Wednesday, April 10, 2013

የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች ተመፅዋች ሆኑ

Written by ናፍቆት ዮሴፍ (ከፍኖተ ሰላም)
የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች ተመፅዋች  ሆኑ
“ከእነ ቤተሠቤ እዚህ ለመድረስ ያየሁትን ፈተና ፈጣሪ ያውቀዋል፡፡ ቤተሰቤ ከቁጥር ሳይጐድል ለአገሬ መሬት በቅቻለሁና ከእንግዲህ የፈለገው ይሁን” አሉኝ፤ ከቤኒሻንጉል ክልል ያሶ ወረዳ ተፈናቅለው በፍኖተ ሰላም ድንጋያማ መጠለያ ውስጥ ያገኘኋቸው አዛውንት፡፡ በአማራ ክልል የከሠላ ወረዳ ተወላጅ የኾኑት አዛውንት፤ ኑሮ አልቃና ቢላቸው በ1997 ዓ.ም ሦስት ልጆቻቸውን ከትዳር አጋራቸው ጋር ይዘው፣የትውልድ ቀያቸውን ለቀው የተሻለ ሥራ ይገኝበታል ወደ ተባሉበት ቤንሻንጉል ክልል ያቀናሉ፡፡ ኑሮአቸውንም በቤኒሻንጉል ክልል ካደረጉ በኋላ ተጨማሪ አራት ልጆችን አፍርተው የቤተሠባቸውን ቁጥር ወደ ዘጠኝ ከፍ ያደርጋሉ፡፡ ላለፉት ስምንት ዓመታት ቀን ከሌት እየሠሩም ኑሮአቸውን መምራት ይቀጥላሉ፡፡ ለዓመታት ከኖሩበት መንደር በድንገት እንዲለቁ ሲገደዱ ግራ የተጋቡት አዛውንት የስምንት ልጆች አባት በመኾናቸው ሲፈናቀሉ ከፍተኛ ውጣ ውስጥ ከተታቸው፡፡
በቀላሉ የሚሳካላቸው አልኾነም፡፡ ‹‹ ከያሶ ወረዳ ውጡ ተብለን ድብደባና እንግልት ሲደርስብን እንደ ሌሎቹ እመር ብዬ መሸሽ አልኾን አለኝ፡፡ ልጆቼንና ባለቤቴን እንዴት ላድርጋቸው? ከአንድ ቤት ዘጠኝ ሰው የትስ ነው መውደቂያችን? ስል ጭንቀት ገባኝ›› የአዛውንቱ ዐይኖች እንባ አቀረሩ፡፡ አሁን አዛውንቱ ብዙ ስቃይ አልፈው በአማራ ክልል ፍኖተ ሰላም ከተማ ከሌሎች 3500 ተፈናቃዮች ጋር ከእነ ቤተሠባቸው በችግር ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በሚኖሩበት አካባቢ የእርሻ ቦታ ባለማግኘታቸው የተሻለ ሥራ ፍለጋ ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ ኑሮአቸውን ከአማራ ክልል ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያዛወሩ የአማራ ተወላጆች ካለፉት ሦስት ሣምንታት ጀምሮ በወረዳው ባለሥልጣናትና ፖሊሶች ከቀያቸው ተፈናቅለው በምስራቅ ጎጃም በጀቢጠናን ወረዳ ፍኖተ ሰላም ከተማ በሚገኝ መጠለያ ውስጥ እንደሚገኙ በደረሰን ጥቆማ መሰረት ወደዚያው አመራን፡፡
ከመጠለያው ወዲህ ከንፈሯ ክው ብሎ ደርቋል በጥቁር መናኛ ሻሽ እራሷን ጠፍንጋ አስራዋለች፡፡ የለበሠችው ቀሚስ ዳር ዳሩ ተተልትሏል፣ የተጫማችው ላስቲክ ጫማ ብዙ ቦታ ተበሣስቷል፡፡ በጠይም መልኳ ላይ ድካምና ተስፋ መቁረጥ ይነበብባታል- በፍኖተ ሰላም ከዳሞት ሆቴል ጀርባ ከአውቶብስ መናህሪያ ዝቅ ብሎ ባለው ‹‹ፍቶተ ሠላም›› ክሊኒክ መግቢያ በር ላይ ያገኘኋት የ27 ዓመቷ ወጣት የአራት ወር ነፍሰ ጡር ናት፡፡ በጉዞዋ በደረሰባት እንግልት በመታመሟ ከመጠለያው ለህክምና ወደ ክሊኒኩ እንደመጣች ነገረችኝ፡፡ “ራሴን ያዞረኛል፣ ሰውነቴን በጠቅላላ ይቆረጥመኛል፣ ያስለኛል፣ በተለይ ሌሊት ሌሊት እንቅልፍ የለኝም” የምትለው ነፍሠ ጡሯ፤ ባደረገችው ምርመራ ደም ማነስ እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንዳጋጠማት ተነግሯታል፡፡
ባለቤቷም የታዘዘላትን መድሀኒት ሊገዛ ሄዷል፡፡ “ቀን ፀሀዩ፤ ማታ ብርዱ በዚያ ላይ ያለ ምንጣፍ ጠጠር ላይ እየተኛሁ ነው ለበሽታ የተጋለጥኩት፡፡ ከዚህ ቦታስ በሕይወት የምገኝ አይመስለኝም” አለች፡፡ ባለቤቷ ተመልሶ ሲመጣ ጨዋታው አላማረውም፡፡ ማንነቴን ጠይቆኝ ከተረዳ በኋላ፤ “እዚህ ያሉ የከተማው አስተዳደሮችና የክልሉ ኃላፊዎች አሁን ያለው ችግር እስኪፈታ ለማንም አትናገሩ ብለውናል” አለኝ፡፡ ‹‹አንዳንድ ጋዜጦች ከመካከላችሁ ያልሆነ መረጃ እየወሠዱና እየጻፉ ጋዜጣ ማሻሻጫ አድርገዋችኋል፤ ስለዚህ ዝም በሉ ተብለናል” የሚል ምላሽ ሠጠኝ፡፡ ችግሩን እንዲነግረኝ ለማግባባት ሞከርኩ፤ “ዋ! ለሠው ቢያወሩት መፍትሄ ካልመጣ ምን መላ አለው እህቴ?” በማለት መልሶ ጠየቀኝ፡፡ በእግራችን እየተጓዝን መጠለያው አካባቢ ደርሰን ነበርና ባለቤቱን ወደመጠለያው አስገብቶ አቧራማው ሜዳ ላይ ተቀምጠን ቀስ በቀስ ወደ ጨዋታ ገባን፡፡
የ31 ዓመቱ ወጣት አዲስ አበባ ውስጥ ለ12 ዓመታት በሎተሪ አዟሪነት ሠርቷል፡፡ ቤተ መንግሥት አካባቢ በሚገኘው ግቢ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ኢትዮጵያ አንድነት ት/ቤት ጐን ከአራት ጓደኞቹ ጋር ቤት ተከራይቶ ይኖር ነበር ፡፡ “አሥራ ሁለት ዓመት አዲስ አበባ ስኖር ለውጥ አጣሁ፡፡ ስለዚህ አገሬ ገብቼ ሚስት አግብቼ ወገኖቼ እንደሆኑት እሆናለሁ ብዬ ጐጃም ገባሁ” የሚለው ተፈናቃይ፤ አገሩ ከገባም በኋላ ተስፋ የሚሠጥ ነገር አልተመለከተም፡፡ ሆኖም ቤተሠቦቹ ልቡ እንዲረጋ በሚል አስቀድሜ ክሊኒክ በር ላይ ያገኘኋትን ጠይም ቆንጆ ልጅ ዳሩለት፡፡ የሙሽርነት ወጉን በአግባቡ ሳይጨርስ ሚስቱን አሣምኖ ይዟት ቤኒሻንጉል ያሶ ወረዳ ጥቅሻ ቀበሌ እንደገባ አጫወተኝ፡ ይህ የሆነው በ1999 ዓ.ም ጥቅምት ወር ላይ ነበር፡፡ ቀበሌዋ እጇን ዘርግታ እንደተቀበለችው ይናገራል፡፡ እንደ ሌሎች ያገሩ ልጆች እርሱም ከጉሙዝ ባለ መሬት ጋር ተስማምቶ ግብርናውን ቀጠለ፡፡ ባለ መሬቱ በሠጠው ቦታ ላይ ጥሩ ቤትም ሠራ፡፡
ህይወት ከአዲሶቹ ሙሽሮች ቤት በፈገግታ ገባች፡፡ ላለፉት ስድስት ዓመታት በጥሩ ሁኔታ ከተደላደለ በኋላ ልጅ ለመውለድ ከባለቤቱ ጋር ተመካክሮ ሚስት ፀነሠች፡፡ የአራት ወሩ ፅንስ ግን ዕድለኛ አልኾነም፤ መፈናቀል ተከሠተ፡፡ “አንተ ታመልጣለህ እኔ አቅመ ደካማ ነኝ፤ ከኅብረተሠቡ ጋር ልሣፈርና ልሂድ›› በማለት ባለቤቱ ቀድማው ወደ ፍኖተ ሠላም ትመጣለች፡፡ እርሱ እንዴት የለፋሁበት በቆሎና ሠሊጥ መና ይቀራል በሚል ብቻውን ጫካ ይገባል፡፡ ወደ እህሉ ክምር ሲመጣ፣ ባለ መሬቱ አሠሪው ሌሊቱን ሲወቃ አድሮ በማዳበሪያ ከቶ ያገኘዋል፡፡ “አሠሪዬ መኪና አምጥቶ የራሱ አስመስሎ የኔንም ጫነልኝ፡፡ 40 ኩንታል በቆሎ በ200 ብር ሂሣብ ሸጬ፣ ስንቄን ይዤ ድብደባና እንግልት ከበዛበት ቀበሌ ለማምለጥ ጥሻ ጥሻውን ስመጣ ሊገድሉኝ ለጥቂት አመለጥኩ›› ነበር ያለኝ፡፡
በፍኖተ ሰላም ባከል መንደር ስድስት ወይም በተለምዶ “ቄራ ሰፈር” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለድንጋይ መጥረቢያነት ሲያገለግል የቆየ ኮረት ድንጋይ የፈሰሰበት ሰፊ ሜዳ ለጠራቢዎቹ ፀሐይ መከላከያ በሚል በተሠራው አምስት ቦታ ላይ ተፈናቃዮቹ ሰፍረዋል፡፡ ወደ መጠለያው ስጠጋ ለእርዳታ ሥራ እንደመጣች የገመትኳት ዩናይትድ ኔሽን ‹‹UN›› የሚል ሰሌዳ የለጠፈች ላንድ ክሩዘር መኪና በመጠለያዎቹ ቦታዎች መሐል ለመሐል ቆማለች፡፡ አምስተኛው መጠለያ አካባቢ ሁለትና ሦስት ፖሊሶች ተመለከትኩና መጠለያው እየተጠበቀ እንደኾነ ገምቼ ራሴን ደበቅ አደረኩ፡፡ ግድግዳ አልባ መጠለያ መጠለያዎቹ በወጣቶች፣ በእናቶች፣ በህፃናትና በአዛውንቶች ተሞልተዋል፡፡ አጠቃላይ ቁጥራቸው ወደ 3500 ይገመታል፡፡ ለመኝታ አይደለም ለመቀመጫ በማይመቸው ድንጋያማ ግርግዳ አልባ ባለ ቆርቆሮ ጣሪያ መጠለያ ውስጥ ደቀቅ ያሉትን ጠጣሮች ደልድለው ጎናቸውን አሳርፈዋል፡፡ ጠንከር ያለ አቅም ያላቸው ደግሞ ራቅ ብለው በመሄድ የባህር ዛፍ ቅጠል መልምለው ለማረፊያቸው ጉዝጓዝ አመቻችተው፣ ቢያንስ ካገጠጡት ጠጠሮች ጉርባጤ ራሳቸውን ይከላከላሉ፡፡ ከዚህ ውጪ ያሉት አብዛኞቹ ግን መሬቱ ላይ ተኝተዋል፡፡ የሸራ ምንጣፍ ያነጠፉ አንዳንድ ሰዎችንም አስተውያለሁ፡፡
የቆርቆሮ ጣሪያ ብቻ ያላቸው ‹‹መጠለያ›› የሚል ስያሜ የተሰጣቸው አምስቱ ቦታዎች በመሙላታቸው ሲመሽ ሜዳው ላይ የሚተኛው ተፈናቃይ ቁጥር እንደሚጨምር ነገሩኝ፡፡ መጠለያውን በዐይኔ ቃኘሁት፡፡ አራስ ሕፃናት ያቀፉ እናቶች፤ ልጆቻቸውን ከንፋስና አቧራ ለመከላከል ይታገላሉ፡፡ ከሞቀ ቤታቸው ወጥተው በደረቅ ሜዳ ተሰጥተው ንፋስና ፀሐይ ሲፈራረቅባቸው ማየቱ መንፈስን ይረብሻል፡፡መብራት የሌለውና እና ለዛ ሁሉ ተፈናቃይ ሁለት የውሃ ቧንቧ ብቻ ባለው መጠለያ፤ እናቶች ባዶ የፕላስቲክ ውሃ መያዣዎችን አንጠልጥለው ውሃ ፍለጋ ወደ ከተማው መሀል ይሄዳሉ፡፡ ተፈናቃዮች በውሃ ችግር የተነሳ በከተማዋ መግቢያ ላይ ወደሚኘው “ላህ” የተባለ ወንዝ እየሄዱ ይታጠባሉ፡፡ ጠዋት እና ማምሻውን ከምግብ ዋስትና የሚቀርብላቸው በነፍስ ወከፍ አንድ እንጀራ በአንድ ጭልፋ ወጥ 11 ሰዓት ላይ ተበልቶ መጠናቀቅ አለበት፡፡
ከዚያ ካለፈ መብራት ስለሌለ ማግኘት አስቸጋሪ ነው፡፡ ያውም ምሳ መመገብ የለም፡፡ ፍኖተ ሠላም አቅራቢያ በምትገኘው ማንኩሳ አካባቢ በአንዲት የገጠር መንደር የተወለደ የ25 ዓመት ወጣት ነው፡፡ የነተበ ቲሸርት ለብሷል፡፡ ቁምጣው ጉልበቱን ሳይነካ ታፋው ላይ ቀርቷል፡፡ የቀኑ ፀሀይና የማታው ንፋስ መፈራረቅ ሰውነቱን ከመሬቱ አፈር ጋር አመሣስሎታል፡፡ የቤተሠቡ መሬት ተሸንሽኖ ለታላላቅ ወንድሞች ሲሠጥ ዕድሜው ገና በመሆኑ ከቤተሠቡ ጉያ አልወጣም ነበር፡፡ “መሬት ጠበበ ደካማ ቤተሠቦቼ ላይ ሸክም አልሆንም ጉልበትና ጤና እያለኝ ሊርበኝ አይገባም፤ በዚያ ላይ ዕድሜዬ ለአቅመ አዳም እየደረሠ ነው ብዬ ነበር፤ በ2000 ዓ.ም ወደ ቤኒሻንጉል የሄድኩት›› የሚለው ወጣቱ፤ በያሶ ወረዳ በብርኮ ቀበሌ ኑሮውን ካደረገ አምስት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ከጉሙዝ ገበሬ የእኩል እያረሠ ሠሊጥ እና በቆሎ እያመረተ በመሸጥ ከራሱ አልፎ ደካማ ቤተሠቦቹን መርዳትም ጀምሮ ነበር፡፡ ወጣቱ እንደሚለው የቋጠረውን ጥሪት ለመሠብሠብ እንኳን ጊዜ ያልሠጠው “የአገራችንን ለቃችሁ ውጡ” ወከባ ባዶ እጁን ፍኖተ ሠላም እንዲመጣ አስገድዶታል፡፡
“በጣም ተስፋ የቆረጥኩት እዛው እያለኹ ነው፡፡ አንድ የክልሉ ፖሊስ ስድስት ሠዓት ላይ አግኝቶኝ ከሁለት ሠዓት በኋላ ስመለስ ባገኝህ በነፍስህ ፍረድ ካለኝ በኋላ ነው›› የሚለው ወጣቱ፤ “ከምሞት ነፍሴን ይዤ ላምልጥ በሚል የምቀይረው ልብስ ሳልይዝ 350 ብር ከፍዬ ወደ ፍኖተ ሠላም መጥቼ መሠሎቼን ተቀላቅያለኹ፡፡ እኔ ጉልበት ኖሮኝ አመለጥኩ፤ እዛው የቀሩት ናቸው የሚያሳዝኑኝ” ይላል፡፡ ተፈናቃዩ ጨርቄን ማቄን ያለ፣ ንብረት እና ቤተሰቡን ለመሠብሠብ የተፍጨረጨረ በድብደባ ለስብራትና ለቁስለት መዳረጉን ይናገራል፡፡ ኢትዮጵያዊያን እናቶች የመውለጃ ወራቸው ከመግባቱ ቀደም ብሎ እንደየ አቅምና ፍላጐታቸው የገንፎ፣የአጥሚት እህሉ፣ የህፃኑ ልብስና መታቀፊያ ይዘጋጃል፡፡ እናት ምጥ ስትያዝ በቤተሰብ በወዳጅ ዘመድ ትከበባለች፡፡ ሁሉም ጭንቀቷን ይጋራል፡፡ ተፈናቃዮቹ እናቶች ግን ይህ ዕድል ተነፍጓቸው በጠጠራማውና ገመናን በማይሸፍነው ሜዳ ላይ በስቃይ ልጅ እየተገላገሉ ነው፡፡ በዚህ ዐሥር ቀናት ውስጥ እንኳን አራት እናቶች በመጠለያው መውለዳቸው ተነገረኝ፡፡ አንጀት የሚጠግን ምግብ፣ ጐን የሚያሞቅ የረባ ልብስ ለማግኘት አልታደሉም፡፡ እነዚህን አራስ እናቶች ከ3500 ተፈናቃይ መካከል ለመለየት ብቸገርም የዐይን እማኞች ጠቁመውኛል፡፡
ከቤኒሻንጉል ሲባረሩ አራስ የነበሩ ወላጆችም በመጠለያው ይገኛሉ፡፡ ለነፍስ ያሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ክርስትና ያልተነሱ ሕፃናትን ለይተው ክርስትና ሲያስነሱና ሲያጽናኗቸው እንደነበርም ነግረውኛል፡፡ በ17 ዓመት ወጣት ጀርባ ላይ የታዘለው በዐይን ግምት ሁለት ዓመት የሚኾነው ሕፃን አፍንጫው ተገባብጦ ቆስሏል፡፡ ወንድሜ ነው ያለችኝን ሕፃኑን ያዘለችውን ወጣት ምን ኾኖ አፍንጫው እንደቆሰለ ጠየቅኳት “የምንተኛበት መሬት ደንጊያ ስለሚበዛው ሲንፈራገጥ ልጦት ነው” አለችኝ፡፡ ድንጋዩ እንኳን ለሕፃን ለዐዋቂም እንደሚያስቸግር አስተውያለሁ፡፡ ከዛሬ ስምንትና ዘጠኝ ዓመታት በፊት ከአማራ ክልል ከተለያዩ ቦታዎች የተሻለ ሕይወት ለመኖር እና እየተባባሠ በመጣው የእርሻ መሬት እጦት የተነሳ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከማይዞን ያሶ ወረዳ ሀሎ ጥቅሻ፣ ሆኒ፣ ሊጐ፣ ባብርኮ፣ ሻብቲ፣ ድልድል፣ ቲኒጆ መጢና ሌሎችም ቀበሌዎች ኑሯቸውን አደረጉ፡፡ አብዛኛዎቹ በአካባቢው ካሉ የጉሙዝ ተወላጆች ጋር በመስማማትና መሬታቸውን የእኩል በማረስ ጥሪት መቋጠርና የጉሙዝ ተወላጆችንም ሕይወት መቀየራቸውን በአፅንኦት ይናገራሉ፡፡
ጥቂቶች ደግሞ በያሶ ከተማ ንግድ ፈቃድ በማውጣት የንግድ ሥራ ማንቀሣቀስና በሕጋዊ መንገድ ለመንግሥት ግብር እየከፈሉ መኖራቸው ቀጥለው ነበር፡፡ በየዓመቱ በአካባቢው ባለሥልጣናት ውጡ እየተባሉ በስጋት ሲናጡ ይቆዩና ተመልሠው መሥራት እንደሚጀምሩ የሚናገሩት ተፈናቃዮቹ፤ አብዛኛው ገበሬ ከጉሙዝ ተወላጆች ጋር ተዋዶና ተስማምቶ፣ ጥሪት አፍርቶ ወልዶና ከብዶ ይኖር ነበር፡፡ የዘንድሮው የ “ውጡሉን” ጥያቄ ግን በጥያቄ ብቻ አላበቃም፡፡ እንደ ተፈናቃዮቹ ገለፃ ያለ ማስጠንቀቂያ ንብረትና ቤተሠብ ሳይሠበስቡ እየተደበደቡና እየተንገላቱ አካባቢውን እንደለቀቁ ይናገራሉ፡፡ ከአካባቢው ጉልበት ያለው እየሮጠ፣ አቅመ ደካማው እየተደበደበ፤ እየወደቀና እየተነሳ መውጣት የቻለው ወጥቷል፡፡ የወረዳው አመራሮች መኪኖች እየጫኑ እዲያደርሷቸው ለሹፌሮች ትዕዛዝ ሲያስተላልፉ፣ ሹፌሮችም አጋጣሚውን በመጠቀም በ300 ብር የሚሔደውን መንገድ ከ350 እስከ 400 ብር እያስከፈሉ፣ የሕዝቡን እንግልት ቢያባብሱትም ዕድለኛ የሚባሉት ነፍሳቸውን ይዘው በፍኖተ ሠላም ከተማ በአንድ የደረቀ መሬት ላይ በብርድና በፀሀይ እየተቆሉ ይገኛሉ፡፡
ተፈናቃዮቹ እንደሚሉት፤ ከባህርዳርና ከየወረዳቸው ኃላፊዎች መጥተው ስብሰባ እና ፍሬአልባ ውይይት እንደሚያደርጉ ይናገራሉ፡፡ “በየጐጣችን ያሉ የወረዳው ኃላፊዎች ለችግሩ መፍትሔ እስኪገኝ ወደየቤተሰባችን እንድንገባ ይነግሩናል” ያሉት ተፈናቃዮቹ፤ “እኛ ቤተሰብ አፍርተን እንዴት ደካማ ቤተሰቦቻችን ላይ ሄደን ሸክም እንሆናለን” የሚል ጥያቄ ለኃላፊዎች ሲያነሱ “እኛ ከክልሉ ታዘን እንጂ እንኳን እናንተን አንድ በሽተኛ የሚያስጠጋ እንኳን ቦታ የለንም” የሚል ምላሽ ማግኘታቸውን በመጠለያው ያሉት ተፈናቃዮች ይገልጻሉ፡፡
በድንጋጤና በወከባ ምንም ሳይዙ በመፈናቀላቸው ወደየትውልድ ቀያቸው ቢመለሱ የሚልሱት የሚቀምሱት እንደሌለ በስብሰባው ላይ ለኃላፊዎቹ ሲናገሩ “እንደምንም ተጠጋግታችሁ ተቀመጡ፤ ምንም ልንረዳችሁ አንችልም” ይሉናል፤ በዚህ አይነት ባዶ ሜዳ ላይ ከሚወድቁ እዚሁ ሜዳ ላይ መንግሥት የፈለገውን ያድርገን በሚል ወዴትም የመሄድ ፍላጐት እንደሌላቸው ይናገራሉ፡፡ “እኛ ከቤኒሻንጉል ስንባረር የክልሉ ተወላጅ ባለመሬቶች ስብሰባ እየተቀመጡ ከወረዳው ባለስልጣናት ጋር ሲሟገቱልን ከርመዋል” የሚለው አንድ ተፈናቃይ፤ “እኛ ምን መብላት እንዳለብንና እንደሌለብን እንድንለይ ያደረጉን እነዚህ ገበሬዎች ናቸው አርሰውና አምርተው ከሚሰጡን ምርት ሚስቶቻችንን ከእንብርክክ የድንጋይ ወፍጮ አውጥተን ዘመናዊ ወፍጮ እስከመትከል እና ባለሀብት እንድንሆን አድርገውናል” ብለው ለያሶ ወረዳ ኃላፊዎች ይነግሩላቸው እንደነበር ተፈናቃዮቹ ይናገራሉ፡፡
የጉምዝ ገበሬዎችን ሰብስበው “እነዚህ ስደተኞች መጀመሪያ ሲገቡ አባባ ይሏችሁ ነበር፣ ከዚያ አቶ እገሌ ማለት ቀጠሉ፣ አሁን ስማችሁን ብቻ ነው የሚጠሩት፣ ነገ ደብድበውና መሬታችሁን ቀምተው፣ ክብራችሁን አዋርደው የቀን ሠራተኛ ያደርጓችኋል፡፡ እነሱ ከመጡ ብዙ ሃብትና ንብረት አፍርተዋል፣ እናንተን እያሰነፉ ራሣቸው ሃብታም እየሆኑ ነው፤ ስለዚህ በአፋጣኝ መውጣት አለባቸው” እያሉ ሊያሳምኗቸው ቢሞክሩም የጉሙዝ ገበሬዎች ከእኛ መነጠሉን አልወደዱትም፤ እየተደበደብን ንብረታችን የትም ተበትኖ ሲቀር እያለቀሱ ሽኝተውናል” ነበር ያለኝ አንዱ ተፈናቃይ፡፡ ተፈናቃዮቹ ወደ ፍኖተ ሠላም ከገቡ ወደ ሦስት ሳምንት እየተጠጋቸው ሲሆን ገና እንደመጡ ያሳረፏቸው ሌላ ቦታ ነበር ፡፡
በዚህም የከተማው ሰውና የሚመለከተው አካል የማያያቸው ቦታ በመሆኑ ከተፈናቃዮቹ ወጣት ወጣቶችና በትምህርታቸው ትንሽ የገፉት ስደተኞችን በማስተባበር መጀመሪያ ካሉበት ቦታ ዋናውን አስፋልት መሃል ለመሃል ይዘው ግር ብለው ወደ አደባባዩ ሲወጡ የከተማው ሕዝብ ግልብጥ ብሎ ወጣ፡፡ ከዚያም የከተማው ኃላፊዎች አሁን ያሉበትን ቦታ እንደሰጧቸውና፣ አሁን ያሉበት ቦታ በፊት ከነበሩበት የሚሻለው ከተማው ውስጥ በመሆኑ የአካባቢው ሰው ለህፃናቱ ውሃም ዳቦም እንዲያቀብላቸው ረድቷቸዋል፡፡ የአካባቢው አርሶ አደር ወደ 15 ኩንታል የሚጠጋ በቆሎ ከማቀጣጠያ እንጨት ጋር ይዞ በመምጣት እየቆላ እንዲመገባቸው ይናገራሉ፡፡ በቄስ መሪነትም ወደ 200 የሚጠጋ እንጀራ ይዘው የደከሙትን እንዲመገቡላቸው ይገልፃሉ፡፡ እንደ ተፈናቃዮቹ ገለፃ በየዕለቱ ለስብሰባ ነው፡፡ መፍትሔ ግን የለም፡፡ ሰው በችጋርና በህመም እየተሰቃየ ይገኛል፡፡ ቀይ መስቀል አልፎ አልፎ ህክምና ቢሰጥም በቂ አለመሆኑን ነግረውኛል፡፡ አንዲት እናት “በቀን ሁለት ጊዜ ለሚሰጡን ብናኝ እንጀራ 50 ዐይነት ካሜራ እተየደቀነ እንቀረጣለን” ብለው አማረዋል፡፡
እኔ በስፍራው በደረስኩበት ዕለት ከአምስቱ በአንዱ መጠለያ ባለው ሜዳ ላይ ሕዝቡ ጨረቃ መስሎ ተሰብስቦ ነበር፡፡ ነፍሰጡሯ እንደነገረችኝ፤ ከቤኒሻንጉል በመጡት ስደኞች ሰበብ በየቦታው ስደት ሄደው የነበሩ ሁሉ ከእነሱ ጋር ያሰፍሩናል በሚል እየተቀላቀሉ በመሆናቸው፤ አሁን የየወረዳውና የክልል ሃላፊዎች እንለያለን በሚል መታወቂያ እየሰበሰቡ እንደነበር አጫውታኛለች፡፡ መንግሥትን ፍለጋ ተፈናቃዮቹ ከመጡ ሁለት ሳምንት አልፎ ሦስተኛውን ጀምረዋል፡፡ በየጊዜው የየወረዳውና የየ ክልሉ “በአማራ ሰንዲ ወንበርማ በተባለ አካባቢ ቤንሻንጉሎች ሰፍረው በሰላም እየኖሩ ነው፡፡ የእነርሱ ክልል ሃላፊዎች እኛን ጠልተው በግፍ ካባረሩን እነሱ ይውጡና ቦታውን እኛ እንስፈርበት የሚል ጥያቄ ለሃላፊዎቹ አንስተን ነበር” የሚለው አንድ ተፈናቃይ፤ “ይሄ የብሔር ግጭት ስለሚያመጣ እንዲህ ዓይነት ጥያቄ ማንሳት አስፈላጊ አይደለም፤ በድጋሚም እንዳታነሱ” በሚል እንዳስጠነቀቋቸው፤ ይገልፃል፡፡
አያይዞም ከዚህ በኋላ የተሻለ መፍትሔ ለማግኘት እስከ 12ኛ ክፍል የተማሩና የተሻለ ብቃት አላቸው ያሏቸውን በመምረጥ ኮሚቴ ማቋቋማቸውን ይናገራል፡፡ በኮሚቴው አማካኝነት ከተፈናቃዩ በነፍስ ወከፍ አምስት ብር ተዋጥቶ ሃያ ሺህ ብር እንደተሰበሰበ የሚናገረው የኮሚቴው አንድ አባል፤ ይህ ሃያ ሺህ ብር በተፈናቃዩ ለተወከሉ ሰዎች ተሰጥቶ መብታቸውን ለማስከበር ለሚደረግ የትኛውም እንቅስቃሴ ሥራ ማስኬጃ ይሆናል ሲል ነበር ያጫወተኝ፡፡ “ ጉዳያችን በየወረዳችን እና በክልሉ መንግሥት እልባት ስላላገኘ፣ የመጀመሪያ ሥራችን ተፈናቃዩን ወክለን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ ጽ/ቤት ለመሄድ ዝግጅት ጨርሰናል” ይላል ወጣቱ ተፈናቃይ፡፡ ሃያ ሺህ ብሩም ለዚሁ እንቅስቃሴ የሚውል ነው፡፡ ከመጠለያው ወጥቼ ኳስ ሜዳውን መሃል ለመሀል ሰንጥቄ ወደመጣሁበት ስመለስ አንድ መልከ መልካም ጐልማሣ ከበረዶ የነጣ ጋቢያቸውን ደርበው፣ ከአንድ ወጣት ጋር ሜዳው ላይ ተቀምጠዋል፡፡
ጥሩ ወዘና ያላቸው በመሆኑ ተፈናቃይ አይመስሉም፡፡ ግምቴም ትክክል ነበር፡፡ ሠላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ስለ ስደተኞቹ አንስቼ መጨዋወት ጀመርን፡፡ “እኔ 58 ዓመት ሙሉ ስኖር የሰው ልጅ እንዲህ ያለ ፈተና ሲቀበል ሳይ የ”በኸሬ” ነው (በአካባቢው አነጋገር የበኸሬ ማለት የመጀመሪያዬ እንደማለት ነው) አሉኝ የአካባቢው ነዋሪ፡፡ “ሰሞኑን አራት ሴቶች እዚህ የምታይው ሜዳ ላይ (መጠለያውን ማለታቸው ነው) ሲወልዱ ስመለከት መፈጠሬን ጠላሁ” በማለት የችግሩን አስከፊነት አስረዱኝ፡፡ ወገን ሲንገላታ ማየት ምን ያህል እንደሚከብድ የተናገሩት የዛው መንደር (የባከል) ነዋሪው ጐልማሳ፤ የተፈናቃዮቹን ችግር ለመስማት “ላህ” የተባለ ወንዝ ሲሄዱ አብረው ሄደው ችግሮቻቸውን እንደሚያዳምጡም አጫውተውኛል፡፡
ምንም እንኳ የእኚህ ሰው ቤት ከመጠለያው ፊት ለፊት ኳስ ሜዳው እንዳለቀ የሚገኝ ቢሆንም ወደ መጠለያው ለመግባት አይደፍሩም፡፡ “ጆሮ ጠቢውና አዋሻኪው ማንና የት እንደሆነ አይታወቅም፤ ከእነሱ ጋር ለመጨዋወት ላህ ወንዝ ነው የምሄደው” በማለት ስጋታቸውን ነግረውኛል፡፡ በዛን ሰዓት ሜዳ ላይ ለምን እንደተቀመጡም ጠይቄያቸው ነበር፡፡ “ይሄ ሁሉ ሰው ሜዳ ላይ እንደጥሬ ፈሶ እንዴት በጊዜ እቤቴ እገባለሁ” የሚሉት እኚሁ የመንደሩ ነዋሪ፤ ሁኔታውን ለመቃኘትና የሰዎችን ሁኔታ ለመታዘብ ሁሌም በዚያ ሰዓት እዛ ቦታ እንደሚቀመጡ ነገሩኝ፡፡ በመጨረሻም “ለመሆኑ አንቺስ ከተፈናቃዮቹ ወገን ነሽ” የሚል ጥያቄ አነሱ፡፡ ለአካባቢው እንግዳ መሆኔን ነግሬያቸው ተሰናበትኳቸው፡፡

World Bank Must End its Support for Human Rights Abuses in Ethiopia

 A multi-billion dollar aid program administered by the World Bank is underwriting systematic human rights abuses in Ethiopia. Last September, Ethiopian victims submitted a complaint about the program to the World Bank Inspection Panel, which is tasked with investigating whether or not the Bank complies with its own policies to prevent social and environmental harm. A meeting of the Bank’s board of directors to discuss the Panel’s preliminary findings was postponed on March 19th due to objections from the Ethiopian government.

Ethiopia is one the largest aid recipients in the world,    receiving approximately US$3 billion annually from external donors. The largest aid program, financed by the World Bank, the UK, the European Commission and other Western governments, is called Promotion of Basic Services (PBS). It aims to expand access to services in five sectors: education, health, agriculture, water supply and sanitation, and rural roads. The PBS program objectives are indisputably laudable and aim to meet a number of dire needs of the Ethiopian population. There is evidence, however, that it is contributing to a government campaign to forcibly resettle an estimated 1.5 million people.

In the lowland region of Gambella, the government’s principle means of delivering basic services is through the implementation of the “Villagization Program”. The government claims that “villagization” is a voluntary process, which aims to “bring socioeconomic and cultural transformation of the people” through the resettlement of “scattered” families into new villages. The services and facilities supported by PBS are precisely the services and facilities that are supposed to be provided at new settlement sites under the Villagization Program.

However, Gambellans, now amassing in refugee camps in Kenya and South Sudan, report that the program has been far from voluntary. When I visited the camps last fall, the refugees reported a process involving intimidation, beatings, arbitrary arrest and detention, torture in military custody and extra-judicial killing. Dispossessed of their fertile ancestral lands and displaced from their livelihoods, Gambella’s indigenous communities have been forced into villages with few of the promised basic services and little access to food or land suitable for farming. Meanwhile, many of the areas from which people have been forcibly removed have been awarded to domestic and foreign investors for large-scale agro-industrial plantations.

In September, Human Rights Watch and my organization, Inclusive Development International, arranged a meeting with the World Bank and five newly arrived refugees in Nairobi. One by one, they gave chilling testimony of the abuses that they and their families have experienced under the Villagization Program. Their testimony corroborated detailed reports about the program by Human Rights Watch and the Oakland Institute.

Yet, despite these credible reports and first-hand accounts that Bank staff heard in Nairobi, the Bank has continued to deny the forcible nature of villagization. The Bank also insists that its project is not linked to the Villagization Program, despite its acknowledgement that it finances the salaries of public servants who are tasked with implementing villagization. These arguments are wholly disingenuous. Donors must accept responsibility for human rights abuses they help make possible and do everything in their power to prevent them. There are ways the Bank can support critical investments in human development while ensuring that it is not underwriting human rights violations. It could, for example, require that the Villagization Program comply with its safeguard policy on resettlement as a condition of its $600 million concessional loan for the latest phase of PBS. If this policy were applied, the government would have to ensure, and the Bank would have to verify, that resettlement is truly voluntary and that the program improves people’s lives.

Yet the Bank and bi-lateral donors have instead chosen a strategy of denial. They have invested too much for too long in Ethiopia to admit that things have gone horribly wrong, and they are too worried about upsetting a critical military ally in a volatile part of the world to start attaching human rights conditions to aid packages.

That is why the World Bank Inspection Panel is so important. After undertaking a preliminary assessment, the Panel determined that the link between PBS and villagization was plausible and it recommended to the Board a full investigation in order to make definitive findings. However, Ethiopia’s representative on the Board has stymied approval of the investigation. A meeting to discuss the Panel’s report scheduled on March 19 was postponed due to resistance from the Ethiopian government, which is vying to set the terms of the investigation.

 The Inspection Panel was established as an independent body that people harmed by World Bank lending practices can access in order to hold the Bank to account. Bank managers and member states are not supposed to interfere in the process. The Bank’s president, Jim Yong Kim, should stand up for accountability and tell the Board to let the Panel do its job. The truth that will come out of this investigation may be inconvenient for the Bank and an important client government, but it will be a rare measure of justice for the Ethiopian people

 Ethiomedia.

የኢትዮጵያና የኤርትራ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ውይይት ተጀመረ

ሚድያ የመሪነቱን ሚና እንዲጫወት ተጠየቀ
በድንበር ግጭቱ ምክንያት የሁለቱም አገሮች መንግሥታት ግንኙነት እስካሁን ሰላምም ሆነ ጦርነት በሌለበት ሁኔታ ያሉ ቢሆንም፣ ከመንግሥታቱ ውጪ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ ለማደስ ይፋዊ ውይይት ተጀመረ፡፡
የኢትዮጵያ ሰላምና ልማት ዓለም አቀፍ ኢንስቲትዩት አስተባባሪነት ባለፈው ቅዳሜ በሒልተን ሆቴል በተዘጋጀው ስብሰባ ስድስት መነሻ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን፣ በኢትዮጵያ በስደት ላይ የሚገኙና በአብዛኛው በዩኒቨርሲቲዎች የመማር ዕድል ያገኙ የኤርትራ ወጣቶች፣ እንዲሁም ደግሞ ከተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት የተወከሉ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል፡፡

በተለይ ኤርትራውያን ወጣቶች በኤርትራ መንግሥት ሚዲያ ሲነገራቸው የቆየው ፀረ ኢትዮጵያዊነት አስተሳሰብ ቢሆንም፣ ወደ ኢትዮጵያ በስንት መከራ ተሻግረው በስደት የሚገኙት ግን ከየትኛውም አገር ከሚገኙት ኤርትራውያን የተሻለ መሆኑንና በሁለተኛ ቤታቸው ያሉ መስሎ እንደሚሰማቸው ተናግረዋል፡፡ በኤርትራ መንግሥት ሲነገራቸው የቆየው የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ ውሸት መሆኑን፣ በኤርትራም ሆነ በሌላ አካባቢ ያሉ ኤርትራውያን ዜጎችን በማስገንዘብ ላይ እንደሚገኙ አክለው ገልጸዋል፡፡ ‹‹የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ እንዲሳካ በኤርትራ ላሉት ዜጎችስ ምን ሊፈይድ ይችላል?›› በሚል ጥያቄ ያቀረቡም ነበሩ፡፡

ከሁለቱም ወገኖች የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ እንዴት መጠናከር እንዳለበት ሐሳቦች ቀርበው፣ የመድረኩ መሪ የቀድሞው የአዲስ አበባ ከንቲባ አምባሳደር ብርሃነ ደሬሳ፣ በተለያዩ አገሮች ከኢትዮጵያና ከኤርትራ በባሰ ሁኔታ በደም የተቃቡ ሕዝቦች ይቅር ተባብለው ተቀራርበው በመሥራት ላይ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱን ለማደስ የመንግሥትም የግሉ ሚዲያም ግንባር ቀደም ሚና እንዲጫወቱ ሐሳብ ቀርቧል፡፡

በኢትዮጵያ በኩል ወጣት ሰለሃዲን እሸቱ ስለ ወጣቶች ዕይታ፣ አቶ ፀጋልዑል ወልደ ኪዳን የሕይወት ተሞክሮአቸውን፣ ወጣት መርከብ ነጋሽ (ከጅማ ዩኒቨርሲቲ) ስለሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ዲፕሎማሲ ምንነት ጥናት ሲያቀርቡ፣ በኤርትራ በኩል በአዲስ አበባ የኤርትራ ስደተኞች ተወካይ ወ/ሮ ሳሊሃ ኢብራሒም የሕይወት ተሞክሯቸውን፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሳምሶን ይሳክ የኤርትራ ወጣቶች ዕይታን በተመለከተ ጥናት አቅርበዋል፡፡ እንዲሁም የሪፖርተር ጋዜጣ የፖለቲካ ዓምድ ጋዜጠኛ የማነ ናግሽ የኢትዮ ኤርትራ ሕዝቦችን ግንኙነት ለማደስ የመገናኛ ብዙኃን ሚና ምን መሆን እንዳለበት በተመለከተ ጥናት አቅርቧል፡፡

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ለካድሬዎች የግል መረጃቸውን እንዲሰጡ እየተገደዱ ነው


images.jpgDSvgsgwg
 
የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች፣የፖሊስ አባላትና ደንብ አስከባሪዎች ቤት ለቤት በመዘዋወር የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የግል መረጃቸውን እንዲሰጡ በማስገደድ ላይ መሆናቸው ታወቀ፡፡

የቤት ለቤት ምዝገባው ወቅት የሚሰበሰበው መረጃ የነዋሪው የትምህትር ደረጃ፣ ሃይማኖትና የስራ አይነት የሚያጠቃልል ነው፡፡

የፍኖተ ነፃነት የመረጃ ምንጮች እንዳስታወቁት የመረጃ ስብሰባው በምርጫ የሚሳተፈውንና የማይሳተፈውን ለመለየትና መንግስት በቅርቡ የቤቱ ሊጀምረው ላሰበው የአንድ ለአምስት ፖለቲካዊ አደረጃጀት የሚረዳውን መረጃ ለማሰባሰብ ነው፡፡

በአንዳንድ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች “ያከራያችኋቸውን ግለሰቦች ስም፣የትምህርት ደረጃና ሃይማኖት ማረጋገጥ አለባችሁ” የሚል ትዕዛዝ እንደተሰጣቸው ለምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ጨምረው እንደገለፁት ሙስሊም ነዋሪዎች በብዛት በሚገኙባቸው አካባቢዎች የተጠናከረ የመረጃ ስብሰባ እየተደረገነው፡፡

ፍኖተ ነፃነት

ESAT Daily News Amsterdam April 09 2013 Ethiopia


በቅድስት ስላሴ በይፋ ትምህርት እንዲቋረጥ ተደረገ

img_4680
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ስላሴ ኮሌጅ ከመጋቢት 30 ቀን 2005ዓ.ም. ጀምሮ መቋረጡን የሚገልፅ ማስታወቂያ በኮሌጁ ግቢ ውስጥ መለጠፉ ተገለፀ፡፡ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች እንዳረጋገጡት ከሆነ ከመጋቢት 30 ቀን 2005ዓ.ም. ጀምሮ ትምህርት መቋረጡን የሚገልፅ ማስተወቂያው በይፋ በኮሌጁ ግቢ ውስጥ የተለጠፈ ሲሆን ማን እንደለጠፈው የሚያረጋግጥ የኃላፊ ስም አለመኖሩም ተጠቁሟል፡፡

የትምህርቱን ሟረጥ ማስታወቂያ የግቢው አስተዳደር አካላት እንደማያውቁት የተገለፀ ሲሆን የኮሌጁ ምክትል አስተዳደር ዲን የሆኑት ዶ/ር አባ ኃይለማርያምም ጉዳዩን ስለማያውቁት በክፍል ውስጥ ገብተው ማስተማራቸው ታውቋል፡፡ የኮሌጁ ትምህርት የተቋረጠበትን ምክንያት ለማጣራት ወደ ቤተክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ወደ ሆኑት ብፁ አቡነ ህዝቄል ጋር ብንደውልም ስብሰባ ላይ ነኝ የሚል መልስ ሰጥተውናል፡፡ በኮሌጁ ከማጋቢት 2 ቀን 2005ዓ.ም. ጀምሮ ተማሪዎች ባነሱት ጥያቄ የምግብ አድማ ማድረጋቸውን ተከትሎ የተቋረጠው ትምህርት ከ2 ሳምንታት በኋላ ከምግቡ በቀር ትምህርቱ ቢጀመርም ተማሪዎቹም ሆኑ አብዛኛው የአስተዳደር አካላት ሳያውቁ በተለጠፈ ማስታወቂያ ትምህርት መቋረጡ ተጠቁሟል፡፡

ፍኖተ ነፃነት

Monday, April 8, 2013

የፍትህ ጋዜጣ አሳታሚ እና የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ከመንግስት ሸሽተው ተሰደዱ!

Araya na mastwalየፍትህ ጋዜጣ አሳታሚ የሆነችው ማስተዋል የህትመት ስራ ድርጅት ስራ አስኪያጅ የነበረው ማስተዋል ብርሃኑ እና የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር እና የፍትህ ጋዜጣ ድረ ገጽ አዘጋጅ የሆነው አርአያ ጌታቸው መንግስትን ሸሽተው ከሀገር ተሰደዱ!
ማስተዋል ብርሃኑ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የሚያዘጋጃት ፍትህ ጋዜጣ አሳታሚ የነበረ ሲሆን በተለይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት በኋላ ፍትህ፤ ”ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሞቱስ ለምን ሞቱ ትላለች…” ተብላ ከሰላሳ ሺህ ኮፒ በላይ እንድትቃጠል ቢደረግም መንግስታችን በቅጡ ስላልተደሰተ በአዘጋጁ ተመስገን እና በአሳታሚው ማስተዋል ብርሃኑ ላይ ክስ መመስረቱ ይታወቃል፡፡ (የማይታወቅ ከሆነ አሁን ይታወቅ)
እነ ማስተዋል ብርሃኑ በተከሰሱበት በዚህ ክስ በ50 ሺህ ብር ዋስትና ተለቀው ለሚያዝያ 17 2005 የተቀጠሩ ሲሆን በክሱ ጥፋተኛ ከተባሉ እስከ አስራ ሰባት አመት እስር ይጠብቃቸዋል፡፡ ማስተዋል ሸሽቶ ከመውጣቱ በፊት የመንግሰት ደህነነት ሰዎች በተደጋጋሚ እየተከታተሉ የእጅ ስልኩን በመንጠቅ ከማን ጋ እንደተደዋወለ እና ምን አይነት መልዕክት (ሜሴጅ) እንደተለዋወጠ በግድ ያዩበት እንደነበር ነግሮኛል፡፡
በነገራችን ላይ የፍትህ አሳታሚ እና ፍትህ ጋዜጣ በቀጠሮ ከተያዘው ክስ በተጨማሪ ወደ አርባ የሚጠጉ በይደር የተያዙ ክሶችም አሉበት፡፡
በተጨማሪም ከስድስት አመታት በፊት የተቃውሞውን ጎራ የተቀላቀለው ወጣት አርአያ ጌታቸው በበኩሉ በተለይ የፍትህ ጋዜጣ ድረ ገጽን ማሰናዳት ከጀመረ ወዲህ የበረታ ክትትል እና ማስፈራሪያ ከመንግሰት የስጋ ዘመዶች እንደደረሰበት ይናገራል፡፡
ከዚህ በፊት አንድ የፌደራል ፖሊስ ኮማንደር በመኪና አፍኖ የማያውቀው ቦታ ከወሰደው በኋላ ለተመስገን ደሳለኝ ከውጪ ሀገር ያሉ አሸባሪ ዲያስፖራዎች የሚያደርጉለት የገንዘብ እርዳታ መኖሩን እና በመሃል ሆኖ ገንዘቡን የሚያቀባብለው ደግሞ እርሱ እንደሆነ ነግሮት፤ ይህንን ድርጊቱን የማያቆም ከሆነ በእህትህ እና በእናትህ ላይ ፈርደሃል ማለት ነው… የሚል ዛቻ አድርሶበታል፡፡
ከአመት በፊት ይህ ማስፈራሪ የደረሰው አርአያ፤ ለቤተሰቦቹ ደህንነት ሲል ቤት ተከራቶ መኖር ቢጀምርም፤ ከአመት በላይ የዘለቀው ይኸው ማስፈራሪያ አሁንም እጅግ ተባብሶ “ከፍትህ ጋዜጣ ጋር ያለህን ግንኙነት አቁም ብለንህ እስካሁን አላቆምክም ስለዚህ እንገድልሃለን!” በሚል ቃል በቃል ማስጠንቀቂያ ሲደርሰው “ገዳዮቹን” መሸሹን ይናገራል፡፡ አርአያ የፍትህ ጋዜጣ ድረ ገጽ አዘጋጅ የነበረ ከመሆኑም በላይ ሰማያዊ ፓርቲን ከመሰረቱት ግንባር ቀደም ወጣቶች አንዱ ነው፡፡
በፍትህ ምክንያት የተሰደዱት ማስተዋል ብርሃኑ እና አርአያ ጌታቸው አሁንም የደህንነታችን ነገር ስጋት ላይ ነው፤ ብለው ያሉበትን ቦታ እንዳልናገር አደራ ብለውኛል፡፡ የምናገረው ነገር ግን አለኝ፤ በአዲስ መስመር እንዲህ እላለሁ፤
እንደዚህ እያባረሩ እና እንደዚያ እያማረሩ ስንት አመት መዝለቅ ይቻላል፡፡ እውነት እውነት እላችኋለው ከጥቂት እርምጃ በኋላ እግራችሁ እግራችሁን ጠልፎ ይጥላችኋል!

 አቤ ቶኪቾው

“መንግስት ለትውልድ የሚተርፍ የማያልቅ እዳ ውስጥ እየገባ ነው”

መንግስት ለትውልድ የሚተርፍ የማያልቅ እዳ ውስጥ እየገባ ነው” መንግሥት የሱቅ ነጋዴ ቢሆን በአንድ ሳምንት ሱቁን ይዘጋ ነበር ትልቁ ሙያ ግሽበቱን ቀንሶ፣ ብሄራዊ ምርቱን አሳድጐ፣ ስራ አጥነትን መቀነስ ነው የዋጋ ግሽበቱ የቱ ጋ ነው የወረደው ---- ስኳር ላይ ነው? ዘይት ላይ ነው? ጤፍ ላይ? ኢህአዴግ በቅርቡ ባህርዳር ላይ ባካሄደው ድርጅታዊ ጉባኤው አጠቃላይ የአገሪቱ ኢኮኖሚ መቀዛቀዝ እንዳሳሰበው ገልጿል፡፡ በሌላ በኩል የዋጋ ግሽበት በከፍተኛ ደረጃ እየቀነሰ መምጣቱን ከማዕከላዊ ስታትስቲክስ ቢሮ የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ አንዳንድ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች እንደሚሉት ኢህአዴግ ቀደም ሲል የተሰጡትን ሙያዊ ምክሮች አለመስማቱ አሁን በኢኮኖሚው ማሽቆልቆል ዋጋ እያስከፈለው ነው፡፡ በ97 ምርጫ ቅንጅትን ወክለው በመወዳደር ፓርላማ የገቡትና በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ከአገሪቱ የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር ክርክርና ሙግት በመግጠም የሚታወቁት አቶ ተመስገን ዘውዴ፤ በአሁኑ ሰዓት መንግሥት ቀንሷል የሚለው የዋጋ ግሽበትም እንደተባለው አለመቀነሱን ይናገራሉ፡፡
የአንድነት ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ሰብሳቢና የመድረክ ስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑትን አቶ ተመስገን ዘውዴን በአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ አድማስ አነጋግሯቸዋል፡፡ ከፓርላማ ከወጡ በኋላ ለምን ከሚዲያው ጠፉ? ወድጄ አይደለም፡፡ አብዛኛው ሚዲያ በገዢው ፓርቲ ቁጥጥር ስር ነው ያለው፡፡ ይኼ ደግሞ ሃቁን የሚናገሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚናገሩት ነገር ለገዢው ፓርቲ ሊዋጥለት ስለማይችል ነገሩን አድበስብሰው ከሚያልፉት ጋር ብቻ ከማቀንቀን ብዬ ነው የጠፋሁት፡፡ የሚዲያ አማራጭ የለንም፡፡ አሉ የሚባሉትን ነፃና ገለልተኛ የፕሬስ ውጤቶች ገዢው ፓርቲ እንዳይታተሙ በማድረጉ ብዙም የሚዲያ እድል ስለሌለኝ ነው እንጂ የምናገረው ነገር በማጣት አይደለም፡፡ አሁን ምን እየሠሩ ነው? ከፓርላማው ከወጣሁ በኋላ በፓርቲዬ “አንድነት” ውስጥ እያገለገልኩ ነው፡፡ የፓርቲው የውጭ ግንኙነት ጉዳይ ኃላፊ ሆኜም እየሰራሁ ነው፡፡
አሁን ያለው ፓርላማ እርሶ ከነበሩበት ፓርላማ አንፃር በሀገሪቱ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ የሚያደርጋቸውን ውይይቶችና የሚያስተላልፋቸውን ውሳኔዎች እንዴት ይገመግሙታል? እኔ በነበርኩበት ፓርላማ ይብዛም ይነስም 172 የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ነበሩ፡፡ እነዚህ አባላት በሙሉ አቋማቸው ግልፅ ነበር፡፡ እዚያ ውስጥ ያለነው የፓርላማ አባላት በተለይ እኔ የነበርኩበት የመጀመሪያው ቅንጅት፣ ቀጥሎም አንድነት የህዝብን አንገብጋቢ ጥያቄዎችና የመንግሥትን ፖሊሲ የመሳሰሉትን አንስተን ወደ ፓርላማው ለማቅረብ ባንችልም በነዚህ ዙሪያ የሚነሱ ሃሳቦችን በቀጥታ በመጋፈጥ ለህዝብ ይጠቅማሉ ያልናቸውን ሃሳቦች በትክክል ህዝቡ እንዲሰማ አድርገን እናቀርብ ነበር፡፡ አሁን ግን ገዢው ፓርቲ ሙሉ ለሙሉ ፓርላማውን ስለተቆጣጠረ የሚወጡት አዋጆች የኢትዮጵያን ህዝብ ሰላም፣ ዲሞክራሲያዊ ነፃነት እና የሰብአዊ መብት ጥበቃ ወደ ኋላ የሚጐትቱ መሆናቸውን ለማሰማት የሚደረጉ ጥረቶች ደካማ ናቸው፡፡
ይሄም ከገዢው ፓርቲ ተፅእኖ የሚመጣ ነው ለማለት እችላለሁ፡፡ ባለፈው ግን ቁጥራችንም ብዙ ስለነበረ በምትሰጠን ጥቂት ደቂቃ ውስጥ ከፍተኛ የህዝብ ስሜትን ሊይዝ የሚችል ክርክር በፓርላማው ውስጥ በማድረግ ለህዝቡ ያለንን ታማኝነትና ቆራጥነት ለማሳየት የቻልንበት ሁኔታ ነበር፡፡ አጠቃላይ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ እየተቀዛቀዘ መሆኑን መንግሥትም አለማቀፍ ተቋማትም ገልፀዋል፡፡ ምክንያቱ ምን ይሆን? እንግዲህ እዚህ ሀገር አንድ ገዢ ፓርቲ ከማዕከል እስከ ቀበሌ ፍፁም በሆነ አስተዳደራዊ የበላይነት እያስተዳደረ ነው፡፡ ኢኮኖሚው በሁለት አሃዝ ጨምሯል ሲባል በእርግጥ ጨምሯል ወይ ብለን ከሦስተኛ ወገን የምናጣራበት መንገድ የለም፡፡ ኢኮኖሚው ላለፉት ሦስትና አራት አመታት እያደገ ነው ሲባል እየሰማን ነው፡፡ የኢኮኖሚ እድገት ዞሮ ዞሮ ተጠቃሚ ማድረግ ያለበት ህብረተሰቡን ነው፡፡ መሠረታዊ የሆኑ ነገሮችን እንደ ምግብ፣ መጠለያና አልባሳትን ማሟላት አለበት፡፡ የኢኮኖሚ እድገቱም በዚህ ነው የሚታየው፡፡ ገዢው ፓርቲ ኢኮኖሚው በሁለት አሃዝ አድጓል ሲል እኛ አልተቀበልንም፡፡ ብሄራዊ ምርት (GDP) ከዓመት ዓመት አድጐ እንኳ ቢሆን ኖሮ የማክሮ ኢኮኖሚ አስተዳደር የሚጠይቀው ብሄራዊ ምርቱን ማሳደግና የዋጋ ግሽበቱን መቆጣጠር ነው፡፡
በማክሮ ኢኮኖሚ አስተዳደር ሙያ፤ ብሄራዊ ምርት (GDP) ማሳደግ ብቻ አይደለም ትልቁ ነገር፣ ኢኮኖሚውን እያሳደጉ የዋጋ ግሽበትን መቆጣጠር ነው፡፡ ትልቁ ነገር ስራ አጥነትን መቀነስ መቻል ነው፡፡ ገዢው ፓርቲ ግን እያየው ያለው ከፖለቲካዊ አንድምታው አንፃር ብቻ ነው፡፡ ብሔራዊ ምርቱ በማደጉ ምክንያት ዜጐች በገቢያቸው ለመተዳደር አለመቻላቸውን እንደ ቁምነገር አይቆጥረውም፡፡ ግን ትልቁ ቁምነገር እሱ ነው፡፡ የዋጋ ግሽበትን መቆጣጠር ሳይቻል ብሄራዊ ምርት አድጓል ማለት በቀኝ ሰጥቶ በግራ እጅ መቀበል ነው፡፡ ምክንያቱም ዜጐች በዋጋ ግሽበት ምክንያት በገቢያቸው መተዳደር ካልቻሉ የብሄራዊ ምርት ማደጉ ትርጉም የለውም፡፡ በማክሮ ኢኮኖሚ አስተዳደር ሙያ፤ ብሄራዊ ምርት አድጓል ማለት መንግሥት ወጪውን ሳይቀንስ ብር እያፈሰሰ ነው ማለት ነው፡፡ ትልቁ ሙያ ያለው ግሽበቱን ቀንሶ፣ ብሄራዊ ምርቱን አሳድጐ ስራ አጥነትን መቀነስ መቻሉ ላይ ነው፡፡ ብሄራዊ ምርቱ በማደጉ ምክንያት ዜጐች ተጠቃሚ ሆነዋል ወይ የሚለው ያልተመለሰ ጥያቄ ነው፡፡
በምሳሌ ላስረዳ፤ የዛሬ አራት ዓመት አምስት ብር በኪሎ የሚሸጥ ሙዝ ዛሬ 12 ብር ነው፣ በተቃራኒው የዛሬ አራት ዓመት 3ሺህ ብር በወር የሚያገኝ የመንግሥት ተቀጣሪ ዛሬም 3ሺህ ብር እያገኘ ነው፡፡ ታዲያ ይኼ ዜጋ እንዴት ነው ከእድገቱ ተጠቃሚ የሆነው፡፡ የብር የመግዛት አቅሙ መሬት ወድቋል፡፡ መንግሥት ግን ብሄራዊ ምርቱ አደገ እያለ ነው፡፡ ምን ጥቅም አለው ይሄን ማለቱ? ዜጐች በገቢያቸው መተዳደር ካልቻሉ፣ ሸማቹ ህብረተሰብ በገቢው መተዳደር ካልቻለ ዋጋ የለውም እያልን ነው፡፡ አሁን የዋጋ ግሽበቱ ወረደ እያሉን ነው፡፡ የቱ ጋ ነው የወረደው? እንደ ኢትዮጵያዊ የምንመገባቸውን ምግቦች እናውቃቸዋለን፡፡ የሰብል ምግቦች ዋጋ ላይ ነው የተሻሻለው? ስኳር ላይ ነው? ዘይት ላይ ነው? ጤፍ ላይ ነው? እስቲ የቱ ላይ ነው የወረደው፡፡ ይኼንን በተገቢው መንገድ ማስረዳት አለባቸው፡፡ የዋጋ ግሽበቱ በአይ ኤም ኤፍ የሐምሌ 2004 ዓ.ም መረጃ መሰረት፤ 33 በመቶ ደርሷል ይላል፡፡
አሁን ደግሞ እነሱ ወደ 12.9 በመቶ ዝቅ ብሏል እያሉን ነው፡፡ በጣም የሚገርም ሂደት ነው፤ የዋጋ ግሽበት ወደ ላይ ለመውጣትም ጊዜ ወስዶ ነው የሚወጣው፡፡ አወጣጡም አወራረዱም የራሱ መንገድ ስላለው የዋጋ ግሽበቱ በአራት እና አምስት ወር ጊዜ ውስጥ ከ33 በመቶ ወደ 12.9 በመቶ ወረደ ማለት መቶ ኪሎ ሜትር በሰዓት እየበረረ የሚሄድ መኪና ከመቅፅበት ቆመ እንደማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሌላ የሚያስከተለው ጉዳት አለ፡፡ ወረደ ከተባለ በምን ምክንያት ነው የወረደው? የወጣውስ በምን ምክንያት ነው? የሚለው ተተንትኖ ሊቀርብ ይገባዋል፡፡ ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ንግግራቸው የሃቅ ነው ማለት አይቻልም፡፡ ለፖለቲካ ፍጆታ የሚነገር ብቻ ይሆናል፡፡ ዛሬ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ በገቢው መተዳደር፣ ልጆቹን ማስተማር፣ የቤት ወጪውን መሸፈን ባልቻለበት ሁኔታ እንዲህ አይነት የፕሮፓጋንዳ ምላሾች አስገራሚ ናቸው፡፡ ገዢው ፓርቲ የመንገድ መሰራትና የህንፃዎች መብዛትን ከፍተኛ የልማት ስኬት አድርጐ ነው የሚወስደው፡፡ ሃቁ ግን ይህ አይደለም፡፡
አስቀድሜ እንዳልኩት የህዝቦች የኑሮ ደረጃ የሚለካው በብሄራዊ ምርት (GPD) እድገት ብቻ አይደለም፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ሂውማን ዴቨሎፕመንት ኢንዴክስ (የሰብዓዊ ልማት መለኪያ) የሚል ሪፖርት አውጥቷል፡፡ በዚያ መለኪያ መሰረት ኢትዮጵያ ከ178 ሀገሮች 174ኛ ደረጃ ነው የተሰጣት፡፡ የመጨረሻውን ረድፍ ነው የያዘችው፡፡ ይኼ ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ እስከ 12 ሚሊዮን የሚደርስ ህዝብ የምግብ ሰቆቃ ያለበት ሀገር ኢኮኖሚው አድጓል ቢባል ትርጉም የሚሰጥ አይደለም፡፡ አሁን ግን እድገቱ ቀንሷል እያለ ነው መንግሥት፡፡ ይኼ ምንን ነው የሚያመለክተው? እንግዲህ ትክክለኛውን እንናገር ከተባለ የዋጋ ግሽበት የሚባለውን ኢህአዴግ አልፈጠረውም፡፡ በማንኛውም ኢኮኖሚ ውስጥ የሚያጋጥም ጉዳይ ነው፡፡ የተለያዩ የኢኮኖሚ “ሳይክሎች” አሉ፡፡ ግሽበት ውስጥ የምንገባው፣ ኢኮኖሚው ሊሸከመው ከሚችለው በላይ ገንዘብ እየታተመ ወደ ኢኮኖሚው ሲገባ ነው፡፡ በመሰረቱ ግሽበት ማለት “ጥቂት ምርትን ብዙ ገንዘብ ሲያሳድድ” ማለት ነው፤ ሌላ ትርጉም የለውም፡፡ አሁን ምርቱ የለም፤ ብዙ ገንዘብ አለ ማለት ነው፡፡ ለዚህ ነው አንድ ዶላር 20 ብር ድረስ እየተመነዘረ ያለው፡፡
እንደዚህ ያሉ የግሽበት ሂደቶች ውስጥ ሲገባ ኃላፊነት የሚሰማው ገዢ ፓርቲ ሊወስዳቸው የሚገቡት እርምጃዎች አሉ፡፡ አንደኛው የመንግሥት ወጪን መቀነስ ነው፡፡ የመንግስት ወጪ እንዲቀንስ የሚደረግበት ምክንያት አለው፣ ኢኮኖሚው መሸከም ከሚችለው በላይ የብር ፍሰት ካለ መንግሥት ወጪውን መቀነስ አለበት፡፡ ይሄን ሌሎች ሀገራት እያደረጉ ያሉት ሞኝ ስለሆኑ አይደለም፤ “ኮንቬንሽናል የማክሮ አስተዳደር” የግዴታ ይሄን ስለሚጠይቅ ነው፡፡ ሌላው የበጀት ጉድለት እንዲጠብ መደረግ አለበት፡፡ እዚህ ግን የበጀት ጉድለቱ እንዲሰፋ እየተደረገ ነው፡፡ ሌላው ዜጐች ከባንክ የሚያገኙት የወለድ መጠንና የባንኮች ተቀማጭ ገንዘብ ከፍ እንዲል ይደረጋል፡፡ ምክንያቱም ገንዘብ ከኢኮኖሚው ውስጥ ለመሰብሰብ ይጠቅማል፡፡ ሌሎችም ብዙ መንገዶችም አሉ፤ መንግሥት ይሄን ለማድረግ አይፈልግም፡፡ ከዚህ አንፃር አሁን እድገቱ ቀነሰ ሲባል ምን ሆኖ ቀነሰ የሚለውን እናነሳለን፡፡ የመንግሥት ወጪ ቀንሶ አይደለም እንዲያውም እየጨመረ ነው ያለው፡፡ የበጀት ጉድለቱ እየጠበበ ነው? አይደለም እንደውም እየሰፋ ነው፡፡ የወለድ መጠኑም እየጨመረ አይደለም፣ ብሄራዊ ባንክም ገንዘብ እያተመ ወደ ገበያው ማሰራጨት አቁሟል ማለትም አይደለም፡፡
ስለዚህ በየትኛውም መንገድ ሚዛን ላይ ሊቀመጥ የሚችል ገለፃ የሌለው ነው፡፡ አሁን ብሄራዊ ምርቱ (GDP) ወርዷል ነው ያሉት፡፡ ቢወርድም እኛ እያየን እንዳለነው የዋጋ ግሽበቱ እየቀነሰ አይደለም፣ የስራ አጥ ቁጥር እየቀነሰ አይደለም፡፡ በተመሳሳይ ኢኮኖሚው ከፍተኛ መቀዛቀዝ ውስጥ ገብቷል እያሉን ነው፡፡ ከ11.5 ወደ 8.5 በመቶ በአራትና በአምስት ወር ጊዜ ውስጥ መውረድ ከፍተኛ ለውጥ ነው፡፡ ኢኮኖሚው የሚመራው በፖለቲካው ስለሆነ የትኛውንም ዓይነት መረጃ ለመቀበል ያስቸግረናል፡፡ ያኔም የሚናገሩት ችግሮችና መፍትሄዎቹ የተዛቡ ናቸው፤ አሁንም የሚናገሩትና መፍትሄ የሚሉት ነገር የላቸውም፡፡ ስለዚህ ኢኮኖሚውን በሙያ፣ በግንዛቤ መተንተን ሳይሆን ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ መጠቀም ነው የያዙት፡፡ የኢኮኖሚው መቀዛቀዝ ምናልባት የገበያ (ግሽበት) መረጋጋት ይፈጥር ይሆን? የኢኮኖሚውን መቀዛቀዝ ከአቶ መለስ ህልፈት ጋር የሚያያይዙትም አሉ፡፡ እርስዎ ምን ይላሉ? አሁን እኮ የኢኮኖሚም ሆነ የገበያ መረጋጋት የለም፡፡ ሀገሪቱ ከፍተኛ የውጭ እዳ አለባት፣ የብር የመግዛት አቅም ተዳከሟል፡፡ በዚህ ሁኔታ መረጋጋት የሚታሰብ አይደለም፡፡ ሀገሪቱ መመራት ያለባት በሲስተም እንጂ በሰዎች ማንነት አይደለም፡፡ በሰዎች ማንነት የሚመራ ኢኮኖሚ አሁን ላለንበት ሁኔታ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡ ያለመረጋጋት እና ከሲስተም ውጪ የሆነ ስራ ነው ውጤቱ፡፡
ኢኮኖሚው በተቀዛቀዘበት፣ ግሽበቱ ባልቀነሰበት ሁኔታ የሀገሪቷ እጣፈንታ ምን ሊሆን ይችላል? አንድ ጊዜ ፓርላማ እያለሁ ትንቢታዊ የሆነ ነገር ተናግሬ ነበር፡፡ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጀርመን ውስጥ የጀርመን መገበያያ ገንዘብ ወርዶ መሬት ስለነካ፣ አንድ ቲማቲምና አንድ ድንች ለመግዛት ጀርመናውያን በከረጢት ሙሉ ብር እየያዙ ይዞሩ ነበር፡፡ ይኼን ለፓርላማ ስናገር፣ ይኼንና የኛን ሀገር ሁኔታ ምን ያገናኘዋል? የሚል ምላሽ ነበር የቀረበልኝ፡፡ አሁን እንግዲህ ወደዚያ ደረጃ እየደረስን ነው ማለት ነው፡፡ ግሽበት “ሀ” ብሎ ሲጀምር ነው ኢኮኖሚው ብዙ ማስታገሻ መርፌ መወጋት ያለበት፡፡ ልማታዊ መንግሥት ነኝ ለሚል የሚቀርቡ መራራ ክኒኖች አሉ፡፡ ከእነዚያ መራራ ክኒኖች አንዱ የምታወጣውን ወጪ ቀንስ የሚለው ነው፡፡ ያንን መራራ ኪኒን አልውጥም በማለቱ ነው ዛሬ ከዚህ ደረጃ ያደረሰን፡፡ ያንን መራራ ኪኒን ውጦ ወጪውን ቢቀንስና በጀት ቢያጠብ ኖሮ፣ እዚህ አንደርስም ነበር፡፡ አሁንም እነዚህ የቀበቶ ማጥበቅ ስራዎች ካልተሰሩ የሚገነባው ልማት ዝም ብሎ ገንዘብ አትሞ ከማፍሰስ ውጪ በምርታማነት ሊገኝ ስለማይችል ኢኮኖሚው ከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገባል፡፡ ይኼ ላይ ላዩን የተቀባባ ነገር እየቀጠለ በህዝቡ ላይ ግን የከተማ ድህነት እየጨመረ፣ የመንግሥት ሠራተኛው በገቢው መተደደር እየተቸገረ፣ ምርት እየጠፋ በሚሄድበት ጊዜ ከፍተኛ የማክሮ ኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ እየገባን ነው የምንሄደው፡፡
ገዢው ፓርቲ አሁን አለች የምትባለውን የኢኮኖሚ እድገት ሊያስመዘግብ የቻለው፣ ከ1997 ዓ.ም በኋላ በወቅቱ “ኦርጅናሉ ቅንጅት” በፈጠረው የሰላማዊ ተቃውሞ ህዝቡ ሌላም አማራጭ አለ ብሎ ማሰቡን መንግሥት ተገንዝቦ ከእንቅልፉ በመንቃቱ ነው፡፡ አሁንም ግን እድገቱ ተገኘ የተባለው ትውልድን ከፍተኛ የውጭ እዳ ውስጥ በማስገባት ነው፡፡ አሁን እኮ መንግሥት ለሁለት ወር የሚበቃ የገቢ እቃ ለማስመጣት የሚያስችል ገንዘብ የለውም፡፡ አንዳንድ ነጋዴዎች ባንክ ውስጥ “ሌተር ኦፍ ክሬዲት” ለመክፈት ቆዩ እየተባሉ ነው፡፡ ሁለተኛ ደግሞ የውጭ እዳው አሳሳቢ ነው፡፡ ለትውልድ የሚተርፍ ተከፍሎ የማያልቅ እዳ ውስጥ እየገባ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በንግድ ከተሻረከቻቸው ሀገራት ጋር በሙሉ ኢ-ሚዛናዊ በሆነ የንግድ ሂደት ውስጥ ነው ያለችው፡፡ ሚዛናዊ ወይም ትርፋማ የሆነ የንግድ ጥምርታ የላትም፡፡ ይኼ መንግሥት እኮ የሱቅ ነጋዴ ቢሆን ኖሮ በአንድ ሳምንት ነው ሱቁን መዝጋት ያለበት፡፡ ምክንያቱም የሚገዛው ከሚሸጠው በእጥፍ የሚበልጥ ነው፡፡ ስለዚህ አንድ ገዢ ፓርቲ በዚህ አይነት ሁኔታ ማስተዳደር አይችልም፡፡
ከዚህ ሁኔታ ውስጥ ለመውጣት ደግሞ አንደኛ ለውጭ ግብይት የሚያቀርበውን ሸቀጥ በአይነት መጨመር አለበት፡፡ ሁለተኛ (Import substitution) የሚባል አለ፡፡ እነዚህ ከውጭ በከፍተኛ ምንዛሬ ተገዝተው የሚገቡትን ተክተን በራሳችን ልንሰራቸው የምንችላቸው ማለት ነው፡፡ ይሄን ለማድረግ የሚችሉ ስራ ፈጣሪዎችን መንግሥት ሊያበረታታቸው ይገባል፡፡ ይኼ እየተደረገ አይደለም፡፡ ስለዚህ መንግሥት ከተቃዋሚ ፓርቲዎችም ጋርም ሆነ ከሌላው ዜጋ ጋር በመመካከር ችግሮች በዘላቂነት የሚቀረፉበትን መንገድ መፈለግ አለበት፡፡ ኢኮኖሚን መገንባት ይቻላል፤ ጤናማ ኢኮኖሚን ለመገንባት ግን የተለየ ሙያዊ ብቃት ይጠይቃል፡፡ ጤናማ ኢኮኖሚ የሚባለው የዋጋ ግሽበትን የተቆጣጠረ፣ ስራ አጥነት እንዲቀንስ የሚያደርግና ብሄራዊ ምርት (GDP) እድገትን የሚያመጣ ነው፡፡ ይሄን ማድረግ ደግሞ ይቻላል፡፡ ከፖለቲካ እይታ ውጪ ብቃቱ ያላቸው ሙያተኞችን አሳትፎ፣ ጤናማ የኢኮኖሚ እድገትን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ መንግሥት በአሁን ሰዓት ከ70 በመቶ በላይ የሚሆነው ኢትዮጵያዊ ከድህነት ወለል በላይ መሆኑንና 30 በመቶው ብቻ በድህነት ውስጥ ያለ መሆኑን እየገለፀ ነው፡፡ እርሶ ይሄን ይቀበሉታል? በመሰረቱ ይኼ ታማኝነት አለው ወይ? የሚለውን ማየት ያስፈልጋል፡፡ ገዢው ፓርቲ ብዙ ጊዜ የሚያወጣቸው መረጃዎች ታሽተው ነው እኛ ጋር የሚደርሱት፡፡
የመረጃ ምንጫችንም ይኸው ገዢው ፓርቲ ብቻ ነው፡፡ ነፃና ገለልተኛ በሆነ አካል ይህን ማረጋገጥ አንችልም፡፡ እኛ ግን አሁን ባለንበት ሁኔታ መጠየቅ የምንችለው፣ የድህነት መጠኑ ወደ 30 በመቶ ወርዷል ከተባለ እንዴት ነው ይሄ ነገር የተፈፀመው? የሚለውን ጥያቄ ነው፡፡ የህዝብ ቁጥር ስለቀነሰ ነው? እንግዲህ የህዝብ ቁጥር በጨመረ ቁጥር ብሄራዊ ምርቱ ለብዙ ህዝብ ነው የሚከፋፈለው፡፡ አሁንም የሚሆነው ፍትሃዊ የሆነ የሀብት ክፍፍል አለ ነው፡፡ አሁን ግን የህዝብ ቁጥር አልቀነሰም፤ መረጃዎች የሚያመለክቱት እንደጨመረ ነው፤ ስለዚህ እንዴት ሆኖ ነው ይኼ ድህነት ቅነሳ ሊመጣ የቻለው? በብሄራዊ ምርት እድገት ነው ከተባለ ደግሞ እድገቱ የከተማ ድህነትን ጨምሯል፡፡ ምክንያቱም የዋጋ ግሽበቱ ትልቁ ቀንበር የሚያርፈው ድሃው ህብረተሰብ ላይ ነው፡፡ ገቢው የተወሰነና ሊጨምር የማይችል ሆኖ የዋጋ ግሽበቱ ግን በልጦታል፡፡ ስለዚህ የከተማ ድህነት እየጨመረ ነው ያለው፣ የገጠሩም በተመሳሳይ ነው፡፡ ከህዝቡ 12.5 ሚሊዮን ያህሉ ከግማሽ ሄክታር በታች ይዞታ ያላቸው ገበሬዎች ናቸው ዝናብ ሲዘንብ ጠብቀው ራሳቸውን መግበው፣ ሌላውን ህብረተሰብ ለመመገብ የሚታትሩት፡፡ ዝናብ ሳይዘንብ ደግሞ እነሱም ተርበው ህብረተሰቡም ይራባል፡፡
ስለዚህ ከድህነት ወጡ የተባሉት የመሬት ይዞታቸው ጨምሮ ነው? ምርታማ ሆነው ነው የሚለውን መመለስ ያስፈልጋል፡፡ እነዚህ 12 ሚሊዮን ገበሬዎች በከፍተኛ ድህነት ላይ ነው ያሉት፡፡ በአለም ባንክ ሪፖርት፤ የገቢ ድህነት ያለባቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡ እሱ ብቻ አይደለም፤ የይዞታ ድህነትም አለባቸው፡፡ እነዚህ ገበሬዎች አሁን ላይ ራሳቸውን የሚያዩት እንደመንግሥት ተቀጣሪ ነው፡፡ ምክንያቱም አሁን ያሉበት መሬት መጥበብና ማነስ ብቻ ሳይሆን ያችም ብትሆን በገዢው ፓርቲ ፈቃድ ስር የዋለች ናት፣ የፖለቲካ ጥገኞች ናቸው፡፡ ስለዚህ በምን ምክንያት ነው እነዚህ ሰዎች ከድህነት የወጡት? የመሬት ይዞታቸው ጨምሯል፣ የአስተራረስ ዘይቤያቸው ተሻሽሏል፣ የምርት ግብአቶች ተሻሽሎ ነው ተብሎ መጠየቅ አለበት፡፡ ቀንሷል የሚለው ሪፖርት እውነት ከሆነ ደስ ይለን ነበር ግን በአይናችን እያየነው አይደለም፡፡ ምክንያታዊም አይደለም፡፡ የገዢው ፓርቲ ኃላፊዎች ይሄን ሲናገሩ ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ሊያስረዱን ይገባል፡፡ መንግሥት በ2004 የበጀት ዓመት የግብርና ምርቱም ቀንሷል፤ የታሰበውን ያክል አይደለም የሚል መረጃም አቅርቧል፡፡
የግብርና ምርታማነት ማሽቆልቆሉ ከምን ጋር ነው የተያያዘ ነው? እንግዲህ እነዚህ ሰዎች በአንድ በኩል የድሃው ቁጥር ቀንሷል እያሉ፣ በሌላ በኩል የግብርና ምርቱ ቀንሷል እያሉን ነው፡፡ ግን ጥያቄው መሆን ያለበት ይህ ለምን ሆነ የሚለው ነው፡፡ ከግብርና ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ ገብተናል? ወደ አገልግሎት ዘርፍ ገብተናል? እነዚህ ናቸው ሊነሱ የሚገባቸው፡፡ አሁን ምርት ቀንሷል እያሉን ነው፡፡ ምርት በአስገዳጅነት የሚመጣ አይደለም፡፡ በአዋጅም የሚገኝ አይደለም፡፡ በነፃ ገበያ፣ በፍላጐት፣ በአቅርቦት አርሶ አደሩ የመሬቱ ባለቤት ሲሆን፣ የግል ፍላጐቱ ሲጨምር፣ ራሱን እንደመንግስት ተቀጣሪ ሳይሆን እንደነፃ ዜጋ መመልከት ሲችል፣ ለራሱ ጥቅም ብሎ መንቀሳቀስ ሲጀምር ነው ምርት የሚጨምረው እንጂ ምርት በአዋጅ አይጨምርም፡፡ ዜጐች በነፃነት ሲንቀሳቀሱ ብቻ ነው ምርት ሊጨምር የሚችለው፤ በትክክል ነገሩ የገባቸው አልመሰለኝም፡፡
ገዢው ፓርቲ ለህዝብና ለሀገር የሚበጁ ደንቦችን ማውጣት ነው እንጂ እዚህ ጋ ስንዴ እዚያ በቆሎ ቀንሱ ብሎ ገበያ ውስጥ ገብቶ የሚያተራምስበት ስርአት እኛ የምናውቀው የለም፡፡ በዚህ መንገድ ደግሞ አንድ አውራ ገዢ ፓርቲ ከማዕከል እስከ ቀበሌ ያስተዳድራል፡፡ ኢኮኖሚውንም እኔ በምለው መንገድ አስተዳድራለሁ በማለት ወደ ባሰ ችግር ውስጥ እያስገባን ነው፡፡ አሁን ጠቅላይ ሚኒስቴሩ የሚሉት ነገር የእሳቸው የአስተዳደር ስራ አይደለም፡፡ በእርግጥ አበዳሪ ድርጅቶችና ሀገራት እንደሚናገሩት አይነት የገበያ ስርአት የምንመሰርት ከሆነ ይኼ የገበያው ድርሻ ነው፡፡ ይሄን በ18ኛው ክ/ዘመን ነው አዳም ስሚዝ የተናገረው፡፡ በዚህ ነው የነፃ ገበያ ስርአት የሚተዳደረው እንጂ በአዋጅ አይደለም፡፡ በአዋጅ ሲተዳደር ነው አሁን ያለበት ቀውስ ውስጥ የምንገባው፡፡ ስኳር በዚህን ያህል ዋጋ ትገዛለህ፣ ጤፍ ከዚህ ቦታ ትገዛለት ሲባል ችግር አለው፡፡
ከፍተኛ መተራመስ የሚያመጣ ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት የማይችልበት አዘቅት ውስጥ የሚያስገባ ነው፡፡ የግብርና ምርታማነት እንደታሰበው አለመሆኑ በአቅርቦት ላይ የሚፈጥረው ተፅእኖ እንዴት ይታያል? ከወራት በፊት በሰማሁት ሪፖርት የግብርና ምርታችን በ5 በመቶ ጨምሯል ብለው ነበር፡፡ አሁን ምርት ከአይን እየጠፋ በመምጣቱ እንደገና ቀንሷል እያሉን ነው፡፡ የቀሰነበትን ምክንያትም በትክክል አያውቁትም፡፡ የዛሬ ዓመት ፓርላማ በነበርኩ ጊዜ የዋጋ ግሽበት ምክንያቱ በጥናት መታወቅ አለበት ብዬ እየጠየቅሁ ነበር፡፡ አሁንም ምርት ጨምሯልም ቀንሷልም ሲሉ ምክንያት የላቸውም፡፡ ከጥቂት ካድሬዎች የሰሙትን ወሬ እያስተጋቡ ነው፡፡ መሰረታዊ የሆነ የምርምር ውጤት ቢኖራቸው ኖሮ የዛሬ ሁለት ወር በ5 በመቶ ጨምሯል የተባለው አሁን ቀንሷል ሊባል አይችልም ነበር፡፡
ይሄ የምርት መቀዛቀዝና የገበያ አለመረጋጋት በህዝብ ዘንድ ሰቆቃ ሊያመጣ፣ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ ሊያስከትልና ዜጐችን አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል ነው፡፡ አሁንም ቢሆን ይሄ ገዢ ፓርቲ የማክሮ ኢኮኖሚ አስተዳደሩን ለመምራት ከፍተኛ ችግር አለበት፡፡ ከፖለቲካ አመለካከት የፀዱ ባለሙያዎች የማግኘት ችግር አለበት፡፡ ከዚያ ውጪ ይሄንን ነገር ለማየት ካልተቻለ በአብዮታዊ ዲሞክራሲና በአንድ ገዢ ፓርቲ አመለካከት ብቻ ይሄን ሰፊ ሀገርና 90 ሚሊዮን ህዝብ አረጋግቶ ለመምራት ያስቸግራል፡፡ እርሶ ፓርላማ በነበሩ ጊዜ ስለፊሲካልና ሞኒተሪ ፖሊሲ ደጋግመው ሲናገሩ ይደመጡ ነበር፡፡ ይሄ ነገር ለአብዛኛው ሰው ግልፅ አይደለም፡፡ ሞኒተርና ፊሲካል ፖሊሲ ማለት ምን ማለት ነው? በእውነት ይሄን ጥያቄ በደንብ ማብራራት የምፈልገው ጉዳይ ነው፡፡ ባለፈው ጊዜም ሆነ አሁን ያለው የሞኒተሪና ፊስካል ፖሊሲ አመራር በከፍተኛ ሁኔታ ስሜቴን የሚነካኝ ነው፡፡ ገዢው ፓርቲ እነዚህን ሃቀኛ በሆነ መንገድ ለማስተዳደር ባለመቻሉ፣ የኢትዮጵያን ህዝብ የኢኮኖሚ ችግር ላይ ጥሏል፡፡
ማክሮ ኢኮኖሚ አስተዳደር ላይ ችግር የፈጠረውም በዚሁ ምክንያት ነው፡፡ ገዢው ፓርቲ በፊሲካል ፖሊሲው ግብር የመጣልና የመሰብሰብ፣ አዲስ ግብር ከፋዮችን ማካተት፣ ፍትሃዊ የሆነ የግብር ስርአት እንዲኖር ማድረግ… እነዚህ ሁሉ የስራ አስፈፃሚው ኃላፊነቶች ናቸው፡፡ ፊሲካል ፖሊሲ የሚባለው ይሄ ነው፡፡ አንድ ኃላፊነት የሚሰማው ገዢ ፓርቲ በሚሰበስበው ግብር ይተዳደራል ማለት ነው፡፡ ሁላችንም በገቢያችን መጠን ለመተዳደር እንደምንሞክረው ማለት ነው፡፡ ከገቢያችን በላይ የምንተዳደር ከሆነ ችግር አለ ማለት ነው፡፡ በፊሲካል ፖሊሲው ያልሰበሰበውን ወይም ያላመረተውን እየበላ ያለው ገዢ ፓርቲ ነው፡፡ ይሄ እንዴት ነው የሚገለፀው ከተባለ፣ ወደ 12 ቢሊዮን ዶላር የውጭ እዳ አለበት፣ የበጀት ጉድለቱ ከገቢው በላይ እየተዳደረ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ የሀገሪቱ ብር የመግዛት አቅም የመጨረሻው ደረጃ ላይ ነው፡፡ ፊሲካል ፖሊሲውን በተገቢው መምራት ያለበት ገዢው ፓርቲ፣ ይሄን በስርአቱ መምራት ሳይችል ሞኒተሪ ፖሊሲውንም ተቆጣጥሮታል፡፡ ብሄራዊ ባንክ ነፃና ገለልተኛ ሆኖ ነው ሞኒተሪ ፖሊሲውን መምራት ያለበት፡፡ ያ ማለት ብሄራዊ ባንኩ ወደ ኢኮኖሚው ውስጥ የሚገባ የገንዘብ መጠንን ያውቃል፡፡ ዜጐች በቁጠባ ሂሳባቸው ምን ያህል ወለድ ማግኘት እንዳለባቸው ያውቃል፡፡ ያ ዜጐች ያስቀመጡትን ገንዘብ በምን ያህል ለኢንቨስተሮች ማበደር እንዳለባቸው ያውቃል፡፡
ስለዚህ ከስራ አስፈፃሚውና ከህግ አውጭው ተፅእኖ ነፃ ሆኖ መምራት አለበት፡፡ ለምሳሌ በአሜሪካ ፌዴራል ሪዘርቭ ቦርድ የሚሉት ነገር አለ፡፡ ይኼ ቦርድ በነፃነት ከገዢው ፓርቲና ከህግ አውጪው ቁጥጥር ውጪ ወደ ኢኮኖሚው የሚገባውንና የሚወጣውን የገንዘብ መጠን - የወለድ መጠን፣ የባንክ ሪዘርቭ መጠንን ቦንድ ሲሸጥ የሚከፈል የወለድ መጠን… እነዚህን ሁሉ በሞኒተሪ ይቆጣጠራል፡፡ አሁን ይሄን በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ብናመጣው ሁለት ነፃና ገለልተኛ የሆኑ አካሎች አሉ፡፡ አንዱ ስራ አስፈፃሚው ነው፤ ፊሲካል ፖሊሲውን የሚመራው፡፡ ሌላው ሞኒተር ፖሊሲውን የሚመራው ብሄራዊ ባንክ ነው ማለት ነወ፡፡ እነዚህ እየተነጋገሩ፣ እየተወያዩ ሚዛናዊና ፍትሃዊ ኢኮኖሚ እንዲኖር ያደርጋሉ ማለት ነው፡፡ አሁን ግን እየሆነ ያለው ጨርሶ ሊጠግብ የማይችለው ስራ አስፈፃሚው፤ ብሄራዊ ባንኩን ብር አትም ይለዋል፣ በራሱ ተፅእኖ ስር የወደቀ ብሄራዊ ባንክ ደግሞ ደሞዙን የሚከፍለው ማን እንደሆነ ስለሚያውቅ የሚፈልገውን ያክል ያትምለታል፡፡ ኢኮኖሚው ግን ያንን ሊሸከም አይችልም፡፡
ስለዚህ ማነው ዋጋ እየከፈለ ያለው? ስንል የኢትዮጵያ ሸማቹ ህዝብ ነው፡፡ እንግዲህ በግልፅ ለማስቀመጥ ፊሲካል ፖሊሲ የምንለው፣ የግብር አሰባሰብና አጠቃቀም ሲሆን ሞኒተሪ ፖሊሲ የምንለው የብሄራዊ ባንኩን ተግባራት የሚያመላክት ነው፡፡ የግብር አሰባሰቡን ማስፋት አለበት ሲባል እንዴት ነው? አሁን ከትናንሽ ነጋዴዎች ላይ ሳይቀር ታክስና ግብር እየተሰበሰበ ነው… እንግዲህ የእኔም ፓርቲ ቢሆን ስልጣን ሲይዝ ግብር ማስከፈሉ አይቀርም፡፡ ግብር ለልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡ አስፈላጊም ነው፡፡ ዜጐች ፍትሃዊ የሆነ ግብር መክፈላቸው የሚደገፍ ነው፡፡ አሁን ችግር እየሆነ ያለው የተሰበሰበው ግብር ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለልማት እየዋለ ነው? የሚለው ነው፡፡ ግን እንደዚህ አይነት የግሽበት አጋጣሚ ውስጥ ስንኖር ገዢው ፓርቲ ግብር የሚከፍሉትን ብቻ ከፍተኛ ተፅእኖ ውስጥ እንዲወድቁ ማድረግ ሳይሆን የማይከፍሉት እንዲከፍሉ መረቡን ማስፋት ነው ያለበት፡፡
ሁሉም የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ ማድረግ ነው ያለበት እንጂ የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን እንዲጐዱና ለመኖር እንዳይችሉ ማድረግ አይደለም፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ግን ህዝቡ እያማረረ ያለው ይሄንን ነው፡፡ ፍትሃዊ ባልሆነ ሁኔታ ግብር ተጣለብን ነው ምሬቱ፡፡ ይሄ ደግሞ ግልፅ በሆነ መንገድ የግብር አጣጣልና አሰባሰብ ሊታይ ይገባል ወደሚለው ይወስደናል፡፡ ድብቅ መሆን የለበትም፡፡ ሌላው ይሄ ገዢ ፓርቲ ማፅዳት ያለበት ሙስናን ነው፡፡ በተለይ ከዚህ ከግብርና ከሌሎች ነገሮች ጋር በተያያዘ ዛሬ ከፍተኛ ሙስና እየተፈፀመ ነው፡፡ በ2009 እ.ኤ.አ ወደ 15 ቢሊዮን ዶላር ከዚች ደካማ ሀገር ወደ ውጭ ወጥቷል የሚል ሪፖርት ቀርቦ ነበር፡፡ ይሄ የገዢው ፓርቲ ባለስልጣኖች ሊያፀዱት የሚገባ ተግባር ነው፡፡ እነሱ የሚነግሩን እዚህ ቦታ የ5 ሺህ ብር ሙስና ተፈፅሟል የሚለውን ነው፡፡ እኛ ግን ማወቅ የምንፈልገው ትላልቆቹን አሳዎች ነው፡፡ ከተማ ውስጥ ያሉት የገዢው ፓርቲ ትላልቅ ባለስልጣኖች ምን እያደረጉ እንዳለ ህብረተሰቡ ያውቃል፤ የማን ህንፃ እንደሆነ፣ የትኛው የገዢው ፓርቲ አመራር ቦታ እንደሆነ ያውቃል፡፡ ስለዚህ ቤቱን የማፅዳት ስራ ከራሱ መጀመር አለበት፡፡

   ምንጭ   አዲስ አድማስ 

አንዱዓለም አራጌ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ሰኞ በዳግም ቀጠሮ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ

የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር  አቶ አንዱዓለም አራጌ፣ አቶ ናትናኤል መኮንን እና እውቁ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ፣ አቶ አንዱዓለም አያሌው፣አቶ ዮሐንስ ተረፈ፣ ሻምበል የሺዋስ ይሁንዓለም፣ አቶ ክንፈሚካኤል ደበበ እና አቶ ምትኩ ዳምጤን ጨምሮ 24 ሰዎች በተከሰሱበት ክስ ከላይ ስማቸው የተጠቀሱ 8ቱ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት የወሰነውን የጥፋተኝነት ውሳኔ በመቃወም ለፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ቢጠይቁም እስካሁን ውሳኔ ሳይሰጥ ለ
አራተኛ ጊዜ ተቀጥሮ ነበር፡፡

 ይሁን እንጂ ሰኞ መጋቢት 30 ቀን 2005ዓ.ም. 6 ኪሎ በሚገኘው የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በተቀጠረው መሰረት ከጠዋቱ 3ሰዓት ውሳኔ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡

 ይህ በእንዲህ እንዳለ ከላይ በተጠቀሰው ክስ ተፈርዶበት አቃቂ ቃሊቲ በሚገኘው ቂሊንጦ ወህኒ ቤት በልዩ ጥበቃ ያለው አቶ ናትናኤል መኮንን የጥበቃ ኃላፊዎች ለአንድ ወር ከቤተሰብ እንዳይገናኝ የወሰኑበትን ቅጣት በመቃወም ለአንድ ሳምንት ምግብ ሳይበላ የርሃብ አድማ ማድረጉን ተከትሎ በእስር ቤት ያሉ ጓደኞቹና ከተከላካይ ጠበቆቹ አቶ አበበ ጉታ እና አቶ ደርበው ተመስገን ጋር ባደረጉት ውይይት አሁን ምግብ መብላት መጀመሩን ጠበቃው አቶ አበበ ጉታ በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡
አቶ አበበ ጉታ አያይዘውም “አቶ ናትናኤልን ካነጋገርን በኋላ ከጥበቃ ክፍል ኃላፊ ከሆኑት ሐጎስ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ብንነጋገርም በቀጥታ የሚመለከተው ኃላፊ ልናገኛቸው ባለመቻላችን የተጣለበት ቅጣት አግባብ እንዳልሆነ እና ቅጣቱም በአስቸኳይ እንዲነሳ በወቅቱ ላገኘናቸው መልዕክት አስተላልፈናል፤ እነሱም ለሚመለከተው የበላይ ኃላፊ መልዕክቱን እንደሚያደርሱ አረጋግጠውልናል” ሲሉ ገልፀውልናል፡:

የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አቶ አንዱዓለም አራጌ፣ አቶ ናትናኤል መኮንን እና እውቁ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ፣ አቶ አንዱዓለም አያሌው፣አቶ ዮሐንስ ተረፈ፣ ሻምበል የሺዋስ ይሁንዓለም፣ አቶ ክንፈሚካኤል ደበበ እና አቶ ምትኩ ዳምጤን ጨምሮ 24 ሰዎች በተከሰሱበት ክስ ከላይ ስማቸው የተጠቀሱ 8ቱ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት የወሰነውን የጥፋተኝነት ውሳኔ በመቃወም ለፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ቢጠይቁም እስካሁን ውሳኔ ሳይሰጥ ለ 4 ጊዜ ተቀጥሮ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ ሰኞ መጋቢት 30 ቀን 2005ዓ.ም. 6 ኪሎ በሚገኘው የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በተቀጠረው መሰረት ከጠዋቱ 3ሰዓት ውሳኔ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከላይ በተጠቀሰው ክስ ተፈርዶበት አቃቂ ቃሊቲ በሚገኘው ቂሊንጦ ወህኒ ቤት በልዩ ጥበቃ ያለው አቶ ናትናኤል መኮንን የጥበቃ ኃላፊዎች ለአንድ ወር ከቤተሰብ እንዳይገናኝ የወሰኑበትን ቅጣት በመቃወም ለአንድ ሳምንት ምግብ ሳይበላ የርሃብ አድማ ማድረጉን ተከትሎ በእስር ቤት ያሉ ጓደኞቹና ከተከላካይ ጠበቆቹ አቶ አበበ ጉታ እና አቶ ደርበው ተመስገን ጋር ባደረጉት ውይይት አሁን ምግብ መብላት መጀመሩን ጠበቃው አቶ አበበ ጉታ በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡

አቶ አበበ ጉታ አያይዘውም “አቶ ናትናኤልን ካነጋገርን በኋላ ከጥበቃ ክፍል ኃላፊ ከሆኑት ሐጎስ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ብንነጋገርም በቀጥታ የሚመለከተው ኃላፊ ልናገኛቸው ባለመቻላችን የተጣለበት ቅጣት አግባብ እንዳልሆነ እና ቅጣቱም በአስቸኳይ እንዲነሳ በወቅቱ ላገኘናቸው መልዕክት አስተላልፈናል፤ እነሱም ለሚመለከተው የበላይ ኃላፊ መልዕክቱን እንደሚያደርሱ አረጋግጠውልናል” ሲሉ ገልፀውልናል፡፡

ምንጭ  ፍኖተ ነፃነት http://www.fnotenetsanet.com/wp-content/uploads/2013/04/Finote-Netsanet-News-PaperNo-71.pdf





 








         

ምርጫ እስኪያልፍ ሙዚቃ ቤቶች የቴዲ አፍሮና የፀጋዬ እሸቱን ዘፈኖች መክፈት ተከለከሉ


በአዲስ አበባ የተለያዩ ስፍራዎች በሚገኙ መዝናኛዎችና ሙዚቃ ቤቶች በሚያዝያ መጀመሪያ የሚደረገው የአካባቢ ምርጫ ሳያልፍ ሀገር ፍቅር ስሜት የሚቀሰቅሱ ዘፈኖችን እንዳይከፍቱ ክልከላ ተደረገ፡፡

ከጥቂት ቀናት በኋላ በሚደረገው የከተማ መስተዳድርና የአካባቢ ምርጫ ብቻውን የሚወዳደረው ኢህአዴግ በካድሬዎቹ አስገራሚ ትዕዛዞችን እየሰጠ እንደሚገኝ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ጠቆሙ፡፡

በአዲሱ ትዕዛዝ መሰረት ምርጫው እስኪያልቅ ድረስ ሙዚቃ ከፍ አድርገው የሚያጫውቱ ሙዚቃ ቤቶችና የመዝናኛ ስፍራዎች የሀገር ፍቅር ስሜት የሚቀሰቅሱና ስለባንዲራ የተዜሙ ዘፈኖችን መክፈት ተከልክለዋል፡፡በትዕዛዙ በተለይ የተከለከሉት የቴዲ አፍሮና የፀጋዬ እሸቱ አዲሱ አልበም ላይ የተካተቱት ዜማዎች ይጠቀሳሉ፡፡

ነጋዴዎቹ “ክልከላው ከምርጫው ጋር ምን እንዳያያዘው አልገባንም፣ሆኖም ከመንግስት የመጣ ትዕዛዝ ስለሆነ ላለፉት ሁለት ሳምንታት ዘፈኖቹን ማጫወት አቁመናል” ብለዋል፡፡

 ነጋዴዎቹ ጨምረው ለፍኖተ ነፃነት እንደገለፁት በተለያየ ጊዜ ለቁጥጥር የሚመጡት የወረዳ ካድሬዎች የተከለከሉትን ዘፈኖች ተከፍቶ ከሰሙ ዛቻና ማስፈራሪያ እንደሚያደርሱባቸው ፡፡ “የቴዲን ዘፈን በተለያዩ ወቅቶች አትክፈቱ ተብለን እናውቃለን” የሚሉት ነጋዴዎቹ የፀጋዬ እሸቱ አዲሱ አልበም ውስጥ ያሉት ሀገርንና ባንዲራን የሚመለከቱ ዘፈኖች በሬዲዮ እየተለቀቁ እነሱ እንዳይከፍቱ መደረጋቸው እንዳስገረማቸው ገለፀዋል፡፡

ምንጮቻችን ተዘዋውረው ያነጋገሯቸው ነጋዴዎች እንደገለፁት ይህ ክልከላ ጎልቶ የታየው በመርካቶና በፒያሳ አካባቢ ነው፡፡

ምንጭ ፍኖተ ነፃነት http://www.fnotenetsanet.com/?p=3853

Sunday, April 7, 2013

የህወሓት/ኢሕአዴግ የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ዘመቻ በአስቸኳይ መቆም አለበት!

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)
Ethiopian People’s Revolutionary Party (EPRP) (ዴሞክራሲያዊ/Democratic)

ዜጎች በሀገራቸው ውስጥ በመረጡት ሥፍራ የመኖር፤ ሠርቶ ሃብት የማፍራት፤ ቤተሰብ የመመሥረት…ወዘተ በማንም ሊሰጣቸው ወይም ሊነፈጋቸው የማይችል ሁለንተናዊ የዜግነትEthiopian People's Revolutionary Party (EPRP Democratic) መብቶቻቸው ናቸው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን በዓለማችን የተነሱ የጎሣ እንቅስቃሴዎች ሁለንተናዊ የዜጎችን መብቶች በሚፃረር መልኩ አንድ-ወጥ የሆነ ወይም ከሌሎች ዘር የፀዳ ሀገርና መንግሥት ለመፍጠር ጥረዋል። ዓላማቸውን ሊያሳኩ ባልተቻሉባቸው ኅብረብሄር በሆኑ አገሮች ውስጥ ደግሞ የኤኮኖሚ፤ የፓለቲካና የወታደራዊ ኃይሉን በአንድ ዘር የበላይነት ለመያዝ ሲባል የዘር ማጽዳት ዘመቻ (ኤትንክ ክለዚንግ)ና የዘር ማጥፋት ዘመቻ (ጄኖሳይድ) ወንጀል መፈጸም የተለመደ ክስተት ሆኗል።
በዘጠናዎቹ መጀመሪያ ላይ የምሥራቁ የሶሻሊስት ካብ በተፈረካከሰበትና የሥልጣን ክፍተት በተፈጠረበት ወቅት፤ እነዚህ የጎሣ የወንጀል ቡድኖች በሕዝብ ውስጥ የነበሩ የፍትህ፤ የእኩልነትና የነፃነት ትክክለኛ ጥያቄዎችን በማጣመምና ለራስ እኩይ ዓላማ በማዋልና ሕዝብን በማሳሳት የጎሣ ወታደራዊ ኃይሎችን በማቋቋም አሰቃቂ የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን ፈጽመዋል። ዓለምአቀፍ የዜና ሽፋን ባገኙት ሀገሮች፤ ለምሳሌ በዩጎዝላቪያ፤ በሩዋንዳ፤ በኮንጎ፤ በሱዳን….ወዘተ ወንጀለኞቹ በዓለምአቀፍ ፍርድ ቤት መፈለጋቸውና አንዳንዶቹም ተይዘው ለፍርድ በመቅረባቸው ዘግናኝ ወንጀላቸውን እንዲያቆሙ ወይም እንዲሰወሩ አድርጓቸዋል። እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገሮች ግን ዓለምአቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ሽፋን ባለማግኘታቸው ወንጀሉ አሁንም በማንአለብኝነት በሰፊ እየተካሄደ ነው።
በኢትዮጵያ ውስጥ ይህ ዓይነቱ ወንጀል የተጀመረው የትግራይን ሪፕብሊክ እንመሠርታለን ባሉት እንደ መለሰ ዜናዊና ስብሃት ነጋ በመሳሰሉት በዘር ጥላቻ አባዜ የተለከፋ ግለሰቦች በድርጅቻቸው ውስጥ የበላይነት ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ ነበር። መሠረታዊ ማጠንጠኛቸው በኢትዮጵያ ውስጥ ለነበረው የባላባታዊ ሥርዓት ጭቆናዎች ተጠያቂው የአማራ ሕዝብ ነው የሚል ነው። ለዚህም ነው ለትግራይ ሪፕብሊክ ምሥረታም እንቅፋት ሊሆን የሚችለው አማርኛ ተናጋሪው ነው በማለት በኢትዮጵያ ውስጥ ፀረ-አማራ ኃይል እንዲፈጥሩና በአማራው ላይ እንዲዘምቱ ያደረጋቸው። አሁንም ከሃያ ሁለት ዓመት አምባገነናዊ አገዛዝ በኋላ የምናየው ይኼው የፀረ-አማራነት ፖሊሲ በተግባር ሲተረጎም ነው። ይህንንም መርዘኛ የህወሓት ፓሊሲ በየቦታው በፈጠሯቸው ተለጣፊ ጅርጅቶችና ባደራጇቸው የጎሣ ወታደራዊ ኃይሎች አማካኝነት የዘር ማጽዳት ዘመቻውን በስፋት ተያይዘውታል።
ከጥቂት ወራት በፊት በጉራፈርዳ ወረዳ የታየው አሁን ደግሞ በቤኔሻጉል-ጉምዝ አካባቢ በሚኖሩ አማርኛ ተናጋሪ ዜጎች ላይ እየተደገመ ነው። ንብረትን ቀምቶ፤ ነፍሰጡርንና አራስን ሳይቀር አፈናቅሎ ማባረርና የድብደባና የግድያ ወንጀሎች በአማራው ሕዝብ ላይ መፈጸሙ ከበፊቱም የነበረውን ፖሊሲያቸውን ተግባራዊ እያደረጉት እንደሆነ የሚያሳይ ነው። ይህ ዓይነቱ ዘግናኝ ወንጀል በተለያዩ ጊዜያትና አካባቢዎች በተለይም በአኝዋኩ፤ በኦጋዴኑ፤ በኦሮሞው፤ በአፋሩ፤ በሙርሲው …ወዘተ ማህበረሰቦች ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ ተፈጽሟል፤ አሁንም እየተፈጸመ ነው። ህወሓት/ኢህአዴግ ይህንን የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚፈጽመበት ዋናው ምክንያት የፓለቲካ፤ የኤኮኖሚና ወታደራዊ የበላይነቱን ለማስጠበቅ ስለሆነ ለዚህ እኩይ ዓላማው መሳካት እንቅፋት ናቸው ብሎ በሚገምታቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ላይ ወደፊትም ተመሳሳይ ድርጊት ከመፈጸም እንደማይቆጠብ ግልጽ ነው።
ህወሓት/ኢህአዴግና ተላጣፊ ድርጅቶቹ አንድ ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ በመረጠው ቦታ የመኖር፤ የመሥራት በሕጋዊ መንገድ ንብረት የማፍራት፤ ቤተሰብ የመመሥረትና ልጆች የማሳደግ የማይገሰስ የዜግነት ሁለንተናዊ መብቱ እንደሆነና ማንም ፈቃድ ሰጪም ከልካይም ሊሆን እንደማይችል፤ ነፃ ፍርድ ቤቶች ባሉባቸው ሀገሮች በዘር ማጽዳት ወይም በዘር ፍጅት የተሰለፉ ቡድኖችም ሆኑ ግለሰቦች ተከሰው በፍርድ ቤት ቅጣት እንደሚበየንባቸው የተገነዘቡት አይመስልም ወይም ሊቀበሉት አይፈልጉም። የአገር ሉዓላዊነት በሚል ሽፋን ከሕግ ተጠያቂነት ማምለጥ እንደማይቻል ሊገነዘቡት ይገባል። በመሆኑም ማንኛውም ለሀገሩ የሚቆረቆር ኢትዮጵያዊ/ት በሀገራችን ውስጥ እየተካሄደ ያለውን የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀል ለዓለም ኅብረተሰብ እንዲያሳውቀና ዓለምአቀፋዊ የዜና ሽፋን እንዲያገኝ ማድረግ ግዴታ አለበት። እንዲሁም በወንጀለኛ ግለሰቦችና ቡድኖች ላይ መረጃዎችን በመሰብሰብ በዓለምአቀፍ ፍርድ ቤት ክስ መመሥረትም መታለፍ የሌለበት ጉዳይ እንደሆነ ልናሳስብ እንወዳለን።
በመጨረሻም ይህን በአደባባይ የሚፈጸመውን የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀል ለአንዴና ለሁል ጊዜ ለማስቆም የሚቻለው የፖሊሲው አራማጅ የሆነውን አምባገነን አገዛዝ በተባበረው የሕዝብ ክንድ ድባቅ ሲመታ ብቻ እንደሆነ ነው። አምባገነኑ አገዛዝ በዴሞክራሲያዊ አስተዳደር እስካልተተካ ድረስ ይህ እኩይ ተግባር እየተስፋፋ መቀጠሉ የማይቀር ነው፤ የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ቤት የሚያንኳኳበት ጊዜም ሩቅ አይሆንም።
የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ተዋናኞች ባለፈው ሰሞን የኢህአዴግ ዘጠነኛ ጉባዔ ተብዮው ላይ ዓይናቸውን በጨው ታጥበው ስለ ዴሞክራሲ፤ ስለመልካም አስተዳደርና ስለሙስና…ወዘተ በመናገር በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ሲያላግጡና ሲመፃደቁ ተስተውለዋል። “ጽድቁ ቀርቶ በወጉ በኮነነኝ” የሚል ይትባሀል እንዳለ እያስታወስን ድምፃችንን ከፍ አድርገን ለህወሓት/ኢህአዴግ ልንነግረው የምንፈልገው በአምባገነኑ አገዛዝ የሚወራለት ዴሞክራሲውና መልካም አስተዳደሩ ቀርቶ ይህን ዘግናኝ የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀል ባስቸኳይ እንዲያቆም ነው!
ዜጎች መብቶቻቸውን በትግላቸው ይጎናፀፋሉ!
የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት ለዘለዓለም ይኖራል!

ም/ጠ ሚኒስትሩ «እስክንድር ነጋን እንፍታ» አሉ

ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ሰኞ መጋቢት 30 ቀን 2005 ዓ.ም በእነ አቶ እስክንድር ነጋ፣ አንዱዋለም አራጌና ሌሎች ባቀረቡት የይግባኝ ጥያቄ ላይ ዉሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ዙሪያ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ዉስጥ ዉይይት እንደተደረገ ፣ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ መጋቢት 18 2005 ዓ.ም ባቀረበዉ ጽሁፍ ዘግቧል።

 read more http://ethioforum.org/wp-content/uploads/2013/04/eskinder2.pdf

Saturday, April 6, 2013

ለ3ኛ ጊዜ ህትመቱ የተቋረጠበት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ” ከእንግዲህ ከጫካ መለስ ባሉ መታገያ መንገዶች በመጠቀም መብታችን እናስከብራለን” አለ

መጋቢት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-እውቁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ይህን የተናገረው ልእልና ጋዜጣ በመንግስት ጫና እንዳድታተም ከታገደች በሁዋላ ነው። ጋዜጠኛ ተመስገን ” የንግድ ሚኒስቴር በልእልና ጋዜጣ የቀድሞ ባለቤትና በአዲሱ ባለቤት መካከል ህገወጥ የሆነ የስም ዝውውር ተደርጓል በማለት የንግድ ፈቃዱ ” እንዲሰረዝ መደረጉን ተነግሯል።

ፍትህ ጋዜጣ በህገወጥ መንገድ እንዳይታተም ከተደረገ በሁዋላ፣ ጋዜጠኛው አዲስ ታይምስ መጽሄትን ከሌላ አሳታሚ ላይ በመግዛት ለተወሰኑ ሳምንታት ሲያሳትም ቆይቷል። መጽሄቷ በተመሳሳይ መንገድ እንድትዘጋ ከተደረገ በሁዋላ፣ ጋዜጠኛ ተመስገን እንደገና ልእልና ጋዜጣን ከሌላ አሳታሚ ላይ በመግዛት ስራውን ለመስራት ሞክሮ ነበር። ይሁን እንጅ ከ100 ሺ ብር በላይ በሆነ ወጪ የገዛው ጋዜጣ ከመንግስት በተላለፈው ጫና እንዳይታተም በድጋሜ ታግዶበታል

ተመስገን በራሱ ስም ፈቃድ አውጥቶ መስራት ከተከለከለ፣ ከእንግዲህ ወዲያ ስለሚኖረው አማራጭ ሲጠየቅ፣ “ያለኝ አማራጭ ከሲቪክ ተቋማት ጋር በመተባበር ፣ ከጫካ ትግል በመለስ ያሉትን የሰላማዋ ትግል አማራጮች በመጠቀም ፣ አስገዳጅ ሁኔታ በመፍጠር መብታችንን እናስከብራለን” ብሎአል።

ጋዜጠኛ ተመስገን ሰሞኑን በገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች ከፍተኛ ወከባ ሲደርስበት እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል። ተመስገን፣ ከ106 ያላነሱ ክሶችም እንዳሉበት ይታወቃል።

ወያኔ በአማራ ተወላጆች ላይ የጀመረውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ እንደቀጠለ ነው

 
ወያኔ ለአማራ ህዝብ፤ ባህልና ታሪክ ያለዉን ጥላቻ ከተራ ጥላቻ አልፎ በተግባር አማራዉን ወደ ማጥቃት ዘመቻ አደገ እንጂ ለአንድም ቀን ቀንሶ አያውቅም። አማራው እንደ ሰው ልጅ የመኖር መብቱ፣ ስብእናው ተገፎ ከቀየው፣ ከመንደሩ የአፈራውን ንብረትና ገንዘብ እየተቀማ መባረሩ፣ መሰደዱ፣ እንግልቱ ሁሉ የወያኔ የበቀል እርምጃ ነው።

በአሶሳ፤ በደኖና በአርባጉጉ ውስጥ አማራ በመሆናቸዉ ብቻ ህጻናት፤ሴቶችና አረጋዉያን በግፍ ተገድለዋል። ባለፈዉ አመት በደቡብ ክልል ጉራ ፈርዳ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ለረጂም አመታት ከአካባቢዉ ኢትዮጵያዊ ወገናቸው ጋር ተግባብተዉ ይኖሩ የነበሩ የአማራ ብሄረሰብ አማራ በመሆናቸዉ ብቻ ለአመታት ያፈሩትን ንብረት ይዞ የመሄጃ ግዜ እንኳን ሳይሰጣቸዉ አከባቢዉን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለቅቀዉ እንዲወጡ እንዲፈናቀሉ ተደርጓል።
ከመጋቢት ወር መጀመሪያ ጀምሮ ወያኔ በአማራዉ ህዝብ ላይ አዲስና ሰፋ ያለ የጥቃት ዘመቻ ጀምሯል። በደቡቡ የአገራችን ክልል በጉራፈርዳ የጀመረዉን አማራውን ነጥሎ የማጥቃትና የማንገላታት ዘመቻ አሁን ደግሞ በሰሜን ምስራቅ የአገራችን ክፍል በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቀጥሏል።

የቅርብ ግዜው ደግሞ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው በምእራብ ጎጃም ዞን በፍኖተሰላም ከተማ ሜዳ ላይ ወድቀው የሚገኙት አማራ አርሶደአሮች የድረሱልን ጥሪ ማሰማታቸውና፤ ብሄረ አማራን እወክላለሁ ባዩ ብአዴን (የህወሃት ቡችላ) ጠበንጃ ደቅኖብን ወደ መጣችሁበት ተመለሱ ከዚህ ጥፉ ሲል አዋከበን፤ የወገን ያለህ ድረሱልን የት እንግባ ልጆቻችን የአውሬ ራት ሆኑ ሲሉ ስቃያቸውን አሰምተዋል። በርግጥ የህወሃት ተለጣፊው ብአዴን ሆዳቸው ስለሞላ ህሊናቸው ታውሮ ይህ በደል የሰው ልጅን የማጥፋት ሴራ መሆኑን እና በዘር ማጥፋት ወንጀል እንደሚያስጠይቅ የተረዱ አይደሉም።
ሰሞኑን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ለረጂም አመታት ከአካባቢዉ ህብረተሰብ ጋር ተቀላቅለው ይኖሩ የነበሩ አያሌ የአማራ ብሄረስብ ተወላጆች ያፈሩትን ንብረት ለመሰብሰብ እንኳን ግዜ ሳይሰጣቸዉ የኔ ብለው ከሚጠሩት የመኖሪያ ቦታቸዉ እንደባዳ እየተገፉ እንዲወጡ ሲደረጉ በአንጻሩ በባህርዳር ከተማ ብአዴን የቱባ ባለስልጣናቱን ከርስ ለመሙላት የክልሉን ህዝብ ጮኸት ጀሮ ዳባ ብሎ ሽርጉድ ሲል የነበረ መሆንን ያገናዘበ ኢትዮጵያዊ ቁጭት በርካታ ነው ።

የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ፡ እርግጥ ነው ይህን ዘረኛ ቡድን ለማስወገድ በሚደረገው መራራ ትግል ሂደት ውስጥ በደልና ሰቆቃው እየበዛ እንደሚሄድ ቢታወቅም ተባብረን ከታገልነው ግን ይህን ልናሳጥረው እንችላለን። አለበለዚያ ግን እስከ መቼ ነው ወገኖቻችን በትውልድ መንደራቸው የሀገር ውስጥ ጥገኛ ጠያቂ የሚሆኑት? የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆች ከቀያቸው የተባረሩት በኢትዮጵያዊ ዜግነታቸው ነው።

ግንቦት 7 ንቅናቄ ይህ የወያኔ ስርአት እስካልተወገደ ድረስ በአማራው የተጀመረው ጭፍጨፋ፣ እንግልት፣ ስደት፣ መከራና ግድያ፤ ህወሃት በሌሎችም አጠናክሮ ይቀጥልበታል ብሎ ያምናል። ስለዚህ ምን እንጠብቃለን በወያኔ ያልተበደለ፣ ያልታሰረ፣ ያልተደበደበ፣ ያልተሰደደ፣ ያልተፈናቀለ፣ ያልተራበ፣ ያልተዋረደ፣ ያልተገደለ ህዝብ የለም። የኢትዮጵያ ህዝብ በወያኔ ጨካኝ ስርአት አማካኝነት በጨለማ ሂዎት ውስጥ እየኖረ ነው።

የሀገራችን ወጣት ሆይ፡ ወጣትነት ሀገር ተረካቢ፣ ባላደራ፣ ለውጥ ፈላጊ፣ ሀገሩን ጠባቂ ነው። ወገንህ ሲገረፍ ሲንገላታ ሲሰደድ ማየት እና ከንፈር መምጠት እሰከ መቼ ይሆን? ሰቆቃቸው፣ ቁስላቸው የድረሱልን ዋይታቸው መቼ ይሆን ተሰምቶን እንባቸውን በአለንላችሁ የወገን ደራሽነት የምንደርስላቸው? የምንጠርግላቸው? ግንቦት 7 ትግሉን የማቀጣጠያ ሰአት ጊዜው አሁን ነው ይላል። ወጣት፣ አዋቂ፣ ጎልማሳ፣ ሽማግሌ፣ ዘር ጾታ ቋንቋ ሳይለየን ወያኔን ለማስወገድ በሚደረገው ትግል ምላሽ ስጡ፣ ተቀላቀሉ። በኢትዮጵያ የጠቆረውን ጨለማ በብርሃን መተኪያ ጊዜ ዛሬ ነው። ይህ ትውልድ የታሪክ ባለእዳ አይሁን።

በወያኔ ውስጥ ያላችሁ ይህ በደል ና ሰቆቃ የሚሰማችሁ ወገኖቻችን የውስጥ አርበኛ የምትሆኑበት ሰአት ላይ ናችሁ። ራሳችሁን እና ወገናችሁን ከቀን ጅብ ስርአት አድኑ። ከነጻነት ማግስት በኋላ ከሚመጣባችሁ ከየት ነበራችሁ ክስ ለመጽዳት ከነጻነት ታጋዮች ጋር አብሩ። ወያኔ ለ21 አመታት ህዝቡን ለማጋጨትና ለማባላት የሚያደርገው ስልት መሆኑን ተረድታችሁ የውስጥ ታጋዮች መሆናችሁን ማሳያ ጊዜው አሁን ነው። አሊያ ግን በአማራው ህዝብና በሌላው ማህበረሰብ ላይ እየተፈጸመ ባለው እጅግ አስከፊ ወንጀል በግልም ሆነ በቡድን፣ የንጹሀንን ደም እያፈሰሳችሁ ያላችሁ ወንጀለኞችና ተባባሪዎች ተብላችሁ፣ ከያላችሁበት ታድናችሁ ለፍርድ እንድትቀርቡ ንቅናቂያችን የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት በግልጽ እንድታውቁት ይገባል።

የሀገራችን ህዝብ ሆይ፡ ዛሬ ኢትዮጵያን ከገባችበት ዘረኛ መቀመቅ ስርአት ውስጥ የሚያወጣት ብቸኛ መፍትሄ፣ ፍርሃታችንን በጥሰን በተባበረ ጉልበትና ድፍረት ወያኔን በሚገባው ቋንቋ ስናናግረው፣ ታግለን ስናስወግደው ብቻ ነው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ኩራትና ክብርን፣ ተሳስቦና ተፈቃቅሮ፣ ተከባብሮና ተቻችሎ የመኖር ጸጋን የምናመጣው። ስለሆነም በየትኛውም አቅጣጫ የሚደረገውን የነጻነት ጉዞ ትግል ትቀላቀሉ ዘንድ ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ጥሪውን በድጋሜ ያቀርባል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!
 

Friday, April 5, 2013

ዳምጠው ወያኔ/ኢሕአዴግና አፈና በኢትዮጵያ

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም
መጋቢት 2005
በቀልድ ልጀምር፤ አንድ ጮሌ የአስመራ ልጅ የእኔ ተማሪ ነበር፤ አንድ ጊዜ የጂኦግራፊ ክፍል ተማሪዎች አንድ ጃፓናዊ አስተማሪ ለመሸኘት ግብዣ አድርገው ነበር፤ በግብዣው ላይProfessor Mesfin Woldemariam is one of Ethiopia's well-known intellectuals የጠቀስሁት ነገረኛ የአስመራ ልጅ (የአስመራ ልጅ የምለው ላርቀው ፈልጌ እንዳይመስላችሁ፤) በአስተማሪዎች ላይ ቀልድ ያሰማ ነበረ፤ ስለኔ ሲናገር፤– መስፍን ወልደ ማርያም የቢሮውን በር ሁልጊዜ ክፍት አድርጎ የሚቀመጠው ለምንድን ነው? ይልና እሱው ሲመልስ፣ በሩን የመዝጋት ሌሎች ዘዴዎች ስላሉ ነዋ! ቀልዱ ለእኔ እንደገባኝ ፊቱን ስለሚያኮሳትር ሰዎች በሩን አልፈው እንዲገቡ አይጋብዝም ማለት ነው፤ በዚያን ጊዜ እኔም እየሳቅሁ እንደተናገርሁት የሱን ፈሪነት በእኔ መልከ-ክፉነት መደበቁ ነው፤ ቀልዱን ያመጣሁበት ምክንያት ወያኔ ለነጻነት የቆመ መስሎ ለመታየት ሳንሱር የሚባለውን የሚታተሙ ጽሑፎችን በቅድሚያ የማስፈተሽ ቀንበር በሕግ አነሣ፤ ሰዎች እውነት መስሎአቸው ቅሪታቸውን እያነጠፉ ጋዜጦችና መጽሔቶችን ማሳተም ጀመሩ፤ ጋዜጦች እንደአሸን ፈሉ፤ መጻሕፍት ታተሙ፤ ጥቂት ቲያትሮችም ታዩ፤ ዘፈኖች ተመረቱ! ነገር ግን የግል ራድዮና ቴሌቪዥን እንዲሁ የብዙ ሰዎች ሕልም ሆኖ ቀረ፤ ብዙ ሰዎች ብዙ ገንዘብ ከሰሩ፡፡
በሕዝቡ ዘንድ የነጻነት ፍቅር እየለመለመ መሄዱን ሲያየው ወያኔ ሆዱ ተንቦጨቦጨ፤ እንቅልፍ እያጣ ሄደ፤ ቀስ በቀስ ግራ እጁን በሕገ መንግሥቱ ላይ ጭኖ በቀኝ እጁ ጎራዴውን መዘዘ፤ ቀስ በቀስ፣ አንድ በአንድ የተለያዩ መብቶችን ለማስከበር የቆሙትን አንቀጾች ሁሉ አስተኛቸው፤ በተገላቢጦሽ መብቶቻቸውን የሚጠይቁ ሰዎችን፣ ስለመብቶች የሚጽፉ ሰዎችን፣ መብቶችን ከጥቃት ለመከላለከል የቆሙ ድርጅቶችን፣ ከወያኔ አመለካከት ውጭ የሆኑ ሰዎችን ሁሉ መንግሥት በመገልበጥ ሴራ፣ ወይም በሽብርተኛነት እየያዘና እያሰረ በመክሰስና በማስፈረድ የማፈን እርምጃዎችን ሁሉ አጠናከረ፤ አንዲህ ያለውን አፈና ማየትና መስማት እየተለመደ መጣ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ በሽብር ስም የሚካሄደው ጥቃትና የሰብአዊ መብቶች ረገጣ እንኳን እኛንና በሽብር ላይ ዓለም-አቀፍ ጦርነት ያወጁትን አሜሪካኖችንም እያስደነገጠ ነው፤ የዓለም የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች ሁሉ፣ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንን ጨምሮ በምሬት እየጮሁ ነው፤ ጋዜጠኞች፣ የሠራተኞች ማኅበሮች፣ የፖሊቲካ ቡድኖች ጭጭ እንዲሉና ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ መንገዱ ሁሉ እየተዘጋባቸው ነው፤ በትግራይ አብርሃ ደስታ የሚባል ወጣት የአፈናውን ድቅድቅ ጨለማ ጥሶ በመውጣት ስለጻፈ አፈናና ማስፈራራት ደረሰበት፤ ‹‹ጭቆናን ስላጋለጥሁ የሕዝብ ጠላት ተባልሁ›› ይላል፤ በቅርቡ እንኳን ሰማያዊ ፓርቲ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል የጠራው የራት ግብዣ እንግዶቹ በተጠሩበት ሰዓት ተሰርዞ ተመልሰዋል፤ ለግራዚያኒ ስለሚሠራው ሐውልት የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ የሞከሩ ኢትዮጵያውያን ታሰሩ፤ እነዚህን ኢትዮጵያውያንን ያሰሩትን ምን እንላቸዋለን? እንግዲህ በኢትዮጵያ ውስጥ ምን የማያሳስር ነገር ሊኖር ይችላል?
የአፈናውን ነገር እነእስክንድር ነጋ፣ እነርእዮት ዓለሙ፣ ውብሸት ታየ … ይመሰክራሉ፤ ለመሆኑ ወደዘጠና ሚልዮን የሚሆን ሕዝብ ያላት አገር ስንት ጋዜጣ፣ ስንት የራድዮ ጣቢያ፣ ስንት የቴሌቪዥን ጣቢያ አላት? ኤርትራ ሦስት የራድዮ ጣቢያዎችና ስድስት ጋዜጦች፣ ጂቡቲ ሦስት የራድዮ ጣቢያዎችና አምስት ጋዜጦች፣ ኬንያ አሥራ ስምንት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች፣ ከሠላሳ በላይ የራድዮ ጣቢያዎች፣ ዘጠኝ ጋዜጦች አሉት፤ ትናንት የተፈጠረው ደቡብ ሱዳን እንኳን ሁለት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች፣ አምስት የራድዮ ጣቢያዎች፣ አምስት ጋዜጦች አሉት፤ ኢትዮጵያ ያላትን እናውቃለን፡፡
ሰንጠረጅ አንድ
የኪስ ስልክ (ሞባይል) እድገት
እ.አ.አ.2008200920102011
አገሮች ሞባይል ለ100 ሰዎች
በደቡብአፍ
91
93
100
127
ኢትዮጵያ
2
5
8
17
ኬንያ
42
49
62
65
ሱዳን
29
36
42
56
ኤርትራ
2
3
4
4
ሶማልያ
7
7
7
7
ጂቡቲ
13
15
19
21
ምንጭ፡- የዓለም ባንክና የዓለም ቴሌኮሚዩኒኬሽን ድርጅት
የአፈናውን ልክ በሁለቱ ሰንጠረጆች ማየት ይቻላል፤ ለንጽጽር የቀረቡት አገሮች የአፍሪካ ቀንድ ጎረቤቶች ናቸው፤ ነገር ግን ላቅ ያለ ግብ ለማመልከት ደቡብ አፍሪካ ተጨምሮአል፤ ለምሳሌ የኪስ ስልኩን ብንወስድ በደቡብ አፍሪካ በመጀመሪያው ዓመት እአአ በ2008 ለአንድ መቶ ሰዎች 91 የኪስ ሰልኮች ነበሩ በ2011 ለመቶ ሰዎች ወደ አንድ መቶ ሃያ ሰባት ደረሱ፤ ይህም አንዳንድ ሰዎች ከአንድ በላይ የኪስ ስልክ አላቸው ማለት ነው፤ከጎረቤቶቻችን መሀል ኬንያ በ42 የኪስ ስልኮች ለአንድ መቶ ሰዎች ጀምሮ በአራተኛው ዓመት ላይ ወደስድሳ አምስት ማደጉ ይታያል፤ ሱዳንም ከሃያ ዘጠኝ ተነሥቶ በአራተኛው ዓመት ወደሃምሳ ስድስት አድጎአል፤ ጂቡቲም ከ13 ጀምራ ወደ 21 ገብታለች፤ ትልቅዋ አገር ኢትዮጵያ በሁለት ጀምራ ከአራት ዓመታት በኋላ ለመቶ ሰዎች አሥራ ሰባት የኪስ ስልኮች አስቆጥራለች፤ በአፍሪካ ቀንድ በኪስ ስልክ የመጨረሻውን ዝቅተኛ ቦታ የያዘች አገር ትልቅዋና በዓመት ከአሥራ አንድ ከመቶ በላይ እድገት ታስመዘግባለች የሚባልላት ኢትዮጵያ ነች፡፡
ሁለተኛው የአፈናው መገለጫ የኢንተርኔት አገልግሎት ነው፤ በኬንያ በ2008 ከአንድ መቶ ሰዎች ውስጥ የኢንተርኔት ተጠቃሚ የነበረው 42 ሲሆን በ2011 ወደ ስድሳ አምስት አደገ፤ በኤርትራ ከ4 ወደ 6 ሲያድግ፣ በኢትዮጵያ አላደገም፡፡
እነዚህ ሁለቱም የመረጃና የእውቀት መተላለፊያ ዘዴዎች ለማናቸውም እድገት ቁልፍ መሆናቸው አያጠራጥርም፤ በተለይም ለነጻነትና ለእውቀት እድገት አስፈላጊዎች በመሆናቸው ለአምባ-ገነኖች እንደጠላት መሣሪያ የሚቆጠሩ ናቸው፤ ችግሩ እውቀት አለነጻነት አይገኝም፤ ነጻነትም አለእውቀት አይገኝም፤ እውቀትና ነጻነት ተነጣጥለው አይገኙም፤ ስለዚህም ነጻነትን ለመግደል የፈለገ እውቀትንም ይገድላል፤ ስለዚህም አምባ-ገነኖች ሞባይልንና (ተንቀሳቃሽ ወይም የኪስ ስልክ) ኢንተርኔትን ማፈን ዋና ተግባራቸው ያደርጉታል፤ በዚህም ምክንያት ሕዝቦቻቸውን በድንቁርና ያዳፍናሉ፤ በደሀነት ያሰቃያሉ፤ በዘመናችን ዋናው የአውቀት መተላለፊያ ኢንተርኔት ነው፡፡
ሰንጠረጅ ሁለት
የኢንተርኔት አገልግሎት እድገት
እ.አ.አ.2008200920102011
አገሮችየኢንተርኔት አገልግሎት ለመቶ ሰዎች
ደቡብአፍ8.510.118.120.9
ኢትዮጵያ0.50.50.81.1
ሱዳን10.2
ኤርትራ4.14.95.46.2
ሶማልያ1.11.21.3
ጂቡቲ2.34.06.57.0
ደቡብ አፍሪካ የገባው ለንጽጽር ነው፤
ምንጭ፡- የዓለም ባንክና የዓለም የቴሌኮሚዩኒኬሽን ድርጅት
የኢንተርኔት አገልግሎት በቅርቡና በርካሽ ወይም በነጻ ከተገኘ ብዙ ሳይለፉ ምንም ዓይነት እውቀት ሊገኝ ይቻላል፤ በሠለጠኑት አገሮች በአንዳንድ ቡና ቤቶች ነጻ የኢንተርኔት አገልግሎት ይገኛል፤ በኢትዮጵያ ውስጥ በኢንተርኔት ለመጠቀም ደህና ገቢ ያለው መሆን ያስፈልጋል፤ከደሀነት ለመውጣትም ሀብታም መሆን ያስፈልጋል!

Fate of stranded Ethiopian migrants in Yemen

Fate of stranded migrants in Yemen ‘very grim’
GENEVA: The plight of thousands of migrants stranded in Yemen after trying to reach Saudi Arabia and the Gulf has
Ethiopian migrants sleep out in the open near a transit centre
Ethiopian migrants sleep out in the open near a transit centre where they wait to be repatriated in the western Yemeni town of Haradh, on the border with Saudi Arabia, March 29, 2012. REUTERS/Khaled Abdullah
reached desperate proportions, the International Organisation for Migration (IOM) warned yesterday.
“The situation of migrants in Yemen is very grim,” IOM spokesman Jumbe Omari Jumbe said.
Yemen has seen a spike in the number of migrants and refugees from the Horn of Africa who risk their lives to cross the Red Sea in smugglers’ boats only to find themselves blocked at the Saudi border.
Numbers have doubled from around 53,000 in 2010 to more than 107,000 last year. Ethiopians make up the overwhelming majority, but others hail from countries such as Somalia and Eritrea.
“In Haradh town, which the migrants see as a gateway to Saudi Arabia and beyond, thousands of migrants roam the streets and sleep rough in the open with no money for food or medicine,” Jumbe said.
“Many migrants visiting IOM’s offices have been rescued from unscrupulous gangs of kidnappers, traffickers and smugglers and are injured, some with broken limbs. Criminal gangs are also reportedly trading in human organs,” he added.
In addition, the hospital mortuary in the northern Yemen town of Haradh is now filled with the unclaimed bodies of migrants, he said.
Funding shortages have forced the IOM to curtail a programme providing free meals to stranded migrants in Haradh from 3,000 a day to just 300 – with only women, the elderly and unaccompanied youngsters now receiving food.
The lack of cash has also forced the organisation to suspend a voluntary repatriation programme which provides migrants with flights home.
The IOM is also working in Ethiopia to try to discourage would-be migrants from making the Red Sea crossing.
“But people are desperate. And because of that desperation, people are sometimes willing to risk everything,” Jumbe said.

All of us can be Part of the Solution

by Abebe Kassa, April 05,2013
To sell Ethiopian agricultural lands to foreign investors, the weyane regime continued with increasing vigor its policy of forced eviction of ethiopians from their own land. The number of evicted people and their sufferings are growing. As Ethiopians hearing the news from different medias the anger is flowing from everywhere. Often news about atrocities committed by the weyane regime ends up being a week or some weeks long concern. It has to be be changed at some point. The anger has to be transformed in to meaningful action. The regime has to feel these atrocities will have consequences.

The recurrent questions among Ethiopians when we hear this kind of atrocities commited by the weyane regime is: what can we do to stop this from happening again? what is the solution? The questions often followed by demand for opposition forces to unite and make formidable force to challenge the regime. Since 2005 the call is not bearing fruit as we wanted it. In 2005 election Kinjit and Hibret did that in Ethiopia when opportunity arised and shaken the regime to its core. Ofcourse many people yearn to see that being repeated to bring back vitality to the struggle. Currently the opposition being fragmented and weyane controlling almost all the resources and institutions in Ethiopia might appear for some weyane is invincible. Gene sharp who wrote extensively on resistance against dictatorship pointed out that the perception of dictators invulnerability against powerlessness feelings by the opposition makes effective resistance unlikely. The wrong perceptions impede effort. In Ethiopian struggle one factor that is oppositions working together can alter that power equation significantly. Many are demanding it too. We know even the news that oppositions are working together will rattle the weyane camp. The challenge is how to achieve that.

We can’t leave the responsibility only for political parties and civic organizations leaders to unite the opposition force and bring the desired change we want. I believe the way is those of us who wants regime change in Ethiopia to involve in the struggle actively. We can be member or supporter of a political party or civic organization. Political parties and civic organizations are not in short supply and most of us can get the choice of our own. No waiting game while we can be part of those who make it happen. We can play part in shaping the struggle. we can not continue to be bystanders till the unity we demand arrives. We can search the solutions while working in the organizations framework. We might start participating in different organizations however as the struggle goes its course and with time we might meet at some point like tributaries merge together to form a river. Intra-organizations negotiations and discussions will bring the ways to cooperate and work together. This way we can accelerate the disintegration of weyane regime. If we involve and contribute what we can in the effort to bring oppositions to work together, we will dismantle the weyane regime for good and lay the foundation of democratic Ethiopia.
To act is to involve in the struggle.

የ እስክንድር ወንጀሉ መምከሩና ኣቅጣጫ ማሳየቱ ብቻ ነው

(ገለታው ዘለቀ)

eskinder_opt
ኣንድ ጊዜ ኣባባ ተስፋየ ከዚያ ከሚያምርባቸው የ ልጆች ክፍለ ጊዜ ዝግጅታቸው ጠፉብኝና ኸረ የት ገቡ? ብየ ኣንዱን ጠየኩ።
“ኣልሰማህም እንዴ ?”
በፍጹም ምን ሆኑ? ደንገጥ ብየ እንደገና ጠየኩ።
 
ያ ሰው እየሳቀ “ባለፈው ጊዜ ኣዲሱ ኣመት የሰላምና የእርቅ ያድርግልን ብለው በመናገራቸው የመንግስት ሰዎች ማን ሲጣላ ኣዩ? ብለው ኣባረሩዋቸው እኮ!” ሲለኝ ለደቂቃዎች እንደዚያ የሳቅኩበት ጊዜ ትዝ ኣይለኝም። የሁለታችንም ሳቅ ካለቀ በሁዋላ እውነተኛው ስሜት ሲመጣ ደሞ ያስለቅሳችሁዋል። ነገሩ እውነት መሆን ኣለመሆኑን ኣጥብቄ ኣልጠየኩም፣ ለነገሩ ከዚያ ቀን በሁዋላም ከብዙ ሰው ይህንኑ ሰማሁ። ነገሩ በትክክል ሆነም ኣልሆነም ያ ሁሉ ሰው መንግስት እንደዚያ ሊያደርግ ይችላል ብሎ ማሰቡ ራሱ ነገሩ መሆኑን ኣለያም ሊሆን መቻሉን ያሳያል። በዚያች ኣገር ምን የማይሆን ኣለና።
 
በዚህ ስደነቅ ስደመም ደሞ ኣንዴ እንዲህ ሆነላችሁ። እንዲሁ ኣንድ ሻይ ቤት ተቀምጨ ወጪ ወራጁን እማትራለሁ። በመሃል ኣንድ ሰው ሳምሶናይት የሚባለውን ቦርሳ ጠልጠል ኣርጎ ገባና ወዲያ ወዲህ ካየ በሁዋላ የኔን ጠረንጴዛ ተጋርቶ ለመቀመጥ በትህትና ጠየቀኝ። ወንበሩን ሳብኩለት። እንደኔው ሻይ በሎሚ ኣዞ ቁጭ ኣለ። ጥቂት ቆየት ካለ በሁዋላ ያቺን ቦርሳውን ከፈተና ኣንዲት ጋዜጣ ኣውጥቶ ዘረጋጋና ማንበብ ጀመረ። ብዙም ሳይቆይ ሁለት ሰዎች ወደ ሻይ ቤቱ ገቡና ከኛ መቀመጫ ትይዩ ተሰየሙ። ኣንዱ የቀኝ እግሩን ቀጥ ኣርጎ ዘርግቶ ነበር የተቀመጠው። በሁዋላ ኬክ ሊመርጡ ሲነሱ እንደሚያነክስ ሳይ እግሩ ኣርቴፊሻል መሰለኝና ኣለ ኣይደለም ኣሳዘነኝ። የሚጠጣውን እየጠጡ ኬካቸውን እየበሉ ያወካሉ። እኔና ከፊቴ ያለው ሰውየ ግን ጸጥ ብለናል። ትንሽ እንደቆየ ያቺን ጋዜጣውን በሽንጡዋ ሸመለለና ወደ ቦርሳው ከተተ። ደሞ ወዲያው ኣጨበጨበና ሂሳብ ከፈለ።
 
እኔም እስካሁን ባናወራም ኣብርን ለትንሽ ሰኣትም ቢሆን ባንድ ጠረንጴዛ በልተን ጠጥተናል ዝም ኣይባልም ብየ ነው መሰለኝ ቻው ለማለት ምንም ኣልቀረኝም።በመሃል ያ ያነክሳል ያልኩዋችሁ ሰውየ ድንገት ወደኛ ዞረና
“ምን ኣልክ ኣንተ? ምን ኣልክ? ድገመው እንጂ…… ልብ በሉ… ሰዎች ልብ ኣርጉ.. ምን ኣልክ ኣንተ?…” እያለ ይጮሃል። ሁላችንም ተደናገጥን። ያ ከኔ ጋር ጠረንጴዛ ተጋርቶ የነበረው ሳምሶናይቱን እንዳንጠለጠለ “ኸረ እኔ ምንም ኣልወጣኝም ጌታየ ምን ነካዎት” ይላል ኣስር ጊዜ። ከዚያ ከሚያነክሰው ጋር ያለው ሰውየም ኣብሮ ያጫፍራል። በሁዋላ ይሄ ከኔጋር የነበረው ሰው መንጨቅ ብሎ ሲወጣ ሁለቱም ተከተሉትና ጭቅጭቁ ከውጭ ቀጠለ።
 
ያው መቼም ሃይ ሃይ ማለት ያገር ባህል ነውና ወደ ውጭ ወጥቼ ኸረ እሱ ምንም ኣላለም ፣ ምንም ሲል ኣልሰማሁትም ተረጋጉ እያልኩ ለመምከር መቼም ያቅሜን ሞከርኩ።
 
ያ የሚያነክሰው እንባው ሁሉ የመጣ ይመስላል። ይገርማል ዋሽቶ የሚያለቅስ ሰው ቢገጥማችሁ ምን ትላላችሁ?
“እንዴት ትሰድበኛለህ……” እያለ ሲሙዋገት ጓደኛውን ጠጋ ብዬ እናገላግላቸው እባክህ ምን ኣለ? ምንም ኣላልም እኮ ኣልኩት።
“የለም የለም እኔ ራሴ ሰማሁት እኮ ወራዳ ነው ሽባ ብሎ ሰደበው እኮ”
ደነገጥኩና መቼ? ብየ ጠየኩ::
 
ወደዚህኛው ሰውየ ዞሬ ትተዋወቃላችሁ እንዴብዬ ጠየኩ::
“በፍጹም ኣንተዋወቅም ኣለ” ግራ የተጋባው ባለ ሳምሶናይቱ ፈጠን ብሎ
“ሂሳብ ከከፈለ በሁዋላ ድምጹን ከፍ ኣርጎ እኮ ነው የሰደበው”
በውነት ግራ ግብት ኣለኝ። ሁዋላ ላይ ይሄ የሚያናግረኝ ሰው ስልኩን ኣወጣና ኣንድ ሁለት ቁጥሮችን ነካካና ወደዛ ዞር ብሎ ጥቂት ኣወራ መሰለኝ። ወዲያው እንደተመለሰ ኣንድ ፖሊስ መጣና ያንን ባለ ሳምሶናይት
“ቅደም ኣለው።
በዚህ ጊዜ ወደ ፖሊሱ ጠጋ ብዬ ምንም እኮ ኣላለም እኔ እዚህ ነበርኩ
ምንድነው ችግሩ ለማለት ሞከርኩ። ፖሊሱ በግንባሩ ጥሩ ኣርጎ ገረፈና ኣስቆመኝ። ባለ ሳምሶናይቱ እንዲሁ “ምን ኣጠፋሁ” እንዳለ ይነዱት ጀመር። ሁኔታው ገርሞኝ ነበርና ባጭር ርቀት መከተል ጀመርኩ። የሚገርማችሁ ያ ቅድም ቀኝ እግሩን ይጎትት የነበረው “ሽባ” ተብየ ተሰድቢያለሁ የሚለው ሰውየ ኣሁን በግራው ማንከስ መጀመሩን ትኩር ብዬ ኣስተዋልኩና የሆነ ነገር እየሆነ እንደሆነ ገባኝ። ብዙም ሳልርቅ ወደ ሁዋላየ ሂሳቤን ለመክፈል ተመለስኩ። ወደ ሻይ ቤቱ በር ስቃረብ ኣንዱ “ወሰዱት ኣይደል?” ኣለኝ:: ኣዎ ወሰዱት ኣልኩና ግን ምንም ኣለማጥፋቱን ኣስረግጨ ነገርኩት። ጥቂት ኣየኝና “ወንድሜ ተጠንቀቅ ከዚህ ከሚያነክሰው ጋር ያለው ሰውየ የነሱ ጆሮ ነው የተለያየ ልብስ እየለበሰ ሲሰልል ነው የሚውለው ተነቅቶበታል” ኣለኝ። እኔም ወዲያው ጠርጥሬ ስለነበረ ገባኝ። እንግዲህ ያን ሰው በዚህ ርካሽ ስራቸው ኣወናጅለው የሆነ ነገር ኣርገውታል ማለት ነው።
 
ባለፈው ጊዜ ግራዚያኒን ለመቃወም ሰልፍ ወጥተው ከነበሩት መካከል ኣንዱ በኢሳት ቴሌቪዥን ኢንተርቪው ተደርጎለት ሲናገር ልብ ይነካል። ሲቪል እየለበሱ መገናኛ እየያዙ እንዴት የስነ ልቡና ጫና እየፈጠሩ እንደሆነ ገለጸ። ኑሮ ኣይደለም የምንኖረው ኣለ። ያሳዝናል። ሃሳብን መግለጽ ጥቂት ኣስተያየት መሰንዘር በስነ ልቡናና በኣካል የሚያስቀጣ ነገር የሆነባት ሃገር ናት ኢትዮጵያ።
መነሻየኮ ስለ እስክንድር ነጋ ነው። ይህን ያመጣሁት በእንዲህ ባለ ኣገር፣ እስክንድርን የመሰለ ፖሊሲ የሚያመነጭ፣ የሰባዊ መብት እንዲከበር ለማድረግ የሚታገል ሰው ስንት ስነ ልቦናዊ ቅጣት እንደሚቀበል ለመገመት እንዲያስችለን ነው ።
 
እስክንድር የታሰረበትን ምክንያት ኣለም ኣውቆታል። እስክንድር የታሰረው በውስጡ ያለው የእኩልነትና የፍትህ ራእይ እንቅልፍ ኣልሰጥ ስላላቸው ነው። ያንን በገቢ ኣለመመጣጠን የሚሰቃየውን ህዝብ እህል በልቶ እኩልነት ሰፍኖ ማየት የሚፈልግ ሰው መሆኑ ነው የ እስክንድር ሃጢያቱ።እስክንድር ቅንና ርህሩህ ነው። የጻፋቸው ጽሁፎች ዋቢዎች ናቸው። የሱ ወንጀል መምከሩ፣ ኣቅጣጫ ማሳየቱ ብቻ ነው።
 የነ ርእዮት ኣለሙም ወንጀል ይሄው ነው። መናገር፣ መምከራቸው ነው ወንጀላቸው።
ግን እውነት ሊሞት ይችላል። መሞት ብቻ ኣይደለም ሊቀበርም ይችላል። ግን ደሞ እውነት መቃብር ፈንቅሎም የመነሳት ሃይል ኣለው። መንግስት ይህን መረዳት ኣለበት።
 
እግዚኣብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ
geletawzeleke@gmail.com

Thursday, April 4, 2013

“አይቴ ብሔሩ ለአማራ . . . የአማራ አገሩ ወዴት ነው?” ኢትዮጵያ አይደለምን?


(ኤፍሬም እሸቴ – www.adebabay.com)፦ በንግግርም ይሁን በጽሑፍ ለማንሣትም ሆነ ለመጥቀስ፣ ለመወያየትም ሆነ ለመከራከር ከማይመቹኝ (discomfort እንዲል ፈረንጅ) የኢትዮጵያ ርዕሰ ጉዳዮች ሁሉ ዘርን፣ ብሔረሰብን የተመለከተው ዋነኛውና አንዱ ነው። ጉዳዩ በዕለት ተዕለት የአገራችን ሕይወት ውስጥ ወሳኙ እና በሁነኛ መልክ ማኅበረሰባዊ ማንነታችንን እየበየነ እንዳለ እያወቅኹም እንዲህ እንደ አሁኑ በአደባባይ ለመውጣት ግን ብዙም አይቀለኝም። ምክንያቱ ሌላ ምንም ሳይሆን ጉዳዩ ያለው ስሱነት (sensitivity) ነው። አሁን ግን ላልፈው አልቻልኩም። አይገባምም። ለምን?
መነሻ
ከአማራ ክልል ወደ ቤኒ-ሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያሶ ወረዳ ተጉዘው የከተሙ በርካታ ሰዎች በወረዳው ባለሥልጣናትና ፖሊሶች፤ ሰብአዊ መብታቸው ተጥሶ ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የሚያትት ዜና የሰሞኑ ኢትዮጵያውያን ድረ ገጾች/መገናኛዎች ዋነኛ ትኩረት ነው። ስለዚሁ ጉዳይ ዜና ያስነበበው “አዲስ አድማስ” ጋዜጣ ጉዳዩን በተመለከተ የሚከተሉትን ቁም ነገሮች አስፍሯል።
  • በሚኖሩበት አካባቢ የእርሻ ቦታ በማጣታቸውና የተሻለ ሥራ ፍለጋ ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ ከአማራ ክልል ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያሶ ወረዳ መሔዳቸውን፣
  • “ከሌላ ቦታ እየመጣችሁና እየሠራችሁ የአካባቢውን ተወላጅ ሰነፍ አደረጋችሁት” በሚል ምክንያት ያፈሩትን ሀብትና ንብረት ሳይሰበስቡ ከክልሉ እንዲወጡ መደረጋቸውን፣
  • አንዳንዶቹ በያሶ ወረዳ ውስጥ የከተማ ነዋሪነትና የንግድ ፈቃድ በማውጣት ላለፉት ሰባት ዓመታት በሥራ ላይ መቆየታቸውን፣ ገሚሶቹ ደግሞ ከ1997 ጀምሮ የቀበሌው ነዋሪ በመሆን ከክልሉ ተወላጆች ጋር በስምምነት መሬት የእኩል እያረሱ የራሳቸውንም የባለመሬቱንም ሕይወት መቀየራቸውን፣
  • በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከማይ ዞን በያሶ ወረዳ ውስጥ በሀሎ ትክሻ፣ ሆኒ፣ ሊጐ፣ ባብርኮ፣ ሻብቲ፣ ድልድል፣ ቲኒጆ መጢና በመሰል ቀበሌዎች በግምት ከስድስት እስከ ዘጠኝ ሺህ የሚጠጉ ከአማራ ክልል የመጡ ሰዎች እንደሚገኙበት፣
  • “የክልሉ ነዋሪ ወዶንና ተቀብሎን በሰላም ነበር የምንኖረው” ማለታቸውን፣
  • ጐጐታ በተባለ ቀበሌ ከአማራ ክልል የመጡ 43 ሰዎች እንዲሁም በሀሎ ሙከአርባ ቀበሌ የ25 ሰዎች መታወቂያ ተቀዳዶ ሲጣል መመልከታቸውን፣
  • “እስከአሁን በወረዳው ፖሊስ ጣቢያ ከታሠሩት በርካታ ሰዎች በተጨማሪ በመኪና ተጭነው ነቀምትና ጊንቢ የተወሰዱት ሰዎች” መኖራቸውን፤ ስንቅ ሊያቀብሉ የሔዱ ሰዎችም መታሰራቸውን፤
  • ወደመጡበት እንዲመለሱ የተወሰነው፤ በብአዴን፣ ኦህዴድ እና የኢሕአዴግ አጋር ፓርቲ በኾነው ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ ፓርቲ (ቤጉብዴፓ) በጋራ ተወያይተው በደረሱበት ውሳኔ መኾኑን ሥራው የወረዳው ብቻ ሳይሆን ከክልል እስከ ቀበሌ ድረስ በትስስር እየተሠራ መኾኑን የያሶ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ሻምበል ዳኛ መግለጻቸውን ዘግቧል።
ይህንን ዜና ከሌላ ተመሳሳይ የቅርብ ጊዜ ታሪክ ጋር ካመሳከርነው ከደቡብ ክልል ጉራ ፈርዳ ወረዳ ከተፈናቀሉት/ እየተፈናቀሉ ካሉት ሌሎች ዜጎች ጉዳይ ጋር ልናነጻጽረው እንችላለን። ሁለቱንም አንድ የሚያደርጋቸው ደግሞ አማርኛ ተናጋሪዎች (አማሮች) መሆናቸው ነው።
ሊወገዝ የሚገባው ተግባር
መነሻው ምንም ይሁን ምን፣ የክልሉ ፓርቲ ከማንም ጋር ይስማማ አይስማማ በነዚህ ዜጎች ላይ የተደረገው ተገቢነት የሌለው ነገር ነው። የዜጎች በአገራቸው ውስጥ የመዘዋወር፣ የመኖር መብት እንዲህ በጥቂት የፓርቲ ሹመኞች መወሰኑ የሚያስጨንቅም የሚያስደነግጥም ምልክት ነው። ከጉራ ፈርዳም ከቤንሻንጉል የተፈናቀሉት ሰዎች “አማሮች” መሆናቸው ደግሞ አጋጣሚ ነው ለማለት በጣም የዋህ (ሲገፋም ጅል) መሆን ይጠይቃል።
በቋንቋ ማንነት ላይ ብቻ በተመረኮዘው የአገራችን ፖለቲካ “አማራ” የሚባል ለብዙዎቹ “ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች” ጠላት የሆነ አካል እንዳለ በጓዳም በአደባባይም ሲነገር ብዙ ጊዜ ሰምተናል። ይህ ‘ፖለቲካ ያባውን – መፈናቀል ቢያወጣው’ (ሆድ ያባውን … እንደሚባለው) ምንጩ የማይታወቅ የማይሆነውም ለዚህ ነው።
ከደቡብም ከቤንሻንጉልም ለመፈናቀል “አማራነቱ” ምክንያት የሚሆንበት ከሆነ “አይቴ ብሔሩ ለአማራ? … የአማራ አገሩ የት ነው?” የትስ ሔዶ ይኑር? ኢትዮጵያ አገሩ አይደለምን?” ለማለት ያስገድደኛል። ደግሞስ አንድ ሰው አማርኛ ስለተናገረ የግድ ወደ አማራ ክልል መሔድ አለበት? ሁሉም ወደየክልሉ የሚለውን አዋጅ ያወጣውስ ማን ነው? አማርኛ የሚናገሩ ነገር ግን “የአማራ ክልል አገራቸው ያልሆኑ” ኢትዮጵያውያን የነገ ዕጣ ፈንታ ምንድር ነው?
የመታወቂያ ነገር
ለረዥም ጊዜ የቀበሌ መታወቂያ ሳይኖረኝ እኖር ነበር። ከዕለታት በአንዱ ቀን ግን የግድ የቀበሌ መታወቂያ ማውጣት የሚያስፈልገኝ ጊዜ ደረሰና እኖርበት ወደነበረው ቀበሌ ሔድኩ። ፎርም ሞላኹ። ከዚያም መታወቂያው ላይ መስፈር ያለበት የብሔረሰብ (እነርሱ እንኳን ብሔር ነው ያሉት) ነገር ተነሣ። መናገር አልፈለኩም። ቀበልዬው ካልተናገርኩ እንደማይሰጠኝ እርግጥ አደረገው። መሞላት አለበት። የዘር ማንዘሬን “ደም” ሁሉ እስኪሰለቸው ደረደርኩለት። በምን ፎርሙላ እንደሆነ ባላውቅም እርሱ ደስ ያለውን አንዱን ቋንቋ ብቻ መርጦ ብሔሬን ሞላው። በመታወቂያዬ መሠረት ቀብልዬው የሞላው ክልልና ብሔር አባል ሆንኩ። መታወቂያ እየታየ ሰልፍ መያዝ ሲጀመር እኔም አቶ ቀበልዬው በሞላው ተርታ የግዴን ልገባ ነው ማለት ነው።
ማንነትን በማወቅ ሰበብ ማንነትን ማጣት
ማንነትን ማወቅ፣ ባህልን መጠንቀቅ፣ ቋንቋን ጠብቆ መቆየት የሚደገፍ ብቻ ሳይሆን መብትም ነው። ነገር ግን አሁን ባለው መንገድ ድንበር እያጠሩ ሰውን ያለ ፍላጎቱ “ሰልፍህ በየት በኩል ነው?” የሚያስብል ብሔረሰባዊ አሰላለፍ ግን ጤናማ ካለመሆኑም በላይ አገር ብለን በጋራ የምንኖርባትን ጎጆ የሚያፈርስ ከፋፋይ አስተሳሰብ ነው። በተለይ እዚህ አሜሪካን አገር ከመጣኹ በኋላ ያየሁት እና እንኳን ቋንቋን ቀለምን ማለትም ነጭ፣ ጥቁር፣ እስያዊ፣ ሂስፓኒክ የሚለውን እንኳን ፎርም ላይ ለመሙላት የሰውየው ብቸኛ ፍላጎት መሆኑን ማወቄ በግዳቸው “ብሔረሰብ እንዲመርጡ” ለሚደረጉ ኢትዮጵያውያን እንዳዝንም፣ እንድቆጭም፣ እንድበሳጭም ያደርገኛል።
ዛሬ አማራ ተብለው እንዲወጡ የተደረጉት ዜጎች ሌላው ሰው “አማራ” ይላቸው ካልሆነ ምናልባት ራሳቸውን በቀበሌያቸውና በትውልድ ቀዬያቸው ከመጥራት የዘለለ ነገር የሚኖራቸው አይመስለኝም። እንዳሁኑ “አማራ ናችሁ” የሚለው አንድ ቃል ሳይጫንባቸው በፊት “አገራችን ጎጃም ነው” ወይም “መንዝ ነው” ይሉ ይሆናል። ኦሮሞውም “ሜታ ነኝ” ወይም “ቦረና ነኝ፣ ወለጋ ነኝ” ይል እንደሁ እንጂ እንደአሁኑ “ኦሮሞነት” አልተጫነበትም ነበር። ሌላውም ሌላውም። ማንነትህን እወቅ በማለት ሰበብ የተጫነበት የቋንቋ ቀንበር ከጎረቤቱ የሚለየውና አርሶ ከሚያድርበት ቀዬ የሚያፈናቅለው ከሆነ ማንነቱ እንደ ዕዳ ተቆጥሮበታል ማለት ነው።
ሌላው የሚያስጨንቀው ጉዳይ ምንነትን በማጠር ሰበብ ክፉ የፖለቲካ ጨዋታ የሚጫወቱ ቡድኖች መኖራቸው ነው። የዚህ ጨዋታ ግንባር ቀደሙ ደግሞ ኢሕአዴግ ራሱ መሆኑን መናገር አገራዊ ግዴታ እየሆነ ነው። ፓርቲው ለጊዜያዊ ፖለቲካዊ ጥቅም አገርን የሚያክል ትልቅ ቤት የሚያፈርስ ቁማር ውስጥ ነው ያለው። የሌሎች ብሔረሰቦችን ድጋፍ ለማግኘት አማራውን የመስዋዕት በግ አድርጎ የማቅረብ ቁማር። ዞሮ ተመልሶ ወደራስ ሊተኮስ (Backfire ሊያደርግ) የሚችል መድፍ መጫወቻ ማድረግ።
መረጫጨት ተጀመረ?
አንድ ሰሞን ዝነኛ የነበረች ቀልድ “መረጫጨት ተጀመረ” ትል ነበር። የንስሐ አባት ጸበል ሲረጩ ለጨዋታ የመሰለው ትንሽ ነካ ያደረገው ሰው “መረጫጨት ተጀመረ?” ብሎ ውኃ ያነሳበት ታሪክ። በዚህ ዓይነቱ ከባድ ርዕስ ላይ ይኼ ቀልድ ስላቅ ሆኖ በውስጤ ብቅ አለ። ዛሬ ያባረሩ ሰዎች በሌላው ዘንድ “መረጫጨት ተጀመረ?” እንደማያሰኝባቸው ማወቅ ተስኗቸው ነውን? ምናልባትም ይህ እንዲሆን ፍላጎት እንዳላቸው ማን ያውቃል። እንደመንደር ጎረምሳ “ሰፈሬ ለምን መጣህ?” ሲሉ ሌላው በተራው እነርሱን “ሰፈሬ ለምን መጣችሁ?” እንዲላቸው ፈልገዋል ማለት ነው? ከዚያስ? ተጠቃሚው ማን ሊሆን? ወይስ ካርዱን የሚጫወተው ዋናው ሰውዬ ከኋላ ሆኖ እንዲስቅ? ኢትዮጵያችን እንደማትጠቀም በርግጠኝነት መናገር እችላለኹ።
ለጊዜው
በእኔ ትንሽ ግምገማ ኢትዮጵያውያን በመታወቂያቸው እና በስማቸው እየተገማመቱ እንዲደባደቡ ትልቅ ፍላጎት አለ። እስካሁን ፍላጎቱ ያልተሳካው በኢትዮጵያውያን አርቆ አሳቢነት ነው። ይህንን የኢትዮጵያውያን አርቆ አሳቢነት በሕይወቱ ያልተረዳ እና በዚህ የዘር ፖለቲካ የተጠመቀ ትውልድ አገሪቱን እየተረከበ ሲመጣ እንዴት እንደምንሆን ግን እግዜር ይወቀው። ባለ ራእዩ ሰውዬ “አንተርሐሙዌ” (Interahamwe) ብለው ያሟረቱት ነገር ላለመድረሱ ማረጋገጫ የሚሰጥ ባገኘኹ በተደሰትኩ።
የቤንሻንጉል ክልል ሰዎችም ሆኑ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ ለዚህ ዕብደት አፋጣኝ መፍትሔ መስጠት አለባቸው። በዚህ ነገር መጠየቅ ሲመጣ ማዕከላዊው መንግሥትም “አልነበርኩበትም፣ የክልሉ ጉዳይ ነው” ማለት አይችልም። መሬት ለሕንዶች በነጻ በማከፋፈሉ ላይ እጁን የሚያስገባው የቤተ መንግሥት አካል ድሃ ገበሬዎች ሲፈናቀሉ የለኹበትም ሊለን አይችልም። የሚሰማውም አያገኝ።
መቼም የእምነት መሪዎቻችን ራሳቸውን ችለው ቆመው “ተዉ” ይላሉ ብለን አንጠብቃቸውም። እንዲህ ዓይነቱ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት እንዲገታ መጠየቅ የሚገባቸው እነርሱ ቢሆኑም – በቅድሚያ። እነርሱ ባይናገሩም ሥልጣን ያላቸው ብቻ ሳይሆኑ ሐሳባቸውን መግለጽ የሚችሉ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ነገሩ ወንጀል መሆኑን መናገር አለባቸው። “ትክክል አይደለም” ለማለት የግድ የአማራነት ቆብ መድፋት አያስፈልገንም። ሰብዓዊነት የሚሰማው በሙሉ ግድ ይለዋል። ለታሪክም ቢሆን። ከጊዜያዊ የፖለቲካ ወገንተኝነት ውጪ ማሰብ የሚያስፈልገው በዚህ ዓይነቱ ጉዳይ ነው። የገዢው ፓርቲ ደጋፊና መሪ የሆኑትም ቢሆኑ ይህንን መቃወም ኢሕአዴግን መቃወም አድርገው መቁጠር አይገባቸውም። እንዲያውም ያስመሰግናቸዋል። ለኅሊናችንና ለልጅ ልጆቻችን ስለምናስረክባት ኢትዮጵያ ስንል “ኧረ በሕግ አምላክ፣ ኧረ በባንዲራው” እንበል።

ይቆየን – ያቆየን