Tuesday, August 12, 2014

ከኢህአዲግ/ወያኔ መላቀቅ ማለት ከድንቁርና ነፃ መውጣት ነው!

August 12/2014
press freedomሰሞኑን የኢህአዲግ/ወያኔ የኮምንኬሽን ሚኒስትር ዴታ የነበሩት አሁን በስደት የሚገኙት አቶ ኤርምያስ ለገሰ የሰጡትን መግለጫ  በኢሳት ቴሌቭዥን እየተከታተልኩ ነበር።አቶ ኤርምያስ ከተናገሩት ውስጥ የኢህአዲግ/ወያኔ አመራሮችም ሆኑ ቡድኑ ባጠቃላይ የተማሩ ኢትዮጵያውያንን ለምን እንደሚያሳድድ ያስረዱበት መንገድ ሚዛን የሚደፋ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።አቶ ኤርምያስ ኢህአዲግ/ወያኔ በመመርያው ውስጥ የተማሩ አባላት ከ 1% እንዳይበልጡ ለምን እንደሚደረግ እና ባጠቃላይ ድርጅቱ የተማሩ ኢትዮጵያውያንን የሚጠላበትን መሰረታዊ ምክንያት ሲያስረዱ እንዲህ ነበር ያሉት (ቃል በቃል ባይሆንም ሃሳቡን እንዲህ ይገለፃል) -
  ”ማየት ያለብን ድርጅቱን የሚመሩት ሰዎች አነሳስን ነው።እነኝህ ሰዎች ገና የ 16 እና 17 ዓመት ልጆች ሆነው ከግብርና ተነስተው (ግብርና የተከበረ ሙያ መሆኑን ሳንዘነጋ) ወደ ውግያ ገቡ።ዋናውን የወጣትነት ጊዜ ማለትም እውቀት የሚቀሰምበት እና የህዝቡን ማህበራውም ሆነ ቤተሰባዊ ሕይወት በማወቅያቸው ጊዜ ሁሉ ለአስራ ምናምን ዓመት የሚያውቁት መተኮስ ነው።አሸንፈው ቤተመንግስት ሲገቡ የመማርያ ጊዜ አልፏል።እኛ ያለፍንበትን የቤተሰብ ሕይወት እና ምክንያታዊነት ላይ የተመሰረተውን የዕውቀት መገብየት ዘመን አያውቁትም።ትምህርት ቤት አያውቁም፣ማህበራዊ ኑሮ አያውቁም።በመሆኑም  የተማረ ሰው አዲስ ሃሳብ ይዞ ከመጣ ይገለብጠናል ብለው ይሰጋሉ።” ነበር ያለው።ሚዛን የሚደፋ አገላለፅ ነው። 
ይህንን የአቶ ኤርምያስ አባባል በሰማሁበት ሰሞን ዛሬ ደግሞ ”የአዲስ ጉዳይ” መፅሄት ባለቤት እና ሶስት አዘጋጆች የመሰደዳቸው ዜና ተሰማ።የጋዜጠኞች መሰደድ እና የግል ሕትመት ውጤቶች መዘጋት በዘመነ ኢህአዲግ/ወያኔ የተለመደ ዜና መሆኑ ይታወቃል። ነገር ግን የሕትመት ውጤቶችን መዝጋት ከፖለቲካዊ አንደምታው በዘለለ የኢህአዲግ/ወያኔ ትውልዱን አደንቁሮ የመግዛት እቅዱ አካል መሆኑን ልብ ማለት ተገቢ ነው።

1/ ”ትምህርት በአብዮታዊ ዲሞክራሲ መጠመቅ ብቻ ነው” ኢህአዲግ/ወያኔ 

ዕውቀትን በመግደል ኢህአዲግ/ወያኔን የሚተካከለው የለም።የተማረው ክፍል ከአብዮታዊ ዲሞክራሲው ጫማ ስር ተንበርክኮ የምልኮሰኮስ እንዲሆን ለማድረግ ሃያ ሶስት ዓመታት ሙሉ ስታትር ተስተውሏል።እዚህ ላይ የዩንቨርስቲ ቁጥር መጨመር ግን በጥራት የወረዱ መሆናቸውን ብቻ ሳይሆን የትምህርት ደረጃው ባጠቃላይ ከሳሃራ በታች ካሉት ሀገሮች ጋርም መወዳደር የማይችል ደረጃ የደረሰው በዘመነ ኢህአዲግ/ወያኔ ነው።
 የዩንቨርስቲ ቁጥር ጨመርኩ ባለበት አፉ  የትምህርት ጥራትን መግደሉን እራሱ ኢህአዲግ/ወያኔም  በተለያየ መድረክ አረጋግጧታል።
እንደ ‘እስስት’ የሚቀያየረው የትምህርት ፖሊሲ በአንድ ሀገር የምንኖር መሆናችን ግራ እስኪገባን ድረስ አንዴ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እስከ 10ኛ ሆነ።ሌላ ጊዜ የለም እስከ 12ኛ ክፍል አደረግነው። መልሰው ደግሞ የሶሻል ትምህርት 30% ሆነ፣ወዘተ እየተባለ በበቂ ጥናት ላይ ያልተመሰረተ የተደናገሩ ዓመታት ሰለባ የሆነው ይሄው ትውልድ ነው።
መምህራን ግራ ተጋብተው ”በአብዮታዊ ዲሞርክራሲ ማደናገርያ ተጠመቁ” ተብለው በተማሪ ካድሬ እንዲመሩ እና እንዲሸማቀቁ የተደረጉት ብቻ ሳይሆን እነኝሁ ትውልድ ቀራጮች እንባ አውጥተው ሲያለቅሱ የታዩት አሁንም በኢህአዲግ/ወያኔ ዘመን ነው።

2/ ”ጫት ቤት እና ሺሻ ቤት ይስፋፋ! መፃህፍት ቤት እና የሚነበቡ የሕትመት ውጤቶችን  ዝጋ!”

ወደ ኃላ ሄደን በ1983 ዓም አዲስ አበባ ስንት የጫት ቤቶች እና ሺሻ ቤቶች ነበሩ? ብለን ብንጠይቅ መልሱ ግልፅ ነው።ባለፉት 23 ዓመታት ውስጥ ከዜሮ ከሚባል ደረጃ ዛሬ የእየደጃፋችን እና የትምህርት ቤቶች መዳረሻዎች ሁሉ በጫት መቃምያ እና በሺሻ ቤቶች እንደተሞሉ እንረዳለን።ለእዚህ ማሳያ የሚሆነን ከዛሬ 23 ዓመታት በፊት በአዲስ አበባ በሚኖሩ ሱቆች ላይ  ”የጫት መሸጫ ሱቅ” ብሎ መለጠፍ አስነዋሪ እና በህብረተሰቡ ዘንድተቀባይነቱ ብቻ ሳይሆን አሳፋሪም  ነበር።
Chat trader2
በኢህአዲግ/ወያኔ ዘመን የተስፋፋው የጫት ገበያ
ብዙም አልቆየ ኢህአዲግ/ወያኔ ስልጣን በያዘ በወራት ውስጥ ”የበለጩ ጫት፣የባህር ዳር ጫት” እና ሌሎችም ማስታወቂያዎች ተኮለኮሉ።ዩንቨርስቲዎች፣የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ወዘተ በጫት ተጥለቀለቁ።ኢህአዲግ/ወያኔ እና ካድሬዎቹ ዋና አቀባባይ እና አሰራጮች ሆኑ።የጫት ሱሱ ከፍተኛ የኢህአዲግ/ወያኔ ባለስልጣናትን ሁሉ በሱስ ተጠምዷል እና አዲሱ ትውልድንም ለማደንዘዝ እንደ አንድ መሳርያ ተጠቀመበት።
የጫት እና ሺሻ ቤቶችን በየመንደሩ ያስፋፋው ኢህአዲግ/ወያኔ በጎን በኩል ደግሞ ወጣቱ በማንበብ እራሱን በእውቀት እንዳያበለፅግ የሰራቸው ሁለት ተጨማሪ ወንጀሎች አሉ።የመጀመርያው ከተሞች መፃህፍት ቤት እንዳይኖራቸው ምንም ባለማድረግ ሲሆን ሁለተኛው የነፃ የህትመት ውጤቶችን ማፈን ነበር

 2.1 ”መፃህፍት ቤት ዝጋ ጫት እና ሺሻ ቤት ክፈት!”

ከሶስት ሚልዮን በላይ ሕዝብ ያላት አዲስ አበባ የጫት ቤት እና ሺሻ ቤቶች ተስፋፉባት እንጂ መፃህፍት ቤት እንዲኖራት ኢህአዲግ/ወያኔ አልፈቀደላትም።በ 1997 ዓም በነበረው ሃገራዊ ምርጫ ቅንጅት ለአዲስ አበባ አቅርቦት የነበረው የምርጫ መቀስቀሻ ነጥቦች ውስጥ አንዱ ”በአዲስ አበባ ውስጥ በእያንዳንዱ ክፍለ ከተማ ውስጥ ቢያንስ አንድ መፃህፍት ቤት መክፈት” የሚል የነበረ መሆኑን የእዚህ ፅሁፍ አቅራቢ ያስታውሳል።ለሀገር ማሰብ ትውልድን በእውቀት ማነፅ እና የማንበብ ባህልን በማዳበር ይጀመራልና ቅንጅት ከየት እንደሚጀመር ያሳየበት ጥበብ የተሞላበት የስራ ዕቅድ ነበር ያቀረበው።
ኢህአዲግ/ወያኔ ስልጣን ከያዘ ወዲህ አዲስ አበባ አንድ ደረጃውን የጠበቀ መፃህፍት ቤት አላየችም።በግል ባንድ ጊዜ ከሁለት እና ሶስት መቶ ሰው በላይ የማያስተናግዱ መፃህፍት ቤቶች በስተቀር ከተማዋ መፃህፍት ቤቶች የሏትም። ማንበብ የማይወዱት ባለሥልጣኖቻችን የኢትዮጵያን ከተሞችም በጨለማ ውስጥ ከትተው ዓመታትን አሳለፉ።እስካሁን ባሉ መረጃዎች አዲስ አበባ ከሶስት ሚልዮን በላይ ነዋሪ ቢኖራትም አሁንም ድረስ በመፃሕፍት ብዛቱም ሆነ በትልቅነቱ የሚጠቀሰው ለሕዝብ ክፍት የሆነው መፃህፍት ቤት ከአርባ ዓመታት በፊት በብላቴ ጌታ ሕሩይ ወ/ሥላሴ የተሰራው ”ብሔራዊ ቤተ መዘክር (ወመዘክር)” ተብሎ የሚጠራው እና ባህል ሚኒስቴር አጠገብ የሚገኘው ብቻ ነው።እዚህ ላይ የዩንቨርስቲዎች ወይንም የድርጅቶች መፃህፍት ቤቶች ለሁሉም ሕዝብ ክፍት ስላልሆኑ የህዝብ መፃህፍት ቤት ተብለው እንደማይወሰዱ ለማሳሰብ እወዳለሁ።
አብዛኛው ወጣት ሥራ አጥ ሆኖ ከቤት  የሚውልባቸው ከተሞች የመፃህፍት ቤቶች ቢስፋፋላቸው በርካታ ጥቅም እንደሚኖራቸው ሳይታለም የተፈታ ነው።የመጀመርያው ጥቅም ጊዜን ከአልባሌ ቦታ ጠብቆ ማሳለፍ ሲሆን ሁለተኛው አዲስ የስራ መስክ ለመፍጠር ከፍተኛ የስነልቦና ልዕልና የመቀዳጀቱ ፋይዳ ነው።ኢህአዲግ/ወያኔ ግን በተቃራኒው ለወጣቱ የደገሰለት የጫት እና ሺሻ ቤቶችን በእጥፍ ማስፋፋት ነው። 

2.3 ‘‘የሕትመት ውጤቶችን ዝጋ! አደንቁረህ ግዛ!”

ኢህአዲግ/ወያኔ መፃህፍት ቤቶችን ብቻ አይደለም ያቆረቆዘው።ላለፉት ሃያ ሶስት ዓመታት እየተከታተለ ሲያጠፋ የኖረው ለትውልዱ ጭላንጭል የዕውቀት ብርሃን የሚፈነጥቁ የነበሩትን የግል የህትመት ውጤቶችን ነው።ትውልድ የማንበብ እና የማወቅ መብቱ የተዘጋው በጣት የሚቆጠሩ የነፃው ፕሬስ ውጤቶችን ነው።ቀደም ብሎ ኢህአዲግ/ወያኔ የግል ፕሬሶችን ሲወቅስ የነበረው ‘የጋዜጠኛ ሙያ የላቸውም፣ተቃዋሚዎች ናቸው’ ወዘተ እያለ ነበር።ሆኖም ግን ይህንን አባባል ገደል የሚከቱ በፖለቲካ ትንታኔ ምጥቀትም ሆነ በምርምር ላይ በተመሰረቱ ጥናታዊ ፅሁፎችን በማተም ዝናን ያተረፉትን እንደ ”አዲስ ነገር ጋዜጣ” እና  ”የአዲስ ጉዳይ” መፅሄትን ለህትመት እንዳይበቁ የጭካኔ በትሩን አሳረፈባቸው። ኢህአዲግ/ወያኔ ትውልዱን አደንቁሮ የመግዛት ደረጃውን ለመረዳት ሃገራችንን ከአሜሪካ እና አውሮፓ ህትመቶች ጋር እያወዳደርኩ አይደለም።ነፃነቷን ካገኘች ገና ግማሽ ክ/ዘመን ካስቆጠረችው  ከኬንያ ጋር ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ሁኔታ ማመላከት ብቻ  የኢህአዴግ/ወያኔ  ”አደንቁረህ ግዛ!” ፖሊሲምን ያህል አስከፊ እንደሆነ በግልፅ ያሳየናል።
ኢህአዲግ/ወያኔ እግር በእግር እየተከታተለ የህዝቡን የዕውቀት እና የማንበብ ባህል የሚገድልበት የግል ህትመት ውጤቶች ከሰማንያ ሶስት ሚልዮን በላይ ለሆነ ሕዝብ በአንድ ሳምንት ውስጥ የሚያሰራጩት የሕትመት ብዛት 20 ሺህ የማይሞላ ሲሆን በሕዝብ ብዛቷ ከኢትዮጵያ ከግማሽ በታች የሆነችው ኬንያ በእየቀኑ ብቻ ”ዴይሊ ኔሽን” የተሰኘው ጋዜጣ ብቻ ከሩብ ሚልዮን በላይ ለሆነ ሕዝብ አዳርሳ ታድራለች።ይህንን ወደ አንድ ሳምንት ስንቀይረው በኬንያ ብቻ ወደ 1.4 ሚልዮን የሚሆን ሕዝብ የሕትመት ውጤቶች በአንድ ሳምንት ውስጥ ይደርሱታል ማለት ነው።ይህ እንግዲህ በድረ-ገፅ የሚያነበውን አይጨምርም።
ኢህአዲግ/ወያኔ የማንበብ እና የማወቅ መብታችንን ማፈኑ ብቻ አይደለም ትውልዱ የማንበብ ባህሉ እንዲሞት በተለዋጭ ግን የጫት እና የሺሻ ሱሰኛ እንዲሆን ተገዷል።ይህ ታሪካዊ፣አድሏዊ እና ዘረኛ ወንጀል ነው።ምክንያቱም ይህ ተግባር በሁሉም የኢትዮጵያ ወጣት ላይ አልተደረገማ! ጫት እንዳይሸጥባቸው ሀሽሽ እንዳይዘወተርባቸው በቂ ቁጥጥር የሚያደርግ ክልል አለና! ”አደንቁሮ መግዛት” ማለት ይህ ነው።ከኢህአዲግ/ወያኔ መላቀቅ ማለት ከድንቁርና ነፃ መውጣት ማለት ነው።ይህ ደግሞ በትውልዱ ላይ የወደቀ ኃላፊነት ነው።ዕውቀት ወይስ ድንቁርና? ለትውልዱ የቀረቡ ሁለት ብቸኛ አማራጮች።

ጉዳያችን 

ነሐሴ 6/2006 ዓም (ኦገስት 12፣2014)

Monday, August 11, 2014

የከዱ የግንቦት 7 አባላት አቶ አንዳርጋቸውን እያሰቃዩ ነው ተባለ፤ * 2 መምህራንና 1 ዳኛ በአንዳርጋቸው ጉዳይ ታፍነዋል

August 11/2014
Andargachew Tsigeየአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን መያዝ ተከትሎ ለወያኔዎች ከአዲስ አበባ እስከ ደብረዘይት ትልቁን የምርመራ ስራ እየሸፈኑ ያሉት ከግንቦት ሰባት ሕዝባዊ ሃይል ጋር በኤርትራ የነበሩ እና ከአቶ አንዳርጋቸው ጋር የፖለቲካ ስራ ሲሰሩ የነበሩ በኋላም ከድተው የገቡ ቅጥረኞች መሆናቸው ታውቋል። እነዚህ ቅጥረኞች ከመጀመሪያው ሰርጎ ገቦች እንደሆኑ ሳይጠረጠር ወደ ግንቦት ሰባት ከገቡ በኋላ ከአቶ አንዳርጋቸው መያዝ ቀደም ብሎ በመክዳት ወደ ወያኔ የተቀላቀሉ ናቸው ሲል ጦማሪ ምኒልክ ሳልሳዊ ዘገበ።
እንደ ምኒልክ ዘገባ ከሆነ በአዲስ አበባ እና በደብረዘይት ትልልቅ ሆቴሎች ተይዞላቸው በምርጥ መኪኖች እየተንሸራሸሩ አቶ አንዳርጋቸውን በማሰቃያ ክፍል ውስጥ በማምጣት እውነቱን አውጣ አንተ እንደዚህ ብለኸን አልነበረም በማለት በተለያየ ጊዜ በስብሰባ እና በውይይት ወቅት የተነጋገሩትን የፖለቲካ ኦፕሬሽኖችን እና የትግል ስትራቴጂዎችን በመጥቀስ ከፍተኛ ስቃይ እና ድብደባ እያደረሱብት ነው።
ከሕወሃት ከአንድ ብሄር ከተመለመሉ መርማሪዎች ጋር በጋራ በምርመራ ላይ የተሰማሩት ሶስቱ የግንቦት ሰባት ከሃዲ አባላት አንዳርጋቸውን በማሰቃየት ላይ ያሉት -
1) ሽታው ሽፈራው ኤርትራ የነበረ የጎጃም ሰው
2) ቴዎድሮስ ስዩም ኤርትራ የነበረ ከአዲስ አበባ የሄደ
3) ኢልያስ ጥረት ጎንደር ውስጥ የነበረ እና ከአንዳርጋቸው ጋር ሲሰራ የነበረ ናቸው ሲል በዝርዝር የጠቆመው ጦማሪ ምኒልክ ሳልሳዊ በወያኔ ተንኮል ተተብትበው ግንቦት ሰባትን በመክዳት ለምቾታቸው የሕዝብን ትግል በጥቅም በመለወጥ በዘመናዊ መኪና እየተንፈላሰሱ በአዲስ አበባ እና ደብረዘይት ምርጥ ሆቴሎች ውስጥ እየተዝናኑ የነጻነት ታጋይ የሆነውን አንዳርጋቸውን በቶርች በማሰቃየት ላይ መሆናቸውን ዘግቧል።
ምርመርውን በመሪነት የሚያንቀሳቅሱት የሕወሓት ደህንነቶች የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ በአከባቤው አንዳርጋቸውን በተመለከተ ለብአዴን ይሁን ለ ኦሕዴድ ሰዎች ምንም አይነት መረጃ እንዳይሰጣቸውና ወደ ማሰቃያ ክፍሉ ምንም እንዳይቀርቡ ከፍተኛ ጥበቃ እየተደረገ እንደሆነ ለማረጋገጥ መቻሉን የገለጸው ጦማሪው ከአንዳርጋቸው ጋር የተያያዘውን የሃገር ውስጥ ኔትወርክ በማፈራረስ ረገድ ከላይ ስማቸው የተጠቀሰው ከሃዲዎች እስከ ክፍለሃገር ድረስ በስፋት እየሰሩ ሲሆን እስካሁን በማፈራረስ ሙከራው ምንም አይነት ውጤት እንዳልገኙ ታውቋል ብሏል።
ጦማሪው ዘገባውን ሲቋጭም “ከአንዳርጋቸው ጋር በተያያዘ ከየክልሉ የግንቦት ሰባት መዋቅር ውስጥ አሉ የተባሉ እየተለቀሙ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ከጎንደር ክፍለሃገር መምህር ተስፋዬ ተፈሪ እና መምህር ጌታቸው የተባሉ የሁለተኛ ደረጃ መምህራን እንዲሁም የጎንደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ እንደሆነ የሚነግረው አቶ አበራ በከሃዲዎች ጥቆማ ከሃምሌ አጋማሽ ጀምሮ ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ የት እንደታሰሩ እንኳን እንደማይታወቅ ተገልጿል።” ብሏል።
ከዘ - ሐበሻ የተወሰደ

ሬድዋን ሁሴን ማናቸዉ? አሁን ላሉበት የፓለቲካ ስልጣን እንዴት በቁ?

August 10/2014

ሙሉ ስማቸው ሬድዋን ሁሴን ይባላል፡፡ በ1987ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በባይሎጂ ከተመረቁ በኋላ በጂንካ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለጥቂት ጊዜ አስተምረዋል፡፡ ከጂንካም ለቀው በአዲስ አበባ አወሊያ ትምህርት ቤት ማስተማር እንደጀመሩ የህይወት ታሪካቸው ይነግረናል፡፡ አወሊያ ት/ቤት በነበሩበት ጊዜም ነው ፖለቲካን ከታች ሀ፣ ሁ፣ ሂ… ብለው መቁጠር የጀመሩት፡፡ የሬድዋን የፖለቲካ ሀ፣ ሁ፣ ሂም የተመሰረተው በሀገራዊ ጉዳይ ላይ ሳይሆን በስልጤ ህዝብ ማንነት ላይ ነበር፡፡ እናም ስልጤ በዞን ደረጃ ባለመዋቀሩ ከአካባቢው ተወላጆች ጋር ሲገናኙ ይቆጩና ይብሰከሰኩ ጀመር፡፡ በእርግጥ ጥያቄያቸው ተገቢ ሊሆን ይችላል፡፡ ሆኖም ይህችን ካርታ ብቻ መዞ ፖለቲካ ውስጥ መግባቱ ለትዝብት መዳረጉ አይቀሬ ነው፡፡ የሆነ ሆኖ ከጥቂት ጊዜያት በኋላም ይኽን ቁጭታቸውን ወደ ተደራጀ የፖለቲካ ትግል በማሸጋገር የስልጤ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ስሕዴፓ) የተሰኘ የተቃዋሚ ድርጅት መሰረቱ፡ ፡ በፓርቲያቸው አስተባባሪነትም የተቃውሞ ሰልፍ እስከ ማድርግ ደረሱ፡፡ 


ምንአልባትም የዛሬው ድርጅታቸው ኢህአዴግ አርቆ አሳቢነት የፈጠረው ይሁን ወይም ሌላ፣ ድንገት የሬድዋንን ፓርቲ የሚቃወም አዲስ ፓርቲ ብቅ አለ፣ በአሁኑ ወቅት የመከላከያ ሚኒስትር በሆኑት ሲራጅ ፈርጌሳ አማካኝነት ይመራ የነበረው ይህ ፓርቲ የስልጤ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ስሕዴድ) ይሰኛል፡፡ … እሾን በእሾህ፣ ፓርቲን በፓርቲ፡፡ እናም የሬድዋን ትግል ከኢህአዴግ ጋር ብቻ መሆኑ ቀርቶ ከሌላኛው የስልጤ ህዝብ ድርጅት ጋርም ሆነ፡፡ በሁለቱ ድርጅቶች መካከልም የከረረ የውክልና ፉክክር ተፈጠረ፡ ፡ በሽግግር መንግስቱ ዘመን ‹‹የኦሮሞን ህዝብ በትክክል የምወክለው እኔ ነኝ›› በሚል በኦነግ እና በኦህዴድ መካከል የነበረው ፉክክር አይነት ወራቤ ላይም ተደገመ፡፡ ቃላቶችን እያሰካኩ ያለማቋረጥ የመናገር ተሰጥኦ ያላቸው ሬድዋንም በአገኙት አጋጣሚ በሲራጅ ፈርጌሳ የሚመራውን ስሕዴድ ‹‹የኢህአዴግ ተላላኪ፣ ተለጣፊ፣ አሻንጉሊት…›› እያሉ ይተቹት እንደነበር የትላንት ትውስታ ነው፡፡ ትውስታችንንም በማስረጃ ለማስደገፍ ያህል ሬድዋን የተቃዋሚ ፓርቲ ሊቀመንበር በነበሩበት ዘመን በ1993 ዓ.ም. ታህሳስ ወር ከታተመው ከጎህ መጽሔት ጋር ከአደረጉት ቃለ መጠይቅ ጥቂቱን እንቀንጭብ፡፡ መጽሔቱም የሳቸውን ድርጅት የማይደግፉ የስልጤ ተወላጆች መኖራቸውን ጠቅሶ ይኼ ከምን የመነጨ እንደሆነ እንዲያብራሩለት ጠየቃቸው፡፡ ሬድዋንም ሲመልሱ እንዲህ አሉ፡- ‹‹…የስልጤን ብሔረሰብ በተለያየ ስያሜ ፈርጀው የተንቀሳቀሱት የብሔረሰቡ ተወላጆች የኋላ ኋላ እውነቱን ቢረዱም ጥቅም ፍለጋ በዚያው ሰክረው ቀሩ እንጂ የተፈጠረው ምስቅልቅል በመጀመሪያ የራሱ የሆኑ መነሻዎች አሉት፡፡›› ሬድዋን ወደ ኢህአዴግ ያዘነበሉትን የስልጤ ተወላጆችን ነው ‹‹ጥቅም ፍለጋ በዚያው ሰክረው ቀሩ›› ሲሉ የወነጅሉት፡፡ በዛ በደጉ ዘመን፡፡ በእርግጥ ዛሬ ሬድዋን እንዲህ ሊሉ አይችሉ፡፡ 

በብራሃን ፍጥነት ራሳቸውም ከዋነኞቹ ኢህአዴጎች አንዱ ሆነዋልና፡፡ ሆኖም ሬድዋን ከኢህአዴግ ተቃዋሚነት ወደ ኢህአዴግ አመራርነት የተሸጋገሩበት ምክንያት ‹‹ጥቅም ፍለጋ በዚያው ሰክረው ቀሩ›› ሲሉ የወነጀሏቸውን ሰዎች ፈለግ ተከትለው ይሁን ወይም የግንባሩ ፖለቲካ አዋጭነት ገብቷቸው ከሳቸው ሌላ የሚያውቅ የለም፡፡

Sunday, August 10, 2014

የአንዳርጋቸዉ ትዉስታዎች

August10/2014

“በእኛ እምነት ታሪክ ከነባራዊ ሁኔታ ዉጭ በምኞትና በዘፈቀደ አይሰራም። የሚሰራ ቢሆን ኖሮ ነገስታቱና አምባገነኖቹ ዘሬም በዙፋናቸዉ ላይ በተገኙ ነበር። ባለንበት ወቅት የኢትዮጵያ ህዝቦች መስቀለኛ መንገድ ላይ ቆመዉ ከዚህ ወዴት እንደሚሄዱ ግልጽ ኢየባልሆነበት ሰዐት ሥልጣን ላይ ያለዉም ሆነ የሌለዉም የግሉን የተስፋ ጎዳናን እዉነተኛዉ የወደፊት ጎዳና አድርጎ የሚያይ ከሆነ ዛሬም እንደ ትናንቱ ከታሪክ መማር አልቻልንም ማለት ነዉ”።
“ከዲሞክራሲ ጋር ሲወዳደር ፍትህ ለሚለዉ ጽንሰ ሀሳብ “ኢትዮጵያዊኛ” ቃላቶች ያሉን መሆኑ የሚያስረግጠዉ ነገር ቢኖር ፍትህ ከማንነታችን ጋር የተቆራኘ መሆኑን ነዉ። ኢትዮጵያዉያን ፍትህ ሲጓደል “በህግ አምላክ” ብለዉ በዳያቸዉን ለማስቆም የሚያሰሙት ጩኸት ፍትህ ከፈጣሪያቸዉ የተሰጠ ከሰብዓዊነታቸዉ ተነጥሎ የማይታይ እሴት አድርገዉ እንደሚመለከቱት የሚያመለክት ነዉ። በምድር ላይም ፍትህ የሚሰጥ ዳኛ ጠፍቷል ብለዉ ሲያስቡ እጃቸዉን ወደ ፈጣሪያቸዉ ዘርግተዉ አንተዉ ፍርዱን ስጠና የሚሉት ከፈጣሪያቸዉ ፍጹምነት የሚመነጭ እዉነተኛ ዳኝነት አለ ብለዉ ስለሚያምኑ ነዉ። ከዚህ በላይ ባጭሩ የተባለዉ የሚጠቁመዉ በኢትዮጵያዉያን ባህልና ስነ ልቦና ዉስጥ የፍትህ ጽንሰ ሀሳብ ያለዉን ትልቅ ትርጉምና ቦታ ነዉ”።
የታሪክን ነባራዊነት፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ለፍትህ የሚሰጠዉን ከፍተኛ ቦታና ለነጻነት ያለዉን አመለካከት በተመለከተ ከዚህ በላይ ያሰማናችሁን ሁለት አዉዶች በሁለት የተለያዩ መጽሐፎቹ ዉስጥ የጻፈዉ ዛሬ ፍትህ አልባ በሆነዉ የወያኔ ስርዐት ዉስጥ ለፍትህ፤ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ ሲል ለፍተኛ ዋጋ እየከፈለ ያለዉ አንዳርጋቸዉ ጽጌ ነዉ። አዎ የፍትህና የነጻነት አርበኛዉ አንዳርጋቸዉ በግልጽ አንዳስቀመጠዉ ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ ፍትህ እስከነ ስሙ ሙልጭ ብሎ በመጥፋቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ሁለት እጆቹን ወደ ሰማይ ዘርግቶ እባክህ አምላኬ “ወይ ዉረድ ወይ ፍረድ” እያለ ፈጠሪዉን እየተማጸነ ነዉ። በእርግጥም ፍትህ ፈጣሪያችን ያደለን ትልቅ ማህበራዊ እሴት ነዉ፤ ሆኖም ይህንን የፈጣሪ ስጦታ እኛን የመሰሉ ሌሎች ሰዎች መጥዉ ሲቀሙንና እንዳሰኛቸዉ ሰረግጡን አንረገጥም ብለን እራሳችንን ነጻ ማዉጣትና የተቀማነዉን ፍትህ ከወያኔ ዘረኞች ቀምተን መልሰን ማህበራዊ እሴት የማድረጉ ኃላፊነት የእኛ የራሳችን ነዉ እንጂ የፈጣሪ አይደለም። ፈጣሪያችን ፍትህና ነጻነትን አንዴ ሰጥቶናል እነዚህን የፈጣሪ ስጦታዎች እንዳንቀማ መጠበቅና ከተቀማን ደግሞ ታግለን ማስመለስ ያለብን እኛ ብቻ ነን።
አንዳርጋቸዉ ጽጌ የአማራዉ ህዝብ ከየት ወዴት በሚለዉ መጽሐፉ ታሪክ ከነባራዊ ሁኔታ ዉጭ በምኞት ወይም በዘፈቀደ እንደማይመራና ከትናንት ታሪካችን ካልተማርን የምንደግመዉ ትናንትናና ከትናንት ወዲያ የሰራናቸዉን ስህተቶቻችንን አንደሆነ በግልጽ አስገንዝቦናል። ይህ የአንዳርጋቸዉ ማስገንዘቢያ ያነጣጠረዉ ለመብቱና ለነጻነቱ መከበር ለሚታገለዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ህዝብ ረግጠዉ እየገዙ ዝንተ አለም መኖር ለሚፈልጉ የወያኔ ዘረኞችም ጭምር ነዉ። ለመሆኑ አንዳርጋቸዉ ከታሪክ አልተማርንም ማለት ነዉ ሲል ምን ማለቱ ነዉ? . . . “አልተማርንም” የሚለዉ ቃል ለአንድ ሰዉ የሚነገር ቃል ሳይሆን ለብዙኋን የሚነገር ቃል ነዉ። በዚህ ብዙኋን ዉስጥ በአንድ በኩል በየዘመኑ እየረገጡ ከሚገዙት የገዢ መደቦች ጋር የሚታገለዉ የኢትዮጵያ ህዝብ አለ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ህዝብን ረግጠዉ እየገዙ መኖር የሚፈልጉ የገዢ መደቦች አሉ። የኢትዮጵያ ህዝብ በ1966 ዓም የፊዉዳል ገዢ መደቦችን አንኮታኩቶ ከጣለ በኋላ ለሚቀጥሉት 17 አመታት ሰዉ በላዉን የደርግ ስርዐት ተሸክሞ ኖሯል። በ1983 ዓም የኢትዮጵያ ህዝብ አሁንም ወታደራዊዉን የደርግ ሰርዐት በህዝባዊ አመጽ ማስወገድ ችሎ ነበር፤ ሆኖም አሁንም ይህ ህዝብ የታገለለት ድል ባለቤት መሆን ባለመቻሉ ዘረኛ አምባገነኖች መዳፍ ዉስጥ ገብቶ ቁም ስቅሉን እያየ ነዉ። አንዳርጋቸዉ ጽጌ ይህንን የጥፋት ዑደት በሚገባ ተገንዝቦ ነዉ ከታሪክ አልተማርንም ብሎ የነገረን።
በ1966 ዓም ጩኸታችን በሙሉ የፊዉዳሉ ስርዐት እንዲፈርስ ነበር እንጂ የምናፈርሰዉ ስርዐት በምን ይተካል ለሚለዉ ጥያቄ መልስ ስላልነበረን በወቅቱ በስራዉ ጠባይ የተነሳ ተደራጅቶ የነበረዉ የወታደሩ ክፍል ስልጣን ተረክቦ አገራችን 17 አመት ሙሉ የደም ባህር ዉስጥ እንድትዋኝ አድርጓታል። የደርግን ስርዐት ለማፍረስ በተደረገዉ ትግል ዉስጥም ከ1966ቱ ስህተታችን ምንም ባለመማራችን መሳሪያ ከታጠቀ ኃይል ሁሉ ጋር ጉሮ ወሸባዬ መዝፈን ጀመርን። ደርግን የሚዋጉ ኃይሎች ሁሉ የህዝብና የአገር ወዳጆች እየመሰሉን በየጫካዉ እየሄድን ተቀላቅለናቸዉና ዛሬ ይሄዉና እኛዉ እራሳችን ያጠናከርናቸዉ ኃይሎች ስልጣን ይዘዉ ካፈረሱት ስርዐት በከፋ መልኩ አገርንም ህዝብንም እያፈረሱ ነዉ። ደርግ ከፊዳሉ ስርዐት ዉድቀት ምንም ባለመማሩ ሃያ አመት ሳይሞላዉ እሱም እንደ ፊዉዳሉ ስርዐት የታሪክ ቆሻሻ ዉስጥ ተጥሏል። ከፊዉዳሉም ከደርግም ስርዐት ዉድቀት መማር ያልፈለጉት የዛሬዎቹ ዘረኞች ደግሞ የማይቀረዉን ዉድቀታቸዉን እየጠበቁ ነዉ። የወያኔ ዘረኞች ከታሪክ አለመማር ካሁን በኋላ ሊገርመን ወይም ሊያጠያይቀን አይገባም፤ እነሱ ወደዱም ጠሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ያስተምራቸዋል። ዛሬ ዋናዉ ቁም ነገር ወይም ትልቁ ጥያቄ እኛ ካለፉት ሁለት ግዙፍ ስህተቶቻችን ተምረናል ወይ የሚለዉ ጥያቄ ነዉ፡፡ ስራችን የወያኔን ስርዐት ማፍረስ ብቻ ነዉ ወይስ ከወያኔ መፍረስ በኋላስ ለሚለዉ ጥያቄ መልስ አለን። ወያኔን እያፈረስን ስንሄድ ከማፍረስ ጎን ለጎን ወያኔን የሚተካ ስርዐት እየገነባን ነዉ ወይስ ሩጫችን ሁሉ ማፍረሱ ላይ ብቻ ነዉ ያተኮረዉ።
የወያኔን ስርዐት ለማፍረስ በሚደረገዉ ትግል ዉስጥ የተቃዋሚ ኃይሎች መሰባሰብና በአንድነት መቆም ቁልፍ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፤ ሆኖም በእኛ እምነት እጅግ በጣም ከባዱና ዉስብስቡ ስራ ወያኔ የፈጠረዉን ዘረኛ ስርዐትና ቆሻሻ ባህል ማፈራረስና በምትኩ ሌላ መገንባት ነዉ እንጂ ወያኔን ማስወገዱ አይደለም። ወያኔ በህዝብ የተጠላና የተተፋ ስርዐት ስለሆነ በራሱ ዉስጥ በሚፈጠር ቀዉስ ወይም በአንድ እራሱን ለህዝባዊ አመጽ ባዘጋጀ ጠንካራ ድርጅት ተጠራርጎ ሊጠፋ የሚችል ድርጅት ነዉ። ለአገራችን ለኢትዮጵያ በጎ የምንመኝና ዛሬ ወያኔን በተለያየ መልኩ የምንፋለም የነጻነት ኃይሎች አጅግ በጣም ሊያሳስበን የሚገባና አገራችን ኢትዮጵያም በቀላሉ የማትወጣዉ ማጥ ዉስጥ የምትገባዉ ወያኔ ከእነዚህ ሁለት መንገዶች በአንዱ ከወደቀ ነዉ። ይህንን ታሪካዊ ጥፋት እዉን ከመሆኑ በፊት መቀየር የምንችለዉ ደግሞ ወያኔ ከወደቀ በኋላ ሳይሆን ዛሬ ለመዉደቅ ሲንገዳገድ ነዉ።
አንዳርጋቸዉ አገራችን ብዙ አደጋዎች ፊቷ ላይ አንደተደቀኑባት በትክክል ካሳየን በኋላ አደጋዎቹን አንዴት መከላከል አንዳለብንም በቃላትና በንድፈ ሃሳብ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በተግባርም በረሃ ዉስጥ ገብቶ መሬት ላይ እየተኛ ያሳየን የተግባር ሰዉ ነዉ። ዛሬ የወያኔ ዘረኞች አንዳርጋቸዉን አስረዉ የሚያሰቃዩት የአንዳርጋቸዉ ዕቅድና የጀመራቸዉ ስራዎች የእነሱን ቆሻሻ ስርዐት ጠራርጎ ኢትዮጵያን እንደሚያጸዳ ከወዲሁ ስለተረዱ ብቻ ነዉ። በእርግጥም አንዳርጋቸዉ የሽብርተኞች ድርጅት መሪ ቢሆን ኖሮ ጨዋዉና አርቆ አስተዋዩ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያሸብረዉ ሰዉ ሲታሰር ደስታዉን ነዉ እንጂ ቁጣዉንና ሀዘኑን አይገልጽም ነበር። የአንዳርጋቸዉ መታሰርና አንደ ማዕበል ገንፍሎ የወጣዉ ህዝባዊ ቁጣ ወለል አድርጎ ያሳየን ነገር ቢኖር አትዮጵያ ዉስጥ አሸባሪዉ ማን እንደሆነ ነዉ።
ወያኔን የሚተካ ጤነኛ አካል ሳናዘጋጅ በጅምላ ወያኔ ይወገድ አንጂ ከዚያ በኋላ ያለዉ አይቸግርም የሚለዉ አባባል አደገኛ አባባል ነዉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ መስማማት አቅቶን ለእነዚህ የቀን ጅቦች የምንሰጣቸዉ ግዜና በየግላችን በተናጠል የምናደርገዉ ጉዞ አገራችን ኢትዮጵያን ከድጡ ወደ ማጡ ይዟት የሚሄድ አጅግ በጣም አደገኛ ጉዞ ነዉ። “እኔም አንዳርጋቸዉ ነኝ” ስንል እናት አገራችን ኢትዮጵያን ከእንደነዚህ አይነት አደጋዎች ለማዳን ምንም አይነት መስዋዕትነት ለመክፈል ተዘጋጅተናል ማለት ነዉ።
የለበስነዉ ልብስ ከመጠን በላይ ሲቆሽሽ ያለን ምርጫ የተዘጋጀ ቅያሪ ካለን እሱን ቀይረን የቆሸሸዉን ማጠብ ነዉ፤ ቅያሪ ካሌለን ግን አዲስ ልብስ መግዛት ነዉ ያለብን እንጂ መቼም ካላበድን በቀር በቆሻሻ የጀቦደ ልብስ ለብሰን አደባባይ አንወጣም። ከ1966ቱና ከ1983ቱ ታሪካዊ ስህተቶች የተማርን ኢትዮጵያዉያንም ማሰብና ማድረግ ያለብን እንደዚሁ ነዉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ ስርዐት ከመጠን በላይ ቆሽሿልና በበረኪና ታጥቦ የሚጸዳ ከሆነ በፍጥነት መታጠብ አለበት፤ አለዚያም ወያኔን ከማስወገዱ ሂደት ጋር ጎን ለጎን የሚሄድ አዲስ ስርዐት በጋራ መገንባት እንዳለብን ለአፍታም ቢሆን ልንዘነጋዉ የማይገባን ኢትዮጵያዊ አደራ ነዉ።
ዛሬ እጁ በዘረኞች ተይዞ የሚሰቃየዉ አንዳርጋቸዉ ጽጌ የኑሮ ጓደኛዉን፤ አንድ ፍሬ ልጆቹንና ወንድሞቹን ትቶ ከሞቀዉ የአዉሮፓ ኑሮ በረሃ ወርዶ የማደራጀትና የማስተባበር ስራ መስራት የጀመረዉ እነዚህ ከላይ የጠቀስናቸዉን የአገራቸን ዉስብስብ ችግሮች በሚገባ ስለተገነዘበና ያለፉት ስህተቶቻቸን ላለመድገም የቆረጠ ሰዉ ስለሆነ ነዉ። አንዳርጋቸዉ ከታሪክ እንማር ሲል የፍትህና የዲሞክራሲ ትግላችን አላማና ግብ ወያኔን መጣል ብቻ ሳይሆን ካሁን በኋላ በሰላምና በእኩልነት ሊያኖረን የሚችል ስርዐትም መገንባት አለብን ማለቱ ነዉ። አንዳርጋቸዉ ፍትህ የምንለዉ ጽንሰ ሃሳብ ከኢትዮጵያዊ ማንነታችን ጋር የተቆራኘ ነዉ ሲል ይህንን ከማንነታችን ጋር የተቆራኘ ትልቅና እጅግ በጣም አስፈላጊ ማህበራዊ እሴት በዘረኞች ተቀምተን እንኳን ሃያ ሦስት አመት አንድ ምሽትስ ቢሆን እንዴት ተኝተን እናድራለን ማለቱ ነዉ። አንዳርጋቸዉ ለአገራችን አንድነትና ለዲሞክራሲ መብታችን መከበር እስከ ሞት ድረስ መሄድ አለብን ሲል ዲሞክራሲ ያልሞረደዉ አንድነት ወይም አንድነት ያልሞረደዉ ዲሞክራሲ እስካልገነባን ድረስ ትግላችን አያቆምም ማለቱ ነዉ።
ዛሬ በአለም ዙሪያ በአራቱም ማዕዘን ኢትዮጵያዉያን “እኔም አንዳርጋቸዉ ነኝ” በሚለዉ መፈክር ዙሪያ የተሰባሰቡት የአንዳርጋችዉ አላማና የአርባ አመት ጉዞ የእነሱም አላማና የወደፊት ጉዞ ነዉ ብለዉ ስለሚያምኑ ነዉ። “እኔም አንዳርጋቸዉ ነኝ” ማለት እኔም ልክ እንደ አንዳርጋቸዉ ጽጌ፤ እንደ እስክንድር ነጋ፤ ሠላማዊት ሞላ፤ በቀለ ገርባ፤ አንዱአለም አራጌና ዞን ናይን ብሎገርስ የመብት፤ የነጻነት፤ እኩልነትና የአገር አንድነት ጉዳይ ያንገበግበኛልና ለእነዚህ እሴቶች መከበር እኔም አንደነዚህ ጀግኖች ኢትዮጰያዉያን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነኝ ማለት ነዉ።በአለማዉ የሚጸና፤ ለአላማዉ ግብ መምታት የተዘጋጀና በህይወቱ የቆረጠን ሰዉ ደግሞ ከድል ወዲህ ማዶ የሚያቆመዉ ምንም ምድራዊ ኃይል የለም።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

ደጋፊዎችን የማሰባሰብ ጥረት

August10/2014
የንቅናቄዓችን ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ በህሊናና የፓለቲካ እስረኞች ሁሉ ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ መክበድ፤ በፀረ-ሽብርተኝነት ስም በሕዝብ ላይ የሚነዛው ወያኔያዊ ሽብር መብዛት፤ እስሩ፣ እንግልቱ፣ መሳደዱ፣ የሀብት ዘረፋው በየዕለቱ እየጨመረ መምጣት እና ለአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ኑሮ እየከበደ መምጣቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከወያኔ ጋር ወሳኝ የሆነ ትግል መግጠሚያ ወቅት ላይ መደረሱ አመላካች ሆኗል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ የትግል መንፈስ መነሳሳት በተጨባጭ ከሚያረጋግጡ አመላካቾች አንዱ የግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አባል ለመሆኑ የሚፈልጉ ዜጎች ቁጥር በከፍተኛ መጠን መጨመር ነው። ይህንን ለውጥ ተከትሎም ግንቦት 7 የአባላት ቅበላን ሥራ ለማፋጠን የሚረዱ እርምጃዎች ወስዷል። ሆኖም ግን በአባላት ቅበላ ወቅት ሊታለፉ የማይችሉ ጥንቃቄዎች መኖር እንዳለባቸው ደጋፊዎችም እጩ አባላትም ይረዳሉ ተብሎ ይታመናል።
በዚህም ምክንያት አሁንም እየጨመረ የመጣን ንቅናቄውን የመቀላቀል ፍላጎትን ለማስተናገድ፤ ለተግባራዊ ሥራዎች የተነሳሱ፣ ዓላማችንና ንቅናቄዓችንን የሚደግፉ ሆኖም ግን በተለያዩ ምክንያቶች በድርጅት አባልነት መቀላቀል የማይችሉ ወይም የማይፈልጉ አባላትን ለማሳተፍ የሚረዳ መዋቅር ማዘጋጀት ተገቢ መሆኑ ታምኖበታል። ስለሆነም እነዚህን ወገኖቻችን የትግላችን አካል ብቻ ሳይሆን የንቅናቄዓችንም አካል ለማድረግ እንዲቻል በአባላት ጉዳይ ሥር የደጋፊዎች ማስተባበሪያ መዋቅር እንዲደራጅ ተደርጓል። ይህ አደራጀት ግንቦት 7ን ለማዘመን እና ለኢትዮጵያዊያን ሁሉ የተመቸ ድርጅት ለማድረግ የሚደረገው ጥረት አካል ነው። ይህ አደረጃጀት በአንድ በኩል የድርጅቱን ምስጢራዊት ለመጠበቅ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ተደራሽ ለማድረግ ባሉ ፍላጎቶች መካከል ያለውን ቅራኔ ለመቅረፍ የቀረበ መፍትሔ ነው።
በዚህም መሠረት በአባልነት ለመመዝገብ ስለእናንተ ምስክርነት መስጠት የሚችል የግንቦት 7 አባል ማቅረብ ለጊዜው ያልቻላችሁ፤ ወይም በሌላ ማናቸውም ምክንያት የግንቦት 7 ደጋፊ እንጂ አባል መሆን የማትፈልጉ ወገኖቻችን ግንቦት 7 ፍላጎታችሁን የሚያሟላ መዋቅር ማዘጋጀቱን በይፋ ያበስራል።
የግንቦት 7 ደጋፊ በግንቦት 7 የውስጥ ጉዳዮች የመወሰን፣ የመምረጥና የመመረጥ መብት አይኑረው እንጂ የንቅናቄው ሙሉ ተሳታፊና ባለቤት በመሆኑ በልበ ሙሉነት “እኔም ግንቦት 7 ነኝ” ማለት ይችላል። የግንቦት 7 ደጋፊ እንደማንኛውም አባል ድርጅታዊ ሥራዎች ሊሰጡት ይችላል።
በደጋፊነት ለመመዝገብ ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ ኢሜል፣ እድሜ፣ ጾታ፣ ከተማና የሚኖርበት ሀገር ብቻ የሚጠይቅ የድህረ ገጽ ቅጽ መሙላት ያስፈልጋል። ይህ ቅጽ በንቅናቄው ድህረ ገጽ ላይ ይገኛል። ደጋፊዎች እውነተኛ ስማቸውን የመስጠት ግዴታ የለባቸውም። አንድ ደጋፊ በየወሩ የሚፈቅደውንና የሚችለውን ያህል ገንዘብ እንደሚያዋጣ ይጠበቅበታል፤ ይህ የደጋፊነቱ አንዱ መገለጫ ተደርጎ ይወሰዳል። ደጋፊ በሚኖርበት ከተማ በሚደረጉ የትግል እንቅስቃሴዎች ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ ይጠበቅበታል፤ ይህም ሌላው የደጋፊነት መገለጫ ነው። ደጋፊዎች የንቅናቄው ሳምንታዊ ጋዜጣና ወርሃዊ ልዩ መልዕክት በግል ኢሜላቸው እንዲደርሳቸው ይደረጋል። ደጋፊዎች በተግባር በሚያሳዩት ተሳትፎ ከአባላት ጋር ቅርርብ በመፍጠር ወደ ከደጋፊነት ወደ አባልነት የሚሸጋገሩትን መንገድ ያመቻችላቸዋል።
በተለያዩ ምክንያቶች ራሳችሁን በህወሓትና ጀሌዎቹ መዋቅር ውስጥ ያገኛችሁና በወያኔ እኩይ ተግባራት የህሊና እረፍት ያጣችሁ የሕዝብ ወገኖች ይህንን መዋቅር ከግንቦት 7 ጋር በምስጢር ለመገናኛነት ተጠቀሙበት። በመከላከያና በፓሊስ እንዲሁም በራሱ በኢሕአዴግ ውስጥ ያላችሁ ወገኖቻችን ይህንን መስመር በግኑኝነት መመስረቻነት ተጠቀሙበት። በወያኔ የስለላ ወዋቅር ውስጥ ያላችሁም እድሉን ተጠቀሙበት።
በድህረ ገጻችን ላይ http://www.ginbot7.org/supporter-form/ በቀጥታ በመመዝገብ የግንቦት 7 ደጋፊ መሆን ይቻላል። ድረገጹ በማይከፈትባቸው ቦታዎች በ supporter@ginbot7.org ይፃፉ።

‹‹አያ ጅቦ ሳታመኻኝ ብላኝ›› በበፍቃዱ ሃይሉ (ከቂሊጦ እስር ቤት)

August 10/2014
10425046_735506299828810_9070794374192798618_n[ከመቶ ሰባት ቀናት እስር በኋላ በፍቄ ሰለ እስሩ ስለ ምርመራው እና ስለ ወደፊት ተስፋቸው ከቂሊጦ እስር ቤት የሰደዳት መልዕክት ይቺትና። እኔ ጽሁፉን ሳነብ የመጣብኝ ሃሳብ እነዚህ ሰዎች በርካታ ንጹሃንን እስከዛሬ ማንም ሳያያቸው ሲያሰቃዩ የስቃዩ ሰለባዎች ዘጋቢዎች እና ጋዜጠኞች ካልሆኑ የስቃያቸውን መጠን የሚገልጹት በእንባ እና... ''ተወው... ተወው አይነሳ...'' በሚል ምሬት ብቻ ነበር። አሁን ግን በራሳቸው ጊዜ ዘጋቢዎችን ወደ ማዕከላዊ እያስገቡ እነሆ የኢህአዴግ ''አመራር ጥበብ''ን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ሰዕላዊ መግለጫ እየሰጡን ነው።
ኢህአዴግ ሆይ፤ በጥፊ በርግጫ አይገኝም ምርጫ፤ እያልን የበፍቄን ጽሁፍ ሁሉም ሰው ያነበው ዘንድ ይሄው...
‹‹አያ ጅቦ ሳታመኻኝ ብላኝ›› በበፍቃዱ ሃይሉ.
‹‹ታዲያ ጥፋቴ ምንድን ነው ትላለህ?!››፣ ብሎኛል አንዱ መርማሪዬ ስለዞን ዘጠኝ እና እኔም እራሴ እንደጦማሪም እንደአራማጅ ተራማጅም ሠራሁ የምላቸውን ነገሮች ዝርዝር ነግሬው ሳበቃ፡፡ በኋላ ላይ በእስር ቤት ቋንቋ ከ‹‹አባሪዎቼ›› ጋር መገናኘት ከተፈቀደልን በኋላ ስንጠያየቅ ለካስ ሁላችንም ይቺኑ ጥያቄ ተጠይቀናል፡፡ ይኼ ነው እንግዲህ የምርመራችንን ሒደት የሚገልፀው ጥያቄ፡፡ ‹‹ተጠርጥረን›› የተያዝንበትን ጉዳይ የሚያረጋግጥ ሥራ ሠርተን ባለመገኘታችን (ወይም ‹‹ባለመናገራችን››) ታዲያ ጥፋትህ ምንድን ነው? ተባልን፡፡ ምርመራው የኛን ነፃ መሆን አለመሆን ለማጣራት ሳይሆን ጥፋት ለማግኘት ነበር፡፡ ብዙዎች ‹መንግሥት ዞን ዘጠኝን ለምን ሁለት ዓመት እንደታገሠው› ግራ በመጋባት ይጠይቃሉ፤ ባሕሪው አይደለምና፡፡ የኢትዮጵያ ሀሳብን የመግለጽ ነጻነት ምኅዳር በቀላሉ እንደገመቱት ተይዘን፣ ተመርምረንና ‹‹ተገኘባችሁ›› የተባልነው ‹‹ የግንቦት 7 [እና ኦነግም ጭምር] አባልነት [ብሎም ግብ አስፈጻሚነት] ›› በሽታ ለተከሳሽነት አብቅቶናል፡፡ ቀጣዩ የክርክር ሂደት ነው፡፡
ከዚያ በፊት ግን ዞን ዘጠኝን በሩቅም በቅርብም የሚያውቁ በግራ መጋባት መልስ እንደሚሹ በማሰብ ይቺን አጭር ማስታወሻ ለመጻፍ ተገድጃለሁ፡፡ የእስራችን ሂደት ምን ይመስላል? የምርመራችንስ? እውን የግንቦት ሰባት አባል ነን? [ታዲያ] ለምን ታሰርን? በቅርቡ እንፈታ ይሆን?
ደቂቅም ይሁን ሊቅ ስለኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እውነታ የሚጽፍ ማንኛውም ሰው [ኢትዮጵያ ውስጥ ሳለ] አንድ ቀን እታሰር ይሆን እያለ መስጋቱ አይቀርም ፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም በአንድ መጽሐፋቸው ላይ ሰው ነገረኝ ብለው የኢትዮጵያ ሕዝብን በሦስት የመደቡት፡- የታሰረ፣ ታስሮ የተፈታ እና ወደፊት የሚታሰር በማለት፡፡ እርግጥ ዞን ዘጠኝ ‹‹ሐሳቡን መግለጽ ፈርቶ ዝም ያለ ሁሉ እስረኛ ነው›› ብሎ መደምደም ሦስቱም ምድብ አንደኛው ውስጥ ያጠቃልለዋል ‹‹የታሰረ›› በሚል፡፡ ዞን ዘጠኞች ጦማራችንን በከፈተን በሁለት ሳምንት ሲታገድብን እና ሌላ ስንከፍት ግና መጨረሻ ላይ ታጋቾቹ እኛ እንደምንሆን እናውቅ ነበር፡፡ ያንን የሚያረጋግጥ ተደጋጋሚ የደህንነቶች ክትትል እና ምልክቶች ስለደረሱን መታሰራችን ማስደንገጡ ባይቀርም ያልተጠበቀ ግን አልነበረም፡፡
እስሩ በክትትሉ የተገኘነውን ስድስት የዞን ዘጠኝ አባላት እና ሦስት ጋዜጠኛ ጓደኞቻችንን መሆኑን በተለይ የጋዜጠኞቹ [ቢያንስ ለእኛ] ያልተጠበቀ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ የኋላ ኋላ ስንመለከተው ግን በእኛ አስታኮ እነሱንም ማሰሩ የታሰበበት ዘመቻ እንደሆነ መገመት አይከብድም፡፡ እኛን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ሒደትም ቢሆን በቅጡ የታሰበበት ነበር ሁላችንም (ከአስማማው በቀር) ከቀኑ በ11፡00 ገደማ በያለንበት ስንያዝ አስማማው በማግሥቱ ታስሯል፡፡ ሌሎቻችን ቤታችን በሚፈተሸበት ሰዓት ሕጉ የሚፈቅድበት ሰዓት(12፡00) አልፎ ነበር፡፡ በቁጥጥር ስር ካዋሉን በኋላ የሕገ-ወጥ አያያዝ ሰለባ የመሆናችን ሂደት የሚጀምረው ከዚህ ነው፡፡
ማዕከላዊን በክፉ ስሙ ቀድሞ ለሚያውቀው ሰው ግቢውን መርገጥ በራሱ ልብን ያርዳል፡፡ ሆኖም በልቤ /ጓደኞቼም እንደእኔ ሳይሰማቸው አይቀርም/ አንደኛ እኛ ጸሐፊ እንጂ ወታደር ወይም ሰላይ ባለመሆናች፣ ሁለተኛ መቼም ከበፊቱ የተሻለ ሰብዓዊ አያያዝ ሳይኖርም አይቀርም የሚል የዋህ ተስፋ በማሳደሬ ብዙም አልተሸበርኩም ነበር፡፡ የገባሁ እለት ከታሳሪዎች በተሰጠኝ ማብራሪያ ‹‹ሳይቤሪያ›› መግባቴን አወቅኩ፡፡ ከዚያ የ HRW-They want confession የተሰኘ ሪፖርት ላይ የተፃፉ ነገሮች ሁሉ ትክክል መሆናቸውን ለመረዳት የፈጀብኝ ከአንድ ሳምንት ያነሰ ጊዜ ነበር፡፡
ምርመራ ማዕከላዊ ስታይል
ምርመራ በማዕከላዊ ከብልጠት ይልቅ ጉልበት ይበዛበታል፡፡ መርማሪዎቹ የምርመራ ችሎታቸው ተጠርጣሪውን የተጠረጠረበትን ጉዳይ ከማውጣጣት ይልቅ የምርመራ ችሎታ እንዳላቸው ለማሳመን የሚጥሩበት ጊዜ ይበዛል፡፡ ይህም አልሰራ ሲል ጥፊ፣ ካልቾ፣ ከአቅም በላይ ስፖርት ማሰራት እና ግርፋት ድረስ ይዘልቃሉ፡፡ ይህ እንግዲህ እኔ ላይ ከተፈራረቁብኝ አምስት መርማሪዎች እና ሌሎችም አብሮ ታሳሪዎቼ ከነገሩኝ የተረዳሁት ነው፡፡ እርግጥ ሌሎች ‹‹እርቃንን ቁጭ ብድግ›› የሰሩ ተጠርጣሪዎችም ገጥመውኛል፡፡ ከባባድ ቅጣት (ወፌ ላላ ግርፋት፣ ጥፍር መንቀል) የደረሰባቸው ሌሎች ታሳሪዎች አብረውኝ የታሰሩ ቢሆንም ይህ የተፈፀመባቸው ግን ወደማዕከላዊ ከመምጣታቸው በፊት ነው፡፡ ከነዚህ መካከል የሀሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ይገኙበታል፡፡ የሚገርመው በዚህ ዓይነቱ ምርመራ የሰጡት ቃል ለማመሳከርያ ማዕከላዊ መምጣቱ ነው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ወደማዕከላዊ ከመዛወራቸው በፊት ከባድ ቅጣት የተቀጡበትን ቦታ የት እንደሆነ እንዳያውቁ አይናቸው ተሸፍኖ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ እሥረኞችም መኖራቸው ነው – የደርግን ‹‹ቤርሙዳ›› ያስታውሳል!
እናም በሚያዋርድ እና ክብርን በሚነካ ስድብ በሚያስፈራ የቤቱ (የማዕከላዊ) ጥላ እና ኃይል በተቀላቀለበት የምርመራ ሂደት የተከሳሽ ቃላችንን ሰጠን፡፡ ቃላችን መቶ በመቶ እውነት አልነበረም፡፡ ጫናው በበረታ ቁጥር መስማት የሚፈልጉትን ‹‹ዓመፅ ለመቀስቀስ ፈልገን›› የመሳሰሉ በራስ ላይ ፈራጅ (Self-incriminating) ሐረጎችን እየተናገርን ነበር፡፡ ያም ግን ለመርማሪዎቻችን በቂ አልነበረም፡፡ ስለዚህ በሚጽፉበት ሰዓት እያንዳንዷን ‹‹ሠራን›› ያልነውን ሁሉ ሊያስከስሰን በሚችልበት ሁኔታ እየገለበጡ እና እየበጠበጡ ፃፉት፡፡ አንዳንዶቻችን እየተከራከርን ሲያቅተን ፍርድ ቤት ይፍታው ብለን ፈረምን፣ቀሪዎቻችን የቻልነውን ያህል ተደብድበንበት ፈረምን፡፡ ‹‹ከተናገርኩት ቃል ውጪ አንድም ቃል አልፈርምም›› በሚል እስከመጨረሻው ታግሎ የተሳካለት አቤል ብቻ ነበር፡፡
በምርመራው ሂደት የተረዳነው ነገር ቢኖር የማዕከላዊ መርማሪዎች ብቃት (Intelligence) አርጩሜ ብቻ መሆኑን ነው፡፡ እኔ ምርመራ ሲባል ይመስለኝ የነበረው ፖሊሶች ተጠርጣሪዎችን ፈፀሙ ስለሚባለው ነገር በቂ መረጃ ይዘው ግፋ ቢል ለምንና እንዴት እንደፈፀሙት ማውጣጣት ነበር፡፡ ‹‹ዕድሜ ለማዕከላዊ›› የተረዳሁት ነገር ቢኖር ምርመራ ማለት ለካስ ‹‹የሠራኸው ወንጀል ምንድን ነው?አውጣት!›› ማለት ኖሯል- ማዕከላዊ ስታይል፡፡ ‹‹ነጻ ነኝ›› ቢሉ ሰሚ የለም፡፡ አንዴ ታስረሃል ወንጀል ሊገኝብህ የግድ ነው፤ ካልሆነ ይጋገርብሃል፡፡
አሁን ሳስበው ማዕከላዊ ፈርሶ በሥር-ነቀል ለውጥ እንደገና መቋቋም ያለበት ተቋም ነው፤ ቢያንስ በሁለት ምክንያት፡፡ አንደኛ የምርመራው ሂደት (በራሳችን ጉዳይ እንደተረዳሁት) ትዕዛዝ አስፈፃሚነት ይስተዋልበታል፡፡ ማለትም በመርህ የሚመራ አይደለም፡፡ ሁለተኛ ምርመራው እውቀት መር አይደለም፡፡ ይህ ደግሞ የአገሪቱን ደህንት አደጋ ውስጥ የሚጥል ጉዳይ በምርመራው ድክመት ሳይታወቅ ሊታለፍ ይችላል፡፡ ይህ ችግር የተከሰተው ደግሞ መርማሪ ፖሊሶቹ ከብቃት ይልቅ ለታዛዥነት የተመቹ ታማኞች ሆነው በመመልመላቸው ነው፡፡
‹‹ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ››
በምርመራው ሂደት የተጨቀጨቅነውም ሆነ ተገድደን የፈረምነው ጽሑፎቻችንን የበይነ መረብ ዘመቻዎቻችንን፣ የወሰድናቸው ስልጠናዎችም ሆኑ አንዳንዶቻችን የሰጠናቸው ስልጠናዎች አመፅ ለማስነሳት መሆኑን ‹‹እመኑ›› በሚል ስለነበር የጠበቅነው ግፋ ቢል በወንጀለኛ መቅጫው አንቀጽ 238 ወይም 257 ሊከሱን አስበው ነው ብለን ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የክስ መዝገቡ ሲመጣ ‹‹ሽብር›› ያውም ከአስራ አምሰት ዓመት እስከ እድሜ ልክ የሚያስቀጣ አንቀጽ 4 መሆኑን ሳውቅ በበኩሌ ሳቄ ነበር የመጣው፡፡
ማስረጃ ተብለው ከክስ መዝገቡ ጋር የተያያዙት በአብዛኛው ጽሑፎቻችን፣ የዘመቻዎቻችን፣ የጋዜጣ መግለጫዎች እና በተለያዩ ሥልጠናዎች ወቅት የተዘጋጁ የሥልጠና መመሪያዎች (Manuals) ናቸው፡፡ ከዚህ በተረፈ ከግንቦት 7 እና ከኦነግ ጋር ያገናኛችኋል የተባልነው በሦስት ‹‹ሰነዶች›› ነው፡፡ አንደኛው ናትናኤል ኢሜይል ውስጥ በጥቅምት 2001 ተልኮለት የተገኘ የግንቦት 7 የዜና መጽሔት ነው፡፡ ይህ እንግዲህ ገና የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ አዋጁ ሳይወጣ፤ ግንቦት ሰባትም አሸባሪ ከመባሉ በፊት መሆኑ ነው፡፡ ሁለተኛ ሶልያና ቤት ተገኘ ተብሎ እናቷ ‹‹ቤቴ ውስጥ አልተገኘም፣አልፈርምበትም›› ያሉት እና ለግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ሰራዊት ምልመላ መመዘኛ ሰነድ ነው፡፡ ይህ የሶሊ የዘለቀ አቋም ለሚያውቅ ሙግት አያስፈልገውም፡፡ እኔ እንደውም ትዝ ያለኝ ከመታሰሬ በፊት የትዊተር ፕሮፋይሏ ውስጥ የነበረው ‹‹no for war›› የሚል መፈክር ነው፡፡ ሦስትኛው ደግሞ ማሕሌት ኮምፒውተር ውስጥ የተገኘው የኦነግ ፕሮግራም ነው፡፡ በርግጥ አብረው የተገኙት የሌሎች የኦሮሞ ፓርቲዎች ፕሮግራሞች ማስረጃ ተብለው አለመቅረባቸው መረዳት ብቻ – እሷም ለምን ፕሮግራሙን እንደያዘችው፤ እነሱም ለምን የኦነግን እንደመረጡ ያጋልጣልና የእመኑኝ ሙግት አያስፈልገንም፡፡ በመሰረቱ ሦስቱንም ‹‹ሰነዶች›› መያዝ ከቡድኞቹ ጋር ግንኙነት መመሥረት የሚሰሩትንም መውደድ ማለት አየደለም፡፡ ይህም ለመሪዎቻችን ባይታያቸውም እንኳ ለወገኖቻችን የጠፋቸዋል ብዬ አላስብም፡፡
ሌላውና በአስቂኝለቱ ተወዳዳሪነት የሌለው ውንጀላ ‹‹48 ሺሕ ብር በናትናኤል በኩል ተቀብለው ተከፋፍለዋል›› የሚለው ነው፡፡ ይህ ብር ፤‹‹አሸባሪ›› ከተባሉት ቡድኖች የተወሰደ እንዲመስል በሚያደናግር አገላለጽ የተጻፈ ቢሆንም የክስ መዝገቡ ውስጥ የተያያዘውና ገንዘቡ የመጣበት ደረሰኝ እንደሚያረጋግጠው የተላከው ከARTICLE 19 ነው፡፡ ይህንን ጨምሮ በእስር ላይ ለምትገኝ ጋዜጠኛ ቤተሰቦች መደገፊያ /ለእስረኛይቱም ማበረታቻ/ የተላከ መሆኑን ለመርማሪዎቹ በዝርዝር አስረድተናቸዋል፡፡ ይህንን እያወቁ ውንጀላውን ማኖራቸው እውነትም እኒህ ሰዎች ወንጀለኞች ናቸው ብለው አምነው ሳይሆን ‹‹ከቻልን አደናግረን እናስቀጣቸዋለን (የማይችሉበት ሁኔታ አይታየኝም)፣ካልቻልን ደግሞ በቀጠሮ ጊዜ እንገዛበታለን፣ ነጻ እስኪወጡም ቢሆን በእስር እናቆያቸዋለን›› የሚል ክፉ ምኞት ነው፡፡
… ሳታመኻኝ ብላኝ!
አህዩት ከታች አያ ጅቦ ከላይ ሆነው ወራጅ ውሀ እየጠጡ ነበር አሉ፡፡ ነገር ያማረው አህዩትን ‹‹አታደፍርሽብኝ›› ሲላት ነገሩ የገባት አህይትም ‹‹ሳታመኸኝ ብላኝ›› አለችው ይባላል፡፡ የኛም ነገር እንደዚያው ነው፡፡
ፖሊስ ሲይዘን እኛ ላይ ይህ ነው የሚባል የመክሰሻ መረጃ አልነበረውም፤ እንዲያውም ከስማችን በቀር የሚያውቁት ነገር አልነበረም፡፡ ሌላው ቀርቶ ከደህንነቶታቸው በአንዱ ልከንላቸው የነበረውን የጽሑፋችንን ስብስብ እንኳን ሳያነቡት ነበር የያዙን፡፡
አሁንም ማስረጃ ብለው ከክስ መዝገባችን ጋር ያያያዙት ቢያንስ በእኔ ግምት ዘጠና በመቶ የሚሆነው ‹‹ሰነድ›› እኛው ነፃ ያወጣናል ብለን የሰጠናቸው ጽሑፎቻችን ናቸው፡፡ በመርማሪዎቻችን ንግግር ውስጥ እኛ ላይ ወንጀል የማግኘት Desperate ፍላጎት አይተናል፡፡ ምናልባትም እንደገመትነው ቢያንስ እስከ 2007ቱ ምርጫ ድረስ ከማኅበራዊ ሚዲያ ገለል እንድንልላቸው ፈልገዋል፡፡ ከዚህ የተሻለም አማራጭ አልታያቸውም ይሆናል፡፡
በእስካሁኑ ሂደት የማዕከላዊን ለገዢው ፓርቲ ወገንተኝነት በዓይናችን አይተን አረጋግጠናል፡፡ ቀጣዩ ደግሞ የፍትሕ ሥርዓቱን በአደባባይ መፈተሽ ይቀረናል፡፡ ለአሁኑ ግን በቅርቡ እንፈታ ይሆን… የሚል ጥያቄ ‹ሕጋዊ› ሳይሆን መላ ምታዊ አማራጮችን እገምታለሁ፡፡
ኢህአዴግ ወይም የኢህአዴግ መንግሥት የሚያዘው ፖሊስ እኛን በቁጥጥር ሥር ሲያውለን ስለወንጀላችን ማረጋገጫ (ጠበቆች Beyond reasonable doubt) እንደሚሉት ዓይነት ባይኖረውም መቼም የሆነች ስህተት ሳላገኝባቸው አልቀርም በሚል ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ወትሮም የተንቦረቀቀ የሚባለው የፀረ-ሸብርተኝነቱ አዋጅ ውስጥ የሚጥለን ነገር በቀላሉ ማግኘት አልቻሉም፡፡ አለመቻላቸው ግን የተነሱበትን እኛን የመክሰስ ዓላማ አላጠፋውም፡፡ የክስ መዝገቡን ሲያዘጋጁ አንድም የረባ ዐረፍተ ነገር ሳይጽፉ ይዘውን ፍርድ ቤት መቅረባቸው በራሱ አንድም የረባ ጥርጣሬና ማረጋገጫ እንደሌላቸው አመላካች ነው፡፡ ቢሆንም በቅርቡ ይለቁናል የሚል ግምት የለኝም፡፡ ለምን;
1ኛ. ኢህአዴግ በጣም የሚናደድባቸው እና ታሳሪውን በሚያዋርድ መልኩ ካልሆነ በቀር ከማያደርጋቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ- አንዴ ያሰረውን ተቺውን ፤ ያውም ብዙ ደጋፊ ያለውን መፍታት ነው፡፡ ኢህአዴግ እንደልጅ እልህ ይጋባል ማለቴ ነው፡፡ (ይህንን ስል የእስራችንን ኢፍትሀዊነት የተመለከቱትን ጩኸቶች መጥላቴ አይደለም፤ ያለ እነርሱ መንፈሳችን አይጠገንም ነበር፡በአደባባይ የምናመሰግንበት ቀን ይመጣል)
2ኛ. መጀመሪያ የተጠራጠሩበት እና ኋላ የዋጧት ጥርጣሬያቸው፤ ማለትም (ምርጫውን ተከትሎ) አመፅ ማስነሳት በሚሉት ጉዳይ ላይ እቅድ እንደሌለን ቢያምኑም እንኳን ምናልባት እምነታቸው ከተሳሳተ Risk መውሰድ አይፈልጉም፡፡ ( መጀመሪያም የቀለም አብዩት ዶክመንተሪ አዝማሚያ ያስታውሷል)
3ኛ. ምንም እንኳን ዓመፅም፤ሽብርም የማስነሳት ፍላጎትም አቅምም፤ እንደሌለን ቢያምኑም የገዥው ፓርቲ ጠንካራ ተቺዎች መሆናችንን ስለሚያውቁ እና ስላልወደዱልን ፍርድ ቤት በምንመላለስበት ረዘም ያለ ጊዜ ባለው እስር ወቅት ቢያንስ የእስርን ምሬት እንድንቀምሳት ይፈልጋሉ፡፡ ቅጣትን ጨርሶ በነፃ መለቀቅ እንደማለት፡፡
4ኛ. ኢህአዴግ መፍረድ አይፈራም፡፡

የሰሞኑ ክስና ሥጋት ውስጥ የወደቀው የግሉ ፕሬስ

August10/2014
የሰሞኑ ክስና ሥጋት ውስጥ የወደቀው የግሉ ፕሬስ

በማተሚያ ቤት ክልከላ ከ“ፋክት” በስተቀር ሁሉም አልታተመም 


ሁሉም ተከሳሾቹ ክስ አልደረሰንም ብለዋል
“የግል ፕሬሱን ለማሸማቀቅና የስነ-ልቦና ጫና ለመፍጠር የተደረገ ይመስላል”
- ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁ
“መንግስት ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን እንደመጥፎ ነገር አናየውም”
- አንተነህ አብርሃም (የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጋዜጠኞች ማህበር ፕሬዚዳንት)
“መንግስት ክስ የመሰረተው ከምርጫው ጋር በተያያዘ ሊሆን ይችላል”
- ዘ ኢኮኖሚስት
የፍትህ ሚኒስቴር ባለፈው ሰኞ ምሽት በኢቴቪ ባወጣው መግለጫ፤ ስርዓቱን በሃይል ለመናድ የአመፅ ቅስቀሳና የሐሰት ወሬዎች በመንዛት፣ ህገመንግስታዊ ስርዓቱ በሃይል እንዲፈርስና ህዝቡ በመንግስት ላይ ያለአግባብ አመኔታ እንዲያጣ የሚያደርጉ የወንጀል ተግባሮችን ፈጽመዋል ባላቸው አምስት መፅሄቶችና አንድ ጋዜጣ ላይ ክስ መመስረቱን ጠቁሟል፡፡
ክስ ተመስርቶባቸው የተባሉት “ፋክት”፣ “ጃኖ”፣ “ሎሚ”፣ “አዲስ ጉዳይ” እና “እንቁ” መፅሄቶች እንዲሁም “አፍሮ ታይምስ” ጋዜጣ አሳታሚዎች በበኩላቸው፤ መከሰሳቸውን በሚዲያ ከመስማታቸው ውጭ ምንም ዓይነት ክስ እንዳልደረሳቸው ገልፀው መከሰሳቸው በሚዲያ መታወጁን ተቃውመውታል፡፡
የግል ፕሬሶቹ መከሰስ በሚዲያ መገለፁን ተከትሎ ማተሚያ ቤቶች “አናትምም” እንዳሏቸው አሳታሚዎች የተናገሩ ሲሆን በዛሬው ዕለት መውጣት ከነበረባቸው የህትመት ውጤቶች ከ “ፋክት” በስተቀር ሁሉም እንደማይታተሙ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡
ክስ ከቀረበባቸው የግል ፕሬሶች አንዱ የሆነው የ“ሎሚ” መፅሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ግዛው ታዬ፤ የክስ ዝርዝር እንዳልደረሳቸውና ጉዳዩን የነገራቸው አካል እንደሌለ ጠቁመው፤ ክሱ በቴሌቪዥን መገለፁ በሚዲያ ተቋሙ ጋዜጠኞች ላይ የስነልቦና ጫና ማሳረፉን ተናግረዋል፡፡ “ቀደም ብሎ እንደታሰሩት ጦማሪያንና ጋዜጠኞች አፈሳ ሊካሄድብን ይችላል በሚል ስጋት ጋዜጠኞች በተረጋጋ ሁኔታ በቢሮአቸው ተቀምጠው ስራቸውን መስራት አልቻሉም” ብለዋል፡፡
መንግስት  የግል ፕሬሶቹ መከሰሳቸውን በሚዲያ ማወጁ ህገ መንግስቱን የጣሰ አካሄድ ነው ያሉት አቶ ግዛው፤ “ከዚህ በፊት በነበረው አሰራር ከፖሊስ ተደውሎ ቀጠሮ ከተሰጠን በኋላ በምንጠየቅበት ጉዳይ ላይ ቃላችንን እንድንሰጥ ይደረግ ነበር፤ ይሄኛው ለየት ያለ አካሄድ ነው” ብለዋል፡፡
የ“አዲስ ጉዳይ” መፅሄት ሥራ አስኪያጅ አቶ እንዳልካቸው ተስፋዬ በበኩላቸው፤ መንግስት ጉዳዩን በተመለከተ በሚዲያ ከገለፀው ውጪ ምንም አይነት ክስ እንዳልደረሳቸው ጠቁመው፣ በዛሬው እለት ይወጣ የነበረው “አዲስ ጉዳይ” መፅሄት ክሱ በቴሌቪዥን ከተነገረ በኋላ ማተሚያ ቤቱ “አላትምም” በማለቱ መጽሔቱለንባብ ባይበቃም ሰራተኞቻቸው ግን ያለምንም መረበሽ በመደበኛ ስራቸው ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
በሚቀጥለው ሳምንት “አዲስ ጉዳይ” ሌላ ማተሚያ ቤት ታትሞ እንደሚወጣ የጠቆሙት አቶ እንዳልካቸው፤ ተመስርቷል በተባለው ክስ ጉዳይ ድርጅታቸው ከህግ አማካሪዎች ጋር እየተማከረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
እንደሌሎቹ ተጠርጣሪ ፕሬሶች ሁሉ የክስ ዝርዝር እንዳልደረሳቸውና የህግ ሰው እንዳላነጋገራቸው የገለፀው የ “ፋክት” መጽሔት አምደኛ ተመስገን ደሳለኝ፤ መፅሄቱ እንደወትሮው መደበኛ ህትመቷ እንደሚቀጥልና በዛሬው እለትም እንደምትወጣ አስታውቋል፡፡ ከማተሚያ ቤት በኩል እስካሁን የገጠማቸው ችግር እንደሌለም ጋዜጠኛ ተመስገን ጨምሮ ገልጿል፡፡
መንግስት በአደባባይ ይፋ ባደረገው ክስ ፕሬሶቹን ወንጀለኛ ሳይሆን ተጠርጣሪ ማለቱን ያስታወሰው ተመስገን፤ ከዚህ መግለጫ ተነስተው “አናትምላችሁም” የሚሉ ማተሚያ ቤቶች ካሉ ትልቅ ስህተት እየሰሩ ነው ብሏል፡፡
በክሱ ተደናግጠን ስራችንን አናቆምም ያለው ጋዜጠኛው፤ “ወደፊት ይመጣል ብለን የምናስበው “የህዳሴ አብዮት” እስኪካሄድ ድረስ ማንኛውንም መስዋዕትነት እንከፍላለን፤ እንደዚህ ያሉ አፈናዎች ለጊዜው ካልሆነ በቀር ዘላቂ አይሆኑም” ብሏል፡፡ “ሠሞነኛው የመንግስት እርምጃ “የህዳሴ አብዮት”ን ለመቀልበስ የሚደረግ መፍጨርጨር ነው፤ ነገር ግን አይሳካላቸውም፤ መከሰሳችንም አዲስ አይደለም፤ በአብዮታዊ ጋዜጠኝነታችን እንቀጥላለን፤ ትግላችን ቀራኒዮ ድረስ ነው” ብሏል፡፡
የ“እንቁ” መፅሄት ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ማህተመወርቅ በበኩላቸው፤ መንግስት ክሱን በአደባባይ ይፋ ካደረገ በኋላ ማተሚያ ቤቶች አናትምም እንዳሏቸውና ዘወትር ቅዳሜ ገበያ ላይ ትውል የነበረችው መጽሔት በዚህ ሣምንት ለገበያ እንደማትበቃ ገልፀዋል፡፡
መንግስት ከዚህ ቀደም በህትመት ውጤቶች ላይ የሚወጡ ፅሁፎች ህግ ጥሰዋል ካለ ዋና አዘጋጁን ይከስ እንደነበር የጠቆሙት አቶ ፍቃዱ፤ በዚህኛው ክስ አሣታሚዎች ላይ ማነጣጠሩ ሚዲያዎቹ እንዲዘጉ ያለውን ፍላጐት ያሣያል ብለዋል፡፡ ቀደም ሲል በመንግስት የሚዲያ ተቋማት በኩል በእነዚህ የህትመት ውጤቶች ላይ ሰፊ የማጥላላት ስራ ሲሰራ መቆየቱን ያስታወሱት ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ፤ በተደጋጋሚ “መንግስት ሆደ ሰፊ ነው፤ ተቀራርበን እንሠራለን” የሚሉ መልዕክቶች በመንግስት ወገን እየተላለፉ ቢቆዩም የመንግስትን ሆደ ሰፊነትና ታጋሽነት በተግባር አላየነውም ብለዋል፡፡ “እንቁ” መጽሔት በፕሬስ አዋጁ መሠረት ክስ ቀርቦበት ወንጀለኛነቱ የተረጋገጠበት ጊዜ አለመኖሩን የጠቆሙት አቶ ፍቃዱ፤ አሁን ግን መጽሔቱ በህትመት ኢንዱስትሪው ይቀጥላል አይቀጥልም የሚለውን ለመወሰን እንደተቸገሩ ገልፀዋል፡፡
ሌላው ክስ የቀረበበት የ“ጃኖ” መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ አስናቀ ልባዊ፤  ምንም ዓይነት ክስ እንዳልደረሳቸው ጠቁመው የክሱ መግለጫ በቴሌቪዥን ከተሰራጨ በኋላ ማተሚያ ቤቶች መጽሔታቸውን አናትምም እንዳሏቸው ገልፀዋል፡፡ “ማተሚያ ቤቶች ፍቃደኛ ካልሆኑ የት ሄደን እናሣትማለን?” ሲሉ የጠየቁት አቶ አስናቀ፤ “የመንግስት መልካም ፍቃድ ከሆነ እንቀጥላለን፤ ካልሆነ ለማቆም እንገደዳለን፤ ነገር ግን ሚዲያው በመንግስት መልካም ፍቃድ ብቻ መንቀሳቀሱ ያሣዝናል” ብለዋል፡፡
በክሱ ውስጥ ያልተካተቱ የግል ፕሬስ አሳታሚዎችና አዘጋጆች በበኩላቸው፤ ሰሞኑን በመንግስት ተመሰረተ የተባለው ክስ የግል ሚዲያውን ስጋት ውስጥ እንደከተተው ተናግረዋል፡፡
የኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ አቶ ጌታቸው ወርቁ፤ “የሰሞኑ የመንግስት ክስ ለተቀሩትም የማስጠንቀቂያ መልዕክት ያስተላለፈ እንደመሆኑ “ማነሽ ባለተራ” እየተባለ በስጋት እንድንሠራ የሚያደርግ ነው፤ ይህ ደግሞ በአሣታሚዎችም ሆነ በጋዜጠኞች ላይ የሚፈጥረው የስነልቦና ጫና በቀላሉ የሚታይ አይደለም” ብለዋል፡፡
ሚዲያና ህዝብ ከሚፈላለጉበት ጊዜ አንዱ የምርጫ ወቅት መሆኑን የጠቆሙት አቶ ጌታቸው፤ ክሱ በመንግስት መገናኛ ብዙሀን ይፋ መደረጉ የግል ፕሬሱን ለማሸማቀቅና የስነልቦና ጫና ለመፍጠር ይመስላል ብለዋል፡፡ “ክሱ በቀጥታ አሣታሚው ላይ እንዲያነጣጥር መደረጉ ከአሣታሚዎች ነፃ ሊሆን ይገባዋል በሚባለው የጋዜጣው ኤዲቶሪያል ፖሊስ ላይ ጣልቃ መግባት እንዲጀምሩ ያደርጋቸዋል” ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀው፤ ይሄ ደግሞ በዚህም ጋዜጠኞች በሙያቸው ነፃ ሆነው እንዳይሠሩ የሚሸብብ የሚዲያ ድባብ ሊፈጠር ይችላል ብለዋል፡፡
“በመግለጫው ላይ ክሱ ህግን በማያከብሩ ሌሎች ሚዲያዎች ላይም ይቀጥላል መባሉ በአጠቃላይ ሃሳብን በነፃነት የመግለጽን መብት ጥያቄ ውስጥ ከትቶ በነፃ ሚዲያው አካባቢ ፍርሃትና መሸማቀቅ እንዲፈጠር ያደርጋል” ሲሉም አክለው ገልፀዋል፡፡
“መንግስት በሚዲያ ክሱን ይፋ ማድረጉ አጠቃላይ የሚዲያ ምህዳሩን ይረብሸዋል” ያሉት የሪፖርተር ጋዜጣ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ መላኩ ደምሴ፤  ከሁለት አስርት አመታት እድሜ ያልዘለለውን ፕሬስ ገና ዳዴ እያለ ባለበት ወቅት እንደመንከባከብ እንዲህ ያሉ እርምጃዎች መወሰዳቸው አግባብ አይደለም ብለዋል፡፡
ክስተቱ በሃገራችን ፕሬሶች ላይ መሠረታዊ ችግሮች እንደሚንፀባረቁ ይጠቁማል የሉት አቶ መላኩ፤ ከመንግስት ባለስልጣናት ጫና ባሻገር የሙያ እውቀት ችግር እንደሚንፀባረቅም ተናግረዋል፡፡ ሚዲያው እየተንቀሳቀሰበት ያለው ድባብ በራሱ ጥሩ አይደለም፤ በዚህ የተነሳ የትኛውም ባለሀብት ወደዚህ ዘርፍ መግባት አይፈልግም ሲሉ በአጠቃላይ ሚዲያው በአሣሣቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ጋዜጠኛ መላኩ ገልፀዋል፡፡
አዲስ የተቋቋመውና እውቅና ለማግኘት በሂደት ላይ ያለው የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ ምክትል ሊቀመንበር ጋዜጠኛ ስለሺ ሃጐስ በበከሉ፤ በመንግስት በኩል እንዲህ መሰሉ እርምጃ እንደሚወሰድ አስቀድሞ ይታወቅ እንደነበር ይናገራል፡፡ ማህበራቸው የመንግስትን እርምጃ እንደሚቃወምና አሁን ባለው የሚዲያ እንቅስቃሴ በተነባቢነትና በተደራሽነት ሰፊ ይዞታ ያላቸውን “ፋክት”፣ “ሎሚ” እና “አዲስ ጉዳይ” መጽሔቶችን መክሰሱ በሚዲያ ባለቤቶች ላይ ብቻ ሳይሆን በአንባቢያን ላይም ተጽእኖ ያሳርፋል ባይ ነው፡፡
ክሱ በራሱ አደናጋሪ ነው የሚለው ጋዜጠኛ ስለሺ፤ በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ መሠረት ጥፋት ካለ በእያንዳንዱ ጽሑፍ ተጠያቂው አካል ይጠየቃል እንጂ ተቋማት ላይ ማነጣጠሩ ተገቢ አይደለም ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጋዜጠኞች ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ አንተነህ አብርሃም በበኩላቸው፤  “ማንኛውም የሚዲያ ተቋም ሲከሰስ አሣሣቢ ቢሆንም መንግስት ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን እንደመጥፎ ነገር አናየውም” ብለዋል፡፡
የክሱ ሂደት ሲታይ መጽሔቶችም ሆነ ጋዜጣው መደበኛ ስራቸውን እንዲሰሩ ቢደረግ መልካም ነው ያሉት አቶ አንተነህ፣ “እኛ እንደ ጥሩ ነገር ያየነው ከሚዲያ ተቋማቱ ጋር ጋዜጠኞች ተደርበው አለመከሰሳቸውን ነው፤ የአሁኑ የመንግስት እርምጃ፣ ጋዜጠኛውን ከመክሰስ ይልቅ ተቋሙም ሃላፊነት እንዲሰማው ለማድረግ የጐላ ጠቀሜታ አለው በሚል የተወሰደ እርምጃ ይመስለኛል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
መንግስት ክሱን በሚዲያ መግለፁ ሁለት አይነት መልዕክት እንደሚኖረው አቶ አንተነህ ጠቁመው፤ አንደኛው ጋዜጠኛ ጥፋት ካጠፋ በህግ እንደሚጠየቅ ያስተምራል፣ በሌላ በኩል ፍርሃት ያሳድራል ብለዋል፡፡ ፍርሃት መፈጠሩ በበጐ የሚታይ አይደለም ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ዞሮ ዞሮ ለህግ የበላይነት ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባ ጠቁመው፤ እርምጃው ከሌሎቹ ጊዜያት በተሻለ ረጋ ተብሎ የተወሰደ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በአሳታሚዎቹና በሚዲያ ተቋማቱ ላይ የተመሰረተውን ክስ በተመለከተ አስተያየት እንዲሰጡ የጠየቅናቸው  የህግ አማካሪና ጠበቃ አቶ አመሃ መኮንን፤ በማናቸውም ወንጀል ጉዳይ የክስ ሂደት የሚጀምረው ከፖሊስ ምርመራ መሆኑን አስረድተው፣ በዚህ ጉዳይ ፍትህ ማኒስቴር ያቀረበው ክስ አሣታሚዎች ላይ በመሆኑ ስራ አስኪያጆች በቀረበባቸው ክስ ላይ ቃል መስጠት አለባቸው ይላሉ፡፡ “ይህ ስለመደረጉ የተሟላ መረጃ የለኝም፤ ነገር ግን በተለያዩ ሚዲያዎች ቃል አለመስጠታቸው እየተነገረ መሆኑን እየሰማሁ ነው ያሉት ባለሙያው፤ “ክሱ ይፋ የተደረገበት መንገድ ትክክለኛ ነው” የምልበት ምንም የህግ ምክንያት የለኝም፤ ምናልባት የህትመት ጉዳይ የሚመረመር ጉዳይ የለውም፤ ጋዜጠኞች ሲከሰሱ የጊዜ ቀጠሮ አይጠየቅባቸውም ቢባልም ማንኛውም ተሠራ የተባለ ወንጀል በፖሊስ በኩል ሣያልፍ ቀጥታ በአቃቤ ህግ ክስ ይመሠረታል ማለት አይደለም፤ የምርምራ መዝገብ በፖሊስ መደራጀት አለበት” ብለዋል - አቶ አመሃ፡፡
“ፍትህ ሚኒስቴር ክስ መስርቻለሁ ብሎ በሚዲያ መናገሩ ከህግ አንፃር ብዙም ጥያቄ የሚያስነሳ አይመስለኝም” ያሉት አቶ አመሃ፤ “ክስ መመስረቱ የተነገረበት መንገድ ህገወጥ ነው ማለት ባይቻልም አላማው ምንድን ነው የሚል ጥያቄ ያስነሳል” ብለዋል፡፡
ከህግ አንፃር በዋናነት ሊታይ የሚገባው የተጠያቂነት ቅደም ተከተል ነው የሚሉት  የህግ ባለሙያው፤ በፕሬስ አዋጁ መሰረት መጀመሪያ የሚጠየቀው ዋና አዘጋጁ መሆኑን ጠቁመው ዋና አዘጋጁ ከሌለ ወይም ኖሮም የአዘጋጅነትን ሃላፊነት መወጣት የማይችል ሆኖ ከተገኘ ብቻ ነው ሃላፊነቱ ወደ አሣታሚው የሚተላለፈው ይላሉ። “ፍትህ ሚኒስቴር ክሱን ያቀረበው አዘጋጆቹን መጀመሪያ ጠይቆ ነው? ሃላፊነታቸውን መወጣት የማይችሉ ሆኖ አግኝቷቸው ነው ወደ አሣታሚዎች የሄደው? የሚለው ግልጽ አይደለም፤ የህግ አካሄድ ጥያቄም ከዚህ አንፃር ሊነሣ ይችላል” ብለዋል አቶ አመሃ፡፡
የክስ ሂደቱ በፍርድ ቤት እየታየ የሚዲያ ተቋማቱ ከህትመት የሚታገዱበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል? ስንል የጠየቅናቸው የህግ አማካሪው፤ አቃቤ ህግ ይታገዱ ብሎ ካመለከተ፣ ተከሳሾች ለእግድ ጥያቄው የሚያቀርቡትን መከራከሪያ ፍ/ቤት አይቶ  ሊያግዳቸው ይችላል ብለዋል።
የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን ባለፈው ሰኔ ወር ታትሞ ከወጣው ዘመን መፅሄት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ “እኛ አገር ነፃ የግል ፕሬሱ ውስጥ ያሉ ሚዲያዎች በርከት ያሉት ነፃ አውጪ ናቸው፡፡ ነፃ አውጪ ከሆኑ ውጊያ ገጥመዋል ማለት ነው፡፡ ውጊያ ከገጠሙ እንደማንኛውም ተዋጊ ይታያሉ ማለት ነው፡፡” ብለዋል፡፡
ታዋቂው መጽሄት ዘ ኢኮኖሚስት ከኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ጋር በተያያዘ ትናንት ለንባብ ባበቃው ዘገባ፣ አገሪቱ ጋዜጠኞችን በማሰር ከኤርትራ ቀጥላ ከአፍሪካ አህጉር በሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ የሲፒጄን መረጃ ጠቅሶ የጻፈ ሲሆን፣ መንግስት በመጽሄቶቹና በጋዜጣው ላይ ክስ የመሰረተው፣ ከመጭው አገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ ጭንቀት ውስጥ በመግባቱ ሊሆን እንደሚችል ግምቱን አስቀምጧል፡፡

Saturday, August 9, 2014

የኢህአዴግ ተወካዮች ምሬታቸውን ገለጹ

August9/2014
የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን በባህርዳር ጀመረ
በባህርዳር ከተማ ተደርጎ በነበረው ስብሰባ ላይ የምክር ቤት አባላት ፣" የህዝብ ወኪሎች ብንሆንም ስራ አስፈጻሚው አካል የምናቀርበውን ሪፖርት አይቀበልም" ብለዋል። አንድ ኢንቨስተር ከአንድ የህዝብ ተመራጭ የተሻለ ተሰሚነት አለው ያሉት ተማራጮች መፍትሄ ለማምጣት ካልቻልን የእኛ ተመራጭነት ምንድነው ሲሉ የምክር ቤት አባላት ጥያቄ አቅርበዋል ::

የህዝብ ተወካዮቹ እንደገለጹት በአሁኑ ጊዜ በፍድር ቤቶች አካባቢ ከፍተኛ ችግር እንዳለም ገልጸዋል። አንድ ተወካይ የመንግስት ሆስፒታሎች እየተዳከሙና መድሃኒቶች እየተሸጡ፣ ህዝቡም ከመንግስት የጤና ተቋማት ይልቅ ወደ ግል እየሄዱ መሆኑን ገልጸዋል።
ህብረተሰባችን ምን ላይ ነው ያለውን የማጥናት ችግር አለ ያሉት ሌላው ተወካይ፣ በምዞርባቸው ቦታዎች ሁሉ ህዝቡ መውደቂያ አጣን ብሎ እንደሚጮህ ተናግረዋል። 

ኢህአዴግ ለመጪው ምርጫ ዝግጅት በሚመስል መልኩ በተለያዩ ደረጃ የሚገኙ የህዝብ ተወካይ የሚላቸውን ሰዎች እየጠራ በማወያየት ላይ ነው።እስካሁን ድረስ በተደረጉት ውይይቶች አብዛኛው ተወያይ በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ሆነ የኢኮኖሚ ና የአስተዳደር ችግሮች እንዳሉ በድፍረት መግለጹን ኢሳት ሲዘግብ መቆየቱ ይተወቃል።

Woyane has no chance but to surrender

August 9, 2014
by Teshome Debalke

Tyrant dies and his rule is over beginsInterestingly, Woyane is determined it can lie, terrorize, kidnap, kill and robe Ethiopians to hang on to power. For the most part, it is because the stooges keep lying to reassure the regime everything is all right as expected in any tyranny. The fact it is vertically integrated tyranny to track the lies and atrocities is not helping it to grasp the reality of what its guerilla tactics is doing either. Essentially, Woyane is an organized mob that happens to capture state power to run racketeering and unable to restrain its hit men it unleashed on the people of Ethiopia.

Therefore, it has no incentive to reform as it would only bring its demise. It has no desire for democratic rule as that would criminalize its robbery and atrocities. It can’t negotiate out of its predicament it put itself in as a self-declared minority ethnic regime.   The only hope it has is to call the truth and ask for forgiveness. But, the way the warlords and cadres are behaving and acting lately it is on for more blood.

Two years ago when I wrote; ‘Last call for Woyane stooges to surrender in peace; the day of reckoning arrived, I was telling the stooges to do themselves a favor and abandon Woyane for democratic rule while they can. When the mastermind of Woyane regime died there was opportunity to bury it with him.

Last year when I wrote; Woyane got it all wrong; it has no way out but the unconditional surrender for democratic rule, I was telling Woyane, no matter what it does it can’t legitimize its rule by committing more and more crimes. It would only make matter worst. Thus, I was advising it to take the only option it has before it is too late.

Both times I wrote I noticed Woyane’s stooges on auto pilot on their late leader legacy doing the last ditch attempts to legitimize Woyanes rule. Using the same terrorism to silent Ethiopians and Development State to robe the nation in daylight they thought would work. I also noticed, the apologist clearly mistook Ethiopians love for our people and country as an opportunity to play us as fools fronting half-witted warlords with a brain the size of a pee and fake diploma is good enough to go on.

When that is not enough, in unprecedented defiant ever seen, Woyane intensified robbing the nation and harassing, jailing and killing Ethiopian from university students, religious worshipers, opposition members, journalist and bloggers and farmers and villagers alike; all with terrorism charge. Essentially, Woyane gone crazy and declared the entire Ethiopians including, in the diaspora terrorists. It is a sign of an organized mob gone insane than a self-declared minority tyranny that would know its limit. I concluded, Woyane is dumber, deafer and blinder than I thought to miss an opportunity for soft landing.

When Andargachew Tsege abduction was confirmed I wrote again; Woyane eat the forbidden fruit’. As I expected, the true color of Woyane & stooges came out in the open for the world to see—proving there is no government in Ethiopia but, a rogue group running racketeering and assassination squad (organized mob).

Woyane blew its last chance to surrender peacefullyandbecamea-‘dead-and- deadly regime’ no propaganda, treat and terror would save its demise and the sign is on the wall.

Admittedly, the oppositions weakness have been seeing Woyane as a typical tyranny than an organize mob it is. That miscalculation cost the struggle enormously in life and resources. Now the world knows the regime operates as an organize mob; treating it as such would save lives, time and resources to accelerate its demise.

Here, it is appropriate to tell the stupidity or criminality of Woyane stooges. Calling an organize mob a government and its daylight robbery Development State will only make you hit men of a mob not law abiding citizens. Therefore, if you are 18 years old and legally sane you should stay as far as you can from Woyane.

The last refuge of organized mob to stay alive

The Economy

A typical tyranny extracts public resource directly from the state vault or through kickback from its cronies and foreign concerns. Not organize mob like Woyane that want it all.

Likewise, the stooges of a typical tyranny live-off picking the public pocket or trickle down benefits. Not the stooges of organize mob like Woyane that empowers its members to rob with impunity and the record show it. No member of the mob broke rank to expose the open economic robbery yet. Instead, legitimizing the robbery in the name of Development State and enforcing the mob rule through terror network became the rallying cry.

Here, Ethiopians must understand It isn’t that easy to walk away from organize mob. If history is a lesson; the initiation crime one commit to join a mob is not enough deterrent not to leave, the rule of a mob; ‘once you are in there is no way out but death’ would deter most, if not all from jumping ship. Therefore, seeing the intellectual stooges in diaspora close rank with foot cadres speaks volume to rule of the mob applies.

The genius of Development State

First, it pains me to see Ethiopian intellectuals are watching on the sideline when the Woyane mob robes the nation in the name of Developmental State and terrorize the population in the name of fighting terrorism. Besides the occasional reactive articles here and there we yet to see institutionalized challenge to stop the criminality of the mob. It is one of the tragedies among many — our do-noting intellectuals left our country and people for the mob bickering on non-issues.

That said, there is nothing wrong with Developmental State as an alternative economic development model providing the State is defined appropriately. But, in Ethiopian case, the State happened to be the Mob of Adwa for the last 23 years. Most Woyane stooges don’t seem to understand the robbery except counting the money on their way to the bank laughing.

Here, it worth to note the real guilty party are the intellectual apologist and the Media outlets that cover up the mob’s crimes and attempt to legitimize it as Developmental State. Their agony they go through to come up with anything that would make the regime other than what it is from their hideout is a sign of self-incrimination, mutilation and deprecation. With ‘no leg to stand on; they are the last hope against hope to make Developmental State anything but….

Sample of what the stooges want to tell us at these late hours of Developmental State tell some of the stories.

The incoherent front Prime Minster Halimariam told us Development State envisioned by his late ‘dear leader’ is the way to go. Listening to the only official interview he gave for an independent Media (CNBC) on the economy tells the story of the fear, double talk and self-incrimination serving a mob posed as a government official. The Adwa mob behind him confusing him further is not helping either.

By rejected the same World Bank the regime relied to validate its bogus double digit economic growth data Hailemariam declared WB is wrong on Ethiopian economy. The evidence he presented was ‘seeing on the ground is believing’ and no longer data is necessary.

When it comes sticking with Developmental State and the local firms’ monopoly of key sectors (the cash cows as he referred them) he declared they are reserved for local companies until they can be strong enough to compete. Essentially, he said; the cash cows will finance the Mob of Adwas’s monopoly of economy sector until they are strong enough to compete with foreign firms; Developmental State at its best.

The more telling news came out of the infamous mouth piece of TPLF in Diaspora. Aiga Forum. In legitimizing TPLF Development State and counter Ethiopians’ demonstration on ‘Ethio-US Business & Investment Summit’ 2014 in Los Angeles California, it reported;

‘(Aigaforum) Aug 1st 2014 – A high level delegation of government officials and leading business companies in Ethiopia held a very successful business summit with US Investors in Los Angeles California.’

But, the only leading company the report mentioned was;

”WAFA, a joint business promotion company owned by Waltainfo and Radio Fana presented a short video that showed highlights of Ethiopia’s rapid development and opportunities waiting”

Apparently Aiga forgot Waltainfo and Radio Fana both are the propaganda outlets owned by TPLF that operate out of public buildings and using public resources. In fact, Aiga’s report was copied word-by-word from Walta info; so much for Ethio-US Business & Investment Summit. It would have been appropriate to call it TPLF-US Business & Investment Summit that is trying to luring US investor disguised as Ethiopian government officials. It is also funny to note, the TPLF has the audacity to do joint venture with itself.

Surprisingly, what is missing in propaganda mouth piece Aiga was the whole scam was organized by TPLF. According to Africa Insider, an online media based in New York on its August 2 2014 reporting said;
“The 4th Ethio-US Business Forum was jointly organized by the Ethiopian Embassy in US and Wafa Marketing & Promotion and is expected to also take place in Los Angeles, California..

In short, the Summit was TPLF-US Business Forum organized by none other than TPLF as the sorry PM hint without saying it and has nothing to do with Ethiopia or the US businesses.


Gezahgen Kebede, the Founder and President of the Ethio-American Trade and Investment CouncilBehind the whole scam is, Gezahgen Kebede, the Founder and President of the Ethio-American Trade and Investment Council (EATIC) in 1993. He is also the Honorary Consul General of Ethiopia in Houston since 2001. A clandestine TPLF operative, Gezahgen is also instrumental to bring Lucy for an extended tour of North American Museums and facilitates TPLF’s affiliate business in US in the name of Ethiopia and Africa.

In addition, he is involved in many activities, including a consultant and executive Vice President of African Affairs at the Tagos Group since 2010, President of the International Trade Center in Huston since 2008, Founder and President of the Texas Africa Business Summit and. He is also is partner with Atara strategy Group that according to its website “provides consulting services on a myriad of issues to sovereign states desiring American businesses to invest in their economies and/or to provide needed manufacturing, construction or service industry expertise’ and list the Grand Ethiopian Renascence Dam as the only project it is involved.

Such-coordinated extortion of Ethiopia by TPLF operatives demands an organize effort to get to the bottom of it. At the meantime, all responsible governments, institutions and business/investors and law enforcement agencies must be notified to the activities of TPLF’s operatives in North America and elsewhere. .

In another development, the plea to the Diaspora to come and invest home (to deprive the opposition support) is coordinated by TPLF intelligent agency and the Foreign Minister and transmitted by the usual Medias. Selam TV interview with another hired warlord is the new TPLF’s campaign to confuse and divide the Diaspora.

Woyane has no chance but to surrender

As the struggle intensifies, there is no place to run no place to hide for Woyane. Showing rosy drama on ETV and terrorizing Ethiopians on the ground is not going to do it. Hiding behind hired ethnic warlords or screaming growth and development isn’t going to cut It. Running ethnic and religious propaganda in disguise isn’t going to help. Crying –terrorist are coming on the shoulders of foreigners is not going to bear fruit anymore. Luring foreign investors to hide behind is an old trick that wouldn’t have traction.

Mark Batterson in his bestselling book titled Praying Circle said “Nothing is as freeing as confessed sin.  Nothing is as isolating as a guilty secret.”
Woyane have no chance but to confess its sin and surrender or live in isolation with its guilty secret until its demise.
As to the sorry Medias and stooges that continue the hide-and-seek game in hope of sustaining the organize mob regime, it worth to note there is no running from the truth but dodging it temporarily
It takes courage to confess the truth and a coward to live in guilt.

ትላንትና መኢአድ ያወጣው የትግል ጥሪ መግለጫ ወያኔን ብቻ ሳይሆን አሜሪካንንም አደናበሯል።

August 9/2014
“መኢአድ ጠንካራ ድርጅት ነው።” በድንገት መኢአድ ቢሮ የደረሱ የአሜሪካ ዲፕሎማቶች
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ከኢሕአፓ ሕዋስ (ሴል) በመቀጠል በብቸኝነት ድርጅታዊ መዋቅሩን በማጥበቅ ታላቅ ስራዎችን የሰራው እና እየሰራ ያለው እንዲሁም በ97 ምርጫ የቅንጅት ማሸነፍ ታላቅ አስታውጾ የነበረው የፕሮፌሰር አስራት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በትላንትና እለት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ባስተላለፈው የትግል ጥሪ የተደናገጡት ወያኔዎች ብቻ ሳይሆኑ የአሜሪካ መንግስት ዲፕሎማቶችም እንደሆኑ ከኤምባሲው የተገኙ መረጃዎች ጠቁመዋል።
ethiopolበትላንትናው እለት የመኢአድ እና የአንድነት አመራሮች በጋር በሰጡት መግለጫ መኢአድ ድርጅታዊ መዋቅሩን ተጠቅሞ የጎዳና ላይ አመጽ እንደሚጠራ እና ሕዝቡ በተጠንቀቅ እንዲጠባበቅ ለምርጫ ቦርድ እና ለወያኔም ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ይታወቃል። ይህ ያሰጋው ወያኔ እንደለመደው ሲራወጥ ሁኔታው እና የመኢአድ ጥንካሬ ያሰጋቸው የአሜሪካ ዲፕሎማቶች በዛሬው እለት የፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ የሆነችዋ የኤምባሲው ዲፕሎማት በመኢአድ ጽ/ቤት በመገኘት አመራሮቹን ማነጋገሯ ታውቋል።
ከጠዋቱ በአምስት ሰአት በአስቸኳይ የፖለቲካ ጉዳይ በመግለጫው ዙሪያ ማብራሪያ ለመጠየቅ መኢአድ ቢሮ የመጡት እና በአሜሪካ ኤምባሲ የፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ ሴት የተመሩት ዲፕሎማቶች የመኢአድን ጠንካራ ፓርቲነት መስክረዋል። በወቅቱ በውይይቱ ላይ እንዲገኙ የተጋበዙት አንድነቶች ኢንጂነር ግዛቸው ብቻቸውን በመምጣት ያልተጠየቁትን ሲቀባጥሩ መስተዋላቸውን ከዲፕሎማቶቹ ጋር በቦታው የነበሩ የኤምባሲው ምንጮች ገልጸዋል።
የመኢአድ አመራር በውይይቱ ወቅት በሃገሪቱ ያሉትን ችግሮች እንዲሁም ምርጫ ቦርድ መኢአድን ለማፍረስ እየሰራ ያለውን ደባ እና መንግስታዊውን በፓርቲዎች ላይ የሚደረገውን ሽብር በዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል። አንዳንድ ለመኢአድ እና ለአንድነት የሚቀርቡ ምንጮች ወያኒ አንድነት ውስጥ ባሉ ሰርጎገቦቹ ን ተጠቅሞ ከውህደቱ በኋላ የመኢአድን ድርጅታዊ መዋቅር ለማፈራረስ ደባ እንደወጠነ ሲጠቁሙ ውህደቱን እንደማይፈልገው ተደርጎ የሚወራው ለይምሰል መሆኑን አክለው ይገልጻሉ። ወያኔ የመኢአድ ድርጅታዊ መዋቅር ክፈረሰለት እፎይ እንደሚል ውስጥ አዋቂ ምንጮች ይናገራሉ።#ምንሊክሳልሳዊ

Friday, August 8, 2014

አቶ ሬድዋን ሁሴን በቨርጂኒያ ውርደት ገጠመው፤ ኢትዮጵያውያኑ ልክ ልኩን ነገሩት (ቪዲዮ)

Augest 8/2014
ስንታየሁ ከሚኒሶታ
አቶ ሬድዋን ሁሴን ለሆዱ ያደረ በአራዳ ቋንቋ ‘ችስታ የወያኔ ተላላኪ’ መሆኑን ያሳየው ዛሬ ነው። በአርሊንግተን ቨርጂኒያ። አሜሪካን ውስጥ “ችስታ” ወይም ገንዘብ መቋጠር ከፈለክ የተራረፉ ልብሶችን የምትገዛበት ሱቅ ማርሻልስ ነው። የኬቨን ኪለር፣ ባናና፣ ቦስ፣ ናይኪ፣ አዲዳስ፣ ቶሚ፣ ኤክስፕረስ እና ወዘተ ታዋቂ የልብስና ጫማ አምራች ድርጅቶች በመደብሮቻቸው በሰዎች ልክ (ሳይዝ) የሰሯቸው እቃዎች ወደ ማለቂያ (ፋሽናቸው ሲያልፍ) የሚልኩት ወደ ማርሻልስ ስቶር ነው። ባጭሩ ማርሻልስን በሃገርኛ “ምናለሽ ተራ” ልትሉት ትችላላችሁ።
አዜብ መስፍን አሜሪካ ስትመጣ ጆርጅ ታውን ወርዳ በጣም ውድ የሆኑ ሱቆች ገብታ በ$10 ሺህዎች የሚቆጠሩ ዶላሮችን ታፈሳለች – የሰረቀችው ስላላት። ቴዎድሮስ አድሃኖም ከደሃው ሕዝብ ከሰረቀው ገንዘብ ቀነስ አድርጎ ኒውዮርክ ላይ ጄ ፕሬስ ቡቲክ ገብቶ በሺዎች ዶላሮች ለልብሶቹ አፍሶ ይወጣል። ታይም ስኩዌር ሄዶ ፎቶ ይነሳል። ተላላኪው ሬድዋን ሁሴን ግን ‘ቺፕ’ ብለው አሜሪካውያን በሚጠሩት ማርሻል የተራረፈ ልብስ ገዝቶ ይወጣል:: ዛሬ የሆነውም ያ ነው። ሰውዬው አሜሪካ መጥቶ አዲስ አበባ ላሉት ባለስልጣኖች ከአሜሪካ የገዛሁት ልብስ ብሎ ለማሳየት ከአሜሪካው ምናለሽ ተራ ሱቅ ልብስ ሊገዛ ገብቶ ተዋርዶ ተመለሰ። ኢትዮጵያውያኑ ተጋፈጡት። ሌባ መሆኑን፤ ገዳይና የገዳይ አገልጋይ መሆኑንም የፊቱ ቆዳ የሳሞራ የኑስን ልብስ እስኪመስል ድረስ ነገሩት።
እንደለመደ አፉን አይከፍት ነገር ያለው አሜሪካ ሆነበት፤ እንዳይደነፋ ኢቲቪና መቀሱ የሉም። ውርደቱን ከኤክስፕረስ በታላቅ ቅናሽ የገዛውን ሰማያዊ ልብስ እንደለበሰ ተከናንቦ ተመለሰ። ወይ ሬድዋን፤ አዜብ ጆርጅ ታውን፣ ቴዎድሮስ ጄፕሬስ ሲገበያዩ አንተ ቺስታና ሆድ አደር ስለሆንክ በማርሻል ውርደትህን አከናነቡህ አይደል? ገና ምን አይተህ? ኢትዮጵያውያኑ የሳሞራ የኑስን ልብስ እንዲመስል ያደረጉልህ ቆዳህ ገና ወደ የት እንደሚሄድ አብረን እናየዋለን።
ሬድዋንን የተጋፈጡትን ብርቱ ኢትዮጵያውያንን እያደነቁ፤ የወያኔ ተላላኪዎችን የማወረዱ ሥራ እንዲቀጥል አደራ እላለሁ። ቪድዮውን እነሆ።



Thursday, August 7, 2014

ታዋቂው ፖለቲከኛና ደራሲ ወጣት አብርሃ ደስታ ዛሬ ፍ/ቤት ቀርቦ የ28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀበት!!

10556491_765691513489600_2991655243642794561_nAugust 7/2014
በአራዳ መጀመሪያ ፍ/ቤት ችሎት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይቀርባል ቢባልም ዘግይቶ 10 ሰዓት ከ25 ላይ ቀርቧል፡፡ ፖሊስ ሀምሌ 3 ቀን ፍ/ቤት ቀርቦ ከግንቦት 7 ጋር በተያያዘ በሽፋን ትሰራለህ በሚል በቁጥጥር ስር አድርጎ ለምርመራ የ28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆበት የነበረ ሲሆን በ28 ቀን ውስጥም ምንም ማስረጃ ለችሎቱ አላቀረበም፡፡ በችሎቱ ላይ የአረና አመራር አቶ ካህሳይ፣የአብርሃ እህት በችሎቱ እንዲታደሙ ተፈቅዶላቸው ገብተዋል፡፡ አብርሃ ደስታ በእስርቤት የደረሰበትን ለችሎቱ ሲያስረዳ እያስገደዱ ቃል ተቀብለውኛል፣ ተደብድቤያለሁ፣ ከውጪ የመጡ የደህንነት ኃይሎች ምርመራ አድርገውብኛል፣ ጨለማ ቤት ለቀናቶች ነበርኩ፣ የማላውቀውንና ያላነበብኩትን እንደፈርም ተደርጌያለሁ፣ የጨጓራ በሽተኛ ሆኜ በግድ እንጀራ እንድበላ ተደርጌያለሁ በማለት ለፍ/ቤቱ አስረድቷል ፡፡ 
ፖሊስ እነዚህ ድርጊቶች በፖሊስ ጣቢያው እንደማይደረጉና ማስረጃ የሌላቸው ውንጀላዎች ናቸው በማለት ያስተባበለ ሲሆን፣ ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ደንበኛቸውን የሚመረምረውን መርማሪ ስም እንዲገለጽ ቢጠይቁም የመርማሪውን ስም አንናገርም ይዞ ፍ/ቤት የሚያቀርበውን ፖሊስ ስም ብቻ ነው የምንናገረው በማለት መልሰዋል፡፡ አቃቤ ህግ ለምርመራ ተጨማሪ የ28 ቀን ቀጠሮ ጠይቆ ፍ/ቤቱ የ28 ቀን ቀጠሮውን ፈቅዶ ለነሐሴ 29 ቀን 2006 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት እንዲቀርብ አዟል፡፡ የፍርድ ቤቱን ሂደት ለመከታተል አረና፣ የአንድነት፣ የሰማያዊ፣ የመድረክ፣የጌዴኦ የፓርቲ አመራሮችና አባሎቻቸው፣ ጋዜጠኞችና ብሎገሮች በርካታ ሰዎች ተገኝተው አብርሃ ወደ ፍ/ቤት ግቢ በሚገባበትና በሚወጣበት ጊዜ በጭብጨባና አይዞህ በማለት አጋርነታቸውን ሲገልጹ ብርሃ ደስታም አንገቱን ዝቅ በማድረግ የታሰሩ እጆቹን ከፍ በማድረግ ምላሽ ሰጥቷል፡፡
ፍኖተ ነጻነት

በአምስት ነጻ ጋዜጦች ላይ ጥቁር ሽብር እየተፋፋባቸው ነው!!

August 7/2014
(ኢ.ኤም.ኤፍ) ከትላንት በስትያ የፍትህ ሚንስትር መስሪያ ቤት በህዝብ መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እና ሬድዮ አምስት ጋዜጦችና መጽሄቶች ህገ መንግስቱን ለመናድ መሞከራቸውን በመግለጽ መግለጫ አውጥቶ ነበር። የመግለጫው ጭብጥ እንደሚያስረዳው ከሆነ፤ አምስት የፕሬስ ውጤቶች መንግስትን ሰላም የነሱ መሆናቸውና ወደፊትም በእንደዚህ መሰል የፕሬስ ውጤቶች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ነው ዛቻ በተቀላቀለበት ሁኔታ የተገለጸው። በአሁኑ ወቅት የሰብ አዊ መብት ገፈፋዎችን ጨምሮ ከህግ ውጭ የሚደረጉ የመንግስት አሸባሪ እርምጃዎችን፣ “ጥቁር ሽብር” የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። ይህ በፕሬስ ውጤቶች ላይ የተካሄደው እርምጃም የ”ጥቁር ሽብር” ሌላኛው ማሳያ በመሆኑ በምሳሌነት የሚጠቀስ ነው።
ጥቁር ሽብር እየተፋፋመባቸው ያሉት የፕሬስ ውጤቶች
ጥቁር ሽብር እየተፋፋመባቸው ያሉት የፕሬስ ውጤቶች
በስም የተጠቀሱት አምስት የፕሬስ ውጤቶች ክስ ሳይመሰረትባቸው፤ ለፖሊስ ቃላቸውን ሳይሰጡ፤ የፍርድ ቤት መጥሪያ ሳያገኙ ነው፤ የፍትህ ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ “አሸባሪ” የሚል ስያሜ ሊሰጣቸው የሞከረው። የፍትህ ሚንስቴር መስሪያ ቤት በዚሁ መግለጫው ላይ “ፋክት፣ ጃኖ፣ ሎሚ፣ አዲስ ጉዳይ፣ እና እንቁ የሚባሉ መጽሄቶችን እንዲሁም አፍሮታይምስ የሚባለውን ጋዜጣ በሚያሳትሙ ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ መስርቻለሁ” ብሏል። ይህ ክስ ፕሬሶቹ በቀጣይ የህትመት ስራዎቻቸውን ለማገድ የታቀደ ሲሆን፤ ይህን ተከትሎ ህትመት ያቆሙ መጽሄቶች እና ጋዜጦች ስለመኖራቸው የታወቀ ነገር የለም።
ትላንት ረቡዕ ለህትመት ወጥቶ የነበረው ሰንደቅ ጋዜጣ ይህን ጥቁር ሽብር አስመልክቶ የፍትህ ሚንስቴርን መግለጫ በማስቀደም የፖለቲካ ፓርቲ ሃላፊዎችንእና ጋዜጠኞችን አነጋግሯል። ስለሁኔታው ተጨባጭ መረጃ ይኖራቹህ ዘንድ የሰንደቅ ጋዜጣን ዝግጅት በፒ.ዲ.ኤፍ አቀናብረን ከዚህ በታች አቅርበነዋል። ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ።