Tuesday, February 25, 2014

"ዩኒፎርሙን አውልቆ ካልሸጠው አንድ ጉራጌ ጄነራል አድርገን ሾመናል።"ጄኔራል ሳሞራ የኑስ

ብአዴን አመራሮች እና በካድሬዎቹ መካከል ከፍተኛ አለመግባባት ተፈጠረ።

February 25/2014
ምንሊክ ሳልሳዊ ፦

 ከሳምንታት በፊት ራሱን የአማራ ክልል ብሎ በሚጠራው የክልል አምባገነን ጁንታ አስተዳዳሪ ነኝ የሚለው የብኣዴን የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ አለምነህ መኮንን በድርጅቱ የውይይት መድረክ ላይ የአማራውን ህዝብ ለሃጫም እና ልጋጋም እንዲሁም መርዝ ብሎ መሳደቡን ተከትሎ በከፍተኛ ደረጃ የውጪ እና የውስጥ ተቃውሞ በየአቅጣጫው እየተነሱ መሆኑን ለምንሊክ ሳልሳዊ የደረሱ መረጃዎች ጠቁመዋል::

ሰሞኑን በብአዴን አመራሮች እና በካድሬዎቻቸው መካከል ግለሰቡን የተመለከተ አለመግባባት መከሰቱን እና ጥያቄዎች ከአባላቱ በስፋት እየመጡ መሆናቸውን የውስጥ ምንጮች ጠቅሰው የአዲስ አበባ እና አከባቢው የድርጅቱ ካድሬዎች ግለሰቡ እና ሁኔታው እርምጃ ሊወሰድበት ይገባል እስከማለት ደርሰዋል:: ይህንን ለመናገር የፈለገው ለምንድን ነው ተልእኮውስ ምንድነው? በሌላው ብሄር ላይ ይህ ነገር ቢነገር የድርጅታችን እርምጃ ምን ይሆን ነበር? ግለሰቡ በህግ ሊጠየቅ ይገባል::የሚሉ እና ተመሳሳይ ጥያቄዎች የተጠየቁ ቢሆንም አመራሮቹ እስካሁን መልስ ከመስጠት ይልቅ ኢዲሞክራሲይዊ በሆነ መንገድ አለመግባባቶችን ከመፍታት ይልቅ በማስፋት መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ ጸረ-... እያሉ ጠያቄዎችን በመወንጀል እና ዋናውን ክትትላቸው ያደረጉት ድምጹን ቀድቶ ማን አውጣው የሚለውን የማይመለስ ጥያቄ ይዘው አደና ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል::

ከድርጅቱ አንዳንድ ካድሬዎች እንደሚሰማው የድምጹን ቅጂ ያወጡት የሕወሓት ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ የሚሉ እና ሕወሓትን በጥርጣሬ የሚይስቡ እንዲሁም ግንቦት ሰባት ናችሁ ብለው እርምጃ ሊወስዱባቸው የሚፈልጉትን የብኣዴን ካድሬዎች ለመዋጥ የተደረገ ሴራ ነው::በድርጅታችን ውስጥ የማይበጁትን አንጠባጥቦ የራሱን ለመሰግሰግ ያሰረው ሕወሓት መንገድ አገኘ ቢሉም በለላ ወገን ደግሞ በድርጅቱ የተማረሩ እና የለውጥ ፍላጎት ያላቸው የብአደን አመራሮች አሹልከው ያወጡት እንደሆነ ይነገራል።ካድሬዎቹ ክፉና ደጉን እንድንለይ ላደረገን ኢሳት ቴሌቭዥን ምስጋና እናቀርባለን ሲሉ ተደምጠዋል:: በአመራሮቹ እና በካድሬዎቹ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት በዚሁ ከቀጠለ አቶ አለምነህ የድርጅት ስራ ብቻ እንዲሰሩ ወደ አዲስ አበባ ለማምጣት እና በክልሉ ላይ የተሰጣቸውን ስልጣን ለስም ብቻ እንዲቀመጥ የሚደረግ እንደሚሆን እና ቀስ በቀስ ከድርጅቱ ገፍቶ በማስወጣት አምባሳደር አድርጎ መሾም የሚሉ አስተያየቶች ከድርጅቱ አከባቢ ተደምጠዋል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የብሄር ተዋፅኦን እና የመኮንኖች ቅነሳን በተመለከተ ከፍተኛ የሆነ ክርክር መነሳቱን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ተናግረዋል:: እንደምንጮቹ ከሆነ በዚህ ሰሞን በተካሄዱ ተከታታይ ምስጢራዊ ስብሰባዎች ላይ የመከላከያ ሰራዊቱ በአንድ ብሄር በተሰበሰቡ ጄኔራሎች የተሞላ ነው: የመኮንኖች ቅነሳ ለምን አስፈለገ? ለምንስ አማራው እና ኦሮሞው ላይ አተኮረ ?ሰራዊቱ እና ቤተሰቡ በኑሮ ውድነት እየዋተተ ነው ከፍተኛ መኮንኖች በሙስና ተዘፍቀዋል ህገመንግስቱ አልተተገበረም የሚሉ የህዝብ አቤቱታዎች ተበራክተዋል ... የሚሉ በሰራዊቱ ውስጥ ተጠንቷል ተብለው በቀረቡ ጥያቄዎች ዙሪያ ክርክር እና ውይይት የተደረጉ ቢሆንም በሕወሓት ጄኔራሎች ማስፈራሪያ እና ዛቻ እንዲሁም ሞራልም ያልጠበቁ ስድቦች ካለውጤት እንደተበተኑ ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ገልጸዋል::

የአንድ ብሄር የበላይነት የምትሉት ለሕወሓት ያላችሁን ጥላቻ ለመግለጽ ነው ያሉት ጄኔራል ሳሞራ ጥያቄውን የፓርቲ ስብሰባ እስኪመስል ድረስ ጮኽውበታል::በትግል የከፈልነው መስዋትነት ውጤት እንጂ ከጎዳና ላይ መጥተን ማእረግ አልተሰጠንም::ከየብሄሩ አስፈላጊ ያልነውን ሊሰራልን የሚችለውን ጄኔራል እያደረግን እየሾምን ነው:: ዩኒፎርሙን አውልቆ ካልሸጠው አንድ ጉራጌ ጄነራል አድርገን ሾመናል። ሲሉ በመከላለያ ኢንዱስትሪ ምክትል አዛዥ ብርጋዴል ጄኔራል ጠና ላይ ተሳልቀውባቸዋል::

የሰራዊቱ መኮንኖችን ቅነሳ በተመለከተ የማይታጠፍ እቅድ ስለሆነ ተግብርዊ ይሆናል ያሉት ሳሞራ ብሄር ለይተን ያደረግነው ሳይሆን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ እና የመከላከያ ሰራዊቱ ተጠንቶ የሚወሰድ ኢርምጃ ነው ብለዋል::ለሰራዊቱ የምናደርገው ድጎማ የለም::ያልተመቸው ካለ ሰራዊቱን መሰናበት ይሽላል ሲሉ በቁጣ የመለሱ ሲሆን ሙስና የሚባለው ማስረጃ ያለው ሄዶ ሊከስ ይሽላል ከዚህ ውጭእ ስም ማጥፋት ነው ሲሉ ተደምጠዋል :;ህገመንግስቱን እና መንግስታዊ ስርኣትን በተመለከተ መልካም አስተዳደር እና ልማት ስለሰፈነ ቢዚህ ልይ ምተኮር ስፈላጊ አይደለም ብለዋል:: ከሰራዊቱ አባልት መሃል ገብተን ያስጠናነው ጥያቄ ነው እየተወይየንበት ያሉትን ሰነድ በተመለከተ ማንም የጦር መኮንን አስተያየት ያልሰጠበት እና ያልጠየቀ ሲሆን ሁሉም በዝምታ በማዳመጥ ሳይወያይ መስማማት አለመስማማቱን ሳይገልጽ የተነገረውን እንደ መመሪያ ተቀብሎት መውጣቱን ምንጮቹ ተናግረዋል::
 ምንሊክ ሳልሳዊ

Monday, February 24, 2014

በባህር ዳር ከተማ የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ እንድምታ (በገዛኸኝ አበበ ኖርዌይ )

February 24/2014

እባካችው እናንተ የፖለቲካ መሪዎች አንድ ሆናችው ሕዝቡን  ለለውጥ አነሳሱት



























ይቼን  አጠር ያለች ጹሁፍ እንድጽፍ ያነሳሳኝ በትናትናው እለት የካቲት 16 2006 ዓመተ ምህረት  የአማራ ክልል በሆነችው በባህር ዳር ከተማ  አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ (አንድነት) ፓርቲ እና መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በቅርቡ የብአዴን/ኢህአዴግ ዋና ፀሐፊ እና የአማራ ክልል ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ አለምነው መኮንን የአማርን ሕዝብ በማዋረደ እና በማናናቅ በአማራ ሕዝብ ላይ የተናገሩትን ስነ ምግባር የጎደለው ንግግራቸውን በመቃወም የጠሩትን  በደማቅ ፣ ደስ በሚል እና በሚያኮራ ሁኔታ የተጠናቀቀውን ታላቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በቪዲዩ ከተመለከትኩኝ በኋላ ነው::

ይህ በትናትናው እለት ተካሂዱ በነበረው  የሰላማዊ ተቃውሞ ሰልፍ ላይ የባህር ዳር ከተማ ሕዝብ በተለይም ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ሆ ብሎ በነቂስ በመውጣት እልህና ወኔ በተሞላበት ትህይንት ማንነቱን በገሀድ ያስመሰከረበት የተቃውሞ ሰልፍ እንደነበር ተመልክቻለው::  ወጣቱ ትውልድ ላይ ቁጭት ፣ ንዴት፣ እልህ እና ወኔ ይታይበታል የወያኔ የጭቆና እና የዘረኝነት አገዛዝ አማሮታል፣ ለውጥንም እንደሚፈልግ በአደባባይ በመጮህ  እየተናገረ ይገኛል:: የመለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ምሬት እና ብሶት ኢህአዲግ እና የኢትዮጵያ ሕዝብን ሆድ እና ጀርባ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል:: ሕዝቡም ከምሬቱ እና ከብሶቱ ብዛት የተነሳ ወኔን እና ድፍረትን በተላበሰ መንገድ ነበር የተቃውሞ ድምጹን ሲያሰማ የዋለው ::

ሕዝቡ በነቂስ ወቶ በድፍረት የተቃውሞ ድምጹን እንዲያሰማ የአንድነት እና የመኢአድ አባላትም ሆነ አመራሮች በአንድነት በመሆን የሰሩት ስራ የሚያስመሰግናቸው እና የሚያኮራ ተግባር ሲሆን ለሌሏቹም የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ትምህርት ሊሆን ይገባል  እላላው ::  የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥን ይፈልጋል::ስለዚህም  ለለውጥ እና ለትግል የሚያነሳሳው ቀስቃሽ አመራርን ይፈልጋል ::ይህን ለውጥ የናፈቀውን እና ነፃነት የናፈቀውን ሕዝብ ለለውጥ ትግል ማነሳሳት የተቀዋሚ ፓርቲ ድርጅቶች ተግባር እና ኀላፊነት መሆን ያለበት ጉዳይ ይመስለኛል :: የተቃዋሚ የፖለቲካ ፖርቲ ድርጅቶች አንድ ሀሳብ ይዘው በአንድ ራዕይ እና ትግል  ወያኔን ለመጣል እና ከስልጣኑ ለማስወገድ  ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎችንም ሆነ ማንኛውንም የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ቢተባበሩ እና ሕዝቡን ቢያነሳሱት ለውጥን ናፋቂው የኢትዮጵያ ሕዝብ በምንም ሁኔታ ውስጥ በማለፍን እና ትግሉ የሚጠይቀውን ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ባገኛው አጋጣሟ ሁሉ ቆራጥቱን እያሳየ እና እያስመሰከረ ይገኛል::

ይህንንም የወያኔ ካድሬዎችም ሆነ ባለስልጣኖች ጠንቅቀው የሚያቁት እና አሳሳቢ ጉዳይ የሆነባቸው ይመስለኛል :: ለዚህም ነው በተለያየ መንገድ በሕዝቡ ላይ የአካልም ሆነ የስነልቦና ጥቃት እያደረሱ የሚገኙት በህዝቡ ላይ እየደረሰ ያለው የአካልም ሆነ የስነልቦና ጥቃትእንዳለ ሆኖ  ወያኔዎች ወጣቱን ለመከፋፈል በተለያየ  ጥቅማጥቅም በማታለለ ለመያዝ እየሞከሩ ይገኛሉ:: ነገር ግን ለሆድ እና ለጥቅማ ጥቅም አልገዛም፣ ለወያኔም ካድሬዎች አላጎበድድም የሚለውን ወገን፤ የዚያ ድርጅት አባል የዚህ ድርጅት ደጋፊ እያለ ተለጣፊ ስም በመስጠት ከትምህርት፤ ከስራ እያፈናቀሉት፤ እያሰሩት፤ እያንገላታቱ ያሉት። ወያኔዎች ምክንያትን እየፈጠሩ ወጣቱን በግፍ በመግደልና በማሰር ትውልዱ በፍርሀት እንዲርድና ከትግል ራሱን  እንዲያገል ለማድረግ እና የራሳቸውን  የስልጣን ዘመን ቋይታቸውን ማስረዘሚያ አማራጭ መንገድ ማሰር፣ መግደል እና ሕዝብን ማወከብ   ነው ብለው ያምናሉ::

ለዚህም ነው ማንኛውም የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴዎች እንዳይሳኩ እና ሕዝብ ተሳትፎ እና እንቅስቃሴ እንዳያደርግ ወያኔዎች ሕዝብን የሚያዋክቡት እና የሚያስሩት ሰሞኑንም የባህር ዳሩ የተቃውሙ ሰልፍ በሚገባ እንዳይካሄድ እና ሕዝቡም ወጥቶ በሰልፉ ላይ እንዳይገኝ ለማድረግ  የወያኔ ካድሬዎች እና የወያኔ ቅጥረኛ ፖሊሶች የባህር ዳር ከተማን ሕዝብ ሲያስፈራሩ፣ ሲረብሹ እና ሲያውኩ እንደነበር መረጃዎች ጠቁመዋል ::  ነገር ግን የወያኔ ወከባ ያልረበሸው  የበባህር ዳር ከተማ  የሚኖረው የአማራው ሕዝብ ፍርሃትን በመስበር   የኢትዮጵያን ስም እየጠራ እና እያወደሰ ዘረኛውን እና አንባገነኑን ፋሽስቱን የወያኔን ኢህአዲግን መንግስት እና ባለስልጣናቶችን  በድፍረት ሲያወግዝ እና ሲያዋርዳቸው ማየት በቂ እና  ኩራት ነው እያልኩኝ ለባህር ዳር ከተማና በአካባቢው ለሚኖረው ሕዝብ ምስጋናዪን አቀርባለው :: በባህር ዳር ከተማ የተደረገውን እልህ እና ወኔ የተሞላበትን አጠር ያለች የተቃውሞ ሰልፍ ቪዲዮ ይመልከቱ ::

ወጣቱ ”ኑሮ መሮኛል” በማለት ቦሌ መንገድ ላይ ራሱን አጠፋ

November 24/2014

በቦሌ መንገድ ላይ ”ኑሮ መሮኛል” በማለት ራሱን ያጠፋው ወጣት በሱፍቃድ በጋሻው














ዛሬ በምሳ ሰዓት አካባቢ፤ በሱፍቃድ በጋሻው የተባለ ዕድሜው በሃያዎቹ ውስጥ የሚገመት ወጣት በቦሌ መንገድ ላይ ከአራት ጊዜ በላይ በተከታታይ ወደ ሰማይ ከተኮሰ በኋላ ራሱን አጠፋ። ራሱን ከማጥፋቱ በፊት ”ኑሮ መሮኛል” ሲል ተሰምቷል።

ቦሌ መንገድ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ በሚገኝ የሕብረት ባንክ ቅርንጫፍ በጥበቃ ሥራ ላይ የነበረው ወጣቱ በሱፍቃድ ለምሳ ተቀይሮ ሲገባ ከሥራ ባልደረባው ላይ የተቀበለውን የጥበቃ መሣሪያ ተቀብሎ ለጊዜው ምን እንደኾነ ያልታወቀ (እስካሁን እኔ ያላወኩት) ነገር እየተናገረ እየሮጠ ወደ ሰማይ አራት ጊዜ ያህል ከተኮሰ በኋላ አገጩ ላይ አስደግፎ ወደ ጭንቅላቱ በመተኮስ ራሱን አጥፍቷል።
በቦሌ መንገድ ላይ ”ኑሮ መሮኛል” በማለት ራሱን ያጠፋው ወጣት በሱፍቃድ በጋሻው
በአሁኑ ሰዓት አስክሬኑን ሰማያዊ የሚበዛበት ዥንጉርጉር ጨርቅ ሸፍነውት መንገድ ላይ ተኝቷል። የደንብ ልብሱን እደለበሰ ሲኾን፤ አጠገቡ በጥይቱ የተበሳ ኮፍያው ወድቋል። የጭንቅላቱ ስጋ እና አጥንቶቹ ተበታትነዋል።

በሱፍቃድ አጋር የተባለው የጥበቃ ሥራ የሚሠራ ኤጀንሲ ተቀጣሪ መኾኑን እና ሕብረት ባንክ ከመጣ ሁለት ወር አካባቢ እንደኾነው የሥራ ባልደረቦቹ ነግረውኛል። አሁን በተገኘ መረጃ ”ኑሮ መኖኛል” ሲል ተሰምቷል። እዛ አካባቢ ያሉ ፖሊሶች ደግሞ በምን እንዳወቁ አላውቅም ከቤተሰቡ ተጣልቶ ነው ብለዋል። አሁን አስክሬኑኑን የፖሊስ መኪና አንስቶታል።


በቦሌ መንገድ ላይ ”ኑሮ መሮኛል” በማለት ራሱን ያጠፋው ወጣት በሱፍቃድ በጋሻው











ምንጭ ኢትዮጵያ ዛሬ

ከኃይለመድህን አበራ እናት ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ!! “ከማጥናት በቀር ሌላ ነገር የማያውቁ፤ የተስተካከሉ ልጆች ነው ያሉን።”

February 24/2014
ረዳት አብራሪ ኃይለመድህን አበራ ባለፈው ሳምንት፤ ሲያበር የነበረውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ጄኔቭ ማሳረፉ የሚታወስ ነው። ከአብራሪው ጋር በተያያዘ እስካሁን እህቱ እና መንድሙ የየራሳቸውን ሃሳብ እና አስተያየት ሰጥተዋል። አሁን ደግሞ ከ እናታቸው ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ ይዘን እንቀርባለን። ቃለ ምልልሱን በድምጽ ያደረገው ዳዊት ሰለሞን ነው። ባህርዳር ላይ የተደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማስተባበር በስፍራው ተገኝቶ ነበር። እናም ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ቃለ ምልልስ አድርጎላቸዋል። በመግቢያውም ላይ እንዲህ የሚል ማስታወሻ ጽፏል። “በባህርዳር ቆይታዬ ከሰሞኑ ዋነኛ የመነጋገሪያ ርዕስ ከሆነው ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ወላጅ እናት ጋር ለጥቂት ደቂቃዎች የመገናኘት እድል ተፈጥሮልኝ ነበር፡፡ እናትየው የወንድማቸውን አርባ አውጥተው ከሩቅ ቦታ መመለሳቸው በመሆኑ ድካም ቢነበብባቸውም ለማቀርብላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት አላመነቱም፡፡ ምስጋናዬን እያቀረብኩ ልጃቸውን የተመለከተ መልካም ዜና እንዲያደምጡ ጸሎቴ ነው::” ብሏል።
ቃለ ምልልሱን ያደረገው – ዳዊት ሰለሞን
ወደ ጽሁፍ የመለሰው – ዳዊት ከበደ ወየሳ
ጥያቄ – ስምዎትን ማን ልበል?
መልስ – የህዝብአለም ስዩም።
ጥያቄ – እስኪ ስለቤተሰብዎ ያውሩኝ? ከባለቤትዎ ጋር ጋብቻ የፈጸሙት መቼ ነው?
መልስ -ከባለቤቴ ጋር ጋብቻ የፈጸምኩት፤ ሃምሌ 12 ቀን 1955 ዓ.ም. ነው። 12 ልጆች ወልደን አሳድገናል። ከአንዷ በቀር ሁሉም ልጆች በኢንጂነሪንግ የተመረቁ፤ ዶክተር የሆኑ ናቸው። ሁሉም ራሱን የጠበቀ ነው።
ጥያቄ – ሁሉም ልጆች ኢትዮጵያ ውስጥ ነው የሚገኙት?
መልስ -ሁለቱ ወንዶች እና ሁለቱ ሴቶች ልጆቼ ውጭ አገር ነው ያሉት።
ጥያቄ – ኃይለመድህን ስንተኛ ልጅዎ ነው?
መልስ -ኃይለመድህን 9ኛ ልጅ ነው።
ጥያቄ – ስለልጆችዎ አስተዳደግ ይንገሩን እስኪ? ባለቤትዎም አራጣ አበዳሪ ናቸው የሚሉ መረጃዎችም ወጥተዋልና ይህንን ጉዳይ ጠቅለል አድርገው ይመልሱልን? (ቀሪውን በPDF ያንብቡ)

Sunday, February 23, 2014

የሸፍጥ ክርክር የሃሰት ክምር የታሪክን እውነታ አይቀይርም! – ከኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ

February  23/2014

የካቲት 3 ቀን 2006 ዓ/ም የወያኔ/ኢሕአዴግ ሊቀ-መንበርና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ለአገር-ውስጥ ጋዘጤኞች በሰጡት መግለጫ ላይ የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ በድፍረት የሰጡት ምላሽ የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴን ብቻ አይደለም መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በእጅጉ ያሳዘነና ያሳፈረ ሆኖ አግኝተነዋል። በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እግር የተተኩት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የተረከቡት የመንግሥት ሥልጣንን ብቻ ሣይሆን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ከበሬታ-አልባነትንም በሚመስል መልክ ነው ይህንን በጣም የተምታታ፤ በተቃርኖዎች የተሞላና በእጅጉ ኃላፊነት-የጎደለው ጋዜጣዊ-መግለጫ የሰጡት።

ወርሃ የካቲት

February 23 /2014

በአገራችን ታሪክ ውስጥ ወርሃ የካቲትን ልዩ የሚያደርጓት ቁም ነገራት አሏት። አስቀድመን ጀግኖቹ አብርሃ ደቦጭ እና ሞገስ አስግዶም ግሪያዚያንን ያስበረገገውን ቦንብ ያፈነዱበት ወር የካቲት መሆኗን ማስታወስ እንወዳለን። በዚህ ምክንያትም በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከ30 ሺህ በላይ ህዝብ ተገድሎ የሰው ደም እንደ ክረምት ጎርፍ ከተማዋን ያጥለቀለቀው በዚህች በየካቲት ወር ነው። በሌላ በኩል ጠላቴ “የአማራ ህዝብ እና ተፈጥሮ “ነው ብሎ በፅኑ የሚያምነው ህወሃት የተወለደው በወርሃ የካቲት ነው። የየካቲት ታሪክ በዚህ ብቻ አያበቃም በወርሃ የካቲት ህወሃት “የመከላከያ ኃይል ቀን “ እያለ ከበሮውን እየደለቀ የሚድሪቷ ከርስ እሰከሚበረበር ድረስ ዳንኪራ ይረግጣል።
ለብዙ ኢትዮጵያዊያን ግን የካቲት የደስታ ወር አይደለችም። የካቲት በግፍ የተገደሉብንን ዜጎቻችንን እያስታወስን ልቦናችን በሃዘን የሚታወክበት እንጂ ሃሴት የምናደርግበት ወር አይደለችም። በየካቲት ወር ግራዚያን “ያገኛችሁትን ኢትዮጵያዊ ሁሉ ግደሉ” ብሎ አዋጅ በማስነገሩ በጭካኔው የምንቆጣበት እንጂ በደስታ የምንሰክርበት ወር አይደለችም። በወርሃ የካቲት የሌላውን ቦታ ሳይጨምር በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከ30ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ሲጨፈጨፉ ከግራዚያን ጎን ቁመው ወገኖቻቸውን ያስጨፈጨፉ ባንዳዎችን እያሰብን አንገታችንን ደፍተን የምናዝንበት ወር እንጂ የደስታ ወር አይደለችም። ወርሃ የካቲት ለኢትዮጵያዊያን በደግ የምትታወስ ወር አይደለችም። በወርሃ የካቲት የተወለደው ህውሃት የተባለው ዘረኛና ዘራፊ ቡድን በአገራችን ላይ ያደረሰውን ግፍ እያሰብን ግፉ እንዲያበቃ አእምሯችን የምንሰበስብበት ወር ነች። ህወሃት በመወለዱ ኢትዮጵያችን የድሆች ሁሉ ድሃ፤የደካሞች ሁሉ ደካማ፤ ልትበታተን አደጋ አፋፍ ላይ ያለች አገር ተብላ ሥሟ በበጎ የማይነሳ አገር እንድትሆን ሆነች።
ህወሃት በወርሃ የካቲት ተወለድኩ ሲል አወጀ። ከዚያም ቀጥሎ እንዲህ አለ “አማራና ተፈጥሮ ጠላቶቼ ናቸው” ሲል ድምፁን ከፍ አድርጎ ጮኸ። ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚያምን ከተገኘም አሸባሪ እና ትምክህተኛ ነውና ይገደል ሲል ያልተፃፈ ህግ አፀደቀ። በየካቲት ወር ይህን የሞት ድምፅ ብዙ ዜጎች በአርምሞና በግርምት ሰሙት። ህወሃት አገሪቷን ክተቆጣጠር በኋላ ከሁለት ሚሊዮን በላይ አማራ የገባበት አልታወቀም ተብሎ ለፓርላማ መሰል አካሉ ሪፖርት ቀረበ። በግራዚያን አዋጅና በህወሃት አዋጅ መካከል ልዩነት የለም። በየካቲት ወር ግራዚያን “ያገኛችሁትን ኢትዮጵያዊ ሁሉ ግደሉ” ብሎ የሞት አዋጅ አወጀ። በዚህ አዋጅ ምክንያት በአንዲት ጀንበር 30ሺህ ኢትዮጵያዊያን በአዲስ አበባ ተፈጁ። ግዲያውን ለማስፈፀም ከፊቱ የቀደሙ በስም ኢትዮጵያዊን በምግባር ግን ፋሽት የሆኑ ምናምንቴዎች ነበሩ። ከእነዚህ ውስጥ የመለስ ዜናዊ እና የስብሃት ነጋ ወላጆች በፍፁም የሚረሱ አይሆኑም። እነዚህ የባንዳ ውላጆች በወርሃ የካቲት “አማራና ተፈጥሮ ጠላቶቼ ናቸው” ብለው አውጀው ህወሃትን መሥርተው ለስልጣን ከበቁ በኋላ 2ሚሊዮን አማራ ጠፋ። በወርሃ የካቲት የተወለደው ህወሃትና ፋሽስቶችን ከሚያመሳስለው ድርጊት መካከል አንዱ ይሄው ነው። በየካቲት የተወደው ህወሃት ኢትዮጵያን በመከራ አረንቋ ውስጥ ደፍቆ እስከ ዛሬ ዘለቀ። በዚህ ምክንያት ወርሃ የካቲት ለኢትዮጵያዊያን ደገኛ ወር አይደለችም።
በኢትዮጵያዊያን ታሪክ ውስጥ የካቲት የምትታወስበት ሌላ አብይ ነገር ደግሞ አለ። አብርሃም ደቦጭና፤ሞገስ አስግዶም የተባሉ ከኤርትራ የመጡ ወጣቶች የኢትዮጵያ ጠላት በሆነው በግራዚያን ላይ የፈፀሙት ጀግንነት ነው። እነዚህ ሁለት ወጣቶች በጨካኙ ግራዚያኒ ላይ በወረወሩት ቦንብ በፋሽስቶቹ መንደር ጉዳት አደረሱ። ይሄ ድርጊት በአርበኝነት ተሠማርተው ለነበሩት ጀግኖች አበረታች ድርጊት እንደነበረ በታሪክ ተመዝግቧል። ከዚህ ድርጊት በኋላ ግን በሦስት ቀን ብቻ በአዲስ አበባ ከተማ ከ30ሺህ በላይ ህዝብ ተገደለ። በዚሁ በየካቲት ወር አብርሃምና ሞገስ አልፈውበታል በተባለው በደብረ ሊባኖስ ገዳም የተገኙ 297 መናኞች እና ሌሎች 23 ኢትዮጵያዊያን በአንዲት ጀንበር እንዲገደሉ ተደረገ። ይሄ ሁሉ ግዲያ ሲፈፀም ቀላል የማይባሉ ባንዳዎች አብረው ከግራዚያን ጎን ቁመው ነበር። እንዲህ ዓይነቱን አሰቃቂ ድርጊት እንዲፈፀም ትእዛዝ የሰጠው ግለሰብ ሃውልት በአደባባይ ይሠራለትና ሥሙም ለዘላለም ይታወስ የሚሉ የፋሽት አቀንቃኞች በተነሱ ግዜ ህወሃቶች ዝምታን መረጡ። እንዲያውም የፋሽቶች ሃውልት በአደባባይ እንዳይቆም ለመቃወም የተነሱ ኢትዮጵያዊያንን በቆመጥ እየደበደቡ የተቃውሞው ድምፅ እንዳይሰማ ሰልፉን በማፈን ለፈሽቶች ያላቸውን ክብር አስመስከሩ። ከወርሃ የካቲት ትዝታዎቻችን መካከል መታወስ ያለበት አንዱ የህወሃት መልክ ይሄው ከፋሽስቶች ጋር የመደጋገፍ ድርጊቱ ነው።
ወርሃ የካቲት ሌላም ገፅታ አላት። በዚህች በየካቲት ወር ህወሃቶች የመከላከያ ቀን እያሉ በስካርና በፈንጠዝያ ያከብራሉ። ኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል ከገነባችም ሃያ አንድ ዓመት ሞላት እያሉም ይዘባትላሉ። እውነቱ ግን አገራችን ኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊቷን ካጣች ሃያ አንድ ዓመት መቆጠሩ ነው። በዘመነ ህወሃት ኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አላት ለማለት በሚያስችል ሁኔታ ላይ የምትገኝ አገር አይደለችም። ብዙ መልክ እና ባህል ባላቸው ዜጎች በቆመች አገር ውስጥ አጠቃላይ የመከላከያ ሠራዊቱ አዛዦች ከአንድ ወንዝ የተቀዱ ፤ከአንድ መንደር የተሰባሰቡ ስለመሆናቸው ቀደም ብለን ያወጣነውን መረጃ ማየት ይረዳል። የእነዚህ ቡድኖች ከአንድ ወንዝ መቀዳታቸው፤ ከአንድ መንደር መሰባሰባቸው ችግር አይደለም፤ችግሩ የሚነሳው ግለሶቦቹ ፍፁም ኃላፊነት የማይሰማቸው፤በአፍቅሮተ ንዋይ የታወሩ፤የአገርና የወገን ፍቅር የሌላቸው ፍፁም ጨካኝና ክፉ ዘረኞች ሁነው የመገኘታችው ነገር ነው አገሪቷን ውሉ ከማይታወቅ ችግር ውስጥ የዘፈቃት። ዛሬ ካርታ ይዘው የቆሙበትን ሥፍራ ለማሳየት የሚደናበሩ ጄኔራሎች ባለሚሊየን ዶላር ሃብት ባለቤት የመሆናቸው ነገር አገሪቷ ከተጋረጡባት ችግሮች መካከል አንዱ ነው። የመከላከያ ቀን ሲከበር የጦሩ አለቆች ከአንድ ምንጭ የተቀዱ ዘራፊዎች፤ነፍሰ ገዳዮችና፤ አለሰፋራቸው ሚሊየነር ነጋዴ ሁነው የመገኘታቸው ነገር አብሮ መታወስ
በየካቲት ወር የመከላከያ ቀን ሲከበር አብረን የምናስታውሳቸው ሌሎች አሳዛኝ እውነቶች ደግሞ አሉ። ከብዙዎቹ ጥቂቶቹን ለማስታወስ ያክል የአገሪቷ መከላከያ ሠራዊት በሠላም አስከባሪ ሥም ሶማሊያ ድረስ ዘልቆ ገብቶ የሚሞትበትንና የሚገድልበትን ምክንያት ዜጎች የማወቅ መብት የላቸውም መባሉን ከመከላከያ ኃይል ቀን አከባበር ጋር አብረን የምናስታውሰው ጉዳይ ይሆናል። ከዚህ ጋር ተያይዞ መታወስ ያለበት እውነት ደግሞ በሠላም አስከባሪ ሥም የህወሃት ጄኔራሎች እየተፈራረቁ በየቀኑ ከ160 ዶላር በላይ ዓበል የመሰብሰባቸው ጉዳይ ነው። ጄኔራል ተብየዎች በየቀኑ ከ160 ዶላር በላይ ሲያጋብሱ ድሃው ወታደር ግን ለምንና ለማን እንደሚሞት ሳያውቅ በወጣበት ይቀራል። አስከሬኑም ክብር አጥቶ በሶማሌ ጎዳናዎች ላይ እየተጎተተ መሳቂያ መሳለቂያ ይሆናል። የህወሃት ጄኔራሎች ግን በዚህ ሁኔታ ዜጎችን እያስፈጁ ለሦስት ወታደር በወር የሚከፈለውን ደሞዝ በየቀኑ ወደ ኪሳቸው እየክተቱ በደስታ ይሰክራሉ።
የመከላከያ ኃይል ቀን ሲዘከር አብረን የምናስታውሰው በአገሪቷ ሥም የተቋቋመው ሠራዊት የገዛ ዜጎቹን ያለ ርህራሄ የሚገድል፤ ኦጋዴን ወርዶ ዘር የሚያጠፋ፤ጋምቤላ ወጥቶ ያገኘውን ሁሉ የሚገድል፤አዲስ አበባ ላይ ከተማሪ ቤት የሚመለስ ህፃንን ሳይቀር ተኩሶ ለመገድል የማይራራ። የሚፈፅመውን የጭካኔ ድሪጊት ከትክክለኛ ኃላፊነቱ ጋር ደባልቆ የሚያይ ቡድን መሆኑንም አብረን ማስታወስ አለብን። ይሄ ሠራዊት ተብሎ የሚጠራው ቡድን ሊጠብቀው የሚገባውን ህዝብ እንዲያሸብርና እንዲገድል ሁኖ የተቀረፀው በህወሃቶች እኩይ አመራር መሆኑንም በየካቲት ወር ክሚከበረው የመከላከይ ቀን ጋር አብረን እናስታውሳለን።
ወርሃ የካቲት የህወሃት የውልደት ወር፤የግራዚያን የግፍ ግዲያ ወር፤የህወሃት መከላከያ ኃይል የሚከበርባት ወር በመሆን እየታወሰች ነው። የካቲት በአገራችን ላይ የሃዘን ድባባ ያጠላባት ወር እንጂ ከበሮ የሚመታባት፤ ዳንኪራ የሚረገጥባት ወር የምትሆን አይደለችም። ህወሃቶች ግን ይህችን ወር እየጠበቁ ከበሯቸውን እየደቁ፤ የምድሪቷ ከርስ እስከሚበረበር ድረስ ዳንኪራ እየረገጡ ይውረገረጉባታል። ለብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ ግን የካቲት የትካዜ ወር እንጂ የደስታ ወር
በመጨረሻም ህወሃቶችን እንዲህ እንላችኋለን !
የካቲትን እየጠበቃችሁ ከበሮ የምትደልቁበት ዘመን እንደሚያበቃ አትጠራጠሩ። ህወሃቶች ሆይ! ስሙን ! አገር አልባ አድርጋችሁናል። የአገራችንን ግርማ አጥፍታችሁ፤ዝናዋን አዋርዳችሁ የደካሞች ደካማ፤የርሃብተኞች ርሃብተኛ እንድትሆን አድርጋችኋል። ዜጎች በማይገባቸው ጦርነት ውስጥ ገብተው አለ በቂ እና አሳማኝ ምክንያት እንዲሞቱ አድርጋችኋል። በዜጎች ደም እየነገዳችሁ ብዙ ሚሊየነር ጄኔራሎችን አፍርታችኋል። ዜጎች ኢትዮጵያ ውስጥ ከምንኖር ሂደን የበርሃ ሲሳይ እንሁን፤ የባህር አዞም ይብላን እያሉ እንዲሰደዱ ምክንያት ሁናችኋል። እናንተ በዚህ ሁኔታ ህዝቡን እያስለቀሳችሁ የካቲት በደረሰች ቁጥር ከበሯችሁን እየደቃችሁ በደስታ ትሰክራላችሁ። ይሄ ግን በዚሁ እንደማይቀጥል እኛ እንነግራችኋለን። ደግሞም አትጠራጠሩ፤ በዚሁ አትቀጥሉም። ከእናንተ ጋር ያሉት ሌሎች ግራዚያኒ ያገኛችሁትን ኢትዮጵያዊ ሁሉ ግደሉ ብሎ ትዕዛዝ ሲሰጥ ከጣሊያን ወታደሮች ለሚወረወርላቸው ፍርፋሪ ብለው ወገኖቻቸውን አሳልፈው እንደሰጡ እንደዚያን ግዜ ባንዳዎች ከማየት የዘለለ የሚባልላቸው ሌላ ነገር የለም። ወገናቸውን ህዝባቸውንና አገራቸውን የካዱ መሆናቸውን እኛ ብቻ ስናሆን ራሳቸውም ጭምር ያውቁታል። ለማንኛውም እናንተም ሆናችሁ ለምናምን ሲሉ ወገኖቻቸውን አሳልፈው የሰጡ የአስቆሮታዊው ይሁዳ ምሳሌዎች ቀናችሁ እየጨለመ መሆኑን ዓይናችሁን ከፍታችሁ እንድታዩ እንመክራችኋለን።
አበቃን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!

Hailemariam Desalegn’s Confused Statements

February 23, 2014
by Amanuel Biedemariam
On February 10, Prime Minister Hailemariam Desalegn of Ethiopia gave reporters access and conducted a press conference. The statements of Hailemariam are fraught with inconsistencies and telling that there is a serious leadership vacuum and lack of direction in Ethiopia. The statements lack principle, direction and strategy. The messages are inconsistent and contradictory to previous statements.
On an interview with Africa Confidential January edition, when asked what’s your Eritrea policy? PM Hailemariam Desalegn said,
“Our Eritrea policy is very clear. These two peoples are very friendly; the normalizing of relations, also with the governments, should come as soon as possible. We have accepted unconditionally the rulings [on the border] and so this has to implemented but with a discussion because the implementation process needs something on the ground since it is a colonial rather than a people’s boundary.” Emphasis added.
For a while, Ethiopians have been expressing anger and concern about the border issue between Ethiopia and Sudan claiming that the minority TPLF regime has unlawfully ceded huge chunks of Ethiopian territories to Sudan. The tenet of their argument is that the signatures of Meles Zenawi and Hailemariam Desaleng are unlawful, null and void based on Article 55(12) of Ethiopian constitution which demands accountability and ratification by parliament. On a recent article, “Save Ethiopia From Chopping Block”,  Dr.Alemayehu G. Mariam wrote,
“It is important to understand and underscore the fact that the “agreement” Meles and Bashir “signed”, by Meles’ own description  and admission, has nothing to do with the so-called Gwen line of 1902 (“Anglo-Ethiopian Treaty of 1902” setting the “frontier between the Sudan and Ethiopia”). It also has nothing to do with any other agreements drafted or concluded by the imperial government prior to 1974, or the Derg regime between 1975 and 1991 for border demarcation or settlement. Meles’ “agreement”, by his own admission, deals exclusively with border matters and related issues beginning in 1996, when presumably the occupation of Sudanese land by Ethiopians took place under Meles’ personal watch.”
Citing Wikileaks, Dr. Al Mariam writes,
“Former TPLF Central Committee member and former Defense Minister Seeye Abraha told” American embassy officials in Addis Ababa that in a move to deal with “on-going tensions between Ethiopia and Sudan”, Meles had turned over land to the Sudan “which has cost the Amhara region a large chunk of territory” and that Meles’ regime had tried to “sweep the issue under the rug.”
It is unlikely that the views and efforts of the people of Ethiopia will ever see the daylight vis-à-vis the border agreements that Meles Zenawi or Hailemariam Desalegn signed or concluded since there is no question on the legitimacy of their positions by the international community. International agreements they signed will undoubtedly stand.
In response to those concerns Hailemariam responded,
“The historical border agreement between the two nations dates back to the time of Emperor Menelik II when the Sudan was under the protectorate of the British Empire. There should not be any confusion on the issue since the agreement that was signed then was evaluated and accepted by successive regimes that came after Menelik’s. The border agreements has been accepted and endorsed by the regimes and that there could not be any new matter that his administration has to deal with. “All that is left is to implement the already demarcated and delimited border agreement. So, there are no issues with the agreement: it is binding; the only thing left is to put posts on these borders.”
Hailemariam claims that Ethiopia is committed to regional peace. Why then is his regime illegally occupying internationally delimitated border with Eritrea? Why the doublespeak? The inconsistencies however are not limited to the border issues. Hailemariam’s positions and actions in Somalia and his view of Uganda’s role on the current conflict on SS are contradictory and dangerous for regional stability and progress. When he addressed Ugandan forces in SS, citing that the problem is political, Hailemariam said,
“We believe that all forces that were “invited” by different forces in that country have to withdraw phase by phase.”
The irony, on the same press conference, while addressing Somalia, Hailemariam claiming to have bilateral agreement with the government in Somalia tried to legitimize the presence of Ethiopian forces in Somalia. He said Ethiopia is in Somalia as AMISOM “based on the “request” of the Somali government.”
Ugandan forces are in S. Sudan based on the “invitation” of the legitimate government of S. Sudan. Why then is Hailemariam seeking or talking political solution for the civil war in South Sudan while interfering in Somalia militarily? Why not political solution in Somalia? Assuming that the government in Somalia is independent and free to request assistance freely as a nation, why deny the same right to the government in South Sudan? Hardly anyone believes that Ethiopian forces are welcome by the people of Somalia. AMISOM or not, Ethiopian forces are not welcome. To the contrary Ethiopia’s incursion into Somalia was not received well.
On a recent interview with the VOA, former U.S. Ambassador to Ethiopia David Shinn said that it is a “mistake” for Ethiopian troops to join the AMISOM force in Somalia.
Peace, security, terrorism and Al Shabab are justifications for Hailemariam to return into Somalia. The reality, however, Ethiopia’s incursions into Somalia is impediment to peace and source of great instability.
Ambassador Shinn continued, Ethiopian move could allow al-Shabab to use it as a “rallying cry to recruit new members.”
Moreover, Hailmariam’s positions are contradictory and self-serving as it regards to IGAD’s role on the current conflicts in the region. Hailemariam evoked IGAD and AU to make a case against the presence of Ugandan troops in South Sudan and ignored the role of IGAD in Somalia. Uganda is in South Sudan based on the request of the sitting government of Salva Kiir Miardet, just like Ethiopia is in Somalia based on claims of a request. Why then Hailemariam undermining IGAD’s role in Somalia?
Hailemariam Desalegn’s Compromised Stature     
By all standards Hailemariam Desalegn is on a tenuous position on many levels for many reasons.
Firstly, he is not from the region of the minority clique ruling the country. Many consider Hailemariam as a figurehead. On the 17 Feb, The Telegraph’s reporter David Blair on his report, “Ethiopian Airlines hijacking: Why co-pilot might have taken extreme steps to leave” wrote,
“Two key “push factors” lie behind this outflow: repression and poverty. Ethiopia is a de facto one-party state, dominated by small autocratic elite. Under the previous Prime Minister, Meles Zenawi, elections were shamelessly rigged and the opposition simply closed down. Many Ethiopians believed that Meles favored his own Tigray-Tigrinya ethnic group, who comprise less than seven per cent of the population, for the most powerful and privileged positions in the land.”
Hence, PM Haileriam Desalegn is considered a transitional figurehead until the election of 2015 and likely to be replaced by another member of the TPLF to pursue Zenawi’s agendas.
Secondly, Hailemariam inherited a country with a diminished regional and international influence for many reasons: A) The US has accomplished much of what it intended in Somalia hence the role required from Ethiopia is diminished. B) George Bush’s Somalia war on terror agenda, which the minority regime exploited extensively seems to have shifted slightly as the government in Somalia is recognized by the international community.
Thirdly, the countries in the region have opposing positions and interests on many areas as recent developments in S. Sudan exposed. Additionally,  these countries have demonstrated ability to compete with Ethiopia on many fronts denying Ethiopia the anchor-state-status it enjoyed unchallenged for a while thus minimized Ethiopia’s exclusive role in that regard.
Fourth, International actors such as China and Russia are playing significant roles to influence events and outcomes to favor their geostrategic interests. To be effective, China and Russia need to include all and play a balanced hand with all the nations in the region further diluting Ethiopia’s once dominant role.
Hailemariam’s Diminished Regional Roles 
One of the strongest suits of Meles Zenawi was the fact that he managed to co-opt influence from the regional actors using any means necessary. That level of influence died with Meles for many reasons:
  • The power transition took a long time to materialize. Between the times Meles was rumored sick, his death and the time it took to complete the transition creating vacuum.
  • The transition was manipulated to appease US interests while the real power remained on the hands of few Tigrayans led by the then Information Minister Bereket Simon who is considered the power controlling Hailemariam.
  • The regional actors are focusing on their own interests. One good example of this is the current conflict in S. Sudan and how it will likely affect the dynamics of the relations between South Sudan, Uganda and Ethiopia regarding the Nile. Hailemariam is forced to wager Ethiopia’s interests regarding the Nile in order to pursue US agendas in South Sudan. No consensus on South Sudan could lead to lack of consensus on issues of mutual importance including the Nile. Meles Zenawi was able to garner consensus and support for Ethiopia’s positions on the Nile which is hard for Hailemariam to replicate.
Furthermore, Uganda, Kenya, South Sudan, Rwanda have mutual interests independent from Ethiopia because all these countries depend on port of Mombasa in Kenya for their imports. This gives Kenya leverage and importance that Hailameariam cannot match.
Moreover, initially, with the help of the US, the regime was able to create alliances with countries in the region specifically to encircle and suffocate Eritrea to submission. At this stage, while Hailemariam desperately tries to pretend that Eritrea is isolated; the reality is Eritrea has turned the table. Eritrea has relations with Uganda, Sudan, Kenya, South Sudan and Egypt. At the current stage Hailemariam has no relation with Eritrea, Egypt, opposing positions with Uganda and South Sudan and Kenya has more interest independent from Ethiopia. In effect, Ethiopia is encircled further diminishing Hailmariam’s roles.
  • Shifting US foreign policy. Recent statements by former US diplomats regarding Eritrea stirred frantic reaction. The TPLF went on a full-fledged PR campaign to attack the issues and the personalities demonstrating fear the minority regime has of losing its status that it depends on for its very survival. On a piece about Zenawi’s legacy “Ethiopia: Revelation of Zenawi’s vision for Tigray,” Robele Ababya wrote,
“When asked, in the aftermath of the 2005 election, what legal authority he had to by-pass the Parliament and declare a state of emergency, Zenawi responded by saying that, after all, the donors did not object to the action he took. His response is solid proof, among others, that the monstrous killer was subservient to the interests of the donors at the expense of the vital interests of poor Ethiopia.”
Without US support the regime cannot survive. Hence fighting to maintain the “special-relation” status with the US is a question of survival. That however is beyond the control of the US as more African nations are looking for partnership with China, Russia, India, Brazil and other countries that are more focused on economic issues that Africa desperately need. This diminished US control of African agendas further diminishing Hailemariam’s role in the region that the late Zenawi enjoyed unchallenged.
Hailemariam Desalegn Lame Duck Personified
In the US, a president is generally considered a lame duck at the end of his tenure or when a successor is elected. What that generally means is, during that phase, if the president is not popular his/her influence could not translate into furthering his/her agendas and naturally no coattails. In reality, however, the president’s power is intact to the point that he/she can even wage wars.
In Hailemariam’s case, however, he is a lame duck in the truest sense because in Ethiopia, power is on the hands of the few repressive Tigrayans that are vying for time until the next election. “Ethiopia is a de facto one-party state, dominated by a small autocratic elite” controlling Hailmariam’s actions and public statements.
In addition, Hailemariam has no constituency inside Ethiopia or the Diaspora. Support for Hailemariam is virtually nonexistent.
Conclusion
The situation in Ethiopia is unsustainable. Ethiopia is under extreme internal and external pressures that will ultimately explode abruptly. As demonstrated above, to further the interests of the super powers, the regime suppressed the people and took unnecessary antagonistic positions by becoming a pseudo-hegemon of the region.   
What the press conference demonstrated is that PM Hailemariam Desalegn tried to address concerns of many stakeholders and failed. He tried to address the concerns of the people of Tigray, US interests, Somalia and regional actors. He tried to address Eritrea in a manner that satisfied TPLF and all Ethiopians and failed.
Ethiopia is on a holding pattern bracing for change on the upcoming election. The questions are many. There exists no political party to challenge the TPLF. What does the US want in this transition? Can the TPLF bring a successor from Tigray and continue the “legacy” of Meles? How would the US react to that?
In the absence of clear leadership direction these questions take on a new meaning enlarging the gap between all the publics. That means PM Hailemariam Desalegn will have to await his fate to be decided by the TPLF as the rest of Ethiopia.
Awetnayu@hotmail.com
-VOA Ethiopian AMISOM Membership Scrutinized
-Ethiopia: PM’s Day With the Press Yohannes Anberbir AllAfrica February 15, 2014
-Alemayehu G. Mariam Saving Ethiopia from the Chopping Block
-The Telegraph David Blair, Ethiopian Airlines hijacking: Why co-pilot might have taken extreme steps to leave 17 Feb 2014
-Africa Confidential January edition

Saturday, February 22, 2014

የመከላከያ ተቋም ተግባር አገርን መጠበቅ ነዉ ወይስ አገርን መዝረፍ?

February 22/201

የአዉሮፓ ቅኝ ገዢዎች አፍሪካን ሲቀራመቱ ባህር ተሻግረዉ በመጡ የነጭ ባዕዳን ኃይሎች መገዛትን መርጦ የአዉሮፓን ወራሪዎች በሰላም በሩን ከፍቶ ወደ አገሩ ያስገባ እንድም የአፍሪካ አገር አልነበረም፤ የኋላ ኋላ ተሸንፈዉ በቅኝ አገዛዝ ቀንበር ስር ቢወድቁም ሁሉም የአፍሪካ አገሮች እንደ አቅማቸዉ ከወራሪ ኃይሎች ጋር ተፋልመዋል። በአንድ ወቅት የቅርብ ጎረቤቶቻችንን ጨምሮ ብዙዎቹ የአፍሪካ አገሮች በወራሪ ኃይሎች ተሸንፈዉ የቅኝ ገዢዎች ቀንበር ጀርባቸዉ ላይ ሲጫን አገራችን ኢትዮጵያ ብቻዋን የአለም ጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተምሳሌት ሆና የኖረችዉ ጣሊያኖች፤ እንንግሊዞችና ፈረንሳዮች ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ለይተዉ ስለወደዷት ወይም ስላከበሯት አይደለም። ይልቁንም ነፃነታችንና የግዛት አንድነታችን ተከብሮ የኖረዉ ኢትዮጵያ እናት አገሩ በጠላት ስትደፈር ከሚያይ ምትክ የሌላት ህይወቱ ብታልፍ ደስ የሚለዉ የኩሩና የጀግና ህዝብ አገር በመሆኗ ነዉ። የሚገርመዉ ይህ ኩሩና ጀግና ህዝብ ጣሊያንን የመሰለ በዘመናዊ መሳሪያ የታጀበ ኃይል ዉርደቱን ተከናንቦ ወደመጣበት እንዲመለስ ሲያስገድድ እንደ ዛሬዉ የተደራጀ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት አልነበረዉም። ዛሬ አራት ኪሎና ስድስት ኪሎ ላይ የተተከሉት ሁለቱ ታሪካዊ ሀዉልቶቻችን የሚነግሩንም ይሀንኑ የኢትዮጵያ ህዝብ በዘመናዊ መልክ የተደራጀ ሠራዊት ሳይኖረዉ የጎበዝ አለቃ እየመረጠ በጣሊያን ፋሺስቶች ላይ የተጎናጸፈዉን አኩሪ ድል ነዉ።
ኢትዮጵያ ዉስጥ ዘመናዊና የተደራጀ መከላከያ ሠራዊት ጥንስስ የተጣለዉ በዳግማዊ ሚኒልክ ዘመነ መንግስት ሲሆን እሱም ቢሆን ከአድዋ ድል በኋላ ቆይቶ የመጣ ክስተት ነዉ። በአፄ ኃ/ሥላሤና በደርግ ዘመነ መንግስት ኢትዮጵያ ለአንድ ፓርቲና ይህ ፓርቲ እወክለዋለሁ ለሚለዉ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ሙያዊ ብቃት የነበረዉ፤ሙያዉን የሚያከብርና ለአገሩና ለወገኑ ታማኝ የሆነ የመከላከያ ሠራዊት ነበራት። የወያኔ ዘረኞች አዲስ አበባን ሲቆጣጠሩ የመጀመሪያ ኢላማቸዉ አድርገዉ ካወደሟቸዉ ዋና ዋና የአገራቸን ተቋሞች ዉስጥ የመጀመሪያዉ ይሄዉ የአገርና የህዝብ ደጀን የነበረዉ ተቋም ነበር። ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ የአገር መከላከያ ሠራዊት እየተባለ የሚጠራዉ ተቋም ለጎጠኞች ጥቅምና የስልጣን መራዘም የቆመ፤ በዘረኝነት የተካፋፈለ፤ ይህ ነዉ ተብሎ የሚጠቀስ ሙያዊ ብቃት የሌለዉና የወገንና የአገር ፍቅር እንዳይኖረዉ ተደርጎ የተደራጀ ሰራዊት ነዉ። ይህንን ሠራዊት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሳይሆን የወያኔ ሠራዊት እያልን የምንጠራዉም በዚሁ ምክንያት ነዉ።
ዛሬ ሙሉ በሙሉ በወያኔ ዘረኞች ቁጥጥር ስር የወደቀዉ የአገር መከላከያ ተቋም የሚታማዉ በዘረኝነት፤ በሙያ ብቃት ማነስና የአንድ ፓርቲ ጥቅም አስከባሪ በመሆኑ ብቻ አይደለም፤ ተቋሙ ከእነዚህ ዋና ዋና ጉድለቶቹ በተጨማሪ በቀድሞዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ተቋም ላይ በፍጹም ያልታዩ ሌሎች ትላልቅ ጉድለቶች አሉበት። ከእነዚህ ጉድለቶች ዉስጥ አንዱ የወያኔ የመከላከያ ተቋም ህገ መንግስቱ ከሰጠዉ ኃላፊነት ዉጭ በንግድና በንብረት ይዞታ ላይ ላይ መሰማራቱ ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ ከዚህ ፀባዩ ጋር ተያይዞ በመከላከያ ሠራዊት ተቋም ዉስጥ ከላይ እስከታች የሰፈነዉ ቅጥ ያጣ ሙሰኝነት ነዉ። ዛሬ የወያኔን የመከላከያ ተቋም፤ የህወሀትን ፓርቲና ኤፎርት በሚል ምህጻረቃል የሚታወቀዉን የወያኔን የገንዝብ ማምረቻ ድርጅት ነጣጥለን ወይም አንዱን ከሌላዉ ለይተን ማየት የማንችልበት ደረጃ ላይ ደርሰናል።
በላፈዉ አመት ወያኔ እራሱ ያቋቋመዉ ፀረ ሙስና ኮሚሺን የገንዘብ ዝርፊያን፤የንብረት መባከንንና መዝረክረክን አስመልክቶ ለፓርላማዉ ባቀረበዉ ሪፖርት ላይ ከጠቀሳቸዉ መንግስታዊ ተቋሞች ዉስጥ ቀዳሚዉን ደረጃ የያዘዉ የመከላከያ ተቋም ነዉ። ሆኖም ፓርላማዉም ሆነ የወያኔ አገዛዝ ለዚህ ሪፖርት የሰጡት ምላሽ የመከላከያና የደህንነት ተቋሞች ከአሁን በኋላ ያሻቸዉን ያክል ገንዝብ ቢዘርፉ የሂሳብ መዝገባቸዉ “ለአገር ደህንነት” ሲባል በኦዲት ኮሚሺን አይመረመርም የሚል ምላሽ ነበር። እንግዲህ ይህ በሙሰኝነት የተጨማለቀ፤ ለህግ የማይገዛና መጠበቅና መንከባከብ የሚገባዉን የአገር ኃብትና ንብረት የሚዘርፍ ተቋም ነዉ ባለፈዉ ሳምንት “የመከላከያ ቀን” ተብሎ አመታዊ በዐል የተከበረለት።
መናገሻ ከተማችን አዲስ አበባ ዉስጥ በየቦታዉ የሚታዩትን ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች ሰርተዉ የሚያከራዩት የወር ደሞዛቸዉ ከ2500 ብር የማይበልጥ መከላከያ ሠራዊት ዉስጥ የተሰገሰጉ የወያኔ ጄኔራሎች ናቸዉ፤ኢትዮጵያ ዉስጥ ትርፋማ በሆኑ ቦታዎች ሁሉ ትላልቅ ሆቴሎች፤ የአገልግሎት ተቋሞችና የንግድ ድርጅቶች ከፍተዉ ቁጥር ስፍር የሌለዉ ኃብት የሚያጋብሱት የወያኔ ጄኔራሎች ናቸዉ፤ ድሃዉና የወያኔ ዘረኝነት ሰለባ የሆነዉ ኢትዮጵያ ሰራዊት ለተመድ ተልዕኮ በተሰማራባቸዉ ቦታዎች ሁሉ ተመድ የሚከፍለዉን የቀን አበል ኪሳቸዉ ዉስጥ እየከተቱ ሚሊዮነሮች የሆኑትና በየዉጭ አገሩ ዉድ መኖሪያ ቤቶችንና የንግድ ተቋሞችን የሚገዙት የወያኔ ጄኔራሎች ናቸዉ። የወያኔ መከላከያ ተቋም ጉድ በዚህ ብቻ አያበቃም፤ ይህንን ወንጀለኛ ተቋም ቃላት እየደረደሩ ለመግለጽ ከመሞከር ይልቅ በጥቅሉ ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ኃብትና ንብረት እንዳሻዉ መዝረፍ እንዲችል የኃይል ሽፋን የሚሰጥ ተቋም ነዉ ማለት የሚበቃ ይመስለናል።
ወያኔና ስር የሰደደዉ ዘረኛ ስርዐቱ ከኢትዮጵያ ምድር ላይ እስካልተነቀሉ ድረስ ወያኔ ዝርፊያዉን የወያኔ መከላከያ ተቋምም የወያኔንና የደገፊዎቹን ዝርፊያ በመሳሪያ ማጀቡ አይቆምም። የወያኔን ዝርፊያ ለማስቆምና አገራችንን ከተጋረጠባት አሳሳቢ አደጋ ለመታደግ ብቸኛዉ መንገድ ወያኔን ከሥልጣን ማስወገድ ብቻ ነዉ። ግንቦት 7 የፍትህ፤የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የጀመረዉ ህዝባዊ ትግል እንደ አገር መከላያከያ አይነቶቹ ቁልፍ የአገር ተቋሞች በሚሰሯቸዉ ስራዎች ሁሉ የአገርንና የህዝብን ጥቅም እንዲያስጠብቁ ለማድረግ ነዉ። የግንቦት 7 ትግል አላማ የመከላከያ፤ የደህንነት፤ የፖሊስና የፍትህ ተቋሞች የአንድ ፓርቲ ጥቅም ማስከበሪያ መሳሪያዎች መሆናቸዉ አብቅቶ የአገርና የህዝብ አለኝታ እንዲሆኑ ነዉ፤ ሆኖም ይህንን ቅዱስ አላማ ወያኔ በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ ተግባራዊ ማድረግ ስለማይቻል ነፃነት፤ ፍትህ፤ዲሞክራሲ፤ ሠላምና እኩልነት የናፈቀዉ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ወያኔን በፍጥነት እናስወግድ ከሚለዉ የአገር አድን አላማ ጎን እንዲሰለፍ ግንቦት 7 የትግል ጥሪዉን ያስተላልፋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

በተጠለፈው አውሮፕላን ውስጥ የነበረው ኢትዮጵያዊ እማኝነት

February 22/2014

“የተሳፋሪው ፍላጎት የሆነ መሬት ላይ ማረፍ ብቻ  ነበር”

በሃዋሳ ከተማ በተለምዶ ኬሮ ሰፈር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ተወልዶ ያደገው ወጣት ምህረቱ ገብሬ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በቀድሞው ሀዋሳ ኮምቦኒ የመጀመርያ ደረጃ ት/ቤት ነው የተከታተለው። የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያና የመሰናዶ ትምህርቱንም በቅዱስ ዳንኤል ኮምቦኒ የሁለተኛ ደረጃና የመሰናዶ ት/ቤት አጠናቋል። ከሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2001 ዓ.ም በሲቪል ምህንድስና የመጀመሪያ ዲግሪውን ካገኘ በኋላም፤ እስከ 2004 ዓ.ም ድረስ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በመምህርነት አገልግሏል፡፡ በመቀጠልም ነጻ የትምህርት ዕድል በማግኘት፣ ወደ ጣሊያን አምርቶ የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርቱን በመከታተል ላይ ይገኛል፡፡

በቅርቡ ለእረፍት ወደ አገሩ የመጣውና በሃዋሳ ቆይቶ ወደ ጣሊያን ለመመለስ አውሮፕላን የተሳፈረው ምህረቱ፣ ባለፈው ሰኞ በረዳት አብራሪው ተጠልፎ ጄኔቭ እንዲያርፍ በተደረገው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 767 አውሮፕላን ውስጥ ከነበሩት 200 ገደማ ተሳፋሪዎች ውስጥ አንዱ ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት በጣሊያን የሚገኘው ምህረቱ፣ የጠለፋውን አጋጣሚ በተመለከተ ጋዜጠኛ አንተነህ  ይግዛው በኢ-ሜይል ለላከለት ጥያቄዎች የሰጠውን ምላሽ  እንደሚከተለው አጠናቅረን አቅርበነዋል፡፡

የጉዞው አጀማመር ምን ይመስል ነበር?

አርፍዶ ወደ አውሮፕላን ጣቢያ መምጣት የሚያደርሰውን ጣጣ ስለማውቀው፣ አውሮፕላኑ ከሚነሳበት 50 ደቂቃ ያህል ቀድሜ ነበር የተገኘሁት፡፡ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ማለት ነው፡፡ ያው ጉዞው ሲጀመር እንደሌላው ጊዜ ሁሉ ስርአቱን የጠበቀና ሰላማዊ ነበር።  አውሮፕላኑ ከበራራ ሰዓቱ ሰባት ደቂቃ ያህል ዘግይቶ ነበር የተነሳው።

አውሮፕላኑ ውስጥ አቀማመጥህ እንዴት ነበር? የት አካባቢ ነው የተቀመጥከው?

የመቀመጫዬ ቁጥር 27F ነበር። የተሳፈርንበት ቦይንግ 767 በርዝመቱ ትይዩ 7 የመቀመጫ መደዳዎች አሉት። ሁለት ሁለት መደዳዎች በሁለቱም ጥጎች እና ሶስት መደዳዎች መሃል ላይ። እኔ የተቀመጥኩት ከመሃል ሶስቱ መደዳዎች የመሃለኛዋ ወንበር ላይ ነበር። ከበስተግራዬ ያለችው ወንበር ላይ የተቀመጡት ሪካርዶ የተባሉ የ85 አመት የዕድሜ ባለጸጋ ጣሊያናዊ ነበሩ፡፡ በቀኜ በኩል እንዲሁ በግምት በስድሳዎቹ ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሌላ ጣሊያናዊ ተቀምጠው ነበር፡፡ ተዋውቀን ነበር፣ አሁን ግን ዘንግቼዋለሁ። ኢትዮጵያን ተዟዙረው እንደጎበኟት እያጫወቱኝ ነው ጉዞውን የጀመርነው፡፡

ጉዞውስ  እንዴት ነበር?

እንደማስታውሰው ጉዞው ሲጀመር ሰላማዊ ነበር። ከፓይለቱ ጋርም ግንኙነት (ኮሙኒኬሽን)  ነበረን፡፡ እኔ ድካም ስለተሰማኝ ወዲያው አሸለብኩ፡፡ በረራው ከተጀመረ በግምት ከ1 ሰዓት በኋላ የሱዳን አየር ክልል ውስጥ ይሆናል ብዬ እገምታለሁ. . . መብራት ሲበራ ከእንቅልፌ ነቃሁ፡፡ የምግብ ሰዓት መድረሱ ገብቶኛል። ወደ ፊት አሻግሬ ሳይ ሆስተሶቹ እያስተናገዱ ከእኔ ፊት 4ኛ ይሁን 5ኛ ረድፍ ደርሰዋል። ሁሉም ተዘገጃጅቶ እየተጠባበቀ ነበር። በዚህ መሃል የፕሌኑ ፍጥነት ሲጨምር ይታወቀኛል፡፡ ከፍታዉም ሲጨምር በጆሮዬ ላይ በሚሰማኝ ስሜት አስተዋልኩ። በተሳፋሪዎች ፊት ላይ የመረበሽ ስሜት ሲፈጠር አየሁ። እኛ  ኢኮኖሚ ክላስ ስለነበርን ከፊት ምን እየተካሄደ እንደነበር አላየንም። በኋላ ስሰማ ከፊት የነበሩትም የቢዝነስ ክላስ ተሳፋሪዎች ምንም መረጃ አልነበራቸውም፡፡

ከዚያም በድምጽ ማጉያው የሆነ ድምጽ ተሰማ፡፡ የረዳት አብራሪው ድምጽ ነበር።

“ተሳፋሪዎች ከ 12 ደቂቃዎች በኋላ ሚላን እናርፋለን” አለ ረዳት አብራሪው፡፡ ጥቂት ቆይቶም፣ “ስለተፈጠሩ አንዳንድ መጉላላቶች ይቅርታ እንጠይቃለን” ሲል አከለ-በእንግሊዝኛና በአማርኛ ቋንቋ። የረዳት አብራሪውን ንግግር ተከትሎ የተወሰኑ ተሳፋሪዎች ማጉረምረም ጀመሩ፡፡ አንዳንዶችም ጮክ ብለው ሲያወሩ ይሰሙ ነበር፡፡ ከኔ በስተግራ በኩል ሶስት አራት መደዳዎችን አልፎ ከፊቴ ተቀምጦ የነበረ አንድ ወፍራም ሰው፣ በጣሊያንኛ ቆጣ ብሎ እየጮኸ ተናገረ - “መጀመሪያ ሚላን ሳይሆን ሮም ነው ማረፍ ያለብን ፣ ወደ ሮም ውሰዱን!” በማለት። ሌሎችም የሰውየውን ሃሳብ ደገፉ፡፡ ምክንያቱም አብዛኛው ተሳፋሪ ወደ ሮም ነበር የሚጓዘው። ረዳት አብራሪው ሚላን ላይ እንደምናርፍ መናገሩ ብዙዎችን አበሳጭቶ ነበር፡፡

እውነቱን ለመናገር፣ እኔ ግን ሚላን እንደምናርፍ ስሰማ ደስ ብሎኝ ነበር፡፡ ምክንያቱም እኔ ሚላን ወራጅ ነኝ፡፡ ረዳት አብራሪው የነገረን አስራ ሁለቱ ደቂቃዎች እየተገባደዱ መሆናቸው ሲገባኝ፣ ከአውሮፕላኑ ለመውረድ መዘገጃጀትና ጓዜን መሸካከፍ ሁሉ ጀመርኩ። ሆኖም  አስራ ሁለቱ ደቂቃዎች አልፈውም አውሮፕላኑ አላረፈም፡፡ ካሁን አሁን ሚላን አውሮፕላን ማረፊያ ደረስን እያልን ስንጠባበቅ፣ ሌላ አስራ ሁለት ደቂቃዎች አለፉ፡፡ አሁንም ሌላ አስራ ሁለት ደቂቃዎች---
ተሳፋሪው ሁሉ ግራ በመጋባት ሰዓቱን ደጋግሞ መመልከትና እርስ በርስ በጥርጣሬ መተያየት ጀመረ። ከአስራ ሁለት ደቂቃዎች በኋላ ሚላን ላይ ያርፋል የተባለው አውሮፕላን፣ ከአንድ ሰዓት ተኩል በላይ በአየር ላይ ቆየ፡፡ የሚገርመው ያን ያህል ጊዜ አየር ላይ መቆየቱ ብቻ አይደለም፡፡ አበራረሩ የተለየ ነበር፡፡ አንዴ ፍጥነቱን ጨምሮ ይከንፋል፣ ከዚያ ደግሞ ፍጥነቱን ይቀንስና ተረጋግቶ ይበራል፡፡ እንደገና ይፈጥናል፣ እንደገና ይረጋጋል፡፡ ግራ ገብቶን እያለን፣ ከመቅጽበት አውሮፕላኑ ማረፊያው ላይ ደርሶ ማኮብኮብ ጀመረ፡፡ ያንን ያህል ግዙፍ አውሮፕላን፣ በዚያች ጠባብ ቦታ ላይ ያለችግር ማሳረፍ መቻሉ፣ የረዳት አብራሪውን ብቃት ያሳያል፡፡ ለማንኛውም አውሮፕላኑ በሰላም አረፈና እኛም እፎይ አልን፡፡

አውሮፕላኑ ካረፈ በኋላ የተሳፋሪዎች ስሜት ምን ይመስል ነበር?

የሚገርመው ነገር፣ አውሮፕላኑ እንዳረፈ በተሳፋሪው ፊት ላይ ከታየው ደስታና እፎይታ በተጨማሪ፣ ተሳፋሪው ለረዳት አብራሪው የሰጠው አድናቆት ነበር፡፡ አብዛኛው ተሳፋሪ ስለረዳት አብራሪው ችሎታ ነበር ተደንቆ የሚያወራው፡፡ በከፍተኛ የአድናቆት ስሜት ተውጠው፣ ለረዳት አብራሪው ያላቸውን አድናቆት በጭብጨባና በፉጨት የገለፁም ነበሩ፡፡ እኔም በደመነፍስ ሳጨበጭብ ነበር፡፡ ሚላን ምድር ላይ በሰላም እንዲያሳርፈኝ ለፈጣሪዬ ያደረስኩትን ጸሎት የማውቀው እኔ ነኝ፡፡

ሚላን እንዳረፋችሁ ነበር የምታውቁት ማለት ነው?

የሚገርመው እኮ እሱ ነው!... አውሮፕላኑ መሬት ከነካ በኋላ ሁሉ፣ ተሳፋሪው በሙሉ ጣሊያን ሚላን እንዳረፈ ነበር የሚያውቀው፡፡ ሚላን እንደምናርፍ ነው ረዳት አብራሪው የነገረን፡፡ ትኬት ከፍለን የተሳፈርነውም ወደ ጣሊያን እንጂ ወደ ስዊዘርላንድ ለመሄድ አልነበረም። በዚህ ቅጽበት ጄኔቭ የምትባል ከተማ በምን ተአምር እንሄዳለን ብለን እናስብ?

ጄኔቭ መሆናችሁን ያወቃችሁት እንዴት ነው?

አውሮፕላኑ በሰላም ካረፈ በኋላ ተሳፋሪው ከጭንቀቱ ተገላግሎ መረጋጋት ጀመረ፡፡ አንዳንዶች ሞባይል ስልኮቻቸውን አውጥተው መነካካት ያዙ። በሞባይላቸው የኢንተርኔት መስመር በመጠቀም ጎግል ማፕ የተሰኘውን የአገራትና የከተሞች ካርታ የሚያሳይ ድረገጽ፣ ጂ ፒ ኤስ ከሚባለው አቅጣጫ ጠቋሚ ቴክኖሎጂ ጋር አያይዘው ሲመለከቱ፣ ፊታቸው ላይ ድንገተኛ መደናገር ሲፈጠር አየሁ፡፡ አንዱ ተሳፋሪ ሞባይሉ ላይ ያየውን መረጃ በመጠራጠር፣ የሌላኛውን ሞባይል ማየት ጀመረ፡፡ “የት ነው ያለነው?” ለሚለው ጥያቄ እርግጠኛ የሆነ መልስ የሚሰጥ ጠፋ፡፡ ግማሹ “ ኦስትሪያ ነን!” ሲል፣ ገሚሱ “የለም ፈረንሳይ ነን!” ብሎ ይመልሳል፡፡ አንዳንዱ “ጀርመን ውስጥ ነው የምንገኘው!” ይላል፡፡ ሌላው “ስዊዘርላንድ ጄኔቭ ነው ያረፍነው!” እያለ ይናገራል፡፡ ጭንቀትና ውጥረት የፈጠረው መደናገር ሊሆን እንደሚችል ያሰብኩት በኋላ ነው፡፡

 ጄኔቭ ማረፋችሁንና አውሮፕላኑ መጠለፉን ያወቃችሁት እንዴት ነበር?

እያንዳንዱ ተሳፋሪ አውሮፕላኑ ያረፈበትን አገርና ከተማ በተመለከተ የየራሱን መላምት እየሰነዘረ ግራ ተጋብቶ ጥቂት ደቂቃዎች አለፉ፡፡ በዚህ መሃል ነው፣ ድንገት የአውሮፕላኑን ዋና አብራሪ ድምጽ የሰማነው። በረራው ከተጀመረ አንስቶ የዋና አብራሪውን ድምጽ ስንሰማ ለመጀመሪያ ጊዜያችን ነበር፡፡ ዋና አብራሪው በጣሊያንኛ ቋንቋ ነበር የሚያወሩት፡፡ በጣሊያን ቆይታዬ የቀሰምኳት ቋንቋ ብዙም የምታወላዳ አልነበረችምና፣ ደቂቃዎችን ከፈጀው የአብራሪው ንግግር የተወሰነችዋን ተረድቼ፣ ቀሪውን ከጎኔ ከተቀመጡት ጣሊያናውያን ጠይቄ ለመረዳት ሞከርኩ፡፡

አብራሪው  ወደመጸዳጃ ቤት ሲወጡ ረዳት አብራሪው በር እንደዘጋባቸው፤ አውሮፕላኑን ለሰዓታት ሲያበር የቆየው ረዳት አብራሪው እንደነበር፤ አውሮፕላኑ ያረፈው ጄኔቭ መሆኑን፤ በተፈጠረው ነገር ማዘናቸውን መግለጻቸውን እንዲሁም እያንዳንዱ ተሳፋሪ የስዊዘርላንድ ፖሊሶች ለሚያደርጉት ምርመራ ተገቢውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ማስተላለፋቸውን ነገሩኝ፡፡ ተሳፋሪው ስለ ጠለፋው ያወቀው በዚህ ጊዜ ነው፡፡

ተጠልፋችሁ ያላሰባችሁት ቦታ እንዳረፋችሁ ስታውቁ ምን ተሰማችሁ?

እውነቱን ለመናገር በወቅቱ የሁሉም ተሳፋሪ ጸሎትና ምኞት በረራው በሰላም መጠናቀቁና አውሮፕላኑ አደጋ ሳያጋጥመው ማረፉ ብቻ ነበር፡፡ የተሳፋሪው ፍላጎት የትም ይሁን የት፣ ብቻ የሆነ መሬት ላይ ማረፍና ከጭንቀት መገላገል ነበር፡፡ አስበው እስኪ… ከአብራሪውም ሆነ ከሆስተሶቹ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት በሌለበት አደናጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነው ለሰዓታት የበረርነው፡፡ ከዚያ ደግሞ… ሮም የማረፍ ዕቅዱ ተሰርዞ፣ ከ12 ደቂቃዎች በኋላ ሚላን እንደምናርፍ ድንገት ተነገረን፡፡ ይሁን ብለን ተቀብለን፣ አስራ ሁለቱን ደቂቃ በጉጉት ስንጠባበቅ ደግሞ፣ ለተጨማሪ አንድ ሰዓት ተኩል ያህል ጊዜ በረራው ቀጠለ፡፡ በዚያ ላይ በረራው ጤነኛ አልነበረም፡፡ አንዴ የሚፈጥን፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ የሚረጋጋ ምቾት የማይሰጥ በረራ ነበር፡፡

በዚህ ሁኔታ ውስጥ ያለ ተሳፋሪ፣ የትም ቢሆን ማረፍን እንጂ፣ማረፊያ ቦታውን አይመርጥም፡፡ እኔም ሆንኩ ሌሎች ተሳፋሪዎች ጉዳዩን ያወቅነው፣ ጠለፋው ከተጠናቀቀና አውሮፕላኑ ጄኔቭ ውስጥ በሰላም ካረፈ በኋላ ዋና አብራሪው ሲነግሩን በመሆኑ እምብዛም አልተደናገጥንም፡፡

ከአውሮፕላኑ ስትወርዱ የነበረው ሁኔታ ምን ይመስላል?

አውሮፕላኑ ጄኔቭ ካረፈ በኋላ በግምት ለአንድ ሰአት ያህል በሩ ሳይከፈት ቆሞ ቆየ፡፡ ዋና አብራሪው ሁሉንም ነገር በግልጽ ከነገሩን በኋላ፣ ከእግር ጣታቸው እስከ ራስ ጸጉራቸው የብረት ጭንብል የለበሱ ሰዎች፣ በሩን በርግደው በፍጥነት ወደ ውስጥ ገቡ። አገባባቸውና መላ ሁኔታቸው አክሽን ፊልም የሚሰሩ ነበር የሚመስሉት፡፡ ሁኔታው እጅግ ያስጨንቅ ነበር፡፡ በመካከል አንደኛው ፖሊስ በእጁ በያዛት አነስተኛ የድምጽ ማጉያ ፈረንሳይኛ በሚመስል እንግሊዝኛ መናገር ጀመረ።

“ዚስ ኢዝ ኤ ፖሊስ ኦፔሬሾን። ዶንት ሙቭ!... ፑት ዩር ሃንድስ ኦን ዩር ሄድ!... ዶንት ሜክ ሙቪ ባይ ሞባይል (በሞባይል አትቅረጹ ማለቱ ነው)” ሲል ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡ ሁሉም እጆቹን አናቱ ላይ ጭኖ ድምጹንም አጥፍቶ አቀረቀረ፡፡ ተሳፋሪው በፖሊሶቹ መሪነት አንድ በአንድ ከአውሮፕላኑ እየወረደ፣ ሁለት ሁለት ጊዜ ተበርብሮ ተፈተሸ፡፡

ፍተሻው እንደተጠናቀቀም በትላልቅ ሽንጣም አውቶብሶች እየጫኑ ወደ ተርሚናሉ ወሰዱን፡፡ ተርሚናሉ ላይ ስንደርስ የሚገርም አቀባበል ተደረገልን፡፡ የምንበላው ቁርስና ሻይ ቡና እንዲሁም ለብርዱ ብርድልብስ ተዘጋጅቶ ጠበቀን፡፡ የህክምና ባለሙያዎችና የስነልቦና ባለሙያዎች እርዳታ ሊሰጡን እየተጠባበቁ ነበር፡፡ አስገራሚ አቀባበል ነው የተደረገልን።

ኢትዮጵያውያንስ አላገኛችሁም?

ተርሚናሉ ዉስጥ ገብተን ትንሽ እንደቆየን አንድ ኢትዮጵያዊ ወደ እኛ ሲመጣ ተመለከትን፡፡ ለጊዜው ስሙ ትዝ አይለኝም። ከኢትዮጵያ ኤምባሲ እንደመጣ ነገረንና ስለሁኔታው ጠየቀን። “አይዟችሁ!... ደርሰንላችኋል!...” የሚል መንፈስ ያለው ማበረታቻ ሰጠን፡፡ ከዚያም የግል ሞባይሉን ከኪሱ አውጥቶ አገር ቤት ያሉ ቤተሰቦቻችን ጋ ደውለን ደህንነታችንን እንድናረጋግጥ ራሱ እየደወለ ያገናኘን ጀመር፡፡

በዚህ ጊዜ ነው፣ በስዊዘርላንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር የመጡት፡፡ በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበርን ኢትዮጵያውያንን አነጋግረው አረጋጉን፡፡ በስተመጨረሻም ከተርሚናሉ እንዲወጡ ስለታዘዙ የማስታወሻ ፎቶግራፍ አብረውን ተነሱና ጉዳያችንን በቅርብ እንደሚከታተሉ ነግረውን አበረታቱንና ሄዱ፡፡ ሌሎች ሁለት የኤምባሲው ባልደረቦችም፣የሚፈቀድላቸው ቦታዎች ላይ ሁሉ እየተገኙ ድጋፍ በማድረግ እስከመጨረሻው አብረዉን ነበሩ።

በእለቱ ስለተከሰተው ሁኔታ ምን ትላለህ?

እናቴ እንደነገረችኝ፣ በህፃንነቴ የወራት ዕድሜ ላይ እያለሁ፣ የሆነ ቀን ከታላቅ ወንድሜ መላኩ ገብሬ ጋር ከጎማ ላስቲክ የተሰራ አልጋ ላይ ተኝቼ ነበር። ቡና ስታፈላ ምንጊዜም ዕጣን ማጨስ እማትዘነጋው እናታችን፣ ያጨሰችዉን እጣን እኛ የተኛንበት አልጋ አጠገብ አስቀምጣው ኖሮ፣ እሷ ጎረቤት ደርሳ ስትመለስ ቤቱ በጭስ ተሸፍኖ ጨልሞ ጠበቃት። ጩኸቷን ለቀቀችው። ጩኸት ሰምቶ የመጣ ጎረቤት ነው አሉ ፈልጎ አግኝቶኝ በመስኮት ወደ ውጭ የወረወረኝ። ምህረቱ የተባልኩትም በዚያ ምክንያት ነው። እንዳጋጣሚ እሳቱ ቀድሞ የተያያዘው ወንድሜ በተኛበት በኩል ስለነበር እሱን ማትረፍ አልተቻለም።

የፈጣሪ ምህረት ዛሬም አልተለየኝም፡፡ በአውሮፕላኑ ላይ ሊደርስ ከሚችለው አሰቃቂ አደጋ አትርፎኛል። እንደትላንትናው ሁሉ ነገዬም በፈጣሪ እጅ እንደሆነች አምናለሁ። እርሱ ይሁን ያለው ሁሉ መልካም ነው። ቸርነቱ አይለየኝና ፍቃዱ ሆኖ ለነገ ካበቃኝ ለልጆቼ የምነግረው ተጨማሪ ታሪክ አግኝቻለሁ።

ደህና ነኝ እንኳን ብላት የማታምነኝ እናቴ ብርሃነማርያም ኪአን፣ እጮኛዬ ዮዲት ቦርሳሞን፣ ወንድሞቼን፣ ብቸኛዋን እህቴን፣ አክስቶቼን ከነቤተሰቦቻቸው፣ ጓደኞቼን፣ስለደህንነቴ የሚጨነቁልኝን ሁሉ ደህና መሆኔን ንገርልኝ። ከሁሉ አስቀድሞ ስለሆነውም ስለሚሆነዉም ክብር ሁሉ የእርሱ ነውና ፈጣሪ የሚገባዉን ክብር እና ምስጋና ይውሰድ።

አዲስ አድማስ

ሰበር ዜና!! አንድነት ለትግል በወጣበት የመድረክ አባል ፓርቲዎች አገዱት

February 22/2014
“አንድነትን በመግፋት መድረክን ወደ አክራሪ ብሔረተኛ ስብስብነት ለመግፋት የተደረገ ስልታዊ ውሳኔ ነው” የአንድነት ፓርቲ ተቀዳሚ ም/ፕሬዝደንት አቶ ተክሌ በቀለ
መድረክ በከፍተኛ ደረጃ የፖለቲካ ውጤት ያመጣ ስራ እየሰራ የሚገኘውን አንድነት ፓርቲን ማገዱ ትዝብት ላይ የሚጥል ውሳኔ ነው፡፡” የአንድነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው
የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፌደራላዊ አንድነት መድረክ አባል ፓርቲዎች አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ማገዳቸውን ዛሬ የካቲት 15 ቀን 2006 ዓ.ም በተደረገው የመድረኩ 9ኛ ጠቅላላ ጉባኤው ላይ አሳውቀዋል፡፡ በጉባኤው አንድነትን ወክለው የተሳተፉት መካከል የአንድነት ፓርቲ ተቀዳሚ ም/ፕሬዝደንት እንዲሁም የመድረክ ም/ሊቀመንበርና የውጪ ግንኙነት ኃላፊ ሆኑት አቶ ተክሌ በቀለ ለፍኖተ ነጻነት እንዳስታወቁት የመድረክ አባል ፓርቲ የሆኑት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስና በፕ/ር በየነ የሚመራው የኢትዮጵያ ማህበረ ዲሞክራሲ ደቡብ ህዝቦች አንድነት ፓርቲ አንድነት ከመድረክ እንዲባረር ቢጠይቁም አረና ትግራይ ለሉአላዊነትና ለዴሞክራሲ አንድነት ላልተወሰነ እንዲታገድ የሚል ሞሽን አቅርቦ በጉባኤው ተቀባይነት አግኝቷል፡፡

አቶ ተክሌ በቀለ የመድረክ አባል ፓርቲዎች አንድነትን ለማገድ የወሰኑባቸው ምክንያዎች አስገራሚ መሆናቸውን ጠቅሰው “የመድረክ አባል ፓርቲዎች አንድነትን ለማገድ የወሰኑት በቅርቡ በተደረገው ጠቅላላ ጉባኤ አንድነት መድረክ ውስጥ ካሉ ፓርቲዎች ጋር ውህደት እንዲፈፀም መወሰኑን፣ አንዳንድ ከፍተኛ አመራሮችም ውህደት እንደሚያስፈልግ በተለያዩ ሚዲያዎች መናገራቸውን፣ የአንድነት ፓርቲ የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገር ድጋፍ ሰጪዎች በመድረክ ስም የፋይናንስ ድጋፍ እንዲደረግ ትብብር አያደርጉም በሚልና ከመድረክ ዕውቅና ውጪ መስከረም 19(ሰላማዊ ሰልፉ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ የማጠቃለያ መርሀ ግብር ነው፡፡) በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂዷል፡፡” የሚሉ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ አክለውም አንድነትን በመግፋት መድረክን ወደ አክራሪ ብሔረተኛ ስብስብነት ለመግፋት የተደረገ ስልታዊ ውሳኔ ነው ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡ አቶ ተክሌ መድረክ የራሱን ዕቅድ አውጥቶ በቁርጠኝነት የማይሰራ በመሆኑ አንድነት በተናጠልና ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር የተለያዩ ስራዎችን መስራቱን ጠቅሰው “በተደጋጋሚ ለመድረክ በዕቅድ የተደገፉ እንቅስቃሴዎችን በማቅረብ በጋራ እንዲሰራ ቢጠይቅም ቀና ምላሽ አግኝቶ አያውቅም፡፡ ይልቁኑም የራሱን ጥፋት በአንድነት ላይ ለማላከክ ይሞክራል ” ብለዋል፡፡
ነገ አንድነትና መኢአድ በባህር ዳር የሚያደርጉትን ሰላማዊ ሰልፍ በማስተባበር ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው የመድረክን ውሳኔ አስመልክተው ለፍኖተ ነፃነት እንደገለፁት “ መድረክ በከፍተኛ ደረጃ የፖለቲካ ውጤት ያመጣ ስራ እየሰራ የሚገኘውን አንድነት ፓርቲን ማገዱ ትዝብት ላይ የሚጥል ውሳኔ ነው፡፡” ካሉ በኋላ “አንድነት የታገደው ውጤታማ ስራ ስለሰራና በሚሊዮኖች ድምፅ ንቅናቄ እና በተመሳሳይ ስራዎች የተቀዛቀዘውን የሰላማዊ ትግል በማነቃቃት ትግሉን ወደ ህዝብ ስላወረደ ነው፡፡” ብለዋል፡፡ አክለውም “መድረክ ውስጥ ካሉት ፓርቲዎች የተሻለ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የሚያደርገው አረና ብቻ ነው፤ የዛሬው ውሳኔ አረናም በቅርቡ የአንድነት እጣ እንደሚገጥመው አመልካች ነው፡፡” የሚል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ “መድረክ እንደዚህ ያለ እገዳ ከመወሰን ይልቅ አንድነትና አረና የጠየቁትን ውህደት ተቀብሎ ፖለቲካውን በአንድ ላይ ማንቀሳቀሱ ለኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ ውጤት እንደሚያስገኝ አንድነት ያምናል፡፡ ስለዚህ መድረክ የወሰነውን ውሳኔ እንደገና አጢኖ የሀገራችንን ፖሊቲካ በውህደት አብረን እንድንመራ እንዲያደርግ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡
ፍኖተ ነጻነት

ባሶንዳ በተባለችዉ የሱዳን ጠረፍ ከተማ 77 ኢትዮጵያዉያን ተገድለዋል ተባለ

February 22/2014

 
ከመተማ ቀጥላ በምትገኘዉ ባሶንዳ በምትባለዉ የሱዳን ጠረፍ ከተማና አካባቢ በኢዮጵያዉን ሽፍቶችና በሱዳን ሽፍቶች መካከል የተነሳዉን ግጭት ተከትሎ አራት ሱዳናዉያን በመሞታቸዉ ሳብያ ለብቀላ የተነሱት ሱዳናዉያን ታጣቂ ሐይላት ኢትዮጵያዉይንን በጅምላ እየገደሉ ነዉ አገር ወገን የድረስልን ሲሉ ወደ ሱዳን በመተማ በኩል የገቡ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች እየተጣሩ ነዉ።

አራት ሱዳናዉያን ስለሞቱ በመቶ ኢትዮጵያዊ ነዉ የምንበቀለዉ ያሉት ሱዳናዉያን እስከ አሁን 77 ኢትዮጵያዉይንን መገደላቸዉን በኩራት ይናገራሉ ያሉት ኢትዮጵያዉያን የአብዛኛዎቹ ሟቾች መቃብር የማታወቅ መሆኑንም ይናገራሉ። በየጫካዉ የተገደሉ ኢትዮጵያዉያን አስክሬናቸዉ ለዱር አራዊት መወርወሩን የሚገልጹት ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ሌላ 42 ኢትዮጵያዉያን የተቀበሩበት መቃበር መኖሩንም ይጠቁማሉ፤ ይህ መቃብር ግን ከሞቱት 77 ሰዎች ጋር የሚያገናኘዉ ነገር ይኑር አይኑር የሚያዉቁት ነገር እንደሌለም ያስረዳሉ ።
 
በህዳር 24/2006 የሱዳኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሊ አህመድ አልቀርዲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ሱዳንና ኢትዮጵያ ያላቸዉን የድንበር ልዩነት አስወግደዉ መስማማታቸዉን ይፋ አድርገዋል። ይህንንኑ ተከትሎ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማሪያም ደሳለኝ ወደ ሱዳን ለስራ ጉብኝት አቅንተዋል። የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኡመር ሐሰን አልበሽር ሁለቱ አገራት በጥበቃ፣በደህንንነት፣ ህገወጥ የሰዉና የ አደንዛዥ እጽ ዝዉዉርን ለመግታት መስማማታቸዉን ገልጸዋል። በሱዳኗ ባሶንዳ የኢትዮጵያዉያን በጅምላ መገደል ከዚሁ የደህንነት ስጋት ጋር ግንኙነት እንዳለዉ ባይታወቅም ሱዳናን ኢትዮጵያ ግድያዉን ለማስቆም ምንም አይነት ጥረት እንዳላደረጉ ከጥቃቱ የተረፉ ኢትዮጵያዉያን ያስረዳሉ ።
 
በየካቲት 11/2006 ህወሃት የተመሰረተበትን 39ኛ አመት ለማክበር የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ልዩ የክብር እንግዳ ሆነዉ መቐሌ ድረስ መምጣታቸዉ ታዉቋል። የሁለቱ አገራት መሪዎች ስለ ቀድሞ ስማእታት ቢናገሩም ወደ ሱዳን በኢኮኖሚ ሳቢያ ተሰደዉ ስለሚሞቱት ኢትዮጵያዉያን ምንም ያሉት ነገር አልነበረም። በባሶንዳ ሱዳን ኢትዮጵያዉያን ነጥሎ የማጥቃቱ ዘመቻ እንደቀጠለ ነዉ! ኢትዮጵያዉያን ወገን ይድረስልን ሲሉም ይጣራሉ።

ዋሽንግተን ዲሲ፤ የካቲት 14/2006 (ቢቢኤን )

የኢቴቪ ዋና ዳይሬክተር ታስረው እንዲቀርቡ ታዘዘ

February 22/2014

በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ጉዳያቸው በፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት እየታየ በሚገኘው 28 ተከሳሾች ላይ ለቀረበ የአቃቤ ህግ የቪዲዮ ማስረጃ አስተርጓሚ እንዲመድብ የታዘዘው የኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት፤ የፍ/ቤቱን ትዕዛዝ ተግባራዊ ባለማድረጉ ዋና ዳይሬክተሩ ፍ/ቤት ታስረው እንዲቀርቡ ታዘዘ፡፡

በእነ አማን አሠፋ መዝገብ በሚገኙ የሽብር ተጠርጣሪዎች ላይ አቃቤ ህግ የሰው ምስክሮችንና በሺዎች የሚቆጠሩ የሰነድ ማስረጃዎችን ለፍ/ቤቱ አቅርቦ ያጠናቀቀ ሲሆን በአረብኛና በኦሮሚኛ ቋንቋዎች ለቀረቡት የቪድዮ ማስረጃዎች ኢሬቴድ አስተርጓሚ እንዲመድብ ከፍ/ቤቱ የተላለፈውን ትዕዛዝ ተግባራዊ አላደረገም ተብሏል፡፡ በዚህም ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ብርሃኑ ኪዳነማርያም ታስረው ፍ/ቤት እንዲቀርቡ ታዟል፡፡

ቀደም ሲል እነዚህን የሽብር ተጠርጣሪዎች አስመልክቶ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን “ጅሃዳዊ ሃረካት” የሚል ዶክመንተሪ ፊልም ተዘጋጅቶ መሰራጨቱ የሚታወስ ሲሆን አቃቤ ህግም በክስ ማመልከቻው፣ ተጠርጣሪዎች የአልቃይዳ ህዋስ ሆነው በአለማቀፍ የሽብር መዋቅር ውስጥ ተሳታፊ እንደነበሩ ማመልከቱ ይታወሳል፡፡ 

[የረዳት አብራሪው ጉዳይ] ሕዝብን አፍኖ እና ረግጦ በመግዛት የስልጣን እድሜን ማራዘም አይቻልም (በገዛኸኝ አበበ ኖርዌይ)

February22/2014

ዘረኛው እና  አምባገነኑ የወያኔ ኢህአዲግ መንግስት ወደስልጣን ወንበር በሀይል ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያን ሕዝብ አፍኖና ረግጦ መግዛትን ተያይዞታል:: በአሁኑ ጊዜ ወያኔ የሚያራምደው በዘረኝነት የተሞላው የተሳሳተ እና የተወላገደ ፖለቲካ ሕዝቡን ከማማርር ባለፈ የኑሮ ውድነቱ፣ ስራ አጥነቱ፣ እና በሀገሪቷ ላይ ክፉኛ ወንጀል መበራከቱ እና  በየሁሉም መስሪያ ቤቶች ከቀን ወደ ቀን ሙስና፣ ሌብነትና አይን ያወጣ ዝርፊያ  እየጨመረ መምጣቱ  የኢትዮጵያ ህዝብ  የሰቋቋ እና የመከራን ኑሮ መኖርን ተያይዞታል::  ወያኔ እያራመደው ያለው በዘር የተሞላ ፖለቲካ አንዱን ዘር ከአንዱ ዘር በማበላለጥ እና በመከፋፈል አንዱን ዘር ከፍ ሌላውን ዘር ዝቅ በማድረግ ፣ እያወረደ እና እየናቀ ዜጓች በገዛ ሀገራቸው እና ምድራቸው ላይ በሰላም እና በነጻነት እንዳይኖሩ ይኼው የወያኔ መንግስት ሲፈልግ ነፍጠኛ፣ ጉርጠኛ፣ትምክህተኛ፣ ተገንጣይ፣አሸባሪ ወዘተ.....  በማለት ሕዝቦችን በማስፈራራት እና ነጻነትን በማሳጣት  በሀይል እና በጉልበት  አፍኖ  እየረገጠ በመግዛት ላይ ይገኛል::

በአሁኑ ወቅት ተማሪው ተምሮ ስራ ለማግኘት እና ለመቀጠር ሰራተኛውም በስራው ገበታው ላይ ለመቆየት እና ስራውን በነጻነት ለመስራት በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ የታወቀ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ጥራት በሌለው የወያኔ የትምህርት ፖሊሲ ከመንግስትም ሆነ ከግል ዩንቨርስቲ እና ኮሌጆች ብዙ ወጣት ተማሪዎች በሀገሪቷ ላይ ትምህርታቸውን ጨርሰው ቢመረቁም በስራ አጥነት እየተንከራተቱ የሚገኙ ዜጓች ቁጥራቸው ከቀን ወደቀን እየጨመረ መምጣቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰ ሲሆን  በአሁን ጊዜ በኢትዮጵያ አንድ ሰው የሆነ መስሪያ ቤት ውስጥም ሆነ ድርጅትውስጥ  ስራ ለማግኛት እና  ለመቀጠር የግድ የወያኔ ኢህአዲግ አባል መሆን የሚጠበቅበት ሲሆን በስራ ገበታም ላይ  ያሉ ሰዎች ቢሆንም እንኮነ በሚሰሩበት ቦታ የግድ የወያኔ አባል እስካልሆኑ ድረስ ነጻነት እንደሌላቸው ፣ ስራቸውንም በነጻነት መስራት እንደማይችሉ የተለያዩም ግፍ እና ጭቋናዎች እንደሚደርስባቸው የታወቀ ነው::

በቅርቡ መምህር አማኑኤል መንግስቱ የተባለ የማዝገበ ብርሀን አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ትምህርት ቤት መምህር የአንድነት አባል በመሆኑ በሚያስተምርበት ትምህርት ቤት የወያኔ ካድሬ በሆነ በትምህርት ቤቱ  አስተዳደር የተለያዩ ዛቻዎችና ማስጠንቀቂያዎች እየደረሱበት እንደሆነ እና ከስራም ሊባረር እንደሚችል የማስንጠቀቂያ ደብዳቤ ከትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር እንደደረሰው የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ መዘገቡን አስታውሳለው:: ይህን እንደምሳሌ አልኩኝ እንጂ በጣም ብዙ ዜጓች ናቸው በየሚሰሩበት መስሪያ ቤቶች በዘር በተበላሸ በወያኔ ፖለቲካ አመለካከት የኢህአዲግ አባል ባለመሆናቸው የሚጨቁኑት ነጻነታቸውን አተው በሀገራቸው ተሸማቀው በወያኔ ካድሬዎች ታፍነውነው እና ተረግጠው የሚኖሩት :: 

የወያኔ ባለስልጣናት ሊያውቁ የሚገባው ነገር ሕዝብን አፍኖ  እና ረግጦ  በመግዛት የስልጣን እድሜን ማራዘም እንደማይቻል ነው :: ዚህ በዚህ ሳምንት የተከሰተው እና የአለም መነጋገሪያ እየሆነ ያለው እና የብዙ አለማት ሚዲያን ቀልብ የገዛው የረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ የአውሮፕላን ጠለፋ ትምህርት ሊሆናቸው ይገባል :: ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ በእኔ አመለካከት ጀግና ነው ክብርም ይገበዋል :: ምንም እንኮን የሰራው ስራ የሚያስፈራ እና ዋጋ የሚያስከፍልም ቢሆንም በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው  የወያኔ የተበላሸ  የፖለቲካ አካሂድ  ምን ያክል የከፋ እንደሆነ ፣ የደህንነት ስጋት ፤የአስተዳደር ብልሹነት እና የዘረኝነት መድልዎን ከመቼውም ጊዜ የባሰ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ  ለአለም ሕዝብ ያመላከተበትን ጀብዱ ፈጽሞል:: ስለዚህ ፓይለት ሃይለመድህን አበራ በዘር ለተረገጦ ፣ ለተገፉ እና ለተጨቋኑ ኢትዮጵያኖች ድምጽ ሆኖል ነው የምለው ::


ፓይለት ሃይለመድህን አበራ አስቦ እና አቅዶ የተነሳበት ዋንኛው አላማ ይኼው ይመስለኛል::  የመንግስት ቃል አቀባይ ተብዪው አቶ ሬድዋን  ፓይለት ሃይለመድህን ሙሉ ጤነኛ ሰው እንደሆነ ለአምስት አመታት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪ ሆኖ እንዳገለገለ ፣ የሽንገን ቪዛ እንዳለው ፣ነጻ ትኪት እንደሚያገኝ እና የትም ሀገር ሂዶ ትምህርቱን መቀጠል እንደሚችል ነገር ግን ፓይለት ሃይለመድህን  ለእራሳቸውም እንደገረማቸው እና እንቆቅልሽ እንደሆነባቸው ሲናገሩ ተደምጠዋል  በርግጥ ልክ ነው ወጣቱ ፓይለት ሃይለመድህን የትም ሀገር ሂዶ አሳይለም የመጠየቅ እድል (opportunity) ይኖረው ነበር  ብዙም ሰዎች በዚህ ጉዳይ ላይ የራሳቸውን ሀሳብ እየሰነዘሩ ሲሆን  በኢትዮጵያ አየር መንገድ በበረራ ደህንነት ስራ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ያገለገለውና በክትትልና ደህንነት ስጋት ከአመት በፊት ድርጅቱን ለቆ በስዊዘርላንድ ጥገኝነት የጠየቀው አንድ የቀድሞው የድርጅቱ ሰራተኛ  አቶ ሚካኤል መላኩ የካፒቴን ሃይለመድህን አበራ የጠለፋ ምክንያት በአየር መንገዱ ውስጥ የሚታየውን የአስተዳደር መበላሸት ለአለም ለማሳየት ሊሆን ይችላል የሚለው ምክንያት አሳማኝ ነው ሲል ከኢሳት ጋር ባደረገው  ቃለምልልስ  የተናገረው ነገር ትክክል ነው ብዪ አምናለው::

ፓይለት ሃይለመድህን አበራ በድፍረት የተሞላ ጀብዶ መፈጸሙ የወያኔን ባለ ስልጣናቶች ያስደነገጠ፣ ያሳፈረ እና ያሸማቀቀ ተግባር ሲሆን  በወያኔ መንግስት በዘር፣በሀይማኖት ተገፍቶ እና ተጨቆኖ ላለው ምስኪኑ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ደስ የሚያሰኝ ተግባር ነው :: ምክንያቱም ህወሃት መራሹ መንግስት እያራመደ ባለው የዘረኝነት ፖለቲካ በሀገሪቱ ላይ ያላው የደህንነት ስጋት፣ አፈና እና ሰበሃዊ መብት ረገጣ ምን ያህል እየከፈ መምጣቱን ለአለም ሕዝብ ያመለከተበት ተግባር በመሆኑ:: ስለዚህ የወጣት ፓይለት ሃይለመድን ጀግንነት የተሞላበት ተግባር ወኔ እና ብርታት ሆኖን በወያኔ ታፍኖ እና ተረግጦ መገዛትን እንቢ በማለት እና የወያኔን በዘረኝነት የተሞላውን ፖለቲካ በመቃወም በአደባባይ በማውጣት ወያኔን በማስረበሽ እና በማስደንገጥ የስልጣን እድሜውን ማሳጠር የመላው ኢትዮጵያኖችን ነጻነት መወጅ የሁሉም ኢትዮጵያዊ የዜግነት ግዲታ መሆን ይጠበቅበታል::

ፍትህና ነጻነት ለሚናፍቅ ኢትዮጵያዊ የማስተላልፈው መልህክት  ህወሃቶች ዜጎችን ከሰው በታች አድርገው ለመግዛት እንዲመኙ ያደረጋቸው በእብሪት የተሞላ የፖለቲካ አካሄድ የሚተነፍስበት ዘመን እሩቅ አይሆንምና አሁንም አትፍሩ።

  ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

gezapower@gmail.com

Friday, February 21, 2014

የብአዴኑ አቶ አለምነው ህዝብን ይቅርታ ጠይቆ ለፍርድ መቅረብ አለበት

February 21/2014
ብስራት ወልደሚካኤል
የብአዴን/ኢህአዴግ ዋና ፀሐፊ እና የአማራ ክልል ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ አለምነው መኮንን በግልፅ እመራዋለሁ የሚለውን ህዝብ በመሳደቡ ያለምንም ማንገራገርና ማምታታት ይቅርታ ጠይቆ እራሱን ለፍርድ ማቅረብ አለበት፣ ማስተዋሉ ካለው፡፡ በርግጥ የኢህአዴግ መሪዎች የህዝብና የሀገር ክብር እንደሌላቸው ግልፅ ነው፡፡ ያው በትዕቢትና በጠመንጃ እንጂ አንዳቸውም ህዝባዊ ፈቃድና ይሁንታ አግኝተው እንደማይመሩ እራሳቸውም ያውቁታል፡፡
ነገር ግን እንደ አቶ አለምነው መኮንን በቆሸሸ አስተሳሰብ ህዝብን ያህል ነገር ባለጌ ስድብ የሚሳደብ አይደለም ህዝብን ቤተሰቡን የመምራት ብቃት አለው ብሎ ማመን ይቸግራል፤ ይበልጥ ለቤተሰቡና ለወዳጅ ዘመዶቹ አዘንኩላቸው፡፡
ብአዴን/ኢህአዴግም ቢሆን ምንም እንኳ ለህዝብ ክብር ኖሮት ባያውቅም አቶ አለምነው መኮንንን በአደባባይ ፍርድ በማቅረብና ከስራ በማሰናበት ተገቢውን ፍርድ ሰጥቶ ተፈፃሚ ማድረግ አለበት እላለሁ፡፡ አለበለዚያ አቶ አለምነውን እከላከላለሁ ብሎ የሚል ከሆነ እራሱ ብአዴን ህዝብን የመምራት ሞራል እንደሌለው አምኖ ስልጣኑን ለህዝብ ማስረከብ አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ከዚህ በኋላ ህዝብን የመምራት፣ ከህዝብ ታክስ መሰብሰብ፣….የሞራል ብቃቱ የለውም፡፡ ሰውዬው የሰደበው የአማራውን ህዝብ ብቻ ሳይሆን መላውን የሀገራችንን ህዝብ ነውና፡፡ ህዝብን የሚንቅና የሚሳደብ በህገመንግስቱም ቢሆን ቅጣቱ ከባድ ነው፣ ህግ የሚያከብርና የሚያስከብር ስርዓት ባይኖረንም፡፡
ስለዚህ የእሁዱ የካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ም. አንድነትና መኢአድ የጠሩት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ከህግም ሆነ ከማህበራዊ እሴት አንፃር ተገቢም ትክክልም ነው፡፡ ስለዚህ ሁሉ የአካባቢው ሰው በሰልፉ ላይ በመታደም እንዲህ ዓይነት ትዕቢተኛ መሪዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ የሞራል የበላይነት በመሆኑ አስተባባሪዎቹን ቀጥሉበት ቢባል የሚበዛ አይሆንም፡፡
ይህ የተቃውሞ ሰልፍ ግን በባህርዳር ከተማ ብቻ መወሰን የለበትም፡፡ ምክንያቱም አቶ አለምነው መኮንን ላይ ገዥው ስርዓት እራሱ በግልፅ የእርምት እርምጃም ሆነ የይቅርታ ማስተባበያ ባለመስጠቱ ሁሉም ገዥውች ተመሳሳይ ንቀትና ትዕቢት እንዳላቸው የሚያመላክት ነውና፡፡ ህዝብን የናቀና የሚሳደብ ሰው ለሰከንድም ቢሆን ሊመራ አይገባም፣የሞራል ብቃቱም የለውም፡፡