Sunday, January 5, 2014

የአንድን ህብረተሰብ ችግር የመረዳትና መፍትሄ የመፈለግ ጉዳይ- ምክንያታዊ፣ ስሜታዊ ወይም ሳይንሳዊ መንገድ! ከፈቃዱ በቀለ

January5/2014

Dr Birhanu nega መግቢያ፣
በመጀመሪያ ደረጃ ውድ አቶ ካሳሁን ነገዎ ታዋቂ ሰዎችን ወይም ምሁሮችን ለቃለ-መጠይቅ እያቀረበ  አስተያየታቸውንና አመለካከታቸውን እንድናዳምጥና ትምህርት እንድንቀምስ የሚያደርገው ጥረት የሚያስመሰግነው ነው። በዚህም መሰረት በአ.አ በ23.12.2013 ዓ.ም ዶክተር ብርሃኑ ነጋን በቅርቡ ለዕትመትና ለንባብ ባበቃው፣ „ዲሞክራሲና ሁለንታዊ ልማት“ በተባለው መጽሀፉ ዙሪያ ምን ማለቱ እንደሆነ ለቃለ-መጠይቅ ጋብዞት አንዳንዶቻችን ለማዳመጥ ችለናል። የቃለ-መጠይቁን ምልልስ በጥሞና ላዳመጠ የዶክተር ብርሃኑ ነጋ መልስ ግልጽና ብዙም  የሚያከራክር ጉዳይ አይደለም።
እንደ ዕውነቱ ከሆነ አዲሱን የዶክተር ብርሃኑ ነጋን መጽሀፍ ለማግኘት ስላልቻልኩና ስላላነበብኩት ስለመጽሀፉ ጥሩና መስተካከል ይገባቸዋል ብዬ በማምነው ላይ ገንቢ ትችት መስጠት አልቻልኩም። መጽሀፉን አግኝቼ ከአነበብኩት በኋላ አስተያየቴን ለመስጠት እሞክራለሁ። ወደ ቃለ-መጠይቁና ምልልሱ ጋ ስንመጣ ከጠያቂው በቀረበለት ጥያቄ ዙሪያ የህብረተሰብአችንን ችግሮች በአጠቃላይ ሲዳስስ፣ መጽሀፉን በመመርኮዝ በተለይም በሶስት መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ እንዳተኮረ ተናግሯል። እነዚህም፣ 1ኛ) የፖለቲካ ችግሮች፣ 2ኛ) የኢኮኖሚ ችግሮችና፣ 3ኛ) የአካባቢ ችግሮች በሚሉት ዙሪያዎች ሰፊ ማብራሪያ ለመስጠት  ሞክሯል። በተለይም ለቃለ-መጠይቁ ክብደት የሰጠው የፖለቲካው ላይ ስለሆነ በዚህ ላይ እሱ በሚመስለው መንገድ ለማብራራት ጥሯል። በእርግጥ ዶክተር ብርሃኑ በትክክል እንዳስቀመጠውና እኛም መቀበል ያለብን፣ እሱ ለንባብ ያቀረበው መጽሀፍ ለውይይት የቀረበና፣ ሰፋ ያሉትን የህብረተሰብአችንን ችግሮች በውይይትና በሂደት ለመፍታት በማመን ብቻ ነው። በእርግጥም የሚያስመሰግነው ነው ። ምክንያቱም ማንኛውም ምሁር አንድ ህብረተሰብን የሚመለከት መጽሀፍ በሚጽፍበትና ለንባብ በሚያቀርብበት ጊዜ፣ ለንባብ የሚቀርበው መጽሀፍ መወያያ እንጂ ያለቀለትና የደቀቀለት፣ የአንድም ህብረተሰብ ችግር በአንድ መጽሀፍ ላይ በቀረበ ሀተታ ሊፈታ ይችላል ብሎ በማመን አይደለም። በዚህ መልክ ከተለያየ አቅጣጫ ተመሳሳይ አመለካከትም ሆነ የተለየ አስተሳሰብ ያላቸው ቢጽፉና ቢያስነብቡን የመጨረሻ መጨረሻ የተወሳሰበውን የአገራችንን ችግሮች ለመፍታት ወደሚያስችለው አቅጣጫ ለመምጣት እንችል ይሆናል። በሌላ ወገን  ግን ይህ ነው ትክክለኛው መንገድ ብሎ አንድ የጠራ መጽሀፍ ጽፎ አንባቢያን እንዲረዱትና እንዲገነዘብት  የሚያደርግ መቶ በመቶ የተረጋገጠ አስተያየት ባይኖርም፣ ለህብረተሰብአችንም ሆነ ለሌሎች ደሀ አገሮች የሚስማማ አጠቃላይ መልስ መስጠት ይቻላል። በሌላ አነጋገር በሊትሬቸርም ሆነ በሳይንስ ታሪክ ውስጥ በተለያዩ አገሮች አንዳንድ የተገለጸላቸው ምሁራን ብቅ ሲሉና የህብረተሰብአቸውን ችግሮች ለመረዳት ሲጥሩ የሚመሩበት ፍልስፍና ወይም ርዕይ ነበራቸው። ይህ ባይሆን ኖሮ ከረዥም ጊዜ የርስ በርስ ትርምስና ጦርነት በኋላ በአውሮፓ ምድር ውስጥ ካፒታሊዝም ባሸናፊነት ባልወጣ ነበር። የሳይንስና የፍልስፋና ጠቢባን በቀደዱት መንገድና ባስተማሩት መመሪያ መሰረት ብቻ ነው የሳይንስና የቴክኖሎጂ ዕድገትና ምጥቀት ሊታይ የቻለው።  አሁን ባለንበት ዓለም ግን  የሌሎችንም ሆነ የኛን አገር የፖለቲካም ሆነ ሌሎች ችግሮች ለመረዳት ያለው ከባድ ነገር፣ በሳይንስና በፍልስፍናዊ ክርክር ዓለም ውስጥ ያለን ሳይሆን በኢንፎርሜሽን ዓለም ውስጥ ስለሆን ሁሉም እንደፈለገው የየአገሩን ችግር  ለመረዳትና ለመተንተን ይፈልጋል። ይህ ዐይነቱ የተሰበጣጠረ አቀራረብ ደግሞ ችግሮችን በጥልቀት ተረድቶ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ በውዥንብር ዓለም ውስጥ እንድንኖር አድርጎናል።
እንደሚታወቀው ዶክተር ብርሃኑም ሆነ እኔና ሌሎች የዛሬው ዓለም ውጤቶች(Zeit Geist) ስለሆን፣ ዛሬ አገራችንም ሆነች ሌሎች አገሮች ያሉበትን ችግሮች ለመረዳት የምንጥረው ዛሬ በሚነፍሰው የአመለካከት ዘዴ ነው። በሌላ አነጋገር በዛሬው ዓለም የተለያዩ አገሮችን ችግር በሳይንስና በፍልስፍና መነጽር ለመገምገምና ለመረዳት የማይሞከርበት ዓለም ውስጥ ነው ያለነው። ስለሆነም አስተሳሰባችንና ሁኔታዎችና ማንበብ እንዲሁም ደግሞ ትንተና መስጠት የምንችለው በኢምፔሪሲስታዊ የሳይንስ መነጽር ብቻ ነው።
የዚህ ጽሁፍ ዓላማ የዶክተር ብርሃኑ ነጋን የቃለ-መጠይቅ ምልልስ ለመተቸት አይደለም። ቃለ-መጠይቁን ሁለቴ ካዳመጥኩኝ በኋላ ያልገባኛና ሌሎችንም ግራ የሚያጋባ በአገራችን ምሁራን ዘንድ የተለመደ የአቀራረብ ስልት አለ ብዬ ስላመንኩ፣ በሱ ዙሪያ አስተያየቴን ለመስጠትና ለመወያየት ነው። እነዚህም ምክንያታዊ፣ ስሜታዊና ፅንፈኛ የሚባሉ ጽንሰ-ሃሳቦች ሲሆኑ፣ ዶክተር ብርሃኑ በነዚህ ዙሪያ በተደጋጋሚ ገለጻ ስጥቷል። በተለይም ያተኮረው ምክንያታዊ በሚለው ፅንሰ-ሃሳብ ዙሪያ ሲሆን ፓለቲኛ ነን ባዮችም ችግር የህብረተሰብአችንን ችግር ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ለመረዳት ያለመቻልና፣ ምክንያታዊ በሆነ ዘዴም ለችግራችን መፍትሄ ለመስጠት ያለመቻል ነው የሚል ነው። ባጭሩ የችግራችን ዋና ችግር ችግሮቻችንን በምክንያታዊ መንገድ ያለመረዳትና ለመተንተን ያለመቻል ነው። ችግሬም በተለይም ምክንያታዊ ሲል ምን ለማለት እንደፈለገ ስላልገባኝ ከህብረተሰብ ችግር አንፃር እንዴት መረዳት ይቻላል ብዬ የራሴን አስተያየት ለመስጠት ነው ይህችን ጽሁፍ ለመጻፍ የተገደድኩት።
የህብረተሰብን ችግር  ምክንያታዊ  ወይስ ሳይንሳዊ በሆነ ዘዴ መረዳት!
         ለምሳሌ በአቶ ዳንኤል ወርቁ ካሳ የታተመውን የእንግሊዝኛ- አማርኛ መዝገበ-ቃላትን ወስደን ስንመለከት ምክንያታዊ የሚለውን ጽንሰ-ሃብ በእንግሊዘኛው ሪዝን(Reason) ከሚለው ትርጉም ጋር የሚመሳሰል ነው። በመዝገበ- ቃላቱም መሰረት፣ ሪዝን የማሰብና የመረዳት ችሎታንም ያጠቃልላል። ይህም ማለት ሶስት ትርጉሞች ሲኖሩት፣ ሶስቱም የተያያዙ ናቸው። በሌላ ወገን ግን ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ምክንያታዊ በሚለው ጽንሰ-ሃሳብ ላይ ብቻ ያተኮረ በመሆኑ እሱ በተነተነው መልክ የሀብረተሰብአችንን ችግር ለመረዳት የተሟላ የመተንተኛና የመረዳት ዘዴ ሊሆን ይችላል ብዬ አልገምትም። ስለዚህም  የሱን አገላለጽ ብቻ ብነወስድና የህብረተሰብ ችግርን እንደመገንዘቢያ ዘዴ ብንጠቀምበት፣ እያንዳንዱ ምሁር የየራሱን ምክንያት ስለሚደረድር ይህ ዐይነቱ ችግርን የመረዳት ዘዴ የህብረተሰባችንን የተወሳሰበ ችግር ጠለቅ ባለ መልኩ እንድንረዳው የሚያስችለን አይመስለኝም።
በአቶ ዳንኤል ወርቁ የተደረሰው የእንግሊዘኛና የአማርኛ መዝገበ-ቃላትም ሆነ የዶክተር ብርሃኑን ትርጓሜ ስንመለከት በአውሮፓ የፍልስፍና ታሪክ ውስጥ ምክንያታዊ ከሚለው አነጋገር ይልቅ አርቆ-ማሰብ ወይም ራሺናል(Rational) የሚለውን ጽንሰ-ሃሳብ ብንጠቀም ችግራችንን ለመረዳት አንድ ርምጃ ተራመድን ማለት ነው።  በፍልስፍና ትምህርት ወይም ክርክር ውስጥ አርቆ-አስተዋይነት ወይም ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ምክንያታዊ የሚለውን መንገድ መከተሉ ብቻ የአንድን ህብረተስብ ችግር ለመረዳት በቂ እንዳልሆነ ፈላስፋዎችና ሳይንቲስቶች ይስማማሉ። ፈላሳፍዎች ኢንተሌክት ወይም ምሁራዊና ኢንተለጀንስ የሚሏቸው ነገሮች አሉ። ይህም ማለት አርቆ-አሳቢነት ወይም ምክንያታዊነት የተሟላ የህብረተሰብ ችግርን  መረዳት ዘዴ ሊሆኑ የሚችሉት በኢንተሌክትና በኢንተለጀንት የጭንቅላት ክፍል ሲታገዙ ብቻ ነው። ይሁንና ግን በአንድ ህብረትሰብ ውስጥ ኢንተለጀንት ስዎች ቢኖሩም ችግሩን በተለያየ መልክ ስለሚተረጉሙት፣ በእነ ፕላቶን መሰረት ማንኛውም ዕውቀት ከሃሳብ መፍለቅና በሃሳብ መታገዝ እንዳለበት ይጠቁመናል። በፕላቶንም መሰረትና፣ በኋላም የሱን ፈለግ ይዘው ማሰተማር በጀመሩት ምሁራን አመለካከት የሰው ልጅ ችግር ሁሉ የተፈጥሮንና የሀብረተሰብን ትርጉም የመረዳት ችግር ነው። በፕላቶንም ዕምነት የሰው ልጅ ሁሉ ችግር የዕውቀት ወይም የአስተሳሰብ ችግር( Problem of Thought) ነው። ይህም ማለት በፕላቶን ዕምነት ዕውቀት በቀጥታ ከምናየው የሚፈልቅና የሚገኝ ሳይሆን ከሚታየውና ከሚጨበጠው አልፈን ሄደን የአንድን ነገር አፈጣጠር ምንነት ስንረዳ ብቻ ነው። ስለሆነም በሱ ዕምነት ወደ ዕውነተኛ ዕውቀት ጋ ለመድረስ ሃይፖቴስስንና ዲያሌክቲክን የመመራመሪያ ዘዴ ማድረግ መቻል አለብን። ይህም ማለት የአንድን ህብረተስብ ችግር ለመረዳትም ሆነ የተፈጥሮን ህግ ለመገንዘብ እየመላለስን መጠየቅ መቻል አለብን። ለምሳሌ የምንጠጣው ውሃ ለምን ከሃይድሮጅንና ከኦክስጂን ቅልቅል ብቻ መገኘት ወይም መፈጠር ቻለ? ለምን ሌሎች ንጥረ-ነገሮች የውሃ ምንጭ ወይም መሰረት ሊሆኑ አልቻሉም ? በዚህ መልክ  ጥያቄን በጥያቄ ብናነሳ የመጨረሻ መጨረሻ ተቀራራቢ መልስ ለማግኘት እንችላለን። በሌላ ወገን ግን ምክንያታዊ የሚለውን ፅንሰ-ሃሳብ ብቻ ወሰደን የአገራችንን ችግር ለማንበብና ለመተንተን የምንሞክር ከሆነ ችግር ውስጥ ልንገባ እንችላለን። ይኸውም ሁሉም በፈለገው መልክ ቀደም ብሎም ሆነ ዛሬ ያለውን የህብረተሰብአችንን ችግር ለመተርጎም ስለሚፈልግ ይህንን አካሄድ እንደሳይንሳዊ ችግርን የመረዳትና የመተንተኛው ዘዴ አድርገን ለመጠቀም ያዳግታል። መፍትሄም ለመፈለግም አይጠቅመንም። በእኔ ዕምነትና በሳይንስ ዓለም ውስጥ የተለመደውን የተለያዩ አንድን ሁኔታ የማንበብ፣ የመረዳትና የመተንተኛ ዘዴዎች ብንጠቀም የችግሩንም ምንጭ ወይም ዋና ምክንያት ለመረዳት ብቻ ሳይሆን መፍትሄም ለመፈለግ ይረዳናል። እነዚህ ደግሞ ከአመለካከት ወይም ከተወሰነ ህብረተሰብአዊ ዕሴት ጋር የተያያዙ ናቸው። 1ኛ)በሃሳብ ላይ የተመረኮዘው ዲያሊሌክቲካዊው የፕላቶን መመርመሪያ ዘዴ፣ 2ኛ) በቀጥታ በሚታዩ ነገሮች ላይ ተመርኩዞ የሚደረግ የመመርመሪያ ዘዴ ወይም ኢምፔሪሲስታዊው መንገድ፣ 3ኛ)  በማቴሪያሊስት ላይ የተመሰረተ የምርምር ዘዴ ወይም ማርክሲስታዊው የምርምር ዘዴ፣ 4ኛ) ከላይ በተጠቀሱት ውስጥ የሚጠቃለሉ የዱርክ ሃይምና የማክስ ቬበር የአገዛዝና የሶሻል ቲዎሪ የምርምር ዘዴዎች።
ዶክተር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ ያለውን የተወሳሰበ ችግር ከብቃት ማነስ ጋርም ለማያያዝ ሞክሯል። ይህ ችግር በመንግስትም ሆነ በተቃዋሚዎች መሀከል ሲንፀባርቅ ሲታይ፣ ችግሩ በተለያዩ ኃይሎች ዘንድ የተለያየ ግንዛቤ እንዳለ ይጠቁማል። በተለይም በተቃዋሚው መሀከል ያለውን ችግር ሲያብራራ፣ የተወሰነው ኃይል  የአገራችንን ችግር `በጥልቀት` ሲመለከትና `ለመፍታት` ሲጥር፣ ሌላው ደግሞ የራሱን አጀንዳ ይዞ በመምጣትና ስሜታዊ ቅስቀሳ በማድረግ የፓለቲካውን መድረክ እንደሚያደፈርሰውና፣ ይህም ዐይነቱም አካሄድ ለተወሳሰበው የአገራችን ችግር ተደራቢ ችግር እንደፈጠረለት  ይጠቁማል።  እዚህ ላይ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ የብቃትን ማነስ ከዕውቀት ጋር መያያዝ እንደሌለበት ለማብራራት ሞክሯል። በእኔ ግምት ግን ብቃት ማነስ የሚለው አባባል በቀጥታ ከዕውቀትና ከልምድ ማነስ ጋር የሚያያዝ ስለሆነ፣  ብቃት ማነስ በሚለው ፈንታ የንቃተ-ህሊና ማነስ የሚለው ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ላነሳው ጥያቄና የህብረተሰብአችንን ችግር ለመረዳትና መፍትሄም ለመፈለግ  የተሻለ አካሄድ ይመስለኛል።
በአውሮፓው የፍልስፍና ታሪክ ውስጥ ንቃተ-ህሊና(Consciousness) ከፍተኛ ቦታን የሚይዝ ሲሆን፣ ብዙ ነገሮችን የሚያጠቃልል ነው። በመጀመሪያ ደረጃ የንቃተ-ህሊና መዳበር እንድናመዛዝን ይረዳናል። ንቃተ-ህሊናችን በዳበረ ቁጥር፣ 1ኛ) ያለፈውን ታሪካችንንም የመረዳት ኃይላችን ከፍ ይላል። ይህም ማለት ያለፈውን ታሪክ በጥቁርና በነጭ እየጻፉ አንዱን ከመፈረጅና ሌላውን ከማወደስ ይልቅ፣ ታሪካዊ ሂደት የቱን ኃህል አስቸጋሪና፣ አንድን ህብረተሰብ ለመሰብሰብና ለመገንባት ምን ምን  ደንቃሮች እንቅፋት እንደሚሆኑ መገንዝበ ያስችለናል። 2ኛ) ከዚህ ስንነሳ የንቃተ-ህሊና መዳበር ህብረተሰብአዊ ኃላፊነት እንዲኖረንና፣ የምናደርጋቸውን ድርጊቶች በሙሉ ከህብረተሰብ ጥቅም ጋር መያያዝና አለመያያዛቸውን እንድንገዘብ ያግዘናል። 3ኛ) የንቃተ-ህሊናችን ሲዳብር ጥሩ ጥሩ ባህሎችን መንከባከብና፣ ከውጭ የሚመጡትን ባሀል ነከ ነገሮች በመለያየትና ጥሩውን መርጦ በማውጣት ካለን ጥሩ ባህል ጋር በማዋሃድ ውስጠ-ኃይሉ ከፍ ያለና የህዝቡን የማሰብ ኃይል የሚያዳብር ባህል እንዲገነባ ማድረግ ይቻላል። 4ኛ) የአንድ ህዝብ፣  በተለይም የምሁር ንቃተ-ህሊና መዳበር ሞራልንና ስነ-ምግባርን እንድናስቀድም ያግዘናል። መናናቅንና ትዕቢትነትን አሽቀንጥረን ጥለን ራስን ዝቅ በማድረግ አንድ ህብረተሰብ እጅ ለእጅ ተያይዞ አገርን ለመገንባት መንገዱን ለማመቻቸት ይረዳናል። 5ኛ)የንቃተ-ህሊና መዳበር በተለይም በዚህ በተወሳሰበ  ዓለም ውስጥ የሚናፈሰውን ዕውቀት መሰል ነገር፣ ግን ደግሞ አገርን የሚያፈራርስና ማህበራዊ አሴትን የሚያበላሽውን በዕውቀት ስም ገብቶ የሰውን ጭንቅላት የሚያዛንፈውንና ዕውነትን ከውሸት ለመለየት የማያስችለውን ኢንፎርሚሽንና ዓለም አቀፋዊ ስምምነትን በደንብ እንድንገነዝብ ይረዳናል። በተለይም በዛሬው ወቅት የምዕራቡ ካፒታሊዝም በሁሉም ዘርፍ ቀዳሚነት አለኝ ብሎ በሚመጻደቅበት ዓለም ውስጥና ብዙ አገሮችን እያሳሳተ ወደ ማህበራዊና የኢኮኖሚ ድቀት ውስጥ ዘፍቀው ከዘለዓለማዊ ባርነት እንዳይወጡ በሚያደረግበት ዘመን የንቃተ-ህሊና ማደግ ከፍተኛ ቦታን ይይዛል። ዞሮ ዞሮ የንቃተ-ህሊና መዳበር ከጥሩ ዕውቀት ጋር የሚያያዝ ነው። ዕውቀት ደግሞ ለዳቦ ተብሎ በአራት ዐመት የኮሌጅ ዲግሪ ወይም በአንድ የዶክትሬት ቴሲስ የሚጠናቀቅ ሳይሆን ከዚያ በላይ እንድንሄድ የሚያደርገንና፣ ትላንታና የተማርነውን እየደጋገምን በመጠየቅ ወደ ሀቀኛው መንገድ ለማምራት የሚያስችለንን መፈለጊያ ዘዴ  ነው።
ከዚህ ስንነሳ በአገራችን የፖለቲካ ተዋናዮች ዘንድ አገዛዙንም ጨምሮ ከፍተኛ የሆነ የንቃተ-ህሊና ማነስ ክፍተት እንዳለ መገንዘብ እንችላለን። ይህም ስለሆነ ነው በተለይም ባለፉት 22 ዐመታት አገራችን በሁሉም አቅጣጫ ከውስጥም ሆነ ከውጭ ስትቦረቦር፣ የህብረተስብአችን ባህላዊ እሴቶች እንዳሉ ሲበጣጠሱና ማንም እየመጣ እንዲጨፍርባቸው ሲደረግ፣ በዕድገትም ስም አገራችን ስትፈራርስና ህዝባችንም ከቤቱ እየተፈናቀለ ሜዳ ላይ እንዲወድቅ ሲደረግ ራሱ ተቃዋሚ ነኝ የሚለው ኃይል  ዝም ብሎ እንዲመለከት የተገደደው። በቁጭት እየተነሳ ጥያቄ በመጠየቅ ሲመራመርና መፍትሄ ሲፈልግ አይታይም።ሲታገልና ሲያታግል አናይም። ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በሚሉት አዲሱ የፈሊጥ አነጋገር እያየ ዝም ብሎ ተቀምጧል።
እንደሚታወቀው በፍልስፍናና በሳይንስ ዓለም ውስጥ አንድን ነገር ለመረዳት አንድ መንገድ ብቻ እንደሌለ በፈላስፋዎች መሀከል ክርክር ነበር። ዛሬም ቢሆን በመጠኑ አለ። ለምሳሌ ኢምፔሪሲስታዊው መንገድ በተለይም ሶፊስቶች ያፈለቁትና፣ ከአስራስድስተኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ የእንግሊዝ ሊበራል ፈላስፎች ያስፋፉትና ዛሬ የዓለም ማህበረሰብ በሙሉ አውቆም  ሆነ ሳያውቅ የሚመራበትና የሚደናበርበት ዘዴ ነው። ይኸኛው መንገድ ከተፈጥሮ ሳይንስ አልፎ ወደ ህብረተስብ ሳይንስና ወደ ፖለቲካ ሳይንስ ድረስ በመዛመት ዓለም ዛሬ ላለችበት የተመሰቃቀለ ችግር ዋናው ምክንያት እንደሆነ ብዙ ፈላስፎችና ሳይንስቲስቶች ይስማማሉ። በተለይም ከ19ኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ የብዙ አገሮች ዕድል በካፒታሊዝም መስፋፋት እየተወሰነ በመምጣቱ ፍልስፍናን የሰው ልጅ ኑሮ መመሪያና የጥበብ መፈለጊያ መሆኑ ሊያከትም በቃ። ስለሆነም የእንግሊዝ ሊበራሎች ፍልስፍና በአሸፋኒት ከወጣ ወዲህ ክስተት ዋናው መመሪያ በመሆን ዕውነትን ለመፈለግ የሚደረገው ጥረት ቆመ። ይህም ማለት ኒውትራል ወይም ገለልተኛ የነበረው የእነ ፕላቶን ፍልስፍና በመገፍተር የመጨረሻ መጨረሻ ርዕዮተ-ዓለምን ተገን ያደረገው ወይም ለአንድ ወገን የሚያደላው ፖዘቶቭ ሳይንስ በአሸናፊነት ሰለወጣ፣ የተፈጥሮና የህብረተሰብ ሳይንስ ገለልተኛ መሆናቸው ቀርቶ የአገዛዝ መሳሪያዎች በመሆን ተፈጥሮንና የሰውን ልጅ መሉ በሙሉ ወደ መቆጣጠሪያነት እንዳመሩ ይነግሩናል። በዚህም ምክንያት በታወቁ ፈላስፋዎች መሰረት የእነ ሬኔ ዴካና የኒውተን ፍልስፍናና ሳይንስ በአሸናፊነት መውጣት ተፈጥሮን ሙሉ በሙሉ ተበዝባዥ ማድረጉ ብቻ ሳይሆን ራሽናል የሚለው ጽንሰ-ሃሳብ  ነጠላ ነገሮችን መተንተኛ ዘዴ ከመሆን አልፎ የሰውን ልጅ ተፈጥሮአዊ የጭንቅላት ባህርዮች፣ ኮመን ሴንስንና በደመ-ነፍስ የማወቅ ችሎታን( Intution) እየገፈተራቸው መጣ። ራሽናሊዝም በካፒታሊዝም ዘመን ወደ ዋጋ ጥቅም(Cost-Benefit) ማስሊያ ዘዴነት ዝቅ በመደረጉ ማንኛውም የምርት እንቅስቃሴና የቴክኖሎጂ ዕድገት ከትርፍና ከዋጋ አንፃር ብቻ የሚታዩና የሚተመኑ ሆኑ። የአገራችንም ምሁራን ችግር ይህንን በተለይም ከ19ኛው ክፍለ-ዘመን መጨረሻ ጀምሮና፣ በ20ኛው ክፍለ-ዘመን ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ወዲህ በአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ሎጂክ የተዋቀረውን አገሮችን በሱ ቁጥጥር ስር ለማድረግ ያስፋፋውን የዘመናዊነት ርዕየተ-ዓለም አለመገንዘብ ነው። ይህ ጉዳይ የኛ አገር ችግር ብቻ ሳይሆን ሶስተኛው ዓለም አገሮች  ተብለው የሚጠሩ  ሁሉ የገቡበት መቀመቅ ነው።
ይህንን እጅግ አስቸጋሪውን በከበርቴው ዓለም ውስጥ ያለውን የተወሳሰበ ሳይንሳዊ አመለካከት ትቼ ወደ ዶክተር ብርሃኑ የቃለ-መጠይቅ ምልልስ ጋ ስመጣ በእኔ ግምትና ዕምነት በአለፉት አርባ ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የተሳተፉና ያለፉ፣ ዛሬም የሚገኙ ምሁራን ችግር የህብረተሰብአችንን ችግር፣ ዶክተር ብርሃኑ በትክክል እንዳለው ችግራችንን ለመረዳት መጣር ሳይሆን በስሜታዊነት በመታገዘና አንድን ሁኔታ በጥቁርና በነጭ በመሳል የማይሆን ንትርክና ግብግብ ውስጥ መግባት ነው። የዚህ ሁሉ ችግር ምንድነው ?
እነሶክራተስና ፕላቶ የግሪክን የረዥም ጊዜ የስልጣኔና የርስ በርስ ታሪክ ካጠኑ በኋላ የደረሱበት መደመደሚያ፣ ላይ እንዳልኩት በዚያን ጊዜ የነበረው ችግር አርቆ የማሰብ ችግር ጉዳይ ነበር። ስለዚህም በእነሱ ዕምነት ለአንድ ህብረተሰብ ችግር ዋናው መፍትሄ ችግርን መደበቅ ሳይሆን ዲያሌክቲካዊ በሆነ መንገድ ወደ ውጭ አውጥቶ በግልጽ መነጋገር ነው። ለዚህ ደግሞ ትክክለኛ ፍልስፍና ያስፈልጋል። ይህ ዐይነቱ የትግልና ሃሳብን ወደ ውጭ አውጥቶ የመከራከሪያ ዘዴ በፖለቲካ ብቻ ሳይሆን በድራማና በልዩ ልዩ ነገሮች ዙሪያ ክርክርና ማስተማሪያ ዘዴ በመሆነ የሰውን ልጅ ጭንቅላት ማረቂያና ማስተማሪያ ዘዴ እንዲሆን ተደርጓል። በተለይም ሶሎን የተባለው ከክርስቶስ ልደት በፊት በአምስተኛው ክፍለ-ዘመን ላይ ስልጣንን የተረከበው መሪ በፍልስፍና በመታገዝ ተግባራዊ ያደረገው የፖለቲካ ሪፎርም ግሪክን በጊዜው ከነበረችበት የህብረተሰብ ቀውስ ለጊዜውም ቢሆን ሊያላቅቃትና፣ ከዚያ በኋላ ሺህ በሺህ ለሚቆጠሩ የሂሳብና የፈላስፋ አዋቂዎች መንገዱን እንደከፈተ ታሪክ ያረጋግጣል።
ወደኛው አገር ስንመጣ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ህብረተሰብአዊ ችግርን በግልጽ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ለመጠየቅና ለመከራከር ወይም ደግሞ ለመወያየት የተለመደ መንገድ አልነበረም። ከአክሱም አገዛዝ ጀምሮ አብዮቱ ፈነዳበት እስከተባለበት ጊዜ ድረስ የተዋቀረውን የአገዛዝ ሁኔታ ስንመለክት ህብረተሰብአችን በስራ-ክፍፍል መዳበር፣ በውስጥ ንግድ እንቅስቃሴ መበልጸግ፣ በእደ-ጥበብ ማበብ፣ በከተማዎች ዕድገትና ሰፋ ባለ ምሁራዊ እንቅስቃሴ የሚገለጽና ጎልቶ የሚታይ ስልጣኔ  ስላልነበር  አመለካከታችንን በማደበርና ትላልቅ የታሪክ ስራዎችን ለመስራት አላስቻለንም። ከህብረተሰብ ሳይንስም ሆነ ከፍልስፍና ዕውቀት አንፃር ሁኔታ ስንነሳ በአንድ ህብረተስብ ውስጥ የማቴሪያል ሁኔታዎች በሚለወጡበት ጊዜ የሰው ልጅ ህብረተስብአዊ ባህርይን የመውሰድና መስልጠን እየጎለመሱ ይመጣሉ። በዚያውም መጠን በጭንቅላቱ ውስጥ ያሉ የተደበቁ ባህርዮቹ በሙሉ በመዳበር ተፈጥሮን የበለጠ መቃኘት ይጀምራል። ስለራሱም ሆነ ስለሌላው ያለው አስተሳሰብ እየተለወጠ በመምጣት የበለጠ ስብአዊነትን እንዲካን ይደረጋል። በዚያው መጠንም ስለህብረተስብ ዕድገትና አኗኗር እንዲሆም ደግሞ ሰለተፈጥሮ ያለው ግምት ይለወጣል። ከፕላቶ ጀምሮ እስከሺለርና እስከ ማክስ ቬበር ያሉ ስራዎችን ላነበበ የምንገነዘበው የሰው ልጅ በአፈጣጠሩ ማህብራዊና ህብረተስብአዊ ቢሆንም፣ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በሚዋቀሩ መጥፎ የአገዛዝና የማቴሪያል ሁኔታዎች አስተሳሰቡ ይታፈናል፤ ይበላሻልም። ከዚህ ስንነሳና አያሌ የህብረተሰብ ሳይንስ ጥናቶችን ሳገላብጥና የህብረተስብአችንን ችግር ለማጥናትና ለመረዳት ስቃጣ የኛ ችግር በመሰረቱ ሰፋ ካለ ምሁራዊ እንቅስቃሴ ጉድለት የተነሳና ነገሮች በግልጽ ለመወያየት ያለመቻል ችግርና ፍላጎት ማጣት ነው። ዞሮ ዞሮ ከአርባ ዐመት የአብዮት መዳፈን በኋላም በሳይንስና በቴክኖሎጂ ዓለም ውስጥ ተቀምጠን እንደዚህ ግራ መጋባት የቻልነውና በቂም በቀል የምንተያየው ያ ፊዩዳላዊ አመለካከት በጭንቅላታችን ውስጥ ስለተቀረጸ ነው።
እንደሚታወቀው ከአብዮቱ በፊትም ሆነ በአብዮቱ አፍላ ዘመን ተራማጅ በሚባሉ ኃይሎች መሀከል ይካሄድ የነበረውን የክርክር ዘዴ ስንመለከት ከአንዳንድ አቀራረቦች በስተቀር አብዛኛው በእንካ ስላንቲሃ ላይ ያተኮረ ነበር። በአብዮቱ ወቅት በተፈጠረው ትርምስ በመጀመሪያው ወቅት ይካሄድ የነበረው ክርክር እንዲዘጋና የጠብመንጃ ትግል ብቻ ነው የሚያዋጣው በማለት ወጣቱን ሁሉ የእርስ በአርስ ጦርነት ውስጥ ማሰማራትና መጨራረስ ሆነ። በሳይንሳዊ መንገድ ከማስተማርና ከማሳመን ይልቅ በተለይም የወጣቱን ጭንቅላት በመጥመድ አርቆ አሳቢነት እንዲወድም ተደረገ። በጊዜው የነበረውም ትግል ስልጣን ለመያዝ ብቻ ስለነበር፣ ሁሉም የደፈጣ ውጊያ ጀመረ። ሳይቀድሙኝ ልቅደም የሚለው አስተሳሰብ በመስፋፋቱ የወጣቱ አስተሳሰብ ተመረዘ። ስልጣን በጠብንጃ ብቻ ነው ሊያዝ የሚችለው፣ አብዮትም ደም በመፍሰስ ብቻ ነው ሊሰምር የሚችለው በማለት የውይይትና የመከራከር ባህል እንዳይዳብር ተደረገ። የተለያዩ ድርጅቶች የየራሳቸውን ካድሬዎች ሲመለምሉ ጋጠወጥነት ተስፋፋ። አብዮቱ ተቀለበሰ ከተባለበት ጊዜና ወታደሩ መሉ በሙሉ ስልጣንን ከጠቀለለ በኋላ ተራማጅ  ነኝ የሚለው ኃይል ጊዜ ወስዶ በማጥናትና በመመራመር በጊዜው የተፈጠረውን ችግር ሊረዳ አልቻለም። ያ በዚያን ጊዜ የተፈጠረው የፅንፈኝነትና የመበጥበጥ ባህል ከደማችን ጋር በመዋሃድ በአጠቃላይ ሲታይ በሳይንስ፣ በፍልስፍናና በቲዎሪ ዙሪያ ምንም ዐይነት ጥናት እንዳይካሄድ ታገደ። የቲዎሪንና የሳይንስን ጥያቄ የሚያነሱ በሙሉ እየተሾፈባቸውና ስማቸው እየጎደፈ የትግል መድረክ የሚባለውን እየጣሉ እንዲወጡ ተገደዱ። ይህ ዐይነቱ ሳይንሰ- አልባና ፍልስፍና አልባ ትግል ለጮሌዎችና ለበጥባጮች፣ እንዲሁም ደረታቸውን እየነፉ ሰውን ለሚንቁ በሩን ከፈተላቸው። ህብረተሰብአዊ ለውጥ ካለሳይንስና ካለቴክኖሎጂ እንዲሁም ካለፍልስፍና የሚመጣ የሚመስለው እዚህና እዚያ ፓርቲዎችን በመመስረት ብዙ ወጣቶችን አሳሳተ። ዛሬም ያለው ችግር ይህ ነው። እንዴት አድርጎ አንድን ህብረተሰብ ካለሳይንስና ካለቴክኖሎጂ መለወጥ ይቻላል?  አንድ ህብረተሰብ በፍልስፍናና በህብረተሰብ ሳይንስ መነፅር እየታየ ካልተመረመረ እንዴት አድርጎ ችግሩን መረዳት ይቻላል? ይህንን ዐይነቱን ግራ የተጋባ አካሄድ ካልተውንና፣ በተለይም ደግሞ ለጮሌዎችና ለሰላዮች መንገዱን እስካልዘጋን ድረስ በሚቀጥሉት መቶ ዐመታትም የኢትዮጵያ ሁኔታ በፍጹም ሊለወጥ አይችልም። ስለዚህም ዛሬ ከገባንበት አስጨናቂ ሁኔታ ለመውጣት የግዴታ የሙጥኝ ብለን ከያዝነው የትግል ዘዴ መላቀቅ አለብን። ፍልስፍናን፣ ሳይንስንና ሶስይሎጂን ያስቀደመ የምርምር ዘዴ ማስቀደምና ወጣቱን ማስተማር መቻል አለብን። ኢትዮጵያን አድናለሁ የሚል ሁሉ ሀቀኛ ነኝ ብሎ እስካመነ ድረስ ከጭንቅላት ተሃድሶ የትግልና የምርምር ዘዴ ውጭ ሌላ የትግል ዘዴ  በፍጹም ሊኖር እንደማይችል መገንዘብ አለበት።
የሀብረተስብአችንን  የተወሳሰበ ሁኔታ የመረዳት ችግር!
        ወደ አገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ስንመጣ የአንድን ህብረተሰብ ሂደትና ዕድገት በህብረተስብና በተፈጥሮ ሳይንስ ለመረዳት ያለመቻል የግዴታ እየመላለስን በብሄረሰቦች መሀከል ያለ ችግር ወይም ደግሞ አንድ ብሄረስብ ብቻ የፈጠረው ችግር  አድርገን እንድንመለከት አድርጎናል። ወደድንም ጠላንም እንኳን በአንድ አገር ውስጥ ያሉ ብሄረሰቦችም ሆነ ከአንድ እናት የሚወለዱ ህጻናት በአሰተዳደጋቸውና ነገሮችን በመቅሰም ተመሳሳይ ዕድገት ሊኖራቸው አይችልም። በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ አንደኛው ከሌላው ቀድሞ ነገሮችን በመማርም ሆነ በመቅሰም ወይም በቁመት በማደግ ሊቀድመው ይችላል። ወደ ህብረተሰብ ታሪክም ስንመጣ በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ በአንድ አካባቢ የሚኖር ህዝብ ወይም ብሄረሰብ ቋንቋን፣ ባህልን፣ ዕደ-ጥበብንና የስራ ክፍፍልን በማዳበር በተፈጥሮ ላይ የተወሰነ የበላይነትን ይቀዳጃል። ከእንስሳ የተሻለ መሆኑን ያረጋግጣል። በዚህ መልክ በአገራችን ብቻ ሳይሆን በተለያዩ አገሮች ቋንቋዎችና ባህሎች በሁሉም አካባቢ ተመጣጣኝ በሆነ መልክ ያደጉበት ሁኔታ የለም።  የየአገሮችን ስልጣኔ ታሪክ ስንመለከት ወደ ባህር አካባቢና ለውጭው ዓለም የቀረቡና ክፍት የነበሩ አገሮች ስልጣኔን ቶሎ የመቀዳጀትና የማዳበር ዕድል አግኝተዋል። ለምሳሌ ከክርስቶስ ልደት በፊት በአምስተኛው ክፍለ-ዘመን የመጀመሪያው ዘመናዊ የግሪክ ስልጣኔ በአዮን አካባቢ የዳበረው ከግብጽ ስልጣኔ ጋር የጠበቀ ግኑኝነት ስለነበረውና ከህንድ ጋር በሚመጡ ፍልስፍናዎች በመተዋወቁ ነበር። የሌሎችም አገሮች ታሪክ ይህንን ይመስላል።
የአገራችንን ታሪክ ስንመለከት የስልጣኔው ታሪክ እጅግ የተወሳሰበና ገና ብዙም ያልተጠና እንደሆነ መገንዝብ ይቻላል። ይሁንና ግን የዛሬው የኢትዮጵያ ስልጣኔ ዋናው መሰረት የተጣለው ከአክሱም አገዛዝ ቀደም ብሎ እንደነበርና፣ ከአራተኛው ክፍለ-ዘመን ከክርስቶስ ልደት በኋላ መልክ እየያዘና የአገዛዝ መዋቅር እየጣለ የመጣ ለመሆኑ ብዙ የታሪክ ማስረጃዎች ያረጋግጣሉ። ይህም የሆነበት ምክንያት የሰሜኑ ክፍል ለባህር የቀረበና ከውጭው ዓለም ጋር የጠበቀ ግኑኝነት ስለነበረው ነው ። በዚህም ምክንያት ከአራት ሺህ ዐመት በፊት የግዕዝ ፊደልን ማፍለቅ ሲቻል፣ ይህ ፊደል ከአራተኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ ስርዓት ባለው መልክ እየተቀነባበረና የመጻፊያና የመነጋገሪያ ዘዴ እየሆነ ይመጣል። በዚያን ጊዜ እንደዚህ ዐይነቱ ፊደልና ቋንቋ ሲዳብር ሌላውን የህብረተሰብ ክፍል ለመጨቆኛ ተብሎ ሳይሆን ማንኛውም ህብረተሰብና የሰው ልጅ እንደሚያደርገው ሁሉ የሰሜኑ የአገራችንም ህዝብ ይህንን ዕድል አገኘ። በዚህም በመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ምድር ውስጥ ከመነጋገሪያ አልፎ እንደመጻፊያ  የሚያገለግል የተሟላ ቋንቋ ማዳበር ተቻለ። ከዚህም አልፎ የሙዚቃን ምት በማዳበርና የሙዚቃን መሳሪያ በመስራት እስከተወሰነም ደረጃ ቢሆን ለስልጣኔው ዕምርታ ሰጠው። ስለሆነም በዚያን ጊዜ የነበረውን አገዛዝና ህዝብ በዚህ የስልጣኔ አፍላቂነቱ ልናመስግነው የሚገባን እንጂ እንደጠላት የምናየው አይደለም። ይህንን የምናደርግ ከሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በየአገሮች ውስጥ ፊደልንና ቋንቋን ያዳበሩትንና ያፈለቁትን፣ እንዲሁም ሳይንስና ቴክኖሎጂ የፈጠሩትን ግለሰቦች በሙሉ  እንደጠላት እያየናቸው ልንፈርድባቸው ነው ማለት ነው። በሌላ አነጋገር በመጀመሪያው ወቅት ስልጣኔዎች ሁሉ የሚፈልቁት ከሰው ልጅ ውስጣዊ ውስጠ-ኃይልና የመስለጠን ፍላጎት የተነሳና፣ እንዲሁም ደግሞ የአካባቢ አመችነትና ከተለያዩ ህዝቦች ጋር በሚደረግው ግኑኝነት አማካይነት  እንጂ የመግዣ ወይም የመጨቆኛ መሳሪያ ይሆናሉ ተብለው በማሰብ አይደለም። ይሁንና ግን ታሪክ እንደሚያረጋግጠው የሰው ልጅና ባህሉ ውስጣዊ-ኃይል ስላላቸው በአንድ ቦታ ረግተው የሚቀሩ አይደሉም። እንደባዮሎጂካዊ ክንውን በሁሉም አቅጣጫ በመስፋፋት ሌሎች የህብረተሰቦች ክፍሎችንም ያዳርሳሉ። ይህ ዐይነቱ ህብርተሰብአዊና ባህላዊ ክንዋኔ ይባላል።
አሁንም ወደ ተጨባጩ የኢትዮጵያ ሁኔታ ስንመጣ የአክሱም አገዛዘ በራሱ ውስጣዊ ድክመትና በዮዲትና በቤጃዎች ወረራ፣ እንዲሁም ደግሞ በአረቦች ግፊት የሩቅ ንግድ መሰመሩ ከተዘጋበት በኋላ ይዳከማል። የመጨረሻ ላይም ይወድማል።  ርዝራዡ ወደ ደቡቡ የኢትዮጵያ ክፍል በመተላለፍ በዛግዌ ዲይናስቲ ዘመነ መንግስት እንደገና ማበብ ቻለ። የዛግዌ ዲይናስቲ ከወደቀ በኋላ በአስራ አራተኛው ክፍለ-ዘመን የግዕዝ ፊደል እንዳለ በመወሰድና በመሻሻል የአማርኛ መነጋገሪያ ሊሆን ቻለ። ይህ ዐይነቱ የዕድገት ሂደት ሊገታ የማይችል ሁኔታ ነው። አማርኛም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በቋንቋና በልዩ ልዩ ባህሎች በመገለጽ መዳበሩ ለጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ ዕድገት ጠንቅ ሳይሆን ያስተባበረንና መነሻችን ለመሆኑ የማይካድ ነው። ይሁንና ግን በዚህ ዐይነት የህብረተሰብ ዕድገት ታሪክ ውስጥ ሌሎች ብሄረሰቦች ተሳትፎ አላደረጉም የሚል ዕምነት የለኝም። ለምሳሌ የሸማን ስራ፣ የጠላንና የካቲካላን አጠማመቅንና እንዲሁም የጤፍ ዘርን እርባታ ስንመለከት ከየት እንደመጡ፣ ማን እንደጀመራቸውና እንዳስፋፋቸው በግልጽ የሚታወቅ ነገር የለም። ይሁንና ግን እነዚህን የመሳሰሉትና በጠቅላላው የአስተራረስ ባህልና የእርሻ ባህል መዳበርና ልዩ ልዩ ሰብሎች መስፋፋት የሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ውጤት ለመሆኑ አይካድም። በሌላ ወገን ግን ከአስራአራተኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ  ከክርስቲያኑ የሰሜኑ ክፍል ወደ ደቡቡ የኢትዮጵያ ክፍል የክርስትናን ሃይማኖትን ለማስፋፋት በሚል እንቅስቃሴና ህብረተስብአዊ ጋብቻ እንደነበር ታሪክ ያረጋግጣል። ይህ እንግዴህ የሆነው አፄ ምኒልክ ወረራ አድርገዋል ከመባሉ ከስደስት መቶ ዐመት በፊት ቀደም ብሎ ነው። በዚህ ዐይነቱ እንቅስቃሴ መሰረት ወደድንም ጠላንም ህብረተሰብአዊ መተሳሰር ሊዳብር ችሏል። አንዳንዶች የኢትዮጵያን ታሪክ ወደ መቶ ዐመት ቀንሰው ለመጻፍና ለማሳመን እንደሚሞክሩት ሳይሆን በተለያዩ የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች መሀከል ያለው መተሳሰርና የባህል ልውውጥ የብዙ መቶ ዐመታት ታሪክን የሚያስቆጥር ነው። በሌሎች አገሮች ህብረ-ብሄር በዚህ መልክ ነው የተዋቀረው። የህብረ-ብሄር ምስረታ እንደቂጣ የሚጠፈጠፍና ወዲያው የሚደርስ ሳይሆን ውጣ ውረድን በማሳለፍ የሚደረግ የአገራዊ ግንባታ ክንዋኔ ነው።
ይህ ዐይነቱ ህብረተስብአዊ እንቅስቃሴና ዕድገት  ፈጣን በሆነ የማቴሪያልና የምሁር እንቅስቃሴ ሊታገዝና ሊዳብር አልቻለም። የአገራችን ከአንድ ሺህ ዐመት በላይ ከውጭው ዕድገት ተገልሎ መኖር የውስጥ ዕድገቷን ሊያግደው ችሏል። በዚህም ምክንያት የተነሳ የህብረ-ብሄር ምስረታ በኢትዮጵያ ውስጥ የአውሮፓውን ዐይነት መንገድ ይዞ ሊጓዝ አልቻለም። አገዛዙም ባለበት ውስጣዊ ድክመት የተነሳ ከፊዩዳል ኖርሞች ባለመላቀቁ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ውስጥ ሊኖር የሚገባው መተሳሰርና መጠናከር እዚህና እዚያ በሚነሱ የፊዩዳል ግጭቶች ፈተና ውስጥ ወድቆ ነበር። ይህ ዐይነቱ ፉዩዳላዊ ፍክክርና ፉክቻ በተለይም የአውሮፓው ካፒታሊዝምና ኢምፔሪያሊዝም እያደገ ሲመጣ ልዩ ዐይነት ውስጠ-ኃይል በማግኘት በተወሰነ አካባቢ የሚገኙ ፊዩዳላዊ አገዛዞች ጥንካሪና በሌላኛው ላይ የበላይነትን የመቀዳጀት ዕድል ሰጣቸው። የአፄ ምኒልክ ጉዞና ኢትዮጵያን አንድ ማድረግ ከዚህ ጋር የተያያዘ ሲሆን፣ በሌላው ወገን ግን አፄ ምኒልክ ሌሎች ከሳቸው በፊት የቀደሙ አገዛዞችን ህልም ነው መጨረሻ ላይ ተግባር ማድረግ የቻሉት። ወረራ እንበላው መስፋፋት በአፄ ምኒልክ አገዛዝ ዘመን ጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ አገር ውስጥ የመጠቃለሉ ሁኔታ የታሪክ ግዴታ ነው። በመሰረቱ አፄ ምኒልክ የአውሮፓ ፍጹም ሞናርኪዎች ከሰሩት የተለየ ስራ አይደለም የሰሩት። የአፄ ምኒልኩ ከአውሮፓው የሚለየው አንደኛ፣ ሰፋ ባለ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የተደገፈ አለነበረም። ይህ ደግሞ የሳቸው ጥፋት አልነበረም። በጊዜው የነበረው የአገራችን ተጨባጭ ሁኒታና የዕውቀት ችግር ነፀብራቅ ነው። ሁለተኛ፣ ኢትዮጵያ እንደ አውሮፓው በሬናሳንስ፣ በሪፎርሚሽንና በኢንላይተንሜንት የጭንቅላት ተሃድሶና የሳይንስ ግኝት ሂደት ውስጥ የማለፍ ዕድል አላጋጠማትም። ሶስተኛ፣ የአፄ ምኒልኩ መስፋፋት ከአውሮፓው ጋር ሲነፃፀር ይህንን ያህልም አረመኔያዊ አይደለም። የአውሮፓው ፊዩዳል ታሪክ ከአገራችን ጋር ሲወዳደር እጅግ የመረረና በጦርነት የታመቀ ለመሆኑ አያሌ የታሪክ ማስረጃዎች ያረጋግጣሉ።
ይሁንና የአፄ ምኒልክ አገዛዝ በተስፋፋበት ቦታ አልገዛም ያሉት ላይ ርምጃዎች ተወስዶባቸዋል። እሳቸው ከሚያውቁት ውጭ አንዳንድ ተገቢ ያልሆኑ ድርጎቶች ተፈጽመው ሊሆን ይችላል። ይሁንና ግን አፄ ምኒልክን እንደወራሪና ህዝብን ጨፍጫፊ አድርጎ መቁጠር ትልቅ የታሪክ ወንጀል ብቻ ሳይሆን፣ የራስንም የታሪክና የባህል ወንጀል ለመሽፈን መጣር ነው። ለምሳሌ ኦሮሞዎች በተስፋፉባቸው ቦታዎች በሙሉ የአማራና የሌሎች ብሄረሰቦችን ወንዶች በመግደለና ብልታቸውን በመቁረጥ ብዙ ግፍ እንደፈጸሙ ይታወቃል። እንዲያውም አፄ ምኒልክ ፈጽመዋል ከተባለው ግፍ ይልቅ የኦርሞዎች መስፋፋት በተለይም በአማራው ብሄረሰብ ላይ ይበልጥ  አሰቃቂ ድርጊት እንደፈጸመ  የታሪክ ማስረጃዎች ያረጋግጣሉ። ይህ ዐይነቱ ድርጊት የጠቅላላው የኦርሞ ብሄረሰብ ድርጊት ነበር ብሎ ግን መወሰድና መፍረድ አይቻልም። ይሁንና ግን ማለት የሚቻለው በጊዜው በኦርሞዎች መስፋፋት የደረሰው ዕልቂት የኦሮሞ ብሄረሰብ ገና በአፍላ ላይ የነበረና ህብረተሰብአዊና ባህላዊ እንዲሁም ሰብአዊ እሴትን ያላዳበረ እንደነበር የሚያረጋግጠው። እንደዚህ ዐይነቱ ከአንድ ብሄረሰብ ግፊትና መስፋፋት የተነሳ በሌሎች ብሄረሰቦች ላይ የሚደረስ አሰቃቂ ድርጊት በግሪክ ዘመን የተለመደ ነበር። ስለዚህም ይህ ዐይነቱ አሰቃቂ ድርጊት የአንድ ብሄረሰብ መለያ አድርጎ መውሰድ ስህተት ነው። ይሁንና ግን እኛ የሰለጠን ነበርን፣ አማራዎች ናቸው የጨፈጨፉን የሚለው ታሪካዊና ሞራላዊ ድጋፍ ሊኖረው በፍጹም አይችልም።
በጊዜው የነበርውን የደቡቡን ክፍል ስንመረምር የምናገኘው መልስ ሁሉም የበለጸገ ወይም በስራ ክፍፍል የዳበረ ህብረተሰብ ወይም ማህበረስብ እንዳልነበራቸው ነው የምንገነዘበው። የሰሜኑም ክፍል ከደቡቡ እምብዛም አይለይም። በፊዩዳል አገዛዝና በክርስትና ሃይማኖች ጭፍን ዕምነት የተነሳ የዕደ-ጥበብና ንግድ ሊዳብሩ አልቻሉም። በዚህም ምክንያት የጠበቀ ህብረተሰብአዊ መተሳሰርና መንሰራሸር(Social Mobility) ሊኖር አልቻለም። ሁኔታውን ጠጋ ብለን በምንመረምርበት ጊዜ በተለይም አንዳንድ የኦሮሞ ኤሊቶች በፈረንጆች እየታገዙ የሚሰጡት ትንተና ፊክሽን ወይም ምንም ሳይንሳዊ ማረጋገጫ የሌለው ሀታት ነው። የኦሮሞ ብሄረሰብ ተሰበጣጥሮ የሚገኝና፣ በሳይንስና በቴክኖሎጂ የሚገለጽ አልነበረም። አብዛኛውም በከብት እርባታ ይተዳደር ስለነበር፣ ከአስራ ስድስተኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ኦሮሞዎች ሲንቀሳቀሱ ቀደም ብለው የነበሩ በደቡብ የሚገኙ ነገስታትንና ስልጣኔዎችን እየደመሰሱና እያፈራረሱ ነው ለመጀመሪያ ጊዘ መቀመጥ የቻሉት። ከአፄ ምኒልክ አገዛዝ መስፋፋት በፊት በአስራሰባተኛውና በአስራ ስምንተኛው ክፍለ-ዘመን በኦርሞ ማህበረሰብ ውስጥ በነበረው ዲይናሚዝም ጋዳ የሚባለው ስርዓት በመፈራረስ ላይ ነበር። አንዳንድ የኦሮሞ ኤሊቶች እንደሚሉን ጋዳ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት አልነበረም። ማርክስና ኢንግልስ ዘ እሪጂን እፍ ፕራይቤት ፕሮፖርቲ በሚለው መጽሃፋቸው ለማሳየት እንደሞከሩት በዚያ አካባቢ በነበረው የህብረተሰብ አወቃቀር የተፈጠረ የሚሊታሪ አደረጃጀት ነው ። ይህም ማለት ጋዳ በመደብ ላይ የተመሰረተና በተለይም ሴቶችን ከግል ሀብት ተሳታፊነት ያገለለ ነበር። ከዚህና ከሌሎች የሀብረተሰብ ታሪክ ዕድገት ሁኔታ ስንነሳ 1ኛ) የኦሮሞ ብሄረሰብ በአንድ አገዛዝ ስር የተዋቀረ አልነበረም። 2ኛ) አገዛዝ ወይም ሁሉንም  የሚያጠቃልል መንግስት አልነበረውም። ይህም ማለት ሰፋ ያለ የቢሮክራሲና የአድሚኒስትሬሽን አወቃቀር አልነበረውም። 3ኛ) በውስጡም የዳበረ የስራ-ክፍፍል ስላልነበረው የተሳሰረ አልነበረም። እንደሌሎች የኢትዮጵያ ግዛቶችም የኦሮሞ ብሄረሰብም በዝቅተኛ የማቴርያል ዕድገት ሁኔታ ውስጥ የሚኖር ነበር። 4ኛ) የኦሮሞ ብሄረሰብ ቋንቋውን ከመናገር አልፎ የራሱን ፊደል የፈጠረ አይደለም። እንደሚታውቀው ከሚነገር ቋንቋ ባሻገር ለአንድ አገዛዝና ህዝብ የስልጣኔ መግለጫ የሚጻፍ ፊደልም መኖር አለበት። በዚህ ብቻ ስለህዝብና ስለህብረተሰብ ማውራት ይቻላል። 5ኛ) ከዚህ ስንነሳ የኦሮም ብሄረሰብ እንደ ህዝብና እንደ ህብረተሰብ ሊታይ የሚችል አልነበረም። ይህ እንግዴህ ከስሜት ውጭ ከሆነ የህብረተስብና የፍልስፍና ሳይንስ ግምገማ ስንነሳ ነው። ከዚህ ውጭ የሚደረግ ንትርክ መደነቋቆር ብቻ ነው። ስለፍልስፍና፣ ስለተፈጥሮ ሳይንስና ስለህብረተሰብ ሳይንስ በምናወራበት ጊዜ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ እንደሚያሳስበን እንደተማርን ሰዎች ከስሜት ውጭ መውጣትና መወያየት አለበን። በጥቁርና በነጭ እየጻፍን  እንደዚህ ተደረግን፣ እንደዚህ ተባልን እያልን ሌላውን የዋሁን ለማሳመን የምናደረገው ሙከራ የመጨረሻ መጨረሻ የስልጣኔውን ጥምና ዕድገት የሚያራዝም ነው ። ወደ ጥፋትም የሚያመራን ነው። የህዝባችንን ሰቆቃ የሚያባብስ ነው። ዛሬ በጥራዝ ነጠቅነትና በአክራሪነት በኢትዮጵያ ላይ የሚዘምተው ጥቂቱ የኦሮሞ ኤሊት ነኝ ባይ በመሰረቱ የኦርሞ ብሄረሰብ ጠላት ብቻ ሳይሆን የጠቅላላውም ጥቁር ህዝብም ጠላት ነው። የሚሰራው ስራ ሁሉ ለነጭ የኦሊጋርኪና ለስለላ ድርጅቶች የሚሰራ ነው የሚያስመስለው። የተወሳሰበውን የአገራችንን ታሪክና በዓለም አቀፍ ደረጃ በግሎባል ካፒታሊዝም የተደረገብንን ግፊትና ዕንቅፋት ከማገናዘብ ይልቅ የነሱን አባባል በማስተጋባት ህዝባችን ስልጣኔ እንዳያገኝ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው። ይህም የሚያሳየው ምንድነው?  ለኦሮምያ ነፃነት እታገላለሁ የሚለው ጥቂት ኤሊት የታሪክ፣ የህብረተሰብ፣ የባህልና የፓለቲካ ነቃተ-ህሊናው በጣም ዝቅተኝ ነው ማለት ነው።
ኢምፔሪያሊዝም፣ ወይም ግሎባል ካፒታሊዝምና የብሄረሰብ ጥያቄና ችግር !
         ዛሬ አገራችን ስላለችበት የተወሳሰበ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የህብረተሰብ፣ የባህል፣ የብሄረሰብና የአካባቢ ቀውስ ከግሎባል ካፒታሊዝም መስፋፋትና አገሮችን በሱ ቁጥጥር ስር ከማዋል ውጭ ነጥሎ ማየት ትልቅ ስህተት ነው። ቀደም ብለው የነበሩ ምሁራንና ዛሬም ያለነው በከፊል የአገራችን የታሪክና የባህል ውጤት ስንሆን፣ በከፊል ደግሞ የግሎባል ካፒታሊዝም ውጤቶች ነን። ሁሉቱም አስተሳሰቦች ጭንቅላታችንን በመቅረጽ በቅራኔ ዓለም ውስጥ እንድንኖር በማድረግ አንደኛውን ከሌላው ለመለየትና ለመመረጥ የማንችልበት ሁኔታ ውስጥ እንገኛለን። እንዲያውም ለአገራችን ትልቁ ውድቀት ከ1940ዎቹ በኋላ የተፈጠረው ዓለም አቀፋዊ ሁኔታና ከግሎባል ካፒታሊዝም ጋር መተሳሰራችን ነው። ለምሳሌ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በፊት ቀደም ብለው ለዕድገት ትግል የጀመሩ አገሮችን ታሪክ ስንመለከት  ከውጭው ዓለም ጋር ግኑኝነታቸውን በመቆጠቡና ለዕድገታቸው የሚያስፈልገውን ብቻ በመውሰድ ህብረተሰባቸውን ለመገንባትና ለመጠንከር ችለዋል። ጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያና ቻይናን መመልከቱ በቂ ነው።
ያም ሆነ ይህ የግሎባል ካፒታሊዝም በአገራችን ውስጥ መስፋፋት በህብረተሰብአችን ውስጥ የነበሩት አነስተኛ ቅራኔዎችን በማጉላትና በማዳበር ቅራኔው እንዲፈታ ከማድረግ ይልቅ በማባባስ የዛሬው ውስብስብ ሁኔታ ውስጥ ሊከተን ቻለ። በተለይም ከየብሄረሰቡ ለወጡ ኤሊት ነን ባዮች የተሳሳተ ንቃተ-ህሊና እንዲያዳብሩ በማድረግ ለህብረተሰብ ግንባታ እንቅፋት ወደ መሆን አመሩ። የመጡበትን ብሄረሰብ ምሽግ በማድረግና ለወጣቱና ለታዳጊው ትውልድ ከተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር የማይጣጣምና የማይረጋገጥ ውሸት በመናገርና በማስፋፋት ጭንቅላቱን በመመረዝ ጥላቻንና ዝቅተኛ ስሜትን አስፋፉ። ስለዚህም ይህ ዐይነቱ ሁኔታ ከኢትዮጵያዊ ስሜትነት ይልቅ ከዚህኛው ብሄረሰብ ነኝ የመጣሁ ብሎ ጎልምሶ እንዲወጣ አደረገው።
እንደሚታወቀው በአፄ ኃይለስላሴ ዘመን የተዋቀረው አገዛዝ ንቃተ-ህሊናው በጣም ደካማ ስለነበር በህብረተሰብአችንን ውስጥ ማቆጥቆጥ የጀመሩትን አደገኛ ስሜቶችን ፈጣንና በተወሳሰበ የኢኮኖሚ ዕድገትና የከተማ ግንባታ ሊገታቸውና ልዩ መልክ ሊሰጣቸው አልቻለም። የአገዛዙ የኢኮኖሚ መሰረትም በጣም ደካማ ስለነበር ማህበራዊ ብሶቶችን ቀስ በቀስ ሊያሰወግድና የህዝባችንን የኑሮ ሁኔታ ሊያሻሽል አልቻለም። ይሁ ሁኔታና ቀስ በቀስ በጎሎባል ካፒታሊዝም በተፈጠረው የተዘበራረቀ ሁኔታና የተበላሸ ንቃተ-ህሊና የውጭው ዓለም ቀስ በቀስ ገብቶ እንዲፈተፍት አስቻለው።
ባለፉት 22 ዐመታት የተካሄደውን የክልልን ፖሊሲና ኢትዮጵያዊ ስሜትን መዳከም ዝም ብሎ ከሰማይ ዱብ ያሉ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያን እንደ ህብረ-ብሄርና እንደ አገር እንዳትኖር፣ ወይም ደግሞ በዘለዓለም የርስ በርስ ትርምስ ውስጥ እንድትኖር ውስጥ ለውስጥ በውጭ ኃይሎች ሲቀነባበርና ጊዜውን ጠብቆ የመጣ ነው። እንደሚታወቀው የምዕራቡ ዓለምና የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም በአፍሪካ ምድር የተጠናከረችና ህዝቦቿ በመፈቃቀር የሚኖሩባትን አገር አይፈልጉም። በህዝብ ቁጥር በፍጥነት እያደጉ የሚሄዱ እንደ ኢትዮጵያና ናይጄሪያ የመሳሰሉ አገሮች በጣም አደገኛ ስለሆኑ በውስጣዊ ጠላትና በውጭ በመወጠር መዳከም አለባቸው። በተለያዩ ዘዴዎች ህዝቡ እረፍት ማጣትና ኃይሉንና ዕውቀቱን ሰብስቦ አንድ ነፃና የጠነከረ አገር መገንባት የለበትም። በተለይም ከአብዮቱ መፈንዳት ጀምሮ የውስጥ ኃይሎችን መርዳትና ረብሻ እንዲፈጠር ማድረግ፣ በዚያውም መጠን ህዝባዊ መተማመንና መተሳሰር እንዳይኖር ማድረግ የምዕራቡ፣ በተለይም የአሜሪካን ኤምፔሪያሊዝም ዋናው የብጥበጣ ዘዴ ነው። ቀደም ብሎ ከተጠነሰሰልን ስትራቴጂና በአብዮቱ ወቅት ኢትዮጵያን በሁሉም አቅጣጫ ማዳከም ጋር ስናያይዘው ወያኔና ሻቢያ የአሜሪካን ፕሮጀክቶች መሆናቸውን መጠራጠር አይቻልም። በዚህ ዐይነቱ ኢትዮጵያን በብሄረሰብም ሆነ በሃይማኖት የርስ በርስ ትርምስ ውስጥ ለመክተት የተለያዩ ኢትዮጵያውያን ኃይሎችም ተሳትፈውበታል። የዛሬው የኢትዮጵያዊነት ስሜት መገርሰስ የወያኔና የሻቢያ ስራ ብቻ ሳይሆን በቀኝና በግራ ስም የሚንቀሳቀሱ ኢትዮጵያውያን ኃይሎችም  ሳያውቁም ሆነ አውቀው የወንጀሉ ተባባሪ ሆነዋል። ዛሬ ያለውም ችግር ስለኢትጵያዊነትና ስለ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ስናወራ ግራ የሚገባን ይህ ዐይነቱ ኢትዮጵያዊነት የፍልስፍናው መሰረት ምን እንደሆነ ስለማናውቅና ትንተናም ስለማይደረግ ነው።
አዚህ ላይ ይህንን በውጭ ኃይሎች የተጠነሰሰልንን ሴራ ተቃዋሚ ነኝ፣ ካለኔ በስተቀር ኢትጵያዊ የለም እያለ እዚህና እዚያ የሚሯሯጠው የቱን ያህል እንደገባው መረዳቱ ከባድ አይደለም።  ነገሩን በጥብቅ ለተከታተለ የተቃዋሚውም ሆነ ሌላው ምሁራዊ ኃይል ይህንን ነገር አለመገንዘቡ ብቻ ሳይሆን እንዲነሳበትም አይፈልግም። እንደሚታወቀው ለአንድ ችግር መንስኤው ብቻ ሳይሆን እንዲፋፋም የሚያደርጉትም ነገሮች በደንብ ካልተጠኑና መከላከያና ማጥፊያ ዘዴ ካልተፈለገ ለብሄረሰብ ችግር ቁልፍ መፍትሄ ማግኘት አይቻልም። ስለዚህም ስለብሄረሰብ ችግር መፍትሄ ለመፈለግ በምንጥርበት ጊዜ ችግሩን ሁለንታዊ በሆነ መልክ ማጥናትና በግልጽ መወያየት ለችግሩ መፍትሄ ለማግኘት መንገዱ የተቃና ይሆናል።  ችግሩን በተራ የብሄረሰቦችን መብት በማወቅ ይፈታል የሚለው አካሄድ ከህብረ-ብሄር ግንባታና ከጠንካራ ኢኮኖሚ ምስረታ ጋር ሊያያዝ በፍጹም አይችሉም። በመሰረቱ በአገራችን ምድር በዚህ አኳያ ያለው ችግር የብሄረሰብ ችግር ወይም መፍትሄ ያለማግኘት ሳይሆን፣ የአገራችን ኢኮኖሚ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ ተመስርቶ ሰፋ ያለ የውስጥ ገበያ ያለመገንባት ችግር ነው። ከዚህም ጋር ተያይዞ የባህላችንና የማህብራዊ ዕድገታችን ቆርቁዞ መቅረት ለብሄረሰብ ችግር መቆጥቆጫ ሊሆን ችሏል።
ከዚህ ስንነሳ ውስጥ ያለውን ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ባህላዊ፣ ማህበራዊና ህብረተሰብአዊ ድክመት በመጠቀም የዛሬው አገዛዝ  በአሜሪካን፣ በእንግሊዝና በአንዳንድ የምዕራብ አገሮች በመታገዝና በማናፈስ ኢትዮጵያዊ ብሄረ-ስሜት እንዳይዳብር ማድረግ ቻለ።። ኢትዮጵያና አማራ ተመሳሳይ ተደርገው በመወሰዳቸው ዘመቻው ሁሉ ኢትዮጵያን በሁሉም አቅጣጫ ማዳከም ሆነ። አገዛዙ ሁሉም ነገር መበወዝ አለበት በሚለው ፍልስፍና ከዚህ አልፎ በመሄድና በግፍ የሚፈስለትን ዕርዳታ በመጠቀም በሌሎች የአፍሪካ አገሮች ተወዳዳሪነት የማይገኝለትን የባህል ውድቀት ውስጥ ከተተን። የግብረ-ሰዶም መስፋፋትና፣ ሴቶች ወደ አረብ አገሮች እየተሸጡ እንዲሄዱ በመደረግና በመደፈር አርግዘው መምጣት ኢትዮጵያዊ ናሽናሊዝም እስከነ አካቴው አንዲጠፋ ለማድረግ የታቀደ ስትራቴጂ  ነው። ወደፊት ኢትዮጵያ የኢትዮጵያውያን አገር ሳትሆን የአረቦች አገር ትሆናለች ማለት ነው። ይህ ነው የረዥሙ ጊዜ ስትራቴጂና የጊዜው ቦምብ።
ስለሆነም በኛ ምሁራን ዘንድ ያለው ትልቁ ችግር ከገዢው መደብ ንቃተ-ህሊና ማነስና ታሪክን ካለማገናዘብ የተነሳ አገዛዙ በውጭ ኃይሎች ጋር በመተባበር የሚያደረገው አገርን ማፈራረስ ያለመረዳት ችግር ነው። በተለይም የተቃዋሚው ኃይልና በድህረ-ገጾች ላይ የሚጽፈው ምሁር ነኝ ባይ ስለ ህብረተሰብ ግንባታ፣ ስለማህበረሰብ፣ ስለ ባህል፣ ስለ ህብረ-ብሄር ምስረታና ጥንካሪ፣ ሁለንታዊ የሆነ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ የኢኮኖሚ ግንባታ አስፈላጊነት ስለማይታየው የዓለምን ፖለቲካ በየዋህነት መነጽር ነው የሚመለከታት። እጅግ የተወሳሰበውንና አደገኛ የሆነውን ዓለም የመመልከት ኃይሉ ደካማ ይመስላል። በዚህም ምክንያት የተነሳ የአገራችንን ችግር በራሳችን ኃይልና ዕውቀት ለመቅረፍና አገራችንን በጠንካራ መሰረት ላየ ለመገንባት የሚያበርክተው አስተዋፅዖ ይህንን ያህልም የሚያመረቃና አስተማማኝ አይደለም።
ከዶክተር ብርሃኑ የቃለ-መጠይቅ ስነሳና ስመረምር የአገራችንን የተወሳሰብ ችግር በጥልቀት ማየትና በግልጽ መነጋገር የሚያስፈልግ ይመስለኛል። የአገራችን የተወሳሰበ ችግር ብልቅና ጥልቅ በሚሉ እግርና እጅ በሌላቸው ፓርቲ ነን ባዮች የሚፈታ አይደለም። የአገራችንን የተወሳሰበ ችግር ለመረዳት፣ እነ ፕላቶ ከክርስቶስ ልደት በፊት በአራተኛው ክፍለ ዘመን በፊት እንዳደረጉት፣ እነዳንቴ በአስራ አራተኛው ክፍለ ዘመን እንዳስተማሩትና የሬናሳንስን በር እንደከፈቱ፣ እነ ሺለር በአስራስምንተኛው ክፍለ-ዘመን እንዳካሄዱት ሰፋ ያለ ምሁራዊና የጭንቅላት ተሃድሶ እንቅስቃሴ በማድረግ ብቻ ነው ሊፈታ የሚችለው። ለዚህ ደግሞ ክፍትና ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል። የራስንም ድክመት መገንዘብ ይጠይቃል
የፖለቲካ አመለካከትና  የፖለቲካ ችግር ጉዳይ !
       ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ስለፖለቲካ ችግር በሚያወራበት ጊዜ እየደጋገመ የተናገረው፣ ስለ ስልጣን ጥያቄ፣ ስለውክልናና ሰለመንግስት ጥያቄ ነው። እንደውነቱ ከሆነ እነዚህ በራሳቸው ሰፊ ትንተና የሚያስፈልጋቸው ናቸው። አጠር ባለ መልክ ለማቅረብ ልሞክር።
በመጀመሪያ ደረጃ የኢትዮጵያ ህዝብ ችግር የውክልና ችግር ወይም ይወከለኛል የሚለውን የማጣት ችግር አይደለም። የኢትዮጵያ ህዝብ ችግር እንደሌሎች የአፍሪካ አገሮችም ችግር የህብረተሰብ ህግ ችግርን የተረዳና፣ እስካሁን ድረስ ሲያስጨንቁኝ የከረሙትን ችግሮች፣ ድህነት፣ መራብ፣ ንጹህ ውሃ ማግኝት፣ ስነ ስርዓት ያለው ቤት፣ የህክምና ጉዳይና የዕውቀት ችግሮችን ደረጃ በደረጃ ሊፈታልኝ የሚችልና ችግሬን የተረዳ ኃይል አለ ወይ? እያለ ሌት ከቀን ይጠይቃል። የኢትዮጵያ ህዝብ ችግር ባለፉት አርባ አምስት ዐመታት በድህነትና በረሃብ ነው የምታወቀው፣ ስለዚህም ከዚህ ዐይነቱ ውርደት ለአንዴም ለመጨረሻም ጊዜ የሚያላቅቀኝን እትዮጵያዊ ኃይል ነው የምመኘው እያለ  ነው ሌት ከቀን የሚጸልየው። ስለዚህም ከጎኔ ሆኖ የሚያታሰተመረኝና ችግሬን የሚጋራ፣ እንዲሁም ከኔ በመማር አዲሲቱንና የተከበረች ኢትዮጵያን የሚገነባልኝን ኢትዮጵያዊ ኃይል ነው የምመኝው እያለ ነው ፈጣሪን የሚማፀነው።
ባለፉት 22 ዐመታት የሚደረገውን በተቃዋሚው ሰፈር ያለውን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ስንመለከት ሁሉም ይህንን ወይም ያንን የፖለቲካ መስመር እንደሚያራምዱ ነው ሲነግሩን የከረሙት። አንደኛው ሊበራል ዴሞክራት ነኝ፣ ሌላው ደግሞ ሶሻል ዴሞክራት ፓርቲ ነኝ በማለት በዚህ ዐይነቱ የፖለቲካ መስመር ለውጥ ለማምጣት እንደሚፈልጉ ነው የሚስብኩት። አሁን ደግሞ ማዕከለኛ የቀኝ መስመር(Centre Right) እናካሂዳለን የሚሉ ብቅ እንዳሉ ሰምተናል። እነዚህና ሌሎችም  ይህንን የመሳሰሉትን ስሞች ለምን እንዳንጠለጠሉ ግልጽ ባይሆንም፣ ሁሉም  በኢትዮጵያ ምድር የገበያን ኢኮኖሚና የሊበራል ዲሞክራሲ ዕውን እንደሚያደርጉ ነው የሚነግሩን። ይሁንና ግን በዚህ ዐይነቱ የፖለቲካ መስመር የተወሳሰበውን የኢኮኖሚ፣ የማሀበራዊ፣ የባህል፣ የህብረተሰብና የፖለቲካ ምስቅልቅልና ችግር እንዴት ደረጃ በደረጃ ሊፈቱ እንደሚችሉ ሲያብራሩ አይሰማም።
በጥብቅ እንደተከታተልኩት ከሆነ የአብዛኛዎቹ ፓርቲ ነን ባዮች ችግር፣ ይኸኛውን ወይም ያኛውን የፖለቲካ መስመር እንከተለለን ሲሉ፣ 1ኛ) የፖለቲካ መስመራቸውን በአንዳች ፍልስፍና ላይ አልመሰረቱም፣ 2ኛ) ስፋ ያለ የቲዎሪ ትንተና አልሰጡም፣ አይሰጡምም። 3ኛ) አብዛኛዎቹ ድርጅቶች ይህንን ወይም ያንን የፖለቲካ መስመር እንከተላለን ሲሉ፣ በመጀመሪያ ደረጃን በሶሻሊዝም ስም በአገራችን ምድር የተፈጸመውን አስከፊ ድርጊት እንደመቀጣጫ በመውሰድ ሲሆን፣ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ  ከሌሎች አገር ልምድ በመነሳት ነው ይህንን መስመር ልንመርጥ የተገደድነው ነው የሚሉን። ትልቁ የአገራችንም ሆነ የብዙ የሶስተኛው ዓለም አገሮች የፖለቲካ እንቅስቃሴ ችግር ከአገራቸው ተጨባጭ የማቴሪያል ሁኔታ፣ ከህዝቡ ንቃታ-ህሊና ደረጃና የሳይኮሎጂካል ሜክ አፕ ሁኔታ በመነሳት ሳይሆን በአቦ ሰጡኝ የምዕራቡን ዓለም ለማስደሰት ብለው የሚይዙት አቋም ነው። ይህ ዐይነቱ ተራ ሎጂክና ሳይንስና ቲዎሪን ያላካተተ ወይም በነሱ ላይ ያልተደገፈ የፖለቲካ መስመር የመጨረሻ መጨረሻ ለሌላ ውዝግብና ትርምስ ዳርጎን ነው የሚሄደው።
በመሆኑም የብዙዎችን ፓርቲዎች አካሄድ ስመለከትና ስመረምር እንዴት አድርገን ስልጣን እንይዛለን ከሚለው ስሌት በመነሳት እንጂ፣ በምን ፍልስፍናና ቲዎሪ ብንደገፍ አፍጦ አግጦ የሚታየውን ችግር አስወግደን የጠነከረችና የተከበረች ኢትዮጵያን እንገነባለን የሚለው ትልቁ የታሪክ ፕሮጀክት አይደለም የሚያሳስባቸው። የፖለቲካ ስልጣን ማነህ ባለሳምንት እንደሚባለው አነጋገር አንዱ ለሌላው የሚሰጠውና የሚያስረክበው ጉዳይ ሳይሆን ማንኛውም ለፖለቲካ ስልጣን እታገላለሁ የሚል ሁሉ የአንድን ትውልድ ዕድል ብቻ ሳይሆን እንዴት አድርጌ ታሪካዊ መሰረት በመጣል ለሚቀጥለው ትውልድ ጥሩና ቋሚ ነገር ማስተላለፍ እችላለሁ ብሎ በመነሳት ለታሪክ የሚዘጋጅበት መድረክ ነው።
በእኛም አገር ሆነ በብዙ የሶስተኛው ዓለም ያለው የፖለቲካ አደረጃጀትና የፅንሰ-ሃስብ ግንዛቤ ለብዙዎች ግልጽ የሆነ አይመሰለኝም። በመጀመሪያ ደረጃ ፓለቲካ አንድን አገር ጥበባዊ በሆነ መልክ ማስተዳደር ማለት ነው። በሁለተኛ ደረጃ፣ የፖለቲካ እንቅስቃሴና ለስልጣን የሚደረገ ትግል ከተራ የፖለቲካ አደረጃጀት የሚያልፍ ነው። ማለትም ለፖለቲካ ስልጣን ትግል ሲደረግ ተራው ህዝብም እያንዳንዱ ፓርቲ ለምን እንደሚታገልና እንዴትስ ቃል-ኪዳን የሚገባውን ተግባራዊ እንደሚያደርግ ማስረዳት አለበት። በሶስተኛ ደረጃ፣ የፖለቲካ ስልጣን ለጥቂት አዋቂ ነን ለሚሉ ፓርቲዎች የሚሰጥ ብቻ ሳይሆን ሰፊው ህዝብም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሊሳተፍበት የሚችልበት ሁኔታ መፈጠር አለበት። ለዚህ ደግሞ የግዴታ የህዝቡ ንቃተ-ህሊናና የመጠየቅና የመከራከር ችሎታ በየጊዜው ከፍ እንዲል አስፈላጊው እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው። በአራተኛ ደረጃ፣ ለስልጣን የሚደረግ የፖለቲካ እንቅስቃሴ በፓርቲዎች መሀከል ውዝግብ እንዲፈጠር የሚያደርግ ሳይሆን በርዕይ ላይ በመመስረት ቀና አመለካከት ያላቸውን ሁሉ በፖለቲካ ክንዋኔ ውስጥ ሊያሳትፍ የሚችል መሆን አለበት።
ከዚህ ስንነሳ በመጀመሪያ ደረጃ እንዴት ስልጣን መያዝ ይቻላል ብሎ ማውጠንጠን ሳይሆን፣ እንዴት አድርጎ የተሰበጣጠረውን ኃይል በአንድ ለአገር ግንባታ በሚያገለግል ፍልስፍና ዙሪያ ማሰባሰብ ይቻላል በሚለው ላይ ነው መወያየት ያለብን። ይህ ማለት ግን አመራር አያስፈልግም ማለት አይደለም። ጥያቄው የኢትዮጵያ የተወሳሰበ ችግር በውክልና ዲሞክራሲ ሊፈታ እንደማይችል ለማሳየትና፣ ትግላችንም ከዚህ ርቆ በመሄድ ህዝቡንም ሊያሳትፍና ለውይይት ጋብዞ የአገሪቱን ችግር በጋር ለመቅረፍ የሚቻልበትን ዘዴ ለመተለም ነው። ከብዙ የሶስተኛው ዓለም አገሮች ልምድ እንደምናየው በየአራት ዐመቱ በሚካሄድ ምርጫ የህዝብ ችግር ሲፈታና መረጋጋት ሲኖር አናይም። በብዙ አገሮች ድህነት፣ በስልጣን ላይ ባሉ ኃይሎች መጎሳቆልና መብትን መገፈፍ፣ ብሄራዊ-ነፃነትን ማጣትና የውጭ ኃይሎች ተገዢ መሆን፣ ባጭሩ ውርደትን ነው የምናየው። ስለዚህም ዶክተር ብርሃኑ በትክክል እንዳስቀመጠው ምን ዐይነት ህብረተሰብ ብንመሰርት ነው እኩላዊነትን ማስፈን የምንችለው? በሚለው ላይ መወያየት ያለብን ይመስለኛል።
ይህ ብቻ ሳይሆን የኢትዮያም ሆነ የብዙ አፍሪካ አገሮች ዋናው ችግር በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ብሄራዊ ሀብት ለመፍጠር ያለመቻል ብቻ ሳይሆን፣ አብዛኛዎቹ መንግስታትና አገዛዞች አንድ ስርዓት ያለው ህብረተሰብ በምን መልክና እንዴት ጥበባዊ በሆነ መልክ እንደሚዋቀርና እንደሚተሳሰር አለመረዳትና ችሎታ ማነስ ነው። አብዛኛዎቹ አገዛዞች የየአገሮቻቸውን ሀብት ዝም ብለው የሚዘርፉና የሚያዘርፉ፣ ለዚህም መብት የተሰጣቸው የሚመስላቸው፣ ወይም ደግሞ የየአገሮቻቸውን ሀብት የግል ሀብታቸው አድርገው የሚቆጥሩ ናቸው። ስለሆነም ህዝባዊ ሀብት የመፍጠርና ታሪክን የመስራት አቅማቸው በጣም የተዳከመ ነው። ስለዚህም በአገራችንም ሆነ በአብዛኛዎቹ አፍሪካ አገሮች ያለው ማህበራዊና የባህል ቀውስ ከዚህ የሃሳብ ግንዛቤና የዕውቀት ጉድለት የተነሳ ነው። ህዝባዊ ሀብት መፍጠር ካልተቻለ ደግሞ የሚከፋፈል ሀብት ሊኖር አይችልም፤ እኩልነትም አይኖርምም። ከዚህ ስንነሳ  መካሄድ ያለበት ትግልና፣ በመሀከላችንም መኖር የሚገባው ውይይትና ክርክር በምን ዐይነት ዘዴ ነው ፈጣን የሆነ ህዝባችንን ከድህነት የሚያላቅቅ የብሄራዊ ሀብት መፍጠሪያ ዘዴ መፈለግ የሚቻለው? እንዴትስ ብናደርግ ነው ከላይ ወደ ታች ሳይሆን ከታች ወደ ላይ የሚገነባ፣ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ሊያካትት የሚችል የኢኮኖሚ ግንባታ ማካሄድ የሚቻለው? በሚለው ላይ ማትኮሩ ለችግራችን መፍትሄ እንድናገኝለት ይረዳናል። ይህ ብቻ ሳይሆን፣ ከአውሮፓም ሆነ ከራሺያና ከቻይና ልምድ እንደምንማራው ዲሲፕሊን በሌለበት፣ የስራ ፍላጎት በመነመነበት፣ መናናቅ በተስፋፋበት፣ ማላገጥና ማሾፍ እንደሙያ በሚያዝብትና፣ በተጨማሪም ደግሞ የተማረው ኃይል ከአገሩ ይልቅ ለውጭ ኃይል የሚሰራና የውጭን ኃይል ትዕዛዝ የሚቀበል ከሆነ ስለ ዕድገትና ድህነትን ስለመቅረፍ ጉዳይ ማውራት በፍጹም አይቻልም።
ስለሆነም በፓርቲዎችም ሆነ በድርጅቶች ዘንድና መሀከል መደረግ ያለበት ትግል እኔ ነኝ የኢትዮጵያን ህዝብ የምወክለው እያሉ ፕሮግራም እየጻፍ ወደ ኤምባሲዎች መሮጥ ሳይሆን፣ ሀቀኛ ነኝ የሚል ሁሉ ፕሮግራም ከመጻፉ በፊት በሃሳብ ዙሪያ ክርክርና ውይይት መክፈት መቻል አለበት። የኢትዮጵያን ሁኔታ በትክክል ለሚያነብ ሰው የአገራችን ችግር በአንድ ፓርቲ ሊፈታና በትከሻው ላይ ሊወድቅ የሚችል አይደለም። የአገራችን ሁኔታ የሁሉንም ኃይል ተሳትፎ ይጠይቃል።  ስለዚህም የፓርቲዎች ቁጥር ወደ ሁለትና ወደ ሶስት ብቻ መቀነስ አለበት። ሌላው ወደ ስራ መሰማራት አለበት። ከዚህ በተረፈ የብሄረ-ሰቦችን ሁኔታ ለተመለከተ፣ ችግሩ የኢትዮጵያ ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ፣ ጉራጌ፣ ወላይታ፣ ኩሎ ኮንታ፣ ወዘተ. ችግር ሳይሆን፣ ከዚህም ከዚያም የተውጣጣው ኤሊት ነኝ ባይ የፈጠረው ችግር ነው። ትላንትና አማራ፣ ዛሬ ደግሞ ትግሬ፣ ነገ ደግሞ እኔ መግዛት አለብኝ በማለት የሚነዛው ከሳይንስና ከፍልስፍና  ውጭ የሆነ አጉል አካሄድ ነው። ከዚህም ሆነ ከዚያ ተውጣጣ፣ ይህም ሆነ ያኛው ኃይል ስልጣን ይዞ መሰረታዊ የኢትዮጵያ ህዝብ ችግር እስካልተፈታ ድረስ የብሄረሰቦች ችግር መልስ ሊያገኝ አይችልም። የማንኛውም ህዝብ ጥያቄ  በመጀመሪያ ደረጃ የመብላትና የመጠጣት ጉዳይ ነው። ከዚያ በኋላ ነው ስለሰፊው የመብት ጥያቄ መወያየት የሚቻለው። ይህም ቢሆን ከግለሰበአዊና ከህብረተሰብአዊ ነፃነት ውጭ ሊታይ የሚችል መሆን የለበትም። ብሄረሰቦችን በክልል እየከለሉ ነፃ ወጥተሃል፣ ሌላው አይድረስብህ ማለት ደንቁረህ ቅር ማለት ነው። እንደዚህ ዐይነቱ  በብሄረሰብ ዙሪያ የሚካሄድ ትግል የተፈጥሮንንም ሆነ የህብረተስብ ሳይንስን ህግ ይፃረራል። በተጨማሪም የብሄረሰቦች ችግር አለ፣ ኢትዮጵያ የብሄረሰቦች እስር ቤት ነች እያሉ ማራባት ታዳጊው ወጣት በማያስፈልግ አስተሳሰብ ጭንቅላቱ በመጠመድ ለዕውቀትና በጋር በመነሳት አገር አንዳይገነባ መንገዱን እንደመዝጋት ይቆጠራል። ከዚህም ባሻገር  እያንዳንዱ ብሄረሰብ ባህሉ ቢጠበቅለት፣ በቋንቋው ቢናገር፣ ሌሎችም ነገሮች ተግባራዊ ቢሆኑለት፣ እነዚህ ሁሉ ነገሮች የኑሮውን ሁኔታ እስካላሻሻሉለት ድረስ፣ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ባለቤት እስካላደረጉትና፣  ሰፋ ባለ የስራ-ክፍፍል ታግዞ ሰፋ ያለና የተወሳሰበ ህብረተሰብ እስካልመሰረተ ድረስ የአንድ ብሄረሰብ ባህል ተጠበቀ አልተጠበቀ ትርጉም የለውም።  በብሄረሰቦች ዙሪያ የሚደረገው ትግልና የብሄረሰብ ርዕይ የመጨረሻ መጨረሻ የየብሄረሶቦችን ኤሊቶች ጥቅም የሚያስጠብቅና የሚጨፍሩበት እንጂ ሰፊውን ህዝብ የሚጠቅም አይደለም። ፕላቶ ከሁለት ሺህ አራት መቶ ዐመት በፊት እንዳለው በጎሳ አካባቢ መደራጀትና የጎሳ ሶሊዳሪቲ ማሳየት አንድን ህዝብ ለሌላ የርስ በርስ ግጭት መጋበዝ ነው።
በተረፈ ቃለ ምልልሱ ለውይይት የሚያመችና ሁላችንንም የሚጋብዝ ነው። ሁሉም በሙያው የአቅሙን ከወረወረና ከተከራከርን መፍትሄ ማግኘት እንችላለን። በምሁሩ ዘንድ መፈራራት መኖር የለበትም። እያንዳንዳችን በምናምነው ርዕይ ወይም ፍልስፍና፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ችግር በዚህ መንገድ ነው ሊፈታ የሚችለው ብለን ማሳየት መቻል አለብን። ሁሉም በአጠቃላይ ዙሪያ ከመሽከርከር ይልቅ በጥልቀትና በርዕይ ደረጃ የሚያምንበትን ወደ ውጭ አውጥቶ ለማነጋገር ቢሞክር ለችግራችን የተሻለ መፍትሄ ማግኘት እንችላለን። መልካም ንባብ !!
ፈቃዱ በቀለ

የሕወሓት አትኩሮት ስልጣን በማስረዘም ላይ ነው እንጂ በዜጎች ደህንነት ላይ አይደለም ::

January4/2014

ሁላችንም በያለንበት የሕወሓትን ስውር እጆች ልናጋልጥ ይገባል::
ዜጎች በየትኛውን የውጭም ይሁን የአገር ውስጥ በባለስልጣናት የሚደርስባቸው መከራና ግፍ መንግስት የለም ወይ ያሰኛል:: እኛ እየተናገርን ያለነው ስለ ፖለቲከ ተቃዋሚዎች ሳይሆን ስለዜጎች ነው:: ስለፖለቲካ ተቃዋሚዎች ራሳቸው እየደሰኮሩት ነው ዜጎች ግን የመኖር የመስራት የማምለክ መብታቸው ሊከበር ይገባል:: ህግ ሲከበር ስልጣን ይረዝማል:: ህግ ሲከበር ዜጎች ሰላም ያገኛሉ:: ኢኮኖሚው ቢዋዥቅ እንኳን ሰላም ካለ ብልሃቱ አይጠፋም::

ሕወሃት መራሹ ኢህኣዴግ ስልጣኑን ለማስረዘም የሚጠቀምበት ስልት የተበላበት እና ያረጀ መሆኑ እሙን ነው::ዜጎች በሃገራቸው መኖር ካልቻሉ ለመኖር ሲሉ የሚፈጥሩት ፍትጊያ ባለስልጣናቱን ከጨዋታ ውጪ አድርጎ በህዝብ እንዲበሉ ያደርጋቸዋል::ዜጎች በገዛ አገራቸው ዛሬም እየተፈናቀሉ ነው::በአለም ላይ ታይቶ የማይታወቅ የፌዴራሊዝም ከፋፍለህ ግዛው ፖሊሲ በዚህ በሰለጠነ ዘመን ተቀባይነት የሌለው እና ለራስ ጦስ የሚሆን እንደሆነ ወያኔዎች ሊረዱት ይገባል:: እንደጫካ የተለመደው ማፊያዊ መሹለኩለክ የትም የማያደርስ አደጋ የሚያስከትል መሆኑን ሊታወቅ ይገባል::
ሕወሓት ስሟንም ሙዷንም ትቀይርልን::በቃ ነቅተናል!!! ከሕወሓት ውጭ ማንም ወንጀለኛ የለም::
ትላንት ዛሬም ነገም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በህገወጥ መንገድ ቢሞት ቢገደል ቢታነቅ ቢታፈን ቢታሰር እና ከነዚህ ነገሮች ጋር በተያያዘ ከሕወሃት ውጭ ማንም ይህን የሚፈጽም የለም :: ይህንን ደሞ እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠንቅቆ አውቆታል:: በቃ ነቅተናል!! ከህወሃት ውጭ ማንም ወንጀለኛ የለም::

በአለማቀፍ ደረጃ ከአሸባሪ ድርጅቶች እኩል ስሟ ሰፍሮ የሚገኘው ሕወሓት በኢትዮጵያ እና በዜጎቿ ላይ በግልጽ እና በድብቅ የተለያዩ ማፊያዊ እርምጃዎችን እየወሰደች ነው::ሕወሓት በተለያዩ የደህንነት መዋቅሯ አማካኝነት ራሷ ከፈጠረቻቸው ከፍተኛ ባለስልጣኖች ጀምሮ እስከ ተራ ዜጎች ድረስ በስውር እጆቿ በልታቸዋለች:: በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ከተሞች በተለያየ ጊዜ ቦምቦችን በማፈንዳት በተቃዋሚዎች ላይ ሰበብ ለመፍጠር ሞክራለች:: በእነዚህ ፍንዳታዎች ያለቁትን ዜጎች አስቧቸው:: ........ኦነግ ሻእቢያ አልሸባብ ቅንጅት አክራሪ ...ምናምን ቢባል ማንም የሚያምን የለም ::አሁንም ያልተነቃ የሚመስላቸው እነዚህ ሰው በላዎች የጫካ ማፊያዊ ድርጊታቸውን እየፈጸሙ ይገኛሉ..በቃ ነቅተናል!!! ከሕወሓት ውጭ ማንም ወንጀለኛ የለም::

ስለዚህ በቃ ነቅተናል ልንል ይገባል:: ሁላችንም በያለንበት የሕወሓትን ስውር እጆች ልናጋልጥ ይገባል:: ሕወሓትን የምንመክረው ግን አመድ ከመሆንሽ በፊት ስምሽን እና ሙድሽን ቀይሪልን ነው::
በቃ ነቅተናል!!! ከሕወሓት ውጭ ማንም ወንጀለኛ የለም::


ሚኒሊክ ሳልሳዊ


Saturday, January 4, 2014

የማይመስል ነገር ለሚስትህ አትንገር! ኢቲቪ ስለ ኢሳት

January 4, 2014
ቢታኒያ አለማየሁ፣ አዲስ አበባ

ዶክመንታሪ ብሎ ዝም! አስቡት እስኪ ኢሃዲግን በሚያክል አፋኝ መንግስት በኢቲቪ ኢሳት ሲብጠለጠል፣’ኢሳት ማለት የኢትዮጵያ ህይዝብ እውነተኛ የመረጃ ወፍጮ ነው!’


Ethiopian Satellite Television (ESAT)

ለምን ግን በዚህ ሰአት ስለ ኢሳት ዶክመንታሪ መስራት አስፈለገ?
-ኢሳት ከተመሰረተ አንስቶ እስካሁን ድረስ በእውነተኛ መረጃ ምንጭነት በመላው የኢትዮጵያ አንጀት ውስጥ ተደላድሎ መቀመጡን ስልሚያውቁ!
-ይከስማል ይጠፋል አቅሙ ይዳከማል ሲሉት እንደ ወይን ጠጅ ከለት እለት እየበሰለና እየጎመራ መምጣቱን ስላዩ!
-በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ተምልካቾች ለኢሳት በመደወል በሚሰጡት አስተያየት ህዝቡ በሚገባ እየተከታተለው መሆኑን ስላረጋገጡ!
-ከዚህ ቀደም ከሰባት ጊዜ በላይ ጃም በማደርግ እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ኢሳት ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርገውን ስርጭት ቢያቛርጡም ኢሳት ግን የተለያዩ የሳተላይት አማራጮችን በመጠቀም ከአንድ አመት በላይ(እስካሁን) ያለ ምንም ችግር ወደ ኢትዮጵያ ማሰራጨ ስለቻለና አሁን ካለው የኢኮኖሚ ሁኔታ አንጻር ጃም ማድረግ ከፍተኛ ወጪ ስለሚጠይቅ!
-ህዝብን አደንቁሮ በኢቲቪ ፕሮፓጋንዳ ብቻ የህዝብን አምሮ ለማደደብ በሚደርገው ጥረት ኢሳት ነጻ ሃሳብ በማነሸራሸር እንቅፋት ስለሆነ!
ባጠቃላይ ኢሳት ለህዝብ እውነትን በመግለጽ ለስረአቱ የእግር እሳት መሆኑ ስለታመነበት:- የኢሳትን ይዘት ተንትኖ እና እውነቱ ይህ ሆኖ ሳለ ኢሳት ግን እንዲህ ይላል በሚል አመክኖዋዊ አስተሳሰብ ከመሞገት ይልቅ፣ ግንቦት ሰባት አሸባሪነው ኢሳት ደግሞ የግንቦት ሰባት ነው ስለዚህ ኢሳት አሸባሪ ነው ብለው ከደመደሙ በኋላ ህዝቡ አሳትን መከታተል እንደ ሽብርትኛነት አድርጎ ቆጥሮት መከታተሉን እንዲያቆም ለማግባባት ቀጥሎም ለማስገደድ ያመች ዘንድ የተሰራ ድራማ ነው! የዘፈን ዳር ዳሩ እስክሳ ነው ትል ነበር አያቴ! የሚገርመው ግን አቶ ሃይለማሪያም እንዳሉት “ግንቦት ሰባት በቅዠትላይ የተመሰረተ ድርጅት” ከሆነ ይህን ያክል ተከታታይ ድራማዎች በመስራት ምን አደከማቸው? በራሱ ጊዜ ከእንቅሉ ይባንንላቸው የለም እንዴ?
እናንት አሸባሪ ኢሳቶች ሆይ ህዝብን እልል እያስባላችሁ አንባገነኖችን እያሸበራችሁ ነውና በርቱ! በርቱ! በርቱ!
ቢታኒያ አለማየሁ

አንድነት 6 5% በወጣቶች የተሞላዉ የአንድነት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ (ካቢኔ)

Januray4/2014
በአንድነት ፓርቲ ምተዳደሪያ ደንብ መሰረት የድርጅቱን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ(ወይንም ካቢኔ) የሚመርጡት የድርጅቱ ሊቀመንበር ናቸው። ሊቀመነንበሩ በጠቅላላ ጉባኤ የሚመረጡ ሲሆን፣ የካቢኔ አባላትን ደግሞ ብሄራዊ ምክር ቤቱ  ያጸድቃል። የብሄራዊ ምክር ቤቱ እሽታ ያላገኘ የካቢኔ አባል ተቀባይነት አይኖረዉም።
Andinet Party Leadership
በዚህ መሰረት አዲሱ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር፣ ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራዉ፣  አሥራ ሁለት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን መርጠዋል። «የካቢኔ አባላቱን ከመምረጤ በፊት፣ አባላቱ አስተያየትና ጥቆማ እንዲሰጡኝ በሩን ክፍት በማድረግ የብዙዎችን አስተያየት ተቀብያለሁ፡፡ ሌላው መስፈርቱ የትምህርት ዝግጅት፣የፖለቲካ ልምድና ተባብሮ የመስራት ባህል ለመመልከት ሞክሪያለሁ፡፡በዚሁ መሰረትም የሚከተሉትን ሰዎች የካቢኔ አባላት እንዲሆኑ ወስኛለሁ» ነበር ያሉት እንጂነር ግዛቸው ሽፈራዉ።  ከካቢኔው አባላት መካከል ከ65 በመቶ በላይ በወጣቶች የተገነባ ነው፡፡ስድስት የማስተርስ አራት ባችለር ሁለት ዲፕሎማ ያላቸው መሆናቸውን ፕሬዘዳንቱ ገልጸዋል፡፡
1) አቶ ተክሌ በቀለ ——- ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዘዳንት
2) አቶ በላይ ፈቃዱ ——– ምክትል ፕሬዘዳንት
3) አቶ ስዩም መንገሻ ——– ዋና ጸሀፊ
4) አቶ ዳንኤል ተፈራ ——– የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ
5)አቶ ሃብታሙ አያሌው ——- የህዝብ ግኑኝነት ሀላፊ
6)አቶ ዘለቀ ረዲ ——— የውጪ ጉዳይ ሀላፊ
7) አቶ አስቻለው ከተማ ——- የፋይናንስ ጉዳይ ሃላፊ
8)አቶ ሰለሞን ስዮም ——– የፖለቲካ ጉዳይ ሃላፊ
9) አቶ ዳዊት አስራደ ——– የኢኮኖሚ ጉዳይ ሃላፊ
10)አቶ አለነ ማህጸንቱ ——- የማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ
11) ወ/ሮ የትናየት ቱጂ ——- የህግና ሰብአዊ መብት ጉዳይ ሃላፊ
12) አቶ ትእግስቱ አወሉ ——- ( የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሃላፊ በመሆናቸው በቀጥታ የካቢኔ አባል ሆነዋል)
አቶ ተክሌ በቀለ ድርጅቱን ለመመራት ከኢንጂነር ግዛቸው ጋር ሲፎካከሩ ጠንካራ የአንድነት አባል ሲሆኑ፣ አቶ በላይ ፈቃዱ ደግሞ የሚሊየነም ድምጽቾ ለነጻነት ግብረ ኃይል እንዲሁም የፍኖት ጋዜጣ ኤዲቶሪአይል ቦርድ ሲመሩ የነበሩ ጠንካራ የደርጅቱ አባል ናቸው።
አቶ ሃብታሙ አያሌው በቅርቡ በኢቲቪ በጸረ-ሽብርተኝነት ሕጉ ዙሪያ በተደረገዉ ክርክር የአንድነት ፓርቲ ወክለው የቀረቡ ወጣት የአንድነት አባል ናቸው። የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበሩት አቶ አቶ ዳንኤል ተፈራ፣ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ ሆነዋል።

ኢቴቪ በዶክመንተሪው የዘነጋቸው እውነታዎች

January 4/2014

ዳዊት ሰለሞን

Ethiopian TV logo - ETV Ethiopiaግንቦት 7፣ኦብነግ፣ኦነግ፣አልሸባብና አልቃይዳ በፓርላማ ሽብርተኛ ተብለው ከተፈረጁ አመታት ተቆጥረዋል፡፡ዛሬ ዶክመንተሪ ሰርቶ እነዚህ ድርጅቶች ሽብርተኛ ለምን እንደተባሉ ማብራሪያ መስጠት የጊዜ ጥያቄ ማስነሳቱ አይቀርም፡፡ነው ሳናውቀው ሽብርተኛ አይደሉም የሚል ጥያቄ ተነስቷል?

እርግጥ ነው ኢቴቪ ፓርቲዎቹን በጸረ ሽብርተኝነት አዋጁ ዙሪያ ሲያከራክር ፓርላማው ከስልጣኑ በመውጣት ድርጅቶችን፣ቡድኖችንና ግለሰቦችን ‹‹ሽብርተኛ ››በማለት መፈረጅ እንደማይገባው የአንድነቱ ተወካይ አቶ ሃብታሙ አያሌው ሞግተው ነበር፡፡የኢህአዴጉ ሽመልስ ከማል ውሳኔው ‹‹ፖለቲካዊ››ነው በማለት እቅጩን ተናግረው ነበር፡፡

በዛሬው ዶክመንተሪ ያየሁት አዲስ ነገር ፓርላማው የተለያዮ ፓርቲዎች ተወካዮች ስብስብ ስለመሆኑ መነገሩ ነው፡፡የኢቴቪ ካሜራ ፓርላማው በተለያዮ ፓርቲዎች ተወካዮች የተሞላ መሆኑን ለማሳየት የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉን እያቀረበና እያራቀ አሳይቶናል፡፡ግርማ ሲቀርቡና ሲርቁ ስንት ሆነው እንደሚታዮ የሚያውቀው የካሜራው ባለሞያ ብቻ ነው፡፡

መንግስት እየተከተለው የሚገኘው መንገድ በየትኛውም መመዘኛ ተገቢ ወይም ስልጡን አይመስለኝም፡፡ብረት ያነሱ ወገኖችን ሽብርተኛ በማለት ሰላማዊ አስተዳደር መገንባት አይቻልም፡፡ደርግ ጫካ የገቡትን የዛሬዎቹን የምኒሊክ ቤተ መንግስት ተቆጣጣሪዎች‹‹ሽብርተኛ፣ገንጣይ፣አስገንጣይ ወንበዴ››በማለት መፈረጁ መዘንጋት የለበትም፡፡ህወሃት ከደርግ በተጨማሪ በአሜሪካ መንግስት ‹‹ሽብርተኛ››ተብለው ከተፈረጁ ቡድኖች አንዱም መደረጉን መርሳት ተገቢ አይመስለኝም፡፡

መንግስት ሆደ ሰፊ በመሆን ሁሉም ሃይሎች በሰላማዊ መንገድ ልዮነቶቻቸውን በመፍታት የተሻለች ኢትዮጵያን እንዲፈጥሩ በሮቹን መክፈት ይጠበቅበታል፡፡በአገር ውስጥ የሚገኙ ድርጅቶችን እንደ ጠላት መመልከቱንና ብቅ ሲሉ በሐሰት ክስ አንገታቸውን እያነቀ ወህኒ መወርወሩን በማቆም የፖለቲካ ምህዳሩን ማስፋት ይኖርበታል፡፡

በእኔ እምነት ኢሳትን የሽብርተኛ ወፍጮ በማድረግና በማለት ተአማኒነት እንዳያገኝ ማድረግ በዚህ ዘመን የሚቻል አይመስለኝም፡፡ለዚህ ፍቱን መድሃኒት ኢህአዴግ የፕሮፓጋንዳ ማሽኑ ያደረገውን ኢሬቴድን ሁሉንም ድምጾች እንዲያስተናግድ መፍቀድ ነው፡፡90 ሚልዮን ህዝብን አንድ የግል (ነጻ)የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ማሳጣት በሰው መረጃ የማግኘት መብት ላይ መፍረድ ነው፡፡የታፈነ ህዝብ አማራጭ ድምጽ ለመስማት መፈለጉ አንቴና ዘርግቶና ሳህን ገዝቶ መዋተቱ አይቀሬ ነው፡፡እናንተ በረሃ እያላችሁ ቪኦኤንና ዶቼቬሌን መስማት ያስቀጣ ነበር፡፡አሁን በትረ መንግስቱን ስትጨብጡ እኛ ካልነው ውጪ ማለት መጀመራችሁ የደርግ ተጋቦሽ ከማለት ውጪ ምን ሊባል ይችላል?

ዶክመንተሪው ኢሳትን እየተጠቀሙ የሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን ለማስፈራራት ነው፡፡መንገዱ ይህ አይመስለኝም፡፡ኢቴቪ በአገሪቱ በሰላማዊ መንገድ እየታገሉ የሚገኙ ፓርቲዎችን እንደ ኢህአዴግ በእኩልነት የሚያስተናግድበትን ሁኔታ ፍጠሩ ፡፡ይህ በሌለበት ኢቴቪን ለብቻችሁ በተቆጣጠራችሁበት፣ኤፍኤሞችን ለሙዚቃ፣ለስፖርትና ለአልባሌ ነገሮች እንዲውሉ ባደረጋችሁበት አገር አማራጭ ተደርጎ የሚታይን ሚዲያ መጠቀም ሽብርተኝነት ነው ማለት ወንዝ አያሻግራችሁም፡፡

አይ ስብሐት ነጋ! (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

January 4, 2014
                                        ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

በቅርቡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከጋዜጠኛነት ተማሪዎች ጋር ባደረገው ውይይት ላይ ሁለት ሰዎች ጽፈው አይቻለሁ፤ ዶር. በድሉ ዋቅጅራ በ
ፋክት ላይ፣ ናስ በላይ አበበ በኢትዮ-ምኅዳር ላይ፤ ሁለቱም ሰዎች አልወደዱለትም ማለት ያንሳል፤ የሚወዱለትና የሚያጨበጭቡለት መኖራቸውም ሳይታለም የተፈታ ነው፤ ነገር ግን ስብሐት ነጋም ሆነ ደጋፊዎቹ አደባባይ ወጥተው ለመከራከር አይችሉም፤ ናስ በላይ አበበ እንደሚነግረን ‹‹አቶ ስብሐት ነጋ የውጭ ሰው እንዳይገባ ከተማሪዎቹ ጋር ተደራድረው ነበር የመጡት፤ ስለሆነም ነበር ከፍተኛ ጥበቃ አልፈን የገባነው፤›› ብቻውን ተናግሮ በጭብጨባ የሚሸኝበት መድረክ በመፈለጉ በከባድ ጥያቄም ቢሆን የሚያጣድፉት ሰዎች እንዳይኖሩ ማረጋገጡ በተማሪዎቹም ቢሆን ውሎ አድሮ ትዝብት ላይ ይጥለዋል።በኢትዮጵያ ውስጥ ሥልጣን ሳይኖረው ባለሙሉ ሥልጣን፣ እውቀት ሳይኖረው ባለሙሉ እውቀት የሆነ ሰው ስብሐት ነጋ ብቻ ነው፤ እንዲያውም ከዚያም አልፎ ራሱን የቻለ ሉዓላዊ ነጻነት ያለው ግለሰብ ነው ለማለት የሚቻል ይመስለኛል፤ በዚህ ግለሰብ ላይ የማደንቃቸው ሁለት ነገሮች ናቸው፤ በሉዓላዊነቱ የተጎናጸፈውን ሥልጣን ሙሉ በሙሉ ይጠቀምበታል፤ ይቆጣኛል ወይም ይቀጣኛል ብሎ የሚፈራው የለም፤ ስብሐት ነጋ የሚፈራው ምንም ነገር የለም፤ ሁለተኛ በሉዓላዊነቱ ያለውን ሙሉ ነጻነት በሙሉ ልብ ይጠቀምበታል፤ ናስ በላይ ከበደ እንዳለው ‹‹የቅብጠት መዘላበድ›› ሊሆን ይችላል፤ ስብሐት ነጋ የተናገረው ነገር ትክክል ይሁን አይሁን ጉዳዩ አይደለም፤ ዋናው ነገር መናገሩ ነው።
ዶር. በድሉ ዋቅጂራ ስለስብሐት ነጋ ከኢትዮጵያዊነት መውደቅ በሚል በጻፈው ላይ ዶር. ዳኛቸውን እንደሚከተለው ይጠቅሳል፤ ‹‹ከኢትዮጵያዊነት መውደቅ ማለት፤ በቃ በአጭሩ (ኢትዮጵያዊ ሆኖ)ኢትዮጵያዊ አለመሆን ነው፤›› በቅንፍ ውስጥ ያለው የኔ ነው፤ ልክ ነው፤ አንድ ግለሰብ በማናቸውም ምክንያት ከኢትዮጵያዊነት ቢወድቅ ኢትዮጵያዊነቱ የከሸፈ ነው ለማለት ይቻላል፤ ነገር ግን ከኢትዮጵያዊነት መውደቅንና ኢትዮጵያዊነትን መጣልን ለይተን ማየት ያስፈልጋል፤ አንድ ሰው በማናቸውም ምክንያት ከፍተኛውን የኢትዮጰያዊነት ባሕርይና ግዴታ መሸከም አቅቶት ቢወድቅ ለዚያ ሰው ኢትዮጵያዊነቱ ከሸፈ፤ ለስብሐት ነጋና ለጓደኞቹ ከከሸፈባቸው የቆየ ይመስለኛል፤ ከራሱ አልፎ የሌሎችን ኢትዮጵያዊነት ለማክሸፍ የሚሞክር ደሞ ከመክሸፍ አልፎአል፤ ከኢትዮጵያዊነት መውደቅ ማለት የከሸፈ ኢትዮጵያዊነት ነው ማለት ነው።
TPLF power broker, Sibehat Negaስብሐት ነጋ ዋና ዓላማው በሙሉ ነጻነት የመጣለትን እንደመጣለት መናገር ነው፤ ምሳሌዎችን እንጥቀስ፤– ሀ) ‹‹ከኢትዮጵያ ሕዝብ በላይ የኤርትራ ሕዝብ ኢትዮጵያዊነት አለው፤›› ስብሐት ነጋ ስለኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ስለኤርትራ ሕዝብ፣ ስለኢትዮጵያዊነት ያለው እውቀት የሚባል ነገር እንዲህ ያለው መዘባረቅ ነው፤ ስብሐት ነጋ ጨረቃ ከጸሐይ የበለጠ ትሞቃለች ቢልም አይደንቀኝም፤ አልከራከረውም፤ ስብሐት ነጋም ብቻውን መናገር እንጂ መከራከር አይፈልግም፤ ለ) ‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ ከኤርትራ ሕዝብ የበለጠ የኤርትራን መሬት ይፈልጋል፤›› እንደምሳሌ ያነሣው አሰብን ነው፤ ባድመን አላነሣም!  እሱና ጓደኞቹ የኢትዮጵያን ወጣቶች በከሸፈ ጦርነት ውስጥ የማገዱት ባድመ ለሚባል መንደር ነው እንጂ አሰብ ለሚባል ወደብ አልነበረም፤ በዚያን ጊዜ ጦርነቱን በመቃወም ድምጼን ያሰማሁት ኢትዮጵያዊ ወይም ኤርትራዊ ሆኜ አልነበረም፤ ሰው ሆኜ ነው፤ ዛሬ ስብሐት ነጋ ሲዘላብድ ኢትዮጵያዊነት የማይታይበትን ያህል ኤርትራዊነትም አይታይበትም፤ በዚህም ጉዳይ ላይ መከራከር አይፈልግም፤ ሐ) ‹‹ለማንኛውም ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ መከልከላቸው የማውቀው ብዙ ነገር የለኝም፤ ይከልከሉም አልልም፤ አይከልከሉም አልልም፤ መብታቸው ነው፤›› ይህ መዘላበድ ካልሆነ ምንድን ነው? ምን ቁም-ነገር ይዞ ነው ይህንን የተናገረው? የገለባ ክምር ውስጥ አንድ ፍሬ መፈለግ ይቀላል።
አንድ ሌላ የስብሐት ነጋ ዘዴ (ዘዴ ካልነው!) ጉዳዩን በሚገባ ሳያጣራ እንደመጣለት ይናገርና ‹‹አላውቅም›› ይላል! የማያውቀውን መዘባረቅ ግን ይችላል፤ ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹የምን ፓርቲ እንደሆነ አይታወቅም፤ የእስላም ፓርቲ ነው?›› ስብሐት ነጋ እውቀትን የሚሻ ቢሆን ለፓርቲዎች እውቅናን የሚሰጠውን መሥሪያ ቤት ያውቀዋል፤ ለምን ብሎ ይጠይቅ? ለምን ብሎ እውነቱን በማወቅ ይታሰር? ትክክለኛ መረጃ ባለማወቅ እንደልብ የመናገርን ነጻነት ይገድባልና ‹‹አላውቅም›› ማለት ለመዘላበድ ይጠቅማል፤ ምንም እንኳን የሰላዮች ሠራዊት እንዳለው ብናውቅም ስለእስላሞችና ስለሰማያዊ ፓርቲ የተናገረውን እንደፖሊቲካ ከወሰደው ደረጃውን ከማሳየት አያልፍም፤ ሰማያዊ ፓርቲን በሁሉም ዘንድ ለማስጠላት የሚከተለውን ይላል፤ ‹‹እስላሞች ወንድሞቻችን የሚሉት ደግሞ የት ያውቁናል? ሲቀጠቅጡን የነበሩ፤ ተራ ሕዝቡም አይወዳቸውም፤›› የጤፍ ቅንጣት የምታህል የማሰብ ተግባር ቢኖርበት ስብሐት የተናገረው ያልተጠረነፉትን እስላሞች በሙሉ የሰማያዊ ፓርቲ ደጋፊ የሚያደርግ መሆኑን መረዳት ይችል ነበር።
ስብሐት ነጋ አንድ መቶ ሃያ ዓመታት ያህል ወደኋላ ቢሄድ ኤርትራ የሚባል አገር አያገኝም፤ በዚያ መሬት ያሉ ሰዎች ላላቸው ወይም ለሌላቸው የኢትዮጵያዊነት ስሜት የስብሐት ነጋን ምስክርነት እንደማይፈልጉ በጣም እርግጠኛ ሆኖ መናገር ይቻላል፤ ለሌሎቻችን ኢትዮጵያዊነትም ቢሆን የስብሐት ነጋ ምስክርነት አያሻንም፤ አሰብን አንሥቶ ብዙ ወጣቶች ያለቁበትን ባድመን ሳያነሣ መቅረቱ በአንድ በኩል፣ አሰብንም ሆነ ባድመን ከሚፈልጉ ወገኖች መሀል እሱ መውጣቱን በጣም ግልጽ አደረገ፤ ወዴት እንደገባ ግን ገና አልነገረንም!!!

ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳ ከማንኛውም የፓርቲ ፖለቲካ ራሳቸውን አገለሉ – “በእድሜ መግፋት በቃኝ አሉ”

Janaury 4/2014

 በቅርቡ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ባደረገው ምርጫ ስልጣናቸውን ለኢንጂነር ግዛቸው ያስረከቡት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ፓርቲያቸው አንድነት የመስራች ጉባኤውን በአዲስ ቪው ሆቴል እያደረገ ባለበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ቀጣይ የፖለቲካ ህይወታቸውን አስመልክቶ የደረሱበትን ውሳኔ አሳወቁ።

የፓርቲውን የመመስረቻ ጉባዬ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቀድሞው የአንድነት ሊቀመንበር ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ‹‹ከአሁን በኋላ ከየትኛውም የፓርቲ ፖለቲካ ራሴን አግልያለሁ፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ዕድሜዬ 70 መድረሱ ነው፡፡ትግሉን ወጣቶች መምራት እንዳለባቸው አምናለሁ፡፡ስለዚህ በቀሪው ህይወቴ ገለልተኛ በመሆን አገሪን ለማገልገል እሰራለሁ፡፡በአንድነት አዲሱ ብሄራዊ ምክር ቤት ከ65ቱ ውስጥ 47 ወጣቶች መሆናቸው አስደሳች ነገር ነው፡፡አዲሱ ፕሬዘዳንት ስራ አስፈጻሚ ውስጥ ከ65% በላይ ወጣቶች እንደሚሆኑ መናገራቸውም ያስደስተኛል፡፡›› ማለታቸውን የአንድነት ፓርቲ ሚድያዎች ዘግበዋል።

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ኢሕአዴግን ሲለቁ አቶ መለስ ዜናዊን “አሁንስ መንግስቱ ኃይለማርያም መሰልከኝ” በሚል በቃኝ ያሉ ሲሆን አሁን ደግሞ ከማንኛውም የፓርቲ ፖለቲካ በቃኝ ያሉት በእድሜ መግፋት ነው።
ዛሬ በአዲስ ቪው ሆቴል ኢንጂነር ግዛቸው በአብዛኛው በወጣት የተያዘውን ካቢኔያቸውን ይፋ አድርገዋል። ዝርዝራቸውም የሚከተሉት ናቸው፦
1) አቶ ተክሌ በቀለ ——- ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዘዳንት
2) አቶ በላይ ፈቃዱ ——– ምክትል ፕሬዘዳንት
3) አቶ ስዩም መንገሻ ——– ዋና ጸሀፊ
4) አቶ ዳንኤል ተፈራ ——– የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ
5)አቶ ሃብታሙ አያሌው ——- የህዝብ ግኑኝነት ሀላፊ
6)አቶ ዘለቀ ረዲ ——— የውጪ ጉዳይ ሀላፊ
7) አቶ አስቻለው ከተማ ——- የፋይናንስ ጉዳይ ሃላፊ
8)አቶ ሰለሞን ስዮም ——– የፖለቲካ ጉዳይ ሃላፊ
9) አቶ ዳዊት አስራደ ——– የኢኮኖሚ ጉዳይ ሃላፊ
10)አቶ አለነ ማህጸንቱ ——- የማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ
11) ወ/ሮ የትናየት ቱጂ ——- የህግና ሰብአዊ መብት ጉዳይ ሃላፊ
12) አቶ ትእግስቱ አወሉ ——- (የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሃላፊ በመሆናቸው በቀጥታ የካቢኔ አባል ሆነዋል)

ምንጭ ዘ-ሐበሻ

ህገመንግስትን የሚቃረን አንቀጽ ከፀረሙስና አዋጅ እንዲሰረዝ ተወሰነ

January4/2014
የፌዴሬሽን ምክር ቤት በፓርላማ የወጣውን ህግ ሲያሻሽል አሁን የመጀመሪይው ነው፡፡ የቀድሞ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ስዬ አብርሃ ተመሳሳይ ጥያቄ አቅርበው ውድቅ ተደርጐባቸው ነበር፡፡ 
“በሚኒስትር ማዕረግ የገቢዎችና ጉምሩክ ባስልጣን ዋና ዳሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ ላይ የቀረበው የሙስና ክስ መታየት ያለበት በከፍተኛ ፍ/ቤት ነው ወይስ በጠቅላይ ፍ/ቤትን” በሚል ለተነሳው ጉዳይ ምላሽ ለመስጠት ለሰዓታት የተከራከሩ የፌደሬሽን ምክር ቤት አባላት፤ የሚኒስትሮች ክስ በጠቅላይ ፍ/ቤት እንዲታይ የሚደነግገው አንቀጽ ከፀረ ሙስና አዋጁ እንዲሰረዝ በ76 የድጋፍና በ8 የተቃውሞ ድምጽ ወሰኑ፡፡ 
የሙስና ክሶችን በቀዳሚነት የመዳኘት ስልጣን የከፍተኛ ፍ/ቤት እንደሆነ የሚገልፀው የፀረሙስና አዋጅ፣ ሚኒስትሮች ሊከሰሱ ግን በቀጥታ ወደ ጠቅላይ ፍ/ቤት እንደሚቀርብ ይገልፃል፡፡ በ1993 ዓ.ም ኢህአዴግ ውስጥ በተከሰተው ፀብ ከፓርቲው አመራርነት የተባረሩት የቀድሞ መከላከያ ሚኒስትር ስዬ አብርሃ፣ በወቅቱ በሙስና መከሰሳቸው የሚታወቅ ሊሆን፣  ጉዳያቸው በቀጥታ በጠቅላይ ፍ/ቤት እንዲታይ መደረጉን ተቃውመው እንደነበር ይታወሳል፡፡ እንደሌሎች ተከሳሾች የአቶ ስዬ ክስ በከፍተኛ ፍ/ቤት እንዲታይ መከራከሪያ ያቀረቡት ጠበቃ፤ አለበለዚያ ግን ይግባኝ የመጠየቅ የተከሳሽ ህገመንግስታዊ መብትን የሚጥስ ይሆናል ብለዋል፡፡  በፀረ ሙስና አዋጅ የተካተተው አንቀጽ ህገመንግስቱን ስለሚቃረን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ቀርቦ ውሳኔ እንዲሰጥበት የአቶ ስዬ ጠበቃ ቢከራከሩም፤ ፍ/ቤቱ ጥያቄውን ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ 
ጥያቄው እንደገና ፍ/ቤት ውስጥ የተነሳው ከአስር አመታት በኋላ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ከፍተኛ ሃላፊዎች ላይ ከተመሰረተው ክስ ጋር ተያይዞ ነው፡፡ በአንድ በኩል ዋና ዳሬክተሩ አቶ መላኩ ፈንታ በሚኒስትርነት ማዕረግ የተሾሙ በመሆናቸው፣ በፀረ ሙስና አዋጁ መሰረት ጉዳያቸው በጠቅላይ ፍ/ቤት መታየት ይገባዋል የሚል አስተያየት ቀርቧል፡፡ የፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ህጐች፣ በበኩላቸው ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል እንደሆነ በህገመንግስት ውስጥ በግልጽ ስለሰፈረ፣ የሁሉም ተከሳሾች ጉዳይ በከፍተኛ ፍ/ቤት መታየት አለበት በማለት ተከራክረዋል፡፡ ፍ/ቤቱም፤ የአዋጁ አንቀፆች ከህገመንግስቱ ጋር እንደሚጋጩ ወይም እንደማይጋይጩ የመወሰንና ለዚህ ክርክር እልባት የመስጠት ስልጣን እንደሌለው በመግለጽ ነው፣ ጉዳዩን ለፌዴሬሽን ም/ቤት ያስተላለፈው፡፡  
በፌደሬሽን ምክር ቤት ስር የተቋቋመው የህገመንግስት ጉዳዮች የአጣሪ ጉባኤ፣ ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ የውሣኔ ሃሳብ ያዘጋጀ ሲሆን፣ የምክር ቤቱ አባላት ለበርካታ ሰዓታት ተከራክረውበታል፡፡ 
“በፀረ ሙስና አዋጅ የተካተተው አንቀጽ ህገ መንግስቱን ስለማይፃረር ባለበት ይቀጥል፤ እንዲያውም ህገመንግስቱን የሚያስከብር ነው” በማለት አስተያየት የሰነዘሩ አባላት፤  “ባለስልጣናት በሙስና ሲባልጉ አምነው የተቀበሉትን ህገመንግስት ስለሚጥሱ ይግባኝ በሌለበት ሁኔታ ፍርዳቸው መታየቱ ተገቢ ነው” ብለዋል፡፡ አንዳንድ የምክር ቤቱ አባላት በበኩላቸው  ጉዳዩ ክብደትና እና ጥልቀት ያለው መሆኑን በመጠቆም ጉዳዩን ለማጤን የተሰጠው ጊዜ አጭር ነው የሚል ሃሳብ አቅርበዋል፡፡ 
በሌላ በኩል፤ “የይግባኝ መብት የሚጣሰው የአቶ መላኩ ብቻ ሳይሆን የአቃቤ ህግም ነው” በማለት የተከራከሩ አባላት፣ ጉዳዩ በከፍተኛው ፍ/ቤት መታየቱ ሁለቱንም ይጠቅማል ብለዋል፡፡ ይግባኝ በሌለበት ሁኔታ ፍርዳቸው መታየት አለበት በሚል የተሰነዘረውን ሃሳብ በመቃወም  ምላሽ የሰጡት የአጣሪ ጉባኤው አባል አቶ ሚሊዮን አሰፋ “የሚኒስትሮች ክስ ከሌላው ሰው ተነጥሎ ይታይ” የሚል ሃሳብ በዜጐች መካከል የመደብ ልዩነት መኖሩን ከሚያመላክት ፊውዳላዊ አስተሳሰብ የሚመነጭ በመሆኑ ተገቢ አይደለም ብለዋል፡፡ 

በመጨረሻም፤ አከራካሪው አንቀጽ ህገመንግስቱን ስለሚቃረን ከፀረ ሙስና አዋጅ እንዲሰረዝ በ76 የድጋፍና በ8 የተቃውሞ ድምፅ የተወሰነ ሆን፣ እንዲህ ዓይነቱ ውሳኔ ለምክር ቤቱ የመጀመሪያው መሆኑን በመጠቆም ታሪካዊ ውሳኔ ነው በማለት አፈጉባኤው አቶ ካሳ ተክለብርሃን ተናግረዋል፡፡ 
ምንጭ አዲስ አድማስ

የመተሃራ ስኳር ፋብሪካ ስራ አስኪያጅን ጨምሮ 7 ከፍተኛ ሃላፊዎች በሙስና ተከሠሡ

January 4/2014

የመተሃራ ስኳር ፋብሪካ ስራ አስኪያጅና ሌሎች ከፍተኛ ሃላፊዎች፤ ዶዘር ለማስጠገን የወጣውን ጨረታ ያለ አግባብ ለአንድ ድርጅት በመስጠት በሙስና የተከሰሱ ሲሆን ፍ/ቤቱ፤ የተከሳሾችን መቃወሚያና የአቃቤ ህግን መልስ መርምሮ ብይን ለመስጠት ለጥር 16 ቀጠሮ ሠጥቷል፡፡ 
ዶዘር ለማስጠገን በወጣ ጨረታ በመንግስት ላይ ከ224ሺ ብር በላይ ጉዳት አድርሠዋል በሚል ክስ የቀረበባቸው የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ አቶ ብዙነህ አሠፋ፣ የንግድ ክፍል ዋና ሃላፊው አቶ አበባዬህ ታፈሠ፣ የግዥ ቡድን መሪው አቶ መስፍን ደምሠው፣ የመስክ መሣሪያ ጥገና አገልግሎት ሃላፊው አቶ አብደላ መሃመድ፣ የጠቅላላ ሂሣብ ቡድን መሪው አቶ በለጠ ዘለለው፣ የማቴሪያል ፕላኒንግና ኢንቨንትሪ ማናጅመንት ቡድን መሪው አቶ ታደሠ ኃ/ጊዮርጊስና  የእቃ ግዥ ባለሙያው አቶ ሣሣሁ ጌታቸው ናቸው፡፡  

የእቃ ግዢው ባለሙያ አቶ ሳሳሁ ጌታቸው፤ “ኮማትሱ 801 ዶዘር” የተሠኘውን ተሽከርካሪ ለማስጠገን ለወጣው ጨረታ ከተለያዩ ድርጅቶች ዋጋ መሠብሠብ ሲገባቸው “አንድ አቅራቢ ብቻ ነው ያለው” በማለት ቲኖስ ኃላ.የተ.የግ.ማ ከተባለው ድርጅት ብቻ ዋጋ  ያቀረቡ ሲሆን የቀሩት የስራ ሃላፊዎች ደግሞ ሶስት እና ከዚያ በላይ ተጫራቾች መሳተፍ እንደሚገባቸው እያወቁ አንድ ብቻ ተጫራች የተሣተፈበትን፣ ተጫራቹም የንግድ ፈቃድ ማቅረቡንና ግብር መክፈሉን ሣያረጋግጡ እንዲሁም አማራጭ የእቃዎች ዋጋ ሣያዩ ግዢው እንዲከናወን በማድረግ በመንግስት ላይ ከ224ሺ ብር በላይ ጉዳት አድርሠዋል  ተብሏል፡
፡ 
አቃቤ ህግ ከክስ ዝርዝሩ ጋር የሠው እና የሠነድ ማስረጃውን አያይዞ ያቀረበ ሲሆን ተከሣሾቹ ከትናንት በስቲያ ለዋለው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት  የክስ መቃወሚያቸውን በጠበቃቸው በኩል አቅርበዋል፡፡ በእለቱ የተከሣሾች ጠበቃ፤ “ከተከሳሾቹ መካከል የጨረታ ኮሚቴ አባል ያልሆኑ ስላሉ ተለያይቶ ይቅረብልን፣ ለክሡ መነሻ የሆነው ዶዘር ለጥገና የገባው በመድህን በኩል ነው፣ የስኳር ድርጅት የግዥ መመሪያ ለመድህን የግዥ መመሪያ አይሆንም” በማለት መቃወሚያቸውን አቅርበው ክሡ እንዲነሣላቸው ጠይቀዋል፡፡ የጨረታ ኮሚቴውን በተመለከተ የተነሣው ጉዳይ ምስክሮቼንና የሰነድ ማስረጃ በማቀርብበት ጊዜ ሊነሳ የሚችል ነው፣ ያለው አቃቤ ህግ በበኩሉ፤ ዶዘሩ የፋብሪካው መሆኑን አመልክቶ፣ ከመድህን ጋር ተያይዞ የቀረበው አግባብ አይደለም፤ በማለት ተከሳሾች ክሱ እንዲነሳ ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ይደረግልኝ ሲል ጠይቋል፡፡ ፍ/ቤቱም ጉዳዩን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለጥር 16 ቀን 2006 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ደላላው የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስን “ካሳ ካልከፈሉኝ እከሳለሁ” አለ

 January 4/2014

 የፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት፣ የቀድሞው ፕሬዚዳንት እና ሴት ልጃቸው በፍርድ ቤት ክስ ቀረበባቸው
- የፕሬዝዳንቱ ጽ/ቤት የህግ ባለሙያ የለውም
- ” የ2.4 ሚሊየን ብር ካሳ ይከፈለኝ” የሚል ደብዳቤ ለፕሬዝዳንቱ ጽ/ቤት ገብቷል

ከምኒልክ ሳልሳዊ

ለቀድሞው ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ አሁን የሚኖሩበትን ቤት አፈላልጎ ያከራያቸው ግለሰብ 360,000 ብር የአገልግሎት ክፍያ አልተከፈለኝም ሲል የቀድሞው ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስን፣ ሴት ልጃቸውን መና ግርማ ጨምሮ የፕሬዝዳንት ጽ/ቤትን ከፕሬዚዳንቱ ቢሮ የጽ/ቤቱን ኦፊሰሮች ወይዘሮ አማረች በቃሎን እና ወይዘሮ አምሳል ፋንታሁንን ከስሷል፡፡

ከሳሹ የአገልግሎት ክፍያውን ከማን ማግኘት እንዳለበት እንዳላወቀና ፍርድ ቤት አጣርቶ እንዲያሳውቀውም ጠይቋል፡፡ የፕሬዝዳንቱ ጽ/ቤት በበኩሉ ክፍያው የመንግስትን ጥቅም ስለሚጎዳና ክሱን ለመከራከርም ጽ/ቤቱ የህግ ባለሙያ ስለሌለው ፍትህ ሚንስትር ወክሎ እንዲከራከርለት የሚጠይቅ ደብዳቤ ለፍትህ ሚንስትር ጽፏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም፣ ከዚህ በፊት ለቀድሞው ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ቤት ለማከራየት ውል ተዋውዬ፣ ቤቴን አሳድሼና ሌሎችንም በርካታ ወጪዎችን አውጥቼ ውሉ ፈርሶብኛል ያሉት ግለሰብ በዚሁ ሳቢያ ለደረሰብኝ ጉዳት የ2.4 ሚሊየን ብር ካሳ ይከፈለኝ የሚል ደብዳቤ ለፕሬዝዳንቱ ጽ/ቤት አስገብቷል፡፡

ይህ ካልሆነ ግን ወደ ፍርድ ቤት እንደሚያመራ አስታውቋል፡፡

የአቦይ ስብሐት ከኢትዮጵያዊነት መውደቅ

Janaury3/2014

‹‹ከኢትዮጵያዊነት መውደቅ ማለት ምን ማለት ነው? አፄ ሀይለስላሴ ከኢትዮጵያዊነት ወድቀዋል የሚል የለም፡፡ ኮሎኔል መንግስቱንም የሚል የለም፡፡ . . . ከኢትዮጵያዊነት መውደቅ ማለት፤ በቃ በአጭሩ ኢትዮጵያዊ አለመሆን ነው፡፡ ሌላ ማንነት መገንባት (IDENTITY DEVELOP) ማድረግ ነው፡፡›› ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ፣ ኢትዮ-ምህዳር፣ ቅጽ 02፣ ቁጥር 47፡፡

ሀሳብን በመግለፅ ነፃነት እጅግ አድርጌ አምናለሁ፡፡ እንዲያውም ብዙዎች ‹የዲሞክራሲ መገለጫው ነፃ-ምርጫ ነው›፣ የሚሉትን ወረድ አድርጌ፣ ‹ዋናው የዲሞክራሲ መገለጫ ሀሳብን የመግለጽ ነፃነት ነው›፣ ብዬ አምናለሁ፡፡ ነፃና ዲሞክራሲያዊ የሚባለው ምርጫ በምስጢር የሚከናወን መሆኑ ነፃ ያለመሆኑ ማስረጃ ሆኖ ይሰማኛል፡፡ ሀሳብን የመግለጽ ነፃነት ግን እንደ ነፃ ምርጫ በምስጢር የሚደረግ አይደለም፡፡ በዚህ ተራ ምክንያት ነው ሃሳብን የመግለጽ ነፃነት፣ ከነፃ-ምርጫ የላቀ ዲሞክራሲያዊ ስርአትን ገላጭ ሆኖ የሚሰማኝ፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ ሀገሬን ሳያት ‹ነፃ› ምርጫን ያህል፣ ሃሳብን የመግለፅ ነፃነት አልተሳካላትም፡፡ ለዚህ ነው ተቃማዊ ፓርቲ መስርተው በ‹ነፃ› ምርጫው ለመሳተፍ ከሚጥሩት የበለጠ፣ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ ነፃነትን ለማበረታታት ለሚውተረተሩት ልቤ የሚደነግጠው፡፡ ለአቦይ ስብሀትም የተለየ ግምት ያደረብኝ በዚሁ የተነሳ ይመስለኛል፡፡ ፓርቲያቸው በተደጋጋሚ በ‹ነጻ› ምርጫ ቢያሸንፍም፣ የዲሞክራሲ መገለጫው ነፃ ምርጫ ነው ብለው አልተቀመጡም፤ ለሃሳብ ነፃነት መረጋገጥ ከፍተኛ ማበረታታት እያደረጉ ነው፡፡ በእድሜዬ፣ በደርግም ሆነ በኢህአዴግ፣ ከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል እንደ እሳቸው የሀገራችንን ሁለንተናዊ ሁኔታ አስመልክቶ በነፃነት (ሀሳቡን በሾመው መንግስት ሀሳብ ሳይቃኝ) የሚገልፅ አላጋጠመኝም፡፡ በዚህ የተነሳ ለአቦይ ስብሀት ትልቅ አድናቆት አለኝ፡፡
ለዚህ ጽሁፌ መነሻ የሆነኝም የአቦይ ስብሀት ህዳር 17፣ 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ተማሪዎች ጋር ያደረጉት ውይይት ነው፡፡ እንደ ብዙዎቹ አወዛጋቢ የአቦይ ስብሀት አስተያየቶች፣ በዚህ ውይይት ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች የሰጡዋቸውን አስተያየቶች አንብቤና ግራ ተጋብቼ ብቻ ላልፋቸው አልፈለኩም፡፡ ጥያቄ አዘል አስተያየቴን ልሰነዝር ወደድኩ፡፡
መቼም ለረዥም አመታት ታግሎና አታግሎ፣ በታላቅ መስዋእትነት በተገኘ ድል፣ የተገኘ ስልጣን ይዞ፣ ሀገርና ህዝብ የሚመራ ሰው በጋዜጣና በመጽሔት፣ በሬዲዮና ቲቪ፣ በስብሰባና በአውደጥናት የሚጽፈውና የሚናገረው፣ ‹ሀሳብን የመግለጽ ነፃነት አለ፤ ሀሳቤን ለመግለጽ አልፈራም› ለማለት ሳይሆን፣ የሚያስተላልፈው ቁምነገር ስለሚኖር ነው፡፡ ለመሆኑ የአቦይ ስብሀት የዩኒቨርሲቲው ንግግር፣ ወደፊት ሀገር ለሚረከቡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሚጠቅም፣ ምን ጠብ የሚል ቁም ነገር (ከእሳቸው የህይወት ልምድና የፖለቲካ ሰውነት አንፃር) አለው?፡፡
እንደ እኔ እምነት ማንም ባለስልጣን እንደሳቸው ቁምነገር ሲናገር ሰምቼ አላውቅም፡፡ አንዱን እውነት ጠቅሼ ልሟገት፡፡ ‹‹ከኢትዮጵያ ህዝብ በላይ የኤርትራ ህዝብ ኢትዮጵያዊነት አለው፡፡›› ብለዋል አቦይ ስብሀት፡፡ ብዙዎች ይህን ሲሰሙ ወይም እንደኔ ተጽፎ ሲያነቡ፣ ውሸት ብለው ደንግጠው አዝነዋል፡፡ እኔ ግን እውነት ተናግረዋል እላለሁ፡፡ በእሳቸው (ምናልባም ደርግን ባስወገዱልን አብዛኞቹ ነፃ አውጪዎቻችን) አመለካከት የእኛ ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያዊነት ከኤርትራውያን ያነሰ ነው፡፡ በመሆኑም ጠንካራ ኢትዮጵያዊነት አላቸው የተባሉት ኤርትራውያን፣ ያነሰ ኢትዮጵያዊ ናችሁ ከተባልነው የበለጠ ኢትጵያዊ መብት ተሰጥቷቸዋል፡፡
ዘመንና አጋጣሚ የመረቃቸው ኤርትራውያን በሀገራቸው ጥሩ ኤርትራዊ፣ በሀገራችንም ጥሩ ኢትዮጵያዊ ናቸው፡፡ እኛ እዚህ ኢትዮጵያዊ እዚያም ኤርትራዊ አይደለንም፡፡ ከኤርትራ ንብረታችን ተዘርፎ ስንባረር፣ የኤርትራ መሪዎች ብቻ ሳይሆኑ የኢትዮጵያም መሪዎች ውሸት ብለው አላግጠውብናል፡፡ ለምን? እዚያ በኤርትራዊነት ስለሚበልጡን መሪዎቹ ዘርፈው አባረሩን፡፡ እዚህ በኢትዮጵያዊነት ስለሚበልጡን መሪዎቻችን አፊዘው ተቀበሉን፡፡ እውነቱን ብለዋል አቦይ ስብሀት! በመሪዎቻችን ሚዛን ኤርትራውያን በኢትዮጵያዊነት ይበልጡናል፡፡ ምን ኤርትራውያን ብቻ! ‹‹ለኤርትራ ብቻ ሳይሆን ለሶማሊያ፣ ለሱዳን፣ ለጅቡቲም፣ ለኤርትራም አትራፊ መሆን የእኛ የቤት ስራ ይመስላል፡፡›› ያሉት አቦይ ስብሀት ጅቡቲ፣ ሱዳንና ሱማሌስ በኢትዮጵያዊነት ስለሚበልጡን አይደል! እንግዲያማ በኮረንቲ በቀን አስሬ መጥፋት እቃችን እየተቃጠለ፣ ቋት የገባ እህል ሳይፈጭ እያደረ፣ በየቢሮው ያለስራ እየተዋለ፣ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ሱዳን ድረስ፣ የኮረንቲ መስመር ዘርግተው ለምረቃ ይሄዱ ነበር!
በቀደም በሳዑዲ አረቢያ በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን መከራና ግድያ በሰላማዊ ሰልፍ እንዳንቃወም የተደረገው በመሪዎቻችን ሚዛን ኢትዮጵያዊነታችን ቀሎ በመገኘቱ ይመስለኛል፡፡ አቦይ ስብሀት እንዳሉት ከእኛ የበለጠ ኢትዮጵያዊነት ያላቸው ኤርትራውያን አዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ቢጠይቁ ይፈቀድላቸው የነበረ ይመስለኛል፡፡
አቦይ ስብሀት እንዳሉት፣ እኛ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያዊነት ሚዛን ከኤርትራውያን ቀለን ብንገኝ ተጠያቂው ማነው? የደርግን የአምባገነን ግፈኛ መንግስት ባንኮታኮተንበት ጀግንነት፣ የኢትዮጵያዊነት ስሜታችንን ለማንኮታኮት የሚታገለው የኢህአዴግ መንግስት አይደለምን? ሀገርን ለማስተዳደር የተሰናዳን ህገ-መንግስት ሀገር ነው የሚሉ አንጋፋ ባለስልጣኖች የሚያስተዳድሩት ህዝብ ነው፣ የኢትዮጵያ ህዝብ፡፡ እናም ዜግነቱ በሀገሩ ሳይሆን በህገ-መንግስቱ እንዲቀረጽ ይፈለጋል፡፡ ህገ መንግስታዊ እንጂ ሀገራዊ ዜግነት አይፈቀድለትም፡፡
አቦይ ስብሃት፣ ‹‹ሀገር ማለት ህገ-መንግስት ነው›› ብለዋል፡፡ ለምን አሉ? ህገ መንግስቱን ያስረቀቀውም፣ ያፀደቀውም ኢህአዴግ ስለሆነ ይመስለኛል፡፡ እስከዛሬ እንደታዘብኩት ኢህአዴግ እንደ ፓርቲ፣ ባለስልጣናቱ እንደ ኢሊት ከ1983 ዓ.ም ቀድሞ የነበረ ሁሉ ነገር እርኩስ፣ ከ1983 ዓ.ም ወዲህ ያመጡት ሁሉ ቅዱስ ይመስላቸዋል፡፡ በአስራ ሰባት አመት ግፈኛ አገዛዝና በሶስት ሺህ ዘመን ሀገራዊ ቅርስና ታሪክ መካከል ያለው ድንበር የደበዘዘባቸው ይመስለኛል፡፡ በዚህም የተነሳ ይመስለኛል ደርግን አሸንፎ መጣል፣ የቀደመውን እሴት ሁሉ የለመጣል ጋራንቲ የሚመስላቸው፡፡ በዚህ አስተሳሰብ የተነሳ የተቻለው ሁሉ ተለውጧል፡፡ አይለወጤ የሆነው (ሆኖ ያስቸገረው) ዜግነታችን ነው – ኢትዮጵያዊነታችን፡፡
ኢትዮጵያዊነታችንን ከሃያ አመት በፊት በተጻፈ ህገ-መንግስት ለመስፈር በአቦይ ስብሃት የተደረገው ድፍረትም ከዚሁ የመነጨ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ በኢትዮጵያዊነት ውቅያኖስ ላይ ሃያ አመት ጠብታ ነው- ያውም የውሽንፍር፡፡ ኢትዮጵያዊነት እኮ እድሜው የትየለሌ፣ ጫፉ ብዙ ነው፡፡ ከንግስተ ሳባ ጋር እየሩሳሌም ድረስ፣ ከኦሮሞ ስደት ጋር ኬንያ ድረስ . . . ወዘተ. የሚዘረጉ ጫፎች ያሉት፣ ሁለንተናዊ ጥሪት ነው፡፡ ጉድፉ ሊነቀስ እንጂ ጨርሶ ሊገሰስ አይችልም፡፡
ዛሬ ኢትዮጵያዊነት በአብዛኞቹ የአለም ሀገሮች (አቦይ ስብሀት እንደነገሩን ከኤርትራ በስተቀር) ዝቅ ተደርጎ የሚታይ ዜግነት ነው፡፡ ለመሰደድ በየኮንቴይነሩ ታጭቀው፣ ታፍነው የሚሞቱት፣ በየበረሃው አሸዋ ጠብሶ የሚያስቀራቸው፣ በተሰደዱበት ሀገር ለሚሰቃዩ ኢትዮጵያውያን ከጉሮሮ የማይወርድ መና ሰጥቶ፣ ሽፍል የማያረጥብ እንባ ረጭቶ ሬዲዮና ቲቪ ላይ አስጥቶ ለፖለቲካው ድርጎ የሚያውላቸው እንጂ፣ ከልቡ የሚረዳቸውና የሚሟገትላቸው መንግስት ያለን አይመስለኝም፡፡
አቦይ መቼም እርሶ ብቻ ሳይሆኑ፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትራችንን ጨምሮ ኢትዮጵያዊነታችንን ዝቅ የሚያደርግ (ስለ ባንዲራ፣ የአክሱም ሀውልት፣… ወዘተ.) ብዙ እንደተባለ ያውቃሉ፡፡ በዚህ ሁሉ ፈተና ኢትዮጵያዊነት ሳይጠፋ በመቆየቱ ህዝቡ ሊመሰገን እንጂ ሊወቀስ የሚገባው አይመስለኝም፡፡ ከተወቀስንም እንደ መንግስት ፍላጎት ኢትዮጵያዊነት ባለመሞቱና ባለመቀበሩ መሆን አለበት፡፡
ለመግቢያ በተጠቀምኩበት የዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ አባባል እንደተገለፀው ንጉሱና ደርግ ስለኢትዮጵያዊነት አብዝተው አንዳንዴም አግንነው (ማጋነኑ ችግር ቢኖረውም) ያስተምሩ ነበር፡፡ ህዝቡ ከሁለቱ መንግስታት ስለሀገር ፍቅርና ኢትዮጵያዊነት ብዙ ተምሯል፡፡ በኢህአዴግስ? በኢህአዴግ መዝገበ ቃላት ውስጥ የሀገር ፍቅርና ኢትዮጵያዊነት የተፃፉ አይመስለኝም፡፡ እና ሃያ አመት ሙሉ እኛ ኢህአዴግ በመዝገበ ቃላቱ ኢትዮጵያዊነትን እንዲጽፍ ስናሳስብ፣ ኢህአዴግ እንደ መዝገበ ቃላቱ ሁሉ፣ ከእኛም ጭንቅላት ሊያጠፋው ሲታገል – ስንጎሻሽም ሀያ አመት አሳለፍን፡፡ እንግዲህ እግዜር ያሳያችሁ ከዚህ ሁሉ በኋላ ነው በኢህአዴግ ውስጥ ከፍተኛ ተደማጭነትና ሃላፊነት ያላቸው (ቢያንስ የነበራቸው) አቦይ ስብሃት ስለኢትዮጵያዊነታችን ማነስ የሚወነጅሉን፡፡
ኢህአዴግ በሀገር ፍቅርና በኢትዮጵያዊነት ላይ ባራመደው አቋም ያተረፈው አለመታመንን ይመስለኛል፡፡ ለዚህ ምስክሩ ደግሞ በምርጫ 97 በተለያዩ ቦታዎች፣ በቅርቡ በአክራሪዎች የደረሱ አደጋዎችን፣ አብዛኛው ህዝብ በመንግስት በራሱ የተፈፀሙ ናቸው፣ በሚል ጥርጣሬ መመልከቱ ነው፡፡ በኢትዮጵያና በናይጄሪያ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ እለት ስለደረሰው አደጋ በዚያው ሰሞን በኢቲቪ የቀረበ የአዲስ አበባ ነዋሪ፣ ‹‹አንዳንድ ሰዎች መንግስት ነው ያደረገው ይላሉ፤ መንግስት እንዴት በገዛ ዜጎቹ ላይ ይህን ያደርጋል››፣ የሚል አስተያየት መሰንዘሩ ለዚህ የቅርብ እማኝ ነው፡፡ በዚህ የተነሳ እንደመንግስት ኢህአዴግ ከኢትዮጵያዊነት ወድቋል፤ እንደ ታላቅ ታጋይና የፖለቲካ ሰው ደግሞ አቦይ ስብሀት ነጋ፡፡
ፋክት መጽሄት

Ethiopia: Dark side of Oromo expansions and Menelik conquests

January 3, 2014
by Abera Tola
Through out history; people have migrated and expanded seeking greener pastures and more land. Globally, most countries have endured and were created thru expansions, wars, assimilation, migration; slavery etc. Even the most developed countries in the world today have dark pasts. For example; millions of Native Americans were exterminated or removed from their homelands while millions more African-Americans underwent the most cruel slavery in world history before the great democracy; the USA; was born. If not for the gradual improvement of human rights in America and its military superiority triggering an economic powerhouse; United States would have been just another poor country facing fragmentation and internal division due to its dark history of conquest and slavery. While Ethiopia did not have as much a bloody history as America; it did experience some conflicts and small level of slavery. Considering how extremely diverse Ethiopia is ethnically, linguistically, politically and religiously, Ethiopia still has been a relatively peaceful country. And that has been one reason why, despite all its problems, its citizens are proud. Case in point: how many poor countries with over ninety native languages and a near 50/50 Islam/Christian population have managed to co-exist or live in relative peace for over thousand years? Not many. But still, Ethiopia has had its share of problems as well. As an Oromo; the two most violent and most important events that impacted my people are the Oromo expansion in the 1500s and the Shewan Menelik expansion of the 1880s. These two events represent the two stages of Ethiopia’s ethnolinguistic evolution.
Stage one: Oromo expansion
After the 1540s; the ethnolinguistic and political shape of the horn of Africa changed forever when the Oromo expanded north into territories dominated by the Amharic speaking people of Abyssinia/Ethiopia as well as the Sidama and the Adal kingdoms. Historians credit our unique Gadaa system for being suitable for warfare and for the successful conquest of present day central; west and eastern Ethiopia by the Oromo. According to Oromo oral accounts and historical records; the Oromo expansion into Abyssinia was disorganized but Oromo raids and attacks of the neighboring people lasted for many decades; leading to the killing of tens of thousands of Amharic speaking people. The powerful Oromo benefitted from its large population and better developed battle strategy. The Oromo expansions were also similar to that of the Ottoman Empire expansion because they both did not always change the religion of their new subjects. With the only exception of the Yejju Oromo imposing Afan Oromo on Amharas in Gondar; the Oromos also never enforced their language on other people. Nonetheless; many Somali, Amharic and Sidama speaking peoples became “tax-paying serfs” for the new Oromo rulers. And having already been weakened by the Adal/Somali conquest of southern Abyssinia; the Amharic & Tigrayan speaking population of Abyssinia lost more lands to the Oromo; including the Shawa and Dawaro regions (Arsi area) that have been Abyssinian territories since the days of their ancient Aksum empire. Today; the descendants of these Oromo settlers makeup the dominant population in Shewa and Arsi. Not only the eastern and southern edges of the Abyssinian highlands but; gradually; even some northern pockets of Abyssinia got conquered by Oromo warlords: which explains why small Oromo communities can still be found as far north as Tigray even today. Thus; in the late 1500s; having lost substantial territories to the Oromo; the Solomonic Dynasty/Abyssinia declined in power for decades. But that century also started the transformation of Abyssinia into a more multi-ethnic entity: one that was forced to incorporate Oromo as one of its citizens.
Stage Two: Menelik/Shewan expansion
Another significant event that greatly impacted the ethnic and political situation in Ethiopia and the region was the Shewan/Abyssinian expansion led by Emperor Menelik II during the late 1800s. Just like the Oromo expansion; the Abyssinian expansion was disorganized since many parts of Abyssinia were in conflict amongst each other. The Shewan part of Abyssinia have been in various small battles against Gondar and Gojjam parts. However; using relatively modern weapons purchased from European countries; the Shewan Abyssinians defeated other Abyssinian regions and then they continued on to re-conquer Oromo territories that were settled by the Oromos since the 1500s. Proportionally; about the same percentage of people might have perished during the Shewan expansion (stage 2) compared to the Oromo expansion (stage 1). However; seen in raw figures; many thousands more were killed during the bloody conquests by Menelik’s Shewan army. As the sign of the times, not many international laws of war exists to stop the atrocities during these wars, or for that matter during any wars around the globe. Yet one undeniable key fact of this war was that the Shewan army was ethnically diverse, even if Amharas were the militarily dominant group in it. Because Oromos settled in Shewa since their 1500s expansion; Shewa was already a melting pot of Amhara and Oromo by the late 1800s. Therefore; the multi-ethnic Shewan army of Emperor Menelik was able to easily defeat various Oromo and southern areas of present day Ethiopia.
Both of these historical events of the 1500s and the 1800s shaped the ethnolinguistic identity of the new Ethiopia.
Conclusion
The most glaring difference between the two events is that one happened in a recent memory and thus it influences the current politics of the region more powerfully. Otherwise; both events are dark and equally violent parts of our history. De-emphasizing or ignoring one event over the other only creates confusion and bitterness among the new generation. An Oromo should not ignore “stage one” and only talk about “stage two.” Similarly; an Amhara should not ignore “stage two” and only talk about “stage one.” The blame game by bringing a biased version of the past only poisons the present. No one side should play the victim game or live in the past, instead of working for a better future; otherwise everyone will fall together.
References
-US Library of Congress Country study: Ethiopia history
- Pankhurst; Richard K.P. The Ethiopian Borderlands: Essays in Regional History from Ancient Times to the End of the 18th Century. The Red Sea Press; Asmara.
- Oromo Oral history

በሞያሌ ከተማ የኦነግ ታጣቂዎች የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ ከተማዋ በመከላከያ ሰራዊት ስትታመስ ዋለች

January 3/2014

ባለፈው ረቡእ ታጣቂዎቹ ከቀኑ 10 ሰአት ገደማ ወደ ከተማዋ በመግባት 3 ጠባቂዎችን በመግደልና አንደኛውን ታጣቂ መሳሪያውን በመቀማትና ልብሱን በማስወለቅ ” ሂድና ለአለቆችህ ንገር” በማለት ጉዳት ሳያደርሱበት መልቀቃቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል። ታጣቂዎቹ አንድ ድግን መትረጊስ፣ አንድ ላውንቸርና አንድ ባዙቃ ማርከው ወስደዋል። ይህንን ተከትሎ በአካባቢው የደረሱት የመከላከያ ሰራዊት አባላት አንዳንድ የከተማ ነዋሪዎችን እየደበደቡ ሲያሰቃዩ መቆየታቸውን ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ለኢሳት ገልጸዋል።

አንድ ሹፌር ለኢሳት እንደገለጹት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተሳፋሪዎች ከመኪና ላይ በመሳወረድ ድብደባ እንደፈጸሙባቸውና እርሳቸውም በጥፊ እንደተመቱ ተናግረዋል ( audio)
“እኛ ለምን እንደተደበደብን አልገባንም” የሚሉት ነዋሪዎች፣ ሁኔታው እስከትናንት ድረስ ውጥረት የነበረበት እንደነበርና ፍተሻው በእየጫካው እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።

ታጣቂዎቹ በነዋሪዎች ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለማድረሳቸውም ተገልጿል።

በጉዳዩ ዙሪያ የሞያሌን አስተዳደር ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም። መንግስትም በጉዳዩ ላይ የሰጠው አስተያየት የለም።
ኦነግ ገዢውን ሀይል በትጥቅ ትግል ለማስወገድ ከሚንቀሳቀሱት ድርጅቶች መካከል አንዱ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የመንግስት ታጣቂዎች በኦጋዴን ውስጥ በሚኖሩ ዜጎች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ኦጋዴን ፕሬስ ዘግቧል።
ልዩ ሚሊሺያ የሚባሉት ሀይሎች ከመከላከያ ሰራዊት አባላት ጋር በወሰዱት እርምጃ ፍሪህ ደሃግ አዳር የተባለው ሰው ሲገደል ሌሎች ደግሞ ቆስለዋል። source ESAT

Friday, January 3, 2014

አንድ ለአምስት – ከቃሊቲ ዉጭ ሌላ ቃሊቲ

January 3/2014

ወያኔ የጫካ ዉስጥ ኑሮ በቃኝ ብሎ አዲስ አበባን ከረገጠ በኋላ ኢትዮጵያ ዉስጥ ብዙ አዳዲስ ቃላት ተፈጥረዋል፤ አንዳንድ አብረናቸዉ ያደግናቸዉ ቃላትና የቦታ ስሞች ደግሞ እየፋፉ መጥተዉ የሌሎች ሰፋ ያሉ ሀሳቦች መግለጫ ሆነዋል። ለምሳሌ የዛሬ ሃያ አምስት አመት ኮሌጅ የጨረሰ ልጅ አባቱን ቃሊቲ መግባቴ ነዉ ብሎ ቢነግረዉ አባቱ . . . . ምንዉ ስራ አገኘህ እንዴ ብሎ ከመጠየቅ ዉጭ በልጁ አባባል በፍጹም አይደነግጥም። ዛሬ ግን “ዕድሜ ለወያኔ” ቃሊቲ ሲባል የማይደነግጥ ኢትዮጵያዊ የለም። በፋብሪካ ማዕከልነቷ ትታወቅ የነበረችዉ ቃሊቲ ዛሬ አጥሩ ዉስጥ ወያኔ አፍኖ የከተታቸዉ ሰላማዊ ዜጎች ከአጥሩ ዉጭ ደግሞ የእነዚሁ ሰላማዊ ዜጎች ቤተሰቦች የሚተራመሱበት የጭንቅና የመከራ አምባ ሆናለች። አዎ ቃሊቲ እንደ አልባኒያዋ ቡሪልና እንደ ሩሲያዋ ሳይቤሪያ ዜጎችን ለማፈንና በዜጎች ላይ ሰቆቃ ለመፈጸም ሆን ተብላ እንደገና የተፈጠረችና አለፍላጎቷ አስቀያሚ ገጽታ የተከናነበች ከተማ ሆናለች። ቃሊቲ ታሪክ ከክፋታቸዉና ከጭካኔያቸዉ ዉጭ በፍጹም የማያስታዉሳቸዉን የሩሲያዉን ጆሴፍ ስታሊንና የአልባኒያዉን ኤንቨር ሆዣን እኛ ኢትዮጵያዉያን አለዝምድናችን በግድ እንድናስታዉሳቸዉ የተገደድንባት የአምባገነንነት ተምሳሌት ናት። የሚገረመዉ ቃሊቲ ወያኔ ተሸክሞ ካመጠልን የጆሴፍ ስታሊንና ኢንቨር ሆዣ መንታ ትዝታዎች አንዷ ናት። ጆሴፍ ስታሊንና ኢንቨር ሆዣ የሩሲያንና የአልባኒያን ህዝብ እስር ቤት ዉስጥ ብቻ አልነበረም ያሰሩት፤ አንድ ለአምስት በሚሉት ማለቂያ በሌለዉ ሰንሰለታቸዉ በመኖሪያ ቤቱ ዉስጥ፤ በሚሰራበት ፋብሪካ ዉስጥ፤ በሚማርበት ት/ቤቶች ዉስጥና በተደራጀበት ገበሬ ማህበር ዉስጥ ጭምር ጭምድድ አድርገዉ አስረዉታል።
የኢትዮጵያን ህዝብ የሚረገጡትንና እንደ እንስሳ እየታሰሩ የሚገረፉበትን መንገድ ለማወቅና ልምድ ለመቅሰም አልባኒያ ድረስ የሄዱት ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች ከአልባኒያ ይዘዉብን የመጡት ቃሊቲን ብቻ አይደለም፤ ከቃሊቲ ዉጭ ህዝብን በሰንሰለት ማስር የሚያስችላቸዉን “አንድ ለአምስት” አደረጃትም ይዘዉ መጥተዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ተግባራዊ አድርገዋል። አንድ ለአምስት ወያኔ ምንም ይበለዉ ምን በግንብና በሽቦ አጥር ያልታጠረ ሰፊ እስር ቤት ነዉ፤ ወይም አንድ ለአምስት – ከቃሊቲ ዉጭ የሚገኝ ሌላ ቃሊቲ ነዉ። ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ በአንድ ለአምስት ሰንሰለት ማሰር ከጀመረ ቆይቷል። ዛሬ ወያኔ ይህንን የእነ ስታሊንን የመከራ ማራዘሚያ ገመድ ከገመደብን ከአመታት በኋላ “እንድ ለአምስትን” እንደገና ማንሳት የፈለግነዉ ጉዳዩ አዲስ ሆኖብን ሳይሆን ሁለት ነገሮች አሳስበዉን ነዉ፤ አንደኛዉ ወያኔ የ“እንድ ለአምስት” አደረጃጀትን የህብረተሰባችን መሰረት ወደ ሆነዉ ወደ ቤተሰብ ደራጃ ሲያወርደዉ በማየታችን ሲሆን፤ ሁለተኛዉ ደግሞ “እሾክን በእሾክ” እንዲሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ከወያኔ ዘርኝነት፤ሰቆቃና ጭቆና ለመላቀቅ ወያኔ የፈጠረዉን አንድ ለአምስት አደረጃት በመሰላልነት ተጠቅሞ እራሱን እንዲያደራጅና ለወሳኙ ፍልሚያ እራሱን እንዲያዘጋጅ ለማሳሰብ ነዉ።
ወያኔ ነገረ ስራዉ ሁሉ ከጉልበትና ከሀይል ጋር የተያያዘ ነዉ፤ ስልጣን የያዘዉ በጠመንጃ ሀይል ነዉ፤ ስልጣን ላይ የቆየዉ በጠመንጃ ሀይል ነዉ። የኢትዮጵያን ህዝብ አንድ ለአምስት እያለ የሚያደራጀዉም በሀይል እያስገደደ ነዉ እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብማ በወያኔ ስር መደራጀት ቀርቶ ወያኔ ድርጅቱ ብቻ ሳይሆን ወያኔ የሚባል ቃሉ እራሱ ከምድረ ኢትዮጵያ ቢጠፋ ደስታዉን አይችለዉም። የሚገርመዉ ወያኔ በዚያ ጠመንጃ በጨበጠበት እጁ የጻፈዉ ህገ መንግስት አንቀጽ 31 ማንኛዉም ሰዉ ለማንኛዉም አላማ በማህበር የመደራጀት መብት አለዉ ይላል፤ ሆኖም ይህ ህገመንግስታዊ መብት ለይስሙላ የተቀመጠ የባዶ ቃላት ክምር ነዉ እንጂ ኢትዮጵያ ዉስጥ ህዝብ በራሱ ፈቃድ መደራጀትም አለመደራጀትም አይችልም። ለመሆኑ ወያኔ በፍጹም በማይመለከተዉ በቤተሰብ ጉዳይ ጣልቃ የሚገባዉ ለምንድነዉ? እኛስ ኢትዮጵያዉያን ይህንን የወያኔ ጣልቃ ገብነት እንዴት አድርገን ነዉ እራሳችንን ነጻ ለማዉጣት የምንጠቀምበት?
በቅርቡ የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለወረዳ ሁለት የላከዉን የቤተሰብ ማቋቋሚያ ቅጽ አስመልክቶ በሰጠዉ ተጨማሪ ማብራሪያ የቤተሰብ ፖሊስ መመስረት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሶ በቤተሰብ መካካል ለሚፈጠሩ አለመግባባቶችና ማህበራዊ ችግሮች መፍትሄዉ ቤተሰብን አንድ ለአምስት ማደራጀት እንደሆነ ተናግሯል። ባለፈዉ ሳምንት አጋማሽ ላይ የወያኔ ባለስልጣኖች በዳግማዊ ሚኒልክ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ዉስጥ ከየትምህርት ቤቱ ለተሰባሰቡ ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች አዲሱን አደረጃጀት አስመልክተዉ በሰጡት መግለጫ በቅርቡ ወደ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ይወርዳል ብለዉ ካሉት የኮማንድ ፖስት አደረጃጀት በተጨማሪ “ትራንስፎርሜሺን ፎረም” እና “የልማት ቡድን” የሚባሉ አደረጃጀቶችም እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል። የወያኔ ዘረኞች ስም እየቀያየሩ ኮማንድ ፖስት አሉት፤ “ትራንስፎርሜሺን ፎረም” ወይም “የልማት ቡድን” የሁሉም አደረጃጀት ተቀዳሚ ተግባር “አንድ ለአምስት” ተብሎ የተጀመረዉን አደረጃጀት ለማጠናከርና ለማስቀጠል ነዉ።
የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን ወይኔ ለራሱ እኩይ አላማ ሲል የጀመረዉንና ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በማጠቃለል ላይ የሚገኘዉን የአንድ ለአምስት አደረጃጀት ወደ “ሚሊዮኖች ለሚሊዮኖች” አደረጀጃት በመቀየር ወያኔን እሱ እራሱ በፈጠረዉ ሰንሰለት ለማሰር ከአሁን የተሻለ ግዜ የሚያገኝ አይመስለንም። “አንድ ለአምስት” ከዛሬ በኋላ ወያኔ ኢትዮጵያዉያንን የሚሰልልበት ሳይሆን ኢትዮጵዉያን የወያኔን የስለላ መረብ የሚበጣጥሱበት፤ የማይተዋወቁ የትግል ጓደኞች የሚተዋወቁበት፤ ድርጅት የናፈቃቸዉ ኢትዮጵያዉያን እራሳቸዉን ከወያኔ አፈና ነጻ ለማዉጣት የሚደራጁበት የዝግጅት ቦታ መሆን አለበት። ወያኔ አንድ ለአምስት ያደራጀዉ የመንግሰት ሰራተኞችን፤ ተማሪዎችን፤ አርሶ አደሮችንና የከተማ ነዋሪዎችን እየነጣጠለ ለየብቻቸዉ ቢሆንም የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ይህንን ወያኔ የፈጠረለትን መድረክ በመጠቀምና የወያኔን የልዩነት ግድግዳ በመሰባበር አንድ ለአምስትን የመገናኛዉና የመደራጃዉ መድረክ ማድረግ አለበት።
ወያኔ ስፍር ቁጥር የሌለዉ የአደረጃጀት አይነቶች እያመጣ የኢትዮጵያን ህዝብ እንደ ቋጠሮ የሚቋጥረዉ እሱ ሊነግረን እንደሚፈልገዉ ለኢትዮጵያ ህዝብ ደህንነት ተጨንቆ ወይም ለአገርና ለህዝብ ሰላምና ዕድገት አስቦ አይደለም። ወያኔ ለህዘብ ሰላምና ደህንነት የሚያስብ ቢሆን ኖሮ ማድረግ ያለበት የኢትዮጵያን ህዝብ መብትና ነጻነት ማክበር እንጂ ኮማንድ ፖስትና አንድ ለአምስት እያለ ህዝብን በማይታይ ሰንሰለት ማሰር አይደለም። ኮሚኒስቶች ከግማሽ ምዕተ አመት በላይ ዜጎቻቸዉን ያሰቃዩበት “አንድ ለአምስት” አደራጃጀት አራት ሰዎች አንዱ በሌላዉ ላይ ስለላ እያካሄድ ለአምስተኛዉ ሰዉ መረጃ የሚያቀብሉበት ጓደኛን ከጓደኛ፤ ተማሪን ከአስተማሪ፤ አንዱን ሰራተኛ ከሌላዉ ሰራተኛ ጋር የሚያጋጭና በህብረተሰብ መካከከል መተማመን እንዳይኖር የሚያደርግ የስቃይ ሰንሰለት ነዉ። ወያኔ ይህንን የስቃይ ሰንሰለት በየቦታዉ ሲዘረጋ ከርሞ ዘንድሮ ካልጠፋ ቦታ ወደ ቤተሰብ ደረጃ እያወረደዉ ይገኛል። ፓርላማዉን ጨምሮ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ስልጣን፤ መከላከያዉን፤ ደህንነቱንና የአገሪቱን የኤኮኖሚ መዋቅር ሙሉ በሙሉ የሚቆጣጠረዉ ወያኔ ይህ ሁሉ አልበቃ ብሎት ፈጣሪ ለአባትና ለእናት የሰጠዉን ብቸኛ ሀላፊነት የራሱ ለማድረግ አንድ ለአምስትን በየቤተሰቡ ለመዘርጋት እየሞከረ ነዉ።
“ፈጣሪ ሊያጠፋዉ የፈለገዉን ያሳብደዋል” ተረት ወያኔን በትክክል የሚገልጸዉ የአባቶቻችን ተረት ነዉ። በእብደት ቢባል፤ በጭቆና፤በዘረኝነት፤ በትዕቢት፤ ወይም ህዝብን በመበደልና አገር በመበተን አገራችን ኢትዮጵያ ከወያኔ የባሰ እብድ በፍጹም ሊመጣባት አይችልም። ይህ ለይቶለት ያበደ ስርዐት የአንድ ለአምስት አደረጃጀትን ብቻ ሳይሆን ካሁን በኋላ የሚወስዳቸዉን ማንኛዉም አይነት እርምጃዎች የኢትዮጵያ ህዝብ እራሱን ከባርነት ነጻ ለማዉጣት መጠቀም መቻል አለበት። ወያኔ በጠመንጃ ሀይል ከቀማን መብቶች አንዱ የመደራጀት መብት ነዉ፤ ሆኖም ለራሱ በሚያመች መንገድ አንድ ለአምስት እያለ እያደራጀን ነዉ። የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን የወያኔን አንድ ለአምስት አደረጃጀት ተጠቅሞ እራሱን ለማደራጀትና ከወያኔ የአፈና ሰንሰለት ለመላቀቅ አመቺ አጋጣሚ ተፈጥሮለታል። ወጣቱ፤ገበሬዉ፤ሠራተኛዉ፤ አስተማሪዉና የከተማ ነዋሪዉ ማህበረሰብ የየራሱን የጎበዝ አለቆች እየመረጠ ወያኔን እራሱ በገመደዉ ገመድ ማሰር ካለበት ግዜዉ አሁን ነዉ።
ከፋሺስት ጣሊያን ወረረ አገራችንን ያዳኗት ጀግኖች አባቶቻችን መሪ የለንም ብለዉ ጠላትን ዝም ብለዉ አልተመለከቱም። እነ በላይ ዘለቀ፤ አብዲሳ አጋና ጃገማ ኬሎ የጎበዝ አለቃ መርጠዉ እራሳቸዉን አደራጅተዉ ነዉ አገራችንን ከአደጋ ያዳኗት። በአምስቱ የትግልና የአርበኝነት ዘመን በትጥቅ፤ በቁሳቁስና በዘመናዊነት የሚበልጣቸዉን የፋሺስት ጣሊያን ጦር አሳፍረዉ ወደመጣበት የመለሱት አባቶቻችን ለድል የበቁት ፋሺስት ጣሊያን በፈጠረዉ የድርጅት መዋቅር ዉስጥ እራሳቸዉን አደራጅተዉ ነዉ። አብዲሳ አጋ ጣሊያንን ያርበደበደዉ በጣሊያን ተራሮችና በረሃዎች ዉስጥ ነዉ። ዘርዓይ ደረስ የጣሊያኖችን አንገት የቀላዉ በሮም አደባባዮች ዉሰጥ ነዉ። ዛሬ በወያኔ ጥቁር ፋሺስቶች እየተገዛ ቁም ስቅሉን የሚያየዉ ኢትዮጵያዊ የእነዚህ ጀግኖች የልጅ ልጅ ነዉና የአባቶቹን ታሪክ በመድገም ወያኔ በፈጠራቸዉ ድርጅቶች ዉስጥ እየተደራጀ እራሱን፤ አገሩንና ወገኑን ነፃ ማዉጣት አለበት።
ወያኔን በህዝባዊ አመጽም ሆነ በህዝባዊ እምቢተኝነት ወይም በሁለቱም የትግል ስልቶች ታግሎ አገራችንን ነጻ ለማዉጣት ከዉጭ የሚመጣ ሀይል የለም፤ ነጻ አዉጪዉም በሚገኘዉ ነጻነት ተጠቃሚዉም ያለዉ እዚያዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ነዉ። ነፃነት ያለትግል ትግል ደግሞ ያለ ድርጅት በፍጹም የሚታሰቡ ነገሮች አይደሉም። ከአላማ ጽናት ቀጥሎ አንድ ህዝብ ነፃኑቱን እንዲጎናጸፍ የሚያስችለዉ ድርጅታዊ ብቃቱ ነዉ፤ ወያኔ የኢትዮጵያ ህዝብ ከሱ ፈቃድና ፍላጎት ዉጭ እንዳይደራጅ አጥብቆ የሚታገለዉ ይህንን ሀቅ በሚገባ ስለሚረዳ ነዉ። ሆኖም የኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነቱን ለመቀዳጀት መታገል ለመታገል ደግሞ ወያኔ ፈቀደም አልፈቀደ ህዝብ በመረጠዉና ይበጀኛል ብሎ ባሰበዉ መንገድ ሁሉ መደራጀት አለበት። የኢትዮጵያ ህዝብ በወያኔ ሰላዮችና ካድሬዎች ተከብቦ እንደሚኖር የታወቀ ነዉ፤ ሆኖም ይህንን ከበባ ጥሶ ለመዉጣት ወያኔ እራሱ ያመቻቸዉ መንገድ አለ፤ እሱም ከሰራተኛና ከገበሬዉ ተነስቶ ቤተሰብ ድረስ የወረደዉ የወያኔ “አንድ ለአምስት” አደረጃጀት መዋቅር ነዉ።
የኢትዮጵያ ህዝብ ባለፉት 35 አመታት በሁለት አምባገነን ስርዐቶች ዉስጥ አልፏልና ስለአምባገነኖችና ስለ አምባገነንነት ብዙ ልምድ አለዉ። ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ አንድ ወጥ በሆነ ድርጅታዊ መዋቅር ዉስጥ የሚያደራጀዉ የህዝብን ስነ ልቦና ለመስበርና ህዝብ በፍርሀት ደመና ተዉጦ እየሰገደ እንዲኖር ለማድርግ ነዉ። የኢትዮጵያ ህዝብ ግን የወያኔን ማንነት በሚገባ የተረዳዉ ስለሆነ የተገነባ ሞራል ያለዉና በራሱ የሚተማመን ህዝብ ነዉ፤ ስለሆነም ወያኔ የፈጠረዉን የድርጅት ጋጋታ እራሱን ነፃ ለማዉጣት ይጠቀምበታል የሚል ሙሉ እምነት አለን። ያለፈቃዳቸዉና ያለ እምነታቸዉ በግዴታ በአንድ ለአምስት ከተደራጁ ሰዎች ከአስር ዘጠኙ ወያኔን የሚቃወሙና የወያኔን ስርዐት ለማፍረስ የሚታገሉ ሰዎች ናቸዉ። እነዚህ ሰዎች ወያኔ ለስለላና ለጭቆና ያዋቀረውን የ“አንድ ለአምስት” አደረጃጀት ወያኔን እራሱን ለመታገልና ብሎም ለማዳከም እንደ መሣሪያ ተጠቅመዉ ይህንን አስከፊ ስርዐት ከጀርባቸዉ ላይ አንከባልለዉ መጣል አለባቸዉ።

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ልዩ ጉባኤው የአቋም መግለጫ

January 3/2014

ዛሬ በደረስንበት 21ኛው ክፍለዘመን በአለማችን የሚገኘው ሕዝብ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶቹ በተከበሩበት ሁኔታ መመራት ይሻል፡፡ በዚህ ዘመን አምባገነን መሪዎችና መንግስታት በየትኛውም መስፈርት ስልጣን ላይ የመቆየት እድል የላቸውም፡፡ በዚህ ረገድ በቅርብ አመታት ውስጥ የማይደፈሩና እንደ ፈርኦን ይመለኩ የነበሩ አምባገነን መንግስታት በህዝባዊ ማዕበል ተጥለቅልቀውና ተንጠው መቀመቅ ሲወርዱ የአለም ህዝብ ሁሉ አስተውሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት የዲሞክራሲና የነፃነት ጥየቄ ከዳቦ ጥያቄ ይበልጥ አንገብጋቢ እየሆነ መጥቷል፡፡

የአለማችን አንድ አካል የሆነችው አገራችን ኢትዮጵያ የዘመናት የስልጣኔ ጉዞዋ የምድራችን ቁንጮ የታሪክ ባለቤት ያደርጋታል፡፡ በየዘመናቱ የተነሱ ገዢዎቻችን ሲጭኑብን የቆዩት የአገዛዝ ቀንበር ወገባችንን ቢያጎብጠውም የኢትዮጵያ አንድነትና ሉኣላዊነት ፍፁም ሳይሸራረፍ ተጠብቆ ዘመን እንዲሻገርና ለትውልድ እንዲተላለፍ የማይሻ ኢትዮጵያዊ የለም፡፡

ወታደራዊው ደርግ ከሥልጣን በተወገደ ማግስት ዲሞክራሲና ነፃነት የሰፈነበት የዜጎች ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች የሚከበሩባትን ኢትዮጵያ ለማየት ያልጓጓ ኢትዮጵያዊ አልነበረም፡፡ ህልማችን በእውነት ሳይፈታ ቀረ፣ ተስፋ ያደረግነው ነገር ከዓመት ዓመት እየጨለመ መጣ፡፡ ኢህአዴግ ባለፉት 23 ዓመታት የምኒሊክን ቤተመንግስት ቢቆጣጠርም የአገርን ህልውና ከመጠበቅና የህዝብ እንባን ከማበስ ይልቅ ዜጎችን መውጪያ መግቢያእያሳጣና የመከራን ገፈት እያስጨለጠ ጉዞውን ቀጥሏል፡፡ ስደቱ፣ እንግልቱ፣ ግርፋቱ፣ እስራቱ፣ ግድያው፣ አፈናው፣ ስቃዩ ከመቀነስ ይልቅ በየጊዜው እየከፋ ይገኛል፡፡

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ይህን ቀንበር ለመስበር እንደ መርፌ ቀዳዳ በጠበበው የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ እየተንቀሳቀሰ በመላው አገሪቱ ህዝብን ለትግል እያሰለፈ ይገኛል፡፡

ይህን እልህ አስጨራሽ ትግል ለመምራት ትልቁ የስልጣን አካል የሆነው ይህ ጠቅላላ ጉባኤ ታህሳስ 19 እና 20 / 2006 ዓ.ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት ባደረገው ከፍተኛ ስብሰባ አያሌ አገራዊ ጉዳዮችን በማንሳት ተወያይቷል፡፡ የፓርቲውን ምክር ቤት ፣ የሥራ አስፈፃሚና የኦዲት ኮሚሽንን ሪፖርት በማድመጥ ጠንካራ ውይይት አካሂዷል፡፡

በመጨረሻም የአገልግሎት ዘመናቸውን ባጠናቀቁት የፓርቲው ፕሬዚደንት የተከበሩ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ምትክ የተከበሩ ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራውን ፍፁም ግልፅና ዲሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ ተክቷል፡፡ የፓርቲውን ብሔራዊ ምክር ቤት እና የኦዲት ኮሚሽን አባላትንም በመምረጥ ጉባኤው ተጠናቋል፡፡

አባላቱ በጉባኤው ማጠናቀቂያ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ የሚከተለውን የአቋም መግለጫና ውሳኔ በማሳለፍ ተጠናቋል፡፡
1ኛ. ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ በአገሪቱ የሚደረገውን የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ ሙሉ ለሙሉ ለማኮላሸት ነጋ ጠባ የሚያጠነጠነው እኩይ ሴራ የህዝቡን ስሜት ወደ ሌላ አቅጣጫ እና ጥግ እየገፋው ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ ፓርቲያችን አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በጀመረው የሰላማዊ ትግል ጉዞ የኢትዮጵያን ህዝብ የስልጣን ባለመብት ለማድረግ እስከመጨረሻው እንጥፍጣፊ በጥብቅ መታገል እንደሚኖርበት ይታመናል፡፡ በመሆኑም እኛ ከመላው አገሪቱ በዚህ ጉባኤ ላይ የታደምን የፓርቲ አባላትና አመራሮች ከመቼውም ጊዜ በላቀ መልኩ ለሰላማዊ ትግሉ ቁርጠኛ መሆናችንን እናረጋግጣለን፡፡

2ኛ. አምባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት የፓርቲያችንን እንቅስቃሴዎች እግር በእግር እየተከታተለና በሀሰት ውንጀላ በማጠልሸት በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዳናገኝ ጠቅልሎ በያዘው የቴሌቪዥን ጣቢያ ሰፊ የሆነ አፍራሽ ተልዕኮን እያስተጋባ ይገኛል፡፡ይህ ጉዳይ ህገ መንግስቱ ለመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ግንባታ ያመቻቸውን መንገድ ሙሉ ለሙሉ የሚጠቅም ነው፡፡ ከዚህ አንፃር አገር እየመራሁኝ ነው የሚለው ኢህአዴግ ፓርቲያችንን ከሽብር ድርጊት ከአሸባሪዎች ጋር ለማቆራኘት የሚያደርገውን እኩይ ሴራ አጥብቀን እናወግዛለን፡፡

3ኛ. በዚህ ልዩ ጉባኤ ወቅት በአካል በመቅረብ በገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ካድሬዎችና ታጣቂዎች በሰሜን ጎንደር ዳባት ወረዳ አርቡር ቀበሌ ነዋሪ የሆነችው የ 8 ዓመቷ ህፃን ስለእናት ማስረሻ ጥላሁን የደረሰባትን እጅግ ዘግናኝና ሰቅጣጭ የአካል ጉዳትአሳይታለች፣ ሁኔታው የጉባኤውን አባላት ክፉኛ ያስቆጣ ሆኗል፡፡ አባቷን እና የቤት እንስሳትን በጥይት ገድለው ህፃን ስለእናትን በጥይት አረር እጇን የቆረጡ እኝህ እኩያን ወንጀለኞች በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን፡፡

4ኛ. የገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ የአመራር ዘመን አገራችን ኢትዮጵያ በታሪኳ እጅግ የተዋረደችበትና ሉኣላዊነቷ የተደፈረበት ወቅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ዜጎች የከፋ የሰብአዊ መብት ጥሰት ይደርስባቸዋል፣ይታሰራሉ፣ ይደበደባሉ፣ ይገደላሉ፣ ይሰደዳሉ ወዘተርፈ፡፡
ለስደት በተዳረጉባቸው አገራትም ዜጎቻችን በግፍ ሲገደሉና ሲደበደቡ እያን ነው፡፡ በቅርቡ በሳውዲ አረቢያና ሰሞኑን ደግሞ በደቡብ ሱዳን ኢትዮጵያዊያን ላይ የደረሰው ሞትና ስቃይ የእያንዳንዳችንን ልብ የሰበረ ጉዳይ ነው፡፡ ለዚህም ተጠያቂው ኢህአዴግ ነው፡፡
በመሆኑም ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ በመላው ዓለም እንደ ወንዝ ዳር አሸዋ ተበትነው ለሚንገላቱ ዜጎች ጉዳይ በአፅንኦት እየተከታተለ እንዲታደግና የመንግስትነት ግዴታውን ባግባቡ እንዲወጣ አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡

5ኛ. በአሁኑ ወቅት የገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ጥቂት ሹማምንት እጆቻቸውን እያስረዘሙ የአገርን ሀብት እየዘረፉ ናቸው፣ ሥርዓቱ ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ በሙስና የተጨማለቀ መሆኑን እየተጋለጠ ነው፡፡ ዜጎች ዛሬ የዕለት ጉርሳቸውን አጥተው ሲራቡና ሲጠሙ፣ወጣቶች የሥራ ዕድል ተነፍጓቸው በአሳፋሪ ሁኔታ ከአገር ሲሰደዱ፣ የኑሮ ውድነቱ ትውልዱን ግራ እያጋባ ነው፣ ህዝቡ ፍትህና መልካም አስተዳደር በማጣት ነጋ ጠባ የዜግነቱ ጉዳይ ጥያቄ በፈጠረበት ሁኔታ የነገዋን ኃያልና የበለፀገች ኢትዮጵያን አይደለም ማየት ይቅርና የህልውናዋ ጉዳይም አጣብቂኝ ውስጥ የገባበት ሰዓት ላይ ደርሰናል፡፡ በአገሪቱም አስከፊ ብሔራዊ ቀውስ ይፈጠራል ብለን እንሰጋለን፡፡

ከዚህ አንፃር ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ብሔራዊ መግባባትን የሚያሰፍን መድረክ እንዲያዘጋጅ አበክረን እንጠይቃለን፡፡
6ኛ. ኢቴቪ የኢትዮጵያ ሕዝብ ልሳንነቱን እርግፍ አድርጎ በመተው የገዢው ፓርቲ አገልጋይ መሆኑን የትኛውም ኢትዮጵዊ የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡፡ አንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ፕሮግራም ላይ በመላው አገሪቱ ሰላማዊ ሰልፍ እና ስብሰባዎችን በጠራበት ወቅት ኢቴቪ ጅሃዳዊ ሃረካት ፊልምን አቀናብሮ ፓርቲያችንን ከአሸባሪዎች ተርታ ሲፈርጀው ቆይቷል፡፡ ሌላው ቀርቶ ጉባኤያችንን ባከናወንበት ታህሳስ 19 ምሽት ኢቴቪ ያንኑ ፊልም በድጋሚ በማቅረብ አንድነት ፓርቲ በደሴ፣ በጎንደር፣ በአርባምንጭ፣ በጂንካ፣ በባህርዳር ወዘተ ካደረጋቸው ሰላማዊ ሰልፎችና በፓርላማ የፓርቲያችን ብቸኛው ተወካይ ስለ ፀረ ሽብር ህጉ አፋኝነት ያነሱትን ሀሳብ ከሽብር ጋር በማያያዝ ከንቱ ዲስኩር ሲያቀርብ ተመልክተናል፡፡ ኢቴቪ የአንድ ድርጅት መሆኑ አብቅቶ የኢትዮጵያን ሕዝብ ዋይታና ብሶት የሚያስተጋባ ግዙፍ የብዙሃን መገናኛ ድርጅት እንዲሆን አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡

7ኛ. ፓርቲያችን አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከተመሠረተበት ዕለት ጀምሮ ከኢህአዴግ አምባገነናዊ አገዛዝ ጋር በብርቱ እየተናነቀ መሪዎቹ እየታሰሩበትና እየተደበደቡበት መዋቅሩን በመላው አገሪቱ ዘርግቶ አመርቂ የትግል ውጤት እያመጣ ቢሆንም የኢትዮጵያን ሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት ለማረጋገጥ የሚቀረው ጉዞ እጅግ ረጅም ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ፓርቲያችን ይህ ታላቅ ጉባኤ የወሰናቸውን ውሳኔዎችና መርሃ ግብሮች በአግባቡ እየተወጣ ታሪክ ይሰራ ዘንድ አጥብቀን እናስገነዝባለን፡፡

በቀጣይ ዓመታት ፓርቲውን በበላይነት እንዲመሩ የተመረጡ አመራሮች ከመቼውም ግዜ በበለጠ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ከአደራ ጭምር እናሳስባለን፡፡

ህወሃት ኢህአዴግ ስራ-ኣጥ ለሆኑ ወጣቶች ስልጠና ለመውሰድ ተመዝገቡ ብሎ በማታለል ወታደራዊ መሰልጠኛ እንዳስገባቸው ታወቀ

January 3, 2o14

በመረጃው መሰረት በአማራ ክልል ጎንድር ከተማ ከተለያዩ ዩንቨርስቲዎችና ኮሌጆች በድግሪና በዲፕሎማ የተመረቁ እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀው ነጥብ ያልመጣላቸው ወጣቶች ሥር-ዓጥ ሁነው የግል ሂወታቸውን ለመምራት ላይና ታች ሢሉ የታዘቡ የከተማዋ አስተዳዳሪውች። በስርዓቱ ላይ ምንም አይነት እምነት እንደሌላቸው በአንፃሩ የሚረዳና የሚደግፋቸዉ አካል ካገኙ በስርዓቱ ላይ እርምጃ ከመውሰድ ወደኋላ እንዳማይሉ ስለተረዱ፤ ወጣቶችን ለመበተን ብለው በመንግስት የሚሰጣችሁ ሞያዊ ስልጠና እንደ አለ ኣስመስለው በማታለል ብር ሽለቆ ወደ ሚገኘው ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምብ እንደወሰድዋቸው ታወቀ::

ይህ በእንዲህ እንዳለ እነዚህ የኢህአዴግ ጸረህዝብ ካድሬዋችና አስተዳድሪች ለወጣቱ እንደማታለያ የሚጠቀሙበት ዘዴ፤ ዘመናዊ በሆነ የሞያ ማሰልጠኛ ማለት የዲዛይን ማውጣት ስራ፤ የብረታብረትና የእንጨት ጥርበት፤ የሾፌርነትና የመካኒክነት ስልጠና ስላለ ሙሉ በሙሉ በቂ የሆነ ስልጠና ወስዳችሁ በማነኛዉም አካባቢ ስራ ተቀጥራችሁ ሂወታችሁን መምራት የሚያስችላችሁን አቅም እንድትጨብጡ መንግስት በቂ የሆነ በጀት መድብዋል ብለው እንደተናገርዋቸው ለማወቅ ተችልዋል::

ይሁን እንጂ በመኪና ጭነው ወደ ብርሽለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምብ ተወስደው ወትሃደራዊ ስልጠና በመጀመራቸው፤ ወጣቶቹ በበኩላቸው የመጣ ይምጣ በለው፤ ለምን በሂወታችን ላይ ትጫወታላችሁ የሚል ጥያቄ እንዳቀረቡላቸውና ለስልጠናው ተቃውመው ሲጠፉ ለተያዙ ወጣቶች እንዳይናገሩ ፈርተው ወደ ስራ ሲያስገብዋቸው ለቀሩት አሰልጥነው በጎጃም አካባቢ ስብስበዋቸው እንደሚገኙ የተገኘው መረጃ ኣስረድተዋል::

Source : ዴ.ም.ህ.ት