Friday, August 16, 2013

የኢህአዴግ አባላት ክርስቶፎር ስሚዝ በሚያረቁት ህግ ላይ የተቃውሞ ፊርማ ማሰባሰብ ጀመሩ

ነሃሴ ፲(አስር)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከደጋፊዎቹ የመረጃ ለውውጥ ለመረዳት እንደተቻለው ኮንግረስ ማን ክሪስ ስሚዝ በቅርቡ በኢትዮጵያ ዙሪያ የግንቦት 7 መሪ ዶ/ር ብርሀኑ ነጋን፣ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ፣ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሀላፊ ሚ/ር ያማማቶ እና ሌሎችንም ታዋቂ ሰዎች በመጋበዝ በኢትዮጵያ ዙሪያ የተለያዩ ሀሳቦችን ማሰባሰባቸው ይታወቃል። ይህንንም ተከትሎ ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶችን እንድታከብርና ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን እንድትገነባ፣ ኮንግረሱ የህግ ረቂቅ እንደሚያዘጋጅ ሚ/ር ስሚዝ ገልጸዋል።

የህጉን መረቀቅ የተቃወሙት የኢህአዴግ ደጋፊዎች  ለሚ/ር ስሚዝ ደብዳቤ መላክ ጀምረዋል። በደብዳቤው ላይ ሚ/ር ስሚዝ በኢትዮጵያ መንግስት አሻባሪ የተባሉትን ሰዎች ለውውይት መጋበዛቸውን አውግዘዋል። በኢትዮጵያ ላይ የሚረቀቀው ህግ የአሜሪካንና የኢትዮጵያን ግንኙነት የሚያበላሽ መሆኑን፣ ኢትዮጵያ በውጭ ተጽኖ አቋሟን የማትቀይር መሆኗንና ሚ/ር ስሚዝም ኢትዮጵያን ለመደገፍ የሚያስችል የህግ ረቂቅ እንዲያዘጋጁ የገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች እየፈረሙ በሚልኩት ደብዳቤ ላይ ተመልክቷል።

አስቸኳይ በሚል ርእስ ለኢህአዴግ አባላት በተላከው የኢሜል መልዕክት ላይ ህጉ የሚረቀቅ ከሆነ በኢትዮጵያ ላይ ከባድ ተጽኖ እንደሚያስከትል ተመልክቷል።

ህዳሴ ካውንስል የሚባለው የኢህአዴግ አባላትንና ደጋፊዎችን የያዘው ቡድን የድጋፍ ፊርማ የማሰባሰብ ተልእኮ የተሰጠው ሲሆን፣ በአጠቃላይ እስከ 10 ሺ የሚደረሱ ፊርማዎችን አሰባስቦ የመላክ እቅድ ተይዟል።
የ1997 ዓም ምርጫን ተከትሎ በኢትዮጵያ ላይ በተመሳሳይ መንገድ የተረቀቀው ህግ ዲኤል ኤ ፓይፐር በተባለው ተቋም ድለላ እንዲቋረጥ መደረጉ ይታወቃል።

ሁሉም የትግራይ ህዝብ የህወሓት ደጋፊ ኣይደለም (አብርሃ ደስታ – ከትግራይ)

የትግራይ ህዝብና ህወሓት! (በአብርሃ ደስታ – ከትግራይ)

abraha desta
እውነት ነው። የህወሓት መሪዎች የትጥቅ ትግሉ ጀመሩት። ደርግ ዓማፅያኑ ለማጥፋትና ትግራይን ለመቆጣጠር የሃይል እርምጃ መውሰድ ጀመረ። ትግራይ የጦርነት ኣውድማ ሆነች። የትግራይ ገበሬዎች በሰላም የእርሻ ስራቸው ማከናወን ኣቃታቸው። የደርግ ወታደሮች ገበሬዎቹን ማስፈራራት፣ ሴቶችን መድፈር፣ ወጣቶችን በግደል (በጥርጣሬ) ተያያዙት።

በደርግ ኣሰራር የተማረረው የትግራይ ገበሬ ጫካ ገባ። እዛው ጫካ ከህወሓቶች ጋር ተቀላቀለ። ኣብዛኛው ታጋይ (ገበሬ ወይ ኣርሶ ኣደር) ደርግን ለመታገል ጠመንጃ ያነሳው በደርግ ስርዓት በነበረ ጥሩ ያልሆነ የሰለማዊ ሰዎች ኣያያዝ እንጂ እንደሚነገረን እንዳልሆነ እንዲታወቅልኝ። በዚ ምክንያት በትግራይ ከኣንድ ቤተሰብ ቢያንስ ኣንድ ታጋይ (የተሰዋም በህይወት ያለም) ነበር (ኣለ)።

ነገር ግን ሁሉም የትግራይ ተወላጅ የህወሓት ደጋፊ ኣይደለም። ምሳሌዎችን ልጥቀስ።

ምሳሌ ኣንድ

የትግራይ ኣርሶ ኣደር የታገለበት ዓላማና የመሪዎቹ ለየቅል ነበር። በ1983 ዓም የህወሓት መሪዎች ኣራት ኪሎ ቤተ መንግስት ከገቡ በኋላ የመሪዎቹ ዓላማ ለታጋይ ገበሬዎቹ ግልፅ ሆነ። በታጋዮቹና መሪዎች የዓላማ ልዩነት ግልፅ ሆነ። ታጋይ ገበሬዎቹ ጥያቄ ኣስነሱ። ጥያቂያቸው ምን ነበር??? ስድስት ጥያቄዎች:

(1) የኤርትራ ረፈረንደም (ነፃነት ወይ ባርነት የሚል ኣማራጭ) ስሕተት ነው፤ ለሀገር ኣንድነት መስራት ሲጠበቅብን ምንሊክ የሰራው ስሕተት እየደገምን ነው (ኃይለስላሴ እንኳ ለማስተካከል ሞክሮ ነበር)።

(2) የባህር በር (ወደብ) ያስፈልገናል። ሁሉም ነገር ለሻዕቢያ መስጠትና ኣገልጋይ መሆን በታሪክ ተጠያቂዎች ያደርገናል።

(3) የተታገልንበት ዓላማ መንገዱ እየሳተ ነው። ዓላማችን ስልጣን መያዝ ብቻ ኣልነበረም፤ ዲሞክራሲ ማስፈን ነው።

(4) ሙስና እየተስፋፋ ነው፣ ትግላችንና መስዋእትነቻን በኣሉታዊ መልኩ ይጎደዋል።

(5) የደርግ መሪዎች እንጂ ሁሉም የደርግ ወታደሮች ጠላቶቻችን ኣይደሉም፤ በመከላከያ ሰራዊታችን ይጠቃለሉ፣ ብዙ የሰለጠኑና የሀገር ሃብት ፈሰስ የተደረገባቸው ናቸው።

(6) ሻዕቢያ ሊወረን እየተዘጋጀ ነው፤ ወታደራዊ ዓቅሙ እየገነባ ነው። እኛ ደግሞ ሀገራዊ መከላከያ ሰራዊት ይኑረን።
የሚሉ ጥያቄዎች ተነሱ። ነገር ግን ጥያቄዎቹ ወድያው ሻዕቢያ ጀሮ ደረሱ። የሻዕቢያ መሪ ኢሳያስ ኣፈዎርቂ ከመለስ ዜናዊ ጋር ተነጋገሩበት። እንደዉጤቱም በ1985 ዓም ከ32, 000 በላይ የሚሆኑ የህወሓት ታጋዮች (ጥያቄ ያነሱ) እንዲባረሩ ተደረገ።

እንኳን የትግራይ ህዝብ በሙሉ፣ ህወሓት የታጋዮቹ ድጋፍ የለውም። መረጃ ስለሌለን ግን ሁሉም የትግራይ ህዝብ የህወሓት ደጋፊ ኣድርገን እናስባለን።

ምሳሌ ሁለት

ሑመራ ኣከባቢ ነው፣ ልዩ ስሙ ማይካድራ። ኣንድ የድሮ ታጋይ ሴት ሦስት ልጆች ብቻዋ ታሳድጋለች። የማይካድራ ህዝብ (እንደሌላው ሁሉ) በመለስ ሞት ምክንያት የሓዘን ሰልፍ እንዲያደርግ በካድሬዎች ታዘዋል። ሴትየዋ በሓዘን ሰልፉ ኣልተገኘችም። በፖሊስ ተይዛ እንድትታሰር ተደረገ (የታሰሩ ብዙ ናቸው ግን ይቺ ሴት መረጥኩኝ)። በፖሊስ ለምን እንዳልተገኘች ተጠየቀች።

ሴትየው: ስራ ስለበዛብኝ ነው ያልመጣሁት

ፖሊስ: ስራ ቢበዛብሽስ??? ስራ ከመለስ ይበልጣል?

ሴትየው: እኔ ኮ ብቻየን ሦስት ልጆች ኣሳድጋለሁ።
ፖሊስ: እና?
ሴትየው: እናማ ስራ ይበልጥብኛል። ደሞኮ ሞት ብርቅ ኣይደለም። መስዋእትነት ኮ እናውቀዋለን። ባሌን ታውቀዋለህ። ታጋይ ነበር። ድሮ ተሰውተዋል። ልጆቹ ማሳደግ ኣይችልም። የኔና የተሰዋው ባለቤቴ ሓላፊነት ተሸክሜ ልጆቻችን ለማሳደግ ሌት ተቀን መስራት ኣለብኝ። መለስ ከሞተ እናንተ ቅበሩት።

ፖሊስ: ኣንቺ ራስሽ ታጋይ ነበርሽ። ባልሽም ተሰውተዋል። መለስ ደግሞ የሰማእታት ኣርኣያ ነው። ስለዚ ልታዝኚለት ይገባል።

ሴትየው: መለስ ከምወደው ባሌ ኣይበልጥብኝም። ኣሳዛኝ መስዋእት ኮ ጫካ ዉስጥ ተሰውተው ያለቀባሪ ተጥለው የቀሩ፣ ሬሳቸው የጅብና ኣሞራ ሲሳይ የሆነ፣ (ኣብ ፈቀዶ ጎቦታትን ሽንጥሮታትን ዝተረፉ) እንጂ ……. መለስ ኮ ብዙ ነገር ኣይተዋል። ኣሁን ደግሞ በክብር፣ በስርዓት እያረፈ ነው። ባሌኮ የቀብር ስነስርዓት ኣልተደረገለትም። ምን ታካብዳላቹ?! በመለስ ሞት ግን ባሌና የትግል ጓደኞቼ (ስውኣት ብፆተይ) ኣስታውሼ ኣዝኛለሁ።

ሴትዮዋ ተፈታች። እኛ ግን የትግራይ ህዝብ በስርዓቱ ደስተኛ ይመስለናል። ዉስጡ እየነደደ ነው።

ምሳሌ ሦስት

በትግራይ ሓውዜን ኣከባቢ ነው። ኣንድ ኣብሮ ኣደጌ (ጓደኛየ) ኣስታወስኩ። ኣብረን እንማር ነበር (እስከ ስድስተኛ ክፍል)። ከስድስተኛ ክፍል በላይ ትምህርቱ መቀጠል ኣልቻለም። የልጁ ኣባት የህወሓት ታጋይ ነበር፤ ተሰውተዋል። ከኣያቶቹ ጋር ይኖራል። ኣያቶቹ ሦስት ልጆች ነበሯቸው። ሁሉም ተሰውተዋል። የቀራቸው የልጅ ልጃቸው (እሱ ብቻ) ነው።

ከሁለት ዓመት በፊት ልጁ ከመንግስት የወሰደውን ብድር መመለስ ስላልቻለ ወደ ሑመራ ኣከባቢ ይጠፋል። ኣያቶቹ ይታሰራሉ።

መታሰራቸው ሰምቶ መጣ። ብዙ ነገር ደረሰበት። የጣብያ (ቀበሌ) ካድሬዎቹ ተቃወማቸው። ካድሬዎቹ ኣስተዳዳሪዎችም ኣባቱ የተሰዋበት ዓላማ ተቃወመ ብለው የኣከባቢው ሰዎች ከነሱ ቤተሰብ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንዳያደርጉ ተነገራቸው። (ያ ሦስት ልጆች የተሰውበት ቤተሰብ እንዲገለል ተደረገ)። በኣሁኑ ሰዓት ግን ይሄን የማግለል ስትራተጂ እየተውት ይገኛሉ።

ምሳሌ ኣራት

በትግራይ ኣስተማሪዎች በገዢው ፓርቲ የሚደርሳቸው ኣስተዳደራዊና ኢኮኖሚያዊ በደል በመቃወም የተለያዩ እርምጃዎች የሚወስዱበት ኣጋጣሚ ኣለ። ተደጋጋሚ የስራ ማቆም ኣድማ ይደረጋል። ኣንዳንዴም የመምህርነት ስራው ጠቅልሎ የመተው ነገር ኣለ። ለምሳሌ ትግራይ ምስራቃዊ ዞን የመማር ማስተማር ሂደቱ ተስተጓጉሏል። ነጋሽ ኣከባቢ በሚገኝ ኣንድ ትምህርትቤት ሁሉንም ኣስተማሪዎች (ዳይሬክተሩ ጨምሮ) ትምህርትቤቱ ዘግተው ጠፍተዋል። ግን የሚዘግበው ሰው የለም።

ምሳሌ ኣምስት

በኣንዳንድ ኢትዮዽያውያን የትግራይ ተወላጆች የኢህኣዴግ መንግስት በመደገፍ ኢትዮዽያውያንን ይበድላሉ ብለው ያስባሉ። ነገር ግን ብዙዎች ይህንን እንደሚቃወሙ እንዴት ልንገራቹ?

ዓረና ትግራይ ፓርቲ በሺዎች የሚቆጠሩ ኣባላት እንዳሉት ሰምቻለሁ። እነዚህ ታድያ ህወሓት የሚቃወሙ ኣይደሉምን? ዴምህት የተባለ ኣማፂ ቡድን 60 ሺ ወታደሮች እንዳሉት ይነገራል። 60 ሺው ትክክል ላይሆን ይችላል። ግን ከ 20-25 ሺ ወታደር እንደሚኖረው ግን ይገመታል። እንዚህ ሁሉ የትግራይ ተወላጆች ናቸው።

በ1997/98 ዓም ከሻዕቢያ ሬድዮ በሰማሁት መረጃ መሰረት (ቃለ መጠይቅ ሲደረግባቸው) ብዙዎቹ የፌደራል ፖሊስ እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊት ኣባላት ነበሩ። ወደ ኤርትራ የገቡበት ምክንያት ሲያስረዱ በ1997 ና98 በነበረ የህዝብ ዓመፅ የተወሰደ እርምጃ በመቃወም ነበር። ስለዚ ሁሉም የትግራይ ህዝብ ገዢው ስርዓት ይደግፋል ብሎ ማሰብ ስሕተት ነው።

በሌላ በኩል ስናየው ደግሞ ስራ ነው። ኣንድ ሰው ስራ ፈልጎ ወደ ፖሊስነት ወይ ውትድርና ሊገባ ይችላል። የእንጀራ ጉዳይ ነው። ከገባ ታድያ (ደመወዙን ለማግኘት) የታዘዘውን መስራት ኣለበት። ካልሰራ ይባረራል፤ ከተባረረ መኖር ኣይችልም (ሌላ ስራ እስካላገኘ ድረስ)። ስለዚ ጠንክሮ ቢሰራ ኣይደንቀኝም።

ባጠቃላይ የትግራይ ህዝብ በሙሉ የህወሓት ደጋፊ ነው ማለት ኣይቻልም። ብዙ የሚቃወም ኣለ። ብዙ የሚጨቆን ኣለ። በትግራይ የሌለው ጭቆናን የሚያጋልጥ ነው። በሌሎች ኣከባቢዎች (ከትግራይ ውጭ) ሰው ሲታሰር ወይ ሲገደል የሚናገርለት ወይ የሚጮህለት ወገን ኣለው። በትግራይ ግን የለም። ኣንዱ ሲታፈን ሌላው ኣብሮ ዝም ይላል። ይሄ ነው ልዩነቱ እንጂ በትግራይ ጭቆና ስለሌለ ኣይደለም።

በመጨረሻም

እንደው ሁሉንም ትተን፣ የትግራይ ህዝብ ህወሓትን ቢደግፍ (ከህወሓት ጎን ቢቆም) ችግሩ ምንድነው? ኣንድ ህዝብ የፈለገውን የመደገፍ ወይ የመቃወም መብቱ የተጠበቀ ነው። የትግራይ ህዝብ ህወሓትን (በፍላጎቱ ኣይደግፍም እንጂ) ቢደገፍ ደስተኛ ነኝ። ምክንያቱ ‘ለምን ህወሓትን ትደግፋለህ?’ ሊባል ኣይገባም። ሌሎች ህዝቦች ህወሓትን የመቃወም መብት ያላቸው ያህል የትግራይ ህዝብም የመደገፍ መብት ኣለው።

ስለዚ (1) ሁሉንም የትግራይ ህዝብ (ብዙዎች እንደሚያስቡት) የህወሓት ደጋፊ ኣለመሆኑ እንዲታወቅ። (2) የትግራይ ህዝብ ህወሓትን ይደግፋል ብሎ መውቀስም ተገቢ ኣይደለም

http://ethioforum.org/





















 

The Heroic Ethiopian Journalist Eskinder Nega

August 15, 2013
by Betre Yacob
Ethiopian prominent Journalist and blogger Eskinder Naga is one of those who have been arrested, interrogated, and threatened in Ethiopia, for exercising freedom of expression. He is currently serving his jail sentence in Kality, a notoriously brutal prison in Addis Ababa, where dozens of political prisoners are suffering. Judged a “terrorist” by the regime’s kangaroo court, he was sentenced to 18 years in prison in 2012, along with other critical journalists and bloggers.
Ethiopia is one of the leading repressive nations in the world. Particularly, the repression of freedom of expression is the most severe in this poor East African nation more than any other country. According to Amnesty International, during the past three years only, over 100 prominent journalists and influential political activists were prosecuted on fabricated charges of terrorism, and too many others were also subjected to harassment, intimidation, threat, and other violence.
Eskinder Naga, 45, is a brave and most admirable journalist and blogger that the world has ever seen. What makes him exceptional is his commitment to freedom of speech even in the face of grave risks. According to his profile, he has courageously worked as a journalist for more than twenty one years and been jailed 8 times in the past two decades only. Until his last day in freedom, he courageously wrote about the political crisis of his impoverished country Ethiopia, and bravely fought falsehoods, brutality, and oppression with the power of words. Today, this exceptional courage, resistance, and commitment to freedom of expression have made him a glorious hero in Ethiopia and a symbol of press freedom in Africa.
Eskinder served as a vital voice for independent journalism in Ethiopia that hungers for access to free information, and as inspiration for many journalists and human right activists. He found 4 most prominent newspapers which were eventually closed by the Ethiopian regime that continues its tight grip on press freedom. He has also worked as a columnist at different publications, and been a contributor of many Ethiopian online medias and news forums.
Eskinder was arrested on 14 September 2011, just a week after he had posted an article which criticises the anti-terrorism law that had been adapted by the Ethiopian government in 2009 to target perceived opponents, stifle dissent, and silence journalists. He was detained without charge and access to a lawyer. The government announced that he was accused of organizing terrorism nearly two months later. During the trial, the prosecutors claimed that Eskinder had been coordinating different activities of terrorism using his constitutional rights to freedom of expression as a cover. The evidences submitted by the prosecutors were, however, relied on his public writings and other journalistic activities. Based on such evidences, Eskinder was finally said “terrorist”, and sentenced to 18 years in prison on 10 November 2012, under the anti-terrorism law he questioned.
When Eskinder was arrested, he was bringing his 6 years old son from kindergarten. According to his wife Serkalem Fasil, the police stopped them on their way and would not even let Eskinder bring the kid home. She said that they had brutally split the boy from his father. She further said that the police officers had been recording and taking pictures as the boy had been crawling on the ground and crying watching his father who had been thrown around and handcuffed. The Committee to Protect Journalists asserted that the charge against Eskinder was baseless and politically motivated in reprisal for his writings, adding: “his conviction reiterates that Ethiopia will not hesitate to punish a probing press by imprisoning journalists or pushing them into exile in misusing the law to silence critical and independent reportings.”
The saddest reality is that the very harsh sentence handed down to Eskinder Nega was not the end but the beginning. On September 2012, the Federal High Court further ordered the property of Eskinder Nega (which includes a house and car) to be confiscated. But, surprisingly, notwithstanding these all painful punishments, Eskinder continues writing his dissenting views. For instance, in his recent article entitled “From Ethiopia’s Gulag”, which was smuggled from the prison, he criticised the Ethiopian brutal regime and recommended the US government to take appropriate action against it. In this article, he also warned that Ethiopia could be imploded in the near future as the result of the standing political and humanitarian crisis.
Born in 1968 in Addis Ababa, Eskinder had studied high school and college in the United States of America (USA). Upon completing his study, he returned to his home land Ethiopia and began to work as a journalist in 1991, with the objective to hold the Ethiopian government accountable to its democratic promise and promote democracy and freedom.
In 2005, following the controversial election in which government troops brutally killed more than 193 unarmed peaceful protesters and wounded another 763, Eskinder was arrested and charged with serious crimes such as treason and genocide. This was for the 3rd time that he was jailed for practicing journalism, but what makes this one too different was that he was not alone but with his then pregnant wife, Serkalem Fasil, a journalist and newspaper publisher, who later gave birth to a son with no pre-natal care in her very small and crowded cell. Eskinder and his wife were released in 2007, by presidential pardon. Up on his release, Eskinder was banned from publishing his newspaper–named Satenaw, and denied a license to launch a new publication. But, this didn’t stop him from speaking out. He was able to write his dissenting views online, until he got arrested.
Eskinder Nega is the recipient of the PEN/Barbara Goldsmith Freedom to Write Award.

Thursday, August 15, 2013

ነግ በኔ አለማለት በወረፋ ለመጠቃት መዘጋጀት ነው!


የወያኔ ጉጅሌ የህዝባችንን መሰረታዊ መብቶች ነጥቆና ረግጦ ለመግዛት ከወሰነ የቆየ ቢሆንም ዛሬ ህዝቡ ብሶቱ እየገነፈለ አደባባይ መውጣቱ አርበትብቶታል። ወያኔ የህዝብን ጥያቄና ኮሽታ በሰማ ቁጥር የህዝብን ደም በግፍ የሚያፈሰውም ከዚህ መርበትበትና ብረገጋው ጋር በተያያዘ ነው።

ከአላንዳች ህዘባዊ መሰረት በጠመንጃ እና በፖሊስ ሃይል ላይ ብቻ ተንጠልጥሎ ቁም ስቅላችንን የሚያሳየን ወያኔ ከህዝብ የበለጠ ሃይል ኖሮት አይደለም። የወያኔ ጉልበትና ግፍ የፀናብን ተከፋፍለን በየተራ ለመቀጥቀጥ ስለፈቀድንለት ብቻ ነው። ወያኔን ያጎለበተው በአንዱ የህብረተሰብ ክፍል ላይ መዐት ሲወርድ ሌሎቻችን ወረፋችን እስኪደርስ ቆመን በመመልከታችን ነው ። ባለፈው ሳምንት የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን የ ክቡር በዓላቸውን በሚያከብሩበት ቅዱስ ቀን በደም ያጠመቃቸው ክርስቲያኑና ሌላው ተመልካች ይሆናል ብሎ ስላመነ ነው። የኦሮሞው ጥቃት ለአማራው ምንም እንዳልሆነ፣ የአማራው ጥቃት ለኦሮሞው፣ ለደቡቡና ለትግሬው ምኑም እንዳልሆነ፣ የደቡቡ ጥቃት ሌሎችን የማያገባና የማይመለከት ነዉ ብለን ስለምናምን ለወያኔ ጥቃት ተመችተነዋል። በአጠቃላይ “ነግ በኔ” ማለት ትተናል። በወረፋ ለማጥቃት ወያኔ አመቻችቶናል። እኛም ተመቻችተናል። የኢድ አልፈጥር እለት እናቶችን፣ ሽማግሌዎችንና ህጻነትን ሳይመርጥ እንደእባብ በዱላ ሲቀጠቅጥ የዋለው የወያኔ ልዩ ሃይል የተማመነው “ነገ በኔ” የሚል ህዝብ ይኖራል ብሎ አለማሰቡና፣ የመከፋፈያ ሴራዪ ሰርቶልኛል ብሎ በማመኑ ነው። ነገሩ ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ ነው። ሁላችንንም ባይንቀን ኖሮ ጥቂቶቻችንን አይደፍረንም ነበር።

ዛሬ የወያኔ ጥቃት ሰለባ ያልሆነ፣ በወረፋው ያልተመታ፣ ያልተገደለ፣ ያልታሰረ፣ ያልተሰደደ፣ ከመኖሪያው ያልተፈናቀለ፣ ከስራው ያልተባረረ የህብረተሰብ ክፍል የለም። ሰራተኛ፣ ምሁራን፣ ገበሬዎች፣ የብሄር ብሄረሰብ ስብስብ፣ ተማሪ፣ መመህር ወዘተ የጥቃት ወረፋ ያልደረሰው የለም።

ጥያቄው ለምን በወረፋ እንደበደባለን? እስከመቼስ ነው ወያኔ የአንዳንዶቻችንን ጥየቄ የሌሎቻችን ማስፈራሪያ እንዲያደርገውና የጥቃት እርምጃውን በየተራ እንዲያፈራረቅብን የምንፈቅድለት? የሚለው ነው ።

ግንቦት 7 ለፍትህ፣ ለነጻነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ዛሬ ወያኔ በሙስሊሙ ወገኖቻችን ላይ የከፈተው የጥቃት ዘመቻ በጋራ መመከት ካልተቻለ ነገ በክርስቲያኑ ወይም በሌላው እምነት ተከታይ ላይ ላለመደገሙ ማረጋገጫ የለም ብሎ ያምናል::

የኢትዮጵያ ህዝብ ከቀን ወደቀን ለነጻነቱና ለማንነቱ ሲል የሚያደርገው ትግልና እንቅስቃሴ እንቅልፍ የነሳቸው እና የእግር ዉስጥ እሳት የሆነባቸው ህወሃቶች፤ የሀገራችንን አንድነት ህልውና እና ማንነት ለማጥፋት፣ ዜጎች ስለመብታቸው እንዳይጠይቁ እየነጣጠሉ እና እየከፋፈሉ በደም የተጨማለቀ እጃቸውን እንደገና በደም እያለቀለቁ ስለሃይማኖታቸው ነጻነት፣ ስለፍትህ እጦት፣ ስለዲሞክራሲ መስፈን በጮኹ አንደበቶች፤ አንደበታቸውን በጥይት ሲዘጉ ማየት በወያኔ ጎራ በእነ ኢቲቪ መንደር የእነ አስረሽ ምችው ድለቃ የተለመደ ነው። ስለዚህ የማንኛውም ዜጋ የእኩልነት፣ የፍትህ፣ የነጻነት ጥያቄ ምላሹ ሞትና መታሰር ከሆነ እስከ መቼ ተራ እንጠብቃለን?

ተቻችለንና ተከባብረን የኖርን ኢትዮጵያውያን ለወያኔ ከፋፍለህ ግዛ እና አጥቃ ፖሊሲ መመቸት የለብንም። በደስታና በሀዘን ሳንለያይ የዘለቀውን አንድነታችን አሁን በዚህ አስከፊና ጨካኝ ወያኔያዊ ድርጊት አዝነን ከንፈራችንን ለሞቱት እና ለታሰሩት በመምጠጥ አይደለም ቁጭታችንና ሀዘናችን መግለጽ ያለብን። ለተጠቁ ወገኖቻችን መከታ ጋሻ ሆነናቸው ቁስላቸው ቁስላችን፣ ደማቸው ደማችን፣ ሀዘናቸው ሀዘናችን፣ ሆኖ ነገ በኔ በሚል ዛሬ ሁሉንም የትግል ስልቶች ተጠቅመን አለንላችሁ በሚል አንድ ላይ ሆነን ስንታገል ብቻ ነው።ቋንቋና ሃይማኖት ቢለያየንም በወያኔ ግፍ ግን ሁላችንም አንድ መሆናችንን ለአፍታ እንኳን መዘንጋት በወረፋ ለመቀጥቀጥ መዘጋጀት ነውና በወያኔ ላይ በአንድነት እንነሳ!!

ግንቦት 7 ንቅናቄ የሀገራችን ህልውናን ለማዳን፣ የሁሉም ዜጋ የእምነት ነጻነት፣ እኩልነት፣ የሰው ልጆች መሰረታዊ ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ ዛሬም በቆራጥ ልጆቹ መሰዋእትነት የወያኔን ዘረኛ አክራሪነት ለመታገል ቃል ኪዳኑን ያድሳል። መላው የሀገራችን ህዝብ ሆይ፡ የነጻነት ጥያቄ ድምፃችሁ፣ ድምጻችን ነው። የጥቃት ወላፈኑ አቃጥሎ ሳይጨርሰን፣ ዳር ሆነን ላንመለከት ወያኔን በማናቸውም መንገድ ታግለን ልንጥለው፣ ልናስወግደው ትግሉን ጀምረናል፡፡ ያለውን ሰቆቃ በማስቆም በወያኔ ከርሰ መቃብር ላይ ኢትዮጵያችን የሁሉም እምነት ተከታዮች ተከባብረውና ተፋቅረው በነጻነት የሚኖሩበት አገር ትሆን ዘንድ እንታገል:: ኑ ተቀላቀሉን! ዳር ሆኖ መመልከቱ ይብቃ! በቃ!!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

የአቶ መለስ መሞት ወደ ውጭ በወጣው 11 ቢሊዮን ዶላር ምርመራ ላይ ተጽኖ መፍጠሩ ተገለጸ

ነሃሴ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከኢትዩጵያ በህገ ወጥ የተሻገረውን 11 ቢሊዩን ዶላር ለማስመለስ እና የባለስልጣናትን የሀብት መጠን ይፋ ለማድረግ የተያዘው ቀጠሮ በመለስ ሞት ምክንያት ዳር ሳይደርስ መቅረቱን የስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኪሚሺን ኪሚሺነር አቶ ዓሊ ሱሊማን ተናገሩ፡፡

አቶ አሊ በጠቅላይ ሚኒስተር መልስ ዜናዊ የስራ ትጋት እና አርቆ  አሳቢነት ምስክርነት ለመስጠት በ ኢቲቪ የፖሊስ ፕሮግራም ላይ በተጠየቁበት ስዓት ነው ይህን የተናገሩት። ይሁን እንጅ የፖሊስ ፕሮግራም  መረጃውን እስካሁን ለህዝብ ይፋ አላደረገውም።

የስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኪሚሺን ኪሚሺነር አቶ ዓሊ ሱለይማን ከመለስ ሞት ጋር በተያያዘ ጥያቄ ቀርቦላቸው ሲመልሱ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሐብት ተጣርቶ የተጠናቀቀ ቢሆንም እስካሁን ይፋ ማደርግ አልተቻለም።  ‹‹የመለስ ሀብት  ቀርቶ የአኗኗራቸውን ሁኔታ እንኳ ምን እንደሚመስል የኢትዮጵያ ሕዝብ ተመልክቶታል፡፡ የመለስን ማንነትና የአኗኗር ሁናቴ ከማንም ያልተለየ ስለመሆኑ ከሞታቸው በስተጀርባ ተመልክተነዋል ያሉት አቶ አሊ፣

‹‹መለስ ይህ ነው የሚባል በምዝገባ የሚታወቅ ሀብት የላቸውም፡፡ እንግዲህ ወደፊት ታሪክ የሚያወጣቸው እና የሚዘክራቸው በርካታ እውነታዎች ይኖራሉ›› በማለት የአቶ መለስን ሀብት ይፋ ለማድረግ የሳቸው መሞት አሉታዊ ተጽኖ ማሳደሩን ገልጸዋል። ‹‹መለስ ምንም አልነበራቸውም›› ሲሉም አቶ አሊ አክለዋል፡፡

በኢትዩጵያ የፀረ ሙስና ተቋም የተቋቁመው በሕዝብ ፣ በዕርዳታ ሰጪ አገራት  እና በዓለማዓቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ግፊት መሆኑን የጠቀሱት አቶ አሊ፣  በሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር አሳሳቢነት ኮሚሽኑን መንግስት ሲያቋቁም የማስተማርና የመመርመሩን ስልጣን ሰጥቶ የመክሰሱን ስልጣን ላለፉት አመታት ሳይሰጥ መቆየቱን ጠቁመዋል።

‹‹መደበኛውን የገንዘብ ዝውውር ባልተከተለ መልኩ በተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ወደ ውጭ ባንኮች 11 ቢሊዮን ዶላር ያህል ገንዘብ እንደ ሸሸ ግሎባል ፋይናንሺያል ኢንተግሪቲን ዋቢ በማድረግ የተለያዩ የኅትመት ውጤቶች አሰነብበዋል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር መወያየታቸውን የገለጹት አቶ አሊ ሱሊማን፣‹‹መጠኑ 11 ቢሊዮን ብር የሚደርስ ይሁን አይሁን ማረጋገጫ የሚሻ ጉዳይ ሆኖ ሀገሪቱ በዚህ ገንዘብ መጠን ተርፎ የሚሸሸ ሐብት አላት ዎይ? የሚለውም ምላሽ የሚሻ ጉዳይ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ችግሩ በየትኛውም ሀገር ያለ ነው ያሉት ኮሚሺነር አሊ ፣ የገንዘቡ መጠን ምንም ያህል ቢሆንም በጉዳዩ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ውይይት አድርገው እንደነበር አጽንኦት ሰጥተው መነጋገራቸውን ገልጸዋል፡፡

ጠ/ሚኒስትሩ  የተጠቀሰው ገንዘብ መጠን አንድ መቶኛም ቢሆን በተባለው መንገድ የሚንቀሳቀስ ስለመሆኑ አስተማማኝ መረጃ ይገኝ እንደሆን ችግሩን ለመጋፈጥ መረጃውን ከለቀቀው ተቋም ዘንድ እንዲረጋገጥ ቁርጠኛ አቋም ይዘው እንደነበረ አቶ ዓሊ ተናግረዋል።  ይህንንም ተከትሎ ኮሚሽነር ዓሊ ለዓለም ባንክ ስብሰባ በሰኔ ወር መጨረሻ አካባቢ ዋሽንግተን ሄደው በነበረበት ወቅት መረጃውን እንዳወጣ ከተነገረለት ግሎባል ፋይናንሺያል ኢንተግሪቲ ተቋም ኃላፊዎች ጋር ተነጋግረው እንደተመለሱ ስለደረሰበት ሁኔታ ለመነጋገር ቀጠሮ እንዲያዝላቸው ባደረጉበት ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ህመም ሲሰሙ እንደተውት እና ጠቅላይ ሚንስትሩ ህይወታቸው ቢያልፍም በሂደት የሚኬድበት ጉዳይ እንዲሆን  ገልፀዋል፡፡

ችግሩን ሙሉ ለሙሉ ማስወገድ ባይቻልም በአስመጪና ላኪዎች  እና በሌሎችም ክፍተት ባላቸው ሂደቶች ላይ አሰራሩን በማጠናከር ችግሩን ለመቀነስ እንደሚሰሩም አስገንዝበዋል፡፡አቶ መለስ ዜናዊ በ6 ሺ ብር ደመዎዝ ብቻ ይተዳደሩ እንደነበር ወ/ሮ አዜብ መናገራቸው ይታወሳል።

ይሁን እንጅ ከሁለት አመታት በፊት አንድ የስፓኒያ ጋዜጣ ወ/ሮ አዜብ በአፍሪካ ካሉ ቀዳማይ እመቤቶች  በአባካኝነት ከሚጠቀሱት በግንባር ቀደምነት ከሚጠቀሱት አንዷ መሆናቸውን ገልጾ ነበር።
ጸረ ሙስና ኮሚሽን አቶ መለስ ከሞቱ ከአንድ አመት በሁዋላም ከአቶ መለስ ውጭ ያሉትን ባለስልጣኖች ሀብት ይፋ አላደረገም። ህዝቡ በአገኘው አጋጣሚ ሆኑ ኮሚሽኑ የባለስልጣኖችን ሀብት ይፋ እንዲያደርግ ሲጠይቅ ቆይቷል።

ነሀሴ 26ን በደቦ ሸኝተን 2006 ዓ.ምን በተስፋ!

(አርአያ ጌታቸው)
 
semayawiparty
የዘንደሮ ክረምት ከቀደምቶቹ በጥቂቱ ጠንከር ያለና ብዙዎችን በተለይም አዲስ አበቤዎችን እያማረረ ነው፡፡ ሌላው “በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ” የሚያስብለው ደግሞ የከተማዋ መንገዶች በአብዛኛው ጥገና ላይ መሆናቸውና በዚህም ሳቢያ የበርካቶች መኖርያና የንግድ ሱቆቻቸው መፍረሳቸው ነው፡፡ ይህንን ሁኔታ በምናብ ለማየት ለምትፈልጉ ቅዳሜ ነሀሴ 4 ቀን 2005ዓ.ም በወጣቺው  ፋክት መጽሄት ላይ ፕ/ር መስፍን እንዲህ ሲሉ ገልጸዋታል “አዲስ አበባ በመሬት መናወጥ ፈራርሳ በመጠገን ላይ ያለች ከተማ ትመስል የለም እንዴ”:: ብቻ ክረምቱም ወደማለፉ እየተቃረበ አዲሱንም ዘመን ለመቀበል ሽርጉዱ ሳይጀመር አይቀርም፡፡
 
ምን ክረምቱ ብቻ ፖለቲካውም ክረምቱን ተከትሎ ከ8 ዓመታት በኋላ እሱም ጠንከር ያለ ይመስላል፡፡ ላለፉት ጥቂት ዓመታት በሀገር ውስጥ ሲደረጉ የነበሩት የፖለቲካ ፓርቲ እንቅስቃሴዎች በአመት ውስጥ እንኳ አንድ የሚረባ ለዜና የሚሆን ስራ ሳይሰሩ በውስጥ ጉዳያቸው ተጠምደው፤ የሀገሪቷን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ከህብረተሰቡ እኩል ተመልካች መስለው ነበር፡፡ ምንም እንኳ የአሁኑ የፖለቲካ ጡዘት መነቃቃት የፈጠረው  ግንቦት 25 በአዲስ አበባ የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ነው ብንልም፤ ላለፉት 2 ዓመታት ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ሰላማዊ ትግሉን በጽናት ሲያካሄዱ የቆዩት የሙስሊሞቹን እንቅስቃሴ ለአፍታም ሳንዘነጋ መሆን ይኖርበታል፡፡
 
ወደዋናው የጽሁፌ አላማ ስመለስ የፊታችን ነሀሴ 26 ቀን 2005ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ አዘጋጅነት የሚካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ከመድረሱ በፊት ከኛ ምን ይጠበቃል የሚለውን መነሻ ሀሳብ ለማቅረብ ነው፡፡ ከዚህ ቀን ቀደም ብሎ አንድነት ፓርቲ ከአዲስ አበባ ውጪ የሚያደርጋቸውን በርካት ሰላማዊ ሰልፎችን እና ስብሰባዎችን ሳልዘነጋ ነው፡፡ ይህ የነሀሴ 26 ግን በይዘቱም በጥያቄዎቹም እንዲሁም በቦታውም ለየት ያለ በመሆኑ የተለየ ትኩረት ይሻል፡፡ በመጀመሪያ በፓርቲው የተነሱት ጥያቄዎች በቀጥታ ከድርጅቱ የተገኛኙ ሳይሆኑ አጠቃላይ ድርጅቱ እታገልለታለሁ ያለውን ህብረተሰብ የሚወክሉ በመሆናቸውም ጭምር ነው፡፡
የተነሱት አራት መሰረታዊ ጥያቄዎች ለማስታወስ ያህል፡-
  • የመጀመሪያው “ለፍትህና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መስፈን የሚታገሉ ጋዜጠኞችን፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና አባላትን በአሸባሪነት ስም ማሰርና ማሰቃየትን አጥብቀን የምንቃወም መሆኑንና እስረኞችንም እንዲፈታ”
  • በሁለተኛ ደረጃ የተነሳው ደግሞ “የዜጎችን ሰብዓዊና ሕገ መንግስታዊ መብቶችን በመጣስ ለዘመናት ከኖሩበት ቦታ ኢሰብዓዊ በሆነ ድርጊት በታጠቁ ኃይሎች እንዲፈናቀሉ ማድረግ የዘር ማጥፋት ወንጀል በመሆኑ የድርጊቱ ፈፃሚዎች ለፍርድ እንዲቀርቡና የተፈናቀሉት ዜጎችም በአስቸኳይ ወደየመኖሪያቸው ተመልሰው እንዲቋቋሙ በመንግስትም ሆነ በግብረ ሰናይ ድርጅቶች አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግላቸው”
  • ሶስተኛው ጥያቄ  “መንግስት በኃይማኖታችን ጣልቃ አይግባ፣ የእምነት ስርዓታችንና የሃይማኖት መሪዎቻችንን እምነታችን በሚፈቅደው ብቻ እናከናውን ያሉ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችን በአሸባሪነት ወንጀል በመክሰስ በእስር እንዲማቅቁና ሰብዓዊ መብታቸው እንዲጣስ መደረጉ እንዲቆምና ያነሷቸውም የእምነት ነፃነት ጥያቄዎቻቸው እንዲከበር”
  • በአራተኛነት የተነሳው “የኑሮ ዉድነትን፣ የሥራ አጥነትንና በሙስና የተዘፈቁ የመንግስት ሌቦችን የሚቆጣጠርባቸውን መንገዶችና ፖሊሲዎች በማዉጣት ሐገራችንን ከቀውስና ዜጎችንም ከሰቆቃ እንዲያወጣ”
የሚል ነው ይህ ጥያቄ በአብዛኛው የስርአቱ ተቃዋሚዎችን የሚወክል በመሆኑ እንዲሁም ይህንን ጥያቄ ለመደገፍ እና ለዚህ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ድጋፍ ለማድረግ የማንንም የፖለቲካ ፍልስፍና ወይም አቋም የማይጻረር እና ሰማያዊ ፓርቲም የራሱን የፖለቲካ ፍልስፍናም ሆነ አቋም ለመጫን ያልሞከረበት በአጠቃላይ የእያንዳንዱ ሀገር ወዳድ ዜጋ መሰረታዊ ጥያቄዎች ናቸው ብዬ ስለማምን ነው፡፡
 
semayawiparty
ምንም እንኳ ፓርቲው ለነዚህ ጥያቄዎች ከመንግስት መልስ እንዲሰጠው ለ3 ወር ጊዜ የሰጠው ቢሆንም፤ ስርዓቱ ግን ይባስ ብሎ አፈናውን በማጠናከር ከማሰርና ከማፈናቀል በዘለለ ንጹሀን ዜጎችን አንድ ተራ ሽፍታ እንኳ የማይፈጽማቸውን በህጻናት እና በእናቶች ላይ ተኩስ መክፈትና መግደል ጀምሯል፡፡
 
ይህ ምናልባት ለኢህአዴግ መራሹ መንግስት አዲስ ታሪኩ ባይሆንም ከ20 ዓመታት በላይ ድርጅቱን በፍጹም አምባገነናዊነት የመሩት አቶ መለስ ሞትን ተከትሎ ተስፋ ላደረጉ ጥቂቶች የስርዓቱን መበስበስና የማይቀየር መሆኑን አሳይቷቸዋል፡፡ ይህንን ስርዓት ከህብረተሰቡ ጫንቃ ላይ ለማንሳት የሚደረገው የሰላማዊ ትግልም ከዚህ የስርዓቱ ባህሪ አንጻር ፍጹም መራርና ከባድ መስዋዕቶችን ሊያስከፍን እንደሚችል መገመት አያዳግትም፡፡
 
ከነዚህ የሰላማዊ ትግሎች ውስጥ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም የተጀመረው የሰማያዊ ፓርቲ እንቅስቃሴ አንዱ ነው፡፡ ፓርቲው ከሰልፉ በኋላ ሲያደርጋቸው የነበሩት እንቅስቃሴዎችም የሚቀጥለው እንቅስቃሴው ከሰልፍ በዘለለ የሰላማዊ ትግል መርሆችን እየተከተለ መሆኑን ያሳያል፡፡ ከዚሁ ጋርም ተያይዞ ነሀሴ 26 የሚደረገው ሰልፍ አዲስ አበባ ላይ መሆኑ የሰልፉ ስኬታማነት አንድነት ፓርቲ በክልሎች ከጀመረው የማንቃት ስራ ጋር ተዳምሮ ለመላዊ የሀገሪቱ ህዝብ ትልቅ መነቃቃትንና ቁርጠኝነት ሊፈጥር ይችላል “አዲስ አበባ ላይ ያካፋው ክልል ላይ ይዘንባል” እንዲሉ ፡፡
 
እንግዲህ ለዚህ ሰልፍ ወደ 15 ያህል ቀናት ይቀሩታል፡፡ በነዚህ በተቀሩት ቀናቶች የዚች ሀገር የቁልቁለት ጉዞ የሚያሳስባችሁ በተለይ ለኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች፤ ለድረ ገጽ ባለቤቶች እና ለማህበረ ድረ ገጽ አክቲቪስቶች ይህንን የነሀሴ 26 ሰልፍ ከቀደመው ግንቦት 25 ሰልፍ ላቅ ባለና የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ጥያቄ ያካተተ ይሆን ዘንድ ከእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ በተለየ መልኩ ያለባችሁን ሀላፊነት ከቡድናዊ ስሜት ወጥታችሁ በሀገራችን በአሁኑ ሰዓት ያለውን የሚዲያ ክፍተት በመሙላት የተጀመረውን ትግል አንድ እርምጃ ወደፊት እንድትገፉ በኢትዮጵያዊ ዜግነቴ እጠይቃለሁ፡፡ እንደምታውቁት በአዲስ አበባ ከሌሎቹ ከተሞች በተለየ የተሻለ የኢንተርኔት ስርጭት ያለበት በመሆኑ በዚህ ከተማ የሚገኘውን ማህበረሰብ ለመቀስቀስና ለማስተማር ማህበራዊ ድረ ገጾች የፈረጠመ አቅም አላቸው፡፡
አርአያ ጌታቸው
አርአያ ጌታቸው
 
የዚህን ክረምት ድብታ ከፖለቲካ ድብታችን ጋር ነሀሴ 26 ሸኝተን የሚቀጥለውን 2006 ዓ.ም በተስፋ እና በመነቃቃት እንጀምረው ዘንድ የሁላችንንም ያላሰለሰ ጥረት ይጠይቃል፡፡ በድጋሚ የሚቀጥሉትን 15 ቀናት ሁላችንም በትጋት እንስራ፡፡
 
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
 

በኖርዌይ “የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል” ድጋፍ አሰባሳቢ ጊዜያዊ ግብረ ኃይል መግለጫ

Ginbot 7 Popular Force (G7PF) is established by freedom-loving Ethiopiansኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን እንደ ወያኔ ዘመን የተዋረዱበት የተናቁበትና የተበደሉበት ጊዜ የለም።በአሁኑ ወቅት አገሪቱና ህዝቧ ከፊታቸው የተጋረጠው ችግር የመሰረታዊ የዲሞክራሲና የሰብኣዊ መብቶች አለመከበር ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የሕልውና ጥያቄና ኢትዮጵያ እንደ አገር የመቀጠልና ያለመቀጠል ጉዳይ ሆኖዋል።

የትጥቅ ትግልም በኢትዮጵያ የወቅቱ የፖለቲካ ሁናቴ እንደ አንድ ምናልባትም እንደ ብቸኛ የትግል አማራጭ እየሆነ ከመጣ ውሎ አድሯል።

“የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል” የወያኔ ግፍና በደል በአንገፈገፋቸው በሃገር ወዳድና ለህዝብ ተቆርቋሪ በሆኑ ወጣቶች፣ ምሁራንና በተለያዩ ዜጎች የተመሰረተ ድርጅት ነው። የዚህ ኃይል ራዕይ ደግሞ ሕዝብ የስልጣን ባለቤት እንዲሆን፣የዜጎች መብቶች፣አገራዊ አንድነት፣ደህንነትንና ጥቅም እንዲከበሩና ጠንካራ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንድትገነባ መስዋዕትነትን በመክፈል አስተዋጾ ማድረግ ነው።

“የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል” ወያኔን በኃይል ለማስወገድ ፣ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ የስልጣን ሽግግር በአገሪቱ እንዲኖር ማስቻል እና ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ጋር ያልወገኑ ነፃ ጠንካራና ብቃት ያላቸው ህገ-መንግስታዊ የመከላከያ፣ የፖሊስ፣የደህንነት ተቋማት እንዲኖሩ አስተዋጽዎ ማድረግን እንደ  አንድ ግብ ይዞ የተነሳ ኃይል ነው።

“በግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል” ውስጥ የተመቻቸ ኑሮአቸውን፣ቤተሰቦቻቸውን እና የሚወዱትን አገርና የሰለጠኑበትን ሙያ እርግፍ አድርገው በመተው ትእግስትን የሚፈታተን መከራና እንግልት የሚበዛበትን የትጥቅ ትግል የተቀላቀሉ በርካታ ምሁራን ይገኙበታል። ይህም ከዚህ በፊት በስፋት የሚታወቀውን “ያልተማረውን ዜጋ ወደ ጦር ግንባር” የመላክና የመስክ ላይ ትግሉም በትምህርት ላይ የተመሰረተ አመራር የማጣት ችግርን የቀረፈ እና ታጋዩ ህብረተሰብ በዕውቀት ላይ በመመርኮዝ “ለምንና ለማን ነው የምታገለውና የምሰዋው” ጥያቄን በሚገባና በጥልቀት የተገነዘበ ኃይል ነው።

ይህንን ለኢትዮጵያና ሕዝቧ መልካም ራዕይ አንግቦ የተነሳ ሠራዊት በተቻለ ሁሉ መደገፍና ደጀንነታችንን ማረጋገጥ የውዴታ ግዴታችን መሆኑን የተገነዘብን በኖርዌይ የምንኖር ኢትዮጵያዊያን አንድ ግዜያዊ  የድጋፍ አሰባሳቢ ግብረኃይል በማቋቋም ከፍተኛ እንቅስቃሴ ጀምረናል።

በግብረኃይሉ መርሃግብር መሰረት መስከረም 28 ቀን 2013 (እ.ኤ.አ) “የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል” አመራር ተወካዮች በሚገኙበት ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በኦስሎ ከተማ ተዘጋጅቷል።

በፕሮግራሙ ላይ ውይይት፣ የገቢ ማሰባሰቢያና የመዝናኛ መርሃግብሮች ተካተዋል። በመሆኑም ነፃነት ለኢትዮጵያ ሃገራችንና ለሕዝቧ ከዚያም በላይ ለእኔ ስብዕና ያስፈልገኛል ብለን የምናምን ሁሉ በዝግጅቱ ላይ በመገኘት ደጀንነታችንን “ለግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል”  እንድናሳይ ጥሪያችንን በትህትና እናቀርባለን።

ነፃነት፣ ፍትህ፣እኩልነትና ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ተከብራ ትኖራለች !!!

በኖርዌይ “የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል”  ድጋፍ አሰባሳቢ ግዜያዊ ኮሚቴ

ኦገስት 14፣ 2013 ኖርዌይ፣ ኦስሎ

የፌስ ቡክ ኢቬንቱን እንዲጎበኙ ተጋብዘዋል
 https://www.facebook.com/events/561604620565318/?fref=ts

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከ‹‹ጽንፈኞች›› ጋር እየተንቀሳቀሱ ነው ያሏቸውን ተቃዋሚ ፓርቲዎች አስጠነቀቁ

-ኦፌኮ ለሙስሊሙ ኅብረተሰብ ሕጋዊ ጥያቄዎች አዎንታዊ ምላሽ እንዲሰጥ ጠየቀ
በኢድ አል ፈጥር በዓልና ከዚያ ቀደም ብሎ በአዲስ አበባና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተቀሰቀሱትን ተቃውሞዎችና ግጭቶች ምክንያት በማድረግ ሰሞኑን መግለጫ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ ‹‹ጽንፈኞች›› ካሏቸው ጋር በመሆን ተቃዋሚ ፓርቲዎች አገር ለማወክ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን በመግለጽ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሰጡ፡፡

ተቃዋሚ ፓርቲዎች ግን የመንግሥትን ወቀሳና ማስጠንቀቂያ ውድቅ በማድረግ መላው ኢትዮጵያዊ ትግሉን እንዲያጠናከር ጥሪ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ 
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ከዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ በአገሪቱ እየተስተዋለ የሚገኘውን የእስልምና እምነት ተከታዮች ተቃውሞ አስመልክቶ ‹‹ጽንፈኞች በሃይማኖት ስም በመንግሥት ሥራ ጣልቃ እየገቡ ነው፤›› ብለዋል፡፡
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ‹‹ጽንፈኞች የሃይማኖት አባቶችን በመግደል፣ በማሸማቀቅ፣ ሕዝበ ሙስሊሙን መፈናፈኛ አሳጥተን የራሳችንን እምነት በኃይል እንጭናለን በሚል እሳቤ ሁከት እየፈጠሩ ነው፤›› ብለዋል፡፡
 
‹‹መንግሥትን መቆጣጠር ይገባል፡፡ የሸሪዓ ሕግን መንግሥት መተግበር አለበት፡፡ ከዚህ ውጭ ምንም ዓይነት እምነትም ሆነ ሃይማኖት አይኖርም፤›› በሚል እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡ መንግሥት ይህ ሁሉ ነገር እየሆነ በትዕግሥት ጉዳዩን ሲከታተል መቆየቱን የሚገልጹት አቶ ኃይለ ማርያም፣ ‹‹መንግሥት ይህንን ያደረገበት ምክንያት ጽንፈኞቹን ከእስልምና እምነት ተከታዮች ለመለየት ነው፤›› ብለዋል፡፡
 
‹‹ጽንፈኞችን›› ለይቶ ለማውጣት መንግሥት የመረጠው ትዕግሥትና ያደረገው ጥረት ውጤታማ በመሆኑ፣ ሕጋዊ ዕርምጃ መውሰድ እንደተጀመረና ይህም ከዚህ በኋላ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡ 
 
‹‹ከጽንፈኞች ጋር ጋብቻ ፈጥረው የአገሪቱን ሰላም ለማወክ እየተንቀሳቀሱ ያሉ አንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እየተሰጣቸው ያለውን ማስጠንቀቂያ የማይቀበሉ ከሆነ ሕጋዊ ዕርምጃ ይወስድባቸዋል፤›› ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡
 
በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋለውን የእስልምና እምነት ተከታዮች ተቃውሞ በተመለከተ በተለያዩ የመንግሥት ኃላፊዎች ተመሳሳይ መግለጫና ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ የቆየ ቢሆንም፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን በዚህ ጉዳይ ላይ እምብዛም ሲናገሩ አይስተዋሉም ነበር፡፡ 
 
የሰሞኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ ግን መንግሥት ጠንከር ያለ ዕርምጃ ለመውሰድ አቋም የያዘ አስመስሎታል፡፡ የእስልምና እምነት ተከታዮች ‹‹መንግሥት የሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይግባ›› የሚል መሠረታዊ ጥያቄ ላይ በመንተራስ እያቀረቡ የሚገኙትን ተቃውሞና ጥያቄ በመደገፍ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ይታወቃል፡፡ 
 
በኢትዮጵያ ውስጥ ሃይማኖትና መንግሥት አንዱ በአንዱ ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገቡ በሕገ መንግሥቱ የሰፈረ መሆኑን በመግለጽ፣ መንግሥት ከሚነሳው ተቃውሞ ጀርባ ጽንፈኝነትና የአንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሌላ ዓላማ መኖሩን በመግለጽ እያስጠነቀቀ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የመንግሥትን ውንጀላ ውድቅ በማድረግ የእስልምና እምነት ተከታዮች እያነሱ የሚገኙትን ተቃውሞ በመደገፍ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡ በአገሪቱ ከሚገኙት ተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ሰማያዊ ፓርቲ፣ መድረክና የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ይገኙበታል፡፡ 
 
የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ባለፈው ሰኞ ባወጣው መግለጫ፣ ‹‹መንግሥት በሕገ መንግሥቱ በተደነገገው መንገድ ብቻ የዜጐችን የእምነት ነፃነት በማክበር፣ ለሙስሊሙ ኅብረተሰብ ሰላማዊና ሕጋዊ ጥያቄዎች አዎንታዊ መልስ መስጠት አለበት፤›› ብሏል፡፡ 
 
መንግሥት የሙስሊሙ ኅብረተሰብን ጥያቄ በሕጋዊ መንገድ ከመመለስ ይልቅ ጣልቃ ገብነቱን የሚቃወሙ የእምነቱን ተከታዮች በአሸባሪነት በመፈረጅ ማሰር፣ መደብደብና መግደልን መፍትሔ አድርጎታል፡፡ በመሆኑም ይህ የመንግሥት ተግባር ለአገር ሰላምና ደኅንነት አስጊ ሁኔታ ፈጥሯል በማለት መግለጫ አውጥቷል፡፡
 
መንግሥት የሙስሊሙ ኅብረተሰብን ሕጋዊና ሰላማዊ ጥያቄዎች በመደፍጠጥ ጭካኔና ሰብዓዊነት የጐደለው ተግባር እየፈጸመ ነው በማለት ኦፌኮ ባወጣው መግለጫ አውግዟል፡፡ 
 
በማከልም፣ ‹‹ሙስሊሙም ሆነ ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ የኢሕአዴግን ኢ-ሕገ መንግሥታዊ ድርጊት በመገንዘብ ትግሉን በሕጋዊና በሰላማዊ መንገድ አጠናክሮ በመቀጠል አንድነቱንና ለሰላማዊ ትግል ትብብሩን ይግለጽ፤›› ሲል ጥሪውን አቅርቧል፡፡ 

Wednesday, August 14, 2013

ኢህአዴግ ከከፍተኛ አበል ጋር ፀረ አንድነት ፓርቲ ስልጠና አዘጋጀ

August 14, 2013
ፍኖተ ነፃነት

አንድነት ፓርቲ የጀመረውን ህዝባዊ ንቅናቄ ለማስተጓጎል ከፍተኛ አበል በመክፈል ለአባላቱ ስልጠና ማዘጋጀቱን ለኢህአዴግ ቅርበት ያላቸው የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ጠቆሙ፡፡

አንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት በሚል መሪ ቃል የጀመረው ህዝባዊ ንቅናቄ ህዝባዊ ተቀባይነት ማግኘቱንና በስኬት መቀጠሉን ተከትሎ ኢህአዴግ “አንድነት ፓርቲንና ንቅናቄውን እንዴት ማስቆም ይቻላል” በሚል በከፍተኛ አመራሮቹ ውይይት ካደረገ በኋላ በመላ ሀገሪቱ ፀረ አንድነት ፓርቲ ስልጠና “ጠንካራ” ላላቸው አባላቱ ለመስጠት መዘጋጀቱን የሚገልፁት ምንጮቹ “ለስልጠናው ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ተመድቧል፤ ኢቲቪና የክልል ሬዲዮ ጣቢያዎችና የመንግስት ጋዜጦች አንድነት ፓርቲ የሸሪአ ህግን በኢትዮጵያ ተግባራዊ ለማድረግ ከሚንቀሳቀሱ ሽብርተኞች ጋር እየሰራ ነው የሚል የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ እንዲከፍቱ ጥብቅ መመሪያ ደርሷቸዋል፡፡” በማለት ጨምረው ገልፀዋል፡፡

ምንጮቹ አክለውም “ኢህአዴግ ከየቀበሌው  እየመረጠ ስልጠና የሚሰጣቸው አባላቱ የአንድነት ፓርቲ አመራሮችንና አባላትን በማሸማቀቅ፣በማስፈራራት፣ በቤተሰቦቻቸውና በሃይማኖት አባቶቻቸው በኩልም ከፖለቲካ እንዲወጡ ተፅዕኖ እንዲደርስባቸው የተቻላቸውን እንዲያደርጉ የሚያበቃ ነው” ብለዋል፡፡

የፍኖተ ነፃነት ምንጮች እንዳረጋገጡት የዚሁ ስልጠና አካል የሆነ  ስልጠና ከነገ ጀምሮ በደቡብ ወሎ ዞን ኩታበር ወረዳ ከየቀበሌው ለተውጣጡ ከ200 በላይ ለሚሆኑ የኢህአዴግ አባላት ለሁለት ቀን ይሰጣል፡፡

ETHIOPIA WITH POUPET HAILEMARIAM DESALEGN

Ethiopia has become the biggest aid recipient in Africa, though Meles’s dead sprit of government is only able to partially stabilize either the country or region.
Ethiopia’s political system and society have grown increasingly unstable largely because the TPLF has become increasingly repressive, while failing to implement the policy of ethnic federalism it devised over twenty two years ago to accommodate the land’s varied ethnic identities. The result has been greater political centralization, with concomitant ethnicisation of grievances. The closure of political space has removed any legitimate means for people to channel those grievances.


The government has encroached on social expression and curbed journalists, politicians, non-gov­ern­men­tal organizations and religious freedoms. The cumulative effect is growing popular discontent, as well as radicalization along religious and ethnic lines. Meles adroitly navigated a number of internal crises and kept TPLF factions under his tight control. Without him, however, the weaknesses of the regime he built will be more starkly exposed.

All-TPLF affair, even if masked beneath the constitution, the umbrella of the EPRDF and the prompt elevation of the deputy prime minister, Hailemariam Desalegn, to acting head of government. Given the opacity of the inner workings of the government and army, it is impossible to say exactly what it will look like and who will end up in charge. Nonetheless, any likely outcome suggests a much weaker government, a more influential security apparatus and endangered internal stability. The political opposition, largely forced into exile by TPLF, will remain too fragmented and feeble to play a considerable role, unless brought on board in an internationally-brokered process. The weakened Tigrayan elite, confronted with the nation’s ethnic and religious cleavages, will be forced to rely on greater repression if it is to maintain power and control over other ethnic elites. Ethno-religious divisions and social unrest are likely to present genuine threats to the state’s long-term stability and cohesion.
So our Ethiopia is now a days on the right time to avoid TPLF/EPRDF and we Ethiopians are make hand to hand and stand up against the regime.
ETHIOPIA WITH OUT TPLF IS FREE!!!


August 14, 2013
 
ፕሮፌሰር በፍቃዱ ደግፌ
Semayawi Party- Ethiopia (Facebook)


ፕሮፌሰር በፍቃዱ ደግፌ በተደጋጋሚ ጊዜአት በአደባባይ ከማይታዩ የሀገራችን አንጋፋ ሊህቃን አንዱ ናቸው። ምሁሩ በበርካታ መድረኮች ባለመቅረብ በቁጥብነታቸው ቢታወቁም ባገኙት መድረክ ግን አነጋጋሪ ርዕሰ ጉዳዮችን ያነሳሉ።

ባለፈው እሁድ ሰማያዊ ፓርቲ ባዘጋጀው የመወያያ መድረክ ላይ ቀርበው ታዳሚዎችን የመሰጠና ያወያየ ኃሳብ አንሸራሽረዋል። በፓርቲው ጽ/ቤት የተገኙ ወጣት ምሁራንም የፕሮፌሰሩን ኀሳብ በሌላ ኀሳብ በመሞገት ምሁራዊ አስተሳሰቦችና ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ጥልቅና ማራኪ ውይይት ተደርጓል።

ፕሮፌሰር በፍቃዱ በመወያያ መድረኩ ላይ ቀርበው የመነጋገሪያ ኀሳቦችን ያቀረቡት ፓርቲው በወጣቶች የሚመራ በመሆኑ አቅጣጫ የሚጠቁሙ ኀሳቦችን ለማሳየት ነበር። ጎን ለጐንም ሀገራዊ ርዕሰ ጉዳዮች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል። ፕሮፌሰሩ በዋናነት የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ማነቆዎች ላይ የመንግስትና የሕዝቡ ሚና ምን መሆን እንዳለበት የራሳቸውን የመፍትሄ ኀሳቦች ሰጥተዋል። ከሁሉም በፊት ግን ፕሮፌሰሩ የሰሞኑ ወቅታዊና አነጋጋሪ ጉዳይ ስለሆነው የኃይማኖት ጉዳይ የተናገሩትን እናስቀድም። ፕሮፌሰሩ በኢትዮጵያ ክርስትናና እስልምና ምን ያህል መስተጋብር ፈጥረው እየኖሩ መሆኑን ከራሳቸው የቤተሰብ አወቃቀር በመነሳት የተናገሩት የታዳሚውን ቀልብ ያሳበ ነበር።

Befekadu Degefe, former Economics Research Fellow at The New School for Social Research
ፕሮፌሰር በፍቃዱ ደግፌ
 
‘‘የእኔ ቅድመ አያት ሙስሊም ናቸው። እናቴ ጌጤ ትባላለች። አያቴ ደግሞ ብሩ ይባላሉ። ቅድመ አያቴ መንሱር የሚባሉ ሲሆን፤ የመንሱር አባት ደግሞ በፈቃዱ ይባላሉ። እኔ በቅድመ አያቴ ስም ነው የምጠራው። ስሜን ያወጡልኝ አያቴ ናቸው። ቀኝ አዝማች ብሩ ይባላሉ። በፍቃዱ ሙስሊም ነው ያገቡት፤ ሰባት ልጆች ወልደው ነበር። ሦስቱ ሙስሊም ሲሆኑ አራቱ ክርስቲያን ሆነዋል። ከነዚህ ውስጥ ሴቷ ሙስሊም አግብታ አብራ ኖራለች። አብረን ነው የምንበላው አብረን ነው የምንኖረው’’ በማለት ለሀይማኖቶች መቀራረብ ከዚህ የተሻለ ማነፃፀሪያ የለም ብለዋል።

ፕሮፌሰሩ ወደ ዋናው ነጥባቸው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ሲመለሱ መነሻ ያደረጉት የሀገሪቱን የድህነት ደረጃ በመጥቀስ ነበር። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በአለም ላይ ማሊ ከምትባል ምዕራብ አፍሪካዊት ሀገር ብቻ ነው የምትሻለው ብለዋል።

‘‘ሀገሪቷ የገበሬና የገጠሬ ሀገር ናት። ስለዚህ ግብርና ትልቁ ስራ ነው። የሀገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት ምንጭ ግብርና ነው። ግብርናው ወደ ኢንዱስትሪ አድጎ ብዙ ሰራተኛ መቀጠር አለበት። ሰራተኛው ከግብርናው ወደ ኢንዱስትሪ መምጣት አለበት’’ ያሉት ፕሮፌሰሩ አሁን ግን ገበሬው ከራሱ አልፎ ከተማን መመገብ ብቻ ሳይሆን የእራሱም ህልውና አደጋ ላይ መውደቁን ነው የጠቀሱት።
‘‘ኢትዮጵያ ባት የሌለው ገበሬ ነው ያላት። ባት የሌለውም ማለት እግሩ አጥንት ነው። የዚህ ሀገር የግብርና ስራ ጉልበት በጣም የሚፈልግ ቢሆንም ገበሬው አቅሙን ያጣ ነው። ይሄ ሀገር እራሱን መመገብ ስላልቻለ በፈረንጅ ቸርነት ያለ ሀገር ነው’’ ሲሉ የጠቀሱት ፕሮፌሰር በፍቃዱ ‘‘ከተሞችም የድህነት መሸሸጊያና መጠለያ ሆነዋል’’ ብለዋል።

ገበሬው የተጎዳ በመሆኑና በቂ ምርት የማያመርት ስለሆነ የኑሮ ውድነት መከሰቱን የጠቀሱት ምሁሩ የኑሮ ውድነቱ ምስጢር አይደለም ብለዋል። የሰራ አጥነት በከተሞች የተስፋፋው ከገጠር ወደ ከተማ የሚፈልሰውና ድህነትን የሚሸሸው ሰው ስለበዛ ነው። ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገው ፍልሰት የተመረቁ ተማሪዎችንም እንደሚያካትት በመግለፅ ከተሞች የሰራ አጥነት ማዕከል ለመሆን በመገደዳቸው የችግር ቋት ሆነዋል።

በአሁኑ ወቅት ያለውን የሀገሪቱን ችግር ለመፍታት አንድ ትውልድ መስዋዕት መሆን እንዳለበትም ጠቅሰዋል። በተለይ አሁን ያለው ትውልድ የድሎት ኑሮ ለመኖር ያለው ዕድል የጠበበ መሆኑንም አስገንዝበዋል።
የሀገሪቱ ሁኔታ ለመቀየር ግብርና ብቸኛው አማራጭ መሆኑንም የጠቀሱት ፕሮፌሰር በፍቃዱ፤ አሁን ሀገሪቱ የምትመካበት ምንም ሀብት ወይም ጥሪት የላትም ብለዋል። ‘‘ሀገሪቱ ቤንዚን የላትም። በእርግጥ ቤኒዚን ሌሎች ሀገሮችን ሲያባልግ አይተናል። ኢትዮጵያ ቤንዚን ከማግኘቷ በፊት ሕዝቡ በጥረቱ መልማት እንደሚችል ማመን አለበት። ከቤኒዚን በፊት የስራ ዲሲፕሊን መቅደም አለበት። ጥረቱ ካለ ቤንዚን ብቻ ሳይሆን ዩራኒየምንም ሆነ ወርቁንና ፕላቲኒየምን አውጥቶ መጠቀም ይቻላል። ጥረቱ መጀመር ያለበት ደግሞ ከግብርናው ነው’’ ብለዋል።

የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ከግብርናው መጀመር አለበት ከተባለ የሀገሪቱ የመሬት ስሪትና ይዞታ መታየት እንዳለበት ነው የገለፁት። ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት ገጠሩ በአንድ አካባቢ ታፍኖ እንዲቀመጥ በመደረጉ ገበሬዎች የሚያርሱት የመሬት ስፋት በከፍተኛ ደረጃ እያነሰ ነው። በመንግስት ስታስቲክስ መሰረት በኢትዮጵያ ከአንድ ሄክታር በታች የሚያርሱ ገበሬዎች ወደ 11 ሚሊዮን ገበሬዎች ናቸው። ከሁለት ሄክታር በታች የሚያርሱ ወደ 14 ሚሊዮን ናቸው። ይሄ ደግሞ ገበሬው ምን ያህል ውልቅልቁ እንደወጣ ያሳያል’’ ብለዋል። በመፍትሄነትም የመሬት ጥበትን የሚቀንሱ አማራጭ የገቢ ምንጮች በመፍጠር መሬቱ ላይ በውርስም ሆነ በሌላ መንገድ የሚደረገው እየቆራረጡ መከፋፈል መቆም አለበት ብለዋል። በመሆኑም አንድ ገበሬ ቢያንስ ሦስት፣ አራት ወይም አምስት ሄክታር በመያዝ ትርፍ ሊያመርት ይገባል። ለዚህ ደግሞ በሀገሪቱ እንደገና የመሬት ክፍፍል ማድረግ ተገቢ ነው ብለዋል። ገበሬውም ለሚወልዳቸው ልጆቹ መሬት እየቆረጠ የሚሰጥበት አካሄድ አንድ ቦታ መቆም አለበት። ልጆቹ ወደ ሌሎች አማራጭ የስራ ዕድሎች መሰማራት አለባቸው ብለዋል። ገበሬው ትርፍ ባመረተ ቁጥር አነስተኛ ኢንዱስትሪ በማስፋፋት ግብርናን ከኢንዱስትሪው ጋር ማመጋገብ ተገቢ እንደሆነም አስረድተዋል።

ግብርናውና ኢንዱስትሪው ከተመጋገበ በኋላ ገበያ መፍጠር ወሳኝ መሆኑንም ፕሮፌሰሩ በገለፃቸው ላይ አፅንኦት ሰጥተውታል። ‘‘የሀገር እድገት መሰረቱ ብዙ ማምረት ነው። በብዛት ያላመረተ ሀገር የኢኮኖሚ እድገት አለ ለማለት አይቻልም። እድገት ያለ ገበያ ደግሞ አይሳካም። በአሁኑ ወቅት የገበያ አማራጭ ሁለት አይነት ሲሆን የውጪና የሀገር ውስጥ ገበያ ነው። የውጪውን ገበያ ለመወዳደር የምርት ጥራት በቂ ነው’’ ያሉት ፕሮፌሰሩ ኢትዮጵያ ካለችበት ስትራቴጂካዊ አቀማመጥ አንፃር ለመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ገበያ ጥሩ ዕድል ያላት መሆኑን ጠቅሰው፤ ‘‘የሰው ኃይላችንን ወደ መካከለኛው ምስራቅ ከምንልክ የግብርና ውጤቶችን ብንልክ የተሻለ አማራጭ ነበር’’ ብለዋል።

መንግስት በኢኮኖሚው ውስጥ ስለሚኖረው ሚና

‘‘በፕሮፌሰር በፍቃዱ እምነት በአሁኑ ወቅት ትልቁ ቀጣሪ መንግስት ነው። መንግስት የሀገሪቱ ግዙፍ ተቋም ነው። በዚህ ሁኔታ መንግስትን ከኢኮኖሚው ማስወጣቱ ተገቢ አይደለም። ተወደደም ተጠላ መንግስት መንገድ፣ ግድብ፣ ትልልቅ ፋብሪካዎችን ካልገነባ ማን ሊገነባው ነው?’’ ሲሉ የሚጠይቁት ፕሮፌሰሩ ከመንግስት ውጪ ያለው ኢኮኖሚ የጉሊት ኢኮኖሚ ነው። የኢትዮጵያን እድገት በኃላፊነት ለመያዝ የሚችል የግል ክፍለ ኢኮኖሚ የለም። ስለዚህ መንግስት የግሉን ሴክተር መፍጠር አለበት። በ1959 ዓ.ም ኮሪያ ከእኛ እርዳታ የምትቀበል ሀገር ነበረች። ሲንጋፖር ብትሄዱ ‘‘የኢትዮጵያ አደባባይ’’ የሚባል ቦታ አለ። በችግራቸው ጊዜ እርዳታ ስለላክንላቸው ነው። ኮሪያም ዘምተናል እና ይሄ ሀገር ትልቅ ሀገር ነበር። ‘‘ትልቅም ነበር ትልቅ እንሆናለን’’ የሚለው አባባል እውነት ነው። ነገር ግን ትልቅ ነበርና ትልቅም እንሆናለን ማለት አሁን ግን ትልቅ አይደለንም ማለት ነው። የምስራቅ ኢሲያ ሀገሮች የኢኮኖሚ ተሞክሮ ለኢትዮጵያ ጠቃሚ መሆኑንም በ1959 ዓ.ም ጀኔራል ቹንኪ ፓርክ የኮሪያን መንግስት ገልብጦ ስልጣን ከያዘ በኋላ የሀገሪቱን የፊውዳል ሐብታሞች ሰብስቦ የግሉን ሴክተር መፍጠር ችሏል። እነ ሳምሰንግ ዘዩናድይ ወዘተን ሊፈጠሩ ችለዋል። በእኛም ሀገር መንግስት ጠንካራ የግል ሴክተር መፍጠር አለበት። መንግስት የግል ሴክተር ይፍጠር ሲባል አሁን እንዳለው መንግስት የግሉን ሴክተር ተክቶ ይስራ ማለት አይደለም ብለዋል።

ጃፓኖች ከድህነት አዘቅት የተነሱት አፄ ቴዎድሮስ በሞቱበት እ.ኤ.አ 1868 ዓ.ም ወደስልጣኔ ማምራት የጀመሩበት ዘመን እንደነበር ያወሱት ፕሮፌሰሩ በዚያን ጊዜ አፄ ቴዎድሮስም ሀገሪቱን ወደ ኢንዱስትሪ የመቀየር ራዕይ የነበረው ንጉስ ነበር ብለዋል። በመሆኑም መንግስት የሀገሪቱን ኢንዱስትሪ ለመቀየር የቅድሚያ ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበትም አስገንዝበዋል። ኢንዱስትሪ ሲባል ግዙፍ ፋብሪካ ማቋቋም ብቻ ሳይሆን የመንደር ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋትና የምርት ሰንሰለትን መመጋገብ መፈጠር አለበት ብለዋል። ለምሳሌ ጥሬውን ጤፍ ከገበሬው ይዞ ወደ ከተማ ከማምጣት እዛው ወፍጮ ቤት በመትከል ኢንዱስትሪ መጀመር ይቻላል። ከወፍጮ ቤቱ ጎን ለጎን ለጤፍ መያዣ ጆንያ ፋብሪካ ማቋቋም ይቻላል፤ ጆንያውን ለማምረት ደግሞ የቃጫ ፋብሪካ እያሉ ምርት የማመጋገብ የምርታማነት ሰንሰለት በመፍጠር ኢንዱስትሪን በመንደር ደረጃ መጀመር እንጂ ግዙፍ ፋብሪካን በማሰብ ሊሳካ አይችልም ብሎ ተስፋ መቁረጥ አይገባም ብለዋል።

ሀገሪቱን ለመለወጥ የትምህርት ስርዓቱም መለወጥ አለበት ያሉት ፕሮፌሰር በፍቃዱ በአፄ ኃይለስላሴ ጊዜ ትምህርት የምንማረው፤ ለልማት ሳይሆን ቋንቋ ለመተርጎም ነበር። በዚያን ጊዜ ወደ ሀገሪቱ የገባው ትምህርት የአርስቶክራት ትምህርት ነበር። የመደብ (class) ትምህርት ነው። ለስነ-ፅሁፍና ከፈረንጆች ጋር ለመግባባት ነበር። አሁን ግን የትምህርት ስርዓቱ ወደ ዳቦ የሚቀየር መሆን አለበት። ነገር ግን እየተሰጠ ያለው ትምህርት እውቀት እንጂ ስኪል የለውም። በአሁኑ ወቅት 27 ከመቶ የዲግሪ ተመራቂዎች ስራ የላቸውም። ዩኒቨርሲቲዎች የስራ አጥ ማምረቻ ሆነዋል። ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡት የተለዩ የነጠሩና የሳይኒስትነት ደረጃ ያላቸውን እንጂ ሁሉንም በጅምላ እንዲገቡ ማድረጉ ኪሳራ ነው። ጥራት ያላቸውን ወደ ዩኒቨርሲቲ እያስገቡ የቀረውን ደግሞ ስኪል እናስተምረው ብለዋል። የትምህርት ስርዓቱ ሰው ሰርቶ ለመብላት የሚያስችል እውቀት እንዲኖረው በሚያስችል መልኩ መከለስ አለበት ሲሉም ገልፀዋል።

በዕለቱ ከነበሩ ወጣት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና የፓርቲው አባላት ለፕሮፌሰር በፍቃዱ ልዩ ልዩ ጥያቄዎች አቅርበውላቸው ነበር። ከነዚህም ጥያቄዎች መካከል ሀገሪቱ የፖሊሲ ሳይሆን የብሔራዊ ስሜት ማጣት ዋነኛ ችግሯ መሆኑ ተጠቅሶ ነበር። ፕሮፌሰሩ ግን የሀገሪቱ ብሔራዊ ስሜት ሙሉ በሙሉ አለመሞቱንም ይልቁኑ በዚህኛው ትውልድ እየተነሳ መሆኑን ከገለፁ በኋላ ‘‘ሐገሪቷ ያጣችው ብሔራዊ ስሜት ሳይሆን ብሔራዊ መሪ ነወ። የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ገዥ እንጂ መሪ አግኝቶ አያውቅም። ልማት በሕዝብ ብቻ ሳይሆን ብሔራዊ ስሜት ባለው መሪ ሊረጋገጥ ይችላል’’ ሲሉ መልሰዋል።

‘‘በተጨማሪም የሀገሪቱ ብሔራዊ ስሜት በአሁኑ ጊዜ በወጣቱ እያንሰራራ ነው።’’ ያሉት ፕሮፌሰሩ ለብሔራዊ ስሜት መጎዳትም ኦነግን ተጠያቂ አድርገዋል። ‘‘በዚህ ሀገር ከመንግስቱ ኃይለማርያም ቀጥሎ ወንጀል የፈፀመው ኦነግ ነው። ኦነግ በሁለቱ ትላልቅ ሕዝቦች መካከል በአማራና በኦሮሞ መካከል ክፍተት እንዲፈጠር ጥረት አድርጓል። በክፍተቱም ወያኔ እንዲገባ አድርጎ ተገዥ አድርጎናል። ወያኔ ደግሞ ያጠፋው ነገር የለም። እኛ ዝም ብለን እየተገዛንለት ነው’’ ብለዋል።

ሰፈራ በተመለከተ የሕዝብ እንቅስቃሴ አስፈላጊ መሆኑን በመግለፅ የሰፈራ ፕሮግራም ደጋፊ መሆናቸውንም ተናግረዋል። ነገር ግን ሰፈራው በዋናነት የሚሰፍረውን ሕዝብ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ማረጋገጥ አስፈላጊ እንደሆነ ጠቅሰዋል። ‘‘ኮንዶሚኒየም የከተማ ሰፈራ ነው’’ ያሉት ምሁሩ፤ ሰፈራ የሕዝብን ቅድሚያ ጥቅም በሚያረጋግጥና ልማትን በተለይም ግብርናን በሚያፋጥን መልኩ ቢፈፀም ችግር እንደሌለው ነው የገለፁት። ለሁሉም ግን ይቻላል፤ እንችላለን ብለን ልንንቀሳቀስ ይገባል ብለዋል።

በዘሪሁን ሙሉጌታ (ሰንደቅ ጋዜጣ)

Tuesday, August 13, 2013

Ethiopia: Where is Religious Freedom Headed?

August 13, 2013
by Alemayehu Fentaw Weldemariam – TRANSCEND Media Service

The fear of an Ethiopian Spring has to be factored in the internal security matrix of a dictatorial regime such as Ethiopia’s, since the populist “spring” events in the MENA region have proven to be a potent means of removing dictatorships in North Africa.  The lesson is powerful.  It is evident that the Ethiopian security apparatus has seriously taken this factor into account with the mounting crackdown on journalists, opposition leaders, and Muslim protesters.

The current Ethiopian regime also has a rational fear of Islamist terrorism.  But it is questionable whether that fear arises from a threat posed by the Ethiopian Muslim population.  I would argue that the threat principally emanates from Al-Shabab in Somalia and the Ogaden National liberation Front (ONLF) in the Somali Region of Ethiopia.  Al-Shabab is part of the international terrorist network of Al-Qaeda, while the ONLF is a domestic insurgent group doubling down on Islamism and ethno-nationalism.  Another domestic insurgent group that might possibly leverage both Islamism and ethno-nationalism is the Oromo Liberation Front (OLF), although that would be a challenge given the OLF’s stated secular policy of religious equality.

It seems to me that it is high-time that the Muslim movement for religious freedom has to prove that it is free of what I call the “mencha menace mentality” of some ethnic and religious groups.  If any one ethnic-based political group, say the OLF or the ONLF, uses this to mobilize its constituencies to take violent action against not only the non-Muslim population but also the government of the day, the movement certainly runs the risk of losing not only any broad-based popular support, but also any legality.

The word “mencha” is for the Oromo machete. It was used recently in a public speech by Jawar Mohammed, a high-flying Oromo and Muslim activist based in the U.S., when he said they would cut the necks of non-Muslims in his hometown in Arsi.  Following this speech, Jawar has turned out to be more of a liability than an asset to the cause of peaceful Muslim protesters.  It was very sad to see a brilliant, Western-educated young man turn himself into a Merchant of Mencha Menace. It seems that he’s completely carried away by Oromo ethno-nationalism so much so that he has deliberately fused altogether the Muslim movement with the Oromo nationalism of OLF.

I am not sure what the peaceful resistance rhetoric of Ethiopian Muslims means in practical terms in the face of the Mencha rhetoric of Jawar, and by extension Badr Ethiopia, an Islamic non-profit based in Washington, D.C., which according to some observers, constitutes the core of the Diaspora support of the movement back home.  Dr. Derese Kassa replied to my recent social media post in the following words, “the one horrifying reality that you aptly pointed out here is the regression of a broad-based popular nonviolent movement for basic human rights sizing itself down both in scale, essence and tactics.  Scale-wise to representing Oromo nationalism. Essence-wise from a social movement to an organized party movement of one or more political groupings. And tactic-wise from nonviolence to violence-talk of mencha mindsets and tone. If these attempts consummate, then we shall talk of the movement in general as the ‘market of menace’”.

There is no more telling example of the growing dominance of this mentality and mode of thinking among the young Oromo elites than what Kadiro Elemo recently posted on social media.  Elemo said, commenting on the police brutality in response to the protests that took place at the Eid Al-Fitr prayers on 7 August 2013, that “[t]he singularity of the image [of] Ethiopia as a Christian island explains the logic of the rise of Muslims with machetes against the Ethiopian forces.”  This is tragic in more than one sense.  I’ve been following the Muslim protests from the start and my heart goes out to the victims of the repression.  But whether he meant that by way of explanation or justification, and if his claim that Muslims are rising with machetes against non-Muslims is correct, which I really doubt, then I don’t see what he is accusing the security forces of perpetrating.  The only logical implication is that the security forces are discharging their duties, i.e., keeping the peace and public order.

Another factor influencing public perceptions has to be the rumor circulating that the ongoing Muslim protests are being supported by Egypt.  It is doubtful that an unstable Egypt is likely to destabilize Ethiopia by sponsoring Ethiopian Muslim protests, especially since the recent Egyptian military ousting of the Morsi-led government.  However, since Morsi and the Muslim Brotherhood have declared an “open option” to restore its regime through the use of any subversive measures, including the military, this “rumor” could become a “fact” in the security mindset of the current Ethiopian government.

My prognosis of the protests is that they will surely grow to such a degree that the Ethiopian Government becomes too frustrated to effectively manage the situation.  However, I do not expect the protesters to resort to violent means in the course of their protests.  My fear is that the government will eventually resort to more force than is warranted under the circumstances, and recent events indicate that this may be already taking place. Since this past Saturday, news reports out of Ethiopia claim that some 12 people have been killed, 35 wounded, and hundreds arrested in Arsi in connection with the Muslim protests, although the Ethiopian state television reduced the numbers of the fatalities to just three.  This is in addition to the killing of seven protesters in Assassa in April 2013 and Gerba in October 2012, which included a large number of wounded and the imprisonment of a number of protesters on terrorism charges.  It is expected that the Muslim protesters will continue to come out en masse on Fridays and that the security forces will be expected to provoke them in order to use deadly force.

Turning to the issue of how justified are the demands of the protestors, that is, to what extent is the Ethiopian government meddling in religious affairs, it is important to consider the legal regime governing religious freedom in Ethiopia.  The Ethiopian constitution provides for freedom of religion and requires the separation of state and religion.  Article 11 provides for the separation of state and religion, and stipulates that state and religion are separate; that there shall be no state religion; and that the state shall not interfere in religious matters and religion shall not interfere in state affairs.  In addition, Article 27 guarantees freedom of religion, belief and opinion and provides that all Ethiopian citizens have the right to freedom of thought, conscience, and religion.  This right includes the freedom to hold or to adopt a religion or belief of one’s choice, and the freedom, either individually or in community with others, in public or private, to manifest this religion or belief in worship, observance, practice, and teaching.

Without prejudice to the provisions of sub-Article 2 of Article 90, believers may establish institutions of religious education and administration in order to propagate and organize their religion.  These protections and rights continue, in that no one shall be subject to coercion or other means that would restrict or prevent his or her freedom to hold a belief of choice and that parents and legal guardians have the right to bring up their children ensuring their religious and moral education in conformity with their own convictions.  The freedom to express or manifest one’s religion or belief may be subject only to such limitations as are prescribed by law and are necessary to protect public safety, peace, health, or the education, public morality or the fundamental rights and freedoms of others, and to ensure the independence of the state from religion.

Nevertheless, the Muslim community in Ethiopia has for nearly two years now been holding protests at mosques around the country against what it perceives as Ethiopian Government interference in religious affairs.  The protesters are demanding that the current government-selected members of the Islamic Affairs Supreme Council (Majlis) be replaced by elected representatives, and that elections for Majlis representatives be held in mosques rather than in the Kebeles.  Some members of the Muslim community accuse the Ethiopian Government of controlling the Majlis and sponsoring the propagation of Al-Ahbash, a little known sect of Islam.  Given the rich and robust legal framework in place for the protection of religious freedom in Ethiopia, what is it that is holding the Ethiopian Government back from respecting religious freedom?  Why does it resist with unwarranted deadly force under the circumstances? Of course, this points to another important factor, namely, Ethiopia’s regional role as the military powerhouse of the Horn of Africa and its international role as key partner in the war on terror in the Horn and continued enjoyment of the assistance that come with the status from the West.  But it does more than anything else confirm our initial proposition. By engaging in a sheer show of force, the regime hopes to deter any future possible mass protests.

Monday, August 12, 2013

የሙስሊም ጥያቄ እና የኢህአዴግ ስጋት

ነሃሴ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ መራሹ መንግስት የሕዝበ ሙስሊሙን ከ18 ወራት በላይ የዘለቀ እንቅስቃሴ በኃይል ለማፈን ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ እየወሰደ ያለው እርምጃ በሙስሊም አባላቱ ዘንድ ቅሬታ ማሳደሩ የግንባሩን ከፍተኛ አመራር ስጋት ውስጥ እንደጣለ የውስጥ ምንጮች ጠቆሙ፡፡

አብዛኛዎቹ የግንባሩ ሙስሊም ከፍተኛ የአመራር አባላትን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ መካከለኛ፣ ዝቅተኛ አመራር አባላት መንግስት በሙስሊሙ ጥያቄ አፈታት ጉዳይ እየተከተለ ባለው ኃይል የተቀላቀለበት እርምጃ  ደስተኛ ካለመሆናቸውም በላይ በየአጋጣሚውም ቅሬታቸውን መግለጽ መጀመራቸው የግንባሩን ከፍተኛ አመራር አስደንግጧል፡፡

ግንባሩ የሙስሊሙ ድጋፍ አለኝ ለማለት ሙስሊም አባላቱን በጉዳዩ ላይ በማወያየትና ርዕዮት ዓለሙን በስልጠና መልክ በማስረጽ፣ አባላቱ ድርጊቱን እንዲያወግዙ ሲያደርግ ቢቆይም በተግባር ግን ሙከራው የሚፈልገውን ውጤት አላስገኘለትም፡፡በዚህም ምክንያት መንግስት ሙስሊሙን በተመለከተ የሚያስባቸውም ሆነ የሚወስናቸው ጉዳዮች በፍጥነት ሕዝበ ሙስሊሙ ጋር መድረሳቸው ከፍተኛ አመራሩን ይበልጥ ስጋት ውስጥ ጨምሮታል፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት ሙስሊሙን ጨምሮ የኢህአዴግ ከፍተኛና መካከለኛ አመራርን በተከታታይ ለማሰልጠን ጥረት ሲደረግ መቆየቱን ያስታወሰው ምንጫችን ሆኖም ስልጠናው በቂ ለውጥ ማምጣት ባለመቻሉ በአሁኑ ወቅት ከሙስሊሙ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ይልቅ በውስጡ የተፈጠረው ቅሬታ ይበልጥ ስጋት ውስጥ ሊከተው ችሏል፡፡ ችግሩን ለመፍታትም
በዚህ ወር መጨረሻ ሊካሄድ ከታሰበው የሰላም ኮንፈረንስ በፊት እንደገና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን በስፋት ለማካሄድ በመዘጋጀት ላይ ነው፡፡በኢህአዴግ ሙስሊም አባላት የተፈጠረው ቅሬታ አሁን በያዘው መልኩ የሚያድግ ከሆነ ግንባሩ እስከ መሰንጠቅ የሚያደርስ አደጋ ውስጥ ሊከተው እንደሚችልም ምንጫችን ጨምሮ ጠቁሟል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ጠ/ሚ ሐይለማርያም ደሳለኝ ድምጻችን ይሰማ በማለት የመብት ጥያቄ ባነሱት እና በአንዳንድ የፖለቲካ ድርጅቶች ላይ መንግስት እርምጃ እንደሚወስድ ገለጸዋል።

የኢህአዴግ ልሳን ከሆነው ዋልታ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ መንግስት ራሱ አክራሪ ብሎ በፈረጃቸው ዜጎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጸዋል። ስም ባይጠቅሱም አንዳንድ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችንም አስጠንቅቀዋል።

የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በኢድ አል ፈጥር እለት በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ በወሰዱት እርምጃ 5 ሰዎች ተገድለዋል።

የሽብርተኝነት ምንጭ ጭቆና ነው! (ገዛኽኝ አበበ ከኖርዌይ)

ከ ገዛኽኝ አበበ
August 12/2013
ደርጎች 'ወንበዴዎች' አሉን፤ ኢህአዴጎች 'አሸባሪዎች' አሉን። ያው ነው፤ ገዢዎች ለስልጣናቸው አስጊ የሆነ ሰው (ወይ ቡድን) ሲያጋጥማቸው ስም ሰጥተው የማጥላላት ዘመቻ ያካሂዳሉ።የስልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም የሚጠቀሙበት ቃላቶች ናቸው ::ይኸውም ያለስማቸው ስም እየሰጡ ያለ ተግባራቸው ተግባር እና ያልሰሩትን ስራ እንደሰሩ በማድረግ ስማቸውን ማጥላላት ነው::
የማጥላላቱ ዘመቻ ዋና ዓላማ ለስልጣን ስጋት የሆኑ ሰዎች ከህዝብ ለመነጠል ነው፣ ድጋፍ እንዳያገኙ ለማድረግ። እንደ እኔ  እንደ እኔ ግን አሸባሪም ሽብርተኛም እነዚው መንግስታቶች ናቸው::
ግን 'ወንበዴዎች' ወይ 'አሸባሪዎች' እንዴት ይወለዳሉ? እንዴትስ ያድጋሉ? የውንብድና ወይ ሽበራ ምንጭ ጭቆና ነው። የጭቆና ምንጭ አምባገነንነት ነው። አምባገነንነት በሰው ህይወት፣ አስተሳሰብና ሃይማኖት ጣልቃ መግባት ይጨምራል።
ህዝብን በሃይል እና በጉልበት  ለመግዛት ጣልቃ መግባት የህዝቦች ነፃነት ማፈን ያመጣል። የሰዎች ነፃነት ማፈን የህዝቦች መብት መጣስ ነው። ህዝቦች መብታቸው ሲጣስ መብታቸውን የሚስያከብሩበት መንገድ ያፈላልጋሉ። ስለዚህም በጉልበት እና በሃይል መብታቸውን እና ነጻነታቸውን ጨፈልቆ እየገዛቸው ካለው ሃይል እራሳቸውን ነፃ ለማውጣት እራሳቸውን ያደራጃሉ ይደራጃሉ ነጻ እንወጣበታለን ብለው በሚያስቡበት በማንኛቸውም መንገድ ይንቀሳቀሳሉ እንግዲህ ይህ ነው መንግስት በማይፈቅደው መንገድ መብታቸው ለማስከበር ሲንቀሳቀሱ 'ሕገወጥ' ተብለው 'ወንበዴዎች' ወይ 'አሸባሪዎች' ይሰየማሉ። መንግስት 'ሕግ ለማስከበር' በሚል ሰበብ የሃይል እርምጃ ይወስዳል። መጀመርያ ሕግ የጣሰ አካል ግን መንግስት ነው፣ የዜጎችን መብት በመጣስ። እናም ችግሩ እየተባባሰ ይሄዳል። ከተባባሰ ደግሞ የሃይል ሚዛን እንጂ የመደገፍና የ መቃወም ጉዳይ አይሆንም::
ስለዚህ ውንብድና ወይ ሽበራ የሚወለደው ከጭቆና ሲሆን የሚያድገውም በመንግስታዊ ያልተፈለገ የሃይል እርምጃ ነው። መንግስት በያዘው መንገድ ከቀጠለ ሀገራችን ወዳልተፈለገ የብሄርና የሃይማኖት ብጥብጥ ልትገባ ትችላለች።
መንግስት ችግሩ የመፍታት ግዴታ እንጂ የማባብስ መብት የለውም። አሁን እየተወሰደ ባለው የሃይል እርንጃ ምክንያት ብዙ ሙስሊሞች ሳያስቡት ወዳልተፈለገ በሃይል መብትን የማስከበር ተግባር ሊገቡ ይችላሉ። በደርጋዊ እርምጃ ምክንያት ብዙ የትግራይ አርሶአደሮች ሳያስቡት ከህወሓት ጎን ተሰልፈው ለመዋጋት ወስነው ነበርና።
  ስለዚህ አሁነም መንግስት ወደደ ጠላም አሁን እየታየ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የሙስሊሞች ጉዳይ መፍትሔ ያሸዋል። ይህም ከሃይማኖት አልፎ የሀገር ጉዳይ እየሆነ የመጣው የመብታችን ይከበር የመብት ጥያቄ የሙስሊሙ ወገኖቻችን ጥያቄ ሳይሆን የእያንዳንዱ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ጥያቄ ነው። የሰዎችን መብት እና ነጻነት በሃል እና ስልጣንን መካታ በማድረግ በጉልበት ተገዙ በማለት ለነጻነቱ ደግሞ የሚነሳ ህዝብ በአሸባሪ ጓራ መፈረጅ ትክክለኝነት አይመስለኝም::

እንደእኔ እንደ እኔ ጅብ እራሱ ነክሶ እራሱ ይጮኸል እንደሚባለው ወያኔም ሕዝቡን በሀይል በጉልበት እየጨቆነ መግዛት እስካለቆመ ድረስ እሱ እንደሚለው ለነጻነት መታገል እና መብታችን ይከብር ብሎ መጩህ ሽብርተኝነት ከሆነ   የኢትዮጵያ ሕዝብ ከወያኔ መንግስት  ጭቆና ነጻ እስኪወጣ ትግሉ ይቀጥላል::

 ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!

Sunday, August 11, 2013

South Africa: Thousands of Ethiopians flock to Durban for a meeting with Dr Berhanu Nega

August 11, 2013
The Horn Times Newsletter 11 August 2013

“Tesmamto Yalebet Eslam Christiyanu
Tezenegash ende Ethiopia mehonu…..” 
 
Dr. Berhanu Nega, Ginbot 7 ChairmanThe song the colorful Ethiopian crowd is currently singing aloud, as thousands of refugees from all occupations, Muslims and Christians begin flocking to the South African port city of Durban for tonight’s extraordinary meeting with their heroic opposition party leader, his Excellency Dr Berhanu Nega via video link at the magnificent Sun Coast Casino conference hall.

According to the organizing Bête-Ethiopia committee spokesperson, the iconic dissident artist/activist Tamagne Beyene and respected spiritual leader Sheik imam Khalid Omar will also speak to the participants via Skype from the US.

However, with their country in turmoil and with the ruling minority junta quickly transforming itself into a killing machine, most refugees the Horn times spoke to appeared very keen to hear what the patriotic academic will have to say on critical issues the nation of 80 million is facing.

“Dr (Berhanu) is an intelligent and street-smart individual with great savoir-faire to be the leader of a proud nation like Ethiopia. For the past decade, my soul searched for a patriotic leader to follow and found one in him. Personally, he is my commander- in- chief. He is fearless, hawkish, and pragmatic; above all, he is an incomparable patriot. The hope of the nation rests on his shoulders. Dear Dr Berhanu, please know that we love you.” Alemeshet Bekele, 24, a refugee in South Africa for 6 years told the Horn Times in Durban.

“Am a proud member of Ginbot-7 political party. Only Ginbot-7 represents the dreams and aspirations of the people of Ethiopia. I urge all Ethiopians to join this unique party to avoid fragmenting the opposition. The ruling junta fears Ginbot-7 because of its popularity and its firm stance on human rights and human dignity.” The philosophical young man added while his boisterous friends clad in the national flag shouted “viva Berhanu Nega!”, “viva Ginbot-7!”, “viva Ethiopian Muslims!”

“I have a bona fide offer for puppet Prime Minister Hailemariam Desalegn.” Another young man, Samuel Alemu cuts in. “quit and flee.” He said to the loud cheer of his friends.

“We are less than four hours before the meeting starts. Look at the popularity of this larger- than- life character Dr Berhanu Nega.  His undimmed pulling power has not fade a bit since 2005 when he made that famous clean sweep of votes in the national elections. We are very eager to hear his plan for the future. The direction his party would take to end the bondage of slavery in Ethiopia will be very crucial for us. Am a bit tense.” Said a 47-year-old chartered accountant who requested anonymity.

The meeting is scheduled to start at August 11, 5:30 pm.
infohorntimes@gmail.com
@infohorntimes

Crime against Humanity in Ethiopia

August 10, 2013

Ethiopian government forces committed atrocities on peaceful Muslims on Eid Al-fater Holiday

FOR IMMEDIATE RELEASE
By Nejashi Justice Council
Ethiopian government forces committed atrocities on peaceful Muslims on Eid Al-fater Holiday.The Ethiopian government forces committed an indiscriminate gross human rights violations and a brutal crackdown on peaceful Ethiopian Muslims during the celebration of Eid-Al-fatr Holiday in Addis Ababa and all over the country. The extent of the atrocity includes killing of five, heavy handed crack down of thousands and the arbitrary detention of Tens of thousands people. The attack disproportionately targeted women including reports of sexual Assault.

In a separate incident, eye witness account and Media sources reported, on August 3 , 2013,at least fourteen people were confirmed to have been killed in the town of Kofele, West Arsi Zone , Oromia Regional State when the Agazi special military brigade fired live ammunition on peaceful protesters.

According to eyewitness who reported to NJC sources, among the victims include an infant, 14 years old boy and elderly people. It has been reported that the killing took place when the Agazi special military brigade trying to arbitrarily arrest the Imam of local Mosque. In addition to those killed, more than 35 people were severely wounded while scores of Muslims arrested.

Ethiopian Muslims have been staging peaceful protest for more than 18 months against government coercive religious conversion to its imported religious sect .The Regime opted to silence Muslim protestors by force and different repressive measures. It is remembered that On October 22, 2012 in Gerba, South Wollo and on April 27, 2012 in Asasa, Arsi Zone the federal police committed similar massacre against Muslims. Nejashi Justice Council believes such despicable use of force against innocent and unarmed civilians throughout the country on the same group because of their faith is a clear case of crime against humanity.

Nejashi Justice Council condemns, in its stricter terms of condemnation, these atrocities committed by the Ethiopian Regime security forces against the innocent Muslims of Addis ababa, Kofele, Dessie, Wolikite and throughout the country. We call all stakeholders, including international community and human right groups at local level to deplore these atrocities on civilian people.

Nejashi Justice Council also calls on the Ethiopian government to halt the bloody response to Ethiopian Muslims’ peaceful demand. The Ethiopian Muslims demand nothing in their peaceful protest but their legitimate and constitutional right.

Saturday, August 10, 2013

ሙስሊም ወገኖቻችን፤ ቁስላችሁን አስራችሁ ከወያኔ ጋር በምናደርገው ፍልሚያ ተቀላቀሉን!!!!

 
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ መግለጫ
ነሐሴ 3 2005 ዓ.ም.
 
በእስልምና እምነት እጅግ በደማቅ ሁኔታ ከሚከበሩት በዓላት አንዱ የሆነው ኢድ አልፈጥር ለ1434ኛ ጊዜ ነሐሴ 2 ቀን 2005 ዓ. ም. በመላው ዓለም በደስታ ሲከበር ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ግን ለዚህ አልታደሉም። በእለቱ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የኢድ ሰላታቸውን ሰግደው ወደ የመኖሪያ ቤቶቻቸው ሲመለሱ ለድብደባ በሠለጠኑ የወያኔ ወታደሮች አሰቃቂ ሰቆቃ ተፈጽሞባቸዋል። በዚህ እለት በአዲስ አበባና እና ሌሎች ትላልቅና ትናንሽ ከተሞች በርካታ ወገኖቻችን ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ አሁን ሕፃናት የወያኔ የጥይት ሰለባ ሆነዋል፤ ከዚያ እጅግ አሰቃቂ ግድያና ወከባ ያመለጡት ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በአስር ሺዎች የሚገመቱ ሙስሊሞች በዓሉን ያሳለፉት በወያኔ ማጎሪያዎች ውስጥ በሕመምና በረሀብ እየተሰቃዩ ነው።

ይህ ለምን ሆነ?

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት ጥንቃቄ የተሞላበት ተቃውሞ ሲያካሄዱ አንድ ዓመት አልፏቸዋል። እጅግ ጨዋ በሆነ መንገድ ላቀረቡት የመብት ጥያቄ በታላቁ በዓል ቀን ወያኔ የእንቢታ ምላሹን ወራዳ በሆነ መንገድ ሰጥቷል። ወያኔ ለሰላማዊ ተቃዉሞ ያለውን ንቀት እናቶችን፣ ሕፃናትንና አረጋዊያንን ጭምር በመደብደብ አሳይቶናል።

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ሕይወታቸው ላለፈ ወገኖቻችን ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል፤ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖቻችን ሕመም ይጋራል። በባለጌ የወያኔ ወታደሮች የተገደለየ፣ የተረገጡ፣ በቆመጥ የተደበደቡ፣ የተሰደቡ፣ የተተፋባቸው ወገኖቻችን ሁሉ ሕመማቸውን ችለው፤ እልሃቸውን ውጠው ለመረረ ትግል እንዲዘጋጁ ግንቦት 7 ጥሪ ያደርጋል።

በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ የደረሰው በደል በሁላችን ላይ የደረሰ ጥቃት፣ በደል ነው። የሙስሊም ወገኖቻችን የመብት ጥያቄ የኢትዮጵያዊያን ተበዳዮች ሁሉ ጥያቄ ነው። እነዚህ ጥያቄዎች በወያኔ አገዛዝ ሥር ምላሽ አያገኙም። ስለሆነም ተባብረን ኢትዮጵያችንን ከወያኔ ፋሽስታዊ አገዛዝ ነፃ አውጥተን ሁላችንም የነፃነት አየር የምንተነፍስባት አገር እናድርጋት ዘንድ ዛሬውኑ የጋራ የትግል ጉዞ እንጀምር።

“ሙስሊም ወገኖቻችን ሆይ! እልሃችሁን ውጣችሁ፤ ቁስላችሁን አስራችሁ ከወያኔ ጋር ለሚደረግ ፍልሚያ ተቀላቀሉን!!!” በማለት ግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ጥሪ ያደርጋል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ

ከፖለቲከኞች በላይ ገኖ የወጣው “ድምጻችን ይሰማ”

ኢህአዴግ አክራሪነትን እየጋበዘ ነው!!


የሰላማዊ ትግል ምንነት ለማይረዱ ትልቅ ትምህርት የሰጠ፣ ኢህአዴግ ፍጹም የሆነ ልምድ ባካበተበትና ኤክስፐርት በሆነባቸው
የትግል ስልቶች ብልጫ ወስዶ ለማንበርከክ እንደሚያስቸግር፣ ሰላማዊ ትግል ከራስና ከስሜት ጋር የሚደረግ ታላቅ አስተምህሮት መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል። የድምጻችን ይሰማ ትግል በዚህ መልኩ በኢትዮጵያ ቀዳሚ ሆኖ ይቆያል” በግል አድራሻ ከተላከ አስተያየት የተወሰደ። በአሃዝ፣ ጉዳቱ በሚገለጽበት መጠን፣ ጉዳቱ የሚገለጽበት ደረጃና የቋንቋው አቅም ልዩነት  ካልሆነ በስተቀር ሁሉም ወገኖች፣ የውጪ ታዛቢዎች፣ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት፣ ራሱ ኢህአዴግ፣ ህወሃትና መላው ወዳጆቹ በአንድ እውነት ይስማማሉ። እሱም ህወሃት ራሱ ባመጣው ጣጣ፣ ራሱ ትዕዛዝ ሰጪ ሆኖ ያደረሰው ሰብአዊና በቀላሉ ሊበርድ የማይችል መከራ እንደሆነ በየአቅጣጫው አስተያየት እየተሰጠ ነው።

ያለ ምንም ማጋነን ኢህአዴግ ደም አፍሷል፣ ህይወት ቀጥፏል፣ አስሯል፣ ገርፏል፣ ፈንክቷል፣ ጣጣው ለሌሎች የሚተርፍ አካሄድ በመከተሉ ችግሩን አወሳስቦታል። ኢህአዴግ ይህንን ሁሉ ርምጃ የሚወስደው “ከብዙ ትዕግስት” በኋላ መሆኑን “በመንግሥት ወግ” ቢገልጽም “የሚያምነው ያገኘ አይመስልም” የሚል ወቀሳም ይሰነዘርበታል። እንደውም “ለየትኛዋ የሚወዳት አገር” በሚል ለፕሮፓጋንዳ አፉን በከፈተ ቁጥር ዘለፋ እየወረደበት ነው።
ኢህአዴግ አቅም አልባ ሆኗል የሚሉ ወገኖች አሉ። እነዚህ ወገኖች ገለጻቸው ለሌላው ግራ የሚያጋባ አባባል ሊሆን እንደሚችል ይገምታሉ። ግን በነሱ እምነት ኢህአዴግ አቅም አልባ ሆኗል። አቅም አልባ ያደረገው “የድምጻችን ይሰማ” የትግል ስልት ነው። ኢህአዴግ ያለውና 4የሚታወቅበት መለያው የታጠቀው መሳሪያ፣ ወታደሩ፣ የፌደራል ሃይሉ፣ የክልል ፖሊስ፣ ፈጥኖ ደራሹ፣ የሰላምና መረጋጋቱ ፣ የስለላ ሃይሉ፣ የአጋዚ ጦሩ፣ የአንድ ለአምስት አወቃቀሩ … ከሁሉም በላይ ደግሞ ጉልበተኛነቱን የሚቆጣጠሩለት የአንድ ብሔር “ታማኝ” ሃይሎች መሆናቸው እንደሆነ አብዛኞች ይስማማሉ።
“ኢህአዴግ አለኝ የሚለውን ጉልበቱን መጠቀም ቢፈልግም መድረኩን ‘በተጠና’ የትግል ስልት በሚፈልገው ደረጃ ሊጠቀም አለመቻሉ በደጋፊዎቹና በራሱ ዘንድ ስጋት ፈጥሯል” የሚሉት አስተያየት ሰጪ “የሙስሊሞች እንቅስቃሴ፣ የዕዝ ሰንሰለታቸውን ጠብቀው የሚያካሂዱት ትግል ኢህአዴግ ጉልበቱን እንዳይጠቀም ከልክሎታል። አሁን እየወሰደ ያለውና የወሰደው የሃይል ጥቃት ሊወስድ ከሚፈልገው ጋር ሲነጻጸር ሃይሉ ሽባ መደረጉን ያሳያል፤ ይህ ደግሞ የሰላማዊ ትግል ውበት ነው” ሲሉ ኢህአዴግ በገባው ጭንቅ መጠን ርምጃ ባለመውሰዱ እንደሚቆጭ ይናገራሉ። በሌላ አነጋገር የሽብር፣ የማሸበርና የመግደል “ጠቢብ” ለሆነው ኢህአዴግ አሁንም ችግሩ የሚፈታው በሃይል፣ በባሰ ሃይል እንደሆነ ከማመን አላፈገፈገም ሲሉ ያብራራሉ።
ኢህአዴግ ነገሮችን እያባባሰ የሰላማዊ ትግሉን ወደ አመጽ ለማስቀየር ሃሳብ ቢኖረውም “የድምጻችን ይሰማ ህብረት አስቀድሞ መረጃ የማግኘትና በሰላማዊ ትግል ተክኖ መገኘት ኢህአዴግ ያሰበውን እንዳይፈጽም አድርጎታል” በማለት አስተያየታቸውን ይሰጣሉ። እነዚህ ክፍሎች ኢህአዴግ “አክራሪነትን የሚሰብኩና የሚያቀነቅኑ አሉ” በማለት ለሚለፍፈው “እስካሁን የአክራሪ ሙስሊም እንቅስቃሴ ስለመታየቱ መረጃ የለም። ከተፈጠረም አክራሪነት እንዲፈጠር ምክንያት የሚሆነው ራሱ ኢህአዴግ ነው። ደም ማፍሰሱን አጠናክሮ በቀጠለና ዜጎችን ማሰሩ በገፋበት ቁጥር ለመሞት የሚዘጋጁ ዜጎች አገር ውስጥ የመኖራቸውን ያህል የወንድሞቻቸውን ጭፍጨፋ በመመልከት የመስዋዕትነቱ ተካፋይ ለመሆን ዓለምአቀፋዊ የሙስሊም ኅብረተሰብ ቁጣ ያስተባብርና ራሱን ችግር ላይ ይጥላል፤ ለአገርም መከራ ይሆናል፡፡”
በተቃራኒው አክራሪነት እየተስተዋለ የመጣው አሁን እንዳልሆነ የሚናገሩ ክፍሎች “በአሁኑ ሰዓት አገራችን ውስጥ ያለው የሃይማኖት ውህደት ቀደም ሲል እናቶቻችንና አባቶቻችን በየዋህነት ሲያደርጉት እንደነበር አይነት ነው ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው” በማለት ይናገራሉ። በማያያዝም እንዲህ ያለው ስጋት በሰላማዊ ትግል ጉልበት አልባ የሆነውን ኢህአዴግ ሃይል እንዲያገኝና ይህንን ሃይል እንዲተማመን አድርጎታል ሲሉ ይከራከራሉ።
ኢህአዴግ መስከሩን፣ አንጎሉ መዞሩንና የሚያደርገው እንደጠፋው የሚናገሩ ክፍሎች እንደሚሉት የኢድ ቀን ኢቲቪ ያሰራጨውን ዜና ቀላል ምሳሌ አድርገው ያቀርባሉ። የድምጻችን ይሰማ መነሻ ምክንያት የሆኑትን አዲሱን የመጅሊስ መሪ በቴሌቪዥን መስኮት አቅርቦ 2“ሙስሊሞች ላይ የወሰዳችሁትና የምትወስዱት ርምጃ የሚደገፍ ነው፣ ትክክል ነው” በማለት ያቀረበው ቃለ ምልልስ “ከስካርም በላይ አዙሪት ነው” ሲሉ የኢህአዴግን የበሽታ መጠን ይገልጻሉ። ሙስሊሙን አንኳን አሰራችሁት፣ ደበደባችሁት፣ ገደላችሁት በሚል ደረጃ “ደግ አደረጋችሁ፣ ርምጃችሁ ትክከል ነው” በማለት ዜና ማሰራጨቱ ኢህአዴግ በራሱ ሚዲያ በችግሩ ላይ እሳት ማርከፉን የሚያመላክት ስለመሆኑ በማሳያነት ያቀርባሉ።
አንድ ጤና ያለው መንግስት የህዝብ ቁጣ ሳይለሳለስ፣ የቁጣውን መንስዔ አደባባይ በማቅረብ “ተጎዳን በሚሉ የህብረተሰብ፣ በተለይም የአንድ እምነት ተከታዮች ፊት ማዘፈን ኢህአዴግን የያዘውን የስካር የዞረ ድምር (ሃንግኦቨር) የማሽተት ያህል ነው” የሚሉት ክፍሎች ኢህአዴግ ቢያንስ ለራሱ፣ ህወሃትና ቁንጮው ላይ ሆነው ሃብት ለሰበሰቡት ሲል እርቅ ሊወርድ የሚችልበትን መንገድ እንዲያስብበት ይመክራሉ። ጉዳዩንም በጥበብ እንዲይዘው ይመክራሉ።
በሙስሊም ወገኖች አወሊያ የተጀመረው የድምጻችን ይሰማ ጥያቄ፣ የኢህአዴግ የጥያቄው አያያዝ ችግር ተዳምሮበት የእምነቱ ተከታዮች ባሉበት ቦታ ሁሉ ተቃውሞው እየተዳረሰ ይገኛል። የአገሪቱን ሙስሊሞች ከጫፍ እስከጫፍ በሚያስገርም የግንኙነት መረብ እያስተባበረ የሚነደው ሰላማዊ ቁጣ የሌሎች እምነት ተከታዮችን ድጋፍ አለማግኘቱን ለኢህአዴግ ሃይል እንደሆነው የሚናገሩ ወገኖች “ይህንን አስመልክቶ በሚቀርበው መረጃ ግራ ተጋብተናል” ይላሉ።
“እንኳን የሌላውን ሃይማኖት የራሳቸውን ሃይማኖትና ስርዓት ማስጠበቅ ያቃታቸው የክርስትናው ሃይማኖት ተከታዮች፣ የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ደገፉ ተብሎ ሲዘገብ ዘገባው ሚዛን የሚደፋ አይሆንም” በማለት የሚከራከሩ ክፍሎች “የክርስትና እምነት ተከታዮች ለእምነታቸው ሊሰጡ የሚገባውን ክብር ከድምጻችን ይሰማ እንቅስቃሴ መማር ከቻሉ ይህ ብቻ በራሱ ይበቃል” በማለት በተቃራኒ ወቀሳ ይሰነዝራሉ። እንደውም የራሳቸውን የእምነት ቤት ማጽዳት ባለመቻላቸው ሊወቀሱ እንደሚገባ መረጃ በማጣቀስ ይከራከራሉ።
በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ላይ ካለው የረዥም ጊዜ የተቀነባበረ ሴራና የምንገኝበት የጂኦ ፖለቲካ ካሸከመን ጣጣ ጋር በማዳመር “ሜዳዎች ሁሉ ሸራተን ሆነው አይዋቡም” የሚል አስተያየት የሚሰጡ ክፍሎች “መተማመን ድሮ ቀረ” ሲሉ የሌሎች እምነት ተከታዮችን ዝምታ ይገልጹታል።
“ሙስሊሞች አብዛኞች በሆኑበት ቦታ ያለ ችግር ቢፈልጉ አክርረው፣ ቢፈልጉ አለዝበው እምነታቸውን ያራምዳሉ። አነስተኛ በሆኑባቸው አገራት ደግሞ ያለውን የአስተዳደር መሰረት የመጋራት ፈተና ይፈጥራሉ” የሚሉት እነዚህ ክፍሎች “እነዚህ በሌሎች አገሮች የታዩ ተሞክሮዎች ከምዕራቡ መገናኛ ውስወሳ ጋር ተዳምረው በክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ላይ ያስቀመጡት ጠባሳ ቀላል አይሆንም። ኢትዮጵያ ውስጥም ይህ ችግር አለ” ባይ ናቸው። በሌላም በኩል በማህበራዊ ድረገጾች አርሲ አርባ ጉጉና ጅማ የተከናወነውን በማንሳት ሰሞኑንን ለመከራከር የሞከሩትን በመጥቀስ የፍርሃቻው ማሳይ አድርገው ያስቀምጡታል።
መሰረታዊ የእምነትና አመራር ጥያቄ በማንሳት ትግላቸውን በተጠና መንገድ የሚያካሂዱት የ”ድምጻችን ይሰማ” የትግል መስመር አስገራሚ እየተባለ ነው። ህብረታቸውና በተዋረድ የሚያካሂዱት መናበብ አስደማሚ ሆኗል። አልፎ አልፎ ከሚሰራጩ ወፍ ዘራሽ5 መልዕክቶች በስተቀር መሪዎችን በመከተል የሚያሳዩት ትብብር የሚያስቀና እንደሆነ እየተነገረ ነው። ተመሳሳይ ዓላማ ይዘው እርስ በርስ የሚቧቀሱት የተቃዋሚ የፖለቲካ ሃይሎች ከድምጻችን ይሰማ “የሰላማዊ ትግል” ቀመር ሊማሩና ይሁንታ ካገኙ ስልጠናም ሊወስዱ እንደሚገባ የሚናገሩ ተበራክተዋል።
እነዚህ ወገኖች እንደሚሉት የሙስሊም ወገኖች ጥያቄና ጥያቄያቸው መልስ ካላገኘ ወደኋላ እንደማይሉ በመደጋገም ይፋ እያደረጉ ነው። ኢህአዴግ ከተካነበት ድርጅቶችን የመሰንጠቅና “የእባቡን አንገት ቁረጥ” ከሚለው የአምባገነኖች መርሁ አንጻር ድምጻችን ይሰማ ውስጥ ዘልቆ መግባት አለመቻሉ አስገራሚ የሆነባቸው ጥቂት አይደሉም። ቅንጅት እንደ ሰደድ እሳት አገር አዳርሶ ኢህአዴግን ባስጨነቀ ማግስት “ሳሎኑ ተበርግዶ ኢህአዴግ ሲንቦጫረቅበት” የተመለከቱ፤ ዓመት ከመንፈቅ ያህል የዘለቀውንና ከዕለት ወደ ዕለት በብቃትም ሆነ የኢህአዴግን መሠሪነት በመመከት እንዲሁም የተጠና የትግል ችሎታ በማሳየት ወደር ያልተገኘለትን የድምጻችን ይሰማ ትግል ከማድነቅ ወደኋላ አይሉም። ለሌሎች ሲመክሩም የመስመርና የትግል አስተላለፍ ለውጥ ለማድረግ አሁንም ጊዜው እንዳላለፈ ሊገነዘቡት ይገባል በማለት ለሌሎች የሰላማዊ ትግል ምንነት ላልገባቸውና የገባቸው መስሏቸው ተስፋ ለቆረጡ ይመክራሉ፡፡
ይህ ሪፖርታዥ የተቀናበረው የዝግጅት ክፍላችን ካነጋገራቸው ወገኖችና በኢሜል ከተላኩ መልክዕክቶችና አስተያየቶች በመመርኮዝ ነው። ለንባብ እንዲያመች የአርታኢ ስራ ከመሰራቱ ውጪ ሙሉ ሃሳቡ የተለያዩ አስተያየት ሰጪዎች ያሰፈሯቸው ነው። አሁንም በዚህ ጽሁፍ ላይ የቀረቡትን ሃሳቦች በማስፋትም ሆነ በመቃወም የሚላኩ ጽሁፎችን ለማስተናገድ ዝግጁ ነን።
(ፎቶዎቹ የተወሰዱት ከቢላል Tube Photos ድረገጽ ነው)
 The maleda times

የእስክንድር ዳግም መታሰር ቤተሰባችን እንዲበተን አድርጓል፡፡ሰርካለም ፋሲል


ሀምሌ16/2005 ዓ.ም. በጣም መጥፎና ጥሩ ስሜት የማይፈጥር ቀን ነበር፡፡ ቤተሰብን፣ ወዳጅ ዘመድን በተለይ የሚወዷትን ሃገር ጥሎ መውጣት ምንኛ ይከብዳል? ከሀገርስ በላይ ምን አለ? አፈር ፈጭቼ ካቦካሁባት፣ ተወልጄ ካደግኩባት፣ ክፉ ደጉን ካየሁባት አገሬ የመውጣቴ የመጨረሻ ቀን መቃረቡን ሳስብ በሕይወቴ አጋጥሞኝ የማያውቅ የመደበት ስሜት ውስጥ ነው የተዘፈቅኩት፡፡

 ከቤተሰብ፣ ከጐረቤት፣ ከወዳጅ ዘመድ የመለያየት መቃረቢያው ክፉኛ ያሳምማል፡፡ ከምንም በላይ በሀገር መኖር ክብር መሆኑን እረዳለሁ፡፡ ከሚወዷት ሃገር ተገፍቶ እና ተገፍትሮ መውጣት ከመርግ የከበደ መሆኑን አሁን መጨረሻው ላይ የግዴን አወቅኩት፡፡ በቅርብ የሚያውቁኝ “ሰርካለም ከምትንሰፈሰፍላት ውድ ሀገሯ ወጥታ ለመኖር እንዴት ጨከነች?” እንደሚሉ እገምታለሁ፡፡ ሀገሬን እጅግ እወዳታለሁና “እንደወጣሁ እቀራለሁ” የሚል ድምዳሜ ላይ አልደረስኩም፡፡

ደሕንነቴ አደጋ ውስጥ ሲወድቅ፣ ውክቢያና እንግልቱ ሲከፋብኝ ግን ለራሴ ብቻ ሳይሆን በአባቱ እስራት ለሚንገላታው ልጄ ስል ይሕን መወሰኔ ግድ ሆነብኝ፡፡ ቤተሰብ ያለው ሰው የሚሰማው የተለየ ስሜት ይኖራል፡፡ ለኔ ሕይወት የራሷ የሆነች ስም ካላወጣችለት በቀር ከመደበኛው የተለየች ሆናብኛለች ማለት እደፍራለሁ፡፡ ሁሌም በውክቢያና እስር፣ በማጠስጠንቀቂያና ማስፈራሪያ ሥር ሆኖ መኖር በእጅጉ ያስመርራል፡፡ የኔ ሕይወት ይሄ ነው፡፡ ባለቤቴ እስክንድር ነጋ ለእስር ከተዳረገ ዓመቱን ሊደፍን ከአንድ ወር ያልበለጠ ጊዜ ነው የቀረው፡፡ በእስር ቤት የተወለደው ልጃችን ናፍቆት እስክንድር ነጋ የአባቱ ናፍቆት እያሰቃየው፣ እንደ እኩዮቹ ከመፈንጠዝና ከመቦረቅ ርቆ በትካዜ ውስጥ መኖሩ በእጅጉ ሲያሰቃየኝ ቆየ፡፡ ከዚህ በኋላ በዚህ እየተሰቃየና እየተጎዳ መኖር አይኖርበትም፡፡

 በእስር ያጣው ውድ አባቱን በየሳምንቱ እያየው ከሚሰቃይ ከሃገር ርቆ “አንድ ቀን እንገናኛለን” የሚል ተስፋ ውስጥ ቢገባ የተሻለ ሊሆንለት እንደሚችልም አምኛለሁ፡፡ ማንም ወላጅ ይሕን ስሜቴን ይረዳኛል ብዬ እገምታለሁ፡፡ ልጃችን ናፍቆት ዕድሜው ከሚችለው በላይ መከራ በመቀበል ከማናችንም በላይ ተጐድቷል፡፡ በትምሕርት ቤት ከአቻ ጓደኞቹ ጋር መጫወት ትቶ ብቻውን አቀርቅሮ መሬት ሲጭር ይውላል፡፡ “አባቴ መቼ ነው የሚመጣው?” ከሚለው የመናፈቅ ጥያቄው ጋር እየታገለ ትምሕርቱን መከታተል የማይችልበት ደረጃ ላይ ደረሰ፡፡ ሞራሉ እየወደቀ ሲሄድ ያየሁ መሰለኝ፡፡

 የወለድኩት ቃሊቲ ወሕኒ ቤት ስለሆነ እንደ እናት ተገቢውን እንክብካቤ እንኳን አላደረግኩለትም፡፡ ከሰው ተነጥዬ የምችለውን ላደርግለት የሞከርኩ ቢሆንም አንድ ሕፃን ሊደረግለት ከሚገባው በትንሹ እንኳን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ልጄ ባህሪው በእጅጉ ተለወጠ፤ ከሰው ጋር መግባባት ተቸገረ፤ ዝምታንና ለብቻው መገለልን ምርጫው አደረገ፡፡ ሰው ይፈራል፤ ከእኔ ከእናቱና ከወንድሜ ጋር ብቻ የሚግባባው ናፍቆት ከሌላ ሰው ጋር መግባባት አልሆንለት አለ፡፡ እኛ ተጐድተን… በስነ ልቦና የተጐዳ ልጅ መፍጠር አይኖርብንም፡፡ እኔና ልጄ ከእስር ስንፈታ፣ አባቱ ተመልሶ ወሕኒ ከወረደ በኋላ ደግሞ የልጃችን የባህሪ ለውጥ እየከፋ ሄደ፡፡ እስቲ ለሰከንዶች ብቻ እንደ አንዲት እናት ሆናችሁ አስቡት፡፡ ማንም የወለደው ልጅ ሲጐዳበት ማየት አይፈልግም፡፡ ዘጠኝ ወር አርግዤው በ1998 ዓ.ም. በእስር ቤት የወለድኩት ናፍቆት እስክንድር ነጋ ላለፉት ሠባት ዓመታት የገፋው የሰቆቃ ኑሮ እንዲበቃው መፈለጌ ነው ወደማልፈልገው ስደት እንዳመራ ያስገደደኝ፡፡ የውክቢያ ዘመኑ ያኔም ዛሬም ፈፅሞ አልተቀየረም፡፡

ባለቤቴ እስክንድር ያለ ፍትሕ መታሰሩ፣ እኔና ናፍቆት የምንመራው የሰቆቃ ሕይወት የብዙሃን ግፉአን ኢትዮጵያውያን ሕይወት ግልባጭ ነው፡፡ በጠመንጃ ታጅቤ ፖሊስ ሆስፒታል የወለድኩት፣ የሕፃንነት ጊዜው የቃሊቲ እስር ቤት በር ተዘግቶበት ያሳለፈው የምወደው ልጄ አዕምሮው እንዳይጎዳ ለጊዜው ከስደት የተሻለ አማራጭ አላገኘሁም፡፡

ጉዞ ወደ አሜሪካ የጉዞዬ ዓላማ ኑሮን በአሜሪካ ማድረግ አይደለም፡፡ የአሜሪካን የተንደላቀቀ ኑሮ ብንፈልግ ኖሮ እኔም ሆንኩ ዛሬ እስር ላይ የሚገኘው ባለቤቴ እስክንድር ነጋ ልጃችንን ይዘን ቀድመን ከሀገር በወጣን ነበር፡፡ እስክንድር ለዓመታት አሜሪካ ኖሮ በሃገሩ ሃሳብን የመግለጽ መብት “ኤክሰርሳይስ” ለማድረግ ነው የመጣው፤ እኔም ብሆን አሜሪካ ደርሼ የተመለስኩት ሃገሬን ስለምወድ እንጂ ሌላ ጥቅም ስላለ ነው፡፡ ሁለታችንም ከሃገር የመውጣት ሃሳቡ አልነበረንም፤ ዛሬ የእኔው ግድ ሆነ፡፡ የልጃችን የአእምሮና ስነ ልቦና ጉዳይ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደረሰ፡፡ ናፍቆት እስክንድር ነጋ ከሰኞ እስከ አርብ በትምሕርት ቤት ሲናውዝ ቆይቶ፣ የቅዳሜና እሁድ የዕረፍት ቀኑን እንደ እኩዮቹ መዝናኛ ቦታ ሣይሆን ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ነው የሚያሣልፈው፡፡ ናፍቆት ለአባቱ ያለው ፍቅር የተለየ ነው፡፡ እስክንድር ዳግም ሲታሰር ልጃችን ናፍቆትን ከትምህርት ቤት እያመጣ እንደነበር ይታወሳል፡፡ መሣሪያ የታጠቁ ፖሊሶች እስክንድርን ሲይዙት፣ ልጃችን ናፍቆት “አባቴን ልቀቁት” እያለ ያለቅስ ነበር፡፡ ይህንን ክስተት እስኪ ለአፍታ መለስ ብላችሁ አስቡት፡፡ እስክንድር ነጋ በሃገሩ የሚኖር ሕጋዊ ሰው፣ ቋሚ አድራሻ ያለውና ፖሊስም ሆነ የደሕንነት ባልደረቦች በፈለጉበት ጊዜ ጠርተው ሊያስሩት እንደሚችሉ ግልጽ ነው፡፡ ልጁን ከትምህርት ቤት ሲያወጣ ጠብቀው በጠመንጃ ከበው፣ እየደነፉ የያዙት እሱንም ሆነ ልጃችንን ለማሳቀቅ እንደሆነ ማንም ሰው ይረዳዋል ብዬ አምናለሁ፡፡ በወቅቱ እስክንድርን የያዙት ሰዎች የልጅ አባት ይሆኑ ይሆናል፡፡ እነርሱ በእስክንድርና በናፍቆት ላይ ያደረሱት ሽብርና ማሸማቀቅ በራሳቸውና በልጆቻቸው ቢፈፀም ምን ሊሰማቸው እንደሚችል ለመገመት ለምን እንደተቸገሩ አይገባኝም፡፡ እናም “ምነዋ! ሰርካለም ከሀገር ወጣች” ብላችሁ ለጠየቃችሁ ምላሼ ይድረሳችሁ፡፡ ወደአሜሪካ የጉብኝት እድሉን ከቅርብ ወዳጃችን ነው ያገኘነው፡፡ ልጄ የተወሰነ ቢሆን ቦታ መቀየር የራሱ የሆነ እገዛ ይኖረዋል ድምዳሜ ላይ በመድረሴ ግብዣውን ተቀበልኩት፡፡ የስማችን መጠሪያ፣ ሃገር ተረካቢው ልጃችን በኛ ዳፋ ሞራሉ ደቆ ሲጐዳ ከማየት እንዲያገግም ስል ይኸው ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ተጉዣለሁ፡፡ (ዘ-ሐበሻ ድረገጽን ሁሌም ያንብቡ)
እስክንድርን ጥሎ መሄድ ባለቤቴ እስክንድር ነጋ እስር ላይ ነው፡፡ የቃሊቲን አታካችና አሰልቺ ጉዞ ተቋቁሞ “ማን ስንቅ ያቀብለዋል?” የሚለው ጥያቄ ውሳኔዬን እንድቀለብስ ሞግቶኝ ነበር፡፡ እሱን ጥሎ መሄድ እጅግ ከባድ ነው፡፡ ለእኔ፣ ላንተ፣ ላንቺ መብት አይደል የታሰረው? እና ለእኔ ሲል ታስሮ እሱን ጥሎ መሄድ እንዴት እደፍራለሁ፡፡ እስክንድር የልጃችንን ጉዳት በመረዳቱ ከሃገር ርቀ ቢቆይ የተሻለ ነገር እንደሚየገኝ ሲያግባባኝ ዓመት አልፎታል፡፡ እስካሁን ሳልቀበለው ቆይቻለሁ፡፡ አሁን ግን እስክንድርም አመረረ፡፡ “ልጃችን ሲጎዳ እምቢኝ ከሃገር አልወጣም ያልሽኝ አንቺ ከእኔ የተሻለ አንፃራዊ ነፃነት ስላለሽ (ስላልታሰርሽ)፣ ነው” የሚለውን ግፊት አጠነከረው፡፡ ቀደም ባሉት ጊዜየት በተደጋጋሚ ወዳጆቻችን የእረፍት ቪዛ ሲልኩልን አሻፈረኝ ብዬ ሳቃጥለው የነበረውን ዕድል ማክተሙን ተረዳሁት፡፡ እስክንድር “እኔ የታሰርኩበት አላማ አለኝ፤ በዚህች ሀገር ፍትህና ዴሞክራሲ እንዲሰፍን አሁንም ትግሌ ይቀጥላል፤ በእስር ቤት የተወለደው ልጄ ግን አዕምሮው ከዚህ በላይ መጐዳት አይኖርበትም፡፡ እና በአፋጣኝ እረፍት እንዲያደርግ ብለሽ ውጡ” ነው ያለኝ፡፡ በሣምንት አራት ቀን የምጠይቀው ባለቤቴን መራቅ ቢከብደኝም በአንድ ነገር ግን ገዘተኝ፡፡
“እስክንድር ቢታሰርም አይሟሟም፤ እኔ ስለፍትህ፣ ነፃነትና ዴሞክራሲ የምናገር እንጂ አሸባሪ አይደለሁም፤ ልጄ ደግሞ በኔ እስር የአባቱን ፍቅር አጥቶ መጨነቅና አእምሮው መጐዳት የለበትም፤ ሲያድግ ጥሩ አእምሮ ኖሮት ሀገሩን እንዲያገለግል ውሳኔዬ ነው” የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱ የጉዞ ውሳኔ ላይ አድርሶኛል፡፡ እናም የእሱን ቃል ማክበር ስላለብኝ ይህን አደረኩ፡፡ ውድ ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቼና እህቶቼ እኛ ማለትም ባለቤቴና እኔ ወደ አሜሪካ የምንሄድበት እድል ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ተፈጥሮልን ነበር፡፡ ግን ለምን ሀገራችንን ለቀን አንሄዳለን ብለን ነው የወሰን ነው፡፡ የኔም ሆነ ባለቤቴ አቋም ተመሳሳይ ነው፡፡ በተለይ ባለቤቴ እስክንድር ነጋ ስለዴሞክራሲ ከሀገር ወጥቶ መታገል በሚለው ነገር ላይ ፈፅሞ እምነት የለውም፡፡ ሰላማዊ ትግል በሀገር ውስጥ ማድረግ ነው የሚል እምነት አለው፡፡ ከዛ በመነሣት ነው ብዙ የቆየ ነው፡፡ አሁን ግን የልጃችን አእምሮ እየተጐዳ በመምጣቱ መቼም ወላድ ….ኢትዮጵያዊ ይመስክር የልጅን ነገር የወለደ ያውቀዋልና ለዛም ስንል የተወሰነ እረፍት ቢያገኝ ብለን ወደ አሜሪካ ይዤው ለመሄድ ተገደድኩ፡፡ ይህ ህፃን በእስር ላይ ተወልዶ የቤተሰብ ፍቅር ያልጠገበ ባይተዋር ልጅ ሆነብን፡፡ በሁሉም መጐዳት የለብንም ልጃችን በእኛ ስህተት ሣይሆን እኛ በምናደርገው ትግል ሁሌም መታሰራችን የፈጠረበት የቤተሰብ እንክብካቤ ማነስ ተጐዳ፡፡ አያት ወይም አጐት እንደ ወላጅ ሆኖ ለማሣደግ ይቸገራል፡፡ ለሀገራችን ስንታገል የልጃችን ጭንቅላት ጐዳት እስክንድርንም እኔንም ለውሣኔ አበቃን፡፡ እስክንድር ብቻውን አይደለም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በቃሊቲ “ዞን 2″ እየሄድ ይጠይቀዋል፡፡

ያለፉት ስድስት አመታት በ1998 ዓ.ም. ታስረን ከእስር ከተፈታን በኋላ ምናልባትም የስድስት አመታት ጊዜያት ተቆጥረዋል፡፡ ለእስክንድር የከበደ ጊዜ ነበር፡፡ የጋዜጣ ፈቃድ አውጥቶ በሞያው ለመንቀሣቀስ ቢፈልግም ፈቃድ የማግኘት እድል ግን ፈፅሞ ማግኘት አልቻለም፡፡ ከዛ በኋላ በፖለቲካዊ ትንታኔዎች ዙሪያ መንቀሣቀስ ጀመረ፡፡ እስክንድር እንደሌሎች ከሀገር እንደወጡ ፖለቲከኞች ውጭ ሆኖ ድምፁን ማሰማት ይችላል፡፡ ግን የእሱ አላማ ህጋዊና ዴሞክራሲያዊ በመሆኑ በሀገር ውስጥ መንቀሣቀስ ጀመረ፡፡ ያ ነገር ግን በጠላትነት አስፈርጆት ሁሌም በክትትል ሕይወት ውስጥ እንዲኖር አደረገው፡፡ እስክንድር ሁሌም “በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ክትትል ስር የወደቀ ነበር” ቤታችን ይጠበቃል፣ እሱም ነፃ ሆኖ መንቀሣቀስ አልቻለም፡፡ እሱን ለመጠየቅ የመጣ፣ ከእሱ ጋር የቆመና የተነጋገር ችግር ይገጥመዋል፡፡ የሰቆቃ ዘመን ነበር ያሣለፈው፡፡ በመጨረሻም ታሰረ፡፡ ዳግም መታሰር ይከብዳል፡፡ እስክንድር ባለፉት 20 አመታት ወይም በኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ” የፕሬሱ ፋና ወጊ ነው” ግን በእስር እጁን እስከመሰበር ደርሷል፡፡ ከአሜሪካ ሀገር ድረስ መጥቶ በዚህች ሀገር ላይ ስለዴሞክራሲ ፣ ነፃነትና መብት የሚናገር ማነው እናም እነዚህ ያለፉት ስድስት አመታት እጅግ ውስብስብና አስቸጋሪ የሆኑ ጊዜያት ነበሩ፡፡
የወጣትነት ዘመን እኔ የወጣትነት ዘመን ምን እንደሆነ አላውቅም፡፡ እኔና እስክንድር ስንገናኝ የ21 አመት ወጣት ነበርኩ፡፡ ከዛ ጊዜ ጀምሮ የመዋከብና በዚህ ሕይወት ዙሪያ የመረጋጋት ሕይወት ሣይኖረን ቆይተናል፡፡ ወጣትነት ብዙ ነገር ማለት ነው፡፡ “ፈፅሞ አላውቀውም” ከእድሜ እኩዮቼ ጋር ሆኖ መዝናናት ፣ በእኔ እድሜ ላይ የምትገኝ ወጣት ልታደርግ የሚገባውን ነገር ፈፅሞ አድርጌ አላውቅም፡፡ በእኛ ስር ሦስት ጋዜጦች ነበሩ፡፡ ምኒልክ፣ አስኳልና ሳተናው፡፡ ሦስቱም በሣምንቱ ውስጥ ይወጣሉ፡፡ እነዚህን ማዘጋጀት መምራት ምን ጊዜ ይሰጣል፡፡ ለዛውም የፖለቲካ ጋዜጣ ማዘጋጀት ቀላል ነገር አይደለም፡፡ በዚህ በሦስት ጋዜጣ ስር ደግሞ ምን ያህል ሠራተኞች አሉ፡፡ እናም ወጣትነቴን አላውቀውም፡፡”ወጣትነት ምንም እንደሆነ ስለወጣትነት የተፃፈውን መፅሐፍ ከማንበብ ባለፈ ይህ ነው የሚባል የወጣትነት ትዝታ ፈፅሞ የለኝም፡፡” በበርካታ ውጣ ውረድ ውስጥ ነው ወጣትነቴን ያሣለፍኩት፡፡ ያ አልፏል ብዙም አልቆጭበትም፡፡ ከዚህ በኋላ ወጣት የሚባል ደረጃ ላይ አይደለሁም፡፡ ባለፉት ጊዜያትም የምቆጭ አይደለሁም፡፡ ስለዴሞክራሲ ስሰራ በመኖሬ ደግሞ እኮራለሁ፡፡
የእስክንድር ዳግም እስር ምን ፈጠረ; የእስክንድር ዳግም መታሰር ቤተሰባችን እንዲበተን አድርጓል፡፡ ማንም ኢትዮጵያዊ በሕይወቱ ሊያደርጋቸው ከሚገባቸው ነገሮች መካከል በትዳር ተጥምሮ ወልዶ መኖር ነው፡፡ ይህ ግን ለእኛ የተፈቀደ አይደለም፡፡ እስክንድር ከጥሩ ቤተሰብ የወጣ ጥሩ አቅም ያለው ነው፡፡ የእሱ ቤተሰብ ምንጭ ጥሩ ነጋዴ ሆነን ተንደላቀን እንድንኖር ያደርገናል፡፡ ግን አልሆነም፡፡ የእሱ ቤተሰብ ንብረት ፈፅሞ በሚገርም መልኩ ሽብርተኛ በሚል ተወረሰ፡፡ በመጨረሻም ይኸው ዳኛ ቤተሰብ በተነ፡፡ እስክንድር 18 አመት ተፈረደበት፡፡እኔም ለልጄ ጭንቅላት ስል ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን ወዳጅ ዘመድ በፈጠረው እድል ተጠቅሜ ወደ አሜሪካ አመራሁ፡፡ ይገርማችኋል እኛ ሰላማዊ ነን ልጃችን አፍ ፈቶ መናገር ከቻል በኋላ አብረን ለመኖር መታገዳችን ምን ያህል ያስቆጫል፡፡ እስክንድር በኢትዮጵያ ዴሞክራሲና ፍትህ የእውነት ካልሰፈነ በቀር በአደባባይ ቢሰቀልና ቢሰቃይ ቦታ የለውም፡፡ ግን ልጃችን ለምን ይሰቃይ የሚል እምነት አለው፡፡ ማንም ቢሆነ የልጁን ስቃይ ማየት አይወድምና፡፡
የሀገር ነገር ይህንን ስል እንባዬ ምን ያህል በአይኔ ላይ እየወረደ እንደጠረኩት አውቃለሁ፡፡ ያለቀስኩበት ዘመን አልፏል፡፡ …. ሀገሬን እወዳለሁ፡፡ ግን መልካም አስተዳደርን እመኛለሁ፡፡ ከሀገሬ አልርቅም ፣ ወደ ሀገሬም እመለሣለሁ፡፡ እኔና ባለቤቴ ለልጃችን ስንል እንጂ የደረሰብን በርካታ ስቃዮች የጐዳን አይደለም፡፡ እናም ሁሌም ቢሆን ኢትዮጵያን እወዳለሁ፡፡ ከሀገሬ መራቅ የምፈልግ አይደለሁም፡፡ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር፡፡ እስክንድር ነጋ ሀገሩን የሚወድ አሜሪካ መኖር እየቻለ ስለሀገሩ ሲል ቃሊቲ /ማረሚያ ቤት/ መኖሪያው የሆነ ሰው ነው፡፡