Saturday, September 12, 2015

የትህዴን መሪ አቶ ሞላ አስገዶም ትግሉን ትቶ ለምን ኮበለለ?

September 12,2013


የትህዴን መሪ አቶ ሞላ አስገዶም ትግሉን ትቶ ለምን ኮበለለ ? ሊፈታ የሚገባ ጥያቄ የትህዴን መሪ አቶ ሞላ አስገዶም የተወሰኑ የትህዴን ሰራዊት ይዞ ሀገር ኢትዮጵያ ኮበለለ ይሄ ዜና ብዙዎቻችን እናዳስገረመ እና  አንዳንዶችንም እንዳሰደነገጠና፣ የተወሰኑ ግለሰቦችን እንደስደሰት እያየነው ያለ ነገርሲሆን የአቶ ሞላ  አስግዶም ከትግል ሜዳው መኮብለል እና ወደ ወያኔ ካምፕ መቀላቀል እኔን ባያስደነግጠኝ እና ባያስደስተኝም የአገር አድን ንቅናቄ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው በተሾሙ በማግስቱ ኮብልለው መጥፋታቸው   በጣም አገራሞትን ጭሮ ጥያቄ ስለፈጠረብኝ  ይችን ትንሽ ነገር ማለትን ወደድኩኝ:: በመጀመሪያ ልናውቀው የሚገባው ነገር እንደዚህ አይነት ነገር በትግል ውስጥ ሊያጋጥም እና ሊከሰት የሚችል እንደሆነ  መገንዘብ ያስፈልገናል::

እውነትና  ንጋትእያደር ይጠራል ቢሆንም ነገሩ እንደእኔ አመለካከት ግን አቶ ሞላ አስግዶም በመጀመሪያም ኤርትራ ተቀምጠው የየትግራይ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴን (ትህዴን) በሊቀመንበርለ ሲመሩት የነበሩት በእርግጥ ጸረ ወያኔ አቋምና አላማ ኖሮቸው ነበር ወይስ ሌላ ስውርና የተደበቀ አጀናዳ በጉያቸው ደብቀው አስመሳይነትን ተላብሰው ውስጥ ውስጡን የየወያኔ ፖለቲካዊ አጀንዳ ሲያስፈጽሙ የነበሩ ሰው ነበሩ ወይ የሚለውን ነገር እንድጠረጥር ቢያደርጉኝም  ምንአልባትም ማን ያውቃል እኝህ ሰው የሆነ ጊዜያዊ ጥቅም መሻት አታሏቸው ይሆን የሚልም ነገር እንዳስብ አድርጎኛል:: ምክንያቱም ለእውነት እንዳንታገል ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል አንዱ ለጊዜያዊ  ጥቅም መታለል በመሆኑ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንኮን ተዘግቦ እንደምናገኘው ኤሳው ለሆዱ ብሎ በምስር ወጥ ብኩርናውን አሳልፎ ለወንድሙ ለያዕቆብ እንደሸጠው ሁሉ ዛሬም በዚህ ዘመን ለጊዜያዊ ጥቅም ተብሎ ማንነትንና ሕሊናን በመሸጥ አስመሳይነትን ተላብሰው ለእውነት ከመቆም ይልቅ የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞችን ተቀብለው ከእውነት ጋር የተጣሉ በርካቶች ሰዎች እንዳሉ እናውቃለን።

 ሰው ለተለያዩ ጥቅሞች ሲል አስመሳይነትን ተላብሶ መኖርን የሚችል ፍጡር ነው::አስመሳይነት ዛሬ የጀመረ ብቻም ሳይሆን በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ አሉታዊ ተጽኖ ከፈጠሩ ጉዳዮች መካከል ትልቁን ስፍራ ይዞ እናገኘዋለን። በጥቅም ታውረው አስመሳይነትን ተላብሰው በጣሊያን ወረራ ዘመን መንገድ እየመሩ ወደ መሀል ሀገር ከማስገባት በተጨማሪም የንጉሠ ነገሥቱ የቅርብ ባልሙዋል ከነበሩ መኩዋንንቶች እና መሳፍንቶች መካከል ሳይቀሩ ለጣሊያን ያደሩ ሰዎችን እንደምሳሌ ማንሳት ይቻላል። እነዚህ በአስመሳይነት የተጠቁ ወገኖች ወይም ሹማምንቶች ህዝቡ ተቃውሞውን በማቆም መሰሪዋ ጣሊያን ይዛው የመጣችውን የይምሰል እውቀት እና ስልጣኔ በመቅሰም ሀገሩን ያለማ ዘንድ በሀሰት ለመሸንገል ሞክረዋል። መረጃ በመስጠት በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ደማቸው በግፍ እንዲፈስ ያደረጉት አስመሳዮች ወይም ጥቅመኞች ናቸው።

ዛሬም አስመሳይ ጥቅመኞች ጊዜያዊ ጥቅምን እና የወያኔን ትርፍራፊ ለመልቀም ቢኮበልሉ ድሩም ከትግል ጉራው የነበሩት  ታሪክን ለመበረዝ፣ የህዝብን ለመግደል ስለነበረ የሚያስደነግጥ ነገር አይኑርም ባይ ነኝ ምክንያቱም ነገም ሌላ ነገር ልንሰማ እንችል ይሆናልና ስለሆንም ማንኛችንም ከአስመሰይነት ተላቀን ማንነትንና ሕሊናን በጥቅም ሳንሸጥ እንደ ዜጋ ለሀገር በማሰብ ለነጻነት፣ ፍትህና ዲሞክራሲ በጽኑ መታገል ይኖርብናል በማለ  ዘመኑን የድል ያድርግልን እላለው።

ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ

  ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!

No comments: