Monday, May 6, 2013

የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት አንዷለም አራጌን እንዳይጠይቁ በልዩ ሀይል ተባረሩ

andinet
 
የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ወጣቱን ፖለቲከኛና የፓርቲው አመራር አንዷለም አራጌን እንዲሁም ሌሎችን የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ለመጠየቅ ቅዳሜ መጋቢት 26 ቀን 2005 ዓ.ም የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ቃሊቲ ቢሄዱም ለመጠየቅ እንዳይችሉ መደረጋቸውንና እስካፍንጫቸው በታጠቁ ልዩ ሃይሎች በግድ ከአካባቢው እንዲርቁ መደረጋቸውን የህዝብ ግንኙነት ክፍሉ አስታወቀ፡፡
 
እንደፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ገለፃ ከፍተኛው ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ወጣቱን ፖለቲከኛና ከፍተኛ አመራር አንዱአለም አራጌና ናትናኤል መኮንን ሽብርተኞች እንደሆኑና በሰላማዊ ትግል ሽፋን ሽብርተኝነትን እንደሚያራምዱ ተደርጎ የቀረበው ሀተታና ውሳኔ እጅግ ያሳዘናቸው በርካታ አመራሮችና አባላቱ በከፍተኛ መነሳሳትና ቁጭት ከ 20 በላይ የሚሆኑ የፓርቲው ሰዎች ከ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ እንኳን አደረሳችሁ ለማለት ቢገኙም የተሰጣቸው ምላሽ አንዷለምን ምግብ ከሚያመላልሱለት ጥቂት ቤተሰቦቹ ውጭ ማንም መግባት እንደማይችል ተገልፆላቸው በታጠቁ ሃይሎች ከአካባቢው እንዲርቁ ተደርገዋል ብሏል፡፡
 
በዕለቱ ቃሊቲ እስርቤት ለመጠየቅ ከተገኙት መካከል ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣ የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ፣ ዶ/ር ያዕቆብ ሀይለማርያም፣ አቶ አክሉ ግርግሬ፣ አቶ ሙላት ጣሰው፣ አቶ ዘካሪያስ የማነብርሃን፣ አቶ ተክሌ በቀለ፣ አቶ ትዕግስቱ አወሉ፣ አቶ ዳንኤል ተፈራና ሌሎችም የፓርቲው አመራሮችና አባላት እንደተገኙ የህዝብ ግንኙነት ያደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡
 
የማረሚያ ቤቱ የወቅቱ ተረኞች የስም ዝርዝራቸውን መታወቂያቸውን እያዩ ከተመዘገቡ በኋላ ከአቅማቸው በላይ እንደሆነ ገልጠው ወደ ዋናው የአስተዳደሩ የመግቢያ በር በመግባት ሃላፊዎችን እንዲያነጋግሩ ነግረዋቸው ወደዚያው በማምራት ቢጠይቁም እንዲጠብቁ ከነገሯቸው በኋላ የተሰጣቸው ምላሽ መጠየቅ አትችሉም የሚል ነው፡፡ ከዚህ በፊት በተለይ አንዷለም አራጌን ከጥቂት ቤተሰቦቹ በስተቀር ማንም እንዳይጠይቀው የተደረገ ሲሆን በተደጋጋሚ ቢያመለክትም ምንም ምላሽ ማግኘት አለመቻሉ ይታወቃል፡፡ ከዚህ በፊት ግን የበዓል ቀናት ብቻ የፓርቲው አመራሮችና የስራ ባልደረቦቹ ለተወሰኑ ደቂቃዎች በጅምላ እንዲጠይቁት ቢደረግም በዘንድሮው የትንሳዔ በዓል ግን የገጠማቸው በልዩ የታጠቁ ሃይሎች መባረር ሆኗል፡፡ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ አካባቢውን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ታጣቂዎች ወረውታል፡፡ ለመጠየቅ የመጡት መጠየቅ መብታቸው እንደሆነ ለማስረዳት ቢሞክሩም እነዚህ ሃይሎች መሳሪያቸውን በተጠንቀቅ በመያዝ ፀብ ለማስነሳት ሙከራ አድርገዋል በማለት የህዝብ ግንኙነት ክፍል ገልፆልናል፡፡ (በፍኖተ ነጻነት የተላከ)

ጎልጉል

Sunday, May 5, 2013

ኦባንግ የኢህአዴግ ደጋፊ ስደተኞችን አስጠነቀቁ

“በአስመሳይ ስደተኞች ላይ በቂ መረጃ አለ”
obang
“ክፉን በክፉ መመከት ባያስደስትም ወቅቱ ያስገድደናል” ሲሉ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር ኦባንግ ሜቶ በተለይ ለጎልጉል ተናገሩ። አገዛዙን ሸሽተው በተለያዩ አገራት ከለላ አግኝተው በስደት የሚኖሩም ሆኑ ጉዳያቸው እየታየ ያሉ ወገኖች አካሄዳቸውን እንዲያስተካክሉ አስጠንቅቀዋል።
 
የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናትና ህግ አውጪዎች፣ የጀርመን የኢሚግሬሽን ሃላፊዎችና ከፍተኛ የፖለቲካ ሰዎች፣ ከኖርዌይ የኢሚግሬሽን ጉዳይ ሃላፊዎችና ተዛማጅ ሃላፊነት ካላቸው የህግ ክፍሎች፣ በካናዳ በተለያዩ ደረጃ ካሉ ባለስልጣናትና ወትዋቾች (አክቲቪስቶች)፣ በስዊድን አንዲሁም በእንግሊዝ በተመሳሳይ ግንኙነት ፈጥረው እየሰሩ መሆኑንን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “አገራቱ የስደት ፈቃድ ካገኙ በኋላ ለስደት ዳረገን ከሚሉት መንግሥት ጋር በቅርብ እየሰሩ ስላሉ አስመሳይ ስደተኞች አስገራሚ መረጃዎች መሰብሰባቸውን አውቃለሁ” ብለዋል።
 
አቶ መለስ በሞቱ በወር ጊዜ ውስጥ ብቻ በካናዳ ቫንኮቨር 27 አንድ አይነት ቋንቋ ብቻ የሚናገሩ ወጣቶች ጥገኛነት መጠየቃቸውን ጉዳዩን በጥብቅ እየመረመሩት ካሉ ክፍሎች ማረጋገጣቸውንና የምርመራውን ውጤት በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ ያመለከቱት አቶ ኦባንግ፣ “ወጣቶቹ ካናዳ የገቡት ለእያንዳንዳቸው 75 ሺህ ዶላር በማውጣት ነው። ይህን ገንዘብ ማን ሰጣቸው? እንዴት አገኙት? እንዴት ከአንድ አካባቢ (ክልል) ብቻ ሊሆኑ ቻሉ? የሚሉት ጉዳዮች ምርመራውን በያዙት ወገኖች ላይ ግራሞት የፈጠረ ትልቅ ጉዳይ ነው” በማለት የጉዳዩን አሳሳቢነት ከገንዘብ ማሸሽ ጋር በማያያዝ አመላክተዋል። ለምሳሌ አንድ ጉዳይ አነሱ እንጂ በመላው ካናዳ በተመሳሳይ የምርመራ ስራ እየተሰራ መሆኑንን ተናግረዋል።
 
የካናዳው አንድ ማሳያ ሲሆን በአሜሪካ ግዙፍ ቪላዎችን እየገዙ ያሉት ክፍሎች ጉዳይ ከገንዘብ ማሸሽ ጋር ተያይዞ እየተመረመረ እንደሆነ አቶ ኦባንግ አስረድተዋል። ጥገኝነት ካገኙ በኋላ “ሊገለን ሲል አመለጥነው” ያሉትን ኢህአዴግን የሚደግፉ ክፍሎች ላይም ለሚመለከታቸው ባለስልጣናትና ተቋማት ከሚቀርበው መረጃ በተጨማሪ ከፍትህ ወዳድ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ጋር ድርጅታቸው በጥምረት እየሰራ መሆኑን አቶ ኦባንግ አልሸሸጉም፡፡
በጀርመን ኑረንበርግ በኢሚግሬሽን ጉዳዮች ዙሪያ የሚሰሩ ባለስልጣናት በተመሳሳይ የምርመራ ስራ እያከናወኑ እንደሆነ ያመለከቱት አቶ ኦባንግ፣ በግል በጉዳዩ ዙሪያ መነጋገራቸውን አስታውቀዋል። የጥገኝነት ፈቃድ ካገኙ በኋላ ዲያስፖራውን በመከታተልና አገር ቤት የሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ለችግር እንዲዳረጉ የሚያደርጉትን ክፍሎች ማንነት ነቅሰው እንደሚያውቋቸው ባለሥልጣናቱ በግንኙነታቸው ወቅት እንዳረጋገጡላቸው አመልክተዋል።
“ኢህአዴግ ለጊዜው የጠመንጃ ሃይል አለው። የገንዘብ አቅም አለው። ወዳጆችም አሉት። እኛ ደግሞ በየአቅጣጫው ፍትህ ወዳድ አጋሮች አሉን። ከነሱ ጋር እየሰራን ነው” በማለት አስረግጠው የተናገሩት ኦባንግ በማንኛውም መስፈርት ስደት ላይ ያሉ ወገኖችን መከታተልና መሰለል ተቀባይነት የለውም ብለዋል።
 
“አሜሪካ፣ ካናዳ፣ ኖርዌይ፣ እንግሊዝ፣ ስዊድንና ጀርመን አገር ባለስልጣናቱ ከበቂ በላይ መረጃ አግኝተዋል። እኛም እየሰራንበት ያለ ተከታታይ ስራ አለ። በየአቅጣጫው የሚደረገው ትግል በቅርቡ ፍሬው መታየት ይጀምራል” የሚሉት ኦባንግ ርምጃው መወሰድ ሲጀምር ከስድስት እስከ አስራ ሁለት ዓመት እስር እንደሚያስከትል፣ ከዚያም የከፋ አደጋ እንዳለው ጠቁመዋል።
በትምህርትና በተለያዩ ስልጠናዎች ወደ ተለያዩ ዓለማት የሚሰማሩ የአገዛዙ አገልጋዮችም ቢሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው የሚያሳስቡት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር “አገዛዙ መድቧቸው በየኤምባሲው ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች፣ የስለላ ሰዎች፣ ከፍተኛ ባለስልጣናት ምስላቸውንና ማንነታቸውን ባደባባይ አይገልጹም። በኤምባሲዎች ድረ ገጽ ላይ እንኳ ስለማንነታቸው በቂ መረጃ ለመስጠት ድፍረት የላቸውም። የስርዓቱ ባህሪና የወንጀለኛነቱ መጠን ራሳቸውን እንዲገልጹ አይፈቅድላቸውም” በማለት በተራ መደለያና ጥቅማ ጥቅም ደረታቸውን እየሰጡ ያሉ ወገኖች አካሄዳቸውን በመመርመርና የሚያስከብራቸውን ተግባር እንዲፈጽሙ ጥሪ አስተላልፈዋል።
 
“ምክር በመለገስ ሰፊ ጊዜ የወሰድነው ክፉን በክፉ የመመለስ እምነት፣ ክፉ እንድናደርግ የሚገፋን ድርጅታዊ አቋም ስለሌለንና የሚጠሉንን ጭምር ነጻ የሚያወጣ ግዙፍ ራዕይ ስላለን ነው” የሚል ጥልቅ አስተያየት የሰነዘሩት አቶ ኦባንግ፣ በአገራቸው መኖር ያልቻሉ ወገኖች ተሰደውም ሰላም ሲያጡ መመልከት ግን የማይቻልበት ደረጃ መድረሱን አመልክተዋል። ከዚህም በተጨማሪ እሳቸው በግል፣ ድርጅታቸው በመርህ የሚታገሉለት የሰዎች መብት መከበር ብሩህ አጀንዳ በዝምታ እንዲቀመጡ እንደማይፈቅድላቸው ተናግረዋል።
 
ከኖርዌይ የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ጋር በተገናኙባቸው ወቅቶች ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ በግልጽ እንደነገሯቸው ያመለከቱት ኦባንግ ሜቶ፣ አሁን ስሙንና ዝርዝር ጉዳዩን ለመናገር ፈቃደኛ ካልሆኑት ክፍል ጋር በጋራ እየሰሩ መሆኑንን ጠቁመዋል። አኢጋን ያቋቋመው የግልጽነትና የተጠያቂነት ግብረ ሃይል አንዱና ትልቁ ስራው እንዲህ ያሉ ጉዳዮችን መርምሮና አጣርቶ ለሚመለከታቸው በማቅረብ ፍትህን መጠየቅ መሆኑንን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “ዝርዝሩን መናገር ቢከብድም ብዙ ስራ እየሰራንበት ያለው የስደተኞች ጉዳይ የሌሎችንም ተሳትፎና ትብብር ይጠይቃል” ብለዋል።
 
“በስሜት መታገል አያዋጣም” የሚል የትግል ማስተካከያ ሃሳብ ፈንጠቅ ያደረጉት አቶ ኦባንግ የስደት ማመልከቻቸው ተቀባይነት አግኝቶ የመኖሪያ ፈቃድ ካገኙ በኋላ አገር ቤት በመመላለስ፣ ህግ በመተላለፍ ለአገዛዙ የሚሰሩ በሙሉ “ብልጥና አዋቂ ነን፣ ባለጊዜዎች ነን” በሚል አስተሳሰብ የሚንቀሰቀሱ አንደማያዋጣቸው ሲያሳስቡ “ለእንደዚህ አይነቶች ሁሉም ዓይነት መንገድ አይሰራላቸውም። ግለሰቦችንና ባለስልጣናትን ሳይሆን አሰራርን በማጭበርበር ይጠየቃሉ። አገራቱ እንደ ኢትዮጵያ ሳይሆን ስራ ላይ የሚውል ህግ አላቸውና ይተገብሩባቸዋል። አሰራራቸው ሲጭበረበር ዝም የማይሉት ለማንም ሲሉ ሳይሆን ለራሳቸው ሲሉ ነው። አሰራር / ሲስተም/ ሲበረዝ የሚያስከትለውን አደጋ ስለሚረዱ የሚታገሱ ካልሆነ በቀር በዝምታ አያልፉም። በኖርዌይም ሊሆን የታሰበው ይህ ነው። አሁንም ዝርዝር መረጃ ለመስጠት እቸገራለሁ” በማለት ነው። አቶ መለስ ህይወታቸው ባለፈ ወቅት በስደት ካምፕ የሚኖሩ ጭምር ለቅሶ መቀመጣቸው በኖርዌይ ሚዲያዎች አስገራሚ ተብሎ መዘገቡ፣ በህዝቡና በፖለቲከኞች ዘንድ መነጋገሪያ አጀንዳ እንደነበር አይዘነጋም።
 
በርካታ አሳዛኝና ህሊናን የሚፈታተኑ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሆነ ያወሱት ኦባንግ ሜቶ፣ ህጻናትን በጉዲፈቻ ስም በመቸብቸብ፣ ሴት እህቶቻችንን አረብ አገራት ያለ ዋስትና በመላክ ከፍተኛ ገበያ እየሰሩ ያሉት የህወሃት ሰዎች እንደሆኑ በበርካታ ማስረጃዎች መረጋገጡን ያስታውሳሉ። አያይዘውም አገራቸውን ለቀው ለስደት የሚወጡትን ወደ ኬኒያ፣ ታንዛኒያና ደቡብ አፍሪካ ብሎም በጅቡቲና በሶማሌ በኩል ገንዘብ እያስከፈሉ የሚያሻግሩት አሁንም እነሱ ናቸው ሲሉ አስቀድመው ስለ ጠየቁት ትብብር ማሳሰቢያቸውን ያጠናክራሉ።
 
“በማስተዋል እንስራ” የሚሉት ኦባንግ በየአቅጣጫው መረጃ ላይ የተኙና፣ በምን አገባኝ ስሜት ዝምታን የመረጡ ወገኖች ያላቸውን መረጃ በመስጠት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ከተለያዩ አካላት ጋር እየሰራ ያለውን ስራ እንዲያግዙ አሳስበዋል። ይህንን ማድረግ አቶ ኦባንግንና እርሳቸው የሚመሩትን ድርጅት መርዳት ሳይሆን ራስንና አገርን መርዳት እንደሆነም አጽንዖት ሰጥተው
ተናግረዋል።

 aba
 
ከተቋቋመ 135ዓመታትን ያስቆጠረው የአሜሪካ ሕግ ባለሙያዎች ማኅበር (ABA) እየተባለ በሚጠራውና 400 ሺህ በላይ አባላት ባሉት የህግ ባለሙያዎች ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ከሁለት ሳምንት በፊት ንግግር እንዲያደርጉ በተጋበዙበት ወቅት አቶ ኦባንግ ሜቶ በርካታ ጉዳዮችን በማንሳት ድጋፍ ጠይቀው አዎንታዊ ምላሽ እንዳገኙ ጠቅሰዋል፡፡ በርካታ የህግ ባለሙያዎች በተገኙበት ስብሰባ ላይ በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ፣ ኢህአዴግ ህግን ከለላ በማድረግ በዜጎች ላይ የሚፈጽመውን ወንጀል፣ ለእንደዚህ ዓይነት ተግባሩ ማስፈጸሚያም የጸረ ሽብርተኝነትን፣ የመያዶችን፣ ወዘተ ህጎች በማውጣት ዜጎችን ለእስር፣ ለስደት፣ ለስቃይ መዳረጉን፣ የፍትህ አካላቱን ህግን በሚያከብሩና ፍትህ በሚያስፈጽሙ ሳይሆን ራሱ በመሠረተው ተቋም እያመረተ ለፖለቲካ መጠቀሚያ እያደረገ መሆኑን፣ ከዚህ አልፎ ደግሞ በስደተኛነት ስም ደጋፊዎቹን ወደ ውጪ በመላክ በሃሰት የኢህአዴግ ሰለባ በማስመሰል በየምዕራቡ ዓለም የመኖሪያ ፈቃድ እንዲያገኙ በማስደረግ መልሶ ስደተኛውን እዲሰልሉና ለሥርዓቱ እንዲሰሩ እያደረገ መሆኑን፣ ወዘተ በስፋት አብራርተዋል፡፡ የባለሙያዎቹ ማኅበር ጉዳዩን በጥልቀት እንደሚያየውና ያለውን ከፍተኛ የሰው ኃይል በመጠቀም ከአኢጋን ጋር እንደሚሰራ ከሌሎች ማኀበራት ጋር በመሆንም በተለይ በምዕራቡ ዓለም የተሰገሰጉትን አስመሳይ ስደተኞች ወደ ፍትህ የማምጣቱ ጉዳይ ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑን ለአቶ ኦባንግና ለድርጅታቸው አረጋግጠዋል፡፡

ምንጭ ጎልጉል
 

Saturday, May 4, 2013

ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ የሪፖርተርስ ዊዝአውት ቦርደርስ የ2013 ሽልማት አሸናፊ ሆነ

 ሚያዚያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በስዊድን በስደት ላይ የሚገኘው የቀድሞው የአዲስ ነገር ጋዜጣ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ ሽልማቱን ያገኘው በኢትዮጵያ በሽብረተኝነትና በህገወጥ መንገድ ወደ አገር በመግባት ተከሰው ከአንድ አመት በላይ ታስረው ከተፈቱት የስዊድን ጋዜጠኞች ከሆኑት ማርቲን ሽብየ እና ጆሀን ፒርሰን ጋር በጋራ በመሆን ነው።

ጋዜጠኛ መስፍን በውጭ አገር ሆኖ ለፕሬስ ነጻነት በመታገሉ ለሽልማት እንደበቃ ድርጅቱ አስታውቋል። ጋዜጠኛ መስፍን “ሽልማቱ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ስራ በመስራት ላይ ላሉ እንዲሁም በእስር ቤት ውስጥ ላሉ የሙያ ባልደረቦቼ እውቅና የሚሰጥ ነው” በማለት ተናግሯል።
ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ የሪፖርተርስ ዊዝአውት ቦርደርስ የ2013 ሽልማት አሸናፊ ሆነ
ሚያዚያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በስዊድን በስደት ላይ የሚገኘው የቀድሞው የአዲስ ነገር ጋዜጣ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ ሽልማቱን ያገኘው በኢትዮጵያ በሽብረተኝነትና በህገወጥ መንገድ ወደ አገር በመግባት ተከሰው ከአንድ አመት በላይ ታስረው ከተፈቱት የስዊድን ጋዜጠኞች ከሆኑት ማርቲን ሽብየ እና ጆሀን ፒርሰን ጋር በጋራ በመሆን ነው።

ጋዜጠኛ መስፍን በውጭ አገር ሆኖ ለፕሬስ ነጻነት በመታገሉ ለሽልማት እንደበቃ ድርጅቱ አስታውቋል። ጋዜጠኛ መስፍን “ሽልማቱ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ስራ በመስራት ላይ ላሉ እንዲሁም በእስር ቤት ውስጥ ላሉ የሙያ ባልደረቦቼ እውቅና የሚሰጥ ነው” በማለት ተናግሯል።

Friday, May 3, 2013

የወያኔ ልማት ሰዋዊ ሽታ የለውም


ሀገራችንን አንቆ የሚገዛው ወያኔ ራሱን የልማት መንግስት ነኝ በሚል ራሱን በሚጠፋ ስእል ላይ አስቀምጦል። በየአመቱ የተጋነነ እና የሌለ ነጠላ የስታቲስቲክ ዜማ እየለቀቀ ያቀርባል። በዴሞክራሲያዊ መንገድ ህጋዊ መሰረት ማግኘት ስለተሳነው በልማታዊ መዝገብ ስም ለመገኘት አይን የአወጣ ሙከራ ያደርጋል።

የወያኔ ልማት ሰዋዊ ሽታ የለውም። ለዘረኛው መንግስት ልማት ማለት ብልጭልጫዊ ነገር ማሳየት እንጂ የሰውን፣ የህዝቡን ጉስቁል ኑሮ መቀየር ማሻሻል መሆኑን አያውቅም። አንድ ሺ አፈናቅሎ አንድ የስርአቱን አገልጋይ ቱጃር ያከብርና አገር ለማ ይለናል። የጋምቤላን አኙዋኮች ከአያት ቅድመ አያት መሬት አፈናቅሎ በርሃብ እየቆላ፣ የአረብና ህንድ የሩዝ ሁዳድ ስላደረገው ብቻ አገር ለማ ከበሮ ደልቁ ይለናል።

ወያኔ ልማት ለሰው መሆኑን ወይ አያውቀውም አሊያም ረስቶታል። በአዲስ አበባና በብዙ አካባቢዎች መንደርን እያፈረሰ የሚበትናቸው ዜጎች፤ ከእነሱ ጋር እድራቸው፣ ሰንበቴያቸው፣ ማህበራቸው፣ ማህበራዊ ህይወታቸው አብሮ እንደሚፈርስ ቢያውቅም ግድ የለውም። የወያኔ ልማት ሰውን ወደተራ እንስሳነት የሚያወርድ የወሮበላ ስራ ነው።

ህወሃት እንደ መንግስት ሱፍ ለብሶ፣ በሌላ በኩል እንደ ኢፈርት ባለቤትነቱ ወዛደር መስሎ ውል ይፈራረማል። ኢፈርት የሚገጣጥመውን መኪና ለመከላከያ ሚኒስተር ይሸጣል፤ እንደ መንግስት በህዝብ ስም እርዳታ ይቀበላል፣ እንደ ወሮበላ ዘራፊ ስማቸውን ቀይረው ወዲያውኑ ዘረፋውን ይጀምራል። ይህን የመሰለ የዘቀጠ ውንብድና በህዝብ ንብረት ላይ እየሰሩ ሌሎችን የወያኔ ግልገሎች ደግሞ ሌቦች፣ ኪራይ ሰብሳቢዎች እያሉ ሲሳደቡ አይናቸውን አያሹም።

የወያኔ አለቆች ድሃ ገበሬዎችን ከመኖሪያቸው ሲያፈናቅሉ ደን ስለጨፈጨፉ ነው የሚል የፈጠራ ክስ ይፈጥሩና የኤፈርት ኩባንያዎች ኢሉ አባቦር ውስጥ የያዩን ደን እየጨፈጨፉና እያጋዩ የሚሰሩትን የዝርፊያ ማእድን ቁፈራ ልማት ነው ይሉናል።

ወያኔ በሚገዛት ኢትዮጵያ ባለሀብት መሆንና ሀገር አልምቶ ራስን መጥቀም ገደብና መስመር አለው። ብዙ ኢንቨስተሮች የወያኔ ባለስልጣንን በአጋርነት፣ በሸሪክነት እንዲያስገቡ ይገደዳሉ። አሊያም ሀብቱን ላለመነጠቅ የፈለገ ሀብታም ልሁን ባይ የዳጎሰ ገንዘብ ለባለስልጣናቱ እጅ መንሻ ለኪስ ተጠይቀው ይሰጣሉ። በአንጻሩ የወያኔን የሀብታምነትን ቀይ መስመር ዘለው እምቢ ያሉ እስር ቤት የተጣሉ፣ የተሰደዱ በተለይ ወያኔ ከሚጠላው የጎሳ ወገን የሆኑ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ፣ የልማት ተስፈኞቹ በቃሊቲና በዝዋይ እስር ቤቶች ተጨናንቀዋል።

ዛሬ ዛሬ ጤፍ ጠፋ ተወደደ፣ ስኳር ጠፋ ምን እንሁን፣ መብራትና ውሃ ጠፋ ፈረቃው በዛብን ሲባሉ፤ መልሳቸው አስገራሚ እና አሳዛኝ ነው፡፡ ይህ ሁሉ የጠፋው፣ የምትራቡት አገሪቱ እያደገች ስለሆነ ነው የሚል የማላገጥ መልስ ይሰጣሉ። የሚሉት እድገት ቁልቁል እንደካሮት እየጨመረ ያለውን ድህነት መሆኑን ማለታቸው ነው።

በኢትዮጵያ የነገሰው ደህነት፣ ከድህነቱ ጋር የተያያዘው መጠነ ሰፊ ተስፋ መቁረጥና ስደት ለወያኔ ምኑም አይደለም። ምናልባትም የአገሪቱን እድገት ያመጣው ነገር ነው በሚል መላምት የሆነ፣ የይሆናል ግምታቸውን ይሰጡናል።

የአደገችና የበለጸገችን ኢትዮጵያ ከመፍጠር ይልቅ በልማት ስም የግል ምቾታቸውንና ድሎቶቻቸውን ለማስጠበቅ፣ ብሎም የስልጣን ጊዚያቸውን ለማራዘም ሲሉ፤ ህዝብን ከቀዪው በማፈናቀል ለርሃብና ለስቃይ ለስደት እየዳረጉት ይገኛሉ።

ህወሃቶች የሀብት ክፍፍል በገጠሪቱ ኢትዮጵያ በሚል የአካባቢውን ነዋሪ በማንነቱ ምክንያት አፈናቅለው የህወሃት አባላትንና ደጋፊዎችን የመጥቀም ስትራቴጂዎችን ቀርጸው ሰፊውን የህዝብ ጉልበት እንደ መዥገር መጠው፣ በቀዪው ያፈራውን ንብረትና ገንዘብ እንኳ ሳይሰበስብ ያፈናቅሉታል። ታዲያ የትኛው የልማት ስትራቴጂ ይሆን ህዝብን ማእከል ያደረገው?

የተማሩ ዜጎች በተማሩበት ሙያ ሰርተው በልማቱ ሂደት ራሳቸውንና ሀገራቸውን እንዳይጠቅሙ አድረገው ራእያቸው በማጨለም በጨፍን የስርአቱ ባሪያ አገልጋይ አሊያም አጨብጫቢ እንዲሆኑ ሆነው ይቀረጻሉ፤ አሊያ ግን መጽዋት ጠባቂ ወይም ከሀገር እንዲሰደዱ ይደረጋሉ።

የወያኔ ልማት ህዝብ ህዝብም፣ ሰው ሰውም አይሸትም! ስለዚህም በአገር አልሚነት ስም ማንንም ማታለል አይችልም። ይህ የዝርፊያና የፈንጋይ የወያኔ ኢኮኖሚ ከራሳቸውና ከጉጅሌዎች ባለፈ ውጭ የሚጠቅመው ኢትዮጵያዊ አይኖርም።
ኢትዮጵያ ለሁሉም ልጆቿ የሚሆን የተፈጥሮ ጸጋ አላት። ምቹ የአየር ንብረት፣ ለም አፍርና በተስተካከለ መልከዓ ምድር የተቸረች ሀገር ነች። ልጆቿ ሁሉ የዚህ ጸጋ ባለቤት እንዳይሆኑ እና ዜጎቿ በእኩልነት ተጠቃሚ ሳይሆኑ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሆነው እንዲሰደዱ እያደረገ ያለው ወያኔ ነው። ወያኔ አልሚ ሳይሆን የልማት ፀርና የአንድነት ቀበኛ ነው።

በኢትዮጵያ ልማትም፣ እድገትም፣ እኩልነትም፣ ሰብአዊ ክብርም፣ ተስፋም፣ በሀገር መኩራትም እንዲኖር ወያኔ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መወገድ አለበት። ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ለነዚህና ለእውነተኛ የሰበአዊ መብት መከበር፣ ሁሉም ዜጎች በሀገራቸው የትኛውም ቦታ በእኩልነት ሰርቶ የማደግ መሰረታዊ መብቶች፤ ህዝብን ማእከል ላደረገ እውነተኛ ልማት እና ሀገራችንን ከመፈራረስ አደጋ ለመታደግ ረጅሙን የትግል ጉዞ በአንድ ርምጃ ጀምሮአል፡፡ እርሰዎስ? ኑ! ተቀላቀሉን፡፡ ድህነት፣ ውርደት፣ ስደት እስከመቼ?

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

Thursday, May 2, 2013

አቶ ሃይለማርያም ለአውሮፓ ህብረት የገባውን ቃል አፈረሰ::የወያኔ የፖለቲካ ፍርድ ቤቱ በእነ እስክንድር ነጋ ላይ ፍርዱን አጸና::



አዲስ አበባ ያሉ ዲፕሎማቶች መታገስ ነው ይላሉ:;
ምንሊክ ሳልሳዊ

ባለፈው የአውሮፓን ህብረት ለመጎብኘት ወደ ብራስልስ ያመሩት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በህብረቱ በቆዩበት ጊዜ ተደጋግሞ ሲነሳላቸው የነበረው ጉዳይ የእስረኞች ጉዳይ እንደነበር ይታወቃል ::በዚህም መሰረት በሕወሓት መራሽነት የሚተሙት አቶ ሃይለማርያም እጅግ ጥብቅ የሆነ ቃል ገብተው ወደ ሃገር ቤት መመለሳቸውን የትላንት ዜናችን ነበር :; እንዲሁም ከዚህ ቀደም በተለያዩ ወቅቶች ሟቹ ጠ/ሚ የተለያዩ ገንዘቦችን እና መደለያዎችን ከህብረት በልማት ስም በመውሰድ ቃል እየገቡ ነገሩ ጎትተውት አልፈዋል:: ህብረቱ የልማት እርዳት ሲያደርግ የነበረ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ያለውን የተካረረ ነገር ላማላልት እና ወደ ስብኣዊ መብቶች ላይ ለማተኮር መሆኑን በተደጋጋሚ ገልጿል::

ከወደ አዲስ አበባ ዛሬ በፍርድ ቤቱ አሳዛኝ ፖለቲካዊ ውሳኔን ተከትሎ በሃገር ውስጥ ያሉ የተለያዩ ዲፕሎማቶች ሁኔታው ከማስገረምም አልፎ አስደንግጦናል ሲሉ ተደምተዋል:: ሆኖም የመንግስታቹህን ጭራ ለመያዝ ይከብዳል የሚሉ ዲፕሎማቶች ነገሮችን በትእግስት መመልከት እና መጠበቅ ነው ሁኔታዎች ሊቀየሩ ይችላሉ የውስጥ አጣብቂኞች የፈጠሩት ውሳኔ ይሆናል ምናልባት......የጀመርነውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እንቀጥላልን ብለዋል::

ዛሬ በጠቅላይ ፍርድቤት የዋለው የፍርድ ሂደት በእስንድር ነጋ የ18 አመት እና አንዷለም ላይ የእድሜልክ እስራት ያጸና ሲሆን ዳኛው የወያኔ ጀሌው ዻኜ መላኩ ክሱም ሆነ ውሳኔው ትክክል እና ምንም አስተያየት ሊደረግለት የማይችል ሲል ከታሪክ ተጠያቂነት የማይድንበትን አስተያየት የሰጠ ሲሆን ሌሎች የጠቅላይ ፍ/ቤ ዳኞች አናየውም ብለው እስከ በላይ አካል ክርክር የተኬደበትን ጉዳይ ከምን ሞራል እንዲህ ሊደመድምበት እንደቻል ጊዜ ይጠይቀዋል::
እንደዚህ አይነት በፍትህ ላይ ጠባብ አመለካከታቸውን እና ጸረ ህዝብ አቋማቸውን የሚያራምዱ ዳኞችን መከታተል እና ከየተደበቁበት ጊዜ ጠብቆ መጋለጥ የዜግነት ግዴታ ነው:: ይህ መንግስት ሲወድቅ በተለያዩ የአውሮፓ እና የአሜሪካ ከተሞች ለመመሸግ እያለሙ የሚገኙት የፍትህ አካላትን መከታተል ግዴታችን ነው::

ከፍርዱ በኋላ "እውነት ነጻ ታወጣናለች!!!" ያለው እስክንድር ነጋ "የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ እውነት በራሱ ጊዜ እንደሚወጣ ለኢትዮጵያውያን ማሳወቅ እንፈልጋለን "ብሏል:የተከሰሱበት ጉዳይ በአሸባሪነት እና አሸባሪ ተብሎ በተፈረጀው ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አላቹህ ተብለው ቢሆንም ከዚህ በፊት ጉዳዩን እንዲያዩት ይግባኙ የቀረበላቸው ዳጛ አማረ አሞኘ ይህን ክስ ለማየት የሚያስችል በቂ ማስረጃ ስላሌለ በነጻ እለቃቸዋለሁ በማለታቸው ጉዳዩ ከሳቸው እጅ ተነጥቆ ፖለቲካዊ ዉሳኔ እንዲሰጥበት ተደርጓል::
በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለው የፍርድ ቤት ስርኣት እና ውሳኔዎች በአለም አቀፍ ደረጃ አነጋጋሪ ከሆነ ረዥም አመታትን ያስቆጠረ ሲሆን የወያኔ ካንጋሮ ፍርድቤት እና ያልሰለጠኑ በፖለቲካ ታማኝነት ዳኛ የሆኑ ያልበሰሉ ካድሬዎች እየወሰዱ ያለው ህገወጥ እርምጃ እና ውሳኔ ነገ እንደማያስጠይቃቸው ሆነው መታየታቸው ሃገር ምን ያህል በፍትህ እጦት ቀውስ ውስጥ እንደሆነች ያሳያል:; ለግል የወያኔ ጥቅማጥቅሞች እና የኑሮ ምጮት እየተገዙ ያሉት የህግን ከለላ እንኳን ምን ያህል ስሜቶችን መረዳት ያልቻሉ ፍርደገምድል ዳኞችን መፋረድ ግዴታችን ነው::
እስክንድር ነጋም ሆኑ ሌሎች እስረኞች ቀን ሳይረዝም በቅርብ ጊዜ እንደሚለቀቁ ባለሙሉ ተስፋ ስሆን ይህ ደሞ ወያኔ እየደረሰ ያለበትን ኪሳራ እያሳየን ነው :: በተለያዩ የአውሮፓ እና የሰሜን አሜሪካ ከተሞች ወያኔ እየደረሰበት ያለውን ውርደት ለማካካስ እየተጠቀመበት ያለው ስልት እንደማያዋጣው ልንነግረው ይገባል::
ዲያስፖራው ትግሉን ያቆማል ብሎ የሚያስብ ከሆነ ዘላለሙን በጫካ ሞኝነት ራሱን የሚነዳው ወያኔ ልክ እያስገባነው መሆኑን አልተረዳውም:; በተከታይነት ደሞ በቀሪ የህሊና እስረኞች ላይ ሊወስን የተዘጋጀውን እየጠበቅን ትግሉ ግን ወያኔ አፈር እስኪገባ እንደሚቀጥል ለመናገር እወዳለሁ :: ትግሉ ይቀጥላል!!!

ምንጭ ምኒልክ ሳልሳዊ

የሕዳሴው” ግድብና ደሞዜ

በፍቃዱ ዘ ኃይሉ

ከስድሰት ወር በፊት እሠራበት የነበረው የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ለግድቡ መዋጮ የፈለግነውን ያክል ገንዘብ የምናዋጣበት ባዶ ቅጽ ላከልን። ብዙዎቻችን የወሩን ሦስት አራተኛ በጥልፍልፍ ብድር የምናሳልፍ በመሆኑ ገሚሶቻችን በትሕትና ማዋጣት እንደማንችል ስንገልጽ ቀሪዎቹ ደግሞ “መቶም፣ ሁለት መቶም በዓመት ክፍያ ይቆረጥብን” ብለው ፈረሙ። ይህ ያላስደሰታቸው አለቆች ከቆይታ በኋላ 50% ደሞዛችንን በዓመት ክፍያ እንድናዋጣ የተጻፈበት ቅጽ ሊያስፈርሙን ሲያመጡ የፈቃደኝነታችን ሥርዓተ ቀብር ተከናወነ። እኔ አልፈርምም አልኩኝ። የድኅረ ምረቃው ት/ቤት ም/ፕሬዚደንት ቢሮዬ ድረስ መጥቶ ተማፀነኝ – “የተቋማችን ስም ይጎድፋል” በማለት። እኔም አልኩት “ወር በገባ በ10ኛው ቀን ከሚያልቀው ደሞዜ ላይ የማዋጣው ገንዘብ የለኝም፣ ከቻሉ የገቢ ግብሬን ይጠቀሙበት – ለማይወክለኝ ግንቦት 20 ድግስ ርችት የሚተኩሱበትንና ከአፌ ነጥለው የወሰዱትን ታክስ መጀመሪያ ባግባቡ ይጠቀሙበት። አሁን ግን አዋጣ ከምትሉኝ ልቀቅ ብትሉኝ እመርጣለሁ። በእኔ ገንዘብ እየተሠራ ኢሕአዴግ ራሱን በኢቴቪ ሲያሞግስ ማየት አልችልም” ብዬ ተንጣጣሁ። አስብበት ብሎ ቅጹን አስቀምጦልኝ ሄደ።

የሕዳሴው" ግድብና ደሞዜ

30 ደቂቃ ቆይቼ ሄድኩና “አሰብኩበት ግን አላዋጣም” አልኩት።

ነገሩ በዚህ ያበቃ መስሎኝ ሳለ የዛሬ ስድስት ወር ገደማ በግል ጉዳዬ ተቋሙን ልለቅ ሳመለክት እና ‘ክሊራንስ‘ ሳዞር የሕዳሴው መዋጮ ቀሪ አምስት መቶ ምናምን ብር አለብህ ተባልኩ። “I was like ‘what?!’” ይሉ ነበት ፈረንጆቹ ቢሆኑ። ድንግጥ አልኩ።

 “ያ አሲዳም ደሞዜ ወትሮም ከብድር ከፋይነት የትም አላደረሰኝ። ለካስ በየወሩ እየተቀነጠበ ነበር የባሰ መቅኖ ያጣብኝ” አልኩና ባሳቤ “በማን ፈቃድ ቆረጣችሁት?” አልኳት ሒሳብ ሠራተኛዋን። የሆነ ዶሴ ፈልፍላ አወጣችና “አቶ በፍቃዱ …. እስካሁን ስላልተቆረጠባቸው … ከዚህ ወር ጀምሮ …” ደብዳቤው እንደቃለጉባኤ ያለ ሲሆን ከግርጌው ፊርማዎች ሰፍረውበታል።

ም/ፕሬዚደንቱ ቢሮ ብስጭቴን ይዤ ሄድኩ። “እኔ የለሁበትም” ተባልኩ። የፋይናንስ ኃላፊውጋ ሄድኩ “ተቋሞች በሙሉ የሠራተኞቻቸውን ደሞዝ አምሳ በመቶ ለማዋጣት ስለተስማሙ ሁሉም ሠራተኛ ግዴታ ማዋጣት አለበት ተብሎ ተወስኗል” አለኝ። “በገዛ ደሞዜ ማን የመወሰን ሥልጣን አለው? የኔ ደሞዝ የመንግሥት ፓሊሲ ለማውጣት የማይተገበረው የድምፅ ብልጫ ለምን ይተገበርበታል?” በማለት አማረርኩ። በጩኸት “እከሳችሀኋለሁ” እያልኩ ዛትኩ።

ከዚያ በኋላ ግን አንደኛ “አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ” መሆኑን እያወቅኩ ለማን እከሳለሁ? ሁለተኛ መቼም ጉዳዩ የአገር ጉዳይ ነው፣ እስኪ ከፕሮፓጋንዳ ተርፏቸው ከሠሩት ይሥሩበት በማለት ቀሪውን ከ‘ፕሮቪደንት ፈንዴ‘ ላይ ከፍዬ ለቀቅኩ። ምናልባትም ከከሰስኩ ተቋሜን ሳይሆን መከሰስ የሚገባውን የምከስበት ቀን ይመጣል!
ይህ ከሆነ ጀምሮ ያተረፍኩት ነገር ብስጭት ነው። ከጉሮሮዬ ነጥዬ ያዋጣሁት እኔ እያለሁ፣ “አባይን የደፈረ ጀግና” ሌላ ነው። እኔ ካሁን አሁን ግድቡ አለቀ ብዬ በጉጉት እጠብቃለሁ፣ የግድቡ ፅንሰት እየተባባሉ በገንዘቤ ደግሰው ይበላሉ፣ ይጠጣሉ፣ ይጨፍራሉ። ይህንንም በኢቴቪ ያስተላልፋሉ።

Tuesday, April 30, 2013

የኢትዮጵያ ፊዴራላዊ ዲሞክራሳዊ አንድነት መድረክ አባል ድርጅቶች በአስቸኳይ እንዲዋሃዱ ጠየቀ

ሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ላለፉት አምስት ወራቶች የመድረክን የሥራ አፈፃፀም ሁኔታ በቅርብ ሲገመግም የነበረው የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት ቅዳሜ ሚያዝያ 19 ቀን 2005 ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት የአራት ፓርቲዎች ስብስብ የሆነው መድረክ እንዲዋሃድ ብሏል ሲል ፍኖተ ነፃነት ዘግቧል።

... ድርጅቱ ላለፉት አራት ዓመታት አሳሳቢ በሆኑና በበርካታ ችግሮች ተተብትቦ የቆየ ቢሆንም ሀገራችን ወደ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለማሸጋገር በተደረገው ትግል ውስጥ የተጫወተው ሚና እጅግ ከፍተኛ መሆኑን የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት አረጋግጧል።

እንደዘገባው ከሆነ ብሔራዊ ምክር ቤቱ በሰየመው ገምጋሚ ኮሚቴ አማካኝነት የመድረክ አጠቃላይ ሁኔታ በስድስት ዋና ዋና ክፍሎች ተገምግሞ የቀረበ ሲሆን በምክር ቤቱ ውይይት ተደርጎበታል። በዚህ የግምገማ ሪፖርት ላይ ብቻ በመወያየት የመድረክ ጉዞ በውህደት እንዲጠናቀቅ የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት ወስኗል።

የሀገሪቱ አጠቃላይ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የጠቀሰው የምክር ቤቱ መግለጫ እራሱን የኢትዮጵያ ሕዝብ በሚፈልገው የለውጥ ደረጃ በማጠናከርና አማራጭ የመፍትሔ አቅጣጫ በማስቀመጥ ሕዝቡን በዙሪያው የማሰባሰብ ሥራ እንዲሰራ ብሄራዊ ምክር ቤቱ ጥሪ አስተላልፏል።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ አባል ድርጅቶች በአስቸኳይ እንዲዋሃዱ ተጠየቀ
ሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ላለፉት አምስት ወራቶች የመድረክን የሥራ አፈፃፀም ሁኔታ በቅርብ ሲገመግም የነበረው የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት ቅዳሜ ሚያዝያ 19 ቀን 2005 ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት የአራት ፓርቲዎች ስብስብ የሆነው መድረክ እንዲዋሃድ ብሏል ሲል ፍኖተ ነፃነት ዘግቧል።

ድርጅቱ ላለፉት አራት ዓመታት አሳሳቢ በሆኑና በበርካታ ችግሮች ተተብትቦ የቆየ ቢሆንም ሀገራችን ወደ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለማሸጋገር በተደረገው ትግል ውስጥ የተጫወተው ሚና እጅግ ከፍተኛ መሆኑን የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት አረጋግጧል።

እንደዘገባው ከሆነ ብሔራዊ ምክር ቤቱ በሰየመው ገምጋሚ ኮሚቴ አማካኝነት የመድረክ አጠቃላይ ሁኔታ በስድስት ዋና ዋና ክፍሎች ተገምግሞ የቀረበ ሲሆን በምክር ቤቱ ውይይት ተደርጎበታል። በዚህ የግምገማ ሪፖርት ላይ ብቻ በመወያየት የመድረክ ጉዞ በውህደት እንዲጠናቀቅ የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት ወስኗል።

የሀገሪቱ አጠቃላይ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የጠቀሰው የምክር ቤቱ መግለጫ እራሱን የኢትዮጵያ ሕዝብ በሚፈልገው የለውጥ ደረጃ በማጠናከርና አማራጭ የመፍትሔ አቅጣጫ በማስቀመጥ ሕዝቡን በዙሪያው የማሰባሰብ ሥራ  እንዲሰራ ብሄራዊ ምክር ቤቱ ጥሪ አስተላልፏል።

Monday, April 29, 2013

TPLF Generals involved in illegal Tantalum trade

April 27, 2013

ESAT News

The discovery of 2500 ons of pure Tantalum in Shakiso and Ansora Woredas, Guji Zone, Oromia Region few years ago by a governmental organization called Kentica Borena Ethiopia Mines Development Share Company, had attracted the attention of many media then.

The export of this strategic and expensive mineral had been suspended after experts of the field unstintingly complained to the late Prime Minister Meles Zenawi saying that the export by the company was hurting the country.

The government had then said the reason for putting the restriction was to establish a new mechanism of handling the mineral as the radioactive rays found in the Uranium have health risks and also to gain better profit by developing the mineral in a modern way. It was also mentioned then that the restriction would be in place until the government builds its own Tantalum Refining Plant.

Ethiopia’s tantalum production took 20% of the world market with a big influence on the world tantalum price. As the Dodd-Frank Act states that companies should make sure that they do not buy conflict minerals and as the largest exporter of tantalum in the world is the war torn country of Democratic Republic of Congo, Ethiopia’s ban had put an immense pressure on the world tantalum market.

Tantalum is a non renewable precious mineral used in mobile phones, wires, computers, televisions, chemical and pharmaceutical products, aerospace, energy and ballistic products.

According to sources working in the company, although the Ethiopian government put the ban on this precious and non- renewable mineral for the above stated reasons, military generals that are members of the Tigrean People’s Liberation Front (TPLF) conspiring with Chinese experts skilled on the extraction of tantalum, have been illegally exporting the mineral via Somaliland using vehicles of the Ethiopian Defense Forces. They have been conducting the smuggling claiming that what was in the vehicles was sand. The Generals amassed millions through this illegal export.

Vehicles of the company of the Defense Forces, which is constructing roads in the region, are being used to smuggle the mineral instead of constructing the roads, sources within the Company said.

Recently, as the government is facing severe financial shortage and following the lifting of the ban, these Generals have started exporting tantalum via Djibouti by forming a share company with a Chinese company.

“Tantalum is a strategic mineral. It is being depleted. If the country runs out of the mineral now, Ethiopia will face bigger problems in the future” the employees said.
The sources said the Generals are conducting the illegal trade in collaboration with Zone officials.
Although ESAT did not confirm, several people living near the extraction sites have died due to the radioactive rays of the mineral. Before the ban, the government sold over 80% of the tantalum in China.

Our efforts to speak to Ethiopian authorities on the issue were unsuccessful.
Backed up by evidence, ESAT had reported that Ethiopian generals own modern buildings and business companies in various parts of the Country.

የጠ/ሚኒስትር ሀይለማርያም ፓርላማ ዉሎ የፓርላማዉን አባላት ጭምር ማስቆጣቱ ታወቀ

የወያኔ ታማኝ ሎሌ የሆነዉ ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ባለፈዉ ሳምንት የፓርላማ ዉሎዉ 40 በ 60 የተባለውን የቤቶች ልማት ፕሮጀክት አስመልክቶ ለቀረበለት ጥያቄ የሰጠዉ ምላሽ ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መልኩ ከዚህ ቀደም ከሳቅና ጭብጨባ ዉጭ ሌላ መቃወም የሚባል ነገር የማያዉቀዉን የወያኔ ፓርላማ ማስቆጣቱ ተሰማ፡፡ ኃይለማርያም ደሳለኝ ይህ እንግዳ የሆነ ተቃዉሞ የገጠመዉ የ2005 በጀት ዓመት የስምንት ወራት ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት ሲሆን የፓርላማዉ አባላት 40 በ 60 የሚባለው የቤት ልማት መቶ በመቶ የመክፈል አቅም ላላቸው ሰዎች ቅድሚያ ይሰጣል የመባሉን ጉዳይ እርግጠኛ ስለመሆኑ ለጠየቀዉ ጥያቄ አዎንታዊ መልስ በመስጠቱ ወይም መቶ በመቶ የመክፈል አቅም ላላቸው ቅድሚያ እንደሚሰጥ በማረጋገጡ ፓርላማዉ በተቃዉሞ ድምፅ ሲሞላ ተስተዉሏል።

ለወያኔ ፓርላማ ቅርበት ያላቸው ምንጮች የፓርላማዉ አባላት ለምን አለወትሯቸዉ ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ላይ እንዳልጎመጎሙ ተጠይቀው በሰጡት መልስ ቀደም ሲል ፕሮግራሙን በተመለከተ ለፓርላማው በቀረበዉ ሪፖርት 40 በ60 የሚባለው ፕሮግራም መካከለኛ ገቢ ያለውን በተለይም በደሞዝ የሚተዳደረውን የህብረተሰብ ክፍል ይጠቅማል ተብሎ መነገሩንና ሆኖም በዕቅድ ደረጃ ለባለአንድ ክፍል መኝታ ቤት 857 ብር፣ለባለሁለት መኝታ ቤት 1 ሺ 337 ብር፣ ለባለሶስት ምኝታ ቤት ደግሞ 2 ሺ133 ብር ለአምስት ተከታታይ ዓመታት በየወሩ መቆጠብ እንዳለበት መታቀዱ የመካከኛ ገቢ ያለውን የህብረተሰብ ክፍል አቅም ያገናዘበ አይደለም የሚል ቅሬታ በፓርላመዉ አባላት ዘንድ በቅሬታ መልክ በተደጋጋሚ ይነሳ እንደነበረ አስታውሰዋል፡፡

በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ መካከለኛ ገቢ አለው የሚባለው በተለይም የመንግስት ሰራተኞች አማካይ ወርሃዊ መካከለኛ ገቢ ከ2 ሺ 500 ብር እንደማይበልጥ ምንጫችን ጠቅሶ ከዚህ ደመወዝ ላይ ዝቅተኛውን በወር 857 ብር መቆጠብ እንዴት ይቻላል ሲል የወያኔን ግራ የሚያጋባ አሰራር ገና ሳይጀመር ጥያቄ ዉስጥ የገባ አሰራር ነዉ ብሎታል፡፡ በዚህ ምክንያት የ40 በ60 የቤት ልማት ፕሮግራም መካከለኛ ገቢ ላላቸዉ ሰዎች ይዘጋጅ እንጂ እካሁን ድረስ እየጠቀመ ያለዉ ከፍተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ነዉ፤ ይህንን ደግሞ ኃ/ማሪያም ደሳለኝም ፓርላማ ዉስጥ ባደረገዉ ንግግር አረገግጦታል ብሏል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ጠ/ሚኒስተር ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ቢሮ አማካይነት በተደረገው ጥናት ለውጪ ኩባንያዎች ዝግየሆነውን የሸቀጦች ችርቻሮ ንግድ ስራ ለመፍቀድ ወይ ሌሎች አማራጮችን ለማየት መሞከሩን የኢሳት ቴሌቭዥንና ሬድዮ ዘጋቢ ጠቅሶ ይህ ነገር ግን ትልልቆቹ ኩባንያዎች በሸቀጦች የችርቻሮ ንግድ እንዲሰማሩ ቢደረግ የአገር ውስጥ አስመጪዎች በአጭር ጊዜያት ውስጥ ከገበያ ውጪ በማድረግ መንግስት ሊቆጣጠረው የማይችለው ገበያ ሊፈጠር ይችላል የሚል ስጋት በመኖሩ በመንግስት ቁጥጥር ስር ሆኖ ዋጋ የማረጋጋትና አነስተኛ ዋጋ ካላቸው ገበያዎች ሸቀጦችን በመግዛት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያቀርብ ኢንተርፕራይዝ እንዲቋቋም ውሳኔ ላይ ተደርሶአል፡፡

የወያኔ ፖሊሶች ከግንቦት7 ህዝባዊ ኃይል ጋር ግንኙነት አለዉ የሚሉትን ወጣት ሁሉ እየከበቡ ማሰር ጀመሩ

የዘረኛዉ ወያኔ የፖሊስና የጸጥታ ኃይሎች በቅርቡ እራሱን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋራ ካስተዋወቀዉ ከግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል ጋር ግንኙነት አለዉ ብለዉ የሚጠረጥሩትን ወጣት እያደኑ ማሰር መጀመራቸዉን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ታማኝ የአገር ዉስጥ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ በዘገበዉ ዜና ገለጸ። ለኢሳት የደረሰው መረጃ መሠረት መሳሪያ አንግበዉ ከአዲስ አበባ በብዛት የተንቀሳቀሱ የፌደራል ፖሊስ አባላት ከባህርዳር በ35 ኪሜ ርቀት ላይ ወደምትገኘዉ መርአዊ የምትባል ከተማ በመሄድ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን አፍነው አዲስ አበባ ዉስጥ ለግዜዉ ወዳልታወቀ ቦታ እንደወሰዷቸዉ ለማወቅ ተችሏል።

ምሽት ላይ አድፍጠዉ መርአዊ ከተማ የገቡት ፖሊሶችና የደህንነት ኃይሎች የአካባቢውን ሰዎች በማስፈራራት ተማሪዎቹን አፍነው የወሰዱዋቸው ሲሆን፣ በወቅቱ አንድ ወጣት ክፉኛ መደብደቡን ለማረጋጥ ተችሏል። አንድ የባህር ዳር ነዋሪ ለግንቦት ሰባት ዜና ዜና ዝግጅት ክፍል ስልክ ደዉለዉ የተማሪዎቹን መታሰርና መደብደብ ካወገዙ በኋላ የኢትዮጵያ ህዝብ አንቅሮ እንደተፋዉና ስርአቱን ለመደምሰስ በእንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝ የተረዳዉ ወያኔ የቀብፀ ተስፋ እርምጃ መዉሰዱ የሚገርም ባይሆንም አይኑ ያተፈበትንና ገደብ የሌለዉ እጁ የደረሰበትን ዜጋ ሁሉ እያፈሰ ማሰር መጀመሩ ህዝብ የጀመረዉን የፍትህ፤ የነጻነትና የደሞክራሲ ትግል አጠናክሮ የድሉን ግዜ ያፋጥነዋል እንጂ አያሳጥረዉም ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የደህንነት ሹም በመሆን ለረጅም ጊዜ ያገለገለዉ የሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ወያኔን በመክዳት የግንቦት7 ህዝባዊ ሀይልን መቀላቀሉ ታውቋል። ሻለቃ መሳፍንት በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ስላለው የዘር ችግር፣ በብአዴን ውስጥ ስለሚነሱ ቅሬታዎች እና መሰል ጉዳዮች ዛሬ ከኢሳት ጋር ሰፊ ቃለምልልስ አድርጓል። ሙሉ ቃለምልልሱ በቅርቡ ይቀርባል።

በአፋር ክልል የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች የሚኖሩበትን ቦታ እኛዉ እናስተዳድዉ የሚል ጥያቄ ማቅረባቸዉ ተሰማ

የአማራን ተወላጆች የገቡበት ቦታ ሁሉ እየገባ ወደ ክልላችሁ ሂዱ እያለና ንብረታቸዉን እየቀማ የሚያፈናቅለዉ የወያኔ አገዛዝ ታማኝ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች አፋር ክልል ዉስጥ በብዛት ሰፍረዉ በሚገኙበት ቦታ እራሳችንን በራሳችን የማስተዳደር መብት የስጠን የሚል ጥያቄ ማቅረባቸዉን ከሰሞኑ ከወደ አፋር ክልል የነፈሰዉ ዜና አስረዳ። በአፋር ክልል የዞን ሁለት ዋና ከተማ በሆነችዉ አብአላ ዉስጥ የሚኖሬት ቁጥራቸዉ 15 ሺ የሚጠጋ የትግራይ ተወላጆች ብዛት ስላለን እራሳችንን የማስተዳደር መብት ይሰጠን ሲሉ ያቀረቡትን ጥያቄ የክልሉ ሰብአዊ መብቶች ሃለፊ የሆኑት አቶ ገአስ አህመድ አዎንታዊ መልስ የማያስፈልገዉና አግባብ የሌለዉ ተራ ጥያቄ ነዉ ሲሉ የትግራይ ተወላጆች ያቀረቡትን ጥያቄ አጣጥዉታል።

አቶ ጋአስ በዱብቲ ከተማ በርካታ የአማራ፣ የኦሮሞ እና የትግራይ ተወላጆች ቢኖርም አንድም ቀን የወረዳ ጥያቄ አለማንሳታቸውን ገልጸው፣ ከመቀሌ በ45 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው አብአላም ከተማ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ያቀረቡት ጥያቄ አሳዛኝ መሆኑን ገልጸዋል። የአፋር ክልል በህወሀት ሰዎች የሚመራ መሆኑን የገለጹት አቶ ገአስ፣ ተወላጆቹ ወረዳ ይሰጠን ከሚሉ ክልሉ የራሳቸው መሆኑን ቢያውቁት ይሻል ነበር ብለዋል። እንደ አቶ ገአስ አባባል አብላ ከተማ ዉስጥ የሚኖሩት የትግራይ ተወላጆች ከተማዋ በራሳቸዉ ቋንቋ ሸከት ተብላ እንድትጠራና እንዲሁም የአፋር ክልላዊ መንግስት በከተማዋ መሬት ለኢንቨስትመንት መስጠት አይችልም የሚሉ ጥያቄዎችን ማንሳታቸዉን ጠቅሰዉ በአሁኑ ጊዜ በአፋር ክልል የህወሀት ባለስልጣናት ግምገማ እያስደረጉና የራሳቸውን ሰዎች እየሾሙ ክልሉን ለውድመትና ለጥፋት እየዳጉት መሆናቸዉን ተናግረዋል።

Saturday, April 27, 2013

አርቲስት ጀማነሽ ሰለሞን ታሰረች


አርቲስት ጀማነሽ ሰለሞን ታሰረች
“የፍርድ ሂደቱ ሲጠናቀቅ ጋዜጣዊ መግለጫ እንሠጣለን” - ከጀማነሽ ጋር የታሰሩ አባት
በተለያዩ የመድረክ ቴያትሮች፣ በቴሌቪዥንና በሬዲዮ ድራማዎች በተለይም “ገመና” በተሰኘው ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ የእናትነት ገፀ - ባህሪን ተላብሳ በመተወን የምትታወቀው አርቲስት ጀማነሽ ሰለሞን ታሰረች፡፡ አርቲስቷ ማክሰኞ ማታ ተይዛ አራት ኪሎ የሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ከታሰረች በኋላ ረቡዕ አመሻሽ ላይ ወደ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ መዛወሯንና ከእርሷ ጋር ሌላ አንዲት ሴትና ሁለት ወንዶች መታሰራቸውን በስፍራው ተገኝተን አረጋግጠናል፡፡ አርቲስት ጀማነሽና አብረዋት የታሰሩት ግለሰቦች ሃሙስ እለት አፍንጮ በር መንገድ አዲስ አበባ ሬስቶራንት አካባቢ በሚገኝ የመጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት ቀርበው ጉዳያቸው የታየ ሲሆን የፊታችን በድጋሚ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፡፡
 
አርቲስቷንና አብረዋት የታሰሩትን ሰዎች ለመጠየቅ ወደ ስፍራው ከመጡ ግለሰቦች ለመረዳት እንደቻልነው፤ አርቲስቷና አብረዋት ያሉት ሰዎች የታሰሩት “ማህበረ ስላሴ ዘ ደቂቀ ኤልያስ” ከተባለው ማህበራቸውና ከሀይማኖት ጉዳይ ጋር በተያያዘ እንደሆነ ጠቁመው ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ ከአርቲስቷ ጋር የታሰሩት አንድ የሃይማኖት አባት፤ ጉዳዩ በፍርድ ቤት የተያዘ በመሆኑ ከፍርድ ሂደቱ በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ፣ አሁን ምንም አይነት ዝርዝር መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ነግረውናል፡፡ አርቲስት ጀማነሽን ሊጠይቋት የመጡ ሰዎችን ለማነጋገር ስትወጣ በተመለከትናት ጊዜ በፈገግታ የታጀበች ሲሆን ጠያቂዎቿ “እንዴት ነሽ ተመቸሽ?” ብለው ሲጠይቋት “እግዚአብሔር ያለበት ቦታ ሁሉ ምቹ ነው” ስትል ምላሽ ሰጥታለች፡፡ አርቲስቷ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ “ተዋህዶ” በሚል ሃይማኖት ውስጥ ተሣታፊ በመሆን አነጋጋሪ ሆና መቆየቷ የሚታወስ ነው፡፡
 
ወረዳ ዘጠኝ ፖሊስ ጣቢያ በተገኘን ጊዜ የሃይማኖቱ ተከታዮች የሚለብሱት የቀስተደመና ቀለማት ያሉት ነጠላ አጣፍታ፣ ፀጉሯንም የቀስተ ደመና ቀለም ዙሪያውን ባቀለመው ሻሽ አስራለች፡፡ ማህበረ ስላሴ ዘ ደቂቀ ኤልያስ “የኢትዮጵያን ትንሣኤ ሊያረጋግጥ ሃያል ባለስልጣን ነብዩ ኤልያስ ከብሔረ ህያዋን ጳጉሜ 1/2003 ዓ.ም ወደ ምድር መጥቶ በመካከላችን ይገኛል፣ ኦርቶዶክስ የሚባለው የሃይማኖት ስም ስህተት ነው ተዋህዶ ነው መባል ያለበት፣ ሰንበት ቅዳሜ ብቻ ነው፣ መለበስ ያለበት እግዚአብሔር ለኖህ ቃል ኪዳን የገባበትን ቀስተ ደመና ቀለማት ያካተተ ጥለት ያላቸው ነጭ አልባሳት ናቸው” የሚሉትን የተለያዩ ጉባኤዎችን እያዘጋጀ የሚያስተምር ማህበር መሆኑን ያነጋገርናቸው የማህበሩ አባላት ገልፀውልናል፡፡
 
 በተለያዩ ገዳማትም የሀይማኖቱ አራማጆች እንደሚገኙና እንደሚያስተምሩ ያገኘናቸው የሃይማኖቱ ተከታዮች ነግረውናል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ ከፖሊስ መረጃ ለማግኘት ጥረት ብናደርግም፣ ከመምሪያው የተፃፈ ፈቃድ ያስፈልጋል በሚል የወረዳው ፖሊስ መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡
 

ህዝቡ በወያኔ ላይ ያለውን ምሬትና ጥላቻ መግለጽ ጀምሯል!

የኢትዮጵያ ህዝብ እውነተኛ ምርጫና የቀልድ ምርጫ ምን ማለት እንደ ሆነ ጠንቅቆ የሚያውቅ መሆኑን በ1997 አም ባደረገው አለምን ባስደመመ ሂደት አስመስክርዋል::

ወያኔና ጀሌዎቹ ግን ዛሬም ሊማሩ አይችሉምና ደግመው ደጋግመው ህዝባችን ሊያሞኙት ይሻሉ በ2002 አ.ም ምርጫ ቦርድ ከሚባለው ሎሊያችው ጋር ሆነው ድምጹን ሰርቀውና አሰርቀው አሽንፍዋል አሽነፍን ብለው አይናቸውን በጨው አጠበው ጨፍር ብለው አደባባይ አስወጡት፤ በጥቃቅን ስም ባደራጁቸው እበላ ባዮች ታጅበውም በአደባባይ አላገጡ በህዝብ ቁስልም ላይ ጨው ነሰነሱ ህዝብም ታዝቦ ዝም አለ ዘንድሮስ?

ዘንድሮ የተለየው ነገር ተቃዋሚዎች ተባብረው 33 የሚሆኑት በአንድ ላይ ቆሙ ከምርጫው በፊት ጥያቄዎችን አንስተው እንደራደርም ብለው ጠየቁ ትእቢተኛው ወያኔም እንደልማዱ አሻፈርኝ የት ልትደርሱ አላቸው ትኩረታቸውን በሙሉ በየቤቱ እየዞሩ ካርድ እንዲወስድ ያስፈራሩት ጀመር የፈራ ወሰደ ያልፈራም ሳይወስድ ቀረ ይህንንም ህዝብ በትዝብት ተመለከተ ፤ካድሬዎቹም ሆነ አለቆቻቸው ወያኔዎች እሁንም ህዝቡን ንቀውታል ምን ያመጣል በሚል ትእቢት ከ99.6 % ወደ 100፥ በመለወጥ ለማሸነፍና ለመጨፈርና ለማስጨፈር ዝግጅታቸውን ማጠናቅቅ ላይ ብቻ አደረጉ።

ተቃዋሚዎችም በአንድ ድምጽ በመሆን የወያኔ የምርጫ አሻንጉሊት ሆነን ለእሱ ፕሮፖጋንዳ መጠቀሚያ አንሆንም ብለው በውሳኔያቸው በመጽናታቸው ወያኔን በእጅጉ አበሳጭቶታል፤ ይሁን እንጅ አጨብጫቢ የሆኑ ፓርቲዎችን መፈለጉ ግን አልቀረም ለምርጫ ጨዋታው አዳማቂነት። የምርጫ ዴሞክራሲያዊነት ከሚለካበት አንዱና ዋናው ፤ ህዝብ የሚፈልጋቸውን መሪዎቹ ያለማንም አስገዳጅነት መርጦ እንደሚሾሙና እንደሚሽር ማመን ሲጀምር መሆኑ ዛሬም ሊዋጥላቸው አልቻለም። ይሁን እንጅ ህዝብ ዛሬ ሳይሆን ከ97 ምርጫ ጀምሮ ወያኔን በህዝብ ድምጽ ተሸንፎ እንደማይወርድ የተገነዘበው አሁን ላይ ሆኖ ሳይሆን ትላንት መሆኑን ወያኔዎች አልተረዱትም ቢረዱትም ለህዝብ ድምጽ ደንታ አልሰጣቸውም።

ስለዚህም የህዝብ የበላይነት ማረጋገጫ የሆነውን ምርጫ ሂደት ወደ ልጆች መጫዎቻነትና ማላገጫ በመቀየር መሬት ላይ የሌለውን ምርጫ በቲቢ ምርጫ እንዳለ ለማስመሰል በኢቲቪ ተወዳድሮ የማሸነፍ ምኞታቸውን መራጭ በሌለበት ምርጫ ለማሳየት ሞክረዋል። ይህም የማስመሰል እና የማጭበርበር አመላቸው ሱስ ሆንባቸው የውድቀታቸውን፣ የሽንፈታቸውን ጽዋ እየተጋቱ እልል ሲሉ ያሳዩናል “በቀሎ እያረረ ይስቃል እንዲሉ”።

የሀገሪቱን ዜጎች በደልና ጥቃት የፍትህ ስርአት የነጻነት ጥያቄ በማፈን የአማራውን መፈናቀል ያልዘገበ ሚዲያና ጋዜጠኞቹ፤ እውን ምርጫ ስላልሆነ ተውኔት የአለቆቻቸውንና የስልጣን ጥመኞችን ውሸት እውነት አድርጎ በማቅረብ አለቆቻቸውን ሲደስቷቸው ሌሎችን ደግሞ አሳዝኗል።

ሚዲያ በታፈነባት ሀገረ-ኢትዮጵያ እንደ ኢቲቪ ያሉ ያዩትን ሳይሆን በወያኔ የተነገሩትን፣ የተዘጋጀላቸውን ሀተታዊ ድራማ በሚዘግቡ፤ እውነታን በማይናገሩ ቡችሎች ስለምርጫ ሲዘምሩ ይታያሉ። ካድሬዎቻቸው እንኳ ወጥተው ባልተሳተፉበት መራጭ የሌለውን፤ ውጤቱ የዜሮዎች ድምር ዜሮ የሆነውን የምርጫ ድራማ ተውኔትና ውርደታቸውን ሲያሳዩ በአንጻሩ ህዝብ እየተፈናቀለ እያዩ እንዳላዩ በመሆን ለማስመሰያ ጭዋታ የሀገሪቱን ንብረትና ሀብት ያባክናሉ።

ይህን ሁሉ ፈተና አልፎና ተገድዶ የሄደው ህዝብም ቢሆን ያገኘውን እድል በመጠቀም ወያኔዎችን ውረዱ፣ በቃችሁ፣ወንጀለኞች ናችሁ፣ የፖለቲካና የሃይማኖት እስረኞችን ፍቱ እና ሌሎችንም የወያኔ ባዶነትን ለመግለጽ ባዶ ወረቀቶችን በመስጠት ጥላቻቸውን በድጋሜ አረጋግጠውላቸዋል። ግንቦት 7 ህዝቡ ያሳየውን እምባይነት እያደነቀ ነገር ግን የወያኔዎችን ጭቆና ተቋቁሞ ትግሉን ከዚህም በላይ በመውሰድ በየአካባቢው በማፋፋም መቀጠልና ነጻ አውጪዎችን ሳይጠብቅ በራሱ ጎበዝ አለቃዎች በመደራጀት አልገዛም ባይነቱን እንዲቀጥል ጥሪውን በዚህ አጋጣሚ ማስተላለፍ ይወዳል።

ንቅናቂያችን ዛሬም ትክክለኛና ህዝብ በነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ተሳትፎ የሚመርጠው አካል፣ እንዲሁም ለህዝብ ተጠያቂ የሆነና ህዝብን የሚፈራ መንግስት፣ በህዝብ የሚሾም፣ የሚሻር አካል ለመፍጠር በቅድሚያ ወያኔን በማስወገድ ብቻ ነው ብሎ ያምናል።

ነጻነትን ለማግኘት ዝም ብለን ስለተመኘነው የሚመጣ አይደለም፣ ዝም ብሎም በራሱ ታምር ሆኖ አይከሰትም፤ ሁሉም ዜጎች ከወያኔ የምርጫ ማጭበርበሪያ ካርድ ወጥተው ተደራጅተውና አደራጅተው በተናጥልም ሆነ በቡድን ወያኔን አስወግዶ በሀገራችን ሁሉም ዜጎች በእኩልነት ተከብረው የሁሉም መሰረታዊ መብቶች ባለቤት ሲሆኑ ነው።

ይህ የሚሆነው ደግሞ ወያኔ እንደ ምጽዋት እስጣችኋለሁ በሚለው መንገድ ሳይሆን ፣ ብቸኛው ምርጫ በሆነው ነጻነታችንን ለማስከበርና የሀገራችንን ህልውና ለመታደግ ማናቸውንም አይነት የትግል ስልቶችን ተጠቅመን ደማችንን አፍሰን አጥንታችንንም ከስክሰን በሚከፈል ዋጋ መሆኑን አምነን ትግሉን በማፋፋም በመሆኑ በተለይም ወጣቶች ትግሉን እንድትቀላቀሉን ጥሪያችን ይድረሳቹሁ እንላለን።

በዚህም አጋጣሚ ግንቦት 7 ለወያኔ አባላት የሚያስተላልፈው መልእክት በፍላጎታችሁ እና በምርጫችሁ የመስራትና የመኖር ሰብአዊ ነጻነታችሁ በወያኔ የፖለቲካ ፓርቲ አሽከር አደግዳጊና ጉዳይ ፈጻሚ በመሆን ብቻ የምታገኙት እርጥባን ሳይሆን በዜግነታችሁና በሰውነታችሁ የተሰጣችሁ መብት በመሆኑ ከፍርሃት ወጥታችሁ ንጹህ ህሊናን ተጥቅማችሁ ወያኔን በማስወገድ በሚደረገው ህዝባዊ ትግል ውስጥ ጊዜው ሳይይረፍድ ከታጋይ ሀይሎች ጋር በመቀላቀል የበኩላችሁን አስተዋጽኦ በማድረግ ኢትዮጵያዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

Thursday, April 25, 2013

Federal police detaining youth suspected of links with GPF

ESAT News
Federal police officers have travelled from the Capital to a town in Northern Ethiopia, Merawi, 35 KM far from Bahir Dar city, to arrest several University students whom ...they suspected of having links with the newly formed Ginbot Seven Popular Forces (GPF).

It has been confirmed that one student was severely beaten when the officers were kidnapping the students. The youth have been taken to Addis Abeba.

In a related report, ESAT has learnt that Major Mesafint Tigabu, who has been an Intelligence Official of one of the member parties of the ruling Front and also of the Ethiopian Defense Forces has joined GPF.

Major Mesafint has conducted an interview with ESAT regarding the nepotism within the Defense Forces, grievances within the Amhara National Democratic Movement (ANDM) and related issues. The full interview will be aired over the coming days.


 

የተመሰገን ደሳለኝ ጉዳይ ለግንቦት 22 ተቀጠረ

በፌደራል አቃቢ ሕግ ተቃውሞ የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የተመስገን ደሣለኝ ምክሥሮች ቃል ሳይሰማ ቀረ፡፡
ተመስገን ደሣለኝ - የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ
ተመስገን ደሣለኝ – የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ 6ኛ ወንጀል ችሎት ተከሣሽ ያቀረባቸውን ምሥክሮች ቃል ለመስማት ለግንቦት 22/2005 ዓ.ም ቀጥሯል፡፡
ፍርድ ቤቱ ቀደ
ም ሲል ባዘዘው መሠረት ምሥክሮቹ የቀረቡ ቢሆንም አቃቢ ሕግ የታዘዙለት የድምፅና የምሥል ማስረጃዎች በእጁ የገቡት “ዛሬ ስለሆነ የምሥክሮቹ ቃል መሰማት የለበትም” ሲል አቤቱታ አቅርቧል፡፡

የተከሣሽ ጠበቆች የተባለውን የድምፅና የምሥል ማስረጃ ቀደም ብለው በታዘዘው መሠረት እንዳስገቡ ገልፀው “ዘግይቷል ቢባል እንኳ የምሥክሮችን ቃል ከመስማት ሊያግድ የሚችልበት ምክንያት የለም” ሲሉ ተከራክረዋል፡፡

ምሥክሮቹ ተቃውሞ ባለማቅረባቸው ምክንያት ፍርድ ቤቱ ቃላቸውን ለመስማት ቀጠሮውን መስጠቱ ታውቋል፡፡

በቤቶች ጉዳይ አቶ ሀይለማርያም የሰጡት መልስ የፓርላማ አባላቱን አስቆጣ

ሚያዚያ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ትላንት የመንግስታቸውን የ2005 በጀት ዓመት የስምንት ወራት ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ...ከፓርላማ አባላት ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች መካከል የ40 በ 60 የተባለው የቤቶች ልማት ፕሮጀክትን አስመልክቶ የሰጡት ምላሽ ባልተለመደ መልክ የኢህአዴግ የፓርላማ አባላትን ጉምጉምታ አስከተለ፡፡

40 በ 60 የሚባለው የቤት ልማት ፕሮግራም ሕዝቡ በአንድ በኩል ቆጥቦ የቤት ባለቤት እንደሚሆን እየተነገረ በሌላ በኩል መቶ በመቶ የመክፈል አቅም ላላቸው ሰዎች ቅድሚያ ይሰጣል የመባሉን ጉዳይ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ መቶ በመቶ ለሚከፍሉ ቅድሚያ እንደሚሰጥ ማረጋገጣቸው የፓርላማ አባላቱን ጉምጉምታ አስከትሏል፡፡

 መንግስት 20 በ80 በሚባለው የኮንዶምኒየም ቤቶች የልማት ፕሮግራሙ ባለፉት ስምንት ዓመታት ጊዜያት ውስጥ ከ350 ሺ በላይ ቤት ፈላጊ በተመዘገበበት በአዲስአበባ ከተማ ብቻ 100ሺ ያህል ቤቶችን መገንባቱን አስታውሰዋል፡፡ የቤት ፍላጎቱን ለማርካት ተጨማሪ 40 በ60 በሚባል ፕሮግራም መካከለኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ለመድረስ፣10 በ90 በሚባለው ፕሮግራም ደግሞ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች የቤት ባለቤት ለማድረግ መታቀዱንና በ10 በ90 ፕሮግራም 35 ሺ ፣በ40 በ60 ወደ 10ሺ ያህል ቤቶች በአዲስአበባ ግንባታቸው መጀመሩንና በቅርቡም የቤት ፈላጊዎች ምዝገባ እንደሚካሄድ ጠቅሰዋል፡፡

 አቶ ኃ/ማርያም አያይዘውም 40 በ60 የሚባለው ፕሮግራም መካከለኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች የሚመለከት በመሆኑ መቶ በመቶ ክፍያ ለሚፈጽሙ ቅድሚያ እንደሚሰጥ ማረጋገጫ መስጠታቸው በኢህአዴግ አባላት የተሞላውን ፓርላማ
ጉምጉምታ አስነስቷል።

ለፓርላማ ቅርበት ያላቸው ምንጮች አባላቱ ያልጎመጎሙበትን ምክንያት ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ ቀደም ሲልም ፕሮግራሙን በተመለከተ ለፓርላማው ሪፖርት በቀረበበት ወቅት 40 በ60 የሚባለው ፕሮግራም መካከለኛ ገቢ ያለውን በተለይም በወርሃዊ ደመወዝ የሚተዳደረውን የህብረተሰብ ክፍል ይጠቅማል መባሉንና ነገርግን ለባለአንድ ክፍል መኝታ
ቤት 857 ብር፣ለባለሁለት መኝታ ቤት 1 ሺ 337 ብር፣ ለባለሶስት ምኝታ ቤት ደግሞ 2 ሺ133 ብር ለአምስት ተከታታይ ዓመታት በየወሩ መቆጠብ እንዳለበት መታቀዱ የመካከኛ ገቢ ያለውን የህብረተሰብ ክፍል አቅም ያገናዘበ አይደለም የሚል ቅሬታ በአባላቱ
ዘንድ በቅሬታ መልክ ተደጋግሞ ይነሳ እንደነበረ አስታውሰዋል፡፡

በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ መካከለኛ ገቢ አለው የሚባለው በተለይም የመንግስት ሰራተኞች አማካይ ወርሃዊ መካከለኛ ገቢ ከ2 ሺ 500 ብር እንደማይበልጥ ምንጫችን ጠቅሶ ከዚህ ደመወዝ ላይ ዝቅተኛውን በወር 857 ብር መቆጠብ እንዴት ይቻላል ሲል ይጠይቃል፡፡ በዚህ ምክንያት የ40 በ60 የቤት ልማት ፕሮግራም ከፍተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የሚጠቅም ነው የሚል ድምዳሜ መኖሩን ምንጫችን አስታውሶ የአቶ ኃይለማርያም ምላሽ ይህን በግልጽ ማረጋገጡ የፓርላማ አባላቱን እንዲያልጎመጉሙ ምክንያት ሆኗል ብሏል፡፡
የ40 በ60 ዓይነት የቤት ልማት ፕሮግራሞች ዓይነተኛ ዓላማ ቁጠባን ማበረታታት ነበር ያለው ምንጫችን አፈጻጸሙ ግን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ቤት ፈላጊዎች ተመዝግበው እንዲቆጥቡ የሚያበረታታ አልሆነም ሲል ያስረዳል፡፡
በተያያዘ ዜና ጠ/ሚ ኃይለማርያም የዋጋ ንረቱ ወደ 7 ነጥብ 6 በመቶ ወርዶአል፣እየተረጋጋ ነው ያሉት ግን በተግባር ያልተቀረፈውን የኑሮ ውድነት ችግር ለመቅረፍ ከውጪ አገር ሸቀጦችን ገዝቶ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያከፋፍል መንግስታዊ የሆነ ግዙፍ ኢንተርፕራይዝ በመቋቋም ላይ መሆኑን ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡
ምንጮቻንን ስለጉዳዩ እንደገለጹት በጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ አማካይነት በተደረገው ጥናት ለውጪ ኩባንያዎች ዝግ የሆነውን የሸቀጦች ችርቻሮ ንግድ ስራ ለመፍቀድ ወይ ሌሎች አማራጮችን ለማየት መሞከሩን ጠቅሶአል፡፡ ነገር ግን ትልልቆቹ ኩባንያዎች በሸቀጦች የችርቻሮ ንግድ እንዲሰማሩ ቢደረግ የአገር ውስጥ አስመጪዎች በአጭር ጊዜያት ውስጥ
ከገበያ ውጪ በማድረግ መንግስት ሊቆጣጠረው የማይችለው ገበያ ሊፈጠር ይችላል የሚል ግምት በመወሰዱ በመንግስት ቁጥጥር ስር ሆኖ ዋጋ የማረጋጋትና አነስተኛ ዋጋ ካላቸው ገበያዎች ሸቀጦችን በመግዛት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያቀርብ ኢንተርፕራይዝ እንዲቋቋም ውሳኔ ላይ ተደርሶአል፡፡

ይህም ሆኖ ግን መንግስት በገበያ ውስጥ ያለውን ድርሻ እየቀነሰ ከመምጣት ይልቅ በየሰበብ አስባቡ የግሉን ዘርፍ ስራዎች ሁሉ ተክቶ ለመስራት የሚያደርገው ጥረት እምብዛም ውጤት እንደማያመጣ ባለፉት ዓመታት በተመሳሳይ ስራ ላይ የቆዩትንና የሙስኞች መቀፍቀፊያ የሆኑትን የሸቀጦች ጅምላ ንግድና አስመጪ ድርጅት (ጅንአድ) እና የእህል ንግድ
ድርጅትን በምሳሌነት የጠቀሱ አስተያየት ሰጪዎች የመንግስትን ዕቅድ አጣጥለውታል፡፡

አስተያየት ሰጪዎች አያይዘውም መንግስት የዋጋ ንረትን የሚያባብሱት የግብርና ምርቶች መሆናቸው እየታወቀ ከውጪ የሚገቡ የፋብሪካ ምርቶች ናቸው በሚል በጠ/ሚኒስትሩ የቀረበው ሪፖርት ተጨባጭነት የጎደለው ነው ሲሉ ነቅፈውታል፡፡

ከግብርና ምርቶች መካከል አብዛኛው ሕዝብ የዕለት ምግብ የሆነው የጤፍ ምርት በአሁኑ ሰዓትም የመረጋጋት ሳይሆን የመጨመር አዝማሚያ እያሳየ መጥቶ አንድ ኩንታል ጤፍ ከ 2,000 ብር በላይ የሚጠየቅበት የሐብታሞች ምግብ ብቻ ወደመሆን መሸጋገሩን በተመለከተ በሪፖርታቸው ሳይጠቀስ መታለፉ አሳዛኝ ነው ብለውታል፡፡

አቶ ኃይለማርያም ከተሾሙ በኋላ የመጀመሪያቸው በሆነው የፓርላማ የከዚህ በፊት ውሎ ላይ የጤፍ ዋጋን መወደድ አስመልክቶ ሕብረተሰቡ የጤፍ ምርትን ከተለያዩ ሰብሎች ጋር በመደባለቅ መጠቀም ቢለምድ ዋጋው ሊረጋጋ እንደሚችል አስተያየት መስጠታቸውን ተከትሎ ለከፋ ትችት ተጋልጠው ከርመዋል፡፡ጠ/ሚኒስትሩን ለትችት የዳረጋቸው ከጥንት ጀምሮ በገጠር አካባቢዎች ሳይቀር በተለምዶ ጤፍን ከማሽላ፣ጤፍን ከበቆሎና ከመሳሰሉ እህሎች ጋር በመደባለቅ መመገብ ለኢትዮጽያዊያን አዲስ ባህል አለመሆኑ እንደነበርም ይታወሳል፡፡

Wednesday, April 24, 2013

ሰበር ፍርድቤቱ በሌለ ንብረት ላይ ውሳኔ መስጠቱ እያነጋገረ ነው

ነዋሪነታቸው ወላይታ ሶዶ የሆኑት አቶ አላሮ አላንቦ ለዝግጅት ክፍላችን ይዘው በቀረቡት ሰነድ እንደሚሉት “ከወ/ሮ አበበች ኩንቼ ጋር ተጋብተን ልጆች ወልደናል ቤት ሠርተናል፤ ንብረት አፍርተናል፡፡ ከ28 ዓመት በፊት በፍ/ቤት ተለያይተናል፡፡

 በወቅቱ በጋራ ያፈራነው ንብረታችንና ቤታችንን እንድንካፈል ተወስኗል፡፡ ያፈራነውን ንብረትም ተዘርዝሯል፡፡ ይሁን እንጂ ንብረቴ ሁለት ቦታ ተከፍሎ ከሚባክን ለልጆቼ ባለበት ሁኔታ በቀድሞ ባለቤቴ እጅ እንዲቀመጥ ወሰንኩኝ ይህንኑ በጋራ ሽማግሌዎች ተስማምተን ለእሷ አስረክቤ ከቤቴ ወጣሁኝ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ቤቱን ግማሹን ለት/ቤት አከራይታ ግማሹን በብቸኝነት ትጠቀምበታለች በጋራ ያፈራነው ንብረትም ቤት ውስጥ በእሷ እጅ ቀርቷል በፍላጎቴ የሰጠኋት በመሆኑ ቅሬታ የለኝም እኔ ልጆቼን ሰብስቤ በማገኛት ወርሃዊ ገቢ ልጆቼን አሳድጋለሁ፡፡ ዘመዶቼ በሚያደርጉልኝ ድጋፍ የግሰብ ቤት ተከራይቼ እኖራለሁ፡፡” በማለት ይዘረዝራሉ፡፡

አቶ አላሮ በመቀጠልም “እውነቱ ይህ ሆኖ ሳለ ከ28 ዓመት በኃላ በፖለቲካ አመለካከቴ እኔን ለማጥቃት የፈለጉ ግለሰቦች ባቀነባበሩት ሴራ የቀድሞ ባለቤቴ በወላይታ ሶዶ ከተማ መርካቶ ክፍለ ከተማ በ900 ካሬ ሜትር ላይ የተሰራ የጋራ መኖሪያ ቤት ስለአለኝ እንዲያካፍለኝ የሚል ክስ መሠረተች፡፡ እኔም ክሱ ደርሶኝ ለፍ/ቤቱ መልስ ሰጠሁኝ፡፡ ከ28 ዓመት በፊት መለያየታችን፤ ያፈራነው ንብረት ተዘርዝሮ በሽማግሌዎች መለያየታችንን፤ በጋራ ያፈራነው መኖሪያ ቤታችን በእሷ እጅ እንደሚገኝ፤ ከዚያ በኋላ ልጆቼን በማሳደግ ማሳለፌን፤ ቤትም ንብረትም ማፍራት አለመቻሌን በስሜ የተሰራ ቤት አለመኖሩን በመግለጽ መልስ ሰጠሁኝ፡፡

ከሳሽ የሆነችው የቀድሞ ባለቤቴም በ300 ካሬ ሜትር ላይ የተሠራውን የአጎቴን ቤት የእሱ ስለሆነ ያካፍለኝ አለች፡፡ ይህ በመጀመሪያ ካቀረበችው ክስ ጋር የማይጣጣም ቤቱም የእኔ አለመሆኑንም አስረዳሁ፡፡ ጉዳዩን የሰማው አጎቴም ጣልቃ ገብ ተከራካሪ ሆኖ በመግባት ቤቱ የእኔ አለመሆኑን ገልጾ የእሱ መሆኑን የሚያሳይ ሠነዶች በመያዝ ተከራከረ፡፡ ማዘጋጃ ቤቱ የሰጠውንም የይዞታ ባቤትነት ካርታ አቀረበ፡፡ ፍ/ቤቱም ለወላይታ ሶዶ ማዘጋጃ ቤት ደብዳቤ ጽፎ በሰሜ ቤት መኖር አለመኖሩን ጠየቀ ማዘጋጃ ቤቱም ለፍ/ቤቱ በጹሑፍ በሰጠው መልስ በአቶ አላንቦ ስም ሰጪ ቤት አለመኖሩን አረጋግጠ፡፡ ክርክሩን የተመለከተው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤቱም ክሱን ውድቅ አድርጎ በነጻ አሰናበተኝ፡፡” ሲሉ ይናገራሉ፡

በመቀጠልም “የቀድሞዋ ባለቤቴ ለከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ጠይቀች::” በማለት ሂደቱን በማስረዳት ይቀጥላሉ፡፡ “ይግባኙን የተመለከተው ከፍተኛው ፍ/ቤት የሥር ፍ/ቤትን ውሳኔ በመሻር ቤቱን እንዲያስረክባት ወሰነ፡፡ የሌለኝን ቤት ከየት አምጥቼ ብዬ ብከራከር አስረክብ! አስረክብ !! ተባልኩ፡፡ እኔም በተራዬ ለጠቅላይ ፍ/ቤቱ ይግባኝ ጠየኩኝ:: የሌለኝን ቤት አስረክብ እየተባልኩ ነው ፡፡

 የማንን ቤት ላስረክብ? ከየት አምጥቼ ልስጣት? ብዬ ተከራከርኩ፤ ጠቅላይ ፍ/ቤቱም የከፍተኛ ፍ/ቤቱን ፍርድ አጽድቆ አስረክብ አለኝ ፌዴራል ሰበር ችሎት ድረስ በይግባኝ ቀረብኩኝ ያላፈራሁትን ቤት ከየት ላምጣ? ማዘጋጃ ቤቱን በስሜ ምንም ቤት እንደሌለኝ እያረጋገጠ ፤አሁንም ቤቱን አስረክብ ተብሎ የመጨረሻ ፍርድ ተሰጠብኝ፡፡ አሁን በአፈጻጸም ለማዘጋጃ ቤቱና በቀበሌ መስተዳድሩ የቤቱ ግምት እንዲቀርብ ተጠየቀ፡፡ አሁንም ማዘጋጃ ቤቱ በስሙ ቤት ስለሌለ ግምት አውጥቼ ማቅረብ አልችልም ብሎ መልስ ሰጠ፡፡

ፍ/ቤቱ የአፈጻጸሙን ትዕዛዝ ቀይሮ አፈጻጸሙን ዳኛ እንዲያስፈጽም ፍ/ቤቱ አንድ ዳኛ መደበ የተመደቡት ዳኛ አሁን አስረክብ እያሉ እያሰቃዩኝ ነው፡፡

 እኔ ደግሞ የሌለኝን ቤት ከየት አምጥቼ ላስረክብ? ብዬ ብጠይቅ ቤቱን ካላስረከብክ ትታሰራለህ እያሉኝ ነው፡፡ የት ሄጄ አቤት እንደምል ግራ ገብቶኛል ኸረ እባካችሁ የሚሰማ የመንግስት አካል ካለ አሳውቁልኝ፡፡ ጉዳዩን አጣርቶ መፍትሔ የሚሰጥ አካልም ካለ አስውቁልኝ:: እየተፈፀመ ያለውንም ጉድ የኢትዮጵያ ህዝብ ይወቅልኝ” ሲሉ በምሬት ተናግረዋል፡፡

በቤንች ማጂ በተነሳ ግጭት ሶስት ተማሪዎች ቆሰሉ

በደቡብ ክልል በቤንች ማጂ ዞን በሚገኘው ሚዛን 2ኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤት በተነሳው ግጭት ሶስት ተማሪዎች መቁሰላቸውና ከሚያዚያ 10 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ ትምህርት መቋረጡን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ጠቆሙ ፡፡

እንደ ፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገለፃ ከሆነ ከሚያዚያ 7 ቀን 2005ዓ.ም. ጀምሮ በትምህርት ቤቱ ተማሪዎችና አስተዳደር አካላት በተነሳ አለመግባባት ከፍተኛ እረብሻ በመፈጠሩ እንደሆነ ተገልጧል፡፡ ለረብሻው መንስኤው ለትምህርት ቤቱ ከአሜሪካ በተሰጠው የትምህርት ዕድል የ12ኛ ክፍል የመሰናዶ ተማሪዎች መካከል በተደረገው ውድድር ከሴቶች ተማሪ መድኃኒት ስታሸንፍ ከወንዶች ደግሞ በጀመሪያ ተማሪ ጌታመሳይ ማሸነፉ ከተጠቆመ በኋዋላ በተደረገ የውጤት ማጣራት ሂደት ተማሪ ዮሐንስ ማለፉ መለጠፉ ነው፡፡

ይህንንም ተከትሎ በተለይ የውድድሩ አዘጋጅ ኮሚቴ በወንዶች ተማሪ ዮሐንስና ተማሪ ጌታመሳይ ውድድር ላይ የውጤት አሰራር ስህተት በመኖሩን በተማሪዎችና በትምህርት ቤቱ መምህራንና አስተዳደር አካላት መካከል በተፈጠረ አለመግባባት መማር ማስተማሩ ሂደት መቋረጡ ተጠቁሟል፡፡
በመጨረሻም በተደረገው የውጤት ማጣራት መሰረት በውድድሩ ያለፈው ተማሪ ዮሐንስ መሆኑንም ምንጮቻችን አስታውሰዋል፡፡
ከረብሻው ጋር በተያያዘ ሚያዚያ 11 ቀን 2005ዓ.ም. በትምህርት ቤቱ አካባቢ ተኩስ መከፈቱና በተፈጠረ ግጭትም 3 ተማሪዎች ቆስለው ወደ ህክምና ጣቢያ መወሰዳቸው ተረጋግጧል፡፡ ይህን ዜና እስከዘገብንበት ድረስም ትምህርት ቤቱ በፌደራል ፖሊስ መከበቡ ተጠቁሟል፡፡

ይህንንም በሚመለከት የትምህርት ቤቱ ዋና ርዕሰ መምህር የሆኑት አቶ አብዱ ካሣ ስለጉዳዩ ስናነሳላቸው አሁን ስለማልችል ከ30 ደቂቃ በኋላ መልሳችሁ ደውሉ ካሉ በኋዋላ ስልካቸውን በመዝጋታቸው ምላሻቸውን ማካተት አልቻልንም፡፡

ምክትላቸው አቶ አበራ ጉልማንም ለማናገር ጥረት ብናደርግም ስልካቸውን ጆሯችን ላይ ዘግተዋል፡፡

ፍኖተ ነጻነት

Tuesday, April 23, 2013

የወንዶ ገነት ኮሌጅ ዲን እና የኮሌጁ የፖሊስ ክፍል አዛዥ ታሰሩ

ሚያዚያ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በአዋሳ ዩኒቨርስቲ ስር የሚገኘው የወንዶገነት የደንና የተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ዲን የሆኑት ዶ/ር ጸጋየ በቀለ እና የኮሌጁ የፖሊስ ክፍል አዛዥ ሻምበል አለማየሁ ወረታ የታሰሩት የመንግስት ባለስልጣናት የኮሌጁን መሬት በመቁረጥ ለአካባቢው ተወላጅ ባለሀብት ለመስጠት የሚደረገውን እንቅስቃሴ በመቃወማቸው ነው።

 አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ዩኒቨርስቲው ባለስልጣን ለኢሳት እንደገለጹት ሁለቱም ግለሰቦች የታሰሩት የአካባቢው ባለስልጣናትየኮሌጁን መሬት በመውሰድ ለአንድ ባለሀብት ለመስጠት የሚደረገውን እንቅስቃሴ ሁለቱ ሰዎች አጥብቀው በመቃወማቸው ነው።

 ሻምበል አለማየሁም ሆኑ ዶ/ር ጸጋየ “መሬቱ የኮሌጁ በመሆኑ ፈርመን አንሰጥም” በማለታቸው ካለፈው አረብ ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኙ ሲሆኑ፣ ባለስልጣኑ እንደሚሉት ጉዳዩ ከዘር ጋር የተያያዘ ነው። ሻምበል አለማየሁ የሲዳማን ህዝብ ለመውጋት ጦር አዘጋጅተዋል የሚል ክስ የቀረበባቸው ሲሆን፣ እሳቸውን ለመያዝ ከ12 በላይ ፖሊሶች ወደ ዩኒቨርስቲው ሲገቡ መጠነኛ ረብሻ ተነስቶ እንደነበርም ለማወቅ ተችሎአል። ሻምበል አለማየሁ በተያዙበት ወቅት ” ወንጀል አልፈጸምኩም ወንጀሌ አማራ መሆኔ ብቻ ነው” በማለት ይናገሩ እንደነበር የአይን እማኞች ተናግረዋል። ወንዶገነት
በጉዳዩ ዙሪያ የአካባቢውን ባለስልጣናትን ለማነጋገር አደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

የወንዶ ገነት ኮሌጅ ዲን እና የኮሌጁ የፖሊስ ክፍል አዛዥ ታሰሩ
ሚያዚያ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በአዋሳ ዩኒቨርስቲ ስር የሚገኘው የወንዶገነት የደንና የተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ዲን የሆኑት ዶ/ር ጸጋየ በቀለ እና የኮሌጁ የፖሊስ ክፍል አዛዥ  ሻምበል አለማየሁ ወረታ የታሰሩት የመንግስት ባለስልጣናት የኮሌጁን መሬት በመቁረጥ ለአካባቢው ተወላጅ ባለሀብት ለመስጠት የሚደረገውን እንቅስቃሴ በመቃወማቸው ነው።
አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ዩኒቨርስቲው ባለስልጣን ለኢሳት እንደገለጹት ሁለቱም ግለሰቦች የታሰሩት የአካባቢው ባለስልጣናትየኮሌጁን መሬት በመውሰድ ለአንድ ባለሀብት ለመስጠት የሚደረገውን እንቅስቃሴ ሁለቱ ሰዎች አጥብቀው በመቃወማቸው ነው።
ሻምበል አለማየሁም ሆኑ ዶ/ር ጸጋየ “መሬቱ የኮሌጁ በመሆኑ ፈርመን አንሰጥም” በማለታቸው ካለፈው አረብ ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኙ ሲሆኑ፣ ባለስልጣኑ እንደሚሉት ጉዳዩ ከዘር ጋር የተያያዘ ነው። ሻምበል አለማየሁ የሲዳማን ህዝብ ለመውጋት ጦር አዘጋጅተዋል የሚል ክስ የቀረበባቸው ሲሆን፣ እሳቸውን ለመያዝ ከ12 በላይ ፖሊሶች ወደ ዩኒቨርስቲው ሲገቡ መጠነኛ ረብሻ ተነስቶ እንደነበርም ለማወቅ ተችሎአል። ሻምበል አለማየሁ በተያዙበት ወቅት ” ወንጀል አልፈጸምኩም ወንጀሌ አማራ መሆኔ ብቻ ነው” በማለት ይናገሩ እንደነበር የአይን እማኞች ተናግረዋል። ወንዶገነት
በጉዳዩ ዙሪያ የአካባቢውን ባለስልጣናትን ለማነጋገር አደረግነው ሙከራ አልተሳካም።