Wednesday, December 25, 2013

ለሕግ የበላይነት መከበር ትኩረት ይሰጥ!

December 25/2013

አሁንም ለሕግ የበላይነት መከበር ትኩረት ይሰጥ!

የሕግ የበላይነት ባለበት ሰላም አለ፡፡ ዲሞክራሲ አለ፡፡ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ አለ፡፡ ልማት አለ፡፡ ብልፅግና አለ፡፡

የሕግ የበላይነት በሌለበት ሰላም ፈጽሞ አይታሰብም፡፡ መረጋጋት አይኖርም፡፡ የሰው ልጅ መብት አይጠበቅም፡፡ ዲሞክራሲን ማሰብ አይቻልም፡፡ ልማትና ብልፅግና ሊኖሩ ይቅርና በሰላም ወጥቶ መግባት ከባድ ይሆናል፡፡ ዜጐች በሕግ የበላይነት ተማምነው እንዲኖሩ ሕግ ሊከበር ይገበዋል፡፡

በተደጋጋሚ እንደምንለው የሕግ የበላይነት ሲከበር ዜጐች በትክክል በሕግ ፊት እኩል መሆናቸውን ይረዳሉ፡፡ የሕግ የበላይነት በሌለበት ግን ዜጐች በሕግ ላይ ሊኖራቸው የሚገባው እምነት ይሸረሸራል፡፡ ሕገወጦች እየፈነጩ የሰውን መብት ሲጥሱና ዜጐችን ሲያሸማቅቁ የሕግ የበላይነት ጥያቄ ውስጥ ይወድቃል፡፡ በተለይ ዜጐች በሕግ የበላይነት መከበር የማይተማመኑ ከሆነ ችግሩ የከፋ ይሆናል፡፡

ብዙ ጊዜ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ይነሳሉ፡፡ ለችግሮቹ መፍትሔ እንደሚፈለግም በተደጋጋሚ ይነገራል፡፡ የመልካም አስተዳደር ዋነኛ እንቅፋት የሕግ የበላይነት ያለመከበር መሆኑ ግን አይወሳም፡፡ ዜጐችን ያላግባብ የሚያንገላቱ፣ ተገቢውን አገልግሎት የማይሰጡ፣ የመብት ጥያቄ ሲቀርብ በአግባቡ የማያስተናግዱ፣ የሥልጣን የመጨረሻው አካል ሕዝብ መሆኑን የማይረዱ፣ በሙስና የተዘፈቁና ለአገርና ለወገን ደንታ የሌላቸው ለሕግ የበላይነትም ደንታ የላቸውም፡፡ ለሕዝብ ቆሜያለሁ፣ ተጠሪነቴም አገልግሎቴም ለሕዝብ ነው ብሎ የሚያስብ ግን ከምንም ነገር በላይ የሕግ የበላይነት እንዲከበር ሽንጡን ገትሮ ይሟገታል፡፡ ለተግባራዊነቱም አስፈላጊውን መስዋዕትነት ይከፍላል፡፡ የሕግ የበላይነት የዜጐች መተማመኛ ዋስትና እንዲሆንም ሌት ተቀን ይደክማል፡፡

የሕግ የበላይነት እንዲከበር እኛ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ኃላፊነት ያለብን ቢሆንም፣ በተለይ ደግሞ ሦስቱ መዋቅሮች ማለትም ሕግ አውጪው፣ ሕግ ተርጓሚውና አስፈጻሚው ታላቅ ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ሕግ አውጪው ፓርላማ የሚያወጣቸው ሕጎች ሳይሸራረፉ ሥራ ላይ መዋላቸውን የመከታተል ትልቅ ኃላፊነት አለበት፡፡ ጥራት የጐደላቸው ለአገርና ለሕዝብ የማይጠቅሙ አንቀጾችን ያዘሉ ረቂቅ ሕጐች ሲቀርቡለት፣ ከሕዝብና ከአገር ጥቅም አንፃር እየመዘነ ጥራት ያላቸው ሕጐች እንዲወጡ ተገቢውን ሚና መጫወት ይኖርበታል፡፡ አገሪቱ ሕግ የሚከበርባት መሆኑን በተጨባጭ ማረጋገጥ አለበት፡፡

ሕግ ተርጓሚው አካል ሕሊናው በመራውና ሕግን መሠረት አድርጐ ለዜጐች ፍትሕ መስጠት አለበት፡፡ በተፅዕኖና ነፃነትን በሚጋፋ መንገድ የሚቀርቡ ክሶችን ውድቅ በማድረግ ዜጐች በፍትሕ ሥርዓቱ ላይ እንዲተማመኑ ሙያዊ ኃላፊነቱን ሊወጣ የግድ ይለዋል፡፡ የፍትሕ ሥርዓቱን ነፃነት የሚፈታተኑ ሕገወጥ ድርጊቶች የሕግ የበላይነትን የሚያዳክሙ በመሆናቸው የዳኝነቱ አካል ለፍትሕና ለርትዕ ሲል መሟገት ይኖርበታል፡፡ የፍትሕ ሥርዓቱ ነፀብራቅ የሆኑ ዳኞች ክብር ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ደኅንነታቸው መጠበቅ አለበት፡፡ እነሱ በተሻለ ሁኔታ በተራመዱ ቁጥር ውጤታቸው ጥሩ ይሆናል፡፡

ከአስፈጻሚ አካል ተፅዕኖ ሳይደርስባቸው ሙያቸውን በሚገባ ሊሠሩበት ይገባል፡፡ ከአድልኦና ከሙስና በራቁ ቁጥር የፍትሕ ተደራሽነት ይጨምራል፡፡ የፍትሕ ሥርዓቱ አካላት የሆኑት ፖሊስና ዓቃቤ ሕግ ሕዝብን የሚያገለግሉት በሕገ መንግሥቱ መሠረት እስከሆነ ድረስ ለሕግ የበላይነት ሊቆሙ ይገባቸዋል፡፡ የፍትሕ ሥርዓቱን የሚገዘግዙ ሕገወጦች በኃይል፣ በማስፈራራትና በገንዘብ ፍትሕን ሊያደናግሩ ሲሞክሩ የማስቆም ወይም ሕግ ፊት የማቅረብ ኃላፊነት አለባቸው፡፡

አስፈጻሚው አካል መንግሥትን እንደመምራቱ መጠን ለሕግ የበላይነት መከበር ትልቅ ድርሻ አለው፡፡ መንግሥት ሕገ መንግሥታዊው ሥርዓት በሰላማዊ መንገድ እየተመራ ዲሞክራሲ እንዲሰፍን፣ ሰብዓዊ መብት እንዲከበር፣ አገር እንዲለማ፣ ወዘተ   ለሕግ የበላይነት መከበር ዋነኛው ተዋናይ መሆን አለበት፡፡ በመንግሥት ውስጥ የተሸሸጉ ሕገወጦችና ግብረ አበሮቻቸው ሕዝቡን እያስለቀሱ የሕግ ልዕልናን ሲጋፉ እንዳላየ የሚያልፍ ከሆነ ወይም ካድበሰበሰ ተጠያቂነት ይኖርበታል፡፡ በፍትሕ ሥርዓቱ ላይ አመኔታ የሚያሳጡ ሕገወጥ ድርጊቶች በተደጋጋሚ ጊዜያት ሲፈጸሙ ዳተኝነት ይታያል፡፡ ይህ ዳተኝነት ደግሞ የአስፈጻሚውን አካል ደንታ ቢስነት ብቻ ሳይሆን ሥርዓቱ ለሕግ የበላይነት ያለውን ክብርና ደረጃ ቁልጭ አድርጐ ያሳያል፡፡ ዜጐች በሕግ ፊት እኩል ናቸው ሲባል ባለሥልጣናትንም ጭምር የሚያካትት በመሆኑ ለሕግ የበላይነት ትኩረት ሊሰጥ ይገባዋል፡፡ ሕግና ሥርዓት በሌለበት ድባብ ውስጥ የሚፈነጩት ሕገወጦችና ሙሰኞች ብቻ ናቸው፡፡ ስለልማት ሲታሰብ ቅድሚያ ለሕግ የበላይነት ይሰጥ፡፡ ሕዝብ በሕግ የበላይነት ጥላ ሥር መተዳደር እንዳለበት ግንዛቤ ይያዝ፡፡ የፍትሕ ሥርዓቱ ያለምንም ጣልቃ ገብነት እየተመራ ነው ሲባል ተግባራዊነቱ ሊረጋገጥ ይገባል፡፡ በንድፈ ሐሳብ ከሚባለው ይልቅ ተግባር ይበልጣልና፡፡

ሦስቱ አካላት እየተናበቡ በሕጋዊ መንገድ ተግባራቸውን ማከናቸወናቸውን የሚቆጣጠር አካል መኖር አለበት፡፡ በሠለጠነው ዓለም ይህ ተግባር የሚዲያው ቢሆንም፣ እንደ አለመታደል ሆኖ በአገራችን የሚዲያው ሚና ተፈላጊ አይደለም፡፡ ለሕግ የበላይነት መስፈን መሥራት የሚገባቸው ሚዲያዎች የሦስቱን መንግሥታዊ መዋቅሮች መናበብና የሕግ የበላይነት መከበሩን ለማረጋገጥ የሚያደርጉት ጥረት ሲመክን ይታያል፡፡ ይህ ችግር ጐልቶ የሚታየው ከአስፈጻሚው አካል በኩል ቢሆንም፣ ሚዲያው በውስጡ ባሉ የተለያዩ ችግሮች ምክንያት የተቆጣጣሪነት ሚናው ያነሰ ነው፡፡ የሲቪል ማኅበረሰቡ አቅም የጫጫ በመሆኑ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ እነዚህ እስኪጠናከሩ ድረስ የሦስቱን መዋቅሮች ተናቦ መሥራት ማረጋገጥ የግድ ይላል፡፡

አለን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የሕግ የበላይነት ጉዳይ ይመለከተናል የሚሉ አካላት  በሙሉ ለተግባራዊነቱ መረባረብ አለባቸው፡፡ የሕግ የበላይነትን የሚያኮስሱ ድርጊቶች በየቦታው ስለሚታዩ ሕግ እንዲከበር ዜጐች በሙሉ ድምፃቸውን ማሰማት አለባቸው፡፡ በሕጋዊነት ሽፋን ሕገወጥ ተግባራት እየተፈጸሙ የሕግ የበላይነት ሲሸረሸር በአገር ላይ እንደተቃጣ አደጋ ሊሰማን ይገባል፡፡ የሕግ የበላይነት በሌለበት ሰላም፣ ዴሞክራሲ፣ ሰብዓዊ መብትና ብልፅግና አይኖሩም፡፡ የሕግ የበላይነት በሌለበት ስለመልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ መነጋገር አይቻልም፡፡  የሕግ የበላይነት በሌለበት ስለአገር ፍቅር፣ መከባበር፣ መቻቻልና በሰላም አብሮ መኖር ማሰብ ከቶውኑም አይቻልም፡፡ የሕግ የበላይነት ሲኖር ግን ሁሉም ነገር ይኖራል፡፡ 

ስለዚህ ለሕግ የበላይነት መከበር ትኩረት ይሰጥ!

ሪፖርተር

ኢትዮጵያ ከግብፅ ጋር የተስማማችባቸውና ያልተስማማችባቸው ነጥቦች ይፋ ተደረጉ

ኢትዮጵያ ከግብፅ ጋር የተስማማችባቸውና ያልተስማማችባቸው ነጥቦች ይፋ ተደረጉ

December 25/2013
ግብፅ የቅኝ ግዛት የውኃ ኮታዋ እንዲከበር አሁንም ጠይቃለች
•ለመስማማት የገባችውን ቃል አፍርሳለች
የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የህዳሴውን ግድብ ግንባታ በተመለከተ ከግብፅና ከሱዳን መንግሥታት ጋር እያደረገ የሚገኘውን ድርድር ውጤት አስታወቀ፡፡ የግብፅ መንግሥት ያቀረባቸው የግዴታ ሐሳቦች በኢትዮጵያ በኩል ተቀባይነት አላገኙም፡፡ 
የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከግብፅና ከሱዳን አቻ ሚኒስቴሮች ጋር በህዳሴው ግድብ ላይ እያደረጋቸው የሚገኙ ድርድሮችን ማክሰኞ ዕለት ለባለድርሻ አካላትና ለመገናኛ ብዙኃን ሲያሳውቅ፣ ኢትዮጵያ ከግብፅ ጋር የተስማማችባቸውንና ያልተስማማችባቸውን ነጥቦች ይፋ አድርጓል፡፡ 
በሚኒስቴሩ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈቅ አህመድ ባቀረቡት ጽሑፍ፣ ሚኒስቴሩና ብሔራዊ የባለሙያዎች ቡድን ሥልታዊና የተጠና እንቅስቃሴ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጐን እንድትቆም ማስቻሉን ገልጸዋል፡፡
ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ባለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ ያቀረበው የመፍትሔ ሐሳብ ሪፖርትን ኢትዮጵያና ሱዳን መቀበላቸውን የገለጹት አቶ ፈቅ፣ ይህ ሪፖርት በግብፅ በኩል ተቀባይነትን ያላገኘ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ 
ነገር ግን የኢትዮጵያና የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባለፈው ዓመት መጨረሻ በአዲስ አበባ ተገናኝተው በተስማሙት መሠረት፣ የሦስቱ አገሮች የውኃ ሚኒስትሮች በቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ተግባራዊነት ላይ ውይይት መጀመራቸውን ገልጸዋል፡፡ 
በጥቅምት ወር መጨረሻ ሱዳን የተገናኙት የሦስቱ አገሮች ሚኒስትሮች በመፍትሔ ሐሳቡ ተግባራዊነት ላይ በመወያየት የሚያመቻችና የሚከታተል ኮሚቴ ለመመሥረት በሐሳብ ደረጃ መስማማታቸውን፣ ነገር ግን በኮሚቴው አባላት ስብጥር ላይ መግባባት ባለመቻላቸው ውይይቱ ተቋርጦ ለሌላ ጊዜ መተላለፉን አስታውሰዋል፡፡ 
የኮሚቴው አባላት ሙሉ በሙሉ የሦስቱ አገሮች ባለሙያዎች ብቻ መሆን አለባቸው በሚለው የኢትዮጵያ ፍላጎት መኖሩና በግብፅ በኩል የውጭ ባለሙያዎች እንዲካተቱ አቋም መያዙ፣ የልዩነቱ ምክንያቶች እንደነበሩ አቶ ፈቅ ገልጸዋል፡፡ 
ይህንን ልዩነት ለመፍታት ከተያዘው ቀጠሮ ቀደም ብሎ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የኢትዮጵያና የሱዳን የጋራ ኮሚሽን ዓመታዊ ጉባዔን ምክንያት በማድረግ ወደ ሱዳን ማቅናቱንና በወቅቱም በሦስቱ አገሮች ድርድር ላይ የሱዳን መንግሥት የኢትዮጵያን አቋም እንዲረዳ ማድረግ መቻሉን አስረድተዋል፡፡ 
የሱዳን የውኃና የኤሌክትሪሲቲ ሚኒስትር መንግሥታቸው የኢትዮጵያን አቋም ሙሉ በሙሉ ከመቀበል ባለፈ፣ በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል የማግባባት ሚና እንደሚኖራት በመተማመን ሁለተኛው የሦስቱ አገሮች ድርድር ከመጀመሩ ቀናት በፊት ወደ ግብፅ ማቅናታቸውን ገልጸዋል፡፡ 
የሱዳን ሚኒስትር በካይሮ ቆይታቸው ከግብፅ ባለሥልጣናት ጋር በመገናኘት የኢትዮጵያን አቋም ማስረዳታቸውንና የግብፅ መንግሥት የኢትዮጵያን ሐሳብ እንደሚደግፍ ተገልጾላቸው መመለሳቸውን አስረድተዋል፡፡
‹‹ግብፅ የህዳሴው ግድብ ከፍታ ዝቅ ይበል የሚል ሐሳቧን፣ እንዲሁም ኢትዮጵያ የገንዘብ ብድር እንዳታገኝ የማደርገውን ሩጫ አቆማለሁ በማለት ለሱዳኑ ሚኒስትር ቃል ገብታ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ሁለተኛው ዙር ድርድር እንዲቀጥል ተደርጓል፤›› ያሉት አቶ ፈቅ፣ በዚህ ድርድር ላይ ግብፅ ይዛ የቀረበችው ሰነድ ከገባችው ቃል የተለየ ነበር ብለዋል፡፡ 
በግብፅ በኩል ለሁለተኛው ዙር ድርድር የቀረበው ሰነድ በሦስቱ አገሮች የሚቋቋመው ኮሚቴ በኢትዮጵያ በኩል የሚገኙ አዳዲስ የጥናት ውጤቶችን እንዲዳስስና የህዳሴውን ግድብ ግንባታ ኮሚቴው እንዲከታተል ይጠይቃል ብለዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የታችኛው የዓባይ ተፋሰስ አገሮች ማለትም የግብፅና የሱዳን የውኃ ደኅንነትና ፍላጐት ሙሉ በሙሉ መከበር አለበት የሚሉ ነጥቦችን በድጋሚ በሰነዱ አካታ ማቅረቧን ገልጸዋል፡፡ 
‹‹ይህንን በጭራሽ ኢትዮጵያ የምትቀበለው አይደለም፤›› ያሉት አቶ ፈቅ፣ በዚህና በሌሎች የመወያያ ነጥቦች ላይ ትኩረት በማድረግ ውይይቱ እንዲቀጥል ለማድረግ እንደተሞከረ ገልጸዋል፡፡ 
በውይይቱ ላይ ግብፅ ከ20 በላይ ባለሙያዎችን እንዳሳተፈች በኢትዮጵያ በኩል ግን ስድስት ባለሙያዎች እንደተወከሉ የሚናገሩት ዳይሬክተሩ፣ በግብፅ በኩል ሆን ተብሎ ውይይቶችን እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ በማጓተት ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎችን የማዳከም ጥረታቸው ውጤት አልባ እንዲሆን በጥንካሬ መሠራቱን ገልጸዋል፡፡ በዚህም ጥረት በሚመሠረተው ኮሚቴ አባላት ስብጥር ዙሪያ ኢትዮጵያ ያቀረበችው ሐሳብ ተቀባይነት ማግኘቱን አቶ ፈቅ ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የኮሚቴው በሚቋቋምበት ዓላማና በተወሰኑ የኮሚቴው ተግባርና ኃላፊነቶች ላይ ኢትዮጵያ ያቀረበቻቸው ሐሳቦች ተቀባይነት ማግኘታቸው ታውቋል፡፡
ኮሚቴው ከዚህ ቀደም በዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን የቀረበውን የመፍትሔ ሐሳብ ተግባራዊነት የመከታተል ዓላማ የሚኖረው በመሆኑ፣ እስካሁን በሦስቱ አገሮች ተቀባይነት ካገኙ የኮሚቴው ተግባርና ኃላፊነቶች መካከል ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ያቀረባቸው ሁለት የመፍትሔ ሐሳቦችን ማስጠናትና የጥናት ውጤቱን ማፀደቅ ይገኝበታል፡፡ ዓለም አቀፍ የባለሙያዎቹ ቡድን ባቀረባቸው ሁለት ሐሳቦች በግድቡ ላይ ተጨማሪ የኃይድሮሎጂ፣ የአካባቢያዊና ማኅበራዊ ጥናቶች እንዲደረጉ ጠይቋል፡፡ 
በመሆኑም ኮሚቴው ለሁለቱ ጥናቶች አማካሪ ድርጅቶችን መቅጠርና ማስጠናት፣ የጥናቱን ሪፖርት መገምገም፣ ማስተካከልና ማቅረብ፣ በዚህ የጥናት ሪፖርት ላይ የኮሚቴው አባላት መግባባት ካልቻሉ ጉዳዩ ለሚኒስትሮች ቀርቦ እልባት እንዲያገኝ፣ በዚህ ካልተፈታ ዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ሙያዊ አስተያየት እንዲያቀርቡ የሚረዳ የቅጥርና የሥራ ዝርዝር ኮሚቴው እንዲያዘጋጅ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ በቀሩ ጉዳዮች ላይ ለመወያየትም ሦስቱ ሚኒስትሮች በቀጣዩ ሳምንት መጨረሻ በሱዳን ተገናኝተው ስምምነት ባልተደረሰባቸው ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በአማካሪ የሚጠኑት ሁለት ጥናቶች ሪፖርት ግምገማ ላይ የኮሚቴ አባላቱም ሆኑ ሚኒስትሮቹ መስማማት ካልቻሉ፣ ሙያዊ አስተያየት የሚሰጥ አማካሪ ለመቅጠር ስምምነት ተደርሷል፡፡ ነገር ግን ሙያዊ አስተያየት የሚሰጠው አማካሪ ቡድን ቅጥር የሚፈጸመው በሦስቱ አገሮች ባለሙያዎች ስምምነት ነው የሚለው ላይ ከስምምነት አልተደረሰም፡፡ ሙያዊ አስተያየት እንዲሰጥ የሚቋቋመው ቡድን በጥናቶቹ የመጨረሻ ሪፖርት ላይ ብቻ አስተያየቱ ይወሰናል በሚለው የኢትዮጵያ አቋም ላይ ያለውን አለመግባባት መቅረፍ ሌላው የውይይቱ አካል ነው፡፡ 
እስካሁን የተደረጉ ድርድሮችን ውጤቶቹን ይፋ ለማድረግ በተዘጋጀው ውይይት ላይ የተገኙት የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አቶ ዓለማየሁ ተገኑ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዚህ ትልቅ አገራዊ ጉዳይ ላይ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ በእጅጉ አድንቀዋል፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አድማሱ ፀጋዬ በበኩላቸው፣ የህዳሴው ግድብ ፕሮጀክት የትኞቹንም የተፋሰስ አገሮች እንደማይጐዳ ለማሳወቅ ዩኒቨርሲቲው በአገር ውስጥ እያደረገ የሚገኘውን እንቅስቃሴ በማስፋት ወደ ጐረቤት አገሮች እንደሚዘልቅ አስረድተዋል፡፡ በዚህም መሠረት በመጪው መጋቢት ወር በሱዳን ሲምፖዚየም ለማዘጋጀት ከካርቱም ዩኒቨርሲቲ ጋር ስምምነት መፈረሙን ገልጸዋል፡፡ 
ሪፖርተር

‹‹በታማሚዎች መነገድ ስንት ያተርፋል?›› (ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ – ከቃሊቲ እስር ቤት)

December 24/2013

“ፀሐይ በሞቀው…” የፍርድ ሂደት ራሴን ለመከላከል አቅርቤው ከነበረው የተከሳሽ የመከላከያ ቃል በኋላ ዳግም ድምጼን ለማሰማት የተመለስኩበት አጋጣሚ ለወራት ሲያሰቃየኝ ለቆየው የኩላሊት ሕመሜ የቃሊቲ ማ/ቤት “የጤና ባለሙያዎች” ምንም ሕክምና ሊሰጡኝ እንደማይችሉ መሆኑ ቅር ያሰኘኛል፡፡ ጥልቅ ፍቅር እና ክብር ላለኝ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ከመልካም ዜና ጋር ብመጣ እንዴት ደስ ባለኝ ነበር፡፡ አልሆነማ!
ጉዳዩን የበለጠ ግልፅ ለማድረግ በተደረገልኝ የኩላሊት የአልትራሳውንድ ምርመራ በተለይ በግራ ኩላሊቴ ላይ በአሳሳቢ ሁኔታ እጅግ የተከማቸ አሸዋ መኖሩ ተረጋግጧል፡፡ በግራም በቀኝም ያሉ ወገኖች ይህን በማንኛውም ጊዜ መመልከት ይችላሉ፡፡ (ለጠላትም ለወዳጅም አላልኩም፡፡ ምክንያቱም በግራና በቀኝ በተሰለፉት ውድ ኢትዮጵያውያን መካከል እየከረረ የመጣ የሀሳብና የመስመር ልዩነት እንጂ ጠብታ የጠላትነት መሰረት እንደሌለ ታሪክና እውነት ይመሰክሩልናል፡፡) ለማንኛውም የቃሊቲዎቹ ሐኪሞች ስቃዬ ሊሰማቸው አልቻለም፤ ወይም አልፈለጉም፡፡ ከቶ ለምን ይሆን?
ይህን አስደማሚ የሰቆቃ ድራማ ከጀርባ ሆኖ እየመራ ያለው ባለ እጀ ረጅሙ ማን ይሆን? ለመሆኑስ አማራጭ በሌላቸው ታማሚዎች ጤንነት መነገድ ስንት ያተርፋል? ምን ይሉት ርካታስ ያጐናፅፋል? ከእኛ ስር የበቀለው የነገይቱ ኢትዮጵያችን ተረካቢ ትውልድስ ይህን አስፀያፊ ድርጊት እንዴት ይመለከተዋል ትላላችሁ? ሁላችንንም ቸርና ፍፁም የሆነው እግዚአብሔር ይርዳን፡፡
በተለይ እኔ ባለሁበት የእስርና የጤንነት ሁኔታ ላይ የሚገለፅ ሀሳብ ስሜታዊነት ሊንፀባረቅበት ቢችል ትረዱኛላችሁ ብዬ አምናለሁ፡፡ ሌሎችን ለመውቀስም፣ የጥላቻ ስሜትንም ለመግለፅ ተደርጎ እንዳይወሰድብኝም በትህትና እጠይቃለሁ፡፡ ክብርና ፍቅር የሚገባችሁ ውድ ኢትዮጵያዊያን በግሌ የእስር ቆይታዬ በነፍሴ ውስጥ እንደ ውቅያኖስ የጠለቀ ፍቅርና የእናንተን አጋርነት በማይነጥፍ አሳቢነት አገኘሁበት እንጂ ጥላቻን አልተማርኩበትም፡፡
እኛ ኢትዮጵያዊያን ነን፡፡ የታሪክ፣ የእምነት፣ የወግና የባሕል በአጠቃላይም የማንነት ፅኑ መሰረት አለን፡፡ ትናንት የመጣን ነገ የምንሔድ አይደለንም፡፡ እንኖራለን፤ ቢያንስ ትውልድ ይኖራል፡፡ ታዲያ እንዴት ህክምና በመንፈግ፣ ከቤተሰብ አርቆ በማሰር (የሁለትዮሽ እንግልት ለመፍጠር በማሰብ) ይህን ማንነት እንጣው? አይሆንም!
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ፡፡
አክባሪ ወንድማችሁ ውብሸት ታዬ /ከቃሊቲ እስር ቤት/፤

Tuesday, December 24, 2013

ሰማያዊ ፓርቲ በአስቸኳይ የግንፍሌውን ጽ/ቤት እንዲለቅ ትእዛዝ ተሰጠው

December 24/2013
Blue Party office
Blue Party office




















ሰማያዊ ፓርቲ ግንፍሌ አከባቢ የሚገኘውን እና በጽ/ቤትነት የሚጠቀምበትን ቢሮ በዛሬው እለት ከሰኣት በኋላ አቶ ሄኖክ የተባሉ አከራዩ ከ አራት ትግሪኛ ተናጋሪ ግለሰቦች ጋር በመምጣት ቤቱን ለነዚህ ግለሰቦች ስለሸጥኩላቸው እንድትለቁላቸው ሲል አሳስቧል:፡ “ቤቱን ገዛሁት” የሚለው ትግሪኛ ተናጋሪ ግለሰብ ቤቱን የገዛሁት ስለሆነ በአስቸኳይ እንድትለቁ ካልሆነ የራሴን እርምጃ እወስዳለሁ ሲል አመራሮቹ ላይ ዝቷል::

ይህ ገዛሁት የሚለው ግለሰብ በማይመለከተው ጉዳይ በመግባት ከዚህ በፊት ልቀቁ ተብላችሁ በተደጋጋሚ እንደተነገራችሁ መረጃው አለኝ በማለት በአመራሮቹ ላይ ቁጣ የተቀላቀለበት ዛቻ በመዛት ሄዷል:; በወቅቱ ይዞት የነበረው ተሽከርካሪ ጥቁር የደህነንት መኪና የሆነች ቶዮታ ኤክስኪዩቲቭ ሲሆን የታርጋ ቁጥሩም ኮድ 2-89176 የሆነ ነው::
ሰማያዊ ፓርቲ ከዚህ ቀደም በመነን አከባቢ ተከራይቶት የነበረውን ጽ/ቤት ገና ሳይገባበት በዝግጅት ላይ እንዳለ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ፖሊሶች እና ቅጥረኞች ተባብረው በተቀናጀ አፈና ቢሮውን መንጠቃቸው ይታወቃል:: የነጠቁትንም ቢሮ ለካድሬያቸው በመስጠት ፔንሲዎን ከፍቶ እየሰራበት ይገኛል::
ምንጭ፡ ሰማያዊ ፓርቲ ብሎግ

Members of the Muslim Arbitration Committee say they were ‘tortured’

ESAT News
December 24, 2013
The members of the Ethiopian Muslims Arbitration Committee that have been detained since last year have said that they were ‘physically and mentally tortured’ in the Central Prison, Addis Abeba.
They said they were forced to stand for over 14 hours per day, were lynched wires until their skins bruised,  shackling them,  blindfolding them and beating the soles of their feet, denying them sleep and prayers, disrespecting their religion and grace, forcing them to shave their beard, denying them visitation by their families, solicitors, doctors and religious leaders, forcing them to do difficult exercises, struck their genitals, were threatened that their children will be killed, their wives will be tortured and a bottled water will be hand on his genital to castrate them.
The Committee members said in their statement that although article 18 Sub Article 1 of the Country’s Constitution states “ Everyone shall have the right not to be subjected to cruel, inhuman or degrading treatment or punishment”, they have been tortured throughout the seasons and were forced to ‘admit, speak and sign’.
They said that had spoken out to the Court about the tortures they had gone through in prisons but it had continued as they returned to their cells from court. They said, when they asked for the respect of the Constitution and rights, the tortures responded saying “tear and throw the Constitution, we came here paying sacrifices”.
They said although it is imperative that their court proceedings have been open, they were closed.
The members of the Committee have said that the unity and respect among Muslims and between Christians and Muslims should be protected. They vowed to continue their peaceful struggle and pay all the sacrifices. They also said that they are ready for the next stage of the peaceful struggle.
The Committee also called on the government to stop the inhuman acts committed in central prisons and release prisoners’ of conscience.

የጥራት እና ደረጃ መዳቢ ባለስልጣን መ/ቤት እና ህ.ወ.አ.ት ነጻነት ይበልጣል (ከጀርመን)፡

December 24/2013

ዛሬ ላስነብባችሁ ያሰብኩት  ቀደም ሲል የጥራት እና ደረጃዎች መዳቢ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ተብሎ ይጠራ ስለነበረው  አሁን ለአራት ተከፋፍሎ እንዲጠፋ ስለተደረገ ተቋም ነው፡፡ መስሪያቤቱ ምርት እና አገልግሎችን  በመቆጣጠር የሸማቹን ደህንነት እና ጤንነነት ማስጠበቅ ፤ የገቢና ወጪ ምርቶችን  ጥራት በመከታተል ጉልህ ድርሻ እንዲያበረክት ታስቦ የተቋቋመ ነው፡፡መስሪያቤቱን ለረጅም ዓመታት በበላይነት ይመሩ የነበሩት አቶ መሳይ ግርማ ሲባሉ በውስጡ የፍተሻ እና ካሊብሬሽን አገልግሎት ዳይሬክትሬት፣የሰርተፊኬሽ አገልግሎት ዳይሬክትሬት፣የኢንስፔክሽን አገልግሎት ዳይሬክትሬት፣የደረጃዎች ዝግጅት ዳይሬክትሬት፣ የስልጠናአገልግሎት  ዳይሬክትሬት እና የፋይናንስ ዳይሬክትሬት እና ሌሎች የአገልግጎች ዘርፎች ነበሩት፡፡አቶ መሳይ መስሪያቤቱን ከ16 ዓመት በላይ አስተዳድረዋል፡፡ድንገት ባልተጠበቀ ሰዓት ከአቶ መሳይ እውቅና ውጭ 3 ሰዎች  አቶ ተክኤ ብርሀኔ ከመቀሌ፣አቶ ደቻሳ ጉሩሙ ከጅማ እና አቶ ዳንኤል ዘነበ ከሀረርጌ ተመልምለው  ወደ መስሪያቤቱ ተመደቡ፡፡ሰዎች ሳይፈለጉ መመደባቸው ብቻ ሳይሆን በወቅቱ እንዲከፈላቸው የተፃፈላቸው የደመወዝ መጠንም በመስሪያቤቱ የደመወዝ ስኬል የሌለ፤ ካላቸው የትምህርት እና የስራ ልምድ ጋር ምንም አይነት ዝምድና ስለሌለው አቶ መሳይ መክፈል አልችልም በማለት አንገራገሩ፡፡እነሱ መች የዋዛ ቢሆኑ እና እስከ ጠቅላይ ጽ/ቤት የተዘረጋ ሰንሰለት ስለነበራቸው በስልክ ተደውሎላቸው ሳይወዱ በግድ መክፈል ጀመሩ፡፡ እነዚህ ሰዎች በ2002 ዓ.ም ለሚካሄደው  ምርጫ ቅድመ ዝግጅት እንዲረዳ ከየክልሉ ተፈልገው የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ሀዋርያ ሁነው ወደ ፌዴራል መንግስት የመጡ ናቸው፡፡ተክኤ በስፓርት ፣ደቻሳ በሂሳብ እና ዳንኤል በማኔጅሜንት ተመርቀዋል፡፡ ሲመጡ የሚያርፉበት የኪራይቤቶች የሚያስተዳድረው ሰፋፊ ግቢ የተዘጋጀላቸው ሲሆን ዳንኤል ከአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ጽ/ቤት አጠገብ፤ተክኤ እና ደቻሳ ደግሞ 22 አካባቢ ባለ ሰፋፊ ግቢ እንዲኖሩ ተመቻችቶላቸዋል፡፡ ዋናው  የቅርብ ጊዜ አላማቸውም በ2002 ለሚደረገው ምርጫ የመንግስት ሰራተኛውን ከኢህአዴግ ጎን ማሰለፍ እና ቀጣይ አመራሮችን ማዘጋጀት ነው፡፡ በዚህም መሰረት ባሉበት ቀበሌ በምርጫ ጣቢያ ሀላፊነት ተመድበው ይሰራሉ፡፡በተጨማሪም መንግስት በቢ.ፒ.አር.(business process reengineering) ብሎ ወደፊት ሊዘረጋ ላቀደው የሰራተኞች ማፈኛ መንገድ የራሱን  ታማኝ  የስለላ ሰዎች ወደ መሲሪያቤቱ ያስገባል፡፡ 
የአዲሶቹን ተመዳቢዎች አመጣጥ ተከተሎ በመስሪያ ቤቱ ከፍተኛ የፍረሃት  ድባብ ተፈጠረ፡፡እነሱ ሰራተኞችን ወደሚጭነው ሰርቪስ ሲገቡ አንድም ሰው ትንፍሽ አይልም፡፡የአውቶቡሱ ሰው ሁሉ በጸጥታ ይዋጣል፡፡ጆሮ ጆሮ እያሉ ያንሾካሽካሉ፡፡በእረፍት ሰሀት እነሱ በተቀመጡበት አካባቢ አብሮ ተቀምጦ ሻይ ቡና የሚል የለም፡፡ሲመደቡ የኮሙኒኬሽን ሰራተኞች ተብለው ሲሆን ከመስሪያቤቱ እውቅና ውጭ ከነአቶበረከት ሰምኦን ጋር በየሳምንቱ ስብሰባ እና የመረጃ ልውውጥ ያደርጋሉ፡፡ከሳይንስና ቶክኖሎጂ ሚኒስትሩ አቶ ጁነዲን ሳዶ ጋር ከፈለጉ በአካል መኪና አዝዘው ካልፈለጉ በስልክ በቀጥታ መገናኘት ይችላሉ፡፡አቶ መሳይ እና ሌሎች የመስሪያቤቱ ከፍተኛ አመራሮች የማያውቁት መረጃ ከነሱ ጋ ይገኛል፡፡በዚህ የአንድ አመት ቆያታቸው በመስሪቤቱ ደጋፊዎችን ማፍራት አልቻሉም፡፡
በ2003ዓ.ም የቢ.ፒ.አር ጥናት ሲጀመር አዲስ የመጡት ካድሬዎች  የጥናት ቡድን መሪ እየተባሉ ተመደቡ፡፡ ቢ.ፒ.አር ለመስራት ቀርቶ ስለመስሪቤቱ አሰራር በቂ እውቀት የሌላቸው ሰዎች መስሪያቤቱን አፍርሶ እንደ አዲስ የማደራጀት ስራ በእነዚህ ሰዎች ስር ወደቀ፡፡በዚህም ተቀራራቢ ስራዎችን በጋራ ማደራጀት በሚል ሰበብ ከብሄራዊ የጨረር መከላከያ አንዱን መምሪያ በማፍረስ፤የክሊነር ፐሮደክሽን መስሪያቤትን ሙሉ በሙሉ፤የሳይንስ መሳሪያዎች መስሪያቤትን ሙሉ በሙሉ አፈራርሰው አነዚህን መስሪያቤቶች ከደረጃ መዳቢ ባለስልጣን መስሪያቤት ጋር በማዋሀድ አራት የተለያዩ መስሪያቤቶችን ለመፍጠር ጥናቱ ተጀመረ፡፡ አዲስ የተጠኑት መስሪያቤቶች 1.Meterology institute, 2.Accreditation biro, 3 .Standards agency 4. Conformity assessment enterprise ይባላሉ፡፡ እነዚህ መስሪያቤቶች በተጠኑበት ወቅት ለጥናት ቡድኑ በየሳምንቱ በጣም ውድ በሆኑ ሆቴሎች የእራት ግብዣ  እየተዘጋጀ ለ6 ወር ያክል ተደከመበት፡፡ወደ መጨረሻው ምእራፍ ሲቃረብ  የጥናት ቡድኑ ሙሉ በሙሉ ናዝሬት ውስጥ ከ10 ቀን በላይ ሆቴል ውስጥ ተቀምጠው እንዲሰሩ ተደረገ፡፡በመጨረሻም የጥናቱን መጠናቀቅ አስመልክቶ  በአቶ ጁነዲን ሳዶ አማካነት አርባምንጭ ለሶስት ቀናት ድል ያለ ግብዣ ተደረገ፡፡ከአርባምንጭ መልስ ሁሉም በሳይንስ እና ቴክኔሎጂ ሚ/ር ስር የሚገኙ ሰራተኛ  ለገሀር በሚገኘው የመንገድ እና  ትራንስፖርት መሰብሰቢያ አዳራሽ ጠቅላላ ስብሰባ ተካሄደ፡፡በስብሰባው የየጥንት ቡድኑ ሀላፊዎች የጥናታቸውን ውጤት ይፋ አደረጉ፡፡የሀገራችን ችግሮች ተዳሰሱ፡፡ለችግሮች መፍትሄ ይሆናሉ የተባሉ አማራጮች ከየአቅጣጫው ጎረፉ፡፡አብዛኞች ወጣቶች ተስፋ ያደረጉትን በየመስሪያቤቱ ያለውን ብልሹ አሰራር እንዴት ማስወገድ እንደሚቻል አስተያየታቸውን ሰጡ፡፡በዚህ ውይይት ከተነሱት ውስጥ እስካሁን የማሰታውሳቸው አቶ ገብረጊዳን ገብረመስቀል በቅጽል ስሙ(GG) “በየመስሪያቤቱ ያለውን የተማረ የሰው ሀይል  እጥረት ለመቅረፍ መንግስት በውጪ የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ገብተው እንዲሰሩ ቢደረግ መልካም ነው፡፡ለምሳሌ እንደ ኢንጅነር ቅጣው እጅጉ አይነት ሰዎች ነበሩዋት ሌሎችም እንዲህ አይነቶች ይኖራሉ ብሎ ተናገረ፡፡”በእረፍት የንግድ ሚኒስትሩ የአቶ ታደሰ ሐይሌ ባለቤት ወ/ሮ አልማዝ ካህሳይ ይህን የተናገረውን ልጅ ጠራቸው እና ስሙን ጠይቃ “አንተማ የእኛው ነህ እየውልህ ኢ/ር ቅጣው በመንግስታችን ላይ ሊሰራ አቅዶት የነበረውን ስለማታውቅ ነው እንዲህ ያልከው፡፡በቶሎ ቀጨው እንጂ ቢቆይ በጣም አደገኛ ነበር፡፡እንዲህ አይነቱን ሰው ስሙን መጥራት የለብህም” አለችው፡፡ይቅርታ ወ/ሮ አልማዝ እኔ እሱን አላውቅም ነበር ሲል መለሰላት፡፡ሌላው ከጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት የመጣ  አቶ ጸጋዬ የሚባል አንድ ተናጋሪ በንግግራቸው መሀል ጣል ያደረጉዋት ቀልድ መሰል መልክት ሁሌም ትከነክነኛለች፡፡አቶ ጸጋዬ “አማርኛ እጅዋን አገኘች በግል ትምህርት ቤት ውስጥ አማርኛ መናገር እና ድንጋይ መወርወር ያስቀጣል ተብሎ በጉልህ ተጽፎ አንድ ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ አንብቤያለሁ” ብለው አረፉ፡፡ሌላው ጠያቂ አብዲ ዱጋ ይባላል፡፡አብዲ ጥያቄውን ያቀረበው ለሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ ነው፡፡ጥያቄው “ኦሮሚያ ክልል ውስጥ አየተካሄደ ያለው የአበባ እርሻ ልማት የአካባቢውን አፈር እና ውሃ እየበከለው ነው፡፡በዚህም የተነሳ እንስሳት ይሞታሉ ሰዎች ይታመማሉ፡፡የሰራተኞችም ህይወት አደጋ  ውስጥ ነው  የሚከፈላቸውም ገንዘብ እዚህ ግባ የሚባል አደለም፡፡እንዲያውም  ባለ ሀብቶች ከሌሎች ሀገሮች ሲባረሩ ነው ወደዚህ ሀገር የመጡት ይባላል እና ይህን እንዴት ያዩታል? ሲል ጠየቀ፡፡አብዲን የገጠመው ከፍተኛ ውግዘት ነው፡፡ለውግዘቱ መነሻም በወቅቱ የአበባ እርሻ ልማት ሲጀመር አቶ ጁነዲን የኦሮሚያ ርእሰመስተዳድር ስለነበሩ እሳቸውን እንደተቃወመ ተቆጠረ፡፡አብዲም ያጠናው ባዮሎጂ ስለነበር ሙያዊ ትንታኔ መስጠቱን ቀጠለ፡፡ክርክሩ እየከረረ ሲሄድ ጓደኞቹ ዝም እንዲል አደረጉት፡፡ስልጠናው ለ5 ቀናት በፍረሃት እንደተዋጠ ተጠናቀቀ፡፡ከዚህ ሰብሰባ መልስ በቀጥታ ሁሉም መስሪያቤት ወደ ሰው ኃይል ምደባ እንዲገባ መመሪያ ተላላፈ፡፡
ስብሰባው አርብ ተጠናቆ ሰኞ ጠዋት አቶ መሳይ ከመስሪያቤቱ በፍቃዳቸው እንዲለቁ  ትእዛዝ እንደተሰጣቸው  ለሚቀርቡዋቸው ሰዎች  ሲናገሩ የኮሚኒኬሽን ሰራተኞቹ እነ ተክኤ ደግሞ  ምደባውን እንዳያስተጉዋጉል በማሰብ አስቀድሞ መባረሩን በየቢሮው እየዞሩ ያውጃሉ፡ይህን ተከትሎ መስሪያቤቱ ሰው የሞተ ያክል በኡኡታ በልቅሶ ታመሰ፡፡አብዛኖች መልካም ተግባሩን ለሰራተኛ አዛኝነቱን እያሰቡ አባታቸውን በሞት የተነጠቁ ያክል ከልብ አዘኑ፡፡በዚሁ እለት የንግድ ሚኒስትሩ የአቶ ታደሰ ሀይሌ ባለቤት ወ/ሮ አልማዝ ካህሣዬ መስሪያቤቱን እንዲያስተዳድሩ ተሾሙ ፡፡የተለያዬ ዳይሬክተሮችን ሹመት ሰጡ፡፡በዚህ ወቅት ቀደም ሲል ወያኔን እንደሚቃወሙ የሚታወቁት እና ከአቶ መሳይ ጋር ቀረቤታ አላቸው የተባሉ ነባር ዳይሬክተሮች ተነስተው በምትካቸው የኢህአዲግ አባላትን መመደብ ተጀመረ፡፡ ምደባውም የሚካሄደው እያንዳንዱ ሰራተኛ እየተገመገመባለው ችሎታ ነው ይባል እንጅ ነገር ግን አስገራሚው እና ያን ያክል የተደከመበት ጥናት የግምገማውን 75% የሚይዘው  ከስራው ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው አመለካካት የሚባል ነገር ነው፡፡ሰራተኞች በወቅቱ ያነሱት የነበረው ጥያቄ አመለካከት በምን ሊለካ ይችላል የእኔን አመለካካት ምን እንደሆነ ማን ያውቀዋል የሚል ነበር፡፡ ግምገማውን የሚሞሉት ቀደም ብየ የጠቀስኳቸው እነ ተክኤ፣ደቻሳ እና ዳናኤል ናቸው፡፡እነዚህ ሰዎች እንደመሰላቸው የግምገማ ነጥቡን መስጠታቸው ሳያንስ ምደባውን በዋናነት የሚመሩት እነሱ ናቸው፡፡ወደ ደረጃ መዳቢ መስሪያቤት የመጡትን የሌላ አዳዲስ  መስሪያቤት ሰራተኞች መልካቸውን ሳይቀር የማያውቁዋቸውን ሰዎች ግምገማ በድፍረት ይሞሉ ነበር፡፡በመሀል በተቃዋሚነት ያልተፈረጁትን እና አባል መሆን የሚፈልጉ ካሉ በምደባ እና በእድገት አያባበሉ ወደ ድርጅቱ የማግባባት ስራ ተከናወነ፡እኔ ስራየን እንጂ የፓርቲ አባል መሆን ፍላጎት የለኝም ያሉት ደግሞ ቀደም ሲል በተለያዩ የውጭ ሀገራት ሳይቀር ከፍተኛ ስልጠናዎችን ተከታትለው ስራቸውን በብቃት ሲወጡ የነበሩ በርካታ ባለሙያዎች አብዮታዊ ዲሞክራሲን ባለመቀበላቸው ብቻ  ዘራቸው እየታየ ከስራቸው ከተባረሩት መካከል ከዚህ  በታች የተዘረዘሩት ለማሳያ ያክል የቀረቡ ሲሆኑ አንድም የትግራይ ብሄር  ተወላጅ አለመባረሩን አንባቢያን ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ሌላው እና አስገራሚው ነገር በወቅቱ  የኦሮሞ ብሄር ተወላጆችን እያገለለ እየተካሄደ ያለው ምደባ ያሳሰባቸው የኢህዴድ አባላት ጥያቄያቸውን ለሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ ቢያቀርቡም ወ/ሮ አላማዝ ካህሳይ እያንዳንዱን ኦሮሞ እቢሮአቸው ጠርተው አርፈው እንዲቀመጡ አለዚያ እንደሚባረሩ በዛቻ ገልጸውላቸዋል፡፡በወቅቱም ከፍተኛ ተቃውሞ ያሰማው አቶ ሙሉጌታ መኮነን ያለስራ ለአንድ ዓመት ደመወዝ ብቻ እየተከፈለው ሊሰራ በማይችል ዘርፍ የቡድን መሪ ሁኖ ሲመደብ በስሩ ግን ምንም ሰው አልነበረም፡፡
ተ.ቁ           ስም    የነበራቸው ሀላፊነት
ብሄር
1አቶ መሳይ ግርማየጥራት እና ደረጃ መ/ቤት ዋና ዳይሬክተር
ኦሮሞ
2አቶ ጋሻው ወርቅነህየጥራት እና ደረጃ መ/ቤት ምክትል ዳይሬክተር
አማራ
3አቶ ተፈራ ማሞየኤሌክትሪክል ላብራቶር  ሃላፊ
ኦሮሞ
4አቶ ሀይሉየመሳሪያ ጥገኛ አገልግሎት ሃላፊ
ኦሮሞ
5አቶ ደሬሳ ፉፋየሰርተፊኬሽን አገልግሎት ዳይሬክተር
ኦሮሞ
6አቶ መስፍንየስልጠና አገልግሎት ዳይሬክተር
አማራ
7አቶ አዱኛው መስፍንየጥራት ማኔጅሜንት አሰልጣኝ
አማራ
8አቶ እንዳየኢንፎርሜሽን አገልግሎት ሀላፊ
አማራ
9አቶ አመሃ በቀለየጥራት ማኔጅሜነት አሰልጣኝ
አማራ
10አቶ ሂርጳየጥራት ማኔጅሜነት አሰልጣኝ
ኦሮሞ
11አቶ መረሳየሰርትፊኬሽን ኤክስፐርት
ኦሮሞ
12አቶ ቴወድሮስ ዘካሪያስየፍተሻ ላብራቶር ኤክስፐርት
አማራ
13አቶ  ልኡልየባህርዳር ቅርንጫፍ  ሀላፊ
አማራ
14 የሰርትፊኬሽን ሲስተም ኦዲተር የነበሩት
ኦሮሞ
15 የድሬደዋ ቅርንጫፍ ሀላፊ የነበሩትአማራ
16 የናዝሬት ቅርንጫፍ ሀላፊ የነበሩትኦሮሞ
17 የሀዋሳ  ቅርንጫፍ ሀላፊ የነበሩትደቡብ
ታማኝ የህወአት አባላት  በባትሪ  ከሌላ ቦታ ተፈልገው ያለ ልምድ  እና ችሌታቸው  በከፍተኛ አመራርነት ሲመደቡ የተለሳለሰ አቋም ያላቸውን እና የአባልነት ጥያቄ ሲቀርብላቸው ጥያቄውን የተቀበሉ ነባር የመስሪያቤቱ ሰራተኞች የፍርፍሪው  ተቋዳሽ ሁነዋል፡፡በዚህ ምደባ እስከቡድን መሪ ያለው ሀላፊነት ያለ ፓርቲ አባልነት ወይም ያለ ትግራይ ተወላጅነት በምንም መልኩ ለተራው ሰራተኛ አይሰጥም፡፡
ተ.ቁ ስም  ቀደም የነበራቸው ሀላፊነትአሁን የተሰጣቸው ሀላፊነትብሄር
1ወ/ሮ አልማዝ ካህሳየየኢንስፔክሽን አገልግሎት ዳይሬክተርየደረዳዎች ዋና ዳይሬክተርትግሬ
2አቶ ወንዶሰን ፍስሃየካሊብሬሽን አገልግሎት ሀላፊ የሜትሮሎጂ ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተርትግሬ
3አቶ አርአያመከላከያ ኢንጅነሪንግየአክረዲቴሽን ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተርትግሬ
4አቶ ጋሻው ተስፋዬየፍተሻ ላብራቶር ኤክስፐርትየተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተርትግሬ
 አቶ ገብሬኝግድ እና ኢንዱስትሪ ኤክስፐርትበደረጃዎች ኢጀንሲ ዳይሬክተርትግሬ
6አቶ ብርሀኑ ተካ ረዳየፋይንነስ አስተዳደር ዳይሬክተርየተስማሚነት ምዘና ድርጅት የፋይናንስ ዳይሬክተርጉራጌ
7ወ/ሮ ገነት ገ/መድህንየፍተሻ እና ካሊብሬሽን  አገልግሎት ዳይሬክተርየአክረዲቴሽን ጽ/ቤት ዳይሬክተርትግሬ
8ወ/ሮ ብርሀን ብሂልየአዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጸሀፊየተስማሚነት ምዘና ድርጅት የሰው ሀብት እስተዳደር ሀላፊትግሬ
9አቶ ብርሀኑ ተካየሰርቪስ ሹፌርየተስማሚነት ምዘና ድርጅት የተራንስፖርት መምሪያ ሀላፊትግሬ
10አቶ ተክኤ ብርሀኔየኮሙኒክሽን ሰራተኛየተስማሚነት ምዘና ድርጅት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተርትግሬ
11አቶ ዳዊት የሰርቪስ ሹፌርየሜትሮሎጂ ኢንስቲቲዩት የትራንትፖርትመምሪያ ሀላፊትግሬ
12አቶ ጸጋዬኢንስፔክተርየአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ሀላፊትግሬ
13አቶ ዘነበኢንስፔክተርየገበያ ጥናት ሀላፊትግሬ
ቀደም ሲል እንደማናኛውም ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳሉ የመንግስት መስሪያቤቶች የሚታዩ ችግሮች ቢኖሩም የተወሰደው እርምጃ ግን የወቅቱን የትግሬዎች የንግድ እንቅስቃሴ ያላንዳች ተቆጣጣሪ እንደፈለጉት ለማሽከርከር ታስቦ አንደሆነ ይታወቃል፡፡ለዚህም መነሻ የሚሆነው በተለያዩ ጊዜያት በቆርቆሮ፣በብረታብረት፣በማዳበሪያ፣በሳሙና፣በከብሪት፣በሲሚንቶ ፣በዘይት፤በጨርቃ ጨርቅ ፣ በባትሪ ድንጋይ፣በኤሌክትሪክ ገመዶች የመሳሰሉት ምርቶች ላይ ተደጋጋሚ ችግር ተከስቶ በበላይ አካል የስልክ ትእዛዝ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ምርቶች ለህብረተሰቡ እንዲሰራጩ ተደርጉዋል፡፡ለአብነት ያክል የአቢሲኒያ ሲሚንቶ ፋብሪካ በጥራት ጉድለት ምክንያት እንዳያመርት አገዳ መስሪያቤቱ ሲያስተላልፍ በወቅቱ የከተማ ሚኒስትር የነበሩት ዶ/ር ካሱ ኢላላ  ፍተሻውን ያከናወኑ ባለሙያዎችን በግላቸው ቢሮ ድረስ በማስጠራት ትክክል አደላችሁም፤ልማታችንን እያደናቀፋችሁ ነው፤ኢንቬስተሮች ወደ ሀገራችን እየመጡ እንዳይሰሩ መሰናክል እየፈጠራችሁ ስለሆነ አቁሙ ሲባሉ የመስሪያቤቱ ሀላፊዎች እገዳውን ባስቸኩዋይ አንዲያነሱ ቀጭን ትእዛዝ አስተላለፈዋል፡፡መስሪያቤቱም እንዲፈርስ የተደረገው ባለሞያዎችም የተፈናቀሉት ሆን ተብሎ ያለ አግባብ  መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲረዳው ያስፈልጋል፡፡

ከችሎቱ ጀርባ ያለው ጥቁር ዳኛ ማነው? (ክፍል አንድ)

December 24/2013
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥር አስር ቀን 2004 ዓ.ም በእነ ርዕዮት አለሙ ላይ ያስተላለፈው የጥፋተኝነት ውሳኔ በችሎቱ የተሰየሙት ዳኞች በነጻ ህሊና የሰጡት ፍርድ ነው ብሎ ያመነ ሰው አልነበረም፡፡ እዚህም እዚያም ሲወራ የነበረው ውሳኔው በመንግስት ፍላጎት ላይ የተመሰረተ መሆኑ ነበር፡፡ ፕሮፌሰር መስፍንን ጨምሮ በርካታ ሰወች ይህንኑ በአደባባይ ጽፈውታል፡፡ ቆየት ብሎ ግን ዳኛው የተጻፈለትን እንዳነበበ የሚገልጹና ተጨማሪ ነገር ለማወቅ የሚገፋፉ መረጃዎች ወደኔ መምጣት ጀመሩ፡፡
እርግጥ የኢትየጵያ የፍትህ ስርአት በተደጋጋሚ ተፈትኖ የወደቀና ነጻነቱ ጥያቄ ውስጥ የገባ ከመሆኑ አንጻር እንዲህ አይነት የጥርጣሬ ድምጾች መሰማታቸው በራሱ ብዙ የሚገርም አይደለም፡፡ በመሆኑም በጉዳዩ ላይ የምር እንዳስብ የሆንኩት ዳኛው የተጻፈለትን እንዳነበበ በመስማቴ ብቻ አይደለም፡፡ ይልቁንም ከዚያ በፊት በነበረው የፍርድ ሂደት ያስተዋልኳቸው ሦስት አጠራጣሪ ክስተቶቸ ናቸው እንደ ጋዜጠኛም ሆነ እንደ ርዕዮት የቅርብ ሰው ስለ ጉዳዩ ብዙ ለማወቅ እንድታትር የገፋፋኝ፡፡
የመጀመሪያው፣ ርዕዮት በማዕከላዊ ምርመራ ላይ እያለች የታዘብኩት ነው፡፡ ርዕዮት በተያዘች በማግስቱ አራዳ ፍርድ ቤት ቀርባ ፖሊስ የ28 ቀን የምርመራ ጊዜ ሲጠይቅ አባቷና ጠበቃዋ የሆኑት አቶ አለሙ ደግሞ ቤተሰብ እንዲጠይቃትና የህግ ምክር እንድታገኝ አመለከቱ፡፡ ዳኛዋም ፖሊስ ይህንኑ እንዲፈጽም አዘውና የ28 ቀን የምርመራ ጊዜ ሰጥተው ችሎቱ አበቃ፡፡ በዚህ ጊዜ ግን ርዕዮት፣ ጠበቃም ሆነ ቤተሰብ ሳታገኝ 28ቱ ቀን አለፈ፡፡
የነበረው አማራጭ የቀጠሮው እለት ጠበቃዋ ገብተው ድጋሜ እንዲያመለክቱ ማድረግ ብቻ ነበር፡፡ እኛም ፍርድ ቤት ስትመጣ ጠብቀን ቢያንስ አይኗን ለማየት ጓጉተናል፡፡ በዕለቱ የሆነው ግን በጣም አስገራሚም አሳዛኝም ነበር፡፡
ቀጠሮው ከሰዓት በኋላ 8 ሰዓት ነበረ፡፡ በዚያን ዕለት ጠዋት 2፡30 ቁርስ ላደርስላት ወደ ማዕከላዊ ስሄድ ከዚያን ዕለት በፊትም ሆነ በኋላ አይቻት የማላውቃት አንዲት ልጅ “ርዕዮትን በሌሊት ወደ ፍርድ ቤት ወስደዋታል ሮጠህ ድረስባት” ብላኝ ካጠገቤ ብን አለች፡፡ ለአቶ አለሙ በስልክ ይህንኑ ነግሬ ወደ ፍርድ ቤቱ አመራሁ፡፡ ቦታው ቅርብ በመሆኑ 10 ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ደረስኩ፡፡ እኔ ወደ ግቢው ስገባ ርዕዮት በፒካፕ መኪና ተጭና እየወጣች ነበር፡፡
የፍርድ ቤቱ የቀጠሮ ሰዓት የተለወጠው ባጋጣሚ ወይም በስህተት ሊሆን ይችላል በሚል ይህ ለምን እንደሆነ መዝገብ ቤቱን ጠይቀን የተረዳነው ኬዙን ያየችው ዳኛ በህመም ምክኒያት ለረጅም ጊዜ ስራ የምትገባው ከሰዓት በኋላ ብቻ መሆኑንና ሁኔታው ለእነሱም እንግዳ ነገር መሆኑን ነው፡፡ ስለዚህም የቀጠሮው ሰዓት ለውጥ በፖሊስ ፍላጎት ሆን ተብሎ ተፈጽሟል ለማለት ይቻላል፡፡ ይህ ማለት በፍርድ ቤቱና በፖሊስ መሀከል ሊኖር የሚገባው መስመር ላይ ችግር አለ ማለት ነው፡፡
ሌላው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለ5 ወራት ያህል ግራና ቀኙን ሲያከራክር ሰንብቶ ታህሳስ 17 2004 ዓ.ም የመጨረሻውን ፍርድ ለመስጠት በተሰየመበት ዕለት የነበረው ሁኔታ እንዲሁ ጥርጣሬውን የሚያጠናክር ነው፡፡ ቀጠሮው ከጠዋቱ 3፡00 የነበረ ቢሆንም በዚያን ዕለት ይሰጣል የተባለውን ፍርድ ለመስማት የተገኙ ሰዎች የችሎቱን አዳራሽ የሞሉት ቀደም ብለው ነበር፡፡ ዳኞቹ 1 ሰዓት አርፍደው 4፡00 ላይ ችሎቱ ተሰየመ፡፡ ወዲያውኑ ውሳኔው ማለቁንና ይሁን እንጂ በኮምፒውተር ተጽፎ ስላላለቀ ከሰዓት በኋላ እናርገው አሉ፡፡ በዚህ ጊዜ የእነውብሸት ጠበቃ አቶ ደርበው “ከሰዓት ሌላ ቀጠሮ ስላለኝ አልችልም” ብለው ከአራት ቀን በኋላ ለታሀሳስ 21 እንዲሆን አማራጭ አቀረቡ፡፡ ዳኛው ግን አልተቀበሉትም፡፡ “እነዚህ ሰወች ያሉት በማረሚያ ቤት ነው፤ ቀጠሮው ከሚራዘም 7 ሰዓት እንገናኝና እስከ 8፡00 እንጨርሳለን” የሚል አማራጭ አቅረቡና በዚሁ ተስማሙ፡፡
የዳኛው ንግግር የሆነ ጥሩ ነገር ሊኖር ይችላል የሚል ተስፋ ስላጫረብን ሁላችንም ከዚያው ሳንወጣ ሰዓቱ እስኪደርስ መንቆራጠጥ ያዝን፡፡
አይደርስ የለ ሰዓቱ ደርሶ ችሎቱ በሚሰየምበት አዳራሽ ተኮለኮልን፡፡ ዳኞቹ ግን በሰዓቱ የሉም፡፡ ግማሽ ሰዓት አለፈ፤ አልመጡም 8 ሰዓት ሲሆን ሁላችንም ቀጠሮ አለኝ ያሉትን ጠበቃ ደርበውን እያየን መሳቀቅ ያዝን፤ ሰዓቱ እየነጎደ ነው፤ 9 ሰዓት ሆነ፡፡ ዳኞቹም አልመጡም ጠበቃ ደርበውም አልሄዱም፡፡ 9፡45 ላይ ዳኞቹ መጡ፡፡ አቶ ደርበው ግን ቀሩ፡፡
ዳኛው ስለማርፈዳቸው ምንም ሳይሉ አሁንም ጽሁፉ ስላልደረሰ በሚል ተለዋጭ ቀጠሮ ለመስጠት አጀንዳቸውን ማገላበጥ ያዙ፡፡ “አራት ቀን ምን ሲደረግ ይራዘማል” ያሉት ዳኛ ከ23 ቀን በኋላ ለጥር 10 2006ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥተው ዕለቱና ችሎቱ አበቃ፡፡ ተስፋችንም እንዲሁ፡፡
ይህ ሁኔታ አንዳች ደስ የማይል ነገር እየተከናወነ እንዳለ የሚናገር መሆኑ እንዳለ ሆኖ ቀደም ሲል ያነሳነውን ጥርጣሬ ወደ እውነት የሚገፋው ተጨማሪ ክስተት፣ ለቀጠሮው መራዘም ምክኒያት ሆኖ የቀረበው ነገር ነው፡፡ የታህሳስ 17ቱ ቀጠሮ ወደ ጥር 10 የተሻገረው ውሳኔው በኮምፒውተር ተጽፎ አለማለቁ ሆኖ ሳለ ዳኛው ጥር 10 ያነበቡት በኮምፒውተር ያልተተየበ የእጅ ጽሁፍ ነበር፡፡ ስለዚህም የቀጠሮ ለውጡ የተካሄደው ከችሎቱ ጀርባ ባለ ሌላ ምክኒያት እንጂ ዳኛው እንዳሉት የኮምፒውተር ጽሁፍ ጉዳይ አይደለም ለማለት ይቻላል፡፡
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱትና ሌሎችም ትንንሽ የሚመስሉ በርካታ ትዝብቶች ዳኛው የተጻፈለትን እንዳነበበ ከሚገልጸው መረጃ ጋር ተደምረው ሲታዩ የሚሰጡትን ትርጓሜ በማስረጃ ለማረጋገጥ መጠነኛ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡
ይህን ለማረጋገጥ ሁነኛና ቀላል ዘዴ ሊሆን የሚችለው በእለቱ ዳኛው ያነበበውን የእጅ ጽሁፍና የዳኛውን ትክክለኛ የእጅ ጽሁፍ አግኝቶ ማመሳሰል ነው፡፡ በዚሁ መሰረት ይህን ለማድረግ የሚያስችሉ ማስረጃዎች ተገኝተዋል፡፡ ማስረጃዎቹ ዳኛው በዕለቱ ያነበበው ጽሁፍ በራሱ በዳኛው የተጻፈ አለመሆኑን የሚያሳዩ ናቸው፡፡
ቀጣዮቹን ሁለት ምስሎች ይመልከቱ
Sileshi Hagos's photo.
Sileshi Hagos's photo.
Sileshi Hagos's photo.

በእስር ላይ የሚገኙት የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች መግለጫ በድምፃችን ይሰማ ይፋ ሆነ

December 24/2013

በእስር ከሚገኙ የህዝበ ሙስሊሙ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የተሰጠ መግለጫ
ሰኞ ታህሳስ 14/2006

ኢትዮጵያ ከአንድ ሺህ አራት መቶ አመታት በፊት የ21ኛው ክፍለ ዘመን ማህበረሰብ ካሰፈነው ፍትህ የላቀ ፍትህ ማስፈን ችላ ነበር። የወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉስ በነቢዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) አንደበት ‹‹በሐበሻ አንድም ሰው የማይበደልበት ንጉስ አለ›› ተብሎለታል። እንዲህ አይነት ፍትህ በዚህ መልኩ ለማስፈን ምን ያህል ፍትሀዊ፣ እውነተኛ እና የሰለጠነ ማህበረሰብ መገንባት እንደሚጠይቅ ግልፅ ነው። በሀገራችን የነበረው ፍትህ በጊዜው ነፃነት እና ፍትህ ፍለጋ ይዋትቱ የነበሩትን ማስጠለል የቻለ እና ዘመናትን ተሻጋሪ ነበር። ግና የዛሬው አሳዛኝ እውነታ ‹‹ሰዎች ስለ ፍትህ ግንዛቤ ባልነበራቸው በዚያ ዘመን የፍትህ ጥግ የደረሰችው አገራችን ሰዎች ሁሉ ወደ ዲሞክራሲ እና ፍትህ ፊታቸውን ሲያዞሩ ለምን ጀርባዋን ሰጠች?›› ብለን እንድንጠይቅ አስገዳጅ ሆኗል።

ፍትህ ዘመን፣ ቦታና ሁኔታ የማይገድበው፣ በሃይማኖት፣ በሃገርና በብሔር ልዩነት የማይደረግበት፣ ሁሉም ለሁሉም እውን ሊያደርገው መጣር ያለበትና ሰው የመሆናችን ሚስጥር የሚፈታበት ጥልቅ እውነታ ነው። ግና ምድራዊም ሆነ ሰማያዊ ህጎች ፍትህን ቢደግፉትም ቅሉ በተጨባጩ ዓለም ግፍና በደል ተንሰራፍቶ ይገኛል። ቀደም ሲል አምባገነኖች በአደባባይ ይፈፅሙት የነበረውን ግፍ በዘመናችን ቅርፁን ቀይረው ፍትህ፣ ነፃነት እና እኩልነትን እየሰበኩ በተግባር ግን የህዝባቸውን ኑሮ የስቃይ ያደርጉታል።
መንግስት በሚዲያና በየስብሰባው ስለፍትህና ዴሞክራሲ በተደጋጋሚ ቢያነሳም መሬት ላይ ያለው ተጨበጭ ፍፁም ለማመን አዳጋች ነው፡፡ በማንኛውም ዘመን አምባገነኖች እንደሚያደርጉት ሁሉ ሰብዓዊነት የጐደለው ኢ-ፍትሃዊ ተግባር እየፈጸመ ሳለ ‹‹ህዝቡ ቦታ የሚሰጣቸው ሥነ-ምግባሮች፣ ህግጋትና መልካም እሴቶችን ለማስጠበቅ›› ሲባል የተሰራ እንደሆነ አድርጎ ለማቅረብ ይሞክራል። በመብት ትግላችን ሂደት ለሃይማኖታቸው ታማኝ በመሆን የፍትህና የነፃነት ጥያቄ ያነሱ ወገኖቻችን ሁሉ በመንግስት አካላት ስደት፣ እስራትና ሞት የደረሰባቸው ህብረተሰቡ የሚያከብራቸውን ስነ-ምግባሮች፣ እሴቶችና ህግጋት ሽፋን በማድረግ መሆኑ በእርግጥም ምጸት ነው።

ሙስሊሙ ህብረተሰብ ያነሳቸውና በወከላቸው ኮሚቴዎች አማካኝነት ለመንግስት ያቀረባቸው ጥያቄዎች ግልጽ፣ ቀላል፣ ሃይማኖታዊና ህገ-መንግስታዊ መብቶች መሆናቸውን መላው ኢትዮጵያዊና ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ያውቀዋል። መንግስት ግን ለሰው እምነት ከባለቤቱ በላይ ተቆርቋሪ፣ ለሃገር ደህንነትና ሰላም የሚያስብ ብቸኛ አካል እና ህገ-መንግስቱን አክባሪና አስከባሪ እንደሆነ በመደስኮር የመብት ጥያቄያችንን የሀሰት ቅርፅ ሊያስይዘው ሞክሯል። በመሰረቱ መንግስት ኃይልና ጉልበት ያለው አካል ሆኖ ሳለ በተቃራኒው ደግሞ ህዝብ ጉልበት ስለሌለው ሰላምንና ደህንነትን አጥብቆ የሚፈልገው ከመንግስት በላይ ህዝብ ነው። ህገ-መንግስት ደግሞ መንግስት ያለውን ኃይል በመጠቀም ህዝብ ላይ ግፍ እንዳይፈፅም የሚገድብ ህግ እንደመሆኑ በመንግስት እንጂ በህዝብ ሊጣስ አይችልም።

ከጅምሩ መንግስት የሙስሊሙ የመብት ጥያቄ ከጀርባው ምንም ሴራ እንደሌለው የሚያውቅ መሆኑን ብንረዳም በአባላቱም ሆነ በማህበረሰቡ ላይ ብዥታ እንዳይፈጥር ዓላማችንን እና ጥያቄዎቻችንን ለሁሉም ግልፅ አድርገናል። ይህም ሆኖ ግን በተለያዩ ብሄሮችና ሃይማኖቶች መካከል መከባበር እንዲኖር የማድረግ ከፍተኛ ኃላፊነት ያለበት መንግስት ሙስሊሙን እርስ በእርስ፣ እንዲሁም ሙስሊሙን እና የሌላ ሀይማኖት ተከታዩን ህብረተሰብ ለግጭት የሚዳርጉ ተግባራትን ሲፈጽም ቆይቷል። አሁንም እያደረገ ይገኛል። ይህ አደገኛ አካሄድ ሊከሽፍ የቻለው በህዝባችን ብስለት እና ጨዋነት ብቻ ነው። ኩሩው የኢትዮጵያ ህዝብ ከህዝበ ሙስሊሙ የመብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የመረጠው በሳል አካሄድ ሊመሰገን የሚገባው ነበር። ይህ በሳል የህዝብ ምላሽ ሙስሊሙን እና ክርስቲያኑን ሊያጋጭ ይችል የነበረውን የመንግስት እንቅስቃሴ ቀልብሶ የህዝባችንን ጨዋነት፣ ተከባብሮ የመኖር ብቃት እና አስተዋይነት ዳግም ማሳየት ችሏል። ክስተቱም በታሪክ መዝገብ ውስጥ በወርቃማ ጽሁፍ የሚሰፍርበትና ለትውልድ የሚተረክበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም።

በህዝበ ሙስሊሙ ላይ የፈጸማቸው በደሎች በህዝቡ ብስለት የከሸፉ ቢሆኑም ለህዝቡ ደንታ የሌለውና ስህተቱን አምኖ መቀበልን ውርደት አድርጐ የሚቆጥረው መንግስት ግን ህዝብ እየተቃወመው ህገወጥነቱን ቀጥሎበታል። በዚህም ምክንያት ‹‹መንግስት በሀይማኖታችን ጣልቃ አይግባብን! ያልመረጥናቸው ህገ-ወጥ የመጅሊስ አመራሮች ወርደው ፍትሀዊ ምርጫ ይካሄድ! የማናምንበት እምነት በግድ አይጫንብን!›› ብሎ የጠየቀውን ህዝብ ከነወኪሎቹ ለእስር፣ ለስደት፣ ለእንግልት እና ለሞት ዳርጓል።

የኢፌደሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 17 ንዑስ አንቀጽ 2 ‹‹ማንኛውም ሰው በህግ ከተደነገገው ስርዓት ውጪ ሊያዝ፣ ክስ ሳይቀርብበት ወይም ሳይፈረድበት ሊታሰር አይችልም›› ይላል። ነገር ግን ለፀጥታ ተግባር የተሰማሩት አካላት ህጉን በመጣስ ሰላማዊ ግለሰቦችን ሲይዙ የታጠቀ የጠላት ኃይል ላይ እንኳ ሊፈፀም የማይገባውን ግፍ፣ ድብደባ፣ ወከባ እና ስቃይ ይፈፅማሉ። ከፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ ሳያገኙና ለባለቤቱ ሳይሰጡ ያስራሉ። ህግ ጥሰው ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት በኋላ የግለሰቦች ቤት ላይ ብርበራ ያካሂዳሉ። በብርበራው ወቅት በሚፈጥሩት ሁከት በቤተሰብ ላይ ከፍተኛ ስጋት እና ድንጋጤ ይፈጥራሉ። ይህ ሁሉ የሚካሄደው ህዝቡ በፍርሃት ከመብት ጥያቄው ወደ ኋላ እንዲል ቢሆንም ውክቢያውና እንግልቱ ግን የመብት ጥያቄው ይበልጥ እንዲፋፋም፣ ህዝቡ ፍርሃቱ ለቅቆት ለነፃነት የሚከፈል መስዋዕትነት ያለውን ልዩ ጣዕም እንዲያጣጥም እና ሙሉ መብቱን ወደ መጠየቅ እንዲሸጋገር ነው ያደረገው።

የህገ-መንግስቱ አንቀጽ 18 ንዑስ አንቀፅ 1 ‹‹ማንኛውም ጭካኔ ከተሞላበት፣ ኢሰብዓዊ ከሆነ ወይም ክብርን ከሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት የመጠበቅ መብት አለው›› ይላል። ህገ-መንግስቱ ይህን ቢልም ዜጐች መሆናችንን ጥርጣሬ ውስጥ በሚከት መልኩ ከያዙን በኋላ በማእከላዊ በክረምት ቀርቶ በበጋ እንኳን ቅዝቃዜው በማይቻለው ‹‹ሳይቤሪያ›› ተብሎ በሚጠራው ጨለማ ክፍል ለ3 ወራት አጉረውናል። መቋቋም የሚያዳግተውን የማሰቃያ ስልታቸውን በመጠቀም ያላሰብነውንና ያልሰራነውን ‹‹እመኑ! ተናገሩ! ፈርሙ!›› ብለው አስገድደውናል።

ለቀጠሮ ፍርድ ቤት ስንቀርብ የደረሰብንን ሰቃይ አሳይተን ቢያንስ ፍርድ ቤቱ ስቃዩን እንዲያስቆምልን ጠይቀን ነበር። ያገኘነው ውጤት ግን ወደ ማዕከላዊ ስንመለስ ከመርማሪዎቹ በቀልና ተጨማሪ ስቃይ ነበር። ፍርድ ቤቱ የደረሰብንን ስቃይና የተከሰስንበትን ጉዳይ አግባብ እንዳልሆነ አይቶ ዋስትና ሰጥቶን ሳለ ፖሊስ የፍርድ ቤትን ትዕዛዝ ጥሶ ዋስትናውን በመከልከል ክስ መስርቶብናል። አሰቃዮቻችን ስለ ህገ-መንግስት እና መብት ስንናገር ‹‹ህገ-መንግስቱን ቀደህ ጣለው!›› እና ‹‹እኛ መሰዋዕትነት ከፍለን ነው እዚህ የመጣነው!›› ወ.ዘ.ተ በማለት ለህግም ሆነ ለሰው ክብር ደንታ እንደሌላቸው አሳይተውናል። ይህ ሁሉ መከራ በተቃራኒው ህገ-መንግስቱን ለማስከበር መታገል የሚያስፈልግበት ትክክለኛ ወቅት ላይ መሆናችን እንዲሰማን፣ እውነተኛ ፅናትና ወኔ እንዲኖረንም አድርጎናል።
በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 19 ንዑስ አንቀጽ 5 ‹‹የተያዙ ሰዎች በራሳቸው ላይ በማስረጃነት ሊቀርብ የሚችል የእምነት ቃል እንዲሰጡ፣ ወይም ማናቸውንም ማስረጃ እንዲያምኑ አይገደዱም። በማስገደድ የተገኘ ማስረጃ ተቀባይነት የለውም›› የሚለውን ድንጋጌ መሠረት በማድረግ እዚያው ማዕከላዊ የምርመራ እስር ቤት እያለን የደረሰብንን ስቃይና እንግልት ገልፀን ክስ አቅርበን ነበር። በምርመራ ጣቢያው ቃላችንን የሰጠነውም ሆነ የፈረምነው ተገደን መሆኑን ገልፀን ውድቅ እንዲደረግ ጠይቀናል። ሆኖም ግን ክሳችን ተዳፍኖ እና ተድበስብሶ እንዲቀር በመደረጉ በጊዜው ምላሽ ሳናገኝ ቀርተናል። ክስ ተመስርቶብን ወደ ከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርበን በኋላም በድጋሚ ጉዳዩን ያስረዳን ሲሆን አሁንም ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ሙሉ ለሙሉ የሚያደምጥበትንና ምላሽ የሚሰጥበትን ቀን እየተጠባበቅን እንገኛለን።

ከቤተሰብ፣ ከጠበቃና ከሀኪም ጋር እንዳንገናኝ አድርገው የፈፀሙብን የህግ-ጥሰት እና አስገድደው በማስፈረም እና ድምፅና ምስላችንን በመቅረፅ የፈፀሙብን በደል በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ቁጥር 424 መሰረት እስከ አስር አመት የሚያስቀጣ ኢ-ሰብዓዊ ተግባር ነው። ነገር ግን የፖሊሱም፣ የዐቃቤ ህጉም፣ የፍርድ ቤቱም አለቃ በሆነውና የፍትህ ስርዓቱን ሰብስቦ በያዘው ገዚው ፓርቲ አምባገነንነት በተቃራኒው እኛ ተከሳሾች ሆነን ጉዳያችን ‹‹በፍርድ ቤት›› በመታየት ላይ ይገኛል።

በማዕከላዊ እስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ስነ-ልቦናዊ እና አካላዊ ስቃይ አድርሰውብናል። ከአስራ አራት ሰዓታት በላይ ያለ እረፍት ቀጥ ብለን እንድንቆም በማድረግ፣ ጀርባችን ሰንበር እስኪያወጣ እና እስኪገሸለጥ ራቁታችንን በሽቦ በመግረፍ፣ በሰንሰለት በማሰር እና ዓይናችንን በጨርቅ በመሸፈን የውስጥ እግራችን እስከሚላጥ ገልብጦ በመግረፍ፣ ቀንና ማታ አሰቃቂ በሆነ ምርመራ እና ድብደባ እንቅልፍ በመንሳት፣ ሃይማኖታችንንና ክብራችንን በመንካት፣ ፂማችንን በመንጨትና እንድንላጭ በማስገደድ፣ እንዲሁም ሰላት በመከልከል፣ ቤተሰብ፣ ጠበቃ፣ ሀኪምና የሃይማኖት አባት እንዳናገኝ በማድረግ፣ ከአቅም በላይ የሆነን ስፖርት በግድ በማሰራት፣ ብልት በመግረፍ፣ ‹‹ልጅህን እንገለዋለን! ሚስትህን አስረን በፊትህ ቶርች እናደርጋታለን! ብልትህ ላይ ሀይላንድ በማንጠልጠል መሀን እናደርግሃለን!›› ሲሉ በማስፈራራት ከፍተኛ የሆነ እንግልትና ስቃይ አድርሰውብናል።
ይህም አልበቃ ብሏቸው በሃገሪቱ የቅጣት ጣሪያ የመጨረሻ የሆነውን የወንጀል አንቀፅ ጠቅሰው ከሰሱን። ‹‹ህገ-መንግስት ይከበር!›› ብለን በጠየቅን ህገ-መንግስትን ለመናድ በመንቀሳቀስ ወነጀሉን። ተቃውሟችን ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ ሳለ ‹‹ከእኛ ውጪ ያሉ እምነቶች ከሃገሪቱ መጥፋት አለባቸው ብለዋል›› ሲሉ ከሰሱን። ሃይማኖታዊ የመብት ጥያቄያችንን ‹‹ድብቅ የፖለቲካ አጀንዳ ነው›› በሚል ሊያጠለሹ ሞከሩ። ‹‹ህዝብ ያልመረጣቸው የመጅሊስ አመራሮች በህገ-ወጥ መንገድ መጥተው አይመሩንም! ፍትሀዊ ምርጫ ይካሄድ!›› ባልናቸው ‹‹መንግስት ይውረድ! መንግስት አያስተዳድረንም! ብለዋል›› በሚል ወነጀሉን።

ያዘጋጁት ክስ የህግ ባለሙያ ቀርቶ ማንም የህግ ግንዛቤ የሌለው ሰው በሚረዳው ደረጃ በህግ ስህተቶችና አመክኖአዊነት በጐደላቸው ሃሳቦች የተሞላ፣ በህግ ወንጀል ያልሆኑ አረፍተ ነገሮች እና ቃላት ወንጀል ተደርገው የተጠቀሱበት ፍፁም ተራ እና የሃገሪቷን የፍትህ ሁኔታ የሚያስገምት ክስ ነው። ምንም እንኳን ‹‹ክሱን ዳኞች ስርዓት ሊያስይዙት ይገባል›› በሚል የፀረ-ሽብር አዋጁን በመቃወም እና ክሱ ላይ ያሉ ስህተቶችን ሁሉ ነቅሰን በማውጣት የክስ መቃወሚያ ያቀረብን ቢሆንም የዳኞች ብይን ክሱን ይበልጥ የማይገባና ውስብስብ አደርጎታል።

ከታሰርን ጀምሮ የደረሱብን የህግ ጥሰቶች እና የፍትህ እጦቱ ከፍርድ ቤት ሂደት ራሳችንን ሙሉ ለሙሉ እንድናገል የሚገፉ ነበሩ። ሆኖም ግን የተወነጀልንበት ክስ ምን ያህል ከእውነት የራቀ፣ ጥያቄያችን ሃይማኖታዊ እና ህገ መንግስታዊ መሆኑን እና እንቅስቃሴያችንም ፍፁም ሰላማዊ እንደነበር ለህዝባችን በፍትህ አደባባይም ጭምር ለማሳየት ስንል የፍርድ ሂደቱ ውስጥ መግባቱ የተሻለ መሆኑን በማሰብ ሃሳባችንን ቀይረናል።
መንግስት በአግባቡ ሊተውነው ያልቻለውን አሳፋሪ የፍርድ ቤት ድራማውን ህዝብ እንዳያይበት ለመሸሸግ በመገደዱ ‹‹የተከሰሱ ሰዎች ክስ ከቀረበባቸው በኋላ ተገቢ በሆነ አጭር ጊዜ ውስጥ በመደበኛ ፍርድ ቤት ለህዝብ ግልፅ በሆነ ችሎት የመስማት መብት አላቸው›› የሚለውን ህገ-መንግስታዊ መብት በመጣስ ችሎቱ ዝግ እንዲሆን ተደርጎ ቆይቷል። በዝግ ችሎቱ የምስክር መስሚያ ጊዜ ብዙ አስገራሚ ድራማዎችን አይተናል። ዓቃቤ ህጎች ዳኞች የሚሰጡትን ብይን እንደማይቀበሉ እስከመግለጽ የደረሱበትን እና ምስክሮችን ማለት ያለባቸውን አሰልጥነዋቸው እንደሚያመጡ አምልጧቸው የተናገሩበትን አጋጣሚ ታዝበናል። በወቅቱ ‹‹ጋዜጠኞች፤ ዲፕሎማቶች እና ህዝባችን ምነው ይህንን አይተው በነበር?›› ብለን ከመመኘት ውጭ ምርጫ አልነበረንም።

ማንኛውም ታራሚም ሆነ ተጠርጣሪ በማረሚያ ቤት ሊያገኛቸው የሚገቡ በህግ የተደነገጉ መብቶች አሉ። መብቶች ግን እንደተለመደው ከወረቀት ዘለው መሬት ጠብ ማለት አልቻሉም። የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ላይ ሲሆን ደግሞ መብቶች በቅጣት ይተካሉ። ካለው የጋራ ችግር በተጨማሪ በእኛ ላይ በተለየ መልኩ በጥላቻ እና በበቀል ስሜት የደረሰብን እንግልት ህሊና ያለውን ሁሉ የሚጎዳ ነው። ከቤተሰቦቻችን መካከል ከጥቂቶች ጋር በስተቀር እንዳንገናኝ ተደርጓል። የምንጠየቅበትንም ሰዓት ከእስረኞች ሁሉ በመለየት በቀን ለሃያ ደቂቃ ብቻ እንዲሆን በማድረግ አድሎ እና መገለል ተፈፅሞብናል። በመካከላችን ልጆቹና ቤተሰቦቹ እንዳይጠይቁት የተደረገም አለ። ከሁሉም በላይ ከባድ ህመም ያለባቸው፤ ሆስፒታል ሄደው እንዲታከሙ የታዘዘላቸው፤ ቀዶ ጥገና እንዲደረግላቸው የተመራላቸው እና በማእከላዊ የደረሰባቸውን ድብደባ ለመታከም የጠየቁ ለዓመት ከአራት ወር በላይ መፍትሄ ሳያገኙ ስቃዩን ይዘው ‹‹የፍትህ ያለህ!›› እያሉ ይገኛሉ። ማረሚያ ቤት የደረሱብን እና እየደረሱብን ያሉ አድሎዎችንና እንግልቶችን ሁሉ ዘርዝረን ጉዳያችንን ለሚመለከተው ፍርድ ቤት ብናቀርብም የማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች ፍርድ ቤት እንኳ ለመቅረብ ፍቃደኛ ሳይሆኑ ሶስት ጊዜ ቀጠሮ አሳልፈዋል።

ሙስሊሙ ማህበረሰብ የመብት ጥያቄ እንቅስቃሴውን ከጀመረ በኋላ መንግስት በነጋዴውና በተማሪው፣ በመንግስት መዋቅር ውሰጥ በሚሰሩ አካላት፣ በሃይማኖት አባቶች እና በአስተማሪዎች፣ እንዲሁም በኢስላማዊ ተቋማት ላይ ሰብዓዊነት የጎደለው እና ህገ-መንግስቱን የሚጻረር የመብት ጥሰት መፈጸሙን ቀጥሎበታል። በበርካታ የክልል ከተሞችና ሙስሊሙ ደስታውን በሚገልጽበት የዒድ ዕለት በአዲስ አበባ ፈጽሞ ልንረሳው የማንችለውና ጭካኔ የተሞላበት ግፍ ፈጽሞብናል። የምንሳሳላቸው እና የምንወዳቸው ወገኖቻችንን እና ቤተሰቦቻችንን ለእስር፣ ለሞትና ለአካል ጉዳተኝነት ዳርጎብናል። ይህ ሁሉ ስቃይ እና መከራ በአንድ በኩል የመንግስትን ግፍ እና ለህግ ተገዢ አለመሆን ሲያጋልጥ በሌላ በኩል የህዝባችንን ፅናት እና ቁርጠኝነት አሳይቶናል። በየትኛውም ሃይማኖት፣ ባህል እና ልማድ ግፍ የተጠላ ሲሆን ለመብት ሲሉ መሰዋት ደግሞ ክብር ነው። ስለዚህ ለሃይማኖታችሁ፣ ለክብራችሁ እና ለደህንነታችሁ ለተሰደዳችሁ፣ ለታሰራችሁ፣ ለተደበደባችሁ እና ቤተሰቦቻችሁን ላጣችሁ ሁሉ ያለንን ክብር እንገልጻለን፤ በሀገራችን ለሚሰፍነው የሃይማኖቶች ነፃነት እና እኩልነት የመሰረት ድንጋይ የሚሆነው ዛሬ እናንተ የከፈላችሁት መስዋእትነት ነውና!
ለሁለት ዓመታት ያለ ምንም መሰላቸት እንግልቱ፣ ማስፈራሪያው፣ እስሩ፣ ድበደባው እና ግድያው ሳይበግራቸው እና ሰላማዊውን የተቃውሞ መስመር ሳይለቁ ለሃይማኖታቸው ያላቸውን ፍቅር ላሳዩ፣ እንዲሁም ይህን ድንቅ ታሪክ ለሰሩ አባቶች፣ የሃይማኖት መሪዎችና አስተማሪዎች /በተለይ ደግሞ ወጣቶች እና ሴቶች/ ያለንን ከፍ ያለ ክብር እና ምስጋና ልናቀርብ እንወዳለን። በሰራችሁት ሁሉ ተደስተናል፤ ኮርተንባችኋልም!
መንግስት የሃይማኖት ግጭት ለመፍጠር ያደረገውን ሙከራ ንቆ በመተውና ጉዳዩን በብስለትና በሰከነ መንፈስ በማየት፣ እንዲሁም እውነታውን ለመረዳት ጥረት በማድረግ ረገድ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን፣ በተለይም ህዝበ ክርስትያኑ ላደረጋችሁት ትብብር ሳናመሰግን አናልፍም። በእውነቱ የሃይማኖት ልዩነት ሳያግደን በህዝብ ደረጃ ተከባብረን ስለመኖራችን ከተነሱ ምሳሌዎች ሁሉ በዚህ ሁለት ዓመት ውስጥ ያሳየነው መከባበር እና አንድነት ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው። ይህ ብሄራዊ አንድነት የበለጠ ተጠናክሮ በጋራ ለምንገነባት ሃገራችን ታላቅ ብርታት እንደሚሆን ጠንካራ እምነት አለን።

በተጨማሪም የፕሬስ ነፃነት በተነፈገበት ተጨባጭ የመብት ጥያቄያችንን እውነታ ለመገንዘብ ማስፈራሪያዎችን እና ዛቻዎችን አልፋችሁ፣ የመንግስትን የተሳሳተ እና ኢ-ህገመንግስታዊ አካሄድ ለይታችሁ ሂደታችን ላይ አዎንታዊ አስተያየቶች እና ገንቢ ትችቶችን ለሰጣችሁ ጋዜጠኞችና በሚዲያው ዘርፍ ለተሰማራችሁ ባለሙያዎች ሁሉ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

ወገኖቻችሁ ያጡትን ፍትህ እና ነጻነት በሃገራችሁ ለማየት በመጓጓት የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ለማበርከት የምትጣጣሩ በስደት የምትገኙ ሙስሊሞችና የሌሎች ሀይማኖቶች ተከታይ ወገኖቻችን በሙሉ ላደረጋችሁት ሁሉ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው። በሀገር ውስጥ ለተጠናከረው የአጋርነት ስሜት የእናንተ አስተዋጽኦ የመጀመሪያውን ድርሻ ይይዛል።

በአጠቃላይ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ነጋዴው፣ አርሶ አደሩ፣ አርብቶ አደሩ፣ ተማሪው፣ ሴቱ፣ ወንዱ፣ ወጣቱ፣ አዛውንቱና ሌላውም፣ እንዲሁም በመንግስት መዋቅር ስር ሆናችሁ የመንግስትን የተሳሳተ አካሄድ ስትቃወሙ የነበራችሁ ዳኞች፣ ዓቃቤ ህጎች፣ አባቶች፣ ፖሊሶች፣ የጦር ሰራዊትና የፓርላማ አባላት በሙሉ ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርብላችኋለን። የጥረታችሁን ፍሬ በቅርቡ ያሳያችሁ ዘንድም አላህን እንለምናለን!
መልእክታችን

1/ በሙስሊሞች መካከል እና በሙስሊሙና በክርስትያኑ መካከል የታየውን አንድነትና መከባበር ሁላችንም በጋራ እንድንጠብቀው፣ እንዲሁም መሰረቱ የፀና ሆኖ እንዲቀጥል ለማድረግ እንድንጥር አደራ እንላለን። ሀገራችን ከእርስ በእርስ ሽኩቻዎች ወጥታ የእድገትና ብልጽግና ጉዞ እንድትጀምር ከተፈለገ ትክክለኛ የሃይማኖት ነፃነት፣ እኩልነት እና መከባበር በቅድሚያ እውን መሆኑ አማራጭ የሌለው ግዴታ ነው። የሃገራችንን እድገት የጋራ አላማ አድርገን፣ የጋራ ተጠቃሚ ሆነን መኖር የምንችለው ስጋትና ጥርጣሬውን በፍቅርና መተማመን ስንተካው ነው።

2/ በፅናት ሰላማዊ የመብት ትግሉን የምንቀጥል መሆኑንና የሚያስከፍለንን መስዋዕእትነት ሁሉ ለመክፈልም ዝግጁ መሆናችንን ለህዝባችንም ሆነ ለመንግስት መልእክት ለማስተላለፍ እንወዳለን። ለቀጣዩ ሰላማዊ የመብት ትግል እርከንም እኛም ህዝባችንም በሙሉ ዝግጅት ላይ መሆናችንንና ለመብታችን ተግተን ሰርተን መስዋዕት ከመሆን ወደኋላ የማንል መሆኑን ስንገልጽ በከፍተኛ ወኔ ተሞልተን ነው!

3/ መንግስት እየፈጸማቸው ያላቸውን ኢ-ህገ መንግስታዊ ተግባራት፣ በህዝበ ሙስሊሙ ላይ እየፈጸመ ያለውን እስራት፣ ግፍ፣ መስጂድ ነጠቃ፣ የሀሰት ውንጀላና የሃይማኖት ሰዎችን፣ ጋዜጠኞችንና የመብት ጠያቂዎችን በሽብርተኝነት መፈረጅና መሰል ህገ መንግስታዊ የመብት ጥሰቶችን በአስቸኳይ እንዲያቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን። በማእከላዊና በተለያዩ እስር ቤቶች የሚፈጸሙት ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶች እንዲቆሙና የህሊና እስረኞችም መለቀቅ እንደሚገባቸው ለመግለጽ እንወዳለን። መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የእውነተኛ ሰላም፣ ፍትህ፣ ዴሞክራሲ እና ልማት ባለቤት ሆኖ ማየት የዘወትር ህልማችን መሆኑንም ሳንገልጽ አናልፍም፡፡

በመጨረሻም በቃል ኪዳናችን ጸንተንና መነሻው ላይ ከነበረው በተሻለ ሁኔታ ተንቀሳቅሰን ፍጹም በሰለጠነና በተጠና መልኩ የተሟላ ፍትህ እና ነፃነት ለማግኘት በጽናት እና በቆራጥነት ሁሉም ባለድርሻ አካል እንቅስቃሴውን ከዳር እንዲያደርስ አደራ ለማለት እንወዳለን። የእንቅስቃሴው ማብቂያ ድልና ስኬት እንደሚሆን አንጠራጠርም!

አላሁ አክበር!

ግልባጭ፡- እዚሁ አገር ውስጥ እና በውጭ አገራት ለሚገኙ የህትመትና የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች

የወያኔ ጋሻ ጃግሬዎች እጣ ፈንታ

December 24/2013

የኢህአዴግ መንግስት እስካሁን በስልጣን ላይ በቆየባቸው አመታት እንደ አንድ የስርዓቱ ግብአት የሚጠቀመው ለፍርሃት አሊያም ለጥቅም ያደሩ አጃቢዎችን  ወደ ኢህአዴጋዊ መዘውሩ በማስገባት መሆኑ የታወቀ ነው። አጃቢዎችን በውድም ሆነ በግድ ወደ መዘውሩ ካስገባ በሁዋላም እንደ ቀደምት የአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች እንዳደረጉት ተገዥውን ህዝብ በእጅ አዙር የሚገዙበት ስትራቴጂያዊ መንገድ በመጠቀም ከየብሄሩ ይመለምላሉ።ይህንን ስልም የወያኔ መንግስት በቀጥተኛ መንገድ ሀገሪቱን በሃይል መግዛት ያቅተዋል ማለቴ አይደለም።እስካሁንም በጉልበት እየገዛ ነውና ! ነገር ግን የእያንዳንዱ ብሄር ብሄረሰብ ህዝቦች በራሳቸው ሰዎች አማካይነት መግዛቱ ድካሙን ያቀልልናል በሚል እሳቤ ነው ።
      ታዲያም እነኝህ አድርባዮች አሳድጎ ለወግ ለማእረግ ያበቃቸውን ምስኪን ህዝባቸውን ለወያኔ መራሹ ቡድን ለጊዜያዊ ጥቅማቸው ሲሉ ሽጠዋልም እየሸጡም ነው።ለሆዳቸው ማደሩንስ ይደሩ ቢያንስ ግን ወክለነዋል የሚሉት ወገናቸው መብቱ ሲገፈፍ፣ መሬቱ ተቆርሶ ለባእድ ሀገር በግፍ ሲሰጥበት ሲቀጥልም ኢሰብአዊ በሆነ ሁኔታ የወያኔ ክንድ ሲያርፍበት ጆሮ ዳባ ልበስ ባይሉ ምንኛ ጥሩ ነበር።ሞት አይቀር ! እምቢ ላገሬ! እምቢ ለወገኔ !  ብለው የሚወሰደውን እርምጃ ቢቀበሉ ብዬ ግን እጅጉን ተመኘሁ።እንደ እኔ ሀሳብ ግን እነኚህ ሰዎች የወገኖቻቸው ስቃይና ዋይታ ሳይሰማቸው ወይንም ሳያንገበግባቸው ቀርቶ አይመስለኝም በፍርሃትና በጥቅም ታውረው እንጂ። "ላሰም ቀመሰ ያው በላ ነውና ተረቱ " ከአህአዴግ ጋር አብረው ህዝቡ ላይ ባደረሱት ሰቆቃ ልክ  ተመጣጣኝ ቅጣት ይገባቸዋል ብዬ አምናለው ።
     የዚህች አጭር ጽሁፌ መነሻ የሆኑኝ ከነዚህ ጋሻ ጃግሬዎች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ አያሌው ጎበዜ የሰሞኑ የስንብት ዜና ስለሆነ ስለ እሳቸው የሰማሁትን ጠቀስ አድርጌ አልፋለው  ።
      ለረዥም አመታት የአማራው ክልል ፕሬዘደንት የነበሩት አቶ አያሌው ጎበዜ በትጥቅ ትግል ውስጥ የነበሩ፤ ከነታምራት ላይኔ፣ አዲሱ ለገሰ፣ ተፈራ ዋልዋ፣ ህላዌ ዮሴፍ ጋር ሆነው በኢህዴን ውስጥ ያገለገሉ ሰው ናቸው። ከስልጣናቸው ተሰናብተው  በሳቸውም  ምትክ  የብአዴን  እና  የክልሉ ምክትል ፕሬዘደንት የሆኑት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው  በምትካቸው  ስልጣኑን  እንደተረከቡም ሰምተናል ። የወያኔ ከፍተኛ ባለስልጣናት እንደሚሉት  ከሆነ፤ “የአሁኑ የስልጣን ሽግሽግ፤ የቀድሞዎቹን ባለስልጣናት በአዳዲስ ሰዎች የመተካካት የስራ ሂደት ነው” ብለዋል።  እንደ አብዛኛው ለሁኔታው ቅርብ የሆኑት ሰዎች አስተያየት “አቶ አያሌው ጎበዜ ስልጣናቸውን የለቀቁት፤ ቀደም ሲል የአማራ ክልል የነበረው እና አሁን የትግራይ ክልል የወሰደው ሰፊ እና ለም መሬት ለሱዳን መሰጠቱን በመቃወማቸው ነው” ይላሉ። ለዚህም እንደማስረጃ የሚያቀርቡት ከ3 ወራት በፊት፤ በመስከረም ወር ላይ በባህር ዳር ተደርጎ በነበረው የድንበር ጉዳዮች ውይይት ላይ፤ አቶ አያሌው ግልጽ በሆነ መንገድ የሃሳብ ልዩነት ማቅረባቸው እንደሆነ ይወራል። እንደሚባለውም ከሆነ በወቅቱ ከህወሃት ሰዎች ጠንካራ የሆነ ጉሸማም ደርሶባቸው ም ነበር።
     የሰሞኑ የጥሎ ማለፍ ውድድር የሚመስለው የሙስና ትርምስ እና በመተካካት ስም ተቀናቃኞቻቸውን ከስልጣን ማባረር በውስጥ ፖለቲካ  እየተካሄደ ያለውን ኩነት  ቁልጭ አድርጎ ያሳያል የሚል ግምት አለኝ። በዚህም ሽኩቻ የተሸነፉት ባለስልጣናት  በወያኔ ዘንድ እንደ ግዞት በሚቆጠረው በአምባሳደርነት ተሹመው ወደ አንዱ ሀገር  እንዲሄዱ ሲደረግ ቀሪዎቹ ነገሩ የከፋባቸው ደግሞ እንዲታሰሩ አሊያም ከሀገር እንዲሰደዱ ይደረጋል ። አቶ አያሌው ጎበዜም በዚሁ መሰረት በአምባሳደርነት ተሹመው ወደ አንዱ ሃገር ሊሄዱ እንደሚችሉ ጭምጭምታ ይሰማል ።
     ለነገሩ በኢህአዴግ  ውስጥ ከሚገኙ አብዛኛው ሰዎች በድርጅቱ ርዕዮተ አለም አምነው የተመዘገቡ እንዳልሆነ በገሀድ ይታወቃል ።ምክንያቱም ድርጅቱ ወጥ የሆነ የፖለቲካ ፍልስፍና የለውም።የሚበዙትንም ሰዎች ወደ ኢህአዴግነት እያመጣቸው ያለው ነገር ጥቅም ብቻ ነው።
       ወደ ጽሁፌ ማጠቃለያ ስገባ ጉድና ጅራት ከወደሁዋላ ነው እንዲሉ ያቺ ወደውም ሆነ ተገደው የተቀመጡባት ወንበር  የአገልግሎት ዘመኗ ሲያከትም ወይም ወያኔ አላምጦ ሲተፋቸው የተፈጠሩበትን ቀን እስኪረግሙ ድረስ እምጥ ይግቡ ስምጥ ሳያውቁ ማጣፊያው ሲያጥራቸው በየጊዜው እየተመለከትን ነው።
      እንኚህ ጋሻ ጃግሬዎች ወያኔ እንደ አሮጌ ቁና አውጥቶ ሲወረውራቸው ከሰፊው ህዝብ ወይም ለአመታት ለጥቅም ሲያድሩለት ለኖሩለት ወያኔ ሳይሆኑ  እንደ ውሃ ላይ ኩበት ሲንሳፈፉ እያየን ነው ። ያለጥርጥር የተቀሩትም አድርባዮች በቅደም ተከተል  የመገፋትን ጽዋ እንደሚጎነጩ አምናለው ።ጊዜ ደጉ ሁሉን ያሳየናል !!!

በእስር ላይ የሚገኙት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ አባላት በእስር ቤት ስቃይ እንደተፈጸመባቸው ገለጹ

December 23/2013

በማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የስነልቦናዊ እና አካላዊ ስቃይ አድርሰውብናል የሚሉት በእስር ላይ የሚገኙት የሙስሊሙ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት፣ የደረሱባቸውን በደሎች ዘርዝርው አቅርበዋል።  ” ከአስራ አራት ሰአት በላይ ያለ እረፍት ቀጥ ብለን እንድንቆም በማድረግ፣ ጀርባችን ሰንበር እስኪያወጣ እና እስኪገሸለጥ ራቁታችንን በሽቦ በመግረፍ፣ በሰንሰለት በማሰር እና አይናችንን በጨርቅ በመሸፈን የውስጥ እግራችን እስከሚላጥ ገልብጦ በመግረፍ፣ ቀንና ማታ አሰቃቂ በሆነ ምርመራ እና ድብደባ እንቅልፍ በመንሳት፣ ሃይማኖታችንንና ክብራችንን በመንካት፣ ጺማችንን በመንጨትና እንድንላጭ በማስገደድ፣ እንዲሁም ሶላት በመከልከል፣ ቤተሰብ፣ ጠበቃ ፣ሀኪምና ሀይማኖት አባት እንዳናገኝ በማድረግ፣ ከአቅም በላይ የሆነን ስፖርት በግድ በማሰራት፣ ብልት በመግረፍ፣ ” ልጅህን እንገለዋለን! ሚስትህን አስረን በፊትህ ቶርች እናደርጋታለን! ብልትህ ላይ ሀይላንድ በማንጠልጠል ማሀን እናደርግሀለን” ሲሉ በማስፈራራት ከፍተኛ ስቃይ አድርሰውብናል ብለዋል።

በህገመንግስቱ አንቀጽ 18 ንኡስ አንቀጽ 1 ” ማንኛውም ጭካሄ ከተሞላበት፣ ኢሰብአዊ ከሆነ ወይም ክብርን ከሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት የመጠበቅ መብት አለው” ቢልም፣ እኛ ግን ” ዜጎች መሆናችንን ጥርጣሬ ውስጥ በሚከት መልኩ ከያዙን በሁዋላ በማእከላዊ በክረምት ቀርቶ በበጋ እንኳን ቅዝቃዜው በማይቻለው ” ሳይቤሪያ” ተብሎ በሚጠራው ጨለማ ክፍል ለ3 ዋር አገሩው መቋቋም የሚአዳግተውን የማሰቃያ ስልታቸውን በመጠቀም አላሰብነውንና ያልሰራነውን ” እመኑ! ተናገሩ! ፈርሙ! ብለው አስገድደውናል”  ሲሉ በመግለጫቸው ጠቀስዋል።

ፍርድ ቤት ስቃዩን እንዲያስቆምልን ብንጠይቅም፣ ያገኘነው ውጤት ግን ወደ ማእከላዊ ስንመለስ ከመርማሪዎቹ በቀልና ተጨማሪ ስቃይ ነበር፣ የሚሉት ኮሚቴዎቹ፣ አሰቃዮቻችን ስለህገመንግስቱ እና መብት ስንናገር ” ህገ-መንግስቱን ቀደህ ጣለው፣ እኛ መስዋትንት ከፍለን ነው እዚህ የመታነው በማለት ለህግም ሆነ ለሰው ክብር ዴንታ እንደሌላቸው አሳይተውናል” ሲሉ አክለዋል።
ከቤተሰብ፣ ከጠበቃና ከሀኪም ጋር እንዳንገናኝ አድረገው የፈጸሙብን የህግ ጥሰት እና አስገድደው በማስፈረም እና ድምጽና ምስላችንን በመቅረጽ የፈጸሙብን በደል በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ቁጥር 424 መሰረት እስከ አስር አመት የ አስቀጣ ኢ-ሰብአዊ ተግባር ቢሆንም የፖሊሱም፣ አቃቢህጉም ፣ የፍርድ ቤቱም አለቃ በሆነውና የፍትህ ስርአቱን ሰብስቦ በያዘው ገዢው ፓርቲ አምባገነንነት በተቃራኒው እኛ ተከሳሽ ሆነን ጉዳያችን በፍርድ ቤት በመታየት ላይ ይገኛል ብለዋል።

መንግስት በአግባቡ ሊተውነው ያልቻለውን አሳፋሪ የፍርድ ቤት ድራማውን ህዝብ እንዳያይበት ለመሸሸግ በመገደዱ የተከሰሱ ሰዎች ክስ ከቀረበባቸው በሁዋላ ተገቢ በሆነ አጭር ጊዜ ውስጥ በመደበኛ ፍርድ ቤት ለህዝብ ግልጽ በሆነ ችሎት የመስማት መብት አላቸው የሚለውን ህገመንግስታዊ መብት በመጣስ ችሎቱ ዝግ እንዲሆን ተደርጎ ቆይቷል የሚሉት የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት፣  በዝግ ችሎቱ የምስክር መስሚያ ጊዜ ብዙ አስገራሚ ድራማዎችን አይተናል፣ አቃቢ ህግ ዳኞች የሚሰጡትን ብይን እንደማይቀበሉ እስከመግለጽ የደረሱበትን እና ምስክሮችን ማለት ያለባቸውን አሰልጥነዋቸው እንደሚያመጡ አምልጧቸው የተናገሩበትን አጋጣሚ ” መታዘባቸውን ይገልጻሉ።

የኮሚቲው አባላት ” በሙስሊሞች መካከል እና በሙስሊሙና በክርስቲያኑ መካከል የታየውን አንድነትና መከባበር በጋራ መጠበቅ እንደሚያስፈልግ መክረዋል።  በጽናት ሰላማዊ የመብት ትግሉን የሚቀጥሉ መሆናቸውንና የሚያስከፍለውን መስዋትንት ሁሉ ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውንም ተናግረዋል። ለቀጣዩ ሰላማዊ የመብት ትግል እርከንም  በሙሉ ዝግጅት ላይ መሆናቸውን” ገልጸው፣ መንግስት በማእከላዊ እስር ቤቶች የሚፈጸሙትን ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች እንዲያስቆምና የህሊና እስረኞችን እንዲለቅ ጠይቀዋል።

ኢሳት ዜና

Monday, December 23, 2013

የኢህአዴግ አዲሱ አሰላለፍ ፪ – ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

December 23/2013

በድህረ-መለስ ኢትዮጵያ የፖለቲካው ሥልጣን በስርዓቱ ልሂቃን መካከል ከሚደረገው የኃይል መተናነቅ አንጻር፣ ዛሬም ከመፈራረቅ ጣጣው የተላቀቀ የማይመስልባቸው ምልክቶች መታየታቸው እንደቀጠለ ነው፡፡ ከአራት ወር በፊት በዚህ መፅሄት ላይ ‹‹አዲሱ የኢህአዴግ አሰላለፍ›› በሚል ባቀረብኩት ፅሁፍ በገዥው ፓርቲ ውስጥ ተፈጥሮ ከነበረው ክፍፍል የትኛው ቡድን የበለጠ ጉልበት አግኝቶ በአሸናፊነት መውጣት እንደቻለ ከገለፅኩ በኋላ ፅሁፉን የቋጨሁት እንዲህ በማለት ነበር፡- ‹‹የፓርቲው የታሪክ ድርሳን እንደሚነግረን ‹ይሆናሉ› የተባሉት ተቀልብሰው፣ ባልተጠበቁ ሁነቶች (የኃይል መገለባበጥ ተከስቶ) ፖለቲካው የሚመራበት አጋጣሚ ሊፈጠር የሚችልበት ዕድል ሊኖር እንደሚችልም መዘንጋት አያስፈልግም፡፡››

እነሆ በዚህ ፅሁፍ ደግሞ በቅርቡ በተጨባጭ የታዩትን አዳዲስ ኩነቶች እና ይህንኑ ተከትለው ሊመጡ ይችላሉ ብዬ የምገምታቸውን ‹የቢሆን ዕድሎች› (Scenarios) ለማየት እሞክራለሁ፡፡ 

ሰላም የራቀው-ኢህአዴግ 

በግንባሩ አባል ድርጅቶች መካከል ዛሬም ድረስ ሙሉ በሙሉ የተረጋጋ ፖለቲካ አልሰፈነም፤ የዚህ ዋነኛ ምክንያቱ ደግሞ፣ ቁልፍ የሥልጣን ቦታዎችን ጠቅልሎ ይዞ በነበረው በቀድሞ ሊቀ-መንበሩ ህልፈት ሳቢያ የተፈጠረው የአመራር ክፍተት እና እርሱን ሊተካ የሚችል መሪ ማግኘት ባለመቻሉ ይመስለኛል፡፡ እንዲህ አይነት አጋጣሚዎችም በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባለ ከሕግ ይልቅ የጠመንጃ ኃይልና የግለሰብ አምባገነናዊነት በገነነበት ሀገር ‹የማይገመቱ ክስተቶች› (Unpredictable Event) ማምጣታቸው የሚጠበቅ ነው፡፡

የሆነው ሆኖ በዚህ አጀንዳ ለመመልከት የምሞክረው ጉዳይ፣ በአሁኑ ጊዜ ሀገር እየመራ ያለው ኃይል ለሁለት የተከፈለ ቢሆንም፣ በአንፃራዊነት በጥምር የሚሰራ መሆኑን በማስረገጥ ነው፡፡ የእነዚህ ሁለት ቡድኖች የጉልበት ምንጭም የታጠቀውን ኃይል በመቆጣጠር እና የፖለቲካውን ሥልጣን በመያዝ ላይ የተመሰረተ ነው፤ ይኸውም ሠራዊቱ እና የደህንነት መስሪያ ቤቱ ሙሉ በሙሉ በህወሓት ሰዎች ሲንቀሳቀሱ፣ ፖለቲካውን ደግሞ የብአዴን መሪዎች፣ ከተወሰኑ የኦህዴድና ደህአዴን የአመራር አባላት ጋር ተባብረው መያዛቸውን የሚያሳዩ ምልክቶች መኖራቸው ነው፡፡
የህወሓት ኃይል

ህወሓት የቀድሞው ፍፁማዊ የበላይነቱን ለመመለስ ዋና ችግር የሆነበት በውስጡ ለተፈጠረው መከፋፈል እስካሁን መፍትሄው ተለይቶ አለመታወቁ ነው፤ ከዚህ ቀደም በዚሁ መፅሄት፣ አንዱ ኃይል የተሻለ ጉልበት በማግኘቱ ሌላኛውን (እነአዜብ መስፍንን ጨምሮ አባይ ወልዱና ቴዎድሮስ ሀጎስን የመሳሰሉ ከፍተኛ ካድሬዎች የተሰባሰቡበትን) በመብለጥ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን እንቅስቃሴያቸውን መገደቡ ተሳክቶለት እንደነበረ ማስነበቤ ይታወሳል፡፡ ይህ ክፍፍል ምንም እንኳ እንደ 1993ቱ ከፓርቲ እስከ ማስወጣት የሚደርስ አለመሆኑ ቢታወቅም፣ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል እና ጌታቸው አሰፋ የተሰለፉበት ቡድን ተፅእኖ ፈጣሪ ሆኖ መውጣት ችሏል፤ ይህም ሆኖ ውስጥ ውስጡን የሚገመደው ተንኮልም ሆነ ሽኩቻ ገና መቋጫ አለማግኘቱ ግልፅ ነው፡፡

በዚህ ፅሁፍ ጠመንጃ የታጠቀውን ክፍል ‹የህወሓት ኃይል› እያልኩ የምገልፀበት ዓብይ ምክንያት፣ በጄነራል ሳሞራ የኑስ ኤታ ማዦር ሹምነት የሚመራው የመከላከያ ሠራዊት እና በማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ጌታቸው አሰፋ ስር ያለው የደህንነት ኃይል ለሚደግፉት ቡድን መጠናከር እያበረከቱት ያለውን አስተዋፅኦ ከግምት በመክተት ነው፡፡ ሁለቱም ሰዎች ለመለስ ፍፁም ታማኝ የነበሩ ቢሆንም፣ ከህልፈቱ በኋላ እንደእርሱ ተጭኖ ሊቆጣጠራቸው የሚችል ጉልበታም ህወሓትን ጨምሮ በሁሉም የግንባሩ አባል ፓርቲ ውስጥ አለመኖሩ፣ በፖለቲካው ‹ቼዝ› የ‹ዘመነ መሳፍንቱ›ን ሚካኤል ስሁል አይነት ሚና እንዲጫወቱ አስችሏቸዋል፤ ሁለቱም ከስራቸው የነበሩትንና ‹ስልጣን ሊጋፉ ይችላሉ› ብለው የጠረጠሯቸውን ባልደረቦቻቸውን አስቀድሞ ገለል ማድረጉ ከሞላ ጎደል የተሳካላቸው ይመስለኛል፡፡

በተለይም ጌታቸው አሰፋ ከራሱ ወንበር አልፎ ከእነአዜብ መስፍንና አባይ ወልዱ ጋር በመተባበር አንድ ቀን በጠቅላላው የመንግስት የሥልጣን እርከን ላይ ‹ናቡቴ ሊሆን ይችላል› የሚል ስጋት ያሳደረበትን እና ‹መለስ ዜናዊ ሞት ባይቀድመው በእርሱ ቦታ ሊተካው ነበር› እየተባለ የሚነገርለትን የመረጃ ኃላፊ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል በሙስና የሚወነጀልበትን መንገድ አመቻችቶ ለእስር ባይዳርገው ኖሮ ‹‹ለቁርስ ያሰቡንን…›› አይነት ታሪክ ራሱን መድገሙ አይቀሬ ነበር ብዬ አስባለሁ፡፡

ጄነራል ሳሞራ የኑስ በበኩሉ ተቀናቃኙ አድርጎ ይመለከታቸው የነበረው ሶስቱ ከፍተኛ መኮንኖች እንደ ወልደስላሴ ‹ፍንቀላ መሳይ ነገር ሊሞክሩ ይችላሉ› ተብለው አይደለም፡፡ የእነርሱ የመጀመሪያው ችግር ከወታደራዊ ዲሲፕሊን በማፈንገጥ አለቃቸውን አለማክበራቸው ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ሳሞራ ‹በየትኛውም ምክንያት ከኃላፊነቴ ብነሳ የቆየ ፋይል አገላብጠው አደጋ ላይ ሊጥሉኝ ይችላሉ› በሚል ስለሚጠረጥራቸው ነው፡፡ እነዚህ መኮንኖች የሰሜን ዕዝ አዛዥ ሌፍተናንት ጄነራል ሰዓረ መኮንን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ መልካም ግንኙነታቸው እንደቀድሞው እንዳልሆነ የሚነገረው የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌፍተናንት ጄነራል አበባው ታደሰ እና የአየር ኃይሉ አዛዥ ሜጀር ጄነራል ሞላ ኃይለማርያም ናቸው፡፡ እናም ሰዓረ እና አበባው በቀጥታ ሠራዊት ከሚያዙበት ቦታ ተነስተው በመከላከያ ሚኒስትር ውስጥ በቢሮ ስራ ላይ ሲመደቡ፣ ሞላም ከነበረበት ኃላፊነት አኳያ ብዙም ይመጥነዋል የማይባል የቢሮ ስራ ተሰጥቶታል፤ በእርሱም ቦታ ሜጀር ጄነራል አደም መሀመድ ተተክቷል፡፡ የሳሞራ እና የሞላ ልዩነት በመለስ ዘመንም በአደባባይ የሚታወቅ እንደነበረ ሰምቻለሁ፡፡

ለጉዳዩ ቅርብ ከሆነ የመረጃ ምንጬ እንዳረጋገጥኩት የአስተዳደር ዘይቤውን በማኪያቬሊያዊ አስተሳሰብ (ከፋፍለህ ግዛ) የሚያሳልጠው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ፣ ለሞላ ትዕዛዝ የሚሰጠውም ሆነ ማንኛውንም ጉዳይ በተመለከተ የሚያነጋግረው የዕዝ ተዋረዱን ጠብቆ በኤታ ማዦሩ በኩል ሳይሆን፣ በቀጥታ በመገናኘት መሆኑ፣ አየር ኃይሉን ከመከላከያ ሚኒስቴር የተገነጠለ አስመስሎት ነበር፤ ይህ ሁኔታም በሁለቱ መኮንኖች መካከል ያለው ግንኙነት የሥልጣን ተዋረድን የጠበቀ እንዳይሆን በማሰናከሉ በጄነራሉ ላይ ደፍሮ የማይናገረው ቅሬታ ሊያሳድርበት ችሏል፤ ከመለስ ህልፈት በኋላም ሳሞራ ሂደቱን ለማስተካከል መሞከሩ፣ በየግምገማው ላይ እስከ መዘላለፍ አድርሷቸው ነበር (በነገራችን ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ እንደ ጦር ኃይሎች አዛዥነቱ፣ ከጄነራሎቹ ጋር መደበኛ /Official/ በሆነ መንገድ ትውውቅ አላደረገም፤ እነዚህ ሶስት ጄነራሎችም ለዚህ አይነቱ የአሰራር መፋለስ ጥፋተኛ የሚያደርጉት አለቃቸውን ሳሞራ የኑስን ነው፤ ከምንጮቼ እንደሰማሁት ከሆነም ከወራት በፊት ኃይለማርያም ደሳለኝ በተገኘበት ‹ጎልፍ ክለብ› በሚባለው የጄነራሎቹ መዝናኛ በተዘጋጀ ፕሮግራም ማጠናቀቂያ ላይ ሳሞራ አንድ ጠረጴዛ ከበው ወደ

ተቀመጡት እነዚህ ጄነራሎች ጋ ሄዶ ‹ኑ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ላስተዋውቃችሁ› ማለቱን እና እነርሱም በጥያቄው ተበሳጭተው ቢሮ ያላቸው መሆኑን እና ክብራቸውን በሚመጥን መልኩ መተዋወቅ እንደነበረባቸው በኃይለ ቃል መመለሳቸውን ነው)

የሳሞራ የኑስ እና ሰዓረ መኮንን መነቋቆር ከትግሉ ዘመን ጀምሮ የመጣ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ሳሞራ ከማንም በላይ የሚፎካከረውም ሆነ መበለጥ የማይፈልገው በሟቹ ጄነራል ኃየሎም አርአያ እንደ ነበር የቀድሞ ጓዶቻቸው ያስታውሳሉ፤ ይህ ሁኔታ ዛሬም ድረስ በስራ ላይ ያሉ መኮንኖችን ‹የሳሞራ› ወይም ‹የኃየሎም ተከታይ› በማለት መከፋፈሉ በጓዶቻቸው እና በፓርቲው መሪዎች አካባቢ የሚታወቅ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ለማዕረግ እድገት የተለየ የድጋፍ አስተያየት የሚያገኙት በዛን ዘመን ‹የሳሞራ ተከታይ› የሚባሉት እየተመረጡ እንደነበረ በወሬ ደረጃ ይናፈሳል (በነገራችን ላይ ጄነራል ሳሞራ ከጤንነት ጋር በተያያዘ በአጭር ጊዜ ውስጥ በጡረታ ይሰናበታል በተባለበት ጉዳይ ላይ እያንገራገረ እንደሆነ ከመከላከያ አካባቢ የሚወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ፤ እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው ደግሞ ‹ለእኔ በጎ አመለካከት የላቸውም› በሚል የሚጠራጠራቸው ጄነራሎች በሥራ ላይ እያሉ የእሱ ጡረታ መውጣት ከመስሪያ ቤቱ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ያደሩ የሙስና ካርዶች የሚመዘዙበትን ዕድል ያሰፋዋል የሚል ነው፤ በተለይም በግዙፍ የቢዝነስ ሥራዎች ላይ በታላቅ ተፎካካሪነት እየተሳተፈ የሚገኘው ‹መቴክ› ምንም እንኳ ማረጋገጫዎች ባይቀርቡበትም በመከላከያ ሥር ከነበረበት ዘመን እስከ 2002 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ ከግዥዎች ጋር ተያይዘው የሚነሱ በርካታ የሙስና ሁኔታዎች በመኖራቸው ነው፡፡

መቴክ ካለፉት አራት ዓመታት ጀምሮ በአዋጅ የልማት ድርጅት እንዲሆን ቢደረግም፣ ዛሬም ዳይሬክተሩ የሠራዊቱ አባል ብርጋዴር ጄነራል ክንፈ ሲሆን፣ መከላከያ ደሞዝ የሚከፍላቸው ጥቂት የማይባሉ ሠራተኞችንም እንዳቀፈ ይታወቃል፡፡ እናም ሳሞራ ሃሳቡ ከተሳካለት ለጥቂት ተጨማሪ ዓመታት በሥልጣኑ ላይ ሲቀጥል፣ አሊያም ‹የወንድ በር› ለማግኘት በትግሉ ዘመን የእርሱ ሰልጣኝ እንደነበረ የሚነገርለትን እና በቅርቡ ብቸኛው ከሜጀር ወደ ሌፍተናት ጄነራል ማዕረግ ያደገው ዮሀንስ ገ/መስቀል እንዲተካው መንገድ ጠረጋውን ማመቻቸቱ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራበት ጉዳይ ይመስለኛል)

ይህም ሆኖ የተኮረኮርን ያህል የምንስቀው ጄነራል ሳሞራ የኑስ በቅርቡ ለታተመው ‹‹ህብረ ብሔር›› መፅሄት ሙስና ለሠራዊቱ አደገኛ መሆኑን እንዲህ በማለት መግለፁን ስናነብ ነው፡-
‹‹ሙስና ሠራዊቱን ሊያበላሸው ይችላል፡፡ ሙስና ፀረ-ልማት ነው፤ ሠራዊቱን ሊበትነው እና ሕዝባዊ ባህሪውን እንዲያጠፋ ሊያደርገው ይችላል፤ አንድ ሠራዊት ሠራዊት ነው የሚባለው እንደ ወታደር እንደ አንድ አካል ሲያስብ እንጂ ለግሉ ሲያስብ አይደለም፡፡ …በአጠቃላይ (ሠራዊቱ) በዚህ ነው የሚፈርሰው፡፡›› 

መቼም ጄነራሉ ይህንን የተናገረው እራሱን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ መኮንኖች እንደ እንግሊዝ ንጉሳውያን ቤተሰቦች በተንጣለለ ቪላ ቤት ውስጥ፣ የተቀማጠለ ኑሮ መኖራቸውን ረስቶት አይመስለኝም፤ ‹ይህ የተንዛዛ ወጪያቸውም የሚሸፈነው ከደሞዛቸው በሚያገኙት ገቢ ነው› ብሎ ቧልት መሳይ ክርክር ሊያመጣ አይችልም፡፡ ይሁንና እታች ያለው ጭቁን የኢትዮጵያ ሠራዊት ምንም እንኳ በአለቆቹ ‹ቴክሳስ›ነት ላይ ለመቆጣት ባይደፍርም፣ እንደማንኛውም ዜጋ ለኑሮ ውድነትና አስከፊ ድህነት የተጋለጠ መሆኑን መካድ አይቻልም፡፡

የሆነው ሆኖ ተሰሚነታቸው እየተቀዛቀዘ የመጣው አቦይ ስብሃት ነጋ ከወራት በፊት ለ‹‹ውራይና›› መፅሔት ‹‹ህወሓት ትንሳኤ ያስፈልገዋል›› በማለት የሰጡትን ምክር ተከትሎ፣ ጄነራል ሳሞራ እና አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ ከድርጅቱ ምክትል ሊቀ-መንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ጋር በመተባበር ህወሓትን ለማጠናከር እና በፖለቲካ ውስጥ የነበረውን የአንበሳውን ድርሻ ለማስከበር (ጉዳዩን ከለጠጥነው ደግሞ ‹ለማስመለስ›) እየሰሩ እንደሆነ ይነገራል (በነገራችን ላይ የሳሞራና ጌታቸው ተፅእኖ መጨመሩን ለመረዳት፣ መከላከያ ‹አገራዊ ጥቅምንና ደህንነትን ለመከላከል› በሚል ‹እጅግ ጥብቅ ሚስጢር ብሎ የሰየማቸውን የሰው ኃይል ፕሮፋይል፣ የሒሳብ መዝገቦችና ሰነዶች እና የክፍያ ማስረጃዎች ለማንም አካል እንዳይገለፅ› የሚያስችለውን ስልጣን፣ ደህንነቱ ደግሞ በስራ ላይ የሚፈፅማቸው ማንኛውም ጉዳዮች ወደፊት በህግ እንዳይጠይቅ እስከ መከላከል የሚደርሰውን አዲስ የተዘጋጁትን አዋጆች ማንበቡ በቂ ነው፡፡ በርግጥ እነዚህ ባለሥልጣናት እንዲህ ባለ ተመሳሳይ መንገድ እንዲጓዙ ያስተሳሰራቸው አንዱ ጉዳይ ‹ህወሓት ተዳከመ፣ ተሸነፈ፣ አበቃለት…› የሚለው የካድሬውና ደጋፊው ቁጭት እንጂ ወትሮም መልካም ግንኙነት ኖሯቸው አይመስለኝም)
ለማንኛውም በጥቅሉ ሲታይ የህወሓት ትልቁ ችግር ተብሎ በአመራር አባላቱ የሚጠቀሰው ‹በዚህ ወቅት ወደፊት መምጣት የሚችሉ ጠንካራ ቴክኖክራቶችን አለማፍራቱ፣ ሁለንተናዊ ድጋፍ የሚያደርግለትን የታጠቀውን ኃይል ተጠቅሞ የፖለቲካ ልዩነቱን ጨፍልቆ በአሸናፊነት ይዞት መውጣት የሚችል መሪ እንዳይኖረው አደረገ› የሚል ነው፡፡ በርካታ የላይኛ እና የታችኛው ካድሬዎችም ‹ለእንዲህ አይነቱ ክፉ ጊዜ ድርጅቱ የሚያስፈልገው፣ በትግሉ ዘመን ልምድ ያካበተ ታጋይ ብቻ ነው› የሚል አቋም እንዳላቸው ይነገራል፡፡ ስርዓቱ ከሚያራምደው ርዕዮተ-ዓለም ጋር ጠንካራ ትውውቅ ያሌለውን እና የትግሉን ዘመን በአሜሪካን ሀገር በማሳለፉ ‹የምዕራባውያን ድጋፍ አለው› ለሚባለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የሚሰጡት ዝቅተኛ አመለካከት መግፍኤም ይኸው ይመስለኛል፡፡

ለነገሩ እርሱም ቢሆን በጠንካራ ድርጅታዊ ዲሲፕሊን ካለመታነፁ እና መሰል ጉዳዮች ጋር በሚያያዙ ምክንያቶች ለትንፋሽ ጊዜ የማይሰጠውን የድርጅት ሊቀ-መንበርነትንም ሆነ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ የሚወራውን ያህል ይፈልገዋል ብሎ መደምደሙ አስቸጋሪ ነው ብዬ አስባለሁ፤ ከዚህ ይልቅ በተፈጥሮ ከታደለው የተግባቢነት ባህሪው አኳያ እንደ ሕዝብ ግንኙነት የመሳሰለ ብዙም የማያጨናንቅ ሥራን ይመርጣል፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ከሰለጠነበት ሙያ ጋር የቀጥታ ተያያዥነት ያለውን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በሚመራበት ዘመን፣ ከውጭ ሀገር በርካታ የተቋረጡ ፈንዶችን እንደገና ለማስለቀቅ መቻሉ እንደ ታላቅ ስኬት የሚወራለት፤ አልፎ ተርፎም ‹ወባን ከኢትዮጵያ ምድር ለማጥፋት ብርቱ ትግል አደረገ› ተብሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሳይቀር እስከ መሸለም የደረሰው እዚህ መስሪያ ቤት እያለ እንደሆነም ይታወቃል፡፡

የፖለቲካውን መዘውር የጨበጠው ኃይል


በሌላ በኩል ደግሞ በፓርቲውም ሆነ በመንግስት አስተዳደር ከህወሓት ሰዎች ትልቁን ስልጣን የያዘው ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ከምዕራባውያን ጋር የቆየ ቀረቤታ እንዳለው ሰምቻለሁ፤ እንደሚታወሰው ደብረፅዮን ከክፍፍሉ በፊት (የደህንነት መስሪያ ቤቱ እንዲህ እንደ ዛሬው እጅግ ዘመናዊ በሆነው የቻይና ቴክኖሎጂ ሳይጥለቀለቅ) ከነበረው ከፍተኛ የሥልጣን ቦታ ላይ ተነስቶ፣ ቁልቁል ወርዶ በሁመራ በአንድ ዞን እንዲሰራ የተመደበው (ሁላችንም ስንገምት እንደነበረው) የአንጃው አባል ወይም ደጋፊ ሆኖ አይደለም፤ ይልቁንም የእነስዬ-ተወልደ ቡድን በመባል የሚታወቀው (‹አፈንጋጩ› ኃይል) ደብረፅዮንን በሲ.አይ.ኤ እና ሞሳድ ወኪልነት የመክሰሱ ጉዳይ የድርጅቱን በርካታ አባላት ቀልብ በመሳቡ፣ መለስ ይህንን ተከትሎ ከሚመጣበት አደጋ ራሱን ለመከላከል የወሰደው እርምጃ በመሆኑ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት እስከ 1998 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ በሁመራና ራያ አካባቢዎች በዞን ደረጃ ለማገልገል ተገዷል፡፡ እናም እርሱን የምዕራቡ ዓለም ፊት-አውራሪ አሜሪካና ሸሪኮቿ ወዳጅ ነው የሚያስብለው በቀድሞ መስሪያ ቤቱ በኩል በነበረው ግንኙነት ይመስለኛል።

የዚህ ቡድን አምበል እንደ ድርጅት ብአዴን ቢሆንም፣ በቋሚ ተሰላፊነት ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ አባዱላ ገመዳ፣ ሙክታር ከድር እና ሬድዋን ሁሴን እንደሚገኙበት ይነገራል፤ ለብአዴን ‹በተሻለ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ላይ ለመገኘቱ መደላድል ፈጥሮለታል› የሚለውን ሙግት ምክንያታዊ የሚያደርገው ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲና ጥናት ምርምር አማካሪ በረከት ስምዖን፣ የኢህአዴግን የካድሬ ማሰልጠኛ ማዕከል በዳይሬክተርነት የሚመራው አዲሱ ለገሰ፣ ደርቦ ይዞት የነበረውን የትምህርት ሚኒስትርነት ለሽፈራው ደሳለኝ በመልቀቅ፣ በአሁኑ ወቅት ሙሉ የስራ ጊዜውን በግንባሩ ፅ/ቤት የሚያውለው ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባኤው ካሳ ተክለብርሃን የያዙት ሥልጣን ያለውን የፖለቲካ አቅም መመዘኑ ይመስለኛል፡፡ በመከላከያ ሠራዊቱ ውስጥም ከሳሞራ አንድ እርከን ዝቅ ባለ ሥልጣን ከሌሎች ሁለት ጄነራሎች ጋር የሚገኘው አበባው ታደሰ እንደ ቀድሞው በዕዝ አዛዥነቱ (በቀጥታ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ወታደሮችን ማንቀሳቀስ የሚችልበት) ላይ ቢሆን ኖሮ ጥንካሬውን የተሟላ ማድረጉ አይቀሬ እንደነበረ መገመት ይቻላል፡፡

ከዚህ ሌላ ለእነበረከት ቡድን ተጨማሪ የፖለቲካ ጉልበት እየሆናቸው ያለው የኃይለማርያም ደሳለኝ ቢሮ እና በአባዱላ ገመዳ አፈ-ጉባኤነት የሚመራው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ነው፡፡ አባዱላ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፖርት ለማቅረብም ሆነ ለመታዘዝ ፍቃደኛ ያልሆኑ አንዳንድ ባለስልጣናት፣ በውስጥ መስመር በሚተላለፍለት ‹ጥቅሻ› በምክር ቤቱ በኩል የሚመለከተው የቋሚ ኮሚቴ አባላት አስጠርቶ የተሰጠውን ኃላፊነት የሚገመግምበት ስልት እየተገበረ ነው፡፡ በአናቱም ምን ጊዜም የሳምንቱን የሥራ መጨረሻ ቀን አርብን ጠብቆ የሚሰበሰበው የሚኒስትሮች ም/ቤትን ከሞላ ጎደል ይህ ቡድን እየጠቀመበት ይመስለኛል፡፡ በርግጥ ሚኒስትሮቹ በሚገናኙበት አብዛኛውን ሰዓት ሳይግባቡ (በጭቅጭቅ) ማሳለፋቸው ይነገራል፤ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ በአቶ መለስ ዘመን ም/ቤቱ የሚሰበሰበው የተለያዩ አጀንዳዎችን ለማቅረብ እና በቀረበው አጀንዳ ላይ ለመከራከር (ለመመካከር) ሳይሆን፣ መለስ ወስኖ የመጣበትን የሥራ ድርሻ ተቀብሎ ለመበተንና ሪፖርት ለመስማት የነበረው አሰራር፣ ዛሬ ተቀይሮ በርካታ የተነቃቁ ሚኒስትሮች የየራሳቸው ሃሳብ ተቀባይነት እንዲያገኝ (ለማንፀባረቅ) የሚታገሉበት መድረክ ወደ መሆን በመሸጋገሩ ነው፡፡ ይህም ሁናቴ ዋናውን የመንግስት ሥራ የመገምገም እና የማስፈፀም አቅምን ሳይቀር ከሚኒስትሮች ም/ቤት ወደ ኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ አሻግሮታል የሚያስብሉ ማሳያዎች አሉ፡፡ ይሁንና በዚህስብሰባ ላይም ቢሆን ደፈር ብሎ ከበረከት ስምዖን እና አባይ ፀሀዬ የተሻለ አዳዲስ ሃሳብ የሚያቀርብ ባለሥልጣን እንደሌለ ሰምቻለሁ (በነገራችን ላይ ምክንያቱን ባላውቅም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹የፖሊሲና ጥናት ምርምር አማካሪ› ተደርገው የተሾሙት በረከት ስምዖን፣ አባይ ፀሀዬ፣ ኩማ ደመቅሳ እና ዶ/ር ካሱ ኢላላ የሥራ ቦታቸው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት ሳይሆን መገናኛ አካባቢ በሚገኝ አንድ ህንፃ ላይ ነው፡፡ የተሰጣቸው ኃላፊነት ኃይለማርያምን በቅርብ እንዲያገኙ ከማስገደዱ እና በግልፅ ከሚታወቀው የአማካሪ አስፈላጊነት አኳያ ካየነው ግን ግራ የሚያጋባ ይመስለኛል)

ጠቅላይ ሚኒስትሩ…

ኃይለማርያም ደሳለኝ ይህንን ቦታ ከያዘ በኋላ፣ ብዙዎች በስልጣኑ የማዘዝ አቅሙ ላይ አመኔታ እንደሌላቸው (አንጋፋ ታጋዮች እንደ ‹አሻንጉሊት› ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ) ደጋግመው መግለፃቸው ይታወሳል፡፡ በግልባጩ ‹አፈንግጦ ለመውጣት መሞከሩ አይቀሬ ነው› የሚሉ ግምቶች ነበሩ፡፡ በርግጥ እነዚህ መላ-ምቶች ዛሬም ድረስ እልባት ባያገኙም፣ እዚህ ጋ ያልጠቀስኳቸው አንዳንድ ጉዳዮች ላይ ያሳያቸው ወጣ ያሉ አቋሞቹን ሳስተውል ግን፣ አሁን ያለው አሰላለፍ (የአነበረከት እና አባዱላ ፖለቲካዊ መጠናከር) ለእርሱም የተረፈው ይመስለኛል፡፡ እንዲሁም ከቤንች ማጂ የተባረሩ አማርኛ ተናጋሪዎችን አስመልክቶ በድርጅቱ ውስጥ ባልተለመደ መልኩ ‹አጥፊዎቹ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ› ከማለት አንስቶ (በነገራችን ላይ በአማካሪ ብዛት እንዲከበብ ካደረገው ምክንያት አንዱ ጓዶቹ በዚህ ንግግሩ መበሳጨታቸው ነው) በቅርቡ ህወሓትን ለመሸምገል በተዘጋጀ መድረክ ላይ ‹ሁኔታዎች እንዲህ እየተካረሩ ከሄዱ ወደ ማሰሩ መግባታችን አይቀርም› በማለት ማስፈራራቱ እና በቴዎድሮስ አድህኖም የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም ላይ የመቆጣቱ ጉዳይ ድረስ የሚካተቱ እውነታዎች ሰውየው የራሱን መንገድ ለመከተል እየሞከረ መሆኑን ያሳያሉ ብዬ አስባለሁ፡፡
የሆነው ሆኖ እነዚህ ሁናቴዎች የፖለቲካውን ጉልበት ሙሉ በሙሉ በብአዴንና በተባባሪነት በጠቀስኳቸው የኦህዴድና ደህአዴን የአመራር አባላት አካባቢ ቢያከማቻቸውም፣ በማንኛውም ሰዓት ያሻውን ማድረግ የሚችለው የታጠቀው ኃይል ደግሞ ከህወሓት ጎን እንደተሰለፈ ይገኛል፡፡ መጪውን ጊዜም አዲስ ክስተት እንድንጠብቅ ገፊ ምክንያት ይህ አይነቱ የኃይል አሰላለፍ ይመስለኛል፡፡

ምን እንጠብቅ?

ከረጅሙ የፓርቲ ፖለቲካና መንግስታዊ መንገራገጮች በኋላ፣ የሁለቱንም የኃይል መሰረቶች ጠቅልሎ በመዳፉ ሥር የከተተው መለስ ዜናዊ በሞተ ማግስት ‹የኃይል መገዳደሮች ሊከሰቱ ይችላሉ› የሚለው የብዙዎቹ ግምት ነበር፤ ከወራት በፊት አስነብቤ በነበረው ከላይ በተጠቀሰው ፅሁፍም ግምቶቹ እውን መሆን እንደ ጀመሩ ማሳያዎች ማቅረቤ ይታወሳል፡፡ ኢህአዴግ ውስጥ ራሳቸውን ያቧደኑት ኃይሎች ዋነኛ ግብ ከሥልጣን የሚነሱ ጥቅሞችና አነስተኛ የየራሳቸው ፓርቲ ፍላጎቶች የፈጠሩት በመሆኑ፣ እንደ ሟቹ ደመ-ቀዝቃዛ አምባገነን አይነት በጠንካራ መዳፍ ሥር የሚያሰባስባቸው ባለመገኘቱ በየጊዜው የኃይል መሸጋሸጎች ሊከሰቱ እንዲችሉ አድርጓቸዋል፤ አሁንም እየተስተዋለ ያለው ይኸው እውነታ ነው፡፡ 

በዚህ አውድ ላይ ቆመን ሊፈጠሩ የሚችሉ የቢሆን ሃሳቦችን ስናስቀምጥም በጠረጴዛው ላይ የምናገኘው ሁለት ዕድሎችን ይመስለኛል፡፡
የመጀመሪያ ሲናሪዮ የሚሆነው ከላይ የጠቀስኩት ቡድንተኝነት እንዳለ ሊቀጥል ይችላል የሚል ነው፤ ይህም የሚሆንበት ምክንያት ባለኝ መረጃዎች መሰረት የፖለቲካውን መስመር የያዘው ቡድን መሪ አባላት፣ አሁን ያላቸውን መንግስታዊ ሥልጣን ጠብቀው መቆየትን መሰረታዊ መሰባሰቢያ አጀንዳ ማድረጋቸው ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የሳሞራና ጌታቸው ጥምረት ህወሓትን ወደ ቀደመው ዘመኑ ለመመለስ ቢሻም፣ ሊሄድበት የሚችልበት መንገድ አደገኛ መሆኑ (ወታደራዊ ላዕላይ መዋቅሩንና የደህንነት ኃይሉን ከመያዙ አኳያ) ሁኔታዎችን ባሉበት ይዞ መቀጠልን በትርፍ-ኪሳራ ስሌት የተሻለ አማራጭ አድርጎ ይወስደዋል ብዬ አስባለሁ፡፡

ሁለተኛው የቢሆን ዕድል፣ ዳግመኛ የኃይል መሸጋሸግ ሊፈጠር መቻሉ ነው፤ ሰዎቹ ጥቅመኛ በመሆናቸው የቋንቋ ተናጋሪነት ልዩነቶቻቸውንና የኋላ የመቆራቆስ ታሪኮቻቸውን ተሻግረው፣ አንዳቸው ከአንዳቸው ጋር ሌላ መልክ ያለው ስብስብ ሊፈጥሩ ይችሉ ይሆናል፤ ይህ አይነቱ አዲስ የኃይል አሰላለፍም፣ ከቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ በፊት በማይታወቀው ተሰዊና ሰዊ ሊጠናቀቅም ይችላል፡፡

በመጨረሻም ምንም ይፈጠር ምን፤ እኛን ሊያግባባን የሚገባው ጭብጥ፣ የትኛውም ቡድን በግንባሩ ውስጥ ቢነሳ፣ የማዕከላዊ መንግስቱን ህልውና ወደሚበታትን ሂደት መግባቱ ሊሰካለት አለመቻሉ ነው፤ ምክንያቱም በዚህ መልኩ ሄዶ የሚጣሉበትን ጠረጴዛ መስበሩ ምን እንደሚያስከትል ያውቁታልና ወደዚህ ምዕራፍ እንደማይሻገሩ አምናለሁ፡፡ ይሁንና ከፓርቲው ዝግነት እና ከፖለቲከኞቹ አቋም የለሽነት አንፃር አሁንም ሆነ በቀጣይ ጊዜያት ከማንም ግምት ውጪ ያሉ ክስተቶች እንደ ደራሽ ውሃ ድንገት ሳይታሰብ ግንባሩን ሊያተራምሱት ይችላሉ ብሎ መገመቱ አግባብ ይመስለኛል፡፡