Wednesday, February 12, 2014

‹‹ከኢትዮጵያ ጋር መታረቅ ስለሚባለው ባልሰማውና ባላስበው እመርጣለሁ›› ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ


February 12/2014



የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት አቶ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ የሥልጣን ዘመናቸውን ከጨረሱ በኋላ፣ የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥታትን ማስታረቅ እንደሚፈልጉ የመንግሥት የቴሌቪዥን ጣቢያ በሆነው ኢቴቪ በይፋ ገልጸው መስመር የያዘላቸው መሆኑንም አሳውቀው ነበር፡፡

በቅርቡ ከኤርትራ ቴሌቪዥን ጋር ሰፊ ቃለ ምልልስ ያደረጉት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ግን ምንም ዓይነት የዕርቅ ፍላጐት እንደሌላቸው የኢትዮጵያ መንግሥት በፕሮፓጋንዳ ብልጫ እየተጠቀመበት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ኢትዮጵያን በተመለከተ ለቀረቡላቸው ጥያቄ የሰጧቸው ምላሾች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

‹‹የሕዝብ ግንኙነት ብልጫ ለማግኘት ነው››

ሁለት የኤርትራ የመንግሥት ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች አንዳንድ የአገር ውስጥና የአካባቢ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ጥያቄዎችን ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ አንስተውላቸዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያና በኤርትራ ግንኙነት ላይ የሰጡት አስተያየት አነጋጋሪ ነው፡፡

በመግለጫው ከተገኙ የመንግሥት ጋዜጠኞች መካከል አንዱ እንዲህ ብሎ ፕሬዚዳንቱን ይጠይቃቸዋል፤ ‹‹ኤርትራና ኢትዮጵያን ለማስታረቅ አንዳንድ ሙከራዎች እየተደረጉ እንደሆነ በሚዲያዎች እየተነገረ ነው፡፡ ይኼ የሚወራው ነገር እውነት ነው ወይ?›› ይላቸዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ለጥያቄው መልስ መስጠት ሲጀምሩ ፊታቸውን ጨለም አድርገዋል፡፡ የሆነ ከውስጥ የሚሰማ የቁጣ ስሜት እንዳለ ያሳብቅባቸዋል፡፡ መልስ መስጠት ቀጠሉ፡፡ ‹‹ከምኡ ዝበሃል ነገር የለን›› [እንደዚያ ብሎ ነገር የለም] በሚል በእምቢተኝነትና በእልኸኝነት ውስጥ ሆነው ንግግራቸውን ቀጠሉ፡፡

‹‹እንደዚያ ብሎ ነገር የለም፡፡ ወያኔ እስኪጠፋ ዕለት እንደዚህ ብሎ ማውራቱ ይቀጥላል፡፡ ዓላማውም የሕዝብ ግንኙነት (PR) ብልጫ ለማግኘት ብቻ ነው፡፡ እንደዚያ በማድረጉ የፕሮፓጋንዳ ትርፍ ያገኝ ይሆናል፡፡ ወያኔ ያላንኳኳው በር የለም፡፡ የልጆች ሥራ ነው የሚመስለው፣›› ኢሳያስ ምላሻቸው በዚህ አላበቃም፡፡

‹‹ምናልባት ቀደም ሲል እንዲህ ተባለ እንዲህ ሆነ እያሉ ሊያታልሉን ሞክረው ይሆናል፡፡ እኔ የሚገርመኝ ጊዜያቸውን በዚህ ለምን እንደሚያጠፉ ነው፡፡ የአዞ እምባ ነው፡፡ እኛን ለማሰይጠን እነሱን መልዓክ ለማስመሰል፡፡ ምንም ባልሰማውና ባላስበው እመርጣለሁ፡፡ በአገር ውስጥም በውጭም ያለው የኤርትራ ሕዝብ ፈጽሞ ስለዚህ ማሰብ የለበትም፤›› ብለዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ በዚሁ ምላሻቸው እየተባለ ያለው የዕርቅ ጥያቄ የውሸት መሆኑን፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የፈጠራ ወሬ መሆኑንና ኤርትራዊያንን ለማሞኘት መሆኑን ይናገራሉ፡፡

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በሰጡት መግለጫ የኢትዮጵያ መንግሥት ዕርቅ ለመፍጠር ‹‹ያላንኳኳው በር የለም›› ካሉ በኋላ ዓላማው እውነት ዕርቅ ፍለጋ ሳይሆን ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሰላም ወዳድ መስሎ ለመታየት ነው የሚል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ ከዚሁ ቀጥሎ የቀረበላቸው ተከታይ ጥያቄም ከዚሁ ጉዳይ ጋር ቅርበት ያለው ነው፡፡

‹‹ከዚህ ጋር በተያያዘ [የቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳይ ምክትል ኃላፊ የነበሩት] ኸርማን ኮኸን የኢትዮጵያንና የኤርትራን ግንኙነት ወደነበረበት መመለስ አለበት በሚል የመፍትሔ ሐሳብ አቅርበዋል፡፡ ይኼና ሌሎች ጽሑፎች የአሜሪካ መንግሥት አቋም ናቸው ብሎ መውሰድ ይቻል ይሆን?›› የሚል ነበር፡፡ የፕሬዚዳንት ኢሳያስ ምላሾች በአብዛኛው በንቀት የተሞሉ የሚመስሉ ነበሩ፡፡ ‹‹አምባሳደሩ ኤርትራን ከብርድ እንታደጋታለን ነው የሚሉት፡፡ የምን ብርድ ነው እኛ ዘንድ ያለው ኤርትራ ገዳም ወጥታለችና ወደ ቤቷ እንመልሳት ነው እኮ የሚሉት፤›› የሚል ምላሽ ፕሬዚዳንቱ ሲሰጡ የቁጭት ስሜት ይነበብባቸዋል፡፡

አምባሳደር ኸርማን ኮኸን የቀድሞ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ኃላፊ ሲሆኑ፣ በምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች የአሜሪካን መንግሥት በውጭ ፖሊሲ ከሚያማክሩ መካከል ናቸው፡፡ ‹‹ኤርትራን መታደግ አሁን ነው›› በሚል በቅርቡ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) በጻፉት የመፍትሔ ሐሳብ፤ ኢትዮጵያ አወዛጋቢውን የባድመ ግዛት ለኤርትራ እንድትሰጥ፣ በሁለቱም አገሮች መካከል ዕርቅ እንዲወርድ፣ ይኼም በአንድ ገለልተኛ የአውሮፓ አገር [ማን እንደሆነ ያልተገለጸ] አነሳሽነት እንዲጀመር የሚሉ ናቸው፡፡ የእሳቸው የዕርቅ ሐሳብ መነሻ ሁለቱም መንግሥታት (ኢትዮጵያና ኤርትራ) በድንበር አካባቢ ባለው ሰላምና ጦርነት አልባ ሁኔታ ተሰላችተዋል፡፡ ሁለቱም መንግሥታት የዕርቅ ፍላጎት አሳይተዋል የሚል ነው፡፡ ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያምና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በተለያዩ ሚዲያዎች የሰጡዋቸው የተለሳለሱ አስተያየቶችን መታዘባቸውን መሠረት ያደረገ ነው፡፡

ኸርማን ኮኸን፣ በተጨማሪ ያነሱት ጉዳይ ኤርትራ በሶማሊያ በምታደርገው አፍራሽ እንቅስቃሴ ምክንያት በፀጥታው ምክር ቤት የተጣለው ማዕቀብ እንዲነሳ የሚል ነው፡፡ ለዚህም እ.ኤ.አ. ከ2009 ዓ.ም. ጀምሮ ኤርትራ አደብ መግዛቷንና አልሸባብን ስለመደገፏ አንድም ማስረጃ አልተገኘም የሚል ነበር፡፡ አምባሳደሩ ጽሑፋቸውን ባወጡበት ወቅት ይኼ አስተያየት ተመድና የአሜሪካ መንግሥት ካቀረቧቸው ሪፖርቶች ጋር የሚቃረን መሆኑ ተገልጿል፡፡

‹‹ከብርድ ሊገላግሉን ነው?›› በሚል ፌዝ መሰል ንግግር የጀመሩት ፕሬዚዳንቱ የአምባሳደሩን ሐሳብ አጣጥለዋል፡፡

‹‹በ[ሸባብ] ምክንያት በኤርትራ ሕዝብ ላይ ከሳሽ ራሳቸው ፈራጅ ራሳቸው ሆነው ቀጥተውናል፡፡ በፈጠራ ታሪክ ነበር ማዕቀብ ያስጣሉብን፡፡ አሁን ደግሞ ከ2009 ጀምሮ ምንም የሉበትም ይላሉ፤›› በማለት ቀደም ሲል ከ2009 በኋላ በኤርትራ ላይ የፀጥታው ምክር ቤት የጣለው ማዕቀብ ድሮም፣ በተፈበረከ ውንጀላ ነው የሚለውን ንግግራቸውን አምባሳደሩ ያረጋገጡላቸው በሚመስል ስሜት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

‹‹ፕሬዚዳንት ኢሳያስ የኤርትራ ዕጣ ፈንታ ከኢትዮጵያ ጋር የተያያዘ ነው ብሎኛል፤›› በማለት አምባሳደሩ ያቀረቡትን አስተያየት ያጣጣሉት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ፣ ‹‹ቆይ ከየት የመጣ ነገር ነው? መቼ የት ነው እንዲህ ያልኩት?›› የሚሉ ጥያቄዎች አቅርበው፣ ‹‹ይኼ ማለት’ኮ ኤርትራ ያለ ኢትዮጵያ የለችም እንደማለት ነው፤›› ብለዋል፡፡

በአጠቃላይ የኸርማን ኮኸን የዕርቅ ሐሳብ በተመለከተ ግን ሌላ ቀደም ሲል የተገመተ መላምት ሰጥተዋል፡፡ የኤርትራና የአሜሪካ ግንኙነትን ለማዳስ ያለመ እንደሆነ በመግለጽ፡፡ ‹‹ሐሳቡ የቀረበበትን ጊዜ፣ ይዘቱን፣ ቋንቋውንና አቀራረቡን ስትመለከተው ይኼው ነው፡፡ ኤርትራ ግን አትፈልገውም፡፡ ከአሜሪካ ጋር የሚሻሻል ዝምድና ምንድን ነው? መጀመሪያ ራሳቸው በራሳቸው በፈጠሩት ውሸት የኤርትራን ሕዝብ ለመቅጣት ከጀሉ፡፡ ‹‹እናዳክማቸዋለን፣ እንቀጣቸዋለን፤›› በማለት ምላሻቸውን ይቀጥላሉ፡፡ አሜሪካውያን ስለኤርትራ ሕዝብ መወሰንም አለመወሰንም መብት እንደሌላቸው በማተኮር፡፡

የወያኔ ሴራ በሚለው ተደጋጋሚ አገላለጻቸው፣ ‹‹በኤርትራ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ጥፋት ከፈጸሙ በኋላ የኤርትራ ወጣቶች ከአገር እንዲኮበልሉ ካደረጉ በኋላ አሁን የምን ዕርቅ ነው?›› የሚል ሐሳብ አቅርበዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በቅርቡ በሱዳን ፕሬዚዳንት አማካይነት ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የዕርቅ ሐሳብ የያዘ ደብዳቤ መላካቸውን አንዳንድ ሚዲያዎች ዲፕሎማቶችን ዋቢ በማድረግ የዘገቡ ሲሆን፣ ፕሬዚዳንቱ ግን የዕርቅ ጥያቄው ከኢትዮጵያ መንግሥት የሚቀርብ መሆኑን፣ እሱም ቢሆን እውነትነት እንደሌለው ነው በዚሁ ቃለ ምልልሳቸው የተናገሩት፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ባለፈው ሰኞ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ በፕሬዚዳንት ኢሳያስ ቃለ ምልልስ ላይ አስተያየት የሰጡ ሲሆን፣ የተባለው ከእሳቸው የማይጠበቅ መሆኑንና በፕሬዚዳንት ኢሳያስ የሚመራው መንግሥት አስመራ እስካለ ድረስ ምንም አዲስ ነገር እንደማይጠብቁ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአሁኑ ንግግራቸው በመስከረም ወር አካባቢ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ሙልጭ አድርገው የካዱት ይመስላሉ፡፡ ኤርትራ ውስጥ ያለው የልማት እንቅስቃሴና ሌሎች የመንግሥት አውታሮች በተለይ በኤሌክትሪክ ኃይል ዕጦት ምክንያት መቆሙን፣ እንዲሁም የአሰብ ወደብ ምንም ጥቅም እየሰጠ እንዳልሆነ ጠቅሰው፣ ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ለመግዛት፣ ወደቡም ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ በማዘጋጀው ለኢትዮጵያ የማቅረብ ዕቅድ እንዳላቸው ተናግረው ነበር፡፡

ይህም በሁለቱም አገሮች መካከል ለሚዲያ ይፋ ያልሆነ የዕርቅ ጥረት ስለመኖሩ፣ እንዲሁም እንደ አምባሳደር ኸርማን ኮኸን የመሳሰሉ ሰዎች ፕሬዚዳንቱ ዕርቅ ማድረግ ይፈልጋሉ የሚል አመለካከት እንዲኖራቸው ሳያደርግ አልቀረም፡፡ የአሁኑ የኢሳያስ አስተያየት ግን የዚህ ተቃራኒ ነው፡፡  

በአሁኑ ንግግራቸው ግን የኤሌክትሪክ ኃይል ከኢትዮጵያ በመግዛት ላይ ከምትገኘው ከሱዳን እንገዛለን ብለዋል፡፡ ይህ የብዙ ኢትዮጵያዊያንን ቀልብ የሳበ ቢሆንም፤ ምን ማለት እንደሆነ ለብዙዎች ጥያቄ ሆኗል፡፡ ቀደም ሲል በጂቡቲ በኩል ወደ ኤርትራ በሚገቡ የቡናና የጤፍ ምርቶች ምክንያት ኤርትራ በዓለም አቀፍ ደረጃ ካሉ ቡና አቅራቢዎች ግንባር ቀደም አድርጓት እንደነበር አንዳንዶች ያስታውሳሉ፡፡

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ከአገር ውስጥ ጉዳዮች በተጨማሪ በምሥራቅ አፍሪካ ፖለቲካ እ.ኤ.አ. በ2014 ምን ዕቅድ እንዳላቸው ጥያቄ የቀረበላቸው ሲሆን፣ ‹‹አሁን አላወራውም እንጂ በክልሉ ጉዳዮች ቀጥተኛ ተሳታፊ ለመሆን ዕቅድ አለን፤›› ብለዋል፡፡ በአካባቢው እየመጣ ያለው ለውጥ የኤርትራን ቀጥተኛ ተሳታፊነት እንደሚጠይቅ የገለጹት ኢሳያስ፣ በአካባቢው ፖለቲካዊ ጉዳዮች ከዚህ በፊት በተለየ ሁኔታ ለለውጦች ምላሽ መስጠት ሳይሆን፣ ቀድሞ ዕርምጃ በመውሰድ የለውጡ አካል ለመሆን የኤርትራ መንግሥት ዝግጅቱን አጠናቋል ብለዋል፡፡ የፕሬዚዳንቱ ንግግር ወዴት እንደሚያመራ ግን አመላካች የለም፡፡ ከዚህ በፊት ጎረቤት አገሮችን በመውረርና በመተንኮስ እንዲሁም በሶማሊያ ጣልቃ በመግባት የሚታወቁት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በተያዘው አዲሱ የአውሮፓውያን ዓመት ግን ሊገልጹ ያልፈለጉት ጉዳይ እንዳለ ጠቁመዋል፡፡

ምንጭ ሪፖርተር

የብአዴን ዋና ጸሃፊ ቤት በፖሊሶች እየተጠበቀ ነው

February 12/2014

የካቲት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ተወላጆች ላይ በጅምላ ፀያፍ ስድብ የሰነዘሩት የብአዴኑ አመራር እና የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የ አቶ ኣለምነው መኮነን መኖሪያ ቤት በድንጋይ መደብደቡን ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ የዘገበ ሲሆን፣ ዜናውን ተከትሎ ኢሳት ባደረገው ማጣራት የባለስልጣኑ መኖሪያ ቤት በ11 ፖሊሶች ሌትና ቀን እየተጠበቀ ነው።
አቶ አለምነው የአማራው ህዝብ የትምክህት ለሃጩን በማራገፍ ከሌላው ህዝብ ጋር ለመኖር መልመድ አለበት በማለት የተናገሩት በክልሉ ውስጥ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል። ወጣቶች በሞባይል ስልካቸው ንግግሩን በመቅረጽ እያሰራጩት ነው።
አቶ አለምነው እስካሁን በይፋ ህዝቡን ይቅርታ አልጠየቁም ወይም በኢሳት የቀረበውን መረጃ ለማስተባበል አልሞከሩም። ኢሳት ም/ል ፕሬዚዳንቱ የተናገራቸው በርካታ ንግግሮች የደረሱት ሲሆን እንዳስፈላጊነቱ ወደ ፊት ለህዝብ ይፋ ያደርጋል።
በሌላ ዜና ደግሞ የአቶ ተመስገን ዘውዴን የህይወት ታሪክ የሚዳስሰውን  መጽሐፍ በማሳተሙ  የስም ማጥፋት ክስ የተመሰረተበት የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ሆነው ደራሲ ዳንኤል ተፈራ ዛሬ በድጋሚ ማዕከላዊ ተጠርቶ ለሰኣታት መታሰሩ ተዘግቧል።
ፍኖተ ነፃነት እንደዘገበው አቶ ዳንኤል ከሰዓታት እስር በሁዋላ  በድጋሚ የተከሳሽነት ቃሉን ሰጥቶ መኪና ሊብሬ በዋስትና አስይዞ ከእስር ተፈቷል፡ የፓርቲው ሌለኛው አመራር አቶ አሥራት ጣሴ ፦”አኬልዳማ ድራማን አስመልክተን መንግስትን የከሰስነው ከኢህአዴግ ፍርድ ቤት ፍትህ እናገኛለን ብለን ሳይሆን ለታሪክ እንዲመዘገብ ነው” የሚል አስተያታቸውን በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ በመፃፋቸው  ታስረው ወደ ቂሊንጦ ወህኒ ቤት የተጋዙት ከቀናት በፊት ነው።
ቀደም ሲልም የፓርቲው አመራር  የነበሩት አቶ አንዷለም አራጌና አቶ ናንትናኤል መኮንን ሀሳባቸውን በመግለፃቸው ሳቢያ የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው በእስር እንደሚገኙ ይታወቃል።

አንድነት እና መኢአድ ብአዴንን በመቃወም የተቃውሞ ሰልፍ ጠሩ

February 12/2014

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ብአዴንን በመቃወም በባህርዳር ከተማ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ጠሩ፡፡ ፓርቲዎቹ ነገ በ4 ሰዓት በአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት በጋራ መግለጫ እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡ ለተቃውሞ ሰልፉ አስፈላጊው የማሳወቅ ተግባር መጠናቀቁ ታውቋል፡፡
አንድነትና መኢአድ እሁድ የካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ም የጠሩት የተቃውሞ ሰልፍ መነሻ ምክንያት እንዲያስረዱ በፍኖተ ነፃነት የተጠየቁት የአንድነት ፓርቲ የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ሰለሞን ስዩም “አማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የብአዴን የጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን የአማራን ህዝብን ክብር የሚያዋርድና በለሌሎች ብሔረሰቦች በክፉ እንዲታይ የሚያደርግ የጥላቻ ንግግር በማድረጋቸውና ብአዴንም እንደ ፓርቲ ማስተባበያም ሆነ የማስተካከያ እርምጃ ባለመውሰዱ የግለሰቡን አቋም እንደሚጋራ ያመለክታል” ብለዋል፡፡
የመኢአድ ም/ፕሬዝደንት አቶ ተስፋዬ መላኩ በበኩላቸው “የአማራ ህዝብን እየመራሁ ነው እያለ እንደዚህ አይነት አስነዋሪ ንግግር ያደረገውን ባለስልጣና የሚወክለውን ፓርቲ ለማውገዝ እንዲሁም ለህግ እንዲቀርብ ለመጠየቅ ነው ሰልፉ የተጠራው” ብለዋል፡፡
የፓርቲዎቹ የባህርዳርና አካባቢዋ መዋቅሮች የተቃውሞ ሰልፉን ለማስተባበር ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን የባህርዳር ከተማና የአካባቢዋ ህዝብ በነቂስ በመውጣት በሰልፉ ተቃውሞውን እንዲገልፅም ጥሪ አቅርበዋል፡

ትግራዊ ማንነት ካለ ኢትዮጵያዊ ማንነትም አለ!

February 12/2014
በአብረሃ ደስታ


“ኢትዮጵያዊ ነኝ፤ ኢትዮጵያዊ ማንነት አለኝ” ብዬ ስል የራሴ (የግሌ) ማንነት የለኝም ማለት አይደለም። የአከባቢ ማንነት የለኝም ማለት አይደለም። የክልል (የብሄር) ማንነት የለኝም ማለት አይደለም። ወይም እነዚህ የተለያየ ደረጃ ያላቸው ማንነቶቼ መጥፋት አለባቸው ማለት አይደለም። እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ ስል የራሴን ማንነት አልቀበልም ማለት አይደለም። የራሴ ማንነት ስላለኝ ነው ኢትዮጵያዊ ማንነት ሊኖረኝ የቻለው። እኔ የግል ማንነት ባይኖረኝ ኑሮ ኢትዮጵያዊ አልሆንም ነበር። ምክንያቱም የግል ማንነት ከሌለኝ የሀገር ማንነት ሊኖረኝ አይችልም። እያንዳንዱ ሰው የግሉ የሆነ ማንነት አለው። የግሉ ማንነት ስላለው ነው ኢትዮጵያዊ ማንነት ያለው። ኢትዮጵያዊ ማንነት ራሱ የቻለ የሁላችን የጋራ ማንነት ነው።
የትግራይ ማንነት ካለን የኢትዮጵያ ማንነት ለምን አይኖረንም? “ትግራዮች አንድ ነን” ካልን “ኢትዮጵያውያን አንድ ነን” ብንል ችግሩ ምንድነው? ኢትዮጵያዊነትኮ ከብሄር (ከክልል) ሰፋ ያለ ሀገራዊ ማንነት ነው። ሀገራዊ ማንነታችንን ብንቀበል ችግሩ ምንድነው?
ኢትዮጵያውያን አንድ አይደለንም አትበሉኝ። ምክንያቱም ኢትዮጵያውያን አንድ ካልሆንን ትግራዮችም አንድ አይደለንም፤ አማራዎችም አንድ አይደለንም፣ ኦሮሞዎችም አንድ አይደለንም። አንድ የሆነ አይኖርም።
“ኢትዮጵያውያን አንድ አይደለንም ምክንያቱም የተለያየ ታሪክና ባህል አለን” አትበሉኝ። ምክንያቱም እያንዳንዱ ግለሰብ፣ አውራጃ፣ ክልል (ብሄር) ወዘተ…ም የተለያየ ታሪክና ባህል ሊኖረው ይችላል። ኢትዮጵያውያን የተለያየ ባህልና ታሪክ ስላለን አንድ አይደለንም ካላችሁኝ ኦሮሞዎችም አንድ አይደሉም እላቸዋለሁ፤ ምክንያቱም የወለጋ ኦሮሞዎች፣ የሸዋ ኦሮሞዎችና የአርሲ ኦሮሞዎች የተለያየ ታሪክና ባህል አላቸው።
ኢትዮጵያውያን የተለያየ ባህልና ታሪክ ስላለን አንድ አይደለንም ካላችሁኝ አማራዎችም አንድ አይደሉም እላቸዋለሁ፤ ምክንያቱም ወለየዎች፣ ጎጃሞችና ጎንደሬዎችም የተለያየ ታሪክና ባህል አላቸው።
ኢትዮጵያውያን የተለያየ ባህልና ታሪክ ስላለን አንድ አይደለንም ካላችሁኝ ትግራዮችም አንድ አይደሉም እላቸዋለሁኝ፤ ምክንያቱም ተምቤኖች፣ ዓድዋዎች፣ ዓጋሜዎች፣ ራያዎች፣ ወልቃይቶች የተለያየ ታሪክና ባህል አላቸው።
“የተለያየነው በቋንቋ ነው” ካላችሁኝ። የተለያየ ቋንቋ የማንነት መለያ መስፈርት ከሆነና እኛ ኢትዮጵያውያን የተለያየ ቋንቋ ስለምንናገር የተለያየን ከሆንን ትግራዮችም አንድ አይደለንም። ምክንያቱም የትግራይ ህዝብ አንድ ቋንቋ ብቻ የሚናገር ህዝብ አይደለም፤ አንድ ዓይነት ባህል ያለው ህዝብ አይደለም። ምሳሌ ኢሮብ (ቋንቋ ሳሆ) የራሳቸው ቋንቋና ማንነት አላቸው። ግን በትግራይ ክልል ዉስጥ ናቸው። በትግራይ ኩናማዎች አሉ (ወልቃይቶች ጨምሮ)። የራሳቸው ባህል አላቸው። ራያዎች የራሳቸው የሚኮሩበት ባህል አላቸው። ስለዚህ በትግራይ ክልል የተለያዩ ባህሎችና ቋንቋዎች አሉ። ግን ትግራዮች (ተጋሩ) አንድ ነን። ተጋሩ አንድ ነን ስንል አንድ ቋንቋ፣ አንድ ባህል ብቻ አለን ማለታችን አይደለም፤ ተጋሩ አንድ ነን ስልን ሌላ ቋንቋ፣ ማንነት፣ ባህል ወዘተ ያላቸው ህዝቦች እውቅና አንሰጥም ማለት አይደለም። ማንነታቸው እንዲቀይሩ እናስገድዳቸዋለን ማለትም አይደለም። ተጋሩ አንድ ነን ስንል የግላችን ማንነት ጠብቀን የጋራ በሆነ የትግራይ ማንነት በአንድነትና በእኩልነት እንኖራለን ማለት ብቻ ነው።
ተጋሩ አንድ ነን። ኢትዮጵያውያንም አንድ ነን። የተለያየ ቋንቋ መናገራችን የተለያየን ስለመሆናችን ማረጋገጫ ሊሆን አይችልም። ስለ ኢትዮጵያዊ ማንነት ስናወራ ስለ ሌሎች ማንነቶች እውቅና እየሰጠን ነው። ምክንያቱም የያንዳንዳችን ማንነት ከሌለ የጋራ ማንነታችን አይኖርም። የያንዳንዱ ግለሰብ ማንነት ካከበርን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ማንነት እናከብራለን። ምክንያቱም ኢትዮጵያዊ ማንነት ማለትኮ የኛ ማንነት ማለት ነው። “እኛ” ማን ነን? እኛ ሁላችን ነን።
ኢትዮጵያዊ ማንነት ከሌለ የክልል (ብሄር) ማንነትም አይኖርም። ኢትዮጵያዊ ማንነት አለ፤ ምክንያቱም የያንዳንዳችን ኢትዮጵያውያን የየግላችን ማንነት አለን።
ኢትዮጵያዊ ማንነትን ስናስቀድም ሁሉም ኢትዮጵያውያንን እናስቀድማለን። የዓድዋ ወይ የራያ ወይ የኢሮብ ማንነት ብናስቀድም እያስቀደምነው ያለነው ህዝብ የአንድ ወረዳ ወይ አከባቢ ብቻ ነው የሚሆነው። የትግራይ ማንነት ብናስቀድምም የምናስቀድመው የትግራይ ህዝብ ብቻ ነው የሚሆነው። ትንሽ ጠበብ ያለ ነው። ሌሎችስ ለምን እንተዋቸዋለን? ሌሎች (አማራዎች፣ ኦሮሞዎች፣ ሶማሌዎች፣ ደቡቦች፣ ዓፋሮች፣ ጋምቤላዎች፣ ቤኑሻንጉሎች፣ ጋምቤላዎች፣ ሃረሪዎች ወዘተ) ለምን በእኩል ዓይን አናስቀድማቸውም?
የትግራይን ማንነት የሚያስቀድም ሁሉ የኢትዮጵያ ማንነትም ማስቀደም አለበት። ምክንያቱም የትግራይን ማንነት ስታስቀድም የሌሎች ወገኖች ማንነት ትተወዋለህ። የኢትዮጵያ ማንነት ስታስቀድም ግን የሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች (የትግራይ ጨምሮ) ማንነት ነው የምታስቀድመው።
በኢትዮጵያዊ ማንነት የማምነው ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ማስቀደምና ማክበር ስላለብኝ ነው። በኢትዮጵያ ዉስጥ እየኖረ የራሱን ብሄር የሚያስቀድም ሰው በሁሉም ብሄሮች (ኢትዮጵያውያን) እኩልነት አያምንም ማለት ነው። በብሄሮች እኩልነት የማያምን ደግሞ የኢትዮጵያን አንድነት ማስጠበቅ አይችልም። ምክንያቱም እኩልነት ከሌለ አንድነት የለም። አንድነት ከሌለ ሀገር የለም። ሀገር ከሌለ ሉአላዊነት የለም። ሉአላዊነት ከሌለ የህዝብ ደህንነት አይጠበቅም። ስለዚህ ኢትዮጵያዊ ማንነት የማያስቀድም ለህዝብ አይበጅም።
አንድ የወረደ ሐሳብ ላንሳ።
የቡድን (የብሄር) መብትን የሚያስቀድመው የኢህአዴግ መንግስት የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች እኩልነት እንዳረጋገጠ ይተርክልናል። ግን በትክክል የኢህአዴግ መንግስት ሁሉንም ብሄሮች በእኩል ዓይን ያያል? ትንሽ እንውረድና …!
በፓርላመንታዊ ስርዓት (ኢህአዴግ የሚከተለው ዓይነት) የሀገር ከፍተኛው የፖለቲካ ስልጣን ጠቅላይ ሚኒስተርነት ነው። ሁሉም ብሄር፣ ብሄረሰቦች እኩል ናቸው ካልን ለዚህ ከፍተኛ የሀገር ፖለቲካዊ ስልጣን እኩል ዕድል አግኝተው መወዳድር አለባቸው።
ታድያ በኢህአዴግ ዘመነ ስልጣን አንድ የዓፋር ወይ የሶማሌ ወይ የቤኑሻንጉል ጉሙዝ ወይ የሃረሪ ወዘተ ተወላጅ የጠቅላይ ሚኒስተርነቱን ስልጣን ለመያዝ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በእኩልነት የመወዳደር ዕድል አለው? በኢህአዴግ ዘመን ዓፋር ወይ ሶማል ወይ ጋምቤላ ጠቅላይ ሚኒስተር ሊኖረን ይችላል? አይችልም። ለምን?
የሀገር ጠቅላይ ሚኒስተር ሁኖ መመረጥ የሚችለው የገዢው ፓርቲ አባል የሆነ ብቻ ነው። አባል መሆን ብቻ በቂ አይደለም። የፓርቲው ሊቀመንበር መሆን አለበት። የፓርቲ ሊቀመንበር የሚመረጠው ከፓርቲው አባል ፓርቲዎች ነው። የኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች የደቡብ፣ ትግራይ፣ አማራና ኦሮምያ ብሄር ተወላጆች ብቻ ናቸው። ድርጅቶቹ ብሄር መሰረት ያደረጉ ናቸው። ስለዚህ በኢህአዴግኛ አሰራር አንድ የዓፋር ወይ የሶማል ወይ የቤኑሻንጉል ወይ የጋምቤላ ተወላጅ ጠቅላይ ሚኒስተር የመሆን ዕድል ወይ መብት የለውም። ይሄ ነው እኩልነት!?
በግለሰባዊ ኢትዮጵያዊ አስተሳሰብ ግን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለማንኛውም ስልጣን ወይ ሐላፊነት እኩል የመወዳደር ዕድል ይኖረዋል። አንድ ኢትዮጵያዊ የሚመዘነው እንደ ሰው (እንደ ዜጋ) እንጂ በመጣበት ብሄር ወይ አከባቢ ወይ በሚናገረው ቋንቋ መሰረት አይደለም። ስልጣን ለመያዝ ወይ ስራ ለማግኘት ኢትዮጵያዊ ዜጋ መሆኑ ብቻ በቂ ነው። ከሌላው ጋር በትምህርት ደረጃው፣ በብቃቱ ወዘተ ይወዳደራል። ምክንያቱም ሁላችን እኩል ነን። ለሁሉም ነገር እኩል ዕድል ይኖረናል።
ስለዚህ ኢትዮጵያዊ ማንነት ማስቀደም የምንፈልገው ሁሉም ዜጋ በእኩል ዓይን ማየት ስለምንፈልግና ጠንካራ ሀገር መመስረት ስላለብን ነው።
ትግራዊ ማንነት ካለ ኢትዮጵያዊ ማንነትም አለ!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።
It is so!!!

የአቶ አለምነው መኮንን መኖሪያ ቤት በድንጋይ ተደበደበ

February 12/2014

የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የብአዴን ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን መኖሪያ ቤት በድንጋይ መደብደቡን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ጠቆሙ፡፡ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች እንጠቆሙት ባሳለፍነው ሳምንት የካቲት 1 እና የካቲት 2 ቀን 2006 ዓ.ም(ቅዳሜና እሁድ) ለሊት በተደጋጋሚ ማንነታቸው ባልታወቀ ግለሰቦች መኖሪያ ቤታቸው በድንጋይ መደብደቡን ተከትሎ ቤታቸው ቀንና ለሊት በፖሊስ እየተጠበቀ ይገኛል፡፡
አቶ አለምነው መኮንን የአማራን ህዝብ የሚያዋርድና የሚዘልፍ ንግግር ሲያደርጉ የተቀዳ ድምፅ ለህዝብ ይፋ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ በብአዴን ውስጥ የንትርክ ምክንያት መሆናቸው አይዘነጋም፡፡

መንታ መንገድ – የኢህአዴግና የአሜሪካ ወዳጅነት ወዴት?

February 12/2014

ቻይና ኢህአዴግን ትታደጋለች? ወይስ ኢህአዴግ ይታዘዛል?
eprdf china usa

አሜሪካኖች ነጻ እንድታወጡን አንጠይቃችሁም። የኢትዮጵያ ህዝብ እንዴት ነጻ እንደሚወጣ ያውቃል። እናንተ ግንበነጻነት መንገዱን ላይ ዕንቅፋት አትሁኑበት … ዶናልድ ያማሞቶ ከዛሬ ስምንት ዓመት በፊት ኢትዮጵያ በመንታመንገድ ላይ ነች ብለኸን ነበር መቼ ነው መንገዱን የምናቋርጠውከመንገዱ ላይ ገለል በሉልን” አቶ ኦባንግ ሜቶ
እንዴት እዚህ ተደረሰ?
የኢህአዴግን የአገዛዝ ዘመን ተቃዋሚዎችን አጃቢ አድርጎ የህግ ሽፋን በመስጠት የሚያራዝመው ዋና ተቋም ምርጫ ቦርድ፣ የፕሬስ ነጻነት፣ የመናገርና የመሰብሰብ ነጻነት፣ የህግ የበላይነት፣ ሕግን የማክበርና የማስከበር ሃላፊነት፤ ወዘተ በኢትዮጵያ ነጻ ከሆኑ ኢህአዴግ ከፊትለፊቱ ካለው ምርጫ የመዝለል አቅም እንደሌለው ይታመናል። ስለዚህም እነዚህን ጉዳዮች ለድርድር አያቀርባቸውም። ኢህአዴግ ከጅምሩ በህዝብ የማይታመነውና እውቅና የሚነፈገው ራሱን በነጻ አውጪ ስም (ህወሃት) የሰየመ መንግስት ስለሆነ ነው። ነጻ አውጪ እየተባለ አገር መምራቱም አቅዶ፤ ተልሞና መድረሻውን አስልቶ የሚጓዝ ስለመሆኑ ያሳብቅበታል። ለዚህም ይመስላል ስርዓቱ በሙስና የሸተተ፣ በግፍ የገለማ፣ የሚመራውን ህዝብ የሚገል፣ የሚያስር፣ የሚያሰቃ፣ መንግስት ሆኖ የሚሰርቅ፣ ብሔራዊ ክብርን የሚጠላ፣ ህብረትንና አንድነትን የሚጠየፍ፣ ጎሳና ጠባብ አመለካከት ላይ የተቀረጸ፣ በተራና በወረደ ተግባሩ ለመንግስትነት የማይመጥን መሆኑን የተረዱት አጋሮቹ አሁን ያመረሩበት ደረጃ ስለመዳረሳቸው ምልክቶች እንዳሉ አቶ ኦባንግ ሜቶ ለጎልጉል ተናግረው ነበር።
ኢህአዴግ ከአሜሪካ ጋር የመሰረተው ግንኙነት ከቶውንም ንፋስ እንደማይገባው ተከታዮቹ ሙሉ በሙሉ ያምናሉ። በተለይም የህወሃት ሰዎች አሜሪካ ከህወሃት ጋር ያሰረችው ቀለበት የሚወይብ አይመስላቸውም። የአሜሪካና የ”ህወሃት ፍቅር” ትምክህት የሆነባቸው የአሜሪካን ባለስልጣናት ህወሃት ኢትዮጵያን እስከ ዘላለም እንዲመራ ልዩ ቅባት እንደቀቡት የሚናገሩም አሉ። አሜሪካ ለህወሃት/ኢህአዴግ የምትሰጠው ጭፍን ድጋፍ ሊጤን እንደሚገባው በማሳሰብ ተስፋ ሳይቆርጡ የታገሉና የሚታገሉ ደግሞ ይህ ትምክህት አንድ ቀን እንደሚተነፍስ በእምነት ሲናገሩ ቆይተዋል።
ኦባንግ ሜቶ
ኦባንግ ሜቶ
ኢህአዴግን በዲፕሎማሲና በሰከነ የትግል ስልት መታገል ይበልጥ አዋጪ እንደሆነ ከሚያምኑት ወገኖች መካከል አቶ ኦባንግ ሜቶ ቅድሚያውን ይይዛሉ። አቶ ኦባንግ የሚመሩት ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) የሚያራምደውን እምነት አስመልክቶ “ከወረቀትና ፒቴሽን ከማስፈረም ያልዘለለ” በማለት የሚቃወሙና የሚተቹ የመኖራቸውን ያህል ልብና ቀልብ ሰብስበው የሚከተሏቸው ወገኖች ቁጥር ከቀን ቀን እየጨመረ ነው። እምነትም እየተጣለባቸው ነው።
በወገኖቻቸው ብቻ ሳይሆን በውጪው ዓለም ያላቸው ተቀባይነት፣ ብሎም አመኔታ እንዲሁ ከፍተኛ ነው። የኢትዮጵያ ወኪል ተደርገው እየተወሰዱም ነው። አቶ ኦባንግ ኢትዮጵያን በመወከል በተለያዩ ታላላቅ መድረኮች ሲሳተፉ የሚያቀርቧቸው ንግግሮችም ቀልብ የሚገዙና መልዕክታቸው የሰፋ በመሆኑ ሰፊ አድማጭ አላቸው። ሰሞኑንን በአሜሪካ ምክርቤት (ኮንግረስ) የጸደቀውን ድንገተኛ ውሳኔ አስመልከቶ “ኢህአዴግ ሳይወድ በግዱ በሩን በርግዶ ይከፍታል” ባይ ናቸው። ውሳኔውንና የውሳኔውን አካሄድ ከአነሳሱ ጀምሮ ጠንቅቀው እንደሚያውቁት ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “አሜሪካ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው እንዲሁ ከመሬት ተነስታ ሳይሆን በከፍተኛ ትግል ነው። ትግሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል የአውሮፓ አገሮችም የአሜሪካን ፈለግ እንዲከተሉ ሥራችንን አጠናክረን ጀምረናል” ብለዋል።
አዲሱ ውሳኔ ሕግ እና የኢህአዴግ ህልውና!
እያነጋገረ ያለው የእርዳታን አጠቃቀም አስመልክቶ ጥር 31 ቀን 2014 በአሜሪካን ኮንግረስ የፀደቀው አዲስ ውሳኔ ሕግ ነው። ውሳኔው አሜሪካ የምትሰጠው ርዳታ በትክክል ህዝብን ሳይጎዳ በስራ ላይ መዋሉንና አለመዋሉን እንዲቆጣጠር ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መ/ቤት (State Department) ትዕዛዝ የተላለፈበት ነው። እንግዲህ ይህ ትዕዛዝ ይፋ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ የሚነሱት መከራከሪያዎች በርካታ ቢሆኑም በምላስ “ነጻ ነኝ” የሚለውና በግብር “ለጌቶቹ ጥሩ ባሪያ” በመሆን 22 ዓመት የዘለቀው ኢህአዴግና ከአሜሪካ ግንኙነታቸው በነበረበት መንገድ ስለመዝለቁ ጥያቄ የሚያስነሳ እንደሆነ አብዛኞች ይስማማሉ። አሜሪካ ከዚህ ውሳኔ የደረሰችው በወፍ ዘራሽ ሳይሆን በሂደት እንደሆነ በመጥቀስ አቶ ኦባንግ ሜቶ ከሚያቀርቡት ሃሳብ ጋር ይስማማሉ።
የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች መረጃ ላይ ተንተርሰው ለሚያወጡት ሪፖርት “ተራ የማበሻቀጪያና የማጣጣያ” መልስ በመስጠት፣ ሲለውም ተቃዋሚዎችን የሚደግፉና የኢህአዴግ የኢኮኖሚና የፖለቲካ እምነት /የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ጎዳና/ “ቅንቅን” የሆነባቸው የምዕራብ አገራት “ተላላኪ” በማስመሰል አሁን ድረስ ሲዘልፋቸው መቆየቱ አይዘነጋም። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ እንደሚሉት አሁን አዲስ ለጸደቀው የአሜሪካ ቅድመ ሁኔታ ላይ ያተኮረ የርዳታ መርሃ ግብር እነዚህ ክፍሎች በቁጥጥርና በክትትል በኩል ሪፖርታቸው ዋና ግብዓት ስለሚሆን ኢህአዴግ መንታ ፈተና ውስጥ እንደሚወድቅ ቅድመ ትንበያዎች አሉ።
በዚሁ መነሻ ኢህአዴግ የህልውናው መሰረት የሆነውን እርዳታ ለማግኘት “የፖለቲካ አመለ ሸጋ ሆኖ የዘጋቸውን በሮች ከፍቶ የሚመጣውን የህዝብ ወሳኝነት መቀበል፣ አሊያም በሂደት ሰልሎና ተሽመድምዶ መክሰም የመጨረሻው እድል ፈንታው ይሆናል” የሚሉ ወገኖች ጥቂት አይደሉም።
ኢህአዴግ በመንታ መንገድ ላይ – የህጉ ተጽዕኖ ከፖለቲካና ኢኮኖሚ አንጻር
ውሳኔውን ከፖለቲካው እንደምታና ከኢኮኖሚው ጣጣ ጋር በማያያዝ አስተያየት የሰጡን እንደሚሉት ከሆነ ጉዳዩ አደጋ አለው። እንደሚታወቀው የኢህአዴግ አገዛዝ ከጠቅላላው የምዕራብ መንግስታት ከሶስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ዕርዳታ በየዓመቱ ያገኛል። ይህ ከፍተኛ መጠን ያለው ዕርዳታ ከአጠቃላይ አመታዊ በጀቱ 50% የሚሆነውን ይሸፍንለታል። ከአሜሪካን ብቻ አንድ ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ዶላር በየዓመቱ በዕርዳታ መልክ ያገኛል። ይህም ከአሜሪካ የሚገኘው ርዳታ ብቻውን የበጀቱን አንድ ሶስተኛውን ይሸፍንለታል።
በዚህ መነሻ የኮንግረሱ ውሳኔ በኢህአዴግ አገዛዝ ላይ ያልጠበቀው ዱብ ዕዳ እንደሆነ በጀርመን የልማት ኢኮኖሚክስ ባለሙያው (Development Economist) ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ ይናገራሉ። ይህ እሳቸው “ዱብዕዳ” ያሉት ውሳኔ የፖለቲካ ውዝግብ ማስነሳቱ የማይካድ ነው። ኢህአዴግ ከአውሮፓና ከአሜሪካ የሚያገኘውን ድጎማና ርዳታ ለምን ተግባር ሲያውለው እንደነበር ከማንም በላይ ጠንቅቆ ስለሚያውቀው ከቅድመ ሁኔታ ጋር የተያያዘ የዕርዳታ አሰጣጥ ከኢኮኖሚ ይልቅ የፖለቲካና የስነልቦናው ተፅዕኖው እንደሚያስከትልበት እኚሁ ምሁር ያስረዳሉ።
ከአጠቃላዩ የማክሮ ኢኮኖሚ አንጻር ውሳኔው ሊያስከትል የሚችለውን ተጽዕኖ በዝርዝር በማስቀመጥ አስቀድሞ መናገር ባይቻልም አሉታዊ ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል መገመት እንደማያዳግት ዶ/ር ፈቃዱ ከጎልጉል ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል። “ከአጭርና ከመካከለኛ ጊዜ አንፃር ስንመለከተው የአገዛዙን የኢኮኖሚ አካሄድ ጥያቄ ውስጥ ሊያስገባ ይችላል” ያሉት ባለሙያው፣ “… ወደፊት አዳዲስ የስራ መስክ መክፈት፣ በኢኮኖሚው ዕድገት፣ በውጭ ምንዛሪ ግኝትና በውጭ ሚዛን ዕድገት ላይ ሊኖረው የሚችለው ተፆዕኖም ቢሆን ይህ ነው ብሎ መናገር አይቻልም። ይሁንና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እርስ በርሱ የተያያዘ ስላልሆነና፣ አብዛኛው ህዝብም በኢንፎርማልና ከእጅ ወደ አፍ በሚገኝ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚተዳደርና የሚሳተፍ ስለሆነ ሊጎዳ የሚችለው በዘመናዊ መስክ የተሰማራውን ሰራተኛና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ነው” በማለት ቅድመ ግምታቸውን ያስቀምጣሉ።
ሲያብራሩም ከቅድመ-ሁኔታና ከጥብቅ ቁጥጥር ጋር የተያያዘ በዕድገት ስም የሚፈስ ዕርዳታ በአጠቃላይ ሲታይ በህዝቡ ኑሮ መዛነፍ ላይ የሚኖረው ተፅዕኖ ዝቅተኛ መሆኑንን የሚያመለክቱት ዶ/ር ፈቃዱ፣ ከ10-11በመቶ “ያለማቋረጥ” አደገ በሚባለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከኢትዮጵያ ህዝብ ኑሮ መሻሻል ጋር ተያያዥነት እንደሌለው ይናገራሉ። ቅድመ ሁኔታ የተቀመጠለት እርዳታ  ቢቀነስ ወይም እንዳለ ቢታገድ በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚያመጣው አሉታዊ ውጤት ምን ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ በቁርጥ ማስቀመጥ እንደሚያዳግትም ባለሙያው ይጠቁማሉ።  በዚህ ዓይነቱ የዕርዳታ አካሄድ እስካሁን የተጎዳው ህዝብ በመሆኑ የዕርዳታው መቀነስ ወይም መታገድ አገዛዙን እንጂ በዚያ አካባቢ የሚኖረውን ህዝብ በቀጥታ የሚመለከት አይሆንም። በህዝብ ኑሮ ላይ የሚከተለውን ማህበራዊ ኪሳራ ተምኖ ማስቀመት ቢችግርም “ወያኔ ቅድመ ሁኔታውን  ተግባራዊ የሚያደርግ ከሆነ በተለይም በቀጥታ በኗሪው ህዝብ ህይወት ላይ አዎንታዊ ውጤት ማሳየቱ ግን የማይቀር ነገር ነው” ሲሉ ግርድፍ ምልከታቸውን ያኖራሉ። በሴፍቲኔት፣ በአነስተኛና ጥቃቅን፣ ወዘተ የህዝቡን ኑሮ እየቀየርኩ ነው የሚለው “ልማታዊው” ኢህአዴግ እንዲህ ዓይነት በቅድመ ሁኔታ የተወጠረ ዕርዳታ በሕዝቡ ኑሮ ላይ ቀውስ ያመጣል በማለት የራሱን ቅንብር እንደሚሰራ የሚከራከሩም አሉ፡፡
ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ
ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ
ፖለቲካዊ ይዘቱን የዳሰሱት ዶ/ር ፈቃዱ ሁለት መሰረታዊ ጉዳዮችን በመጠቆም ለውይይት የሚጋብዝ ፍንጭ ሰጥተዋል። “ውሳኔ ሕጉ ያካተታቸው ቅድመ ሁኔታዎች ከረዥሙ አጠቃላዩ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታ አንፃር ስናየው ግን በዕውነቱ እንደዚህ ዓይነቱ ከቅድመ-ሁኔታ ጋር የተያያዘ ዕርዳታ ላይጎዳው ይችላል። አገዛዙ ከምዕራቡ አገራት የሚመጣበትን ግፊት የሚቋቋም መስሎት የሚታየው ከሆነ ፊቱን ወደ ቻይናና ወደ ሌሎች ቅድመ ሁኔታን ከማያሰቀድሙ አገሮች ዕርዳታ በማግኘት ከአሜሪካን የሚሰጠውን ዕርዳታ ሊያካክስና በነበረበት ሁኔታ ለመቀጠል መንፈራገጡ” አንደማይቀርም አመላክተዋል። ይህ ግምታቸው ግን ጥርጣሬያቸው እንዳለ ሆኖ ነው።
“ኢትዮጵያ ካለችበት የጂኦ ፖለቲካ፣ የአፍሪካ ህብረት ዕምብርትና መቀመጫም ስለሆነች ቻይናዎች ከራሳቸው የንግድ መርህ አንጻር ዕርዳታውን ከመስጠት ወደኋላ ሊሉ አይችሉም” ሲሉ የጉዳዩን ሌላ መልክ ያሳዩት ዶ/ር ፈቃዱ፣ አማራጩ ከአሜሪካንም ሆነ ከተቀረው የምዕራቡ ዓለም ጋር ተላትሞ ወደ ቻይና ፊትን በማዞር የሚደመደም ከሆነ አገዛዙ ዕድሜውን ለማሳጠር ራሱ እንደወሰነ የሚቆጠርበት ይሆናል። ኢህአዴግ አምርሮና የመጣው ይምጣ በሚል ቅድመ ሁኔታዎችን አላሟላም፣ ዕርዳታችሁንም አንፈልግም የሚል ከሆነ አሜሪካን አማራጭ ለመፈለግ ልትሞክርና ይህንንም እንደማስፈራሪያ ተጠቅማ ልትለሳለስ” እንደምትችል ዶ/ር ፈቃዱ አመላክተዋል።
እንደወያኔ የሚታዘዝላት ድርጅትና መሪ እስካላገኘ ድረስ ኢህአዴግ ላይ አደጋ እንዲነግስ ወይም ከነጭራሹ እንዲወገድ አሜሪካ ትሰራለች ብለው እንደማያምኑም ገልጸዋል። “እንዲያውም” አሉ ዶ/ር ፈቃዱ “በኮንግረሱ የፀደቀው ህግና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር (State Department) እንዲቆጣጠረው የተደረገው የዕርዳታ አሰጣጥ ዘዴ፣ የኦባማ አስተዳደር ሌላ መንገድ ፈልጎ ኮንግረሱን በማለፍ፣ በቀጥታ ከአሜሪካን የውጭ ዕርዳታ አሰጣጥ ጋር ባልተያያዘ መንገድ የኢህአዴግን አገዛዝ በተዘዋዋሪ ሊረዳበት የሚችልበት መንገድ እንደሚኖር መጠራጠር ይቻላል” ሲሉ ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ። ገደቡ በተለይም አገዛዙ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሰላም ጥበቃን፣ የፀረ-ሸበርተኝነትን፣ የድንበር ጥበቃንና እንዲሁም የመከላከያ አዛዡን ስታፍ ሰራተኞች ስለማይመለከት ተጽዕኖው በወታደሩ ላይ ዝቅ ያለ መሆኑንን አንደማሳያ ይጠቁማሉ።
ፍርድ ቤቶችን ከፖለቲካ ተፅዕኖ ቁጥጥር ስር ውጭ ማድረግ፣ የሚዲያ፣ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽና የመሰብስብ ነፃነት፣ እንዲሁም ሌሎች በቅድመ ዕርዳታው መስፈርት ሆነው የተዘረዘሩትን አንኳር ጉዳዮች ኢህአዴግ አጥብቆ የሚፈራቸውና ህልውናውን አደጋ ላይ የሚጥሉት በመሆናቸው በቀላሉ ለመቀበል የሚያዳግተው መስፈርቶች እንደሆኑ ለማንም ግልጽ ነው ሲሉ ዶ/ር ፈቃዱ ተናግረዋል። ይልቁኑም “እስካሁን ድረስ ለምን ዘገዩ? የሚመለከተው አካልም ሆነ የኦባማ አስተዳደር እስካሁን ድረስ ምን አስጠበቃቸው? አሁን ምን አዲስ ነገር ታያቸው? እስካሁን ድረስ የኢትዮጵያ ህዝብ ይሰቃይ ላይ አልነበረም ወይ? ለ22 ዓመታት የአገዛዙ የጭቆና ድርጊት ከአሜሪካ መንግስት የተሰወረ ጉዳይ ነበር ወይ? የሚሉት ጉዳዮች ሲነሱ የጸደቀውን ህግ ጉዳይ በጣም እንቆቅልሽ ያደርገዋል” በማለት ከጉዳዩ ጀርባ አንድ በጊዜ ሂደት እየጠራ የሚሄድ ጥቅል ጉዳይ ስለመኖሩ አመላካች እንደሆነ ምሁሩ ያስረዳሉ። በዚሁ መነሻ ፓለቲካዊ ትርጉሙ በቀላሉ ሊታለፍ የማይችልና ለአገዛዙ አስቸጋሪ ሁኔታ የሚፈጥርበት እንደሚሆን መገመቱ ከባድ እንዳልሆነ ይገልጻሉ።
“በሌላ ወገን ግን ለነፃነትና ለዲሞክራሲ ለሚደረገው ትግል አዎንታዊ ተፅዕኖ ያለውን ያህል፣ የራሱ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖም ሊኖረው ይችላል። ምናልባት አገዛዙ የተወሰኑ ነገሮችን የሚያሟላ ከሆነ ተቃዋሚው ኃይል ወደ መመቻመች /ኮምፕሮማይዝ/ ውስጥ በመግባት ለአጠቃላይ ነፃነት የሚደረገው ትግል አደጋ ውስጥ እንዲወድቅ ያደርገዋል። ይህ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ የነጻነትና የብልጽግና ጉዳይ የዓለም አቀፍ ኮሚኒቲው በሚፈልገው አካሄድ ብቻ የሚወሰን ይሆናል ማለት ነው” ሲሉ አጠቃላይ ስጋታቸው ያስቀመጡት ዶ/ር ፈቃዱ፣ አጠቃላይ ህዝቡን የሚጠቅም የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የሀብት ክፍፍል፣ በተለይም የመሬት ጥያቄ፣ እስከዛሬ ድረስ የተፈጠረው አዲስ የይዞታና የህብረተሰብ ግኑኝነት፣ የኢትዮጵያ ህዝብና ዲሞክራቶች በሚፈልጉት መንገድ ላይፈቱ በሚችሉበት ሁኔታ መሰናክል ይደርስበታል። ስለዚህ ይህ ዓይነቱ ውሳኔ ህግ የዛሬው አገዛዝ ወደፊት በስልጣን ዙሪያ ሊኖረው የሚችለው ተሳትፎ፣ የኃይል አሰላለፍ ጉዳይና የፓለቲካው አወቃቀርና አካሄድ ጉዳይ ላይ፣ የኢኮኖሚያዊና የህብረትሰብ ግኑኝነት፣ ማለትም የሀብት ክፍፍልና አዲስ ሀብት በአዲስ የኢኮኖሚ ፖሊሲ መሳሪያ የመፍጠር ጉዳይ፣ የማህበራዊ ጥያቄ ጉዳይ፣ እነዚህና ሌሎች ለአገሪቱ የወደፊት እንደህብረተሰብ መኖርና መገንባት አንፃር በሰፊው ካልታየና ተቃዋሚ በሚባለው ጭንቅላት ውስጥ ካልተብላላ አደጋም ሊኖረው ይችላል።
በሌላ አነጋገር የዕድገታችንን ጉዞ ሊያጣምመው ይችላል። ምክንያቱም ይህ ዓይነቱ ውሳኔ ህግ እስከተወሰነ ደረጃ ድረስ ቢሟላና አገዛዙም እንደፖለቲካ ኃይል ተፎካካሪ ሆኖ የሚቆይ ከሆነ ወደፊት ለሚወሰዱ አገርን የሚጠቅሙ የዕድገት ዕርምጃዎች መሰናክል እንደሚሆን መጠርጠር ይቻላል። በሌላ አነጋገር የኢትዮጵያ ህዝብ ከዚህ አገዛዝ ባሻገር ሊገነባው የሚችለው አዲስ ኢትዮጵያ የብዙ ዓመታት ህልም ሆኖ ሊቀር እንደሚችል የራሳቸውን አማራጭ ምልከታ አስቀምጠዋል። ሌላኛውንም መንገድ አካተዋል።
በሌላው በኩል ደግሞ ይህ ውሳኔ ህግ በገዢው መደብ ውስጥ ቅራኔን መፍጠሩ እንደማይቀር፣ ህይወታቸውን ከአሜሪካን መንግስት ጋር ያያዙ ኃይሎች፣ በተለይም ግፊቱ እየበዛ ሲሄድ ወደፊት የሚመጣባቸውን አደጋ በማጤን ውሳኔ ህጉን በከፊልም ሆነ መሉ በሙሉ ተግባራዊ እናድርግ በሚሉ (ዘመናዊ ወያኔዎች) እና ውሳኔ ህጉን አንቀበልም በሚሉ አክራሪ ኃይሎች መሀከል ፍጥጫ መፈጠሩ እንደማይቀር ዶ/ር ፈቃዱ ግምገማቸውን አኑረዋል።
ቀጥሎስ?
በጉዳዩ ዙሪያ ከጎልጉል ጋር ወደፊት ሰፊ ቃለ ምልልስ ለመስጠት ፈቃዳቸውን የገለጹት አቶ ኦባንግ “እዚህ የተደረሰው በወፍ ዘራሽ ዝም ተብሎ አይደለም፤ ብዙ ተለፍቶ ነው። የአውሮፓ አገራት ተመሳሳይ ጥያቄ ሲቀርብላቸው አሜሪካን ምክንያት ሲያደርጉ ነበር። አሁን ሊያቀርቡ የሚችሉት አንዳችም ምክንያት የለም። አጠናክረን ስራችንን እንሰራለን። ሰክነን እንታገላለን። ኢህአዴግ ሳይወድ በግዱ በሩን ይከፍታል” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ከአውሮፓ አገራት ጋር አጋሮቻቸው በመሆን ስራቸውን በአዲስ መልክ እያጠናከሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል። ይህንን አዲስ ህገ ውሳኔ በማስረጃነትና በማቅረብ የአውሮፓ መንግሥታም ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ፤ በሚሰጡት ዕርዳታም ሆነ ድጎማ ላይ ኢህአዴግን ተጠያቂ በማድረግ የፖለቲካ ምህዳሩ እንዲሰፋ መርዳት ባይችሉም እንኳን ኢትዮጵያውያን ለሚያደርጉት ትግል እንቅፋት እንዳይሆኑ አበክረን እንወተውታለን ብለዋል አቶ ኦባንግ፡፡
አዲስ ስለ ጸደቀው ውሳኔ ህግ ለተጠየቁት “ብዙ ለመናገር ጊዜው ገና ነው። ኢትዮጵያዊያን በጎሳና በዘር የደም አዙሪት ውስጥ እየፈሩ እንዲኖሩ ሲደረግ የነበረው ድጋፍ ግን ማክተሚያው የተቃረበ ይመስለኛል፤ ኢህአዴግ እኔ ሥልጣን ከለቀቅሁኝ በአገሪቷ ውስጥ ደም መፋሰስ ይሆናል፤ ኢንተርሃምዌ የዘር ዕልቂት ይካሄዳል፤ የአፍሪካ ቀንድም ቀውስ ውስጥ ይገባል፣ ወዘተ በማለት እየዘላበደ የተቃዋሚውን ኃይል ከማዳከም አልፎ ሕዝቡ ፍራቻ ውስጥ በማስገባት አሜን ብሎ እንዲኖር የተጠቀመበት ማደንዘዣ ኃይሉ እየደከመ መጥቷል፤ ይኽኛው የውጭው ነው” የሚል ጥቅል መልስ ሰጥተዋል።
የመንታው መንገድ መሃንዲስ – ቻይና?
ቻይና ከኢህአዴግ በተለይም ከህወሃት ከፍተኛ ሰዎች ጋር አላት ከሚባለው “የተለወሰ ሽርክና” አንጻር አሜሪካ የምትሰጠውን የበጀት ድጎማና ርዳታ በየዓመቱ እየሸፈነች ኢህአዴግን ትታደጋለች የሚለው ጉዳይ ቻይና ከምትከተለው መሰረታዊ የንግድ እምነትና አንጻር በዜሮ የሚባዛ እንደሆነ ይነገራል። ቻይና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ነዳጅና ማዕድን እየተከተለች የምትገባበት ኢንቨስትመንት እያከሰራት እንደሆነ የሚናገሩ ክፍሎች ቻይና የሃይል ሚዛኑን ተመልክታ ርምጃዋን ከማስተካከል ያለፈ ስራ እንደማትሰራ ይናገራሉ።
china_africa_usበሌላ በኩል ደግሞ ሰሞኑን ይፋ ሆኖ የሰነበተውና የቻይናን “የዓይን ቀለም” የቀየረው የጃፓኑ ጠ/ሚ/ር የኢትዮጵያ ጉብኝትና የፖለቲካ መሞዳሞድ በቻይናና በኢህአዴግ መካከል የግንኙነት መሻከር እንደሚፈጥር የፖለቲካ እሳቤ አለ፡፡ ኢህአዴግ ከቻይና ታሪካዊ ጠላት ጃፓን ጋር በግልጽ ይህንን ዓይነቱን “ያደባባይ ፍቅር” ማሳየቱና የፖለቲካ ቅርጫ ውስጥ መግባቱ የምዕራቡ ወዳጅ ከሆነችው ጃፓን ጋር በመወገን በምዕራባውያን የድጎማ ዕቀባ ጭስ እንዳይታፈን መተንፈሻ እየፈለገ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
ሰጥቶ በመቀበል፣ አበድሮ በመውሰድና የአምባገነኖችን ህልውና ለማስጠበቅ የሚውል ቴክኖሎጂን በመገንባት አፍሪካን እያለበች ያለችው ቻይና ኢህአዴግ ከምዕራባውያን የሚያኘው እርዳታ ቢቋረጥበት ከብድር በዘለለ በየዓመቱ ሌሎቹ እንደሚያደርጉት በጀት እየደጎመች የኢህአዴግን  ነፍስ ለመጠበቅ የምትምልበት ዘመን ሊኖር እንደማይችል ከግምት በላይ የሚናገሩ ክፍሎች፣ ኢህአዴግ መለሳለስ በመሳየት ቆዳውን ሊቀይር ይችላል የሚለው እምነት አላቸው። አሜሪካ አሁን የያዘችው አቋም ከምትከተለው አዲሱ ፖሊሲዋና በሂደት የኢትዮጵያ ጉዳይ ተመርምሮ የተያዘ ስለሆነ እንደ HR2003 በውስዋስ (ሎቢ) ሊቀለበስ የሚችል እንዳልሆነ አጥብቀው ይናገራሉ።
ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር መጀመሪያ ላይ ለጎልጉል አስተያየት የሰጡ ዲፕሎማት ጠቅሰን ገመዱ በኢህአዴግ ላይ እየከረረ እንደሚሄድ በዘገብን ወቅት “ኢህአዴግ በቅርቡ የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች እስር ቤቶችን እንዳይጎበኙ እንደከለከለው ማድረግ አይችልም … በደቡብ ሱዳን ያለው የፖለቲካ ቀውስ፣ በሶማሊያ ጭብጡ ያለየለት ሁከት፣ በኤርትራ ያለው የዛለ መንግስት እጣፈንታና የኢትዮጵያን ህዝብ በዘር ከፋፍሎ ጥቂቶች እንዲበለጽጉ ያደረገው ኢህአዴግ መጨረሻው አሜሪካንን በእጅጉ ሃሳብ ላይ ጥሏታል። በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያ ውስጥ እየሰፋ የሄደው ቁርሾና የጥላቻ ፖለቲካ ሳይፈነዳ ኢህአዴግን ማረቅ የአሜሪካ ቀዳሚ አጀንዳ ሆኗል። ይህንን አጀንዳ አሜሪካ በቀላሉ ተጭበርብራ የምትቆልፈው አይሆንም። ኢህአዴግ በጎሳ ደምና እኔ ከሌለሁ አገርና አፍሪካ ቀንድ ይተራመሳል በሚል የሚነግደውን ንግድ አሜሪካኖቹ ተረድተዋል ብለን ነበር፡፡ የአሜሪካው ምክርቤት እንደራ የሆኑት ክሪስ ስሚዝ “በሽብር ዙሪያ ከአሜሪካ ጋር ተባብሮ መስራት ህዝብን ለማፈንና ረግጦ ለመግዛት ዋስትና አይደለም” በማለት መናገራቸውን ከዲፕሎማቱ አስተያየት ጋር አክለን ነበር፡፡
አዲስ የወጣውን ውሳኔ ህግ አሜሪካ በኢህአዴግ ላይ ፊቷን እያዞረች መሆኗን ማሳያ ነው በማለት የሚወስዱ ክፍሎች ይህ ህግ ከቀድሞው HR2003 ፈጽሞ የተለየ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ የዛሬ አስር ዓመት፤ HR2003 በምክር ቤት ደረጃ የእንደራሴዎችን ከፍተኛ ድጋፍ ካገኘ በኋላ የሕግ መወሰኛ ም/ቤት (ሴኔት) አጽድቆት በፕሬዚዳንቱ ተፈርሞ የአሜሪካ ፖሊሲ እንዳይሆን በመደረጉ ተቋማዊና አስተዳደራዊ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ጉዳዮች መከኑ። በወቅቱ የህጉ መርቀቅና እንዲጸድቅ የተጀመረው እንቅስቃሴ ያስበረገገው ኢህአዴግ ጡረተኛ የሴኔት አባላት ከሚመሩት ዲኤልኤ ፓይፐር ከተባለ የውስዋስ (ሎቢ) ቡድን ጋር ከፍተኛ በጀት በጅቶ ታገለ። ባፈሰሰላቸው መጠን ወትዋቾቹ ባልደረቦቻቸውን ጠመዘዙና ህጉ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምትከተለው አዲስ የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ህግ እንዳይሆን ተደረገ።
አሁን አዲስ የወጣው ህገ ውሳኔ ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡ ምንም ዓይነት በገንዘብ ለኢትዮጵያ ፖሊስና የጦር ኃይል ከመለቀቁ በፊት የኢህአዴግ ሸሪክ የሆነውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር መስሪያቤት ገንዘቡን ለሚፈቅደው የምክርቤት አከፋፋይ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ውስጥ የህግ አካላት በነጻነት የሚሰሩ መሆናቸውን፣ የመናገር፣ የመሰብሰብ፣ የሃይማኖት ነጻነት መኖሩን፣ የተቀናቃኝ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማኅበራትና ጋዜጠኞች ያለ ወከባና አፈና ሊሰሩ መቻላቸውን ማረጋገጫ መስጠት አለበት፡፡ በሌላ በኩልም በሶማሊ ክልል የሰብዓዊ መብትና ግብረሰናይ ድርጅቶች በነጻነት መንቀሳቀስ መቻላቸውን፣ ለወታደርና ለፖሊስ ኃይላት ስልጠና የሚሰጠው ገንዘብ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ ለሚገኙ ክፍሎች እንዳይደርስ የሚያረጋግጥ ሰነድ፣ እነዚህን መብቶች በጣሱ የሠራዊቱና የፖሊስ አባላት ላይ ምርመራ በማድረግ ደረጃ የኢትዮጵያ መንግሥት የወሰዳቸውን እርምጃዎች ምን እንደሆኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል፡፡
ከዚህም ሌላ “የልማት ዕርዳታ” እና “የኢኮኖሚ ድጋፍ ፈንድ” በሚል ለታችኛው ኦሞ ሸለቆና በጋምቤላ ለሚኖሩ የሚሰጠው ዕርዳታ በምንም ዓይነት መልኩ ነዋሪዎቹን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ አስገድዶ በማፈናቀል ተግባር ላይ እንዳይውል፤ የነዋሪዎቹ ህይወት በሚያሻሽል ሥራ ላይ ብቻ የሚውል መሆኑ እና ከነዋሪዎቹ ጋር በምክክር የሚደረግ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር መ/ቤት ማቅረብ አለበት፡፡ መ/ቤቱ ይህንን ሳያረጋግጥ ገንዘብ መውሰድ አይችልም፡፡ ኢህአዴግን ለመደገፍ በሚል የተዛባ መረጃ በማቅረብ ገንዘቡን ወስዶ ለኢህአዴግ እንዲደርስ ቢያደርግ እንኳን የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች የኢትዮጵያን ሁኔታ አስመልክቶ የሚያወጡት ዘገባ ዕውነቱን ቁልጭ አድርጎ የሚያጋልጥበት ይሆናል፡፡ ከውጭ ጉዳይ ሚ/ር በተጨማሪ የገንዘብ ሚ/ር መ/ቤት (Department of Treasury) በኢትዮጵያ ውስጥ አስገድዶ ከመኖሪያ ቦታ ከማፈናቀል ጋር በተያያዘ ለሚደረግ እንቅስቃሴ ምንም ዓይነት ዕርዳታ እንዳይሰጥ ለዓለምአቀፉ የፋይናንስ ተቋም ዋና ዳይሬክተር መመሪያ እንዲሰጥ ታዟል፡፡
ይህንን እና የመሳሰሉ የትም የማያፈናፍኑ መመሪያዎች ያካተተው ውሳኔ ህግ የራሱ የሆኑ ተጽዕኖዎች ያመጣል እየተባለ በሚጠበቅበት ሁኔታ ለሚከሰት ማናቸውም ዓይነት ክፍተት ቻይና ከኢኮኖሚ ጥቅሟ አኳያ ለኢህአዴግ መድህን ሆና ልትቀርብ የምትችልበት ሁኔታ በብዙዎች አንድ አመኔታ የሚጣልበት አይደለም፡፡ በውጭ ምንዛሪ እጥረት ውስጥ ያለው ኢህአዴግ ከመጪው ምርጫ አኳያ እንዲህ ዓይነት በቅድመ ሁኔታዎች የታጠረ ህገ ውሳኔ አክብሮ ይቀበል ይሆን? ወይስ ፊቱን በአሜሪካ ላይ በማዞር በእብሪት ቻይናን ታደጊኝ ይላታል? መንታው መንገድ በዚህ የሚያቆም አይመስልም – የራሱን መንታ መንገዶች እየከፈተ ይሄዳል የሚሉ ፍንጮችም እየታዩ ነው፡፡
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ 

የጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ መልዕክት ከዝዋይ ማረሚያ ቤት፡ ሰው ለሆኑ ሰዎች በሙሉ!

February 12/2014

በጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፤ ከዝዋይ ማረሚያ ቤት



‹‹ይህንን ስለመሳሰሉ ጉዳዮች መወያየት ክልክል ነው፡፡›› በማለት በተንጎላጀጀ ድምፅ ጠባቂው ተናገረ፡፡ ቀጠል አደረገናም ‹‹መነጋገር የምትችሉት ስለቤተሰብ ጉዳዮች ብቻ ነው›› በማለት ተናገረ፡፡ ይህን ከላይ ያለውን ሐሳብ የሚመለከት ማንኛውም አንባቢ፣ ጉዳይ የተፈፀመው እዚህችው እማማ ኢትዮጵያ ሰማይ ስር ባሉ አጃኢበኛ እስር ቤቶች፣ ቤተሰብ መጠየቂያው እንደሆነ መጣራቱ አይቀርም፡፡

ይሁንና በመግቢያው ላይ ያለው ጽሑፍ ተቀንጭቦ የተወሰደ ‹እናት› ከተሰኘውና እ.ኤ.አ. በ1906 ከታተመው የስመ ጥሩው ሩስያዊ ደራሲ ማክሲም ጎርኪይ ታሪካዊ ልቦለድ ገፅ 102 ላይ ነው፡፡ የዛሬ 108 ዓመት አካባቢ ማለት ነው፡፡ አቤት ርቀቱ!… ይህ ርቀት ግን ለእኛ ምንም ማለት ያልሆነ ይመስላል፤ ለምን? ቢሉ ዛሬም ይህንንና ይህን የመሳሰለውን አስፍተን እየሠራን እንገኛለን፡፡ እንዲያውም በአንዳንድ ሁኔታዎች እየተጓዝን ያለነው የቁልቁለት ሩጫ በእጅጉ አሳሳቢ ሆኖ ይገኛል፡፡

የነገሮች ሁሉ መድረሻ እስር ቤቶች እየሆኑ መጥተዋል፡፡ ‹ጠበቅ ያለ እርምጃ፣ የማያዳግም እርምጃ፣ የማስወገድ እርምጃ፣…› ወዘተ የሞሉ ከሕግ መርሕዎች ሳይሆን ከጥላቻ ፖለቲካ የሚመነጩ ፀያፍ አነጋገሮችን በሕዝብ የመገናኛ ዘዴዎች ሲተላለፉ እየሰማን እየታዘብን ነው፡፡ ቃል በቃል ‹ቀይ ሽብር ይፋፋም› ብሎ ማወጅ የቀራቸው የሕግም የግብረገብም ሚዛን ያልወጣላቸው ቀረርቶች በተለይ በእስር ቤት የምንገኝ ኢትዮጵያውያንን እየሰበሰቡን ይገኛሉ፡፡

በኢ.ቴ.ቪ. የአብዮታዊ እርምጃ ፕሮግራሞች በቀረቡ ማግስት አሁን በዝርዝር ብለው የብዙ ቤተሰቦችን ስሜት ሊያሸማቅቁ የሚችሉ ሰቆቃና እንግልቶች በአስደማሚ ስልት ተቀናብረው ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡ እስኪ የተወሰኑትን እንይ፡፡ ማንኛውም ታሳሪ ቤተሰብ በቅርብ ሊጎበኘው በሚችለው እስር ቤት ይታሰር የሚለው ሕግ የተሻረው በእኛ ላይ ነው፡፡ ዝዋይ የአገራችን ‹ሳይቤሪያ ግዞት› ማለት ናት፡፡ ቤተሰብ ያን ያህል የበርሃ ጉዞ አቋርጦ የእኛዋ ሳይቤሪያ ሲደርስ በአድካሚና ግብረ-ገብ በጎደለው ፍተሻ መከራውን ማየቱ አንሶ ጆሮ ግንዱ ላይ በቆሙ የቤተሰብ አገናኞች ቤተሰባዊ ገመናውን አሳልፎ ይሰጣል፡፡ ሕፃናት ልጆች ወላጆቻቸው አንድ ላይ ሆነው ናፍቆታቸውን መወጣት አይችሉም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ፖሊሶቹ ሲዘናጉልን ልጆቻችንን አቅፈን እንስማለን፡፡ ይህ ከሆነ ቁጣና ዘለፋው ምንም አይደለም፡፡ ግን በሁኔታው ሕፃናቱ ክፉኛ ይበረግጋሉ፣ የእኛ ስጋት ይጋባባቸዋል፤ በዚህም መንፈሳቸው እርብሽብሽ ብሎ ወደቤታቸው ይመለሳሉ፡፡

ሁኔታው በዚህ አያበቃም፡፡ ምንም እንኳን የመጠየቂያ ሰዓቱ በግልፅ የተቀመጠ ቢሆን ከቤተሰቦቻችን ጋር ገና መነጋገር ስንጀምር ‹‹በቃ… ቶሎ ጨርሱ›› የሚባልባቸው ጊዜዎች ብዙ ናቸው፡፡ ቀጥሎ የሚመጣው የእስር ቤት ማኅበራዊ ጉዳዮችን ማለትም ለሳሙና፣ ለምግብ ማጣፈጫ፣ ለሻይ ለቡና፣ ለውስጥ አልባሳት፣ ለውኃ ማከሚያ/ውኃ አጋር/ ወዘተ፤ ገንዘብ የሚያስፈልገን ቢሆንም እና እንደሚያስፈልጉ ቢታወቅም ጉዳዩ ለይቶለት የማሰቃየት፣ ማንገላታት፣ መበቀል ሆኗልና ለአንድ ወር ከአንድ መቶ ብር በላይ መጠቀም እንዳንችል የተከለከልን የመሆኑ አሳፋሪ ሐቅ ነው፡፡ ይህ እየተፈፀመ ያለው ደግሞ ዝዋይ እስር ቤት ውስጥ ብቻ ነው፡፡ በዚህ የተነሳም ለመግለጽ በሚከብድ ሁኔታ ሰብኣዊ ክብራችንን የማዋረድ ሙከራዎች እየተፈፀሙ ነው፡፡

በአገራችን ላይ እኔ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን የጨረስኩት ዝዋይ በመሆኑ ብዙ ወዳጅ ዘመዶቼ በእዚህ ይገኛሉ፡፡ ሆኖም ለአካባቢው ነዋሪዎች በሳምንት እንዲጠይቁን የተፈቀደላቸው አንድ ቀን /ረቡዕ/ ብቻ ሲሆን ‹‹የት ነው የምታውቁት? እንዴት አወቃችሁት? ምንድን ነው የሚያመላልሳችሁ?›› በሚሉትና በሌሎችም ጥያቄዎች ተደናግጠው መምጣቱን እርግፍ አድርገው ትተውታል፡፡

ሀገሩ ሞቃታማ ነውና በዚያ ላይ በእያንዳንዱ ቤት እስከ 150 ሰው ይታሰርበታል፡፡ ይህ ሁሉ ተደማምሮ እስረኛው የቱንም ያህል ፅዳቱን ለመጠበቅ ቢሞክርም የተባዩ መርመስመስ የእነ ትኋን እንዲህ መራባት፤ ለማሰብ እንኳን ይዘገንናል፡፡ ሌሊቱን ሙሉ ገላን ሲቆፍሩ ማደር ነው፡፡ ሊናገሩት ይከብዳል፣ አንባቢንም ቅር ያሰኛል፤ ግን ይህ የፊልም ትረካ ሳይሆን በእማማ ኢትዮጵያ ልጆች ላይ ሆን ተብሎ እየተፈፀመ ያለ ደባ ነው፡፡ […] ግን የባሰ አታምጣ ማለት ነው!

ግን የባሰ ነገር አለ፡፡ አፈር ቅጠል የማይል ምግብ ይቀርብናል፡፡ ‹በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ› ከፍተኛ የውኃ እጥረት /ዝዋይ ሀይቅ አናት ላይ ተቀምጠን/ አለ፡፡ የእስር እስር እንዲሉ ጄኔራል መኮንኖቹን ጨምሮ አብዛኛዎቹ አባሪዎቻቸውና ሌሎች ሌሎች የተወሰንን እስረኞች የምንገኘው በልዩ ቅጣት ጭለማ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ይህንን ሁሉ እንደምንም ለመቋቋም ጥረት ማድረግ ይቻል ይሆናል፡፡ አዲሱ ስልት ግን መዘዙ በጣም አደገኛ በመሆኑ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ፣ እያንዳንዱ ሃይማኖት ያለው፣ ፈርሐ እግዚአብሔር ያለው፣ እያንዳንዱ የመሠረታዊ ሰብኣዊ መብቶችና ነጻነቶች መከበር የሚያሳስበው እያንዳንዱ ሰው የሆነ ሰው ሁሉ ሊያውቀው ይገባል ስንል ድምፃችንን እናሰማለን፤ በሕክምና ንፍገት ወደሞት እየተገፋን ነው፡፡

ከወር በፊት ገደማ ወጣቱ የአንድነት ፓርቲ አባል ናትናኤል መኮንን ለሕክምና በሪፈር ወደ ቃሊቲ ተልኮ የነበረ ቢሆንም፣ የዛኑ ዕለት ሕክምናውን ተነፍጎ ከሌሊቱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ እንዲመለስ ተደርጓል፡፡ እስካሁን በሕመሙ እየተሰቃየ ይገኛል፡፡ የኢብአፓ ሊቀመንበር የነበረው ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር እንደዚሁ ለተጨማሪ ሕክምና ሪፈር ተብሎ ሲጠባበቅ ከቆየ በኋላ ዘዴው ተፈፃሚ ሆነበት እጁን አጣጥፎ ተቀምጧል፡፡ ከሕመሙ ጋር በተያያዘ በአካሉ ላይ አሳሳቢ ሁኔታ እየታየበት ይገኛል፡፡ ከዚህ ቀደም ገልጬው የነበረው የእኔ የኩላሊት ሕመም አሁን ለመቀመጥም፣ ለመንቀሳቀስ እያወከኝ የሚገኝ ሲሆን፣ እኔን ከቃሊቲ ዝዋይ ለማምጣት የተደረገው የተቀናጀ መረብ ሩብ ያህሉን ለሰብኣዊነት አውለውት ቢሆን ኖሮ እኔም ፋታ፣ እነሱም እርካታ ባገኙ ነበር፡፡ ሕመም ካልታከመ መጨረሻው ሞት ነው፡፡ የሞቱም ሰዎች አሉ!

የጄኔራል መኮንኖቹ አባሪዎች የነበሩት ኮረኔል ተስፋዬ ኃይሉ እና ኢንጂነር ክፍሌ ስንሻው፣ በዶክተር መረራ በሚመራው ኦሕኮ ፓርቲ አባል የነበሩት አሕመድ ነጃሺ፣ በጭለማ ቤት የከረመው ተስፋሀን ጨመዳ፣ የቤንሻንጉሉ አዛውንት ወዘተ ተገቢውን ሕክምና በማጣት ሕይወታቸውን ያጡ የእማማ ኢትዮጵያ ልጆች ናቸው፡፡ እንዴት ሕክምና ይከለከላል!? ግፍና ጭቆና ተቃውመው ደማቸውን ያፈሰሱና አጥንታቸውን የከሰከሱ ታጋዮችን በሥልጣን ማግስት ከፍርድ በመለስ በየእስር ቤቱ ያሉ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻቸው በሕክምና እጦት ሲረግፉ በእርካታ ማርመምን ከየት ተማሩት!? የኢትዮጵያ ሕዝብስ ምን ይላል!? ሰው የሆኑ ሰዎች ሁሉ ከቶ ምን ይላሉ!?

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

(ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚታተመው ኢትዮ-ምኅዳር ጋዜጣ የተወሰደ)

PM Hailemariam Desalegn Press Conference with Journalist on Current Issues

የአ.አ ፍትህ ቢሮ የሙስሊሙን ትግል አዳክመውልኛል ያላቸውን የመንግስት ሃላፊዎችን እና የህገ ወጡ መጅሊስ አባላትን በሽልማት አንበሸበሸ

February11/2014



ከአብዱ ዳውድ ኡስማን
መንግስት በኢስላም ሀይማኖት ላይ ጠልቃ እንደገባ የህወሃት መስራች አቦይ ስብሃት ለመጀመሪያ ጊዜ አምነዋል ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ አማካኝነት የተዘጋጀው ይሄው የሽልማት ስነስርዐት ዋነኛ አላማው የሙስሊሙ ትግልን ለማዳከም ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል ያላቸውን የመንግስት አካላትና የህገ ወጡ መጅሊስ አባላትን ለማነቃቃት እንደሆነ ታውቋል ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በቀጣይ ከምርጫ ቅስቀሳ ጋር ተያይዞ ለሚኖረው እንቅስቃሴ አባላቱ በሞራል እንዲሰሩ ለማድረግ ታስቦ እንደሆነ በስብሰባው የነበሩ ምንጮች ገልፀዋል ፡፡
ከትላት በስቲያ እሁድ የካቲት 2\2006 ከጠዋቱ 3፡30 ጀምሮ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የስብሰባ ማእከል በተካሄደው በዚህ የሽልማት ስነስርዐት ላይ የህወሃት አባት የሚባሉት አቦይ ስብሃትን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ሃላፊ አቶ ፀጋዬ ሀይለማሪያም ፣ የህገ ወጡ መጅሊስ ፕሬዚደንት ዶክተር አህመድ አብዱረህማን ፣ የፌዴራሉ ህገ ወጥ መጅሊስ ምክትል ፕሬዚደንት ታጋይ(ሸይክ ከድር ) ፣ የአንዋር መስጂድ ኢማም ሀጂ ጡሃ ሃሩን ፣ የ10 ሩም ክፍለ ከተማ ሃላፊዎች ፣ የወረዳና የክፍለ ከተሞች መጅሊስ አመራሮች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ፡፡

ከሽልማቱ ቀደም ብሎ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ መስተዳድሩ የ42 መስጂዶችን ካርታ ለአዲስ አበባ ህገ ወጡ መጅሊስ ፕሬዚደንት ዶክተር አህመድ እንዳስረከቡ ገልፀዋል ፡፡ በቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫም የመጅሊሱ አባላትም ሆኑ ሌሎች አካላት ከዚህ ቀደም ወደ 54 መስጂዶች ካርታ እንደሰጠን በዛሬው እለት ደግሞ የ42 መስጂዶችን ካርታ እንደሰጠን ለሙስሊሙ በማስተጋባት የምርጫ ስራ እንዲሰራ ጠይቀዋል ፡፡
በእለቱ የሙስሊሙን ትግልና ኢስላምን አዳክመዋል የተባሉ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ፣ እንዲሁም የህገ ወጡ መጅሊስ አባላት ከአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን ተሸላሚዎቹ በየተራ ንግግር አድርገዋል ፡፡ የሙስሊሙን እንቅስቃሴ በጥረታቸው እንዲገታ አድርገዋል ተብለው ሽልማቱ ከተበረከተላቸው መካከል አቦይ ስብሃት ነጋ ፣ ዶክተር አህመድ አብዱረህማን ፣ ሸህ ጡሃ ሃሩን ፣ የ10ሩም ክፍለ ከተማ ህግና ፍትህ ቢሮ ሃላፊዎች እና የ10ሩም ክፍለ ከተሞች የመጅሊስ ሊቀመንበሮች እንደሆነ ታውቋል ፡፡

ከሽልማቱ በኋላ ንግግር ያደረጉት አቦይ ስብሃት መንግስት በሙስሊሙ ጉዳይ ጠልቃ እንደገባ የሚያረጋግጠውን ንግግራቸውን አድርገዋል ፡፡ አቦይ ስብሃት በአዳራሹ ለተገኘው ሰው ባደረጉት ንግግር “ … ማንኛውም ነገር ከፍተኛ ጥረት ከተደረገበት ስኬት ይኖረዋል ፡፡ የሙስሊሙ ትግል ሲጀመር በጣም ተደናግሮን ነበር ፡፡ በኋላ ብዙ አስበንበት ስናበቃ ለምን መንግስትን የሚደግፍ መጅሊስ አናቋቁምም አልንና ጥረት ጀመርን ፡፡ እኔ እራሴ ሄጄ ግዴላችሁም ከየክፍለ ከተማው ሙስሊም ሆነው መንግስትን የሚደግፉ ሁለት ወይም ሶስት ሰዎችን ብቻ ፈልጉልኝ አልኩ …፡፡

የጀመርነው ከቦሌ ክፍለ ከተማ ነው ፡፡ ወደ አምስት ሰዎችን አገኘንና እነሱን አደራጀን ፡፡ በኋላ ሌሎችም ክፍለ ከተሞች የቦሌን ተሞክሮ እንዲተገብሩ አደረግን ፡፡ ሁሉም ክፍለ ከተሞች ጥቂት ሙስሊሞችን አደራጁ ፡፡ ከዚህ በኋላ ነገሩ ሁሉ የተቃና ሆነ ፡፡ እኛም በሁሉም ክፍለ ከተሞች በተወሰኑ ሰዎች መደራጀቱን ስናውቅ ጉዳዩን የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮና ክፍለ ከተሞች እንዲረከቡንና በበላይነት እንዲቆጣጠሩት አደረግን ፡፡ እንዲህ እያለ የሄደው ጥረት አሁን አክራሪዎችን ለማቆም የሚያስችል ጉልበት እንድናገኝ ረድቶናል … ” ብለዋል ፡፡


(የአዲስ አበባ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ)   
ይህ የአቶ ስብሃት ነጋ ንግግር መንግስት በሙስሊሙ ጉዳይ ጠልቃ አልገባሁም እያለ ከሚያስተባብለው ጋር የሚጋጭ እንደሆነ ተገልፇል ፡፡ በበርካታ ጉዳዮች ንግግር ያደረጉት አቦይ ስብሃት ኢስላምን የሚያጥላላ ንግግርም አድርገዋል ፡፡ “ ቅድም የፌዴራሉ መጅሊስ ምክትል ሰብሳቢው ሸህ ከድር እንዳለው የዱሮው እስልምና ሌላ ነው ፡፡ እኔ ከድርን በፊት ጀምሮ ትግራይ ውስጥ አውቀዋለሁ ፡፡ ምርጥ የህወሃት ታጋይ ነበር ፡፡ አብሮን ታግሏል ፡፡ አሁን ደግሞ ሙስሊሙን እያገለገለ ነው ፡፡ እስልምና እነዚህ የታሰሩት ሰዎች እንደሚሉት አይመስለኝም ፡፡ እስልምና እነዚህ ሰዎች እንደሚያሳዩት ዓይነት ዕምነት ከሆነ እንደ ዕምነት አያስፈልግም ፡፡ ፈፅሞ ሰዎቹ ለሀገር አይሆኑም ” ብለዋል ፡፡ በዚህ ንግግራቸው በቦታው የነበሩ ሙስሊሞችም ጭብጨባ ለግሰዋቸዋል ፡፡

የፌዴራሉ ህገ ወጥ መጅሊስ ምክትል ፕሬዚደንት የሆኑት ሸህ ከድርም በጫካ ከነ አቦይ ስብሃት ጋር ስላሳለፉት የትግል ህይወት እና በልጅነታቸው ስለቀሩት ቁርዐን አጠር ያለ ንግግር አድርገዋል ፡፡


ሌላኛው ተሸላሚ የሆነው የአዲስ አበባ ህገ ወጡ መጅሊስ ፕሬዚደንት ዶክተር አህመድ ሲናገርም “ መስጂዶቻችንን ሁሉ ተረክበናል ፡፡ መስጂዶች የማይሆን ዳዕዋ ማድረጊና የተቃውሞ መፈንጫ እንዳይሆኑ የሁሉም መስጂዶች ኢማም እንዲቆጣጠሩ ስልጠና ሰጥተናቸዋል ፡፡ አቶ ድሪባ ኩማም ዛሬ ለ42 መስጂድ ካርታዎን እውቅና እንደሰጡልን አረጋግጠዋል ፡፡ ከዚህ በኋላ ልማታችንን ማፋጠን ነው ፡፡ በቀጣይ ከመንግስታችን ጎን ሆነን እንሰራለን ” ብለዋል ፡፡

ለአቦይ ስብሃት ነጋ እና ዶክተር አህመድ አብዱረህማን ለጊዜው ምንነቱ ያልታወቀ ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን የአንዋር መስጂድ ኢማም ሃጂ ጡሃ ሃሩን ላፕቶፕ ፣ የ10ሩም ክፍለ ከተማ ፍትህ ቢሮ ሃላፊዎች ደግሞ ለእያንዳንዳቸው ዘመናዊ ሞባይል እንደተሸለሙ ታውቋል ፡፡ ሌሎቹም እንዲሁ በተዋረድ ሽልማቱ እንደተበረከተላቸው ምንጮች ገልፀዋል ፡፡

በመጨረሻም የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ሃላፊው አቶ ፀጋዬ ሀይለማሪያም ተሸላሚዎቹ ሙሉ ለሙሉ ያልቆመውን የሙስሊሙን ትግል ለማዳፈን ጠንክረው እንዲሰሩ ፣ እንዲሁም በቀጣይ ምርጫውን አስመልክቶ ከመንግስት ጎን ሆነው እንዲሰሩ የሚያሳስብ ንግግር ካደረጉ በኋላ ተሰብሳቢዎቹ ወደተዘጋጀላቸው ምሳ እንዲሄዱ አብስረው የሽልማቱ ስነ ስርዐት እንደተጠናቀቀ ምንጮች ጨምረው ገልፀዋል ፡፡
አላህ በዳዬችን ያዋርዳቸው !!

Tuesday, February 11, 2014

ዓረና የህወሓት የልደት በዓል ህዝባዊ ስብሰባ አስተጓጐለብኝ አለ

February 10/2014

ዓረና፤ በትግራይ ሁመራ ከተማ ህዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ ፍቃድ ካገኘ በኋላ ወሩ የህወሓት 39ኛ ዓመት የልደት በዓል የሚከበርበት ወቅት ነው በሚል የከተማው አስተዳደር ስብሰባውን እንዳገደበት የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ አብርሃ ደስታ ገለፁ፡፡

አቶ አብርሃ ደስታ ለአዲስ አድማስ እንደጠቆሙት፤ ባለፉት ሳምንታት በሁመራ ከተማ ህዝባዊ ስብሰባ ለማካሄድ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የሰነበቱ ሲሆን፤ ስብሰባውን ቅዳሜ እና እሁድ እንዳያደርጉ ተከልክለው ለትናንት አርብ ፈቃድ አግኝተው ነበር፡፡ ይሁንና በሰላማዊ መንገድ ህዝባዊ ጥሪ አድርገን ቅስቀሳውን በተሳካ ሁኔታ ከፈፀምን በኋላ በህወሓት የልደት በዓል ተጨናንቀናል፤ የተቃውሞ ስብሰባ ማድረግ አትችሉም፤ ህገወጥ ናችሁ” ተባልን ብለዋል - አቶ አብርሃ፡፡

ህዝባዊ ስብሰባው  በፓርቲው ፖሊሲ፣ በኢትዮ-ኤርትራና ኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይ እንዲሁም በአገር ሉዓላዊነት ዙርያ የሁመራን ህዝብ ለማወያየት ያለመ ነበር ያሉት የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ አባል፤ ኢህአዴግ የተለያየ ምክንያት ይደርድር እንጂ ስብሰባችንን ያስተጓጐለው ፓርቲያችን ስጋት ስለሆነበት ነው ብለዋል፡፡

ከሁለት ሳምንት በፊት ፓርቲው በዓዲግራት ስብሰባ ለማካሄድ ቅስቀሳ ሲያደርግ፣ አባላቱ እንደተደበደቡና እንደታሰሩበት አቶ አብርሃ አስታውሰዋል፡፡

አዲስ አድማስ

የአዲስ አበባ ከንቲባና ፖሊስ ኮሚሽነር በ“አንድነት” ተከሰሱ

February 10/2013

«ከንቲባ ድሪባ ኩማና ኮሚሽነሩ መከራከሪያቸውን ለፍ/ቤት ያቀርባሉ »
«አንድነት፣ የመንግስት አካላትን በተከታታይ እከሳለሁ ብሏል»
አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት)፣ የአዲስ አበባ ከንቲባና የፖሊስ ኮሚሽነራቸው ላይ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 8ኛ ወንጀል ችሎት ክስ የመሰረተ ሲሆን ተከሳሾች መልሳቸውን ይዘው እንዲቀርቡ ለየካቲት 24 ቀን 2006 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጠ፡፡
አንድነት ፓርቲ፤ “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” የተሰኘ አገር አቀፍ የ3 ወር ንቅናቄ ማጠቃለያን በአዲስ አበባ ባካሄደበት ወቅት በከተማ አስተዳደሩና በፖሊስ ኮሚሽን እስርና ወከባ እንደተፈፀመበት ገልፆ፤ በደላቸውን በማስረጃ በመዘርዘር ክስ መመስረቱን አስታውቋል፡፡
በፖሊስ ተፈፀመ በተባለ በደል ከንቲባውን በቀጥታ ለምን እንደከሰሰ ፓርቲው ሲያስረዳ፣ የአዲስ አበባ መተዳደሪያ ቻርተር ከንቲባው የከተማዋን ፖሊስ የእለት ተእለት እንቅስቃሴ የመቆጣጠር ኃላፊነት እንዳለበት ስለሚደነግግ ከንቲባውን በቀጥታ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል ብሏል፡፡
ቅስቀሳ ላይ የነበሩ የፓርቲው አመራሮችና አባላት በጅምላ በፖሊስ ታስረው መዋላቸውን ፓርቲው ጠቅሶ፣ የቅስቀሳ ቁሳቁስ ተነጥቀናል፤ ፖስተሮችን እንዳንለጥፍ ተከልክለናል ብለዋል። የፖሊስን የእለት ተእለት እንቅስቃሴ የመከታተል ሃላፊነት የተጣለባቸው ከንቲባውና ኮሚሽነሩ፣ የፖሊስን ህገወጥ ተግባር በቸልታ አልፈውታል ብሏል – አንድነት ፓርቲ፡፡
“በቂ ማስረጃ ከተደራጀ በኋላ ነው ወደ ክስ የሄድነው” ያሉት የፓርቲው አመራሮች፤ ክሱን የመሰረቱት ጠበቃ ተማም አባቡልጉ እና ረዳታቸው መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ከንቲባውና ኮሚሽነሩ የካቲት 24 ቀን መልሳቸውን ካቀረቡ በኋላ መጋቢት 2 ቀን ክርክር ይካሄዳል ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ ፍ/ቤት የለም ብለው እንደሚያምኑ የተናገሩት የፓርቲው መሪዎች፤ የመንግሥት አካላት የሚፈፅሙትን አፈና በይፋ ወደ ፍ/ቤት በመውሰድ የፍትህ ስርአቱን መፈተንና ለህዝብ ማጋለጥ አንዱ የትግል አላማችን ነው ብለዋል፡፡
ከሰኔ እስከ ነሐሴ 2005 ለ3 ወራት፣ “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል በመላ አገሪቱ የተደረጉት ሰላማዊ ሰልፎችና ህዝባዊ ስብሰባዎች ህዝብን በማነቃቃት ስኬታማ ውጤት አግኝተንባቸዋል ሲሉ የፓርቲው መሪዎች ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል፤ በፀጥታው ኃይል እና በገዢው ፓርቲ ካድሬ መካከል ልዩነት አለመኖሩን አይተናል፤ በአገሪቱ በተዘረጋ የአፈና መዋቅር ከፍተኛ የህግ ጥሰት እንደሚፈፀም አረጋግጠናል ያሉት የፓርቲው መሪዎች፤ የመንግስት ጫና ሳያሸብረው ፓርቲው ተመሳሳይ ንቅናቄዎችን በተከታታይ ያዘጋጃል ብለዋል፡፡
“የፀረ-ሽብር አዋጁን ለማሰረዝ የሰበሰባችሁትን ድምፅ የት አደረሳችሁት” የሚል ጥያቄ ከአዲስ አድማስ የቀረበላቸው አመራሮቹ፤ “የተሰበሰበውን የህዝብ ድምፅ ወደ ፍ/ቤት ለመውሰድ የህግ ባለሙያዎች እየመከሩበት ነው፣ በሁለተኛ ዙር የክስ ሂደት ውስጥ የሚካተት ይሆናል ብለዋል፡፡ በተካሄደው የ3 ወር የህዝብ ንቅናቄም መንግሥት ለጉዳዩ ይበልጥ ትኩረት እንዲሰጥ ፓርቲው ጫና ማሳረፉን የሚያመለክቱ ውጤቶች መታየት መጀመራቸውን የጠቀሱት የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌው፤ የፀረ-ሽብር አዋጁ ከመፅደቁ በፊት ለህዝብ ውይይት መቅረብ ሲገባው አዋጁ ወጥቶ ብዙዎችን ሰለባ ካደረገ በኋላ መንግስት ራሱን ለመከላከል የፕሮፖጋንዳና የስልጠና ዘመቻ ጀምሯል ብለዋል፡፡ ይህም ፓርቲያቸው ይዞት የተነሳው ጥያቄ ጫና ማሳረፉንና ትክክለኛ እንደነበር የሚያረጋግጥ መሆኑን አቶ ሃብታሙ ገልፀዋል፡፡

“ማንም ሰው ወይም አካል ከህግ በላይ ሊሆን አይችልም” ያለው ፓርቲው፤ ህግ በሚጥሱ የመንግስት አካላት ላይ በተከታታይ ክስ እመሰርታለሁ፤ በቅርቡም በመንግሥት ከፍተኛ አመራሮችና በገዢው ፓርቲ ላይ ተጨማሪ ክስ ለመመስረት እየተዘጋጀሁ ነው ብሏል፡፡
አዲስ አድማስ

ደራሲና የአንድነት አመራር አባል፣ አቶ አንዳርጌ መስፍን ፖሊስ ፊት እንዲቀርቡ ታዘዙ

February 10/2014

ወጣቱ ፖለቲከኛና ደራሲ አቶ ዳንኤል ተፈራ ፖሊስ ጣቢያ እንዲቀርብ መጠየቁ በስፋት መዘገቡ ይታወቃል። አቶ ዳንኤል መጀመሪያ ላይ እንዲቀርብ የተጠየቀዉ በስልክ፣ ሲሆን፣ ሕጋዊ መጥሪያ ወረቀት ካልመጣለት በቀር ለመቅረብ ፈቅደኛ ሳይሆን እንዳልቀረ ለማወቅ ተችሏል።
ከአቶ ዳንኤል ተፈራ በተጨማሪ፣ የአንድነት ብሄራዊ ምክር አባል የሆኑትና በርካታ መጽሃፍት በመጻፍ የሚታወቁት አዛዉንቱ 
አቶ አንዳርጌ መስፍንን፣ ፖሊስ ለመከሰስ እንደተዘጋጀ፣ እንዲቀርቡም እንዳዘዘ ለማረጋገጥ ችለናል።
አቶ አንዳርጌ መስፍን ከጻፏቸው በርካታ መጽሃፍት መካከል «ጥቁር ደም» የሚለው ታዋቂ መጽሃፍ ይገኝበታል። ከአቶ መለስ ዜናዊ ሕልፈት በኋላም፣ «የመለስን ራእይ እናስቀጥላለን» የሚል አቶ መለስን እንደ አምላክ የማቅረብ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ከልክ ባለፈበት ወቅት «በሞት መንፈስ አገር ሲታመስ» የሚል መጽሃፍን የጻፉ ደራሲ ናቸው።
አቶ አንዳርጌ መስፍን፣ በአንድነት ፓርቲ ዉስጥ በአዲሱና ከዚያም በፊት በነበረው የብሄራዊ ምክር ቤት አባል አመራር አባል ሆነው እያገለገሉ ሲሆን፣ የፍኖት ጋዜጣ ኤዲቶሪያል ቦርድ ዉስጥ ሰርተዋል።
ኢሕአዴግ በአቶ ዳንኤል ተፈራና አንዱ አንዳርጌ መስፍን ላይ ምን አይነት ክስ እንደሚያቀርብ ገና የታወቀ ነገር ባይኖርም፣ የአንድነት አመራር አባላትን እና ደጋፊዎች ለማስፈራራት፣ ለፍርድ ቤት መመሪያ በመስጠት፣ እስከ ስድስት ወራት የእስራት ቅጣት ሊበየንባቸዉ እንደሚችል የአንድነት አመራር አባላት ይናገራሉ።
በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት የሰጡን የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌዉ ፣ አቶ ዳንኤልም ሆነ አቶ አንዳርጌ መስፍን ፍጹም ሰላማዊ፣ ሰው አክባሪና አገር ወዳድ እንደሆኑ በመግለጽ፣ በነርሱ ላይም ሆነ በሌሎች የአመራር አባላት ላይ እየተደረገ ያለው ጥቃት፣ በሕዝብ ዘንድ የበለጠ ተቀባይነትን ድጋፍ እያገኘ የመጣዉን የአንድነት ፓርቲ ሆን ብሎ ለማዳከም ሲባል በፖለቲካዊ ዉሳኔ የሚደረግ እንደሆነ አስረድተዋል።
«ወያኔ የሚል ቃል ተጠቅመሃል» በሚል ክስ እርሳቸዉም ቀርቦባቸዉ ከአሥራ አንድ ጊዜ በላይ፣ ፍርድ ቤት እየተመላሱ እንደሆነ የገለጹት አቶ ሃብታሙ «ያለ ምንም ጥርጥር ወደፊት እንሄዳለን። መታሰሩ በጣም ቀላል ነገር ነዉ። የሰላማዊ ትግሉ ይቀጥላል» ሲሉም የርሳቸውም ሆነ የሌሎች የአመራር አባላት መታሰር አንድነትን እንደ ፓርቲ፣ ትግሉን እንደ ትግሉ የሚያጠናክር እንጂ የሚጎዳ እንዳለሆነ አሳስበዋል።

Monday, February 10, 2014

አዲስ አበባ እና ጅማ ሌሊቱን በግድግዳ መፈክሮች ደምቀው አደሩ

February 10/2014

ድምጻችን ይሰማ/ሰኞ የካቲት 3/2006

በትናንትናው ሌሊት በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች እና በጂማ ከተማ በርካታ የግድግዳ ላይ መፈክሮች ተጽፈው ማደራቸው ተዘገበ! በጂማ በራሪ ወረቀትም ተበትኗል!!!

በአዲስ አበባ ወደአስኮ በሚወስደው መንገድ በጀኔራል ዊንጌትና አካባቢው፣ እንዲሁም በጦር ሀይሎች መስመር እስከ ቤተል ድረስ ባሉ ቦታዎች በግድግዳዎች ላይ ተጽፈው ያደሩት እኒሁ መፈክሮች የሰላማዊ ትግሉን መንፈስ የሚያንጸባርቁና የህዝበ ሙስሊሙ መብት እንዲከበር፣ ታሳሪዎችም እንዲፈቱ የሚጠይቁ ነበሩ፡፡ ከተጻፉት መፈክሮች መካከል ‹‹ድምጻችን ይሰማ! ኮሚቴው ይፈታ! ህገ መንግስቱ ይከበር! የታሰሩት ይፈቱ!›› የሚሉት ጎልተው የወጡ መሆኑም ታውቋል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ በጂማ ከተማም በግድግዳዎች ላይ በርካታ መፈክሮች ተጽፈው ማደራቸው የተዘገበ ሲሆን በከተማዋ ሌሊቱን እጅግ በርካታ በራሪ ወረቀት ተበትኖ ማደሩና የከተማዋ አስተዳደርም በሁኔታው መደናገጡን ማወቅ ተችሏል፡፡

ካሁን ቀደምም በተለያዩ ጊዜዎች ብሶቱን በግድግዳ ላይ ጽሁፎች (ግራፊቲ) ሲገልጽ የቆየው የኢትዮጵያ ህዝበ ሙስሊም ከሁለት አመታት በላይ በሰላማዊ መንገድ ሲታገል የቆየ ሲሆን የተለያዩ የሰላማዊ ትግል ዘዴዎችን በመጠቀምም ለመብቱ መከበር የሚያደርገውን ጥረት ቀጥሏል፡፡


የአየር ኃይል አባሉ ም/መቶ አለቃ ዳንኤል የሽዋስ ሥርዓቱን ከድቶ አርበኞች ግንባርን ተቀላቀለ

February 10/2014

የደብረዘይት አየር ኃይል አባል የነበረው ምክትል መቶ አለቃ ዳንኤል የሽዋስ ሥርዓቱን በመቃወም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊትን መቀላቀሉን አርበኛ ኑርጀባ ለዘ-ሐበሻ በላከው ዜና አስታወቀ።


                                                   (የአርበኞች ግንባር ሠራዊት – ፎቶ ከፋይል)

እንደ አርበኛ ኑርጀባ ዘገባ አምባገነኑ የወያኔ ቡድን የታጠቀ ኃይሉን መከታ በማድረግ ንጹሃን ዜጎችን ያለ አግባብ እየጨፈጨፈ የስልጣን ዕድሜውን ለማስቀጠል የሚያደረገውን እንቅስቃሴና በሰራዊቱ ውስጥ የነገሰውን የአንድ ቡድን የበላይነት በመቃወም የደብረዘይት አየር ኃይል አባል የነበረውና L-39 ስኳድሮን ተዋጊ ጀት አብራሪ የነበረው ም/መ/አለቃ ዳንኤል የሽዋስ አገዛዙ የሚያደርስበትን ጭቆናና እንግልት ይበቃል በማለት ወደ ኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ተቀላቅሏል።

“የደብረዘይት አየር ኃይል አባልና L-39 ስኳድሮን ተዋጊ ጀት አብራሪ የነበረው ም/መ/አ ዳንኤል የሽዋስ ተቃዋሚዎችን ትደግፋለህ ከእነሱም ጋር የጠበቀ ግኑኝነት አለህ በሚል ምክንያት ተጠርጥሮ ያለምንም ወንጀል ለአምስት ወር ያህል ታስሮ እንደነበርና ከእስር እንደተለቀቀም በወያኔ የደህንነት አባሎች አማካኝነት በአይነ ቁራኛ ክትትል ይደረግበት እንደነበርም” ማስታወቁን የገለጸው የአርበኛ ኑርጀባ ዘገባ “በም/መ/አ ዳንኤል የሽዋስ የወያኔው የደህንነት አባሎች ጥላቻና ጥርጥር ምክንያት እንደገና ከተቃዋሚ ኃይሎች ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን ደርሰንበታል በማለት ወደ እስር ቤት እንዳስገቡትና ለ23 ቀናት በደብረዘይት እስር ቤት ከቆየ በኋላ ከእስር ቤት አምልጦ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊትን መቀላቀሉን ገልጿል” ብሏል።

በሌላ ዜና በሁመራ አካባቢ የሚኖሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ደጋፊዎች ናችሁ በማለት ታስረው የነበሩ 10 ሰዎች ላይ ከ6 ዓመት እስከ 25 ዓመት በመፍረድ ወደ መቀሌና ሽሬ እስር ቤት እንደወሰዱዋቸው ታውቋል።

በመቀሌ እስር ቤት በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ደጋፊነትና በተለያየ የአሸባሪነት ሰበብ እየፈጠረ የሚያስረው የወያኔው አገዛዝ በመቀሌ እስር ቤት ብቻ 36,900 እስረኛ የሚገኝ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 4500 የሚሆኑት ሴቶች እንደሆኑ ታውቋል።

በዚሁ እስር ቤት ሰዎችን በሌሊት እየቀሰቀሱ በመውሰድ ደብድበው የሚመልሱ ሲሆን፣ አንዳንዶች ደግሞ በዚያው እንደወጡ እንደሚቀሩ ከአካባቢው የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

የወያኔ ካድሬዎችም በዚሁ በመቀሌ እስር ቤት ውስጥ በሚገኙ ሴቶች ላይ የወሲብ ጥቃት እንደሚፈጽሙባቸው መታወቁን የዘገበው አርበኛ ኑርጀባ፣ በዚህም ምክንያት ሁለት ሴቶች መፀነሳቸውና አስፈላጊውን እንክብካቤ ባለማግኘታቸው ሕይወታቸው እንዳለፈ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል ብሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዳንሻ አካባቢ በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ስም በሕዝቡ ላይ እያደረሰ ያለው እንግልት ተጠናክሮ ቀጥሏል።
የወያኔው ገዥ ቡድን በዚሁ አካባቢ እየደረሰበት ባለው ወታደራዊ ጥቃት ሳቢያ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር እንደ ምሽግ የሚጠቀመው እናንተን ነው በማለት የአካባቢውን ህብረተሰብ ያሰቃይ እንደነበር ይታወሳል።

በአሁኑ ወቅት ብዛት ያላቸው የዳንሻና የአካባቢው ነዋሪዎችን እያሰረ ሲሆን፣ የሚሰጠው ምክንያት ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ያስታጠቃችሁን መሣሪያ አምጡ፣ ከእነሱ ጋርም ቀጥተኛ ግኑኝነት እንዳላችሁም ደርሰንበታል በሚል ወደ እስር ቤት እያጎራቸው ይገኛል ሲል አርበኛ ኑርጀባ ለዘ-ሐበሻ የላከውን ዜና አጠናቋል።

 ዘ-ሐበሻ 

የአቶ አሥራት ጣሴ እስር የኢህአዴግ የጉልበት ፖለቲካ ማሳያ ነው!

February 10/2014

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ የተሠጠ መግለጫ

ፓርቲያችን አንድነት በተደጋጋሚ ከገዥው ፓርቲ ህግን ከለላ በማድረግ እና የመንግስትን ሥልጣን በመጠቀም የሚደርስበትን ከፍተኛ አፈና ተቋቁሞ የኢትዮጵያን ህዝብ ሉዓላዊ የስልጣን የበላይነት ለማረጋገጥ ትግሉን አጠናክሮ መቀጠሉ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡
በተለይም ፓርቲያችን በመላው የሀገራችን ክፍል የዘረጋውን መዋቅር በህዝባዊ አቅም ወደ ተሻለ ደረጃ በማሸጋገር በአምስት ዓመት ስትራተጂክ ዕቅዱ መሰረት እያከናወነ ያለው ህዝባዊ ንቅናቄ እና በተሳካ ሁኔታ ጠቅላላ ጉባዔ አካሂዶ ዴሞክራሲያዊ የአመራር ሽግግር ማድረጉ በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ ትልቅ ተስፋ ያሳደረ ቢሆንም ገዥውን ፓርቲ በአንጻሩ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደከተተው ይስተዋላል፡፡
ኢህአዴግ ቀደም ሲል የፓርቲያችንን እንቅስቃሴ በመከታተል ከከፍተኛ አመራሮች መካከል አቶ አንዱዓለም አራጌ፤ ናትናዔል መኮንን እና ሌሎች በርካታ አባላትን የተለያየ ምክንያት ፈጥሮ እየወነጀለ ለእስር መዳረጉ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህም በድንገት የተደረገ ሳይሆን የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር እና የኢህአዴግ ሊቀመንበር አቶ መለስ ዜናዊ በግልጽ በፓርላማ ተገኝተው ‹‹አንድነት ፓርቲ እግር ሲያወጣ እግሩን እንቆርጣለን›› ባሉት መሰረት የፈጸሙት ነበር፡፡
አሁንም የራዕያቸው አስቀጣይ ነን የሚሉ የገዥው ኃይሎች ፈለጋቸውን ተከትለው የአውራ ፓርቲ (የአንድ ፓርቲ ስርዓት) ለመገንባት አንድነትን በጉልበት ፖለቲካ ማጥፋት እንደ ብቸኛ መንገድ ወስደው እየተረባረቡ ይገኛሉ፡፡ በመላው የሀገራችን ክፍል በርካታ አባሎቻችን ከስራ ተፈናቅለዋል፤ በግፍ ከሀገራቸው እንዲሰደዱ ተደርገዋል፤ ታስረዋል፤ ተደብድበዋል፡፡ ይህም በየጊዜው በፓርቲያችን ልሳን በመረጃ ተደግፎ ለህዝብ ይፋ የተደረገ ሲሆን፤ በአጠቃላይ በፓርቲያችን አመራር እና አባላት ላይ የተፈጸመውን የሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰት ባመላከትንበት ሪፖርትም ተካተቶ ለህዝብ ይፋ ተደርጓል፡፡
በተለይም የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት በሚል የተካሄደውን ህዝባዊ ንቅናቄ ተከትሎ ፓርቲያችን በተንቀሳቀሰባቸው አሥራ አንድ የሀገራችን ከተሞች ጉልህ ሚና የተጫወቱ እና በህዝብ ተቀባይነት ያላቸውን አባላት ምክንያት እየፈጠሩ እና የፍትህ ስርዓቱን የፖለቲካ መሳሪያ እያደረጉ ለእስር እና ለእንግልት መዳረጉን አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡
ኢህአዴግ ገና በጊዜ የጀመረው የ2007 ዓ.ም የምርጫ ዘመቻ የተለመደውን የጉልበት ፖለቲካ የተከተለ ሲሆን በቅርቡ በምዕራብ ሸዋ ዞን ለንሴቦ ወረዳ አቶ አለማየሁ ለሬቦ የተባሉ የሲተዳማ ዞን የአንድነት ስራ አስፈጻሚ በአዲስ አበባ ተገኝተው የፓርቲ ጉባኤ ተሳትፈው ሲመለሱ በቁጥጥር ስር ውለው ለ22 ቀናት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በእስር ቤት ከተሰቃዩ በኋላ መንግስትን ሰድበዋል የሚል ክስ ተመስርቶባቸው በዋስ ተለቀዋል፡፡ ይህንን ተከትሎ በየካቲት 30 ቀን የፓርቲያችን ከፍተኛ አመራር (የብሄራዊ ምክር ቤት አባል) የሆኑት አቶ አስራት ጣሴ ፍርድ ቤትን ዘልፈዋል ተብለው ለእስር የተዳረጉ ሲሆን ሌሎች አራት ከፍተኛ የፓርቲ አመራሮች ሊታሰሩ ሴራ እየተሸረበባቸው መሆኑን ምንጮች ለፓርቲያችን እያረጋገጡ ይገኛሉ፡፡
የፍትህ ስርዓቱን ዋነኛ የፖለቲካ መሳሪያ ያደረገው የኢህአዴግ መንግስት አቶ አስራት ጣሴን ለማሰር እንደ ምክንያት የተጠቀመው በአዲስ ጉዳይ መጽሄት 197 ቅፅ 7 ያወጡትን ጽሑፍ ሲሆን አጠቃላይ መልዕክቱም በኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ የሌለ መሆኑን፤ ህጎች አፋኝ መሆናቸውን፤ ኢ.ቲቪ የሰራቸው አኬልዳማ፤ ጀሃዳዊ ሃረካትና ሌሎች ለፖለቲካ ጥቃት ማድረሻ የተቀነባበሩ ድራማዎች ህገ ወጥ መሆናቸውን የሚገልጽ ነው፡፡ ይህ የፍትህ ጥያቄ ደግሞ አቶ አስራት ጣሴ ገና በጠዋት ለትግል የወጡበት፤ ከመሰሎቻቸው ጋር ሆነው አንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍት ፓርቲ እንዲመሰረት በርካታ መስዋዕትነት የከፈሉበት የፖለቲካ አላማቸው እና የፓርቲ አቋም መሆኑ ይታወቃል፡፡
‹‹የኢህአዴግ መንግስት ከሚመራቸው ፍርድ ቤቶች ፍትህ ይገኛል ብለን ሳይሆን ለታሪክ እንዲመዘገብ ወደ ፍርድ ቤት እንሄዳለን›› ሲሉም የግል ሃሳባቸው ብቻ ሳይሆን በብዙ አንቀጽ የተጠቀሰ የፓርቲያቸው አቋም ስለመሆኑም ማሳያ ነው፡፡ ከዚህም በላይ ኪሊማንጃሮ የተባለው ድርጅት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር በመንግስት ተቋማት ላይ ያደረገው ጥናት እንደሚያሳየው በህዝብ ከማይታመኑ ተቋማት መካከል ፍርድ ቤቶች በአንደኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡ ናቸው፡፡
ከነዚህ በህዝብ ከማይታመኑ ተቋማት ፍትህ አይገኝም ብሎ ማመን እና እምነትን መንገርም ሆነ መጻፍ ህገ መንግስታዊ መብት መሆኑ እየታወቀ በአካል ባልተገኙበት ችሎት በአካል ተገኝቶ ችሎትን ያወከ ወይም የዘለፈ በሚቀጣበት ፍታብሔር አንቀጽ 480 ቀርበው እንዲያስረዱ ከተጠሩ በኋላ ለእስር ተዳርገዋል፡፡ ይሁን እንጂ የተጠሩበት የፍታብሔር አንቀጽ የሚያዘው ጥፋታኛ ሆነው የተገኙ ቢሆን እንኳ በአነስተኛ የገንዘብ መቀጮ የሚቀጣ እንጂ ለእስር የሚያበቃ አልነበረም፡፡
ኢህአዴግ ይህንን እያደረገ ያለው ቀናቶች ወደ 2007 ዓ.ም ምርጫ እየገሰገሱ እና ፓርቲያችንም በህዝባዊ አቅሙ እየጎለበተ በመምጣቱ ካለቃቸው እንደተማሩት እግር ያወጣ ፓርቲያችንን እግር በመቁረጥ፤ አመራሩን ህግን ከለላ አድርገው ለእስር በመዳረግ፤ እንዳይጽፍ፤ እንዳይነገር እና በፍርሃት ቆፈን ተይዞ አንገቱን እንዲደፋ በማድረግ በምርጫ ሜዳው ከጀሌዎቻቸው ጋር ሩጠው አሸንፈናል ብሎ ለማወጅ የሚደረግ አስነዋሪ ዘመቻ ነው፡፡
ነገር ግን እንዲህ ያለው አምባገነናዊ ተግባር ትግላችንን የበለጠ አጠናክረን በመግፋት ሰላማዊ ትግሉ የሚጠይቀንን መስዋዕትነት ለመክፈል የሚያበረታን እንጂ ወደኋላ የማይመልሰን መሆኑን ዛሬም እንደ ትላንቱ ለመላው ህዝባችን እናረጋግጣለን፡፡
የፍትህ ስርዓቱም ከአንድ ፓርቲ ወገንተኝነት እንዲወጣ እና በግፍ የታሰሩ አመራሮቻችንንም በነጻ እንዲያሰናብት እንጠይቃለን !!!!
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!

የካቲት 1 ቀን 2006ዓ.ም

ሰበር ዜና – ዳንኤል ተፈራ ቃል እንዲሰጥ በፌደራል ፖሊስ ታዘዘ

February 10/2014

የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ የሆነው ወጣቱ ፖለቲከኛና ደራሲ ዳንኤል ተፈራ ማዓከላዊ ወንጀል ምርመራ በመቅረብ ቃሉን እንዲሰጥ በፌደራል ፖሊስ ታዘዘ፡፡ ፍኖተ ነፃነት ምንጮችን ዋቢ በማድረግ አቶ ዳንኤል ተፈራን ጨምሮ በአራት የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት ላይ ክስ ለመመስረት ጥረት እየተደረገ መሆኑን መዘገቧ ይታወሳል፡፡

በቅርቡ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ አስራት ጣሴ፣ በክስ ሂደት ላይ የነበረው የአኬልዳማ ዶክመንተሪ በድጋሚ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መታየቱን ተከትሎ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ ከፃፉት አስተያየት ጋር በተያያዘ “ዘለፋ አዘል ጽሑፍ” ጽፈዋል በሚል ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲያስረዱ ትዕዛዝ በተላለፈባቸው መሰረት በፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት የተገኙ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ለ7 ቀን ታስረው በቀጣዩ ሳምንት እንዲቀርቡ በማለት የእስር ትዕዛዝ ወስኖባቸዋል ፡፡ በማሰር እና በማንገላታት ስልጣን ለመቆየት የሚደረገው አፈና ቀጥሏል ዜጎችን በማሰርና በማስፈራራት የትጀመረውን ትግል ማፈን እንድማይቻል መቼ ይሆን የሚገንዘቡት? ትግሉ ይቀጥላል! የአምባገነኑ ዘረኛ አገዛዝ ያከትማል!!

1610073_10152193473611870_527946694_n

Sunday, February 9, 2014

አረናዎችን ለመገድል ህወሃት እያሴረ ነዉ ተባለ

February 9/2014

ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለመዋሃድ ንግግር እያደረገ ያለው የአረና ፓርቲ፣ ከሕወሃት ጋር ከፍተኛ የሰላማዊ ትግል ትንቅንቅ ላይ እንደሆነ በስፋት እየተነገረ ነዉ። በቅርቡ በአዲግራት ሊደረግ ታስቦ በነበረዉ ሕዝባዊ ስብስባ ከሌላ አኡራጃዎች የመጡ የሕወሃት ካድሬዎችና ዱርዬዉን ድንጋይ እየወረወሪ ሲበጠብጡ፣ የአመራር አባላትን ሲደበድቡ እንደነበረ የሚታወስ ነዉ። ህወሃት እነዚህ ዱርዮዎችን አሰማርቶ የሽብር ተግባራትን በመፈጸሙ ምክንያት፣ ስብሰባዉን ማድረግ ካለመቻሉ የተነሳ፣ የአዲግራት ሕዝብ አማራጮችን እንዳይሰማ ተደርጓል።
በተመሳሳይ ሁኔታ በሁመራ ሕወሃት በሕግ ተፈቅዶ የተጠራን የአረና ስብሰባ በኋይል ለማጨናገድ ችሏል። አረናዎች ሳይታክቱ በየከተሞቹ የሚያደርጉት ሰላማዊ እንቅስቃሴዎች ፣ በሌላ ብኩል ደግሞ ህወሃት እያሳያቸው ያለው ፍጹም ጸረ-ሰለማ እና ጸረ-ዲሞርካሲ ተግብራት አብዛኛዉን የህወሃት ደጋፊ የነበሩትን ሁሉ እያስገረመና እያስቆጣ ሲሆን፣ በርካታ ሕወሃቶች ወደ አረና እየተጎረፉ እንደሆነ ምንጮች ይጠቁማሉ።
ከዚህም የተነሳ ሕወሃት የአረናን ግለት መግታት ስላልቻሉ የአመራር አባላቱን የመግደል ሴራ አያሴሩ መሆናቸውን የሚገልጹ ዘገባዎች እየተነበቡ ናቸው።
የአረና ከፍተኛ አመራር አባል የሆኑት አቶ አብርሃ ደሳታ በዚህ ጉዳይ ላይ በፌስቡክ የጻፉትን እንደሚከተለዉ አቅርበናል፡
=========================
ሑመራ (ዳንሻ) በነበርኩበት ግዜ ከተወሰኑ የቀድሞ የህወሓት ታጋዮች ጋር ተገናኝቼ ነበር። ሁለት ታጋዮችን የነገሩኝ ላካፍላቹ። “ለምንድነው የትግራይን ህዝብ ፈሪ የሆነው?” አንድ ጓደኛዬ የጠየቀው ነበር። ታጋይ አንድ (ወንድ ነው) ሲመልስ “የትግራይን ህዝብ ፈሪ የሆነው ከድሮ ጀምሮ የህወሓትን ጭካኔ ስለሚያውቅ ነው። ህወሓት ሰው በሊታ መሆኗ የትግራይ ህዝብ በደንብ ያውቃል” አለ። “እሺ የትግራይ ህዝብስ ይፍራ እናንተ ታጋዮችስ ለምን ትፈራላቹ?” ብዬ ጠየቅኩ። ታጋይ ሁለት (ሴት ናት) “እኛ ታጋዮችምኮ የህወሓትን ጭካኔ በደንብ እንረዳለን። ከህዝብ በላይ ህወሓትን የምናውቃት እኛ ነን። አብዛኞቹ የህወሓት ታጋዮችኮ በህወሓት የተረሸኑ ናቸው። በደርግ ከተገደሉብን ብፆት (ጓዶች) በራሷ በህወሓት የተገደሉ ይበዛሉ። በህወሓት እንደተረሸኑ እያወቅንም ‘በጦርነት ተሰውተዋል’ ብለን ነው የምንናገረው። አብዛኞቻችን እናውቀዋለን። ግን እንፈራለን። አሁን ግን ማንን እንደምንፈራ አላውቅም” አለች። “ፍርሓት ፍርሓት … መጨረሻ ድፍረት ይሆናል” ብዬ ተሰናበትኳቸው።
የህወሓት መሪዎች ተስፋ ከመቁረጣቸው የተነሳ የዓረናን መሪዎች እስከመግደል ሊደርሱ እንደሚችሉ አንድ የህወሓት የደህንነት ሐላፊ ዛሬ አጫውቶኛል። ተስፋ የቆረጡበት ምክንያት … የራሳቸው (የህወሓት) አባላትም ዓረናዎች የሚያነሷቸው ሐሳቦች እያነሱ ስለሚጠይቁና በብዛት ከህወሓት አባልነት እየለቀቁ በመሆናቸው ነው። ባሁኑ ግዜ በትግራይ ክልል የሚገኙ የህወሓት አመራር አባላት በየዞኗቸው ተሰብሰበው የሚገኙ ሲሆን ከሚያነሷቸው ሐሳቦች በመነሳት የህወሓት መሪዎች በአባሎቻቸውም እምነት የላቸውም። እስካሁን ድረስ በሰሩት ወንጀል ምክንያት ተጨናንቀዋል። (ሁሉም አመራር አባላት በየዞን ከተሞች የተሰበሰቡ ሲሆን የተምቤኖች ግን ለየት ይላል። ተምቤኖች ጠንከር ያለ ተቃውሞ ያነሳሉ በሚል ስጋት ለብቻቸው በዓድዋ ከተማ እንዲሰበሰቡ ተደርጓል። ሌሎች የማእከላዊ ዞን አባላት ግን በአክሱም ይገኛሉ)። የህወሓት የ አባላት ለስብሰባ ሲገቡ ሞባይላቸው እንዲዘጉ በጥብቅ ይታዘዛሉ። የመሪዎች ንግ ግር መቅረፅ በጥብቅ የተከለከለ ነው። ህወሓት እንኳንስ ህዝብ የራሱ አባላትም አይመርጡትም። የሰሩት ወንጀል ራስ ምታት ሁኖባቸዋል። ስልጣን መልቀቅ የሞትን ያህል አስፈርቷቸዋል። በዚሁ አካሄዳቸው ደግሞ በስልጣን ሊቆዩ እንደማይችሉ በሚገባ ተረድተዋል።
ህወሓት ፍፁም አምባገነንነቱን እያጠናከረ ነው። ትናንት ዓርብ በሑመራ ከተማ ሰዓት እላፊ ማወጁ ይታወሳል። በዓረና እንቅስቃሴ በጣም የሰጋ ህወሓት ዛሬ የዓረና አባላትን ሲያስፈራራ ዉሏል። አቶ መሰለ ገብረሚካኤል የተባሉ የዓረና ስራ አስፈፃሚ አባልና የምዕራባዊ ዞን የዓረና አባላት አስተባባሪ ዛሬ ታስረው እየተገረፉ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል። የዓረና ፓርቲ ቢሮ (በሑመራ) በህወሓት ካድሬዎች ዛሬ ተዘርፏል፤ ኮምፒተሮች ተወስደዋል (የአቶ መሰለ የግል ላፕቶፕም ጭምር በባለስልጣናቱ ተዘርፋለች)። የመንግስት ስልጣን የያዘ አካል እንዲህ የተራ ሽፍታ ስራ ሲሰራ ይደንቃል። ለአምባገነናዊ ስርዓት አንምበረከክም። ማሸነፋችን አይቀርም።