Tuesday, May 14, 2013

ኢትዮጵያ በፍጥነት ወደኋላ እየገሰገሰች ነው!


Ethiopian Author and writer from Norway
ጌዲዮን ከኖርዎይ
 
የኢትዮጵያ እድገት መቼም በጣም አስገራሚና አነጋጋሪ መሆን ከጀመረ ሰነባበተ፥፥ ውሸት ሲደጋገም ውነት ይሆናል አለች ቻይና! አቶ መለስ ዜናዊ እንደቀልድ የተናገሩት ነገር ስር ሰዶ አሁን አሁን በሳቸው አጠገብ ያለፉት ሁሉ አብረው አጮሁት፥፥ የሚገርመው ነገር ግን አውሮ ፓውያንም አብረው አጮሁት እንደውም ስራቸውን በርዳታ ስም እንደፈለጋቸው እንዲያሮጡ መልካም አጋጣሚን የፈጠረላቸው ይመስላል።

Ethiopians meeting in Norway, discussion on current issues

ከግራ ወደ ቀኝ ሀይኪ ሆልማስ፣ ፒተር ኤስ. ጊትማርክ እና ዶ/ር ሚሊዮን በላይ

ግንቦት 13,2013 ቀን በኦስሎ ከተማ ሊተራቱር ህውስ በተባለው አዳራሽ ውስጥ ይህንኑ የኢትዮጵያን እድገት ለማስተጋባት በኖርዌጂያን ዴቨሎፕመንት ፈንድ በተባለ ድርጅት አማካኝነት Ethiopia – the reality behind the media በሚል ርእስ በተጠራው ስብሰባ ላይ ኖርዌጂያን ፖለቲከኞችና የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች በእንግድነት በተገኙበት የውይይት መድረክ ላይ በርካታ ወድ ኢትዮጵያውያን በኖርዎይ እንዲሁም ኖርዌጂያን በቦታው ላይ ተገኝተው ነበር።
ተጋባዥ ከነበሩት እንግዶች መካከል፥
  • ኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት ሚኒስቴር ሃይኪ ሆልሞስ ከሶሻል ሌፍት ፓርቲ
  • ፒተር ጊትማርክ የኖርዌጂአን ኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ የኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት ዋና ቃልአቀባይ እና
  • ዶክተር ሚሊዮን በላይ ኢኮሎጂካል ለርኒንግ እና ኮሚዩኒቲ አክሽን ዳይሬክተር ከኢትዮጵያ ሲሆኑ ስብሰባውን የመሩት አቶ አንድሪው ክሮግሉንድ የኖርዌጂያን ደቨሎፕመንት ኤንፎርሜሽን ኤንድ ፖሊሲ ዋና ክፍል ሃላፊ ነበሩ።
ውይይቱን በይበልጥ ያተኮረው በስልጣን ላይ ባሉት አቶ ሃይኪ ሆልሞስ የኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት ሚኒስቴር እና በአቶ ፒተር ጊትማርክ የኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ የኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት ዋና ቃል አቀባይ መካከል ቢሆንም ዶክተር ሚሊዮን በላይ ብዙ ለመናገር ከኢትዮጵያ መንግስት ብዙም ፍቃድ የተሰጣቸው አይመስልም ነበር።

Ethiopian in the Diaspora, Norway meeting

ይሁን እንጂ አቶ ሃይኪ ሆልሞስና በአቶ ፒተር ጊትማርክ መካከል የነበረው የልዩነት አቋም አቶ ሃይኪ ሆልሞስ ኢትዮጵያ ውስጥ እድገት አለ ስለሆነም የገንዘብ እርዳታ ማድረጋ እንቀጥላለን የሚል ሲሆን አቶ ፒተር ጊትማርክ በበኩላቸው አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ አለ ስለሚባለው እድገት ጥርጣሬ እንዳላቸውና እንዲሁም በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሰብአዊ መብት ረገጣ ከግዜ ወደጊዜ እየተባባሰ በመምጣቱ ኖርዎይ የምታደርገውን የገንዘብ እርዳታ እንድታቆም እንዲሁም እርዳታው አስፈላጊ ከሆነም በስልጣን ላይ ላለው መንግስት ሳይሆን ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚደርስበት መንገድ መፈለግ አለበት ሲሉ የሳቸው ፓርቲም በስልጣን ላይ ከወጣ ይህው እርዳታ እንደሚቌረጥና በማንኛውም ጊዜ ይህ ሁኔታ ሲሻሻል እርዳታው እንዴት እንደሚቀጥል የሚታይ ይሆናል ብለዋል።

እንዲሁም ከተሳታፊዎች መካከልም ብዙ ጥያቄዎች ለዶክተር ሚሊዮንና ለአቶ ሃይኪ ሆልሞስ የተሰነዘረ ሲሆን የተሳታፊው አቋም የነበረው፥ የኖርዎይ መንግስት እየሰጠ ያለው የገንዘብ እርዳታ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው መንግስት ህዝቦችን ለማፈን እያተጠቀመበት ነው፥ እርዳታው መረዳት ላለበት ህዝብ አልደረሰም፥ የሚሉና በርካታ የተቃውሞ መልክቶችን ያዘኡ ነበሩ።

በመጨረሻም ምንም እንኳን ከተሰብሳቢው በርካታ የወቅታዊ የሃገራችን አንገብጋቢ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለውይይቱ ተጋባዥ እንግዶች የቤት ስራ የሚሆኑ በርካታ ጥያቄዎች በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

No comments: