በበደኖ፣ በአርባጎጎ የተጀመረውና በሰው ልጅ ላይ ይፈፀማል ተብሎ በማይታሰበው ኢ- ሰባአዊ ድርጊት ግድያ ተባብሶ ዛሬ ጋምቤላ የጥቃቱ መንደር ባለተራ ሆናለች።
ወደ ኋላ ባለፉት 9 አመታት በጋምቤላ ምድር በወያኔ ጥይት የተገደሉ፣ የተጨፈጨፉ ከ400 በላይ ንጹሃን አኙዋኮችን ማጣታችን ይታወሳል። ያ ሀዘንና ሰቆቃ፣ ጠባሳው ሳይጠፋ ዛሬ ደግሞ ሌላ ዋይታ፣ ግድያ፣ እንግልት፣ ጮኸት በዛው ቦታ በጋምቤላ እንደና እየተሰማ ነው።
ህወሃት/ኢህአዴግ የሚከተለው የዘረኝነት ፖሊሲ አስተዳደር ስልጣኑን እስከጠበቀለት ድረስ ማናቸውንም ዜጋ መግደል፣ማሰር፣ ማባረር እንደሚችል የጋምቤላው ክልል አስተዳደር ደረታቸውን ሞልተው ነግረውናል።
ይህ ዘር ላይ ያነጣጠረው ጭፍጨፋ የጋምቤላን ህዝብ መሬቱንና ቀን ከሌት ደከመኝ ሳይል ያፈራውን ንብረቱን በመንጠቅ፤ የተማረውን የክልሉን ተወላጅ በትውልድ – መንደሩ ስደተኛ፣ የበይ ተመልካች እንዲሆንና እንዲቆጭ እያደረጉት ነው። በተለይም በሀገሩ ምድር በመኖሩ ወንጀለኛ፣ ሽብርተኛ በማድረግ ዜጎች ስለመብታቸው እንዳይጠይቁ የማስፈራራት፣ የወዮላችሁ ዘመቻ ላይ ናቸው ወያኔዎች።
ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚገርመው: መንግስት የሆነ አካል ቻይና የተበደለን አዳማጭ፣ ፍትህ ሰጭ መሆን ሲገባው ፣ ገዳዩም አሳሪውም ፈራጁም መንግስት መሆኑ እንቆቅልሽ ይሆንበታል። ይሄው አካል ቅንጣት ያህል ርህራሄ በሌለው የንጹሃን የሰው ልጅን ክቡር ሂዎት በማጥፋት ይህንንም እንደሚቀጥልበት በራሱ ልሳን የቲቪ መስኮት የተገደሉ ወጣት አኙዋኮችን ሬሳቸውን ከመሳሪያ ጋር በማሳየት እኛ ደም የጠማን ርካሽ አውሬዎች ነን ይሉናል። ከአውሬም አውሬ ሽብርተኞች ናቸው።
በርግጥም ነው ከወደ ባህርዳር ከተማ የክልሉ ተወላጆች በአማራነታችን ምክንያት ከቤንሻንጉል ክልል ተባረርን ለስደት፣ ለእንግልት፣ ለርሃብ ተዳረግን፣ የወላጅ መካን ተበራከተ፣ እኛስ ይሁን ለጋ ህጻናት በምን በደላቸው፣ ሀጺያታቸው ይንገላቱ? እባካችሁ ለወገናችን አልቅሱ፣ ለአማራው አንቡ፣ አቤት ልንል በደላችንን ልናሰማ በሄድን ቤንሻንጉል ሄዳችሁ እንደገና ጠይቁ፣ አይመለከተንም፤ አሁን ግቢውን ለቃችሁ ውጡ ተብለን በፌድራል ተዋከብን፣ ተደበደብን፣ የት እንሂድ? ተቃጠልን የሚል ስቃይም ሰምተናል።
እንግዲህ ወገን የትኛውን ጩኸት፣ የትኛውን ስቃይ ትመርጣላችሁ? በክብር ነክ ስድብ ውርደት መኖር? በአሰቃቂ ጭፍጨፋ ግድያ እጃቸው በደም የተላወሰውን የወያኔን ጎራ ፉከራ ማየትና ከንፈርን መምጠት? ወይስ ለነጻነት ጮራ ፍንጠቃ፣ ለድምጽ አልባዎቹ ዜጎች ድምጽ ለመሆን ከሚታገለው የህዝባዊ ሃይሎች ጎራ መቀላቀል? መልሱን መልሱት።
ግንቦት 7 ንቅናቄ ሀገርን የማዳን ተስፋን አርግዞ ረጅሙን ጉዞ በአንድ ርምጃ ጀምሮታል። የህዝባችን ሰቆቃ በየደቂቃዎች፣ በየሰእታቱ፣ በየቀናቱና ሳምንታቱ የምንሰማው የወገናችን የስቃይ ጣእር የድረሱልን ጥሪ ደወል ለሁሉም የሀገራችን ህዝብና ለነጻነት ታጋዮች ነውና እጅ ለእጅ ተያይዘን ለጥሪው እንድረስ። ከዚህ በላይ ውርደት፣ ስቃይ፣ እንግልት፣ ስደት፣ ሰቆቃ የምናስተናግድበት፣ የምንችልበት አንጀት የለንም። የኢትዮጵያ ወጣት ሆይ በእኛ ይብቃ ብለህ ትግሉን ተቀላቀል።
ዜጎች ፍትህን በሰውነታቸውና በዜግነታቸው ሳይሆን በመደብ ጀርባቸው፣ በዘርና በጎጥ ማንነታቸው በችሮታ የሚሰጥበት የወያኔ ዘመን ላይ ነን። የጋምቤላና የተቀረው ህዝባችን በወያኔ ጥይቶች እየተገደሉ ሲሰደዱ፣ ንብረት አልባ ሲሆኑ፣ ኑሮ ከእጅ ወደ አፍ ሲሆንባቸው፤ በአንጻሩ የወያኔ ጀሌ አጫፋሪ የሆኑ የስርአቱ አገልጋዮች የህወሃት ሰዎች 90 ፐርሰንት በግል ኢንቨስተርነት ታዋቂ ናቸው። ይህ የሚያሳየው የአንድ ፓርቲ ፈላጭ ቆራጭነት አይሎ መንግስት የህዝብ ንብረት ቀማኛ ዘራፊ መሆኑን ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ የዜጎች ሂዎት በእብሪተኞች መቀጠፉ እንዲበቃ፣ እንዲያቆም ወያኔን እንታገለው ዘንድ የወጣቱን ህዝባዊ ሃይል የመቀላቀል ጊዜ አሁን ነው።
ሀገራችን መንግስት አልባ ሆናለች፣ ሀገራችን በወንበዴዎች እየተመራች ነው። በሀሰት ወንጃዮች፣ በሀሰት አሳሳሪዎች፣ አዘራፊዎችና ዘራፊዎች፣ አሰቃዮች የነገሱበት ሰአት ላይ ነች ኢትዮጵያ! ስለዚህ ፍትህን ከተቀበረችበት የማውጣት ጥሪ በድጋሜ ይድረሳችሁ።
ግንቦት 7 ለፍትህ፣ ለነጻነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ቀድሞውንም የኢትዮጵያ ህዝብ ፍትህ የማግኘት ተስፋው በወያኔ ተቀብሯል ብሏል። ዛሬ ወያኔ በሀገራችን ፍትህን በመግደል እየዘራ ያለውን አደገኛ መርዝ ለወደፊቷ ኢትዮጵያ እጣ ፈንታ አስቸጋሪ በመሆኑ፤ ላንመለስ ወደኋላ፣ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳንል፣ የፍትህ ቡራኬን ለኢትዮጵያ ህዝብ ለማቃበል፣ ዲሞክራሲን ለማስፈን ወያኔን አስገድዶ ለማስወገድ ትግሉን ጀምረናል።
ወንጀለኞችን ወደፍርድ አደባባይ ለማቅረብ፣ ለድምጽ አልባዎቹ ድምጽ ለመሆን የጥሪ ድምጻችንን ሰምታችሁ ኢትዮጵያዊ የሞራል ግዴታችሁን ትወጡ ዘንድ በራችን ክፍት ነው።ኑ እንታገለው፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!