Friday, September 13, 2013

Ethiopian journalist on hunger strike over mistreatment in prison (IMW)

September 13, 2013 

IMWF calls for reinstatement of visitation privileges

SSSAs stories about the political crisis in Cairo have been dominating the news from Egypt, there has been limited coverage on a brewing international conflict between Egypt and Ethiopia – two countries that do not share a border but are indivisibly connected by the Nile, the world’s longest river.

Amid works to construct a giant hydro-electric dam, and much to the anger of the Egyptian government, Ethiopia has started diverting the Blue Nile, a tributary of the Nile, prompting a furious debate about if and how the “Great Ethiopian Renaissance Dam” will affect Egypt’s water security.
While there may not be a definite answer anytime soon on whether this dam will have any impact on water security in Egypt, there is no doubt that it has already negatively impacted press freedom in Ethiopia. Earlier this summer, for instance, the Committee to Protect Journalists reported that Ethiopian officials arrested a reporter seeking to interview people evicted from their homes in the region where the contentious hydro-electric dam is being built. More notable, however, was the arrest of Ethiopian columnist Reeyot Alemu more than two years ago.
A critic of the government writing for the now-defunct newspaper Feteh, Alemu had raised questions about the funding and merits of the dam shortly before she was arrested on bogus terrorism charges and sentenced to 14 years in jail.
Although two of the three terrorism charges against her were later dropped on appeal and her sentence reduced to five years, Alemu continues to suffer from her government’s efforts to silence dissenting voices and scare independent journalists into self-censorship. A tumor in Alemu’s breast remains untreated as she is denied access to medical care, and threats of solitary confinement linger over her every move in Ethiopia’s notoriously ill-maintained Kaliti prison.
While the Ethiopian leadership insists on the country’s adherence to the rule of law, there seems to be little doubt in the international community that Alemu’s arrest and conviction was politically motivated: The International Women’s Media Foundation honored Alemu with its Courage in Journalism Award last year, and in May 2013, the United Nations Educational, Scientific and Cultural Organization (UNESCO) recognized her “commitment to freedom of expression” with itsGuillermo Cano World Press Freedom Prize. In July, a delegation of the European Parliament’s Subcommittee on Human Rights, scheduled to meet with Alemu, was denied access to Kaliti prison, prompting questions by members of the European Parliament over Ethiopia’s commitment to human rights.
According to the Committee to Protect Journalists, Ethiopia jailed more journalists than any other country in Africa in 2012 (with the exception of Eritrea), and 45 Ethiopian journalists have been forced into exile since 2008. Swedish journalist Martin Schibbye who gained first-hand experience with Ethiopia’s crackdown on press freedom after being arrested there himself in June 2011, delivers a damning verdict on the rule of law in Ethiopia: “There is no such thing as an independent justice system, it’s completely politicized. If the order comes from the federal level that Reeyot is to let go, she will be free. But if they feel that they gain more from keeping her in prison, they will keep her locked up. This decision lies entirely in the hands of the Ethiopian government,” he said.
But the Ethiopian authorities seem to be determined to keep Alemu silenced. Earlier this week, as Ethiopians were preparing for their New Year’s celebration, prison officials denied Alemu visits from anyone but her parents. It remains unclear whether the decision to keep her separated from her friends, siblings, and fiance is in response to an open letter Alemu wrote in August, criticizing Ethiopia’s Anti-Terrorism Proclamation, but it appears to be unlikely that the timing of the new restrictions is coincidence.
Protesting the prison’s decision to deny her visits from friends and relatives, Alemu has gone on hunger strike. The IWMF is deeply concerned about Alemu’s health and well-being, and calls on the decision-makers at Kaliti prison to re-instate Alemu’s full visitation privileges immediately.

ርእዮት አለሙ እና የእስር ጉዳይ በደረጀ ሃብተ ወልድ

september 12, 2013

ጋዜጠኛና መምህርት ርዕዮት ዓለሙን ለመታሰር ካበቃት ወንጀል አንዱና ዋነኛው ፦”… በቃ!” ተብሎ የተፃፈን ጽሁፍ ፎቶ ማንሳቷ ነው። .. ለኔ ይገርመኝ የነበረው፤ርዕዮትንም ከሙያና ከሞራል አንፃር ያስወቅሳት የነበረው.. “በቃ!” ተብሎ የተፃፈውን ጽሁፍ ዝም ብላ ብታልፈው ነበር። የልማታዊ ጋዜጠኛ አንዱና ዋነኛ ተግባር በህዝብና በመንግስት መካከል እንደ ድልድይ ሆኖ መንግስት (ጥሩም ይሁን መጥፎ)ምን እየሠራ እንደሆነ፤ ህዝቡም ስለ መንግስት ምን እያሰበና ምን እያለ እንደሆነ የሀቅ መረጃ ማቅረብ ነው። ከዚህ አንፃር ርዕዮት ፦”ህዝቡ በቃ እያለ ነው..” የሚል መረጃ በፎቶ ማንሳቷና በብዙሀን መገናኛ ለማቅረብ ማሰቧ ያሸልማት እንደሆነ እንጂ በፍፁም ሊያስከስሳት አይችልም። “በቃ!” የሚል ፅሁፍ በየቦታው እየተፃፈ ባለበት ሁኔታ “ህዝቡ ኑሮው ተሻሽሏል፣ አኮኖሚው አድጓል፤ ልማቱ እጎመራ ነው…” እንድትል ተፈልጎ ከሆነ፤ ያ የህዝብ ግንኙነት ወይም የካድሬ ሥራ እንጂ የጋዜጠኛ ተግባር አይደለም።

…ሀቁ ይኸው ነው። ደርግ የጠመንጃ ታጋዮቹን እንዳሰቃየበት በዶክመንተሪ ፊልም እያሰማመረ የሚተርክልን ኢህአዴግ፤ የብዕር አርበኞችን እያሰረ፣አስሮም እያሰቃየ ነው። ደርግ፤ የያኔዋን የኢህአፓ ታጋይና የ አሁኗን ኢህአዴግ ወይዘሮ ታደለች ሀይለሚካኤልን ነፍሰ-ጡር እያለች ማሰሩን- ለደርግ ጨካኝነትና አረመኔነት እንደማመሳከሪያ እያቀረበ “ጉድ!”ሲለን የነበረው ኢህአዴግ፤ የታሪክ ሀዲዱ ብዙም ሳይጓዝ -ጋዜጠኛዋንና ነፍሰ-ጡሯን ሰርካለም ፋሲልን አስሮ እዚያው እስክትወልድ ድረስ በወህኒ እንደተዋት ህያው ምስክሮች ነን።

ኢህአዴጎች ደርግን የሚከሱበትና የሚወቅሱበት ሞራል ብቻ ሳይሆን ታሪክም የላቸውም። ሳይውል ሳያድር ያን ታሪክ እነሱም እየደገሙት ነውና።

በኮንዶሚኒየም ቤቶች ሺያጭ ሥም ስደተኛውን የወያኔ ጭሰኛ ለማድረግ የተጀመረው እንቅስቃሴ ይከሽፋል::

September 12, 2013

ወያኔ እንደ ድርጅት የሚፈልገውን የፖለቲካ ጥቅም የሚያስገኝለት እስከመሰለው ድረስ በህዝብና በአገር ላይ የማይፈጽማቸው ምንም አይነት እኩይ ተግባሮች እንደማይኖሩ በተግባር ያስመሰከረ ድርጅት ነው::
ለአብነት ያህል ለመጥቀስ ፤
  1. ድርጅቱ ገና ትግራይ በረሃ ውስጥ ትግል ላይ በነበረበት ወቅት የትግራይን ወጣቶች ከትምህርት ገበታቸው እያነቀ በመውሰድ አላማውን በግልጽ ላልተረዱትና ላላመኑበት ጦርነት ማግዶአቸዋል:: በዚህም የተነሳ ወያኔ እራሱ ይፋ ባደረገው አሃዝ ብቻ ቁጥራቸው 60 ሺህ የሆኑ ለጋ ወጣቶች ላለፉት 22 አመታት የህዝባችንን ስቃይና መከራ እያራዘመ ያለውን የድርጅቱን መሪዎች ሥልጣን ላይ አውጥቶ ለማንገስ ከፍተኛ የህይወት መስዋዕትነት ከፍለዋል ::
  2. የአገራችንን ክብርና መልካም ገጽታ እስከዛሬ አበላሽቶ ባለፈው በዚያ አስከፊ የ1977ቱ ድርቅ ወቅት ለትግራይ ተጎጂዎች ከአለም አቀፍ ለጋሾች የተበረከተውን የነፍስ አድን እህል በሱዳን በኩል ወደውጭ አሳልፎ በመቸብቸብ መሪዎቹና ተከታዮቻቸው ለተንደላቀቀ ኑሮ ሲበቁ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ህጻናት፤ አሮጊቶችና አዛውንቶች እንደቅጠል እንዲረግፉ ምክንያት ሆኖአል::
  3. የትግራይ ህዝብ ተማሮ በመንግሥት ላይ እንዲያምጽ ለመቀስቀስ በደሃው አቅማችን የተገነቡ ትምህርት ቤቶችን፤ የህክምን አገልግሎት መስጫ ተቋሞችን ፤ ድልድዮችንና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን በፈንጂና በመድፍ ከማውደም አልፎ የተሳሳተ መረጃ ለደርግ በመስጠት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ህዝብ ለገበያ እንደወጣ ሃውዜን ከተማ ላይ በጠራራ ጸሃይ እንዲጨፈጨፍ አድርጎአል::
  4. የደርግ አገዛዝ ከተወገደ ቦኋላ ሥልጣን ላይ ለመደላደል የሚያስችል ድጋፍ ለመሸመት ሲባል የአገራችንን ሉአላዊ ጥቅም ለባዕድ አሳልፎ የሰጠ በርካታ ግልጽና ድብቅ ውሎችን ከ3ኛ አካላት ጋር ፈጽሞአል :: ከውሎቹ አንዱ የህዝባችንን ትኩረት ለማስለወጥ ካለፈው 2 አመት ጀምሮ በሰፊው እየተዘመረለት የሚገኘው የአባይ ወንዝን የመጠቀም መብታችንን የሚጻረር እንደነበረ ጉልህ ማስረጃ አለ::
  5. በሚሊዮን የሚጠጋ ህዝባችንን ከቀያቸው በማፈናቀል ለም መሬታችንንና ድንግል የተፈጥሮ ሃብታችንን ለህንድ ፡ ለቻይናና ለአረብ ከበርቴዎች በመቸብቸብ በገዛ አገራችን የባዕድ አሽከር እንዲንሆን ፈርዶብናል::
  6. በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሴት እህቶቻችን ለባርነት ሥራ ወደ አረብ አገር በመላክ ከፍተኛ ሰቆቃ እንድፈጸምባቸው በማድረግ ብሄራዊ ክብራችንን ኩራታችንን የሚያጎድፍ ተግባር ፈጽሞአል::
  7. በሙስናና ዘረፋ የተጨማለቀ ሥርዓት በማቋቋም አብዛኛው ህዝባችን ከወለል በታች ወደወረደ የድህነት አረንቋ ውስጥ ገብቶ የቁም ስቃይ እንዲቀበል አድርጎአል::
  8. መብታቸውን ለማስከበር በጠየቁ ወገኖቻችን ላይ እስከ አፍንጫው የታጠቀ ጦር በማዝመት በርካቶችን አስጨፍጭፎአል፤ ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሎአል ፤ ለእስርና ለስደት ዳርጎአቸዋል:: ወዘተ
ወያኔ ይህንንና ግዝፈታቸው ከዚህ የከበዱ በርካታ ሰቆቃዎችን በአገርና በወገን ላይ እየፈጸመ የአገዛዝ ዘመኑን ሊያራዝም የቻለው፤
  1. ህዝባችን በዘር ፤ በቋንቋና በሃይማኖት ተከፋፍሎ እርስ በርሱ እንዳይተማመንና የጎሪጥ እንድተያይ ሌት ተቀን ተንኮል በመሸረቡ
  2. የጦር ሃይል ፤ የፖሊስ ሠራዊት፤ የደህንነትና ሌሎች የኢኮኖሚና ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋሞች በሙሉ ከአንድ አካባቢ በተሰባሰቡ የጥቅም ተጋሪዎች ቁጥጥር ሥር እንዲወድቅ ተደርጎ እሺ ያለውን በጥቅም እምቢ ያለውን ደግሞ በጠመንጃ ሃይል ጸጥ ለጥ ለማድረግ በመመኮሩ፤
  3. ከራሳቸው የግል ሚቾትና ቅንጦት አሻግረው በወገንና በአገር ላይ እየተፈጸመ ያለውን ሰቆቃ ማየት የማይፈልጉ ወይም የማይችሉ ተፈጥሮአዊ ባህሪያቸው “ እኔ ከሞትኩ ሠርዶ አይብቀል “ ካለቺው እንስሳ የማይለይ ሆዳሞች ከተለያየ የህበረሰተሰብ ክፍል ተመልምለው ከአገዛዙ ዙሪያ በሎሌነት ለመሰለፍ በመቻላቸው እንደሆነ ይታወቃል::
በሌላ አገላለጽ ወያኔ የአገዛዝ እድሜውን ለማራዘም የፈጸመውና እየፈጸመ ያለው ቀደም ሲል ፋሽስት ጣሊያን የአገራችንን ህዝብ በባርነት ለመግዛት አድርጋው ከነበረው ቅስም ሰባሪ እርምጃዎች በባህሪም ሆነ በአይነት አንድ መሆኑ ግልጽ ነው:: ለመብቱና ለነጻነቱ ቀናዕ የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ትናንት ለጣሊያን መደለያዎች ተታሎ ወይም የሃይል እርምጃ ተንበርክኮ ነጻነቱን አስነጥቆ ለመኖር እንዳልፈቀደ ሁሉ ዛሬም ከአገሩ የሰሜን ክፍል የበቀሉ ባንዳዎች በጉልበታቸውም ሆነ ሌሎች መሸንገያዎች የሚያደርጉትን አሜን ብሎ እስከወዲያኛው ለመገዛት ፈቃደኛ አለመሆኑን በሚያደርገው ተቃውሞ እየገለጸ ነው::
ይህንን ሃቅ የተረዳው ወያኔ የጭቆና ክንዱን ለማፈርጠም የሚያስፈልገውን ገንዘብ በስደት ውጭ አገር ከሚኖረው ኢትዮጵያዊ ለመሰብሰብና የተቃውሞ እንቅስቃሴውን ለማዳከም በኮንዶሚኒየም ቤት ሽያጭ ሥም አዲስ እቅድና ስልት ነድፍ መንቀሳቀስ ጀምሮአል::
ብቸኛው የፓርላማ ተወካይ የሆኑት አቶ ግርማ ሠፉ በቅርቡ ከኢሳት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ እንዳረጋገጡት ወያኔ በስደት ለሚኖረው ኢትዮጵያዊ የነደፈው የኮንዶሚኒየም ቤት ሺያጭ ዋና አላማ አገር ቤት ውስጥ እየተፏፏመ የመጣውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመምታት በተለያዩ የምዕራብ አገሮች ከፍ ብለው እየተደመጡ ያሉትን ድምጾች አሰቀድሞ ለማዳከም በመፈለጉ እንደሆነ አያጠራጥርም::
ምንም እንኳን ለራሳቸው ማንነትና ስብእና ክብር የሌላቸው አንዳንድ ዜጎች “የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ” በሚል ፈሊጥ በዚህ የወያኔ ወጥመድ ውስጥ ለመውደቅ ውር ውር እያሉና በየአገሩ የሚገኘውን የወያኔ ኤምባሲ በር ማንኳኳት የጀመሩ መኖራቸው ባይካድም አንድ ወቅት ላይ ግር ግር ፈጥሮ ወዲያው እንደተጨናገፈው የአባይ ቦንድ ሺያጭ የታሰበውን ያህል ውጠት እንደማያስገኝ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል::
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በስደት የሚኖረው ሁሉም ኢትዮጵያዊ አገሩንና ወገኖቹን ጠልቶ ሳይሆን የተሰደደው ለዘመናት የዘለቀው ኢፍትሃዊነት የፈጠረው ኋላ ቀርነትና ድህነት አገሩ ላይ ለመኖር ያለውን ምኞትና ተስፋ አጨልሞበት አለያም በፖለቲካ ችግር ምክንያት ህይወቱን ለማቆየት ተገዶ ነው ብሎ ያምናል::
በዚህም የተነሳ ማንኛውም ስደተኛ ስደት የሚያስከትለውን ማህበራዊና ሥነ ልቦናዊ ቀውሶች ተቋቁሞ አንድ ቀን አገሬ ገብቼ ከወገኖቼ ጋር በሠላም እኖርበታለሁ ብሎ ያጠራቀማትን ጥሪት በከፍተኛ ንቅዘትና ሙሰኝነት ወደ መጨረሻው ታሪካዊ ሞቱ እየወረደ ያለውን የወያኔ ሥርዓት ተማምኖ በማውጣት ቦኋላ እንዳይጸጸት ወገናዊ ምክሩን ይለግሳል::
ወያኔ ለዲያስፖራው ያዘጋጀው የኮንዶሚኒዬም ቤቶች ሺያጭ የፖለቲካ ድጋፍ ለማግኘት የታለም የከተማና የገጠር ህዝባችንን የወያኔ ጭሰኛ ያደረገ የአገር ውስጥ ፖሊሲ አካል ነው:: ከ7 አመት በፊት ኮንዶሚኒዬም ቤት ለማግኘት ለተመዘገቡ 800 ሺህ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ያልተዳረሰ ቤት እንዴትና በምን ስሌት ነው በሰው አገር ያውም በአንጻራዊ ምቾት ለምንኖር ዜጎች የታሰበልን ብሎ እራስን መጠየቅ ከትዝብትና ከታሪክ ተወቃሽነት የሚያድን ተግባር ነው ::
ሃብት በተትረፈረፈበትና የሚበላ የሚጠጣ ነገር ከሰው ተርፎ ቆሻሻ ገንዳ ውስጥ በሚጣልበት አሜሪካና አውሮጳ ለምንኖር ዜጎች ከሚስኪኑ ህዝባችን ጉሮሮ በተነጥቀ ገንዘብ ቤተመንሥት ውስጥ ተዘጋጅቶ የተላከ ምግብና መጠጥ ለመደለያነት ሲያጓጉዝ የኖረ መንግሥት አሁን ደግሞ በኮንዶሚኒየም ቤት ሥም ቢመጣብን ጥፋቱ የሱ ሳይሆን የእኛ ለክብራችንና ለነጻነታችን ዋጋ የማንሰጥ ስግብግቦች መሆኑን ምን ጊዜም መዘንጋት የለበትም::
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በስደት ውጭ አገር የሚኖር ማንኛውም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ወያኔ በኮንዶሚኒዬም ቤት ሽያጭ ሥም ትግሉን ለማዳከም የዘረጋውን ይህንን የተንኮል ሴራ እንዲያከሽፍ ወገናዊ ሃላፊነት እንዳለበት ያስገነዝባል::
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !

Wednesday, September 11, 2013

በበዓል ቀን የርሃብ አድማ – ርዕዮት ምን ልትነግረን ነው?

September 11th, 2013 
በብሄራዊ በዓላት ቀን በአብዛኛው ከወደ እስር ቤት የሚሰማው ዜና አስደሳች ነበር፡፡ይህንን አጼዎቹ ፣ሰው በላው የደርግ ስርዓትና ብሶት ወለደኝ ያለን ኢህአዴግ ሲያደርጉት ቆይተዋል፡፡ በዘንድሮው አዲስ አመትም የመንግስትን ይቅርታ በማግኘት ከወዳጅ ዘመዶቻቸው የተቀላቀሉ ስለመኖራቸው ተሰምቷል፡፡በአዲሱ ዓመት ይቅርታ ከተቸራቸው እስረኞች መካከል ታዋቂ ፖለቲከኞች፣አክቲቪስቶችና ጋዜጠኞች አለመኖራቸው ተፈቺዎቹ በደረቅ ወንጀል ታስረው የነበሩ መሆናቸውን ለመናገር ብዙ መድከም አይጠይቅም፡፡
1185860_10200561003368447_1105290103_nመንገስት ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፣ሂሩት ክፍሌና ዘሪሁን ገ/እግዚአብሄር አቅርበውት ለነበረ የይቅርታ አቤቱታ የእምቢታ ምላሽ መስጠቱም ይቅርታ የሚገባውና የማይገባው በመንግስት ማውጫ ውስጥ ስለ መኖሩ ማሳያ ነው፡፡የይቅርታው ጉዳይ ለጊዜው ይዘግይልንና በጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ላይ በበዓል ቀን ስለ ተፈጸመ ግፍ ላካፍላችሁ፡፡ ጋዜጠኛዋን በበዓሉ ዋዜማ ለመጠየቅ ወደ ቃሊቲ አምርተን ነበር፡፡በመጠየቂያ ሰዓት መድረስ የቻልን ቢሆንም ጥበቃዎቹ
‹‹ርዕዮት የምትጠየቀው በዋናው በር ሆኗል፡፡ስለዚህ ወደ ዋናው በር ሂዱ››
አሉን፡፡ዋናው በር ፈጣን ተራማጅ በ10 ደቂቃ የሚደርስበት በመሆኑ ሰዓቱ እንዳይረፍድና እንዳንከለከል በማለት መሮጥ ጀመርን፡፡
ዋናው በር ግብረ ገብነት አልያም ፖሊሳዊ ስነ ምግባር በዞረበት ለሰላምታ እንኳ አግኝቷቸው የማያውቁ የሚመስሉ ጠባቂዎች
‹‹በዚህ በኩል እስረኛ አይጠየቅም ሂዱ ››
አሉን፡፡ ግትር ብለን በዚህ በኩል ግቡ ተብለናል አልን፡፡ሰዓቱ እየሄደ ፖሊሶቹም በአቋማችን የበለጠ በመበሳጨት እየዛቱ ነው ፡፡በመካከሉ የርዕዮት ታናሽ እህት እስከዳር አለሙና እጮኛዋ ስለሺ ሀጎስ ከግቢው ውስጥ እየተጣደፉ ወጡ፡፡ ስለሺ አንገቱን አቀርቅሮ እጆቹን እያወናጨፈ ብቻውን ያወራል፣እስከዳርን በሙሉ አይን ማየት ያስፈራል፡፡ ፊቷ በርበሬ መስሎ በእንባ ጎርፍ እየታጠበች ነው፡፡አብሮኝ የነበረው ሰውና እኔ ለመግባት እናደርግ የነበረውን ትንቅንቅ በመተው ሁለቱን ለማጽናናት እና ምን እንደተፈጠረ ለማወቅ መወትወቱን ተያያዝነው፡፡
ርዕዮት ቤተሰቦቿን እንዳገኘች
‹‹ያለሁበት ሁኔታ አስቸጋሪ ነው፣ችግር ውስጥ ነኝ››
ትላቸዋለች፡፡በዚህ ወቅት በዙሪያዋ የነበሩ ሴት ፖሊሶች ጋዜጠኛዋ ላይ በመጮህ
‹‹ስለ ራስሽ ብቻ አውሪ››
ይሏታል፡፡
‹‹የነገረችን እኮ ስለ ራሷ ነው››
የእስከዳር ምላሽ ነበር፡፡ በዚህ መሃል በጊዜያዊነት የሴቶች ዞን ሃላፊ የሆነች ፖሊስ
‹‹እናንተ አቅማችሁ ጋዜጣ ላይ ነው ከፈለጋችሁ ሂዱና እንዳንጠይቃት ተከለከልን በሉ፡፡››
በማለት በዚህ ቦታ ለመጥቀስ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የሚያቅበንን የስድብ መዓት በስለሺ ፣በርዕዮትና በእህቷ ላይ ታወርዳለች፡፡
ርዕዮት ሁኔታውን መቋቋም ተስኗት ሃላፊዋን ለምን እንዲህ አይነት በደል እንደምትፈጽምባት ለመጠየቅ ስትሞክር እየገፈታተሩ ወደ ውስጥ እንድትገባ በማድረግ እነ ስለሺን ግቢውን እንዲለቁ ያደርጋሉ፡፡
በንጋታው መስከረም 1/2006 ነው፡፡የመንግስት ሃላፊዎችና የሃይማኖት አባቶች የቴሌቭዥኑን መስኮት በአዲስ አመት ቀና መልዕክት አጨናንቀውታል፡፡አዲስ ቀን አዲስ ገጠመኝ እንደሚፈጥር ተስፋ ያደረጉት የርዕዮት ቤተሰቦች ከቃሊቲ አልቀሩም፡፡ነገር ግን የሰሙት ነገር በቀኑ እንጂ በአስተዳደሩ መካከል ለውጥ ወይም ዕድሳት አለመኖሩን ነው፡፡ለካ የአዲስ አመት በጎ መልእክት የሚያስተላልፉልን መሪዎቻችን ያሉት
‹‹በድሮው ቀን ነው፡፡››
ርዕዮትን እንዲጠይቁ የተፈቀደላቸው
‹እናቷ፣አባቷና የነፍስ አባቷ ብቻ ናቸው››
እነ ስለሺ ከቃሊቲ ሃላፊዎች ዛሬ ያደመጡት መንፈስ ሰባሪ ቃል ነው፡፡ የህግ ባለሞያው አቶ አለሙ ጌቤቦ ድርጊቱ ህገ መንግስታዊ ጥሰት እንደሆነ በመግለጽ ቃሊቲ ደርሰው ልጃቸውን ሳይጠይቁ ተመልሰዋል፡፡ወላጅ እናቷ ያመጡትን ምግብ ለማስገባት ቢሞክሩም ርዕዮት በቃሊቲ የሴቶች ዞን ጊዜያዊ ሃላፊ እየደረሰባት የሚገኘውን ህገ ወጥ ድርጊት ለመቃወም የርሃብ አድማ በመጀመሯ እናት ያመጡትን ምግብ የሚቀበላቸው አላገኙም፡፡
ወዳጄ ስንቶቻችን ነን አዲሱ ዓመት በጾም ቀን ዋለ ብለን የተከፋን?ይህው እንግዲህ በዓሉን ርዕዮት በርሃብ አሳልፋዋለች፡፡
የርዕዮት የርሃብ አድማ መልእክቱ ግልጽ ነው፡፡አቅም ያላት በራሷ ላይ በመሆኑ ራሷን በመቅጣት ህገ ወጦችን እምቢ አለቻቸው በዚህ ሰላማዊውን ታጋይ ማህተመ ጋንዲን መሰለችው፡፡ሰዎቹ እየበሉ በርሷ ላይ የሚፈጽሙት በደል እየተራበች በምታስተላልፈው መልእክት የህሊና ርሃብተኞች መሆናቸውን ይነግራቸዋል፡፡
ከቃሊቲ ውጪ ያለንም ምግብ ወደ አፋችን ባስጠጋን ቁጥር ርዕዮት የቃሊቲ አጥር ሳይበግራት ትመጣብናለች፡፡በምግብ ብቻ በማይኖርባት አለም በምግብ ብቻ ለመኖር ለምናደርገው ከንቱ ሩጫም ርሃቧ ትልቅ ደወል ይሆንብናል፡፡ 

በአዲስ ዓመት አስገራሚ ዜና ከቃሊቲ – ‹‹ከአንድነት›› የሚል ጽሁፍ የሰፈረበት ኬክ ቃሊቲ እንዳይገባ ተደረገ – ፍኖተ ነጻነት

September 11, 2013

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አመራሮች እድሜ ልክ ተፈርዶበት በቅጣት ቤት የሚገኘውን ሰላማዊ ታጋይ አንዷለም አራጌን
‹‹እንኳን አደረሰህ አዲሱ ዓመት ፍጹም ነጻነትህን የምትቀዳጅበት እንዲሆን እንመኛለን እንታገላለንም››
በሚል ስሜት ተነሳስተው ኬክ በማስጋገር
‹‹ከአንድነት››
የሚል ጽሁፍ አጽፈውበታል፡፡
የአንዷለም ጠያቄዎች በሩን አልፈው የያዙትን ኬክ ለማስፈተሸ አስቀማሽ ጋር እንደደረሱ አስቀማሹ ኬኩንና የተጻፈበትን እየተመለከተ አንዴ ቆዮኝ ብሎ ጥሏቸው ሄደ፡፡ አስቀማሹ ሃፊዎቹን አስከትሎ መጣ ፡፡የሆነ ነገር ትከሻቸው ላይ የደረደሩ ሃላፊ ኮስተር ብለው
ኬኩ አይገባም እናንተ ግን መግባት ትችላላችሁ›
ይላሉ፡፡ የኬኩ በደል ምን እንደሆነ ሲጠይቁም
‹‹ከአንድነት››
ይላል አሏቸው፡፡
አንድነት በምርጫ ቦርድ እውቅና የተቸረው ቢሮ ያለው ሰላማዊ ፓርቲ ነው፡፡ አንዷለምንም እናንተ ሽብርተኛ በማለት አሰራችሁት እንጂ እስከሚታሰርበት ቀን ድረስ
የፓርቲው የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊ ነበር፡፡››
ይሏቸዋል፡፡
ኬኩን አንድነት ከሚለው ውጪ ይዛችሁ መግባት ትችላላች ከዚህ ውጪ አናስተናግድም ሃላፊው ይላሉ፡፡ የአንድነት አመራሮች በበኩላቸው ኬኩ ህገ ወጥ ነገር እስካልሰፈረበት ድረስ አንድነት የሚለውን የፓርቲያችንን ስም አንፍቅም፡፡ ፍላጎታችሁ ሰላማዊውን ታጋይ እንዳንጠይቀው ለማድረግ በመሆኑ እኛም አንገባም በማለት ግቢውን ለቅቀው ወጥተውላቸዋል፡፡1185993_10151839340271870_915504360_n

የእባብ ልጅ እፉኝት !! ስለ አቶ ሽመልስ ከማል

September 11, 2013

(አቶ ሽመልስ ኃይለየሱስ) ጥቂት መረጃዎች ሃጂ ከማል ሐጂ በብሄር ቀቤና ሲሆኑ ሚስታቸው (የአቶ ሽመልስ ከማል እናት) ወሮ አበባ ሁሴን ደግሞ በአባት የጅማ ኦሮሞ፣ በእናት ወርጂ ናቸው። ሃጂ ከማል ሃጂ ኢትዮጵያ ሃጃጆችን መርተው በሄዱበት ወቅት ከንጉስ ፋይሰል ጋር ፎቶ ተነስተዋል። ገና ከጅምሩ የኃይለ ስላሴ ቤተመንግስት ድረስ ይገቡ ነበር።

የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ለማፈን መሳሪያ ሆነው ሰርተዋል። በመጨረሻ ንጉሱ  ክርስትና ያስነሷቸው ሲሆን ቤተሰባቸውን ሁሉም ክርስትና አስነስተዋል። ወሮ አበባ ሁሴን ለሃጂ ከማል ሃጂ አራት ወንድና አራት ሴት ልጆችን ወልደዋል። ሃጂ ከማል ክርስትና ከተነሱ በኋላ ኃይለየሱስ ተሰኝተዋል። አንዳንዶች ‹‹ቀድሞውኑ በሙስሊም ስም (ሽፋን) ኖሩ እንጂ ሙስሊም አልነበሩም፤ ኢስላምን የሚያጥላላና የሙስሊሙን የመብት ጥያቄ የማፈን ስራ ሲሰሩ ራሳቸውን ሃጂ ከማል ሃጂ ብለው ይጠራሉ እንጂ መች ሙስሊም ነበሩ?›› ይሏቸዋል።

የግለሰቡ መኖሪያ ቤት ጥቁር አንበሳ ጋር (ሜትሮሎጂ) እና የስልጤ መስጅድ መካከል ነበር። ግለሰቡ ሙስሊሙን ለማጠቃት ለአፄ ኃይለስላሴ ወሳኝ ስራ ስለሰሩ በ1956 የሰላም ማህበር ሲዘጋ በአውራጃ ገዥነትና የንብረት ክፍል ኃላፊነት ቦታዎች ላይ ተሹመው ነበር።ምንሊክ ሳልሳዊ

ስለ አቶ ሽመልስ ከማል ጥቂት መረጃዎች

‹‹አቶ ሽመልስ ከማል ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ተቀጥረው ከመስራታቸውም ባሻገር በጊዜው መንግስትን ይተች የነበረውን ‘’ኒሻን’’ የተባለ የራሳቸውን ጋዜጣ እስከማቋቋም የደረሱ ሲሆን፤ አቶ ሪድዋን ሁሴንም እንዲሁ ተቀዋሚ ፓርቲ መስርተው የፓርቲ ሊቀመንበር ከመሆናቸውም ባሻገር በ1992 ዓ.ም ፓርቲያቸውን ወክለው ለምርጫ በመቅረብ የኢህአዴግ ተወዳዳሪን በማሸነፍ ፓርላማ እስከመግባት እንደደረሱ ይታወሳል። እነዚህ ግለሰቦች ገዢው ፓርቲ ካመቻቸላቸው የጥቅመኝነት ስልጣን የሚያመጣላቸውን ጥቅም ተከትሎ ፍላጎታቸውን ማርካት ሲጀምሩ መሰረታዊ ከሆነው ለሰው ልጆች የመቆርቆር ሃሳባቸው ጋር እረፍት የሚነሳ የህሌና ጫና ውስጥ መግባታቸውን አይቀሬ ያደርገዋል።›› (ሙሉነህ አያሌውና ኃ/መስቀል በሸዋም የለም፣ የመለስ ውርሶች ታህሳስ 2005 ገፅ 210)
• የአቶ ሽመልስ አባት ሃጂ ከማል ሃጂ ሁለት መፅሃፍ የፃፉ ሲሆን የመጀመሪያው ‹‹የመካና መዲና ሚስጢር›› ሲሰኝ መፅሃፉ ከአዲስ አበባ ተነስተው ለሃጅ በሚል መካ የተጓዙበትን ሂደት ይተርካል። መጽሀፉ በተዘዋዋሪና በቀጥታ ኢስላምን ያጥላላል። ‹‹ለምን ድሬ ሼህ ሁሴን እያለ ሃጅ እንሄዳለን? በደንብ ብንይዘው አናጅናን (ሼህ ሁሴን) ለቱሪዝምና ለሃጅ ምትክ አድርገን እንጠቀማለን›› የሚል መልእክት ያስተላልፋል፡፡ ከዚህም አልፎ ‹‹ነብዩ (ሰዐወ) ድሬ ሼህ ሁሴንን ሳይዘይር ሃጅ የሄደ ሃጁ ተቀባይነት የለውም ብለዋል›› እስከማለት የደረሰ ቅጥፈት አካቷል፡፡ ‹‹ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ስለምን የዓረብኛ ስም ያወጣሉ? ለምን የአማርኛ መጠሪያ ስም አያወጡም?›› እስከማለት ይደርሳል፡፡ ኢስላም ሴቶችን እንደሚበድልና ሌሎች ተመሳሳይ ነጥቦችንም ይዳስሳል። ሌላኛው መፅሃፍ ‹‹የህሊና ግዳጅ›› የሚሰኝ ሲሆን ዓላማ አድርጎ የተፃፈው ‹‹የአፄ ኃይለስላሴ መንግስት ሙስሊሞችን ይበድላል›› ለሚሉ ሙስሊሞች ምላሽ እንዲሆን ነው። ጸሐፊው በመፅሃፋቸው ‹‹የአፄ ኃይለ ስላሴ መንግስት ሙስሊሙን ይበድላል ብለው ሃጅ ላይ ወረቀት የበተኑና በውጭ ሚዲያዎች የፃፉትን የተሳሳተና ሃሰተኛ ድርጊት እያየሁ አላህ የውመል ቂያማ እንዳይጠይቀኝ ነው ይህን የፃፍኩት›› ይሉናል። ‹‹ሰሃቦችን በስደት ሲመጡባት ያስተናገደች ሃበሻ እንዴት ሙስሊሞችን እየበደለች ነው ተብሎ ይፃፋል?›› ሲሉም ይሞግታሉ። ሁለቱም መፅሃፍቶች ያኔ በንጉሱ ዘመን ህዝበ ሙስሊሙን ያስቆጡ ነበሩ።
• ግለሰቡ ከ1953-1956 ‹‹የሰላም ማህበር›› የተባለው የሙስሊሞች ማህበር መሪ ነበሩ። ድርጅቱን ሙስሊም አባቶች የእስላም ማህበር ብለው ሲያቋቁሙ አፄ ኃይለ ስላሴ ስያሜውን ‹‹የሰላም ማህበር›› በሚል እንዲቀየር አስገደዱ። በድርጅቱ ውስጥ አመዴ ለማ (ፊታውራሪ) እና ሃጂ በሽር ዳውድን ጨምሮ በርካታ አባቶች ነበሩ። ስለ ግለሰቡ (ሐጂ ከማል) መሰሪነት ፊታውራሪ አመዴ ለማና ሃጂ በሽር ዳውድ ግለ ታሪካቸውን በፃፉበት መፅሃፍቶቻቸው ጠቅሰዋል። ልጃቸውንና የኢህአዴግ ባለስልጣንን አቶ ሽመልስ ከማልን በመፍራት ስማቸውን ሳይጠቅሱ ድርጊቱን ብቻ የጠቀሱ ቢሆንም ሃጂ በሽር ዳውድ ግን በረቂቁ ላይ ጠቅሰውት በታተመው ላይ ስማቸው ወጥቷል። ‹‹የግለሰቡ ስም ረቂቁን ባረመው ዶ/ር ኢድሪስ ሙሀመድ ተቀንሶ ይሆን?›› የሚለው ጥያቄ እንዳለ ሆኖ ስማቸው ቢወጣም ድርጊታቸው ግን በመጽሀፉ ውስጥ ተጠቅሷል።ምንሊክ ሳልሳዊ
• ሃጂ ከማል ሐጂ በብሄር ቀቤና ሲሆኑ ሚስታቸው (የአቶ ሽመልስ ከማል እናት) ወሮ አበባ ሁሴን ደግሞ በአባት የጅማ ኦሮሞ፣ በእናት ወርጂ ናቸው። ሃጂ ከማል ሃጂ ኢትዮጵያ ሃጃጆችን መርተው በሄዱበት ወቅት ከንጉስ ፋይሰል ጋር ፎቶ ተነስተዋል።
• ገና ከጅምሩ የኃይለ ስላሴ ቤተመንግስት ድረስ ይገቡ ነበር። የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ለማፈን መሳሪያ ሆነው ሰርተዋል። በመጨረሻ ንጉሱ ክርስትና ያስነሷቸው ሲሆን ቤተሰባቸውን ሁሉም ክርስትና አስነስተዋል። ወሮ አበባ ሁሴን ለሃጂ ከማል ሃጂ አራት ወንድና አራት ሴት ልጆችን ወልደዋል። ሃጂ ከማል ክርስትና ከተነሱ በኋላ ኃይለየሱስ ተሰኝተዋል። አንዳንዶች ‹‹ቀድሞውኑ በሙስሊም ስም (ሽፋን) ኖሩ እንጂ ሙስሊም አልነበሩም፤ ኢስላምን የሚያጥላላና የሙስሊሙን የመብት ጥያቄ የማፈን ስራ ሲሰሩ ራሳቸውን ሃጂ ከማል ሃጂ ብለው ይጠራሉ እንጂ መች ሙስሊም ነበሩ?›› ይሏቸዋል።
• የግለሰቡ መኖሪያ ቤት ጥቁር አንበሳ ጋር (ሜትሮሎጂ) እና የስልጤ መስጅድ መካከል ነበር። ግለሰቡ ሙስሊሙን ለማጠቃት ለአፄ ኃይለስላሴ ወሳኝ ስራ ስለሰሩ በ1956 የሰላም ማህበር ሲዘጋ በአውራጃ ገዥነትና የንብረት ክፍል ኃላፊነት ቦታዎች ላይ ተሹመው ነበር።
• በደርግ ጊዜ ጡረታ ወጥተው ታመው ወደ ቤት ገቡ። ለሁለት ወራት ያክል በአልጋ ላይ ተኝተው አንዲት ቃል ሳይወጣቸው በመጨረሻ ሞቱ። ሙስሊሞች ‹‹ዱዓችን ሰራ›› ብለው አላህን አመሰገኑ። በተክለ ሀይማኖት ቤተክርስቲያንም ተቀበሩ።
• ግለሰቡ ከመሞታቸው አስቀድሞ ገና ታመው በተኙበት ነበር ባለቤታቸው ወ/ሮ አበባ ሳዑዲ ዓረቢያ ይኖሩ ከነበሩና አቶ ከድር ማሜ ከተሰኙ የባሌ ሰው ጋር ቅርርብ የጀመሩት። ቅርርባቸው በመጀመሪያ ግለሰቡ ለእረፍት ሲመጡ የእሳቸውን ዕቃ በማሻሻጥ ላይ ነበር የተመሰረተው። በኋላ ላይም ግለሰቡ ወ/ሮ አበባን ጨምሮ ቤተሰቡ ወደ ኢስላም እንዲመለስ አደረጉ። ከአቶ ሽመልስ በስተቀርም ሁሉም ሰለሙ። ወ/ሮ አበባም ፀጉር መግለጥና ሱሪ መልበስ ትተው ሂጃብ መልበስ ጀመሩ። በኋላ ላይም ከአቶ ከድር ማሜ ጋር ተጋቡ፡፡
• ግለሰቡ ወ/ሮ አበባን ይዘው ወደ ሳዑዲ ገቡ። በዚያም ወ/ሮ አበባ እየሰሩ ልጆቻቸውን ማሳደግ ጀመሩ፡፡ የበኩር ልጅ የነበሩት አቶ ሽመልስ ግን ሊሰልሙ ፈቃደኛ አልነበሩም። እናታቸው ወ/ሮ አበባ ‹‹ሽመልስ ግትር ነው›› ይሉ ነበር።
• በህግ የተመረቁት አቶ ሽመልስ በከፍተኛ ፍ/ቤት ይሰሩ ነበር። ከዚያም ሪፖርተር ጋዜጣ፣ ቀጥሎም ኒሻን ጋዜጣ ላይ ይሰሩ ነበር። በዚህ ጊዜ ነበር ኢህአዴግ አስሮ የገረፋቸው። ከእስር ሲለቀቁ አቶ ሽመልስ ኢህአዴግን ተቀላቀሉ። በዚህን ጊዜ ነው ‹‹ሰለሙ›› የተባለው፤ ቤተሰቦቻቸው ግን አሁንም ድረስ ‹‹የሱ እስልምና ያን ያህል ነው›› ይላሉ (እናቱን ጨምሮ)። የአቶ ሽመልስ ወንድም መሰለ ኃይለየሱስ ሲሰልሙ አብደላ ሃጂ ከማል ተብለው ነበር፡፡ ሌላኛዋ መስከረም የምትባለው ደግሞ እንግሊዝ ኗሪ ናት፤ ሌላኛው ወንድማቸው የአየር መንገድ ቴክኒሻን የነበሩ ሲሆን እንግሊዝ ገብተዋል፤ ሌላኛው ደግሞ ኤሌክትሪሻን ሲሆኑ የሚኖሩት በአሜሪካ ነው፡፡ ወ/ሮ አበባም ልጆቻቸው ጋር አሜሪካና እንግሊዝ ይመላለሱ ነበር፡፡ የአቶ ሽመልስ ሌላኛዋ ሴት እህት ደግሞ በገነት ሆቴል ውስጥ፣ ኋላ ላይ ደግሞ መሿለኪያ አካባቢ ጅምር ቤት ነበራት፤ ባሏ ጀርመን ሃገር ስለሚኖር ጀርመን ትመላለሳለች።
• ከቤተሰቡ ኢስላምን አጥብቀው የያዙት ኢንጅነር አብደላ ከማል (ቀድሞ መሰለ ኃይለየሱስ ይባሉ የነበሩት) ናቸው፡፡ ሃይማኖተኛ መሆናቸውን ብዙዎች ይመሰሩላቸዋል።
• አቶ ሽመልስ ‹‹ሰለመ›› ከተባሉ በኋላ ከአህባሽ አደሬ ጓደኞቻቸው ጋር ይቅማሉ፤ ያጨሳሉ፤ ከነሱ ስርም አይጠፉም፤ በዚህ ጊዜ ነበር ወደ አህባሽ እምነት የገቡት።
• በ1992 ምርጫ ‹‹ለሙስሊሙ እሰራለሁ›› በሚል የአካባቢው ሙስሊሞች በመስጅድ ጀምዓ ፖስተር አሳትመውላቸው፣ በራሪ ወረቀት በትነውላቸው እንዲመረጡ ቀስቅሰዋል። ከተመረጡ በኋላ ግን ለግል ጥቅማቸውና ለፓርቲው መስራታቸውን ቀጥለዋል።
• በ1996 ሸህ አብደላ አል-ሃረሪ ወደ ኢትዮጵያ በመጡበት ጊዜ አቶ ሽመልስ ከማል ግለሰቡን ቦሌ ጃፓን ኤምባሲ አቅራቢያ ባለ ቪላ ቤት ሄደው ከጎበኙት ባለስልጣናት አንዱ ነበሩ። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነበር ፓርቲው ውስጥ ያሉትን ሙስሊሞች እኔ ብርቱና ታዋቂ ሸህ (ሸህ አብደላ አል-ሃረሪን) ይዣለሁ፤ እናንተም እርሳቸውን በሸህነት ያዙ፤ ያለ ሸህ እንዴት ይዘለቃል?›› በማለት ለማሳመን መጣር ጀመሩ፡፡ በኋላ ላይም በመኖሪያ ቤታቸውና በቢሮ የሸህ አብደላ አል-ሃረሪን ፎቶግራፍ በፍሬም በማድረግ ለጥፈዋል።
• አቶ ሽመልስ ከማል ከአህባሾች ጋር እንቅስቃሴያቸውን የቀጠሉ ሲሆን በተለያዩ አጋጣሚዎች መንግስት እያደረገ ባለው አህባሽን የማስፋፋት ስራ ላይ ተጠይቀው (በግል) ‹‹ልክና ተገቢ ነው፤ የሼኻችንን ስም የሚያጠፉት ውሃብዮች ናቸው፤ የሚጠቀስባቸው ሁሉ ሃሰት ነው›› በማለት ተከላክለዋል።
• አቶ ሽመልስ ከማል ከዚህ ቀደም ከጋብቻ ውጭ አንድ ልጅ የወለዱ ሲሆን ያሳድጉ የነበሩትም እናታቸው ነበሩ። በአሁኑ ሰዓት አቶ ሽመልስ ልክ እንደ አባታቸው ከመንግስት ጋር ሆነው ፀረ-ሙስሊም ንግግርና ድርጊት እየፈፀሙ ይገኛል።
• የአባትየው ሃጂ ከማል ሃጂ መፅሃፍቶች ሁለቱም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኬኔዲ ላይብረሪ ውስጥ ይገኛሉ። ‹‹የመካና መዲና ጉዞ ሚስጥር›› ከሚለው መጽሀፋቸው ኮት ተደርጎ ‹‹የኃይለ ስላሴ ዕቅድ በመጅሊስ ተሳካ›› በሚል ርዕስ ሚሌኒየም ላይ ተፅፎ ነበር። ከዚያ አርቲክል ሃሳቦችንና ጥቅሶችን ማግኘት ይቻላል። በመፅሃፍቶቹ ላይ የግለሰቡ ፎቶግራፍ ከነቤተሰባቸው (በ1960ዎቹ የተነሱት) አለበት። ካዕባ ፊት ለፊት የተነሱት ፎቶግራፍም አለበት። በመልክ አባትና ልጃቸው አቶ ሽመልስ ኮፒ ናቸው፤ በመልክም ሆነ በግብር!
• የፊታውራሪ አመዴ ለማና የሃጂ በሽር ዳውድ መፅሃፍም እንዲሁ በገበያ ላይ አለ።
• በ1990ዎቹ ሂክማ ጋዜጣ ላይ ‹‹ሃጂ ከማል ሃጂ ዛሬም ይኖሩ ይሆን?›› በሚል ርዕስ ስለ ግለሰቡ ድርጊትና ታሪክ ተፅፎ ነበር።
• የአፄ ኃይለስላሴ ደህንነት ለንጉሱ በፃፈው ሪፖርት ላይ ስለሃጂ ከማል ሃጂ ተጠቅሷል። ‹‹ሙስሊሙን እንዴት እንምታው?›› የሚል ነበር የሪፖርቱ ዓላማ። ሪፖርቱ ብሄራዊ ቤተ መፅሃፍትና ቤተ መዛግብት (ከኢቲቪ ጀርባ) ውስጥ በልዩ ጥበቃ ክፍል ውስጥ ይገኛል።ምንሊክ ሳልሳዊ

Tuesday, September 10, 2013

Hailemariam calls opposition parties that deny the existence of extremism in Ethiopia as “destructors and betrayers”

ESAT News
September 10, 2013
Prime Minister Hailemariam Dessalegn, in an interview with the government owned Daily Newspaper, Addis Zemen, said “if opposition political parties have democracy, good governance, development and peace as their agendas, then they should condemn extremism and terrorism standing with the government”.
Hailemariam also said “if these people (oppositions) think that there is no extremism and terrorism in Ethiopia, then these people are not living in Ethiopia. Not only in Ethiopia, they do not even know what is going on around the world. Thus, they do not the responsibility and the capacity to lead the people and practice politics. If they think they have the capacity, and if they keep on denying the fact that extremism and terrorism are growing in Ethiopia and is affecting the people, then the aim of these forces are not ready to compete and win in a peaceful, legal political system”.
He also advised all to impede the activities, to compete and in a peaceful, legal system and when they fail to win, if they say “if I lose it, the Nation should burn”, then they are destructors.
Hailemariam said in the protest, which was co-organised with the government, over 600,000 people took part showing that “extremist forces have been alienated from the people”.
It has been reported that the “anti-extremism” themed protest held in Addis Abeba last week has been directly led by the government and local district officials have been forcing citizens to put their signatures to affirm that they were taking part in the demonstration

Monday, September 9, 2013

የጠ/ሚ ባለቤት በቤተመንግስት ኑሮ መሰላቸታቸውን ገለጹ

ጳግሜ ፬(አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቀዳማዊት እመቤት ሮማን ተስፋዬ የቤተመንግስት ኑሮ የሚመች አለመሆኑንና የቀድሞ ጠ/ሚኒስትርንም አኗኗር በማየት ያዝኑ እንደነበር ተናግረዋል።

ቀዳማዊት እመቤቷ ትላንት ከወጣው መንግስታዊው ዘመን መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ የቤተመንግስት ሕይወት አስደሳች አይደለም ብለዋል፡፡ “ የቤተመንግስትን ሕይወት ለማንም ተመኝቼው አላውቅም፡፡ የሴቶች ጉዳይን ስናቋቁም ስምንት ወር ተመላልሼበታለሁ፡፡ ዛሬ እናንተ ተፈትሻችሁ እንደገባችሁት እኛም ተፈትሸን ነበር የምንገባው፡፡ እዚህ ግቢ ስገባ ወደጠ/ሚኒስትሩ ቤተሰቦች መኖሪያ ማዶ እያየሁ አዝንላቸው ነበር፤ግን ለሰው አላወራም፡፡ እዚህ ግቢ ውስጥ የሚኖር ሰው እንዴት ተበድሎአል እያልኩ እገረም ነበር፡፡ እና እኔን ኑሪ ቢሉኝ የማላደርገው መስሎ ይሰማኝ ነበር፡፡    ብለዋል፡፡

አስተዳደጌ ያስተማረኝ ከሌሎች ጋር በጋራ መኖርን ነው ያሉት ቀዳማዊት እመቤት ሮማን ራስን ለማዝናናት፣ዞር ብሎ ቡና ለመጠጣት ፣ዘመድ ጓደኛ እንደልብ ለማግኘት አስቸጋሪ መሆኑን በመጥቀስ ከዚህ አንጻር  የቤተመንግስት ሕይወት ነጻነት የለውም ሲሉ አስረድተዋል፡፡

“ለአንዳንዶች የቤተመንግስት ሕይወት የተንደላቀቀ መስሎ ይሰማቸዋል” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄም በአጭሩ እንደሚታሰበው ዓይነት አይደለም ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

የቀድሞ ኑሮአቸው ከአሁኑ በምን ይለይ እንደሆነ ተጠይቀውም የምግብ ማብሰያውና የአዘገጃጀቱ ሁኔታ ለየት እንደሚያደርገው ተናግረዋል፡፡ “ቤተመንግስት የበሰለው ነገር በንጽሕና የሚቀርብበት ነው፡፡ አዘጋጆቹ በዘርፉ ሙያው ያላቸው ናቸው፡፡ ብዙ ዓመት ያገለገሉ ወጥ ቤቶች አሉ፡፡ ከዚህ ውጪ እንግዲህ ጥበቃው አለ፤ይህው ነው” በማለት አስረድተዋል፡፡
ወ/ሮ ሮማን ከጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አብራክ የወለዱዋቸው የ23፣የ20 እና የ18 ዓመት ሶስት ሴት ልጆች እንዳሉዋቸውም በቃለምልልሳቸው ተናግረዋል፡፡

ባለቤታቸው አቶ ኃይለማርያም በአመራራቸው አስቸጋሪ ሁኔታ ያጋጥማቸው እንደሆን ተጠይቀውም ሲመልሱ አስቸጋሪ ነገር እንኩዋንስ አገር የሚያክል ነገር በመምራት ላይ ቀርቶ ታችም ሞልቱዋል፡፡ “አሁን ያለንበት የግሎባላይዜሽን ዘመን ነው፡፡ ብዙ ዓለምአቀፋዊ ይዘት ያላቸው ጠቃሚም ጎጂም ነገሮች አሉ፡፡ የኢትዮጽያ ሕዝብ አሁን ለመብቱ መታገል ተለማምዶአል፤ መጠየቅን ለምዶአል፡፡  ፈጣን ዕድገትን ይፈልጋል፡፡ ሠላምን፣ ተረጋግቶ መኖርን ይፈልጋል፡፡ መልካም አስተዳደርን ይፈልጋል፤ መልካም አስተዳዳር ሲባል ደግሞ በውስጡ ብዙ ጉዳዮች አሉት፡፡ እና ይህን ሁሉ ፍላጎት ይዞ ሕዝብን የሚያረካ አመራር መስጠት እያደገ የሚሄድ ነው” ብለዋል፡፡

ቀዳማዊት እመቤት ሮማን ከቀድሞዋ እመቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ቤተመንግስቱን ተረክበው ከባለቤታቸውና ልጆቻቸው ጋር የቤተመንግስት ኑሮ ከጀመሩ ገና አንድ ዓመት አልደፈኑም፡፡

ወ/ሮ ሮማን የቤተ-መንግስት ኑሮ ነጻነት እንዳይኖረው የተደረገበትን ምክንያት አላብራሩም፣ ነጻነት እንዲኖረው ለማድረግም ምን ምን እርምጃዎች መወሰድ እንዳለባቸው አልዘረዘሩም። ወ/ሮ ሮማን  ህዝቡ ስለመብቱ መታገል ተለማምዷል በማለት መናገራቸው በቅርቡ የተቃዋሚ ድርጅቶች ካደረጉት ሰልፍ ጋር ይያያዝ አይያያዝ ወይም፣ ይህ ልምምድ ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በሁዋላ ፣ በአቶ ሀይለማርያም የስልጣን ጊዜ የመጣ ክስተት መሆኑንና

ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ በኢትዮጵያ ውስጥ አክራሪነት የለም የሚሉ የተቃዋሚ ድርጅቶች አጥፊዎች፣ከሃዲዎች ናቸው አሉ

ጳግሜ ፬(አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትሩ ትላንትና እና ዛሬ ለሕትመት በበቃው ከመንግስታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ላይ እንደተናገሩት “የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በርግጥም ለኢትዮጽያ ሕዝብ ዴሞክራሲ፣መልካም አስተዳደር ልማትና ሠላምን ለማምጣት አጀንዳ አድርገው የሚንቀሳቀሱ ከሆነ አክራሪነትንና ሽብርተኝነትን ከመንግስት ጎን ተሰልፈው ሊያወግዙ ይገባል ብለዋል፡፡

” በኢትዮጽያ አክራሪነትና ሽብርተኝነት የለም ብለው የሚያስቡ ከሆነ እነዚህ ሰዎች በኢትዮጵያ ውስጥ የሉም ማለት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ብቻም ሳይሆን በዓለም ላይ እየተካሄደ ያለውን አያውቁም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የፖለቲካ ስራና ሕዝቡን ለመምራት የሚያስችል ትልቅ ኃላፊነትና ብቃቱ የላቸውም ማለት ነው፡፡  ብቃቱ አለን ብለው የሚያስቡ ከሆነ ዓለማዊውንና አገራዊ ሁኔታ በአግባቡ ገምግመው ሸብርተኛነትን እንደዚሁም አክራሪነትንና ጽንፈኝነትን በኢትዮጽያ እያቆጠቆጠ የመጣና ሕዝቡን በግላጭ እየጎዳ ያለ እንደሆነ ማንም

 የሚያውቀውን እየካዱ የሚሄዱ ከሆነ እነዚህ ሰዎች ዓላማቸው ሰላማዊ፣ሕጋዊና ለአገሪቱ የሚጠቅም የፖለቲካ ስርዓት
ውስጥ ተወዳድረው ለማሸነፍ የተዘጋጁ ኃይሎች አይደሉም ማለት ነው” ብለዋል፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አሁንም ቢሆን ከድርጊታቸው ታቅበው በሰላማዊ፣ሕጋዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ ተወዳድረው ማሸነፍ እንዳለባቸው የመከሩት አቶ ኃ/ማርያም ፣ ተወዳድረው ማሸነፍ ሲያቅታቸው ከእኔ የቀረ እንደሆነ አገሩቱዋ ትቀጣጠል

ዓይነት ሁኔታ ውስጥ የሚገቡ ከሆነ አጥፊዎች ናቸው ማለት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ አቶ ኃ/ማርያም ባለፈው ሳምንት እሁድ በተካሄደውና በመንግስት በሚደገፈው የአደባባይ ሰልፍ ከ600ሺ በላይ ሕዝብ
መውጣቱን አስታውሰው ይህ አክራሪ ኃይሎች ከሕዝቡ መነጠላቸውን ያሳያል ብለዋል፡፡ አክራሪና ጽንፈኛ ኃይሎች ከሕዝቡ ከተነጠሉ አስተዳደራዊና ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ቀላል ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት እሁድ በአዲስአበባ በመስቀል አደባባይ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠርተውታል የተባለው ሰልፍ በቀጥታ በመንግስት የተመራ ሲሆን የቀበሌ ሹማምንት በየቤቱ እየሄዱ ነዋሪዎች በሰልፉ ላይ እንዲገኙ የግዳጅ ፊርማ ሲያስፈርሙ እንደነበር መዘገቡ የሚታወስ ነው፡፡

አሸባሪው ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ በሰሜን ዋልታ

September 6, 2013

ስደተኛው ጋዜጠኛ የቋንቋ ትምህርት ቤቱ የደረሰው አምስት ደቂቃ አርፍዶ ነበር። በትምህርት መጀመሪያው ቀን ማርፈዱ እያሳፈረው ያልተያዘ ወንበር ፈልጎ ተቀመጠ። ክፍት ቦታ ያገኘው አንድ ቻይናዊና አንድ ፓኪስታናዊ የተቀመጡበት ጠረጴዛ ዙርያ ነበር። “ዑመር እባላለሁ” አለው ፓኪስታናዊው። “ጄን” ብሎ እጁን ዘረጋለት ቻይናዊው። “ጌቱ” በማለት ተዋወቃቸው ከደቂቃዎች በኋላ ሌላ ፓኪስታናዊ መጥቶ አብሯቸው ተቀመጠ። በእረፍት ሰሃት ዞር ዞር እያለ እያለ ሲመለከት የትምህርት ቤቱ መግቢያ በር አካባቢ አስር የሚሆኑ ከአፍሪካ የመጡ ስደተኛ ተማሪዎች ለብቻቸው ነጠል ብለው ያወራሉ። ሊቀላቀላቸው ስላልፈለገ ነጠል ብሎ ለብቻው ቆሞ በማስታወሻ ደብተሩ ላይ መሞነጫጨር ጀመረ።
በተከታታይ ቀናት ራቅ ብሎ ለመታዘብ ሞከረ። ለምን እንደሆነ ባይገባውም አፍሪካውያኑ ለብቻቸው ነጠል ብለው ነው የሚሰባሰቡት። አብሯቸው ነጠል ብሎ መሰብሰቡን አልፈለገውም። ራቅ ብለው ወደቆሙት ፓኪስታናውያንና ቻይናዊ የክፍል ጓደኞቹ ሄዶ ተቀላቀላቸው። ሜክሲኳዊ የክፍል ጓደኛቸው ተጨምሮ እየተቀላለዱ መሳቅ ጀመሩ።
መርማሪው ፖሊስ የጋዜጠኛውን ፋይል በትኩረት እያገላበጠ ይመለከታል። “በቋንቋ ትምህርት ቤት እያለ አብዛኞቹ ጓደኞቹ ፓኪስታናውያን ነበሩ። ለምን ፓኪስታናውያንን በጓደኝነት መረጠ!? ለምንስ በፌስቡክ ገፁ ላይ በአገሩ የሚደረገውን የሙስሊሞች እንቅስቃሴ አብዝቶ ይደግፋል? ለምንስ አብዝቶ የአልጃዚራን ዜና ይከታተላል?” የሚለውን እንዳነበበ “መልስ የሚሻ ጥያቄ” ብሎ ቀና አለ።
ጋዜጠኛው፣ ስልክ አናግሮ እንደጨረሰ ወደ መፅሃፍ መደርደሪያው ሄዶ አንድ መፅሃፍ አንስቶ አልጋው ላይ በጀርባው ወደቀ። መፅሃፍ ቢይዝም የሚያስበው ከደቂቃዎች በፊት ደውላ ስላናገረችው ልጅ ነበር። እንዴት አድርጎ እንደሚረዳት አልገባውም። ስልኩን አንስቶ ደወለላት።
“አግኝቼ ላወራሽ እችላለው?” አለ በአካል አይቷት የማያውቃት ሴት ደውላ ችግሯን ከነገረችው በኋላ የሰማው ነገር ሰላም ቢነሳው።
ተገናኙ።
ያስጨነቃት ታሪኳን ትነግረው ጀመር።
በፓልቶክና በስካይፕ ለተዋወቀችው ሰው ሚስጥሯን ሁሉ ነገረችው። አሳየችው። ችግሩ ጠይም ይሁን ቀይ አለማወቋ ነው። የምታውቀው ነገር ኢትዮጵያዊ መሆኑን ብቻ ነው። እሷ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ተወልዳ ያደገች ኢርትራዊት ነች።
ቅዳሜና እሁድ ምሽት የስነፅሁፍ ውይይት የሚደረግበት የፓልቶክ ግሩፕ ውስጥ እንደሚሳተፍና ስነፅሁፍ ስለምትችል በፓልቶክ ቡድኑ ውስጥ ገብተህ ጓደኛ ብታደርገውና ምን አይነት ሰው እንደሆነ ብትነግረኝ ከዛ ውጪ ምንም አልጠይቅህም ብላ ጠየቀችው።
እምቢ አላላትም። “እሞክራለሁ”  አላት እንጂ።
በሌላ ቀን ሌላ ጥያቄ ይዛ መጣች። መጀመርያ “ቀይ ይሁን ጠይም ምን አይነት ሰው እንደሆነ ብቻ ንገረኝ” ነበር ያለችው። ቀጥሎ ግን ጥያቄዋ ወደ “አንዴ አግኝተህው አድራሻውን ብታገኝልኝ አበባ ይዤ እቤቱ ሄጄ” ወደ ማለት ተቀየረ። ሊረዳት እንደሚገባው ቢያውቅም የጥያቄዎችዋ ማደግ እያስፈራው መጣ።  ግን እንደሚረዳት ቃል ገብቶላታልና የፓልቶክ ቡድኑ ቋሚ ታዳሚ ሆነ።
ኮምፒውተሩ ላይ አፍጥጦ ቀለማትን እየቀያየረ የቢዝነስ ካርድ ዲዛይን ለማስዋብ ይጥራል። ዲዛይኑን የሚሰራው ለአንዲት ኤርትራዊት ነው። የሚሰራላት በነፃ ነው። በነፃ የሚሰራላት ጀማሪ ነጋዴ ስለሆነች ብዙ ወጪ ይበዛባታል ብሎ ስላሰበ  ነው። የቢዝነስ ካርድ ዲዛይን እንዲሰራላት የጠየቀችው ለሌላ ኤርትራዊ የሰራውን የሬስቶራንት የምግብ ዝርዝር የያዘ ዲዛይን ተመልክታ ነው። ለነገሩ ከኤርትራዊው የሬስቶራንት ባለቤት ለሰራበት ገንዘብ አልተቀበለውም። ለእሱም “ወጪ በዝቶብሃል” ነበር ያለው ለሬስቶራንት እድሳት ያወጣውን ወጪ ስለሚያውቅ።
መርማሪው ፖሊስ የጋዜጠኛውን ፋይል እያገላበጠ እየተመለከተ እያለ ጉዳዩን እንዲከታተሉ ካዘዛቸው ፖሊሶች አንዱ ያመጣውን መረጃ ደጋግሞ አነበበው። “አሸባሪው ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ ኤርትራውያንን የሚጠላም ዘረኛ ነው። ጊዜ ሳንወስድ ከኮሚኒቲው እንዲገለል ማድረግ አለብን። ሌሎችን መበከል የለበትም” ነበር የሚለው መረጃው።
መርማሪው መረጃውን በሚያነብበት ሰሃት ጋዜጠኛው የሰራውን የቢዝነስ ካርድ ዲዛይን ለመስጠት ወደ ኤርትራዊቷ ሱቅ እየሄደ ነበር።
ከኤርትራዊትዋ ችግር ጋር የሚመሳሰል ታሪክ ያገኝ እንደሆነ ኢንተርኔት ላይ መረጃ ሲያፈላልግ አንድ መረጃ አገኘና በግርድፉ ተረጎመው በጋዜጣው ላይ ሊያወጣው።  የፅሁፉን ርዕስ “ስሜታዊ ዘማዊነት” አለው።
ስሜታዊ ዘማዊነት አብዛኛውን ጊዜ የሚከሰተው ወይም  አለ የሚባለው አንድ ሰው ከሚስቱ ወይም አንዲት ሴት ከባልዋ ውጪ ሌላን ሰው በወሲባዊ ስሜት ከተመኘችውና/ከተመኛትና/ ልታገኘው ካለመች ነው።
አብዛኛውን ጊዜ ስሜታዊ ዘማዊነት የሚጀምረው ደስተኛ ስላልሆኑበት ትዳርዎ ከሌላ ሰው ጋር/የተቃራኒ ፆታ/ ጋር መወያየት፣ መነጋገር ወይም ምክር መጠየቅ ወይም ብሶትዎትን መተንፈስ በጀመሩ ጊዜ ነው።
ከትዳር አጋርዎ ጋር አተካራ  ውስጥ ወይም አለመጣጣም ውስጥ በመግባትዎ ምክንያት ብቻ ላለመግባባታችሁ ምክንያት ስለሆኑት ጉዳዮች ከትዳር አጋርዎ ጋር ከመወያየት ይልቅ ስላጋጠመዎት ችግር ለሌላ  ሰው መተንፈስ ይፈልጋሉ። አብዛኛውን ጊዜ በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሰዎች ሊያዋሩት ወይም ችግራቸውን ሊያካፍሉት የሚፈልጉት ሰው አብሯቸው የትዳር አጋራቸውን ሊረግምላቸው ወይም እነሱ ልክ እንደሆኑ ሊነግራቸው ለሚችል ሰው ነው። ነገር ግን ይህ ትልቅ ስህተት ነው።
ትዳርዎ እንዳሰቡት ሳይሆን ሲቀር ወይም በሚመኙት መንገድ መጓዝ ሳይችል ሲቀር ሚስጥራዊ የሚስጥር ተጋሪዎችዎን አጥብቀው እየፈለጓቸው ይሄዳሉ፤ ለምን ቢሉ ያለነሱ ውዳሴያዊ ወይም ሽንገላዊ ቃላት ህይወትዎ ባዶ እንደሆነ ይሰማዎታልና ነው። ለትዳርዎ ጤናማ አለመሆን የእርስዎም ስህተት እንዳለበት የሚሞግቶትን ህሊናዎትን አሸንፈው ፀጥ የሚያስብሉት በሚስጥራዊ ወዳጅዎ የከንቱ ውዳሴ ቃላት ነው:: በዚህም ምክንያት በትዳርዎት ውስጥ የሚያጋጥምዎትን እያንዳንዱን ችግር ሁሉ /ሚስጥር መሆን ይገባቸው የነበሩትን ጨምሮ / ይዘው ለውይይት ወደ ሚስጥራዊ ወዳጆችዎ ይሄዳሉ። እንደነዚህ አይነት ወዳጆች ደግሞ ደጋግመው የሚነግሩዎት አንድ ነገር ነው - የትዳር አጋርዎ  እርስዎን የመሰለ ሰው በማግኘቱ ምን ያህል የታደለ እንደሆነ:: ከባሰም እነሱ በእሱ ቦታ ቢሆኑ ኖሮ ስለሚያደርጉት ነገር:: በአብዛኛው ጊዜ እርስዎ በትዳርዎ ውስጥ እንዲኖሩ የሚመኙትንና የነገሩዋቸውን ነገሮች ያደርጉ እንደነበር ይደሰኩሩሎታል። ይህን አይነቱን የቃላት ኳኳታ/ዲስኩር/  ደጋግመው በሰሙና ትዳርዎም እንዳሰቡት ባልሄደ ቁጥር አማካሪዎትን ለፍትፈታዊ ጓደኝነት እየተመኙዋቸው ይሄዳሉ::
ባለንበት ዘመን እንዲህ አይነት ስሜታዊ ዘማዊነት ከሚከሰትባቸው ቦታዎች ወይም መንገዶች አንዱ ኢንተርኔት ነው:: በኢንተርኔት ማለትም በፌስቡክ፣ በስካይፕ፣ ወይም በሌላ መንገዶች በሚፈጠር ጓደኝነት በእየዕለቱ የሚያጋጥም ክስተት ነው- ስሜታዊ ዘማዊነት::
በርካታ ሰዎች በኢንተርኔት ‘ቻት ሩሞች’ ስለተለያዩ ጉዳዮቻቸው ቢወያዩም፣ ስለትዳራቸው መላ ቢጠይቁም፣ ከመጠየቅም አልፈው ከሚስጥራዊ ጓደኛቸው ጋር በስሜታዊ ዝሙት ቀልጠው ቢገኙም በጓደኝነታቸው መሃል ስሜታዊ ዘማዊነት መኖሩን አምነው ለመቀበል ይቸገራሉ:: ስሜታዊ ዘማዊነት በ ‘ፎን ወይም ቪዲዮ ሴክስ’ ይገለፃል። ለዚህም ነው በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ያለፉ በስተመጨረሻ ወደ ፀፀትና ጭንቀት የሚያመሩት።
መቼ ነው ስሜታዊ ዘማዊነት አለ የሚባለው!? ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ነጥቦች በእርስዎና  በሚስጥራዊ የሚስጥር ተጋሪዎ መካከል ካለ አይጠራጠሩ በስሜታዊ ዘማዊነት አለም ውስጥ እንዳሉ
  • ሚስጥራዊ ጓደኛዎትን በማሰብ በወሲባዊ ስሜት የሚቃጠሉ ከሆነ
  • ለሚስጥራዊ ወዳጅዎ ልዩ ስጦታዎችን የሚሰጡ ከሆነ/በተለይ በአካል የምትገናኙ ከሆነ/
  • የትዳር አጋርዎን ጭራሽ ቸል ያሉ ከሆነ
  • የትዳር አጋርዎን ከሚስጥራዊ ጓደኛዎት ጋር ማነፃፀር ከጀመሩና የሚስጥር ጓደኛዎት የሚሻል መስሎ ከተሰማዎት አይጠራጠሩ በስሜታዊ የዝሙት ባህር ውስጥ ለመስመጥ ብቅ ጥልቅ እያሉ ነው::
ታዲያ ከስሜታዊ ዘማዊነት ለማምለጥ መፍትሄው ምንድን ነው!? መልሱ ቀላል ነው:: በትዳርዎ ውስጥ የሚያጋጥሙዎትን እያንዳንዷን ችግር ጊዜ ሳይሰጡ በመነጋገር ለመፍታት ይሞክሩ:: ከትዳር አጋርዎ ጋር የሚያሳልፉት በቂ ጊዜ ይኑርዎት:: የትዳርዎን ገበና በፍፁም ለውጪ ሰው አይንገሩ:: የግድ መንገር ወይም ማዋየት ከፈለጉም በፍፁም ለተቃራኒ ፆታ አይንገሩ ወይም አያማክሩ/ያ ሰው የቤተሰብዎ አባል እስካልሆነ ድረስ/ ከስሜታዊ ዘማዊነት ለማምለጥ:: በተለይ በተለይ ማንነቱን ለማያውቁትና በኢንተርኔት ለተዋወቁት ሰው ገበናዎን በፍፁም አይንገሩ ሳይሆን ጭራሽ አያስቡት!
መርማሪው ፖሊስ በፋይሉ ላይ  “ለኤርትራውያን መረጃው በአስቸኳይ መረጃው ሊሰጣቸው ይገባል። ኤርትራውያንን የሚጠላ ዘረኛ አሸባሪ ጋዜጠኛ መሆኑ ሊነገራቸው ይገባል” በማለት ውሳኔውን ፃፈ።
ይቀጥላል


Friday, September 6, 2013

Educated Ethiopians are joining armed movements (Andargachew Tsige)

የጋራ ንቅናቄው ከሰማያዊ ፓርቲ ጎን ይቆማል!

September 6, 2013
 

የወጣት አመራሮቹን ሰላማዊ የትግል መስመር ይደግፋል!

Ethiopian newsያለፈው እሁድ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ጠርቶ በነበረው የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ላይ በህወሃት/ኢህአዴግ የተወሰደውን ጽንፈኛ፣ አክራሪና አጸያፊ የውንብድና ተግባር የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ይኮንናል፤ ያወግዛል፡፡ ፓርቲው ሰልፉን ለማካሄድ ከሁለት ወራት በፊት ፈቃድ ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም ቅዳሜ ነሐሴ 25፤2013 የፌዴራል ፖሊስና የደኅንነት አባላት የፓርቲውን ጽ/ቤት ጥሰው በመግባት የፈጸሙት ተራ የውብንድና ተግባር ብቻ ሳይሆን የህወሃት/ኢህዴግን ማንነት በግልጽ ያሳየ ለመሆኑ ከማንም በላይ ተግባሩ ራሱ ምስክር ነው፡፡
በዕለቱ እንደሆነው የህወሃት/ኢህአዴግ አሸባሪ ፖሊሶች የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤትን ከመውረራቸው በፊት ኤሌክትሪክ መስመሩን ቆርጠዋል፡፡ በቀጣዩም ለእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ዝግጅት እያደረጉ የነበሩትን አመራሮችና ፈቃደኛ ሠራተኞችን ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ ከደበደቡና ካሰቃዩ በኋላ ለሰዓታት አስረዋቸዋል፡፡ ወጣቶቹ ከተፈቱ በኋላ ለእሁዱ ስብሰባ ተመልሰው ዝግጅት እንዳያደርጉ የህወሃት/ኢህአዴግ አሸባሪዎች የፓርቲዉን ጽ/ቤት እስከ እሁድ ድረስ በመቆጣጠር ኮምፒውተሮችን፣ የጽህፈት መሣሪያዎችን፣ ሠንደቅዓላማዎችን፣ መፈክሮችን፣ … በማውደም፤ የሚፈልጉት በመውሰድ ሰልፉ እንዳይካሄድ አድርገዋል፡፡ ይህንን ተግባር የሚመሰክር ከበቂ በላይ የፎቶግራፍ፣ የሰው፣ … ማስረጃ ቢኖርም ህወሃት/ኢህአዴግ ሁሉንም በመካድ ለዓለምአቀፍ ሚዲያ አንዳች ነገር እንዳልተደረገ በመናገር የተለመደውን ዓይን ያወጣ ቅጥፈት ደግሟል፡፡

ጥያቄው ግን ሰላማዊ ሰልፍ እናድርግ ያሉ ቁርጠኛ ወጣቶች ያነሱት ይህ የመብት ጥያቄ ለምን ህወሃት/ኢህአዴግን ለምን አሸበረው? ለምንስ እንዲህ ያለውን ራሱን የሚያጋልጥ ተግባር እንዲፈጽም አደረገው? መልሱ ህወሃት/ኢህአዴግ ልምድ በሌለውና በማያውቅበት የሰላማዊ ትግል ጠንክረው ስለመጡበት ብቻ ነው! ለዚህ ደግሞ ለሁለት ዓመታት ያህል በጽናት መብታቸውን ለማስከበር የሚታገሉት ሙስሊም ወገኖቻችንና ሰሞኑን በአንድነት ፓርቲ የተጀመረው ሰላማዊ እንቅስቃሴዎች ማስረጃዎች ናቸው፡፡

ህወሃት/ኢህዴግ ባስቀመጠው ትዕዛዝ መሠረት የሰማያዊ ፓርቲ ለእሁዱ ሰልፍ ከሁለት ወር በፊት ደብዳቤ አስገብቶ ፈቃድ ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም ባለፈው ሰሞን ህወሃት/ኢህአዴግ ባቀናበረው የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ “አሸባሪነትንና አክራሪነትን” ለማውገዝ ሕዝቡ ሰልፍ እንዲወጣ ጥሪ አድርጎ ነበር፡፡ በጥሪ ብቻ ያላበቃው ዘመቻ የከተማው ነዋሪ በግድ፣ በማስፈራራት፣ በጉቦ፣ … ሰልፍ እንዲወጣ የተቀናበረም ነበር፡፡ ይህ ሰልፍ በሚካሄድበት ቀን ታቅዶ የነበረው የሰማያዊ ፓርቲ ትዕይንተሕዝብ ካልተጨናገፈ በስተቀር ህወሃት/ኢህአዴግ በጠራው በራሱ ሰልፍ ላይ የሚደርስበት ክስረት መራራ እንደሚሆን ግልጽ ነበር፡፡

ከሰልፉ ጥሪ በፊት በተካሄደው ጉባዔ ወቅት “በኢትዮጵያ ህዳሴ የሃይማኖቶች ተስማምቶ መኖር” አስፈላጊነት የተሰበከ ሲሆን ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ደሳለኝ በወቅቱ “የሃይማኖት አክራሪነትን” እንዲያጋልጡ ተሰብሳቢዎቹን በመጠየቅ መንግሥት በዚህ ዙሪያ የሚወስደውን እርምጃ አንደሚቀጥልበት አስጠንቅቀው ነበር፡፡ ቅዳሜ በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት የተፈጸመው ተግባር አሸባሪና አክራሪ ራሱ ህወሃት/ኢህአዴግ መሆኑን ያጋለጠበት ነው፡፡

የሃይማኖት ተቋማት ጉዳይ ያገባኛል በማለት ጉባዔ የሚጠራው ህወሃት/ኢህአዴግ፤ “በሃይማኖታችን ጣልቃ አትግባ፤ የራሳችንን መሪዎች እንምረጥ፣ መብታችን ይከበር” በማለት ላለፉት ሁለት ዓመታት ያህል እየጮሁ ያሉትን ሙስሊም ወገኖቻችን የመብት ጥያቄ መመለስ ያልፈለገ ወይም ያልቻለ ነው፡፡ ከዚህ ይልቅ ግን የራሱን ካድሬዎች በሃይማኖት መሪነት ሽፋን በመሾምና ሙስሊሙን ኅብረተሰብ በመከፋፈል የአፈናና የመብት ረገጣ ተግባሩን ቀጥሎበታል፡፡ ይህ የህወሃት/ኢህአዴግ አሠራር በሌሎች ሃይማኖቶችም የቀጠለ ለመሆኑ በሃይማኖት ተቋማት ስም የተጠራው ጉባዔና ሰልፍ በቂ ምስክር ነው፡፡

ህወሃት ገና ከጥንስሱ የሃይማኖት ጉዳይ የማይስበው፤ በበረሃው ቆይታ በተደጋጋሚ በአሸባሪነት ተግባር ላይ ለመሠማራቱ የተመሰከረለት መሆኑ፤ ራሱን በፈጣሪ የለሽ የሌኒኒስታዊ ፍልስፍና ያጠመቀ መሆኑ ራሱ የመሰከረውና በግልጽ የሚታወቅ ሆኖ ሳለ አሁን “በኢትዮጵያ የሃይማኖት ጉዳይ ያገባኛል፤ የሃይማኖት አክራሪነትን እታገላለሁ” ማለቱ ጅብ በማያውቁት አገር ሄዶ የአህያ ቁርበት አንጥፉልኝ ያለው ዓይነት ነው፡፡

በአመሠራረቱ የተለያዩ ኢትዮጵያውያንን የሚወክለው ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በኢትዮጵያ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ እያደረጉ ካሉት “የድምጻችን ይሰማ” ሙስሊም ወገኖች፣ የአንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምጽ፣ የሰማያዊ ፓርቲና ሌሎች ወገኖች ጋር ያለውን ኅብረት ይገልጻል፡፡ የጋራ ንቅናቄው ባለው ዓለምአቀፋዊ ዕውቅናና ግንኙነት በመጠቀምም የህወሃት/ኢህአዴግን ቋት ለሚሞሉት ለለጋሽ አገራት፣ ለሕግ ተቋማት፣ ለሰብዓዊ መብት ድርጅቶች፣ ለሚዲያ ተቋማት፣ ወዘተ በአገራችን ላይ እየተፈጸመ ያለውን የመብት ረገጣ ያሳውቃል፡፡ የህወሃት/ኢህአዴግን አገዛዝ እስካሁን የፈጸመውን የሽብር ተግባርና ወደፊት ለሚያደርሰው ማንኛውም በደል በቀጥታ ተጠያቂ እንዲሆን መረጃው በሕግ ተመዝግቦ እንዲቀመጥ ያደርጋል፡፡

በአገራችን በ1997 የተደረገውን ምርጫ ተከትሎ በሟቹ ጠ/ሚ/ር ቀጥተኛ ትዕዛዝ ህወሃት/ኢህአዴግ የፈጸመው የ193 ዜጎች ግድያ፣ የፖለቲካ መሪዎች እስር፣ አፈና፣ የመብት ረገጣ፣ … ያስከተለውን ፍርሃት ለመጀመሪያ ጊዜ በመግፈፍ የፖለቲካ ትዕይንተሕዝብ ያደረገው የሰማያዊ ፓርቲ ነው፡፡ “ድምጻችን ይሰማ” የሚያደርጉት በትክክለኛ የሰላማዊ ትግል መርህ ላይ የተመሠረተው እልህ አስጨራሽና መስዋዕትነትን የሚጠይቅ ትግል እንዳለ ሆኖ የሚሊዮኖች ድምጽ እንቅስቃሴም ከዚህ ጋር አብሮ ተጠቃሽ ነው፡፡

አርቆአሳቢና ራሳቸውን በሰላማዊ ትግል ዲሲፒሊን ያነጹ ወጣቶች ተሰባስበው በሰማያዊ ፓርቲ ሥር የሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሰላማዊ ትግል በትክክለኛው መንገድ ከተከናወነ በኢትዮጵያ እንደሚሠራ በተግባር ያስመሰከረ ነው፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን “ሰላማዊ ትግል ከኢትዮጵያ የፖለቲካ አንጻር አይሠራም” የሚለውን ስሜታዊ አስተሳሰብ ከሥሩ የመታ ትግል በመሆኑ የጋራ ንቅናቄው ለሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችንና አመራሮች ከፍ ያለውን አድናቆት ይሰጣል፡፡ በተለይም በሰላማዊ ትግል መስመር ስማቸው በዓለም የሚጠራው መሃትማ ጋንዲ፣ ዶ/ር ኪንግ፣ ማንዴላ፣ … በወጣትነታቸው ይህንን ዓይነቱን የትግል መስመር ከመምረጣቸው አኳያ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች የተጠና እንቅስቃሴና የዓላማ ጽናት ሌሎችም የእናንተን መስመር እንዲከተሉ የሚያደፋፍር እንጂ በምንም ዓይነት መልኩ የያዛችሁትን እርግጠኛ አቋም እንድትመረምሩ ሊያደርጋችሁ እንደማይገባ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በአጽዕኖት ያስታውቃል፡፡ ለመስከረም 12፤ 2006 ዓ.ም. የተጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ሁሉም ሰላም ወዳድ ወገኖች ድጋፋቸውን እንዲሰጡት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ከዚህ በፊት በሊቢያ በቅርቡ በግብጽ አሁን ደግሞ በሶሪያ ሕዝብን እያስተላለቀና እጅግ ደም እያፋሰሰ ያለውን ዕልቂት ተመልክታችሁ አገራችሁን በምንም ዓይነት መልኩ ወደ ደም መፋሰስና ዕልቂት እንዳትገባ የሚደርግ ሰላማዊ የትግል መስመር መምረጣችሁ የጋራ ንቅናቄው ምስክርነት የሚሰጠው ነው፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግ ከየትኛውም የአመጽና የሽብር ተግባር ጋር በግድ በማያያዝ ሊኮንናችሁ፣ ሊወነጅላችሁ፣ ወዘተ ቢሞክርና ወደፊትም ይህንኑ ለማድረግ ቢያስብ እስካሁን የፈጸማችሁት ሰላማዊ ሥራችሁና የትግል ስትራቴጂያችሁ በገሃድ የሚመሰክረው ከመሆኑ ባሻገር የጋራ ንቅናቄው ዓለም ሁሉ ይህንን ምስክርነት እንዲያውቅ በማስረጃነት የሚያስመዘግበው ነው፡፡

ትክክለኛውን የትግል መርሆ የተከተለ ሰላማዊ ትግል ከዚህ በፊት የሠራና አሁንም ከኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ መተግበር እንደሚችል ጠንቅቆ ያወቀው ህወሃት/ኢህአዴግ፤ በሰላማዊ የትግል መስመር የሚነሱትን ሁሉ ገና በእንጭጩ ሲቀጭ ቆይቷል፡፡ ተስፋ በማስቆረጥ፣ በመከፋፈል፣ በማሰር፣ በማሰቃየት፣ በመግደል፣ ወዘተ የፓርቲ አመራሮችን ያስወግዳል፤ ትግሉ ወደ ተራው አባል ከመዝለቁና አባሉ በራሱ አመራርና የትግሉ ባለቤት መሆን ከመቻሉ በፊት ይበታትናል፡፡ ይህንን የሚያደርገው ከባህርይውና ከለመደው የደም ማፍሰስ አገዛዝና ትግል ውጪ ያለ አካሄድ ሥልጣኑን ስለሚያናጋውና መጨረሻውን ስለሚያቃርበው ነው፡፡

እንዲህ ዓይነቱ የትግል መስመር ተጠናክሮ ወደ ሙሉ ህዝባዊ እንቅስቃሴና እምቢተኝነት ከተቀየረ ህወሃት/ኢህአዴግ መመከት የማይችልበት ደረጃ ስለሚደርስ ህልውናው ያከትማል፡፡ “ሥልጣን ወይም ሞት” በማለት የፖሊስና የመከላከያ ኃይሉን እስካፍንጫው በማስታጠቅ ዕድሜውን እየገፋ ያለው ህወሃት/ኢህአዴግን ወደ ሙሉ ህዝባዊነት የተቀየረ ሰላማዊ ትግልን መቆጣጠርም ሆነ ማጨናገፍ አይችልም፡፡ ለዚህ ነው ሰላማዊ ትግል በህዝቡ ዘንድ በሙላት ሳይሰርጽና መርሆዎቹ ተግባራዊ ሳይሆኑና ገና በጅምሩ ማጥፋት፣ ማውደም፣ ማሰቃየት፣ ወዘተ የሚፈልገው፡፡ በወጣቶች የተገነባው የሰማያዊ ፓርቲ ላይ እየረደሰ ያለው ሁኔታ ይህንኑ የሚያመለክት ነው፡፡

ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በኢትዮጵያ የማኅበራዊ ፍትሕ መስፈን የሚታገል እንደመሆኑ በሰላማዊ የትግል መስመር ላይ ያሉ ድርጅቶችንም ሆነ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎችን ይደግፋል፤ ያበተረታታል፡፡ በሰላማዊ የትግል መስመር የሚመጣ ለውጥ በአገራችን ያለማቋረጥ ሲፈስ የቆየውን የደም ጎርፍ እንዲቀጥል፤ ቂምና በቀል እንዲስፋፋ፤ መጪውን ትውልድ በፍርሃትና በማያቋርጥ የደም መፋሰስ አዙሪት ውስጥ እንዲገባ የሚያደርግ ሳይሆን፤ በፍትሕ ላይ የተመሠረተ ዕርቅ እንዲሰፍን፤ የአንዱን ነጻነት ብቻ የሚያስከብር ሳይሆን “ሁላችንም ነጻ ካልወጣን ማንም ብቻውን ነጻ ሊሆን አይችልም” በሚል የጠነከረ ምሶሶ ላይ የሚገነባ ነው፡፡ በአገራችን ለዓመታት የተረጨውንና እስከ ቤተአምልኮዎች የዘለቀውን የዘር ፖለቲካና የዘረኝነት አመለካከት ማምከን የምንችለው በሌላ መንገድ ሳይሆን በሰላማዊ መንገድ “ከጎሣ ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ” እንስጥ የሚለውን ታላቅ መርህ ከፍ ስናደርግ እንደሆነ የጋራ ንቅናቄው ያምናል፡፡ ይህንን አመለካከት ከሚጋሩ ሁሉ ጋር በጋር ይሠራል፤ ይንቀሳቀሳል፡፡

በአገራችን ላይ እስካሁን በበሽታ፣ በረሃብ፣ በድህነት፣ በእርስበርስ ጦርነት፣ … ብዙ ደም ፈስሷል፡፡ ከዚህ በኋላ የምንሄድበት መንገድ ይህንኑ እንዲቀጥል የሚያደርግ በጭራሽ ሊሆን አይገባውም፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግም ይህንኑ ሊያስተውልና “በለመድኩት የአፈና አካሄድ እቀጥላለሁ” ከሚለው ዕብሪተኛ አስተሳሰቡ ሊመለስ ይገባዋል፡፡ በውስጡ ያሉት የትግራይ ተወላጆችም ይሁኑ ሌሎች የአገራቸው ጉዳይ የሚያሳስባቸው ኢትዮጵያውያን በግልጽ የሚወጡበትና የህወሃት/ኢህአዴግ አሠራርን በግልጽ በመተቸት ሁላችንም ወደ ዕርቅ የምንመጣበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ ሥርዓቱ “ከእንጥሉ መበስበሱን” ሟቹ ጠ/ሚ/ር የመሰከሩለት በመሆኑ ምንም የሚደበቅ ነገር ስለሌለ ጉዳዩን ይፋ ለማውጣት የሚያስፈራ ነገር የለም፡፡ የጋራ ንቅናቄው ይህንን የጥሪ ደወል እስካሁን ሲያሰማ ቆይቷል፤ አሁንም ይህንኑ ይደግማል፡፡ ሆኖም ይህ በህወሃት/ኢህአዴግ ውስጥ ላሉትና ለመሰል ድቃይ ድርጅቶች የምንሰጠው “ከሥርዓቱ ተለዩ” የሚለው ጥሪ የሚያቆምበት ወቅት ላይ ነን፡፡ ምላሽ የመስጫው ጊዜ ነገ ወይም አንድ ቀን ሳይሆን ዛሬ፤ አሁን ነው፡፡ የአፈናና የጭቆና ሥርዓት ጸንቶ አይቆይም፡፡ እንኳን እንደ ህወሃት/ኢህአዴግ ያለው ዘረኝነትን መመሪያው፤ የአገር ውርደት ክብሩ የሆነ አገዛዝ ይቅርና በህዝባዊነታቸውና ብሔረተኝነታቸው የተመሰከረላቸው አገዛዞችም ጨቋኝ በመሆናቸው ብቻ እንደማይነሱ ሆነው ወድመዋል፤ ፈርሰዋል፡፡

ፈጣሪ ሁላችንንም የማስተዋልና ትክክለኛውን መንገድ የመምረጥ ጥበብ ይስጠን፡፡ የልቦና ዓይናችንን ከፍቶ የዘረኝነትን፣ የጥፋትን፣ የብቀላን፣ የውድመትን አስከፊነት እንድናስተውልና የሰላምንና የዕርቅን መንገድ እንድንመርጥ ይርዳን፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ የመረጣችሁትን ሰላማዊ መንገድ በምንም አትቀይሩት፤ ከእርሱ የሚበልጥም ሆነ የሚሻል መንገድ የለምና!! ሌሎች የእናንተን ዓይነት መንገድ አስቀድመው ከጀመሩ ጋር በኅብረትና በመቻቻል ሥሩ፡፡

ለውጥ በአገራችን ይመጣል! ይህ የማይቀር ሃቅ ነው! ኢትዮጵያ ነጻ ትወጣለች፤ ነጻ የምትወጣው ግን በሌላ ነጻ አውጪ ሳይሆን “ነጻ አውጪ ነኝ” የሚለውን ጭምር ነጻ በሚያወጣው እውነትና ፍትህ ነው፡፡

ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ

ለዚህ ደብዳቤ ምላሽም ሆነ ለተጨማሪ መረጃ ለአኢጋን ሚዲያና ሕዝብግንኙነትን ግብረኃይል (media@solidaritymovement.org) በመጻፍ ወይም ድረገጻችንን (www.solidaritymovement.org) በመጎብኘት ለመረዳት ይችላሉ፡፡

ከሁሉም የዐለም አቅጣጫዎች (አሜሪካንና አውሮፓን)ጨምሮ ብዙ ኢትዮጲያውያን ምሁራን መሳሪያ አንስተው ለመታገል ጫካ ገብተዋል :- አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ

ከሁሉም የዐለም አቅጣጫዎች (አሜሪካንና አውሮፓን)ጨምሮ ብዙ ኢትዮጲያውያን ምሁራን መሳሪያ አንስተው ለመታገል ጫካ ገብተዋል። ይህን ያሉት ለስራ ጉዳይ አሜሪካን ያሉት የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ዋና ፀሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ዛሬ ከኢሳት ቲቪ ጋር ባረጉት ቃለ ምልልስ ነው ።  በትግሉ ጉዳት ለሚደርስባቸውም ለቤተሰብ ማቋቋሚያ ፈንድ ተቋቁሟል።በኤርትራ ኖረውና ተዘዋውረው ባዩት መሰረት ከፕሬዝዳንቱ እስከገበሬው ድረስ ከኢትዮጲያውያውያን ጋር በወንድማማችነት መኖር ይፈልጋሉ ብለዋል አቶ አንዳርጋቸው። ስለ አሰብ እና ስለ አሁን ስላለውም መከለከያ አመራር  በተመለከተም ተናግረዋል።
ከሁሉም የዐለም አቅጣጫዎች (አሜሪካንና አውሮፓን)ጨምሮ ብዙ ኢትዮጲያውያን ምሁራን መሳሪያ አንስተው ለመታገል ጫካ ገብተዋል :- አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ



Thursday, September 5, 2013

በአንድነት ፓርቲ ላይ የሚደርሰው ወከባ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሚታየው ምዝበራ አንድ የፖሊስ ኢንስፔክተር መገደላቸው የእለቱ ዋና ዋና የዜና ርእሶች ናቸው

በአዳማ/ ናዝሬት  የአንድነት ፓርቲ አባላት መዋከባቸው ታውቀ

ነሃሴ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድነት ፓርቲ በመጪው እሁድ በከተማዋ ለሚያደርገው የተቃውሞ ሰልፍ የቅስቀሳ ወረቆቶችን ሲበትኑ የነበሩ ወጣቶች ለአጭር ጊዜ ተይዘው ተፈተዋል። ፓርቲው ሰለማዊ ሰልፍ እንዲአካሂደ ፈቃድ ከተሰጠው በሁዋላ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ እንጅ ወረቀት የመበተን ፈቃድ አልተሰጣችሁም በሚል ሰበብ ወጣቶቹ እንዲታሰሩ መደረጉ ታውቋል።

ኢሳት ከኢህአዴግ የአዳማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ባገኘው አስተማማኝ መረጃ ፣ ፖሊሶችና የደህንነት ሀይሎች ፓርቲው የሚያደርገውን ቅስቀሳ እንዲያስተጓጉሉ ተልእኮ ተሰጥቷቸዋል። በኦሮሚያ ክልል ነፍጠኞች ተመልሰው ስልጣን የሚይዙበት እድል ሊፈቀድላቸው አይገባም በማለት የኦህዴድ አመራሮች በመናገር ላይ ናቸው።

ከእነዚሁ ምንጮች ለመረዳት እንደሚቻለው የተቃዋሚ ድርጅቶች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ፣ በግንባሩ ውስጥ ከሚታየው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ፣ የፓርቲውን ከፍተኛ አመራሮች አስጨንቋቸዋል። ከሁሉም የኢህአዴግ ድርጅቶች  በኦህዴድ አባላት ዘንድ ከፍተኛ አለመረጋጋትና ተስፋ መቁረጥ እንደሚታይ የሚገልጹት ምንጮች ሙስና በከፍተኛ ሁኔታ መስፋፋቱንም ይገልጻሉ።
የአንድነት ፓርቲ በናዝሬት የሚያካሂደው ሰልፍ ለኦህዴድ ከፍተኛ ራስ ምታት ሆናል በማለት እነዚሁ ምንጮች ተናግረዋል። በሚቀጥሉት ተከታታይ ቀናትም ወከባው እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

አንድነት ፓርቲ በባሌ ሮቤ ለማካሄድ አቅዶት የነበረው ሰልፍ በኦህዴድ አመራሮች እንዲስተጓጎል መደረጉ ይታወቃል።

የአንድነት ፓርቲ የጠራው አዲስ አበባው ሰላማዊ ሰልፍ ከ33ቱ ፓርቲዎች ጋር በጥምረት ይደረጋል


አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ‹‹የሚልዮኖች ድምጽ ለነጻነት››በሚል መሪ ቃል የጀመረው ህዝባዊ ንቅናቄ መስከረም 5/2006 በአዲስ አበባ በሚደረግ ሰላማዊ ሰልፍ ይጠናቀቃል፡፡ፓርቲው በተለያዮ የአገሪቱ ክፍሎች ያደረጋቸውን ህዝባዊ ስብሰባዎችና ሰላማዊ ሰልፎች በአንክሮ ሲከታተሉ የቆዮት 33 ፓርቲዎች በአዲስ አበባ የሚደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ በጋራ ለማድረግ ስምምነታቸውን በመግለጽ በዛሬው ዕለት በአንድነት ዋና ጽ/ቤት ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡


33 ፓርቲዎችን በመወከል ንግግር ያደረጉት አቶ ሔርጫፉ አዴሎ ‹‹አንድነት በህዝባዊ ንቅናቄው ሲያነሳቸው የነበሩ ጥያቄዎች አንድነትን ብቻ የሚመለከቱ አይደሉም ፡፡እኛም የምንታገልላቸው እንዲመለሱ የምንፈልጋቸው ጥያቄዎች በመሆናቸው ትግሉን በአንድነት ለማደረግ ስምምነት ላይ ደርሰናል››ብለዋል፡፡

 የአንድነት የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ የሆኑት አቶ ስዮም መንገሻ ‹‹አንድነት በአብሮነት የመስራት ስስት የለበትም፡፡እንኳን ከ33 ፓርቲዎች ጋር ይቅርና በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲገነባ በሰላማዊ መንገድ ከሚታገል ፓርቲ ጋር በሙሉ ለመስራት በራችን ክፍት ነው፡፡››በማለት የፓርቲውን አቋም አንጸባርቀዋል፡፡

 አንድነት ፓርቲ በጎንደር፣በደሴ፣በአርባ ምንጭ፣በባሌ ሮቢ፣በወላይታ፣በፍቼና በሌሎች ከተሞች ባደረጋቸው ሰላማዊ ሰልፎችና ህዝባዊ ስብሰባዎች ያጋጠሙትን የመብት ረገጣዎቸ፣ኢ ህገ መንግስታዊ ጥሰቶች፣ድብደባዎችና ህገ ወጥ እስራቶች በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ይፋ አድርጓል፡፡በፍቼ ድብደባ የደረሰባቸው የፓርቲው ሁለት አባላት ነብዮ ባዘዘውና መሳይ ትኩ በአካል በመቅረብ ለጋጠኞች የደረሰባቸውን ድብደባ አስረድተዋል፡፡እጁ ላይ በድብደባው ምክንያት ስብራት የደረሰበት መሳይ በፋሻ የተጠቀለለ እጁን በማሳየት ‹‹ሁላችንም እናንተ ጋዜጠኞችም ባላችሁ መሳሪያ እስክሪብቶ እውነቱን በመጻፍ ይህንን አምባገነን ስርዓት መታገል ይጋችኋል››ብሏል፡፡

33 ፓርቲዎች በወርሃ መስከረም ቀጠሮ ስለያዙበት የአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ያወጡት መግለጫ የሚከተለው ነው፡፡

የሐምሌ ጨረቃ አንዷለም አራጌ ዋለ (ከቃሊቲ ማጎሪያ) ክፍል ሁለት

September 5, 2013

በሀገሬ ሰማይ ስር በሚደረገው የተቃውሞ ፖለቲካ እንቅስቃሴ ከኢዴፓ እስከ አንድነት ፓርቲ ድረስ በመሳተፍ ለአስራ ሶስት ዓመታት ያህል የምችለውን አስተዋጽኦ አድርጌያለሁ፡፡ ይህ ኩነትም የፓርቲዎችን ጓዳ ፈትሼ ግንዛቤ እንዳገኝ ስላመቻቸልኝ፣ በቀጣይ ህዝባችን የፖለቲካና ሰብአዊ መብቶቹ ተከብረው ነፃነቱን እንዳያገኝ እንቅፋት ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ የማስባቸውን ነጥቦች እንደሚከተለው ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡

 1. እንደ ገዥው ፓርቲ፣ ተቃዋሚ ድርጅቶችም ከኋላቀሩ የፖለቲካ ባህላ ለማስጀመር ከመስራት ይልቅ ሳያውቁት ከዘመነ-መሳፍንት የተቀዳውን የፖለቲካ ባህል በተሻለ ተግባራዊ ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ ዛሬም ይታያሉ፡፡

2. የእስከ ዛሬውን የከሸፈ ሂደት የገመገመና የኢትዮጵያን ህዝብ ለአንዴና ለመጨረሻ ከተጫነበት የጭቆና ቀንበር ለማላቀቅ የሚያስችል በውል የታሰበበትና የተጠና የፖለቲካ ቀመር እጦት በተቀቃዋሚ ፓርቲዎች ዘንድ በጉልህ ይንፀባረቃል፡፡
3. የማያምኑበትን መቃወም ተገቢ የሆነውን ያህል የየራሳችንም ህፀፆች ያለርህራሄ ማየት፣ አይቶም ነቅሶ ማውጣት ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን በተቃዋሞ ጎራ ባለነው ፖለቲከኞች ላይ ይህንን የማድረግ ችግር ይታይብናል፡፡ ህፀፆችን ቀድሞ ማየቱ ከሌላ ወገን የሚሰነዘረው ነቀፋ ምክንያቱን ለመረዳት እድል ይሰጣል፡፡ በትችት ከመሰበርም ይታደጋል፡፡
4. ከ1960ዎቹ ጀምሮ የኢትዮጵያ ፓርቲዎች መለያ ከሆኑት አንዱ ‹ግትርነት› መሆኑ አከራካሪ አይመስለኝም፡፡ ይህ ሁኔታ በፓርቲዎች መካከል ብቻ ሳይሆን፣ በራስ ፓርቲ አባላት ውስጥም የሚፈጠሩ ችግሮች ከግትርነት የሚነሱ ናቸው፡፡ ‹‹መሸነፍ››፣ ‹‹ማሸነፍ››፤ ‹‹መንበርከክ››፣ ‹‹ማንበርከክ›› በሚለው የጫወታ ህግ ታስረን በቆምንበት ስንረግጥ በአስከፊው የመከራ ዘመን እንድንቆይ አድርጐናል፡፡ ችግር የመፍቻ ስልትም ሆነ ባህል አላዳበርንም፡፡ እንዲያውም የትግሉ እንቅስቃሴ ከአገዛዙ ጋር መሆኑ ቀርቶ በእኛ መካከል ሆኗል፡፡
5. የተወሰኑ ሰዎች ‹‹በሰላማዊ ትግል›› ውስጥ ቢሆኑም ‹‹በዚህ መንገድ አገዛዙን ታግሎ ማሸነፍ አይቻልም›› የሚል እምነት ስላደረባቸው በግማሽ ልብ የሚያደርጉት ትግል ትርጉም ያለው አስተዋፆ እንዲያበረክቱ አላስቻላቸውም፡፡ ሰላማዊ ትግል ራሱን የቻለ ትልቅ እምነት መስጠትና ስነ-ምግባር ያለው መሆኑን ይዘነጋሉ፡፡
6. አንዳንድ የተቃዋሚው የትግል ጐራን የሚቀላቀሉ ግለሰቦች በስሜት ብቻ በመመራት አባል የሚሆኑበት አገጣሚ ብዙ መሆኑ ለተደራጀ ትግል እንቅፋት ሆኗል፡፡ ይህንን በምሳሌ ለማስረዳት ከአንድ የቀበሌ ካድሬ ጋር ስለተጣሉ ብቻ አባል የሚሆኑ ሰዎች፣ አገዛዙን ለመቀየር የሚጠይቀውን መስዋዕትነት ከፍሎ ከማሸነፍ ይልቅ እልሃቸው ሲበርድ የውሃ ሽታ ሆነው መቅረታቸው ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡
7. አገዛዙ አንዳንድ ጠንካራ አባላትና አመራር ላይ ጥቃት ማድረስ ሲጀምር ተደናግጦ ማፈግፈጉም ሌላ ችግር ነው፡፡ ይህ ሁኔታ የነፃነት ትግል አልጋ በአልጋ እንደሆነ ከመጠበቅ የሚመነጭ ይመስለኛል፡፡
8. የፓርቲ አባላት ከአመራር እስከ ተራ አባላት፣ ከገጠር እስከ ከተማ ንቃተ-ህሊናቸውን የሚያዳብሩና የርዮተ-ዓለም ትጥቆችን የሚያስታጥቁ ስልጠናዎችንና የውይይት መድረኮችን የመፍጠር ችግርም ተጠቃሽ ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ ድንገተኛና በቂ ዝግጅት ያልተደረገበት እንቅቅስቃሴ ይደረጋል ውጤቱም አመርቂ አይሆንም፡፡
9. የዓለም አቀፍ ሰላማዊ ትግል ተሞክሮዎችን ከኢትዮጵያ ታሪክ፣ ፖለቲካ፣ ባህል እና ተጨባጭ ወቅታዊ ሁኔታዎች አንፃር ተቃኝተው ተግባራዊ የሚያደርጉበትን ሁኔታ የመፍጠር ችግር ይታያል፡፡
10. የቁርጠኝነት ችግር፡- የአገዛዙ አውራዎች ወጥተው በመገናኛ ብዙሃን ፉከራና ቀረርቶ ሲያሰሙ ተደናግጦ ወደዋሻ መግባትና የትግሉን ሙቀት ማቀዝቀዝም እንዲሁ መፍትሄ የሚፈልግ ጉዳይ ነው፡፡
11. በእቅድ የመመራት ችግር፡- በገዥው ፓርቲ ትንኮሳ ወይንም መግለጫ ላይ ተመስርቶ የእሳት አደጋ ስራ መስራት፡፡
12. ተቀባይነት ያለውና ህዝብ በቀላሉ የሚረዳው አስተሳሰብ፣ ታማኒነት ያለው ንግግር የተጨባጭ ተግባር ባለቤት ያለመሆን ችግር፡፡
13. ተጠራጣሪነት፡- አብሮ ታግሎ ለውጤት ለመብቃት መተማመንን መፍጠር የመጀመሪያው ተግባር ሊሆን ሲገባው መተማመን በጎደለበት ሁኔታ ፓርቲዎች አብረው ለመስራት ቢሞክሩም ሩቅ መገዝ አይችሉም፡፡ አሉባልታ ከግልፅነት ይልቅ እድል ይሰጠዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ትግሉ ያለባለቤት ይቀመጣል፡፡
14. መናናቅ፡- ጥቂት ንብረትና ጥቂት አባላት ያሏቸው ፓርቲዎች ከሌሎች ፓርቲዎች በጥቂቱ መሻላቸው ትግሉን ያጠናቀቁ ያህል ይኮፈሳሉ፡፡ በሌላ ወገን ያሉትም ጉድለቶችን በማስተካከል ወደፊት በትጋት ሊፋታ ሲገባ ስራቸውን ትትው መዘላለፍ ውስጥ ይገባሉ፡፡
15. የፓርቲ አመራሮች ታላቅ የመሆን ቅዠት፡- ከዘመነ-መሰፍንት የተቀዳው የፖለቲካ ባህላችን ብዙ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን በማስጎምዠት እንቅልፍ ይነሳናል፡፡ የፕሮግራም ሆነ የአሰራር ልዩነት ሳይኖር ለስልጣን በሚደረግ ፍልሚያ ፓርቲን የሚያህል ተቋም ለሁለት ይከፍሉታል፡፡ በቲኒኒሽ ቢሮዎች ትልልቅ ሽኩቻዎች ይደረጋሉ፡፡ ትልልቅ ስም ያላቸው አመራሮች በጥቃቅን ጉዳይና ከስልጣን ጋር በተያያዙ ችግሮች ተጠልፈው ይወድቃሉ፡፡ የማያበራ ችግርም ይፈጠራል፡፡ ዓላማችን ትልቅነት እንኳ ቢሆን ትልቅ መሆን የሚቻለው በአስተሳሰብና በተግባር ልቆ በመገኘት እንጂ በብልጣ ብልጥነት ሊቀ-መንበር ተብሎ በመሰየም አለመሆኑን ይዘነጉታል፡፡
16. የሰላማዊ ትግልን ባህሪያት የትግል ስልቶችና ግቦቹን በሚገባ አለመተንተን ወይንም ግልብ በሆነ ግንዛቤ ተመስርቶ መንቀሳቀስ፡- ከ1960ዎቹ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እንቅስቃሴ ጀምሮ የሀገራችን የፖለቲካ ትግል በሰላማዊ መንገድ ወጣ ገባ እያለም ቢሆን ተሞክሯል፡፡ በኢህአዴግ የ22 ዓመታት አገዛዝም ለቁጥር የሚያታክቱ ፓርቲዎች በሰላማዊ መንገድ እንታገላለን ብለው ቢደራጁም አብዛኛው የትግሉን ባህሪ አለማወቃቸው በትብብር የሚመጣ ውጥን አዘግይተዋል፡፡
17. ትግሉን የህዝብ የማድረግ ችግር፡- በሀገራችን በተደረጉ የሰላማዊ ትግል ሙከራዎች ላይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚያነሷቸው አጀንዳዎችን የሕዝብ በማድረግ እንዲታገልባቸው ሲያደረጉ አይታይም፡፡ ትግሉ ግብ ሊመታ የሚችለው ህዝቡ በትግሉ ከልብ አምኖ መታገል ሲችል ነው፡፡ ሆኖም ወደ ህዝብ ባለመውረዱ ጥቂት አመራሮች ሲታሰሩ ወይንም ቢሮዎች ሲዘጉ ትግሉም የመዳፈን አዝማሚያ ሲያሳይ አስተውለናል፡፡
18. የተፅኖ ማዕከሎች ያለመኖር፡- ተቃዋሚ ፓርቲዎች እራሳቸው አፈና ውስጥ ሆነው የአፈና ቀንበር ለመስበር የሚሰሩ በመሆናቸው የአቅም ውሱንነቶች አለባቸው፡፡ ስለዚህ ያላቸውን የገንዘብና የሰው ሃይል አብቃቅተው የተሳካ ትግል ማድረግ ይችሉ ዘንድ የተወሰኑ የተፅኖ ማዕከላትን መፍጠር ይጠበቅባቸዋል፡፡ ደቡብ ህበረት በ1992 ዓ.ም. ብሔራዊ ምርጫ ሃድያ አካባቢ ያደረገው ተጋድሎ ለተነሳው ሃሳብ ጥሩ ምሳሌ ይመስለኛል፡፡
19. ትኩረት የተነፈገው የፓርቲዎች የገንዘብ የማሰባሰቢያ ስትራቴጂ፡-  በገንዘብ አቅርቦት ምክንያት በርካታ እቅዶች ወደተግባር ሳይለወጡ ይቀራሉ፡፡ በየክፍለ ሀገሩ ራሳቸውን ለመስዋዕትነት ያዘጋጁ አባሎቻቸውን ከማዕከል ጋር ግንኙነት እንዲኖራቸው በማድረግ ትግሉን አጠናክሮ ከመግፋት ይልቅ የቢሮ ኪራይ እንዲላክላቸው በመወትወት ጊዜያቸውን ሲያባክኑ ይታያሉ፡፡ በሂደትም እየተሰላቹ ከትግሉ ያፈገፍጋሉ፡፡ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ስትራቴጂ አዘጋጅቶ የገንዘብ ጥያቄን በማያሻማ መልኩ መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡ ይኽንን ማድረግ ሳይቻል በሰላማዊ ትግል ብዙ ርቀት መሄድ አይቻልም፡፡ የሚኖረው ዕጣ ፈንታ እንደአንዳንዶቹ ፓርቲዎች ጓዝን ጠቅልሎ ቀለብ ለማስፈር ለገዥው ፓርቲ ማደር ነው፡፡
ከሞላ ጎደል የኢትዮጵያን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቀይደው የያዙና ሰላማዊ ትግሉን ወደፊት አላራምድ ካሉ ችግሮች ውስጥ እነዚህ ዋነኞቹ ናቸው ብዬ አስባለሁ፡፡ እናም ፓርቲዎቹ በሰላማዊ ትግል የኢትዮጵያን ሕዝብ የነፃነቱ ባለቤት እንዲሆን በሚያስችል መንገድ ለመምራት ከዚህ አንፃር ራሳቸውን ቢፈትሹ የተሻለ ነው፡፡
ይህንን ሀሳብ ከጠባቡ የእስር ክፍሌ የላኩት ፓርቲዎች፣ አመራሮቻቸውና አባላቻቸው እንዲዳከሙ ወይም ተነሳሽነታቸውን አኮስሼ ከጫወታ ለማስወጣት ከመፈለግ ሳይሆን የተሻ አቅምና ስትራቴጂ አዳብረው ለውጤት እንዲበቁ ብሎም የኢትዮጵያን ህዝብ ከአፈና አዙሪት ለማውጣት እንዲችሉ ከልቤ በቅንነት በመመኘት መሆኑን እንደምትረዱኝ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
ሌላው መረሳት የሌለበት እውነታ በፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ በተለያዩ የሀላፊነት ደረጃ ባሳለፍኳቸው እስራ ሶስት ዓመታት በፓርቲም ሆነ በግለሰብ ደረጃ ለታየው ድክመት እኔም ሀላፊነት የምወስድ መሆኔን ነው፡፡ እንዲሁም ካሉብኝ ውሱንነቶች አንፃር አቀራረቤ የጅምላ በመሆኑም ምንም እንኳን በአጠቃላይ የዴሞክራሲ ትግሉ ላይ በተናጠል ለውጥ ማምጣት ባይችሉም ሁልጊዜም የተሻለ የተደራጀ፣ የተሻለ ዴሞክራሲያዊ አሰረራር የነበራቸው ፓርቲዎች እንደነበሩ አይካድም፡፡ እናም ሁሉንም በአንድ አይነት ደረጃ ማስቀመጥ እንዲመጣ ለምንሻው መሻሻልም በጐ አስተዋፆ እያበረክትም፡፡ በግለሰብ ደረጃ ቢሆን ሁሉንም አንድ ቅርጫት ውስጥ መወርወር ተገቢ አይደለም፡፡ ለስልጣን የማይቋምጡ፣ ቀን ከሌት ሰርተው የማይሰለቹና ለሀገራቸውና ለህዝባቸው ችግር ቅድሚያ የሚሰጡ (በጣም ጥቂት ቢሆኑም) ግለሰቦች መኖራቸውን በዚህ አጋጣሚ ማስታወሱ ተገቢ ነው፡፡ የዚህ ፅሁፍ አላማም እንዲህ አይነት ግለሰቦች ተበራክተው ወደ ስብስብ ደረጃ እንዲደርሱ ማበረታታት ነው፡፡
የሆነ ሆኖ ከፍ ብዬ ያነሳዋቸው ከግማሽ ምዕተ-ዓመት በላይ ውል አልባ ያደረጉ ችግሮችን መፍታት ለነገ የማይባል ስራ ነው፡፡ ይህን ዓላማ ከግብ ለማድረስም ከዚህ በታች የምጠቅሳቸው ነጥቦች አስፈላጊ ናቸው ብዬ አምናለሁ፡፡
1. በየጊዜው ለምናስመዘገባቸው ለውጦች እውቅና በመስጠት በተገኘው ድልም  እየተበረታታን ነፃነት እኛ እስከታገልን ድረስ በተጨባጭ የምናሳካው ግብ መሆኑን ማመን፡፡
2. አገዛዙን ለማሸነፍ ተቀዳሚው ተግባር ራሳችንን ማሸነፍ መሆኑን ተገንዝቦ ህዝብን ከስሜት በፀዳ መልኩ በሀላፊነት ስሜት ማደራጀትና ለውጤት ለማብቃት መስራት፤
3. ሰላማዊ ትግል ለውጤት የሚበቃው በዕውነት፣ በፍቅርና ከዚያም በሚመነጭ ፅናት ላይ ተመስርተን ተግባራዊ ስናደርገው መሆኑን መገንዘብ፤
4. ገዥዎች በአፈ-ሙዝ ስጋን ሊገድሉ ሲያደቡ፣ ክፉ ሃሳባቸውንና ተግባራቸውን በአሳማኝ ምክንያቶችና በተገራ ሰብዕና ላይ ተመስርቶ ለመለወጥ መስራት፡፡
5. ፍርሃትን መግደል፡- ፍርሃትን ማሸነፍ ባልቻልን ቁጥር ሰላማዊ ታጋዮች የመሆን ዕድላችን በዚያው መጠን መቀነሱ አይቀሬ ነው፡፡ የፍርሃት እስረኞች በሆንን ቀጥር አገዛዙ የጭቆና ሰንሰለቱን ለማጥበቅ ስለሚበረታ ፍርሃትን ግዴታ ማሸነፍ ያስፈልጋል፡፡ የአገዛዙን ቁንጮዎችም ሆነ ማንኛውንም ሃላፊ መፍራትና ክብሩን ማዋረድ አያስፈልግም፡፡ ትግሉ የእነርሱ አይነት የህዝብ ጌቶች ለመፍጠር ሳይሆን የህዝብ አገልጋዮችን ለመፍጠር ነውና፡፡
6.  ሰላማዊ ትግል ለውጤት የሚበቃው ከበቀልና ግብታዊ ከሆኑ እርምጃዎች እራሳችንን ስናፀዳ ነው፡፡ አላማችን የማንም ክብር የማይደፈርባትና የሁላችንም ሉዓላዊነት የሚከበርባት ልጆቻችንም በኩራት የሚኖሩበትን ሀገር መፍጠር ነው፡፡
7. የአገዛዙ የአፈና እርምጃዎችና በህዝብ ዘንድ ሽብርን ለመንዛት የሚያደርጋቸው የሀሰት ዶሴዎች ለተጨማሪ ትግል መነሳት እንዳለብን የሚያስገነዝቡ እንጂ ፈፅሞ ወደኋላ እንድናይ የሚያደርጉን አለመሆናቸው፡፡
8. በየጊዜው የአቋማችንን፣ የትግል ስልታችንን ትክክለኛነት መፈተሽ በወቅቱም እርምት መውሰድ ወሳኝ ነው፡፡
9. ሁልጊዜም ቢሆን ተሳስተን ገዥዎቻችን መጠላት፣ ለበቀል መዘጋጀትም ሆነ በእነርሱ ላይ በመዛት ወደፊት በሚመጣው ንጋት ስጋት እንዲገባቸው ማድረግ አያስፈልግም፡፡ አይገባምም፡፡
10. አገዛዙ ለህዝብ ፈቃድ ለመገዛት ተነሳሽነት ሲወስድ ማበረታታት እንጂ እንደተዳከመና እንደተንበረከከ እንዲሰማው ማድረግ ተገቢ አይደለም፡፡
11. የኢትዮጵያን ህዝብ ለዘመናት ከስብዕና ሚዛን ያወረደውን የጭቆና ስርዓት መታገል የህይወት ዘመናችን ዓላማ አልፋና ኦሜጋ ሊሆን ይገባዋል፡፡ በግለሰብ ደረጃ ያሉን ህልሞችና ጥቅሞች ሊሳኩ የሚችሉት ትልቁ ችግራችንን በጋራ ስንፈታ ነው፡፡ ሁለንተናችን አንድ ላይ የተገመደ መሆኑን ለአፍታም መዘንጋት አይገባንም፡፡
12. በረጅሙ ታሪካችን ተሳክቶ የማያውቀውን የድሎች ሁሉ አውራ ማስመዝገብ የምንችለው ትግሉ የሚጠይቀውን የመስዋዕትነት ደረጃ ከወዲሁ ተረድተን በስነ-ልቦናም ስንዘጋጅ ነው፡፡ ምናልባት አንዳንዶቻችን የትግሉ ፍሬ ተቋዳሾች ለመሆንም እንደርስ ይሆናል፤ መንገዳችን ላይ መታሰርና መንገላታት ብቻ ሳይሆን ሞትም አድፍጦ ሊጠብቀን ይችላል፡፡  ይኽንንም አውቀን በቁርጠኝነት መግፋት ብቻ ነው ያለን አማራጭ፡፡
13. ሁልጊዜም በአቋራጭ እና የትግል አጋሮቻችን መስዋዕት በማድረግ ለውጤት ለመብቃት መሞከር አይገባንም፡፡ ትግላችን ግልፅነትና ንፅህና የተሟላ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ነገ ልንፈጥር የምንመኘውን መልካም ነገር፣ ዛሬ በምናደርገው መልካም ተግባሮች የተሞላ መሆን ማስመስከር አለብንና፡፡
14. የአገዛዙን ባህሪዎችና ‹‹የእግር ቆረጣ›› ስልቶች ቀድሞ በመረዳት የተጠና አፀፋዊ እርምጃ ለመውሰድ አስቀድሞ መዘጋጀትም ያስፈልጋል፡፡
15. በዘረኝነት ወጥመድ ተጠልፎ ላለመውደቅ መጠንቀቁም ተገቢ ይመስለኛል፡፡ አገዘዙ ስልጣን ላይ መቆየት እስከቻለ ድረስ የኢትዮጵያ ህዝብ በዘረኝነት ወረርሽኝ ቢጠቀም አንዳች ቅሬታ የሚገባው አይመስልም፡፡ ያዝ ለቀቅ እያደረገ ሲንቀሳቀስ እንደምናየው ስልጣኑን የሚነቀንቅ ከመሰለው የሃይማኖት አሊያም የዘር ግጭት ቀስቅሶ መልሶ እራሱን ግጭት አርጋቢና መፍትሄ ፈላጊ አድርጐ ለማቅረብ ይሞክር ይሆናል፡፡ በእኛ በኩል ሊያዝ የሚገባው ግልፅ አቋም በየትኛውም ዘመን ቢሆን አንዱ ህዝብ ሌላውን ጨቁኖ ባለማወቁ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ በየትኛውም ወቅት ቢሆን ኢትዮጵያውያን አማኞች የወንድሞቻቸውን የማምለክ ነፃነት ተጋፍተው አያውቁም፡፡
ሕዝብ በጋራ የአምባገነን መሪዎች የአፈና ሰለባ ነው፡፡ ሰውን በአስተሳሰቡ እንጂ በዘሩ መመዘን የጀመርን ቀን ያን ጊዜ ከሰብዓዊነት ሚዛን እንወጣለን፤ ከስልጣኔ ሃዲድ እንስታለን፡፡ የሰላማዊ ትግል የመጨረሻ ግብ ፍቅር፣ ወንድማማችና አስተማማኝ ነፃነት ሆኖ ሳለ ለዘረኝነት እድል በሰጠን መጠን የትግላችን አላማ ይከሽፋል፡፡ ዘረኝነት ኢሰብዓዊነት ነው፡፡ ዘረኝነት ከትንሽና ክፋት ከተጠናወተው ሰብዕና የሚመነጭ መርዝ ነው፡፡ በዘረኝነት ሰንሰለት ተጠፍንገን ለውጤት ለመብቃት ብንሰራም ፈጣሪም ከእኛ ጋር አይቆምም፤ ዓላማው በሰው ልጆች መካከል ፍቅርና አንድነት እንጂ ጥላቻና መለያየት አይደለም፡፡ ጊዜም ከእኛ ጋር አይተባበርም፡፡ ለኢትዮጵያውያን ሁሉ እኩልነት፣ ነፃነትና ክብር ከልብ ስንቆም ያን ጊዜ የፈጣሪ ሀያል ክንድ ከእኛ ጋር ይሆናል፡፡
16. ሚስጥራዊነትና ሰላማዊ ትግል ጋብቻ ሊፈፅሙ አይገባም፡፡ የምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ሁሉ ውጤታቸውም ጭምር በይፋ ማወቅ ለሚፈልግ ሁሉ ግልፅ ማድረግ ይገባል፡፡ አገዛዙ እንኳን በሚስጥር የሚደረግ እንቅስቃሴ አግኝቶ በይፋ የሚደረጉ የትግል እንቅስቃሴዎችንም እስካልተመቹት ድረስ አይኑን በጨው ታጥቦ የሽብር ካባ እየደረበ ትግሉን ለማምከን ሲሞክር እያየን ነው፡፡ የአገዛዙ ክፉ ሃሳብና ተግባር እንዳለ ሁኖ ግልፅነት በህዝብና በትግሉ መካከል ያለውን ቁርኝት ያጠብቀዋል፡፡ ህዝቡም የፕሮፓጋንዳ ሰለባ እንዳይሆን ይረደል፡፡ ስለዚህ በምንም አይነት መልኩ ከመጋረጃ ጀርባ የሚደረጉ የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴዎች ሊኖሩ አይገባም፡፡
17. የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴዎች ትኩረት በማዕከል በሚደረግ ዝግጅት ብቻ ሳይሆን በየአካባቢው ያሉ አባላት አጠገባቸው ባሉ አመራሮች አማካኝነት በተጨባጭ ችግሮች፣ በእውቀትና በጥሩ ዝግጅት ላይ የተመሰረቱ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ሲችሉ ለትግሉ ግብዐት ይሆናሉና፡፡ ሌሎች የፓርቲ ቅርንጫፎችም ከእነርሱ ተሞክሮ እንዲወሰዱ ማድርግ በተቻለ መጠንም በየቦታው ያሉ አባላትና ነዋሪው ህዝብ ስለሰላማዊ ትግል ተጨባጭ ትምህርት በመቅሰም እንዲንቀሳቀስ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
18. የሰላማዊ ትግል ፈርጦች የሆኑት ማህተመ ጋንዲና ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር በተለያየ ወቅት የተናገሩትን ተመሳሳይ ይዘት ያለውን ሃሳባቸውን አፅንዎት ሰጥተን ልንወስደው ይገባል፡፡ ማህተመ ጋንዲ ‹‹ማንም ሰው ያለፈቃዱ አንዳች ነገር እንዲያደርግ ምንም አይነት ምድራዊ ሃይል ሊያስገድደው አይችልም፡፡›› ሲሉ፣ ዶ/ር ኪንግም ‹‹እስካልተጐነበስን ድረስ ማንም ሊጋልበን አይችልም፡፡›› ማለቱ ይታወሳል፡፡ ይህ አንድ አይነት መልዕክት የሚያስተላልፈው የሁለቱም የነፃነት ታጋዮች አባባል በየትኛውም ሀገር በጭቆና ቀንበር ስር ለሚማቅቅ ህዝብ የሚሰራ እውነታ ነው፡፡ ስለዚህም ከቆምንለት ህዝባዊ፣ ዴሞክራሲያዊ መንግስት የተመሰረተባት የወንድማማችነት፣ የፍቅርና የነፃነት ማማ የሆነች ሀገር የመገንባት ግባችን ሊመልሰን የሚችል አንዳች ሃይል እንደሌለ ተገንዝበን በፅናትና በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ ይገባናል፡፡
እንደ መውጫ
ከመተኛት አልፎ እንደ ልብ መንቀሳቀስ በማይቻልበት ጠባብክ የእስር ክፍሌ ሆኜ ጎኔን ወለል ላይ፣ ጆሮዬን ወደምድር አስጠግቼ ልዳበስውና ልጨብጠው የማልችለውን ድምፅ ላደምጥ ሞከርኩ፤ እናም የአለፈው እና የአሁኑን የዘመን ዱካ ከእነአፈ እና ግሳንግሱ እየራቀ ሲሄድ፤ የመጭው ዘመን የነፃነት ድምፅና ጭቆናን የማይቀበል ትውልድ ኮቴ እየቀረበ ሲመጣ ይሰማኛል፡፡ ይህ ድምፅ ዕውን እንዲሆን ጊዜውም እንዲፈጥን፣ አባቶቻችን የዳር ድንበር ነፃነት ለማስከበር እንደዘመቱት እኛም የሰላም፣ የፍቅር፣ የወንድማማችነትና የፅናት ሰይፍ ታጥቀን የመትመም ለነገ የማያድር ሀላፊነት አለብን፡፡
ጉዞአችን ምንም ያህል አዝጋሚና በውጣ ውረድ የተሞላ ቢሆንም የምንወዳትን አዛውንት ሀገራችንን ከዘመናት የስቃይ ፅንሷ ነፃነትን የምትገላገልበት ወቅት ስለመቅረቡ ለሰከንድም አልጠራጥርም፡፡ የሐምሌና ነሐሴ ድቅድቅቅ ጨለማ፣ አጥንት ሰብሮ የሚገባ ብርድ ያኮራመታቸው እፀዋት በመስከረም ወር ከአፅናፍ አፅናፍ በሚዋኘው የብርሃን ጅረት ሁለንተናቸው ተፍታቶ ለአይን የሚማርኩ የተፈጥሮ ፀጋዎች መሆናቸውን በኩራት እንደሚያውጁ ሁሉ፣ ኢትዮጵያውያንም ዕድሜ ጠገቡን የአገዛዝ ቀንበር ከጫንቃችን አውርደን በመጣል፣ ሀገራችን ከዳር ድንበር ነፃነት ጋር ብቻ ተያይዛ የምትጠቀስ አለመሆኗን በተጨባጭ በማረጋገጥ በኩራት በሀገራችን መኖር እንጀምራለን፡፡ ሀገራችን የሰብዓዊ ክብር ማማ የምትሆንበት ዘመን እነሆ እየገሰገሰ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ያ ዘመን በመሬታችን ሲደርስ ‹‹ኢትዮጵያ የአፍሪካ መዲና…›› የሚለውን የኩኩ ሰብስቤ ዜማ ከተወሰኑ የግጥም ማስተካከያዎች ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘን ከልብ መዘመራችንም አይቀሬ እንደሆነ አምናለሁ፡፡
አዛውንቷ ሀገራችን የሰብዓዊ ክብር ማማ፣ ‹‹የአፍሪካ ገናና›› ትሆን ዘንድ ነፃነትን በእርጋታ፣ በትዕግስትና አስተዋይነት በተሞላበት ሁኔታ የምናዋልድ ጥበበኛ ሀኪሞ ልንሆን ይገባናል፡፡ ሀገራችን በተለያየ ወቅት ነፃነትን ብታረግዝም ፅንሱን ከእነነፍሱ ለማዋለድ እስከዛሬ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ያልተሳኩ ነፃነትን የማዋለድ ጥረቶችም በባለታሪኳ ሀገራችን ላይ አገዛዙ እረግጦ በመግዛት ለመቀጠል የሚያደርገው የሞት ሽረት ትግል ሲጨመርበት፣ ሀገራችንን ፈፅሞ ወደ ማንመኘው የውድቀት አፋፍ ይዟት እንዳይወርድ ጥብቅ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል፡፡ ይኽን ማድረግ ካልቻልን በምክንያት የማንመራ፣ በስሜትና ኋላቀርነት አረንቋ የምንዳክር ልጆቻችን የሚያፍሩብን፣ መጭው ትውልድ የሚወቅሰን አባቶች እንዳንሆን ስጋቴ ፅኑ ነው፡፡
ስለዚህ በድቅድቁ የጭቆና ሌሊት ላይ ለዘላለም የማትጠልቅ የነፃነት ፀሐይ እስትከሰት ትግላችን ሊቀጥል የገባዋል፤ በድቅድቁ የአፈና ሌሊት ጨረቃ ያለማቋረጥ እስክትሰለጥን ጤፍ የሚያስለቅም ጣፋጭ ፍቅር የሚያስኮመኩም፣ ዜጐች ያለአንዳች ስጋት የሚመላለሱበትና የዱር አራዊትም ጭምር ለአደን ያለመከልከል እንዲወጡ የሚያስችል ብርሃኗን በምድራችን ላይ እስክትረጭ ትግላችን ከቀድሞ በበለጠ ደረጃ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፤ ሀገራችን የረጅም ዘመን እርግዝናዋን በሰላም ተገላግከላ የምድር ሁሉ ፈርጥ እስክትባል ድረስ የነፃነትንና የወንድማማችነት ንጋት የተራባችሁ ኢትዮጵየውያን ሁሉ የፍቅርና የፅናት ዝናራችሁን ታጥቃችሁ ትግላችሁን ቀጥሉ፡፡ አዎ! ነፃነት እንደቀትር ብርሃን ፍቅርም እንደሃይለኛ ጅረት የሀገራችን ምድር ሞልቶ ይፍሰስ!! ነፃናት፣ ነፃነት፣ ነፃነት፤ እደግመዋለሁ አሁንም ነፃነት!!!

የህወሃት ክፍፍል ከሙስና እስከ ፖለቲካ አመለካከት ውጥረት…..ህወሃት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶአል

September 5, 2013
ምንሊክ ሳልሳዊ

በአዜብ ዳፋ አቦይ ስብሃት ሊዳፋ ???

ሕወሓት አዲስ አበባ ላይ በግምገማዊ ውጥረት ተከሽኖ አባላቱ እርስ በእርስ እያባላ አጣብቂኛዊ ስብሰባ ተቀምጧል:: ስብሰባው ታዲያ በነአዜብ የታለመው አሉ በእባባዊ መርዛቸው ሾልከው እስካሎጡ ድረስ አቦይ ስብሀትን ነው ::አቦይ ስብሃት ቤተሰቦቻቸውን በተደላደለ ኑሮ አውሮፓ ውስጥ አንፈላሰው እያኖሩ ጣሊያን በሚገኙ ሁለት ልጆቻቸው ስም በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ዶላር እያሸሹ ይገኛሉ አንደናው ይገኛሉ አንደናው ልጃቸው የሕወሓት ተተኪ ለመሆን ኮሚኒስታዊ ስልጠና በቻይና ሲወስድ የተመደበለት ባጀት ለሶስት ተማሪዎች የሚመደብ ስለሆነ የሚሉ ስሞታዎች መቅረብ ጀምረዋል ሽማግለው ደሞዙ በሺዎች የሚቆጠር ብር የሚኖረው ግን በሚሊዮኖች የሚሉ ትንኮሳዎች በነበረከት ቡድን እየተለጠፉበት ነው::


አብዛኛው የሕወሓት ካድሬ በደብረጺሆን ጉያ የተሸሸገ ሲሆን የውሳነ ሰጪነት መሉ ስልጣኑን የተቆጣጠረው ደብረጺዮንን መከታ አድርጎ በሙስና የሚተየቁ ካሉ የጠየቁ ዘንድ ግፊት እያደረጉ ነው::የብኣዴኑ በረከት ስምኦን በሞተ የስልጣን እርከን ላይ በመሆን እየተንደፋደፈ በመለስ ራእይ ውስጥ ተሸሽጎ ለማምለጥ ቢሞክርም በፍርሃት እና በስጋት ራሱ አስሮ ውርደቱን እየጠበቀ ነው:ሲሉ ካድሬዎቹ ይተቹታል::የደህንነት ባለስልጣኑን ወልደስላሴን መያዝ ተከትሎ በስብሰባ የተወጠረው ሕወሓት ማን ወደ ሙስናው ዘብጥያ ይውረድ የሚለውን ወይንም የረጋጋ የሚለውን ለመናገር በአጣብቂኝ ውስጥ ነው::
በሁለት ሃይሎች መካከል የተነሱ ፍትጊያዎች ማብቂያቸው በሰረ ሙስና እና በመለስ ራእይ ስም ውስጥ እየተሹለከለከ ነው::የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም የመለስን ራእይ ሽፋን አድርጎ የሚውረገረገው የበረከት ቡድን በአቦይ ስብሃት እና አባይ ጸሃዬ በኩል በትችት ፍልጥ የተመታ ሲሆን መለስ ዜናዊን በተመለከተ በሚደረጉ የፖለቲካ ፍጆታዎች ላይ የላቸውን አቋም አቶ በረከት በፍጥነት እንዲያጡ ሲደረግ ከሚዲያው ጎራም ተጠልዘው ወተዋል::
ሕወሓት ሰላሙን አጥቷል::በቀጭን ገመድ ታንቆ ለመሞት እያጣጣረ ያለበት ሰአት ላይ ካድረው ስብሰባ ተቀምጦ ድርጅታችንን እናድን እያለ ሲሆን የመለስ ድርጅታዊ የማፊያዊ አመራር በሞት ከተኮላሸ በኋላ ድርጅቱ እና አባላቱ በተለይ አመራሩ ተከፋፍሎ እየተባላ እየተናከሰ ነው::

ልማት ምንድ ?እውን የወያኔ መንግስት ልማታዊ ነው?

         
በዶ/ር ታደሰ ብሩ

1. መግቢያ

“ሰላም ምንድነው?” በሚል ርዕስ ለፃፍኩት መጣጥፍ ከደረሱኝ በርካታ አስተያየቶች ውስጥ “በነካ እጅህ ልማት ምን ማለት እንደሆነ ብትገልጽልን” የሚለው ጥያቄ ለዚህ ጽሁፍ ምክንያት ሆኗል።

ከአሰልቺ የወያኔ ካድሬዎች ክርክሮች አንዱ “ልማታችን፣ ልማታችን” መሆኑ የማውቀውና በራሴም ላይ ከተራ ማሰልቸት በላይ የመብት ጥሰቶች ያደረሰብኝ ጉዳይ ነው። ወያኔ በአገራችን ላይ ላሰፈነው አገዛዝ ተቀባይነት (ligitimacy) ዋነኛ መከራከሪያው “ለኢትዮጵያ ልማትን ያመጣሁ፤ አሁንም በማምጣት ላይ ያለሁ መንግሥት ነኝ። ለወደፊቱም ኢትዮጵያን ለማልማት ከኔ የተሻለ የለም” የሚል ነው። በዚህ ክርክር ውስጥ (1) ከዚህ በፊት በአገሪቱ ውስጥ ልማት የሚባል ነበር አልነበረም፤ (2) እኔ ልማትን እያመጣሁ ነው፤ ሌላውን ቻሉት፤ እና (3) ለወደፊቱም ከኔ የተሻለ ኢትዮጵያን ማልማት የሚችል የሌለ በመሆኑ ለኢትዮጵያ ሲባል እኔ ለረዥም ጊዜ በስልጣን መቆየት አለብኝ የሚል መልዕክት አለው።

በዚህ ጽሁፍ እነዚህን ሶስቱም መከራከራዎች ውሸት መሆናቸውን ለማስረዳት እሞክራለሁ። ከሁሉ አስቀድሞ ግን “ልማት” በተሰኘው ጽንሰ ሀሳብ ላይ የጋራ ግንዛቤ እንያዝ።

2.የልማት ትርጉም

በዛሬቷ ኢትዮጵያ መብራት ሲቋረጥ፤ ውሀ ሲጠፋ፤ ጤፍ ሲወደድ፤ መንደሮች ሲፈርሱ፤ የመኪና አደጋ ሲበዛ፤ ገበሬዎች ሲፈናቀሉ ሰበቡ ልማት ነው። ማናቸውም ችግር “እድገት ያመጣው ነው፤ ቻሉት” እየተባለ ይታለፋል። ለረሀብ፣ ለጥማት፣ ለበሽታ እና መሰል መጥፎ ነገሮች ልማት ምክንያት ሆኖ ሲቀርብ፤ “መብቴ ይከበርልኝ ብሎ መጠየቅ “በፀረ-ልማትነት” ሲያስከስስ “ለመሆኑ ልማት ምንድነው?” የሚል የጅል አልያም የልጅ የሚመስል ጥያቄ ለማንሳት እንገደዳለን።  ………..

ሙሉ ጽሁፉን ከዚህ ላይ ያንብቡ (PDF)