Thursday, August 29, 2013

“በሬ ሆይ ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ” እንዳይሆን እንጠንቀቅ

ቢከፍቱት ተልባ የሆነውና ላይ ላዩን ሲያዩት ልማት የሚመስለው የወያኔ ኢኮኖሚ “ልማትና እድገት” የገንዘብ ካፒታል የሚያገኘው እንደሌሎቹ በእድት እንደሚገሰግሱ ታዳጊ አገሮች የእንዱስትሪ ሸቀጥ አምርቶ ለአለም ገቢያ አቅርቦና ሽጦ አይደለም። ተሰራ የተባለው ብልጭልጭ ነገር ሁሉ የሚሰራው የድህነት ጌቶች “Lords of Poverty” በሆኑት አለም አቀፍ ተቋሞችና ሀገሮች በሚገኝ እርዳታ ነው። ወያኔ እራሱ በፈጠሩ ችግር ተሰዶ በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊም ለወዳጅ ዘመድ የሚልከው የውጭ ምንዛሬም ሌላው የወያኔ የገንዘብ ምንጭ ነው። በዚህ ላይ የሀገሪቱ የተፈጥሮ ሀብት የሆነውን ለም መሬት በገፍ ለባዕድና ለሀገር ውስጥ የወያኔ ቤተኞች በመቸብቸብ የሚገኝ ገንዘብ አለ። መቼም ኢትዮጵያዊው በገዛ ሀገሩ የኩርማን መሬት ባለርስትና መብቱ ከተነጠቀ ቆይቷል። ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ ባለርሰተቹ ወያኔና ጉጅሌዎቹ ብቻ ናቸው።
የሀገሪቱ የገንዘብ ሀብት ብዙ ጊዜ የሚገባው ከግርጌው በተቀደደ ቋት ውስጥ ስለሆነ ለዘላቂ ልማትም ሆነ ገንዘቡን ለሚቀራመቱት ወያኔዎች በቂ አልሆነም።
ይህንን ቀዳዳ ቋት ለመሙላት ወያኔ ሰሞኑን የፈጠረው ዘዴ ህዝቡን የቤት ባለቤት ላደርግህ ስላሰብኩ አስቀድመህ ገንዘብህን አምጣ የሚል ዘዴ ነው። ሃያ-ሰማኒያ አርባ-ስልሳ ወዘተ የሚል ዘዴ ተገኝቷል። ይህ አርባ ስልሳና ሃያ ሰማንያ የሚሉት ፈሊጥ የኢትኦጵያ ደሃ ህዝብ ነገ ያልፍልኛል እያለ ሆዱን ቋጥሮና አንጀቱን አስሮ ያፈራትን ገንዘብ እንዲሰጣቸው የታለመ የጮሌዎች የገንዘብ መሰብሰቢያ ዘዴ ነዉ።
በተለይ የውጭ ምንዛሬ ያስገኛል ተብሎ የታመነበት 40/60 የሚባል ዘዴ በየኢምባሲው በወረቀት ላይ በተሰሩ ቆንጆ የቤትና የኮንዶሚኒየም ንድፎች አሸብርቆ መጥቷል።
ይህችን የጭልፊት ኢኮኖሚ ማየት የተሳናቸው የዋህ ኢትዮጵያውያን በየባዕድ ሀገሩ ለፍተው ያፈሯትን ጥሪት ይዘው በየኢምባሲው ለምዝገባ ሲጋፉ ማየት እጅግ በጣም ያሳዝናል። ብዙ ኢትዮጵያውያን ይህንን የዝርፊያ ኢኮኖሚ የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ በሚል ፈሊጥም የገቡበት አሉ። ራሳቸውንም ሀገራቸውንም እያዘረፉ መሆኑ የገባቸው አይመስልም። ወያኔ ይልቁንም የገቢያው መድራት ስላስጎመጀው ለውጭ ነዋሪ ያዘጋጀውን 40/60 አቁሞ የተሻለ ጥቅም የሚያስገኝ መንገድ እያሰላ ነው።
ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ይህን የድቡሽት ላይ ቤት እንሰራለን ብለው ያሰቡ ወገኖች ሁሉ የወያኔን ቀዳዳ ኪስ ከመሙላታቸው በፊት ጥቅሙን፤ ጉዳቱንና ትርጉሙን አገላብጠው እንዲያዩ ይመክራል። በተለይ በወያኔ ስር በሚገኝ ንብረት ያልፍልኛል ብለው በስደት ኑሮ ያፈሩትን ገንዘብ የነጻነታቸዉ መያዣ ተደርጎ ለባሰ ውርደት እንዳይዳርጋቸው ግንቦት ሰባት ወገናዊ ምክሩን ይመክራል።
ቤት አልባ ሆኖ በየመንገዱ ላይና በየደሳሳ ጎጆዉ ታጉሮ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ወገናችን በየዕለቱ እየጨመረ ባለበት በአሁኑ ወቅት ከነሱ እየተዘረፈ በሚሸጥ ንብረት ሀብት ለማፍራት መሞከር ለህሊናም የሚቀፍ ነው።
የወያኔ የቤት ስራ ፕሮጀክት ገንዘብ መልቀሚያና ጥቂት ባለሟሎቻቸውን መጥቀሚያ እንጂ ለዚህ ሁሉ የውጭ ነዋሪ የሚደርስም አይደለም። ወያኔ አስቀድሞ ከወለድ ነጻ የሆነ ገንዘብ ከሰበሰበ በኋላ ገንዘቡን ተጠቅሞ ከአምስትና አስር አመት በኋላ ቤቱንም ገንዘቡንም ማግኘት ላይቻል ይቻላል። ወያኔም ተጠያቂነትን የማይወድ አገዛዝ መሆኑን ካሁኑ አለመገንዘብም ራስን ጨፍኖ ለመሞኘት መፍቀድ ነው።
የወያኔ 40/60 ገንዘብ መሰብሰቢያ እንጂ ህዝብ መጥቀሚያ አይደለም። ወያኔዎች ሊጠቅሟቸው የሚፈልጉ ዜጎችን ከፈለጉ በየጎዳናው ላይ ያገኟቸዋል ለምን እነሱን አየረዷቸዉም?
በተለይ በውጪ የምንኖር ኢትዮጵያውያን በፍጹም ድህነትና የወያኔ ዝርፊያ ተዋርዶ የሚኖረውን ህዝባችንን እያየን የዚህ ግፈኛ መንግስት መሳሪያ ከመሆን አልፈን ራሳችንንም ለተዋራጅነት እንዳንዳረግ እንጠንቀቅ!
ድል ለኢትዮጵያ ሀዝብ!!

በብሔርተኝነት ስም ታሪክንና የኢትዮጵዊነትን መንፈስ ማጣጣል ተቀባይነት የለውም

August 29, 2013
በፍቅር ለይኩን

በአንድ ወቅት በደቡብ አፍሪካዊቷ ከተማ በኬፕታውን የሚኖር አንድ በንግድ ሥራ የሚተዳደር  ኢትዮጵያዊ ጎልማሳ አንድ አሳዛኝ ገጠመኙን እንዲህ አጫውቶኝ ነበር፡፡ ይህን ታሪኩን ያካፈለኝ ኢትዮጵያዊ ጎልማሳ የሥራ ቦታው ላይ ከአንድ ከኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ጋር በተነሳ ጠብ በተፈጠረ ግጭት የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ የሆነው ጓደኛውን አንድ የፊቱን ጥርሱን በቦክስ ያወልቀዋል፡፡ የጥርሱን መውለቅ የሰሙ የዚህ ሰው ጓደኞችም ተሰባስበው ይህን ሰው ካልገደልን በማለት ሲጋበዙ ነገሩ በሰላም ያልቅ ዘንድ አንዳንድ የሚያውቋቸው ሰዎች ለሽምግልና ጣልቃ ይገባሉ፡፡

በሽምግልና ድርድር ላይ እያሉም የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ የሆነው ጓደኛውን ጥርስ ያወለቀው ሰው የአያቱ ስም የኦሮሞ ስም ሆኖ ይገኛል፡፡ እነዛም በእንዴት ተደፍረን፣ ይህን ሰው ካልገደልን በማለት ሲዝቱ የነበሩ የኦሮሞ ብሔር ተወላጆችም፣ ይኽ ሰው ለካ ወገናችን ነው በማለት ለበቀል ያነሱትን ሰይፋቸውን ወደ ሰገባው ይመልሳሉ፡፡ ሐሳባቸውን በመቀየር ጉዳዩ በሰላም ተቋጭቶ፣ በሃያ ሺሕ የደቡብ አፍሪካ ራንድ ካሳ ክፍያ እንዲጠናቀቅ ተስማምተው እርቅ ማውረዳቸውንና አያቴ ስም የኦሮሞ ስም በመሆኑ ከጉድ ወጣሁ ሲል በግርምት መንፈስ ሆኖ ገጠመኙን አጫወተኝ፡፡

ይህ ሰው እስከዛች ቀን ድረስ ስለ አያቱ ኦሮሞነትም ሆነ ስለመጣበት ብሔር ወይም ጎሳና ማንነት በቅጡ አስቦ ወይም ትዝ ብሎት እንደማያውቅና ይህ ገጠመኙ ግን ከሚኮራበት ከኢትዮጵያዊነት ማንነቱ ባሻገርም ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ስለሰኟት ሕዝቦቿ ታሪክ፣ ባህል፣ ማንነትና ቅርስ ለማጥናት የማንቂያ ደወል ሆነኝ ሲል ነግሮኛል፡፡ በነገራችን ላይ ይህ ሰው በተለያዩ ጊዜያት ወደ ደቡብ አፍሪካ በስደት የገቡና ኖሮአቸውን በዛው ያደረጉ የኦሮሞ ተወላጆች ለደቡብ አፍሪካ መንግሥት የፖለቲካ ጥገኝነት ጥያቄ በሚያቀርቡበት ወቅት የተፈጠረውን እሰጥ አገባም እንዲህ ጨምሮ ተርኮልኛል፡:

የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ሆኑ ስደተኞች ለፖለቲካ ጥገኝነት ብቁ የሚያደርጋቸውን ቅፅ በሚሞሉበት አጋጣሚ አብዛኛው የኦሮሞ ተወላጆች ዜግነት ወይም አገር በሚለው ክፍት ቦታ ላይ ‹‹ኦሮሚያ›› በማለት በመሙላታቸው የደቡብ አፍሪካ ‹‹ሆም አፌር ቢሮ›› የሥራ ባልደረቦች እኛ ‹‹ኦሮሚያ›› የሚባል አገር አናውቅም በማለታቸው በተነሳ ክርክር፣ እነዚህ የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ የሆኑ የፖለቲካ ጥገኝነት ፈላጊዎች፣ ‹‹ኦሮሚያ በቀድሞዋ አቢሲኒያ በአሁኗ ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ስር ምትማቅቅ አገር ናት፡፡›› በማለት በማስረዳት ዜግነት በሚለው ክፍት ቦታ ላይ ‹‹ኦሮሚያ›› የሚለው ማንነታቸው እንዲሞላላቸው ቢጠይቁም ተቀባይነት በማጣታቸው እየጎመዘዛቸው ቢሆንም የማያምኑበትን የኢትዮጵያዊ ዜግነት በክፍት ቦታው ላይ ይሞሉ እንደነበር ይህ ሰው ጨምሮ ነግሮኛል፡፡

ይህንና ይህን የመሳሰሉ ብሔርን ማእከል ያደረጉ አሳዛኝ ገጠመኞች በኢትዮጵያም ሆነ በውጭ አገር ተደጋግመው የሚከሰቱ መሆናቸው ደጋግምን ያየነውና የሰማነው እውነታ ነው፡፡ በአውሮፓ፣ በአሜሪካ፣ በአውስትራሊያና በደቡብ አፍሪካ ዛሬ ዛሬ በትግሬ፣ በአማራ፣ በኦሮሞ … ወዘተ ስምና ማንነት የራሳቸውን ወሰን ወስነውና አጥር ከልልው የሚኖሩና ይህና ያ ብሔር በእኔና በዚህ ብሔር ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው በደል፣ ግፍና ጭቆና አድርሶብናል በሚል የየራሳቸውን የጭቆና ታሪክና የተጋድሎ ገድል ጽፈውና አጽፈው ያሉ፣ ከዚህም የተነሳ ደግሞ ለበቀል የሚፈላለጉና በጎሪጥ የሚተያዩ ሕዝቦች ኢትዮጵያ በምትባለው ምድር ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ነው፡፡

ይህን ከላይ በመግቢያችን የገለጽኩትን አሳዛኝ ገጠመኝ ወይም ታሪክ ለዚህ ጹሑፍ መግቢያ ይሆነኝ ዘንድ የመረጥኩት ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ ስለ ኢትዮጵያዊነትና ኦሮሙማ (ኦሮሞ ናሽናሊዝም) በተመለከተ ‹‹በገዳ ዶት ኮም›› እና በሌሎች በተለያዩ ድረ ገጾች ሰፋ ያለ ውይይትና ክርክር ተደርጎ ነበር፡፡ በዚህ ከስምንት የማያንሱ ማእከላቸውን አውሮፓና አሜሪካ ያደረጉ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና የኦሮሞ ምሁራን ባደረጉት ውይይትና ክርክር ከተሳተፉት ፖለቲከኞችና የኦሮሞ ምሁራን መካከል ዶ/ር በያን አሶቦና ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ይኸው የኢትዮጵያዊነትና የኦሮሙማ ሙግትም የፓል ቶክ ዋና የመወያያ ርዕስ ሆኖ ነበር፡፡ ይህ ውይይትና ክርክር ገና ሳይበርድና ሳይቋጭ ነበር በዛው ሰሞን ወጣቱ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁርና ተንታኝ ጃዋር ሙሐመድ ከአልጄዚራ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ለዓመታት በዘለቀው የኦሮሞ ጥያቄ፣ የነፃነት ትግል ታሪክ ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ ትንታኔ የሰጠው፡፡ ጃዋር I am First Oromo. Ethiopia is imposed on me የሚለው አቋሙን ግልጽ ካደረገ በኋላ የኦሮሞን ታሪክና የኦሮሞን የዓመታት ጥያቄ በተመለከተ የፖለቲካ ተንታኙን የጃዋርን ትንታኔና አቋም በመቃወምም ይሁን በመደገፍ የተለያዩ ሐሳቦች መንሸራሸር ጀመሩ፣ አሁንም ድረስም እየተንሸራሸሩ ነው፡፡

ባለፉት ሰሞናትም በተለያዩ በይነ መረቦችና በማኅበራዊ ድረ ገጾች ላይም የጃዋርን ሐሳብ ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች በየበኩላቸው አቋማቸውን ለመግለጽ ሞክረዋል፡፡ አንዳንዶችም ስድብ ቀረሽ በሚመስል ጨዋነትና ቅንነት በጎደለው መንፈስ ጃዋር ባነሳው ሐሳብ ላይ የውይይት መድረኩን የሚያጠለሹና የሚበርዙ እሳቤዎችን ከስድብ፣ ከዛቻና ከማስፈራሪያ ጭምር ሲያዘንቡም ታዝበናል፡፡ ከዚህ ውጪ ደግሞ ሰብአዊ ፍቅር፣ ጨዋነትና ቅንነት በተሞላበት መንፈስ ከኦሮሞም ይሁን ከሌላ ብሔር ተወላጆች ዘንድ፣ ሚዛናዊ የሆነ፣ ከጭፍን ጥላቻና ከበቀል ስሜት በጸዳ መንፈስ  ሐሳባቸውንና አቋማቸው የገለጹም ጥቂት ጸሐፊዎችና ተንታኞችም ብቅ ብቅ ብለው ነበር፡፡

እኔም በዚሁ ሰሞነኛ በሆነው የኦሮሞ ሕዝብን ታሪክና ጥያቄ በተመለከተ ለኦሮሞ ሕዝብ ነፃነትና መብት ቆመናል በሚሉ አንዳንድ የኦሮሞ ምሁራንና ፖለቲከኞች ዘንድ በኦሮሙማ (በኦሮሞ ናሽናሊዝም)፣ በኢትዮጵያ ታሪክና በኢትዮጵያዊነት ላይ በሚያነሷቸው አንኳር ሐሳቦችና በሚያራመዱት አቋሞቻቸው ዙሪያ ላይ ጥቂት የመወያያ ሐሳቦችን ለማጫር ወደድኩ፡፡

በእርግጥ ይህ ለውይይት ማጫሪያ እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ አጭር ጽሑፍ የኦሮሞ ተወላጅ ምሁራንና ፖለቲከኞችን፣ አሊያም ደግሞ በኦሮሞ ሕዝብ ስም ተቋቋመው እየተንቀሳቀሱ ያሉ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ታሪክና በኢትዮጵያዊነት ላይ ያላቸውን አቋማቸውንና ለኦሮሞ ሕዝብ አለን ስለሚሉት የትግል አቅጣጫዎቻቸውን ለመተንተን፣ ለመተቸትና ለመገምገም አይደለም አነሳሱ፡፡ ይህን ለማድረግ እንሞክር ቢባል እንኳን በእነዚህ ጥቂት ገጾች ለመሞከር የሚታሰብ አይሆንም፡፡

ለዚህም እንደ ዋና ሆነው ከሚነሱት ዐበይት ምክንያቶች መካከል ደግሞ በኦሮሞ ሕዝብ ስም እየተንቀሳቀሱ ያሉ በዓላማም በአቋምም የተለያዩ ፓርቲዎች መኖራቸው፡፡ እንዲሁም እነዚሁ ፓርቲዎችም የኦሮሞን ሕዝብን ታሪክና ጥያቄ  በተመለከተ የሚያራምዷቸው አቋሞችና ጥያቄዎች ‹‹ከባርነት ወይም ነፃነት›› ወይም ደግሞ ‹‹ከአቢሲኒያ/ከዛሬዋ ኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ነፃ የመውጣት ጥያቄ ነው፡፡›› ከሚለው ፖለቲካዊ አቋም አንስቶ በተለያዩ የኦሮሞ ተወላጅ ምሁራንና ፖለቲከኞች ዘንድ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች ባሉ የኦሮሞ ሕዝብ ታሪክ፣ ባህል፣ እምነትና ቅርስ አኳያ ያሉት አመለካከቶችና ትንታኔዎች መንገዳቸው የየቅል መሆኑን ነገርዬውን ቀላል አያደርገውም ብዬ ስለምገምት ነው፡፡

ለአብነትም ያህል የኦሮሞን ብሔርተኝነት በእጅጉ ያራምዱና ‹‹የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ የነጻነት ጥያቄ ነው፡፡›› ሲሉ የነበሩ አንዳንድ የኦሮሞ ምሁራንና ፖለቲከኞች በጊዜ ሂደት ኦሮሞ በኢትዮጵያ በቆዳ ስፋት ትልቁና የሕዝቡም ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ውስጥ ግዙፍ ሆነ ቦታ ሊሰጠው ይገባል፣ የኦሮሚፋም በኢትዮጵያ የፌዴራል መንግሥት ፖለቲካ አሥተዳደር ውስጥ የፌዴራል መንግሥቱ  ቋንቋ መሆን የሚችልበት መንገድ ሊታሰብብት ይገባዋል፣ የሚሉ የተለሳለሱ አቋሞችን የሚያራምዱ የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ፖለቲከኞችም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብቅ ብቅ ማለታቸውንም ታዝበናል፡፡
ስለሆነም በዚህ ጽሑፍ የኦሮሞን ታሪክ፣ ባህል፣ ማንነት፣ የኦሮሞን የመብት ጥያቄና ትግል ተመለከተ በፊትም ሆነ በተለይም ደግሞ ከሰሞኑን የፖለቲካ ተንታኙ ጃዋር ሙሐመድ ባነሳው የኢትዮጵያዊነትና የኦሮሙማ አንኳር እሳቤዎች ላይ ተመርኩዤ ጥቂት ነገሮችን ለማለት ወደድኩ፡፡

እንደሚታወቀው ባለፉት ሁለት ዐሥርት ዓመታት ውስጥ የእከሌ ብሔር ወይም ጎሳ በዚህኛው ብሔር ወይም ጎሳ ላይ ለፈጸመው በደልና ጭቆና በሚል ያልተወራረዱና ጊዜ እየጠበቁ ቦግ እልም የሚሉ ምሬቶችን፣ ቁጣዎችንና የበቀል ሰይፎችን በተለያዩ የአገራችን ክልሎች መከሰታቸውን ታዝበናል፡፡ ይህን እኩይ የሆነ የበቀል ሒሳብ በማወራረድ የተጠመዱ አንዳንድ ፓርቲዎች፣ ፖለቲከኞችና ግለሰቦችም ሆን ብለውና ያልተገባ ፖለቲካዊ ትርፍ ለማግበስበስ ሲባል እውነታን በማጣመም በሚጻፏቸውና በሚያጽፏቸው የተዛቡ የታሪክ ድርሳናትና ገድሎቻቸው፣ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ትናንትና ያልነበረ ዛሬም የሌለ ቅዠት ወይም ሕልም ነው እስኪባል ድረስ ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በርካታ ትንታኔዎቻቸውን ሰምተናል፣ የዳጎሱ ጥናታዊ ጽሑፎቻቸውንም አስነብበውናል፡፡
በዚህ እነዚሁ የብሔር ፖለቲካ ጽንፈኞች፣ በቀልን ሰባኪዎች፣ የብሔራዊ መግባባትና እርቅ ተቀዋሚዎች በተጻፉ የተዛቡ ታሪኮችና ያልተወራረዱ የበቀል ሒሳቦች ክፉ ስብከት የተነሣም ለዘመናት ተዋደውና ተከባብረው፣ በጋብቻና በአምቻ ተሳስረው፣ እኔ ትብስ አንተ ትብስ ብለው የኖሩ ሕዝቦች የተሳሰሩበትን የአንድነት ድርና ማግ ለመበጠስ ሲባል የተደረጉ አያሌ ዘመቻዎችንም በዘመናችን በሐዘንና በግርምት ሆነን አስተውለናል፡፡

ዛሬም ድረስ ለኦሮሞ ሕዝብ መፍትሔው የእኔ የፖለቲካ አቅጣጫ ነው የሚሉ በርካታ የኦሮሞ ምሁራን፣ ፖለቲከኞችና ፓርቲዎች በአገር ውስጥና በውጭ አገር ሆነው ለኦሮሞ ሕዝብ ይጠቅማል በሚሉት መንገድ የራሳቸውን አቋም በማራመድ ይጻፋሉ፣ ይወያያሉ፣ ይከራከራሉ፣ ይሟገታሉም፡፡

ይሁን እንጂ እስካሁኗ ቅጽበት ለኦሮሞ ሕዝብ ነፃነት፣ መብትና ጥቅም ቆመናል በሚሉት በበርካታ የኦሮሞ ፖለቲከኞች፣ ምሁራንንም ሆነ ፓርቲዎች ዘንድ ቢያንስ ባለፉት ሁለት ዐሥርተ ዓመታት የኦሮሞን ሕዝብ ታሪክና ጥያቄ በማስተጋባትና በመፍትሔ አቅጣጫዎችም ዙሪያ በሚያራምዱት አቋማቸው እርስ በርሳቸው የተለያዩና የተከፋፈሉ መሆናቸውን በተለያዩ አጋጣሚዎች ዐይተናል፡፡ በዋነኝነት የኦሮሞ ሕዝብን ጥያቄ ለመፍታት ከእኔ ወዲያ ለአሳር በማለት ሲምል ሲገዘት የነበረው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በዕድሜ የሚያክለውና የሚስተካከለው ባይኖርም ዛሬም ድረስ በተለያዩ ታሪካዊና ፖለቲካዊ ውስብስብ ችግሮች ተተብትቦ እየዳከረ ያለ ፓርቲ መሆኑን የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡
በተጨማሪም ባለፉት ዓመታት በፓርቲው አመራሮቹ መካከል በተፈጠረ ልዩነትና ውዝግብ የፓርቲው ህልውና አበቃለት እስኪባል ድረስ የነበረውና አሁንም በያዝ ለቀቅ በፓርቲው ውስጥ የሚነሱት ወጀብና ዐውሎ ንፋሶች ዛሬም ድረስ ገና መፍትሔና መቋጫ ያገኙ አይመስሉም፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው፣ ነፃነትን የማወጅ፣ ሉዓላዊነትን የማስከበር፣ የማንነት፣ የታሪክና ፖለቲካ ጥያቄ ነው፣ በማለት ጽንፈኛ አቋሙን በሚያራምደው ኦነግና ደጋፊዎቹ ዘንድ ዛሬም ድረስ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በሸዋው ንጉሥ በምኒልክ ሰይፍ ተቀጥቅጦ በአማራ ታሪክና ማንነት ላይ የተገነባ ነው የሚለው መከራከሪያቸው አሁንም ድረስ በአቋም ደረጃ በግልጽ የሚንጸባረቅ ነው፡፡

ወጣቱ የፖለቲካ ምሁርና ተንታኝ ጃዋር ሙሐመድም ይህንኑ ሐሳብ በመድገም እንዲህ ብሎአል፡- ‹‹ … ኢትዮጵያን የመሠረታት የሦስትዮሽ ጦርነት ግብግብ ነው፡፡ በአማራው፣ በኦሮሞው፣ በትግሬው ግብግብ ውስጥ ወደ መጨረሻ ላይ በአመራር ስር የበላይነቱን የያዘው አማራው ነበር፡፡ በዚህ የተነሳ አሁን የምናያት ኢትዮጵያ ማንነቷ በአማራ ባሕላዊ ሥርጭትና  በአማራ ፖለቲካ የተገነባች ነች፡፡ … የኢትዮጵያ አገራዊ ማንነት የምንለውም የአማራ ባህላዊ ማንነት ነው፡፡›› ሲል ከኢትዮጵያ ታላቅ ሥልጣኔ፣ ታሪክና ከኢትዮጵያዊነት መንፈስ ወይም ማንነት ጋር የሚጣረስ ድምዳሜን ሰጥቶአል፡፡

ይህ ዓይነቱ ትንታኔ የኢትዮጵያን ታሪክ በአግባቡ ያለመረዳት ቀውስ ወይም ደግሞ ሆን ብሎ  የታሪክ እውነታን የማዛባት ዘመቻ ነው የሚመስለው፡፡ ኢትዮጵያ የምትባለው ምድርና ሕዝቦቿ ትናንትና ከመቶ ዓመት በፊት ምኒልክና ተከታዮቹ በኃይልና በሰይፍ በሚፈልጓት ቅርፅና ይዘት ቀጥቅጠው የፈጠሯት እንጂ የሚለው መከራከሪያ ሐሳብ በምንም መንገድ ውኃ ሊያነሳ የሚችል ሐሳብ አይመስለኝም፡፡ ይህ ዓይነቱ አመለካከት ከሺሕ ዓመታት በፊት ጀምሮ በገናና ሥልጣኔዋና ታሪኳ በዓለም መድረክ ስሟ ገኖ የወጣውን፣ ከአፍሪካ አልፎ በሰሜን አሜሪካና በካረቢያን በባርነትና በቅኝ ግዛት ቀንበር ስር ተይዘው ሲማቅቁ ለነበሩ ሕዝቦች የነፃነት ምድር፣ የጥቁር ሕዝቦች ተስፋ ‹‹የጥቁር ሕዝቦች የከነዓን ምድር›› በሚል በሰቀቀንና በናፍቆት ሲያስቧትና ሲዘክሯት የኖረችውን ኢትዮጵያን ህልውና የመካድ ያህል የሚቆጠር ይመስለኛል፡፡

ኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት መንፈስ የነፃነት ተምሳሌት፣ የአንድነትና የፍቅር ኪዳን ሆኖ በብዙዎች ልብ ውስጥ ሲንቀለቀልና ለዘመናት ሲያበራ የኖረ እውነት መሆኑን መካድ አንችልም፡፡ ከአፍሪካ አስከ አሜሪካ፣ ካረቢያና ጃማይካ ይህ ኢትዮጵያዊነት መንፈስ በእውቁ የነፃነት ታጋይ በእነ ማርከስ ጋርቬይ፣ በሬጌው ንጉሥ በእነ ቦብ ማርሌይ፣ በእነ ፒተር ቶሽ፣ በአፍሪካውያኑ የነፃነት አባቶች፣ በእነ ጆሞ ኬንያታ፣ በንኩርማ፣ በማንዴላና በበርካታ የነፃነት ታጋዮች ዘንድ የሞራልና ወኔ ስንቅ ሆኖ ያገለገለ፣ ክቡር ታሪክ፣ ሕያው አሻራና ቅርስ መሆኑን መዘንጋት ከታሪክ ሐቅ ጋር መጣላት ነው የሚሆነው፡፡

በተጨማሪም ለዚህችው በሺሕ ዘመናት ገናና ሥልጣኔዋ፣ ነፃነቷ፣ ታሪኳና ሉዓላዊነቷ ሲሉ በዐድዋ ጦር ግንባር ከወራሪው የአውሮጳ ኃይል ጋር አንገት ለአንገት ተናንቀው ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ለሕዝቦቿም ነፃነት ዋጋ የከፈሉትን የኦሮሞ ተወላጆቹን የእነ ባልቻ አባ ነፍሶን፣ የእነ ደጃዝማች ገረሱ ዱኪን፣ የእነ ራስ አበበ አረጋይን፣ አውሮጳ ምድር ድረስ ዘልቆ በሮማ አደባባይ የኢትዮጵያውያንን አይበገሬነትና ለነፃነታቸው ቀናኢ ሕዝብ መሆናቸውን ያሳየውን የአብዲሳ አጋንና የበርካታ እልፍ የሚሆኑ የኦሮሞ ልጆችን ለሰው ልጆች ነፃነት የፈሰሰ ደምና መሥዋዕትነት ማራከስ ነው የሚሆነው፡፡

ከሰሞኑን የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩና አንጋፋው ፖለቲከኛ ፕ/ር መረራ ጉዲና፡- ‹‹የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምስቅልቅል ጉዞና የሕይወቴ ትዝታዎች፡- ከኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ እስከ ኢህአዴግ›› በሚል ርዕስ በጻፉት መጽሐፋቸውም በዓድዋው ጦርነት ከየትኛውም ሕዝብ ይልቅ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ጦር አዝማቾችና ጀግኖች ታላቅ መሥዋዕትነት መክፈላቸውን በመግለጽ የዓድዋ ድል የምኒልክን ቅኝ ግዛት ዘመቻ ያጠናከረ ዓውደ ግንባር ነው የሚለውን ሐሳብ አጣጥለው በመከራከር ጽፈዋል፡፡

በተጨማሪም ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ታላቅነትና አይበገሬነት በኦሎምፒክ መድረክ ከፍ ያደረጉ አበበ በቂላ፣ ዋሚ ቢራቱ፣ ቀነኒሳ በቀለ፣ ብርሃኔ አደሬ፣ ጌጤ ዋሚ፣ ጥሩነሽ ዲባባ፣ ፋጡማ ሮባ፣ ደራርቱ ቱሉ … እነዚህ ሁሉ በሮጡበት መድረክ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ብሔርና ሃይማኖት ሳይለዩ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ አብረው ሮጠዋል፣ ስለ ኢትዮጵያ ክብርና ድልም አብረው አምጠዋል፣ ተጨንቀዋል፡፡ በባርሴሎና ኦሎምፒክ መድረክ አበባችን ደራርቱ ቱሉ በአሥር ሺሕ ሜትር የመጀመሪያቱ አፍሪካዊት ሴት ወርቅ ሜዳሊስት በሆነችበት ድሏ የአገሯ ብሔራዊ መዝሙርና ሰንደቅ ዓላማ በስፔን ሰማይ ላይ ሲናኝና ከፍ ብሎ ሲታይ በጉንጯ ላይ ኮለል ብሎ የፈሰሰውን ዕንባዋን የታዘብን ሁሉ፣ በኢትዮጵያዊነት ኩራትና አይበገሬነት መንፈስ አብረናት በደስታ ሲቃ አንብተናል፣ መሬት ስመናል፡፡

ይህን ታሪክ በወርቅ ቀለም የጻፈውን የበርካታ ኦሮሞ ጀግኖችን ገድልና ለኢትዮጵያዊነት የተከፈለ መሥዋዕትነትን ማቃለልና ታሪክን ማዛባት ጤነኛ አካሄድ አይደለም፡፡ በዘመናችን ኦሮሙማን/የኦሮሞን ብሔርተኝነት በእጅጉ የሚሰብኩና የሚያራግቡ ሰዎች በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ኦሮሙማን ወይም የኦሮሞ ብሔርተኝነነትን ለመገንባት ሲሉ የኢትዮጵያን የሺሕ ዘመናት ታሪክ፣ ሥልጣኔ፣ ቅርስና የኢትዮጵያዊነትን መንፈስ ማጣጣልና መንኳሰስ ጤነኛ አካሄድ አይመስለኝም፡፡

ኢትዮጵያዊነት እንደ ኮሶ ተበጥብጦ በግድ እያነገፈገፈን የተጋትነው፣ እየቀፈፈንና እየኮሰኮሰን የተደረበብን ማንነት ብለው ለሚከራከሩ ሰዎች በእርግጥም በግድ ሳይወዱ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ተቀበሉ ብሎ ማስገደድ እንደማይቻል አሳምሬ አውቃለሁ፡፡ ኢትዮጵያዊ ለመሆን ያለመፈለግ መብታቸውንም በግሌ አከብራለሁ፡፡ ይሁን እንጂ ታሪክን በማዛባት ጥቁር ሕዝቦች፣ መላው አፍሪካና በአጠቃላይ ነፃነትን አፍቃሪ የሆኑ ሕዝቦች ልብ ውስጥ ትልቅ ዋጋና ክብር ያለውን የኢትዮጵያዊነትን መንፈስ ማራከስ፣ በኢትዮጵያና በሕዝቦቿን ታሪክ፣ ቅርስና ማንነት ላይ መዘባበት ጤነኛ አካሄድ እንዳልሆነ አሁንም በድጋሚ አስረግጬ ለመናገር እወዳለሁ፡፡

ከሰባት የሕወሓት የልኡካን ቡድን አባላት ሶስቱ በአሜሪካ ጥገኝነት ጠይቀዋል::

August 29, 2013

ከሰባት የሕወሓት የልኡካን ቡድን አባላት ሶስቱ በአሜሪካ ጥገኝነት ጠይቀዋል:: “የመለስ ፋውንዴሽን፣ የአባይ ግድብና የ40/60 የቤቶች ግንባታ ገንዘብ አዋጡ” ሕወሐት ባለስልጣናት የአሜሪካ ቆይታ፤ የከዱ አሉ (ከኢየሩሳሌም አርአያ) በአባይ ወልዱ የሚመራውና ሰባት ከፍተኛ የሕወሐት ባለስልጣናት የተካተቱበት ቡድን በአሜሪካ አራት ከተሞች ባካሄደው ስብሰባ በተለይ በላስቬጋስ ጠንካራ ተቃውሞ እንደገጠመው በስፍራው የተገኙ ምንጮች አስታወቁ። ቡድኑ በዋሽንግተን ኢትዮጲያ ኤምባሲ በጀመረውና በመቀጠል በላስቬጋስ፣ ሲያትልና ካሊፎርኒያ ከተሞች ባካሄደው ስብሰባ “አላማ” አድርጎ የያዛቸው ጉዳዮች እንደነበሩ የጠቆሙት ምንጮች፣ እነሱም፥ “የመለስ ፋውንዴሽን፣ የአባይ ግድብና የ40/60 የቤቶች ግንባታ.” ሲሆኑ፣ ለነዚህ ማስፈፀሚያ “ገንዘብ አዋጡ” የሚለው ዋናው ግብ እንደነበር አስረድተዋል።
በተለይ ደግሞ « በትግራይ ተወላጁ ዘንድ ሕወሐት የለም፣ ተከፋፍሏል፣ ተዳክሟል፣ ፓርቲው ሰው የለውም፤» የሚለውን እራሱ ቡድኑ በማንሳት ለገዛ ጥያቄው መልስ ሲሰጥ « ሕወሐት አሁንም ሃይል አለው፤ አልተዳከመም» በማለት አድራጊ- ፈጣሪ በመሆን ስልጣኑን በበላይነት ተቆጣጥሮ እንደያዘና ቡድኑ የመጣውም “አይዟችሁ” ለማለት እንደሆነ መገለፁን በቅርብ የተከታተሉት ምንጮች አስታውቀዋል። ቡድኑ በተጨማሪም ፥ « ልማት አልምተናል፤ ትግራይ እየለማ ነው፤ ህዝቡን ተጠቃሚ እያደረገነው ነው» ከማለቱ ባሻገር « በትግራይ ተወላጁ ላይ አደጋ ተደቅኗል፤ የሙስሊሙ፣ የትምክህተኞችና የሽብርተኞች አደገኛ እንቅስቃሴ እያንዣበበ መሆኑን፣…የተደቀነብህን አደጋ ከጎናችን ሆነህ ተከላከል፤ ያለበለዚያ ግን ሊያጠፉህ ነው፤» ሲሉ መናገራቸውን የገለፁት ምንጮች አክለውም፣ « አባላት የሆናችሁ ተወደደም ተጠላ መሬትና መኖሪያ ቤት እንሰጣችኋለን፤ ለዚህም ከእኛ ጎን መሰለፍ አለባችሁ» በማለት ሊሸነግሉ መሞከራቸውን ጠቁመዋል። ከዋሽንግተን ስብሰባ (ለሁለት ተከፍሎ ነው የተካሄደው) በኋላ ወደ ሶስቱ ከተሞች ተከፋፍለው እንደሄዱ ሲታወቅ፥ ሲያትል አቶ ብርሃነ ማረት፣ እንዲሁም ላስቬስጋስ አባይ ወልዱና ተክለወይኒ አሰፋ መሄዳቸው ታውቋል።
በተለይ በላስቬጋስ ጠንካራ ተቃውሞ የገጠማቸው እነአባይ ስብሰባው ከቀኑ 2፡00 ሰዓት ይጀመራል ተብሎ ከአራት ሰዓት በኋላ ዘግይቶ አመሻሽ ላይ መጀመሩን ምንጮች ገልፀዋል። ስብሰባው ሲጀመር ከላይ የተገለፁትን ጉዳዮች ያደመጠው ተሰብሳቢ ተከታዮቹን ጥያቄ አቀረበ፤ « ዴሞክራሲ አለ ትላላችሁ፣ ነገር ግን ዴሞክራሲ የለም፤ በሃሳብ የሚቃወማችሁን ታስራላችሁ፣ ታንገላታላችሁ፣ የሰብአዊ መብት ረገጣ ታካሂዳላችሁ፤ ከእናንተ የተለየ ሃሳብ ያለውን ትፈራላችሁ፤ ለምንድነው ይህን ሁሉ የምታደርጉት?....በማ.ረ.ት.(ማህበር ረድኤት ትግራይ) በትግራይ ሕዝብ ስም የምትሰበስቡትን ገንዘብ ለአራጣ ብድር እና ለፖለቲካ መጠቀሚያ በመሳሪያነት እያዋላችሁት ነው። ለምን?....ትእምት (ኤፈርት) ማነው ባለቤቱ?..በማን ነው የሚመራው?..ማነው የሚቆጣጠረው?..ለመሆኑ ኦዲት ተደርጎ ያውቃል ወይ?..እነማናቸው እየተጠቀሙበት ያለው?» የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ጥያቄዎች እንደነበሩ ምንጮቹ የጠቆሙ ሲሆን፣ አባይ ወልዱ « እኔ አልመልስም፣ ተ/ወይኒ መልስ ይስጥበት» ቢሉም ነገር ግን ግልፅና አግባብ ያለው ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ወደ ማመናጨቅና ቁጣ ያመሩት ተ/ወይኒ በዚህ ድርጊታቸው በርካታ ተሰብሳቢዎችን እንዳሳዘኑ አስረድተዋል።
በዚህ የተበሳጨው ተሰብሳቢ « ጥያቄያችን አልተመለሰም» በማለቱና ሁከትና ያለመደማመጥ በማየሉ ስብሰባው እንዲቋረጥ መደረጉን የጠቆሙት ምንጮች፣ የጥያቄና ተቃውሞው መብዛት ያስደነገጣቸው ባለስልጣናቱ የመረጡት ማምለጫ በላስቬጋስ ተወካያቸው በሆነውና መድረክ ሲመራ በነበረው አቶ ተወልደ በኩል፥ « አዳራሹን የተከራየንበት ሰአት አብቅቷል፤ ስለዚህም ስብሰባው አብቅቷል » በማለት በአስቂኝ ሰበብ መቋረጡን አያይዘው ገልፀዋል። እነአባይ ከአዳራሹ ሲወጡ ቀድሞ ውጭ ሆኖ ይጠብቃቸው በነበረው ተሰብሳቢ ውግዘትና ስድብ እንደደረሰባቸው ያስታወቁት ምንጮች « ሌባ..ሌባ…ሙሰኞች..» የሚሉ ተቃውሞዎች ጎላ ብለው እንደተሰሙ አመልክተዋል።
ስብሰባዎቹን የታዘቡ ወገኖች በሰጡት አስተያየት እንዲህ ብለዋል፤ « በአንድ በኩል ልማት እያካሄድን ነው፤ እያሉና ገንዘብ እየጠየቁ በሌላ በኩል “ትግራዋይ አደጋ ተደቅኖብሃል፣ ከጎናችን ሆነህ ተከላከል፤” ማለት እርስ በርሱ የሚጋጭና ድጋፍ የማግኛ የፖለቲካ የፖለቲካ ቁማር ነው። ያልተጠየቁትን የፓርቲውን ህልውና (ስለ ሕወሐት) አንስቶ መነገሩም አስገራሚና አጠያያቂ ነው።» ሲሉ ትዝብታቸውን የጀመሩት እነዚህ ወገኖች በማያያዝም፥ « እነዚህ ሰባት ባለስልጣናት ወደ አሜሪካ የመጡት ከነዘመዶቻቸው፣ ጋሻ ጃግሬዎቻቸው ሲሆን፣ ባለስልጣናቱ የመንግስት ወኪሎች እንደመሆናቸው - በማን ገንዝብ ነው የሚንቀሳቀሱት?..የሚለው መጠየቅ አለበት። በሕዝብ ገንዝብ እየተንፈላሰሱ እንደሆነ ግልፅ ነው።
የትግራይ ተወላጁን ብቻ ለይተው ስብሰባ የሚጠሩት ለምንድነው?...በእርግጥ ስላሰቡለት ነው?...የሚሉት ሲፈተሹ .መልሱ በጭራሽ አይደለም ነው። አላማቸውና ትኩረት የሰጡት የትግራይ ተወላጁን እየተንከባከቡት እንደሆነና ተጠቃሚ መሆኑን ለማሳየት በመፈለግ፣ እግረ-መንገዳቸውን ከቀሪው ኢትዮጲያዊ ወገኑ ጋር በመነጠል..ድጋፍ ለማግኘትና በውስጣቸው የተፈጠረውን ቀውስ በዚህ በኩል ቀዳዳውን ለመድፈን የሚደረግ የስልጣን እድሜ ማራዘሚያ ስልት ነው። ..ደግሞስ ሕወሐት “አጋር” ከሚላቸው ብ.አ.ዴ.ን፣ ኦ.ህ.ዴ.ድ.፣ ደቡብ ሕዝቦች ተለይቶ፣ በሕዝብ ገንዘብ ስብሰባ የሚጠራበትና ያሻውን የሚያደርግበት አግባብ ምንድነው?..የሚለው ከዚህ ጋር መታየት ያለብት ነው። ፖለቲካዊ ፍጆታና ማንአለብኝነት በፓርቲው በመነገሱ እንደሆነ ደግሞ ግልፅ ነው።» ብለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፥ አሜሪካ ከመጡት ሰባት የሕወሐት ባለስልጣናት መካከል- ማለትም አባይ ወልዱ፣ ብርሃነ ኪ/ማሪያም፣ ተ/ወይኒ አሰፋና ዳንኤል አሰፋ በዋነኛነት ሲጠቀሱ፣ ከሰባቱ ሶስቱ ስብሰባውን ሳያካሂዱ ከቡድኑ ተገንጥለው በአሜሪካ መቅረታቸውን ምንጮች አረጋግጠዋል። ቤተሰቦቻቸውን ይዘው (ልጆቻቸውን ጭምር) በመምጣት አሜሪካ ጥገኝነት ጠይቀው መቅረትን የመረጡት ባለስልጣናት ውስጥ የሕወሐት ማ/ኮሚቴ አባላት እንዳሉ ያረጋገጡት ምንጮች

የእኛ “መንግስት” (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ)

August 29, 2013

“በእያንዳንዱም መንግስት የሚያድሩ ብዙ ልዩ ልዩ ነገዶች ይኖሩ ይሆናል፡፡ ስለ ሆነ መንግስት አንዱን ነገድ አጥቅቶ ሌላውን ነገድ ለመጥቀም ሥራው አይደለም፡፡ አስተካክለን ካሰብን ዘንድ መንግስት መቆሙ ለሕዝቡ ሁሉ ጥቅም ነው፡፡ ጥረቱም ህዝቡን ሁሉ በትክክል ለመጥቀም ያልሆነ መንግስት ሊቆም አይችልም፡፡ ለአንዱ ነገድ ወይም ለጥቂት ሰዎች ብቻ ማድላት ለመንግስት የሚገባ ሥራው አይደለም” ይህንን መግቢያ የወሰድኩት በልዑል የኢትዮጵያ መንግስት አልጋ ወራሽ ተፈሪመኮንን ማተሚያ ቤት የካቲት 1 ቀን 1917 ዓ.ም ከታተመው የነጋ ድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ‹‹መንግስትና የሕዝብ አስተዳደር›› መፅሀፍ ነው፤ ዛሬም ያለንበትን ዘመን ይዋጃልና፤ በተለይ ስለ‹‹ነገድ›› የተጠቀሰውን አርቀን ሰቅለን፣ ‹‹ለጥቂት ሰዎች ብቻ ማድላት›› የምትለዋን ሀረግ በወጉ ካጤንናት ለጊዜያችን በልክ የተሰፋች መሆኗን ለመረዳት አስቸጋሪ አይደለም፡፡Journalist Temasegan Dasaleg
እናም የስርዓቱን የአስተዳደር ዘይቤ ያለፍርሃት አደባባይ ካዋልነው የቀድሞ ገዥዎቻችን የተጓዙበትን ጎዳና እየተከተለ መሆኑን ለመተንተን የምሁራንን ጥናት መጠበቅ ግድ አይለም፤ ምክንያቱም ለዓመታት የተመለከትነው እውነታ የሚነግረን የአመራሩን እና በዙሪያው የሠፈሩ የጥቅም ተጋሪ ግለሰቦችን ብልፅግና ታሳቢ ያደረገ፣ ከታግሎ መጣል ህግ የተቀዳ፣ የራስ ሀገርንና የራስ ሕዝብን በምርኮ ያስገበረ ፖለቲካ መንበሩን ነው፤ ገብር፣ ገብር፣ ገብር…!!
ዛሬ መንገድ ዳር ረሀብ አዙሮ የጣለው ወንድምህ ስቃይ እንደ ጥላ የሚከተልህ፤ ህፃናት በትምህርት ገበታቸው ላይ በጠኔ ተሸንፈው መመልከቱ የሰርክ አሳዛኝ ክስተት የሆነብህ ከሰው ሰራሽ ችጋር፣ ከሰው ሰራሽ የቀዬ ፍንቀላ፣ ከሰው ሰራሽ እርዛት… የመነጨ መርገምት እንጂ የሰማይ ቁጣ አይምሰልህ፤ እመነኝ መለስም ሆነ ተተኪዎቹ ስኬት አድርገው የሚሰብኩትም ይህንን ነው፤ ‹ሀገር አቀናን!› የሚሉትም ይህንን ነው፤ ሰሞኑን የሚያሰለቹህ ተረኛ ምሁራንም ‹‹ትምህርትና ጤናን በተመለከተ መለስ ‹እልል› የሚያስብል ሥራ ሰርቷል›› የሚሉህ ጣራና ግድግዳ እየቆጠሩ ነው፤ ይህ አይነቱ መደዴ ሙገሳም ለፕሮፓጋንዳ የሚሆን ሪፖርት ለማዘጋጀት ከሚረዳ ቁጥር የዘለለ አበርክቶ አንደማይኖረው አትዘንጋ፡፡
እውነት እውነት እልሀለሁ፡- ይህ የሆነበት ብቸኛው ምክንያት መንግስት በስልጣን ላይ ስለሚቆይበትመንገድ ብቻ መጨነቅን ግዴታው በማድረጉ ነው፤ ይህንን ለመረዳትም እያገባደድን ባለው ክረምት የመንግስት ትኩረት በምን ላይ አንደሆነ የሚያሳይ ማስረጃን ጨርፌ ላሳይህ፡፡
ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- የእስልምና እምነት ተከታዮች መንግስት በሃይማኖታቸው ጣልቃ መግባቱን በመቃወም እና የታሰሩ ኮሚቴዎቻቸው እንዲፈቱ በመጠየቅ እያደረጉ ያለውን ትግል በሰላማዊ መንገድ አጠንክረው ሲቀጥሉ፤በተቃራኒው ‹‹ፀጥታ አስከባሪዎች›› አንዳንዴ በጥይት፣ አንዳንዴ በአስለቃሽ ጢስ፣ አንዳንዴ በማጋዝ…ምላሽ ሲሰጡ…
በርግጥ መንግስት ከኃይል እርምጃው በተጨማሪ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎችን (በምን አግባብቶ ወይም በምን አስፈራርቶ እንደሆነ ባይታወቅም) ወደ አደባባይ በማስወጣት መብት ጠያቂዎቹን ከ‹‹አክራሪ››ነት እና ‹‹ወሃቢዝም››ነት ጋር አያይዘው የውግዘት በረዶ እንዲያዘንቡባቸው እያደረገ ነው፡፡ ኢቲቪም ይህንን ኩነት እየተከታተለ ማራገቡን ቀጥሎበታል፤ ‹‹የቲፒ ከተማ ነዋሪዎች ‹አክራሪዎችን አወገዙ››፤ ‹‹በደቡብ ወሎ ኩታ በር ዞን አንድነት ፓርቲ ህገ-ወጥ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰልፍ ተካሄደ››፤ ‹‹የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ‹የሼሁ ግድያ ድራማ አይደለም› አሉ፣ ‹የሼህ ኑሩ ኢልም ነው፣ የአሸባሪዎች ብር ነውም›ብለዋል››፤‹‹የመርሀቤቴ ነዋሪዎች ፅንፈኞችን በመቃወም የአቋም መግለጫ አወጡ››፤…
ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- አንድነት ፓርቲ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የ‹‹ፀረ-ሽብር ሕጉ›› እንዲሰረዝና የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ እና የአዳራሽ ስብሰባዎችን እያካሄደ ነው፤ መንግስትም አንዳንዴ የአፀፋ የድጋፍ ሰልፍ ሲያካሄድ፤አንዳንዴ የአዳራሽ ስብሰባዎች ከመካሄዳቸው አስቀድሞ ‹መጋኛ› ሲሆንባቸው፤ አንዳንዴም የአስተባባሪዎቹን መኪና ጎማ ሲያፈነዳ፤ አንዳንዴም አዳራሽ ከልክሎ ሲያደናቅፋቸው… መዋሉ ፋታ የነሳው ይመስላል፤ በወላይታ የተጠራውን የአዳራሽ ስብሰባም ‹በጠቅላይ ሚኒስትሩ የትውልድ ቦታ እንዴት ተደርጎ!›› ያሉ ካድሬዎች የአንድነት ሰዎችን አዋክበው ስብሰባውን አክሽፈዋል፤
ክረምቱእንዲህእየተገባደደነው፡-ገዥው ፓርቲ ‹የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ አንደኛ ሙት ዓመት አከብራለሁ› በሚል መላ ኢትዮጵያን ችግኝ መትከያ፣ መላ ዜጎቿን ደግሞ ወደ አርሶ አደርነት በአስማት የቀየራቸው አስመስሏቸዋል፤ቴሊቪዥንና ራዲዮንም አስፈላጊነታቸው በየመንደሩ ችግኝ መተከሉን እየተከታተሉ መዘገብ ብቻ እስኪመስል ድረስ እንዲህ ሲሉ ጀምበር ወጥታ ትጠልቃለች፡- ‹‹የላይ አርማጮህ ነዋሪዎች ችግኝ ተከሉ››፣ ‹‹በመቀሌ ከተማ ‹ዘመቻ መለስ› በሚል የችግኝ ተከላ ተካሄደ››፣ ‹‹አቃቂ ኮረብታ ላይ በሚሊዮን የሚቆጠር ችግኝ በኦሮሚያ ፌደራል ፖሊስ አባላት ተተከለ፤ ቦታውም ‹መለስዜናዊ ኮረብታ› ተብሎ ተሰይሟል››፣ ‹‹በምዕራብ ሀረርጌ አስራ ሰባት ሚሊዮን፣ በወልበራ አስራ አራት ሚሊዮን ችግኝተ ተክሏል››፣ ‹‹በመንዝ ላሎ ወረዳ ተቆጥሮ የማያልቅ ችግኝ ተከላ ተደርጓል››፣ ‹‹የብአዴን አመራርና ካድሬ በባህር ዳር ከተማ በቢሊዮን የሚቆጠር ችግኝ ተከሉ፤ በፕሮግራሙ ላይ ጓድ አዲሱ ለገሰ ‹ችግኝ የምንተክለው አገሪቱ በአረንጓዴው ልማት በአለማችን ማግኘት የሚገባትን ቦታ እንድታገኝ ለማድረግ ነው› ሲል፣ ጓድ በረከት ስምዖን ደግሞ ‹ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በአለማችን በአንድ ጊዜ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ችግኝ እየተከሉ ያሉባት ብቸኛ ሀገር ናት› ብሏል››፤‹‹ዝክረ መለስ 1ኛ ዓመት መታሰቢያን ምክንያት በማድረግ ከሐምሌ አስራ አምስት ቀን ጀምሮ ሁሉም ቀበሌዎች በስሙ ‹ፓርክ› ሰይመው ችግኝ ተከላ እያካሄዱ›› መሆኑን ደግሞ የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ መግለፁን የአማራ ክልል ብዙሃን መገናኛ ዘግቧል፤ ‹‹በወልቂጤ ከተማ በተደረገው ችግኝ ተከላ ላይም አንዲት ወጣት ‹መለስ ለሴቶች የተለየ አመለካከት ነበረው›› ማለቷም በዘገባው ተጠቅሷል፤ …ማን ነበር የመለስ ራዕይ ‹ችግኝ መትከል ነው› ያለው? …ኢህአዴግ ይሆን?
ከዚሁ ጎን ለጎን (አሁንም ሙት ዓመቱን ለማሰብ) በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የእግር ጉዞ ተደርጓል፣ የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓትም ተካሄዷል፤መነሻውን መቀሌ፣ መድረሻውን አዲስ አበባ ያደረገ ‹‹የመለስ ቱር አረንጓዴ ልማት›› የብስክሌት ውድድርም ሊጠናቀቅ ገና አንድ ሳምንት ይቀረዋል፤ በብሄራዊና ሀይማኖታዊ በዓላት ቀንለሃያ አንድ ጊዜ ይሰማ የነበረው የመድፍ ድምፅም፣ የመለስን አንደኛ ሙት ዓመት ለማብሰር ተተኩሷል፤ …በግድ አልቅሱ፣ በግድ ተዝካር አውጡ፣ በግድ ችግኝ ትከሉ፣ በግድ ተወያዩ፣ በግድ አደባባይ ውጡ፣ በግድ የፎቶ ግራፍ ኤግዚቢሽን ጎብኙ፣ በግድ.. ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ እና የትምህርት ሚኒስትሩ ሽፈራው ሽጉጤ ከአንድ ሺህ ሰባት መቶ በላይ ለሚሆኑ የዩኒቨርስቲ ከፍተኛ መምህራን ‹የአቅም ግንባታ ስልጠና› እየሰጡ ነው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምሁራኖቹን ማሰልጠን ያስፈለገበት ምክንያት ‹‹ብቃት ያለው ምርጥ የተማረ ኃይል ለማፍራት››መሆኑን ቢነግርህ አይግረምህ፤ ይህ ኢትዮጵያ ነውና የዐዋቂነት ማረጋገጫው መማር፣ ማንበብ፣ መመራመር… አይደለም፣ የፖለቲካውን ኃይል መያዝ እንጂ፤ ‹ስልጣን ላለው ሁሉምሚስጥረ-ጥበብይገለፅለታል› እንዲል አብዮታዊ ዲሞክራሲ መለስ ዜናዊም በሁሉም መስክ ‹አስተማሪ› ነበር፤ የህግ ባለሙያዎችን ሰብስቦ የሀገሪቱን ወንጀለኛ መቅጫ ህግ ትርጓሜ ሲተነትን ደጋግመህ ሰምተኸዋል፤ በቀጣዩ ቀን ደግሞ ለግብርና ባለሙያዎች ከውሃ ማቆር እስከ በላብራቶሪ የሚዳቀል ምርጥ ዘር ድረስ ባሉጉዳዮችዙሪያ የሁለት ቀን ማብራሪያ መስጠቱን ታስታውሳለህ፤ እመነኝ ተተኪው ጠቅላይ ሚኒስትርም ይህንኑ ነው እያደረገ ያለው፤ የሆነ ሆኖ ኃ/ማርያም ለምሁራኖች ከሙያቸው ጋር ስለተያያዙ ጉዳዮች ጭምር በሰጣቸው ስልጠና ላይ እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀርቦለት ነበር ‹‹የኢንዱስትሪዎች በበቂ ሁኔታ አለመኖሩ፣ በክፍል ውስጥ የምናስተምረውን ንድፈ ሃሳብ በተግባር ለማሳየት እንቅፋት ሆኖብናል››፤ በርግጥጠቅላይ ሚንስትሩ‹‹መፍትሄ››ያለውን የተናገረው ብዙም ሳይጨነቅ ‹‹እኔ ኢንዱስትሪን ‹ዲፋይን› የማደርገው ግብርናም ኢንዱስትሪ ነው ብዬ ነው››በማለት ነበር፤…ግና!ይህ እንዴት ሊሆን እንደሚችል በተጨባጭ አላብራራም፡፡ለምሳሌ ህክምና የሚያጠና ተማሪ በምን መልኩ በሞፈርና ቀንበር የተግባር ልምምድ ማድረግ እንደሚችል፤ወይም ፖለቲካ ሳይንስ የሚያጠና ተማሪ የተግባር ልምምዱን በግብርና ኢንዱስትሪ እንዴት ሊወጣው እንደሚችል? ማለቴ ነው፡፡
ለዓመታት በርካታ ምሁራን ብቃት አልባ ተማሪዎች እንደ ሰማይ ከዋክብት የመብዛታቸው መንስኤን ከትምህርት ፖለሲው ጋር የሚያነፃፅሩበትን ሀቲት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ ባገኘው የሀገር መሪነት ስልጣን ገልብጦ በዩንቨርስቲ ቆይታው መምህራኖቹ የነበሩትንም ጭምር ‹‹አቅም አንሷችኋልና-እገነባችኋለሁ›› ሲል ከመስማት የከፋ እንደ ሀገር ክሽፈት የለም (በነገራችን ላይ ከወራት በፊት ለኃይለማርያም ደሳለኝ፣ በረከት ስምዖን፣ ቴውድሮስ አዳህኖም፣ ሶፍያን አህመድ በአጠቃላይ ሁሉም የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት አንድ ህንዳዊ ፕሮፌሰር በኢህአዴግ ጽ/ቤት ‹‹ልማታዊ መንግስት›› እንዴት ውጤታማ ሊሆን እንደሚችል ሲተነትንላቸው፣ እነርሱም ደብተርና እስክርቢቶ ይዘው በንቃት ሲከታተሉ የቴሌቪዥ ዋና ዜና ሆኖ የቀረበበትን ምክንያት ዛሬም ድረስ ሊገለፅልኝ አልቻለም፤ በተለይም ፕሮፈሰር እንድርያስ እሸቴ ‹‹በቃሉ የፀና…›› በሚል ርዕስ መለስን አስመልክቶ በተዘጋጀ ዶክመንተሪ ፊልም ላይ ‹‹በዓለማችን ለመጀመሪያ ጊዜ ልማታዊ ስርዓተ መንግስት ‹ዴሞክራሲያዊ ሊሆን ይችላል፤ መሆንም አለበት› ብሎ በአደባባይ የተከራከረው እኔ እስከማውቀው ድረስ መለስ ነበር›› ማለቱን፣ ተተኪዎቹ ፍልስፍናውን ገና እየተማሩት ከመሆኑ አንፃር ስናየውሀገራችን ያለችበት ሁኔታ ጉዞው ወዴት ነው? ያስብላል፡፡ …ከቶስ በተማሪ ፖለቲከኛ የሚተዳደር ሕዝብ ከኢትዮጵያ በቀር ወዴት ይኖራል?)
ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- የህዳሴውን ግድብ ከዳር ለማድረስ በቂ ገንዘብ ስላልተገኘ ተደጋጋሚ የቦንድ ሽያጭ እየተካሄደ ነው፤ አንዳንድ የመንግስት ሰራተኞችም በካድሬ ባልደረቦቻቸው ጫና በድጋሚ ቦንድ ለመግዛት መወሰናቸው ተሰምቷል፤ በርግጥ ከፍተኛ የኢህአዴግ የአመራር አባላት በአውሮፓ፣ በሰሜን አሜሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ቦንድ እንዲገዙ ለመቀስቀስ የአዘጋጇቸው ስብሰባዎች ‹‹ቅድሚያ የዜጎች መብት ይከበር›› ባሉ የሀገራችን ልጆች መክሸፉም የክረምቱ የመንግስት ዋና ሥራ ነው፤ ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- በነቢብ የኢትዮጵያ፣ በገቢር የገዥው ፓርቲ የግል ንብረት የሆነው ቴሌቪዥን ጣቢያ ባለፉት ሶስት ወር ብቻ ከሃያ በላይ ‹‹ዶክመንተሪ ፊልም›› አሳይቷል (ገና ይቀጥላልም) በርዕሳቸው እንደሚከተለው እንዘርዝራቸው፡- ‹‹ኢፍቲን›› በሶማሊያ ላይ የሚያጠነጥን፣ ‹‹የጥቁር ህዝቦች ልሳን (መለስ በአፍሪካ)››፣ ‹‹ከፓን አፍሪካ እስከ አፍሪካ ህዳሴ›› የጠቅላይ ሚንስትር መለስን ህይወት የሚዳስስ፣ ‹‹ዘመነ አፍሪካ››፣ ‹‹የአፍሪካ ልሳን-መለስ››፣ ‹‹መለስ ማን ነው?››፣ ‹‹ሀገሬ-ቤቴ››፣ ‹‹ባለራዕዮቹ›› ስራ ፈጠራ ላይ የሚያተኩር፣ ‹‹ደውል›› እና ‹‹ደውል 2›› ህገወጥ-የሰዎች ዝውውርን በተመለከተ (በተለያያ ጊዜ የተላለፉ)፣ ‹‹የዲያስፖራ የልማት እንቅስቃሴ››፣ የካርታ ስራ ድርጅትን በተመለከተ፣ ‹‹የጥልቅ አስተሳሰብ ባለቤት›› በፕ/ር እንድርያስ እሸቴ ህይወት ዙሪያ የሚያጠነጥን፣ ምድር ባቡር ኮርፕሬሽንን በተመለከተ፣ ‹‹ያልተለመደ ጉብኝት›› የአዲስ አበባ አስተዳደር የአምስት ዓመት የመንግስት ግንባታዎችን በተመለከተ፣ ‹‹ሼህ ኑር ለምን ሞቱ?›› የደሴውን ሼህ ኑር ይማምን ግድያ በተመለከተ፣ ‹‹የተስፋ ስንቅ››፣‹‹በቃሉ የፀና›› በድህረ መለስ ላይ የሚያተኩር፣ ‹‹ያልተጠኑ ገፆች›› በመለስ ዜናዊ ህይወት ዙሪያ (በርግጥ በዚህ ፊልም እህቱ ጠላ፣ ወንድሙ አንባሻ በመሸጥ መተዳደራቸውን በምስልም በድምፅም ማቅረቡ ምን የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ተፈልጎ እንደሆነ ለማወቅ ግራ ያጋባል፤ …ምናልባት እንዲያ እየዘረፈ ለቤተሰቦቹ ‹ሶልዲን› የማይሰጥ ‹ቆነቋና› ነበር ለማለት ይሆን? ወይስ ለአዜብ መስፍን ‹የወር ቀለባችንን እንቸገራለን› የአንድ ሰሞን ማስተዛዘኛ ምስክር ፍለጋ ነው?
በጥቅሉ ለኢህአዴግ ሕዝብን የማስተዳደር፣ ሀገርን የመምራት መገለጫ ይህ ነው፤ ሌላ አይደለም፤ ግና! ለዘመናት ያልተመለሱ ጥያቄዎቻችን ዛሬም መጮኻቸውን አላቋረጡምና እነሆ እንዲህ ቀጥለዋል፡- ሀገር ማስተዳደር ‹መለስ ጀግና ነበር› እያሉ ማሰልቸት ነውን? የመንግስትስ ስራ (ግዴታ) ምንድር ነው? ሀገሪቱን ‹‹መለስ-ፓርክ›› ወደሚል ስያሜ ከመቀየራችሁ በፊት፣ ለጤፍ ዋጋ አለቅጥ መናር ምክንያቱን ስለምን መመርመር ተሳናቸው? ሀገሪቱን በ‹አራጣ› እንደያዘ ስግብግብ ነጋዴ በሚሊዮኖች ህይወት ላይ የማይሞላ ‹ሳፋ› ደቅኖ አዋጣ፣ ግዛ፣ ክፈል፣ ገብር… እያለ የሚያስጨንቀው ማን ነው? ስለመለስ ‹የሃሳብ ምጡቅነት› መስካሪ ምሁራኖቻችን ለጎዳና ኑሮ የተዳረጉ ኢትዮጵያውያን ስንት ሚሊዮን እንደደረሱ እና እልፍ አላፍት ታዳጊዎቻችን በሴተኛ አዳሪነት እንደተሰማሩ የምትነግሩን መቼ ነው?እንዲህ የመሆኑ ምክንያትስ በማን ይሆን? ‹የሁለት ዲጂቱ›ዕድገት ሸክምን የማለዘብ አቅም ከሌለውፋይዳው ምንድር ነው? ‹ሳቅ ትዝታ› ስለሆነባቸው ጎጆዎች ለምን አትነግሩንም? መለስ ‹ያለመለማት› ኢትዮጵያ ወዴት ትሆን? ‹ፖለቲካ› ማለትስ ይህ ነውን? …ነጋ ድራስ ገ/ህይወት እንዳሉት ‹‹…መንግስት መቆሙ ለሕዝቡ ሁሉ ጥቅም ነው፡፡ ጥረቱም ህዝቡን ሁሉ በትክክል ለመጥቀም ያልሆነ መንግስት ሊቆም አይችልም፡፡›› የመተራረሚያው ጊዜም በጣም ያለፈ ይመስለኛል፡፡ አገዛዙን ‹እንደ መንግስት› መቀበሉም እንዲሁ፡፡

Wednesday, August 28, 2013

የዱርየው ወያኔ መንግሥት የውሸት አምራች ፋብሪካዎች ይዘጉ

August 28, 2013

ተሾመ ደባለቄ
‘የሌባ ዓይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያድርቅ’ ሲል የሀገሬ ሰው ሀገር ያወቀውን ፀሐይ የሞቀውን ሌባ ጨዋ ለማስመሰል የሚያጋጋው ውሸት ሲያሰለች ነው። እንደዚሁም መንግሥት ነኝ ተባዩ ወያኔም የውሸት ጋጋታው ሰውን አሰልችቶት እውነትም ቢናገር እነኳን የሚያምነው አጥቶ ሙጥኝ የያዛቸው መዋቅሮች ‘ውሸታም’’ ና  ‘ሌባ’ የሚል ስም አትረፈዋል።
woyane propaganda machine
ውርደት ያተረፈው ወያኔ የውሸት ጋጋታው አልበቃ ብሎት ለምን እውነት ተነገረ ብሎ ድርጅት መዘጋት ባልደረቦችን ማሳደድ፣ ማሰርና  እስከመግደል ደረጃ ደርሷል። በራሱ ውሸት ያበደው ወያኔ በአካባቢው ከሚያጎበድዱለት ጉጅሌዎቹ መሃል አብደሃል በሙስና ተዘፍዝፈሃል የሚለው ጠፍቶ እንደመሸበት ሰካራም ቤቱ ጠፍቶት በየሰዉ ቤት እያንኳኳ በራሱ ውሸት ተሸብሮ ህዘብን ማሸበሩን ቀጥሎበታል።
በመሰረታዊ ውሸት ላይ የተመሰረተው ወያኔ ‘ድንጋዩ ዳቦ ነው’ ብላችሁ ተቀበሉ እያለ መከራውን ሲያይ አዝለውት የሚዞሩት ጉጅሌዎቹ የውሸቱ ሸክም በዝቶባቸው  ሲዘላበዱና  በህዘብ መሳለቂያ ሲሆኑ ማየት ያሳፍራልም ያሳዝናል።
በዕውነቱ ውሸቱ በዝቶ የራሱ ነፍስ ፈጥሮ ወያኔን ማስተዳደር ከጀመረ ሰንብቷል ማለት ሀሰት አይሆንም። ይህ ከመሰረቱ በውሸት የተገነባው መንግስት ነኝ ባዩ ቡድን ወደሃላ መመለስ ስለማይችል የባሰ እያበደ ይሄዳል አንጂ እውነትን ለመቀበል ችሎታም አቅምም ሊኖረው አይቻልም። ስለሆነም እራሱን ወጥመድ ውስጥ አግብቶ ለማምለጥ ሲፈራገጥ ወገን እያቆሰለና አገር አያደማ መሆኑ ሊያስገርመን አይገባም።
ሆዳቸውን በውሸት የሞሉት ጉጅሌዎቹም ቢሆኑ ሆድን ከእውነት መርጠው እየቃዡ ምላሰቸው ተቆላልፋል። እውነት መናገርም የሚያጎርሳቸውን እጅ መንከስ ስለሆነባቸው እውነት የሚናገረውን መናከስ የሚረዳቸው መስሏቸው ሲዘላብዱ በህዘብና በሀገር ሲያፌዙ ይገኛሉ።
የቸገረው እርጉዝ ያገባል እንደሚባለው ቀንደኛው የውሸት መሪ ካለፈ ጀምሮ ውሸቱን ማስተዳደር አቅቷቸው ያዙኝ ልቀቁኝ እያሉ ሲዘባርቁ ለተመለከታቸው አብደው ሊያሳብዱ የተነሱ እንደሆኑ ግልጽ ነው። በእርግጥኝነት ሊባል የሚቻለው እብድ ማበዱን ካላመነ ጤነኛ ነኝ ብሎ እራሱን ስለሚያሳምን በእብዶች መሀል አንድ ጤነኛ ቢኖር እንኳን እንደ እብድ ስለሚቆጠር ያበዱትን ባልደረቦቹን ሊረዳቸው አይችልም።
የብዙሃን መገናኛ ላይ ያሰፈሰፉት ካድሬዎችን ብናስተውል የወያኔ ውሸት የራሱን ነፍስ እንዳላው ያረጋግጥልናል። እነዚህ የብዙሃን መገናኛ ተባዮች የውሸት ፋቢሪካ ሆነው በሶስት ፓኬጅ እያሸጉ ውሸትን ሊሸጡ ሲሯሯጡ ይታያሉ።
አንደኛው ፋብሪካ የውሸቱ ጥሬ ዘር የሚያመርተው በወያኔ የሚተዳደሩት መዋቅሮች ሲሆን የውሸት ምሶሶና በምንጭነት ፊት ቀዳሚ ሲሆን የህዋዓት ዋና መሳሪያ ነው። ሆኖም መንግሥት ነኝ የሚለው ወያኔ ስለተቆጣጠራቸው የሚያምናቸው አጥተው ወንዝ እንደሚያከራትተው ግንድ ይወዛወዛሉ።
በሁለተኛ ደረጃ ያሉት የውሽት ፋብሪካዎች ወያኔ በካድሬዎቹ ያደራጃቸው መዋቅሮችና የብዙሃን መገናኛዎች (በተለይም በስደት ላይ ያለውን ወገን ለማወናበድ) የተዋቀሩ ናቸው። እነኝህ መዋቅሮች በወያኔ ጥሬ ወሸትና ገንዘብ የሚታገዙ ስለሆኑ አላማችው በግል ስም ወያኔ በመንግሥት ስም መሸጥ ያቃተውን ውሸት ዳግም ማሸግና መሸጥ ነው። እነዚህ ግለሰቦች ወያኔ ከመጣ ጀምሮ ማንነታቸው የማይታወቅ (ጎሬላዎች) ናቸው። ከተጋለጡት መሃል የአይጋ-ፎረም ባለቤት ኢሳያስ አፅብሃ  ከሳኖዜ ካሊፎሪኒያና የትግራይ-ነት ባለቤት ሚካኤል አባይ ከዴንቨር ኮለራዶ ይገኙበታል።
በሶስተኛ ደረጃ ያሉት የውሸት ፋብሪካዎች ደግሞ በነጻ ፕሬስ ስም የሚነግዱ መዋቅሮች ሲሆኑ እነሱም በሁለት ይከፈላሉ። አንዱ በወያኔና ባልደረቦቹ የሚተዳደሩ የውስጥ ሚስጥረና ድጋፍ ያለቸውና ዜጋ ለማወናበድ የተደራጁ የብዙሃን መገናኛ መዋቕሮች ናቸው። በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በተቃዋሚ ስም የተደራጁ አስመሳይ መዋቅሮች ናቸው። የሁለቱም አላማ አንድ ቢሆንም የውሸትን ማሸግና መሸጥ መንገዳቸው ይለያያል። ነገር ግን ሁለትም የወያኔን ሥርዓት በተወሰነ ደረጃ ይገስጻሉ ግን አላማቸው ወያኔን ማቆየት ስለሆነ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ እነዳይነኩ የታዘዙ ይመስላሉ። ሁሉቱም ከውጭ ሚዲያ የመጣን ወያኔን የሚያሞግስ ዜና አያመልጣቸውም ወይን ይፈጥራሉ። ሁለቱም ህዘብ ላይ የሚደርሰውን ግፍና ዘረፋ  ለመሸፈንና ለማደናገር ዘመቻ ላይ የተሰማሩ ናቸው። ሁሉቱም በጋዜጣ ስም አሰመስለው የፐሮፖጋነዳ  ሥራ ለመስራት ውስጥ ለውስጥ የተደራጁ የሥርዓቱ  ጉጅሌዎች ናቸው።
በውሸት ላይ የተሰማሩት የወያኔ ባልደረባና አስመሳይ ጋዜጠኞች ሥራዓቱ እየፈራረሰ ሲመጣ የሚያደርጉት ስለጠፋባቸው ወያኔን ለማዳን ያላቸው ብቻ ምርጫ የእስላም አሸባሪ መጣባችሁ እያሉ ማስፈፈራራት አዲሱ ሞያቸው ሆኗል። እሱንም ጉዳይ በተለያየ የውሸት ማቀነባበር መንገድ እያዘጋጁ ህዘብን በማተራመስና ለወያኔ ጊዜ ሊገዙለት እየጣሩ ነው።
ለምሳሌ ቀንደኛዎቹ የወያኔ የዜና መዋቅሮች የውሸት ቲያትር እያሰሩ ሲያሰራጩ በግል የዜና መዋቀር ስም የሚቀሳቀሱት ደግሞ ቲያትሩን እውነት ለማስመሰል የውጭ አከራሪዎችን ዜና በማነፈስ ህዘብን ቢያንስ እንዲጠራጠር አልያም እንዲያምን ይጥራሉ። ከዚህ በፊትም በአማራው ህብረተሰብ ላይ ያወረዱበት የውሸት ዘመቻ ስኪ ሆነ ብለው ስለሚያምኑ በእስልም ተከታዮች ወገኖቻችን ላይ እየመከሩት መሆኑ በግልጽ ይታያል።
ወገንም የነፃ ብዙሃን መገናኛዎችም የፖሎቲካና የሲቪክ መዋቅሮችን እነኚህን የውሸት ፋበሪካዎችንና የሚያንቀሳቅሷቸውን የውሸት መልክተኞች ማወቅ ማጋለጥና ከዛም አልፎም ማዘጋትና ተጠያቂ ማድርግ ግድ ይላል።
ትግሉ ማንንም ግለሰብንና ቡድን የውሸት ፋበሪካ ሰለባ እንዳይሆን የመከታተልና የመቅታት ዋናው ስራው መሆን ይኖርበታል። የወያኔ ሥርዓት እየገማ በመጣ ቁጥር ባልደረቦቹ እያባሱ መግማታቸው አይቀሬ ስለሆነ እያናዳንዱ ዜጋ እነኝህን የውሸት መልክተኞች መከታተል ሀላፊነት አለበት። የውሸት ፋብሪካ መዘጋትና ሥራ አስኪያጂዎች መቅጣት የዲሞክራሲ ትግል ዋናው ምሶሶ ስለሆነ ፋብሪካዎቹም ሆነ ሥራአስኪያጆቹ ዕውነት ያመርታሉ ማለት የህልም እነጀራና ሞኝነት ነው።
የኢትኦጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ከመጣ ጀምሮ እንቅልፍ የነሳቸው የወያኔ ካደሬዎችና ተጠቃሚዎች የገዢውን ቡድን ውሸት እያሰራጩ ኢሳትን  የሚያጋልጠውን እውነት ሊነኩት አቅቷቸው አይናቸውን ጨፍነው ጆሯቸውን ደፍነው ቅዠት ውስጥ እንዳሉ እራሳቸው ይመሰክራሉ።  ኢሳት አንዱ ትልቁ ሥራው እንኝህን የወያኔን ውሸት ፋብሪካና ቸርቻሪ ባለቤቶችን ለህዘብ ማጋለጥና ማንነታቸውን ህዝብ እንዲያውቃቸው ማድረግ ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነቱን በቶሎ የሚጎናፀፈውና የወደፊት ሰላምና ብልጽግና የሚያገኘው የውሸት ፋብሪካዎች ሲዘጉና የእውነት ፋብሪካዎች ሲስፋፉ ነው።  ይህ መሰረታዊ መፍቴህ የውሸት ፋበሪካ ባለቤቶችን እያሳበዳቸው ጨርቃቸውን ጥለው እየሮጡ እነዳሉ ግልጽ እየሆኑ መጥተዋል። ሆኖም በቂ ትኩረት ተሰጥቶት ስላልተሰራ ተደብቀው ውሸትን ማምረትና መቸርቸር ሥራቸውን ቀጥለዋል።  በድርጅት ከመስራት በግለሰብ መሥራት የባህል ድክመት ብዙዎቹን የነፃ ሚዲያዎችን ያዳከመና የውሸት ፋብሪካዎችን እድል ከፍቶላቸዋል ማለት ይቻላል።
የውሸት ፋብሪካዎችን ለማዘጋት ባለቤቶቹንም ለመቅጣት እንዘጋጅ እንደራጅ
ድል ለኢትዮጵያ ህዘብ

በመጪው እሁድ በአዲስ አበባ ሰማያዊ ፓርቲ እና ኢህአዴግ በየፊናቸው ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ተከትሎ አዝማሚያው ወደ ውጥረት እያመራ መሆኑን ታዛቢዎች ገለጹ።

ነሃሴ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰማያዊ ፓርቲ ቀደም ካሉት ጊዜያት ጀምሮ ለነሐሴ 26 ቀን 2013 ዓመተምህረት ሰልፍ እንደሚጠራ አስታውቆ የቅስቀሳ ሥራ መሥራት በጀመረበት ጊዜ፤ ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ሰሞኑን  በዚያው ቀን ሰልፍ ለማድረግ ጥሪ ማቅረቡ ያታወቃል።
በተለይ በኢህአዴግ የሰልፍ ጥሪ  የሴትና ወጣት ማህበራት፣የመንግስት ሠራተኞች፣ የሀይማኖት ተቋማትና  ሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጭምር በግዳጅ እንዲወጡ መታዘዛቸው፤ ሁኔታውን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ይወስደዋል ተብሎ ይጠበቃል።
ሰማያዊ ፓርቲ፤የ አፍሪካ መሪዎች አዲስ አበባ ላይ በተሰበሰቡበት ወቅት ሰልፍ ለማድረግ  ወስኖ ሳለ፤  የአዲስ አበባ መስተዳድር የሰላማዊ ሰልፍ ፈቃድ ክፍል ፤ወቅቱ የመሪዎች ስብሰባ ከመሆኑ አንፃር በዕለቱ በቂ ሀይል እንደሌለውና ሰልፉን ለሳምንት እንዲያሸጋግሩ በጠየቀው መሰረት፤ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፉን ማሸጋገሩ ይታወሳል።
ይሁንና ያን ውሳኔ ያሳለፈው የመስተዳድሩ የሰልፍ ፈቃድ ክፍል ፤ ኢህአዴግ-ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ ሊያደርግ ባቀደበት ተመሣሳይ ቀንና ከተማ ውስጥ ሰልፍ ለማድግ ሢነሳ ምንም አለማለቱ ታዛቢዎችን አስገርሟል።
ኢህአዴግ-የሸህ ኑሩን ሞት ተከትሎ በሌሎች ክልሎች እንዳደረገው ሁሉ በአዲስ አበባ ሊያደርገው በተዘጋጀው ሰልፍም የሙስሊሞችን የመብት ይከበር እንቅስቃሴ ከሽብርተኝነትና ከጽንፈኝነት ጋር በማያያዝ በሰልፈኛው ለማስወገዝ መዘጋጀቱ ታውቋል።
ከዚህም ሌላ የገዥው ፓርቲ ተቃዋሚዎች ሰልፍ በሚወጡበት ዕለት -ኢህአዴግ የከተማዋን ነዋሪዎች በግዳጅ “እኔን ደግፋችሁ ውጡ”ማለቱ፤ በህብረተሰቡ ዘንድ አላስፈላጊ መቃቃርን፣ መወጋገዝንና መለያዬትን  ለመፍጠር በማሰብ  ጭምር ነው የሚሉ አስተያየቶችም እየተሰነዘሩ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ  መንግስት  የጠራውን ሰልፍ እንዲሰረዝ ሰማያዊ ፓርቲ ጠየቀ።
ፓርቲው፦”መንግሥት ለተፈጠረው ችግር በአስቸኳይ ማስተካከያ እንዲያደርግ እንጠይቃለን!!”በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫ፤ ሰማያዊ  ፓርቲ ግንቦት 25/2ዐዐ5 ዓ/ም. ታላቅ ህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ማድረጉን አስታውሶ፦” መንግሥት ላቀረብናቸው ጥያቄዎች በሦስት ወር ውስጥ መልስ የማይሠጥ ከሆነ በተጠናከረና በተደራጀ መልኩ ጥያቄያችንን በድጋሚ በህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ እንደምናቀርብ በግንቦት 25/2ዐዐ5 ዓ/ም. በተደረገው ሠልፍ ላይ ለህዝብ ቃል በገባነው መሠረት ነሃሴ 26/2ዐዐ5 ዓ/ም. በድጋሚ ሰልፍ ጠርተን አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረግን መሆኑን ለህዝብ በልዩ ልዩ መገናኛ ዘዴዎች ገልፀናል” ብሏል።
ከዚህ በተጨማሪም ለሰልፉ በሰላም መጠናቀቅ አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግልን አዋጁ በሚጠይቀው መሠረት ለአዲስ አበባ መስተዳድር ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ማስታወቂያ ክፍል ጉዳዩን እንዲያውቀው አድርገናል ብሏል-ሰማያዊ ፓርቲ።
ይሁን እንጂ ፓርቲያችን የተቃውሞ ሰልፍ በጠራበት ግዜና ቦታ ላይ በሌላ አካል ሰልፉ መጠራቱን በትናንትናው ዕለት ነሀሴ 20 ቀን 2005 ዓ.ም በመንግሥት ቴሌቪዥን ዜና ሰምተናል ያለው ሰማያዊ ፓርቲ፤ከዚህም በላይ  የመንግሥትን መዋቅር በመጠቀም  ዜጐች በዚህ ሰልፍ ይገኙ ዘንድ  በግድ እንዲፈርሙ እየተደረገ መሆኑን ከአዲስ አበባ ኗሪዎች አረጋግጠናል ሲል አትቷል።
ሰማያዊ ፓርቲ አስፈላጊውን የህግ ቅድመ ሁኔታ አሟልቶ ነሐሴ 26/2ዐዐ5 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ የጠራውን የተቃውሞ ሰልፍ ለህዝብ ያሳወቀና አስፈላጊውን ዝግጅት ያጠናቀቀ በመሆኑም፤ ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ በጠራበት ቀንና ሠዓት በሌሎች አካላት የተጠራው ሰልፍ ከመረጃ እጥረት ከሆነ እንዲሠረዝ እንጠይቃለን ሲልም  ኢህአዴግ የጠራውን ሰልፍ እንዲሰርዝ  ጠይቋ ል።
ሰማያዊ ፓርቲ በማያያዝም፦”ይህ ካልሆነ ግን ሰማያዊ ፓርቲ በህጋዊ መብቱ የሚያደርገውን የተቃውሞ ሰልፍ ሆን ብሎ ለመረበሽና አቅጣጫውን ለማስቀየስና በዜጐች መካከል ግጭት ለመፍጠር የታቀደ ስለሆነ ለሚፈጠረው ችግር ተጠያቂ መንግሥት መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብና የሚመለከታቸው አካላት እንዲያውቁት በአፅንዖት እንገልፃለን፡፡” በማለት አሣስቧል።

የግንቦት7 አባላት ናቸው የተባሉ ሰዎች ክስ ተመሰረተባቸው

ነሃሴ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከተለያዩ የአማራ አካባቢዎች ተያዙ የተባሉ 10 ሰዎች ዛሬ በአቃቂ 4ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል።
ዘመኑ ካሴ ከተባለው ሰው በስተቀር ሌሎች 9ኙ ተከሳሾች ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ለህዳር 2 ቀን፣2006 ዓ/ም ቀጠሮ ተሰጥቶአቸዋል።
ፍርድ ቤት ከቀረቡት መካከል የባህርዳር ከተማና ዙሪያዋ ነዋሪዎች የሆኑት አሸናፊ አካሉ፣ ደህናሁን ቤዛ፣ ምንዳየ ለማ፣ አንሙት የኔዋስ፣ ሳለኝ አሰፋ ፣ የክልሉ የማረሚያ ቤት ረዳት ምክትል ኢንስፔክተር ሙሉየ ማናየ ፣ ጸጋው ካሳ ፣ የአለም አካሉና ሙሉ ሲሳይ ይገኙበታል።
በግለሰቦች ላይ የተመሰረተው ክስ አሸባሪ ከሆነው ግንቦት 7 ጋር ግንኙነት በመፍጠር ጥቃት ለማድረስ ተንቀሳቅሰዋል ሚል ነው።
በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት የግንቦት7 ሊ/መንበር ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ መንግስት መብቱን የጠየቀውን ሁሉ ግንቦት 7 እያለ መወንጀሉ የተለመደ ባህሪው ነው ብለዋል
ገዢው ፓርቲ በመጪው እሁድ በሀይማኖት ጉዳይ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን በተመለከተ ምን አስተያየት አለዎት የተባሉት ዶ/ር ብርሀኑ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ህዝቡን በሀይማኖት ለማጋጨት ላቀደው እቅድ በተመለደ ትእግስቱ እንዲያከሽፈው ጠይቀዋል።

የኢህአዴግ ስውር ሴራ በሮቤ ከተማ ተጋለጠ!!!

ሐገሪቷን የሚያስተዳድራት ማነው? የባሌ ሮቤ ሰላማዊ ሰልፍ ለምን ተደናቀፈ? ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ ማብራሪያ የሚሊየኖች ድምፅ ለነፃነት ንቅናቄ በአራቱም የኢትዮጵያ ማዕዘናት የነፃነት ድምፅ ማስተጋባት ከጀመረ እንሆ ዛሬ ስልሳሰባተኛ(67) ቀኑን ይዟል። ፓርቲያችን በእዚህ ታላቅ ሕዝባዊ የነፃነት ንቅናቄ መሪር የሆነ ውድ ዋጋ እየከፈለ ድምፅ አልባ ለሆኑትሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን ድምፅ በመሆኑ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል።

 ላለፋት ስምንት ዓመታት ሰቆቃ እና ግፍ በገዢዎቻችን ሲፈፀምበት የኖረው የገጠሩም ሆነ የከተማው ታላቁ ህዝባችን‘አንድነት ፓርቲአችን አስትንፋሳችን’ በማለት አንድነት ፓርቲ ባመቻቸለት ህዝባዊ ስብሰባዎች እና ሠላማዊ ሠልፎች በነቂስበመውጣት የታፈነ ብሶቱን በግልፅ በአደባባይ ላይ በማሰማቱ ኢህአዴግ እና ህዝቡ ዛሬም ድረስ ተለያይተው እንዳሉ አንድነት ፓርቲበማያወላዳ ሁኔታ በሚሊዮኖች ድምፅ ንቅናቄ በህዝባችን መሀል በመገኘት አረጋግጧል። 

ኢህአዴግ የቀረው በውሸት እና በሴራ የተሞላ የቅጥፈት ፕሮፖጋንዳ ብቻ መሆኑን ይበልጥ ያረጋገጠልን የባሌ ዞንአስተዳደር እና የሮቤ ከተማ አስተዳደር ያዘጋጁት በሀገር ሽማግሌዎች ስም የተቀነባበረው የእናደራድራችሁ አሳፋሪ ድራማለኦህዴድም ሆነ ለኢህአዴግ ታላቅ ውድቀት ነው።

አንድነት ፓርቲ በባሌ ሮቤ ከተማ ሠላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ህጉ በሚያዘው መሰረት ነሐሴ 13/2005 የሰላማዊ ሰልፍማሳወቂያ ደብዳቤ ለከተማዋ አስተዳደር አስገባ። ጉዳዩን የሚከታተሉት የፓርቲው ተወካዮች ደብዳቤው ከገባ ከ48 ሠዓት በኋላ ወደመደበኛ ቅስቀሳቸው መግባት እንደሚችሉ ህጉ እንደሚፈቅድላቸው የተረዱት የፓርቲያችን ትንታግ ታጋዮች ጊዜ ሳያባክኑየተዘጋጀውን የቅስቀሳ በራሪ ወረቀት በከተማ ውስጥ ማሰራጨት ጀመሩ።

ሁኔታውን በቅርብ ሲከታተሉት የነበሩት የፌደራል መንግስት እና የክልሉ መንግስት ከሮቤ ከተማ አስተዳደር ጋርበመቀናጀት አንድነት ፓርቲ ላይ ያጠመዱት ሴራ ለመተግበር የከተማው ከንቲባ አቶ አብዱል ላጥፍ ነሓሴ 13/2005 ለገባላቸውየፓርቲው ደብዳቤ መልስ ያሉትን ነሓሴ 13/2005 ቀን እንደ ተፃፈ ተደርጎ ፓርቲው አላማ ያሉትን ዘርዝረው ነሓሴ 17/2005 ዓ.ምደብዳቤ ለፓርቲው ተወካዮች ሰጡ። የተባሉትን ሰበቦች እና ምክንያቶችን በሙሉ አሟልቶ ፓርቲው የእዚያኑ ዕለት በደብዳቤ ምላሽቢሰጥም የከተማው አስተዳደር ባለስልጣኖች ከንቲባውም ጭምር ቢሮአቸውን ዘግተው ጠፉ። መዝገብቤትም ለማስገባትየተደረገው ጥረት በመዝገብ ቤት ሰራተኞች እምቢ ባይነት ሳይሳካ ቀረ። የአምባ ገነኑን የኢህአድግ ባለስልጣኖችን ነውረኛ ስራቀድሞ የሚያውቀው የአንድነት ፓርቲ የተዘጋጀውን ደብዳቤ በሪኮማንዴ በፓስታ ቤት በኩል አንዲደርሳቸው በማድረግ ምንምመፈናፈኛ ሰበብ እንዳያገኙ አደረገ።

ግራ የገባቸው የከተማው አስተዳዳሪዎች ተሰባስበው ከላይ በተሰጣቸው ትእዛዝ መሰረት አንድነትን የማጥቅያ ሌላ ሴራተጠቅመው መጥታችሁ የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያውን ቅፅ ሙሉ በማለት ለተወካዮቻችን ጥሪ አደረጉ። የፓርቲው ተወካዮችስራቸውን እየሰሩ ቅፁን የሚሞሉ እና የሚፈርሙ አባላትን በመመደብ ተወካይ ብቻ ወደ ወስተዳድሩ ፅ/ቤት ላኩ። የጠበቃቸው ግንየተቀናጀ ሴራ ነው። አንድነት ፓርቲን በህግ የሚያስጠይቅ እንዲሁም ያዘጋጁትን የሀይል ርምጃ ህጋዊ የሚያደርግ፤ ደብዳቤ ካስገባን48 ሰዓታት ባነሰ ጊዜ ሰልፍ እወጣለሁ ብሎ ፓርቲው ነሓሴ 17/2005 ደብዳቤ እንዳስገባ ተደርጎ ይህንኑ ቀን የጠቀሰ ቅፅአዘጋጅተው የአንድነትን ተወካዮች አንዲፈርሙ ተጠየቁ። ቀድሞውኑ ሴራው የገባው የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር በሰጠውመመርያ መሰረት ቅፁ ላይ የምንፈርመው ደብዳቤአችንን ያስገባንበትን ነሐሴ 13/2005 ቀን ከጠቀሰ ብቻ ነው በማለት የአንድነትተወካዮች አንፈርምም አሉ።

አንድነት ፓርቲን በጉልበትም በህግም ለማኮላሸት ኢህአድግ ያዘጋጀውን ሴራ በጥበብ ማክሸፍ ተቻለ። ኢህአዴግ ለሌላሴራ ማቀንቀኑን ወድያውኑ ተያያዘው።

የፓርቲው ቀስቃሽ ቡድን በ50‚000 የሚገመት በራሪ ወረቀት መበተኑን እና ከ5‚000 በላይ ፖስተር በእለቱ በመለጠፍየፓርቲውን መልእክት ለታፈነው የሮቤ ከተማ ህዝብ አደረሰ። በሁለት መኪና መጠነኛ ቅስቀሳ ካደረገ ከ 1፡00 ሰዓት በኋላመኪናዎቹ ከነቀስቃሽ ቡድኑ ከነሀሴ 18/2005 እስከ እሁድ ነሀሴ 19/2005 ድረስ በታጣቂዎች ከቆሙበት አንዳይንቀሳቀሱ ታገቱ።የትራፊክ ፖሊሶችም መኪናዎቻችንን በማገት ያለቆቻቸውን ትዕዛዝ ተግባራዊ አደረጉ። በዚህ መሀል ነው በሽማግሌ ስምያደራጃቸውን 15 የሚሆኑ የኦህዴድ ካድሬዎች “ነገ የሚከሰተው ደም መፋሰስ አሳስቦን ነው የመጣነው እናወያያችሁ” በማለትከምሽቱ 1፡30 ባረፍንበተ ሆቴል ተሰባስበው የመጡት። ለሀገር ሽማግሌ ክብር የሚሰጠው አንድነት ፓርቲ ሽማግሌዎች የተላኩበትንዝርዝር መልእክት ካዳመጠ በኋላ የእሁዱን ሰላማዊ ሰልፍ በምንም ተአምር እንደማንሰርዘው፤ ይልቁንም የከተማው መስተዳድርለፖሊስ የሀይል እርምጃ ውሰዱ ብሎ ያስተላለፈውን መመሪያ እንዲስብና ህገመንግስቱን እንዲያከብር ሽማግሌዎቹ ምክራቸውንለገዢው ፓርቲ ባለ ስልጣኖች እንዲለግሱ መልእክት በመንገር ውይይቱ ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ተጠናቀቀ። 

በኢህአድግ የተለመደቀመር የቅስቀሳ ጊዜያችንን በጉልበት እና በማስመሰል ለመስረቅ የተደረገውን የተለመደ ቅንብር አንድነት ፓርቲ ቀድሞ የሚያውቀውጉዳይ በመሆኑ ሁለት ተደራዳሪዎችን ብቻ በመመደቡ ሌላው ግብረኃይል ሳይዘናጋ የቅስቀሳ ወረቀቱን በማሰራጨቱ ኢህአዴግያሰበውን አንድነትን የመነጠል ሴራ ሳይሳካለት ቀርቷል።

እነዚያው የሀገር ሽማግሌዎች የተባሉ ግለሰቦች “መስተዳድሩ አሁን ሊያነጋግራችሁ ዝግጁ ነው። ቢሮ ድረስ ኑ እናተወያዩ” በማለት በሰላማዊ ሰልፉ ቀን እሁድ ከጥዋቱ 1፡00 ሰዓት እኛን ቀጥረውን በሰዓቱ ስንደርስ የኦሆዴድ ባለስልጣኖች ግንየጠዋቱ የቅስቀሳ ስዓታችንን ለመስረቅ ከጠዋቱ 1፡40 በሁለት ኮብራ መኪና እና ታርጋ በሌላት በአንድ መኪና በደህንነት ባለስልጣኖች ታጅበው መጡ።
ውይይቱ በዞኑ ም/አስተዳዳሪ አቶ ሰሎሞን አወያይነት የከተማው ከንቲባ፣ የኦሆዴድ ተጠሪ የኮምኒኬሽን ኃላፊ ሌሎችምከ15 ያላነሱ ባለ ስልጣኖች እንዲሁም በርካታ የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት ሦስት የመንግስት ካሜራዎች ተጠምደው ውይይቱተጀመረ።

የሽማግሌ ካባ የለበሱት የኦሆዴድ ካድሬ የሆኑት የሀገር ሽማግሌዎች ተወካይ ነኝ ያሉት ግለሰብ ውይይቱን በንግግርሲጀምሩ “እናንተ የነፍጠኛን ስርዓት ልታመጡብን ነው። እኛን ሳታነጋግሩ ሳንፈቅድላችሁ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንዴትአሰባችሁ? አሁንም ይህንን ሰላማዊ ሰልፍ አታደርጓትም። የሮቤ ህዝብ እኛን ዎክሎናል መንግስት እንኳን ቢፈቅድላችሁ እኛሽማግሌዎች አይደረግም ብለናል አቁሙ” በማለት የተጫኑትን ዉሳኔ በሚደንቅ ሁኔታ አስተላለፉ። በእዚያው መድረክየኢህአዴግ/ኦህዴድ ማንነት እና ጭንብል ለዓለም ህዝብ ተጋለጠ። አንድነት ፓርቲም ይህንን ከላይ እስከታች ባሉ ባለስልጣኖችየተቀነባበረውን ድራማ በካሜራ ቀርፆ ያስቀረ በመሆኑ በእጃችን የሚገኘውን የውይይቱን ይዘት የያዘውን ቨድዮ እንድትመለከቱበአክብሮት  እየጋበዝን አንድነት ፓርቲ የኢህአዴግን እውነተኛ ገፅታ በመረጃ ማጋለጡን  አጠናክሮ ዛሬም ነገም ይቀጥላል።

በሮቤ ከተማ ለቅስቀሳ የተላከው ቡድን በመስተዳድሩ ባለስልጣናት ትእዛዝ ከምሽቱ 4፡00 ስዓት አልጋ ከያዙበትታይታኒክ ሆቴል በግፍ ተባረው፤ የያዙትን ቦርሳ እንኳን ከመኝታ ክፍላችው ሳያወጡ በግፍ አውላላ ሜዳ ላይ ወንጀልእንዲፈፀምባቻው የከተማው መስተዳድር የፍፀመውን መንግስታዊ ውንብድና ፓርቲአችን በዝምታ የሚያልፈው ጉዳይ አይደለም።የመኪና ሹፊሮቻችንን በውድቅት ሌሊት ጭንብል ባጠለቁ ከ 20 በላይ ታጣቂዎችን በማሰማራት በማስወረር በጉልበት ክፍላቸውውስጥ በመግባት ስለተፈፀመው ወንጀል አንድነት ፓርቲ በህግ የሚጠይቅ ሲሆን ታላቁ የሮቤ ከተማ ነዋሪ ህዝብ መብቱንለማስከበር ያደረገውን ትንቅንቅ አንድነት ፓርቲ ከልብ ያደንቃል። ምስጋናውንም በእዚህ አጋጣሚ ያቀርባል።

ድል ለታፈነው የኢትዮጵያ ህዝብ!!!

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ
ነሐሴ 21 ቀን 2005 .
አዲስ አባባ¾

 (ምንጭ፡- ሰንደቅጋዜጣ 9ኛ ዓመት ቁጥር 416 ረቡዕ ነሐሴ 22/2005)

ከወራት በፊት ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ በረከት ስምዖን፣ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት በህንዳዊ ፕሮፌሰር ሲማሩ ነበር(ተመስገን ደሳለኝ)

28/08/2013

“በእያንዳንዱም መንግስት የሚያድሩ ብዙ ልዩ ልዩ ነገዶች ይኖሩ ይሆናል፡፡ ስለ ሆነ መንግስት አንዱን ነገድ አጥቅቶ ሌላውን ነገድ ለመጥቀም ሥራው አይደለም፡፡ አስተካክለን ካሰብን ዘንድ መንግስት መቆሙ ለሕዝቡ ሁሉ ጥቅም ነው፡፡ ጥረቱም ህዝቡን ሁሉ በትክክል ለመጥቀም ያልሆነ መንግስት ሊቆም አይችልም… ለአንዱ ነገድ ወይም ለጥቂት ሰዎች ብቻ ማድላት ለመንግስት የሚገባ ሥራው አይደለም” ይህንን መግቢያ የወሰድኩት በልዑል የኢትዮጵያ መንግስት  አልጋ ወራሽ ተፈሪመኮንን ማተሚያ ቤት የካቲት 1 ቀን 1917 ዓ.ም ከታተመው የነጋ ድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ‹‹መንግስትና የሕዝብ አስተዳደር›› መፅሀፍ ነው፤ ዛሬም ያለንበትን ዘመን ይዋጃልና፤ በተለይ ስለ‹‹ነገድ›› የተጠቀሰውን አርቀን ሰቅለን፣ ‹‹ለጥቂት ሰዎች ብቻ ማድላት›› የምትለዋን ሀረግ በወጉ ካጤንናት ለጊዜያችን በልክ የተሰፋች መሆኗን ለመረዳት አስቸጋሪ አይደለም፡፡

እናም የስርዓቱን የአስተዳደር ዘይቤ ያለፍርሃት አደባባይ ካዋልነው የቀድሞ ገዥዎቻችን የተጓዙበትን ጎዳና እየተከተለ መሆኑን ለመተንተን የምሁራንን ጥናት መጠበቅ ግድ አይለም፤ ምክንያቱም ለዓመታት የተመለከትነው እውነታ የሚነግረን የአመራሩን እና በዙሪያው የሠፈሩ የጥቅም ተጋሪ ግለሰቦችን ብልፅግና ታሳቢ ያደረገ፣ ከታግሎ መጣል ህግ የተቀዳ፣ የራስ ሀገርንና የራስ ሕዝብን በምርኮ ያስገበረ ፖለቲካ መንበሩን ነው፤ ገብር፣ ገብር፣ ገብር…!!
ዛሬ መንገድ ዳር ረሀብ አዙሮ የጣለው ወንድምህ ስቃይ እንደ ጥላ የሚከተልህ፤ ህፃናት በትምህርት ገበታቸው ላይ በጠኔ ተሸንፈው መመልከቱ የሰርክ አሳዛኝ ክስተት የሆነብህ ከሰው ሰራሽ ችጋር፣ ከሰው ሰራሽ የቀዬ ፍንቀላ፣ ከሰው ሰራሽ እርዛት… የመነጨ መርገምት እንጂ የሰማይ ቁጣ አይምሰልህ፤ እመነኝ መለስም ሆነ ተተኪዎቹ ስኬት አድርገው የሚሰብኩትም ይህንን ነው፤ ‹ሀገር አቀናን!› የሚሉትም ይህንን ነው፤ ሰሞኑን የሚያሰለቹህ ተረኛ ምሁራንም ‹‹ትምህርትና ጤናን በተመለከተ መለስ ‹እልል› የሚያስብል ሥራ ሰርቷል›› የሚሉህ ጣራና ግድግዳ እየቆጠሩ ነው፤ ይህ አይነቱ መደዴ ሙገሳም ለፕሮፓጋንዳ የሚሆን ሪፖርት ለማዘጋጀት ከሚረዳ ቁጥር የዘለለ አበርክቶ አንደማይኖረው አትዘንጋ፡፡
እውነት እውነት እልሀለሁ፡- ይህ የሆነበት ብቸኛው ምክንያት መንግስት በስልጣን ላይ ስለሚቆይበትመንገድ ብቻ መጨነቅን ግዴታው በማድረጉ ነው፤ ይህንን ለመረዳትም እያገባደድን ባለው ክረምት የመንግስት ትኩረት በምን ላይ አንደሆነ የሚያሳይ ማስረጃን ጨርፌ ላሳይህ፡፡
ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- የእስልምና እምነት ተከታዮች መንግስት በሃይማኖታቸው ጣልቃ መግባቱን በመቃወም እና የታሰሩ ኮሚቴዎቻቸው እንዲፈቱ በመጠየቅ እያደረጉ ያለውን ትግል በሰላማዊ መንገድ አጠንክረው ሲቀጥሉ፤በተቃራኒው ‹‹ፀጥታ አስከባሪዎች›› አንዳንዴ በጥይት፣ አንዳንዴ በአስለቃሽ ጢስ፣ አንዳንዴ በማጋዝ…ምላሽ ሲሰጡ…
በርግጥ መንግስት ከኃይል እርምጃው በተጨማሪ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎችን (በምን አግባብቶ ወይም በምን አስፈራርቶ እንደሆነ ባይታወቅም) ወደ አደባባይ በማስወጣት መብት ጠያቂዎቹን ከ‹‹አክራሪ››ነት እና ‹‹ወሃቢዝም››ነት ጋር አያይዘው የውግዘት በረዶ እንዲያዘንቡባቸው እያደረገ ነው፡፡ ኢቲቪም ይህንን ኩነት እየተከታተለ ማራገቡን ቀጥሎበታል፤ ‹‹የቲፒ ከተማ ነዋሪዎች ‹አክራሪዎችን አወገዙ››፤ ‹‹በደቡብ ወሎ ኩታ በር ዞን አንድነት ፓርቲ ህገ-ወጥ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰልፍ ተካሄደ››፤ ‹‹የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ‹የሼሁ ግድያ ድራማ አይደለም› አሉ፣ ‹የሼህ ኑሩ ኢልም ነው፣ የአሸባሪዎች ብር ነውም›ብለዋል››፤‹‹የመርሀቤቴ ነዋሪዎች ፅንፈኞችን በመቃወም የአቋም መግለጫ አወጡ››፤…
ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- አንድነት ፓርቲ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የ‹‹ፀረ-ሽብር ሕጉ›› እንዲሰረዝና የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ እና የአዳራሽ ስብሰባዎችን እያካሄደ ነው፤ መንግስትም አንዳንዴ የአፀፋ የድጋፍ ሰልፍ ሲያካሄድ፤አንዳንዴ የአዳራሽ ስብሰባዎች ከመካሄዳቸው አስቀድሞ ‹መጋኛ› ሲሆንባቸው፤ አንዳንዴም የአስተባባሪዎቹን መኪና ጎማ ሲያፈነዳ፤ አንዳንዴም አዳራሽ ከልክሎ ሲያደናቅፋቸው… መዋሉ ፋታ የነሳው ይመስላል፤ በወላይታ የተጠራውን የአዳራሽ ስብሰባም ‹በጠቅላይ ሚኒስትሩ የትውልድ ቦታ እንዴት ተደርጎ!›› ያሉ ካድሬዎች የአንድነት ሰዎችን አዋክበው ስብሰባውን አክሽፈዋል፤ ክረምቱእንዲህእየተገባደደነው፡-ገዥው ፓርቲ ‹የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ አንደኛ ሙት ዓመት አከብራለሁ› በሚል መላ ኢትዮጵያን ችግኝ መትከያ፣ መላ ዜጎቿን ደግሞ ወደ አርሶ አደርነት በአስማት የቀየራቸው አስመስሏቸዋል፤ቴሊቪዥንና ራዲዮንም አስፈላጊነታቸው በየመንደሩ ችግኝ መተከሉን እየተከታተሉ መዘገብ ብቻ እስኪመስል ድረስ እንዲህ ሲሉ ጀምበር ወጥታ ትጠልቃለች፡- ‹‹የላይ አርማጮህ ነዋሪዎች ችግኝ ተከሉ››፣ ‹‹በመቀሌ ከተማ ‹ዘመቻ መለስ› በሚል የችግኝ ተከላ ተካሄደ››፣ ‹‹አቃቂ ኮረብታ ላይ በሚሊዮን የሚቆጠር ችግኝ በኦሮሚያ ፌደራል ፖሊስ አባላት ተተከለ፤ ቦታውም ‹መለስዜናዊ ኮረብታ› ተብሎ ተሰይሟል››፣ ‹‹በምዕራብ ሀረርጌ አስራ ሰባት ሚሊዮን፣ በወልበራ አስራ አራት ሚሊዮን ችግኝተ ተክሏል››፣ ‹‹በመንዝ ላሎ ወረዳ ተቆጥሮ የማያልቅ ችግኝ ተከላ ተደርጓል››፣ ‹‹የብአዴን አመራርና ካድሬ በባህር ዳር ከተማ በቢሊዮን የሚቆጠር ችግኝ ተከሉ፤ በፕሮግራሙ ላይ ጓድ አዲሱ ለገሰ ‹ችግኝ የምንተክለው አገሪቱ በአረንጓዴው ልማት በአለማችን ማግኘት የሚገባትን ቦታ እንድታገኝ ለማድረግ ነው› ሲል፣ ተመስገን ደሳለኝጓድ በረከት ስምዖን ደግሞ ‹ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በአለማችን በአንድ ጊዜ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ችግኝ እየተከሉ ያሉባት ብቸኛ ሀገር ናት› ብሏል››፤‹‹ዝክረ መለስ 1ኛ ዓመት መታሰቢያን ምክንያት በማድረግ ከሐምሌ አስራ አምስት ቀን ጀምሮ ሁሉም ቀበሌዎች በስሙ ‹ፓርክ› ሰይመው ችግኝ ተከላ እያካሄዱ›› መሆኑን ደግሞ የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ መግለፁን የአማራ ክልል ብዙሃን መገናኛ ዘግቧል፤ ‹‹በወልቂጤ ከተማ በተደረገው ችግኝ ተከላ ላይም አንዲት ወጣት ‹መለስ ለሴቶች የተለየ አመለካከት ነበረው›› ማለቷም በዘገባው ተጠቅሷል፤ …ማን ነበር የመለስ ራዕይ ‹ችግኝ መትከል ነው› ያለው? …ኢህአዴግ ይሆን?
ከዚሁ ጎን ለጎን (አሁንም ሙት ዓመቱን ለማሰብ) በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የእግር ጉዞ ተደርጓል፣ የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓትም ተካሄዷል፤መነሻውን መቀሌ፣ መድረሻውን አዲስ አበባ ያደረገ ‹‹የመለስ ቱር አረንጓዴ ልማት›› የብስክሌት ውድድርም ሊጠናቀቅ ገና አንድ ሳምንት ይቀረዋል፤ በብሄራዊና ሀይማኖታዊ በዓላት ቀንለሃያ አንድ ጊዜ ይሰማ የነበረው የመድፍ ድምፅም፣ የመለስን አንደኛ ሙት ዓመት ለማብሰር ተተኩሷል፤ …በግድ አልቅሱ፣ በግድ ተዝካር አውጡ፣ በግድ ችግኝ ትከሉ፣ በግድ ተወያዩ፣ በግድ አደባባይ ውጡ፣ በግድ የፎቶ ግራፍ ኤግዚቢሽን ጎብኙ፣ በግድ..
ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ እና የትምህርት ሚኒስትሩ ሽፈራው ሽጉጤ ከአንድ ሺህ ሰባት መቶ በላይ ለሚሆኑ የዩኒቨርስቲ ከፍተኛ መምህራን ‹የአቅም ግንባታ ስልጠና› እየሰጡ ነው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምሁራኖቹን ማሰልጠን ያስፈለገበት ምክንያት ‹‹ብቃት ያለው ምርጥ የተማረ ኃይል ለማፍራት››መሆኑን ቢነግርህ አይግረምህ፤ ይህ ኢትዮጵያ ነውና የዐዋቂነት ማረጋገጫው መማር፣ ማንበብ፣ መመራመር… አይደለም፣ የፖለቲካውን ኃይል መያዝ እንጂ፤ ‹ስልጣን ላለው ሁሉምሚስጥረ-ጥበብይገለፅለታል› እንዲል አብዮታዊ ዲሞክራሲ መለስ ዜናዊም በሁሉም መስክ ‹አስተማሪ› ነበር፤ የህግ ባለሙያዎችን ሰብስቦ የሀገሪቱን ወንጀለኛ መቅጫ ህግ ትርጓሜ ሲተነትን ደጋግመህ ሰምተኸዋል፤ በቀጣዩ ቀን ደግሞ ለግብርና ባለሙያዎች ከውሃ ማቆር እስከ በላብራቶሪ የሚዳቀል ምርጥ ዘር ድረስ ባሉጉዳዮችዙሪያ የሁለት ቀን ማብራሪያ መስጠቱን ታስታውሳለህ፤ እመነኝ ተተኪው ጠቅላይ ሚኒስትርም ይህንኑ ነው እያደረገ ያለው፤
የሆነ ሆኖ ኃ/ማርያም ለምሁራኖች ከሙያቸው ጋር ስለተያያዙ ጉዳዮች ጭምር በሰጣቸው ስልጠና ላይ እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀርቦለት ነበር ‹‹የኢንዱስትሪዎች በበቂ ሁኔታ አለመኖሩ፣ በክፍል ውስጥ የምናስተምረውን ንድፈ ሃሳብ በተግባር ለማሳየት እንቅፋት ሆኖብናል››፤ በርግጥጠቅላይ ሚንስትሩ‹‹መፍትሄ››ያለውን የተናገረው ብዙም ሳይጨነቅ ‹‹እኔ ኢንዱስትሪን ‹ዲፋይን› የማደርገው ግብርናም ኢንዱስትሪ ነው ብዬ ነው››በማለት ነበር፤…ግና!ይህ እንዴት ሊሆን እንደሚችል በተጨባጭ አላብራራም፡፡ ለምሳሌ ህክምና የሚያጠና ተማሪ በምን መልኩ በሞፈርና ቀንበር የተግባር ልምምድ ማድረግ እንደሚችል፤ወይም ፖለቲካ ሳይንስ የሚያጠና ተማሪ የተግባር ልምምዱን በግብርና ኢንዱስትሪ እንዴት ሊወጣው እንደሚችል? ማለቴ ነው፡፡
ለዓመታት በርካታ ምሁራን ብቃት አልባ ተማሪዎች እንደ ሰማይ ከዋክብት የመብዛታቸው መንስኤን ከትምህርት ፖለሲው ጋር የሚያነፃፅሩበትን ሀቲት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ ባገኘው የሀገር መሪነት ስልጣን ገልብጦ በዩንቨርስቲ ቆይታው መምህራኖቹ የነበሩትንም ጭምር ‹‹አቅም አንሷችኋልና-እገነባችኋለሁ›› ሲል ከመስማት የከፋ እንደ ሀገር ክሽፈት የለም (በነገራችን ላይ ከወራት በፊት ለኃይለማርያም ደሳለኝ፣ በረከት ስምዖን፣ ቴውድሮስ አዳህኖም፣ ሶፍያን አህመድ በአጠቃላይ ሁሉም የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት አንድ ህንዳዊ ፕሮፌሰር በኢህአዴግ ጽ/ቤት ‹‹ልማታዊ መንግስት›› እንዴት ውጤታማ ሊሆን እንደሚችል ሲተነትንላቸው፣ እነርሱም ደብተርና እስክርቢቶ ይዘው በንቃት ሲከታተሉ የቴሌቪዥ ዋና ዜና ሆኖ የቀረበበትን ምክንያት ዛሬም ድረስ ሊገለፅልኝ አልቻለም፤ በተለይም ፕሮፈሰር እንድርያስ እሸቴ ‹‹በቃሉ የፀና…›› በሚል ርዕስ መለስን አስመልክቶ በተዘጋጀ ዶክመንተሪ ፊልም ላይ ‹‹በዓለማችን ለመጀመሪያ ጊዜ ልማታዊ ስርዓተ መንግስት ‹ዴሞክራሲያዊ ሊሆን ይችላል፤ መሆንም አለበት› ብሎ በአደባባይ የተከራከረው እኔ እስከማውቀው ድረስ መለስ ነበር›› ማለቱን፣ ተተኪዎቹ ፍልስፍናውን ገና እየተማሩት ከመሆኑ አንፃር ስናየውሀገራችን ያለችበት ሁኔታ ጉዞው ወዴት ነው? ያስብላል፡፡ …ከቶስ በተማሪ ፖለቲከኛ የሚተዳደር ሕዝብ ከኢትዮጵያ በቀር ወዴት ይኖራል?)
ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- የህዳሴውን ግድብ ከዳር ለማድረስ በቂ ገንዘብ ስላልተገኘ ተደጋጋሚ የቦንድ ሽያጭ እየተካሄደ ነው፤ አንዳንድ የመንግስት ሰራተኞችም በካድሬ ባልደረቦቻቸው ጫና በድጋሚ ቦንድ ለመግዛት መወሰናቸው ተሰምቷል፤ በርግጥ ከፍተኛ የኢህአዴግ የአመራር አባላት በአውሮፓ፣ በሰሜን አሜሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ቦንድ እንዲገዙ ለመቀስቀስ የአዘጋጇቸው ስብሰባዎች ‹‹ቅድሚያ የዜጎች መብት ይከበር›› ባሉ የሀገራችን ልጆች መክሸፉም የክረምቱ የመንግስት ዋና ሥራ ነው፤
ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- በነቢብ የኢትዮጵያ፣ በገቢር የገዥው ፓርቲ የግል ንብረት የሆነው ቴሌቪዥን ጣቢያ ባለፉት ሶስት ወር ብቻ ከሃያ በላይ ‹‹ዶክመንተሪ ፊልም›› አሳይቷል (ገና ይቀጥላልም) በርዕሳቸው እንደሚከተለው እንዘርዝራቸው፡- ‹‹ኢፍቲን›› በሶማሊያ ላይ የሚያጠነጥን፣ ‹‹የጥቁር ህዝቦች ልሳን (መለስ በአፍሪካ)››፣ ‹‹ከፓን አፍሪካ እስከ አፍሪካ ህዳሴ›› የጠቅላይ ሚንስትር መለስን ህይወት የሚዳስስ፣ ‹‹ዘመነ አፍሪካ››፣ ‹‹የአፍሪካ ልሳን-መለስ››፣ ‹‹መለስ ማን ነው?››፣ ‹‹ሀገሬ-ቤቴ››፣ ‹‹ባለራዕዮቹ›› ስራ ፈጠራ ላይ የሚያተኩር፣ ‹‹ደውል›› እና ‹‹ደውል 2›› ህገወጥ-የሰዎች ዝውውርን በተመለከተ (በተለያያ ጊዜ የተላለፉ)፣ ‹‹የዲያስፖራ የልማት እንቅስቃሴ››፣ የካርታ ስራ ድርጅትን በተመለከተ፣ ‹‹የጥልቅ አስተሳሰብ ባለቤት›› በፕ/ር እንድርያስ እሸቴ ህይወት ዙሪያ የሚያጠነጥን፣ ምድር ባቡር ኮርፕሬሽንን በተመለከተ፣ ‹‹ያልተለመደ ጉብኝት›› የአዲስ አበባ አስተዳደር የአምስት ዓመት የመንግስት ግንባታዎችን በተመለከተ፣ ‹‹ሼህ ኑር ለምን ሞቱ?›› የደሴውን ሼህ ኑር ይማምን ግድያ በተመለከተ፣ ‹‹የተስፋ ስንቅ››፣‹‹በቃሉ የፀና›› በድህረ መለስ ላይ የሚያተኩር፣ ‹‹ያልተጠኑ ገፆች›› በመለስ ዜናዊ ህይወት ዙሪያ (በርግጥ በዚህ ፊልም እህቱ ጠላ፣ ወንድሙ አንባሻ በመሸጥ መተዳደራቸውን በምስልም በድምፅም ማቅረቡ ምን የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ተፈልጎ እንደሆነ ለማወቅ ግራ ያጋባል፤ …ምናልባትእንዲያ እየዘረፈ ለቤተሰቦቹ ‹ሶልዲን› የማይሰጥ ‹ቆነቋና› ነበር ለማለት ይሆን? ወይስ ለአዜብ መስፍን ‹የወር ቀለባችንን እንቸገራለን› የአንድ ሰሞን ማስተዛዘኛ ምስክር ፍለጋ ነው?
በጥቅሉ ለኢህአዴግ ሕዝብን የማስተዳደር፣ ሀገርን የመምራት መገለጫ ይህ ነው፤ ሌላ አይደለም፤ ግና! ለዘመናት ያልተመለሱ ጥያቄዎቻችን ዛሬም መጮኻቸውን አላቋረጡምና እነሆ እንዲህ ቀጥለዋል፡- ሀገር ማስተዳደር ‹መለስ ጀግና ነበር› እያሉ ማሰልቸት ነውን? የመንግስትስ ስራ (ግዴታ) ምንድር ነው? ሀገሪቱን ‹‹መለስ-ፓርክ›› ወደሚል ስያሜ ከመቀየራችሁ በፊት፣ ለጤፍ ዋጋ አለቅጥ መናር ምክንያቱን ስለምን መመርመር ተሳናቸው? ሀገሪቱን በ‹አራጣ› እንደያዘ ስግብግብ ነጋዴ በሚሊዮኖች ህይወት ላይ የማይሞላ ‹ሳፋ› ደቅኖ አዋጣ፣ ግዛ፣ ክፈል፣ ገብር… እያለ የሚያስጨንቀው ማን ነው? ስለመለስ ‹የሃሳብ ምጡቅነት› መስካሪ ምሁራኖቻችን ለጎዳና ኑሮ የተዳረጉ ኢትዮጵያውያን ስንት ሚሊዮን እንደደረሱ እና እልፍ አላፍት ታዳጊዎቻችን በሴተኛ አዳሪነት እንደተሰማሩ የምትነግሩን መቼ ነው?እንዲህ የመሆኑ ምክንያትስ በማን ይሆን? ‹የሁለት ዲጂቱ›ዕድገት ሸክምን የማለዘብ አቅም ከሌለውፋይዳው ምንድር ነው? ‹ሳቅ ትዝታ› ስለሆነባቸው ጎጆዎች ለምን አትነግሩንም? መለስ ‹ያለመለማት› ኢትዮጵያ ወዴት ትሆን? ‹ፖለቲካ› ማለትስ ይህ ነውን?…ነጋ ድራስ ገ/ህይወት እንዳሉት ‹‹…መንግስት መቆሙ ለሕዝቡ ሁሉ ጥቅም ነው፡፡ ጥረቱም ህዝቡን ሁሉ በትክክል ለመጥቀም ያልሆነ መንግስት ሊቆም አይችልም፡፡›› የመተራረሚያው ጊዜም በጣም ያለፈ ይመስለኛል፡፡ አገዛዙን ‹እንደ መንግስት› መቀበሉም እንዲሁ፡፡

መንግሥት ለተፈጠረው ችግር በአስቸኳይ ማስተካከያ እንዲያደርግ እንጠይቃለን! ሰማያዊ ፓርቲ

August 28, 2013
ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ


semayawi party's protest call in Addis Ababaፓርቲያችን ሰማያዊ በህገ መንግሥቱ በተደነገገው ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቱን ተጠቅሞ ለመንግሥት ጥያቄዎችን በማቅረብ ግንቦት 25/2ዐዐ5 ዓ/ም. ታላቅ ህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ አድርጓል፡፡

መንግሥት ላቀረብናቸው ጥያቄዎች በሦስት ወር ውስጥ መልስ የማይሠጥ ከሆነ በተጠናከረና በተደራጀ መልኩ ጥያቄያችንን በድጋሚ በህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ እንደምናቀርብ በግንቦት 25/2ዐዐ5 ዓ/ም. በተደረገው ሠልፍ ላይ ለህዝብ ቃል በገባነው መሠረት ነሃሴ 26/2ዐዐ5 ዓ/ም. በድጋሚ ሰልፍ ጠርተን አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረግን መሆኑን ለህዝብ በልዩ ልዩ መገናኛ ዘዴዎች ገልፀናል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ለሰልፉ በሰላም መጠናቀቅ አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግልን አዋጁ በሚጠይቀው መሠረት ለአዲስ አበባ መስተዳድር ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ማሰወቂያ ክፍል ጉዳዩን እንዲያውቀው አድርገናል፡፡

ይሁን እንጂ ፓርቲያችን ህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ በጠራበት ግዜና ቦታ ላይ በሌላ አካል ሰልፉ መጠራቱን በትናንትናው ዕለት ነሀሴ 20 ቀን 2005 ዓ.ም በመንግሥት ቴሌቪዥን ዜና ሰምተናል፡፡ በተጨማሪም ለመንግሥት መዋቅር ዜጐች በዚህ ሰልፍ እንዲወጡ በግድ እንዲፈርሙ እየተደረገ መሆኑን ከአዲስ አበባ ኑዋሪዎች አረጋግጠናል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ አስፈላጊውን የህግ ቅድመ ሁኔታ አሟልቶ ነሐሴ 26/2ዐዐ5 ዓ/ም. በመስቀል አደባባይ የጠራውን ተቃውሞ ሰልፍ ለህዝብ ያሳወቀና አስፈላጊውን ዝግጅት ያጠናቀቀ በመሆኑ ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ በጠራበት ቀንና ሠዓት በሌሎች አካላት የተጠራው ሰልፍ ከመረጃ እጥረት ከሆነ እንዲሠረዝ እየጠየቅን ይህ ካልሆነ ግን ሰማያዊ ፓርቲ በህጋዊ መብቱ የሚያደርገውን የተቃውሞ ሰልፍ ሆን ብሎ ለመረበሽና አቅጣጫውን ለማስቀየስና በዜጐች መካከል ግጭት ለመፍጠር የታቀደ ስለሆነ ለሚፈጠረው ችግር ተጠያቂ መንግሥት መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብና የሚመለከታቸው አካላት እንዲያውቁት በአፅንዖት እንገልፃለን፡፡
በመጨረሻም መንግስት ዜጐችን ያለፈቃዳቸው በማስፈረም ተገደው ሰልፍ እንዲወጡ ማድረግ ህገ ወጥ ስለሆነ፣ በአስቸኳይ እንዲያቆም እንጠይቃለን፡

Tuesday, August 27, 2013

ህወሓቶች ‘ሁኔታችን አይታቹ ደግፉን’ ይሉናል

ባለፈው ሳምንት ነው፤ በአንድ የሰሜን አሜሪካ ከተማ። የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናት በሰሜን አሜሪካ በሚካሄደው የተጋሩ ፌስቲቫል ተገኝተው ድጋፍ ለማሰባሰብ በረሩ። ከትግራይ ተወላጆች ጋር ለመወያየት መድረክ ተከፈተ። ተሳታፊዎቹ ስለ ልማትና መልካም አስተዳደር ችግር፣ ስለ ሐውዜን ጉዳይ፣ በትግራይ ተወላጆች ስለሚደርስ የሰብአዊ መብት ጥሰት ወዘተ አንስተው ይጠይቃሉ። ባለስልጣናቱም ሲመልሱ፣ “እኛ ‘ኮ ብዙ ጠላቶች አሉብን። እኛን ለማጥፋት የሚሯሯጡ ኃይሎች አሉ። እኛ'ኮ 'ትግሬ ወደ መቀሌ ዕቃ ወደ ቀበሌ' የሚሉን ሞታችንን የሚጠባበቁ ኃይሎች ይዘን ነን ያለነው። ይህ ሁኔታችን እያወቃቹ እንዴት እንዲህ ዓይነት ጥያቄ ትጠይቃላቹ? እንዴት ህወሓትን ይህን ያህል ትጠላላቹ? ሁኔታችን ኮ መረዳት አለባቹ።"

ይገርማል። ህወሓቶች ጥያቄ መመለስ ሲያቅታቸው 'ጠላት እየመጣ ነው፣ ህወሓቶች ከሌለን የትግራይ ህዝብ አደጋ ዉስጥ ይወድቃል' ይሉናል። መጀመርያ የትግራይን ህዝብ ጠላት ማነው? ለምንስ ጠላት ሆነ? ጥላቻው ማን ፈጠረው? 'የትግራይ ህዝብ ጠላት አለው' ብለን እንኳ ከተነሳን ማድረግ ያለብን የትግራይን ህዝብ ማፈን አይመስለኝም። ምክንያቱም ህዝብ ማፈን ህዝቡ ደካማ እንዲሆን ማድረግ ነው። ደካማ ከሆነ ደግሞ ለጥቃት ይዳረጋል።

በትግራይ ህዝብ ያንዣበበ አደጋ ካለ መፍትሔው ሌሎች ህዝቦች መበደል ነው? አይመስለኝም። በትግራይ ህዝብ ስም ሌሎች ህዝቦች መበደል ጠላትን ማፍራት ነው። በትክክል ስጋቱ ካለ የትግራይ ህዝብ መብቱ ተከብሮለት አማራጭ የፖለቲካ ድርጅት እንዲኖረው ሊፈቀድለት ይገባል እንጂ ሊታፈንና ሊዳከም አይገባም።

የትግራይን ህዝብ ከጥቃት ማደን የሚችሉ የህወሓት ባለስልጣናት ብቻ ናቸው ያለ ማነው?

Tigray Republic flaunting her wealth at glittering TDA functions across the globe.

(Getahune Bekele-South Africa)


Created by the dead enclave hero Meles Zenawi and officially known as the regional state of Tigray, state within a state and the birthplace of the current ruling party in Ethiopia, Tigre People Liberation Front/TPLF; Tigray republic is holding its glittering annual Tigray Development Association/TDA functions around the world with tyrannized and indigent Ethiopian taxpayers footing the huge bill.
abay wAfter a week long music and dance spectacle in various US cities, where scrumptious meals and champagne were made available with gay abandon, TDA delegation led by the belligerent and the most feared TPLF warlord, Tigray republic president Abbay Woldu(pictured), arrived here in London for Saturday’s (24 August 2013 similar extravaganza) on Friday night.
After lavish welcoming ceremony and stopover at TPLF flag- adorned Ethiopian Embassy in London, the warlord headed to one of London’s expensive five star hotels in Mayfair’s Stratton Street with his massive Tigre entourage.
An Ethiopian business executive Ergibe Mekonnen, 48, a London resident for twenty years told the Horn Times that she spotted warlord Abbay Woldu late Saturday night at 51 Buckingham Gate with two female companions.
In addition, the Horn Times learned that as it was in the US last week, meetings and musical and cultural celebrations were only for the republic’s citizenry. Agendas and resolutions were top guarded secrets. No journalists from the exiled free press were allowed near the TDA festivals and paying Tigre members had to produce special barcoded TDA IDs to secure entrance.
Hence, it appeared difficult to verify the widespread rumor that if warlord Abbay Woldu indeed threatened Ethiopian Muslims and the opposition UDJ party with all-out military assault similar to the 2005 onslaught.
“Am sorry. I cannot go to a segregated ethnocentric celebration of a minority group. This is a sign of sheer madness and backwardness by TPLF warlords. We paid a huge price to overthrow the communist regime of Mengistu to see a better Ethiopia. Am an academic from Tigray. I supported Woyyane anticipating a united, democratic, and prosperous Ethiopia. Instead, look at what we are getting. A crazy warlord coming to London in the 21st century to chair a meeting of his clan. What a shame.” A college professor based in the UK told the Horn Times asking us not to publish his name for security reasons.
“It is time for the people of Tigray to rise up and say to the warlords ‘NOT IN MY NAME’. When Meles Zenawi was still alive, we repeatedly raised the issue of putting Tigray first in every aspect should not be allowed to develop in to some sort of naked ethnic apartheid. That is what we see today. While Other Ethiopian resource- rich provinces struggle to hold their annual meetings at home how do resource- poor Tigray afford to stage multi-million dollar events in New York, Paris, and London? Moreover, if they have nothing to hide why exclude non-Tigre Ethiopians from attending the gathering? This does not auger well for the coming generations of Tigray. TPLF is ostracizing the people of Tigray.” The heavily bearded academic with pure British accent added.
Describing the TDA extravaganza held in Washington Dc and London repulsive, irresponsible, and shameful, another Tigray born medical practitioner who distanced himself from the profane clannish celebration said thieving TPLF warlords do not have both the wisdom and sensitivity to rule Ethiopia.
“As distance from the sea continues to hamper development, Ethiopia remains the second poorest nation in Africa after Niger. Millions go to bed hungry and a third world epidemic known as polio is spreading like wild fire. Shortage of hard currency is also making life unbearable in the land locked nation of 80-million. So tell me, what is there to celebrate? Ethiopians are in desperate need of a regime change. It is time for the outdated junta to leave.
ashenda-tigrai
Ashenda Tigray festival to be staged around the world soon… (Pic aiga forum)
“We have to strongly condemn wild clannish celebrations such as this and the Tigray martyrs day fiesta for the sake of our children. Moreover, I believe the equal distribution of wealth is the hallmark of 21stcentury democracy. Beating drums to celebrate the emphatic economic successes of one region at the expense of the other regions is very dangerous. It is a clear sign of terrible misrule. I don’t know where we are heading to…,” the London based medical practitioner told the Horn Times. We withhold his name  for security reasons.
To balance the report, the Horn Times then contacted the office of the president of the regional state of Tigray based in Mekele, Ethiopia as to find out  who funded warlord Abbay Woldu’s trip to the US and Europe. However, a certain Giday Solomon arrogantly refused to comment warning the Horn Times that referring to his boss as warlord is an insult to the dignity of the entire TPLF leadership.
After our daylong attempt to get hold of Washington and London based Tigray Development Association fat cats proved unsuccessful, the Horn Times finally contacted TPLF cash cow, EFFORT, one of huge TPLF owned companies capable of sponsoring multi-million dollar TPLF functions anywhere in the world.
“We don’t know what you are talking about. Man up and ask the honorable Tegadelti (Abbay Woldu) himself. Am sure he will give you a sweet answer.” A woman who refused to give her name sarcastically replied and declined to take further questions from “the diaspora media.”
Meanwhile, according to information obtained from two major TPLF websites known as the aiga forum and Tigray online, diaspora TPLF cadres are preparing to stage yet another multi-million dollar Tigray cultural festival named “ASHENDA TIGRAY” in Washington, New York, Melbourne, Paris, London, and various other European cities in the coming weeks.

ተስፋሁንን መግደል ለኢህአዴግ ተስፋ ይሆናታልን….!?



ተስፋሁንን መግደል ለኢህአዴግ ተስፋ ይሆናታልን….!?

bbbአብዲሳ የብዙ ጊዜ ወዳጄ ነበር፡፡ በየገጠሩ እየዞርን በርካታ ስራ አብረን ሰርተናል፡፡ የዋህነቱ እጅግ በጣም አስገራሚ ነበር፡፡ በየክልሉ ስንዞር አበሉን የሚጨርሰው “ቸገረኝ” ላለው ሁላ መበስጠት እንደነበር አብረነው የሰራ ሁላ እርሱን የምንለይበት ባህሪው ነው፡፡ ይሄ ልጅ በአንዱ ቀን ለስራ ልንሄድ የተቀጣጠርንበት ቦታ ሆነን ስንጠብቀው ስንጠብቀው ሳይመጣ ቀረ… ስልኩን ብንደውልልት አይሰራም፡፡ ካለንበት እየተንቆራጠጥን… ወደ ሶስት ሰዓት ድረስ ዘግይተን ጠበቅነው የውሃ ሸታ ሆነብን… ምን ሆነ ብለን እየተጨነቅን እንጀራ ነውና ጉዟችንን ቀጠልን…

አብረን ስንጓዝ ከነበርነው መካከል አብዲሳን በቅጡ የምናውቀው ሰዎች “ይሄኔ አንድ የታመ ሰው አጋጥሞት ሆስፒታል ሳላደርስ አልሄድም ብሎ ነው…” ….ወይ ደግሞ “…አንዱ ገንዘብ ተቸግሮ አጋጥሞት  ምንም ሳያስቀር ገንዘቡን ሰጥቶ ወደ እኛ መምጫ ራሱ ተቸግሮ ይሆናል …” ካልሆነ ግን “…ዘራፊዎች አግኝተው ጉድ አድርገውት ሊሆን ይችላል…. እያልን መገመታችንን ተያያዝነው…

ግምታችን ሁሉ ትክክል አልነበረም፡፡

አብዲሳ በስንተኛው ጊዜ በቴሌቪዥን መስኮት መታየቱን ሰማን… በየዋህነቱ የተቸገረ በመርዳቱ የምናውቀው አብዲ “አሸባሪ” ተብሎ በመንግስት ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ አብዲሳ “አሻባሪ” ከተባለማ እኛ ምን ልንባል ነው… ብለን ራሳችንን እንደ ነውጠኛ የምናየው እኛ በጣም ተደነቅን!

አብዲ ወደ አምስት ወራት በማዕከላዊ፣ ወደ አምስት አመት በቃሊቲ እንዲሁም ሁለት ሶስት አመት ነው መሰለኝ በዝዋይ ማሰሪያ ቤቶች ቆይቶ ነፃ ነህ ተብሎ እስኪሰናበት ድረስ በአስር ቤቱ ውስጥ ሲደርስበት በነበረው መከራ ብዙ ጉዳት ደርሶበታል፡፡ ታድያ ከእስር ቤት ሊወጣ አካባቢ አንድ ባለስልጣን ብጤ ሰውዬ ጎብኝተውት ነበር፡፡

እስር ቤቱ እንዴት ነበር… ሲሉ ጠየቁት፡፡ አብዲሳ ምን አላቸው መሰልዎ… እስር ቤቱ እንዴት እንደሆነ ራስዎት ገብተው ካላዩት በስተቀር እንዲህ ነው ብዬ  ብነግሮት አይገባዎትም ፡፡ አላቸው፡፡

ይሄው ሰሞኑን ወንድማችን ተስፋሁን ጫመዳ በእስር ቤት በደረሰበት ስቃይ የተነሳ ህይወቱ ማለፏን ሰማን፡፡ ተስፋሁን በ1999 ዓ.ም መንግስት ኬኒያ ድረስ አፍኖ ወሳጆቹን ልኮ ለኬኒያ ፖሊስ ሽልጉን ከፍሎ፤ (የኬኒያ ፖሊስ እንኳንስ ከፍለውት እንዲሁም ጤዛ ነው) ብቻ በትብብር ወደ አዲስ አበባ ተወስዶ ነበር… ከዛም በታሰረበት ሆኖ ሞተን ሰማን!

ለዚህ ጉዳይ የሚሰማ ቢኖር የኬኒያን መንግስት ራሱ ፍርድ ቤት ማቆም የሚገባ ይመስለኛል፡፡

ፍርድ ቤት ሳይቀርብ ራሱ፤ በነፍስ ማጥፋት ወንጀል እግዜሩም እኛም የምንጠይቀው ግን የገዛ መንግስታችን ነው፡፡ አዎ መንግስታችን እጁ ላይ የተለያዩ ሀገራት ብድር ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ሰዎች እምባ የተለያዩ ሰዎች ደምም አለበት፡፡

ተስፋሁን ለምን እንዲሞት ተፈረደበት… እውን ለሀገሪቱ ደህንነት ስጋት ሆኖ ነውን… የሚለውን በፍጹም!!! ለማለት፤ እነ አብዲሳን ያየነው እኛ ምስክሮች ነን፡፡ ምስኪኑ አብዲሳ ስምንት አመት ታስሮ በነፃ ከመፈታቱ በፊት “የሀገር ስጋት ሽብርተኛ!” ተብሎ ነበር የታሰረው፡፡  በእስር ቤት የደረሰበትን ስቃይ ሰው ሆኖ መፈጠርን የሚያስጠላ ነው፡፡ የነገረኝን በሙሉ ለማሳየት በፊልም እንጂ ጽሁፍ የሚገልፀው አይደለም፡፡

እሺ ኢንጂነር ተስፋሁን የኦነግ ወይም የሌላ ተቃዋሚ አባል ወይም ደጋፊ ወይም እንዳሻቸው ይሁኑ ባይ ነው እንበለው፡፡ ግን እርሱን በመግደል የሚቃወሙ ሰዎችን ተስፋ ማስቆረጥ አልያም  ቁጥራቸውን መቀነስ ይቻላል….

ኢህአዴግ በጫካ እያለች ታጋዮቿ እና ሰላዮቿ ደርግ በቁጥጥር ስር ሲያውላቸው ቀጥታ አብዮታዊ እርምጃ ይወስድባቸው ነበር፡፡ ውጤቱ ግን ምንድነው  የሆነው… ብለው የጠየቁ እንደሆ፤  ውጤቱ ብሶቱን እያጠነከረው ቁጭቱን እያባሰው እምቢ ባይነቱን እያበረታው ነው የሄደው…!

ዛሬ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ኢትዮጵያውያን በእስር ቤት ውስጥ ፍዳቸውን እያዩ ነው… የምር ለኢህአዴግ እናስባለን የምትሉ ሰዎች የእነ ተስፋሁን ግድያ የኢህአዴግ ተስፋ ሟጠጡን ያሳያልና…. ይሄ ነገር መሞቻሽ ነው ብላችሁ ምከሯት፡፡ እምቢ ካለች ግን መከራው ይመክራታል፡፡

ምክር!

ባለስልጣኖቻችን ሆይ እናንተ ማረሚያ ቤት የምትሏቸው እስር ቤቶች መግደያ ቤት እየሆኑ ነው፡፡ ብልጥ ከሆናችሁ…. አብዲሳ እንዳለው ራሳችሁ ገብታችሁ ሳታዩት በፊት በእስር ለሚማቅቁ ወገኖቻችን መላ ፈልጉ!
ተስፋሁን ጫመዳ ነፍሱን ከደህናው ስፍራ ያሳርፍልን! ለቤተሰቦቹም መጸናናትን ይስጥልን!

http://www.abetokichaw.com/

ተስፋሁንን መግደል ለኢህአዴግ ተስፋ ይሆናታልን….!?



ተስፋሁንን መግደል ለኢህአዴግ ተስፋ ይሆናታልን….!?

bbbአብዲሳ የብዙ ጊዜ ወዳጄ ነበር፡፡ በየገጠሩ እየዞርን በርካታ ስራ አብረን ሰርተናል፡፡ የዋህነቱ እጅግ በጣም አስገራሚ ነበር፡፡ በየክልሉ ስንዞር አበሉን የሚጨርሰው “ቸገረኝ” ላለው ሁላ መበስጠት እንደነበር አብረነው የሰራ ሁላ እርሱን የምንለይበት ባህሪው ነው፡፡ ይሄ ልጅ በአንዱ ቀን ለስራ ልንሄድ የተቀጣጠርንበት ቦታ ሆነን ስንጠብቀው ስንጠብቀው ሳይመጣ ቀረ… ስልኩን ብንደውልልት አይሰራም፡፡ ካለንበት እየተንቆራጠጥን… ወደ ሶስት ሰዓት ድረስ ዘግይተን ጠበቅነው የውሃ ሸታ ሆነብን… ምን ሆነ ብለን እየተጨነቅን እንጀራ ነውና ጉዟችንን ቀጠልን…

አብረን ስንጓዝ ከነበርነው መካከል አብዲሳን በቅጡ የምናውቀው ሰዎች “ይሄኔ አንድ የታመ ሰው አጋጥሞት ሆስፒታል ሳላደርስ አልሄድም ብሎ ነው…” ….ወይ ደግሞ “…አንዱ ገንዘብ ተቸግሮ አጋጥሞት  ምንም ሳያስቀር ገንዘቡን ሰጥቶ ወደ እኛ መምጫ ራሱ ተቸግሮ ይሆናል …” ካልሆነ ግን “…ዘራፊዎች አግኝተው ጉድ አድርገውት ሊሆን ይችላል…. እያልን መገመታችንን ተያያዝነው…

ግምታችን ሁሉ ትክክል አልነበረም፡፡

አብዲሳ በስንተኛው ጊዜ በቴሌቪዥን መስኮት መታየቱን ሰማን… በየዋህነቱ የተቸገረ በመርዳቱ የምናውቀው አብዲ “አሸባሪ” ተብሎ በመንግስት ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ አብዲሳ “አሻባሪ” ከተባለማ እኛ ምን ልንባል ነው… ብለን ራሳችንን እንደ ነውጠኛ የምናየው እኛ በጣም ተደነቅን!

አብዲ ወደ አምስት ወራት በማዕከላዊ፣ ወደ አምስት አመት በቃሊቲ እንዲሁም ሁለት ሶስት አመት ነው መሰለኝ በዝዋይ ማሰሪያ ቤቶች ቆይቶ ነፃ ነህ ተብሎ እስኪሰናበት ድረስ በአስር ቤቱ ውስጥ ሲደርስበት በነበረው መከራ ብዙ ጉዳት ደርሶበታል፡፡ ታድያ ከእስር ቤት ሊወጣ አካባቢ አንድ ባለስልጣን ብጤ ሰውዬ ጎብኝተውት ነበር፡፡

እስር ቤቱ እንዴት ነበር… ሲሉ ጠየቁት፡፡ አብዲሳ ምን አላቸው መሰልዎ… እስር ቤቱ እንዴት እንደሆነ ራስዎት ገብተው ካላዩት በስተቀር እንዲህ ነው ብዬ  ብነግሮት አይገባዎትም ፡፡ አላቸው፡፡

ይሄው ሰሞኑን ወንድማችን ተስፋሁን ጫመዳ በእስር ቤት በደረሰበት ስቃይ የተነሳ ህይወቱ ማለፏን ሰማን፡፡ ተስፋሁን በ1999 ዓ.ም መንግስት ኬኒያ ድረስ አፍኖ ወሳጆቹን ልኮ ለኬኒያ ፖሊስ ሽልጉን ከፍሎ፤ (የኬኒያ ፖሊስ እንኳንስ ከፍለውት እንዲሁም ጤዛ ነው) ብቻ በትብብር ወደ አዲስ አበባ ተወስዶ ነበር… ከዛም በታሰረበት ሆኖ ሞተን ሰማን!

ለዚህ ጉዳይ የሚሰማ ቢኖር የኬኒያን መንግስት ራሱ ፍርድ ቤት ማቆም የሚገባ ይመስለኛል፡፡

ፍርድ ቤት ሳይቀርብ ራሱ፤ በነፍስ ማጥፋት ወንጀል እግዜሩም እኛም የምንጠይቀው ግን የገዛ መንግስታችን ነው፡፡ አዎ መንግስታችን እጁ ላይ የተለያዩ ሀገራት ብድር ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ሰዎች እምባ የተለያዩ ሰዎች ደምም አለበት፡፡

ተስፋሁን ለምን እንዲሞት ተፈረደበት… እውን ለሀገሪቱ ደህንነት ስጋት ሆኖ ነውን… የሚለውን በፍጹም!!! ለማለት፤ እነ አብዲሳን ያየነው እኛ ምስክሮች ነን፡፡ ምስኪኑ አብዲሳ ስምንት አመት ታስሮ በነፃ ከመፈታቱ በፊት “የሀገር ስጋት ሽብርተኛ!” ተብሎ ነበር የታሰረው፡፡  በእስር ቤት የደረሰበትን ስቃይ ሰው ሆኖ መፈጠርን የሚያስጠላ ነው፡፡ የነገረኝን በሙሉ ለማሳየት በፊልም እንጂ ጽሁፍ የሚገልፀው አይደለም፡፡

እሺ ኢንጂነር ተስፋሁን የኦነግ ወይም የሌላ ተቃዋሚ አባል ወይም ደጋፊ ወይም እንዳሻቸው ይሁኑ ባይ ነው እንበለው፡፡ ግን እርሱን በመግደል የሚቃወሙ ሰዎችን ተስፋ ማስቆረጥ አልያም  ቁጥራቸውን መቀነስ ይቻላል….

ኢህአዴግ በጫካ እያለች ታጋዮቿ እና ሰላዮቿ ደርግ በቁጥጥር ስር ሲያውላቸው ቀጥታ አብዮታዊ እርምጃ ይወስድባቸው ነበር፡፡ ውጤቱ ግን ምንድነው  የሆነው… ብለው የጠየቁ እንደሆ፤  ውጤቱ ብሶቱን እያጠነከረው ቁጭቱን እያባሰው እምቢ ባይነቱን እያበረታው ነው የሄደው…!

ዛሬ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ኢትዮጵያውያን በእስር ቤት ውስጥ ፍዳቸውን እያዩ ነው… የምር ለኢህአዴግ እናስባለን የምትሉ ሰዎች የእነ ተስፋሁን ግድያ የኢህአዴግ ተስፋ ሟጠጡን ያሳያልና…. ይሄ ነገር መሞቻሽ ነው ብላችሁ ምከሯት፡፡ እምቢ ካለች ግን መከራው ይመክራታል፡፡

ምክር!

ባለስልጣኖቻችን ሆይ እናንተ ማረሚያ ቤት የምትሏቸው እስር ቤቶች መግደያ ቤት እየሆኑ ነው፡፡ ብልጥ ከሆናችሁ…. አብዲሳ እንዳለው ራሳችሁ ገብታችሁ ሳታዩት በፊት በእስር ለሚማቅቁ ወገኖቻችን መላ ፈልጉ!
ተስፋሁን ጫመዳ ነፍሱን ከደህናው ስፍራ ያሳርፍልን! ለቤተሰቦቹም መጸናናትን ይስጥልን!

http://www.abetokichaw.com/