Saturday, September 12, 2015

መልካም አዲስ ዓመት – ድጋፍ ለአገር አድን ንቅናቄ

September 12, 2015
def-thumb“የኢትዮጵያ አገር አድን በዲሞክራሲ የጋራ ንቅናቄ” ምስረታ ዜና በአዲስ ዓመት መባቻ መሰማቱ ትልቅ የምሥራች ነው። ይህንን ንቅናቄ ለመመስረት ከፍተኛ ጥረት ያደረጉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ምስጋና ይገባቸዋል።
የኢትዮጵያ አገር አድን በዲሞክራሲ የጋራ ንቅናቄ መመስረት የህወሓት አገዛዝን ተጋግዞ ለመጣል ከማስቻሉም በላይ ድሉ የአንድ ወይም የጥቂት ድርጅቶች ድል ከመሆን ይልቅ የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ድል እንዲሆን ያስችላል። ከዚህም በተጨማሪ ከህወሓት አገዛዝ በኋላ የተባበረች ኢትዮጵያ እንደምትኖረን ማስተማመኛ ከሚሰጡን ነገሮች ዋነኛው ዛሬ የምናደርጋቸው ትብብሮች ናቸው። የአገር አድን ንቅናቄ ዛሬ የምናደርገውን ትብብር መዋቅራዊ ገጽታ የሚሰጠው እና ዘለቄታነት እንዲኖረው የሚያግዝ በመሆኑ ለአገራችን ለኢትዮጵያ እና ለሕዝቧ የሚሰጠው ጥቅም ዘርፈ ብዙ ነው።
የአንድን ድርጅት ጥንካሬ ከሚወስኑ ነገሮች ዋነኛው የአባላቱና ደጋፊዎቹ ጥንካሬ ነው። የአገር አድን ንቅናቄም ጥንካሬ ከሚወስኑት ነገሮች ዋነኛው አባላትና ደጋፊው ናቸው። የአገር አድን ንቅናቄ እንዲጎለብት የምንመኝ ሁሉ ለንቅናቄው መጠናከር የምናበረክተው አስተዋጽኦ አለ። ከሁሉ አስቀድሞ ኢትዮጵያ አገራችን ከግዛቷ ውስጥ የሚገኙ ማኅበረሰቦች ሁሉ አገር መሆኗን እና እያንዳንዱ ማኅበረሰብ ከሌላው ጋር እኩል መብት ያለው መሆኑን መቀበልና በተግባርም ማሳየት ይገባል። እያንዳንዱ ዜጋ እና እያንዳንዱ የኅብረተሰብ ክፍል ከሌሎች ወንድሞቹና እህቶቹ ጋር በጋራ አገራችን የማዳን እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆን ሁኔታዎችን ማመቻቸት ያስፈልጋል። በምናደርጋቸው ፓለቲካዊና ማኅበራዊ እንቅስቃሴዎች ሁሉ የዜጎችና የማኅበረሰቦች በእኩልነት መሳተፍ እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ መሆኑን ተረድተን መንቀሳቀስ ይኖርብናል። ለህወሓት “ከፋፍለህ ግዛ” ፓሊሲ መመቸት የለብንም። በዘር፣ በሃይማኖት፣ በጾታ፣ በእድሜም ሆነ በቋንቋ ሳንከፋፈል የጋራ ትኩረታችንን የጋራ ቤታችን የሆነችውን ኢትዮጵያን ማዳን ላይ እናድርግ።
በኢትዮጵያ፣ በዳር አገር እና በውጭ አገራት የሚገኙ የአርበኞች ግንቦት 7 አባላትና ደጋፊዎች ከሕይወት መስዋትነት ጀምሮ በጊዜዓቸው፣ በገንዘባቸውና በእውቀታቸው ንቅናቄዓቸውን ሲረዱ ቆይተዋል። በአሁኑ ሰዓት በበርካታ የዓለም ከተሞች እየተደረጉ ያሉት የገቢ ማሰባሰቢያ ዘመቻዎች የሚያመለክቱት የአርበኞች ግንቦት 7 አባላትና ደጋፊዎች ምን ያህል የነፃነት ትግሉ የጀርባ አጥንት መሆናቸው ነው።
አርበኞች ግንቦት 7 ይህ ድርጅታዊ ፍቅርና ተነሳሽነት ወደ አገር አድን ንቅናቄውም እንዲሸጋገር ይሻል።ከአሁን በኋላ የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት እና ደጋፊዎች የአገር አድን ንቅናቄውን የማጠናከር ኃላፊነት አለባቸው። በዚህም ምክንያት የአርበኞች ግንቦት 7 አባላትና ደጋፊዎች በሚያደርጓቸው የትግል እንቅስቃሴዎች ሁሉ የሌሎች ዲሞክራሲያዊ የኢትዮጵያ ኃይሎች ተሳትፎ እንዲኖርበት ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ሕዝብን የማስተባበር ሥራ በሁሉም ቦታዎችና በሁሉም እርከኖች መሠራት ይኖርበታል። ይህ የሁለገብ የትግል ስትራቴጂዓችን አንዱ አካል በመሆኑ አባላት ግንባር ቀደም ሚና እንዲጫወቱ አርበኞች ግንቦት 7፡ የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ያሳስባል።
አርበኞች ግንቦት 7 ለአባላቱና ደጋፊዎቹ እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ “እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰን፤ አዲሱ ዓመት የድል ዓመት እንዲሆንልን በጽናት እንታገል” ይላል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

Friday, September 11, 2015

የፌስቡክ ተቃዋሚዎች አብዮታዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው መሆኑ በአባይ ወልዱ የሚመራው የህወሓት አንጃ አሳወቀ።

September 11,2015


የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) በመቀሌ ከተማ ባደረገው ስብሰባ ላይ በጥንቃቄ ተመርጠው የተጠሩ ታማኝ ካድሬዎችና አባላት የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰሙ፡፡ የትግራይ ፌስቡክ ተጠቃሚዎች አብዮታዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው መሆኑ በአባይ ወልዱ የሚመራው የህወሓት አንጃ አሳወቀ። አንጃው ይህንን አብዮታዊ እርምጃ እንደሚወስድ ያሳወቀው “12ተኛ ጉባኤ እንዴት አለፈ …?” በሚል አጀንዳ በየመንግሥት መስርያ ቤቶች፣ ከመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች፣ የክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ካድሬዎችና ነዋሪዎች ውይይት በተካሄደበት ጊዜ ነው።

በመቀሌ ማዘጋጃ ቤት ማክሰኞ 3/13/2007 ዓም በአቶ ተስፋአለም ተወልደብርሃን (የመቀሌ ከንቲባ)፣ አቶ አሰፋ ተገኝ ምክትል ከንቲባ የተመራ ስብሰባ የተካሄደ ሲሆን “የህወሓት ጉባኤ ምን ይመስላል?” የሚል አጀንዳ ተሰጥቶት ነበር። የትግራዩ አንጃ በጉባኤው ወቅት በፌስቡክና በተባራሪ ወሬ የአቶ አባይ ወልዱ ስም ክፉኛ ጠፍቷል በሚል እሳቤ የስም እዳሴ እያካሄዱ ነው።

1) ህወሓት ተከፋፍሏል የሚል ወሬ ውሸት ነው።

2) ዳዊት ገብረእግዚአብሔር በትግራይ የሰጠው ቃለ መጠይቆች ውሸት ናቸው።

3) በፌስቡክ የሚሰራጩ መልዕክቶች ውሸት ናቸው፤ እንዳታምኑ።

4) የጉባኤው ተሳታፊዎች ሚስጢር እንዲጠብቁ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም በቀጥታ ስርጭት ሊባል በሚችል ደረጃ የስብሰባው መረጃ በፌስቡክ ተዘግቧል።

5) በአሁኑ ሰዓት ሁለት ዓይነት ጠላቶች አሉን። ፊት ለፊት ወጥተው የሚታገሉን እንደ ዓረና የመሰሉ እና በውስጣችን ሆነው የሚታገሉን ኪራይ ሰብሳቢ ሃይሎች (ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በፌስቡክ ደረጃ ህወሓት መስለው ጀርባችን የሚወጉን ሃይሎች) ናቸው።

6) አባይ ወልዱ ሙስናን የሚጠየፍ፣ ታግሎ የሚያታግለን ጀግናና ብቁ መሪ ነው።

7) በፌስቡክ ተጠቃሚዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን።

8) ጉባኤው ፍፁም ዲሞክራሲያዊና በድል የተጠናቀቀ ነበር ወዘተ የሚል ሃሳብ ወደ ተሳታፊዎች አቅርበዋል።

ተሰብሳቢዎቹ ታማኝ ካድሬዎችና አባላት በጥንቃቄ የተመረጡ ቢሆኑም ያቀረቡት ሃሳብና ተቃውሞ ግን ስብሰባው ላዘጋጀው አካል አስደንጋጭ ነበር።ከተሳታፊው የቀረቡት ጥያቄዎች፤

ሀ) አባይ ወልዱ በጉባኤተኛ በ20ኛ (የፌስቡክ ማህበረሰብ ከክፍል 20ኛ፤ ከዩኒት 1ኛ ብሎ የቀለደበት ነው) ደረጃ ተመርጦ እያለ በሊቀመንበርነት እንዴት ሊመረጥ ቻለ? እዚህ ላይ የጉባኤው ዲሞክራሲያዊነት የቱ ላይ ነው?

ለ) እነ አርከበ በድምፅ እንዲሳተፉ የተደረገበት፣ ለማዕከላዊ ኮሚቴ እንዳይወዳደሩ የተከለከሉበት አሰራር በየትኛው ደንብ ይገኛል?

ሐ) ዘመኑ ያመጣው የፌስቡክ ቴክኖሎጂ ህዝቡ እንዳይጠቀም እርምጃ እንወስዳለን ማለታችሁ ጊዜው የ21ኛ ክፍለ ዘመን መሆኑ ስላልገባችሁ ነው? የሃይል እርምጃው ቴክኖሎጂውን ምን ያህል ይቆጣጠረዋል ብላችሁ ታስባላችሁ?

መ) አቶ ዳዊትና ተቃዋሚ ድርጅቶች የሚነሱት ጉዳይ በመሬት ያለና በየዕለቱ የሚያጋጥመን ሃቅ ሆኖ ሳለ አትመኑት፤ ውሸት ነው፤ ማለታችሁ ችግሮቹን ለመፍታት አቅም እንዳጠራችሁ አያመላክትም ወይ? የሚሉትና ሌሎች ፈታኝ ጥያቄዎችና ሃሳቦች የቀረቡ ሲሆኑ የመቀሌ ከንቲባና ምክትሉ የሚመልሱት አጥተው አንገታቸው አቀርቅረው በሃፍረት ከስብሰባው ወጥተዋል።

የተለያዩ የቢሮ ሃላፊዎች የመሩት የመንግስት ሰራተኞች ስብሰባዎች እየተካሄዱ ያሉ ሲሆኑ ዘመቻው አቶ አባይ ወልዱ የደረሰባቸው የይውረድልንና የስም ማጥፋት ዘመቻና የጠፋው ስም እንደገና የማደስ ስራ ተጠምደው ይገኛሉ። የዚህ ዘመቻ ትኩረት ተደርጎ ያለው ፌስቡክና የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ናቸው። ሰብሳቢዎች በተለያዩ መድረኮች ፌስቡክ ወጣቱ ትውልድ በአሉታዊ ጎን እያበላሸው፣ የተቃውሞ መንፈስ እየበረዘውና እየበከለው በመሆኑ መንግስት እርምጃ ይወስዳል በማለት አዋጅ እያስነገሩ ይገኛሉ።

በክፍለ ከተሞች ከተካሄዱ ስብሰባዎች የሓወልቲ፣ ዓይደር፣ ሓድነትና ቀዳማይ ወያነ ተሰብሳቢዎች ከፍተኛ ውጥረት የተፈጠረ ሲሆን ባለመግባባት ሊበተን ችለዋል። ፌስቡክ አስመልክተው ከቀረቡት የአብዮታዊ እርምጃ ይወሰዳል ዛቻ ለትግራዩ አንጃ ደጋፊዎች የቀረበ ግምገማ “በቁጥር እኛ እንበዛለን፣ ለኢንቴርኔት አክሰስ እኛ እንቀርባለን፣ እነዚህን በጣት የሚቆጠሩ የፌስቡክ ተቃዋሚዎች መቃወምና ማሸነፍ ለምን አቃተን…?” የሚል ቁጭት አቅርበዋል።

እቺ ነገር መንግስቱ ሃይለማርያም “ትጥቅ አቀረብን፣ ስንቅ አቀረብን፣ አሁን የቀረን ልብ ማደል ነው። እንደ ወያነ ጠንክራችሁ አትዋጉም ወይ…!” ብሎ ያደረገው የተስፋ መቁረጥና የስርዓቱ ማብቅያ አመላካች ንግግር በእጅጉ ይመሳሰላል።
የህወሓት አንጃዎች ክፍፍል ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን በነዶ/ር ሰለሞን ዑንቋይ ለቀናት የፈጀ ሽምግልና ከመበተን እንደዳኑ ፀሓይ የሞቀ ሃቅ ለመካድ ቢሞክሩም ከህዝቡ የተሸፈነ ግን አልነበረም።

አሁን በመላ የትግራይ ወረዳዎች የአባይ ወልዱን ስም ለመገንባት ከፍተኛ ጥረት በመካሄድ ላይ ይገኛል። የአዲስ አበባው አንጃ ፊታውራሪ የሆኑት ደብረፅዮን በ12ኛ ጉባኤ ላይ በፌስቡክ የሚነሱ ሃሳቦች እንደ ትልቅ የሃሳብ ምንጭ ተቆጥረው በጉባኤው ቀርበው እንደተወያዩበትና ለጉባኤው እንደ ግብአት እንደተጠቀሙበት ለቪኦኤ መግለፃቸው ይታወሳል።

የአባይ ወልዱን ስም ለማጥፋት አገልግሎት ላይ ውለዋል የተባለው ፌስቡክና ተቃዋሚ ተጠቃሚዎች አብዮታዊ እርምጃ ይወሰድባቸዋል። የእርምጃው ዓይነት ምን ሊሆን እንደሚችል እስካሁን በውል አልታወቀም። ሆኖም የኢንቴርኔት ማእከላት ሊዘጉ ይችላሉ። ማነው ትግራይ ሰሜን ኮርያ ያላት? ያው ውድድራችን ከሰሜን ኮርያ መሆኑ ነው። ትግራይ ለምትገኙ ፌስቡክ ተጠቃሚዎች ኢትዮጵያውያን አብዮታዊ እርምጃ እንዳይወሰድባችሁ የመንፈስ ዝግጅት ብታደርጉ እንመክራለን።

ነፃነታችን በእጃችን ነው…!

Tuesday, September 8, 2015

OLF and TPDM expected to join Patriotic Ginbot 7

September 8, 2015

Update: Our earlier report regarding the armed groups merger expectation confirmed with slight change. Please listen the latest ESAT News.

Four Ethiopian armed groups merged and form United Movement (ESAT)
Four Ethiopian armed groups merged and form United Movement for the Salvation of Ethiopia through Democracy. Dr. Berhanu Nega became the leader of the United Movement. More…
——————————————————-
Eritrean Press reported Tigray Peoples Democratic Movement (TPDM) and Oromo Liberation Front (OLF) lead by Brigadier General Kemal Gelchu expected to join Patriotic Ginbot 7 Movement for Unity and Democracy.
Ever since the arrival of Prof. Berhanu Nega (Patriotic Ginbot 7 Chairman) and other Patriotic Ginbot 7 leaders in Eritrea, there has been a rumour that merger talks between the three major Ethiopian armed fronts are underway.
Also Patriotic Ginbot 7’s short social media update strengthen the above news:
#Ethiopia, Breaking News is on the way! Stay tuned. A major political shift into high gear to take action on the minority led TPLF.
While the united Ethiopian front against Ethiopia’s tyrannical regime Tigrayan People’s Liberation Front (TPLF) in progress, Asmara’s Ministry of Information statement accused TPLF’s war drums against Eritrea.
According to Agence France-Presse Eritrea’s Ministry of Information says:
War-like rhetoric from Ethiopia’s main party in the ruling coalition — the Tigrayan People’s Liberation Front (TPLF) — had increased.
“The TPLF’s sabre-rattling has been a common staple throughout winter. And this has been ratcheted up in the past few weeks,” said the information ministry statement, released Monday.
Asmara said its progress had sparked “frustration bordering on insanity in the camp of the TPLF and its key sponsors.”
Patriotic Ginbot 7 fighters

ሻዕቢያ ህወሃትን አስጠነቀቀ

September 8,2015
የጦርነት አታሞ እየተመታ ነው፤ “ሳንጃም ተስሎብኛል”
melesna isayas
ቀደም ሲል የአባትና ልጅ “አፈጣጠርና ግንኙነት” የነበራቸው ወዳጆች ሻዕቢያና ወያኔ ያልተጠናቀቀውን የባድመን ጦርነት ካካሄዱ በኋላ ለዳግም ግጥሚያ ዝግጅት እያደረጉ ነው። “የጦርነቱ ሁኔታ” ያሳሰበው ሻዕቢያ በማስታወቂያ መ/ቤቱ በኩል ለህወሃት ማጠንቀቂያ ሰጥቷል። ከጥቂት ሳምንታ በፊት ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ እንደዘገበው በዘገበው መሠረት መግለጫው ህወሃት ኤርትራን እንዲወጋ የአሜሪካንን ይሁንታ አግኝቷል ብሏል።
የፈረንጅ የቀን አቆጣጠር የሚከተለው ሻዕቢያ በማስታወቂያ መ/ቤት በኩል 4 September 2015 ያወጣው መረጃ እንደጠቆመው ህወሃት የተለመደውን የጦርነት አታሞ እየመታና ሳንጃ እየሳለ እንደሆነ ጠቁሟል። የህወሃት አገዛዝ “ሌሎች ክፍሎች ከኤርትራ ጋር እንዳይወግኑ ትንኮሳ እያደረገ” መሆኑን የጠቆመው መግለጫ ወያኔ በኤርትራ ጦርነት ማካሄድ እንዲችል ከአሜሪካ ይሁንታ ማግኘቱን በገሃድ እየተናገረ እንደሚገኝ ጠቅሷል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ከአራት ሳምንታት በፊት “ኢህአዴግ በኤርትራ አራት አቅጣጫዎች ጥቃት ሊሰነዝር አስቧል፤ አሜሪካ ሃሳቡ ቀርቦላታል ተብሏል” በሚል ርዕስ ባስነበበው ዜና ላይ እንዲህ ብሎ ነበር። “አሜሪካ ኢህአዴግ “አሸባሪ” ብሎ የሚፈርጃቸውን በሙሉ በሽብርተኛነት በመፈረጅ የመን የተጫወተችውን አይነት ሚና እንድትደግም ተጠይቃለች። … አሜሪካ የቀረበላትን ጥያቄዎች ስለመቀበሏ ያልጠቀሱት የመረጃው ባለቤቶች፣ ኤርትራ ውስጥ መተራመስ ሳይፈጠርና ክልሉና ቀጣናው ሳይናጋ ጥንቃቄ የተሞላበት ርምጃ ቢወሰድ አሜሪካ ተቃውሞ እንደማይኖራት ማረጋገጫ መስጠቷን አመልክተዋል። ይህ አቋም ኦባማ አዲስ አበባ ከመሄዳቸው በፊት በተለያዩ ደረጃዎች ተመክሮበት ከስምምነት የተደረሰበት ስለመሆኑም ገልጸዋል።”
ሻዕቢያ ይህንን ቢልም በአገር ውስጥ የሚታየው ሁኔታ ግን ጦሩን ከአንድ ስፍራ የማንቀሳቀስ ሂደት እየተደረገ እንደሆነ ይታያል። ለዚህም የሚሰጠው ምላሽ ቀለል ያለ ብወዛ እንደሆነ ቢነገርም ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለየት ባለ መልኩ በአማራው ክልል የሠራዊቱ ቁጥር እየጨረ መምጣቱ ከሥፍራው የሚገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከአንድ ዓመት በፊት የአሰብ ወደብ እንዲታደስና በአዲስ መልክ እንዲደራጅ መደረጉ ከተለያዩ ምንጮች ሲነገር የቆየ መሆኑ ይታወሳል። ከዚህ ጋር በተያያዘ በሰሞኑ የህወሃት “ጨዋታ” የአዲስ አበባው አንጃ ይመራሉ የተባለላቸው አርከበ ዕቁባይ ከጥቂት ወራት በፊት የኤርትራንና አሰብ ጉዳይ በተመለከተ “ኤርትራም ሁኔታ መቀየሩ አይቀርም፤ አሁን ያለው ሁኔታ ለዘለዓለም ይኖራል ብለን አንገምትም። በእኔ ግምት በሚቀጥሉት አስር ዓመታት ውስጥ ለውጥ ይመጣል ባይ ነኝ። የኤርትራን ወደብ እንጠቀማለን” ማለታቸው የሚጠቅሱ አስተያየት ሰጪዎች በወያኔና በሻዕቢያ መካከል የሚወራው የጦርነት ዝግጅትና አታሞ ግራ የሚያጋባ እንደሆነ ይናገራሉ።
ከጎልጉል የተወሰደ

በኤርትራ የሚገኙ አራት በትጥቅ ትግል የተሰማሩ ንቅናቄዎች የኢትዮጵያ አገር አድን በዴሞክራሲ የጋራ ንቅናቄ በሚል ስያሜ በይፋ መሰረቱ

 September 8,2015
editorial of allianceበኤርትራ የሚገኙ አራት በትጥቅ ትግል የተሰማሩ ንቅናቄዎች የኢትዮጵያ አገር አድን በዴሞክራሲ የጋራ ንቅናቄ በሚል ስያሜ  በይፋ መሰረቱ::የጋራ ንቅናቄውን የመሰረቱት ድርጅቶቹ  የጋራ ንቅናቄ ምስረታ በማስምልከት  ድርጅታዊ መግለጫ አውጥተዋል 
የኢትዮጵያ ህዝብ የኣገሩን ሉዓላዊነትና ኣንድነት ኣስከብሮ የኖረ ብቻ ሳይሆን ኣፍሪካውያን ወንድሞቹና እህቶቹ ከቀኝ ኣገዛዝ ነፃ እንዲወጡ የራሱ ኣስተዋፅኦ ያደረገ ጀግና ህዝብ ነው። ሆኖም ይህ ጀግና ህዝብ ከኣብራኩ በወጡ ገዢዎች ነፃነቱ ተገፎ፤ መብቶቹ ተረግጠው የመከራ ኑሮ እየገፋ ኣያሌ ዘመናት ኖሯል። ይህ የመከራና የሰቆቃ ኑሮ ዛሬም ኣላበቃም፤ እንዲያውም “ከጭቆና ነፃ ኣወጣንህ” እያሉ የሚሳለቁበት ግፈኛ ገዢዎች የጫኑበት የስቃይ ቀንበር ተሸክሞ የውርደት ኑሮ እየኖረ ነው። የጋራ ንቅናቄ ምስረታ በማስምልከት የወጣን ድርጅታዊ መግለጫ  ለማንበብ ይህን ይጫኑ Read more  የኢትዮጵያ አገር አድን በዴሞክራሲ የጋራ ንቅናቄ 2008

Sunday, September 6, 2015

Millions at risk as severe drought hits Ethiopia

September 6,2015
Addis Ababa - Around 4.5 million Ethiopians could be in need of food aid because of a drought in the country, the UN has said.
Hardest-hit areas are Ethiopia's eastern Afar and southern Somali regions, while pastures and water resources are also unusually low in central and eastern Oromo region, and northern Tigray and Amhara districts.
Reacting to the UN's claims that the number in need had increased by more than 55% this year, Alemayew Berhanu, spokesperson for Ministry of Agriculture, told Al Jazeera that Ethiopia had "enough surplus food at emergency depots and we're distributing it".
"When we were informed about the problem, the federal government and the regional state authorities started an outreach programme for the affected people," he said.
In August, the Ethiopian government said that it had allocated $35m to deal with the crisis that has been blamed on El Niño, a warm ocean current that develops between Indonesia and Peru. The UN says it needs $230m by the end of the year to attend to the crisis.
"The absence of rains means that the crops don’t grow, the grass doesn’t grow and people can’t feed their animals," David Del Conte, UNOCHA'S chief in Ethiopia, said.
One farmer in the town of Zway told Al Jazeera that he was selling personal belongings to stay alive.
"There is nothing we can do. We don't have enough crops to provide for our families. We are having to sell our cattle to buy food but the cattle are sick because they don't have enough to eat," Balcha, who has a family of nine, and grows corn and wheat, said.
El Niño
The onset of El Niño means the spatial distribution of rainfall from June to September has being very low. According to the UN children's agency (Unicef), the El Niño weather pattern in 2015 is being seen as the strongest of the last 20 years.
Experts say it could be a major problem for the country's economy, as agriculture generates about half of the country's income.
Climate shocks are common in Ethiopia and often lead to poor or failed harvests which result in high levels of acute food insecurity.
Approximately 44% of children under 5 years of age in Ethiopia are severely chronically malnourished, or stunted, and nearly 28% are underweight, according to the CIA World Factbook.
Unicef says that about 264 515 children will require treatment for acute severe malnutrition in 2015 while 111 076 children were treated for severe acute malnutrition between January and May 2015.
Aljazeera

Saturday, September 5, 2015

አርበኞች ግንቦት 7 ለ1 ሰዓት የፈጀ ውጊያ ማድረጉን አስታወቀ * ገድያለሁ፣ መሳሪያም ማርኬያለሁ ብሏል

September 5,2015
የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ የውስጥ አርበኞች በህወሓት አገዛዝ መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት በመሰንዘር ለአንድ ሰዓት የዘለቀ ከባድ ውጊያ አድርገው ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን አስታወቀ::
Arebegnoch Ginbot 7

የአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞች ህወሓት "ክልል አንድ" እያለ በሚጠራው በጎንደር-ወልቃይት ደጃች ሜዳ ወረዳ አቤራ ቀበሌ ስልኪ ዳግባ በተባለው ቦታ ነሃሴ 23 2007 ዓ.ም በህወሓት መከላከያ ኃይል ላይ ድንገተኛ የተኩስ ውርጅብኝ በመክፈት ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ወታደሮችን ገድለውና አቁስለው ድል ተቀዳጅተዋል፡፡

በአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞችና በህወሓት የመከላከያ ሰራዊት መካከል የተካሄደው ድንገተኛ የሆነ ከባድ ፍልሚያ እኩለ ቀን ላይ ከ6፡30 ጀምሮ እስከ 7፡30 ለአንድ ሰዓት የዘለቀ ሲሆን ምሳ በመመገብ ላይ እያለ ባልገመተው ሁኔታና ባለሰበው አሳቻ ሰዓት ድንገተኛ ተኩስ ተከፍቶበት የእሳት ዝናብ በላዩ ላይ የወረደበት የህወሓት ሰራዊት አብዛኛው ተበታትኖ ከአካባቢው የሸሸ ሲሆን የአፀፋ ተኩስ ከፍቶ ለአንድ ሰዓት ለመከላከል የሞከረው ደግሞ ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል፡፡

የውስጥ አርበኛው ሽምቅ ተዋጊ ኃይል መትረየሶችን ጨምሮ በርካታ ክላሽን ኮቮች ከነመሰል ጥይቶቻቸው ለመማረክ ችሏል፡፡
የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ከሰኔ 25 2007 ዓ.ም እስከ ሀምሌ ወር መጀመሪያ በወልቃይት ቃፍታ መሲን፣ ኮርጃሙስ፤ ማይ ሰገን፣ ንኳል ሳግላ፣ በዋልና ማይ እምቧ ላይ በህወሓት መከላከያ ሰራዊት ላይ ተከታታይ ጥቃቶችን በመክፈት በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ የሆነ እልቂትና ኪሳራ በማድረስ ተደጋጋሚ ድሎችን መጎናፀፉ አይዘነጋም፡፡

Thursday, September 3, 2015

ረሀብን ለማጥፋት ህወሓትን ማስወገድ

September 3, 2015
def-thumbረሀብ በአገራችን ላይ እያንዣንበበ ነው። በአፋርና በሱማሌ ከከብቶች አልፎ ሕፃናት እየሞቱ ነው። የረሀቡ አደጋ ወደ ኦሮሚያና ሌሎች የደቡብ ገጠሮች እየተዛመተ ነው፤ ሰሜን ኢትዮጵያም ከአደጋ ውጭ አይደለም።
“ከአስር ዓመታት በላይ በተከታታይ በየዓመቱ ከአስር በመቶ በላይ የኢኮኖሚ እድገት አሳይተናል” የሚለው ዓይን ያወጣ ውሸት፤ “ድህነትን ተረት እናደርጋለን” የሚለው ጉረኛ መፈክር፤ “መካከለኛ ገቢ ያላቸው አገሮች ተርታ እንደርሳለን” የሚለው ባዶ ተስፋ፤ የወያኔዎችና ጀሌዎቻቸው በፎቅና ቪላዎች መንበሽበሽ፤ የድግሶችና የስብሰባዎች መብዛት ለሕዝባችን ቁርስ፣ ምሳና እራት አልሆኑም።
አገዛዙ ጉራውና ባዶ ተስፋ መስጠቱ እንዳለ ሆኖ የረሀቡን ምክንያት በተፈጥሮ ላይ ማላከኩን ተያይዞታል። ለመሆኑ ተፈጥሮ ብቻውን እየተደጋገመ ለሚመጣ ችጋርና ቸነፈር በቂ ምክንያት ሆኖ ያውቃልን? አስከፊ የረሀብ ዜናዎች የሚሰማባቸው አገሮች በሙሉ ነፃነት የታፈነባቸው አገሮች መሆናቸው የአጋጣሚ ጉዳይ ነውን? ለምንድነው አንድ ዓይነት ችግር እየተደጋገመብን መላ መፈለግ ያቃተን? መልሱ አጭርና ቀጥተኛ ነው። “ችግር የመሳካት እናት” የምትሆነው በነፃነት ማሰብ የሚችል ጭንቅላት ሲኖር ነው። በባርነት ጨለማ ውስጥ ያለ ጭንቅላት ለችግሮች መፍትሄ የማፍለቅ አቅም የለውም። እንዲያውም እንዲህ ዓይነቱ ድኩም ጭንቅላት ችግሮችን ማሸነፍ ሳይሆን ተሸናፊነትን ተቀብሎ ከችግሮች ጋር ተስማምቶና ተወዳጅቶ መኖርን ይመርጣል። ነፃነት ያለው ሕዝብ ረሀብን እንደሚያሸነፍ ተደጋግሞ የታየ ጉዳይ ነው። ለዚህም ነው ረሀብን የተፈጥሮ ሚዛን መዛባት ውጤት ብቻ አድርጎ ማቅረብ እውነትን መሸፈጥ የሚሆነው። ረሀብ የብልሹ አስተዳደር ውጤት ነው።
አገራችንን የረሀብ ቀጠና ካደረጉ የ24 ዓመታት የህወሓት “ድሃን ዘርፈህ ብላ” የኢኮኖሚ ፓሊሲ ውጤቶች መካከል አንዳንዱን ለአብነት ያህል መዘርዘር ይቻላል።
1. ገበሬና መሬት ተለያይተዋል። ለም መሬቶች በኢንቨስትመንት ስም በዘመኑ የህወሓት ጉልተኞች በመያዛቸውና እነሱ ደግሞ በተራቸው ለባዕዳን እየሸጡ በመሆኑ ባለሀገሩ ጭሰኝነት እንኳን አጥቶ ለቀን ሠራተኝነትና ልመና ተዳርጓል። አዳዲሶቹ ባለሃብቶች ለፈጣን ኪስ መሙላት እንጂ ለዘለቄታ የአፈር ልማት ፍላጎቱም እውቀቱም የላቸውም። በዚህም ምክንያት ገበሬው ትንሽ የዝናብ ዝንፈት እንኳን መቋቋም እስከማይችልበት ደረጃ ተዳክሟል።
2. በዘር ላይ በተመሰረተ ክልላዊ ድንበር ሳቢያ ኢትዮጵያዊያን ገበሬዎች በአገራቸው ውስጥ ተዘዋውረው መሥራት አልቻሉም። ከሰሜን ወደ ደቡብ ከተሰደደ የአገራችን አርሶ አደር ይልቅ ለቻይና ገበሬ መሬት ማግኘት ይቀለዋል። እንዲያውም ኢትዮጵያዊው ድሀ ገበሬ በዱላ ሲባረር፤ ከውጭ አገር የመጣው ቱጃር ገበሬ ብድርና ማበረታቻዎች ይሰጠዋል።
3. ደኖቻችን ተጨፍጭፈው፣ ለም መሬታችን ተሸርሽሮ በማለቁ የግብርናችን ምርታማነት በእጅጉ ቀንሷል። በዘመነ ወያኔ የደን ጭፍጨፋና የመሬት መሸርሸር በአስደንጋጭ ሁኔታ ጨምሯል። አገሪቷ በፍጥነት ወደ ምድረበዳነት እየተቀየረች ነው።
4. ፋይዳ ያለው የስነ ሕዝብ ፖሊሲ ባለመኖሩ የሕዝብ ብዛት አሻቅቧል። እንደ ኢኮኖሚው ሁሉ ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ ብዛት ሊቆጣጠር የሚሞክረው ቢሮ ውስጥ ቁጭ ተብሎ በሚደረግ የቁጥር ጨዋታ ነው። የስታተስቲክሱ ባለሥልጣን ቁጥራችንን በትክክል ሊነግረን ባይፈልግም እንኳን ረሀብ መብዛታችንን እየነገረን ነው።
5. የህወሓት ባለሥልጣኖችና በየክልሉ ያደራጇቸው ምስለኔዎች ራሳቸውን ባለሚሊዮኖች አድርገዋል። እነዚህ በአንድ ጀምበር የበቀሉ ቱጃሮች ከገንዘብ በተጨማሪም የጄኔራልነት፣ የሚኒስቴርነት፣ የክልል ገዢነት፣ እጅግ ቢያንስ የቢሮ ኃላፊነት ሥልጣንን ኪሳቸው ውሰጥ ከተዋል፤ ልባቸው የተመኘውን ዲግሪ ሸምተዋል። የመንግሥት ሥልጣንና ሃብት ይኸን ያህል የተቆራኙበት ሥርዓት በኢትዮጵያ ኖሮ አያውቅም። የጥቂቶች ያለአገባብና ያለቅጥ መክበር በአንፃሩ ደግሞ የብሃኑን ሕዝብ መደህየት ድህነትን መዋቅራዊ አድርጎታል።
6. በአቋራጭና በፍጥነት ለመክበር አስተማማኙ መንገድ የገዛ ራስ ጥረትና ታታሪነት ሳይሆን ቅጥፈት፣ አጭበርባሪነትና ሎሌነት መሆኑን የወያኔ ካድሬዎች በተግባር እያሳዩ ጥሮ ማደርን “ኋላ−ቀር አሠራር” አድርገውታል። በህወሓት የኢኮኖሚ ፓሊሲ የተበረታቱት አድርባይነት፣ ስንፍናና እና ልመና ችግርን የመጋፈጥ አቅማችንን ሰልበውታል።
እነዚህና የመሳሰሉት ጭብጦችን በማንሳት የረሀቡ መሠረታዊ ምክንያት የህወሓት አገዛዝ እንጂ ተፈጥሮ አለመሆኑን አስረግጠን እንናገራለን። ሕዝባችን በነፃነት ማሰብ፣ መመራመር፣ መፈተሽ ቢችል ኖሮ ረሀብን ማጥፊያ ብልሃት ማግኘት ባላቃተውም ነበር። ወደፊትም ቢሆን ተፈጥሮ እኛ እንደፈለግናት አትሆንም፤ መተማመኛችን የሰው ልጅ ወሰን የለሽ የፈጠራ ችሎታና ችግሮችን የመፍታት አቅም ነው። ለዚህ ደግሞ ችግሮችን በልጦ መገኘት ያስፈልጋል። ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከችግሮች በታች ሆኖ መፍትሄ ከአገዛዙ የሚጠብቅ ደካማ እንዲሆን አድርጎታል። በዚህም ምክንያት ነው የችግሮቻችን ቁንጮ ራሱ ወያኔ ነው የምንለው።
ህወሓትን ከመንግሥት ሥልጣን ሳናስወግድ ድህነትንና ረሀብ እናስወግዳለን ማለት ዘበት ነው:: ድህነት የህወሃት ዋነኛ የገቢ ምንጭ በመሆኑ ህወሓት ሥልጣን ላይ እስካለ ድረስ በወሬ ካልሆነ በስተቀር ድህነት በተግባር ሊቀጭጭ አይችልም። ችጋርና ህወሓት እጅና ጓንት ናቸው። ረሀብ የህወሓት ባለውለታ ነው። ረሀብ የህወሓት የቁርጥ ቀን አጋሩ ነው። ህወሓት በረሃ እያለ በአሸዋ የተሞሉ ጆንያዎችን እህል አስመስሎ በመሸጥ ለእርዳታ በመጣ ገንዘብ ራሱን አደራጅቷል። ስልጣን ከያዘም በኋላ “ረሀብን እየተዋጋሁ ነው” በማለት የምዕራባዊያንን ድጋፍ ለማግኘት ጠቅሞታል። ረሀብና ችጋር የወያኔ “ጪስ አልባ” እንዱስትሪዎች ናቸው። ሕዝባችን ተራበ ማለት የወያኔ ኩባንያዎች ሥራ አገኙ ማለት ነው። ህወሓት ረሀብን ለመቀነስ ቅንጣት ታህል ፍላጎት ቢኖረው ኖሮ በዚህ ወር ውስጥ በተደረጉ ስብሰባዎች በወጣው ወጪ ብቻ በአገራችን ላይ ያንዣበበውን ረሀብ በቁጥጥር ማዋል በተቻለ ነበር።
አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ለወገኖቻቸን መራብ ተጠያቂው የህወሓት ዘረኛ አገዛዝ ነው ይላል። ረሀብን ከኢትዮጵያ ምድር ለዘለቄታው ለማስወገድ የህወሓት አገዛዝን አስወግደን በምትኩ ለሕዝብ ደህንነት የቆመ፣ በሕዝብ የተመረጠ እና ከሕዝብ አብራክ የወጣ መንግሥት እንዲኖረን እንታገል ይላል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Tuesday, September 1, 2015

በጀኔራል ሳሞራ የኑስ እየተመራ በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው ስብሰባ ያለመፍትሄ ተበተነ

September 1,2015
samora yunus
በጀኔራል ሳሞራ የኑስ እየተመራ በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው የመከላከያ  ከፍተኛ አዛዦች ግምገማዊ ስብሰባ ያለመፍትሄ መበተኑን ለማወቅ ተችሏል።በመረጃው መሰረት- በአዲስ አበባ ከተማ በጀኔራል ሳሞራ የኑስ የተመራው የገዥው መንግስት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አዛዦች ከነሃሴ 12 ቀን 2007 ዓ/ም ጀምሮ ሲካሄድ እንደቆየ የገለፀው መረጃው፤ የስብሰባው አጀንዳም መንግስት አዲስ የመከላከያ ሰራዊት አሰልጥኖ ይለቃል ወደ እናንተ ሲደርስ ግን በርካታው ሰራዊት ይጠፋል ምክንያቱ ምንድንነው? ስራችሁ ምንድንነው? የሚሉና ሌሎችም በመድረክ መሪው በሳሞራ የኑስ የቀረቡ ሲሆን በርካታዎቹ በተቃውሞ ድምፅ ስለተቃወሙት በመካከላቸው ልዩነት ተፈጥሮ ስብሰባው ያለ ፍሬ ነገር እንደተበተነ ለማወቅ ተችሏል።

መረጃው ጨምሮም- ግምገማው በከፍተኛ አዛዦች ዘንድ መረዳዳት ያልነበረው ስብሰባ እስከ ታች እዞች የወረደ ሲሆን በተለይ በሰሜን እዝ ከሚገኙ ሬጂመንቶች በሚጠናቀቀው አመት ብቻ በረከት ያለ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች በመጥፋታቸው ዋና መነጋገሪያ አጀንዳ በመሆኑ አንዳንድ አዛዦች ከስራቸው ታግደው በመቐለ ስታፍ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።

Thursday, August 27, 2015

መልዕክት በድሆች ድህነት ለመክበር መሯሯጥ ላይ ላሉ የዲያስፓራ ማኅበረሰብ አባላት !


August 27, 2015
def-thumbየግል ኑሮን ለማደላደል ሲባል የወያኔ አባል መሆን “ወይን ለመኖር” የሚል ስያሜ ከተሰጠው ዓመታት ተቆጥሯል። “ወይን ለመኖር” ዜጎች ነፃነታቸውን ለጥቅም አሳልፈው የሚሸጡበት፤ የሰው ልጅ ክብር የሚዋረድበት ገበያ ነው። በወይን ለመኖር “የገበያ ህግ” መሠረት እያንዳንዱ ዜጋ ሊያገኘው መብቱ የሆነውን አገልግሎት እንዲያገኝ የህወሓት፣ የብአዴን፣ የኦህዴግ፣ የደህዴግ፣ የአብዴፓ፣ የቤጉህዴፓ፣ የጋህአዴን፣ የሀብሊ ወይም የኢሶዴፓ አባል መሆን፤ አልያም መደገፍ ግዴታ ነው። እነዚህ ሁሉ ድርጅቶች የህወሓት ተቀጽላ ወያኔዎች ናቸው። የእነዚህ ድርጅቶች አባል ወይም ደጋፊ ያልሆነ እንኳስ የመንግሥት አገልግሎት ሊያገኝ ጥሮ ግሮ ያፈራውንም ይነጠቃል።
በዚህም ምክንያት፣ በገጠር ያለው አርሶ አደር ቁራጭ የእርሻ መሬት፣ የግብርና ባለሙያዎች የምክር እገዛ፣ የማዳበሪያና ዘር ግዢ፣ ብድር ወይም እርዳታ ለማግኘት በአካባቢው ባለ የወያኔ ድርጅት አባልነት መመዝገብ፤ አንድ ለአምስት መደራጀት እና የወያኔን የስልጣን እድሜ የሚያራዝሙ ነገሮችን መሥራት ይጠበቅበታል። በከተሞች ውስጥም ሥራ ለመቀጠር፣ ለደረጃ እድገት፣ የመኖሪያ ቤት (ኮንዶሚንየም) ለመግዛት ሲባል መወየን አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ ሆኗል:: በንግዱም ዘርፍ የንግድ ፈቃድ፣ የሥራ ቦታ እና የባንክ ብድር ለማግኝት፣ የመንግሥት ጨረታዎችን ለማሸነፍ፣ ከጉምሩክ እቃ ለማስለቀቅ፣ የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት መወየን ግዴታ ነው።
“ወይን ለመኖር” የኢትዮጵያን ሕዝብ ያዋረደ፤ ለትውልድ የሚተርፍ የማኅበራዊ ስነልቦና ኪሳራ ያደረሰ እና ደካማውን ወያኔን ጠንካራ በማስመሰል በሕዝብ የትግል መንፈስ ውስጥ ፍርሃትን የረጨ መሆኑ ግንዛቤ እየዳበረ በመጣ መጠን እየቀነሰ የመጣ ክስተት ነው። በአሁኑ ሰዓት ከቀድሞው እጅግ በተሻለ ኢትዮጵያ ውስጥ የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን ራሳችንን ከህወሓት ባርነት እያላቀቅን ምሬታችንን በግልጽ መናገር የጀመርንበት ወቅት ነው፤ ከዚያም አልፎ የህቡዕ ተግባራዊ የትግል እንቅስቃዎችን ማድረግ ደረጃ ላይ ደርሰናል።
አገር ውስጥ እየተዋረደ የመጣው “ወይን ለመኖር” በአገዛዙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካይነት በውጭ አገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን (ዲያስፓራ) መካከል ነፃነታቸውን በጥቅም የሚለውጡ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን ፍለጋ ተሠማርቷል። አገዛዙ ተስፋ ያደረገው ያህል ባይሆንም ጥረቱ የተወሰነ ውጤት እያስገኘለት ነው። በጥቅማ ጥቅም እየደለለ ካመጣቸው ውስጥ በስርዓቱ ብልሹነት ያዘኑና የተሰማቸውን በግልጽ የተናገሩ መኖራቸው የሚያስደስትና የሚያበረታታ ቢሆንም ከመንደር ካድሬዎች ባነሰ ተለማማጮችና አጎብዳጆች በማየታችን ተሸማቀናል። ኢትዮጵያ ውስጥ ካለነው አብዛኛው ሕዝብ አንፃር ሲታይ በተሻለ የኑሮ ደረጃ ላይ ከሚገኙት ዲያስፓራዎች መካከልም ነፃነታቸውን በጥቅም ለመለወጥ የሚፈቅዱ መገኘታቸው አሳዛኝ ነው። እነዚህ ክብራቸውን በጥቅም የለወጡ ዲያስፓራዎች ዓለም ባንክንና የዓለም የገንዘብ ድርጅትን (IMF) ተክተው ህወሓት ስላስገኘው ፈጣን እድገት በአገዛዙ ራድዮ እና ቴሌቪዥን ሲነግሩን መስማት ያሳፍራል። የህወሓት አገዛዝ “ፍትህን፣ መልካም አስተዳርንና ዲሞክራሲን አስፍኗል፤ ይህንንም መጥተን በዓይኖቻችን ተመልክተናል” እያሉ የግፉን ገፈት እየቀመስን ላለነው ሲነግሩን መስማት ያማል።
እነዚህ ወገኖቻችን ህወሓትን በማሞካሸት የሚያገኙት መሬት ብዙ ድሆች የተፈናቀለቡት፤ ለእነሱ በብላሽ የተሰጠው ብድር በረሃብ ለሚጠቃ ወገን የተላከ እርዳታ መሆኑ ማሳሰብ ይገባል። ከህወሓትና አጫፋሪዎቹ ጋር ተስማምተው ባገኙት ገንዘብ የሚቆርሱት እያንዳንዱ እንጀራ የብዙ ወገኖቻችን ደምና እንባ የፈሰሰበት መሆኑ ማስገንዘብ ያሻል። ከህወሓት ጋር በማበር በወገኖቻችን ድህነትና ችጋር እየከበሩ ያሉ የዲያስፓራ ማኅበረሰብ አባላት ከዚህ እኩይ ሥራቸው እንዲታቀቡ ማስጠንቀቅ ይገባል። እኚህ ወገኖች የራሳቸው ክብር ማጉዳፋቸውን ብቻ ሳይሆን የልጅ ልጆቻቸውም የሚያፍሩባቸው መሆኑን ማስታወስ ይገባል። ከዚህም አልፎ የዛሬ ተግባራቸው ነገ በህግ የሚያስጠይቃቸው መሆኑን ሊያውቁ ይገባል።
አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ለግል ጥቅማቸው ሲሉ የአገዛዙን እድሜ በማራዘም ላይ የተሰማሩ፤ በድሆች ድህነት ለመክበር በመሯሯጥ ላይ ያሉ፤ ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ለአገዛዙ ጥብቅና የቆሙ የዲያስፓራ አባላት ከዚህ ተግባራቸው እንዲታቀቡ ያሳስባል።
አርበኞች ግንቦት 7 “ከህወሓት ውድቀት በኋላ ያለው ጊዜ ለእናንተም ከዛሬው የተሻለ ይሆናል። ዛሬ ከህወሓት ጋር ያላችሁን ሽርክና አቋርጡ። ለነፃነት የሚደረገውን ትግል እርዱ፤ መርዳት ባትችሉ እንቅፋት አትሁኑ፤ አለበለዚያ ግን ከተጠያቂነት የማታመልጡ መሆኑን እወቁ” ይላል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!! !

Wednesday, August 26, 2015

በዜጎች ላይ የሚፈፀመዉ ሰቆቃ አሁንም እየቀጠለ ነው!!

August 26,2015
amharic hateta
በሺዎች የሚቆጠሩ በርካታ ሰዎች በየክልሉ በተቋቋሙ እስር ቤቶች ዉስጥ ክስ ሳይመሰረትባቸዉ እንደሚታሰሩና፤ ግርፋት ሰቆቃና ድብደባ እንደሚደርስባቸዉ አልፎ ተርፎም እንደሚገደሉ ከኢትዮጵያ ህዝብ የተሰወረ አይደለም።
በኢትዮጵያ የህግ አስፈፃሚ አካላት የሆኑት ፖሊሰ፤ ፍርድ ቤቶችና ወህኒ ቤቶች ኢህአዴግ ቁጥጥር ስር ሙሉ በሙሉ ከመዉደቃቸዉ ሌላ የአገሪቱ የተወካዮች ምክር ቤት እንኳ ሊያዝዛቸዉ እንደማይችል በተለያየ ወቅት ተመስክሯል።
የፖሊስ ጣቢያዎች፤ የአስተዳደር ጽ/ቤቶች፤ወታደራዊ ካምፖች፡ ህጋዊ እስር ቤቶች፡ ሚስጢራዊ ስዉር እስር ቤቶች፡ በሀገረ ማርያም፤ ሁርሶ፤ ዴዴሳ፤ አጋርፋ፤ ዝዋይ፤ ጦላይ፤ቃሊቲ፤ማእከላዊ፤ በየክልል ወህኒ ቤቶችና በተለይ በአዲስ አበባ ዘመናዊ ቪላዎች በመከራየት በእስር ቤትነት ከመጠቀሙም በላይ በእስረኞች ላይ ሰቆቃ፤ ግርፋትና ድብደባ መፈፀሚያ በማድረግ እንደሚገለገልባቸዉ ይታወቃል።
የአለም አቀፍ የሰብኣዊ መብት ድንጋጌም ሆነ ህወሀት/ኢህአዴግ ያፀደቀዉ የአገሪቱ ህገ መንግሰት በማንም ሰዉ ላይ ሰቆቃ፡ ግርፋትና ድብደባ እንዲሁም ጭካኔ የተመላበት ኢ-ሰብኣዊ ድርጊትም ሆነ ስብዕናን የሚያዋርድ  ተግባር ሊፈፅምበት እንደማይገባ ይጠቅሳል። ይሁን እንጂ ይህ በእስራት ወቅትና ከእስራት ዉጭ በመንግስት የፀጥታ ሃይሎች፤ የደህንነት፤ የፖሊስ፤ የድርጅቱ ካድሬዎችና ወታደሮች አማካይነት በመላዉ የአገሪቱ ክልሎች በዜጎች ላይ የሚፈፀም የየቀኑ ተግባር ነዉ። ይህን በመፈፀም ማእከላዊ የምርመራ ድርጅት በመባል የሚታወቀዉ እስር ቤትና የደህንነት ተቋም የናዚ ጀርመን ይጠቀምባቸዉ ከነበሩት የማጎሪያ ካምፖች ያልተናነሰ እንደሆነ ይነገራል።
ዜጎች በኤሌክትሪክ ገመድና በሌሎችም ነገሮች በመጠቀም እጆቻቸዉ በሰንሰለትና በካቴና ታስረዉ ግድግዳ ላይ በተመቱ ምስማርና ችካሎች እንዳይንቀሳቀሱ ተወጥረዉ፤  የዉስጥ እግራቸዉንና መላ አካላቸዉን በጠቅላላ አዕምሯቸዉን እስኪስቱ ድረስ መደብደባቸውና የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት የፀጥታ ሃይሎች ሱዳን፤ የመን፤ ኬንያ፤ ሶማሊያና ጅቡቲ ድረስ ድንበር ዘልቀዉ በመግባት የሚፈልጓቸዉን ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች አፍነዉ መዉሰዳቸዉና ሊያመጧቸዉ ያልተሳካላቸዉን እንደሚገድሉ የኢትዮጵያ ህዝብ በሚገባ ያዉቀዋል።
የመንግስት የፀጥታ አስከባሪዎች ሌሎች ታጣቂዎች በቀን በአደባባይ የመንግስትን የፖለቲካም ሆነ የኢኮኖሚ ፖሊሲ የሚቃወሙ ናቸዉ በሚሏቸዉ ላይ ግድያ እስከመፈፀም ያልተገደበ መብት አላቸዉ፤ በእያንዳንዱ የገበሬ ማህበር ቤት እየዞሩ ኢህአዴግን መምረጥ እንዳለባቸዉና ይህን ማድረግ ካልቻሉ ግን ምንም አይነት የመንግስት አቅርቦት እንደማያገኙ፤ ቤተሰቡ የመስራትም ሆነ የመማር እድል እንደማይኖረዉ በግልፅ የተነገረበት ሁኔታ እንደነበርና ኢህአዴግን ያልደገፉ ድሃ ገበሬዎች ማዳበሪያና ሌሎች የእርሻ ግብኣት ድጋፎች እንዳይደረግላቸዉ መከልከላቸዉን የሰብኣዊ መብት ተሟጋቾች አጋልጠዋል።
ኢህአዴግ የፖለቲካ አላማዉን ለማስፈፀም ላለፉት 24 አመታት በመንግስት ስልጣን ላይ ተቀምጦ በደህንነትና በወታደራዊ ተቋሞቹ አማካይነት የአገሪቱን ፖለቲካ በግሉ ለመቆጣጠር፤ በጎሳና በዘር ላይ የተመሰረተ ፕሮግራም በማካሄድ፡ በፖለቲካና በሲቪክ ማህበራት ድርጅቶችና በሰላማዊ ዜጎች ላይ ይፈፅማቸዉ የነበሩትና ዛሬም የሚፈፅማቸዉ የሽብር ተግባሮች ለመሆናቸዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠንቅቆ ያዉቃል።
እናም የህወሃት/ኢህአዴግ መንግሰት “በሽብርተኝነት” “የአገርን ሰላም በማደፍረስ” “ህገ መንግስታዊዉን ስርአት በመናድ ” “በዘር ማጥፋት” “በአገር መክዳት”   ወዘተ… የሚሉትን የወንጀል ክሶች የሚጠቀምበት ለምን አላማ እንደሆነ ግልፅ በመሆኑ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሳይበረከክ በኢህ አዴግ ስርዓትና ተቋማቱ ላይ የጀመረውን ተቃውሞውን በማጠናከር ማስቀጠል ይግባል።

Tuesday, August 25, 2015

Ethiopia needs $230-million worth food aid

August 25, 2015
(Reuters) – The number of Ethiopians who will need food aid by the end of this year has surged by more than 1.5 million from earlier estimates due to failed rains, United Nations agencies said on Monday.Ethiopians needing food aid
Ethiopia needs an extra $230 million from donors to secure aid for a total of 4.5 million people now projected to require assistance this year, the Office for the Coordination of Humanitarian Affairs (UNOCHA), the World Food Programme (WFP) and the U.N. children’s agency UNICEF said in a statement.
The country of 96 million people is one of Africa’s fastest-growing economies, but failed rains have devastating consequences for food supplies.
“The belg rains were much worse than the National Meteorology Agency predicted at the beginning of the year. Food insecurity increased and malnutrition rose as a result,” said David Del Conte, UNOCHA’s acting head of office in Ethiopia, referring to the short, seasonal rainy season that stretched from February to April.
Areas normally producing surplus food in the Horn of Africa country’s central Oromia region were also affected by shortages, the statement said, adding lack of water had decreased livestock production and caused livestock deaths in other pastoralist areas.
Meteorologists have warned that the El Nino weather phenomenon, marked by a warming of sea-surface temperatures in the Pacific Ocean, is now well established and continues to strengthen. Models indicate that sea-surface temperature anomalies in the central Pacific Ocean are set to climb to the highest in 19 years.
The El Nino can lead to scorching weather across Asia and east Africa but heavy rains and floods in South America.
The United Nations cautioned that the anomaly could further affect Ethiopia’s “kiremt” rains that stretch from June to September.
“A failed belg followed by a poor kiremt season means that challenges could continue into next year,” said John Aylieff, WFP’s Ethiopia representative.

Saturday, August 22, 2015

በሶማሊያ ሀገር ህይወታቸው እያለፈ ያሉ የኢትዮጵያ ወታደሮች ቁጥራቸው እየጨመረ ነው

August22,2015

ethiopia millitary in somaliaእየተላኩና ህይወታቸው እያለፈ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ወታደሮች ከቀን ወደ ቀን ቁጥራቸው እየጨመረ እንደሆነ ከተለያዩ ያገራችን አካባቢዎች የደረሰን መረጃ አስታወቀ።በሶማሊያ ሃገር እየሞቱ ያሉትን የኢትዮጵያ ወታደሮች ቁጥራቸው ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የሟቾቹ ቤተሰብ በየግዜው በቴለፎን መርዶ እየደረሳቸው እንደሆነ የገለፀው መረጃው በተለይም የኦሮሚያ ክልል ህዝብ ለምንድነው ስልጣን ላይ ያለው ስርዓት የሞቱት ልጆቻችን የማይነግረን በመሰረቱ ልጆቻችን ወደ ሶማልያ አገር ሂደው እንዲያልቁ የሚደረገውስ ለምን ዓላማ ነው? የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቀው ግልፅ በሆነ መንገድ መነገር አለበት በማለት ጥያቂያቸውን እያቀረቡ መሆናቸው ተገለጸ።
ይሁን እንጂ የኢህአዴግ ባለስልጣን አልሸባብን ለማጥፋት በሚል ምክንያት ከሃያላን መንግስታት የሚያገኙትን ዶላር ለመሰብሰብ ካልሆነ ከአገሩ ውጭ እየሄደ ህይወቱን እያጣ ላለው ወጣትና ቤተሰቦቹ ግን ምንም ዓይነት ደንታ እንደሌላቸው የሟቾች ቤተሰብና አንዳንዱ የአገራችን ምሁራኖች አስተያየታቸው እየሰጡ መሆናቸው አስታውቋል።
በተመሳሳይ አንድ በትግራይ ማእከላዊ ዞን፤ ተምቤን ዓብይ ዓዲ ውስጥ የሚኖሩ ወላጅ ልጃቸው በሶማልያ ሃገር ሄዶ መሞቱ ለምን አላማ ሲባል ነው ብለው መጠየቃቸው ባለፈው የዜና እወጃችን መገለፁ ይታወቃል።

ሆዳም ቢሰበሰብ መግላሊት ኣይከፍትም

August 22, 2015
ከብርሃኑ ተስፋዬ
የሰይጣኑን ሙት ኣመት ለማክበር በሚዘጋጁበት ወቅት ወያኔዎች ሆዳም ዲያስፖራዎችን ወደ ኣዲስ ኣበባ ጋብዘው ቡራ ከረዩ የሚሉበት ሁኔታ ስለገረመኝ ነው ይህን ጽሁፍ ለንባብ የማቀርብላችሁ። በመሆኑን መልካም ንባብ።Ethiopian Diaspora
መነሻ
በመጀመሪያ የሰው ልጅ ከትውልድ ቀየው ወደ ተለያዩ ቦታ ወይም የኣለም ክፍሎች የሚሰደደው ኣንድም በሃገሩ ባለው የፖሊቲካ፣ የሶሽያልና የኢኮኖሚ ሁኔታ ኣለመመቻቸት ነው ቢባል ማጋነን ኣይሆንም። እውነቱና ሀቁም ይህ ሆኖ ሳለ የተሰደደበት ችግር በሚቀረፍበት ጊዜ ኣንድም በኣካል ኣሊያም በሃሳብ፣ ማቴሪያል፣ ወይም በገንዘብ ለሃገሩ ኣስተዋጾ ያደርጋል። ይህንን ኣይነት ሁኔታ ሊፈጠር የሚችለው ግን በተሰደደበት ወቅት የነበረው የመንግስት ስርኣት ሲቀየር የሚከተላቸው ፖሊሲዎች ዲያይስፖራውን እንደ ኣንድ ኣገር ገንቢ ኣካል ቆጥሮ በእኩልነት ማሳተፍ የቻለ እንደሆነ ነው።
በኣንድ ጥናት እንደሚያሳየው በአሜሪካ ከሚኖሩ የኢትዮጵያ፣ ጋናና ዚምባዌ ዲያስፖራ አባላት(2010) በ2009 ብቻ የኣመታዊ ምርታቸውን 6.5 ፣ 7.5ና 34.4 በመቶ ወደየሃገሩ ተልኩዋል። ይህም ባንድ በኩል ከዲያስፖራው ወደ ሃገር ከሚገባው የክህሎት፣ የፖሊቲካ፣ የባህልና ሶሺያል ካፒታል በተጨማሪ የተገኘ ነው ቢባል ማጋነን ኣይሆንም።
ይህን በመነሻ ያነሳሁት ለመንደርደሪያ ይሆን እንጅ ዋናው ሃሳቤ ይህን ሃሳብ ይዤ ለመሙዋገት ኣይደለም። ሆኖም የዲያስፖራውን ሃይል ባግባቡ መጠቀም የሚፈልጉ መንግስታት ካሉ ያለውን እምቅ ሃይል ለማመላከት ብቻ ነው።
መረማመጃ
ኣሁን በኣለም ላይ ተበትኖ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ኣንድም የጉጅሌው ሰለባ የነበረ ወይም በነበረው የፖሊቲካ ኣመለካከቱ ሳይደነብር በሃገሩ መኖር ያልቻለ ስብስብ ነው ቢባል ማጋነን ኣይሆንም። ይህን ስል ግን በቅርብ ጊዜ በስወር ለስለላ የተሰማሩ የጉጅሌው ኣባላት የሉም ለማለት ኣይደለም። እነዚህ ግን ኣምላክ ምስጋና ይግባዉና የጉጅሌው መሪ ተብየ በሞተ ማግስት በየድንኩዋኑ ሙሾ ሲወርዱ ስላገኘናቸው እርቃናቸውን ለማስቀረትና መስመራቸው ወዴት እንደሆነ መለየት ተችሉዋል። ከነሱ በተጨማሪ በጉጅሌው ተሳደድን ተገረፍን መብታችን ተገፈፈ ብለው ይጮሁ የነበሩ ሆኖም ትንሽ ትንፋሽ ሲያገኙ ማንነታቸው ገሃድ የወጡ የሆዳም ስብስቦች ኣደባባይ ወጥተዋል። በመሆኑም ነው ባሁኑ ጊዜ ባለም ላይ ከተበተነው ኢትዮጵያዊ ውስጥ ሆዳሞች ብቻ ተለይተው ወደ ሃገር ለበኣል የታደሙት።
ማንም ሰው ወደ ሃገሩ በመሄድ ቤተዘመዱንም ሆነ የተወለደበትን ቀየ ጉዋደኞቹንም ሆነ ሃገሩን መጎብኘት የለበትም የሚል እምነት የለኝም። ሆኖም ግን በውጭ ሃገር ኢትዮጵያዊነት ሲዋረድ ካዋራጆቹ ጋር ኣብሮ የሚጨፍረውን ወያኔን፣ (ሳውድ ኣረቢያ፥ ሊቢያ፥ የመን፥ሌሎች ኣረብ ሃገሮች) መልካም ገጽታ ኣለኝ ብሎ እንዲያናፍስበት የፖሊቲካ መጠቀሚያ ለመሆን ባህር ኣቓርጦ በጎርሻ በሚኖር እናት፣ ኣባት፣ ወንድምና እህት ላይ መሳለቅ ህሊናቢስ መሆን ነው።
ሌላው ኣስገራሚው ደግሞ ትላንት ጎረቤቱና የመንደሩ ገበሬ የተፈናቀለበትንና በረንዳ የተወረወርበትን ቦታ ለዚህ እኩይ ስራ እጅ መንሻነት ውሰድ ሲባል እሽ ብሎ ተቀብሎ የራሱን ፍላጎት ብቻ መመልከቱ ከሆዳምነት የመጨረሻው ሆዳምነቱን የሚያመላክት ነው።
ባሁኑ ወቅት ተሰባስበው የታደሙትን የዲያስፖራ ኣባላት በተናጠል ብንመለከት በውስጣቸው የተሰባሰቡት ኣንድም በወያኔ ድርጎ የራዲዮ ጣቢያ፣ የውይይት መድረክ ኣልያም ወያኔ ከህዝብ በዘረፈው ሀብት መዋእለ ንዋይ ተሰጥቶዋቸው ገበሬውን በማፈናቀል ቦታ የተረከቡ ናቸው። ኣንዳንዶቹም በሚኖሩበት ሃገር መንግስት ድጎማ የሚኖሩና የወር ገቢያቸወ እንኩዋን ድርጅት ለመመስረት ከወር ወር የሚያኖራቸው ኣለመሆኑን እያወቅን በሶስት ወር ሁለት ጊዜ ወደ ሃገር እንዲጉዋዙ የተደረጉ ናቸው።ይሁን እንጅ ይህ ሁኔታ ኣሁን ለምን ኣስፈለገ የሚለው መሰረታዊ ጥያቄን ማንሳት ያስፈልጋል።
ወያኔዎች ኣንድ ኣለመግባባት በመሃከላቸው በሚኖርበት ጊዜም ሆነ በሃገሪቱ ያለው ትግል ትንሽ ጉልበት ያወጣ ከመሰላቸው ጊዜ መግዣ የሚሉት ዘዴ ኣላቸው። ይህንን በ1997ቱም ምርጫ፣ ህዋህት በሚሰነጠቅበት ወቅት፣ ኣርዮስ መሪያቸው በማቀዝቀዣ በነበረበትም ሆነ ኦባማ ለጉብኝት ከመምጣቱ በፊት ያከናወኑዋቸውን ሸረኛ ስራዎች ማስታወስ ግድ ይላል። እነዚህን ነፍሱን ኣይማረዉና ለገሰ ዜናዊ ወጣት በነበረበት ጊዜ ይተኛበት በነበረው መኝታ ቤት ግድግዳ ላይ የዚያን ጊዜ ያስቀመጠውን “procratination is a theft of time” የሚል ኣባባል መቃብር ከመውረዱ በፊት ለወያኔዎቹ ጥሎ መሄዱን ያረጋግጥልኛል።በወቅቱ ይህ ኣባባል ያመለክት የነበረው የፊዳሉን ኣስተዳደር የመሬት ላራሹ መፈክርን ተግባራዊ ኣለማድረግን የሚያመላክት የነበረ ቢሆንም ከዚያ ትምህርት ቤት የተማረውን የከፋፍለው ግዛ ከ17 ኣመት በሁዋላ ተገባራዊ እንዳረገው ሁሉ ይህንንም መቃብር ይዞት ኣለመውረዱ ርዥራዦቹ እየተጠወሙበት ይገኛል።
ወያኔ ባሁኑ ጊዜ ይህ ዘዴ ኣሁን ያፈለገው በተላያዩ የውስጥና የውጭ ችግሮች መሆኑን በሚከተለው ለማሳየት እሞክራለሁ።
1. በሃገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ እየታገሉ ያሉትን ተቃዋሚዎች ለማስመመሰያነት እየተጠቀመበት ያለው ድራማ በምርጫ 2007 እርቃኑን እንዲወጣ ካደረጉት በሁዋላ ወያኔ ከህዝቡ ልብ ብቻ ሳይሆን ኣንዳንድ የራሱ ኣባላት ምን እየተደረገ ነው የሚል ጭምጭምታ መጀመራቸው ብሎም ኣንዳንድ የተቃዋሚ ድርጅት ኣባላት የወደፊቱ የትግል ኣቅጣጫ ምን መምሰል ኣለበት የሚለው ጥያቄ እያጫረባቸው መሆኑን በገሃድ እየተመለከተው በመሆኑ፣
2. በጎረቤት ሃገር ያሉ በሁለገብ ትግል የሚያምኑ ታጋዮች በመሃከላቸው ያለውን መለስተኛ ኣለመግባባት ወደ ጎን ትተው ኣይናቸውን በቀጥታ ወደ ኢላማቸው ለማነጣጠር በጋራ ለመስራት ኣንድ እርምጃ ወደፊት መጉዋዛቸው፣
3. ወያኔ ከኣለም የረድኤት ድርጅቶችና ኣበዳሪዎች ከሚያገኘው የውጭ ምንዛሪ ቀጥሎ ያለው የገቢ ምንጭ ዲያስፖራው ኣንድም ለቤተሰቡ ኣልያም በኢንቨስትመንት መልክ ወደ ሃገር የሚያስገባው ሲሆን ከዚህ ባሻገር ለዚህ ግንባታ ለዚህ ማስፋፊያ በሚል የልመና ኣቁማዳ ይዞ ሊሰበስበው ያቀደው የውጭ ምንዛሪ በትንታግ ታጋዮች በተለያዩ ኣካባቢዎች ሊሳካለት ባለመቻሉ፣
4. በሃገራችን በያመቱ 7.5 ሚሊዮን ገበሬዎች በበጎ ኣዳራጎት (safety net) ድጋፍ ይኖራሉ፣ ሆኖም ሃገሪቱ በምትከተለው ደካማና ያልተጠና የግብርና ፖሊሲ የተነሳ ራሱዋን በምግብ እህል ልትችል የቻለችው በሃይለ ማርያም ደሳለኝ ኣንደበት ብቻ በመሆኑ ባሁኑ ወቅት 4.5 ሚሊዮን ለረሃብ ኣደጋ የተጋለጡ መሆናቸው በኣለም መገናኛ መነገሩ፣
5. በተለያዩ ሜዲያዎች በሃገሪቱ የሚካሄደው የሰብአዊ መብት ረገጣና የህዝቦች ሰቆቃ የየእለት የመወያያ ርእስ በመሆኑና በሌሎችም ምክንያቶች የህዝባችንን የትኩረት ኣቅጣጫ ማስቀየስ በማስፈለጉ የተዘጋጀ ድራማ ነው።
ለዚህ ድራማና ዘፈን ደግሞ ኣጃቢ በማስፈለጉ በዲያስፖራው የተነገሩ መሰረታዊ ባይሆኑም ወቅታዊ ችግሮች በቅመምነት እንዲስተናገዱ ማድረግ ደግሞ ወያኔ የተካነበት መሆኑን ደደቢት ላይ ተነስታ ሳሞራን የጠየቀችው ኣርቲስትን ማጣቀስ ብቻ በቂ ይመስለኛል። በመሆኑም ወያኔ በውስጡ ያሉትን ኣለመግባባቶች ሽፋን መስጠት በመፈለጉና መቶ በመቶ ኣብላጫ ድምጽ ኣግኝቼ ኣሸነፍሁ የሚለውን የ2007 ምርጫ ተከትሎ ሊያዋቅር የሚፈልገውን የክልልና የዞን ምክር ቤት እስኪያዋቅር ድረስ ከምንሰማቸው ነጠላ ዜማዎች ኣንዱ ኣካል እንጅ ዲያስፖራው በጉቦ የተሰጠውን መሬትም ሆነ ንብረት ሸጦ ወደመጣበት እንደሚመለስ ወያኔም ያውቀዋል ዲያስፖራውም የለመደው ነው። ከዚህ ጋር ግን ኣብሮ መታሰብ ያለበት ይህች ዘለል ዘለል እቃ ለማንሳት ነው እንዲሉ የተለየ ቡድን ግን (ትክክለኛ ወያኔዎች) በልጅ ኣመካኝቶ ይበላሉ ኣንጉቶ እንደሚባለዉ ኣባላቶቻቸውን ለመጥቀም የተዘጋጀ መሆኑን ላፍታም መዘንጋት የለብንም።
ማሳረጊያ
ከላይ የጠቀስኩዋቸው መሰረት በማድረግ ሃሳቤን ለማጠቃለል ይረዳኝ ዘንድ ትናንት የሰማሁትን ባለ ፭ ሚሊዮን ባውንድ ኣጉዋጉዋዥ ኣብዛኛዎቻችን ስንሰማ ግር ያለን እንኖራለን ሆኖም በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት ብዙ ሚሊዮኖች ቡልጋሪያ ሃንጋሪና ኡክሬይን ድረስ ተጭነው ሄደው የጦር መሳሪያ መገዛቱን ደግሞ እንረሳለን። በመሆኑም ኣሁን የተሰባሰበው የዲያስፖራ ጋጋታ ኣቅጣጫ ማስቀየሻ በመሆኑ እንደኔ ኣመለካከት ምን ቢሰበሰብ መግላሊት ኣይከፍትም ነውና ኣይናችንን ከኩዋሱ ላይ ማድረግ ብቻ ነው የሚጠበቅብን። በመሆኑም ያለን ባለን ሁሉ ትግሉ ኣንድ እርምጃ እንዲሄድ የየራሳችንን ኣስተዋጾ ማድረጉ ወሳኝነት ኣለው።
ኢትዮጵያ በልጆችዋ ታፍራና ተከብራ ትኖራለች
chillalo@gmail.com

Monday, August 17, 2015

አምባገነንነትና የነፃነት ጥያቄ!

August 17,2015
ANBAGENEN amahric
የኢህአዴግ ስርዓት በአለፉት 24 ዐመታት ያዋቀራቸው ወታደራዊና የፀጥታ ኃይሎችን ተጠቅሞ የሰፊውን ህዝብ ነፃነት መግፈፍ፤ ውስጥ ለውስጥ የማይስማሙትን ማሰርና መግድል ካለምንም የርዕዮተ-ዓለም መሰረት የሚካሄዱ ከውጭ ኃይል ጋር በጥቅም በመተሳሰር በህዝባችን ላይ ዘመናዊ ባርነት እንዲፈጸም ሆን ብሎ እየተንቀሳቀሰ ነው።
የወያኔ ኢህአዴግ የመንግስት መከላከያ ሃይል፤ የፀጥታውና የፖሊሱ አወቃቀር ካለውጭ ዕርዳታና ምክር እንዲሁም ስልጠና በራሱ ኃይል የተደራጀ የሚል ሰው ካለ በዓለም አቀፍ ደረጃ ምን እንደሚካሄድ አያውቅም ማለት ነው። ስለዚህም ለነፃነት የሚደረገው ትግል ብዙ የማይታሰቡ ጥያቄዎችን ይዞ መምጣቱ ብቻ ሳይሆን በአንድ አገዛዝ መገርሰስ ወይም መወገድ ብቻ አንድ ህዝብ ነፃነቱን ሊቀዳጅ እንደማይችል ከብዙ አገሮች ታሪክ የምንማረው ሀቅ ነው።
በተለይም ያለፈውን የሰላሳና አርባ ዐመታት የህዝቦችን የነፃነትና የዴሞክራሲ ትግል ስንመለከትና ስናጠና በአብዛኛው የሶስተኛው ዓለም አገሮች የህዝብ ነፃነት ተግባራዊ ሊሆን ያልቻለው የአብዛኛው ህዝብ ጥያቄ ሳይንሳዊና ፍልስፍናዊ በሆነ መንገድ መፈታት ስላልተቻለ ብቻ ነው።
አንደሚታወቀው  በዓለም አቀፍ ደረጃ ካፒታሊዝም ከተስፋፋና የበላይነትን ከተቀዳጀ ወዲህ ጭቆናዊ አገዛዝ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊስፋፋና አብዛኛዎቹ የሶስተኛው ዓለም አገሮች በወታደራዊ ሃይል ስር በመዋላቸው ምክንያት በዓለም አቀፍ የጭቆናና የአፈና ሰንሰለት ውስጥ ገብተው ለስቃይ እንዲፈረዱ ግድ ሆኗል።
የጥሬ-ሀብት ጥናቶች እንደሚያረጋግጡት አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች ይህንን የተትረፈረፈ ጥሬ ሀብታቸውን እያወጡ በስርዓት ለመጠቀም፤ ህዝቦቻቸውን ከድህነት በማላቀቅ ስነ-ስርዓት ያለው ኑሮ ለመገንባትና ህዝቦቻቸውን ለማስከበር ያልቻሉት ከላይ በተዘረዘረው የወታደራዊና የስለላ የጭቆና ሰንሰለት ውስጥ ስለተካተቱና በአሜሪካንና በተቀረው የምዕራቡ ካፒታሊዝም የብዝበዛ አስተሳሰብ ውስጥ ተቀነባብረው ሀብታቸውን በስርዓት እንዳይጠቀሙ ስለተደረጉ ነው።
በአብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች የተዋቀረው የመንግስት አሰራር በመሰረቱ የህዝቦች አለኝታና የሀብት ፈጣሪ መሳሪያ ወይንም መንገዱን የሚቀይስ ሳይሆን ድህነት እንዲስፋፋና ሁሉም ዜጋ በስርዓቱ ስር ሆኖ እንዲገዛና አስከፊ የኑሮ ሁኔታ እንዲያሳልፍ ነው የሚደረገው።
በሳይንስና ምንም አይነት ፍልስፍና ባልተከተለ መንገድ የተዋቀሩ የመንግስታት አሰራሮች፤ ስነ-ምግባርና ሞራል የጎደላቸው ማህበራዊ ህብረተሰባዊ፤ ባህላዊና ታሪካዊ ኃላፊነት በሚያሸክም መንገድ ስላልተቀመጡ ሁሉም ነገር በተራ ታዛዥነት እንዲፈፀም ምክንያት ሁኗል።
ወደ አገራችንም ስንመጣ የስርዓቱ የአሰራርና የአወቃቀር ስርዓት ከተቀሩት የአፍሪካ አገሮች እምብዛም የሚለይ ሳይሆን የባሰ መሆኑን የሚያከራክረን አይደለም። አንድ ህዝብ ዕውነተኛ ነፃነቱን ሊቀዳጅ የሚችለው ይህ ዐይነቱ እንደሰንሰለት የተያያዘ የጭቆና አገዛዝ ለዕውነተኛ ነፃነት እጦት ዋናው ምክንያት እንደሆነና የድህነትንም አፍላቂና የተስተካከለ ዕድገት እንዳይኖር የሚያግድ መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ ሲገባ ብቻ ለነፃነት የሚደረገው ትግል የተቃና ይሆናል።
በሌላ አነጋገር ለዕውነተኛ ነፃነት እታገላለሁ የሚል ሁሉ አገራችን ውስጥ ላለው ፀረ ህዝብ ስርዓትና የአብዛኛዎችን የአፍሪካ አገዛዞች አወቃቀር በሚገባ መገንዘብና ከዚህ በመነሳትም እስካሁን በተካሄደው የትግል መንገድ ዕውነተኛውን የህዝብ ነፃነት ማምጣት እንደማይቻል መረዳት ይኖርበታል።

ዴምህት

Sunday, August 16, 2015

ኢትዮጵያዊነትና ብሄራዊ ስሜት

August 16, 2015
ሻለቃ አብርሃም ታከለ
በረጅሙ ዘመን ታሪካችን ኢትዮጵያዊነትንና ብሄራዊ ስሜታችንን የሚፈታተኑ ሁኔታዎች መከሰታቸዉ ተስተዉሏል። ይህ አባዜ ዛሬም ድረስ አልተወንም።
ባዕዳን ወራሪዎች ካደረሱብን መከራና በደል ይልቅ ይበልጥ አድቅቆን የነበረዉ በአገዛዝ ስም ወገኖቻችን የሚጭኑብን ኢ-ሰብአዊ የሆነ የግፍ ቀንበር መሆኑን አንስተዉም። ከእኛ በፊት የነበሩት ኢትዮጵያዉያን እንዲያ ሆነዉ አልፈዋል። በደም በአጥንታቸዉ ዋጅተዉ ባቆሙት ነፃነት ላገር እንደእንግዳ ለወገን እንደባዳ ተቆጥረዉ በነፃነትና በባርነት መካከል ባለዉ ድንበር መሃል ሲታሹ ለእፎይታ ሳይበቁ ተሰናብተዋል።”እምሽክ ድቅቅ አርጎ እኔን ከበላኝ ነጭ ጅብ ጥቁር ጅብ ምን አስመረጠኝ ” እስከማለት መድረሳቸዉም በዚህ የተነሳ ነዉ።
ይህንን እያንጎራጎሩ ኖረዉ ይኸዉ ወደ መቃብር ወርደዋል። ይህ ለመሆኑ እርግጥ ነዉ። ተረትም አይደለም የተፈፀመ እዉነት። “እናት ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ” የተባለዉም በአብዛኛዉ ሕዝብ ስቃይና ሞት ጥቂቱ ተንደላቃቂና ፈላጭ ቆራጭ ስለሆነ ነዉ። ይህን ያሉትም እኒያዉ ለአገር አንድነትና ሉአላዊነት ዉድና ተተኪ የማይገኝለትን ሕይወታቸዉን ቤዛ ያደረጉና አካላቸዉን ያጎደሉ ሃቀኛ ዜጎች ናቸዉ። ይህ ግፍ በሕዝቡ ላይ ተፈጽሟል። ይህ ሁሉ አበሳና መከራ በሕዝቡ ላይ ደርሷል። ይሁን እንጂ ይህች አገራችን ታላቅ ከመባል የተዛነፈበት እስከቅርብ ግዜ ድረስ የለም። ሕዝቡም ቢሆን አገሩን አሳልፎ የሰጠ የሚል አሳፋሪ ስም በታሪክ አልተፃፈበትም።ረሃብ ድርቅ ድህነት ቢፈታተነዉም የነፃነት ሸማዉን ሳያስገፍፍ የአገሪቱን ሉአላዊነት አስከብሮ ኢትዮጵያዊነትን አዉርሶ ወር ተራዉን ጨርሶ አልፏል። መቸም ቢሆን የሕዝብ ዋና ኩራት በዜግነት መተማመን ነዉ። ይህን መተማመን ያጠነከረ ሕዝብ ለማናቸዉም ምድራዊ ሃይል ተንበርካኪ አይሆንም። በኢትዮጵያዊነት የማመን ጥኑ ማተብ ነዉ።የኢትዮጵያ ሕዝብ ቋንቋ ባሕልና የተለያየ እምነት ሳይከፋፍለዉ በአንድነትና በመተሳሰብ እንዲዘልቅ ያስቻለዉ። የትግራይ ነፃ አዉጪ የነፍሰገዳዮች ቡድን አገዛዝ ይህን የተከበረ የጀግንነት ኩራት ሊነጥቀን እየዳዳ ነዉ።
በዚያ ነዲድ የኢትዮጵያዊነት ስሜት ላይ በረዶ ሊሞጅርበት ሌት ተቀን እየደከመ ነዉ። ከሁሉ በፊት ኢትዮጵያዊነትን ማሰብና ማስቀደም የቀድሞ ሥርአት ናፋቂ ሽብርተኛ ትምክህተኛ እያሰኘ ነዉ። ኢትዮጵያዊነት ነፍጠኛነት ከሚል የተሳሳተ የዘረኝነት ድምዳሜ ላይ እያደረሰ ነዉ። ኢትዮጵያዊነት ሁሉም ብሄረሰቦች የሚጠለሉበት አንድ ጃንጥላቸዉ ሆኖ እንዲዘልቅ የምንመኘዉን ያህል በዜግነት የመተማመን ስሜት እንደጠላ ቂጣ እለት ከእለት እየተሸራረፈ በጊዜ ሂደት ዉስጥ ተሟጦ እንዳያልቅና ጭራሹን እንዳይጠፋ የተቆርቋሪዎች ስጋት ከሆነ ሰንብቷል።
በመናወዝ ላይ የሚገኘዉ ይህ ትዉልድ ስለኢትዮጵያዊነትና ስለብሄራዊ ስሜት ጭብጥ እንስጥህ ቢሉት “አቦ ተወን….አትደብረን! ቢል አይፈረድበትም። ይህን በማለቱ ሊወቀስም ሊነወርም አይገባም። ለእርሱ ኢትዮጵያዊነት ጦርነት ስደትና ሞት ሆኖ ነዉ የሚታየዉ። ለእርሱ ኢትዮጵያዊነት ቀይ ሽብር ነጭ ሽብር ሆኖ ነዉ የሚቆጠረዉ። ለእርሱ ኢትዮጵያዊነት የእትብት አፈር ክልል አብሮ ማደግ፣ጎሰኝነትና ይህን ሃሳብ የማይቀበለዉን ወገን ማሰደድ ማፈናቀል ማሰርና መግደል ሆኖ ነዉ የሚታሰበዉ።
በዘመናችን አገርና ትዉልድ እሳትና ጭድ ሲሆኑ ተመልክተናል። ተካፋይም ሆነናል። የሃይማኖት አባቶች የመልካም ሥነ ምግባርን ትምህርት በመስጠት ፋንታ ከአምባገኖች ጋር ወግነዉና በዘር ተደራጅተዉ በመንፈሳዊ ሳይሆን በአለማዊ ሕይወት ዉስጥ ሲዳክሩ እያየን ነዉ።
አድርባይነትንና ጎሠኝነትን ተፀይፎ እዉነትን መቀበል አለመቻል ኢትዮጵያዊነትን ብቻ ሳይሆን እኔነትን ፈልጎ ለማግኘት አለመፍቀድ ይሆናል። በቅድሚያ ኢትዮጵያዊነት የዜግነት ስሜት። ከዚያ እኔነት።
የስነ ልቡና ጠቢባን ራስን ለማወቅ በጠቀሱት ቁም ነገር “አንተነትህ አንተ እስከምታዉቀዉ ድረስ ነዉ” ይላሉ እኛም እንደዚያዉ ነን። የምናዉቀዉ ይህንኑ ነዉ። የምናሳድገዉም፤ ለትዉልድ የምናስተላልፈዉም ይህንኑ ነዉ። ኢትዮጵያዊነትን።
ይህ ሳይሆን ሲቀር ዘዋሪ እንደሌለዉ ካሚዎን ነዉ የምንሆነዉ። ሁላችንም ጠፍተን አገርም ዜጋም። እና ሁላችንም ተፈላላጊ ሆነን። አገርን ወይንም ኢትዮጵያዊነትን ያየህና ወዲህ በለኝ! እንደሚባለዉ ዓይነት። መሆኑ ነዉ።

Saturday, August 15, 2015

የማለዳ ወግ…ለአሚራና ቤተሰቦቿ የጎደለው ፍትህ … !

Augest 14,2015
Amira
Amira
==================================
* ህጻን የደፋረን የ4 ወር እስር መቅጣት ምን ይሉታል ?
* ፍርዱ ቅጣት ነው?  ወይስ ማበረታታት ?
* ህግ አውጭና አስፈጻሚ አካላት ወዴት ናችሁ?
* ወላጆቿ " ወላጅ ይፍረደን፣ህዝብና ሀገር ይፍረደን!"ይላሉ
የኢፊድሬ ህገ መንግሰት ሴቶች  ልክ  እንደ  ወንዶች  በሕገ-መንግሥቱ  እኩል  መብትና  ጥበቃ  እንዲሰጣቸው ይደነግጋል ትግበራውን መከታተልና ማስፈጸም ያለባቸው ህግ እውጭና አስፈጻሚ አካላት የሴቶችን መደፈር ለመከላከል የከበደ ኃላፊነት እንዳለባቸው ይህው የፈረደበት ህገ መንግስት ያስረዳል  ! ዳሩ ግና አልፎ አልፎ የሚሰማ የሚታየው የነገር ጭብጥ ውጤት ህግ አውጭና የሚያወጡት ህግ ደንብና መመሪያ ከወንጀል ፈጻሚው ባልተናነሰ በህግ አስከባሪና አስፈጻሚዎች ህጉ ይጣሳል ። ህግ ተጥሶ የዜጎች ሰብአዊ መብት መዳጡ  በአደባባይ እየተሰማና እየታየ ህግ አውጭ አካላት የሚወስዱት እርምት እርምጃ አያስደስትም ። የሴት ጠለፋ በተለይም በህጻናትና ታዳጊዎች ላይ የሚፈጸም አስገድዶ  መድፈር ዝርዝሩ ሰፋ ያለ ይሆናል ። ዳሩ ግን የህግ እውቀት ኖሮኝ ያንን ለመተንተን ባይዳዳኝም በህግ አስከባሪዎች ፍትህ እየጎደለ በዜጎች ላይ የሚፈጸመው በደል ዘልቆ ቢያመኝ እንደ ዜጋ በጎደለው ፍትህ ተቃውሞና በቅሬታየ ዙሪያ የዜጋ ድምጼን ማሰማት ግድ ብሎኛል ...
ዛሬ ዛሬ የምንሰማው ሰው በሰው ላይ ቀርቶ በእንስሳ ላይ መፈጸም የሌለበትን ርክሰት የተጠናወተው ወንጀል ጀሯችን ሆኗል ። በተለይ በአቅመ ደካማ ህጻናት ታዳጊዎችና በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ወንጀል እያደር መክፋቱ  ጸሀይ የሞቀው እውነት ሆኗል። በዚህ ረገድ እየተኬደ ያለውን የከፋ ወንጀል ሳስበው " ወደ የት እየሄድን ይሆን?  " እያልኩ ያስፈራኛል  ! የአጉራ ዘለል አስገድዶ የመድፈር ወንጀለኞች መስፋፋት ፣ እያደር ውሎ አዳራችንና አብሮነታችን እንዳያጎድፈውም በአስፈሪ የታሪክ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን  !  ሴሰኛ ወንጀለኛ ሽምጥ ጋልቦ  እዚህ ሲደርስ ወንጀሉን በጥብቅ ተከታትሎ የማያዳግም ቅጣት አርአያነት ያለው ውሳኔ ቢሰጥ ዛሬ እዚህ ባልተደረሰ ነበር ፣ ይህ አይፈጸምምና ፣ ይህ አልተደረገምና ዛሬ ውርደትን መከናነብ ግድ ብሎናል ።  የተከናነብነው ውርደት ምክንያት የሆነን ወንጀልም ሊሰሙት ከሚችሉት በላይ ሰቅጣጭና የከበደ እየሆነ ለመምጣቱ ብዙ ማሳያዎችን ማቅረብ አይገድም  !
ይህን ሁሉ የምለው በአንዲት የ4 ዓመት ከ6 ወር ብላቴና ተዳጊ ላይ የተፈጸመው ወንጀልና ተመጣጣኝ ያልሆነውን የፍርድ ውሳኔ ወደምቃዎምበት የማለዳ ወጌ የመረጃ ግብአት ለመዝለቅ ነው   ! እንደኔ የፍትህ መዛባት ዘልቆ ያመማችሁ ተከተሉኝና ፍርዱን ስጡ ... !
በያዝነው ሳምንት ማህበራዊ መገናኛ ድህረ ገጾችን ቀልብ የሳበው ጉዳይ መካከል የ4 ዓመት ከ6 ወሯ ታዳጊ  መደፈርን ተከትሎ የተላለፈው ዜና የብዙዎቻችን ቀልብ ስቧል ። ለዚህ መሰሉ ዜና አዲስ ባይንሆንም ብላቴናዋ  መደፈሯ ሳይሰማ ባሳለፍነው ሳምንት ሀሙስ  በመጨረሻ ው የፍርድ ውሳኔ ጋር ሰማን ፣ በውሳኔውም ደፋሪው የ4 ወር እስራት ቅጣት ፍርድ መሰጠቱን በአንድ ላይ ሲነገረን ማመን ከተቸገሩት መካከል አንዱ ነበርኩ።  የጉዳዩን ጭብጥ ለማጣራት ባደረግኩት ሙከራ ያገኘሁት መረጃ ይዠ የዜጋ ተቃውሞ ድምጼን በማለዳ ወጌ ላሰዳ ስውተረተር በድሬ ትዩብ ስሟን በመጥቀስ በጉዳዩ ዙሪያ የቀረበ አንድ ዘገባ ለወጌ መረጃ ግብአትነት ተጠቅሜበታለሁ ። ትክክለኛ ስሟ ስለመሆኑ ግን ማረጋገጫ አላገኘሁም ። ስሟ ቢታወቅም መግለጹ አስፈላጊ ባለመሆኑ የድሬ ትዮብን ስም ተቀብየ እዘልቃለሁ ።  ከዚሁ በተጨማሪ ሌላም ሌላ መረጃዎችን ለማሰባሰብና ለማጣራት ሞክሬ በእርግጥም ወንጀሉ ለመሰራቱና ፍርደ ገምድል ብይን የመሰጠቱ ሁነኛነት አረጋግጫለሁ  !
የተሰራጩ መረጃዎች እንደሚስረዱት ታዳጊዋን የ4 ዓመት ከ6 ወር ተዳጊዋን አሚራ ትባላለች ።  ኑሮዋም አዲስ አበባ አቃቂ ክፍለ ከተማ እንደሆነ ተጠቁሟል። ደፈረ የተባለው አስነዋሪ ወንጀል ፈጻሚ የ25 ዓመት ጎረምሳ ነው። በችርቻሮ ንግድ የሚተዳደሩት የአሚራ ቤተሰቦቿ ቤት ጎን ተከራቶ ነበር አሉ ።
ከውሳኔው አስቀድሞ ተከሳሽ አሚራን ስለመድፈሩ ክስ ቀርቦበት ፣ ጉዳዩ በፖሊስ ቀርቦና ተጣርቶ ተከሳሽ ተይዞ በፊዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአቃቂ ቃሊቲ ፍርድ ቤት ችሎት የቀረበ ሲሆን በ30 ሽህ ብር ዋስትና ተለቀቀ።  ክሱን በዋስ ወጥቶ እንዲከላከል በፊዴራድ  ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአቃቂ ቃሊቲ ፍርድ ቤት ወሰነ ። ያ ከሆነ በኋላ ባሳለፍነው ሳምንት ተከሳሽ  ለብይን ቀረበ ። ፍርድ ቤቱ በፖሊስ የቀረበለትም ምርመራ ተመልክቶ በሰጠው ውሳኔ " ተከሳሽ ድንግልናዋን ባይገስም በእጆቹ የማህጸኗ ግድግዳ የመሰንጠቅና የመላላጥ  ጉዳትና ማድረሱና በማህጸኗ የመቅላት ምልክት በመታየቱ  !" በሚል ማስረጃ  ፍርድ ቤተ ተከሳሽን " ሞከርክ " በሚል ወንጀለኛ ሲል የ4 ወር እስራትን አስተላልፎበታል ። ይህው ፍርድ ቤት ገና የትምህርት ገበታ ያልቀመጠችን ታዳጊ ብላቴና አመራን  የደፈረበትን የጨካኝ ድርጊት ከደፈረ ሞከረ ቀይሮ በቀረበ ማስረጃ በፍትሀ ብሔር ህግ 6264 ሀ መሰረት ውሳኔ መሰጠቱ ተነግሮናል ። አስገራሚ ፣ አስደንጋጭና አሳዛኝ የፍርድ ውሳኔ !
ክሱን አቀለለ ወደተባለው ምክንያት ስንሄድ ደግሞ ይበልጡኑ እንታመማለን ... ወንጀለኛው  " የሳንባ ነቀርሳ በሽተኛና በቀጣዩ አመት ተመራቂ !" መሆኑን በቅጣት ማቅለያነት አቅርቦ በፍርድ ቤቶ ተቀባይነት ማግኘቱ አገኘ ብለውናል  ። ለእኔ  የክስ ማቅለያ የቀረበው ሀሳብ የተማረ የተመራመረው " የዩኒቨርሲቲ ተማሪ " ነኝ ባይ ወንጀለኛ ነው ፣  ምንም የማታውቅን እምቦቃቅላ ታዳጊ ገላን በአሻው መንገድ አድርጎ ገፎታል ፣ ገፈፋውም የተፈጸመው በአንድ አዋቂ መሆኑ ብቻ ወንጀሉን ሊያከብድ እንጅ ሊያቀል ባልተገባ ነበር ባይ ነኝ ። ይህ ያቀረበው የክስ ማቅለያ ይልቁንም በሰነድ ተረጋግጦ ክሱን ማጠንከር ሲገባው ክሱን ማቅለያ ሆኖ መቅረቡና ከምን ወደ ምን እንደቀለለ ያልተገለጸው ማቅለያ ተቀባይነት ማግኘቱ በራሱ  በምንም ሚዛን ፍትሃዊነት የለውም  ! ይህን ለመናገር ሰብእናና የራስን ፍርድ መስጠት እንጅ ግዴታ ህግ ማጥናት አያስፈልገውም ...
የህዝብን መብት ለማስጠበቅ የተሰየሙትን የፍትህ አካላት የሙያ ብቃት ጥያቄ  ውስጥ የጣለው ይህ መሰሉ አሳዛኙ የፍትህ ውሳኔ ማህበረሰቡ በፍትህ እንዳይተማመን ከማድ ረግ ባሻገር በህግ ጥላ ስር መጠበቁን በጥርጣሬና እንዲ ያይ እንደሚያደርገው ጥርጥር የለኝም ። ከዚህም አልፎ ተርፎ በአሚራ ደፋሪ ላይ የተላለፈው ውሳኔ ሀገሬው  ፍትህ አጥቶ የሚንገዋለል እንዲሆን አድርጎታል ወደሚል መደምደሚያ አድርሶኛል ... የአስገድዶ መድፈር ወንጀለኞ ች ጉዳይ መስፋፋትና ገደብ ማጣት በተደጋጋሚ በመንግ ስት ላይ የሰላ ወቀሳ ይቀርባል ። በተለይም የህግ ጥበቃ ውንና ቅጣቱን ከማጠንከሩ በተጓዳኝ ተማኝነት እንጅ የሙያ ብቃት ሚዛን ሆኖ ቅጥር ስለማይፈጸም ተደጋጋሚ ችግሮች ተስተውለዋል ። የፍትህ አካላት ብዛት እንጅ ጥራት የጎደላቸው መሆኑ ከዚሁ ጋር ይጠቀሳል ።  የተባለውን ወቀሳ እውነታነት እንዳለው ለመረዳት የአሚራን አይነት በደል ተሰርቶ የተሰጠውን ውሳኔ መመልከት ብቻ  ማየት ከበቂ በላይ ይመስለኛል  ።
በአሚራ ውሳኔ አሰጣጥ  እንዳየነው ከምንም በላይ የፍትህ ስርአቱ በወንጀለኛውም ሆነ በጠበቆች የቀረበውን የተውተፈተፈ መከላከያና ቅጣት ማቅለያ መቀበላቸው ለፍትህ አካላት የደረሱበትን ደረጃ ያሳይ ከሆነ መልካም ነው ። የአሚራን ጉዳይ በግርድፉ ላየ ለተመለከተው   ጥፋታቸውን በአዞ እንባ ለመሸፋፈን ከተጉ ወንጀለኞች ጎን ለገንዘብ ብለው ጥፋቱን ለማቅለል ሚሞግቱት ጠበቆች ሰብዕና ያማል ፣  የዳኞቹ ውሳኔ አሰጣጥና ውሳኔ ማቅለያ አቀባበል ደግሞ  ይገርማል ፣ ይደንቃል ... !  ይህ መሰል ከእውነታው ጋር የሚጋጭ የተፋለሰ ፍርድ  በአደባባይ ሲሰጥ ህጉን ማስከበር ያለባቸው አቃቤ ህግ ተወካዮች የታሉ  ? ፍትህ ወዴት ነህ  ?  ያስብላል ...
በሰብዕና ላይ ወንጀል ሲሰራ በቸልተኝነት መመልከት ሊቆም ይገባል ።  የሴቶችን መብት ለማስከበር ተብሎ የወጡት ሕጎች  ተፈጻሚ  ይሆኑ ዘንድ  የኢትዮጵያ  ሰብአዊ  መብት  ኮሚሽን  አካል  የሆነ  የሴቶችና ሕጻናት  ጉዳዮች  ብሔራዊ  ኮሚሽንን  በ2005  ዓም መቋቋሙን ከሰማን አመታት ተቆጥረዋል ።  ኮሚሽኑ በሴቶችና  በሕጻናት ለሚፈጸሙ የሰብአዊ  መብት  ጥሰት  ተገን እንደሚሆን ቢጠቀስም ለአሚና የጎደለ ፍትህ ድምጹን ሲያሰማ አለመታየቱ ግር ያለው እኔን ብቻ ከሆነ መልካም ነው ፣ ግን አይመስለኝም ። " መብቷ ይከበር ፣ ፍትህ ጎድሎባታል፣  ፍትህ ታግኝ " የምንላት  ታዳጊዋ አሚራ ያለ ፈቃዷ አይደለም ገላዋ የጸጉር መጠምጠሚያ "ሂጃቧ " ሊነካ አይገባም ፣ ከተነካ ህግ ተጥሷል ! አሚና ድንግልናዋ አልተገሰሰም ፣ ማህጸኗ ግን ተነካክቷል ብሎ ወንጀለኛን ከአስገድዶ መድፈር ወንጀል ማራቅ ፣ ማሸሸት ፍትህን ማረጋገጥ ሳይሆን ፍትህን ማርከስ አድርጌ ነው የምቆጥረው ።  ወንጀለኛው " አስገድዶ የደፈረ " ለመባል አሚራ በጭካኔ ተደፍራ እንደተገደለችው እንደ ሀና ኦላንጎ መሆን አልነበረባትም  ! አሚራም ሀና እንደሆነችው ባትሆንም በአሚራም ማህጸን ዙሪያ ክብረ ነክ የመድፈር ሙከራ አድርጓል ። የቀረበው ማስረጃ የሚየስረዳው አርቆ አሳቢው የተማረ ጎልማሳ ምንም በማታውቀው የ4 ዓመት ከ6 ወር ታዳጊ ህጻን ላይ ወንጀል አስገድዶ መድፈር ለመሆኑ ሌላ ከበቂ በላይ ማስረጃ  አለ ብየ አላምንም!
የሴቶችና ሕጻናት  ጉዳዮች  ብሔራዊ  ኮሚሽንን  ሴቶች  ሥርዓተ-ፆታን  መሠረት  ያደረገ  ጥቃት ደርሶባቸው እንዲህ ሲመለከት አብሮ ከተጎጅ ወገኖች ጎን  መቆም ፣ የሕግ  ጥበቃ  ማቆም ፣ የህግ ጠበቃ የማቆም አቅም ከሌለው  የህግ ጥሰቱን በአደባባይ ተቀውሞ ስታዳጊዋ ብላቴና ስለአሚራ ፍትህ ማግኘት ድምጹን ሊያሰማ ይገባል !
በፍርድ ገምድሉ ውሳኔ ያዘኑ ቤተሰቦች  ወላጆቿ ፍትህ ጎድሎባቸው " ወላጅ ይፍረደን፣ህዝብና ሀገር ይፍረደን!" ማለታቸው ስሰማ የእነሱም ጩኸትና አቤቱታ የእኔም ለአሚራና ቤተሰቦቿ ፍትህ ርትዕ ይከበርላቸው የሚል ጥያቄ እንዳነሳ አድርጎኛል  ! ከምንም በላይ የሴት ልጅ በረከት የታደልኩ አባት እንደመሆኔ የሴት ልጅን ወሰን የሌለው ፍቅር አውቀዋለሁና ከአሚራ ቤተሰቦች ጋር ልቤ በሀዘን ተሰብሯል ፣ በጎለው ፍትህ አምርሬም አዝኛለሁ ... !
ፍትህ ለህጻን አሚራና ቤተሰቦቿ ስል እጠይቃለሁ  !
ነቢዩ ሲራክ
ነሀሴ 5 ቀን 2007 ዓም

Friday, August 14, 2015

የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አዛዦች በከፍተኛ ስብሰባ ተጠምደዋል::

August14,2015

sirag fergesa and samora
የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አዛዦች በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በከፍተኛ ስብሰባ ላይ መጠመዳቸውን ከቦታው ያገኘነው መረጃ አስታወቀ:: በአዲስ አበባ ከተማ ከሃምሌ 25 ቀን 2007 ዓ/ም ጀምሮ በከፍተኛ የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች ሳሞራ የኑስና ሲራጅ ፈርጌሳ ስብሰባ መካሄዱና በስብሰባው እንደመወያያ ርእስ ሁኖ የቀረበውም አዲስ ሰራዊት ቢጨመርም አብዛኛው የሚፈርስና የሚበታተን በመሆኑ አሁንም የሰራዊቱ ይዘት አነስተኛ ነው። እናንተ ምን እያደረጋችሁ ነው? ለምንድነው የማትቆጣጠሩት የሚል እንደነበር መረጃው አስረድቷል።
የክፍለ-ጦሮች አመራሮች የቀረበላቸውን ጥያቄ መመለስ እንዳልቻሉ የገለጸው መረጃው ስብሰባው ወደ ታች በመስመራዊ መኮነን ደረጃ ወርዶ በተለይ ከሻንበል በላይ በተደረገው ስብሰባ ላይ የሰራዊቱ መፍረስ ምክንያት በከፍተኛ የሰራዊቱ አዛዦች ውስጥ ብልሹ አሰራር፤ ወገናዊነትና አድልዎ በመኖሩ ነው ብለው መናገራቸው ተገልጿል።
መረጃው በማከልም- የበላይ የሰራዊቱ አዛዦች ከተራ ወታደሮችና የበታች የሰራዊቱ አዛዦች የነጠቁትን ገንዘብ የግል ኑሮአቸውን እያመቻቹበት ነው ተብሎ በስብሰባው በተነገረበት ግዜና የተሰጠውን ሃሳብ ተከትሎ የድጋፍ ድምፅ በተሰማበት ወቅት የመድረኩ መሪዎቹ ድንጋጤና ፍርሃት እንደተሰማቸውና በከባድ ስጋት ላይ በመውደቃቸው ምክንያት አመራሮቹ ስብሰባውን ለማካሄድ መቸገራቸውን መረጃው አክሎ አስረድቷል።

Thursday, August 13, 2015

የኤልያስ ገብሩ ቆይታ ከጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጋር (ዝዋይ እስር ቤት)

August 13, 2015
በኤልያስ ገብሩ
  • ታገሉ! ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (ከዝዋይ እስር ቤት)
  • ተመስገን ደሳለኝ ስለሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ፍርድም ሀሳቡን ሰንዝሯል
Temesgen Desalegn Fteh newspaper editor
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
ቦሌ አካባቢ ብርዱ ጠንከር ያለ ነበር፡፡ ከቦሌ ብራስ ወደሚሊኒየም አዳራሽ በሚወስደው ቀጭን መንገድ ላይ ወንዱም ሴቱም በፍጥነት ይራመዳል፡፡ ከታክሲ በሁለቱም አቅጣጫዎች የወረዱ ሰዎች ወደመደበኛ ሥራቸው ለመግባት ብሎም የግል ጉዳያቸውን ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ ነበር – ከትናንት በስትያ ሰኞ (ነሐሴ 04 ቀን 2007 ዓ.ም) ጥዋት 1፡45 ሰዓት፡፡
እኔ እና ወዳጄ አቤል ዓለማየሁ ወደከአዲስ አበባ 160 ኪሎ ሜትር ርቀት ወደሚገኘው ዝዋይ እስር ቤት አምርተን ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬን እና ተመስገን ደሳለኝን ለመጠየቅ በዚህ ቀን ቀጠሮ ይዘን ነበር፡፡ አቤል ከቀጠሯችን 20 ደቂቃ ዘግይቶ፣ ቦሌ ጫፍ ደረሰና ወደቃሊቲ መናሃሪያ ሁለት ታክሲዎችን በመጠቀም ደረስን፡፡ ወደዝዋይ የሚጭኑ ሚኒባስ ታክሲዎች እና ‹‹አባዱላ/ዶልፊን›› የሚል መጠሪያ የተቸራቸው የህዝብ ማመላለሻ መኪኖች ቢኖሩም በተለምዶ ‹‹ቅጥቅጥ›› የሚባለውን መካከለኛ አውቶቡስ ምርጫችን አደረግን – የትራፊክ አደጋን በመስጋት፡፡
የተሳፈርንበት አውቶቡስ፣ ከቃሊቲ ትንሽ ወጣ ካለ በኋላ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፣ በእስር ላይ የሚገኙትን የግንቦት 7 ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ “ልማቱን አሳዩኝ” ሲለን ከከተማ ወጣ እያደረግን የምነሳየው… [እውነት ግን፣ በከባድ እስር ላይ መሆናቸው የሚገመተው አቶ አንዳርጋቸው ‹ልማቱን አሳዩኝ› ይሏቸዋልን?!]›› ሲሉ ለቪኦኤዋ ጋዜጠኛ ትዝታ በላቸው የገለጹትን፣ የአዲስ አበባ አዳማ አዲሱ የፍጥነት መንገድ (Express way)ን ተቀላቀለ፡፡ በዚህ መንገድ ሁለታችንም ሄደን አናውቅም ነበር፡፡ ሆኖም እስከዛሬ ካየኋቸው የመኪና መንገዶች በደረጃው ከፍ ያለ ይመስላል፡፡ [በሀገራችን አምረው የተሰሩ የመኪና መንገዶች በጥቂት ዓመታት ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ የመቦርቦር፣ የመፈረካከስ፣ ውሃ የማቆር ችግሮች ገጥሟቸው እንዲሁም ከመንገዱ ዳር እና ዳር የሚገኙ የብረት አጥሮች ተሰርቀው፣ ተገጭተው፣ ተጨረማምተው፣ ተነቃቅለው … አደጋ ሲያደርሱና የተለመደ የሬንጅ የመለጠፍ ሥራ ሲሰራላቸው በገሃድ የምናየው ሀቅ መሆኑን ማስታወስ ግን የግድ ይላል] ይሄኛው መንገድ ከጠቀስኳቸውና ካልጠቀስኳቸው ችግሮች ምን ያህለ ነጻ ነው? ለሚለው ትክክለኛ መስክርነት መስጠት ያለበት ለእውነት የቆመ የዘርፉ ባለሙያ ቢሆንም በኢህአዴግ ‹ልማት› ላይ የጥራት መተማመኛ ማግኘት እጅግ ከባድ መሆኑን ግን አምናለሁ፡፡ አስፋልቱ ለፍጥነት አመቺ መሆኑን ግን በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡
በሶስት ሰዓታት ጉዞ ዝዋይ በመድረስ ምሳ ከበላን በኋላ ወደእስር ቤቱ የፈረስ ጋሪ መጠቀም ግዴታችን ነበር፡፡ አቧራማው አስቸጋሪ መንገድ፣ ከፊሉ ደቃቅ አሸዋ መልበስ ጀምሯል፡፡ የእስር ቤቱ የማስፋፊያ ግንባታ ሥራ፣ በፊት ውብሸትን ለመየጠቅ ስመጣ ከማውቀው ተፋጥኗል፡፡ አንዱ የሥርዓቱ “የልማት ውጤት” እስረኛ ማብዛት አይደለ ታዲያ?!
ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ላይ የምንጠይቀውን እስረኛ በማስመዝገብ ተፈትሸን ገባን፡፡ ሁለት እስረኛ በአንዴ መጠየቅ ስለማንችል እኔ ተመስገን ጋር፣ አቤል ደግሞ ውብሸትን ለመጠየቅ ተስማምተን ነበር፡፡ አቤል ውብሸትን ከጠየቀ በኋላ እንደምንም ብሎ ተመስገንን ለመጠየቅ ጥረት እንደሚያደርግ ግን ቀድሞ ነገረኝ፡፡
ተመስገን እና ውብሸት የታሰሩበት ዞን ስለሚለያይ እኔ እና አቤል ሌላ የውስጥ ፍተሻ ካደረግን በኋላ መለያየታችን ግድ ነበር፡፡ የእስር ቤቱ ፖሊሶች የሚኖሩበትን ጉስቁልና ያጠቃቸው፣ መኖሪያ ቤቶችን አልፌ መጠየቂያው ጋር ደርሼ የታሳሪው ስም ያለባትንና በፖሊሶች የምትጻፈዋን ቁራጭ ወረቀት እስረኛን ለሚጠራው ፖሊስ ሰጠሁትና በአጣና እንጨት ርብራብ በተሰራው መጠየቂያው አግዳሚ ላይ ተቀመጥኩ፡፡ ከቅርብ ርቀት የፖሊሶች ማማ ይታያል፡፡ መሳሪያ የታጠቁ ፖሊሶች ማማው ላይና ከማማው ሥር በዛ ብለው ተቀምጠው ያወጋሉ፡፡ አብዛኞቹ ፖሊሶች ከላይ የለበሷት እና “Federal prison” የሚል የታተመባት አረንጓዴ ዩኒፎርምም በፀሃይ ብዛት ነጣ ወደማለት ደርሳለች፡፡ አንዱ ፖሊስ መጣና ከእኔ በትንሽ ሜትር ራቅ ብሎ ተቀመጠ፡፡ ‹‹አዳማጭ ነው›› አልኩ በልቤ፡፡ ወደፊት ለፊቴ ወደሚታየኝ የእስር ቤት ግቢ አማተርኩ፡፡ ለእይታ የሚጋብዝ አንዳች ነገር አጣሁ፡፡ የተበታተኑ ዛፎች፣ ቅርጽ አልባ ሳሮች፣ አስታዋሽ ያጡ አረሞች፣ ግድግዳ እና ጣራቸው በቆርቆሮ የተሰሩ የእስረኛ መኖሪያዎች፣ …ብቻ ጭርታ እና ድብታ የወረረው የግዞት መንደር ይመስላል፡፡
ከአንደኛው የእስረኛ ቆርቆሮ ቤት ጣሪያ ላይ ሁለት ተለቅ ተለቅ ያሉ ሙቀት ማቀዝቀዣዎች ይሽከረከራሉ፡፡ ወደፖሊሱ ዞሬ ‹‹ለሙቀት ነው?›› አልኩት ወደ ጣራው በመጠቀም፡፡ ‹‹አዎ፣ ወባ አደገኛ ነው›› አለኝ፡፡ ‹‹እስረኞች ሲታመሙ እንዴት ይሆናሉ?›› ስል ጥያቄ ሰነዘርኩ፡፡ ‹‹ያው እዚሁ ይታከማሉ›› አለኝ ድምጹን ቀሰስ አድርጎ፡፡ የእኔም ሆነ የእሱ ልብ፣ በማረሚያ ቤቱ (በእነሱ አጠራር) በቂ ህክምና እንደማይሰጥ ግን ያውቃል ብዬ አሰብኩ፡፡ ቀጭኑ ፖሊስ፣ ‹‹ለወባ ህመም ምግብ ወሳኝ ነው›› አለኝ አስከትሎ፡፡ ‹‹በቂ ምግብ የለም ማለት ነው?›› ስል ድጋሚ ጠየኩት፡፡ ‹‹በፊት በፊት አቀራረቡ ዝም ብሎ ነበር፤ ሙያ ባሌላቸው ሴቶች ነበር የሚሰራው፡፡ አሁን ግን ለውጥ አለ›› አለኝ፡፡ ‹‹ምን አይነት ለውጥ? ጥቂትም ቢሆን ታስሬ፣ ለእስረኞች የሚቀርበውን በጣም ደረጃውን ያልጠበቀ ምግብ አይቻለሁ›› አልኩት፡፡ ‹‹በፊት ጥቁር ጤፍ ነበር የሚቀርበው፤ አሁን የነጭ ጤፍ እንጀራ ነው የሚበሉት፤ እስረኞች ችግር የለባቸውም፤ ባለሙያ ሴቶችም ናቸው የተቀጠሩት …›› ‹‹(ውስጤ አላመነምና) ለእስረኛ የነጭ ጤፍ እንጀራ እያቀረባችሁ ነው?!›› …‹‹አዎ›› ብሎ ሊያብራራልኝ እያለ ከታች ከርቀት ‹‹አረንጓዴ ኮፊያ፣ ቲ-ሸርትና ስካርፍ ያደረገ ሰው አየሁ፡፡ ትኩረቴን ከፖሊሱ አዙሬ ቁልቁል ተመለከትኩ – ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ነበር፡፡ ተሜም፣ ረጋ ብሎ በራስ በመተማመን መንፈስ ወደመጠየቂያው ሥፍራ ቀረብ ብሎ ጠያቂውን ለማወቅ ጥረት አደረገ፡፡ ሳየው አንዳች የሀዘን ስሜት ውስጤ ገባ፡፡ ቆሜ ጠበኩት፡፡ ፈገግ እያለ መጣና ተጨባብጠን አራት አምስቴ ያህል ተቃቀፍን፡፡ ‹‹በዚህ በጸሐይ ለምን መጣህ?›› ሲል ጠየቀኝ፡፡ ከአቤል ጋር መምጣታችንን፣ እሱ ውብሸትን ሊጠይቀው መሄዱን ነገር ግን ከቂሊንጦ በኋላ እስከአሁን ዝዋይ ድረስ መጥቼ ባለመጠየቄ የጸጸት ስሜት ውስጤ እንዳለ ገለጽኩለት፡፡ ‹‹መንገዱ ረዥም ነው፣ ባትመጡም እረዳለሁ›› ካለ በኋላ፤ ‹‹ምን አዲስ ነገር አለ?›› በማለት ፊት ለፊት በእንጨት አጥር ተከልለን በመቀመጥ ጨዋታችንን ቀጠልን፡፡
‹‹አሁን ምን እየሰራችሁ ነው?››፣ ‹‹ክስህስ እንዴት ሆነ?››፣ ‹‹አዲስ ጋዜጣ ለማቋቋም ለምን ጥረት አታደርጉም?›› ከተመስገን በተከታታይ የተነሱ ጥያቄዎች ነበሩ፡፡ አጠር አጠር አድርጌ መለስኩለት፡፡ የጋዜጣ /የመጽሔት ህትመትን ድጋሚ መጀመር የግድ አስፈላጊ መሆኑን ግን ተመስገን አጽንኦት የሰጠበት ጉዳይ ነበር፡፡ …ስለተወሰኑ ጋዜጠኞችና የዞን 9 ጦማሪያን ከእስር መፈታት፣ ስለኦባማ የአዲስ አበባ ጎብኝት፣ በቂሊንጦ ዞን አንድ ከእነአብበከር አህመድ፣ ጦማሪ አቤል ዋበላና ዘላለም ክብርት ጋር ስለነበረው ቆይታ፣ እሱ ወደዝዋይ ከወረደ በኋላ እኔም በዚያ ዞን ገብቼ በነበረበት ጊዜ እነአቡበከር፣ አቤልና ዘላለም እሱን በተመለከተ ስለነገሩኝ ነገሮች ሳቅ እያልን አወጋን፡፡
ሰፊ ውይይት ያደረግነው በሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ በቅርቡ ከ7 እስከ 22 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ፍርድን በተመለከተ ነበር፡፡ ‹‹እኛ ከሙያ ጋር በተያያዘ ነው የታሰርነው፡፡ ታስረንም እንወጣለን፡፡ ከባዱ የሙስሊሞቹ እስር ነው፡፡ ኢህአዴግ እውነተኛ ሰላም ከፈለገ እነአቡበከርን በነጻ መፍታት አለበት፡፡ እኔ የእነሱ መከላከያ ምስክር ሆኜ ምስክርነቴን ሰጥቻለሁ፡፡ በወቅቱ ዘንግቼው ያልተናገርኩት አንድ ነገር ነበር፤ አሁን ሳስበው ትንሽ ይቆጨኛል – በተናገርኩ ብዬ፡፡ ያኔ (በምስክርነት ጊዜ)፣ ‹የኮሚቴዎቹ እንቅስቃሴ ሰላማዊ ነበር ወይስ አልነበረም?› የሚለው ጥያቄ በራሱ መነሳት አልነበረበትም፡፡ እንቅስቃሴያቸው፣ ሰላማዊ ባይሆን ኖሮ እንዴት ሶስት ዓመት ሙሉ በክስ ሂደት ይቀጥላል?! ሰላማዊ ስለሆኑ እኮ ነው፣ ባለፉት ሶስት ዓመታት ምንም ያልተፈጠረው፡፡ እስኪ በእነሱ አንድ የተሰበረ መስታወት አለ?! ቅንጣት የወደመ ንብረት አለ?! የማንንስ ሕይወት አጠፉ?! በእነሱ የተፈጠረ አንድም ነገር የለም፡፡ ጥያቄያቸው ኃይማኖታዊ እንጂ ፖለቲካዊ አይደለም፡፡ ፖለቲካዊ ቢሆን ኖሮ ትግሉ አቅጣጫውን ይቀይር ነበር፡፡ ‹የመጅሊስ አመራሮችን ካለመንግሥት ጣልቃ ገብነት እንምረጥ!› ነው አንዱ ሰላማዊ ጥያቄያቸው፡፡ ያው ምስክር ስትሆን ከዚህም ከዚያ ጥያቄ ሲነሳ ስለምትዘናጋ መመስከር ያሰብከውን ነው ቅድሚያ የምትሰጠው እንጂ አሁን የምልህን ያኔ ብገልጸው በጣም ደስ ይለኝ ነበር …›› በማለት በኢትዮጵያ ውስጥ ከታሪክ አኳያ፣ በሁለቱ ትልልቅ ሃይማኖት ተከታዮች መካከል ስለነበረው ግንኙነት በዝርዝር የራሱን ምልከታ እና ሀሳብ ደጋግሞ አወጋኝ፡፡ ኃይማኖታዊ መቻቻል ነበር ወይስ አልነበረም? የሁለቱም እምነት ተከታዮች ጉርብትና ነበራቸው ወይስ አልነበረባቸውም በሚሉት አንኳር ጉዳዮችም የራሱን አቋም አንጸባረቀልኝ፡፡
ኡስታዝ አቡበከር አሕመድን አስመልክቶም አንድ ጥሩ ምሳሌም አንስቶልኝ ነበር ተመስገን፡፡
‹‹አሁን ባለሁበት ዞን፣ በአንድ የወንጀል ክስ ግብረ-አበር ተብለው አምስት ዓመት የተፈረደባቸው አንድ ቄስ አሉ፡፡ እኚህ ቄስ ለጠበቃ የሚከፍሉት አጥተው የጠበቃ ክፍያ የፈጸመላቸው አቡበከር እንደሆነ ነግረውኛል››
እኔም ፣ በህዳር ወር ቂሊንጦ ዞን አንድ በነበርኩበት ጊዜ ከዚህ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ነገር፣ ስለአቡበከር ሰምቼ ነበር፡፡ ታሪኩ እንዲህ ነው፡- አንዱ እነአቡበከር ይገኙ በነበረበት ዞን 1 8ኛ ቤት ውስጥ የቀጠሮ እስረኛ ነበር፡፡ ዋስትና ይጠየቅና በዚህ ክፍል ውስጥ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩ አንድ የናጠጡ ሀብታም (ልጃቸው 22 አካባቢ እጅግ ዘመናዊ ሆቴል አለው) ጋር ጠጋ ብሎ ለዋስትና የሚሆን ብር ተጨንቆ በአክብሮት ይጠይቃቸዋል፡፡ እሳቸውም ‹‹እኔም እንደአንተው እስረኛ እኮ ነኝ!›› በማለት ይመልሱለታል፤፡፡ ልጁም ያዝናል፡፡ ይህ ጉዳይ አቡበከር ጆሮ ይገባና ለልጁ የሚስፈልገውን የዋስትና ብር ከፍሎ ልጁን ከእስር እንዲወጣ አድርጎታል፡፡ እንግዲህ፣ ከሁለቱ እውነተኛ ምሳሌዎች በመነሳት፣ አቡበከር ለወገኖቹ ሃይማኖትን መሰረት ሳያደርግ፣ በሰብዓዊነት ደግ መሆኑን እንማራለን፡፡
ከተመስገን ጋር በነበረን ሰፋ ባለ የጨዋታ ጊዜ፣ ከጎኔ የነበረው ፖሊስ በተመስጦ ቢያዳምጥም፣ አንዴም አላቋረጠንም ነበር፡፡ …ስለ 100% ቱ የዘንድሮ ምርጫ ፍጻሜ፣ በሰሞኑ በአፋር ክልል ስለደረሰው የድርቅ አደጋ፣ በአይ ኤስ አሸባሪ ቡድን ስለተቀሉና ስለተገደሉት ኢትዮጵያኖች፣ ድርጊቱን በማውገዝ በመስቀል አደባባይ በተጠራው ሰልፍ ላይ ስለተፈጠረው ረብሻ፣ ጉዳትና እስር ተመስገን የራሱን አተያይ በስሜት ተውጦ የግሉን ሀሳብ አብራራልኝ፡፡ በተጨማሪም፣ አይ ኤስ ያንን ድርጊት፣ ያንን ጊዜ መርጦ አደረገ ያለበትን የራሱን የተለየ (ከማንም ያላደመጥኩትን፣ ተጽፎም ያላነበብኩትን) ሀሳብ አጋራኝ፡፡ የተለየ ሃሳብ በመሆኑም ‹‹አሃ!›› ብያለሁ፡፡
ከተመስገን በጣም የገረመኝ፣ የማስታወስ ችሎታው ነበር፡፡ በጥቅምት ወር፣ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ‹‹ጥፋተኛ›› በተባለበት ማግስት ጥዋት አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ልጠይወቅ ሄጄ በማያመች ሁኔታ ውስጥ ሆነን አብዮትን አስመልክቶ የተለዋወጥናቸውን ሃሳቦችን፣ እንዲሁም ከአቤል ጋር ቂሊንጦ ስንጠይቀው ያነሳናቸውን ሀሳቦች ድጋሚ በማስታወስ በዚህ ቀን ለተነሱት ርዕሰ ጉዳዮች የውይይት ማጠናከሪያ ሀሳብ ሲያደርጋቸው አስተውያለሁ፡፡
ለተመስገን አሁን ስለሚገኝበት ዞን ሁኔታ ጥያቄ አቀረብኩለት፡፡ ቀደም ሲል ከእነውብሸት ጋር አብሮ እንደነበረ ጠቅሶ፣ ‹‹የኢትዮጵያ ገመና›› በሚል ርዕስ በእስር ቤት ውስጥ ስላወቀው ነገር ሁለት ተከታታይ ጽሑፎችን ካወጣ በኋላ ወደዚህ ዞን መዘዋወሩን ይገልጻል፡፡ አሁን ባለበት ክፍል 80 የሚሆኑ እስረኞች አብረውት አሉ፡፡ ብዙዎቹ ከደቡብ ክልል የመጡ ናቸው፡፡ ከእሱ ጋር አንድም የፖለቲካ እስረኛም ሆነ ጋዜጠኛ አብሮት የለም፡፡ [አቶ በቀለ ገርባ ከወራቶች በፊት የ3 ዓመት ከ7 ወር የእስር ጊዜያቸውን አጠናቅቀው ከዝዋይ እስር ቤት በተፈቱ ማግስት ተመስገን ከባድ ወደሆነው ወደዚህ ዞን መሸጋገሩን ነግረውኝ ነበር] አሁን ባለበት ዞንም ከእሱ ጋር እስረኞች እንዳያወሩ እና እንዲያገልሉት በዘዴ ተደርጓል፡፡ ከእሱ ጋር በቅርበት ሆነው የሚያወሩ ካሉ፣ እንደትልቅ ተስፋ በሚጠብቁት አመክሯቸው ላይ እንደመፍረድ ይቆጠራል እንደተመስገን አባባል፡፡ ‹‹በዚህ ጉዳይ ማናቸውም ላይ አልፈርድም፤ ከእኔ ጋር አውርተው የአመክሮ ጊዜያቸውን እንዲያጡ አልሻም፡፡ ግን እንዲህ ያደረጉት ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች ቢሆኑ ኖሮ ይሰማኝ ነበር፡፡›› ሲል ያለበትን ከባድ ሁኔታ ያስረዳል፡፡
‹‹ማንበብ፣ ማጸፍስ ትችላለህ?›› ሌላኛው ጥያቄዬ ነበር፡፡ ‹‹መጽሐፍ አይገባም ተልክሏል፤ ያነበብኳቸው ጥቂት ልብወለድ መጽሐፍቶች አሉ፡፡ መጻፍ ትንሽ ጀምሬ በእስረኞች በኩል ተጠቁሞ የጻፍኩት ተወሰደ፡፡ ሁለት ሶስቴ ለመጻፍ ሞክሬ ነበር፡፡ ግን ተመሳሳይ እርምጃ በመወሰዱ ተውኩት፡፡›› ይላል ተመስገን፡፡ ‹‹ቀኑን እንዴት ነው የምታልፈው?›› የሚለው የመጨረሻ ጥያቄዬ ነበር፡፡ ‹‹ሁለት የማውቃቸው የአዲስ አበባ ልጆች አሉ፤ ጫናውን ችለው ያናግሩኛል፡፡ ከእነሱ ጋር ቼዝ እጫወታለሁ፡፡ የእግር ኳስ ፕሮግራም የሚተላለፍባቸው ቻናሎች ቢኖሩም መገለሉን አስበውና ደስ ስለማይለኝ ወደክፍሌ እገባለሁ›› የሚለው የተመስገን መልስ ነበር፡፡
ተመስገን አቤልን ከርቀት አይቶት ‹‹ያ አቤል ነው አይደለ?›› አለኝ፡፡ ዞሬ አየሁት፣ አቤል ውብሸትን ጠይቆት ከርቀት ወደመውጪያው በር እየሄደ ነበር፡፡ ‹‹ግን እንዴት አስገቧችሁ?፤ ይመልሱ ነበር እኮ›› አለኝ፡፡ አቤልም ተመስገንን ተመስገንም አቤልን ማግኘት ፈልገው ነበር፡፡ ብዙም ሳይቆይ አቤል አንዱን ፖሊስ እንደምንም አናግሮ ተመስገንን ሊጠይቅ መጣ፡፡ ተቃቅፈው ተሳሳሙ፡፡ የሶስትዮሽ ጨዋታችንን ለግማሽ ሰዓት ያህል አደራነው፡፡ ተመስገን ከታሰረ በኋላ የግራ ጆሮው እንደማይሰማለት እና ወገቡም ሕክምና በማጣቱ አሁንም ድረስ እንደሚያመው አልሸሸገንም – ‹‹እዚህ ያለው መድኃኒት ፓናዶል ብቻ ነው›› በማለት፡፡ አያይዞም ‹‹ሰው መጥቶ ሲጠይቅህ ደስ ይላል፤ ጥሩ እንቅልፍ ትተኛለህ፤ግን የመንገዱን ርቀት ሳስበው ሰው ባይመጣ እላለሁ›› አለን በድጋሚ፡፡
የእስረኛ መጠየቂያ ጊዜ መጠናቀቁን ፖሊሶች ነገሩንና ተቃቅፎ መለያት ግድ ሆነ፡፡ ‹‹አይዞህ የምትባል አይደለህምና ሰላም ሁን›› አልኩት፡፡ ‹‹ምን መልዕክት አለህ?›› ስል የመጨረሻ ጥያቄዬን ሰነዘርኩለት፡፡ ተመስገንም ‹‹ታገሉ!›› ሲል መለሰና በመጣበት መንገድ ቻው ብሎን እርምጃውን ቀጠለ፡፡ ሲሄድ አራት እና አምስት ጊዜ ያህል ዞረን አየነው፡፡ ስለገኘነው ደስ ቢለንም በሳሮች መካከል ባለው መንገድ ወደታሰረበት ክፍል ሲያመራ ማየት ዳግመኛ የመረበሽ እና የማዘን ስሜት በውስጤ ፈጥሮብኝ ነበር፡፡ ስሜቱ በጣም የሚገባው በቦታው ላይ ሲገኙ ነው!
ተመስገን፣ ያመነበትን ሀሳብ በድፍረት ስለጻፈ ነበር በኢ-ፍትሃዊነት ሶስት ዓመት እስር የተፈረደበት፡፡ ሰው መታሰሩ ሳያንስ፤ ከቤተሰቡ፣ ከወዳጁ፣ ከዘመዱ፣ ከጓዳኞቹ እርቆ እንዲታሰር ማድረግ ሌላ ቅጣት ነው! ሰው መታሰሩ ሳያንስ፣ ህክምና መከልከሉ፣ በሌሎች እስረኞች እንዲገለል መደረጉ፣ መጽሐፍ ማንበብ እና የግል ማስታወሻዎቹን እንዳይጽፍ መከልከሉ ይሄም ሌላ ቅጣት ነው! ሰው ግን በስንቱ ይቀጣል?! እንዲህም ሆኖ፣ ትናንት የምናውቀው ጋዜጠኛ ተመስገን፣ አሁንም ድረስ ያ ያመነበትን የመናገር ድፍረቱ፣ መንፈሳዊ ብርታትና ጥንካሬው አብሮት አለ!!! አካል ቢታሰር ህሊና መቼም አይታሰር!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!