Wednesday, January 8, 2014

2014፡ የኢትዮጵያ የአቦ-ጉማሬው ትውልድ ዓመት- ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

Janaury 8/2014

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

(ክፍል አንድ) 2014 የኢትዮጵያ የአቦ -ጉማሬው ትውልድ የሚነሳሳበት ዓመት፣
እ.ኤ.አ በ2013 በመጀመሪያው ሳምንት ባቀረብኩት ሳምንታዊው ትችቴ ዓመቱ “የኢትዮጵያ የአቦሸማኔው (የወጣቱ ትውልድ) ዓመት ይሆናል “የሚል ትንበያ ሰጥቼ ነበር፡፡ እንደትንበያውም ዓመቱ የኢትዮጵያ የአቦሸማኔው (ወጣቱ) ትውልድ ታላቅ የስኬት ዓመት ሆኖ ተጠናቅቋል፡፡

 2014 ደግሞ “የኢትዮጵያ የአቦ-ጉማሬው ትውልድ ዓመት ይሆናል” የሚል ትንበያ እሰጣለሁ፡፡  የአቦ-ጉማሬው ትውልድ በአፈጣጠሩ የጉማሬው (የቀድሞው ትውልድ) አባል ሲሆን በተግባራዊ እንቅስቃሴው ግን እንደ አቦሸማኔው (ወጣቱ ትውልድ) የሚያስብ፣ አቦሸማኔውን የሚመስል እና እንደ አቦሸማኔው ሁሉ የክንውን ድርጊቶችን የሚፈጽም የማህበረሰብ ክፍል ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የአቦ-ጉማሬው ትውልድ ለፍትህ እና ለነጻነት በሚደረገው የትግል ሂደት ላይ የጉማሬው (የቀድሞው ትውልድ) የሚያንጸባርቃቸውን ድክመቶች በሚገባ የተገነዘበ እና እነዚህን ግድፈቶች በማስወገድ የወጣቱን የትግል መንፈስ እና ወኔ ወደ ላቀ የእድገት ምዕራፍ ለማሸጋገር በአንድ ዓላማ ለአንድ ዓላማ ከአቦሸማኔው (የወጣቱ) ትውልድ ጎን በመሰለፍ የሚሰራ የህብረተሰብ ክፍል ነው፡፡
                                                                                                                                    
የኢትዮጵያ የአቦ-ጉማሬው ትውልድ በአፈጣጠሩ ልዩ የሆነ የትውልድ  ዝርያ ነው፡፡ ይህ ትውልድ በተፈጥሮው ድልድይ ቀያሽ እና በኃይል አሰላለፍ ላይ ያለውን ወቅታዊ እና ነባራዊ ሁኔታ በተገቢው መንገድ እያጠና ወጣቱን ትውልድ ለድል የሚያበቁ የኃይል ምንጮችን ቀጣይነት ባለው መልክ የሚፈበርክ የህብረተሰብ አካል ነው፡፡ የአቦ-ጉማሬው ትውልድ ወጣቱን ከቀዳሚው ትውልድ የሚያገናኙ ጠንካራ ትውልድ አገናኝ የትውልድ ድልድዮችን የሚገነቡ ናቸው፡፡ ደኃውን ከሀብታም የሚያገናኙ ድልድዮችን የሚገነቡ ናቸው፡፡ ህዝቦችን ከአምባገነናዊ ስርዓት ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሚያሸጋግሩ ድልድዮችን የሚገነቡ ናቸው፡፡ በጎሳ የተለያዩ ህዝቦችን የሚያገናኙ ድልድዮችን የሚገነቡ ናቸው፡፡ “ክልላዊ ደሴቶች (የጎሳ መንደሮች ወይም ባንቱስታንስ)” ተብለው ተነጣጥለው የሚኖሩ ህዝቦችን የሚያገናኙ ድልድዮችን የሚገነቡ ናቸው፡፡ በቋንቋ፣ በኃይማኖት እና በክልል ተነጣጥለው የተቀመጡ ህዝቦችን የሚያገናኙ ድልድዮችን የሚገነቡ ናቸው:: ባለመተማመን ሸለቆዎች፣ በእምነት ማጣት ጥልቅ  ገደሎችና   እና  በጥርጣሬ ጎርፍ ወንዞች ላይ ድልድዮችን የሚገነቡ ናቸው፡፡ ብሄራዊ ዕርቅ ለማውረድ እና የብሄራዊ አንድነትን ለማምጣት ህዝቦችን የሚያገናኙ ድልድዮችን የሚነገነቡ ናቸው፡፡ በአገር ቤት ውስጥ ያሉትን ወጣቶች በውጭ አገር ከሚኖሩት የዲያስፖራ ወጣቶች ጋር የሚያገናኙ ድልድዮችን የሚገነቡ ናቸው፡፡ የአቦ-ጉማሬው ትውልድ ለመሻገር አስቸጋሪ በሆኑ የውኃ አካላት ላይ ድልድዮችን የሚገነቡ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ የአቦ-ሸማኔው ትውልድ አባላት ኃይል አባዥዎችም ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ዘለቄታ ያለው መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት እንዲቻል የአቦሸማኔው ትውልድ አባላት ከእራሳቸው እውቀት፣ ዘዴ እና ልምድ አኳያ በመቀመር የወጣቱን ኃይል፣ ፍቅር እና ጽኑ ዓላማ በአግባቡ ያለምንም ብክነት በስራ ላይ እንዲውል ያደርጋሉ፡፡ በግትር የአምባገነኖች ተለዋዋጭ ባህሪያት ላይ የእራሳቸውን ፈጠራ በመጠቀም በወሳኝ ጉዳዮች ላይ የወጣቶች የለውጥ አራማጅነት የትግል መንፈስ ውጤታማ እና ስኬታማ እንዲሆን ያደርጋሉ፡፡

የአቦ -ጉማሬው ትውልድ አባል በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል!

የኢትዮጵያ የአቦሸማኔ ትውልድ በአስፈሪ ዕጣ ፈንታ ውስጥ፣

በእኔ አስተያየት የኢትዮጵያ 21ኛው ክፍለ ዘመን ግንባርቀደም ችግር ሆኖ የሚቀርበው የኢትዮጵያ ወጣቶች ችግር ነው፡፡ በአሜሪካ የህዝብ ቆጠራ ቢሮ ትንበያ መሰረት ከ37 ዓመታት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር አሁን ካለበት ደረጃ በሶስት እጥፍ በማደግ 278 ሚሊዮን በመሆን ኢትዮጵያን ከዓለም በህዝብ ብዛት ከአንድ እስከ አስር ደረጃ ከሚይዙ አገሮች ተርታ ውስጥ ምድብተኛ ያደርጋታል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕድገት ላለፉት አስርት ዓመታት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው የመጣው፡፡ እ.ኤ.አ በ1967 የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር 23.5 ሚሊዮን ነበር፡፡ በ1990 ወደ 51 ሚሊዮን ያደገ ሲሆን በ2003 ደግሞ ቁጥሩ እየጨመረ በመምጣት 68 ሚሊዮን ደረሰ፡፡ በ2008 ይህ ቁጥር እየጨመረ በመምጣት ወደ 80 ሚሊዮን ከፍ አለ፡፡ በ2013 የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት ከ94 ሚሊዮን በላይ እንደሚደርስ ተገምቷል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ወደ 70 በመቶ (66 ሚሊዮን) የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ከ35 ዓመት በታች እንደሆነ ይገመታል፡፡ እ.ኤ.አ ከ1995 ጀምሮ የኢትዮጵያ ህዝብ ዓመታዊ አማካይ የዕድገት መጣኔ ከ3 በመቶ በላይ እንደሆነ ቀጥሏል፡፡

ኔልሰን ማንዴላ እንዲህ በማለት አመላክተዋል፣ “ልጆቻችን ታላቅ ኃብቶቻችን ናቸው፡፡ ልጆቻችን የወደፊት ተስፋዎቻችን ናቸው፡፡ የልጆቻችንን መብት የሚጥስ ማንም ቢሆን የህዝባችንን የትስስር ክር የሚበጥስ እና አገራችንን የሚያዳክም ነው፡፡“ ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ወጣቶች የአገሪቱ ታላቅ ኃብቶች ናቸው ብለን ካሰብን እና በአሁኑ ጊዜ በታላቅ አደጋ ውስጥ ይገኛሉ ከተባለ የሀገሪቱ የወደፊት ዕጣ ፈንታም በአደጋ ላይ መሆኑን በግልጽ ያመላክታል፡፡ የኢትዮጵያ ታላቅ ኃብቶች ተረስተዋል፣ መብቶቻቸው ተደፍጥጠዋል፣ ወርቃማው ጊዚያቸው፣ ዕውቀታቸው፣ ጉልበታቸው እና ብሩህ አዕምሯቸው ለሀገር ጥቅም ሳይውል ቀርቷል፣ እንዲሁም ባክኗል፡፡ “ኢትዮጵያ ዝቅተኛ የሆነ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት የቅበላ መጣኔ (Enrollment Rate) ከሚያስመዘግቡ በዓለም ላይ ከሚገኙ አገሮች አንዷ ናት፡፡…የአፍሪካ የህዝብ እና የጤና ምርምር ማዕከል ባቀረበው ዘገባ መሰረት በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት እያሽቆለቆለ እና የክፍል ደጋሚ ተማሪዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣት፣ እንዲሁም በጾታ፣ በገጠር እና በከተማ መካከል የሚታየው ሰፊ ልዩነት የአገሪቱ ከባድ ፈተናዎች ሆነው ቀጥለዋል፡፡“ የከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመግባት፣ ወይም ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ስራ የማግኘት ዕድላቸው የመነመነ ሆኗል፡፡

እ.ኤ.አ በ2012 ዩኤስኤይድ/USAID በኢትዮጵያ ላይ ባደረገው ጥናት መሰረት “ኢትዮጵያ 50 በመቶ የከተማ ወጣቶች ስራ አጥ መጣኔ/Unemployment Rate በማስመዝገብ ከፍተኛ ደረጃ የያዘች መሆኗን እና 85 በመቶ ገደማ የሚሆነው ህዝብ በሚኖርበት የገጠር አካባቢ ያለው ወጣት ከፍተኛ በሆነ ስውር ስራ አጥነት/underemployment/disguised unemployment ውስጥ ተተብትቦ ይገኛል፡፡“ በማለት የጥናት ውጤቱን ይፋ አድርጓል፡፡ በ2012 በዓለም አቀፍ የዕድገት ማዕከል/International Growth Center በተባለ ድርጅት በተደረገ የወጣት ስራ አጥነት ሌላ የጥናት ዘገባ መሰረት “የአሁኑ የኢትዮጵያ የ5 ዓመት የልማት ዕቅድ ማለትም እ.ኤ.አ ከ2010/11–2014/15 ድረስ በሚዘልቀው ገዥው አካል የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ/Growth and Transformation Plan እያለ በሚጠራው ዕቅድ ውስጥ የወጣቶች የስራአጥነት ጉዳይ አልተካተተም…“ ያ ጥናት “እ.ኤ.አ በ2011 38 በመቶ የሚሆነው ወጣት መደበኛ ባልሆነው የስራ ዘርፍ ተቀጥሮ የሚገኝ“ ሲሆን “ዝቅተኛ ተከፋይነት ያላቸው እና የምርት ጥራታቸውም ዝቅተኛ የሆኑ“ እንደነበሩ የጥናቱ ግኝት አመላክቷል፡፡ በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች ስራ አጥ ሆነው ይገኛሉ፡፡ ሆኖም ግን ስራአጥ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን   ወደፊትም ተቀጣሪ የመሆን ዕድል የላቸውም፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ወጣቶች ከትምህርት አደረጃጀቱ እና አሰጣጡ አንጻር የጥራት ጉድለት የሚንጸባረቅበት በመሆኑ መሰረታዊ የሙያ ክህሎት ያልጨበጡ በመሆናቸው ነው፡፡ ወጣቶቹ በስራ ላይ ለመቀጠር የሚችሉት በሰለጠኑባቸው እና ክህሎት በጨበጡባቸው የሙያ ዘርፎች በመንግስት ስር ያሉ ቀጣሪ መስሪያ ቤቶች ተቀጣሪዎችን በብቃታቸው እና በተወዳዳሪነታቸው መዝነው ሳይሆን አብዛኛውን ጊዜ ከገዥው አካል ጋር ካላቸው የፖለቲካ እና የማህበራዊ ግንኙነት ቅርርብ አንጻር የፓርቲ አባል በመሆን ብቻ ነው፡፡ ማንኛውም ወጣት ኢትዮጵያዊ በትክክል የእራሱን ጥረት አድርጎ የዩኒቨርስቲ ዲግሪ ከመያዝ ይልቅ የገዥውን ፓርቲ የአባልነት ካርድ መያዝ የበለጠ ዋጋ እንዳለው ይገነዘባል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ መሬት የሌላቸው የገጠር ወጣቶች ወደ ከተማ ስራ ፍለጋ በገፍ በሚመጡበት ወቅት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የመጣውን ከገጠር ወደ ከተማ ፍልሰት፣ ስራ አጥነት እና ተስፋ የማጣት ቀውስ የበለጠ እያወሳሰበው ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ወጣቶች አጠቃላይ የአገሪቱን የማህበራዊ ችግር ቀውሶች ቀንበር የመሸከም ኃላፊነት ወድቆባቸዋል፡፡ እንደሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ጎል/GOAL ዘገባ ከሆነ በመንገዶች ላይ በመንከላወስ የሚኖሩ 150,000 ህጻናት ሲኖሩ ከእዚህ ውስጥ 60,000 የሚሆኑት የአገሪቱ ዋና ማዕከል በሆነችው በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ናቸው፡፡ ህጻናት ቤትአልባ የሚሆኑባቸው እና ወደ መንገድ የሚወጡባቸው የመጀመሪያዎቹ ዓመታት በአማካይ 10 እና 11 ዓመት ዕድሜ ሲያስቆጥሩ ነው፡፡ ወጣቶች በኤችአይቪ ኤድስ እና በሌሎች በግብረስጋ ግንኙነት በሚተላለፉ በሽታዎች የመጠቃት ዕድላቸው እየጨመረ በመምጣት ላይ ይገኛል፡፡ የተሻለ ዕድል ማግኘት ያልቻሉት በርካታዎቹ የኢትዮጵያ ወጣቶች በአደንዛዥ ዕጽ እና አልኮል እንዲሁም በዘሙት አዳሪነት እና በሌሎች የወንጀል ድርጊቶች ተዘፍቀው ይገኛሉ፡፡ ምንም ዓይነት የትምህርት ዕድል እና ስራ ያላገኙ የከተማ ወጣቶች ዕጣፈንታቸው ስራየለሽ፣ ቤትየለሽ፣ እረዳትየለሽ እና ተስፋየለሽ መሆን ብቻ ሆኗል፡፡

ከአስርት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል “የብሄራዊ ወጣቶች ፖሊሲ” ሰነድ አዘጋጀ እና “44 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ከፍጹም የድህነት ወለል በታች ነው“ በማለት መግለጫ ሰጠ፡፡ በዚህ ዓይነት የድህነት ሁኔታ ውስጥ ወጣቱ በከፍተኛ ሁኔታ ለጥቃቱ ተጋላጭ የሆነ የህብረተሰብ ክፍል ነው… ከስራ አጥ ወጣቱ አብዛኛውን የሚሸፍኑት ሴት ወጣቶች የመሆናቸው ሀቅ በአብዛኛው በሚባል መልኩ የችግሩ ሰለባ ወጣት ሴቶች መሆናቸውን ያመላክታል፡፡” በአጠቃላይ መልኩ ሲታይ “የብሄራዊ ወጣቶች ፖሊሲ” ተብሎ የሚጠራው የድርጊት መርሀግብር ለገዥው አካል እና ለፓርቲው ደጋፊነት መመልመያ ሰነድነት ከማገልገል በዘለለ የፈየደው ነገር የለም፡፡ የዚህን ፖሊሲ የማስፈጸም ብቃት ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማድረስ “መንግስት የመምራት፣ የማስተባበር፣ የማዋሀድ እና የመገንባት ኃላፊነት ተጥሎበታል” በማለት በግልጽ አስቀምጦታል፡፡ ሆኖም ግን የዓለም አቀፉ የዕድገት ማዕከል የጥናት ውጤት በግልጽ እንደሚያመለክተው ከ2010/11-2014/15 ድረስ ለአምስት ዓመታት በሚዘልቀው የአሁኑ የኢትዮጵያ የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ ቀጥታ የወጣቱን የስራ አጥነት የሚመለከት ጉዳይ አልተካተተም፡፡ “ብሄራዊ የወጣቶች ፖሊሲ ሰነድ” በተግባር ላይ ያልዋሉ የብሄራዊ ወጣት ፖሊሲዎች ዓለም ዓቀፋዊ የመረጃ ቋት በመሆን ላለፉት አስርት ዓመታት በመደርደሪያ ላይ ተቀምጦ አቧራ በመጠጣት ላይ ይገኛል፡፡

የሁለት ትውልዶች ትረካ፣ በኢትዮጵያ የጉማሬው እና የአቦሸማኔው ትውልዶች ተቀራርቦ የመነጋገር አስፈላጊነት፣

አሁን በኢትዮጵያ የሰዓት አቆጣጠር መሰረት ስንት ሰዓት ነው? በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የአቦ-ገማሬው ትውልድ ሰዓት ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ የአቦሸማኔው እና የጉማሬው ትውልዶች ተቀራርበው ለመነጋገር እና ብሄራዊ ዕርቅ ለማውረድ ጥረት የሚያደርጉበት የመጨረሻው ሰዓት ነው፡፡ ጊዜው የኢትዮጵያ እረፍትየለሾቹ የአቦሸማኔው ትውልዶች እና ተራማጁ፣ ብሩህ አዕምሮ ያላቸው እና አርቆ አሳቢነት የተላበሱት የጉማሬው ትውልዶች በአንድ መድረክ በአንድነት ተቀራርበው የሚያስቡበት እና በአንድነት ወሳኝ እርምጃ የሚወስዱበት ጊዜ ነው፡፡ አሁን ጊዜው 2014 ነው፡፡

ተቀራርቦ መነጋገር ስል በአቦሸማኔው እና በጉማሬው ትውልድ መካከል በግልጽ እና ግልጽ ባልሆኑ መድረኮች ሁሉ… ማለትም ከእራት ግብዣ አዳራሾች እስከ አካዳሚክ የጥናት ማዕከሎች፣ ከቤተክርስቲያኖች እና መስጊዶች እስከ ሲቪክ ድርጅቶች እና ማህበራት ድረስ የሚያካትት የንግግር እና የውይይት መድረኮችን ማለቴ ነው፡፡ የመነጋገሪያ አጀንዳዎቹ ያልተወሰኑ ሊሆኑ ይችላሉ፣ ነገር ግን ዓላማዎች አንድ ዓይነት ናቸው፡፡ በአሮጌዎቹ ሀሳቦች ላይ ጥያቄዎችን ለማንሳት እና ጥሩዎችን ለማካተት አስፈላጊ ያልሆኑትን ደግሞ ለማስወገድ የንግግር መድረኮች ሊኖሩን ይገባል፡፡ አሮጌዎችን፣ ጠባብ አስተሳሰቦችን እና ለሰላም እና እድገት እንቅፋት የሚሆኑ አሉታዊ እንቅስቃሴዎችን ለመለወጥ የንግግር መድረኮች አስፈላጊዎች ናቸው፡፡ ስለፖለቲካ፣ መንግስት እና ህዝብ አዳዲስ ሀሳቦችን ለማመንጨት የንግግር መድረኮች አስፈፈላጊዎቻችን ናቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ቀፍድደው ከያዙን የማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮች በድል አድራጊነት ለመውጣት የንግግር መድረኮችን በማመቻቸት ገንቢ እና አዳዲስ የመፍተሄ ሀሳቦችን በማመንጨት የውይይት መድረኮችን ማዘጋጀት ይኖርብናል፡፡ ላለመስማማትም ቢሆን በሰለጠነ እና በመከባበር ላይ በተመሰረተ አቀራረብ የንግግር መድረኮችን በማዘጋጀት ስምምነት ማድረግ ይቻላል፡፡ ስህተቶችን በማረም ወደ ትክክለኛው መንገድ ለመምጣት እንዲቻል ተቀራርቦ መወያየት አስፈላጊ እንደሆነ እርስ በእራሳችን መተማመን አለብን፡፡ ይህንን ከባድ ኃላፊነት ለመሸከም እና ለማስተባበር የሚችለው “አዲሱ ትውልድ” ያስፈልገናል፡፡ ሀሳበ ሰፊዎቹ የአቦሸማኔው እና ተራማጅ የጉማሬው ትውልዶች የውይይቱን ሂደት ሊያፍጥኑልን ይችላሉ፡፡

የውይይቱ ዓላማ ያልሆነው የቱ ነው? እንዲካሄድ የሚፈለገው ውይይት አንዱ ሌላውን ጥላሸት ለመቀባት፣ ለመካሰስ እና አንዱ በሌላው ላይ ጣቶቹን ለመቀሰር አይደለም፡፡ እንደዚሁም ደግሞ ቀደም ሲል በተከናወኑ እና ባልተከናወኑ ድርጊቶች ላይ የሆድ ቁርጠት፣ የልብ ስብራት፣ ወይም ጥርስ መንከስ ድርጊቶችን ለማበረታታት አይደለም፡፡ የአቦ-ጉማሬው ትውልድ ኃላፊነት የያዘባቸው የንግግር መድረኮች ሁለት ዓላማዎችን ያካተቱ ናቸው፡፡ እነሱም 1ኛ) ዓለም አቀፋዊ ዕርቅ በማውረድ የንግግር ስራውን መጀመር እና 2ኛ) በአቦሸማኔው እና በጉማሬው ትውልዶች መካከል ባለው የስራ ክፍፍል እና ሚና መግባባት ላይ መድረስ ናቸው፡፡

“የቋንቋ” መግባባት ችግር ባለበት ሁኔታ ዓለም አቀፋዊ መግባባት ሊኖር አይችልም፡፡ በጸጥታ በሚናገሩት የኢትዮጵያ የጉማሬው ትውልድ አባላት እና በዚያ በማይሰማው ንግግር ከኢትዮጵያ የአቦሸማኔው ትውልድ ጋር የመግባባት ችግር አለ የሚል ጽኑ እምነት አለኝ፡፡ ጥቂት ምሳሌዎችን እስቲ እንመልከት፡፡ ብዙዎቻችን የጉማሬው ትውልድ አባላት ስለለውጥ ስናነሳ የሚታየን ነገር በአሁኑ ወቅት በስልጣን ላይ የሚገኘውን ገዥ አካል ከስልጣን መንበር ላይ በማስወገድ እራሳችንን ከስልጣን ወንበር ላይ ፊጥ ማድረግ ነው፡፡ በስልጣን ላይ ያሉት ሰዎች መጥፎዎች ናቸው፣ እኛ ግን ጥሩዎች ነን፡፡ አይደለም እኛ የተሻልን ነን፣ በእርግጥም እኛ እጅግ የተሻልን ነን፡፡ በአሁኑ ጊዜ በስልጣን ላይ ያሉት የጉማሬው ትውልድ አባላት እራሳቸውን ብቸኛ የለውጥ ሀዋርያ አድርገው ያስባሉ፡፡ እኛ የጉማሬው (የቀድሞው) ትውልድ አባላት ስለአመራር ጉዳይ ስናነሳ የአዲሱ ትውልድ አባላት የእኛን ትዕዛዞች ብቻ እንዲከተሉ እንፈልጋለን፣ ምክንያቱም እኛ ኃይል፣ ልምድ፣ ዘዴዎች እና/ወይም እውቀት ያለን አድርገን እንቆጥራለን፡፡ የኢትዮጵያ የአቦሸማኔው ትውልድ የበግ መንጋ ሆነው እኛን የሚከተሉ ብቻ እንጅ እነርሱ መልካም ነገሮችን በውል የሚያጤኑ እና ወሳኝ ድርጊቶችን ሊፈጽሙ የሚችሉ ልዩ ችሎታ እና የአመራር ብቃት ያላቸው ወጣቾች እንዳሉ ለመቀበል በጣም እንቸገራለን፡፡ ወጣቶቹ ከእኛ በተለየ መልኩ የእራሳቸው ልዩ የሆነ እና የእራሳቸው ነጻነት እንዲኖራቸው እንፈልግም፡፡ በአጠቃላይ ወጣቱን አሳንሶ የማየት ባህል ተጠናውቶናል፡፡ ወጣቱ ኃይል ዝቅ ያለ ዳኝነት የመስጠት ወይም ነገሮችን በጥልቀት የመረዳት ችሎታ ስለሚያንሰው የእኛን የበግ ጠባቂነት ሚና ማግኘት እና እኛ የምንነግራቸውን ብቻ መከተል አለባቸው እያልን አስተያየት እንሰጣለን፡፡ “ልጆችመታየት አንጂ መደመጥ የለባቸውም”፣የሚሉ ጊዜ ባለፈባቸው የአረጁ እና የአፈጁ አባባሎች ወጣቶቹን ዝቅ አድርገን እንመለከታለን፣ እንዲህ እያልንም እንተርትባቸዋለን፣ “ልጅ ያቦካው ለእራት አይበቃም“፡፡ የወጣቶቹን ሀሳቦች አናከብርም፣ ወይም ደግሞ ለየት ያለ ነገር ሲያቀርቡ እና የተሻሉ ነገሮችን ሲሰሩ እየተመለከትን አድናቆት አንቸራቸውም፣ ነገር ግን እነሱን ለመተቸት እና ለማውገዝ የሚቀድመን የለም፡፡

እኛ የጉማሬው ትውልድ አባላት ስለስልጣን ስንነጋገር ምንም ዓይነት ተጠያቂነት እና  ግልጽነት በሌለው መልኩ ስልጣንን እንድንይዝ እንገልጋለን፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ያለው የጉማሬ ትውልድ ስልጣኑን የሚጠቀምበት ለመከፋፈል እና ለመግዛት ነው፣ ስልጣናቸውን በስልጣን ላይ ለመቆየት ከህግ አግባብ ውጭ ይጠቀሙበታል፣ ስልጣናቸውን ከህግ አግባብ ውጭ በመጠቀም ላይ ይገኛሉ ምክንያቱም ማድረግ ይችላሉና፡፡ ከስልጣን ውጭ ያሉ የጉማሬው ትውልድ አባላት ስልጣን ማግኘትን ይፈልጋሉ ምክንያቱም የላቸውምና፣ ምክንያቱም ስልጣን በእራሱ ሁሉንም ነገር ነውና፡፡ የጉማሬው ትውልድ አባላት ስልጣን ያጡትን ወይም ስልጣን የሌላቸውን  ስልጣን እንዲያገኙ አያደርጉም፡፡ በኢትዮጵያ ያሉት ወጣቶች ምንም ዓይነት ስልጣን የሌላቸው እና ስልጣን አልባ የህብረተሰብ ክፍሎች ናቸው፡፡ ይህም ማለት 70 በመቶ (66 ሚሊዮን) ያህሉን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚይዘው የህብረተሰብ ክፍል ስልጣን የለውም፡፡

የኢትዮጵያ የአቦሸማሜው ትውልድ በአቦ-ጉማሬው ትውልድ ላይ እምነት አጥቷል የሚል ጽኑ እምነት አለኝ፡፡ ያ እምነት ወደ መተማመን ሊመለስ የሚችለው በጋራ በመከባበር እና በመግባባት እንዲሁም በመተማመን እና በመቀራረብ ብቻ ነው፡፡ ወጣቶቹ ከእኛ ጋር እኩል እንደሆኑ እና እነሱን በአግባቡ በማስተናገድ መተማመን እና እርቀሰላምን ማውረድ ይቻላል፡፡ የኢትዮጵያ ወጣቶች ለሀገራቸው ያሏቸው ሀሳቦች እና  ራዕዮች ጠቀሜታቸው ከእኛ ሀሳቦች እና ራዕዮች ያላነሱ መሆናቸውን ሙሉ በሙሉ መቀበል አለብን፡፡ ከወጣቶቹ ጋር በእኩልነት በመከባበር እና ተቀራርቦ በመወያየት የጋራ ችግሮቻችንን መፍታት አለብን፡፡

የጉማሬዎቹ አስተምህሮ ለአቦሸማኔው ትውልድ፣

የአቦሸማኔው ትውልድ አባላት ከእኛ ከጉማሬው ትውልድ አባላት ጋር ተቀራርበው መነጋገር ለእነሱ በጣም አስፈላጊና ጠቃሚ ነው ፡፡ ምሳሌ በማቅረብ የጉማሬው ትውልድ ትምህርት ማስተማር ይችላሉ፡፡ ከታላላቆቻቸው ስህተቶች ሊማሩ የማይችሉ ወጣቶች ተመሳሳዮቹን ስህተቶች ይደግማሉ፡፡ እኛ የጉማሬው ትውልድ አባላት ብዙ ስህተቶችን ሰርተናል፡፡ ሁለተኛው ትምህርት የአቦሸማኔው ትውልድ አባላት የጉማሬውን ትውልድ አባላት ድክመቶች ማሸነፍ እና የእራሳቸውን አዲስ ጅምሮች መተግበር ነው፡፡ የጉማሬው ትውልድ ለአቦሸማኔው ትውልድ ሊያስተምሯቸው የሚችሏቸው ነገሮች የድፍረት ወኔን፣ መተማመንን፣ ለበጎ ነገር መስዕዋትነት መክፈልን፣ ታማኝነትን፣ መንፈሰ ጠንካራነትን፣ ችግሮችን በጽናት የመቋቋም ችሎታ የማዳበርን፣ ለውሳኔ ተገዥነትን፣ እና ችግሮችን በድል አድራጊነት እንዴት መውጣት እንደሚቻል ማስተማር ከብዙዎች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ “ክብር እና ሞገስ አጥተን” በታላቅ ችግር ላይ ነን፡፡ እነዚህን ክብር እና ሞገሶች ለመመለስ ግን በጋራ ሆነን መሞከር እና ለመተግበር መሞከር ነው፡፡ የአቦሸማኔ ትውልዶችን ከግትርነት፣ ከቁጣ፣ ከጥርጣሬ፣ ከታጋሽየለሽነት፣ ከሙስና፣ ካለመቻቻል፣ ስልጡን ያልሆነ አካሄድን ካለመከተል፣ ከፍርሀት፣ መጥፎ ነገር ከማድረግ፣ ከበቀልተኝነት እና እራስን ከማድነቅ በማለት በእርግጠኘነት የአቦሸማኔውን ትውልድ ለማስተማር ይቻላል፡፡ የአቦሸማኔውን ትውልድ ግልጽ የሆኑ ውይይቶችን በማድረግ በግል እና በህዝብ ህይወት ላይ የተጠያቂነት እና ግልጽኘነት የማስተማር ዘዴን በማሳየት የአቦሸማኔውን ትውልድ ማገዝ እንችላለን፡፡

የአቦሸማኔው አስተምህሮ ለጉማሬው ትውልድ፣

የአቦሸማኔው ትውልድ የፖለቲካ እና የማህበራዊ ችግሮችን በሰላማዊ እና ኃይልን ባልተጠቀመ መልኩ ሰላማዊ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ለጉማሬው ትውልድ ማስተማር ይችላሉ፡፡ ወጣቶቹ የሚማሩት እና የሚሰለጥኑት የጦር ተዋጊዎች እንዲሆኑ ብቻ ለማድረግ ብቻ አይደለም ነገር ግን የሰላም ጠበቃዎች እንዲሆኑ ጭምር እንጅ፡፡ ወጣቶቹ ጤናማ የህብረተሰብ ግንኙነቶችን የመፍጠር እና የጎሳ፣ የኃይማኖት ጽንፈኝነትን እና የዘር ጥላቻን የማስወገድ ችሎታ አላቸው፡፡ ወጣቶቹ የህብረተሰብ ትብብሮችን፣ ፍቅርን፣ መግባባትን፣ ሰላምን፣ አንድነትን እና ተስፋን የሚፈጥሩ አስፈላጊ ጉዳዮች ሁሉ ለጉማሬው ትውልድ ማስተማር ይችላሉ፡፡ ሁላችንም በሰላም፣ በእኩልነት እና ፍትህ በነገሰበት መልኩ የምንኖርባት “አዲሲቷን ኢትዮጵያ” ለመገንባት የሚያስችል ችሎታ እንዳላቸው ለጉማሬው ትውልድ ማስተማር ይችላሉ፡፡ የአቦሸማኔው ትውልድ አባላት ከተፈቀደላቸው እና በማህበራዊ እና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ እውነተኛ ተባባሪ እና አጋር እንዲሆኑ ከተደረጉ ለውጥን የሚያመጡ የለውጥ ዘዋሪነት ሚና ሊጫወቱ የሚችሉ መሆናቸውን ለጉማሬው ትውልድ ማስተማር ይችላሉ፡፡ ወጣቶቹን በጥሞና የምናዳምጣቸው ከሆነ እራሳችንን ከእራሳችን እንድንጠብቅ ሊያደርጉን ይችላሉ፡፡ ይኸንን ጉዳይ እናስብ! ወጣቶቹ ከጎሳ እስር ቤቶች ግድግዳዎች ሰብረን እንድንወጣ፣ ከምናባዊ ፍርሀቶች እንድንላቀቅ እና የሌሎቸን ሀሳቦች ያለመቀበል እና መጥፎ ሀሳቦች ዓይናችንን እንዳያይ ሸፍነው “አዲሲቷን ኢትዮጵያ” ከአድማሱ ባሻገር እንዳናይ አድርገውን የነበሩትን እንድናስወግድ ሊረዱን ይችላሉ፡፡

ኢትዮጵያውያን እንደ አገር እና እንደ ህዝብ ህልውናቸው ተጠብቆ እንዲቆይ ከተፈለገ ያ ህልውና የሚወሰነው በፈጣሪነት፣ በአዕምሯዊ ሃይል እና ጥንካሬ፣ መንፈሰ ጽናት፣ መልካም አመለካከት እና  በወጣቶቹ መንፈሰ ጠንካራነት እና በሚከፍሉት መስዋዕትነት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ያ ሁኔታ በወጣቶች ላይ ከባድ ሸክምን ይጥላል፡፡ ወጣቶቹ ያንን ከባድ ሸክም፣ ከባድ ስራ እና ታላቅ መስዋዕትነት በመክፈል የአንበሳውን ድርሻ መያዝ አለባቸው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ኢትዮጵያውያን እንደ ሀገር እና እንደ ህዝብ ህልውናቸው ተጠብቆ እንዲቆይ ከተፈለገ ያ የመቆየት ህልውና የሚወሰነው የቀድሞው ትውልድ አባላት ለአዲሱ ትውልድ አባላት ቀልጣፋ እና ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ማድረግ ስንችል ነው፡፡ እኛ የጉማሬው ትውልድ አባላት የምንችለውን ነገር ሁሉ በማድረግ የአቦሸማኔዎቹ (ወጣት) ትውልድ እምነት እንዳያጡ እና ውድቀት እንዳይደርስባቸው ተጋድሎ ማደረግ ይጠበቅብናል፡፡ ወጣቶቹ ይህንን ሲያደርጉ ማበረታታት፣ ማገዝ እና ደጋግመው እንዲሰሩት ድጋፍ መስጠት ይኖርብናል፡፡ ትግሉ የፈለገውን ያህል ረዥም ጊዜ ቢወስድም ምንጊዜም ቢሆን ከወጣቶቹ ጎን መሰለፍ አለብን፡፡ ከወጣቶቹ ጋር መወያየት እና መነጋገር አለብን፡፡ ወጣቶቹን መደገፍ እና መውደድ ይኖርብናል፣ ወጣቶቹ በአዲሲቱ ኢትዮጵያ የፕሮጀክት የግንባታ መስክ ላይ ሆነው በጽናት እየሰሩ አስከቆዩ ድረስ ለእነሱ ውኃ ማቀበል እና ሌሎችንም ድጋፎች በደስታ በማድረግ መደገፍ ይኖርብናል፡፡

የኢትዮጵያ ወጣት ኃይል ምንም ማንም ሊያቆመው የማይችል ኃይል ነው፡፡ የኢትዮጵያን ተወርዋሪ የአቦሸማኔ ትውልድ ሊያቆመው የሚችል ምድራዊ ኃይል፣ እስካፍንጫው የታጠቀ አምባገነን ኃይል ሊያሸንፈው የሚችል ኃይል የለም፡፡ እኛ የቀድሞው ትውልድ አባላት ምንጊዜም ቢሆን የሚከተለውን የድሮ አባባል ልንከተል ይገባል፣ “ልታሸንፋቸው አለመቻልህን ካረጋገጥህ ተቀላቀላቸው፡፡“ የአቦሸማኔውን (የወጣቱን) ትውልድ በውይይት እንቀላቀል፡፡ ከእነርሱ ጋር ቀረብ በማለት እንወያይ፣ ምን ፍላጎት እንዳላቸውም እንጠይቃቸው፡፡ የእኛን ምክር የሚወዱ እና የሚፈልጉ ከሆነ ይህንን በለጋሽነት እና በነጸነት እንችራቸው፡፡ የእኛን ቴክኒካዊ እገዛ የሚፈልጉ ከሆነ ዕገዛውን እናድርግላቸው፡፡ የሞራል ድጋፋችንን የሚፈልጉ ከሆነ ለእነሱ እናደርግላቸው፡፡ የማቴሪያል ድጋፍ የሚፈልጉ ከሆነ ለእነርሱ የገንዘብ መዋጮ በማሰባሰብ ድጋፍ እናድርግ፡፡ ወጣቶቹ ታላቅ ሸክሞችን ከጫንቃቸው ላይ ለማውረድ፣ ድልድይ በሚገነቡበት ጊዜ፣ የመንገድ ጥገና በሚያካሄዱበት ጊዜ እና ተራሮችን በሚወጡበት ጊዜ በትህትና የተሞላን ውኃ አቀባያቸው ሆነን መቅረብ አለብን፡፡ ለወጣቶቻችን የኃይል ምንጮች መሆን አለብን!

(ክፍል ሁለት ይቀጥላል፡፡)

ታህሳስ 29 ቀን 2006 .

ኢትዮጵያ ከግብፅና ከሱዳን ጋር ያደረገችው ድርድር ያለ ውጤት ተጠናቀቀ

January 8/2014
‹‹ግብፅ ስምምነት የተደረሰበትን ጉዳይ ለመቀልበስ እየጣረች ነው›› መንግሥት
የታላቁን የህዳሴ ግድብ በተመለከተ ሦስተኛ ዙር ድርድራቸውን ለመቀጠል የተገናኙት የኢትዮጵያ፣ የግብፅና ሱዳን የውኃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ሳይግባቡ ቀሩ፡፡ ሦስተኛው ዙር ድርድር ያለውጤት ቢበተንም ውይይቱን በሌላ ጊዜ ለመቀጠል ተስማምተዋል፡፡
የሦስቱ አገሮች ሚኒስትሮች ከዚህ ቀደም ሁለት ዙር ድርድሮችን በማካሄድ በኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ላይ ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ያቀረበውን ምክረ ሐሳብ ተግባራዊ መሆኑን የሚከታተል ኮሚቴ ለማቋቋም መስማማታቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ 
የውኃ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ ቀሩ በተባሉ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ሦስተኛ ዙር ድርድር ለማካሄድ በያዙት ቀጠሮ መሠረት ባለፈው ቅዳሜ ካርቱም የተገናኙ ቢሆንም፣ በግብፅ በኩል የቀረበው ሐሳብ ቀደም ባሉት ድርድሮች እልባት ያገኙ ጉዳዮችን የሚቀለብስ በመሆኑ፣ በኢትዮጵያ በኩል ተቀባይነት አለማገኘቱን በኢትዮጵያ የውኃ፣ የመስኖና የኢነርጂ ሚኒስቴር የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈቅ አህመድ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ 
የሦስት አገሮች ሚኒስትሮች ከዚህ ቀደም በነበሩ ሁለት ድርድሮች ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ያቀረበውን ምክረ ሐሳብ ተግባራዊ ለማድረግና ተግባራዊነቱን የሚከታተል ኮሚቴ ለማቋቋም ስምምነት የደረሱበት ጉዳይ መሆኑን ያስታወሱት አቶ ፈቅ፣ በሦስተኛው ዙር ድርድር ይህንን ኮሚቴ የሚቆጣጠር ሌላ ዓለም አቀፍ አማካሪ ይቋቋም የሚል ሐሳብ ግብፅ ይዛ በመቅረቧ ላለመግባባቱ ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ 
ቀደም ሲል እንዲቋቋም የተስማሙበት ኮሚቴ ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ያቀረበውን ምክረ ሐሳብ ለመተግበርና ተግባራዊነቱን መከታተል መሠረታዊ ኃላፊነቱ ሲሆን፣ ሦስቱን አገሮች የሚወክሉ ዜጎች ብቻ የኮሚቴው አባላት እንደሚሆኑ መዘገቡ ይታወሳል፡፡
የኮሚቴው አባላት ስብጥርን በተመለከተ በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል ከፍተኛ ልዩነት ተንፀባርቆ ነበር፡፡ በመጨረሻ ግን የኮሚቴው አባላት በሦስቱ አገሮች የሚወከሉ ዜጎች ብቻ ይሁኑ በሚለው የኢትዮጵያ አቋም ላይ ስምምነት ተደርሷል፡፡ ይህ ኮሚቴ ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ያቀረበውን ምክረ ሐሳብ ተግባራዊ ለማድረግ የውጭ አማካሪ ቅጥር የመፈጸምና አማካሪው የሚያቀርበውን ሐሳብ ገምግሞ የውሳኔ ሐሳብ የማቅረብ ኃላፊነት እንደሚኖረው፣ ለዚህና ለሌሎች ኃላፊነቶቹ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሦስቱ አገሮች ይሸፍኑ በማለት ተደራዳሪዎቹ ተስማምተው እንደነበር ይታወሳል፡፡ 
በሦስተኛው ዙር ድርድር ሌሎች ወሳኝ ጉዳዮች ይነሳሉ ተብሎ ተጠብቆ የነበረ ቢሆንም፣ የግብፅ ተደራዳሪዎች ተጨማሪ ዓለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት እንዲቀጠር መጠየቃቸውን አቶ ፈቅ ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡ 
ግብፆች እንዲቀጠር የጠየቁት ዓለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት ከዚህ ቀደም ስምምነት የተደረሰበት ኮሚቴ ኃላፊነቶችን በበላይነት የመከታተል ድብቅ አጀንዳ እንዳለው መረዳት የተቻለ መሆኑን አቶ ፈቅ ገልጸዋል፡፡ 
‹‹አማካሪ ለመቅጠር ቅጥሩን የሚያማክር አማካሪ ድርጅት መቅጠር ተቀባይነት የሌለው አሠራር ነው፡፡ የዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ቡድን ያቀረበውን ምክረ ሐሳብ ተግባራዊነት ለመከታተል የሦስቱ አገሮች ባለሙያዎች በቂ ናቸው፤›› የሚል አቋም  በኢትዮጵያ በኩል መያዙን፣ በዚህ ላይ መግባባት ባለመቻሉም ድርድሩ መቋረጡን አስታውቀዋል፡፡ 
‹‹በግብፅ በኩል ድብቅ ዓላማ ካልተያዘ በቀር አማካሪ ለመቅጠር ሌላ አማካሪ መቅጠር ታይቶ አይታወቅም፤›› ያሉት አቶ ፈቅ፣ ጉዳዩ ግን ተደጋጋሚ ውይይትን የሚጠይቅ በመሆኑ ለቀጣይ ውይይት በመስማማት መበተኑን ገልጸዋል፡፡ ቀጣዩ ውይይት መቼ እንደሚካሄድ ቀን ባይቆረጥም በግብፅ በኩል ይገለጻል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ድርድሩ የሚካሄደው በኢትዮጵያ፣ በግብፅና በሱዳን መካከል ቢሆንም የሱዳን መንግሥት የህዳሴውን ግድብ ጠቀሜታ በመገንዘብ የኢትዮጵያ መንግሥት አቋምን ማራመድ መርጧል፡፡ ይህ በመሆኑም ድርድሩ በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ያለው በዋናነት በኢትዮጵያና ግብፅ መካከል መሆኑን የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አቶ አለማየሁ ተገኑ ባለፈው ሳምንት ለፓርላማ ካቀረቡት ሪፖርት መረዳት ተችሏል፡፡ 
 

አርቲስት ነዋይ ደበበ በተወዛገበ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ የሙያ ጓደኞቹ ገለጹ

January8/2014

ከሮቤል ሔኖክ

ከዓመታት በፊት በዋሽግተን ዲሲ ለሚታተመው ባውዛ ጋዜጣ “በ2001 ዓ.ም ወደ ሃገሬ እገባለሁ” በሚል ድምፃዊ ነዋይ ደበበ ሲናገር የቅርብ ወዳጅ አርቲስቶቹ “ሃገርህ መግባቱንስ ግባ፤ ግን ከሌሎቹ አርቲስቶች ተማር፤ አንተም ሃገርህ መግባትህን ግባ ግን ስለፖለቲካው ለየትኛውም የመንግስት ሚድያ አትናገር” የሚል ምክር ተሰጥቶት ነበር። ነዋይ ሲፈጥረው ግልጽ ሰው በመሆኑ የሚጠቅመውን እና የሚጎዳውን የሚያውቅ ሰው አይደለም እንደ ሙያ አጋሮቹ ገለጻ።

ይህ አርቲስት ለትዳሩ ፍቺ ያበቃውም ይኸው ግልጽነቱ ነው ይላሉ እነዚሁ ምንጮች። ለኮንሰርት ሌላ ሃገር ሄዶ ከአድናቂዎቹ ጋር ለሚስት የማይነገር ነገር ቢፈጽም እንኳ ለባለቤቱ ከመናገር አይደብቅም። “ሀመር መኪናዬን ይዤ ኢትዮጵያ ገባሁ” ብሎ ለሃገር ቤት ሚድያዎች ያወራውም ይኸው የሚነገር እና የማይነገር ነገርን ካለማወቁ የተነሳ ነው።


ነዋይን በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች ተዘዋውሮ የሙዚቃ ኮንሰርቶች እንዲሰራ ካደረጉት ሰዎች ውስጥ አንዳንዶቹ ለዚህ ዜና ዘጋቢ እንደተናገሩት “ድምጻዊውን ለራሱ የማያውቅ” ሲሉ ይገልጹታል ከሌላ አርቲስቶች ጋር በማነጻጸር። ይኸው ድምፃዊ ኮንሰርት ተጠርቶ ከፕሮሞተሮች ከሰርን የሚል ምክንያት ሲቀርብለት ገንዘብ እንደማይጠይቅም ይነገርለታል። ሌሎቹ ስለመዝፈናቸው እንጂ ፕሮሞተሩ ከሰረ አለከሰረ ግድ እንደሌላቸው ያገናዝቧል። በዚህ ሁኔታ ነዋይ በኪሳራ ውስጥ ወደቀ፤ ሚስቱንም በትዳሩ ላይ ስለሚፈጽመው ነገር ስለማይደብቅ ሕይወቱ ተመሳቀለ። በዚህ ሁኔታ ወደ ሃገሬ በ2001 እገባለሁ ሲል ሲናገር በሙያ አጋሮቹ ተመከረ። “እባክህ ሃገርህ መግባትህን ግባ ግን በመንግስት ሚድያዎች ቀርበህ ባከበረህ ሕዝብ ፊት እንዳትዋርድ”

ነዋይ ሃገር ቤት ገና ከመግባቱ አዲስ አበባን ሳያያት ኤርፖርት ላይ ተቀበሉት።

እነ ራድዮ ፋና “ሃገሪቷን እንዴት አየሃት?” ሲሉ ጠየቁት

ሃገሪቱን ተዘዋውሮ ያላየውና ገና ከአውሮፕላን እንደወረደ የተናገረው ነዋይ የኢትዮጵያ ሕዝብ በልማት ውስጥ እንደሚገኝ፤ ሃገሪቱም እንደተለወጠች ተናገረ። ልብ በሉ ገና ከኤርፖርት ወርዶ አላየም።

ነዋይ ድሮ ሃገሩን እንዳልወደደና በሕዝብ እንዳልተፈቀረ ይህን ከተናገረ በኋላ በጣም ተናቀ። ከአሜሪካ በሚስቱ አማካኝነት ይዞት የነበረው ገንዘብ አለቀና አላሙዲንን ፍለጋ ሮጠ። በሸራተን ጋዝ ላይት የሚያመሹ የአላሙዲ ተላላኪዎች ነዋይ “አላሙዲንን አገናኙኝ” እያለ ሲለምመጥ እነሱ ይስቁበት ‘አላሙዲ አሁን በዚ አለፈ፤ በዚያ ሄደ” እያሉ ይስቁበት፤ ያቁለጨልጩት ጀመር። በሕዝብ የተከበረ ዘፋኝ በአላሙዲ ተላላኪዎች መሳለቂያ ሆነ።

ነዋይ ኢትዮጵያ ገብቶ በተቸገረበት ወቅት ራድዮኖች እየደወሉ ፕራንክ ኮል እያደረጉ ይሳለቁበት ገባ። በወያኔ መንግስት ፈቃድ ተሰጥቷቸው እየሰሩ የሚገኙ ራድዮኖች ነዋይን ፕራንክ እያደርጉ ሲሳለቁበት እንዴት ያሳቅቅ። ድሮ ይቃወምባቸው የነበሩ ወያኔዎች በሳቅቅቅ፣ ነዋይ ግን ስቅቅ። ነዋይ ግን አልገባውም። እንደውም ተወዛግቦ ራድዮኖቹ ለሱ ያዘኑ እየመሰለው ያለ የሌለውን ይቀባጥራል። “ሙዚቃ የሚያቀናብርልኝ አጣሁ” እያለም በግልጽ ፕራንክ ላደረጉት ራድዮኖች መጠላቱን ተናገረ። ይኸው ምስክርነቱ የነሰይፉ መሳቂያ ሲሆን፦



ነዋይ ምስኪን ነው። ሰው ሲስቅበት አያውቅም። ወያኔዎች እየተጠጉ “ጥሩ ሥራ ሰራህ you did good” ሲሉት ጥሩ እየመሰለው አቶ መለስን ሲቃወም እንዳልነበር ነጠላ ዜማም ሰራላቸው። የአቶ መለስ ሞት ሰሞን በወያኔ ደጋፊዎች ዘንድ የተሰጠው ሙገሳ ልቡን ነፍቶት እንደነበር የሙያ አጋሮቹ ይናገራሉ። ሆኖም ግን ነዋይ ኢትዮጵያ ሄዶ ባለማወቅም ይሁን በማወቅ የሰራውን ስህተት ወደ ዋሽንግተን ዲሲ በመጣበት ጊዜ በደረሰበት ተቃውሞ ተደናግጦ “እኔ እኮ ለአቶ መለስ የዘፈንኩት ሰዎች አሳስተውኝ ነው” ሲል ተናገረ።

ነዋይ በነዋይ ይሳሳታል – ይህን አይተናል – ከአላሙዲ ፍራንክ ሲቀበል። ነዋይ በሴት ይታለላል – ለሚስቱ ተናገሮ ፈታዋለች። አላሙዲ ሊያስታርቁ ሲዊድን ድረስ ጠርተዋቸው የሆነውን ነገር ወደፊት እንጽፈዋለን። – ነዋይ በውዝግብ ላይ እንዳለ ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ሲሄድ ከተመከረው ምክር፤ እዛ ከሄደ በኋላ ባለማወቅ በሰራው ስህተት፤ መለስ ከሞቱ በኋላ በተሸወደው ሽወዳ (እሱ እንዳለው) አይተናል።
ግን አሁንስ?

ያኔ ሁለት ጣቱን ለቅንጅት በመቀሰሩ የተነሳ የመንግስት ጋዜጠኞች ባገኙት ቁጥር ካሁን ካሁን ታሰርኩ ብሎ የሚበረግገው ነዋይ ደበበ፤ ለመለስ ብትዘፍን ያዋጣኻል – “እሺ”፤ ለአባይ ቦንድ ግዢ ኮንሰርት ዱባይ ሂድ “እሺ”… “እሺ” ባይ አርቲስት ሆኖ ቀረ። ሚስቱ የክሊኒክ ማናጀር አድርጋ አሜሪካ አስቀምጣው እንዳልነበር በርሷ ላይ ሲቀማጠል ተራ ሆኖ አረፈው። አሁን ከሰሞኑ ደግሞ በገና በዓል ዝግጅት ላይ አገራችን በዴሞክራሲ መመንጠቋንና የዘንድሮውን ገና በደርግ ዘመን ከነበረው ልዩ የሚያደርገው የአሁኑ በዴሞክራሲያዊ ስርዓት መታጀቡ ስለመሆኑ ሲናገር እያየን ነው። አይ ነዋይ የአርቲስት ምሁርi እነ በቀለ ገርባ፣ እነ እስክንድር ነጋ፣ እነ አንዷለም አራጌ፣ ላሊሴ ኦልባና፣ ርዕዮት አለሙ የታሰሩት ዴሞክራሲ ስላለ ነው? ለነገሩ ነዋይ ካሳሳተው ነዋይ ምን ይጠበቃል?

እንደ ሙያ አጋሮቹ ገለጻ ከሆነ ነዋይን ወሰድ መለስ የሚያደርገው የአእምሮ መወዛገብ ከፍርሃት፣ ከፍቺና የሚጠብቅን ዝና ካለማግኘት ጋር የተይያዘው የአእምሮ ጭንቀት ነው።

ዋናውን “ሌባ” ማን ይከሰዋል?

January 8/2014

አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ የ“ሰው” ንግድ!
ethio human trafficking


ኢህአዴግ ልዩ ምክንያት ከሌለው በስተቀር የውጪ ጠላት አያፈራም የሚሉ በርካታ አስተያየት ሰጪዎች አሉ። ምክንያት ካለው ግን ቅንድቧን አንደተላጨችው ነገረኛ ሴት ለመጋጨት ይፈጥናል። ከፊትለፊቱ ገንዘብ ካየ ደግሞ ኢህአዴግ ገደል ሜዳው ነው የሚሉም አሉ። ገንዘብ በሌለበት ቦታ ኢህአዴግ አይታይም በማለት ከበረሃው ኑሮ ጀምሮ የሚከሱት ጥቂቶች አይደሉም። በቅርቡ በሳዑዲ አረቢያ ምድር በሁለት ምድብ ተከፍለው የሚሰቃዩትን ወገኖች አስመልክቶ የያዘው አቋምም ከዚሁ መርሁ የተቀዳ እንደሆነ የሚከራከሩ በርካታ ናቸው። “ምን ያድርግ የኖረው የአገሪቱ ችግሮች ሁሉ ተቆልለው እሱ ላይ ወደቁ” በማለት ኢህአዴግን ለኢትዮጵያ የተቀመጠ “የተቀባ” መፍትሔ አድርገው የሚያወድሱ አሉ።
ኳስ ሜዳ ያደገችው ኑሪያ መሐመድ አሁን የምትኖረው ኳታር ነው። ኑሮ እንዳሰበችው የተመቻቸ ባይሆንላትም ወደ አገርዋ ለመመለስ አትፈልግም። አታስበውም። “ኢትዮጵያ ምን አለ?” ከማለቷ በቀር ለምክንያቷ ብዙ ማብራሪያ መስጠት አትፈልግም። አገሯ እሷንና መሰል ወገኖቿን ለማኖር አልቻለችም። በኳታር ባይመቻትም የታናናሽ እህቶቿንና የምትወዳቸውን እናቷን ጉሮሮ መሸፈን የሚያስችላትን አቅም አግኝታለች። ይህ ለእርሷ ታላቅ በረከት ነውና ችግሯን በበረከቷ እያዋዛች ትኖራለች። በኳታር በረሃ!!
ኑሪያ ኳታር የሄደችው አሜሪካን ግቢ በሚገኝ አንድ የጉዞ ወኪል ቢሮ ውስጥ ሰዎችን ወደ አረብ አገራት የመላክ ህጋዊ ፈቃድ አለው በተባለ ሰው አማካይነት ነው። የላካትን ሰው በአካል አታውቀውም። ቢሮውንም የረገጠችው የመጓጓዣ ቲኬትና ሰነዶቿን ለመቀበል ብቻ ነው። በወቅቱ እዛው ቢሮ ወደ ሳዑዲ ለመሔድ በዝግጅት ላይ የነበረች እህት ተዋውቃለች። ልጅቷ ከደቡብ ክልል ሆሳዕና ከተማ የመጣች ነበረችና ቤቷ ወስዳ ጋብዛታለች። በዚያው በመሰረቱት ጓደኝነት ከያሉበት ሆነው ይጠያየቁ ነበር። እድሜ ለጊዜና ለስልጣኔ!!
ኑሪያ እንደምትለው ጓደኛዋ ወደ ጅዳ ለመሄድ እንደትችል ቤተሰቦቿ የሚያርሱባቸውን ሁለት በሬዎች ሸጠዋል። ገንዘብ በአራጣ ተበድረዋል። አሁን የተፈጠረው ትርምስ ከመከሰቱ ስድስት ወር በፊት በህጋዊ መንገድ ሳዑዲ አረቢያ ሄዳ የነበረችው ጓደኛዋ “ህገወጥ” ተብላ ተመልሳለች። ቅድሚያ እቅዷ ለቤተሰቦቿ ሁለት በሬዎች መግዛትና የተበደሩትን ገንዘብ መክፈል ሲሆን፣ በየደረጃው ሌሎች እቅዶችም ነበሯት።
ሁሉም እንደታሰበው ሳይሆን ቀረና የኑሪያ ጓደኛ እዳ ተሸክማ ቤተሰቦቿ ዘንድ ገባች። በሬዎች የሉም፣ እዳ አልተከፈለም። አርሶ ለመብላትም አልተቻለም። ኑሪያ ስለ ጓደኛዋ ብዙ ተናግራለች። በኳታር ከምትኖር ሌላ ጓደኛዋ ጋር በመሆን የአቅሟን ለመርዳት ሞክራለች። ወደ ፊትም ከእህቶቿ ለይታ እንደማታያት ገልጻለች። መንገዱ ካለም “ከኢትዮጵያ የማይሻል ነገር የለምና እወስዳታለሁ” ብላለች።
የሚገርመው የኑሪያ ጓደኛ በህጋዊ መንገድ የላካት ድርጅት ዘንድ ስትሄድ የተሰጣት መልስ ነው። በስም የጠራችውና እሷን የላካት ሰው የለም። ድርጅቱ የጉዞ ወኪል ሆኖ ይሰራል። ሰውየው ግን የለም። ሌሎችም ተመሳሳይ ጥያቄ ለተመሳሳይ ድርጅቶች ያቀርባሉ። ላኪዎቹ የውሃ ሽታ ሆነዋል። መልስ የለም … እንቆቅልሽ!!
ባለኮብራዎቹ ሰው ነጋዴዎች
ባለ ኮብራዎቹ የጉዞ ወኪል ድርጅት ባለንብረቶች ናቸው። ለጸሎት ወደ ጅዳ የሚሄዱትን መንገደኞች በኮታ እየተከፋፈሉ የጉዞ ቲኬትና ማረፊያ በማዘጋጀት ብር ሲያመርቱ ኖረዋል። ከአንድ ሰው እስከ አምስት ሺህ ብር ድረስ ንጹህ ትርፍ ያተርፋሉ። ስለ ስራው የሚያውቁ “ዝርፊያ” የሚሉትን ስራ ህጋዊ ለማድረግ በማህበር ተደራጅተው ሊቀ መንበር፣ ምክትል ሊቀመንበር፣ ጸሐፊና ገንዘብ ያዥ፣ እንዲሁም የኦዲት ኮሚቴ አቋቁመው ኢህአዴግ ህጋዊ እውቅና አጎናጽፏቸዋል።
infinitiወደ ሳዑዲ ለጸሎት የሚደረገው ጉዞ እጅግ ከፍተኛ ገንዘብ የሚገላበጥበት በመሆኑ በማህበር የተደራጁት ነጋዴዎች ሳዑዲ ድረስ በመሄድ ለጸሎት የሚሄዱ ምዕመናን የሚያድሩበትን፣ ስለ አጠቃላይ የጉዞ ኮታና ስለ ጉዞ መስፈርቶች ከመንግሥት አካላት ጋር ይነጋገራሉ፤ ያቅዳሉ። አንዳንዴም የመጅሊሱን ስራ ይሰሩለታል። የኢህአዴግንም የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ስራ ያከናውኑለታል። በዚህ ያልተገደበ የስልጣንና የስራ ደረጃቸው ባከማቹት ሃብት ተብለጭልጨዋል። የሚያሽከረክሩት ኮብራ ነው። አንዳንዶቹ ፊታቸው የሚፈርጥ ይመስላል። ኑሯቸው የተቀናጣ ሲሆን ከትምህርት ጋር ብዙም የሚዋደዱ አይመስሉም። የሃብታቸውን መጠን በልጆች ብዛት፣ በዘመናዊ መኪናና በሌሊት የዝግ ቤቶች በመመንዘር ከማሳየት የዘለለ የሚስብ ነገር የላቸውም። ሰውነታቸው ግዙፍና አብዝተው ጫት የሚጠቀሙ የሺሻ ወዳጆች ናቸው። ቢሯቸው ውስጥ ለእለት ጉርስ ሳይሆን “ሱስ” የሚሆኑ ቁሳቁሶች አሉ። በዚህ መካከል በድንገት በተደረገ የመጅሊስ ሹም ሽር መሰረታቸው ቆዳ ንግድ የሆነው ሃጂ ኤሊያስ ሬድዋን ወደ መጅሊስ ተመርጠው ገቡ።
ሃጂው ንግዱን ከውጪ ሆነው ጠንቅቀው ስለሚያውቁት የመጅሊሱን ወንበር እንደተቀመጡበት አፍታም ሳይቆዩ ዘመቻ “የጉዞ ወኪል” ጀመሩ። ጉዞ ወደ ጅዳ አድርገው ከሳዑዲ ባለስልጣናት ጋር መከሩ። አዲስ መስመር ዘርግተው መጡና ከማህበራዊ ጉዳይ ጋር ስትራቴጂ ነደፉ። ጎን ለጎን በዘመዶቻቸው ስም የጉዞ ወኪል ድርጅቶችን ከፈቱ።
ዳግም ወደ ሳዑዲ በመሔድ ራሳቸው በዘመድ አዝማድ ስም ከፍተዋቸዋል ለተባሉት ስምንት የሚደርሱ የጉዞ አመቻች ድርጅቶችና ቁጥራቸው በጣም ውስን ከሆኑ ሌሎች የቀድሞ ድርጅቶች በስተቀር የተቀሩት ተቀባይነት እንዳይኖራቸው በመጅሊሱ ሰም ከስምምነት ላይ ደረሱ። ሳዑዲ ድረስ በመሄድ ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ባካሄዱት የፊርማ ስምምነት የቀድሞዎቹን የንግዱ ፈጣሪዎች አራገፉዋቸው። ድርጊቱና ውሳኔው ድንጋጤ ፈጠረ።
በድንገት የገንዘብ ምንጫቸው የደረቀባቸው ባለኮብራዎቹ በግልና በድርጅት ተሯራጡ። ሃጂ ኤሊያስ ሙሉ የኢህአዴግ ድጋፍ ስለነበራቸው የሚነቀንቃቸው ጠፋ። አሸነፉ። ንግዱንም አስተዳደሩንም ተቆጣጠሩት። ያለ ከልካይ ብር ያመርቱ ጀመር። አምርተው የሚያቋድሱት የማይገፋ ሃይል ስላደራጁ እሳቸውን ለማሳጣት የሚደረጉ ሙከራዎች መዝናኛዎቻቸው ሆኑላቸው። በጉዳዩ ዙሪያ ሚዲያዎች ሲጠይቁዋቸው ያረገፉዋቸውን የቀድሞ ቱጃሮች አፈር ከመሬት እያስገቡ ከመናገር ውጪ አንዳችም ስጋት አልነበረባቸውም።
ባለኮብራዎቹ ገንዘብ በማፍሰስ ከዳር እስከዳር ቢሮጡም የሃጂ ኤሊያስን ሃይል መግፋት ተሳናቸው። ስልት በመቀያየር ሞከሩ አልሳክም ሲል ሁሉም ባይሆኑም አንዳንዶቹ ከባለ ጊዜዎቹ ጋር ሽርክና መስርተው ተገን በማግኘት ንግዳቸውን ለማስፋት ወሰኑ ። በዘመኑ ቋንቋ ድርጅታቸው ቀይጠው “ዲጂታል” ሆኑ። ሃጂ ኤሊያስ በተራቸው ተገዘገዙ። በመጨረሻም ኢህአዴግ በቃውና ከሃጂ ኤሊያስ ጋር የነበረውን ፍቅር ጨረሰ። ቀን ጠብቀው ሃጂ ኤሊያስን አሰናበቱዋቸው። በየአቅጣጫው ጠላት ያበዙት ሃጂ ኤሊያስ ከፍተኛ ሃብት ስላላቸው ከዛሬ ነገ ይከሰሳሉ ሲባል ሳይሆን ቀረ። እንደውም አክሲዮን ማህበር ከፍተው እየሰሩ ነው።
ዲጂታሎቹ የሰው ነጋዴዎች
በጉዞ አመቻችነት ስም ተደራጅተው ቀስ በቀስ ሰው መነገድ የጀመሩት “ዜጎች” ካዝናቸው ማፈስ የለመደውን ጥቅም ሲያጣ ሁሉም ባይሆኑም በከፊል መልካቸውን ቀይረው “ከባለ ጊዜዎች” ጋር በየፊናቸው ተጎዳኙ። ድርጅታቸውን ለጋራ ባለቤትነት መስዋዕትነት አቅርበው “ካድሬ ተኮር” አካሄድ ጀመሩ። ለከርሳቸው ሲሉ የካድሬ ሚና መጫወት ጀመሩ። አብረዋቸው በተቀናጇቸው የጊዜው “ፊት አውራሪዎች” አማካይነት “አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ” ስብዕና የተላበሱ “የሰው ነጋዴ ሆኑ” በሌላ ቋንቋ “ዲጂታል” ሆኑ።
ድህነት ካቃጠላቸው ወገኖች ላይ ገንዘብ ለመሰብሰብ እየተገለባበጡ ድፍን አረብ አገራት ሰራተኛ የማስቀጠር ህጋዊ ውክልና በአጋሮቻቸው አማካይነት ተረከቡ። ሃጂ ኤሊያስ የቆረጡትንና ወደ ራሳቸው ካዝና ያዞሩትን ንግድ መልሰው ገቡበት። ያልቻሉና በቀደመው “ያረጀ/አናሎግ” አካሄድ የዘለቁ የያዙትን ይዘው ተንጠባጠቡ። ቀደም ሲል ባከማቹት ሃብት ስራ ቀየሩ።AlAmoudi_Saudi
ስራው ከፍተኛ ገንዝብ የሚያስገኝና አንዳችም ኪሳራ ስላልነበረው የከፍተኛ ባለሃብቶችንም ቀልብ ስቦ ነበርና በዚህ ሁሉ ሂደት ውስጥ “የሰው ንግድን” ስራ በጅምላ ለመቆጣጠር የአብዮታዊ ዲሞክራሲን ስብዕና የተላበሱት በረጅሙ አቅደው ተንቀሳቀሱ። ከስራቸው ባሉት ጭፍራዎቻቸውና የአብዮታዊ ዲሞክራሲ አመራሮች ታግዘው ባደባባይ ከመንግሥት ጋር በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ወደ ሳዑዲ ለመላክ ተፈራረሙ። አዲሱ ጠ/ሚኒስትርም ሳዑዲ 50ሺህ ሰራተኛ ሃይል ትፈልጋለች ሲሉ ተናገሩ። አቶ መለስ የጀመሩትን ለማስቀጠል ክርስቶስን ወደ ኋላ አድርገው የሚምሉት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ስራው በህጋዊ መንገድ እንደሚሰራም ወተወቱ።
ቅምጦቹን ሚዲያዎች ጨምሮ ሁሉም በየደረጃው ዜናውን አራገቡት። “የኢትዮጵያን ድህነት ታሪክ አደርጋለሁ” በማለት የሚወተውቱን ሼኽ መሐመድ አላሙዲ በስተመጨረሻ የሰው ንግድ ውስጥ መግባታቸው ታወጀ። “ዘመነ ዲጂታል”!! እርሳቸው በህግ ከገቡት ውል ጋር ተያይዞ ወደ ሳዑዲ የሄዱት ዜጎች ብዛት መረጃው ባይገለጽም ታይቶ በማታወቅ መልኩ ዜጎቻችን “ከአገር ውጡ” ተብለው ሲገደሉ፣ አስከሬናቸው አደባባይ ሲጎተት፣ ሴቶቻችን ሲደፈሩ፣ ወገኖቻችን ማጎሪያ ገብተው ሲሰቃዩ፣ ከሰብአዊነት ውጪ ሲሰቃዩ፣ የሰይፍና የካራ ስለት ሲሳልባቸው፣ የጦር መሳሪያ ሲሳብባቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ተሰማ፣ ታየ፣ ተመሰከረ። ይህንን አስደንጋጭ ድርጊት ለመቃወም ወይም በህግ ለመጠየቅ አንድም በገሃድ ወጥቶ ሃላፊነት የወሰደ የንግዱ ተዋናይ አለመኖሩ ሃዘኑን ድርብ አደረገው። ቢያንስ እርሳቸው ይህንን ድርጊት በመቃወም ወይም ሃዘናቸውን በመግለጽ ግንባር ቀደም አለመሆናቸው በርካታ ጥርጣሬዎችን አነገሰ። ከሳዑዲ ጋር በተያያዘ ቀደም ሲል የሚነሱ ሃሜቶችን አስታወሰ። ዛሬስ ሳዑዲ ምን አዲስ ነገር አጋጠማትና ነው ወደ እንደዚህ ያለው አስከፊና አስነዋሪ ተግባር ለመሸጋገር የወደደችው?
ኢህአዴግ ስልጣን በያዘ ማግስት ጀምሮ
ኢህአዴግ ስልጣን በያዘ ማግስት ዜጎችን ለስራ ወደ ተለያዩ አረብ አገራት የሚልኩትን በማደን አከሰማቸው። በየመንደሩ በደላላ የሚሰሩትንና ቢሮ ከፍተው የሚንቀሳቀሱትን ህጋዊ ፈቃድ እንዲያወጡ በማወጅ ኢህአዴግ ንግዱን ወደ ራሱ ሰዎች በተለይም ለህወሃት ምርጦች አስተላለፈው። አዲሱን አሰራር ተከትሎ በቦሌ ቪላ ቤት ውስጥ በተከፈቱ ቢሮዎች ሰዎች አገራቸውን ጥለው ለመውጣት ለአይን የሚታክት ሰልፍ ያደርጉ ጀመር። ድሆች ተሰልፈው ተዘረፉ። ባደባባይ ህጋዊ ፈቃድ አላቸው የተባሉ ባለጊዜዎች ከድሃው ላይ በቀሙት ገንዘብ ኑሯቸውን አመቻቹ። ቀደም ሲል ቤህሩት፣ ኳታር፣ ዱባይ፣ ኩዌት፣ … ዘመድና ጓደኞች የነበራቸው በተባራሪ ጀምረውት የሰፋው የሰው ንግድ ኢህአዴግ ካስቆመውና በራሱ ሰዎች ከተካው በኋላ የተከለከሉት የቀድሞዎቹ ሰው ነጋዴዎች ለአዳዲሶቹ “ኩባንያዎች/ኤጀንሲዎች” ሰው አቅራቢ ደላላ ሆነው ማገልገል ጀመሩ። ደላላ መሆን ያልፈቀዱትም ለኢሚግሬሽን ባለስልጣኖች የደንቡን እየከፈሉ ስራቸውን ይሰሩ ቀጠሉ።
አገሪቱ ውስጥ በተፈጠረው የስራ እድል መመናመንና ወገን እየለየ የሚከናወነው የስራ እድል ተስፋ ያስቆረጣቸው እየበረከቱ በመሄዳቸው ኤጀንሲ ከፍቶ መስራት ታላቅ ቢዝነስ ሆነ። በዚህም የተነሳ ታዋቂ ሰዎችና የፖለቲካ ሹመኞች ከሰው ንግድ ጀርባ ሆነው መጫወት ጀመሩ። በእንዲህ መልኩ የመንግስት ከፍተኛ ሰዎች ያሉበት ዝርፊያ ተከናወነ። ሌቦቹም፣ ህግ አስከባሪዎቹም ራሳቸው ስለሆኑ ለህዝብ በደል ጆሮ የሚሰጥ ጠፍቶ የድሆች እምባ ተደፋና ቀረ።
በመርከብ ስራ እናስቀጥራለን በማለት የድሮው አውሮፕላን ማረፊያ የተሰራውን ድራማ ለአብነት እናንሳ። ቢሮው በአደባባይ ማስታወቂያ አስነግሮ ስራ ሲጀምር የድሃ ልጆች መርከብ ላይ ስራ እናገኛለን በማለት የሚያርሱበትን በሬ በመሸጥ፣ የእርሻ መሬታቸውን በማስያዝ ተበድረው፣ የቤተሰቦቻቸውን ንብረት ሸጠው፣ የሚፈለግባቸውን ከፈለው ተመዘገቡ። አስቀድሞ የህክምና ምርመራ ማድረግ ግዴታ ነው ተብሎ አንድ የግል ክሊኒክ ብቻ በመሄድ 500 ብር እየከፈሉ ከጉበትና ከሳንባ በሽታ ነጻ የሆኑበትን ማስረጃ እንዲያመጡ ተደረገ። አራት ጉርድ ፎቶግራፍ ያስፈልጋል በሚል አሁንም አንድ ቦታ ብቻ እየሄዱ 50 ብር እየከፈሉ ፎቶ እንዲነሱ ተደረገ። በጥቅሉ አንድ ሰው ገና ሳይመዘገብ 550 ብር ይከፍላል።
ማስታወቂያው የጨበጣ መሆኑ ሲታወቅ የድርጅቱ ባለንብረት ካገር ወጡ ተባለ። ጉዳዩ ሲጣራ 11 ሺህ የሚጠጋ ሰው በሰልፍ ከመመዝገቢያ ውጪ ለፎቶና ለሜዲካል ብቻ ከ6.5 ሚሊዮን ብር ገደማ ተሰብስቧል። የህክምና ክሊኒኩ ባለቤትና የፎቶ ቤቱ ባለቤት ስራ እናስቀጥራለን በሚለው የቁጭበሉ ድርጅት ውስጥ መስራች ናቸው።
ገንዘቡ ከተበላ በኋላ ድሆች የደም እንባ ሲያነቡ “ድርጅቱ ተዘግቷል። ሰውየው አገር ለቀው ወጥተዋል” ከመባሉ ውጪ የተወሰደ አንድም ርምጃ የለም። ገንዘቡን ከዘረፉት መካከል አሁንም ሹመት የሚፈራረቅላቸው አሉ። የሚገርመው ይህ ሁሉ ሲሆን ኢህአዴግ ደጅ፣ ኢህአዴግ አፍንጫ ስር፣ በራሱ አባላት፣ በራሱ ዳኞችና በራሱ የጸጥታና የፍትህ አስከባሪ ሃይሎች ፊት መሆኑ ነው። ከዚህ አንጻር ይመስላል በርካታ አስተያየት ሰጪዎችና የአረብ አገራት ሰለባ ከሆኑት መካከል ከኢህአዴግ “ተቆርቋሪነት አይጠበቅም” ሲሉ የሚደመጠው።
አስካሉካ ትሬዲንግ ደቡብ አፍሪካ ዓለም ዋንጫ ማየት ለሚፈልጉ እንደሚያመቻች ጠቅሶ በመንግሥትና በግል ሚዲያዎች ማስታወቂያ አስነገረ። አቶ ሳምሶን ማሞና ኢቲቪ ቅስቀሳውን ተያያዙትና የሰው ጎርፍ ከደቡብ ኢትዮጵያ ጎረፈ። በተለይም የሃድያ ዞን አስተዳደር ልዩ መድረክ አዘጋጅቶ ቅስቀሳው ተካሄደ። ዜጎች የመንግስት ሰዎችንና ሚዲያዎችን አምነው በሰው 32ሺህ 582 ከ65 ሳንቲም ከፍለው ተመዘገቡ። 1200 ሰዎች ይህንን ገንዘብ ገቢ አደረጉ። በዚህም 40 ሚሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ ተሰበሰበ።wegagan
አሳዛኙ ጉዳይ ገንዘቡ ገቢ የሚደረገው የህወሃት ንብረት በሆነው የወጋጋን ባንክ ሲሆን፣ ከስራው በስተጀርባ “አንቱ” የሚባሉት የህወሃት ሰዎች አንዳሉበት የአደባባይ ምስጢር መሆኑ ነው። ቀበና በተከፈተው የአስካሉካ ቢሮ ሰዎች ጉዳያቸውን ለመከታተል ሲመላለሱ ጊዜ ነጎደ። ዓለም ዋንጫ ሲቃረብ የደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ ተጠይቆ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ አስታወቀ። አስካሉካም ግቢውን በፖሊስ እያስጠበቀ ገንዘባቸውን የዘረፋቸውን ለመመልከት ተጸየፋቸው። ሁከት ፈጣሪ ናቸው አስብሎ በፖሊስ አደባባይ ላይ አስደበደባቸው። ቀበናና የቀበና ጎዳና ይፍረዱት እንጂ ብዙ ግፍ ተሰራ። በተፈጠረው ሁኔታ የተደናገጡና ወፍጮ ቤት ውስጥ ተጠግተው ያድሩ ከነበሩት ዜጎች መካከል የአስካሉካ ባለቤት አገር ጥለው መጥፋታቸው ማስታወቂያውን በሰራው የመንግስት መገናኛ ይፋ ሲሆን ራሳቸውን ያጠፉ አሉ። ኢህአዴግና የፍትህ አካላቱ ከተቀሙት ንጹሃን ይልቅ ያለ አንዳች ብጣሽ የፈቃድ ወረቀት ድሆችን ሲዘርፍ የነበረ ማጅራት መቺ በልጦባቸው ድሆችን ቀጠቀጡ። ጎዳና ለጎዳና አሳደዱ። ሁሉም ነገር ታሪክ ከሆነ በኋላ ፖሊስና መንግሥት የአዞ እንባ አነቡ። የከረከሱ መኪናዎችና 5ሚሊዮን የሚሆን ገንዘብ ማገዳቸውን አበሰሩ። አቶ ግርማይ ገ/ሚካኤልንም ከተሰወሩበት ጀርመን አገር ለፍርድ አዲስ አበባ እንዳስመጣ አስታወቀ። ድሆች ግን ተዘርፈው ቀሩ። ለሞቱትም ነፍስ ይማር። ቂሙ ግን ቀን የሚቆጥር ነው።
ከድህነት በላይ ክህደት ያደቀቃቸው ዜጎች
በዱባይ፣ በኳታር፣ በኩዌት በሳዑዲ እና በተለያዩ የስደት ምድር ድህነትን ለማሸነፍና የመንግስት ሸክም ላለመሆን በሚንከራተቱ ወገኖች ላይ በተደጋጋሚ ለጆሮ የሚዘገንኑ በደሎች ተፈጽመዋል። ከፎቅ የተወረወሩ አሉ። በፈላ ውሃ የተቀቀሉ አሉ። በስለት የተወጉና የታረዱ አሉ። ማን እንዳደረገው ባይታወቅም የተሰቀሉ ጥቂት አይደሉም። በመርዝ ህይወታቸው ያለፈ … ተዘርዝሮ አያልቅም። ከሁሉም በላይeth saudi dubai ኤምባሲዋ በር ላይ ከለላ አገኛለሁ ያለች ወገናችን እንደ ውሻ እየተጎተተች ህይወቷ ሲያልፍ የሚያሳየውን ትዕይንት ለሚያስታውሱ ኢህአዴግ ድህነት በሚያሰቃያቸው ወገኖች ላይ በግልጽ ክህደት የፈጸመ ስለ መሆኑ ነው።
በሌላ በኩል ኢህአዴግ በተለይም ህወሃቶች በተመደቡበት የቆንስላ ጽ/ቤቶች፣ እንዲሁም ድንበር በማሻገር ህገወጥ ከሚሏቸው ስደተኞች ገንዘብ የሚያግበሰብሱ መሆኑ፣ በሌላ በኩል በርካታ ስራውን የሚሰሩ ኤጀንሲዎች የህወሃት ሰዎች መሆናቸው፣ በመንግስት ደረጃም ሰዎችን ወደ አረብ አገር ለመላክ በኦፊሻል የተዋዋለው ኢህአዴግ መሆኑ በየትኛውም ደረጃ በዜጎች ላይ ለሚደርሰው በድል ተጠያቂ ከመሆን እንደማያመልጥ የሚስማሙ ይበረክታሉ።
በሳዑዲ አረቢያ መከራ እየተጋፈጡ ያሉ ዜጎች ህገወጥ ይሁኑም ህጋዊ የስራ ተቀጣሪዎች አገር አላቸው። በጠመንጃና ደም በማፍሰስ በጉልበት የሚገዛቸውም ቢሆን አገራቸውን የሚመራ ድርጀትና “ጉልቻ” ፓርላማ አላቸው። በዘር እየለየ ድጋፍ የሚሰጥና ለወደፊቱ ቂም የሚያከማች ድርጅት ቢያረክሰውም የሚኮሩበት ባህልና ወግ አላቸው። ገንዘብ ካገኘ ገደል የማይታየው ኢህአዴግ ከድህነታቸው በላይ ክህደት ቢፈጽምባቸውም እጁን ዘርግቶ የሚቀበል ቤተሰብ ከድህነቱ በላይ ተካፍሎ መብላት የሚያስጨንቀው ማህበረሰብ አካል ናቸው።
ከድሆች ገንዘብ እየሰበሰቡ የሚንደላቀቁ ሁሉ በቅድሚያ ከራሳቸው ህሊና፣ ቀጥሎም ከተጎጂዎችና በዙሪያቸው ካሉ ወገኖች እንዲሁም አገር ወዳዶች የበቀል ቋት ውስጥ ከቶውንም አይወጡም። ኢህአዴግ በተለይም ህወሃት የተሸከመውን የነፍጥ ብዛትና የሰበሰበው የሃብት ክምችት ትምክህት ሆኖባቸው ወገኖቻቸው ላይ ለሚሳለቁ “ወዮልኝ” አብዛኞች እየራባቸውና ችግር እያዳፋቸው በጥጋብ ድሃው ህዝብ ላይ ለምታገሱ አሁንም “ወዮልኝ”። የበቀል ሽታው እየናኘ ነውና “ከወዮልኝ” እንድንሰወር ይሁን። አገር ውስጥ ያላችሁ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አላችሁ? ኢህአዴግና ጭፍራዎቹ የደርግ ያበቃበት ዘመን ዛሬም ይመጣልና አስቡ። የመጣል ቀን ቀጠሮ የለውም። አሁን ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ካለው የሃዘንና የድህነት መጠን አንጻር የሚያጨካክነውን አስተሳሰብ ወደ መደጋገፍ ለመቀየር ትጉ!!the bees
አንድ አገር ያላት ዜጋ አደባባይ ተገድላ አስከሬኗ ሲጎተት፣ አንድ ወገንና አገር ያለው ጀግና ድህነት ክብሩን አሳጥቶት አስከሬኑ በስለት ሲወጋ ከማየትና አህቶቻችን ሲደፈሩ እየሰማ ቁጣውን በትዊተርና በፌስቡክ የሚገልጽ መንግስት ለዜጎቹ ማፈሪያ ነው። ይህንን ያህል ተለሳላሳሽነትስ መነሻው ምንድ ነው? ኢህአዴግ ልዩ በጥቅሙ ካልተነካ በስተቀር፣ ኢህአዴግ በተለይም ህወሃት የሚጎዳበት ነገር ከሌለ በስተቀር ሁሉም ሰላም፣ አገር አማን ነው ማለት ነውን? አገርን፣ ዜጎችንና ብሄራዊ ክብርን በጎጥ ሂሳብና በከርስ መጠን በመለካት መኖር መጨረሻ ላይ ዋጋ ያስከፍላል። ታሪክም የሚነግረን ይህንኑ ነው። ዳሩ ምን ያደርጋል ሌባ ሌባን አይከስ?

http://www.goolgule.com

Tuesday, January 7, 2014

ትግሉ ለኦሮሞ ሕዝብ መብት ወይንስ ለዝና እና ለጥላቻ ??

January7/2014
=== ቁጥር አንድ ልናውቀው የሚገባ ይህን የጥላቻ ዘመቻ የከፈቱት እና ያበረታቱት ማናቸው? ‪
ምንልክ ሳልሳዊ
ኦቦ ሜንጫ እና ተባባሪዎች ማንን መታገል እንዳለባቸው እንዴት መታገል እንዳለባቸው እኛ እንነግራቸውም:: ምንኛውም የነጻነት ታጋይ ነኝ የሚል ግለሰብም ይሁን ቡድን ነጻ አወጣዋለሁ የሚለውን ሕዝብ ካለበት የጭቆና ቀንበር ነጻ ለማውጣት ይታገላል እንጂ በሞተ እና ባፈጀ አሮጌ ታሪክ ላት አትኩሮ አንድን ዘፋኝ ተከትሎ እይጮህም:: ይህ ሴራ ሌላ ድብቅ አላማ እንዳለው ይታወቃል::መታገል የሚገባቸው በኦነግ ስም እና በአሸባሪነት ስም እየተለጠፈባቸው የሚገደሉ የሚታሰሩ የሚሰቃዩ ድምጻቸው ሰሚ ላጣ ኦሮሞዎች መሆኑን እያወቁ ..በኦሮሞ ሕዝቦች ላይ የሕወሓት መራሹ መንግስት እና አሽከሩ ኦሕዴድ የሚፈጽሙትን ርህራሄ የለሽ ስቃይ መታገል ሲገባቸው ከ100 አመት በፊት የነበረ ታሪክ እያነሱ አንድን ግለሰብ እየጠሩ መናከስ እና ማናከስ አያዛልቅም::
ይህ የተጀመረው የማያዋጣው ዘመቻ የትም እንደማያደርስ እና በራሳቸው ጦር ራሳቸውን እንደሚወጉት ልንነግራቸው እየፈቀድን እያደረጉ ያሉት ዘመቻ አምባገነናዊ የሕወሓት ስርኣትን እድሜ ከማስረዘም እና የኦሮምን ሕዝብ ወቅታዊ ጭቆናን ከማባባስ አያልም:: የኦሮሞን ሕዝብ ረስተው በስሙ ሽፋን የሚያውደለድሉት ጽንፈኞች ዋና እና ድብቁ አላማቸው የኦሕዴድን ሕወሓታዊ አጀንዳ ማስፈጸም መሆኑ ግልጽ የሆነ ጉዳይ ነው:: ትግሉ ማተኮር ያለበት በደለ እና ኮካኮላ ላይ አሊያም ቴዲ አፍሮ እና ምንሊክ ላይ ሳይሆን የኦሮሞን ሕዝብ ካለው ጭቆና የሚላቀቅበት መንገድ ላይ ሊሆን ይገባዋል::
የዘመቻው አካላት በጥላቻ የተሞላ አጀንዳቸውን እያራገቡ ሲገኙ አብዛኛው አጀንዳቸው ውሸትን የያዘ እና ነገ ሊያፍሩበት የሚችል ነገር መሆኑን እያወቁት ነው:: የዘመቻው ዋና ግብ የሕወሓት ስልጣንን ከማስረዘም ውጪ ለኦሮሞ ሕዝብ የሚፈይድለት አንዳችም ነገር የለም:: የዘመቻው መሪዎች ነን የሚሉ ግለሰቦች በሃሰት የተሞሉ እና በሃገር ውስጥ ያለውን የሕወሓት/ኦሕዴድን አምባገነናዊ የስልጣን ተጽእኖ ተገን አድርገው ለገዢው ፓርቲ የሚሰሩ የጥላቻ አራማጅ ቡድኖች ስብስብ ናቸው::እነዚህ ሰዎች አወናባጆች ሲሆን በተፈበረከ ውሸት ተጀቦነው ከገዢው ፓርቲ ጋር የሚሰሩ መሆናቸው በይፋ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው:; መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ይህንን ዘመቻ የጀመሩት ሰዎች የሕወሓት ጉዳይ አስፈጻሚ ከሆነው ከኦሕዴድ ባለስልጣናት ጋር የጠበቀ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን በድብቅም በገሃድም ድጋፍ ይሰጣቸዋል::
እነዚህ የዘመቻው አራማጆች በዚህ ብቻ አላበቁም.. ከሕወሓት ሁነኛ ሰዎች ከሆኑት ክስብሃት ነጋ እና ቡድናቸው ጋር ቁርኝት ፈጥረዋል አይዟቹህም ተብለዋል::ከቀድሞ የኦነግ ስብርባሪዎች እና ጸረ ኢትዮጵያ አቋም ካላቸው የሻእቢያ ቡድን አባላት እና የሻእቢያ ደጋፊ ከሆኑ ዲያስፖራ ኤርትራውያን ጋርም ሰፋ ያለ ግንኙነት አላቸው:: እንዲሁም
ለስልታን ከሚቀላውጡ እና የሃገር ጉዳያቸውን መነገጃ ካደረጉት ሰዎች ጋርም እንዲሁ ግንኙነት አላቸው::የእነዚህ ሰዎች አላማ ሳይውቁም ይሁን እያወቁ የሕወሓት መጠቀሚያ መሆን ነው:: የሚገርመው ከእነዚህ ሁሉ ሰዎች ጋር የሚያደርጉት ግንኙነት በሚጠሉት አማራኛ ቋንቋ ነው::
‪‬የኦቦ ሜንጫ እና የተባባሪዎቹ ድብቁ አጀንዳ === ሊያውቁት የሚገባ ሁለት
 አጥፊው እና አልሚውን መለየት አልቻልንም ይላል አቶ ውብሸት ወርቃለማሁ .. አሁንም እንደምናየው መንግስት ነኝ የህዝብ አስተዳዳሪ ነን የሚሉ ባለስልጣናት የተለያዩ ጽንፈኛ ሰዎችን በጥቅም በመግዛት በመደለል እና የወረደ አስተሳሰባቸውን በማበረታታ በገሃድ ልማትን እየሰበኩ በሃገር ላይ ከፍተኛ ጥፋት እና መተላለቅ እንዲከሰት መንገድ እየጠረጉ ይገኛሉ::ሞተው በተቀበሩ ጨቋኝ እና ተጨቋኝ ታሪኮች ከምናላዝን አንድ ወጣት ዘፋኝ በፈለገው መንገድ ቢዘፍን የሃሳብ ነጻነቱን በጭፍን ከምናወግዝ እጅግ አሳሳቢ የሆነው ነገር የኦሮሞ ሕዝብ ብየእስር ቤቱ ታጉሮ አስታዋሽ አጥቶ እየተሰቃየ ለምን ለእሱ ጩኸታችንን አናሰማለትም:አንድም ቀን ለኦሮሞ ህዝብ ሰብኣዊ መብት ሲናገሩ ያልተሰሙ ሰዎች ዛሬ ብቅ ብቅ ማለታቸው ድብቅ አጀንዳቸው ተለይቷል::
ልብ ብለን ካነበብን ቤልጅግ አሊ ዘመንን ለማሰር በሚለው ክታቡ ወያኔዎች ሃገራችንን ለማፍረስ የማይጠቀሙበት መንገድ የለም። በማካከላችን አንቀላፊዎች(Sleepers)ያስቀምጡብናል። ቀኑ ሲደርስ ያነቋቸዋል። ሰሞኑን በእነ ጃዋር ያየነው ይህንን ነው። እነ ጀዋር ሲነቃባቸው ሌሎች ይላካሉ። እኛም ምሩን ብለን እንቀበላቸዋለን። ለወራት ካመሱን በኋላ ያደረሱትን ጉዳት አድርሰው ተልዕኳቸው ተፈጽሟልና ይሸሸጋሉ። ሌሎች በምትካቸው ይመደቡልናል . . . እንዲህ እንዲህ እያልን ዓመት እንቆጥራለን . . .። መቼ ይሆን እያየን አለማየታችንን የምንገነዘበው? መቼ ይሆን ከተኛንበት የቁም እንቅልፍ የምንነቃው? መቼ ነው ሰው ነኝ ወይስ በሰው ምስል የቆምኩ “ሰው“ ብለን ራሳችንን የምንመረመረው። ብልህን አንዴ ያሞኙታል፤ ሞኝን ግን ዘንተለት እንዲሉ ነውና ከእንቅልፋችን እንንቃ። ብሎናል:: ከዚህ የምንረዳው ለጥቅም የሕዝቦችን ነጻነት እና መብት አዝለው የሚመጡትን ሰዎች በመንከባከብ አገርን እየገደልን መሆናችንን ነው::
በቁጥር አንድ ጹሁፍ ላይ እንደጠቀስኩት ኦቦ ሜንጫ እና የመለመላቸው ወገኖቹ የተሰጣቸውን ተልእኮ ለማሳካት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም::ከተለያዩ አካላት በመስራት የተለያዩ የማእረግ ስሞችን በማግኘት በአዋቂነት ሽፋን የሕወሓት አላማ በማስፈጸም ለራሱም ጥቅምና ዝናን ለማግኘት እየተንቀሳቀሰ ነው:: እሱና እሱን የሚከተሉ ግለሰቦች አውቀም ይሁን ሳያውቆ የታሪክ አተላ በመሆን አገር ቤት ለሚገኘው ወገናቸው ሞት እየደገሱ እንደሆን አልተረዱትም::የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ቢካሐድ ኖሮ በተገኘበት ቦታ ሁሉ የሃገሩን ተወላጆች እና መጠዎች በሚል ደሞ ሌላውን ብሄር በመጨፍጨፍ ወንጀሉን ዛሬ አክቲቭኢስት ነን በሚሉት ቦይኮቶች ላይ እንደሚለጥፉ ቢታቀድም ሳይሳካላቸው ቀርቷል: ጃዋር እና ተከታዮቹ በኦሮሞ ፈርስት ስም በተለያዩ ሃገራት ለልመና በመዞር ያገኙትን ገንዘብ የት እንዳደረጉት ካለመታወቁም በላይ እየሰሩት ያለው ድራማ ግን ሃገርን ለውድመት የሚዳርግ መሆኑን ሊረዱት ፈቃደኛ አልሆኑም:: ኦቦ ሜንጫና ተከታዮቹ በሕወሓት ሳምባ በሚተነፈሰው ኦሕዴድ ጋር በመቀናጀት በኢሮሚያ ክልል የሚኖሩ ኦሮሞ ባልሆኑ ዜጎች ላይ እንዲወሰድ ያቀዱት እቅድ ሲከሽፍ ማየቱ ምንኛ እንደሚያስደስት የታወቀ ነው::
የስልጣን ማስረዘሚያ ስልታቸውን በየቀኑ እየቀየሱ እና እየለዋወጡ የሚገኙት ሕወሓቶች ሳያውቁት ሳያስቡት ተባባሪዎቻቸውን ከተቃዋሚ ከፍተኛው አክል አግኝተዋል:; የተቃዋሚ ጎራ ከስልታናቸው የተገፉትን ለስለላ የተሰማሩትን እና የተለያዩ እንከኖች ያዘሉትን የገዢው ፓርቲ ዝባዝንኬዎችን በመቀበል ካለማእረጋቸው ማኤረግ በመስጠት ለግል ዝናቸው እና ጥቅም ሲሰሩ የኦሮሞ ሕዝብ ግን አሁንም በጭቆና እግር ተወርች ታስሮ እየተሰቃየ ይገኛል:: ከዚህ ቀደም ከገዢው ፓርቲ ከኮበለለ ሰው እንደሰማነው በኢትዮጵያ እስር በቶች የሚገኙት የኦሮሞ ተወላጆች ናቸው::ለእነዚህ የኦሮሞ ተወላጆች ከመከራከር እና ከእስር እንዲፈቱ ከመጮህ ይልቅ ባረባው እና ምንም ለውጥ እና ፋይዳ በማይኖረው የገዢውን ፓርቲ ገበናዎች በሚሸፍኑ ጉዳዮች ላይ ማላዘን የኦሮሞን ህዝብ በቁሙ ከነህይወቱ እንደመቅበር ነው:: ስለዚህ ተሌኮ ያላቸውን ሰዎች ተወት አድርገን በነሱ እየተመራን በጭፍን የምንጓዝ ሰዎች ይህንን መደናበራችንን ሰከን ባለ መልኩ ብናስበው መፍትሄው በእጃችን መሆኑን ለመናገር እወዳለሁ::

ዲታ መንግሰትና ምስኪን ህዝብ (ግርማ ሠይፉ ማሩ)

Janaury 7/2014

የ“አባት ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ” የሚባል አባባል አለ፡፡ ይህን አባባል ሰረዳው ዘራፊዎችን ማስቆም ካልቻልክ
በዘረፋወ በመሳተፍ የድርሻህን ማንሳት ችግር የለውም የሚል እንደምታ እንዳለው ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት
ይመስለኛል በአብዛኛው የመንግሰት በሚባለው ንብረት ላይ በዘረፋ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ድርሻቸውን እንደወሰዱ
እየተሰማቻው ይህን በማድረጋቸው አንድም ቅሬታ አይታይባቸውም፡፡ ይልቁንም የጀግንነት ሰሜታቸው ሀይሎ
ይህን ዘረፋ የሚጠየፉትን እንደ ጅል መቁጠር እየተለመደ መጥቶዋል፡፡ በዘረፋው ላይ ያልተሳተፉም ቢሆኑ ይህ
የመንግሰት የሚባለው ንብረት ሲዘረፍ ከመመልከት ዘለው ለምን አይሉም፡፡ አንድ አንዶች ደግሞ በመዝረፍ
ባይሳተፉም በማዘረፍ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ለመዝረፍም ለማዘረፍም ጥሩ ማሳያ ነው ብዬ ነው የማምነው፡፡

የአዲሰ አበባ መንገዶች ባለስልጣን አሰርቶት ከአገልግሎት ውጭ ሆኖ የነበረው ከመሰቀል አደባባይ ቃሊት ያለው መስመር አሰፋልቱ እየፈረሰ ሰፊ ጉድጓድ እየተማሰ አደሲ ቁፋሮ እየተካሄደ ሰመለከት ከባከነው ገንዘብ ይልቅ ያብከነከነኝ ተጠያቂነትን እንዲያረጋግጡ፣ ካልቻሉም እራሳቸው የሚጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትራችን የሰጡት ማብራሪያ ትውስ ብሎኝ ለምን መዋሸት ያስፈልጋል ብዬ ጉዳዩን ማንሳት ወደድኩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመዝረፍ ተሳትፈዋል ለማለት መረጃም ማስረጃም የሌለኝ ቢሆንም ሲዘረፍ ዝም ብሎ በመመልከት እና ሲከፋም ለማዘረፍ ከለላ እየሰጡ መሆናቸው ግን የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡

ከመስቀል አደባባይ ቃሊቲ ድረስ ያለው መንገድ አንድ ዓመት እንኳን ሳያገለግል በመንገዱ አሰፋልት መሆን ምክንያት የተማሪዎችን  ህይወት መቅጠፍ ሳይበቃው ይህን ሊከላከል ይችላል የተባለ የብረት አጥር ግንባትን ጨምሮ ከፍተኛ ገንዘብ ከንቱ ቀርቶዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ዋነኛ ተጠያቂ መሆን ያለበት የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ሲሆን፤ የባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ሃላፊ ጉዳዩን፤ የባቡር መስመሩ ድንገት በመምጣቱ ነው የሚል አስተያየት መስጠት ዕቅድ አልባ መንግስት መሆኑን ማሳያ ነው፡፡ ይህ በሚመለከት ሃሳቡን ያጋራኝ በመንገድ ዘርፉ ኃላፊ የሆነ ሰው የነገረኝ ደግሞ፤ በባቡር ኮርፖሬሽን ቦርድ ውስጥ የአዲስ አበባ መንገዶች መስሪያ ቤት ኃላፊ ያሉበት መሆኑን አስተያየታቸውን አሰገራሚ ያደርገዋል ነው ያለኝ፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ኃላፊው ባቡር መስመሩ መንገዱን ሊጠቀምበት ይችላል የሚል ግምት ነበር ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትራችንም የዚህ ሰበብ አውቀው ይሁን ሳያውቁ ሰለባ የሆኑ ይመስለኛል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ማስተባበያ በሰጡበት ወቅት ባለ ሞያ መሐንዲስ መሆናቸውን ጠቅሰው ከላይ ያለው አሰፋልት ብቻ ስለሚነሳ ከሰር ያለው ሙሊት ስራ ላይ ይውላል በዚህ የተነሳ ብክነቱ ዝቅተኛ ነው ብለው ለኢትዮጵያ ህዝብ ገልፀው ነበር፡፡ የነበራቸው መረጃ ይህ ከሆነ አሁን እያየን ያለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ሳይሆን እንደ አዲስ ተቆፍሮ ሌላ እየተሞላ ነው፡፡ አሁንም ጉዳዩ ቀላል ነው ሊሉን አይችልም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዋሽተውናል፤ አልዋሸውም የሚሉ ከሆነ ደግሞ በሹሞቻቸው ተታለዋል፡፡ ሰለዚህ የተሳሳተ መረጃ የሰጧቸውን ይጠይቁልን ወይም እራሳቸው ኃላፊነቱን ይውሰዱ፡፡ ይህ የጠቅላይ ሚኒሰትሩ አሰተያየት የህዝብ ሀብት ብክነት ሲነገራቸው እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ከለላ መስጠታቸው ተባባሪነታቸውን ነው የሚያሳየው፡፡ አሁንም አሰቸኳይ እርምጃ እንዲወስዱልን እንጠይቃለን፡፡ በቅርቡ ደግሞ ከፍተኛ ወጪ የተደረገበት ግንባታ ከተከናወነ በኋላ መፍረሱን አስመልክቶ መስሪያ ቤቱ ኃፊዎች የሰጡት አሰተያየት አሁንም ያስገርማል፡፡

ዲዛይን ለውጥ በመደረጉ የተነሳ ግንባታው መፍረሱን አረጋግጠው፤ እንደዚያም ቢሆን ወጪው የሚመለከተው
ግንባታውን የሚያከናውነው የቻይና ድርጅት ነው፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ኮንትራቱ ሰሰጥ ዲዛይንም ግንባታንም የሚጨምር የኮንትራት ዓይነት ስለሆነ ነው ብለውናል፡፡ እንዲህ ከሆነ ደግሞ ይህ ኮንትራት የተሰጠበት ዋጋ እንደፈለጉ አባክነውም ቢሆን አትራፊ ያደርጋቸዋል  የሚል እንደምታ በጆሮዋችን ያቃጭላል፡፡ ድሮም ቢሆን ገንዘብ ይዞ መጥቶ ዲዛይንም ግንባታም ለመስራት የሚገባበት ውል ሰላማዊ እንደማይሆን ልባችን ያውቀዋል፡፡ ለማነኛውም ይህ የባቡር ፕሮጀክት ተጠናቆ ሰራ ሲጀምር ወጪውን በግራም በቀኝ አሰበን በወቅቱ ካለው ዋጋ አንፃር ማየታችን የግድ የሚል ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ዋነኛ ዘራፊው የቻይና መንግሰት ሲሆን አዘራፊው ደግሞ የብድር ስምምነት የገባው የፌዴራል መንግሰትና የባቡር ኮርፖሬሽን ነው፡፡ የእነዚህ አካላት ሀለቃ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ናቸው፡፡
ከመንገድ ጋር በተያያዘ የማንረሳቸው በባቡር ግንባታ ስም የህዝብን ሃብት ያባከኑት ከሾላ ገበያ፣ በለም ሆቴል ወደ ቀለበት መንገድ ማቋረጫ መንገድ፤ በደሳለኝ ሆቴል ሳርቤት የሚወስዱት መንገዶች አገልግሎት ሳይሰጡ መፍረሳቸው የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ሃላፊዎችን እንቅልፍ ይሰጣቸው እንደሆነ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ምን ችግር አለው ለዘመናዊ ባቡር ሲባል ነው ብለው በሚዲያ የሚሰጡት መልስ ውሃ የሚቋጥር አይሆንም፡፡ አሁንም በድፍረት ሚዲያ እየወጡ ይህን መልስ የሚሰጡ ሰዎች ትዝብት ላይ ከመውደቅ ባለፈ ይህ ሰበብ ግብር ከፋዩን ዜጋ እንደማያሳምነው መረዳት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህን የሚዲያ ዘማቻ አሁንም አላቆሙም፤ ልብ ማለት ግን የተሳናቸው ይመስለኛል፡፡

በከተማችን በከፍተኛ ወጪ እየተገነቡ ያሉት የትራፊክ መብራቶች ለመፍረስ አንድ ወር ሲቀረው የሚሰሩ መሆናቸው የዚህ መብራት ባለቤት ማን ነው? የሚል ጥያቄ ያስነሳል:: የመንገድ ማካፈያዎች፣ አደባባዮች የሚሰሩት በጥቃቅን በተደራጁ ይሁን በኮንትራክተር መፍረሳቸው እየታወቀ የሚገነቡበት ምክንያት ግራ የሚያጋባ ነው፡፡ የጥላሁን ገሠሠ አደባባይ የሚባለው የተጠናቀቀው እንደሚፈርስ ግርማ ሠይፉ ማሩ ታውቆ ሌሎች መንገዶች መፍታውቆ ሌሎች መንገዶች መፍረስ ከጀመሩ በኋላ ነው፡፡ ይህን ተግባር ለማከናወን ውል ተገብቶ እንኳን ቢሆን ገንብቶ ከማፍረስ ተደራድሮ ሀብት እንዳይባክን ማድረጊያ “አስገዳጅ ሆኔታዎች” የሚል የውል አንቀፅ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ይህ የኮንትራት አስተዳደር ሀሁ ነው፡፡በግርግር የሚባክነው ግን ከፍተኛ የሆነ የህዝብ ሀብት መሆኑ ተዘንግቷል፡፡ ህዝብና መንግሰት የተለያዩበት ሀገር የመንግሰት ሀብት የሚባለውን መዝረፍ ለፅድቅ እንደሚደረግ ተግባር ይወሰዳል፡፡

 በነገራችን ላይ በመርዕ ደረጃ የመንግሰት የሚባል ነገር የለም፡፡ መንግሰት ህዝብ በመወከል ለህዝብ የጋራ ጥቅም የሚውል የጋራ የሚባሉ ንብረቶች ሊኖሩት ይችላሉ፡፡ ከዚህ ጋር ተሰማሚ የሆነው የህገ መንግሰት አንቀፅ 89፡3 “መንግሰት መሬትንና የተፈጥሮ ሀብትን በህዝብ ስም በይዞታው ስር በማድረግ ለሕዝብ የጋራ ጥቅምና እድገት እንዲውሉ የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡” ይላል፡፡ በተቃራኒ ደግሞ የሚቆመው አንቀፅ 40፡3 “የገጠርም ሆነ የከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሀብት ባለቤትነት መብት የመንግስትና የህዝብ ብቻ ነው” በማለት መንግሰት እራሱን ከህዝብ የተለየ ሌላ አካል አድርጎ ያስቀምጣል፡፡ አሁን በተግባር ያለውም የመንግሰት ባለቤትነት እንጂ የህዝብ ባለቤትነት አይደለም፡፡ ለመንግሰት ንብረት ዜጎች የማይቆረቆሩት የመንግሰት የሆነ የእነርሱ ባለመሆኑ ነው፡፡ የእኛ መንግሰት ከህዝብ ይበልጣል፤ ለዜጎች የሚያስፈልገውን እየነፈገ ለራሱ ጡንቻ ማደበሪያ የሚሆነውን ሀብት፣ ንብረት ያፈራል፡፡ በዚህም ህዝብን ይጨቁናል፡፡ ይህም ሆኖ የመንግስት የሆነ የማንም ስለአልሆነ ቀዳዳ ያገኘ ሁሉ ይዘርፋል ያዘርፋል፡፡


አሁን እዚህም እዚያም የሚባክነው ገንዘብ በእኔ እምነት የህዝብ ንብረት ነው፡፡ መንግሰትም በህዝብ ስም የማስተዳደር ስራ እንዲሰራ የተቀመጠ እንጂ ንብረት እንዲያፈራ የተቀመጠ አካል አይደልም፡፡ የህዝብን ንብረት ሲያስተዳድር የሚያባክን ደግሞ ሃላፊነቱን በአግባቡ ባለመወጣቱ ምንም ዓይነት ሰብብ ሳያቀርብ ቦታውን መልቀቅ ይኖርበታል፡፡ እንቢ ካለም ባለቤት የሆነው ህዝብ ማስለቀቅ ይኖርበታል፡፡ምን ያደርጋል ህዝቡ ይህ የሚሰራው ስራ በገንዘቡ ወይም በስሙ ልጆቹና የልጅ ልጆች በሚከፍሉት ዕዳ መሆኑን እንዲዘነጋ እና መንግሰት በቸርነት የሚሰራው እስኪመስል ድረስ የተሳሳተ ፕሮፓጋንዳ ሰለባ እየሆነ ነው፡፡ የዚህ ፕሮፓጋንዳ ዓላማ አንድና አንድ ነው፡፡ መንግስትን ከተጠያቂነት ማሽሽ፤ ንብረት ሲያባክንም የራሱን ንብረት እንዳባከነ እንዲቆጠር ማድረግ፡፡ ከተቻለም የመንግሰት ንብረት መዝረፍ ነውር እንዳልሆነ ማስጨበጥ ናቸው፡፡

ልብ በሉ የባቡር መስመር፣ የመንገድ. የቴሌ፣ የመብራት መሰረተ ልማቶች የሚገነባልን ዲታ መንግሰት ነው ያለን፡፡ መንግሰት ቸርነቱ የበዛ፣ እንዲሁም ደግ ሲሆን መንግሰት ለህዝቦቹ የሚያስብ አንድ አካል ነው፡፡ ህዝብ ደግሞ እነዚህ ሁሉ የመሰረተ ልማቶች የሚያስፈልጉት ምሰኪን ከመንግሰት እጅ የሚጠብቅ፡፡ የሚገርም ነው!! የገዛ ንዘቡን እና ንብረቱን እንዲያስተዳድር የተቀመጠ አካል አዛዥ ናዛዥ ሲሆን፤ ባለ ገንዘቡ ደግሞ ምስኪን ተመፅዋች የሚኮንበት ጥቂት ሀገሮች ካሉ አንዷ ምስኪኗ ኢትዮጵያና ህዝቦቿ ናቸው፡፡

ቸር ይግጠመን!!!!



Teddy Afro will Sue Tigest Geme(Oromo First Genocidal Activist) for defamation

January 7/2014

gemejj
Tigest Geme  is known for her extreme  hate for Ethiopians specifically to Orthodox Christians.She is one of Jawar’s follower and Oromo first  Genocidal activist and currently resides in Portland. Tigist  has falsified and fabricated defaming Teddy Afro. Thus, it is imperative for Teddy Afro to take on the needed legal action against such extremists. This also goes for the recent Teddy Afro song Tikur Sew which was taken and made into an Anti-Amhara ,Orthodox and Menelik II song. This is a copyright violation not to mention inciting genocide against Orthodox and Christians in general .
The recent ongoing controversy on Teddy Afro by minute small group of Oromo extremists has reached fever peach high. I came across an article written on the controversy by an individual named Tigist Game, and I must say I have not come across an article that is so full of mendacity and vitriol. She engages in presenting falsity to justify her genocidal ideology and mentality. I will cover each of her claims paragraph by paragraph and try to expose much of her inconsistencies and fabrications. Teddy Afro’s statements.

“Enqu editors circulated the magazine’s December issue (pictured above) via email featuring Teddy and his beloved emperor side to side on its cover with a comment that reads, “For me, Menelik’s unification campaign was a Holy War.” A few days later, amid protests on social media, the publishers shelved the comment and sought to dismiss the controversy by saying it was a technical glitch in their system.” First of all, Teddy Afro never made such a statement. Yes, it is true the magazine had at first published alleging Teddy Afro had given those statements, but the magazine did retract its words, and in fact, Teddy Afro also gave a statement specifically detailing that the questions were about Adwa and nothing else. However, even if he gave those statements he has right to speak his mind! However, the deliberate twisting of words to assassinate someone’s character is nothing new to Neo-Nazil Oromo extremists.
“As Hallelujah Lulie points out in a blog post at Horn Affairs, on a closer reading, the Enqu publishers retraction doesn’t hold much water. First, a direct quote from a source cannot in any way be a “technical glitch.” Second, as Lulie rightly notes, every news organization has established workflows and mechanisms for editorial oversight. It is therefore preposterous and unethical for Enqu editors to downplay and fix quotes by caving to pressures from Teddy and his handlers. Third, by lionizing one of Ethiopia’s most ruthless tyrants – one whose historical atrocities amount to genocide against several nations and nationalists in southern Ethiopia including the Oromo, Kafficho, Wolayita, Sidamo and many others – Teddy has already condoned these atrocities. He has never been shy about his saintlike admiration for the loathed emperor.
Teddy Afro does not need to be pressured to change his mind. He is a well-spoken individual who is articulation goes beyond than just playing around with empty rhetoric. He is a profound artist who weaves art and history together boldly. We all know where Jah Yasterseryal song cost him. If Tigist Geme things Teddy Afro is somehow afraid to speak his mind then she is hugely mistaken. Furthermore, she classifies Ethiopian rulers as being, “Ethiopia’s most ruthless tyrants – one whose historical atrocities amount to genocide against several nations and nationalists in southern Ethiopia including the Oromo, Kafficho, Wolayita, Sidamo and many others.” Notice how she presents a selective picture of Ethiopian leaders and does not provide any context and attempts to classify it as genocide in the current context.
First and foremost what she is classifying as genocide is one of the thousands of wars that have taken place in the various regions in Ethiopia. Notice how she also attempts to garner the support of the Southern people and also attempt to attribute the same defeatist and victimization ideology to them. Once again, she argues selectively and attempts to speak for the Southern people under her Oromo extremist ideology. The irony is that many of these ethnic groups detests Oromo extremists because historically have dominated those same groups she accuses Menelik II of oppressing. In fact, the land of these ethnic groups were changed to Oromo names because they were conquered by them. Furthermore, Menelik II is not loathed by the majority of Ethiopians! On the contrary, he is only loathed by extremists like herself because they refuse to see beyond their hateful religious and ethno-nationalist radical goal. Therefore, Teddy Afro does not condone anything! Like any other Ethiopian, he wishes to celebrate our victories!
In an interview with EBS’s Kassa Show, dressed in a royal knight-like wear, Teddy flamboyantly showed off portraits of kings Menelik and Haileselassie in his living room while boasting about the need to understand history and the past to create a better future.”“Even if one accepts Enqu’s botched retraction as plausible, Teddy has already done enough damage to his reputation. To be sure, as a private citizen, Teddy has every right to admire or immortalize whomever he so chooses. But he is a public figure. His music and words have significant influence. His willful ignorance and simplistic interpretation of historical events and figures have generational consequences. For the Oromo and other nations in the south, Teddy’s actions amount to exculpating Hitler of the Holocaust.” Teddy Afro’s reputation is still intact! If Ms. Tigist Geme means reputation with extremists like herself than that is true because Teddy’s love message in incongruent with their extremist’s hateful ideology. As stated earlier, his music has and continues to be at the forefront at uniting people, and presently he is the most sought out artist.
Tigist Geme has neither the moral ground nor the education to give advice to Teddy Afro because any one that has a depth understanding of what Hitler did and what the Holocaust was about would not spew nonsense nor make such a ridiculous and ludicrous comparison with Menelik II. Perhaps it escapes Tigist Geme that the Nazi’s were in the business of gassing people in gas chamber or how people who did not fit into the Arayan’s race concept of “fitness” were disposable? I could go on and list for hours on end on the atrocities of the Nazis, but doing so would mean entertaining the epitome of stupidity. Therefore, I will not do it! However, one can easily assume how drunk the extremists have gotten with such hate! She further goes on and states. “It is time that Teddy is stopped. Such revisionist historiography and hagiography has no place in our time. It took decades of sustained struggle to correct the falsified Ethiopian history written by court historians, not least those who worked for Menelik. It is unthinkable to assume a return to an era where history is written to fulfill the interests of those who seek to maintain the status quo.” It is evident reading this statement that she does not understand what revisionism denotes and how she is contradicting herself.

According to the Webster dictionary revisionism or a revisionist is, “support of ideas and beliefs that differ from and try to change accepted ideas and beliefs especially in a way that is seen as wrong or dishonest.” Obviously, she not only lacks the understanding of the definition but the concepts of how history is written and merited. In other words, her and her likes hold the revisionist position. One of the individuals who they love to hate is Abba Baherey. Aba Bahere was a Christian Monk who wrote on the Oromo expansion, culture, and identity in an utmost detail.
According to Hassan Mohamed, who is an author of Oromo historical literature, states that Abba Baharey is the first person to have written about the Gada system which these extremist Oromos radicals hate with a passion. Abba Baharey, as many historians, was biased of course. However, his writings cannot be entirely dismissed as being biased because it is part of history and perspective of his. For argument sake, we will dismiss Aba Baharey to suit Tigist Geme and her minion Oromo extremists. Now the question is what about foreign writers? Are they biased too? Well of course they can be but in most cases they are not. A perfect book that can perhaps appease them is that of, “Futuh Al-Habasha: The Conquest of Abyssinia (Futuh Al-Habasa).” It was written by Sihab ad-Din Ahmad bin Abd al-Qader bin Salem bin Utman. The book was written Sihab ad-Din Ahmad bin Abd al-Qader bin Salem bin Utman, and in the book he perfectly documents how the Oromos expanded along with Muslims all the way to Shewa, Gojam, Gonder, Wello and so forth. This is one of the many Oromo expansions which you will not hear from Tigist Geme or her minions because revealing those facts would dismantle the premise of their ideological position and mission.
The goal of these extremists is fundamentally to play the victimization role and use the TPLF (Tigray Peopl’s Liberaton Front) to grab power and hopefully create and independent Oromo state. The idea is that they want to galvanize the vast majority of Oromos and have them subscribe to their ideology. The irony, however, these extremists have an exclusive ideology which is based on double extremism. The first is religious extremism which is Islamic fundamentalism and the second a segment within the Oromo. On the surface, however, they want to ride the wave by making their extremists agenda as being that of the Southern people and Oromo at large.

ሕዝባዊ ብሶት – የከተማ አብዮት? – ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

January 7, 2014

ባለፈው ሳምንት ኢህአዴግ በከተሞች ላይ የቋጠረውን ስር የሰደደ ጥላቻ ከነመግፍኤው ጨርፈን ከተመለክተን በኋላ፤ ለዛሬ፣ ታላላቅ ግድፈቶቹ ሕዝባዊ ተቃውሞ ለመቀስቀስ ሊኖራቸው የሚችለውን አስተዋፅኦና በአደባባዩ የሚነሱትን ዋና ዋና ጥያቄዎች ለመዘርዘር፤ እንዲሁም ‹‹ማኦኢዝም›› የሚበይነውን ከገጠር የሚነሳ ብረታዊ ትግል፣ ከሰላማዊው የከተማ አብዮት አንፃር ለመፈተሽ ቀጠሮ መያዛችን ይታወሳል፡፡ እናም እንዲህ እንቀጥላለን…
 የኢህአዴግ ግድፈቶች
ፈረንጅኛው ‘Achilles Heels’ በሚል ስያሜ የሚገልፃቸው እና አማርኛው ደካማ ጎኖች ብሎ የሚሰይማቸው የስርዓቱ ታላላቅ ግድፈቶች ከዕለት ዕለት ራሳቸውን ማብዛታቸው ፍፃሜው የሚተነበይ አድርገውታል፤ ይኸውም ብሔር ተኮር ጥያቄዎች አለመመለሳቸው፣ ውጤት አልባው የገጠር ፖሊሲ፣ የድህረ-ደርግ የዴሞክራሲ ሽግግሩ መክሸፍ (ከፖለቲካ፣ ከሰብዓዊ እና ሀሳብን በነፃነት ከመግለፅ አንፃር)፣ የኢኮኖሚ እድገት አለመኖር፣ ድህነት ከቀድሞውም በበረታ መልኩ መስፋፋቱ፣ የትምህርት ፖሊሲው ክስረት፣ የስራ-አጥ ቁጥር አለቅጥ ማሻቀብ፣ የራስ አስተዳደር (Self-adminstration) ሙሉ ለሙሉ አለመተግበር (ከስልጤ እስከ ቁጫ ያሉ የማንነት ጥያቄዎች መቆሚያ ማጣታቸው)፣ የመሬት ፖሊሲው የአርሶ አደሩን የነፍስ ወከፍ የይዘት መጠን ከአንድ ሄክታር ማሳነሱ፣ የከተሞች ስራ-አጥነት በወጣት ከተሜ የተማሩ ልጆች ላይ መብዛቱ፣ በልማታዊ መንግስት ትግበራ እና በብሄር ፌደራሊዝም መሀከል የማይታረቁ ቅራኔዎች መኖራቸው፣ ከተሜነት እየተስፋፋ ሲመጣ በብሔር ፖለቲካ ሞት ላይ ግለሰባዊነት እንደሚነግስና ኢህአዴግም ይህንን ተቃርኖ ተከትሎ የርዕዮተ-ዓለም መሸጋሸግ ማድረግ የማይችል መሆኑ እና መሰል ተቋማዊ ክስረቶች በቀጣይ ሊያርማቸው የማይቻለው ታላላቅ ግድፈቶች በመሆናቸው እንደተለመደው ውጤቱ ቀድሞ የሚታወቀውን የይስሙላ ምርጫ ከመጠበቅ ይልቅ የአደባባይ ተቃውሞን ለማማተር ሥረ-ምክንያት ሊሆን መቻሉ አጠራጣሪ (አከራካሪ) አይደለም፡፡
ጉዳዩን በሚገባ ለማስረገጥ ከኢህአዴግ አጠቃላይ ህልውናዊ ባህሪ አኳያ ከላይ ከጠቀስኳቸው ነጥቦች ሊፈታቸው የማይቻላቸው ‹ብሎኖች› መሀከል ሶስቱን (ዋነኞቹ ናቸው ከሚል አረዳድ) በጨረፍታ በአዲስ መስመር እንያቸው፡፡
ያ ሁሉ ነጋሪት የተጎሰመለት የድህረ-ደርግ የዲሞክራሲ ሽግግር ‹ተስፋ› ሙሉ በሙሉ ሞት የታወጀበት አሁን በምንጠራው የ97ቱ ምርጫ ማግስት ነበር፡፡ ይህንንም ተከትሎ አቶ መለስ ‹ልማታዊ መንግስት› የሚል ሀልዮት ይዞ ብቅ ማለቱ ይታወሳል፤ በወቅቱ (1998 ዓ.ም ይመስለኛል) በማንችስተር ዩንቨርስቲ በመገኘት ቀጣዩ የስርዓቱ ማዋቀሪያ ምሶሶ አድርጎ ሃሳቡን ያብራራው የምርጫ ፖለቲካ፣ የሰብዓዊ መብቶችን እና መሰል ዲሞክራሲያዊ ዕሴቶችን ጨፍልቆ ‹በአብዮታዊ› መንገድ ልማት ማምጣትን ቀዳሚ ግቡ እንደሚያደርገው በመፎከር ጭምር ነበር፤ ይሁንና ፅንሰ-ሃሳቡን በቅርበት ስንመለከተው፣ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ አውድ፤ በተለይም ስርዓቱ ካነበረው ቋንቋ ተኮር ፌደራሊዝም ጋር በማይታረቁ ቅራኔዎች መሞላቱን ለመረዳት አያዳግትም፡፡
ለዚህ ክርክር ማስረገጫ ይሆን ዘንድም ከተቃርኖዎቹ ውስጥ ሁለት ነጥቦችን ብቻ እናንሳ፤ የመጀመሪያው ልማታዊ መንግስት ‹የዜጎች የክሂል ልቀትን በመንተራስ ብቻ የተሳለጠ ቢሮክራሲን መገንባትና ተቋማዊነትን ማጎልበት ያስፈልጋል› ከሚለው መደምደሚያ አንፃር ነው፤ በርግጥ ይህ ሃሳብ ስኬታማነቱ የታየው በአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ሀገራት ውስጥ ቢሆንም፣ በሙያ ብቻ ስርዓቱ ሲዋቀር ግን የተለየ የቡድን ጥቅሞችን ለማስፈፀም እንደማይመች ተግባራዊ ተሞክሮዎቹ ይናገራሉ፡፡ ከዚህ አኳያም የገዥው ፓርቲ የፌደራሊዝም ቅርፅ በግልባጩ የብሔር ማንነቶችን ተቀዳሚና ብቸኛ ተቋማዊነትን መገንቢያ አማራጭ ማድረጉ ከተጠቀሰው የልማታዊ መንግስት ጭብጥ ጋር በቀጥታ ያላትመዋል፡፡ እናም ከላይ እስከታች ያለው የስልጣን አወቃቀሩ የላቀ ክሂልን ረግጦ የብሔር ተዋፅኦን ለመጠበቅ በማለም ብቻ የተወሰነ ስርዓታዊ መልክ መያዙን ስንመለከት፣ ገዥዎቻችን ሀልዮቱን ለመተግበር ሲንቀሳቀሱ በሁለት ምርጫዎች ቅርቃር ውስጥ እንዲወድቁ መገደዳቸው የማይቀር ጉዳይ ሆኖ እናገኘዋለን፤ እነርሱም የፌደራሊዝሙን ቅርፅ ወደ መልከአ-ምድራዊ (Geographical) መቀየር፣ አሊያም ‹‹ልማታዊ መንግስት ነን›› የሚለውን አሰልቺ ፕሮፓጋንዳ አራግፎ መጣል የሚሉ ናቸው፡፡ ይህንን ደግሞ ኢህአዴግ
ከግትረኛነት ባህሪው አንፃር ይቀበለዋል ተብሎ አለመጠበቁ አንዱ ህልውናዊ ግድፈቱ ያደርገዋል፡፡
ሌላው ተጣራሽ ርዕሰ-ጉዳይ በስልጣን ኢ-ማዕከላዊነትና በማዕከላዊ መንግስት መጠናከር መካከል ያለው ነው፤ በሁለት አስርታቱ ስርዓታዊ ሙከራ፣ የበዛው ከወረቀት ላይ ባይዘልም፣ በጥቂቱም ቢሆን ኢ-ማዕከላዊ ለማድረግ ስለመጣሩ የምናውቀው እውነት ነው፡፡ ይሁንና የልማታዊ መንግስት ፅንሰ-ሀሳብ ማዕከላዊ አስተዳደሩ ሙሉ በሙሉ አጠቃላይ የስልጣን ገፆችን ጠቅልሎ እንዲይዝ ያስገድደዋል፡፡ ይህንንም ስልጣን በማከፋፈል ላይ የሚመሰረት ግጭት ህልውናዊ ድክመቱ አድርገን ልንወስደው እንችላለን፡፡
ሁለተኛው አስረጂ ጭብጥ የብሔር ማንነትን ዘላለማዊ የስርዓት መልክ ማድረጉ፣ ከከተሜነትና የከተሞች መስፋፋት ጋር አብሮ እየገነገነ ከሚመጣው ግለሰብኝነት (የግለሰብ መብትን ማስቀደም) ጋር ሊኖረው የሚችለው ግጭት ነው፡፡ በስነ-ማህበረሰብና ፖለቲካል ኢኮኖሚ አስተምህሮቶች መሰረት (በዋናነት በምዕራባዊ ሥልጣኔ)፣ የከተሜነት ዕድገት መገለጫ ኢህአዴግ ቀን-ከሌሊት እንደሚለፍፈው የፎቆች መደርደርና የመንገድ መስፋፋት ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም ከተሜነት ማለት ከጋርዮሽ ማንነት እየተላቀቁ በመምጣት የግል የሆኑ አለማዊ ዕይታዎችን በማጎልበት፣ በመረጡት ማንነትን መተርጎሚያ ፈር ከሚተሳሰሩ ዜጎች ጋር ህብረት መፍጠር የሚለው አንድምታ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ምክንያቱም በፆታ፣ በሙያ፣ በኃይማኖት አሊያም በተመረጠ ርዕዮተ-ዓለም ስር ምክንያተኝነትን ብቻ በመንተራስ ‹መደራጀት› የከተሜነት ቀዳሚ መለዮ ነውና፡፡ ይህንን ድምዳሜ በተለይም በአዲስ አበቤዎች ዘንድ እየመጣ ካለው የከተሜነት ባህሪ እና ከብሔር ፖለቲካው ጋር ስናስተያየው ‹‹የማይታረቀው ቅራኔ›› (በካርል ማርክስ አባባል) እነበረከት ስምዖን ፊት ይቆማል፡፡ ኢህአዴግ ይህ ተፈጥሮአዊ የማህበረሰብ ዕድገት እንኳ እንደሚገታው አለማሰቡ ከህልውናዊ ግድፈቶቹ አንዱ አድርገን ልንቆጥረው እንገደዳለን፡፡
ርዕሰ-ጉዳያችንን ለመጠቅለል የምጠቅሰው የመጨረሻው ማሳያ፣ ስርዓቱ የተነሳበትን የራስ ዕድል በራስ በመወሰን መብት ላይ ትገበራው የሚያሳየውን ሀሳዊነት ነው፤ ወታደራዊው ደርግ ይከተለው የነበረው ‹አሀዳዊ አስተዳደር›፣ ቋንቋን መሰረት ባደረገው ፌዴራሊዝም ከተተካ በኋላ ስለ ጉዳዩ ያጠኑ ምሁራኖች ‹‹የስልጤ ሞዴል›› እያሉ የሚጠሩትን ይህንን ጭብጥ፣ ግንባሩ እየመረጠ መስጠቱን የሚዘክሩ በዜጎች ደም የተፃፉ የዳጎሱ ታሪኮች ያረጋግጡልናል፡፡ እንደ ምሳሌም የሲዳማንና ሰሞኑን እየታዘብን ያለውን የቁጫን የማንነት ጥያቄዎች ብቻ መጥቀስ በቂ ይመስለኛል፤ ሲዳማ በሀገሪቱ ሕገ-መንግስት መሰረት ክልል ለመሆን የሚያስፈልጉትን መስፈርቶች ሁሉ ቢያሟላም የተሰጠው ምላሽ ለዓመታት ሞትና እስርን በጥያቄው አራማጆች ላይ እንደ ሐምሌ ዝናብ መዘርገፍ ሲሆን፣ ከሲዳማ ቁጥር በታች ያላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ደግሞ በክልል ደረጃ የመዋቀር መብታቸው ሲከበር ተመልክተናል፡፡ ይህንንም የተዛነፈ የመብት ትግበራን በመሰረታዊ የስርዓቱ ክሽፈትነት ልንቆጥረው እንደምንችል ይሰማኛል፡፡ የተቃውሞ መድረኩን ከውስጥም ከውጭም የሞሉት ኃይሎች ዋነኛ ጥያቄም፣ የብሔራችን መብት አልተከበረም የሚለው መሆኑ (በመጠኑ ላይ ባንስማማም፣ ቡድኖቹ ከየብሔራቸው ደጋፊ እንዳላቸው አይካድምና) ስርዓታዊ ሽንፈቱን ያበዛዋል፡፡ በአናቱም በስልጤው ሞዴል ግፊት ወደ አደባባይ የመጡት የወለኔና የቁጫ የማንነት ጥያቄዎች የሚጠቁሙት አንዳች ነገር ቢኖር፣ የስርዓቱ ቁንጮዎች የተጠቀሰውን ስታሊኒስታዊ የራስ ዕድል በራስ የመወሰን ጉዳይ በሕገ-መንግስታቸው ውስጥ ሲከቱት፣ ኢትዮጵያን በመሰለ ባለብዙ ቋንቋ ተናጋሪ ዜጎች ሀገር ጥያቄው ማቆሚያ እንደማይኖረው አለማሰባቸውን ነው፡፡
በእነዚህ የኢህአዴግ ታላለቅ ግድፈቶች ህላዊነት ከተስማማን የለውጥ መንገዱንም አንስቶ መነጋገሩ የግድ አስፈላጊ ነውና ወደዚያው እንለፍ፡፡
የከተማ አብዮት ሲባል…
በዚህ ተጠይቅ የምናየው አማራጭ የለውጥ መንገድ ያለንበት ሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን የሚበይነውን ሰላማዊ የከተማ አብዮት ብቻ ሳይሆን፣ ረዥም ዓመታትን ወደ ኋላ ተጉዘን በአማራጭነት ይተገበሩ የነበሩትንም ጭምር ነው፤ ምክንያቱም በኢትዮጵያችን ዛሬም ከተቃውሞ ስብስቡ መካከል ሁለቱንም ስልት የሚያቀነቅኑ የፖለቲካ ድርጅቶች መኖራቸው እውነት ነውና፡፡
ምንም እንኳ ጥያቄያቸው፣ አመሰራረታቸው እና የሚከተሉት ርዕዮተ-ዓለም ፍፁም የተለያየ ቢሆንም፣ ከኦነግ እስከ ኦብነግ፤ ከአርበኞች ግንባር እስከ ግንቦት ሰባት (ሁሉን አቀፍ የሚሉት ስልት እንደተጠበቀ ሆኖ) ድረስ የሚጠቀሱ ድርጅቶች ከከተማ አብዮት የ‹ማኦኢዝም›ን (ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረግ ጦርነት ላይ የሚያተኩር) የትግል ስልት እንደ ብቸኛ አማራጭ መውሰዳቸው የታወቀ ነው፡፡ ለዚህ ሁሉ ተቃውሞ መነሾ የሆነው ራሱ ኢህአዴግም ወደ ስልጣን የመጣበት መንገድ ሳይቀነስ ሳይጨመር ይኸው እንደነበረም አይዘነጋም፡፡
በኢትዮጵያ የፓርቲ ፖለቲካ መቀንቀን ከተጀመረበት 1960ዎቹ አጋማሽ አንስቶ የተመሰረቱ ግራ ዘመም ድርጅቶች በሙሉ ‹‹መንፈሳዊ አባት›› አድርገው የሚወስዱት የማኦ ዚዱንግ (Mao Zedong) የቻይና ኮምኒስት ፓርቲ (CCP) ለጥቂት ዓመታትም ቢሆን አራምዶት የነበረው የትግል ስልት ከከተማ ወደ ገጠር የሚነሳ እንደነበረ ይታወሳል፤ ይሁንና ሲሲፒ እ.ኤ.አ. በ1927 ዓ.ም. የፀደይ ወራት በሻንጋይ ሼክ (Chiang Kai-shek) ከሚመራው ‹‹Kuomintang›› (KMT)፣ የደረሰበትን ከባድ ወታደራዊ ጡጫ መቋቋም ተስኖት ከጠንካራ መሰረቶቹ ሻንጋይ እና ክንቶን (ዛሬ ስሟ ‹ጉዋንዡ› /Guangzhou/ በሚል ተቀይሯል) ከተሞች ወደ ገጠር ማፈግፈጉን ድርሳናቱ ይናገራሉ፡፡ ከዚህ በኋላም የእነ ማኦ ድርጅት ‹የሠራተኛ መደብ› የሚል አጀንዳውን አርቆ ሰቅሎ፣ እንደ አዲስ በገበሬ ሰራዊት በመዋቀር የትጥቅ ትግልን ከገጠር የመጀመር ጠቀሜታ ሰባኪ ብሎም የገበሬ አምባገንነት አቀንቃኝ ሆኖ ብቅ ማለቱን ከታሪክ ንባብ መረዳት ይቻላል፡፡ በነገራችን ላይ ሲሲፒ የስልት ለውጥ ከማድረጉ በፊት ከ11 ሺ ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት የሚሸፍነውን ‹‹ረጅሙ-ጉዞ››ን (Long march) በፅናት መጨረሱ የዓላማ ፅናቱን ያሳያል፡፡
እነ ማኦ ለመስማት ከሚዘገንነው መስዋዕትነት በኋላ ለሥልጣን የበቁት ድርጅታቸው በተመሰረተ በሃያ ስምንተኛ አመት (እ.ኤ.አ. በ1949 ዓ.ም) ነበር፡፡ ከዚህ በኋላም በተለያዩ የዓለማችን ሀገራት የሚኖሩ ሕዝቦች ‹ጭቆናን ለማስወገድ› በሚል ‹ግራ ዘመም› ድርጅት መስርተው በእምቢተኝነት ሲያምፁ፣ ማኦኢዝም የትግል ስልት የሚበይነውን በገበሬዎች በተደራጀ ሰራዊት ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረግ ሽምቅ ውጊያን እንደሁነኛ አማራጭ መከተላቸውን ታሪክ ይነግረናል፡፡ በአናቱም የማኦ አስተምህሮ ‹በገበሬ አብዮት› የሚመሰረትን የ‹እርሻ መር ኢኮኖሚ ማህበረሰብ› (Agrarian society) መፍጠርን እና የከተሞችን ፖለቲካል ኢኮኖሚ በማፈራረስ የገበሬውን ሁለንተናዊ ከፍታ ማረጋገጥ ላይ ማተኮሩ በዚህ መንገድ ወደ ሥልጣን የወጡ ገዥዎቻችንን ባህሪ ለመዳኘት ይረዳናል፡፡
እነሆም በዚህ ትውልድ መቀመጫቸውን በሀገራችን የጠረፍ ከተሞች አሊያም በአውሮፓና አሜሪካ ያደረጉ ብረት ያነሱ ድርጅቶች ከላይ በተጠቀሰው የታሪክ ንባብ ከተመዘኑ፣ አንድም የመረጡት የትግል ስልት ዘመኑን የሚዋጅ ነው ብሎ ለመቀበል ያዳግታል፤ ሁለትም በለስ ቀንቷቸው ያሰቡት መሳካት ቢችል እንኳ፣ በእንዲህ አይነት መልኩ ባንክ ዘርፈው፣ መሰረተ ልማቶችን አውድመው፣ ንፁህን ዜጎችን ለህልፈት ዳርገው፣ የቅርብ ጓደኞቻቸውን ሰውተውና ጠብ-መንጃ ተሸክመው ወደ ቤተ-መንግስት የሚመጡበት መንገድ፣ ከዓመታት በፊት መለስና ጓዶቹ ‹ታግለናል፣ ሞተናል፣ ደምተናል… እናም ምርጥ ምርጡ ለእኛና ለቤተሰቦቻችን ብቻ› በሚል ድምዳሜ ካዘጋጁት ‹መፅሀፍ› አንድ ገፅ ገንጥለው ‹‹የሞትንም እኛ፤ ያለንም እኛ…›› ወደሚል የአምባገነኖች ጠርዝ መገፋታቸው አይቀሬ ይመስለኛል፡፡
በተጨማሪም ‹‹ጨቋኝ ጨቋኝን ሊተካው ይችላል›› እንዲል አርስቶትል ኢህአዴግ ለአስራ ሰባት ዓመታት በዱር-በገደል ወጥቶና ወርዶ፣ አስከፊ መስዋዕትነትን ከፍሎ፣ አራት ኪሎ ከደረሰ በኋላ፣ ያነበረው ስርዓት ካመፀበት የመንግስቱ ኃይለማርያም አስተዳደር ጋር ያለው ልዩነት የስም ብቻ መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡ ይህ ሁኔታም ነው በብረት የታጠረ፣ ደም አፋሳሽና የተናጥል አሸናፊነትን በሚያውጅ ስብከት ላይ ብቻ የተገነባው የትግል ትርጓሜ ዛሬም እንደአዲስ የመከለሱ ዜና በስጋት ያነጠበን፡፡ በርግጥም የጭቆናን ሸክም ከትከሻ ለማውረድ ሲባል የተካሄዱ መራራ ትግሎች ውጤታቸው ጨቋኞችን መቀያየር መሆኑና የትንቅንቁ ወራቶች መርዘም ያስከተሉት ኪሳራዎች ከዘመኔ ቀድሞ የነበረውን የማኦን መንገድ የታሪክ መዛግብት ላይ ብቻ ተወስኖ እንዲቀር በመገደብ ለአማራጭነት እንኳ እንዳይበቃ አድርገውታል፡፡ የዚያን ዘመን የጨቋኞች አገዛዝ ውርስን ለመከተል ወቅቱ አመቺ አለመሆኑንና የሥልጣን ወንበርን ለጊዜውም ለማሰንበት ዘመን-ወለዱን አመቻማች አምባገነንትን መጠመቅ ማስፈለጉም የትግሉ ስያሜ በድጋሚ ለብይን እንዲቀርብ ተጨማሪ ኃይል ሆኗል፡፡ ርዕዮተ-ዓለማዊ ልዩነቶች እስኪዘነጉ ድረስ መጥበባቸው፣ ክስተቶች ከአንድ ሀገር ድንበር መዝለላቸው እንዲሁም ወቅታዊዎቹ የለውጥ ስኬቶች በጋራ የቀድሞውን የአብዮት መስመር በጥርጣሬ እንድንመለከተው ፈርደውበታል፡፡ ዛሬ ላይ አብዮት ቃሉ ብቻ እስኪቀር ድረስ ተነቅሎ ነባር የመዳረሻ መንገዶቹ ፈራርሰዋል፤ በፍርስራሹ ላይም አዲስ ትርጓሜ ተቸክችኮበታል፡፡
እነዚህና መሰል ሁነቶች የለውጡን መንገድ ለመቃረም ፊታችንን ወደ አውሮፓውያኖቹ የ‹ብርቱካናማ› እና የ‹ፅጌረዳ› አሊያም ወደ አረቡ የ‹ፀደይ› አብዮት እንመልስ ዘንድ ያስገድዱናል፡፡ ይህ ግን እነ ሌኒን ያራምዱትና ይመክሩት ከነበረው በከተሞች ውስጥ ከሚደረገው የትጥቅ ትግል ፍፁም የተለይ ይመስለኛል፡፡ በርግጥም እንዲህ አይነቱ አማራጭ በ1966ቱ አብዮት ማግስት በራሳችን ሰዎች ተሞክሮ ከመክሸፉም በላይ ሀገሪቱን ወደ ቀለም ሽብር ከቷት መቼም ሊተካ የማይችል ዋጋ ማስከፈሉ ሁሌም በቁጭት የምናስበው ታሪካችን ነው፡፡ እናም ለእኔ ትውልድ የለውጥ ጥያቄ ከሰላማዊው የከተማ አብዮት ውጪ ያሉ አማራጮች ከጠቀሜታቸው ይልቅ ጥፋታቸው አመዝኖ ነው የሚታየኝ፡፡ በተለይም ነባሩን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል (የ‹ጦር አርበኝነት›ን በ‹ሲቪል ጀግንነት›) ለመቀየርም ሆነ፣ ከእርስ በርስ እልቂት፣ ከደም መፋሰስ፣ ከደካማው ኢኮኖሚ መንኮታኮት፣ ካለመረጋጋት… ለመታደግ ብቸኛ መፍትሄ ይኸው ነው፡፡ በተጨማሪም ከከተማ መነሳቱ ለአገዛዙ ምሰሶ፤ ለሀገሪቱ ደግሞ ስጋት የሆኑትን የሃይማኖት እና ብሔር (ቋንቋ) ልዩነቶችን ተሻግሮ፣ በአንድ ሀገር በእኩል ማንነት ላይ የሚያሰባስብ ኃይል ይፈጥራል ብዬ አስባለሁ፡፡
በነገራችን ላይ ለእንዲህ አይነቱ አደገኛ ስጋት መቃረባችንን የሚያሳየው በይበልጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከተቃውሞ ስብስቡ አካባቢ የሚሰማው ከሀገር ይልቅ የትውልድ መንደርን የማስቀደም ድምፅ ነው፡፡ ይሁንና ይህ መንገድ የትም ሊያደርስ ካለመቻሉም በላይ ላለፉት ሃያ ዓመታት የጭቆና ቀንበርን ትከሻችን ላይ እንዲከርር አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ እናም ወደ ተናፋቂው የነፃነት ምኩራብ ሊያደርሰን የሚችለው ድምዳሜ ስርዓቱ ትግራይን ከኦሮሚያ፣ ወይም ከአማራ… የበላይ አድርጎ ያስተዳድራል ለሚሉ ከፋፋይ አሉባልታዎች ጆሮ መንፈግ ብቻ ነው፤ የአንዳንድ ብሔር ተኮር ድርጅት አፈ-ቀላጤዎችም ንጉሳዊውን ዘመን የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ወኪል ለማስመሰል መሞከራቸውም ሆነ ህወሓት የተሰኘው የማፍያ ቡድን የሚፈፅመውን ግፋአዊ አገዛዝ በየትኛውም መስፈርት ከትግራይ ህዝብ ጋር ለማያያዝ የሚያደርጉትን ጥረት ማክሸፉ ከአብዮቱ ቅድመ ዝግጅቶች አንዱ ይመስለኛል፡፡
የሆነው ሆኖ ‹አብዮት የራት ግብዣ አይደለም› እንዲል ማኦ፣ አሁን እየተናገርንለት ያለው ሰላማዊው የከተማ ተቃውሞ የጠብ-መንጃውን ያህል ባይሆንም እንኳ ዋጋ ማስከፈሉ አይቀሬ መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡ በየትኛውም ሀገር ያሉ አምባገነን ገዥዎች በሕዝባዊ እምቢተኝነት አደባባይ የወጡ ተቃዋሚዎቻቸውን ወደ ቤተ-መንግስታቸው እንዲገቡ ሲፈቅዱ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም፡፡
እንዲያውም በግልባጩ በጦር ሠራዊትና በደህንነት ኃይል ለማስፈራራት ሲሞክሩ፣ ከተቃዋሚዎቻቸው የተወሰኑትን በመቀጣጫነት በጥይት ሲያስደበድቡ፣ አስተባባሪዎቹን ሲያስሩ፣ የአገዛዛቸውን የብረት መዳፍ ይበልጥ ሲያጠነክሩ… ይስተዋላሉ፡፡ ይሁንና ይህ አይነቱ የጭካኔ እርምጃ አምባገነኖችን ከአብዮቱ ወላፈን ሊታደጋቸው አለመቻሉን ማረጋገጥ ካስፈለገ ቱኒዝያ ጥሩ ማሳያ ትመስለኛለች፡፡ አደባባዩን ከማማተር አስቀድሞ ግን አብዮቱ መያዝ ስለሚገባው ባህርያት ጥቂት ነጥቦችን ማንሳት ሳያስፈልግ አይቀርም፡፡
የለውጡ መስመር አንዱ መለዮ መሆን የሚኖርበት የትኞቹንም ጨቋኝ ህጎችን በአደባባይ መጣስ ነው፤ እዚህ ቦታ ለመሰለፍ ጠይቀን ተከለከልን፤ ደጋፊዎቻችንን እንዳንሰበስብ አዳራሽ አጣን… እና መሰል ቀልዶችን በመተው አዋጆቹን (እንደ ፀረ-ሽብር እና የፕሬስ አዋጅ ውስጥ ያደፈጡ ቀፍዳጅ አንቀፆችን) በግላጭ በመጣስ በገፍ ወደዘብጥያ ለመውረድ መወሰን የአብዮቱ ዋና አካሄድ መሆን የሚኖርበት ይመስለኛል (በዚህ አውድ አንድ የቢሆን ምሳሌ እናንሳ፤ አሁን ካሉት ህጋዊ ፓርቲዎች መካከል አንዱ በአንድ ክፉ ቀን የፓርቲው የህጋዊነት ማረጋገጫ በሎሌው የምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት ቢሰረዝና እኛም አማራጭ አካሄዶችን ስለማሰላሰላቸው ብንጠይቅ፣ ‹‹ጨዋታው ፈረሰ…›› ብለው ወደየቤታቸው ገብተው ይቀመጡ ይሆናል ከሚለው ውጪ የምናገኘው ምላሽ ምን ሊሆን ይችላል?)
ሌላኛው ነጥብ ቡድናዊ መሰባሰቢያ መስፈርቶችን ይመለከታል፤ በአረቡ ፀደይ እንዳስተዋልነው (ስለአረቡ ዓለም አብዮት ባህሪያት ከፍትህ ጋዜጣ እስከ ፋክት መፅሄት ድረስ በተደጋጋሚ ሊብራራ ተሞክሯልና እዚህ መድገም አያስፈልግም) የፆታን፣ የኃይማኖትን፣ የመደብን፣ የአንድ ርዕዮተ-ዓለምን አሊያም የብሄር ልዩነቶችን በመሻገር ሁለንተናዊ የዜግነት ነፃነቶችን መሻትን ብቻ ማዕከል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ሁለንተናዊ የዜግነት ነፃነቶች ሲባል ደግሞ የኃይማኖት፣ የፖለቲካና የሲቪል መብቶች መከበር ማለት መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ የትኞቹንም የቡድንም ሆነ ግለሰብ ተኮር ጥያቄዎች ይህንን ነፃነት በማስከበር ትግል ውስጥ ማስመለስ እንደሚቻል መታወቁ የአብዮቱን መሪ ቡድኖች መልከዓ-ባህሪ በዜግነት ላይ ብቻ እንዲቆም ያደርገዋል፤ ይህ ክንውንም፣ በአንድ በኩል የስርዓቱን የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ሲያከሽፍ፣ በሌላ በኩል የተሻለች ሀገር ለማቆም የማይነቃነቅ ጠንካራ መሰረት ይጥላል (በነገራችን ላይ ከዚህ ቀደም ፋክትን ጨምሮ በአራቱም የህትመት ውጤቶች ያነሳኋቸው የፈራ ይመለስ፣ ሞት የማይፈሩ ወጣቶች፣ ለምን ትፈራለህ? የታህሪር ናፍቆት፣ የዘገየው አብዮት፣ የግፉአን ዕድሜ ምን ያህል ይረዝማል? አደባባዩ ምን ያህል ይርቃል? የመሳሰሉት ቀዳሚ ድምፆች በዚህ አይነቱ ሰላማዊ የከተማ
አብዮት የሚበየኑ መሆኑን ማስታወስ ያስፈልጋል)
የአብዮቱ ግቦች…
በጥቅሉ እዚህ ድረስ ስንነጋገርበት የነበረው የከተማ አብዮት እንደ ሊቢያ ወይም ሶርያ ለእርስ በእርስ እልቂት የሚዳርግ ደም አፋሳሽ አለመሆኑ ግልፅ ይመስለኛል፡፡ በዚህ አውድ ትኩረት ሊሰጥበት የሚገባው አንኳር ጉዳይ የአረቡን መነቃቃት ተከትሎ በሞሮኮ፣ የመን እና ኳታር እንደታየው አይነት፣ ከስር ነቀል ለውጥ ይልቅ የፖለቲካ ማሻሻያዎች እንዲደረጉ የአምባገነኑን አገዛዝ እጅ መጠምዘዙ ላይ ነው፤ ይህ ይሆን ዘንድም የሚከተሉት ጥያቄዎች ወደ አደባባይ መሰባሰብ የሚያስችሉን የጋራ አጀንዳ (የአብዮቱ ግቦች) ቢሆኑ ለስርዓቱ ‹‹የወንድ በር››፤ ለምንወዳት ሀገራችን ደግሞ የተስፋውን መንገድ ጠራጊ የሚሆኑ ይመስለኛል፡፡
ከፊታችን ያለው የ2007ቱ አምስተኛ ዙር አገር አቀፍ ምርጫ ከመደረጉ በፊት፣ ያን ጊዜ የ97ቱ ቅንጅት ፓርላማ ለመግባት በቅድመ ሁኔታነት አንስቷቸው የነበሩትን ከፊል ጥያቄዎች ጨምሮ ሌሎችም በዚህ ፅሁፍ የተካተቱ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣቸው ዘንድ ከሥራ ማቆማ አድም አንስቶ ከአገዛዙ ጋር አለመተባበርን የሚያካትትና ለውጡ እስኪመጣ በተከታታይ (በብሔር አግላይ ያልሆነ) መሬት አንቀጥቅጥ የተቃውሞ ሰልፍ መሰል እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ራስን ማዘጋጀት ይጠይቃል፤ ጥያቄዎቹም የሚከተሉት ናቸው፡-
1/ ሁሉንም የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር መፍታት፤
2/ እስከ ዛሬ ድረስ በሀገር ጥቅም ላይ ለተፈፀመው ጥፋትም ሆነ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ለደረሰው ጅምላ ጭፍጨፋ፣ እስር፣ እንግልት፣ አካል መጉደል እና ስደት ኃላፊነት ወስዶ በአደባባይ ይቅርታ መጠየቅ (ካሳ የሚገባቸውን መካስ)፣ ለብሔራዊ ዕርቅ መደላድል መፍጠር፤
3/ አፋኝ የሆኑትን የፀረ-ሽብር፣ የፕሬስ፣ የመያዶች እና የፖለቲካ ማሻሻያ አዋጆችን መሻር፤
4/ ዜጎች በሚያምኑበት የፖለቲካ አስተሳሰብ የመደራጀት መብታቸውን ያለአንዳች ገደብ መልቀቅ፤
5/ ከሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በእኩል ደረጃ መወያየትና መደራደር፤
6/ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድን ነፃና ገለልተኛ መሆኑን በሚያረጋግጥ ሁኔታ እንደገና ማቋቋምና የአቅም ብቃቱን መገንባት፤
7/ ፍትሐዊ የመንግስት ሚዲያ አጠቃቀም እንዲኖርና የግል የኤሌክትሮኒክስም ሆነ የህትመት ሚዲያዎች ያለ ከልካይ እንዲኖሩ መፍቀድ፤
8/ የፍ/ቤትን እና የሌሎች የፍትህ አካላትን ነፃነት ማረጋገጥ፤
9/ የፖሊስ፣ የመከላከያና የደህንነት ተቋማት ከፖለቲካ ገለልተኛ እንዲሆኑ ማድረግ፤
10/ ከላይ የተጠቀሱትን ጉዳዮች ተፈፃሚ የሚያደርግ ለየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት የማይወግን ነፃ የሆነ አካል ማቋቋም የሚሉት
ጥያቄዎች የመንደርደሪያ ነጥብ መሆን የሚችሉ ይመስለኛል፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

ታዋቂው ሙዚቀኛ አሊ ቢራ ከነጃዋር ጋር በኦሮሞ ፈረስት ካምፔን ውስጥ መሳተፍ አነጋጋሪ ሆንዋል

January6/2013
ኦሮሞ ፈርስት በሰሜን አሜሪካ ባሳተመው ፖስተር ላይ አሊ ቢራ አብሮ መውጣቱ ጉዳዩን አነጋጋሪ አድርጎታል:: አቶ ዶር አሊ ቢራ በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ክብር ያለው ግለሰብ ሲሆን አሁን በዚህ እድሜው በለየለት የዘረኝነትና የሀይማኖትን  እልቂት ከሚሰብከው ጃዋር  ጋር መሳተፉ ጉዳዩን አሳዛኝ ያደርገዋል:: በርግጥ አቶ አሊ ቢራ ከጃዋር ጋር በሀይማኖትም በዘርም ሚዛመዱ በመሆናቸው የቅርብ ግንኙነት እንዳላቸው ሚታወቅ ነው:: ሆኖም ግለሰቡ ካለው የህዝብ ፍቅርና እድሜ  አንጻር እንዲህ አይነት በለየለት የዘር ና ሀይማኖትን በአደባባይ ከሚሰብክ ግለሰብ ጋር አብሮ በአደባባይ ይሰራል የሚል ግምት አልነበረም:: ኢትዮጵያውያን ይህንን በአመክሮ እንዲያዩት እንመክራለን
url-1