Wednesday, December 11, 2013

“የወደፊቷ ደቡብ አፍሪካ ከማንዴላ ጋር መያያዟን እጠራጠራለሁ” ፕሬዚዳንት መንግሥቱ

December 11/2013

ለማንዴላ የገንዘብ ድጋፍ ሰጥተናል፣ ታምመው አስታመናል
mengistu-hailemariam


የኔልሰን ማንዴላን ሕልፈት በማስመልከት አውስትራሊያ ከሚገኘው ኤቢኤስ ሬዲዮ የአማርኛ አገልግሎት ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል፡፡ መንግሥቱ ለሬዲዮው በሰጡት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፣ በእሳቸው በትረ ሥልጣን ወቅት ማንዴላ የአገሪቱን ከፍተኛ የክብር ሽልማት ከመጎናፀፈቸውም ባሻገር፣ የአንድ መቶ ሺሕ ዶላር ገንዘብ ተበርክቶለቸዋል፡፡ ይህና ቀሪው ንግግራቸው እንዲህ ቀርቧል፡፡
‹‹ማንዴላና የተወሰኑ ተከታዮቻቸው ወደ ኢትዮጵያ በስውር መጥተው፣ ወታደራዊ ሥልጠና አግኝተውና እግረ መንገዳቸውን ሞሮኮን ጐብኝተው ወደ ደቡብ አፍሪካ ማምራታቸውን ተገንዝቤያለሁ፡፡
‹‹በዚያን ጊዜ አሜሪካኖች በአማካሪነት ኢትዮጵያ ውስጥ ነበሩ፡፡ እስራኤሎችም ነበሩ፡፡ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ግንኙነት የነበራቸው በመሆኑ የማንዴላን ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘትና ወታደራዊ ሥልጠና በመከታተል እግር በእግር እየተከታተሉ መረጃ ሲሰበስቡ ስለሰነበቱ፣ ሰውየው አገራቸው እንደደረሱ ወዲያውኑ እጃቸው ተይዞ ወህኒ ቤት ገብተዋል፡፡
‹‹በሮቢን ደሴት ውስጥ ብቻ ሳይሆን በተለያየ ጊዜ ከአንድም፣ ሁለት ሦስት ጊዜ ጆሃንስበርግ ውስጥ ታስረዋል፡፡ የመጨረሻውና ትልቁ ለ27 ዓመት የታሰሩበት ጊዜ ነው፡፡
‹‹እኔ ማንዴላን በስም እንጂ በገጽ አይቼ አላውቅም፡፡ ልጆች ሆነን በምንሰማው ሁሉ ስለአፓርታይድ ያለንን ጥላቻ በተለያየ መልኩ የምንገልጽ ሰዎች ነበርን፡፡ በኢትዮጵያ አብዮት ወቅት ተለቅቀው በመጀመሪያ ደረጃ ዚምባቡዌ በሁለተኛ ደረጃ ኢትዮጵያ መጥተዋል፡፡ እንደ አጋጣሚ በዚያን ጊዜ የአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ በሚካሄድበት ጊዜ እሳቸውም የስብሰባው ተሳታፊ ነበሩ፡፡ አጋጣሚ ሆኖ ጤናቸው በጣም የተጐሳቆለና ብርድ ቢጤም መትቷቸው ታመው ስለነበር እኛ ዘንድ ከአንድ ሳምንት በላይ አስታምመናል፡፡ ጠና ያለ በሽታ ስለነበር ሐኪሞች ተሰባስበው የሚቻለውን ሕክምና ሁሉ አድርገው አስታምመናል፡፡
‹‹ስለታሪካቸው፣ ስለ ወህኒ ቤቱ፣ ስለሌላውም ሁሉ በሰፊው አነጋግሬያቸው አጫውተውኛል፡፡ በመጨረሻም የጠየቁኝ ነገር ነበር፡፡ የዚያን ጊዜ ከእስር ቤት እንደወጡ ስለዓለም ወቅታዊ መረጃ ያላቸው ግንዛቤ ውስን ስለነበረ እንዴት ሆኖ ነው ሶቪየት ኅብረት እንዲህ ዓይነት ሥራ የሠራው? ለመሆኑ ዓለም አቀፋዊ ስብሰባ አልተደረገም ወይ? አልተነጋገራችሁም ወይ? በዚህ መልኩ እንዴት ነው አብዮት የተቀለበሰው፣ ወዘተ በማለት እነ ጐርባቾቭ ስለሠሩት ሥራ በመጸጸት፣ የእኔ አገር ለሶሻሊዝም በጣም የተመቻቸች (ፈርታይል) ነች፤ የምናራምደው ይኼንኑ ነው አሉኝ፡፡ አይ እንደዚህ ዓይነት ውሳኔ ላይ ከመድረስዎ በፊት እስቲ ጊዜውንና ወቅቱን ይዩት፡፡ እርስዎ ዓለምን የሚያውቁበት ሁኔታ በእስር ቤቱ ምክንያት ምን እንደሚመስል ትንሽ ሰንብተው ይመልከቱና የሚወስዱትን ዕርምጃ ቢያመዛዝኑ ይሻላል፡፡ እኔ የምደግፈውና እናንተም ያነሳችሁት መፈክር ‹አንድ ሰው አንድ ድምፅ› (ዋን ማን፣ ዋን ቮት) ባላችሁት መርህ መሠረት የደቡብ አፍሪካ ሕዝብ ነፃነቱን ያግኝና ከዚያ በኋላ የትኛውን የዕድገት አቅጣጫ እንከተል የሚባለውን ነገር ልታዩት ትችላላችሁ አልኳቸው፡፡ ይህን ያህል ነው የተነጋገርነው፡፡
‹‹በእኛ በኩል ምን የምንረዳው ነገር ካለ ብንላቸው ምንም ነገር የለም፡፡ በአሁኑ ጊዜ በፖለቲካ ውሳኔ ነው የተፈታሁት፡፡ ነፃነታችንም በዚሁ መልኩ የተገኘ ስለሆነና ሌላ ትግል የሚጠይቅ ባለመሆኑ ምንም ዕርዳታ አያሻኝም አሉ፡፡ እኔ እንኳ ትጥቅ ወይም ሌላ ያስፈልግ ይሆን በሚል ነው የጠየቅኳቸው፡፡ ለሰውየው ትልቅ ክብር ስላለኝ በመሪ ደረጃ ያን ጊዜ ባይሆኑም አውሮፕላን ማረፊያ ድረስ ሸኘኋቸው፡፡ የዚያን ጊዜ ኦሊቨር ታምቦ በፅኑ ታሞ ስለነበር እርሱን ስዊድን ሄጄ ልጠይቅና ህንድ ደርሼ ወደ አገሬ እመለሳለሁ አሉኝ፡፡
‹‹መቼም ከእስር ቤት ነው የወጡት፡፡ ምንም ነገር የላቸውም በሚል ግምት አንድ መቶ ሺሕ የአሜሪካ ዶላር ቼክ ሰጠኋቸው፡፡ ከዚያ በኋላ የተገናኘነው ዚምባቡዌ ነው፡፡ ዚምባቡዌ በዚያን ጊዜ የገለልተኛ ንቅናቄን ታስተናግድ ስለነበር በዚያን ጊዜ ነው የተገናኘነው፡፡
mengie and madiba‹‹ብዙ ሰዎች ሰውየውን ለማነጋገር ያስቸግሩ ስለነበርና የነበራቸውም ጊዜ በጣም ውስን ስለበር እኔም በዚያ ላይ ተጨምሬ ማስቸገር አልፈለግሁም፡፡ ማንዴላ እንደ ብርቅ ናቸው፡፡ ግማሹ ቀርቦ ለማነጋገር፣ ምን ዓይነት ሰው ነው፣ ምንስ ይመስላል በሚል ብዙዎች መሪዎች ከፍ ያለ ጉጉት ስለነበራቸውና የማነጋገር ጊዜ ስላነሰ፣ እኔ በዚህ ጊዜ ፕሮቶኮሌን ልኬ ሳነጋግራቸው፣ በከፍተኛ ችግር ውስጥ ያሉ ሰው ናቸው፡፡ እንጃ ምን ያህል እንደሚያነጋግሩዎት አሉኝ፡፡ አይ እንግዲያውስ እግረ መንገዳችንን ስብሰባው ላይ እንዴት ነዎት? ተሻለዎት? ምን አዲስ ነገር አለ? አልኳቸው፡፡ አመሰግናለሁ ኢትዮጵያ ውስጥ ለተደረገልኝ ሁሉ በሚል ተለያየን እንጂ የሰፋ ውይይት አላደረግንም፡፡
‹‹ኢትዮጵያ በመጡ ጊዜ እንደሚታወሰው በከፍተኛ ክብርና ሥርዓት በወቅቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረውን የኢትዮጵያን የክብር ኰርዶን ነው የሸለምናቸው፡፡ ስለተደረገው ትግልና ስለሳቸው ማንነትም ሰፋ ያለ ንግግር አድርጌያለሁኝ፡፡ በዚያው መሠረት እሳቸውም አንፃራዊ መልስ ቀደም ብሎ ኢትዮጵያን እንዴት እንደሚያውቋት፣ ኢትዮጵያ ብቸኛ የነፃነት ኰከብ ሆና እንደኖረችና ከልጅነት ጀምሮ ኢትዮጵያን ሲያስቡ፣ እንደተስፋ ሲመለከቱ የኖሩ መሆናቸውን፣ በሒደትም ያዩትና የተገነዘቡት ይኼንኑ መሆኑን የሚገልጽ ታሪካቸውን ተናግረዋል፡፡ ዛሬ ተመልሼ መጥቼ መካከላችሁ ስቆም የሚሰማኝ እንደገና የመወለድ ዓይነት ነው በሚል በጣም ልብ የሚነካ ንግግር አድርገዋል፡፡ ከዚያ በኋላ ዚምባቡዌ ከመገናኘታችን በቀር አላገኘኋቸውም፡፡ ከፕሬዚዳንትነት ወርደው ሌሎች ሥራውን በሚመሩበት ጊዜ ብዙ ኢትዮጵያውያን ችግር ይደርስባቸው ስለነበር ኢትዮጵያውያንን አትንኩ፣ አገራቸው ነው፣ ይኑሩ ተንከባከቧቸው ብለው በታቦ ምቤኪ ጊዜ በመናገራቸው ዛሬ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ይኼ ነገር በከፍተኛ ደረጃ ይሰማቸዋል፡፡ የሰሞኑም ሐዘን በኢትዮጵያውያን ላይ ልዩ ስሜት እንደሚያሳድርባቸው አልጠራጠርም፡፡ ይኼን ነው የማውቀው፡፡ ሌላው ጽፈዋል፡፡ ‹ረጅሙ ጉዞ› የሚውን መጽሐፍ ጽፈዋል፡፡ እዚያ መጽሐፍ ውስጥ ስለኢትዮጵያ የሚያውቁትን፣ ያዩትንና የተደረገላቸውን ነገር አትተው በአክብሮትና በፍቅር ጽፈዋል፡፡ ይኼንን ነው ስለማንዴላ የማስታውሰው፡፡
በማንዴላ ሕልፈት ምን ተሰማቸው?
እዚህ በደቡባዊ አፍሪካ አካባቢ የምንገኝ ሰዎች የሰውየውን የጤና ሁኔታ እናውቃለን፡፡ በየጊዜውም እንሰማለን፡፡ መሪዎች ወንድሞቼም ሁሉን ነገር ስለሚያውቁ ይነግሩኛል፡፡ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ሰውየው ዕድሜያቸው ውስን እንደሆነ ስለምናውቅ፣ ሆስፒታልም ለመጀመሪያ ጊዜ በረጅሙ መቆየታቸው፣ ልባቸው በከፍተኛ ደረጃ መታወኩ ብሎም መናገር እንደተሳናቸውና እንዳይሞቱ ያህል ይጠበቁ ስለበር፣ ነገ ተነገወዲያ ከማለት ባሻገር ስለሰውየው በቂ ግንዛቤ ስለነበር፣ ሕልፈታቸው እንግዳ ወይም ያልተጠበቀ ነገር አልሆነም፡፡ ያዘንነው ቀድም ብሎ ስለሆነ ሞታቸው ለኔ በግሌ ልዩ ሁኔታ አልፈጠረም፡፡
ወደፊት እንዴት ያስታውሷቸዋል?
እኔ እዚህ ቁጭ ብዬ ስለደቡብ አፍሪካ መተንበይ ያስቸግረኛል፡፡ በውጪው ዓለም በብዙ እንደሚነገረው ለረዥም ጊዜ በእስር መማቀቃቸውና ለነፃነት መታገላቸው ብዙ ብዙ የሚደነቅ፣ የሚወደዱበት፣ የሚከበሩበትና ጀግና የሚያሰኛቸው ሥራ ቢኖርም በሌላ በኩል ደግሞ ውስጥ ያሉ የትግል አጋሮቻቸውንና ጓዶቻቸው በአንዳንድ ችግርና ድክመት ምክንያት ደስተኞች አይደሉም፡፡ ተቃዋሚም አላቸው፡፡ ይኼንን የውጭው ዓለም በውል የሚያውቀው አይመስለኝም፡፡ እስር ቤት በነበሩ ጊዜ ረዥምና ሰፊ ውይይት ተደርጎ ነው እንለቃችኋለን ነፃነታችሁን ታገኛላችሁ፣ አመራርም ላይ ትቀመጣላችሁ፤ ነገር ግን በምንም ዓይነት ሁኔታ ደቡብ አፍሪካን ልትለውጡ አትችሉም፡፡ የነጩን ኅብረተሰብ ሀብት ንብረት ልትነኩ አትችሉም፤ ወይም የጊዜውን ሶሸሊዝም ወይም ማኅበራዊ ሥርዓት የሚባል ነገር አይታሰብም፡፡ በዚህና በዚያ ዓይነት ሁኔታ እንድንኖር ፈቃዳችሁ ከሆነ ነፃነታችሁን ለመስጠት በሚል መንገድ ከውስጥም ከውጭም ከፍተኛ ተፅዕኖ የተደረገባቸው ሰዎች ናቸው፡፡ በዚህ ሁኔታ ወጥተው ያለውን ሥርዓትና ኢኮኖሚ እንዳለ ተቀብለዋል፡፡ በዚህ ምድር በጥቁር ሕዝብ ላይ ግፍ ተፈጽሞ እንደሆነ ደቡብ አፍሪካን የሚያክል የለም፡፡
መግደል፣ መግረፍ፣ ማሰቃየት፣ ማሰርና ማስራብ ብቻ ሳይሆን ወይም ኢሰብዓዊ የጉልበት ሥራ ማሠራት ብቻ ሳይሆን ጥቁሮች እንዳይራቡ፣ እንዳይወለዱ በየምክንያቱና በጤና ችግር ወደ ሆስፒታል በሚሄዱበት ጊዜ በሚስጥር እንዳይወልዱ እያመከኑ የኖሩ ናቸው የአፓርታይድ አራማጆች፣ ነጮቹ፡፡ ብዙዎቹ ጥቁሮች ለዚህ ያላቸው ጥላቻ ወሰን የለውም፤ መናገር ያቅታል፡፡ በእንዲህ ዓይነት መንገድ ከእነሱ ጋር መኖር አለበት ወይ? የሀብት ክፍፍሉና የኑሮ ሁኔታም በእንዲህ ዓይነት መልኩ መቀጠል አለበት ወይ? የሚሉ ብዙ ተቃዋሚዎች አሉ፡፡ ማንዴላ የሚታሰቡበትና የሚከበሩበት የ27 ዓመት እስር ብሎም ደግሞ ነፃነት የማምጣቱ ጥረት አሁን ያለችውን ደቡብ አፍሪካ የመፍጠሩ ነገር እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የወደፊቷን ደቡብ አፍሪካ በሚመለከት አዲሱ ትውልድ ያለው ዓላማ ከእነማንዴላ የተለየ ነው፡፡ ዛሬ ነፃነት አለ ብለው ብዙዎች አያምኑም፡፡ የነፃነት ሰንደቅ ዓላማ ነው የምናውለበልበው እንጂ ሁሉም ነገር የነጮች በመሆኑ፡፡ ተወላጁ ቦታ የለውም ተብሎ ስለሚታመንና እውነትም ስለሆነ የወደፊቷ ደቡብ አፍሪካ ከማንዴላ ጋር መያያዟን እጠራጠራለሁ፡፡ (ሪፖርተር)

የምስራቅ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ፪ – ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

December 11/2013

ባለፈው ሳምንት የምስራቅ ኢትዮጵያ ፖለቲካን ተጨባጭ እውነታዎችን ቃኝቼ ተከታዩን ክፍል በይደር አቆይቼው እንደነበረ ይታወሳል፤ እነሆም ዛሬ እንዲህ እቀጥላለሁ፡-
ሐረር እንደ ማሳያ
(መቼም ኢህአዴግ በብቸኝነት የሚኩራራበት የፖለቲካ ‹ስኬት›፣ ለዘመናት አንድ ሆኖ የኖረ ሕዝብን ‹ብሔር ብሔረሰቦች› በሚል ከፋፋይ የ‹ክርስትና ስም› እጥምቆ በአደባባይ ማስጨፈር ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ ርግጥ ነው በአንድ ወቅት በፍትህ ጋዜጣ ላይ ‹‹የብሔር ብሔረሰቦች መብት እስከ መጨፈር›› በሚል ርዕስ የታተመ መጣጥፍን ተከትሎ ‹ፀረ-ብሔር ብሔረሰቦች› ተደርጌ በተመሰረተብኝ ክስ ፍርድ ቤት መመላለሴ ዛሬም ድረስ መቋጫ አላገኘም፤ ርግጥ ነው ኢትዮጵያውያን ወንድም እህቶቼ በስታዲዮሞች እየተሰባሰቡ የራስ ፀጉራቸው ላይ ላባ ሰክተው፣ ቆዳ አገልድመው እየዘለሉ ትርኢት ከማሳየት ባለፈ የመልካም አስተዳደር፣ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ መብቶቻቸው ተጠቃሚ መሆን አልቻሉም፡፡ …እውነታው ይህ ቢሆንም ወደ አጀንዳችን /የከሸፈው ፌደራሊዝምን/ ወደ መፈተሹ በአዲስ መስመር እንመለስ፡፡

ቋንቋን መሰረት ያደረገው ኢህአዴግ ሰራሹ ‹ፌደራሊዝም› አወቃቀር የሀገሪቱ መፃኢ ዕድል የተቋጠረበት ‹የሰዓት ቦንብ› መሆኑን ለመረዳት የምስራቅ ኢትዮጵያዋን ሐረር እንደ መሳያ መውሰዱን ግድ የሚያደርጉ በርካታ ገፊ ምክንያቶች አሉ፡፡ እንደሚታወቀው የሐረር ከተማ አመሰራረት ብዙሃኑ ህዝብ ከሚኖርበት ‹ጀጎል› ከተሰኘው በግንብ የተከለለ ቅፅር ጋር ይያያዛል፡፡ በ16ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ራሳቸውን ከብሔር ወረራ ለመከላከል በአካባቢው ነዋሪዎች እንደታነፀ በርካታ ድርሳናቶች የሚናገሩለት ጥንታዊውና ታሪካዊው የጀጎል ግንብ በአምስት (ሐረር፣ ኤረር፣ ሠንጋ፣ ቡዳ እና በርበሬ በር በሚባሉ) በሮች የተከፋፈለ ነው፡፡

ጀጎል ከ40ሺ ለማያንሱ የክልሉ ነዋሪዎች መጠለያ ሲሆን፣ ከነዚህ ውስጥ ከዘጠኝ ሺህ በላይ የሕዝብ ቁጥር ያላቸው የሐረሪ ተወላጆች እንደሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ይህም ሆኖ መስከረም 30 ቀን 1997 ዓ.ም. ‹‹የሐረሪ ሕዝብ ክልል መንግስት ሕገ-መንግስት›› በሚል ርዕስ ተሻሽሎ የፀደቀው አዋጅ፣ ስርዓቱ በአደባባይ ከሚመፃደቅበት ቋንቋን መሰረት ያደረገ ‹ፌደራሊዝም› የሚቃረኑ እና ከዴሞክራሲ ባህሪያት ጋር የሚጋጩ በርካታ አንቀፆች የታጨቁበት መሆኑ ለጠቀስኩት ሀገራዊ ስጋት መነሻ ነው፡፡ ለማሳያም ያህል የክልሉ ምክር ቤት ይቋቋምበታል ተብሎ በሕገ-መንግስቱ ውስጥ የተካተተውን የምርጫ ሕግ መመልከት የሚችል ይመስለኛል፡፡ ይህ ሕገ-መንግስት ተሻሽሎ ከመፅደቁ ሶስት ዓመት ቀደም ብሎ በስታስቲክ ባለሥልጣን ይፋ የተደረገው መረጃ የክልሉ ነዋሪ ህዝብ ብዛት በጥቅሉ 131,139 እንደሆነ ይገልፅና በየብሔሩ ሲከፋፈል ደግሞ ኦሮሞ 41%፣ አማራ 22.77%፣ ሐረሪ 8.65%፣ ጉራጌ 4.34% ሶማሌ 3.87%፣ ትግራይ 1.53%፣
አርጎባ 1.26% መሆኑን ይዘረዝራል፤ በስፋት የሚነገሩ ቋንቋዎችም ኦሮምኛ 56%፣ አማርኛ 27.53%፣ ሐረሪ 7.33%፣ ሶማሊኛ 3.70%፣ ጉራጌኛ 2.91%… ነው ይለናል፡፡

በመሬት ያለው እውነታ ይህ ቢሆንም የክልሉ ሕገ-መንግስት ደግሞ በአንቀፅ 49 ‹‹የሐረሪ ሕዝብ ክልል ምክር ቤት›› በሁለት ጉባዔዎች እንደሚመሰረት ከገለፀ በኋላ፣ እነርሱም ‹‹የህዝብ ተወካዮች ጉባኤ›› እና ‹‹የሐረሪ ብሔራዊ ጉባዔ›› እንደሆኑ ይነግረናል፤ ይኸው አንቀፅ በቁጥር 2 እና 3 ላይ ‹የሕዝብ ተወካዮች› ሃያ ሁለት፣ የሐረሪው በብሔሩ ተወላጆች ብቻ የሚወከሉ 14 አባላት ይኖሩታል ይላል፡፡ ይህ ሁኔታ በምርጫ ወቅት እንዴት እንደሚተገበር ደግሞ በአንቀፅ 50 ላይ ‹‹የጉባዔዎች አከፋፈል፣ አወካከልና አመራረጥ›› በሚል ርዕስ ስር እንደሚከተለው ተብራርቷል ‹የሕዝብ ተወካዮች› ለተሰኘው ጉባኤ ከጀጎል ነዋሪዎች አራት፣ ከጀጎል ውጪ ከሚገኙ የከተማና የገጠር ቀበሌ ገበሬ ማህበራት 18 አባላት ይመረጡበታል፡፡ ለሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ደግሞ በክልሉና ከክልሉ ውጪ በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች ከሚኖሩ የሐረሪ ብሔረሰብ ውስጥ 14 አባላት ይመረጡበታል፡፡ ይሁንና ሕጉ ብዙሃኑን የአካባቢው ነዋሪዎች የፖለቲካ ውክልና ከመንፈጉ በተጨማሪ ከክልሉ ተቋማትም ሆነ መብቶች እንዲገለሉ አድርጓቸዋል፡፡ በተለይም በራሱ በመንግስት መረጃ ሳይቀር በተወላጅነትም ሆነ ቋንቋውን በመናገር ከኦሮሞ ብሔር ቀጥሎ በሁለተኛነት የሚገኙት፣ እንዲሁም አብላጫውን የፖለቲካ ስልጣን ከያዘው ከሐረሪ ብሔረሰብ አባላት ከእጥፍ በላይ ቁጥር እንዳላቸው የተረጋገጠው አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች በዞን ደረጃ እንኳ እንዲዋቀሩ አለመደረጉ ‹ፌደራሊዝሙ› ከአፋዊነት አለማለፉን ያመላክታል (በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች በዞን ደረጃ እንዲዋቀሩ የተደረጉ ጥቂት የማይባሉ ብሔሮች እንዳሉ ልብ ይሏል) እንዲህ አይነቱ አደረጃጀት ሌላው ቢቀር እንኳ በዚህ ዘመን ፋሽን ከሆነው ‹‹ውጡ፣ ክልላችሁ አይደለም!›› ከሚለው ነውረኛ
ፖለቲካ የመታደግ ጉልበት ሊኖረው የሚችልበት ዕድል ሰፊ ነው፡፡ በርግጥ ይህ ሁናቴ ዛሬም ድረስ መፅናቱ ‹ብሔረሰቡን እወክላለሁ› የሚለው የእነ አዲሱ ለገሰ ብአዴን ከተላላኪነት ያለፈ ሚና እንደሌለው የሚያመላክት ይመስለኛል፡፡

የሆነው ሆኖ የሙግቱ ዋነኛ መግፍኤ የጀጎል ነዋሪ ከሆኑት ውስጥ ከሶስት እጅ ለሚልቁት አራት፣ ለተቀሩት ጥቂት ሐረሪዎች ደግሞ አስራአራት የምክር ቤት ወንበር ከመስጠቱ ጋር ይያያዛል፡፡ በዚህ ሕግ መሰረት በጀጎል የምርጫ ክልል ከአራቱ ወንበሮች ውጪ ሐረሪ ያልሆነ የትኛውም ፓርቲም ሆነ ግለሰብ ለውድድር መቅረብ እንደማይችል በግልፅ ተደንግጓል፡፡ እንዲህ አይነቱ አናሳዎችን በብዙሃኑ ላይ የሚሾም ኢ-ፍትሃዊ የሥልጣን ክፍፍል አብዛኛውን የክልሉ ነዋሪ በገሃድ እየተንፀባረቀ ላለው ባይተዋር አገዛዝ ከማጋለጡም በላይ፣ ከመልካም አስተዳደር ጋር በአዋጅ የተፋታ እስኪመስል ድረስ በሙስናና በአድሎአዊነት ለተተበተበ ስርዓት ዳርጎታል፤ ይህ ሁኔታም በህዝቦች መካከል መከፋፈል እንዲፈጠርና በጥላቻ ምሽግ ውስጥ እንዲያደፍጡ ማስገደዱ አይቀርም፡፡

በጥቅሉ የብዙዎችን መብት ጨፍልቆና አንዱን ነጥሎ ተጠቃሚ የሚያደርግ ስርዓት ማንበር የማታ ማታ ጊዜውን ጠብቆ ከሚፈነዳ አደጋ ጋር ማላተሙና የብሔር ግጭት የመቀስቀስ መዘዝ ማስከተሉን አስቀድሞ ለማወቅ ነብይ መሆን አይጠበቅም፤ የኢህአዴግ ‹‹እኔ ከሌለሁ ኢትዮጵያ ትበታተናለች›› ፉከራም ይህን መሰል ተንኮል ከገመደው የክልል አወቃቀር ቀመር ጋር የተያያዘ ይመስለኛል፡፡ በርግጥ ወደ እንዲህ አይነቱ ድምዳሜ የሚገፋን የሃሳቡ አመንጪዎችም ሆኑ መበታተናችን አይቀሬ እንደሆነ የሚያረዱን ራሳቸው የኢህአዴግ መስራቾች መሆናቸው ነው፡፡ በተቀረ ‹የምንከተለው የፌደራል ስርዓት ቋንቋን መስፈርት ያደረገ ነው› እስከተባለ ድረስ በሐረሪ ያለው አስተዳደር በራሱ በኢህአዴግ አጋፋሪነት በፀደቀው ህገ-መንግስትም ጭምር ተቀባይነት እንደሌለው ከገዥዎቻችን የተሰወረ አለመሆኑ አከራካሪ አይደለም፡፡ በነገራችን ላይ የሐረሪ ብሔራዊ ሊግ ከፈለገ በክልሉ ምክር ቤት ሰላሳ ስድስቱም ወንበሮች ላይ የመወዳደር መብት ተሰጥቶታል፡፡ በግልባጩ ኦህዴድን ጨምሮ በሐረሪ ብሔረሰብ አባላት ያልተመሰረተ ማንኛውም የተቃዋሚ ፓርቲ ከሃያ ሁለቱ ወንበር ውጭ በአስራ አራቱ ላይ እጩ ማቅረብ እንደማይችል በሕግ ታውጇል፤ የስራ ቋንቋንም በተመለከተ በክልሉ ነዋሪዎች ከአማርኛ ቋንቋ በሁለት እጅ ያነሰ ተናጋሪ ያለው ሐረሪ እና በስፋት የሚነገረው ኦሮምኛ ብቻ እንዲሆኑ መደረጉም ራሱ አገዛዙ ከሚያቀነቅንለት የቋንቋ ‹ፌደራሊዝም› ጋር ይጣረሳል፡፡ በርግጥም የስርዓቱ ‹ኤጲስ ቆጶሳት› ደጋግመው ‹ለአስራ ሰባት ዓመታት የታገልነው ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአፍ መፍጫ ቋንቋው እንዲማር፣ እንዲዳኝ፣ እንዲተዳደር… ነው› የሚሉት ሀቲት ማደናገሪያ መሆኑን ለመረዳት ከዚህ የበለጠ ክስተት ሊኖር አይችልም፡፡

በአናቱም የክልሉ ፕሬዝዳንት እና ም/አፈ ጉባዔ ከሐረሪ ብቻ የሚመረጡ ሲሆን፣ ዋናውን አፈ-ጉባዔ ደግሞ በጋራ ሁለቱ ጉባኤዎች እንደሚመርጧቸው በአዋጅ ተደንግጓል፡፡ እንዲሁም በፌደራሉ ህገ-መንግስት ላይ የተካተተውና አጨቃጫቂው ‹‹የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት›› የተሰጠው በተናጠል ለሐረሪ ብሔረሰብ ብቻ ነው፡፡ ይህ አይነቱ ልዩ ችሎታም ሆነ ከላይ የተጠቀሰው ልጓም አልባ ሥልጣን በሌሎች ክልሎች በተመሳሳይ መልኩ ለሚገኙ ብሔሮች አልተሰጠም፤ ለምሳሌ በደቡብ ሲዳማ፣ ስልጤ፣ ጉራጌ…፤ በአማራ ክልልም የአገው ብሔረሰብ ከሐረሪ የበለጠ ቁጥር ቢኖራቸውም በዞን ደረጃ እንዲዋቀሩ ከመፍቀድ ያለፈ ያገኙት ልዩ መብት የለም፡፡

በነገራችን ላይ ሐረሪ እንዲህ ለሀገር አንድነት አስጊ በሆነ መልኩ እንዲደራጅ የተደረገው በተወላጆቹ ፍላጎት እና ጥያቄ ነው የሚል እምነት የለኝም፤ ምክንያቱም የብሔረሰቡ አባላት እንደማንኛውም ዜጋ በኢትዮጵያዊነታቸው የሚያምኑና የሚኮሩ መሆናቸውን ከታሪክ መረዳቱ አያዳግትም፡፡ እናም በግሌ የዚህ ሁሉ መግፍኤ ስልጣኑን ለማስጠበቅ ኤርትራን እና አሰብን የመሰለ የሀገር ጉሮሮ (ወደብ) ኃላፊነት በማይሰማው መልኩ አሳልፎ የሰጠው ኢህአዴግ እንደ መጠባበቂያ አስልቶ ያጠነጠነው የተንኮል ድር ይመስለኛል፡፡ የክልሉ ህገ-መንግስትም ሆን ተብሎ ወደ አንድ ወገን እንዲያጋድል መደረጉ (በአንዳች ክፉ ቀን ሊመዘዝ የሚችል አደገኛ የፖለቲካ አጀንዳ ማቀፉ) ከላይ የጠቀስኳቸውን ማሳያዎች ያስረግጥልናል፡፡
የኃይማኖት መቻቻል… 

የሐረሪ ክልል ሌላኛው ችግር የኃይማኖት ልዩነት ያነበረው ውጥረት ለነዋሪው ሕዝብ ተጨማሪ ስጋት መፍጠሩ ነው፡፡ ከዓመታት በፊት በእንግሊዝ ዋና ከተማ ለንደን አልቃይዳ እንዳቀነባበረው የታመነውን የቦንብ አደጋ አድርሷል ተብሎ ተጠርጥሮ ከተያዘ በኋላ ዘግይቶ በነፃ የተለቀቀው ሐምዲ ኢስሐቅ የሐረሪ ተወላጅና የጀጎል ልጅ መሆኑ ክልሉ በማዕከላዊ መንግስቱ በአይነ ቁራኛ እንዲታይ አድርጎት እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ሐምዲ በአደጋው ተጠርጥሮ ጣሊያን ሮም ውስጥ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ለዜናው ከፍተኛ ሽፋን መስጠታቸውን ተከትሎ፣ በወቅቱ አንድ ጊዜ ብቻ ታትማ የጠፋችው ‹‹መዝናኛ›› መፅሔት ባቀረበችው ሰፊ ዘገባ እንዲህ በማለት ማስነበቧ አይዘነጋም፡- ‹‹በሐረር ጥብቅ የእስልምና ሃይማኖት ትምህርት ስር እየሰደደ ነው፡፡ አንዳንድ ሃይማኖተኞች እስከ ፓኪስታንና አፍጋኒስታን በመዝለቅ የእስላማዊ ትምህርትና ትግል ስልጠናን በመቅሰም እንደሚመለሱ ተረድቻለሁ፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በቁጣና በቁጭት የሚመለከቱት ቁጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡ ‹እውነት ከእኛ መካከል የተፈጠረው ሐምዲ ይህንን ሰርቶ ከሆነ አደንቀዋለሁ› ብሎኛል አንድ ወጣት፡፡››

በ2004 ዓ.ም. አፈንዲ ሙተቂ በተባለ ፀሐፊ ተዘጋጅቶ፣ የቅጂ መብቱን በመጋራት የሐረሪ ባህል፣ ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ወጪውን በመሸፈን ‹‹ሐረር ጌይ›› በሚል ርዕስ ባሳተመው መጽሐፍ ላይም ሐረር ‹‹እስላማዊ ከተማ ናት›› ተብሎ መገለፁ በራሱ የሚያመለክተው ጉዳይ አለ፤ መቼም ዓለማዊቷን ከተማ ‹እስላማዊት›› እያለ የሚጠራን መጽሐፍ መንግስታዊው ተቋም አሳትሞ ማሰራጨቱ፣ ሃይማኖትና መንግስት የተነጣጠሉ ናቸው ብሎ በአዋጅ ለሚለፍፈው ኢህአዴግ መራሹ ስርዓት ምፀት ይመስለኛል፡፡ በርግጥም ‹‹ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት›› የሚሉትንም ሆነ፣ ሐረርን እስላማዊ ለማድረግ የሚያሴሩትን እንዲህ አቅፎና ደግፎ ‹በኃይማኖታችን መንግስት ጣልቃ አይግባ› ያሉ መዕምናን ተወካዮችን (መንፈሳዊ መሪዎችን) ሰብስቦ ማሰሩ አገዛዙ የመጨረሻው አፈና ደረጃ ላይ መድረሱን የሚያመላክት ነው፤ የፖለቲካ ተንታኞችም ‹መንግስታዊ ሽብርተኝነት› የሚሉት ይህ አይነቱን ተግባር ነው ብዬ አስባለሁ፡፡

ድሬዳዋ 
ሌላኛው የምስራቅ ኢትዮጵያ ውጥንቅጥ የፖለቲካ መገለጫ የድሬዳዋ አስተዳደር ነው፡፡ ኢህአዴግ ወደ ሥልጣን በመጣባቸው የመጀመሪያዎቹ ዓመታትና በቀድሞዎቹ ስርዓታት ድሬ በሀገሪቱ ግንባር ቀደም የንግድ እንቅስቃሴ ከሚደረግባቸው ጥቂት ከተሞች አንዷ እንደነበረች ነዋሪዎቿ ዛሬም ድረስ በትዝታ ያስታውሳሉ፡፡ ለዚህም እንደምክንያት የሚጠቀሰው በዳግማዊ አፄ ምኒሊክ ዘመነ መንግስት ከአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ እና ጁቡቲ ድረስ ተዘርግቶ የነበረው የባቡር መስመር ነው፡፡ ይሁንና ኢህአዴግ ትግል ላይ በነበረበት ወቅት ከፍተኛ ሕዝባዊ ተቃውሞ ያሰሙበት ከነበሩ የሀገሪቷ ከተሞች ድሬዳዋ አንዷ መሆኗ ቂም እንዲይዝባት ከመግፋቱም በላይ ‹የነፍጠኛ መከማቻ› ተብላ በ‹ጥቁሩ› መዝገብ መስፈሯ ባለፉት ሃያ ሁለት የስልጣን ዓመታት ባለችበት ትረግጥ ዘንድ በማይታየው የስርዓቱ ‹ክፉ እጅ› ለመዳመጥ ዳርጓታል፡፡

የሆነው ሆኖ ድሬ በተጧጧፈ የንግድ ሂደት ደምቃ የምትታይበት ያ የመኸር ዘመኗ እንደ ጉም በንኖ፣ ለአስከፊ ድህነትና ሥራ እጥነት እጅ መስጠቷን ለማስተዋል ከተማዋን ለጥቂት ሰዓታት ብቻ ተዟዙሮ መቃኘቱ በቂ ይመስለኛል፡፡ ርግጥ ነው የኢኮኖሚዋ ዋልታ ከምድር ባቡርና ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪክ (ኮተን) በተጨማሪ ሕጋዊም ባይሆን የኮንትሮባንድ ንግድ እንደነበረ ይታወቃል፡፡ ይሁንና ዛሬ ከሞላ ጎደል ሶስቱም የሥራ ዘርፎች በጥልቅ እንቅልፍ የተወሰዱ መስለዋል (ምንም እንኳ ከታማኝ ምንጭ ባላረጋግጥም ኮንትሮባንዱ ‹ፖለቲካዊ ቡራኬ› ማግኘት በቻሉ የስርዓቱ የጥቅም ተጋሪዎች በድብቅ እንደሚሰራ ይነገራል) ምድር ባቡርን በተመለከተ ግን በህይወት ለመኖሩ ደፍሮ የሚከራክር ይኖራል ተብሎ አይታሰብም፡፡ 

በርግጥ ለድርጅቱ መፍዘዝ ብሎም መክሰም እንደምክንያት የሚቀርበው ‹ኪሳራ› ቢሆንም ስማቸውን መናገር ያልፈለጉ፣ የተቋሙ የሒሳብ ሠራተኛ የነበሩ አንድ የድሬዳዋ ነዋሪ በዚህ አይስማሙም፤ እንደእርሳቸው አገላለፅ መስሪያ ቤቱ ለኪሳራ የተዳረገው የህወሓት ሰዎች ከጀርባ ባሴሩበት ደባ ነው፤ ‹‹በኤፈርት ስር ከተቋቋሙ ድርጅቶች አንዱ የሆነው የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ላይ የተሰማራው ‹ትራንስ› ከጅቡቲ የሚጫኑ እንደ የዕርዳታ ስንዴና ማዳበሪያ መሰል ምርቶችን በጨረታ እንዲያሸንፍ ይደረግና በጣም እርካሽ በሆነ ዋጋ ለምደር ባቡር የኮንትራት-ኮንትራት ይሰጠዋል፤ ይህ ሁኔታም እየተደጋገመ ሲሄድ ድርጅቱን ለኪሳራ ዳረገው፤ በዚህ ላይ ማነጅመንቱ በተቋሙ ንብረትና ጥቅም ላይ ሙስና ሲፈፅም፣ የስርዓቱ መሪዎች አይተው እንዳላየ ያልፉ ነበር፤ ሠራተኛ ማህበሩ ሳይቀር በግልፅ ለፀረ-ሙስና ሪፖርት ያቀረበባቸው፣ ነገር ግን በሕግ ያልተጠየቁ የአስተዳደር ኃላፊዎች አሉ›› ሲሉ ገደል አፋፍ ስለቆመው የቀድሞ የድሬ ‹ደም-ስር› ምድር ባቡር በቁጭት ይናገራሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት የድርጅቱ ንብረት በሙሉ በመከላከያ ቴክኖሎጂ (መቴክ) ለሚመራው የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ተላልፎ ተሰጥቷል፡፡ ከሰራተኞቹም አብላጫው ተባርረው አምስት መቶ ለሚሆኑት ኢንዱስትሪው ከጥቅምት 30 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ ደሞዝ እየከፋላቸው እንደሚገኝና ከነበሩት 19 ሞተሮች (ባቡር) መካከልም አገልግሎት የሚሰጡት አራት ብቻ እንደሆኑ የድርጅቱ ቅርብ ሰው አረጋግጠውልኛል፡፡ ከአዲስ አበባ-መተሀራ እና ከካሳራት-ኤረር በጠቅላላ 114 ኪ.ሜ. ለሚሸፍን የድልድይ (ሀዲድ) ዕድሳት ይውል ዘንድ የአውሮፓ ህብረት የለገሰውን 60 ሚሊዮን
ዩሮንም (ከ1.1 ቢሊዮን ብር በላይ የወሰደው የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ የረባ ስራ ሳይሰራ ‹‹ቄሱም ዝም…›› መሆኑ ብዙዎችን ግራ ከማጋባቱም በላይ በሀገሪቷ ኃላፊነት የሚሰማው መንግስት ያለመኖሩ ማሳያ ነው፡፡

በአናቱም መንግስት ሕገ-ወጡን የኮንትሮባንድ ንግድ በኃይል ሲያስቀር፣ ካለበት ኃላፊነት አኳያ አማራጭ የስራ ዘርፎችን አለመፍጠሩ ለችግሩ መባባስ ዋነኛ ምክንያት ሆኖ ይቀርባል፡፡ በተለይም በከፍተኛ ባለስልጣናት አንደበት ሳይቀር የ‹ደረቅ ወደብ› አገልግሎት መስጫ በድሬዳዋ እንደሚመሰረትና ለአካባቢው ነዋሪ አማራጭ የሥራ ዕድል እንደሚሆን ተደጋግሞ ከተነገረ በኋላ፣ ሃሳብ ተቀይሮ ሞጆ ላይ እንዲመሰረት መደረጉ ከተማዋ ‹አልቦ ተቆርቋሪ› መሆኗን እንደሚያሳይ በአንድ ወቅት የመስተዳደሩ ምክር ቤት አባል የነበሩ ግለሰብ ይናገራሉ፡፡ የግለሰቡ መከራከሪያ ‹‹ድሬዳዋ ለጁቡቲ ካላት ቅርበት አኳያ የከባድ መኪናዎችን ምልልስ ያፈጥነዋል፤ ይህ ደግሞ በወደብ ላይ ለሚከማቹ ጭነቶች የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ ያስቀራል›› የሚል ነው፡፡ በርግጥም ከአዲስ አበባ እምብዛም ከማትርቀው ሞጆ ይልቅ፣ ለእንዲህ አይነቱ አገልግሎት ድሬዳዋ የተሻለች መሆኗን ለመረዳት ጥናትና ምርምር የሚጠይቅ አይመስለኝም፡፡

የድሬ ፖለቲካ…
የድሬዳዋ ነዋሪዎችን በተመለከተ በ1998 ዓ.ም (በፈረንጆች 2007 ዓ.ም) በስታስቲክ ባለስልጣን የተደረገው ቆጠራ እንደሚያሳየው አጠቃላይ የሕዝብ ብዛቷ 341 ሺህ 834 ሲሆን፤ ኦሮሞ 45%፣ ሶማሌ 24.3%፣ አማራ 20.7%፣ ጉራጌ 4.5%፣ ትግራይ 1.2%፣ ሐረሪ 1.01% ቁጥር አላቸው፡፡ በስፋት የሚነገሩ ቋንቋዎች ደግሞ ኦሮምኛ 46.1%፣ አማርኛ 33.2%፣ ሶማሊኛ 13.4%… መሆናቸውን ይዘረዝራል፡፡ ይሁንና ድሬ በተፃፈው ሕግ እንደ ሀገሪቱ መዲና አዲስ አበባ በፌደራል መንግስት ስር መዋቀሯ ቢደነገግም፣ በገሃድ ያለው እውነታ የሚያሳየው (በተለይም ከምርጫ 97 በኋላ) ኦህዴድና ሶሕዴፓ (የሶማሌ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ) ባልተፃፈ ሕግ በሚፈራረቁበት አድሎአዊና ብልሹ መስተዳደር ውላ-ማደሯን ነው፤ በርግጥም ዛሬ በሥልጣን ላይ ካለው የኦህዴዱ አሳድ ዚያድ በፊት፣ የከንቲባነትና የምክትሉን ወንበር አንድ የምርጫ ዘመንን ዕኩል በመክፈል ሁለቱ ድርጅቶች በየሁለት ዓመት ተመንፈቁ ሲቀያየሩበት መቆየታቸው የሚያመላክተው ዓብይ ጉዳይ ፌደራሊዝሙ በሕይወት ለመኖሩ በ‹ሳይንስ›ም ቢሆን ሊረጋገጥ አለመቻሉን ነው፡፡

በድሬዳዋ የሚታየው ሌላኛው ‹ፌደራሊዝማዊ› ፌዝ፣ ከነዋሪው ሕዝብ ቁጥር ኦሮምኛ ተናጋሪው 46.1% ሆኖ ሳለ የሥራ ቋንቋ አማርኛ መሆኑ ነው፤ ማንነትን በ‹ቋንቋ› የሚወስነው ኢህአዴግ ድሬዳዋ ላይ ተመሳሳይ መንገድ አለመከተሉ (…መቀነቱ ማደናቀፉ) በኦሮሞ ተወላጆች ላይ የሚደረገውን ተቋማዊ ጫና የሚያመላክት ይመስለኛል፡፡ መቼም ሌላው ቢቀር እንኳ ቢያንስ ራሱ የቀረፀው ‹ፌደራሊዝም› ሁለቱንም የሥራ ቋንቋ ማድረግ የሚቻልበት በቂ መፍትሄ እንደማያጣ ግልፅ ነው፡፡ ይህ ኩነት ኦህዴድም ልክ እንደ ብአዴን ከተላላኪነትና ቱርጁማንነት ያለፈ የፖለቲካ ቁመና የለውም ወደሚል ጠርዝ ይገፋል (በነገራችን ላይ የአጀንዳው ተጠየቅ በዚህ መልኩ የቀረበው ከራሱ ከኢህአዴግ ርዕዮተ-ዓለም አንፃር እውነታውን ለመፈተሽ ሲባል ነው እንጂ በግሌ የብሔር ፖለቲካ ለኢትዮጵያችን ይበጃታል ብዬ ስለማምን አይደለም)

እንደ መውጫ

ቋንቋ ተኮር ፌደራሊዝሙ ኢህአዴግ ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ እንደ አዲስ ሀገር ማዋቀሪያ አማርጭ ፖሊሲ ተደርጎ ሲጠነሰስ የፌደራሊዝሙ ቅርፅ አገሪቱን ይበታትናል ከሚለው ድምፅ ባላነሰ፣ ደርዝ ያለው ሙግት ሆኖ ቀርቦ የነበረው በሀገሪቱ የረዥም ጊዜ የሕዝብ ለሕዝብ ፖለቲካዊ ግንኙነት በአንድ ቋንቋ ብቻ የሚወሰን ማህበረሰባዊ ቡድን (ብሔር) ካለመገኘቱ ባለፈ፣ ያንን የተወሰነ ቋንቋ የሚናገረው ስብስብ በአንድ በተወሰነ መልክዐ-ምድራዊ ቅፅር ውስጥ አይገኝም የሚል ነበር፡፡ ይህንን ክርክር ከዚህ ፅሁፍ አውድ አንፃር ተጨባጭ የሚያደርገው የጠቀስኳቸው ሁለቱ የምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ናቸው፡፡ በሁለቱም ክልል ውስጥ ከኦሮሞ እስከ ትግሬ፣ ከአማራ እስከ ሶማሌ… ከጠንካራ ኢኮኖሚያዊ አደረጃጀትና የየራስ ወጥ መለዮ ጋር መገኘታቸው መልክዐ-ምድራዊውን የፌደራሊዝም ቅርፅ ትክክለኛ አማራጭነት ለማስረገጥ በቂ ማሳያዎች ይመስሉኛል፡፡
ከዚህ ባሻገር የኢህአዴግ ‹ፌደራሊዝም› እንኳን ድርጅቱ ሥልጣን ላይ ባለበት ወቅት ቀርቶ፣ በሕዝባዊ ማዕበል በሚወድቅበት ጊዜም ቢሆን በአንድ ጀንበር መቀየር እንደማይቻል ቢታወቅም ሂደታዊ የእርምት አካሄድ ብቸኛው ፖለቲካዊ ትክክለኝነት ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ይህ ፌደራሊዝም የብሔር ግጭትን ከመከላከል በላይ ተራምዶ፣ ሰሞኑን እንዲያ ‹አሸሼ-ገዳሜ› የሚባልለትን በሕዝቦች መካከል አንድነት ሊያጠብቅ ቀርቶ በአግባቡ ባለመተግበሩ (ለምሳሌ በሐረሪና ድሬዳዋ የሚገኙ፣ ነገር ግን በክልሎቹ ስልጣን ውስጥ ያልተወከሉ ብሄሮች) የተፈጠሩት ኩነቶች ወደሰዓት ቦንብነት እየተቀየሩ የመጡትን የተለያዩ ቋንቋ ተናገሪዎች የእርስ በእርስ ትንቅንቆች
መግራት ከማይችልበት ደረጃ ላይ እየደረሰ ነው፡፡ ይህ ኩነት “ደግሞ የእዚህች አገር ህልውናን ለመፈታተን ጥቂት ጊዜያቶችን ብቻ መጠበቅ የማይቀር ዕጣ ፈንታ ያደረገው ይመስለኛል፡፡

THE FUTURE IS IN OUR HANDS

December 11, 2013
Imru Zelleke (Ambassador)
The high fever that has spread the all over the Diaspora seems to have simmered down to a tolerable level. Most of refugees in Saudi Arabia have been repatriated home and the few left will get back soon. Those still in jeopardy are the ones under care of the UNHCR in Yemen, for whom a permanent residence is to be found. Otherwise Ethiopians refugees are in dire and precarious conditions in Middle East and African countries where they are abused and often killed.Ethiopian foreign workers in Saudi Arabia
The refugees that have returned seem to have fallen from the frying pan into the hot brazier. It is said that upon arrival home whatever processions (money, jewelry, valuable items) they have manage to save are confiscated by the regime, and they are forced to go back to their Kilil of origin; places where they run away from to begin with. The problem has evidently moved from Saudi Arabia back to Ethiopia their home land.
Without indulging into a lengthy and verbose discourse it should be obvious that the core of the problem is at Home in Ethiopia. People living in peace and freedom in their own country do not migrate unless they are subject to extremely unfavorable conditions at home. Ethiopians love their country and are not traditionally migrants, it is only in the last four decades of the post-revolutionary era that such mass migration has been occurring. Moreover, Ethiopia has presently the highest brain drain in the world. This trend will certainly continue as long as the coercive ethnic dictatorship at home is not removed and replaced by an all embracing national democratic system of governance.
At the cost of many precious lives and resources, attempts to establish a government based on democracy and freedom have been many throughout the years. Alas, all have failed ignominiously leaving in their wake a people deprived of freedom, basic rights reduced to beggary and mendacity in their own land. We all know the degradation and humiliation that our society is subjected too, yet we don’t seem to react as we should against such perfidy; but for making long winded statements and pursuing a plethora of people and political groups who so far have led us to nowhere.
We are ninety million man and women, the ruling gang count maybe a few thousand at the center, are they really invincible? No! their strength is our weakness and incoherent attitude towards our own existence. The ordinary people in Ethiopia have realized a long time ago that their fate is in their hands, they have risen and demonstrated more than once their patriotism and ultimate desire for freedom and justice. It is time to give them a helping hand, free of ulterior motifs. Actually they don’t even need us, all the resources required are available at home. This said, we in the Diaspora that enjoy unlimited economic and political resources, could accelerate the process and bring about peace and a promising future to our brethren in Ethiopia.
We have all the human and materiel means in our hands, let’s abandon all these squabbles and divisions amongst ourselves and make a common front to liberate the country from the scourge that is destroying it. Let’s make a real brotherly effort for an ETHIOPIAN RENAISSANCE. The high spirit of patriotism and indignation that has risen amongst the Diaspora, offers the opportunity to form a broad national political movement that will help install a genuine democracy in Ethiopia. For my part I am willing to assist and help a truly made effort to realize this goal.
If we fail our people in this noble endeavor, it we will be a disavowal of our own humanity for which future generations not forgive us.
Respectfully.
Imru Zelleke.

THE FUTURE IS IN OUR HANDS

December 11, 2013
Imru Zelleke (Ambassador)
The high fever that has spread the all over the Diaspora seems to have simmered down to a tolerable level. Most of refugees in Saudi Arabia have been repatriated home and the few left will get back soon. Those still in jeopardy are the ones under care of the UNHCR in Yemen, for whom a permanent residence is to be found. Otherwise Ethiopians refugees are in dire and precarious conditions in Middle East and African countries where they are abused and often killed.Ethiopian foreign workers in Saudi Arabia
The refugees that have returned seem to have fallen from the frying pan into the hot brazier. It is said that upon arrival home whatever processions (money, jewelry, valuable items) they have manage to save are confiscated by the regime, and they are forced to go back to their Kilil of origin; places where they run away from to begin with. The problem has evidently moved from Saudi Arabia back to Ethiopia their home land.
Without indulging into a lengthy and verbose discourse it should be obvious that the core of the problem is at Home in Ethiopia. People living in peace and freedom in their own country do not migrate unless they are subject to extremely unfavorable conditions at home. Ethiopians love their country and are not traditionally migrants, it is only in the last four decades of the post-revolutionary era that such mass migration has been occurring. Moreover, Ethiopia has presently the highest brain drain in the world. This trend will certainly continue as long as the coercive ethnic dictatorship at home is not removed and replaced by an all embracing national democratic system of governance.
At the cost of many precious lives and resources, attempts to establish a government based on democracy and freedom have been many throughout the years. Alas, all have failed ignominiously leaving in their wake a people deprived of freedom, basic rights reduced to beggary and mendacity in their own land. We all know the degradation and humiliation that our society is subjected too, yet we don’t seem to react as we should against such perfidy; but for making long winded statements and pursuing a plethora of people and political groups who so far have led us to nowhere.
We are ninety million man and women, the ruling gang count maybe a few thousand at the center, are they really invincible? No! their strength is our weakness and incoherent attitude towards our own existence. The ordinary people in Ethiopia have realized a long time ago that their fate is in their hands, they have risen and demonstrated more than once their patriotism and ultimate desire for freedom and justice. It is time to give them a helping hand, free of ulterior motifs. Actually they don’t even need us, all the resources required are available at home. This said, we in the Diaspora that enjoy unlimited economic and political resources, could accelerate the process and bring about peace and a promising future to our brethren in Ethiopia.
We have all the human and materiel means in our hands, let’s abandon all these squabbles and divisions amongst ourselves and make a common front to liberate the country from the scourge that is destroying it. Let’s make a real brotherly effort for an ETHIOPIAN RENAISSANCE. The high spirit of patriotism and indignation that has risen amongst the Diaspora, offers the opportunity to form a broad national political movement that will help install a genuine democracy in Ethiopia. For my part I am willing to assist and help a truly made effort to realize this goal.
If we fail our people in this noble endeavor, it we will be a disavowal of our own humanity for which future generations not forgive us.
Respectfully.
Imru Zelleke.

እዩኝ እዩኝ ደብቁኝ ደብቁኝን ያመጣል :: አቶ ሀብታሙ አያሌው = ከኢህአዴግ ወደ መድረክ የተላከ ሰርጎ - ገብ

December 11/2013
ምኒልክ ሳልሳዊ

እዩኝ እዩኝ ደብቁኝ ደብቁኝን ያመጣልጋሻው መርሻእንዳለመታደል ሆኖ የሀገራችን ፖለቲካ የሚተረማመሰው በአማተሮችና ሆድ - . አደር አሽከሮች ነው ይህ በመሆኑ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከገዥው ፓርቲ ጋር ከሚደርጉት ትግል የበለጠ የሚያደክማቸው አግድም / ሆርዞንታል / እርስ በርስ የሚያካሂዱት መቦጫጫቅ ነው ለዚህ ደግሞ ምቹ ሁኔታዎችን በማመቻቸት በኩል የራሳቸው አስተዋጽኦ ሚያደርጉ ሰርጎ - . ገቦች በየዘመኑ ይነሳሉ ምንም እንኳን ይህ አላስፈላጊ መሸነቋቆጥና ስድብ / መተቻቸት አላልኩም / የማልወደው ቢሆንም የአውራው ፓርቲ የውስጥ አርበኞች የትግሉን ስሜት ለማቀዝቀዝ የሚያደርጉት እሰጥ አገባና , አጀንዳ መዘዛ , እውነተኛ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና ሀገር ወዳድ ዜጎች ባላወቁት ወጥመድ እየገቡ መሆኑን ስመለከት የሚያውቁትን መረጃ አለማጋለጥ የሚረጩትን መርዝ ሰርጎ እንዲገባ እገዛ ማድረግ መስሎ ስለተሰማኝ ይህንን እውነት ለመከተብ ተነሳሁ .

 ለጽሁፌ መነሻ የሆነኝ ነሀሴ 11 በወጣው ላይፍ መጽሄት ላይ አቶ ሀብታሙ አያሌው ያደረገው ቃለ መጠይቅና ከዚህ በፊት ያደረጋቸው አፍራሽ ንግግሮች ናቸው . እውነቱን ከማሳየት ውጭ ሌላ ምንም አላማ የሌላት ይህች አጭር ጽሁፍ ተናጋሪውና አንባቢዎች በቅን ልቡና ያነቡልኝ ዘንድ በቅድሚያ አሳውቃለሁ . ደራሲ በዓሉ ግርማ የህሊና ደወል በሚለው መጽሀፉ ገጽ 173 ላይ በአንደበቱ እየሸነገለ ከሀዲ የሆነውንና በኢትዮጵያ ስም እየማለ የይሁዳን ገጸ ባህሪ የሚተውነውን ኢትዮጵያዊ ሲገልጸው - ውዲቷ ሀገሬ እናት ኢትዮጵያ ብሎ ባንደበቱ የሚያሞጋግሰኝ ሞልቷል በየ ቤቱ ምላስ አልነበረም እኔን የቸገረኝ ቤዛ የሚሆን እጅ ነው ያጠረኝ ባፉ ተናግሮ በጁ ከሚክደኝ ከወጣቱ ትውልድ ከሸክም አድነኝ . ይላል ባለ ብሩህ አእምሮው ደራሲ በዓሉ ግርማ . ከኢህአዴግ ቤት በመተጣጠፍ ስልት ሰተት ብሎ ወደ አንድነት ም / ቤት የገባው አክሮባቲስቱ ሀብታሙ አያሌው እና ግብረ አበሮቹ በአፋቸው ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያሉ በተግባራቸው ግን የታጋዩንና የህዝቡን ስሜት ለማቀዝቀዝ ሲታትሩ እንመለከታቸዋለን . ለመሆኑ ሀብታሙና መሰሎቹ ስለ ኢትዮጵያ የመናገር ሞራል አላቸው ? ራሳቸውን የታጋይ ቁንጮ አድርገው የሚቆጥሩት በምን መስፈርት ነው ? እነዚህንና መሰል ጥያቄዎችን አንባቢ የሚፈርዳቸው ሆኖ አቶ ሀብታሙ በላይፍ መጽሄት ላይ ወደ ቀባጠራቸው ጉዳዮች እንለፍ .

  ከኢህአዴግ ፓርቲ ስለለቀቀበት መንገድ ሀብታሙ ከኢህአዴግ ፓርቲ የለቀቀበትን መንገድ ሲያብራራ « ኢህአዴግ ቤት እያለሁ ወፍራም ደመወዝ ነበረኝ መኪና ተመድቦልኝ የተለያዩ አበሎች ይከፈለኝ ነበር ....... » ነገር ግን ኢህአዴግ ለተቃዋሚዎች ያዘጋጀውን ጽዋ መጠጣት ለእኔ ክብር እንደሆነ በማሰቤ በቃኝ ለማለት አልተቸገርኩም ይለናል . ከኢህአዴግ ጋር ፍች የፈጸመበትን ምክንያት በሀብታሙ አንደበት ሲገልጽ አንባቢን ያማልላል . ይቀጥልና ኢህአዴግ ቤት ሀሳብ መሸጥ ስለማይቻል ወጥቻሁ ይለናል . አባባሉ እውነት ነው ኢህአዴግ ቤት ህሊና እንጅ ሀሳብ አይሸጥም . እውነተኛው የአወጣጡ ምክንያት ይህ ነው ? የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም . ይህ ከነበረስ ኢህአዴግን ከለቀቀበት 2002 ዓም ጀምሮ አንድነት እስከገባበት 2005 ዓም ድረስ የት ነበር ? ስለዚህ ጉዳይ በተለያዩ ቃለ መጠይቆች ሀብታሙ አያነሳልንም . መቸም እንደ እየሡስ ክርስቶስ ገዳም ገብቶ የሚል የዋህ አይኖርም . በቅርብ የሚያውቁት ምክንያቱን ሲገልጹ ከአስካሉካ ትሬዲንግ ጋር በተያያዘ በተፈጠረው ውዝግብ የድርጅቱ ባለቤት በስደት ወደ ጀርመን ሀገር ሲያቀና ሀብታሙ በበኩሉ ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደሄደ ነው .

  ለመሆኑ የተቃዋሚዎችን ጽዋ ለመጨለጥ የቆረጠ ሰው ደቡብ አፍሪካ ምን ወሰደው ? አንዳንዶች በደቡብ አፍሪካው የአለም ዋንጫ ሰዎችን ወደ ደቡብ አፍሪካ እልካችኋለሁ እያለ በወገኖቻችን ላይ የተለያየ ግፍ ሲፈጽም ከነበረው አቶ ግርማይ ብርሀኔ ጋር ንክኪ የነበረው ሀብታሙ የተነሳው የተቃውሞ ወጀብና የተዘረፍን ለቅሶ ሁለቱንም ለስደት ዳርጓቸዋል በሚል ይስማማሉ . ለዚህም እንደመከራከሪያ የሚያቀርቡት አቶ ግርማይ ብርሀኔ ከጀርመን ተይዞ ሲመጣ ሀብታሙ የመከላከያ ምስክር ሆኖ መቅረቡን ነው . ድንቄም የጠቃዋሚን ጽዋ መጨለጥ ¡ ¡ ¡ ከዚህ ሁሉ በኋላ በሀገር ወዳድ ወጣቶች የተመሰረተውን ባለራዕይ ወጣቶች ማህበርን በአቦሸማኔ ፍጥነት ወደ አንድነት ብሄራዊ ምክር ቤት ለማሳለጥ ተጠቅሞበታል . ወደ አንድነት ም / ቤት ከመግባቱ እና የፈረመበት ብዕር ሳይደርቅ የተለመደውን እንካ ስላንትያ ዲስኩሩን ከፓርቲው እውቅና ውጭ ከመድረክ አመራሮች . ጋር በመሆን ጀመረ ዘመናቸውን በሙሉ ለሀገር ሲታገሉ የኖሩ አዛውንት ምሁራንን በአላዋቂ ብዕሩ ያበሻቅጣቸው ገባ መድረክ መፍረስ አለባት ; . መድረክ የፓርቲዎች ሳይሆን እንደ አፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብስብ ነው , የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ከአንድነት የወጡት አቅም ስላልነበራቸው ነው , ወዘተ የሚሉ አፍራሽ ንግግሮችን ከአንድነት ፓርቲ እውቅናና ፈቃድ ውጭ ሲናገር እውነት ይህ ሰው ከኢህአዴግ ለቆ ወጥቷል ? ያስብላል .

 በዚህ ንግግሩም የመድረክ ከፍተኛ አመራሮች ከኢህአዴግ ወደ መድረክ የተላከ ሰርጎ - . . ገብ መሆኑን ይስማማሉ አንድነት ከመድረክ መውጣት አለበት , መድረክ በአስቸኳይ ይፍረስ , ምናምን የሚሉትን የፓርቲውን ሊቀመንበር ጨምሮ የአንድነት አባላትና አመራሮች አይስማሙበትም ከዚህ በመቀጠል መድረክን የማፍረስ ተልዕኮ አልሳካ ሲል ሰማያዊ አልዋሀድም አለ ሲል ዘለፋ ጀመረ ለመሆኑ ትናንት ስለመፍረስ ባወራበት አንደበት ዛሬ ስለ መዋሀድ የማውራት ሞራል ከየት አገኘ ( ከዚያው ከላኩህ ሰዎች ካልሆነ ) . እንግዲህ ይህ ሰው ነው ኢህአዴዴግ ቤት ሀሳብ መሸጥ አይቻልም የሚለን . ስልብ አሽከር በጌታው እቃ ይኮራል . በጌቶቹ ሀሳብ እንጅ በራሱ ላለመመራቱ አንዱ ማሳያ ይህ እንፍረስ እንዋሀድ ዝባዝንኬው ነው . ሌላው በዚሁ መጽሄት ላይ ሀብሙ እንዳለው " የራስን ገጽታ ለመገንባት የሌሎችን መልክ ማቆሸሽ " የሚለው አባባል በአግባቡ ሊገልጸው የሚችለው ኢንጅነር ይልቃል ጌትነትን ወይስ አቶ ሀብታሙን ? መልሱን አንባቢ ይፍረድ . ለምሳሌ መጋቢት 8/2005 ዓም ግራዚያኒን ለመቃዎም የተደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ ያነሳሱት አቶ ታዲዎስ ታንቱ ናቸው . ለዚህም ተገቢ አክብሮት ሊቸራቸው የሚገባ ቢሆንም ሌሎች መድረኩን በመቆጣጠር የማይገባቸውን ውዳሴ ለመሸመት ተጠቅመውበታል ሲል ሰማያዊ ፓርቲን ይከሳል . ለመሆኑ በዚህ ሰልፍ የማይገባውን ውዳሴ የሸመተው አቶ ሀብታሙ ወይስ ሰማያዊ ፓርቲ ? መቸም ሀብታሙ ሰማያዊ ፓርቲ ያደረገውን አስተዋጽኦ ረስቶት ከሆነ ደግሜ ላስታውሰው እወዳለሁ . የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ሰልፉን ለማሳካት ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ቁርጠኛ ከመሆናቸው በላይ የሚያፈልገውን ሙሉ ወጭ / የቲሸርት , የህትመት ጨምሮ / , መኪና , ጀነሬተርና ሞንታርቦ በመከራየት ያደረጉትን ክብር ያለው ስራ ልንክደው አንችልም . ሌላው ደግሞ በሰልፉ ዋዜማ ለቅስቀሳ የወጡትን የፓርቲውን አባላትና የማህበሩን አመራሮች በቁጥጥር ስር ሲውሉ የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች እኛንም እሰሩን በማለት ፖሊስ ጣቢያ ገብተው አንወጣም በማለታቸው ለእስርና ድብደባ መጋለጣቸውን ሀብታሙ አልሰማም እንዴ ? በጣም የሚያስገርመው በሰልፉ እለትም የፓርቲውን ሊቀመንበር ኢ / ር ይልቃል ጌትነትን ጨምሮ እነ ዶ / ር ያዕቆብ ኃ / ማርያም , አቶ ታዲዎስ ታንቱ ; እንዲሁም ከ 40 በላይ ወጣቶች ሲታፈሱ የጸጥታ ሀይሎች ሀብታሙን እንድንይዝ አልታዘዝንም ብለው በግልጽ መናገረቸው ኢህአዴግ የሀብታሙ መታሰር ከእነዚህ ሰዎች በላይ ኪሳራ ውስጥ የሚጥለው ሆኖ ወይስ የሚሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በሀብታሙ ፊታውራሪነት እንዲመራ ተፈልጎ ? ይህ ሁሉ ሆኖ ታዲያ ዛሬ ሌሎች ተጠቅመውበታልን ምን አመጣው ? ሰው ተጠቀመበት የሚለው ሂሳብ ይወራረድ ቢባል እንኳን የሀብታሙን ያክል ውዳሴ ለመሸመት የተሯሯጠና የደከመ የለም .

  ከ 1997 በኃላ ባለው የተቃውሞ ጎራ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ያክል ሰፊ መሰረት እና አደረጃጀት ያለው ፓርቲ አልተፈጠረም ብየ አምናለሁ . ለአንድነት ፓርቲ ነባር አባሎችና አመራሮች ብሎም አሁን እያደረገ ላለው እንቅስቃሴ ተገቢውን ክብር እሰጣለሁ . ነገር ግን አንድነት ገርበብ አድርጎ የከፈተውን በሩን በደንብ ካልዘጋ ወይም ጠንካራ ጥበቃ ካልቀጠረ ባጭር ጊዜ ውስጥ ወጣ ወጣና እንደ ሸንበቆ .............. ! እንዳይሆን ስጋት አለኝ . እስከ መቼ ድረስስ ነው አንድነት የኢህአዴግ ካድሬዎችን አመራር እያደረገ የሚቀጥለው . ለዚህ መከራከሪያ ደግሞ የፓርቲውን ሊቀመንበር ጨምሮ , ስየ አብርሀ , ሀብታሙና ጓደኞቹ እንዲሁም የአቋም አልባ መገለጫ የኢንጅነር ግዛቸው ሽፈራው መውጣትና መግባት የአንድነትን ነባር አባሎችና አመራሮች ያስኮርፋልና ቢታሰብበት እላለሁ . ባጠቃላይ ቆራትና ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ የሆኑ አባሎች የሞሉበትን አንድነት ከተቀላቀለ አጭር ጊዜ የሆነው / የፈረመበት ቀለም ያልደረቀው / ሀብታሙ ኢህአዴግ ባስታጠቀው የሴራ ፖለቲካ ከኔ በላይ ተቆርቋሪ የለም በሚል አስመሳይነት ከፓርቲው ነባር አባላት በላይ አድራጊ ፈጣሪ ሆኖ ፓርቲውን ወደ አዘቅት ለመክተት ሲጣደፍ ሲታይ , ለፓርቲው የመሪነት መስፈርት ከኢህአዴግ ቤት መምጣት ብቻ ይሆን እንዴ . ወይም የፓርቲው ነባር አባላት ለአመራርነት አይመጥኑም ? ያስብላል .

  ሌላው ሊተኮርበት የሚገባው የሀብታሙ ሴራ በቀጣይ የአንድነት የአመራር ምርጫ ቁልፍ ቁልፍ ቦታዎችን በእርሱና በጓደኞቹ ካልተያዙና ሽማግሌዎች / በእርሱ አገላለጽ / ገለል ካላሉ ፓርቲውን የመሰንጠቅና ሌላ ፓርቲ የማቋቋም አላማው እንዳለው ነው . ለዚህ አላማው ማስፈጸሚያ በዙሪያው የሚሰበስባቸው ጭፍራዎቹ ከፍተኛ ድርሻ ይኖራቸዋል የሚል ግምት አለኝ . እየሱስ ክርስቶስ በምድር ሲመላለስ ሌጊዎን የተባለውን የሰይጣን ጨፍራ ከሰውየው ላይ ወጥቶ ወደ እሪያዎቹ / አሳማዎቹ / እንዲገባ እንደገሰሰው ሁሉ ሀብታሙና መሰሎቹን ሌጊዎን ሆይ ከአንድነት ቤት ውጡና ወደ ዘመዶቻችሁ ግቡ እላለሁ . ይሁንና ግለሰቡ በቅርቡ ማንነቱ ተጋልጦ በአደባባይ እርቃኑን እንደሚቀር አልጠራጠርም . እስከዚያው ድረስ የክቡር ዶ / ር ጥላሁን ገሰሰን እንክርዳድ እንክርዳድ የተንከረደደ ስንዴ መስሎ ገብቶ ስንቱን አሳበደ . የሚለውን ዘፈን ጋብዘነው ብንለያይስ ?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ! !

ዶ/ር ቴዎድሮስ የሳዑዲውን ጉዳይ ለግል ዝና ማግኛ አውለኸዋል በሚል በጓዶቻቸው መወቀሳቸውን ለመንግስት ቅርብ የሆነ ሚዲያ ዘገበ

December 11/2913

 የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በሳዑዲ አረቢያ በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ጥፋት ተከትሎ በፌስቡክ እና በትዊተር አማካኝነት ለሕዝብ መረጃ መስጠታቸው በኢሕአዴግ ባለስልጣናት ዘንድ እንዳልተወደደና እንደተተቹበት ለመንግስት ቅርብ እንደሆነ የሚነገርለይ ድሬ ቲዩብ የተባለው ድረ ገጽ ዘገበ። “የዶ/ር ቴዎድሮስ ግልጽና ተወዳጅ የዲፕሎማሲ ስልት በፖለቲካ ጓዶቻቸው ዘንድ እንዳስወቀሳቸው ተነገረ” ሲል ዘገባውን ያሰፈረው ድሬ ቲዩብ ዶ/ሩን በማሞካሸት ባቀረበው ዘገባው “አብዛኛው ፖለቲከኛጋ የማይታይ ቀለል ብሎ የሚያሸንፍ ስብዕና (Disarming Personality) የተላበሰና እንደሌሎቹ የተጠና ፖለቲካዊ ዲስኩር የማይደረድር፤ ካለበት የስልጣን ከፍታ አንጻር እሱን ማግኘት አይከብድም…በለውጥ ሀይል የተሞላና አብረውት ቢያወጉ የማይሰለች ተወዳጅ ነው የሚሉት ብዙዎች ናቸው የሚለው ዘገባ…አሁን አሁን ግን ይህ ባህሪ በፖለቲካ ጓዶቻቸው እንዳልተወደደላቸው ነው የሚነገረው፡፡” ሲል ገልጾታል።

ድረ ገጹ ጨምሮም “በሶሺያል ሚዲያው ንቁ ተሳታፊ የሆኑት ዶ/ር ቴዎድሮስ በሳዑዲ ተመላሾች ዙሪያ በዋናው ሚዲያና በሶሺያል ሚዲያው ላይ በተደጋገሚ መታየታቸውና የነበራቸው ንቁ ተሳትፎ ከሁለት ሳምንታት በፊት በተደረገ አንድ ስብሰባ ላይ “ክስተቱን ለግል ዝና ማግኛነት አውለኸዋል” በሚል በፖለቲካ ጓዶቻቸው አስወቅሷቸዋል፡፡” ካለ በኋላ በተጨማሪም “በስብሰባው ወቅት ካስወቀሷቸው ጉዳዮች ሌላኛው፣ ለሳዑዲ ተመላሾች ማቋቋሚያ ባለሀብቶች የ7 ሚሊየን ብር እርዳታና ከተመላሾቹ የተወሰኑትንም በመቅጠር የስራ ዕድል ለመስጠት የተስማሙበት ጉዳይ ሲሆን፤ ይህ የዶ/ር ቴዎድሮስ አካሄድ ግን በመንግስት ለተመላሾቹ የተያዘውን በአነስተኛና ጥቃቅን የማደራጀት እርምጃ ይቃረናል በሚል ነበር በፖለቲካ ጓዶቻቸው ያስወቀሳቸው፡፡” በማለት የውጭ ጉዳይ ሚ/ሩንና በድርጅታቸው ውስጥ የተፈጠረባቸውን ወቀሳ ዘግቦታል።
ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በቀጣዩ ምርጫ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ/ር ሊሆኑ ይችላሉ፤ ለዚህም ነው በግል ዝና ግንባታ ላይ የተሰማሩት የሚሉ አስተያየቶች በተደጋጋሚ ሲደመጡ መቆየታቸው ይታወሳል።

አንዱዓለም አራጌ ከእስር ቤት “እኔ እስሩ አልከበደኝም፤ በጣም ያሳዘነኝ ግን በኔ መታሰር ልትጠቀሙበት አልቻላችሁም” አለ

December 11/2013

(ዘ-ሐበሻ) የ2005 ዓ.ም የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ምርጥ ተብሎ የተሰየመውና በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት የሚገኘው ወጣቱ ታጋይ አንዱዓለም አራጌ እስር ቤት ሊጠይቁት ለሄዱት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች መልዕክት አስተላለፈ። በጣም ማዘኑንም ገለጸ።

ዕድሜ ልክ እስራቱን ተቀብሎ እስር ቤት የሚገኘው አንዷለም አራጌ “ይቅርታ አልጠይቅም” በሚል እስካሁን በእስር ቤት እየማቀቀ ሲሆን “በእኔ መታሰር ብዙ ልትጠቀሙበት ስትችሉ አለመጠቀማችሁ ያሳዝነኛል:: እኔ አሁን በእስር ባለሁበት ሰዓት የኢትዮጵያን ሕዝብ የነፃነት ትግሉን ወደ ፊት ለመግፋት አጋጣሚ ሊሆንላችሁ ቢችልም አልተጠቀማችሁበትም ” ሲል የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን መውቀሱን የዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች ገልጸዋል።

“እኔ መታሰሩና፤ በእስር ቤት እየደረሰብኝ ያለው ስቃይ አልከበደኝም። የከበደኝ ግን በኔ መታሰር ልትጠቀሙበት አለመቻላችሁ ነው። በኔ መታሰር መንግስት ብዙ ጫና ውስጥ እንዳለ ይታወቃል። በኔ መታሰር ብዙ ሥራ ልትሰሩበት፤ ትግሉን ወደፊት ልታስኬዱበት ስትሉ ይህን አላደረጋችሁም” ያለው አንዷለም አራጌ አሁንም የመንፈስ ጥንካሬው አብሮት እንዳለ በ እስር ቤት ካነጋገሩት ወገኖች መካከል ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል።

አንዷለም አራጌ የፌደራሉ ማረሚያ ቤት የሚጠይቁህን ሰዎች ስም ዝርዝር አስመዝግብ ተብሎ ተጠይቆ የነበረ ሲሆን እርሱ ግን ማንም ሰው መጥቶ ሊጠይቀኝ መብቱ ነውና ስም ዝርዝር አውጥቼ አልሰጥም ሲል ፈቃደኛ አለመሆኑን ዘ-ሐበሻ ከዚህ ቀደም መዘገቧ አይዘነጋም።

ሰመጉ በቤንሻንጉል ጉሙዝ የሰብአዊ መብት ጥሰት መፈጸሙን አስታወቀ

December 10/2013
 (አንድ)ቀን ፳፻፮ /  ኢሳት ዜና :-በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተለያዩ ዞንና ወረዳዎች አማራ ናችሁ ተብለው በተባረሩ በሺዎች በሚቆጠሩ ዜጎች  ላይ የሰብአዊ መብት ጥሰት እና አካላዊ ጉዳት እንደተፈፀመ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ባካሄደው ጥናት አረጋግጧል ፡፡
በክልል በተለያዩ ዞንና ወረዳዎች ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ቁጥራቸው ከ10 ሺህ  በላይ የሚገመቱ ዜጐች ለረዥም አመታት ይኖሩበት ከነበረው አካባቢያቸው የዚህ ክልል “ተወላጆች አይደላችሁም” በማለት በሀይልና በግዳጅ ቤት ንብረታቸውን ጥለው ከመጋቢት 15/2005 ዓ.ም ጀምሮ እንዲሰደዱ መደረጋቸውን  ተቋሙ አውስቷል፡፡
በዚህም ምክንያት ህፃናትና ሴቶች እንዲሁም አቅመ ደካማዎች በቂ ምግብና ህክምና ባለማግኘታቸው በከፍተኛ ችግር ላይ ወድቀው እንደነበር ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዞን ቡለን ወረዳ ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ተወካዮቻቸው አቤቱታና የምስክርነት ቃል ማረጋገጡን የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ያካሄደው ጥናት አመልክቷል፡፡
ጉባኤው  በአካባቢው በመገኘት የጉዳዩን ስፋትና ተፈናቃዩች በዚህ ጊዜ የሚገኙበትን አጠቃላይ ሁኔታ ለማጣራት መቻሉንም ገልጿል።
ተፈናቃዮቹ አሁን የሚገኙበት ሁኔታ አስቸጋሪ ነው ያለው ሪፖርቱ፤ በአንዳድ አካባቢዎች ለምሳሌ በካማሼ ዞን ተፈናቃዮቹ ወደ ቦታቸው እንዲመለሱ የተደረገ ቢሆንም ከተመለሱ በኃላ ንብረታቸው በመወሰዱና በመጥፋቱ ለመቋቋምና ወደ ነበሩበት የኑሮ ሁኔታ ለመመለስ አልቻሉም ። ለእርሻ ግብዓት የሚሆኑ እንደ ዘር ፣ማዳበሪያ የመሳሰሉትን ለመግዛት አለመቻላቸውን፤ ብድርም ለመውሰድ ሲጠይቁ ብሔረሰባቸው እየተጠቀሰ አድልዎ እየተፈፀሙባቸው እንደሚገኝ የሰመጉ ባለሙያዎች በአካባቢዉ ተገኝተው ባጣሩበት ወቅት ከተጐጂዎቹ አንደበት ለመረዳት ችለዋል፡፡ በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በባሩዳ ቀበሌና በአካባቢው ካሉት ቀበሌዎች የተፈናቀሉት ሰዎች
ብዛት 5 ሺ እንደሆነ የተፈናቃዮዎቹ ተወካዩች የገለፁ ሲሆን እነዚህ ተፈናቃዮች በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ በሚገኙት ጓንጓና ቻግኒ ከተሞች ውስጥ በብዛት ይገኛሉ፡፡ ይሁንና በሌሎች አካባቢዎችም በዘመድ ወዳጅ ቤት ውስጥ ተጠግተው እንደሚገኙ የተወሰኑ ተፈናቃዮችና ተወካዮቻቸው ቻግኒ ከተማ ውስጥ ለሰመጉ ባለሙያዎች ለማጣራት በሄዱበት ወቅት አረጋግጠውላቸዋል፡፡ በተለይም ይህንን የማጣራት ስራ በሚሰሩበት ወቅት በቻግኒ ከተማ ውስጥ ብቻ በተለያዩ ቦታዎች ተበታትነው የሚገኙ ተፈናቃዮች ብዛት 500 እንደሚደርስ በአካል ተገኝተው ለመረዳት ችለዋል፡፡
ተፈናቃዮቹ ለሰመጉ እንደሚያስረዱት የደረሰባቸውን ከፍተኛ በደልና እንግልት እንዲሁም የሚገኙበትን አስቸጋሪ ሁኔታ በተለያዩ የሀገር ውስጥ ጋዜጦችና የውጭ ሚዲያ በመናገራቸው ምክንያት እስራት ዛቻና ክትትል እየተፈፀመባቸው እንደሆነና በከፍተኛ ስጋት ላይ እንደሚገኙ በምሬትና የተስፋ መቁረጥ ስሜት በዶቢ፣ ያሶ፣ ባሩዳ ከተማ የተፈናቃይና ተወካዮቻቸው ለሰመጉ ያቀረቡት አቤቱታና የምስክርነት ቃል አስረድቷል፡፡
ለረዥም አመታት ያፈሯቸውን ንብረቶችና የእርሻ መሬታቸውን በአካባቢው ባለስልጣናትና በሌሎች ብሔረሰብ አባላት መነጠቃቸው፣ በባሩዳ ከተማ ህጋዊ በሆነ መንገድ ያፈሯቸው የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶቻቸውን እንዳያዙበት መደረጋቸው፣ መታወቂያ እንዳያወጡ መከልከላቸው፣ ልጆቻችው በትምህርት ቤቶች ውስጥ ገብተው እንዳይማሩ የተለያዩ አድልኦና ጫና እንዲደርስባቸው መደረጉ፣ በእርሻ ስራ የሚተዳደሩትን አርሶ አደሮችንም የምርጥ ዘርና ማዳበሪያ “የዚህ ክልል ተወላጅ አይደላችሁም” በሚል አድልኦ እንደሚደረግባቸውና እንደሚከለከሉ፣ በጥቅሉም ”እናንተ የዚህ ክልል ባለቤት አይደላችሁም ስለዚህ ለቃችሁ ውጡ” መባላቸውንና ይህንንም በተቃወሙት ላይ ዛቻ፣ ድብደባ፣ ንብረት ነጠቃና ለእሰራት ጭምር እንደተጋለጡ የተፈናቃይ ተወካዮች ለሰመጉ በፃፉት ከ140 በላይ ተፈናቃዮች ፊርማ ያረፈበት ማመልከቻና የተለያዩ ሰነዶች አመልክተዋል፡፡
የባሩዳ ቀበሌ ተፈናቃዮች “  በአካባቢው አስተዳደር አካላትና በሌሎች የክልሉ ብሄረሰብ አባላት የተነጠቁትን የተለያዩ ንብረቶች ተመላሽ አለመደረጉን ፣በአሁኑ ወቅት ከሌሎች ብሄረሰቦች እየተለዩ ማስፈራሪያና ድብደባ እየተፈፀመባቸው  መሆኑ፣ ምንም አይነት እገዛና ማቋቋሚያ አለመደረጉ፣ የእርሻ ግብዓትን እንደ ዘር ማዳበሪያ ያሉ ግብዓቶችን “እናንነተ የዚህ (ብሄር) አባላት ናችሁ” በማለት እየተከለከሉ ነገር ግን ለሌሎች እየተሰጠ እንደሚገኝና በፌዴራል መንግስት አማካኝነት ቢመለሱም የዞንና የቀበሌ አስተዳደር አካላት “እናንተ ከዚህ ክልል ውጪ ናችሁ” በማለት ልዩ ልዩ አድልዎና መገለል እየተፈፀመባቸው እንደሚገኝ ለሰመጉ አመልክተዋል፡፡
ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ የአማራ ተወላጆች ለረዥም አመታት ይኖሩበት ከነበረው ቦታ “ የዚህ አካባቢ ሰዎች አይደላችሁም” በማለት ከተፈናቀሉ በኋላ ወደ ነበሩበት ቦታ ይመለሱ እንጂ ምንም አይነት እገዛ ከመንግስት እንዳልተደረገላቸውና ይባስ ብሎም እንግልትና የተለያዩ አስተዳደራዊ በደሎች እየተፈፀመባቸው እንዳለ ዘጋቢያችን ሪፖርቱን ተከትሎ ባደረገው ማጣራት ለማረጋገጥ መቻሉን ገልጿል።

Tuesday, December 10, 2013

አዳዲስ መረጃዎች በኢትዮጵያውያን የሳዑዲ አረቢያ ውሎ ዙሪያ (ከነብዩ ሲራክ ከሳዑዲ አረቢያ)

ጅዳና ጀዛን – በጅዳ እና በጀዛን የሚገኙ የህግ እስረኞች በህግ ተይዘው ፍርድ ከተሰጣቸው በኋላ ለአመታት የሚጉላሉ እና በጥርጣሬ ተይዘው ፍርድ ቤት ያልቀረቡ ዜጎች የድረሱልን ጥሪ ተበራክቷል። “ትኩረቱ ሁሉ ወደ ሃገር ተመላሾች መሆኑ ብቻ ሳይሆን ድሮም ተረስተናል አሁንም ተረስተናል! ” እያሉ ነው! የሰሚ ያለህ!

ጅዳ – ከጅዳ ወደ ሃገር ቤት የሚተመለሱ ዜጎች ቁጥር ወደ 60 ሽህ መጠጋቱን መረጃ ደርሶኛል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት ከአሰሪዎች ጋር የትሰሩ ማናችሁም ዜጎች ያለማወላወል በሰላም ወደ ሃገር ግቡ በሚል ባሳለፍነው ያሰራጨው ጥብቅ ማሳሰቢያን ተከትሎ ወደ ሃገር ቤት ለመግባት የሚዘጋጁት ዜጎች ቁጥር ከፍ እያለ መጥቷል። ከዚሁ ጋር በተያያዥ “የሳውዲ ህግ ተለዋዋጭ ነው ፣ የምህረት አዋጁን ያራዝሙት ይሆናል!” በሚል ያልተጨበጠ ተስፋን የሰነቁ በሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መዘናጋት አግባብነት እንደሌላውና ” ህገ ወጥ ” በሚል የተፈረጁ ከሃገር ይውጡ የሚለው ትዕዛዝ ከሳውዲው ንጉስ ቀጥተኛ የተላለፈ የማይታጠፍ ትዕዛዝ መሆኑን መራጃ ስለሆነ ዜጎች መዘናጋትን አስወግደው ያለማወላዎል ቁርጣቸውን አውቀው ይህን መልካም እድል ተጠቅመው ወደ ሃገር ቢገቡ ይሻላል ” በሚል የሳውዲና የመንግስታችን ተወካዮች በአጽንኦት በመምከር ላይ ናቸው!
ደማም – ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ በደማም የሚገኙ ኢትዮጵያንን ወደ ሃገር መግባት ለማመቻቸት የሄዱት ልዑካን ከፊል ስራቸውን ሰርተው ቢመለሱም እጃችሁን ለመንግስ ት ስጡ የተባሉ ዜጎች አሻራ ለመስጠት እየተጉልሉ በመሆኑ ተሰምቷል። “ከስራ ወጥተን ከምንኖርበት ቤት ተፈናቅለን እየተቸገርን ነው !” ብለዋል።
ጀዛን – መኖሪያ ፍቃድ እያለን በመኖሪያ ቤታችን፣ በስራና በየመንገዱ በሚደረግ ፍተሻ ወደ ለእስር የተዳረጉ ዜጎች ጅዳ ለሚገኙት የጅዳ ቆንስል ም/ ኃላፊ ለአቶ ሸሪፍ በተደጋጋሚ አቤቱታ ቢያሰሙም ሃላፊው ከማረጋገት ከመርዳት ይልቅ እያበሳጩን ነው ብለውኛል። ቆንስል ጀኔራል አቶ ዘነበ ከበደ አልሰሙ ይሆን?
December 10/2013

ሪያድ – በመንፉሃና በአካባቢው የሚኖሩ ቪዛን በደላላ ገዝተው የመጡ ዜጎች ትናነት ከእኩለ ቀን እስከ ምሽት የሚከተሉት ጥያቄዎች ተሰብስበው በሪያድ ለኢትዮጵያ ኢንባሲ አቅርበዋል ። የማመልከቻና ጥያቄዎቻቸውን በጽሁፍ ልከውልኛል …
” ይድረስ ለኢትዮጵያ ኤምባሲ ዋናው ጽህፈት ቤት ሪያድ ።በቅድሚያ የማክበር ሰላምታችንን እያቀረብን በመቀጠል መልስ የሚሹ ጥይቄዎችን ለተከበረው ኤምባሲ በማቅረብ ኤምባሲያችንም ከሚመለከታቸው የሣዑዲ አራቢያ መንግስት ባለስልጣን ጋር በመነጋገር ይፈታልን ዘንድ ቀጣይ ጥያቄዎችን እናቀርባለን ።እነሱም
1: ነፃ የሙያ ቅየራ /free profishional change/ ይፈቅድልን ።
2 : ነቅል ከግለሰብ ወደ ሸሪካ እንድናደርግ ይፈቀድልን ።
3 : በሆነ ባልሆነ ምክንያት የሚደረግ የእቃማ በላግ ይቁምልን ።
4 : ፖሊሲ ባልተፈፀመ ወንጀል ይዞ ማሰር ያቁምልን ።
5 : ፖሊስ ባልተፈፀመ ወንጀል ይዞ እያንገላታን ያለ ፍርድ ከፍለህ ውጣ እያሉ የሚፈፅሙት ምዝበራ ይቁምልን ።
6 : ኢትዮጵያዊያን በኢትዮጵያዊያን ላይ የሚፈፅሙት የአየር በአየር ንግድ ከአንዳንድ ሳኡዲዎች ጋር በመሆን ቀርቶ ስራ እና ሠራተኛው በቀጥታ እንዲገናኙ ይደረግልን ።
7 : ለዕድሳት የሚሰጡ ኢቃማዎች በጊዜ ታድሰው ይመለሱልን።
8 : የሳኡዲ ወጣቶች በራሳችን እና በሴት እህቶቻችን ላይ የሚፈፅሙት እንደ ዘረፋ እና አስገድዶ መድፈር አጠቃላይ ወከባ እና በደል ይቁምልን ።
9 : ይህ ሁሉ የማይቻል ከሆነ የተከበረው ኤምባሲያችን ያወጠነውን የዕቃማ ሙሉ ወጪ ከነሞራል ካሳው ጠይቆልን በሰላማዊ መንገድ ወደ ሃገራችን የምንገባበትን ሁኔታ ይጠይቅልን።
በማለት ለተከበረው ኤምባሲ የምናቀርበው እኛ ሪያድ የምንኖር. ቁጥራችን በቀላሉ 1000 የሚጠጋ በመንፉሃ እና በዙሪያ ያለን ኢትዮጵያዊያን ነን።እቃማ ይዘን ስራ ተከልክለን ያለን የተበደልን እና ነገን ያላወቅን የኢትዮጵያ ዜጎች ነን አፋጣኝ መፍትሔ ይፈለግ ” የሚል ማመልከቻ ከ1000 በላይ ፊርማ ያሰባሰቡ ወገኖች በትናንትናው እለት የሪያድ ኢንባሲንና ከሃገር ቤት የመጡትን ከአምስት በላይ ከፍተኛ ዲፕሎማቶችን መፍትሔ ፈልግው አቤት ቢሉም መላ ማግኘቱ ቀርቶ ” ጥያቄያችሁ አግባብነት የለውም ፣ ይህንን የማይሆን ጥያቄ እንዳትንገላቱ ወደ ሃገር በሰላም ግቡ! ” የሚል መልስ እንደተሰጣቸው ገልጸውልኛል!
ወደ ሃገር የሚገቡ ዜጎች ስጋት: የሳውዲን ሁከት ተከትሎ “ወደ ሃገራችሁ እንኳን ደህና መጣችሁ! ” ያለን መንግስት በአስከፊው ስደት ከምንበላው ቆጥበን የጠራቀምነውን ንብረት ይዘው ሰገቡ መመሪያ እየተባለ የሚቀረጡበትና የንብረት መውረስ በማዋከቡ ዜና ሃገር ውስጥ በሚወጡ መገናኛ ብዙሃን እየተነገረ ነው ። ይህ መሰል አሰራር ጉዳይ ነዋሪውን በጣሙን አሳስቦታል።መንግስት ከቀረጥ ነጻ ለተቸገሩት ይፈቅዳል ተብሎ ሲጠበቅ ይህ አሳዛኝ ዜና በእርግጥም አሳዛኝ እስከፊ ነው።
ተቃዋሚ ተብለው የተፈረጁት ስጋት: በተለያየ አጋጣሚዎች መንግስት የሚያወጣቸውን መመሪያዎች በመቃዎም ሃሳብ የሰጠ ፣ በድምጻችን ይሰማ ደጋፊነት የተጠረጠረ እና በሳውዲ የመንግስት ተወካዮች የአስተዳደር በደል የሰላ ሂስ በማቅረባቸው በአይነ ቁራኛ እንታያለን ያሉ ዜጎች ወደ ሃገር ስንገባ እንዳንዋከብ እንሰጋለን በሚል ስጋታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው። ይህን ስጋት ይዥ የጠየቅኳቸው አንድ የጅዳ ቆንስል ከፍተኛ ሃላፊ ” ስጋቱ አይኖር ማለት ባይቻልም ይህን መሰል ስራ እስካሁን በገቡትበላይ አልተሰራም ፣ ከዚህ በኋላም ማሳደድ ማዋከብ ማሰር ብሎ ነገር አይኖም። ያመ ሆኖ በአልም አቀፉ ኢንተር ፖል ተፈላጊ የሆኑ ካሉ ይጠየቃሉ! ” ብለውኛል!
መረጃው በሹክሹክታ ቢደርሰኝም መረጃው እውነትነት አለው ፣ እናም በጅዳና በሪያድ የሚገኙ የመንግስታችን ተወካዮች ህዝባዊ አስቸኳይ ጥሪ በመጥራት በነዋሪው የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ይመልሱ ዘንድ እመክራለሁ!
ጀሮ ያለው ይስማ!

Israel Follows Saudi Arabia, Planning Deportation of 500 African Migrants

December 10/2013
ראש-הממשלה-בנימין-נתניהו-עם-מסתנן-בלתי-חוקי-צילום-פלאש-90
As Ethiopians removed from Saudi Arabia continue filing back into the country, Israel is also planning to deport 500 Ethiopians, possibly as early as January 2014.
Approximately 60,000 migrants from African countries – particularly Eritrea and Sudan, which make up the lion’s share at some 90 percent of the total – have entered Israel in recent years through the Sinai Peninsula. This has led to fears that the Jewish character of the country of 7.8 million is being threatened, as stated by Prime Minister Benjamin Netanyahu in a speech in May 2012.for more click here 

የወያኔንን ስርዓት ለማስወገድ በጋራ የሚደረግ ትግል ወሳኝ ነው !!! (ከገዛኽኝ አበበ ከኖርዌይ)

December 10/2013
ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ
ለአንድ ሀገር የሚያስፈልገው ዋንኛው እና ቁልፉ ነገር ሰላም እና ነጻነት ነው:: ሰላም እና ነጻነት በሌለበት ሀገር የሚኖሩ ዜጓች፣   መብታቸው ይረገጣል ፣ ነጻነታቸው ይታፈናል  ዜጓች ለእስር፣ ለሞት፣ እና ለስደት ይደጋሉ:: ማንኛውም ሰው በሚኖርበት ሀገር በሚኖርበት ሰፈር ወይም አካባቢ እና በሚኖርበት ቤት ውስጥ በሰላም እና በነጻነት መኖርን ይፈልጋል::ነጻነት በምንም ዋጋ ሊተመን የማይችል ትልቅ ጸጋ ነው:: የሰው ልጆች በነጻነት በሚኖሩበት ሀገር መብታቸውን አስከብረው እና መብታቸው ተከብሮላቸው በሰላም እና በፍቅር በሀገራቸው ላይ ሲኖሩ ይታያሉ:: እንደ አለመታደል ሆኖ ሀገራችን ኢትዮጵያ በአለም ላይ ካሉት ሀገራት በግንባር ቀደምነት  የሰው ልጆች ነጻነታቸውን እና መብታቸውን የሚገፈፉበት ሀገር፣ የሀገሪቷ ዜጓች በጨቋኙ ገዥ ስርዓት ነጻነታቸውን ተገፈው ባሪያ ሆነው የሚኖሩበት ሀገር እንደሆነች በየጊዚው የሚወጡ አለም አቀፍ ሪፖርቶች ያስረዳሉ:: ወያኔ ኢህአዲግ የስልጣን ወንበሩን በሀይል ከተቆናጠጠበት ጊዜ ጀምሮ በየጊዜው በህዝባችን ላይ የሚያደርሰው ግፍ እና ጭቆና እየጨመረ መምጣቱ በአደባባይ የሚታይ እውነታ ነው:: ከዚህም የተነሳ በሀገራቸው ላይ የነጻነትን ሀየር መተንፈስ ያልቻሉ በየትኛውም ክልል ላይ የሚገኙ የሀገሪቷ ዚጓች በሀገራቸው ላይ መማር፣ መስራት፣ እና መኖርን እየቻሉ በሀገሪቷ ላይ እየተካሄደ ካለው አፋኝ እና ጨቋኙ ወያኔያዊ ስርዓገበሬው፣  ተማሪው፣  ፣ አስተማሪው ፣ ነጋዲው፣ ጋዜጠኛው ፣ ስፖርተኛው፣ ዘፋኙ፣ አርቲስቱ፣ ወዘተ...... በሁሉም እርከን ላይ የሚገኛው የህብረተሰብ ክፍል ሀገሩ ላይ በሰላም እና በነጻነት መኖርን ስላልቻለ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ በየጊዜው ለስደት ሲዳረግ ይታያል  :: ዋናው እና ወሳኙ ነገር ግን ከሁለት አስርት አመታት በላይ የዜጓችን መብት እያፈነ እና ነጻነታቸውን እየረገጠ ህዝባችንን ለስደት እያደረገ ያለውን ያለውን ይኼን ሰይጣናዊ እና አረመናዊን የወያኔን ስርዓት እንዴት እና ማን ያስወግደው የብዙዎቻችን ነጻነትን እና ፍትህን ናፋቂ ኢትዮጵያኖች ጥያቄ ነው ::

ት የተነሳ ሀገራቸውን እየጣሉ ይሰደዳሉ :: ማንኛውም ሰው ሀገሩን ጥሉ መሰደትን የሚፈልግ ያለ አይመስለኝም በሀገሩ ላይ በነጻነት እና በሰላም መማር መስራት እና መኖርን እስከቻለ ድረስ ::በአንድ ሀገር ላይ መልካም የሆነ መንግስታዊ አስተዳደር የማይካሂድ ከሆነ  አብዛኛውን ጊዜ ዜጓች ለስደት ይደረጋሉ በኢትዮጵያም እየሆነ ያለው ይህ ነው በአሁኑ ሰአት ለስደት የሚዳረገው የሀገራችን ዜጋ ሁሉም የማእበረሰብ ክፍል ነው::

በርግጥ በአሁኑ ሰአት ይህንን ስርዓት በመቃወም በሀገር ቤትም ከ ሀገር ቤትም ውጭ ብዙ የፖለቲካ ድርጅቶች እንደተቋቋሙ እና በተለያየ መንገድ እራሳቸውን እያደራጁ   እንዳሉ የምናየው እና የምንሰማው ነገር ሲሆን::የእነዚሀ  የፖለቲካ ድርጅቶች መብዛት የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ  ሁላችንም በሀገራችን ላይ እንዲሆንልን የምንመኘውን እና የምንናፍቀውን የወያኔን መንግስት አስወግዱ ፍትህ፣ ሰላምን እና ነጻነትን  ያመጣልን ይሆን? የብዙዎቻችን ጥያቄ ይመስለኛል::

 እንደእኔ እንደእኔ በየጌዜው ቁጥራቸው እየጨመረ የሚመጣው የፖለቲካ ድርጅቶች መብዛት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላሙን እና ነጻነቱን ያመጣል የሚለው እመነቱ ባይኖረኝም ብዙም ተቀውሞ የለኝም :: ዋናው አላማ የወያኔን መንግስት ለመቃወም የተቋቋሙ የፖለቲካ ድርጅቶች ለተነሱለት ዓላማ በእውነተኛ ትግል ውስጥ  እስከሚገኙ ድረስ ምንም ጉዳት የለውም ::  ነገር ግን በአንዳንድ  የተቀዋሚ ፖለቲካ ድርጀቶች መካካል እየሆነ እና እያየነው ያለው ነገር አንባ ገነኑን የወያኔ ኢህአዲግን ስርአት ለመቃወም የተነሱ ማንኛውም የተቀዋሚ ድርጅቶች እራሳቸውን እንዲፈትሹ የሚገፋፋ ነገር ነው :: ይህን ያሉኩበትም ምክንያት አለኝ አንዳንዶች የፖለቲካ ድርጅቶች ለምን ዓላማ እንደተነሱ እንኮን የተነሱበትን ዓላማ የዘነጉት ይመስለኛል ምክንያቱም በአሁኑ ሰአት ሁሉም ሰው ሆነ ማንኛውም የተቃዋሚ ድርጅቶች ሊዋጋው እና ሊታገለው የሚገባ ትልቁ ቁጥር አንድ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላት የወያኔ ኢህአዲግ መንግስት መሆን ሲገባው በአንዳንድ የተቃዋሚ ድርጅቶች እንደምናየው አንዱ የሌላውን ትግል ማንቆሸሽ እና ማጣጣል አላስፈላጊ እና ለነጻነት ለምናደርገው ትግል እንቅፋት የሚሆን ይመስለኛል::

በርግጥ በአሁኑ ሰአት ከሀገር ውጭ ሆነው እራሳቸውን መስዕዋት በማድረግ የወያኔን መንግስት እየተፋለሙ ያሉ ድርጅቶች ከሌሎች አጋሮቻቸው ጋር ጥምረትን በመፍጠር እና አብሮ በመታገል ዘረኛውን የወያኔን መንግስት በቁርጠኝነት እየተፋለሙት እና የወያኔን መንግስት እያስደነበሩት እንደለ የምንሰማው ዜና እሰየው የሚያስብል እና በርቱ የሚያሰኝ ቢሆንም ገና ግን ይቀራል ባይ ነኝ:: የጠላቴ ጠላት ወዳጂ ነው እንደሚባለው ማንም የፖለቲካ ድርጅት በማንኛውም መንገድ እና ማንኛውንም ስልት በመጠቀም ይሁን  የወያኔን እርኩስ ድርጊት ለመቃወም እስከተነሳ ድረስ ልንደገፈው እና ልናበረታታው ይገባል ባይ ነኝ :: እያንዳንዱ የፖለቲካ ድርጅት ወያኔን የሚታገልበት እና ወያኔን በመረጥኩት በዚህ መንገድ ብሂድ እና ብታገል እጥለዋለው ብሏ የሚያምንበት የእራሱ የሆነ እቅድ እና አላማ ሊኖረው ይችላል ነገር ግን ማንኛውም የተቃዋሚ የፓለቲካ ድርጅት በእኔ መንገድ እሳካልሂዱ ድርስ ብሎ ትክክል አንዳይደሉ መቁጠር  አግባብ የሆነ አይመስለኝም:: የትኛውም  የፖለቲካ ድርጅት በየትኛውም መንገድ ይሁን ይታገል እያንዳንዳችን ትኩረት ማድረግ ያለብን የጋራ ጠላታችንን የወያኔን መንግስት እና ስርዓት በጋራ ሆነን በአንድነት በመረባረብ ማስወገድ ለማያቋርጥ ሰላም እና ለዘለቂታዊ ነጻነት ወሳኝ ነው ባይ ነኝ:: በተናጥል እና እያንዳንዱ የተቃዋሚ ድርጅት ብቻውን የሚያደርገው ትግል የትም አያደርሰውም ምን አልባት ጊዚያዊ ድልን ሊያገኝ ይችል ይሆናል ግን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ጨቋኙን የወያኔንን ስርአት አስወግዶ ዘለቂታ ያለው ሰላም እና ነጻነትን በሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ ለማምጣት  በህብረት መታገል ይጠበቅብናል እያልኩኝ ይኼን አረመናዊ የወያኔን ስርዓት በጽናት እና በቁርጠኝነት እየታገላችው ያላችው የፖለቲካ ድርጅቶች የተነሳችውለት ዓላም የወያኔ ስርዓት እስኪወገድ ድረስ እጅ ለእጅ በመያያዝ በጋራ ትግላችውን አጠንክሩ ነጻነት እና ሰላም በሀገሩ ላይ የናፈቀው የኢትዮጵያ ህዝብ የወያኔ የዘር ፖለቲካ ሳይዘው አማራው ፣ጉራጌው፣ ኦሮሞው፣ ትግሪው፣ጋምቤላው ወዘተ ...... መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከጓናችው ይቋማል ባይ ነኝ::

ኢትዮጵያ በቆራጥ ልጆቿ ትግል ነፃ ትሆናለች!

በብሔር ፖለቲካ ሥር “የተቀበረው ፈንጂ”!

December 10, 2013 

(ከዋለልኝ እስከ ህወሃት/ኢህአዴግ)
article 39


የብሔር ጥያቄ በኢትዮጵያ ምላሽ እንዳገኘ የሚያስተጋባው ኢህአዴግ “የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች” በዓልን ማክበር ከጀመረ ስምንት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በአንፃሩ “ተመልሷል” የተባለው ጥያቄ እንደተቀበረ ፈንጂ በየጊዜው በየቦታው እየፈነዳ በህይወት፣ በንብረትና በኢትዮጵያዊነት ላይ አደጋ ማድረሱን ዳዊት ሰለሞን ሁነቶችን በመጥቀስ ይሞግታል፡፡
ከአስርት አመታት በፊት
የኢትዮጵያ ተማሪዎች በለውጥ አብዮት ናፍቆት እየተናጡ ነው፡፡ እዚህም እዚያም በተፈጠሩ ቡድኖች የማርክሲስት-ሌኒንስት ፍልስፍናን የሚሰብኩ የርዕዮተ ዓለም ጽሁፎች ይነበባሉ፡፡ ተማሪው ይከራከራል፣ የሌኒኒዝም ፍልስፍና ቀለም ቀለም መሽተት ለጀመረው የ1960ዎቹ ትውልድ ልብ የቀረበ ሆኗል፡፡ ፍልስፍናውን በአገራቸው የፖለቲካ ግለት ለመተርጐም የቋመጡት ወጣቶች በሁለት ጠርዝ ተሰልፈው በኢትዮጵያ ያለው “የመደብ ወይስ የብሔር ጭቆና ነው” በሚል በጠረጴዛ ዙሪያ ይፋለማሉ፡፡
የብሔር ጭቆና በአገሪቱ መስፈኑን ለማሳመን ሽንጣቸውን ገትረው ይከራከሩ ከነበሩ ተማሪዎች መካከል የብዙዎችን ቀልብ ለመስረቅ የበቃው ዋለልኝ መኮንን በተማሪዎች መጽሔት “On the Question of Nationalities in Ethiopia” የሚል ጽሑፉን ማስነበብ ጀመረ፡፡ ዋለልኝ በጽሑፉ ኢትዮጵያ አንድ አገር ሳትሆን ብዛት ያላቸው ብሔሮች በአማራ የበላይነት ተጨፍልቀው የሚኖሩበት መሆኗን ሞገተ፡፡ የዋለልኝን መከራከሪያ የተቀበሉ ተማሪዎች የብሔር ጥያቄን ዋነኛ መፈክራቸው አድርገው አረፉት፡፡ በአገሪቱ የሰፈነው ጭቆና የመደብ መሆኑን በመግለጽ “አንዱን ብሔር ጨቋኝና ሌላውን ተጨቋኝ” በማድረግ የተነሱትን እነ ዋለልኝን የተቃወሙ ተማሪዎች የብሔር ጭቆናን በሚያስተጋቡ ተማሪዎች “የነፍጠኛ ልጆች” የሚል ተቀጥላ ተበጀላቸው፡፡
ዋለልኝ ከማርክሲስት – ሌኒኒስት ፍልስፍና በቀጥታ የገለበጠባቸውን ቃላቶች በመጠቀም ኢትዮጵያን “የብሔሮች እስር ቤት” በማለት ሰየማት፡፡ በዋለልኝ እንደተዋወቀ የተነገረለትን የተጨቆነ ብሔርን ነፃ የማውጣት ፍልስፍና የትግራይ ተማሪዎች መሬት ላይ ለማዋል በማቀድ የነጻ አውጪነት ቡራኬን ተቀብለው ደደቢት በረሃ ገቡ፡፡ ወጣቶቹ ትግላቸውን በማስመልከት በእጅ ጽሑፍ ባሰፈሩት የመጀመሪያ ማኒፌስቷቸው ትግራዋይ በአማራ ጨቋኝ ብሔር ሲጨቆን መቆየቱን በመግለጽ ጨቋኙን (አማራን) ብሄር በጠብ መንጃ ትግል በመፋለም ትግራይን ነፃ ለማውጣት መነሣታቸውን አወጁ፡፡ በለስ የቀናቸው የትግራይ ነፃ አውጪዎች መላዋን ኢትዮጵያን በመዳፋቸው ስር ካስገቡ በኋላ በ1987 በጸደቀው ህገ መንግሥት የጆሴፍ ስታሊንን የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች አተረጓጐም ሳይጨምሩና ሳይቀንሱ እንዲሰፍር በማድረግ የስታሊን ደቀ መዛሙርት መሆናቸውን በተግባር አሳዩ፡፡
የአገሪቱ የመንግሥት አወቃቀርም ብሔር ተኮር ፌዴራሊዝም እንዲሆን ተፈረደበት፡፡ ከብዙ አስርት አመታት በኋላ በዋለልኝ መኮንን “የብሄሮች እስር ቤት” ተብላ ከተጠራችው ኢትዮጰያ የተጨቆኑ ብሄሮችን ነፃ ለማውጣት ብሶት አርግዞት እንደወለደው የነገረን ገዥው ፓርቲ ራሱን በነጻ አውጪዎች ሰረገላ ካስቀመጠ 22 ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ የነገው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓልም በገዥው ፓርቲ እምነት ጥያቄው ምላሽ ለማግኘቱ አይነተኛ ማሳያ ነው፡፡ ለፓለቲካ ፍጆታ እየዋለ ከሚገኘው ህዳር 29 በስተጀርባ መሬት የረገጡ እውነታዎችን ለመፈተሽ የተነሱ ሰዎች ከ73 የሚልቁ ብሄር ተኮር የፖለቲካ ድርጅቶችን ያገኛሉ፡፡ የእነዚህ ፓርቲዎች ዋነኛ የትግል ማዕቀፍ “ጥያቄው” አለመመለሱን የሚያሳይ ነው፡፡ በአገሪቱ ከመቼውም ግዜ በላይ መንግስትን በትጥቅ ትግል ለማንበርከክ ዱር ቤቴ ያሉ “ብሔር ተኮር” ድርጅቶች ስለመኖራቸውም እየተደመጠ ነው፡፡
በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ጭምር ዘውጌ ተኮር ግጭቶች በስፋትና በብዛት እየተደመጡ ነው፡፡ “በኢትዮጵያዊነት” ጥላ ተሰባስበው የትውልድ መንደራቸውን በመልቀቅ በሌሎች ክልሎች ሀብትና ንብረት ያፈሩ ኢትዮጵያዊያን በገዛ አገራቸው እንደ ባይተዋር ተቆጥረው “እየተገደሉ ነው፡፡ በአሩሲ፣ በአርባጉጉ፣ በበደኖ፣ በአፋር፣ በትግራይ፣ በወለጋ፣ በአሰበ ተፈሪ፣ በጋምቤላ፣ ኦጋዴን፣ ጉራፈርዳና በቦረና “ከክልላችን ውጡ” የተባሉ የሌላ ክልል ተወላጆች ተፈናቅለዋል፣ ንብረታቸውን ተዘርፈዋል፣ ከእነ ህይወታቸው ጉድጓድ ውስጥ ተወርውረው ሴቶቻቸው ተደፍረዋል፡፡
በዘመነ ደርግና ከዚያ ቀደም በነበሩ አስተዳደሮች ግጭቶች የሚነሱባቸውና የሰው ህይወት ለከፋ ጉዳት የሚጋለጥባቸው አጋጣሚዎች የነበሩ መሆናቸውን መካድ ባይቻልም እነዚህ ግጭቶች ግን ይነሱ የነበሩት በግጦሽ መሬት ፍለጋ እንደነበር መዘንጋት አይገባም፡፡ በአገሪቱ የጐሳ ፖለቲካ አየሩን ከተቆጣጠረበት ከ22 ዓመታት ወዲህ ግን የግጭቶች ይዘትና መንስኤ ወደ አንድ ጫፍ በማዘንበል ላይ ይገኛል፡፡ “ክልላችንን ለቅቃችሁ ውጡ” የሚለው ድምፅ በሁሉ ልብ ማስተጋባት ሲጀምር “በህዝብ መካከል አለመተማመንን በመዝራት በመጨረሻ የሚያሳጭደው ውጤት አገርን ለመበታተን ይዳርጋል፡፡ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል የሚከበረውም “እኛና እነርሱ” በሚል መንፈስ መሆኑም የተቀበረው ፈንጂ ሰዓቱን እየሞላ እንዲሄድ ከማድረግ ውጪ የሚፈይደው ነገር ስለመኖሩ ብዙዎች ይጠራጠራሉ፡፡
ሁሉም የራሱን መንደር እየፈለገ ወደቀረበው እንዲሄድ የሚያደርግ መድረክ መፈጠሩን የሚተቹት ዶክተር ዘውዱ ውብእንግዳ “የፌደራሊዝም ታሪካዊ አመጣጥ” በሚለው መጽሐፋቸው ትዝብታቸውን እንዲህ ያሰፍራሉ፡፡ “በደርግ ዘመን ቀበሌዎች ስብሰባ ህዝቡን ሲጠሩ በ … ቀበሌ የምትገኙ … አዳራሽ ስብሰባ ስላለ እንዳትቀሩ ይሉ ነበር፡፡ አሁን ግን … ብሔር ተወላጅ የሆናችሁ … አዳራሽ እንድትገኙ ማለት ተጀምሯል፡፡ በፊት በአንድ ቀበሌ መኖር የአብሮነት መለኪያ ተርጐ ይወሰድ ነበር፡፡ አሁን ግን በአንድ ቀበሌ መኖር ብቻ በቂ ሳይሆን የብሔር ማንነት እንደመታወቂያ እየተወሰደ ነው” ይላሉ፡፡ ልዩነቶቻችን ጐልተው እንዲታዩ የሚደረጉባቸው መድረኮች በመንግሥት አታሞ እየተጐሰመላቸው አጀንዳ ሲሆኑ ከማየት የበለጠ ህመም የሚፈጥር ነገር የለም፡፡
በዓሉ የሚከበርባቸው ሥነ ሥርዓቶች ለኢህአዴግ ቱባ ባለስልጣናት አትሮንስ በመሆን ከማገልገል በዘለለ የብሔር ፖለቲካው፣ ፌዴራሊዝሙና የክልል መንግሥታት ነጻነት ለውይይት የሚቀርብባቸው መድረኮች አለመዘጋጀታቸውና እስካሁን ብሔርን/ዘውጌን ተገን በማድረግ በተፈጠሩ ቀውሶች ዙሪያ ውይይት የሚደረጉባቸው መንገዶች አለመፈጠሩ በእኔ እምነት በዓሉን “ከፈንጠዝያ” የዘለለ አያደርገውም፡፡ የአማራው ባህል ለትግሬው፣ የጉራጌው ለኦሮሞው፣ የከምባታው ልጅ ለስልጤው እየተሰጠች ያደግንባት አገር፣ አፋሩ ለሃድያው ዘብ የሚቆምባት ምድር ያፈራችን ሰዎች ለአክሱም ሀውልት ጋምቤላው የሚጨነቅባት የቅኖች ምድር ኢትዮጵያ በብሔር ፖለቲካ በናወዙ ጥቂት ቡድኖች ትልቁን ምስል ጠብቃ እንድትኖር እነዚህ መድረኮች “የእኛና የእነርሱ” የሚሉ ስሜቶች ስር ሳይሰዱ የሚቀርቡባቸው ሊሆኑ ይገባል፡፡ ያን ጊዜም “የተቀበረው ፈንጂ” ይመክናል፡፡
የብሔር ፖለቲካ መዘዝ
በአገሪቱ ከ84 የሚልቁ ብሔረሰቦች እንዳሉ ከመነገሩ ባሻገር የትኛው የማኀበረሰብ ክፍል ብሔር፣ የትኛው ብሔረሰብ ወይም ሕዝቦች የሚሰኙት የትኞቹ እንደሆኑ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ በአንዳንድ አደባባዮች የጆሴፍ ስታሊንንና የዋለልኝ መኮንን ንግግሮች እንደወረደ በመደስኮር “አንደበተ ርትዕ” ተብለው የነበሩት አቶ መለስ ዜናዊ እንኳን እነዚህን የማኀበረሰብ ክፍሎች ሳይተነትኑ አልፈዋል፡፡ ከስምንት ዓመት ወዲህ መንግሥት የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል በተለየዩ ሥነ ሥርቶች እንዲከበር እያደረገ ነው፡፡
በዚህ ቀን ከተለያዩ የማኀበረሰብ ክፍሎች የመጡ ሰዎች በመሰባሰብ እለቱን ይዘክራሉ፡፡ በዚህ ቀን እንኳን የትኛው ብሔር፣ የትኛውብሔረሰብ፣ የትኞቹ ደግሞ ህዝቦች መሆናቸው አይታወቅም፡፡ ነገር ግን ፍቺ ባልተገኘበት ሁኔታ በዓሉ ይከበራል፡፡ ሌላው አስገራሚ ነገር በህገ መንግሥቱ “ሕዝቦች” ተብለው የተጠቀሱ ክፍሎች ምንም አይነት መገለጫ የሌላቸው መሆኑ ነው፡፡ ለምሣሌ ህገ መንግሥቱ ስለመሬት የሚለውን እንውሰድ፡፡ መሬት የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ስለመሆኑ ተጠቅሷል፡፡ በዚህ መነሻነትም ክልሎች በቋንቋ መነሻነት የየራሣቸውን ወሰን እንዲካለሉ ተደርገዋል፡፡ ህዝቦችስ? ነገሩን ትንሽ ለጠጥ በማድረግ እንውሰደው፡፡
በጉራፈርዳ ሰፍረው የነበሩ አማሮች “እንደ ህገወጥ ሰፋሪ ታይተው በክልሉ መንግሥት ውሣኔ ለአመታት ይዘውት የቆዩትን መሬት ጥለው እንዲሰደዱ ተደርገዋል፡፡ መሬቱን እንዲለቅቁ የተደረጉት “የክልሉ ተወላጅ” ባለመሆናቸው ብቻ ነው፡፡ እነዚህ ወገኖች የክልሉ ተወላጅ ባይሆኑም ሕዝብ በመሆናቸው እንደ ህገ መንግሥቱ የመሬት ባለይዞታነት መብታቸው ሊከበርላቸው ይገባ ነበር፡፡ የፌዴራሊዝሙ ተሳክሮት ዶክተር ዘውዱ በመጽሐፋቸው ለፌዴራል መንግሥት ምስረታ መንስኤ የሚሆን መሠረታዊ ነጥብ “ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ መንግስታት ወይም የየራሣቸውን መንግሥታዊ አስተዳደር ያካበቱ ሕዝቦች በፈቃደኝነት ላይ ተመስርተው የሚያቋቁሙት ሦስተኛ መንግሥት ነው፡፡ ስለሆነም ፌዴራላዊ መንግሥት ከትንሹ ቁጥር ሳንነሳ የሦስት መንግሥት ጥምር ነው” ይላሉ፡፡ በዘውዱ ገለፃ ፌዴራሊዝምን በማስተዋወቅ የመጀመሪያዋ ተጠቃሽ አገር ለመሆን የበቃችው ለ100 ዓመታት ያህል በእንግሊዝ ቅኝ ተገዝታ የነበረችው አሜሪካ ናት፡፡
ቅኝ ገዢዋ እንግሊዝ ሀገሪቱን በ13 የቅኝ ግዛት አስተዳደሮች በመከፋፈል ስታስተዳድር ቆይታለች፡፡ አሜሪካኖች ራሣቸውን ነፃ ካወጡ በኋላ ተከፋፍለው የነበሩት ክልሎች በፌዴራሊዝም አማካኝነት መልሰው አንድነታቸውን አግኝተዋል፡፡ ሌሎች በቅኝ ግዛት ስር የነበሩና የተለያዩ አስተዳደሮችም የአሜሪካውን ፌዴራሊዝም በአርአያነት በመከተል የተበታተኑት አንድ መሆን ችለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ የመንግሥት አወቃቀር ግን የጐሳ በመሆኑ በአለም ከሚታወቀው የፌዴራሊዝም አመሰራረት ጽንሰ ሀሣብ ያፈነገጠ ነው፡፡
በህገ መንግሥቱ ድንጋጌ መሠረት የክልል መንግሥት ለማቋቋም መመዘኛ ሆኖ የቀረበው ብሔር፣ ብሔረሰብና ሕዝቦች በሚል መነሻነት ነው፡፡ አስቀድሜ ለመግለጽ እንደሞከርኩት በአገሪቱ ውስጥ ከ84 የሚልቁ ብሔረሰቦች ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን ክልል እንዲመሰረቱ እውቅና የተሰጣቸው ዘጠኙ ብቻ ናቸው፡፡ ቀሪዎቹስ? ለምን ክልል የመመስረት መብትን ተነፈጉ?
በህገ መንግሥቱ በዘጠነኛ ክልልነት የተቀመጠው “የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል” ተብሎ እንዲቀመጥ ተደርጓል፡፡ የፌዴራሉመንግሥት ክልሎች የተመሠረቱት ቋንቋን ማዕከል ባደረገ መልኩ ቢሆንም ይህ ወደ ደቡብ ሲያመራ “ጂኦግራፊያዊ” እንደሆነየተፈለገበት መንገድ ለማንም ግልጽ አይደለም፡፡ በደቡብ ክልል ከ46 የሚልቁ ብሔረሰቦች ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ብሔረሰቦች በሌሎች ክልሎች የሚገኙ ብሔረሰቦች የራሣቸውን ክልልና መንግሥት የሚመሰርቱበትን መብት ሲጐናጸፉ በደቡብ ያሉት ግን ይህንን መብት ተነፍገዋል፡፡
የፌዴራሊዝሙ አወቃቀር በቋንቋ በአንድ ቦታ ሲሰራ በሌላ ቦታ በጂኦግራፊ መሆኑም የአወቃቀሩን ተሳክሮት ወለል አድርጐ ያሳያል፡፡ በጎሳ ላይ የተንጠለጠለ የመንግሥት አወቃቀር በሩዋንዳ፣ ሶማሊያ፣ ኮሶቮና ሩሲያን በመሳሰሉ አገራት የፈጠረውን ሰብአዊ ቀውስ የተመለከቱ ሰዎች የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥት የአወቃቀር ተሳክሮት በአገሪቱ ላይ በጊዜ የማይተነብይ ምስቅልል ሊፈጥር እንደሚችል ይጠቁማሉ፡፡ (ዳዊት ሰለሞን)

ከጎልጉል ድረገጽ የተወሰደ

Doctor Arkebe Oqubay flying like a pig

December 10, 2013
by Abebe Gellaw
Until recently, Arkebe Oqubay was known to have spent much of his life on projects of bloody conflicts, corruption, tyranny or gross violation of human rights. It was a  total surprise when one of TPLF’s topguns was introduced as a record-breaking scholar.
It emerged that Arkebe has been bragging to friends, relatives and admirers since last October that he got a Ph.D from the University of London’s School of Oriental and African Studies (SOAS) with great honor and distinction. He claimed that he shattered academic records, an achievement that guaranteed his name a special place in the honor list of the school. That is good for him, but why is SOAS contradicting this amazing scholar who claims to be the first to hold his PhD in record time and first for his unblemished dissertation?Arkebe Oqubay was known to have spent much of his life on projects of bloody conflicts
On November 8th, Isayas Astebeha Abaye, a well-known apologist and flunkey of the dictatorship in Ethiopia, published a “breaking news” story on Aigaforum.com trumpeting Arkebe’s miraculous and unique intellectual prowess.
According to Isayas Astebeha Abaye, who got the story from the horse’s mouth:
This week Dr. Arkebe Oqubay was recognized as an outstanding Scholar in the Academic [sic] circles of London. He broke the academic record of doctoral school in the University of London (School of Oriental and African Studies) for the first time by finishing the four year program within 23 months with high honor and great distinction. In this century old institution (established in 1916), the doctoral program is set for four years maximum to defend and finish the doctoral thesis. Most of the candidates defend and finished with difficulties and hardship (if they are lucky and extraordinary).Arkebe has finished [sic] within 23 months and surprised the department of Development Studies, the university professors and students altogether [sic]. Never heard of such great achievements in such short period of time, what a person!!!!!!! His external examiners from Cambridge and other well known [sic] academic institutions awarded him “PASS WITH OUT [sic] CORRECTION” on the spot; which means great distinction with great honor (never happened and never heard of).Arkebe did it!!!! His name and his country’s name is in the history book of this famous University [sic]. What an achievement!!! We are proud of him!!! Congratulations to Dr. Arkebe Oqubay. [That was Isayas Abaye’s badly scripted story, which not only breaks all the basic rules of news reporting but also published online WITHOUT CORRECTION or verification.]
The brazen “story” about Arkebe’s amazing accomplishments in London trended well on the social networking sites creating buzz and excitement among TPLF’s faithful drones who danced and ran victory laps to Isayas Abaye’s song: “Dr Arkebe breaks the record in a century old Academic Institution [sic].”
The big trouble with Arkebe’s “record-breaking” academic achievement is that it was manifestly false. As the story was evidently dubious and nonsensical, we had to send a copy of Aigaforum’s story to SOAS and the University of London for fact-checking and verification. The school’s Directorate of External Relations spent almost three weeks digging through its records trying to verify the identity of the phenomenal scholar “whose name and his country’s name” were said to have entered the “history books”, just to borrow the words of the amateur reporter.
After careful and lengthy investigation, Vesna Siljanovska, SOAS’s communication officer, verified that Arkebe Oqubay Metiku had indeed completed his doctoral studies at SOAS in October 2013. While trying to avoid some of the most awkward questions about the newmint scholar, she disclosed that his dissertation focused on the “industrial policy of Ethiopia”. Siljanovska also indicated that the school never heard of the “scholar’s” record-breaking feats.
SOAS communication officers also tried to explain that the so-called record-breaking achievement is common not only at SOAS but also in other UK universities. “Like many other UK universities, a PhD is usually at least three years in length but candidates can apply to submit after two years of full – time enrolment subject to the approval of the Supervisory Committee and the Associate Dean (Research) of the relevant Faculty. While the majority of candidates studying for a PhD in the UK complete within three years, there are a number of students who complete in a longer or shorter time period,” SOAS said in a carefully crafted statement.
Prof. Christopher Cramer, who teaches in the Department of Development Studies at SOAS, also declined to discuss details about Arkebe’s miracles due to the university’s privacy policy. But Cramer wrote in an email that Arkebe achieved nothing extraordinary or unprecedented as claimed in the Aigaforum story. Prof. Cramer was clearly amused by the claim the first “no corrections thesis,” but he declared that the pompous claim was “completely untrue”.
Asked what Arkebe’s new research finding could be on “industrial policy in Ethiopia” that he and his TPLF tyrannical clique formulated and imposed on the poor nation that they have brutalized and robbed for over two decades, Prof. Cramer, who was apparently the good doctor’s adviser, also declined to comment. It should be remembered that Arkebe was one of the architects of the Endowment Fund for the Rehabilitation of Tigray (EFFORT), the illegal TPLF-controlled business conglomerate that is widely accused of symbolizing apartheid-like crony capitalism sucking the blood and gnawing the bones of the poor people of Ethiopia
One of Ethiopia’s leading rights advocates, Prof. Alemayehu Gebremariam, finds the revelation quite interesting. He says  the fact that Arkebe was approved to do his dissertation on “industrial policy in Ethiopia”, a policy paper that he and his TPLF sidekicks had been toying around since TPLF took power in 1991, raises legitimate questions.
“If Arkebe had indeed finished his dissertation in “record time”, it is because he was copyediting his old policy papers instead of doing original research, which is what a doctoral dissertation is supposed to be,” the professor said.
“If Arkebe’s dissertation is of such an exceptional scholarly and scientific quality sufficient to shift paradigms, why is it not published in whole or in part in the leading scholarly journals of the world?” he asked.
Arkebe has a history of being a clumsy publicity hog. When he was the mayor of Addis Ababa, he once plastered his mugshot on huge promotional billboards under the guise of raising awareness on the HIV/AIDS epidemic. Azeb Mesfin, wife of the late dictator Meles Zenawi and Arkebe’s arch foe, reportedly ordered the removal of his outsize images from the city centers just within a few days. She reportedly felt that Arkebe would say and do anything for self-promotion and self-aggrandizement.
Prof. Alemayehu wonders why TPLF’s tyrannical midgets seek to puff themselves up as intellectual giants. “Those who aspire to achieve terminal degrees do so because they love research, discovery of new knowledge, truth and make significant contributions to the body of knowledge in their field of study. Conferring a Ph.D. on the unenlightened is like dressing a hoodlum in a designer suit. It looks good but everyone knows that the man under the suit is still a hoodlum,” he commented.
Isaias Abaye and his bosses should take their own advice. He recently warned us about Member of the European Parliament and a great friend of Ethiopia, the Honorable Ana Gomes, who reduced the late tyrant Meles Zenawi into dust with her sharp commentary. To the dismay of Zenawi’s worshippers like Isayas, she bluntly stated that the demise of the cruel and deceitful dictator was a good opportunity for Ethiopia.
In his silly tantrums against the respected MEP, Isayas lamented:   “Unlike the early days of the online media, we have all learned not to be easily shocked, surprised, or overly excited by what we read online. Mostly, we try to verify the reliability and reputation of the source. When we read Ana Gomez’s [sic] interview with a journalist from a local private media, we didn’t even doubt the authenticity of this story knowing it is the angry Hana Gobeze….
Perhaps Isaias and Arkebe do not realize that in  the Information Age liars, cheats, con artists and fibbers do not last a nano second without being exposed. Maybe the entire pack of TPLF’s liars, robbers and tyrants can take a lesson from this amusing episode. They should know, “Three things cannot be long hidden: the sun, the moon, and the truth.” If Arkebe must be extolled for breaking records, it should be for “record breaking lies” and for telling lies with disgrace. But he must know that his lies will NOT PASS WITHOUT CORRECTION.
It is said that old habits die hard. Sadly Arkebe miserably failed to learn that knowledge must be based on truth. It also appeared that SOAS also failed to equip its windbag graduate with the basic skills of researching at least easily detectable and verifiable facts. Yet SOAS can be forgiven as neither PhD nor professorship changes the character of pigs that are identical with the ones in George Orwell’s Animal Farm. .
In the footsteps of their fallen demigod Meles Zenawi, TPLF’s dictators, robber barons, torturers and their heartless accomplices such as Arkebe and pedler of lies Isayas Abaye have a guaranteed place, not in honor books, but in the trashbin of history. No unimpressive PhD, professorship or self-imagined glories and trophies will change the fate of these dictatorial fibbers.
In the world of Aigaland’s Animal Farm, pigs may soar and fly in the skies. But in the real world we all live in, TPLF’s pigs can only dream of being eagles or falcons. Whatever any pigs dream of, they have to live with the fact that they are just pigs. This is the inconvenient truth that no genius pig with a PhD from SOAS, Harvard or Stanford can change and refute.
Speaking of stellar academic achievement, a recent true story about a truly outstanding Ethiopian scholar has filled our hearts with joy and pride. It was disclosed a couple of weeks ago that Dr. Mulatu Lemma, an award-winning mathematicsDr. Mulatu Lemma, an award-winning mathematics professor professor at Savannah State University, was honored as the 2013 Georgia Professor of the Year by the Carnegie Foundation for Advancement of Teaching and the Council for the Advancement of Support of Education (CASE).His name and his country’s name is in the history book of academia for being one of the top mathematics professors in the United States. What an achievement!
It should be noted that Arkebe’s record-breaking tall tales of being the most outstanding PhD holder in the entire history of SOAS, even if his dream for academic grandiose has now fallen apart, must be recognized at least for the effort. The “scholar”, who has not yet published a single academic paper or a mini-newspaper article, must be honored namedDoctor Arkebe Kedadaw!
While the warriors of truth and freedom such as Eskinder Nega, Reeyot Alemu, Andualem Aragie, Bekele Gerba and Ustaz Abubakir, are languishing in TPLF dark dungeons, Arkebe had the luxury of jetting to Europe in search of academic grandiose. Quite certainly Arkebe is unlikely to get the honors and accolades he craves badly while he is alive. So just like Zenawi, he deserves to be honored with a state funeral!

በኢትዮጵያ ከግማሽ ክ/ዘመን በላይ የቆየማንዴላን የተመለከተ የደህንነት ሚስጥር ዛሬ ይፋ ሆነ።ሚስጥሩን ማንዴላም እስካሁን ድረስ አይውቁትም።

ኔልሰን ማንዴላ የደቡብ አፍሪካ የፀረ-አፓርታይድ (የዘር-መድሎ) ተዋጊ አርበኛ መሆናቸው ይታወቃል።ለእስር የተዳረጉት ኢትዮጵያ ውስጥ ወታደራዊ ስልጠና ወስደው እንደተመለሱ ነበር። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ 1962 ዓም ማንዴላ በኢትዮጵያ ቆይታቸው በወቅቱ ለማንዴላ ኢትዮጵያ ፓስፖርት በመስጠት አጋርነቷን የገለፀች ብቸኛ ሀገር ነበረች።
ከዘመናት በኃላ ማንዴላ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ወቅት የግድያ ሙከራ ተደርጎ እንደነበር ሚስጥሩን ከግማሽ ክፍለዘመን በላይ ይዘው የቆዩ በቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ዘመን የኢትዮጵያ ፖሊስ መኮንን ዛሬ ጥቅምት 15/2006 ዓም ለመጀመርያ ጊዜ በሸገር ራድዮ የዜና እወጃ ላይ ገልፀዋል።
ሻምበል ጉታ ዲንቃ በንጉሡ ዘመን የፖሊስ መኮንን ነበሩ። ማንዴላን በከፍተኛ ሚስጥር እንዲጠብቁ ኃላፊነት ከተሰጣቸው ጄኔራል ታደሰ(የማንዴላ አሰልጣኝ በወቅቱ ኮ/ል የነበሩ)፣ኮ/ል ፍቃደ እና ሻምበል ፈቃደ ውስጥ ነበሩ።ዛሬ የ76 አምቱ የእድሜ ባለፀጋ ሻምበል ጉታ ዲንቃ ለሸገር ሲናገሩ እንዲህ አሉ።
” ማንዴላን እንድጠብቅ ኃላፊነት የተሰጠኝ እኔ ነበርኩ።ማንዴላ የሚያድሩበት እና ወታደራዊ ስልጠና የሚወስዱበት የኮልፌ የፖሊስ ማሰልጠኛ ቦታ በተለይ እርሳቸው የሚገኙበት ቦታ ‘የፈንጅ ወረዳ’ ነበር የሚባለው።ከአራታችን በቀር ማንም ወደ እርሳቸው ቦታ ዝር ማለት አይችልም። ሲተኙ መስኮት ከፍተው ነው የሚተኙት።አንድ ቀን ታድያ አብሮኝ ከሚሰራው የፖሊስ ባልደረባዬ በጥብቅ እንደሚፈልገኝ ነገረኝ።ጣይቱ ሆቴል ተቀጣጠርን እና ሃሳቡን ገለፀልኝ።” ካሉ በኃላ አሁን አዲስ አበባ ላፍቶ አካባቢ ነዋሪ የሆኑት ሻምበል ጉታ በመቀጠል እንዲህ ብለዋል-
”ጣይቱ ሆቴል የወሰደኝ ሰው ለጊዜው 2000 ፓውንድ በወቅቱ አስቡት 2000 ፓውንድን እና ሰጥቶ እንዲህ አለኝ- ‘ሁለት ዕድል ከፊታችን ተቀምጧል።ሊያመልጠን አይገባም።ከፍተኛ ገንዘብ እናገኛለን።ቀጥሎም ወደ ውጭ ሀገር የመሄድ ዕድል አለን።ከአንተ የሚጠበቀው ማንዴላ በተኛበት ዛሬ ሌሊት በመስኮት ገብተህ በገመድ አንቀህ ግደል እና ውጣ እንደወጣህ መኪና ተዘጋጅቶ ይጠብቅሃል ከእዚህ የውትድርና ሕይወት እንገላገላለን’ አለኝ። እኔም ጉዳዩን ከሰማሁ በኃላ በጉዳዩ የተስማማሁ መስዬ ቀጥታ ለጀኔራል ታደሰ ነገርኩኝ። ጉዳዩ በሚስጥር ተይዞ ይህንን ያደረጉት ሰዎች ተደረሰባቸው እና ከሀገር እንዲወጡ(እንዲባረሩ) ተደረጉ ይህ ሚስጥር ለዘመናት ከእኔ ጋር የኖረ ነው።ጉዳዩን ማንዴላም አያውቁትም።” ብለዋል።
ኔልሰን ማንዴላ በወቅቱ እንደ ሻምበል ጉታ ዲንቃ አይነት ታማኝ የኢትዮጵያ የፖሊስ መኮንን ባይገጥማቸው ኖሮ የደቡብ አፍሪካ የነፃነት ታሪክ ሂደትም ሆነ የነፃነት ትግሉ ታሪክ ሌላ መልክ በያዘ ነበር።ይህ ጉዳይ እጅግ ትልቅ ጉዳይ ነው።የኢትዮጵያ ፖሊስ ለአፍሪካ ያደረገው አስተዋፆ የሚያጎላ፣ኢትዮጵያ ለደቡብ አፍሪክ ያደረገችው ትልቅ አስተዋፆ በመሆኑ በኢትዮጵያ የዜና አገልግሎቶች ሁሉ ትኩረት ተሰጥቶት የዓለም አቀፍ የዜና ሽፋን እንዲያገኝ ጥረት ማድረግ ለኢትዮጵያ ፋይዳው ብዙ ይመስለኛል።
በመሆኑም ቢያንስ ለሻምበል ጉታ ዲንቃ የኢትዮጵያ ፖሊስ ጠርቶ ከማዕረግ እስከ ሽልማት ከእዚህ ባለፈም ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠት እና ማንዴላ በሕይወት ዘመናቸው ሳሉ ሻምበል ጉታ ደቡብ አፍሪካ ድረስ ሄደው እንዲያገኙዋቸው ማድረግን ሁሉ ይጠይቃል።ጉዳዩ የደህንነት ሚስጥር የነበረ በመሆኑ በወቅቱ ግድያውን ሊፈፅም የሞከረው አካል ወይንም ሀገር (ማንነቱን ሻምበል ጉታ አልገለፁም (የተባረሩት ዜጎች የየት ሀገር እንደነበሩ አልገለፁም) ዛሬ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ለሚኖረው ግንኙነት ጥላ እንዳያጠላ ስጋት ስለሚሆን ዜናው በተፈለገው ደረጃ ለዓለም ሕዝብ እንዳይደርስ የሚደረጉ ስውር ስራዎች እንደማይጠፋ ማጤን ሌላው ሥራ ሊሆን ይችላል።
በመጨረሻም ሻምበል ጉታ ዲንቃ ለሕዝብ ወጥተው ዛሬ ላይ ምንም ምስጢርነት የሌለውን ጉዳይ ለሕዝብ በመንገራቸው ሊመሰገኑ ይገባል።