Friday, January 17, 2014

የፌዴራል ፖሊሲ አጽቢን ቶቆጣጥሯታል ፣ ሕወሃቶች በሕዝቡ ተናደዋል ፣ ህዝቡም ጥያቄዉን አላቆመም (አቡጊዳ )

January 17/2014

የፌዴራል ፖሊሲ አጽቢን ቶቆጣጥሯታል ፣ ሕወሃቶች በሕዝቡ ተናደዋል ፣ ህዝቡም ጥያቄዉን አላቆመም
ከመቀሌ በስተሰምኔ 70 ኪሎሜተር ርቃ በምትገኘው የአጽቢ ከተማ በሕዝቡና በሕወሃቶች መካከል ትላንት የተፈጠረው ዉዝግብ ዛሬም ቀጥሎ ዉሏል። የአካባቢዉ ፖሊስ አቅም በማጣቱ በብዙ መኪና በተለያዩ አቅጣጫዎች፣ ኬሎች አካባቢዎች፣ ተጭነው የመጡ ፌዴራል ፖሊሶች ከተማዋን እንደ ጦር ካምፕ ወረዋታል። ወደ አካባቢዉ የደረሱ የሕወሃት አመራሮች በሕዝቡ ላይ ዛቻን ስድብ እያወረዱበት ነዉ። በሕዝቡ መናደዳቸውን እየገለጹ ነዉ። ሕዝቡ የታሰሩ እንዲፈቱ እየጠቀ ነዉ። ከታስሩት ዉስጥም የ16 አመት ወጣት ይገኝበታል። ወደ ከተማዋ መግባትና መዉጣ አይቻልም። የከተማዋ ነዋሪዎች፣ በየትኛዉም መንግስት እንዲህ አይነት ግፍ አይተን አናውቅም እያሉ ነዉ።
ሰሞኑን የሕወሃት/ኢሕአዴጉ አቶ በረከት ስምኦን፣ ገበሬዉን የፈለገ ነገር ብናደርገዉ የም አይሄዱም በማለት በገዳ ቴሌቭዥኝ (ትንሿ ኢቲቪ) መናገራቸው ብዙዎች እያነጋገረ እንደሆነ ይታወቃል። ነገር ግን በአጸቢ፣ ትግራይ በገበሬዎች ላይ እየተደረገ ያለው አሳዛኝ ግፍ ፣ ገበሬዉ በስፋት በስፋራዉ ተገኝቶ ችግሩን የሚነግርለት ባለመኖር እንጂ ፣ ገበሬዉ ከሃያ አመታት በላይ ግፍ እየተፈጸመበት እንደሆነ በግልጽ ያሳየ ነው።
ከአንድነት ፓርቲ ጋር የቅርብ ግንኙነት ያለዉና ለዉህደትም ጥያቄ ያቀረበዉ፣ የአረና አመራር አባል፣ አብርሃ ደሳት ከመቀሌ ዛሬ አርብ ጥር 9 ቀን በፌስቡክ ያስተላለፈዉን እንደሚከትለው አቅርበናል፡
የአፅቢ ዓመፅ (ክፍል ሰባት)
——————————–
ግጭቱ ቆሟል። መከላከያ ሰራዊት የሃይል እርምጃ ከመውሰድ ታቅቦ ህዝቡ እንዲበተን ተማፅኗል። በፖሊስ የታሰሩትን ነገ (ዛሬ ዓርብ 09/05/06 ዓም) እንደሚፈቱ ቃል ገብቷል። ድርማው ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት (7:00) ላይ ተፈፅሟል። ድርድሩ ዛሬ ዓርብ ይቀጥላል።
የዓመፁ ምክንያት
Basic Cause: የፍትሕ እጦት
የአፅቢ ወንበርታ ወረዳ አስተዳዳሪዎችና ፖሊስ በህዝቡ ጥሩ ስም የላቸውም። አስተዳዳሪዎች የህዝብን የፍትሕ ጥያቄ በአግባቡ ከመመለስ ይልቅ ህዝቡን ማስፈራራት ይቀላቸዋል። ህዝቡ ደግሞ የሚፈራ አይደለም። የወረዳው አስተዳዳሪ ጥያቄ ለሚያነሱ ዜጎች ተቃዋሚዎች እንደሆኑ ይሰብካል፤ ተቃዋሚዎች እንደሚያጠፋም ይዝታል (ህዝብ ሰብስቦ)። ወጣቶች መንግስትን እንዳይቃወሙ ወላጆቻቸውን ያስፈራራል። የፍትሕ ጥያቄ የሚያነሳ ሰው የመንግስት አገልግሎት አያገኝም፤ የፍርድቤት አገልግሎት አያገኝም፣ ፍትሕ ተከልክሏል። የህወሓት አገልጋይ ካልሆነ መሬት አይሰጠውም፣ መስኖ እንዲጠቀምም አይፈቀድለትም። ማዳበርያ እንዲወስድ ይገደዳል፣ ለመውሰድ ፍቃደኛ ያልሆነ ይታሰራል፣ ይሰቃያል። በአፅቢ ወንበርታ የፍትሕ ጥያቄ ማንሳት ክልክል ነው።
ፖሊስም እንደፈለገ ሰው ያስራል፤ ይገድላል። በፖሊስ የተገደሉ የአከባቢው ኗሪዎች አሉ። ፖሊስ ሰዎች አስሮ ይገርፋል። የወረዳው ፖሊስ በህዝቡ በጣም ይጠላል። ባጠቃላይ የአፅቢ ወንበርታ ህዝብ በመንግስት እምነት የለውም። ህወሓትን አይደግፍም። አስተዳዳሪዎቹ ህዝቡን በአሸባሪነት ፈርጀውታል። ህዝቡና አስተዳዳሪዎቹ በፍትሕ እጦት ምክንያት ሆድና ጀርባ ከሆኑ ቆይተዋል።
Immediate Cause: የካሳ ጥያቄ
በአፅቢ ወንበርታ ወረዳ “ሕኔቶ” ተብሎ በሚጠራ መንደር በመንግስት ባጀት የተገነባ ግድብ አለ። ግድቡ የተቆፈረ ትልቅ የውኃ ጉድጓድ ነው። የውኃ ጉድጓዱ የተቆፈረበት ቦታ ሰፊ የእርሻና የግጦሽ መሬት ነበር። ቁፈራው ሲጀመር ለባለ መሬቶቹ ተገቢ ካሳና ተለዋጭ መሬት እንደሚሰጣቸው በመንግስት ቃል ተገብቶላቸው ነበር። ባለመሬቶቹም በጉዳዩ ተስማምተው ጉድጓዱ ተቆፈረ (ግድቡ ተገነባ)። ለገበሬዎቹ የተገባ የካሳ ቃል ግን አልተተገበረም። መንግስት ቃሉ አጠፈ። ገበሬዎቹ በተደጋጋሚ ጠየቁ። መልስ አላገኙም። የወረዳው አስተዳዳሪዎች ህዝቡን ሰብስበው ምንም ዓይነት የካሳ ጥያቄ እንዳያነሳ አስጠነቀቁት።
ባለ መሬቶቹ መሬት አልባ ሆኑ (በፍትሕ እጦት ምክንያት)። ካሳም አልተከፈላቸውም። ተለዋጭ መሬት ስላልተሰጣቸው የመስኖ ተጠቃሚም መሆን አልቻሉም። በመስኖው እንዲጠቀሙ መሬት የተሰጣቸው የተወሰኑ የስርዓቱ አገልጋዮችና ሌሎች ከግድቡ በመስኖ መጠቀም የሚችሉ (በቶፖግራፊ ምክንያት) የሌላ ቁሸት (ቀበሌ) ናቸው።
በግድቡ ምክንያት መሬታቸው ያጡ ገበሬዎች (ካሳ ያልተከፈላቸው) ልጆቻቸውን ወደ ስዑዲ በመላክ ይተዳደሩ ነበር። አሁን ይጠውሯቸው የነበሩ ልጆቻቸው አብዛኞቹ ከስዑዲ ተመልሰዋል። መሬት ወይ ካሳ ይፈልጋሉ። እንደገና ጥያቄው ተነሳ። አስተዳዳሪዎችም “አርፋቹ ተቀመጡ፤ አለበለዝያ ከዚህ እናጠፋችኋለን። ለተቃዋሚዎች (ጥያቄ ለሚያነሱ ማለት ነው) ቦታ የለንም። ጥያቄም አናስተናግድም” የሚል የማስፈራርያ መልስ ተሰጣቸው።
ጥያቄ የሚያነሱ ገበሬዎች ከግድቡ መስኖ ከሚጠቀሙ ገበሬዎች ጋር በጉዳዩ ተወያዩ። “መንግስት ካሳ ይክፈለን፤ እናንተም ከኛ ጋር ጠይቁ። አግዙን ወይም ደግሞ እናንተ ካሳ ክፈሉን” የሚል ሐሳብ አነሱ። ምክንያቱም ግድቡ ያለው በሰዎች መሬት ላይ ነው። ባለመሬቶቹ ተመልካቾች ሌሎች ተጠቃሚዎች የሚሆኑበት ሁኔታ ፍትሐዊ አይደለም የሚል የክርክር ሐሳብ ተነሳ። ባለ መስኖዎቹም በካሳ ጥያቄው ተስማምተው መንግስት ለገበሬዎቹ ካሳ መክፈል እንዳለበት ሐሳብ ቀረበ።
አስተዳዳሪዎችም ካሳ እንደማይከፍሉ አረጋገጡ። ህዝብ ካመፀ የሃይል እርምጃ እንደሚወስዱ አስጠነቀቁ። ባከባቢው የነበሩ አስራ አምስት ምልሻዎች ትጥቃቸው በሃይል እንዲፈቱ ተደረገ። ግጭት እንደሚነሳ ታወቀ።
የ ሐሙስ ዓመፅ
ካሳና ተለዋጭ መሬት የተከለከሉ ገበሬዎች ዓመፅ ጀመሩ። ዓመፁ የተጀመረው “ግድቡ በመቆጣጠር” ነበር። መፍትሔ እስኪገኝ ድረስ በግድቡ የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ (የመስኖ ስራ ጨምሮ) እንዲቆም አደረጉ። “ግድቡ መሬታችን ነው፤ ተገቢውን ካሳ ካልተሰጠን ዉኃችን አንሰጥም” አሉ። ግድቡን ለማስለቀቅ የፖሊስ ሃይል ተላከ። ዓመፁና ግርግሩ ተጀመረ። ፖሊስ መቆጣጠር ስላልቻለ መከላከያ ሰራዊት ገባ።
ስለዚህ የዓመፁ መነሻ የፍትሕ እጦት ነው። መንግስት የገባውን ቃል ባለማክበሩ የተፈጠረ ዓመፅ ነው።
አሁን ከወረዳ አስተዳደሩ የደረሰኝ መረጃ እንደሚያመለክተው የወረዳው አስተዳዳሪዎች የህዝብ ዓመፅ ከሽብርተኝነትና ተቃዋሚ ፓርቲዎች (ዓረና) ጋር በማገናኘት ዜጎችን ለማስወንጀል ተዘጋጅተዋል። ሌላኛው ዕቅድ ደግሞ ህዝቡን ለመከፋፈል ያለመ ስትራተጂ እየቀረፁ ነው (መስኖው የሚጠቀምና የማይጠቀም በማለት ለሁለት ሊከፍሉት ነው)። በአንድ በኩል ለዓመፁ ተቃዋሚ ፓርቲን ተጠያቀ ማድረግ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በመስኖው የሚገለገሉ ገበሬዎች ከአስተዳዳሪዎቹ ጎን እንዲሰለፉና ህዝቡ እንዲከፋፈል ለማድረግ እያሴሩ ነው። ከተሳካላቸው ህዝብ ከህዝብ ጋር በማጣላት እነሱ ከሐላፊነት ለማምለጥ መመኮራቸው አይቀርም። ህዝብ ይህን የህወሓት ከፋፋይ ስትራተጂ ነቅቶ መጠበቅ አለበት። (እኛን ያልደገፈ መስኖ አይጠቀምም በማለት መስኖ ተጠቃሚዎቹ በ አስተዳዳሪዎች ጎን ለማሰለፍ ጥረት ሊያደርጉ ይችላሉ)።
ዓርብ 09/05.06 ዓም ከጠዋቱ 3:05 ተፃፈ
የአፅቢ ዓመፅ (ክፍል ስምንት)
—————————–
ህዝቡ እየተሰባሰበ ነው፣ የፌደራል ፖሊስ እየገባ ነው
አከባቢው በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ይገኛል። የአፅቢ ወንበርታ ህዝብ (ሕነይቶ) በፖሊስ የታሰሩትን ወገኖቹ ለመቀበል ባከባቢው እየተሰባሰበ ነው። የተያዙትን ሰዎች ግን እስካሁን ድረስ ባከባቢው የሉም። በነሱ ምትክ ብዙ የፌደራል ፖሊሶች አከባቢውን (ከመከላከያዎች ጋር በመሆን) እየተቆጣጠሩት ይገኛሉ።
ትናንት በፖሊስ ተይዘው ወዳልታወቀ ስፍራ የተወሰዱ ያከባቢው ኗሪዎች ብዛታቸው በዉል አይታወቅም። ህዝብ እያየ ፖሊስ እየደበደበ የወሰዳቸው አራት ሰዎች ግን የሚከተሉ ናቸው።
(1) ታደሰ ሃይሉ
(2) አሰፋ ካሕሳይ
(3) ገብረእግዚአብሄር ገብረሚካኤል
(4) የአቶ ግርማይ ግብረየሱስ ልጅ (የ16 ዓመት ወጣት) ናቸው።
የአፅቢ ወንበርታ ህዝብ በታሪክ ይህን ያህል ግፍ ያደረሰበት መንግስት እንዳልነበረ አስተያየት ሰጪዎች እየተናገሩ ነው። አስተያየት ሰጪዎቹ ለመብት ጥያቄ ይህን ያህል ግፍ መፈፀም አግባብነት የለውም ይላሉ።
የተፈጠረ አዲስ ነገር ካለ አቀርባለሁ።
(ዓርብ ጠዋት ከረፋዱ አምስት ሰዓት ነው የተፃፈው)።
የአፅቢ ዓመፅ (ክፍል ዘጠኝ)
ህዝቡ እንዳይንቀሳቀስ በፌደራል ፖሊስ ተከቧል
———————————————
አሁን ዓርብ ከጠዋቱ አምስት ሰዓት ተኩል ነው። ዓመፁ ወደ ሌላ አከባቢ እንዳይሰፋ በመፍራት የፌደራል ፖሊሶች አከባቢው ከበውታል፤ ህዝቡም በፖሊስ ተከቧል። የፖሊስ አዛዦች ህዝቡን እያስፈራሩ ይገኛሉ። ህዝቡም መብቱ እንዲከበርለትና ታፍነው የተወሰዱ ወገኖቹ (ትናንት ማታ በተገባላቸው ቃል መሰረት) እንዲፈቱ እየጠየቀ ነው። አከባቢው ግን ተከቧል። ካከባቢው መውጣትና ወደ አከባቢው መግባት ተከልክሏል። አንድ ባህረ ገብሩ የተባለ ያከባቢው ኗሪ ካከባቢው ወደ አፅቢ ከተማ ሲጓዝ በፖሊስ ታፍኖ ወዳልታወቀ ቦታ ተወስዷል።
ህዝቡ ታፍነው የተወሰዱ ያከባቢው ኗሪዎች ፖሊስ ይደበድባቸዋል፣ ይገድላቸዋል በሚል ስጋት ተጨናንቀዋል። ሳይፈቱም ህዝቡ እንደማይበተን አስታውቀዋል። የፖሊስ ማስፈራርያው ግን አይሏል። ባከባቢው በዜጎች ላይ ግፍ ሲደርስ የተለመደ በመሆኑ የተያዙት ሰዎች ድብደባና ግድያ እንደሚጠብቃቸው ይገመታል።
ባከባቢው (አፅቢ ወንበርታ) እስካሁን ድረስ (ከዚህ ቀደም ማለት ነው) ታደሰ ጊደይ አባዲ የተባለ የሩባ ፈለግ ኗሪ በመንግስት አካላት በጥይት ተገድላል። የአቶ ገብረሂወት (ስሙ ለግዜው አልያዝኩትም) ልጅም በመንግስት አካላት በጥይት ተመቶ ህይወቱ አልፏል። አቶ ገብረሚካኤል ተስፋይ (ጣብያ ፈለገወይኒ)፣ አቶ ታደሰ መዝገቦ (ጣብያ ሩባ ፈለግ)፣ አቶ ህይወት አባይ (ጣብያ ሩባ ፈለግ) ወዘተ በፖሊስ ድብድባ (ቶርቸር) እንደደረሰባቸው ታውቋል: ከፍተኛ የስነ ልቦና ጉዳት ደርሶባቸዋል።።
ከዚህ በመነሳት ታፈነው በተወሰዱ ዜጎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የህዝብ ቅሬታ አለ። ፖሊስ ግን ህዝቡን ከቦ አላንቀሳቅስ ብሏል።
(በ 5:55 ተለጥፏል)።
የአፅቢ ወንበርታ ህዝባዊ ዓመፅ (ክፍል አስር)
የህወሓት አመራር አባላት ባከባቢው ይገኛሉ
————————————
አከባቢው በብዙ የወረዳና የክልል ፖሊሶች፣ የፌደራል ፖሊሶችና መከላከያ ሰራዊት ተከቦ ህዝቡም እንዳይንቀሳቀስ ታግቶ በመከላከያ ሰራዊት የታጀቡ የዞንና ክልል አስተዳዳሪዎች (የህወሓት ባለስልጣናት) ህዝቡን እያነጋገሩ ነው። ባለስልጣናቱ ህዝቡ ዓመፁ የቀሰቀሰው ማን እንደሆነ፣ ለምን የሃይል መንገድ መጠቀም እንደመረጠ ወዘተ በማስፈራራት እየጠየቁ ነው። ህዝቡም የመሬቱ ካሳ ወይ ተለዋጭ መሬት የማግኘት መብቱ እንዲከበርለት፣ ታፍነው የተወሰዱ እንዲፈቱ ይጠይቃል። መግባባት የለም። የህዝቡ ጥያቄ ያናደዳቸው አስተዳዳሪዎች ህዝቡ ትናንት የቀሰቀሰው ዓመፅ “ስህተት” መኖሩ ካላመነ ወደ ቤቱ እንዲሄድ እንደማይፈቅዱለት እያስፈራሩት ነው። ህዝቡ በሃይል ዓፍነው ይዘውታል (በፀጥታ ሃይል ብዛት)። የኢህአዴግ የደህንነት ሰዎች እዛው ይገኛሉ። ካከባቢው ለመውጣትና ወደ አከባቢው ለመግባት የሞከሩ የአከባቢው ኗሪዎች እየታሰሩ ነው። እስካሁን ሰባት ሰዎች ታስረዋል (አንድ ሃፍቱ ገብረመድህን የተባለ የቀድሞ የመከላከያ ሰራዊት አባል ጨምሮ)።
ዓርብ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ተኩል ተፃፈ።
የአፅቢ ወንበርታ ህዝባዊ ዓመፅ (ክፍል አስራ አንድ)
————————————
-
ትልቁ ኪሳራ
የትናንትው የአፅቢ ወንበርታ ህዝባዊ ዓመፅና የፖሊሶች ተኩስ (የነበረውን አጠቃላይ ግጭት) በካሜራና በሞባይል ሲቀርፁ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ። የግጭቱ ሙሉ ሂደት ቀርፀው ለህዝብ ለመበተን ዉቅሮ ከተማ ሊገቡ ሲሉ በልዩ የህወሓት የደህንነት ሃይሎች ተይዘዋል። ታፍነው ወዳልታወቀ ቦታ ተወስደዋል። ሞባይላቸውና ካሜራቸው ተነጥቀዋል። ህወሓቶች የአፅቢ ወንበርታ ህዝብ በደልና ዓመፅ ሌሎች ህዝቦች እንዳይሰሙት ለማፈን በማቀድ ቪድዮውን ይዘውታል። መረጃው መበተኑ ግን አይቀርም። ለኔ ግን ትልቅ ኪሳራ ነው።
ይህን የተደረገው ዓርብ 09/05/06 ዓም ከቀኑ ስምንት ከአርባ (8:40) ነው።
አቡጊዳ 

PM’s adviser says ‘however we treat farmers, they won’t rise’

ESAT News
January 17, 2013
The former Minister of Communications and now the advisor of Prime Minister Hailemariam Dessalegn, Bereket Simon, said at a recent meeting and evaluation with ministers and top leadership of the Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) “because farmers are happy with the works we have done for them so far, they will come to any demonstration if we call them, sleep if we order them and bear anything this government does
As 30% of our expenses is covered by foreign aid, to be clear from external dependency we have to get an income that covers our expenses, said Bereket admitting that just after the 2005 general election was held, foreign powers had stopped giving us aid because we had arrested the opposition.
He also recollected that during the drought that occurred in 1992, the Head of the American aid organisation had said that they would not give them an aid unless they changed their land policy.
EPRDF is giving training to all its members from the top to the bottom brass on how they could win the upcoming general election in 2015. The Front as well as Bereket are fully confident that they will win the election. Cadres of EPRDF are also reportedly engaged in the organisation of farmers through a one-to-five system of organisation and distributing pieces of land to disgruntled youth in rural areas.

Semayawi Party - the Newest Opposition Sensation - Raises New Hopes

January17/2014

Seattle is one of the hotspots of American cities that attract Ethiopian opposition groups.

For instance, the latest visitor to Seattle was Yilkal Getnet, chairperson of Semayawi Party, the newest and youngest opposition sensation that has raised the hopes of the Ethiopian people for change.

Semayawi Party has also sparked questions like will it succeed in the place where others failed? Will it endure, and eventually remove the hopelessly corrupt and ruthless TPLF/EPRDF regime?




Answers may be mixed but one glaring credit to Semayawi Party is that its defiant actions have helped wake up the opposition party Medrek from its deep sleep. It was Semayawi Party that held an opposition rally in Addis Ababa, despite ruling party threats of arrests and beatings. It was also Semayawi Party that travelled to Benishangul Gumuz to show support to those who were being uprooted from their homes because of their Amhara ethnicity. It was a wake-up call for others.

There are marked differences between Semayawi Party and the other leading opposition party known closely to the Diaspora, and that is Medrek.

One difference is while Medrek is led by veterans of the non-violent form of struggle during EPRDF's 23 years of rule, Semayawi is a new comer that was born out of the womb of Andinet, which until recently was a Medrek founding member. And Semayawi is almost exclusively a youth organization, a major asset given that 70 percent of the Ethiopian population is under 35 years of age.

The toddling Semayawi Party has already won the endorsement of Alemayehu Gebremariam, a prominent political science professor at University of California in St. Bernadino. "I've thrown my trust behind Semayawi Party because I believe that they are capable to bring about the desired political change in Ethiopia," Almariam said, when he addressed Seattle on January 12.

For the young Semayawi Party, it was an accolade that came at the right time and was rare among other opposition parties.

To the Ethiopian Diaspora, specially to Seattle, Semayawi Party was embraced as a force promising to effect change. This is felt, among others, when the fearless Yilkal wisely addressed some thorny issues such as Emperor Menelik as well as the merits of a non-violent form of struggle as opposed to the destructive armed struggle which, even if won, favors the coming to power of an armed group, and hence the vicious cycle of dictatorship.

The Seattle audience rewarded Semayawi Party by raising $14,500 right away, and this was a generous amount given that it was Semayawi's first-ever visit to North America, and yet the outcome has been better than what Medrek had experienced in Seattle.

Medrek's last delegation consisting of veterans Seeye Abraha and Merera Gudina didn't leave a good taste in the mouth of the Diaspora opposition. The time coincided with the death of the tyrant Meles Zenawi. So, Medrek's delegate Seeye seized the moment and lectured about how Meles was respected by the Ethiopian people.

"When the body of Meles arrived at Bole Airport at night," Seeye said, "the residents of Addis Ababa came out en masse, wailed in public, and despite a heavy downpour, escorted the coffin. By the time they got to the palace, it was 2:00AM."

Seeye's remarks raised the eyebrows of the audience. He didn't stop there either, and continued to pour lavish words of praise over the ruthless tyrant who reduced Ethiopia to a landlocked nation that he successfully tormented along ethnic lines.

"The Ethiopian people have relatively prospered during EPRDF's peace-time rule of over 20 years," Seeye said, without blinking his eyes.

Is this really Seeye Abraha or Shimelis Kemal? The audience was confused. He said much more but what's already mentioned is suffice to give the reader a clue.

Merera Gudina, long known for his incisive remarks against the EPRDF regime, also joined the Seeye chorus, and looked timid and subdued.

"We don't go by the interest of the Ethiopian Diaspora," Merera said. He told the audience in Amharic: "Benante Wuha Lik anihedim; Ager Bet Balew Wuha Lik Enjee!" (በእናንተ ውሃ ልክ እንሄድም፣ አገር ቤት ባለው ውሃ ልክ እንጂ!)

The message was clear. It is 'We don't listen to you.' If so, why the trouble of coming to the Diaspora?
It was very clear Medrek, or in Seeye's case Andinet, was in big trouble. Seeye was much more sounding like EPRDF I wonder how his former comrades in the ruling party failed to roll out a Red Carpet upon his arrival at Bole Airport.

But wait? Hasn't he already quit Andinet for a high-paying job with the UN Peacekeeping force? [The Americans had reportedly asked Meles if there was a problem hiring Seeye for the job. Meles said he had no problem. Some say Seeye's eulogy, despite his suffering in prison for years, was a tribute for Meles].
Medrek had sent two delegations to America. Seeye and Merera to the West Coast, which was a disaster. Medrek's image was saved thanks to the accomplishments by the charismatic Temesgen Zewde of Andinet and Gebru Asrat of Arena as Medrek's East Coast delegates. This writer was in Washington, DC as well when the two veterans addressed the audience which was very much appreciative of the way how Temesgen and Gebru addressed key national issues as 'opposition leaders.'

Today Andinet has pulled itself out of Medrek, and with the return of Engineer Gizachew Shiferaw as chairperson of the party, one new question everyone asking is "Again?". Well, will Gizachew be a comformist to the decadent EPRDF rule, or a born-again defiant figure in the face of EPRDF ruthlessness? Time will tell.

For now, it looks like Semayawi Party has had an auspicious moment in North America. Kudos to the youth!

 Ethiomedia

አቶ መላኩ ፈንታ ክሴ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ይታይልኝ አላልኩም አሉ

January17/2014

አቶ መላኩ ፈንታ ክሴ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ይታይልኝ አላልኩም አሉ
‹‹የቀረበብኝ ክስ ብዙ በመሆኑ መቃወሚያ ለማቅረብ ረዘም ያለ ቀጠሮ ይሰጠኝ›› አቶ ገብረ ዋህድ ወልደ ጊዮርጊስ 
-  አቶ ጌቱ ገለቴና ሌሎች ተጠርጣሪዎች በጋዜጣ እንዲጠሩ ታዘዘ
በተጠረጠሩበት ከፍተኛ የሙስና ወንጀል፤ በፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ ክስ ተመሥርቶባቸው ላለፉት ስምንት ወራት በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ፣ ‹‹ክሴ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ይሁን ብዬ የጠየቅኩት እኔ አይደለሁም፤›› አሉ፡፡
አቶ መላኩ ተቃውሞአቸውን ያቀረቡት ጥር 6 ቀን 2006 ዓ.ም. የተጠረጠሩበትን ክስ እየመረመረው ለሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 15ኛ ወንጀል ችሎት ነው፡፡ እሳቸው ሳይጠይቁና ምንም ሳይናገሩ በርካታ የመገናኛ ብዙኃን እሳቸው እንደጠየቁና እንደተከለከሉ አድርገው መዘገባቸውን በመቃወም፣ እንዲስተካከል ወይም ታርሞ እንዲዘገብ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ጠይቀዋል፡፡ 
ፍርድ ቤቱ በበኩሉ በሰጠው ምላሽ እንደገለጸው፣ ጥያቄውን ያቀረበው ፍርድ ቤቱ ነው፡፡ የመገናኛ ብዙኃን ከፍረጃ ጋር በማያያዝ ዘገባ እንዳያስተላልፉ ከማስጠንቀቂያ ጋር የሰጠውን ትዕዛዝ ካስታወሰ በኋላ፣ ሁሉም የመገናኛ ብዙኃን በትክክል ባይዘግቡም ሁሉም ደግሞ ተሳስተዋል ማለት እንደማይቻል ገልጿል፡፡ ፍርድ ቤቱ ከዚህ በላይ የሚለው ነገር እንደሌለ በማሳወቅ ተከሳሾቹ ጠበቆቻቸውን አማክረው የስም ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞብናል የሚሉ ከሆነ፣ የሚመለከተውን አካል መጠየቅ እንደሚችሉ አስረድቷል፡፡ 
ሌላው ፍርድ ቤቱ በዕለቱ መዝገቡን ቀጥሮ የነበረው የአቶ መላኩን ክስ የማየት ሥልጣን ያለው ፍርድ ቤት የትኛው እንደሆነ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከሕገ መንግሥት አጣሪ ኮሚሽን በደረሰው የምርመራ ውጤት ላይ ውሳኔ ሰጥቶ እንዲያሳውቀው የሰጠውን ትዕዛዝ ለመጠባበቅ እንደነበር ለችሎቱ አስታውቋል፡፡ 
በመሆኑም ፌዴሬሽን ምክር ቤት ታህሣሥ 24 ቀን 2006 ዓ.ም. ባደረገው ውይይት፣ የአቶ መላኩን ክስ የማየት ሥልጣን ያለው ከፍተኛው ፍርድ ቤት መሆኑን በማሳወቁ፣ በእነ አቶ መላኩ ፈንታ ላይ የተመሠረተው ክስ በመደበኛነት እንደሚቀጥል አሳውቋል፡፡ 
የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ የክስ መግለጫ እንደሚያስፈልገው በመጠቆም፣ ተከሳሾች የክስ መቃወሚያ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑም በችሎት ተነግሯቸዋል፡፡ ተጠርጣሪ ተከሳሾቹ በክሱ ላይ ቅሬታ እንዳላቸውና መቃወሚያ እንደሚያቀርቡ ተናግረው፣ ከክሱ ስፋት አንፃር ረዘም ያለ ጊዜ እንዲሰጣቸው ሲያመለክቱ፣ የአዲስ ኢንተርናሽናል ካርዲያክ ሆስፒታል ባለድርሻ የሆኑት ተጠርጣሪ ተከሳሽ ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ ተቃውሞአቸውን ለፍርድ ቤቱ አቅርበዋል፡፡ 
‹‹ጠበቆች እየጠየቁ ያሉት ረጃጅም ጊዜ በመሆኑ እኛ የተፋጠነ ፍትሕ የማግኘት መብታችንን ያጣብብብናል፡፡ የምንፈልገው አጭር ቀጠሮ እንዲሆንልን ነው፤›› በማለት አመልክተዋል፡፡ አብዛኛዎቹ ተጠርጣሪ ድጋፋቸውን ሰጥተዋቸዋል፡፡ 
የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የሕግ ማስከበር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ገብረ ዋህድ ወልደ ጊዮርጊስ ግን የእነ ዶ/ር ፍቅሩን ተቃውሞ በመቃወም፣ ‹‹እኔ ብዙና ሰፊ ክስ አለብኝ፡፡ ጠበቆቼ በደንብ ተረድተውና አብራርተው የክስ መቃወሚያ እንዲያቀርቡ ረዘም ያለ ቀጠሮ ይሰጠን፤›› በማለት ለፍርድ ቤቱ አመልክተዋል፡፡ 
ፍርድ ቤቱ የተጠርጣሪ ተከሳሾቹን ማመልከቻ ከሰማ በኋላ ብይን ሰጥቷል፡፡ በሰጠው ብይንም፣ በተጠረጠሩበት የተለያየ የሙስና ድርጊት ወንጀል ክስ ቢመሠረትባቸውም በችሎት ሊቀርቡ ያልቻሉት አቶ ጌቱ ገለቴን ጨምሮ ሌሎችም ግለሰቦች በጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግላቸው ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ እንዲሁም በችሎት ተገኝተው ክሳቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙትና የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግን ክስ በሚመለከት መቃወሚያ እንዳላቸው ያመለከቱ ተጠርጣሪዎች ለጥር 29 ቀን 2006 ዓ.ም. ተቃውሞአቸውን እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

መሬታቸው ለህንድ ሻይ ልማት ኩባንያ መሰጠቱን የተቃወሙ ኢትዮጵያውያን ከመንግስት ዱላ ገጠማቸው

January 17/2014

ሰንደቅ ጋዜጣ ከአዲስ አበባ እንደዘገበው፦

በጋምቤላ እና በሸካ አዋሳኝ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ህዝቦች መካከል 100 ሺ የሚሆኑ የሸካ ተወላጆች 3012 የሚደርስ ሄክታር መሬት ከአካባቢያችን ጥብቅ ደን ተወስዶ ቨርዳንት ሃርቨስት አግሮ ኢንዱስትሪ ለተሰኘ የህንድ ኩባንያ መሰጠቱን በመቃወማችን ጉዳት እየደረሰብን ነው ሲሉ የብሔሩ ተወላጆች ምሬታቸውን ለሰንደቅ ጋዜጣ ገለጹ። በክልሉ እንደተካተቱት ሌሎች አምስት ብሔሮች ስድስተኛ ሆነን አልተመዘገብንም፤ ልጆቻችን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ማስተማር አልቻልንም፤ በክልሉ ተገቢ የሆነ የመሰረተ ልማት ግንባታ ተጠቃሚ አልሆነም፤ ለዚህም አካባቢው የሚካሄደውን ኢንቨስትመንት ተቃዋሚ እንደሆነ ተደርጎ መታሰቡ አግባብ አለመሆኑን የሸካ ህዝቦች ተወካይ በመሆን አቤቱታቸውን ለማሰማት የመጡት አቶ ታምሩ አምበሉ አስረድተዋል።


በጋምቤላ ክልል የመጀንግ ዞን አመራር የሆኑት አቶ ይማም ቃሪስ በበኩላቸው ይህንን አቤቱታ የሚያሰሙት ጥቂት ግለሰቦች የራሳቸውን ፖለቲካዊ ፍላጎት ያላቸውና ተጨፈጨፈ የሚሉትም ጥብቅ ደን ሳይሆን ቁጥቋጦ ነው ብለዋል። አክለውም እንደጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ደንብና አሰራር መሰረት የህንዱ ኩባንያ መሬቱን እንዲያለማ መፍቀዳችን ትክክል ነው ይላሉ።

የሸካ ህዝቦች ለዘመናት ጠብቀው ባቆዩት ጥብቅ ደን ውስጥ ማር በማምረት እንደሚተዳደሩ ያስረዱት አቤቱታ አቅራቢዎቹ የአካባቢውን ህዝብ ባላማከለ መልኩ ጥብቅ ደኑን እንዲጨፈጨፍ ማድረግ ከውስጡ የሚመነጩትን ወንዞች መጉዳት ነው ሲሉ ከአካባቢ ጥበቃ አንፃር መፍትሄ ሊበጅለት ይገባል ይላሉ። ይህንንም አስመልክተው በ1999 ዓ.ም የብሔር ብሔረሰቦች መብት ተጠቃሚዎች አይደለንም በሚል ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የ1200 ሰዎችን ፊርማ አሰባስበው የመብት ጥያቄ አቅርበው እንደነበር በማስታወስ፤ የመብት ጥያቄያቸው ሳይመለስ እስከ 2002 ዓ.ም መጠበቃቸውንና አልፎም የህዝቡን ዋና መተዳደሪያ የሆነውን ጥብቅ ደን ለማጥፋት ምክንያት ሆኖብናል ይላሉ።

በተለይም የህንዱ ቨርደንት ሃርቨስት አግሮ ኢንዱስትሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መዠንገር ዞን ጎደሬ ወረዳ የጎማሬ ቀበሌ አስተዳደር በሸካ ክልል ውስጥ ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግለትን 3012 ሄክታር ጥብቅ ደን ለሻይ ልማት መፈቀዱ አግባብ አይደለም ሲሉ በተለያዩ መንገዶች አቤቱታቸውን አሰምተዋል። “እኛ ምንም አይነት ኢንቨስትመንትን የመቃወም ኀሳብ እንደሌለን እንዲታወቅልን እንፈልጋለን” የሚሉት የህዝቡ ተወካዮችና አቤቱታ አቅራቢዎች፤ ይህ ቦታ አማራጭ ቢፈለግለት ይሻላል። ደን ከጠፋ ዘራችን የአኗኗር ባህላችን ሁሉ ይጠፋል የሚል እንደሆነም ተናግረዋል። ያም ሆኖ ለኩባንያው ግንባታ ሲባል በ67 ሄክታር ላይ የሚገኝ ደን ተጨፍጭፎ 1640 በላይ ጣውላዎች ወጥተው ተገኝተዋል ሲሉ አስረድተዋል።

ይህን ጉዳይ አስመልክቶ የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት አቶ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በወቅቱ ለአካባቢ ጥበቃ ኃላፊ በፃፉት ደብዳቤ፤ በጋምቤላ አካባቢ ያለውን የተፈጥሮ ደን ያለበት ሰፊ መሬት ደኑ በጣም ጥቅጥቅ ያለና ለአየር ጥበቃ ሊቆይ የሚገባው ሆኖ ሳለ ለሻይ ልማት ኢንቨስትመንት ተሰጥቶ ሊመነጠር ስለመሆኑ የአካባቢው ህዝብ ይህን ችግር ለማሳወቅ ሰዎች ወክሎ መላኩን በመግለፅ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ ማሳሰባቸውን ተናግረዋል።

በበርካታ ባለሙያዎች ጥናት ተደርጎለት የአካባቢው የደን ሀብት እንዲጠበቅ ቢወሰንም አሁንም ድረስ የተሰራ ስራ አለመኖሩንና የአካባቢው ህዝብም ስጋት ላይ መሆኑን በመጥቀስ ህዝብና መንግስት ጉዳያችን ተረድቶ ጥብቁን ደን ከጥፋት ይከላከለው ዘንድ ድምጻችንን እናሰማለን ብለዋል፤ አቤቱታ አቅራቢዎቹ።

የመጀንግ ዞን አመራር በሰጡት ምላሽ ቦታው ጥናት ተደርጎበት ለልማት የተመራ መሆኑን በመግለፅ፤ ኩባንያው የሻይ ልማት ስራውን ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ እየሰራ እንደሚገኝና ነገር ግን ጥቂት የግል ፍላጎት ያላቸው ግሰቦች እንቅፋት የሚሆን እንቅስቃሴ አድርገዋል ሲሉ ይወቅሳሉ።

ዘ-ሐበሻ

አንድነት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ማካለል ዙሪያ ሕዝባዊ ውይይት ሊያደርግ ነው

January 16/2014

ከያሬድ አማረ/ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ

አንድነት ፓርቲ ጥር 18/2006ዓ.ም በኢትዮ ሱዳን ድንበር ማካለል ዙሪያ ከህዝብ ጋር ውይይት እንደሚያካሂድ አስታወቀ።

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በኢትዮ ሱዳን የድንበር ማካለል በሚል በሁለቱ መንግስታት ብቻ በሚስጥር በተያዘው መርሀ ግብር ዙሪያ ከህዝብ ጋር ውይይት እንደሚያደርግ ተገልጧል፡፡

ፓርቲው በመጪው ጥር 18ቀን 2006ዓ.ም የሚያካሂደው ህዝባዊ ውይይት በኢትዮጵያ በመንግስትና በሱዳን መንግስት መካከል ይፋ ባልሆነው የድንበር ማካለሉ ሂደት ግልፅነት የጎደለው የድንበር ማካለል በሚል ሽፋን ሊደረግ የታሰበና በአካቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ለሰቀቀን የዳረገ ከመሆኑም ባሻገር በጉዳዩ አሳሳቢነት ዙሪያ መወያየት አስፈላጊ በመሆኑ ፓርቲው ከህዝብ ጋር ተወያይቶ ግልፅ አቋሙን የሚያሰቀምጥበት በመሆኑ የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ሁሉ በውይይቱ ላይ በመገኘት ሃሳቡን እንዲገልፅ አንድነት ጥሪውን አቅርቧል፡፡

በሌላ ዜና አንድነት ፓርቲ ለአማራ ክልል እና ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢትዮ ሱዳን ድንበር ማካለል ጉዳይ በአጭር ግዜ ውስጥ ለህዝብ ግልፅ እንዲሆን በደብዳቤ አሳሰበ።

አንድነት ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደርና ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በኢትዮ ሱዳን የድንበር ማካለል ዙሪያ ግልፅ የሆነ ማብራሪያ በአጭር ግዜ ውስጥ ለህዝብ እንዲሰጥ በደብዳቤ ጠይቋል።

የአንድነት ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ለፍኖተ ነፃነት እንደገለፁት ኢህአዴግ በሉአላዊ ግዛት ማስከበር ጉዳይ የግዴለሽ አመለካከት ያለው በመሆኑ ብሔራዊ ጥቅማችንን ሊጎዳ የሚችል እርምጃ ሲወስድ በመቆየቱና የተለማመድው በመሆኑ አሁንም በተለመደው ግብሩ ለህዝብ ግልፅ ባልሆነ ሁኔታ ሊካሄድ የታቀደው የድንበር ማካለል የኢትዮጵያን ጥቅም ባላስጠበቀ መንገድ ሊፈፀም እንደሚችል ፓርቲው ከፍተኛ ስጋት ስላደረበት ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለና በሚስጥር የያዘው የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳደርም ሆነ ጠቅላይ ሚንስትሩ ስለ ድንበር ማካለሉ አጠቃላይ ዝርዝር ሁኔታ ለህዝቡ በአጭር ግዜ ውስጥ ግልፅ የሆነ ማብራሪያ እንዲሰጥ በደብዳቤ መጠየቃቸውን ገልፀዋል፡፡

Thursday, January 16, 2014

ሕወሃት የትግራይን ሕዝብ እያሸበረ ነዉ ፣ ድብደባዉ፣ ለቅሶው፣ ተኩሱ ተጧጡፏል

January 16/2014

 አፅቢ ወንበርታ በምስራቅ ትግራይ የምተገኝ ወረዳ ናት። በ2007 ሕዝብ ቆጠራ መሰረት፣ ከመቶ አሥር ሺህ በላይ ነዋሪዎች ያሏት ናት። የአጽቢ ወረርታ ወረዳ ተብላ ትታወቃለች። በወረዳዋ መሃከል የምትገኝዉ ከተማ የአጽቢ ከተማ ናት። ከመቀሌ70 ኪሎሜተር በስተሰሜን፣ ከአዲግራት 94 ኪሎሜተር በስተደቡብ፣ከዉቅሮ 20 ኪሎሜተር በስተ ምስራቅ የምትገኝ ናት።

 የዚህ ከተማ ነዋሪዎች በከፍተኛ ዉሃ እጥረት ምክንያት ከሕወሃት/ባለስልጣናት ጋር ትልቅ ዉዝግብ ላይ ናቸው። በከተማዋ የሚኖሩ ገበሬዎችን የሚወክሉ አራት አዛዉንት ታግተው የታሰሩ ሲሆን፣ ሕወሃቶች ሕዝቡን እየደበደበ፣ እያሰቃዩ፣ መሳሪያም እየተኮሱ ነዉ። ሕዝቡ ለተወሰነ ጊዜ ፖሊሶችን አግቶ ፣ የወከሉን ገበሬዎች እንዲፈቱ የሚል ጥያቄ አቅርቦ የነበ ረ ቢሆን፣ ከለለኦች ወረዳዎች አካባቢዉን የማያወቅ ታጣቂዎቹን በማስመጣት ሕዝቡን እየደበደቡት ነዉ።

በቅርቡ ከአንድነት ፓርቲ ጋር ለመዋሃድ ጥያቄ ያቀረበዉና በድርድር ላይ የሆነዉ የአረና ትግራይ አመራር አባል፣ አብርሃ ደስታ፣ በፌስ ቡክ ከመቀሌ የዘገቡትን እንደሚከተለው አቅርበናል ፤ ይከታተሉ።

ሰበር ዜና

የአፅቢ ግጭት (ክፍል አንድ)

ባሁኑ ሰዓት (ሓሙስ 08/05/06 ዓም ከቀኑ 11:30 ጀምሮ) በአፅቢ ወንበርታ ወረዳ (ጣብያ ሩባ ፈለግ ቁሸት ሕኔቶ) በህዝብና አስተዳዳሪዎች መካከል (በውኃ አጠቃቀም ምክንያት) በተፈጠረ አለመግባባት ሃይለኛ አምባጓሮ ተፈጥሯል። ፖሊሶች ተኩስ ከፍተዋል (ከ11:30 እስከ 11:40 ሰዓት ባለግዜ ለሰላሳ ሰባት (37) ግዜ ተተኩሷል)። ምልሻዎች በተጠቀቅ ይገኛሉ። የመንግስት የሚድያ ሰዎች ሂደቱ እየቀረፁት ነው። የቆሰለ ውይም የሞተ ሰው ስለሞኖሩ ወይ አለመኖሩ በግርግሩ ምክንያት ለማወቅ አልተቻለም። ተኩሱ እየቀጠ ነው። ተጨማሪ መረጃ አቀርባለሁ።

የአፅቢ ግጭት (ክፍል ሁለት)

በአፅቢ ወንበርታ ወረዳ ህዝብና አስተዳዳሪዎች መካከል ባጋጠመ ግጭት ፖሊስ ቢተኩስም ችግሩ ከፖሊስ አቅም በላይ በመሆኑ አሁን አስተዳደሩ የመከላከያ ሰራዊትን እርዳታ ጠርቷል። አሁን የመንግስት ምልሻዎች በአከባቢው እየተሰማሩ ይገኛሉ። በግጭቱ የተሳተፈው ኗሪ ህዝብ ከሺ በላይ ይሆናል። እስካሁን ድረስ የኗሪው ህዝብ ተወካዮች የነበሩ አራት ሰዎች የት እንደገቡ አይታወቅም። ፖሊሶች ህዝቡን ለመበተን ሃይል ቢጠቀሙም ህዝቡ ግን አራቱ ተወካዮቹ ካልተለቀቁ ላለመበተን አድማ መቷል። ህዝብ እየተሰባሰበ ነው። (የተኩስ ድምፅ በስልክ አስደምጠውኛል)።

የአፅቢ ግጭት (ክፍል ሦስት)

በአፅቢ ወንበርታ በተከፈተው ግጭት የመንግስት ፖሊሶች ተኩስ መክፈታቸው፣ አርሶአደሮች መደብደባቸው፣ እንዲሁም አራት የኗሪዎቹ ተወካዮች በሃይል አስረው ወዳልታወቀ አከባቢ መውሰዳቸው ታውቋል። ህዝቡም (የአከባቢው ምልሻዎች ሳይቀሩ) አስራ ሁለትፖሊሶችና አንድ የመንግስት ምልሻ ከበው አግተው ይዟቸው ቆይተዋል። አራቱ የህዝቡ ተወካዮች እስካልተለቀቁ ድረስ ፖሊሶቹ እንደማይለቀቁ የአርሶ አደሮቹ ተወካዮች አሳውቀው ነበር። አሁን በተደረገ ድርድር አራቱ ተወካዮች ይፈታሉ፣ በህዝቡ ታግተው የነበሩ  አስራ ሁለት ፖሊሶችም ይለቀቃሉ። ህዝቡ የአራቱ ሰዎች መለቀቅ እየተጠባበቀ ይገኛል። ፖሊሶቹ ተለቀዋል፤ አራቱ ገብሬዎች እስኪፈቱ ድረስ ግን እዛው ይቆያሉ። መከላከያ ሰራዊት ጥሪ ቢቀርብላቸውም እስካሁን ድረስ (እስከ ምሽቱ 1:30) ባከባቢው አልደረሱም።

የአፅቢ ግጭት (ክፍል አራት) 

ድርድሩ አልተሳካም፡ ተኩስ ተከፍቷል ህዝብ እየተደበደበ ነው

ፖሊሶች አራት የኗሪዎቹ ተወካዮች በሃይል ሲወስዱ የአፅቢ ህዝብም አስራ አራት ፖሊሶችና አንድ ምልሻ አግተው ነበር። ህዝቡ ፖሊሶቹ እንዲለቅ አስተዳደሩ ደግሞ አራቱ ተወካዮች እንዲለቅ ድርድር ተጀምሮ ነበር። በድርድሩ መሃል የወረዳው አስተዳደር አዲስ ሃይል በመጥራት (ከሌላ ወረዳና ከክልል አስተዳደር የፀጥታ ሃይሎች በመላክ) ህዝብ በተሰበሰበብት መተኮስ ጀመሩ (ከምሽቱ 2:30-2:56)።ምልሻዎቹና ወታደሮቹ የታገቱትን ፖሊሶች ለማስለቀቅ እስከ ሁለት መቶ (በኗሪዎቹ ግምት መሰረት) የሚደርስ ጥይት በመተኮስ የታገቱት ፖሊሶችን ማስለቀቅ ችለዋል። እስከ ሁለት ሺ የሚጠጋ ህዝብ ተሰብስቦ እየጨኸ ይገኛል። አሁን (ከምሽቱ ሦስት ሰዓት) ብዙ ምልሻዎች የጫኑ ብዙ መኪኖች ወደ አከባቢው እየገቡ ነው። በሌላ አቅጣጫ (በስተ ሰሜን በኩል) ደግሞ ሌሎች ብዙ መኪኖች እየገቡ ነው (ምልሻ  ወይ ፖሊስ ወይ ወታደሮች መሆናቸው ግን በትክክል አይታወቁም)። ህዝብ በዱላ መደብደብ ጀምረዋል። ህዝቡ እየጮኸና ፈጣሪው እየለመነ ነው። የህዝቡ ጩኸትና ለቅሶ በስልክ መስማት ችያለሁ። እያናግሩኝ ያሉ ሰዎችም መረጋጋት ተስኗቸዋል። አሁን ከምሽቱ 3:05 ሁነዋል። 

የ አፅቢ ግጭት (ክፍል አምስት)

ተኩሱ ቆሟል፣ ምልሻዎቹ ለሁለት ተከፍሏል፣ወታደሮች ገብተዋል

ታግተው የነበሩ የመንግስት ፖሊሶች ሌሎች ፖሊሶችና ምልሻዎች በከፈቱት ተኩስ ተለቀዋል። አሁን ህዝቡና የመንግስት ምልሻዎች 
በሜትሮች ርቀት ተለያይተው ማዶ ለማዶ ይተያያሉ። የአፅቢ ወንበርታ ተወላጆች የሆኑ የመንግስት ምልሻዎች የመንግስት አካላትን ከድተው ከህዝቡ ጎን ተሰልፈዋል (ከአንድ ምልሻ በስተቀር ሁሉም የአፅቢ ወንበርታ ምልሻዎች ከህዝቡ ጎን ይገኛሉ)። ሁለቱም ምልሻዎች (የአፅቢ ወንበርታና አስተዳደሩ ከሌላ ወረዳ ያስመጣቸው) ተፋጠዋል። አሁን 3: 15 በደራ ጣብያ ገብረኪዳን ልዩ ስሙ “አፅገበት” የሚባል ቦታ የነበሩ ወታደሮች (መከላከያ ሰራዊት) ባከባቢው ደርሰዋል። እስካሁን ምንም ዓይነት እርምጃ አልጀመሩም። ፀጥታ ሰፍነዋል።ህዝቡ ግን እንደተሰበሰበ አለ። “ተወካዮቻችን ፍቱልን” እያለ ይገኛል። አሁን ከምሽቱ 3:24 ነው። 

 የአፅቢ ግጭት (ክፍል ስድስት) 

ወታደሮቹ ህዝብ እንዲበተን ጥሪ አቀረቡ

በሰባት መኪኖች ሙሉ ተጭነው ወታደሮች ገብተው አከባቢው ተቆጣጥረውታል። “የዞን አስተዳዳሪዎች ነን” ያሉ ባለስልጣናት ህዝቡ “የአሸባሪነት ተግባር” እያከናወነ መሆኑ በርቀት ተናግረዋል። ህዝቡም “አሸባሪዎች እናንተ ናች ሁ፤ ልጆቻችን ፍቱልን” እያለ ሲጮህ ነበር። በመጨረሻም ወታደሮቹ ህዝቡ እንዲበተን ማስጠንቀቅያ ቢሰጡም አራቱ የአፅቢ ወንበርታ ልጆች ካልተፈቱ እንደማይበተን አስታውቀዋል። መከላከያውና አስተዳዳሪዎቹ ቢያስፈራሩም ህዝቡ ግን ለመበተን ፍቃደኛ አልሆነም። ዘጋቢዎቼ ወደ ቤታቸው እየተንቀሳቀሱ ነው። ነገ እንገናኝ። አሁን ከምሽቱ 3:55 ነው። ቸር ያሰማን።

 




























“የአንድነት ፓርቲ የመጪው ጊዜ ፈተና” – የመልስ መልስ ለአቶ ግርማ ካሳ እና ለመሰሎቻቸው – ከፋሲል የኔዓለም (ጋዜጠኛ)

January16/2014

“የአንድነት ፓርቲ የመጪው ጊዜ ፈተና” በሚል ርዕስ ለጻፍኩት ጽሁፍ ስለሰጡት ምላሽ ከልብ አመሰግናለሁ። ሀሳቦችን በጨዋ መንገድ ማንሸራሸር ለእድገት ይጠቅማልና ሁላችንም ይልመድብን እላለሁ። ስለአንድነት ፓርቲ ተቆርቋሪ ሆነው የሰጡት መልስ ብዙም እንዳላረካኝ ስገልጽልዎ በከፍተኛ አክብሮት ነው። ማንም ጤናኛ ሰው በአገር ውስጥ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ዴሞክራሲያዊ ለውጥ እንዲመጣ ይፈልጋል። አንድነት ፓርቲ በዚህ እምነት የሚያደርገውን ትግልም አደንቃለሁ። ይሁን እንጅ የትግል ፍሬ መለኪያው ሂደት ሳይሆን ውጤት ነውና አንድነት ፓርቲ፣ ኢ/ር ግዛቸው ሊሄዱበት ባሰቡት መንገድ ከተጓዘ፣ ውጤታማ ይሆናል የሚል እምነት የለኝም። እርስዎ በዚህ አስተያየት አልተስማሙም። አለመስማማትዎን ሁለት ቁምነገሮችን በማንሳት ለማሳየት ሞክረዋል፤ እኔም በእነዚህ ነጥቦች ላይ ተመስርቼ የመልስ መልስ አቀርባለሁ።

አንደኛ፤ አንድነት ፓርቲ፣ የአገሪቱ የህግ አካል የሆነውን ፣ የምርጫ ስነምግባር መመሪያው እስካሁን አለመፈረሙ ስህተት ነበር፣ አሁንም ፈርሞ ከኢህአዴግ ጋር መነጋገር አለበት የሚል መከራከሪያ አቅርበዋል። የስነምግባር መመሪያውን ፈርመው ለድርድር ተቀምጠው የነበሩት የቀድሞው የመኢአድ ሊቀመንበር ኢ/ር ሃይሉ ሻውል በመጽሀፋቸው የተናገሩት ሰነዱን መፈረም ያዋጣል አያዋጣም የሚለውን ለማየት ይረዳናልና ልጥቀስ፤-

” ከኢህአዴግ ጋር ያደረግነውን ድርድር በተመለከተ አንዳንዱ ‘ ወደሰለጠነ ፖለቲካ ልንገባ ይሆን?’ ብሎ በደህና ሁኔታ ያየው ወገን ነበር። ሌላው ወገን ግን ‘እንዴት ያሰረውን ሰው ሄዶ እጅ ይጨብጣል’ የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አሰምቷል። የ2002ቱን የምርጫ ስነምግባር ሰነዱን ስንፈርም ተቃውሞ እንደሚኖር ሳናውቅ ቀርተን አይደለም። ፊርማው ብቻውን ለእኛ ደስታን የሚሰጠንም ሆኖ አልነበረም።ሌላኛው አማራጭና አስተሳሰብ ግን ግብዝነትናን የሚያጠናክርና የሰላም ሂደትን የሚገታ ይሆናል የሚል ግምት መያዛችን አንዱ ምክንያታችን ነው። በወቅቱ እኛ ሰነድ መፈረማችን ለህዝብ ምን ፋይዳ አለው የሚለውንም በአግባቡ አይተነዋል። እኛ ያሰብነው ወረቀት ቢሮ ውስጥ ይፈረማል፣ ያልቃል የሚል ነበር። እነሱ ግን አምባሳደሮች ጋብዘው፣ ሚዲያዎችን ጠርተው የተለየ ዝግጅት አደረጉ። ነገሩን ለዓለም ለማሳወቅ መፈለጋቸው ለሁሉም ግልጽ ሆነ። በዚያን ወቅት እኛ የማናውቀው ውጥረት ነበረባቸው የሚል የዘገየ ግምት ተከሰተልኝ ። እኔ እንደሚመስለኝ የአውሮፓ ህብረት ታዛቢዎች የመታዘብ ይሁንታ የሰጡት ያ ስምምነት ስለተፈረመ ይመስላል። መኢአድ ሰነዱን የፈረምንበት ዋናው ምክንያት ግን የ500 ስቃይ ላይ የነበሩ እስረኞችና የቤተሰቦቻቸው ሰቆቃ አሰቃይቶን ነው። እኔን በተመለከተ ኢህአዴግ ወደ እኛ አስገባነው ብሎ ቢያስወራም አልሰመረለትም።”

(ህይወቴና የፖለቲካ እርምጃየ፣ ሃይሉ ሻውል፣ ገጽ139)።

አቶ ግርማ እዚህ ላይ አራት ነጥቦችን ላንሳ። አንደኛው፣ አቶ ሃይሉ እንዳሉት የስነምግባር መመሪያው ለኢህአዴግ አለማቀፍ ተቀባይነትን ለማሰጠት ጠቅሟል። ቢያንስ የምርጫ ታዛቢ እንዲላክ አድርጓል። የታዛቢው የመጨረሻ ሪፖርት ባያምርም። ሁለተኛ አቶ ሃይሉ 500 ሰዎችን ከእስር ለማስፈታት ብለው እንጅ ሙሉ በሙሉ አምነውበት ሰነዱን አለመፈረማቸውን ገልጸዋል። ልብ ይበሉ አቶ ግርማ! ከ80 ሚሊዮን እስረኞች የተፈቱት 500 ዎቹ ብቻ ናቸው። 80 ሚሊዮኑ ህዝብ ከእስር እንዲፈታ ስንት የምርጫ ስነምግባር ፊርማዎችን መፈረም ይኖርብን ይሆን? ሶስተኛ ፣ መኢአድ ፊርማውን መፈረሙ ህዝቡ እንዲከፋፈል አድርጎታል። አንድነትስ ተመሳሳይ ነገር አይሰራም ብለው ያስባሉ? የሚከፋፈለውን ህዝብ አንድ ለማድረግ እርስዎ የህዝብ ግንኙነት ስራ ለመስራት ተዘጋጅተዋል? አይርሱ ፖለቲካ 50 በመቶው ገጽታ ( image) ነው። አራተኛ፣ ኢህአዴግ የፊርማውን ስነስርአት ለራሱ የፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ተጠቅሞበታል። በድብቅ ይፈረማል የተባለውን ፊርማ ለአደባባይ አብቅቶታል። በአንድነት ላይስ እንዲህ እንደማይደረግ ምን ዋስትና አለ? በህዝቡ ላይ የሚፈጥረውን አሉታዊ ስሜትስ እንዴት ነው መቋቋም የሚቻለው?

ኢ/ር ሃይሉ ሻውል አያበቁም፣ ይቀጥላሉ ” በሌላ በኩል ከህዝቡ ወገን ደግሞ ” ሃይሉ ከዳን” የሚልም ነበር። ውጪ አገር ያሉትማ በኢንተርኔት ላይ ፎቶግራፌን እያገላበጡ እኔ ለቀድሞው ጠ/ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ እጅ እንደምነሳ አስመስለው ሲዘልፉኝ ከርመዋል።… የሰነዱ መፈረም ለ2002 ምርጫ ዝግጅት ለእኛ አባላት ትንሽ ፋታ ሰጥቷል። ገጠር ሲታገሉ የሰነበቱት እሳት ውስጥ ነበሩ፤ ከፊርማው በሁዋላ ለአጭር ቀናት ቢሆንም በመጠኑ ማስፈራራት ጋብ አለ።” ይሄ ፊርማውን በመፈረም የተገኘ ጥሩ ዜና ነው አቶ ግርማ። ግን ይቀጥል ይሆን ? እንመልከተው፦ ” ምርጫው እየተቃረበ ሲመጣ ግን ሁሉም ነገር ተረሳና ኢህአዴግ የተለመደ ጭቆናውን ማስፋፋት ተያያዘው… መኢአድ ከ2002 ምርጫ ጋር ተያይዞ ከኢህአዴግ ጋር የስነምግባር ደንቡን ከፈረመ በሁዋላ በኢህአዴግ በኩል የተገቡ ቃሎች ባለመተግበራቸው ከጋራ መድረኩ ራሱን አግልሏል። ኢህአዴግ ሁሉም ነገር በቁጥጥር ስር እንዲሆን ፈለገ። በመድረኩም እንነጋገር ብለን የምንጠይቀውን አጀንዳ አይቀበሉትም። የሄ ከሆነ የጋራ ስምምነት የምክክር አይደለም ብለን ተውነው። ስንመለከተው ኢህአዴግ ትእዛዝ የሚያስተላልፍበት መድረክ ስለሆነ ለኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ግንባታ ጸር እንጂ ጠቃሚ አለመሆኑን በገሀድ ታየ። ገዢው ፓርቲ በዚህ በጋራ መድረክ አባልነት የቀጠሩትን ፓርቲዎች ደመወዝ መሰል ድጎማ እየከፈለ በቁጥጥር ይዟቸው ቀጥሎአል።በ2002 የስነምግባር ደንቡን ብንፈርምም የእኛ አባሎች ላይ የሚደርሰው ወከባና እንግልት ከዚያ በሁዋላ እየቀጠለ መጣ…” ይሉና አቶ ሀይሉ ይቀጥላሉ…

አቶ ግርማ ካሳ እንግዲህ አንድነትንም ወደዚህ የአራዊቶች ጉባኤ ( ፋቡላ) በመክተት ፓርቲውን በኢህአዴግ ቁጥጥር ስር ሊያደርጉት እና ደሞዝ ሊያሰፍሩለት ያስባሉ ማለት ነው። ለአንድነት ፓርቲ ታጋዮች ካለኝ ከበሬታ አንጻር ፓርቲው በኢህአዴግ ቁጥጥር ስር እንዲሆን አልመኝም። ወርሃዊ ደሞዝ እንዲሰፈርለትም አልሻም።ምክንያቱም እንዲህ አይነቱ አካሄድ ለዲሞክራሲ የሚደረገውን ትግል የሚገድል ነውና ።

መድረክም አንድነትም ፊርማውን እስከዛሬ ባለመፈረማቸው የረባ ውጤት አላገኙ ይሆናል፤ ነገር ግን ” No to cheating!” በማለታቸው ከመኢአድ የተሻለ ክብር እና ድጋፍ አግኝተው እንደነበር አንዘነጋውም።

ሁለተኛው መከራከሪያዎ አቶ አንዱዓለምንና ናትናኤልን በተመለከተ የሰጠሁትን አስተያየት ተንተርሶ የቀረበ ነው። እኔ አንድነቶችን ከመከፋፈል ማዳን እንጅ፣ እነሱን የመከፋፈል አላማ የለኝም፣ በፍጹም!። ይሄን ስጽፍም ፓርቲውን ከመከፋፈል ለማዳን እንጅ ለሌላ አላማ አይደለም። ወ/ት ብርቱካን እስር ቤት ከገባች በሁዋላ ፓርቲዋ ( አመራሩ) ረስቷት ነበር። እንዴያውም አንዳንዶች “እንኳን ታሰረች” ሳይሉ ሁሉ አልቀረም። ያን ጊዜ ማን ነበር ለብርቱካን አብዝቶ የጮኸው? ዲያስፖራው እና በተለይ ኢሳት አልነበሩምን? የካናዳው ልጅ ተክሌ ” ብርቱካኔ ብረሳሽ ቀኜ ይርሳሽ” ብሎ ዜማ ያወጣላት አምስተርዳም የኢሳት ስቱዲዮ ውስጥ ሆኖ ነው። በወቅቱ የነበሩ ባልደረቦቼ ብርቱካንን በተመለከተ ብዙ ዝግጅቶችን ይሰሩ ነበር። ምንም እንኳ ኢሳት እዚህ ውስጥ እንዲገባ ባልሻም፣ “የኢሳቱ ባልደረባ” እያሉ ስለጻፉና በተዘዋዋሪም እኔ የጻፍኩትን የኢሳት አቋም አድርገው ለማሳየት ስለሞከሩ ትንሽም ብትሆን እውነቱን ለመናገር ይጠቅማል ብየ ስላሰብኩ ነው ኢሳትን መጥቀሴ። ( በነገራችን ላይ ኢሳት የግል አስተያየቴን እንዳልጽፍ እያደረገኝ ነው፣ በግሌ የምጽፈውን አንባቢዎች ” የኢሳት አቋም አድርገው ይወስዱብኝ ይሆን” እያልኩ በመስጋት፣ መጻፍ እየፈለኩ አልጽፍም፤ ለሀሳብ ነጻነት በሚታገል ድርጅት ውስጥ የምሰራ ሰው፣ በዚሁ ድርጅት መልሼ መታፈኔ ይገርመኛል፤ ያፈነኝ ግን ድርጅቱ ሳይሆን፣ ሰዎች ከድርጅቱ ጋር ያያይዙብኝ ይሆን የሚለው ፍርሀት ነው።)

አንዱዓለምና ናትናኤል የብርቱካን እጣ እንዲገጥማቸው አልሻም። በፓርቲው ሸውራራ አካሄድ ስነልቦናቸው እንዲጎዳም አልፈልግም፤ የስነምግባር ደንቡን መፈረም አንዱዓለምን እና ናትናኤልን ከእስር እንደያማያስፈታ አስረግጬ መናገር እችላለሁ። እነሱን የማያስፈታ ሰነድ ደግሞ ጥንቅር ብሎ ይቅር። አንዱዓለምና ናትናኤል በመረሳታቸው እጅግ ያንገበግበኛል። የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጉና የገንዘብ መዋጮ የመሰብሰቡ ስራ እንኳ ቆሟል። ይሄ አልበቃ ብሎ በደንብ ባልተጠና የፖለቲካ አካሄድ ስነልቦናቸው ሲጎዳ አይቶ በሁዋላ ከመጸጸት አሁን የሚመስለንን መናገሩ ይጠቅማል እንጅ አይጎዳም።

እነ አንዱዓለም ያልመከሩበት ፖሊሲ በምንም ታዕምር ተግባራዊ መሆን የለበትም! አንዱዓለም የታሰረው ሮቢን አይላንድ አይደለም! ማማከር ይችላል። አንዱዓለም ” አይቃወምም ፣ ይስማማል” በሚል የሚቀርበው መከራከሪያ ብዙ መንገድ አይወስድም።

አንዱአያም አራጌ ” ያልተሄደበት መንገድ” በሚለው መጽሀፉ በገጽ 58 ላይ ስለ አምባገነኖች ባህሪ የጠቀሰው ትክክለኛ ነው እላለሁ ” የአለም ታሪክ እንደሚያሳየው አምባገነኖች በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣናቸው ለቀው አያውቁም። እንደውም እነርሱ ስልጣን ከለቀቁ ሀገር እንደሚበታተን፣ ህዝብ እንደሚጨራረሽ የማስፈራሪያ ፕሮፓጋንዳ ይነዛሉ። ፈርተው ያስፈራሉ። ይሄ ባህሪያቸው መሆኑን መረዳትና ያለመዘናጋት መታገል ያስፈልጋል… ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ አሁን ያለውን አገዛዝ ለህዝብ ፈቃድ እንዲገዛ የግድ ማለት ያስፍልጋል።”


እኔ ነገ ስለሚሆነው ነገር ነው የምጽፈው፣ ትክክል መሆንና አለመሆኔን ለማየት ትንሽ ጊዜ መጠበቁ የሚሻል ይመስለኛል። ተሳስቼም ከሆነ ያን ጊዜ ሂሳቤን አወራርዳለሁ። ( በነገራችን ላይ አንድ ጊዜም እንዲሁ ሰማያዊ ፓርቲ በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ማቀዱን በመቃወሜና ቀኑን እንዲቀይረው በመጠየቄ ብዙ ትችቶችን አስተናግጃለሁ፤ በሁዋላ ፓርቲው ( የእኔን ምክር ሰምቶ ይሁን አይሁን አላውቅም) ቀኑን ቀየረው፤ ለወረደብኝ ትችት ግን ሂሳቡን ያወራረደልኝ ሰው አልነበረም፤ ሲጽፉብኝ የነበሩ የማውቃቸው ሰዎች ሳይቀር ድምጻቸውን አጠፉ። እኔ ከተሳሳትኩ ሂሳቤን እንደማወራርድ ቃል እገባለሁ፣ ለመመጻደቅ ሳይሆን ለእድገት ይጠቅማል ብየ ስለማምን ነው።)
ዘ -ሐበሻ

የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት የመቀባት አባዜ – ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

January16/2014

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ያለው ገዥው አካል በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ንጉስ የነበሩት የዳግማዊ አጼ ምኒልክ መቶኛ የሙት ዓመት በዚህ በያዝነው ዓመት (በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር) እየተከበረ ባለበት ወቅት ሙሉ ጊዜውን በመስጠት ንጉሱ የሰሩትን ታላቅ ስራ ሁሉ በማጣጣል እና ጥላሸት በመቀባት ዘመቻ ላይ በመጠመድ ታሪክ የማጠልሸት ድራማውን በመተወን ላይ ይገኛል፡፡ የታሪክ ማጠልሸት ዘመቻው በዋናነት እየተከናወነ ያለው ለገዥው አካል ቅርበት ባላቸው ታማኝ ሎሌዎች፣ የጥቅም ተጋሪዎች እና የእራሳቸው ስብዕና በሌላቸው አሻንጉሊቶች አማካይነት ነው፡፡ ገዥው አካል ሲያስነጥሰው መሃረብ ይዘው በሚቀርቡ አጎብዳጆቹ አማካይነት የጥላቻ መርዛማ ቃላትን፣ የሚቆጠቁጡ ባዶ ዲስኮሮችን እና እርባናየለሽ ምዕናባዊ ስዕል በአዕምሮው ላይ እየፈጠረ አጼ ምኒልክ የግዛት ማስፋፋት ጥማታቸውን ለማርካት ሲሉ በዜጎች ላይ የጭካኔ ተግባራትን እንደፈጸሙ በማስመሰል ለምንም የማይጠቅሙ እርባናየለሽ እና ተራ አሉባልታዎችን በማሰራጨት ላይ ይገኛል፡፡


የገዥው አካል ድንጉላ አገልጋዮች በማናቸውም የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በመሰማራት ታሪካዊ ቅጥፈቶችን፣ አሳሳች ዘገባዎችን፣ የሀሰት ታሪክ ፈጠራዎችን፣ ሆን ተብሎ በሀሰት ላይ የተመሰረቱ መረጃዎችን እና ነጭ ውሸቶችን እንደ በቀቀን እየደጋገሙ በማሰራጨት ላይ ይገኛሉ፡፡ የዕኩይ ዓላማው አራማጆች በታላቁ የኢትዮጵያ መሪ ላይ ግነታዊ ኩምክና በመስራት፣ በማዋረድ እና እውነተኛውን ስብዕናቸውን ጥላሸት በመቀባት የስሜት ፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ውስጥ በመዘፈቅ ጌቶቻቸውን ለማስደሰት በታለመ ዕኩይ ምግባር ላይ ተጠምደው ይገኛሉ፡፡ የታላቁ መሪ ነብስ ከስጋቸው ከተለየች ከአንድ መቶ ዓመታት የጊዜ ቆይታ በኋላ የተቀበረን ጉዳይ በማንሳት ታላቁን መሪ ሰይጣናዊ ስብዕና እንደነበራቸው ለማስመሰል በማሰብ የዕኩይ ምግባር ጎተራዎቹ የቻሉትን ያህል ጥረት ለማድረግ ሞክረዋል፡፡ አቶ መለስ ዜናዊ በህይወት ከተለዩ ሁለት ዓመታት እንኳን ሳይሞላቸው የዕኩይ ምግባራት ቋቶቹ የኢትዮጵያ አዳኝ መልዓክ ሊያደርጓቸው ይፈልጋሉ፡፡

በአሁኑ ጊዜ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ላይ በተከፈተው የገፍ ወይም የኃይል የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ወይም ደግሞ የአጼ ምኒልክን የሙት መንፈስ ደጋግመው በማንሳት ፍጹም ጥላቻ እና የጥላቻ አመለካከት እንዲንሰራፋ በገዥው አካል ስልታዊ እና የተቀነባበረ ዘመቻ የማካሄድ አመክንዮ ለማንም ቢሆን ሊደንቅ አይገባም፡፡ ሀቁ አንድ እና አንድ ብቻ ነው፡፡ የኸውም የምኒልክን ስም ጥላሸት በመቀባት (ሰይጣናዊ ስብዕና በመስጠት) በሚሽከረከር ጉዳይ ላይ ብቻ የሚቆም ጉዳይ አይደለም፡፡ ነገር ግን በቅርቡ በህይወት የተለዩትን የገዥውን አካል የአለቆች ሁሉ አለቃ (Capo di tutti capi) አቶ መለስ ዜናዊን በመላዕክነት ቀብቶ ለማቅረብ የታቀደ ዕኩይ ምግባር ነው፡፡

ዳግማዊ ምኒልክን ጥላሸት የሚቀቡ ሙትመንፈሶች፣
በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ላይ እየተካሄደ ያለው ከፍተኛ ጥላሸት የመቀባት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ያነጣጠረው የኢትዮጵያን ታሪክ በመፋቅ በአቶ መለስ ዜናዊ የመላዕክነት የህይወት ታሪክ (የመላዕክነት ትረካ) በመተካት የታላቋን ሀገር ትክክለኛ ታሪክ እንደገና ለመጻፍ፣ አዛብቶ ለመጻፍ፣ ገልብጦ ለመጻፍ፣ አወዛግቦ ለመጻፍ፣ በመቀባባት የሚያምር አስመስሎ ለማቅረብ እና እውነተኛውን ታሪክ ለማስወገድ በመደረግ ላይ ያለ ከንቱ ሙከራ ነው፡፡ የአጼ ምኒልክን ታሪክ በመሰረዝ የዘመናችን የ”አፍሪካ ታላቁ መሪ” በማለት የመለስ ዜናዊን ታሪክ ለመጻፍ ይፈልጋሉ፡፡ በሀሰት እምነት ላይ በመመስረት መለስ “አዲሱ የአፍሪካ መሪ ዝርያ“፣ መለስ “የዴሞክራሲያዊ ልማታዊ መንግስት ቀያሽ”፣ መለስ “በዓለም አቀፋዊ የሙቀት እና የአየር ጸባይ ለውጥ የአፍሪካ ጠበቃ”፣ መለስ “ከጂ-8 እና ጂ-20 መሪዎች ጋር በመሆን ክርናቸውን የሚያሳዩ አፍሪካዊ መሪ”፣ መለስ “የቻይና-አፍሪካ የትብብር መድረክ የቤጂንግ ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጉባኤ ሊቀመንበር”፣ መለስ የሶማሌ ጅሃዲስቶች እና አሸባሪዎች አስወጋጅ”… ተብለው ከእውነተኛ ስብዕናቸው ውጭ በሆነ መልኩ እንዲመለክባቸው ይፍልጋሉ፡:

የታላቁን መሪ የዳግማዊ ምኒልክን ስብዕና ጥላሸት በመቀባት አቶ መለስን ቅብዓ መልዓክ (የተቀባ መልዓክ) ለማድረግ ይፈልጋሉ፡፡ ለመሆኑ አጼ ምኒልክን ጥላሸት የሚቀቧቸው ለምንድን ነው? ምክንያቱም አጼ ምኒልክ በአመራር ጥበባቸው እና በትግላቸው ግጭትን በመፍጠር ሲናቆሩ ከነበሩት ባላባቶች፣ ለስልጣን ብቻ ከሚቋምጡ ከተለያዩ አካባቢያዊ ንጉሶች፣ ከተለያዩ ልዕልቶች የቅምጥል የአገዛዝ ስርዓት፣ እና ከጎጣዊ ምስለኔዎች የተበታተነ አገዛዝ በማላቀቅ ዘመናዊቷን የአፍሪካ ብሄር ታላቋን ኢትዮጵያን በመመስረታቸው ብቻ ነው፡፡ የዕኩይ ምግባር አራማጆች አጼ ምኒልክን ጥላሸት ይቀቧቸዋል፣ ምክንያቱም ምኒልክ ታላቆቹን የአውሮፓ ኢምፔሪያሊስት ኃያላን በጦር ሜዳ ውሎ በማሸነፍ አንጸባራቂ ድል በመቀዳጀት የኢትዮጵያን ዘለቄታዊ ነጻነት ያጎናጸፉ እና የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ያስከበሩ ጀግና መሪ በመሆናቸው ነው፡፡ ጥላሸት ይቀቧቸዋል ምክንያቱም ምኒልክ እውነተኛ የአፍሪካ መሪ በመሆናቸው ነው፡፡ የአጼ ምኒልክን ስም በማጥፋት እና ለኢትዮጵያ ህዝብ ያበረከቱትን የውርስ ትሩፋታቸውን በማንቋሸሽ ለአቶ መለስ ክብር ለመስጠት እና ከእርሳቸው የሚገኘውን ውርስ ብጹዕ/ቅዱስ ለማድረግ ይፈልጋሉ፡፡

ገዥው አካል የአጼ ምኒልክን ታሪክ በእራሱ ታሪክ ለመተካት ይፈልጋል፡፡ አጼ ምኒልክ የባቡር ሀዲድ በመዘርጋት የመጀመሪያው አፍሪካዊ መሪ ነበሩ፡፡ ይህንን አንጸባራቂ ታሪክ በመለወጥ አቶ መለስ ረዥም፣ ቆንጆ እና ቀላል የባቡር ሀዲድ ሲስተም በኢትዮጵያ ለማምጣት የመጀመሪያው መሪ ነበሩ በማለት የታሪክ ባለቤትነት ሽሚያን ለማጎናጸፍ ይፈልጋሉ፡፡ አጼ ምኒልክ የስልክ እና የቴሌግራፍ አገልግሎትን በአፍሪካ አህጉር በማስተዋወቅ የመጀመሪያው አፍሪካዊ መሪ ነበሩ፡፡ እ.ኤ.አ በ1889 አሌክሳንደር ግራህም ቤል “የድምጽ መነጋገሪያ መሳሪያ” የፓተንት ዕውቅና ካገኙበት 13 ዓመታት በኋላ እና በአጼ ምኒልክ ቤተመንግስት የመጀመሪያው የስልክ መስመር በተዘረጋበት ጊዜ በቴክኖሎጂው ሁኔታ ጭንቀት ውስጥ ገብተው የነበሩት የቤተክህነት ሰዎች ይህ የሰይጣን ስራ ነው በማለት ንጉሱ እንዲያስወግዱት በጠየቋቸው ጊዜ አጼ ምኒልክ ለቴክኖሎጂው ጠቀሜታ ካላቸው ጽኑ እምነት አኳያ ሳያስወግዱት ቀርተዋል፡፡ በአስርት ዓመታት ጊዜ ውስጥ አጼ ምኒልክ አዲስ አበባን በምስራቅ ኢትዮጵያ ከምትገኘው የሀረር ከተማ ጋር የሚያገናኝ የስልክ መስመር በመዘርጋት መርቀው ከፈቱ፡፡ ያንን አንጸባራቂ ታሪክ ወደ ጎን በማለት የአሁኖቹ ገዥዎች በኢትዮጵያ ዘመናዊ የመገናኛ ቴክኖሎጂ ሲስተምን በኢትዮጵያ ያመጡ አቶ መለስ ዜናዊ እንደሆኑ አድርገው ያቀርባሉ፡፡ እውነታው ግን በተገላቢጦሽ በአፍሪካ የስልክ እና የቴሌግራፍ መስመር በመዘርጋት ግንባርቀደም የነበረችው ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከአፍሪካ በመጥፎ የተንቀሳቃሽ ስልክ እና የኢንተርኔት አግልግሎት አጠቃቀም ሳቢያ በመጨረሻው እረድፍ ላይ ትገኛለች፡፡ ባለፈው ሳምንት የዎል ስትሪት መጽሄት/Wall Street Journal እንደዘገበው በኢትዮጵያ ውስጥ አርሶ አደሮች የተንቀሳቃሽ ስልኮች ቢይዙም “ችግሩ የግንኙነት መስመር ለማግኘት ብዙ ማይሎችን (ኪሎሜትሮችን)መጓዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡“ በማለት የችግሩን አሳሳቢነት አመላክቷል፡፡ ኢትዮጵያ በመጥፎ የኢንተርኔት አገልግሎት አጠቃቀም ከአፍሪካ ከመጨረሻዎቹ ሀገሮች በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡

የዘመኑ ገዥዎቻችን አጼ ምኒልክ የሴቶችን ጡት ቆርጠው የሚጥሉ ጨካኝ ንጉስ እንደሆኑ አድርገው ታሪክን አዛብተው ለመጻፍ ይፈልጋሉ፡፡ ጨካኝነት ከተነሳ ዘንድ ከአቶ መለስ ዜናዊ የበለጠ ጨካኝ እና አረመኔ ይኖራልን? አቶ መለስ እራሳቸው እ.ኤ.አ በ2005 በተደረገው ሀገራዊ ምርጫ መጭበርበር ምክንያት ተቃውሟቸውን ለመግለጽ በወጡ ያልታጠቁ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ለአነጣጥሮ ተኳሽ ጦራቸው ትዕዛዝ በመስጠት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲገደሉ አድርገዋል፡፡ ይህንን እልቂት አስመልክቶ በእራሳቸው በአቶ መለስ ልዩ ትዕዛዝ ጉዳዩን እንዲያጣራ የተሰየመው የአጣሪ ኮሚሽን ምርመራውን አካሂዶ ባቀረበው ዘገባ መሰረት በአቶ መለስ ቀጥታ ትዕዛዝ እና ቁጥጥር አማካይነት የፖሊስ እና የደህንነት ኃይሎች በዕቅድ ተይዞ እና ሆን ተብሎ ታስቦበት 193 ሰላማዊ ሰዎች እንዲገደሉ እና ሌሎች 763 ሰዎች ደግሞ ከባድ ቁስለኛ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ እ.ኤ.አ በ2004 አቶ መለስ እራሳቸው ለታጣቂዎቻቸው ትዕዛዝ በመስጠት በምዕራብ ኢትዮጵያ በጋምቤላ 400 ሰላማዊ ዜጎች እንዲያልቁ አድርገዋል፡፡ ኦጋዴን እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የተካሄደውን የአየር ድብደባ እና መንደሮችን በማቃጠል የጥቃት ሰለባ ያደረገው ወንጀል የተፈጸመው በአቶ መለስ ስልጣን ልዩ ትዕዛዝ ነበር፡፡ በአቶ መለስ ትዕዛዝ በኦጋዴን ታጣቂ ኃይሎች ሴቶችን አስገድደው ደፍረዋል፣ መንደሮችን አቃጥለዋል፣ ህዝቡን በሽብር ቆፍን ውስጥ ለመሸበብ ሲባል “የመቀጣጫ ግድያዎችን” ማለትም በህዝብ ፊት በአደባባይ በስቅላት እንዲሁም ጭንቅላትን ቆርጦ የመጣል ወንጀሎች እንዲፈጸሙ ተደርጓል፡፡ የተባበሩት መንግስታት የሂዩማን ራይትስ ዎች ተሟጋች ዳይሬክተር/United Nations Advocacy Director for Human Rights Watch ስቴቭ ክራውሻው በኦጋዴን አካባቢ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ወንጀል “ትንሿ ዳርፉር” በማለት አመሳስለው ገልጸውታል፡፡

ገዥዎቻችን አጼ ምኒልክን የኦሮሞ ህዝቦች ጠላት እንደሆኑ አድርገው ታሪክን በመበረዝ የታሪክ ድሪቶ አቀነባብረው እንደገና የጎደፈ ታሪክ ለመጻፍ ይታትራሉ፡፡ አቶ መለስ በህይወት ቢኖሩ ኖሮ እሳቸው እና የዕኩይ ምግባር አጋሮቻቸው በኦሮሞ ህዝብ ላይ እስከ አሁን ድረስ ያልተነገረውን እና ለመናገር የሚዘገንነውን በሰው ልጆች ላይ የፈጸሙትን ወንጀል ወደ ፍትህ አደባባይ በማቅረብ እንዲታይ ለማድረግ ከበቂ በላይ መረጃዎች አሉ፡፡ እ.ኤ.አ በ2012 ፍሪደም ሀውስ/Freedom House የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ባቀረበው ዘገባ መሰረት አቶ መለስ እና አገዛዛቸው በኦሮሞ ህዝብ ላይ ሰፊ የሆነ የአድልኦ እና የጭቆና መረብ በመዘርጋት ተግባራት ላይ ተጠምደው ቆይተዋል፡፡ አቶ መለስ የኦሮሞ ነጻነት ግንባርን እንቅስቃሴ በመገደብ ብዛት ያላቸው ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የሚጠረጠሩ የድርጅቱን አባላት እና መሪዎችን ከህግ አግባብ ውጭ በቁጥጥር ስር በማዋል በማጎሪያ እስርቤት አስገብተው ሲያሰቃዩ ቆይተዋል፣ አሁንም በመሰቃየት ላይ ይገኛሉ፡፡ እ.ኤ.አ በ2001 የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ስልጣናቸውን ሲለቁ እንደተናገሩት “ወደ 25,000 የሚሆኑ የኦሮሞ ህዝቦች ከኦሮሞ ህዝቦች ነጻነት ግንባር ጋር በተያያዘ የገዥው አካል ክስ ምክንያት በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች እና በአዲስ አበባ ከተማ እስር ቤቶች ታስረው በመማቀቅ ላይ ነበሩ፡፡” በማለት ይፋ አድርገዋል፡፡ የመለስ የትግል ጓድ እና የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ስዬ አብርሃ በሚያስገርም ሁኔታ እንደተመለከቱት “ቃሊቲ እስር ቤት ኦሮምኛ ይናገራል፣ በዚሁ ግቢ በአንድ በመቶዎች የሚቆጠሩ እስረኞችን በሚይዝ ካምፕ ውስጥ 99 በመቶ የሚሆኑት እስረኞች ኦሮሞዎች ናቸው፡፡ አብዛኞቹ እስረኞች ደግሞ የታሰሩበት ምክንያት ምን እንደሆነ አያውቁም፣ ሆኖም ግን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ተጠርጣሪ በመባል ዓመታትን በእስር ቤት በማስቆጠር ላይ ይገኛሉ፡፡“ በማለት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡

እ.ኤ.አ በ2006 ጂሃዲስቶች (አሸባሪዎች) የሶማሌን አገር ወረዋታል እና የሶማሌ መንግስት ጣልቃ ገብቸ ጂሃዲስቶችን እንዳስወጣለት “ጋብዞኛል” በሚል ተንኮልን ያዘለ ሰበብ ምክንያት አቶ መለስ በሶማሌ አገር ላይ ወረራ አካሂደዋል፡፡ አቶ መለስ በቴሌቪዥን ቀርበው እንዲህ ብለዋል፣ “የአገራችንን ሉዓዋላዊነት ለማስከበር እና በእስልምና ፍርድ ቤቶች ህብረት እና በሌሎች ጸረ ኢትዮጵያ ኃይሎች በመታገዝ የሚያደርሷቸውን ተደጋጋሚ አደጋዎች ለመግታት ሲባል የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ወዳልፈለገው ጦርነት እንዲገባ ተገድዷል፡፡“ በተመሳሳይ መልኩ በዴሴምበር 27 2006 የአቶ መለስ ሰራዊት እና ታንኮች የሞቃዲሾን ከተማ ወረሩ፡፡ እ.ኤ.አ በኦገስት 2007 የአቶ መለስ ሰራዊት በሶማሌ ውስጥ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ተገታ፣ በሰው ህይወት ላይ የደረሰው ኪሳራ አስደንጋጭ ነበር፡፡ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን የሶማሌ ዜጎች ህይወት የተቀጠፈ ሲሆን ከ870,000 በላይ የሚሆኑት ዜጎች ደግሞ ሞቃዲሾን ለቀው ለመሰደድ ተገደዋል፡፡ በ2006 በሞቃዲሾ ከተማ ወደ 1.2 ሚሊዮን ገደማ የሚሆን ህዝብ ነበር፡፡ ከአቶ መለስ የሶማሌ ወረራ በኋላ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች “ከአፍሪካ በጣም አስቀያሚ አስከፊ የሰብአዊ መብት ሁኔታ ያለበት“ በማለት የሶማሌን የሰብአዊ መብት አያያዝ በተጨባጭ ገልጸውታል፡፡

አጼ ምኒልክ ከአውሮፓውያን ወራሪ ኃይሎች ጋር የመከላከል ጦርነትን በማካሄድ በድል አድራጊነት ተወጥተዋል፡፡ አጼ ሚኒልክ የአውሮፓ ኃያል ከሚባል አገር ጋር ጦርነት በማድረግ በጦር ሜዳ ድል አድርገው ወራሪው ኃይል በመጣበት እግሩ ጓዙን ጠቅልሎ እንደ ውሻ ጅራቱን በእግሮቹ መካከል ወትፎ እንዲመለስ በማድረግ በአፍሪካ ታሪክ የመጀመሪያው መሪ መሆናቸው የሚካድ ጉዳይ አይደለም፡፡ አጼ ምኒልክ ወራሪውን የኢጣልያንን ጦር አምባላጌ እና መቀሌ ላይ ድል አድርገዋል፡፡ እንዲሁም እ.ኤ.አ በ1896 አድዋ ላይ ወሳኙን ፍልሚያ በማድረግ የአድዋን ጦርነት በድል አድራጊነት ተወጥተዋል፡፡ “ኋላቀር አፍሪካውያን ጥቁሮች” ወታደሮች ኃያሉን የአውሮፓ ኢምፔሪያሊስት የጦር ኃይል ያሸንፋል የሚል እምነት በማንም አውሮፓዊ የተገመተ አልነበረም፡፡ አጼ ምኒልክ በዘመናዊ መሳሪያ ትጥቅ፣ በስልት እና በቁሳቁስ አቅርቦት በዘመኑ በጣም የተጎዱ መሪ ቢሆኑም ቅሉ የብሩህ አዕምሮ ባለቤት እና ወታደራዊ ስልት የሚያውቁ በመሆናቸው ውጊያውን በማካሄድ ጦርነቱን አሸንፈው በአንጸባራቂ ድል በመታጀብ የነጮችን የበላይነት እና አይበገሬነት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ በማስወገድ ለጥቁር ህዝቦች በአጠቃላይ ለአፍሪካውያን ደግሞ በተለይ የኩራት ፈርጥ ለመሆን በቅተዋል፡፡ ብዙ የአውሮፓ ኃያላን አገሮች አጼ ምኒልክን በማታለል እና በማጭበርበር ከኢትዮጵያ ግዛት ቆርሰው በመውሰድ ኢትዮጵያን ቅኝ ተገዥ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ1889 አጼ ምኒልክ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የሚገኙ ግዛቶችን አስመልክቶ ከኢጣሊያ መንግስት ጋር የውጫሌ ስምምነትን አጸደቁ፡፡ በውል ስምምነት ሰነዱ የኢጣሊያንኛው ትርጉም ከኢትዮጵያ የአማርኛ ትርጉም ጋር የማይመሳሰል መሆኑን አጼ ምኒልክ እንደተገነዘቡ እና ኢትዮጵያ በኢጣሊያን ጠባቂነት የሚለውን ሀረግ ሲመለከቱ የውል ስምምነቱን በማውገዝ አፈረሱት፡፡
የገዥው አካል አፈቀላጤዎች አቶ መለስ ኢትዮጵያ የአህጉሩ ታላቅ አገር እንድትሆን ጥረት ያደረጉ እና የአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ መሪ እንደሆኑ በማድነቅ እና ስብዕናቸውን ከፍ ከፍ በማድረግ የአሁኑን የኢትዮጵያ ታሪክ ደልዘው በእርሳቸው ተተክቶ እንዲጻፍ ነው በመዋተት ላይ የሚገኙት፡፡ አቶ መለስ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት ያስከበሩ መሪ እንደሆኑ አድርገው ለማሳየት ይፈልጋሉ፡፡ እውነታው ግን የተገላቢጦሹን ያመላክታል፡፡ እ.ኤ.አ ከ1998-1999 ድረስ የባድሜን የግዛት ወሰን ለማስከበር በተካሄደው የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ጦርነት የአቶ መለስ ጦር የ80,000 ኢትዮጵያውያንን ህይወት ያለምንም ወታደራዊ ስልት በጭዳነት ለመስዋዕትነት ዳርጎ ወታደራዊ ድልን ተቀዳጅቶ ነበር፡፡ በወገኖቻችን የህይወት እና ንብረት መስዋዕትነት የተገኘውን ድል ሰራዊቱ ገና አጣጥሞ ሳይጠግብ የኢትዮጵያው መሪ አቶ መለስ ከመቅጽበት በመገለባበጥ ባድሜን በዓለም አቀፋዊ የስምምነት ውል በማስቀየድ ለኤርትራ መንግስት ቡራኬ ብለዋል፡፡ በምንም ዓይነት መልኩ በየትኛውም አገር አንድ ወታደራዊ ኃይል እጅግ ከባድ መስዋዕትነትን ከፍሎ ያገኘውን አንጸባራቂ ድል ለተሸናፊው ጠላቱ በፈቃደኝነት መልሶ የሰጠበት የጦርነት ታሪክ የለም፣ ተመዝግቦም አያውቅም፡፡ እ.ኤ.አ በ1991 ወታደራዊውን አምባገነን ደርግን በትጥቅ ትግል ካስወገዱ በኋላ በአሜሪካ መንግስት አደራዳሪነት የሽግግር ስምምነቱ በሚፈረምበት ወቅት እኒሁ የኢትዮጵያው መሪ አቶ መለስ በኤርትራ የወሰን ግዛት ዳርቻ ላይ የምትገኘውን ከቀይ ባህር ጋር በመግቢያ እና በመውጫነት ለኢትዮጵያ ህዝብ የባህር በር በመሆን አገልግሎት የምትሰጠውን የአሰብን ወደብ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት እንድትካለል የቀረበውን ሀሳብ አልቀበልም በማለት አሁንም በድጋሜ ለኤርትራ መንግስት ቡራኬ በመስጠት ይደልዎ ብለዋል፡፡ አቶ መለስ የኢትዮጵያን ግዛት ለባዕድ ኃይል በመስጠት ታላቋን አገር ወደብአልባ በማድረግ በፈጸሙት የአገር ክህደት ወንጀል ብቸኛው ተጠያቂ ናቸው፡፡ አሁንም ተከታታይነት ያለውን የትራጄዲ ድራማ በመቀጠል በሚስጥር በተደረጉ ስምምነቶች የይስሙላው ፓርላማ ለስሙ እንኳ መከረበት ሳይባል ምንም ሳይታሰብበት በጥድፊያ እኒሁ የኢትዮጵያው “መሪ” አሁንም የኢትዮጵያ አንጡራ ግዛት የሆነውን መሬት ለሱዳን መንግስት እንደ የገና ስጦታ የእጅ መንሻ ቡራኬ አድርገውታል፡፡ እኒሁ የኢትዮጵያው መሪ አቶ መለስ በድብቅ እና ታማኝነት በጎደለው መልኩ የአገሪቱን እጅግ በጣም ለም የሆነውን በሚሊዮኖች ሄክታር የሚቆጠር መሬት ዕዳቸውን እንኳ ውል ባለው መልክ ለመክፈል ለማይችሉ የአየር ባየር ጭልፊት ነጋዴዎች አሁንም ለእጅ መንሻ አቅርበዋል፡፡

አጼ ምኒልክ የኢትዮጵያን አንድነት በማጠናከር ዘመናዊ የመንግስት መዋቅር ዘርግተዋል፡፡ አቶ መለስ ግን ምዕናባዊ ዘመናዊነትን አምጥተዋል፡፡ አቶ መለስ ያለሐኪሞች እና መድኃኒት ሆስፒታል ገንብተዋል፡፡ በአንድ ወቅት ሐኪሞች አያስፈልጉንም በማለት በይፋ ተናግረዋል፡፡ ብቃት ያላቸው የዩኒቭርስቲ መምህራን እና ፕሮፌሰሮች፣ መጻህፍት፣ ቤተ መጻህፍት፣ ወይም ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ሳይኖር ዩኒቨርስቲዎችን ገንብተዋል፡፡ የመጸዳጃ ሲስተም የሌላቸውን ህንጻዎች ገንብተዋል፡፡ አጼ ምኒልክ ኢትዮጵያን የምዕራቡ ዓለም ስልጣኔ ትሩፋት ተቋዳሽ እንድትሆን አድርገዋል፡፡ አቶ መለስ “ልማታዊ መንግስት” የሚል እርባናየለሽ ህልዮት ከምስራቅ ኢስያ ሀገራት አምባገነኖች ኮርጀው በማምጣት ኢትዮጵያን ወደ ኋላ መልሰዋታል፡፡ እ.ኤ.አ በ1991 ስልጣን ከያዙ በኋላ አቶ መለስ ዘመናዊውን የኢትዮጵያ መንግስት አወቃቀር በማፈራረስ ወዲያውኑ አገሪቱን ክልል እየተባለ በሚጠራው ወይም የአፓርታይድ አይነት ባንቱስታንስ ወይም ክልሊስታንስ የተባለ የመከፋፈል ተልዕኮውን አጠናቀቀ፡፡ አቶ መለስ በሀሰት ላይ በመመስረት ባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ ዕድገት አስመዝግበናል፣ እና “ኢትዮጵያ ነዳጅ ወደ ውጭ ከማይልኩ የሰብ ሰሀራ አፍሪካ አገሮች መካከል ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት የምታስመዘግብ አገር ናት” በማለት በሸፍጥ ለማሳመን በመወትወት ላይ ይገኛሉ፡፡ እውነታው ግን ኢትዮጵያ በዓለም ከሚገኙ የመጨረሻዎቹ ደኃ አገሮች ከመጨረሻው በሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ አገር መሆኗን “ኢትዮጵያ ለምንድን ነው ደኃ የሆነችው?” በማለት ቀደም ሲል ባዘጋጀሁት ትችቴ ላይ በግልጽ አስቀምጨዋለሁ፡፡

አጼ ምኒልክ የኢትዮጵያ “ህዳሴ” መሪ ነበሩ፡፡ አገራቸውን ለማጠናከር እና ዘመናዊ ለማድረግ ወሳኝ የሚባሉ እርምጃዎችን ወስደዋል፡፡ ለዘመናዊ ቴክኖሎጂ ልዩ ትኩረት በመስጠት ለአገራቸው አዲስ ዓይነት የግንኙነት ስርዓት እንዲዘረጋ አድርገዋል፡፡ አጼ ምኒልክ አገራቸው ኢትዮጵያ የስልክ እና የቴሌግራፍ እንዲሁም ዘመናዊ የፖስታ አገልግሎት ተጠቃሚ እንደትሆን አድርገዋል፡፡ አጼ ምኒልክ የኤሌክትሪክ አገልግሎት በአዲስ አበባ ከተማ እንዲጀመር አድርገዋል፡፡ የመጀመሪያዋን በሞተር ኃይል የምትንቀሳቀስ አውቶሞቢል ወደ ሀገራቸው ያስገቡ አጼ ምኒልክ ናቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የማሪያ ቴሬዛ ገንዘብን የማይመች የገንዘብ መገበያያን በዚያን ዘመን በዓለም ገበያ ላይ በመገበያያነት አገልግሎት ስራ ላይ ይውሉ በነበሩ በመዳብ የወርቅ ቁራጭ የገንዘብ ሳንቲሞች በመተካት ዘመናዊ የገንዘብ ግብይትን በኢትዮጵያ አስጀምረዋል፡፡ አጼ ምኒልክ ከምንም ከማንም በላይ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ቅድሚያ ይሰጡ ነበር፡፡ አጼ ምኒልክ እ.ኤ.አ በ1894 ከጅቡቲ እስከ አዲስ አበባ የሚዘልቅ የባቡ ሀዲድ መስመር ለመዘርጋት ከፈረንሳይ መንግስት ጋር የስምምነት ውል ፈረሙ፡፡ በተመሳሳይ ዓመት የአውሮፓ ኃያላን አገሮች አፍሪካን እንደ ቅርጫ ስጋ የሚከፋፍለውን የአውሮፓ ቅኝገዥዎች የበርሊን ጉባኤን አካሄዱ፡፡ በዚያን ጊዜ ፈረንሳዮች የነበራቸውን ኃይል በመተማመን ከባቡር ሀዲዱ ጋር በተያያዘ መልኩ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለመዳፈር ሲሞክሩ አገር ወዳዱ መሪ ፈረንሳዮችን ጭጭ እንዲሉ አድርገው በ1906 የአገራቸውን ሉዓላዊነት ካስጠበቁ በኋላ ነው ቀዝቀዝ ማለት የጀመሩት ሐዲዱም መሰራት የቀጠለው ፡፡ እንግዲህ እንዲህ የነበረውን አንጸባራቂ ታሪክ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ያለው ገዥው አካል የውሸት የአቶ መለስን ትረካ በማጉላት የህዳሴው መሪ፣ በአፍሪካ ታሪክ እስከ አሁን ድረስ ታይቶ የማይታወቅ የኤሌክትሪክ ኃይል ግድብ ገንቢ፣ የድልድዮች ገንቢ፣ የመንገዶች እና የባቡር ሀዲዶች… በማለት ታሪክን አዛብቶ ሸውራራ ታሪክ ለመጻፍ እየተውተረተረነው ያለው፡፡

አጼ ምኒልክ የፊውዳል መንግስታት የበላይ የነበሩ መሪ ነበሩ፡፡ በወቅቱ በአገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ በነበረበት ጊዜ ማድረግ የሚፈልጉትን ማድረግ የሚችሉ አፍሪካዊ መሪ ነበሩ፡፡ በእግዚአብሄር በአላህ ፈቃድ አንዲት የተባበረች እና የተከበረች ኢትዮጵያን ለተተኪው ትውልድ አውርሰው አልፈዋል፡፡ የአቶ መለስ ጠንካራው የውርሳቸው ትሩፋት በአፍሪካ የመጀመሪያውን ፈላጭ ቆራጭ አምባገነናዊ አገዛዝ ማውረሳቸው ነው፡፡ በሁፊንግተን ፖስት ትችቴ/Huffington Post Commentary በግልጽ እንዳስቀመጥኩት “ዴሞክራሲ የህዝብ፣ በህዝብ፣ ለህዝብ የቆመ የመንግስት አስተዳደር ከሆነ የማፊያ አገዛዝ/thugocracy ደግሞ (የወሮ በላ) የሌቦች፣ ለሌቦች በሌቦች የቆመ የወሮ በላ መንግስት አስተዳደር ነው፡፡“ በግልጽ አባባል የማፊያ አገዛዝ የሚሽከረከረው በወሮበላ ሌቦች እና በዘራፊዎች ነው፡፡ በማፊያ የአገዛዝ ስርዓት የፖለቲካ ስልጣንን ሙዝዝ ብሎ መያዝ እና እንደ መዥገር መጣበቅ ዋናው ተግባሩ ሲሆን ገዥው አካል የህዝብን ገንዘብ በመዝረፍ እና ለብዙሀኑ ህዝብ ህልውና የቆሙትን መሰረታዊ አገልግሎቶች ውሱን ሀብቶች በመቀራመት ግላዊ ሀብትን ለማጋባስ ነው፡፡

የአቶ መለስ የማፊያ (የወሮ በላ) አገዛዝ በሰነድ ብቻ ተመዝግቦ የሚያዝ ሳይሆን በቀድሞው የመከላከያ የትግል ጓደኛቸው ጭምር የአይን ምስክርነት የተሰጠበት ጉዳይ ነው፡፡ ገና ከጫካ ትግል ሲጀምሩ አቶ መለስ እና የትግል ጓዶቻቸው የሌቦች አስተዳደራዊ ስርዓት ነበር የዘረጉት፡፡ እ.ኤ.አ በ1980ዎቹ የመጀመሪያ ዓመታት ለረሀብ ሰለባ ለወደቀው የትግራይ ህዝብ እርዳታ ተብሎ ከእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች የተላከውን ከ10 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚሆን ገንዘብ ከተሰጠበት ዓላማ ውጭ አማጺው ቡድን ለጦር መሳሪያ መግዣ እና እራሳቸውን ማበልጸጊያ አድርገውታል፡፡ በቅርብ እየወጡ ያሉ ዘገባዎች እንደሚያመላክቱት ከግማሽ በላይ የሚሆነው የአገሪቱ ኢኮኖሚ በአቶ መለስ ባለስልጣኖች፣ ደጋፊዎች፣ ሎሌዎች፣ ጓደኞች፣ የስራ ባልደረቦች እና ሌሎች ቁጥጥር ስር ተቀፍድዶ ይገኛል፡፡ ሙስናን በሚመለከት የዓለም ባንክ “ሙስናን በኢትዮጵያ መመርመር” በሚል ርዕስ የተወሰኑ አገሮችን ባናሙናነት ወስዶ በማጥናት ባወጣው ባለ500 ገጽ የግኝት ዘገባ መሰረት ሙስና እና የህዝብን ሀብት መዝረፍ በኢትዮጵያ ዋና መገለጫ ሆኗል በማለት ደምድሟል፡፡ ዘራፊነት አና ሙስና የአቶ መለስ የመጨረሻው ውርሳቸው ነው፡፡

አጼ ምኒልክን መጥላት ይወዳሉ፣

ጥላቻ የነብሳችን የመጨረሻው የበሽታ ምልክት ነው፡፡ ጥላቻ ኢምክንያታዊ ነው ወይም አመክንዮ የለውም፡፡ በጥላቻ ላይ የተጻፉ በርካታ ሳይንሳዊ ጽሁፎች እንደሚያመለክቱት በጥላቻ የተመረዙት ምንጊዜም ይጠላሉ ምክንያቱም ይፈራሉ፣ ደህንነት አይሰማቸውም፣ ምቀኞች ናቸው፣ ወይም ደግሞ እራሳቸውን ይጠላሉ ምክንያቱም የጥላቻቸው መነሻ እና መድረሻ እነዚሁ በጥላቻ የተሞሉት ግብዞች ናቸውና፡፡ ከሁሉም በላይ በጥላቻ የተሞሉት ወገኖች እራሳቸውን ይጠላሉ ምክንያቱም ብቁነት የጎደላቸው፣ ኃይልየለሽነት፣ ተስፋቢስነት፣ እና የእረዳትየለሽነት ስሜት የተጠናወታቸው ነው፡፡

ማንዴላ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ሰው በቆዳው ቀለም፣ ወይም ደግሞ በማንነቱ፣ ወይም በኃይማኖቱ ምክንያት ብቻ ማንም ማንንም ሊጠላ አልተወለደም፡፡ ሰዎች መጥላትን መማር አለባቸው፣“ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያሉትን የገዥው አካል ኃላፊዎች ሁኔታ በማስብበት ጊዜ በማንዴላ ፍልስፍናዊ ግምገማ ላይ አምነት ማጣት ይቃጣኛል፡፡ ማንዴላ እንዲህ በማለትም አክለዋል፣ “መጥላትን የሚማሩ ከሆነ ፍቅርን ሊማሩም ይችላሉ፣ ምክንያቱም ፍቅር ከተቃራኒው የበለጠ በሰው ልጅ ልብ ውስጥ የመስረጽ ተፈጥሯዊ ባህሪ አለውና፡፡“ ተቃራኒውን በተጨባጭ የሚያመላክቱ በርካታ መረጃዎች ቢኖሩም የማንዴላ መርሆዎች በስልጣን ላይ ባሉት ባለስልጣኖች ሁሉ ሊተገበሩ እንደሚችሉ ጽኑ እምነት አለኝ፡፡
በመርህ እና በተግባርም እንደሚታየው በጋንዲ መርሆዎች መሰረት ለመኖር ጥረት ማድረግ አለብን፣ “ኃጢያተኛውን ሳይሆን ኃጢያቱን እንጥላ፣“ በጥላቻ የተመረዙትን የምንጠላ ከሆነ የእነርሱ የመስታወት ነጸብራቅ እንሆናለን፣ እራሳችንም የምንጠላቸውን እንሆናለን፣ እንደ ሰው ስብዕና አቶ መለስን እና መሰሎቻቸውን የምንጠላ ከሆነ እነርሱኑ ሆን ማለት ነው፡፡ የምንጠላ ከሆነ ምግባራቸውን እንጅ እንደ ሰው እራሳቸውን መሆን የለበትም፡፡

ጥላቻ ጠንካራ ኃይል ነው፡፡ በናዚዝስቶች የተሰራጨው ጥላቻ አገሮችን በጠቅላላ እንዲጠፉ አድርጓል፡፡ በሩዋንዳ የተከሰተው ጥላቻ የሚሊዮኖችን ሩዋንዳውያን ህይወት ቀጥፏል፡፡ በዳርፉር የተቆሰቆሰው ጥላቻ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሱዳን ዜጎችን ህይወት አጥፍቷል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በተከሰተው የኃይማኖት ጥላቻ በናይጄሪያ እና በመካከለኛው አፍሪካ ሬፑብሊክ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በመሞት ላይ ይገኛሉ፡፡ በምንም ዓይነት መንገድ ወደ ጥላቻ መግባት የለብንም፡፡

በዓለም ላይ ሁለት ዓይነት ህዝቦች እንዳሉ አምናለሁ፡፡ “ጎረቤትህን እንደ እራስህ ውደድ“ የሚለውን ወርቃማ ህግ የሚከተሉ ህዝቦች አሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ “የመዳብ ህግ” እያልኩ በምጠራው “ጎረቤትህን እንደ እራስህ ጥላ“ እያሉ የሚኖሩ ህዝቦች አሉ፡፡ በጥላቻ የተሞሉ ሰዎች የእራሳቸውን እረዳትየለሽነት፣ የደህንነት እጦት ስሜት፣ የጥፋተኝነት ስሜት እና በጥላቻቸው መሳሪያነት ድርጊቶችን በመለወጥ አሸናፊነትን የሚጎናጸፉ ይመስላቸዋል፡፡ ሌሎችን በመጥላት የራሳቸውን የበታችነት ስሜት እና የእራስን ዋጋ ዝቅ አድርጎ የማየት ችግራቸውን በማስወገድ እራሳቸውን ከፍ ያደረጉ ይመስላቸዋል፡፡ አጼ ምኒልክን የሚጠሉ ሰዎች በእርግጥ አይጠሏቸውም፣ እራሳቸውን የሚጠሉ እና ምኒልክን ለመሆን የሚያስቡ ምኒልክ የሚያደርጓቸውን ነገሮች ሁሉ ተምሳሌት ለማድረግ የሚጥሩ ናቸው፡፡

በአሁኑ ጌዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ላሉት ሁሉ አዝንላቸዋለሁ፡፡ በእርግጥ በጣም አዝንላቸዋለሁ፡፡ እነዚህ በጥላቻ የተሞሉት ወገኖች የኢትዮጵያን ታላላቅ መሪዎች እና የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት በመቀባት በቅርቡ በህይወት የተለዩትን መሪያቸውን እና የሁለት አስርት ዓመታት ኃጢያታቸውን በማስሰረይ ብጹ የሚያደርጓቸው ይመስላቸዋል፡፡ የአጼ ምኒልክን እና የቀዳማዊ ኃይለስላሴን በጎ ተግባራት ጥላሸት በመቀባት የአቶ መለስን ስብዕና የሚገነቡ ይመስላቸዋል፡፡ የአጼ ምኒልክን ሐውልት ከህዝባዊ ቦታዎች በማራቅ እና የአቶ መለስን እርካሽ ወረቀት ፎቶግራፎች በየመንገዶች ላይ በመለጠፍ አቶ መለስን ወደ መልዓክነት ያቀረቧቸው ይመስላቸዋል፡፡ አቶ መለስ የአጼ ኃይለስላሴ ሀውልት ከንክሩማህ ቀጥሎ በአፍሪካ ህብረት ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዳይቆም ሽንጣቸውን ገትረው ተከራክረዋል፡፡ ሆኖም ግን ንክሩማህ እራሳቸው የአጼ ኃይለስላሴ ያልተጠቆጠበ ጥረት ባይኖር ኖሮ የአፍሪካ ድርጅት እውን መሆን አይችልም ነበር በማለት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ያሉት ባለስልጣኖች የጥላቻቸው ባህሪ እና አተገባበር ነጻብራቅ ረዘም ያለ ጊዜ የቆየ ቢሆንም ለዚህ ምክንያታዊ መግለጫ አላገኘሁለትም፡፡ ብዙ ሰዎች በፍርሀት እና በጭንቀት ላይ ያሉ ሰለ ወደፊት ምንይመጣል አያሉ ነው ምክንያቱም በቀጣይነት የሚከሰተው ሁኔታ የማይታወቅ እና ለመተንበይም አስቸጋሪ የሆነበት ሁኔታ ሰለሆነ ነው፡፡ ያለፈውን ጊዜ፣ የጥንት 19ኛውን ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ የሚፈሩትን ሰዎች በትክክል ለመረዳት አልችልም፡፡ በሞያዬ ካለኝ ልምድ አንጻር ያለፈውን ጊዜ የሚፈሩ እና የሚሸበሩ ወንጀለኞ ይሄዉም በፊት በፈፀሙት ወንጀል የሚያዙ ሰለሚመስላቸውና ሰለሚፈሩ ነው:: በስልጣን ላይ ያሉ አምባገነኖች ስልጣናቸውን ከህግ አግባብ ውጭ በመጠቀም የሰላማዊ ዜጎችን መብት የጣሱ እና የደፈጠጡበትን ወንጀል ለመደበቅ ሲሉ ጥላቻን በማራመድ እና ከፋፍሎ መግዛትን አጀንዳቸው አድርገው ይይዙታል ከሚል መደምደሚያ ላይ ደርሻለሁ፡፡ በኢትዮጵያውያን ልዩ ልዩ ጎሳዎች ላይ ጥልቅ ጥላቻና እና ፍርሀትን በመፍጠር ለፈጸሟቸው እኩይ ተግባራት ተጠያቂ እንዳይሆኑ እና ኃላፊነትን እንዳይወስዱ የጥላቻ መንፈስን እንደ መርህ በመያዝ ያራምዳሉ፡፡ በህዝቦች መካከል ጥላቻን በመዝራትም በኢኮኖሚያዊ ችግሮች ምክንያት ተወጥረው ያሉትን ዜጎች ሀሳቦች ለማስቀየሻ ይጠቀሙበታል፡፡

በጥላቻ የተሞላን ሰው እንደ እራስህ ውደድ፣

ወርቃማው ህግ እንዲህ ይላል፣ “ጎረቤትህን እንደ እራስህ ውደድ፡፡“ እኔ ደግሞ እንዲህ እላለሁ፣ “የሚጠላህን እንደ እራስህ ውድ፡፡“ ከመጥላት ይልቅ መውድደ የተሻለ ነገር ነው፡፡ ጥላቻ ወርዋሪውን ተመልሶ እንደሚጎዳ ቦንብ ነው፡፡ መጀመሪያ ከሚወረውረው ሰው እጅ ይወጣል ተመልሶ ግን በጥላቻ የተሞላውን ሰው እራሱን ይጎዳዋል፡፡ የማንዴላን አባባል በመዋስ፣ ጥላቻ የነብስ መርዝ ነው፡፡ በጥላቻ የተሞሉት በሚጠሉበት ጊዜ መርዝን ይጠጣሉ እናም የሚጠሏቸው እንዲሞቱ ይጠብቃሉ፡፡ በስልጣን ላይ ያሉ ሁሉ ጥላቻን ማራመድ እንዳለባቸው ልዩ ምክር የሚሰጥ ለየት ያለ የፍልስፍና ዓይነትም አለ፡፡ ጥላቻ ሁልጊዜ የተጠላውን ሰው የተወደደ እና የተከበረ ስብዕና ያለው እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ተቆናጥጠው ያሉ ወገኖች በዱሮዋ ደቡብ አፍሪካ ከነበሩት የአፓርታይድ መሰል የመንፈስ ጓዶቻቸው ትምህርቶችን ሊማሩ ይገባል፡፡ የአፓርታይድ ጌቶች የማንዴላን ስብዕና፣ አመራር እና ክብር ለበርካታ አስርት ዓመታት ለማዋረድ ፈለጉ፡፡ ማንዴላ አሸባሪ እና ኮሙኒስት ናቸው በማለት ማንኛውንም ዓይነት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ከፈቱባቸው፡፡ ይንንም ምክንያት በማድረግ ማንዴላ በእስር ቤት በቆዩባቸው ጊዚያት ሁሉ ምንም ዓይነት የፎቶግራፍ ምስላቸው እንዳይወጣ አደረጉ፡፡ ሆኖም ግን ያልታሰቡ አጋጣሚዎች ተከሰቱ፡፡ በሂደት ጊዜ እያለፈ እና የጸረ አፓርታይድ ንቅናቄው እየተጠናከረ ሲሄድ ማንዴላን አሳንሶ የማየት አባዚያቸው የማንዴላን የመላዕክነት ደረጃ ከፍ እያደረገ ወደ ዓለም አቀፋዊ ተምሳሌነት እንዲሸጋገሩ እገዛ አደረገላቸው፡፡ ከዚህ ሊወሰድ የሚችለው ታላቅ ቁምነገር የአጼ ምኒልክን እና የአጼ ኃይለስላሴን ስብዕና ዝቅ ለማድረግ ጥረት ባደረጉ ቁጥር እነዚህ መሪዎች በኢትዮጵያ የወጣቶች ትውልድ የአስተሳሰብ አድማስ ዘንድ የበለጠ ክብር እና ሞገስን እየተቀዳጁ ታዋቂ እየሆኑ ይሄዳሉ፡፡ በእነዚህ መሪዎች ላይ የማያቋርጥ እና ዘለቄታዊ ያለው የማዋረድ ዘመቻ ባደረጉ ቁጥር የቀድሞው ትውልድ ጉዳዩን የበለጠ እንዲገመግመው እና አቋሙን እንዲያጠናክር ያደርገዋል፡፡
ፍቅር ከጥላቻ በላይ ዘልቆ መሄድን ይጠይቃል፡፡ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ እና ማንዴላ በሰዎች እና በህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ፍቅር ያለውን የማይበገር የአሸናፊነት ኃይል፣ እንዲሁም ፍቅር በዘር፣ በጎሳ እና በኃይማኖት የተዘራን የጥላቻ ካንሰር የመፈወስ ችሎታ እንዳለው በግልጽ አስተምረውናል፡፡ ማንዴላ ለመጥላት እና በቀልን ለመፈጸም ምክንያት አላቸው፡፡ ለ27 ዓመታት የማንዴላ ስም የእስረኛ ቁጥር 46664 ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በፌብሯሪ 1990 ጧት ከእስር ቤት ተለቅቀው ከእስር ቤቱ በር ሲወጡ ከሚሊዮን ዶላር ዋጋ በላይ የሚያወጣውን ፈገግታቸውን አሳይተዋል፡፡ ለ27 ዓመታት ከቤተሰቦቻቸው ነጥለው በእስር ቤት ውስጥ ባማቀቋቸው የአፓርታይድ ጌቶች ላይ ምንም ዓይነት የጥላቻ ስሜት አላሳዩም፡፡ ማንዴላ ታላቅ ትምህርት አስተምረውን አልፈዋል፣ እንዲህ በማለት፣ “እየተራመድኩ ወደ በሩ በምቃረብበት ጊዜ ይህ ሁኔታ ወደ ነጻነት እየመራኝ እንደሆነ አስብ ነበር፡፡ የበቀልተኝነት ስሜቴን እና ጥላቻዬን እዚያው እስር ቤት ጥዬው ካልወጣሁ እዚያው እስር ቤት እንዳለሁ እቆጥረዋለሁ፡፡“ በማለት የጥላቻን መጥፎነት በግልጽ ተናግረዋል፡፡ ማንዴላ ፍጹም የጥላቻ እስረኛ አልነበሩም፡፡ እስረኛው የአፓርታይድ ጥላቻ ነበር፣ እናም አስረኞቹ የአፓርታይድ አለቆች እና ጌቶች ነበሩ፡፡ ማንዴላ ከእስር ቤት በመውጣት በጥላቻ ሰንሰለት ከአፓርታይድ ግንብ ጋር የታሰሩትን እውነተኞቹን የአፓርታይድ እስረኞች ከጥላቻ፣ ከፍርሀት፣ እና ከበቀልተኝነት ነጻ ለማውጣት ተንቀሳቅሰዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያሉት ገዥዎች በጥላቻቸው የሚቀጥሉ ከሆነ በደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ በስልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ የደረሰው ዕጣ ፈንታ የሚደርስባቸው መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡ በአፓርታይድ የአገዛዝ ዘመን ጊዜ “ነጻዎቹ” ነጮች እውነተኛው የማይቀረው የብዙሀን አገዛዝ በሚመጣበት ጊዜ ለብዙ ጊዜ በጭቆና ቀንበር አስረው ሲያማቅቋቸው የነበሩት ጥቁር አፍሪካውያኖች ምን ሊያደርጓቸው እንደሚችሉ ሌት እና ቀን ያሰላስሉ ነበር፡፡ በጥቁር አፍሪካውያን ላይ የነበራቸው ጥላቻ እንቅልፍየለሽ ሌሊቶችን ብቻ እንዲያሳልፉ አላደረጓቸውም፣ ሆኖም ግን ልቦቻቸው፣ አዕምሯቸው እና ነብሳቸው እንዲሁም ስብዕናዎቻቸውም ጭምር እንዲሰበሩ አደረጋቸው እንጅ፡፡ ሙት መንፈሶች አደረጓቸው፣ ነጻ ሆነው ባሏቸው ኃብቶቻቸው ለመደሰት ባለመቻል የቁም ሙት አደረጓቸው፣ እንዲሁም በኤሌክትሪክ እና በእስር ቤት የሽቦ አጥር ታጥረው የእራሳቸው ጎረቤቶች የእስር ቤት በሮች ሆኑባቸው፡፡ በእርግጥ በጦር ካምፕ የሚኖሩ ህዝቦች ሆኑ፡፡

ምንጊዜም የተሻለ መንገድ አለ፡፡ የጥላቻ ትችት ከማቅረባችን በፊት እውነተኛውን ነገር ለማወቅ የበለጠ ጽናት ሊኖረን ይገባል፡፡ ስለዳግማዊ አጼ ምኒልክ፣ ስለ አጼ ኃይለስላሴ፣ ስለ ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም እና ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እውነኛውን ነገር ማቅረብ ይኖርብናል፡፡ እነርሱን መጥላት ሳይሆን ከስህተቶቻቸው እንማር፣ እኛ በህይወት ያለነው የእነርሱን ስህተት መድገም የለብንም፡፡ ጥላሸት በመቀባት ላይ ላለመሰማራት ከእነርሱ ስህተት እንማር፣ ነገር ግን የእርቅን መንገድ በመፈለግ የእነርሱን ስህተቶች እናርም፡፡ ከኢትዮጵያ ወጣቱ ትውልድ ጋር ህብረት በመፍጠር ማንም ወንድ ወይም ሴት በማንነቱ/ቷ፣ በዘሩ/ሯ ሳይሆን ሰው በመሆኑ/ኗ፣ አፍሪካዊ/ት እና ኢትዮጵያዊ/ት በመሆናቸው ብቻ በመመልከት አዲሲቷን ፍቅር የነገሰባት ኢትዮጵያ ለመገንባት እንነሳ፡፡ ማንም ወንድ ወይም ሴት ባለው/ላት ስልጣን በመመካት ባልታጠቁ ዜጎች እና በሰላማዊ ሰዎች ላይ የጦር እልቂት ሊያዝዝ/ልታዝዝ የማይችሉበት እና ይህ ዓይነቱ አስተሳሰብም ሊወገድ የሚችልበት ነጻ ህሊናን በመፍጠር አዲሲቷን ፍቅር የነገሰባት ኢትዮጵያ ለመገንባት እንነሳ፡፡ በእያንዳንዱ/ዷ ግለሰብ የጎሳ፣ የእምነት ወይም የቋንቋ ልዩነት ሳንፈጥር በአንድነት በመሆን የእያንዳንዱ/ዷ ዜጋ መብት እና ክብር የሚጠበቅበትን ህብረተሰብ ለመፍጠር እንነሳ፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ነው የወደፊቱን ብሩህ ዘመን ለመፍጠር የምንችለው፡፡ ለብዙ ጊዜ በመቆየት በጊዜ ደመና ተሸፍኖ የደበዘዘውን ነገር ቆፍሮ በማውጣት እና ጥላሸት በመቀባት አይደለም ፍቅር የነገሰበትን የወደፊቱን ትውልድ መገንባት የምንችለው፡፡

በጥላቻ ንግግር አንዘን ወይም ደግሞ አንቆጣ፡፡ ምንም ዓይነት እርባና የለውም፡፡ ይልቁንም ጥላሸት የመቀባት ዘመቻውን በሰከነ መልክ እናጋልጥ፡፡ መላዕክ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ስህተት እና ውሸት መሆኑን እና የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት ለመቀበት እና ለመበረዝ የሚደረገውን መዋተት እናጋልጥ፡፡ ከጥላቻ አራማጆች ጋር በማበር እራሳችንን ወደ ጭቃ እና የሚያጣብቅ ቆሻሻ ውስጥ አንጣል፡፡ እንዲህ የሚሉትን የጆርጅ በርናርድ ሻውን ምክሮችን በፍጹም መርሳት የለብንም፣ “ከብዙ ጊዜ በፊት ከአሳማ ጋር ማጥ ዉስጥ ላለመታገል ትምህርት አግኝቻለሁ፣ ለመታገል ከሞከርክ ቆሻሻ ትሆናለህ፣ አሳማው ግን ማጡን የነብሱን ያህል ይወደዋል፡፡“ ጥላቻን ሙያ አርገው ከሚኖሩ ሰዎች ጋር የጥላቻ ቃላትን መለዋወጥ ከአሳማ ጋር በጭቃ ማጥ ውስጥ የነጻ ትግል ውድድርን እንደማድረግ ይቆጠራል፡፡

ጥላቻን ወደ ፍቅር መለወጥ
በጥላቻ መንፈስ የተሞሉት ወገኖች ይጥሉ እና ይዋሹ፡፡ ስለዚያ ጉዳይ የምናደርገው አንዳች ነገር የለም፡፡ በእራሳችን የሀይል ንፍቀ ክበብ ውስጥ ያለን ልዩ ችሎታ እራሳችንን ከጥላቻ ወደ ፍቅር ከመቀየር ላይ ነው፡፡ በእርግጥም አሉታዊ ኃይሎችን ወደ አዎንታዊ ኃይሎች የመቀየር ችሎታ አለን፡፡ ከጥላቻ ወደ ፍቅር ለመቀየር እንችላለን፣ ይህን የምናደርገው ግን ነገሩ ቀላል ስለሆነ አይደለም ይልቁንም የበለጠ ከባድ ስለሆነ እንጅ፡፡ ፍቅር በግለሰብ ደረጃም ይሁን፣ በሌሎችም ይሁን፣ በማህበረሰቡ ወይም በአጠቃላይ በህዝቡ ላይ ይሁን ለተግባራዊነቱ ታላቅ ስራ መስራትን ይጠይቃል፡፡

ከማህተመ ጋንዲ እና “እውነተኛው ኃይል”/Satyagraha ከሚሉት አቀራረባቸው እስቲ ትምህርት እንቅሰም፡፡ ጋንዲ እንዲህ በማለት ገለጻ አድርገዋል፣ “እውነት/satya ፍቅርን በማጎናጸፍ የመንፈስ ጽናትን ይወልዳል፣ እናም ከኃይል ጋር ተመሳሳይ በመሆን ያገለግላል፡፡“ ዓላማው በጥላቻ የተሞላው/ችው እንዳያስገድድ/እንዳታስገድድ በማድረግ ሀሳባቸውን ለማስለውጥ ነው፡፡ በተግባራዊነት ሁኔታው ስንመለከተው ዓላማው በጥላቻ የተሞላውን/ችውን ጥላቻ ማራመድ የእራሱን/ሷን ልብ፣ አዕምሮ እና ነብሳቸውን የሚጎዳቸው መሆኑን በማሳመን እንዲቀየሩ ለማድረግ ነው፡፡ ከማንኛውም ጉዳትን ከሚያመጡ ነገሮች ሁሉ የሚጠብቁን እራስን፣ ማህበረሰቡን እና አገርን መውደድ ነው፡፡ በጥላቻ ከተሞሉት ወገኖች ፍቅር የተሞሉ ወገኖችን ለማፍራት እውነተኛውን ኃይል/Satyagraha በተግባር እናውል፡፡

ከዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ የምንማራቸው በርካታ ቁምነገሮች አሉ፣ እንዲህም በማለት ያስተምሩናል፣ “ጨለማን ጨለማ አያስወግደውም፣ ብርሃን ብቻ ነው ያንን ማድረግ የሚችለው፡፡ ጥላቻን ጥላቻ ሊያስወግደው አይችልም፣ ፍቅር ብቻ ነው ያንን ማድረግ የሚችል፡፡“ ብለዋል፡፡ እንዲህ በማለትም አስተምረዋል፣ “ይቅርታ የማድረግ ችሎታችንን ማሳደግና ማጠናከር ይኖርብናል፡፡ ይቅርታ የማያደርግ/የማታደርግ ሰው ለማፍቀር ኃይል የለውም/የላትም፡፡ በመጥፎነታችንም ላይ ጥሩ ነገሮችም አሉ፡፡ በመጥፎ ነገሮቻችን ላይም ጥሩ ነገሮች አሉ፡፡ ይህንን ሁኔታ ባወቅን ጊዜ ጠላቶቻችንን ከመጥላት በመጠኑም ቢሆን እንታቀባለን፡፡“ ይቅርታ አድራጊነት እና እርቅ ብቸኞች የጥላቻ ፈውስ እና መድኃኒቶች ናቸው፡፡
ከዘመናችን ታላቅ ቀልድ አዋቂ ከቻርለስ ቻፕሊን እንኳ ትምህርት መቅሰም ይኖርብናል፡፡ እንዲህም ይለናል፣ “የሰው ልጅ ጥላቻ ያልፋል፣ እና አምባገነኖችም ይሞታሉ፣ እናም ከህዝቦች የነጠቁት ስልጣን ተመልሶ በህዝቡ እጅ ይገባል፡፡ ስለሆነም የሰው ልጅ ሟች እስከሆነ ድረስ ነጻነት ከናካቴው ሊጠፋ አይችልም፡፡“ ነጻነት በጥላቻ ከተሞሉት የሰው ዘሮች ሁሉ የበለጠ እድሜ አለው፡፡ በጎሳ ማንነት መፈረጅን እርግፍ አድርገን እንተው እና ሰው በመሆናችን ብቻ በኢትዮጵያዊነታችን እና በአፍሪካዊነታችን እንኩራ፡፡

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ላሉ የማስተላለፈው መልዕክት፣

በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ሆነው ጥላቻን ለሚያራግቡት አጭር መልዕክት አለኝ፡፡ በአሁኑ ጊዜ የምትቆሰቁሱት የዘር እና የጎሳ ጥላቻ ፍላጻ በአንድ ወቅት ተመልሶ እራሳችሁ ላይ ይሰካል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የአጼ ምኒልክን ክብር እና ዝና ለማንቋሸሽ በታለመ ዕኩይ ምግባር ጡት ቆራጭ አረመኔ ነበሩ በማለት በመሳለቅ እና በማፌዝ ላይ ትገኛላችሁ፡፡ በአሁኑ ጊዜ አጼ ምኒልክን እንዲጠሉ የሚሰበክላቸው ሰዎች ነገ ደግሞ አቶ መለስን እንዲጠሉ የማይሰበክበት ምክንያት አይኖርም፡፡ የእናንተ ታላቁ ባለራዕይ መሪ አቶ መለስ በኦጋዴን፣ በጋምቤላ፣ በአዲስ አበባ እና በሌሎችም ቦታዎች በንጹሃን ዜጎች ላይ በፈጸሟቸው የጅምላ እልቂቶች ሳቢያ በድንጋይ እና በእብነበረድ በተቀረጹ ሃውልቶች ላይ ሆነው ሁለተኛው ሮዶልፍ ግራዛኒ በመባል የሚታወሱበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም፡፡ ዛሬ ጓደኞች ብላችሁ የያዛችኋቸው ሰዎች ነገ ቀንደኛ ጠላቶቻችሁ ሆነው ይቀርባሉ፡፡ ዛሬ የእናንተ ጠላቶች አድርጋችሁ ጥላሸት የምትቀቧቸው ሰዎች ነገ ጽዋው ሞልቶ እጣ ፈንታችሁ ደርሶ የዘራችሁትን የምታጭዱበት ጊዜ ሲመጣ የእናንተ ጓደኞች ሆነው ይቀርባሉ፡፡

ዳግማዊ አጼ ምኒልክ መልዓክ ወይም ጭራቅ አልነበሩም፡፡ ሰይጣን ወይም ደግሞ እግዚአብሄርም አልነበሩም፡፡ የተቀሩት የአፍሪካ አገሮች በኃአውሮፓ ኢምፔሪያሊስት ኃይሎች ሲቆራረሱ፣ መጫወቻ ሲሆኑ፣ ሲነሱ ሲጣሉ፣ ሲበጠሱ ሲቀጠሉ፣ ሲሸጡ እና ሲለወጡ እንዲሁም ሲጋዙ በነበረበት ጊዜ አጼ ምኒልክ ደግሞ ኢትዮጵያን ሲያጠናክሩ እና ሲያዘምኑ የነበሩ የተከበሩ አፍሪካዊ ንጉስ ነበሩ፡፡ ዳግማዊ አጼ ምኒሊክ በአንድ መለኪያ ብች ይገምገሙ፣ በእውነት! የታሪክ ሰዎች እውነታውን መናገር አለባቸው፣ እና ሁሉንም እውነታዎች፣ ሌላ ምንም ነገር ሳይሆን ስለምኒልክ ያለውን እውነታ ብቻ፡፡ ለአጼ ምኒልክ 100ኛ ሙት ዓመት መታሰቢያ ሲባል እ.ኤ.አ በ1909 በኒዮርክ ታይምስ ባሮን ዲ ጃርልስበርግ የተባለ የቤልጄም አሳሽ ለዳግማዊ አጼ ምኒልክ ምስክርነት ለጋዜጣው ቃል በመስጠት የተዘገበውን በከፊል ምስከርነት እውነታ መረጃ እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ፡፡ ይህ ታሪካዊ የምስክርነት መረጃ ዳግማዊ አጼ ምኒልክን ከሰሯቸው ስራዎች አንጻር በትክክለኛው የታሪክ ሚዛን ላይ በማስቀመጥ እንዲገመገሙ ያስችላል የሚል ጽኑ እምነት አለ፡፡

ዳግማዊ አጼ ምኒልክ የዘውድ ስልጣኑን ለመቆናጠጥ ትግል ማድረግ ከጀመሩበት ከ20 ዓመታት በኋላ አቢሲኒያን ከከፊል የኋላቀርነት አገዛዝ በማውጣት ወደ አውሮፓውያን የንጉሳዊ ህገመንግስት የአገዛዝ ስርዓት ምሳሌነት አሸጋግረዋታል… እራሳቸውን ነጻ እና በእራስ የሚተማመኑ አድርገው የሚቆጥሩት ዘ እምነገደ የይሁዳ አንበሳ ስዩመ እግዚአብሔር የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ዘ ኢትዮጵያ የኢጣሊያንን የቅኝ ግዛትነት ፍላጎት አምባ ጋሪማ ላይ ጦርነት ገጥመው በአሸናፊነት እንዳንኮታኮቱት… አጼ ምኒልክ ከአጼ ዮሀንስ ህልፈተ ህይወት በኋላ እ.ኤ.አ ኖቬምበር 4 1889 የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ሆነው ሲሰየሙ የአቢሲኒያን መንግስት ከመሰረቱት የአካባቢያዊ መንግስታት በሙሉ ቅቡልነት አልነበራቸውም፡፡ ከብዙ ድካም እና ትግል በኋላ ነው እነዚህን የአካባቢ ገዥዎች እና ንጉስነታቸውን አንቀበልም ያሉትን አማጺ ገዥዎች በማሳመን እና በኃይል በማንበርከክ በመጨረሻ ስኬታማ ለመሆን የበቁት… ከዚያ በኋላ የአጼ ምኒልክ ዋና ዓላማ የነበረው የአውሮፓን ስልጣኔ ወደ አገራቸው ማስገባት ነበር፡፡ ንጉሱ የፊውዳሉን ህግ በማፈራረስ በእርግጥም በግዛታቸው እስከ አሁንም ድረስ ጨርሶ እንዳልጠፋ እና ባሮችን ነጻ በማውጣት የባሪያ ንግድን በማጥፋት በግዛታቸው በሙሉ ከክፍያ ነጻ የሆነ የትምህርት ስርዓትን ዘርግተዋል፡፡ በዚህም መሰረት እንደማንኛውም የአውሮፓ ሀገር ሁሉ በቀጣዮቹ ትውልዶች ትምህርት በመላ የአቢሲኒያ ግዛት ውስጥ የሚስፋፋ ይሆናል፡፡

ምኒልክ በመላ አፍሪካ በስልጣን ላይ ካሉ መሪዎች ሁሉ ልዩ ባህሪ ያላቸው ናቸው፡፡ እንደ የዲፕሎማሲ ሰው፣ እንደ ገንዘብ ኃላፊ፣ እንደ ወታደር ከሌሎች ወንድማዊ ንጉሶች የቅርበ መረጃዎችን በመውሰድ በእራሳቸው አካሄድ እንደሚመስላቸው የሚተረጉሙ ንጉስ ናቸው፡፡ እንደ ወታደር እና እንደ የዲፕሎማሲ ሰው የኢጣሊያኖችን በአቢሲኒያ መሸነፍ ለንጉሱ እንደ መልካም አጋጣሚ ምን ያህል ጠቃሚ የሆኑ ንጉስ መሆናቸውን አሳይተዋል፡፡ በቅርብ ዓመታት ደግሞ የገንዘብ ብልህ ጥንቁቅ አያያዝ ምኒልክን ልዩ ያደርጋቸዋል፡፡ ስለገንዘብ እንደ ወጣትም፣ የዙፋን ስልጣናቸውን ከመያዛቸው እና በዙፋኑ ላይ ከተቀመጡም በኋላ በፓሪስ የስቶክ ገበያ ትንበያን/Paris Bourse ላይ ተሳትፎ ማድረጋቸው መልካም ተፈጥሯዊ ችሎታ ያላቸው መሆኑን ያመላክታል፡፡ እነዚህ ጠቃሚ ትንበያዎች የነበሩ ሲሆን ምኒልክ የዙፋን ስልጣኑን ከያዙ በኋላ ለመቋረጥ ችለዋል… የገንዘብ አሰራር ስርዓታቸውን በማስፋት እስከ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ድረስ በማስፋት በአሜሪካ የባቡር ሀዲድ ካምፓኒዎች ላይ ትልቅ የድርሻ ባለቤት ለመሆን በቅተዋል፡፡ ከአሜሪካ የሴኪዩሪቲ ሰርቲፊኬቶች እና ከፈረንሳይ እና ከቤልጄም ባለሀብቶች ጋር ከ25 ሚሊዮን ዶላር ያላነሰ መዋዕለ ንዋይ በስራ ላይ እንዲውል አድርገው ነበር፡፡

በጣም የሚያስገርመው የአቢሲኒያው ደብዛዛ ንጉስ በሁሉም ነገሮች ላይ ያላቸው ሁለገብ እውቀት ነው፡፡ በጣም ምጡቅ የቋንቋ ችሎታ የነበራቸው ሲሆኑ ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዝኛ እና ጣሊያንኛ ቋንቋዎችን አቀላጥፈው መናገር ይችላሉ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ለመንግስታዊ ስራቸው ሙሉ ጊዜ ሰጥተው የሚሰሩ ሲሆን በአውሮፓ የሚዘጋጁ ጽሁፎችንም የመከታተል ዕድል ስላላቸው እና በትኩረት ስለሚከታተሉ አዲስ መጽሀፍ በወጣ ቁጥር ስለደራሲው ሲጠየቅ አዲስ አይሆኑም፡፡ ባዲሳባ ቤተመንግስት በሰዎቻቸው በሚታወቁበት መጽሀፍትን በማሰባሰብ ስራቸው እውቅና እንዲሰጣቸው ሲባል በተዘጋጀው ስብሰባ ላይ በተገኙበት ዕለት በቤተ መጻህፍታቸው ከ20 ሺህ ያላነሱ ጥራዞች መገኘታቸው ልዩ ኩራት እንዲሰማቸው አድርጓል፡፡ የምኒልክ መጻህፍትን የማሰባሰብ የትርፍ ጊዜ ስራ በጥንት የአፍሪካ እና የኢስያ ስልጣኔዎች ዘመንም የሚደረግ ነበር፡፡

በአጼ ምኒልክ ላይ የጥላቻ ዘመቻ ከሚያደርጉት ወገኖች ጋር የማቀርበው መደራደርያ ፣
በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ላይ የጥላቻ ዘመቻ ስለማሰራጨት ጉዳይ የማቀርበው መደራደርያ አለኝ ፡
በአጼ ምኒልክ ስብዕና ላይ የምታደርጓቸውን ውሸቶችና ቅጥፈቶች የምታቆሙ ከሆነ እኔም ስለአቶ መለስ የምናገራቸውን እውነቶችመናገር አቆማለሁ!

ጥር 7 ቀን 2006 ዓ.ም
ዘ -ሐበሻ

ፕ/ር በየነ “የአካኪ ዘራፍ ትግል አክሳሪ ነው፤ የስሜት ፖለቲካ ያብቃ” አሉ

January16/2014

“ከኤርትራ ጋር መስማማት አግባብ ነው፤ ግን ፍርሃቻ አለኝ”
beyene petros



“የአካኪ ዘራፍ ፖለቲካና ከስሜት ያልጸዳ የፖለቲካ ትግል መሪውንም ሆነ አምኖ የሚመራውን ህዝብ ለድል” እንደማያበቃ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ገለጹ። ከኤርትራ ጋር ስምምነት ቢደረግ መልካም መሆኑን፣ ነገር ግን ስምምነቱ የመሪዎችና የፖለቲከኞች ሳይሆን የህዝብን ስሜት የጠበቀ ሊሆን እንደሚገባውም ጠቁመዋል።
ከጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ጋር በተለይ ቃለ ምልልስ ያደረጉት ፕ/ር በየነ “አሁን ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሁኔታ ከመቼውም ጊዜ በላይ አስተዋይነት የሚፈልግ፣ ዘመናዊ የትግል ስልት የሚጠይቅ ነው” በማለት ተናግረዋል። በቃለ ምልልሳቸው ደጋግመው  “አሁን በተያዘው የአካኪ ዘራፍ መንገድ የትም አይደረስም” በማለት ምክንያታቸውን ዘርዝረዋል።
ትንንሽ ጠርዝ በመያዝ የትም የማይደርስ ትግል ከየአቅጣጫው እንደሚፈለፈል ፕ/ር በየነ አመልክተዋል። በዚሁ የተነሳ ስትራቴጂካልና ታክቲካል ጉዳይ የመለየት አቅም አናሳ በመሆኑ የፖለቲካው መንደር የርስ በርስ ንትርክና ውግዘት ሊሆን እንደቻለ ገልጸዋል። ለዚህም ተጠያቂዎችና ቅድሚያ ተወቃሾች ህዝብና አገር የምትፈልጋቸው የዘመናዊ ለውጥ መሪዎች መሆን ሲገባቸው የዳር ተመልካች የሆኑት የአገሪቱ ልሂቃን እንደሆኑም በግልጽ ተናግረዋል።
“ችግሩ በአገር ውስጥ ባሉት ልሂቃን ላይ ጎልቶ ቢታይም፣ በውጪው ዓለም ባሉት ምሁራኖችም ላይ ተመሳሳይ ችግር አለ” የሚሉት ፕ/ር በየነ “እነዚሁ ክፍሎች ትግሉን ከመቀላቀል ይልቅ እኛን በመውቀስ አገራዊ ሃላፊነታቸውን የተወጡ መስለው ይታያሉ” ሲሉ ስሜታቸውን ገልጸዋል።
“የፖለቲካው መስመር ክፍተትን አይወድም” በማለት የሰከነ አመለካከት ላላቸውና ከስሜት ፖለቲካ ነጻ ለሆኑት ዜጎች መልዕክት ያስተላለፉት ዶ/ር በየነ፣ ሰዓትና በጀት በመመደብ የተለየ አመለካከት ያላቸውን ክፍሎች ሰድቦ የማሰደብ ተግባር ሲከናወን ማየታቸው በጅጉ እንደሚያሳዝናቸው ተናግረዋል። በጦር መሳሪያና በሃብት ብዛት መፎካከር ባይቻልም፣ በሰብአዊ ብቃት ኢህአዴግን መፎካከር እንደሚቻል የጠቆሙት ዶክተሩ የተቃዋሚው ሰፈር በተቃራኒው የተፈረካከሰ፣ እርስበርስ ለመባላት ቅድሚያ የሚሰጥ፣ የትግል ስልቱም ሆነ አቅሙ ስትራቴጂካዊና ታክቲካል ጉዳዮችን መለየት በማያስችል ደረጃ የተዋቀረ መሆኑ ትግሉን ፍሬ አልባ እንዳደረገው ተናግረዋል።
beyene_petros“ለአውራነት/ኮርማነት የታሰበ በሬ ተመልሶ ላሚቱን ጠባ” በሚል በሃድያ የሚነገር ተረት በማስታወስ ሃሳባቸውን ያጠናከሩት ዶ/ር በየነ፣ የዚህ ሁሉ ችግር መንስዔው የልሂቃኑ ዝምታ እንደሆነ አመልክተዋል። አገራቸውን ወደ ተሻለ መንገድ ለማሸጋገር የሚችሉ ሁሉ ዝምታቸውንና ዳር ቆመው የሚመለከቱትን የአገራቸውን ውድቀት እንዲታደጉ ጥሪ አቅርበዋል። ዶ/ር ነጋሶ የወሰዱትን ርምጃ በማንተራስ ስለ ፖለቲካ ጡረታም ተጠይቀው መልስ ሰጥተዋል።
“እናንተ አርጅተሃል ካላችሁ እንጂ እኔ አላረጀሁም። ጤነኛ ነኝ። የነጋሶን ያህል እድሜም የለኝም” በማለት መልሳቸውን ይጀምራሉ። በማያያዝም “ልተውስ ብል እንዴት ብዬ?” ሲሉ ይጠይቃሉ። “ልሂቃኑ ዳር ቆመው ተመልካች ሆነዋል። በዚህ ላይ የምመራቸውና ውህደት የፈጠሩት የደቡብ ህብረትና የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራት ፓርቲ አደራውን ከኔ አላወረዱም። አሁን በቃኝ ማለት ሰራዊት በትኖ እንደሚፈረጥጥ መሪ የመሆን ያህል ነው።”
ኸርማን ኮህን በቅርቡ ይፋ ያደረጉትን የእርቅ ሃሳብ አስመልከቶ ማብራሪያ ሰጡት ዶ/ር በየነ “በአልጀርሱ ስምምነት መሰረት የሚደረግ ስምምነት ከቶውንም ቢሆን ተቀባይነት የለውም። ከኤርትራ ጋር እርቅ መልካም ቢሆንም በፖለቲከኞችና በውስን ሃይሎች ፍላጎት ተከናውኖ ሰዶ ማሳደድ እንዳይሆን እፈራለሁ” ብለዋል። ከዚሁ ጋር በማያያዝ አሜሪካ በኢህአዴግና በወያኔ የፖለቲካ እምነት ደስተኛ እንዳልሆነች ተናግረዋል። ድጋፍ የምትሰጠው ከፍቅር ብዛት እንዳልሆነ በማመልከት የተቃዋሚው ክፍል ይህንኑ ቀዳዳ ሊጠቀምበት ይገባል ብለዋል። “ታዲያ” አሉ ፕ/ር በየነ “ታዲያ በማንጓጠጥና በዘለፋ ሳይሆን በሰከነ መንፈስና ስሜትን በገደለ አስተዋይነት” ሊሆን ይገባል። በመጪው ምርጫ የ1997 ምርጫ ዓይነት ሁኔታ እንዲፈጠር ዘመቻ መጀመሩንና የድጋፍ ፍንጭ መታየቱን የገለጹት ዶ/ር በየነ ስለ ሃይል አማራጭና ኢህአዴግ፣ በተለይም ህወሃት ውስጥ አለ ስለሚባለው የመፈረካከስ ችግር ተጠይቀው “ጦርነት የሁለት የጎበዝ አለቆች ጸብና ድብድብ ነው። ከአሁን በኋላ እኔ ላገሬ ጦርነት አልመኝም” በማለት ከምክንያታቸው ጋር አስቀምጠዋል። ህወሃትና ኢህአዴግ ውስጥ አለ ስለተባለ የመፈረካከስ ችግር “የዋህነት አይጠቅምም፣ በስሜትና በአካኪ ዘራፍ ፖለቲካ የሚመጣ ለውጥ ይኖራል ብዬ አላስብም” ብለዋል። ስለ ስጋታቸውም ተናግረዋል።
“ወያኔ የሚባለውና ተዘጋጅቶ አገሪቱን የተቆጣጠረ ሃይል ለሰበሰበው ሃብትና ንብረት ሲል ፖለቲካውን በበላይነት ለመምራት ከቀን ወደ ቀን የሚፈጽመው ጥፋት ህዝብ እያማረረ መጨረሻው አገሪቱን ወደ ጥፋት እንዳይወስድ ነው። የከፋቸው በጨመሩ ቁጥር ችግሩ መከሰቱ አይቀርምና በጥበብ ታግሎ ካሰቡት ለመድረስ እነሱ ከሚያስቡት በተለየ በልጦ ማሰብና መታግል አስፈላጊ ነው። ለዚህም የልሂቃኑ ዳር ቆሞ መመልከት መቆም አለበት” ብለዋል። በማያያዝም ዲያስፖራው አገር ውስጥ ለሚታገሉ ድርጅቶች ልዩነት ሳያደርግ ድጋፍ ሊሰጥ እንደሚገባ አሳስበዋል። ድጋፉም ሆነ እገዛው ሰክኖ ለማሰብ እንደሚመነጭም ገልጸዋል። ዶ/ር በየነ ጴጥሮስ በተለይ ከጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ያደረጉትን ሙሉ ቃለ ምልልስ በቀጣይ ይዘን እንቀርባለን።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ