Wednesday, February 24, 2016

ጎጃሜው ጎንደሬው retarded (ኋላ ቀር) ነው ትላለች የፓልቶክ ታዳሚዋ ሚሚ ስብሃቱ

February 24,2016

ነጻው ፕሬስ በታፈነበት፣ እስክንደር ነጋ፣ ተመስገን ደሳለኝ፣ ዉብሸት ታዬ፣ ጌታቸው ሽፈራው የመሳሰሉ አንጋፋ ጋዜጠኖች ብእር በማንሳታቸው ብቻ ሲታሰሩ፣ ቁጥራቸው እጅግ በጣም ብዙ የሆኑ ጋዜጦች ሲዘጉ፣ እንደ ኢሳት፣ አሜሪካን ድምጽ፡ራድዮ ያሉ ጃም ሲደረጉ፣ የተለያዩ ድህረ ገጾች ብሎክ ሲደረጉ፣ የተወሰኑ የሜዲያ ሰዎች ነን የሚሉ፣ የሕወሃትን የዉሸት ፕሮፖጋንዳ በማሰራጨት ሌትና ቀን የሚሰሩ ጋዜጣኛ ተብዬ ካድሬዎች ግን ራዲዮ፣ ቴሌቭዝን ማሰራጨት ፣ ጋዜጣዎች ያለ ምንም ችግር ማተም ተፈቅዶላቸው ሕዝቡን እያደነቆርይ እንደሆነ ይታወቃል።
ከነዚህ የሜዲያ ሰዎች ነን ባዮች መካከል የቀድሞ የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ባልደረባ የነበረቸውና የሕወሃት አገልጋይ የሆነችው ሚሚ ስብሃቱ ትገኝበታለች። ሚሚስ ስብሃቱ ለሕወሃት ባለስልጣናት ቀጥታች ግንኙነት ያላት ሲሆን፣ በተለያዩ ጊዘያታ በዛሚ ራዲዮ ባለስልጣናትን ታቀርባለች። በሕወሃት ጓዳ የሚነገረውን በማንጸባረቅ የምትታወቀዋ ሚሚ ስብሃቱ አስደንጋጭና የሕወሃት ዉስጣዊ አስተሳሰብ የሚያመላከት ጸያፍ ንግግር ተናግራለች።
አማራው በተለያየ መልኩ አንድ የሆነ አይነት ግጭት ፈጥረን ትግሬውን  ለመከፋፈል ለመበጣጠስ ነው የሚፈለጉት። ከተነቃባቸው ቆይተዋል” ስትል “አማራ” ብላ የጠራችው ማህበረሰብ “ትግሬ” ብላ በጠራችው ማህበረሰብ ላይ ችግር እንዳለው ትናገራለች። የትግራይ ህዝብ በወሎ፣ በጎንደር ከሚኖረው ኢትዮጵያዊ ወንድሙ ጋር ለዘመናት በሰላም በፍቅር የኖረ፣ የተዋለደ፣ የተዛመደ እንደሆነ ይታወቃል። ሆኖም ይሄን ለዘመናት አብሮ የኖረን ህዝብ በማለያየት ስልጣኑን ለማቆየት የሚፈለገው የሕወሃት መርዛማን ፖሊሲ ነው ሚሚ ስብሃቱ ለማንጸባረቅ የሞከረቸው።
“Yes   ጎጃሜው retarded ነው። ጎንደሬው ጠላት ነው። ሊሸለሙ አይገባቸዉም። retarded ናቸው። በአስተሳሰብ በጭንቅላት በጣም ዝቅ ያሉ ናቸው “  ስትል የበላይ ዘለቀን  ልጆች ጎጃሜዎችን፣ የመይሳው ካሳን ልጆች ጎንደሬዎችን ሰድባለች። “ ኢትዮጵያዊነት ያልተላበሰ አካሄድን የሚከተሉ ስለሆኑ እነዚህ ዝቅተኞች እያልን refer እናደርጋቸዋለን። ዝቅተኛ ፣ retarded ፣ idiot  ብለን ልንጠራቸው እንችላለን”  ስትል ለህዝቡ ያላትን ንቀት ገልጻለች።
ሚሚ ስብሃቱ በገሃድ ተናገርችው እንጂ ፣ ይህ አይነቱ በጎንደር፣ በጎጃም፣ በወሎ፣ በሰሜን ሸዋ የሚኖረው፣ “አማራ” ብለው የሚጠሩትን ግን ግን የብዙ ብሄረሰቦች ድብልቅ የሆነውን አማርኛ ተናገሪ ህዝብን፣ ላለፉት 25 አመታት ህወሃት እንደ ጠላት ሲያይ እንደነበረ የተለያዩ መረጃዎች ያሳያሉ።
“ወደድክም ጠላህም ዋጋ ተከፍሎ መጥተናል። End of the story ፡፡ለሚቀጥለው ደግሞ እንጸልይላቸዋleን። አይ ጎንደር የትኛው ፈንዲሻ እንደሚመጣ” ስትል በድጋሚ እየሳቀች በጎንደሬዎች ላይ አሹፋለች። የሚሚ ስብሃትን ንግግር ያዳምጡ::


No comments: