Monday, July 21, 2014

ኢትዮጵያ፣የወንጀለኞች መናኸሪያ አገር

July 21, 2014
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ 
በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ቡድን የሆነውን ግንቦት ሰባት የፍትህ፣ የነጻነት እና የዴሞክራሲ ንቅናቄ እየተባለ የሚጠራውን ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንዳርጋቸው ጽጌን በቀን ብርሀን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጸ፡፡ እንደ ገዥው አካል ዘገባ ከሆነ የኢትዮጵያ የደህንነት አገልግሎት ከአቻው ከየመን መንግስት የደህንነት ጥበቃ አባላት ጋር በመቀናጀት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በየመን ሰንዓ በኩል አድርገው ወደ ኤርትራ ለመግባት ሙከራ ሲያደርጉ በቁጥጥር ስር አውሎ ወደ ኢትዮጵያ የላካቸው መሆኑን ገልጿል፡፡ አንዳርጋቸው ጽጌ በትውልድ ኢትዮጵያዊ ሆነው የእንግሊዝ ዜግነት ያላቸው ሰው ናቸው፡፡ የየመን ባለስልጣኖች አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በቁጥጥር ስር አውለው በኢትዮጵያ ላለው ገዥ አካል አሳልፈው ከመስጠታቸው በፊት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከእንግሊዝ ኮንሱላር ባለስልጣኖች፣ ከህግ ወኪሎች እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር መገናኘት እንዲችሉ ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ አድርገዋል፡፡
በገዥው አካል በሚስጥር ተቀርጾ ለ63 ሰከንዶች ያህል በአየር ላይ በዋለው የቪዲዮ ክሊፕ (ቁራጭ) አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በገዥው አካል ተጠልፈው መያዛቸውን በማስመልከት በተረጋጋ መንፈስ አስተያየታቸውን ሲሰጡ ተስተውለዋል፡፡ ከሁሉም በላይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በማራኪዎቻቸው ላይ ምንም ዓይነት ቁጣ እንደሌላቸው እና ከእራሳቸው ህሊና ጋር በሰላም እንደሚኖሩ በሙሉ የእራስ መተማመን መንፈስ ተናግረዋል፡፡ እኒህ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰው በእራሳቸው ፈቃድ በነጻነት የሚናገሩት ነው ወይስ ደግሞ በማራኪዎቻቸው አስገዳጅነት የተነገራቸውን እንደ በቀቀን እንዲደግሙ ተገድደው ነው? አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ንግግራቸውን ሲያደርጉ በሚስጥር ለለፕሮፓጋንዳ ትርፍ ሲባል በቪዲዮ ክሊፕ እየተቀረጹ መሆናቸውን አልተገነዘቡም ነበርን? የቪዲዮ ክሊፑ አቶ አንዳርጋቸው በተረጋጋ መንፈስ በነጻነት እራሳቸውን እየተከላከሉ ንግግራቸውን ሲያደርጉ የሚያሰማ ነበር ወይስ ደግሞ በማራኪዎቻቸው ፊት ቀርበው የምህረት ልምምጥ ጥያቄ ሲያቀርቡ ይታዩ ነበር? በቪዲዮ ክሊፑ ተቀርጾ የተለቀቀው ድምጽ የአቶ አንዳርጋቸውን ደጋፊዎች፣ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን እና የእንግሊዝን መንግስት ለማታለል ሲባል የተደረገ የመድረክ ትወና ሙከራ ነውን? የአቶ አንዳርጋቸው ማራኪዎች እና አሳሪዎቻቸው አቶ አንዳርጋቸውን በመጥለፍ በቁጥጥር ስር ከማዋላቸው በፊት ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከአቶ አንዳርጋቸው ጋር ምን ሲሰሩ ቆዩ? ለእነዚህ እና ለመሳሰሉት ጥያቄዎች መልስ አላገኘሁም ሆኖም ግን በሚሽከመከሙ የጅብ መንጋዎች እና ጥርሳቸውን ባገጠጡ በቀልተኞች ፊት ቀርበው እንደዚያ ባለ በተረጋጋ መንፈስ፣ ሰብዕና እና የመንፈስ ጥንካሬ ሲናገሩ በማየቴ የተሰማኝ አድናቆት ወደር የለውም፡፡
ገዥው አካል አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን እ.ኤ.አ ጁን 23/2014 ጠልፎ በቁጥጥር ስር ማዋሉን በይፋ ከገለጸ ከሁለት ሳምንታት በኋላ የቪዲዮ ክሊፑን ለምን እንደለቀቀ ግልጽ አይደለም፡፡ በእኔ እምነት ገዥው አካል በአቶ አንዳርጋቸው ንግግር በርካታ የፕሮፓጋንዳ ዓላማዎችን ለማሳካት ጥረት ያደርጋል፣ ከእነዚህም መካከል፣ 1ኛ) ገዥው አካል ብቃት ያለው የስለላ መዋቅር እንዳለው እና ለጠላቶቹ እና ለተቃዋሚዎቹ ቢያንስ በምስራቅ አፍሪካ አካባቢ ምንም ዓይነት ነገር ሊያመልጠው እንደማይችል ያለውን ብቃት እና የመፈጸም ችሎታ ለግንቦት ሰባት እና ለሌሎች ተቃዋሚ ኃይሎች አስረግጦ ለመንገር የታለመ ነው፣ (በነገራችን ላይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በገዥው አካል የደህንነት ኃይሎች ተጠልፈው በቁጥጥር ስር የዋሉበት ሁኔታ በአንድ ወቅት ከአንድ በአዲስ አበባ ከሚኖር ዘመድኩን ከሚባል ፖሊስ አለቃ ጋር የአሜሪካ ሬዲዮ የአማርኛው ድምጽ የደረገውን ቃለመጠይቅን አስታወሰኝ፡፡ የቪኦኤ ጋዜጠኛ መልዕክቱን በአየር ላይ ካዋለ በኋላ ዘመድኩን ዘጋቢውን ጋዜጠኛ እንዲህ በማለት አስጠነቀቀ፣ “አንተ ዋሽንግተን ወይም ደግሞ መንግስተ ሰማያት ብትኖር ጉዳዬ አይደለም፣ ደንታ የለኝም! ሆኖም ግን አንተን ባለህበት መጥቸ በቁጥጥር ስር አውዬ አመጣሀለሁ፣ ይህንን ልታውቅ ይገባል!!) ገዥው አካል አቶ አንዳርጋቸውን በቁጥጥር ስር ማዋሉ የዘመድኩንን የእብደት ዛቻ በየመን አገር በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የተገበረው ይመስላል፡፡
ገዥው አካል ጠላቶቹ ዋሽንግተንም ይሁን ወይም መንግስተሰማያት ይኑሩ በየመን ትራንዚት ሲያደርጉ በቁጥጥር ስር ሊያደርጋቸው እንደሚችል በቂ መልዕክት ማስተላለፍ እንደሚችል ለማስረገጥ ጥሯል ፡፡ 2ኛ) በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የአካል ወይም የስነልቦና ስቅይት ያልተደረገ መሆኑን፣ መብታቸው ያልተገፈፈ እና በአግባቡ የተያዙ መሆናቸውን በማሳየት በህብረተሰቡ ላይ ተይዞ ያለውን እምነት ለማስተባበል ነው፡፡ 3ኛ) በእርግጠኝነት አቶ አንዳርጋቸው በደህና ሁኔታ የተያዙ መሆናቸውን እና ክበራቸውም የተጠበቀ መሆኑን ለማሳየት (አቶ አንዳርጋቸው ገጽታቸው የተጎዳ አይመስልም ቢያንስ በፊታቸው ላይ በግልጽ የሚታይ ሰንበር ወይም ሌላ የተጫረ ምልክት አይታይም፡፡) በቪዲዮ ክሊፑ ላይ አቶ አንዳርጋቸው ሁልጊዜ እንደሚታዩት ሆነው ለፖሊስ ቃለመጠይቅ እንደሚሰጡ የሚመስል የተረጋጋ መንፈስ ይታይባቸዋል፡፡ አሳሪዎቻቸው አቶ አንዳርጋቸውን የተረጋጉ እና ከድሮው የተለየ ሆነው እንዳይታዩ፣ ጭንቀት፣ እና በመጠለፋቸው ምክንያት የተለየ ውጥረት እንዳይታይባቸው ለማድረግ ይፈልጋሉ፡፡ 4ኛ) አቶ አንዳርጋቸው በእስር ቤት የማሰቃየት ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል ወይም ደግሞ ሊፈጸምባቸው ይችላል የሚለውን የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ትችት አስቀድሞ ለማጥፋት እና አፍ ለማስያዝ የታለመ ነው፣ 5ኛ) ግንቦት ሰባትን እና አመራሩን ለማሸማቀቅ እና ገዥው አካል የድርጅቱን ውስጣዊ ደህንነት ዘልቆ የገባ መሆኑን እና የድርጅቱን ስስ ብልቶች በማውጣት ለመዘገብ እንዲቻል በማስመሰያነት ለመጠቀም ነው፣ 6ኛ) ግንቦት ሰባት የተባለው ድርጅት በጥሩ ሁኔታ የተፐወዘ መሆኑን እና በአቶ አንዳርጋቸው መያዝ ምክንያት ድርጅቱ አቅመቢስ ሽባ  እንደሆነ እና ማንኛውንም መረጃ ከእርሳቸው በማሰቃየት እና በሌላ መንገድ መውሰድ እንደሚችሉ ለማሳየት የታቀደ ነው፣ 7ኛ) በጠቅላላው የኢትዮጵያን ተቃዋሚ ኃይሎች ተስፋ ለማስቆረጥ እና ገዥው አካል የዓለም አቀፍ ህግን የበላይነት በመጣስ ከዚህ ቀደም ለበርካታ ጊዚያት እንዳደረጉት ሁሉ ከዓለም አቀፍ ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች በድብቅ ይሁንታን ለማግኘት የታሰበ ሰንካላ ምክንያት ነው፣ 8ኛ) የሸፍጥ ህልዮት ቀማሪዎች የእራሳቸው የሆነ መግለጫ የሚኖራቸው እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ፡፡
ገዥው አካል አቶ አንዳርጋቸውን በማፈን እና በቁጥጥር ስር በማዋል ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን ዓላማዎች ማሳካት አለማሳካቱ ወደፊት የሚታይ ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን የገዥው አካል አባላት የሻምፓኝ ጠርሙስ በመክፈት በማፈኑ እኩይ ተግባር ስኬታማ በመሆን በማታ ቸበርቻቻ ዳንስ ያካሂዳሉ፡፡ ገዥው አካል በአሁኑ ጊዜ በአቶ አንዳርጋቸው ላይ ባደረገው እኩይ የማፈን ድርጊት ላይ ድልን ተቀዳጅቷልን? ማንም ሰው ቢሆን የአንድ ድርጅታዊ ተቋም ነብስ፣ አካል እና አእምሮ ሊሆን እንደሚችል እጠራጠራለሁ(ከመለስ ዜናዊ በስተቀር)፡፡ የአቶ አንዳርጋቸው መታፈን በግንቦት ሰባት እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያስከትል ይችላል ብሎ መደምደም ምክንያታዊ ሊሆን ይችላል፡፡ ለዚያ ድርጅት መጥፎ ዕድል ሆኖ ጉዳት ያደርስበታል የሚል ጥርጣሬ የለኝም፡፡ በተመሳሳይ መልኩ አቶ አንዳርጋቸው መረጃ እንዲሰጡ ለማስገደድ የማሰቃየት እርምጃ ሊወሰድባቸው ይችላል ብለው የሚያምኑ ሰዎች ትክክል ለመሆናቸው ወደፊት ጊዜ የሚነግረን ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን የህብረተሰብ ሳይንሳዊ ጥናት መረጃ እና ትንታኔ በግልጽ እንደሚያሳየን በተራ የማሰቃየት የወንጅል ምርመራ እና ልዩ የወንጀል ምርመራ ውሸትን እንጅ እውነትን ሊያመጣ አይችልም፡፡
ለመረጃ ጉዳይ ከአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጋር ተገናኝቸ ወይም ደግሞ ተነጋግሬ አላውቅም፡፡ ከእርሳቸው ጋር በቪዲዮ ቴፕ ተቀርጾ የተለቀቀውን ንግግር ከመስማት እና ስለእርሳቸው በድረገጽ የተለቀቀውን የሰዎች አስተያየት ከማንበብ በስተቀር ሌላ የማውቀው ነገር የለም፡፡ ገዥው አካል አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በሽብርተኝነት ወንጀል ክስ በመመስረት የይስሙላው የዝንጀሮው ፍርደ ቤት የሞት ቅጣት ሊበይንባቸው እንደሚችል አውቃለሁ፡፡ ለዚህም ነው ለዚህ ለዝንጀሮው የፍትህ አካል እና በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የሚደረገውን ልዩ የወንጀል ምርመራ ዓለም አቀፍ የህግ የበላይነትን ምክንያት በማድረግ ይህንን ትችት ለመጻፍ የተገደድኩት፡፡
የጸረ ሽብርተኝነትን ህግ በመጠቀም የዓለም አቀፍ የህግ የበላይነትን በመጣስየሚካሄድ መንግስታዊ ሽብርተኝነት እና ውንብድና፣
የማንኛውም የጨነገፈ መንግስት መለያ ባህሪ የህግ የበላይነት አለመኖር ነው፡፡ የጨነገፈ ወንጀለኛ መንግስት መገለጫ ባህሪ የህገመንግስት የበላይነትን እና ዓለም አቀፋዊ ህግን አስከፊ በሆነ መልኩ መደፍጠጥ ነው፡፡ በመርህ ደረጃ ቦኮ ሃራም እየተባለ በሚጠራው በናይጀሪያ በሚንቀሳቀሰው አሸባሪ ድርጅት በናይጀሪያ በ300 ልጃገረዶች ላይ ከሶስት ወራት በፊት በፈጸመው ውንብድና እና በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የወሰደው እብሪተኝነት የተሞላበት አፈና መካክል ትንሽ ልዩነት ብቻ ነው ያየሁት፡፡ ገዥው አካል አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አሸባሪ ናቸው በማለት በሌሉበት የጸረ ሽብር ወንጀል (የጸረ ሽብር አዋጅ ቁጥር 652/2009) እያለ በሚጠራው የዜጎች የማጥቂያ መሳሪያ ክስ በመመስረት የሞት ፍርድ ሊበይንባቸው እንደሚችል ክርክር ሊያቀርብ ይችላል እ.ኤ.አ ከ2006 ጀምሮ በማቀርባቸው ትችቶቸ ለመጠቆም እንደሞከርኩት ገዥው አካል የፖለቲከ ተቀናቃኞቹን ለማጥቃት በአገር ክህደት እና በሽብርተኝነት በመወንጀል በኢትዮጵያ በይስሙላው ፍርድ ቤት እየተጠቀመ በህግ ሰበብ ሲገድል እና ሲያስር እንዲሁም ሲያሰቃይ ቆይቷል፡፡ አሁንም ይህንኑ እኩይተግባሩን በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ በርካታ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የመንግስት የሰብአዊ መብት ጥበቃ መምሪያ ዓመታዊ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት የኢትዮጵያ የጸረ ሽብር ህግ ኢላማ ያደረገው ገዥው አካል የፖለቲካ ተቀናቃኞችን እና ተቃዋሚዎቹን፣ አክቲቪስቶችን፣ ጋዜጠኞችን እና ጦማሪያንን እንደዚሁም የህትመት ሜዲያዎችን መገደብን በመፈጸም በይስሙላው የፍትህ አካል አማካይነት ጥቃቶችን መሰንዘር ነው፡፡ በገዥው አካል በሽብርተኝነት ክስ የተመሰረተባቸው ወገኖች የሞት ፍርድ እንደሚበየንባቸው ጸሐይ የሞቀው እና የታወቀ የገዥው አካል መርህ ነው፡፡ እውነታው ሲታይ ግን በኢትዮጵያ የይስሙላው ፍርድ ቤት አማካይነት በጸረ ሽብር ህጉ በመጠቀም በንጹሀን ዜጎች ላይ የሚበየነው ኢፍትሀዊነትን የተላበሰው ፍርደ ገምድል ውሳኔ በጅቦች ፍርድ ቤት በአጋዘኖች ላይ ከሚበየነው የሞት ፍርድ ውሳኔ ጋር አንድ እና ተመሳሳይ ነው፡፡ ነጻ የፍትህ ስርዓት ከሌለባት አገር እና ዳኞችም በሚነገራቸው መሰረት ብቻ እንዲወስኑ በሚገደድቡት ሁኔታ የሞት ፍርድ ፍትሀዊነትን ሊያገኝ እና ነጻ በሆነ መልኩ ምርመራ ተካሂዶበት የሚሰጥ ውሳኔ ሊሆን አይችልም፡፡
የገዥውን አካል የጸረ ሽብር ህግ አዋጅን ህግ ነው ለማለት ያስቸግራል፡፡ አዋጅ ቁጥር 652 የጫካ ህግ ነው፡፡ የአምባገነን መንግስት አሸባሪ ነው (“Ethiopia: Dictatorship is State Terrorism”) በሚል ርዕስ ባቀረብኩት ትችቴ ላይ በግልጽ ለመጠቆም እንደሞከርኩት አዋጅ ቁጥር 652 አሁን በህይወት በሌለው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ በዘፈቀደ ተፈብርኮ የተረቀቀ እና በይስሙላው ፓርላሜንት የጸደቀ ንጹሀን ዜጎችን ለማጥቃት የወጣ ቀያጅ ህግ ነው፡፡ ያ አስቀያሚ አዋጅ በሁሉም ታላላቅ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ውግዘት እና ትችት ሲቀርብበት ቆይቷል፡፡ ለምሳሌ ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አዋጁ በጣም የተለጠጠ እና የትርጉም ግልጽነት የጎደለው እና ንጹሀን ዜጎችን እና የፖለቲካ አመጸኞችን  ለማጥቃት የታለመ ነው በማለት ያንን አዋጅ በጥሩ ሁኔታ ተችቶታል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የመንግስት መምሪያ እንኳን የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያ የጸረ ሽብር ህግ በጣም አስቀያሚ እና የፖለቲካ ተቀናቃኞቹን ለማጥቃት እና ለማሰቃየት የሚጠቀምበት የማጥቂያ መሳሪያ ነው በማለት ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ገልጿል፡፡ የበለጠ የከፋው ነገር ደግሞ በጸረ ሽብር ወንጅል በተጠረጠረ ግለሰብ ላይ መለስ ዜናዊ እና አፈቀላጤዎቹ አስቀያሚ በሆነ መልኩ በጸረ ሽብር ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው የክስ ሂደቱ እየታየ ባለበት ሁኔታ ከህግ አግባብ ውጭ በማን አለብኝነት የተጠርጣሪዎችን ህግመንግስታዊ መብት በመደፍጠጥ በንጹሀን ዜጎች ላይ የይስሙላው ፍርድ ቤት ኢፍትሀዊ ውሳኔ እንዲሰጥ በማሳሳት እና ስልጣንን እንደ ማስፈራሪያ በመጠቀም ኢፍትሀዊ ውሳኔ እንዲሰጥ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ እንደዚሁም ደግሞ በሽብር ወንጀል ተጥርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ዜጎች ዋስትና የማግኘት መብታቸውን ተነፍገው በተጠረጠሩበት ጉዳይ ምርመራ በሚካሄድበት ጊዜ ከህግ አግባብ ውጭ መረጃ እንዲሰጡ ለማስገደድ በሚል እኩይ ድርጊት የአካል እና አእምሮ ማሰቃየት ድርጊት ይፈጸምባቸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ገዥው አካል በፍርድ ቤቶች ላይ የፖለቲካ ጫና በማድረግ የፍርድ ቤቶች ውሳኔ በአገር ክህደት እና በጸረ ሽብር ወንጀል ተብሎ ብይን እንዲሰጥ ያስገድዳሉ፡፡
ዓለም አቀፍ ህግን ለህገወጦች መስበክ፣ 
የህግ የበላይነትን በኢትዮጵያ ላለው ገዥ አካል መስበክ መናገር እና መስማት ለማይችሉት ዱዳዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እየጠቀሱ ማስተማር እና በባልጩት ድንጋይ ላይ ውኃ እንደማፍሰስ ያህል ነው፡፡ በአንድ ጆሮ ይገባ እና በሌላው ባዶ ጆሮ ወጥቶ ይበናል፡፡ የህግ የበላይነት እንዲሰፍን እንደሚታገል የህገ መንግስት የህግ ባለሙያ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል የህግ የበላይነትን፣ ዓለም አቀፍ ህግን፣ የእራሱን ህገ መንግስት እና ሌሎችንም እንዲያከብር መስበክ እና ማስተማሬን መቀጠል አለብኝ፡፡ ያም ሆነ ይህ ድምጼን ከፍ አድርጌ መናገር አለብኝ ምክንያቱም ይህንን ለማድረግ የሞራል ግዴታ አለብኝና፡፡ ነገሮች ሁሉ እየተበላሹ የህግ የበላይነት እየተደፈጠጠ እየተመለከቱ የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ በማለት ዝምታን የሚመርጡ የሸፍጠኞች የህግ የበላይነት በትክክለኛው የህግ የበላይነት ላይ ድልን እንዲቀዳጅ የሚፈቅዱና የሚመኙ ከገዥው አካል ጋር የሚሞዳሞዱ ሸፍጠኞች ብቻ ናቸው፡፡
ገዥው አካል ከየመን መንግስት ጋር በመተባበር አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ማፈኑ ልዩ “የአፈና ወንጀል” እየተባለ የሚጠራውን የወሮበልነት ወንጀል ፈጽሟል፡፡ የማዕከላዊ ምርመራ የደህንነት መስሪያ ቤት እየተባለ የሚጠራው አፋኝ ቡድን ከሌላ ሉአላዊነቱ ከተጠበቀ ሀገር ጋር በመመሳጠር በሌላ አገር እስር ቤት ውስጥ በሽብር ወንጀል የተጠረጠረ በሚል እኩይ ድርጊት አንድን ንጹህ ሰው በቁጥጥር ስር ማዋል ከፌዝ ያለፈ ፋይዳ የሚኖረው አይሆንም፡፡ ማሰቃየት በሚፈጸምበት አገር በማሰቃየት የሀሰት በግዴታ የሚሰጥ መረጃ አንዱ መለያ ባህሪ ነው፡፡ ከሎጅስቲክ አንጻር ሲታይ በሽብር ወንጀል ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች በውጭ አገር መሬት በባለስልጣኖች በቀጥጥር ስር ውለው ወደ ዘብጥያ በመወርወር ወደ ሌላ መንግስት የማሰቃየት በተመላበት ሁኔታ የአካል እና የስነ ልቦና ሰለባ ለሚያደርግ ምርመራ እና ጥያቄ እንዲዛወሩ ይደረጋል፡፡
በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል ዜጎችን አፍኖ በመሰወር ወንጀል ልምድ እረገድ አዲስ አይደለም፡፡ በእርግጥ ይህንን ዓይነት የወንጀል ድርጊት በመፈጸም ከማንም በላይ የቀዳሚነቱን ስፍራ የያዘ የማፍያ ቡድን ነው፡፡ እ.ኤ.አ ከ2007 ጀምሮ በጠቅላላው ከ100 በላይ የሚሆኑ ተጠርጣሪ ሽብርተኞች በሶማሊያ እና በኬንያ በቁጥጥር ስር ውለው በገዥው አካል እና በዩናይትድ ስቴትስ የደህንነት እና የህግ አስፈጻሚ ባለስልጣኖች ለምርመራ ወደ ኢትዮጵያ እንዲዛወሩ ተደርገዋል፡፡ ማናቸውም እስረኛ ለተከሰሰበት የምርመራ ጉዳይ ጠበቃ እንዲያቀርብ አልተፈቀደለትም፡፡ አብዛኞቹ እስረኞች በምርመራ ወቅት የአካል እና የስነልቦና ስቅይት እንዲደርስባቸው ተደርጓል፡፡ በተጨባጭ ለማየት ከሁሉም በላይ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል ያሲር ቲናዊ የተባለውን ወዲያውኑ ወደ ግብጽ እንዲሄድ የተደረገውን እና በቀጣይም ወደ ሶሪያ እንዲተላለፍ የተደረገውን በምርመራ እረገድ አስተናግዷል፡፡ መሀመድ ዓሊ ኢሴ እና ኦማር ቢን ሀሰን የተባሉትም ለኢትዮጵያ ተላልፈው ተሰጥተዋል፡፡ ኢሴ የተባለው የአፈና ሰለባ በኢትዮጵያ መርማሪዎች በኤሌክትሪክ ንዝረት እንዲሰቃይ ተደርጓል፡፡    
ልዩ የአፈና ወንጅል በማንኛውም የሰብአዊ መብት ጥበቃ መጽሐፍ ማንኛውንም ህግ ይደፈጥጣል፡፡ የአፈናው ሂደት የግዳጅ ጠለፋ እና አፍኖ መሰወርን ያካትታል፡፡ የአፈና ወንጀል ሰለባው ከህግ አግባብ ውጭ በውል ላልታወቀ ጊዜ ከማንም ጋር እንዳይገነኝ ሆኖ በእስር እንዲቆይ ይደረጋል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ላልተወሰነ ጊዜ በምርመራ እንዲቆዩ ሆኖ ከዚሁ ጋር በተያያዘ መልኩ የአካል እና የአዕምሮ ስቅይት እንዲደርስባቸው ይደረጋል፡፡ የአፈና ወንጀሉ ሰለባ የሆነው ዜጋ ወደ አፈና ወንጀሉ መዳረሻ ከመሄዱ በፊት የህግ አማካሪ የማግኘት ዕድል አይሰጠውም፡፡ የአፈና ወንጀል ሰለባ የሆኑ ዜጎች ከቤተሰቦቻቸው፣ ከጓደኞቻቸው እና ከጤና ሞግዚቶቻቸው ጋር እንዳይገናኙ ክልከላ ይደረግባቸዋል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ለብቻቸው በአንድ በሚስጥር በተያዘ እስር ቤት ውስጥ እንዲታሰሩ በማድረግ በቀጥጥር ስር ውለው ለምን ወደ ፍርድ ቤት እንደቀረቡ እንደቀረቡ የመጠየቅ መብት የላቸውም፡፡ 
ስለማሰቃየት (ሰቆቃ) ዓለም አቀፍ ስምምነቶች፤
መንግስታዊ ድጋፍ ካለው የማሰቃየት ድርጊት ነጻ የመሆን መብት መሰረታዊ እና ዓለም  አቀፍ መብት ሆኖ በዓለም አቀፍ ህግ ስምምነቶችን አካትቶ የያዘ መርህ ነው፡፡ መንግስታት በፍጹም እና በአስገዳጅ ሁኔታ ውል በመግባት የጥቃት ሰለባ የሆነው ግለሰብ ቅጣት፣ ማሰቃየት፣ ወዘተ ይደርስበታል ተብሎ በሚጠረጠር ቦታ እንዲሄድ አይደረግም፡፡ ይህ ዓይነት ግዴታ ዋና መሰረታዊ ሲሆን በሁሉም መንግስታት ዘንድ የተፈጻሚነት ግዴታ ያለበት ሲሆን ከዚህ ስምምነት ሊወጣ ወይም ደግሞ በተጻራሪ መልኩ ሊቆም አይችልም፡፡ ይህ ጉዳይ የስምምነቱን ፊርማ ቢፈርሙም ባይፈርሙም በሁሉም መንግስታት ዘንድ ተግባራዊ ይሆናል፡፡
ስለማሰቃየት ያለው ስምምነት እና ሌሎች ጭካኔ የተሞላባቸው፣ ኢሰብአዊ ወይም ደግሞ የማዋረድ ስምምነት ወይም ቅጣት በኢትዮጵያ እ.ኤ.አ ማርች 14/1994 እና በየመን ደግሞ እ.ኤ.አ ኖቬምበር 5/1991 ተፈርሟል፡፡ አንቀጽ 3 ዓለም አቀፍ የማሰቃየት ስምምነቶች/ Convention Against Torture (CAT) በተለይ አንድ ግለሰብ በማሰቃየት አደጋ ላይ ሊወድቅ የሚያስችል በቂ መረጃ እስከተገኘ ድረስ የመንግስት ፓርቲዎች የማስወገድ፣ የመመለስ ወይም ደግሞ አንድን ተጠርጣሪ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ መንግስት የማዛወር መብት ይሰጣል፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ስለመኖር እና አለመኖር ጉዳይ ተወዳዳሪ ባለስልጣኖች አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ሁሉንም ታሳቢዎች ማለትም በመንግስታት ላይ የብዙሀን ሰብአዊ መብት መረገጥን ያካትታል፡፡ አንቀጽ አንድ ማሰቃየትን እንደሚከተለው ይገልጸዋል፣ “ከአንድ ሰው ወይም ደግሞ ከሌላ ሶስተኛ ሰው መረጃን በኃይል አስገድዶ ለመውሰድ ወይም ደግሞ ተገድዶ በኃይል እንዲያምን ለማድረግ በመርማሪ ወይም ደግሞ በህዝብ ባለስልጣንነት ደረጃ ላይ ያለ ሰው በሌላ በሚጠረጠር ሰው ላይ የሚፈጸም ማንኛውም አካላዊ እና አእምሯዊ ጉዳት ወይም ማሰቃየት ማለት ነው“
ማሰቃየት እና አግባብ ያልሆነ አያያዝ በኢትዮያ ላለው ገዥ አካል ጥሩ የንግድ መሳሪያዎች ናቸው፡፡ በኢትዮያ በሚሰነፍጠው የማጎሪያ እስር ቤት ለብቻ ማድረግ እና ማሰር በእራሱ ማሰቃየት ማለት ነው፣ እናም በሰው ልጅ ላይ የሚፈጸም አሰቃያሚ ወንጀል ነው፡፡ ማንም ቢሆን በኢትዮጵያ ያለውን አስፈሪውን እና አስደንጋጩን የገዥውን አካል የባርነት የእስር ቤት አያያዝ ስርዓት ለማወቅ በመንግስት ስምምነት መሰረት የእንግሊዝ ዜጋ በሆኑት በኮሎኔል ሚካኤል ዴዋር የተዘጋጀውን የሚስጥር የእስር ቤት ዘገባ ማንበብ ብቻ በቂ ነው፡፡ ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት በኢትዮጵያ የደህንነት ኃይሎች የሚፈጸመውን የማሰቃየት እና አግባብ ያልሆነ የእስር ቤት አያያዝን በማስመልከት በተለያየ መልኩ አዘጋጅቶ ዘገባ አቅርቧል፡፡ “በኢትዮጵያ ሰላማዊ አመጸኞችን፣ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባላትን እና የሽምቅ ቡድን አባላትን ይረዳሉ ተብለው የሚጠረጠሩትን እንዲሁም በሽብርተኝነት የሚጠረጠሩትን ንጸሀን ዜጎች  በፖሊስ፣ በወታደር እና በሌሎች የደህንነት አባላት ማሰቃየት እና አግባብ ያልሆነ የእስር ቤት አያያዝ እንዲፈጸምባቸው በመቅጣት የንጹሀን ዜጎችን የሰብአዊ መብቶች በመደፍጠጥ ላይ ይገኛል“ የሚል ዘገባ አውጥቷል፡፡ በማዕከላዊ እና በመንግስት ተወካይ በሆኑት በአዛዦች፣ በጨካኝ ወታደሮች እና በፖሊስ ኃላፊዎች የሚፈጸመው የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ እና አግባብ ያልሆነ ስልታዊ የሰብአዊ መብት አያያዝ ተንሰራፍቶ የሚገኝ መሆኑን በግልጽ ያመላክታል፡፡ በብዙ አጋጣሚዎች በሂዩማን ራይትስ ዎች በተዘጋጀው ዘገባ መሰረት ወታደራዊ አዛዦች በግልጽ በሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ሂደቱ ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ አድርገዋል”:: የማሰቃየት ስልቶች እና ዘዴዎች የተለያዩ መከሰቻዎች አሏቸው፣ ከእነዚህም ውስጥ፣ “በተደጋጋሚ እና በአሰቃቂ ሁኔታ በዱላ መደብደብ፣ በኤሌክትሪክ ገመድ መግረፍ፣ በጠብመንጃ አፈሙዝ ና ሰደፍ መደብደብ፣ በብረት ቁራጭ ወይም በሌሎች ጠንካራ በሆኑ የመደብደቢያ ቁሶች መምታት በአብዛኛው የተለመዱ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ማጥቂያ መሳሪያዎች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ፖሊስ እና ወታደሮች ሌሎች የማሰቃያ ዘዴዎችን ማለትም የጥቃት ሰለባውን ጭንቅላት ዘቅዝቆ በበርሜል ውስጥ ካለ ውኃ ውስጥ መጨመር፣ የጠቃቱ ሰለባዎች ተዘቅዝቀው ባሉበት ወቀት በተደጋጋሚ መደብደብ፣ በጠርሙስ የተሞላ ውኃ በወንዶች ብልት ላይ ማንጠልጠል እና በጠጣር አሸዋ ላይ የጥቃቱ ሰለባዎች ለበርካታ ሰዓት በባዶ እግራቸው እንዲሮጡ ወይም ደግሞ እንዲንከባለሉ ማስገደድ የመሳሰሉትን ይጠቀማሉ፡፡ አንዳንድ የጥቃቱ ሰለባዎች ዘለቄታዊነት ላለው ጉዳት ይዳረጋሉ፣ ጥቂቶች ደግሞ በማሰቃየት ወቅት ህይወታቸው ያልፋል…ኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ያላት እና ለማስገደድ የሚያስችሉ ዓለም አቀፍ እና አገራዊ ግዴታዎችን የሚወጡ ህጎች ቢኖሯትም በተግባር ላይ የሚውሉት በጣም አናሳ በሆነ መልኩ ነው፡፡ በጣም ጥቂቶች የማሰቃየት ተግባራት ወዲያውኑ እንዲፈጸሙ ይደረጋሉ፣ በጣም አናሳ የሆኑት ብቻ ለህግ ስርዓት ሂደት ይቀርባሉ“
ገዥው አካል በግንቦት ሰባት እና በሌሎች ተቃዋሚ የፖለቲካ አባላት እና አመራሮች ላይ ማሰቀየት ይፈጽማል፣ በአንዳርጋቸው ጽጌ ላይ መረጃን በኃይል ለማስወጣት ሲባል የሰብአዊ መብት ረገጣ ይፈጸማል የሚለው በርካታ የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችን አሳስቧል፡፡ ይኸ ስጋት በቀላሉ የሚታለፍ አይደለም፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል ከጫካ ጀምሮ ባለው ታሪኩ በንጹሀን ዜጎች ላይ ማሰቃየት መፈጸም ልምዱ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል በተደጋጋሚ የሚጠቀምባቸውን አራት አስቀያሚ የሆኑ የማሰቃያ ዘዴዎችን እና እስረኛን ከህግ አግባብ ውጭ አያያዝን አቀርባለሁ፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያዋ የሴት የፖለቲካ አመራር የነበረችው ብርቱካን ሚደቅሳ ለብቻዋ በአንዲት ጠባብ የእስር ቤት ክፍል ውስጥ ሆና ለወራት የስነ ልቦና እና የአካል ስቅይት እንዲደርስባት በማድረግ በሞት በተለየው በመለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ በ2008 እንድትማቅቅ ተደርጋለች፡፡ መለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ በ2010 ስለብርቱካን ሚደቅሳ የብቻዋን መታሰር ጉዳይ አስመልክቶ ጥያቄ ሲቀርብለት እንዲህ የሚል የቀልድ ምላሽ ሰጥቶ ነበር፣ “የብርቱካን የጤና ሁኔታ በመጨረሻ እንደሰማሁት ከሆነ በጣም በጥሩ ሁኔታ ላይ ያለ ነው፣ ትንሽ ኪሎ የመጨመር ሁኔታ አሳይታለች፣ ሆኖም ግን ከዚህም በላይ እንቅስቃሴ ከለማድረጓ በስተቀር በጥሩ ሁኔታ ላይ ትገኛለች…“ ብሎ ነበር፡፡ በብርቱካን ላይ መለስ ሲያራምድ የነበረውን አስመሳይ የእስር ቤት አያያዝ በማስመልከት በብርካታ ትችቶቸ ላይ ዘገባዎችን ሳዘጋጅ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ2010 የኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት ቀንዲል የሆነው እስክንድር ነጋ እና ባለቤቱ የሰርካለም ፋሲል በእስር ቤት ለደረሰባቸው ኢሰብአዊ እና ጭካኔ የተሞላበት የእስር ቤት አያያዝን በማስመልከት ለኮሎምቢያ ዩኒቨርሰቲ ለፕሬዚዳንት ለሊ ቦሊንገር እንዲህ የሚል ደብዳቤ ጽፈው ነበር፣ “… በአፍሪካ በመጥፎነቱ በጣም አስቀያሚ በሆነው የዜጎች የማጎሪያ እስር ቤት ምክንያት በሰርካለም አካላዊ እና ስነልቦናዊ ጥቃት በመፈጸም በእስር ቤት የወለደችው ህጻን ከሚገባው ክብደት በታች መሆኑ እና ህይወቱን ለማዳን በሙቀት መስጫ መሳሪያ/incubator እየታገዘ ህይወት የማዳኑ ስራ በእስር ቤቱ ሀኪሞች ከፍተኛ ጥረት አማካይነት እንዲተርፍ የተደረገውን ህጻን አስመልክቶ ገዥው አካል ምንም እንዳልተደረገ ሙጥጥ አድርጎ ክዷል፡፡“
እ.ኤ.አ በ2010 ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ተንከባካቢ ኮሚቴ/CPJ ወጣት ሴት ጋዜጠኛ በሆነችው ርዕዮት ዓለሙ ላይ የተፈጸመውን የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ እና ከህግ አግባብ ውጭ የሆነ የእስር ቤት አያያዝ በማስመልከት በእስር ቤት የተፈጸመባትን የሰብአዊ ድፍጠጣ ነቅሶ በማውጣት እንዲህ የሚል ዘገባ አቅርቧል፣ “ለጉዳዩ ቅርብ የሆነ አንድ ጋዜጠኛ ለዓለም አቀፍ ሴቶች ሜዲያ ፋውንዴሽን/International Women’s Media Foundation የሰጠው ዘገባ ከሆነ የእስር ቤቱ ኃላፊዎች ርዕዮት ዓለሙን ባሳየቸው መጥፎ ስነምግባር በሚል ምክንያት ብቻዋን በአንዲት የእስር ቤት ክፍል ውስጥ ለሁለት ወራት ያህል ለመቅጣት በሚል ታስራ እንድትማቅቅ ከመደረጉም በላይ በእስር ቤቱ የጥበቃ አባላት የሰብአዊ መብቷ እንዲጣስ ተደርጓል፡፡ ሲፒጀ መረጃውን ነጻ በሆነ መልኩ አጣርቶታል፡፡ ርዕዮት በጡቷ ላይ የተከሰተውን እብጠት በሚመለከት ቀዶ ጥገና ከተደረገላት በኋላ በቂ የሆነ ህክምና እንዳታገኝ ተደርጓል… እ.ኤ.አ ማርች 2014 ሰባት ወጣት የሰማያዊ ፓርቲ ሴት አባላት በቁጥጥር ስር ውለው ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል፣ እንዲሁም ዓለም አቀፍ የሴቶች በዓልን ምክንያት በማድረግ በ5 ኪ/ሜ የመንገድ ላይ እሩጫ በማካሄድ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ እና ሰብአዊ መብታቸው እንዲከበር  በመጠየቃቸው ብቻ ለእስር ተዳርገዋል፡፡ በገዥው አካል እጅ የስቅይት እና ግርፋት፣ ከህግ አግባብ ውጭ የሆነ የሰብአዊ መብት አያያዝ እና የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ያልተፈጸመባቸው በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወንዶች፣ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት፣ ሰላማዊ አመጸኞች፣ የሲቪል ማህበረሰቡ መሪዎች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና ሌሎችም ማግኘት እና መግለጽ ያዳግተኛል፡፡
ከገዥው አካል መካከል አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ተዋርዶ፣ ተሸማቅቆ እና ክብሩን አጥቶ ማየት የሚፈልጉ እንዳሉ እገምታለሁ፡፡ በቀልተኝነት፣ ቂምን ቋጥሮ ለመበቀል ጥረት ማድረግ ለእነርሱ ልክ እንደ እናት ጡታቸው ነው፡፡ ገዥው አካል የጠላቶቹን እና የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችን አያያዝ በማስመልከት የጥላቻ፣ የይቅርታ ቢስነት እና መጥፎ አስተሳሰብ ከግምት ውስጥ በማስገባት ጥንቃቄ የተሞላበት የሰነድ ጥናት ምርመራ ቢደረግ በማያጠራጥር ሁኔታ በወንጀል ላይ ተዘፍቆ ይገኛል፡፡ ገዥው አካል አባላት የጉዳት ሰለባዎቹ በታላቅ ስቃይ ላይ ሆነው ሲሰቃዩ ማየት ከምንም በላይ ያስደስተዋል ወደሚል መደምደሚያ ላይ ደርሻለሁ፡፡ የገዥው አካል ሊቁ ባለ ራዕይ መሪ እና በአሁኑ ጊዜ በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ የእርሱን ተቃዋሚዎች ማሰቃየት፣ ማዋረድ እና ስብዕናቸውን ጥልሸት መቀባት ከማናቸውም ነገር ሁሉ ታለቅ እርካታን እና ደስታን ይሰጠው ነበር፡፡ ብርቱካን ሚደቅሳን ለማዋረድ እና ከሰብአዊነት ውጭ ለማድረግ ሲያደርግ በነበረው እርባናቢስ ስሌት በጣም አዝን እና አበሳጭ ነበር፡፡ መለስ ማንኛውንም የሰብአዊ መብት አብሮነት ክብር፣ ደግነት እና ምህረት በአፍ ጢሙ በመድፋት በተጠናወተው እርኩስ መንፈሱ ብርቱካንን ለመጨቆን እና ለማዋረድ ጥረት ሲያደርግ ነበር፡፡ እዚህ ላይ ዋናው ሊጤን የሚገባው ጉዳይ እነዚህ የመለስ ደቀመዝሙሮች የባለራዩን መሪያቸውን ዕኩይ የበቀልተኝነት አምልኮ በአቶ አንዳርጋቸው ላይ ለመድገም ሸብረብ ከማለት እንደማይቆጠቡ እገምታለሁ፡፡ ዋናዎቹ የገዥው አካል በአቶ አንዳርጋቸው መጠለፍ ብቻ እና መታሰር ይደሰታሉ የሚል እምነት የለኝም፡፡ ከግንቦት ሰባት ጋር ያላቸውን ጦርነት ማሸነፍ ብቻውን በቂ አይደለም፡፡ ይልቁንም ነብስያቸውን የሚያስደስታቸው ጠላቶቻቸውን ይዘው ማሰቃየት፣ ማዋረድ፣ ጥላሸት መቀባት እና ሰብአዊ ክብራቸውን በማዋረድ ስብዕነቸው ኮስሶ  ማየት ነው፡፡ ኃይል ስልጣን ባልተማሩ ደንቆሮ በቀልተኛ ቡድኖች እጅ መያዝ አደገኛ ነው፡፡
የየመን የማሰቃየት ስምምነት እዳ፣
አንድ እያወቀ ዓለም አቀፍ ህግን በመጣስ ሌላ መንግስትን የሚረዳ ወይም እገዛ የሚያደርግ መንግስት (የማፈን ወንጀለኛ) መጥፍ ድርጊትን የመፈጸም ዕዳ አለበት፡፡ የመን አቶ አንዳርጋቸውን አሳልፋ በኢትዮጵያ ላላው ገዥ አካል በመስጠቷ (አስገድዶ መሰወር እና በሚስጥር በማሰር ማሰቃየት መፈጸም) ገልጽ የሆነ ዓለም አቀፍ የማሰቃየት ስምምነት ህግን መጣስ ማለት ነው፡፡ የየመን  መንግስት እያወቀ በማሰር፣ የሎጂስትክስ ስራ በመስራት እና የማሰቃየት ስራ ሊሰራበት እንደሚችል እያወቀ አቶ አንዳርጋቸውን በኢትዮጵያ ላለው ገዥ አካል የደህንነት ኃይል  አሳልፎ የመስጠት የወንጀል እዳን በመፈጸሙ ምክንያት ተጠያቂ ነው፡፡
የማሰቃየት ዓለም አቀፍ ስምምነት አንቀጽ 3 ሰብአዊ መብትን በመጣስ ረገድ አንድ ሰው በኃይል ታፍኖ በሚወሰድበት ጊዜ ሊደርስበት የሚችለውን ማሰቃየት በሚመለከት በርካታ ጉዳዮችን ይዳስሳል፡፡ የመን ይህንን አስፈላጊ ጉዳይ ወደ ጎን በመተው አቶ አንዳርጋቸውን በኢትዮጵያ ላለው ገዥ አካል አሳልፋ ሰጥታለች፡፡ የየመን መንግስት ዲፕሎማሲያዊ በሆነ መንገድ በኢትዮጵያ ላለው ገዥ አካል ማሰቃየትን እንዳይፈጽም ዋስትና አልሰጠችም፡፡ እ.ኤ.አ ጁላይ 7/2014 የየመን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀሚድ አል አዋዲ ለየመን ታይምስ መጽሔት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ኢትዮጵያ እና የመን እ.ኤ.አ በ1999 የሚፈለጉ ግለሰቦችን አሳልፎ ለመስጠት ባደረጉት ስምምነት መሰረት ዕቀባ የተጣለበትን የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ የሆነው የግንቦት ሰባት ዋና ጸሀፊ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በአዲስ አበባ ላለው ገዥ አካል አሳልፋ መስጠቷን ይፋ አድርገዋል፡፡ በዓለም አቀፍ የማሰቃየት ህግ መሰረት የየመን ግዴታ ምንድን ነው? የመን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በኢትዮጵያ ላለው ገዥ አካል አሳልፋ በመስጠቷ አርገድ በዓለም አቀፍ ህግ መሰረት ተጠያቂ ወንጀለኛ ናት፡፡
ከዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አንጻር የቬይና ሰምምነት፣
እ.ኤ.አ በ1963 የተፈረመውን የቬይና ስምምነትን ያጸደቁ 177 አገሮች አሉ፡፡ ኢትዮጵያ እና ሌሎች በደርዘን የሚቆጠሩ አገሮች ማለትም ቡሩንዲ፣ ቻድ፣ ኮሞሮስ፣ ጊኒ ቢሳው፣ ፓላው፣ ሳን ማሪኖ፣ ሴራሊዮን፣ ሶሎሞን አይላንድስ፣ ደቡብ ሱዳን ስምምነቱን ሳይፈርሙ ቀርተዋል፡፡ የመን እ.ኤ.አ ኤፕሪል 10/1986 በመፈረም የስምምነቱ አባል ሆናለች፡፡
የቬይና ስምምነት አንቀፅ 36 አንድ የሌላ አገር ዜጋ በወንጀል ወይም በስደተኝነት ክስ ሳቢያ በቁጥጥር ስር ሲውል ወይም ሲታሰር በቁጥጥር ስር የዋለው ግለሰብ ለተወሰኑ መብቶቹ መጠበቅ ምክር ሊሰጠው ይገባል፡፡ በግልጽ ለማስቀመጥ አንቀጽ 36 መንግስታት ከዚህ ቀጥሎ የሚከተሉትን ተግባራት እንዲፈጽሙ ግዴታ ያስገባል፣ 1ኛ) አንድ በቀጥጥር ስር ስለዋለ ግለሰብ ወዲያውኑ ሳይዘገይ ለተቋቋመው ፍርድ ቤት ማሳወቅ ይኖርበታል፣ 2ኛ) በቀጥጥር ስር የዋለው/ችው ግለሰብ መብታቸውን አውቀው እንዲጠቀሙ ምክር ቤቱ አስፈላጊውን ምክር ይሰጣል፣ 3ኛ) ምክር ቤቱ የኮንሱላር ምክር ቤት ባለስልጣኖች እስረኞችን እንዲጎበኝ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡
የመን ሆን ብላ እና እያወቀች አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለእንግሊዝ ኤምባሲ እና በሳና ላለው ኮንሱላር ሳታሳውቅ በኢትዮጵያ ላለው ገዥ አካል በመስጠቷ እ.ኤ.አ በ1963 የተፈረመውን የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የቬይናን ስምምነት ጥሳለች፡፡ የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ እንዲህ ብሏል፣ “ከቬይና ስምምነት በተጻረረ መልኩ አቶ ጽጌን በቁጥጥር ስር በመዋላቸው እና ከዚህ ቀደምም የሞት ፍርድ የተበየነባቸው በመሆኑ ጉዳዩ የሚያሳስበን በመሆኑ ከየመን መንግስት ባለስልጣኖች ያልተቋረጠ መረጃ እንጠይቃለን“ የሚል መግለጫ ሰጥቷል፡፡ ከእንግሊዝ መንግስት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የተሰጠውን መግለጫ የአዞ እንባ ማንባት እንበለው? ይህንን ጉዳይ በእንግሊዝ መንግስት የግዛት ክልል አፈር ላይ የተወለዱትን እና ሌሎችን የእንግሊዝ ዜግነት ያላቸውን ዜጎች በአንድ ዓይነት መልኩ ያለማስተናገድ አድሏዊ አሰራር ብለን እንፈርጀው?
በሽብርተኝነት ወይም በዓለም አቀፍ ህግ ላይ ጦርነት ማወጅ? 
የጸረ ሽብር ጥረቶች በወሮበሎች ላይ የሚደረግ ትክክለኛ አካሄድ ቢሆንም በሽብርተኝነት ላይ ጦርነት ማወጅ በዓለም አቀፍ ህግ ላይ ጦርነት ማወጅ ሊሆን አይገባም፡፡ ህዝቦች ሽብርተኝነትን የመዋጋት ግዴታ አለባቸው፣ እናም ጉዳት እና አደጋ የሚያደርሱትን አድኖ በመያዝ ወደፊት በሰው ልጆች ደህንነት ላይ የሚሰነዘሩ የሽብር ጥቃቶችን ማክሸፍ እና ሰላምን ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ ዓለም አቀፋዊ ሽብርተኝነትን ለማሸነፍ እን ድልን ለመቀዳጀትም በህግ አስፈጻሚዎች፣ በደህንነት ሰራተኞች እና በውጭ ግንኙነት ባለስልጣኖች መካከል ዘለቄታነት ያለው ዓለም አቀፋዊ ትብብር ማድረግን ይጠይቃል፡፡ ሆኖም ግን እንደዚህ ያሉ ጥረቶች በህገወጥ መንገድ ወይም ደግሞ ስምምነቶችን እና የተለመዱትን ዓለም አቀፍ ህጎች በመጣስ መተግበር የለባቸውም፡፡ የዓለም አቀፍ ህግን መከተል ሽብርተኝነትን ማፋጠን ወይም ደግሞ ለተግባራዊነቱ እገዛ ማድረግ ማለት አይደለም፡፡ የህግ የበላይነትን አጥብቆ መያዝ እና መተግበር እንዲሁም የሰለጠነውን ዓለም ህዝቦች ለህዝብ ደንታ ከሌላቸው ከሽብርተኞች እና ከወሮበሎች የመለየት አካሄድ እንጂ፡፡ መንግስታት የተጠረጠሩ ግለሰቦችን ለመያዝ እና የህግ ሂደታቸውንም ለመከታተል ብዙ ዓይነት የህግ ማዕቀፎች እና መሳሪያዎች አሏው፡፡ ንጹሀን ዜጎች አፍኖ የመውሰድ ወንጀል በዓለም አቀፍ ህግ ፊት ታላቅ ወንጀል ነው፡፡ ማንም መንግስት ቢሆን ማንንም ግለሰብ ቢሆን በሌላ አጥቂ መንግስት የማሰቃየት ጉዳት ሊደርስበት እንደሚችል ለማወቅ የሚያስችል በቂ መረጃ እያለው አሳልፎ የመስጠት መብት የለውም፡፡ ይህ ዓለም ህግ በምንም ዓይነት መልኩ ሊሸራረፍ አይችልም፡፡
ስለዓለም አቀፍ የህግ የበላይነት መከበር የሚደረገው ትግል በኃላቀርነት፣ በጨካኝነት፣ በእጦት እና በኢሰባዊነት ላይ የሚደረግ የስልጣኔ ትግል ነው፡፡ ለህግ የበላይነት እንቅፋት እና ኋላቀር መሆን ለህገወጥ ሽብርተኞች ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ ይልቁንስ የህግ የበላይነትን በተግባር ለማሳየት ቃል ለገቡት ወሮበላ ቃል አባዮች ጭምር እንጂ፡፡ አሉታ ኮንቲኑዋ! (ትግሉ ይቀጥላል!)
እንደ ህገመንግስታዊ የህግ ባለሙያነቴ ከዩኤስ አሜሪካ ታዋቂ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ከሆኑት ለሁዊስ በራንዲስ ጋር እንዲህ በማለት ከተናገሩት ጋር ከልብ እስማማለሁ፣ “የእኛ መንግስት ጠንካራ ነው፣ ትግህ መምህር ነው፣ ለደግም ይሁን ለመጥፎ ነገር ሁሉንም ህዝብ በእራሱ አምሳል እያደረገ ያስተምረናል… መንግስቱ ህግ የሚጥስ ከሆነ ህግን የመናቅ አስተሳሰብን ያራምዳል፣ እያንዳንዱ ሰው በእራሱ ህግ እንዲሆን ያደርጋል፣ በዚህም መሰረት ስርዓተ አልበኝነት ይነስራፋል፡፡ የደግ ሰዎችን የሞራል ስብዕና እንዲከስም በማድረግ የመጥፎዎችን እንዲጠናከር ያደርጋል፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሽብረተኝነት ድጋፍ በመስጠት የደግ ሰዎችን የሞራል ስብዕና ይሸረሽራል፡፡ ህገወጥ መንግስት ሽብርተኝነትን ይጋብዛል፡፡“ በማለት በግልጽ አስቀምጠውታል፡፡ የሌላ አገር ሰላማዊ ዜጋን አፍኖ ለሌላ ወንጀለኛ መንግስት አሳልፎ የሚሰጥ የማፈያ ወሮበላ መንግስት በእራሱ ምሳሌነት ሽብርተኛለትን ይፈጥራል!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ሀምሌ  11 ቀን 2006 .

Sunday, July 20, 2014

የኢትዮጵያው ጓንታናሞ ቤይ ‹‹ ማዕከላዊ ››

July20/2014
ዳዊት ሰለሞን
maeklawi prison
ማዕከላዊ
አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ሂዩማን ራይትስ ዎች እንዳለፉት አመታት ሁሉ የኢትዮጵያን መንግስት የሚያስቆጣ ባለ 70 ገጽ ሪፖርት ከሁለት ሳምንታት በፊት ይፋ አድርጓል፡፡ የተቋሙን ሪፖርት ከሌላው ጊዜ የተለየ የሚያደርገው በአንድ ርዕሰ ጉዳይ በአንድ ተቋም  በማጠንጠኑ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የወንጀል ምርመራ ማዕከሎች መካከል በአዲስ አበባ ዕምብርት በሚገኘው ማዕከላዊ ተጠርጣሪዎች ግርፋት፣ማሰቃየትና ድብደባ እንደሚፈፀምባቸው ሪፖርቱ አትቷል፡፡
አሜሪካ በሁለቱ የኒውዮርክ መንትያ ህንጻዎቿ ላይ በአልቃይዳ የተቀነባበረ ጥቃት ከተሰነዘረባት በኋላ ‹‹ሽብርተኛ›› በማለት የሰየመችውን ቡድን አባላት ከምድረ ገጽ ለማጥፋት በጆርጅ ቡሽ ፊት አውራሪነት የሽብር ቡድኑ ዋነኛ መጠለያ ያለቻችትን አፍጋኒስታንን ወረረች፡፡ በዘመቻው በቁጥጥር ስር የዋሉ የአልቃይዳ አባላትና ተጠርጣሪዎች በጄኔቭ ስምምነት መሠረት በህግ የመዳኘት መብት እንዳያገኙ ለማድረግ የቡሽ አስተዳደር ከግዛቱ ውጪ በኩባ ድንበር የሚገኘውን ጓንታናሞ ቤይን ከዛሬ አስር አመታት በፊት ከጦር ካምፕነት ወደ ማሰቃያ ማዕከልነት አሸጋገረው፡፡
‹‹በሽብርተኝነት›› ተጠርጥረው ወደ ጓንታናሞ ቤይ እንዲገቡ የተደረጉ ተጠርጣሪዎች የዜግነት ስብጥር የሚበዛበት ቢሆንም አንዳንድ መረጃዎች የሚበዙት ተጠርጣሪዎች አፍጋናዊያን፣ ኢራቃዊያን፣ የመናዊያን፣ ሊቢያዊያንና ግብጻዊያን ስለመሆናቸው ይጠቁማሉ፡፡ ከታሳሪዎቹ መካከል 99 ከመቶ ያህሉም የሙስሊም እምነት ተከታዮች ናቸው፡፡
አሜሪካ በህገ መንግስቷ ተጠርጣሪዎች ዋስትና፣ ጠበቃ፣ ጎብኚና ነጻ የፍትህ ስርዓት  እንዲያገኙ ለማድረግ ቃል የገባች ቢሆንም በጓንታናሞ ቤይ የተጣሉ ተጠርጣሪዎች ለረዥም አመታት ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እንዳይታይ፣ ጎብኚዎች እንዳያገኙ፣ ግርፋትና ስነ ልቦናዊ የሆነ ቶርቸር እንዲደርስባቸው በማድረግ ከህገ መንግስቷ የተጣረሰ ኢ ሰብአዊ ድርጊት ስትፈጽምባቸው ቆይታለች፡፡
እስረኞቹን አጋቾቻቸው እጅና እግሮቻቸውን ለ24 ሰዓታት በሰንሰለት በማሰር ሲያሰቃዩአቸው ቆይተዋል፣ በረመዳን የጾም ወቅት እስረኞቹ የሃይማኖታቸውን ትዕዛዝ ለመፈጸም ከምግብ ተከልክለው ወሩን ለማሳለፍ ቢዘጋጁም የማጎሪያው ሃላፊዎች ሀይልን በመጠቀም በቀን ለሁለት ጊዜያት ምግብ እንዲመገቡ በማድረግ ጥቃት ፈጽመውባቸዋል፡፡
የአሜሪካ መንግስት (የቡሽ አስተዳደር) ይህንን ግፍ በጓንታናሞ ቤይ ሲፈጽም የከረመው በገዛ ዜጎቹ ላይ ባይሆንም በሰብአዊ ፍጥረት ላይ የሚደርስን በደል የአገሪቱ ህዝብ በራሱ እንደደረሰ በመቁጠር የቡሽን የበቀል እርምጃ በተለያዩ መድረኮች ሲቃወም ተስተውሏል፡፡
ጥቁር አሜሪካዊው ባራክ ሁሴን ኦባማ ለፕሬዝዳንትነት ያደርጓቸው በነበሩ ቅስቀሳዎች ‹‹ጓንታናሞን›› ከተመረጡ እንደሚዘጉ መግለጻቸውም በአስገራሚ ሁኔታ የአገራቸውን ህዝብ ድጋፍ እንዲያገኙ ረድቷቸዋል፡፡ ኦባማ የማሰቃያ ማዕከሉን ለመዝጋት ፕሬዝዳንት ሆነው ከተመረጡ በኋላ እንቅስቃሴ ቢጀምሩም ከተፎካካሪዎቻቸው ጠንከር ያለ ተቃውሞ ማስተናገዳቸው አልቀረም፡፡ አሁን የኦባማ ምኞት እውን ሆኖ ጓንታናሞ ሙሉ ለሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ተዘግቷል፡፡ ፍትህ ተነፍገው የወታደሮች መጫወቻ ሆነው የቆዩ ተጠርጣሪዎችም በወታደራዊ ፍርድ ቤቶች እንዲቀርቡ ተደርገዋል፣የሚበዙትም ከአልቃይዳ ጋር ምንም አይነት የሚያገናኛቸው መስመር እንደሌለ በመረጋገጡ ከቤተሰቦቻቸው እንዲቀላቀሉ ተደርገዋል፡፡

      በኢትዮጵያው ጓንታናሞ ቤይስ?
የዛሬው የአፍሪካ ህብረት ህንጻ የቆመበት መሬት በዘመነ ደርግ ላቅ ያለ የስቃይ ምድር ነበር፡፡ ከርቸሌ ብዙ ሺህ ወጣት ኢትዮጵያዊያንን በልታለች፣ በወታደራዊው መንግስት ላይ ተቃውሞን ያሰሙ ዜጎች በከርቸሌ ፊደል የማይተርከውን ስቃይ አስተናግደዋል፡፡ በኢትዮጵያውያኑ የለቅሶና የደም መሬት ላይ የአፍሪካ መሪዎች አመታዊ ስብሰባቸውን ለማድረግ ሲመጡ በቻይና እርዳታ የተሰራላቸውን ህንጻ ውበት እንጂ በከርቸሌ የፈሰሰው ደም፣ የባከነው አእምሮና የተፈፀመው ግፍ አይታሰባቸውም፡፡ በዘመነ ደርግ ለከርቸሌ እስረኞችን ይመግብ የነበረው የምርመራ ማእከል ደግሞ ማዕከላዊ ነው፡፡
ማዕከላዊን በመገንባት የተቃዋሚዎቻቸውን በአደባባይ ለመገንፈል ያሰፈሰፈ ቁጣ መሸበብ የጀመሩት አጼ ኃይለስላሴ ናቸው፡፡ ንጉሱ ተማሪዎችን፣ አመጽ ያማራቸውን ወታደሮች፣ ስልጣኔ የሸተታቸውን ሰራተኞችና የባላባት ጭሰኛ መሆን የመረራቸውን ገበሬዎች በምስጢር ፖሊሶቻቸው አማካኝነት እያደኑ ማስፈራሪያና ግርፊያ ይፈጽሙባቸው እንደነበር ለዚህ ፊቸር ያናገርኳቸው ሰዎች እማኝነታቸውን ሰጥተውኛል፡፡ ደርግ የንጉሱን ወንበር በመገልበጥ ስጣኑን እንደተረከበ የተነሳበትን ተቃውሞ ለማፈን ከሁሉም የማጎሪያ ካምፖች በተሻለ ማዕከላዊን ስለመጠቀሙ በዛ ያሉ ምስክሮችን መቁጠር ይቻላል፡፡
የኢህአፓ ወጣቶች በማዕከላዊ የሚያውቁትን ምስጢር እንዲያወጡ፣ያልተያዙ ጓደኞቻቸውን እንዲጠቁሙ በሚል በወታደሮች ተደብድበዋል፣ ሴቶቹ ተደፍረዋል፣ በኤሌከትሪክ ሽቦ ተጠብሰዋል፣ ጥፍሮቻቸው በጉጠት እንዲነቀሉ ተደርገዋል፣ ሰውነታቸው ተገልብጦ ውስጥ እግራቸው በበሬ ቆለጥ ተገርፏል፡፡ ድብደባውን መቋቋም ተስኗቸው ይህችን ጨካኝ አለም የተሰናበቱ የት የሌለ ናቸው በማዕከላዊ፡፡የወቅቱ የምርመራ ሰራተኞች ብቃት የሚለካው እየገረፉና እያሰቃዩ በሚያገኙት መረጃ እንጂ መረጃውን ለማግኘት በሚጠቀሙት ፖሊሳዊ የምርመራ ጥበብ አልነበረም፡፡ይህ ጥበብም እነሆ እስካሁን ድረስ እየተወራረሰ ይገኛል፡፡
በ1983 የሰርዓት ለውጥ ተደርጎ ራሱን ነጻ አውጪ በማድረግ የሚቆጥረው ኢህአዴግ ስልጣነ መንግስቱን ሲቆናጠጥ ማዕከላዊ ዑደቱን እንዲያቋርጥ አለመደረጉን በየጊዜው ከማዕከላዊ የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡
በ1987 ዓ.ም የፀደቀው ህገ መንግስት ተጠርጣሪዎች ህገ ወጥ ለሆነ አያያዝ እንደማይደረጉ፣ ኢሰብአዊ የሆነ ጥቃት እንደማይደርስባቸው፣ በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ፣ በምርመራ ወቅት የሰጡትን የእምነት ክህደት ቃል በፍርድ ቤት መለወጥ እንደሚችሉ ቢደነግግም በማዕከላዊ እነዚህ ህገ መንግስታዊ መብቶች ሆን ተብለው እንደሚጣሱ በምርመራ ጣብያው ዘግናኝና የሰቆቃ ጊዜያትን ያሳለፉ ሰዎች ይናገራሉ፡፡
ሂዩማን ራይትስ ዎች ላወጣው ሪፖርት እማኝ እንደሆኑ የተነገረላቸው 35 በማዕከላዊ የነበሩ እስረኞችም የተናገሩት ለወራት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ መቆየታቸውን፣ በጨለማ ቤት መክረማቸውን፣ ከጠያቂዎች ጋር እንዳይገናኙ መደረጋቸውንና በምርመራ ወቅት ግርፋት፣ ማሰቃየትና ማስፈራራቶች ይፈፀምባቸው እንደነበር ነው፡፡
ከሪፖርቱ ውጪ ጀሚል አክበር፣ ስዬ አብርሃ፣ ደበበ እሸቱና ኢንጂነር ኃይሉ ሻወል በጻፏቸው መጻህፍት በማዕከላዊ የምርመራ ማእከል ቆይታቸው ለጆሮ የሚሰቀጥጡ ስቃዮችን ማለፋቸውንና መስማታቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ የመጻሕፍቱ መልእክት አንድና አንድ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የመንግስታት ለውጥ ቢደረግም ማዕከላዊ ግን የየስርዓቱን ተቃዋሚዎች፣ ጋዜጠኞችና ተቺዎች ማሰቃ በመሆኑ ቀጥሏል፡፡
      ጣውላ፣ ጨለማ ቤትና ሸራተን በማዕከላዊ
በማዕከላዊ የምርመራ ማዕከል እንዲገቡ የተፈረደባቸው ዜጎች ቆይታ ለሚያደርጉባቸው ክፍሎች ተገቢ ነው ያሏቸውን ስያሜዎች አውጥተውላቸዋል፡፡ ጨለማ ቤት እጅግ ቀዝቃዛና ዘና ብሎ ለመተኛት የማያወላዳ የተፈጥሮ አልያም የሰው ሰራሽ ብርሃን አልቦ ነው፡፡ ወደዚህ ክፍል የሚገቡ ሰዎች ቀንና ሌሊት በጨለማ የሚዋጡ በመሆናቸው ሰዓት፣ ቀንና ምሽትን ለመለየት ይቸገራሉ፡፡ የቅንጅቱ ሊቀመንበር የነበሩት ኃይሉ ሻውል በቅርቡ ባሳተሙት መጽሐፍ ለ28 ቀናት ጨለማ ቤት እንዲቆዩ መደረጋቸውን በመጨረሻም መርማሪዎቹ ‹‹መብራት የሚሰራልን አጥተን ነው ይቅርታ›› በማለት አምፑል በማስገባት እንዳበሩላቸው ገልጸዋል፡፡ እንደ ሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት ሪፖርት ከሆነ በዚህ ጨለማ ክፍል የቆዩ ሰዎች ጊዜያቸውን በማጠናቀቅ ወደ ውጪ ሲወጡ ለከፍተኛ የአይን ህመም ይዳረጋሉ፡፡
ጣውላ ቤት የተሻለ ስፋትና አጋር እስረኛ የሚገኝበት ከመሆኑ ባለፈ በጨለማ የተዋጠ ነው፡፡ ቤቱ ከጣውላ የተሰራ በመሆኑም ድምጽ ከየትኛው ክፍል እንደሚመጣ አይታወቅም፡፡ ይህም እስረኞቹ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እንዲያንጎረጉሩ፣ የመሰላቸውን እንዲናገሩ ይረዳቸዋል፡፡ አንደኛው እስረኛ ለመጸዳዳት ከክፍሉ ወጣ በሚልበት አጋጣሚም ከሌላው እስረኛ ጋር የሚገናኝበት፣ የሚተያይበት በመሆኑም ለታሳሪዎቹ ህይወት እንድትሸታቸው ያደርጋል፡፡ ሸራተን በማዕከላዊ የቅንጦት ክፍል ነው፡፡ የክፍሉ ስፋት በመጠኑ የሚያወላዳ ከመሆኑም በላይ የመብራት ባለቤት ነው፡፡በዛ ያሉ እስረኞች የሚገኙበት በመሆኑም በማዕከላዊ እንደ ቅንጦት ተቆጥሮ ሸራተን ለመሰኘት በቅቷል፡፡ ሸራተን የገቡ እስረኞች በአብዛኛው የምርመራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ በመሆናቸው በጨለማ ቤትና በጣውላ ቤት ያሳለፉትን መከራ እያነሱና እየጣሉ ከሌሎች ታሳሪዎች ጋር ፍርድ ቤት የሚያሳልፍባቸውን ውሳኔ ይጠባበቃሉ፡፡

           የመንግስት ምላሽና ሪፖርቶች
ሂዩማን ራይትስ ዎቹ በኢትዮጵያ እስር ቤቶች ኢሰብአዊ ድርጊቶች እንደሚፈጸሙ ሲያጋልጥ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ የመንግስት ኃላፊዎችም ሪፖርቱን ከመንግስት ተቃዋሚዎች የተሰበሰበና እውነታውን የማያሳይ በማለት ከማጣጣል ተቆጥበው አያውቁም፡፡
የአሜሪካ መንግስት /ስቴት ዲፓርትመንት/ በሚያወጣቸው ሪፖርቶች የእስረኞች አያያዝ እንዳሳሰበው የገለጸባቸው አጋጣሚዎች በዛ ያሉ ናቸው፡፡ በ2007 ኤፕሪል በዊኪሊክስ አማካኝነት የወጣ መረጃም በኢትዮጵያ የሚገኙ እስረኞችን ጉዳይ በቅርበት የሚከታተሉት የፕሪዝን ፌሎው ሺፕ መስራች ፓስታር ዳንኤል ለአሜሪካ ኤምባሲ ሰዎች መንግስት በእስረኞች ላይ ግርፋት፣ ማስፈራራትና ማሰቃየት እንደሚፈጽም መናገራቸውን አትቶ ነበር፡፡ በቅርቡ ሂዩማን ራይትስ ዎች  ላወጣው ሪፖርት የመንግስት የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ሽፈራው በጽሁፍ እንዲሁም የመንግስት ኮሚኒኬሽን ምክትል ኃላፊ አቶ ሽመልስ ከማል  ለኤኤፍፒ በሰጡት ምላሽ ክሱን አጣጥለውታል፡፡
በማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ ቆይታ አድርገው የነበሩት ሁለቱ ስዊዲናዊያን ጋዜጠኞች ማርቲን ሺብዬና ዮሃን ፒርሰን ‹‹ፖሊስ ሁሉም ነገር የሚያልቀው በፍርድ ቤት እንደሆነ ይናገራል፣ ነገር ግን ሁሉም ነገር የሚሆነው በምርመራ ወቅት ነው፡፡ ፖሊስ በሀይል ተጠርጣሪዎች የተጠረጠሩበትን ጉዳይ መፈፀማቸውን እንዲያምኑ ያደርጋል›› ይላሉ፡፡
በሪፖርቱ ዙሪያ ለኤ.ኤፍ.ፒ በእስር ላይ ስለምትገኘው ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ የተናገሩት ወላጅ አባቷና ጠበቃዋ አቶ አለሙ ጌቤቦ ለሦስት ወራት ያህል ልጃቸውን በማዕከላዊ ማየት እንዳልቻሉ በመጥቀስ በእነዚያ 90 ቀናት ውስጥ ከቤተሰብና ከጠበቃዋ ለይተው ምን ሲፈጽሙባት እንደቆዩ እንደማያውቁ ተናግረዋል፡፡ ርዕዮትን ከሦስት ወራት በኋላ እንዲመለከቷት ሲፈቀድላቸው ተጎሳቁላ ማግኘታቸውንና ለዘጠኝ ቀናት ያህል ምግብ ሳትመገብ መቆየቷን መረዳታቸውን መስክረዋል፡፡
በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ወደ ማዕከላዊ የገቡ ሌሎች ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ከርዕዮት ጋር የሚመሳሰል ታሪክ እንዳላቸው የታሳሪዎቹ ቤተሰቦች ይናገራሉ፡፡
ፓስተር ዳንኤል በእስር ቤቶች ኢሰብአዊ ድርጊት የሚፈጽሙ መርማሪዎች መኖራቸውን መንግስት ከደረሰበት በኋላ የሚበዙትን ከስራ እንዳባረራቸው ለአሜሪካው ዲፕሎማት መናገራቸውን ዊኪሊክስ ቢዘግብም የመረጃ መረቡ ባወጣው ሪፖርት ፓስተሩ ነገሩን ለማድበስበስ ያህል እንደተናገሩት እንደቆጠረባቸው አትቷል፡፡
በምርመራ ላይ የቆዩ ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት በሚቀርቡባቸው አጋጣሚዎች በምርመራ ወቅት ድብደባ፣ ማስፈራራትና ማሰቃየት እንደደረሰባቸው የተናገሩባቸው አጋጣሚዎችም በዛ ይላሉ፡፡  ዳኞች እንዲህ አይነት የመብት ጥሰት አቤቱታ ሲቀርብላቸው ፖሊሶች ላይ ጫን ያለ እርምጃ እንዲወሰድ አለማድረጋቸው የምርመራ ውስጥ ስቃዩ እንዲቀጥል የበኩሉን አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

            የእኛ ኦባማ የት ነው?
የኢትዮጵያ መንግስት ኃላፊዎች የሰብአዊ መብት ተቋማት፣ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ድርጅቶች አልያም የአለም ባንክ ለሚያወጧቸው ሪፖርቶች የሚሰጧቸው ምላሾች አንድ ጫፍ የረገጡ ናቸው፡፡ የሪፖርቶቹን መውጣት ተከትሎ ጉዳዩን ለማጣራት ገለልተኛ ቡድን እንዲዘጋጅ የተደረገበት ጊዜ የለም፡፡ ጆርጅ ቡሽም እንዲህ ነበሩ፡፡ በጓንታናሞ ለሚፈጸም የሰብአዊ መብት ጥሰት ጆሮ አልነበራቸውም፡፡ ወታደሮቻቸው ሴት እስረኞችን እንደሚደፍሩ፣ ታሳሪዎችን በረመዳን የጾም ወቅት በኃይል እንዲመገቡ ማድረጋቸው፣ ተጠርጣሪዎች ለወራት ፍትህ ሳያገኙ መቆየታቸው ሲነገራቸው ለመስማት አልፈቀዱም፡፡ በፕሬዝዳንቱ እምነት እየተሰቃዩ የሚገኙት ሰዎች ሳይሆኑ ‹‹ሽብርተኞች›› ናቸው፡፡
ኦባማ ግን እንደ ቡሽ በጭፍን ጥላቻ የታወሩ አልነበሩም፡፡ ጓንታናሞ የሰብአዊ መብት ረገጣ የሚፈፀምበትና አሜሪካ ቆሜለታለሁ ለምትለው ዲሞክራሲ ተቃራኒ መሆኑን በመረዳት ጓንታናሞን ላይከፍቱት ቆለፉት፡፡
የእኛው ማዕከላዊ በእኛው ዜጎች እኛው ላይ ኢ- ህገ መንግስታዊና ኢሰብአዊ ድርጊት የሚፈፀምበት ማዕከል ነው፡፡ በጓንታናሞ አሜሪካዊያኑ የገረፉት፣ ያሰቀዩት አፍጋኑን፣ ግብጻዊውን፣ ኢራቃዊውን፣ አፍሪካዊውን ነው፡፡ በማዕከላዊ መሰቃየቱንና ህገ መንግስታዊ መብቱ እንደተጣሰበት የሚናገረው ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ ኦባማ ጓንታናሞን ስለ አሜሪካዊያን አልዘጉትም፡፡ ስለ ፍትህ እንጂ፡፡ የእኛ ኦባማ ለጊዜው እዚህ ነኝ ባይለንም የመጣ ቀን ግን ማዕከላዊን ስለእኛ ይዘጋዋል፡፡
ከዘ-ሐበሻ የተወሰደ

የአሜሪካ ብሄራዊ የበረራ ባለስልጣን የአሜሪካ መንገደኞች አውሮፕላኖች በኢትዮጵያ የአየር ክልል እንዳይበሩ ጥብቅ ማሳሰብያ አስተላለፈ። ምክንያቱንም ሲገልጽ "የኢትዮጵያ መንግስት የመንገደኞችን አውሮፕላን ሊመታ ይችላል" ብሏል።

July 20, 2014
(WP) – After Flight 17 was shot down in eastern Ukraine on July 17, the Federal Aviation Administration expanded an existing regulation that prohibited certain flights from operating in the region. The FAA regularly issues airspace restrictions and prohibitions for U.S. aircraft traveling through potentially hostile airspace.Flight operations are prohibited in Ethiopian
Here’s where the FAA has issued flight advisories and prohibitions for U.S. aircraft as of July 18.
Ethiopia
Flight operations are prohibited in Ethiopian airspace north of 12 degrees latitude. The FAA also warns that Ethiopian forces may fire upon aircraft crossing into Ethiopian airspace from northeastern Kenya. View document »
Kenya
The advisory states that “recent, credible information indicates a potential near-term terrorist attack against U.S. and Western interests in Kenya,” warning against attacks using MANPADS. View document »
Somalia
Flight operations are prohibited in Somalian airspace at or below 20,000 feet, except where necessary for takeoff in an adjacent country. View document »

ምናምንቴዎች በሠለጠኑ ግዜ ህዝብ ያልቀሳል !!!

July20/2014

ኢትዮጵያ ላይ ጥቂት ምናምንቴዎች ሰልጥነው ህዝቡን እያስለቀሱት ነው። ኢትዮጵያዊያን ለብዙ ዘመን በብዙ ሃዘንና እንባ ውስጥ መኖራቸው የታወቀ ነው። የአሁኑ ሃዘን እንዲሁ ተራ ሃዘን፤ ልቅሶውም ተራ ልቅሶ አይደለም። መራር ሮሮ እንጂ። ይህን የህዝብ ሮሮ የሚሰማ መንግስታዊ አካልም የለም። በ“Global terrorist database” ውስጥ የሥም ዝርዝሩ ተመዝግቦ የሚገኘው “የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ” ነኝ የሚለው ቡድን መንግስ ነኝ ቢልም የመንግስት መልክና ባህሪይ ሊኖረው አልቻለም። ህወሃት መንግስታዊ አሸባሪ እንጂ የኢትዮጵያ መንግስት ለመሆን የሞራልም ሆነ የእውቀት ብቃት ያለው ቡድን አይደለም።
ህወሃት ከተፈጠረ ጀምሮ የብዙ ንፁህ ዜጎችን ደም አፍሷል። ብዙ ዜጎችን ለስቃይ እና ለስደት ዳርጓል። ብዙ ቤተሰብን በትኗል። በተለይ ጠላቴ ነው ብሎ የሚያምነውን የአማራ ህዝብ ለማጥፋት ሴቶችን መካን የሚያደርግ ክትባት እስከ መከተብ ደርሷል። በዚህም የአማራው ቁጥር ከነበረው ቀንሶ ተገኝቷል። ይህ አሸባሪ ቡድን በኦጋዴን፤ በአፋርና በጋምቤላ የፈፀመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ዓለም ያወቀው ነው። በኦሮሚያ የፈሰሰው የንፁሃን ዜጎች ደም ከምድር ወደ ሰማይ እየጮኸ ነው። በአዲስ አበባ እና በደቡብ የተበተነውን የቤተሰብ ብዛት ቆጥረን አንዘልቀውም። በትግራይ የሚገኙ ምርጥ ኢትዮጵያውያን በሙሉ አልቀዋል። የተረፉ ጥቂቶች ቢገኙም መግቢያ መውጪያ አጥተው በሁለት ሰይፍ የሚቆረጡ ሁነዋል።
የትግራይ ነፃ አውጪዎች ያተረፉልን ነገር ቢኖር ውርደት ነው። ውረድቱ የከበዳቸው ዜጎች ራሳቸውን በእሳት አቃጥለዋል። ገደል ውስጥ ራሳቸውን ወርውረው የሞቱም አሉ። ህወሃቶች ባሉበት ከምንኖር ብለው ስደተን መርጠው የበርሃ ንዳድ፤ የባህር ዐዞ እራት የሆኑ ብዙ ናቸው። በባእዳን አገር ውስጥም ማረፊያ አጥተው የሚንከራተቱም ቁጥራችው በቀላል የሚገመት አይደለም። ይህ የህወሃት መራር ፍሬ ነው።
አዎን በአገራችን ላይ እነዚህ እግዜርን የማያውቁ የሰይጣን ድንኳኖች ከሰለጠኑ ዘመን ጀምሮ የንፁህ ሰው ደም ሳይፈስ የዋለበት ቀን የለም። ህወሃቶች የትልቁንም የትንሹንም ደም በማፈሰስ የሚረኩ፤ ቤተሰብንም በትነው ድሃ አደግ በማድረጋቸው የሚደሰቱ ፍጡራን ስለመሆናቸው የእስከዛሬው ምግባራቸው ቋሚ ምስክር ነው። ለስልጣን ካላቸው ሥሥት የተነሳም ከባዕዳን ጋር እየተመሳጠሩና ብዙ ሚሊዮን ገንዘብ እየከፈሉ ነፍሰ ገዳዮችንና አፋኞችን ቀጥረው ዜጎችን እስከማሳፈን ደርሰዋል። የዚህ ዕኩይ ተግባር ሰለባዎች ብዙ ናቸው። ታላቁ ሰው አንዳርጋቸው ፅጌ የዚህ እኩይ ተግባር ሰለባ ከሆኑ ብዙ ኢትዮጵያዊያን መካከል አንዱ ነው።
ጠላቶቻችን(ህወሃቶች) እና ወዳጆቻችን በሙሉ ስሙን ! አንዳርጋቸው የተነሳው ፡
  • ሚዛኑን ስቶ መሳለቂያ የሆነው ፍትህ ወደ ሚዛኑ ለመመለስና ፍጹም የህግ የበላይነትን በአገራችን ለማስፈን ነው።
  • የነፃነት ትርጉም ሳይገባው ስለነፃነት ሊነግረን ሳይሆን የነፃነትን ጣዕም አጣጥሞና ተርድቶ ከምር ኢትዮጵያዊያን ያለፍርሃት በነፃነት እንዲኖሩ ለማስቻል ነው።
  • ጥቂቶች ብዙሃኑን ተጭነው፤ ብዙሃኑም ጥቂቶቹን ተሸከመው መከራቸው በዝቶ የሚኖሩበት ሥርዓት ተወግዶ ሁሉም ዜጎች በእኩልነት እንዲኖሩ ለማደረግ ነው።
  • ጠባብ ጎሰኛነት ተወግዶ ሁሉም በኢትዮጵያዊነቱ ኮርቶ በሠላም መኖር የሚችልበት ንፁህ አገር እንድትኖረን ለማድረግ ነው።
  • ከዚያች ድሃ አገር ላይ እየዘረፈ በውጭ አገራት ባንኮች ውስጥ የሚደብቅ ይሄን ማድረግ ካልቻለም መሬት ምሶ የዘረፈውን ገንዘብ የሚቀብር ዘራፊ ቡድን ሳይሆን ያለውን ሁሉ ለአገሩና ለህዝቡ ለመስጠት ከልቡ ያመነ መሪ አገሪቷን የሚመራበት ሥርዓት እንዲዘረጋ ለማድረግ ነው።
  • ኢትዮጵያችን በውሸታሞች፤ ለህዝባቸው ክብር በሌላቸው፤ህዝባቸውን በሚንቁ፤ ከራሳቸውው ፍላጎት ውጪ ሌላ ወገን ህዝብ ማለትን በማያውቁ ደካሞች መገዛቷ አክትሞ ህዝቡን ፈርቶና አክብሮ የሚመራ፤ ህዝብ ላይ የሚጫን ሳይሆን በህዝብ የተመረጠና የተወደደ መሪ እንዲኖራት ለማብቃት ነው።
ግንቦት ሰባትንና መሪውን አንዳርጋቸው ፅጌን በህወሃቶች ዘንድ አሸባሪ እንዲሆኑ ያደረጓቸው እነዚህ ከላይ ለመዘርዘር የሞከርናቸው ቁም ነገሮች ናቸው እንጂ እንደ ህወሃቶች ግንቦት ሰባት ባንክ ሲዘርፍ፤ የእምነት ሥፍራዎችን ሲያወድም፤ ትምህርት ቤቶችን ሲያፈራርስ፤ የቀደመው ትውልድ በደምና አጥንቱ ያቆየውን ድንበር ቆርሶ ሲሸጥ፤ የአገሪቷን ለም መሬት ለባእዳን ሲሸጥ፤ አንዱን ጎሳ ከሌላው ጋር አጋጭቶ ደም እንዲፈስ ሲያደርግ ተገኝቶ አይደለም።
ባንክ መዝረፍ፤ የእምነት አምባዎችን ማርከስ፤ ትምህርት ቤቶችን ማውደም፤ የአገሪቷን ድንበር እያፈርሱ ለባዕዳን አሳልፎ መስጠት፤ ለም መሬቶችን ለባዕዳን መቸብቸብ፤ በህዝቦች መካከል ጥላቻን መዝራት፤ ከድሃ ጉሮሮ ላይ ሠርቆ በውጪ አገራት ባንኮች ውስጥ ገንዘብ ማጠራቀም ህወቶች እንደ ሙያ የተያያዙት የእለት ተዕለት ተግባራቸው ነው። ግንቦት ሰባት የተነሳው እንዲህ ዓይነት ነውረኞችን ከተቆናጠጡበት የስልጣን ወንበር ላይ አውርዶ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያዊያን የምትሆን አገር እንድትሆን ለማድረግ ነው። የመሪያችን የአንዳርጋቸው ፅጌም ምኞት ይሄው ነው። ኢትዮጵያን ከጥቂት ዘረኞችና ዘራፊዎች እጅ አውጥቶ የብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ አገር እንድትሆን ማድረግ።
ይሄ የኢትዮጵያ ውድ ልጅ በነውረኞቹ የትግራይ ነፃ አውጪዎች እጅ ገብቷል። ነፃ አውጪ ነን ባዮቹ አንበሳውን ከበው ለመቦጫጨቅ እንደሚያጓሩ ጅቦች ዓይናቸውን አጉረጥርጠው እያሰቃዩት ይገኛሉ። ምንም እንኳ ይሄ ታላቅ ሰው በነፍሰ ገዳዮቹ እጅ ቢወድቅም እርሱ የጀመረው የነፃነት ጥያቄ የሚሊየኖች ጥያቄ ሆኖ ከመቸው ግዜ በላይ ሚሊየኖችን አስነስቷል። በዓለም ዙሪያ “እኔም አንዳርጋቸው ነኝ፤ እኔም ግንቦት ሰባት ነኝ” የሚሉ ድምፆች ከፍ ብለው እየተሰሙ ነው። አንዳርጋቸውን ማሰር እንጂ እርሱ የጀመረወን የነፃነት ጥያቄ፤ እርሱ የዘረጋውን የትግል መስመር ማሰር አይቻልም። ለዚህም ነው አንዳርጋቸው የማይጨበጥ ፅኑ መንፈስ ነው የሚባለው።
ግንቦት ሰባት የፍትህ፤ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ህወሃት የተባለው ዘረኛ እና የወሮበላዎች ቡድን የገነባው የሰይጣን ድንኳን ፈርሶ ፍትህ፤ነፃነት እና እውነተኛ ዴሞክራሲ ተገንብቶ እስከሚያይ ድረስ የጀመረውን ሁለ ገብ ትግል አጠናክሮ ይቀጥላል።
የተከበራችሁ ያገራችን ዜጎች ሆይ ስሙን ! እኔም አንዳርጋቸው ነኝ ማለታችሁ አንድ በጎ እርምጃ ነው። እኔም አንዳርጋቸው ነኝ ማለት አንዳርጋቸው ራሱን አሳልፎ ለሰጠው ድንቅ ዓላማ ራሳን አሳልፎ መስጠት ማለት መሆኑንም መረዳት ያስፈልጋል። አንዳርጋቸው የቆመለትን ዓላማ ለማስፈፀም እኛ ወደ እናንተ እሰከምንመጣ መጠበቅ የለባችሁም። በያላችሁበት አምስትም ስድስትም አስርም እየሆናችሁ የአርበኝነት ተግባር መፈፀም መጀመር አለባችሁ። የቀደመዉ ትውልድ ፋሽት ጣሊያንን በየመንደሩ እየተደራጀ እና የጎበዝ አለቃ እየመረጠ መፋለሙን አስታወሱ። እናንተም ከምታምኑት ጋር እየተደራጃችሁና የጎበዝ አለቃ እየመረጣችሁ የዘመኑን ፋሽስት ልትፋለሙት ይገባል። ዘመቻ አንዳርጋቸው ማለት እኔ ለነፃነቴ፤ እኔ ለፍትህ እና ለህግ የበላይነት፤ እኔ ከዘረኞቹና ከሌቦቹ ህወሃቶች የፀዳች አገር ለመፍጠር ተነስቼአለሁ ማለት ነው። ለዚህም ዓላማ ለመሞትና ለመግደል ዝግጁ ነኝ ልትሉ ግዜው አሁን ነው። እንደ ቀድሞ ዝም ብላችሁ የምትሞቱ ሳትሆኑ ለመግደልም የምትችሉ መሆኑን በተግባር ማሳየት መቻል አለባችሁ።
“ትግሬን ነፃ” እናወጣለን ብላችሁ የተነሳችሁ እናንት ነውረኞች ሆይ ስሙ ዓይናችሁ እያየ፤ ጆሯችሁም እየሰማ ከወገኖቻችን ጎን ሁነንና እጅ ለእጅ ተያይዘን ልትገነቡ የሞከራችሁትን የዘረኝነትና የዝሪፍያ መረብ እንበጣጥሰዋለን። እናንተ ዘረኞችና ዘራፊዎች ስሙ! ህዝብን እንዳስለቀስዋችሁ መቀጠል እንደማትችሉ እርግጠኛ ሁኑ። አገራችን ኢትዮጵያም እናንተን ከመሰሉ ምናምንቴዎች ፀድታ ህዝቦቿም በነፃነት የሚኖሩበት ግዜ እሩቅ አይደለም። ያን ግዜ በእናንተ ነውሮኞች ግፍ የሚያለቅስ ህዝብ አይኖርም። አበቃን!!!
ድል ለኢትዮጵያችን ይሁን !!!!

‹‹የአንዳርጋቸው ጽጌን የሞት ቅጣት ሊያፀኑ የሚችሉት ፕሬዚዳንቱ ናቸው›› ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ

July 20/2014
ባለፈው ዓርብ በጽሕፈት ቤታቸው ከጋዜጠኞች ጋር የተወያዩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የሞት ቅጣት ሊፀና የሚችለው በፕሬዚዳንቱ ይሁኝታ ብቻ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ላይ ያላት የመሪነት ሚና እንዳልቀነሰ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ መንግሥታቸው የአገር ውስጥ የግል ዘርፉን ለማበረታታት እየሠራ እንደሆነና የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትን እያሰረ ያለው በፖለቲካ አቋማቸው የተነሳ እንዳልሆነም ገልጸዋል፡፡ የደመወዝ ጭማሪውን መጠንም ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡

ዓርብ ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም. ከ9፡00 ጀምሮ ከሁለት ሰዓት በላይ በፈጀው ጋዜጣዊ መግለጫቸው ከጋዜጠኞች በርካታ ጥያቄዎችን ያስተናገዱ ሲሆን፣ ከእነዚህም አንዱ ሪፖርተር የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ በድጋሚ የማይታይ ከሆነ የሞት ፍርዱ ተፈጻሚ ይሆናል ወይ? ሲል የጠየቃቸው ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሞት ፍርድ ተፈጻሚ የሚሆነው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ካፀደቁት በኋላ እንደሆነ አስታውሰው፣ ይኼን ጥያቄ መመለስ የሚችሉት ፕሬዚዳንቱ ብቻ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ የነበራት ተሰሚነትና ተፅዕኖ ፈጣሪነት ስለመቀነሱ የተጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በደፈናው የኢትዮጵያ ተቀባይነት ቀንሷል ከማለት ይልቅ በየትኛው ዘርፍ እንደሆነ ተለይቶ ጥያቄው ቢቀርብ የተሻለ እንደሚሆን ካስረዱ በኋላ፣ በእሳቸው እምነት የኢትዮጵያ የመሪነት ሚና አሁንም እየቀጠለ ለመሆኑ ማሳያ የሚሏቸውን ጉዳዮች ጠቅሰዋል፡፡ የመጀመርያው ጉዳይ በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ላይ የአፍሪካውያንን ድምፅ ማሰማት ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ተፅዕኖ አሁንም ጉልህ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ እንደ ምሳሌም በዴንማርክ ጠቅላይ ሚኒስትር በሚመራው የአረንጓዴ ዕድገት ፎረም ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትሯ አማካይነት የቦርድ አባል ሆና መመረጧን ጠቅሰዋል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2015 የሚጠናቀቀው የምዕተ ዓመቱ የልማት ግቦች ከተጠናቀቀ በኋላ ስለሚቀጥለው ሁኔታ አፍሪካ ያላትን ድምፅ ለማሰማት ከተወከሉት አገሮች መካከል አንዷ ኢትዮጵያ እንደሆነችም አመላክተዋል፡፡ የዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት (አይሲሲ) አፍሪካ ላይ በተለየ ሁኔታ ትኩረት አድርጎ መሥራቱን ለመቃወም የተደረገውን ትግል በስኬት ለመደምደም፣ በተለይ የኬንያ ፕሬዚዳንት ክስ በሥልጣን ላይ እስካሉ ድረስ እንዳይነሳ ለማድረግ የኢትዮጵያ መሪነት ሚና ጉልህ እንደነበርም ጠቅሰዋል፡፡ ይኼን ስኬት የጠቀሱት ባለሥልጣናት ከተጠያቂነት ቢያመልጡ ደስተኛ ስለሆኑ ሳይሆን፣ የአገሮች ሉዓላዊነትና የሕዝቦች ምርጫ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ስለሆነ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እስርም የተለየ ፖለቲካ ስለሚያራምዱ የተወሰነ ውሳኔ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያንና አካባቢውን በሽብርተኝነት ለማናጋት በተቀናጀ ሁኔታ ከሚሠራው የሽብር መረብ ጋር ግንኙነት ፈጥረው በመገኘታቸው እንደሆነ አመልክተዋል፡፡ የጦማርያኑና የጋዜጠኞቹ ጉዳይም ከተመሳሳይ መረብ ጋር የተገናኘ እንደሆነ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ መንግሥታቸው የዜጎችን ሰላማዊ ኑሮ ለማረጋገጥ የሽብርተኝነት መረቡን ለመበጣጠስ የጀመረውን ስኬታማ ሥራ አጠናከሮ እንደሚቀጥልም ማረጋገጫ ሰጥተዋል፡፡ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ሥር ተወሽቀው የሽብር ተግባር ላይ ተሳታፊ የነበሩ ጥቂት ግለሰቦች ታሰሩ ማለት የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ታሰሩ ማለት እንዳልሆነም በመጠቆም፣ ለምርጫ 2007 ገዥው ፓርቲና ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እያደረጉት ያለው ዝግጅት ሊስተጓጎል እንደማይችልም አመላክተዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት አቶ አንዳርጋቸውና ግንቦት 7 ብቻቸውን ኢትዮጵያ ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ከባድ እንደማይሆን ቢገባውም፣ እነዚህ የሽብር ቡድኖች የተደገፏቸውና የሚተማመኑባቸው አገሮች ጋር ከሠሩ ጉዳቱ ከባድና አካባቢያዊ ተፅዕኖ ሊኖረው እንደሚችል ግን አስረድተዋል፡፡ በዚህም የተነሳ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በቁጥጥር ሥር መዋል በሽብርተኞቹ ላይ የሚያመጣው ተፅዕኖ ከባድ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ከአስመራ ወደ ደቡብ ሱዳን ለመዘርጋት የተሞከረው መረብ እየተበጣጠሰ ለመምጣቱ የአቶ አንዳርጋቸው መያዝ ማሳያ እንደሆነም አመልክተዋል፡፡ በቅርብ ጊዜያት የጋምቤላ ንቅናቄና የኦብነግ አባላት በቁጥር ሥር መዋላቸውም የሽብር ቡድኑ አባላት የሌላ አገር ዜግነት ቢኖራቸውም፣ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም እስከነኩና ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ባለው የሽብር ወንጀል እስከተካፈሉ ድረስ ዕርምጃ ከመውሰድ ኢትዮጵያን የሚያቆማት አካል እንደሌለም አስታውቀዋል፡፡ በተለያዩ ሙያዎች ውስጥና በፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ በመጠለል የሽብር ወንጀል ላይ ተካፋይ ከሆኑ በኋላ ከተጠያቂነት ለማምለጥ የውጭ ኃይሎችን በተለይም ኤምባሲዎችን በመጠቀም የኢትዮጵያን መንግሥት ለመጠምዘዝ ሙከራዎች እየተደረጉ እንደሆነ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የዜጎችን ሕገ መንግሥታዊ መብት በማክበር ሕጋዊ ዕርምጃ ከመውሰድ የሚያግዳቸው ኃይል እንደሌለ አመልክተዋል፡፡

በተደጋጋሚ የፋይናንስ ችግር የለም በሚል መንግሥታቸው ቢገልጽም፣ በዚህ ችግር በተለይ የአገር ውስጥ የግሉ ዘርፍ እየተጠቃ ስለመሆኑ የተጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ መንግሥት ለብድር ያስቀመጠውን ገንዘብ አሟጦ ጥቅም ላይ የሚያውል አካል ባልመጣበት ሁኔታ የገንዘብ ችግር አለ ማለት ተገቢ እንደማይመስላቸው ገልጸዋል፡፡ 70 በመቶ የባንክ ብድር ለማግኘት 30 በመቶ የፕሮጀክት ወጪ ማሳየት የሚጠይቅ ሕግ ያለ ሲሆን፣ የውጭ ባለሀብቶች ይህን 30 በመቶ ማሽንን በኮላተራልነት እያቀረቡ እያለ ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች መከልከሉ አግባብነት ያለው ስለመሆኑ የተጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የውጭ ባለሀብቶች ፋብሪካ በመንቀል ሲመጡ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስለሚያመጣ የተፈቀደ ቢሆንም ይህን የማድረግ አቅም ያለው የአገር ውስጥ ባለሀብት እስከመጣ ድረስ መንግሥት ለአገር ውስጥ ባለሀብቱ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚያጤነውም ቃል ገብተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ መንግሥታቸው ይፋ ባደረገው የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ ጭማሪ መጠን ላይ የተጠየቁ ሲሆን፣ በሐምሌ ወር መጨረሻ እስኪገለጽ ድረስ የመንግሥት ሠራተኞች በትዕግሥት እንዲጠባበቁ ጠይቀው፣ ገና የደመወዝ ጭማሪው መጠን ሳይታወቅ በአንዳንድ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ መታየቱ አሳሳቢ መሆኑን ግን ተቀብለዋል፡፡ መንግሥት የደመወዝ ጭማሪ ያደረገው ባለፉት ሁለት ዓመታት በገንዘብና በፊሲካል ፖሊሲው እንዲሁም በአስተዳደራዊ ዕርምጃዎች አማካይነት የዋጋ ግሽበቱን ኢኮኖሚያዊ ጤንነት ጋር በተጣጣመ መልኩ በአንድ አኃዝ እንዲገደብ ካደረገ በኋላ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡ የዋጋ ግሽበቱ የመንግሥት ሠራተኛውን ብቻ ሳይሆን በዝቅተኛ ደመወዝ ኑሯቸውን የሚገፉ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ እንደሚጎዳ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም፣ የዋጋ ግሽበትን ጉዳት በሚፈለገው መጠን መቀነስ ባይቻልም አነስተኛ ገቢ ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ገቢያቸው እንዲጨምርና የሥራ ዕድል እንዲፈጠርላቸው ለማድረግ መንግሥታቸው የተለያዩ ጥረቶችን እያደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የደመወዝ ማስተካከያው የሚደረገው የመንግሥት ሠራተኞችን ኑሮ ለማሻሻል ቢሆንም፣ ስግብግብ ነጋዴዎች የሚያደርጉት የዋጋ ጭማሪ ችግር እንዳይፈጥር መንግሥት ቁጥጥር እንደሚያደርግና አደብ እንዲገዙ ለማድረግ ዕርምጃ ሊወስድ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡፡ ይሁንና በአሁኑ ጊዜ መንግሥት ነጋዴዎቹን የማሳመንና የማስረዳት ሥራ እየሠራ መሆኑን በመጠቆም፣ ከሕጋዊ ዕርምጃ ባለፈ ማግባባት መምረጡን አስረድተዋል፡፡ ሕጋዊ ዕርምጃ የሚወሰደው ስግብግብ ነጋዴዎች ካስገደዱ ብቻ እንደሚሆንም አመላክተዋል፡፡

ምንጭ ሪፖርተር


Saturday, July 19, 2014

አቶ አንዳርጋቸው ታፍኖ የተወሰደበት ቦታ እስከአሁን አልታወቀም ነገር ግን በደህንነት ሰዎች በደረሰበት ድብደባ ራሱን በመሳቱ ለህክምና ከአዲስ አበባ ውጪ ይዘውት ወጠዋል የሚሉ አስተያየቶች እየተበራከቱ ነው።

July 19, 2014
አባይ ሚዲያ 
አቶ አንዳርጋቸው ታፍኖ የተወሰደበት ቦታ እስከአሁን አልታወቀም ነገር ግን በደህንነት ሰዎች በደረሰበት ድብደባ ራሱን በመሳቱ ለህክምና ከአዲስ አበባ ውጪ ይዘውት ወጠዋል የሚሉ አስተያየቶች እየተበራከቱ ነው።
ዛሬ የአዲስ አበባ ምንጫችን ብዙ ቦታዎችን ለማካለል ሞክሬ ነበር ነገር ግን የአንዳርጋቸው ይኖርበታል ተብሎ የሚገመቱ ቦታዎችን ማግኘት እንዳልቻለ ይሁን እንጂ ከደህነነት ሰዎች አንዱ በሆነ መኖሪያ ቤት ውስጥ ሊኖርም እንደሚችል የግል አስተያየቱን ልኮልናል።
ዘጋቢያችን አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በማናገር አቶ አንዳርጋቸው በአሁኑ ሰአት ከሰውነት ክፍሉ ውስጥ አንዱን ሰብረዉት ወይም ቆርጠውት እንደሚሆን  ስቃዩን በማብዛት ነገር ግን  እንዳይሞትባቸው ከአዲስ አበባ ውጪ ለህክምና ይዘውት ወጥተው ይሆናል የሚል በርካታ አስተያየቶች  መሰብሰቡን ዘግቦል።
አዲስ አበባ ላይ ሊያክሙት አይችሉም እንዴ ብለን ላነሳንለት ጥያቄ ሲመልስ፡ ይህን በአዲስ አበባ ሆስፒታሎች ሊያደርጉት አይችሉም 1ኛ መረጃው ይወጣባቸዋል የራሳቸውን ሆስፒታል እንኮን አዲስ አበባ ላይ አያምኑትም። በወያኔ ውስጥ ውጥረት አለ! ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሰውየውን ምን ማድረግ እንደሚገባቸው ግራ የገባቸው ይመስላል። ስለዚህ እውነትም በአካሉ ላይ ጉዳት ደርሶበት ከሆነ ወደ ማይታወቅበት ስፍራ ወስደው ሊያሳክሙት ይችላሉ የሚለው ገዢ ሃሳብ ያመዝናል።
ይሁን እንጂ አቶ አንዳርጋቸው በሚያደርሱበት ጭካኒያዊ ድብደባ ሂወቱ በድንገት ሊያልፍ የሚችልበት አጋጣሚም ከፍተኛ ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ ኢቲቪ ድብደባውን በመደበቅ በደረሰበት አደጋ  ሂዎቱ በእስር ቤት አለፈ የሚል ዜና ሊያሰማን ይችላል የሚል ስጋት አለኝ ሲል አያይዞ ስጋቱን ገልጾልናል።
በዚህ አጋጣሚ አቶ አንዳርጋቸውን የታፈነበትን አካባቢ እና ቦታ ለድህረ ገጻችን ከሀገር ውስጥ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን መረጃ ለምትሰጡን አባይ ሚዲያ ማበረታቻ እንደሚሰጥ ማሳወቅ እንፈልጋለን፡፡

የሰማያዊ ፓርቲዋ ወጣት ወይንሸት ሞላ ተፈንክታ፣ እጆቿ በፋሻ ጠቅልሎ፣ ሰውነቷ ዝሎ ፍርድ ቤት ቀረበች

July 19/2014
(ፎቶው የተገኘው ከሰማያዊ ፓርቲ ነው)
(ፎቶው የተገኘው ከሰማያዊ ፓርቲ ነው)
በትናንትናው እለት የአንዋር መስጊድ አካባቢ የሕወሓት አስተዳደር በንጹሃን የእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ አሰቃቂ እርምጃ እየወሰደ በሚገኝበት ወቅት መርካቶ አካባቢ ለሥራ ጉዳይ ሄዳ የነበረችው የሰማያዊ ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤትና የሴቶች ጉዳይ አባል ወጣት ወይንሸት ሞላ በደህነንቶች ታፍና ከተወሰደች በኋላ ከፍተኛ ድብደባ ሲፈጸምባት ቆይቶ በዝግ ችሎት ቀርባ 14 ቀን የምርመራ ቀጠሮ ተጠየቀባት።
የነፃ አሳቢ ዜጎች መሰቃያ በሆነውና ከማዕከላዊ አጠገብ በሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እስር ቤት ውስጥ የምትገኘው ወጣት ወይንሸት ማንም ሰው እንዳይጠይቃት በፖሊሶቹ መከለከሉ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
ዛሬ ረፋዱ ላይ ሜክሲኮ አካባቢ ያለ ፍርድ ቤት የቀረብቸው ወጣት ወይንሸት ምንም እንኳ ችሎቱ በዝግ ቢደረግም ጭንቅላቷ ተፈንክቶ፣ ቀኝ እጇ በፋሻ ተጠቅልሎና አንገቷ ታስሮ የተመለከቷት ሲሆን የህግ አማካሪ እንዳታገኝም ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ መከልከሉን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አረጋግጠዋል።
ከ ዘ-ሐበሻ የተወሰደ

የፕሬስ አፈናው በ”ሎሚ” መጽሔት ተጀመረ

July19/2014
ሐምሌ 7 ቀን 2006 ዓ.ም ከመንግስት በተላኩ ኃይሎች የ‹‹ሎሚ›› መጽሔት ቢሮ ‹‹ያለ ንግድ ፍቃድ›› በሚል ሠበብ ታሸገ፡፡ እነዚህ ከየትኛው ወገን እንደተላኩ ያልታወቁት ኃይሎች በቢሮ ውስጥ የነበሩትን የሂሳብ ሠነዶች ‹‹ይዘን እንሄዳለን፣ አትሄዱም›› በሚል በተፈጠረው እሰጥ አገባ ምክንያት ስልክ ደውለው ቁጥራቸው ከ20 ያላነሱ የታጠቁ የፌደራል ኃይሎችን በመጥራት እንዲሁም በድርጅቱ ውስጥ የሚገኙትን ንብረቶችና ወረቀቶችን ጨምሮ እንዳናወጣ በመከልከልና በማስፈራራት አስቀድመው ታዘው ይዘውት የመጡት ወረቀት “ያልታሰደ ንግድ ፍቃድ” የሚል ቢሆንም፣ ንግድ ፍቃዱ የታደሰበትን ማጋገጫ ሲመለከቱ ደግሞ ፊት ለፊታችን ወረቀቱን በመሠረዝ “ያለ ንግድ ፍቃድ” በሚል ጽፈው አሽገውታል፡፡ በወቅቱ ሐምሌ 12 ቀን 2006 ዓ.ም ለንባብ የምትበቃው ‹‹ሎሚ›› መጽሔት ወደ ማተሚያ ለመግባት በዝግጅት ላይ እንዳለች ይህ ችግር መፈጠሩ በሎሚ አባላቶች ላይ ግሬታን ቢፈጥርም፣ በተወሰደው ሕገ-ወጥ እርምጃ ሳንደናገጥ ከምንገባበት አንድ ቀን ዘግይተንም ቢሆን በተከፈለው ከፍተኛ መስዋዕትነት ማተሚያ ቤት ልናስገባ ችለናል፡፡ በወቅቱም ቢሮአችን እንደሚታሸግ ለምን አስቀድማችሁ በደብዳቤም ሆነ በስልክ አላሳወቃችሁንም ቢባሉም ‹‹የእናንተ ስፔሻል ኬዝ ነው፤ እኛ ከላይ ታዘን ነው›› የሚል ምላሽ ሠጥተዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የሎሚ መጽሔት አጋር ሆና በሣምንት ሁለቴ ለንባብ የምትበቃው ‹‹አፍሮ ታይምስ›› ጋዜጣም ከወዲሁ ልትዘጋ እንደምትችል አሁን በእስር ላይ የሚገኙት የዞን 9 አባሎች ያውቁ እንደነበር መረጃዎች እየጠቆሙ ይገኛሉ፡፡ ይኸውም እነዚሁ ኃይሎች ከመጀመሪያው ቀን በተለየ ሁኔታ በበነጋታው ተደራጅተው በመምጣት “ሠነዶችን እንፈልጋለን” በሚል ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በፌደራል ኃይሎች የታገዘ የ5 ሠዓታት ፍተሻ (ከብርበራ አይተናነስም) ከአካሄዱ በኋላ በቢሮ ውስጥ የሚገኙትን የሂሳብ ሠነዶች በሙሉ ሰብስበው ወስደዋል፡፡ ሆኖም ግን የምንፈልገው የሂሳብ ሠነዶችን ይበሉ እንጂ፣ በቢሮው ውስጥ የሚገኙትን በተለያዩ ጊዜ የታተሙ የሎሚ መጽሔቶች፣ የአፍሮ ታይምስ ጋዜጦችና በእጅ ጽሁፍ የተተየቡ ወረቀቶችን አንድ በአንድ ሲፈትሹ ተስተውሏል፡፡ ይሄ ሕገ-ወጥ እርምጃ የእኛ የፕሬስ ውጤቶች በሆኑት ሎሚ መጽሔትና አፍሮ ታይምስ ጋዜጣ ላይ ሆነ ተብሎ ለማጥቃት የታለመ መሆኑን የሚያመለክተው እነዚሁ ያልታወቁት ኃይሎች አስቀድመው ከመምጣታቸው በፊት ‹‹የአፍሮ ታይምስ ቢሮን ለማሸግ እየመጣን ነው›› በማለት የደወሉ ቢሆንም፣ ቢሮ ድረስ መጥተው የነበሩትን ሠነዶች ከወሰዱ በኋላም ከአለቆቻቸው ጋር በስልክ በመነጋገር ሊያሽጉበት ይዘውት መጥተው የነበረውን የማሸጊያ ወረቀት ሳያሽጉበት ተመልሰዋል፡፡

በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከአንድ ወር በፊት ገዢው መንግስት ነፃውን ፕሬስ ጥላሸት በመቀባትና እርምጃ እንደሚወስድ (ሎሚ መጽሔትን ጨምሮ) በፈበረካቸው የተለያዩ ዶክመንተሪዎቹ ሲዝት የቆየ ሲሆን፣ አሁን አፈናውን በሎሚ መጽሔት ‹‹አሃዱ›› ብሎ ጀምሯል፡፡ ሎሚ መጽሔትም ሆነ አፍሮ ታይምስ ጋዜጣ እራሱ ገዢው መንግስት ባወጣው የፕሬስ አዋጅ መሠረት ሕግና ደንቡን ተከትለን ለኢትዮጵያ ሕዝብ አማራጭ ድምጽ በመሆን ተገቢውን መረጃ በወቅቱ እያደረስን ቢሆንም፣ ይህንን ያልወደደው ገዢው መንግስት ነፃ ፕሬሱን ከነአካቴው ለማጥፋት የተለያዩ ወጥመዶችን እያዘጋጀ መሆኑን አንባቢያን እንድታውቁልን እንፈልጋለን፡፡ ውድ አንባቢዎቻችንም ይሄንን ተገንዝባችሁ እስከመጨረሻው ድረስ የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመቀበል ከጎናችን እንድትቆሙ እናሳስባለን፡፡

ለዴሞክራሲ ነፃነት በሚደረግ ትግል የሚሸበረው ማን ነው?!

July 19, 2014
ጌታቸው ፏፏቴ
መግቢያ፦ በሜዳ የሚደረገው ትግል እየጠነከረ ሲሄድና ዳሩ መሃል እየሆነ ሲመጣ ነገሮች ሁሉ አዳጋች ሲሆኑ ገዥዎች በሥልጣን ለመሰንበት የሚወስዷቸውን እርምጃዎች ከዚህ ቀደም ደርግ ይወስድ ከነበረው ርምጃ በቂ ትምህርት አግኝተናል። በጭፍን አስተሳሰብ ዐይኑ ያልወደደውን ሁሉ ወደ እስር ማጋዝና ነጻ ርምጃ በሚል ፈሊጥ በጅምላ ሕዝብ ጨፍጭፏል። «የፍየል ወጠጤ ልቡ ያበጠበት»ሳይባል የተገደሉትን ብርቅየ የኢትዮጵያ ልጆችማ ቤት ይቁጠራቸው።

ህወሃት አሁን የሚገኘበት ደረጃ የሚያሳየውም ያነውኑ ነው። በሰላማዊ መንገድ መታገል በራሱ በህወሃት ሕግ የተፈቀደ ነበር። ነገር ግን አንዲት ጠጠር ሳይወረውሩና ቅጠል ሳይበጥሱ ሕጉ በሚፈቅድላቸው መንገድ በመሄድ እየታገሉ ባሉ የተቃዋሚ ኃይሎች ላይ ህወሃት ያደረሰባቸውን እንግልት እስራትና ንብረት ዘረፋ ተመልክተናል። በአብዛኛው እኔ በመጣሁበት መንገድ ካልመጣችሁ በማለት ገፊ ሁኔታዎችን እየተነኮሰም ነው። የሰላማዊ ትግሉን እንዳይቻል አድርጐታል እንጅ ቢቻል በሰላማዊ መንገድ ታግሎ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ ሥልጣን መረከብ ወይም ማስረከብ የ21ኛው መቶ ዓመት ሥልጡን ህዝብ ጨዋ ሥነ-ምግባር ነበር። እነዚህ የኛ ድናቁርቶች ግን በሕገ-አራዊት እየተመሩ ነገር የሚገባቸው ሆነው አልተገኙም።

እነዚህ የዘረኛ ሥርዓት(አፓርታይድ)አራማጆች መንገዱ ሰለጠኝ ብላ ገበያውን አልፋ ሄደች እንዲሉ ኅሳዊ መሲኅ ለህዝብ ተቆርቋሪ በመምሰል የአጼውን ሥርዓት አውግዘው ነበር።ደርግ ይፈጽማቸው የነበሩ መጠነ ሰፊ ግፎችንም አጋኖ በማቅረብ የህዝብ መቀስቀሻ በማድረግ ተጠቅመውባቸዋል። ስለ ደርግ ፋሽስታዊ ድርጊት እየሰበኩ ግን ራሳቸው ከደርግ በከፋ ሁኔታ በራሳቸው አባልና በሕዝብ ላይ አሰቃቂ ተግባሮችን ይፈጽሙ ነበር። በተለይም በገበያ ቀንና በቤተክርስቲያን እንዲሁም ሕዝብ በብዛት በሚኖርባቸው መንደሮች ሆነ ብለው ጦርነት በመጫር ያስጨረሱት ሕዝብ የሚያስከፍላቸው ዋጋ በፍጹም ሊዘነጋ የሚችል አይደለም። አሁን ደግሞ በትረ ሥልጣኑን ከጨበጡ በኋላ መደበኛ ተግባራቸው ሕዝብን ማሰቃየት መግደልና ማሰደድ በነሱ መንደር እንደ አንድ ትልቅ እድገት የሚታይ ሆኗል። በህወሃት ጋብቻ ከመፈቀዱ በፊት ግንኙነት ፈጽማችኋል ተብለው የተገደሉ፤ኢትዮጵያዊ አስተሳሰብ(አመለካከት) አላችሁ ተብለው በሽዎች የሚቆጠሩ የህወሃት መከላከያ ሠራዊት አባላት ደብዛቸው መጥፋቱን የማያውቅ ይኖራል ብየ አልገምትም። የራሱን አባላት እየበላ የመጣው ህወሃት ነጻነት እናገኛለን ብለው ቦንብ እንደጨበጡ ታንክ ላይ የሚወጡ ወጣቶችን ህይወት ደመ-ከልብ (የውሻ ደም) ሆኖ ጥቂቶችን በመያዝ ዘልቆ አሁን ያሉበትን ደረጃ እየተመለከትን ነው። የሚያሳዝነው ነገር ቢኖር እኛ ሰዎች ለምን ካለፈው ስህተትና ውድቀታችን ተምረን ትክክለኛውን መንገድ መያዝ እንደማንችል ነው። አሁን ያለው የህወሃት የመከላከያ ሠራዊት ፤ የፖሊስ ሠራዊትና የሰላዩ ቡድን(የህወሃት ደህንነት) ደህንነቱን ደህንነት ሲሰልለውና ሲያስረው፤ፖሊሱን ፖሊሱ ሲያስረው፤የመከላከያ ሠራዊቱ በኋላውና በፊቱ በሁለት ጥይት ሲመታና ደብዛውን ሲያጠፉት ምን እየጠበቀ ነው?

በትክክለኛው አተረጓጎም ህወሃትን መግለጽ የተቻለ ባይሆንም በገደምዳሜው በቅርቡ በናይጀሪያ አዲስ ስያሜ ይዞ ብቅ ያለው«ቦኮሐራም» ሕጻናትን እያፈነ ድራሻቸውን እንዳጠፋው ህወሃት ለ23 ዓመታት ያህል በቆየበት የግዛት ዘመኑ ተኪ የማይገኝላቸው ኢትዮጵያውያንን በልቷል። አሁንም ከኢትዮጵያም አልፎ እጁን በማስረዘም የኢትዮጵያ አጎራባች በሆኑ አገሮች እየፈጸመ ያለው የጠለፋ ተግባር ኢትዮጵያውያንን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያሳስብ ጉዳይ ነው። ወራሪው የህወሃት ቡድን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተህዶ ቤተክርስቲያንና በአማራ ነገድ ሕዝብ ላይ ፋሽስታዊ ዘመቻ ከጀመረ አርባ ዓመት አሳልፏል።አሁንም ያን የአውሬ ፋሽስታዊ ባህሪውን አጠናክሮ ቀጥሎበታል። ከምርጫ 1997 ዓ/ም ወዲህ ህወሃት ያደረጋቸውን እንቅስቃሴዎች ስንመለከት ድሮ አውሬ የነበረ ቢሆንም አሁን ደግሞ አውሬነቱ ብሶበት ቀጥሏል። በቤተክርስቲያን በኩል አሁን ያለውን ሁኔታ ስንመለከት ህወሃት ተሳክቶለታል የሚያስብል አንድምታ አለ።ህወሃታዊ ቤተክርስቲያናት አገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በውጭው ዓለምም እንደ-አሸን ፈልተዋል።በውጭው ዓለም የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ሥርዓቱ ያሰደደው ሆኖ ሳለ ለዚህ ስደተኛ ኢትዮጵያዊ የውጭው ስደተኛው ሲኖዶስ ወይም ህወሃታዊ ያልሆነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በቂ ነበር።ህወሃት ግን በስደትም በሰላም እንዳንኖር እያደረገ ያለ መሆኑን ነቅቶ የጠበቀው ያለ አይመስልም።የትግሬ ቤተክርስቲያን፤ የኦሮሞ፤ የአማራ …ወዘተ እየተባለ ለሕይወቱ ዋስትና አጥቶ የተሰደደውን ኢትዮጵያዊ ሰላም እንዲያጣና ተከፋፍሎ እንዲቆም አድርጓል።

የአማራውን ነገድ ዘር ማጥፋትና ማስወገድ በተመለከተ መደረግ ያለበትን ሁሉ ህወሃት ያደረገ ቢሆንም መላውን የአማራ ህዝብ ለማጥፋት አልተቻለም።በርግጥ ሮጠው የሚቀድሙ፤ታግለው የሚጥሉትንና ተናግረው የሚያሰሙትን የክፉ ቀን ደራሽ ቁርጠኛ ትውልደ አማራዎች ቀጥፎ በልቷል።እንዴት እነማንን?የሚል ጥያቄ የሚያነሳ ካለ በሕይወቱ እንዳለ አድርጎ መቁጠር ያስቸግራል።ለሆዱ ያደረውን ዐሣማ ፍጡር(ሆዳም አማራ)ሆዱን በማምለክ ከህወሃት ለሚጣልለት ፍርፋሪ ሲል የራሱን ህዝብ ማዋረዱ ማሳደዱና ነዳጅ ሆኖ ማስፈጀቱ የሚያስከፍለውን ዋጋ ይህ ነው ባይባልም መታሰብ ይኖርበታል።ከዚህ ባሻገር ያለው ትውልደ አማራ ግን ለምን ያንጎላቻል ብሎ መጠየቅ ተገቢ ስለሆነ ተጠየቅን እንካችሁ እላለሁ።

ዛሬ በአብዛኛው ድምጻቸውን ከፍ አድርገው የሚያሰሙት ትውልደ አማራ የሆኑ ወጣቶች ናቸው ይህን ጩኸት ህወሃት አልወደደውም ምክንያቱም የቤት ሥራውን መጨረሱን በራሱ ሚዲያ ተናግሮ ስለነበር አሁን ያለው ትውልድ የህወሃት ሰለባ አለመሆኑን በማስመስከሩና ታሪኩን የጠበቀ ሆኖ በመገኘቱ እነ አባይ በረከትና አዲሱ ለገሠ(የመለስ ራእይ አስፈጻሚዎች) ሌላ አይነት መንገድ እየተከተሉ እንደሆነ ማሳያዎችን በሰሞኑ አስመስክረዋል።

የዛሬዎቹ ዘመናዊ ፋሽስት መሪዎች በርሃ እያሉ ድሎት ጎድሎባቸው አያውቅም የቀን ሐሩር የሌሊት ቁር አቀበት ቁልቁለት አልወጡ አልወረዱም፤ አውደ ውጊያ ውስጥ ገብተው ማንነታቸው አልተፈተነም።ታጋዩንም ሆነ ህዝቡን ግራ በማጋባት የዛሬዋን ወንበር የሚጨብጡበት መንገድ ነበር ያጠኑ የነበረው።ቀኝም ነፈሰ ግራ ለአርባ ዓመት ያህል ጥርሳቸው እስኪነቃነቅ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሀብት ግጠው በልተዋል፤አለ የለም የሚባለውን የህዝብ ሀብት ዘርፈው በውጭው ዓለም ከፍተኛ የንግድ ቱጃሮች ሆነዋል።የሀገሪቱን ሀብት ለመጥፎ ተግባር እንዲውል በማድረግ መንገዱ ሁሉ ቀና እንዲሆንላቸው የሚቃወማቸውን የአንድነት ኃይልም ማስጠለፍ ጀምረዋል።

የህወሃት ቡድን የፀረ ሽብር ሕግ ሲያወጣ ከህዝብ የተነጠለ መሆኑን ያስመሰከረበት ወቅት ሲሆን ይህ የአሸበሪ ህግ እማን ላይ እንደሚመዘዝ አስቀድሞ ገብቶኛል።መፍትሔው ግን ያ አልነበረም የኢትዮጵያ ሕዝብ የጠማው መልካም አስተዳደር፤የሕግ የበላይነትና ሰላም ነበር።ከህዝቡ መሀል የፈለቁ ሥርዓቱን የሚቃወሙ ሰላም ፤የህግ የበላይነትና መልካም አስተዳደር እንዲኖር የሚታገሉትን ማጥመድ የህወሃት ዋና ተግባርእንደሚሆን እገምት ስለነበር ያ ያሰጋኝ ነገር እውን ሆነ። እውነቱን እንነጋገር ካልን አልቃይዳንም ሆነ አልሸባብን የሚቀርበው ህወሃት እንጅ የተቃዋሚ ኃይሎች ወይም የኢትዮጵያ ህዝብ አይደለም።ሩዋንዳ፤ ደቡብ ሱዳንና ሶማሌ የተዘመተውም የዶላር ጥማትን ለማርካት እንጅ ሰላምን ለማምጣት አለመሆኑን እርግጠኛ ነበርኩ አሁንም ነኝ።

በተደጋጋሚ ለሚዲያዎች በማቀርባቸው ጹሑፎቼ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ የሚሰማኝን ለአንባብያን ሳቀርብ እውቀቱ ያለው የረሳውን አስታውሶ ጠንከር ያለ ጹሑፍ እንዲያወጣ ሲሆን ጥሩ ምልክቶችንም አይቸበታለሁ።በአንድ አገር የአሸባሪ ሕግ ሲወጣ ካለው ነበራዊ ሁኔታ ተነስቶ መሆን እንዳለበትና ሕዝብን የሚያሰጋ ሲሆን እንደሆነ ይገባኛል። የህወሃት የአሸባሪዎች ሕግ መሠረቱ ግን በትረ ሥልጣን ላይ ያለው ቡድን አጭበርብሮ ሥልጣን የያዘ በመሆኑ እድሜውን ለማራዘም ያለመው ፈጠራ እንጅ ሕዝብን እያሸበረ ያለውማ ህወሃት ነው።ህወሃት በንግግር ከተሸበረ፤በሚፃፍ ነገር ከተሸበረ፤በተደራጀ ኃይል ከተሸበረ፤የአመጽ ትግል በጀመረ ኃይል ከተሸበረ፤የእምነት ነፃነት ይከበር ብሎ የተመመ ሕዝብ ቁጣ ካሸበረው የማን ጥፋት ነው?ጎበዝ ልብ በሉልልኝ ጅራፍ ራሷ ገርፋ እራሷ ትጮሃለች አይደለም እንዴ?

አንዳርጋቸው ጽጌ ዛሬ በራእዩ የሚገዛት የማቹ መለስ ዜናዊ የትምህርት ቤት ጓደኛ እንደነበር ሰምቻለሁ የመለስ ራእይ አስፈፃሚዎች ከየመን መንግሥት ጋር በመመሳጠር አንዳርጋቸው በጎዞ ላይ እንዳለ የመን ውስጥ ስናዐ ላይ ተጠልፎ ለወሮ በላው ህወሃት ቡድን ተላልፎ ተሰጥቶ በደህንነት ኃይሎች እንደ እባብ እየተቀጠቀጠ እንዳለ ይታወቃል።

አንዳርጋቸው ማድረግ የሚገባውን አድርጓል ቀሪውን ሂሳብ ድርጅቱ ይወጣዋል ብየ አስባለሁ።አስቂኙ ትራጀዲ ግን ወጣት የህወሃት አፓርታይድን የሚታገሉ የተቃዋሚ ድርጅት አባላትን ለቅሞ ወደ እሥር ቤት ማስገባት ምን አመጣው?የሚለው ነው።

ከሕዝብ ተነጥሎ በኃይል ሕዝብን አንበርክኮ መግዛት የማይቻል መሆኑን ህወሃቶች ከደርግ ወታደራዊ አገዛዝ መማር ካልቻሉ እዳውን መቀበል ያለበት ያው ባለእዳው እንጅ ማንም ሊሆን አይችልም።ቁም ነገሩ ግን በኢትዮጵያ በቅድመ አብዮትና ድሕረ አብዮት ተዋናኝ የነበርን መሪና ተመሪዎች በፈጸምነው ከባድ ወንጀል የነገውን አገር ተረካቢ ትልድ እጣ ፈንታ ላይ መርዝ መጨመራችን ለምን አናቋርጥም?አብርሃ ደስታ ወጣት ነው፤የሽዋስ አሰፋ ወጣት ነው፤ሀብታሙ አያሌው ወጣት ነው። ሁሉም ወደ እሥር ቤት የተጋዙት የሕሊና እሥረኞች ወጣቶች ናቸው ታዲያ ለምንና እንዴት እንዲሰቃዩ ተወሰነ? እኔ እንጃ ሂሳቡ ሲወራረድ ህወሃቶች መድረሻችሁን ሳስብ ክፉ ቀን ይታየኛል።

የነገሩን ክብደት ወደ ሚዛን ወይም ስኬል እንውሰደው ከተባለ በዚህ ሰው በላ ሥርዓት የተጠራቀመ ቡድን እኩል ይሰፈራል ብየ አላስብም ምክንያቱም አድማስ የጠበበት ፤ለሆዱ ያደረ ፤ተገዥነቱን አምኖ የተቀበለ ድብልቅ አንድ ላይ ያለ ስለሆነ ትንሽም ብትሆን የህዝቡ ብሶት ረፍት የሚነሳው ካለ በጊዜ ቦታውን እንዲፈልግ አቅጣጫ ማሳየት ይገባናል።ኢትዮጵያ የዳቦ ቅርጫት ነበረች አዎ! ኢትዮጵያ የአለም ስደተኞች መጠጊያ ነበረች አዎ! ኢትዮጵያ ነፃነቷን አስከብራ የኖረችና ኃያላን የአውሮፓ ወራሪዎችን ያንበረከከች አገር ነች አዎ! ኢትዮጵያ የዓለም ትውልድ የመጀመሪያ አገር ነች አዎ! አሁንስ? ዛሬ እያየን ያለው ግን የዚያን ግልባጭ ነው።ለምን እንዴት? ችግሩ ምንድን ነው?

እንግዲህ እነዚህን የመሳሰሉ ችግሮች ከፊታችን ተጋርጠው እያለ ነው በጎሳ(በዘር) በሥልጣን ጥማትና በተራ ጓደኝነት ትልቁን የሀገር ጉዳይ ዘንግተን እሰጥ አገባ እያልን ህወሃትን ከዚህ ያደረስነው። ደወሉ የመጨረሻው መሆኑን ህወሃት/ኢህአዴግ የተረዳ መሆኑን በግልጽ በመናገር አቅጣጫችን ስለህወሃት አራዊታዊ ባኅሪና ጨፍጫፊነት የምንሰብክበት ጊዜ ሳይሆን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የተቃዋሚ ኃይሎች ወደ አንድነት እንዲመጡ ተፅዕኖ ማሳደር ፤ከምንም በላይ የሕዝቡን ጉዳይ ወደ ጎን በመተው ሥልጣንን መሠረት ያደረገ አተካራ ላይ የሚገኙትን የተቃዋሚ ኃይሎች ሕዝብ እንዲያገላቸው ማድረግና በሀገር ቤትም ሆነ በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ አንድ ሁለት እያለ በመሰባሰብ ከህወሃት የሚሰነዘርበትን ማኛውም ጥቃት መመከት ከሚችልበት ደረጃ ማድረስ የህወሃትን ግብዓተ መሬት ፍጻሜ ማፋጠን አለብን። ይህ ሀገርን የማዳን ወይም ኢትዮጵያን የማቆየት ወይም ስትጠፋ ተስማምቶ እንደ ማጥፋት ስለሚቆጠር የኢትዮጵያን ሕዝብና ኢትዮጵያን የሚወድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ጥርሱን ነክሶ ወገቡን አጥብቆ አስሮ መታገል ያለበት አሁን በመሆኑ አብረን በጋራ እንነሳ ኢትዮጵያን እናድን።

ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቿ በክብር ትኖራለች!!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!


Friday, July 18, 2014

Ethiopia charges journalists with 'terrorism'

July18/2014

Three journalists and seven bloggers, in prison since April, accused of plotting "to destablise the nation".

A group of Ethiopian bloggers and journalists held in jail for nearly three months have been charged with terrorism for having links to an outlawed group and for planning attacks, a judge said.
The seven members of the blogging collective Zone Nine and three journalists were arrested in April, prompting an outcry from rights groups who said the case was an assault on press freedom.
"They took training in how to make explosives and planned to train others," Judge Tareke Alemayehu told the court on Friday.
The judge said their work was a cover for "clandestine" activities and accused them of plotting "to destabilise the nation".
The group is accused of planning attacks in Ethiopia and working in collusion with the US-based opposition group Ginbot 7, labelled by Ethiopian authorities as a terrorist organisation.
Charges rejected
The Zone Nine website, proclaiming "we blog because we care!" features mostly social and political commentary, often critical of the government.
Nine of the accused smiled and waved to friends and family as they entered the packed courtroom. The tenth defendant is being charged in absentia.
The lawyer for eight of the suspects dismissed the charges.
"We don't believe that there is any credible substance," Amaha Mekonnen told AFP.
Rights groups have accused Ethiopia of using the anti-terrorism laws to silence dissent and jail critics.
Several journalists have been jailed under the law, including two Swedish journalists sentenced to 11 years in prison in 2012. They were pardoned after serving 15 months.
The dissident blogger Eskinder Nega is serving an 18-year sentence for having links with Ginbot 7, which calls for the violent overthrow of the ruling party.
The trial for the bloggers and journalists is expected to resume on August 4.
Source

ጁምዓ በፖሊስ ጥቁር ሽብር ተናወጠ

July18/2014
ዛሬ አርብ ጁምዓ ነበር። የረመዳን ጾም እንደመሆኑ መጠን፤ ለስግደት በጣም ብዙ ሺህ ህዝብ ወደ ታላቁ አንዋር መስጊድ ሄዷል። ከኢህአዴግ ጋር ተመሳጥረው ሙስሊም ወንድሞቻቸውን አሳልፈው በሰጡ እና የ”ኮሚቴ አባሎች” ይፈቱ በሚሉ ሰላማዊ ሙስሊሞች መካከል የተፈጠረው ውጥረት አሁንም እንዳለ ነው። ኢህአዴግ መራሹ መንግስትም ይህን የመከፋፈል አጋጣሚ በመጠቀም፤ “ድምጻችን ይሰማ” የሚሉ ወገኖችን በመደብደብ እና በማሰር መፍትሄ ለማግኘት የሚያደርገውን ጥረት ቀጥሏል። ይህ አይነቱ በጨለምተኝነት ላይ የተመሰረተ የኢህአዴግ ድርጊት፤ በህዝብ ላይ የሚተገበር “ጥቁር ሽብር” ከማለት ውጪ ሌላ ትርጉም የሚሰጠው አይደለም። ለዚህም ነው በርእሳችን ላይ “ጁምዓ በፖሊስ ጥቁር ሽብር ተናወጠ” ያልነው።  ይህ ሽብር እና ነውጥ ምን ይመስል እንደነበር የበለጠ ለመረዳት በስፍራው ተገኝተው፤ የአይን ምስክር ሆነው ዘገባቸውን ያቀረቡትን የጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና የጌታቸው ሽፈራውን ዜና መመልከት በቂ ነው። በቅድሚያ ጋዜጠኛ ኤልያስን ዘገባ እናስቀድማለን።
ፖሊስ አዲስ1
በብጥብጥ የተቋጨው የጁምዓ ስግደት በአንዋር መስጊድ (ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ)
መጽሐፍ ሳነብ ስለነበር በጣም አምሽቼ የተኛሁት፡፡ ጠዋት አረፍጄ ተነሳሁ፡፡ ቁርሴንም ሳልበላ ወደ አንዋር መስኪድ አመራሁ፡፡ ከፒያሣ ጀምሮ መንገድ የተዘጋጋ ስለነበረ፤ ከሦስት ሙስሊም ወንድሞቼ ጋር አንድ ላዳ ታክሲ ኮንትራት ይዘን አቆራረጥን ታላቁ አንዋር መስኪድ ደረስን፡፡ አካባቢው በሙስሊሙ ማኅበረሰብ ተሞልቷል፡፡ አብዛኛው ምንጣፍ እና ካኪ ወረቀት አንጥፈው ለጁምዓ ጸሎት እና ለስግደት ተቀምጠዋል – አስፋልቱን ጭምር ተጠቅመውበታል፡፡ ለመቀመጫ ቦታ ያላገኙት ቆመው ከመስኪዱ በአረብኛ ቋንቋ የሚነገረውን ምስጋና (ትምህርት) በጥሞና እየተለታተሉ ነው፡፡
በርከት ያሉ ፖሊሶች በመስኪዱ አቅርቢያ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ቆመዋል – ረዥም ሽመል ይዘዋል! እኔም እንደ ጋዜጠኛ የሙስሊሞቹን ሰላማዊ ተቃውሞ ለመከታታል በማሰብ ነው አንዋር መስኪድ የተገኘሁት፡፡ ከመስኪዱ ራቅ ብዬ በመቆም ሁኔታውን መከታተል ጀመርኩ፡፡ ነገሮች ሰላማዊ ነበሩ፡፡ ከሥፍራው ከተገኘሁ ከአሥራ አምስት ደቂቃ በኋላ በመስኪዱ ዋና በር አካባቢ ወረቀቶች ወደ ላይ ይበተኑ ጀመር፡፡ ሦስት፣ አራት ቦታም ተመሳሳይ ወረቆች መበተናቸውን ቀጠሉ፡፡ 
ወዲያው፣ ከርቀት ከመስኪዱ በስተቀኝ በኩል ረብሻ ነገር ተመለከትኩ፡፡ ድንጋይ ሲወረውር እና ፖሊሶች ዱላ እንደያዙ ሲሯራጡም ማየት ችያለሁ፡፡
አድማ በታኝ ፖሊሶች በጅናድ በኩል አድርገው ወደ አንዋር መስኪድ ሲሄዱ (ኢ.ኤም.ኤፍ)
አድማ በታኝ ፖሊሶች በጅናድ በኩል አድርገው ወደ አንዋር መስኪድ ሲሄዱ (ኢ.ኤም.ኤፍ)

አፍታም ሳይቆይ አካባቢው በሰዎች ሩጫ፣ በረብሻና በፖሊሶች ማሳደድ ትርምስምሱ ወጣ፡፡ ብዙ ሰው በአካባቢው ወደሚገኙ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች እየዘለለ መግባት ጀመረ፡፡ ነገሮች ለአፍታ ጋብ ያሉ ቢመስሉም ሁኔታው በድጋሚ ተቀሰቀሰ፡፡ በርካታ ፖሊሶች ወደ መኖሪያ ሰፈሮች እና ግቢዎች ውስጥ ዱላቸውን ይዘው በመግባት ሰዎች ማባረር፣ ማሳደድና በዱላ መማታት ጀመሩ፡፡ 
እኔም ከሦስት ፖሊሶች ጋር ከአንድ መኖሪያ ግቢ ውስጥ ተፋጥጬ ነበር፡፡ አንድ ዱላ ሲሰነዘርብኝ በእጄ ተንቀሳቃሽ ኮምፕዩተር (ላፕቶፕ) ይዤ ስለነበረ እሱ ከፍ በማድረግ ዱላው የላፕቶፕ ቦርሳዬ ላይ አረፈ፡፡ የቀኝ እጄ ጠቋሚ ጣት ግን ከበትሩ ማምለጥ ሳይቻለው ቀረ፡፡

ጥቁር ሽብር
… ከበሩ ፊት ለፊት የነበሩት ፖሊሶች ጥለውን ሄዱ፡፡ ወደ አሜሪካን ግቢ በጉራንጉር ውስጥ አልፌ ብሄድም ድብደባው እና ወከባው በዚህ አለ፡፡ ብዙ ወጣቶች ተደብድበው፣ ጭንቅላታቸው ተበረቃቅሶ ደም በደም ሆነው ተመልክቻለሁ፡፡
በዛሬው ዕለት ምስቅልቅሏ የወጣውን መርካቶ በቻልኩት አቅም ለማየት ችያለሁ፡፡ ሱቆች ተዘጋግተዋል፡፡ አንዋር መስኪድ በፌዴራል ፖሊስ ባልደረቦች እና መኪኖች ተከብቦ ነበር፡፡ አድማ በታኝ ፖሊሶችም በምዕራብ ሆቴል ቁልቁል በሰልፍ ሲያዘግሙ እና ሰፊዋ መርካቶ በፌዴራል ፖሊሶች ተወርራ ነበር፡፡
በጥቅሉ በዛሬው የአንዋር መስኪድ የጁምዓን ጸሎት ተከትሎ የተፈጠረው ሁኔታ አሳዛኝ እና ዘግናኝ ሆኖብኛል፡፡
————————
የጋዘጠኛ ኤልያስ ገብሩ ዘገባ እዚህ ላይ ያበቃል። ከስፍራው ሌላም ዘገባ ደርሶናል።ጌታቸው ሽፈራው በስፍራው ተገኝቶ ያየው እና የታዘበውን እንዲህ አስቀምጦታል።
መንግስት በህዝብ ላይ ያደረሰው ሽብር ካበቃ በኋላ።
መንግስት በህዝብ ላይ ያደረሰው ሽብር ካበቃ በኋላ። (ፎቶ ኢ.ኤም.ኤፍ)
ጭካኔ በአንዋር መስጊድ!
እነዛ ሰላማዊ ሙስሊም ወጣቶች ያለ ርህራሄ እንደዳጉሳ ሲወቀጡ አየሁ፡፡ ህጻን፣ ሽማግሌ፣ ሴት፣ ርጉዝ ሳይባል
በጭካኔ ተደበደቡ፡፡ ታፈሱ! አንዱ ደብድቦ ያሳለፈውን ሌላኛው በተራው ይቀበለዋል፡፡ ተዝለፍልፎ የወደቀ የወደቀበት ላይ ይወቀጣል፡፡ ወጣቶቹ አገር ሰላም ነው ብለው ለመስገጃ የወሰዷቸው መስገጃ ወረቀቶች ደም
በደም ሆነዋል፡፡
ፖሊስ አዲስ2
ፖሊስና ደህንነቶች በድብደባው ቢሳተፉም ያለ ርህራሄ ወጣት አዛውንቱን በቆመጥ የተደባደቡት ከየ
ጎዳናው የተለቀሙት ወጣቶች ናቸው፡፡
አንዳንዶቹ የጎዳና ተዳዳሪዎች ለመሆናቸው አለባበሳቸው በግልጽ ያሳያል፡፡ ፖሊስ አትደብድቡ እያላቸው
እንኳን የሚሰሙ አይደለም፡፡ ሽጉጥ ማቀባበል የማይችሉት ሽጉጥ ተሰጥቷቸው ሲያስፈራሩ ካርታው ሲወርድባቸው ተመልክቻለሁ፡፡
በወቅቱ የሰማያዊ ፓርቲ የሰማያዊ ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆነችው ወጣት ወይንሸት ሞላ አብራኝ ነበረች፡፡ አንዋር መስጊድ በወንዶች መግቢያ ፊት ለፊት ካለው ህንጻ ላይ ሆነን ሁነቱን ስንከታተል ከአሁን ቀደም የሚያውቃትና ከህንጻ ላይ ሆኖ ሲቀርጽ የነበር ደህንነት ብቻዋን ነጥሎ እየደበደበ ወሰዳት፡፡
‹‹ለምን ተወስዳታለህ!›› ብዬ በጠበኩበት ወቅት ከእነዛ ከመንገድ ተለቃቅመው ለድብደባ የተሰማሩት ወጣቶች መካከል አንዱ ሽጉጥ አወጣብኝ፡፡ ለመሳሪያ ልምድ የሌለው በመሆኑ ካርታው እግሩ ስር ወደቀበት፡፡
ወይንሸትን ይዘውም ወደ ውጭ ከነፉ!
ፖሊስ አዲስ3
ወይንሸት ከተያዘች በኋላ የእነዛ አረመኔዎች ዱላ እኛም ላይ አረፈ፡፡ ፖሊሶች ደክሟቸውን ይሁን አዝነው
ሲተውን ከየት እንደመጡ የማይታወቁት ወጣቶች ግን እስኪበቃቸው ደብድበውናል፡፡
በድብደባው መሃል አንድ ፖሊስ ክርስቲያን መሆኔን በመግለጽ ከአዛውንቶችና ከህጻናት ጋር ስለቀላቀለኝ እንደነዛ ወጣቶች ተዝለፍልፎ ከመውደቅ ተርፌያለሁ፡፡
እንግዲህ አንድ አገር እስከኖርን ድረስ፣ ጭቆናውም የሁላችን እስከሆነ ድረስ ሁላችንም ነጻ ካልወጣን ማንም ነጻ ሊወጣ አይችልምና እኔም እንደወንድሞቼ በአጠና ተደብድቤ ተለቅቄያለሁ፡፡ ግን አልተሰማኝም፡፡ ከእኔው ይልቅ የማይችሉት ዱላ ያረፈባቸው ህጻናትና አዛውንቶች ጣር ልብ ይሰብራል፡፡ ወይንሸት ላይ ያረፈው በትር ያማል!
ኢ.ኤም.ኤፍ

የዘንድሮ እስር ‹‹ጸበል ቅመሱ›› ሁነብኝ ጃል! (ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ)

July18/2014

(የህገ-መንግሥቱ አንቀጽ 30 ሳይሻር ተሽሮ ከሆነ መሻሩን ተቃዋሚዎች ይወቁት!)
========
የምንወዳት ኢትዮጵያ ሀገራችን በተለያዩ ሥርዓታት ውስጥ የተለያዩ የሰዎችን እስር አስተናግዳለች፤ ዛሬም እያስተናገደች ትገኛለች፡፡
በ97 ዓ.ም ምርጫውን ተከትሎ የቅንጅት አመራሮች፣ የግል ጋዜጠኞችና የሲቪክ ማኅበራት አመራሮች …ታስረው ከአንድ ዓመት ከዘጠኝ ወራት በኋላ በይቅርታ፣ በነጻ …መፈታቸው ይታወሳል፡፡ ከዚህ ጊዜም በኋላ፣ በተለይ አፋኝ በሆነው የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጁ ብዙዎች ታስረዋል፣ እየታሰሩም ይገኛሉ፡፡
ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ጎዳና
ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ጎዳና
በዘንድሮ ዓመት ግን የምናየው እስር የተለየ ሆነብኝ፡፡ የሕገ- መንግሥቱን አንቀ ጽ 30 መሰረት በማድረግ ሰላማዊ ሰልፍ የሚጠሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች እና አባላቶቻቸው ለሰልፉ ቅስቀሳ በሚያደርጉበት ወቅት እየተያዙ ለቀናቶች ታስረው መፈታት የተለመደ ሆነ፡፡ (ወይ ይህ የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 30 ሳይሻር ተሽሮ ከሆነ መሻሩን ተቃዋሚዎች ይወቁት!)
አንድነት እና ሰማያዊ ፓርቲዎች ይሄንን እርምጃ ዘንድሮ በደንብ አይተውታል ብል ማጋነን አይሆንብኝም፡፡ ይሄም ብቻ አይደለም፣ ጋዜጠኞች፣ ጦማሪያኖች፣ ፖለቲከኞችና በርካታ ዜጎች በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ታስረዋል፣ ክስም ተመስርቶባቸዋል፡፡
በዛሬው ዕለት ደግሞ የምርጫ ሥነ-ምግባር ደንቡን በመፈረም የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባል የሆነው ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) የፊታችን ቅዳሜ ሜክሲኮ በሚገው የመብራት ሐይል አዳራሽ ህዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ አቅዶ ስድስት አባላቱ ዛሬ ቂርቆስ አካባቢ በመኪና ህዝቡን በመቀስቀስ ላይ እያሉ መታሰራቸውን ሰማን፡፡
ፖሊስም ‹‹የስብሰባ እንጂ የቅስቀሳ ፈቃድ አልያዛችሁም›› በማለት ጥዋት አካባቢ በፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እንዳሰራቸው እና የፓርቲው አመራሮች በፖሊስ ጣቢያ ድረስ በመገኘት ከኃላፊዎቹ ጋር ቢነጋገሩም ልጆቹ ቃላቸውን መስጠታቸውንና ፖሊስ ልቀቃቸው የሚል ትዕዛዝ ሲደርሰው እለቃቸዋለሁ ማለቱን ወዳቻችን ዳዊት ሰለሞን በፌስ ቡክ ገጹ ዛሬ አስነብቦን ነበር፡፡
እኔም እንደጋዜጠኛ ጉዳዩን ለማጣራት የቀድሞ የኢዴፓ ሊቀመንበር ወደሆኑት አቶ ሙሴ ሰሙ ተንቀሳቃሽ ስልክ ላይ ደውዬ እውነት መሆኑን አረጋግጫለሁ፡፡ እንዲያውም፣ አቶ ሙሼ የተደረገው ነገር አግባብ አለመሆኑን በመጥቀስ በነገው ዕለት በግል መኪናቸው ቅስቀሳ ለማድረግ ማቀዳቸውን አጽንኦት ሰጥተው ነግረውኛል፡፡
እንዲሁም፣ በዛሬው ዕለት በእነሀብታሙ አያሌው የክስ መዝገብ አንድነት ፓርቲ ላቀረበው አቤቱታ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በአራዳ ፍርድ ቤት ለማድመጥ በችሎት ተገኝተው የነበሩ ስድስት የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አባላት (ዳንኤል ፈይሳ፣ አብነት ረጋሳ፣ ጥላዬ ታረቀኝ፣ ፋሲካ አዱኛ፣ ብርሀኑ ይግለጡና መሰለ አድማሴ) በደህነት ሃይሎች ተይዘው በቶዮታ ደብል ጋቢና ኮድ 3-50559 መኪና ወደ ማዕከላዊ መወሰዳቸውን የፍኖተ ነፃነት የማዕከላዊ ምንጮች ገልጸው ነበር፡፡ ከሰዓታት በኋላም የታሰሩት የፓርቲው አባላት ተፈትዋል፡፡
እስያዊቷ ሀገር ማሌዥያ፣ የመንገደኛ አውሮፕሏኖቿ አንዴ ሲሰወሩ፣ አንዴ ሲከሰከሱና በሮኬት ሚሳይል ሲመቱ ዛሬም ድረስ ደርሰዋል፡፡ በዛሬው ዕለት እንኳን ከሆላንድ አመስተርዳም ወደ ማሌዥያ ኩዋላላምፑር ሲጓዝ የነበረ ቦይንግ 777 የመንገደኞች አውሮፕላን በሮኬት ሚሳይል ተመትቶ (በራሽያ መሆኑ እየተነገረ ነው) በዩክሬን ግዛት በመከስከስ 295 ሰዎች አልቀዋል፡፡ 
በሀገራችን ደግሞ ሁሉን ዓቀፍ የእስር እርምጃ በመንግሥታችን እየተወሰደ መመልከቱ ቀጥሏል፡፡ ለዚህም ነው፣ በርዕሴ ‹‹የዘንድሮ እስር ‹‹ጸበል ቅመሱ›› ሁነብኝ ጃል!›› በማለት የገለጽኩት፡፡
ወዳጄ ዳዊት ሰለሞንም “Ethiopia the land of prisoners” (ኢትዮጵያ የእስረኞች ምድር) የሚል መልዕክት ከአምስት ሰዓታቶች በፊት በፌስ ቡክ ገጹ አስፍሮ ተመልክቻለሁ፡፡ ማሌዥያ በአውሮፕላን አሳዛኝ አደጋ ጣጣ በዓለም ስትታወቅ እኛ ደግሞ ዜጎችን በገፍ መማሰር እንታወቅ?!
እኔ ደጋግሜ ብያለሁ፣ እስር መፍትሄ አይደለም፡፡ ዜጎችን ማሰር ብዙ የማይገርምበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡ መንግስታችን ሆይ! ዜጎችን የማሰር ጉዞውን በአንክሮ አስብበት! አሊያ… ከባድ ነው! መዘዝ አለው፡፡
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር! —

በወቅታዊ የአገራችን ጉዳይ… ማን ምን አለ?

July18/2014
ኢ.ኤም.ኤፍ) ሰሞኑን ከታሰሩት ጋዜጠኞች እስከ አንዳርጋቸው ጽጌ እና የሙስሊም ኮሚቴዎች ድረስ ሰዎች የየራሳቸውን ሃሳብ እና አስተያየት ይሰጣሉ። እነዚህ ሃሳብ እና አስተያየቶች ሚዛን የሚደፉ ሆነው ስላገኘናቸው፤ ለናንተም ለታሪክም ለህትመት ማብቃቱ መልካም ነው ብለን አሰብን። በመሆኑም የጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ፣ አበበ ገላው አቡ ዳውድ ኡስማን እና ዮናታን ተስፋዬ ያሉትን አቅርበንላችኋል። ከዚህ ቀጥሎ ይነበባል።
ኤልያስ ገብሩ ስለሃብታሙ አያሌው የተናገረው….
ዛሬ በእስር ላይ የሚገኘውን የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የሕዝብ ግንኘነት ኃላፊ የሆነውን ሀብታሙ አያሌውን በሥራ አጋጣሚ ቅርበት አውቀዋለሁ፡፡
በእሱ ላይ የነበረኝን ጥያቄ አቅርቤለትም ደስ ብሎት፣ በዝርዝር መልሶልኝ አስረድቶኛል፡፡ጥቂት የማይባሉ ሰዎች ‹‹ሀብታሙ ትናንት እንዲህ ነበር፣ እንዲያነው …ወዘተ›› እያሉ ሚዛን የማይደፉ ንግግሮችን ሲናገሩ በእርጋታ አድምጫቸው አውቃለሁ፡፡ ሰዎች ይህንን መሰል ሃሳብ የማንሸራሸር መብት አላቸው ብዬ አምናለሁ፡፡
እኔ ግን፣ ሀብታሙን ሳውቀው ንቁ፣ ብዙ ሃሳቦች ያሉት፣ ስለሀገሩ ያገባኛል የሚል፣ ደፋር ሆኖ ያመነበትን በድፍረት የሚናገር፣ እንደ ንቁ ፖለቲከኛ ለጋዜጠኞች መረጃን በዝርዝር የሚሰጥ፣ ኃይማኖተኛ፣ ፈገግታ የማይለየው፣ ጎበዝ የአደባባይ ፖለቲከኛ የሆነ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡
ለሚነሳለት ሃሳብ ወይም ትችት ሃሳብን በሃሳብ የሚመልስ ልጅነው – ሀብታሙ፡፡
(አንዳንዶች የቀረበላቸውን ሀሳብ ወይም ትችት ፊት ለፊት መመለስ ወይም መሞገት ሲያቅታቸው ወደስድብ እና ዘለፋ ወይም ወዳልታሰበ ሀሳብ ሲነጉዱ እያየሁ ፈገግ እላለሁ፣ እስቃለሁ፣ ከምር ያስቁኛል)
ሃብታሙን ግን ሃሳብን በሃሳብ ከሚመልሱ ውስን የኢትዮጵያ ልጆች መካከል አንዱ ሆኖ አገኘሁትና ደስም አለኝ፡፡ ጠንካራ እና ጀግና ልብስላለውም ወደድኩት!
———————————————–
አበበ ገላው ስለወቅታዊ ሁኔታ የተናገረው…
በአሁኑ ግዜ መታሰር የሚያስፈራበት ግዜ አልፏል። ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ሰው እኛንም እሰሩን እያለ ነው። ሽብረተኛ ተብሎ መከሰስ የሚያስከብር እንጂ የሚያሸማቅቅ መሆኑ ቀርቷል።
የተቃዋሚ ፓርቲዎች በጋራ በሺዎች የሚቆጠሩ አባላቶቻቸውን ሰብስበው እኛም አሸባሪዎች ነን እሰሩን ብለው አደባባይ በየግዜው በተከታታይ እንዲወጡ ቢያደርጉ ብዙ ሰው ፍርሃቱ የበለጠ ይለቀዋል። ለሚታሰሩ ሰዎች እና ለቤተሰቦቻቸው ድጋፍ የሚያደርጉ ስብስቦች በየአካባቢው ሊቋቋሙ ይገባል። አንዱ ሲታሰር ያልታሰረው ድጋፍ ያድርግ። እስኪሚሊዮኖችን ሲያስሩ እናያቸዋለን።
እነርሱ በፍርሃት ሰውን ሁሉ አሸባሪ እያሉ የሚኖርበት ግዜ በጋራ ትግል ማክተም ይገባዋል።
——————————————–
‪አቡ ዳውድ ኡስማን የሙስሊም ኮሚቴዎችን የፍርድ ሂደት አስመልክቶ ያስተላለፈው መልእክት
የኮሚቴዎቻችን እና  የወንድሞቻችን የመከላከያ ምስክር ለፍርድ ቤቱ የማስደመጡ ሂደት በነገው ዕለት ሃምሌ 10 በከፍተኛው ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት እንደሚካሄድ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ከዚህ ቀደም ሲካሄድበት ከነበረው ከቃሊቲ 08 አዳራሽ ለውጥ ተደርጎ ከሲ ኤም ሲ አደባባይ ወደ ቀኝ 200 ሜትር ገባ ብሎ ባጃጆች ካሉበት ወደ ቀኝ ታጥፎ ዲቦራ ት/ቤት አካባቢ በሚገኘው በከፍተኛ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት እንደሚካሄድ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ ይህ ችሎት አዲስ የተገነባ እና ሰፊ የችሎት አዳራሽ እንዳለው ተዘግቧል፡፡
ህዝበ ሙስሊሙም የተለመደውን አጋርነቱን በችሎቱ በመገኘት ለኮሚቴዎቻችን እና ለወንድሞቻችን ሊገለፅ ይገባል፡፡
ፍትህ ለኮሚቴዎቻችን እና ለመላው ሙስሊም ይሁን!!
አላህ ይፈርጃቸው!!
———————————-
ዮናታን ተስፋዬ ስለፍርድ ቤቶች እና የፍርድ ሂደቱ የተናገረው
ፍርድ ቤት ምንም ፍትህ እንደማይገኝ እያወቅነው ለምን ራሳችንን እንደምናታልል አይገባኝም፡፡ ለምን በፍርድ ቤቱና በፍርድ ሂደቱ ተስፋ እንደምናደርግ ልረዳውአልቻልኩም፡፡ ሁሉ ነገር ታፍኖ ሀግ የማያከብር አምባገነን እንኳን ፍርድ ቤት ቀርበው ገና ሳይታሰሩ ውሳኔ አሳልፎ አይናችን ላይ ድራማ እየሰራ እኛ አሁንም ፍርድ ቤት ላይ አይናችን አልተነቀለም፡፡
ለታገቱት ታጋዮች አጋርነትን ማሳየታችን እንደተጠበቀ ሆኖ ፍርድ ቤቱን ትተን ሁላችንም ተራችን ደርሶ እክንታፈን መታገል አለብን፡፡
መታሰር ተራ ነገር እንደሆነ እስካሁን የሄድንበት መንገድ አመላካች ነው፡፡ ስለዚህ በፍርድ ቤት ውሎ ወሬ ጉጉት ከሚገድለን ሀሳባችንና ጉልበታችንን ከምናባክን ለወያኔም ከምንመቸው ትግሉን ማፋፋም ይሻለናል፡፡ ያኔ ሁላችንም ታስረን ሁላችንም ነፃእንወጣለን፡፡ እስከዚያው ጪአማራጭ የለም፡፡ ማንም ለኛ የሚቆምልን የለም እያንዳንዳችን ስለእውነት በፅናት መቆም አለብን፡፡
ራሳችንን ነፃ እናውጣ!