Tuesday, September 17, 2013

በሐሮ ወንጪ ቅ/ገብርኤል አንድነት ገዳም ላይ የቦምብ ጥቃት ተፈጸመ

september 17/2013

-መነኰሳቱ ገዳሙን ለቀው እንዲወጡ ዛቻና ማስፈራሪያ እየተደረገባቸው ነው -አስተዳደሩ ለመነኰሳቱ ተደጋጋሚ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት አልፈቀደም -‹‹ከዚህ ቦታ ባትመጡ ይሻል ነበር፤ ብትውሉ አታድሩም!›› /ጥቃት ፈጻሚዎቹ/ source Hara Tewahdo በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀ/ስብከት ወንጪ ወረዳ ሐሮ ወንጪ ቀበሌ በሚገኘው የሐሮ ወንጪ መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል አንድነት ገዳም ላይ የቦምብ ጥቃት መፈጸሙ ተገለጸ፡፡ ጥቃቱ የተፈጸመው ጳጉሜ ፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ምሽት 5፡00 ላይ ወደ ገዳሙ ቅጽር በተወረወረው ቦምብ ነው፡፡

በገዳሙ የኪዳነ ምሕረት፣ ቅዱስ ገብርኤል፣ ቅዱስ ዑራኤልና ቅድስት አርሴማ ታቦታት መኖራቸውን የገለጹት የገዳሙ አበምኔት መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ገብረ እግዚአብሔር ኣብርሃ፣ የተወረወረው ቦምብ በገዳሙ ቅጽር ውስጥ ቢፈነዳም በመነኰሳቱ ላይ ያደረሰው ጉዳት አለመኖሩን ለዜና ሰዎች ተናግረዋል – ‹‹ቢፈነዳም እርሱ ከልሎናልና ጉዳት አላደረሰብንም፡፡››
የአንድነት ገዳሙ አስተዳደር በቁጥር 17/2005 በቀን ፭/፲፫/፳፻፭ ለሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ፣ ለወንጪ ወረዳ መስተዳደርና ፖሊስ ጽ/ቤት በጻፈው የድረሱልን ጥሪ÷ ከዚህ ቀደም የገዳሙን ይዞታ በመጋፋት፣ መነኰሳቱና መናንያኑ ገዳሙን ለቀው እንዲሄዱ ተደጋጋሚ ዛቻና ስድብ በማሰማት የሚታወቁ 18 ግለሰቦችን በስም ለይቶ በመዘርዘር በጥቃቱ አድራሽነት እንደሚጠረጥራቸውና በቁጥጥር ሥር ውለው ሕጋዊ ርምጃ እንዲወሰድባቸው ጠይቋል፡፡ በስም ከተዘረዘሩት 18 ግለሰቦች መካከል ጌቱ ታደሰ እና መኰንን ካሳ የተባሉ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች የኾኑ የቀበሌው ነዋሪዎች በዋና አስተባባሪነት ተጠቅሰዋል፡፡Haro Gedam Appeal
ደብዳቤው ‹‹ፀረ ሃይማኖት የኾኑ ግለሰቦች›› ሲል የገለጻቸውና በቡድን የሚንቀሳቀሱት እኒህ አካላት፣ በገዳሙ ላይ ከዘጠኝ ጊዜ በላይ የተለያዩ ጥቃቶችን በገዳሙና በገዳማውያኑ ላይ በማድረስ ንብረት ማውደማቸውንና መነኰሳቱን ማሳደዳቸውን ጠቅሷል፡፡ ‹‹ለቀበሌው ብዙ ጊዜ አመልክተናል፤ ከአቅሜ በላይ ነው በማለቱ መፍትሔ ሳናገኝ እስከ አሁን አለን›› በማለት ከግለሰቦቹ ጥቃት ባሻገር አስተዳደራዊ በደልም እየተፈጸመ እንደሚገኝ ደብዳቤው አጋልጧል፡፡
የወረዳውና ቀበሌው ባለሥልጣናት በተገኙበት ነሐሴ ፳፱ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ከነዋሪው ጋራ በተደረገ ውይይት ሕዝቡ በቡድን እየተንቀሳቀሱ በገዳሙ ላይ ጥቃት የሚያደርሱ ግለሰቦችን የጠቆመ ቢኾንም ተገቢው ርምጃ ባለመወሰዱ÷ ግለሰቦቹ ገዳሙ በሚገለገልበት የውኃ ታንከርና የሶላር ቴክኖሎጂ ላይ ባደረሱት ጉዳት ሲስተሙ ለብልሽት ተደርጓል፤ መነኰሳቱ በሱባኤ ላይ ባሉበት ቀን ለቀን ወደ ገዳሙ ክልል ገብተው በይዞታው ላይ ችግኝ ከመትከል፣ የገዳሙ መውጫና መግቢያ በኾነ ቦታ ላይ አጥር ከማጠር አልተከለከሉም፤ ገዳማውያኑንም ‹‹ከዚህ ቦታ ባትመጡ ይሻል ነበር፤ ለዛሬ ብቻ ነው የምትኖሩት፤ ብትውሉ አታድሩም›› እያሉ በስልክና በአካል በተደጋጋሚ ዛቻና ስድብ ከማስፈራራት አልታቀቡም፡፡
‹‹በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በየዕለቱ ጨለማን ተገን በማድረግ የሚሰነዘርብን ጥቃት በዘመናዊ የጦር መሣርያ ጭምር የታገዘና በቀጣይም እየተጠናከረ እንደሚሄድ ያሳያል›› ያለው የገዳሙ አስተዳደር÷ ነሐሴ ፲፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ከሌሊቱ 7፡40 ዘመናዊ የጦር መሣርያ ታጥቀው ወደ መናንያኑ መኖርያ የመጡት ግለሰቦቹ በመናንያኑ መኖርያዎች ላይ የድንጋይ ውርጅበኝ ማዝነባቸውን፣ ጥይት መተኰሳቸውን፣ ገዳሙን በጥበቃ እንዲያገለግሉ የተቀጠሩ የአካባቢው ተወላጆች ሥራቸውን እንዲተዉ ያልተሳካ ሙከራ ማድረጋቸውን አስታውሷል፡፡
ገዳሙ ይዞታውን በሕግ ያረጋገጠበት ደብተር እንዳለው የጠቀሰው አስተዳደሩ የሹራብ ሽመና፣ የዶርና እንስሳት ርባታን ጨምሮ ራሱን የሚያግዝበት የልማት ጅምሮችና ዕቅዶች ቢኖሩትም ፍትሕ እያጡ በሚሰደዱት መነኰሳት ምክንያት ጥረቱ እየተሰናከለ ነው፤ በገዳሙ ምሥረታ ከነበሩት 15 መነኰሳት መካከልም ጸንተው የቀሩት በጣት የሚቆጠሩ ናቸው፡፡
ወረዳው በተለይ ከ፳፻፬ ዓ.ም ጀምሮ ከገዳሙ ለሚቀርቡለት አቤቱታዎች ሁልጊዜ ተስፋ ይሰጠናል እንጂ የተጨበጠ ነገር አላስገኘልንም፤ ትኩረትም አይሰጡትም ያለው አስተዳደሩ÷ ‹‹መንግሥት ለሃይማኖታችንና ለገዳማችን ልማት የማይተኙልንን ፀረ ሃይማኖት የኾኑ ግለሰቦች››በአስቸኳይ በቁጥጥር ሥር እንዲያውልና ሕጋዊ ርምጃ እንዲወስድባቸው ጠይቋል፡፡
የሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት ጥቃቱ በተፈጸመባቸው አጋጣሚዎች ሁሉ መረጃው እንዲደርሰው ሲደረግ የቆየ በመኾኑ ‹‹ማመልከቻ አስገቡ›› ከሚለው ቸልተኝነቱ ተላቆ ገዳማውያኑ አስፈላጊውን ሕጋዊና አስተዳደራዊ እገዛ እንዲያገኙ ፈጥኖ መንቀሳቀስ ይኖርበታል፡፡
የሐሮ ወንጪ መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል አንድነት ገዳም መቋቋም በ፲፱፻፺፪ ዓ.ም መልአከ ሰላም አባ ገብረ ማርያም ኣብርሃ በተባሉ መነኮስ የተጀመረ ሲኾን የተገደመው ደግሞ ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ሀ/ስብከቱን (ደቡብ ምዕራብ ሸዋን) ከምዕራብ ሸዋ ሀ/ስብከት ጋራ ደርበው በሚያስተዳድሩበት በ፲፱፻፺፱ ዓ.ም. እንደኾነ የገዳሙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
* * *
መንሥኤው አክራሪነት ይኹን ጥቅመኝነት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ በበርካታ መንገዶች እየተፈጸመ ለሚገኘው ግልጽ ጥቃትና አስተዳደራዊበደል የወንጪ ሐሮ መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል አንድነት ገዳም ልዩ አይደለም፡፡ ለመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ፴ኛእና ፴፩ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በቀረቡ የ፳፻፬ ዓ.ም. እና ፳፻፭ ዓ.ም. የአህጉረ ስብከት ሪፖርቶች እንደሚያስረዱት÷ እምነታችኹን ለውጡ እያሉ ማወክ፤ የማንነት/ባህል ወረራ፣ የጠብ አጫሪነት፣ የቅርስ ዝርፊያና የታቀደ ቃጠሎ አለመገታት፣ ማስረጃ በሌለው የይገባናል ጥያቄ ይዞታን መንጠቅ፣ ለሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ሥራና ለልማት የቦታ ጥያቄ ምላሽ አለመስጠት፣ በፍትሕ አካል የተሰጠን ውሳኔ ፖሊስ አለማስፈጸም በየጊዜው እየገጠሙን ያሉ ችግሮቻችን ናቸው፡፡
‹‹የልዩ እምነት ተከታይ የኾኑ ባለሥልጣናት በመንግሥት ስም በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚያደርጉት ተጽዕኖና አድልዎ›› በዓመቱ ካጋጠሙ ችግሮች መካከል በዋናነት ያስቀመጠው የ፳፻፭ ዓ.ም. የአጠቃላይ ጉባኤው ሪፖርት፣ በሲዳማ ሀ/ስብከት ሥር የወንዶ ገነት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን መካነ መቃብር ፕሮቴስታንቶች በግድ እየተቀበሩበት መቸገሩን ይጠቅሳል፡፡ ይኹንና ቤተ ክርስቲያን ከሥር ፍ/ቤት እስከ ሰበር ድረስ ተከራክራ መብቷን ብታስከብርም የፍርድ ውሳኔ የሚያስፈጽም አካል በመጥፋቱ ጉዳዩ ወደ ፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር እንዲሄድ ወይም የክልሉ ፖሊስ ባለመፈጸሙ በሕግ እንዲጠየቅ አለመደረጉን ሪፖርቱ ገልጧል፡፡ በደቡብ ወሎ ሀ/ስብከት ለቤተ ክርስቲያን መሥሪያ ቦታ ሲጠየቅ በጎ ምላሽ አልተገኘም፤ የልማት ቦታም ያለሊዝ ሊፈቀድ አልቻለም፡፡ በምዕራብ ሸዋ ሀ/ስብከት አራት አብያተ ክርስቲያን በመናፍቃን ተዘርፈው እስከ አሁን የፍርድ ቤት አላገኙም፡፡
በመንበረ ፓትርያርክ ደረጃ የተጠቃለለው የ፳፻፬ ዓ.ም. የአህጉረ ስብከቱ ሪፖርት በምሥራቅ ሐረርጌ፣ በሀዲያና ሥልጢ አህጉረ ስብከትየቤተ ክርስቲያን ይዞታ በሌሎች እንደተነጠቀና የመንግሥት ሓላፊዎች ለቤተ ክርስቲያን ፍትሕ እንደነፈጉ፣ ለልማት ሥራ፣ ለግንባታ ፈቃድ መስተዳድሮቹ በቂ ትብብር እንደማያደርጉ ይገልጻል፡፡ በደቡብ ኦሞ ሀ/ስብከት የሦስት አብያተ ክርስቲያን ምእመናን ሰፈር በኢአማንያን በመቃጠሉ ምእመናን አካባቢያቸውን ለቀው ለመሰደድ ተገደዋል፡፡
በደቡብ ምሥራቅ መቐለ ሀ/ስብከት ከካህናት ይኹን ከምእመናን የቅ/ሲኖዶስ መመሪያ ተላልፈውና የቃለ ዐዋዲ ድንጋጌ ጥሰው ሲገኙ ለሚሰጣቸው የቅጣት ውሳኔ አፈጻጸም ፖሊስ ከፍ/ቤት ትእዛዝ ካልተሰጠኝ አላስፈጽምም ብሏል፡፡ በጅማ ሀ/ስብከት እምነታችሁን ለውጡ እያሉ ምእመናንን ማወክ፣ በሰሜን ወሎ እና በመተከል አህጉረ ስብከት የፕሮቴስታንቶች ትንኮሳና የባህል ወረራ፣ የተሐድሶ መናፍቃን በጥቅም ያስከዷቸው ‹ካህናት› ተመልሰው የአገልግሎት ዕንቅፋት መፍጠራቸው በሪፖርቱ ዝርዝር ተጠቅሷል፡፡
በየአህጉረ ስብከቱ በገዳም፣ ደብርና ገጠር ሥሪት የሚገኙ አብያተ ክርስቲያን ይዞታቸውን በባለቤትነት መታወቂያ ካርታ ለማረጋገጥ የሚያደርጉት ጥረትና ያስገኙት ውጤት የሚያስመሰግናቸው ነው፡፡ ይዞታን በባለቤትነት መታወቂያ ካርታ ማረጋገጡ አብያተ ክርስቲያኑ ከሰበካ ጉባኤ ዓመታዊ አስተዋፅኦ፣ ከሙዳይ ምጽዋትና ስእለት ገቢዎች ባሻገር ማኅበረ – ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ባላቸውና መንፈሳዊ አገልግሎቱን የሚያጠናክሩ የራስ አገዝ ልማት እንቅስቃሴዎችንም ለማድረግ ወሳኝነት ይኖረዋል፡፡ ይኹንና በአንዳንድ አጋጣሚ በጉልሕ እንደሚስተዋለው በመንግሥት መዋቅር ባሉና የእነርሱን ብልሹ አሠራር ተገን ባደረጉ ግለሰቦችና ቡድኖች በየጊዜው የሚፈጸመውን ግልጽ ጥቃትና አስተዳደራዊ አድልዎ ለመግታትና በብቃት ለመመከት ቅ/ሲኖዶስ በጥብቅ ሊመክርበትና የሚመለከተውን የመንግሥት አካልም በማትጋት የአገልጋዮችንና ምእመናንን መብት ሊያስከብር ይገባል፡፡
በሰላምና ልማት ጉዳዮች ላይ አብሮ መሥራት፣ የዜጎችን ሰላም፣ ደኅንነት፣ ማኅበራዊ ኢኮኖሚያዊ ዋስትና ማረጋገጥ የመንግሥት ግዴታ እንደኾነ የሚገልጹ መንግሥታዊ ሰነዶች÷ መንግሥታዊ አገልግሎትን የሚሰጥ ማንኛውም ሓላፊ ይኹን ሠራተኛ ተግባሩን ከራሱም እምነት ጭምር ገለልተኛ በኾነና በእኩልነት መንገድ መካሄዱን ማረጋገጥ እንደሚገባው ያሳስባሉ፡፡ ሓላፊዎቹና ሠራተኞቹ ገለልተኝነትን ለድርድር ከሚያቀርቡ ስሕተቶችን መጽዳታቸውን፣ የአንዱ ወይም የሌላው እምነት ውግንና እንዳላቸውና አድልዎ ለመፈጸም የተዘጋጁ ከሚያስመስሏቸው አቀራረቦች ራሳቸውን መጠበቃቸውን፣ የሕዝቡን ከፍተኛ አመኔታ ባተረፈ አኳኋን ሥራቸውን ማከናወናቸውን ማረጋገጥ ይገባቸዋል፡፡
በተጨባጭ ሃይማኖታዊ ውግንና የሚያሳዩ አመራሮች እንዲሁም ከጥንቃቄ ጉድለት የሃይማኖት አድልዎ እንዳለ አስመስለው የሚያሳዩ ድርጊቶች/ዝንባሌዎች በአፋጣኝ መስተካከል እንደሚኖርባቸው የሚያሳስቡት ጽሑፎቹ፣ ‹‹ካልተስተካከሉም ከመንግሥት ሓላፊነት ተነሥተው የሃይማኖት መምህርነትን ወደሚቀጥሉበት አቅጣጫ ማመላከት ይገባል›› በማለት የመንግሥትን አቋም ያስቀምጣሉ፡፡
በቀበሌ ይኹን በወረዳ የመስተዳድሩ አንዳንድ ባለሥልጣናት አይዞህ ባይነትና ሽፋን ያላቸው የሚመስሉትና የሐሮ ወንጪ ቅ/ገብርኤል አንድነት ገዳም ንብረትን በተደጋጋሚ ከማውደምና መነኰሳቱን ከማሳደድ አልፈው የቦምብ ጥቃት ለማድረስ የተደፋፈሩት የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ የኾኑ ግለሰቦች፣ መንግሥት በጽሑፉ ያተተውን የፀረ አክራሪነት አቋምና እንቅስቃሴ በግልጽ የሚፃረሩ ናቸው፤ በድብቅም በገሃድም የሚደግፏቸው ባለሥልጣናትም ከጥቃት አድራሾቹ ጋራ ‹‹ዘይትና ሞተር ኾነው የሚሠሩ››፣ ዋጋ የሚያስከፍሉ እንጂ በአስተዳደር ሓላፊነታቸው የሰላምና መረጋጋት ምንጭ ሊኾኑ አይችሉም፡፡
ስለዚህም አፋጣኝ የማስተካከያ ርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችንም ችግሩ በየደረጃውና በወቅቱ እልባት እንዲሰጠው ከማድረግ ባሻገር ተቋማዊ ህልውናዋንና ነጻነቷን በሚያስከብር አኳኋን መሠረታዊ መፍትሔ እንዲያገኝ በከፍተኛ አመራሯ አማካይነት መንቀሳቀስ ይገባታል፡፡ ሳይዘገይ ዛሬውኑ!

734 ሚሊዮን 600 ሺ ብር የመዘብሩ የስራ ሃፊዎች አለመቀጣታቸውን መረጃዎች አመለከቱ

መስከረም ፮(ስድት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲስ ከስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሺን የተገኝው መረጃ እንደሚያመለክተው ከተለያዩ የፌደራል መስሪያ ቤቶች 734 ሚሊዮን 6 መቶ ሺ ብር የመዘብሩ የስራ ሃፊዎች በተጣራ መረጃ ክስ ቢመሰረትባቸውም የውሳኔ ቅጣት እንዳልተላለፈባቸው ታውቋል።
ለረጅም ጊዜ በተደረገ ምርመራ ተጣርቶና መስረጃ ተገኝቶባቸው ከ2004 ዓም ጀምሮ ክስ የተመሰረተባቸው የተለያዩ የሙስና ወንጀሎች የውሳኔ ሀሳብ እንዳልተላለፈባቸው ከመሰሪያ ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ላይ  94 ሚሊዮን 300 ሺ ብር  ከትምህርት ተቋማት ግንባታ ጋር በተያያዘ የተፈጸመ የሙስና ወንጀል ምርመራ ተጠናቆ ክስ ቢመሰረትም በቂ ውሳኔ ሳያገኝ ቀርቷል።
ከአራዳ ክ/ከተማ መልሶ ማልማት ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ  ህገወጥ የካሳ ክፍያ በመፈጸሙ ሦስት የምርመራ መዝገቦች ተጠናቀው በ2004 ዓ.ም ክስ ቢመሰረትም የቅጣት ውሳኔ አላገኝም።
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሀራጅ ሽያጭ ጋር በተያያዘ የ12 ሚሊዮን ብር እና የ34 ሚሊዮን ብር ህገወጥ ብድርን እንዲፈፀም ያደረጉ አካላት በቂ የሰነድ ማስረጃ እንደተገኘባቸው ቢገለጽም እርምጃ ሳይወሰድ ቀርቱዋል፡፡
በቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ከመመሪያና አሰራር ውጪ ለግለሰቦች የስልክ መስመር እንዲዘረጋ በማድረግ በህገወጥ መንገድ ወደ ውጭ ሀገር ስልክ በማስደወል በመስሪያ ቤቱ ላይ 14 ሚሊዮን ብር ጉዳት መድረሱን የተመለከተ  ሁለት ምርመራዎች ተጠናቀው በክስ ሂደት ላይ ሲሆኑ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች በሚፈጥሩት ጫና ክሱ እየተጓተተ ነው።
በትግራይ ክልል የሚገኘው በሼባ የብረታ ብረት ማቅለጫ ፋብሪካ ለፋብሪካው የተዘረጋው የኤሌክትሪክ ፍጆታ ቆጣሪ መሳሪያ ሥራውን በአግባቡ እንዳይሰራ በማድረግ መብራት ሀይል ከሽያጭ ማግኘት ይገባው የነበረውን ገቢ በማስቀረት በአገር ላይ  65 ሚሊዮን 300 ሺ ጉዳት በመድረሱ ምርመራው ተጣርቶ ለወሳኝ አካል ቢተላለፍም ውሳኔ ሳያገኝ ቀርቷል።
በተመሳሳይ በኦሮምያ ክልል በደብረዘይት የሚገኝ የግል የብረታ ብረት ማቅለጫ ፋብሪካ ለፋብሪካው የተዘረጋው የኤሌክትሪክ ፍጆታ ቆጣሪ መሳሪያ ሥራውን በአግባቡ እንዳይሰራ በማድረግ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ከሽያጭ ማግኘት ይገባው የነበረውን ገቢ በማስቀረት በአገር ላይ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረሱ ምርመራው አጣርቶ የፀረ ሙስና ኮሚሺን ቢልክም የፍትህ መጓተት ታይቶበታል።
በመብራት ሀይል አላግባብ በ 248 ሚሊዮን 900 ሺ ብር የተፈጸመ የ4 ሺ4 መቶ 70 ትራንስፎርመሮች አለም አቀፍ ግዢ በሁለት የምርመራ መዝገቦች የተጣራ ቢሆንም ውሳኔ አልተሰጠበትም።
ንብረቱ የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የብረት ማኑፋክቸሪንግ ማሽን ግንባታ ኢንዱስትሪ የሆነ ግምቱ  4 ሚሊዮን 7 መቶ ሺ የሆነ የብርና የነሃስ ሜዳልያ ከግምጃ ቤት በመጥፋቱ ተመርምሮ የተረጋገጠ ቢሆንም ውሳኔ አላገኘም።
በተንዳሆ ፕሮጀክት ከግብር ጋር በተያያዘ በመንግስት ላይ     ጉዳት በመድረሱ ምርመራው ተጠናቆ ክስ ተመስርቷል። በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ በሊዝ እንዲስተናገድ የተወሰነለትን የመኖሪያ ቤት ኅ/ሥ/ማ ያለ ሊዝ በማስተናገድ የተሰጠ 30 ሺ 3 መቶ 32 ካ/ሜ ቦታ ምርመራ ተጠናቆ ክስ የተመሰረተ ቢሆንም ውሳኔ አላገኘም።
ለብሄራዊ ባንክ በሽያጭ ከሚቀርብ ወርቅ ጋር በተያያዘ የባንኩ ሰራተኞችና ነጋዴዎች በመመሳጠር 63 ሚሊዮን ብር በመመዝበር አስቀድሞ ተከሰው የነበሩ አሁን ጥፋተኛ ተብለው ጉዳዩ ለቅጣት ውሳኔ ተቀጥሯል።
በቂርቆስ ክ/ከተማ በልማት ተነሺዎች ስም ከመመሪያ ውጪ ግምቱ 13 ሚሊዮን 3 መቶ ሺ የሆነ 2, ሺ 1 መቶ 45 ካ/ሜትር ትርፍ መሬት አላግባብ በተሰጣቸው እና ከካሳ ክፍያም ጋር በተያያዘ  5 ሚሊዮን 2 መቶ ሺ ብር በትርፍ የተከፈላቸው ግለሰቦች ጉዳይ፤ በኢትዮጵያ የመድሃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ ሀዋሳ ቅርንጫፍ በእምነት ማጉደል ወንጀል ግምቱ ብር 1 ሚሊዮን 7 መቶ ሺ የሆነ መድሃኒት ተመዝብሮ ለግል ጥቅም መዋሉ እና በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በተደረገ የ100 ሚሊዮን የእህል ግዢ ጨረታ ግለሰቦች ሀሰተኛ ሰነድ በማቅረብ ጨረታውን ያሸነፉ መሆኑ በተደረገው ምርመራ በመረጋገጡ ጨረታው እንዲሰረዝና በግለሰቦቹ ላይ ክስ እንዲመሰረት የተደረገባቸው በጥቅሉ ከህዝብ በግብር የተሰበሰበ በርካታ ገንዘብ በአንድም በሌላ መልኩ በከፍተኛ አመራሮች ተጽእኖ በ2004 እና በ2005 ዓ.ም ተጣርቶ ለፍርድ ሰጭው አካል ቢተላለፍም ውሳኔ ሳይሰጥባቸው ቀርተዋል፡፡
ከ 7 መቶ ሚሊዮን  ብር በላይ የመዘበሩ የስራ ሃፊዎች አልተቀጡም ሲል ከፀረ ሙስና ኮሚሺን የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡፡ አሀዙ በ2005 የተፈጸመውን ሙስና አላካተተም።
ባለፉት 22 የኢህአዴግ የአገዛዝ አመታት የተፈጸሙና በጸረ ሙስና ኮሚሽን ያልተጣራ በሙስና የተዘረፈ ገንዘብ በቢሊዮኖች እንደሚቆጠር ይገመታል።

Monday, September 16, 2013

“የበሰበሱት” ህወሃት እና ሻዕቢያ


አንዱ ሌላውን የማጥፋት እሽቅድድም!


አምባገነነኖች ከሚታወቁበት አንዱና ዋንኛ መለያቸው መካከል ሁለተኛ ሰው አለማዘጋጀታቸው ነው። አቶ መለስ በድንገት ሲስፈነጠሩ በውል የታየው አስከሬን ደብቆ ድብብቆሽም የዚሁ ውጤት ነው። ኢሳያስ ከስልጣን ቢወገዱ ማን ይተካቸዋል? የሚለው ችግርም ጎልቶ የሚታየው ከዚሁ የአምባገነኖች በሽታ አንጻር ነው።
ግጭትና ችግር ከመፈጠሩ በፊት የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ደወል የሚያንጫርረው ዓለምአቀፉ የግጭት ቡድን (International Crisis Group) ፍርሃቻም ከዚሁ የመነጨ ይመስላል። በኤርትራ ህዝቡ በቃኝ ወደ ማለቱ ደረጃ መቃረቡን የሚጠቁመው የዘንድሮው ዓመት ሪፖርት ኤርትራ በቅርቡ መንግስት አልባ የመሆን እድሏ ሰፊ እንደሆነ ያወሳል። በቅርቡ “የሚከሽፉ መንግስታት” በሚል ስማቸው ከተዘረዘሩት ውስጥ አገሮች መካከል ኢትዮጵያም ተመልክታለች።
tplf-vs-eplf
እኩል ወደ ስልጣን የመጡት ሻዕቢያና ወያኔ ደረጃቸው ቢለያይም ሊድኑ በማይችሉበት ደረጃ መበስበሳቸው በገሃድ የሚታይ እውነት እንደሆነ አብዛኞች ይስማማሉ። ከበሰበሱበት ባህርና ችግር ለመውጣት አግባብ ያለውን መንገድ ከመከተል ውጪ አንዱ ሌላውን ቀድሞ ለማጥፋት እሽቅድድም መርጠዋል። የዚሁ የእሽቅድድማቸው መድረሻ መሰረት ደግሞ አንዱ ለሌላው ተቃዋሚ ምርኩዝና አጋር የመሆንና አንዱ በሌላው መንኮታኮት የግል ትርፍን አስጠብቆ ለመዝናናት እንጂ ህዝብን ማዕከል ያደረገ አይደለም።
ኤርትራ “በነጻ” ምድሯ ላይ “አቅፋና ደግፋ” የያዘቻቸው የኢህአዴግ ተቃዋሚዎች የሚታይ ውጤት ባለማስመዝገባቸው ተግባር ለሚናፍቁ ወገኖች ጉዳዩ “ከበሰበሰ ባህር” አይነት ሆኖባቸው ዓመታት ተቆጥረዋል። ሰሞኑንን ከኢሳት ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት የግንቦት7 ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ይፋ ያደረጉት መረጃ አዲስ የውይይት አጀንዳ ዘርግቷል።
በኤርትራ መንግስት በኩል የሚደረገው ድጋፍ “ባለ አራትና አምስት ኮከብ ሆቴል ውስጥ ተቀምጦ የመታገል ያህል ነው” በማለትandargachew ያሞካሹት አቶ አንዳርጋቸው “ታይቶ የማይታወቅ፣ ከሚገባው በላይ የበዛ” ሲሉ የገለጹት የኤርትራ ድጋፍ አስቀድሞም ቢሆን ውጤት ማስመዝገብ ያልቻለው ኤርትራ በከተሙ ተቃዋሚዎች ችግር እንጂ በኤርትራ መንግስት እንዳልሆነ በቅርብ ሆነው ማየትና መረዳታቸውን በመግለጽ ምስክርነት ሰጥተዋል።
ይህ መረጃ ከተሰራጨ በኋላ ከኢህአዴግ ወገን ሁለት አንኳር ጉዳዮች ተሰምተዋል። በኤርትራ ላይ መከላከልን መሰረት ያደረገው ፖሊሲ “ተመጣጣኝ ርምጃ መውሰድ” በሚል በመቀየሩ ኢህአዴግ ባልተጠበቀ ወቅትና ጊዜ አስቀድሞ ጥቃት ለመሰንዘር እንደሚችል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ለኤርትራ ያዘጋጀላትን አዲስ የአስተዳደር ቅርጽ ተግባራዊ የሚያደርጉ ድርጅቶችን ወደ ግንባር መግፋት የሚሉት የመጀመሪያዎቹ ሲሆኑ ሁለተኛው ግን ከወትሮው ለየት ያለ ሆኖ ተገኝቷል።
አዲስ ራዕይ የሚባለው የኢህአዴግ ልሳን ይፋ እንዳደረገው ወደ ጎረቤት አገራትም ሆነ ሌሎች አካባቢዎች የሚሰደዱ ዜጎች በተቃዋሚ ወገን ለውትድርና እየተመለመሉ እንደሆነና ይህ ሁኔታ በዝምታ ከታየ ስርዓቱ ችግር ሊገጥመው እንደሚችል አመላክቷል። ከዚህም ጋር ተያያዥነት ባለው መልኩ ሌሎች ወገኖች ግብጽ እጇን የዘረጋችላቸው ክፍሎች ስለመኖራቸው መረጃዎች እንዳሉ ለማሳበቅ ሲሞክሩ ሰንብተዋል። ከዚህ አንጻር ቀደም ሲል ከነበሩት የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች በተለየ መልኩ ኢህአዴግ ስጋት ውስጥ ስለመሆኑ ይሰማል።
ከላይ የቀረቡት ሁለቱ አንኳር ጉዳዮች መላምት ሳይሆኑ በውል የተቀመጡ እውነታዎች ናቸው። ኢህአዴግ አደራጅቷቸው የስደት ፓርላማ የመሰረቱ የኤርትራ ተቃዋሚዎች ዝግጅታቸውን ተያይዘውታል። እነዚህ የብሔር ድርጅቶች የሚበዙበት ጥምረት ህወሃት እንደሚያስበው ወደ ስልጣን ከደረሱ ኤርትራን ቢያንስ በስምንት “ብሔር ተኮር” ክልል ይከፍሏታል። በአሜሪካ ኒው ጀርሲ ጠቅላይ ግዛት ሮዋን ዩኒቨርስቲ የማርኬቲንግ መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር በርሀ ሃብተጊዮርጊስ በ9/8/2010 ለጀርመን ሬዲዮ እንደገለጹት “ኢትዮጵያ በራሷ ልክ የተሰፋ መንግሥት ነው ለማቋቋም የምትፈልገው፤ ይህ አይሳካም” በማለት ተናግረው ነበር። መምህሩ አያይዘው በቋንቋና በብሔር ኤርትራን የመተልተል እቅድ መያዙንም አጥብቀው ተናግረዋል። ህወሃት ይህንኑ አላማውን ለማሳካት ሲል ከሰላማዊ ድርድር ማፈግፈጉን አመልክተዋል።
ኤርትራ ጨለመች – “ከወያኔ ይልቅ ጨለማ !!”
በበርካታ የኤርትራ ተወላጆች ዘንድ አንድ ትልቅ ስጋት አለ። በኤርትራ ቆላማ ክፍል የሚኖሩ ሙስሊሞች ቋንቋቸው አረቢኛ እንዲሆን ምኞት አላቸው። ቁጥራቸው ከክርስቲያኑ ስለሚበልጥ ይህንኑ የብሔር ጥያቄ ላይ የተንጠለጠለ በራስ ቋንቋ የመስራት መብት እንዲከበር ይፈልጋሉ። ከዚህም በላይ በደገኞች እጅ የተያዘውን የስልጣን ሞኖፖሊ አጥብቀው ይቃወሙታል።
ከሐምሌ 24 – ነሃሴ 3 ቀን 2010 ዓ ም ድረስ “ብሔራዊ ጉባኤ ለዴሞክራሲ ለውጥ” በሚል ርዕስ አዲስ አበባ ተደርጎ በነበረው ጉባኤ ጥምረት የፈጠሩት አስር ተቃዋሚዎች ከበርካታ ጭቅጭቅ በኋላ አቋም አድርገው የወሰዱት “የቋንቋና የብሔር መብት ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ ነው” በሚል ነው። በወቅቱ የተያዘውን አቋምና የጉባኤው የመጨረሻ ውሳኔ ይፋ ሲሆን የተገለጸው ኢሳያስ ሲወገዱ ስልጣን ተረክቦ ኤርትራን የሚያስተዳድር የስደት ፓርላማ ለማቋቋም ነበር።
eritrea-opposition-conferenceከ330 በላይ ተወካዮች ከተገኙበት ስብሰባ ውስጥ 55 አባላት ያሉበት አደራጅ ኮሚሽን በማቋቋም የተጠናቀቀውን ጉባኤ አስመልክቶ ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ “ተቃዋሚዎች አቋማቸው ግልጽ አይደለም” በማለት ለመቃወም ጊዜ አልወሰዱም። ከእርሳቸው በተለየ ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ትምባሆ ሞኖፖል ዋና ስራ አስኪያጅና የንግድ ምክር ቤት ጸሐፊ የነበሩት አቶ ረዘነ ሃብቱ በበኩላቸው ህግና ህገ መንግስት እንደማያውቅ የጠቀሱት ስርዓት አሁን ባሉት ተቃዋሚዎች ሊተካ እንደሚችል እምነታቸውን ያስቀምጣሉ።
በኮታ የሚሸጥ ቁራሽ ዳቦ ለመግዛት ሌሊት የሚሰለፉት የኤርትራ ተወላጆች፣ ኑሮ ቢግልባቸውም፣ የመኖር አቅም ቢያጡም፣ ውትድርናና የነጻ አገልግሎት ቢያንገሸግሻቸውም፣ በነጻነት የመደራጀትና በሰውነት ብቻ ሊያገኙት የሚገባቸው መብቶች ባይኖሩዋቸውም፣ ከሁሉም በላይ አሁን መብራት በሳምንት በፈረቃ አንድ ጊዜ ቢደርሳቸውና በሳምንት ስድስት ቀን በጨለማ ቢቀመጡም “ወያኔ” ያበጀው ስርዓት እንዲመሰረትላቸው አይመኙም።
አስገራሚው አቋማቸው ሁሌም የሚመዘነው ከ”ወያኔ” ጋር እንጂ ከጥቅል የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንዳልሆነ በይፋ ይናገራሉ። የህወሃት ሰዎችና ደጋፊዎችም ይህንን አቋም ይረዱታል። ኢሳያስን ለማስወገድ የሚደረገው ጥረት በተፈለገው ፍጥነት ሊተገበር ያልቻለበት አንዱና ትልቁ ምክንያት ይህ በመሆኑ “ኢሳያስን ከአህጉርና ከዓለም ኣቀፍ ፖለቲካ በመነጠል አስልሎ ማጥፋት” የሚለውን ሁለተኛው ስልት ኢህአዴግ ዘግይቶም ቢሆን ለመጀመር መገደዱንና በስተመጨረሻ ውጤት እንዳገኘበት ይገልጻሉ።
በዚሁ የማስለል ስልት ወንበራቸው የተፈረካከሰው አቶ ኢሳያስ “የኤርትራ ወጣቶች እንዲሰደዱ የአሜሪካ የስለላ ድርጅት እየሰራ ነው” በማለት በጃንዋሪ 2013 የፈረንጆች አዲስ ዓመት ተናግረዋል። ችግር የሚቆላውን ህዝብ “የኤርትራ ህዝብ ችግር የለበትም ቀልማጣ ነው” ሲሉም አሙቀውታል። ኤርትራ በውጪ አገር መንግስታትና በኢትዮጵያ አማካይነት ጫና እንደተደረገባት መሆኑና መሸሸግ አልተቻላቸውም። ሰሞኑንን ለቅዱስ ዮሐንስ በቃለ ምልልስ መልክ ለህዝባቸው የደሰኮሩት ኢሳያስ የአገሪቱ ወጣቶች ለመኮብለላቸው ምክንያቱ ችግር ሳይሆን ኢትዮጵያንና አሜሪካንን ግንባር ቀደም ተጠቃሽ አድርገዋል። የኢሳያስ ደጋፊ ምሁራን ሳይቀሩ ህወሃት ኤርትራን ከዓለምአቀፍ መድረክ በመነጠል እንደጎዳቸው ማመናቸውን የሚገልጹ እንደሚሉት ህወሃት “የኤርትራን መንግስት በሚገባ አስልሎታል። አቅም አልባና የቀጣናው ተራና ውዳቂ፣ ህግና ወግ የማያውቅ ዱርዬ መንግስት ተደርጎ እንዲሳል አድርጎታል” ይላሉ። አያይዘውም “ህወሃት በግብሩ ከሻዕቢያ ባይሻልም በጉዳይ አስፈጻሚነትና አፍሪካ ህብረትን በወጉ መቆጣጠር በመቻሉ የውጭ ገጹን ማሳመር በመቻሉ ከሻዕቢያ የተሻልኩ ነኝ ብሎ ማሳመን ችሏል፡፡”
eritreans in line
በኤርትራ የዳቦና ወተት ወረፋ (ፎቶ: ኒው ዮርክ ታይምስ)
በዚሁ መነሻና በውስጥ የማህበራዊና የኢኮኖሚ ቀውስ እየወላለቁ አሉት ኢሳያስ ከስጋትና ከፍርሃቻ እንደሆነ በሚያስታውቅ ጎልዳፋ ፍልስፍና “ኤርትራ በኢትዮጵያ ቅኝ ግዢ ስር ነበረች ተብሎ በተደጋጋሚ ሲወራ ለወያኔዎች ኩራት ሆኗቸዋል” ሲሉ ለተደገሰላቸው ድግስ የኤርትራ ተወላጆችን እልህ ውስጥ የሚከትት ንግግር አሰምተዋል። በርካቶች ኢትዮጵያን ዝቅ አድርገው የተመለከቱ መስሏቸው ቢናደዱም አቶ ኢሳያስ ግን በሳቸው ዘመን ኤርትራ በህወሃት ቅኝ ግዢ እንዳትያዝ ማስጠንቀቂያ ማስተላለፋቸው እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎች ለጎልጉል ተናግረዋል። ጳጉሜን 2፤ 2005ዓም (በሴፕቴምበር 7፤ 2013) አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ኤርትራ ለኢትዮጵያዊያን ነጻ መውጣት ሊታመን የማይችል ድጋፍ እየሰጠች ነው ባሉበት ማግስት ኢሳያስ “ለመሆኑ ኢትዮጵያ የተፈጠረችው መቼ ነው?” በማለት እንደ አንድ ታሪክ አልባ አገር አበሻቅጠው ማቅረባቸው ቀደም ሲል የነበረውን ቅሬታና ጥርጣሬ እንዲያገረሽ አድርጎታል የሚሉ ወገኖችም አልታጡም።
ህወሃት ልክ እንደነ ኦህዴድ፣ ብአዴን፣ ደኢህዴን እና መሰል ድቃይ ድርጅቶች ኤርትራን እንዲመሩ ያደራጃቸውን ክፍሎች አስተምሮና አንቅቶ ከመዘጋጀቱ ጋር ተዳምሮ ኢሳያስን ጤና የነሳቸው ጉዳይ ዓለምአቀፉ የግጭት ቡድን (International Crisis Group) በዝርዝር ያስቀመጣቸው መሰረታዊ ጉዳዮች የኤርትራን መንግሥት በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ስለከተቱት ነው። በጦር አመራሮችና በፖለቲካ ክንፎች ውስጥ የተከሰተ አለመተማን፣ ተሞክሮ ከሸፈ የተባለው መፈንቅለ መንግሥት፣ የማስታወቂያ ሚኒስትር የነበሩት አሊ አብዶን ጨምሮ የቅርብ ታማኞች መክዳት፣ የወጣቶች አገር ጥሎ መኮብለል፣ እስር፣ የኑሮ ውድነት፣ የምንዛሬ ችግር መባባስ ህወሃት ለሚወስድባቸው ማንኛውም ርምጃ መቋቋም የሚችሉበት ትከሻ ስለሌላቸው እንደሆነ ከግምት በላይ አስተያየት የሚሰጥበት እውነት ነው። በስንቅና ትጥቅም ደረጃ አይመታጠኑም የሚሉ ባለሙያዎችም ካላይ በቀረበው ሃሳብ ይስማማሉ።
ምንም ሆነ ምን ህወሃት ኢሳያስን አስወግዶ አሻንጉሊት መንግስት ከሚያስቀምጥላቸው ይልቅ የኤርትራ ተወላጆች ከኢሳያስ ጋር በመሆን መሰቃየትን እንደሚመርጡ ቀደም ሲል ታጋይ የነበረችና አሁን በስደት ላይ የምትገኝ የኤርትራ ተወላጅ ትናገራለች። ባልደረባዋም ሃሳቧን ይጋራታል። “በየትኛውም መመዘኛ ህወሃት (ወያኔ) ኤርትራ ላይ አሻንጉሊት መንግስት አስቀምጦ አይገዛንም። ኢሳያስ ይሻለናል። በብሄር ሊበጣጥሱንና እኛ በማያቋርጥ ችግር ውስጥ ስንኖር እነሱ ሊስቁብን ነው” በማለት አንገቱን እያወዛወዘ አስተያየቱን ሰጥቷል። ሁለቱም ስማቸው እንዳይገለጽ ጠይቀዋል።
ሻዕቢያ ኢትዮጵያ ጠንካራ ሉአላዊ አገር እንድትሆን ይፈልጋል?
“ለኢትዮጵያዊያን አገራቸው ክብራቸው ናት። ማንም በታሪካቸውና በማንነታቸው እንዲሳለቅ አይወዱም። መለስ የሚባሉት ክፉ መሪ ህዝብ እንደረገማቸው ያለፉት ኢትዮጵያንና ታሪኳን ከፍ ዝቅ በማድረግ በማራከሳቸው ነው። ታሪካችንን ወደ 100 ዓመት በማኮሰስ፣ ሰንደቃችንን ከተራ “የመገነዣቸው እራፊ” ጋር በማመሳሰላቸው ሲተፉና ሲወገዙ ኖረው መሞታቸውን በማውሳት  ኢሳያስ ደፍረውና ታብየው “ለመሆኑ ኢትዮጵያ ማን ናት?” ለማለት የተነሱበትን ምክንያት በማስቀደም አስተያየታቸውን ይጀምራሉ።
“በስብሶ ሊወድቅ የደረሰ ስርዓት የሚመራ፣ በልመናና ከስደት በሚገኝ ቀረጥ የምትተዳደር፣ ዳቦ በራሽንና በወረፋ የሚሸጥበት አገር እየመሩ፣ በ20ኛው ክፍለዘመን በኩራዝ የምትበራ አገር ይዘው  ራሱን ችሎ የሚኖርን ህዝብ መተንኮስ አግባብ አይደለም” በሚል ኢሳያስን የተቃወሙ ጥቂት አይደሉም። የኢሳያስ ንግግር በስደት “መብታቸው ተከብሮ” አዲስ አበባና የተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚኖሩ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ የራሳቸውን አገር ሰዎች ጭምር የሚያስደስት እንዳልሆነ፣ ይልቁኑም የሚያሸማቅቅ እንደሆነ ነው የሚሰማው። የዚያኑ ያህል “ጨንቋቸው ነው። ምን ይበሉ? አዲስና ለህዝብ ጥቅም ያለው ወሬ ሲጠፋ ከታሪክና ከምኞት ጋር መጣላት የጊዜው አማራጫቸው ነው” በማለት ያጣጣሏቸውና ምላሽም እንደማያስፈልጋቸው የገለጹ ጥቂት አይደሉም።
አቶ ኢሳያስ ሲፈልጋቸው “ኢትዮጵያ በቅኝ ስትገዛን ኖራለች፤ ነጻነት እንፈልጋለን” በሚል በሺህ የሚቆጠሩ ንጹሃን ህይወትን የገበሩት ሳያንስ ዛሬ፣ “ለመሆኑ ኢትዮጵያ መቼ ነው የተፈጠረችው” ሲሉ ጠይቀው “ኢትዮጵያ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ድል የተቀዳጁ ለጥቅማቸው ማስጠበቂያ ሲሉ የፈጠሯት አገር መሆኗን ነው እኔ የማውቀው” ማለታቸው ኢሳያስ መቼም ቢሆን ኢትዮጵያ ላይ ያላቸው አመለካከት የጸዳ እንዳልሆነ የሚያረጋግጥ ይሆናል። ከዚህ አንጻር ብቻ ሳይሆን በበርካታ ጉዳዮች ችግር ቢኖርብንም “ኢሳያስን ጠንቀቅ” የሚሉ ወገኖች ለክብር ቅድሚያ እንዲሰጥ ይመክራሉ።
-   ማታ ነው ድሌ” ማን?
“ሻዕቢያና ኢህአዴግ ተመሳሳይ ፖሊሲ መከተል ጀምረዋል” የሚሉ የጎልጉል የዘወትር አስተያየት ሰጪ “ኢህአዴግ ሶማሊያ ላይ የሚከተለውን ፖሊሲ ሻዕቢያም እየተገበረው ነው” ይላሉ። አያይዘውም “ኢህአዴግ በሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር መስራትና፣ ኢትዮጵያ የምታስቀምጠውን አጀንዳ የሚሸራርፍ መንግስት በማዕከላዊ መንግስትነት እንዲቀመጥ እንደማትፈልግ ሁሉ፣ አሁን አሁን ኤርትራም የጀመረችው የኢትዮጵያን ተቃዋሚዎች በዚሁ መልኩ የማደራጀት ስራ ነው” በማለት ይዘረዝራሉ።
በሶማሊያ ከኢህአዴግ ሃሳብ ውጪ ለመንቀሳቀስ የሚያስብ ማዕከላዊ መንግስት ብቅ ቢል ወዲያው መብራቱን ያጠፉበታል። በደቡብ ሱዳን ያለው እውነታ ተመሳሳይ ነው። ደቡብ ሱዳን እየተመራች ያለችው በኢህአዴግ፣ በተለይም በህዋሀት ሰዎች መሆኑንን የሚያመለክቱት አስተያየት ሰጪ፣ “ያለ ምንም ማመንታት ኤርትራ ከውስጥ ያለባት ችግሯ፣ በዓለምአቀፍ ደረጃ የደረሰባት ኪሳራና በመንግሥቱ ውስጥ ከተፈጠረው መፈረካከስ ጋር ተዳምሮ የጎረቤቶቿ እድል ይገጥማታል። ኢሳያስ ያበቃላቸዋል። ኢህአዴግ የሰራው መንግስት ይቋቋማል” ብለዋል።
ኢህአዴግ በአገር ውስጥ ያለበት ቀውስ ቀኑን ጠብቆ የሚፈነዳ እንደሆነ ያመለከቱት አስተያየት ሰጪ “የተለየ ነገር ካልተፈጠረ በስተቀር ኢሳያስ አሁን ባሉበት ደረጃ ለኢህአዴግ ስጋት አይሆኑም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ኢህአዴግ በግፍ፣ በኑሮ ውድነት፣ ፍትሃዊ ባልሆነ የሃብት ክፍፍል፣ በሙስና፣ ወዘተ የፈጠረው ምሬት ከመጠን ያለፈ ቢሆንም እንደ ሻዕቢያ በቀላሉ የሚናድበት ደረጃ ያለ እንደማይመስላቸው የገለጹት አስተያየት ሰጪ “ኢህአዴግን ከምንም በላይ የሚያሰጋውና የሚያስጨንቀው የከረረ ሰላማዊ ትግል ነው። በትክክለኛ መርህ ላይ የተመሠረተ እውነተኛ ሰላማዊ ትግልና ሕዝባዊ እምቢተኝነት ስለማይገባውና በጉዳዩ ላይ በቂ ተሞክሮ ስለሌለው የሚያሸብረውና አስገድዶ ወደ ድርድር የሚያመጣው እሱ ብቻ እንደሆነ አምናለሁ” ሲሉ አስተያየታቸውን አጠቃለዋል። በሌላ ወገን ደግሞ የተቃዋሚዎች አቅም ከቀድሞው በተለየ የተጠናከረና የፕሮፓጋንዳውን ዘመቻ በማሳደጋቸው ምን አልባት መከላከያ ሰራዊቱ አካባቢ የመከፋፈል ችግር ሊፈጠር ይችላል የሚል ግምት ያላቸውም ብቅ እያሉ ነው።

ለጥንቃቄ፦ ካድሬዎች በሞቫይል ስልክ እያደናበሩ ነው!

September 16, 2013

 የህወሓት መሪዎች የመረጃ ምንጮቼ ለመሰለልና ምናልባት ኔትዎርክ እንዳለኝ ለማወቅ ከኔ ጋር ቅርበት ወዳላቸው ሰዎች (በካድሬዎቻቸው በኩል) ‘አብርሃ ደስታ’ መስለው በመደወል ዜጎችን እያወናበዱ መሆናቸው ደርሼበታለሁ። ‘አብርሃ ደስታን ሊያውቁ ይችላሉ’ ተብለው ለሚገመቱ ሰዎች (ካድሬዎቹ) እየደወሉ ‘አብርሃ ደስታ ነኝ፤ ….. ለምናምን ነገር ፈልጌሃለሁ፣ የት ነህ፣ መረጃ ስጠኝ ወዘተረፈ …’ እያሉ ንፁሃን ዜጎች እያደናበሩ ነው። ዜጎች ለማደናበርና ለመሰለል  ከተዘጋጁ ካድሬዎች (የአብርሃን ጉዳይ ለማጥናት) ወደ ሐውዜን ተልከው የጥፋት ተልእኳቸውን እየፈፀሙ ያሉ 13 ግለ ሰቦች ሲሆኑ በመቐለ ደግሞ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ አሉ። ወደ ሐውዜን ከተላኩ የተወሰኑ ስም ዝርዝራቸው ደርሶኛል።

ስለዚህ በሐውዜን፣ መቐለ እንዲሁም በሌሎች አከባቢዎች የምትገኙ ጓደኞቼ 'አብርሃ ደስታ ነኝ' ብሎ ለሚደውልላቹ ማንኛውም ሰው ከማመናቹና መረጃ ከመስጠታቹ በፊት እንድታረጋግጡ በትህትና አሳስባለሁኝ። 'አብርሃ ደስታ ነኝ' የሚል ደዋይ ካጋጠማቹ የተደወለላቹሁ ስልክ ቁጥር በፌስቡክ መልእክት አድርሱኝ። ማንነቱ አጣርተን እናጋልጠዋለን። ስልክ ቁጥሬን የምታውቁ ካላቹ ደግሞ እኔ መሆኔን ደውላቹ አረጋግጡ፤ አደራ።
ሰሙኑ አቶ አባይ ወልዱ ታማኝ የተባሉ የፓርቲው ሰዎች ሰብስቦ በአብርሃ ደስታ እንቅስቃሴዎች ላይ ጠንከር ያለ የስለላ ተግባር መከናወን እንዳለበት ትእዛዝ ሰጥተዋል። የአባይ ወልዱ ዛቻ ትርጉም የሚሰጠው ባይሆንም ጥንቃቄ ማድረጉ ግን ጠቃሚ ነው። ምክንያቱም ቴሌን በሕገወጥ መንገድ ለፓርቲ ስለላ እየተጠቀመ ነው። ብዙ ጉዳትም ሊያደርስ ይችላል።
ህወሓት የመንግስት ሃብት (ቴሌን) ለግል (ለፓርቲ) ጥቅም በማዋል በሙስና ሊከሰስ በተገባ ነበር። ለካ ቴሌን ለፓርቲ ጥቅም ለማዋል ነው በመንግስት ቁጥጥር ስር እንዲውል የተደረገው።
ግን...
በአሁኑ ሰዓት የደህንነት ሰዎች በጣም ተዳክመዋል። በስለላ እየተሰማሩ ያሉ የደህንነት ሰዎች ሳይሆኑ ተራ (ግን ታማኝ የሚባሉ) ካድሬዎች ናቸው። እነዚህ ሆድ-አደሮች ማሸነፍ ደግሞ ቀላል ነው።
It is so!!!

Sunday, September 15, 2013

የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያድርቅ !!! (ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ)

September 15/09/2013

ከገዛኸኝ አበበ

የወያኔ መንግስት በዓባይ ግድብ ሰበብ የባንድ ሽያጭ ለማድረግ እና በውጭ አገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ገንዘብ ለመዝረፍ  በየሀገሩ የሚያደርገውን የአባይ ቦንድ ሽያጭ ጉዞ ቀጥሏበታል :: ነገር ግነ  ወያኔ በየ ሀገሩ እያደረገው ያለው ጉዞ ግን እንደሰበው  ሳይሆንለት ውርደትን እና አፍረትን መቅመሱን  ስራዬ  ብሎ ተያይዞታል በ Calgary ካናዳ ፣በ ኖርዌይ ኦሰሎ እና ስታቫንገር ከተማ ፣ በ አሜሪካ Houston ፣ በደቡብ አፍሪካ እና በተለያዩ አገራት እንዲሁም በቅርቡ በስዊድን  ጉተን በርግ ከተማ የወያኔ አሽከሮች  በቆራጥ ኢትዮጵያኖች ጀግኖች ልጆች ቡጤ ሳይቀር ቀምሰው አንገዳቸውን ደፍተው በውርደት  የተከራዪትን አዳራሸ ለቀው የወጡበት ትርዒት አስቂኝ እና አስገራሚ ነበር::

ነገር ግነ  ወያኔ በአባይ ግድብ  የቦንድ ሽያጭ ስም ገንዘብ ለመዝረፍ  በየ አገሩ እያደረገው ያለው ጉዞ ግን እንደሰበው  ሳይሆንለት ውርደትን እና አፍረትን መቅመሱን  ስራዬ ብሎ ተያይዙት እያለ  የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያድርቅ እንዲሉ የወያኔ አሽከሮቸ   በውጪ ሀገር በሚኖረው ኢትዮጵያውያን ዘንድ በየ ሀገሩ ምን ያከል እንደተጠሉ  እና ተቀባይነት እንደሌላቸው ልባቸው እያወቀው ነገር ግን በእንቢርተኝነት ልባቸው የደነደነ የወያኔ ተላላኪዎች ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ በማሰብ አይናቸውን በጨው ታጥበው በአባይ ግድብ የቦንድ ሽያጭ ስም በየ ሀገሩ እየዞሩ የኢትዮጵያውያንን ገንዘብ ለመዝረፍ የሚያደርጉትን ጉዙ አላቆሙም :: ነገር ግን አሁንም ወደፊትም መቺም እና የትም ቢሁን ወያኔ የሚሳካለት አይመሰለኝም  ሊያጋጥመው እና ሊሆንበት የሚችለው ይኺው ነው :: ምክንያቱም ነፃነት ናፋቂው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈልገው እና ቅድሚያ በኢትዮጵያ ላይ እንዲሆን የሚመኛው የተወቀ እና ግልጽ ነው::

ከአባይ መገደብ በፊት ዘረኝነት ይገደብ ፣ ፍትህ እና ነፃነት ያስፈልገናል፣ በግፍ እና በጭካኔ የታሰሮት ዜጎቻችን ይፈቱ ፣ ወያኔ ሌባ ነው እና የመሳሰሉትን ቃላቶች  ሲሆኑ እነዚህንም ቃላቶች   ወያኔ  ሊሰማው እና ሊቀበለው የማይፈልገው ነገር ግን በአባይ ግድብ ስም የቦንድ ሽያጭ ገንዘብ ከሕዝቡ ለመዝረፍ በሚያደርገው ሮጫ የትም ሀገር  ወያኔ ሊያጋጥመው የሚቸሉ የነጻነት ድምጹች ናቸው :: ይህም  በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች ድምጽ ብቻ ሳይሆን  በነጻነት የመናገር እና የመቃወም መብቶቻቸው ተገፎ በአረመኔው እና በጨካኙ የወያኔ መንግስት መብቶቻቸው ተረግጡ እና ተገፎ  በወደዱት እና በመረጡት ሳይሆን በጉልበተኛው መንግስት በጉልበት እየተገዙ ያሉት የመላው አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ድምጽ ነው :: ይህም የኢትዮጵያ ሕዝብ ለወያኔ መንግሰት ያለውን መጥፎ ጥላቻ እና በእዚህ አረመኔ የወያኔ መንግስት መገዛት ምን ያክል እንዳንገሸገሸው  በተግባር የሚያሳይ ነው ::  ስለዚህ የወያኔ ባለስልጣኖች በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ  መቼም ቢሆን የትም ቢሆን ተቀባይነት እንደሊላቸው ሊያውቆት እና ሊገነዘቡት ይገባል::

 አሁንም ወደፊትም ውርደት እና ውድቀት ለወያኔ

    ድል ለኢትዮጵያ ሕዘብ !!!

በቅርቡ ወያኔ በስዊድን ጉተን በርግ ከተማ የደረሰበትን አሳፋሪ ውርደቱን በቪዲዪው ላይ ይመልከቱ





የሌባ ዓይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያድርቅ !!! (ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ )

September 15/09/2013

ከገዛኸኝ አበበ

የወያኔ መንግስት በዓባይ ግድብ ሰበብ የባንድ ሽያጭ ለማድረግ እና በውጭ አገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ገንዘብ ለመዝረፍ  በየሀገሩ የሚያደርገውን የአባይ ቦንድ ሽያጭ ጉዞ ቀጥሏበታል :: ነገር ግነ  ወያኔ በየ ሀገሩ እያደረገው ያለው ጉዞ ግን እንደሰበው  ሳይሆንለት ውርደትን እና አፍረትን መቅመሱን  ስራዬ  ብሎ ተያይዞታል በ Calgary ካናዳ ፣በ ኖርዌይ ኦሰሎ እና ስታቫንገር ከተማ ፣ በ አሜሪካ Houston ፣ በደቡብ አፍሪካ እና በተለያዩ አገራት እንዲሁም በቅርብ በስዊድን  ጉተን በርግ ከተማ የወያኔ አሽከሮች  በቆራጥ ኢትዮጵያኖች ጀግኖች ልጆች ቡጤ ሳይቀር ቀምሰው አንገዳቸውን ደፍተው በውርደት  የተከራዪትን አዳራሸ ለቀው የወጡበት ትርዒት አስቂኝ እና አስገራሚ ነበር::

 ወያኔ በስዊድን ጉተን በርግ ከተማ የደረሰበትን አሳፋሪ ውርደቱን በቪዲዪው ላይ ይመልከቱ




ነገር ግነ  ወያኔ በየ አገሩ እያደረገው ያለው ጉዞ ግን እንደሰበው  ሳይሆንለት ውርደትን እና አፍረትን መቅመሱን  ስራዬ ብሎ ተያይዙት እያለ  የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያድርቅ እንዲሉ የወያኔ አሽከሮቸ   በውጪ ሀገር በሚኖረው ኢትዮጵያውያን ዘንድ በየ ሀገሩ ምን ያከል እንደተጠሉ  እና ተቀባይነት እንደሌላቸው ልባቸው እያወቀው ነገር ግን በእንቢርተኝነት ልባቸው የደነደነ የወያኔ ተላላኪዎች ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ በማሰብ አይናቸውን በጨው ታጥበው በአባይ ግድብ የቦንድ ሽያጭ ስም በየ ሀገሩ እየዞሩ የኢትዮጵያውያንን ገንዘብ ለመዝረፍ የሚያደርጉትን ጉዙ አላቆሙም :: ነገር ግን አሁንም ወደፊትም መቺም እና የትም ቢሁን ወያኔ የሚሳካለት አይመሰለኝም  ሊያጋጥመው እና ሊሆንበት የሚችለው ይኺው ነው :: ምክንያቱም ነፃነት ናፋቂው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈልገው እና ቅድሚያ በኢትዮጵያ ላይ እንዲሆን የሚመኛው የተወቀ እና ግልጽ ነው::

ከአባይ መገደብ በፊት ዘረኝነት ይገደብ ፣ ፍትህ እና ነፃነት ያስፈልገናል፣ በግፍ እና በጭካኔ የታሰሮት ዜጎቻችን ይፈቱ ፣ ወያኔ ሌባ ነው እና የመሳሰሉትን ቃላቶች  ሲሆኑ እነዚህንም ቃላቶች   ወያኔ  ሊሰማው እና ሊቀበለው የማይፈልገው ነገር ግን በአባይ ግድብ ስም የቦንድ ሽያጭ ገንዘብ ከሕዝቡ ለመዝረፍ በሚያደርገው ሮጫ የትም ሀገር  ወያኔ ሊያጋጥመው የሚቸሉ የነጻነት ድምጹች ናቸው :: ይህም  በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች ድምጽ ብቻ ሳይሆን  በነጻነት የመናገር እና የመቃወም መብቶቻቸው ተገፎ በአረመኔው እና በጨካኙ የወያኔ መንግስት መብቶቻቸው ተረግጡ እና ተገፎ  በወደዱት እና በመረጡት ሳይሆን በጉልበተኛው መንግስት በጉልበት እየተገዙ ያሉት የመላው አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ድምጽ ነው :: ይህም የኢትዮጵያ ሕዝብ ለወያኔ መንግሰት ያለውን መጥፎ ጥላቻ እና በእዚህ አረመኔ የወያኔ መንግስት መገዛት ምን ያክል እንዳንገሸገሸው  በተግባር የሚያሳይ ነው ::  ስለዚህ የወያኔ ባለስልጣኖች በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ  መቼም ቢሆን የትም ቢሆን ተቀባይነት እንደሊላቸው ሊያውቆት እና ሊገነዘቡት ይገባል::

 አሁንም ወደፊትም ውርደት እና ውድቀት ለወያኔ

    ድል ለኢትዮጵያ ሕዘብ !!!

Saturday, September 14, 2013

ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ እሁድ ሴፕቴምበር 22 ቀን 2013 በዋሽንግተን ዲሲ / ቨርጂኒያ


         
እሁድ ሴፕቴምበር 22 ቀን 2013 በዋሽንግተን ዲሲ/ ቨርጂኒያ የግንቦት 7 ንቅናቄ አመራር የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በሚገኙበት በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ ከሕብረተሰቡ ጋር ውይይት ለማድረግ  ታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባ  ተዘጋጅቷል..
ቀን : እሁድ  ሴፕቴምበር 22 2013
ሰአት: 2.00 pm – 6:00 pm
ቦታ : ሸራተን ናሽናል ሆቴል (ከዳማ ምግብ ቤት አጠገብ የሚገነው)
900 South Orme Street, Arlington, VA
መግቢያ: $20
ለተጨማሪ መረጃ: 571-239-7001
የግንቦት 7  የፍትህ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ

እኔ ባልፍም እንኩዋን ሺህ ርዕዮቶች ስላሉ በርቱ አትደናገጡ “

September 14, 2013
by  Sekedar alemu
Reeyot-Alemu
* የርዕዮት ደህንነት አደጋ ላይ መሆኑን እንድታዉቁት ስል ነዉ ይህንን በብዙ ሀዘን ዉስጥ ሆኜ የጻፍኩላችሁ
ትላንትና እንደሁል ጊዜዉ ስንቅ ይዤላት ወደ ቃሊቲ ሔድኩ በር ላይ ያለዉ ፖሊስ “የርዕዮት እህት ነሽ አይደል እሱዋን መጠየቅ አትችይም በአስተዳደር በኩል ሔደሽ ጠይቂ” አለኝ፡፡ እንዳዘዘኝ በአስተዳደር በር በኩል ሔድኩ ወደ ዉስጥ በስንት ትግል ከስለሺ (የርዕዮት እጮኛ) ጋር ገባን፡፡

ከብዙ ጥበቃ በሁዋላ በብዙ ፖሊሶች ታጅባ መጣች ፊትዋ ተለዋዉጦ ስለነበር ምን እንደሆነች ስጠይቃት ከእናት፡ አባት እና ንስሃ አባት ዉጪ ማንም ሊጠይቃት እንደማይችል እና የእነሱን ስም እንድትሰጥ እንደተጠየቀች እና አሚናዘር የሚትባል የሴቶች ክፍል ሀላፊ አልጋዋ ድረስ በመምጣት እንደሰደበቻትና እንደዛተችባት እየነገረችኝ እያለ አሚናዘር የተባለችዉ ሃላፊ ወደኛ በመምጣት ርዕዮትን በማመናጨቅና በመስደብ ከኛ ልትወስዳት ስትሞክር ለምን እንደሆነ ስጠይቃት “ከዛሬ ወዲህ ዐይኑዋን አታዩትም ማንም እኔን ሊያዝ አይችልም የእናንተ ጋዜጣና ሚዲያ ምን እንደሚያመጣ እናያለን ” በማለት ርዕዮትን በማዋከብ እና በመጎተት እየሰደቡ ወሰዱዋት፡፡ ምድር ላይያሉ ሰቅጣጭ እና ለህሊና የሚከብዱ ስድቦችን አወረዱብን በዚህ መሀል ርዕዮት ድምጹዋን ከፍ አርጋ “የማልጨርሰዉን ነገር አልጀምርም እኔን ለማንበርከክ እና ለማሸማቀቅ ክሆነ መቼም አላረገዉም ትገይኝም ከሆነ ነይ ተኩሺ ” ስትል ጎትተዉ ወሰዱዋት፡፡ እኛንም ከጊቢዉ አዋክበዉ አስወጡን፡፡

ዛሬ በዐል ስለሆነ ምን አልባት ሊያስገቡን ይችላሉ ብለን ነበር ሁላችንም ወደ ቃሊቲ የሔድነዉ፡፡ የሆነዉ ግን በጣም አሳዛኝ ነበር፡፡ በር ላይ ደርሰን ስንጠይቅ (ቤተሰቦችዋና ጓደኞችዋ) አሚናዘር ላስፈቅድ ብላ በር ላይ ያለችዉ ፖሊስ ወደ ዉሰጥ ገባች ትንሽ ቆየት ብላ ተመለሰችና አባትና እናት ብቻ ነዉ የሚገቡት ያልችዉ አሚናዘር ብላ እኔና ስለሺ ጓደኞችዋንም ጨምሮ መግባት እንደማንችል ተነገረን የዚን ጊዜ አባታችን “የእነሱን ህገወጥ ስራ እንደማይተባበር እና እኛ ተከልክለን እሱ እንደማይገባ ነገራቸዉ” እናታችን እንድትገባና ሁኔታዋን አይታ እንድትነግረን የያዝነዉን ምግብ ይዛ ገባች፡፡ በጣም በሀዘን የያዘችዉን ምግብ ይዛ ተመለሰች ምነዉ ስንላት ርዕዮት የርሃብ አድማ እንዳደረገች እና ቤተሰብ የማይገባላት ከሆነ አድማዉን እንደምትቀጥል እንደነገረቻት እናም በጣም ያስደነገጠንን ዜና ነገረችን “አጠገቡዋ ኮ/ል ሐይማኖት (የ ገብሩዋድ ባለቤት) እንዳመጡዋትና የርዕዮትን አልጋ በማስጠጋት እሱዋነ ከጎንዋ አድረገዋት እሱዋም ሙሉ ለሊት እየሰደበቻትና እየዛተች እንዳሳደረቻት ህይወትዋ አደጋ ላይ መሆኑን አንድ ነገር ቢፈጠር በህመም እንዳልሆነ እንድታዉቁት እኔ ባልፍም እንኩዋን ሺህ ርዕዮቶች ስላሉ በርቱ አትደናገጡ” የሚል መልእክት ነገረችን፡፡

አስረዉ ሲያበቁ እንኳን ምነዉ ቢተዋት? በዚህ ከቀጠለ እህቴን ነገ ለማግኘቴ ምን ያህል እርግጠኛ እንደምሆን አላዉቅም!!!!!
ሉሉዬ የሚታልፊበት መከራሽን አምላክ ይይልሽ!!!!

* ይህ ጽሁፍ በተለያዩ የፌስ ቡክ አድራሻዎች የተስተናገደ አሳዛኝ ማስታወሻ ነው። ጽሁፉን በዋናነት ያተመ ትክክለኛ ምንጭ ካለ ለማረም ዝግጁ ነን። ጽሁፉን እንድናስተናግድ ለላክልን ደንበኛችን እናመሰግናለን። ርዕየትና ሌሎች ውድ ወገኖቻችንን እናስባቸው!!
 
Sources:-  Daniel Haregawi Timeline(FB)

Friday, September 13, 2013

Ethiopian journalist on hunger strike over mistreatment in prison (IMW)

September 13, 2013 

IMWF calls for reinstatement of visitation privileges

SSSAs stories about the political crisis in Cairo have been dominating the news from Egypt, there has been limited coverage on a brewing international conflict between Egypt and Ethiopia – two countries that do not share a border but are indivisibly connected by the Nile, the world’s longest river.

Amid works to construct a giant hydro-electric dam, and much to the anger of the Egyptian government, Ethiopia has started diverting the Blue Nile, a tributary of the Nile, prompting a furious debate about if and how the “Great Ethiopian Renaissance Dam” will affect Egypt’s water security.
While there may not be a definite answer anytime soon on whether this dam will have any impact on water security in Egypt, there is no doubt that it has already negatively impacted press freedom in Ethiopia. Earlier this summer, for instance, the Committee to Protect Journalists reported that Ethiopian officials arrested a reporter seeking to interview people evicted from their homes in the region where the contentious hydro-electric dam is being built. More notable, however, was the arrest of Ethiopian columnist Reeyot Alemu more than two years ago.
A critic of the government writing for the now-defunct newspaper Feteh, Alemu had raised questions about the funding and merits of the dam shortly before she was arrested on bogus terrorism charges and sentenced to 14 years in jail.
Although two of the three terrorism charges against her were later dropped on appeal and her sentence reduced to five years, Alemu continues to suffer from her government’s efforts to silence dissenting voices and scare independent journalists into self-censorship. A tumor in Alemu’s breast remains untreated as she is denied access to medical care, and threats of solitary confinement linger over her every move in Ethiopia’s notoriously ill-maintained Kaliti prison.
While the Ethiopian leadership insists on the country’s adherence to the rule of law, there seems to be little doubt in the international community that Alemu’s arrest and conviction was politically motivated: The International Women’s Media Foundation honored Alemu with its Courage in Journalism Award last year, and in May 2013, the United Nations Educational, Scientific and Cultural Organization (UNESCO) recognized her “commitment to freedom of expression” with itsGuillermo Cano World Press Freedom Prize. In July, a delegation of the European Parliament’s Subcommittee on Human Rights, scheduled to meet with Alemu, was denied access to Kaliti prison, prompting questions by members of the European Parliament over Ethiopia’s commitment to human rights.
According to the Committee to Protect Journalists, Ethiopia jailed more journalists than any other country in Africa in 2012 (with the exception of Eritrea), and 45 Ethiopian journalists have been forced into exile since 2008. Swedish journalist Martin Schibbye who gained first-hand experience with Ethiopia’s crackdown on press freedom after being arrested there himself in June 2011, delivers a damning verdict on the rule of law in Ethiopia: “There is no such thing as an independent justice system, it’s completely politicized. If the order comes from the federal level that Reeyot is to let go, she will be free. But if they feel that they gain more from keeping her in prison, they will keep her locked up. This decision lies entirely in the hands of the Ethiopian government,” he said.
But the Ethiopian authorities seem to be determined to keep Alemu silenced. Earlier this week, as Ethiopians were preparing for their New Year’s celebration, prison officials denied Alemu visits from anyone but her parents. It remains unclear whether the decision to keep her separated from her friends, siblings, and fiance is in response to an open letter Alemu wrote in August, criticizing Ethiopia’s Anti-Terrorism Proclamation, but it appears to be unlikely that the timing of the new restrictions is coincidence.
Protesting the prison’s decision to deny her visits from friends and relatives, Alemu has gone on hunger strike. The IWMF is deeply concerned about Alemu’s health and well-being, and calls on the decision-makers at Kaliti prison to re-instate Alemu’s full visitation privileges immediately.

ርእዮት አለሙ እና የእስር ጉዳይ በደረጀ ሃብተ ወልድ

september 12, 2013

ጋዜጠኛና መምህርት ርዕዮት ዓለሙን ለመታሰር ካበቃት ወንጀል አንዱና ዋነኛው ፦”… በቃ!” ተብሎ የተፃፈን ጽሁፍ ፎቶ ማንሳቷ ነው። .. ለኔ ይገርመኝ የነበረው፤ርዕዮትንም ከሙያና ከሞራል አንፃር ያስወቅሳት የነበረው.. “በቃ!” ተብሎ የተፃፈውን ጽሁፍ ዝም ብላ ብታልፈው ነበር። የልማታዊ ጋዜጠኛ አንዱና ዋነኛ ተግባር በህዝብና በመንግስት መካከል እንደ ድልድይ ሆኖ መንግስት (ጥሩም ይሁን መጥፎ)ምን እየሠራ እንደሆነ፤ ህዝቡም ስለ መንግስት ምን እያሰበና ምን እያለ እንደሆነ የሀቅ መረጃ ማቅረብ ነው። ከዚህ አንፃር ርዕዮት ፦”ህዝቡ በቃ እያለ ነው..” የሚል መረጃ በፎቶ ማንሳቷና በብዙሀን መገናኛ ለማቅረብ ማሰቧ ያሸልማት እንደሆነ እንጂ በፍፁም ሊያስከስሳት አይችልም። “በቃ!” የሚል ፅሁፍ በየቦታው እየተፃፈ ባለበት ሁኔታ “ህዝቡ ኑሮው ተሻሽሏል፣ አኮኖሚው አድጓል፤ ልማቱ እጎመራ ነው…” እንድትል ተፈልጎ ከሆነ፤ ያ የህዝብ ግንኙነት ወይም የካድሬ ሥራ እንጂ የጋዜጠኛ ተግባር አይደለም።

…ሀቁ ይኸው ነው። ደርግ የጠመንጃ ታጋዮቹን እንዳሰቃየበት በዶክመንተሪ ፊልም እያሰማመረ የሚተርክልን ኢህአዴግ፤ የብዕር አርበኞችን እያሰረ፣አስሮም እያሰቃየ ነው። ደርግ፤ የያኔዋን የኢህአፓ ታጋይና የ አሁኗን ኢህአዴግ ወይዘሮ ታደለች ሀይለሚካኤልን ነፍሰ-ጡር እያለች ማሰሩን- ለደርግ ጨካኝነትና አረመኔነት እንደማመሳከሪያ እያቀረበ “ጉድ!”ሲለን የነበረው ኢህአዴግ፤ የታሪክ ሀዲዱ ብዙም ሳይጓዝ -ጋዜጠኛዋንና ነፍሰ-ጡሯን ሰርካለም ፋሲልን አስሮ እዚያው እስክትወልድ ድረስ በወህኒ እንደተዋት ህያው ምስክሮች ነን።

ኢህአዴጎች ደርግን የሚከሱበትና የሚወቅሱበት ሞራል ብቻ ሳይሆን ታሪክም የላቸውም። ሳይውል ሳያድር ያን ታሪክ እነሱም እየደገሙት ነውና።

በኮንዶሚኒየም ቤቶች ሺያጭ ሥም ስደተኛውን የወያኔ ጭሰኛ ለማድረግ የተጀመረው እንቅስቃሴ ይከሽፋል::

September 12, 2013

ወያኔ እንደ ድርጅት የሚፈልገውን የፖለቲካ ጥቅም የሚያስገኝለት እስከመሰለው ድረስ በህዝብና በአገር ላይ የማይፈጽማቸው ምንም አይነት እኩይ ተግባሮች እንደማይኖሩ በተግባር ያስመሰከረ ድርጅት ነው::
ለአብነት ያህል ለመጥቀስ ፤
  1. ድርጅቱ ገና ትግራይ በረሃ ውስጥ ትግል ላይ በነበረበት ወቅት የትግራይን ወጣቶች ከትምህርት ገበታቸው እያነቀ በመውሰድ አላማውን በግልጽ ላልተረዱትና ላላመኑበት ጦርነት ማግዶአቸዋል:: በዚህም የተነሳ ወያኔ እራሱ ይፋ ባደረገው አሃዝ ብቻ ቁጥራቸው 60 ሺህ የሆኑ ለጋ ወጣቶች ላለፉት 22 አመታት የህዝባችንን ስቃይና መከራ እያራዘመ ያለውን የድርጅቱን መሪዎች ሥልጣን ላይ አውጥቶ ለማንገስ ከፍተኛ የህይወት መስዋዕትነት ከፍለዋል ::
  2. የአገራችንን ክብርና መልካም ገጽታ እስከዛሬ አበላሽቶ ባለፈው በዚያ አስከፊ የ1977ቱ ድርቅ ወቅት ለትግራይ ተጎጂዎች ከአለም አቀፍ ለጋሾች የተበረከተውን የነፍስ አድን እህል በሱዳን በኩል ወደውጭ አሳልፎ በመቸብቸብ መሪዎቹና ተከታዮቻቸው ለተንደላቀቀ ኑሮ ሲበቁ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ህጻናት፤ አሮጊቶችና አዛውንቶች እንደቅጠል እንዲረግፉ ምክንያት ሆኖአል::
  3. የትግራይ ህዝብ ተማሮ በመንግሥት ላይ እንዲያምጽ ለመቀስቀስ በደሃው አቅማችን የተገነቡ ትምህርት ቤቶችን፤ የህክምን አገልግሎት መስጫ ተቋሞችን ፤ ድልድዮችንና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን በፈንጂና በመድፍ ከማውደም አልፎ የተሳሳተ መረጃ ለደርግ በመስጠት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ህዝብ ለገበያ እንደወጣ ሃውዜን ከተማ ላይ በጠራራ ጸሃይ እንዲጨፈጨፍ አድርጎአል::
  4. የደርግ አገዛዝ ከተወገደ ቦኋላ ሥልጣን ላይ ለመደላደል የሚያስችል ድጋፍ ለመሸመት ሲባል የአገራችንን ሉአላዊ ጥቅም ለባዕድ አሳልፎ የሰጠ በርካታ ግልጽና ድብቅ ውሎችን ከ3ኛ አካላት ጋር ፈጽሞአል :: ከውሎቹ አንዱ የህዝባችንን ትኩረት ለማስለወጥ ካለፈው 2 አመት ጀምሮ በሰፊው እየተዘመረለት የሚገኘው የአባይ ወንዝን የመጠቀም መብታችንን የሚጻረር እንደነበረ ጉልህ ማስረጃ አለ::
  5. በሚሊዮን የሚጠጋ ህዝባችንን ከቀያቸው በማፈናቀል ለም መሬታችንንና ድንግል የተፈጥሮ ሃብታችንን ለህንድ ፡ ለቻይናና ለአረብ ከበርቴዎች በመቸብቸብ በገዛ አገራችን የባዕድ አሽከር እንዲንሆን ፈርዶብናል::
  6. በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሴት እህቶቻችን ለባርነት ሥራ ወደ አረብ አገር በመላክ ከፍተኛ ሰቆቃ እንድፈጸምባቸው በማድረግ ብሄራዊ ክብራችንን ኩራታችንን የሚያጎድፍ ተግባር ፈጽሞአል::
  7. በሙስናና ዘረፋ የተጨማለቀ ሥርዓት በማቋቋም አብዛኛው ህዝባችን ከወለል በታች ወደወረደ የድህነት አረንቋ ውስጥ ገብቶ የቁም ስቃይ እንዲቀበል አድርጎአል::
  8. መብታቸውን ለማስከበር በጠየቁ ወገኖቻችን ላይ እስከ አፍንጫው የታጠቀ ጦር በማዝመት በርካቶችን አስጨፍጭፎአል፤ ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሎአል ፤ ለእስርና ለስደት ዳርጎአቸዋል:: ወዘተ
ወያኔ ይህንንና ግዝፈታቸው ከዚህ የከበዱ በርካታ ሰቆቃዎችን በአገርና በወገን ላይ እየፈጸመ የአገዛዝ ዘመኑን ሊያራዝም የቻለው፤
  1. ህዝባችን በዘር ፤ በቋንቋና በሃይማኖት ተከፋፍሎ እርስ በርሱ እንዳይተማመንና የጎሪጥ እንድተያይ ሌት ተቀን ተንኮል በመሸረቡ
  2. የጦር ሃይል ፤ የፖሊስ ሠራዊት፤ የደህንነትና ሌሎች የኢኮኖሚና ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋሞች በሙሉ ከአንድ አካባቢ በተሰባሰቡ የጥቅም ተጋሪዎች ቁጥጥር ሥር እንዲወድቅ ተደርጎ እሺ ያለውን በጥቅም እምቢ ያለውን ደግሞ በጠመንጃ ሃይል ጸጥ ለጥ ለማድረግ በመመኮሩ፤
  3. ከራሳቸው የግል ሚቾትና ቅንጦት አሻግረው በወገንና በአገር ላይ እየተፈጸመ ያለውን ሰቆቃ ማየት የማይፈልጉ ወይም የማይችሉ ተፈጥሮአዊ ባህሪያቸው “ እኔ ከሞትኩ ሠርዶ አይብቀል “ ካለቺው እንስሳ የማይለይ ሆዳሞች ከተለያየ የህበረሰተሰብ ክፍል ተመልምለው ከአገዛዙ ዙሪያ በሎሌነት ለመሰለፍ በመቻላቸው እንደሆነ ይታወቃል::
በሌላ አገላለጽ ወያኔ የአገዛዝ እድሜውን ለማራዘም የፈጸመውና እየፈጸመ ያለው ቀደም ሲል ፋሽስት ጣሊያን የአገራችንን ህዝብ በባርነት ለመግዛት አድርጋው ከነበረው ቅስም ሰባሪ እርምጃዎች በባህሪም ሆነ በአይነት አንድ መሆኑ ግልጽ ነው:: ለመብቱና ለነጻነቱ ቀናዕ የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ትናንት ለጣሊያን መደለያዎች ተታሎ ወይም የሃይል እርምጃ ተንበርክኮ ነጻነቱን አስነጥቆ ለመኖር እንዳልፈቀደ ሁሉ ዛሬም ከአገሩ የሰሜን ክፍል የበቀሉ ባንዳዎች በጉልበታቸውም ሆነ ሌሎች መሸንገያዎች የሚያደርጉትን አሜን ብሎ እስከወዲያኛው ለመገዛት ፈቃደኛ አለመሆኑን በሚያደርገው ተቃውሞ እየገለጸ ነው::
ይህንን ሃቅ የተረዳው ወያኔ የጭቆና ክንዱን ለማፈርጠም የሚያስፈልገውን ገንዘብ በስደት ውጭ አገር ከሚኖረው ኢትዮጵያዊ ለመሰብሰብና የተቃውሞ እንቅስቃሴውን ለማዳከም በኮንዶሚኒየም ቤት ሽያጭ ሥም አዲስ እቅድና ስልት ነድፍ መንቀሳቀስ ጀምሮአል::
ብቸኛው የፓርላማ ተወካይ የሆኑት አቶ ግርማ ሠፉ በቅርቡ ከኢሳት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ እንዳረጋገጡት ወያኔ በስደት ለሚኖረው ኢትዮጵያዊ የነደፈው የኮንዶሚኒየም ቤት ሺያጭ ዋና አላማ አገር ቤት ውስጥ እየተፏፏመ የመጣውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመምታት በተለያዩ የምዕራብ አገሮች ከፍ ብለው እየተደመጡ ያሉትን ድምጾች አሰቀድሞ ለማዳከም በመፈለጉ እንደሆነ አያጠራጥርም::
ምንም እንኳን ለራሳቸው ማንነትና ስብእና ክብር የሌላቸው አንዳንድ ዜጎች “የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ” በሚል ፈሊጥ በዚህ የወያኔ ወጥመድ ውስጥ ለመውደቅ ውር ውር እያሉና በየአገሩ የሚገኘውን የወያኔ ኤምባሲ በር ማንኳኳት የጀመሩ መኖራቸው ባይካድም አንድ ወቅት ላይ ግር ግር ፈጥሮ ወዲያው እንደተጨናገፈው የአባይ ቦንድ ሺያጭ የታሰበውን ያህል ውጠት እንደማያስገኝ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል::
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በስደት የሚኖረው ሁሉም ኢትዮጵያዊ አገሩንና ወገኖቹን ጠልቶ ሳይሆን የተሰደደው ለዘመናት የዘለቀው ኢፍትሃዊነት የፈጠረው ኋላ ቀርነትና ድህነት አገሩ ላይ ለመኖር ያለውን ምኞትና ተስፋ አጨልሞበት አለያም በፖለቲካ ችግር ምክንያት ህይወቱን ለማቆየት ተገዶ ነው ብሎ ያምናል::
በዚህም የተነሳ ማንኛውም ስደተኛ ስደት የሚያስከትለውን ማህበራዊና ሥነ ልቦናዊ ቀውሶች ተቋቁሞ አንድ ቀን አገሬ ገብቼ ከወገኖቼ ጋር በሠላም እኖርበታለሁ ብሎ ያጠራቀማትን ጥሪት በከፍተኛ ንቅዘትና ሙሰኝነት ወደ መጨረሻው ታሪካዊ ሞቱ እየወረደ ያለውን የወያኔ ሥርዓት ተማምኖ በማውጣት ቦኋላ እንዳይጸጸት ወገናዊ ምክሩን ይለግሳል::
ወያኔ ለዲያስፖራው ያዘጋጀው የኮንዶሚኒዬም ቤቶች ሺያጭ የፖለቲካ ድጋፍ ለማግኘት የታለም የከተማና የገጠር ህዝባችንን የወያኔ ጭሰኛ ያደረገ የአገር ውስጥ ፖሊሲ አካል ነው:: ከ7 አመት በፊት ኮንዶሚኒዬም ቤት ለማግኘት ለተመዘገቡ 800 ሺህ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ያልተዳረሰ ቤት እንዴትና በምን ስሌት ነው በሰው አገር ያውም በአንጻራዊ ምቾት ለምንኖር ዜጎች የታሰበልን ብሎ እራስን መጠየቅ ከትዝብትና ከታሪክ ተወቃሽነት የሚያድን ተግባር ነው ::
ሃብት በተትረፈረፈበትና የሚበላ የሚጠጣ ነገር ከሰው ተርፎ ቆሻሻ ገንዳ ውስጥ በሚጣልበት አሜሪካና አውሮጳ ለምንኖር ዜጎች ከሚስኪኑ ህዝባችን ጉሮሮ በተነጥቀ ገንዘብ ቤተመንሥት ውስጥ ተዘጋጅቶ የተላከ ምግብና መጠጥ ለመደለያነት ሲያጓጉዝ የኖረ መንግሥት አሁን ደግሞ በኮንዶሚኒየም ቤት ሥም ቢመጣብን ጥፋቱ የሱ ሳይሆን የእኛ ለክብራችንና ለነጻነታችን ዋጋ የማንሰጥ ስግብግቦች መሆኑን ምን ጊዜም መዘንጋት የለበትም::
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በስደት ውጭ አገር የሚኖር ማንኛውም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ወያኔ በኮንዶሚኒዬም ቤት ሽያጭ ሥም ትግሉን ለማዳከም የዘረጋውን ይህንን የተንኮል ሴራ እንዲያከሽፍ ወገናዊ ሃላፊነት እንዳለበት ያስገነዝባል::
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !

Wednesday, September 11, 2013

በበዓል ቀን የርሃብ አድማ – ርዕዮት ምን ልትነግረን ነው?

September 11th, 2013 
በብሄራዊ በዓላት ቀን በአብዛኛው ከወደ እስር ቤት የሚሰማው ዜና አስደሳች ነበር፡፡ይህንን አጼዎቹ ፣ሰው በላው የደርግ ስርዓትና ብሶት ወለደኝ ያለን ኢህአዴግ ሲያደርጉት ቆይተዋል፡፡ በዘንድሮው አዲስ አመትም የመንግስትን ይቅርታ በማግኘት ከወዳጅ ዘመዶቻቸው የተቀላቀሉ ስለመኖራቸው ተሰምቷል፡፡በአዲሱ ዓመት ይቅርታ ከተቸራቸው እስረኞች መካከል ታዋቂ ፖለቲከኞች፣አክቲቪስቶችና ጋዜጠኞች አለመኖራቸው ተፈቺዎቹ በደረቅ ወንጀል ታስረው የነበሩ መሆናቸውን ለመናገር ብዙ መድከም አይጠይቅም፡፡
1185860_10200561003368447_1105290103_nመንገስት ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፣ሂሩት ክፍሌና ዘሪሁን ገ/እግዚአብሄር አቅርበውት ለነበረ የይቅርታ አቤቱታ የእምቢታ ምላሽ መስጠቱም ይቅርታ የሚገባውና የማይገባው በመንግስት ማውጫ ውስጥ ስለ መኖሩ ማሳያ ነው፡፡የይቅርታው ጉዳይ ለጊዜው ይዘግይልንና በጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ላይ በበዓል ቀን ስለ ተፈጸመ ግፍ ላካፍላችሁ፡፡ ጋዜጠኛዋን በበዓሉ ዋዜማ ለመጠየቅ ወደ ቃሊቲ አምርተን ነበር፡፡በመጠየቂያ ሰዓት መድረስ የቻልን ቢሆንም ጥበቃዎቹ
‹‹ርዕዮት የምትጠየቀው በዋናው በር ሆኗል፡፡ስለዚህ ወደ ዋናው በር ሂዱ››
አሉን፡፡ዋናው በር ፈጣን ተራማጅ በ10 ደቂቃ የሚደርስበት በመሆኑ ሰዓቱ እንዳይረፍድና እንዳንከለከል በማለት መሮጥ ጀመርን፡፡
ዋናው በር ግብረ ገብነት አልያም ፖሊሳዊ ስነ ምግባር በዞረበት ለሰላምታ እንኳ አግኝቷቸው የማያውቁ የሚመስሉ ጠባቂዎች
‹‹በዚህ በኩል እስረኛ አይጠየቅም ሂዱ ››
አሉን፡፡ ግትር ብለን በዚህ በኩል ግቡ ተብለናል አልን፡፡ሰዓቱ እየሄደ ፖሊሶቹም በአቋማችን የበለጠ በመበሳጨት እየዛቱ ነው ፡፡በመካከሉ የርዕዮት ታናሽ እህት እስከዳር አለሙና እጮኛዋ ስለሺ ሀጎስ ከግቢው ውስጥ እየተጣደፉ ወጡ፡፡ ስለሺ አንገቱን አቀርቅሮ እጆቹን እያወናጨፈ ብቻውን ያወራል፣እስከዳርን በሙሉ አይን ማየት ያስፈራል፡፡ ፊቷ በርበሬ መስሎ በእንባ ጎርፍ እየታጠበች ነው፡፡አብሮኝ የነበረው ሰውና እኔ ለመግባት እናደርግ የነበረውን ትንቅንቅ በመተው ሁለቱን ለማጽናናት እና ምን እንደተፈጠረ ለማወቅ መወትወቱን ተያያዝነው፡፡
ርዕዮት ቤተሰቦቿን እንዳገኘች
‹‹ያለሁበት ሁኔታ አስቸጋሪ ነው፣ችግር ውስጥ ነኝ››
ትላቸዋለች፡፡በዚህ ወቅት በዙሪያዋ የነበሩ ሴት ፖሊሶች ጋዜጠኛዋ ላይ በመጮህ
‹‹ስለ ራስሽ ብቻ አውሪ››
ይሏታል፡፡
‹‹የነገረችን እኮ ስለ ራሷ ነው››
የእስከዳር ምላሽ ነበር፡፡ በዚህ መሃል በጊዜያዊነት የሴቶች ዞን ሃላፊ የሆነች ፖሊስ
‹‹እናንተ አቅማችሁ ጋዜጣ ላይ ነው ከፈለጋችሁ ሂዱና እንዳንጠይቃት ተከለከልን በሉ፡፡››
በማለት በዚህ ቦታ ለመጥቀስ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የሚያቅበንን የስድብ መዓት በስለሺ ፣በርዕዮትና በእህቷ ላይ ታወርዳለች፡፡
ርዕዮት ሁኔታውን መቋቋም ተስኗት ሃላፊዋን ለምን እንዲህ አይነት በደል እንደምትፈጽምባት ለመጠየቅ ስትሞክር እየገፈታተሩ ወደ ውስጥ እንድትገባ በማድረግ እነ ስለሺን ግቢውን እንዲለቁ ያደርጋሉ፡፡
በንጋታው መስከረም 1/2006 ነው፡፡የመንግስት ሃላፊዎችና የሃይማኖት አባቶች የቴሌቭዥኑን መስኮት በአዲስ አመት ቀና መልዕክት አጨናንቀውታል፡፡አዲስ ቀን አዲስ ገጠመኝ እንደሚፈጥር ተስፋ ያደረጉት የርዕዮት ቤተሰቦች ከቃሊቲ አልቀሩም፡፡ነገር ግን የሰሙት ነገር በቀኑ እንጂ በአስተዳደሩ መካከል ለውጥ ወይም ዕድሳት አለመኖሩን ነው፡፡ለካ የአዲስ አመት በጎ መልእክት የሚያስተላልፉልን መሪዎቻችን ያሉት
‹‹በድሮው ቀን ነው፡፡››
ርዕዮትን እንዲጠይቁ የተፈቀደላቸው
‹እናቷ፣አባቷና የነፍስ አባቷ ብቻ ናቸው››
እነ ስለሺ ከቃሊቲ ሃላፊዎች ዛሬ ያደመጡት መንፈስ ሰባሪ ቃል ነው፡፡ የህግ ባለሞያው አቶ አለሙ ጌቤቦ ድርጊቱ ህገ መንግስታዊ ጥሰት እንደሆነ በመግለጽ ቃሊቲ ደርሰው ልጃቸውን ሳይጠይቁ ተመልሰዋል፡፡ወላጅ እናቷ ያመጡትን ምግብ ለማስገባት ቢሞክሩም ርዕዮት በቃሊቲ የሴቶች ዞን ጊዜያዊ ሃላፊ እየደረሰባት የሚገኘውን ህገ ወጥ ድርጊት ለመቃወም የርሃብ አድማ በመጀመሯ እናት ያመጡትን ምግብ የሚቀበላቸው አላገኙም፡፡
ወዳጄ ስንቶቻችን ነን አዲሱ ዓመት በጾም ቀን ዋለ ብለን የተከፋን?ይህው እንግዲህ በዓሉን ርዕዮት በርሃብ አሳልፋዋለች፡፡
የርዕዮት የርሃብ አድማ መልእክቱ ግልጽ ነው፡፡አቅም ያላት በራሷ ላይ በመሆኑ ራሷን በመቅጣት ህገ ወጦችን እምቢ አለቻቸው በዚህ ሰላማዊውን ታጋይ ማህተመ ጋንዲን መሰለችው፡፡ሰዎቹ እየበሉ በርሷ ላይ የሚፈጽሙት በደል እየተራበች በምታስተላልፈው መልእክት የህሊና ርሃብተኞች መሆናቸውን ይነግራቸዋል፡፡
ከቃሊቲ ውጪ ያለንም ምግብ ወደ አፋችን ባስጠጋን ቁጥር ርዕዮት የቃሊቲ አጥር ሳይበግራት ትመጣብናለች፡፡በምግብ ብቻ በማይኖርባት አለም በምግብ ብቻ ለመኖር ለምናደርገው ከንቱ ሩጫም ርሃቧ ትልቅ ደወል ይሆንብናል፡፡ 

በአዲስ ዓመት አስገራሚ ዜና ከቃሊቲ – ‹‹ከአንድነት›› የሚል ጽሁፍ የሰፈረበት ኬክ ቃሊቲ እንዳይገባ ተደረገ – ፍኖተ ነጻነት

September 11, 2013

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አመራሮች እድሜ ልክ ተፈርዶበት በቅጣት ቤት የሚገኘውን ሰላማዊ ታጋይ አንዷለም አራጌን
‹‹እንኳን አደረሰህ አዲሱ ዓመት ፍጹም ነጻነትህን የምትቀዳጅበት እንዲሆን እንመኛለን እንታገላለንም››
በሚል ስሜት ተነሳስተው ኬክ በማስጋገር
‹‹ከአንድነት››
የሚል ጽሁፍ አጽፈውበታል፡፡
የአንዷለም ጠያቄዎች በሩን አልፈው የያዙትን ኬክ ለማስፈተሸ አስቀማሽ ጋር እንደደረሱ አስቀማሹ ኬኩንና የተጻፈበትን እየተመለከተ አንዴ ቆዮኝ ብሎ ጥሏቸው ሄደ፡፡ አስቀማሹ ሃፊዎቹን አስከትሎ መጣ ፡፡የሆነ ነገር ትከሻቸው ላይ የደረደሩ ሃላፊ ኮስተር ብለው
ኬኩ አይገባም እናንተ ግን መግባት ትችላላችሁ›
ይላሉ፡፡ የኬኩ በደል ምን እንደሆነ ሲጠይቁም
‹‹ከአንድነት››
ይላል አሏቸው፡፡
አንድነት በምርጫ ቦርድ እውቅና የተቸረው ቢሮ ያለው ሰላማዊ ፓርቲ ነው፡፡ አንዷለምንም እናንተ ሽብርተኛ በማለት አሰራችሁት እንጂ እስከሚታሰርበት ቀን ድረስ
የፓርቲው የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊ ነበር፡፡››
ይሏቸዋል፡፡
ኬኩን አንድነት ከሚለው ውጪ ይዛችሁ መግባት ትችላላች ከዚህ ውጪ አናስተናግድም ሃላፊው ይላሉ፡፡ የአንድነት አመራሮች በበኩላቸው ኬኩ ህገ ወጥ ነገር እስካልሰፈረበት ድረስ አንድነት የሚለውን የፓርቲያችንን ስም አንፍቅም፡፡ ፍላጎታችሁ ሰላማዊውን ታጋይ እንዳንጠይቀው ለማድረግ በመሆኑ እኛም አንገባም በማለት ግቢውን ለቅቀው ወጥተውላቸዋል፡፡1185993_10151839340271870_915504360_n

የእባብ ልጅ እፉኝት !! ስለ አቶ ሽመልስ ከማል

September 11, 2013

(አቶ ሽመልስ ኃይለየሱስ) ጥቂት መረጃዎች ሃጂ ከማል ሐጂ በብሄር ቀቤና ሲሆኑ ሚስታቸው (የአቶ ሽመልስ ከማል እናት) ወሮ አበባ ሁሴን ደግሞ በአባት የጅማ ኦሮሞ፣ በእናት ወርጂ ናቸው። ሃጂ ከማል ሃጂ ኢትዮጵያ ሃጃጆችን መርተው በሄዱበት ወቅት ከንጉስ ፋይሰል ጋር ፎቶ ተነስተዋል። ገና ከጅምሩ የኃይለ ስላሴ ቤተመንግስት ድረስ ይገቡ ነበር።

የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ለማፈን መሳሪያ ሆነው ሰርተዋል። በመጨረሻ ንጉሱ  ክርስትና ያስነሷቸው ሲሆን ቤተሰባቸውን ሁሉም ክርስትና አስነስተዋል። ወሮ አበባ ሁሴን ለሃጂ ከማል ሃጂ አራት ወንድና አራት ሴት ልጆችን ወልደዋል። ሃጂ ከማል ክርስትና ከተነሱ በኋላ ኃይለየሱስ ተሰኝተዋል። አንዳንዶች ‹‹ቀድሞውኑ በሙስሊም ስም (ሽፋን) ኖሩ እንጂ ሙስሊም አልነበሩም፤ ኢስላምን የሚያጥላላና የሙስሊሙን የመብት ጥያቄ የማፈን ስራ ሲሰሩ ራሳቸውን ሃጂ ከማል ሃጂ ብለው ይጠራሉ እንጂ መች ሙስሊም ነበሩ?›› ይሏቸዋል።

የግለሰቡ መኖሪያ ቤት ጥቁር አንበሳ ጋር (ሜትሮሎጂ) እና የስልጤ መስጅድ መካከል ነበር። ግለሰቡ ሙስሊሙን ለማጠቃት ለአፄ ኃይለስላሴ ወሳኝ ስራ ስለሰሩ በ1956 የሰላም ማህበር ሲዘጋ በአውራጃ ገዥነትና የንብረት ክፍል ኃላፊነት ቦታዎች ላይ ተሹመው ነበር።ምንሊክ ሳልሳዊ

ስለ አቶ ሽመልስ ከማል ጥቂት መረጃዎች

‹‹አቶ ሽመልስ ከማል ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ተቀጥረው ከመስራታቸውም ባሻገር በጊዜው መንግስትን ይተች የነበረውን ‘’ኒሻን’’ የተባለ የራሳቸውን ጋዜጣ እስከማቋቋም የደረሱ ሲሆን፤ አቶ ሪድዋን ሁሴንም እንዲሁ ተቀዋሚ ፓርቲ መስርተው የፓርቲ ሊቀመንበር ከመሆናቸውም ባሻገር በ1992 ዓ.ም ፓርቲያቸውን ወክለው ለምርጫ በመቅረብ የኢህአዴግ ተወዳዳሪን በማሸነፍ ፓርላማ እስከመግባት እንደደረሱ ይታወሳል። እነዚህ ግለሰቦች ገዢው ፓርቲ ካመቻቸላቸው የጥቅመኝነት ስልጣን የሚያመጣላቸውን ጥቅም ተከትሎ ፍላጎታቸውን ማርካት ሲጀምሩ መሰረታዊ ከሆነው ለሰው ልጆች የመቆርቆር ሃሳባቸው ጋር እረፍት የሚነሳ የህሌና ጫና ውስጥ መግባታቸውን አይቀሬ ያደርገዋል።›› (ሙሉነህ አያሌውና ኃ/መስቀል በሸዋም የለም፣ የመለስ ውርሶች ታህሳስ 2005 ገፅ 210)
• የአቶ ሽመልስ አባት ሃጂ ከማል ሃጂ ሁለት መፅሃፍ የፃፉ ሲሆን የመጀመሪያው ‹‹የመካና መዲና ሚስጢር›› ሲሰኝ መፅሃፉ ከአዲስ አበባ ተነስተው ለሃጅ በሚል መካ የተጓዙበትን ሂደት ይተርካል። መጽሀፉ በተዘዋዋሪና በቀጥታ ኢስላምን ያጥላላል። ‹‹ለምን ድሬ ሼህ ሁሴን እያለ ሃጅ እንሄዳለን? በደንብ ብንይዘው አናጅናን (ሼህ ሁሴን) ለቱሪዝምና ለሃጅ ምትክ አድርገን እንጠቀማለን›› የሚል መልእክት ያስተላልፋል፡፡ ከዚህም አልፎ ‹‹ነብዩ (ሰዐወ) ድሬ ሼህ ሁሴንን ሳይዘይር ሃጅ የሄደ ሃጁ ተቀባይነት የለውም ብለዋል›› እስከማለት የደረሰ ቅጥፈት አካቷል፡፡ ‹‹ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ስለምን የዓረብኛ ስም ያወጣሉ? ለምን የአማርኛ መጠሪያ ስም አያወጡም?›› እስከማለት ይደርሳል፡፡ ኢስላም ሴቶችን እንደሚበድልና ሌሎች ተመሳሳይ ነጥቦችንም ይዳስሳል። ሌላኛው መፅሃፍ ‹‹የህሊና ግዳጅ›› የሚሰኝ ሲሆን ዓላማ አድርጎ የተፃፈው ‹‹የአፄ ኃይለስላሴ መንግስት ሙስሊሞችን ይበድላል›› ለሚሉ ሙስሊሞች ምላሽ እንዲሆን ነው። ጸሐፊው በመፅሃፋቸው ‹‹የአፄ ኃይለ ስላሴ መንግስት ሙስሊሙን ይበድላል ብለው ሃጅ ላይ ወረቀት የበተኑና በውጭ ሚዲያዎች የፃፉትን የተሳሳተና ሃሰተኛ ድርጊት እያየሁ አላህ የውመል ቂያማ እንዳይጠይቀኝ ነው ይህን የፃፍኩት›› ይሉናል። ‹‹ሰሃቦችን በስደት ሲመጡባት ያስተናገደች ሃበሻ እንዴት ሙስሊሞችን እየበደለች ነው ተብሎ ይፃፋል?›› ሲሉም ይሞግታሉ። ሁለቱም መፅሃፍቶች ያኔ በንጉሱ ዘመን ህዝበ ሙስሊሙን ያስቆጡ ነበሩ።
• ግለሰቡ ከ1953-1956 ‹‹የሰላም ማህበር›› የተባለው የሙስሊሞች ማህበር መሪ ነበሩ። ድርጅቱን ሙስሊም አባቶች የእስላም ማህበር ብለው ሲያቋቁሙ አፄ ኃይለ ስላሴ ስያሜውን ‹‹የሰላም ማህበር›› በሚል እንዲቀየር አስገደዱ። በድርጅቱ ውስጥ አመዴ ለማ (ፊታውራሪ) እና ሃጂ በሽር ዳውድን ጨምሮ በርካታ አባቶች ነበሩ። ስለ ግለሰቡ (ሐጂ ከማል) መሰሪነት ፊታውራሪ አመዴ ለማና ሃጂ በሽር ዳውድ ግለ ታሪካቸውን በፃፉበት መፅሃፍቶቻቸው ጠቅሰዋል። ልጃቸውንና የኢህአዴግ ባለስልጣንን አቶ ሽመልስ ከማልን በመፍራት ስማቸውን ሳይጠቅሱ ድርጊቱን ብቻ የጠቀሱ ቢሆንም ሃጂ በሽር ዳውድ ግን በረቂቁ ላይ ጠቅሰውት በታተመው ላይ ስማቸው ወጥቷል። ‹‹የግለሰቡ ስም ረቂቁን ባረመው ዶ/ር ኢድሪስ ሙሀመድ ተቀንሶ ይሆን?›› የሚለው ጥያቄ እንዳለ ሆኖ ስማቸው ቢወጣም ድርጊታቸው ግን በመጽሀፉ ውስጥ ተጠቅሷል።ምንሊክ ሳልሳዊ
• ሃጂ ከማል ሐጂ በብሄር ቀቤና ሲሆኑ ሚስታቸው (የአቶ ሽመልስ ከማል እናት) ወሮ አበባ ሁሴን ደግሞ በአባት የጅማ ኦሮሞ፣ በእናት ወርጂ ናቸው። ሃጂ ከማል ሃጂ ኢትዮጵያ ሃጃጆችን መርተው በሄዱበት ወቅት ከንጉስ ፋይሰል ጋር ፎቶ ተነስተዋል።
• ገና ከጅምሩ የኃይለ ስላሴ ቤተመንግስት ድረስ ይገቡ ነበር። የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ለማፈን መሳሪያ ሆነው ሰርተዋል። በመጨረሻ ንጉሱ ክርስትና ያስነሷቸው ሲሆን ቤተሰባቸውን ሁሉም ክርስትና አስነስተዋል። ወሮ አበባ ሁሴን ለሃጂ ከማል ሃጂ አራት ወንድና አራት ሴት ልጆችን ወልደዋል። ሃጂ ከማል ክርስትና ከተነሱ በኋላ ኃይለየሱስ ተሰኝተዋል። አንዳንዶች ‹‹ቀድሞውኑ በሙስሊም ስም (ሽፋን) ኖሩ እንጂ ሙስሊም አልነበሩም፤ ኢስላምን የሚያጥላላና የሙስሊሙን የመብት ጥያቄ የማፈን ስራ ሲሰሩ ራሳቸውን ሃጂ ከማል ሃጂ ብለው ይጠራሉ እንጂ መች ሙስሊም ነበሩ?›› ይሏቸዋል።
• የግለሰቡ መኖሪያ ቤት ጥቁር አንበሳ ጋር (ሜትሮሎጂ) እና የስልጤ መስጅድ መካከል ነበር። ግለሰቡ ሙስሊሙን ለማጠቃት ለአፄ ኃይለስላሴ ወሳኝ ስራ ስለሰሩ በ1956 የሰላም ማህበር ሲዘጋ በአውራጃ ገዥነትና የንብረት ክፍል ኃላፊነት ቦታዎች ላይ ተሹመው ነበር።
• በደርግ ጊዜ ጡረታ ወጥተው ታመው ወደ ቤት ገቡ። ለሁለት ወራት ያክል በአልጋ ላይ ተኝተው አንዲት ቃል ሳይወጣቸው በመጨረሻ ሞቱ። ሙስሊሞች ‹‹ዱዓችን ሰራ›› ብለው አላህን አመሰገኑ። በተክለ ሀይማኖት ቤተክርስቲያንም ተቀበሩ።
• ግለሰቡ ከመሞታቸው አስቀድሞ ገና ታመው በተኙበት ነበር ባለቤታቸው ወ/ሮ አበባ ሳዑዲ ዓረቢያ ይኖሩ ከነበሩና አቶ ከድር ማሜ ከተሰኙ የባሌ ሰው ጋር ቅርርብ የጀመሩት። ቅርርባቸው በመጀመሪያ ግለሰቡ ለእረፍት ሲመጡ የእሳቸውን ዕቃ በማሻሻጥ ላይ ነበር የተመሰረተው። በኋላ ላይም ግለሰቡ ወ/ሮ አበባን ጨምሮ ቤተሰቡ ወደ ኢስላም እንዲመለስ አደረጉ። ከአቶ ሽመልስ በስተቀርም ሁሉም ሰለሙ። ወ/ሮ አበባም ፀጉር መግለጥና ሱሪ መልበስ ትተው ሂጃብ መልበስ ጀመሩ። በኋላ ላይም ከአቶ ከድር ማሜ ጋር ተጋቡ፡፡
• ግለሰቡ ወ/ሮ አበባን ይዘው ወደ ሳዑዲ ገቡ። በዚያም ወ/ሮ አበባ እየሰሩ ልጆቻቸውን ማሳደግ ጀመሩ፡፡ የበኩር ልጅ የነበሩት አቶ ሽመልስ ግን ሊሰልሙ ፈቃደኛ አልነበሩም። እናታቸው ወ/ሮ አበባ ‹‹ሽመልስ ግትር ነው›› ይሉ ነበር።
• በህግ የተመረቁት አቶ ሽመልስ በከፍተኛ ፍ/ቤት ይሰሩ ነበር። ከዚያም ሪፖርተር ጋዜጣ፣ ቀጥሎም ኒሻን ጋዜጣ ላይ ይሰሩ ነበር። በዚህ ጊዜ ነበር ኢህአዴግ አስሮ የገረፋቸው። ከእስር ሲለቀቁ አቶ ሽመልስ ኢህአዴግን ተቀላቀሉ። በዚህን ጊዜ ነው ‹‹ሰለሙ›› የተባለው፤ ቤተሰቦቻቸው ግን አሁንም ድረስ ‹‹የሱ እስልምና ያን ያህል ነው›› ይላሉ (እናቱን ጨምሮ)። የአቶ ሽመልስ ወንድም መሰለ ኃይለየሱስ ሲሰልሙ አብደላ ሃጂ ከማል ተብለው ነበር፡፡ ሌላኛዋ መስከረም የምትባለው ደግሞ እንግሊዝ ኗሪ ናት፤ ሌላኛው ወንድማቸው የአየር መንገድ ቴክኒሻን የነበሩ ሲሆን እንግሊዝ ገብተዋል፤ ሌላኛው ደግሞ ኤሌክትሪሻን ሲሆኑ የሚኖሩት በአሜሪካ ነው፡፡ ወ/ሮ አበባም ልጆቻቸው ጋር አሜሪካና እንግሊዝ ይመላለሱ ነበር፡፡ የአቶ ሽመልስ ሌላኛዋ ሴት እህት ደግሞ በገነት ሆቴል ውስጥ፣ ኋላ ላይ ደግሞ መሿለኪያ አካባቢ ጅምር ቤት ነበራት፤ ባሏ ጀርመን ሃገር ስለሚኖር ጀርመን ትመላለሳለች።
• ከቤተሰቡ ኢስላምን አጥብቀው የያዙት ኢንጅነር አብደላ ከማል (ቀድሞ መሰለ ኃይለየሱስ ይባሉ የነበሩት) ናቸው፡፡ ሃይማኖተኛ መሆናቸውን ብዙዎች ይመሰሩላቸዋል።
• አቶ ሽመልስ ‹‹ሰለመ›› ከተባሉ በኋላ ከአህባሽ አደሬ ጓደኞቻቸው ጋር ይቅማሉ፤ ያጨሳሉ፤ ከነሱ ስርም አይጠፉም፤ በዚህ ጊዜ ነበር ወደ አህባሽ እምነት የገቡት።
• በ1992 ምርጫ ‹‹ለሙስሊሙ እሰራለሁ›› በሚል የአካባቢው ሙስሊሞች በመስጅድ ጀምዓ ፖስተር አሳትመውላቸው፣ በራሪ ወረቀት በትነውላቸው እንዲመረጡ ቀስቅሰዋል። ከተመረጡ በኋላ ግን ለግል ጥቅማቸውና ለፓርቲው መስራታቸውን ቀጥለዋል።
• በ1996 ሸህ አብደላ አል-ሃረሪ ወደ ኢትዮጵያ በመጡበት ጊዜ አቶ ሽመልስ ከማል ግለሰቡን ቦሌ ጃፓን ኤምባሲ አቅራቢያ ባለ ቪላ ቤት ሄደው ከጎበኙት ባለስልጣናት አንዱ ነበሩ። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነበር ፓርቲው ውስጥ ያሉትን ሙስሊሞች እኔ ብርቱና ታዋቂ ሸህ (ሸህ አብደላ አል-ሃረሪን) ይዣለሁ፤ እናንተም እርሳቸውን በሸህነት ያዙ፤ ያለ ሸህ እንዴት ይዘለቃል?›› በማለት ለማሳመን መጣር ጀመሩ፡፡ በኋላ ላይም በመኖሪያ ቤታቸውና በቢሮ የሸህ አብደላ አል-ሃረሪን ፎቶግራፍ በፍሬም በማድረግ ለጥፈዋል።
• አቶ ሽመልስ ከማል ከአህባሾች ጋር እንቅስቃሴያቸውን የቀጠሉ ሲሆን በተለያዩ አጋጣሚዎች መንግስት እያደረገ ባለው አህባሽን የማስፋፋት ስራ ላይ ተጠይቀው (በግል) ‹‹ልክና ተገቢ ነው፤ የሼኻችንን ስም የሚያጠፉት ውሃብዮች ናቸው፤ የሚጠቀስባቸው ሁሉ ሃሰት ነው›› በማለት ተከላክለዋል።
• አቶ ሽመልስ ከማል ከዚህ ቀደም ከጋብቻ ውጭ አንድ ልጅ የወለዱ ሲሆን ያሳድጉ የነበሩትም እናታቸው ነበሩ። በአሁኑ ሰዓት አቶ ሽመልስ ልክ እንደ አባታቸው ከመንግስት ጋር ሆነው ፀረ-ሙስሊም ንግግርና ድርጊት እየፈፀሙ ይገኛል።
• የአባትየው ሃጂ ከማል ሃጂ መፅሃፍቶች ሁለቱም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኬኔዲ ላይብረሪ ውስጥ ይገኛሉ። ‹‹የመካና መዲና ጉዞ ሚስጥር›› ከሚለው መጽሀፋቸው ኮት ተደርጎ ‹‹የኃይለ ስላሴ ዕቅድ በመጅሊስ ተሳካ›› በሚል ርዕስ ሚሌኒየም ላይ ተፅፎ ነበር። ከዚያ አርቲክል ሃሳቦችንና ጥቅሶችን ማግኘት ይቻላል። በመፅሃፍቶቹ ላይ የግለሰቡ ፎቶግራፍ ከነቤተሰባቸው (በ1960ዎቹ የተነሱት) አለበት። ካዕባ ፊት ለፊት የተነሱት ፎቶግራፍም አለበት። በመልክ አባትና ልጃቸው አቶ ሽመልስ ኮፒ ናቸው፤ በመልክም ሆነ በግብር!
• የፊታውራሪ አመዴ ለማና የሃጂ በሽር ዳውድ መፅሃፍም እንዲሁ በገበያ ላይ አለ።
• በ1990ዎቹ ሂክማ ጋዜጣ ላይ ‹‹ሃጂ ከማል ሃጂ ዛሬም ይኖሩ ይሆን?›› በሚል ርዕስ ስለ ግለሰቡ ድርጊትና ታሪክ ተፅፎ ነበር።
• የአፄ ኃይለስላሴ ደህንነት ለንጉሱ በፃፈው ሪፖርት ላይ ስለሃጂ ከማል ሃጂ ተጠቅሷል። ‹‹ሙስሊሙን እንዴት እንምታው?›› የሚል ነበር የሪፖርቱ ዓላማ። ሪፖርቱ ብሄራዊ ቤተ መፅሃፍትና ቤተ መዛግብት (ከኢቲቪ ጀርባ) ውስጥ በልዩ ጥበቃ ክፍል ውስጥ ይገኛል።ምንሊክ ሳልሳዊ

Tuesday, September 10, 2013

Hailemariam calls opposition parties that deny the existence of extremism in Ethiopia as “destructors and betrayers”

ESAT News
September 10, 2013
Prime Minister Hailemariam Dessalegn, in an interview with the government owned Daily Newspaper, Addis Zemen, said “if opposition political parties have democracy, good governance, development and peace as their agendas, then they should condemn extremism and terrorism standing with the government”.
Hailemariam also said “if these people (oppositions) think that there is no extremism and terrorism in Ethiopia, then these people are not living in Ethiopia. Not only in Ethiopia, they do not even know what is going on around the world. Thus, they do not the responsibility and the capacity to lead the people and practice politics. If they think they have the capacity, and if they keep on denying the fact that extremism and terrorism are growing in Ethiopia and is affecting the people, then the aim of these forces are not ready to compete and win in a peaceful, legal political system”.
He also advised all to impede the activities, to compete and in a peaceful, legal system and when they fail to win, if they say “if I lose it, the Nation should burn”, then they are destructors.
Hailemariam said in the protest, which was co-organised with the government, over 600,000 people took part showing that “extremist forces have been alienated from the people”.
It has been reported that the “anti-extremism” themed protest held in Addis Abeba last week has been directly led by the government and local district officials have been forcing citizens to put their signatures to affirm that they were taking part in the demonstration

Monday, September 9, 2013

የጠ/ሚ ባለቤት በቤተመንግስት ኑሮ መሰላቸታቸውን ገለጹ

ጳግሜ ፬(አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቀዳማዊት እመቤት ሮማን ተስፋዬ የቤተመንግስት ኑሮ የሚመች አለመሆኑንና የቀድሞ ጠ/ሚኒስትርንም አኗኗር በማየት ያዝኑ እንደነበር ተናግረዋል።

ቀዳማዊት እመቤቷ ትላንት ከወጣው መንግስታዊው ዘመን መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ የቤተመንግስት ሕይወት አስደሳች አይደለም ብለዋል፡፡ “ የቤተመንግስትን ሕይወት ለማንም ተመኝቼው አላውቅም፡፡ የሴቶች ጉዳይን ስናቋቁም ስምንት ወር ተመላልሼበታለሁ፡፡ ዛሬ እናንተ ተፈትሻችሁ እንደገባችሁት እኛም ተፈትሸን ነበር የምንገባው፡፡ እዚህ ግቢ ስገባ ወደጠ/ሚኒስትሩ ቤተሰቦች መኖሪያ ማዶ እያየሁ አዝንላቸው ነበር፤ግን ለሰው አላወራም፡፡ እዚህ ግቢ ውስጥ የሚኖር ሰው እንዴት ተበድሎአል እያልኩ እገረም ነበር፡፡ እና እኔን ኑሪ ቢሉኝ የማላደርገው መስሎ ይሰማኝ ነበር፡፡    ብለዋል፡፡

አስተዳደጌ ያስተማረኝ ከሌሎች ጋር በጋራ መኖርን ነው ያሉት ቀዳማዊት እመቤት ሮማን ራስን ለማዝናናት፣ዞር ብሎ ቡና ለመጠጣት ፣ዘመድ ጓደኛ እንደልብ ለማግኘት አስቸጋሪ መሆኑን በመጥቀስ ከዚህ አንጻር  የቤተመንግስት ሕይወት ነጻነት የለውም ሲሉ አስረድተዋል፡፡

“ለአንዳንዶች የቤተመንግስት ሕይወት የተንደላቀቀ መስሎ ይሰማቸዋል” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄም በአጭሩ እንደሚታሰበው ዓይነት አይደለም ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

የቀድሞ ኑሮአቸው ከአሁኑ በምን ይለይ እንደሆነ ተጠይቀውም የምግብ ማብሰያውና የአዘገጃጀቱ ሁኔታ ለየት እንደሚያደርገው ተናግረዋል፡፡ “ቤተመንግስት የበሰለው ነገር በንጽሕና የሚቀርብበት ነው፡፡ አዘጋጆቹ በዘርፉ ሙያው ያላቸው ናቸው፡፡ ብዙ ዓመት ያገለገሉ ወጥ ቤቶች አሉ፡፡ ከዚህ ውጪ እንግዲህ ጥበቃው አለ፤ይህው ነው” በማለት አስረድተዋል፡፡
ወ/ሮ ሮማን ከጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አብራክ የወለዱዋቸው የ23፣የ20 እና የ18 ዓመት ሶስት ሴት ልጆች እንዳሉዋቸውም በቃለምልልሳቸው ተናግረዋል፡፡

ባለቤታቸው አቶ ኃይለማርያም በአመራራቸው አስቸጋሪ ሁኔታ ያጋጥማቸው እንደሆን ተጠይቀውም ሲመልሱ አስቸጋሪ ነገር እንኩዋንስ አገር የሚያክል ነገር በመምራት ላይ ቀርቶ ታችም ሞልቱዋል፡፡ “አሁን ያለንበት የግሎባላይዜሽን ዘመን ነው፡፡ ብዙ ዓለምአቀፋዊ ይዘት ያላቸው ጠቃሚም ጎጂም ነገሮች አሉ፡፡ የኢትዮጽያ ሕዝብ አሁን ለመብቱ መታገል ተለማምዶአል፤ መጠየቅን ለምዶአል፡፡  ፈጣን ዕድገትን ይፈልጋል፡፡ ሠላምን፣ ተረጋግቶ መኖርን ይፈልጋል፡፡ መልካም አስተዳደርን ይፈልጋል፤ መልካም አስተዳዳር ሲባል ደግሞ በውስጡ ብዙ ጉዳዮች አሉት፡፡ እና ይህን ሁሉ ፍላጎት ይዞ ሕዝብን የሚያረካ አመራር መስጠት እያደገ የሚሄድ ነው” ብለዋል፡፡

ቀዳማዊት እመቤት ሮማን ከቀድሞዋ እመቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ቤተመንግስቱን ተረክበው ከባለቤታቸውና ልጆቻቸው ጋር የቤተመንግስት ኑሮ ከጀመሩ ገና አንድ ዓመት አልደፈኑም፡፡

ወ/ሮ ሮማን የቤተ-መንግስት ኑሮ ነጻነት እንዳይኖረው የተደረገበትን ምክንያት አላብራሩም፣ ነጻነት እንዲኖረው ለማድረግም ምን ምን እርምጃዎች መወሰድ እንዳለባቸው አልዘረዘሩም። ወ/ሮ ሮማን  ህዝቡ ስለመብቱ መታገል ተለማምዷል በማለት መናገራቸው በቅርቡ የተቃዋሚ ድርጅቶች ካደረጉት ሰልፍ ጋር ይያያዝ አይያያዝ ወይም፣ ይህ ልምምድ ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በሁዋላ ፣ በአቶ ሀይለማርያም የስልጣን ጊዜ የመጣ ክስተት መሆኑንና

ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ በኢትዮጵያ ውስጥ አክራሪነት የለም የሚሉ የተቃዋሚ ድርጅቶች አጥፊዎች፣ከሃዲዎች ናቸው አሉ

ጳግሜ ፬(አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትሩ ትላንትና እና ዛሬ ለሕትመት በበቃው ከመንግስታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ላይ እንደተናገሩት “የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በርግጥም ለኢትዮጽያ ሕዝብ ዴሞክራሲ፣መልካም አስተዳደር ልማትና ሠላምን ለማምጣት አጀንዳ አድርገው የሚንቀሳቀሱ ከሆነ አክራሪነትንና ሽብርተኝነትን ከመንግስት ጎን ተሰልፈው ሊያወግዙ ይገባል ብለዋል፡፡

” በኢትዮጽያ አክራሪነትና ሽብርተኝነት የለም ብለው የሚያስቡ ከሆነ እነዚህ ሰዎች በኢትዮጵያ ውስጥ የሉም ማለት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ብቻም ሳይሆን በዓለም ላይ እየተካሄደ ያለውን አያውቁም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የፖለቲካ ስራና ሕዝቡን ለመምራት የሚያስችል ትልቅ ኃላፊነትና ብቃቱ የላቸውም ማለት ነው፡፡  ብቃቱ አለን ብለው የሚያስቡ ከሆነ ዓለማዊውንና አገራዊ ሁኔታ በአግባቡ ገምግመው ሸብርተኛነትን እንደዚሁም አክራሪነትንና ጽንፈኝነትን በኢትዮጽያ እያቆጠቆጠ የመጣና ሕዝቡን በግላጭ እየጎዳ ያለ እንደሆነ ማንም

 የሚያውቀውን እየካዱ የሚሄዱ ከሆነ እነዚህ ሰዎች ዓላማቸው ሰላማዊ፣ሕጋዊና ለአገሪቱ የሚጠቅም የፖለቲካ ስርዓት
ውስጥ ተወዳድረው ለማሸነፍ የተዘጋጁ ኃይሎች አይደሉም ማለት ነው” ብለዋል፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አሁንም ቢሆን ከድርጊታቸው ታቅበው በሰላማዊ፣ሕጋዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ ተወዳድረው ማሸነፍ እንዳለባቸው የመከሩት አቶ ኃ/ማርያም ፣ ተወዳድረው ማሸነፍ ሲያቅታቸው ከእኔ የቀረ እንደሆነ አገሩቱዋ ትቀጣጠል

ዓይነት ሁኔታ ውስጥ የሚገቡ ከሆነ አጥፊዎች ናቸው ማለት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ አቶ ኃ/ማርያም ባለፈው ሳምንት እሁድ በተካሄደውና በመንግስት በሚደገፈው የአደባባይ ሰልፍ ከ600ሺ በላይ ሕዝብ
መውጣቱን አስታውሰው ይህ አክራሪ ኃይሎች ከሕዝቡ መነጠላቸውን ያሳያል ብለዋል፡፡ አክራሪና ጽንፈኛ ኃይሎች ከሕዝቡ ከተነጠሉ አስተዳደራዊና ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ቀላል ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት እሁድ በአዲስአበባ በመስቀል አደባባይ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠርተውታል የተባለው ሰልፍ በቀጥታ በመንግስት የተመራ ሲሆን የቀበሌ ሹማምንት በየቤቱ እየሄዱ ነዋሪዎች በሰልፉ ላይ እንዲገኙ የግዳጅ ፊርማ ሲያስፈርሙ እንደነበር መዘገቡ የሚታወስ ነው፡፡