Thursday, September 24, 2015

የኢትዮጵያ የድርቅ ሁኔታ እየተባባሰ መጥቶአል፣ መንግስትም ችልተኝነትን አብዝቶአል

September 24,2015
በሃገሪቱ እየተስፋፋ የመጣውን አረንጓዴው ድርቅ እየተባለ የሚጠራው ከፍተኛ ረሃብ በመላው ሃገሪቱ እየተስፋፋ የመጣ ሲሆን በአሁን ሰአት በሰሜኑ ክልል ምስራቅ እና ደቡቡን በከፊል ከማጥቃቱም በላይ ከፍተኛውን ህዝብ ወደ ስደት ሲዳርግ ብዙሃኑን ደግሞ በተለያዩ የሃገሪቱ ትልልቅ ከተሞች ለልመና እንዲሰደዱ አድርጎአል ። በተለይም የገበሪው የዚህ አመት የምርት ሁኔት ማሽቆልቆል እና መንግስት በገበሬው ህዝብ ላይ የሚያሳርፈው ጫና ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ ፣ምርቱን ማምረት ያልቻለው እና ያሉትን የቀንድ ከብቶችንም ለመሸጥ ወደ ከተማ የሚያጓጉዘው ገበሬ በፖሊሶች እየተነጠቀ ለጨረታ ሲቀርብበት ገበሬውን ለረሃብ እና ለከፍተኛ ችግር እንዲሁም ቤተሰቡን በየሜዳው ትቶ እንዲሄድ እያእረገው ነው ሲሉ ከአዲስ አበባ የተሰራጨው ሪፖርት ያመለክታል ።

ባሳለፍነው ሁለት ወራት የመንግስት ኮሙኒኬሽን ምንስቴር የሆኑት አቶ ሬድዋን ሁሴን ገበሬው ክብቶቹን በወቅቱ ስላላጠጣ ነው ብለው በአደባባይ ዋሽተውት የነበረውን ዘገባ እንደገና መልስ ብለው እርዳታ ያሽናል ብለው የአለም መንግስታትን መማጸን የቻሉበት አጋጣሚ እንደነበር ቢታወስም የጉዳዩ ተያያዥነት የመጣው የኢትዮጵያ መንግስት ኦባማን እና ሌሎች የአፍሪካ መሪዎችን ለመቀበል ያቀረበውን በጀት እንዳይቆረጥበት ያዘጋጀው እቅድ ነሲሉ ይሄውም ከ8፣ሚሊዮን ኣሜሪካን ዶላር በላይ ለዚኢያ ስብሰባ የታቀደ አላማ ላይ እንዲውል ሃገሪቱ ለስብሰባው መበጀቷን ሪፖርቱ ያመለክታል ፤ ይህ በእንዲህ እንዳለ ፕረዚዳንት ኦባማ ለሶስት ቀን ጉብኝቱ ብቻ 2.4 ሚሊዮን ዶላር ብቻ የከፈለ ሲሆን ይህም ከሁለት መቶ አባል ሰራተኞቹ እና የአየር ሃይል አባላቶቹ ጭምር እና ፣የበረራ ቁጥጥር ክፍል የሚያደርጉትንም የሚጨምር እንደሆነ ገለጸዋ አብራርቶአል ሆኖም  ሌሎች የአፍሪካ መሪዎች ግን በአፍሪካ የኢኮኖሚ ደረጃ ብች ሊንቀሳቀሱ የሚችሉ ሲሆን ይህን ያህል ወጭ የሚሸፍኑ ኣልሆኑ ይታወቃል በዚህ ጉዳይ ላይ ሃገሪቱ ከትርፍ ይልቅ በኪሳራ ልትንቀሳቀስ ትችላለች የሚለው ከፍተኛ ግምት የተሰጠው ከመሆኑም በላይ መንግስት ለሃገሩ እና ለህዝቡ እንዲሁም  ለህልውናው ቸልተኛ በመሆኑ አስጊ ሁኔታ ላይ ነው ያለነው ሲሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

No comments: