  እየጠጣህ ጦርነት እንዲከፈት ማዘዝ ትችላለህ። ተቀናቃኝህን ሁሉ እንደሆነ እስር ቤት ሰደሃቸዋል። የዘፋኙንም ስም ከማዶ ሰፈር ካሉ መሰሎችህ ጋር ሆነህ ስሙን አስጠፍተሃል። ከእዚህ በኃላ ማዶ ያሉ መሰሎችም ሆኑ አንተ አንድ አይነት ጫወታ ላይ ገባችሁ ማለት ነው። መንደር ከመንደር እየቆጠረ ህዝቡ ሲባላ እነርሱ በውስኪ አንተም በኮኛክህ መዝናናት ፈታ! ማለት ነው።

ፎርሙላ (ቀመር) አራት 

ጦርነቱ  ሲደረግ አንተ በሰፈርህ ሰዎች ላይ ንጉስ  ሆነህ ”ካለእርስዎ አመራር የት እንደርሳለን?” ስትባል ጀነን፣ ጎምለል ማለት ነው። አሁን ጥሩ ጊዜ መጣልህ የሀብት መጠንህ ይጨምራል። ምክንያቱም የሰፈርህንም ሆነ የማዶ ሰፈር ሰዎችን ገንዘብ ወደ ኪስህ እየከተትክ አለምህን መቅጨት ትችላለሃ!። በመካከል ታድያ ሥራ አትፍታ እዛኛው ማዶ የራሱ የሰፈሩን ሰዎች የመሰሉ ሰዎች ሰው እየላክ ”የእዝህኛው ሰፈር ሰዎች እናንተን ይጠላሉ ተጠንቀቁ!” ማለት ለእራስህም ሰፈር ሰዎች እንዲሁ ተመሳሳይ ነገር ጣል ማድረግ።ግጭቱ በደንብ አልጋጋልም  ካለህ ቀድሞ ከመቶ ዓመት በፊት የነበሩ የአንተ ሰፈር ሰዎች ”የሰሩት ኃጢያት አለ” የሚል የሐሰት ታሪክ ማዶ ሰፈር ካለው መሰልህ ጋር በሚስጥር ተነጋግረህ  ”ማስታወሻ” በሚል ስም የቂም ሐውልቶችን በየሰፈሩ መደርደር በተለይ ሴቶች ስሜታቸው የሚነካ የሰውነት ክፍል ለምሳሌ ጡት እና ጣት የመሳሰሉ የሰውነት ክፍሎች ተቆርጠው ነበር ብለህ ሃውልት መስራት። ያኔ ወጪ ወራጁ ”ህም! ድሮ እንዲህ አድርገዋል አሉ” እያለ ከንፈር እንዲነክስ ማገዝ። አዎ ማገዝ።

ፎርሙላ (ቀመር) አምስት 

የሰፈርህ እና የማዶ ሰፈር ሰዎች አንድ መሆናቸውን ሊሰብኩ የሚነሱ ከመከከልህ ከተነሱ ወይንም ደግሞ የእዚህ አይነት አስተሳሰብ አላቸው የምትላቸውን ገልሰቦችም ሆነ የሃይማኖት ሰዎች ማኅበራት በሙሉ ተለጣፊ ስም መስጠት “አጎብዳጆች፣ አሸባሪዎች፣ የሰፈሬን ሰዎች ሰላም የሚያናጉ፣ ዥንጉርጉር አብዮት ሊያስነሱ ያቀዱ” እያልክ ማሰር እና መግደል።

መደምደምያ 

በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት እና በባህር ማዶ እና በሀገር ቤት በጎሳቸው ላይ እራሳቸውን ያነገሱ እና ኢትዮጵያዊነትን የሚያጥላሉ ሁሉ ሲጠቀሙበት የሰነበቱት የጎሳ ፖለቲካ ፎርሙላ  ይሄው ነው። ኢትዮጵያ በእናንተ ዘመን አልተፈጠረችም እንዴት እንደምትኖር ታውቅበታለች። ግዴላችሁም ይህች ሀገር አምላክ አላት። በኢትዮጵያዊነት ላይ ጥላቻ ያደረበት ለጥላቻውም አስር ምክንያት ቢደረድር በመንግሥትነትም ሆነ በተቃዋሚነት ቢሰየም፣ የቂም ሐውልቶችን እንደ አሸን ቢያፈላም ሆነ በነፃነት ስም ከመቶ ዓመት በፊት ይህ ትውልድ ላልኖረበት ዘመን እየጠቀሰ ለስልጣን መወጣጫ ሊጠቀም ቢሞክርም  ከህዝብ ፍርድ አያመልጥም። አሁንም ግዴላችሁም ይህች ሀገር ጎሳ እና ብሔር የማያውቁ ለሰው ልጆች በሙሉ የሚፀልዩ ቅዱሳን እና የሚሰማቸው አምላክም አሏት። አሁንም ኢትዮጵያዊነት የጋራ መጠለያችን ነው። የጎሳ ፖለቲካ ፎርሙላ-ቀመራችሁ  ተነቅቶበታል።

ያምማል! አፍንጫን ሲመቱት ዓይን ያለቅሳልና!! – በደቡብ ኮርያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ድምጽ

May 5/2014
እኛ የኦጋዴን፣ የኣማራ፣የኦሮሞ፣የትግራይና የደቡብ ብሄር ተወላጆች ኣዲስ ኣበባን ለማስፋፋት በሚል ሽፋን በኣዲስ ኣበባ ዙሪያ የሚገኙ ድሃ የኦሮሞና ሌሎች ገበሬዎችን ግፍ በጥብቅ የምናወግዝ ሲሆን በቅርቡ በሃረማያ፣ በኣምቦ እና በሌሎች ኣካባቢዎች የሚኖሩ የኦሮሞ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ የኢትዮጵያ መንግስት የወሰደውን ግድያና በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን ሊገልጹ በወጡ ተማሪዎች ላይ እየተወሰደ ያለውን የድብደባና የማጉላላት ዘመቻ በጥብቅ እናወግዘዋለን። ገዳዮቹም የጊዜ ጉዳይ እንጂ በፍትህ ፊት ቀርበው የእጃቸውን እንደሚያገኙ ኣንጠራጠርም።
እኛ ኢትዮጵያዊያን ልብ ልንል የሚገባው ጉዳይ ባለፉት ዘመናት እንደታዘብነው የኢህዓዴግ መንግስት ሲያሻው ብሄር እየለየ ሲያሻው በጅምላ ሰላማዊና ለውጥ ፈላጊ ዜጎችን ሲያሰቃይ ሲገድል ቆይቱኣል። ኣንዴ ኦሮሞን፣ ኣንዴ ደቡብ ሲዳማን፣ ኣንዴ ኣማራን፣ ኣንዴ ኦጋዴንን፣ኣንዴ ጋምቤላን ወዘተ ሲያጠቃ ተላላ ሆነን የተጠቃው ቡድን ብቻ ለብቻው ትንሽ ጮሆ ዝም ስለሚል የግፉ ጊዜ ሊረዝምብን ችሏል። ኣሁን ግን የኢትዮጵያ ህዝብ የመንግስትን የከፋፍለህ ግዛው ዘዴ ሊነቃበትና ኣፍንጫን ሲመቱት ኣይን ያለቅሳል እንደሚባለው ኣንዱ ሲጠቃ ሌላውም ሆ! ብሎ በመነሳት ይህንን ኣስከፊና በዓለም የሌለ ብሄርተኛ ኣገዛዝ ኣሽቀንጥሮ መጣል ይገባዋል።በሌላ በኩል የኦሮሞ ወገኖቻችን ያነሱትን የፍትህ ጥያቄ ለማጣመምና ብሄርን ከብሄር ለማጋጨት የኢህዓዴግ ካድሬዎች ሊሯሯጡ እንደሚችሉ እየተገነዘብን ይህንን ጉዳይ የኦሮሞ ተማሪዎች ይስቱታል ብለን ኣናምንም። መንግስት በተለይ በኣሁኑ ሰዓት የቀለም ዓብዮት ሊነሳብኝ ይችላል የሚል ትልቅ ስጋት ስላለበት ህዝቡን በሃይማኖትና በብሄር በመከፋፈልና ከፍተኛ የሆኑ የፍትህና የዴሞክራሲ ጥያቄዎች በጋራ እንዳይነሱ ስለሚፈልግ ብሄርተኝነትንና ጠባብነትን ለብሶ እንደለመደው እያጋጨ በስልጣን ለመቆየት መፍጨርጨሩ ኣይቀርምና በማናቸውም ተቃውሞዎቻችን ውስጥ ለወያኔ እድል ፈንታ መስጠት የለብንም።
በሌላ በኩል ለውጥ ለማምጣት የሚታገሉ ዴሞክራት የፖለቲካ ፓርቲዎችም ቢሆኑ ኣንድ ብሄር ተለይቶ ሲጠቃ ሁሉን
የማንቀሳቀስና ለጋራ ትግል ቆራጥ የጥሪ ደወል የማሰማት ሃላፊነት ኣለባቸው ብለን በጽናት እናምናለን።
የጀግናው ብእረኛ እስክንድር ነጋ ነገር፣ በቅርቡ ደግሞ ወደ ዘብጥ የወረዱት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያንና ጋዜጠኞች ጉዳይ እንቅልፍ የነሳን ጉዳይ ነው። እነዚህ ወጣት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን በሰፊው እስር ቤት የሚገኘውን የኢትዮጵያን ህዝብ የነጻነት እጦት ኑሮ ተምሳሊት ኣድርገው ይንቀሳቀሱ የነበሩ ለጋ ወጣቶች ወደ እስር ቤት መውረዳቸው ከሰፊው እስር ቤት ወደ ጠባቡ መግባታቸውን ከማሳየቱም በላይ የታሰሩት ግለሰቦቹ ብቻ ሳይሆኑ ኣላማቸው በመሆኑ ሌላው የዞን ዘጠኝ እስረኛ የሆነው ኢትዮጵያዊ ሁሉ መንግስት የነጻነት ጥያቄውን ወደ ወህኒ መወርወሩን የሚያሳይ በመሆኑ ምን ያህል መንግስት በጭካኔ ስራው ሊቀጥል እንደ ወሰነ ያሳያል። በመሆኑም የነዚህ ወገኖች መታሰር፣ የፖለቲካው ምህዳር ምን ያህል እየጠበበ መምጣቱን፣ መንግስት ለህዝቡ ያለው ንቀት ጫፍ መርገጡን ያሳያል። በመሆኑም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በብሄርና በሃይማኖት ሳይከፋፈል የኦሮሞ ወገኖቻችንን ወቅታዊ ጥያቄና የጋዜጠኖቹን እስር ጉዳይ ወደ ኣጠቃላይ ፍትህና ዴሞክራሲ ጥያቄ ከፍ ኣርገን በያለንበት እንነሳ :: ዴሞክራሲና ፍትህ ሲሰፍን ጥያቄዎቻችን ሊፈቱ ይችላሉና ኢትዮጵያዊያን በጋራ ለለውጥ እንድንነሳ ወገናዊና ወንድማዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!
የማትከፋፈል ኢትዮጵያን ለትውልድ እናሳልፋለን!