Sunday, February 9, 2014

ሕወሓት ከመለስ ጋር አብሮ ተቀብሯል – ክፍል 2

February 9/2014
ከነፃነት አድማሱ
ሰው ልጅን ነፃነት የማይገባው ነፃ አውጪ!! !!


























በትግራይ የህወሓት እኩይ ተግባር በቅርብ የተከታተሉት አንድ የሽሬ እንዳስላሴ አዛውንት እንዲህ በማለት በምሬት ይገልፁታል። “ደርግ ሰው ገድሎ በአደባባይ ይፎክር ነበር። ዛሬ ህወሓት ግን ሰው ገድሎ ልቅሶ ይደርሳል” ሲሉ የድርጅቱን እርኩስነት፣ አስከፊነትና የሰብኣዊ ፍጡር ባላንጣነት ካለፈው የደርግ አገዛዝ ጋር በማነፃፀር ቁጭታቸውን በትካዜ ሲናገሩ አጋጥሞኛል። የዛሬው ፅሑፌም ካለፈው ክፍል አንድ የቀጠለ ነው። በክፍል አንድ የተነሱ ዋና ዋና ጥያቄዎችም በኋላ በዝርዝር ለማስቀመጥ እሞክራለሁ። ለዛሬ ግን ቀደም ብዬ በክፍል አንድ የጀመርኩትን “አደናግረህ፣ አስፈራርተህ፣ አሸብረህ፣ ወገን ከወገኑ ጋር አናቁረህና ለያይተህ ግዛ” የሚለውን የህወሓት የደደቢት የደንቆሮ ፍልስፍናና መፈክር በሚመለከት አጭር ማጠቃሊያ በማከል ፅሑፌን እቋጫለሁ።

አዎ!! ህወሓት ለትግራይ ህዝብ ሶስት ጊዜ ገድለታል። መጀመሪያ ኤርትራን ከእናት ሀገርዋ ገንጥሎ ነፃ ለማውጣት በአስር ሽዎች
የሚቆጠሩ የትግራይ ለወጋ ወጣቶች የሻዕቢያን ህይወት ለማዳን ሲባል በሳሕል በረሃ የአሞራ ሲሳይና የአቶ ኢሳያስ አፈ ወርቂ የስልጣን ማዳበሪያ ሆኖው እንዲቀሩ አድርጓል። ሁለተኛው አስከፊ ሞት ህዝቡ የባህር በሩን በመዝጋት ሉዓላዊነቱንና ብሄራዊ ጥቅሙን ከእጁ ነጥቀው ለማዕዳን አሳልፈው በመስጠት በህዝቡ ደም ቀልደዋል። ሶስተኛው አሳፋሪው ሞት ደግሞ ህዝቡ “ሻዕቢያ ይወረናል” እያለ ሲጮኽ ጆሮ ዳባ በመስጠት እንደገና ተመልሶ በኤርትራ ዳግም እንዲወረር በማድረግ ብሄራዊ ክብሩን እንዲደፈር፣ ዳር ድንበሩንና አንጡራ ሀብቱን እንዲዘረፍ፣ እንደ ዓይደር ትምህርት ቤት የመሳሰሉትን ጨምሮ ዳግም የሐውዜን ዓይነት እልቂት እንዲፈጠር አድርጓል። በአጠቃላይ የትግራይ ህዝብ ለባዕድ ጅብ አሳልፈው በመስጠት ለኤርትራ ነፃነት የከፈለውን የወጣቶቹን መስዋእትነት ደመ ከልብ ሆኖ እንዲቀር ተደርጓል።

ይህ በዓይናችን ያየነው በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ ተሰምቶ የማይታወቅ ብሄራዊ ውርደት፣ ሐፍረትና የታሪክ ጉድፍ መሆኑን ማንም ሀገር ወዳድ ዜጋ ሊገነዘበውና ሊቆጨው የሚገባ ጉዳይ ነው። በአባቶቻችን ተጠብቆ የቆየውን ክብራችንና ዳር ድንበራችንን የባዕዳን ደላላ በመሆን ያስደፈረ፣ ያዋረደ፣ የቸረቸረና ይቅር የማይባል ሀገራዊ ክሕደት የፈፀመው በሻዕቢያ ጡጦ ያደገው ህወሓት መሆኑን በያለንበት ለልጅ ልጆቻችንም ሳይቀር መናገርና ማስተማር መቻል አለብን።

አዎ!! የትግራይ ህዝብ ችግር በዚህ ብቻ አላበቃም። ቀደም ሲል ደርግን አሸንፈው ወደ አዲስ አበባ ብሄራዊ ቤተ መንግስት ገብተው ስልጣናቸውን ለማጠናከርና ለማደላደል ህዝቡን እንደ መሳል አድርገው ከተጠቀሙበት በኋላም ዛሬም ትግራይ የርስ በርስ መበላላት፣ ግድያ፣ ድብደባ፣ አድልዎ፣ ዝርፊያና ሕግ አልባ ድርጊቶችን የሚፈፀምባት የጥፋትና የጭቆና ሞዴል ሆና ትገኛለች። የንፁኃን ደም የስልጣናቸው መቋደሻና መናገሻ አድርገው የሚጠቀሙ የህወሓት ሰበው በላ ካድሬዎችና መሪዎቻቸው ህዝቡን በመናቅና በማንቋሸሽ “ብንደበድብ የት ትደርሳለህ?!! መሳሪያውና ነፍጡ እንደሆነ በእጃን ነው። ከኛ በላይ ነፋስ እንጂ ሌላ ሀይል የለም። ረግጠን ብንገዛህና የፈለግነው ብናደርገህ ማን ያድናሃል?!! ከኤርትራም ሆነ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር እንደሆነም አጣልተናሃል።!! ስለሆነም ወደድክም ጠላህም ከእጃችን አታመልጥም። ስለዚህ አርፈህ ተገዛ።!! አፍህን ያዝ!! በነፃ መናገር ማን አስተማረህ? …. እያሉ እንደ ህፃን ልጅ በአለንጋ ሲገርፉትና በአደባባይ ሲቀጠቅጡት ይገኛል።

ታዲያ!! ለዚህ ሚስኪን ህዝብ ጠበቃ፣ ደራሽና አለሁልህ ባይ ማን ይሆን?። ትግራይ ብዙ ጀግኖች እንዳልወለደች ሁሉ ዛሬ በባዕድ ወረራ ጊዜ እንኳን በምንም መልኩ ያልታየ ጉድ እያየን ነው። ሰዎች በገዛ ሀገራቸው ጠላት እየተባሉ በአደባባይ የሚደበደቡባት፣ በእስር ቤት ቁም ስቃይ የሚታይባት፣ ህዝቡ ባለቤትና አቤት የሚልበት የፍትሕ ቦታ አጥቶ በሆዱ እያለቀሰ የሚኖርባት ምድራዊት ሲኦልና የጭካኔ ሞዴል ሆና እስከመቼ ትቆይ? እውነት ለራሳቸው ነፃ ያልወጡ የሻዕቢያ ተላላኪ የሆኑት የህወሓት ማፍያ መሪዎች የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ናቸውን? ለሚለው ጥያቄ መልሱና ፍርዱ ለአንባቢዎቼ ትቻለሁ።

ይሁን እንጂ ለባዕድ የማይንበረከክ፣ ጀግናና አትንኩኝ ባይ ህዝብ በላዩ ላይ ይህ ሁሉ ግፍ ሲፈፀምበት እየታየ ለምን ዝም ተባለ?
በአካባቢው ሰው የለም ወይ? ያ ሁሉ ጀግና እየተባለ በትጥቅ ትግል ያለፈውና ራሱን ነፃ አውጪ ነኝ ሲል የነበረው ሰፊው የህወሓት ታጋይስ የት ገባ? የለውጥ ቀዳሚና ግንባር ቀደም መሆን የነበረበት የትግራይ ምሁሩና ተማሪውስ ምን ዋጠው? የትግራይ ተወላጅ ሆኖ የገዛ ወንድሙ በአደባባይ እንደ ውሻ በዱላ መደብደብስ የትግራይ ህዝብ ባህል ነው ወይ? ዛሬ በትግራይ ምድር ምን ዓይነት ትውልድ ነው እየተፈጠረ ያለው።? ችግሩ ለምን በትግራይ ያን ያህል የከፋ ሊሆን ቻለ።? ሌላው ኢትዮጵያዊስ በትግራይ አካባቢ ስለሚፈፀመው አስነዋሪ ተግባር ግንዛቤው ምን ያህል ነው።? የሚሉና ሌሎች ተዛማጅ ጥያቄዎችን በመጨመር በሚቀጥለው ሶስተኛ ክፍል ፅሑፌን አስር  ነጥቦችን ያካተተ ዝርዝር ሓተታ ይዤ እቀርባለሁ። በቸር ሰንብቱልኝ!!




















 











አረናዎችን ለመገድል ህወሃት እያሴረ ነዉ ተባለ

February 9/2014

ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለመዋሃድ ንግግር እያደረገ ያለው የአረና ፓርቲ፣ ከሕወሃት ጋር ከፍተኛ የሰላማዊ ትግል ትንቅንቅ ላይ እንደሆነ በስፋት እየተነገረ ነዉ። በቅርቡ በአዲግራት ሊደረግ ታስቦ በነበረዉ ሕዝባዊ ስብስባ ከሌላ አኡራጃዎች የመጡ የሕወሃት ካድሬዎችና ዱርዬዉን ድንጋይ እየወረወሪ ሲበጠብጡ፣ የአመራር አባላትን ሲደበድቡ እንደነበረ የሚታወስ ነዉ። ህወሃት እነዚህ ዱርዮዎችን አሰማርቶ የሽብር ተግባራትን በመፈጸሙ ምክንያት፣ ስብሰባዉን ማድረግ ካለመቻሉ የተነሳ፣ የአዲግራት ሕዝብ አማራጮችን እንዳይሰማ ተደርጓል።
በተመሳሳይ ሁኔታ በሁመራ ሕወሃት በሕግ ተፈቅዶ የተጠራን የአረና ስብሰባ በኋይል ለማጨናገድ ችሏል። አረናዎች ሳይታክቱ በየከተሞቹ የሚያደርጉት ሰላማዊ እንቅስቃሴዎች ፣ በሌላ ብኩል ደግሞ ህወሃት እያሳያቸው ያለው ፍጹም ጸረ-ሰለማ እና ጸረ-ዲሞርካሲ ተግብራት አብዛኛዉን የህወሃት ደጋፊ የነበሩትን ሁሉ እያስገረመና እያስቆጣ ሲሆን፣ በርካታ ሕወሃቶች ወደ አረና እየተጎረፉ እንደሆነ ምንጮች ይጠቁማሉ።
ከዚህም የተነሳ ሕወሃት የአረናን ግለት መግታት ስላልቻሉ የአመራር አባላቱን የመግደል ሴራ አያሴሩ መሆናቸውን የሚገልጹ ዘገባዎች እየተነበቡ ናቸው።
የአረና ከፍተኛ አመራር አባል የሆኑት አቶ አብርሃ ደሳታ በዚህ ጉዳይ ላይ በፌስቡክ የጻፉትን እንደሚከተለዉ አቅርበናል፡
=========================
ሑመራ (ዳንሻ) በነበርኩበት ግዜ ከተወሰኑ የቀድሞ የህወሓት ታጋዮች ጋር ተገናኝቼ ነበር። ሁለት ታጋዮችን የነገሩኝ ላካፍላቹ። “ለምንድነው የትግራይን ህዝብ ፈሪ የሆነው?” አንድ ጓደኛዬ የጠየቀው ነበር። ታጋይ አንድ (ወንድ ነው) ሲመልስ “የትግራይን ህዝብ ፈሪ የሆነው ከድሮ ጀምሮ የህወሓትን ጭካኔ ስለሚያውቅ ነው። ህወሓት ሰው በሊታ መሆኗ የትግራይ ህዝብ በደንብ ያውቃል” አለ። “እሺ የትግራይ ህዝብስ ይፍራ እናንተ ታጋዮችስ ለምን ትፈራላቹ?” ብዬ ጠየቅኩ። ታጋይ ሁለት (ሴት ናት) “እኛ ታጋዮችምኮ የህወሓትን ጭካኔ በደንብ እንረዳለን። ከህዝብ በላይ ህወሓትን የምናውቃት እኛ ነን። አብዛኞቹ የህወሓት ታጋዮችኮ በህወሓት የተረሸኑ ናቸው። በደርግ ከተገደሉብን ብፆት (ጓዶች) በራሷ በህወሓት የተገደሉ ይበዛሉ። በህወሓት እንደተረሸኑ እያወቅንም ‘በጦርነት ተሰውተዋል’ ብለን ነው የምንናገረው። አብዛኞቻችን እናውቀዋለን። ግን እንፈራለን። አሁን ግን ማንን እንደምንፈራ አላውቅም” አለች። “ፍርሓት ፍርሓት … መጨረሻ ድፍረት ይሆናል” ብዬ ተሰናበትኳቸው።
የህወሓት መሪዎች ተስፋ ከመቁረጣቸው የተነሳ የዓረናን መሪዎች እስከመግደል ሊደርሱ እንደሚችሉ አንድ የህወሓት የደህንነት ሐላፊ ዛሬ አጫውቶኛል። ተስፋ የቆረጡበት ምክንያት … የራሳቸው (የህወሓት) አባላትም ዓረናዎች የሚያነሷቸው ሐሳቦች እያነሱ ስለሚጠይቁና በብዛት ከህወሓት አባልነት እየለቀቁ በመሆናቸው ነው። ባሁኑ ግዜ በትግራይ ክልል የሚገኙ የህወሓት አመራር አባላት በየዞኗቸው ተሰብሰበው የሚገኙ ሲሆን ከሚያነሷቸው ሐሳቦች በመነሳት የህወሓት መሪዎች በአባሎቻቸውም እምነት የላቸውም። እስካሁን ድረስ በሰሩት ወንጀል ምክንያት ተጨናንቀዋል። (ሁሉም አመራር አባላት በየዞን ከተሞች የተሰበሰቡ ሲሆን የተምቤኖች ግን ለየት ይላል። ተምቤኖች ጠንከር ያለ ተቃውሞ ያነሳሉ በሚል ስጋት ለብቻቸው በዓድዋ ከተማ እንዲሰበሰቡ ተደርጓል። ሌሎች የማእከላዊ ዞን አባላት ግን በአክሱም ይገኛሉ)። የህወሓት የ አባላት ለስብሰባ ሲገቡ ሞባይላቸው እንዲዘጉ በጥብቅ ይታዘዛሉ። የመሪዎች ንግ ግር መቅረፅ በጥብቅ የተከለከለ ነው። ህወሓት እንኳንስ ህዝብ የራሱ አባላትም አይመርጡትም። የሰሩት ወንጀል ራስ ምታት ሁኖባቸዋል። ስልጣን መልቀቅ የሞትን ያህል አስፈርቷቸዋል። በዚሁ አካሄዳቸው ደግሞ በስልጣን ሊቆዩ እንደማይችሉ በሚገባ ተረድተዋል።
ህወሓት ፍፁም አምባገነንነቱን እያጠናከረ ነው። ትናንት ዓርብ በሑመራ ከተማ ሰዓት እላፊ ማወጁ ይታወሳል። በዓረና እንቅስቃሴ በጣም የሰጋ ህወሓት ዛሬ የዓረና አባላትን ሲያስፈራራ ዉሏል። አቶ መሰለ ገብረሚካኤል የተባሉ የዓረና ስራ አስፈፃሚ አባልና የምዕራባዊ ዞን የዓረና አባላት አስተባባሪ ዛሬ ታስረው እየተገረፉ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል። የዓረና ፓርቲ ቢሮ (በሑመራ) በህወሓት ካድሬዎች ዛሬ ተዘርፏል፤ ኮምፒተሮች ተወስደዋል (የአቶ መሰለ የግል ላፕቶፕም ጭምር በባለስልጣናቱ ተዘርፋለች)። የመንግስት ስልጣን የያዘ አካል እንዲህ የተራ ሽፍታ ስራ ሲሰራ ይደንቃል። ለአምባገነናዊ ስርዓት አንምበረከክም። ማሸነፋችን አይቀርም።

እውን ሻዐቢያ እና ህወሀት ተጣልተዋልን?

February 8/2014
ሁኔ አቢሲኒያዊ

ማማ እና የሾላ ወተት ሁለቱም ወተት ናቸው የሚለያቸው ነገር ቢኖር ማማ ማማ መባሉ ሲሆን ሾላ ደግሞ ሾላ መባሉ ነው እንደዚሁ ህወሀት እና ሻዐቢያም የስም እንጂ የይዘትም ሆነ የአላማ ልዩነት የሌላቸው ጸረ ኢትዮጵያዊ ናቸው፡፡ ፀረ ኢትዮጵዊ መሆናቸው ሀቅ እና ምስጢር ያልሆነ ነው ይልቁንስ በዚህች አነስተኛ ጦማር ማሳየት የፈለኩት ሻዐቢያን አምነው የኢትዮጵያን ፖለቲካ ለመቀየር ከኢሳያስ ጋር ስለተወዳጁ ወገኖቻችን ጉዳይ ነው።
ምርጫ 2002 በተቃረበበት ወቅት በኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ቀረበ የተባለው እና በፊታውራሪ ህወሀቶች ጭምር ድጋፍ ተሰጥቶት ነበረ የተባለው የስልጣን እንልቀቅ ጥያቄ ውድቅ የተደረገው እኛ ስልጣን ከለቀቅን ሻዐቢያ በእጅ አዙር ሀገሪቷን ሊመራት ስለሚችል ስልጣን መልቀቃችን ሊታሰብ የማይችል ነው ሲሉ በተላላኪ ጋዜጠኞቻቸው በኩል አስነገሩ ብዙሀኑ ምስኪን የግል ጋዜጦችም ይህንን ጉዳይ አንስተው ከሁሉም ጆሮ እንዲዳረስ አደረጉ፡፡ ይህ ሁኔታ ወያኔ ኢህአዴግን በሁለት መንገድ ተጠቃሚ አደረገው እነርሱም፡-
1. ሻዐቢያ እውነትም ፀረ ኢትዮጵያዊ ነው ኢህአዴግ ከወደቀ ደግሞ ሻዐቢያ ኢትዮጵያን ይቆጣጠራል የሚለው አስተሳሰብ ውስጥ ብዙሀኑ ኢትዮጵያዊ ጥልቅ ብሎ እንዲገባ ያስቻለ ሲሆን
2. በሌላ በኩል ዲያስፖራ ላይ የመሸጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች እነ ኦነግ ከኢሳያስ ጋር ተለጥፈው ለምን ውጤታማ ሳይሆኑ ቀሩ እንኳን ብለው ሳያጤኑ ሻዐቢያ የወያነ ጠላት ስለሆነ ለእኛ እና ለሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ብቸኛው ኢትዮጵያን ነጻ የማውጫ መንገድ አስመራ ላይ መክተም ነው ብለው አውጀው የማይታመነውን ኢሳያስን አምነው አስመራ ከተሙ፡፡
እነዚህ ሁለት ከላይ የጠከስኳቸው ሁለት አብይት ጉዳዮች ወያኔን ተጠቃሚ ያደረጉ እንዲሁም የኢትዮጵያን ፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲዳከሙ ምክንያት የሆኑ ጉዳዮች ነበሩ፡፡
– እውን ህወሀት እና ሻዐቢያ ተጣልተዋል ወይስ ጥላቸው ለሚዲያ እና ለህዝቡ ጆሮ ብቻ ነው?
- ኤርትራ የከተሙ ፓርቲዎችስ ስለምን ውጤታማ አልሆኑም?
- እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ እስኪ በቅድሚያ ይህንን ሀሳብ በአዕምሯችን እናሰላስለው
- ሻዐቢያ አሰብ የራሱ እንዲሁም የኤርትራ ንብረት እንደሆነ ያምናል
- ህወሀትም አሰብ የኤርትራዊያን ንብረት እና ሀብት ነው ብሎ ያምናል
በተቃራኒው ብዙዎቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አሰብ የኢትዮጵያ ነው አልፎም ተርፎ የኤርትራን መገንጠል የማይደግፉ ናቸው ታድያ የኛ ፓርቲዎች እንደምን ብለው ነው ኢሳያስን አምነው አስመራ ላይ የከተሙት እውን ኢሳያስስ አሰብ የኢትዮጵያ ናት ብለው የሚሰብኩት ተቃዋሚዎች ይሻሉታል ወይስ ኤርትራ ነጻ ሀገር ነች አሰብም የኤርትራ ነች የሚለው ወያኔ?
ህወሀት እና ሻዐቢያ በስልጣን ላይ ለመቆየት የማይገድሉት ሰው የማይቆፍሩት መሬት የለም በኤርትራ ሪፈረንደም ወቅት እስካሁን ትርጉሙ ሊገባኝ ባልቻለ መልኩ የመለስ ዜናዊ እናት ኢትዮጵያ ሬድዮ ላይ ቀርባ ኤርትራዊያን ነጻ ሀገር ስለሆኑ እንኳን ደስ ያላቹህ ያሉ ሲሆን ነጻነቱም እንደሚገባቸው ተናግረዋል ነገር ግን ከአመታት በኋላ እነዚሁ የህወሀት ባለስልጣናት እናቶቻቸውን ሁሉ ያስደሰተውን መልካ ግኑኝነት ወደኋላ ብለው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ተፈጠረ ተባለ እና ከ 78000 በላይ ወጣት ኢትዮጵያዊያን እንዲፈጁ ተደረገ ይህም ጠንካራ የነበረውን የኢትዮጵያ ወጣት እሳት ውስጥ የማገደ ብሎም የቀረው ጠንካራ ወጣት እንዲሰደድ ምክንያት የፈጠረ ሴራ ነበር በጦርነቱ መሀል መሪዎቻችን ምን ያደርጉ እንደነበር በቅርቡ ዊኪሊክስ ላይ ካየነው በኋላ ጦርነቱ የድንበር ሳይሆን ወጣት የማስፈጃ እንደነበር ለመረዳት ተችሏል፡፡

በአንድ ወቅት መሳሳት ልማዱ የሆነው ስብሀት ነጋ አዳልጦት በብሄራዊ ቲያትር የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ህዝቦች እጅግ የሚዋደዱ እና ወንድማማች ህዝቦች ናቸው ካለ በኋላ ኤርትራን የሚወር አንድ ሀገር ቢመጣ ቀድመን ጦራችንን ከኤርትራ ወንድሞቻችን ጋር እናሰልፋለን በማለት መናገሩን ለሚያስታውስ ግለሰብ ግን ህወሀት እና ሻአቢያ ተጣልተዋል የሚለው ብሂል እውነታነቱ ለኢቲቪ ተመልካች እንጂ ማሰብ ለሚችል ሰው መራር ቀልድ ነው የሚሆነው፡፡
ከሰሞኑ ደግሞ በኤርትራ የሚገኙ የት.ብ.ዴ.ን አባላት ነጻ እናወጣዋለን ያሉትን የትግራይ ህዝብ ነጻ ከማውጣት ይልቅ ወታደሮቻቸው አስመራ ውስጥ ኬላ ጠባቂ እንደሆነ በማህበራዊ ድህረ ገጾች አነበብኩ የተጠበኩት ነገር ስለሆነ ባይገርመኝም የወያኔን እድሜ እያራዘመን እንደሆነ ሲገባኝ ግን አዘንኩኝ በነገራችን ላይ የኤርትራ ተቃዋሚዎችንም ሰብስቦ በመያዝ ረድፍ ህወሀትም ለሻዐቢያ ውለታ እየሰራ እንደሆነ ጠጋ ብሎ የሻዐቢያ ተቃዋሚዎችን ያነጋገረ ግለሰብ የሚረዳው ሀቅ ነው፡፡
ስለ ሻአቢያ ደህንነት ከህወሀት በላይ የሚጨነቅ ሊኖር ይችላል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው ሻዐቢያ ማለት ለህወሀት ዘብ ነው ህወሀት ለሻዐቢያም እንደዛው እናም ከሻዐቢያ ጋር በመወዳጀት ወያኔን እንጥላለን ሀገራችንንም ነፃ እናወጣለን ማለት ሞኝነት ስለሆነ ቆም ብለን አካሄዳችንን ማሳመር ይኖርብናል፡፡
ሁኔ አቢሲኒያዊ
ከፒተርቦሮው ዩ.ኬ

ወያኔ ቅዠት እንጂ ራዕይ የለውም!


ትላንት የተናገሩትን ዛሬ፤ ዛሬ የተናገሩትን ነገ የማይደግሙ ከሀዲ አንባገነን እና ዘረኛ ቡድኖች የስልጣን ኮረቻ በሀይል ከተፈናጠቱበት እለት ጀምሮ የተለያዩ የማወናበጃ ዘዴዎችን እየተጠቀሙ የበርካታ ንጹሀን ዜጎችን ህይወት ቀጥፈዋል አስቀጥፈዋል፡፡እንኳን እንደጠላት የሚቆጥሩትንና በመርሃ ግብራቸው ነድፈው መጥፋት አለበት ብለው የፈረጁትን ህዝብ ቀርቶ አርነት እናወጣሀለን እያሉ ክእናንተ በመፈጠራችን ኮራንባችሁ የሚሏቸውን የትግራይን ንጹሀን ዜጎች ሳይቀር የራሳቸውን የስልጣን ዕድሜ ለማራዘም ውድ ህይወታቸውን እንዲገብሩ አድርገዋል፡፡ የሀውዚንን ጭፍጨፋ አቀናብረዋል፣በ1991ዓ.ም በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል በተደረገው ጦርነት ከ70000 በላይ የጠርነቱ ሰለባ ሁነዋል፡፡አልሻባብን ለመደምስስ በሚል በሶማሊያ በረሃ የረገፉትን ወታደሮች ቤት ይቁጠራቸው፡፡ስልጣን ለወያኔ ከምንም ነገር በላይ ነው፡፡ ስልጣን ከሉአላዊነት፣ከባህር በር ፣ከሀገርና ከህዝብ እንደሚበልጥባቸው ከመጀመሪያው ጀምሮ የወሰዷቸው እርምጃዎች ማሳያ ናቸው፡፡የገንዛ ሀገሩን ቆርሶ ለሱዳን የሚሰጥ፣የባህርበር አያስፈልገኝም የአሰብን ወደብ ውሰዱት፣ኤርትራ እንድትገነጠል ፈቅጃለሁና እውቅና ስጡልኝ እባካችሁ እያለ የአለም መንግትታትን የተማጸነ፣የገንዛ ዞጎቹን አፈናቅሎ ለውጭ ባለ ሀብቶች መሬታቸውን የሚሰጥ፤የሀገሪቱን ሀብት ለተደራጁ ወንበዴወች የሚያስዘርፍና የሚዘርፍ፤ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦችን አጥፍቼ ታላቋን ትግራይን እመሰርታለሁ ብሎ የሚንቀሳቀስ አንባገነን እንዴት ያለ ሀገራዊ ራዕይ ነው የሚኖረው፡፡

ዘረኛው መንግስት በተለያዩ ጊዜያት እንዱን ብሄር በሌላው ብሄር ላይ በማነሳሳት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩት ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው ሀብትና ንብረታቸውን ተዘርፈው ለከፍተኛ ችግር ሲዳረጉ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ለእልፈት ተዳርገዋል፡፡የፖለቲካ ፓርቲዎችና ጋዜጠኞችን በሽብር ስም እያሰረ ንጹሀንን ሲያሸብር ቆይቷል፡፡በርካታ ፓርቲዎች በሰርጎ ገብ ሰላዮች የተነሳ ይዘውት የተነሱትን አላማ እና የህዝብ አደራ እዳር ሳያደርሱ በጅምር ቀርተዋል፡፡በወያኔ መሰሪ ተንኮል በተቀነባበረ ሴራ ጦርነት ውስጥ ያልገባ ክልልና ብሄር ባይገኝም ውጤቱ እንደሚፈልጉት ስላልሆነላቸው እና የኢትዮጵያ ህዝቦችም ባላቸው አርቆ አስተዋይነትና ረጅም ጊዜ በሰላም አብሮ የመኖር ባህሉ በመታገዝ የፕሮፖጋንዳቸው ሰለባ ባለመሆናቸው ለወያኔዎች ትልቅ ራስ ምታት ጥሮባቸዋል፡፡እስካሁን ሲጫወትበት የነበረውን ካርድም እንዲቀይርም ተገዷል፡፡ አዲሱ የመጫወቻ ካርድም ከብሄር ግጭት ወደ ሐይማኖታዊ ግጭት ለማሸጋገርም የሚያስችለውን “ጀሀዳዊ ሀረካት”የተሰኘ ዘጋቢ ፊልም በመስራት ከ1500 አመት በላይ አብረው የኖሩትን ሁለቱን ታላላቅ እምነቶች ማለቂያ ወደሌለው ጦረነት በመማገድ የስልጣን ጊዜውን ለማራዘም ቢምክርም እናንተ ከመጣችሁት ገና 21 ዓመታችሁ ነው እኛ ደግም ለረጅም ጊዜ በፍቅር አብረን ኑረናል፤ የጋራ ጠላታችን ዘረኛው ወያኔ ነው፡፡እኛ ከእነሱ እንሻላለን አንለያይም እያሉ በየአደባባዮ አንገት ላንገት ተቃቅፈው እየተላቀሱ ቁጭታቸውን ሲገልጹ መመልከት የተለመደ ተግባር ነው፡፡ሰሞኑን ለኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕርግራም ሙኒክ ላይ የታየውም ህብረት የዚሁ አካል ነው፡፡

እንዴት እንደ ኢትዮጵያ ያለች ታላቅ ሀገር እና እንደ ኢትዮጵያውያን ያሉ ቀደምት ህዝቦች እንደ ወያኔ ባሉ ትንሽ ሰዎች ይገዛሉ?እንዴት የአለም ማህበረሰብ በሀሰት የወያኔ ፕሮፖጋንዳ ሲታለል ይኖራል?እስከመቼ ብቻቸውን በምርጫ ተወዳድረው አሸነፍን እያሉ ሲያላግጡ ይኖራሉ? ወያኔዎችስ በቀጣይ ምን የማደናገሪያ ስልት ያመጡ ይሆን? እኔ በበኩሌ በቃ ብያለሁ፡፡ ወያኔ ራዕይ የለውም ኑሮትም አያውቅም፤ ወደፊትም አይኖረውም፡፡የወያኔ ሀገር እና ህዝብ የማውደም ቅዠት እንጂ ሀገራዊ ራዕይ ብሎ ነገር አያውቅም፡፡በጋራ ጠላታችን ላይ በጋራ እንነሳ!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

Saturday, February 8, 2014

December 10/2013
ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ
ለአንድ ሀገር የሚያስፈልገው ዋንኛው እና ቁልፉ ነገር ሰላም እና ነጻነት ነው:: ሰላም እና ነጻነት በሌለበት ሀገር የሚኖሩ ዜጓች፣   መብታቸው ይረገጣል ፣ ነጻነታቸው ይታፈናል  ዜጓች ለእስር፣ ለሞት፣ እና ለስደት ይደጋሉ:: ማንኛውም ሰው በሚኖርበት ሀገር በሚኖርበት ሰፈር ወይም አካባቢ እና በሚኖርበት ቤት ውስጥ በሰላም እና በነጻነት መኖርን ይፈልጋል::ነጻነት በምንም ዋጋ ሊተመን የማይችል ትልቅ ጸጋ ነው:: የሰው ልጆች በነጻነት በሚኖሩበት ሀገር መብታቸውን አስከብረው እና መብታቸው ተከብሮላቸው በሰላም እና በፍቅር በሀገራቸው ላይ ሲኖሩ ይታያሉ:: እንደ አለመታደል ሆኖ ሀገራችን ኢትዮጵያ በአለም ላይ ካሉት ሀገራት በግንባር ቀደምነት  የሰው ልጆች ነጻነታቸውን እና መብታቸውን የሚገፈፉበት ሀገር፣ የሀገሪቷ ዜጓች በጨቋኙ ገዥ ስርዓት ነጻነታቸውን ተገፈው ባሪያ ሆነው የሚኖሩበት ሀገር እንደሆነች በየጊዚው የሚወጡ አለም አቀፍ ሪፖርቶች ያስረዳሉ:: ወያኔ ኢህአዲግ የስልጣን ወንበሩን በሀይል ከተቆናጠጠበት ጊዜ ጀምሮ በየጊዜው በህዝባችን ላይ የሚያደርሰው ግፍ እና ጭቆና እየጨመረ መምጣቱ በአደባባይ የሚታይ እውነታ ነው:: ከዚህም የተነሳ በሀገራቸው ላይ የነጻነትን ሀየር መተንፈስ ያልቻሉ በየትኛውም ክልል ላይ የሚገኙ የሀገሪቷ ዚጓች በሀገራቸው ላይ መማር፣ መስራት፣ እና መኖርን እየቻሉ በሀገሪቷ ላይ እየተካሄደ ካለው አፋኝ እና ጨቋኙ ወያኔያዊ ስርዓገበሬው፣  ተማሪው፣  ፣ አስተማሪው ፣ ነጋዲው፣ ጋዜጠኛው ፣ ስፖርተኛው፣ ዘፋኙ፣ አርቲስቱ፣ ወዘተ...... በሁሉም እርከን ላይ የሚገኛው የህብረተሰብ ክፍል ሀገሩ ላይ በሰላም እና በነጻነት መኖርን ስላልቻለ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ በየጊዜው ለስደት ሲዳረግ ይታያል  :: ዋናው እና ወሳኙ ነገር ግን ከሁለት አስርት አመታት በላይ የዜጓችን መብት እያፈነ እና ነጻነታቸውን እየረገጠ ህዝባችንን ለስደት እያደረገ ያለውን ያለውን ይኼን ሰይጣናዊ እና አረመናዊን የወያኔን ስርዓት እንዴት እና ማን ያስወግደው የብዙዎቻችን ነጻነትን እና ፍትህን ናፋቂ ኢትዮጵያኖች ጥያቄ ነው ::

ት የተነሳ ሀገራቸውን እየጣሉ ይሰደዳሉ :: ማንኛውም ሰው ሀገሩን ጥሉ መሰደትን የሚፈልግ ያለ አይመስለኝም በሀገሩ ላይ በነጻነት እና በሰላም መማር መስራት እና መኖርን እስከቻለ ድረስ ::በአንድ ሀገር ላይ መልካም የሆነ መንግስታዊ አስተዳደር የማይካሂድ ከሆነ  አብዛኛውን ጊዜ ዜጓች ለስደት ይደረጋሉ በኢትዮጵያም እየሆነ ያለው ይህ ነው በአሁኑ ሰአት ለስደት የሚዳረገው የሀገራችን ዜጋ ሁሉም የማእበረሰብ ክፍል ነው::

በርግጥ በአሁኑ ሰአት ይህንን ስርዓት በመቃወም በሀገር ቤትም ከ ሀገር ቤትም ውጭ ብዙ የፖለቲካ ድርጅቶች እንደተቋቋሙ እና በተለያየ መንገድ እራሳቸውን እያደራጁ   እንዳሉ የምናየው እና የምንሰማው ነገር ሲሆን::የእነዚሀ  የፖለቲካ ድርጅቶች መብዛት የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ  ሁላችንም በሀገራችን ላይ እንዲሆንልን የምንመኘውን እና የምንናፍቀውን የወያኔን መንግስት አስወግዱ ፍትህ፣ ሰላምን እና ነጻነትን  ያመጣልን ይሆን? የብዙዎቻችን ጥያቄ ይመስለኛል::

 እንደእኔ እንደእኔ በየጌዜው ቁጥራቸው እየጨመረ የሚመጣው የፖለቲካ ድርጅቶች መብዛት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላሙን እና ነጻነቱን ያመጣል የሚለው እመነቱ ባይኖረኝም ብዙም ተቀውሞ የለኝም :: ዋናው አላማ የወያኔን መንግስት ለመቃወም የተቋቋሙ የፖለቲካ ድርጅቶች ለተነሱለት ዓላማ በእውነተኛ ትግል ውስጥ  እስከሚገኙ ድረስ ምንም ጉዳት የለውም ::  ነገር ግን በአንዳንድ  የተቀዋሚ ፖለቲካ ድርጀቶች መካካል እየሆነ እና እያየነው ያለው ነገር አንባ ገነኑን የወያኔ ኢህአዲግን ስርአት ለመቃወም የተነሱ ማንኛውም የተቀዋሚ ድርጅቶች እራሳቸውን እንዲፈትሹ የሚገፋፋ ነገር ነው :: ይህን ያሉኩበትም ምክንያት አለኝ አንዳንዶች የፖለቲካ ድርጅቶች ለምን ዓላማ እንደተነሱ እንኮን የተነሱበትን ዓላማ የዘነጉት ይመስለኛል ምክንያቱም በአሁኑ ሰአት ሁሉም ሰው ሆነ ማንኛውም የተቃዋሚ ድርጅቶች ሊዋጋው እና ሊታገለው የሚገባ ትልቁ ቁጥር አንድ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላት የወያኔ ኢህአዲግ መንግስት መሆን ሲገባው በአንዳንድ የተቃዋሚ ድርጅቶች እንደምናየው አንዱ የሌላውን ትግል ማንቆሸሽ እና ማጣጣል አላስፈላጊ እና ለነጻነት ለምናደርገው ትግል እንቅፋት የሚሆን ይመስለኛል::

በርግጥ በአሁኑ ሰአት ከሀገር ውጭ ሆነው እራሳቸውን መስዕዋት በማድረግ የወያኔን መንግስት እየተፋለሙ ያሉ ድርጅቶች ከሌሎች አጋሮቻቸው ጋር ጥምረትን በመፍጠር እና አብሮ በመታገል ዘረኛውን የወያኔን መንግስት በቁርጠኝነት እየተፋለሙት እና የወያኔን መንግስት እያስደነበሩት እንደለ የምንሰማው ዜና እሰየው የሚያስብል እና በርቱ የሚያሰኝ ቢሆንም ገና ግን ይቀራል ባይ ነኝ:: የጠላቴ ጠላት ወዳጂ ነው እንደሚባለው ማንም የፖለቲካ ድርጅት በማንኛውም መንገድ እና ማንኛውንም ስልት በመጠቀም ይሁን  የወያኔን እርኩስ ድርጊት ለመቃወም እስከተነሳ ድረስ ልንደገፈው እና ልናበረታታው ይገባል ባይ ነኝ :: እያንዳንዱ የፖለቲካ ድርጅት ወያኔን የሚታገልበት እና ወያኔን በመረጥኩት በዚህ መንገድ ብሂድ እና ብታገል እጥለዋለው ብሏ የሚያምንበት የእራሱ የሆነ እቅድ እና አላማ ሊኖረው ይችላል ነገር ግን ማንኛውም የተቃዋሚ የፓለቲካ ድርጅት በእኔ መንገድ እሳካልሂዱ ድርስ ብሎ ትክክል አንዳይደሉ መቁጠር  አግባብ የሆነ አይመስለኝም:: የትኛውም  የፖለቲካ ድርጅት በየትኛውም መንገድ ይሁን ይታገል እያንዳንዳችን ትኩረት ማድረግ ያለብን የጋራ ጠላታችንን የወያኔን መንግስት እና ስርዓት በጋራ ሆነን በአንድነት በመረባረብ ማስወገድ ለማያቋርጥ ሰላም እና ለዘለቂታዊ ነጻነት ወሳኝ ነው ባይ ነኝ:: በተናጥል እና እያንዳንዱ የተቃዋሚ ድርጅት ብቻውን የሚያደርገው ትግል የትም አያደርሰውም ምን አልባት ጊዚያዊ ድልን ሊያገኝ ይችል ይሆናል ግን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ጨቋኙን የወያኔንን ስርአት አስወግዶ ዘለቂታ ያለው ሰላም እና ነጻነትን በሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ ለማምጣት  በህብረት መታገል ይጠበቅብናል እያልኩኝ ይኼን አረመናዊ የወያኔን ስርዓት በጽናት እና በቁርጠኝነት እየታገላችው ያላችው የፖለቲካ ድርጅቶች የተነሳችውለት ዓላም የወያኔ ስርዓት እስኪወገድ ድረስ እጅ ለእጅ በመያያዝ በጋራ ትግላችውን አጠንክሩ ነጻነት እና ሰላም በሀገሩ ላይ የናፈቀው የኢትዮጵያ ህዝብ የወያኔ የዘር ፖለቲካ ሳይዘው አማራው ፣ጉራጌው፣ ኦሮሞው፣ ትግሪው፣ጋምቤላው ወዘተ ...... መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከጓናችው ይቋማል ባይ ነኝ::

ኢትዮጵያ በቆራጥ ልጆቿ ትግል ነፃ ትሆናለች!

ግን እስከ መቼ?



ሰሞኑን በሳውድ አረብያ በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ዘግናኝ እና አረመናዊ ድርጌት ከመቼውም ጌዜ በላይ ልቤን ክፉኛ ነው የሰበረው::

ወያኔ በባሕርይው ጅብና ውሻ ነው:: (ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ)

February 8 / 2014

አውሬ አውሬነቱን አይረሳም” አለ ልበል ተወልደ (ተቦርነ) ስለአንበሣው ቀላቢውን መግደል ሲያወራ አሁን? አዎ፣ ብሏል፡፡ እውነት ነው ፤ አውሬ አውሬነቱን አይረሳም፡፡ ወያኔም ወያኔነቱን አይረሳም – እባብ የትምና መቼም ቢሆን እባብነቱንና የወጣበትን ጉድጓድ እንደማይረሣ ሁሉ፡፡ ወያኔ ፀረ-ኢትዮጵያ ነው፤ ወያኔ ፀረ-አማራ ነው፤ ወያኔ ፀረ-ሃይማኖት ነው፤ ወያኔ ፀረ-ሰላምና ፀረ-ዴምክራሲ ነው፡፡ ወያኔ ኢትዮጵያንና ትውፊቶቿን ለማጥፋት የተነሱ የውጭ ኃይላት ብቸኛ ወኪል ነው - ‹የአድኅሮት ኃይላት ተላላኪ፣ የኢምፔሪያሊዝምና የቢሮክራሲያዊ ካፒታሊዝም አራማጅ ቅጥረኛ› ልበልና የደርግን ዘመን አብዮታዊ ትዝታ ልቀስቅስባችሁ ይሆን? ወያኔ እነኚህን መሰሎቹን የተፈጥሮ ሣይሆን የተጋቦት ባሕርያቱን መቼም አይረሳም - ቢጠግብም - ቢወፍርም -አገርና አካባቢ ቢለውጥም - እርስ በርሱ ቢጣላም - በሎሚ ተራ ተራ አንዱ አንዱን ቢያስርና ቢገርፍም - በማንኛውም ረገድ ወያኔ የተነሣበትን የወያኔነት ጠባይና ምግባሩን አይረሳም፡፡

 በዚያ ላይ ደግሞ ሰውን ጨምሮ በብዙ እንስሳት የማይታይ አንድ እጅግ አስገራሚ ጠባይ አለው፤ ያም “አህያ ለአህያ ቢራገጥ ጥርስ አይሳበርም” እንዲሉ በወያኔዎች መካከል ደም እስከመቃባት የደረሰ ጠብና ቅራኔ በነሣም እንደቃል ኪዳን ሆኖ ወያኔ ወያኔን ለሌላ አካል አጋልጦ የማይሠጥ መሆኑ ነው፤ ለዚህም ነው አቶ ስዬ አብርሃ ለአሳሪው ለአቶ መለስ ዜናዊ ሞት ፍራሽ አንጥፎ ከነቤተሰቡ ልቅሶ ተቀምጦ እንደነበር መስማት የቻልነው - መቼም ስዬ እንደክርስቶስ መሓሪ ወይም እንደእግዚአብሔር ሁሉን ታጋሽና ቻይ ሆኖ ነው ብንል ራሱ ስዬ ይታዘበናል - ይህ አስገራሚ ክስተት ከዘረኝነትና ከጎጠኝነትጋር የተያያዘ መሆን አለበት፡፡ ይቅርታ ይደረግልኝና ያን ሁሉ ግፍና በደል በኔና በቤተሰቤ ያደረሰብኝ ደብረታቦሬ የ‹ሀገር መሪ› ቢሞት ከሞራልና ከሃይማኖት እንዲሁም ከባህል አንጻር በደስታ ጮቤ መርገጡ ቢቀርብኝ ማቅ መልበሱና ሀዘን መቀመጡ ግን በሟቹ የመቀለድ ያህል እንደሚያስመስልብኝ እገምታለሁና የምሞክረው አይመስለኝም፡፡ የነእንትና ነገር ግን ‹አታሃዛዚቡና› እንደተባለው ነው፡፡ እያልኩ ያለሁት በመለስም ሆነ በሌሎች ወያኔዎች የተበደሉ ወያኔዎች አይዘኑ አይደለም፡፡ ከፈለጉ ቅጥ ባለው መንገድ ማዘን ይችላሉ፤ በይሉኝታቢስነታቸው ቀጥለውበት ትዝብት ውስጥ መግባትን ከቁብ ካልጣፉት ደግሞ ፊታቸውን መንጨትና ሰባትም ዐሥራ አራትም ዓመት ከል መልበስ ይችላሉ፡፡ መጠቆም የፈለግሁት የነሱን ጠብ በውኃ እንደሚፀዳ ተራ ነገር የሚቆጥሩ ሲሆኑ፣ በሌሎች ላይ ቂምና የነገር ቁርሾ ከቋጠሩ ግን ባላጋራዎቻችን ናቸው ብለው የፈረጇቸውን ዕድለቢስ  ወገኖች መቀመቅ ካላስገቡ በቀላሉ የማይለቁ እጅግ ሲበዛ መርዘኛ መሆናቸውን ነው፡፡  

አለመለከፍ ማለት ቀድሞውን ወያኔን አለመሆን ወይም ወያኔን ሆኖ አለመፈጠር ነው እንጂ አንዴውኑ በወያኔነት ልምሻ ከተኮደኮዱ በኋላ የፈውሱ ነገር አዳጋች ነው - በተለይ እንዳሁኑ ዘመን ጊዜ እየነጎደ በሄደ መጠን የተፈጠሩበትን ዕለት እስከመራገም ለሚያደርስ አሰቃቂ የመጨረሻ ዕጣ ይዳርጋል፡፡ ከዚህ ከወያኔው ዓይነት የዘረኝነት ልክፍት የሚፈወሱና ጤነኛ ሰው የሚሆኑ - ጤነኛ ሆነውም አውቀው አምነውበትም ይሁን ሳያውቁ ተታልለው የበደሉትን ሀገርና ሕዝብ ለመካስ የሚተጉ እጅግ ጥቂቶች ናቸው - ያም እንደገና የመወለድ ያህል መታደል ነው - ለነሱም ለሀገርም፡፡ እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች ደግሞ የዕንቁ ያህል ውድ ናቸው፤ በቀላሉና የትም አናገኛቸውም፡፡ እናም እንግባባ - ወያኔ ወያኔነትን የትም ሆኖና በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ሆኖ  ለአፍታም አይዘነጋትም፡፡ መዘንጋት ለኅልውናው አደጋ እንደሆነ ያህል ስለሚቆጥረው ይመስለኛል፡፡ አንዲት ማረሚያ ቤት የምትገኝ  የወያኔ ወታደር ከዚህ በፊት በጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ላይ ፈጸመችው የተባለው አስነዋሪ የዘረኝነት ድርጊትም ከዚህ ጋር በቀጥታ የሚገናኝ ነው - ለዚህች ደንቆሮ ‹እሥረኛ› ወያኔነት ማለት የገነትም የመንግሥተ ሰማይም ገዢ ነው - ‹እሥር ቤቱና አሣሪዎቹ እኛው እስከሆን ድረስ፣ ገዢዎቹ እኛው እስከሆን ድረስ ይበልጥ እሥረኛ ሌሎች እንጂ እኛ አይደለንም› ብላ ሳታምን አልቀረችም(ይህ ዓይነቱ ከፍተኛ ሞኝነት የሚነበብበት የወያኔዎች አካሄድ የጆርጅ ኦርዌልን “All animals are equal, but some animals are more equal than the others.” የሚለውን ያስታውሰኛል፡፡) የብዙዎቹ ወያኔዎች መርሆ  እነዚህ ብሂሎች ልብ እንድንል ያደርጉናል፡- “የዘሬን ብተው ያንዘርዝረኝ”፣ “ትንሽ ሥጋ እንደመርፌ ትወጋ” ፤ “የሥጋ ትል የዘመድ ጥል” ፣ በእንግሊዝኛው ደግሞ  “Blood is thicker than water.”  ይህ የወያዎች ‹የዋህነት› የሚያሳየን ግን የእግዚአብሔርን መንገድና ትክክለኛውን ማኅበረሰብኣዊ የዕድገት ደረጃን ሣይሆን በዝቅተኛ የንቃትና የዕውቀት ደረጃ የሚገኙ የሌሎች እንስሳትን ነሲባዊ የመሳሳብ ጠባይ ነው፡፡ ሰው ከሰውነት ደረጃ ወርዶ እንዲህ ያለ የደምና የአጥንት ማነፍነፍ ቅሌት ውስጥ ሲገባ ማየት ደግሞ በማኅበረሰብም ይሁን በሀገር ደረጃ ከፍተኛ አለመታደልና የሀፍረት ምንጭም ነው፡፡
የተወልደ በየነ ንግግር እንደዐረብ ጣቢያ ድንገት ጣልቃ ገብቶብኝ በርሱ አባባል ጀመርኩ እንጂ አነሳሴ ቲቪ እያየሁ ሳለ በተጓዳኝ እያነበብኩት በነበረውና አሁን በጨረስኩት አንድ ድንቅ መጣጥፍ ላይ ተመርኩዤ የበኩሌን ጥቂት ለማት ነበረ፡፡ ይህን መጣጥፍ ያገኘሁት በዘሀበሻ ድረ ገጽ ላይ ነው - በፒዲኤፍ የቀረበና ከሰሞነኛ መጣጥፎች ቀልቤን ክፉኛ የሳበ ቆንጆ ጽሑፍ ነው፡፡ ይህ ግሩም ጽሑፍ የቀረበው ከአንድ በስደት ላይ እንደሚገኝ የገለጸ የቀድሞ የመንግሥት ሚዲያ ዘጋቢና የኮሚኒኬሽን ባለሙያ ነው፡፡ ጽሑፉ የሚያትተው ወደፊት መጽሐፍ ሆኖ ይወጣል ከተባለና አንድ የወያኔ ከፍተኛ ባለሥልጣን ይሄው የመንግሥት ሚዲያ ዘጋቢ ከሀገር ሊወጣ ሲል  ለሰባት ሰዓታት ያህል በመቅረፀ ድምጽ አጋዥነት ሰጠው ከተባለው የኑዛዜ ቃል ተቀንጭቦ የቀረበ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ ርዕሱ “በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ ከሚገኝ የልብ ወዳጄ ጋር በአገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያደረግሁት ምሥጢራዊ ውይይት” ይላል፡፡ ትንሽ ረዘም ቢልም መነበብ ያለበት ማለፊያ ጽሑፍ ነውና እባካችሁ አንብቡት - ሀገር በጣር ላይ እያለች ለማንበብ መድከም የለብንም፡፡ በተፋፋመ ጦርነት ውስጥ ገብቶ ለሀገር መዋደቅስ አለ አይደል? እየቀነጨብኩ ለፈርጥ ያህል በዚች መጣጥፍ ውስጥ በመጠኑ እንዳልጠቅስላችሁ ጽሑፉን ከፒዲኤፍ ወደወርድ ስለውጠው አንዳንድ ሆሄያት ቅርጻቸው እየተንሻፈፈብኝ ተቸገርኩ፡፡ ወያኔ ኢትዮጵያን ለማጥፋት የሚተገብራቸውን ሥልቶች ብዙዎቹን ታገኙበታላችሁ፡፡ ወያኔ የቱን ተመርኩዞ የቱን እንደሚያጠፋና ቀጥሎም አንዱን ለማጥፋት የተጠቀመበትን ምርኩዝ ሰባብሮ የትም እንደሚጥል - ባጭሩ ሕወሓት አስብቶ አራጅ መሆኑን ትረዱበታላችሁ›፡፡ በምታምኑት ይሁንባችሁና ግዴላችሁም አንብቡት!
ወያኔ በባሕርይው እንደጅብም፣ እንደውሻም፣ እንደዓሣማም፣ እንደእስስትም፣ እንደእባብም … ነው፡፡ ለወያኔ የባሕርይ መግለጫነት የማይሆኑ ርግብን የመሳሰሉ የዋሃን ፍጡራን ብቻ ናቸው፡፡ በተረፈ ወያኔ ማለት የክፋት ተምሳሌት የሆኑ የተፈጥሮም ይሁኑ ሰው ሠራሽ ነገሮች ውሁድ ሥሪት ነው፡፡ የክፋት አድማሱ ደግሞ ወሰን የለውም፡፡ ድንበር የለሽ ክፋት ደግሞ ድንበርን ተሻግሮ ብዙ ዘመናትን የማጣቀስ ጠባይ አለው፡፡ ለዚህ ነው የክፋት አምባሳደሩ ወያኔም ሞተ ሲሉት እየተነሳ በአፈ ታሪክ ዘጠኝ ነፍስ ያላት መሆኗ እንደሚወራላት ድመት እስካሁኒቷ ቅጽበት ድረስ በአፀደ ሕይወት ሊገኝ የቻለው፡፡
የወያኔ ውሻዊ ባሕርይ፡፡ ውሾች እርስ በርስ ሊዋደዱም ላይዋደዱም ይችላሉ፡፡ ግን ግን እነሱም ልክ እንደብዙዎቹ እንስሳት ዘር መንጣሪና ከ”species”ኣቸው ውጪ ከሌሎች ጋር እምብዝም አይቀላቀሉምና በአደንም ሆነ በሥሮት ወቅት  አይለያዩም፡፡ ወያኔዎች ከውሻ የወሰዱት ጠባይ ታዲያ ውሾች በግላቸው የፈለጉትን ያህል ይጣላሉ፣ ይነካከሳሉም እንጂ የውጪ ጠላትና የአደጋ ሥጋት ከተደቀነባቸው ቂጣቸውን ይገጥሙና ያን ጠላት በጋራ ይከላከላሉ፤ በክፉ ቀን በመካከላቸው ንፋስ አይገባም፡፡ አጥንት ላይ የተፋጠጡና የሰገሌን ጦርነት በውሻኛ “version” ሊደግሙት የተዘጋጁ ውሾች ሳይቀሩ ያን ሆድ-ተኮር ጠብ በጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት አቁመው የመጣባቸውን የጋራ ጠላት በጋራ ይጋፈጣሉ፤ በውነቱ ይህ መልካም ጠባይ ነው፡፡ በወያኔዎች ላይ ብቻ ተወስኖ መቅረቱና በሰባና ሰማንያ ሚሊዮን በሚገመተው አጠቃላዩ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲሁም በሌሎች የፖለቲካና ማኅበረሰብኣዊ ስብስቦች ዘንድ አለመሥራቱ ግን ያሳዝናል፤ ይቆጭማል፡፡ እነሱ ብልጥ ሲሆኑ ሌላው ጅላንፎ ሆኖ እስከወዲያናው በሚመስል ሁኔታ ሲጃጃል መታዘብ ትልቅ ቁጭት ነው፡፡ ከውሻ እንኳን መማር ያቃታቸው ኢትዮጵያውያን ተቃዋሚዎች ወያኔ በቀደዳለቸው የልዩነት መስመር እየተመሙ ለወያኔው ዕድሜ መራዘም ጠንክረው በመሥራት ላይ ይገኛሉ፡፡ መቼ ነፍስ እንደሚያውቁና ለከርታታው ‹ሕዝባቸው› መሢሕነታቸውን እንደሚያሳዩ አናውቅም፡፡ ውሻ በበጎም ሆነ በክፉ ብዙ ተጠቃሽ ባሕርያት ቢኖሩትም ለጊዜው ይህ በቂየ ነው፡፡
የወያኔ ጅባዊ ጠባይ፡፡ ጅብ ፈሪ ነው፡- ወያኔም በጣም ፈሪ ነው፡፡ ገደልኩት ብሎ የሚያምነውን ‹ጠላቱን› እንኳን የሚፈራና መቃብር ውስጥም ገብቶ ዐፅምን በምናባዊ የስድብና የምፀት ጅራፍ የሚገርፍ፣ በሙታንም ላይ የሚሣለቅና የሚቀልድ ነው - ወያኔ፡፡ ለምሳሌ አማራንና ኦርቶዶክስን ገድሎ እንደቀበራቸው በወያኔዊ መድረኮች ካላንዳች ሀፍረትና ይሉኝታ እየተደሰኮረ ነው፡፡ ግዴለም ሞቱ እንበል፡፡ በሕይወት ያሉ እየመሰለው ታዲያን በባነነ ቁጥር በሚናገራቸው የዕብሪት ቃላቱና በሚያከናውናቸው ፀረ-ሕዝብ ተግባራቱ  ለትዝብት እንደተዳረገ አለ ፡፡ ፍርሀት በራስ የመተማመን ችሎታን ያሳጣል፤ ፍርሀት ቤቱን የሠራበት ሰው እንደመለስ ተሳዳቢና አሽሟጣጭ ይሆናል፡፡ ፍርሀት ያሸነፉትን ጠላት እንዳላሸነፉት በማስቆጠር ቀን በእውን ሌት በውን እያስባተተና እያስቃዠ ወንጀለኛና ኃጢኣተኛ ያደርጋል፡፡ የወያኔ ወንጀል እየተቆለለ ሄዶ ለፍርድ አስቸጋሪ እስኪሆንበት ድረስ ፈጣሪን እያስጨነቀ ያለው እንግዲህ ከዚህ መሠረታዊ ምክንያት በመነጨ መሆን አለበት፡፡ እንዲያ ባይሆንስ ቁናው ከሞላ ሰንብቷል፡፡
ጅብ ሆዳም ነው፡፡ የጅብ ሆድ ደግሞ የሚመርጠው የለም፡፡ ያገኘውን እየሰለቀጠ ወደጎሬው ይገባል፡፡ የነጋበት ጅብ በተለይ አይጣል ነው፡፡ ወያኔ እንደዛሬው ሳይነጋበትም ሆነ እንደዱሮው በጊዜ ያገኘውን ሁሉ ማግበስበስ መነሻና መድረሻ ዋና ጠባዩ ነው፡፡ ወያኔ አይጠግብም - እምብርት የለውምና፡፡ ከመሰል ሰብኣዊ ጅቦች ጋር ሆኖ ኢትዮጵያን ራቁቷን እያስቀራት ያለ ወያኔ ነው፡፡ ጅብ ሆዳም ብቻ አይደለም፡፡ የብዙ ብልሹ ምግባራት ተምሳሌት ነው፡፡ ለአብነት እርስ በርሱ አይተማመንም፡፡ ከዚያም የተነሣ ሲሄድ እንኳን ፊትና ኋላ ሆኖ ሳይሆን ጎን ለጎን ሆኖ ነው ይባላል፤ በተለይ የቆሰለ ጅብ በመንጋው ውስጥ ካለ በጣም ካልተጠነቀቀ በስተቀር ከአህያ ያልተናነሰ ዕድል እንደሚገጥመው ይነገራል - በቁሙ ነው አሉ እሚዘረጥጡት፡፡ ወያኔም እንደዚሁ ነው፡፡ አይተማመኑም፤ እርስ በርስ ይበላላሉ፡፡ ተባልተው ተባልተው መጨረሻቸው ደርሷል እየተባለ ነው አሁን፡፡ ለሰው ማን እንዲህ ሹክ እንደሚለው አላውቅም፤ ግን ‹መዥገሩ ወያኔ በደም አብጦና በደም ሰክሮ ሊፈርጥና ሊበታተን ነው› እየተባለ በየቦታው ሲወራ እሰማለሁ - ወፍ ትሆናለች እንዲህ እያለች ምሥጢር እያወጣች ያለች - እንዳፏ ያድርግልን፡፡ ለመሆኑ ግና - መለስ ብለን መለስን ስናስታውስ የወዲ ዜናዊ ሠይፍ ያልቀላው ትላልቅና ትናንሽ ወያኔ አለ ወይ? እንዴ፣ ያልተቆረጠመ ሰው እኮ የለም፤ የመለስ ነዲድና ፍላጻ ሞኛሞኙንና ቅን ታዛዡን ብቻ መርጦ ትቷል፡፡ በልዩ ወርቃማ ዕድል ከዐይኑ የተሠወሩበት ጥቂት ብልጣብልጦችና አድርባዮች ለዘር እንዲተርፉ የመለስ ውቃቢ አምላክ ምሯቸው እንደሆነ እንጂ መለስ የፈጀው ሕዝብ እኮ በውነቱ ከግምት በላይ ነው፤ መለስ ዜናዊ? ኧሯ! በጊዜ መሰብሰቡ በጄ(ን/-ኣቸው(?)) እንጂ ከርሱ ሾተል ማን ሊተርፍ ይቻለው ነበር? በተለይ እሱ የወያኔ ባለሥልጣን ከሆነበት የብረት ትግሉ የመጀመሪያ ዓመታት ጀምሮ በዚህ ሰውዬ ሥውርና ግልጽ ትዕዛዝ እንዲሁም የሽርና የተንኮል ሤራ በመርዝና በጥይት ብዙ የወያኔ ታጋይ እንዳለቀ ለጉዳዩ ቅርበት ባላቸው ሃቀኛ ወገኖች የተጻፉ ድርሳናት ይመሰክራሉ - የገብረ መድኅን አርአያ ጽሑፎችን ያነቧል፡፡ ይሄ ሁሉ እየታወቀ ግን መለስን እስከማምለክ ተደርሷል - ምክንያቱም መለስን መቃወምና መንቀፍ ማለት ከጥቅምና ከጋርዮሽ ዘውጋዊ ቁርኝት ጋር ይጣረሳላ! ምክንያቱም መለስን መቃወም ማለት አሁን የተደረሰበትን የአንድ ብሔር ሸፋፋና ቅጥየለሽ “የበላይነት” ሊያሳጣ እንደሚችል ይታመናላ! ድንቄም የበላይነት! የበላይ የሆኑትስ እየተበደሉና እየተረገጡ የሚገኙት በርካታ ሚሊዮን ወገኖች ናቸው፡፡ የበላይ የሆኑትስ እየተራቡና እየተጠሙ፣ እየታረዙና እየታመሙ፣ እየተጋዙና እየተገደሉ፣ በእሥርና በስደት አሰቃቂ ሕይወትም መከራቸውን እየበሉ ያሉት ምሥኪኖች ናቸው፡፡ የበላይ የሆኑትስ በገዛ ሀገራቸው እንደሦስተኛና አራተኛ ዜጋ ተቆጥረው የማንኛውም የኢኮኖሚና የፖለቲካ መብታቸው ሳይከበርላቸው እንደከብት እንዲኖሩ የተገደዱ ትግሬውን ጨምሮ የየትኛውም ዘውግ አባላት ናቸው፡፡ የበላይ የሆኑትስ ለኅሊናቸው ያደሩና ሀገራቸውን ከወያኔ ጋር ተባብረው ያልሸጡ የሁሉም ዘውግ አባላት ወገኖቻችን ናቸው፡፡ ማን የበላይ ማን ደግሞ የበታች እንደሆነ በጊዜ ሂደት የምናየው ይሆናል፡፡ በጮማ ግሣትና በውስኪ ብስናት ሕዝብ ላይ እያቀረሹ መኖር የበላይነት መገለጫ ሳይሆን የአውሬነትና የእንስሳነት ጠባይ ማሳያ ነው፡፡ ኤዲያ … በቃኝ እባክሽ፤ አናጋሪዎች!
    ወያኔ ኢሕአዴግ ኢትዮጵያን በሀይል መግዛት ሕዝብን በአፈናና በእንግልት ማሰቃየት ከጀመረ ሀያ ሁለተኛ ዓመቱን ለማክበር ባለበት በዚ ጊዜ በኢትዮጵያ ላይ ብዙ ለውጦች እንዳመጣ እና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ወደ ተሻለ የእድገት ደረጀ እያመራ እንዳለ የሕዝቡም የኖሩ አቀጣጫ እንደተለወጠ አፉን ሞልቶ ሲናገር እንስመዋለን ወያኔ ኢሕአዴግ የፖለቲካ ስልጣኑን ለማስረዘመ ይህንን ይበል እንጅ ሀቆ ግን ይህ አይደለም በኢትዮጵያ ላይ የሚደረጉ አለም ዓቀፍ ጥናቶች እና አሀዞች እንደሚያሳዩት ወያኔ በስልጣን በቆየባቸው በእነዚህ ሁለት አስር ዓመታቶች በአገሪቷ ላይ አስከፊ ድህነት እንደሰፈነ ፣ የስራ አጥ ቁጥር እንዳሻቀበ እና ፣ ሰበዓዊ እና ፣ ዲሞክራሳዊ መብቶች ክብር አልባ ሆነው ፣ የገአሪቷ ዜጕች የኖሮ ደረጃ ከቀነ ወደ ቀን እንዳሽቆለቆለ ነው::

      ወያኔ ኢሕአዴግ በሀገሪቷ ላይ አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ እንደል ይለፍልፍ እንጂ አሁንም እየታየ ያለው ሀቅ ግን በአገሪቷ ላይ የአንድ ብሔር ብቻ የበላይነት የሚነጸባረቀበት መሪዎች የፖለቲካ ስልጣንን ለግል ጥቅም ማካበቻ የሚጠቀሙበት ዘረኛ እና ጨቆኝ ስርዓት የነገሰባት አገረ አንዶ ኢትዮጵያ ናት :: ይህንንም ብልሹ እና አስከፊ ስርዓት የሚቃወሞ እና የሚተቹ ሰዎች በማን አለብኝነት በወያኔ የግፍ በትር በየእስር ቤቱ በስቃይ መከራ  እየተንገላቱ እንደሚገኙ እና አብዛኛውም የአገሪቱ ሕዝቦች የተበላሸው የወያኔ ስርዓት በፈጠረው የኖሮም ሆነ የፖለቲካ ጫና በመሸሽ አገራቸውን ትተው ለስደት እና ለመከራ ሲዳረጉ የአብዛኞችም ሕይወት ያሰቡበት ሳይደርሱ አልፉል :: መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ኢትዮጵያ ሕዝብ በብዛት ከሚሰደድበት አገር ተርታ እንደምትመደብ እና ወያኔ አገሪቱን ወደተሻለ የእድገት ደረጃ እየመራ እንዳለ ይናገር እንንጂ አገሪቷ ግን ከታች ካሉ የደሃ አገሮች ግንባር ቀደም እንደሆነች እና አገሪቷ ወደመጥፎ አቅጣጫ እያመራች እንዳለነወ የሚያመለክተው::

  የዜጎች የመብት እረገጣ ፣ አፈና ፣ስቃይ  ከመቼውም በላቀ ጊዜ ላይ ይገኛል:: አገሪቷም በመጥፎ ሁኔታ ውስጥ ናት:: ለዚህም ነው የኢትዮጵያ ፊዲራላዊ አነድነት መድረክ መጋቢት 17 ቀን 2005 የአገሪቱን ጊዚያዊ ሁኔታ አስመልከቷ  በሰጠው ጋዚጣዊ መግለጫ ላይ  አገሪቱ መስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች ያለው::

   አሁን ላይ እንደሚታየው አገሪቷ ተጨባጭ ሁኔታ በጣም አስከፊ እና አሳሳሳቢ ሁኔታ ላይ ነው ::  ለተቀዋሚ የፖለቲካ ድርጅቷች ደግሞ  ጥሩ መነሳሳት የሚሆን አጋጣሚ  እና በወያኔ መንግስት ላይ ስር ነቀል ርምጃ ለመውሰድ የሚነሳሱበት ወቅት ነው :: በርግጥ  በአሁኑ ሰዓት በወያኔ ኢሕአዴግ መካከል አይለኛ የሆነ የእርስ በእርስ ሽኩቻ እና እርስ በእርስ የመናናቅ ፣ ያለመከባባር እና የመከፋፈል ትርምስ እንዳለ ለከፍተኛ ባለስልጣን ሳይቀር በድርጅቶ ውስጥ እየሆነ ያለው ሁኔታ አሳሳቤ እንደሆነባቸው ምንጮች ገልጸዋል:: ይህ ሁሉ የሚያሳየው የወያኔ ኢሕአዴግ የስልጣን ዘመን እየተፍረከረከ መምጣቱን ነው :: በአሁኑ ሰዓት የወያኔ ካድሪዎች ተደናግጠዋል ምን እየሰሩ እንዳለ እንኮን አያውቆትም ሰሞኑን በባሕር ዳር በተካኤደው ዘጠነኛው የኢሕአዴግ ጉባኤ ላይ የየነው ይህንኑ ነው::

   የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር ባለቤት አዜብ መስፍን ባለቤታቸው ያገኘው ሰለነበረው የወር ደሞዝ ስትናገር በጣም አሳፋሪ እና ሴትየዋንም ለትዝብት የሚዳርጋት ንግግር ነበር የተናገረቸው :: አንዳንድ የፖለቲካ ሰዎች እንደሚሉት ሴትየዋ ይህን ንግግር ልትናገር የቻለችበት ምክንያት ኢሕአዴግ ውስጥ አዲስ የተሹሞትን ሰዎች በነገር ሸንቆጥ ለማድረግ እንደሆነ




የአንድነት መሪዎች መታሰርን አይፈሩም – ግርማ ካሳ

February 8/2014

አዲሱ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ግዛቸዉ ሽፈራዉ፣ ለገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ የሰላምና የእርቅ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል። «ኢሕአዴግ እኛን እንደ ጠላት እና ሽብርተኛ ማየቱን ማቆም አለበት። እኛም ደግሞ ኢሕአዴግን እንደ አዉሬ ማየት ማቆም አለብን። ከጥላቻ ፖለቲካ በመዉጣት ችግሮቻችንን በሰላም መፍታት መማር አለብን» ሲሉ ነበር፣ ለአገር በሚጠቅሙ በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ከኢሕአዴግ ጋር ለመስራት፣ ያሉትን ልዩነቶችን በዉይይት ለመፍታት አንድነት ፍላጎት እንዳለው የገለጹት።
ይህ የአንድነት ዘመናዊ፣ የሰለጠነ፣ የፍቅርና የመግባባት ፖለቲካ፣ በኢህአዴግ ዉስጥ ያሉ ሞደሬቶችን ሳይቀር፣ አብዛኛዉን ኢትዮጵያዊ ያስደሰተ ቢሆንም፣ ስልጣኑን በያዙ በኢሕአዴግ አክራሪዎች ዘንድ ግን የተገኘዉ የአጸፋ ምላሽ የሚያስደስት አይደለም። ገዥዊ ፓርቲ ኢሕአዴግ ፣ አሁንም የአንድነት ፓርቲን እንደ ጠላት በማየት ፣ አንድነትን ለማዳከም አሳዛኝና አሳፋሪ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ነዉ። ወደ መሃል መጥተዉ፣ ለዉይይት ይዘጋጃሉ ብለን ስንጠብቅ፣ ጭራሹኑ እያከረሩ ነዉ። የታሰሩ የሕሊና እስረኞቹን ይፈታሉ ብለን ስንጠብቅ፣ ጭራሽ የጊዜ ገደባቸው የጨረሱ እንደ አቶ በቀለ ገርባ ያሉ እስረኞችን አንፈታም እያሉ ነዉ። ጭራሽ ሌሎች ሰላማዊ የፖለቲካ ታጋዮችን በተለይም ከአንድነት ፓርቲ እያሰሩና ለማሰርም እየተዘጋጁ ነዉ።
ለረዥም ጊዜ የአንድነት ፓርቲ ዋና ጸሃፊ ሆነው ያገለገሉትና፣ አሁን ደግሞ የብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት፣ አቶ አስራት ጣሴ በአሁኑ ጊዜ ታስረዋል። የታሰሩት በአንድ ጋዜጣ ላይ፣ «በፍርድ ቤቶች ፍርድ ማግኘት አይቻልም» በማለታቸው ነዉ። እዉነትን በመናገራቸው።
የአንድነት ልሳን ፍኖት ጋዜጣም፣ በፍትህ ሚኒስቴር ዉስጥ ያሉትን ምንጮች በመጥቀስ፣ በኢሕአዴግ ጽ/ቤት ትእዛዝ፣ አቶ ዳንኤል ተፈራ እንዲሁም ሌሎች የአንድነት አመራር አባላትን ለማሰር የክስ ሰነድ እንደተዘጋጀም ዘግቧል።
ይህ የአንድነት አመራር አባላትን ለማሰርና ለማዋከብ የሚደረገዉ ጥረት፣ ምክንያቱ አንድና አንድ ነዉ። ኢሕአዴግ፣ የአንድነት ፓርቲ አሰላለፍ በጣም ስላሰጋዉ፣ መሪዎችን በማሰርና የፓርቲዉን አባላትና ደጋፊዎች በማስፈራራት፣ ፓርቲዉን ከወዲሁ ለማዳከም ነዉ።
የአንድነት ፓርቲ በአሁኑ ወቅት፡
1) ከሰማያዊና ከኤዴፓ በስተቀር፣ ከበርካታ ደርጅቶች ጋር ለመዋሃድ ትልቅ ሥራ እየሰራ ነዉ። በተለይም ከመኢአድ እና ከአራና ጋር ዉይይቱ ሥር የሰደደ ይመስላል።
2) በአድዋ ከተማና በአዲስ አበባ፣ የአድዋን ድል በአል ለማክበር፣ እንዲሁም፣ በአማራዉ ክልል የሚኖረዉን ሕዝብ የተሳደቡ የብአዴን አመራር አባል ለፍርድ እንዲቀርቡ የሚጠይቅ፣ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በባህር ዳር ለማድረግ አቅዷል።
3) የሚሊየነም ድምጽ ለነጻነት ክፍል ሁለት ዘመቻ በቅርብ ጊዜ ዉስጥ ይፋ ለማድረግ በዝግጅት እንዳለ ይነገራል።
እነዚህና የመሳሰሉት የአንድነት እንቅስቃሴዎች፣ የፖለቲካዉን አስተላለፍ በእጅጉ የሚቀየሩ እንደመሆናቸው፣ በገዢው ፓርቲ ዉስጥ ያሉ ፖሊሲ አዉጭዎችን ማሳሰቡ አያስገርምም። አንድነት፣ የኢሕአዴግ ስርዓት ለመቀየር ና ለዉጥ ለማምጣት ሰላማዊና ሕግን በተከተለ መንገድ ስራዉን ሲሰራ፣ ኢሕአዴጎችም በስልጣናቸው ለመቆየት የራሳቸዉን ሥራ መስራት የሚጠበቅ ነዉ። የሚያወቁትና የለመደባቸው ደግሞ ዜጎችን ማሰርና ማዋረድ ስለሆነ ይኸዉ እያሰሩ ነዉ።
ይህ በኢሕአዴግ፣ አመራር አባላቱን በማሰር አንድነቶች ለማስፈራራት የሚደረገዉ እንቅስቃሴ የሚሰራ ግን አይመስለኝም። የአንድነት ፓርቲ መሪዎች፣ ትግሉን ሲቀላቀሉ፣ እንደሚታሰሩ፣ ሊገደሉ እንደሚችሉ በማወቅ ነዉ። በብርቱካን ሚደቅሳ፣ በአንዱዋለም፣ በእስክንደር ነጋ …የሆነዉን ያውቃሉ። ነገር ግን ከምቾታቸዉና ከጥቅማቸው ይልቅ አገራቸውን ያስቀደሙ በመሆናቸው ፣ ለእስራቱም ሆነ ሊመጣ ለሚችለው መከራ የተዘጋጁ ይመስላል።
እንግዲህ መልእክቴ ይሄ ነው። ኢሕአዴግ በአንድነት ፓርቲ ላይ በአንድ በኩል የያዘዉን ጠመንጃ ተጠቅሞ ጫና ሲያሳደር፣ አገር ቤት ያሉ ታጋዮች ሕይወታቸውን መስመር ላይ አድርገዉ ዋጋ ለመክፈል ሲዘጋጁ፣ እኛ ደግሞ የአንድነት ፓርቲን ከመቼዉም ጊዜ በበለጠ በመርዳትና በመደገፍ ማጠናከር አለብን። የአራት ኪሎ ባለስልጣናት በያዙት ዱላ ይተማመናሉ። አንድነት፣ በኔ እና በ እናንት፣ በኛ ፣ አገር ቤት ባለነውም ሆነ በዉጭ በምንኖር ፣ በኢትዮጵያ ህዝብ ጉልበት ይተመመናል።
እንግዲህ ጨዋታዉ ተጀምሯል። ፊሽካዉ ተነፍቷል። ተስፋ ቆርጠን፣ «አይቻልም» ብለን ሜዳዉን ለቀን ከወጣን በፎርፌ ዜሮ ገባን ማለት ነዉ። ነገር ግን ዝምታ፣ ተስፋ መቁረጥ አይሁን። ሁላችንም የድርሻችንን እንወጣ።
ለኢሕአዴጎች ይህንን እላለሁ። «ጸሃይ ሳትጠልቅ ቀናዉን ነገር ማድረግ ተማሩ። ትንሽ እንኳ የሰላም ነገር ልባችሁ ይግባ። ይህ በሌሎች ላይ የመዘዛችሁት ሰይፍ መልሶ እናንተኑ ነዉ ስለሚበላችሁ ሰይፋችሁን ወደ ሰገባው መለሱና ለሰላም እጆቻችሁን ዘርጉ»

“የአቶ አስራት ጣሴ እስር ፖለቲካዊ እንደምታ ያለው ይመስላል” – አቶ ተክሌ በቀለ

February 8/2014

(ፍኖተ ነፃነት) አንድነት ፓርቲ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት “አኬልዳማ” በሚል ርዕስ ያቀረበው ዶክመንተሪ ፊልም የፓርቲያችንን ስም ያጎደፈ ነው በሚል የከፈተው ክስ በሂደት ላይ እያለ ዶክመንተሪ ፊልሙ በድጋሚ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መታየቱን በማውገዝ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት የፃፉትን የግል አስተያየት ተከትሎ “በፍርድ ቤቱ ላይ ዘለፋ” ሰንዝረዋል በሚል ለእስር መዳረጋቸው ፖለቲካዊ አንድምታ እንዳለው ተጠቆመ፡፡


                                            አቶ አስራት ጣሴ

የአቶ አስራት የህግ ጠበቃ አቶ ተማም አባ ቡልጉ በትላንትናው ዕለት ጥር 30 ቀን 2006 ዓ.ም በዋለው ችሎት በቅድሚያ የስነ -ስርአት ጥያቄ ለማቅረብ እንዲፈቀድላቸዉ በመጠየቅ የሚከተለዉን የስነ-ስርአት ጥያቄ አቅርበዋል “ደንበኛዬ የተጠሩበት መንገድ ላይ የስነ-ስርአት ጥያቄ አለኝ ፡፡ በችሎት ያልነበሩ ሰውን በሌላ ቦታና መጽሔት በሰጡት አስተያየት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 480 ሊጠየቁ አይገባም” ብለዋል ፡፡ አስከትለውም የተጠቀሰውን አንቀፅ ቃል በቃል በማንበብ በአንቀፁ ሊጠየቁ የሚገባቸው በችሎት ተገኝተው የፍርድ ቤቱን ሂደት ያወኩ እንደሆነ ብቻ መሆኑን በማስመር “የኔን ደንበኛ ከውጪ ተጠርተው መጠየቅ አይችሉም፤ ደንበኛዬ ብዚህ ችሎት ተማጋች አይደሉም በስፍራውም አልነበሩም፤ ጥፋት ሰርተዋል ቢባል እንኳን በዚህ አንቀፅ ሊጠየቁ አይገባም ፡፡” በማለት ተከራክረዋል፡፡


ሆኖም የጠበቃውን መከራከሪያ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ፍርድ ቤቱ ባለመቀበሉ አቶ አስራት ስለተጠሩበት ጉዳይ ጠበቃ ተማም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በምላሻቸውም “ደንበኛዬ ይህን ችሎት በተለየ በሚመለከት አልፃፉም፤ አቶ አስራት የገለፁት አጠቃላይ እውነታን ነው፡፡ ኢህአዴግ ስላቋቋማቸው ፍርድ ቤቶች ነው በአጠቃላይ የጻፉት፡፡ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 29 መሰረት ስለፍርድ ቤትም ሆነ በማንኛውም ጉዳይ ላይ መጻፍም ሆነ አመለካከት የማበጀት መብት አላቸው፡፡” በማለት ምላሻቸውን አቅርበዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም ውሳኔውን በ8፡30 እንደሚያቀርብ ቀጠሮ ሰጠ፡፡
ከሰአት በኋላ በችሎቱ ቀጠሮ መሰረት የቀረቡት አቶ አስራት ጣሴ ባልተጠበቀ ሁኔታ ጥፋተኛ ተብለው ለቅጣት ውሳኔ ከሰባት ቀናት በኋላ እንዲቀርቡ እስከዛውም በእስር እንዲቆዩ ተወስኖባቸዋል፡፡

ከውሳኔው በኋላ ለፍኖተ ነፃነት አስተያየታቸውን እንዲሰጡ የተጠየቁት የአንድነት ፓርቲ ተቀዳሚ ፕሬዝዳንት አቶ ተክሌ በቀለ እስሩ ፖለቲካዊ እንድምታ ሊኖረው እንደሚችል ተናግረው፣ “አቶ አስራት ጣሴ ፓርቲዎችን በማቀራረብ ረገድ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ኢህአዴግን አስደንግጦታል እስሩም የአስራትን አስተዋፅኦ ለመገደብ የተደረገ ይሆናል፡፡” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ አያይዘውም በቅርቡ በአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት ና ስራአስፈፃሚ የፓርቲዎችን የውህደት ድርድር እንዲመሩና የፓርቲውን አማካሪ ምክር ቤት እንዲያቋቁሙ ኃላፊነት እንደተሰጣቸውም ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፡ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ

ግንቦት 7 በአለም ዙሪያ ከሚገኙ አባላቱ ጋር መከረ

February 8/2014

ግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት በተዘጋጀ የድርጅቱ የስራ እቅድ ላይ በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ ዓባላቶቹ ጋር አመርቂ ውይይት አካሄደ። ባለፈው ቅዳሜና እሁድ የተደረጉትን እነዚህን አሳታፊ ውይይቶች የንቅናቄው ከፍተኛ አመራሮች እንደመሯቸውም ተያይዞ ተጠቅሷል።
በሁሉም ቦታ ፍጹም አሳታፊ የነበረውንና ሰአታትን የወሰደውን ይህን ውይይት የመሩት እነኝህ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ከድርጅቱ ምስረታ እስካሁን ድረስ ያለውን የድርጅቱን ጉዞ ባጭሩ ማብራራታቸውን የጠቀሰው ዘጋቢያችን ለቀጣይ ሁለት አመታት ምን መደረግ አለበት የሚለውን የስራ እቅድ ለተሳታፊዎች በማቅረብ ከፍተኛ ውይይት ከተደረገበት በሗላ በሁሉም ቦታ በአባላት ሙሉ ድምጽ ተቀባይነት አግኝቶ መጽደቁን ዘጋቢያችን ጨምሮ ገልጿል።
በስብሰባው ወቅት ለፍትህ፡ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ የሚደረገው ጉዞ ከታሰበው እቅድ በላይ በፍጥነት እየተጓዘ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ይህም በአባላቱ ከፍተኛ ቁርጠኝነት የተገኘ መሆኑ በየውይይቱ በአጽንኦት ተገልጿል። እኛ ከተባበርን የምንፈልገውን ከማድረግ የሚያግደን ሃይል የለም፣ የወገኖቻችን ስቃይ የሚያበቃበት የድሉ ምዕራፍ ላይም እንገኛለን ስለሆነም ሁላችንም በከፍተኛ የትግል መንፈስ ለመጨረሻው የድል ጉዞ በከፍተኛ ወኔ እንነሳ በሚል የትግል ጥሪም ተላልፏል።
በየከተሞች ከነበሩ የውይይቱ ተሳታፊዎች ለተነሱ በርካታ ጥያቄዎች አጥጋቢ ምላሽ የተሰጠ ሲሆን አባላቱ በአዲስ የስራ መንፈስና ወኔ ለእቅዱ ስኬት እንደሚሰሩ መናገራቸውን የጠቆመው ዘጋቢአችን በአካል በስልክና በመሳሰሉት የመገናኛ መንገዶች ያነጋገራቸው በተለያዩ ከተሞች ውይይቱን የተሳተፉ አንዳንድ የድርጅቱ አባላት በተለይም በቀረበው የሁለት አመቱ የስራ እቅድ ደስተኞች በመሆናቸው ለስኬቱም ከምን ግዜውም በላይ እንደሚሰሩና ትግሉ ለሚጠይቀው ሁሉ መስዋእትነትን ለመክፈል ራሳቸውን ማዘጋጀታቸውን ዘጋቢያችን ጨምሮ ገልጿል።

ብሄሬ ኢትዮጵያዊነት ነዉ

February 8/2014
 ግርማ ካሳ

ከበደ ካሳ የሚባሉ አፍቃሪ ኢሕአዴግ ግለሰብ “አንዳንድ ሰዎች «ብሄር ..?» ተብለው ሲጠየቁ «ኢትዮጵያዊ!!!…» እያሉ የሚመልሱት፣ የራሳቸዉን ማንነት የኢትዮጵያ ማንነት አድርገው ያስቀመጡና በራሳቸው ማንነት የሌሎቹን ለመጨፍለቅ የሚያልሙ – የቅዠት ታንኳ ቀዛፊዎች ናቸው…. ተዛብታችሁ ሌላንም ለማዛባት ለምትፈልጉ ሁሉ ኢትዮጵያዊነት ዜግነት እንጂ ብሄር አይደልም። ኢትዮጵያ ሃገር እንጂ የአንድ ሕብረተሰብ ክፍል መለያ አይደለም።” የሚል አባባል ፌስቡክ ላይ ለጥፈው አነበብኩ።
በአንቀጽ 39 ንኡስ አንቀጽ 5 ላይ የኢትዮጵያ ፌዴራል ሕገ መንግስቱ እንዲህ ይላል ፡
























“በዚህ ሕገ መንግስት ብሄረሰብ፣ ሕዝብ» ማለት ከዚህ ቀጥሎ የተገለጸዉን ባህርይ የሚያሳይ ማህበረሰብ ነዉ። ሰፋ ያላ የጋራ ጠባይ የሚያንጸባርቅ ባህል ወይም ተመሳሳይ ልምዶች ያላቸው፣ ሊግባቡበት የሚችሉበት የጋራ ቋንቋ ያላቸው፣ የጋራ ወይም የተዛመደ ሕልዉና አለን ብለው የሚያምኑ፣ የስነ-ልቦና አንድነት ያላቸውና በአብዛኛዉ በተያያዘ መልክአ ምድር የሚኖሩ ናቸው»
እንግዲህ እዚህ ላይ እናስተዉል። ለብሄር የተሰጠው ትርጉምና ለብሄረሰብ የተሰጠው ትርጉም አንድ አይነት ነዉ። በአጭሩ ብሄር ማለት ብሄረሰብ ማለት ነዉ በሕገ መንግስቱ መሰረት።

ብሄር በእንግሊዘኛ ኔሽንስ ማለት ነዉ። «ዩናይትድ ኔሽንስ» ስንል የተባበሩት መንግስታት (የተባባሩት አገሮች ማለታችን ነዉ) ። እንደሚገባኝ ኢትዮጵያ እንጂ፣ ኦሮሞ፣ ወይንም፣ ትግሬ ወይንም ወላይታ የተባበሩት መንግስታት አባል አይደሉም።
«ብሄር» የሚለዉን ቃል የመጀመሪያ አመጣጥ ስንመለከት ፣ ከግእዝ የተወሰደ እንደሆነ እንረዳለን። ትርጉሙም በግእዝ አገር ማለት ነዉ።
ስለዚህ ኢሕአዴግን እና ኦነግ በሕገ መንግስቱ ብሄር የሚለዉን ቃል ያኔ የወሸቁት፣ ኢትዮጵያን እንደ አንዲት አገር ሳይሆን የተለያዩ የአገሮች ስብሰብ እንደሆነች ለማሳየት፣ በፈለጉ ጊዜ ደግሞ ከኢትዮጵያ ለመለየት አማራጭ እንዲኖራቸው ከመፈለግ የተነሳ ነዉ።

ፕሮፌሰር ተኮላ ሃጎስ ደግሞ ብሄር ብሄረሰብና ሕዝብ የሚለውን ለምን ሕገ መንግስቱ ዉስጥ እንደገባም ሲጽፉ የሚከተለዉን ነበር ያሉት፡
“The phrase “the nations, nationalities and peoples” thus found in the Ethiopian Constitution is a legacy from the writings of immature and juvenile diatribe of badly educated and socially disfranchised and radicalized students of Haile Selassie I University of the 1970s. It is the ersatz voice of Meles Zenawi forcing himself through the 1995 Constitution on the People of Ethiopia his narrow and ignoramus ideas on the history of Ethiopia and the process of nation building”
ስለዚህ «ብሄርህ ምንድን ነዉ ?» ተብሎ አንድ ሰው ሲጠየቅ «ኢትዮጵያዊነት» ብሎ ከመለሰ፣ በትክክለኛዉ የግእዝ አተርጓጎም እና በአለም አቀፍ ማህበረሰብ ዘንድ ብሄር የሚለው ቃል ያለው አጠቃቀም አንጻር፣ ትክክለኛ መልስ ነዉ።
«ብሄረሰብህስ ምንድን ነዉ ? » የሚል ጥያቄ ቢነሳስ ?

አንድ መርሳት የሌለብን ነገር አለ። አብዛኛዉ ኢትዮጵያዊ የተደባለቀ ነዉ። ሰሜን ጎንደና ሰሜን ወሎ ከሄዳችሁ ትግሪኛ ተናጋሪዉና አማርኛ ተናጋሪዉ ተደበላልቋል። ኦሮሚያ ዉስጥ በሸዋ፣ በሰሜን እና በምስራቅ ወለጋ..፣ አማራዉ ክልል ደግሞ በወሎ ፣ ኦሮሞኛ ተናጋሪው ከአማርኛ ተናጋሪው ተደባልቋል። በምስራቅ ሃረርጌና በባሌ ደግሞ ሶማሌዉና ኦሮሞዉ የተደባለቀበትም ሁኔታ አለ። በደቡብ ክልል ከሄድን፣ ወላይታዉ ከሲዳማው፣ ከንባታዉ ከሃዲያዉ …ሁሉም ተበራርዟል። ስለዚህ በአሥር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን የብዙ ብሄረሰቦች ድብልቅ ናቸው። በመሆኑም «ብሄረሰብህ ምንድን ነዉ?» ተብለው ሲጠየቁ እዚም እዚያም በመሆናቸው፣ ለመመለስ ይቸግራቸዋል። ስለዚህ በአጭሩ በብሄረሰባቸው ወይንም ዘራቸው ሳይሆን በኢትዮጵያዊነታቸው መለየትን ይመርጣሉ። ከነዚህ ሰዎች መካከል አንዱ እኔ ነኝ።

አቶ ከበደ፣ ኢትዮጵያዊያን፣ ብሄራችን ኢትዮጵያዊነት ነው ማለታቸው፣ የሌሎችን ማንነት ለመጨፍለቅ እንደመሞከር አድርገውም ወስደዉታል። አንድ ሰው «ኦሮሞ ነኝ፣ ትግሬ ነኝ ወዘተረፈ » የማለት መብቱ ከተከበረለት፣ ሌላው «አይ እኔ በዘሬ መለየት አልፈልግም፣ በኢትዮጵያዊነቴ ነዉ መለየት የምፈልገው » ካለ የርሱስ መብት ለምን አይከበርለትም ? ኦሮሞ፣ ወይም ትግሬ ፣ ወይም አማራ ያለመባል መብቱ መጠበቅ የለበትምን?
በኢሕአዴግ መንግስት፣ ይሄ መሰረታዊ መብት እየተጠበቀ አይደለም። እያንዳንዱ ዜጋ፣ እነርሱ ብሄር ብሄረሰብ የሚሉት አንዱ የዘር ሳጥን ዉስጥ መግባት አለበት። ያ ካልሆነ መታወቂያ እንኳ ማግኘት አይቻልም።

እንግዲህ ይሄንን ነዉ የምንቃወመው። «ለአገራችን የሚያዋጣዉ ዘር ላይ ማተኮር ሳይሆን፣ሥራ ላይ ማተኮር ነዉ። መመዘን ያለብን በዘራችን ሳይሆን በስራችን መሆን አለበት» እያልን ነዉ።

አፋን ኦሮሞ፣ ትግሪኛ፣ ጉራጌኛ፣ ሃምባሻ፣ ቆጮ ….በተለያዩ የአገራችን ግዛቶች ያሉ የተለያዩ ባህሎች፣ ቋንቋዎችን ፣ ምግቦች …ሁሉም «ኢትዮጵያዊነት» ናቸው። ሁሉም የኢትዮጵያ መገለጫዎች ናቸው። ኢትዮጵያ አንድ ወጥ አይደለችም። የተለያዩ ባህሎችን ፣ ቋንቋዎች፣ በአጭሩ የተለያዩ ብሄረሰቦች ያሉባት አገር ናት። ቢራቢሮዎችና አበባዎች የተለያዩ ቀለማቶቻቸው ዉበታቸው እንደሆነ፣ የኢትዮጵያም ዉበቷ ብሄረሰቦቿ ናቸው።

ግርማ ጌታቸዉ ካሳ
ዘብሄረ ኢትዮጵያ ( የዶር ፍቅሬ ቶሎሳን አባባል ልዋስና)

የመሬት ቅርምት በአስቸኳይ ይገታ!!!

February 8/2014

“የግብርና ሚኒስትር” በሚል “የሆድ ሲያውቅ፤ ዶሮ ማታ” ስያሜ የወያኔ የመሬት ሽያጭ ጉዳይ አስፈፃሚው የሆነው የሥርዓቱ ቀንደኛ አገልጋይ “መሬት መቀራመት ኢትዮጵያን ጭራሽ አይመለከታትም” ብሎ ሲናገር የሰማነው እና ያነበብነው በከፍተኛ ትዝብት ነው።
ለመሆኑ የመሬት ቅርምት ከኢትዮጵያ በላይ ማንን ሊመለከት ነው? ሱዳንን፣ ኤርትራን፣ ሳውዲን፣ ቻይናን፣ ህንድን ወይስ አሜሪካን? ከራሱ ከወያኔ ሹማምንት የተራረፈው መሬት ለአረብ አገራትና ለእስያ ቱጃሮች በነፃ የሚታደለው ኢትዮጵያ ውስጥ አይደለምን? ባዕዳን የሚረከቡት መሬት ስፋት በሄክታር መለካት ሲሰለቻቸው “ቤልጂየምን የሚያክል” እያሉ በስጦታ ያገኙትን መሬት በአገር ስፋት የሚለኩት ኢትዮጵያ ውስጥ አይደለምን? የመሬት ቅርምት ኢትዮጵያን ካልተመለከተ ከቶ ማንን ሊመለከት ነው?
ወያኔ ለም መሬት ለራሱ ማግበስበሱ ሳያንስ “ልማታዊ ባለሀብቶች” እያለ ለሚያሞካሻቸው ለቅርብም ለሩቅም አገራት ቱጃሮች ሰጥቶ ባለሀገሩን አርሶ አደር ሜዳ ላይ በተነ። መጤው ቱጃር ባለመሬት ሆኖ ባለሀገሩ ለስደት አሊያም ለቀን ሠራተኝነት ተዳረገ። ይህ ግፍ የሚፈጥረው ስቃይ የማይበቃ ይመስል “በእቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ” እንዲሉ መሬት ሻጩ “የመንግሥትና የሕዝብ ሀብት የሆኑ ነፃ መሬቶችን ብቻ ነው ለሰፋፊ የግብርና ኢንቨስትመንት የምንሰጠው። ማንም ከቀዬው አልተፈናቀለም” እያለ ይዘባበትብናል። “የመንግሥትና የሕዝብ ሀብት” የሚባለው መሬት የወያኔ የግል ሀብት ከሆነ ሃያ ሶስት ዓመታት መቆጠራቸው እኛ ብቻ ሳንሆን እሱም ያውቀዋል።
አባቶቻችንና እናቶቻችን ለብናኝ አፈር በመሰሰት ጎብኚዎችን እግር አሳጥበው ሲሸኙ እንዳልነበር ዛሬ በልማት ስም ከጋምቤላ እስከ መተማ፣ ከባሌ እስከ ሰላሌ፣ ከከፋ እስከ አፋር ያለው መሬታችን በሙሉ ወይ በወያኔ ሹማምንት አሊያም በባዕዳን ቱዳሮች ይዞታ ሥር ሆኗል። ኢትዮጵያዊያን አርሶ አደሮች፣ ወንዶችና ሴቶች፣ ጎልማሳዎችና ወጣቶች፣ ሕፃናት ሳይቀር የአዳዲሶቹ ባለመሬቶች ተቀጣሪዎች ሆነዋል። ጉልተኛው ሥርዓት ከቀድሞው በባሰ መልኩ ተመልሶ መጥቷል።
ወያኔ እንደሚያወራው ሰፋፊ መሬቶችን የመስጠት ዓላማው ግብርናችንን ለማዘመን ከሆነ ኢትዮጵያዊያን ባለሀብቶች ጠፍተው ነው እሩቅ ምስራቅ እስያ ድረስ የተጓዘው? እነሱስ ለምንድነው ለሊዝ የሚጠየቁትን እዚህ ግባ የማይባለውን ገንዘብ እንኳን ከራሷ ከኢትዮጵያ ተበድረው የሚከፍሉት? ይህ ምን ዓይነት ሥርዓት ነው? ከዛሬ አርባና አምሳ አመታት በፊት በሁመራ፣ ተንዳሆና ስምጥ ሸለቆዎች ውስጥ ሰፋፊ ዘመናዊ እርሻዎች የነበሯቸው ኢትዮጵያዊያን ነበሩ። ያኔ ኖረው ዛሬ እንደምን ላይኖሩ ቻሉ? የመሬት ባለቤት የመሆን መብት ያለው ኢትዮጵያዊ ወያኔ ብቻ እንዲሆን የተደረገው ለምንድነው? ኢትዮጵያ፣ ወያኔ ወይም የወያኔ አሽከር ላልሆነ ኢትዮጵያዊ ምኑ ነች? ባለሃገሩን መሬት አልባ፤ ባዕዳንን ደግሞ ባለመሬት ማድረግ ምን ያስከትላል?
ኢትዮጵያ ውስጥ መሬት እጅግ ከፍተኛ ዋጋ ያለው ግብዓት መሆኑ ከማንም የተሰወረ አይደለም። ኢትዮጵያ ውስጥ መሬት ከግብዓትም በላይ የፓለቲካ ሥልጣን ምንጭም ነው። ለዚህም ነው በኢትዮጵያ ፓለቲካ የመሬት ጥያቄ ቁልፍ የፓለቲካ ጥያቄ ሆኖ የቆየው። ደርግ መሬትን ከጉልተኞችም ከአርሶ አደሮችም በአዋጅ ቀምቶ የመንግሥት በማድረግ መንግሥትን አሳብጦ ገበሬውን አዳከመው። ወያኔ ይኸንኑ መሬት ያለአዋጅ ከመንግሥት ቀምቶ የራሱ በማድረግ ራሱን አሳብጦ ገበሬውን ከቀደሞው በባሰ አዳከመው። አሁን ደግሞ ይባስ ብሎ ይህንኑ መሬት ለባዕዳን በመስጠት ገበሬውን በአጠቃላይ ከመሬት ነጥሎ የቀን ሠራተኛ እያደረገው ነው። ይህ ከጪሰኝነት እጅግ የባሰ ባርነት ነው።
በወያኔ እና ታማኝ ተላላኪዎቹ እየተፈፀመ ያለው የመሬት ቅርምት ኢትዮጵያዊያንን አገር የሚያሳጣ፤ ስብዕናችንን የሚያዋርድ፤ ክብራችንን የሚገፍ፤ ሀብታችንን የሚያዘርፍ በመሆኑ በአስቸኳይ መቆም ይኖርበታል።
ሰው ባገሩ ሰው በወንዙ
ቢበላ ሳር ቢበላ መቅመቆ
ይታወቅ የለም ወይ ሰውነቱ ታውቆ
ግንቦት7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ለባዕዳን መሬታችንን፣ አገራችንን፣ ነፃነታችንን ሰጥተን ከሚገኘው ጥቅም … ባለቅኔው እንዳለው … ሰውነታችን ታውቆ፣ ክብራችን ተጠብቆ ሳርም ይሁን መቅመቆ መብላት እንመርጣለን። የመሬት ቅርምት በአስቸኳይ ይገታ። አገራችንን ለማዳን ቆርጠን እንነሳ።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Friday, February 7, 2014

አንድነት መግለጫ – የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ የማድረግ ትግላችን ተጠናክሮ ይቀጥላል!!!

February 7/2014

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)
=================================
አንድነት መግለጫ – የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ የማድረግ ትግላችን ተጠናክሮ ይቀጥላል!!!
ከአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ!!!
አንድነት መግለጫ –  የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ የማድረግ ትግላችን ተጠናክሮ ይቀጥላል!!!
ፓርቲያችን አንድነት ከቆመላቸው ክቡር አላማዎች አንዱ የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን ማድረግ ነው፡፡ የህግ የበላይነትና ፍትሃዊነት ለአንድ ሀገር ምሰሶ ሆነው እያለና እንዲሁም ለህግ የበላይነት መስፈን ትልቁ ባለድርሻ ገዢ የሆነው ፓርቲ ሊሆን እንደሚገባ እየታወቀ የተገላቢጦሽ ሆኖ ህግ አስከብራለሁ የሚለው አካል ሕግ ሲጥስ፤ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ሲገፍ ዝም ማለት አይቻልም፡፡ ህገ ወጥነትን መታገልና ብሎም ለሕግ ማቅረብ ግዴታ እንደሆነ አንድነት ያምናል፡፡
እንደሚታወቀው ፓርቲያችን ህጋዊ መብቱን ተጠቅሞ ሠላማዊ በሆነ መንገድ ለሦስት ወር የቆየ ሚሊዮኖችን ያሳተፈ ህዝባዊ ንቅናቄ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡ በዚህ ሂደት ግን ህጋዊ ከለላ ሊሰጡን ከሚገባ የመንግሥት አካላት የተለያዩ ጥቃቶች ተፈጽመውብናል፡፡ ስልጣናቸውን ካለ አግባብ በመጠቀምም ቁሳዊና ሞራላዊ ጥቃት አድርሰውብናል፡፡ ጥቃቱ በመላ ኢትዮጵያ እንቅስቃሴ ባደረግንባቸው ሁሉ ሲሆን አባሎቻችንና አመራሮች እንዲታሰሩ ተደርጓል፣ በራሪ ወረቀቶች ተነጥቀዋል፣ ተዋክበዋል፡፡
በክልል ከተሞች ያየነው ማሰርና ማዋከብ ዋና ከተማ በሆነችው አዲስ አበባ በድጋሚ ሲፈፀም ስናይ ግን እጅግ አዝነናል፡፡ የሠላማዊ ሠልፍ እውቅና ደብዳቤ የሰጠን የአዲስ አበባ መስተዳድር፤ ህግ የጣሰ ድርጊቱን ማስቆም ያልቻሉት የአዲስ አበባ ከንቲባና ያለምንም ማስረጃ፣ ህጋዊ ወረቀት እንዳለን እያወቀ በጠዋት አስሮ ማታ ሲፈታ የነበረው የአዲስ አበባ ፖሊሲና ማስቆም ያልቻሉት የፖሊሲ ኮሚሽነሩ ለደረሰብን ህገ ወጥ ድርጊት ዋነኛ ተጠያቂዎች ናቸው ብለን እናምናለን፡፡
ፓርቲያችን በህገ መንግሥቱ አንቀጽ 9 መሠረት ህገ መንግሥቱን ተቀብሎ የተቋቋመ መሆኑ እየታወቀ የአዲስ አበባ አስተዳድር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆኖ እያለ እንዲሁም የአዲስ አበባ ፖሊስን የእለት ተእለት ሥራ የሚቆጣጠር ሆኖ እያለ ሠላማዊና ህጋዊ እንቅስቃሴያችንን ለመገደብ ስልጣናቸውን ያላግባብ በመጠቀም አባሎቻችን በገፍ እንዲታሰሩ፣ አመራሮቻችንን ከቅስቀሳ ቦታ ላይ አፍሰው በመውሰድ ታስረው እንዲውሉ፣ የቅስቀሳ ቁሳቁሶች እንዲነጠቁና ፖስተሮች እንዳይለጠፍ ተደርጓል፡፡
በህገ መንግሥቱ አንቀጽ 3ዐ ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው አንድነት ፓርቲ አላማውን ለማሳካትና በህገ መንግሥቱ የተሰጡትን መብቶች ለመጠቀም የመቃወምና ሠላማዊ ሠልፍ የመጥራት መብት ቢኖረውም ይሄ መብቱ ህግ በመጣስ እንዲቆም ተደርጓል፡፡ ስለዚህ የአዲስ አበባ መስተዳድር በአዋጅ ቁጥር 3/83 አንቀጽ 7 መሠረት የአንድነት የሠላማዊ ሠልፍ ጥያቄ ተቀብሎ የማስተናገድና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መስሪያ ቤት የማዘዝና ጥበቃ የማድረግ ኃላፊት ቢጣልበትም ኃላፊነቱን መወጣት ባለመቻሉ በህግ እንዲጠየቅ አድርገናል፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ ቁጥር 573/2ዐዐዐ አንቀጽ 46 ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው ፓርቲያችን የቅስቀሳ ሥራ ለመስራት ምንም ተጨማሪ ፈቃድ የማያስፈልገው ቢሆንም ፖሊስ ይህንን በተላለፈ መልኩ ያለ በቂ ምክንያት እስር ፈጽሟል፡፡ ህግን ባልተከተለ መልኩ በአባላትና ደጋፊዎች ላይ ወከባና ማስፈራሪያ በመፈፀማቸው በህግ እንዲጠየቁ አድርገናል፡፡
ማንም ሰው ወይም አካል ከህግ በላይ ሊሆን አይችልም፡፡ ህገ ወጥነትን መታገስም በራሱ ወንጀልን ማበረታታት ነው፡፡ ስለዚህ የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ የማድረገ ትግላችን ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ በቅርቡም በመንግስት ከፍተኛ አመራሮችና በአጠቃላይ በገዢው ፓርቲ ላይ ክስ ለመመስረት በሂደት ላይ መሆናችን እንዲታወቅ እንፈልጋን፡፡ ይህ ህግን በማስከበር ላይ ትኩረቱን ያደረገው ንቅናቄ ‹‹Millions of voices for justice›› የህግ የበላይነት እስከሚከበር ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ በዚህ አጋጣሚ የፍትሕ ተቋማቱ ግራ ቀኙን በመመርመር ለህግ የበላይነት መረጋገጥ እንደሚሰሩ ተስፋ እናደርጋለን፡፡
የሚሊዮኖች ድምፅ ለፍትህ!!!
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ
ጥር 29 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አባባ

የሃይማኖት ተቋማትን በሚመለከተው አዋጅ ላይ የሚመክር ስብሰባ በአዋሳ ተጠራ

February 7/2014
ጥር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የተዘጋጀው  የእምነት አኩልነትና ተቻችሎ የመኖር የሃይማኖት እሴትን ሊያጎለብት ይችላል የተባለ ረቂቅ አዋጅ ላይ የሚመለከታቸውን ወገኖች ሃሳብ ለማሰባሰብ  ከነገ ጥር 30 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ቀናት በአዋሳ ከተማ እንደሚካሄድ ምንጮቻችን ጠቆሙ።
በዚሁ ስብሰባ ላይ በዋንኛነት የሚሳተፉት በአገሪቱ አሉ የሚባሉት 945 ያህል የእምነት ተቋማት መሆናቸውም ታውቆአል፡፡ መንግስት የሙስሊም ማህበረሰብ የመብት ጥያቄ ማንሳታቸውን ተከትሎ ለውይይት በተደጋጋሚ ሲያገኛቸው የነበሩትን የመፍትሄ አፈላላጊ ኮምቴ አባላት በአክራሪነትና በሽብርተኝነት ወንጅሎ እስር ቤት ከከተተ ወዲህ “መንግስትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው፣አንዱ በሌላው ስራ ጣልቃ አይገባም” የሚለውን ሕገመንግስታዊ ድንጋጌ በመዘንጋት በሃይማኖት ጉዳይ እጁን ሙሉ በሙሉ ማስገባቱን ታዛቢዎች ይገልጻሉ፡፡
መንግስት ረቂቅ ህጉ  በሃይማኖት ስም  ይደረጋሉ የሚላቸውን የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን ለመግታት ይስችለኛል ብሎ ያምናል። የሃማኖት ተቁዋማቱ በስብሰባው ላይ እንዲገኙ ከመጋበዝ ባለፈ የረቂቅ አዋጁ ኮፒ አስቀድሞ እንዲደርሳቸው እንዳልተደረገ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡
የሃይማኖት ተቋማት የሕግ ሰውነትን በተመለከተ ለመጀመሪያ ጊዜ በሕግ የተደነገገው በ1952 ዓ.ም በወጣው የፍትሐ ብሔር ሕግ ነው፡፡ የፍትሐ ብሔር ሕጉ በወቅቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አቋቁሞ፣  ሌሎች የሃይማኖት ተቋማት ሕጉን ተከትሎ በሚወጣ ልዩ ደንብ እንደሚመዘገቡ መደንገጉ ይታወቃል፡፡ በደርግ ዘመንም ሃይማኖትን የተመለከተ ድንጋጌ ወጥቶ አያውቅም።
ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ያወጣው ሕገ መንግሥት በአንቀጽ 27 ላይ ማንኛውም ሰው የማሰብ፣የህሊናና የሃይማኖት ነጻነት እንዳለው በግልጽ ደነግጋል፡፡ይህ መብት ማንኛውም ሰው የመረጠውን ሃይማኖት ወይም እምነት የመያዝ ወይም መቀበል ፣ሃይማኖቱንና እምነቱን ለብቻ ወይም ከሌሎች ጋር በመሆን በይፋ ወይም በግል የማምለክ፣የመከተል፣የመተግበር፣የማስተማር ወይም የመግለጽ መብትን ያካትታል፡፡ከዚህ በተጨማሪም የሃማኖት ተከታዮች ሃማኖታቸውን ለማስፋፋትና ለማደራጀት የሚያስችላቸውን የሃማኖት ትምህርትና የአስተዳዳር ተቋማት ማቋቋም እንደሚችሉና ወላጆች ህጋዊ ሞግዚቶች በእምነታቸው መሰረት የሃይማኖታዊና የመልካም ስነምግባር ትምህርት በመስጠት ልጆቻቸው የማሳደግ መብት እንዳላቸው ደንግጓል።

የአንዷለም አራጌ የውሳኔ አሁንም ቀጠሮ ተራዘመ፤ ኢሕአዴግ 4 የአንድነት አመራሮችን ሊያስር መሆኑ ተሰማ

February 7/2014

ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያውያን ዘንድ የዓመቱ ምርጥ ሰው በሚል የተሰየመው ወጣቱ ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ በካንጋሮው ፍርድ ቤት ዕድሜ ልክ ዕስራት እየተፈርደበት መሆኑ ይታወሳል። ወጣቱ ፖለቲከኛ ለሰበር ሰሚ ችሎት አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን ለውሳኔ ከተቀጠረ በኋላ አሁንም እንደዚህ ቀደሙ ቀጠሮው መራዘሙን የዜና ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ጠቁመዋል።

አቶ አንዷለም አራጌ የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት ወህኒ እየተሰቃየ ቢሆንም “የእኔን መታሰር ተቃዋሚዎች ሊጠቀሙበት አልቻሉም” ሲል መናገሩ አይዘነጋም። ዛሬ ፍርድ ቤት መቅረብ የነበረበት አንዷለም በዳኞች የተለመደ ምክንያት ቀጠሮው ለመጋቢት 8 ቀን 2006 እንዲተላለፍ ተወስኗል። ዛሬ አንዷለም ላይ ምን ይወሰን ይሆን የሚለውን ለማየት በርካታ ሰዎች ስድስት ኪሎ በሚገኘው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ታድመው እንደነበርም የደረሰን መረጃ ያመልከታል።

የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዘጋቢ ነብዩ ሃይሉ እንደዘገበው ኢህአዴግ አቶ ዳንኤል ተፈራን ጨምሮ አራት የአንድነት አመራሮችን ለማሰር መዘጋጀቱ ተጋለጠ። በዘገባው መሠረት ወጣቱ ፖለቲከኛና ደራሲ ዳንኤል ተፈራን ጨምሮ 4 አመራሮችና አባላት እንዲታሰሩ ኢህአዴግ ወስኗል፤ የክስ ቅድመሁኔታዎች በፍርድ ቤት መጠናቀቃቸውን ታውቋል፡፡


የፍትህ ሚ/ር ምንጮች እንዳስታወቁት በኢህአዴግ ጽ/ቤት ትዕዛዝ ክስ እንዲከፈትባቸውና እንዲታሰሩ የተወሰኑት የአንድነት አባላት በርካታ ናቸው፡፡ ሆኖም የመጀመሪያው ዙር ክስና እስር በ4 አመራሮችና አባላት ላይ ያነጣጠረ ነው ይላል የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዘገባ።

የመሬት ቅርምት በአስቸኳይ ይገታ!!!

February 7/2014

“የግብርና ሚኒስትር” በሚል “የሆድ ሲያውቅ፤ ዶሮ ማታ” ስያሜ የወያኔ የመሬት ሽያጭ ጉዳይ አስፈፃሚው የሆነው የሥርዓቱ ቀንደኛ አገልጋይ “መሬት መቀራመት ኢትዮጵያን ጭራሽ አይመለከታትም” ብሎ ሲናገር የሰማነው እና ያነበብነው በከፍተኛ ትዝብት ነው።
ለመሆኑ የመሬት ቅርምት ከኢትዮጵያ በላይ ማንን ሊመለከት ነው? ሱዳንን፣ ኤርትራን፣ ሳውዲን፣ ቻይናን፣ ህንድን ወይስ አሜሪካን? ከራሱ ከወያኔ ሹማምንት የተራረፈው መሬት ለአረብ አገራትና ለእስያ ቱጃሮች በነፃ የሚታደለው ኢትዮጵያ ውስጥ አይደለምን? ባዕዳን የሚረከቡት መሬት ስፋት በሄክታር መለካት ሲሰለቻቸው “ቤልጂየምን የሚያክል” እያሉ በስጦታ ያገኙትን መሬት በአገር ስፋት የሚለኩት ኢትዮጵያ ውስጥ አይደለምን? የመሬት ቅርምት ኢትዮጵያን ካልተመለከተ ከቶ ማንን ሊመለከት ነው?
ወያኔ ለም መሬት ለራሱ ማግበስበሱ ሳያንስ “ልማታዊ ባለሀብቶች” እያለ ለሚያሞካሻቸው ለቅርብም ለሩቅም አገራት ቱጃሮች ሰጥቶ ባለሀገሩን አርሶ አደር ሜዳ ላይ በተነ። መጤው ቱጃር ባለመሬት ሆኖ ባለሀገሩ ለስደት አሊያም ለቀን ሠራተኝነት ተዳረገ። ይህ ግፍ የሚፈጥረው ስቃይ የማይበቃ ይመስል “በእቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ” እንዲሉ መሬት ሻጩ “የመንግሥትና የሕዝብ ሀብት የሆኑ ነፃ መሬቶችን ብቻ ነው ለሰፋፊ የግብርና ኢንቨስትመንት የምንሰጠው። ማንም ከቀዬው አልተፈናቀለም” እያለ ይዘባበትብናል። “የመንግሥትና የሕዝብ ሀብት” የሚባለው መሬት የወያኔ የግል ሀብት ከሆነ ሃያ ሶስት ዓመታት መቆጠራቸው እኛ ብቻ ሳንሆን እሱም ያውቀዋል።
አባቶቻችንና እናቶቻችን ለብናኝ አፈር በመሰሰት ጎብኚዎችን እግር አሳጥበው ሲሸኙ እንዳልነበር ዛሬ በልማት ስም ከጋምቤላ እስከ መተማ፣ ከባሌ እስከ ሰላሌ፣ ከከፋ እስከ አፋር ያለው መሬታችን በሙሉ ወይ በወያኔ ሹማምንት አሊያም በባዕዳን ቱዳሮች ይዞታ ሥር ሆኗል። ኢትዮጵያዊያን አርሶ አደሮች፣ ወንዶችና ሴቶች፣ ጎልማሳዎችና ወጣቶች፣ ሕፃናት ሳይቀር የአዳዲሶቹ ባለመሬቶች ተቀጣሪዎች ሆነዋል። ጉልተኛው ሥርዓት ከቀድሞው በባሰ መልኩ ተመልሶ መጥቷል።
ወያኔ እንደሚያወራው ሰፋፊ መሬቶችን የመስጠት ዓላማው ግብርናችንን ለማዘመን ከሆነ ኢትዮጵያዊያን ባለሀብቶች ጠፍተው ነው እሩቅ ምስራቅ እስያ ድረስ የተጓዘው? እነሱስ ለምንድነው ለሊዝ የሚጠየቁትን እዚህ ግባ የማይባለውን ገንዘብ እንኳን ከራሷ ከኢትዮጵያ ተበድረው የሚከፍሉት? ይህ ምን ዓይነት ሥርዓት ነው? ከዛሬ አርባና አምሳ አመታት በፊት በሁመራ፣ ተንዳሆና ስምጥ ሸለቆዎች ውስጥ ሰፋፊ ዘመናዊ እርሻዎች የነበሯቸው ኢትዮጵያዊያን ነበሩ። ያኔ ኖረው ዛሬ እንደምን ላይኖሩ ቻሉ? የመሬት ባለቤት የመሆን መብት ያለው ኢትዮጵያዊ ወያኔ ብቻ እንዲሆን የተደረገው ለምንድነው? ኢትዮጵያ፣ ወያኔ ወይም የወያኔ አሽከር ላልሆነ ኢትዮጵያዊ ምኑ ነች? ባለሃገሩን መሬት አልባ፤ ባዕዳንን ደግሞ ባለመሬት ማድረግ ምን ያስከትላል?
ኢትዮጵያ ውስጥ መሬት እጅግ ከፍተኛ ዋጋ ያለው ግብዓት መሆኑ ከማንም የተሰወረ አይደለም። ኢትዮጵያ ውስጥ መሬት ከግብዓትም በላይ የፓለቲካ ሥልጣን ምንጭም ነው። ለዚህም ነው በኢትዮጵያ ፓለቲካ የመሬት ጥያቄ ቁልፍ የፓለቲካ ጥያቄ ሆኖ የቆየው። ደርግ መሬትን ከጉልተኞችም ከአርሶ አደሮችም በአዋጅ ቀምቶ የመንግሥት በማድረግ መንግሥትን አሳብጦ ገበሬውን አዳከመው። ወያኔ ይኸንኑ መሬት ያለአዋጅ ከመንግሥት ቀምቶ የራሱ በማድረግ ራሱን አሳብጦ ገበሬውን ከቀደሞው በባሰ አዳከመው። አሁን ደግሞ ይባስ ብሎ ይህንኑ መሬት ለባዕዳን በመስጠት ገበሬውን በአጠቃላይ ከመሬት ነጥሎ የቀን ሠራተኛ እያደረገው ነው። ይህ ከጪሰኝነት እጅግ የባሰ ባርነት ነው።
በወያኔ እና ታማኝ ተላላኪዎቹ እየተፈፀመ ያለው የመሬት ቅርምት ኢትዮጵያዊያንን አገር የሚያሳጣ፤ ስብዕናችንን የሚያዋርድ፤ ክብራችንን የሚገፍ፤ ሀብታችንን የሚያዘርፍ በመሆኑ በአስቸኳይ መቆም ይኖርበታል።
ሰው ባገሩ ሰው በወንዙ
ቢበላ ሳር ቢበላ መቅመቆ
ይታወቅ የለም ወይ ሰውነቱ ታውቆ
ግንቦት7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ለባዕዳን መሬታችንን፣ አገራችንን፣ ነፃነታችንን ሰጥተን ከሚገኘው ጥቅም … ባለቅኔው እንዳለው … ሰውነታችን ታውቆ፣ ክብራችን ተጠብቆ ሳርም ይሁን መቅመቆ መብላት እንመርጣለን። የመሬት ቅርምት በአስቸኳይ ይገታ። አገራችንን ለማዳን ቆርጠን እንነሳ።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

አቶ አስራት ጣሴ ታሰሩ

Febriuary 7/2014

(ዘ-ሐበሻ) የኢሕአዴግ አስተዳደር ለፕሮፓጋዳና ዜጎችን ለማስፈራሪያ የሠራውን “አኬልዳማ” ዶክመንታሪ ፊልም በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ከታየ በኋላ በፊልሙ ላይ አስተያየት ሰጥተዋል፤ መንግስትንም ዘልፈዋል በሚል የተከሰሱት የአንድነት ፓርቲ የምክር ቤት አባል አቶ አስራት ጣሴ ታሠሩየዘ-ሐበሻ የአንባቢያን አስተያየት ይጠበቃል።

ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው በፊልሙ ላይ የተሰማቸውን አስተያየት ሰጥተዋል የሚባሉት አቶ አስራት በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ አስተያየታቸውን በመስጠታቸውና በዚህ ጽሑፍ ላይም መንግስት ላይ ዘለፋ አዘል ቃላት ተጠቅመዋል በሚል ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲያስረዱ ትዕዛዝ የተላለፈባቸው ሲሆን፤ በዚህም መሠረት ዛሬ ፌብሩዋሪ 7 ቀን 2014 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቢቀርቡም፤ የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤቱም ለ7 ቀናት ያህል ታሰረው በቀጣይ ሳምንት እንዲቀርቡ የ እስር ት ዕዛዝ በማስተላለፉ አቶ አስራት ጣሴ ወህኒ ወርደዋል።

 

ብሄሬ ኢትዮጵያዊነት ነዉ

February 7/2014

ከበደ ካሳ የሚባሉ አፍቃሪ ኢሕአዴግ ግለሰብ “አንዳንድ ሰዎች «ብሄር ..?» ተብለው ሲጠየቁ «ኢትዮጵያዊ!!!…» እያሉ የሚመልሱት፣ የራሳቸዉን ማንነት የኢትዮጵያ ማንነት አድርገው ያስቀመጡና በራሳቸው ማንነት የሌሎቹን ለመጨፍለቅ የሚያልሙ – የቅዠት ታንኳ ቀዛፊዎች ናቸው…. ተዛብታችሁ ሌላንም ለማዛባት ለምትፈልጉ ሁሉ ኢትዮጵያዊነት ዜግነት እንጂ ብሄር አይደልም። ኢትዮጵያ ሃገር እንጂ የአንድ ሕብረተሰብ ክፍል መለያ አይደለም።” የሚል አባባል ፌስቡክ ላይ ለጥፈው አነበብኩ።
በአንቀጽ 39 ንኡስ አንቀጽ 5 ላይ የኢትዮጵያ ፌዴራል ሕገ መንግስቱ እንዲህ ይላል ፡
























“በዚህ ሕገ መንግስት ብሄረሰብ፣ ሕዝብ» ማለት ከዚህ ቀጥሎ የተገለጸዉን ባህርይ የሚያሳይ ማህበረሰብ ነዉ። ሰፋ ያላ የጋራ ጠባይ የሚያንጸባርቅ ባህል ወይም ተመሳሳይ ልምዶች ያላቸው፣ ሊግባቡበት የሚችሉበት የጋራ ቋንቋ ያላቸው፣ የጋራ ወይም የተዛመደ ሕልዉና አለን ብለው የሚያምኑ፣ የስነ-ልቦና አንድነት ያላቸውና በአብዛኛዉ በተያያዘ መልክአ ምድር የሚኖሩ ናቸው»
እንግዲህ እዚህ ላይ እናስተዉል። ለብሄር የተሰጠው ትርጉምና ለብሄረሰብ የተሰጠው ትርጉም አንድ አይነት ነዉ። በአጭሩ ብሄር ማለት ብሄረሰብ ማለት ነዉ በሕገ መንግስቱ መሰረት።

ብሄር በእንግሊዘኛ ኔሽንስ ማለት ነዉ። «ዩናይትድ ኔሽንስ» ስንል የተባበሩት መንግስታት (የተባባሩት አገሮች ማለታችን ነዉ) ። እንደሚገባኝ ኢትዮጵያ እንጂ፣ ኦሮሞ፣ ወይንም፣ ትግሬ ወይንም ወላይታ የተባበሩት መንግስታት አባል አይደሉም።
«ብሄር» የሚለዉን ቃል የመጀመሪያ አመጣጥ ስንመለከት ፣ ከግእዝ የተወሰደ እንደሆነ እንረዳለን። ትርጉሙም በግእዝ አገር ማለት ነዉ።
ስለዚህ ኢሕአዴግን እና ኦነግ በሕገ መንግስቱ ብሄር የሚለዉን ቃል ያኔ የወሸቁት፣ ኢትዮጵያን እንደ አንዲት አገር ሳይሆን የተለያዩ የአገሮች ስብሰብ እንደሆነች ለማሳየት፣ በፈለጉ ጊዜ ደግሞ ከኢትዮጵያ ለመለየት አማራጭ እንዲኖራቸው ከመፈለግ የተነሳ ነዉ።

ፕሮፌሰር ተኮላ ሃጎስ ደግሞ ብሄር ብሄረሰብና ሕዝብ የሚለውን ለምን ሕገ መንግስቱ ዉስጥ እንደገባም ሲጽፉ የሚከተለዉን ነበር ያሉት፡
“The phrase “the nations, nationalities and peoples” thus found in the Ethiopian Constitution is a legacy from the writings of immature and juvenile diatribe of badly educated and socially disfranchised and radicalized students of Haile Selassie I University of the 1970s. It is the ersatz voice of Meles Zenawi forcing himself through the 1995 Constitution on the People of Ethiopia his narrow and ignoramus ideas on the history of Ethiopia and the process of nation building”
ስለዚህ «ብሄርህ ምንድን ነዉ ?» ተብሎ አንድ ሰው ሲጠየቅ «ኢትዮጵያዊነት» ብሎ ከመለሰ፣ በትክክለኛዉ የግእዝ አተርጓጎም እና በአለም አቀፍ ማህበረሰብ ዘንድ ብሄር የሚለው ቃል ያለው አጠቃቀም አንጻር፣ ትክክለኛ መልስ ነዉ።
«ብሄረሰብህስ ምንድን ነዉ ? » የሚል ጥያቄ ቢነሳስ ?

አንድ መርሳት የሌለብን ነገር አለ። አብዛኛዉ ኢትዮጵያዊ የተደባለቀ ነዉ። ሰሜን ጎንደና ሰሜን ወሎ ከሄዳችሁ ትግሪኛ ተናጋሪዉና አማርኛ ተናጋሪዉ ተደበላልቋል። ኦሮሚያ ዉስጥ በሸዋ፣ በሰሜን እና በምስራቅ ወለጋ..፣ አማራዉ ክልል ደግሞ በወሎ ፣ ኦሮሞኛ ተናጋሪው ከአማርኛ ተናጋሪው ተደባልቋል። በምስራቅ ሃረርጌና በባሌ ደግሞ ሶማሌዉና ኦሮሞዉ የተደባለቀበትም ሁኔታ አለ። በደቡብ ክልል ከሄድን፣ ወላይታዉ ከሲዳማው፣ ከንባታዉ ከሃዲያዉ …ሁሉም ተበራርዟል። ስለዚህ በአሥር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን የብዙ ብሄረሰቦች ድብልቅ ናቸው። በመሆኑም «ብሄረሰብህ ምንድን ነዉ?» ተብለው ሲጠየቁ እዚም እዚያም በመሆናቸው፣ ለመመለስ ይቸግራቸዋል። ስለዚህ በአጭሩ በብሄረሰባቸው ወይንም ዘራቸው ሳይሆን በኢትዮጵያዊነታቸው መለየትን ይመርጣሉ። ከነዚህ ሰዎች መካከል አንዱ እኔ ነኝ።

አቶ ከበደ፣ ኢትዮጵያዊያን፣ ብሄራችን ኢትዮጵያዊነት ነው ማለታቸው፣ የሌሎችን ማንነት ለመጨፍለቅ እንደመሞከር አድርገውም ወስደዉታል። አንድ ሰው «ኦሮሞ ነኝ፣ ትግሬ ነኝ ወዘተረፈ » የማለት መብቱ ከተከበረለት፣ ሌላው «አይ እኔ በዘሬ መለየት አልፈልግም፣ በኢትዮጵያዊነቴ ነዉ መለየት የምፈልገው » ካለ የርሱስ መብት ለምን አይከበርለትም ? ኦሮሞ፣ ወይም ትግሬ ፣ ወይም አማራ ያለመባል መብቱ መጠበቅ የለበትምን?
በኢሕአዴግ መንግስት፣ ይሄ መሰረታዊ መብት እየተጠበቀ አይደለም። እያንዳንዱ ዜጋ፣ እነርሱ ብሄር ብሄረሰብ የሚሉት አንዱ የዘር ሳጥን ዉስጥ መግባት አለበት። ያ ካልሆነ መታወቂያ እንኳ ማግኘት አይቻልም።

እንግዲህ ይሄንን ነዉ የምንቃወመው። «ለአገራችን የሚያዋጣዉ ዘር ላይ ማተኮር ሳይሆን፣ሥራ ላይ ማተኮር ነዉ። መመዘን ያለብን በዘራችን ሳይሆን በስራችን መሆን አለበት» እያልን ነዉ።

አፋን ኦሮሞ፣ ትግሪኛ፣ ጉራጌኛ፣ ሃምባሻ፣ ቆጮ ….በተለያዩ የአገራችን ግዛቶች ያሉ የተለያዩ ባህሎች፣ ቋንቋዎችን ፣ ምግቦች …ሁሉም «ኢትዮጵያዊነት» ናቸው። ሁሉም የኢትዮጵያ መገለጫዎች ናቸው። ኢትዮጵያ አንድ ወጥ አይደለችም። የተለያዩ ባህሎችን ፣ ቋንቋዎች፣ በአጭሩ የተለያዩ ብሄረሰቦች ያሉባት አገር ናት። ቢራቢሮዎችና አበባዎች የተለያዩ ቀለማቶቻቸው ዉበታቸው እንደሆነ፣ የኢትዮጵያም ዉበቷ ብሄረሰቦቿ ናቸው።

ግርማ ጌታቸዉ ካሳ
ዘብሄረ ኢትዮጵያ ( የዶር ፍቅሬ ቶሎሳን አባባል ልዋስና)