Wednesday, March 12, 2014

በሐረር ከተማ አንድ የገበያ ማዕከል በእሳት ቃጠሎ ወደመ

march12/2014

የተቃጠለው ንብረት ከአሥር ሚሊዮን ብር በላይ ተገምቷል

በሐረሪ ክልል ሐረር ከተማ ውስጥ በታችኛው ሸዋበር አካባቢ በሚገኘውና ‹‹መብራት ኃይል ግቢ የገበያ ማዕከል›› በሚል መጠሪያ የሚታወቀው የገበያ ማዕከል፣ የካቲት 30 ቀን 2006 ዓ.ም. ከምሽቱ 2፡35 ሰዓት ላይ መነሻው ባልታወቀ የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ ተቃጥሎ መውደሙ ተጠቆመ፡፡

ከሦስት ዓመታት በፊት ‹‹በድንገት የተፈጠረ ነው›› በተባለ ተመሳሳይ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ መውደሙ ለሚታወሰው የሸዋበር የገበያ ማዕከል ተጐጂዎች፣ የክልሉ መንግሥት ‹‹ቋሚ የገበያ ማዕከል እስከሚገነባ ድረስ›› በሚል ከበፊቱ የገበያ ማዕከል ፊት ለፊት አስፓልት ተሻግሮ በሚገኘው የኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ይዞታ በሆነ ሰፊ ቦታ ላይ እንዲነግዱ ፈቅዶላቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡

በወቅቱ ተጐጂ የነበሩ የከተማው ነዋሪ ነጋዴዎች ላለፉት ሦስት ዓመታት ሲነግዱ የክልሉ መንግሥት ዘመናዊ የሆነና ‹‹ደከር›› የተባለ የገበያ ማዕከል መገንባቱን በማስታወቅ ወደዚያ እንዲገቡ ሲወተውታቸው እንደነበር ጉዳቱ የደረሰባቸው አንዳንድ ነጋዴዎች ገልጸዋል፡፡

አዲስ የተገነባው የገበያ ማዕከል ከከተማው ወጣ ብሎ ገጠራማ ቦታ ላይ ስለሚገኝ ለገዥም ሆነ ለሻጭ የማያመች በመሆኑ፣ ሁሉም ነጋዴዎች አለመስማማታቸውን የገለጹት ተጐጂዎቹ፣ ድንገት ተነሳ የተባለው ቃጠሎ ምናልባት ሆን ተብሎ ቦታውን በዚህ አጋጣሚ ለማስለቀቅ የተደረገና የታሰበበት ሳይሆን እንደማይቀር መጠራጠራቸውን ገልጸዋል፡፡

የወደሙት ሱቆች ከ200 በላይ ሊሆኑ እንደሚችሉና ከአሥር ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ይኖራቸዋል የሚሉት ነጋዴዎቹ፣ የተወሰነውን እንኳን ለማትረፍ በሚል የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎችን የጠሩ ቢሆንም፣ ውኃ ካለመኖሩም በተጨማሪ በወቅቱ ደረሱ የተባሉት የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎች የሚረጩት ውኃ እሳቱን ከማጥፋት ይልቅ ሲያባብስ በማየታቸው የሚረጨውን ፈሳሽም መጠራጠራቸውን ተናግረዋል፡፡

ቤተሰቦቻቸውን የሚረዱበት፣ ልጆቻቸውን የሚያስተምሩበትና ራሳቸውን የሚያስተዳድሩበት ንብረታቸው በእሳት እንደወደመባቸው ነጋዴዎች፣ መጋቢት 1 ቀን 2006 ዓ.ም.  ወደ ሐረር ከተማ ከንቲባ ቢሮ የሄዱ ቢሆንም ተስፋ የሚሰጥ ነገር ካለማግኘታቸውም በተጨማሪ፣ በፖሊስ እንዲበተኑ በመደረጋቸው በየጐዳናው ላይ ሲያለቅሱ መዋላቸውን ገልጸው፣ በየበረዳንው ላይ የተኙና የተወሰኑትም ራሳቸውን ስተው ወደ ሆስፒታል የገቡ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

ከቃጠሎው የተረፈ ነገር ይኑር ወይም አይኑር ተጠግተው ማረጋገጥ ሳይችሉ የገበያ ማዕከሉ በግሬደር መታረሱን የገለጹት ተጐጂዎቹ፣ የክልሉ መንግሥት በገበያ ማዕከሉ ምን ያህል የንግድ ዕቃዎች ይንቀሳቀሱ እንደነበር ስለሚያውቅ፣ ቢያንስ ቢያንስ መቋቋሚያ የሚሆንና ሥራ የሚጀምሩበት ቦታና መነሻ ካፒታል ሊሰጣቸው እንደሚገባ ጠይቀዋል፡፡

ከሦስት ዓመታት በፊት የተቃጠለው የገበያ ማዕከል ያለምንም ግንባታ ታጥሮ መቀመጡን የገለጹት ነጋዴዎቹ፣ ቦታውን ለኢንቨስተሮች ለመስጠት አሁን የተቃጠለውም ለተመሳሳይ ጉዳይ ስለሚሆን የእነሱን ጉዳይ ለጊዜው እንጂ ግርግሩ ካለፈ በኋላ ዘወር ብሎ የሚያየው እንደሌለና ሥጋት እንደገባቸውም ገልጸዋል፡፡

በእሳት ቃጠሎ የወደመው የገበያ ማዕከል በአንድ በኩል ገደል በመሆኑ በርካታ ሌቦች ከእሳቱ ጋር እየተሻሙ ብዙ ንብረቶችን መዝረፋቸው በመታወቁ፣ ፖሊስ በርካቶቹን በቁጥጥር ሥር አውሎ የተወሰነ ዕቃ እያስመለሰ ቢሆንም፣ የትኛው ዕቃ የማን እንደሆነ መለየት ስለማይቻል ከመወረስ ያለፈ ፋይዳ እንደሌለው ነጋዴዎቹ ገልጸዋል፡፡

በሐረር ከተማ የታችኛው ሸዋበር መብራት ኃይል የገበያ ማዕከል የካቲት 30 ቀን 2006 ዓ.ም. ምሽት ላይ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ ወደሙ ስለተባሉት ሱቆች ማብራሪያ እንዲሰጡ የክልሉ ማዘጋጃ ቤት፣ ፖሊስና የሚመለከተው አካልን ለማግኘት የተደረገው ጥረት ‹‹ስብሰባ ላይ ናቸው›› በሚል ምላሽ አልተሳካልንም፡፡ በሐረር ከተማ በታዋቂው የጀጐል ግንብ ውስጥ የሚገኘው ‘መጋላ ጉዶ’ ባህላዊ የገበያ ማዕከልና ሌሎች ከትናንሽ የባህል ገበያዎች መኖራቸው ይታወቃል፡፡ የካቲት 30 ቀን 2006 ዓ.ም. የተቃጠለው የታችኛው ሸዋበር መብራ ኃይል የገበያ ማዕከል ግን በኮንትሮባንድ የሚገቡ ትላልቅና አነስተኛ ዘመናዊ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ልብሶችና ሌሎችም ሸቀጣ ሸቀጦች የሚገኙበት ታዋቂ ገበያ መሆኑንም ነጋዴዎቹ አውስተዋል፡፡

በሐረር ከተማ የገበያ ማዕከል ላይ የደረሰውን የእሳት ቃጠሎ በሚመለከት የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) መግለጫ አውጥቷል፡፡ የክልሉ መንግሥት የእሳት ቃጠሎ የደረሰባቸውን ወገኖች ማፅናናት ሲገባው በተቻኮለና በተመሳሳይ ቀን የተቃጠለውን የገበያ ማዕከል በግሬደር ማረሱን ተቃውሟል፡፡ ችግሩን ቆም ብሎ በማሰብ ሌላ ጉዳት እንዳይደርስ መጠንቀቅና መፍትሔ መስጠት እንዳለበትም ኢዴፓ አሳስቧል፡፡

የፕሬዚዳንቱን ይቅርታ የማድረግ ሥልጣን የሚቀንስ አዋጅ ቀረበ

march12/2014

-የፓርላማ አባላት ከሕገ መንግሥቱ ጋር እንዲጣጣም ጠይቀዋል


የአገሪቱ ፕሬዚዳንትን ለሕግ ታራሚዎች ይቅርታ የማድረግ ሥልጣን የሚቀንስ አዲስ ‹‹የይቅርታ አሰጣጥና አፈጻጸም ሥነ ሥርዓት›› ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማው ቀረበ፡፡ አንዳንድ የፓርላማው አባላት ረቂቅ አዋጁ ከሕገ መንግሥቱ ጋር ይቃረናል በማለት እንዲስተካከል ጠይቀዋል፡፡

የፕሬዚዳንቱን ሥልጣንና ተግባር የሚዘረዝረው የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 71 (7) ‹‹ፕሬዚዳንቱ በሕግ መሠረት ይቅርታ ያደርጋል›› በማለት ይደነግጋል፡፡

በ1996 ዓ.ም. የወጣው በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ የሚገኘው የይቅርታ ሥነ ሥርዓት አዋጅም በሕገ መንግሥቱ ለፕሬዚዳንቱ የተሰጠውን ይቅርታ የማድረግ ሥልጣን ያጠናክረዋል፡፡ በዚህ አዋጅ መሠረት ፕሬዚዳንቱ የይቅርታ ቦርድ የውሳኔ ሐሳብን መሠረት በማድረግ፣ እንዲሁም በውሳኔ ሐሳቡ ላይ የቀረቡ መረጃዎችን ፕሬዚዳንቱ በራሱ መመዘን ለሕግ ታራሚዎች ይቅርታ እንዲያደርግ ወይም እንዲከለክል ሥልጣን ይሰጠዋል፡፡ የፕሬዚዳንቱን ይቅርታ ያገኘ ታራሚ በሕጉ መሠረት የተጣለበትን ጥሶ የተገኘ ከሆነ በይቅርታ ቦርዱ የውሳኔ ሐሳብ አቅራቢነት ፕሬዚዳንቱ የሰጠውን ይቅርታ የማንሳት መብት በዚሁ በሥራ ላይ ባለው አዋጅ ለፕሬዚዳንቱ ተሰጥቷል፡፡

ባለፈው ማክሰኞ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ግን፣ ‹‹ፕሬዚዳንቱ የይቅርታ ቦርድን የውሳኔ ሐሳብ መሠረት በማድረግ ይቅርታ ይሰጣል፤›› ሲል በረቂቁ ክፍል ሁለት አንቀጽ 4 (1) ላይ አስቀምጧል፡፡ በማከልም ቦርዱ ለፕሬዚዳንቱ የሚልከው የውሳኔ ሐሳብ ይቅርታ የተወሰነላቸውን ታራሚዎች በመተለከተ ብቻ ነው፡፡

 በቦርዱ ውሳኔ አቅራቢነት ፕሬዚዳንቱ ቀደም ሲል የሚሰጠውን ይቅርታ የመሰረዝ መብት አሁን በሥራ ላይ ባለው አዋጅ ቢኖረውም፣ ለፓርላማው የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ግን በፕሬዚዳንቱ የተሰጠ ይቅርታ ተጥሶ ወይም የተጭበረበረ መሆኑ ሲረጋገጥ ቦርዱ ያለፕሬዚዳንቱ ውሳኔ በራሱ እንዲሰረዝ ያደርጋል ይላል፡፡ ‹‹ቦርዱ ይቅርታ የሚሰጣቸውን ሰዎች ብቻ ለይቶ ለፕሬዚዳንቱ ስለሚያቀርብ ፕሬዚዳንቱም በቦርዱ የውሳኔ ሐሳብ መሠረት ብቻ ይቅርታ ስለሚሰጡ የይቅርታ መሰረዝን በተመለከተ ወደ ፕሬዚዳንቱ የውሳኔ ሐሳብ ማቅረብ ተገቢነት የለውም፤›› በማለት ከረቂቅ አዋጁ ጋር የተያያዘው ማብራሪያ ያስረዳል፡፡

የተሰጠ ይቅርታ ዋጋ የሚያጣባቸው ምክንያቶች ሁለት መሆናቸውን፣ እነዚህም የተሰጠው ይቅርታ በተጭበረበረ ማስረጃ ላይ የተመሠረተ እንደሆነና ይቅርታው ሲሰጥ የተቀመጠው ቅድመ ሁኔታ ከተጣሰ የሚሉ ምክንያቶች ናቸው፡፡ ሕገ መንግሥቱ ለፕሬዚዳንቱ የሚሰጠውን ለታራሚዎች ይቅርታ የማድረግ ኃላፊነት ይጋፋል በማለት አንዳንድ የምክር ቤቱ አባላት ረቂቅ አዋጁ መስተካከል እንደሚገባው ጠይቀዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ በቦርዱ ውሳኔ ይቅርታ ይሰጣሉ በማለት ረቂቅ አዋጁ ያስቀምጣል፡፡ ነገር ግን ፕሬዚዳንቱ ባይቀበሉትስ? ይህ ማለት ውሳኔው ያለቀው እታች ነው ማለት ነው በማለት የረቂቅ አዋጁን ድንጋጌ ተችተዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ የሰጠውን ይቅርታ ቦርዱ ያለፕሬዚዳንቱ እውቅና ማንሳት እንደሚችል የሚገልጽ ድንጋጌ መካተቱ ተገቢ አለመሆኑን አባላቱ ገልጸዋል፡፡

 ከዚህ በተጨማሪም የፕሬዚዳንቱ ይቅርታ የመስጠት ሥልጣን እንዳስፈላጊነቱ አግባብ ላለው የክልል መንግሥት አካል በውክልና መስጠትና የይቅርታ ጥያቄዎችን የሚመረምረው ቦርድም በተመሳሳይ በክልል ለሚቋቋሙ ቦርዶች ውክልና ሊሰጥ እንደሚችል በረቂቅ አዋጁ ተካቷል፡፡ ረቂቅ አዋጁ በሥራ ላይ ካለው አዋጅ በተለየ ሁኔታ ይቅርታን የሚያስከለክሉ ወንጀሎችን ይዘረዝራል፡፡ ሙስና፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ግብረ ሰዶም፣ ሽብርተኝነት፣ አደገኛ ዕፅ ማምረት፣ ማዘዋወር፣ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም፣ በመሠረተ ልማት አውታሮች ላይ የሚፈጸም ወንጀል፣ በሴቶችና በሕፃናት ላይ የሚፈጸም የጠለፋና የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ይህ ቢሆንም መንግሥት የይቅርታ ዓላማን ያሳካል ብሎ ካመነበት በረቂቅ አዋጁ ይቅርታን የሚያስከለክሉ ወንጀሎች ምክንያት ሆነው ሊቀርቡ እንደማይችሉ ረቂቅ አዋጁ ይደነግጋል፡፡

 በተጨማሪ መንግሥት በሚያወጣው ደንብ መሠረት በሚዘረዘሩ ሌሎች ወንጀሎች ይቅርታ የማይጠየቅባቸው ሊኖሩ እንደሚችሉ ያስቀምጣል፡፡ የፓርላማው አንዳንድ አባላት ከላይ የተጠቀሰውን ድንጋጌ፣ ረቂቅ አዋጁ ይቅርታ የሚከለከልባቸውን ወንጀሎች መዘርዘር ከጀመረ በኋላ ሌሎች ወንጀሎች ደግሞ በሚወጣ ደንብ እንዲዘረዘሩ ማለቱ ግራ እንደሚያጋባቸው፣ የወንጀል ዓይነቶቹን  ሙሉ በሙሉ መዘርዘር ወይም ይቅርታ የሚያስከለክልባቸውን መርህ ብቻ ማስቀመጥ ነው በማለት እንዲስተካከል ጠይቀዋል፡፡

ረቂቅ አዋጁ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕግ አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ ለሚመራው የፓርላማው የሕግ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር ዕይታ ተመርቷል፡፡

የአውሮፓ ሕብረት በአዲስ አበባ መንግስትን እና ተቃዋሚዎችን እያነጋገረ ነው

march12/2014

የፖለቲካ ምህዳር መስፋት፣ የ2007 ምርጫ፣ የታሳሪዎች ጉዳይ በአጀንዳነት ተነስቷል
ከዘሪሁን ሙሉጌታ

በአውሮፓ ኅብረት የአፍሪካና የኢትዮጵያ ቋሚ አምባሳደር የኢትዮጵያ መንግስትንና የተቃዋሚ ፓርቲዎችን እያነጋገረ ነው። የኅብረቱ ቋሚ አምባሳደር አማካኝነት መካሄድ የጀመረው ውይይት በሀገሪቱ የፖለቲካ መህዳር መስፋት፣ በ2007ቱ ምርጫ፣ ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ የታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች እንዲሁም በሀገሪቱ ስላለው የሰብአዊና የዴሞክራሲ መብቶች ዙርያ መሆኑ ታውቋል።

ባለፈው ዓመት የኅብረቱ ቋሚ አምባሳደር በመሆን የተሾሙት አምባሳደር ቻንታል ሔብሪች ኅብረቱን በመወከል በኢትዮጵያ ውስጥ የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የበለጠ የሚከበሩበትን ገንቢ አማራጭ እያፈላለጉ ነው። በዚህም የአምባሳደሯ እንቅስቃሴ መሠረት የካቲት 26 ቀን 2006 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በመገኘት ከሌሎች የአውሮፓ ሀገራት አምባሳደሮች ጋር በመሆን በሀገሪቱ አጠቃላይ የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ዙሪያ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ውይይት አካሂደዋል። አምባሳደሩ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ውይይት ካካሄዱ ከአምስት ቀናት በኋላ በሀገሪቱ ካሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አንዱ ከሆነው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አመራር አባላት ጋር በጽ/ቤታቸው ውይይት አካሂደዋል::

በአውሮፓ ኅብረት የአፍሪካና የኢትዮጵያ አምባሳደር ቻንታል ሔብሪች ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ጋር በተወያዩበት ወቅት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳሩ ዴሞክራሲያዊ ሕጋዊ መሠረት የተከተለ እንዲሆን የኢትዮጵያ መንግስት በርካታ ስራዎችን እየሰራ ላይ ቢሆንም፤ የበለጠ መሻሻል በሚገባቸው ቀሪ ስራዎች መወያየታቸው መዘገቡ ይታወሳል። በተጨማሪም በመጪው ዓመት የሚካሄደው ብሔራዊ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ በሚሆንበት ጉዳይ ላይ መወያየታቸው አይዘነጋም።

በተመሳሳይ ባለፈው ሰኞ መጋቢት 1 ቀን 2006 ዓ.ም በአውሮፓ ኅብረት ጽ/ቤት የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራውና የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ከኅብረቱ አምባሳደር ቻንታል ሔብሪች እንዲሁም በአውሮፓ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድና የህንድ ውቅያኖስ ክፍል ኃላፊ ጋር ውይይት አካሂደዋል። በውይይቱም በአጠቃላይ ፓርቲው እያደረገ ስላለው እንቅስቃሴና “የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት” በሚለው የፓርቲው ክፍል ሁለት ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ላይ ማብራሪያ መጠየቃቸውን፣ የገዢው ፓርቲ የመሬት ፖሊሲ በሀገሪቱ መሬት የጥያቄ የኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ጥያቄ በመሆኑ በጥቅሉ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ጤናማ እንዳይሆንና መንግስታዊ የሙስና ሥርዓት እንዲጎለብት መደረጉን አርሦ አደሩም ከድህነት እንዳይወጣ በማድረግ ዋነኛ የዴሞክራሲ ማፈኛ መሆኑን ማስረዳታቸውን በውይይቱ የተሳተፉት አቶ ሀብታሙ አያሌው ለሰንደቅ ጋዜጣ ገልፀዋል።
ከዚህ ጎን ለጎን በእስር ስለሚገኙ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች የፓርቲው አመራሮችን በተመለከተ ማብራሪያ መስጠታቸውን፣ አቶ አስራት ጣሴ ስለታሰሩበት ምክንያት፣ ምርጫ 2007 ላይ ፓርቲው ስላለው አቋም፣ በኢትዮጵያ የመብት ጥሰቱ በምን ደረጃ ላይ እንዳለና በስቴት ዲፓርትመንት ሪፖርት፣ የሚዲያ ሞኖፖሊና የግል ፕሬሱ ወዳከም ጋር የተያያዙ ችግሮች ዙሪያ ውይይት ማካሄዱን ከአቶ ሀብታሙ ገለፃ መረዳት ተችሏል።
በመጪው ሚያዚያ ወር ብራስልስ ላይ የአውሮፓ ኅብረትና የአፍሪካ ኅብረት በሚያካሂዱት የግራ ስብሰባ ላይ የአንድነት ፓርቲ ተወካይ ተገኝቶ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ ላይ ንግግር እንዲያደርግ ጥያቄ መቅረቡንም አቶ ሀብታሙ አያይዘው ገልፀዋል።

የአውሮፓ ኅብረት በገዢው ፓርቲ እና በተቃዋሚዎች መካከል ገንቢ ውይይት ተደርጎ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓቱ ከፍ ማድረግ አለበት ያሉት አቶ ሀብታሙ፣ ይህ ካልሆነ ግን በምስራቅ አፍሪካ አደገኛ ወደሆነ የፖለቲካ አለመረጋጋት ሊፈጠር እንደሚችል ገልፀዋል።

የአውሮፓ ኅብረት ከተለያዩ ሀገራት ጋር ሰፊ የልማት፣ የቴክኒክ ድጋፎች እንደሚያደርግ ይታወቃል። በምትኩ ሀገራቱ የዜጎቻቸውን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲያከብሩ ከፍተኛ ግፊት ያደርጋል። ኢትዮጵያም የሎሜ ኮንቬንሽንን እ.ኤ.አ በ1975 ዓ.ም ከፈረመች ጊዜ አንስቶ ከኅብረቱ ጋር የልማት ትብብር መስርታለች፤ ኅብረቱም በአውሮፓ የልማት ፈንድ (European Development Fund) (EDF) እገዛ ያደርጋል። በተለይ በትራንስፖርት፣ በገጠር ልማት፣ ባልተማከለ የማኅበራዊ አገልግሎት ድጋፍ፣ በንግድ፣ በጾታ በሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ እና በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ ሀገሪቱን ይደግፋል። የድጋፍ መጠኑም በቅርቡም ወደ 600 ሚሊዬን ፓውንድ ይደርሳል።

አዲሲቷ የኅብረቱ ቋሚ አምባሳደር በመንግስትና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል የተካረረውን ግንኙነት በማለዘብና ወደ ገንቢ ውይይት እንዲመጡ ማበረታታታቸው በበጎ ዓይን እየታየላቸው ነው። አምባሳደር ቻንታል ባለፈው ዓመት የሹመት ደብዳቤአቸውን ከማስገባታቸው በፊት በአውሮፓዊቷ ኪርጊስታን ሀገር የኅብረቱ ቋሚ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል። የቤልጂየም ተወላጅ የሆኑት አምባሳደር ቻንታል በኢትዮጵያ የኅብረቱ ቋሚ አምባሳደር የነበሩትና ባለፈው ግንቦት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን የሀገራቸውን ልጅ አምባሳደር ቫቪየር ማርሻልን ተክተው ወደ ኢትዮጰያ መምጣታቸው ይታወሳል።

(ዜናው የተገኘው ዛሬ በአዲስ አበባ ከታተመው ሰንደቅ ጋዜጣ ነው)

“ኢህአዴጋዊ ምርጫ” በሰሜን ኮሪ

march12/2014

ኪም ጆንግ ኧን 100% ድምጽ በማግኘት አሸንፈዋል!
kim un


ድምጽ የመስጫው ጊዜ ተጠናቅቆ የምርጫ ጣቢያዎች ድምጽ መቁጠር በጀመሩ ጊዜ ኪም ጆንግ ኧን የማሸነፋቸው ጉዳይ አሳስቧቸው በስጋት ውስጥ ነበሩ፡፡ ቆጠራው ተጠናቀቀ፤ ውጤቱ ይፋ ሆነ፤ አሸናፊው ታወጀ፤ ኪም ጆንግ ኧን ሥልጣን ከያዙ የመጀመሪያውን ምርጫ በ100% አሸነፉ፤ ከጭንቀታቸው አረፉ፤ ሕዝቡም በደስታ ፈነጠዘ፣ የክት ልብሱን ለበሰ፤ በአደባባይ ወጥቶም ዳንኪራ ረገጠ፡፡
korea2እሁድ በተደረገው ምርጫ የተሰጠውን እያንዳንዱን ድምጽ ኪም ጆንግ ያለተቀናቃኝ የራሳቸው አድርገዋል፡፡ በየአምስት ዓመቱ በሚካሄደው ምርጫ የተሳተፈው ሕዝብ የምክርቤት አባላትንም መርጦዋል፡፡ በደንቡ መሠረት ምርጫው የሚካሄደው ለምክርቤት ምርጫ ሲሆን የተመራጮች ዝርዝር ውጤት ከመታወቁ በፊት የሰሜን ኮሪያ ዜና አገልግሎት ኪም ጆንግ ኧን ያለተቀናቃኝ በተወዳደሩበት ወረዳ አንድም ተቃዋሚ ድምጽ ሳይሰጥባቸው የሁሉንም መራጭ ይሁንታ በማግኘት መመረጣቸውን ዘግቧል፡፡ ያለፈው ምክርቤት 687 መቀመጫ የነበሩት ሲሆን የአሁኑ ምን ያህል እንደሚኖረው እስካሁን አልታወቀም፡፡
ኪራይ ሰብሳቢነት የሚያጠቃቸውና የኒዎሊበራል አቋም የሚያራምዱ ጽንፈኛ ኃይሎች ታላቅ ተጋድሎና መስዋዕትነት የተከፈለበትን ምርጫ በማጣጣል ልማታዊውን መሪ መመረጥ ለመቃወም ቢሞክሩም “ምርጫው የኮሪያ ሕዝብ በታላቁ መሪ ኪም ጆንግ ኧን ላይ ያለውን ቁርጠኛ አቋም ያሳየበትና በእርሳቸው ራዕይ ለመመራት መወሰኑን በአንድ ድምጽ የገለጸበት ነው” በማለት የሰሜን ኮሪያ ዜና አገልግሎት አጣጥሎታል፡፡
ምርጫ በተደረገበት እያንዳንዱ ወረዳ አንድ ተወዳዳሪ ብቻ የቀረበ ሲሆን መራጮች ድምጽ ሲሰጡ የሚመርጡት በተወዳዳሪው ስም አቅጣጫ “እመርጣለሁ” ወይም “አልመርጥም” የሚል ብቻ እንደነበር ተገልጾዋል፡፡ በህመምና በተለያዩ ምክንያቶች በምርጫ ጣቢያዎች ተገኝተው መምረጥ ለማይችሉ ተንቀሳቃሽ የምርጫ ሳጥን ተዘጋጅቶ ያሉበት ቦታ የምርጫ ኮሮጆ በመውሰድ ድምጻቸውን እንዲሰጡ መንግሥት ያመቻቸላቸው መሆኑን የሰሜን ኮሪያ መንግሥታዊ ዜና አገልግሎት ጨምሮ ዘግቧል፡፡korea4
የሰሜን ኮሪያው ተሞክሮ በየአምስት ዓመቱ ምርጫ የማድረግ ልምድ ላላቸው አገራት ተምሳሌት ከመሆኑ አኳያ በርካታ ልምምድ ሊወሰዱበት የሚችሉ እንደሆነ ምርጫውን የታዘቡ ገለልተኛ ያልሆኑ ወገኖች ይናገራሉ፡፡ በተለይ በአንድ የምርጫ ቀበሌ አንድ ተመራጭ ብቻ “በማወዳደር” አላስፈላጊ የሆኑና የማያሸንፉ ተወዳዳሪዎችን በማስወገድና ወጪን በመቀነስ ልማታዊ ምርጫን ማበረታታት ከአሁኑ ሊታሰብበት እንደሚገባ እነዚሁ ክፍሎች ተናግረዋል፡፡
በምርጫው ወቅት አብዮታዊና አውራ ፓርቲያዊ ቀስቃሽ ዜማዎች የተሰሙ ሲሆን ሰሜን ኮሪያን ለ46ዓመት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በጠ/ሚ/ርነት እና በፕሬዚዳንትነት አገልግለው የተሰውትን የቀድሞውን ባለራዕይ መሪ፣ የኮሪያ ላብአደር ፓርቲ ሊቀመንበር፣ የጦር ኃሎች አዛዥ፣ ማርሻል እና የሪፑብሊኩ ዘላለማዊ መሪ ኪም ኢል ሱንግን የሚያወሱ “በሌጋሲ” የተሞሉ ዜማዎችም ቀርበዋል፡፡

የሀገራችንን ድንበር ለሱዳን መስጠቱን እንደሚቃወሙ በፊርማዎ ያስመዝግቡ

march12/2014
























የሀገራችንን ዳር ድንበር ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት በገዥው ህውሀት/ኢህአዴግ እና በሱዳን መንግስት መካከል እየተካሄደ ያለውን ሴራ እንቃወማለን፡፡

ይህ ሴራ የሚካሄደው ህዝብን በማይወክል ጠባብ ቡድን በመሆኑ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጀርባ የሚፈጸመውን ማንኛውንም ውል እንደማንቀበል ካሁኑ እንዲታወቅልን ለተባበሩት መንግስታት፣ ለአፍሪካ ህብረት እና ለሌሎችም አለም አቀፍ ድርጅቶችና መሪወች የሚቀርብ የተቃውሞ ፊርማ በማሰባሰብ ላይ እንገኛለን።

እርስም ስዎን በማስፈር የዚሁ ታሪካዊ እንቅስቃሴ አካል እንዲሆኑ በትህትና እንጠይቃለን። የናት ሀገራችን ኢትዮጵያ ዳር ድንበር ሲደፈር ሁሉም የሚችለውን ማድረግ ሀገራዊ ግዴታው ነው።

ለመፈረም የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ

Tuesday, March 11, 2014

ሞት የስብሐት ነጋ በርን እያንኳኳ ነው (ሁኔ አቢሲኒያዊ ከፒተርቦሮው ዩ.ኬ)

March 11, 2014

አቶ ስብሃትን ጠጋ ብለው የሚያውቁት ሰዎች “አቦይ ብላችሁ አትጥሩት። አባታዊ አንደበትና ምግባር የለውም እርሱን አቦይ ማለት ትግራይ የሽማግሌ መሀን እንደሆነች መቁጠር ነው” ይሉታል፡፡
ሰውዬው ስብሐት ነጋ የህወሓትን አመሰራረት ቅድመ ታሪክ ለሚያውቅ ሰው ምን ያህል ተንኮለኛ እና በዘር ልክፍት የተለከፈ እንደሆነ ግልጽ ይሆንለታል፡፡ በ1963 ዓ.ም እንደተመሰረተ የሚነገርለት ማገብት (ማህበር ገስገስቲ ብሔረ ትግራይ) የተመሰረተው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የትግራይ ተወላጅ ተማሪዎች ነበር፡፡ የማህበሩ ተልእኮም የተለያዩ የበጐ አድራጐት ስራዎችን በክረምት ወደ ትግራይ በመሄድ ማከናወን የሚል ነበር፡፡ በሂደት ሙሉ በሙሉ ወደ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ በመቀየር ለተሐህት/ህወሓት መመስረት መሰረት ሆነ ለዚህ ዓላማ የማስቀየር ስራ ትልቁን አስተዋፅኦ ካደረጉት መካከል ደግሞ ዛሬ ታሞ የሚማቅቀው ስብሐት ነጋ አንዱ ነው፡፡Sebhat Nega TPLF king maker
ስብሐት ነጋ የህወሀትን መስመር እና ዓላማ መሀንዲስ ከመሆንም አልፎ እስከዛሬ ለብዙ ሰዎች ምስጢር በሆነ መልኩ መለስ ዜናዊንም ወደ ህወሀት ሊቀመንበርነት ብሎም የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስተር ያደረገ እና በህወሀት ክፍፍል ወቅትም ትልቅ ሚና ከነበራቸው ቀደምት የህወሀት ታጋዮች አንዱ ነው፡፡
ለባለፉት 23 ዓመታት የኢትዮጵያን ህዝብ ከጀርባ ሆነው ሲያንቀጠቅጥ የነበረው አይተ ስብሐት ነጋ እርሱም ተራው ደርሶ ቤልጅየም ብራሰልስ በሚገኘው ሴንት ሚካኤል ሆስፒታል Hôpital Saint Michel – (Brussels) መመላስ ከጀመረ 11 ዓመታት እንደሞላው የውስጥ አዋቂዎች ቢገልፁም የበሽታው አይነትና የሰውዬው የጤንነት ሁኔታ እስካሁን ድረስ ከቅርብ ሰዎች ውጪ ሳይወጣ ቀርቷል ሆኖም የህወሀት የውስጥ ሹኩቻን ተከትሎ ሚስጥሮ እያፈተለኩ መውጣታቸውን ቀጥለው ዛሬ ስለ ስብሀት ነጋ ጤንነት በተመለከተ ለዚህ ጽሁፍ ፀሀፊ አፈትላኪ መልዕክት ደርሷል፡፡
ከታማኝ ምንጮች የተገኙት መረጃዎች እንደሚያሳዩት ሰውዬው ማለትም ስብሐት ነጋ brainstem glioma በተባለ የካንሰር አይነት መጠቃቱን ገልፀዋል፡፡ ይህ የካንሰር አይነት በብዛት በህፃናት ላይ የሚታይ ሲሆን በአዋቂዎች ዘንድ ግን በዚህ የካንሰር ዓይነት የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከ100,000 አንድ እንደሆነ የሳይንስ ማስረጃዎች ያሳያሉ፡፡
Brainstem glioma ስለተባለው የካንሰር አይነት መንስዔ እስካሁን የህክምና ባለሙያዎች ምንም ያሉት ነገር ባይኖርም በካንሰሩ የተጠቃ ሰው ግን ከፍተኛ የሆነ የራስ ህመም፣ ራስን የመቆጣጠር እና የማስመለስ ችግር እንደሚያጋጥመው ያስረዳሉ፡፡
በዚህ ካንሰር ተጠቅተው ወደ ህክምና ከሄዱ ሰዎች መካከል 37% የመኖሪያ እድሜያቸው ቢበዛ ዓንድ ዓመት 20% ያህሉ ሁለት ዓመት 13% ቢበዛ ቢበዛ ከሶስት አመት በላይ በህይወት የመኖር እድላቸው አነስተኛ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
ከህወሀት አፈትልኮ የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ስብሐት ነጋ ባለፉት 11 ዓመታት ቤልጂየም ሲመላለስ የነበረው በዚሁ የካንሰር ምክንያት እንዳልነበረ እና የዚህ አይነት የካንሰር ተጠቂ እንደሆነ የተነገረው ፌብራዋሪ 9 እለተ እሁድ ቀን እንደነበር ጨምረው ገልፀዋል፡፡
የአቶ ስብሐት ነጋን መታመም ተከትሎ በሰውዬው ላይ በየዕለቱ የተለያየ ባህሪ እንደሚመለከቱ ገልፀው በተደጋጋሚ ከተለያዩ ስብሰባዎች ላይ አቋርጠው እየሄዱ እንደሚገኙ አክለው ገልፀዋል፡፡
በጦርነቱ ዘመን የትግራይ ህዝብ እጅግ የከፋ ድርቅና ረሀብ ሲፈራረቅበት፤ ከመሀል አገር የእርዳታ እህል እንዳይደርሰው መንገድ በመዝጋት፤ እነሱ በተቆጣጠሩት አካባቢና ባልተቆጣጠሩትም አካባቢ “እኛ ነን ለህዝባችን ረድኤት ድርጅቶች የሚያቀርቡትን እርዳታ ማደል ያለብን” ብለው የተባበሩት መንግስታትን ግራ አጋብተው ለረሀብተኛው እንዲያከፋፍሉ መድሀኒትና ምግብ ይሰጣቸው የነበሩ ሲሆን ያንን በብዙ ሚሊዮን የሚገመት የእርዳታ እህልና ቁሳቁስ ከአረብ ነጋዴዎች ጋር በመመሳጠር በቀጥታ ባህር እያሻገሩ በመሸጥ፤ በኩንታሎች አሸዋ እየሞሉ ለጋሾችን በማታለል እንዲገዙአቸው በማድረግ፤ በሚሊዮን ዶላር ሲንበሸበሹ፤ የጦር መሳሪያ ሲሸምቱ፤ የትግራይ ህዝብ እንደቅጠል ይረግፍ ነበር። እነሱ በየጫካው ከሰራዊቱ እየተሸሸጉ አረቄ ጠግበው ከውሽሞቻቸው ጋር ከበሮ እየደለቁ እየጨፈሩ ይዳሩ እንደነበር ህወሀትን ጥለው የኮበለሉ የቀድሞ አባላቶች የሚገልፁ ሲሆን ለእነዚህ ሁሉ ግፍ እና በደል መፈፀም ከፍተኛ ሚና የነበራቸው እኚሁ የካንሰር ተጠቂ ነበሩ፡፡
ሞት ፍትሃዊ ነው በቅርቡ እንኳን አፈ ቀላጤ መለስ ዜናዊን ከህወሀት አለማየው አቶምሳን ከኦህዴድ ( ኦህዴድ ብዬ ስጠራው የዋሸው ይመስለኛል) የወሰደ ሲሆን አሁን አፉን ከፍቶ ከስብሐት ነጋ ደጃፍ ደርሷል ስብሀት ነጋም ሞትን ወደ ቤቱ ላለማስገባት ከአዲስ አበባ ወደ ብራሰልስ በየዕለቱ እየተመላለሰ ይገኛል ግና ሞትን ሸሽቶ እስከመቼ ሊደበቅ እስከ አንድ ወር ወይስ?

HACKERS WITHOUT BORDERS

march 10/2014

Before Edward Snowden sparked a global debate about government surveillance, it was a fact of life for Tadesse Kersmo. During Ethiopia’s national elections, in 2005, he and his wife campaigned for the country’s pro-democracy party, the Coalition for Unity and Democracy, which achieved a sweeping victory in the capital of Addis Ababa. But, when the results were overturned and protests broke out amid allegations of fraud, the ruling party quickly began cracking down on the opposition. Observers from the European Union reported extensive human-rights violations in the months that followed, including nearly two hundred demonstrators killed by security forces and tens of thousands more imprisoned.

Kersmo evaded arrest and moved to the countryside, but his ties to the opposition subjected him to continued threats, harassment, and intense monitoring long after the election. “It is common wisdom that the phones are tapped,” he told me, in a tired baritone, over Skype. “People would call me and tell me, ‘We are following you, we know what you’re doing, we know where you are.’ ” On three separate occasions between 2005 and 2007, Kersmo was detained and beaten. At one point, he was told that his family would find his dead body in the streets, because the prisons were filled to capacity. When that seemed imminent, in 2009, Kersmo and his wife fled to the U.K., where they were granted asylum. There he continued his work as a university lecturer and a senior member of Ginbot 7, an exiled pro-democracy party that the Ethiopian government labelled a terrorist group in 2011, under a vague and widely condemned proclamation.

Kersmo and his wife thought that their new life in the U.K. would take them out of the government’s sights. But, in April of last year, Kersmo read a report from the University of Toronto’s Citizen Lab, a nonprofit research group that scans the Internet to expose government-sponsored spyware and cyberattacks, showing evidence of a malware campaign targeting Ethiopian dissidents. The report describes a malicious file that, when opened, silently installs monitoring software on the victim’s computer. When Kersmo noticed that the malware “baited” its victims using photos of Ginbot 7 members, including those of himself, he decided to have his machine examined by Citizen Lab.

The group found traces of FinSpy, part of an “intrusion” software suite known as FinFisher, which first made headlines in 2011, after a sales contract was discovered inside the headquarters of the Egyptian secret police, following the ouster of President Hosni Mubarak. The spyware was capable of stealthily transmitting Kersmo’s chats, Web searches, files, e-mails, and Skype calls to a server somewhere in Ethiopia. “The feeling was shock—that they are still following us, even here,” Kersmo told me. “It goes beyond my personal security. All Ethiopians living in the U.K., United States, and elsewhere are unsafe now.”

The other week, Privacy International, a U.K.-based human-rights organization, filed a criminal complaint on Kersmo’s behalf, making him the first U.K. resident to challenge the use of hacking tools by a foreign power. “This case would be important to all refugees who end up in countries where they think they are safe,” Alinda Vermeer, a lawyer with Privacy International, who filed Kersmo’s complaint, told me in a phone interview. That sense of safety is illusory, she said, because countries armed with tools like FinSpy insure that refugees “can be spied on in an equally intrusive way as they were back at home.” Worse, the surveillance also reveals with whom the victims have been communicating, potentially endangering the lives of contacts and relatives still residing in their home country.

Kersmo’s dilemma is becoming more common, particularly among journalists and activists seeking political freedoms beyond their country’s borders. The Electronic Frontier Foundation recently filed a suit similar to Kersmo’s against the Ethiopian government, on behalf of a U.S. citizen living near Washington, D.C., where most of the country’s Ethiopian-American population lives. (Fearing government reprisal, the plaintiff asked to use a common Ethiopian name, “Kidane,” as a pseudonym during the proceedings.) In a different report, released last month, Citizen Lab revealed evidence of an attack on Ethiopian Satellite Television, a news service with offices in the U.S. that serves as an alternative to state-controlled media in Ethiopia. A mysterious source had made three attempts to send malicious files to employees, claiming that they were news articles; the files contained a small program that exploits a security flaw in Microsoft’s Windows operating system, allowing it to silently install Remote Control System, a spyware tool similar to FinSpy.

The growing surveillance-technology industry—including the companies Gamma International and Hacking Team, the European developers of FinSpy and Remote Control System—has been valued at five billion dollars. Proponents defend such commercial spyware by noting that it helps authorities catch terrorists and other serious criminals. But Gamma will not disclose which countries it sells its products to, nor is it particularly eager to take responsibility for how they are used. In 2012, Martin J. Muench, the company’s founder, told Bloomberg News that his company has “no control; once it’s out there it’s basically with the country” to use the tools ethically. (Gamma did not respond to a request for comment.)

The Milan-based Hacking Team claims that it monitors its software, and has the ability to disable functionality if it believes that clients “have used Hacking Team technology to facilitate gross human rights abuses.” According to its customer policy, the company’s sales are reviewed by “an outside panel of technical experts and legal advisors,” which looks for “red flags,” including “credible government or non-government reports reflecting that a potential customer could use surveillance technologies to facilitate human rights abuses.” Like Gamma, Hacking Team also refuses to name which countries use its products, but it denied allegations in a recent report by Citizen Lab that claimed Remote Control System was used in twenty-one countries, including Azerbaijan, Uzbekistan, Saudi Arabia, and Sudan. A spokesperson, Eric Rabe, told Mashable that the Citizen Lab report is “not an accurate list of nations where Hacking Team clients are located,” but refused to elaborate on the company’s vetting process.

Regardless, the increased scrutiny of commercial spyware has led some countries to tighten regulations regarding its sale, particularly across national borders. In 2012, the U.K. government informed Gamma, which has offices in Andover, England, that it needs to obtain licenses to sell FinSpy outside the country, citing laws that control the export of cryptography. Alinda Vermeer, of Privacy International, explained that, while export controls under the Wassenaar Arrangement—which regulates weapons and technologies with potential military applications within forty-one nations—were recently updated to restrict spyware, the new terms haven’t yet been adopted by all participating countries. This means that, while future deals will be regulated in some countries, past purchases and current efforts from spyware companies around the world have relatively few rules to follow—and more people like Kersmo are bound to get caught in the crosshairs. “There is a social obligation for corporations,” Kersmo said. “Selling this kind of software to irresponsible governments is irresponsible.”

Joshua Kopstein is a cyberculture journalist from New York City.

Photograph: Raphael Satter/AP

የአዉሮፓ ሕብረት የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄን በተመለከተ አንድነትን አነጋገረ

march10/2014

በኢትዮጵያ የአዉሮፓ ሕብረት ልኡካን ቡድን መሪ አምባሳደር ቻንታል ሔበሬሽ፣ በአዉሮፓ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ እና የሕንድ ዉቂያኖስ አካባቢ ዴስክ ኦፌሴር ቪክቶሪያ ጋርሲያ ጉሌን እንዲሁም ቶማስ ሁይገባርቴስ የተሰኙ ፣ የአዉሮፓ ሕብረት ሃላፊ ፣ በነርሱ አነሳሽነት፣ ከአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባላት ጋር ሰፊ ዉይይት አደረጉ።


ከአንድ ሳምንት በፊት በኢትዮጵያ ስላለው የዲሞክራሲ ግንባታ ዙሪያ ከጠ/ሚኒስተር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር እንደተነጋገሩ የገለጹት የአዉሮፓ ሕብረት ባለስልጣናት፣ የአንድነት ፓርቲ በጠራዉ የሚሊዮኖች ድምጽ ሁለተኛ ዙር ንቅናቄ እንዳሳሰባቸው በመገለጽ፣ አንድነት በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ዙሪያ፣ ፓርቲው ፍቃደኛ ከሆነ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው፣ ጠይቀዋል።

የአንድነት ፓርቲ ወክለው ከአዉሮፓ ሕብረት ጋር የተነጋገሩት ሊቀመንበሩ ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራዉና የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊው አቶ ሃብታሙ አያሌው በበኩላቸው ያሉትን ሁኔታዎች ለማስረዳት ሞክረዋል።

አንድነት አሁን የሚያደርገው የሚሊዮነሞች ንቅናቄ ከዚህ በፊት ከተደረገው የቀጠለ እንደሆነ ያስረዱት የአንድነት አመራር ፣ ፓርቲዉ አዲስ አበባ ጨምሮ በ17 ከተሞች ፣ በፍትህ እና በላንድ ሪፎርም ዙሪያ ፣ ከሕዝብ ጋር ዉይይቶችን እንዲሁም ሰላማዊ ስለፎች እንደሚያደርግ ገልጸዋል። አንድነት ከዚህ በፊት ባደረጋቸዉ በርካታ ሰልፎች አንዳች አይነት በሰውም ሆነ በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ የገለጹት የአንድነት አመራር አባላት ፣ ወደፊት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች፣ ሰላማዊና ሕዝባዊ እንደሚሆኑ በማስረዳት ፣ አንድነት አገር አቀፍ መዋቅሩን እያሰፋ እንደሆነም ለማሳየት ሞክረዋል።

የአዉሮፓ ሕብረት ተወካዮች፣ አንድነት ይዞት የተነሳዉ የመሬት ጥያቄ ተገቢና ወቃታዊ፣ ለኢትዮጵያ ጥቅም የሚያመጣ እንደሆነ የገለጹ ሲሆን፣ በመጪው የ2010 ምርጫ ዙሪያ አንድነት ያለውን አቋም እንዲያስረዳቸው ጠይቀዋል። «ለምርጫ አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገን ነው። በሁሉም ክልሎች ለፌዴራልም ሆነ ለክልል ተወዳዳሪዎች ከወዲሁ እያዘጋጀን ነው» ሲሉ የመለሱት የአንድነት አመራሮች ፣ በምርጫ መሳተፉና አለመሳተፉ ግን ወደፊት የሚወሰን እንደሆነ ገልጸዋል። «ኢሕአዴግ ሁሉንም ነገር ከዘጋዉና የፖለቲካ ምህዳሩን ካጠበበው. የምርጫ ቦርድ የመሳሰሉ ተቋማት ገለልተኝነት ከሌላቸው፣ ምርጫ መሳተፉ ዋጋ እንደማይኖረዉ የገለጹት የአንድነት አመራራ፣ በምርጫዉ ጉዳይ፣ ኳሷ ኢሕአዴግ ሜዳ ላይ እንዳለች አስረድተዋል።

የፖለቲካ እስረኞችን ሁኔታ የጠየቁት የአዉሮፓ ሕብረት ተወካዮች «እስረኞችን ለመጠየቅ ይፈቅድላቹሃል ወይ ? » ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ፣ አንዱዋለም አራጌን አንድ ጊዜ ለመጠየቅ እንደቻሉ ነገር ግን ርዮት አለሙን፣ እስክንደር ነጋ እና ናትናኤል ሞኮንን እንዳይጠይቁ መከልከላቸውን የአንድነት አመራሮች አስረድተዋል።

በፊታችን ኤፕሪል በብራሰልስ፣ በአዉሮፓ ሕብረት እና በአፍሪካ ሕብረት መካከል ስብስባ እንደሚደረግ የገለጹት የአዉሮፓ ሕብረት ተወካዮች፣ የአንድነት ፓርቲ በስብሰባው እንዲገኝ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ በገዠዉ ፓርቲ ዘንድ የፊታችን ምርጫ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ እንደሚሆን ቃል እንደተገባላቸው ተናግረዋል።

የአንድነት አመራሮች ግን ገዢዉ ፓርቲ የሚናገራቸውና ተግባራቶቹ አንድ እንዳልሆኑ፣ ይሄ ነው የሚባል፣ የዲሞክራሲ ግንባታዉን የሚያግዝ የተጨበጠ እርማጃ እንዳልወሰደ መረጃ ላይ በመደገፍ ገለጻ አድርገዉላቸዋል። «ጋዜጦቻችንን ማተም አልቻልም። ደጋፊዎቻችን ይታሰራሉ። ከሥራ ይባረራሉ። ሰልፍና ስብሰባዎች ስንጠራ ብዙ ጊዜ እንግልት ይደርስብናል» ሲሉም በአገዛዙ እየተፈጸሙ ያሉ ከፍተኛ የሰባአዊ መብት ጥሰቶችን ዘርዝረዋል።

በዉጭ አገር ስላሉ ኢትዮጵያዉያንም የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል። «በዉጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ወደ 2 ሚሊዮን ይጠጋል። በርካታ ደጋፊዎች አሉን። በተለያዩ ቦታዎች በተለይም በአሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች አሉን» ያሉት የአመራሩ አባላቱ፣ የድጋፍ ድርጅት ዉስጥ የሌሉ፡ ነገር ግን የምናደርጋቸውን ከፓርቲ በላይ የሆነውን የሚሊየኖች ንቅናቄን የሚደገፉ በርካታ ኢትዮጵያዊ የሲቪክ እና የፖለቲካ ድርጅቶች እንዳሉም አስረድተዋል። የትግሉ አካል ከሆኑና በዉጭ ካሉ ኢትዮጵያዉያን ጋር ለመነጋገር፣ አንድነት የልኩካን ቡድኖች በቅርቡ ወደ ዉጭ እንደሚያስማራም ለአዉሮፓ ሕብረት ተወካዮች ገልጸዋል።

በአገሪቷ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት እንዲቻል የተሻለዉና የሰለጠነው አማራጭ፣ መነጋገር እንደሆነ ያስረዱት የአንድነት አመራር አባላት፣ አንድነት ከኢሕአዴግ ጋር ሆነ ሽብርተኞች ተብለው ካልተሰየሙ ደርጅቶች ጋር ሁሉ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለመነጋገር ፍቃደኛ እንደሆነ፣ ለዚያም ጥሪ እንዳቀረቡ ገልጸው፣ አገዛዙ ግን ቅድመ ሁኔታዎች እያስቀጠ በተደጋጋሚ ለመነጋገር ፍቃድኛ እንዳለሆነ ተናግረዋል።

ፍኖተ ነፃነት

Monday, March 10, 2014

ዛሬ ከጠዋቱ አራት ሰዓት ላይ ፍርድ ቤት የቀረቡት የሰማያዊ ፓርቲ ሁለት ከፍተኛ አመራሮችና አባሎች ለመጋቢት 5 ተቀጠሩ

march 10/2014
ዛሬ ከጠዋቱ አራት ሰዓት ላይ ፍርድ ቤት የቀረቡት የሰማያዊ ፓርቲ ሁለት ከፍተኛ
እሁድ ለት በተካሄደው የሴቶች 5000 ሜትር ሩጫ ላይ ለነፃነት እንሩጥ በሚል መርህ በሩጫው ላይ በመሳተፍ በርካታ ፖለቲካዊና መሀበራዊ ጥያቄዎችን ያነሱ የሰማያዊ ፓርቲ የሴቶች ጉዳይ ሀላፊዎችና አባላት እንዲሁም ሰፍራው ንበረቶ ነን ቻቸውን ይዘው የነበሩ ሁለት የፓረቲው ከፍተኛ አመራሮች እና አንድ አባል ታፍሰው ወደ ሾላ የካ ፖሊሰ መምሪያ መወሰዳቸው ይታወቃል ፡፡
በዛሬው እለትም ፍርድቤት ቀርበው የተከሰሱበትን ምክንያት መርማሪ ፖሊሱ /ኮማንደር የማታ/አብራርቷል፡፡ የተከሰሱበት ምክንያት እሁድ በተካሄደው የሴቶች ሩጫ ላይ ተመሳስሎ በመግባት የጣይቱ ልጆች ነን ፣ የምኒልክ ልጆች ነን ፣ ኑሮ መረረን ፣ የህሊና እስረኞች ይፈቱ በሚል ሁከትን ለማነሳሳት ቀስቅሳችኋል የሚልኘ ሲሆን መርማሪው መረጃ አሰባስቤ ስላልጨረስኩና መረጃዎቼን ያጠፋሉ ሰዎችንም እንዳይመሰክሩ ያስፈራሩብኛል በተጨማሪም ብዙዎቹ ቋሚ አድራሻ የሌላቸው ስለሆነ መረጃ እስካሰባስብ የ15 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ ብሏል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮችም እድል እየጠየቁ ለማስረዳት ጥረት ያደረጉ ሲሆን የተከሰሱበት ምክንያት ሀሳባቸውን በአጋጣሚው በነፃነት በመግለፃቸውና በተባለው መልኩ ሳይሆን አስበው እና ሩጫውንም እንደማንኛውም ሴት ኢትዮጵያዊ ቲሸርት ገዝተውና ተመዝግበው ሲሆን አሉ የተባለውን እንዳሉ አስረግጠው ነገር ግን ሁከት አለማስነሳታቸውንም እንዲሁም ሩጫው ሲጠናቀቅ አፍሰው እስርቤት እንደወሰዷቸው ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል፡፡ አብረው የታሰሩት ወንዶችም በወቅቱ በቦታው የጓደኞቻቸውን እቃዎች ተሸክመው ሩጫውን እስኪፈፅሙ እየጠበቁ በነበረበት ሰዓት ሴቶቹን እየለቀሙ ሲወስዱ ለምንድነው የምትወስዷቸው በማለታቸው ብቻ አብረው እንደታሰሩ ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል፡፡ አክለውም እኛ ህጋዊ ሰውነት ያለን የፓርቲ አመራሮችና አባላት ነን ስራችንም በዚሁ በአዲስ አበባ ሆኖ ሳለና በተፈለግን ጊዜ የምንገኝበት ግልፅ አድራሻ በምርመራ ወቅት ተመዝግቦ እያለ ዋስትና አይሰጣቸው የተባለው ተቀባይነት የለውም እንዲሁም መረጃ ላሰባስብ የሚለውም ምክንያት ሁሉም ንብረቶቻችን በወቅቱ ተወስደው በፖሊሶች እጅ የሚገኝ ስለሆነ ተገቢ አይደለም በሚል ፍርድ ቤቱን ሞግተዋል፡፡
ክሱን የሚመራው ኮማንደር ይህን በማስተባበል የዋስትና መብታችን ይከበር ማለታቸውን “ፍርድ ቤቱ እንደሚያውቀው በሀገሪቱ ያለው ነገር የታወቀ ነው የአሸባሪዎች ስጋት አለ እና ከዛ ጋር የሚተባበሩ ተልዕኮ ያላቸው ስለሆኑ ለማጣራት ጊዜ ያስፈልገኛል” በማለት የዋስትና መብታቸው እንዲነሳ ጠይቋል፡፡
በመጨረሻ ዳኛው ኮማንደሩ ይህን ለማጣራት የጠየቀው ጊዜ የተንዛዛ ስለሆነ በአምስት ቀን ውስጥ አጣርቶ ለአርድ መጋቢት 5 እነዲቀረቡ አዞአል ለታሰሪዎቹም ፓርቲው አሰፈለጊውን ሁሉ ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
በሀገር ወሰጥ ሆነ ከሀገር ውጭ ሆናችሁ ደጋፍ ላደረጋችሁልን ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን፡፡

ሐረር በእሳት አደጋ፣ በጥይት ሩምታ፣ በሕዝባዊ ተቃውሞና በቆመጥ ድብደባ ስትታመስ ዋለች

march10/2014

ዘ-ሐበሻ እንደዘገበው በሐረር ትናንት ምሽት ከግምት ከሶስት ሰዓት ተኩል ጀምሮ ልዩ ስሙ መብራት ሃይል ተበሎ በሚታወቀው የገበያ ቦታ በተነሳ እሳት አደጋ የበርካታ ነጋዴዎች ንብረት ከወደመ በኋላ “የእሳት አደጋውን የክልሉ መንግስት ሆን ብሎ ያቀነባበረው ነው” በሚል የአካባቢው ነዋሪ በዛሬው ዕለት ተቃውሞን ለመግለጽ አደባባይ ወጥቶ እሳቱን ለማጥፋት ውሃ ያልነበረው የክልሉ የእሳት አደጋ ማጥፊያ የተቃውሞ ሰልፈኛውን ለመበተን ውሃና አስለቃሽ ጭስ ሲጠቀም ዋለ። የክልሉ ፖሊስም በጥይት ሩምታ በማውረድ፣ በቆመጥ በመደብደብ ሰልፈኛውን ሲበትን መዋሉን ለዘ-ሐበሻ ከስፍራው የደረሱ ዜናዎች አመልክተዋል።



የዘ-ሐበሻ ተባባሪ ዘጋቢዎች ከሐረር በትናንቱ የእሳት አደጋ ቃጠሎ ንብረታቸው ከወደመባቸው መካከል የተወሰኑትን በማነጋጋር ባጠናቀሩት መረጃ “የክልሉ መንግስት ነጋዴዎቹ ይሰሩበት የነበረውን ቦታ ይፈልገው ነበር። በተደጋጋሚም እንዲነሱ ጠይቋል። ነጋዴዎቹ ከዚህ ቀደም ከ3 ዓመታት በፊት ሸዋበር አካባቢ በተመሳሳይ ሴራ ንብረታቸው የተቃጠለባቸው መሆኑን እና በትናንቱ አደጋ ንብረታቸው ሙሉ በሙሉ በመውደሙ ለተቃውሞ አደባባይ እንዳስወጣቸው መረዳት ችለናል።

በመብራት ሃይል የገበያ ቦታ የተነሳው እሳትን ለማጥፋት የተደረገው ርብርቦሽ በጣም ደካማ እንደነበር የሚገልጹት እነዚሁ ነጋዴዎች ከድሬደዋ እና ከጅጅጋ የእሳት አደጋ ማጥፊያ ብርጌድ እስኪመጣ ድረስ ብዙ ንብረት ወድሟል። እሳቱ ሳይስፋፋ ነጋዴዎቹም የተወሰነ ንብረት እንኳ ከእሳቱ እንዲያተርፉት አለመደረጉን የገለጹት እነዚሁ ባለንብረቶች መንግስት ወዲያውኑ የተቃጠለውን አካባቢ በግሬደር ማረሱ አስገራሚ ሆኖባቸው ነጋዴዎቹ ዛሬ አደባባይ ወጥተው ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ነበር።

በብሶት የተወጠረው የሃረር ሕዝብ ባስነሳው ተቃውሞ የክልሉ ፖሊስ በአስለቃሽ ጭስ፣ በቆመጥ ድብደባ፣ በውሃ፣ በጥይት ሲበትን የዋለ መሆኑን የገለጹት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች በርካታ ሰዎች መታፈሳቸውንም ገልጸዋል።

በዚህ የተቃውሞ እንስቃሴ ላይ የሞተ ሰው እንዳለ ለማረጋገጥ ያደረግነው ሙከራ ባይሳካም በርካታ ሰዎች መቁሰላቸው ግን ተሰምቷል።
ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱን እንመለሳለን።

ኢህአዴግ ዳግም በክፍፍል ጎዳና...? (ተመስገን ደሳለኝ)

march10/2014

ከዚህ ቀደም በተለያየ ጊዜ በተዘጋጁ ሁለት ፅሁፎች፣ የድህረ መለስን ኢህአዴግ የኃይል አሰላለፍ ለማመልከት መሞከሬ የሚታወስ ቢሆንም፤ ዛሬም ያልተጠበቁ ክስተቶችን ማስተዋላችን አልቀረም፡፡ በርግጥ «አዲሱ የኢህአዴግ አሰላለፍ ፪» በሚል ርዕስ ቀርቦ በነበረው ተጠየቅ ከሞላ ጎደል ሀገሪቷን እንደንጉስ ሚካኤል ከጀርባ ሆነው የሚያሽከረክሯት ህወሓት እና ብአዴን መሆናቸው የተጠቀሰበት አውድ ብዙም አልተቀየረም፡፡ ይሁንና በኦህዴድ እና ደኢህዴን ውስጥ እየታየ ያለው የእርስ በእርስ መተጋገል መደምደሚያ ምናልባት ወቅታዊውን መልከአ ኢህአዴግ ሊለውጠው የሚችልበት አጋጣሚ እንዳለ እገምታለሁ፤ ማን ያውቃል? ...እነዚህን ኩነቶች ታሳቢ አድርገን የገዢው ፓርቲ አክራሞትን በአዲስ መስመር ጨርፎ ወደመመልከቱ እንለፍ፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ «ብላቴኖች»

ክልሉን የሚያስተዳድረው የደኢህዴን የአመራር አባላት በስርዓቱ ልሂቃን የፖለቲካ ግምገማ ገና «ብላቴና» ተደርገው የሚወሰዱበት የትምክህት ዘመን አላከተመም፡፡ በርግጥ ድርጅቱ ደርግን ለመጣል በተደረገው የትጥቅ ትግል ላይ የተሳተፈ ባለመሆኑ፣ ዛሬም ፖለቲካን (ሀገር ማስተዳደርን) በበረሃው ትግል ተፈትኖ ከማለፍ ጋር ከሚያጋምዱት የግንባሩ ጉምቱ መሪዎች ዘንድ፣ ይህን መሰል ማጣጣያ የሚጠበቅ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ለደኢህዴን ደካማነት በምክንያትነት የሚነሳው ጉዳይ ከአወቃቀሩ ጋር የሚያያዝ ነው፤ ይኸውም በክልሉ የሚገኙ 56 የተለያዩ ዘውጎችን ማቀፉ ለመከፋፈል አደጋ በቀላሉ የሚጋለጥበትን ዕድል የማስፋቱ እውነታ ነው፡፡ ይህም ሆኖ ከክልሉ ነዋሪዎች በቁጥር የሚልቁት የወላይታና የሲዳማ ተወላጆች፣ በደኢህዴን ውስጥ ያላቸው ተሰሚነት (ተፅዕኖ) የገዘፈ መሆኑን ለመረዳት፣ ሕገ-መንግስቱ ከፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ የፓርቲውን ሊቀ-መንበርነትም ሆነ የክልሉ ፕሬዚዳንትነት ከሁለቱ ብሔሮች በቀር፣ ለሌሎቹ የሰማይ ያህል የራቀ ያደረገውን «ዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት» መጥቀሱ በቂ ነው፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የፓርቲው ሊቀ-መንበር ኃይለማርያም ደሳለኝ የያዘውን መንግስታዊ ስልጣን የሚመጥን ተሰሚነት ለማግኘት ድርጅታዊ ድጋፍ ማሰባሰብ ላይ ያተኮሩ የሚመስሉ ክስተቶችን ሲከውን ታዘብናል፡፡ ኩነቱን በስነ-አመክንዮ ለማጠናከር ጥቂት ማሳያዎችን ላቅርብ፡- በጠቅላይ ሚኒስትርነት መንበር ላይ ከተቀመጠ በኋላ፣ በደኢህዴን ውስጥ ያሉ የተወሰኑ ተገዳዳሪዎቹን ከኃላፊነታቸው ከማንሳትም አልፎ፣ ደጋፊዎቹ (ታማኞቹ) እንደሆኑ የሚነገርላቸውን በከፍተኛ ሥልጣን ላይ አስቀምጧል የሚያስብለው፣ ከወራት በፊት በፓርቲውም ሆነ በደቡብ ክልል ከእርሱም የበለጠ ተሰሚነት የነበረውን ሽፈራው ሽጉጤን አንስቶ፤ ትጉህ አገልጋዩ እንደሆነ የሚነገርለትን ደሴ ዳልጌን ተክቶታል፤ በቅርቡ ደግሞ ሌላኛው ‹የደኢህዴን ቁልፍ ሰው› የሚባለው የፖለቲካ (የድርጅት) ጉዳይ ኃላፊ እና የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አለማየሁ አሰፋን ያለአንዳች ኮሽታ «በትምህርት ስም» ከቦታው አንስቶታል (ይህ ጉዳይ እስከአሁን ድረስ መንግስታዊው ሚዲያ የዜና ሽፋን አላገኘም)፡፡ በግልባጩ ታማኝነታቸውን ያስመሰከሩ፣ ከሲዳማ ብሔር ውጪ ያሉ ጓዶቹን በፌደራል መንግስቱ ወሳኝ የስልጣን እርከኖች ላይ አስቀምጧል፡፡ ለማሳያ ያህልም አሰፋ አብዩ /ሀድያ/፣ ወርቅነህ ገበየውን ተክቶ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር፤ ደበበ አበራ /ከፋ/፣ የኢህአዴግ ዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ፤ ውዱ ሀቶ /ሸካ/፣ የፀረ ሙስና ምክትል ኮሚሽነር፤ አማኒኤል አብርሃም /ወላይታ/፣ በሚኒስቴር ዴኤታ ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕዝብ አደረጃጀት አማካሪ፤ ሰለሞን ተስፋዬ /ጉራጌ/፣ በተመሳሳይ ማዕረግ የፕሬስ አማካሪ፤ ካይዛ ኬ (ጂንካ) በገቢዎች ባለስልጣን የገብረሀዋድን ቦታ ተክቶ የገባ እና የፌደራል ዋና ኦዲት መስሪያ ቤት ምክትል ኃላፊ ተደርጋ የተሾመችውን የወላይታዋ ተወላጅን መጥቀስ ይቻላል (ከደኢህዴን የሥራ-አስፈፃሚ አባላት መካከል የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትሩ ሬድዋን ሁሴን እና መከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈጌሳም የሲዳማ ተወላጅ አለመሆናቸውን ልብ ይሏል) ይህንን ጉዳይ እንዲህ በብሔር ደረጃ ቁልቁል አውርደን እንድንመለከተው የሚያስገድደን ስርዓቱ ከሚያራምደው የፖለቲካ ፍልስፍና እና በክልሉ እየተነሱ ካሉ የማንነት ጥያቄዎች ጋር የመቆራኘቱ አንድምታ ነው፡፡ በተለይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሲዳማዎች ራሳቸውን ችለው
በክልል ደረጃ ለመዋቀር ተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርበው አያሌ መስዋዕትነትን መክፈላቸው ይታወሳል (በኢህአዴጋዊ የክልል አሰያየም ቀመር ሕገ-መንግስታዊ ድጋፍ ያላቸው መሆኑ ሳይዘነጋ)፡፡ ይሁንና ጥያቄው ተቀባይነት ቢያገኝ የክልሉ አስተዳደር መቀመጫ የሆነችውን አዋሳን ከመውሰዳቸውም በላይ፣ ሊያስከትል የሚችለው አለመረጋጋት ሲታከልበት፣ ህዳጣን ልሂቃኑን የኢኮኖሚ ጥቅመኝነት ያሳጣቸዋል፡፡ ይህ ስጋትም በደኢህዴን ውስጥ ከሲዳማ ተወላጆች ውጪ ካሉ የአመራር አባላት ድርጅታዊ ድጋፍ ለማግኘት ብርቱ ትግል ከሚያደርገው ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር በወሳኝ ሰዓት፣ መሀል መንገድ ላይ ቢያስተቃቅፋቸው የማይታመን አይሆንም፡፡

የእነዚህ አዳዲስ ኩነቶች (ሹም ሽሮች) መግፍኤ፣ በሁለት የቢሆን ሃሳቦች ተነጣጥለው ሊታዩ ይችላሉ፡፡ የመጀመሪያው ኃይለማሪያም ደሳለኝ የጠቅላይ ሚንስትርነት ሹመቱን ተከትሎ ‹በዚህ ላይ ፈርም›፣ ‹ይህንን ተናገር›፣ ‹እንዲህ አይነት አስተያየት ስጥ!!› ወዘተ የሚሉ ከጀርባ ሆነው የሚሾፍሩት የአለቆቹ ቀጭን ትዕዛዛትን የሚገዳደርበት ፖለቲካዊ ጉልበት ለማሰባሰብ እና በቁርጥራጭ ጨርቅ በተጣጣፈው እናት ድርጅቱ ውስጥ ያሉ ችግሮችን ስልታዊ በሆነ መልኩ አስወግዶ ቅቡልነቱን ለማጠናከር እንቅስቃሴ ጀምሯል የሚል ሊሆን ይችላል፡፡
ሌላኛው ደግሞ ከኢትዮጵያውያንም አልፎ በውጪ ዜጎች ሳይቀር ‹ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሻንጉሊት ነው› የሚለውን እምነት ለማስቀየር በህወሓትና ብአዴን እየተደረገ ያለ ፖለቲካዊ ጨዋታ ሊሆን የመቻሉ ጉዳይ ነው፡፡

ኦህዴድ

ባለፉት የህወሓትም ሆነ የአቶ መለስ ዜናዊ የበላይነት በገነኑባቸው ዘመናት፣ ኦህዴድ ምንም እንኳን ስርዓቱን ካነበሩ የግንባሩ አባል ድርጅቶች አንዱ መሆኑ ባይካድም፣ በስጋት መታየቱ የአደባባይ እውነታ ነው፡፡ እንዲያውም በአንድ ወቅት አቶ መለስ ራሱ «ኦህዴድ ሲፋቅ ኦነግ ነው» ማለቱ አይዘነጋም፡፡ ከሶስት ያላነሱ የስራ አስፈጻሚ አባላቱ፣ ድርጅቱን ከድተው ኦነግን መቀላቀላቸውም የውንጀላው ማሳያ ተደርጎ እስከመወሰድ ደርሶ ነበር፡፡ ይህ ሁኔታም ኦህዴድን የተረጋጋ አመራር እንዳይኖረው ከማደናቀፉም ባሻገር፣ በተቀነባበረ ማኪያቬሊያዊ ሴራ እርስ በርስ በማይተማመኑና በተከፋፈሉ ሰዎች ስር እንዲቆይ አስገድዶታል፡፡ ግና፣ ኩነቱን ምፀት የሚያደርገው ህወሓት በረሃ እያለ ያሳትመው በነበረው ልሳኑ «የኦሮሞ ጥያቄና የኢትዮጵያ አብዮት» በሚል ርዕስ ባሰራጨው ፅሁፍ ኢህአፓን «የኦሮሞ ሕዝብ በነፍጠኛው ላይ የነበረውን ተገቢ ጥላቻ በማራገብ ፋንታ ለማብረድ በተጨባጭ ተንቀሳቅሷል» («የትግል ጥሪ» 3ኛ ዓመት ቁጥር 10፣ 1979 ዓ.ም) ሲል ይከስሰው እንደነበረ ማስተዋላችን ነው፡፡

በአናቱም አቶ መለስ እስከ ህልፈቱ ድረስ በኦህዴድ ደስተኛ እንዳልነበረ ይነገራል፡፡ ይህ ግን ‹የኦሮሞን ሕዝብ በአግባቡ አላገለገለም› ከሚል ቁርቆራ የተነሳ አይደለም፤ እንዲህ አይነቱ ስሜት ሌላውን ክልል ቀርቶ ትግራይንም የሚመለከት ቢሆን አሳስቦት አያውቅምና፡፡ የእርሱ ቅሬታ ‹ህዝቡን አሳምነውም ሆነ ጠርንፈው ከድርጅቱ ጎን አላሰለፉትም›፣ ‹ሁላችንንም በሚያሳጣ መልኩ ዘረፋ ውስጥ ገብተዋል›፣ ‹ዲሲፕሊን የላቸውም...› የሚሉና ሌሎች መሰል መነሾዎች ናቸው፡፡ እንዲህ ያለ የድርጅቱ «እንዝህላልነት» ደግሞ የህዝቡ ልብ ይበልጥ ኦነግን እንዲናፍቅ ማስገደዱን መለስ ዜናዊ ጠንቅቆ ያውቅ ነበር፡፡ ለዚህም ይመስለኛል የክልሉን ባለስልጣናት ሁሉ ወደ ጎን ብሎ እታች ድረስ በመውረድ የወረዳ አመራሮችን ቀጥታ ያለ ሥልጣን ተዋረድ በስልክ እስከማናገር የተገደደባቸው ቀናት የበዙት፡፡ በርግጥ በድርጅቱ ስብሰባዎች ላይ መተላለፍ ያለባቸውን ውሳኔዎች በፅሁፍ መስጠት እና ለአመራርነት የሚመረጡ ሰዎችን መመደብ ድረስ ባሉ ጉዳዮች ጣልቃ የመግባቱ ነገር ማንም አሌ የማይለው በግልፅ ይታይ የነበረ ክስተት ነው፡፡

የሆነው ሆኖ ከምንጮቼ እንዳረጋገጥኩት አባዱላ ገመዳ ዕድሜውን ሙሉ ሲፈራ የኖረው መለስ ዜናዊን ብቻ ነበር፤ መለስ ደግሞ ይህችን ምድር ለመጨረሻ ጊዜ ከተሰናበታት አንስቶ የተቆጠሩት በርካታ ወራት ፍርሃቱን ጥሎ ነፃነቱን እንዲጎናፀፍ ለመርዳት ያስችሉታል ብዬ አስባለሁ፡፡ እናም በዚህ መልኩ ተፈጥሮ ያመቻቸለትን ታሪካዊ አጋጣሚ ተጠቅሞ ይደቆስ የነበረውን ኦህዴድ ከወደቀበት ለማንሳት ሙከራዎችን እያደረገ ይመስለኛል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኦህዴድ በሚያደርጋቸው ስብሰባዎች ላይ የሚቀርቡ አንዳንድ አጀንዳዎችና አቋሞችን የአባዱላ ግፊት እንዳለባቸው ስናስተውል፣ «ጄነራሉ» ወሳኝ ሰው ለመሆን እያደረገ ያለው የጥንጣን ጉዞ ምን ያህል እየሰመረለት እንደሆነ ለመረዳት ያስችላል፡፡ ይህንን መከራከሪያ ከለጠጥነው ደግሞ፣ ከህወሓት/ብአዴን ጋር ትከሻ መገፋፋት ጀምሯል ወደሚል ጠርዝ ይገፋናል፡፡ ይህም ባይሆን እንኳ ከኃይለማርያም ደሳለኝ የተሻለ ተሰሚነት እንዳለው ለመናገር የሚያስደፍሩ ማስረገጫዎች አሉ፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ ቀን የከዳ ዕለት በተናጠል በኃላፊነት ሊያስጠይቁት የሚችሉ ጉዳዮችን ሳይቀር፣ በያዘው ሕገ-መንግስታዊ ሥልጣን ከመወሰን ይልቅ በቡድን እንዲያልቅ ሲስማማ፤ በግልባጩ አፈ-ጉባኤው ከዚህ ቀደም በምክር ቤቱ ውስጥ ተነስተው ለአቶ መለስ ይቀርቡ የነበሩ ጉዳዮችን ወዲያውኑ መፍትሔ እንዲያገኙ በማድረግ ሲቋጫቸው ተደጋግሞ ተስተውሏል፡፡ ኦህዴድንም በሚመለከት ‹በድርጅታዊ መደጋገፍ› ስም ማንም ጣልቃ መግባት እንደማይችል በይፋ እስከ መናገር መድረሱን ምንጮች ጠቅሰውልኛል፡፡ በቀጣይ አመት የሚደረገውን አምስተኛ ዙር አገር አቀፍ ምርጫን አስመልክቶም እየተደረገ ባለው ዝግጅት በሃሳብ አመንጭነት እየተሳተፈ ነው፡፡ ከጥቂት ወራት በፊት ለምክር ቤቱ የቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ ከሁሉም የመንግስት መስሪያ ቤት ለተወከሉ እና ምርጫ ቦርድ ሀላፊዎች /ፕሮፌሰር መርጋ በቃና እና ዶ/ር አዲሱ ገ/እግዚአብሔር በተገኙበት/ «የአውራ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ባህሪያት» በሚል ርዕስ ጥናታዊ ፅሁፍ ማቅረቡ አስረጅ ሆኖ ሊወሰድ ይችላል (በነገራችን ላይ ስርዓቱ በምርጫ ስም የሚፈፅመውን ደባ ፍንትው አድርጎ የሚያሳየው፣ ሁለቱ የቦርዱ ኃላፊዎች የዚህ አይነቱ ውይይት ላይ ተሳታፊ መሆናቸው ነው)፡፡ እንዲሁም ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተ በአዳማ ለክልል አፈ-ጉባኤዎች ሰፊ ትንተና ሰጥቷል፡፡

የአባዱላ ገመዳንና የበረከት ስምኦንን መገፋፋት በጨረፍታም ቢሆን ሊያሳይ የሚችለው ሌላኛው ሁነት ደግሞ ወ/ሮ አና ጎሜዝን አስመልክቶ ሊነሳ የሚችለው ነው፡፡ በረከት «የሁለት ምርጫዎች ወግ» በሚለው መጽሐፉ «የቅኝ-ገዥነት መንፈስ ያልለቀቃት» ብሎ የገለፃትን አና ጎሜዝ (የመለስ በስድብ የተሞላ የኢትዮጵያን ሄራልድ ጋዜጣ መጣጥፍ ሳይዘነጋ)፣ ከሁለት ወራት በፊት አዲስ አበባ በመጣችበት ወቅት አባዱላ በጓዳዊ ስሜት እንዳስተናገዳት ራሷ ከመመስከሯም በዘለለ፣ እነርሱም በአዲስ ዘመን ጋዜጣቸው «እየተመካከርን ነው» የሚል የወዳጅነት መንፈስ የረበበበት የፎቶ ዘገባ ማቅረባቸውን እናስታውሳለን፡፡ ይህች ተራ የምትመስል ሁነት ለበረከት የምታስተላልፈው መልዕክት ቢኖር ‹እናንተ እንደሰይጣን የረገማችሁትን ሁሉ እየተከተልን አንረግምም» የምትል እኩዮች ነን አይነት ትከሻ መጋፋት ትመስለኛለች፡፡

በአናቱም አባዱላ አብዛኛው የኦህዴድ አመራርን በዙሪያው ማሰባሰብ ስለመቻሉ ይነገራል፡፡ ከዚህ ቀደም በአደባባይ እስከመዘላለፍ የተደራረሱትን አቶ ሙክታር ከድርንም ከጎኑ ማሰለፍ ችሏል፡፡ በአንድ ወቅት የግል ጠባቂው የነበረውና አሁን የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆነው አብይ አህመድ በእንዲህ አይነቱ ጊዜ ውለታ ለመመለስ የሚያደርገው ተጋድሎ የማይናቅ ጠቀሜታ አስገኝቶለታል፡፡ የሰሞኑ ሹም ሽርም የራሱ የሆነ አንድምታ አለው፡፡ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ በማዕከላዊ ኮሚቴ ድምጽ ከስልጣኑ የተሻረው የክልሉ ፕሬዚዳንት አለማየሁ አቱምሳ (እርሱን ማንሳት የሚችለው ጠቅላላ ጉባኤው ብቻ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ በርግጥ ሰውየው አሁን አልፏልና በባህላዊ ልማዳችን መሰረት ነፍስ ይማር ብለን እናልፋለን) በ2002ቱ ምርጫ ማግስት አቶ መለስ ከካድሬዎቹ ይሁንታ ውጪ አባዱላን ለመተካት ያመጣው እንደነበር ይታወሳል፡፡ (በነገራችን ላይ በወራት እድሜ ውስጥ በመለስ የተሾሙ የክልል ፕሬዚዳንቶች ከኃላፊነታቸው ሲነሱ ከሽፈራው ሽጉጤ እና አያሌው ጎበዜ ቀጥሎ አለማየሁ አቱምሳ ሶስተኛው ሰው መሆኑ ነው) የድርጅቱ ሊቀ-መንበር እና ምክትል ሆነው የተመረጡት ሙክታር ከድርና አስቴር ማሞም የአባዱላን የበላይነት ለመቀበል ግለ- ሂሳቸውን ውጠዋል፡፡ ይህም ሆኖ የክልሉ አስተዳዳሪ ማን ይሆናል? የሚለው ጥያቄ ገና መልስ አላገኘም፡፡

ምናልባት (ከስራ አስፈፃሚዎችም መካከል መምረጥ እንደሚቻል ታሳቢ ተደርጎ) በሌሎች አካባቢዎች እንደታየው ከድርጅቱ ሊቀ-መናብርት (ሙክታርና አስቴር) አንዳቸውን መሾም ቢፈልጉ እንኳ ዕውን የሚሆንበት ዕድል የለም፡፡ ምክንያቱም እነርሱ የህዝብ ተወካዮች እንጂ የጨፌ ኦሮሚያ ም/ቤት አባል አይደሉምና፡፡ በእኔ ግምት እስከሚቀጥለው የምርጫ ዘመን ድረስ ቦታው አዲስ ሰው ሳይሰየምበት በምክትል ፕሬዚዳንቱ አብዱል አዚዝ ስር እንዳለ የሚቆይ ይመስለኛል፡፡

ከምርጫው በኋላስ? ....አፈ-ጉባኤው በኦህዴድ ውስጥ ለማስፈን እየሞከረ ካለው «አምልኮ አባዱላ» ተነስተን «ተገፈተርኩበት!» የሚለውን ያደረ ቁጭቱን ስንደምርበት ወንበሩን ራሱ ይይዘው ይሆናል ከሚል ጠርዝ ያደርሰናል፤ አሊያም ከሽርኮቹ ሙክታር ከድር እና ወርቅነህ ገበየው አንዳቸውን አሾሞበት በጨፌ ኦሮሚያም የሚካኤል ስሁልን መንፈስ ማንበሩ አይቀርም ብሎ ቅድመ ግምት ማስቀመጥ ይቻላል (ይህ መላምት የህወሓት-ብአዴን ጥንካሬ በዚሁ ከቀጠለ እና የእነርሱ ፍላጎት ደግሞ የተለየ ከሆነ ከህልም ሊዘል አለመቻሉን በማመን ላይ የተመሰረተ ነው)

ኦህዴድን ካነሳን የሌንጮ ለታን ኦዴግን መፃኢ እድልም መመልከት ግድ ይለናል፤ ምክንያቱም ኦዴግ አገር ውስጥ ገብቶ በሰላማዊ መንገድ መታገል ወስኖ ጨርሷልና፤ ሂደቱንም ለማመቻቸት ከግንባሩ መሪዎች አቦ ሌንጮ ለታ፣ ዶ/ር ሌንጮ ባቲ፣ ዶ/ር ዲማ ነጎዎ፣ ዶ/ር ታደሰ ኤባ እና ዶ/ር በየነ አሰቦ ጋር ከስምምነት ለመድረስ፣ ኢህአዴግ በውጪ ሀገር ከሚገኙት የጄኔራል ታደሰ ብሩ ልጆች በተጨማሪ፣ ፕ/ር እንድሪያስ እሸቴ፣ ፕ/ር ኤፍሬም ይስሃቅ፣ ፓስተር ዳንኤል፣ ሻለቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ፣ ሻለቃ ደራርቱ ቱሉ፣ አባቢያ አባጆቢር፣ አቶ በቀለ ነዲ (የአዋሽ ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ የነበሩ)፣ ወ/ሮ ሙሉ ሰለሞንን የመሳሰሉ አደራዳሪዎችን ማሳተፉ ይነገራል፡፡

ይህም ሆኖ ድርድሩ በስኬት ተቋጭቶ ኦዴግ ሀገር ቤት መግባት ቢችል እንኳ፣ ኦህዴዶች ‹አያሰጋንም› የሚል እምነት እንዳላቸው ሰምቻለሁ፡፡ ግና፣ ያለፉት ሁለት አስርታት ዘግናኝ ክስተቶች አሻራ ዛሬም በረዣዥሞቹ የባሌ ተራሮች በጉልህ ተቸክችኮ የመታየቱ እውነታ፣ በስርዓቱ ላኮረፈው የኦሮሚያ ህዝብ፣ ኦዴግን አማራጭ የሚያደርግበት «አኪር» ሸሽጎ ይዞ እንደሆነ ማን ያውቃል? ይህ እንግዲህ እነ ሌንጮ «ካዳሚ» ለመሆን አይመጡም በሚል ስሌት ከተቃኘ ነው፡፡ ይሁንና ከድርድሩ ጀርባ ያለውን እንቆቅልሽ ለመፍታት ጊዜ የሚጠይቅ ቢሆንም፣ ጉዳዩን ውስብስብ የሚያደርጉ ክስተቶችን ግን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ይኸውም በአፈ-ጉባኤ አባዱላ ፊት አውራሪነት ስር ለመጠናከር እየሞከረ ያለው ኦህዴድ፣ ከሰዎቹ ሀገር ቤት መግባት ምን ያተርፋል? ምንስ ያጣል? ከሚለው ጋር ይያያዛል፡፡

መቼም የኦዴግን መምጣት፣ ኦቦ ሌንጮ «እንጮቴ» (ተወዳጅ ባሕላዊ ምግብ ነው) በአይኑ ላይ እየተመላለሰ እንደሆነ ከሰነዘረው ቀልድም ሆነ «ከሌሎች የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ዘመናዊ ፌደራሊዝምን እመሰርታለሁ» ብሎ በደምሳሳው ከገለፀው ዓላማው ጋር አያይዞ ማለፍ አይቻልም፡፡ አሊያም ያኔ እርሱ ሸገርን ተሰናብቶ ሲወጣ ገና ያልፀደቀውን አንቀፅ 39ን «አስፈፅማለሁ» በሚል ቀቢፀ-ተስፋ ተገፍቶ ነው ማለትም አይቻልም፡፡ በግልባጩ አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ‹የኦዴግ መሪዎች በኦነግ ዘመን ለእስር የዳረጓቸውን በሺ የሚቆጠሩ የኦሮሚያ ተወላጆችን ለማስፈታት ሲሉ፣ በታማኝ ተቃዋሚነት ለመታገል ወስነው ነው የሚመጡት› የሚለውን መከራከሪያቸውን ለመቀበል የሚቸግረው ደግሞ፣ እስረኞቹን መፍታት ለሃያ አመታት ያህል በክልሉ ላይ ሰላማዊ ዜጎችን በማሰር የሚታወቀውን ኦህዴድን ሊያሳጣ የመቻሉ ነገር ነው፡፡ ያም ተባለ ያ፣ «ለሁሉም ጊዜ አለው» እንዲል ጠቢቡ

ሰለሞን ሁሉም ቋጠሮ ጊዜ የሚፈታው ይሆናል፡፡ አሁን ላይ እርግጠኛ መሆን የሚቻለው በኦህዴድ ውስጥ አባዱላ ገመዳ ወሳኝ እየሆነ የመምጣቱ እውነታ ብቻ ነው፡፡

ህወሓት-ብአዴን

በዋናነት ሀገሪቷን እንደሚያሽከረክሯት የሚነገርላቸው ህወሓት እና ብአዴን፣ በመጪዎቹ ጊዜያት ‹ኢህአዴግ ለዳግም ክፍፍል ሊዳረግ ይችላል› በሚል ፍርሃት ድርና ማግ ሆነው እየሰሩ ስለመሆኑ እየሰማን ነው፡፡ በርግጥ ‹መለስ ህወሓትን አዳክሞ ነው ያለፈው› የሚል የትግርኛ ተናጋሪዎች ድምፅ መሰማት ከጀመረ ሰነባብቷል (በነገራችን ላይ ከ2000 ዓ.ም ወዲህ የህወሓትን የምስረታ በዓል የካቲት 11ን በብሔራዊ ደረጃ ማክበር መቅረቱን በይፋ ከማወጃቸውም በላይ፣ መለስ ራሱ ለመጨረሻ ጊዜ በመቀሌው የሰማዕታት አዳራሽ የተገኘው 35ኛው ዓመት በተከበረበት ወቅት ነበር፡፡ ይሁንና ከህልፈቱ በኋላ ድርጅቱ የደረሰበትን ድክመት ለመሸፋፈን በደመቀ መልኩ እያከበረው ይገኛል፤ ለዚህም ይመስለኛል በአምናውም ሆነ በዘንድሮው በዓል ላይ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ መቀሌ የሞቀ ተገኝቶ ንግግር ከማድረግም አልፎ ከሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኡመር ሀሰን አልበሽር ጋር በትግሉ ዘመን በተቀነቀኑ ዜማዎች ሲደንስ በቴሌቪዥን መስኮት ተመልክተን ሦስተኛው ሚሊንየም ገባ እንዴ? ብለን ግራ የተጋባነው፡፡ አልበሽርስ አንድ ቻርተር አውሮፕላን ለክልሉ በስጦታ ያበረከተው ዕውን በዓሉን አስመልክቶ ነው? ወይስ በምትኩ የተሰጠው ነገር ኖሮ? መቼም የህወሓት የምስረታ በዓል እንዲህ ሊያስፈነጥዘው እይችልም)

‹ህወሓት ተዳክሟል› የሚለውን ቅሬታ የሚያሰሙ የቅርብ ሰዎች፣ ድርጅቱ አቅምና ልምድ በሌላቸው መሪዎች ስር ማደሩን ይጠቅሳሉ፡፡ ተስፋ የጣሉበት ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤልም ቢሆን ከአምባገነንነቱም በላይ ሀሳቡን አፍታቶ የማስረዳት ችሎታው ደካማ መሆን መፍትሄውን አርቆ ሰቅሎታል፡፡ እንደ ድርጅቱ የቅርብ ሰዎች አገላለፅ የ«ጠንካራ ተተኪ» አልቦነትን ለመረዳት፣ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ኃላፊነቱ በተነሳው አቶ ዘርዓይ አስገዶም ቦታ ላይ የዋልታ ስራ አስኪያጅ መመደቡ እና ራሱ ዘርዓይም በጓሮ በር የብሮድካስት ባለስልጣን ሆኖ መሾሙን (አዲስ ፊት አለመታየቱን) መመልከቱ በቂ ነው፡፡ በቅርቡ የዶክትሬት ዲግሪውን ያገኘው አርከበ እቁባይም ለአመራርነት ለቀረበለት ጥያቄ እያንገራገረ እንደሆነ ተሰምቷል፤ አቦይ ስብሃት ነጋም ኢ-መደበኛ በሆነ የጠረጴዛ ወግ ህወሓት «በግብር በላ» መሪዎች እጅ መውደቁን በቁጭት መናገራቸው ይጠቀሳል፡፡ ይሁንና በዚህ ቀውጢ ወቅት ሁለት ተቋማት ድርጅቱን ለጊዜውም ቢሆን ፖለቲካዊ ጉልበቱን እንዳይነጠቅ ታድገውታል፡፡

 ደህንነቱ እና ሰራዊቱ፡፡

የሆነው ሆኖ ህወሓት ዛሬም ከብአዴን ጋር በማበር (በአባይ ፀሐዬ እና በበረከት ስምኦን የፊት መሪነት) የፖለቲካው አሽከርካሪነቱን እንዳስከበረ ይገኛል፡፡ ሁለቱ ሰዎች የስርዓቱን ርዕዮተ-ዓለምንም (በተለይም አብዮታዊ ዲሞክራሲን) ከሌሎች ጓዶቻቸው በበለጠ ማብራራት እንደሚችሉ ይነገራል፡፡ በጅጅጋ ከተማ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በተከበረበት ወቅትም ሆነ ከሳምንታት በፊት በመቀሌ ከተማ በተዘጋጀ መድረክ አባይ ፀሐዬ የርዕዮተ-አለሙ «ተንታኝ» ሆኖ የቀረበው ከዚህ አኳያ ነበር፡፡ በአናቱም አባይ እና በረከትን ጨምሮ ከኦህዴድ ኩማ ደመቅሳ፤ ከደኢህዴን ዶ/ር ካሱ ኢላላ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር አማካሪ ሆነው መሾማቸው ይታወሳል፡፡ በዋናነት ለኢህአዴግ የስልጣኑ መሰረት (ከታጠቀው ኃይል እና ኢኮኖሚያዊ ጥንካሬው በተጨማሪ) ‹በልማታዊ መንግስት፣ በጥርነፋ፣ ሳር-ቅጠሉን በማደራጀት፣ የብሔር ጉዳይን በማጎን እና መሰል ጭብጦችን በማስጮኽ የሚያምታታበት ርዕዮተ-ዓለሙ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የእነ በረከት የተሰሚነት ምስጢርም ከዚሁ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በርግጥም የካቲት 14 ቀን 2006 ዓ.ም. የተሰበሰበው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከልን ለማቋቋም የሚያስችል ደንብ ማፅደቁን እና የአራቱም ድርጅት የአመራር አባላት የተወከሉበት ከመሆኑ አኳያ፣ ቦታው ከማማከር የዘለለ የስራ ድርሻ እንዳለው መገመት አያዳግትም (በነገራችን ላይ የመለስ ፖለቲካ ሰለባ የሆነው የብአዴኑ ተፈራ ዋልዋ ድምፁን አጥፍቶና ከውጥንቅጡ አርባ ክንድ እርቆ በእንጦጦ ተራራ እና በረዣዥም ህንፃዎች አናት በመፈናጠጥ ቴሌስኮፑን ግራና ቀኝ እያዟዟረ ከዋክብት ሲመለከት መዋልን አይነት ፀጥተኛ ህይወት፣ አንዳንድ የቀድሞ ጓዶቹም ለተረፈቻቸው እድሜ የሚመኙት ይመስለኛል)
ለውጥ ይኖር ይሆን?

የስርዓቱ ልሂቃን ብሔሮቻቸውን ማዕከል ባደረገ መልኩም ይሁን፣ በሥልጣን ከፍታ ከሚያገኙት ግላዊ ጥቅማ-ጥቅም በመነሳት፣ ከላይ ለመተንተን እንደሞከርኩት ባለ የመከፋፈል መሰል ሂደት ውስጥ እንኳን ቢያልፉ በቀጣይ ጊዜያት ‹የፖለቲካ ማሻሻያ ያደርጋሉ› ብሎ ለማመን ነገሮች በእጅጉ አስቸጋሪ ናቸው፡፡ ለዚህም ሶስት ነጥቦችን እናንሳ፡- የመጀመሪያው የሀገሪቱ የደህንነት መዋቅር አደረጃጀት ባህሪ ነው፡፡ እንደሚታወቀው በእነ ጌታቸው አሰፋ የሚመራው የደህንነት ተቋም በሚታዩና በማይታዩ ድርጊቶች ለህወሓት የተገዛ ነው፡፡

ከዚህች ሀገር ጀርባ ለተፈፀሙም ሆነ ገና ለሚፈፀሙ ድርጅታዊ እና ግለሰባዊ (ባለሥልጣናዊ) ወንጀሎች አስፈፃሚና በደል አንፂ ነው፡፡

ወጣቱ አና ለነጻነት የሚደረግ የትግል መስዕዋትነት (ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ)

march 10/2014


የአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ህልውና የሚወሰነው ወጣቶች ባላቸው ሚና ላይ ሲሆን በብዙ ሀገራት እንዳየነው እና እንደተመለከትነው ወጣቶች ስለ ነፃነታቸው ፊት ለፊት መንግስታትን በመጋፈጥ ለመብታቸው ታግለዋል መስዋህትነትም በመክፈል የፈለጉትን አለማና ግብ አሳክተዋል::ለዚህም የሰሜን አፍሪካ አገሮችንና የመካከለኛው ምሥራቅን የለውጥ አብዮት ያቀጣጠሉትን ወጣቶች ዞር ብሎ መመልከት ያሻል:: የአንባ ገነኖች የስልጣን አገዛዝ አልዋጥላቸው ያላቸው እነዚህ የሰሜን አፍሪካ አገሮች እንደነ ግብጽ ፣ ቱኒዚያ እና ሊቢያ ያሉ ሀገሮች የሚኖሩ ወጣቶች በጊዜው ለናፈቁት እና ለተመኙለት ነጻነት ብዙ መስዋትነትን በመክፈል ዓላማቸውን አሳክተዋል:: በወቅቱ የነበረው የዓረብ የፖለቲካ ትኩሳት መነቃቃት ለብዙ ሀገራት ወጣቶች ትምህርት ሰጥቶ ያለፈ ታሪክ ነው::

ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ ስንመለስ የኢትዮጵያን የፖለቲካ አካሄድ ወደ ኋላ ዞር ብለን በምናይበት ጊዜ በኢትዮጵያ ሲደረግ በነበረው የፓለቲካ እንቅስቃሴ ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ትልቁን ሚና ይጫወት እንደነበር ከታሪክ መረዳት እንችላለን::እነሆ በኢትዮጵያ ረዥም ታሪክ ውስጥ እያንዳንዱ ትውልድ በተለያየ ጊዚና ወቅት የራሱን አሻራ ጥሎ አልፏል፡፡ በተለይ በንጉሡ ጊዜ የመሬት ላራሹንና ሌሎችንም የፖለቲካዊ ጥያቄዎች አንግቦ ሲንቀሳቀስ የነበረው የተማሪ ንቅናቄ ዛሬ ላይ በኢትዮጵያ የፖለቲካ የታሪክ ጉዞ ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው  ሲሆን  በዚያን ጊዜው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የነበሩትና ግንባር ቀደሞቹ ዋለልኝ መኮንንና ጥላሁን  ግዛው በድንገት በወታደራዊው ኃይል ቁጥጥር ሥር ለወደቀው የተማሪው አብዮት ተጠቃሾች ሲሆኑ፣ በዘመኑ ለነበረው ሃይለኛ እና ወኔን የታጠቀ  ትውልድም መታወቂያ ሆነው ማለፋቸውን የታሪክና የፖለቲካ ተንታኞች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የሚያወሱት የታሪክ ትውስታ ነው፡፡

 ከቅርብ አመታት በፊትም ማለትም በ97 ምርጫ  ሁሉም ሰው እንደሚያስታውሰው  ይህ ወቅት ኢህአዴግ ወጣቶችን ሙሉ በሙሉ የገፋበት ወቅት ጊዜ እንደነበር እና መንግስት ስራ አጥተው የሚንከራተቱ ወጣቶችን “አደገኛ ቦዘኔ” የሚል ታፔላ በመስጠት የተለያዩ እስሮችና የማንገላታት እርምጃዎችን የወሰደበት እና  የፈፀመበት ወቅት እንደነበር በብዙዎች ዘንድ ይታመናል፡፡ ይህ አይነቱ የመንግስት ግብታዊ እርምጃ ወጣቱን ወደ ተቃውሞ ጐራ እንዲያዘነብል አድርጐታል፡፡ ለዚህም ይመስላል በወቅቱ በምርጫ 97 ዋዜማ ኢህአዴግ ያቀረባቸውን የተለያዩ ማባበያዎች “አደገኛ ቦዘኔ ራሱ ወያኔ” የሚል ዜማ በማቀንቀን ለተቃዋሚዎች ድጋፍ የሰጠው፡፡ ኢህአዴግ በምርጫ 97 የደረሰበትን አስደንጋጭ ሽንፈት ተከትሎ በተፈጠረው ውዝግብ ቀዳሚ ተጠቂ የሆነውም ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል እንደነበር እናስታውሳለን፡:ለዚህም ነው ምርጫ 97 ተከትሎ በጊዜው በአቶ መለስ መንግስት ከሃያ ሺ በላይ ወጣቶች በእስር ቤቶችና በወታደራዊ ካምፖች ታሰረው  የተሰቃዩት እና ከ200 በላይ የሆኑ ባብዛኛው ወጣት የሆኑ ንፁሀን ዜጐች  በግፍ በአደባባይ የተገደሉት::ይህንን ለነጻነት ትግል የተደረገን የወጣቶች የህይወት መስዋትነት ሁል ጊዜ ስናስታውሰው የምንኖረው ነው::

እንደሚታወቀው በአሁን ወቅት በሀገራችን ኢትዮጵያ ከሚኖረው ህዝብ ከፍተኛውን ቁጥር ይዞ የሚገኘው  ወጣቱ  የህብረተሰብ ክፍል መሆኑ ይታወቃል:: ይህንንም ተከትሎ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከወጣቶች ብዙ የምትጠብቀው ነገር መኖሩ የማያጠያይቅ እውነታ ነው;; ምክንያቱም የኢትዮጵያ ሀገራችን የወደፊት  ሁለንተናዊ ህልውናዋ ያለው እና የሚወሰነውም በእነዚሁ በዛሬዎቹ የኢትዮጵያ ወጣቶች ስለሆነ :: ከላይ እንደገለጽኩት በሀገራችን ኢትዮጵያ ከሚኖረው ሕዝብ አብዛኛውን ቁጥር የያዘው ወጣቱ እንደመሆኑ ይሄ ወጣት የህብረተሰብ ክፍል በስልጣን ላይ ባለው ስርዓት  ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ፍላጐቱ ሊሞላለት አልቻለም:: ከዚያም ባለፈ ወጣቶች የነጻነትም ሆነ የመብት  ጥያቄያቸውን ወይም ፍላጐታቸውን መግለጥ እና መናገር  የሚችሉበት አግባብ የተዳፈነ በመሆኑ፣ በአለም ላይ ኢትዮጵያን የተገፉ ወጣቶች የበረከቱባት ሀገር እና ሀገራቸውን እየጣሉ ከሚሰደዱ ወጣቶች መካከል ቅድሚያውን እንድትይዝ አድርጓታል፡፡

የወያኔ ኢህአዲግ መንግስት በስልጣን በቆየባቸው ባለፉት አመታቶች እየበደለ እና እያሰቃየ ያለው በመላ ሀገሪቱ ላይ የሚኖረውን ሁሉንም  የህብረተሰብ ክፍል ቢሆንም ይበልጥኑ በወያኔ ራዳር ውስጥ በመግባት በአገዛዙ ጭቆናና ግፍ እየደረሰበት ያለው በሀገራችን የሚኖረው ወጣቱ ዜጋ መሆኑ የታወቀ ነው:: ዛሬ የአማራው፣ የትግራዩ፣ የጋምቤላው፣ የኦሮሞው ፣የደቡቡ፣ የአፋሩ መላው የኢትዮጵያ ወጣት ዜጋ ለነጻነቱ በሚያደርገው ትግል በወያኔ ጨካኝ መንግስት እያተደበደበ፣ እየታሰረና እየተገደለ ለነጻነቱ መስዕዋትነትን በመክፈል ላይ ይገኛል :: ለዚህ ማሳያ የሚሆነን  በሀገራቸው ፖለቲካ በመሳተፍ የተቃዋሚዎችን ጐራ የተቀላቀሉ  እንደነ አንዱ አለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንን እና ኦልባና ሌሊሳ የመሳሰሉ ወጣት ፖለቲከኞች እንዲሁም እንደነ  እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ እና ርዮት አለሙን የመሳሰሉ የወደፊቶ ኢትዮጵያ ተስፈኞች  ብዙ የምትጠብቅባቸው  ወጣት ጋዜጠኞች የወያኔ  መንግስት እያራመደ ካለው የዘረኝነት ፖለቲካ የተለየ አቋም በመያዛቸው እና  በተለያዩ ጋዜጦች ላይ ሀሳባቸውን በመግለፃቸው ብቻ በአሸባሪነት ተከሰው ወደ እስር ቤት በግፍ መወርወራቸው የኢትዮጵያ ወጣቶች በገዥው ስርዓት ምን ያህል መብታቸው እየተረገጠ  እና ነጻነታቸው እየታፈነ በወያኔ የግፍ አለንጋ እየተገረፉ እንደሚኖሩ አመላካች ነው፡፡

የወያኔ  መንግስት በወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል እየወሰዳቸው ያለው እነዚህ በግፍ የተሞሉ እርምጃዎች ወጣቶች እጃቸውን አጣጥፈው እንዲቀመጡ አላደረገም፡፡ ይባሱኑ ወጣቱ ሀይሉን እያጠናከረ እና ወደ ተቃዋሚ ጎራ በመግባት ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለወያኔ ኢህአዲግ መንግስት የእግር እሳት እየሆነበት ይገኛል.: በዚህ አጋጣሚ በትናትናው እለት በአዲስ አበበ በተካሄደው የሴቶች 5ሺ ሜትር ሩጫ ላይ ተሳታፊ የነበሩትን እና የተለያዩ ፖለቲካዊ ጥያቄዎችን በማንሳት ነጻነት፣ እኩልነት፣ ፍትህ፣ ዴሞክራሲ እንዲሁም ርዕዮትና ሌሎች የህሌና እስረኞች ይፈቱ እያሉ ሲጮኹና ድምጻቸውን ሲያሰሙ የዋሉትን የሰማያዊ ፓርቲ አባላት  ወጣት ሴቶች እህቶቻችንን ሳላደንቅ አላልፍም :: በጣም የሚያኮራ ተግባር በመፈጸም ምንም ነገር ሳይፈሩ ለወያኔ መንግስት የፍም እሳት በመሆን የተነሱለትን አላማ ‹‹ለነጻነት እንሩጥ››  የሚለውን መሪ ቃል  በማሳካተቸው  ጀግኖች ብያቸዋለው:: በነገራችን ላይ እነዚህ ወጣት ሴት እህቶቻችን ሮጫቸውን ጨርሰው ሲገቡ ለታገሉለት ነጻነት መስዋዕትነትን ከፍለዋል:: ሲከታተሏቸው በነበሩት የወያኔ ተላላኪዎቸ በሆኑት የፖሊስና የደህንነት ኃይሎች መያዛቸውና መታሰራቸው ተገልጾል::

የነጻነት፣ የእኩልነት፣ የፍትህ፣ እና የዴሞክራሲውን ጥያቄ  የሰማያዊ ፓርቲ ፣ የአንድነት ፓርቲ  ወይም የሌሎቹ የፖለቲካ ድርጅቶች ጥያቄ ብቻ ሳይሆን  የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄ በተለይም የኢትዮጵያውያን ወጣቶች ጥያቄ መሆን ይገባዋል::  ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወጣት የኢትዮጵያን ህልውና ለማስጠበቅ በተለያየ የትግል መስክ በመሰማራት ኢትዮጵያችንን ከወያኔ ፋሽስታዊ ስርዓት ለመታደግ፣ የሀገራችንን ሕልውናና ክብር ለመመለስ በወያኔ መንግስት ላይ የፍም እሳት በመሆን መነሳት በእንቢ አልገዛም ባይነት መንፈስ በጽናት በመታገል ከወያኔ የዘረኝነት አገዛዝ ኢትዮጵያንና እራሱን ነጻ በማውጣት ለታሪክ የራሱን አሻራ ጥሎ ማለፍ ይጠበቅበታል::

 የድል ቀን እንዲፋጠን ሁላችንም ወጣቶች  ኢትዮጵያን ከወያኔ አረመናዊ ስርዓት ነፃ ለማውጣት እጅ ለእጅ ተያይዘን እንነሳ !


gezapower@gmail.com




   

የኢሕአዴግ አባል ፓርቲዎች በዶ/ር ደብረጽዮን ፍቃድ ካልሆነ ምንም ዓይነት ውሳኔ መስጠት እንደማይችሉ ተገለጸ

march10/2014



የደህንነት ሹሙ አቶ ጌታቸው አሰፋና ባለስልጣኖቻቸው በሙስና እና በዘረፋ ላይ ተሰማርተዋል
የፍርድ ቤቶች እና የተቃዋሚ ፓርቲዎችን እንቅስቃሴ ማኮላሸት ለአለቃ ጸጋዬ በርሄ ተሰቷቸዋል
የጦር ሰራዊቱን በተጠንቀቅ የሚከታተሉ ወታደራዊ ደህንነቶች ተደራጅተው በየእዙ ተበትነዋል


ምኒልክ ሳልሳዊ

በመከላከያ ሰራዊት የሕወሓት መኮንኖች ስር የሰደደው የሙስና እና የዘረፋ አድራጎት በደህንነት መስሪያ ቤት ውስጥም ከሹሙ ከአቶ ጌታቸው እና ከባለስልጣኖቻቸው ጀምሮ እስከ ገራፊዎች ድረስ መንሰራፋቱን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል:: እንደውስጥ አዋቂ ምንጮቹ መረጃ ከሆነ የደህንነት ባለስልጣኖቹ የተዘፈቁበት የሙስና ተግባር በተጨማሪ ዘረፋን እና ሴት መድፈርን እንዲሁም የቡድን ወንጀሎችን ያካተተ መሆኑ ተጠቁሟል::በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ባለሃብቶችን በማስፈራራት ከፍርድ ቤት ትእዛዝ ውጪ በማሰር እንዲሁም የሙስና ወንጀል ተገኝቶብሃል ይህን ያህል ገንዘብ አምጣ ካላመጣህ እንገድልሃለን እስከማለት በከመድረሳቸውም በተጨማሪ ይህንን ጉዳይ ለፖሊስ የጠቆመ ባለሃብት በማፈን ንብረቱ ባማገድ እና በተለያዩ ስልቶች የተጠየቀውን ገንዘብ እንዲሰጥ በማስገደድ ላይ መሆናቸውን ምንጮቹ ጠቁመዋል::

ከዚህ ቀደም በሙስና የተከሰሱ የስርኣቱ ባለስልጣናትን ተገን በማደርግ በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ ባለሃብቶችን በመከታተል እና ደህንነት ቢሮ ድረስ በመውሰድ በሙስና ከታሰረው ስም እየተጠቀሰ … ከሚባል ባለስልጣን ጋር ግንኙነት አለህ ማስረጃ ተገኝቶብሃል በማለት በፈጠራ ወንጀል ባለሃብቱን በመዝረፍ ስራ ላይ ተሰማርተው የነበረ እና እንዲሁም የአዲስ አበባን ቆነጃጅት ቢሯቸው ድረስ በግብረአበሮቻቸው አፋኝነት እና አስገዳጅነት በመውሰድ ካለፍላጎታቸው አስገድደው በመድፈር ላይ ናቸው ያሉት ምንጮቹ ተራ የደህንነት አባላት ለዚሁ ተልእኮ ተሰማርተው የሚሰሩት ምንም አይነት ወንጀል በቡድን ሲፈጽሙ የሚጠይቃቸው አለመኖሩን የሕዝቡን በደል የከፋ አድርጎታል::

ኢትዮጵያውያን በሕወሓቱ የደህንነት መዋቅር የሚመራ የሽብር ተግባራትን አጥብቆ ስለሚፈራ እና በየጊዜው በሕወሓት ደህንነቶች መሪነት የሚወሰዱ እርምጃዎች በሃገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ስጋትን በመፍጠራቸው በየእስር ቤቱ የሚካሄዱ ሕገወጥ ጸረ ፍትህ ተግባራት እና የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች የኢትዮጵያውያን የቀን ተቀን አጀንዳ ሆነው መምጣታቸው ገዢው ፓርቲ ሕዝቡን ምን ያህል እንዳሸበረ ይጠቁማል ሲሉ ምንጮሹ አክለው ገልጸዋል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሕወሓትን ሳይጨምር ብኣዴን ኦሕዴድ ደኢሕዴግ እና አጋል የክልል ጎሳ ፓርቲዎች ከአቶ ደብረጽዮን በሚወርድ ትእዛዝ ካልሆነ በስተቀር ምንም አይነት እርምጃ በፍቃዳቸው መፈጸም እንደማይችሉ ተነግሯቸዋል:: በቅርቡ የአቶ አለማየሁ አቶምሳን ሞት ተከትሎ አፈጻጸሙ በዶ/ር ደብረጽሆን መልካም ፍቃድ እንደሆነ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የተባለው የኦሕዴድ ሙክታር ከድር አቶ አለማየሁ ደክመው እያየ እና እያወቀ ሆስፒታል እንዲሄዱ አስቸኳይ ትብብር እንዲደረግ ወይዘሮ አስቴር ማሞ ስትጠይቀው ለዶ/ር ደብረጽሆን ነግረሽ አስፈቅጂ በማለት ሕወሓት በኦሕዴድ አናት ላይ ምን ያህል እየሸና እንዳለ እንዲሁም በሞራላቸው አመራሮቹ እንዳይራመዱ እያደረገ እንዳለ ፍንትው አድርጎ ያሳየ ነው:: ማንኛውም የኢሕኣዴግ አባል እና አጋር ድርጅት በድርጅቱ ሊቀመንበር ወይንም ምክትል አማካኝነት በቅድሚያ ለዶ/ር ደብረጺሆን ሪፖርት ማድረግ እና ሁኔታው ታይቶ ፈቃድ እና ውሳነ ካልተሰጠው በስተቀር መፈጸም እንደማይችል ትእዛ መተላለፉ ሲታወቅ በአዲስ አበባ እና በክልል ያለው የፍርድ ቤቶች እና የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ በአለቃ ጸጋይ በርኸ ስር ክትትል እየተደረገ እርምጃ የሚወሰድበት መሆኑ ሲታውቅ የጦር ሰራዊቱን በተመለከት በተዋረድ የሚያስተዳድሩ የወታደራዊ ደህንነት የሕወሓት መኮንኖች ተደራጅተው በየእዙ መመደባቸው ታውቋል:

Saturday, March 8, 2014

ለአቶ ዓለማየሁ አቶምሳ ፍትሃትና ሽኝት ሲባል ቅዳሴ መቋረጡ ምዕመናኑን አሳዘነ

march8/2014

የኦህአዴድ ሊቀመንበርና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት የሆኑት ዓለማየሁ አቶምሳ የቀብር ስነ ሥነ ሥርዓት በቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ዛሬ ተፈጸመ። የርሳቸውን ሞት ተከትሎም ዛሬ 5 ኪሎ በሚገኘው ቅድስተ ማርያም ቤተክርስቲያን የክልሉ ፕሬዚዳንትን ፍትሃትና በአዲስ አበባ ስታዲየም የተደረገውን የሽኝት መርሃ ግብር ምክንያት በማድረግ ከጠዋቱ 8:30- እስከ 9፡00 ሰዓት ማለቅ የነበረበት ቅዳሴ ተቋርጦ በጠዋቱ 7 ሰዓት ላይ መፈጸሙ ምዕመናኑን ማስቆጣቱን ለዘ-ሐበሻ የደረሱት መረጃዎች ያመለክታሉ።

ለአቶ ዓለማየሁ አቶምሳ ስንብት በአዲስ አበባ ስታዲየም ሲደረግ ቅርብ ቤተሰቦቻቸው፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣ የፌደራል መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የተለያዩ ክልሎች የስራ ሃላፊዎች ከመኖሪያ ቤታቸው ጀምሮ እንዳጀቧቸው የገለጹት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደ የስንብት መርሃ ግብር ላይ ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም “አቶ ዓለማየሁ ደርግን ለመጣል የነበረውን ትግል በወጣትነታእው ጀምሮ ተቀላቅለው በተለይ ለኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲና ፍትህ ማግኘት የታገሉ፤ እስከ ሕልፈታቸው ድረስም ታግለው የተሰዉ ታላቅ ሰው ናቸው። እነ አቶ ዓለማሁ ቢሰውም ያፈሯቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ተከታዮች ትግሉን ያስቀጥላልይ፤ በመሰዋታቸው ለቁጭትና ለላቀ ትግል የሚያነሳሳን ነው” ሲሉ አወድሰዋቸዋል።

የኢሕአዴግ መንግስት ሕገመንግስቱን በጣሰ ሁኔታ ፓርላማው ሳይሰበሰብ የሶስት ቀን ብሔራዊ ሐዘንና ባንዲራ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ በመላው ሃገሪቱ ማወጁ አነጋጋሪ በሆነበት ሰዓት በሃይማኖት ተቋማት ውስጥም መዋቅር በመዘርጋት ቅዳሴ እስከማቋረጥ መድረሱ ብዙዎችን አስቆጥቷል። “በዚህ ታላቅ ጾም ወቅት ልጆቻችንን ለማቁረብ በፓትሪያሪኩ መቀመጫ በቅድስተ ማርያም ቤተክርስቲያን ተገኝተን እያስቀደስን ባለንበት ወቅት ልጆቻችንን እንዳናቆርብ የአቶ ዓለማየሁ አቶምሳ ፍትሃትና ሽኝት አለብን በሚል ቅዳሴው 7 ሰዓት ላይ እንዲቋረጥ መደረጉ አስቆጥቶኛል” ሲል አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ምዕመን ለዘ-ሐበሻ ገልጿል።

በቅድስተ ማርያም ቤ/ክ የተገኙት ምእመናን “ባለስልጣኑ ሕይወታቸው በማለፉ እናዝናለን፤ እግዚአብሔር ገነትን ያውርሳቸው፤ ሆኖም ግን እኩለ ቀን ላይ ለሚደረግ ቀብር የእኛን መብት ጥሶ ቅዳሴውን ማቋረጥ አግባብ አይደለም” የሚል አቋም ያለቸው ምዕመናን “ይህ የሚያሳየው የመንግስትን በሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ መግባትን ነው” ብለዋል።

“በባለስልጣኑ ፍትሃት እና ሽኝት ላይ ቤተክርስቲያን ሰው ወክላ መላክ ትችላለች፤ በዚህ ዓብይ ጾም ወቅት ልጆቻችንን ሳናቆርብ ቅዳሴ ማቋረጥ ግፍ ነው” ሲሉ ሌላው አስተያየት ሰጪ ለዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ተናግረዋል።

አቶ አለማየሁ አቶምሳ በታይላንድ ባንኮክ በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ45 አመታቸው የካቲት 26 ቀን 2006 ዓመተ ምህረት ነው ያረፉት። በምስራቅ ወለጋ ቢሎ ቦሼ ወረዳ ከአባታቸው አቶ አቶምሳ ሚጃ እና ከእናታቸው ወይዘሮ አየለች ብሩ በ1961 ዓ.ም መወለዳቸውን ከዚህ ቀደም መዘገባችን አይዘነጋም።
ዘ-ሐበሻ

የመንግስት አፈና የሚበዛው በትግራይ ነው ወይስ በአማራው ተወላጅ ወይንስ በሌላው ዘር ላይ ?

march8/2014
አብርሃ ደስታ
"'አብርሃ የመሃል አገር ሰዎችን ለማስደሰት ሲል የትግራይን ህዝብ ችግር በትግርኛ ከመፃፍ ይልቅ በአማርኛ ይፅፋል። የሚመረጠው በትግራይ ሁኖ ሳለ የሚሰራው ግን ለኢትዮጵያውያን ነው' የሚል አስተያየት ይሰጣል። ምን ትላለህ?" የሚል አስተያየት ደረሰኝ።
ብዙ ግዜ የምፅፈው ስለ ትግራይ ህዝብ ችግር ነው። ግን በአማርኛ ነው የምፅፈው። አዎ! በትግራይ ህዝብ ችግር (ዓፈና) ላይ የማተኩርበት ምክንያት በትግራይ ብዙ ያልተጋለጡ ዓፈናዎች፣ በደሎች መኖራቸው ስለማውቅ ነው። በሌላ ክልል ዓፈናና በደል የለም ማለቴ አይደለም። አለ። ነገር ግን (አንደኛ) በትግራይና በሌሎች ክልሎች የተወሰነ ልዩነት አለ። በሌላ ክልል ዓፈና ሲደርስ የደረሰውን በደል የሚያጋልጡ ጎበዝ ጋዜጠኞች አሉ። በሌሎች ክልሎች በደል ሲፈፀም የመጋለጥ ዕድሉ ሰፊ ነው። በትግራይ ያሉ ጋዜጠኞች ግን የህዝብን ችግር በማጋለጥ ህዝብን ከማገልገል ይልቅ ገዢውን መደብ በመደገፍ ራሳቸው በኢኮኖሚ መበልፀግ ይመርጣሉ። ለህዝብ የቆመ የትግራይ ጋዜጠኛ አላየሁም። አሁን ግን ብዙ የትግራይ ሙሁራን የትግራይን ችግር በፌስቡክ እያጋለጡ ይገኛሉ። አሁን ትግራይ በጥሩ ደረጃ ትገኛለች (ዓፈናን በማጋለጡ ዘርፍ)። ዕድሜ ለፌስቡክ ጓደኞቼ።
(ሁለተኛ) ጨቋኞቹ ባለስልጣናት ትግርኛ ተናጋሪ እንደመሆናቸው መጠን በትግራይ ህዝብ ላይ የሚደርስ በደል እንደሌለ ተድርጎ ሊታሰብ እንደሚችል በመገንዘብ ነው። ስርዓቱ ለትግራይ የቆምኩ ነኝ እያለ ትግራይን ክፉኛ እንደሚበድል ላይታወቅ ወይ ላይጠረጠር ይችላል። ስለዚህ የትግራይን ህዝብ በደል ካልተጋለጠ በደል እንደሌለ ሊቆጠር ይችላል። በደል እንደሌለ ከተቆጠረ ህዝቡ እንደተበደለ ይቀጥላል። ችግሩ ካልተጋለጠ መፍትሔ አያገኝም። መፍትሔ ካላገኘ ህዝቡ ይጨቆናል። ህዝቡ ከተጨቆነ ነፃነት ያጣል። ነፃነት ካጣ ይዳከማል። ከተዳከመ አያድግም። ካላደገ ከድህነት አይላቀቅም። ከድህነት ካልተላቀቅ የገዢዎች ማጫወቻ ይሆናል። ይህም ያሳምማል። ስለዚህ የትግራይ ህዝብ ችግር መጋለጥ አለበት።
የመሃል አገር ሰዎች (ሌሎች ኢትዮጵያውያን ለማለት ተፈልጎ ከሆነ) የትግራይ ህዝብ ችግር ሲጋለጥ የሚደሰቱ ከሆነ በትክክል የትግራይ ህዝብ ወዳጆች ናቸው ማለት ነው። የትግራይን ህዝብ ችግር ሲጋለጥ የሚናደዱ የህወሓት ካድሬዎች ብቻ ናቸው። ምክንያቱም የህዝብ ችግር ሲጋለጥ ገመናቸው ነው አብሮ የሚጋለጠው። ጨቋኝነታቸው ሲጋለጥ የስልጣን ዕድሜያቸው ያጥራል። የህወሓት ካድሬዎች ሃይማኖታቸው ስልጣን እስከሆነ ድረስ የትግራይ ህዝብ ችግር ሲነሳ ይደነግጣሉ፣ ይፈራሉ። በደላቸው እንዲጋለጥ አይፈልጉምና። አንድ ህዝብ የሌላን ህዝብ ችግር ከተጋራ ለህዝቡ ያለውን ድጋፍ፣ አብሮነት እያሳየ ነው ማለት ነው።
"የሚመረጠው በትግራይ ሁኖ ሳለ ለኢትዮጵያውን ነው የሚያገለግለው" የሚል ሐሳብም ተነስቷል። ኢትዮጵያውያንን ባገለግላቸው ደስተኛ ነኝ። እንዳውም ከኢትዮጵያውያን አልፎ አፍሪካውያን፣ ከአፍሪካውያን አልፎ የዓለም ህዝብ ባገለግል ደስታው አልችለውም። ግን ባለኝ የዓቅም ዉሱንነት ምክንያት እስካሁን የምፅፈው ስለ ትግራይ ህዝብ ብቻ ነው።
ዓላማዬ ህዝብን ማገልገል ነው (ፖለቲካ ስለሆነ ብቻ አይደለም)። የህዝብ ነፃነት እንዲከበር እጥራለሁ። የህዝብ ነፃነት የሚከበረው ዴሞክራሲ ሲኖር ነው። ዴሞክራሲ የሚኖረው የህዝብ ድምፅ ሲከበር ነው። የህዝብ ድምፅ የሚከበረው ፍትሐዊ ምርጫ ሲኖር ነው። ፍትሓዊ ምርጫ የሚኖረው አማራጭ የፖለቲካ ፓርትዎች ሲኖሩ ነው። ፓርቲዎች ከሌሉ አማራጭ የለም። አማራጭ ከሌለ ምርጫ የለም። ምርጫ ከሌለ የህዝብ ድምፅ የለም። የህዝብ ድምፅ ከሌለ የህዝብ ስልጣን የለም። የህዝብ ስልጣን ከሌለ ዴሞክራሲ የለም። ዴሞክራሲ ከሌለ ነፃነት የለም። ነፃነት ከሌለ ትርጉም ያለው ህይወት የለም።
ህዝብ ለነፃነቱ ሲል የስልጣን ባለቤት መሆን አለበት። የስልጣን ባለቤት ለመሆን አማራጭ የፖለቲካ ሐሳቦች ያስፈልጉታል። ስለ ተለያዩ የፖለቲካ ሐሳቦች በቂ መረጃ ሊኖረው ይገባል። በቂ መረጃ እንዲኖረው ነፃና ገለልተኛ ሚድያ መኖር አለበት። ያለ ገለልተኛ ሚድያ ዴሞክራሲ እውን ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም ህዝብ ከጭቆና ለማዳን ከፈለገን ማስተማር አለብን። ህዝብ ሲያውቅና ሲደራጅ ብቻ ነው መብቱንና ነፃነቱን መጠየቅ የሚችለው። ስለዚህ የኔ ዓላማ ህዝብን ማስተማር ነው። የማድረገውን ይህንን ነው።
ዓላማዬ መመረጥ አይደለም። ስልጣን መያዝ አይደለም። ህዝብን የማስተምረው ለመመረጥ ቢሆን ኑሮ በተለያዩ አከባቢዎች አልንቀሳቀስም ነበር። ምክንያቱም ለመመረጥ አንድ ኮንስቲቱወንሲ በቂ ነው። እንበልና ለመመረጥ እፈልጋለሁ። የሚመርጠኝ ህዝብ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው። በኢዮጵያውያን ካልተመረጥኩ በትግራይም አልመረጥም። ምክንያቱም በኢትዮጵያውያን አትመረጥም ከተባልኩ 'እነሱ ድምፅ አይሰጥሁም' እየተባልኩ ነው። ኢትዮጵያውያን ድምፅ ካልሰጡኝ ትግራዮችም ድምፅ አይሰጡኝም። ምክንያቱም ኢትዮጵያ አንድ የምርጫ ጣብያ አይደለም፤ ትግራይም አንድ የምርጫ ጣብያ አይደለም። ወደ ድምፅ ቆጠራ ከገባን እኔ ልወዳደር የምችለው (ከተወዳደርኩ ማለቴ ነው) በአንድ ወረዳ ብቻ ነው። ስለዚህ ዓላማዬ ለመመረጥ ከሆነ በአንድ ወረዳ ብቻ መንቀሳቀስ በቂ ነው ማለት ነው። ትግራይ አንድ ወረዳ አይደለችም። ስለዚህ ዓላማዬ ለመመረጥ ብቻ እስካልሆነ ድረስ በሁሉም የኢትዮጵያ አከባቢዎች እዞራለሁ፣ አስተምራለሁ።
ስለ ቋንቋ ጉዳይም ተነስቷል። እኔ የምፅፈው በአማርኛ ነው። ወላጆቻችን በቋንቋችን እንድንናገር ታግለዋል ምናምን የሚል ነገር ይነሳል። ወላጆቻችን የታገሉት የቋንቋ ነፃነታችንን ለማስከበር ነው። የቋንቋ ነፃነት አለ የሚባለው አንድ ሰው ያለምንም ተፅዕኖ በመረጠው ቋንቋ በፈለገው ግዜና ቦታ መጠቀም ይችላል ማለት እንጂ ገዢዎችን በመረጡለት ቋንቋ ብቻ እንዲናገር ይገደዳል ማለት አይደለም። በፈለኩት ቋንቋ መናገር እችላለሁ። በትግርኛ ወይ በሌላ ቋንቋ የመናገር መብት አለኝ፤ ማንም አይከለክለኝም።
በመረጥኩት ቋንቋ እናገራለሁ። ቋንቋ የሚመረጠው አንባቢዎች መሰረት በማድረግ ነው። ለትግራይ ሰዎች ብቻ የሚፃፍ ከሆነ በትግርኛ ይፃፋል። ምክንያቱም በትግርኛ ቋንቋ በመፃፍ አንድን መልእክት ለትግራይ ሰዎች ማስተላለፍ ይቻላል። መልእክቱ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን እንዲዳረስ ተፈልጎ ከሆነ ደግሞ በአማርኛ ይፃፋል፤ ምክንያቱም ኢትዮጵያውያን አማርኛ ያነባሉ (የትግራይ ሰዎችም ጭምር)። ምክንያቱም በትግርኛ ከተፃፈ ከትግራይ ዉጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን አያነቡትም። ምክንያቱም ትግርኛ አይችሉም። ለዓለም ህዝብ ከሆነ ደግሞ በእንግሊዝኛ ይፃፋል። ምክንያቱም ማንበብ እንዲችሉ። የአፍ መፍቻ ቋንቋዬ ትግርኛ ስለሆነ ብቻ ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ወይ የዓለም ህዝቦች በትግርኛ መፃፍ አለብህ ተብዬ አልገደድም።
የትግራይ ችግር በአማርኛ የምፅፍበት ምክንያት የትግራይ ችግር ሁሉም ኢትዮጵያውያን እንዲያውቁት ስለምፈልግ ነው። ምክንያቱም የትግራይ ህዝብ ችግር የመላው ኢትዮጵያውያን ችግር ነው። ምክንያቱም ተጋሩ ኢትዮጵያውያን ናቸው። በተጋሩ የሚደርስ ችግር በኢትዮጵያውያን የሚደርስ ችግር ነው። ስለዚህ ሁሉም የሚመለከተው አካል ማወቅ አለበት።
በአንድ ህዝብ አንድ አከባቢ ችግር ሲደርስ ሁሉም ወገኖች በአንድነት መቆም አለባቸው። በአንድነት ለመቆም መረጃ ሊያገኙ ይገባል። በትግራይ የሚደርስ በደል ለትግራዮች ብቻ የሚተው አይደለም። ሁሉም ኢትዮጵያውያን ይመለከታቸዋል። በኦሮሞዎች፣ በአማራዎች፣ በሶማሊዎች፣ በጋምቤላዎች፣ በደቡቦች፣ በዓፋሮች፣ በሃረሪዎች፣ በቤኑሻንጉሎች ወዘተ የሚደርስ ችግር ለትግራዮች ይመለከታቸዋል። ስለዚህ የትግራይ ችግር ሌሎች ወገኖች እንዲጋሩትና ከትግራይ ህዝብ ጎን እንዲሰለፉ ከተፈለገ በአማርኛ መፃፍ አለበት (አማርኛ ይችላሉ በሚል እሳቤ ነው)።
በኦጋዴን የሚደርስ ችግር የትግራይ ሰዎች እንዲያውቁትና ከኦጋዴን ህዝብ ጎን እንዲሰለፉ ከተፈለገ የኦጋዴን ህዝብ ችግር በአማርኛ መፃፍ አለበት። የቋንቋ ነፃነት ተብሎ የኦጋዴን ህዝብ ችግር በሶማሌኛ ቋንቋ ከተፃፈ እኛ የትግራይ ሰዎች ስለደረሰው ችግር መረጃ አይኖረንም። መረጃ ከሌለን አናግዛቸውም። ካላገዝኛቸው የህዝቦች አንድነት አይኖርም። የህዝቦች አንድነት ከሌለ በያንዳንዳችን የሚደርስ በደል መታገል ይከብደናል። ምክንያቱም የአንድን ህዝብ በደል ለማስወገድ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ህዝቦች ትብብር ይጠይቃል። ጭቆና ማስወገድ የሚቻለው በትብብር እንጂ በተናጠል አይደለም።
የህዝቦችን አንድነት በማስጠበቅ ጨቋኞችን ማስወገድ እንችላለን። ትግላችን በተናጠል ካደረግነው ግን ሊከብደን ይችላል። ምክንያቱም ስለያንዳንዳችን ችግር መረጃ ካልተለዋወጥናን ካልተጋራን በአንዱ ላይ የደረሰውን በደል ሌላኛው ስለማያውቅ ላይደግፈን (ወይ ባለማወቅ ጨቋኙን ስርዓት ሊደግፍ) ይችላል። ስለዚህ ካለመተዋወቅና ካለመረዳዳት እርስበርሳችን እየተፋጀን የጨቋኞችን መሳርያ እንሆናለን።
የህዝቦች ነፃነት እንዲከበር የህዝቦች አንድነት ይኑር። የህዝቦች አንድነት እንዲኖር የጋራ መግባባት ይኑር። የጋራ መግባባት እንዲኖር ስለሚደርሱብን በደሎች መረጃ እንለዋወጥ። መረጃ ለመለዋወጥ የጋራ የምንግባባበት ቋንቋ(ዎች) ይኑረን።
ስለዚህ በአማርኛ የምፅፈው የትግራይ ችግሮች ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ለማካፈልና የህዝቦች አንድነት ለማስጠበቅ እንጂ አማርኛ የበላይ ወይ የበታች ቋንቋ ስለሆነ አይደለም። ቋንቋ መግባብያ ነው (ከፈለጋችሁ ማንነትም ጭምር ነው በሉኝ)።
ተግባባን???
It is so!!

ብሄር ብሄረሰብ፤ የዘር ፓለቲካ…

March 7, 2014
ደስታው አንዳርጌ (ዶ/ር)
እውቀት ይስፋ፣ ድንቁርና ይጥፋ
ይህ ነው የኢትዮጵያ ተስፋ።
ተስፋ ገብረሥላሴ
ፊደል የቆጠርሁት በአገራችን የህትመት ፋናወጊ (እና አርበኛ) የሆኑት ተስፋ ገብረሥላሴ ያሳትሟት በነበረው የባለ ፲ ሣንቲም ፊደል ነበር። ከፊደሏ ሽፋን ላይ ታዲያ ‘ተስፋገብረሥላሴ ዘብሄረ ቡልጋ’ ይላል። መጠየቅ እወድ ነበርና መርጌታን ‘የንታ ብሄረ ቡልጋ ምን ማለት ነው?’ ብየ ጠየኳቸው። የንታም ልጄ ብሄር ማለት በግእዝ አገር ማለት ነው። ቡልጋ ደሞ ሽዋ ክፍላገር ውስጥ የሚገኝ አውራጃ ነው። የተስፋ ገብረሥላሴ አገር እዚያ ነው፤ አሉኝ።
ከዚያ አስኮላ ትምርት ገብቸ ፬ኛ ክፍል ህብረተሰብ መጽሀፍ ውስጥ የኢትዮጵያ ‘ብሄረሰቦችን’ የሚያሳይ ስዕል ተደርድሮ አየሁ። በተለይ ሲዳማን የዎከሉት ቆንጃጅት ሙገጫ ሲዎግጡ የሚያሳየው ስእል አይረሳኝም። ይሁን እንጅ ብሄረሰብ የሚለው ቃል አልገባኝም ነበርና አስተማሪየን ጠየኳት። እሷ ግን ጎሳ፣ ነገድ ቅብጥርሴ ብላ የባሰ ግራ አጋባችኝ። ደግነቱ ማታ ማታ የንታ ዘንድ ወንጌል እማር ነበርና ወንበር ከመጀመሩ በፊት ቀደም ብዬ ሄጄ የንታን ‘ብሄረሰብ ምን ማለት ነው?’ ብዬ ጠየኳችው። የንታም ብሄር ማለት አገር ነው፣ ሰብ ደሞ ሰው ማለት ነው። እንግዲህ ብሄረሰብ ያው የሰው አገር መሆኑ ነዋ አሉኝ። የበለጠ ግራ ተጋባሁ። ህብረተሰብ መጽሀፌ ውስጥ ያዬሁት የሚያማምሩ ቆንጃጅትን ምስል እንጅ ወንዝ ወይ ጋራና ሸንተረር አልነበረማ።Ethiopia and Eritrea map
ሁሉ ሆነና ደርግም በኢሕአዴግ ተተካ። አሁን ግራ ያጋባኝ የነበረው ‘ብሄረሰብ’ የሚለው ቃል ‘ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች’ ተብሎ ተራብቶ መጣ። የግዕዙን ቀጥተኛ ትርጉም ካየን እንግዲህ አገራት፣ የሰው አገራትና ህዝቦች እያልን መሆኑ ነው። ይሁንና ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ተብለው ይጠሩ የነበሩት የሁሉም ቋንቋ ተናጋሪዎች አሁን ‘ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች’ ሆነው የተባዙት አንዳንዶቹ ብሄረሰቦች ወደ ብሄርነት ሌሎቹ ደግሞ ወደ ህዝብነት ተለውጠው ይሁን በሌላ ምክንያት በውል አይታዎቅም። በአንጻሩ አሁን የኢትዮጵያ ህዝብ ብሎ ነገር የለም። በኢትዮጵያ ሕገ፡መንግስት ውስጥ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚል ቃል አይገኝም። ፖለቲከኞችም ‘የኢትዮጵያ ህዝቦች’ እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ ሲሉ አትሰሙም። ይህ አጋጣሚ የሚመስለው ካለ እሱ የዋህ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ማለት (ልክ በኢህአዴግ የመጀመሪያዎቹ ሰባት የስልጣን አመታት ኢትዮጵያ አገሬ የሚል ዘፈን እንደማዳመጥ ያለ) በትምክህተኝነት ሊያስከስስ የሚችል የፖለቲካ ፋውል መሆኑን እያንዳንዱ ካድሬ ስለሚረዳ ነው።
የኢትዮጵያ ሕገ፡መንግስት በአገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ ስልጣኑም ሆነ ምድሩ አንዲሁም በላዩና በውስጡ ያለው ሀብት ሁሉ ‘የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች’ የጋራ ሀብት ነው ይላል። ይህ ደግሞ ከሌሎች ኣገሮች ሕገ፡መንግስታት ሁሉ ልዩ ያደርገዋል (ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የሚለው ሀረግ እንደ ዋሊያ ኢትዮጵያ ብቻ ነው የሚታወቀው)። ይህ ይገርመኝ ነበርና ከአስር ኣመታት በፊት ከህገ፡መንግስት ጋር በተገናኘ የመመረቂያ ጽሁፍ ሳዘጋጅ ለመሆኑ አነዚህ የኣገሪቱን የፖለቲካ ስልጣንና ሀብት ኣንድም ሳያስቀሩ ጠቅልለው የያዙ ፍጡራን በትክክል አነማን ናቸው? ኣንዳቸው ከሌላቸው የሚለዩት በምን ነው? በአገሪቱ ውስጥስ ስንት ብሄሮች፣ ስንት ብሄረሰቦችና ስንት ህዝቦች አሉ? ለምሳሌ የቀበሌ መታወቂያ ስትወስድ ብሄርህን ተጠይቀህ ጉራጌ ብለህ ከሞላህ በኋላ ማታ በኢቲቪ የጉራጌ ብሄረሰብ ስላስመዘገበው ልማት ትሰማለህ። ታዲያ ብሄርና ብሄረሰብ አንድም ሁለትም ናቸው? ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎችን ይዠ መልስ ፍለጋ ሰነዶች ማገላበጥ ነበረብኝ። የህገ፡መንግስቱን ረቂቅ (ፕሪፓራቶሪ ዎርክስ) ሳይቀር አገላብጨ የሚረባ ነገር ላገኝ አልቻልሁም። ሕገ፡መንግስቱን በማርቀቅ የጎላ ድርሻ ነበራቸው የሚባሉትን ሰዎችም ጠይቄ ያገኘሁት ውጤት ኣልነበረም። በጣም ተገረምሁ። በአገራችን ላይ ከፈጣሪ ቀጥሎ ሁሉን ሀብትና ስልጣን ‘የተቆጣጠሩት’ ግኡዛን ማንነት እንዴት አይታዎቅም? ይህ እኮ እጅግ መሰረታዊ ጥያቄ ነው።
በተለይ ህዝቦች የሚለው ቃል ግራ አጋቢ ነው። በአለም ላይ አንድ ቋንቋ ተናጋሪ ወይም እንድ አይነት ማንነት ያላቸው ሰዎች ብቻ የሚኖሩባቸው አገራት ከአምስት አይበልጡም፤ ይህም ቢሆን በጣም የሚያከራክር ነው። ይሁን እንጅ የብራዚል ህዝቦች ወይንም የኬንያ ህዝቦች ቢባል እንግዳ ነው የሚሆነው። ምክንያቱም ህዝብ በትርጉሙ ያልተወሰነ ቁጥርና ማንነት ያላቸው ሰዎችን ያካተተ የጥቅል (የወል) ስም ስለሆነ ነው። ለዚህም ነው የአለም ህዝብ ቁጥር እንጅ የአለም ህዝቦች ቁጥር የማንለው። በርግጥ ፈረንጆቹም ከቅኝ በፊት ይኖሩ የነበሩ ቀደምት ጎሳዎችን (ትራይብስ) ለማመልከት ኢንዲጅነስ ህዝቦች ወይም አማዞን ውስጥ የሚኖሩ ህዝቦች ይላሉ። ይህ ግን ቀደምት ጎሳዎችን (ነገዶችን)የሚተካ ተለዋጭ ቃል እንጂ ተደራቢ ስያሜ አይደለም። ስለሆነም ቀደምት ጎሳዎችና ኢንዲጅነስ ህዝቦች አይሉም። እንዲያውም ኢንዲጅነስ ህዝቦች የየአገራቸው (ሰፊ)ህዝብ አካል ናቸው። ለምሳሌ የካናዳ ህዝብ በአገሩ የሚኖሩ ኢንዲጅነስ ህዝቦችን ያጠቃልላል። በዚህ አግባብ ከመደበኛ ሰዋሰው ርባታ ተቃራኒ ቢመስልም በአንድ አገር ውስጥ ህዝብ የሚለው ቃል ህዝቦች ከሚለው ቃል ይሰፋል ማለት ነው። ከላይ በጠቀሁት ምሳሌ የካናዳ ህዝብ ካናዳዊያንን በሙሉ ሲያመለክት የካናዳ ኢንዲጅነስ ህዝቦች ግን የካናዳ ህዝብ አካል የሆኑ (ከአጠቃላዩ ህዝብ ፭ ፕርሰንት እንኳን የማይሞሉ) ግን ደግሞ የየራሳቸው የተለየ ማንነት ያላቸውን ነገዶችን ብቻ የሚያመለክት ነው። በሁሉም አገሮች የሚኖሩ የተለያዬ ቋንቋና ማንነት ያላቸው ሁሉ በአንድ ላይ የዚያ አገር ህዝብ ተብለው ነው የሚታዎቁት።
ወደ አገራችን ስንመጣ ግን ሁለት አደናጋሪ ነገሮችን እናገኛለን። የመጀመሪያው ህዝቦች የሚለው ቃል አግባብ በሌላው አለም እንደሚታወቀው ሁሉ ቀደምት ነዋሪወችን (ኢንዲጅነስ ትራይብስ) ለማመልከት ነው እንዳይባል ኢትዮጵያ ውስጥ ቀደምት ያልሆነው ማን እንደሆነና ማን ከማን እንደሚቀድም አይታወቅም። እንዲያውም ሁሉም ‘ብሄር ብሄረሰቦች’ ቀደምት ነዋሪወች ናቸው ማለት ይቻላል። ቢያንስ ይህ ላለመሆኑ ተቃራኒ ማስርጃ የለም (እንዲያውም እኮ እንደ ሳይንሱ ከሆነ የአለም ህዝብ ሁሉ የተገኘው ከኢትዮጵያ ነው)። ‘ህዝቦች’ የሚለው ቃል አንዳንዶች እንደሚሉት አናሳ ቁጥርና አገራዊ የፖለቲካ ተሳትፎ ያላቸውን የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪዎችን ለማመልከት ነው እንዳንል እነሱው መልሰው ታዳጊ ብሄረሰቦች (አንዳንዴ አናሳ ብሄረሰቦች) ሲሏቸው እንሰማለን። ያ ከሆነ ደግሞ ብሄር ብሄረሰቦች በሚለው አገላለጽ ብንስማማ እንኳን ‘ህዝቦች’ የሚለው ቃል አላስፈላጊ ድግግሞሽ ከመሆንና ከማደናገር ኣልፎ የሚጨምረው ነገር የለም ማለት ነው። ሁለተኛውና በጣም የሚገርመው በአለም ላይ ባልተለመደ ሁኔታ በአገሪቱ የሚኖሩት ‘ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች’ በአንድላይ የኢትዮጵያ ህዝብ አይሆኑም። ይህ የሆነው አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባት ሕገ፡ መንግስታዊ ቃልኪዳን ገብተናል ያሉት ‘ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች’ የሚጋሩት ማንነት ሳይኖራቸው ቀርቶ ይሁን በሌላ ምክንያት አይታወቅም። ለነገሩ የአንድ አገር ህዝብ አካል ለመሆን የዚያ አገር ዜጋ ከመሆን ሌላ ምን የተለየ የጋራ ማንነት ያስፈልጋል?
ግድየለም፤ ያ ሁሉ ፖለቲካ ነው ብለን እንለፈው። እኛስ ቢሆን ቃላትን (አንደኣብዛኛዉ ነገራችን) እንደልባችን የምንጠቀመው ለምን ይሆን? ኢትዮጵያ በዘር ተከፋፈለች፣ የዘር ፖለቲካ ያጠፋናል፣ የጦር ሰራዊቱ ከኣንድ ዘር በወጡ አዛዦች ቁጥጥር ስር ነው፣ አቶ እከሌ በተቋሙ ውስጥ የነገሰውን ዘረኝነት በመቃዎም ስልጣናቸውን ለቀቁ፣ ወዘተ…በየቀኑ የምንሰማው ሮሮ ነው። ለመሆኑ ዘር ምንድን ነው? ኢትዮጵያ ውስጥ ስንት ዘር አለ? ለምሳሌ አማራ አንድ ዘር ትግሬ ደግሞ ሌላ ዘር ናቸው? ከሆነስ ከየት ነው የመጡት? እንደሚታወቀው ያን ያህል ሩቅ ከማይባል ጊዜ በፊት ግእዝ እንጂ ትግርኛም አማርኛም ኣልነበሩም። ታዲያ ያኔ ትግሬ ነበር? ኣማራስ? ሌላው ቀርቶ ሴሜቲክ፣ ኩሽቲክ የሚባለውስ ምናልባት ቋንቋን ከመግለጽ (ይህም አከራካሪ ይመስለኛል) የዘለለ ያለው አንድምታ ምንድን ነው? ለነዚህ ጥያቄዎች መልስ መስጠት ችሎታየም አላማየም አይደለም፤ ነገር ግን በጥንቃቄ መታየት የሚገባቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች ይመስሉኛል። እንዲያውም ስለማንነታችን ሳይንሳዊ ብንሆን ብዙ ችግራችን የሚቃለል ይመስለኛል። ኢሕአዴግ ኢትዮጵያ ውስጥ ‘ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች’ እንጅ እናንተ ቦታ የላችሁም፤ መሬቱ በሙሉ የእነሱ በመሆኑ እናንተ የመሬት ባለቤት መሆን አትችሉም ሲለን ቢያንስ እነዚያ ‘ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች’ በትክክል እነማን እንደሆኑ እንዲነግረን እንጠይቃለን። በአንጻሩ ደግሞ እኛ የዘር ፖለቲካ ወዘተ…ስንል ምን ማለታችን እንደሆነ መረዳትና ማስረዳት ያለብን ይመስለኛል።
destawats@yahoo.com
በዚሁ ላብቃ።
ሰላም