Monday, May 13, 2013

የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የህግ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አስመላሽ ወ/ስላሴ ታሰሩ

የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የህግ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አስመላሽ ወ/ስላሴ መታሰራቸው ተሰማ። አቶ አስመላሽ ግንቦት 1 ቀን የተባረሩት የፍትህ ሚኒስትሩ የመስራቤታቸውን የዘጠኝ ወር ሪፖርት ሲያቀርቡ ሪፖርታቸውን አጣጥለውባቸው ነበር። ሪፖርትር የአቶ በርሃንን መነሳት በዘገበበት ዜናው እንደዘገበው አቶ አስመላሽ በርካታ ጉዳዮች መቀየር አለባቸው በማለት... ሚኒስትሩን አሳስበው ነበር።  

 ከጉምሩክ የህግ ክፍል ጋር በተያያዘ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩት አቶ አስመላሽ ከአቶ መለስ ጀርባ ጥቁር መነጽር ተላብሰው በመቀመጥ ይታወቃሉ። ከዚህም በላይ በህግ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ በመስጠትና ለህግ የበላይነት በመቆርቆር በተደጋጋሚ በፓርላማ የሚደሰኩሩ ሰው ነበሩ።

No comments: