Tuesday, April 28, 2015

“መንግሥት የሌለው እዚህ ብቻ ነው!” የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መግለጫ

April 28, 2015
ባለፈው ሳምንት አይ ሲስ ባሰራጨው ቪድዮ ኢትዮጵያውያኖች በሁለት የተለያዩ ቦታዎች ተከፍለው ሲገደሉ አይተናል። ስለቪድዮው ብዙ ማለት ቢቻልም ወገኖቻችን የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ካገራቸው ውጥተው መከራተታቸው ለዚህ አይነቱ አሰቃቂ ሞት ዳርጓቸዋል።ከአገራቸው የወጡት እየኖሩ ከመሞት ለመትረፍ ቢሆንም በስደት ደግሞ እጅግ መራራውን የሞት ጽዋ ጠጥተዋል። ይህ የወገኖቻችን ዕልቂት በዓለማችን ሊይ በሚገኝ በምንም ዓይነት ቋንቋ፣ አገላለጽ፣ አጻጻፍ፣ እንባ፣ ወዘተ ሊገለጽ የማይችል ነው። ረዳት አልባ ሆነው የተመለከትነው ትዕይንታቸውም በውስጣችን ለዘመናት የማይሽር ቁስል  ይዞ ይቀመጣል። 
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዲይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ሁለንም ኢትዮጵያውያን ዘር፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖት፣ ቦታ፣ ወዘተ ሳይለዩ ይህ በአገር ወገን ላይ የደረሰው ሃዘን በጋራ በመሆን እርስ በርስ በመጽናናት፣ በመበረታታት እንዱወጡ፤ ላልችንም በተመሳሳይ የስቃይና የመከራ ሁኔታ ሊይ የሚገኙትን ወገኖች በመርዳት የሚችለበትን መንገድ እንዲቀይሱ አሳስበዋል። 
አቶ ኦባንግ ሲቀጥሉም፤ “በአለም ዘሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የእነዚህን ለሃይማኖታቸው የቆሙ ጀግና ወገኖቻችንን ተመልክቷል፤ የሞት ከበሮ ቢደለቅባቸውም ሳይፈሩና በድፍረት ሰብዓዊነታቸውን በናቁባቸው አረመኔዎች ፊት ለእምነታቸው ቆመዋል፤ “እኔም ሆንኩ በጋራ ንቅናቄያችን ሥር የሚገኙ ቤተሰቦችና ላልች እጅግ በርካታ ወገኖች የተሰማንንን ጥልቅ ሃዘን በምንም ዓይነት ቃልት መግለጽ አንችልም፤ ይህንን ፍጹም አረመኔያዊ የሆነ፤ አንዳች ሰብዓዊነት የሌለበት ደርጊት ባሉት ቃላት ሁሉ ተጠቅመን እናወግዛለን፤ ልጃቸውን፣ ወንድማቸውን፣ አጎታቸውን፣ ወገናቸውን፣ ወዘተ ላጡት ቤተሰቦች እንደ እነርሱ እኩል ማዘን ባንችልም የአንዱት ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል እንደ መሆናችን ይህንን መራር ሃዘን የራሳችን አድርገን በመውሰደ አብረናችሁ እናዝናለን፤[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]
Public outrage in Ethiopia

ሰማያዊ ፓርቲ መንግስት የከፈተበትን የጥላቻ ዘመቻ በአስቸኳይ እንዲያቆም አሳሰበ

April 28, 2015
መንግስት ሊቢያ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ላይ አሰቃቂ እርምጃ የወሰደውን አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም ራሱ በጠራው ሰልፍ ላይ ከህዝብ የገጠመውን ተቃውሞ ተከትሎ ሰማያዊ ላይ የጥላቻ ዘመቻ እንደከፈተበትና ይህንን የጥላቻ ዘመቻውን እንዲያቆም ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳስቧል፡፡Semayawi Parties latest press conference
መንግስት የጠራውን ሰልፍ ከማንም ተቃዋሚ ፓርቲ ቀድሞ የደገፈው ሰማያዊ እንደሆነ የገለጸው መግለጫው ‹‹የዜጎችን ስቃይ ለፖለቲካ ፍጆታ ማዋል የፈለገው ህወሓት/ኢህአዴግ ሰማያዊ ፓርቲ በወገኖቻችን ላይ ለሚደርሰው በደል መፍትሄ እንዲሰጥ መወትወቱ፣ የፖለቲካ ልዩነታችንን ወደ ጎን አድርገን በሰልፉ ላይ መገኘታችን እንዳላስደሰተው ከሰልፉ ቀን ጀምሮ በፓርቲያችን ላይ የተከፈተው ዘመቻ ትልቅ ማሳያ ነው፡፡›› ብሏል፡፡
ከሰልፉ ማብቃት ጀምሮም ጉዳዩን ገና ፖሊስ ሳይመረምረው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት ሚኒስትር ሬድዋን ሁሴን ሰማያዊ ፓርቲ ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት እየጣረ ነው በሚል መወንጀላቸውን፣ የመንግስት ሚዲያዎች ሰማያዊ ፓርቲ ሁከትና ብጥብጥ ሊያስነሳ ነው ብለው ሚዛናዊ ያልሆነ መረጃ ማሰራጨታቸውንና አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም ተብለው በተጠሩ ሰልፎችም ሁሉ መንግስት ሰማያዊ ፓርቲ ለመቃወም እየተጠቀመባቸው መሆኑን መግለጫው አትቷል፡፡
በተጨማሪም በሰልፉ ዕለት የሰማያዊ አባላት ገና ሰልፉ ሳይጀመርና መስቀል አደባባይ ሳይደርሱ እንዲሁም ሰልፉ ካበቃ በኋላ እየታደኑ ሲታሰሩ መስቀል አደባባይ ላይ የተያዙት የኢህአዴግ አባላት ከቀበሌ ደብዳቤ እያመጡ መፈታታቸው መንግስት ሰማያዊን በሀሰት ለመወንጀል መነሳቱን ያሳያል ብሏል፡፡ በሌላ በኩል 6 ያህል የሰማያዊ አባላት በታሰሩበት ሁኔታ መንግስት 7 አመራሮችና 20 ያህል አባላት ታስረዋል ማለቱ ትክክል አለመሆኑንና ከመጀመሪያውም 6 አባላቱ የታሰሩበት መንገድና አሁንም በሰማያዊ ላይ የሚቀርበው ክስ መሰረተ ቢስ ነው ብሎታል፡፡
‹‹ይህ በህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት አማካኝነት እየቀረበ ያለው ክስ እና የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ህወሓት/ኢህአዴግ ለዜጎች ህይወት የማይጨነቅ እና በዜጎች ሞት የራሱን የፖለቲካ ትርፍ ለማጋበስ እና ጠንካራ ተቃዋሚ የሆነውን ሰማያዊ ፓርቲን ለማጥቃት እየተጠቀመበት መሆኑን በተጨባጭ የሚያሳይ ነው፡፡›› ሲልም የመንግስትን ተግባር ተቃውሟል፡፡ በፍርድ ቤት ውሳኔ ያልተሰጠበትን ጉዳይ ተጠርጣሪ ከማለት ይልቅ ወንጀለኞች ናቸው በማለት በህገወጥ ስራ እንደተሰማራ ያሳያል ሲልም ወቅሷል፡፡
‹‹መንግስት እና የመንግስት መገናኛ ብዙሀን ከዚህ አኩይ ተግባራቸው የማይታቀቡ ከሆነ፣ የሰማያዊን ስም በሀሰት በማጠልሸት ስራ ላይ የተሰማሩ የመንግስት ተቋማትን እና ግለሰቦችን በህግ ፊት ለማቆም ይገደዳል›› ያለው መግለጫው ሌሎች ተከታታይነት ያላቸውን እርምጃዎችም እንደሚወስድና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሰማያዊ ፓርቲ ለሚያደርጋቸው ህዝባዊ ጥሪዎች በንቃት ተዘጋጅቶ እንዲጠብቅ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ አባል ስንታየሁ ቸኮል በደህንነቶች ታፈነ

April 28.2015

የቀድሞው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ የነበረው እና በአሁኑ ወቅት የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ዛሬ ሚያዝያ 20/2007 ዓ.ም በደህንነቶች ታፍኖ ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዱን ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
ዛሬ ጠዋት 12 ሰዓት ላይ አራት ሲቪል የለበሱ ደህንነቶች ‹‹ትፈለጋለህ!›› በማለት በመኪና አፍነው ወዳልታወቀ ቦታ የወሰዱት ሲሆን ለእስሩ ምንም አይነት ምክንያት ወይንም መጥሪያ እንዳልሰጡት ምንጮቻችን ገልጸውልናል፡፡ ቤቱን የፈተሹት አራቱ ደህንነቶች ምክንያታቸውን እንዲያስረዱት የጠየቀው አቶ ስንታየሁ ላይም ከፍተኛ ድብደባ እንደፈፀሙበት ለማወቅ ተችሏል፡፡

Monday, April 27, 2015

ኢትዮጵያ ውስጥ የግብረሰዶማዊነት ትምህርት እየተሰጠ ነው – አደጋ ላይ ነን!

April 27,2015
ካስደነገጥኳችሁ አዝናለሁ ግን በጣም መደንገጥ አለባችሁ፡፡በመላው የአዲስ አበባ የመንግስት ሁለተኛ ደረጃ ትምርህት ቤቶች ማለት ይቻላል በነSave The Children ፊት አውራሪነት እየተሰጠ ያለው የግብረሰዶማዊነት ትምህርት ተጠናክሮ እየቀጠለ መሆኑን ሳረዳችሁ ከፍተኛ ሀዘን እየተሰማኝ ነው፡፡እስካሁን ከ40 በላይ የሚሆኑ የአዲስ አበባ ት/ቤቶች ውስጥ ለውስጥ በአንድ ክፍለ ጊዜ በ120 ብር በተቀጠሩ የየትምህርት ቤቱ የባዮሎጂና የአይሲቲ መምህራን አማካኝነት እየተሰጠ ነው፡፡ሁለት አይነት ነው ትምህርቱ፡፡Life Skill (ላይፍ እስኪል) እና Comprehensive Sexuality Education (ከምፕሬኤንሲቭ ሴክሽዋሊቲ ኤጁኬሽን) የሚባሉ፡፡በሁሉም ትምህርት ቤቶች የመጀመሪያ ዙር ስልጠናው አልቋል፡፡ሁለተኛ ዙሩ የተግባር ትምህርት ነው፡፡ በቪዲዮና በተግባር እንቅስቃሴ የተደገፈ፡፡ ከሚሰጡት ትምህርቶች መካከል FREE KISSING (በፍሪ ኪሲንግ) እና MASTERBATION (ማስተርቤሽን)የሚባሉ የልቅ ወሲብ አይነቶች አሉበት፡፡ ልቅ ስል በ FREE KISSING (በፍሪ ኪሲንግ) ጊዜ ጾታ ሳይለይ የፈለጉትን ደፍሮ መሳም ሲሆን በ MASTERBATION (ማስተርቤሽን) የሚለው ደግሞ ሴቶችም ወንዶችም በቪዲዮ የታገዘ የ Pornography (የፖርኖ) ፊልሞች እያዩ እንዲተገብሩት የታሰበ ነው፡፡ ለዚህም አላማ ከየትምህርት ቤቱ ጎበዝ የተባሉ ተማሪዎች ተመርጠው ተዘጋጅተዋል፡፡

ጉዳዩ እስከ ትምህርት ሚኒስተርና ቢሮ ቢደርስም እስካሁን መልስ ሊሰጡ አልቻሉም፡፡አንዳንድ የክፍለ ከተማ ሀላፊዎች እንዳሉት እነSave The Childern (ሴቭ ዘቺልድረን) በኢትዮጵያ የተለያዩ ስራዎች ስለሚሰሩልን አቁሙ ብንላቸው ግንኙነታችን ይበላሻል፡፡በላይ አመራሩም ዘንድ ያለው እሳቤና አቋም ይሄ ነው ብለዋል፡፡የተከበራችሁ የአዲስ አበባና በመላው ኢትዮጵያ የምትገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ፤ ወላጆች ፤ቤተሰቦች ይህ የምነግራችሁ ነገር ተራ አሉባልታ አለመሆኑን በተለያየ ጊዜ ለማሳያ የተለጠፉ መረጃዎችን አይታችሁ መፍረድ ትችላላችሁ፡፡ የተከበራችሁ ተማሪዎች ወላጆች እና በዚህ ጉዳይ እንደ እኔ የተንገበገባችሁ ሁሉ አደጋ ላይ ነን፡፡በተለይ ድርጅቶቹ ነገሩን እንዲሰሩላቸው የመረጧቸውን ሰዎች ለመግዛት እያወጡት ያለው ምራቅ የሚያስውጥ ገንዘብ በየክፍሉ ከሚያስተምሩላቸው መምህራንና ከተባባሪ የትምህርት ቤት አስተዳደሮችም አልፎ እስከ ላይ ድረስ ኪስ ሳያሞቅ አልቀረም፡፡ የእናንተ እርዳታ ቆፍጠን ያለ ውሳኔ ያስፈልጋል፡፡

ተማሪዎችና ወላጆች በአዲስ አበባ በብዛት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ላይ ቢያነጣጥርም ነገሩ በኦሮሚያ፣ በአማራና በሌሎች ክልልሎች ግን እስከ ታችኛው ክፍል ድረስ በስነተዋልዶ፣በጸረኤድስና በስርአተ ጾታ ሰበብ የግብረሰዶማዊነት ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን ሳረጋግጥላችሁ በአውነት ነው፡፡ ስለዚህም ተማሪዎች፣ ወላጆች የሚመለከታችሁ ሁሉ አይናችሁን ወደ ትምህርት ቤት አንሱ!! ተማሪዎች በገንዘብ በተደለሉ ግለሰቦች እተረጨባቸው ያለውን መርዝ አስቁሙ፡፡በተለይ በአሁኑ ወቅት አስረኛና አስራ ሁለተኛ ክፍሎች ትምህርት በጨረሱበት ጊዜ እየሆነ ያለው ተማሪዎችን በክረምት ትምህርትና ስልጠና ሰበብ ለዚህ ተግባር እየመዘገቡ ያሉ ትምህርት ቤቶች እንዳሉ ልነግራችሁ እችላሁ፡፡ሴቭ ዘቺልድረን በክረምት ወራት ትምህርት ቤቶችን በክረምት ትምህርት አሳቦ በመከራየት የሰዶማዊነት ትምህርት ሊሰጥ መሆኑን ስነግራችሁ ያለምንም ጥርጥር ነው፡፡አስካሁን የግብረሰዶማዊነት ትምህርት ሁለተኛ ዙር ለመስጠት ፈቃደኛ ሆነው ካሉ ትምር ቤቶች መካከል፡ ሚኒሊክ፤መድሀኒአለም፣ባልቻ አባነፍሶ፣ኤስኦኤስ፣ህዳሴ፣አፍሪካ ህብረት፣የካቲት 23 ፣መነን፣አየርጤና እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ይህ ነገር ሀሰትነው ብላችሁ የምትጠራጠሩ ከሆነ በተለይ ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተለይ ወላጆች አንደኛ በየክፍለ ከተማ የሚገኙ የስርአተ ጾታ ሀላፊዎችን ፣በአዲስ ትምህርት ቢሮ በተለይ አቶ ሀይለ ስላሴ የተባሉ የስራ ሀላፊን መጠየቅ ይቻላል፡፡በተጨማሪም በኢትዮጵያዊነት ድምጽ ላይ የተለጠፉ የመማሪያ ሰነዶችን ማየት ይቻላል፡፡ወላጆች ልጆቻችሁን አድኑ!!

የተከበራችሁ ተማሪዎች በየትኛውም አጋጣሚ በትምህርት ቤትም ሆነ ከትምህርት ቤት ውጪ በስነተዋለዋልዶና ስርአተ ጾታ ስም የሚሰጠውን ፍጹም የግብረሰዶማዊነት ትምህርት አንማርም ንድትሉ ብትሉም እራስን የማዳንና የመከላከል ተግባርና እርምጃ መሆኑን አውቃችሁ በዚህ ተግባር ላይ የተሳተፉ መምህራንም ሆኑ በገንዘብ ተደልለው ሊያስተምሩ የተዘጋጁ ተማሪዎችን አምርራችሁ እንድታገሉ ሁላችንም በፈጠረን አምላክ ስም እለምናቿለሁ!!

ኢትዮጵያ የግብረሰዶማዊነት መቀበሪያ ትሆናለች እንጂ መቼም ከግብረሰዶማዊነት ጋር አትጋባም!!
ጭንቀት ካደረበት መምህር

Thursday, April 23, 2015

የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያቀረቡት አስቸኳይ ጥሪ

April 23,2015

የተከበራችሁ ወገኖቼ፤ ከሰላሳ በላይ የሆኑ ወገኖቻችን አይ ሲስ በተሰኘ ህሊና ቢስ፣ ፀረ-ሰው እና ፀረ-ስልጣኔ ቡድን በሊቢያ በአሰቃቂ ሁኔታ የመገደላቸው መርዶ ከትናንት ወዲያ ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓም ደርሶን ኢትዮጵያዊያን በያለንበት በመሪር ሀዘን ውስጥ ነን። ዛሬ “እግዜር ያጥናህ” ወይም “እግዜር ያጥናሽ” የሚባል ሰው የለም። ሁላችንም ሀዘንተኞች ነን። ካጣናቸው ቁጥራቸው በብዙ እጥፍ የሚበልጥ ወገኖቻችን አሁንም በአራዶች መዳፍ ውስጥ መሆናቸው ሀዘናችን እጅግ የበረታ ያደረገዋል። ቁጥራቸው በትክክል የማይታወቅ ሆኖም በሺህ የሚገመቱ ኢትዮጵያዊያን ዛሬም ሊቢያ ውስጥ ናቸው። በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን አሁንም ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ናቸው። ሌሎች በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ደግሞ በየመን ከሰማይም ከምድርም በቦንብና በጥይት እየተማገዱ ነው።
ለምንድነው ኢትዮጵያዊያን እንዲህ እሳት ውስጥ ለመማገድ የምንደፍረው? መልሱ ግልጽ ነው። አገር ውስጥ ተስፋ የለም፤ ወያኔዎች ተስፋችንን አጨለሙት። ከሳዉዲ በመከራ የተመለሱ ወንድሞቻችን ናቸው በሊቢያ በኩል ለመሰደድ ሲሞክሩ በአይ ሲስ ተይዘው የታረዱት። ወያኔዎች አገራችንና ክብራችን ዘረፉን። ወያኔዎች ስብዕናችንን ገፈፉን።
የዘመኑ ጥቂት የህወሓት ቱጃሮች ፎቆችን እየገነቡ በነሱ መጥገብ እኛ እንድናገሳላቸው ይፈልጋሉ። የኢትዮጵያ ሕዝብ መራቡ፣ መታረዙ፣ መደህየቱ እውነት ነው፤ ሆኖም ግን “ተራብኩ”፣ “ታረዝኩ”፣ “ደኸየሁ” ብሎ መናገር አይችልም። እውነት መናገር ያስቀጣል፣ ያስወነጅላል። በፍርደ ገምድል ችሎት እውነት መናገር “ሽብርተኛ” ያስብላል። እስር ቤቶችን የተሞሉት ለእውነት፣ ለፍትህ፣ ለነፃናትና ለእኩልነት በቆሙ ሰዎች አይደለምን?
በአይ ሲስ ያሳረደን ማነው? መልሱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግልጽ ነው። ያዋረደን፣ በአይ ሲስ ቢላዋ ያሳረደን ህወሓት ነው። እንደ አገርና እንደ ሕዝብ የደረሰብን ውርደት የትም ብንሄድ የምናመልጠው አልሆነም። በአገር ውስጥ የደረሰብንን ውርደት ለማምለጥ ስንሰደድ ውርደት ተከትሎን ይመጣል።
ወገኖቼ፤ ለኛ ለኢትዮጵያዊያን ከኢትዮጵያ የተሻለች አገር ሊኖረን አይችልም። ዛሬ የመሸሻ ጊዜ አይደለም። አገራችንን ከወያኔ ነጥቀን፤ በአገራችን ኮርተን በሰላም መኖር እንሻለን። ይህ መብታችን ነው። አገራችን የኛ ነች። አገራችን የጥቂት ወያኔዎች መፈንጫ አይደለችም።
ወገኔ፤ ዛሬ ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓም በአርበኖች ግንቦት 7 ስም የማደርግልህ ጥሪ አድምጠኝ። በሀይማኖት፣ በብሔር፣ በጾታ ልዩነት ሳታደርግ ዛሬ በአንድነት እንደተሳህ አንድነትህን እንደጠበቅህ ቀጥል። አንድነትህን ለመሸርሸር ወያኔ የማይፈነቅለው ድንጋይ አይኖርም፤ ለወያኔ ዱለታ ጆሮህን አትስጥ። የወያኔ አገዛዝ እንዲያበቃ በአንድነት ተነስ። ዛሬ የጀመርከው ትግል እዳር ሳይደርስ እረፍት የለንም።
አርበኞች ግንቦት 7፣ ከትግራይ፣ ከኦሮሚያ፣ ከአፋር፣ ከኦጋዴን፣ ከጋምቤላ፣ ከቤሻንጉል ድርጅቶች ጋር በመጣመር የአገር አድን ኃይል የመገንባት ሥራውን እያጠናቀቀ ነው። እኛ ልጆችህ በብሔርም ሆነ በሀይማኖት ሳንከፋፈል፤ ከትግራይ እስከ ኦጋዴን፤ ከአፋር እስከ ጋምቤላ ሁሉንም የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ባካተተ ስብስብ ውስጥ አብረን ህወሓትን እየታገልን ነው። ይህ ትግል ግን የአንተ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል ነው። የትግሉም የአገሪቷም ባለቤት አንተ ነህ። ስለሆነም ተነስ! “እንቢኝ” በል። ዘርፈ ብዙ የትግል ስልቶችን በመጠቀም ወያኔን አዳክም። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! በትግልህ ፍሬ የአገርህ ባለቤት ሁን።
የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ሆይ!እናንተ የሕዝብ አካላት ናችሁ። የደረሰብንን ብሔራዊ ውርደት እያያችሁ፤ እሮሮዓችን እየሰማችሁ በሕዝብ ላይ መተኮስ በራሳችሁ ጭንቅላት ላይ መተኮስ ማለት መሆኑን ለደቂቃ እንኳን አትዘንጉ። ይልቁኑ ዛሬውኑ ነፃነትና ፍትህ ከጠማው ወገናችሁ ጎን ቁሙ።
የኢትዮጵያ ወጣቶች፤ የወጣትነት የፈጠራ ችሎቻችሁ መፈተኛው አሁን ነው። ለእያንዳንዱ ጥቃቅን ጉዳይ መመሪያ እስኪሰጣችሁ አትጠብቁ። እያሰላችሁ፣ እያጠናችሁ፣ እያደባችሁ፣ ወያኔን ታገሉ።
የታፈረች፣ የተከበረችና የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን እናደርጋለን።
ብርሀኑ ነጋ
የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር
ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓም

ኢትዮጵያኖቹ በ ISIS ሲገደሉ በግድ እንዲያይ የተደረገው ታዳጊ ህፃን

April 23,2015

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2007(ኤፍ.ቢ.ሲ) የ16 ዓመቱ ኤርትራዊ ስደተኛ ናኤል ጎይቶም የኤይ ኤስ ታጣቂዎች ኢትዮጵያውያኑን እና ኤርትራውያኑን በግፍ ሲቀሉ እና ሲረሸኑ እንዲመለከት መደረጉን ይናገራል።

ታዳጊው ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ታይምስ ከተሰኘው ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ እንደተናገረው፥ ታጣቂው የአይ ኤስ ቡድን ይህን አሰቃቂ ድርጊት አስገድዶ እንዲመለከት አድርጎታል።

ይህ አሰቃቂ ድርጊት ከተከናወነ ከጥቂት ቀናት በኋላ ከሌሎች አራት ኤርትራውያን ጋር በሊቢያ ታስረውበት ከነበረው ካምፕ ማምለጣቸውንም ተናግሯል።

በእዚህ አረመኔ ቡድን ከመቀላት ለማመለጥ መሞከር አዋጭ መሆኑን የተናገረው ናኤል፥ ከቡድኑ ካምፕ ካመለጡ በኋላ እርዳታ የሚያገኙበት ስፍራ እስኪደርሱ ድረስ ለአራት ቀናት ያህል በሊቢያ በረሃ ውስጥ መጓዛቸውን ይተርካል።

ከአንድ ወር ለሚበልጥ ጊዜ በፅንፈኛው አይ ኤስ ቁጥጥር ስር በነበሩበት ወቅትም “ከመሞት እና እስልምናን ከመቀበል የቱን ትመርጣላችሁ”? የሚል ምርጫ እንደተቀመጠላቸው እና በወቅቱ ሙስሊም መሆንን እንደሚመርጡ እና እንዋጋላችኋለን ሲሉ መናገራቸውንም ያስታውሳል ታዳጊው።

ናኤል ኢትዮጵያውያኑ እና ኤርትራውያኑ በአይ ኤሴስ ከተያዙ በኋላ በአንድ ትልቅ ጉድጓድ መቀመጣቸውንም ተናግሯል ።

ከእለታት በአንዱ ቀንም 47 ያህል ኢትዮጵያውያንን እና ኤርትራውያንን ጥቋቁር እና ብርቱካናማ ልብሶችን አልብሰው ወደ ሜዲትራኒያን ባህር ዳርቻ እንዲሁም ሊቢያ በረሃ እንደወሰዷቸው እና እሱም ይህን ይመለከት ዘንድ አብሯቸው እንደወሰዱት ከዚያም ይህን ጭካኔ የተመላበት ድርጊት እንዲመለከት መደረጉንም ይናገራል።

ታዳጊው በአይ ኤስ እንዴት ተያዘ?

ናኤል እንዴት በፅንፈኛው የአይ ኤስ እጅ እንደተያዘም ያብራራ ሲሆን፥ 10 ኤርትራውያን ሴቶችን እና 8 ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 61 ከሚሆኑ ስደተኞች ጋር ከአንድ ወር በፊት በሱዳን አድርግው ደቡብ ሊቢያን ሲያቋርጡ በአይ ኤስ ታጣቂዎች መያዛቸውን እና ሀይማኖት ነክ ጥያቄዎች መጠየቃቸውን ያስታውሳል።

ከመካከላችሁ ማን ነው ሙስሊም? ብለው እንደጠየቋቸው ነገር ግን ክርስቲያን የሆንነው መስቀል እና ክርስቲያን መሆናችንን የሚያሳዩ መንፈሳዊ ምስሎችን በመያዛችን በወቅቱ ማንነታቸንን መደበቅ አላስቻለንም ብሏል።

በአይ ኤስ ካምፕ ውስጥ ከ300 እስከ 400 የሚሆኑ የፅንፈኛው ቡድን አባላት የሚገኙ ሲሆን፥ ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን ተይዘው በካምፑ ውስጥ እንዲገቡ ሲደረግ፣ ሶማሊያውያን ግን መሄድ ወደፈለጉበት እንዲጓዙ ይፈቀድላቸው እንደነበር ይተርካል።

ናኤል ኤይ ኤስን አስቀድመው የተቀላቀሉ እና ለሽብር ቡድኑ የሚዋጉ ሶስት ኤርትራውያን የነበሩ ሲሆን፥ እነሱ ይረዱናል ብለን ስንጠብ ግን ስለኛ ምንም ስሜት አልተሰማቸውም ሲል ታሪኩን ያወጋል።

ናኤልን ጨምሮ ዮሃንስ መብራቱ፣ ቶማስ ገብረህይወት፣ አብርሃም ናይዝጊ፣ አማን ሺሻይ የተሰኙ ታዳጊ ኤርትራውያንም ከአይ ኤስ ካመለጡ እና ከአራት ቀናት አድካሚ የበረሃ ጉዞ በኋላ አንድ ሱዳናዊ አግኝቷቸው በሰሃራ በረሃ በርካታ ስደተኞች ወደሚገኙበት የስደተኞች መጠለያ እንዳደረሳቸው ገልጿል።

ታዳጊው ህይወቱን ማትረፍ ቢችልም ባየው እና በደረሰበት መከራ እና እንግልት ሳቢያ ውስጡ መጎዳቱን ነው የተናገረው።

አይ ኤስ ከ30 ደቂቃ በማያንስ የተንቀሳቃሽ ምስል (ቪዲዮ) በአለም ዙሪያ ባሰራጨው መልዕክቱ 30 ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን ንፁሃን ዜጎችን ገሚሱን በሜዲትራኒያን ባህር ዳርቻ ሲቀላ፥ ገሚሱን ደግሞ በሊቢያ በረሃ በጥይት በመተኮስ ሲገድል ማሳየቱ ይታወሳል።
ምንጭ፦ http://www.ibtimes.co.uk

ሽብርን በማሸበር!! ሰማያዊ ፓርቲ “ሊታረድ ነው”

April 23,2015

tplf and isis
* ሕዝብ ዋስትናና መተማመን አጥቷል
ረቡዕ ዕለት ኢህአዴግ በጠራው ሰልፍ ዜጎች ስሜታቸውን ሲያንጸባርቁ የተሰጣቸው ምላሽ ሽብርን በአሸባሪነት አመጣጥኖ የመመለስ አይነት እንደሆነ ተጠቆመ፡፡ የሰላማዊ ሰልፉ አጠቃላይ ገጽታና የሕዝብ ስሜት በአገሪቱ የዋስትና ማጣት ስሜት እየገዘፈ መሄዱን የሚያሳይ ሆኗል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ሊታረድ ነው፤ በሰሜን አሜሪካ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ ባሉት ይልቃል ላይ እዚያው እንዲቀሩ ተጽዕኖ ይደረጋል ተብሏል፡፡
በአይሲስ የታረዱትና የተረሸኑትን “ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን እያጣራሁ ነኝ” ሲል የነበረው ኢህአዴግ እንዴት እንዳጣራ ለሕዝብ ባያሳውቅም ወዲያው ሕዝባዊ ለመሆን በመመኘት በአገሪቷ ላይ የሐዘን ቀን ከማወጅ በተጨማሪ ሕዝቡ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲወጣ ጥሪ አድርጎ ነበር፡፡ አንድ የጎልጉል አስተያየት ሰጪ “ሕዝቡ ለ24 ዓመታት በሐዘን ላይ ነው ሦስት ቀንማ ምን አላት” በማለት እንደተሳለቁት የተሰጠውን ትዕዛዝ ተከትሎ ሕዝቡ ገና ከጠዋቱ ጀምሮ ተንቀሳቅሷል፡፡ በየቦታው የኢህአዴግ ካድሬዎችና ፖሊሶች መሰለፍ የሚገባውን ከማይገባው ለመለየት ሙከራ ቢያደርጉም በእጅጉም አልተሳካላቸውም፡፡
ይህንን ሰላማዊ ሰልፍ ከሕዝቡ በተጨማሪ ኢህአዴግ የደፈነባቸውን የፖለቲካ ምህዳር በራሳቸው እያሰፉ የሚንቀሳቀሱት ጥቂት የተቀናቃኝ ፓርቲዎች ድጋፍ ሰጥተውታል፡፡ መድረክ እና ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፉን እንደሚያከብሩ ድጋፍም እንደሚሰጡ በይፋ ባወጡት መግለጫዎች አስታውቀው ነበር፡፡ ይህም በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚደረገውን ሽብር የሚቃወሙ መሆናቸውን ለሚያሸብራቸው ኢህአዴግ በአገራዊ አጀንዳ ላይ አብረው እንደሚቆሙ ኅብረት ያሳዩበት እንደሆነ በብዙዎች ተስተውሏል፡፡
ይሁን እንጂ ሰልፉ ኢህአዴግ ቀደም ሲል በቀላጤው ሬድዋን አማካኝነት የሞቱት “ኢትዮጵያውያን ስለመሆናቸው” ዕውቅና ነፍጎ በሰጠው መግለጫ የተቆጣው ሕዝብ የሰልፉን ዓላማ ኢህአዴግ ከተመኘውና ከፈለገው ውጪ አድርጎታል፡፡
ከለቅሶ ቤት ጀምሮ “መንግሥትን አንፈልግም” በማለት ቁጣ የተሰነዘረ ሲሆን አብዛኞች ግን “መንግሥት የለንም” ሲሉ ድርብ ሃዘናቸውን ገልጸዋል፡፡
ገዳዩ ባለካራው አሸባሪ ድርጅት ለፈጸመው ወንጀል ይሉኝታ ሳይዘው እንደ ታላቅ ገድል በቪዲዮ አስደግፎ ሲያቅራራ ዓለም ምስሉን ባደባባይ አይቷል፡፡ ሚዲያዎችም ተቀባብለውታል፤ መንግሥት ነን ብለው የተቀመጡት እነሬድዋን እንደ አንድ ሰው ሚዲያዎችን ተከታትለው መረጃውን አግኝተውታል፡፡

ፎቶ Addis Fortune
በኢህአዴግ ቋንቋ “ህገወጥ” የሚባሉት ሥራ ፈላጊዎች ድንበር አቋርጠው ሲወጡ ህጋዊ የጉዞ ሰነድ የላቸውም፡፡ ኢህአዴግ በሊቢያ የቅርንጫፍ ጽ/ቤት የለውም፡፡ አፈቀላጤውና “የፌስቡኩ ሚ/ር ዶሮ እንኳን የሞተች ሳይመስላቸው “እውነት ኢትዮጵያውያን ሞተው እንደሆነ እናጣራለን” በማለት የተናገሩት ከካራም በላይ የሕዝብን ስሜት ያረደ ስለመሆኑ አብዛኞች ይስማማሉ፡፡ የረቡዕ ተቃውሞና ቁጣም ብዙ የተከማቹ መነሻዎች ቢኖሩትም አስኳሉ ጉዳይ ግን ክህደቱ እንደሆነ ይታመናል፡፡
“ያገር አንበሳ የውጭ ሬሳ”፣
“እግዚአብሔር ነው ለእኛ ኃይላችን አንመካም በጉልበታችን”፣
“ደማችን ይመለስ፣ ይታፈስ”፣
“አቤት ቆሻሻ”፣
“አይሲስ በካራ እናንተ በዱላ”፣
“አትመጣም ወይ መንጌ አትመጣም ወይ”፣ …
የሚሉ መፈክሮችን በኢህአዴግ ቁልፍ የአስተዳደር ቦታዎች አጠገብ ሰልፈኞች ሲልፉ ማሰማታቸውና በተለይ “ደማችን ይታፈስ” ሲሉ የጮኹት ዛሬ የተወለደ መፈክር አይደለም፡፡ ኢትዮጵያውያን ስለ አሸባሪ ከመስማታቸው ውጪ አሸባሪ መሆኑ በታወቀ ድርጅት ኢትዮጵያ ጥቃት ደርሶባት አያውቅም፡፡ ዊኪሊክስ ምስጋና ይድረሰውና ማን አሸባሪ እንደሆነ፣ ማን እንደሚያፈነዳ፣ ማን አንደሚያስፈነዳ፣ ማን ቀጣሪ እንደሆነ፣ በግልጽ ታክሲ ውስጥ ማን ቦምብ እንደሚያፈነዳ በግልጽና ማስተባበያ ሊቀርብበት በማይችልበት መልኩ አስቀምጦታል፡፡ ሐቁ ይህ ይሁን እንጂ ኢህአዴግ ካዝናው በጎደለ ቁጥር ኢትዮጵውያንን እየማገደ ከአሸባሪዎች ጋር የገባው እሰጥ አገባ የሰላማዊ ነዋሪዎችን የዋስትና ስሜት ከድህነቱ ጋር አብሮ ሰልቦታል፡፡
ሚያዚያ 26፤ 2006ዓም (ሜይ 4፤ 2014) አንድነት በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ “ለሥራ ብለን አባል አንሆንም” እያሉ ያዜሙት ሰላማዊ ሰልፈኞች በገሃድ እንዳስታወቁት የስደቱ ምንጭ ድህነት ነው፡፡ ጥቂቶች ሲበሉ አብዛኞች የገንዳ ውስጥ ትራፊ እንኳን ስላረረባቸው ነው፡፡ መረራ ጉዲና እንዳሉት “የራበው ሕዝብ መሪዎቹን ይበላል” ነውና ነገሩ ይህ ሕዝብ ወደ በቀል ከመሄዱ በፊት ቢሳደብ በምን መስፈርት ጥፋተኛ ይባላል? አረመኔያዊ በሆነ ስሜት ሊቀጠቀጥና አስፋልት ላይ እንዲጎተት ይፈረድበታል? ስለምንስ በጅምላ ይታሰራል? እንዲህ ያለው ሽብርን ባሸባሪነት የመቃወም ስሜት ቁጣውን ያበርደዋል ወይስ ይጨምረዋል? ሕዝብ ስሜቱን እንዲገልጽ ተጋብዞ የተሰማውን ስሜት ሲገልጽ መቀጥቀጥና መጨፍጨፍ ካራን በዱላ የመቀየርና አይሲስ የሚለውን ስም ኢህአዴግ በሚለው ለውጦ ሕዝብን ከማሸበር በምን ይተናነሳል? ሕዝብን ለተቃውሞ ውጡ ብሎ ጋብዞ በጭስ እያፈኑ እንደ እባብ መቀጥቀጥ የቦታ ልዩነት ካልሆነ በስተቀር አዲስ አበባ ላይ የተቀጠቀጠው ሕዝብ በአሁኑ ጊዜ ሊቢያ ከታሰሩትና ከታገቱት በምን ይለያል?
ሁልጊዜ እንደሚባለው የማስተዋልና የሕዝብን ስሜት ጠብቆ የመጓዝ ነገር ለእኛ አገር እርም ሆኗል፡፡ ከዛሬ 24ዓመት ጀምሮ የሕዝብን ብሔራዊ ስሜት፣ ብሔራዊ ኩራት፣ ብሔራዊ ማንነት፣ የእምነት መከባበር፣ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ቀስ በቀስ ሥሩን እየበጣጠሰ በቂምና በቁርሾ በመተካት እዚህ ያደረሰን ኢህአዴግ ትላንትና የተመሠረተውን የሰማያዊ ፓርቲ ለዚህ ዓመጽ ተጠያቂ ማድረጉ ከፌዝ በላይ ፌዝ መሆኑን አብዛኛዎች ተናግረዋል፡፡ ሌሎች ፓርቲዎችን ቅርጫ ሲያደርገው እንደጸና የቀረውን የሰማያዊ ፓርቲን ኢህአዴግ ሊያርደው ቢላውን ስሎ መጨረሱን በቀላጤው አማካኝነት ይፋ አድርጓል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የፓርቲው መሪ በሰሜን አሜሪካ በሥራ ጉብኝት ላይ በሚገኙት ይልቃል ጌትነት ላይ ተጽዕኖ በማድረስ እዚያው እንዲቀሩ የማድረጉን ሥራ ኢህአዴግ ከወዲሁ መጀመሪ ጎልጉል የደረሰው መረጃ ያመለክታል፡፡ ኢህአዴግ ተቀናቃኞቹን ከፊቱ በማራቅ የተካነ እንደመሆኑ እምቢ ያሉትን እስር ሲወረውር ሌሎችን አስፈራርቶ ወይም አበስ አድርጎ አገር ለቅቀው በመሄድ ከፊቱ እንዲርቁ ሲያደርግ የኖረበት አሠራር ነው፡፡
መቼ እንደሚባረሩና ከኢህአዴግ ጋር ያላቸው የሥራ ጊዜ እስከ መቼ እንደሚዘልቅ ያላወቁት አቶ ሬድዋን ሰማያዊ ፓርቲን የማረዱን ሥራ አረጋግጠዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በጉዳዩ ላይ መግለጫ እንደሚያወጣ የሚጠበቅ ቢሆንም የአፈቀላጤ ሬድዋን ዛቻ “በሉ ተብለው” የታዘዙበት እንደሆነ ግን ግልጽ ነው፡፡

ከጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የተወሰደ

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

April 23,2015
መንግስታዊ ሽብር የህዝብን ቁጣ ያባብሳል እንጂ መፍትሔ አይሆንም!
ዛሬ ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም የተወካዮች ም/ቤት የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፉን እንደሚደግፍ እና ደጋፊዎቹና አባላቱ በሰልፉ ላይ እንዲገኙ በትናንትናው እለት ጥሪ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡ ይህን ተከትሎም እንደማንኛውም ዜጋ በሰልፉ ሊገኙ የሄዱ የፓርቲው አመራሮች እና አባላት ገና ወደ መስቀል አደባባይ ከመድረሳቸው በፊት እየታደኑ የታሰሩ ሲሆን የተቀሩት ደግሞ ሰልፉን ለመሳተፍ በቦታው ተገኝተው ነበር፡፡
ሰልፉ በርካታ ዜጎች በቁጭት እና በሃዘን የተገኙበት መሆኑንም ሁሉም ሰው የሚገነዘበው ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ የሰልፉ ተካፋዮች ተቃውሟቸውን ንግግር በሚያደርጉ ሰዎች ላይ በማሰማት ገለፁ፡፡ ይህን ተከትሎም ፕሮግራሙን በችኮላ ያጠናቀቀው መንግስት ሰልፈኛው እንዲበተን መልዕክት በማስተላለፉ የተቆጡ ዜጎች ጋር ግጭት ፈጠረ፡፡
ለህዝብ ቁጣ እና ተቃውሞ ክብር እና ተገቢውን መልስ የማይሰጠው መንግስት በዜጎች ላይ የወሰደው የጭካኔ እርምጃ በእጅጉ የሚያሳዝን እና በጥብቅ ሊወገዝ የሚገባ ነው፡፡ በእርግጥ ስርዓቱ ለዚህ መሰሉ የሀይል እና የጭካኔ እርምጃ አዲስ ባይሆንም የአሁኑ ግን የተለየ የሚያደርገው ማንም ሰው ሊጠብቀው እና ሊያስበው በማይችለው መልኩ በወገኖቻችን ሞት እና በመንግስት ቸልተኝነት ልቡ ያዘነውን እና ተቃውሞ በማሰማት ላይ የነበረውን ህዝብ "ሰልፍ አልቋል ተበተኑ" በሚል ሰበብ የወሰደው እርምጃ በሀዘናችን ላይ ሀዘን መደረቡ ነው፡፡
በእለቱ ከተፈፀሙት አስከፊ ሁኔታዎች የባሰው ግን መንግሰት የወሰደውን እርምጃ ለመካድ እና በህዝብ የደረሰበትን ከፍተኛ ተቃውሞ ለመደበቅ የህዝብን ቁጣና ሀዘን የሰማያዊ ፓርቲ የፖለቲካ አጀንዳ እንደሆነ አድርጎ በኮምኒኬሽን ፅህፈት ቤት በኩል የወጣው መግለጫ ይዘት ነው፡፡ በዚህ መግለጫ እንደተገለፀው በመስቀል አደባባይ የተገኙ ዜጎች ማሰብ የማይችሉና በነሲብ እንደሚነዱ ሁሉ "ሰማያዊ ፓርቲ ለአመፅ አነሳሳቸው" ማለት ሀዘን የገባውን እና የተቆጣን ህዝብ መሳደብ ነው፡፡ ህዝብን መናቅ ነው፡፡ ከአንድ መንግስት ነኝ የሚል አካል የሚጠበቀውን ኃላፊነት ከመውሰድ እና ተቃውሞዎችን በአግባቡ ከመፍታት ጋር የማይተዋወቀው የኢህአዴግ ስርዓት ቁጣቸውን በገለፁ እና መንግስት በዜጎች ላይ በተደጋጋሚ የሚያሳየውን ቸልተኝነት በተቃወሙ ዜጎች ላይ የወሰደው የጭካኔ እርምጃ ሳያንስ ከአንድ የፖለቲካ ድርጅት ጋር አዛምዶ ተቃውሟቸውን ማጠልሸት በፍፁም ተቀባይነት የሌለው አፀያፊ ተግባር ነው፡፡ መንግስት ነኝ ከሚል አካል በፍፁም የማይጠበቅ ስህተት ነው፡፡ አዲስ አለመሆኑ እና መደጋገሙ ደግሞ እጅግ እንድናዝን ያስገድደናል፡፡
ከራሱ ታሪክ እና ተሞክሮ መማር ያልቻለው የኢህአዴግ ስርዓት በተደጋጋሚ የሚፈፅማቸው የመብት ጥሰቶች እና ተቃውሞን በሀይል ለመፍታት የሚወስደው እርምጃም ችግርን፣ ቁጣን ከማባባስ በስተቀር መፍትሔ ካለመሆኑም በላይ በሰላማዊ መንገድ የስልጣን ሽግግር እንዲካሄድ እና የአመፅና የጦርነት አዙሪት እንዲከስም ጭቆናን ተቋቁመን የምናደርገውን ትግል ለማኮላሸት መሞከሩ የከፋ አደጋ እንዳለው ለማስገንዘብ እንወዳለን! የህዝብን ጥያቄ ያለፍርሃት በማንሳት እና ተቃውሞ በማሰማታችን እየደረስብን ያለውን አፈና ችለን በምናደርገው ትግል ውስጥ እንዲህ መሰሉ የስም ማጥፋት ዘመቻና የፈጠራ ክስ ይበልጥ ትግሉን እንደሚያጠናክረውም እናስገነዝባለን!
በተያያዘም ዛሬ በተጠራው ሰልፍ ለመካፈል ሲሄዱ የታሰሩ፤ መንግስት በወሰደው የሀይል እርምጃ የታሰሩ እና የታሰሩትን ለመጠየቅ እስር ቤት ሄደው በዛው የታሰሩ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው (እነዚህ እስካሁን በእርግጠኝነት ማጣራት የቻልነው ብቻ መሆኑ ይታወቅ)፡-
1- ወይንሸት ሞላ - የድርጅት ጉዳይ አባል (ወደ ሰልፉ በመሄድ ላይ ሳለች ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስጢፋኖስ አካባቢ ተይዛ ታስራለች)
2- ጠና ይታየው - የ2007 ሀገራዊ ምርጫ የተ/ም/ቤት ተወዳዳሪ (በሀይል እርምጃው ወቅት ተደብድቦ የታሰረ)
3- ኤርምያስ ስዩም - የፓርቲው አባል (በሀይል እርምጃው ወቅት ተደብድቦ የታሰረ)
4- ማስተዋል ፈቃዱ - የፓርቲው የቂርቆስ ክ/ከተማ አስተባባሪ (በሀይል እርምጃው ወቅት ተደብድቦ የታሰረ)
5- ዳንኤል ተስፋዬ - የፓርቲው የጉለሌ ክ/ከተማ አስተባባሪ (በሀይል እርምጃው ወቅት ተደብድቦ የታሰረ)
6- ቴዎድሮስ አስፋው - የአዲስ አበባ ምርጫ ጉዳይ ኮሚቴ ህ/ግንኙነት (በሀይል እርምጃው ወቅት ተደብድቦ የታሰረ)
7- እስክንድር ጥላሁን - የ2007 ሀገራዊ ምርጫ የተ/ም/ቤት ተወዳዳሪ (የታሰሩትን ለመጠየቅ ምግብ ይዞ በሄደበት የታሰረ)
8- ይድነቃቸው አዲስ - የ2007 ሀገራዊ ምርጫ የተ/ም/ቤት እጩ ተወዳዳሪ (የታሰሩትን ለመጠየቅ ምግብ ይዞ በሄደበት የታሰረ)
በሌላ በኩል እነዚህ አባላቶቻችን በታሰሩበት እስር ቤቶች በርካታ ወጣቶች ታስረው ይገኛሉ፡፡ በስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ - ካሳንቺዝ፣ አምቼ ፖሊስ ጣቢያ - ቦሌ፣ በአድዋ የካ ንዑስ ፖሊስ ጣቢያ - አዋሬ፣ በየካ ፖሊስ መምሪያ - ኮተቤ፣ ኮልፌ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ፣ ላንቻ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ - ቂርቆስ እና በሌሎች ፖሊስ ጣቢያዎች በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መታሰራቸውንም ለማረጋገጥ ችለናል፡፡
በመሆኑም መንግስት ራሱ በጠራው ሰልፍ ላይ በነቂስ ወጥተው ተቃውሟቸውን በገለፁ ዜጎች ላይ የወሰደውን የጭካኔ እርምጃ አጥብቀን እያወገዝን የታሰሩት ዜጎችም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ባስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን፡፡
በሰልፈኞች ላይ እንግልት፣ እስርና አሰቃቂ ድብደባ የፈፀሙ እና ትእዛዝ ያስተላለፉ በሙሉ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጥይቃለን! የመንግስት ጽ/ቤት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ባወጣው የፓርቲያችንን ስም የሚያጠፋ እና የሚወነጅል ብሎም የህዝብን ሀዘንና እና ቁጭት የሚያባብስ መግለጫም በእጅጉ ያስቆጣን መሆኑን እያሳወቅን ይህን በፓርቲያችን ላይ የተቃጣ ህገወጥ ውንጀላና የህዝብን ብሶት እና ተቃውሞ ያቃለለ ድርጊት በቀላሉ የሚታለፍ አለመሆኑን ማስገንዘብ እንወዳለን!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ሚያዝያ 14 2007 ዓ.ም
አዲስ አበባ

Wednesday, April 22, 2015

“ETHIOPIA, A COUNTRY WITHOUT A GOVERNMENT”

April 22, 2015

“Ethiopia, a country without a govrnment!” The protest slogan shouted out by Ethiopan mourners in the streets of Addis Ababa yesterday following the massacre of Ethiopian christinas in Libya

SMNE Press ReleaseProtest in Addis Ababa against ISIS and their own government
On Sunday, April 19th, the Islamic State (IS) released a video depicting the gruesome killing of Ethiopian Christians in Libya. It is said to have been carried out at two separate locations; one where they were shot in the head and the other where they were decapitated. It has been upsetting for anyone to see; however, it has been especially heart-rending to the people of Ethiopia.
Mr. Obang Metho, the Executive Director of the Solidarity Movement for a New Ethiopia (SMNE), is calling onProtest in Addis Ababa against the killing of Ethiopians in LibyaEthiopians from every ethnicity, religion, region and political viewpoint to come together in unity to mourn for these Ethiopians who have lost their lives and to find ways to protect the many others who remain in dangerous situations.
The SMNE is a non-violent, non-political social justice movement of diverse Ethiopians whose work has largely focused on the widespread human rights crimes and systemic injustices perpetrated by the current regime of Ethiopia against its own people. Due to massive outflows of Ethiopians to other countries, the SMNE has also advocated for the countless refugees and migrant workers throughout the world. The SMNE is located outside of Ethiopia due to extreme restrictions on such work within the country.
Mr. Metho states:
Ethiopians all over the world are grieving the loss of these brave Ethiopians, who were willing to stand up for their faith as Christians despite the threat of death from people who despise their own God-given humanity—for who else could commit such evil?
No words can describe the shock, grief, and compassion so many of us feel at this time for the families and friends of those so coldly murdered. We give our heartfelt condolences and wholly condemn these acts. We stand strong together as one Ethiopian family, no matter whether or not we share the same religion, ethnicity, political view, age, gender or any other characteristics; for, we are first and foremost human beings, created with intrinsic worth and dignity by an Almighty God. The pain of this tragedy should never let us forget our shared humanity simply because some have descended into such moral depravity. God calls us to be above this.
In the last weeks and month, Ethiopians fleeing their homes due to the threat of arrest, persecution, human rights abuses, land evictions, repression, ethnic apartheid policies, endemic poverty and those who are desperately seeking a better life, have encountered terrifying situations where their vulnerability has been exploited, leading to injury, danger, and death at the hands of others.
Just last week, on April 16th, mobs of South Africans in Durban attacked, beat, and murdered Ethiopian immigrants in their country. Three Ethiopians died, including two young men who were set on fire and burned alive. Reportedly, many of those threatening them are neighbors who see the influx of foreign migrants and refugees as competitors for jobs and opportunities due to high unemployment in the country. On Sunday, these foreign nationals were warned that any persons possessing a foreign passport or without a South African identification card, would be assaulted. Many fled their homes out of fear.
In another location, also occurring on Sunday, an overcrowded boat carrying between 700 and 950 migrants from Libya to Italy capsized in the Mediterranean Sea. Only a small number of them survived. It is believed that many were Ethiopians.
Last month in Yemen, many Ethiopians were trapped in the fighting going on between the rebels that overthrew the government of Yemen and those defending it. It is believed that numbers of Ethiopians were killed in the bombing by Saudi Arabia as well as by the fighting going on within the country. Ethiopians have been desperately trying to find a means to leave the country, but few wanted to return to Ethiopia. It is believed that close to 100,000 Ethiopians are still stranded there and remain in imminent danger.
The timing of all of these incidents makes the massacre in Libya all the worse. As Ethiopians, the shared sorrow we feel at the loss of our people is overwhelming. From the news reports we hear that thirty Ethiopian Christians lost their lives in Libya. Those murdering them claimed they were taking revenge on these Christians for Muslim blood and called Ethiopia “a nation of the cross.” However, Ethiopia has been a nation that has demonstrated how Christians, Jews and Muslims have been able to peacefully live side by side for hundreds of years, often intermarrying. As a result, they are related by blood, not only by the nation they share.
In fact, Ethiopian Muslims have publically come out with one of the strongest statements seen in regards to their total condemnation of these killings by IS. They are standing together with their fellow Ethiopians against the murder of innocent civilians, calling it “immoral, illegal, barbaric, and in direct contravention” of their beliefs. They state: “We therefore, condemn in the strongest terms the killings of our fellow Ethiopian brethren in Libya and asking justice be served to the perpetrators of these crimes.”
In other words, this act by IS is not about religion, but instead is about power, ambition, greed, hatred, self-interest and self-worship; claiming to be carrying out God’s work while actually violating God-given principles.
To outsiders, these thirty victims may be numbers, but to us they have names, ages, life stories and relationships with the people they have left behind. Some families are only now finding out that their son, husband, father, brother, cousin, or friend is among the victims; with others it may take longer. Some may remain unnamed; however, they died for their faith and are now gone from this world of greed, guns, barbarism, and selfish interest. Christians strongly believe that when a Christian believer is gone from this world, each will be welcomed by name, one by one, to their heavenly home. As it says in the Bible, “…absent from the body, present with the LORD.” [2 Corinthians 5:8] This is comforting to many of us.
Most of these were young men with dreams for a better life that will never be realized now. Although they knew it would be a dangerous journey, they risked it for many reasons—threat of arrest, persecution, or lack of freedom, but also because they may have wanted jobs and an education so as to help their families back home. They may have wanted to make the way for others to follow later—wives, children, parents, sisters and brothers. They are gone now and it has left a big hole in our hearts and souls.
In Ethiopia, the reaction from the government to these tragedies has been reprehensible and shameful. The current one-party government of the Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) has been in power since 1991. It is a coalition of four ethnic-based parties representing four of the eighty or more ethnic groups in Ethiopia and four out of nine of its regions. Worse yet, the EPRDF is controlled by one ethnic-based party, the Tigrayan People’s Liberation Front (TPLF), which represents one region and one ethnic group made up of 6% of the total population. A minority of Tigrayans, making up the Central Committee make all the decisions in the land. They control every sector of society and have exploited the opportunities, the resources and the economy for their own benefit, leaving out the majority. This is why people of Ethiopia regard the regime’s system as being ethnic apartheid. This is apparent in the wide disparity between those within the TPLF and those not included.
For example, while regime cronies have accumulated great wealth, the majority of Ethiopians remain impoverished, despite claims of double-digit economic growth. No wonder people are leaving the country in such large numbers. Therefore, the inadequate response to these crises is not surprising. This is not a regime that cares about its own people, only its own survival and international public image.
The regime’s first response to the massacre of Ethiopian Christians was to distance themselves from the emotions or any responsibility surrounding this brutal event until the victims were positively identified as truly being Ethiopians despite the fact that the killers had already named them as such. This angered many Ethiopians. Once there was proof of the nationality of the victims, the TPLF/EPRDF made a public statement on April 20 claiming their government had been on the “frontlines against terrorists for a number of years and [had] been a leader in the fight against terrorism and violent extremism”, self-righteously saying: “There could never be any excuse for such deliberate crimes against humanity…. The Government of the Federal Democratic Republic of Ethiopia strongly condemns the brutal murder of innocent people.”
However, this regime is well- known for its extra-judicial killings, massacres of innocent civilians, torture, the arrest of journalists, religious leaders and activists and human rights reports that document their own crimes against humanity. This includes the US State Department’s Annual Human Rights Report on Ethiopia.
Mr. Metho explains why such claims upset so many Ethiopians:
To outsiders who are wondering why Ethiopians are suffering all over the world—in Saudi Arabia, Dubai, Lebanon, Yemen, Kenya, Libya, Malta, South Africa, Egypt, Sudan, South Sudan, Uganda, and in other places—you should know that it is not by accident. Some people may even be tired of hearing about the trials and hardships of Ethiopians, believing it is about poverty rather than oppression because Ethiopia is so often portrayed as a democratic government as recently as this past week by the Undersecretary of the US State Department, Wendy Sherman, the fourth highest-ranking official there. As these accounts of the killing of Ethiopian Christians in Libya and South Africa come out, Ethiopians will tell you that this is not the first time they have witnessed this kind of thing.
Look at the silent genocide in the Ogaden region of Ethiopia—still ongoing, the massacre in the Amhara region in the nineties, the massacre of 424 civilian leaders in the Gambella region in 2003, the killing of 197 student protestors following the flawed 2005 election, the killing and mass arrests of the Oromo, the ongoing assault on the Afar people, and the ongoing human rights crimes in every region of the country. One of those killed by IS was a student leader who protested the regime’s eviction of Oromo from their homes in Addis Ababa and was going to be arrested, forcing him to flee the country. If you ask the people, the ruling ethnic-apartheid regime in Ethiopia is the IS or terrorist of Ethiopians, despite portraying themselves to outsiders as a government of the people.
On April 20, the TPLF/EPRDF declared that there would be three days of mourning for the victims and that flags would be at half-mast. The Ethiopian Parliament was to convene to discuss the situation; however, only 56% of the parliament’s 547 members showed up on April 21 to participate. Why? How much do they care?
The regime is also making decisions as to how Ethiopians can grieve, but they are denying Ethiopians their cultural way of grieving for the loss of loved ones, which is always done by gathering people together. Instead people are to remain in their homes to grieve alone. They are not to come out in the streets or to set up tents for people to congregate. This is outrageous. This regime should allow people to freely grieve the way they want. If they want to cry out in the streets as they sometimes do; they should be allowed to do so. When the former prime minister, Meles Zenawi, died, mourning in the streets was orchestrated and went on for days.
Allegedly, the TPLF/EPRDF has now called on religious leaders to tell Ethiopians not to leave the country for other places. In doing this, they essentially blamed the victims for putting themselves in harm’s way. They fail to acknowledge their own responsibility in it—that the mass exodus of Ethiopians had nothing to do with their own brutal, ethnic-apartheid policies they followed.
Religious leaders should be genuine and stand with the families in distress. They should also be free to speak the truth—that the source of the problem is the lack of good governance, the lack of opportunity for the people, and the favoritism of one ethnic minority over all others—more specifically, TPLF regime cronies, over everyone else, including other Tigrayans. The minority controls everything while the majority continues to leave the country. Regardless of any warning from the regime or from religious leaders, danger will not prevent the majority from leaving due to the terrible conditions within the country. Only genuine change will reduce the flow of Ethiopians to other places.
The regime is also putting the blame on human traffickers for what is happening. Mr. Metho challenges this thinking as another effort to avoid accountability. He says:
Yes, traffickers take advantage of the vulnerable and the desperate, but what is at the root of the problem? Why are so many continuing to leave the country regardless of the risk? The TPLF/EPRDF must look at themselves first. In fact, some allege that there is evidence that regime cronies are closely linked to the traffickers, those in international employment agencies, those giving working visas and passports, and others along the way.

Ethiopians have taken to the streets:

On April 21, with heavy emotions, the people of Ethiopia have come out in large numbers on the streets of Addis Ababa to grieve together for their fellow Ethiopians. Mr. Metho states:
Like the Biblical Good Samaritan, who did not ask the religion, ethnicity, or political view of the wounded man on the side of the road before helping him, we call on Ethiopians to do the same. Show compassion towards the hurting, putting humanity before ethnicity, religion or any other of our human differences. This is a basic principle of the SMNE. This is a time to stand for God-given values of life, liberty and loving one’s neighbor as oneself for no one will be free to live or worship freely without caring about the freedom, justice, religious freedom, and well being of others—another primary principle of the SMNE.
The death of our people should unify us as one people regardless of our differences. If we had a government that respected the value and dignity of all of its people, and if we as people honored God by following what is right, true, and good; the root cause for our people being scattered throughout the world may be reversed. If Ethiopia were a home where we could actually live and thrive, we would not be hearing of such tragic and horrific acts against our people.
Instead, when these problems happen, the current regime has repeatedly demonstrated a desire to minimize the problem in order to protect their own interests, fearing a backlash. This means blocking media coverage, blaming the victims, putting pressure on religious leaders to cover for them, inciting ethnic and religious divisions, polarizing groups and people, and denying their own injustices and human rights crimes against the innocent people of Ethiopia. Mr. Metho goes on to say:
These Ethiopians in Libya, South Africa, in Yemen and in the Mediterranean Sea have died senseless deaths; but let Ethiopians come together to mourn, repent of our wrongs and pray that God will bring good out of what was intended for evil so these precious people have not died in vain.
It is God who condemns the bloodshed of the innocent as something that pollutes the land and the soul of those involved. Yet, it is the same faith of these victims in Libya that calls for forgiveness and reconciliation between God and humankind and between our fellow brothers and sisters.
May Ethiopians of every faith cry out to God for our deliverance, mourning our failures and seeking the moral transformation of ourselves, our people, our society, and this regime.
May our religious leaders be strengthened to resist human manipulation; and to instead, be courageous, standing true to the One who has called them to Him—their Creator.
May we all become reconcilers, defenders, and peacemakers in our beloved country—excluding no ethnic group, no religious group or anyone else, because no one is free until we all are free! Even if we are imperfect and flawed in carrying it out; because of that, with God’s help, let us be ready to forgive, to restore, and to live rightly to the best of our ability.
May God protect those still in danger or difficulty, both within Ethiopia and in places all over the world. LONG LIVE ETHIOPIA!
For more information, contact Mr. Obang Metho, Executive Director of the SMNE. Email: Obang@solidaritymovement.org

ወያኔ በሚሞቱትም በሚሰደዱትም ደስተኛና ተጠቃሚ ነው

April 22, 2015
አንዷለም
ወያኔን እንቅልፍ የሚነሳው ነገር ቢኖር ኢትዮጵያውያን በሰላም ውለው መግባታቸው ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላም ውሎ ካደረ አንድ ቀን ቀፎው እንደተነካበት ንብ ገንፍሎ ወጥቶ የሚውጠው ይመስለዋል ስለዚህም የጅምላ ሞት፤ስደት፤ እልቂት እንዲኖር ጠንክሮ ይሰራል ሲደርስም ሲበዛ ይደስታል።
የወያኔ ጥቅሞችን ላስረዳ።Ethiopian refugees heading to Yemen
1. ወጣቱ (በወያኔ ቋንቋ አደገኛ ቦዘኔው) አገር ውስጥ ከተቀመጠ በችጋር ተገፍቶ አንድ ቀን መነሳቱና የግፍ ወያኔያዊ አገዛዝን ከምድረ ገጽ ማጥፋቱና የበይ ተመልካችነቱም ሊያበቃ እንደሚችል ወያኔ ጠንቅቆ ያውቃል፤ ስለዚህም ደላላዎቹን በመላ አገሪቱ በማሰማራት፤ በቀላሉ ቀይባህርን ተሻግሮ ሳውዲ አረቢያ በመግባት ቤተሰቦቹን ሀብት በሀብት ማድረግ እንደሚቻል ይሰብካል። በሌላም በኩል በኬንያ አቋርጦ በቀላሉ ደቡብ አፍሪካ መግባትና በአጭር ጊዜ ሚሊዮነር መሆን እንደሚቻል ምሳሌ እየጠቀሱ የወያኔ ደላላዎች ያለመታከት ይሰብካሉ፤ የጉዞ ዶኩመንት የሚያስፈልገውንም በድርጅታዊ አሰራር ያሟላሉ፤ ለዚህም ወላጅ ተበድሮም ቢሆን ይከፍላል። ሌላው የወያኔ ደላላ ደግሞ በሱዳን ተሻግሮ ሊብያን አቋርጦ በአጭር እርቀት የባህር ላይ ጉዞ ጣሊያን መግባት አዲሱ የመክበሪያ ዘዴ መሆኑን ምሳሌ እየጠቀሰ ያስተምራል የሚያሻግሩ ሰዎችም እንዳሉ ጭምር ይናገራል፤ ያመቻቻል። የሊብያው ካልተሳካ ወደእስራኤል መሻገርም አማራጭነቱ በወያኔ ደላሎች በብርቱ ይሰበካል።
ስለዚህም ወጣቱ ከአገር እንዲወጣ ወያኔ የሚችለውን ሁሉ ያደርጋል፡ ቀይ ባህር ሰጠሙ፤ ለአካል ክፍሎቻቸው ሲባል ሲናይ በርሃ ውስጥ ታረዱ፤ አይኤስኤስ አረዳቼው፤ ሜዲትራንያን ባህር ሰጠሙ፤ በታንዛንያና በማላዊ በርሃዎች ውስጥ በኮንቴነር ውስጥ ታፍነው አለቁ በወያኔና ደላላዎቹ ቤት ለዜናም አይበቃም። የድለላውን ከፍለዋል፤ የተበላ እቁብ!!
2. ተሳክቶላቸው ወደሶስተኛ አገር ደርሰው መስራት ከጀመሩ ወጣቶቹ የተበደሩትን ለመክፈልና ቤተሰብም ለመርዳት ገንዘብ መላክ ይጀምራሉ። ወያኔም ዶላር እየተቀበለ እንደፈለገ የሚያትመውን ብር ለቤተሰብ ይሰጣል። አገር ውስጥ ያለው ቤተስብም እንጄራ ድሎት ቢሆንበትም ሩዝም ቀምሶ ነገን ተስፋ እያደረገ ይኖራል።
ስለዚህም ወያኔ አደገኛ ስደትን ያበርታታል።
ምናልባት አንዳንድ የወያኔ ባለስልጣናት በቴሌብዥን ቀርበው ስደትን ሲቃወሙ ሰምታችሁና የልማታዊ መንግስታችንን ስም አጠፋህ ብላችሁ በሽብርተኝነት በሽመልስ ከማል አቃቤ ህግነትና በተከበሩ ዳኛ ልኡል ዳኝነት ልትከሱኝ ላሰባችሁ እበላ ባዮች አንድ ቀላል ጥያቄ ልጠይቃችሁ?
ሁላችንም እንደምናውቀው ወያኔ አንድ ለአምስት በሚለው መጠርነፊያው እያንዳንዱን ሰው 3 ና 4 ጊዜ በቤተሰቡ፤በመስሪያቤቱ፤ በሙያ ማህበሩና በሌላም የጠረነፈው በመሆኑ በእያንዳንዱ ቤትና መስሪያቤት የተተነፈሰው ብቻ ሳይሆን የተላሰውም ለወያኔ በመዋቅሩ መሰረት ሪፖርት ይደረጋል። እመኑኝ ዛሬ ወያኔ ደላላዎቹን ከዛሬ ጀምሮ በውሸት እያተለላችሁ ሰው እንዲሰደድ ማደረጋችሁን አቁሙ ካለ ያኑ ቀን ይቆማል። ይህን ስል ሃይለ ማርያም፤ ደመቀ ወይም አባዱላ እንዲህ አለ ብላችሁ መንግስት ተናገረ የምትሉ ቁጭ በሉ ላሞኛችሁ መሆኑን እዎቁ።
ስለዚህ ወያኔ በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ ይህ ነገር ይቀጥላል፤ ጎበዝ መሞታችን ካልቀረ በክብር ለአገር በአገራችን መሬት እንሙት።
የሞቱትን አምላክ ያስባቸው፤ ከተመሳሳይ አደጋ ለመዳን ወያኔን ማስዎገድ ብቼኛው መፍትሄ ነው።

Tuesday, April 21, 2015

በግፍ ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖቻችንን በተመለከተ የአርበኖች ግንቦት 7 መግለጫ

April 21,2015
ሀያ ስምንት ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን አይ ሲስ በተሰኘ ህሊና ቢስ፣ ፀረ-ሰው እና ፀረ-ስልጣኔ ቡድን በሊቢያ በአሰቃቂ ሁኔታ የመገደላቸው መርዶ ዛሬ ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓም ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ደርሷል። ይህ አሰቃቂ መርዶ ልብን የሚሰብር ነው። አይ ሲስ በጥንት በጭለማ ዘመን እንኳን ባልነበረ ጭካኔ ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ ሰዎችን በማረድ የሚደሰት፤ በሰው ዘር ሁሉ ላይ የመጣ አውሬ መሆኑን ነብዩ መሐመድ አትድረሱባቸው ያሏቸውንም ኢትዮጵያዊያንን ጭምር በማረድ አረጋገጧል። ይህ አሰቃቂ ተግባር ምንም ዓይነት አመክኖ ሊቀርብለት የማይችል አረመኔዓዊ የሽብር ጥቃት ነው።
አርበኞች ግንቦት 7:የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በወገኖቻችን ላይ በደረሰው አሰቃቂ ግድያ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል፤ ለሟች ቤተሰቦችና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን ይመኛል። ኢትዮጵያዊያን ሁሉ አይ ሲስን በጥብቅ እንዲያወግዙ፤ በአመቻቸው መንገዶች ሁሉ እንዲታገሉት አርበኞች ግንቦት 7 ያሳስባል።
በዚህ አጋጣሚ የአይሲስን የሽብር ተግባራት ከእስልምና እምነት ጋር ማያያዝ ፈጽሞ ትክክል እንዳልሆነ፤ ብዙሃን ሙስሊሞች የአይሲስና መሰል ቡድኖችን አካሄድ የሚቃመው መሆኑን አርበኞች ግንቦት 7 ማስገንዘብ ይሻል። ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ከክርስቲያን ወገኖቻቸው ጋር ተዋደውና ተፋቅረው የኖሩና እየኖሩ ያሉ ሲሆን የሁለቱ ሀይማኖቶች ተከታዮች ተደጋግፎ መኖር ለሀገራችን ህልውና ወሳኝ ጉዳይ መሆኑ የአርበኞች ግንቦት 7 እምነት ነው።
በያዝነው ሣምንት በወገኖቻችን ላይ እልቂት ሲደርስ የሊቢያ ብቸኛ ክስተት አይደለም። በደቡብ አፍሪቃ ወገኖታችን ከነሕይወታቸው በእሳት ተቃጥለው ተገድለዋል፤ በስለት ተዘልዝለዋል፤ ንብረታቸውን ተዘርፈዋል። በዛሬው ዕለት 700 ዜጎች የሜዲተራኒያን ባህር በጀልባዎች ሲሻገሩ መስመጣቸው ተሰምቷል። በየመን ደግሞ በርካታ ወገኖታችን በጦርነት እሳት ውስጥ እየተማገዱ ናቸው።
ኢትዮጵያዊያን በአገራችን የሰፈነውን የነፃነት እጦት፣ የፍትህ መጓደልና የኑሮ መክበድ ሸሽተን በሄድነት አገር ሁሉ የሚጠብቀን አሰቃቂ ሞትና ውርደት ሆኗል። ኢትዮጵያ ለኑሮ ያልተመቸችን በህወሓት አገዛዝ ብሉሽነት መሆኑ ጥርጥር የለውም። ይህንን ብልሹ አገዛዝ አስወግደን በምንወዳት አገራችን ተከብረን መኖር እንችላለን። ለኢትዮጵያዊያን ከኢትዮጵያ የተሻለ አገር የለም።
አርበኖች ግንቦት 7: የኢትዮጵያዊያን መከራ እንዲያበቃ ስደት ይብቃ ይላል። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እንደዝንባሌውና እንደችሎታው በሕዝባዊ አመጽ አሊያም የሥራ ቦታውና መኖርያው ሳይለቅ በሕዝባዊ እምቢተኝነት በተደራጀ መንገድ የህወሓትን አገዛዝን ይታገል። በሕዝባዊ አመጽና በሕዝባዊ እምቢተኝነት የህወሓት ፋሽስቶችን አስወግደን በአገራችን በነፃነትና በክብር እንድንኖር ሀይማኖትም ሆነ የዘር ሀረግ ሳይለየን በጋራ እንታገል የሚል ጥሪ ያቀርባል።
ዘላለማዊ ክብርና እረፍት ለግፍ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን

Statement of Patriotic Ginbot 7 on Fellow Ethiopians who were Victims of barbarians

April 21.2015
It is with deep distress that the people of Ethiopia have heard the barbaric killing of twenty eight fellow Ethiopians in Libya on April 19, 2015 by the barbaric and medieval cowards of ISIS. This group, who belong to the darkest of dark ages, and takes pleasure of its barbarism, has killed desperate, defenseless Ethiopian migrants who have no other objective other than seeking a better life outside of their country. By so doing, the barbaric and criminal beasts have demonstrated beyond the shadow of a doubt that they have a serious quarrel with humanity itself, not to mention the fact that they don’t even know what prophet Mohammad, in whose name they kill, has said about Ethiopia and Ethiopians in the wholly book and the story of the Fist Hegira.
Patriotic Ginbot 7 for Unity and Democracy Condemns this heinous crime on our fellow citizens and calls on all Ethiopians to condemn it in no uncertain and clear terms and put up a united fight against this barbaric group in all ways and means we can.
We also take this opportunity to reiterate the fact that the barbaric terrorism perpetrated by this group which calls itself ISIS, has nothing to do with the religion of Islam as what it does is against the teachings of Islamic. Our country Ethiopia is holy to both Moslems and Christians. Moslems and Christians in in Ethiopia live and have lived as a family harmonisly , exemplary tolerance and respect of one another’s religions. As Ethiopians, we will keep priding ourselves of this exemplary unity between Moslems and Christians and consider it as pivotal feature for our survival as a country in bad and good times for over millennia.
The tragedy that has befallen on our fellow country and people over the last week has not been only the murder of our fellow Ethiopians in Libya. In South Africa fellow Ethiopians were also murdered in cold blood and burned with fire alive. During the same week we have also heard the drowning of a ship in the Mediterranean Sea that we believe has carried large number of Ethiopians who perished along with 700 other people. In Yemen thousands of Ethiopians are living in the middle of the hell of war.
Ethiopians who flee injustice and economic hardship in their country are facing humiliation, death and hopelessness in a way that we have rarely seen in our history. There is no question that the source of all these hardship is the corrupt dictatorship of the TPLF that is ruling Ethiopia with iron fist and with callous disregard for the welfare of Ethiopians. We, as an organization of democracy and justice, believe that the removal of this regime from power is the only way to reverse this tragedy that we are subjected to live in. For Ethiopians, there is no place better than Ethiopia and we are determined to make it one.
Patriotic Ginbot 7 calls on Ethiopians to once and for all end this tragedy by fully engaging in the struggle everywhere, in places where we live and work , contribute towards an organized resistance to the TPLF brutal rule. We call on all Ethiopians from all walks of life , including Ethiopians of every religion and ethnic group to come together, join hands and struggle in unison to remove this regime. We can never forget that the TPLF is the source of this unending tragic life of our people.


    Eternal peace for those who lost their lives by barbarians!

    Sunday, April 19, 2015

    ሕወሓት የሚመራው መንግስት በአይሲኤስ የተገደሉ ኢትዮጵያውያንን ካደ * “የተገደሉት ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን አላረጋገጥኩም” አለ

    April 19 ,2015


    ethiopian killed by isil 1











     ሁሌም በዜጎቹ ጉዳይ ከበዳይ ወገን ጋር አብሮ በመሰለፍ ዜጎቹን የሚያዋርደው የሕወሓት የሚያስተዳድረው የኢሕ አዴግ መንግስት በሊቢያ አይሲኤስ የገደላቸውን 28 ኢትዮጵያውያንን ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን ማረጋገጫ አላገኘሁም አለ::

    ሕወሓት የሚመራው መንግስት ባወጣው መግለጫው “አይሲኤስ የተባለው አለም ዓቀፍ አሸባሪ ቡድን በሊቢያ በሚኖሩ ስደተኞች ላይ ፈፅሜያዋለሁ በሚል በቪዲዮ ያሰራጨው ዘግናኝ የግድያ ተግባር የኢትዮጵያ መንግስት እንደሚያወግዝ ሲገልጽ” ስደተኛ እንጂ ኢትዮጵያውያን ማለት አልፈቀደም::
    ሕወሓት የሚመራው መንግስት ዜጎቹን በመካድ በአቶ ሬድዋን ሁሴን በኩል የሰጠው መግለጫ ላይ እንዲህ ይላል:-
    “በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 11 ቀን 2007 ዓመተ ምህረት የተለያዩ አለም ዓቀፍ ሚዲያዎች ባሰራጩት ዘገባ አይ ኤስ የተባለው አሸባሪ ቡድን ግድያ የፈፀመባቸው ስደተኞች ኢትዮጵያውያን እንደሆኑ ቢገልፁም በግብፅ ካይሮ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ግን ስደተኞቹ ኢትዮጵያውያን ስለመሆናቸው ማረጋገጫ እንዳልሰጠም ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
    አሸባሪው ቡድኑ ለህልፈት የዳረጋቸው ዜጎች ኢትዮጵያውያን ቢሆኑም ባይሆኑም መንግስት በንፁሃን ላይ የሚፈፀም ይህን መሰል አፀያፊና ዘግናኝ የሽብር ድርጊት አጥብቆ ይኮንናል ብለዋል፡፡”
    በግልጽ ኢትዮጵያውያንን የመሰሉ ሰዎች ታርደውና ተገድለው ባህር ላይ ተጥለው መንግስት ገና ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን አላረጋገጥኩም ማለቱ ዜጎቹን በመካድ የታወቀው የሕወሓት መንግስት ዳግም እርቃኑን ቀርቷል:: በቅርቡ እሳዑዲ አረቢያ በየመን እና በደቡብ አፍሪካ በዜጎቹ ላይ ክህደት የፈጸመው ይኸው አምባገነን መንግስት በሊቢያ የሚገኙ ዜጎቹን መካዱ ብዙዎችን አሳዝኗል::
      ምንጭ /ዘ-ሐበሻ

    Friday, April 17, 2015

    ወገን ይጠቃል፣ እነርሱ ዳንኪራ ይመታሉ

    April 17,2015
    ግርማ ካሳ
    የአልመነህ ዋሴ ዋዜማ ዘገባ መስረት፣ የናይጄሪያው ተመራጭ ፕሬዘዳንት መሀመድ ቡሃሪ ፓርቲ እና የሃገሪቱ የሲቪል ማህበረሰብ አባላት፣ የደቡብ አፍሪካ መንግስት በዉጭ ሃገር ዜጎች ላይ የሚፈጸመዉን ጥቃት ካላስቆመ በናይጄሪያ ያሉ የደቡብ አፍሪካ ኩባንያዎችን ለማዘጋት እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው። የ48 ሰዓት ገደብ የያዘ ማስጠንቀቂያቸዉን ሌጎስ ለሚገነው የደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ አስገብተዋል።


    በተያያዘ ዜና ዋዜማ የናይጄሪያ ፓርላማ አባላት መንግስታቸው አምባሳደሩንስ ከደቡብ አፍሪካ እንዲጠራ መጠየቃቸዉን ጥቅሷል። በዘገባዉ መሰርት የፓርላማ አባላቱ የደቡብ አፍሪካ መንግስት ለአፍሪካዊያን ስደተኞች በቂ የደህንነት ጥበቃ ካላደረገ፣ ተጨማሪ ዲፕሎማሲያዊ የአጸፋ እርምጃ እንዲሰደም ጠይቀዋል። 
    ናይጄሪያዊያኖች ይህን አይነት ዉሳኔ ሲያሳልፉ፣ አንድ ዜጋ ገና አልሞተባቸዉም። ሆኖም በሌሎች አፍሪካዉያን ላይ የደረሰው እነርሱም ላይ እንደደረሰ አድርገው ስለወሰዱት ነው፣ በደቡብ አፍሪካ ያየነዉን ዘግናኝናአ እንሣዊ ተግባር ያወገዙት።
    በደቡብ አፍሪካ በተነሳዉ ግጭት በርካታ ኢትዮጵያዉያን ሞተዋል። አንገታቸው ላይ ጎም ተደረጎ እንዲቃጠሉና በማቼቲ (መጥረቢያ ነገር) ሲቆራረጡ፣ በየመንገዱ እንደከብት ሲደበደቡ የሚያሳይ ምስሎችን እና ቪዲዮዎችንም አይተናል። አለም ሁሉ ወገዛ ሲያቀርብ፣ እነ ቢቢስ፣ አልጃዚራ፣ ቪ.ኦኤ ፣ የናይጄሪያ፣ የማላዊ፣ የሞዛምቢክ የበርካታ አፍሪካ አገሮች ሜዲያዎች በስፋት ሲዘገቡ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ምንም ነገር እንዳይሰማ መደረጉ፣ የሕወሃትን ምመንግስት ምንነት በገሃድ በድጋሚ ያሳየ ነው።
    የኢትዮጵያ ህዝብ በወገኖቹ ላይ የደረሰውን ምንም ነገር እንዳይሰማ ተደረጎ፣ ሌላው ይቀር ጸሎት እንኳን እንዳያደርግ ሁሉንም ደብቀዉታል።
    እንግዲህ አንድ ጥያቄ ልጠይቅ ? መሪያችን ማን ነው ? የፓርላማ ተወካዮቻችንስ ማን ናቸው ? የ”ኢትዮጵያ” መሪ ሙሃመድ ቡሃሪ ነው፣ የፓርላማ ተወካዮቻችን ደግሞ የናይጄሪያ ፓርላማ አባላት ናቸው ብልን እንንሳሳታለን ? እስቲ አስቡት በደብቡ አፍሪክካ ላሉ ወገኖቻችን እየተሟገቱ ያሉት፣ በዝዙማ መንግስት ላይ ጫና እያሳደሩ ያሉት እነ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ፣ እነ አባ ዱላ ሳይሆኑ እነ ፕሬዘዳንት ሞሃመድ ቡሃሪ ናቸው።
    በዚህ አጋጣሚ ለናይጄሪያኖች ያለኝ ከበሬታ እገልጻለሁ። THANK YOU OUR NIGERIAN BROTHERS !!! WHEN OUR OUR OWN GOVERNMENT DID NOT CARE YOU STOOD FOR US.

    ሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ ፖስተሮች በገዥው ፓርቲ እየተቀደዱብኝ ነው ሲል ገለጸ

    April 17,2015
    • ‹‹ወንብድና ነግሷል›› አቶ ዮናታን ተስፋዬ
    የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ፖስተሮች በገዥው ፓርቲ ካድሬዎች ሆን ተብለው እየተቀደዱበት እንደሆነ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለፀ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ የለጠፋቸው ፖስተሮችን የገዥው ፓርቲ ካድሬዎች እየተከታተሉ እንደቀደዷቸውና ላያቸው ላይ ማስታወቂያ እንዲለጠፍባቸው እየተደረገ መሆኑን አቶ ዮናታን ገልጸዋል፡፡
    ‹‹ፖስተሮቹ የተቀደዱት አንድ ቦታ ላይ አይደለም፡፡ በአሁኑ ወቅት ሰማያዊ ፓርቲ ወደ ህዝብ እንዳይደርስ እያደረገ የሚገኘው ገዥው ፓርቲ ሆን ብሎ እየተከታተለ እያስነሳ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ የሰማያዊ ፖስተሮች ሲቀደዱ የኢህአዴግ ፖስተሮች ላይ ግን ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም፡፡ ይህ ከፍርሃቱ የመነጨ ነው›› ያለው አቶ ዮናታን ተስፋዬ የገዥው ፓርቲ ካድሬዎች የሰማያዊ ፓርቲን ፖስተሮች እየቀደዱ ከህዝብ እንዳይደርስ ለማድረግ ቢጥሩም በህዝቡ ትብብር አማራጫቸውን በማቅረብ ላይ በመሆናቸው ገዥው ፓርቲ ባሰበው መልኩ እንቅፋት መፍጠር እንዳልቻለ አስታውቋል፡፡
    ‹‹ውንብድና ነግሷል›› ያለው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ሆኖም ሰማያዊ ይህን የገዥው ፓርቲ ህገ ወጥነት በሞራል የበላይነት እና ከህዝብ ጋር በመተባበር እስከመጨረሻው ድረስ ለህዝብ እንደሚያጋልጥ ገልጾአል፡፡ የገዥውን ፓርቲ ድርጊት ሰማያዊ ፓርቲ ለምርጫ ቦርድም እንደሚያሳውቅ የገለጸው አቶ ዮናታን ፓርቲው ይህን የሚያደርግው ሂደቱን ለመጠበቅና የትግሉ አንድ አካል በመሆኑ እንጅ ምርጫ ቦርድ በጉዳዩ ላይ መፍትሄ ይሰጣል ብለን አይደለም ብሏል፡፡
    አቶ ዮናታን አክሎም ‹‹ኢህአዴግ ወደ ህዝብ እንዳንደርስ የቻለውን ሁሉ ሊያደርግ ይችላል፡፡ በቀጣይነትም የዕጩዎችን ፎቶዎችና ሌሎች ፖስተሮችን ስንለጥፍ እንደሚቀዱ እናውቃለን፡፡ እኛም ወደ ትግሉ ስንገባ ኢህአዴግ እንዲህ አይነት ባህሪ እንዳለው ስለምናውቅ ይበልጡን ትግላችን እናጠናክራለን እንጅ ወደኋላ አንልም፡፡ እሱ 20 ፖስተሮችን ሲቀድ እኛ 40 ፖስተሮችን እየለጠፍን ወደ ህዝብ እንደርሳለን፡፡›› ሲል ገልጾአል፡፡