Saturday, September 5, 2015

አርበኞች ግንቦት 7 ለ1 ሰዓት የፈጀ ውጊያ ማድረጉን አስታወቀ * ገድያለሁ፣ መሳሪያም ማርኬያለሁ ብሏል

September 5,2015
የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ የውስጥ አርበኞች በህወሓት አገዛዝ መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት በመሰንዘር ለአንድ ሰዓት የዘለቀ ከባድ ውጊያ አድርገው ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን አስታወቀ::
Arebegnoch Ginbot 7

የአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞች ህወሓት "ክልል አንድ" እያለ በሚጠራው በጎንደር-ወልቃይት ደጃች ሜዳ ወረዳ አቤራ ቀበሌ ስልኪ ዳግባ በተባለው ቦታ ነሃሴ 23 2007 ዓ.ም በህወሓት መከላከያ ኃይል ላይ ድንገተኛ የተኩስ ውርጅብኝ በመክፈት ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ወታደሮችን ገድለውና አቁስለው ድል ተቀዳጅተዋል፡፡

በአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞችና በህወሓት የመከላከያ ሰራዊት መካከል የተካሄደው ድንገተኛ የሆነ ከባድ ፍልሚያ እኩለ ቀን ላይ ከ6፡30 ጀምሮ እስከ 7፡30 ለአንድ ሰዓት የዘለቀ ሲሆን ምሳ በመመገብ ላይ እያለ ባልገመተው ሁኔታና ባለሰበው አሳቻ ሰዓት ድንገተኛ ተኩስ ተከፍቶበት የእሳት ዝናብ በላዩ ላይ የወረደበት የህወሓት ሰራዊት አብዛኛው ተበታትኖ ከአካባቢው የሸሸ ሲሆን የአፀፋ ተኩስ ከፍቶ ለአንድ ሰዓት ለመከላከል የሞከረው ደግሞ ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል፡፡

የውስጥ አርበኛው ሽምቅ ተዋጊ ኃይል መትረየሶችን ጨምሮ በርካታ ክላሽን ኮቮች ከነመሰል ጥይቶቻቸው ለመማረክ ችሏል፡፡
የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ከሰኔ 25 2007 ዓ.ም እስከ ሀምሌ ወር መጀመሪያ በወልቃይት ቃፍታ መሲን፣ ኮርጃሙስ፤ ማይ ሰገን፣ ንኳል ሳግላ፣ በዋልና ማይ እምቧ ላይ በህወሓት መከላከያ ሰራዊት ላይ ተከታታይ ጥቃቶችን በመክፈት በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ የሆነ እልቂትና ኪሳራ በማድረስ ተደጋጋሚ ድሎችን መጎናፀፉ አይዘነጋም፡፡

No comments: