Wednesday, July 30, 2014

የዞን ዘጠኝ ጦማርያንና ጋዜጠኞችን ክስ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ (አስቂኙ ክስና አስቂኙ ማስረጃ)

July 30/2014

zone 9



















አገራችን ኢትዮጵያ በጥሩ ልትጠራባቸው የምትችላቸው ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው በድህነት በሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ በሙስና እና ሃሳብን ነጻነት በመግለጽ መብት የተለመዱ የምናፍርባቸው ጉዳዩች ሆነውመቀጠላቸው እሙን ነው፡፡ ሃሰብን በነጻነት መግለጽን አስመልክቶ ሶስት ወራትን ከፈጀ ምርመራ በኋላ በብዙ የፓሊስ ድብብቆሽሂደት የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ላይ ባለፈው አርብ ክስ መመስረቱም አብሮ ይታወሳል:
ጓደኞቻችን ከታሰሩ ጊዜ ጀምሮ መንግሰት ያቀረበውን ውንጀላ አስመልክቶ በተለያየ ወቅት ሃሳባችንን ለመግለጽ አስበን ምናልባትየምንሰጠው ሃሳብ አሁንም በመንግሰት እጅ የሚገኙት ጓደኞቻችን ላይ ሊኖረው የሚችለውን ተጽእኖ በመፍራት እነዲሁም ለመንግሰትእድሉን በመስጠት ኦፌሻል ክሱን እስክናይ ድረስ በጠቅላላ ሃሳቦች ላይ አስተያየት ከመስጠት ውጨ ብዙም ሳንል ቆይተናል፡፡ አሁንግን ክሱ አንድ የዞን 9 ጦማሪን ጨምሮ በይፋ በመመስቱ እነዲሁም በክሱ ላይ ተጠቀሱት ክሶች አንዳቸውም እውነት ባለመሆናቸውክሱን አስመልክቶ ዘርዘር ያለ ማብራሪያ መስጠት እነዳለብን ተሰምቶናል፡፡
ክሱ በአጭሩ
በአስሩ ተከሳሾች ላይ የተጠቀሱት የክስ አይነቶች ሁለት ሲሆኑ አንዱ የሽብር ተግባርን ማቀድ ማሴር ማነሳሳትና መፈጸም ሲሆን(የጸረ ሽብር ህጉ አንቀጽ አራት) ሁለተኛው ህገ መንግሰታዊ ስርአቱን በሃይል መናድ( የወንጀለኛ መቅጫ ህጉ አንቀጽ 238)የሚሉ ናቸው ፡። ክሱ ላይ በፓርላማ በሽብተኝነት ላይ ከተፈረጁ ድርጅቶች ቀጥታ ትእዛዝ በመቀበል በህቡእ በመደራጀት የሽብርተግባር ላይ መሰማራት እና የመሳሰሉት ክሶች በዝርዝር ቀርበዋል፡፡ ከሶቹ ሲጠቃለሉ
1. ከግንቦት ሰባት ጋር እና ከኦነግ ጋር ግንኙነት መፍጠር ትእዛዝ መቀበል
2. ስሙ ባልተጠቀሰ የህቡእ መደራጀት እና ስራ ክፍፍል መፍጠር
3. Security ina boxን ጨምሮ ስልጠና መውሰድ
4. አመጽ ቡድኖችን ማደራጀትና አመጽ ማነሳሳት  የሚሉት ዋናዋናዎቹ ናቸው፡፡

ከግንቦት ሰባት ጋር እና ከኦነግ ጋር ግንኙነት መፍጠር ትእዛዝ መቀበል
ከዚህ በፊትምእነደተናገርነው  ማንኛቸውም የዞን9 ጦማርያን በፓርላማ በሽብርከተፈረጁ ወገኖች ጋር ምንም ግንኙነት የለንም፡፡  ብዙ  የዞን9 ነዋሪያንንም አንደሚረዱት አብዛኛዎቹ የዞን9 ጦማርያን እነዚህአካላት ላይ በሚያደርጉት ከፍተኛ ትችት እየታወቁ ጉዳዩን ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ለማያያዝ መሞከር ፣መንግስት የፈረጃቸውንድርጅቶች እነደፈለገ ማንንም ሰው ለመክሰስ አንደሚጠቀምበት ከማሳየት ባለፈ ትርጉም የማይኖረው ነው፡፡ ለማጠቃለል ያህልማንኛቸውም የዞን9 አባላት አገር ውስጥም ሆነ ውጪ አገር ያለ የፓለቲካ ደርጅት አባላት አይደሉም፡፡ ይህንን የሚያሳይ መረጃምመንግሰት ለማቅረብ አንደማይችልም አናውቃለን፡፡ ( የማስረጃ ዝርዝር ላይ ወደታች የምንመለስበት ይሆናል)

ስሙ ባልተጠቀሰ የህቡእ መደራጀት እና ስራ ክፍፍል መፍጠር
በክሱ ላይ ስሙያልተጠቀሰ የህቡእ ሽብር ድርጅት በመመስረት ተከሰናል፡፡ በመሰረቱ መንግስት ዞን9 የሚለውን ስም አንድም ቦታ በክሱ ላይለመጠቀም ያልፈለገው የጦማርያኑን ቡድን ይበልጥ ታዋቂ እነዳይሆን ለማድረግ አንደሆነ አንገምታለን፡፡ ይህ አስቂኝ ክስ አንድምቦታ ላይ የዞን9 ስም ባያነሳም በደፈናው በህቡዕ መደራጀት ብሎ ከሶናል፡፡ በመሰረቱ መንግሰት እኛን ለማግኘት ምንም አይነትየደህንነት ስራ እነዳላስፈለገው አናውቃለን፣. ምክንያቱም ሁሉም የዞን ፱ ጦማርያን ስማቸውና ፎቶአቸውን ማስቀመጣቸው ቋሚየምንስማማበት እሴት ስለነበር ነው፡፡ የምንጽፈው ነገር በተናጠል ሃላፊነትን አንድንወስድ አንዲሁም ሌሎችን ሃሳብ መግለጽንለማበረታታት በማሰብ በአደባባይ  እነዲታይ የወሰነውን የጦማርያንንስብስብ ‹‹ህቡዕ›› ብሎ መጥራት ማንን ለማሞኘት አንደሆነ ግልጽ አይደለም፡፡ ዞን፱ ድብቅ እነዳልሆነ እያንዳንዱ ጽሁፍምበተናጠል ሃላፊነቱን የሚወስድ ጸሃፊ የቡድን ጽሁፎች ሲሆኑ ደሞ የቡድን ሃላፌነት አንደምወስድ ማንም የጦማራችን አንባቢያውቀዋል፡፡ መንግስት የዞን፱ አይነት ጦማሮችንም ሆኑ የአንተርኔት አንቅስቃሴዎቸን የሚመዘግብበት አሰራር አለመኖሩ ደሞ የእኛጥፋት ተብሎ ሊቆጠር አይችልም፡፡ተሰብስቦ መጦመርን የሚከለክል ምንም አይነት የህግ ክልከላም የለም፡፡ በመሆኑም ተሰብስበንመጻፋችን  ራሳችንን ገልጸን ሃሳባችንን መግለጻችን የጣስነው ምንምሕግ የለም፡፡ፓሊስም ሆነ መንግሰት ሶስት ወር በፈጀ ምርመራው ህቡዕን ትርጉም ትርጉም በሚገባ አለማወቁም ጉዳዩን አስተዛዛቢባስ ሲልም መሳለቂያ ያደርገዋል፡።

Security in a boxን ጨምሮ ስልጠና መውሰድ
Security in a box ኢንተርኔት ላይ የሚገኝ የኢንተርኔትአንቅስቃሴን በጥንቃቄ ለማድረግ የሚረዳ ኦፕን ሶርስ የስልጠና ማንዋል ሲሆን ይህንን ስልጠና መውሰድ በምንም መልኩ ወንጀልሊሆን አይችልም፡፡ ይህ የስልጠና ማንዋል ለማንኛውም የሰብአዊ መብትና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት የሚያሳስባቸው ሰዎችአንዲያገኙት ሆኖ የተዘጋጅ  ፍሮንት ላየን ዲፌንደርስ እናታክቲካል ቴክ የተባሉ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማት ያዘጋጁት ስልጠና ነው፡፡ በመሰረቱ ይህንን ስልጠና ወንጀል አድርጎከማቅረብ በፊት ጎግል ላይ አስገብቶ መፈለግና ውጤቱን ማየት ከአንደዚህ አይነት አሳፋሪ ክስ ያድን ነበር፡፡ ይህ በበጎ መልኩአንረዳው ካልን የፍትህ አካላቱ ከቴክኖሎጂ ጋር ያላቸውን ከፍተኛ ርቀት የሚያሳይና መንግሰትም በሰፊውና በቅንጅት ሊሰራበትየሚገባ ክፍተት ሲሆን ከዚያ ባለፈ ካየነው ደሞ መንግሰት እሱ የማያውቀውን ማንኛውንም ነገር ያለምንም የህግ ክልከላ  ወንጀል ብሎ ለመፈረጅ ያለውን ጉጉት ያሳያል ያ በራሱ ደሞ መንግስትንራሱን ህገ ወጥ እነደሚያደርገው ያለምንም የህግ እውቀት ማሰብ ብቻ ለሚችል ሰው የሚገለጥ ሀቅ ነው፡፡
በዚህ አጋጣሚ ወንጀልተብለው የተለያዩ ስልጠናዎች በሚል የተጠቀሱት የኮምኒኬሽን ስልጠና የስትራቴጂክ ስልጠና የአድቮኬሲ ስልጠና የመሳሰሉትመሆናቸውን ለመጥቀስ አንወዳለን፡፡ በመሰረቱ በተለያዩ ድርጅቶች ግብዣ ስልጠና መውሰድና የሰብአዊ መብት ፎረሞች ላይ መገኘትንወንጀል የሚያደርግ ህግ አለመኖሩን መንቀሳቀስም የዜጎች ሰብአዊ መብት መሆኑን ለአቃቢ ህግ ህግና ፓሊስ ካላወቁ ማን ሊያውቅነው ??
የተደራጁት የአመጽቡድኖችን ማደራጀት  እና 48 ሺህ ብር ለአመጽ ማከፋፈል
መንግሰት የአመጽቡድኖችን ማደራጀት በሚል ያቀረበውን ክስ ለመመለስ ያህል አንድ ጥያቄ ብቻ አንጠይቃለን? የታሉ የተደራጁት ቡድኖች?  ምንም የተደራጀ ቡድን በሌለበት ይህንን ክስ ማቅረብ በፍትህ ስርአቱማፌዝ ካልሆነ በስተቀር ሌላ ምን ይባላል? በ48 ሺህ ብር የአመጽ ማነሳሳት ክሱን ከብሩ ማነስ በላይ ይበልጥ አስቂኝየሚያደርገው የማስረጃው ዝርዝር ላይ ያለው ማስረጃ እና ክሱ የተለያዩ መሆናቸው ነው፡፡ ክሱ 48,000 ብር ከውጪ በመቀበልበማለት በደፈናው ላኪውን ሳይጠቅስ ያለፈው እና ለሽብር ተግባር የተባለው አርቲክል 19 ከተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅትለታሰሩ ጋዜጠኞች ቤተሰቦች የሚደረግ ድጋፍ ሲሆን በወቅቱ ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ ባንክ ስለሚሰራ ተቀብሎ ለጋዜጠኛ ርዩት አለሙቤተሰቦች እስር ቤት መመላለሻ ተብሎ የተሰጠ ድጋፍ ነው፡፡
የተያያዘው የባንክደረሰኝም ያንን የሚያሳይ ሲሆን ክሱ ላይ በይፋ መጥቀስ ያልተፈለገው ለምን ይሆን? (ጦማርያኑ እና ጋዜጠኞቹን መታሰር ተከትሎመንግስት ፋይል የከፈተበትን ከሰብአዊ መብት ተቋማት ነን ከሚሉ ድርጅቶች የሃሳብና የገንዘብ ድጋፍ በመቀበል ሶሻል ሚዲያንበመጠቀም አመጽ ማነሳሳት የሚለውን ክስ ተከትሎ የተባበሩት መንግሰታት የሰብአዊ መብት ጉባኤ ከአለም አቀፍ ተቋማት ጋር በጋራመስራት ወንጀል ሊሆን አይገባም በሚል ርእስ እስሩን የሚያወግዝ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል)
ማስረጃውሲገመገም
እስካሁን በእጃችን የደረሰውን የማስረጃ ዝርዝር በሶሰት ከፍለን ማየት አንችላለን ፡፡ከማስረጃ ዝርዝሩ ውስጥ አብዛኛውን ቦታ የሚይዘው በተለያየ ወቅት የተጻፉ የጦማርያኑ ጽሁፎች ሲሆኑ ጋዜጠኞቹ ላይ ደሞ ጭራሽየመረጃ ዝርዝር ለማቅረብም አልተቻለም፡፡(አቃቤ ህግ የሁሉንም የበይነ መረብ ዘመቻዎች መግለጫ እና እቅድ እንደማስረጃአቅርቧል)  በሁለተኛ ደረጃ የቀረቡት የተለያዩ የጉዞ ትኬቶችአለም አቀፍ ስብሰባ ማስታወሻዎች አንዲሁም ፕረዘንቴሽኖች  ሲሆኑሁሉም ጦማርያኑ ያደረጓቸው አለም አቀፍ ጉዞዎችን የሚያሳዩ የተሳተፉባቸው ሰብአዊ መብትና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትየተመለከቱ የአፍሪካ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጉባኤ የተደረጉ ጉዞዎችን ናቸው፡፡
በማስረጃ ዝርዝር ውስጥከተካተቱት የሽብር ተግባር የተደረጉ ጉዞዎች ተብለው መሆኑ ይበልጥ ክሱን አሳፋሪ ያደርገዋል፡፡ መንግሰት ጉዞዎቹ የተደረጉትምሆነ የስልጠና ግብዣዎቹ የመጡት ከአለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት አንደሆነ እያወቀና እና ማስረጃው ላይም በግልጽእየታየ የሽብር ቡድኞች ብሎ ግንቦት ሰባትና ኦነግን ጣልቃ ማስገባቱ አስገራሚ ነው፡፡ (የፍርድ ሂደቱ ላይ እነዚህ ተቋማት ጋርየተደረጉ ግንኙነቶቸን አንዴት ብለው በፓርላማ ከተፈረጁ የሽብር ተቋማት ጋር እነደሚያገናኛቸው አብረን የምናየው ይሆናል)  በሶስተኛ ደረጃ የተቀመጡት ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ የተደረጉ የስልክልውውጦች ሲሆኑ በፍርድ ቤት ሂደቱ ውስጥ በዝርዝር የምናያቸው ይሆናል፡፡ በመጨረሻም ተከሳሽ ቤት ተገኘ የተባለውና ፓሊሶች ራሳቸው ያመጡት ከግንቦት ሰባት ጋር የተገናኙ ዶክመንቶች እናየአባላት መጽሄት ሲሆን በፍተሻው ወቅት ፓሊሶች ራሳቸው ፍሪጅ በስተጀርባ አገኘን ብለው በፍተሻ ወቅት ከፍተኛ አለመግባባትተፈጥሮ የራሳቸውን ምስክሮች ብቻ አስፈርመው መሄዳቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
እንዲሁም ፓሊስ 18 የሰው ማስረጃ ለማሰማት የስም ዝርዝር ማስገባቱን እና የስም ዝርዝሩም እጃችን ላይ የሚገኝ ቢሆንም ከፍርድቤት ለሚመጣው የፍርድ ውጤት ሳይሆን በአጠቃላይ የፍትህ ስርአትን ማክበር ሃላፊነት ስላለብን ብቻ እዚህ ጽሁፍ ውስጥ ላለማካተትወስነናል፡፡
እንደማጠቃለያ
የዞን፱ ጦማርያን ከዚህ በፊትም በተለያየ ወቅትአንደተናገርነው የመንግሰት ይህን ሁሉ ጊዜ ወስዶ ይዞ የመጣው ማስረጃ የአደባበይ ጽሁፎች እና በተለያየ ወቅት የተደረጉ የአደባባይሁነቶች( public events) ጥርቅም መሆኑ የክሱን ፓለቲካዊነት ያረጋገጠ ነው፡፡ ጦማርያኑ የፍርድ ቤት ስርአቱን የተለያዩአለም አቀፍ የወንጀል ስነስርዓት ደረጃን በጠበቀ መልኩ ህጉን አክብረው የሚከታተሉ ሲሆን እኛም ሂደቱን በተቻለ መጠን ለዞን ፱ነዋሪያን ለማሳየት ለማሳወቅ የምንጥር መሆኑን ለማሳወቅ አንወዳለን፡፡ በተደጋጋሚ ተፈትኖ የወደቀው የአገራችን ፍርድ ቤት እና የፍትህስርአት ገለልተኝነት ይህንን እድል በመጠቀም ራሱን ለማሻሻል መፍቀዱን እነዲያሳይና ፍርድ ቤቱ ማስረጃዎቹን አይቶ ክሱን እነዲዘጋጥሪ እያደረግን ይህንን በማድረግ የአገሪቱን የፍትህ ሂደት አንድ ደረጃ የማራመዱን እድል ዳኞች እንዲጠቀሙበት መንግስትን ከወራትበፌት የሰራውን ስህተት ለማስተካከል እድሉ ዛሬም ያልመሸ መሆኑን ለማስታወስ አንወዳለን፡፡
የታሰራችሁ ጦማርያንን እና ጋዜጠኛ ወዳጆቻችን ለከፈላችሁት መስዋእትነት ውለታችሁ አለብን፡፡ እንኮራባችኋለን!!
ማስረጃ ተብለው የቀረቡ ሰነዶች ለፈገግታ ያህል
ዞን ዘጠኝ ላይ የታተሙ ጽሁፎች
  1. ነጻነትና ዳቦ - በናትናኤል ፈለቀ
  2. ሳንሱር ዋጋ ያስከፍላል - በናትናኤል ፈለቀ
  3. ስደትና ፍቅር - በሰለሞን አብርሃም(ከአውሮጳ)
  4. ዋኤል ጎኒሞ ኢትዮጵያዊ ቢሆን ኖሮ ….? - በበፍቃዱ ሃይሉ
  5. ልማታዊ ጋዜጠኝነት ወይስ ይሁንታን ማምረት? - በእንዳልካቸው ሃይለሚካኤል
  6. እኛና ሶማልያ – በናትናኤል ፈለቀ
  7. ድምፃችን ይሰማ - በእንዳልካቸው ሃይለሚካኤልና እና በፍቃዱ ሃይሉ
  8. እንዴት እንደመጥ - በማህሌት ፋንታሁን
  9. የመለስ ውርስ እና ራዕይ - በሶሊያና ሽመልስ
  10. የቅድመ ምርመራ ቅድመ ምርምራ - በማህሌት ፋንታሁን
  11. ትግራይና ሕዋሐት ምንና ምን ናቸው ? -በበፍቃዱ ሃይሉ
  12. ህግ ምርኩዝ ነው ዱላ በዘላለም ክብረት

ከበፍቃዱ ብሎግ(www.befeqe.com) የተገኙ 
  1. ከ21 አመት በኋላ ዴሞክራሲ ሲሰላ
  2. ኢትዮጵያ ውስጥ የመንግስት መመሪያ በማክበር መሥራት ይቻላል?
  3. አብዮት ወረት ነው
  4. የእህአዴግ ‹‹ትርፍ›› እና ኪሳራ
  5. የኢትዮጵያ መንግስት መጠላቱን የሚያሳብቁ ምልክቶች
  6. ከእከሌን አሰሩት እስከ እከሌን አገዱት
  7. ሰማኒያ ሚሊዮን እስከምንደርስ እንታገላለን
  8. “ድር ቢያብር” ለአምባገነኖች ምናቸው ነው ?
ከሌሎች ብዙ ዝርዝሮች በጥቂቱ

  1. “ኢትዮጵያዊ ማንነት ከሌለ ትግሬያዊ ማንነት የለም” – (በአብርሃ ደስታጽሑፍ ከፌስቡክ የተወሰደ) /በበፍቃዱ ቤት የተገኘ/
  2. “መንግስት የለም ወይ ?” የምንና ምን አይነት መንግስት(የመስፍን ነጋሽጽሑፍ ከፌስቡክ የተወሰደ ) /በበፍቃዱ ቤት የተገኘ/
  3. የሁለተኛው ዘመቻ ዕቅድ ( ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አሁኑኑ)
  4. የ2ኛው ዘመቻ ጋዜጣዊ መግለጫ (ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አሁኑኑ)
  5. ዳዊት ሰለሞን ስለአዲሱ የጋዜጠኞች ፎረም ፕሬዚዳንት ፌስቡክ  ላይ የፃፈው እና አጥናፍ ለበፍቄ ኢሜል የደረገለት ጽሑፍ
  6.  “ፍርሃታችንየት ያደርሰናል ?” በሚል በኤልያስ ገብሩ ተጽፎ በፍቄ ላፕቶፕ ውስጥ የተገኘ(ለዕንቁ መጽሄት ተዘጋጅቶ ያልታተመ ጽሑፍ)
  7. የ3ኛው ዘመቻ ጋዜጣዊ መግለጫ ( ዴሞክራሲን በተግባር እናውል የሰላማዊሰልፍ መብታቸን ይመለስ)
  8. “ሰልፍና ሰይፍ ” በሚል በበፍቄ ተጽፎ ነገር ግን ያልታተመ ጽሁፍ ከላፕቶፑ
  9. የ1ኛው ዘመቻ ጋዜጣዊ መግለጫ(draft ሕገ መንግሰቱ ይከበር)
  10. የ4ኛው ዘመቻ ዕቅድ( ኑ ኢትዪጲያዊ ህልም አብረን እናልም)
  11. ጋዜጠኛ አስማማው ለድምፃችን ይሰማ የፌስቡክ ገጽ ያዘጋጀቸው ጥያቄዎችከኢሜሉ (ለአዲስ ጉዳይ መጽሄት)
  12. ስለ ዞን 9 ዘመቻዎች globalvoicseonline.org ላይ የታተሙጽሑፎች
  13. በናትናኤል በኩል ለርዕዮት ዓለሙ ቤተሰቦች ከ Article 19 የተላከ48,170.25(ብር) የዌስተርን ዩኒየን ኮፒ
  14.  “የተቃውሞሰልፉ ዕድሎች እና ተግዳሮቶች” በሚል አዲስ ጉዳይ ላይ የታተመ ጽሁፍ (draft)
  15. ማሒ ስለ ርዕዮት ዓለሙ እና ስለ አዲስ ዘመን “አዝማሚያ ጥናት ” በቀልድየጻፈችው ጽሑፍ፡፡
  16. የዞን 9 ወደፊት ለመስራት የታቀዱ ሶስት ፕሮጄክት ፕሮፓዛሎች ( ምርጫ2007 ሪፓርት የማድረግ ስራ፣ የኢትዮጲያ የነጻነት ኢንዴክስ ማዘጋጃት ስራ ፣ ገጠሪቷ ኢትዮጲያ ላይ ለመስራት የታሰበ ዶክመንተሪእቅድ)
  17. እና ሌሎችም ትርኪሚርኪዎች (ለምሳሌ የዳንኤል ብርሃነ ጽሑፍ፣ የናቲ የ10ኛክፍል ግጥም)

የግል ሚዲያው “በፀረ ሽብር ህግ” ሊበላ ይሆን? [ኣቶ ግርማ ሠይፉ ማሩ]

July 30/2014
የመንግሰትን ቀጣይ እርምጃ የሚያሳዩ ተከታታይነት ያላቸው በግል ሚዲያዎች ላይ የሚደረጉ ዘመቻው ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ መልክቶች እየታዩ ነው፡፡ በቀጣይ ለሚቀርበው ዶክመንተሪ ተጋባዥ አንግዳ ሆኜ ለቆርጦ ቀጥሉ ኢቲቪ ቃለ ምልልስ እንደሰጣቸው ጥያቄዎቹ ደረስውኝ ተመልክቸዋለሁ፡፡ የጥያቄዎቹን ዝርዝር እንተወው እና ዓላማው ግን ባለፈው ከቀረበው ዘጋቢ ፊልም የተለየ ነገር የለውም፡፡ በነገራችን ላይ ባለፈው የቀረበውም ዘጋቢ ፊልም ላይ እንድሳተፍ ተጠይቄ እንደማይሆን ገልጨላቸው ነበር፡፡ ውሳኔዬ ትክክል መሆኑን ዘጋቢ ፊልሙን ካየሁ በኋላ ገብቶኛል፡፡ የዘጋቢ ፊልሞቹ ዋና ግብ “የኢህአዴግን አብዮታዊ ዲሞክራሲን መንገድ አምነው ያልገበሩ የግል የሚዲያ ተቋማትን ለማጥፋት ጥርጊያ መንገድ ማመቻቸት ነው፡፡” የግል ሚዲያውን ማጥፊያ መንገዶች ሁሉን አቀፍ ናቸው፡፡ በዋነኝነት ኤኮኖሚያዊ የሚባለው ሲሆን ይህም በምንም ሁኔታ ከመንግስት ወይም “ከልማታዊ ባለሀብቶች” ገንዘብ እንዳያገኙ ማድረግ ሲሆን ከአንባቢ የሚሰበሰቡትንም ገንዝብ ለእዕትመቱ ቀጣይነት እንዳይመች የሚቻለውን ቀዳዳ ሁሉ መዝጋት፤ ይህ የማይሳካ ቢሆን በአሰተዳደራዊ ዘርፍ እንዲወሰድ የተቀመጠው ፍርድ ቤትን በመጠቀም ጋዜጠኞችን ማስር ነው፡፡ ይህ በመጨረሻ የተቀመጠው አማራጭ የውጭ ሀይሎች የማይቀበሉትም ቢሆን መጠቀም ሲያስፈልግ መጠቀም ግድ ነው፡፡ ይህ ሃሳብ የኔ የዚህ ፅሁፍ አቅራቢ አይደለም፡፡ አቶ መለስ ዜናው አዘጋጅተውት ኢህአዴግ የሚባለው ፓርቲ እንደ መርዕ ተቀብሎት አሁን በአቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ የገዢነት ዘመንም የሚቀጥል የሟቹ ጠቅላይ ሚኒሰትር የራዕይ ክፍል ነው፡፡ ይህን ራዕይ አላስቀጥልም ሚዲያ በዓለም ተቀባይነት ባለው መስፈርት አራተኛ መንግሰት እንዲሆን አደርጋለሁ ይሉናል ብለን ብንጠብቅም ሊሆን የቻለ ነገር የለም፡፡

ለዚህም ማሳያው ባለፈው ሳምንት የቀረበው ዘጋቢ ፊልም ነው፡፡ ክሱም በቀጣይ ዝም ብሎ ተራ ክስ እንደማይሆን ምልክቶች መጥቀስ ይቻላል፡፡ ዜጎችን አሸባሪ በማለት ክስ በመመስረት ታዋቂ የሆኑት ግለሰብ በዋና ተዋናኝነት የቀረቡበት ሲሆን ይህ ዘጋቢ ፊልምም ለቀጣይ ለሚያዘጋጁት ክስ መንደርደሪያ ሊሆናቸው ይችላል፡፡ ስለዚህ በሽብርተኝነት የሚከሰሱ ሚዲያዎችና አምደኞች እንደሚኖሩ መጠበቅ ይኖርብናል፡፡ እዚህ አካባቢ እስክንድር፣ ርዕዮት፣ ውብሸት ሰለባ የሆኑለት የግል ሚዲያ ተሳትፎና ሃሳብን የመግልፅ ነፃነት መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡ ሀቃቢ ህጉ ከሰጡት አሰተያየት ሳይሆን ስንት ሰው ከሰው ወህኒ የወረወሩበትን አዋጅ ሰም በትክክል መጥራት አለመቻላቸው ነው፡፡ ለነገሩ “የሽብር ህጉ” እያሉ ሲጠሩት ትክክለኛ የተፃፈ ስሙ ባይሆንም እውነተኛ ምግባሩን ግን መግለፁን አልዘነጋሁትም፡፡ በተደጋጋሚ “የሽብር ህጉ” እያሉ ሲጠሩት አዘጋጁ ጋዜጠኛም አውቆ መሆን ይኖርበታል ይህን ክፍል ማስተካከል ያልቻለው፡፡ የውስጥ አርበኝነት ይሆን ብለን ታዝበን ከማለፍ አንባቢም ልብ ካላለው ለማስታወስ ብዬ ነው፡፡ ይህ “የሽብር” ያሉትን ህግ መቼ እንደምንገላገለው ባናውቅም ግብሩ ግን አሸባሪነት መሆኑ ተገልፆልናል፡፡

የብሮድካስት ባለስልጣን ምክትል ኃላፊ ቀደም ሲልም ከበላያቸው ለስሙ ኃለፊ የነበረ ቢሆንም በመሰሪያ ቤታቸው አድርጊ ፈጣሪ እንደ ነበሩ ታውቆ ያደረ ጉዳይ ነው፡፡ እርሳቸው ከሰጡት ውስጥ ድንቅ የሆነብኝ ግን 45 ሺ ታትሞ ሁለትና ሶሰት ሺ ነው የሚሸጠው የሚለው ክፍል ነው፡፡ ከዚህ ቀጣይ ያለው ነገር ግልፅ ነው፡፡ ክቡርነታቸው እንደነገሩን እነዚህ ጋዜጦች የሚደጉማቸው አንድ ኃይል አለ የሚል ነው፡፡ ይህ ሀይል ደግሞ ሀገሪቱን ለማተራመስ የሚሰራ መሆኑ ነው፡፡ ለምሳሌ እኔ አምደኛ ሆኜ እንኳን አንድ መፅሄት በነፃ እንደማልወስድ እግረ መንገዴን ብነግራቸው ጠቃሚ ይመስለኛል፡፡ ቅዳሜ ሳልገዛ ካመለጠኝ እሁድ ከገበያ ላይ እንደማላገኝው ልባቸው ያውቀዋል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ለብሮድክሳት ባለስልጣኝ ሃላፊ ሁለት ሺ ኮፒ ለኢህአዴግ አባላትም እንደማይበቃ አልተረዱትም፡፡ በዚህ ክፍል አንባቢ እንዲረዳልኝ የምፈልገው አንድ እውነት ከሻቢያ፣ ከግብፅ፣ ከግንቦት ሰባት፣ ወይም አንድ የውጭ ሀይል የሚል ክስ ታሳቢ መደረጉ ነው፡፡ ክሱ ልክ መሆኑ አያስጨንቃቸውም ማንን ፈርተው ልክ እንዲሆን ይጨነቃሉ፡፡ በዚህ ጉዳይ ስንወያይ አንድ ወዳጄ ያለኝን ማንሳት ይጠቅማል፡፡ እነዚህ ሰዎች ቤተሰብ ዘመድ የሚባል የላቸውም ወይ? ይታዘበናል አይሉም ወይ? ነው ያለኝ፡፡ እኔም ደገምኩት አፈርኩ ለእናንተ ስል ብዬ፡፡

ለነገሩ እነዚህ ጋዜጦች በዚህን ያህል ዝቅተኛ ኮፒ የሚሸጡ ከሆነ መንግሰት የሚባል አካል ለምን ተሸበረ? ለምንስ ዘጋቢ ፊልም መስራ አሰፈለገው? ብለንም ልንጠይቅ እንገደዳለን፡፡ ሌላው ጥያቄ ደግሞ እነዚህ የውጭ የሚባሉ ሀይሎች የማይሸጥ ጋዜጣና መፅሔት ታትሞ ቢቀመጥ የሚያስቡተን ሀገር የመበተን ሴራ እንዴት ይሳካል ብለው ነው ድጋፋቸውን የሚቀጥሉት? ብለን ጠይቀን እንለፍ፡፡

ሌላው አስቂኝ ክስ ደግሞ “አሻጥረኛ አከፋፋዮች” የሚለው ነው፡፡ አቶ ሽመልስ ከማል አዲሰ ዘመን ከገበያ ልትወጣ የተቃረበችው በእነዚህ አሻጥረኛ አከፋፋዮች ሴራ እንደሆነ ምክር ቤት ቀርበው ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ የኢዲስ ዘመንን ይዘት ማስተካከል ሲያቅታቸው የመጣላቸው ሰብብ አድርገን መውሰድ ያለብን አይመስለኝም፡፡ ዋናው ግብ አከፋፋዮችን በይፋ በማውገዝ ለቀጣይ እርምጃ ማዘጋጀት ነው፡፡ እነዚህ አከፋፋዮችን ማጥፋት ደግሞ የግል ሚዲያ ዕትመቶች ወደ ህዝብ እንዳይቀርብ ማድረጊያ ወሳኝ መንገድ ተብሎ እየታሰበ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የዚህ ክስ ተጋሪ የሆኑት አቶ እውነቱ በለጠ የኮሚኒኬሽን ሚኒሰቴር ዴህታ ናቸው፡፡ የአቶ ሽመልስን አሳበ በመጋራት በዘጋቢ ፊልሙ ላይ ተመሳሳይ ሃሳብ አንፀባርቀዋል፡፡ ሰለዚህ የመንግሰት ኮሚኒከሽን ሚኒሰትር መሰሪያ ቤት የግል ሚዲያውን የሚያሽከረክሩት ዋናኛ ሞተሮች “አሻጥረኛ አከፋፋዮች ናቸው የሚል ስምምነት ላይ መድረሱን መረዳት ተገቢ ነው፡፡ ከዚያስ …… ወደፊት የምናየው ይሆናል፡፡
እነዚህ ከላይ የተቀሰኳቸው ሁለት የመንግሰት ተቋማት በግብ ከመስማማታቸው ውጭ የሚያቀርቡት ሃሳብ ግን ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለየቅል እንደሆነ አይረዱትም፡፡ በእነዚህ ሁለት የመንግሰት ተቋማት ውስጥ የግል ሚዲያውን በማጥፋት ዙሪያ ስምምነት አለ፤ ሁለቱም በየፈርጃቸው ግን ሊወስዱ ያሰቡት መንገድ የተለያየ እና የሚቃረን ነው፡፡ የብሮድካስት ባለስልጣን ዕትመቶቹ አይሸጡም፤ እነዚህ ሚዲያዎች በውጭ ሀይል ድጋፍና ዕርዳት ሀገር ለማፍረስ የሚሰሩት ይላል፡፡ የመንግሰት ኮምኒኬሽን መስሪያ ቤት ሃላፊዎች ደግሞ እነዚህ የግል ሚዲያዎች በከፍተኛ ደረጃ እንዲታተሙ እና እንዲሰራጩ የሚያደርጉት አከፋፋዮች ናቸው፡፡ የመንግሰት ልሳን እንዳይሽጥ በማድረግ ጭምር እያሉን ነው፡፡

አቶ ብርሃኑ አዴሎ “በፀረ ሽብር አዋጅ” ዝግጅት ወቅት የነበራች የሞቀ እና ሰሜት የተሞላበት ተሳትፎ ታይቶ ለዘጋቢ ፊልም መቅረባቸው አንዱ ቢሆንም የሀቃቢ ህጉን በዘጋቢ ፊልም ላይ ያደረጉትን ንቁ ተሳትፎ ወስደን ጉዳዮን ስናየው በቀጣይ ክሱ “የሽብርተኝነት” እንደሚሆን መጠርጠር ብቻ ሳይሆን መዘጋጀትም ይኖርብናል፡፡ እግረ መንገዳቸው ግን አማረልኝ ብለው ያነሱትን የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ቋሚ አምደኛ መሆን ትክክልም ተገቢም እንዳልሆነ ለማስረዳት የሄዱበት ርቀት ነው፡፡ ዝም ብሎ ለማስታወስ ያህል በአዲስ ነገር ጋዜጣ የኢህአዴግ አባል የሆነ ቋሚ አምደኛ ነበር፡፡ ይህ ጋዜጣ ግን በመንግሰት ጥርስ ተነክሶበት ከገበያ የወጣ፤ ምርጥ ልጆቹም የተሰደዱበት ነው፡፡ በአቶ ብርሃኑ አዴሎ አመክንዮ ከሄድን ኢህአዴግና አዲሰ ነገር ግንኙነት ነበራችው ልንል ነው? እኔ በምፅፍበጽ ፋክት መፅሄት ላይ አባል የሆኑኩበትን ፓርቲ እያብጠለጠሉ ይፅፋሉ፤ በግሌ የፖለቲካ አቋሜንም ሆነ ማህበራዊ ብሎም ኢኮኖሚያዊ ምልከታዬን አሰፍራለሁ አቶ ብርሃኑን ጨምሮ ብዙ እንባቢዎች እንዳሉኝ ከሚደርሰኝ መረጃ አውቃለሁ፡፡ ይህ እኔ አባል የሆኑኩበት ፓርቲና ሚዲያውን ምን ያገናኛቸዋል፡፡ አንድ እውነት ግን አለ፡፡ ይህውም የህዝብ ሚዲያዎች በኢህአዴግ ታግተው የአብዮታዊ ዲሞክራሲ እኩይ አስተሳሰብ ማረጋቢያ የሆኑ ሲሆን የተገፉት ደግሞ አማራጭ አሳቦችን ለማቅረብ አሁን የግል ሚዲያዎች ምቹ ናቸው፡፡ ለምሳሌ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ብዙ ሚሊዮን ተመልካች እንዳለው እናውቃለን፡፡ እድሉን ብናገኝ ከ20 ሺ ኮፒ በላይ በሳምንት ከማይታተሙ መፅሄቶች ይልቅ ኢቲቪን እንመርጥ ነበር፡፡ የተዘረፈው የህዝብ ሚዲያ ለህዝብ ጥቅም የሚውልበት ቀን እሰኪደርስ ግን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ እንጠቀማለን፡፡ ይህ ምርጫ ሳይሆን ተገደን የገባንበት ነው፡፡ የግሉ ሚዲያ ለጊዜው የተገፉትን መወከሉ ስህተት የለበትም፡፡ ይልቁንም ሊበረታት የሚገባው ነው፡፡

ኢህአዴግ የህዝብ ውሳኔ የማይቀበል ፓርቲ እንደሆነ ዋነኛ ማሳያ ሊሆን የሚችለው አሁን በግል ሚዲያዎች ላይ የያዘው አቋም ነው፡፡ ያለምንም ጥርጥር አሁን በገበያ ላይ ያሉት ዕትመቶች በገበያ ላይ እንዲኖር የኑሮ ሸክሙን አቻችሎ በውድ ጋዜጣና መፅሄት የሚገዛ ህዝብ ነው፡፡ ይህ ህዝብ ደግሞ ለግል ሚዲያው የድጋፍ ድምፅ እየሰጠ መሆኑን መረዳት አለብን፡፡ የማይፈልገውን መፅሄት በገንዘቡ ገዝቶ ቤቱ የሚገባ ጅል አይደለም፡፡ አንዳንዱ መፅሄት ሲገዛ ለታሪክ ጭምር የሚቀመጥ ብሎ ነው፡፡ ኢህአዴግ በዚህ ጉልበቱ ይህን የህዝብ ድምፅ ሊያሸንፍለት የሚችል ሚዲያ ሊያዘጋጅ አልቻለም፡፡ ስለዚህ አሁን የያዘው መንገድ እነዚህን የህዝብ ድምፆች ለማፈን የሚቻለውን ሁሉ ማድረግ ነው፡፡ እነዚህ የህዝብ ድምፆች ደግሞ እንዲታፈኑ የተፈለገው ከቀጣይ ሁለት ሺ ሁለት ምርጫ ጋር ተዳምሮ ካደረበት ስጋት የሚመነጭ ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ አሁን በቅርቡ የሚደረገው የደሞዝ ጭማሪ የግል ሚዲያዎችን ተገዢነት እንደሚጨምረው ይገመታል፡፡ ምክንያቱም ብዙ የመንግሰት ሰራተኞች ሊኖራቸው የሚፈልጉትን መፅሄት መግዛት ባለመቻላቸው በማንበብ ብቻ ተገድበው ነበር የሚል እምነት ስለአለኝ ነው፡፡
ቸር ይግጠመን

6000 አዳዲስ የደህንነት አባላት ስልጠና እየተሰጣቸው ነው።

July 30/2014
ለብአዴን አባላት እድሉ አልተሰጣቸውም።
ምንሊክ ሳልሳዊ
በቀጣዩ ጊዜያት የግንቦት ሰባት የተባለው የተቃዋሚ ቡድን በሃገር ውስጥ ሰርጎ በመግባት ከፍተኛ የሆነ የከተማ ውስጥ መስፋፋት ይፈጥራል ጥቃት ያካሂድብናል በሚል ስጋት መነሾ ጭንቀት ያደረበት የወያኔው ጁንታ ከመቀሌ እና ከደቡብ እንዲሁም የተወሰኑ ከኦሮሚያ ክልል የተወጣጡ 6000 አዳዲስ የደህንነት አባላት በአዋሳ በደብረዘይት እና በአዲስ አበባ ለሶስት ተከፍለው ስልተና እየተሰጣቸው መሆኑ ታውቋል።የኢሕአዴግ አንዱ ክፍል እንደሆነ ለሚትወቀው የብኣዴን አባላት እና ካድሬዎች በዚህ የደህንነት ስልጠን ላይ እንዲሳተፉ እድሉ አልተሰጣቸውም።

በቀጣይነት ግንቦት ሰባት እና ተባባሪዎቹ የሚወስዱት እርምጃ ስጋት የሆነበት ወያኔ የሚያሰለጥናቸውን የደህንነት አባላቱን በሃገር ውስጥ በሚገኙ የተመዘገቡ የተቃዋሚ ድርጅቶች መዋቅር ውስጥ እና በኢሕአዴግ የወረዳ መዋቅሮች ውስጥ በማቀናጀት እንደሚመድባቸው እና እንዲሁም በጎረቤት አገራት በድንበር ከተሞች እና በዋና ዋና ከተሞች እንደሚመደቡ የህብረተሰቡን እንቅስቃሴ እና የግንኙነት መረብ በማጥናት መረጃ በመሰብሰብ ሪፖርት እንደሚያደርጉ ታውቋል።

ከዚህ ቀደም በዚህ የደህንነት መዋቅር ስራ ላይ የተመደቡ የወያኔ አባላት ይህን ያህል የሚያረካ ውጤት እና መረጃ ካለማምጣታቸውም በላይ አሁን ከሚመደቡ ጋር በጋራ እንዲሰሩ እንደሚደረግ ታውቋል።

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የሕወሓት መንግስት በአንዳርጋቸው ላይ ላወጣው ቪዲዮ ምላሽ ሰጡ

July29/2014
የግንቦት 7 ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የሕወሓት መንግስት ከ3 ቀን በፊት በቲቪ በማሳየት ላቀረበው ቪድዮ ምላሽ ሰጡ። ቪድዮው የተዘጋጀው የሰውን አንገት ለማስደፋትና ለፕሮፓጋንዳ መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር ብርሃኑ በአቶ አንዳርጋቸው እጅ ምንም ዓይነት ምስጢሮች እንደሌሎ ተናግረዋል። አቶ አንዳርጋቸው ሰጥተውታል ለተባለው ፓስወርድም “የኦፕሬሽናል ጉዳዮችን የያዘ ፓስወርድ አይደለም፤” ያሉት ዶ/ር አንዳርጋቸው የሰጠው ፓስወርድ የተለያዩ ጥናቶችን የያዘ እንጂ ወያኔ ቢያገኘውም ባያገኘውም ምንም የሚጎዳ ነገር አይደለም ብለዋል። ዶ/ሩ ከጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ጋር በኢሳት ቲቪ የተነጋገሩበት ቪድዮ ይኸው።


Tuesday, July 29, 2014

41 አለማቀፍ ድርጅቶች የታሰሩት ጋዜጠኞችና ጦማርያን በአፋጣኝ እንዲፈቱ ጠየቁ

July 29/2014

የጸረ ሽብርተኝነት ህጉ ይሻሻል ብለዋል
ከዚህ በፊት በሽብርተኝነት የተፈረደባቸው እንዲፈቱ ጠይቀዋል
41 የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ የፕሬስ ነጻነት አቀንቃኞች፣ አለማቀፍና ክልላዊ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማትና የሙያ ማህበራት መንግስት በቅርቡ የሽብርተኝነት ክስ የመሰረተባቸውን ጋዜጠኞችና የዞን 9 ጦማርያን በአፋጣኝ እንዲፈታ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ከትናንት በስቲያ በላኩት ደብዳቤ መጠየቃቸውን ብሉምበርግ ኒውስ ዘገበ፡፡
ሂዩማን ራይትስ ዎች፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ አርቲክል 19 ምስራቅ አፍሪካ፣ ሲቪል ራይትስ ዲፌንደርስ፣ ወርልድ አሊያንስ ፎር ሲቲዝን ፓርቲሲፔሽን፣ ፔን አሜሪካና የመሳሰሉት አለማቀፍ ድርጅቶች በጋራ በጻፉት ደብዳቤ፣ መንግስት ጋዜጠኞችንና ጦማርያንን በሽብርተኝነት እየከሰሰ ለእስር መዳረጉን መቀጠሉ ያሳስበናል፣ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተገቢነት የሌለው በመሆኑ መገታት ይኖርበታል ብለዋል፡፡
ሶስቱ ጋዜጠኞችና ስድስቱ ጦማርያን ሶስት ወራት ለሚሆን ጊዜ ይህ ነው የሚባል ክስ ሳይመሰረትባቸው ያለአግባብ በእስር ላይ መቆየታቸውንና አንዳንዶቹም በምርመራ ወቅት እንግልት እንደደረሰባቸው መናገራቸውን የጠቀሰው ደብዳቤው፣ ይህም አግባብ አለመሆኑን ገልጿል፡፡
ጋዜጠኞቹና ጦማርያኑ በተመሰረተባቸው የሽብርተኝነት ክስ በረጅም አመታት እስር ብሎም በሞት ሊቀጡ እንደሚችሉ ስጋታቸውን የገለጹት ድርጅቶቹ፤ ይህም አለማቀፍ ህጎችን የሚጥስና በቀጠናው የተረጋጋ ሰላምና ደህንነት ለመፍጠር የሚደረገውን አለማቀፍ ጥረት ዋጋ የሚያሳጣ እርምጃ ይሆናል ብለዋል፡፡
መንግስት አግባብነት በሌለው የጸረ ሽብርተኝነት ህግ በቁጥጥር ውስጥ አውሎ ክስ የመሰረተባቸውን ጋዜጠኞችና ጦማርያን በአፋጣኝ ከእስር እንዲለቅ አስፈላጊውን ሁኔታ እንዲያመቻቹ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ጥያቄ ያቀረቡት እነዚህ ድርጅቶች፤ ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ በጸረ ሽብር ህጉ ተከሰው የተፈረደባቸው ዜጎች ጉዳይ አግባብ አለመሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሳይቀር እንዳመነበትና እንዳወገዘው አስታውሰዋል፡፡
ከጋዜጠኞቹና ከጦማርያኑ በተጨማሪም፣ ከዚህ በፊት በሽብርተኝነት ተከሰውና ተፈርዶባቸው ያለአግባብ በእስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በሙሉ መንግስት በአፋጣኝ እንዲፈታና የጸረ ሽብርተኝነት ህጉንም አለማቀፍ የሰብዓዊ መብቶች መስፈርቶችን በሚያሟላ መልኩ እንደገና አሻሽሎ እንዲያጸድቅ ጠይቀዋል፡፡ኢትዮጵያ የአለማቀፉ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ስምምነትና የአፍሪካን የሰብዓዊና የህዝብ መብቶች ኮንቬንሽን ፈርማ የተቀበለች ሃገር እንደመሆኗ፣  መንግስት አለማቀፍ ህጎች የጣሉበትን ግዴታ በማክበር መሰረታዊ መብቶቻቸው ተጥሰው ለእስር የተዳረጉ ዜጎችን በሙሉ ከእስር እንዲለቅ ጠይቀዋል፡፡
ደብዳቤውን የጻፉት ድርጅቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. Amnesty International 
2. ARTICLE 19 Eastern Africa 
3. Central Africa Human Rights Defenders Network (REDHAC), Central Africa 
4. CIVICUS: World Alliance for Citizen Participation 
5. Civil Rights Defenders, Sweden 
6. Coalition pour le Développement et la Réhabilitation Sociale (CODR UBUNTU), Burundi 
7. Committee to Protect Journalists 
8. Community Empowerment for Progress Organization (CEPO), South Sudan 
9. Conscience International (CI), The Gambia 
10. East and Horn of Africa Human Rights Defenders Project 
11. Egyptian Democratic Association, Egypt 
12. Electronic Frontier Foundation 
13. Ethiopian Human Rights Project (EHRP) 
14. Elma7rosa Network, Egypt  15. English PEN 
16. Freedom Now 
17. Front Line Defenders, Dublin  18. Human Rights Watch 
19. International Women’s Media Foundation (IWMF) 
20. Ligue des Droits de la personne dans la region des Grands Lacs (LDGL), Great Lakes 
21. Ligue Iteka, Burundi 
22. Maranatha Hope, Nigeria 
23. Media Legal Defence Initiative
24. National Civic Forum, Sudan 
25. National Coalition of Human Rights Defenders, Kenya 
26. Niger Delta Women’s movement for Peace and Development, Nigeria 
27. Nigeria Network of NGOs, Nigeria
28. Paradigm Initiative Nigeria, Nigeria
29. PEN American Center  30. PEN International
31. Réseau africain des journalistes sur la sécurité humaine et la paix (Rajosep), Togo
32. Sexual Minorities Uganda (SMUG), Uganda
33. South Sudan Human Rights Defenders Network (SSHRDN), South Sudan 
34. South Sudan Law Society, South Sudan
35. Tanzania Human Rights Defenders Coalition, Tanzania 
36. Twerwaneho Listeners Club (TLC), Uganda 
37. Union de Jeunes pour la Paix et le Développement, Burundi
38. WAN-IFRA (The World Association of Newspapers and News Publishers)
39. West African Human Rights Defenders Network (ROADDH/ WAHRDN), West Africa
40. Zambia Council for Social Development (ZCSD), Zambia
41. Zimbabwe Human Rights NGO Forum, Zimbabwe

“ዶ/ር ኢንጂነር” ሳሙኤል ዘሚካኤል ኬኒያ ላይ ተይዞ ወደ ሃገር ሊመለስ ነው ተባለ

July29/2014
eng samuel z
(ዘ-ሐበሻ) አነጋጋሪው ‘ዶ/ር ኢንጂነር ሳሙኤል ዘሚካኤል’ ኬንያ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሉን እና ወደሃገር ቤትም እንደሚመለስ ኢቶሚካሊንክ የተባለው የራድዮ ፕሮግራም ከአዲስ አበባ አስታወቀ።
በከተማው ውስጥ የማይገባውን የትምህርት ደረጃና ማዕረግ ጭኖ ሕዝብን ሲያታልል ነበር የተባለው ሳሙኤል ዘሚካኤል በመገናኛ ብዙሃን ድርጊቱ ከተጋለጠ በኋላ በርካታ ነጋዴዎች እና ግለሰቦች በዚህ ሰው ተጭበርብረናል በሚል ክስ መመስረታቸው የታወቀ ሲሆን በኢንተርፖል አማካኝነት ከኬንያ ወደ ኢትዮጵያ ተላልፎ እንደሚመጣ ይጠበቃል።
ራድዮው እንደዘገበው ዶ/ር ኢንጂነር ሳሙኤል ዘሚካኤል ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።

California Congressman demands the release of Andargachew Tsige

July29/2014
Press Release
WASHINGTON – Rep. Dana Rohrabacher on Monday urged Ethiopia’s prime minister to release Andargachew Tsige, a native-born opposition leader with British citizenship who last month was extradicted to the African nation from Yemen under questionable circumstances.
In a letter to Prime Minister Hailemarian Desalegn, the California Republican wrote: “Mr. Andargachew is a British citizen and a leader for political reform in Ethiopia. He should be released and allowed to return to his family immediately. Any maltreatment or harm to him, or other prodemocracy activists, in your country only serves to widen the gap between our two countries.”
Andargachew was traveling from Dubai to Eritrea on June 23 when, stopping over in Yemen, he was forcibly flown back to Ethiopia, which he fled in 2005 following protests of the nation’s elections. He was granted asylum in Britain, where his wife currently lives. British officials have expressed concerns that his extradition was not properly handled.
The activist was charged with terrorism and sentenced to death in absentia. In his letter to the Ethiopian prime minister, Rohrabacher added concerns from the United States. His letter follows:
July 28, 2014
His Excellency Hailemariam Desalegn
Prime Minister
Federal Democratic Republic of Ethiopia
Office of the Prime Minister
P.O. Box 1031
Addis Ababa, Ethiopia
Dear Mr. Prime Minister,
According to recent news reports, late last month the Ethiopian government arranged for the international kidnapping of opposition leader Andargachew Tsige and his forcible return to your country.
Mr. Andargachew is a British citizen and a leader for political reform in Ethiopia. He should be released and allowed to return to his family immediately. Any maltreatment or harm to him, or other pro-democracy activists, in your country only serves to widen the gap between our two countries.
All legitimate national governments have a responsibility to respect the human rights of their citizens. The current rulers of Ethiopia only continue to isolate themselves by violating the human rights of Ethiopian citizens, especially democratic political leaders. Mr. Andargachew should be released without delay and allowed to return home.
Sincerely,
Dana Rohrabacher
Chairman
Subcommittee on Europe, Eurasia, and Emerging Threats
House Committee on Foreign Affairs

Hailemariam Desalegn got “F” for Communication

July 29, 2014
by Abebe Gellaw
A couple of weeks ago, I wrote a critical commentary on the incompetence of the accidental Prime Minister of Ethiopia. However, some apologists of the tyrannical TPLF regime shouted that my commentary on Puppet Hailemariam Desalegn (PHD) was an unsubstantiated attack against the ceremonial PM.
As a follow-up, Addis Voice has produced a well-substantiated parody that exposes PHD’s incompetence and confusion in collaboration with American language and communications expert, J Davidson. Mr. Davidson has analysed publicly available speeches of PHD, the frequent errors he makes and the messages he tries hard to convey to the world in English.
“After considering a number of criteria, I have to give him a big F in communication skills,” he said.
It is very evident that the TPLF regime is facing deep leadership crisis. After PHD, the regime remains leaderless. Puppet Hailemariam Desalegn (PHD) is only following the orders of his dozens of TPLF bosses rather than leading the pack.
Despite being propped up by three deputy Prime Ministers and a dozen of “advisers” like Bereket Simon and Abay Tsehaye that pull the strings of control on him behind the scene, PHD is still fragile and weak. His incompetence, shallowness, opportunism and confusion is too evident to miss whenever he appears in public.
There is a big difference between a puppet and a leader. Unlike puppets, leaders are not made. Because leadership requires exceptionally inherent qualities, it is said that leaders are rather born, not made. Real leaders that can command respect and admiration have exceptional communication prowess. As the American author and presidential speechwriter said: “The art of communication is the language of leadership.”
“If I were him, I would certainly use an interpreter. He certainly has no command of the English language, which is obviously an international language. Instead of expressing himself clearly, he is miscommunicating with the world,” he said.
Addis Voice invite you to watch the video and judge for yourself. Ethiopia is being led by incompetent demagogues under the leadership of a clueless puppet. The TPLF regime is a total joke.

Monday, July 28, 2014

ኢቲቪ ለሁለተኛ ጊዜ አቶ አንዳርጋቸውን ያቀረበበት ቪድዮ ዓላማው እና ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚሰጠው ትርጉም

July28/2014
የጉዳያችን ማስታወሻ
ኢቲቪ ከአለቆቹ ተዘጋጅቶ የቀረበለትን ቪድዮ ለሁለተኛ ጊዜ አሳይቷል።ፊልሙ ከ አስራ አምስት ጊዜ በላይ ከመቆራረጡ በላይ ባጠቃላይ አንዳችም የተለየ መረጃ ስርዓቱ አለማግኘቱን በትክክል ያሳያል።የተጠቀሱት ስሞች በሙሉ ዓለም ዓቀፍ ሚድያውም የሚያውቃቸው ግለሰቦችን ነው።ከእዚሁ ጋር ተያይዞ ግን ፊልሙ ሲጀምር  ከአቶ አንዳርጋቸው ድምፅ ጀርባ በግርፋት ላይ ያለ ሰው የሲቃ ድምፅ በዕርቀት ይሰማ ነበር።ይህ ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ ድርጅቶችም ሆነ በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን እንደ ማስረጃ አድርገው ለዓለም አቀፉ ሕብረተሰብ ማሳየት የሚችሉበት ማስረጃ ነው።ለምሳሌ ድምፁን ለብቻው መለየት እና በዓለም አቀፍ ሚድያዎች እንዲሰማ ማድረግን ይጨምራል።አሁን ወደ ሁለቱ ነጥቦች ልመለስ የቪድዮው ዓላማ እና ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚሰጠው ትርጉም -

1/ የቪድዮው ዓላማ

የቪድዮው ዓላማ ሁለት ናቸው -
ሀ/ የኢህአዲግ/ወያኔ ደጋፊዎችን ለማፅናናት
የመጀመርያው አላማ የኢህአዲግ/ወያኔ ደጋፊዎችን ለማፅናናት ነው።ይህ ማለት ለኢህአዲግ/ወያኔ ደጋፊዎች መረጃ እያገኘን ነው ብሎ ባላገኙት መረጃ ለማፅናናት ነው።በተለይ ለየመን መንግስት የተከፈለው በሚልዮን የሚቆጠር ዶላር ጉዳይ እራሱ በኢህአዲግ/ወያኔ ባለስልጣናት መካከልም መተማመን አልፈጠረም።ከኢህአዲግ/ወያኔ ባለስልጣናት መካከል ማን ማን ነው? የሚለው ጥያቄ ውጅንብር እርስ በርስ ፈጥሯል።ለምሳሌ የኮምፕዩተር ፓስ ዎርድ ለኢትዮጵያ ሕዝብ a b c d  ብሎ የመጥቀስ ጉዳይ በየትኛውም ዓለም ተሰምቶ የማይታወቅ ግን መረጃ ሳያገኙ ''አገኘን'' ብሎ ለማሳመን ''እናቴ ትሙት አግኝቻለሁ እመኑኝ'' ብሎ ደጋፊዎችን ለማሳመን የተሞከረ ሙከራ ነው።ይህኛው ዓላማ ሙሉ በሙሉ አልተሳካም።

ለ/ ሕዝቡን ''እባካችሁ ወደ ትጥቅ ትግል አትግቡ'' ለማለት
ሁለተኛው አላማ ሕዝቡን ለማስፈራራት ነው።አቶ አንዳርጋቸው ከተያዙ ወዲህ የኢትዮጵያ ህዝብ ለትግል መነሳሳት ከፍተኛ መሆን ለኢህአዲግ/ወያኔ ትልቅ ስጋት መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው።ይህንን ለመግታት ደግሞ የተለያየ ስነ-ልቦናዊ ጦርነት ለማድረግ የሚረዳው አቶ አንዳርጋቸው የትጥቅ ትግል 'አድካሚ' መሆኑን ሲናገሩ ማሳየት ነው።እዚህ ላይ ኢህአዲግ/ወያኔ ያልተረዳው ነገር ግን ይህ ጉዳይ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አዲስ ነገር አለመሆኑን እና ቀድሞ የሚያውቀው መሆኑን ነው።አዎን!የትጥቅ ትግል አድካሚ ነው።አቶ አንዳርጋቸውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ''ጀግና'' ብሎ ያወደሰበት አንዱ አግባብ እራሱ እኮ ከባዱን የትጥቅ ትግል ከሰላሳ ዓመት የአውሮፓ ኑሮ በኃላም ለሀገራቸው መስዋዕት ለመክፈል መነሳታቸው ነው።ይህ ማለት ኢቲቪ አቶ አንዳርጋቸው ሲናገሩ ባያሳይም ህዝቡ ቀድሞ ያውቀዋል።እናም የፊልሙ ዓላማ እዚህም ላይ ሙሉ በሙሉ አልተሳካም።

2/ ቪድዮው ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚሰጠው ትርጉም 

ኢህአዲግ/ወያኔ  ትልቁ ክሽፈቱ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከሃያ ሶስት ዓመት በኃላም አለማወቁ ነው።ለእዚህም ጉልህ ማሳያ የሚሆነን ኢቲቪ የህዝቡን ስነ-ልቦና አገኘሁ ብሎ የሚሰራው ፕሮፓጋንዳ እና ኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚያሳድረው ተፅኖ ግን በተቃራኒው የበለጠ የስርዓቱን ደካማነት መሆኑን ስንመለከት ነው።በእዚህ ቪድዮ ላይም ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚሰጠው ትርጉም ኢህአዲግ/ወያኔ ካሰበው ተቃራኒ መሆኑን በሚከተሉት ሶስት ነጥቦች ማየት እንችላለን።ቪድዮው ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚሰጠው ትርጉም -
ሀ/ ግንቦት 7 ጠንካራ ድርጅት መሆኑን
ፊልሙ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያሳየው አንዱ ነገር ግንቦት 7 አደረጃጀቱም ሆነ የሰው ኃይሉን ጥንካሬ ነው።ለእዚህም ማስረጃው አቶ አንዳርጋቸው ከጠቀሱት ውስጥ ድርጅቱ  በመረጃ ቴክኖሎጂ (አይ ቴ)ሙያ የተቀላቀሉት ግለሰቦች በ ፒ ኤች ዲ ደረጃ መሆናቸውን ነው።በመረጃ ቴክኖሎጂ ፒ ኤች ዲ ደረጃ የደረሱ ባለሙያዎች ምን ያህል ጥራት ያላቸው ባለሙያዎች መሆናቸውን በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች የሚመሰክሩት ይህንኑ ነው።የኢትዮጵያ ህዝብም የሚረዳው ከእዚህ የተለየ አይደለም።ህዝቡ ''ለካ ኢህአዲግ/ወያኔ በመረጃው ዘርፍም ተበልጠሻል'' የሚል ሃሳብ ብልጭ ሲልበት አስተውሉ።

ለ/ በሀገር ውስጥም እራሱን አደራጅቶ ስርዓቱን መዋጋት እንደሚችል
በቪድዮው ላይ ህዝቡ እራሱን በሕቡ ማደራጀቱ ከአቶ አንዳርጋቸው አንደበት ተቆራርጦም ቢሆን መስማቱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ በሀገር ውስጥ በሕቡም የመደራጀት አስፈላጊነትን አመላክቷል።ነፃነት የሚፈልግ ሕዝብ ነፃነት ስለማጣቱ ማንም ሊነግረው አይችልም።ላለፉት 40 ዓመታት ኢትዮጵያ ያለፈችበት የፖለቲካ ታሪክ የሚያሳየን ይህንን ነው።በሕቡ መደራጀት ኢህአዲግ/ወያኔም እራሱ የኖረበት ነው።ይህንን የኢትዮጵያ ሕዝብ ያውቀዋል።ዛሬ ግን  ኢቲቪ ለሕዝቡ በአቶ አንዳርጋቸው አማካይነት በማሳሰቡ ጥሩ አጋጣሚ ነው።

ሐ/ ''አሸባሪ'' የሚለው የወል ስም ለኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ መሰጠቱን
ሕዝብ እኮ አስተዋይ ነው።በደንብ ይመለከታል፣ያጤናል በመጨረሻም ፍርዱን ይሰጣል።እስካሁን ኢቲቪ እና ጌቶቹ ''አሸባሪ'' ሲሉ የተሰሙት በትጥቅ ትግል የሚዋጉትን ብቻ አይደለም።ጋዜጠኞችን፣ደራስያንን፣የሃይማኖት ሰዎችን፣ብሎገሮችን፣ተማሪዎችን፣መምህራንን፣ገበሬዎችን እና የከተማ ሰላማዊ ነዋሪዎችን ሁሉ ነው።የኢትዮጵያ ሕዝብ ደግሞ ከእነኝህ ሁሉ ውጭ አይደለም።ይህ ማለት በኢህአዲግ አስተሳሰብ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ ''አሸባሪ'' ተብሎ ተፈረጀ ማለት ነው።ስለዚህ አቶ አንዳርጋቸውን እና ዓላማቸውን ሕዝብ የበለጠ እየወደደው፣እያከበረው እና እየተቀላቀለው ይመጣል።በመሆኑም የፊልሙ ዓላማ ሙሉ በሙሉ ከሽፏል።ህዝቡ ኢህአዲግ/ወያኔን ''አሸባሪ'' የሚለው እራሱ ነፃነት ያጣውን ሕዝብ በሙሉ መሆኑ የታወቀ ነው።ሕዝብ በሙሉ ''አሸባሪ'' ሲባል ደግሞ ያለው አማራጭ አንድ ነው።ነፃነቱን ከአሸባሪ መንግስት መንጭቆ መውሰድ።ይህ የማይቀር መጪው ክስተት ነው።

በመጨረሻም አንዲት ነገር ሳላነሳ አላልፍም በእዚሁ ፊልም ላይ አቶ አንዳርጋቸው ከተናገሩት ለኢህአዲግ/ወያኔ ያልገባው ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ያስተዋለው ጉዳይ።አቶ አንዳርጋቸው  ዶ/ር ታደሰን ዛሬም ወያኔዎች ፊት ''ታዴ!'' ነው ያሏቸው።ይህ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያሳየው ነገር አለ።የዓላማ ፅናታቸው በጊዜ እና በቦታ አለመወሰኑን።

ጉዳያችን
ሐምሌ 21/2006 ዓም (ጁላይ 28/2014)

ፖሊቲካና የግለሰብ ጠባይ (ፕ/ር መስፍንወ/ማርያም)

July 28, 2014

ለእኔ ፖሊቲካና የግለሰብ ጠባይ እንደውሃና ዘይት የማይደባለቁ ነገሮች ይመስሉኛል፤ አጼ ምኒልክ ‹‹አመልህን በጉያህ›› ያሉት ለዚህ ሳይሆን አይቀርም፤ ዘይትና ውሀ በባሕርያቸው የሚለዩትን ያህል ፖሊቲካና ግለሰብም የባሕርይ ልዩነት አላቸው ማለት ነው፤ የወያኔ መሪዎች ምንም ነገር የማይሰምርላቸው፣ ከመጀመሪያውኑ እነዚህን ሁለት የማይደባለቁ ባሕርዮች አደባልቀው በመንሣታቸው ነው፤ ፖሊቲካ ለማኅበረሰቡ መቆርቆር ነው፤ ለሕዝቡ መቆርቆር ነው፤ ለአገር መቆርቆር ነው፤ የፖሊቲካ መነሻም ይኸው መሆን አለበት፤ ዓላማውም የማኅበረሰቡ፣ የሕዝቡ ልማት እንጂ ጥፋት አይደለም፤ የነበረውንና ያለውን ማጥፋት የፖሊቲካ ዓላማ ሊሆን አይችልም።

የደርግ መንደር ምሥረታ የሕዝብ ዓላማ ነበረው፤ የዓላማው መሣሪያ ግን የሕዝብ ሳይሆን ወታደራዊ ጉልበት ነበር፤ በዚህም ምክንያት የሕዝብ ዓላማ ያለው ሥራ የሕዝብን ህልውና በሚፈታተን የጉልበት መንገድ መከተሉ ዓላማው እንዳይሳካ፣ ሕዝብና አገዛዙ ባላንጣዎች ሆኑ፤ ጥሩው ዓላማ በከሸፈ ጉልበተኛነት ሳይሳካ ቀረ፤ በመንደር ምሥረታው ዓላማ ደርግ ክፋት ወይም ቂም ቋጥሮ አልተነሣም፤ ስሕተቱ ከውትድርና ባሕርይ የመጣ ይመስለኛል::

 ማጥፋት ዓላማ ሲሆንና ጉልበት የማጥፋት መሣሪያ ሲሆን ፍጹም የተለየ ነው፤ማጥፋት የሚመጣው ከግል ጠብና ከግል ቂም ነው፤ የራሱን ወይም የአባቱን፣ ወይም የእናቱን ቂም በልቡ ቋጥሮ ፖሊቲካ ውስጥ የሚገባ ሰው ለጥፋት የተዘጋጀ ነው፤ ለጥፋት የተዘጋጀ ሰው ፖሊቲካ ውስጥ ሲገባ እሳት አደጋ መኪና ላይ ቆሞ ቤት እንደሚያቃጥል ሰው ነው፤ አታላይ ነው፤ ዓላማውንም የዓላማውንም መሣሪያ አያውቅም፤ የሚንቀሳቀሰው በጥላቻና በቂም ነው፤ ወይ የሕጻን ልጅ ወይም የተስፋ-ቢስ ደደብ ጠባይ ነው፤ እንዲህ ያለ ሰው ፖሊቲካ ውስጥ የሚገባውም በዚሁ በደደብነቱ ምክንያት ነው፤ የደደቡ ፖሊቲከኛ ሥራ የማያስወቅሰው ፖሊቲከኛውን ብቻ አይደለም፤ በዚያ ፖሊቲከኛ የሚመራው ሰው ሁሉ አብሮ የሚወቀስ ነው፤ እንዲያውም በፖሊቲከኛው እውቀትና ችሎታ ማጣት የተነሣ የሚደርሰው ስቃዩና መከራው፣ ችግሩና አበሳው በዚህ ዓይነቱ ፖሊቲከኛ ላይ አይደርስም፤ ሰቃዩንና መከራውን፣ ችጋሩንና አበሳውን የሚጋፈጠው በዚህ ዓይነቱ ፖሊቲከኛ የሚመራው ሕዝብ ነው፤ ሕዝብ መሪውን በትክክል መምረጥ ያለበትም ለዚህ ነው፤ ተንጋሎ የተፋ ለራሱ ከፋ የሚባለው ይደርሳል።

 ዛሬ እያጎረሰ ምረጠኝ የሚለው ነገ ቆዳህን ልግፈፍ ይላል፤ እንደምንሰማው ወደቦሌ አካባቢ ‹መቀሌ› የሚባል የሰማይ-ጠቀስ ፎቆች መንደር አለ ይባላል፤ የዚህ መንደር ባለቤቶች የወያኔ ባለሥልጣኖች ለመጦሪያቸው የሠሩአቸው ናቸው ይባላል! በአንጻሩ እኔ የማውቀው አንድ ወያኔ አለ፤ በውጊያ ላይ በደረሰበት ጉዳት ይመስለኛል አንድ ዓይኑን ክፉኛ የታመመ ነው፤ ስለሚሸፍነው የጉዳቱን መጠን ባላውቅም ጉዳቱ ይሰማኛል፤ ሚስትና ሁለት ልጆች አሉት፤ ሚስቱ ጠዋት በጀርባዋ ከባድ ነገር አዝላ ልጆቿን ወደተማሪ ቤት ታደርሳለች፤ እንደምገምተው አንድ ቦታ ገበያ ዘርግታ የምትሸጠውን ትሸጣለች፤ ወደማታም እንደጠዋቱ ተጭና ወደቤትዋ ከልጆችዋ ጋር ትመለሳለች፤ የዚህ አንድ ጉዳተኛ ወያኔ ቤተሰብና የባለሰማይ-ጠቀስ ሕንጻ ባለቤቶች የሆኑት ወያኔዎች ኑሮ የሰማይና የመሬት ያህል የተራራቀ ነው፤ ለአንድ ዓላማ አብረው የተነሡ ሰዎች በሃያ ዓመታት ውስጥ ይህንን ያህል መራራቃቸው በጣም ያሳዝናል ብሎ ማለፉ አይበቃም፤ ደሀው ወያኔ ሕመሙንና ስቃዩን የምገነዘብበት መንገድ ባይኖረኝም አንድ ዓይኑን ማጣቱ ብቻ ጉዳቱን ያሳየኛል፤ እንግዲህ ባለሰማይ-ጠቀስ ወያኔዎችና ይህ ደሀ ወያኔ በጦርነት ላይ ያደረጉት አስተዋጽኦ በጉዳታቸው ቢመዘን የዚህ ደሀ ወያኔ እንደሚበልጥ አልጠራጠርም፤ ቢያንስ እንደአንዳንድ መሪዎቹ አልሸሸም፤ ታዲያ በምን ተበላልጠው እነሱ እዚያ ላይ እሱ እዚያ ታች ሆኑ? ይህንን አሳዛኝና አገርንና ሕዝብን የሚጎዳ ሁነት የሚያመጣው እሳት አደጋ መኪና ላይ ቆሞ ቤት እንደሚያቃጥለው ሰው ያሉ ፖሊቲከኞች-ነን-ባዮች የተዛባ ሚዛን ነው፤ በዚህ የተዛባ ሚዛን በየጦር ሜዳው አሞራ የበላቸው የታደሉ ናቸው፤ ተስፋቸው ትርጉም አጥቶ ሳያዩ፣ ውርደት ሳይሰማቸው፣ ችግርንና ግፍን ሳይቀምሱ ቀርተዋል፤ ለነገሩ ነው አንጂ እንኳን ወያኔ በሥልጣን ምኞት ከወገኑ ጋር የተዋጋውና ከኢጣልያ ወራሪ ጦር ጋርም የተዋጉት አርበኞችም ተመሳሳይ ዕድል ገጥሟቸው ነበር፤ ዛሬ ኢትዮጵያን ለክፉ ነገር የዳረጋት የእነዚህ ሰዎች ጡር ይመስለኛል።

የፖሊቲካ ተግባሮቻቸውን ከግል ጠባዮቻቸው እየለዩ የሚኖሩ ፖሊቲከኞች በአንዳንድ አገር አሉ ለማለት ይቻላል፤ ከአውሮፓ ስዊድንና ኖርዌይ፣ ስዊትዘርላንድ፣ ከእስያ ዛሬን እንጃ እንጂ በነኔህሩ ዘመን ህንድ የሚጠቀስ ነበር፤ በአብዛኞቹ አገሮች ግን ፖሊቲከኞቹ እንደየደረጃቸው ለሀምሳ፣ ለሠላሳ፣ ለሀያ፣ ለአሥር ሰዎች የሚበቃ የተሟላ ቤት ውስጥ አምስት መቶ ሰዎችን የሚያስተዳድር ደመወዝ እያገኙ የሚኖሩ ሲሆኑ ምግባቸው ግን አብዛኛውን ጊዜ የአንድ ሰው ይመስለኛል፤ የዚህ ትርጉሙ ምንድን ነው? ለፖሊቲከኞቹ መቀማጠል በላባቸው የሚከፍሉት ደሀዎች ናቸው፤ ከተፎካካሪዎቻቸው ተንኮል የሚጠብቋቸው ደሀዎች ወታደሮች ናቸው፤ ምርጫ ሲደርስ በነቂስ ወጥተው ፖሊቲከኞቹን የሚመርጧቸው ጦማቸውን የሚያድሩት ደሀዎች ናቸው፤ እነዚህም ጊዜያዊና ትንሽ የግል ጥቅምን ከዘላቂው የአገርና የሕዝብ ጥቅም መለየት ያልቻሉ የሕዝብ ክፍሎች ከተበላሹት ግለኛ ፖሊቲከኞች የማይለዩ ናቸው።

ወደፍሬ ነገሩ ልምጣና፤- በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ፖሊቲከኞች የሚወጡትና የሚወርዱት ለየትኛው ዓላማ ነው?

1. የበትረ መንግሥቱን ሥልጣን ከወያኔ ፈልቅቆ ለማውጣትና ለመያዝ?
2. በምክር ቤት ገብቶ የወያኔ አጫፋሪ በመሆን ደህና ደመወዝና ነጻ ቤት ለማግኘት?
3. ከውስጥ ሆኖ ወያኔን ለማጋለጥ?

የኢትዮጵያ ሕዝብ የፖሊቲካ ቡድኖችን ሲደግፍ የፖሊቲካ ቡድኖቹን ዓላማዎች አጣርቶ በማወቅ መሆን አለበት፤ አለዚያ በሎሌነት እየኖሩ ጌታ መለወጥ ነው።

ኦሮሞ እና እስልምና በ“ሕዳሴ አብዮት” መስመር (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ)

July28/2014

በወርሃ-ግንቦት ላይ ለዘመናት የተንሰራፋውን ሀገራዊ ደዌ ይፈውሳል ብዬ ተስፋ ስለማደርግበት “የሕዳሴ አብዮት” በሶስት ተከታታይ ክፍሎች ለመዳሰስ መሞከሬ ይታወሳል፡፡ በወቅቱ መጪው የ “ሕዳሴ አብዮታችን” መፍትሔ ሊሰጥባቸው ከሚገቡ ጉዳዮች መሀል በዋነኝነት የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪው ማሕበረሰብ እና የእስልምና እምነት ተከታዮች የመብት ጥያቄን በተመለከተ በጥቅሉ ጠቃቅሼው አልፌ ነበር፡፡ ሆኖም ‘ሰፋ ብሎ ቢዳሰስ’ የሚሉ በተለያየ መንገድ የሚቀርቡ ጎትጓች ድምፆች መበራከታቸው የመነሻ ሃሳቡን ፈታ አድርጌ እንዳቀርብ አስገድዶኛል፤ እንግዲህ ይህ ጭብጥም የዛው ተከታይ መሆኑ ይሰመርልኝ፡፡

የኦሮሞ ጥያቄ'

በኢትዮጵያችን ከሚገኙ በርካታ ብሔሮች መካከል አብላጫውን ቁጥር የሚይዘው ኦሮምኛ ተናጋሪው ቢሆንም፣ ለዘመናት ይደርሱበት ከነበሩ ሥርዓታዊ በደሎች እና የባሕል ጭፍለቃዎች ዛሬም በምልአት ነፃ እንዳልወጣ በቂ ማሳያዎች አሉ፡፡ በ1960ዎቹ አጋማሽ የአገሪቷ አደባባዮች የዘመኑን መንፈስ በተረዱ ቁጡ ወጣቶች መጥለቅለቁን ተከትሎ፣ ‹በንጉሣዊው አገዛዝ ግብዓተ-መሬት ላይ የመጨረሻዋን ድንጋይ ለማስቀመጥ› በሚል ሰበብ ቤተ-መንግስቱን መቆጣጠር የቻለው ወታደራዊው ደርግ፣ ህልቆ መሳፍርት በሌለው መስዋዕትነት የተገኘውን ወርቃማ ዕድል ከጅማሮው አጨናፍጎታል፡፡ በግልባጩ አብዮቱን ካጋሙት ገፊ-ምክንያቶች ዋንኞቹ ለሆኑት የብሔርና የሕዝባዊ መንግስት ምስረታ ጥያቄዎች፣ መፍትሄ ይስጥ አይስጥ እስኪረጋገጥ ድረስ መታገስ ያልፈለገው ህወሓት፣ ጉዳዩ በደም መፋሰስ ብቻ እንደሚፈታ አውጆ ጫካ ሲገባ አዲሱ መንግስት ገና የ6 ወር ጨቅላ እንደነበረ አይዘነጋም፡፡ ይሁንና ታሪክ በአስከፊ መልኩ ራሱን ሲደግም ያስተዋልነው ወታደራዊውን መንግስት መንፈቅ-ዓመት ያህል እንኳ መታገስ ያልፈቀደው ይህ ቡድን፣ ለጥያቄዎቹ መልስ ሳይሰጥ ከሁለት አስርታት በላይ ያለመንግራገጭ በሥልጣን ለመቆየት ባለመቸገሩ ነው፤ ርግጥ የእኔ ትውልድም የእድሜውን እኩሌታ በትግስት መጠበቁ የአደባባይ እውነታ ቢሆንም፣ ተጨማሪ የቻይነት ዓመታት ይኖራሉ ብዬ ግን አላስብም፤ አብዮቱን ምኩንያዊ የሚያደርገውም ይህ ነው፡፡

…እነሆም ከአራት አስርታት በላይ ሲንከባለሉ የቆዩት የኦሮሞ ጥያቄዎች በ“ሕዳሴ አብዮት” ይፈቱ ዘንዳ፣ ሊተኩርባቸው የሚገቡ አንኳር አጀንዳዎችን በሁለት አውድ ከፍለን እንመለከታለን፡፡


ኢህአዴግ-መራሹ መንግስት ጥያቄዎቹን ከወረቀት ድንጋጌ (ከአፋዊነት) እና ከፕሮፓጋንዳ ሽንገላ ባለፈ፣ እውነተኛ መፍትሔ በሚያስገኝ መልኩ እልባት ሊያበጅላቸው አልፈቀደም፤ ባለፉት ሃያ ሶስት ዓመታት ‹‹አነበርኩት›› የሚለው ቋንቋ ተኮር ፌዴራሊዝም የይስሙላ ስለመሆኑ ለመገንዘብ፣ ዛሬም ከደርዝን በላይ የፖለቲካ ድርጅቶች የራስ አስተዳደር ጥያቄን አንግበው በትግል መድረክ መገኘታቸውን ማየቱ በቂ ነው፡፡ የክልሉ ‹‹ገዥ›› እንደሆነ የሚነገርለት ኦህዴድም ቢሆን፣ የህወሓቱ የአማርኛ ክንፍ እንደሆነው ብአዴን ሁሉ፣ የኦሮምኛ ክንፍ ከመሆን አለማለፉን፣ የብሔሩ ልሂቃንን ጨምሮ የፌደራል ሥርዓቱን አወቃቀር ያጠኑ በርካታ ምሁራን ማስረጃ እያጣቀሱ ያጋለጡት እውነታ ነው፡፡ ሕዝቡም በየጊዜውና በየአጋጣሚው የሚያነሳው ጥያቄ አሁንም ተግ አለማለቱ የልሂቃኑ ማስረጃ መሬት መርገጡን ያስረዳል፡፡ በቅርቡ አፈ-ጉባኤ አባዱላ ገመዳ ስለሕጋዊነቱ በድፍረት የደሰኮረለት የማስተር ፕላኑ ጥያቄ በኃይል መጨፍለቅም በገዥው በኩል ሕገ-መንግስቱ አፈር ለብሶ እንዳበቃለት ተናግሮ አልፏል፡፡በተጓዳኝ የክልሉ ነዋሪ በተፈጥሮ ሀብቱ ተጠቃሚ እንዳይሆንና ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዳይኖር ከመደረጉ ባሻገር፤ ከሕዝቡ ቁጥር ብዛት አኳያ ኦሮምኛ በሁለተኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋነት እንዲያገለግል ኦህዴድ ተፅእኖ የሚፈጥር አልሆነም፤ ሌላው ቀርቶ ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ ያነሱ ፖለቲከኞች ‹‹ኦነግ›› ተብለው የምድር ፍዳቸውን ሲቀበሉ የታደጋቸው የለም፡፡ የዚህ እኩይ ድርጊት ተጠያቂም ጉልበተኛው ህወሓት ብቻ ነው ማለት ገራገርነት ይመስለኛል፤ የገዛ ወገኑን አሳልፎ የሰጠው ኦህዴድም ጭምር የድርሻውን መውሰዱ አይቀሬ ነውና፡፡ ይህም ሆኖ ከአንዳንድ ምልክቶች በመነሳት ጥያቄዎቹ መልስ እስካላገኙ ድረስ፣ የቱንም ያህል የእስር ቤት ደጃፎች ከዚህም በላይ ቢጨናነቁ፣ የቱንም ያህል የእስረኞቹ ሰቆቃ እያደር ቢበረታ ከእንግዲህ በኦሮሚያ ምድር በፍርሃት ዝም-ጭጭ ብሎ የሚተኛ ሊኖር እንደማይችል ዛሬ ላይ ቆሞ መናገሩ ‹‹ሟርተኛ›› አያስብልም፡፡


የኦሮምኛ ተናጋሪውን ያደረ ቅራኔ በመፍታት የአንድነት ዘብ ለማድረግ፣ የሀገሪቱ ታሪክ እና ባሕል በዳግም ብያኔ መታደሱ ግድ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ የክልሉ ማሕበረሰብ በዘመናዊው መንግስት ምስረታም ሆነ ከባእድ ወረራ መታደጉ ላይ ታላቅ አበርክቶ ቢኖረውም፣ በሀገሪቷ ታሪክ ውስጥ ሚናው ደብዝዞ መገለፁ ጎምዛዛ እውነት ነው፤ የቋንቋው ተናጋሪ ያልሆነው አብዛኛው ኢትዮጵያዊም ይህንን አምኖ ሊያርመው ቀርቶ፣ እውቅና ሊሰጠው እንኳ አለመፍቀዱ፣ ጉዳዩን ወደሰሞነኛው ‹‹ውጡ ከሀገራችን›› አይነቱ አስደንጋጭ ኩነት ገፍቶታል፡፡ ከዚህ በተቃራኒው በጥቂት የብሔሩ ልሂቃን የሚንፀባረቀው (ሀገርን ለፍርሰት ሊያጋልጥ የሚችለው) ሸውራራ የታሪክ አረዳድን እና የቅኝ አገዛዝ ትርክትን ማጥራት ሌላው ወሳኝ የቤት ሥራ ሆኗል፤ ምክንያቱም ከጥያቄው ጋር ተያይዘው የሚነሱ የተቃውሞ ድምፆች ማጠንጠኛ ‹ባሳለፍነው መቶ ዓመት ለቅኝ አገዛዝ ተዳርገናል፣ ሥርዓታዊ በሆነ መዋቅር የሥልጣን ባይተዋር ሆነን ቆይተናል፣ ከሌላው ሕዝብም በተለየ መልኩ ከሰብአዊ ፍጡር በታች ተቆጠረን ተረግጠናል…› የሚል መንፈስ እንዲይዝ እየተለጠጠ ነው፡፡ ይህ የታሪክ ትንተና ስሁት መሆኑን የምንረዳው በየትኛውም መንግስታዊ ሥልጣን ጊዜ (ሀገሪቱ በጦር መሪዎችም ሆነ በነገሥታቱ ጠንካራ መዳፍ ስር በተያዘችበት ዘመን) በግንባር ቀደምትነት በመንበሩ ላይ ይፈራረቁ ከነበሩት አማርኛና ትግርኛ ተናጋሪዎች የማይተናነስ እኩል ሚና እንደነበራቸው የቋንቋው ተናጋሪ ምሁራን በማስረጃ አስደግፈው ባዘጋጇቸው ድርሳኖቻቸው ያተቱትን ስናስተውል ነው፡፡

ለማሳያም ‹‹የጎንደር ዘመን›› ተብሎ ከሚጠቀሰው (እ.ኤ.አ ከ1636-1769 ዓ.ም ድረስ የዘለቀው) ማዕከላዊ መንግስት ውድቀት በኋላ የተተካውና ‹‹ዘመነ መሳፍንት›› እየተባለ የሚጠራው አገራዊ የአስተዳደር ዘይቤ ጠንሳሽና ተግባሪ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች እንደነበሩ ማስታወሱ በቂ ነው፡፡ በወቅቱ የመንግስቱ መቀመጫ ከሰሜን ጎንደር ወደ ደብረታቦር የተዘዋወረ ሲሆን፣ የግዛት ወሰኑ ደግሞ ጎንደርን፣ ወሎን፣ ጎጃምን፣ ከፊል ሸዋንና ትግራይን የሚያካትት እንደነበር መዛግብቱ ያወሳሉ፡፡ በዘመኑ ሥልጣኑን የጠቀለሉትና ‹‹የጁ (ወራ-ሼክ) ስርወ-መንግስት›› በሚል ስም የሚጠሩት የአሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች እንደነበሩ የብሔሩ ምሁራን ነግረውናል፡፡ እያገባደድነው ባለው በዚህ ዓመት ‹‹የውገና ድርሰቶችና የታሪክ እውነቶች›› በሚል ርዕስ ዳጎስ ያለ ጥራዝ ያሳተሙት ታቦር ዋሚ ‹‹በኢትዮጵያ ታሪክ ዘገባዎች አላግባብ ዘመነ መሳፍንት ሲባል የቆየው የየጁ ዘመንና ታሪካዊ ሚና›› በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር በርካታ መጽሐፍትና የጥናት ጽሑፎችን በመጥቀስ ሥልጣኑ በኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች እጅ እንደነበረ በስፋት አብራርተዋል፡፡ ታቦር በትርክታቸው ‹‹የጁ ከሰሜን ኢትዮጵያ የኦሮሞ ነገዶች አንዱ እንደሆነና ቀስ በቀስም ይህ ስም የጎሳው ብቻ ሳይሆን ሕዝቡ የሰፈረበት አካባቢ ጭምር መጠሪያ እንደሆነ በርካታ ጸሐፍት ይመሰክራሉ›› (ገፅ 287) ሲሉ በአባሪ ማስረጃዎች አስደግፈው አቅርበዋል፡፡ ሥርወ-መንግስቱ በሥልጣን ላይ የቆየበት ጊዜያትንም ‹‹ከጎንደር ዘመነ-መንግስት ማብቂያ እስከ አፄ ቴዎድሮስ መነሳት ድረስ የነበሩትን ዓመታት ሁሉ ያካትታል›› (ገፅ 293) በማለት ገልፀውታል፤ ይህንን በአሃዝ እናስቀምጠው ብንል ደግሞ ወደ 86 ዓመት ገደማ ልንቆጥር እንገደዳለን፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ‹‹የኦሮሞ ታሪክ›› የተሰኘው መጽሐፍ ጸሐፊ እሸቱ ኢረና ዲባባም መከራከሪያውን እንዲህ ሲሉ ያጠናክሩታል፡- ‹‹ጎንደር የሃበሻ መንግስት (አቢሲኒያ)ማዕከል በነበረችበት ወቅት የኦሮሞ ህዝብ በአካባቢው ሰፍሮ ይኖር እንደነበረና ወሳኝ ሚና ለረጅም ጊዜ ነበረው፤ እ.ኤ.አ. ከ1853-1854 በጎንደር በእስር ላይ የነበረው ጀርመናዊ ሰዓሊ በሰራቸው ምስሎች ኦሮሞ በወቅቱ በአካባቢው ገዢ እንደነበር እርሱም ከአካባቢው ኦሮሞ ሴት እንዳገባ፤ ምስልዋንም ሰርቶ እነዚህ የስዕል ስራዎቹ እ.ኤ.አ. በ1868 ዓ.ም በለንደን ከተማ በመጽሐፍ መልክ ታትሞ ወጥቶ ይገኛል፡፡ በአካባቢው ሰፍረው ይኖሩ ከነበሩት የኦሮሞ ጎሳዎች ውስጥ የቦረና ኦሮሞ አንዱ መሆኑን ኤች ሙሬይ በ1830ዎቹ ባሳተመው ጽሑፍ ውስጥ ከጠቀሰ በኋላ ኦሮሞ እንደ ሕዝብ በደንቢያ በጎጃም፣ በዳሞትና በአንጎት አካባቢዎች ሰፍሮ እንደሚገኝ ተጠቅሷል፡፡›› (ገፅ 83-84)

 ራሱ የክልሉ መንግስትም፣ በባሕልና ቱሪዝም ቢሮው በኩል  ‹‹የኦሮሞ ታሪክ እስከ አስራ ስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን›› በሚል ርዕስ ባሳተመው መጽሐፍ ‹‹…‹ወራ- ሼክ› የሚለው የቤተሰቡ መጠሪያ በየጁ ኦሮሞዎች ዘንድ ታላቅ ዝና ከማግኘቱም በላይ በአጠቃላይ የየጁ ኦሮሞዎች ቀደምት መንግስት መነሻ ወይም አባት ተደርጎ እስከመቆጠር ደረሰ ይባላል›› (ገፅ 281) ሲል ገልጿል፡፡

በግልባጩ የአፄ ምኒሊክ ፈረስ ሐረርና አርሲ መርገጡን ‹‹የቅኝ-ግዛት ወረራ›› አድርገው የሚያቀርቡ ዘመነኛ ‹‹ፖለቲከኞች››፣ ይህ አይነቱን ጥሬ ሀቅ ለመቀበል ቀርቶ ለመስማት አይፈቅዱም፡፡ የጠቀስኳቸው ድርሳናትም የሚነግሩን ኦሮሞ ከሌላው ብሔር ጋር ትንቅንቅ ገጥሞ በለስ ቀንቶት ድል ባደረገ ቁጥር መንግስታዊ ሥልጣን መጠቅለሉን ብቻ አይደለም፤ በሀገሪቱ ታሪክ ጭቆና እንጂ ቅኝ አገዛዝ የሚባል ነገር አለመኖሩንም ጭምር ነው፡፡ ከኤርትራ እስከ ሞያሌ፤ ከጋምቤላ እስከ ሶማሌ በተዘረጋው ሰፊ የኢትዮጵያ ግዛት ላይ በተደጋጋሚ ከተቃጡ የባዕዳን ወረራዎች በቀር፣ ቅኝ-ገዢም ሆነ ቅኝ-ተገዢዎች ስለመኖራቸው የሚያትት አንድም የታሪክ መረጃ ተፈልጎ ታጥቷል፡፡ መቼም ‹‹ድሮ ነፃ ሀገር ነበረን›› በሚል ዛሬ ላይ የመገንጠልን ጥያቄ ሲያነሱ፤ አሊያም አንድ ብሔርን በነፍጠኛነትና በወራሪነት ሲኮንኑ የምናደምጣቸው ጠርዘኛ ልሂቃን ‹የኦሮሚያ የግዛት ወሰን ጎንደርን እና ትግራይን ያጠቃልል ነበር› ስለማለታቸው ሰምተን አናውቅም፡፡ መቀመጫውን ደብረታቦር ላይ አድርጎ ከትግራይ እስከ ሸዋ ያስተዳድር የነበረ ሥርወ-መንግስት፣ የበለጠ ጉልበተኛ ተነስቶበት፣ በተራው ከመንበሩ በኃይል ሲገለበጥ ቅኝ-አገዛዝና ኢ-ሰብአዊ ብሎ ለመኮነን መሞከሩ ውሃ የሚያነሳ ሙግት ሊሆን አይችልም፡፡ እዚህ ጋ ሊዘነጋ የማይገባው ጉዳይ፣ በተለይም ከአፄ ምኒሊክ መንገሥ ወዲህ የኦሮሞ ማሕበረሰብ ቋንቋውን ጨምሮ የባሕል እሴቶቹ ተውጠው፣ የአገሪቱ ወካይ እንዳይሆኑ መጨፍለቃቸውን ነው፤ እንደምሳሌም የገዳ ሥርዓት ምንም እንኳ ሁሉንም የቋንቋው ተናጋሪ ያቀፈ ባይሆንም (የ‹‹ጊቤ ግዛት›› ተብለው የሚታወቁት፡- ጅማ፣ ሊሙ፣ ጎማ፣ ጉማ እና ጌራ ከገዳ ይልቅ በንጉሣዊ ሥርዓት ሲተዳደሩ፤ ወለጋና ኢሊባቡርን የመሳሰሉ አካባቢዎችም በ‹‹ሞቲ›› ይመሩ ስለነበር) የአክሱም ሐውልትን ወይም የጎንደር ግንብን ያህል በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ቦታ አለማግኘቱ አይካድም፡፡ እንዲሁም በሌላ ቋንቋ ተናጋሪው ዘንድ ‹‹ጣኦት ማምለክ›› ተደርጎ የሚቆጠረው የኢሬቻ ክብረ-በዓል አረዳድ ስሁት ስለመሆኑ ቢረፍድም የመስከሩ ጠቀሜታ የጎላ ነው፡፡ ይህ የምስጋና ሥነ-ስርዓት በአገሪቱ ታሪክ ተገቢውን የክብር ስፍራ ሳያገኝ መገፋቱን በማመን፣ ሚዛንን ማስተካከል ግድ ይላል፡፡ በጥቅሉ ምግቡ፣ አለባበሱ፣ ሙዚቃውና መሰል እሴቶቹ በትልቁ የታሪካችን ገፅ በበቂ ደረጃ አለመወከላቸውን ዛሬም ለማድበስበስ መሞከሩ መፍትሔውን ከማራቅ፤ አሊያም ልዩነትን ከማስፋት ያለፈ ፋይዳ አይኖረውም፡፡ መቼም በዛሬይቱ ኢትዮጵያ፣ የመገንጠል ጥያቄ ያነሱ ቡድኖች መኖራቸው ደብቀን የምናስቀረው ሚስጥር አይደለም፤ ከኦሮሚያ እስኪ ኦጋዴን፤ ከጋምቤላ እስከ ቤንሻንጉል ድረስ ይህን ለማስፈፀም የሚተጉ የታጠቁ ኃይሎች ተፈጥረዋልና፡፡ በርግጥ እነዚህ ኃይሎች የቆሙበት መሰረት ማሕበረሰቡን የሚወክል ነው ወይስ የራሳቸውን የሥልጣን ጥማት ብቻ የሚያረካ? የሚለው ገና ያልጠራ፣ አሁንም አጥጋቢ መልስ ያላገኘ ጥያቄ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ፖለቲካዊው ፍላጎት ማሕበራዊ ውሉን የዋጠው ይመስላል፡፡

ኤርትራን ያጣንበት ምክንያትም ከዚህ ብዙም እንደማይርቅ ጥርጥር የለውም፡፡ አሁንም የዚህን ጥያቄ ውል ከሳትን ሌላ የምናጣው ክፍለ-አካል መኖሩ አይቀሬ ነው፡፡ ስለዚህም ነው በ‹‹ሕዳሴው አብዮት›› እንደ አዲስ በምትገነባው ኢትዮጵያችን ጥያቄዎቹ በቀዳሚነት ምላሽ ሊያገኙ ይገባል ብዬ የምከራከረው፡፡ በለውጡም፣ እነዚህ ጎታች የፖለቲካ አቋሞች እና አቀንቃኞቹ ዘላቂ መፍትሔ አግኝተው የአንድነት ዘመን አብሳሪ እንደሚሆኑ አልጠራጠርም፡፡

በተቀረ በኦሮሞ ላይ አንድ ብሔር በተለየ መልኩ በደል አድርሷል፣ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ፈፅሟል… መሰል ትርክቶች ጭራና ቀንድ ተሰክቶባቸው ግብረ-ሂትለርና ፋሽስታዊ ድርጊቶች ተመስለው የሚቀርቡበት አውድ ከተራ ጊዜያዊ የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳነት ያለፈ፣ በዕውን ለመፈፀማቸው ምንም አይነት የታሪክ ሰነድ አልተገኘም፡፡ ከጥቂት ሳምንት ቀደም ብሎ በዚህ ርዕሰ-ጉዳይ ዙሪያ ከታሪክ ምሁሩ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ጋር ስንወያይ ‹‹ወደ አኖሌ (አርሲ) ከዘመተው የአፄ ምኒሊክ ሠራዊት መካከል አብላጫው ኦሮሞ ነው›› ሲሉ መግለፃቸውም፣ ከዶ/ሩ የትምህርት ደረጃ፣ ከረዥም ዓመት የሥራ ልምዳቸው እና ከቋንቋው ተናጋሪ አብራክ የተገኙ ከመሆናቸው አኳያ ችግሩን ወደ አንድ ብሔር ማላከኩ ስህተትለመሆኑ ሁሉንም የሚያስማማ ይመስለኛል፡፡ ታቦር ዋሚም ከላይ በጠቀስኩት መጽሐፍ (ከገፅ 275-278) ከአማራው ነገስታቶች ጋር ጋብቻ የፈፀሙ ኦሮሞ ንጉስና ንግስት በማለት በስዕላዊ መግለጫ አስደግፈው ያቀረቡት የቋንቋው ተናጋሪ ንጉሦችና ነገስታት ስም ዝርዝር እንደተጨማሪ ማስረጃ ሊወሰድ ይችላል፡፡ ጸሐፊው ለማሳያነት ከጠቀሷቸው ውስጥ የአፄ ቴዎድሮስ-እቴጌ ተዋበች፣ የአፄ ምኒሊክ-ጣይቱ ብጡል፣ የንግስት ዘውዲቱ-ወሌ ብጡል፣ የአፄ ኃይለስላሴ-እቴጌ መነን፣ የምኒልክን እህት ያገቡት-ንጉስ ሚካኤል… የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት እንደነበሩ አትተዋል፡፡ ከዚሁ ጋርም አያይዘው በተለያየ ጊዜ በሀገሪቷ የተከሰቱት የኃይል ግጭቶች አሰላለፍ በብሔር ከመቧደን ይልቅ፣ በሥልጣንና በጥቅመኝነት ላይ የተመሰረቱ እንደነበረ ፈራ-ተባ እያሉም ቢሆን እንዲህ ሲሉ ገልፀውታል፡- ‹‹በጣም የሚገርመው ከሣህለ ሥላሴ ጊዜ ጀምሮ እስከ አፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግስት ድረስ በኦሮሞው ላይ ሲካሄዱ ለነበሩት ዘመቻዎች ሁሉ ግንባር ቀደም ተዋናዮቹ በተለያዩ ምክንያቶች ከነገሥታቶቹ ጋር ጊዜያዊና ዘላቂ ዝምድና የፈጠሩ እራሳቸው ኦሮሞዎች መሆናቸው ነው፡፡ …(ራስ ጎበና) እኚህ የኦሮሞ መስፍን የታወቁ ፈረሰኛ፣ ጀግና፣ ተዋጊና ወታደራዊ ስትራቴጂስት ከመሆናቸው በላይ በኦሮሞ የውጊያ ስልትና በኦሮሞ ሥነ-ልቡና ላይ የጠለቀ እውቀት ነበራቸው፡፡

ይህንን ብቃት ሙሉ በሙሉ ለምኒሊክ አገልግሎት አውለውታል፡፡ ከሁሉም በፊት ምኒልክ ሳይሆኑ የኦሮሞን ግዛት ያሸነፉት ራስ ጎበና ነበሩ፡፡›› (ገፅ 499-500 እና 503)፡፡ ይህን መሰሉ የኃይል ትንቅንቅ ከአርሲና ባሌ በፊት ቤጌምድርና ትግራይ ውስጥ በተከሰተበት ወቅት ኦሮምኛ ተናጋሪው በአሸናፊነት በመውጣቱ ለ86 ዓመት ያህል ሥልጣን ይዞ መቆየቱን ከላይ አይተናል፡፡ መቼም የጁዎች፣ ጎንደሮችን ድል አድርገው ሥርወ-መንግስታቸውን ደብረ ታቦር ላይ የመሰረቱት በምርጫ ካርድ (ያለነፍጥ) ነበር ካልተባለ በቀር፣ አንዱን ወገን ለይቶ በሂትለርነት መኮነኑ ፍትሃዊ ካለመሆኑም ባለፈ፤ የሚጠቅመው ከመከራ ነፃ እንዲወጣ የምንዋትትለትን ሕዝብ ሳይሆን፣ የአገዛዙን ዕድሜ ለማራዘም ነው፡፡

በተጨማሪም በራሱ በቋንቋው ተናጋሪዎች ብቻ ከተዘጋጁ ድርሳናት የጠቀስኳቸው እነዚህ ሁነቶች፣ በማስረጃ ያልተደገፈውን (አፈ-ታሪኩን) የአኖሌ ጡት ቆረጣ ትርክት ተአማኒነት ያሳጡታል፡፡ ከዚህ ባለፈ የተሸነፈ ሠራዊትን እጅ-እግር መቁረጥ ምኒሊክም ሆኑ ከእርሳቸው በፊት የነበሩ ገዥዎች ይፈፅሙት የነበረ ጭካኔ መሆኑ አይስተባበልም፤ እንዲያውም በአንድ ወቅት አፄ ቴዎድሮስ፣ በሸዋ ላይ ሾመውት የነበረው የምኒሊክ አጎት አቤቶ ሠይፈ ‹‹ሸፍቶብኛል›› በሚል አንኮበር ድረስ መጥተው ወግተው ድል ካደረጉት በኋላ ሠራዊቱ በሙሉ አንድ እጅና አንድ እግሩ እንዲቆረጥ ማድረጋቸውን ተከትሎ፡- “አፄ ቴዎድሮስ እጅግ ተዋረዱ የሸዋን ሰው ሁሉ እጅ ነስተው ሄዱ”ተብሎ መገጠሙ የጉዳዩን እውነታነት ለማሳየት በቂ ነው፡፡ (የእስልምና እምነት እና የኦሮምኛ ተናጋሪው ማሕበረሰብ ጥያቄዎች፣ በ‹‹ሕዳሴ አብዮት›› የሚኖራቸውን የመፍትሔ ሃሳብ በተመለከተ ሳምንት እመለስበታለሁ)

Sunday, July 27, 2014

የ53 አመቱ አባት የጥቁር ሽብር ሰለባ አስገራሚ ክስተት

July 27/2014
ቢቢኤን ራድዮ እንዳቀረበው፦
መንግስት ሀምሌ 11 በወሰደው የጭካኔ ተግባር ወጣቱ ወንዱ ሴቱ ህጻናቱ አዛውንቱ የጥቁር ሽብሩ ሰለባ ሁነዋል፡፡ የዚህ ጥቃት ሰለባ ከሆኑት መካከል የ53 አዛውንት ሰው ይገኙበታል፡፡ ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት የርሳቸውን በከፍተኛ ድብደባ የቆሰለ ሰውነት ነው፡፡
የ53 አመቱ ሰው ከቢቢኤን ሬድዪ ጋር የደረሰባቸውን ነገር አስመልክቶ ቆይታ አድረግዋል፡፡ ሙሉዉን ቆይታ ከራሳቸው አንደበት የምትሰሙት ይሆንና በመጠኑ ቀንጭበን በጽሁፍ እናካፍላችሁ፡፡
Muslim abat
የጁምአን ሶላት በአንዋር መስጅድ ለመስገድ ዘግየት ብለው ስለደረሱ ውጭ አስባልት ላይ ነበር መስገጃ ካኪ ያነጠፉት፡፡ ምንም ተቃውሞ ባልተጀመረበት ሶላትም ባልተሰገደበት ሁኔታ ፖሊሶች መስግጃውን አንሱ በማለት ትንኮሳ ጀመሩ ይላሉ ግለሰቡ፡፡ እርሳቸውም ከእድሚያቸው አንጻር ሁኔታዎቹን ለማረጋገት ይሞከራሉ፡፡ በዚህ ሰአት ግን የፖሊሶቹ ምላሽ ያልጠበቁት ነበር ፡፡ በያዙት ዱላ ለሶላት የተሰበሰበውን ምእምናን መደበደብ ጀመሩ፡፡ እኚህ አባትን በርካታ ፖሊሶች ከበው ይደብድቡዋቸው ጀመር፡፡
የዱላ ውርጅብኝ የበዛባቸው አባትም ወደ መዲና ህንጻ ሩጠው ይገባሉ፡፡ ፖሊሶች ተከትለው ከገቡ በሁላ እየጎተቱ መሬት ላይ በመዘርጋት ዘግናኝ ድብደባ እንደፈጸሙባቸው ይናገራሉ፡፡ በዚህ ብቻ አላበቃም፡፡ ከእድሜያቸው አንጻር በዚሁ እንኩዋን አልተዋቸውም፡፡ በጾመኛ አንጀታችው እየደበደቡ ወደ ልኩዋንዳ ፈጥኖ ፖሊስ ማሰልጠኛ ወሰዱዋቸው፡፡
ልኩዋንዳ ሲደርሱ እሳት እየነደደ ነበር ይላሉ፡፡ ከዛም የሴቶችን ጅልባብ ሀይማኖታዊ አልባሳት የሳቸውም ኮፍያ ጭምር በሳት ተቃጠለ፡፡ ወደ ሰፊ ሜዳ ከወሰዱዋቸው በሙሉ በግራና በቀኝ ዙርያውን ፖሊሶች ተደርድረው በመሃል እየቀጠቀጡ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጸመባቸው፡፡ በ120 በ90 ሜትር የሚሆነውን ሜዳ እያዞሩ ቀጠቀጡን ሲሉ ይናገራሉ አዛውንቱከድብደባውም ሌላ ኮፍያቸው ጫማቸው ተቃጥልዋል፡፡ አጸያፊ ስድብም ተሰድበዋል፡፡ ዱላቸው ተሰባብሮ ሲያልቅ እሳት ረመጡን እንዲረግጡ አድረገዋቸው፡፡ እስከ ሌሊቱ 9 ሰአት ይህ ሁሉ ሲፈጸምባቸው ጾመኛ ነበሩ፡፡
ዘጠኝ ሰአት ላይ አውጥተው ጣልዋቸው፡፡ ሌሊት ለተሃጁድ ሶላት የሚሄዱ ሰዎች ሲያገኙዋቸው አለቀሱ፡፡ የ53 አመቱ አባት ጀርባቸው በምስሉ እንደሚታየው ቆስሉዋል:: ራሳቸው ተፈርክስዋል፡፡
በመጨረሻም ምን ይላሉ ሲል የቢቢኤን ጋዜጠኛ አብዱረሂም ላቀረበላቸው ጥያቄ አዛውንቱ አስገራሚ ምላሽ ሰጡ፡፡ እንዲህም አሉ ”የደረሰብኝ ነገር የሰው ልጅ በወገኑ ላይ የሚፈጸመው ተግባር አይደለም፡፡ ይህም ሁኖ ግን ሰላማዊነታችንን በፍጹም መተ ው የለብንም፡፡ ድምጻችን ይሰማ ጁምአ ቢጠራ ሰባራ እጄን ወንድሞቼ ጋር እሰለፋሉ የምንፈልጋት ሰላማዊ ትግል ውጤት እስክትመጣ ሌላ ምን አደረጋለሁ፡፡ ለሙስሊሙ የማስተላልፈው ሰላማዊ ትግላችን መቀጠል አለበት፡፡ ይህን ስል ሁሉም ይደብደብ ማለቴ ሳይሆን እውነተኛ ነጻነታችን የምትከበርባት ሀገር እስክትመጣ መታገል አለብን፡፡ አንድነታችን ይዘን ጥያቄያችን እስኪመለስ እነሱ ይግደሉን እነሱ ይጨፍጭፉን እኛ በሰላማዊ ትግል አሻራችንን እናሳረፍ፡፡ በኔ የደረሰው ኢምንት ነው በጥይትም የተመቱ አሉ እንበርታ ይላሉ የ53 አመቱ አባት፡:
ለመስማት ተከታዩን ሊንክ ይጫኑ
http://goo.gl/pYP0hD
በጣም አነስተኛ መጠን ያለው ሊንክ
http://goo.gl/NBc1Kx