Monday, March 23, 2015

የሕወሓት መንግስት በኤርትራ ላይ የአየር ጥቃት ፈጸምኩ የሚለው ቅዠት ነው ተባለ * “እንኳን የአየር ድብደባ ይቅርና ሞቅ ያለ ጭብጨባም አልተሰማም

March 23,2015
ዘ-ሐበሻ) የሕወሓት መንግስት በኤርትራ በማይ እዳጋ የሚገኘው የሚሻዕ ወርቅ ማዕድን ካምፓኒ ላይ የአየር ጥቃት አደረስኩ ብሎ ከገለጸ በኋላ የኤርትራ መንግስት በኢትዮጵያ ምንም አይነት ጥቃት እንደደረሰበት የገለጸው ነገር አልነበረም:: አስመራ የሚገኙ የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንደሚሉት ከሆነ በማይ እደጋ እንኳን የአየር ድብደባ ይቅርና ሞቅ ያለ ጭብጨባም አልተሰማም::
Vandalism
በኤርትራ ይህን የወርቅ ማዕድን የሚያወጣው የካናዳው የማዕድን አውጪ ድርጅት (NEVSUN RESOURCES LTD) ማምሻውን በድረገጹ (www.nevsun.com) ባወጣው መግለጫ የአየር ጥቃት እንደደረሰበት አልገለጸም:: ድርጅቱ ማርች 13 ቀን 2015 ልክ በማንኛውም መስሪያ ቤት እንደሚደርስ አደጋ መጠነኛ መሰባበር የደረሰበት ቢሆንም ጥገና አድርጎ ወደ ስራ እንደሚመለስ ገልጿል:: ይህ ጉዳት የደረሰበት የሕወሓት መንግስት እንደሚለው በአየር ጥቃት እንደሆነ ካምፓኒው ያስቀመጠው ነገር የለም::
የሕወሃት መንግስት ለምን ይህ ዜናን ማሰማት ፈለገ? የሚለውን ዘ-ሐበሻ ወደ አስመራ ምንጮቿ ጋር ደውላ የነበረ ሲሆን ምንጮቹም “የሕወሓት መንግስት ይህን ዜና ማሰራጨት የፈለገው ከፍራቻ የተነሳ ነው:: በዚህ በሚሻዕ የወርቅ ማዕድን ማውጫ በማንኛውም ድርጅት ውስጥ እንደሚፈጠር መጠነኛ የማሽኖች መሰባበር አደጋ መፈጠሩን የወያኔ ደህነንቶች መረጃ አላቸው:: የዚህ ድርጅት አካባቢ ደግሞ የኢትዮጵያ ነፃነት ታጋዮች የሚገኙበት ወታደራዊ ካምፖች አሉ:: አደጋው ከደረሰ ከአንድ ሳምንት በኋላ የሕወሓት መንግስት በኤርትራ ላይ የአየር ጥቃት እንደፈጸመ ማውራቱ ከገባበት ውጥረት የሕዝቡን አመለካከት ለመቀየር ነው” ብለዋል::
በተለይም በጎንደር አካባቢ በሕወሓት ወታደሮች እና በጎንደር ሕዝብ መካከል በተፈጠረው ውጥረት በዛሬው ዕለት 4 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎና ሰሞኑንም ሕዝቡ ጠመንጃ እየያዘ ጫካ እየገባ በመሆኑ ይህን ለማስቀየስ የሕወሓት መንግስት የቀየሰው የፕሮፓጋንዳ ስልት ነው ሲሉ እነዚሁ ወታደራዊ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል::

Sunday, March 22, 2015

ማንኛውም ተቃዋሚ ድርጅት ስርዓት ከሌለው ከርቸሌ እንከተዋለን የሚል ማስፈራርያ ኃይለማርያም ደሳለኝ አሰሙ

March 22,2015
ማንኛውም ተቃዋሚ ድርጅት ስርዓት ከሌለው  ከርቸሌ እንከተዋለን ይህንንም ለማድረግ አቅም አለን የሚል ማስፈራርያ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ አሰምተዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ትናንትና በጅማ ከተማ ተገኝተው ይህን አድርገን ነጻነት አመጣን ዲሞክራሲን እየቀዳን ለህዝቡ አከፋፈልን አሉ። የጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪወች እንዳደረሱኝ መረጃ ከሆነ ሚኒ ኃይለማርያም ኔትወርክ አዘግተው በጅማ ዩኒቨርስቲ ውስጥ አድረዋል ።

ከንግግራቸው ውስጥ ፈገግ ካሰኘኝ ልለፍ ፣ሚኒ ኃይሌ እንዲህ አሉ ማንኛውም ተቃዋሚ ድርጅት ስርዓት ከለለው አቅም አለን ከርቸሌ እንከተዋለን አቤት አቤት ወግ መዓረጉ እንዳይቀር እኮ ነው የትኛው አቅም ነው ? ትልቅ መስኮት የሌለው ቤት ሰርቶ እስረኛ ማጠራቀሜውን ነው ፣ሠላማዊ ሰልፍ ሲወጣ ንጹህን ህዝብ በፖሊስ ማስደብደቡን ነው ?? ድንቄም አቅም አያ!!!!! ባዶ እጁን ከሚታገል ህዝብ ጋር መሳሪያ ታጥቆ አቅም አለን ሲል ከአንድ መሪ ተብሎ ከተወከለ አሻንጉሊት የማይጠብቅ የቂል ንግግር ።
የዩኒቨርስቲ ተማሪወችን ስብሠባ እንዳይካፈሉ አግደዋቸዋል ።

አቅማችሁን ለኤርትራ መንግስት አሳዩ እንጅ ከእኛ ላይ ቦተሊካችሁን አትንፉብን ።

ለማንኛውም በተያየዘ ዜና ላይ በኤርትራ የጦር ማካማች ሎጀስቲካ ላይ ያአደረሱት የአየር ጥቃት መግለጫው ጅማ ላይ ሳይሆን ቢቢሲ ወይም አልጀዚራ ላይ ቢሆን አሸናፊነትን አልያ ውድቀትን ሊያመጣ ይችላል እንላለን።

ሠላማዊ ትግላችን ነፃነት እስኪታወጅ እኩልነት እስኪሰፍን ይቀጥላል! – የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ

Marrch 22,2015
የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ በሃገራችን ኢትዮጵያ አስተማማኝና ዘለቄታዊ ሠላም፣ እኩልነት፣ ፍትህና፣ የፖለቲካ መረጋጋት ይሰፍን ዘንድ ቀና ራዕይ አንግበው በተሰባሰቡ ወጣት ኢትዮጵያውያን የተመሰረተ፤ በሃገራችን ብቸኛው በወጣቶች የተገነባና የሚመራ ንቅናቄ ነው። ንቅናቄአችን ላለፋት አመታት የንቅናቄውን አቅም ለማጐልበት፤ ሰፊና ጠንካራ መሰረት ያለው ሁለገብ ተቋም ለመገንባት፤ የድርጅታዊ መዋቅሩን ጨምሮ ሌሎች ወሳኝ መሰረታዊ የማስፋፋትና የማደራጀት ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል። በመሆኑም ዛሬ ንቅናቄያችን ከአምባገነኑ የህወሓት/ኢህአዴግ የደህንነት መረብ የፀዳ፤ እራሱን ከማንኛውም የውስጥና የውጭ ጥቃት በአስተማማኝ ሁኔታ የመከላከል ብቃት ያለው፤ በርካታ እንቅስቃሴዎችንና ዲሲፕሊኖችን በተቀናጀ መልኩ ማከናወን የሚችል ጠንካራ ተቋም መሆን ችሏል።
የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ ከአጠቃላይ የህዝብ ብዛት ከ75% በላይ የሚሆነው ወጣቱ በመሆኑ፤ ይህ ወሳኝ የህብረተሰብ ክፍል የዲሞክራሲ ሥርዓትን ለመመስረትና ለማጐልበት በሚደረግ ትግል ውስጥ ግንባርቀደም ሚና የመጫወት ትውልዳዊ ሃላፊነት እንዳለበት በፅኑ ያምናል። በመሆኑም ንቅናቄአችን ይህን ፅኑ እምነት መሰረት በማድረግ፤ ወጣቱ ትውልድ ሃላፊነት የመረከብና በብቃት የመወጣት፤ እንዲሁም በተደራጀ መልኩ በጋራ የመሥራትና ለውጤት የመብቃት ሙሉ አቅሙ እንዲኖረው ለማስቻል መጠነ ሰፊ እቅዶችን ነድፎ በመተግበር፤ የወጣቱን እምቅ ችሎታና ብቃት በተግባር አስመስክሯል። ንቅናቄአችን ከተመሰረተበት ከ2003 ዓ.ም. ጀምሮ በርካታ ተግባራትን ያከናወነ ሲሆን፤ በተለይ በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገራት የሚኖሩ ወጣቶችን ወደተመሰረተለት ታላቅ ራዕይ ለማምጣት የግንኙነትና የመረጃ ልውውጥ መረብ በመሆን፤ ብሎም በአለም ዙሪያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን በስሩ በማደራጀትና በማንቃት ለሃገር ተቆርቋሪ ዜጋን በአስተማማኝ ሁኔታ መገንባት ችሏል።
የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ በሃገሪቱ ዲሞክራሲያዊ ስርአትን ለማስፈን በሚደረገው ትግል የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማበርከትና የተነሳለትን ታላቅ ራዕይ እውን ለማድረግ፤ ከሌሎች የፖለቲካ፣ የሲቪክና፣ የሰባዊ መብቶች ድርጅቶች ጋር በመተባበርና ጠንካራ ስምምነቶችን በመመስረት በስፋት እየሰራ ይገኛል። ንቅናቄአችን በሰላማዊ የትግል ስልት በሃገራችን ለውጥ እንዲመጣ ከሚታገል ማንኛውም ተቋም ጋር በመተባበርና በመደገፍ በርካታ ተግባራትን ያከናወነ ሲሆን፤ በተለይ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላለፉት ሦስት ተከታታይ አመታት ባካሄዷቸው ሠላማዊ መብትን የመጠየቅና የማስከበር እንቅስቃሴዎች የሚሠማውን ከፍተኛ አድናቆት እያስታወቀ፤ በቀጣይ ለሚያደርጉት ሠላማዊ እንቅስቃሴዎች ሁሉ፤ አባላቱን በማስተባበርና ሙሉ ሃይሉን በመጠቀም ስኬታማ እንዲሆን የሚሰራ መሆኑን ከወዲሁ ቃል በመግባት ያረጋግጣል። ከዚህም በተጨማሪ በወጣቶች የተገነባውን የሰማያዊ ፖርቲን በአዲስና በተቀናጀ መልኩ ድጋፍ ለመስጠት ሰፋ ያለ እቅድ ይዞ ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን በሙሉ ልብ ያረጋግጣል።
የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ አባላት፤ እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ ወጣት ሆይ፤ ዛሬ ሃገር እያለህ እንደሌለህ፤ መስራት እየቻልክ ተመፅዋች፤ ተምረህ ራስክን ማሻሻል እየቻልክ እድሉን ተነፍገህ፤ በችሎታህ ሳይሆን ለገዢው መደብ ባለህ ቀረቤታ ከሃገርህ ማግኘት የምትችላቸው እድሎችህን ሁሉ ተነጥቀህ፤ እጣ ፈንታህ በጥቂት ግለሰቦች በጐ ፈቃድ ስር ብቻ መውደቁን ካንተ በላይ የሚያውቀውና የሚገነዘበው የለም። በመሆኑም ሳትፈልግ የተጫኑብህ ምስቅልቅልና ጥልቅ ችግሮችን አስወግደህ፤ በተሻለ የህይወት ተስፋ የመተካት አቅሙም ጉልበቱም ያንተ ነውና፤ ከዛሬ ጀምሮ ቆርጠህ በመነሳት፤ ብሎም ከሰማያዊ ፓርቲ ጐን በፅናት በመቆምና ሙሉ ድጋፍ በመስጠት፤ እንዲሁም የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ትግልን የሚመራው አካል (ድምፃችን ይሰማ) አመራር ፍፁም ሠላማዊና በሳል መሆኑን ስለምትረዳው፤ በመሆኑም የሚቀርበው የአመራር ብቃት ነፃነትህን ለማስከበር በቂ የትግል ስትራተጂ እንደሆነ ስለሚታመን፤ የሚካሄደውን ትግልና የሚተላለፈውን የትግል መመሪያ በቅርበት በመከታተልና ተግባራዊ በማድረግ፤ ወደ ታሪካዊው የለውጥ ጐዳና በሙሉ ልብ ተቀላቅለህ ታሪካዊ ሃለፊነትህን ትወጣ ዘንድ፤ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ በአክብሮት ሃገራዊ ጥሪውን ያቀርባል።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄunnamed

ሦስት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ግንቦት ሰባትን ለመቀላቀል ድንበር ሊያቋርጡ ሲሉ መያዛቸው ተሰማ

March 22,2015
‹‹ቤተሰቦቻቸው ምግብና ልብስ ማስገባታቸውን ሰምተናል›› ሰማያዊ ፓርቲ
semayawi63-300x252የሰማያዊ ፓርቲ የአደረጃጀት ጉዳይ ምክትል ኃላፊ የነበሩት አቶ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ፣ የምክር ቤት አባል የነበረችው ወ/ሪት ኢየሩሳሌም ተስፋውና የሕዝብ ግንኙነት ኮሚቴ አባል አቶ ፍቅረ ማርያም አስማማው ትክክለኛ ቀኑ ባይታወቅም፣ ከሁለት ሳምንታት በፊት ድንበር አቋርጠው ኤርትራ በመግባት ግንቦት ሰባትን ሊቀላቀሉ ሲሉ መያዛቸው ተሰማ፡፡
የፓርቲው አባላት በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ ፍርድ ቤት ቀርበው የ28 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው መሆኑ እየተነገረ ቢሆንም መቼ፣ እንዴትና በማን ተይዘው የትኛው ፍርድ ቤት እንደቀረቡ ሪፖርተር ለማጣራት ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡
በቁጥጥር ሥር ውለዋል ስለተባሉት ሦስቱ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ጉዳይ ማብራሪያ እንዲሰጡ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ፣ የፓርቲያቸውን አባላት መታሰር የሰሙ ቢሆንም በቂ መረጃ እንደሌላቸው ገልጸዋል፡፡ የተጨበጠ ነገር ማግኘት እንደተሳናቸው የሚናገሩት አቶ ዮናታን፣ ቤተሰቦቻቸው ምግብና ልብስ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማዕከል (ማዕከላዊ) እንደወሰዱላቸው መስማታቸውን ጠቁመው፣ በአካል ያግኟቸው አያግኟቸው ግን እንዳላወቁ አስረድተዋል፡፡
እሳቸው ግን መቼ እንደታሰሩና የት እንደታሰሩ አለማወቃቸውንና ከ15 ቀናት በፊት ሌላ የፓርቲው ተወዳዳሪ ዕጩ መታሰሩን አስታውሰው፣ ምናልባት በዚያን ጊዜ ታስረው ሊሆን እንደሚችል ገምተዋል፡፡ በቁጥጥር ሥር የዋሉት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሁዳዴን ፆም በጸሎት ለማሳለፍ እንደሄዱ የሚናገሩት አቶ ዮናታን፣ የትና መቼ እንደሄዱ ግን ግልጽ አላደረጉም፡፡ በቁጥጥር ሥር ውለዋል የተባሉት አባላት ቀደም ባሉት ጊዜያት ንቁ ተሳትፎ የሚያደርጉና በፓርቲው ውስጥ ኃላፊነት የነበራቸው ቢሆንም፣ በአሁኑ ጊዜ ግን ከኃላፊነት ተነስተው አባል ብቻ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡
አቶ ፍቅረ ማርያም ግን እስካለፈው ሳምንት ድረስ ሥራ ላይ እንደነበሩ አቶ ዮናታን ጠቁመዋል፡፡ ‹‹ብዙ ሰዎች በየድረ ገጹ ብዙ ነገር ይጽፋሉ፡፡ ትክክለኛውን ነገር ግን ማግኘት አቅቶናል፤›› የሚሉት አቶ ዮናታን፣ ማዕከላዊ ምርመራ ሄደውም ሆነ ሰው ልከው ምንም ያገኙት ምላሽ ባለመኖሩ፣ እስከሚጣራ ድረስ አስተያየት መስጠት እንዳልቻሉ ተናግረዋል፡፡
ጊዜው የምርጫ ወቅት በመሆኑ በጣም ሥራ እንደሚበዛባቸው ገልጸው፣ አሁን መናገር ባይችሉም ወደፊት ሁኔታውን ተከታትለው ይፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡
ምንም እንኳ ሦስቱ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በጎንደር በኩል አድርገው ወደ ኤርትራ ለመሻገር ሲንቀሳቀሱ ድንበር አካባቢ በፀጥታ ኃይሎች መያዛቸውን ፓርቲው ቢያውቀውም፣ የተፈጠረውን ጉዳይ ለምን ይፋ አያደርግም ተብሎ በማኅበራዊ ድረ ገጾች ወቀሳ እየቀረበበት ነው፡፡ በተለይ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች በቁጥጥር ሥር የዋሉትን የአባላቱን ጉዳይ በተመለከተ ወቅታዊ መረጃ አለመስጠታቸው ያበሳጫቸው የተለያዩ ግለሰቦች በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ እስካለፈው ዓርብ ሌሊት ድረስ ምንም ዓይነት ምላሽ አላገኙም፡፡
ኤርትራ በመግባት ግንቦት ሰባት የተባለውን ድርጅት ለመቀላቀል ድንበር አካባቢ ተይዘዋል ስለተባሉት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በመንግሥት በኩልም እስከ ዓርብ ሌሊት ድረስ ምንም የወጣ መረጃ አልነበረም፡፡ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ከተባሉ የመንግሥት ተቋማትም መረጃ ማግኘት አልተቻለም፡፡ ግንቦት ሰባት የተባለው ድርጅት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሌሎች የአገር ውስጥና የውጭ ድርጅቶች ጋር በአሸባሪነት መሰየሙ አይዘነጋም፡፡

Friday, March 20, 2015

ተቀላቀሉን፤ ካልሆነም በያላችሁበት ቦታ ተደራጁ!

March 20,2015
pg7-logoህወሓት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ስለሚያደርሰው ዘርፈ ብዙ በደል ብዙ የተነገረለትና የተፃፈበት ብቻ ሳይሆን እየኖርንበት ያለ ሀቅ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብም የሚደርስበትን ስቃይ መታገስ ወደማይችልበት ጫፍ መድረሱ በሰበብ አስባቡ በሚፈነዳዱ ተቃውሞዎች የሚታይ ሀቅ ሆኗል።
በሌሎች አገሮች እንዲህ ዓይነት የሕዝብ ምሬት ሲኖር በጥቂት ግለሰቦችና ቡድኖች ጥሪ ሕዝብ ግልብጥ ብሎ አደባባይ ይወጣል። ከሕዝብ አብራክ የወጣው ጦር ሠራዊትና ፓሊስ ከተበደለው ሕዝብ ጎን በመቆም አምባገነኖችን አስወግዶ የሽግግር መንግሥት ያቆማል። በቅርብ ጊዜያት በሕዝባዊ እምቢተኝነት መንግሥት በተቀየረባቸው አገሮች ያየነው እንደዚህ ዓይነቱን ሀቅ ነዉ።
አገራችን ውስጥ ያለው ሁኔታ ግን ከዚህ በእጅጉ ይለያል። ህወሓት ኢትዮጵያ ውስጥ የገነባው የጦርና የፓሊስ ሠራዊት አመራር በዘር የተደራጀ በመሆኑ የሕዝቡን አጠቃላይ ብሶት ደግፎ ሊቆም ይችላል ብሎ መጠበቅ አይቻልም። ሠራዊቱ እንደ ተቋም ከተበደለው ሕዝብ ጎን እንዲቆም በመጀመሪያ በራሱ በሠራዊቱ ውስጥ ሥር ነቀል ለውጥ መካሄድ አለበት።በዚህ አቅጣጫ የሚሠሩ ሥራዎች እንደተጠበቁ ሆነው፤ ሠራዊቱ ዘረኛ ገዢዎቹን አስወግዶ እስኪመጣ መጠበቅ አይቻልም፣ አይገባምም። በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ፣ ሕዝባዊ እምቢተኝነት በሕዝባዊ አመጽ መታገዝ አለበት የሚለው ሁለገብ የትግል የትግል ስትራቴጂ ተመራጭ እንዲሆን ያደረገው ዋነኛ ምክንያት የሠራዊቱ ዘረኛ አወቃቀር ነው። በመረጥነው የትግል ስትራቴጂ መሠረት በሁለቱም ግንባሮች – ማለትም፣ በሕዝባዊ አመጽ እና በሕዝባዊ እምቢተኝነት ግንባሮች ሥራዎች መሠራት አለባቸው። ሁለገብ የትግል ስትራቴጂ እምንፈልገው ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ላይ እንዲያደርሰን የኢትዮጵያ ሕዝብ በሁለቱም የትግል ስትራቴጂዎች አኳያ መደራጀት ይኖርበታል። ሕዝባዊ የአርበኛ ሠራዊት ማደራጀት እንደሚያስፈልግ ሁሉ በኢትዮጵያከተሞችና ገጠሮች፤ በሥራና በመኖሪያ አካባቢዎች በምስጢር የተደራጁ ሕዝባዊ የአርበኛ ሲቪል ክበቦችም በብዛት መደራጀት ይኖርባቸዋል።
በዚህም ምክንያት አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ ከህወሓት ዘረኛ ፋሽስታዊ አገዛዝ ነፃ ለመውጣት የሚመኝ ኢትዮጵያዊ ሁሉ እንዲደራጅ ጥሪ ያቀርባል! እያንዳንዱ ነፃነት ፈላጊ ኢትዮጵያዊ ከሚያምነውና ከሚመስለው ወዳጁ ጋር ይቧደን፤ ቡድኑንም በሥርዓትና በሚስጢር ያደራጅ።
ከእንግዲህ “ምን እንሥራ? ትግሉን እንዴት እንርዳ?” እያሉ ለሚጠይቁ ወገኖቻችን በሙሉ መልሳችን “ከቻላችሁ ተቀላቀሉን፤ ካልሆነም በያላችሁት ተደራጁ” የሚል ነው። ድርጅት ኃይል ነው። መደራጀት በራሱ ትልቅ ሥራ ነው። ድርጅት ድርጅት የሚሆነው ደግሞ በሥርዓት ሲዋቀርና በሥነሥርዓት ሲመራ ነው። ስለሆነም ነፃነት ናፋቂ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሌላ አደራጅና አስተባባሪ እንዲመጣለት ሳይጠብቅ በራስ አነሳሽነት እንዲደራጅ ይህ ጥሪ ተላልፏል።
በሥርዓት የተደራጀ ስብስብ ሲኖር የሚሠራ ሞልቷል። ይህንን መንገርም አያስፈልግም። የተደራጀ ስብስብ ራሱ ሥራዎችን አቅዶ መሥራትም ይችላል። የሚከተሉት ነጥቦች ለአብነት ተዘርዝረዋል።
  1. የተደራጀ ስብስብ ጠላትና ወዳጁን ይለያል። የጠላቱን ጥንካሬና ድክመቱን ከራሱ ጥንካሬና ድክመት ጋር መዝኖ የወገን ኃይልን ጥንካሬ የሚያጎለብቱ፤ ድክመቶቹን የሚቀንሱ እርምጃዎችን በመውሰድ አቅሙን ይገነባል።
  2. የተደራጀ ስብስብ የጠላትን እንቅስቃሴ እየሰለለ መረጃ ለነፃነት ኃይሎች እንዲደርስ ያደርጋል።
  3. የተደራጀ ስብስብ የተቀናጀ የሕዝባዊ እንቢተኝነት ተግባራትን ይፈጽማል። ለምሳሌ፣በሥርዓቱ የደረሰበትን ምሬት በወረቀት ገንዘብ፣ በአስፋልት፣ በታክሲዎችና በግድግዳዎች ላይ ይጽፋል፤ ገንዘቡን የኤፈርት ንብረት ከሆነው ውጋጋን ባንክ ያስወጣል፤ መዋጮዎችና ግብር ያጓትታል ከዚያም አልፎ አልከፍልም ይላል።
  4. የተደራጀ ስብስብ በሥርዓቱ ላይ ለማመጽ ሁኔታዎችን ያመቻቻል። ሁኔታች ተሟልተው አመጽ ሲቀሰቅስ ደግሞ ትግሉ ግቡን ሳይመታ እንዳይበርድ ፀንቶ ይቆማል።
  5. የተደራጀ ስብስብ ወዳጆቹን አስተባብሮ በጥንካሬው ላይ ተመርኩዞ በአካባቢው ባለ የህወሓት ኃይል ላይ ክንዱን ያነሳል።
በአርበኞች ግንቦት 7 እምነት የኢትዮጵያ ሕዝብ አስተባባሪና መመሪያ የሚጠብቅበት ጊዜ አልፏል። ህወሓት የዘረጋው የአፈና ሥርዓት የጠበቀ ትስስርና ቁጥጥር ያለው ድርጅት ማቆም እንዳይቻል አድርጓል። ስለሆነም ያለን አማራጭ በርካታ ያለዘወትር የበላይ አካል ትክክል ራሳቸውን በራሳቸው ማስተዳደር የሚችሉ ስብስቦችን በመላው የአገራችን ክፍሎች በአፋጣኝ ማደራጀት ነው። ይህንን ደግሞ ማድረግ ይቻላል።
ወቅቱ ህወሓትን ከጫንቃችን ላይ ለማውረድ የምንደራጅበት ነው። ድርጅት ኃይል ነው፤ አደራጅና አስተባባሪ ሳንጠብቅ በራስ ተነሳሽነት ዛሬውን እንደራጅ!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

Tuesday, March 17, 2015

ከምርጫው በፊት ልናደርገው የሚገባ ሌላ ምርጫ (ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ ሌና)

ከገዛኸኝ አበበ ኖርዌይ ሌና

Bilderesultat for gezahegn abebe photoበኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ስርዓት በማስመልከት በተለያዩ ድረገጽ እና የዜና አውታሮች ላይ የህዝብን ንቃተ ህሊና ሊይጎለብቱ የሚችሉ የተለያዩ ዘገባዎች ይቀርባሉ። በተለይም ደግሞ ፍትህ፣ነጻነት፣እኩልነትን አስመልክቶ እንዲሁም ሊጀመር ጥቂት ጊዜያት የቀረውንና የኢትዮጵያዊያንን አዕምሮ በያዘው የሀገራችን ምርጫ ዙሪያ መነጋገሩ፣ መከራከሩ እና  ከምርጫው በፊት  መስተካከል የሚገባችውን ነገር ማውሳቱ የሰሞኑ ዓቢይ ጉዳይ ሆኗል። በርግጥ የ1997ቱ ምርጫ የህዝብ ቅስም የተሰበረበት እና እስከአሁንም ድረስ የኢትጵያ ህዝብ ስብራት ያላገገመበት ሁኔታ በስፋት ይታያል። በመሆኑም እንደ እኔ እምነት ፍትህ ከሌለበት ሀገር ከፊታችን ካለው ምርጫ ምንም ይፈጠራል ብዬ የምጠብቀው ነገር ባይኖርም ግን ጥቂት የሚባሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች  ምርጫውን አስመልክቱ እየሰሩት ያለው ቅስቀሳ እና ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የወያኔን መንግስት ከስልጣኑ በማውረድ፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነት እየከፈሉት ያለው መስዋትነትና ሊያስመሰግናቸው ይገባል ባይ ነኝ   እርግጥ ነው ከሁሉም አቅጣጫ የሚስተጋባው የኢትዮጵያዊ ድምጽ ሀገርን ከመውደድ እና ለሀገር ነጻነት እንዲሁም ሉአላዊነት የሚከፈል መስዋዕትነት እስከሆነ ድረስ ትግሉ ይፋፋም ይቀጥል ያስብላል።
           
               ፍትህ የሰፈነበት ምርጫ ሊካሄድ የተገባ መሆኑን ሁላችንም እንስማማበታለን። የሁላችንም የኢትዮጵያ ልጆች ናፍቆት ሰላም የሰፈነባት ሀገር ላይ ምርጫው የህዝብ እንዲሆን ነው። ይህም ህልም በምድራችን ላይ ተጨባጭ ይዞታ ኖሮት  ተግባራዊ ቢሆን ሀገራችን ምን አይነት ቅርጽ ሊኖራት እንደሚችል ማሰብ ከባድ አይደለም። ስለሆነም በአሁን ወቅት   በምድሪቷ ላይ እየገነነ የመጣው ግፋዊ  አገዛዝ ወደበለጠ ደረጃ ደርሶ እጅግ ከመክፋቱ በፊት የትውልድ ሁሉ ናፍቆት የሆነውን እኩልነት እና  ህዝብ ለብዙ ጥፋት ታልፎ በተሰጠበት እንዲሁም ከሀገሪቷ ፊት ለፊት ታላቅ የሆነ ክስረት ተጋርጦ ባለበት የአምባገነን ስርዐት ዘመን የሰከነና የተረጋጋ ህይወትን በኢትዮጵያ ላይ ለማምጣት ታላቅ የሆነ ርብርቦሽ ያስፈልጋል።

           ይህንን በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የዘቀጠ የፓለቲካ ስርዐት ወደኋላ ከተጎተተበት ኢፍትሐዊ አሰራሩ ተናጥቆ ለማውጣት እና የሰለጠኑ ሀገራት ወደደረሱበት የነጻነትና እና የእኩልነት ክልል ለማድረስ ከጨዋታ ውጪ የተደረጉት የኢትዮጵያ ምሁራን እና ከማንኛውም የእድገት  እንቅፋቶች የጸዳ አላማ ያላቸው ሀገር ወዳዶች የተዘጋባቸው በር ክፍት ሆኖ  በሁሉም ሀገራዊ አቅጣጫ ጉዳይ ላይ ለምድራቸው የሚቻላቸውን አስተዋጾ እንዲያደርጉ በተለይም ደግሞ ከፊት ለፊታችን በወያኔ ቁጥጥር ስር ያለው ምርጫ በህዝብ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን የኢትዮጵያ ሊሂቃን እድሉ ያለምንም ተጽእኖ በነጻነት ተሰጥቷቸው እንዲሳተፉ ማድረግ ተመራጭነት አለው። ይህን መሰሉ ተግባር በምድሪቷ ላይ የጸና እስከሚሆን ድረስ  እንዲሁም የገዥውን ቡድን እድሜ መቀጠል ፣ የተመዘበሩ ኮሮጆዎች እና የምርጫ ዕቃ ዕቃ ጨዋታ ወቅታቸውን እየጠበቁ ያለፈውን ልማዳቸውን ለመድገም የሚደረጉት እንቅስቃሴዎች ተፈጻሚ ከመሆናቸው በፊት በሁሉም አቅጣጫ መታገል እንደሚገባን እና ከምርጫው በፊት ህዝባዊ አመጽ እንደ አማራጭ ከመውሰድ  በስተቀር በሌላ መንገድ ወያኔን ማክሸፍ እንደማይቻል ሊታወቅ ይገባል።

              እውነታውን በመሸፋፈን  ወያኔ በምግብ ራሳችንን ችለናል እያለ  በሚቀልድበት በዚህ የረሀብ ዘመን ዘወትር ሽቅብ እየወጣ ሰማይ ለመንካት እየተመነጠቀ ስላለው የኑሮ ውድነት ህዝቡም ሲያወራ ወያኔም ስለ ‹‹11%›› እድገት ሲደሰኩር፣ ህዝብ ስለ ስራ-አጥነት እና  እርዛት ሲያወራ ወያኔ ‹‹ስለኢንቨስትመንት መስፋፋት›› ሲያብራራ፣ ህዝብ ስለረሃብ ሲያወራ መንግስት ‹‹ስለጥጋብ›› መፈክሩን ሲያሰማ ፤ ህዝብ ስለዳቦ ሲጮህ የወያኔ መንግስት ‹‹ስለመሰረተ ልማት›› እያወሩ እርስ በርስ መግባባት ተስኗ ቸው 23ኛ አመት ዐመት አልፎ ተጋምሷል ። ይህ ያላቻ ጋብቻ ይባላል። በድግሳቸው ቀን  አንዱ የደስታ ሌላኛው የሃዘን ሻማ በማብራት አክብረው አሳልፈዋል፡፡ ከእንደዚህ አይነት ስርዓት አልባ ገዢ ጋር ፍቺ ብቸኛ አማራጭ ነው። ምርጫውም ፍትሀዊ እና የህዝብ ካልሆነ በስተቀር ለኢትዮጵያዊያን የሚያመጣው ምንም አይነት ፈውስ እንደሌለው የታወቀ ይሁን። ይልቁኑም የከዚህ በፊቱን ውሸት እና ማስመሰል ረቀቅ ባለ ማደናገሪያው ለመድገም እየተሯሯጠ መሆኑ ግልጽ በሆነበት በዚህ ወቅት አምባገነኑን ወያኔን ከምርጫው ውጭ ለማድረግ በየትኛው ጎዳና ብንሔድ በትግላችን ግቡን እንደምንመታ  እና የተለያዩ የትግል ልምድ ስልቶች ልውውጥ አድርገን ሀይላችንን በማጠናከር በአንድ የተባበረ ኢትዮጵያዊ ክንድ ከምርጫው በፊት ህዝባዊ አመጽን  የሁላችን ምርጫ ይሁን በማለት መነሳት አለብን።

              የኔ የግል ምልከታዬ በአሁን ሰአት ሀገራችን ባለችበት ደረጃ የትግላችን ኢላማ እና መድረሻው መሆን የተገባው አስቀድሞ በሐስት የወያኔ ነቢያቶች ለተነበዩለት   ምርጫ ተባባሪ ሆኖ በመሰለፍ አምባገነኑ አገዛዝ እንዲቀጥል አስተውጽኦ ማበርከት ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚወስነውሀገር የምትተዳደርበት ልማታዊ የሆነ ህግ በምድሪቷ ላይ የበላይ እንዲሆን የዜጎች እኩልነት እና ሰብዓዊነት የሚከበሩባቸው ስርዓት በማስፈን ወያኔ በጭቆና የተቆጣጠርውን ስልጣን በመቀማት የህዝብ የስልጣኑ ባለቤት ሆኖ  ፍጹም የሆነ ብሩህ ተስፋ የሚታየባትን ኢትዮጵያን መፍጠር  ነው።

                  መቼውንም ቢሆን ወያኔ ለነጻ ፍትሀዊ ምርጫ እና ለኢትዮጵያ ህዝብ የበላይነት ለምን አልቆመም ተብሎ አይጠየቅም። ምክንያቱም ይህ ቡድን "ከጅብ ጅማት የተሰራ ክራር ምንጊዜም ቅኝቱ እንብላ እንብላ ነው" እንዲሉ ከፅንሰቱም ፀረ ኢትዮጵያዊ መሆኑ የታወቀ ነው። ከዚህ አስከፊ ስርዓት መልካም የሆነ አስተዳደር መጠበቅ የሚታሰብ አይደለምና እንደገና ሌላ ምዝበራ በሀገርችን ላይ ከመፈፀሙ በፊት ምርጫው ጋር ሳንደርስ በፊት የህዝባዊ አመፅ ትግልን በመምረጥ ወደ ውጤት እንጓዝ።  ምርጫው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚመርጠው እና የሚወዳደረው እንጂ ለተሳትፎ ብቻ ብቅ ብሎ በወያኔ ሻጥር የሚሸነፍበት ሊሆን አይገባም።
                           ለውጥ የግድ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ሁሉንም የማይጠቅም ቢሆን እንኳን ለብዙኃኑ ሲባል የግድ መምጣት አለበት፡፡ የለውጥ ፍርሐትን አስወግደን በቂ ዝግጅት በማድረግ በተገቢው መንገድ ወያኔን ማስወገድ  ይቻላል፡፡ ለውጥ የሚመጠበትን መንገድ ፈርቶ እና ህዝባዊ አምፅን  ተቃውሞ  ለውጥን መጨበጥ ዘበት ነው፡፡ ‹‹መፍራት ያለብን ፍርሐትን ራሱን ነው›› እንዲሉ ፍራንክሊን ሩዝቬልት፡ የትኛውንም ወደኋላ የሚጎትተንን ፍርሀት ትተን ድጋሚ በምርጫው ከመጭበርበራችን በፊት አስቀድመን በህዝባዊ አመጽ መታገንልን እንምረጥ። ከምርጫው በፊት የኢትዮጵያውያን ምርጫ  በህዝባዊ አመጽ ትግል ለዘመናት በአንባገነንነት በስልጣን ላይ ተቀምጦ ህዝብን በማሰር ፣ በመግደል ላይ ያለውን አረመናዊ መንግስት ከስልጣን ላይ ማውረድ ይሆን ነው  መልዕክቴ ።
gezapower@gmail.com

                የሕዝብ ትግል ያቸንፋል !!!

ወያኔና ሽብርተኛነት

March 17,2015
ፕ/ር መስፍን ወልደ-ማርያም
terrorist-cat
ወያኔነትና ሽብርተኛነት ትናንት ምን ዓይነት ግንኙነት ነበራቸው? ዛሬ ምን ዓይነት ግንኙነት አላቸው?
ወደዚያ ከመሄዳችን በፊት የአሸባሪነት የተግባር መገለጫው ምንድን ነው? ብለን እንጠይቅ፤ አሸባሪነት፡-
• ያለውን የሥልጣን ሥርዓት የማፍረስ ዓላማ ያለው ነው፤
• ዓላማውን ለማሳካት ጉልበቱን የሚያፈረጥመው ከሥርዓቱ ጠላቶች በሚያገኘው፡–
• የመሣሪያ እርዳታ፣
• የእውቀት ድጋፍና ገንዘብ
• ዓላማውን ለማሳካት
o ሰዎችን ገድላል
o ያስራል፤ ያሰቃያል
o ይዘርፋል፤ ይቀማል፤
• ዓላማውን ለማሳካት
o ሃይማኖቶችንና ባህልን ያዳክማል፤
o የጥንት ታሪክ ማስታወሳዎችንና የቆዩ መጻሕፍትን ያጠፋሉ፤
o የፖሊቲካ እምነትን ያግዳል፤
o የመሰብሰብ ነጻነትን ይከለክላል፤
o የመደራጀት ነጻነትን ይከለክላል፤
o ሀሳብን የመግለጽ ነጻነት ይከለክላል፤
o ጉልበትን ወደሥልጣን ይለውጣል፤
• አንድ ዓላማ፣ አንድ እምነት፣ አንድ ሀሳብ፣ አንድ ዘዴ አንድ መንገድ በቀር ሌላው ሁሉ ይዘጋል፤ ይህንን ጥርነፋ የሚቃወም ሁሉ አሸባሪ ተብሎ ይታሰራል፤ የሲአይኤ ሰላይ ተብሎ ተሰቃይቶ ይሞታል፤
ከዚህ በላይ የተዘረዘረት በሙሉ የሽብርተኞች ወንጀሎች የሚባሉ ናቸው፤ እነዚህን እንደመመዘኛ አድርገን በአንድ በኩል ወያኔን፣ ከተፈጠረ ጀምሮ እስካሁን የሚያድርገውንና እያደረገ ያለውን በማስታወስ፣ በሌላ በኩል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትና በሽብርተኛነት ተከስሰው በእስር ቤት የሚገኙት ሰዎችን
• እስክንድር ነጋ፣ ርእዮት ዓለሙ፣ ተመስገን ደሳለኝ
• የዞን ዘጠኝ በመባል የሚታወቁት ወጣቶች፣ (ማኅሌት ፋንታዬ፣ አጥናፍ ብርሃኔ፣ ኤዶም ካሣዬ፣ አቤል ዋበላ፣ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ፣ ተስፋ ዓለም ወልደየስ፣ ዘለዓለም )
• አንዱዓለም አራጌ፣ አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ
• ሌሎች ከግንቦት ሰባት ጋር ንክኪ አላችሁ ተብለው የታሰሩት
ስናመዛዝን በሽብርተኛነት መመዘኛዎቹ ከብደው የሚታዩት የትኞቹ ናቸው? የአሸባሪነት የተግባር መግለጫ ተብለው በተዘረዘሩት ውስጥ ባሉት ዓላማዎችና መንገዶች የሚንቀሳቀሱት የትኞቹ ናቸው? ወያኔ ነው ወይስ የታሰሩት ሰዎች? ሽብርተኛ ተብለው ከታሰሩት ውስጥ ባንክ ሲዘርፍ የተያዘ አለ? እኔ አስከማውቀው የለም፤ ከወያኔ ውስጥስ ባንክ የዘረፈ አለ? ራሱ መለስ ዜናዊ በኩራት ነግሮናል! በሌሎች ወንጀሎችም ቢሆን ያው ነው፡፡
ተጨማሪ ማስረጃ የሚሆነው የዓለም የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች ሁሉ በወያኔ በሽብርተኛነት የታሰሩት ሁሉ እንዲፈቱ እየወተወቱ በአንጻሩ የወያኔን የሰብአዊ መብቶችን መጣስ እያወገዙ ነው፤ ስለዚህ ጋዜጠኞችንና የፖሊቲካ ሰዎችን እየለቀሙ በሽብርተኛነት እየወነጀሉ በየእስር ቤቱ መወርወሩ አላዋጣም፤ አዝማሚያው እንደሚያሳየው የወያኔ ጸረ-ሽብርተኛ መምሰል ለሲአይኤም የሚሸጥ ሊሆን የሚችል አይመስልም፡፡
በዚያ ላይ ሽብርተኞች በኢራቅና በአፍጋኒስታን አድርገው የመን ገብተዋል፤ ከየመን ሶማልያ ቅርብ ነው፤ ኬንያን እየፈተሹት ነው፤ የሱዳን ትርምስ ሽብርተኞችን እንደሚጋብዝ ጥርጥር የለም፤ የናይጂርያው ወደሱዳን ሲጠጋ መፈናፈኛ ይጠፋል፤ በሽብርተኛነት የተከሰሰችው ኤርትራ ለመሸሸጊያ ትሆን ይሆን?
ጤናማ ሰው ሆኖ ሽብርተኛነትን የሚደግፍ ያለ አይመስለኝም፤ ዛሬ በኢራቅ የሚደረገውን በየቀኑ ስንመለከት ወደቤታችን አልተጠጋም ብለን ልንዝናና የምንችልበት ሁኔታ ላይ አይደለንም፤ በዋልድባና በበዙ ሌሎች ቦታዎች የኢትዮጵያ ቅርሶች አደጋ ላይ መሆናቸው ይሰማናል፤ ግን በአቅመ-ቢስነት በዝምታ እንመለከታለን፤ ይህንን የአዳፍኔ የፖሊቲካ አቅጣጫ ለመለወጥ የሃሳብ መለዋወጫ መድረክ የሚፈጥሩትን ወጣቶች ሁሉ በእስር ቤቶች እያጎሩ ነው፤ አዲስ የፖሊቲካ መድረክ እንፍጠር ብለው በሰላማዊ መንገድ የፖሊቲካ ትግል የጀመሩትን ሁሉ እያሰሩ ነው፤ በትግራይ ውስጥ አረና በትግራይ ያለውን የፖሊቲካ መሻገት ለማጥራት እንዳይሞክር እየተደረገ ነው፤ ከዚህ በፊት ገብሩ ዓሥራት የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኅብረትን በክፉ የጭካኔ ዘዴ እንዳዳከመ አሁንም አረናን ለማዳከም እየተሞከረ ነው፡፡
መቼ ነው ወያኔዎችና ሎሌዎቻቸው ነገን የማየት ዓይኖች የሚያበቅሉት?
መጋቢት 1/2007

ልዩነታችን ጌጣችን፤ አንድነታችን ህልውናችን ነው

March17,2015
pg7-logoኢትዮጵያ ስንል ብዙ የተለያዩ ዘውጎች፤ ብዙ የተለያዩ ቋነወቋዎችና ሀይማኖቶች በአንድነት ይዛና አስተሳስራ ብዙ ፈተ ናዎችን በማለፍ ለረጅም ዘመናት ህልውናዋን ጠብቃ የቆየች ሀገር መሆንዋ መታወቂያዋ ሀገር ማለት ነው። እንዳ ሳለ ፈችው ረጅም ዘመናት ሁሉ እንደየዘመኑ በህልውናዋ ላይ ይቃጣ የነበረውን ጥቃት እነዚያ በዘውጎች፤ በቋነወቋዎችና ሀይ ማኖቶች የተንቆጠቆጡት ልጆችዋ በአንድነት በመሰለፍ ብሎም ድል በመምታት ህልውናዋን አስጠብቀው መዝለቃቸው የነጻነት ሀገር የመሆን መለያዋ ምክንያቶች መሆናቸውንም የሚያሳይ ነው።
ይህ ልዩነታችንን ጌጡ አድርጎ ያስተሳሰረን ኢትዮጵያዊነት በነፃነት የዘለቀ ህዝብ ከማድረግ አልፎ በአንድ ወቅት የስልጣኔ ምንጭና የአለማችን ሀያል ህዝብ ከመሆን ጫፍ አድርሶን እንደነበር አይዘነጋም። በዚያው ልክ ይህ በልዩነታችን ላይ የተገነባ አንድነታችን ሲላላ ህልውናችን ከገደል አፋፍ ላይ የደረሰበት ዘመንም በታሪካችን ውስጥ መታየቱ አልቀረም። “ዘመነ-መሳፍንት” በመባል የሚታወቀው ጥቁር የታሪካችን ክፍል አንዱ ተጠቃሽ ሲሆን ሌላው ዛሬ የምንገኝበት የወያኔ ዘረኛ ዘመን ነው። ትናንት በዘመነ መሳፍንት ህልውናችን አደጋ ላይ ወድቆ ነበር፤ ዛሬም በወያኔ ዘረኞች ዘመን ህልውናችን ከከፋ አደጋ ላይ እንዲገኝ ተደርጓል። በአጭሩ ልዩነታችን ጌጣችን አንድነታችን ደግሞ የህልውናችን ማስጠበቂያ ዋነኛው ቁልፍ መሆኑን መገንዘብ ለማናም አያዳግትም።
ሌላው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በታሪካችን ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ በህልውናችው ላይ የከፋ አደጋ ያንዣበበት ወቅት ላይ መገኘታቸው ከማንም የተሰወረ አይደለም። ዘመነ መሳፍንት ትናንት ቋንቋ ዘውግና ሀይማኖት ሳይለይ በእያንዳዱ ኢትዮጵያዊ ህይወት ላይ አስከትሎት የነበረውን ችግርና በሀገሪቱም ከአዘቅት የከተተ ከመሆኑም በላይ ይኸው እስከዛሬ ድረስ ውደ ቀድሞ ታላቅነቷ ለመመለስ ከባድ መሰናክል ተክሎ ማለፉን ከትናንት ታሪካችን መረዳት እየተቻለ ዛሬ በእኛ ዘመን ዳግም ከትናንቱ የከፋ ጥልቅ አዘቅት ውስጥእንድንፈቅ በዘረኞች እየተገፋን መሆኑንና ሊያስከትል የሚችለውንም ውጤት ለመረዳት የተለየ እውቀት አይፈልግም። ዛሬ ይህ ልዩነትን እያጎሉና ቂም በቀልን እየዘሩ መጓዛ የጥቂቶች ፍላጎት መሆኑ ባይካድም ከዚህ ቀደም ያስከተለውንና ዛሬም እየታየ ያለውን አደጋ ተገንዝቦ ከወዲሁ መከላከል የእያንዳዳችን ሀላፊነት ሊሆን ይገባል።
ጥቂቶች የህዝብ አሳቢ በመምሰል የሚረጩት የልዩነት መርዝ በሌሎች ሀገራት ላይ ያስከተለውን ፈተናም እንዲሁ ቆ ም ብሎ መፈተሽና ውጤቱንም መመዘን የፈሰሰ ውሀን አፋሽ ከመሆን ማዳኑን መጠራጠር የለብንም። የሶቭየት ህብረት መ ፍረስ፤ የዩጎዝላቪያ እርስ በርስ መባላት፤ የሶማልያ መቋጫ ያጣ ትርምስ ……. ወዘተ ንፁሀንን በገፍ የበላና ዜጎችን ለኢኮኖሚ ድ ቀት የዳረገ፤ በገፍ ስደትን ያስከተለ፤ የጦርነቶቹ መዘዝ ከልጅ ልጅ የማይታረቅ ቂም እያስቋጠረ መገኘቱ ሲታይ ዛሬ በእ ኛም ሀገር ጥቂት የመገንጠል አባዜ የተጠናወታቸው ይዘውን ሊጓዙ የሚፈልጉበትን መንገድ የት ሊያደርሰን እንደሚችል ከራ ሳችንም ያለፈ ታሪክ ሆነ በአለማችን ላይ የታዩ ክስተቶች ውጤት የሆነውን ትርምስና ሽብር በመመልከት ልንማርበትና ከወዲሁ አንድነታችንን በማጠናከር ለመከላከል መስራት ግድ ይለናል።
ከላይ እንደ ምሳሌ የተጠቀሱት ሀገራት በመበታተን ያተረፉተረ ሽብረ፤ ጦርነት፤ ስደትና ድህነት መሆኑ የታዘብነው የዘመናችን ክስተት ሲሆን ቀደም ሲል ለሁለት ተከፍላ የነበረችው ጀርመን ዳግም ከሁለትነት ወደ አንድነት መምጣቷዋ በሰጣት ሁለንተናዊ ጥንካሬ የዓለምችን ታላላቅና ሀብታም ሀገራት በኢኮኖሚ ውድቀት ሲመቱ ያለአንዳች ጭግር የፈተናውን ወቅት ያለፈች ሀገር ለመሆን መብቃትዋን ከአንድነት ሊገኝ የሚችለውን ሁለንተናዊ ጥንካሬ አጉልቶ የሚያሳይ ነው። ሌላው ከሀ ገራችን ህልውናን የማስጠበቅ ፍልሚያ ታሪኮች ውስጥ ጎላ ብሎ የሚታየው የአድዋ ጦርነትና ድል የአንድነትን ዋጋ ከፍ አድርጎ የሚያሳይ አኩሪ ታሪክ ነው። በዘመናዊ የጦር መሳሪያ ተማምኖ የመጣውን ወራሪ የኢጣልያ ጦር በተመጣጣኝ የጦር መሳሪበ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ተማምኖ የመጣውን ወራሪ የኢጣልያ ጦር በተመጣጣኝ የጦር መሳሪያና የሰለጠነ ሰራዊት ሳይሆ ን ቋንቋ፤ ዘውግና ሀይማኖት ሳይለያቸው ሁሉም በአንድነት ለሀገራቸው ህልውናና ለነፃነታቸው በአንድነት በመቆማቸው የተ ገኘ ድል መሆኑም መዘንጋት የለበትም።
ኢትዮጵያችን ደሀ ናት? አዎ ደሀ ናት። ህዝቧም ለዘመናት አንባገነን ስርአቶች እየተፈራረቁበት ህይወቱ የስቃይና የመከራ ሆኖ ቆይቷል? አዎ ቆይቷል። ሀገራችንን ከድህነትና ከዃላ ቀርነት፤ ህዝቧንም ከስቃይና ከመከራ ህይወት አውጥቶ የተሻለ ሀገር፤ ለመፍጠር ዛሬ የወያኔ ዘረኛ ቡድን የሚያራምደው የመንደር ፖለቲካ እውን መፈትሄ ነውን? ብለን ስንጠይቅ ያለፉት 23 የወያኔ የስልጣን ዘመናት እውነቱን ቁልጭ አድርገው ያሳያሉ። በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅ ህዝብ በጅምላ ስደት፤ ለቁጥር በሚታክት ሁኔታከመኖሪያ ቀዬ መፈናቀል፤ እስር ቤት በእስር ቤተረ መገንባት፤ እናትና ልጅ ተፈራርተው መመካከር ያልቻሉበት ዘመን፤ ድህነት ከሚባለው ደረጃ ተወርዶ ጭራሽ የሆቴል ትርፍራፊ በጉርሻ የሚሸጥበት ዘግናኝ ወቅት ላይ ለመገኘት ምክኒያት ከመሆኑም በላይ ሀገር አለኝ ብሎ መኩራት እንኳ ከማይቻልበት ህልውናችን ከከፋ አደጋ ላይ የሚገኝበት ወቅት ሆኖ እናገኘዋለን።
ዜጎችን ነቋንቋ በዘውግና በሀይማኖት ከፋፍሎ ለመግዛት የሚያራምደው በታኝ የጥፋት ፖለቲካ ሌላው ቢቀር ዛሬ በቀን ሶስት ጊዜ በልቶ የማደር ሰዋዊ መብት እንኳ ማስከበር ከማይቻልበት ሁኔታ ላይ መደረሱ ከእያንዳዱ ኢትዮጵያዊ የተሰወረ አይደለም። በአንባገነኖች የተጫነበትን የአገዛዝ ቀንበር አስወግዶ የነፃነት አየር የሚተነፈስበት፤ ፍትህ የሰፈነበትና መብቶች የተከበሩበት ሀገር ለመፍጠር በተከፊለ የህዝብ ልጆች የህይወት ዋጋ ለስልጣን የበቃው ወያኔ በማር በተለወሰ መርዘኛ የዘር ፖለቲካው ሳቢያ የተገኘው ውጤት የእለት ጉርስን እስከማጣት የደረሰ ሆኗል ማለት ነው።
በአጭሩ ዛሬ ከ23 አመታት በዃላ እንደ ትናንቱ ሁሉ ይህን ርእሰ-ጉዳይ ማንሳታችን ያለ ምክንያት አይደለም። ይህ በለዩነታችን መካከል ለመገንባት ደፋ ቀና የሚባልለት የልዩነት አጥር እስካሁን የተፈለገውን ያህል ባይሳካም በጠንካራው አንድነታችን ላይ ያጠላው ጥላ ለምን አይነት አሰቃቂ ህይወት የዳረገን መሆኑና ጥያቄዎቻችን ለሆኑት ፍትህ፤ እኩልነትና ነፃነት ምላሽ ከማስገኘት ይልቅ ይባስ ለከፋ አፈናና አገዛዝ የዳረገን መሆኑን ተገንዝበን ቀኑ ሳይመሽ ከወዲሁ ለመፍትሄው በጋራ መስራትብቸኛ አማራጭ መሆኑን ሁሉም እንዲገነዘበው ነው።
3000 ዘመን ያለ ፈተና የተቆጠረ የነፃነት ዘመን አይደለም። የገጠሙን ፈተናዎች በሙሉ በልዩነቶቻችን ላይ በተገነባው ጠንካራ ኢትዮጵያዊ አንድነታችን ተጠብቆ የተገኘ እንጂ…… ዛሬም ቢሆን ዜጎች ልዩነቶቻቸውን የጥንካሬያቸው መሰረት በማድረግ በአንድነት ነፃነታቸው የተረጋገጠበት፤ መብቶቻቸው የተከበሩበት፤ ፍትህ የሰፈነበት ሀገር ለመፍጠር የተጀመረውን ሁለገብ ትግል በማጀብ ከዳር ለማድረስ ለመነሳት ያለፉት 23 አመታት ከበቂ በላይ መሆኑን አጢነን በቃ የምንልበት ወቅት ላይ እንደምንገኝ ለማሳሰብ ነው።
ትናንትም ዛሬም ነገም ልዩነቶቻችን ጌጣችን አንድነታችን ህልውናችን መሆናቸውን ተረድተን ሳይመሽ ሁላችንንም በእኩልነት የማታስተናግድ የሁላችንን ኢትዮጵያ ለመገንባት እንነሳ!!!!!
ኢትዮጵያችን ለዘላለም ትኑር!!!!

Sunday, March 15, 2015

እንግሊዝ በኢትዮጵያ ያለው ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት አፈጻጸም ያሰጋኛል አለች!!!

March 15,2015
የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ ላልተገባ ዓላማ እየዋለ ነው በሚል ተችታለች

የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መጋቢት 3 ቀን 2007 ዓ.ም. ባወጣው የ2014 (እ.ኤ.አ.) የሰብዓዊ መብትና የዴሞክራሲ ሪፖርት፣ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ላይ ኢትዮጵያ በምትፈጽማቸው ገደቦች ሥጋት እንደገባው አስታወቀ፡፡ የፀረ ሽብርተኝነት አዋጁ ላልተገባ ዓላማ እየዋለ ነው በሚልም ተችቷል፡፡

የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ በቁጥጥር ሥር የዋሉት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላት፣ ጋዜጠኞች፣ ሰላማዊ ተቃዋሚዎችና ሌሎች አካላት ሕጉ ተጠቅሶ የተከሰሱት የመሰብሰብና ሐሳባቸውን በነፃነት የመግለጽ መብታቸውን ለመጠቀም ሙከራ ሲያደርጉ እንደሆነ ሪፖርቱ ይጠቁማል፡፡
በዓመቱ የዞን ዘጠኝ አባላት የሆኑ ሰባት ጦማሪያንና አቶ ተመስገን ደሳለኝን ጨምሮ 17 ጋዜጠኞች በቁጥጥር ሥር እንደዋሉም ሲፒጄን በመጥቀስ ሪፖርቱ አትቷል፡፡ ይህም ጋዜጠኞችን በማሰር ኢትዮጵያ ከዓለም በአራተኝነት ደረጃ እንደሚያስቀምጣት አመልክቷል፡፡ 30 ጋዜጠኞች በዓመቱ ከአገር እንደተሰደዱ የገለጸው ሪፖርቱ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የመክሰስ ሐሳብ ስለሌለው ሊመለሱ ይችላሉ ማለቱንም ጠቅሷል፡፡

እንግሊዝ ኢትዮጵያ የኦሮሚያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት 20 ጋዜጠኞች የተባረሩት በክልሉ የተከሰተውን የተማሪዎች አመፅ በዘገቡበት ተቺ አቀራረብ የተነሳ እንደሆነም እንደሚታመን ጠቅሷል፡፡ የአምስት መጽሔቶችንና የአንድ ጋዜጣ ኅትመት የተቋረጡትም በመንግሥት ውሳኔ እንደሆነ አመልክቷል፡፡ በአገሪቱ የኤሌክትሮኒክ ሚዲያ ተደራሽነት የተገደበ እንደሆነም ሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡ የግል አሳታሚዎች በተመጣጣኝ ዋጋና በአስተማማኝ ሁኔታ የማተሚያ ቤት አገልግሎት ማግኘት አለመቻላቸውም እንደ ሳንካ እንደሚቆጠር ገልጿል፡፡ ለጋዜጠኞች የሙያ ሥልጠና በመስጠትም ረገድ የኢትዮጵያ መንግሥት የሚጠበቅበትን እየሠራ እንዳልሆነ ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡
ሪፖርቱ የእንግሊዝ መንግሥት በሚዲያ ነፃነት ላይ መንግሥት የሚፈጽማቸውን ገደቦች በሚመለከት ከኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር መነጋገሩንም ያስታውሳል፡፡ በተለይም በመስከረም 2007 ዓ.ም. በተመድ የሰብዓዊ መብት ካውንስል በዓለም አቀፍ ወቅታዊ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ግምገማ (UPR) ላይ፣ ኢትዮጵያ ምርጫ 2007 ከምርጫ 2002 በተቃራኒ ወካይና አሳታፊ እንዲሆን ተጨባጭ ዕርምጃ እንድትወስድ የእንግሊዝ መንግሥት ምክረ ሐሳብ ሲሰጥ ተቀብላው የነበረ ቢሆንም፣ ዕርምጃዎቹ እስኪወሰዱ እንግሊዝ አሁንም እየጠበቀች እንደሆነ ገልጿል፡፡

እንግሊዝ በፕሬስ ነፃነት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖራቸዋል ብላ ያመነችባቸውን ጉዳዮች በፍርድ ቤት መከታተሏንና ይህም ዓለም አቀፍ ደረጃ መሟላቱን ለመገምገም እንደረዳ ተገልጿል፡፡ ባለፈው ዓመት በግንቦትና በሐምሌ ወራት የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምኅዳሩና ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት አስፈላጊ እንደሆነ በመግለጫው መጠቆሙን ያስታወሰው ሪፖርቱ፣ ኅብረቱ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ጦማሪያን፣ ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች የፍርድ ሒደት ሰብዓዊ መብታቸውን ባከበረ መንገድ እንዲካሄድ መጠየቁን አመልክቷል፡፡

የእንግሊዝ መንግሥት የፕሬስ ነፃነትን ማክበር የኢትዮጵያን ዴሞክራሲ እንደሚያጠናክርና ተጠያቂነትን በማረጋገጥ በአገሪቱ ዘላቂ መረጋጋትን ለማስፈን እንደሚያግዝ እምነት እንዳለው ሪፖርቱ ገልጿል፡፡

በሪፖርቱ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ያለውን አስተያየት የተጠየቁት የመንግሥት የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን፣ ‹‹ኢትዮጵያ ራሷን ከሽብርተኝነት ለመጠበቅ የምታደርገው ዕርምጃ አግባብ አይደለም የሚሉ አካላት ለተመሳሳይ ሥጋት ተመሳሳይ ዕርምጃ ሲወስዱ፣ የእነሱ ድርጊት ተገቢ የመንግሥት ሥራ የሚሆንበት አመክንዮ አይገባኝም፤›› ብለዋል፡፡ ይሁንና መንግሥት ሪፖርቱን በዝርዝር ከተመለከተ በኋላ ምላሽ  እንደሚሰጥበት ገልጸዋል፡፡

Friday, March 13, 2015

በህወሓት ላይ የሚቀርቡ ተቃውሞዎች ሁሉ ወደ እምቢተኝነት ይደጉ!

March 13,2015
pg7-logoየኢትዮጵያ ሕዝብ በአለፉት 23 ዓመታት በህወሓት ዘረኛ አገዛዝ የደረሰበት ስቃይ እንዲቀንስ፤ ገዢዎቹ ከጫንቃው እንዲወዱ፤ ህወሓትን አውርዶ የሚፈልጋቸው መሪዎችን በነፃነት እንዲመርጥ ሲጠይቅና አቤቱታ ሲያሰማ ቆይቷል። በ1997 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሕዝብ ምኞት የሚሳካ መስሎ የታየ የነበረ ቢሆንም በአገዛዙ አረመኔዓዊ እርምጃ ተሰናክሏል። ከጥቂት ዓመታት ወዲህ “ድምፃችን ይሰማ” የሚሉ አቤታዎች ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች መምጣት ጀምሯል – “ድምፃችን ይሰማ ሙስሊሞች”፣ “ድምፃችን ይሰማ ኦርቶዶክሶች”፣ “ድምፃችን ይሰማ መምህራን”፣ “ድምፃችን ይሰማ ተማሪዎች”፣ … ወዘተ። በተለይ ሙስሊም ወገኖቻችን በተደራጀ መንገድ “ድምፃችን ይሰማ” እያሉ ሲወተውቱ ሦስት ተከታታይ ዓመታት አልፈዋል። ወገኖቻችን “ድምፃችን ይሰማ” በማለታቸው ተደብድበዋል፣ ታስረዋል፣ ተገድለዋል።
አቤቱታ የሚሰማ ጆሮ የሌለው አገዛዝ ሲገጥም ምን ይደረጋል? ለአቤቱታ አቅራቢው ያለው ምርጫ ከሁለት አንድ ነው። ወይ አቤቱታን እርግፍ አድርጎ ጥሎ በደልን ተቀብሎ “እህህ !” እያሉ መኖር፤ አሊያም “በቃኝ፣ እንቢ አልገዛም” ማለት፤ ሦስተኛ ምርጫ የለም።
አቤቱታ ሰሚ ሲያጣ እና ሕዝብ መሮት “እንቢኝ፣ አልገዛም” ሲል ነው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ተቀሰቀሰ የሚባለው። ሕዝባዊ እምቢተኝነት ብዙ መልኮችና ቅርጾች ቢኖሩትም ዋነኛዎቹ መገለጫዎች ሁለት ናቸው። አገዛዙ ሕዝብ እንዲያደርግ የሚፈልገውን አለማድረግ እና/ወይም አገዛዙ ሕዝብ እንዲያደርግ የማይፈልገውን ማድረግ።
ለምሳሌ፣ አገዛዙ ሹማምንቱ እንዲከበሩ፣ ሕዝብ እንዲታዘዝላቸው ይፈልጋል፤ እንቢ ያለ ሕዝብ ግን የአገዛዙን ሹማምንት ይንቃል፣ በየደረሱት ያዋርዳቸዋል፣ “አልታዘዛችሁም” ይላቸዋል። ማንኛውም መንግስት የዳኝነት ሥርዓቱ እንዲከበርለት ይፈልጋል፤ በደል የመረረው ሕዝብ ግን የአምባገነኖች ችሎት ውሳኔ አይቀበልም፤ ዳኞችንም ዳኝነትንም አያከብርም። ሕዝብ የመንግሥትን ግብር በወቅቱ እንዲከፍል የማንኛውም መንግሥት ፍላጎት ነው። በመንግሥት ያመረረ ሕዝብ ግን ግብር አይከፍልም፤ መክፈል ግድ ከሆነበትም አዘግይቶ፣ አስለፍቶ ነው። የመረረው ሕዝብ ምሬቱን መፃፍ በሌለበት ቦታ ይጽፋል። በደል የበዛበት ሕዝብ “ዝም በል” ሲሉት ይናገራል፤ “ተናገር” ሲሉት ዝም ይላል።
አገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ የሕዝባዊ እምቢተኝተኝነት እርምጃዎች ጅምሮች እየታዩ ነው። በአማራ ክልል፣ ሕዝብ በሹማምንት ላይ የራሱን እርምጃ መውሰድ ጀምሯል። ሕዝብ ራሱ የፓሊስንም የፍርድ ቤትንም ሥራ ተክቶ እየሠራ ነው። ይህ መበረታታት ያለበት ትልቅ እርምጃ ነው። እንደዚሁም ሁሉ በተለይ ወጣቶች ብሶቶቻቸውን በብር ኖቶች ላይ ጽፈው ገበያው እንዲያዘዋውራቸው እያደረጉ ነው። ይህም “የወረቀት ገንዘብን ለተሠራበት ዓላማ ብቻ ተጠቀሙ” የሚለውን ህግ በመጣስ ለቅስቀሳ ሥራ መጠቀም በመሆኑ የሕዝባዊ እምቢተኝነት አካል ነው። በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ በርካታ የወረቀት ገንዘቦች በምሬት መግለጫነት ይውላሉ ተብሎ ይገመታል።
በተጓዳኝ በርካታ አማራጭ ስልቶች ሥራ ላይ መዋል ይኖርባቸዋል። ለምሳሌ፣ ተቀማጭ ገንዘብን ከህወሓት ባንኮች ማውጣት በቀላሉ ተግባራዊ ሊደረግ የሚችል ስልት ነው። በውጋጋን ባንክ ተጀምሮ ወደ አንበሳ ኢንተርናሽናል ከዚያም ወደ ንግድ ባንክ ማሸጋገር ይቻላል።
በወገኖቻችን ላይ የግፍ ፍርድ የሚያስፈርዱ አቃቢያነ ህግ እና የግፍ ብይኖችን የሚሰጡ ዳኞች በቸልታ ሊታለፉ አይገባም። በእስር ቤቶችም በወገኖቻችን ላይ ሰቆቃ እየፈፀሙ ያሉ ጨካኞች ከሰላማዊ ሕዝብ ጋር ተደባልቀው ሰላማዊ ሕይወት እንዲመሩ ሊፈቀድላቸው አይገባም። እነዚህ ሁሉ ሊወገዙ፣ ሊገለሉ፣ በየደረሱበት ሊዋረዱ ይገባል።
በአገዛዙ መንግሥታዊ መዋቅር ውስጥ የሚገኙ ወገኖቻችን በሥራቸው ላይ መለገም ተቀባይነት ያለው በጎ ተግባር እንደሆነ ሰፊ ግንዛቤ ሊያገኝ ይገባል። ከአምባገነን ሥርዓት ጋር መተባበር እኩይ ተግባር ሲሆን አምባገነን ሥርዓትን ከውስጥ መቦርቦር ደግሞ የሚበረታታ ሰናይ ሥራ ነው።
ለወያኔ አገዛዝ ግብር መክፈል የምናቆምበት ሰዓትም ተቃርቧል። በራሳችን ገንዘብ ገዳዮቻችን እንዲሰለጥኑብን መፍቀድ የለብንም። ስለሆነም “ግብር አንከፍልም”፤ “መዋጮዎቻችሁ አይመለከቱንም” የምንልበት ቀን ቀርቧል።
በፋይዳ የለሽ ምርጫ የሀገር ሀብት ሲመዘበር ማየት አንሻም። በአግባቡ ለማይቆጠር ድምፃችን አንድም ደቂቃ የምናባክንበት ምክንያት የለምና ሁላችንም የምርጫ ካርዶቻችንን ቀዳደን ቁርጭራጮቹን በየመንገዱ ልንበትናቸው ይገባል።
እነዚህን እነዚህን የመሳሰሉ ናቸው የሕዝባዊ እምቢተኝነት የመጀመሪያ ደረጃዎች። እነዚህን እያደረግን በምስጢር መደራጀታችንን እንቀጥል። ከጥቂት በኋላ አምባገነኑን ሥርዓት የሚያንበረክክ ኃይል እንፈጥራለን። ጥቃት ቢደርስ የሚመክት ኃይል የተደራጀ በመሆኑም ሕዝባዊ እምቢተኝነትና ሕዝባዊ አመጽ ተቀናጅተው እንዲሄዱ ይደረጋል።
አርበኞች ግንቦት 7:የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሕዝባዊ እምቢተኝነትንና ሕዝባዊ አመጽን አቀናጅቶ ለመምራት የተዘጋጀ፤ ለዚህ የሚያበቃው ድርጅታዊ አቅም እየገነባ ያለ ድርጅት ነው። አርበኞች ግንቦት 7 “እንሰባሰብ በወያኔ ላይ የምናቀርባቸው ተቃውሞዎች በሙሉ ወደ እምቢተኝነት ከፍ እናድርጋቸው” ይላል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Ethiopia: Human Rights Abusers should be barred from the United States

March 13, 2015
Laura Hruby
Ethiopian Desk Officer
Office of East African Affairs
Bureau of African Affairs
Washington D.C. 20520
Tel: (202) 647-6473
Email: HrubyLP@state.gov
Date: March 11. 2015
Re: Human Rights Abusers should be barred from the United States.
We are writing this letter to lodge a formal complaint to why Mr. Abdi Mohamud Omar, the Somali Regional President of Ethiopia, was permitted an entry visa to the United States. To the best of our knowledge, this is the third time Mr. Abdi Mohamud Omar was allowed to enter the United States, despite his cruel human rights record which the State Department is clearly knowledgeable. In January of 2011, Mr. Omar’s first visit to the United States, the good offices of our two Minnesota Senators, Senator Amy Klobuchar and Senator Al Franken, as well as Congressman Keith Ellison have personally contact the State Department and pleaded to stop Mr. Omar’s entry to the United States.
Mr. Abdi Mohamud Omar, the Somali Regional President of Ethiopia
Mr. Abdi Mohamud Omar, the Somali Regional President of Ethiopia
We are again at your mercy to consider our request. We are vehemently protesting the decision to allow Mr. Omar to enter the United States. Mr. Omar and his delegation are known human rights violators who have earned despicable record in their part for the suffering of the Ogaden Somali civilians in Ethiopia. Mr. Omar, who leads the delegation, is the person who is responsible for the creation and maintenance of the brutal paramilitary force called Liyuu Police whose mission is to perpetuate dreadful crimes against innocent civilians. Under the supervision of Mr. Omar, thousands of people have been mass executed, tortured, raped, and displaced. The crimes he is responsible for has been cited in many reputable reports published by independent organizations like the Human Rights Watch, Amnesty, and your own Department of State’ yearly Human Rights report which highlights these unspeakable crimes in details. Mr. Omar uses the Liyuu Police to solely created fear of terrorizing the population. The Liyuu Police are systematically unleashed on the population to commit crimes against humanity. The magnitude of their oppression is intense and widespread. Please view the attached testimonies as evidences to show you that Mr. Omar’s forces perpetuating unabated arbitrary arrests, open executions, torture, imprisonment without fair trail, and mass disappearances. Moreover, Mr.Omar’s troops are using rape as a weapon to suppress innocent and defenseless women.
We believe it was wrong for the State Department to issue a diplomatic visa to a registered human rights violator and his associates. The United States law prohibits entry to anyone with this distained record. We should comply with these rules when issuing visas. We are respectfully requesting from your office to enforce the rule governing “No Safe Haven: Law Enforcement Operation against Human Rights Violator in the U.S. Law”. It is only fair that Mr. Omar and his delegation should immediately be removed from the United States ‘soil. We appreciate for your understanding in this urgent matter.
Evidences against Mr. Omar and his delegation.
Abdullahi Hussein’s testimony at Frontline Club Oslo, Norway. Abdullahi Hussein was Abdi Mohamud Omar’s personal assistant and cameraman.
https://vimeo.com/88461621
Ethiopian military displays dead bodies of civilian & freedom fighters for public fear
https://www.youtube.com/watch?v=18PC38rplr0
Dictator Meles Zenawi’s Ogaden Genocide – Ethiopia
https://www.youtube.com/watch?v=UeR3AmFOzOc
https://www.youtube.com/watch?v=TcSZg_lgFxM
Human Rights Watch Publication
http://www.hrw.org/news/2008/06/12/ethiopia-army-commits-executions-torture-and-rape-ogaden
Martin Plaut
https://martinplaut.wordpress.com/2014/01/31/silence-and-pain-ethiopias-human-rights-record-in-the-ogaden/
Martin Schibble and Johan Persson testimony
https://www.youtube.com/watch?v=gL6p6GgUKts
http://www.tesfanews.net/ethiopia-may-stand-trial-for-genocide/
http://www.svt.se/nyheter/varlden/in-english-a-wave-of-ethiopian-atrocities-against-villages-in-ogaden
U.S. Department of State Human Rights Report 2013
http://www.ice.gov/human-rights-violators-war-crimes-unit
CC. Linda Thomas-Greenfield, Assistant Secretary of State for African Affairs.
CC. Governor of Minnesota, Mark Dayton
CC. Senator Amy Klobuchar
CC. Senator Al Franken
CC. Congressman Keith Ellison
CC. Congressman Erik Paulsen
CC. Congresswoman Betty McCollum
CC. Mayor Betsy Hodges
CC. Department of Homeland Security
CC. Immigration and Customs Enforcement
CC. National Public Radio
CC. Huffington Post
Thank you,
Ogaden American Community of Minnesota.
3055 Old Hwy 8,
Minneapolis, MN 55418

Tuesday, March 10, 2015

‹‹ኢህአዴግ እያታለላችሁ ነው፡፡ እናንተም ለመታለል ዝግጁ ሆናችኋል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

March 10,2015
(ነገረ ኢትዮጵያ) የአውሮፓ ህብረት ዛሬ መጋቢት 1/2007 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው ጽ/ቤቱ ባደረገው ስብሰባ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በተጋባዥ እንግዳነት ተገኝተው ከህብረቱ ተወካዮች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ኤምባሲ ያላቸው 20 ያህል የህብረቱ አባል አገራት በተገኙበት ስብሰባ ላይ አብዛኛዎቹ በአምባሳደሮቻቸው እንዲሁም ቀሪዎቹ በምክትል አምባሳደሮቻቸው ተወክለው የተገኙ ሲሆን ተወካዮቹ ወቅታዊ የምርጫ ሂደት እንቅስቃሴና የሰማያዊን የምርጫ እንቅስቃሴ፣ በምርጫው ሂደት እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች፣ የፓርቲው አማራጭ ፖሊሲዎች፣ የድርጅቱን ጥንካሬ፣ የአንድነት አባላት ወደሰማያዊ መምጣታቸው ለትግሉ የሚኖረው ትርጉምና ሌሎችም ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለኢ/ር ይልቃል ጌትነት ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በበኩላቸው ሰማያዊ ፓርቲ ከ200 በላይ ዕጩዎች በህገ ወጥ መንገድ እንደተሰረዙበት፣ የፓርቲው የቅስቀሳ መልዕክቶቹ ከ6 ጊዜ በላይ በሚዲያ እንዳይተላለፍ መከልከሉን፣ የተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ድብደባ፣ እስራትና ወከባ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ጠቅሰው በምርጫ ሂደት ኢህአዴግ አፋኝነቱን አጠናክሮ መቀጠሉን ገለጸዋል፡፡
በሌላ በኩል የአንድነት አባላት ሰማያዊን መቀላቀላቸው ትግሉን እንደሚያጠናክረው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በአንድነትና መኢአድ ላይ የተፈፀመው ህገ ወጥ ተግባር መሆኑን እንዲሁም ኢህአዴግ ተቃዋሚዎችን በኃይል እያጠፋ ‹‹ከእኔ ውጭ አማራጭ የለም›› የሚል አቋሙን ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ማሳየት እንደሚፈልግ ለህብረቱ ተወካዮች አስረድተዋል፡፡

‹‹የአውሮፓ ህብረት ችግር የኢትዮጵያን ችግር በአውሮፓውያን ተቋማትና የስነ ልቦና ልክ ማየቱ ነው›› ያሉት ኢ/ር ይልቃል የአውሮፓ ህብረት ‹‹የተቃዋሚዎች አማራጭ ፖሊሲያቸው ምንድን ነው?›› በሚል የሚያነሱትን ተደጋጋሚ ጥያቄ አስታውሰው መደረጀትና መናገር ያልቻለውን የኢትዮጵያን ህዝብ በአውሮፓ ተቋም አይን አይቶ እንዲህ አይነት ጥያቄዎችን ማንሳቱ ከኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር ብዙም እርባና እንደሌለው ገልጸዋል፡፡ ‹‹በእኛ አገር የፖለሲ አማራጭ ለማቅረብ አይቻልም፡፡ ሚዲያው በገዥው ፓርቲ የተያዘና የተቃዋሚዎችን ሀሳብ የማያስተናግድ ዝግ ሆኗል፡፡ እናንተ እንደምትገምቱት የፖሊሲ አማራጭ ለማቅረብ አመች ሁኔታዎች ቢኖሩ ተቃዋሚዎች ከኢህአዴግ የተሻለ ምሁርራንና ሀሳብ ስላላቸው ዝርዝር ፖሊሲያቸውን ለማቅረብ አይቸገሩም ነበር፡፡›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ኢህአዴግ ‹‹ተቃዋሚዎች የተበታተኑና የተዳከሙ በመሆናቸው ለቀጠናው ሰላም አማራጩ እኔ ብቻ ነኝ›› ብሎ የአውሮፓ ህብረትን እንደሚያታልል የገለጹት ኢ/ር ይልቃል ‹‹ኢትዮጵያውያን ካላቸው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ማየት ስላልቻላችሁ ኢህአዴግ እያታለላችሁ ነው፡፡ እናንተም ለመታለል ዝግጁ ሆናችኋል፡፡›› ሲሉ የአውሮፓ ህብረትን ወቅሰዋል፡፡

Monday, March 9, 2015

የኢትዮጵያ ጠላት ወያኔ – ወያኔ ብቻ ነዉ!

March 9,2015
pg7-logoባለፈዉ ሳምንት አይጋፎረም የሚባለዉና የወያኔን ቱልቱላ በዉጭ አገሮች የሚያናፍሰዉ ድረገጽ ከነብስ አባቱ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአደራ የተሰጠዉን አንድ የመላምት ድርሰት የፊት ለፊት ገጹ ላይ ለጥፎት የህዝብን ስሜት የኮረኮረ እየመሰለዉ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት ከተነሳ ከሁለት ሺ አመታት በኋላ ይሁዳዊ ክህደት ሲክድ እጅ ከፍንጅ ተይዟል። የሚገርመዉ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙር ሆኖ ሳለ ያንን የመሰለ የክህደት መንፈስ ልቡ ዉስጥ ያስቀመጠለት ሰይጣን እንደሆነ ሁሉ አዲስ ዘመንና አይጋ ላይ የወጣዉን ጽሁፍ የጻፈዉ ግለሰብም የወያኔ ጌቶቹን ምክር ተቀብሎ አሜን አለ እንጂ የዚህ የዉሸት ድርሰት ጠንሳሾች በሰይጣን የሚመሰሉት የወያኔ መሪዎች ናቸዉ። የጽሁፉ ደራሲ ነኝ ግለሰብ የወያኔን ትዕዛዝ ከመቀበል ዉጭ ያደረገዉ ነገር ቢኖር ስሙ ከፅሁፉ አርዕስት ስር እንዲቀመጥ መፍቀዱ ብቻ ነዉ – ለዚያዉም የብዕር ስም!
አገሮች፤ ድርጅቶች ወይም የፖለቲካ ፓርቲዎች የፕሮፓጋንዳ ጦርነት ዉስጥ ሲገቡ በዉሸት ዉስጥ እዉነት ወይም በእዉነት ዉስጥ ዉሸት እየሸነቆሩ ነዉ የፕሮፓጋንዳቸዉ ኢላማ የሆነዉን የህብረተሰብ ክፍል ቀልብ ለመግዛት የሚፍጨረጨሩት እንጂ ዉሸትን በዉሸት ለዉሰዉ ቢያቀርቡማ ህዝብ እንኳን ሊያምናቸዉ ደግሞ ሊሰማቸዉም ፈቃደኛ አይሆንም። ይህ ከሰሞኑ አይጋፎርምና አዲስ ዘመን ላይ የወጣዉ ጽሁፍ ግን ምንም አይነት የፕሮፓጋንዳ ህግ አይከተልም፤ ምክንያቱም ጽሁፉ የተጻፈዉ ህግ የሚባል ነገር በሌለባትና ወያኔና ግብረ አበሮቹ እራሳቸዉ ህግ በሆኑበት አገር ዉስጥ ነዉ። ጽሁፉ ሲጀምር በዉሽት ይጀምርና መሀል ላይ ዉሸቱን በዉሸት አጠናክሮ በዉሸት ይደመደማል። እንደዚህ አይነት የዉሽት ክምር የሚመጣዉ ደግሞ ከሌላ ከየትም ሳይሆን በዉሸት ተወልደዉ፤ በዉሸት አድገዉ በዉሸት ከሸበቱት የወያኔ መሪዎች ብቻ ነዉ። ዉድ አድማጮቻችን የዚህ ጽሁፍ አላማ ለሻዕቢያ ጥብቅና መቆም አይደለም፤ ሻዕቢያ ከኛ በላይ ለራሱ ጥብቅና መቆም ይችላል። የዚህ ጽሁፍ ብቸኛ አላማ የኢትዮጵያ ህዝብ ገንበዙን፤ ሀብቱንና ጉልበቱን አስተባብሮ መዋጋት የሚገባዉ ቀንደኛ ጠላቱ ወያኔ መሆኑን መናገር ነዉ። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ትናንት ሲከናዉን የምናዉቀዉንና አይናችን ፊት ተፈጽሞ ከ “ሀ” ወደ “ፐ” የተጻፈዉን ታሪክ ዛሬ ወያኔና ቡችሎቹ ከ “ፐ” ወደ “ሀ” ሲያነብቡትና የኢትዮጵያን ህዝብ ለማሳሳት ሲሞክሩ ዝም ብለን አንመለከትምና ይህንን የዉሸት ክምር ከመሰረቱ መናድ እንፈልጋለን።
ይህንን በዉሸት የተጀቦደ የወያኔ ቡትቶ እንዳለ ማቅረቡ የአድማጭን ጆሮ ማደንቆር ስለሚሆን አንሞክረዉም። ሆኖም ወያኔ በተከበበና አንድ እርምጃ ወደማይቀረዉ ዉድቀቱ በቀረበ ቁጥር የሚመዝዛቸዉን አገር የሚገዘግዙ መጋዞች የኢትዮጳያ ህዝብ ከአሁኑ አዉቆ እንዲጠነቀቅ ስለምንፈልግ የፅሁፉን ጎላ ጎላ ያሉ የዉሸት ምሶሶዎች እንዳሉ ለማቅረብ እንገደዳለን።
የመመሪያዉ አይን ያወጣ ዉሸት “በወቅቱ ኢሕአዴግ ከበረሀ ይዞት የመጣው መደበኛ ያልሆነ ሰራዊት ብቻ በእጁ ነበር። ቀድሞ የነበረው የኢትዮጵያ መከላከያ ሀይል፣ የምድር ጦሩ፣ ታንከኛው፣ መድፈኛው፣ አየር መከላከያው፣ አየርሀይሉ፣ ባህር ኃይሉ፣ ኮማንዶው ሰራዊት፣ ፖሊስና ሌሎችም ሙሉ በሙሉ ተበትነዋል” ይላል። ይህ ዉሸት ከተለመዱት የወያኔ ተራ ዉሸቶች ጋር ሲተያይ ተጠንቶበት በጥንቃቄ የተዋሸ ዉሸት ይመስላል። የቀድሞዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ወራዊት ሰራዊት አባላት በገዛ ፈቃዳቸዉ የተበተኑ ይመስል የዚህ ጽሁፍ ጸሀፊ የቀድሞዉ የመከላከያ ኃይል ሙሉ በሙሉ ተበትነዋል እያለ ነዉ የሚነግረን። በእርግጥም ቁጥሩ ከ300 መቶ ሺ በላይ የሚሆን ሰራዊት የኢትዮጵያ ሠራዊት መሆኑ ተረስቶ የደርግ ጦር፤ የትምክህተኞች ኃይል ወይም የነፍጠኞች ምሽግ እየተባለ በወያኔ ዘረኞች ተበትኖ በምትኩ በአንድ ዘር የበላይነት ላይ የተመሰረተ የመከላከያ ኃይል ተገንብቷል። የቀድሞዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የማን ሠራዊት እንደነበር፤ ለምንና በማን እንደተበተናና በምትኩም የተገነባዉ ሠራዊት ለማን ጥቅም እንደቆመ የኢትዮጵያ ህዝብ አንደ ጥቁር ነጭ ለያይቶ የሚያዉቀዉ ሀቅ ነዉና ከዚህ በላይ የምንለዉ ምንም አይኖርም።
ከአንድ ወር በፊት የኢትዮጵያ ሳቴላይት ቴሌቭዥንና ሬድዮ ጋዜጠኞች በኢትዮጵያና በኤርትራ ህዝብ መካከል ሊኖር የሚገባዉን ግኑኝነትና ኤርትራ ዉስጥ እየተካሄደ ነዉ የሚባለዉን የኢትዮጵያ ህዝብ የነጻነት ትግል እንቅስቃሴ አስመልክቶ እዉነቱን ለህዝብ ለማሳወቅ ታሪካዊ ጉዞ ወደ አስመራና የኤርትራ በረሀዎች አድርገዉ ነበር። በጉዟቸዉ ወቅት ጋዜጠኞቹ ሰፋ ያሉ ጉዳዮችን የዳሰሰ ቃለ መጠይቅ ከኤርትራዉ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር አድርገዉ ነበር። ይህ ማን ምን ሰራ የሚለዉን ጥያቄ በታሪክ ወደ ኋላ እየሄደ የሚመልሰዉና በአይነቱ ልዩ የሆነዉ የፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ቃለመጠይቅ በመገናኛ አዉታሮች መሰራጨት ሲጀምር የኢትዮጵያ ህዝብ ከደደቢት ዉሸትና ተረት ዉጭ ሌላ ሲሰማ የሚያመዉ ወያኔ እንደለመደዉ ሲወራጭና እዉነትን ለመጋረድ ሲፍጨረጨር ታይቷል።
የኢትዮጵያን ህዝብ እንዳሰኛቸዉ የሚረግጡት፤ የሚያስሩት፤ የሚገድሉትና በተለይ በቅርቡ የመስፋፋትና የማፈናቀል ፖሊሲያቸዉን የሚቃወመዉን ሁሉ “ልክ እናስገባዋለን” ብለዉ የዛቱት የወያኔ መሪዎች የእነሱን ጠላትነትና ስር የሰደደ ፀረ ኢትዮጵያ አቋም ሸፍነዉ ኤርትራን የኢትዮጵያ ዋነኛ ጠላት አድርገዉ ማቅረብ ጀምረዋል። የሚገርመዉ ይህ ሁሉ አልበቃ ብሏቸዉ የፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ቃለ መጠይቅ በኢሳት ቴሌቪዥን በሚተላለፍበት ወቅት በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በተለይ ሰሜን ኢትዮጵያ ዉስጥ ቀድሞዉኑም ከብልጭ ድርግም አልፎ የማያዉቀዉን አሌክትሪክ ጭራሽ እንዲጠፋ አድርገዋል።
ሻዕቢያና ህወሓት የትጥቅ ትግል በሚያካሄዱበት ግዜ የተነሱበትን ዋነኛ አላማ ለማሳካት የተለያዩ የፕሮፓጋንዳ ጨዋታዎችን ተጫዉተዋል። ከእነዚህ የፕሮፓጋንዳ ጨዋታዎች ዉስጥ አንዱ ኢትዮጵያ ኤርትራን በቅኝ ግዛትነት ይዛለች የሚለዉ ፕሮፓጋንዳ ነዉ።የሚገርመዉ ይህንን ፕሮፓጋንዳ ከባለቤቱ ከሻዕቢያ ይበልጥ የተሸከመዉና ያርገበገበዉ ህወሓት ህወሓት ዉስጥ ደግሞ መለስ ዜናዊና ስብሀት ነጋ ናቸዉ። ይህ ደግሞ ዛሬ እኛ ፈጥረን የምናወራዉ ወሬ ሳይሆን በቦታዉ የነበሩና ህወሓትን የፈጠሩት እን ገብሩ አስራትና እነ ገ/መድህን አርአያ በግልጽ የሚናገሩት እዉነት ነዉ። የትናንቱን የኢህአፓ የበረሃ ዉስጥ ታሪክ ትዝ ለሚለን ደግሞ ህወሓትንና ኢህአፓን ጦር አማዝዞ ለአያሌ ኢትዮጵያዉያን ህይወት መጥፋት ምክንያት የሆነዉ ኢህአፓ ይህንኑ የወያኔን ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ናት የሚለዉን መዝሙር አልዘምርም በማለቱ ነበር። እንግዲህ ዛሬ ይህ ሁሉ መረጃና ይህ መረጃ በእጃቸዉ ላይ ያለ ሰዎች በህይወት እያሉ ነዉ የወያኔ አይነ አዉጣዎች “ከመጀመሪያዉም ሻዕቢያ እንደሚለፈልፈዉ ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት አልነበረችም፤ ይህ የእነ ኢሳያስ እብደት ነዉ እያሉ የራሳቸዉን ቀን የቆጠረ ዕብደት የሚነግሩን። በ1967 ዓም እግራቸዉ የደደቢት በረሃን ከረገጠበት ግዜ ጀምሮ በ1983 ዓም አዲስ አበባን እስከተቆጣጠሩበት ግዜ ድረስ በወዶ ገባነት ከገበቡበት ከሻዕቢያ ጉያ ያልተለዩትና አጠገባቸዉ ያለችዉን አክሱም ፅዮንን ትተዉ ሻዕቢያን ሲሳለሙ የከረሙት የወያኔ መሪዎች ዘንድሮ ሳይታሰብ በድንገት ቀኝ ኋላ ዙር ብለዉ ከሻዕቢያ ጋር የነበራቸዉን አለመግባባት መናዘዝ ጀምረዋል። በተለይ “ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ናት” ብለዉ እራሳቸዉ በጻፉት ማኒፌስቶ ዉስጥ ያሰፈሩትን ቃል ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ የረሳ መስሏቸዉ የክህደት ጫጫታ መደርደር ጀምረዋል።
አገራችን ኢትዮጵያ በየዘመኑ በአንድነቷና በሉዓላዊነቷ ላይ የዘመቱ ብዙ ታሪካዊ ጠላቶች ነበሯት፤ ዛሬም አሏት፤ ሆኖም የኢትዮጵያ ህዝብ በረጂም ዘመን ታረኩ ዉስጥ እንደ ወያኔ ህልዉናዉን፤ አንድቱንና የወደፊት ተስፋዉን ያጨለመበት የዉጭም የዉስጥም ጠላት አጋጥሞት አያዉቅም። የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች መብታቸዉ፤ ነጻነታቸዉና እኩልነታቸዉ ተከብሮ የኖሩበት ዘመን ባይኖርም ኢትዮጵያ እንደ ወያኔ ዘመን በዘር የተከፋፈለችበትና የመበታተን አደጋ ያጋጠማት ግዜ የለም። ዛሬ የኢትዮጵያን አንድነትና የህዝቦቿን መብትና ነጻነት መከበር አጥብቀዉ የሚሹ ወገኖች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሊዋጉት የሚገባ ብቸኛ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት ጠላት ወያኑ ወይም ህወሓት ነዉ። የኢትዮጵያህዝብ መከፈል የሚገባዉን መስዋዕትነት ከፍሎ ወያኔን በአጭር ግዜ ዉስጥ ካላስወገደ የአገራችን ህልዉና በቀላሉ የማይጠገን አደጋ ዉስጥ መዉደቁ አይቀርም።
ይህ የአገራችን አንድነት አደጋ ላይ የመዉደቁ ዜና እጅግ በጣም የሚያስፈራና የሚያሳዝን ዜና ነዉ። ደግነቱ የሚያስደስተን፤ ተስፋችንን የሚያለመልምና አንገታችንን ቀና የሚያሰደርግ ዜናም አለ። ወያኔ አገራችን ላይ ይዞት የመጣዉ አደጋ ከወዲሁ የታያቸዉ ኢትዮጵያዉያን የአባቶቻችዉን ፈለግ ተከትለዉ ዱር ቤቴ ብለዉ ወያኔን በሚገባዉ ቋንቋ ለማነጋገር ተዘጋጅተዋል።የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔንና ወያኔ የፈጠረዉን ዘረኛ ስርዐት ደምስሶ ፍትህ፤እኩልነትና ነጻነት የሰፈነባትን ኢትዮጵያ ለመገንባት በሚየደርገዉ ትግል የመጀመሪያዉ ምዕራፍ ዉስጥ እንደ ኤርትራ ህዝባነ መንግስት አጋር ሆኖ የተሸከመዉ ሌላ አገርም መንግስትም የለም።የኤርትራ ህዝብና መንግሰት ወያኔ የሚባል ነቀርሳ ከስሩ እስካልተነቀለ ድረስ የአፍሪካ ቀንድ የሰላም አየር እየተነፈሰ በሠላም መኖር እንደማይችል ከተረዱ ቆይተዋል። ስለዚህም ነዉ የኢትዮጵያን ህዝብ የነጻነት አርበኞች አስጠግተዉ አስፈላጊዉን እርዳታ ሁሉ የሚያደርጉላቸዉ። ዛሬ ኢትዮጵያንና ኤርትራን የሚመሩ መሪዎችና መንግስታት ዘሏአለማዊ አይደሉም፤ የሁለቱ አገሮች ህዝብ ወንድማማችነትና ጉርብትና ግን ዘለአለማዊ ነዉ። በዚህ ዘሏአለማዊ ወዳጅነትና ጉርብትና ዉስጥ የስግብግቦቹ የወያኔ መሪዎች አመለካከት “እኔ ከሞትኩ ሠርዶ አይብቀል” ካለችዉ እንስሳ የሚለይ አይደለም።ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ቃለመጠይቅ በግልጽ እንደሰማነዉ በኤርትራ በኩል ያለዉ አመለካከት ለኢትዖጵያነ ለኤርትራ ህዝብ ታሪካዊ ትስስር፤ ጉርብትናና ወደፊት ወዳጅነት እጅግ በጣም ከፍተኛ ግምት የሚሰጥ አመለካከት ነዉ። አርበኞች ግንቦት ሰባትና የኤርትራ መንግስት በኤርትራና የኢትዮጵያ ህዝብ የተሳሰረ የጋራ ዕድገት፤ ብልጽግናና መልካም ጉርብትና ላይ እንደ ነቀርሳ የተተከለዉ ዘረኛዉ የወያኔ ስርዐት ነዉ ብለዉ ያምናሉ። ይህ ነቀርሳ በተባበረ የህዝብ ትግል መነቀል አለበት ብለዉም ያምናሉ።
“አህያዉን ፈርቶ ዳዉላዉን እንዲሉ” ዛሬ ወያኔ “ኤርትራ” “ኤርትራ” እያለ የአዞ የሚያነባዉ እሱ ባልተገራ አንደበቱ ሊነግረን እንደሚፈልገዉ ኤርትራ በእርግጥም የኢትዮጵያ ጠላት ሆና አይደለም። ጉዳዩ ወዲህ ነዉ። ወያኔ በኤርትራ አሳብቦ ለኢትዮጵያ ህዝብ መብትና ነጻነት የቆሙ ኃይሎችን ቆርጦ ተነስቷል፤ ይህንን ለማወቅ ደግሞ ብዙ መረጃ መሰብሰብ አያስፈልግም። እራሳቸዉ የወያኔ መሪዎች በየመድረኩ የተናገሩትንና ቡችሎቻቸዉ ደግሞ በቅርቡ አዲስ ዘመን ላይ የጻፉትን ጽሁፍ ማንበቡ ይበቃል – እንዲህ ሲሉ ነበር የጻፉት “አለም አቀፍ ሕጉን ማክበር በሚል እንጂ ዛሬ ይህንን ደባና ሴራውን በጣጥሦ በመጣል ከነሎሌዎቹ ድባቅ በመምታት ከነበረ ወደአልነበረ በመለወጥ ያለአንዳች እንቅፋት ይሕንን ዘመን የማይሽረው ጸረ ኢትዮጵያ ሀይል ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና እፎይታ ማስገኘት ይቻላል፡፡ ኢትዮጵያ ቆርጣ ስትነሳ የሚገታት አንድም ሀይል የለም” የኢትዮጵያ ወጣት፤ ሠራተኛ፤ ገበሬ፤ የመከላከያ ሠራዊት አባላትና ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! ወያኔ ምን ያህል አንተንና አገርህን አንደሚጠላ ባለፉት ሃያ አራት አመታት በግልጽ አሳይቶሀል። ዘንድሮ ደግሞ በተለይ ባለፉት ሦስት ሳምንታት አንተና ልጆችህ በየቀኑ እያደገ በሚሄደዉ የኑሮ ዉድንት እየነደዳችሁ ወያኔ ግን አገራችንን በዘር ከፋፍሎ ለመግዛት የመሠረት ዲንጋይ ያኖረበትን ቀን ለማክበር ከአንድ መቶ ሚሊዮን ብር በላይ አባክኗል። ከዚህ በተጨማሪ ነብሰ ገዳይ ፖሊሶቹን አሰማርቶ አባቶችህ አድዋ ላይ ያጎናፀፉህን አንጸባራቂ የጥቁር ህዝብ ድል በሆታና በእልልታ እንዳታከብር አድርጓል።
ባጠቃላይ አርባኛዉ አመት የህወሓት ምስረታና የኢትዮጵያ ህዳሴ የሚል አዲስ የመላምት ታሪክ እንዲጻፍ እያደረገ በአባቶችህና በእናቶችህ ደም የደመቀዉን ትልቁን የአድዋ ድል ታሪክ እንዲደበዝዝ አድርጓል። የኢትዮጵያ ህዝብ ጨዋ ነዉ- በእርግጥ የኢትዮጵያ ህዝብ ጨዋ ነዉ። ኢትዮጵያዉያን ታጋሾች ናቸዉ? ያለምንም ጥርጥር ኢትዮጵያዉያን አለም የሚያዉቃቸዉ ታጋሾች ናቸዉ። ነገር ግን ትዕግስትም ሆነ ጨዋነት ትርጉም የሚኖራቸዉ ህዝብ መብቱና ነጻነቱ ተከብሮ በማንነቱ ኮርቶ መኖር ሲችል ብቻ ነዉ። እየተረገጠ፤ ልጆቹ ከጉያዉ እየተወሰዱ እየተረሸኑና ታሪኩ ፤ አንድነቱና ብሄራዊ ማንነቱ ሲዋረድ የሚታገስና አንገቱን ደፍቶ የሚኖር ህዝብ የለም። በሳምንቱ መግቢያ ላይ ያከበርነዉ የአድዋ ድል በዐልም የሚያሳስበን ይህንን እዉነት ነዉ። የዚህ ዘመን ኢትዮጵያዊ አባቶቹና እናቶቹ በነጭ ፋሺስቶች ላይ በተጎናፀፈት የአድዋ ድል መኩራት ብቻ ሳይሆን የሱም ልጆች አባቶቼ ብለዉ አንዲኮሩበት የአድዋን ድል በዛሬዎቹ ጥቁር ፋሺስቶች ላይ መድገም አለበት። አድዋ የእኛ የኢትኦጵያዉያን ብቻ ሳይሆን የአለም ጥቁር ህዝብ በነጭ ወራሪዎች ላይ የተጎናፀፈዉ አንፀባራቂ ድል ነዉ። አድዋ ትዕግስትና ጨዋነት ለማይገባቸዉ እብሪተ ችና ትዕቢተኞች ቆራጡና ጀግናዉ የኢትዮጵያ ህዘብ የማይረሳ ትምህርት ያስተማረበት ቦታ ነዉ። ዛሬ ደጃፋቸዉ ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ የሰራዉን ገድል የረሱና አድዋ ላይ ታሪክ ሲሰራም ቢሆን ባንዳዎች የነበሩ የባንዳ ልጆች ከቅኝ ገዢዎች ባልተለየ ጭካኔ፤ ዝርፊያና ጥላቻ አገራችን ኢትዮጵያን እንዳልነበረች እያደረጓት ነዉ። የዛሬዉ ትዉልድ ኢትዮጵያዊ ከዚሁ ከአድዋ አፈር በቅለዉ በራፋቸዉ ላይ ህዝብ የሰራዉን ታሪክ እየፋቁ የራሳቸዉን የመላ ታሪክ የሚጽፉ ከዲዎችን አባቶቹ ለፋሺስቶች ያስተማረዉን ትምህርት ለነዚህ ፋሽስቶችም እንደገና ማስተማር አለበት።

Ethiopia: Digital Attacks Intensify (Human Rights Watch)

March 9, 2015
(New York) – The Ethiopian government has renewed efforts to silence independent voices abroad by using apparent foreign spyware, Human Rights Watch said today. The Ethiopian authorities should immediately cease digital attacks on journalists, while foreign surveillance technology sellers should investigate alleged abuses linked to their products.Ethiopia: Stop Using Anti-Terror Law to Stifle Peaceful Dissent
Independent researchers at the Toronto-based research center Citizen Lab on March 9, 2015, reported new attempts by Ethiopia to hack into computers and accounts of Ethiopian Satellite Television (ESAT) employees based in the United States. The attacks bear similarities to earlier attempts to target Ethiopian journalists outside Ethiopia dating back to December 2013. ESAT is an independent, diaspora-run television and radio station.
“Ethiopia’s government has over the past year intensified its assault on media freedom by systematically trying to silence journalists,” said Cynthia Wong, senior Internet researcher at Human Rights Watch. “These digital attacks threaten journalists’ ability to protect the safety of their sources and to avoid retaliation.”
The government has repressed independent media in Ethiopia ahead of the general elections scheduled for May, Human Rights Watch said. Many privately owned print publications heavily self-censor coverage of politically sensitive issues or have shut down. In the last year, at least 22 journalists, bloggers, and publishers have been criminally charged, at least six publications have closed amid a campaign of harassment, and many journalists have fled the country.
Many Ethiopians turn to ESAT and other foreign stations to obtain news and analysis that is independent of the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front. However, intrusive surveillance of these news organizations undermines their ability to protect sources and further restricts the media environment ahead of the elections. Government authorities have repeatedly intimidated, harassed, and arbitrarily detained sources providing information to ESAT and other foreign stations.
Citizen Lab’s analysis suggests the attacks were carried out with spyware called Remote Control System (RCS) sold by the Italian firm Hacking Team, which sells surveillance and hacking technology. This spyware was allegedly used in previous attempts to infect computers of ESAT employees in December 2013. If successfully installed on a target’s computer, the spyware would allow a government controlling the software access to activity on a computer or phone, including email, files, passwords typed into the device, contact lists, and audio and video from the device’s microphone and camera.
Citizen Lab also found that the spyware used in the attacks against ESAT appeared to have been updated as recently as December 2014. On November 19, a security researcher, Claudio Guarnieri, along with several nongovernmental organizations, publicly released a tool calledDetekt, which can be used to scan computers for Hacking Team RCS and other spyware. Citizen Lab’s testing determined that Detekt was able to successfully recognize the version of RCS used in a November attack, but not the version used in a December attack. Citizen Lab concluded that this may indicate that the software had been updated sometime between the two attempts.
These new findings, if accurate, raise serious concerns that Hacking Team has not addressedevidence of abuse of its product by the Ethiopian government and may be continuing to facilitate that abuse through updates or other support, Human Rights Watch said.
Hacking Team states that it sells exclusively to governments, particularly law enforcement and intelligence agencies. The firm told Human Rights Watch in 2014 that “we expect our clients to behave responsibly and within the law as it applies to them” and that the firm will suspend support for its technology if it believes the customer has used it “to facilitate gross human rights abuses” or “who refuse to agree to or comply with provisions in [the company’s] contracts that describe intended use of HT [Hacking Team] software.” Hacking Team has also stated that it has suspended support for their product in the past, in which case the “product soon becomes useless.”
Media reports and research by independent human rights organizations in the past year have documented serious human rights violations by the Ethiopian government that at times have been facilitated by misuse of surveillance powers. Although spyware companies market their products as “lawful intercept” solutions used to fight serious crime or counterterrorism, the Ethiopian government has abused its counterterrorism laws to prosecute bloggers and journalists who merely report on public affairs or politically sensitive issues. Ethiopian laws that authorize surveillance do not adequately protect the right to privacy, due process, and other basic rights, and are inconsistent with international human rights requirements.
Hacking Team previously told Human Rights Watch that “to maintain their confidentiality” the firm does not “confirm or deny the existence of any individual customer or their country location.” On February 25, 2015, Human Rights Watch wrote to the firm to ask whether it has investigated possible abuse of its products by the Ethiopian government to target independent media and hack into ESAT computers. In response, on March 6 a representative of the firm emailed Human Rights Watch that the company “take[s] precautions with every client to assure that they do not abuse our systems, and, we investigate when allegations of misuse arise” and that the firm is “attempting to understand the circumstances in this case.” The company also stated that “it can be quite difficult to get to actual facts particularly since we do not operate surveillance systems in the field for our clients.” Hacking Team raised unspecified questions about the evidence presented to identify the spyware used in these attacks.
Human Rights Watch also asked the company whether contractual provisions to which governmental customers agree address governments’ obligations under international human rights law to protect the right to privacy, freedom of expression, and other human rights. In a separate March 7 response from the firm’s representative, Hacking Team told Human Rights Watch that the use of its technology is “governed by the laws of the countries of our clients,” and sales of its technology are regulated by the Italian Economics Ministry under the Wassenaar Arrangement, a multilateral export controls regime for dual-use technologies. The company stated that it relies “on the International community to enforce its standards for human rights protection.”
The firm has not reported on what, if any, investigation was undertaken in response to the March 2014 Human Rights Watch report discussing how spyware that appeared to be Hacking Team’s RCS was used to target ESAT employees in 2013. In its March 7 response, the company told Human Rights Watch that it will “take appropriate action depending on what we can determine,” but they “do not report the results of our investigation to the press or other groups, because we consider this to be an internal business matter.”
Without more disclosure of how Hacking Team has addressed potential abuses linked to its business, the strength of its human rights policy will be in question, Human Rights Watch said.
Sellers of surveillance systems have a responsibility to respect human rights, which includes preventing, mitigating, and addressing abuses linked to its business operations, regardless of whether government customers adequately protect rights.
“Hacking Team should publicly disclose what steps it has taken to avoid abuses of its product such as those alleged against the Ethiopian government,” Wong said. “The company protects the confidentiality of its customers, yet the Ethiopian government appears to use its spyware to compromise the privacy and security of journalists and their sources.”