Wednesday, October 16, 2013

ሁላችንም ለእውነተኛ ትግል መስዋዕት ለመሆን እራሳችንን ማነሳሳት ይጠበቅብናል::

Oktober 16/2013
ከገዛኸኝ አበበ ኖርዌይ

ዛሬ ሀገራችን ኢትዮጵያ ካለችበት የኢህአዲግ ስርአት ለመላቀቅ እና ከገባችበት ፖለቲካዊ ማህበራዊ እና ኢኮኖሜያዊ ውድቀት ወጥታ ህዝቡም ከወያኔ ስርዓት ተላቋ ወደ ተሻለ እና ወደ ተረጋጋ ሕይወት ለመድረስ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ድርሻ መወጣት እና በሁሉም አቅጣጫ እና በሚችለው መንገድ መታገል ይጠበቅበታል:: ዛሬ ላይ ወያኔ ኢህአዲግ የእምነታችንን ነጻነት እያሳጣን የዜጎቻችን ሰብዓዊ መብት እየረገጠ እና የዜግነት ክብራችንን እና ነፃነታችንን በመግፈፈ የባርነት ኑሮ እየኖርን እንገኛለን::  ግን እስከ መቼ ብለን እራሳችንን ልንጠይቅ ያስፈልጋል::

 ይህንን ጨቆኝ እና ገዳይ ስርዓት በቃወም ለእምነታቸው ነጻነት ለዜጓች ሰብዓዊ መብት መከበር እየታገሉ  ያሉ ብዙ ወንድሞቻችን እና ህህቶቻችን  ለእንግልት ፥ ለእስር እና ለስቃይ ተዳርገዋል እስከ አሁን ድረሰ ደግሞ ባልሰሩት በደል በእስር ላይ የሚገኙ ወገኖቻችን በእየ እስር ቤቱ መስዋትን እየከፈሉ ይገኛሉ :: እውነታኛ ትግል መስዋትነትን የሚጠይቅ ሲሆነ  ሁላችንም ለዚህ ትግል በአንድነት በመተባበር መነሳሳት  ይጠበቅብናል ::  በአንድነት ተባብረን ከታገለን የኢትዮጵያን ትንሳዬ የምናይበት ቀን ሩቅ መስሎ አይታየኝም::

ይህን ትግል ለተወሰኖ ሰዎች እና ለተወሰኑ ፖለቲካ ፖርቲዎች የምንተወው ሳይሆን በማንኛውም መንገድ እና አቅጣጫ ትግሉን እያካሄዱ ያሉትን አብረን ከጓናቸው ልንቋም ትግሉን ልናቀጣጥለው እና በምንችለው መንገድ ልንደግፋቸው ይገባል ባይ ነኝ ::

  ዛሬ ላይ ወያኔ ኢህአዲግን እየተቃወሙ ያሉ የተቀዋሚ ፓርቲዎች ሁለት አይነት አመለካከት እና እምነት ይዘው ኢህአዲግን እየተፋለሙት ይገኛሉ:: በአንድ ወገን ትግላችንን በሰላማዊ መንገድ በማካሄድ ኢህአዲግን ማዳከም ማሽመድመድ  እና ማስወገድ ይቻላል የሚል ሲሆን በሌላው ወገን ያሉት ደግሞ ወያኔ ኢህአዲግን የምንለማመጥበት ዘመን አብቅቷል ወያኔ ክብር የማይወድለት ስለሆነ በትጥቅ ትግል በመደራጀት እና በመታገል ነው ኢህአዲግን ማስወገድያለብን  የሚል አመለካከት አላቸው :: ይህንንም እምነታቸውን እውን ለማድረግ  ሰላማዊን ትግል የሚያምኑት ይዘው የተነሱትን ዓላማ ላማስፈጸም በቆራጥነት በመነሳት በብዙ መንገድ እየሞከሩት እና ለሰላማዊ ትግል ህዝቦችን እያደራጁ  ይገኛሉ::  ነገር ግን ይህ የፓርቲዎች አካሄድ እና እያደረጉት ያሉት ሰላማዊ ትግል ለገዢው ፓርቲ ለኢህአድግ የተዋጠለት አይመስልም::  ብቻውን በአንባ ገነንነት እና በማን አለኝነት ህዝብና በሀይል  እና በጉልበት መግዛት የለመደ ስለሆነ ለዚህ ለሰላማዊ ትግል የተነሱትን የፖለቲካ ፓርቲዎች ሃይላቸውን ለማዳከም ንብረታቸውን በማውደም መሪዎቻቸውን እና አባሎቻቸውን በማሰር ዋጋ እያስከፈላቸው ይገኛል:: እያየነው ያለውም ይህንኑ ነው  ባለፈው ጊዜ የሰማያዊው ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ወያኔ ኢህአዲግ እያደረሰባቸው ስላለው ግፍ እና ጫና ሲናገሩ የትኛውንም አይነት መስዋዕት ልንከፍል ዝግጁ ነን  ነበር ያሉት  ኢንጅነሩ ሲናገሩ እስከ ህይወት መስዋዕትነት ልንከፍል እንችላለን ከትግላችን ግን የሚያቆመን የለም ብለዋል::  በርግጥ ማንኛውም ትግል መስዋዕትነት ይጠይቃል:: በቆራጥነት እና በጽናት ከታገልን ግን የተከፈለውን ያህል መስዋዕት ተከፍሎ ለውጥን ማምጣቱ አይቀርምና ::

በሌላው ወገን ያሉት ደግሞ ወያኔ ኢህአዲግን የምንለማመጥበት ዘመን አብቅቷል ወያኔ ክብር የማይወድለት ስለሆነ በትጥቅ ትግል በመደራጀት መታገል አለብን የሚል እምነት ይዘው በሚችሉት መንገድ ሁሉ መስዋዕትን ለመክፈል ቆርጠው የተነሱትን ቆራጦች በየአቅጣጫው ለዓላመቸው መስዋትነትን እየከፈሉ ሲገኙ ሕይወታቸውንም መስዕዋት ለማድረግ መነሳታቸውን በቆራጥነት እየወጁ እንደሆነ እናውቃለን::  ወያኔን ለማስወገድ በሁሉም አቅጣጫ የምናደርገው ጉዙ እና ትግል ቀላል የማይሆን መስዋዕት የሚያስከፍልም ቢሆን በእውነትእና በቁርጠኝነት ከታግለን ኢትዮጵያን ከዚህ አስከፊ ስርዓት ነፃ የምናወጣበት ቀን ቅርብ ነው::  ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ደግሞ ለዘመናት ሲገዛን ፣ ሲጨቁነን እና ሲያሰቃየን የነበረውን ይህን ዘረኛ መንግስት ይበቀኻል በቃህ ብለን በእውነት ከእነዚህ ፓርቲዎች ጓን በመቆም እና በመሰለፍ ለእውነተኛ ትግል እራሳችንን ማነሳሳት  ይጠበቅብናል :: ጌዚያችንን መስዋዕት፣ ገንዘባችንን መስዕዋት ፣ዕውቀታችንን መስዋዕት ፣ ለማድረግ ቆርጠን እንነሳ:: ከእነዚህ ፓርቲዎች ጎን እንቁም ትግሉንም እንቀላቀል::

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ 

ለአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ፍትሕ አይቀሬ ናት

October 16, 2013

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ
ማስታወሻ ለአንባቢው፡፡ ባለፈው ሳምንት ሐተታዬ ‹‹የዘር አደን›› በሚል አሉባልታዊ ክስ  የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በተሰነዘረበት ክስ ደግፌው ተሟግቼለታለሁ፡፡ በዚህም ሳምንት ድጋፌን በመቀጠል እነዚህ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች የፈጠሙትን ግፍና በደል ጭቆና በመዘርዘር ራሳቸውን ነጻ በማድረግ የአይ ሲ ሲን (የኣለም ወንጀለኛ ፍርድ ቤት) ስም በማብጠልጠልና የቆመለትን ዓላማ የሳተ በማስመሰል ገዢዎችና አስፈጻሚዎ ቡችሎቻቸው ያነሱዋቸውን ማስረጃ ቢስ ውንጀላዎች በተጨባጭ ማስረጃ ድርጊቶታቸውንና ሸፍጣቸውን ይፋ ለማድረግ ወስኛለሁ፡፡ የኦክቶበር 11-12, 2013 የአፍሪካ አንድነት ‹‹መሪዎች›› የጨረባ ስብሰባ የተጠራውም ቴአትራዊ የልብ ወለድ ሴራ ለማካሄድና ነጻ ለመምሰል የሚያስችላቸውን ቅጥፈት ለማናፈስ ነው፡፡international criminal court
በኔ እምነት አይ ሲ ሲ የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ሕግጋት ትክክለኛውና ጠንካራው ምልክት ነው፡፡ አይ ሲ ሲ ላለፉት ጥቂት ዓመታት ስራውን በማከናወን ላይ ነው፡፡እስካሁን ያስመዘገባቸው ውጤቶች ጥቂት ቢሆኑም ለወደፊቱ ግን ያሻቸውን በደልና ግፍ ፈጥመው ግድያና አስገድዶ መድፈርን ሰብአዊ መብት በደልን አዘው በማስፈጸም በሥልጣናቸውም አላግባብ ባልገውና ተጠቅመው፤ ሃገርን አራዉተው፤ ሕዝብን በበደልና ግፍ ጫና አጉብጠውና አንበርክከው፤ በነጻ ሲቀመጡና ሲንደላቀቁ የነበሩትን እያጋለጠ ለፍርድ ለማቅረብ የሚችል ጠንካራ ተቋም እንደሚሆን እምነቴ ነው፡፡  የአፍሪካ ጨቋኝና የግፍ በደል ባለቤት የሆኑት ገዢዎች በሕዝቡ ላይ ሊኩራሩና ሊደነፉ፤ የሕግ የበላይነትን በመጨፍለቅ ሊቀጥሉ ይጥሩ ይሆናል፤ አሁን ግን አይ ሲ ሲ ስለመጣባቸውና ለሕዝቡ ወግኖ ስለቆመ ስሙ በተጠራ ጊዜ እየተርበደበዱና መግቢያ እያጡ በመሄዳቸው የአይ ሲ ሲን ስም በማጉደፍ ነጻ ለመሆን ቢጥሩ መንገድ ሁሉ፤ በደላቸው ሁሉ፤ ግፋቸው ሁሉ አይ ሲ ሲን እየቀሰቀሰባቸው በመሆኑ ኦክቶበር 13 2013 የቁም ተዝካራቸው ማውጫ አድርገው ሊሰባሰቡ ነው፡፡
በኦክቶበር 11-12,  2013 አድመኞቹ የአፍሪካ ‹‹መሪዎች›› አስተጋቢው የእንግዳ መቀበያ የአፍሪካ አዳራሽ በመሰባሰብ አብዛኛዎቹ በሮም ከጸደቀው ደንብ (አለም ኣቀፍ ዉል) በመውጣት በደስታ ተሞልተው የዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤትን የሞት ውሳኔ ያስተላልፋሉ፡፡ ቀብሩንም ለማስፈጸም የኢትዮጵያ የይስሙላ ጠቅላይ ሚኒስትርና የአፍሪካ  አንድነት ተዘዋዋሪ የ2013ቱ ሊቀመንበር ሃይለማርያም ደሳለኝ ነው፡፡ ስብሰባውንም ሲከፍት ‹‹ዛሬ በዚህ የምጽዋት አዳራሻችን የተሰባሰብነው አይ ሲ ሲን ለማወደስ ሳይሀሆን ልንቀብረው ነው….›› በማለት ይሆናል፡፡ የዚህ የቀብር ጥድፍም ሰበቡ የኬንያው ፕሬዜዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኬንያ በተካሄደው የ2007 ምርጫ ወቅት በፈጸመው የሰብአዊ መብት ግፍ ለመጠየቅ ኖቬምበር 12 2013 ለፍርድ ሊቀርብ በመሆኑ ነው፡፡ በተመሳሳይ ወንጀልም ምክትሉ ዊሊያም ሩቶ ፍርዱ በሄይግ የዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ መታየት ከጀመረ ሁለተኛ ወሩ ነው፡፡ የአፍሪካ አንድነት በኬንያታ እና በሩቶ ላይ የተመሰረተውን ክስ ዘዴ ፈልጎ ካላነሳ በስተቀር ‹‹የኑክሊየር ፈንጂ መቃወሚያውን›› በመጠቀም ከአይ ሲ ሲ አባልነት ለመውጣት እንደሚችልም በማስፈራራት ላይ ነው፡፡
ላለፉት ጥቂት ወራት ሃይለማርያም በአይ ሲ ሲ ላይ የቃል ጦርነት ሲያካሂድ ነበር፡፡ ባለፈው ግንቦት የጃጀዉና በቅዠት ዓለም ያለው ሮበርት ሙጋቤን በመደገፍ በአይ ሲ ሲ ላይ ውንጀላ አካሂዷል፡፡ ግልጽና ማስረጃው ከመጠን ያለፈውን ግፍ ለፈጸመ የአፍሪካ ገዢ ጥብቅና መቆምና ሕዝብን ለባሰ ግፍ ማብቃት የሃይለማርያም የአፍሪካ ወቅታዊ ሊቀመንበርነት ተግባር ሆኗል፡፡ ሃይለማርያም ቃላትን በማሰባሰብና ከጀርባ ባሉት ሽነቋጭ አለቆቹ በመመራት ግራ የገባውን አባባል በመጠቀም አይ ሲ ሲ ‹‹99 በመቶ›› የሆኑት በደለኛ ተከሳሾች አፍሪካውያን በመሆናቸው  የዘር አደን ላይ ነው የሚል መሰረተ ቢስ ወሬ እየነዛ ነው፡፡
ባለፈው ሳምንት በተካሄደው 68ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ስብሰባ ላይ ባሰማው ወሬው፤ አይ ሲ ሲ የኬንያታንና የሩቶን ክስ በማንሳት ጉዳዩ በኬንያ ባለስልጣናት እንዲታይ ማድረግ አለበት በማለት የማይገባ  የድፍረት ጥያቄ አንስቷል፡፡ ሆኖም ኬንያታ ከተሰነዘረበት ወንጀል ነጻ ሳያደርገው፤ ማድረግ ያሰበው ግን ኬንያታ ራሱ በሚያዘውና መመርያ በሚሰጠው ችሎት ይዳኝ ለማለት ነው፡፡ አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ ይይላሉ ሲተርቱ፡፡ ባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያና ናይጄርያ  ለአይ ሲ ሲ ይጋባኝ ሰሚ የኬንያው ክስ እንዲነሳ ያቀረቡትን የጽሁፍ ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል፡፡
ሃይለማርያም የዚህ ተቀባይነት የሌለው አሳፋሪ ጉዳይ አፈጉባኤ ሆኖ የመገኘቱ ምጸታዊ መነሾ አስገራሚ ነው፡፡ 34 የአፍሪካ ሃገራት የሮምን ደንብ/ዉል የፈረሙበት ሲሆን (አይ ሲ ሲ ሰን በማቋቋም ወንጀሎችን በመመርመር ሰብአዊ መብት ጥሰትን የዘር ጭፍጨፋን ግፍ በማጥራት ለፍርድ እንዲያቀርብ ውክልናና ስልጣን ሰጥቶታል):: እስከሁንም ኢትዮጵያ የዚህ ሕግ አባል ለመሆን ፊርማዋን ነፍጋ ቆይታለች፡፡ የሃይለማርያም የሥላጣን አባት ይህን ሕገ ደምብ ላለመፈረም ወስኖ ያቆየው ምናልባትስ አይ ሲ ሲ እንደማይለቀውና ወንጀሉን አጥርቶ እንደሚፋረደው ተገንዝቦ ይሆን? ለፊርማውም ችግር የሆነበት ሰበብ ሕጉን ፈርሞ ከተቀበለው የፊርማው ቀለም ሳይደረቅ በሰራቸው ሕገ ወጥ ተግባራት በፈጃቸውና ባስፈጃቸው ንጹኃን ዜጎች ሳቢያ አይ ሲ ሲ በሩን እንደሚያንኳኳና ለሕግ እንደሚያቀርበው ጠንቅቆ በመረዳቱ ነው?  እነዚያስ 34 ሃገራት ሕጉን አጽድቀው አይ ሲ ሲን ሲያቋቁሙ አይ ሲ ሲ የአፍሪካ ጋሻ መከታ ሆኖ ወንጀለኞችን አላንዳች አድልዎ እያደነ ለፍርድ እንደሚያቀርባቸው አልተገነዘቡትም ነበር?
አይ ሲ ሲን በአፍሪካ አለሳልሶ የመግደል ጥበብ የሃይለማርያም ተንኳሽና የሚያስቆጣው ክሱ የሚያሳየው፤ አይ ሲ ሲን ከአፍሪካ በድል በማስወጣት እራሱን ‹‹ጭራቅ
ገዳዩ ጀግና›› ላመሰኘት የተነሳሳ መስላል፡፡ (የሱ ቀደምት የሥልጣን አባቱም ‹‹የአዲሱ ትውልድ አፍሪካዊ መሪ›› በሚል መጠርያ ለራሱ የፈረስ ስም ሰጥቶ፤ ታላቅ በመሆን በሽታ ተለክፎ ለማይለቅና ለማይድን እጀሰብ ተዳርጎ ነበር::) የነገሩ እውነታ መሰርት ግን በዚህ አካሄድ የሃይለማርያምና የጸረመስቀል ተዋጊዎቹ አካሄድ በኬንያዊያን ባለስልጣናት ላይ የተመሰረተውን ክስ ለማስነሳት፤ በብዛት ከአይሲ ሲ አባልነት መውጣትን እንደማስፈራሪያና ማገቻ በማድረግ ወንድሞቹን ኬንያታንና ሩቶን ከአይ ሲ ሲ ማነቆ በማላቀቅ፤ ወደፊት በእነሱ ላይ ሊደርስ የማይችለውን አይቀሬውን ህጋዊ የክስ እርምጃ አስቀድሞ ለመዝጋት የሚያደርገው የአልሞት ባይ ተጋዳይ የሕልም ሩጫ ነው፡፡ አፍሪካን በሚገባት ከፍተኛ የአመራር ስልጣን ላይ ላመስቀመጥ የሚጥረውን አይ ሲ ሲን ለማጥፋት ከንቱ ጥረት ከማድረግ ይልቅ ሃይለማርያምና መሰል ግፈኛ ገዢዎች ራሳቸውን ከግፍ ባህሪና ልምዳቸው በመመለስ እንደሰው በማሰብ ለሰብአዊ ፍጡራን ተገቢውን አገልግሎት ለማከናወን ቢተጉ ይበጃቸዋል፡፡
በኦክቶበር 11-12 2013 በአፈሪካ አንድነት ስለ አይ   ቀብር ስለሚደረገው ንግግር ቅድመ ትርኢት
የአፍሪካ ‹‹ገዢዎች›› በኦክቶበር 11-12 2013 በአፍሪካ አንድነት በሚሰባሰቡበት ጊዜ ስለሚያካሂዱት እብደት ቀረሽ ጸረ አይ ሲ ሲ  ዘመቻ በቂ ግንዛቤ አለን፡፡ የንግግራቸው መነሾና አካሄድየ አይ ሲ ሲን ወኔ ለመገድልና ተግባሩን ለማገድ አስቀድሞ ንድፉ በአምባሳደር ቋሚ ተወካይ ማቻሪያ ካማው፤ በኬንያ በተባበሩት መንግስታታ ቋሚ ሚሲዮን በኩል ለአምባሳደር ሜናንካዶ (የሴኪውሪቲ ካውንስል የሜይ ወር 2013 ሊቀመንበር) በተዘጋጀው ባለ 13 ገጽ ሚስጥራዊ ሰነድ ተዘርዝሯል፡፡
1. መላ የሌለውና ቅጥ ያጣ እርማት የተካሄደበት የካማው ሚስጥራዊ ሰነድ፤
ኬንያታን ሩቶ ከአይ ሲ ሲ ማነቆ ሊላቀቁ ይገባል ምክንያቱም እነሱን ለክስ ማቅረብ የኬንያን ልኡላዊነት ነጻነት የሚጥስ ነው፡፡ እንደ ካማው አባባል ‹‹የኬንያታና የሩቶ ክስ ራሱን ለሚያስተዳድረው መንግስታችን በውስጥ ጉዳያችንና በሃገራችን ኬንያና በልኡላዊነታችን ላይ የተቃጣ ውርደት ነው በማለት ይከራከራል፡፡ የኬንያ ልኡላዊነት ከኬንያ ውስጥና ውጭ የተለያዩ ተዋንያንን በመጠቀም ለወቀሳ እየተዳረግን ነው፡፡እንዳለፈውና እንደተለመደው የሲቪሉን ማህበረሰብ በማነሳሳት የራሱን ፖሊሲ እንዲቃወም በመደረግ የሮምን ስምምነት ሰበብ በማድረግ አይሲሲን በአስፈጻሚነት እየተጠቀሙበት ነው፡፡›› ነጻነት ለአፍሪካውያን ጨካኝና አረመኔ ገዢዎች የመጀመርያው ስደተኛ ነው፡፡ አሁን የአፍሪካን ነጻነት ለማስከበር በማለት የሚንደፋደፉት አስመሳይ የአፍሪካ ጨቋኞች በኖቬምበር 2010 ምርጫ ወቅት ፈረንሳይ በቀጥታ በአይቮሪኮስት ግጭት ጣልቃ በገባችበት ወቅት፤ ገዳም እንደገባች አይጥ ተሸጉጠው ትንፍሽ ሳይሉ ፈረንሳይ የቀድሞ ቅኝ ግዛቷን መልሳ ስተወር አንዲት ቃል አልተነፈሱም፡፡ የአፍሪካ አንድነትም ቢሆን በዝምታ ተቀምጦ ጠበይ ተመልካች በመሆን ከጎን ሆኖ ከመመልከት አላለፈም፡፡ በጃንዋሪ 2013 ፈረንሳይ የሰሜን ማሊን ከሽብርተኞች ወረራ ነጻ ለማውጣት ጣልቃ ሲገባ የአፍሪካ መሪዎች የፈረንሳይን ጦር ለማስወጣት የነጻነትንና የልእልና ማስከበርን ጉዳይ አላነሱም፡፡ አሁንም እንደገና የአፍሪካ አንድነት ከተመልካችነት አላለፈም፡፡
በወንጀል ፤ በሰብአዊ መብት ጥሰት፤በጦር ወንጀለኛነት፤በዘር ማጥፋት ለሚሰነዘር ክስ ሉአላዊነት ሕጋዊ መከላከያ አለያም የፖለቲካ ውይይት ሁኖ አይቆምም፡፡ አሁን በአፍሪካ ፈላጭ ቆርጫ ገዢዎች የሚነሳው የሉአላዊነት ጥያቄ አይ ሲ ሲ የተጣለበትን አደራ ላማዘናገት ሆን ተብሎ የተነሳና ቀድሞ ከነበሩት የንጉሳዊ ገዢዎች በምድራዊ ዳኝነት እንጠየቅም ሥዩመ እግዚአብሔር ነን እንደሚሉት ለመሆን የታቀደ ዘዴ ነው፡፡ ሕገ ወጥ የሆነውን የአፍሪቃ ፈላጭ ቆራጭ ገዢ ሊዳኘው የሚገባውና የሚችለው ሌላው ሕገወጥ አፍሪካዊ ገዢ መሆን አለበት ነው የሚሉት፡፡
2.      ኬንያታና ሩቶ ከክስ ነጻ የመሆን መብት አላቸው ምክንያቱም በማርች 2013ቱ ምርጫ ‹‹ንጹህ›› ናቸው ስለተባሉ፤ካማው ኬንያታና ሩቶን በተመለከተ ሁለቱ ሰዎች ንጹሃን ብቻ ሳይሆኑ በክፍተኛው የመንግስት ስልጣን ላይ ስለተቀመጡ ሃለፊነትም አለባቸውና ክሱ ሊሰረዝላቸው ይገባል በማለት ይሞግታል፡፡ አይ ሲ ሲ የከፈተው የክስ
መዝገብ የሚዘጋበት ምክንያት ኬንታና ሩቶ የፈጸሙት የሰብአዊ መብት ድፍረትና ጥሰት በፍትህ አደባባይ ቆሞ ስለሚመሰክርባቸውና ለፍርድ ሊያቀርባቸው ስለሚችል የንጹሃን ግፍና በደል በነሱ የስልጣን ወንበር መያዝ ተቻችሎ ነጻ ሊሆኑ ይገባል ነው፡፡  እነዚህ ሁለት ዋናና ምክትል ገዢዎች የኬንያውያን ሁሉ መተሳሰርያ በመሆናቸውና ሕዝቡም በፍቅር ስለመረጣቸው፤ 86 በመቶ ድምጹን ሰጥቶ መንበራቸው ላይ ስላስቀመጣቸው ክሱ ሊሰረዝላቸው ግድ ነው፡፡ ካሙ ክርክሩን በመቀጠል፤ የሮሙ
ስምምነት ኬንያታንና ሩቶ ሊያካትት አይገባም፤ምክንያቱም በአሁኑ ጊዜ ከፍተኛውን የሃገሪቱን አመራር በዋናነትና በምክትልነት የያዙ በመሆናቸውና የኬንያ ሪፑብሊክ የመከላከያ አዘዦች በመሆናቸው፤ነው ይለናል፡፡ ካሙንን ግራ ያጋበው ነገር ኬንያታና ሩቶ ንፁህነታቸውን ለማረጋገጥ መመረጥ አያስፈልጋቸውም፡፡ ማንም ሰው ቢሆን በፍርድ ሸንጎ ወንጀለኛ እስካልተባለ ድረስ ንጹህ ነውና፡፡ ስለዚህም በተጠረጠሩበት ወንጀል ኣይ ሲ ሲ የሚለው ችሎት ፊት ቀርበው ንጸህናቸውን በነጻ የፍትሕ ስርአት ያረጋግጡ ነው እንጂ ወንጀለኞች ናቸው ብሎ አልደመደመም፡፡ የሁለቱ ባለስልጣናት በአጥጋቢ ውጤት ከመመረጣቸው ጋር የተሰነዘረባቸው ተጠርጣሪነት አንዳችም ግንኙነት የለውም፡፡ ጥያቄው በ2007-08 በስልጣን ላይ በነበሩበት ግዜ ተፈፀሙ በተባሉ ወንጀሎች ነው፡፡ ኬንያታና ሩቶ የሃገሪቱ መሪዎች መሆናቸው ከሕጉ ጋር የሚያገናኘው ሰበብ የለውም፡፡ የሮም ስምምነት አንቀጽ 27 ማንኛውም ተጠርጣሪ አይሲሲ ችሎት ቀርቦ ንጽህናውን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል ይላል፡፡ ስምምነቱ ማንንም በእኩል ደረጃ ይመለከታል፡፡ ማንንም ከማንም በስልጣን ደረጃ አያመዛዝንም ለአይ ሲ ሲ ምንኛውም ተጠርጣሪ እኩል ነው፡፡ ተመራጭ ፕሬዝዳንትም ይሁን የፓርላማ አባል የመግስት ባለስልጣንም ሆነ ተራ ዜጋ ለአይ ሲ ሲ ችሎትና መመርያ ሁሉም እኩል ናቸው፡፡
በኬንያታና በሩቶ ላይ የተመሰረተው ስንኩል ክስ (የተባበሩት መንግሥታት ሴኩሪቲ ካውንስልና በኬንያም መንግሥት ወንጀል መስራታቸው ሳይተላለፍለት ነው) በአግባቡ ምርመራና ማጣራት ሳይካሄድበት ነው ይላሉ፡፡ የአይ ሲ ሲ ክስ ተቀባይነት የሌለው ምስክሮቹንም አስጠንተው ያቀረቧቸው ናቸው፡፡ ተጠቂ ነን ብለው የቀረቡትም ሃሰተኞች አለያም ተመርጠው የተሰየሙ ናችው፡፡ የምስክርነት ቃላቸውም ደካማና የማያሳምን ነው፡ በማለት ካሙ ይከራከርላቸዋል፡፡ ምስክሮች  በመደለያ የተገዙ ያንንም ነው አይደለም ብሎ የሚወስነው የአይ ሲ ሲ ችሎት ነው፡፡ ምናልባትም ምስክሮቹ ተአማኒነት የሌላቸው በጥቅማ ጥቅም የተገዙ ናቸው የሚባልም ከሆነ የካሙስ መንግስት ማስረጃውን በማቅረብ ሊቃወም ይችላል፡፡
4.      የአቃቤ ሕግ ቢሮ ሚዛናዊ ባልሆነ መልኩ በኬንያታና በሩቶ ላይ የክስ ምስረታውን ተከሳሾቹን በሚጎዳ መልኩ እያካሄድ ነው ለፍትሕ በእኩል መልኩ የተከናወነ አይደለም በማለት ተጠርጣሪዎቹን ተከሳሾች ፍትሕ በአግባቡ ነጻ ናቸው አይደሉም ከማለቱ ይልቅ አይ ሲ ሲንና የአቃቤሕግ ቢሮን በሃሰት በመወንጀልና ፍትሕ ገደል ይግባ ለኛ በሚመቸን መልኩ የማይሰራም አይ ሲ ሲ ፍርስርሱ ይውጣ የሚል ነው የካማው ቅጥ ያጣ ሙግት፡፡ ፍትሕ ለመዛባቱ የካማው መንግስት ማስረጃ ካለውና በፊትም ሆነ አሁን ኬንያታንና ሩቶን ፍትሕ ይነፍጋቸዋል ብሎ ካሰበ ወደ ፍርዱ መድረክ በማቅረብ ሕዝብ እንዲያውቀው ሊያደርግ ይገባዋል፡፡ በተቃራኒው ካማውና የአፍሪካ መሪዎች ሊያደርጉና ለማድረግም በመጣር ላይ ያሉት አንዳችም እውነትነት የሌለው የክስ ዳውላ በመዘርገፍና እርፍት የለሽ የድረሱልን ጥሪ በማሰማት ዓለምን ሊያሳምኑ በመጣር ላይ ናቸው፡፡ እውነት ካላቸው እነካማው አለን የሚሉትን የፍትህ ግድፈት አደባባይ ያውጡት፡፡
5. አይ ሲ ሲና የአቃቤው ሕግ ቢሮ ማንም የማይቆጣጠረውና ከሕግ ውጪ ለማንም ተጠያቂ ያልሆነ ባለሥልጣን ነው ለመጀመርያ ጊዜ ቋሚ ዓለም አቀፋዊ ተቋም የሃገራትንና የዜጎቿን ሕጋዊ ግዴታ ለመመልከትና ለመወሰን ወንጀልም ሲያገኝባቸው በአግባቡና በስርአት ቅጣት ለመጣል ተመስርቷል፡፡ አይ ሲ ሲ ብቃቱን በተመለከተ በማንኛውም መልኩ ለዓለም አቀፍ ሕግጋት ምን እንደሚያስፈልገው ሲረዳ የመከራከሪያው የመጨረሻ ቃላት አይ ሲ ሲ ሲወስን በማንኛውም መንግስት ቁጥጥር ስር አለያም ትእዛዝ ሳይሆን ዓለም አቀፍ ሕግጋት በሚመሩበት ስርአት ብቻ መሆኑን ነው፡፡ ካሙ የሚያውቀውና የሚለውም ሆነ አይ ሲ ሲ ያድርግ የሚለው አለቆቹ በሚወነጀሉበት ጥፋታቸው ሁሉ አስቀድሞ እነሱ የሚያዙት ችሎታቸው ጉዳዩን ይመርምር ነው፡፡ የሚያውቀውና የሚከተለው አሁን ምርመር ይደረግባቸው የተባሉት አለቆቹ ሲያስሩ ሲገድሉ ሲያሰቃዩ ፍርድ አልነካቸውምና አሁን እንዳይነካቸው ይደረግ ነው፡፡ ካሙ ችግሩና በሽታው አለቆቹ የሚመሩበት ያልተጻፈ ሕግና ያልተሰጣቸውን ስልጣን መጠቀም ስለሆነ በዚያው መሰረት ይዳኙ ነው፡፡ አይ ሲ ሲ የሚታዘዘውም ሆነ የሚመራው በዓለም አቀፉ የፍትሕ ስርአት ነውና ማንንም አይጠላም ማንንም ከማንም አስበልጦ አያፈቅርም፡፡ ካሙ ለምን አንድ አቃቤ ሕግ ብቻውን ያጣራው ጉዳይ ተቀባይነት ያገኛል ነው፡፡ አይ ሲ ሲ ደግሞ አቃቤ ሕግ ግድፈት አለበት የሚል ማንኛውም ተጠርጣሪ አለያም ዜጋ መስረጃውን አቅርቦ ሊሞግተው ይችላል ነው፡፡
የአፍሪካን ዲክታተሮችና ጭፍሮቻቸው ስለ ‹‹ቁጥጥር አልባ ሥልጣን›› ሲያወሩ ማዳመጥ የአዞ እንባ እንዲሉ አይነት ነው፡፡ የኬንያን ባለስልጣነት መጠን የለሽ የስልጣን ክልል በመጠኑም ቢሆን ለመቆጣጠር ያስቻለው በ2010 የወጣው ሕገመንግስት ነው፡፡ በኬንያ ስርአት አልበኝነትን ሕገወጥነትን ለመከላከል ሲባል የወጣው አዲሱ ሕገመንግስት  ነው መሰረት የጣለው፡፡ ማንም ሊረዳው የሚገባው አዲሱ የኬንያ ሕገመንግስት በ2007 በተከሰተው የምርጫ ውዝግብ ሳቢያ በተካሄደው ውይይት ላይ ተመስርቶ መረቀቁና መጽደቁ ነው፡፡ ኬንያታና ሩቶ በዚያው ሕገመንስት ደንብና ስርአት  ውስጥ በተካተተው መመርያ መሰረት ነው ለፍርድም ሊቀርቡ ማዘዣ የወጣባቸው፡፡
በአፍሪካ የሕግ የበላይነት እነ ካማው መሰረተ ቢስ የሆኑ በርካታ ጥያቄዎችን በማንሳት ሕዝብንና መንግስታትን በማታለልና መንገድ በማሳት አለቆቻቸውን ነጣ ለማድረግ ይጥራሉ፡፡ እነ ሃይለማርያም ደሳለኝ የአይ ሲ ሲ አካሄድ ማንም ግፈኛና ወንጀለኛ ከነጉድፉ ተሸሽጎ እነዳይኖርና ግፍና በደሉን በማር ቀብቶ ለማስመሰያነት እንዳዋለ እንዳይኖር  የማድረግ ስልጣኑ ማነህ ባለሳምንት ይለናል በማለት አስቀድመው ለራሳቸው የሚጠቅም ከለላ ለመፍጠር ነው ጥረታቸው፡፡ የዓለም ሕግ ተፋለሰ ሲሉ እስከ ዛሬ ድረስ እነዚህ የኡኡታ አሰሚዎች የፈጸሙትን የሕግ መፋለስ በመዘንጋት ሳይሆን አውቀው ትክክለኛ መስለው ለመታየት እንጂ በአይ ሲ ሲ አካሄድ የተፋለሰ አንዳችም ሕግ የለም፡፡ አለ ከተባለ ደግሞ ከነማስረጃው ማቅረብ እንጂ ከንቱ የጋጋኖ ጨኸት የትም አያደርስም፡፡ የአፍሪካ አንድነት ደንብም ቢሆን በአፍሪካ ውስጥ ሰብአዊ መብት ሊከበርና ሊጠበቅ እንደሚገባው ይደንግጋል፡፡ ስለመልካም አስተዳደርም በደንቡ ላይ አስፈሯል፡፡ ማንም ከወንጀል ነጻ ሊሆን እንደማይችል ደንቡ ያናገራል፡፡
በኦክቶበር 13 ለቁጥር የሚጣክቱት መሪዎች ከሮሙ ስምምነት ለመውጣት ማሴር ማለት ሕግ አልበኝነትና የራሳቸው የአፍሪካ አንድነት የሚተዳደርበትን ደንብ መጣስ መሆኑን መዘንጋት ነው፡፡ ተጠያቂነትን ያወጁ ሃገራት ተጠየቁ ሲባሉ ሕጉን ያወጣነው ሕዝብን ለመቅጣት እንጂ እኛ ልንጠየቅበት አይደለም ማለት ምን የሚሉት፡፡ በጣም ቀላል የሆነና የማይቀር ምርጫ አለን፡፡እነዚህን በአፍሪካ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ሆነው ግፍን በመፈጸምና ሃላፊነትን አላግባብ በሚጠቀሙ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ከሮም ውልና ስምምነት የመውጣት አድማቸው ላይ አቋም በመያዝ መመጎት ቢያንስ  የነዚህን እኩዮች አድማ የሚቃወሙትን ተቆርቋሪ ወገኖች ማገዝ ነው፡፡ ለዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት መቆምና መወገን ማለት አፍሪካ ውስጥ በመግዛትና ግፍ በመፈጸም ያሉትና ባለስልጣናት መሞገት ነውና አብረን ሆነን ከአፍሪካ ጫንቃ ላይ እንዚህን ጋሬጣዎች እንንቀስ! አይ ሲ ሲን የመደገፊያው ወቅት አሁን ነው::

አለማቀፍ ጠበቆች የኢትዮጵያን ባለስልጣናት ለፍርድ ለማቅረብ እንቅስቃሴ ጀመሩ

ጥቅምት (አምስት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-በወጣት አብዱላሂ ሁሴን አማካኝነት በኢትዮጵያ የኦጋዴን ክፍል የተፈጸመውን የጦር ወንጀልና የሰብአዊ መብት ጥሰት ፊልም የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም በስዊድን ቁጥር አንድ ቴሌቪዥን በትናንትናው እለት መቅረቡን ተከትሎ አለማቀፉ ጠበቆች ጉዳዩን ወደ አለማቀፍ ፍርድ ቤት ለመውሰድ እንቅስቃሴ ጀመረዋል።
ወጣት አብዱላሂ ለኢሳት እንደገለጸው ፊልሙ ከተላለፈ በሁዋላ ሚዲያዎች ሸፊ ሽፋን የሰጡት ሲሆን፣ ስቴላም የተባሉ የ አይ ሲ ጄ ጠበቃ ጉዳዩን ፍርድ ቤት እንደሚያቀርብ በሬዲዮ ይፋ አድርገዋል።
የስዊድን የጦር ወንጀል ኮሚሽን ፍርድ ቤትም ማስረጃዎችን በመመርመር ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ለመውሰድ ከወጣት አብዲ ጋራ ቀጠሮ ይዘዋል። ጠበቆቹ ጄኔቫ ካለው አይሲጄ ጋር  እና ከሌሎችም የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን ጉዳዩን ወደ አለማቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ለመውሰድ እንደሚሞክሩ ተናግሯል።
ትናንት በተላለፈው ፊልም ውስጥ ከዚህ በፊት በኢሳት ያልቀረቡ መረጃዎች መቅረባቸውን ወጣት አብዲ ገልጿል።
ልዩ ፖሊስ እየተባለ በሚጠራው ሀይል የተፈጸመ የዘር ማጥፋት ወንጀልን የሚያሳይ መረጃ መካተቱትን፣ የክልሉን ፕሬዚዳንት የተቸች አንዲት  ሴት በኦበነግ አባልነት ስትፈረጅ የሚያሳይ መረጃ ተካቶበታል ። የክልሉ ፖሊስ ሀላፊው በእስር ላይ የሚገኙትን ሴቶች በመድፈር ብዙ ህጻናት በእስር ቤት ውስጥ መወለዳቸውን በፖሊሶች በራሳቸው ሲነገር የሚያሳይ ፊልም መካተቱትን ወጣት አብዱላሂ ገልጿል።
ፊልሙ ” የዲክታተሮች እስረኞች” የሚል ርእስ ተሰጥቶታል።
ጉዳዩን በማስመልከት የአለማቀፍ የህግ ባለሙያዎች ኮሚሽን በእንግሊዝኛ ኢንተርናሽናል ኮሚሽን ኦፍ ጁሪስትስ  ኮሚሽነር የሆኑት ስቴላ ጋርደ ለኢሳት እንደገለጹት የወንጀሉን ፈጻሚዎች ወደ ፍርድ ለማቅርብ የሚችሉትን ሁሉ እንደሚጥሩ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የአለማቀፍ ወንጀል ( ICC) ፈራሚ አገር ባለመሆኑዋ ማስረጃውን በቀጥታ ለፍርድ ቤቱ መላክ እንደማይቻል የገለጹት ኪሚሽነር ጋርደ፣ ይሁን እንጅ ሰቆቃን ለመከላከል የተቋቋመው  ኮሚቴ ( Committe Against Torture) ፈራሚ አገር በመሆኑ ጉዳዩን በዚሁ በኩል ለመከታተል እና የስዊድን  ፖሊስ ምርመራ ጀምሮ እርምጃ ለመውሰድ  እንዲችሉ ጥረት እንደሚያደርጉ ለኢሳት ገልጸዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰብአዊ መብት ኮሚቴ እነዚህን ማስረጃዎች እንዲያገኙ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
የኖርዌይ የቴሌቪዥን ጣቢያም ፊልሙን በቅርቡ ያሰራጫል ተብሎ ይጠበቃል። ፊልሙ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ተተርጉሞ በተለያዩ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን ይቀርባል።
በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ መንግስት የሰጠው አስተያየት የለም።

Tuesday, October 15, 2013

ስንቱን አጣን! (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

October 14, 2013
 
Prof. Mesfin Woldemariamእንደኢትዮጵያ ባለ ኋላቀር አገር አገር ውስጥ መሠልጠን ብዙ ችግር አለበት፤ እኔ ራሴ በኮምፒዩተር መጻፍ ከጀመርሁ ሠላሳ ዓመት ሊሆነኝ ነው፤ ታዲያ መብራት ጠፋና የምሠራው ባጣ የቆዩ ወረቀቶችን ሳገላብጥ አንድ እአአ በዲሴምበር 26 1965 ከዱሮ ተማሪዬ የተጻፈልኝን ደብዳቤ አገኘሁ፤ በዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በነበረ ከአንድ በጣም ጎበዝ ወጣት የተላከልኝ ነበረ፤ ከተመረቀ በኋላ በአንድ ኩባንያ ውስጥ ተቀጥሮ ለጥቂት ዓመታት ሠርቶ ትምህርቱን ለመቀጠል ወደአሜሪካ ሄዶ በሎዝ አንጄለስ አካባቢ ከሚገኝ ትምህርት ቤት ገብቶ ነበር፤ ደብዳቤውን የጻፈልኝ ከዚያ ነው፤ ደብዳቤው ሰባት ገጾች አሉት፤ ከሰባቱ ገጾች አምስቱ ስለኢትዮጵያ ያለውን ስጋት የሚገልጽ ነው፤ በሎዝ አንጀለስ አካባቢ ካሉ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት በሚያደርግበት ጊዜ ሁሉ ብዙዎቹ የሚያሳዩት የመንደረኛነት ስሜት እያበሳጨው የተማሩት ሰዎች በእንደዚህ ያለ ማኅበረሰባዊ ኋላቀርነት ውስጥ ሆነው ኢትዮጵያ የምትባለው አገር እንዴት መራመድ ትችላለች? እያለ ይሰጋ ነበር።
 
ደብዳቤውን ላቋርጥና ስለሰውየው ትንሽ ልናገር፤ ተማሪ ሆኖ ክፍል ውስጥ ምንም ነገር የማያሳልፍ በጣም ተከራካሪ ተማሪ ስለነበረ አደንቀው ነበር፤ አንድ ጊዜ እንዲያውም የዘውድ መንግሥት ደጋፊ ነኝ አልሁና አንዴት በትከሻው ላይ ጭንቅላት ያለው ሰው ዓመቱን በሙሉ የዘውድ አገዛዝ የሚያደርስብንን በደልና ችግር ሲነግረን ቆይቶ አሁን ደግሞ ያንን ደጋፊ ነኝ ይላል ብሎ ወረፈኝ፤ ልጁን ስለማውቀው አነጋገሩ አሳቀኝ እንጂ አላስቆጣኝም፤ ጥያቄህ ይገባኛል፤ ግን እኔን ሳትወርፈኝ መጠየቅ ትችል ነበር በዬ ቢቀበለውም ባይቀበለውም ለጥያቄው መልሱን ሰጠሁት፤ በኋላም ጥሩ ጓደኛዬ ነበር።

ከአሜሪካ ትምህርቱን ጨርሶ እንደመጣ ተገናኘንና ወደቀድሞ ሥራው ወደወንጂ ተመልሶ እንደሆነ ስጠይቀው ‹‹እንዴት ብዬ! ዕድሜ ልኬን የፈረንጅ አሽከር ሆኜ መኖር አልፈልግም፤ አሁን ደግሞ ያስተማረኝን ሕዝብ ላገልግል እንጂ!›› ነበር ያለኝ፤ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና በወንጂ ባሉት ደመወዞች መሀከል ከፍተኛ ልዩነት ነበረ፤ ቁም-ነገረኛነቱን፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያለውን ታማኝነት፣ የግል ጥቅሙን ቀንሶ ኢትዮጵያን ለመርዳት ባሳየው ተግባራዊ አርአያነት የማደንቀው የወታደር ልጅ ነው።

ይህ ሰው በደርግ ጊዜም አልሸሸም፤ በአንድ ኢንዱስትሪ ውስጥ በሥልጣን ቦታ ላይ ነበር፤ ወያኔ/ኢሕአዴግ ወንበሩን ሲይዝ እንደዚህ ያሉ ሰዎች የማይፈለጉ መሆናቸው ሲታወቅ አገሩን ጥሎ ተሰደደ፤ በትልቅ ዓለም-አቀፍ መሥሪያ ቤት ጥሩ ሥራ አግኝቶ ዕድሜው ለጡረታ እስቲደርስ ቆየ፤ ወደሚወዳት አገሩ ለመመለስ አልቻለም፤ ከአንድ የትምህርት ቤት ጓደኛው ጋር ግንኙነት እንዳለው አውቃለሁ፤ አንድ ቀን ስለዚሁ የጋራ ጓደኛችን ስናወራ ለምን ወደኢትዮጵያ እንደማይመለስ ጠየቅሁ።

የዚህ ወጣት አጎት በወታደርነት ኢትዮጵያን ለረጅም ጊዜ በክብር ያገላገለ ነው፤ ይህ ሰው ወያኔና ሻቢያ በተጣሉ ጊዜ ዜግነታቸው በጉልበት እየተገፈፈ ከአገራቸው እንዲወጡ ከተደረጉት ሰዎች አንዱ ነው፤ በዚያን ጊዜ በሌላ የኤርትራ ተወላጅ ላይ የተፈጸመውን ግፍ ራሱ ሰውዬው በአሜሪካ ድምጽ ራድዮ ሲናገር የሰማሁት የሚከተለውን ነው፤– ‹‹ለኢትዮጵያ በአለኝ ሁሉ አገልግያለሁ፤ ኢትዮጵያን ሳገለግል አንድ እግሬን አጥቻለሁ፤ አንድ ሰው ለአገሩ ከዚህ የበለጠ ምን ያደርጋል?›› ብሎ ሲናገር አስለቅሶኛል።

የኔ የቀድሞ ተማሪና ወዳጅም ለምን ወደኢትዮጵያ እንደማይመለስ ሲጠየቅ ‹‹ለጋሼ (ማለት ለአጎቱ) ያልሆነች ኢትዮጵያ ለእኔ አንዴት ትሆነኛለች? በማለት በጥያቄ መለሰ አሉ፤ አባቱ ያገለገላትን፣ አጎቱ የለፋላትን፣ አያት ቅድመ-አያቶች የሞቱላትንና የደሙላትን አገር እንዲህ በቀላሉ ማጣት ነፍስን ያቆስላል፤ የነዚያን ሰዎች ሁሉ መስዋእት ያከሽፋል፤ ያረክሰዋል፤ ይህንን የተገነዘቡና ያዘኑ፣ ያለቀሱ ሰዎች ናቸው –

እናት ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ፣
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ!

Sunday, October 13, 2013

ስብሃት ነጋ ወንጀል ፈፀሙ፤ በአሁን ሰአት በፖሊስ እየታደኑ ነው

October 13, 2013


በአሌክሳንደሪያ ቨርጂኒያ ከአንድ ሰአት በፊት ስብሃት ነጋና አብሯቸው የነበረ ግለሰብ በአንድ ኢትዮጲያዊ ላይ ከፍተኛ ድብደባ ፈፅመው ማምለጣቸውን ማረጋገጥ ተችሏል። መስፍንsebehat nega one of the founders of TPLF የተባለው ኢትዮጲያዊ በአሁኑ ሰአት በሆስፒታል የሚገኝ ሲሆን የሲቪሊቲ ሩም ፓልቶክ አዘጋጅ አባ መላ በስልክ አግኝቶት ስለሁኔታው ያነጋገረው ሲሆን፤ መስፍን እንደገለፀው በድብደባው ጅርባው እንደተጎዳና ብዙ ደም እንደፈሰሰው ገፆዋል። እነስብሃት ድብደባውን ሲፈፅሙ በቅርብ ርቀት ቪዲዮ እየተቀረፁ እንደነበረና ይህኑን ማስረጃ ለፖሊስ መስጠታቸው ታውቋል። ድርጊቱ ከተፈፀመ በኋላ ፖሊስ በአካባቢው ፈጥኖ የደረሰ ሲሆን፣ በአሁን ሰአት እነስብሃትን ለመያዝ ፖሊስ መሰማራቱ ታውቋል።




Friday, October 11, 2013

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ወደ ፖሊስ ጣብያ ተወሰዱ

October 11, 2013
 
በአሁኑ ወቅት በመነን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በቁጥጥር ስር የነበሩት የፓርቲ አመራሮች ወደ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ መወሰዳቸዉን አሁን የደረሰን መረጃ ይገልፃል፡፡
 
ጉዳዩ እንደዚህ ነው መንግስት ነኝ ባዩ በስራው ግን ከማፍያ ቡድን እምብዛም የማይለየው ህወሀት/ኢህአዴግ በተለየም የሰማያዊ ፓርቲ እና የአንድነት ፓርቲ አጠናክረው የቀጠሉት የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ ስጋት ውስጥ ጥሎታል።

“ሳይቃጠል በቅጠል” እንዲሉ ይህን ህዝብ ውስጥ በፍጥነት እየሰረጸ የመጣውን እንቅስቃሴ ድምጽ በሌለው መሳሪያ ለማዳከምና ብሎም ለማምከን ህወሀት/ኢህአዴግ እየተከተለ ያለው ስልት ቡድኑ ምን ያህል “የሞራል የበታችነት” እንደተላበሰ የሚያሳይ ነው።

የሰማያዊ ፓርቲ የካቲት 12(መነን) አካባቢ አዲስ የተከራየውን ጽህፈት ቤት ለመረከብ ጥቅምት 1/2006 ዓ.ም በቦታው ይገኛል። ይሁንና ቀድመው በቦታው የተገኙ የህወሀት/ኢህአዴግ ሰዎች ቤቱን እኛ ቀደም ብለን የተከራየነው ስለሆነ የሚገባው ለኛ ነው በማለት ወዝግብ ያነሳሉ… እንግዲህ አንባብያን እራሱን መንግስት ብሎ የሚጠራው ሀይል የሰፈር “ጢቦ” ሆኖ መጣ ማለት ነው…
ይህ በዚህ እንዳለ ነው አሁን በቅርቡ የክፍለ ከተማዉ ፍትህ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጌታሁን አማረ ፤ የወረዳዉ አስተዳደር ሃላፊዎች ፤- የወረዳ 3 ስራ አስፈፃሚ አቶ አማረ ቤካ ፤ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ አማረ አቡጤ ፤ መነን አካባቢ ፖሊሶች ፤ ፌደራል ፖሊሶች እና ሲቪል የለበሱ የደህንነት አካላት በጋራ በመሆን ኢንጅነር ይልቃልን ጨምሮ ሌሎች የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችችን ወደ ወደ መነን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወሰዷቸው።

የሰማያዊ ፓርቲ ሁኔታውን እንዲህ በማለት በፌስ-ቡክ ገጹ ላይ ጠቅሶታል፣
የኢህአዲግ አፈና በሰማያዊ አመራሮች እና አባላት ላይ ተጠናክሮ ቀጥሏል!!!

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ዉስጥ ለሰማያዊ ፓርቲ ጽህፈት ቤት ተከራይቶ የነበረዉን ቤት ከዛሬ ጥቅምት 1 2006 ጀምሮ ለመጠቀም በሄዱበት ጊዜ የክፍለ ከተማዉ ፍትህ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጌታሁን አማረ ፤ የወረዳዉ አስተዳደር ሃላፊዎች ፤- የወረዳ 3 ስራ አስፈፃሚ አቶ አማረ ቤካ ፤ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ አማረ አቡጤ ፤ መነን አካባቢ ፖሊሶች ፤ ፌደራል ፖሊሶች እና ሲቪል የለበሱ የደህንነት አካላት በጋራ በመሆን በማይመለከታቸዉ ጉዳይ የፓርቲዉን ከፍተኛ አመራሮች

1. ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት(ሊቀ መንበር)
2. አቶ ስለሺ ፈይሳ (ምክትል ሊቀመንበር)
3. አቶ ይድነቃቸዉ ከበደ (የህግ ጉዳይ ሃላፊ)
4. አቶ እንዳሻዉ እምሻዉ (የጽህፈት ቤት ሃላፊ)
5. አቶ በቃሉ አዳነ (ምክር ቤት አባል )
6. አቶ ዮናስ ከድር (የምክር ቤት አባል)
7. አቶ ብርሃኑ ተክለ-ያሬድ (አባል)
ወደ መነን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል፡፡ ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እንገልፃለን፡፡

Thursday, October 10, 2013

አያ ጅቦ ሳታመካኝ ብላኝ !!!

Oktober 10/2013

ኃይለማሪያም ደሳለኝ በአንድ ወቅት ዉሸትን የማያዉቅ ጠንካራ ክርሰቲያን ነዉ ተብሎ ሲነገርለት ሰምተን ነበር፤ ታድያ ይህ ሰዉ መለስን ሲተካ ብዙዎች በጥርስ የለሽ አንበሳነቱ ቢስማሙም ዉሸት እንደ ንጉስ በነገሰባት ኢትዮጵያ ዉስጥ ዉሸት የማያዉቅ መሪ መጣ መባሉ ብዙዎቻችንን ነጻነት የተገኘ ያክል አስደስቶን ነበር። ሆኖም ከወያኔ ጋር የዋለ ሰዉ እራሱን ሆኖ መክረም አይችልምና ኃይለማሪያምም ባስቀመጡት ቦታ የማይገኝ የሌላ መንደር ሰዉ ሆኖ ተገኘ። በዚህም የዜጎችን ተሰፋ አመከነ፤ ደስታቸውንም ወደ ኃዘንና ትካዜ ለወጠው።

ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ላይ በመገናኛ ብዙኋን ፊት ያየዉን አላየሁም፤ የሰማዉን አልሰማሁም፤ ያልሆነዉን ሆነ የሆነዉን ደግሞ አልሆነም እያለ ሽምጥጥ አደርጎ የካደዉ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፤ በእርግጥም ጎበዝ የመለስ ዜናዊ ተማሪ መሆኑን በተግባር አስመስክሯል። ኃይለማሪያም ባለፈዉ ዓርብ አንድ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶ ነበር። ይህ ግለሰብ በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫዉ ኢትዮጵያን ያክል ትልቅ አገር ከሚመራ ሰዉ ቀርቶ ከአንድ ተራ የቢሮ ተላላኪ እንኳን የማይጠበቅ መልስ ሲመልስ ተስተዉሏል።

ኃይለማሪያም በጋዜጣዊ መግለጫዉ ወቅት ከቀረቡለት ብዙ ዲሪቶ ጥያቄዎች ውስጥ አንዱ አገር ቤት ውስጥ እየተደረገ ያለው ሠላማዊ ሰልፍ ጉዳይ ነበር። ኃይለማሪያም አገር ቤት የሚደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች “በራሳቸው የሚደረጉ ሳይሆኑ ከኋላ ባሉ ሌሎች ኃይሎች መሪነት የሚደረጉ” ናቸው ሲል ተናግሯል። ኃይለማሪያም ጌቶቹ ፊቱን በጨርቅ አስረዉት የኢትዮጵያ ህዝብ ችግር፤ መከራና ስደት አልታይ ብሎት ነዉ አንጂ ወያኔን የመሰለ ነብሰ ገዳይ ባለበት አገር ዉስጥ የህዝብን ብሶት የሚያስጋቡ ጥያቄዎች በየቀኑ ይመነጫሉ አንጂ ከዉጭ አገርማ አይመጡም። በሌላ በኩል ደግሞ ይሄዉ ኢትዮጵያ በቅርቡ ያፈራቸዉ ዋሾ ሰዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች የሚያደርጉት ሠላማዊ እንቅስቃሴ የአሸባሪዎች እጅ ያለበትና፤አማኞቹ ሃይማኖታቸውን የወደዱ መስሏቸው ሳያውቁ የገቡበት ስለሆነ እንዲታረሙ እንመክራቸዋለንም” ብሏል። እዚህ ላይ በግልጽ እንደምናየዉ ኃይለማሪያም ደሳለኝ እመራዋለሁ የሚለዉን ህዝብ ጥቅምና ፍላጎት ፈጽሞ ሊረዳ አልቸለም፤ ስለዚህ ምክር የሚያስፈልገዉ መብትና ነጻነት ምን እንደሆኑ ገብቶት የሚታገለዉ የአትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን ኃይለማሪያም እራሱ ነዉ።

እኛ ግንቦት ሰባቶች ወያኔን የመሰለ ጨካኝ እና ምንም አይነት አገራዊ ኃላፊነት የማይሰማውን ዘራፊና ዘረኛ ቡድን በሠላማዊ መንገድ የሚጋፈጡ ወገኖቻችንን እናደንቃለን። እነዚህ ወገኖቻችን ኃይለማሪያም ደሳለኝ እንደሚለው የማንንም አጀንዳ የተሸከሙ ሳይሆኑ የራሳቸው የሆነ አጀንዳ ያላቸውና ኃይለማሪያም በዉክልና ለሚያስረግጣቸዉ ወገኖቻችዉ መብትና ነጻነት የሚታገሉ ጅግኖች ናቸዉ። አጀንዳቸውም የተደበቀ ወይም ከጀርባውም ሌላ ነገር ያለው አጀንዳ አይደለም።አጀንዳቸው ግልጽ እና የታወቀ የነፃነት፤ የእኩልነት፤የፍትህና የሠላም አጀንዳ ነው። ኃይለማሪያም ደሳለኝ የዜጎችን ጥያቄ አድምጦ መልስ መስጠት ሲገባው እነዚህን የኢትዮጵያን ህዝብ አጀንዳ ተሸክመው የሚታገሉ ወገኖች ደካሞች አድርጎ ለመሳል የሚያደርገዉ ሙከራ አንድም በተቃዋሚዎቹ ዙሪያ የተሰባሰበውን የሰው ኃይል ካለማወቅ፤ አለዚያም ደግሞ “ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ይሏታል ጅግራ” እንደሚባለው ነገር ነው።

ሌላው ኃይለማሪያም የሚናገረዉ ቃል ጠፍቶት በተደጋጋሚ ሲንተባተብ የታየዉ በሽብርተኝነት አካባቢ የተጠየቀዉን ጥያቄ ሲመለስ ነዉ። በእኛ እይታ ኢትዮጵያ ዉስጥ ዋነኛው አገር በቀል አሸባሪ ህወሃት እና ህውሃት ብቻ ነው። ህወሃት ስልጣን ላይ ያቆየኛል ብሎ ከገመተ የማይመሰርተው የክስ ዓይነት፤ የማያፈሰው የንጹህ ሰው ደም ፤የማያፈነዳው የቦንብ እና የፈንጂ ዓይነት እንደሌለ ከሃውዜን እስከ አዲስ አበባ ያሉ መንገዶች ቋሚ ምስክሮች ናቸው። ይህንን እኩይ ተግባሩን ዓለም ሁሉ እንደሚያውቀው በዊክ-ሊክ ላይ የወጣው መረጃም አሳይቷል።
የህውሃት ታማኝ ሎሌ የሆነዉ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሠላማዊ ትግሉን ለማፈን ከፈለገ በትግሉ ዙሪያ የተሰባሰቡትን ዜጎች ከሌላ ከማንም ጋር ማነካካት አያስፈልገውም። ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ ሁሉ አንደ ኃይለማሪያም ሞቶ የተቀበረን ሰዉ ራዕይ የተሸከሙ የአመለካከት ደሃዎች ሳይሆኑ የራሳቸው አስተሳሰብና ህያዉ ራዕይ ያላቸው ዜጎች ናቸው። አነዚህን ሠላማዊ ታጋዮች ከማይገናኝ ሌላ ኃይል ጋር አቆራኝቶ ለመምታት መሞከር ለኃይለማሪያምም ሆነ ለጌቶቹ አይበጃቸዉም። ዛሬ በወያኔ ነብሰ ገዳይ ወታደሮች ተከብቦ እዩኝ እዩኝ የሚለዉ ኃይለማሪያም ደሳለኝም የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጣ የነደደ ቀን ደብቁኝ ማለት ይመጣልና ያ ቀን ከመምጣቱ በፊት የበደለዉን ህዝብ ይቅርታ ጠይቆ የነጻነት ኃይሎችን እንዲቀላቀል ወገናዊ ምክራችንን እንለግሳለን።

በመጨረሻም ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ስለ ግንቦት ሰባት ተጠይቆ ሲመልስ ግንቦት ሰባት “በህልም ውስጥ ያለ ድርጅት” ነው ብሏል።

ታድያ ምነዉ ተኝቶ ህልም የሚያልም ድርጅት ኃ/ማሪያምንና ጌቶቹን እንዲህ ያቃዣቸዋል? ለምንስ ይሆን ወያኔና ታማኝ ሎሌዉ ኃ/ማሪያም ያገኙትን ሁሉ ግንቦት ሰባት እያሉ የሚያስሩት፤ የሚደበድቡትና የሚገድሉት? ያገኛችሁትን ሁሉ የግንቦት ሰባት አባል እያላችሁ ትከሳላችሁ? ለምንስ በግንቦት ሰባት ስም ታስራላችሁ? ትገርፋላችሁ? ትገድላላችሁ? ተኝቶ ለሚያንቀላፋ ድርጅት ለምን ትሸበራላችሁ፤ ለምንስ እንቅልፍ አጥታችሁ ትባዝናላችሁ? ግንቦት ሰባት እናንተ አልገባችሁም አንጂ መነሻውንና መድረሻውን አጥርቶ የሚያውቅ፤ ከደመናው ባሻገር ፍንትው ያለ የነፃነት ዉጋገን የሚታየው ባለ ታላቅ ራዕይ ድርጅት ነው። አስኪ ምናልባት ቢገባችሁ ተረት ቢጤ እንንገራችሁ፤

“አንዲት ሚዳቋ ነበርች አሉ። ሚዳቆ ከመሬት ገንዘብ ተበድራ ሲትኖር ከእለታት አንድ ቀን መሬት አፍ አውጥታ ብድሬን መልሽ አንጂ ብላ ትጠይቃታለች። ሚዳቆዋም ደንግጣ ከነበረችበት ቦታ ፈትለክ ብላ ወደ ተራራ ጫፍ ላይ ወጥታ እፎይ ያንን ድምጽ ከአሁን በኋላ አልሰማም አለች። መሬትም በይ ብሬን ክፈይኝ ስትል ዳግም ጠየቀቻት። እንዴ ይህች መሬት የሌለችበት ዬት አገር ሊሂድ ብላ ሚዳቆ ወደ ማይታወቅ ቦታ ተፈተለከች። ከዚያም እያለከለከች በቃ አሁንስ አታገኚኝም ስትል አሁንም መሬት ብቅ ብላ እየጠበኩሽ ነውኮ ብድሬን ክፈይ እንጂ ስትል ጠንከር አድርጋ ጠየቀቻት። ሚዳቆዋም መሬት የሌለችበት ልትደረስ ስትበር ስትበር ሳንባዋ ፈንድቶ ሞተች”ይባላል።

የፍትህ፤ የእኩልነት፤ የነፃነትና የዲሞክራሲ ጥያቄዎች እንደ መሬት ናቸው። የትም ሂዱ፤ የትም ግቡ ይከተሏችኋል። መስጊድ ዉስጥ አሉ፤ ቤተክርስትያናት ውስጥ አሉ። ቤተመንግሰት ዉስጥም አሉ። የሌሉበት ቦታ የለም። መፍትሄው እንደ ሚዳቆዋ መሸሽ አይደለም። መፍትሄው ዜጎች የሚያነሷቸውን የፍትህ፤ የእኩልነ፤ የነፃነትና የዲሞክራሲ ጥያቄዎችን አድምጦ ትክክለኛ መልስ መስጠትና ከዕዳ ነጻ መሆን ብቻ ነዉ ። ከዚህ ዉጭ ጥያቄን ላለመስማት ወይም ሰምቶ ለመደፍጠጥ የሚደረገው ከንቱ ሩጫ መጨረሻው እንደ ሚዳቆዋ መፈንዳት እንጂ ህይወት አይሆንላችሁም።

እኛ ግንቦት ሰባቶች ዘረኛዉንና አሸባሪውንና የወያኔ ስርዐት ለመደምሰስና ህዝብ በነፃነት ያለፍርሃት የሚኖርበትን አገር ለመፍጠር ቆርጠን ተነስተናል። ከእንግዲህ የሚያቆመን ምንም ነገር የለም። የምንታገለዉ ለህዝብ ጥያቄያችንም ህዝባዊ ጥያቄ ነዉና እኛም አንደጥያቄዉ በየመስጊዱ፤ በየቤተክርሲቲያኑና በየሰፈሩ ዉስጥ አለን።እኛ የሌለንበት ስፍራ የለም። በዚህ አጋጣሚ የዘመናት ትግላችን ፍሬዉ የሚታይበት ቀን እጅግ በጣም ቅርብ ነዉና የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም አገር ተረካቢ የሆነዉ ወጣቱ ትዉልድ እራሱን፤ ወገኖቹንና እናት አገሩን ለማዳን የሚደረገዉን የነጻነት ትግል እየመጣ እንዲቀላቀል ወገናዊ ጥሪያችንን አቅርበናል። ኑ እና ተቀላቀሉን።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Hailemariam Defends Anti-Terror Law, Condemns Critics (Video)

Oktober 10/2013         
Hailemariam Desalegn
 Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn defended the controversial anti terrorism law.

Answering questions at his office last week, Mr. Hailemariam claimed that enacting such legislation was necessary to keep the nation safe from terrorist attacks.

Amnesty International, Human Rights Watch and the Committee to Protect Journalists have been vocal critics of the anti-terrorism law. The law’s critics call it an effective tool for silencing dissent saying some of the provisions would violate the right to freedom of expression and association.

One of the controversial provisions of the anti terrorism proclamation states that “whosoever writes, edits, prints, publishes, publicizes, disseminates, shows, makes to be heard any promotional statements encouraging, supporting or advancing terrorist acts stipulated under this Proclamation is punishable with rigorous imprisonment.”

In June 2011, Ethiopian parliament has officially proscribed Ginbot 7, OLF & ONLF as terrorist organizations.


Stop The Killing and Injustices Being Committed Against The Oromo People. By;- Mekonenn Elalla

Oktober 09/2013

The united nation international human right convention paragraph 9, 10, and 11 declare no citizen of any country shall be arrested without reasonable ground of conviction; and if he or she is indicted in any kind of charge or wrong doing, it states the right of the subject to be presented in front of a legitimate court in early possible time. The protocol also clearly illustrates that until the legitimate court sentences the subject as guilty, his or her right of innocence must be respected and maintained. The 1991 Ethiopian government constitution which is based itself on the international human right protocol has also declares this right in its chapter 17 paragraph 2 that no citizen of the country shall be arrested without a warrant issued from a legal court; and if this is done properly, his or her right to stand in face of a legal body to get a trial no later than sooner must be guaranteed. Ethiopia is not only among those countries that drafted and ratified the international human right convention, it is also one of the pioneer fifty-one countries who found the United Nation.

Since the musketeers and bourgeois rule of Amhara, through the military junta of DERG, and till the current tribal regime of TPLF, the Oromo people are being subjected to a continuous persecution, imprisonment and killing savagely. Particularly, the bourgeois Amharas' vicious killing that unleashed on Oromo people has left a big black hole in our history and the scar will remain unforgettable across time and generation. Even today, the Amharas' disregard, contempt, and demeaning towards the mass Oromo people rights, norms, and values is highly pronounced and appalling  in magnitude as before if not more.
The tribal TPLF regime which spent 17 years of guerrilla fighting in jungle before coming to power in 1995 to govern the country for the last 22 years does not seem to have any concern or knowledge for the internationally accepted human right protocols leave aside to abide by the rules and regulations. By its very nature, TPLF is a jungle born tribal party which is incapable to administer Ethiopia in respect of contemporary, civilized thinking of governance. Its inadequacy to lead the country has proved itself in these 22 years when it induces the rule of jungle, force and terror to stay in power. Here after, no one expects TPLF to realize the importance of freedom and democracy to govern a sovereign country. If one thinks that the time is still early for this tribal regime to update itself and respect civilian rights, he or she must be the one who dreams the sun to rise on west and set in the east. No one is optimist to any form of positive change as long as this government is on power.
More than ever, today, the Oromo people which constitute the majority of the total population have become determined not to sustain any form of oppressions. Incarcerating and killing Oromos who ask their rights, administering severe corporal punishment on those who exercise their freedom of speech and press, exiling those who stand against any kind of partial or racist treatment, and persecuting Oromo scholars to flee the country are among the major administration policies of TPLF. In general, what the regime is committing against the Oromo people could be considered as an act of genocide. For the world surprise, those codes of crimes TPLF penalized in life or death sentence are undisputed human rights across the continents including Africa. Unfortunately, even if TPLF is not exercising it in reality, some of the charges that many Oromo people are being left in prisons are clearly stated as civil rights on the constitutional documents (papers) of the country. To TPLF shame and guilt, as if the country has two distinct constitutions and two classes of citizens, rules and regulations that deny the very rights of some are being implemented to liberate and empower others.
The tribal regime of TPLF that segregates citizens in race and language for preferential access of education, work and safe life has faced a strong reaction and opposition from Oromo people which make more than half of the population count. This abundance put imminent threat to TPLF that it will be overwhelmed by number and power. This in turn brings a continuous persecution and a deliberate, systematic, or wanton infliction of physical or mental suffering for Oromo people regardless of sex, age and region across the country. The case of those 69 Oromo innocents who are suffering in prison not for any justified reason or crime but simply for being Oromo and asking their rights is a simple justification for TPLF's aggression.
Since the onset of TPLF regime, the number of Oromo people put behind bars and racked at different places in Kality, Zeway, Shewarobit, and Diredawa is getting higher. Those 69 Oromo prisoners, who are collectively jailed under the command of the deceased Prime Minister Meles Zenawi, just a year and two months before his death, have faced a gruesome torture in their prison cells. These prisoners have neither been tried in front of any legal court nor have knowledge for what kind of transgression they committed to end up in prison. Recently, after being told to get a hearing on 6th of July, suddenly they received a prolongation of date by four months on which they expressed their deep discontent and appealed to the office of the Prime Minister. However, their right to appeal for the PM office triggered the prison management’s anger and they become subjected for harsh and sever punishment from the authorities. These innocent prisoners put in a group, tied their hands and feet to endure a shocking revenge. Some of the hospital source have disclosed many of them have been left with sever physical injuries. Among those who have been tortured in inhumane manner, eight of them were critically injured and lost their conscious before taken to a hospital. According to eye witnesses, prior to their severe corporal punishment, those 69 prisoners were grouped in to three. These people have also testified that the walls and floors of those rooms where the prisoners savagely tortured were stained with blood and had been washed and cleaned for a day long.
In addition to this, Engineer Tesfahun Chemeda, who lost his life after a long time imprisonment and torture in Kality prison, is regrettable, unforgettable and unforgivable loss for us, Oromo people as a whole. This act of crime will never stop or pull back our struggle against TPLF regime; and we keep shouting to expose its offence against Oromos to the world wide nations. We will never surrender until a neutral body examines the cause of his death and we, as Oromo, and his beloved family get justice against the killers.
This crime and inhumane treatments of TPLF being administered on Oromo people is a part and parcel of a day to day gruesome acts of the regime against the nation and nationalities of Ethiopia. Therefore, the Oromo Libration Front calls every individual citizen of the country to feel and consider this oppression as a crime committed against his or her livelihood to stand together to pull out the already rotten government. When the Oromo people are attacked, Afar, Sidamo, Somalis, Wolitas, and other nation and nationalities should come forward reinforce the struggle since TPLF dictatorial rule and oppression is without exception. As the Oromo Libration Front is committed and making life sacrifices to bring a revolutionary change, it calls other oppressed groups to join its struggle to eradicate the regime and to smash its racial and partial yoke the people have been carrying for the last 22 years.
 

Tuesday, October 8, 2013

ወያኔ ኢህአዲግ ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም የቆመ መንግስት አይደለም ::

Oktober 8/2013
ከገዛኽኝ አበበ

ሀገር ማለት የተለያዩ ብሄሮች ፣ የተለያዪ ጓሳዎች እና የተለያዩ ሃይማኖቶች ያሎቸው ሰዎች መኖሪያ ናት :: እኛም ሀገራችን ብለን የምንጠራት ሀገራችን ኢትዮጵያ አኩሪ ታሪክ ያላት የተለያዩ ህዝቦች መኖሪያ ሀገር ስትሆን ሕዝቦቾም ለዘመናት በፍቅር፣ በመተሳሳብ ፣ በመከባባር እና በመተባባር አብሮ ሲኖር የነበሩ ህዝቦች እንደነበሩ ከታሪክ መረዳድ እንችላላን::ይችን ሀገራችንን ኢትዮጵያን በተለያዩ ጊዜና ዘመናትም  የተለያዩ መንግስታቶች ለዘመናት በመፈራረቅ መርተዋታል መንግስታቶችም የኢትዮጵያን አንድነት እና ሎአላዊነትን ጠብቀው ህዝቡም ኢትዮጵያዊነቱን ጠብቆ እና አስከብሮ እንዲኖር የበኩላቸውን አስተዋጹ አብርክተው አልፈዋል:: ጀግኖች አባቶቻችንም የኢትዮጵያ ሕዝብም ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያ አንድነት ሲሉ ደማቸውን አፍስሰዋል፣ አጥንታቸውን ከስክሰዋል ፣ ህይወታቸውንም መሰዋት አድርገው አሳልፈው ሰተዋል :: ምክንያቱም ኢትዮጵያውነት ኩራት ኢትዮጵያውነት ፍቅር ኢትዮጵያውነት አንድነት መሆኑን ከመሪያቸው ተምረውታልና::

 መሪው የኢህአዴግ ወያኔ መንግስትም ወደ ስልጣን ብቅ ካለበት ቀን ጀምሮ ሀገርን በመሸጥ ፣ በመገንጠል እና ሕዝብንም በዘር፣በብሔር፣ በጓሳ እና በቋንቋ በመከፋፈል ኢትዮጵያዊነትን የማጥፋት ርኩስ ተግባሩን እየገፋ ባለበት በእነዚህ አስርት አመታት ውስጥ ግን  ኢትዮጵያውነት ኩራት መሆኑ ቀርቶ ውርደድ፣ ስደት መከራ እና ስቃይ መሆኑ እየጨመረ መጥቶል::

  በእነዚህ አመታቶች ኢትዮጵያውነት የሀገር ስሜትና ወኔ ከህዝብ ዘንድ የጠፋበት እና ሕዝቡም እንደ ዜጋ መኖር በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ ይገኛል ::በእነዚህ አመታቶች ውስጥ ለሕዝቡና ለኢትዮጲያዊነት ግድ በሌለው በዚህ ሰይጣናዊ እና አረመናዊ አገዛዝ ስር ብዙዎች ታስረዋል፣ ተገለዋል፣ ወላዱች እንዳይወልዱ መካን ተደርገዋል ሕዝቦች ቄያቸውን መሬታቸውንና ሀብት ንብረታቸውን በግፍ ተነጥቀው ለስደት እና ለመከራ ተዳርገዋል፣እናቶች ልጆቻቸው በግፍ ተገሎባቸዋል ይህ ነው የማይባል ብዙ ብዙ ግፍ በሕዝብ ላይ ተፈጽሞል :: ከእለት ወደ እለትም ሕዝባችን መኖር በማይችልበት አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ይገኛል:: ዘሬ በየቤቱ በዚህ ጨቋኝ ስርዓት የማይማርር የለም::  የሕዝብም የመኖር ሁኔታ ጥያቄ ውስጥ ነው :: የወያኔ ኢህአዲግ መንግስት ለሕዝብ ምንም የጠቀመው ነገር የለም:: ይልቁንስ በሀገር ሀብት እና ንብረት በማን አለብኝነት እንደፈለጋቸው ሲፈነጥዙ ኖረዋል አሁንም እየኖሩ ይገኛሉ::

  መንግስታት ሀገርን ሊያስተዳድሩ እና ሊመሩ ወደ ስልጣን ሲመጡ የሀገርን ሉአላዊነትን እና የሕዝብን ጥቅም ለማስከበር ነበር በተቃራኔው ግን  እንደ አለመታደል ሆኖ  ሀገራችን ኢትዮጵያ ሕዝቦቾም ለዚህ ባለመታደል መብታቸውን እና ነጻነታቸውን ለመስከበር እንደ ሰው መኖር በሚችሉበት ሁኔታ በነጻነት ለመኖር በመፈለግ በየቀኑ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሕዝቦች ሀገራቸውን በመልቀቅ ወደተለያዩ ሀገሮች ለስደት ይዳረጋሉ :: በብዛት ወደየ ሃረብ ሀገሩ የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ዜጎቻችን ለተለያየ እንግልት መከራ እና ስቃይ እንዲሁም ለሞት የሚዳረጉ ሲሆን በየቀኑ የብዙዎቹ ህይወት እንደዋዛ ያልፋል::

ነገር ግን ሕዝባችን በየቦታው እና በየአረብ ሀገሩ አሰቃቄ ድብደባ ግፍ እና ግድያ ሲፈጸምበት ሀገርን እየመራው ነው ሕዝብንም እያስተዳደርኩኝ ነው የሚለው  የወያኔ ኢህአዴግ መንግስት አንድም ቀን የዚህ ሕዝብ መከራ እና ችግር ግርፋት እና ሰቃይ ሞቱ ግድ ሲለው እና ለሕዝቡ አለኝታነቱ ሲቆም አይተን አናውቅም::ስለዚህ የኢህአዲግ መንግስት  ለኢትዮጵያም ለኢትትዮጵያ ሕዝብም እስከ አሁንም ምንም የጠቀመው ነገር የለም አሁንም ወደፊትም አይጠቅምም :: ለሀገር እና ለሕዝብ ጥቅም ቆሚያለው የሚል መንግስት የሀገርን ሉአላዊነት ሲያስከብር የሕዝብን ደህንነት እና ጥቅም ሲያስከብር ብቻ ነው::

  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖር




የዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ጀርባ ሲገለጥ ምንሊክ ሳልሳዊ

Oktober 8/2013

ፕ/ት ሆነው የተመረጡት ሙላቱ ተሾመ ትምህርታቸውን በሰባዎቹ አመታት የተከታተሉትና “ዶ/ር” የሚል ማእረግ ያገኙት በቻይና ነው። በትምህርታቸው በጣም ደካማ ነበሩ። ሙላቱ ሁለት አመት ወድቀው ከመባረር የተረፉት በነዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አማካይነት ሲሆን፣ በወቅቱ ዶ/ር ነጋሶ ያሉበት ኮሚኒቲ ለዩኒቨርሲቲው ያቀረቡት የextension ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ መቀጠል እንደቻሉ፣ እንዲሁም ቻይና በነበሩ ጓደኞቻቸው እገዛ ለመጨረስና “ዶ/ር” ለመባል እንደበቁ፣ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ ምሁር በወቅቱ አጋልጠው ነበር። 

ምሁሩ ጉዳዩን ለማጋለጥ የተነሱት ዶ/ር ነጋሶ በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ ማቀረባቸውን ተከትሎ በስብሰባ ላይ « መንግስቱ ሃ/ማሪያምን መሰልከኝ» ሲሉ አቶ መለስ ዜናዊን ተናግረው ስብሰባውን ጥለው በመውጣታቸው፣ ከዚያም ዶ/ር ሙላቱ በያዙት አቋምና ጭራሽ «ነጋሶ መጠየቅና መታሰር አለበት» በማለት ከመለስ ወግነው በመናገራቸው ምክንያት እንደሆነ ተመልክቷል።
ከዩኒቨርሲቲ ጀምሮ የረዷቸውና የኦ.ህ.ዴ.ድ አባል እንዲሆኑ ያደረጓቸው ዶ/ር ነጋሶ ሆነው ሳለ፣ ያን ሁሉ ውለታ ረስተውና በአደርባይነት ተሰልፈው እንዴት «ነጋሶ መታሰር አለበት» ብለው በጭፍን ይፈርዳሉ?..ሲሉ ምሁሩ በግርምት በወቅቱ ጠይቀዋል። ለአቶ መለስ ባሳዩት ታማኝነት ዶ/ር ነጋሶን ተክተው ፕ/ት እንዲሆኑ በወቅቱ ታጭተው የነበረ ቢሆንም፣ እንዲሰረዝ የተደረገው «የፓርቲ አባል ያልሆነ ነው ፕ/ት መሆን የሚችለው» የሚልና በተጨማሪ የቀድሞውን ፕ/ት ዶ/ር ነጋሶን ከፖለቲካ ተሳትፎ ውጭ የሚያደርግ አሳፋሪ ህግ በመለስ እንዲወጣ በመደረጉ ነበር።
ሌላው አነጋጋሪ ነጥብ ይህ አዋጅ ሳይሻር፣ ማለትም « የፓርቲ አባል ያልሆነ ግለሰብ ፕ/ት ይሆናል» የሚለው ህግ በአዋጅ ሳይሻር፥ የገዢው ፓርቲ አባል የሆኑት ሙላቱ ተሾመ ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸው አስገራሚና ምን ያክል ለራሳቸው ህግና አዋጅ እንደማይገዙ የሚያሳይ ሆኗል። በሌላም በኩል “ዶ/ር” ሙላቱ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት፣ መጋቢት 1996ዓ.ም ፓርቲው ባደረገው ግምገማ በአቶ መለስ ከተዘለፉት አንዱ ሲሆኑ፣ ጉዳዩን በመንተራስ «ኢትኦጵ» ጋዜጣ «ከሕወሐት መንደር ከቃረምኩት» በሚል አምዱ በወቅቱ ይፋ ባደረገው መረጃ እንደዘገበው፥ « አቶ መለስ ንቀት በተሞላበት ሁኔታ “ ሙላቱ - አንተን ሚ/ር አድርጌ መሾሜን ረስቸዋለሁ። ያለስራ በሚ/ርነት የተጎለትክ ነህ፤ እዛው ጃፓን አምባሳደር እንደሆንክ ብትቀር ይሻላል።
..ኦ.ህ.ዴ.ድ ማለት ለትግል ፈጥረነው የት እንደገባ የማይታወቅ ድርጅት ነው።” » በማለት መለስ ዜናዊ መናገራቸውን አመልክቶ ነበር። የ“ዶ/ር” ሙላቱ ባለቤት ወ/ሮ መአዛ አብርሃም ትባላለች። ሸንቃጣዋና የደስ ደስ ያላት መአዛ አንድ ጃፓናዊ አግብታና ልጅ ወልዳ በቶኪዮ ከተማ ትኖር ነበር። እራሷን በጣም ስለምትጠብቅና አለባበሷን (አጭር ሚኒ ቁምጣ ነው የምትለብሰው) ለተመለከታት በወጣትነት የእድሜ ክልል እንደሆነች አድርጎ ይገምታታል፤ ሃቁ ግን ወ/ሮ መአዛ 53 አመት እድሜ ይሆናታል። ከሙላቱ ተሾመ ጋር የተዋወቁት ጃፓን ነበር። መአዛ በጣም ብልጥ ሴት ናት። በጃፓን የኢትዮጲያ አምባሳደር የነበሩት ሙላቱ ተሾመን ታጠምዳለች። ያጠመደችው ወላጅ አባቷ አቶ አብርሃም ነጋ በቀይ ሽብር ወንጀል ተከሰው ስለታሰሩ ነበር።
ጃፓናዊ የልጇን አባት ባሏን በመግፋት አምባሰድሩን ትቀርባለች። እንዳጋጣሚ አቶ ተሾመ የስራ ጊዚያቸውን ጨርሰው አገር ቤት ሲመጡ አብራ ትመጣለች። ክዛም ወላጅ አባቷን እንዲያስፈታላት ትጠይቃለች። የተጠየቁት ሙላቱ « ይህን በጭራሽ አልችልም። እነመለስ ከሰሙ ከእንጀራዬ ወዲያው ያባርሩኛል። ይህን ጥያቄ ዳግም እንዳትጠይቂኝ።» ይላሉ። ወላጅ አባቷ በ2000ዓ.ም ከእስር ተፈቱ። ወ/ሮ መአዛ ጃፓናዊ ባሏንና ልጇን በመተው ለፈፀመችው የትዳር ማፍረስ ተግባር ወደዛች አገር ዳግም እንዳትገባ ውሳኔ ስለተላለፈባት፣ ከ”ዶ/ር” ሙላቱ ጋር መጠቃለልን መረጠች። መአዛና ሙላቱ አንድ ልጅ አፍርተዋል። ሙላቱ ተሾመ በ1994ዓ.ም በሰባት ሚሊዮን ብር በቦሌ ያስገነቡት ዘመናዊ ቪላ በወር 36ሺህ ብር እንደሚከራይ ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን፣ ቪላውን ለመገንባት ገንዘቡ በሙስና እንዲገኝ ትልቅ ሚና የተጫወቱት ባለቤታቸው ወ/ሮ መአዛ መሆናቸው ታውቋል።

የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የግብረሰዶም አራማጆች “የመደራጀት መብታችን ይከበር” የሰጡት አስቂኝ ምላሽ

Oktober 7/2013

በቅርቡ አንድ የመዲናችን የግል ኮሌጅ በሥራ አመራር የትምህርት ዘርፍ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ሲያስመርቅ፤ ግብረ ሰዶማዊነት በአገራችን እያስከተለ ስላለው አደጋ የሚያስቃኝ በጥናት የተደገፈ ጽሑፍ ቀርቦ ነበር፡፡ ፅሁፍ አቅራቢው፤ የግብረሰዶም አራማጆች ለኢትዮጵያ መንግስት “የመደራጀት መብታችን ይከበር” በሚል ያቀረቡትን ጥያቄና የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር የሰጡት ምላሽ በሚል ያቀረቡት ቀልድ ለአንባቢያን የሚያስተላልፈው ቁም ነገር አያጣምና ልጥቀሰው። ጠ/ሚኒስትሩ የመብት ጠያቂዎቹን ተወካዮች አስጠርተው እንዲህ አሏቸው፡:

“እንድትደራጁ ከመፍቀዳችን በፊት ጥያቄያችሁ ከሕግ፣ ከሞራል፣ ከባህል፣ ከሥነ ምግባር…አንፃር ተቀባይነት ይኖረው አይኖረው እንደሆነ ማጣራት አለብን፡፡ ይሄን ለማጣራት ደግሞ የእናንተም ትብብር ያስፈልገናል፡፡ የመጀመርያው ተግባራችሁ የሚሆነው የድጋፍ መጠየቂያ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ነው፡፡ የሰልፉ መነሻ መሐል መርካቶ ይሆናል፡፡ ድምፃችሁን እያሰማችሁ፣ መፈክሮቻችሁን በጽሑፍ ይዛችሁ በመጀመሪያ የምታልፉት በራጉኤል ቤተክርስቲያን በኩል ይሆናል፡፡ በመቀጠል አንዋር መስጊድን ታቋርጣላችሁ፡፡ ከዚያ ወደ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ትዘልቃላችሁ፡፡ በአፍንጮ በር በኩል በ6 ኪሎ ዩኒቨርስቲና የሰማዕታት ሐውልትን ካለፋችሁ በኋላ፣ በ4 ኪሎ ዩኒቨርስቲ በኩል የነፃነት ሐውልትን አቋርጣችሁ፣ በሁለቱ ቤተመንግስቶች መሐል በመጓዝ መስቀል አደባባይ መድረስ ከቻላችሁ፣ የመደራጀት ጥያቄያችሁ ምላሽ ያገኝ ይሆናል”

Monday, October 7, 2013

ሊበሏት የፈለጓትን አሞራ ይሏታል ጅግራ

Oktober 7/2013

ባለፈዉ ዐርብ መስከረም 25 ቀን 2006 ዓ.ም. የወያኔዉ ሎሌ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ አዲስ አበባ ዉስጥ ለአገር ዉስጥና ለዉጭ አገር ጋዜጠኞች በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በየእሁዱ ለሚጠሩት ሰልፍ ጥበቃ ማድረግና በየእሁዱ ተመሳሳይ ጥያቄ ማድመጥ መንግስትን ከሚገባዉ በላይ ያሰለቸዉ ስለሆነ እነዚህ አንድ አይነት ጥያቄ ያነገቡ ሰልፎች የሚቀጥሉ ከሆነ የተቃዉሞ ሰልፍ ማድረግ ይከለከላል በማለት ጌቶቹና ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች የመብትና የነጻነት ጥያቄ የሚያነሳ ማንንም ሰዉ ለማሰር፤ ለመደብደብና ለመግደል ያላቸዉን እቅድ በግልጽ ተናግሯል። የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ ባቀረቡ ቁጥር መሪዎቻቸዉ የሚታሰሩባቸዉ፤ አባላቶቻቸዉ የሚደበደቡባቸዉና ቢሯቸዉ ተሰብሮ ንብረታቸዉ የሚዘረፍባቸዉ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ድርጅቶች አንድም ቀን ሰለቸን ሳይሉ ደብዳቢዉ፤ አሳሪዉና የተቃዋሚ ድርጅቶችን ቢሮ እየሰበረ ንብረታቸዉን የሚዘርፈዉ ወያኔ ሰላማዊ ሰልፍ “ሰለቸኝ” ማለቱ ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረግ ምንም አይነት ትግል የሱን የስልጣን “ዘለአለማዊነት” የሚጻረር መስሎ ከታየዉ ምንም ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ የማይመለስ ፀረ ህዝብ ኃይል መሆኑን እንደገና አረጋግጧል።
 
ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከዚህ ቀደም ቤት ውስጥ ሆነው ይጠይቁት የነበረውን ጥያቄ አሁን አደባባይ ወጥተዉ መጠየቅ መቻላቸዉ ዲሞክራሲያዊ ስኬት ነው ያለዉ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ በሌላ በኩል ደግሞ ሰላማዊ ሰልፍ በችርቻሮ የሚሰጥ የወያኔ ችሮታ ይመስል ሰልፉ በየእሁዱ የሚቀጥል ከሆነ ሰልችቶናልና እንከለክላለን ማለቱ እንደ ግንቦት 7 እምነት ቀድሞዉንም ቢሆን ወያኔ ሰላማዊ ሠልፍ ማድረግ ይቻላል ብሎ ፈቃድ የሰጠዉ ለዲሞክራሲ ካለዉ እይታና እራሱ የጻፈዉን ህገ መንግስት ተከትሎ ሳይሆን እርዳታ ሰጪ ምዕራባዉያን አገሮችን ለማስደሰት ብቻ ነዉ።

አገር ዉስጥ የሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከቅርብ ግዜ ወዲህ የተቀናጀ ትግል ማድረግ በመጀመራቸዉ ክፉኛ የተደናገጠዉ ወያኔ “ሊበሏት የፈለጓትን አሞራ ይሏታል ጅግራ” አንደሚባለዉ እነዚህን ኢትዮጵያ ዉስጥ ፍትህ፤ እኩልነትና፤ ዲሞክራሲ እንዲሰፍን የሚታገሉትን ፍጹም ህዝባዊና ፍጹም ሰላማዊ የሆኑ ድርጅቶች ለማጥፋት ሰበብ ሲፈልግ የተለመደዉን ግንቦት 7 የሚል ዘፈኑን መዝፈን ጀምሯል። የወያኔ አገዛዝ በአፉ አንደሚናገረዉ ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚያስብና የሚጨነቅ ከሆነ ማድረግ ያለበት ከኢትዮጵያ ህዝብ ለሚቀርብለት ጥያቄ ተገቢዉን ምላሽ መስጠት ብቻ ነዉ። አለዚያ ህዝብ ጥያቄ ባነሳና ለመብቱና ለነጻነቱ በታገለ ቁጥር የሐይማኖት አክራሪዎች፤ የቀድሞ ስርዐት ናፋቂዎች ወይም የግንቦት ሰባት ተከታዮች ናችሁ እያለ ቢያቅራራ እንዲህ አይነቱ የተለመደ የአምባገነኖች ቀረርቱ ያ የማይቀረዉ ክፉ ቀን ሲመጣ ስንቅ እንደማይሆነዉና ከህዝባዊ ቁጣ እንደማያድነዉ ከወዲሁ ሊገነዘብ ይገባል። ደግሞም ግንቦት 7 አላማዉ፤ ለህዝብ ያለዉ ክብርና ለኢትዮጵያ አንድነት ያለዉ ቀናኢነትና የማያወላዉል አቋም በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ በአጭር ግዜ ዉስጥ ከፍተኛ ተወዳጅነትን አስገኝቶለታልና የወያኔን የዕለት በዕለት አስተዋዋቂነት በፍጹም አይሻም።

ግንቦት 7 አላማዉና ፍላጎቱ እንደ ስሙ ፍትህ፤ ነጻነትና ዲሞክራሲ ነዉና የህዝባዊ ትግላችን አላማ ወያኔንና ዘረኛ ስርዐቱን መደምሰስ ብቻ ሳይሆን አገራችን ዉስጥ የህግ የበላይነት ሰፍኖ ኢትዮጵያ ዛሬም ነገም ከሽብርተኝነት የነጻች አገር አንድትሆን ነዉና ወያኔ ያሰኘሰዉን ቢናገር ወይም እንዳሰኘዉ ቢፎክር ንቅናቄያችን ከዚህ ህዝባዊ አላማዉ ንቅንቅ እንደማይል ለወገንም ለጠላትም ማረጋገጥ ይፈልጋል። ግንቦት 7 የኢትዮጵያና የህዝቦቿ ዋነኛ ጠላት ወያኔ ነዉ ብሎ ያምናል፤ ስለሆነም የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ክንድ ያነጣጠረዉ በዚሁ በዋነኛዉ የህዝብና የአገር ጠላት ላይ ብቻ እንደሆነ ኢትዮጵያዉያንና ለኢትዮጵያ ህዝብ ሰላምና ብልጽግና የሚመኙ ሁሉ እንዲገነዘቡለት ይፈልጋል።

ግንቦት 7 ህዝባዊ አላማ አንግቦ፤ ግብ አስቀምጦና ወዳስቀመጠዉ ህዝባዊ ግብ የሚያደርሰዉን የትግል ስልት በጥንቃቄ ነድፎ የሚንቀሳቀስ ህዝባዊ እንቅስቃሴ ነዉ። ግንቦት 7 ወያኔና ዘረኛ ስርዐቱ ተደምስሰዉ ኢትዮጵያ በዜጎቿ ሙሉ ፍላጎትና ፈቃድ ብቻ የምትመራ አገር የመሆኗ ሀቅ የማይቀርና ምንም አይነት ምድራዊ ኃይል ገድቦ ሊያቆመዉ የማይችል ህዝባዊ ማዕበል ነዉ ብሎ ያምናል። ግንቦት 7 በዚህ አጋጣሚ በየዋህነት ተሳስተዉና ግዜያዊ ጥቅም አታሏቸዉ ከሚንቋቸዉና እንደ ቤት ዉስጥ ዕቃ ከሚጠቀሙባቸዉ ዘረኞች ጋር እጅና ጓንት የሆኑ እንደ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ አይነቶቹ የዋሆች የበደሉትን ህዝብ ይቅርታ ጠይቀዉ ህዝባዊ ትግሉን እንዲቀላቀሉ ወገናዊ ጥሪ ያቀርብላቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ ግንቦት 7 ባለፉት ሁለት አመታት በተለይም ከወያኔዉ ቁንጮ ሞት በኋላ ከወያኔ ጋር ከፍተኛ ቅራኔ ዉስጥ የገባችሁ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶችና በድርጅቶቹ ዉስጥ የምትገኙ የኢትዮጵያ ህዝብ ወገኖች ወያኔን ለማስወድ ከዛሬ የተሻለ ግዜ አይመጣምና ኑና በጋራ ጠላታችን ላይ እንዝመት የሚል ህዝባዊ ጥሪዉን ያስተላልፋል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

Sunday, October 6, 2013

ወያኔና ጽንፈኝነቱ ! ኢትዮጵያ ውስጥ ወያኔን መቃወም ብቻ ሳየሆን አለመደገፍ በራሱ ከተቃዋሚነት ጎራ ይፈርጃል ።

Okteber6/2013

ወያኔ ከጽንሰቱ ጀምሮ ፣ ውለደቱና እድግቱ የሆነው ጽንፈኝነትና ዘረኝነት ሆኖ ከሚታወቅበት ተነስተን ባሁኑ ወቅት አክራሪነትን ሲቃወም እና ሌሎችን ሲወነጅል መስማቱ <ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ> ያስብላል ።
ኢትዮጵያ ውስጥ ወያኔን መቃወም ብቻ ሳየሆን አለመደገፍ በራሱ ከተቃዋሚነት ጎራ ይፈርጃል ።
ነጋዴው ለሃገሪቱ የሚያስመዘግበው የንግድ ዕድገትና ለዜጎች የሚከፍተው የስራ ዕድል እና ተያያዥ አስተዋጾኦች ባሻገር ወያኔን መደገፉን በተለያየ መልኩ ካላስመሰከረና በተጨማሪም ንግድ ቤቱ ግድግዳ ላይ የማቹን ጠ/ሚ ፎቶ በመስቀል የመለስ አምልኮ ተከታየነቱን ካላረጋገጠ ያገልግሎቱ ጠቀሜታ በ ዜሮ ተባዝቶ ከንግዱ አለም ጨዋታ ውጪ ይደረጋል።

ገበሬው ማዳበሪያ ለማግኘትና ዘርቶ ለማጨድ ወያነ ባዘጋጀለት መንገድ ብቻ መግዋዝ ይኖርበታል። ይህን ማድረግ ካልቻለ ግን ከፍተኛ ትጽእኖ የሚደርስበት ሲሆን ከዚያም አልፎ በቀጥታ የሚያረሰው መሬት ተነጠቆ ለልመና ለስደት ሊዳረግ ይችላል።

የሀይማኖት አባቶች የመለስን አምልኮ ካለስብኩ በተቃዋሚ ፓለቲከኞች ጎራ ይምድባሉ
የመንግስት ሰራተኛ ሆኖ ለመቀጠር ቢጫው የወያነ የአባልነት ካርድ ከትምረት ማሰረጃና ከስራ ልምድ በላይ ዋንኛ የቅጥር መስፈረት ነው ።

ተማሪውም ከከፍተኛ የት/ም ተቐማት ተመርቆ ለመውጣት (የትምር ጠራት ችግሩ እነዳለ ሆኖ) የወያኔ አባልነት ፎርም እንዲሞላ ይገደዳል።
ፍርድ ቤቶች በህግ የበላይንት ሳይሆን ለወያኔዎች በሚመች መልኩ በንጹሀን ዜጎች ላይ በግፍ ይፈርዳሉ።

ዜጎች መኖሪአቸው ተነጥቆ ለወያኔ አባላትና ለደጋፊዎቻቸው ተሰጥቶ ለጎዳና ህይወት ይዳረጋሉ ።

ሰላማዊ ታጋዮች ፣ጋዜጠኞች ግለሰቦች የሀይማኖት መሪዎች ለወያኔ ያልተመቸ ማንኛውም ዓየነት እንቅስቃስ የሚያደርግ አካል በአሸባሪነትና በአክራሪት ተፈርዶበት እስር ቤት ይወርወራሉ።

ወያኔ አገራችንን ከተቆጣጠረበት ጀምሮ እስካሁን ድርስ ስንፈኝነትንና እና አክራሪነትን በተቀነባበረ መልኩ ሬት ሬት እያለን ሲግተን የቆየና ዘረኝነትን በየቦታው ሲሰብክና ህዝቡን ሲያወክ የኖረና በተግባር ያሳየን መሰሪ ቡድን አሁን ደሞ ባዲስ መልኩ በቲዮሪ ላስተምራችሁ ብሎ የዩነቨረሲቲ ተማሪዎችን እያስገደደ ይገኛል። ይህ ባዲስ መልኩ የሚንቀሳቀሱበት አካሄድ ጤናማ ያልሆነና ሰራአቱ የህብረተሰቡን ያመለካከት አቅጣጫ በማስቀየር የፈለጉት ኢሰባዊ የሆነወን ያገዛዝ እድሜያቸውን ለማራዘም ያቀዱት ነገር እነዳለ ያሰታውቃል።
ወያኔን የሚያሰጋው እና እንዲህ እንቀልፍ የሚነሳው የወጣቱ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ እያደረገ ያለውን አምጽ እነድሆነ የታወቃል። ወጣቱ ትውልድ ዘመናዊ ባርነትን እሺ ብሎ የማይቀበል ተፈጥሮ ሰጠችውን ነጻነት በአምባገነኖች ሲነጠቅ ዝም የማይል በመሆኑ ለወያኔ አገዛዝ የማያመች ሆኖበታል ።
ሰሞኑን ሀገር ውስጥ እየታየ ያለው በተለይ ወያኔ በኢትዮጵያ ውስጥ ያጸደቀው የጸረሽብር ህግ ሳይገታው ህዝቡ ለነጻነቱ ለመታገል ዝምታን ሰብሮ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞውን በገለጸበት እና ባሳየው ወኔና ቁጣ ወያኔን ማሸበሩ በወቅቱ ከድሬዎችና ፈደራል ፖሊስ ካደርጉት ህገወጥ እንቅስቃሴ ማረጋገጥ ይቻላል። ወያኔን እነቅለፍ መነሳት እና እነዲ ማሸበር ልኛ የነጻነት ቀናችን መቅረቡን ከበስበስ የቆየው ለወያኔ አገዛዝ ደግሞ መውደቂያው መቅረቡ የሚያሳይ ነው ።

Saturday, October 5, 2013

ወያኔ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ በማጓጓዝ ስራ መጠመዱ ተሰማ

Oktober 5/013
ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የሚወስዱ አዉራ መንገዶች ታንኮችን፤ መድፎችንና ሌሎችም ከባድ የጦር መሳሪያዎችን በተሸከሙ ከባድ ወታደራዊ የጭነት ማመላለሻ ከሚዮኖች እየተጨናነቁ መሆኑን ኢሳት ቴሌቪዥንና ሬድዮ የአይን እማኞችን ጠቅሶ ዘገበ። ወያኔ ከኤርትራ ጋር ባለበት የድንበር አተካሮ ብዙም ዉጥረት በማይታይታይበት በአሁኑ ወቅት የጦር መሳሪያዎቹን በዚህ ደረጃ ለማንቀሳቀስ ለምን እንዳስፈለገ ብዙም የሚታወቅ ነገር ባይኖርም አንዳንዶች ወይኔ ሀይሉን ለማሳየት የሚያደርገዉ ከንቱ የእዩኝ እዩኝ ዘመቻ ነዉ ሲሉ ሌሎች ደግሞ በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢ ከቀን ወደ ቀን እያየለ የሚጣዉን የአማጽያን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ነዉ ይላሉ። ያም ሆነ ይህ ወታደራዊ እንቅስቃሴዉን አስመልክቶ ከአገዛዙ ባለስልጣናት የተሰጠ መግለጫ ካለመኖሩም በላይ ሦስተኛ አካላት ጉዳዩን ለማጣራት ከመንግስት ጋር ያደረጉት ግንኙነትም ፍሬ አልባ ሆኗል።
ሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ፤ ጎንደርና አፋር ዉስጥ የወያኔን ስርዐት በኃይል ለመናድ የሚንቀሳቀሱ አያሌ መሳሪያ ያነገቡ ድርጅቶች የሚገኙ ሲሆን እነዚህ ላለፉት ሃያ አመታት በተናጠል ወያኔን የተዋጉ ኃይሎች ከቅርብ ግዜ ወዲህ የጋራ ግንባር እየፈጠሩ መምጣታቸዉ ወያኔን እንዳሳሰበዉና ክፉኛ እንዳስደነገጠዉም ታዉቋል። እንደብዙ የፖለቲካ ተንታኞች ግምት ይህ ከሰሞኑ የታየዉ ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴም የዚሁ ድንጋጤ ዉጤት ነዉ የሚሉ ብዙዎች ናቸዉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ አዲስ አበባን ጨምሮ በየክልሉ የነጻነት ኃይሎችን ለመቀላለቀል የሚደረገዉ እንቅስቃሴ እያደገ መምጣቱ ሌላዉ የወያኔ ስጋት ስለሆነ የሰሞኑ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የሚደረገዉ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ከመሀል የአገሪቱ ክፍሎች ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የድንበር አካባቢዎች የሚወስዱ መንገዶችንና ኬላዎችን ለመዝጋት ነዉ የሚሉም አልታጡም። በዚህ ተኬደ በዚያ የሰሞኑ የወያኔ ወታደራዊ ሩጫ አላማዉ ባዕዳንን ለመከላከል ሳይሆን ለአገር አንድነትና ለህዝብ መብትና ነጻነት የሚታገሉ ኃይሎችን ለማፈን ነዉ።

ግንቦት7 የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለወገኑ ነጻነት የሚቆምበትን መንገድ እያዘጋጀ መሀኑን ገለጸ

Oktober 5/2013

ግንቦት ሰባት የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በወያኔ የዘረኝነት አለንጋ የሚለበለበዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እራሱንና ወገኑን ነጻ የሚያደርግበትን መንገድ መከላከያ ሰራዊቱ ዉስጥ እየቀየሰ መሆኑን የንቅናቄዉ ዋና ጸሀፉ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ተናገሩ። ዋና ጸሀፊዉ ይህንን የተናገሩት ኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ ዉስጥ የግንቦት ሰባት ኃይሎችን ለመርዳት በተደረገዉ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ ባሰሙት ንግግር ነዉ። አቶ አንዳርጋቸው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቱን አስመለሰክተዉ ባደረጉት ንግግር እንደዚህ አይነቱ ወገናዊ ዝግጅት በአንድ በኩል በግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል አባላት ዉስጥ ከፍተኛ መነቃቃት የሚፈጥር ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ወራዊቱ የተጣለበት ህዝባዊ አደራ ምን ያክል ከፍተኛ መሆኑን የሚያስታውሰን ነው ብለዋል።
በቅርቡ ከኢትዮጵያ አየር ሀይል ከድተው ህዝባዊ ሰራዊቱን ስለተቀላቀሉት ጀግኖች ተጠይቀዉ በሰጡት መልስ የአየር ኃይል አባላቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዉ ንቅናቄያቸዉ በመከላከያ ሰራዊት፤ በደህንነት መስሪያ ቤትና በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ዉስጥ ወያኔ ሊደርስበት በማይችልበት መልኩ የግንኙነት መስመር እየዘረጋ መሆኑን ገልጸዋል።
ኖርዌይ ኦስሎ ዉስጥ የተካሄደዉን አይነት የግንቦት ሰባት ኃይሎች የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በሌሎች አገሮችና ከተሞች ዉስጥ ለማድረግ እቅድ አላችሁ ወይ ተብለው የተጠየቁት አቶ አንዳርጋቸው፣ ህዝባዊ ሀይሉ ከተግባር ጋር በተዛመደ መልኩ የገቢ ማሰባሰብ ዝግጅት መርሀ ግብሩን ይፋ እስከሚያደርግ ድረስ በህዝባዊ ሀይሉ ወይም በግለሰቦች ስም ምንም አይነት የገቢ መሰባሰቢያ ዝግጅት እንደማይደርግ ገልጸዋል። በሌላ ዜና ደግሞ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኖርዌ፤ ሲዉድንና በአካባቢዉ አገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጋር እንደተወያዩ ለማወቅ ተችሏል። በዚህ ዉይይታቸዉ ወቅት አቶ አንዳርጋቸው የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይልን ዓላማዎች፤ ተልዕኮዎችና ራዕይ በማስተዋወቅ ህዝባዊ ሃይሉ ከምስረታው ጀምሮ አሁን ድረስ ያለበትን ደረጃ በምስልና በጽሁፍ በተደገፈ ገለጻ ለተሰብሳቢው አቅርበዋል።
ከአቶ አንዳርጋቸው እስካሁን ድረስ የተካሄደዉ የህዝባዊ ኃይሉ ስልጠና የንቅናቁዉን የአመራር አካላት ያካተተ መሆኑን ጠቅሰዉ ወታደራዊ ስልጠናዉ የበታችና የበላይ የሚባል ልዩነት እንደሌለበት አስገንዝበዉ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይል የተመሰረተዉ ቤተሰባቸውን፤ ስራቸውን፤ገንዘባቸውንና የተደላደለ ኑሯቸውን ትተው ከኢትዮጵያና ከመላው ዓለም በተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን እንደሆነ እንደሆነ ገልጸዋል። የግንቦት ሰባት ዓላማ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ማስፈን ብቻ ሳይሆን ባለፉት 22 ዓመታት ኢትዮጵያውያን የተገፈፉትን ክብራቸውን ማስመለስ ጭምር መሆኑን አቶ አንዳርጋቸው አስምረውበታል።

ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሰልፍ ላይቀጥል ይችላል አሉ

Saturday, 05 October 2013
f44997cb312b542bbd55c895274ee230_XLተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚያደርጓቸው የተቃውሞ ሰልፎች ተደጋጋሚና መንግስት አቋም የያዘባቸውን ጉዳዮች የሚያነሱ እንደሆኑ የጠቆሙት ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ፤ መንግስት ለእያንዳንዱ ሰልፍ ጥበቃ ማድረግ ስለማይችል ሰልፎቹ በተለመደው መልኩ ላይቀጥሉ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ ትናንት በጽ/ቤታቸው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ የሚያነሷቸው ጥያቄዎች የራሳቸው የፓርቲዎቹ ሳይሆኑ የሌሎች ሃይሎች እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡
ፓርቲዎቹ ሰልፍ ማካሄድ ህገመንግስታዊ መብታቸው መሆኑን የጠቀሱት ጠ/ሚኒስትሩ፤ መንግስት በተደጋጋሚ ጥበቃ ሲያደርግ ቢቆይም፣ በሰልፎቹ የሚነሱት ጥያቄዎች ፋይዳ ቢስ ከመሆናቸውና ከፓርቲዎቹ ብዛት አንፃር መንግስት በቀጣይ ለሰልፎች ጥበቃ ለማድረግ የሚቸገርበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል አስረድተዋል፡፡
ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ መንግስት በተደጋጋሚ ምላሽ የሰጠባቸውን ጥያቄዎች መላልሰው የሚያቀርቡት በመንግስት ላይ ጫና በመፍጠር አቋሙን ለማስቀየር በማሰብ ሊሆን ይችላል ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ፤ ይሄ ግን በፍፁም የማይሳካ ሃሳብ ነው ብለዋል፡፡ “ግንቦት ሰባት” በቅርቡ መንግስትን ለመጣል ወታደራዊ እርምጃ እንደሚወስድ በይፋ መግለፁን በተመለከተ ተጠይቀው ሲመልሱም፣ የፓርቲው አመራሮችና ደጋፊዎች ተጨባጭ ያልሆነ ህልም ውስጥ ሆነው የተናገሩት ነገር እንደሆነና ከህልማቸው ሲነቁ እውነታውን እንደሚገነዘቡት ጠ/ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ ኢህአዴግ ውስጥ መከፋፈልና የሃይል መጠባበቅ አለ የሚለውን መረጃ በተመለከተም “ይህ የአንዳንድ አፍራሽ ሃይሎች ከንቱ ምኞትና ተጨባጭ ያልሆነ አሉባልታ ነው” ሲሉ አጣጥለውታል፡፡

Friday, October 4, 2013

ገዢው ፓርቲ በጠራቸው ስብሰባዎች ላይ ሁሉ ተቃውሞ ገጠመው

Oktober 4 / 2013

መስከረም ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ባለፈው ሳምንት በመላ አገሪቱ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችን እየሰበሰበ በ2005 የስራ አፈጻጸምና የ2006 ዓም በጀት እቅድ ትግበራ ላይ ሲያወያይ ቢሰነበትም፣ ለኢሳት ሚደርሱት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በሁሉም ቦታዎች ላይ በተደረጉት ስብሰባዎች ከፍተኛ ተቃውሞ አጋጥሞታል።

በአዳማ የተካሄደውን ስብሰባና ተሰብሳቢዎች ያቀረቡዋቸውን ቅሬታዎች ኢሳት ቀደም ብሎ የዘገበ ሲሆን፣ በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን በአርማጭሆ ወረዳ የነበረው ስብሰባም እንዲሁ በተመሳሳይ ተቃውሞ መጠናቀቁን በውይይቱ የተሳተፉ የመንግስት ሰራተኞች ገልጸዋል።

በውይይቱ ላይ በርካታ አጀንዳዎች የነበሩ ሲሆን፣ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ የተነሱት ጉዳዮች ተሰብሰባዊውን በከፍተኛ ሁኔታ አወዛግበዋል።

በ2006 ዓም የጸረ ሰላም ወይም የጥፋት ሀይሎችን ማምከን የሚል በእቅድ እንዲካተት በቀረበው አጀንዳ ላይ ጸረ ሰላም ማን ነው የሚለው ጥያቄ በተሰብሳቢው ተነስቶ የመድረኩ መሪዎች የተለያዩ መልሶችን ሰጥተዋል። የዞኑ የጸጥታ ጉዳዮች ሀላፊ የሆኑት አቶ ወርቁ ሀ/ማርያም ” ነሀሴ ወር ገደማ 30 የሚሆኑ ሰዎች በጎንደር ከተማ ህዝቡን ተነስ በማለት ሲቀሰቅሱ የነበሩ ሰዎች ጸረ ሰላም ሀይሎች ናቸው።” በማለት አንድነት ፓርቲ በጎንደር ያካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ በምሳሌነት አንስተዋል።

ሌላው የሲቪል ሰርቪስ ባለስልጣን የሆኑት አቶ ገዛሀን ተክሌ በበኩላቸው ” የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን ተሰጠ ብሎ መናገር ጸረ ሰላምነት ነው” ሲሉ አብረራርተዋል። ባለስልጣኑ አክለውም ህገመንግስቱን ለመጣስ የሚነሳ ሁሉ ጸረሰላም ተብሎ ይፈረጃል ብለዋል።

የጸጥታ ጉዳዮች ዘርፍ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ደግሞ ” ከመድረክ አፈንግጦ መውጣትና ሳያስፈቅዱ መናገር፣ ሳያስፈቅዱ ጽሁፍ መጻፍና ማሰራጨት፣ ሳያስፈቅዱ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ፣ በጥፋት መልእክተኝነት ያስፈርጃል ሲል ገልጸዋል።
አቶ ፈንታ የተባሉ ባለስልጣንም እንዲሁ ” የጎንደርን መሬት ኢህአዴግ አሳልፎ እየሰጠ ነው ” ብሎ መናገር ጸረ-ሰላም ተግባር ነው በማለት የራሳቸውን ትርጉም አቅርበዋል።

ስለ ጸረ ሰላም ሀይሎች፣ አክራሪነትና ሽብረተኝነት ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ ትምህርት እንዲሰጠጥ በቀረበው ሀሳብ ላይ ደግሞ በስብሰባው የተሳተፉ ተቃውሞአቸውን ገልዋል። ተሳታፊዎቹ ከ15 ዓመት በታች ያሉ ህጻናትን ስለ ሽብረተኝነት፣ አክራሪነትና ጸረሰላም ሀይሎች ማስተማር በህጻናቱ ላይ የስነልቦና ጫና ይፈጥራል በማለት ተከራክረዋል።

ሌላው አወዛጋቢ የነበረው ነጥብ ” ኢህአዴግ የ2006 እቅድን ተቋሞችን በድርጅት አባላት በመሙላት እናሳካለን በማለት ያቀረበው ” ሲሆን፣ ተሰብሳቢዎቹ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ሁሉ በድርጅት አባላት ከሞላችሁ የተቃዋሚ ድርጅት አባላትን ምን ልታደርጉዋቸው ነው?” በማለት ጥያቄ አንስተዋል።

ለሱዳን ተላልፎ የተሰጠውን መሬት በተመለከተ የአካባቢው ሰራተኞች የሁለቱን

Ethiopia: Anti-Terrorism Law Among Targets of Addis Ababa Protest

October 4, 2013   

PRESS RELEASE

A major street protest took place in Addis Ababa on 29 September in response to a call from Unity for Democracy and Justice, an opposition political party headed by the previous president, Dr. Negasso Gidada.

The demonstrators protested against the arbitrary detention of journalists, human rights activists and dissidents, which is made possible by the 2009 anti-terrorist law.

Independent estimates put the number of demonstrators at between 12,000 and 15,000 while government sources said they were a few hundred.

The urgent need to amend this repressive law was of one of the recommendations that Reporters Without Borders included in its submission on Ethiopia to the United Nations Human Rights Council for the 19th Universal Periodic Review session to be held between April and May next year.

“The anti-terrorism law is one of the most serious obstacles to the promotion and protection of freedom of information in Ethiopia,” Reporters Without Borders said. “Ever since its adoption, the government has used it as a legal tool to clamp down on dissidents and create a cloud of fear that limits the ambition and activity of the media.

“Without taking any position on the politics of the demonstrators, we urge the government to respond to the widespread demand by concerned citizens and activists for immediate and participatory reform of the anti-terrorism law. We also call on the government to respect the freedom of expression of all news and information providers, regardless of their political views.”
According to the organizers, the demonstration’s aim was not only to
condemn the law but also to demand the release of opposition members and journalists who have been jailed under it. They include activist Eskinder Nega, detained since 15 September 2011 for alleged “links with terrorist organizations and conspiracy to harm national security”.

Journalists Reyot Alemu, winner of the 2013 UNESCO/Guillermo Cano press freedom prize, and Woubeshet Taye, the deputy editor of the Amharic-language weekly Awramba Times, have been detained under this law since June 2011.

Reyot Alemu has been reportedly subjected to mistreatment including solitary confinement, minimal access to medical care and restricted visits from family and friends. They are serving jail terms of five and 14 years respectively, on charges of “conspiring with a terrorist organization and taking part in planning terror attacks”.

Two Swedish journalists working for the Kontinent news agency, reporter Martin Schibbye and photographer Johan Persson, were arrested on 1 July 2011 after illegally entering Ethiopia’s southeastern Ogaden region from Somalia with members of the separatist Ogaden National Liberation Front (ONLF) with the aim of investigating human rights violations in the region. Sentenced to 11 years in prison on a charge of “terrorist activities”, they were released after 450 days in detention thanks to pressure from the international community.

In an interview for Reporters Without Borders, Schibbye said: “The mere fact that these protests are taking place is a positive sign in Ethiopia. This shows the growing implication of the youth, namely through social networks, and their refusal to live in a society where journalists and dissidents can be jailed arbitrarily.”

Ethiopia is ranked 137th out of 179 countries in the 2013 Reporters Without Borders press freedom index.