Monday, December 15, 2014

አቶ ሽመልስ ከማል ከአቶ ሬድዋን ሁሴን ጋር በመጋጨታቸው አኩርፈው ቤት መቀመጣቸው ተሰማ

December 15,2014
የመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ ሽመልስ ከማል ከ ሚኒስትሩ ሬድዋን ሁሴን ጋር መግባባት ባለመቻላቸው አኩርፈው ቤት በመቀመጥ መደበኛ ሥራቸውን እያከናወኑ አለመሆኑን  ምንጮች ገልጸዋል። አቶ ሽመልስ ከደባል ሱስ  ጋር በተያያዘ በመደበኛ የስራ ሰዓታቸው ሊገኙ ባለመቻላቸው ሚኒስትሩ ይህን ባህሪያቸውን እንዲያስተካክሉ ቢነግሩዋቸውም ሊያስተካክሉ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የተፈጠረ መሆኑን ምንጮች ይገልጻሉ። የአቶ ሽመልስን   ሃላፊነት ደርበው እየሰሩ ያሉት በቅርቡ ከዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዳይሬክተርነት ተነስተው የመንግስት ኮምኒኬሽን ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን የተሾሙት አቶ እውነቱ ብላታ ናቸው።

አቶ ሽመልስ በቅርቡ የታዩት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ ሊቀመንበር በመሆናቸው በድርጅቱ ስብሰባ ላይ ብቻ ነው፡፡ የፕሬስ ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ ሰብስቤ ከበደ ከአቅም ማነስና የመልካም አስተዳደር ችግር ጋር ተያይዞ በድርጅቱ ጋዜጠኞች እየቀረበባቸው ያለውን ግልጽ ትችትና ቅሬታ በተደጋጋሚ ስብሰባዎች ላይ በመገኘት ከማስተባበላቸውም በተጨማሪ ጥያቄውን የሚያነሱ ጋዜጠኞችን እስከማስፈራራት የደረሰ ንግግር ሲያደርጉ የተሰሙት አቶ ሽመልስ፣  መደበኛ ስራቸውን መተዋቸው በኮምኒኬሽን መ/ቤቱ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖአል፡፡

አቶ ሽመልስ ከማል በአቶ በረከት ስምኦን ደጋፊነት የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ስራአኪያጅ የነበሩ ሲሆን፣  የ97 ምርጫን ተከትሎ የቅንጅት አመራሮችና ጋዜጠኞች በተከሰሱ ወቅት አቃቤ ሕግን ወክለው ሐሰተኛ መረጃዎች እንዲቀርቡና ሐሰተኛ ምስክሮችን በገንዘብ በመግዛትና በመደለል ለኢህአዴግ ውለታ ለመስራት የጣሩ ሰው መሆናቸው ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጅ አቶ በረከት ከጤና ጋር በተያያዘ ስራቸውን እየተዉ በመምጣታቸው አቶ ሽመልስ ብቸኛው ደጋፊያቸውን አጥተዋል። አቶ ሽመልስ አቶ በረከትን የመተካት ህልም ቢኖራቸውም ሳይሳካላቸው አቶ ሬድዋን ቦታውን እንዲወስዱ ተደርጓል። በሁለቱ ባለስልጣኖች መካከል ባለው ልዩነት የተነሳ፣ አቶ ሽመልስ ከስራቸው የሚባረሩበት ቀን እሩቅ ላይሆን እንደሚችል ወይም በገዛ ፈቃዳቸው ስራቸውን በመልቀቅ ከአገር ለመውጣት ሙከራ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ታዛቢዎች ይገልጻሉ። የአቶ ሽመልስ የስልጣን ቆይታ በከፍተኛ ህመም ከሚሰቃዩት ከአቶ በረከት ስምኦን ህልውና ጋር የተያያዘ መሆኑን ታዛቢዎች ይናገራሉ።

ምንጭ ኢሳት ዜና

አየር መንገድ የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራርን ከስራ አባረረ

December 15,2014
• ‹‹በፖለቲካ አመለካከቴ ምክንያት ሁልጊዜም እኔን ማባረር ይፈልጋሉ›› አቶ ወሮታው ዋሴ
























የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰማያዊ ፓርቲ የፋይናንስ ጉዳይ ኃላፊ የሆኑትን አቶ ወሮታው ዋሴን ከስራ አባረረ፡፡ አቶ ወሮታው ከስራ የተባረሩት ጥፋት ያጠፋን ሰራተኛ አልቀጣህም በሚል ሲሆን በእሳቸው ስር የነበረውና አጠፋ የተባለው ሰራተኛ ጉዳይ ተመርምሮ ወደ ስራ መመለሱ ታውቋል፡፡

አቶ ወሮታው ከእሳቸውም በላይ ጉዳዩ የሚያገባው የማኔጅመንት አባል በተመሳሳይ ጉዳይ የአምስት ቀን ደመወዝ ብቻ ሲቀጣ እሳቸው ከስራ መባረራቸው በፖለቲካ አመለካከታቸው ላይ የተመሰረተና ፖለቲካዊ ውሳኔ እንደሆነ ያሳያል ብለዋል፡፡ ከስራቸው ይሰራ የነበረው ሰራተኛ ጥፋተኛ አለመሆኑን የገለጹት አቶ ወሮታው ‹‹በፖለቲካ አመለካከቴ ምክንያት ሁልጊዜም እኔን ማባረር ይፈልጋሉ›› ሲሉ የተባረሩት በፖለቲካ አመለካከታቸው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

አቶ ወሮታው ዋሴ ከሁለት አመት በፊት በኢሜል ለህዳሴው ግድብ ገንዘብ እንዲያዋጡ በተጠየቁበት ወቅት ለተላከው የኢሜል መልዕክት አልከፍልም ብለው በመመለሳቸው ‹‹ሰራተኛ በማሳመጽ፣ የኢንዱስትሪ ሰላም በማናጋት›› በሚል ተከሰው ተባርረው ከሁለት አመት በኋላ በፍርድ ቤት ወደ ስራ መመለሳቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በወቅቱ አየር መንገድ አቶ ወሮታው ዋሴ ካሳ ተከፍሏቸው እንዲለቁ ይግባኝ ጠይቆ የነበር ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለሁለት አመት ካራዘመ በኋላ ወደ ስራ እንዲመለሱ አዝዞ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ ጥፋተኛ ነው ብሎ ያባረራቸው አየር መንገድ ወደ ስራ በተመለሱ በ15 ቀናት ውስጥ ሰርተውበት ወደማያውቁት ክፍል በማዘዋወር እድገት አግኝተው የማኔጅመንት አባል እንደሆኑ እንደገለጸላቸው የሚናገሩት አቶ ወሮታው እድገቱ ሰራተኛ ሲባረር የመክሰስ መብት ስላለው፣ በተቃራኒው ግን ሳይፈልጉት በእድገት የማኔጅመንት አባል እንዲሆኑ የተደረገው የማኔጅመንት አባል የሆነ ግለሰብ ቢባረርም የመክሰስ መብት የሌለው በመሆኑ ሆን ተብሎ ለማባረር የተደረገ ስልት ነው ብለዋል፡፡ አቶ ወሮታው በወቅቱ ይህን እድገት አልቀበልም ብለው እንደነበርም ገልጸውልናል፡፡

አቶ ወሮታው ዋሴ አሁን ከስራ ባባረራቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ለ14 ዓመታት ያህል ማገልገላቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡


ምንጭ ነገረ ኢትዮጵያ

በአፈና፣ በኃይል እርምጃና በውንብድና መብታችንን ለድርድር አናቀርብም! ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሰጠ መግለጫ

December15,2014
• ትግሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

እኛ 9 ፓርቲዎች በትብብር ለመሥራት በፈጸምነው ስምምነት ያወጣነውን የጋራ ዕቅድ ለማስፈጸም ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ስንገባ ህገ መንግስቱ፣ የምርጫና የሰላማዊ ሠልፍና ህዝባዊ ስብሰባ አዋጆች በሚፈቅዱት መሰረት ያቀረብናቸውን ጥያቄዎች በቢሮክራሲያዊ ሴራና ማስፈራራት ለማፈን የአዲስ አበባ መስተዳድር የተከተለውን ህገወጥ አካሄድና ይህንኑ ተከትሎ የተወሰዱትን የኃይል እርምጃዎች በሚመለከት ፡- 

1ኛ/ ‹‹በቢሮክራሲያዊ ሴራ የዜጎችን ህገመንግሥታዊ መብት ማፈን ሠላማዊ ትግሉን አያቆመውም !!››በሚል ርዕስ ሕዳር 08 ቀን 2007 ዓ.ም.

2ኛ/ ‹‹ማስፈራራትና አፈና የዲሞክራሲ ጥያቄዎችንና ሠላማዊ ሕዝባዊ የለውጥ ንቅናቄዎችን አይቀለብስም!!›› በሚል ርዕስ ሕዳር 17 ቀን 2007 ዓ.ም. መግለጫዎች ማውጣታችን፣ እንዲሁም በአባል ፓርቲዎቻችንን አማካኝነት -


1. ‹‹ የህገ መንግሥቱ የበላይነትና የዜጎች ህገ መንግሥታዊ መብት እንዲረጋገጥ ›› ለተከበሩ የተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ፣


2. ‹‹በአገሪቱ ህገመንግሥትና ህጎች የተረጋገጡ የዜጎች መብቶች እንዲተገበሩ ›› ለተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ህዳር 24/2007 ዓ.ም ጥያቄ ማቅረባችንና በግልባጭ ለ- ኢትዮጵያ ሰብዐዊ መብት ኮሚሽን፣- የህዝብ እንባ ጠባቂና -ሰብዐዊ መብት ጉባኤ ማሰማታችን ይታወሳል፡፡


የእነዚህ መግለጫዎችም ሆነ ደብዳቤዎች ይዘት ሲጠቃለል ‹‹የአገሪቱ ህገመንግሥት ይከበር ›› የሚል ጥያቄና መስተዳደሩ በሚወስዳቸው ህገወጥ እርምጃዎች ከያዝነው ህጋዊና ሠላማዊ ትግል የማናፈገፍግና የትኛውንም መስዋዕትነት በመክፈል ለህገመንግሥታዊ መብታችን መከበር የጀመርነውን የጋራ ትግል እንደምንገፋበት፣ የአዲስ አበባ መስተዳድር ከህገ ወጥ ድርጊቱ እንዲታረም፣ ጥሪ ማቅረብና ግልጽ አቋማችንን ማሳየት ነበር፡፡ በዚሁ ሂደት ያጋጠሙንን ህገወጥ ድርጊቶች በሙሉ በዝርዝር ለህዝባችንና ለባለድርሻ አካላት በሙሉ በፕሬስ ሬሊዞችና ዕለታዊ የውሎ ዘገባና ዜናዎች አድርሰናል፡፡ ግን ሰሚ ጆሮ ሊናገኝ አልቻልንም፡፡ የአዲስ አበባ መስተዳድር የመረጠው መንገድ ለጥያቄዎቻችንና ጥሪዎቻችን ተገቢውን ህጋዊ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በህገ ወጥ ድርጊቱ መግፋትና ጥያቄዎቹን በኃይል እርምጃ ማፈን ነው፡፡ አፈ ጉባኤውም ሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምንም ባለማለታቸው መስተዳድሩ ‹‹በያዝከው ግፋበት ፈቃድ›› በማግኘቱ ለበለጠ ህገወጥነትና የኃይል እርምጃ በመበረታታት ለህዳር 27 እና 28 ቀን 2007 በጠራነው ህጋዊ ሠላማዊ ሠልፍ ሂደት ላይ በሰጠው ከመንግሥት የማይጠበቅ የቅጥፈት መግለጫ ፣ በዕለቱ በሠላማዊ ዜጎች ላይ በተወሰደው አረመኔኣዊ እርምጃና ጥይት እራሱ ገሎ እራሱ ይጮኃል እንዲሉ በንጹኃን የመብት ጠያቂ ዜጎች ላይ የተለመደውን የፈጠራ ክስ ለመፈብረክ በተጠቀመው ነጭ ውሸት አረጋግጧል ፡፡ የአብነት ማሳያዎችም--


1. ኢቲቪ/ኢብኮ/ ሰሚ ባላገኘው የ‹‹ማስፈራሪያ›› ማስጠንቀቂያው ‹‹በሌላ ቦታ እንዲያደርጉ›› የቀረበላቸውን አማራጭ ባለመቀበልና እዚያው ካልሆነ ሞተን እንገኛለን በማለት ‹‹አሉ›› ያለው እኛ ዓርብ(26/03/07) ከሰዓት በኋላ እስከ ቀኑ 10፡30 ድረስ ውሳኔ ከማይሰጡ (ሥልጣኑ ከሌላቸው) የመስተዳድሩ ሹማምነት ጋር ቆይተን ‹‹የማሪያም በር›› ልንሰጣቸው ከሞከርነው ጋር የማይጣጣምና መግለጫው ‹‹ ባይበላስ ቢቀር›› የሚያስብል መሆኑ፤


2. ከ80 በላይ ንጹኃን የመብት ጤቂ ዜጎች ላይ የተፈፀመው እስራትና ከ50 በላይ በሆኑት ላይ የ ለማመንና መቀበል የሚያስቸግርና (በተለይ በሴት እህቶቻችን ላይ)አረመኔያዊ ድብደባ (ፖሊስ ጣቢያ ግቢ ውስጥ ጭምር) በተፈጸመበት የተሞከረው ‹‹ ከባድ የኮንስትራክሽን መሣሪያ በኪሳቸው ደብቀው›› ልማቱን አደናቀፉ ዓይነት የፈጠራ ውንጀላና ክስ ማቅረባቸውን፤ መጥቀስ ብቻ ይበቃል፡፡


በመሆኑም መስተዳድሩ ከሠልፉ ዕለት በፊትና እስከዛሬ እነዚህን ዓይን ያወጡ ህገመንግሥቱን የደፈጠጡ የአደባባይ እውነታዎች ለመሸፈን በፓርቲዎች ላይ በተለመደው መንገድ በህዝብ ሃብት የሚተዳደሩትን የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን በተለይም ኢቲቪ/ኢብኮ/ በመጠቀም በሰራው የበሬ ወለደ ፕሮፖጋንዳ ማንነቱን ፍንትው አድርጎ ለህዝብ አሳይቷል፣ ራቁቱን አስቀርቶታል፣ተጋልጦበታል፡፡


በእኛ በኩል ከሂደቱም ሆነ ከተወሰደው እርምጃና ከተሞከረው ርካሽ ፕሮፖጋንዳ ለቀጣዩ የጋራ ትግላችን ብዙ ተምረንበታል፤ አስተምረናል፣አትርፈንበታል እንጂ ከዓላማችን አልተገታንም፣ ቃላችንን አላጠፍንም፡፡በመሆኑም


1. ከዚህ በኋላ ለሰልፍም ሆነ ስብሰባ ገዢው ፓርቲ በዘመናት በማለማመድ ፈቃጅ ሆኖ ለመታየት ያደረገውን ጥረት ሰብረን ዕውቅና ከመስጠት ያለፈ ህጋዊ ሥልጣን የሌለው መሆኑን እንዲያውቅ/እንዲማር አድርገናል፤


2. በማስፈራራት ትግሉን መግታት እንደማይቻልና ለዚህም ለነጻነታቸውና ክብራቸው የቱንም መስዋዕትነት ለመክፈል የተዘጋጁ ታጋዮች በተለይም ወጣቶች መኖራቸውን አሳይተናል፤


3. የህዝቡ የለውጥ ፍላጎት የደረሰበትን ደረጃና የንቃተ ኅሊና መዳበር ከክልል ጭምር በመምጣት በጋራ ትግሉ በመሳተፍና የትግል አጋርነታቸውን በመግለጽ ባደረጉት አስተዋጽኦና በመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ፕሮፖጋንዳ ያለው እምነት መሟጠጡን ፣እንዲሁም የገዢው ፓርቲ በሠላማዊ ትግል ያደረበትን የፍርኃትና ሥጋት ደረጃ ለክተንበታል፤


4. ህዝቡ ለፈጠራ ወንጀሎች እንዳይፈራና ይልቁንም በመንግሥት አሠራርና አመራር ላይ ያለው እምነት ከጥያቄ እንዲወድቅ፤ፖሊስንና ፍርድ ቤቶችን ጨምሮ አስፈጻሚ አካላት ያለባቸውን ተጠያቂነት እንዲረዱና ራሳቸውን እንዲጠይቁ የሚያስችል ስሜት ፈጥረናል፤


በአጠቃላይ የገዢውን ፓርቲ እየባሰ የመጣውን አምባገነናዊ ባህሪይ አጋልጠን ፣ኢትዮጵያዊያን ለተባበረ የጋራ ትግል ያላቸውን ድጋፍ በተግባር ተመልክተን፣ የጀመርነው የ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› ፕሮግራማችንን ትክክለኛለትና ተቀባይነት ለክተን ትግሉ ወደማይቀለበስበት የላቀ ደረጃ መሸጋገሩን አረጋግጠናል፡፡ስለሆነም የጋራ ትግላችንን አጠናክረን በበለጠ ጽናትና የኃላፊነት መንፈስ በጥበብ በመምራት እንደምንቀጥል እያረጋገጥን የሁለተኛውን ዙር ፕሮግራም ዕቅድ በቅርብ ጊዜ እንደምናሳውቅ እየገለጽን -


1ኛ/ በአገር ቤትና በውጪ የምትገኙ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ከጎናችን በመቆም ላደረጋችሁት ሁለንተናዊ ድጋፍ፣ በአምባገነኑ ሥርኣት የተወሰደብንን አረመኔያዊ እርምጃ በመቃወም በሰልፍ፣ በመግለጫ፣በታሰርንበት አስፈላጊውን በማቅረብና ተመላልሳችሁ በመጠየቅ … የትግሉ ባለቤትነታችሁን ላረጋገጣችሁና አጋርነታችሁን ለገለጻችሁና ላኮራችሁን ክፍ ያለ ምስጋናችን እያቀረብን፣በዚህ ረገድ ድምጻችንን ከህዝባችንና ከዓለም ህዝብ ዘንድ በማድረስ ፣ከወገኖቻችን ጋር በማወያየት ከፍተኛውን ሚና ለተጫወታችሁ በአገር ቤትና በውጪ ለምትገኙ መገናኛ ብዙኃን አድናቆታችንን እየገለጽን በቀጣዩ ፕሮግራማችንም ከጎናችን እንድትቆሙ ፣


2ኛ/ገዢው ፓርቲ/መንግሥት የወሰደውን ኢህገመንግሥታዊና ህገወጥ እርምጃና አሰራር አጥብቀን እየተቃወምን፣ይህ ዓይነቱን ለማንም የማይበጅ አካሄድ መርምሮና የህዝቡን የለውጥ ፍላጎት ተረድቶ ቆም ብሎ ራሱን እንዲፈትሽ፣ከገባበት ፍርኃትና ሥጋት ተላቆ ለህዝብ ጥያቄዎች ተገቢውን ወቅታዊ ምላሽ በመስጠት ህገመንግሥቱን አክብሮ እንዲያስከብር፤


3ኛ/ የዓለም አቀፉ ማኅበረ ሰብ አባላትም ተገቢውን አዎንታዊ ተጽዕኖ በገዢው ፓርቲ/መንግሥት ላይ በማሳረፍ ለሰብዐዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበርና ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድታበረክቱ፤ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ያለመስዋዕትነት ድል የለምና ትግሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ሕወሐት ደ/ፂዮንን ጠ/ሚ/ር ለማድረግ አቅዷል * የአዜብና የደህንነቱ ሹም ያልታሳካ እቅድ

December14,2014
(ከኢየሩሳሌም አርአያ)
Debretsionየጠ/ሚ/ር ስልጣን ወደ ሕወሐት ለመመለስ የፓርቲው ቁልፍ አመራሮች በምስጢር ሲመክሩ መስንበታቸውን የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። በአቶ ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል፣ አባይ ፀሐዬ፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ጄ/ል ሳሞራ የኑስ፣ ፀጋይ በርሔ፣ አርከበ እቁባይና ስብሃት ነጋ የሚመራው የሕወሐት ከፍተኛ አመራሮች ከዚህ ቀደም ሲካሂዱት በነበረውና ህወሀት የጠ/ሚ/ ርነት ስልጣን መልሶ መያዝ ይኖርበታል፣ የሚለውን ምክክር ከዳር ለማድረስ አቋም መያዘያቸውን ያስታወቁት ምንጮቹ በተለይ በቅርቡ የተካሄደው የአራቱ ፓርቲዎች ጉባኤ ላይ በብአዴንና ኦህዴድ በኩል ቅሬታና ተቃውሞ እየበረታ በመምጣቱ የሕወሐት አመራሮች ስልጣኑን በእጃቸው ለማስገባት ቆርጠው መነሳታቸውን አስረድተዋል።
 በብአዴን በኩል የአቶ በረከት ስሞን ከስልጣን መገፋት በደጋፊዎችቻቸውና አመራሩ በኩል ቅሬታ መፍጠሩን የጠቆሙት ምንጮቹ በረከት ስሞን የጠ/ሚ/ር ሃ/ማርያም አማካሪ ተብለው ቢሾሙም ነገር ግን በጠ/ሚ/ር ፅ/ቤት ቢሮ እንዳልተሰጣቸውና የተሰጣቸው ካዛንቺስ አካባቢ የሚገኘው የቀድሞ የደህንነት ቢሮ መሆኑን ምንጮቹ ገልፀው በዚህ ቢሮ ኩማ ደመቅሳ እንደሚገኙና በጠ/ሚ/ር ፅ/ቤት አዲስ ቢሮ ተገንብቶ ይሰጣችኋል የተባለው ተግባራዊ እንዳልሆነ አያይዘው አስረድተዋል። በጠ/ሚ/ር ፅ/ቤት ቢሮ የተሰጣቸውና ከአቶ ሃ/ማርያም እያንዳንዷ እንቅስቃሴ ያልተለዩት አርከበ እቁባይ፣ አባይ ፀሐዬና ፀጋይ በርሄ ሲጠቀሱ በም/ጠ/ሚ/ር ቦታ ደብረፂዮን መኖራቸውን ምንጮቹ አመልክተዋል። ለሕወሐት አመራሮች ሌላው ራስ ምታት የሆነባቸው የኦህዴድ ፓርቲ ከሕወሐት እኩል መገዳደር እያሳየ መምጣቱ ነው ያሉት ምንጮቹ በተለይ ከአቶ መለስ ሞት በኋላ ኦህዴድ የተለያዩ የስልጣን ጥያቄዎች በማንሳት ድፍረት እያሳየ መጥቷል ብለዋል።
 ሕወሐት የጠ/ሚ/ርነት ስልጣኑን መቆጣጠር የፈለገበት አንዱ ምክንያት ይህ መሆኑን ምንጮቹ አልሸሸጉም። በኦህዴድ በኩል የጠ/ሚ/ር ስልጣን ለኦሮሞ ይገባል በሚል ከዚህ ቀደም የነበረው የሕወሀት ስልጣንን አንሰራፍቶ የመያዝ አካሄድ መገታት አለበት የሚል አቋም እንደተያዘ ያስረዱት ምንጮቹ በተለይ የህወሀት አመራር የኦህዴድ አካሄድ እንዳልተዋጠለትና ከዚህ ቀደም ማን ጠ/ሚ/ር ስልጣን ይያዝ የሚለው የህወሀት ምክክር በእንጥልጥል ቆይቶ በቅርቡ ግን ዶ/ር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል ስልጣኑን መያዝ አለበት የሚል ውሳኔ ላይ መድረሱን ምንጮቹ አስገንዝበዋል። የደብረፂዮን ወደ ጠ/ሚ/ር ስልጣን የማምጣት እቅድ በተመለከተ አርከበ እቁባይ ተቃውሞ አሰምተው መከራከራቸውንና በመጨረሻ ግን ኦህዴድና ብአዴን ለመጨፍለቅ ሲባል አርከበ መቀበላቸውን ምንጮቹ አመልክተዋል። የህወሀት አመራሮች ከስምምነት የደረሱበትን ጉዳይ ከቀጣዩ ምርጫ በኋላ ጠ/ሚ/ር አቶ ሃ/ማርያም ደሳለኝን ከብቃት ማነስ ጋር በማያያዝ ከስልጣን ለማውረድና በምትካቸው የጠ/ሚ/ርነቱን ቦታ ለደብረፂዮን ለመስጠት መወሰናቸውን ምንጮቹ አጋልጠዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አዜብ መስፍን ከባለቤታቸው ህልፈት በኋላ የፓርቲው ሊቀመንበርና የጠ/ሚ/ር ስልጣን ለመረከብ አቅደው እንደነበረ ታማኝ ምንጮች አጋለጡ። የደህንነት ዋና ሹም የነበረው ወ.ስላሴ ወ/ሚካኤልን ከፊት በማስቀደም ወ/ሮ አዜብ የሞከሩትና በፓርቲው አንዳንድ አመራሮች “መፈንቅለ ድርጅት ሙከራ” ሲሉ ፈረጀውታል። ከምንጮቹ የተገኘው ዝርዝር መረጃ ተከታዩን ይመስላል። አቶ መለስ ዜናዊ መሞታቸውን ተከትሎ በሕወሐት ውስጥ ሁለት አይነት ቡድኖች ብቅ አሉ። ወ/ሮ አዜብ የድርጅቱ ሊቀመንበር በመሆን የጠ/ሚ/ር ስልጣኑን ለመረከብ ካልሆነም ምክትል ጠ/ሚ/ርነትን ለመቆናጠጥ ከፍተኛ ፍላጐት አሳደሩ። ከአዜብ ጐን የቆሙት በረከት ስሞኦን “የመለስን ራዕይ የማስፈፅመው እኔ ነኝ” ሲሉ ለካድሬዎቻቸው ቀሰቀሱ። በአንፃሩ እነስብሃት ነጋ ከጀርባ የሚመሩትና ፀጋይ በርሄ፣ ጌታቸው አሰፋ፣ አርከበና ደብረፂዮን ያሉበት ቡድን በተቃራኒው ቆሞ በውስጥ አድፍጦ የፖለቲካ መስመሩን እያስተካከለ ነው። አዜብ ከጐናቸው ያሰለፏቸው የደህንነት ሹም ወ/ስላሴ፣ ገ/ዋህድን እንዲሁም ሚሊየነሩ ነጋ ገ/እግዚያብሄር መቀሌ ድረስ ኔትዎርክ ዘረጉ።
 አዜብን የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጐ ለማስመረጥ አዜብ የመደቡት በ10ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በአቶ ነጋ በኩል ወጪ እየተደረገ በነወ/ስላሴ አማካይነት ለበርካታ ካድሬዎች ይታደል ጀመር። አዜብ ያንን ሁሉ ገንዘብ ያለምንም ጠያቂ ፈሰስ ማድረጋቸውና ያለመጠየቃቸው አስገራሚ ነበር። ለካድሬዎች በነፍስ ወከፍ ከ3 እስከ 8 ሚሊዮን ብር ተከፋፈለ። ካድሬው ድምፅ ለአዜብ በመስጠት የሕወሐት ሊ/መንበር ማድረግ እንዲሁም ወ/ስላሴን በፓርቲው ማ/ኮሚቴ አባልነት ለማስመረጥ በተጨማሪ ጌታቸው አሰፋን እንዳይመረጥ ማድረግ የሚሉ መመሪያዎች ገንዘቡን ለሚቀበሉ ካድሬዎች ጥብቅ መመሪያ ከነወ/ስላሴ ተላለፈ። ካድሬው እነወ/ስላሴ የሰጡትን ገንዘብ በመቀበል ትእዛዙን ተፈፃሚ እንደሚያደርግ ነገራቸው። ጉዳዩን ሰምተው እንዳልሰሙ የሆኑት እነጌታቸው አሰፋ በጐን ካድሬውን እያስጠሩ « የሚሰጧችሁን ገንዘብ ተቀበሉ። የሚሏችሁን እሺ በሉ። በጉባኤው ላይ ግን ከእኛ ጐን ትቆማላችሁ» ሲሉ በማስጠንቀቂያ መልክ ነገሩ። ካድሬው ከነጌታቸው ጐን እንደሚቆም ቃል ገባላቸው። እነወ/ስላሴ፣ አባይ ወልዱ፣ ገ/ዋህድ..እንዲሁም በባለሃብት ሽፋን የአዜብን ተልእኮ ለማስፈፀም ሲሯሯጡ የከረሙት ነጋ ገ/እግዚያብሄር ጉባኤው ሳምንት እየቀረው በመቀሌ “ቡቡ ሂልስና አክሱም” በመሳሰሉ ሆቴሎች ካድሬውን በግብዣ ሲያንበሸብሹ ሰነበቱ።
የጉባኤው እለት ደረሰ። ለሕወሐት ሊቀመንበርነት እጩዎች ሲጠቆሙ ወ/ስላሴ እጅ በማውጣት “አዜብ መስፍን” ሲል ጠቆመ። ተሰብሳቢው ድጋፍና ተቃውሞ ሲጠየቅ 12 ጣቶች (ድምፆች) ብቻ ሲደግፉ የተቀረው አዜብን በመቃወም ውድቅ አደረገው። አባይ ወልዱ፣ ወ/ስላሴ፣ ቴዎድሮስ ሃጐስ፣ ትርፉ፣ በየነ፣ ገ/ዋህድ…ለአዜብ ድጋፍ ከሰጡ 13 ድምፆች ይጠቀሳሉ። አዜብ « የመለስ ራዕይ ሳይበረዝ ሳይከለስ ለማስቀጠል..» አልጨረሱም የመድረኩ መሪ ጣልቃ ገብተው « ስነ ስርዓት ..አሁን የእጩዎች ምርጫ እያካሄድን ነው» ሲል አርከበ ቀበል አድርግው « የመለስ ራዕይ የሚባል የለም። የፓርቲው ራዕይ ነው ያለው» ሲሉ አዜብ በግልምጫ እያዩ ተናገሩ። ካድሬው እንደካዳቸው ያወቁት አዜብ ንዴት በገፅታቸው ላይ ይነበብ ነበር። ብሽቀት የገባው ወ/ስላሴ እቅዳቸውን ጌታቸው እንዳኮላሸው የተረዳ ይመስላል። እጁን በማውጣት « ጌታቸው አሰፋ ለማ/ኮሚቴ አባልነት አይመጥንም። ሰካራም ነው፣ ሴሰኛ (ሴት በማማገጥ) ነው። ውሎና አዳሩ ሸራተን ነው። እንዳውም አቶ መለስ ዜናዊ በጌታቸው ዙሪያ ማጣራት እንዲካሄድ ያስጀመረው ምርመራ ነበር። ውሳኔ ሊሰጥበት ጫፍ ሲደርስ እንዳጋጣሚ ሞት ቀደመው። ስለዚህ ጌታቸው ለፓርቲው ማ/ኮሚቴ አባልነት አይመጥንም» በማለት በእልህ ስሜት ይናገራል። አስመላሽ ወ/ስላሴ (በቅፅል ስማቸው አባይ ነብሶ- በፓርላማ ከመለስ ዘናዊ ኋላ አዘውትረው የሚቀመጡና ጥቁር መነፅር የሚያጠልቁ አይነስውር) እጃቸውን በማንሳት በዚህ ዙሪያ መናገር እንደሚፈልጉ ይጠይቃሉ።
 ሲፈቀድላቸው እንዲህ አሉ፥ « አሁን ወ/ስላሴ እንዳለው በጌታቸው ዙሪያ ማጣራት ስናካሂድ ከነበርነው ሶስት ሰዎች አንዱ እኔ ነኝ። እንድናጣራ ያዘዘን መለስ ነው። የቀረበልን ጥቆማ “ጌታቸው ቪላ ቤት ገንብቷል፣ ሙስና ውስጥ ገብቷል” የሚሉ ነበሩ። ረጅም ጊዜ ስናጣራ ቆየን። ነገር ግን የተባለውን ቤትም ሆነ በሙስና ያፈራው አንዳች ነገር ልናገኝ አልቻልንም። ከዚያ በጌታቸው ላይ ጥቆማውን ያቀረበው ወይም ያመጣው ማነው?.ብለን ስንጠይቅ ወ/ስላሴ መሆኑን አወቅን። በወ/ስላሴ ዙሪያ ለምን ማጣራት አናካሂድም ብለን ጀመርን። በስሙ፣ በወንድምና እህቱ እንዲሁም በቤተሰቡና በሌሎች ግለሰቦች በሙስና መበልፀጉን አረጋገጥን» በማለት የሙስናውን ማስረጃ በዝርዝር አባይ ነብሶ ለጉባኤው አቀረቡ። ለማ/ኰሚቴ የተጠቆመው ወ/ስላሴ 2 ድምፅ ብቻ በማግኘቱና ከጨዋታ ውጭ በመሆኑ ኩም አለ። ጉባኤው በነጌታቸው አሰፋ ድል አድራጊነት ተጠናቀቀ። 
የሙስናዋን ፋይል የያዙት ጌታቸው አሰፋ በቅድሚያ ያደረጉት ወ/ስላሴን ከስልጣን ማባረር ነበር። ከዛም እነገ/ዋህድን ጨምሮ ለአዜብ ገንዘብ ሲረጩ የነበሩትን እነነጋ ገ/እግዚያብሄርን በሙስናው ፋይል እስር ቤት መክተት የሚለውን እቅድ ተግባራዊ አደረጉ። የደህንነቱን ቢሮ እንዳሻው ይፈነጭበት የነበረውና የአቶ መለስና አዜብ ቀኝ በመሆን አገሪቱን በአፈና መዋቅር ሲያሰቃያት የከረመው ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል በበርካታ የደህንነት አባላት ጥርስ የተነከሰበት ጭምር ነበር። ይህን የሚያውቁት ጌታቸው አሰፋ በደህንነቶች ለተከታታይ ቀናት ወ/ስላሴ እንዲደበደብ ማድረጋቸውን ማረጋገጥ ተችሏል።

Sunday, December 14, 2014

የፈሪ ዱላ ነፃነትን አያስቀርም !

December 14,2014
ህወሃቶች ኢትዮጵያን “ለመምራት” ያላቸው አቅም ተሟጦ አልቋል። ፍርሃት አቅላቸውን አስቷቸዋል። ፍርሃታቸው ጭካኔን ወልዷል። ይህ ጭካኔያቸው ወሰን አጥቷል። ልጥ ባዩ ግዜ እባብ እየመሰላቸው ልጡን በቆመጥ ሲደበድቡ ውለው ያድራሉ። ፍርሃት ያ ደካማ ማሰቢያቸውን ጥርቅም አድርጎ ዘግቶታል። የፈሪ ዓይን ማየት እንደማይችል፤ ጆሮውም መስማት እንደተሳነው ከህወሃቶች ተርድተናል።
እኛ ግን እንዲህ እንላለን ህወሃቶች ዓይናችው እያየ፤ ጆሮዋቸውም እየሰማ የኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነቱን ይቀዳጃል። እውነት እውነት እንላችኋለን የነፃነቱ ግዜ እሩቅ አይደለም። ህወሃቶች ከነፍርሃታቸው ወደ መረጡት መቃብራቸው መውረዳቸው እንደማይቀር ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ የለንም።
የኢትዮጵያ ህዝብ ምርጫ ነፃነት ነው።ይህን ነፃነት ከህወሃቶች እጅ ለምነን የምናገኘው አይደለም። ነፃነታችንን ታግለንና አሸነፈን የምንቀዳጀው ንፁህ ሃብታችን ነው። ይህን ንፁህ ሃብታችንን በቀማኞች አስነጥቀን ዝም ብንል እርግማን ይሁንብን ያሉ ኢትዮጵያዊያን እያደረጉ ያሉት ትግል ተስፋ ሰጪ ነው። በተለይም ወጣቶች እምቢ ለክብሬ፤ እምቢ ለነፃነቴ እምቢ ለማያውቁን ህወሃቶች ማለታቸውን ስናይ ተስፋችን ከመቸውም ግዜ በላይ ለምልሟል።
ህወሃቶች ኃላፊነት የሚሰማቸው ቢሆኑ ኑሮ “በሃሳባችሁ ባንስማም ልዩነታችሁን መግለፅ የምትችሉበትን መብት ለማስከበር እሰከ ሞት ድረስ እንቆማለን” ይሉ ነበር። አለመታደል ሁኖ ህወሃቶች አገር፤ ህዝብ፤ ወገን የሚባል ቋንቋ በውስጣቸው የለም። ኢትዮጵያም አገራቸው አትመስላቸውም፤ ህዝቡም ወገናቸው እንደሆነ አይሰማቸውም። ህወሃቶች በወንድምና እህቶቻቸው አጥንት ላይ ቁመው ለኢትዮጵያና ለህዝቧ ጠላት መሆንን መርጠዋል። ለነፃነት ብለው በትግል ሜዳ የተሰው ጓዶቻቸውን ሞትም ከንቱ ሞት አድርገው አስቀርተውታል። ይሄ እርግማን ነው።ይሄ እርግማን ደግሞ አሁን ባሉት ህወሃቶች ብቻ የሚቆም ሳይሆን ወደ ልጅ ልጆቻቸው እንደሚሸጋገር ህወሃቶች ለማሰብ አቅቷቸዋል።
ህወሃት የስለጠነ ፖለቲካ አያውቅም። የነፃነትንም ትርጉም ሳያውቅ ነፃ አውጪ ነኝ ይላል። በአገሪቷ ጫንቃ ላይ መቆየት ብቻ የህልውናየ መሠረት ነው ብሎ ካመነም ቆይቷል። ይህን የህልውናየን መሠረት የሚነካ ሁኔታ ከተፈጠረም ጠመንጃየ መመኪያ ጉልበቴ ነው የሚል የማይናወፅ አቋምም ይዟል። ይህ አቋሙ አገሪቷ ከተጋረጡባት አደጋዎች መካከል አንዱ ሁኖ ይታየናል። የዚህ አቋም መዘዙ አሁን ባለው ትውልድ ብቻ የሚያበቃ አይደለም። ወደ ቀጣዩ ትውልድ ተሸጋግሮ የአገሪቷ ዜጎች በሠላም አብረው የሚኖሩበትን እድል እንደሚያበላሸው ህወሃቶች አያውቁም ማለት አይቻልም። ተደጋግሞ እንደተነገረው በህወሃቶች ዘንድ ትውልድ የሚባል ቋንቋ እንዲጠፋ በመደረጉ ለመጪው ትውልድ የሚተርፍ ቂም ትተው ለማለፍ ሳያቅማሙ እየሰሩ ይገኛሉ።
የኢኮኖሚ መዋቅሩ በእነርሱ ብቻ መያዙ ነገ ለእነርሱ ልጆች የደም እንጀራን እንደሚያተርፍላቸው እንዲገነዘቡ ማድረግ ተገቢ ይመስለናል።በህወሃቶች አስተሳሰብ ሌላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ድሃ አድርገን ከያዝነው ከዕለት ጉርሱ አልፎ ሂዶ ነፃነትን ይጠይቀናል ለነፃነት የሚከፍለውንም ዋጋ ለመክፈል አቅም አይኖረውም የሚል ሙት ፍልስፍና መመሪያቸው ሁኗል። እኛ ብቻ በኢኮኖሚ ጎልበትን ሌሎቹን የእኛ ጥገኛ ካደረግን ለዘላለም ከነ ልጅ ልጆቻችን ነግሰን እንኖራለን የሚል ቅዥት ውስጥ ሁነው አገሪቷን ወደ ትርምስ እየወሰዷት እንደሆነ እያየነው ነው።ህወሃቶች ከእህል ውሃ የዘለለ ራዕይ እንደሌላቸው የሚታወቅ ነው። ራዕይ አልባዎች ተደራጅተው አገር መምራት ሲጀምሩ አገሪቷና ህዝቧ በሙሉ ራዕይ አልባ ይሆናሉ። መፅሃፍ እንደሚነግረን ደግሞ “ራዕይ አልባ አገር ይጠፋል” ይላል። የህወሃቶች ምኞት ይሄው ነው። እኛ ከሌለን ኢትዮጵያ አትኖርም የሚል ክፉ ምኞት።
ኢትዮጵያዊያን ሆይ !
ህወሃት የጭለማን መንገድ መርጧል። ይሄ መንገዱም አገሪቷንና ህዝቧን ወደ መቀመቅ እየጨመራት ነው። አገሪቷን አስይዞ ከግል ኩባንያዎች ብድር እስከ መለመን ደርሷል። ቀጣዩ ትውልድ ከሚወርሰው ቂምና በቀል በተጨማሪ በእዳ የተያዘ ትውልድ ይሆናል። በቀላል አነጋገር ትውልዱ የባዕድ ተገዢ እንዲሆን ተፈርዶበታል። ህወሃቶች ለመጪው ትውልድ የሚሰጡት ስጦታ ባርነትን እንዲሁም ቂምና በቀልን እንጂ ነፃነትንና አብሮ መኖርን አይደለም።
እንግዲህ ህወሃቶችን አደብ ማስያዝ የዚህ ትውልዱ ግዴታ ይሆናል። ህወሃት ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ውሳኔ ሰጪነት ካልተወገደ በቀር በኢትዮጵያ መረጋጋት አይኖርም። ችጋርም አይጠፋም። የንፁህ ሰው ደም ከመፍሰስ አይቆምም። አገሪቷም በእዳ ላይ እዳ ከመጨመር አትመለስም።
ይህ ሁኔታ መቆም እንደሚኖርበት አሁን ሁሉም ተገንዝቧል። ይህ ሁኔታ ግን እንዲሁ በከንቱ የሚቆም አይሆንም። ለዚህ የሚከፈል የደም መሥዋዕትነት የግድ ሁኖብናል። ፍትህ፤ እኩልነት እና ነፃነት የደም ውጤቶች ናቸው። ያለ መሠዋዕትነት የሚመሠረት ፍትህ አይኖርም፤እኩልነትም ቢሆን የብዙዎችን መስዋዕትነት ይጠይቃል፤ የነፃነት ቀንዲል የሚለኮሰው በደም አቀጣጣይነት ነው። ህወሃቶች መሽቶ በነጋ ቁጥር የንፁህ ደም ያፈሳሉ። ዝም ያሉትም ሞት አልቀረላቸውም፤ የተናገሩትም የውርደት የሞት ፅዋቸውን እየተጎነጩ ነው፤ ሌሎቹም ከሞት በባሰ ሁኔታ በየማጎሪያ ቤቱ የመከራ ፅዋቸውን እየተጋቱ ነው። ይሄ የውርደት ታሪክ መቀየር ይኖርበታል።
የሠማያዊ ፓርቲ ፅ/ቤት ጥበቃ ሠራተኛ የ72 ዓመቱ አቶ ቀኖ አባጆቢርን ለእስር የዳረገ አገዛዝ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው።የ72 ዓመት ኢትዮጵያዊ ሽማግሌን አንኳ የሚፈራ ቡድን ነው አገሪቷን የተቆጣጠራት። አቶ ቀኖ የእለት ጉርሳቸውን ለመሸፈን ደመወዝ ተቆርጦላቸው የጥበቃ ሥራ የሚሰሩ እንጂ የፓሪት አባል አልነበሩም ሆኖም ግን ታፍነው ለእስር ተዳርገዋል። የህወሃቶች ግፍ ማብቂያ እና ወሰን አጥቷል።እነዚህ ቡድኖች እየፈፀሙ ያሉት ግፍ ጥላቻን እየወለደ፤ ቂምን እየተከለ ቀጥሏል። የህዝቡ ቂም እንደ ተዳፈነ እሳት የሚቀጣጠልበትን ግዜ እየጠበቀ ነው።ይህ ግዜ የመጣ ቀን ህወሃቶች እና አሸከሮቻቸው ወየውላቸው።ያ ግዜ ደግሞ ያለ ጥርጥር በእርግጠኝነት ይመጣል።ፈጥኖ እንዲመጣ በእኛ በኩል የሚቻለንን ሁሉ እያደረግን ነው።
ከህወቶች በተጨማሪ በዚያች አገር ታሪክ ውስጥ ፌዴራል ፖሊስ ተብለው የተደራጁት እና ከሰው መፈጠራቸውን የረሱ ቡድኖች መኖር በብርቱ ያሳስበናል። የፌዴራል ፖሊስ አባላት እየፈፀሙ ያሉት ጭካኔ አስገራሚ ነው። የዝህ ጦር አባላት ሰው ሁነው መፈጠራቸውን እስክንጠራጠር ድረስ አስገርመውናል። እንግዲህ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ብዙ ግዜ ማሳሰቢያ ልከንላችኋል። አሁንም በተጨማሪ እንነግራችኋለን። ነገራችንንም ለታሪክ ይቆይ ዘንድ በመዝገብ እናኖረዋለን። አሁን የጭካኔ ሰይፋቸሁን መዛችሁ እንደ ፈለጋችሁ የምትገሏቸው ዜጎች ወገኖቻችሁ መሆናችሁን አትርሱ። ነገ ቢርባችሁ የሚያበሏችሁ፤ ብትወድቁ የሚያንሷችሁ፤ ብትጠሙ የሚያጠጧችሁ ዛሬ በያዛችሁት ጠመንጃ የምትገድሏችው ወገኖች ናቸው። እናንተ ግን ይሄን እውነት ለማየት አዚም የተደረገባችሁ ይመስላል።
ፌዴራል ፖሊሶች ታዝዤ ገደልኩ በማለት የምታመልጡ እንዳይመስላችሁ። ታዝዤ ገደልኩ ማለት ሥራየ መግደል ነው ማለት ነው። ሥራው መግደል የሆነ ማንም ይሁን ማን ወንጀለኛ ነው። ወንጀለኛ ደግሞ ተመጣጣኝ የሆነ ቅጣት መቀጣቱ አይቀርም። ስለሆነም የፌዴራል ፖሊስ አባላት በሰላማዊ መንገድ ኑሮ ተወወደብኝ የሚለውን ወንድማችሁን በቆመጥ ደብድቡ ስትባሉ አይ ሠላማዊ ሰውን እጠበቅ ዘንድ እንጂ እደበድብ ዘንድ ህግ አይፈቅድልኝም ማለት ስትችሉ ያገኛችሁትን ሁሉ እየሰበራችሁ መኖራችሁን እያየነው ነው። ይሄ በምንም መሥፈርት ትክክል አይደለም። አንዱ ታዝዤ ወንድምህን ወይም ልጅህን ወይም ደግሞ አባትህን ገደልኩ ቢልህ ምንድ ነው የሚሰማህ? መቸስ ታዘህ ነው እንግዲህ ምን ይደረጋል እንደማትል እርግጠኞች ነን። እኛ ሁላችን አንተ የፌዴራል ፖሊስ አባል በምትፈፅመው ጭካኔ በእጅጉ ተጎድተናል።የያዘከው ጠመንጃ የሸንበቆ ምርኩዝ የሚሆንበት ግዜ ወደ አንተ ፈጥኖ እየመጣ ነው። አሁን የያዝከው ቆመጥ ተሰብሮ ይወጋሃል በተወጋህ ግዜ ግን ዞር መግቢያ እንዳታጣ ለራስህ ተጠንቀቅ። አዛዦችህ እንደሆነ የአገሪቷን ንብረት ዘርፈው ወደ ውጭ አገር አሽሽተዋል፤ የቀረውንም በዘመድ አዝማዶቻቸው ሥም ብዙ ህንፃዎችን አሰርተው እየተዘባነኑበት ነው። አንተ ግን ከቀሪው ወገንህ ጋር ደም ትቃባለህ። ነገ ሌላ የተለየ አዲስ ቀን ነው። አዲስ ቀን በሆነ ግዜ መግቢያ እንዳታጣ አሁኑኑ ራስህን ከዘረኞች፤ ከዘራፊዎችና ከግፈኞች ጎን አግልለህ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን እንድትሰለፍ ደግመን ደጋግመን እንመክርሃለን። ይሄን ምክር አልስማ ካልክ ግን የሚመክርህ መከራ በደጅህ ፈጥኖ ይመጣል።
በመጨረሻም ህወሃቶችን ለማስወገድ የሚደረገው ትግል ተፈፍሞ መቀጠል የኖርበታል። ሁሉም በሚችለውና በሚያምነበት መንገድ ሳያቅማማ ይታገል። በሁሉም መንገድ የሚደረገው ትግል ፍሬ አፍርቶ በነፃነት እንደሚቋጭ ባለ ሙሉ ተስፋ ነን። እኛ የጀመርነውን ሁለ-ገብ ትግል አጠናክረን ተያይዘነዋል። ዕለት ዕለት እየጎለበትን እየሄድን ነው። አደረጃጀታችንም መሠረት ይዟል። ካሁን ወዲያ ትግላችንን የሚያቆም ምድራዊ ኃይል የለም። ነፃነታችንን ሳንቀዳጀ የጀመርነውን ትግል አናቆምም።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !

አዜብ መስፍን ከባለቤቷ ህልፈት በኋላ የፓርቲው ሊቀመንበርና የጠ/ሚ/ር ስልጣን ለመረከብ አቅዳ እንደነበረ ታማኝ ምንጮች አጋለጡ።

December 12,2014
በና ደብረፂዮን ያሉበት ቡድን በተቃራኒው ቆሞ በውስጥ አድፍጦ የፖለቲካ መስመሩን እያስተካከለ ነው። አዜብ ከጐናቸው ያሰለፏቸው የደህንነት ሹም ወ/ስላሴ፣ ገ/ዋህድን እንዲሁም ሚሊየነሩ ነጋ ገ/እግዚያብሄር መቀሌ ድረስ ኔትዎርክ ዘረጉ። አዜብን የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጐ ለማስመረጥ አዜብ የመደቡት በ10ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በአቶ ነጋ በኩል ወጪ እየተደረገ በነወ/ስላሴ አማካይነት ለበርካታ ካድሬዎች ይታደል ጀመር።

አዜብ ያንን ሁሉ ገንዘብ ያለምንም ጠያቂ ፈሰስ ማድረጋቸውና ያለመጠየቃቸው አስገራሚ ነበር። ለካድሬዎች በነፍስ ወከፍ ከ3 እስከ 8 ሚሊዮን ብር ተከፋፈለ። ካድሬው ድምፅ ለአዜብ በመስጠት የሕወሐት ሊ/መንበር ማድረግ እንዲሁም ወ/ስላሴን በፓርቲው ማ/ኮሚቴ አባልነት ለማስመረጥ በተጨማሪ ጌታቸው አሰፋን እንዳይመረጥ ማድረግ የሚሉ መመሪያዎች ገንዘቡን ለሚቀበሉ ካድሬዎች ጥብቅ መመሪያ ከነወ/ስላሴ ተላለፈ። 

ካድሬው እነወ/ስላሴ የሰጡትን ገንዘብ በመቀበል ትእዛዙን ተፈፃሚ እንደሚያደርግ ነገራቸው። ጉዳዩን ሰምተው እንዳልሰሙ የሆኑት እነጌታቸው አሰፋ በጐን ካድሬውን እያስጠሩ « የሚሰጧችሁን ገንዘብ ተቀበሉ። የሚሏችሁን እሺ በሉ። በጉባኤው ላይ ግን ከእኛ ጐን ትቆማላችሁ» ሲሉ በማስጠንቀቂያ መልክ ነገሩ። ካድሬው ከነጌታቸው ጐን እንደሚቆም ቃል ገባላቸው። እነወ/ስላሴ፣ አባይ ወልዱ፣ ገ/ዋህድ..እንዲሁም በባለሃብት ሽፋን የአዜብን ተልእኮ ለማስፈፀም ሲሯሯጡ የከረሙት ነጋ ገ/እግዚያብሄር ጉባኤው ሳምንት እየቀረው በመቀሌ “ቡቡ ሂልስና አክሱም” በመሳሰሉ ሆቴሎች ካድሬውን በግብዣ ሲያንበሸብሹ ሰነበቱ።

የጉባኤው እለት ደረሰ። ለሕወሐት ሊቀመንበርነት እጩዎች ሲጠቆሙ ወ/ስላሴ እጅ በማውጣት “አዜብ መስፍን” ሲል ጠቆመ። ተሰብሳቢው ድጋፍና ተቃውሞ ሲጠየቅ 12 ጣቶች (ድምፆች) ብቻ ሲደግፉ የተቀረው አዜብን በመቃወም ውድቅ አደረገው።

Saturday, December 13, 2014

አገር ውስጥ እየኖሩ መሞት፣ በስደት ጉዞ መሞት፣ በስደት እየኖሩ መሞት!

December 13,2014
“መጪው ጊዜ ከኢህአዴግ ጋር ብሩህ ነው!”
ethiopians and their plight

* አገር ውስጥ “ባርነት”፤ ከአገር ተሰድዶ “ባርነት”

ከጥቂት ቀናት በፊት በአገራቸው መኖር ያቃታቸው 70 ኢትዮጵያዊያን ቀይ ባህርን በጀልባ አቋርጠው ወደ የመን ሲያመሩ በደረሰ አደጋ ሁሉም መሞታቸው ተገልጾዋል። ኢህአዴግ እነዚህ በእርግጥ ኢትዮጵያውያን ለመሆናቸው ማስረጃ እንደሌለውና “እያጣራ” መሆኑን በቃል አቀባዩ በኩል ተናግሯል፡፡
በዚህ ዓይነት ሁኔታ ከአገራቸው እየተሰደዱ ለባህር፣ ለአውሬ፣ … የተዳረጉት ወገኖቻችን ብዛት ተቆጥሮ አያልቅም፡፡ ይህንን ሁሉ አልፈው ወዳሰቡት የደረሱት ደግሞ በስደት የሚኖሩባቸው በተለይ የአረብ አገራት ይህ ነው የማይባል ሰቆቃ ይደርስባቸዋል፡፡ ይህንን ሁሉ የሚሰማው ወገን አሁንም በየኤምባሲው ቪዛ ለማስመታት በተገኘው ቀዳዳ ከአገሩ ለመውጣት ይጥራል፡፡ በዚህ በኩል ያልተሳካለት ድንበር በማቋረጥ አስጨናቂውንና አስፈሪውን ጉዞ ይጀምራል፡፡
“አገር እየለማች” ነው ለሚለው ኢህአዴግ ይህ ምንም ዓይነት ምላሽ የሚሰጥበት ባይሆንም አሁንም “ለጊዜው የምጠብሰው ትልቅ አሣ አለና ጊዜ የለኝም” በማለት መስማት የተሳነው መሆኑን ይናገራል፡፡ አሽቃባጭ ካድሬዎቹም በየማኅበራዊ ድረገጾችና መገናኛ ብዙሃን “መጪው ጊዜ ከኢህአዴግ ጋር ብሩህ ነው” ይሉናል፡፡
በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ የስደት ህይወት ለመምራት እየወሰኑ የሚሄዱት ወገኖቻችን ከሚያስቡበት አገር ሲደርሱ ስለሚሆነው ሰሞኑን የወጣው የ2014 “የባርነት መለኪያ ዘገባ” በዘመናዊ ባርነት ውስጥ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን ቁጥር 390ሺህ እንደሚገመት ተናግሯል፡፡ (የጎረቤት ኬኒያ65ሺህ እንኳን አልደረሰም)
ከአረመኔ የባህር ላይ አስተላላፊዎች ያመለጡት ወይም “በልማት እየተመነደገች” ካለችው አገራቸው ኑሮን ማሸነፍ እያቃታቸው ወደ አረብ አገራት “በቪዛ” የሚወጡት በ“Global Slavery Index” መለኪያ መሠረት ለዘመናዊ ባርነት የሚጋዙ ናቸው፡፡
አገር ውስጥ ያለው “ዘመናዊ ባርያ” ኑሮን ማሸነፍ ያቃተውና የሰው ልጅ ሊሰራው የማይገባውን ሥራ የሚሠራ እንደሆነ ዘገባው ጠቆሟል፡፡ ከገጠር ወደ ከተማ የሚሰደደውና እዚያም በኑሮ ስቃይ ውስጥ የሚገባው ወላጅ ልጆቹን ለጎዳና ተዳዳሪነት፣ ለልመናና ለወሲብ ንግድ አሳልፎ ይሰጣል፡፡ ወደ ት/ቤት መላክ የሚገባቸው ህጻናት ሊሠሩት ቀርቶ ሊያስቡት የማይገባ እጅግ ዘግናኝና ሰቅጣጭ ሥራዎችን እንዲሰሩ ይገደዳሉ፡፡refugees and their boat
በአፍሪካ ቀዳሚውን ሥፍራ የያዘው የመርካቶ አካባቢ የመሸታና የሴተኛ አዳሪ ቤቶች ክምችት እንደሆነ የጠቆመው ዘገባ የዘመናዊ ባርነቱን ሁኔታ ይዘረዝራል፡፡ በዚህ ሁኔታ ከአገር ውስጥ “ዘመናዊ ባርነት” ያመለጡት ወደ አረብ አገራት “ለውጭ አገር ዘመናዊ ባርነት” ገንዘባቸውን እየከፈሉ ራሳቸውን በፈቃደኝነት ይሰጣሉ፡፡
በዚህ የባርነት ንግድ ያልጠገበው ኢህአዴግ በቅርቡ በሳውዲ የሆነውን የወገን ሰቆቃ ቸል በማለት የተቋተረጠበትን ገቢ እንደገና ለመጀመር “ሕግ እያረቀቀ” መሆኑ ተሰምቷል፡፡ ባርነቱን በመቀጠል ሽያጩን ለማጧጧፍና ትርፉን ለማጋበስ ረቀቅ ባለ ሁኔታ ዝግጅቱን አድርጓል፡፡ ባለሥልጣናቱም የአረቡን አገራት ጎብኝተው “በባርነት ንግዱ” ላይ ተስማምተው መጥተዋል፡፡ ይህንን “መልካም ዜና” የሰሙት “ተስፈኛ ዘመናዊ ባሪዎችም” ዓይናቸውን ጨፍነው ወደ ጭለማው ለመግባትና ህይወታቸውን ለባርነት አሳልፈው ለመስጠት ሙሉ ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡ እስከዚያው ለመጠበቅ ያልቻሉትና “ከአገር ውስጥ ዘመናዊ ባርነት” ሞትን የመረጡት አሁንም ድንበር እያቋረጡ ወደ ባህር ይጓዛሉ፡፡
ባለፉት የመጋቢትና የሚያዚያ ወራት ቁጥራቸው ከመቶ የሚያልፍ በተመሳሳይ አደጋ ሰጥመዋል፤ ለቀብር ሳይበቁ በውሃ ተበልተዋል፡፡ ያገራቸው “ህዳሴና ልማት” ሊያኖራቸው ያልቻለው አውሮጳን አልመው እስከዚያው የአረቢያ ምድርን ተስፋ አድርገው በምድርና በባህር የሚሰደዱት ኢትዮጵያውያን ቁጥር እየጨመረ ከመሄድ በቀር የመቀነስ ሁኔታ አይታይበትም፡፡ አውሮጳን ሳያልሙ “ለዘመናዊ ባርነት” ወደ አረቢያ የሚሰደዱት ምንም ተስፋ በሌለበት ሁኔታ እንኳን ከእነርሱ በፊት ሄደው የተሳካላቸውን ሰዎች በማሰብ እነርሱም ከእነዚያ መካከል እንደሚሆኑ በመገመት ጉዞ ያደርጋሉ፡፡ ከደረቁ ምድር ገና ለመሳፈር ሲነሱ ለባህር ወንበዴዎች ገንዘባቸውን ይከፍላሉ፤ ከዚያም ሲያልፍ የአካል ክፍላቸውን እያወጡ ይሸጣሉ፤ እዚያው በኢንፌክሽን ይሞታሉ፤ ከዚህ ያመለጡትና “ባርነትን” ተስፋ ያደረጉት ደረቅ ምድር ሳይደርሱ በባህር ይሰጥማሉ፡፡ ከዚህ ሁሉ የተረፉት ጥቂቶች ከባህርና ከአጓጓዥ አውሬዎች አምልጠው “ለዘመናዊ ባርነት ብቁ” ይሆናሉ፡፡ በባርነት “ያተረፉትን” ገንዘብ ወዳገራቸው ይልካሉ፤ ያገራቸውን “ኢኮኖሚ በድርብ አኻዝ” ያሳድጋሉ፤ “በልማቱ መስክ” ይሳተፋሉ፤ … “መጪው ጊዜ ከኢህአዴግ ጋር ብሩህ ነው!”

The US Government Must Implement Congress’ Stance Against Forced Evictions in Ethiopia

December 12, 2014
Oakland, CA – The Oakland Institute applauds the US Congress for adopting language in the 2015 Omnibus Appropriations Bill that ensures US funding to Ethiopia will not be used to support forced evictions in the country.
A man on his plot of land in Kir, a resettlement village in Gambella
A man on his plot of land in Kir, a resettlement village in Gambella, Ethiopia, March 22, 2012 AFP/Getty Images
This provision in the bill acknowledges the ongoing crisis of human rights abuses resulting from forced evictions and land grabbing in Ethiopia and prevents US assistance from being used to support activities that directly or indirectly involve forced displacement in the Lower Omo and Gambella regions. Furthermore, it requires US assistance to be used to support local community initiatives aimed at improving livelihoods and be subject to prior consultation with affected populations. The bill also opposes US funding to international financial institutions such as the World Bank for programs that could lead to forced evictions in Ethiopia.
Several reports from the Oakland Institute have exposed the scale, rate, and negative impacts of large-scale land acquisitions in Ethiopia that will forcibly displace over 1.5 million people. This relocation process through the government’s villagization scheme is destroying the livelihoods of small-scale farmers and pastoralist communities. Ethiopian security forces have beaten, arrested, and intimidated individuals who have refused to relocate and free the lands for large-scale agricultural plantations.
Ethiopia’s so-called development programs cannot be carried out without the support of international donors, particularly the US, one of its main donors. Oakland Institute’s on-the-ground research has documented the high toll paid by local people as well as the role of donor countries such as the US in supporting the Ethiopian policy.
With this action, the US Congress clearly sends a message to both the Ethiopian government as well as the US administration that turning a blind eye to human rights abuses in the name of development is not acceptable. The new Bill reiterates provisions already contained in the 2014 Appropriations Bill, however, to date no evidence has been made available to demonstrate how US agencies and International institutions have implemented the provisions of the previous Bill. As the oversight authority of the State Department, Congress must ensure that the law is fully upheld and implemented. This warrants thorough scrutiny of USAID and World Bank programs to Ethiopia and their role in the forced resettlements and human rights abuses.Other human rights abuses – including the unlawful extradition and detainment of two Ethiopian-born individuals holding citizenship in Britain and Norway – abound, making strong action by the US Government imperative.
Thus, while the Oakland Institute applauds the US Congress for continuing its commitment to funding meaningful development work in Ethiopia, we believe that more needs to be done. We are calling on members of the Congress to demand that monitoring and reporting from the US State Department, Treasury, USAID, and other involved institutions begin immediately.
Source: Okland Institute

Friday, December 12, 2014

አስራ አንዱን የማዕከላዊ ገራፊዎችን እወቋቸው

December 12,2014
ከዳዊት ሰለሞን
በማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ ጋዜጠኞችን፣ፖለቲከኞችን፣የሀይማኖት ምሁራንና ያለ ምንም ተሳትፎ ኦሮሞዎች በመሆናቸው ብቻ በኦነግነት ተጠርጥረው ታስረው የነበሩ መተኪያ አልባ ዜጎችን በማሰር ቃላት ሊገልጸውና የሰው ልጅ ሊሸከመው አይችልም ተብሎ የሚታሰብን ሰቅጣጭ ድርጊት በመፈጸም ረገድ ወደር የሌላቸው ገራፊዎች ስም ዝርዝር ይፋ ተደርጓል፡፡እነዚህ ሰዎች አሁንም በዚሁ ድርጊታቸው ጸንተው ወንድሞቻችንን እያሰቃዩ የሚገኙ በመሆናቸው ህዝብ ሊያውቃቸውና ቀን ሲወጣም ፍትህ ሊጠይቅባቸው ይገባዋል፡፡

ስማቸው የተጠቀሱትን ሰዎች የምታውቁ አልያም በእነዚህ ሰዎች በማዕከላዊ ምርመራ ወቅት ስቃይ የደረሰባችሁ ዜጎች መረጃውን ልታዳብሩት ወይም ሊጨመሩ የሚገባቸውን ገራፊዎች ልታጋልጡ ትችላላችሁ፡፡
ethiopia-torture-620ገራፊዎቹ ነጭ ወረቀት በማቅረብ ተጠርጣሪዎች ፊርማቸውን እንዲያኖሩ የሚያስገድዱ፣ገልብጠው የሚገርፉ፣በወንድ ብልት ላይ ውሃ የተሞላ ላስቲክ በማንጠልጠል የሚያሰቃዩ፣ሴት እስረኞችን ጡታቸውን በበትር የሚደበድቡ፣ሰውን ካልደበደቡ ስራ ያልሰሩ የሚመስላቸው ቃሉ ከገለጻቸው ‹‹አረመኔዎች››ናቸው፡፡ምናልባት የፍትህ ጸሀይ ወጥታ ህዝብ አሸናፊ ሲሆን እነዚህ ሰዎች ይፈጽሙ የነበሩትን ግፍ በአደባባይ እንዲመሰክሩ ይደረጉ ይሆናል፡፡
ቤተሰብ፣ ዘመድ፣ወዳጆቻቸውም ስማቸውን ተመልክተው የህሊና ዕዳ ይፈጥሩባቸው ይሆናልና ስማቸውን ይፋ ማድረጉ ብዙ ጥቅም ይኖረዋል ባይ ነኝ፡፡
1. ታደሰ መሰረት የማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ኃላፊ
2. ዩሀንስ ኢንስፔክተር
3. ተዘራ ቦጋለ ኢንስፔክተር
4. ብርሃነ ኢንስፔክተር
5. ከተማ ኢንስፔክተር
6. ሰይድ አሊ ኢንስፔክተር
7. ገብረመድህን ኑር ኢንስፔክተር
8. ሙልጌታ ኢንስፔክተር
9. አሰፋ ትኩት ምክትል ኢንስፔክተር
10. ታደሰ አያሌው ኢንስፔክተር
11. በለጠ ኢንስፔክተር

Thursday, December 11, 2014

የኢትዮጵያ መንግሥት ገመና (ተመስገን ደሳለኝ)

December
ተመስገን ደሳለኝ  (ከዝዋይ እስር ቤት)
Temesgen Desalegn behindbarመሐሙድ የሱፍ የተወለደው በ1980ዓ.ም ከሶማሌ ክልል ርእሰ-መዲና ጅጅጋ 500 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘውዶሀን ከተማ ነው፡፡ ለቤተሰቡ ሰባተኛ ልጅ ሲሆን፤ አምስት እህቶችእና ሦስት ወንድሞች አሉት፡፡ በጅጅጋ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እስከ አስረኛ ክፍል ድረስ መዝለቁቢሳካለትም፤ ከዚህ በላይ ግን ሊቀጥል አልተቻለውም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የኢትዮጵያመንግስት የደህንነት ሠራተኞች የ1999ዓ.ም የግንቦት ሃያ በዓል በጅጅጋ ከተማ ስታዲዬም በተከበረበት ዕለት፣ የኦጋዴን ነፃአውጪ ግንባር (ኦብነግ) በሰነዘረው የቦንብ ጥቃት ተሳትፈሃል በሚል ለእስር በመዳረጉነው፡፡ ይህንን ተከትሎምከምድራችን አስከፊ ማሰቃያዎች መካከል ግንባር ቀደም በሆነውና የክልሉ
ነዋሪ “ጄል-አዳብ” (የገሃነም እስር ቤት) እያለ በሚጠራው ማጎሪያ ውስጥ እጅግ በጣም የከፋ ምድራዊ መከራ እንደተቀበለሀዘን በተጫነው ድምፅ ይናገራል፡፡ በሠውነቱ የተለያዩ ክፍሎች ላይ እንደ ፍም ቀልተው የሚታዩት ጠባሳዎቹም ያሳለፈውንሥቃይ አፍ አውጥተው ይመሰክራሉ፡፡ ለአራት ወራት ያህል አንድ ክፍል ውስጥ ለብቻው ተቆልፎበት፤ ሃያ አራት ሠዓታትሙሉ እጆቹ በካቴና ተቀፍድደው፣በቀን ከአምስት ጊዜ በላይ ለምርመራ እየተጠራ ያለዕረፍት ከባድ ስቅየት (ቶርቸር)ሲፈፀምበት ቆይቷል:፡ በመጨረሻም ለአንዲትም ቀን የፍርድ ቤት ደጅ ሳይረግጥ፣ ለኦብነግ አባላት አንድ ፓኬት ሲጋራሲያቀብል እጀ-ከፈንጅ ተይዟል በሚል ክስ የጅጅጋ ዞን ፍርድ ቤት በሞት እንዲቀጣ መወሰኑን እዛው እስር ቤት ሆኖከኢትዮጵያ ሬዲዮ የዜና እወጃ  እና ከቪኦኤ ሶማሊኛ ፕሮግራም ሠምቷል፡፡
ከፍርዱ በኋላም በተመሳሳይ ወንጀል ከተከሰሰ አንድ እስረኛ ጋር በካቴና ተጠፍሮ በቀን አንድ እንጀራ ለሁለት ተካፍሎእንዲበላ እንደ ውሻ እየተወረወረለት 60 ቀናትን አሳልፏል፡፡ መሐሙድ በተለይም በእንቅልፍ ወቅት እርሱ ወይምየሰንሰለት ደባሉ የተገላበጠ እንደሆነ ካቴናው የሚያደርስበትን የመለብለብ ቃጠሎ ሲያስታውስ ዓይኖቹ በእንባ ይሞላሉ፡፡በአሁኑ ወቅት በዝዋይ ማጎሪያ ከባድ ጥበቃ ለሚደረግባቸው ብቻ በተመደበ ‹‹ዘጠነኛ ቤት›› ውስጥ አስራ አንድ ሶማሊኛተናጋሪዎችን ጨምሮ በድምሩ ሰላሳ አራት ሰዎች ጋር ከዛሬ ነገ የግፍ ፍርዱ ተፈጻሚ ሊሆንብኝ ይችላል በሚል ሰቀቀንእየባነነ በስጋት ተጠፍንጎ መኖር ከጀመረ እነሆ ሰባት ዓመት ሊደፍን ሦስት ወራት ብቻ ቀርተውታል፡፡
የተዋረደው የፍትሕ ሥርዓት!. . .
ርግጥ ነው ይህ በጨረፍታ ያቀረብኩት አሳዛኝ ታሪክ የመሐሙድ የሱፍ ብቻ አይደለም፡፡ ሌሎች ሰባት ‹‹አባሪዎቹ››ስቃዩንም ሆነ የሞት ፍርዱን ይጋሩታል (በነገራችን ላይ በአንድ መዝገብ የተወነጀሉት እነዚህ ስምንት የሞት ፍርደኞች፡-መሐድ ኢብራሂም፣ አረብ ሰዋኔ ዱልባንቲ፣ ሐሰን መሐመድ ዑስማን፣ ሐሰን መሐመድ ዓሊ፣ ሙክታር መሐመድ ዓብዱላሂ፣ከድር ሽኩር ሙሳ እና ካሚል ዓብዱልናስር እንኳን በጋራ መንግሥት ላይ ሊያሴሩ ቀርቶ እርስ በርስም የተዋወቁት እስር ቤትውስጥ ነው፡፡ ከጅጅጋ ወደ ዝዋይ ‹‹ዘጠነኛ ቤት›› ተዘዋውረው በርካታ ዓመታትን ያሳለፉትም በጭካኔው ወደርእንደማይገኝለት የሚነገረው የክልሉ ፕሬዚዳንት አብዲ
በአደራ እንዲቀመጡ በመተላለፋቸው መሆኑን ነግረውኛል፡፡) እንደ መሐሙድ ሁሉ እነርሱም ፍርድ ቤት ቀርበውአያውቁም፤ ምንም ዓይነት የሰውም ሆነ የሰነድ ማስረጃ አልተቆጠረባቸውም፡፡ እዚህ ጋ የማነሳው አሳዛኝ ገጠመኝከመካከላቸው አንዳቸውም ራዲዮ ስላልነበራቸው የተጣለባቸውን የሞት ፍርድ ውሳኔ የሠሙት፣ ዜናው ከተላለፈ ከበርካታቀናት በኋላ ሬዲዮ ካላቸው እስረኞች መሆኑ
ነው፡፡ ይህ እጅግ አሳፋሪና አስደንጋጭ መንግሥታዊ ውንብድና በደንብ ይብራራ ዘንድ ለተከሳሶቹ ከተሰጣቸው ባለ አንድገፅ የክስ ቻርጅ የሁለቱን ብቻ በአዲስ መስመር እጠቅሳለሁ፡-‹‹በሶማሌ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ አቃቤ ሕግና ፍትሕቢሮ በሶማሌ ክልላዊ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
ጅጅጋ
የዐ/ሕግ/መ/ቁ 90/2000
ዝዋይ እስር ቤት ያለው
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከሳሽ፡- ዐ/ሕግ
ተከሳሽ፡- ሐሰን መሐመድ ዑስማን (ሐንን መድቤ)
ዕድሜ፡- 21
ሥራ፡- ተማሪ
አድራሻ፡- ጅጅጋ ከተማ፡- 06 ቀበሌ
ወንጀል
በ1996ዓ/ም የወጣውን የኤ.ፌ.ዴ.ሪ የመ.መ.ሥ.ሥ.ህ.ቁ. 240(3) እና 251(መ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፣
የወንጀል ዝርዝር
ተከሳሽ ከመስከረም 1999 ዓ.ም. ጀምሮ እራሱን ኦ.ብ.ነ.ግ. እያለ ከሚጠራው ተቃዋሚና አሸባሪ ድርጅት ጋር በራሱፈቃድ
በዚሁ በጅጅጋ ከተማ ከላይ በተጠቀሰው ዓመተ-ምህረት አባል በመሆን በጫካ በዚሁ አካባቢ ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ጋርበከተማም
ሆነ በጫካ በመገናኘት በኢኮኖሚ ረገድ የሚያስፈልጋቸውን፡- ጫማ፣ ልብስ የመሳሰለውን እዚያው ድረስ ሄዶ በማቀበልአብሮ
ሲንቀሳቀስ በመቆየቱ ተከሶ ቀርቧል፡፡››
ሁለተኛው የክስ ቻርጅ ደግሞ እንዲህ ይነበባል፡-
‹‹በሶማሌ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ አቃቤ ሕግና ፍትሕ ቢሮ
በሶ/ክ/መ/ ጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
ጅጅጋ
የዐ/ሕ/መ/ቁ 90/2000
ከሳሽ፡- ዐ/ሕግ
ተከሳሽ፡- መሐድ ሼክ ኢብራሂም
ዕድሜ፡- 28
ሥራ፡- የለውም
አድራሻ፡- ጅጅጋ ከተማ፡- ቀበሌ 05
1ኛ ክስ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ/ም የወጣውን የኤ.ፌ.ዴ.ሪ የመ/መ/ህ/ ቁ. 241 እና 251(መ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ በ1998 ዓ.ም. ወራትና ቀኑ በውል ካልታወቀ ጊዜ ጀምሮ እራሱን ኦ.ብ.ነ.ግ. እያለ ከሚጠራው ተቃዋሚ የፖለቲካ
ድርጅትና አሸባሪ ጋር በራሱ ፈቃድ አባል በመሆን ከዚህ ሕገ-መንግሥቱን ከሚፃረር ድርጅት በቀጥታ ፌዴሬሽኑእንዲከፋፈል፣ ክልሉን
የመገንጠል ዓላማ ለማሳካት ይህንኑ ድርጅት ከዚሁ በጅጅጋ ከተማ ለጊዜው ካልተያዘ ግብረ-አበሩ ጋር በመሆን ይህንኑአሸባሪ ድርጅት
በሚያስፈልገው ማቴሪያል ሁሉ፡- ጫማ፣ የፖሊስ የደንብ ልብስ፣ መድሃኒት. . . የመሳሰለውን በማቀበሉ፡፡
2ኛ ክስ
ወንጀሉ
በ1996ዓ/ም የወጣውን የኤ.ፌ.ዴ.ሪ የመ/መ/ህ/ ቁ. 36 (ለ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከ1996 ዓ.ም. ጀምሮ የተለያዩ መ/ቤቶች ማለትም፡- የክልሉ ት/ቢሮን፣ የቀብሪ-ደሐር ት/ቢሮን፣ እንዲሁም የMSF
እና የተለያዩ መሥሪያ ቤቶችን እና የትምህርት ተቋማትን ማህተም በማስመሰል አትሞ እና የኃላፊዎችን ፊርማ ዓይነትአስመስሎ
በማስፈር ሐሰተኛ ሰነድ አዘጋጅቶ በመገኘቱ ተከሶ ቀርቧል፡፡››
(ሁሉም የክስ ቻርጆች ማኅተም እና አንጋው አፈወርቅ ምንተስኖት የተባለ የክልሉ ዐቃቤ ሕግ ፊርማ አላቸው)
እነሆም ያለአንድ ምስክር፣ ያለምንም የሰነድ ማሰረጃ፣ አንድም ቀን ችሎት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃል ሳይጠየቁ እና
ሳይከራከሩ (ያውም የዞን ፍርድ ቤት) በነዚህ በስም በጠቀስኳቸው በስምንቱ ኢትዮጵያውን ላይ የሞት ቅጣትን የመሰለየመጨረሻ
ውሳኔ እንደቀልድ አስተላልፎባቸዋል፡፡ (በነገራችን ላይ ሌሎች 13 የኢትዮጵያ-ሶማሌ ተወላጆችም በተመሳሳይ የሐሰትውንጀላ የዕድሜ
ልክ እስር ተፈርዶባቸው ዝዋይ ይገኛሉ፡፡ የሚገርመው ጉዳይ ደግሞ ም ቢሆኑ መጀመሪያ ተጠርጥረው በተያዙበት ወንጀልአይደለምየተጠየቁት፡፡ ጉዳዩ ጭራሽኑ በምርመራም ወቅት አልተነሳም) መቼም በዚህ መልኩ በተቀናበረ የውሸት ክስ ከ20-27 ዓመት የሚገኙ
ወጣቶችን በሲኦላዊ እሳተ-ነበልባል ስቅየት ውስጥ እንዲያልፉ ከማድረግም በዘለለ፣ ብሩህ ቀናቸውን አጨልሞ ላይመለሱወደመቃብር
የሚሸኝ ቅጣት ሲጣል ከመመልከት የበለጠ የትኛውንም ዜጋ የሕሊና ስቃይ ውስጥ ከትቶ፣ አንገት አስደፍቶ፣ በቁጣ ቀስቅሶ
ወደአደባባይ የሚያወጣ ገፊ-ምክንያት አለ ብዬ አላምንም፡፡

ማነው ተጠያቂው?
በእነዚህ ንፁሃን ኢትዮጵያውያን ላይ ‹በጄል-አደብ› የደረሰባቸው በነውረኝነት የታጀለ ኢ-ፍትሐዊ ፍርድ እና ስቅየት፣
የሥርዓቱን እውነተኛ ማንነት ገሃድ የሚያወጣ ተጨባጭ ተግባር መሆኑ ባይካድም፡ ይህንን አረሜናዊ ድርጊት በፊት-አውራሪነት
የመሩት፡- ኮሎኔል ሞኒ መንገሻ በጊዜው የክልሉ የፀረ-ሽብር ግብረ-ኃይል ዋና ኃላፊ የነበረ አሁን ወደአዲስ አበባ ተቀይሮ‹ሕገ-ወጥ
የሠው ዝውውር ወንጀል መከላከል› ኃላፊ፣ ቢኒያም የተባለ የክልሉ የደህንነት ኃላፊ፣ ሻለቃ ዘገየ በክልሉ የፌዴራል ፖሊስኃላፊ፣
ወልደአራዌ የክልሉ ፖሊስ ም/ኮሚሽነር፤ እንዲሁም ሻለቃ ወንድሜ፣ ሻለቃ በለጠ እና ታሰረ የተባሉ ኃላፊነታቸውንለይተው
የማያስታውሷቸው ግለሰቦች መሆናቸውን ግፉአኖቹ በተሰበረ ልብ፣ ምሬት በሞላው ድምፅ፣ ተስፋ በቆረጠ ስሜትሲተርኩልኝ ዓይኖቼ
ላይ የተቋጠረው የእንባ ከረጢት ገንፍሎ እንዳይፈስ ብርቱ ትግል ማድረጌን አልሸሽግም፡፡
የሆነው ሆኖ እነዚህ የሥርዓቱ ሹማምንት የፍርድ ቤት ደጅ ሳይረግጡ፣ የሞት ቅጣት እንዲተላለፍባቸው ባደረጓቸው
ምስኪኖች ላይ የማሰቃያ ጥበቦቻቸውን በሙሉ ከሞከሩባቸው በኋላ፡- ‹‹ሞት እንፈርድባችኋለን!!›› እያሉ ያስፈራሯቸውናይዝቱባቸው
ነበር፤ እነርሱም፡- ‹‹እናንተ ፍርድ ቤት ናችሁ እንዴ?›› ብለው በግርምትና ባለማመን ሲጠይቋቸው፣ ማናአህሎኝነትያሳበጣቸው የፀጥታ
ኃላፊዎች እንዲህ በማለት አስረግጠው መልስ መስጠታቸውን ሰምቻለሁ፡-
‹‹አዎን! ፍርድ ቤት ማለት እኛ ነን!!››
በርግጥ ከዚህ ሁሉ መከራ በኋላ የተላለፈባቸው ውሳኔ፣ ያውም በሞት እንዲቀጡ የሚል መሆኑን ስናስተውል የዛቻውን
መነሾ መረዳቱ አዳጋች አይሆንብንም፡፡ በአናቱም በምርመራ ወቅት ዕድል ፊቷን ያዞረችበትን ተጠርጣሪ እዛው እስረኛ ፊትበሽጉጥ
ግንባሩን በርቅሰው እንደ መናኛ ነገር ሜዳ ላይ ይዘረጉት እንደነበረ የዓይን እማኞች ይመሰክራሉ፡፡
በጥቅሉ ይህ ሁነት በሀገሪቱ አለቅጥ የተንሰራፋውን የፍትሕ እጦት፣ የሠብአዊ መብት ጥሰት፣ ዳኞች ከሕግ ይልቅ ከቤተ-
መንግሥት በሚላክላቸው የፍርድ ውሳኔ ንፁሃኑን ለምድራዊ ስቃይ ከመዳረግም አልፈው ተርፈው በጭካኔሕይወታቸውንም
እንደሚነጠቁ በቂ ማስረጃ ይመስለኛል፡፡

‹‹ጄል-አዳብ››
የክልሉ ኗሪዎች ‹‹ጄል-አዳብ›› (የገሃነም እስር ቤት) እያሉ የሚጠሩት የጅጅጋው ማሰቃያ ቤት ክፍሎች የተሠሩት አራትመቶ
ታሳሪዎችን እንዲይዙ ታስቦ ቢሆንም፣ አብዛኛውን ጊዜ ከአራት ሺህ በላይ ታሳሪዎች እንደሚታጎሩበት አረጋግጫለሁ፡፡ይህም አንድ
ሰው ከአንድ ሰዓት በላይ በእንቅልፍ ማሳለፍ እንዳይችል አድርጎታል፡፡ ምክንያቱም ቦታውን ለተረኛው የመልቀቅ ግዴታአለበትና፡፡
ምናልባት እንቅልፍ ቢጥለው እንኳ ተረኞቹ ቀስቅሰው (ጎትተው) ያስነሱታል፡፡
ከ‹‹ጄል-አዳብ›› በሕይወት ተርፎ የሚወጣ ሰው ዕድለኛ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ በዚህ ቦታ ከቤተሰብ ጋር መገናኘት ጭራሽ
አይሞከርም፡፡ ማሰቡ እንኳ እንደ ቅንጦት ነው የሚታየው፡፡ በእስር ቤቱ አጥር ሦስት መቶ ሜትር ክልል ርቀት ዙርያ ውስጥመገኘትም
ለከባድ ስቃይ (አንዳንዴም ለሞት ቅጣት) ይዳርጋል፡፡ በሃያ አራት ሰዓት አንዴ፣ አንድ እንጀራ ለሦስት እየተቃመሱለአምስት ዓመት
በዛ እስር ቤት ያሳለፈ ምስኪን አጋጥሞኛል፡፡ ይህ ወጣት በ2004ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ ሦስት ዓይነት ተላላፊ በሽታ(ተቅማጥ፣
ሰውነትን የሚያሳክክና ጉሮሮን አሳብጦ ለአዕምሮ መቃወስ የሚዳርግ) ተከስቶ በቀን እስከ አስራ አራት ሰው ድረስ ይሞትእንደነበር
ያስታውሳል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ሕክምና ብሎ ነገር አልነበረም፡፡ እንዲያውም በግልባጩ የክልሉ አስተዳዳሪዎችጭካኔያቸውን (ኢ-
ሠብአዊነታቸውን) ወለል አድርገው የሚያሳብቁ ድርጊቶች መፈፀማቸውን አላቋረጡም፡፡ ለማሳያ ያህልም እስረኛው ከሌሊቱስድስት
ሰዓት ላይ በአንድ ድምፅ እንዲህ የሚል መፈክር እንዲያሰማ መገደዱን እዚህ ጋ መጠቀስ ይቻላል፡-
‹‹መለስ ዜናዊ ሐኖላዶ!›› (መለስ ዜናዊ ለዘላለም ይኑር!)
‹‹አብዲ ሑመድ ዑመር ሐኖላዶ!››
‹‹ኢትዮጵያ ሐኖላዶ!››
ኦብነግ ሐዳኦዶ!›› (ኦብነግ ይውደም!)ሌላው አስገራሚ ጉዳይ ቤተሰብ ታሳሪ ልጁ በሕይወት ይኑር ይሙት የሚያውቀውከማጎሪያው በስንት ጊዜ አንዴ የሚፈታ
ሰው ሲገኝ ብቻ የመሆኑ እውነታ ነው፡፡ እናም ድንገት በአንዲት ‹ዕድለኛ› ቀን አንድ ታሳሪ ከ‹‹ጄል-አዳብ›› የተለቀቀእንደሆነ ወሬው
ከመቅጽበት ይዛመትና ለሳምንታት አሊያም ለወራት የእስረኛው ቤት በእንግዶች እስከ አፍ-ገደፉ ጢም ብሎ ይውላል፡፡የተለመደ
ነውና እሱም ያለመታከት የቀረበለትን ጥያቄ በሚከተለው መልኩ ሲመልስ ይከርማል፡-
‹‹ኦ!… እገሌ ከሞተ እኮ ሁለት ዓመት አለፈው›› ፤ “እገሌማ ሲያሳዝን! ካረፈ ገና አንድ ወሩ ነው”፤ “ኦ! እገሌ ለወደፊቱ
እግዜር ይጠብቀው እንጂ እስካሁን በሕይወት ይገኛል…” ወዘተ ወዘተ. . .

Politicians, diplomats react to release of CIA torture report

December 11,2014
CIA torture report

Politicians and diplomats are reacting to the release of a highly controversial and inflammatory report on CIA interrogation techniques following the 9/11 attacks.
American embassies and diplomats abroad are preparing for potential backlash.
Texas Tech professor Tibor Nagy, the former US Ambassador to Ethiopia and Guinea, says the report is like waving a red flag in front of a raging bull.
“I wouldn’t want to be a US ambassador right now in certain parts of the world having to face what the reaction might be because this is the kind of thing that could push some people over the edge,” Nagy said. “All of this information has basically been out there, but to put it together and wrap a ribbon around it… There are a lot of people who don’t really need an excuse to go out and do awful things against Americans and America. It’s a wonderful excuse for them.”
Texas Senator Ted Cruz says the release of the report is endangering Americans and that it’s time for Senate Democrats to put the safety of Americans first, and scoring political points last.
Here is Senator Cruz’s statement in full:
“Within 48 hours, President Obama has set Guantanamo Bay detainees free, and Senate Democrats have endangered Americans all over the world by releasing classified tactics, which have since rightly been outlawed, used by the intelligence community in the aftermath of the 9/11 terrorist attacks. The Democrats’ foreign policy – defined by a series of actions designed to appease our enemies and diminish the capability and morale of our military men and women – is profoundly dangerous.
“Every civilized nation agrees that torture is wrong. But today’s partisan report will endanger lives, drive away our allies – who have never been more needed than now – and undermine the ability of our intelligence officers and soldiers to protect our national security. After six years, enough with saying ‘everything is George W. Bush’s fault.’ It’s sad that, with all the threats we face across the globe, Senate Democrats are still more interested in scoring political points against the Bush Administration than in working together to keep America safe and our military strong.”
Source: FOXNews.com

Wednesday, December 10, 2014

በፓርቲያችን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች ላይ በተፈጸመው አምባገነናዊ የጭካኔ እርምጃ ከትግላችን አናፈገፍግም! ‪ከሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ም/ቤት የተሰጠ መግለጫ

December 10,2014
ሰማያዊ ፓርቲን ጨምሮ ዘጠኝ ትብብር የፈጠሩ ፓርቲዎች በህዳር ወር ያወጡት መርሐ ግብር አንድ አካል የሆነውን የ24 ሰዓት የተቃውሞ የአደባባይ ሰልፍ ለመተግበር ሥራ ላይ የነበሩ አመራሮች፣ አባሎቻችና ደጋፊዎቻችን ላይ አምባገነኑ ስርዓት በወሰደው የግፍ እርምጃ ምክንያት ከፍተኛ ድብደባ ደርሶባቸው በጨለማ ክፍል ውስጥ በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡

እስረኞቹ በጨለማና ቀዝቃዛ ክፍል፣ አንድ ራሱን ‹‹መንግስት ነኝ›› የሚል አካል ‹‹እስር ቤት›› ብሎ ዜጎችን ሊያጉርበት ይችላል ተብሎ የማይጠበቅ ሽንት ቤትና ጋራዥ ውስጥ መታሰራቸው አልበቃ ብሎ በቤተሰብ እንዳይጠየቁ ተደርገዋል፡፡ በድብደባው ምክንያት ራሳቸውን የሳቱና ከፍተኛ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው አመራሮቻችን፣ አባላትና ደጋፊዎቻችን የህክምና አገልግሎት ማግኘት አልቻሉም፡፡ አገዛዙ ይህን ሁሉ ግፍ የሚፈጽመው ለሰላማዊ ታጋዮች ባለው ጥልቅ ጥላቻና ጭካኔ በተሞላበት እርምጃው ከትግሉ ያፈገፍጋሉ ከሚል ስሌት ነው፡፡

ሆኖም እኛ ወደ ወደ ትግሉ ስንገባ ትግሉ ምን ያህል መስዋዕትነት እንደሚያስከፍል በሚገባ እናውቀዋለንና በየትኛውም መንገድ ስልጣኑን ለማስጠበቅ የሚጥረው ህወሓት/ኢህአዴግ መሰል የጭካኔ እርምጃ እንደሚወስድ የምንጠብቀው ነው፡፡ በመሆኑም አገዛዙ የወሰደውና ወደፊትም ሊወስደው የሚችለው ከዚህ የባሰም አረመኔነት የተሞላበት እርምጃ ይበልጡን ያጠናክረናል እንጅ ከትግላችን ቅንጣት ያህል ወደኋላ እንድናፈገፍግ የሚያደርገን አለመሆኑን መግለጽ እንወዳለን፡፡

ህወሓት/ኢህአዴግ አከብረዋለሁ እያለ ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ የሚጠቀምበትን ህገ መንግስት ራሱ እየናደው ‹‹ጅራፍ ራሱ ገርፎ..›› እንዲሉ ህገ መንግሥታዊ መብታቸውን በመጠቀም ህጋዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ የነበሩ አመራሮቻችን፣ አባሎቻችንና ደጋፊዎቻችን ላይ ‹‹ህገ መንግስቱን በመናድ›› የሚል ክስ አቅርቦባቸዋል፡፡ የሰልፉን ተሳታፊዎች ደብድቦና አፍሶ ባሰረበት ወቅት ‹‹ምንም ችግር ሳይፈጥሩ በቁጥጥር ስር ውለዋል›› እንዳላለ ከስርዓቱ ቁጥጥር ያልወጣው የህግ አካል ‹‹መስቀል አደባባይ ላይ ንብረት ወድሟል፡፡›› በሚል ሌላ ክስ አቅርቧል፡፡ ስርዓቱ ፓርቲያችንና ትብብሩ በጀመረው ሰላማዊ ትግል በመደናገጡ የሚይዘው የሚጨብጠው እንዳጣ ህወሓት/ኢህአዴግ የሚዘውራቸው ተቋማት የተለያየ የፈጠራ ክስና ዘገባ ማቅረባቸው ዋነኛ ማሳያ ነው፡፡

ምክር ቤቱ ፓርቲያችን በሚያደርጋቸው ቀጣይ እንቅስቃሴዎች ሁሉ ተገቢውንና አስፈላጊውን ውሳኔ እንደሚሰጥ መግለጽ ይወዳል፡፡ በዚህ የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ ውስጥ ግምባር ቀደም የሆኑ አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎችን ጨምሮ በአሁኑ ሰዓት በእስር ለሚገኙና የህወሐት/ኢህአዴግ የግፍ ሰለባ ለሆኑ ጓዶቻችንና የትግል አጋሮቻችን ሁሉ ያለንን አክብሮት ስንገልጽ ምን ጊዜም ከጎናቸው እንደሆንንና ሰላማዊ ትግሉ በበለጠ ሁኔታ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በማረጋገጥ ነው፡፡

ስለሆነም በሀገራችን ህዝባዊ ሥርዓት ለማምጣትና በህግ የበላይነት የሚያምን መንግስት ለመመስረት በምናደርገው ትግል ሁሉ የሚጠበቅብንን መስዋእትነት ለመክፈልና ሀገራዊ ግዴታችንን ለመወጣት ዝግጁ መሆናችን እየገለጽን መስዋዕትነት ለመክፈል የተዘጋጀንለትና የምናከብረው ህዝብ ከጎናችን እንዲቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት

ህዳር 30/2007 ዓ.ም

አዲስ አበባ

ኑ! ራሳችንን ነጻ በማውጣት የሀገራችንን እጣ ፈንታ እንወስን!!!

blue