Saturday, June 28, 2014

የአማራን ህዝብ በማጥፋት ወያኔና ተቃዋሚው በጋራ እየሰሩ ነው

June28/2014



አቶ አዲሱ አበበ አርብ ጁን 20 2014 በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ያስተላለፉትን ቃለ መጠይቅ ቃል በቃል በጽሁፍ ገልብጨ ከአውዲዮው ጋር እንድልክላችሁ ያነሳሳኝ ሆን ተብሎ በአማራው ህዝብ ላይ የሚፈጸመው ዘር ማጥፋት፣ ድርጊቱን ቀጥታ በሚፈጽሙት አካላት ብቻ ሳይሆን የወያኔ ትግሬዎችን የጎሳ ፖለቲካ እንቃወማለን የሚሉ ሳይቀሩ ሆን ብለው የተሰሳተ መረጃ በመስጠት በአማራው ህዝብ ላይ የክህደት ስራ እየሰሩ ለመሆኑ ለመጠቆም እና አንባቢም ቃለ መጠየቁን በማንበብም ሆነ ቃለ መጠየቁን ከተለያዩ ድህረገጾች በመስማት ያራሱን ፍርድ እንዲሰጥ ነው። በአማራው ህዝብ ላይ የሚፈጸመው የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ዘመቻ በወያኔና የሱ ተናካሽ ውሾች በሆኑ የብሄር ድርጅቶች ብቻ ሳይሆን፤ በኢትዮጵያ ስም የተደራጁ ፓርቲዎች፣ ድርጅቶች፣ ሬዲዮ ጣቢያዎች፣ ድህረገጾች ወዘተ ጭምር በጋራ የሚተባበሩበት ለመሆኑ የሚጠይቅ አይምሮ ያለው ያስተውለው።
ተፈናቃዮች አማራ ናችሁ ተብለን ከወለጋ ተፈናቀልን እያሉ፤ አቶ አዲሱ አበበ አማረኛ ተናጋሪዎች ተፈናቀሉ ይላሉ። በአማረኛ ተናጋሪነት ከሆነ ከወለጋ የተጠየቁ አፈናቃዮችኮ በአማረኛ ነው ከአቶ አዲሱ አበበ ጋር የሚነጋገሩት፤ አቶ አዲሱ አበበ የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ጋዜጠኛ ስለሆኑ፣ እንዲሁም የአሜሪካ መንግስት ከምንም ጊዜ ይበልጥና ከማንም በላይ የወያኔ ትግሬዎችን መንግስት በገንዘብና በሰው ሀይል ስለሚረዳ አቶ አዲስ አበበ ከቀጣሪያቸው አቋም ውጭ ሊሆኑ አይችሉም ብንል፡ ከአማራው ኪስ በሚወጣ መዋጮ የሚንቀሳቀሱ እንደ ኢሳትና ሌሎችም በየሀገሩና በየከተማው የተቋቋሙ ሬዲዮ ጣቢያዎችና ድህረገጾች፣ የአማራው ህዝብ አማራ በመሆናችን ብቻ ተነጥለን፤ ሀብትና ንብረታችን ተዘርፎ፣ ተደብድበን፣ ከፊሎችም ተገለው ከሞት አምልጠን እዚህ ደረሰን ሲሉ፣ ”ከባለቤቱ ይበልጥ ያወቀ ቡዳ ነው” እንደሚባለው፤ አማራ ስለሆኑ አይደለም፤ አማረኛ ተናጋሪ ስለሆኑ ነው ብለው በአማራው ህዝብ ላይ አማራ በመሆኑ ብቻ ወንጀል እንደላልተፈጸመበት አድርገው የተዛባ ማስተባበያ ለህዝብ ጀሮ ያቀርበዋል።  ከዚህ ተጨማሪ ስለዚህ መፈናቀል የዘገቡ ኢትዮጽያዊ የሚባሉ ድህረገጾችና ሬዲዮ ጣቢያዎች ብዙም ባይሆኑ፣ ለይስሙላ የዘገቡም ዘግበውም በነጋታው ከድህረገጻቸው ያነሱ ድህረገጾችንም ታዝቤአለሁ።
ብአዴን ማን ነው ሲሉ አቶ ገብረመድህን አርአያ ሰፋ ያለ መረጃ ሰጠውናል። ብአድኖች ከመጀመሪያው ”አማራ ህዝብ ጠላት አይደለም” ያሉትን የገደሉና ከዚያም በአማራው ህዝብ ላይ በየክፈለሀገሩ እየዞሩ የአማራውን ህዝብ ነጥለው በመሪነት ያስገደሉና ያሰደዱ ለመሆኑ መረጃዎች አሉ። አሁንም ከዚህ ቃለ መጠየቅ እንደምንረዳው የኦሮሞና የአማራው ክልል ባለስልጣኖች ይሄን ያህል አፈናቅሉ፤ ይሄን ያህል ግደሉ፤ ይሄን ያህል ደግሞ ለፖለቲካ መልሱ እየተበሉ በእቅድ የሚፈጽሙት የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል መሆኑን ቃለ መጠይቁ ይጠቁማል።
በአቶ አዲሱ አበበና በሬዲዮ ጣቢያቸው ላይ እንዲያውም ስለመፈናቀሉ በመዘገባቸው ባለውለታ እንጂ ቅሬታ የለኝም። ሌሎች በተቃዋሚነት ተሰልፈናል የሚሉ ግን አሁንም ቢሆን ለይስሙላ የሚጠይቁት ”ወደ ቀያቼው እንዲመለሱ” የሚል ነው። አንድ ሰው አማራ በመሆኑ ብቻ ሀብት ንብረቱ ተዘርፎ፤ አቅመ ደካማ የሆኑ ሚስት ልጆቹ፣ በእድሜ የገፉ እናት አባት ተገለው፤ ቤቱ ተቃጥሎ ”ወደ ቀያቸው ይመሰለሱ” የሚለው ፍርድ በአማራው ህዝብ ላይ ለሚፈጸመው የዘር ማጥፋትና ማጥዳት ወንጀል ተባባሪነት ካልሆነ በቀር ትክክለኛ ፍርድ አለመሆኑን ህሌናችሁ ፍርድ ይስጥ።
አንድ ሰው አማራ በመሆኑ ብቻ ሀብት ንብረቱን ተቀምቶ፣ የተገደለው ተገሎ የሚፈናቀል ከሆነ፤ አንድ ከአማራ ወላጆች የተወለደ ኢትዮጵያዊ መብቱ ተከብሮ ለመኖሩ የጊዜና የቦታ አለመገጣጠም ካልሆነ በቀር ዛሬ ወለጋ በሚኖሩ አማሮች ላይ የደረሰው መገደልና መፈናቀል በሱ ወይም በሷ ላይ እንደማይደርስ ምንም አይነት መተማመኛ የለም። ብሄረተኝነት የግለሰቡን ብሄር አንጂ የግለሰቡን ሰብአዊ ባህሪ አይቶ ይህ ደግ ነው ተወው፣ ያ ክፉ ነው በለው አይልም። ስለዚህ ማንም ከአማራ ወላጆች የተወለደ ሁሉ በወያኔ ትግሬዎችና የነሱም ተናካሽ ውሾች በሆኑ የብሄር ድርጅቶቹ አንዲሁም ከሀገር ውጭ መረጃ በማጣመም፣ በአማራው ህዝብ ላይ የሚፈጸመውን ወንጀል በማስተባበልና ማእቀብ በማድረግ ከወያኔ ትግሬዎች ጋር በአጋርነት የተሰለፉ ሬዲዮ ጣቢያዎችና ድህረገጾች የአማራን ህዝብ በማጥፋት ወንጀል እየተባበሩ ለመሆኑ ከኔ ጽሁፍ ይልቅ ትንሽ ማሰብ የሚችል ጭንቅላት ያለው ሰሞኑን በወለጋ በአማራው ህዝብ ላይ በተፈጸመው ግድያና መፈናቀል ድህረገጾችን አይቶ፣ ሬዲዮ ጣቢያዎችን አዳምጦ ይፍረድ።
ከግለሰብ የተወረወረ ትዝብት
ቃለ መጠይቁን ለማዳመጽ ይሄንን ይጫኑ፣ በጽሁፍ ለማንበብ ከታች ያለውን ይመልከቱ
የአሜሪካ ራዲዮ ጣቢያ ከተፈናቃዮች ጋር ያደረገው ቃለ መጠይቅ፣
ጁን 20 2014
ከወለጋ በተለይም ከግንቢና ከቄለም ከግንፍሌ ወረዳ ተባረርን ደግሞ ቤት ንብረታችን ተቃጠለ ያሉ የአማረኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን በአሁኑ ወቅት ባህር ዳር እንደሚገኙ ይናገራሉ። ቁጥራቸው እስከ 3000 ይደርሳል የሚሉ እነዚህ ተፈናቃዮች የአማራው ክልል አስተዳደር መፍትሔ እንዲፈልግላቸው በመጠባበቅ ላይ መሆኑንም ተመልክቷል። የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት በበኩሉ የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ100 በታች ነው ይላል። አዲሱ አበበ ተፈናቃዮችንና ጉዳዩ የሚመለከታቸውን የመንግስት አካላት አነጋግሮ ተከታዩን አጠናቅሯል።
አቶ ጋሻው ፈቃደ የተባሉና ሌላ አንድ ስሜ አንዳይገለጽ ያሉ ተፈናቃይ ጨምረን አወያየን፣ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉት የምእራብ ወለጋ ዞን ተፈናቃዩ ከወር በላይ ሆኖናል ብለው ይጀምራሉ።
አሁን 1 ወር ከምናምን እየሆነው ነው ምክንያቱ የድሮ ታሪክ ነው የሚያነሱት፤ ሚኒሊክ እንደዚህ አድርጎን፣ እንዲህ አድርጎን ነው የሚሉት፤ በጣም አሳደዱነ፤ የከተማው ህዝብ እንዳለ ወጥቷል እንደገና ባለስልጣኖች ደግሞ አሉበት፡ ፖሊሶች እነዚህ አድማ በታኝ የሚባሉት አብረው ነው ሲዘርፉና ሲደበድቡን የዋሉ ማለት ነው። አማራ የተባለውን።
እኮ ምክንያቱ ምንድነው አሉዋችሁ፤ በትክክል?
ምክንያቱ የድሮ ታሪክ ነው፣ እነሱ እንገነጠላለን ምናምን ነው የሚሉት፤ እራሳችን ነጻ እናወጣለን፤ አማራን አንፈልግም፣ አማራ ይውጣልነ ነው። እና ህይወታችን የተረፈው በስንት ነገር ነው። ኮርኒስ እየገባን ጫካ እየገባን በስንት ነገር ነው። ብዙ ሰው ሞቷል።
ስንት ጊዜ ሆኖት እርሶ ወለጋ ሲኖሩ?
እኔ 11 ዓመቴ ነው፣ ወደ 5 ቤተሰብ አስተዳድራለሁ፣ ሱቅም ነበረኝ፣ ጣቃ አከፋፍል ነበር፣ ጣቃውን እንዳለ ዘርፈውኛል።
ስንት ሰው ከዚያ ተሰደደ? ከወለጋ ከግንቢ በተለይ? እርሶ ካሉበት
ቢያንስ ከ8000 የማያንስ ህዝብ ነው።
ባህርዳር የአማራው አስተዳደር አለ እዚያ ደግሞ ሄዳችሁ አላመለከታችሁም? ምን አሉዋችሁ?
ወደ ቤታችሁ ተመለሱ ነው የተባልነው፣
ወዴት ወደቤታችሁ?
ወደነበራችሁበት ተመለሱና እናረጋጋለን ምናምን ነው ያሉን፤ እነሱ ደግሞ አሁን እራሱ አልተውም
ሌላው አቶ ጋሻው ፈቃደ ይባላል፤ የመፈናቀላችንን ምክንያት በውል አልተረዳነውም፤ ይሉና ይቀጥላሉ።
ምክንያቱ ምን  እንደሆነ እኛ ያወቅነው ጉዳይ የለም፣ ለኛ በኳስ ነው ምናምን ነው የሚሉት
ኳስ ማለት
በባህርዳር ከተማ ላይ ኳስ ጨዋታ ተካሂዶ ነበር፣ የአማራ ክልል ህዝብ ኦሮሞዎችን ጋላ! ጋላ! አሉን፣ እና የኛ ሰው ደግሞ የተደበደበ ሰው አለ። እያሉ ነው ለኛ ሲናገሩት የነበረው።
እናንተ እዚያ አልሄዳችሁም? ለምን እናንተን ውጡ አሉዋችሁ ብዬ ነው?
እኛም ግራ የገባን እኮ እሱ ነው፣ ከዚያ ወደዚያ ሰው ተይዞ መመከር እያለበት ለምን በስመ አማራ ለምን እኛ ይሄን ያክል መበደል አለብን የሚለውንኮ አቤቱታ ስናቀርብ አቤቱታችንን እዚህ ደግሞ አልቀበልም ያሉ።
ስንት ሰው ነው በጠቅላላ የተፈናቀለ ወይም እንዲወጣ የተደረገው?
ቢያንስ ከግንቢ ከተማ ብቻ አንድ 3000 ሰው ይሆናል። ያልወጣም እዚያ የቀረም ህዝብ አለ፤ በቃ ህይወታችን እስከሚያልፍ መጠበቅ ነው እንጂ ያለብን እንዴት እናደርጋለን?
ሌላ ሰው ሳናግር እንዲሁ ከ2000 ሰው በላይ ነው የሚሉኝ፤ ይሄን ያህል ሰው ሲፈናቀል እዚያ አካባቢ አስተዳደሩ፤ የፖሊስ ጣቢያው፤ የመንግስት ባለስልጣናት የሉም? ወይም እናንተ ሄዳችሁ አቤት ለማለት አልሞከራችሁም? አቶ ጋሻው።
ሄደን አቤት ብለናል፤ ግን ሊቀበሉን አልቻሉም፣ ሄደንም አመልክተናል አቤቱታችንን እያቀረብን ነው እኛ ያለነው አሁን ለነሱ
ለማን ነው አቅርበን እንቢ አሉን የሚሉኝ?
ርእሰ መስተዳደር ሄደን ነበር እኛ፣ ርእሰ መስተዳደሩ
ለማን ነው አቅርበን ነበር የሚሉኝ፣ ለባህርዳር?
አዎ ባህርዳር ከተማ ላይ፣
እና ምን ተባል…?
ከ5 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት ተቀጠርን፣ 8 ሰዓት ደግሞ ውጡ አሉን።
ሰው ምረጡ ተብሎ ሰው መርጣችሁ ከላካችሁ እንዴት እንደገና ውጡ ይላሉ ብዬ ነው። ማ ቢሮ ነበር ልትገቡ የፈለጋችሁ?
እዚያ እርሰ መስተዳደሩ ላይ፤ በቃ አስተዳደሩ፤ እሱን ፈልገን ነበር እኛ ርእሰ መስተዳደሩን
ፕሬዜዳንቱ ቢሮ ነው ወይስ ምክትላችው ወይስ ጸሀፊ ጋ ወይም
አዎ፣ ርእሰ መስተዳደሩ ቢሮ ነው እንጂ
ለመሆኑ የአካባቢው ባለስልጣናት ምን አሉ? እናንተስ አቤት ብላችሗል? ላልሁት ጥያቄ የጸጽታ ሀላፊ ናቸው፤ እርሳቸው ሁሉንም ያውቃሉ፤ በማለት የአንድ ሰው ስምና ቁጥር ሰጠውኝ ደወልሁ
አቤት፤ አቤት
እንደምን ዋሉ? አቶ አወቀ
አቤት፤ ማን ልበል?
አዲሱ እባላለሁ፤ ከዋሽንግቶን ነው የምደውለው፤ ከአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ
ይሄን ስልክ አላውቀውም፤ ከየት ነው?
እንዳልሁት ከአሜሪካ ነው የምደውለው፤ ከአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ፣ ከዋሽንግቶን፣ ከቪኦኤ
ከዚያ አካባቢ ተፈናቀልን የሚሉ ሰዎች ኢንተርቪው አድርጌ ነበር፤ እና እርሶ የሚያውቁትን ነገር ቢነግሩኝ?
ከየት?
ከቄለም አካባቢ፤ ከግንቢም አማረኛ ተናጋሪዎች
የት ሄድን? ወዴት ተፈናቀልን አሉ?
ተባረው ባህር ዳር ጎጃም ውስጥ ነው  ያሉት፤ ሰፈራ ጣቢያ አግኝተው?
ማን ነው ያባረረው?
እርሶ የሚያውቁትን እንዲነግሩኝ ነው አቶ አወቀ፤ አሁን የምደውለው ነዋሪዎችም ባለስልጣናት ናቸው ያባረሩን ይላሉ፤ ሁለቱንም
እነማን ናቸው እነሱ መጀመሪያ?
የሰዎቹን ስማቸውን ነው የሚፈልጉት?
አዎ
በሺዎች የሚቆጠሩ ናቸው፤ ነገረ ግን ጥያቄዬ ከቄለምና ከግንቢ አካባቢ እንዲባረሩ ሆኖዋል ወይ? እንዲወጡ ተደርጓል ወይ? የጸጽታ ክፍሉ የሚያውቀው ነገር አለ ወይ? እምሎት።
እኔ የጸጽታ ክፍል አይደለሁምና ከህዝብ ነኝ፤ እና ማን ነው ያለ? መጀመሪያ ንገረኝ፣
እርሶ ……
ከዚያ በሗላ ነው የማውቀውን የምስጥህ እንጂ የሆነም ያልሆነም ነገር ልሰጥህ አልችልም ማነው ያለህ?
አቶ አወቀ የጸጽታ ሀላፊ ናቸው ተብሎ ነው ስልኩ የተሰጠኝ ልክ አይደለም?
ውሸት ነው፤ የጸጽታ ሀላፊ አይደለሁም። እኔ ሌላ ስራ ነው ይዤ ያለሁ፤ የጸጽታ ሀላፊውን ልትጠይቅ ትችላለህ።
እርሶ በምን ውስጥ ነው ያሉት? ስለዚህ ጉዳይስ የሚያውቁት ጉዳይ የለም።
እኔ የድርጅት ጽህፈት ቤት ነኝ
የተባረሩ አማረኛ ተናጋሪዎች ስለመኖራቸው አያውቁም?
የተባረሩ የሉም። ያባረረም የለም።
የእርሶ ቢሮ ሀላፊነቱ ምንድን ነው? አቶ አወቀ፤ የድርጅት ጉዳይ ሲሉ ምንድን ነው የምትሰሩት?
የኦህዲድ የድርጅት ጉዳይ ነው
እና የኦህዲድ ጽህፈት ቤት ይሄን አያውቅም?
የተባረረ ሰው የለም እያልሁህ እኮ ነው፣ በራሳቸው ፍላጎት ሊሄዱ ይችላሉ እንጂ ያባረረ ሰው የልም፡ እያልሁህ እኮ ነው፤ ቄለብ ወለጋ ስትል ከቄለብ ወለጋ የተባረረ ሰው የለም። እንደዞኑ የምናውቀው ነገር የለንም።
ከትናት በስቲያ ማክሰኞ ወደ ኦሮሚያ የመንግስት ኮሚኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮ ደወልሁና የቢሮ ሀላፊዋን ወይዘሮ ራዲያ ኢሳን አገኘሁ። ምንም የምናውቀው ነገር የለም አሉኝ። ዛሬስ ያውቁ እንደሆን ብዬ እንደገና ወደ ወይዘሮ ራዲያ ቢሮ ደወልሁ፣ በቁጥሩ ላይ ነው ያልተስማማነው እንጂ ማወቁን ያውቃሉ።
ሁለት ሺ ሶስት ሺ ተፈናቀለ የምትለው አይደለም
ከነሱ የሰማሁትን ነው
መቶ የማይሞሉ ሰዎች ናቸው
ከሁለት ቦታ ነው የሰማሁት ከግንቢና ከቄለም
አዎ ቄለም ወለጋ አሼ ቀበሌ ነች አይደለ፤
አዎ አሼ ቀበሌ ነው ያሉኝ
የሆነ ወንጀል ተፈጽሞ ነበረ
ማን ነው የፈጸመው?
እንድ ሰው ሞቶ ነበር፤ የኦሮሞ ብሄር ተወላጅ የሆነ ቀጥሎ ደግሞ ሁለት ሰዎች ባልታወቁ ሰዎች ተገለዋል፤ ከፍርሀት ተነስተው ነው እነዚህ ሰዎች ክልል ሶስት የሄዱት፤ መንግስት ..
ከፍርሃት ማልት?
መንግስት፤ ፖሊስ፤ እዚያ ያለው አስተዳደር የሚባለው ስህተት ነው። አሁን እንዲያውም ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ እየተደረገ ነው ያለው
ቁጥሩ አይደለም ወሳኙ፤ ነገር ግን ሰዎቹ ሁለት ሺ ሶስት ሺ ይላሉ፤ እርሶ 100 አይሞላም ይላሉ። ግን በፍርሀት ነው የወጡት የሚሉኝ ለምን ነው የፈሩት?
ነገርሁህ እኮ፤ በዚያ ቀበሌ አካባቢ ወንጀሎች ተፈጽመዋል፡ እንደነገርሁህ ወንጀሉን ይፈጽማሉ ተብሎ የሚገመተው ያው እየተፈለገ ነው።
ሁለት ሰው ወይም ሶስት ሰው ወንጀል ተፈጸመበት ሞተ ብለውኝል፤ መቶ የማይሞሉ ሰዎች ደግሞ ፈርተው ወጡና፣ እነዚህ ሁሉ የሚፈሩበት ምክንያት በመጠርጠር ስማቸው ተነስቶ ነው? ነገሩ ትንሽ የሚየያዝ አልሆነልኝም።
የተጠረጠሩ አይደለም። እኔ እስከማውቀው ድረስ ፍርሀት በቃ፤ አሁን ነገርሁህ እኮ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ አስተዳደሩም እየሰራ ነው፤ ወደ ንብረታቸው እንዲመለሱ ማድረግ ነው።
እነዚህ ከመቶ የማይሞሉ እርሶ እንዳሉት ሲሰደዱ ወይም መፈናቀላቸውን መቼ ነው የእርሶ ቢሮ ያወቀው?
እንደ መንግስት ይሔን ሁለቱም የክልሉ መንግስታት ያውቁታል፤ የምናስተዳድረው ያው አንድ ሀገር ነው፤ ያው ክልሎች እራሳቸውን ያስተዳድሩ እንጂ መናበቡ ነገር አለ።
ይሄ ከሆነ መናበቡ አለ፣ ትናት ስደውል ምንም የምናውቀው የለም ብለውኛል። እና መቼ ነው ያወቁት? የእርሶ ቢሮ ያወቀው
አሁንም አሁንም አንተ የምትለው ከ2000 እስከ 3000 የምትለው አንተ ያነሳህልኝ ቁጥርና እኔ የማውቀው ቁጥር በጣም ስለሚለያይ
ቁጥሩ አይደለም ወሳኙ፤ አንድም ሰው ቢሆን ብዙ አመት ከኖረበት መፈናቀሉ ሊያሳስበን ይገባል ማለቴ ነው። ቁጥሩ አይደለም ወሳኙ፤ አሁን ደግሞ ፌደራል እዚያ ሄዶ እንዲያረጋጋ ተብሏል ተባለ፤ ነገር ግን ፌደራል አልሄደም። እንዲያውም እዚያ ያሉት ሰዎች እንዲወጡ እየተደረገ ነው የሚሉኝ ሰዎቹ።
እንግዲህ እኔ አሁን ያለኝን ትክክለኛ መረጃ ነው እየሰጠሁህ ያለሁት
እሺ
መንግስት እዚያ ያለው አስተዳደር የማረጋጋቱ ስራ ሌሎችም እንዳይፈናቀሉ ማለት የወጡትም ደግሞ እንዲመለሱ አማራ ክልል መንግስት ጋርም እየተናበቡ እየተሰራ ነው።
በጣም አመሰግናለሁ ሰላም ይዋሉ
እሺ
ለመሆኑ የአማራው ክልል ርእሰ መስተዳድር ምን እያደረገ ነው? ወደ አማራው ብሄራዊ ክልል መንግስታዊ ጽህፈት ቤት ደውዬ ፕሬዜዳንቱ የሉም ስለተባለ ወደ ሌላው ከፍተኛ ባለስልጣን ወደ አቶ ሰማ ቢሮ ተመራሁ፤ ከባለጉዳይ ጋር መሆናቸውን የገለጹልኝ ጸሀፊያቸው ወይዘሮ አዝመራ ከ 5 ደቂቃ በሗላ እንድደውል ነገሩኝ፣ ደወልሁ፤ አሁንም ከባለጉዳዩ ጋር እንዳሉ ናቸው ተባለ፤ ከ15 ደቂቃ በሗላ ደውል ተባልሁ፤ ደወልሁ፣ አስቼኳይ ስራ ገጥሟቸው አሁን ከቢሮ ወጡ ተባለ፤ በዚሁ አበቃሁ። በሌላ ጊዜ እንሞክራቸዋለን፤ የተፈናቃዮችን ሁኔታም እንከታተላለን፤ ላሁኑ በዚሁ ላብቃ፣ ሰላም።

Friday, June 27, 2014

በመቀሌ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቃዉሞ ሰላማዊ ሰልፍ ሊደረግ ነው

June 26/2014

ሰኔ ቅዳሜ 21 ቀን ፣ በመቀሌ ከተማ የተቃዉሞ ሰላማዊ ሰልፍ እንደተጠራ፣ የአረና አመራር አባል አቶ አብርሃ ደስታ ገለጹ። ሰልፉ በከተማዋ አስተዳደር እውቅና እንዳገኘ የገለጹት አቶ አብርሃ፣ በባህር ዳር፣ በደሴ፣ በአዲስ አበባ እንዲሁም በሌሎች በርካታ ከተሞች እንደታየው የመቀሌ ሕዝብ የሕወሃት ደጋፊ እንዳልሆነ የሚያሳይበት አጋጣሚ እንደሚሆን አስረድተዋል።
«የትግራይ ህዝብ እስካሁን ድረስ ሰለማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቱ ተነፍጎ ይገኛል። በአላማጣ፣ ኲሓ፣ አይናለም፣ መቐለ (ገፊሕ ገረብ)፣ ሓውዜን፣ ዓዲግራት ወዘተ ዜጎች ሰለማዊ ሰልፍ ለማድረግ መክረው በፌደራል ፖሊስ ተደብድበዋል፣ ታስረዋል፣ ተገርፈዋል፣ ተገድለዋል። ስለዚህ ቅዳሜ ጥዋት ሰለማዊ ሰልፍ የሚጀመርበት ታሪካዊ ቀን ይሆናል። በመቐለ ታሪክ ለመጀመርያ ግዜ የተፈቀደ የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ይደረጋል ማለት ነው» ያሉት አቶ አብርሃ ለሰላማዊ ሰልፍ አስተዳደሩ እውቅና መስጠቱ በራሱ ትልቅ ነገር እንደሆነ ገልጸዋል።
ሰልፉ ቅዳሜ ጥዋት በ3:00 ሰዓት ከአደባባይ ዘስላሴ (ባዛር) ተነስቶ በሓውዜን አደባባይ አልፎ ሮማናት አደባባይ አቋርጦ አብርሃ ካስትል ሆቴል ከደረሰ በኋላ ወደ ናሽናል ሆቴል ታጥፎ በጤና ጣብያ በኩል ላዕለዋይ ፍርድቤት ደርሶ ሮማናት አደባባይ ላይ በ 6፡00 ሰዓት ይጠናቀቃል።
ዉስጡን ዉስጡን ቅስቀሳ የተጀመረ ሲሆን፣ የአደባባይ ቅስቀሳ ነገ አርብ ቀን ሰኔ 20፣ ፖሊሶች ካላስተጓጎሉ እንደሚደረግም ታወቋል።
ከአንድ አመት በፊት በሚሊዮኖች ድምጽ፡ለነጻነት መርህ ሥር በመቀሌ ከተማ የአንድነት ፓርቲ ሰልፍ ጠርቶ እንደነበረ ይታወቃል። በወቅቱ አስተዳደሩ አስፈላጊዉን እውቅና ሰጥቶ ፣ በመቀሌ የአንድነት አባላት በአደባባይ ቅስቀሳ ካደረጉ በኋላ፣ ሰልፉ ነገ ሊደረግ ዛሬ ማታ፣ የአመራር አባላትን በሙሉ እንዲታሰሩና ለሰልፉ የሚያስፈልጉ መሳሪያዎች/መኪናዎች እንዲታገቱ በመደረጋቸው፣ ሰልፉ መስተጓገሉ ይታወቃል።

Thursday, June 26, 2014

የወያኔን የጥፋት ድግስ እናምክን!

June 26/2014
ኢትዮጵያን የሚገዛው ጉጅሌ ሀገራችንን እየወሰደበት ያለው አደገኛ አቅጣጫ አሳሳቢ ከመሆን አልፎ የአደጋውን መራራ ፍሬ ማየት ከጀመርን ሰነበትን። የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ወሳኝ ከሆነው የወደፊቱ የጋራ ጥቅማቸውና ህልውናቸው በበለጠ ልዩነታቸውና ያለፈ ታሪካቸው እንደዋናው ነገር እየተቆጠረ ለሚሰበከው ስብከት የኢትዮጵያ ህዝብ አስተዋይ ባይሆን ኖሮ እስካሁን ብዙ ጥፋት በደረሰ ነበር።
ህወሃት በህዝቡ ውስጥ የኖረውን ልዩነት የጠብ፣ የግጭትና የመፈራራት መሰረት በማድረግ በሥልጣን ላይ ለመቆየት ካለው ምኞት የተነሳ በመደዴ ካድሬዎቹ አማካኝነት ለዘመናት አብሮ የኖረውን ህዝብ በማቃቃር እኩይ ተግባር ላይ ተጠምዶ ይገኛል።
ህወሃት ይህን የማጋጨት ስራ በተለይ በስልጣን የመቆየት ፍርሃት ባባነነው ቁጥር የሚጠቀምበት መሳሪያ አድርጎታል። በባህርዳር ላይ የብሄረሰቦች ኳስ ጭዋታ ውድድር ምክንያት አድርጎ፣ መደዴ ካድሬዎቹን አሰማርቶ ስታዲዮም ውስጥ ኦሮሞዎች እንዲሰደቡ ካደረገ በኋላ ነገሩን ከማረጋጋት ይልቅ በኦሮሞኛ የቴሌቪዥንና ሬድዮ፣ ኦሮሞዎች በአማራዎች ተሰደቡ ብሎ ያስነገረው ለምንድን ነው? ከዚያ በኋላ በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ቁጣና ጠብ ለመቀስቀስ ብሎም በዚህ ጠብ ውስጥ ገላጋይ በመምሰል የአንዱ ብሄር ጠባቂ መስሎ ለመታየት ጉዳዩን ባልተረዱ የዋሆች ውስጥ ለመግባት ይፈልጋል። በአማራ ተወላጆች አካባቢ እኛ ከሌለን ኦሮሞ ይፈጇቹኋል፤ በኦሮምያም በሶማሊያም እንዲሁ በተዘጋ በር ውስጥ በተቃራኒው ዘረኝነትንና መከፋፈልን በመስበክ ንጹሃኑ ህዝብ ከፍርሃት ተነስቶ ተገዥ ደጋፊዎቹ እንዲሆኑ በማድረግ ላይ መሆኑንም ያልገባቸው የዋሆች ይኖራሉ። ህወሃትንና ባህርዩን በቅጡ ለምናውቀው ወገኖች ግን ይህ ተንኮሉ ትልቅ ሚስጥር አይደለም።
የጉጅሌው ቡድን የራሱን ስልጣንና የዝርፊያ ኢኮኖሚ ኮርቻ ለማደላደል እስከረዳው ወይም የሚረዳው መስሎ እስከታየው ድረስ ደሃ ገበሬዎችን ማፋጀትን፣ ህዝብን እርስበርስ ማናከስን፣ የቂም መርዝ መዝራትን የሚያየው እንደ ፖለቲካ ጥበብ ነው።
ጉጅሌው ብልጠት መስሎት የጎሰኝነትንና የማንነትን ደመነፍስ የሚነካ ፕሮፖጋንዳ በህዝቡ ውስጥ በመንዛት ሊያደርስ የፈለገው ጥፋት በአብዛኛው ህዝብ ዘንድ ስላልሰራለት የራሱን ሎሌዎችና ተካፋይ መደዴ ካድሬዎችን በማሰማራት የጭካኔ ስራዎችን በማካሄድ ላይ መሆኑን በብዙ መረጃዎች አረገጋግጠናል። በአሁኑ ወቅት በየቦታው የሚካሄደውን የህዝብ ማፈናቀልና ግጭት የሚመራው ራሱ ህወሃት ያሰማራቸው ካድሬዎች እንጂ በራሱ በህዝቡ ተነሳሽነት እንዳልሆነ ሁላችንም ልናውቅ ይገባል። በዚህ ሳይጣናዊ አካሄድ ለምትደርሰው ለያንዳንዷ ጉዳት ሀላፊነት የሚወስደውም ራሱ ህወሃት መሆኑን ግንቦት 7 አጥብቆ ያምናል።
ህወሃት መቃብር አፋፍ ላይ ሆኖ የሚደግስልንን የጥፋት ድግስ ለማምከን የየብሄረሰቡ ልሂቃን ሁሉ አንድ ላይ ሆነን ህዝባችንን እንድንታደግ ግንቦት 7 ለሁሉም የነጻነት ሃይሎች ጥሪውን ያቀርባል።
ግንቦት 7 በዚህ የህወሃት የጨለማ መንገድ ላይ የሚያበራውን የብርሃን ችቦ ይበልጥ በማብራት ላይ ይገኛል። ሁላችንም በምናገኘው የብርሃን ሃይል ጨለማው ላይ እያበራን ከማሳየት አልፈን ወደ መቃብሩ ልንገፋው ይገባል።
ግንቦት 7 በኢትዮጵያ የማንነትና የብሄር ብሄረሰብ ጉዳዮች በሰለጠነ መንገድ እና በመደማመጥ ሁሉንም ተጠቃሚ በሚያደረግ መንገድ መፍታት እንደሚቻል ያምናል። ይልቁንም የወደፊቱ የህዝባችንና የሀገራችን ጥቅም ይበልጥ የሚከበረው በስብጥርነታችን ላይ በምንገነባው አንድነት መሆኑን ያምናል።
የተከበራችሁ የአገራችን ዜጎች የነጻነታችን ጊዜ ቅርብ ነው። ህወሃት መቃብር አፋፍ ላይ ሆኖ ያዘጋጀልንን የጥፋት ድግስ፣ ሀገራችን የጋራ ጠላት በመጣባት ጊዜ ሁሉ እንደምታደርገው በአንድ ላይ ታግለን የጋራ ታሪክ እንሰራ ዘንድ የዘወትር ጥሪያችን እናቀርባለን።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!

በምስራቅ እዝ የመከላከያ መኮንኖች መካከል ውስጣዊ ውጥረት ሰፍኗል።

June26/2014
ምንሊክ ሳልሳዊ

በወያኔ መኮንኖች እና በኢትዮጵያ የመከላከያ ስራዊት መኮንኖች መካከል በፖለቲካ እና በጥቅማ ጥቅም ጉዳዮች ዙሪያ ውስጥ ውስጡን እየተካረረ የመጣው አተካራ ከባድ ውጥረት መፍጠሩን በእዙ የሚገኙ መኮንኖች የተገኘው መረጃ ጠቁሟል። ሕገመንግስታዊ ጥያቀዎችንእና ወታደራዊ ጥቅማ ጥቅሞችን የሚተይቁ መክንኖች ከየክምፑ ተለቅመው ወደ ሰሜን እዝ እና ወደ ሶማሊያ ከሄደው ጦር ጋር እንዲቀላቀሉ ከተደረገ በኋላ ውጥረቱ እየሰፋ መምጣቱ ታውቋል።

ከዚህ ቀደም የተነሱ ሕገመንግስታዊ ጥያቄዎችን የሕወሓት ከፍተኛ መኮንኖች የጥያቄው ባለመብቶችን ወደ ሌላ አከባቢ በመቀየር የቀሩትንም በጥቅም ለመያዝ ቢሞክሩም ያላዋጣቸው ሲሆን ክመሃል ሃገር ሰልጥነው የተመደቡትም ወታደራዊ ደህንነቶች የአንድ ብሄር አባላት ስለሆኑ የመከላከያ ሰራዊቱ የበታች መኮንኖች በጥርጣሬ ስለሚመለከቷቸው የተላኩበትን ግዳጅ በብቃት መፈጸም ባለመቻላቸው ምንም አይነት ውጤት አለማምታታቸው ችግሩ ዳግም እንዲያገርሽ ሆኗል።

በወታደራዊ ደህንነቶች አማካኝነት እንቆጣጠረዋለን ብለው የምስራቅ እዝ ከፍተኛ የሕወሓት መኮንኖች ያሰቡት ጉዳይ ዳግም ውጥረት መፍጠሩ በድንበሩ አከባቢ ስጋት ስለፈጠረ ወደ አከባቢው አዲስ የመከላከያ ሰራዊት አንድ ሻለቃ ጦር እንዲመደብላቸው ጠይቀዋል።

የምስራቅ እዝ ምኮንኖች አብዛኛው ስራቸው የኮንትሮባድ ተግባራትን መፈጸም መዝረፍ እና ሴቶችን መድፈር መሆኑ ይታወቃል። የሕወሓት መኮንኖች ሌላውን አስፈላጊውን ሕግ የሚፈቅደውን ጥቅማ ጥቅም በመከልከል ከፍተኛ በድል እያደረሱ ሲሆን በሶማሊያ ክልል ውስጥ በዘረጉት ከፍተኛ የቢዝነስ ስራ ውስጥ ማንም ሌላ ሰው እንቅስቃሴ ማድረግ የማይችል ሲሆን እነሱ በሚሰሩ ቢዝነስ ውስጥ የሚገባ ንብረቱ እንደሚወረስ ታውቋል፡፤ የሞባይል ቀፎዎችን እና የኢሌክትሮኒስ ዕቃዎችን በሕገወጥ መንገድ ጭነው ካለፍተሻ ወደ መሃል ህገር በማምጣት በይርጋ ሃይሌ ሕንጻ ካሉ ወኪሎቻቸው ጋር በመተባበር በመላው ሃገሪቱ እንደሚያከፋፍሉ ታውቋል።

እሥረኛው ጠቅላይ ሚንስትር ደሳለኝ ኃይለማርያም በምግብ ራሳችን ችለናል ማለቱ ከምኑ ላይ ነው ስህተቱ?!

June 26, 2014
በጌታቸው ፏፏቴ
መግቢያ፦ ህወሃት/ኢህአዴግ ኢትዮጵያዊ የሆነ አጀንዳ እንደሌለውና ሊኖረውም እንደማይችል ከተቋሙ መሠረታዊ ፕሮግራም በመነሳት ግንቦት 20/1983 በሚል ባቀርብኳት ጦማሬ አስረግጨ አሳውቄ ነበር። እነዚህን የምልበት ምክንያት ከባዶው ተነስቼ ሳይሆን ድርጅቱ ከፈጸማቸውና እየፈጸማቸው ካለው ፀረ-ሕዝብና አሰቃቂ ዘግናኝ ተግባሮቹ በመነሳት እንደሆነ እንዲታወቅልኝ እወዳለሁ።የዚህ ድርጅት መነሻውም ሆነ የመጨረሻ ግቡ ከተቻለ የህወሃት/ኢህአዴግ ትውልዶች ብቻ የሚኖሩባት ኢትዮጵያን መፍጠር አለዚያም ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚያምነውን ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነገድ ተራ በተራ እያዘናጉ መጨረስና አገሪቱንም ለባእዳን እንዳወጣች ሸጦ ኢትዮጵያ የምትባል አገር እንዳልነበረች ማድረግ እንደሆነ ለማንም ስውር ሊሆንበት አይገባም።

ድርጅቱ ቀደም ሲል ጫካ ውስጥ በትግል በነበረበት ወቅትም ሆነ የመንግሥት ሥልጣን ከያዘ በኋላ የፈፀማቸውና እየፈፀማቸው ያሉት አፀያፊ ድርጊቶች ታይተው ያማያውቁ የኢትዮጵያዊነት ሞራልና ስብእና የጎደላቸው ስለመሆናቸው ብዙ የተባለ ሲሆን አንድ ግልጽና ቀላል አስረጅ መጥቀስ የበለጠ እውነታውን ያሳያል ብየ አስባለሁ።

የፌደራል መንግሥት እየተባለ የሚጠራ የይስሙላ መንግሥት ቢኖርም የመንግሥትንም ሆነ የድርጅትን ሥራ ጠቅልሎ የሚያከናውነው ህወሃት/ኢህአዴግ ነው። በግንባሩ ውስጥ የተካተቱት ድርጅቶች የመወሰንና መመሪያ የማውጣት ሥልጣን ባይኖራቸውም በህወሃት በጎ ፈቃድ የሌሎችን ነፃ ተፎካካሪዎች እድል ለመዝጋት የግል ባንኮችን ኮታው እንዲሸፍኑ ተደርጎ በሥራቸው የሚያንቀሳቅሱት ባንክ አላቸው።እነዚህ ባንኮች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ሥራ ከጨዋታ ውጭ ለማድረግ ሆን ብሎ የታቀደ ሲሆን ኢትዮጵያውያን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተበድረው ሊሰሩ ያሰቡትን ተግባር እንዳያከናውኑ የሚያደርግ ተንኮለኛ ሴራ ነው።ከነዚህ ከተጠቀሱት የህወሃት አዳማቂ ድርጅቶች ባንክ ብድር ተበድሮ ኢንቨስት ለማድረግ ቢታሰብ ደግሞ አይሞክሩትም እንጅ የግድ መሟላት ያለበት አንድ ነገር አለ። ይኸውም የህወሃት/ ኢህአዴግን የአባልነት ካርድ መያዝ ይኖርባቸዋል ማለት ነው።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን እንቅስቃሴን ለመግታትና የውጭ ምንዛሬ እንዳያገኝ ከማድረጉ አልፎ ባንኩ ራቁቱን እንዲቀር ያደረጉ ሌሎች የተቀነባበሩ ተንኮለኛ ተግባሮችም ተፈጽመዋል እነሱም ከባለ ሥልጣናቱ ቀጭን ትእዛዝ እየተሰጠ የግንባሩ አባላትና ደጋፊዎች በኢንቨስትመንት ስም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገንዘብ እንዲበደሩ ይደረጋል። ገንዘቡን ወስደው ከተጠቀሙ በኋላ ለባንኩ መክፈል የሚገባቸውን የተጠቀሙበትን የአገልግሎት ዋጋ(interst) መክፈል ይገባቸዋል ነገር ግን ይህ ሊሆን ይቅርና ዋናውን ብድርም አሻፈረን አንከፍልም ብለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኪሳራ እንዲደርስበት አድርገዋል።ይህችን ትንሽ ምሳሌ ያቀረብኩት የሌሎቻችሁንም ስሜት ለመቀስቀስ እንጅ ወንጀሉማ ስፍር ቁጥር የለውም እያልኩ ወደ ተነሳሁበት ነጥብ ልግባ።

አዎ! አቶ ደሳለኝ ኃይለማርያም በግንቦት 20 ንግግሩ ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን መቻሏን ተናግሯል።ንግግሩን ሰምቸዋለሁ።ነገር ግን ስለማን እንደተናገረ ለማወቅ ለኔ ጊዜ አልወሰደብኝም።የኢትዮጵያ እድገትና ብልጽግና ወይም የልማታዊ መንግሥቱ መርህ ህወሃት/ኢህአዴግን፤ የግንባሩ አባላትንና ደጋፊዎችን ብቻ የሚመለከት እንጅ ሌላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚመለከት ጉዳይ አይደለም።ወደፊትም እንዲኖር የሚታሰበው ትውልድም በዚህ ዘረኛ ድርጅት ፕሮግራም ተኮትኩቶ የሚወጣን ትውልድ እንጅ ሌላ ኢትዮጵያዊ ትውልድ እንዲሆን በፍጹም አይታሰብም ይህን ነው ማወቅ ያለብን።

ቀደም ሲል በአንድ ጹሑፌ ላይ ደርግ ከወደቀ በኋላ በሠራዊት ግንባታና አደረጃጀት ጉዳይ ላይ የተፈጸመ አሳዛኝ ድርጊት ጠቅሸ ነበር። ይኸውም ህወሃት አሰልፎት የነበረው ሠራዊት ከፍተኛ ቁጥር የነበረው መሆኑና የአዲሱ የሠራዊት አደረጃጀት ደግሞ ክልሎች ባላቸው የሕዝብ ብዛት ነው ስለሚል የህወሃትን ሠራዊት ላለመበተን ሲባል የተወሰደው እርምጃ አማርኛ የሚችለው የህወሃት ሠራዊት የመከረኛውን አማራ ሕዝብ ኮታ እንዲሸፍን ማድረግ ነበር ። የቀረውን በትግራይ ሕዝብ ባዛት መጠን ማሰለፍና ኢትዮጵያዊነት መንፈስ የተላበሱትን ደግሞ መዳረሻቸውን በማጥፋት ህወሃት ዓላማውን ስኬታማ ለማድረግ ችሏል።አሁን ደግሞ የህወሃት አባላት የኦሮምኛ ቋንቋ እንዲማሩና የኦሮሞውን ክልል በቁጥጥር ሥር ለማዋል የተወሰደውን አቋምና በየዐረብ አገሩ በዐረብኛ ቋንቋ የሰለጠኑ ወጣቶች ለማፍራትና በየኮሚኒቲውና ኤምባሲው ለመሰግሰግና የስለላ ተግባራትን ለማካሄድ ሲባል የሀገሪቱ ሀብት(ገንዘብ)ለዚህ ወጭ መሸፈኛ እየተመዘበረ ያለበት መሠረታዊ ምክንያት (አንድምታው )ህወሃት ወለድ የሆነ አዲስ ትውልድን የመገንባትና
የመትከል አባዜ ነው።

ህወሃት ጫካ ውስጥ በነበረበት ወቅት ወደ ፊት ድርጅቱ ወደየት እንደሚሄድ የሚያሳይ ማኒፌስቶ በ1976 ዓ/ም ማውጣቱ ይታወቃል።ከ1983ዓ/ም ከደርግ መውደቅ በኋላ ግን ህወሃትን እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ድርጅት በመቁጠር ሕዝቡ የተዘናጋበት ጉዳይ ቢኖር የህወሃትን የመጨረሻ ግብ መርሳቱ ነው።ህወሃት ለ23 ዓመታት ያህል በኢትዮጵያ ያደረገው ቆይታ ኢትዮጵያዊ በመሆን ሳይሆን እንደ ጣሊያንና ድርቡሽ(የመሐዲስት) ወራሪ ኃይል በኢትዮጵያ ውስጥ መጥፋት ያለበትን ለማጥፋት ሊዘረፍ የሚችለውን የሀገሪቱ ሀብት ለመዝረፍና ኢትዮጵያን በታትኖ በማጥፋት ለትውልደ ህወሃት የሚሆነውን አዲሱን የህወሃት ሥርዎ መንግሥት ለማመቻቸት ነው።

ከአፋር ጀምሮ የኤርትራን አጎራባች ድንበሮች እያጠቃለለ ከሰሜን ወሎ የማይጨው አውራጃን እንዳለ በመውሰድ ሰሜን ጎንደር ጠልምት ወልቃይት ጠገዴን፤አርማጭሆን እያጠቃለለ መተማን ሙሉ በሙሉ ካርታው ውስጥ ያስገባና ሽንፋና ቋራን ዘልቆ እስከ ጋምቤላና ቤንሻንጉል እየመረሸ ወለጋንም ሸረፍ በማድረግ በመውሰድ ”ታላቋን ትግራይ ሪፐብሊክ” መገንባት ነው።ይህ ተግባር ባሳለፍናቸው የህወሃት 23ዓመታት ሲተገበር ቆይቷል። አሁንም ዋናው ግብ እሱ በመሆኑ ሰላዮችን ካድሬውንና የህወሃትን የመከላከያ ሠራዊት እንዲሁም በውጭ ያደራጁትን የህወሃት አባል “ከሱዳን ተመላሽ ወገን”በማለት እያሰፈሩ ይገኛሉ። እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ሊነሳ ይችላል ይህን መሬት ለሱዳን ሰጥተውት የለም ወይ?የሚል ሊሆን ይችላል።አስቀድሞ ማለቅ ያለበት ተግባር ስለ አለ እንጅ በህወሃት ሰፍሳፋ ተፈጥሮ ይህን የመሰለ ለምና ውሃ ገብ መሬት ለሱዳን? እንዴት ብሎ? ወደ ፊት በሰፊው እናየዋለን።

አቶ ደሳለኝ ኃይለማርያም፦ የኢትዮጵያን ሕዝብ እንደማይወክልና ለኢትዮጵያ ሕዝብ የቆመ አለመሆኑ ግልጽ ቢሆንም ቢያንስ ሲወራ ሊሰማ ይችላል ብየ እገምታለሁ እዛው ከመዲናችን አዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑ በየሆቴሉ የቆሻሻ መጣያ የተጣለ ትራፊ ምግብ ለማግኘት የሚደክሙትን፤በየትምህርት ቤቱ በርሃብ ጠኔ የሚወድቁትንና መማር አልችል ያሉ ወጣቶች በሞሉባት አዲስ አበባ ፤ከሀገሪቱ ሕዝብ 1/3ኛው ቁጥሩ ከ30ሚሊዮን የማያንስ የኢትዮጵያ ሕዝብ በርሃብ አደጋ ላይ ያለ መሆኑን ዓለም አውቆትና የውጭ እርዳታ እየተጠበቀ ባለበት ወቅት «በምግብ ራሳችን ችለናል» ብሎ መናገር ምንያል ቅጥፈት የተሞላበት ንግግር እንደሆነ ለማንም ግልጽ ነው?

አቶ ደሳለኝ ኃይለማርያም፦ ህወሃት/ ኢህአዴግና የፌደራል መንግሥትን ምንነት ገና የገባው አለመሆኑን የሚያመላክቱ ብዙ ነገሮችን ሲናገር ተስተውሏል።ከኤርትራ ጋር ስለሰላም ለመመካከር ዝግጁ መሆኑንና በሌላ ወገን ደግሞ ኤርትራን የአሸባሪዎች ደጋፊ ናት የሚል ክስ መስል ነገር ሲናግርም ተደምጧል ሁለቱ የሚቃረኑ ሃሳቦች መሆናቸውን መመርመር አልቻለም።መራሾቹ ነብሰ ገዳዮች ስብሃት ነጋ ፤ ስዩም መስፍን ፤ አባይ ፀሐየ ፤ አዲሱ ለገሰ ፤ ብረከት ስምኦን ፤ አርከበ እቁባይ ፤ሕላዊ ዮሴፍ፤ታደሰ ካሣ፤ ደብረጽዮንና ቴዎድሮስ አድሃኖም አንብብ ብለው የሚሰጡትን ጹሑፍ ከማንበቡ በፊት ቢያነበው ቢያንስ ለያዘው ሥልጣን የሚመጥን ሀሳብ ባገኘ ነበር ።ነገር ግን ከዚህ በላይ የጠቀስኳቸው የጠቅላይ ሚንስትሩ የካቢኔ አባላትና የጡረታ አማካሪዎቹ እሱን እያጋፈጡ የውስጥ ፍላጎታቸውንና የተነሱበትን ዓላማ እያስፈጸሙ ይገኛሉ። አቶ ደሳለኝ ኃይለማርያም የህወሃት ጠቅላይ ሚንስትር ሁሌ ስለአንተ የሚጻፉ ጹሑፎችን አንብባቸው አንድ ቀን ልብ ትገዛ ይሆናል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ስህተቱ ከምኑ ላይ ነው በሚል ርእስ የገባሁት ስህተት አልተናገረም ለማለት ሳይሆን ጹሑፌ ትኩረት እንድትስብ በማሰብ ነው እንጅ ስህተቱንማ ከቁመቱ በላይ በሚደርስ አዘቅት ተዘፍቆበታል። አቶ ደሳለኝ ኃይለማርያም ወደታች ወርዶ በቀበሌ የሚኖረውን የከተማውንም ሆነ የገጠሩን ነዋሪ ኢትዮጵያዊ የሚያይበት እድል ቢኖረው ምን ሊለን እንደሚችል መገመት አያዳግትም። ዳሩ ግን እሱ ራሱ በግዞት ላይ ያለ እስረኛ ስለሆነ ያሳዝነኛል።

የህወሃት እንባ ጠባቂዎች በትክክል በልተው ያድራሉ ። ምክንያቱም ሕሊናቸውን ለሆዳቸው ሲሉ ሸጠውታልና።አባላቱ ሁሉ በእጃቸው ሁሉ በደጃቸው ስለሆነ ምን አጥተው? እንኳን ሦስት ጊዜ አስር ጊዜስ ቢበሉስ ምን ጎድሎባቸው? እላይ ያለው ቱባ-ቱባ ባለሥልጣን በልቶ ማደር ብቻ ሳይሆን ከሚፈለገው በላይ የጠገቡና የጥጋብ ቁምጣናቸውን በአረቄ ለማወራረድ ሲደፈርሱ የሚያድሩ፤ ሰማይ ውረድ የሚሉ ጥጋበኞች፤ ሰማይ ጠቀስ የሆኑ ፎቆች ያላቸው፤ሀብት ተብሎ የሚቆጠረው ሁሉ የነሱ ያደረጉ፤ መሬትን የነሱ ያደረጉ፤ የበርካታ ሆቴሎች ባለቤት፤ልጆቻቸው ከፍተኛ ወጭ እየተከፈለላቸው ውጭ አገር ተልከው የሚማሩ፤ የፓርቲ ልብስ የሚገዙት ውጭ አገር ነው፤ ጉንፋን በያዛቸው ቁጥር የሚታከሙትም ውጭ አገር በሚገኙ ሆስፒታሎች ነው።ይህ ሁሉ የሚደረገው ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ሀብት እየተዘረፈ ነው።

የአቶ ደሳለኝ ኃይለማርያም የግንቦት 20 ቆርፋዳ ንግግር ቢያንስ የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖሚ ያለበትን ደረጃና ሁኔታ አለማወቅ ራሱን ችሎ ኢትዮጵያ በምን ዓይነት ድናቁርቶች እየተመራች መሆኗን ከማሳየቱም በላይ አምራችና መሬት እንዳይገናኙ የተደረገበትን መሠረታዊ ምክንያት አለማወቁ የግለሰቡን ጥሬነት ያሳያል።ለባዕዳን የተሸጠው መሬት እንዳለ ሆኖ የቀረው መሬት ላይ ኢትዮጵያዊ ኢንቨስተሮችና አርሶ አደሩ ለማምረት እድሉ ቢፈጠርላቸው ኢትዮጵያ ከራሷ አልፎ ሌሎችን የጎረቤት አገሮች ሊመግብ የሚችል ምርት ማምረት ትችል ነበር።

አብዛኛው ከደቡብ እስከ ምዕራብ ያለውን የሀገሪቱን ክፍል ወስደን ብንመለከት ለም ድንግልና የተለያዩ አዝእርቶችን ሊያመርት የሚችል መሬት እንዳለ ይታወቃል።ከደርግ መውደቅ በኋላ ከ1985 እስከ 1987ዓ/ም በነበረው ወቅት የነበረውን የሕዝቡ ተነሳሽነትና በምእራብ ጐንደርና ምእራብ ጐጃም ብቻ የነበረው የምርት ውጤት ሲታይ ተስፋ ሰጭ ነበር። ሁመራና መተማ ተከማችቶ የነበረውን ማሽላ፤ ሰሊጥና ጥጥ ለማጓጓዝ የነበርውን የተሽከርካሪና የመደብር እጥረት አስታውሳለሁ።ያን ተነሳሽነት ግን ገዥዎቻችን ቀልጥፈው አጠፉት። የመሬት መጠቀሚያና የእርሻ ግብር ክፍያውን እላይ ሰቀሉት ኢንቨስተሩም የሥራ ፈቃዱን መመለስ ጀመረ። ህወሃትን እሰየው አሰኘ ታይቶ የነበረው ተስፋ ጨለመ።

አድንቁረህና አስርበህ ግዛው መሆኑንንም አሳዩን።ያን ተስፋ የተጣለበትን የደቡብ ምእራብና ሰሜን ምእራብ መሬትም ለሱዳን አስረክበው ዛሬ የሱዳን ገበሬዎች በህወሃት የመከላከያ ሠራዊት እየታጀቡ አባቶቻችን ደም አፍስሠው አጥንታቸውን ከስክሰው ውድ ሕይወታቸውን ገብረው ያቆዩትን መሬት እያረሱት ይገኛል።አቶ ደሳለኝ ኃይለማርያም ለማወቅ የተሳነው እንዲህ አይነቱን ሀቅ ነው።በዚህ የኢትዮ-ሱዳን ድንበር በቀዳማዊ ኃይለሥላሤ ዘመነ መንግሥት በነበረው ፓርላማ ውስጥ እንስጥ አንስጥ በሚል ሃሳብ ተነስቶ አብዛኛው የፓርላማ አባል ለዚህ ቆላማ መሬት ብለን ወዳጅነትን ከሱዳን ከምናጣ ይውሰዱት ሲል ጥቂት የፓርላማ አባላት በድርጊቱ ተቆጥተው ፓርላማው ውስጥ በወንበር መደባደብ እንደተጀመረና ወዲያውኑ ለሱዳን ይሰጥ የሚለው ውሳኔ ተሽሮ ድንበሩ እስከ አሁን የኛው ዘመን ድረስ በጦር ኃይል ሳይሆን በህዝብ የጎበዝ አለቆችና በራሱ ትጥቅ ተከብሮ የኖረ መሬታችን ነው ዛሬ ለሱዳን የተሰጠው።

አሁን ያለው ፓርላማ ፓርላማ ነው ለማለት እንደማይቻል ይታወቃል።የካድሬ ስብስብና እጅህን አውጣ ሲባል ብቻ እጁን እያወጣ ድምጽ የሚያስቆጥር እንጅ በኢትዮጵያዊነት ስሜትና ወኔ ለሀገር የሚጠቅም ሃሳብ ያመነጫል ተብሎም ተስፋ የሚጣልበት ፓርላማ አይደለም። ለግልጥቅሙና ለሆዱ የተሰለፈውን ህወሃት ከየትም ለቃቅሞ የሰበሰበው ጥርቅም ነው። አንድ ሳይጠቀስ መታለፍ የሌለበት ጉዳይ ግን»- እንደ ሟቹ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ላይ የጥፋት መርዙን የተከለ አልነበረም እሱ ወደ መጨረሻው ከተጓዘ በኋላም ዛሬ እየገዙን ያሉት እኩያን “ በመለስ ራእይ” ስለሆነ እነዚህን ስንኩሎች ነቅለን ካልጣልን እፎይ የምንልበት፤በኢትዮጵያ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚተከልበት፤የሕግ የበላይነት የሚሰፍንበት፤ኢትዮጵያውያን ተፋቅረውና ተከባብረው በጋራ በእኩልነት የሚኖሩባት ኢትዮጵያን ማሰብ አይቻልም።

መፍትሔ አልባ የሚፈጠር ችግር የለም። እኛን ለገጠመን ድቅድቅ የጨለማ ዘመን ደግሞ መፍትሔ አለው ብየ አስባለሁ።”የፀደይ አብዮት”በመባል የሚታወቀው የሕዝብ አመጽ የቱኒዚያን፤የግብጽን፤የየመንን፤የሊቢያን፤የሶርያን አሁን ደግሞ የኢራንን መሬቶች እንዳንቀጠቀጠና እያንቀጠቀጠ እንደሚገኝ ይታወቃል።አዎ! ብዙ መስእዋትነት ተከፍሎበታል ቢከፈልበትም ትርጉም ያለው ውጤት ደግሞ አስገኝቷል።በእኛም አገር ትግሉ አፈና የበዛበት ቢሆንም አላቋረጠም።ዳሩ ግን የተከፈለው መስእዋትነትና የተገኘው ውጤት ሲመዘን ብዙ ጎደሎዎችን አሳይቷል።አንደኛ ትግሉ ከየግል ፍላጎት የሚነሳና የተናጠል መሆኑ ፤ሁለተኛ ሁሉንም የሕ/ሰብ ክፍል በአንድ ጊዜ ያነቃነቀ አለመሆኑ፤ሦስተኛ በሳምንት አንድ ጊዜ ወይም አንድ ቀን ብቻ የሚደረግ ትእይንተ ሕዝብ እንጅ ቀጣይነት የሌለው መሆኑ፤አራተኛ በሕዝብ የሚደረጉት ትእይንተ ሕዝቦች ታክቲክ ለገዥው ቡድን የተጋለጡ መሆናቸው ነው።

የማይሳሳት ቢኖር የማይሰራ ወይም የማይንቀሳቀስ ብቻ ነው።እኛ ኢትዮጵያውያን ህወሃትን ለማስወገድ በተመቸው መንገድ ሁሉ አንድ እርምጃ ወደፊት ተጉዘናል።ስንጓዝ ደግሞ ስህተቶች ተፈጽመዋል ስለሰራን ተሳስተናል ትልቁ ጉዳይ ግን ከስህተት መማርና ከዚያ አደጋ የመውጣቱ ቅልጥፍና ጉዳይ ነው ወሳኙ።አውቀንም ሆነ ሳናውቅ ከችግር ጋር ያጋፈጠንን ህወሃትን ጡንቻው እንዲያብጥና ጠንካራ ጠላታችን እንዲሆን አብቅተነዋል። ምክንያቱም የጠላትን ጠንካራና ደካማ ጎን መገምገም አልቻልንም። የህወሃት ጠንካራ ጎን እርስ በርሳችን እንድንባላ ማድረጉ ሲሆን ይህን አሜን ብለን ተቀብለነዋል።እስከ መቼ? ደካማ ጎኑ ህወሃት የማይወደው “ሕብረት ወይም አንድነት ስንፈጠር ነው”ካልተሳሳትኩ ቁልፉ እዚህ ላይ ነው ያለው።ወደዚህ እንዳንመጣ ያደረገው ደግሞ ከሥልጣን ጥማት ጋር የተያያዘና እኔ ከሁሉም የላቅሁ ነኝ የሚል ኋላ ቀር አስተሳሰብ ነው። በዚህ ላይ የሕዝብን ሉዓላዊነት የሚፈልገውን የመሾም የማይፈልገውን የመሻር ሥልጣኑን የማይቀበል አመለካከት ተሸክመን በመጓዛችን ምክንያት ነው።

ስለዚህ በኢትዮጵያ ሥር ነቀል ለውጥ ለማምጣት ተቻችሎ አንድነትን መገንባት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጎች በመተሳሰብ በፍቅር በጋራና በእኩልነት ለመኖር የሚያስችል ራእይ ይዞ መታገል አግባብ ነው ብየ አስባለሁ።

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላዓለም ትኑር!!!

እያንዳንዳችን ራሳችን ነፃ ለማውጣት እንታገል!!

በቀጣዩ እስከምንገናኝ ለዛሬ ያለኝን እዚህ ላይ ጨረስኩ።

የደመወዝ ጭማሪው የዋጋ ንረት እንደማያስከትል ግልጽ መደረግ አለበት!

June25/2014

የዋጋ ንረትን በተመለከተ ሰሞኑን ሁለት ተቀራራቢ የሆኑ ክስተቶች ተሰምተዋል፡፡ የመጀመሪያው የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለሥልጣን የግንቦት ወር 2006 ዓ.ም. የዋጋ ንረትን በማስመልከት ያወጣው ሪፖርት ሲሆን፣ ሁለተኛው

መንግሥት የዋጋ ንረትን በማይቀሰቅስ ሁኔታ ለመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ለማድረግ መወሰኑ ነው፡፡ ይህ ውሳኔ ለሠራተኛው ሕዝብ መልካም ብሥራት ነው፡፡ ነገር ግን የተጠና መሆን አለበት፡፡

የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለሥልጣን ሪፖርት እንደሚያሳየው በግንቦት ወር የአገሪቱ አጠቃላይ የዋጋ ንረት 8.70 በመቶ በማስመዝገብ፣ በመላ አገሪቱ ባለፉት 15 ወራት የዋጋ ንረቱ በነጠላ አኃዝ እንደቀጠለ ነው፡፡ የዋጋ ንረቱ እ.ኤ.አ. ከማርች 2013 ጀምሮ በነጠላ አኃዝ መቀጠሉን ለመንግሥት እንደ ስኬት እንደሚታይ ሪፖርቱ ያብራራል፡፡ የዋጋ ንረቱ በነጠላ አኃዝ መቀጠሉ አዎንታዊ ገጽታ ነው፡፡

ይሁንና መንግሥት ከሐምሌ ወር ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ እጨምራለሁ ሲል ያቀረበው ታሳቢ ጭማሪው የዋጋ ንረት የማያስከትል መሆኑን ነው፡፡ ጥያቄ የሚነሳውም እዚህ ላይ ነው፡፡ የደመወዝ ጭማሪ ሲደረግ የዋጋ ንረት እንደማይባባስ የሚደረገው ምን ዓይነት ዕርምጃዎችን ወይም መለኪያዎችን በማሰብ ነው? ለመንግሥት ሠራተኞች የሚደረገው የደመወዝ ጭማሪ ኢኮኖሚው ተረጋግቶ መቀጠል በሚችልበት ሁኔታ ተጠንቶ ተግባራዊ እንደሚደረግ መንግሥት መወሰኑ ተገልጿል፡፡ ይህ እንዴት ተግባራዊ ይሆናል የሚለው ጥያቄ ደግሞ መነሳቱ የግድ ነው፡፡

ከዚህ ቀደም በአገሪቱ ተከስቶ የነበረው አጠቃላይ የዋጋ ንረት እስከ 40 በመቶ ደርሶ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ የኅብረተሰቡን ኑሮ በምን ያህል ደረጃ አመሰቃቅሎት እንደነበርም አይዘነጋም፡፡ የዋጋ ንረቱ አሁን በነጠላ አኃዝ ላይ ቢገኝም የዚያን ጊዜው ቁስል እስካሁን ድረስ አልሻረም፡፡ ከመደበኛው የዋጋ ንረት በተጨማሪ ሰው ሠራሽ የሚባለው የዋጋ ንረት በኢትዮጵያ የግብይት ሥርዓት ውስጥ ጉልህ ሥፍራ አለው፡፡ ይህ በዋጋ ግሽበት ጠባቂነት ባህሪ (Inflation Expectation ምክንያትምበገበያው ውስጥ የሚከሰት የዋጋ ንረት በተደጋጋሚ በሕዝቡ ኑሮ ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡

መንግሥት ለሠራተኞቹ ያደረገው የደመወዝ ጭማሪ የዋጋ ንረትን እንደማያባብስ ሲያስታውቅ ለሕዝቡ በግልጽ ማስረዳት አለበት፡፡ ገበያው በጠባቂነት ባህሪ ውስጥ በሚገኝበት በዚህ ጊዜ የደመወዝ ጭማሪም ይባል ማስተካከያ የራሱን ተፅዕኖ ይዞ ይመጣል፡፡ ደመወዝ ተጨመረ ሲባል ምርቶችን ወይም አገልግሎቶችን የሚያቀርቡ ወገኖች (በአቅርቦትና በፍላጎት ላይ ለውጥ ባይኖርም) ገበያ ውስጥ ይመጣል ብለው የሚያስቡትን ለውጥን በማስላት ጭማሪ ያደርጋሉ፡፡ ለምሳሌ የመኖሪያ ቤቶችን የሚያከራዩ ሰዎች በአንድ በኩል ተከራዮቻቸው የደመወዝ ጭማሪ ተደርጎላቸዋል በሚል እሳቤ፣ በሌላ በኩል ደግሞ አጠቃላይ የሸቀጦች ዋጋ መጨመሩ አይቀርም በሚል ግምት የኪራይ ጭማሪ ያደርጋሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ ምንም እንኳን የደመወዝ ማሻሻያው በተጨባጭ በፍላጎትና በአቅርቦት ላይ ይህ ነው የሚባል ለውጥ ባያመጣም፣ ማሻሻያው ግሽበትን ያባብሳል ብለው የሚጠብቁ የገበያ ተዋናዮች ሰው ሠራሽ ግሽበት እንዲቀሰቀስ አደረጉ ማለት ነው፡፡ ገበያው የጠባቂነት ባህሪ ተላብሷል የሚባለው ለዚህ ነው፡፡

የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ተደርጎላቸው መልሰው ለዋጋ ንረት የሚያስረክቡት ከሆነ ጭማሪው ትርጉም አልባ ስለሚሆን፣ መንግሥት በተጨባጭ የዋጋ ንረት እንደማያጋጥም ማረጋገጫ መስጠት አለበት፡፡ አንድ የመንግሥት ሠራተኛ ያገኘው ጭማሪ በሕይወቱ ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ የማያመጣለት ከሆነ ጭማሪው ፋይዳ አይኖረውም፡፡ አረፋ የመጨበጥ ያህል ይሆንበታል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ለውጤታማ ሥራ አገር አቀፍ ዕውቅና መስጠት ተገቢ ነው በማለት የደመወዝ ጭማሪውንና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞችን ሲያበስሩ፣ የመንግሥት ሠራተኞች በሰው ሠራሽ የዋጋ ንረት እንዳይመቱም ማሰብ ይኖርባቸዋል፡፡

ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለሥልጣን ሰሞኑን ባወጣው ሪፖርት የዋጋ ንረቱን ከድርብ አኃዝ ወደ ነጠላ አኃዝ ለማውረድ ከፍተኛ ሥራ መሠራቱን አስታውቋል፡፡ መንግሥት ገበያውን ለማረጋጋት የተለያዩ ዕርምጃዎችን መውሰዱንም አስረድቷል፡፡ ከእነዚህም መካከል እንደ ስንዴና ዘይት የመሳሰሉ ምርቶችን በመደጎም፣ ዱቄትና አንዳንድ እህሎች ላይ የነበረውን ታክስ በመቀነስና በማንሳት፣ እንዲሁም በዋጋ ንረት ላይ ይታይ የነበረውን ፈታኝ ሁኔታ በማርገብ ጥረቶች መደረጋቸውን አመልክቷል፡፡

በእነዚህ ሁሉ ጥረቶች ተገኝቷል የተባለው ተስፋ ሰጪ ባለአንድ አኃዝ የዋጋ ንረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀጠለ መሄድ ሲገባው ወደ ኋላ ከተመለሰ አደጋ አለው፡፡ ገበያው የጠባቂነት ባህሪ ስላለው በደመወዝ ጭማሪው ምክንያት ሰው ሠራሽ የዋጋ ንረት መከሰቱ አይቀርም፡፡ ገንዘብ የያዙ ሰዎች ወደ ገበያው በስፋት በገቡ ቁጥር አቅርቦትና ፍላጎት ስለማይጣጣሙ የዋጋ ንረት ይቀሰቀሳል፣ ገበያውም በዋጋ ንረት ይመታል የሚል የተለመደ እሳቤ ስላላቸው በብዛት ምርቶችን ለመሸመት ሲንቀሳቀሱ ሰው ሠራሽ ጭማሪዎች ይታያሉ፡፡ ይህ ደግሞ የተለመደ የገበያ ባህሪ ነው፡፡

መንግሥት የሚያደርገው የደመወዝ ጭማሪ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ማሰብ ያለበት ይህንን የገበያ የተለመደ ባህሪ ነው፡፡ የደመወዝ ጭማሪው ኢኮኖሚው ተረጋግቶ በሚቀጥልበት ሁኔታ ተጠንቶ ተግባራዊ ይሆናል ሲልም ጥናቱ ምን እንደሆነ ማሳየት ይጠበቅበታል፡፡ ከዚህ ቀደም የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር በማሰብ በተወሰኑ ምርቶች ላይ የዋጋ ጣሪያ ሲቀመጥ የተፈጠረውን ውዝግብና ውጤቱን እናስታውሰዋለን፡፡ በዚያ ውሳኔ ምክንያት የደረሰው ቀውስ እስካሁን ድረስ አሻራው አለ፡፡

ስለዚህ መንግሥት የዋጋ ንረት ሳይባባስና ኢኮኖሚው ተረጋግቶ ይቀጥላል ከሚለው መግጫው ባሻገር የኢኮኖሚ ባለሙያዎችን ምክር እንደ ግብዓት ለመጠቀም ፍላጎቱን ማሳየት አለበት፡፡ የዋጋ ግሽበት ጠባቂነት ባህርይ የተፀናወተው የአገሪቱ የግብይት ሥርዓት ፈር እንዲይዝና የሚደረገው የደመወዝ ጭማሪ ዓላማውን እንዲያሳካ ከተፈለገ፣ መንግሥት የዋጋ ንረት እንደማይከሰት አመላካች ነገሮችንና የፖሊሲ ዕርምጃዎችን ማሳየት የግድ ይለዋል፡፡ የደመወዝ ጭማሪው በዋጋ ንረት የሚመታ ከሆነ ልፋቱ በሙሉ ገደል ይገባል፡፡ በመሆኑም መንግሥት የዋጋ ንረት የማያጋጥም መሆኑን አመላካቾችን የማሳየት ኃላፊነት አለበት!

Wednesday, June 25, 2014

አብዛኛው ህዝብ ለመንግስት ጥላቻ አለው” ሲል አንድ ከኢህአዴግ የወጣ ሰነድ አመለከተ

June25/2014
በአማራ ክልል ለሚገኙ አመራሮችና አባላት የተደረገውን ስልጠና አስመልክቶ ከብአዴን ጽህፈት ቤት በቁጥር ብአዴን 145/10/ኢህ/06 ለኢህአዴግ ጽ/ቤት  አዲስ አበባ በሚል የተጻፈው ደብዳቤ “አብዛኛው ህዝብ አሁንም ለመንግስት ከፍተኛ ጥላቻ” ማሳየቱን ገልጿል።

የብአዴን አመራር እና አባላቱ ከሰላም የዘለለ የልማት ለውጥ አለመምጣቱን፣ ኢህአዴግ ቢቀጥል ባይቀጥል ግድ እንደሌላቸው፣  እንዲሁም መንግስትን በትክክለኛ ዋጋው ሳይሆን በፍርሃት እንደሚያመሰግኑ በሰነዱ ላይ ተዘርዝሮ ቀርቧል።

“የኢትዮጵያ ህዝቦችና አገራዊ ህዳሴያችን” በሚለው የማጠቃለያ ግምገማ ሰልጣኞቹ ” ስለአገራቸው ታሪክ ብዙ ትምህርት መቅሰማቸውን፣ የህዳሴውን ጉዞ ለማሳካት ድርጅቱ እየከፈለ ያለውን መስዋትነት፣ የኢትዮጵያ ገናና ስልጣኔ ለምን እንደወደቀ፣ የህዳሴ ጉዞውን ሊያሳካ የሚችል መንግስት ያለ መሆኑን፣ የብዝህነትና እኩልነት ሀገራዊ ጠቀሜታ ፣ የአማራ ገዢ መደብ ሌሎች ብሄሮችና ብሄረሰቦችን ብቻ ሳይሆን አማራውን ጭምር እንደጨቆነ” የሚያሳይ ትምህርት መውሰዳቸውን ሰነዱ ያመለክታል።
በስልጠናው የብአዴን ታሪክ አብሮ መቅረቡንና ሰልጣኞችም የብአዴንን ታሪክ በማወቃቸው መርካታቸውን ሰነዱ አክሎ ይዘረዝራል።

“ግልጽነት ያልተያዘባቸውና በተግባራዊ እንቅስቃሴ ተከታታይ ውይይትና ስራ የሚጠይቁ ጉዳዮች ምንድን ናቸው?” በሚለው ንጹስ ርእስ ስር ደግሞ ” አሁንም ድረስ ብአዴንን የማይቀበሉ እና ከ97 ጋር በተያያዘ በመንግስት ላይ ተቃውሞ የሚያሰሙ ድምጾች አሉ፣ ነገር ግን የመንግስትን የሃይል እርምጃ ተከትሎ በፍራቻ እንዲኖሩ ማድረግ ተችሎአል።” ሲል አስቀምጧል።
“በውይይቱ ወቅት የታዩ የአመለካከት ችግሮች ምንድን ናቸው?” በሚለው ንዑስ ርዕስ ስር በርካታ ችግሮች ተዘርዝረው ቀርበዋል። ” በ1989 ዓም የነበረው የመሬት ክፍፍል ለቢሮክራቶች ለምን 4 ቃዳ መሬት ተሰጠ? በአማራ ክልል ብቻ የአርሶ አደር መሳሪያ ለምን ተነጠቀ? ልማቱ ወደ ትግራይ ይሄዳል፣ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት አስመራንና አሰብን መያዝ ነበረብን” የሚሉት ጥያቄዎችና አስተያየቶች በሰልጣኞች መቅረቡን ያወሳል።

ሰነዱ በስልጠናው የታዩ ደካማና ጠንካራ ጎኖችንም ይዘረዝራል። ሰልጣኙ እርስ በርስ በመተጋገዝ፣ በመማማር ተሞክሮውን በማካፈልና በመተራረም የነበረው ሁኔታ በሚለው ንጹስ ርእስ ስር ደግሞ ” አሁንም ለመንግስት ህዝቡ በአብዛኛው ጥላቻ ማሳየቱ” የሚል ሰፍሮአል።

የብአዴን አመራርና አባላት ” በአብዛኛው ከሰላም የዘለለ የልማት ለውጥ የለም ” ብለው እንደሚያምኑ፣ “ኢህአዴግ ቢቀጥል ባይቀጥል ደንታ እንደማይሰጣቸው”፣ እንዲሁም “መንግስትን በትክክል ዋጋ ሳይሆን በፍርሃት እንደሚያመሰግኑ” በሰነዱ ማብቂያ ላይ ተገልጿል።

ሰነዱን ለኢሳት የላኩትን የኢህአዴግን ከፍተኛ አመራሮች እንደወትሮው ሁሉ በህዝብ ስም ለማመስገን እንወዳለን።

 ኢሳት ዜና :

‹‹ …ያኔ በምወደው የጋዜጠኝነት ሙያ እየሰራሁ እቀጥላለሁ›› ጀግናው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ (ከቃሊቲ እስር ቤት)

June 25, 2014

በጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ
ቅዳሜ ሰኔ 14 ቀን 2006 ዓ.ም ከታች በፎቶግራፍ የምንታይ [ፎቶግራፉን ያነሳው አብነት ረጋሳን ጨምሮ] fጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በዓለም የጋዜጠኞች እና የዜና አታሚዎች ማኅበር የዓመቱ የወርቅ ብዕር የ “pen Golden of freedom 2014″ ተሻላሚ በመሆኑ ‹‹እንኳን ደስ ያለህ›› ለማለት ኬክ አስጋግረን ወደቃሊቲ አምርተን ነበር፡፡

ቁጥራችን መብዛቱ በቃሊቲ ያሉ ፖሊሶችን ግር ማሰኘቱ አልቀረም ነበር፡፡ ተፈትሸን ስንገባ አንድ የፖሊስ ኃላፊ አስቁመውን ‹‹የመጣችሁበትን ነገር አውቀነዋል፣ ቀለበት ይዛችኋል›› አሉን – ቆጣ በማለት፡፡ እኛ አስክንድር ነጋን እና አንዷለም አራጌን ልንጠይቅ እንደመጣን አስረዳናቸው፡፡ በዕለቱ አንዲት በቃሊቲ የታሰረች ሙስሊም እና በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ታስሮ የሚገኝ ሙስሊም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የጋብቻ ሥነ-ሥርዓት የሚያደርጉበት ፕሮግራም በመኖሩ መረጃው ለፖሊሶች በመድረሱ ነበር ፖሊሱ እኛን እንዲጠየቁ ያስገደዳቸው፡፡ [የሙሽሮቹን ጉዳይ ጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞን በፌስ ቡክ ገጹ ከሁለት ቀን በፊት ጽፎታል]
ገሚሶቻችን እስክንድርን አስጠራን፡፡ የተወሰኑ ደግሞ አንዷለምን በማስጠራት እየተቀያየርን ሁለቱንም ለማነጋገር እንደተለመደው አቅደን ነበር፡፡ ሆኖም ፖሊሶቹ እስክንድርን ያስጠራን ጠያቂዎች ወደ አንድ ጥግ እንድንሆን ነገሩን፡፡ የአንዷለም ደግሞ በአንድ ሌላ ጥግ ላይ እንዲሆኑ ተደረገ፡፡ እስክንድር ተጠርቶ መጣ፡፡ በወቅቱ እስክንደርን ሳየው የ18 ዓመት ወጣት መስሎ ታየኝ፡፡ ጂንስ ሱሪ ከእጅጌ ጉርድ ሸሚዝ ጋር አድርጓል፡፡ ፊቱ ላይ ተፈጥሯዊ ወዙ ያንጸባርቃል፡፡ እውነተኛ ውስጣዊ ፈገግታውን ለሁላችንም ቸረን፡፡ በሽቦ ውስጥ አሳልፍን ጣቶቹን በየተራ ጨበጥናቸውና በዕለቱ ስለተደረገው የአጠያየቅ ሁኔታ ነገርነው፡፡ ‹‹ለምን እንዲህ ይደረጋል? በማለት አጠገቡ የነበረውን ፖሊስ ቆጣ ብሎ ጠየቀው፡፡ ‹‹ሰው ስለበዛ!›› የሚል አጭር ምላሽ ፖሊሱ ሰጠ፡፡ እስክንድር ደጋግሞ ጥያቄውን አቅርቦ ነበር፡፡ ‹‹በቃ የመጠየቂያዋ ጊዜ አጭር በመሆኗ ተወው›› አልኩት፡፡ ‹‹አይ! መሆን የለበትም፣ ኃላፊዎቹን ስመለስ አነጋግራለሁ›› ካለ በኋላ ከጠያቂዎቹ ጋር መጫወት ጀመረ፡፡
እስክንድር አብሮን በነበረበት አጭር ጊዜ ብዙ ጠቃሚ የሆኑ ሃሳቦችን ከሰላማዊ ምክሮች ጋር ለግሶናል፡፡
በመጨረሻም ይህቺን መልዕክት አስተላልፏል፡-
‹ሀገር ስትወረር ወይም ጠላት በሀገር ላይ ጦርነት ሲያውጅ ሁሉም ኢትዮጵዊ በአንድነት ‹‹ሆ!›› በማለት የተቃጣውን ወረራም ሆነ ጦርነት ለመመከት እንደሚንቀሳቀስ ይታወቃል፡፡ ዛሬ ላይ ደግሞ ሁላችንም ዴሞክራሲ ያሻናል፡፡ ሁላችንም ሀገር ሲወረርብን እና ጦርነት ሲታወጅብን በአንድነት እንደምንቆመው ሁሉ ይህንን ያጣነውን ዴሞክራሲ ለመጎናጸፍ፣ ሁላችንም በሰላማዊ መንገድ አጅ ለእጅ ተያይዘን እና አንድ ሆነን መታገል ይኖርብናል፡፡ ከትግሉም በኋላ ለውጥ ይመጣል፡፡ ያኔ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በሀገራችን ስለሚፈጠር ሁሉም በየመንገዱ ይጓዛል፡፡ ለምሳሌ እኔ፣ ምንም የምፈልገው ሥልጣን የለም፡፡ ፍላጎቴም አይደለም! የሕይወት መስመሬ ጋዜጠኝነት ነው፡፡ ያኔ በምወደው የጋዜጠኝነት ሙያ እየሰራሁ እቀጥላለሁ፡፡ የህይወት መስመሩ ፖለቲከኝነት የሆነም ሰው በዚያው ይቀጥላል፡፡ ምሁሩም አካዳሚካዊ ነጻነት ስለሚያገኝ ወደሚወደው የትምህርት፣ የምርምርና ጥናት ዘርፍ ላይ በነጻነት ይሰማራል – ሌላውም በመንገዱ፡፡ ይህ እንዲፈጠር ግን ዛሬ ላይ በጋራ መታገል የግድ ይለናል!››
….‹‹እንኳን ደስ ያለህ›› በማለት ይዘን የሄድነውን ኬክ ሰጠነው፡፡ ሽልማቱ የእኔ ብቻ አይደለም›› በማለት ደስ ብሎት ተቀበሎን በዚያ በሚማርከው ፈገግታው ‹‹ቻው›› ብሎ እጁን በማውለብለብ ተለየን፡፡ አንዷምን መጠየቅ ያልቻልነው ጠያቂዎች ከርቀር ስሙን ጠርተን በእጅ ሰላምታ፣ አክብሮታችንንና ፍቅራችንን ለገስነው፡፡ አንዷለምም በእጆቹ ከንፈሩን እና ልቡን እየነካ ልባዊ ሰላምታውን ሰጠን፡፡ …እኛም ቃሊቲን ተሰናብተን ወጣን፡፡
ለሐሳብ ልዕልና እንኑር!

በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብትን የደፈጠጡ አገር አልባ ናቸው!

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ወንጀል ፍፃሜ መሪ ተዋንያን ሆነው ከቆዩ በኋላበመሰደድ በአሜሪካ እራሳቸውን ደብቀው በተቀመጡ የሰብአዊ መብትደፍጣጮች ላይ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የፍትህ መምሪያ ጥቆማእንዲቀርብለት ኢትዮጵያውያንን/ትን በማበረታታት ላይ ይገኛል፡፡
እነዚህ በሰው ልጆች ላይ ወንጀልን የፈጸሙ ጨካኞች በሰው አገር ሄደው ተደብቀዋል፡፡ እነዚህ ወንጀለኞች በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በበማታለል  ገብተው ለ30 ዓመታት ተደብቀዋል፡፡ እነዚህ በሰው ደም የተዘፈቁ ወንጀለኞች በቀላሉ ሊያዙ በሚችሉበት አገር በመሄድ ለድፍን ሶስት ዓመታት የተደበቁም አሉ ፡፡
እነዚህ የሰብአዊ መብት ደፍጣጭ ወንጀለኞች ከኒዮርክ እስከ ሎስአንጀለስ ባሉ ታላላቅ ከተሞች እራሳቸውን ደብቀው ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል፡፡ እነዚህ የፉኝት ዘሮች ማንም አይነካንም በሚል የእብሪት ስሜት ህዝብ በሚሰበሰብባቸው የአደባባይ ቦታዎች እና በእምነት ተቋማት ሳይቀር ደረታቸውን ገልብጠው ይንፈላሰሳሉ፡፡ በየቡና ቤቶች እና ምግብ ቤቶች ሲወጡ ሲገቡ ይውላሉ፡፡ በጎዳናና በመንደር መንገድ ላይ ይንፏቀቃሉ፡፡ የተማሩም አሉባቸው ያልተማሩም አሉባቸው፡፡ በስልጣን ላይ በነበሩባቸው ጊዚያት የዘረፏቸውን ገንዘቦች በውጭ ባንኮች አጭቀዋል፡፡ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የንግድ ተቋማትን በማንቀሳቀስ ንብረት አፍርተዋል፡፡ ሌሎቹም  ኑሯቸውን ለመምራት እና ዓላማዎቻቸውን ለማሳካት የአገልግሎት ሰራተኞች ሆነው ህይወትን በችግር መግፋት ላይ ይገኛሉ፡፡ ከንጹሀን የግፍ ሰለባዎች ጋር የሞት ዋስትና ተፈራርመዋል፡፡ ንጹሀን ዜጎችን ጨፍጭፈዋል፣ አስጨፍጭፈዋል፣ ረሽነዋል፣ አስረሽነዋል፣ ገድለዋል፣ አስገድለዋል፣ ፈጅተዋል፣ አስፈጅተዋል፡፡
በምርመራ ላለመያዝ የሀሰት ስሞችን በመቀያየር ማንነታቸውን በመደበቅ ሲንገዋለሉ እና ሲንከላወሱ ይውላሉ፡፡ ሲገርፏቸው እና ሲያሰቃዩአቸው በነበሩት የወንጀል ሰለባዎቻቸው እና መብቶቻቸውን በተደፈጠጡት ወገኖች በውል ይታወቃሉ፣ ሆኖም ግን እነዚህ የግፍ ሰለባዎች እነዚህን ጨካኝ አረመኔ ወንጀለኞች ለዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የፍትህ አካላት በምን ዓይነት መንገድ ለህግ እንደሚያቀርቧቸው አያውቁም፡፡ የግፍ ሰለባዎቹ እነዚህን ሲያሰቃዩአቸው የነበሩትን ወንጀለኞች በየቀኑ ባዩ ቁጥር የቅዥት ህይወትን በመምራት ላይ ሲሆኑ በሌላ በኩል ደግሞ ግድያ፣ ማሰቃየት፣ እና ሌሎች በሰው ልጆች ላይ ወንጀል የፈጸሙ ግፈኞች በእነርሱ የእውቀት ደረጃ  ምንም የሚመጣብን ነገር የለም በሚል ትዕቢት በመታበይ በሰላም እና ደህንነታቸው ተጠብቆ እንደሚኖሩ እምነት አድርገዋል፡፡
እነዚህ ግፈኛ አረመኔዎች የሰው ልጆችን ሰብአዊ መብቶች የደፈጠጡ እና በአሁኑ ጊዜ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ እራሳቸውን ደብቀው የሚገኙ የቀድሞው የኢትዮጵያ የደርግ ወታደራዊ አምባገነን መንግስት ከፍተኛ እና ዝቅተኛ ባለስልጣናት ናቸው፡፡
እነዚህ ግፈኛ አረመኔዎች የሰው ልጆችን ሰብአዊ መብቶች የደፈጠጡ እና በአሁኑ ጊዜ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ እራሳቸውን ደብቀው የሚገኙ የህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ህወሐት) እና እራሱ ቀፍቅፎ የፈጠረው የይስሙላው እራሱን “የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሚክራሲያዊ ግንባር” እያለ የሚጠራው ቡድን ከፍተኛ እና ዝቅተኛ ባለስልጣናት ናቸው፡፡
እነዚህ  የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች በለመደው አጭበርባሪ አንደበታቸው የአሜሪካንን የጥገኝነት እና ዜግነት መስሪያ ቤት ተቋም ስርዓትን በማታለል የአሜሪካንን የኗሪነት ወይም የዜግነት ፈቃድ ያገኙ ናቸው፡፡
እነዚህ  ወንጀለኞች የገዳይ እና አስገዳይነት ወንጀላቸው ተረስቶ ምንም ነገር እንደማያመጣባቸው በማሰብ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በምቾት እና በተድላ መኖር እንደሚችሉ እምነት አላቸው፡፡
እነዚህግፈኞችለአሜሪካፍርድቤቶችለፍትህለፍርድ  መቅረብአለባቸው!
እነዚህ በአሜሪካ አገር እራሳቸውን ደብቀው የሚገኙ  በሰው ልጆች ላይ ወንጀልን የፈጸሙ የኢትዮጵያ ግፈኞች አንዳንድ ጊዜ ወንጀል ከፈጸሙባቸው የግፍ ሰለባዎቻቸው ጋር በአጋጣሚ ይገናኛሉ፡፡ እ.ኤ.አ ሜይ 2011 ከፈለኝ ዓለሙ ወርቁ (ተለዋዋጭ ስም የሚጠቀም ፣ ሀብታብ በርሄ ተማኑ፣ “ቱፋ“፣ ከፈለኝ ዓለሙ) የተባለው ጨፍጫፊ ወንጀለኛ ኢትዮጵያ በነበረበት ወቅት ሲያሰቃያቸው ከነበሩት የግፍ ሰለባዎች መካከል ከአንደኛው ጋር ዴንቨር ኮሎራዶ ከተማ ፊት ለፊት ተገናኙ፡፡ ከፈለኝ ወርቁ እ.ኤ.አ በጁላይ 2004  ሀብታብ በርሄ  ተማኑ በሚል የሀሰት መታወቂያ በመጠቀም ነው ስደተኛ በመምሰል ወደ አሜሪካ የገባው፡፡ እ.ኤ.አ በ1970ዎቹ መጨረሻ አካባቢ እራሱን “ደርግ“ እያለ የሚጠራ ጨካኝ አረመኔ ወታደራዊ አምባገነን መንግስት በኢትዮጵያ ከህግ አግባብ ውጭ ንጹሀን ዜጎችን የሚገድል እና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን የሚያሰቃይ “ቀይ ሽብር” የተባለ ዘመቻ አወጀ፡፡ በዚያን ጊዜ ከፈለኝ ዓለሙ ወርቁ  የእስር ቤት የጥበቃ አባል ነበር፡፡ እ.ኤ.አ  በ1978 ሳሙኤል ከተማ የተባሉ የፖለቲካ እስረኛ አብረዋቸው የነበሩትን እስረኞች ይህ ወርቁ የተባለ ጨፍጫፊ ሲያሰቃይ እና ሲገድል የነበረ መሆኑን የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ1977 አበበች ደምሴ የምትባል የ16 ዓመት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የነበረች እስረኛ “ወርቁ እየተኮሰ ሰዎች ገና አካለ መጠን ያልደረሰ ልጅን ጨምሮ ሲገድል አይቻለሁ“ የሚል የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ ወርቁ  “በወለሉ ላይ የፈሰሰውን የሟቾቹን ደም በተገኘው ሁሉ በምላሳችንም ጭምር እንድናጸዳው“ ለሌሎቻችን እስረኞች ትዕዛዝ ሰጥቷል ብለዋል፡፡ ወርቁ በአበበች ጭንቅላት ላይም ኤኬ – 47 አውቶማቲክ ጠብመንጃ አነጣጥሮ የነበረ ቢሆንም በእግዚአብሔር ታምር ህይወታቸው የተረፈ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
እንደ ፍርደ ቤቶች ዘገባ ከሆነ እ.ኤ.አ በ2013 ወርቁ  በህገወጥ መልክ ዜግነትን በመግዛት ወይም በማግኘት፣ ማንነትን በመደበቅ ወንጀል፣ በማጭበርበር እና ህገወጥ ቪዛ በመውሰድ እና በመጠቀም፣ እንዲሁም ሌሎች የተጭበረበሩ ሰነዶችን በማቅረብ የሚሉ የተለያዩ ክሶች ቀርበውበታል፡፡ በዩናይትድ ስቴትስ የወረዳ ፍርድ በ5 ቀናት የፍርድ ቀጠሮ ሂደት እ.ኤ.አ ሜይ 23/2014 በዋለው ችሎት ወርቁ በሁሉም ክሶችጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ 22 ዓመታት እስር እንዲቀጣ ተበይኖበታል፡፡ በአጠቃላይ  ከዜግነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ መልኩ ለሚሰሩ ወንጀሎች በፌዴራል እስር ቤት ከ18 ወራት በላይ የእስራት ብይን አይሰጥም፡፡ ሆኖም ግን ብይኑን የሰጡት ዳኛ የዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል  ዳኛ ጆን. ኤል. ካኔ የወርቁ የጥፋተኝነት ወንጀል በጣም አስደንጋጭ እና ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡ ዳኛ ካኔ እንዲህ በማለት ገለጻ አድርገዋል፣ “ይህችአሜሪካ አገር የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች መጠለያ ዋሻ የመሆን አደጋ ጋር በተያያዘ መልኩ ከፍተኛው የእስር ብይን መሰጠቱ ተገቢ ነው“ ብለዋል፡፡
ከፈለኝ ዓለሙ ወርቁ  የፍርድ ሂደት ጉዳይ ይዘውት የነበሩት የዩናይትድ ስቴትስ ፌዴራል  ጠበቃ ጆን ዋልሽ እንዲህ በማለት አውጀዋል፣ “የእኛ የፍትህ ስርዓት በአንድ ወቅት አሸባሪው ወንጀለኛ ተከላካይ  ሲያሸብረው ከነበረው ስደተኛ ማህበረሰብ ላይ በተሳካ ሁኔታ እንዲወገድ አድርጓል፣ እናም ይህንን በማድረግ የእኛን ህጎች ብቻ አይደለም ከጥፈተኝነት ነጻ ያደረግነው ሆኖም ግን እዚህ እኛ አገር ውስጥ እየኖሩ ያሉትን የተከላካዩን የግፍ ሰለባዎች መብት ማስከበር ጭምር እንጅ፡፡“ በአሁኑ ጊዜ ፍትህ ተረጋግጧል/ሰፍኗል፡፡ የወንጀሉ ተከላካይ የሆነው ከፈለኝ ዓለሙ ወርቁ  ለሰራው ወንጀል ከፍተኛ የሆነውን የእስር ብይን በመወሰን “ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የኗሪነት እና የጥገኝነት ህጓን በማጭበርበር ከለላ ለማግኘት ከውጭ ሲገድሉ እና ሲያሰቃዩ ቆይተው ወደ አሜሪካ ለሚመጡት ወንጀለኞች በሰላም ለመኖር መደበቂያ ዋሻ አትሆንም” በማለት ዳኛ ጆን ካኔ ጠንካራ የሆነ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ባለፈው ሳምንት በስደት በአሜሪካ አገር የሚኖረው የኢትዮጵያ ታዋቂው የምርመራ ጋዜጠኛ አበበ ገላው አንድ ቴዎድሮስ ባህሩ የሚባል “የኢትዮጵያ ሰይጣናዊ አቃቤ ህግ የነበረ“ (አሜሪካ ሊታይ በሚችል ቦታ ላይ እራሱን ደብቆ) አግኝቷል፡፡ ቴዎድሮስ ባህሩ ሲልቨር ስፕሪንግ ሜሪላንድ   በሚባል ቦታ ኗሪ የሆነውን  “በሰላማዊ አመጸኞች፣ በነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች እና በተቃዋሚ የፖለቲካ አባላት ላይ የጸረ- ሽብር አዋጅ እየተባለ የሚጠራውን የንጹሀን ዜጎች ማጥቂያ መሳሪያ በማድረግ ፍትሀዊ ያልሆነ እና ከህግ አግባብ ውጭ የዘፈቀደ እስራት ላይ የሙሉ ፈቃደኝነት ተዋናይ ሆኖ በመስራት “ በሚል ክስ አበበ ገላው መስርቶበታል፡፡ እንደ አበበ ገለጻ ከሆነ ባህሩ “ወንጀላቸው የህወሐትን ሙስና እና አምባገነናዊ አገዛዝ መቃወማቸው ብቻ በሆኑት ንጹሀን ዜጎች ላይ ለቁጥር የሚያዳግቱ የፍብረካ የአገር ክህደት እና የሽብር ወንጀል ክሶችን በመዘርዘር ዜጎች ያለስራቸው በሀሰት አንዲሰቃዩ እና ስብዕናቸውም እንዲገፈፍ በማድረግ ታላቅ ወንጀል ሰርቷል የሚል ነው፡፡“
አበበ ውንጀላውን እንዲህ በማለት አቅርቦታል፣ “ቴዎድሮስ ባህሩ ከህወሐት (በኢትዮጵያ የገዥው አካል ፓርቲ) ዓቃብያነ ህጎች መካከል አንዱ ሲሆን በፖለቲካ እስረኞች ላይ ማለትም በእነ እስክንድር ነጋ፣ አንዷለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንን፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ ውብሸት ታዬ፣ በቀለ ገርባ፣ ኦልባና ሌሊሳ፣ በሙስሊሙ ማህበረሰብ መሪዎች ላይ እና ጆሀን ፔርሰን እና ማርቲን ሽብዬ በተባሉ ሁለት የስዊድን ጋዜጠኞች ላይ የሽብር ክሶችን እንዲፈበርክ ሰልጥኖ እና ተቀጥሮ በወሰደው ስልጠና መሰረት ሲያስፈጽም የቆየ“ ተጠርጣሪ ነው የሚል ነው፡፡ አበበ በመቀጠልም “ባህሩ የዩናይትድ ስቴትስ ዜግነት ያገኙትን እና ሌሎችንም ንጹሀን ዜጎች ማለትም ኦባንግ ሜቶን፣ ኒያሚን ዘለቀ፣ ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ፣ ኤፍሬም ማዴቦ፣ ፋሲል የኔዓለም፣ መስፍን ነጋሽ እና አብይ ተክለማርያምን በሽብርተኝነት ክስ እንዲመሰረትባቸው አድርጓል“ ብሏል፡፡
በኤሌክትሮኒክ በተደረገ ግንኙነት ባህሩ ለአበበ እንዲህ የሚል መልዕክት አስተላልፏል፣ በሀሰት የተፈረከውን የእስክንድር ነጋን እና የሌሎችን ከላይ የተጠቀሱትን ተከላካዮች ሳቀርብ “ስራዬ ትዕዛዞችን ብቻ መቀበል ነበር“፡፡ በሚያስገርም ሁኔታ ቴዎድሮስ ባህሩ የናዚ የሰብአዊ መብት ደፍጣጭ ወንጀለኞች “በኑርምበርጉ የጦር ፍርድ ቤት” ቀርበው በተጠየቁበት ጊዜ ያነሱትን መከላከያ ሀሳብ እንዳለ ደግሞታል፡፡ በዚያን ወቅት አዶልፍ ኤክማን የተባለው ወንጀለኛ በጦር ፍርድ ቤቱ የፍርድ ሂደት እየተካሄደ ለጥያቄ በቀረበበት ጊዜ እንዲህ የሚል የምስክርነት ቃል ሰጥቶ ነበር፣ “እራሴን ለስልጣን ስራዎቼ ለቢሮዬ ቃልኪዳን ታማኝ ሆኘ እራሴን ማስገዛቴ እና ታዛዥ ሆኘ በማስፈጸሜ ጥፋተኛ ነኝ፡፡ አይሁዶችን ሆን ብዬ በማጥቃት እና በስሜታዊነት እንዲገደሉ አላደረግሁም፡፡ ያንን ያደረገው መንግስት ነው፡፡“ ከዚህ ጋር በተመሳሰለ መልኩ ቴዎድሮስ ባህሩም ለስልጣን ስራው ሲል ንጹሀን ዜጎችን አልነካሁም ነው የሚለው፡፡ትእዛዝ ብቻ ነው የተቀበልኩት ::  ለዚህ በሸፍጥ ለተሞላው የወንበዴ ቡድን ታማኝ ሎሌ እና አገልጋይ በመሆን ለሰራቸው ጥፋቶች ሁሉ ኃላፊነት የለኝም ነው የሚለው፡፡ እስክንድር ነጋን፣ ርዕዮት ዓለሙን፣ ውብሸት ታዬን ወይም ሌሎች በደርዘን የሚቆጠሩ ንጹሀን ዜጎችን “ሆን ብሎ እና በስሜታዊነት” አላጠቃሁም፣ ያንን የፈጸመው መንግስት ነው ይላል ቴዎድሮስ ባህሩ ፡፡     
ሰርካለም ፋሲል በቴዎድሮስ ባህሩ ላይ የመሰረተቻቸው ክሶች፣
የህወሐት ገዥ አካል እርሷን እና ባለቤቷን እስክንድር ነጋን ወደ እስር ቤት እስከወረወረበት ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት ጋዜጠኛ እና አሳታሚ ሆና ስትሰራ በቆየችው ሰርካለም ፋሲል በቴዎድሮስ ባህሩ ላይ በጣም ጠንካራና ማስረጃ የሞላው ክስ አቅረባለች፡፡ ሁለቱም ሰርካለም እና እስክንድር (በአሁኑ ጊዜ በሀሰት የሸፍጥ ክስ ተመስርቶበት የ18 ዓመታት እስራት ተበይኖበት ከመሀል ከተማ በጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ በሚገኘው በታዋቂው የ “መለስ ዜናዊ የቃሊ እስር ቤት”በመማቀቅ ላይ ያለው) በዘመናዊ የአፍሪካ የነጻ ጋዜጠኞች ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በገዥው አካል ጥቃት የተፈጸመባቸው እና ከፍተኛ የሆነ ዓለም አቀፋዊ አድናቆትን ያገኙ ሰላማዊ ጋዜጠኞች እስክንድርና ሰርካለም ናቸው፡፡ ባለፉት ሶስት ዓመታት ውሰጥ እስክንድር እያንዳንዱን ታዋቂ እና ታላላቅ ዓለም አቀፋዊ የፕሬስ ሽልማቶች  አሸናፊ ነበር ::  ከሁለት ሳምንታት በፊት በተወካዩ አማካይነት የተቀበለውን የ2014 ወርቃማ የብዕር የነጻነት ሽልማት ጨምሮ በዓለም ታዋቂና ተወዳጅ ተሸላሚ ሆኗል፡፡ ሰርካለምም እንደዚሁ “ዓለም አቀፍ የሴቶች ሜዲያ ፋውንዴሽን” ከተባለው ዓለም አቀፍ የፕሬስ ድርጅት አደጋ ተደቅኖ ባለበት ሁኔታ የተለዬ ጀግንነትን ለሚያሳዩ ጋዜጠኞች ”ለደፋር ጋዜጠኝነት ሽልማት“ የሚለውን ጨምሮ በርካታ ዓለም አቀፍ የፕሬስ ሽልማቶችን አግኝታለች፡፡
በተቀዳ የድምጽ/ኦዲዮ ቃለ መጠይቅ ሰርካለም ቴዎድሮስ ባህሩ በቀላሉ “ትዕዛዝን ብቻ በመቀበል” የሰራ አይደለም፡፡ ይልቁንም ከፍርድ ቤቶች ውጭ ወደ እስር ቤት እንዲገባ እና እንዲወጣ ትዕዛዝ ከሚሰጡት ሰዎች አንዱ ነበር ብላለች፡፡ ሰርካለም በተጨባጭ እንዳስቀመጠችው ባህሩ ባለቤቷን የገዥውን አካል ትዕዛዝ ተቀብሎ ከመተግበርም ባሻገር “ሆን ብሎ እና ስሜታዊነት በተሞላበት ሁኔታ” ሲያሰቃየው እንደደነበረ ገልጻለች፡፡ እንደ ሰርካለም አባባል ከሆነ ባህሩ ቁጡ፣ ጨካኝ፣ ችግር ፈጣሪ፣ ምህረት የለሽ እና ሩህሩህነት የማይሰማው አረመኔ አቃቤ ህግ ነበር ብላለች፡፡ እንደ ባለሙያ ዓቃቤ ህግ የሚገባውን ህጋዊ ስርዓት ተከትሎ  የሚሰራ ሳይሆን እንደ ፖለቲካ አቃቤ ህግ ተከላካዮችን ያድን ነበር፡፡ ባህሩ ተከላካዮችን አሳንሶ ለማሳየት በፍርድ ቤቱ ችሎት ፊት ሁሉንም አጋጣሚዎች ሁሉ ያደርግ ነበር፡፡ ተከላካዮች ምንም ዓይነት ወንጀል ያልሰሩ ነጻ መሆናቸውን ሊያስረዱ የሚችሉ ሰነዶችን እና ምስክሮችን በሚያቀርቡበት ጊዜ ሁሉ እነዚህን በሚያስተባብል መልኩ ተቃውሞዎችን እያቀረበ ይከላከል ነበር፡፡ ተከላካዮች ፍትሀዊ ብይን እንዳያገኙ እና ማለቂያ በሌለው ረዥም ቀጠሮ እየተመላለሱ እንዲጉላሉ በማሰብ እንዲሁም የፍርድ ሂደቱን ስርዓት በማጣመም ከፍትህ አካላት የአሰራር መርህ ውጭ በሆነ መልኩ ፍትህን ሲያዛበ ነበር፡፡ የጥፋተኝነት ውሳኔ ለማሰጠት በማሰብ የተፈበረኩ እና የሀሰት ማስረጃዎችን ያቀርብ ነበር ብላለች፡፡
ሰርካለም በተለየ መልኩ ቴዎድሮስ ባህሩ በእራሱ አቅም እና እንደ መንግስት ዓቃቤ ህግ እያወቀ ሆን ብሎ እና የያዘውን ስልጣን ለእኩይ ተግባር በማዋል በእርሷና በባሌቤቷ የክስ ሂደት ላይ የህግ የበላይነትን ሲያጣምም ቆይቷል በማለት ውንጀላ አቅርባበታለች፡፡ እ.ኤ.አ በ2011 ባህሩ በባለቤቷ ላይ መሰረተ ቢስ ክስ በመመስረት፣ የሀሰት ማስረጃ እና የሀሰት ምስክር በማቅረብ እውነታውን እያወቀ ሆን ብሎ ሲያጣምም ነበር በማለት ወንጅላዋለች፡፡ ሰርካለም ውንጀላዋን በመቀጠል ባህሩ እስክንድርን የግንቦት ሰባት ድርጅት አመራራ በመሆን ወጣቶችን እየመለመለ ለሽብር ጥቃት ሲዳርግ ነበር ብላለች፡፡ ባህሩ ይህንን ውንጀላ ለማስተባበል የሚያስችል ምንም ዓይነት ማስረጃ ለማቅረብ አልቻለም፡፡ ሆኖም ግን  የሸፍጥ ስራውን ለማከናወን ከዳኞች ጋር የሸፍጥ ዱለታ በማካሄድ ጥፋተኛ እንዲባል አስደርጓል፡፡ ሰርካለም ባህሩ እና ብርሀኑ ወንድምአገኝ የተባሉ ሁለት ዓቃብያነ ህጎች በግል የቤተሰቦቿን ንብረቶች፣ ቤቶቻቸውን፣ መኪኖቻቸውን እና ሌሎችን የግል መጠቀሚያ ቁሳቁሶችን ጨምሮ ከህግ አግባብ ውጭ እንዲነጠቁ በማድረጉ ሂደት ላይ ተባባሪ ነበሩ በማለት ውንጀላ አቅርባባቸዋለች፡፡ ባህሩ እያወቀ ስልጣኑን ከህግ አግባብ ውጭ በመጠቀም ሆን ብሎ እና ሌሎችን የኢትዮጵያን የነጻውን ፕሬስ ጋዜጠኞች ለማጥቃት እንደ ሰርካለም አባባል ዓለም አቀፍ የፕሬስ አሸናፊ ተሸላሚ የሆኑትን እነ ርዕዮት ዓለሙ፣ ውብሸት ታዬ እና ሌሎችም ፍትሀዊ ዳኝነት እንዳያገኙ በማድረግ ደባ ፈጽሟል ብላለች፡፡
ሰርካለም በቴዎድሮስ ባህሩ ላይ ያቀረበችው ውንጀላ በተለይም የህግ የበላይነትን ከማስጠበቅ አኳያ እና የመንግስት ዓቃብያነ ህጎች ንጹሀን ዜጎች የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ሰለባ እንዳይሆኑ በመከላከል ሂደት ላይ የሚጫወቱትን ቁልፍ ሚና በሚመለከት በርካታ የህግ ጥያቄዎች እንዲነሱ አድርገዋል፡፡ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ህግ ዓቃብያነ ህጎች የሰብአዊ መብት ጥበቃ ንቁ ተከላካይ መሆን እንዳለባቸው እና የአገር እና ዓለም አቀፍ ህጎች ታማኝነት እና የሰብአዊ መብት መርሆዎች በከፍተኛ ደረጃ መጠበቅ እንዳለባቸው ይጠይቃል፡፡ ዓቃብያነ ህጎች ለፍትሀዊ ዳኝነት ሂደት እና ለፖለቲካ ዓላማ ሲባል ኃላፊነቶቻቸውን በአግባቡ ሳይወጡ የሚቀሩ ቢሆን የህግ የበላይነት መርሆዎችን ብቻ አይደለም እየጣሱ ያሉት፣ ሆኖም ግን ቆመንለታል የሚሉትን የፍትህን ጠቅላላ መጨንገፍ የሚያመላክት ስለሆነ የእነርሱ መኖር በእጅጉ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡
ሁለቱም ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ እና ዓለም አቀፍ የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ስምምነቶች/ሲፖመስ (ዩናይትድ ስቴትስ ሲፖመስን በኢትዮጵያ ህገመንግስት አንቀጽ 13(1)) ላይ የተቀመጠውን “እያንዳንዱ ሰው በነጻ እና ገለልተኛ በሆነ የፍትህ አካል ችሎት ፍትህን የማግኘት እና የመደመጥ መብት እንዳለው እና ማንኛውም በግለሰቦች ላይ የሚመሰረትን የወንጀል ክስ ለመከላክል መብት እንዳለው የሚደነግገውን እና እ.ኤ.አ በ1992 ያጸደቀችውን፣(ሰፖመስ በአንቀጽ 14፡ የአፍሪካ ቻርተር ሰዎች እና በህዝቦች መብቶች (አቻሰህመ) ከአንቀጽ 6-8 የተዘረዘሩትን መመልከት ይቻላል)፡፡ የሮማ ዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይሲሲ) የወንጀለኞች ፍትህ የማግኘት መብት መርሆዎችን በግልጽ ያስቀምጣል (ከአንቀጽ 22-33) እና የፍትሀዊ ዳኝነት (ከአንቀጽ 62 – 67) በግልጽ ተመልክቷል፡፡ ለሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ሰላባዎች ካሳ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ህግ እና ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ህግ መጣስን አስመልክቶ (በተባበሩት መንግስታት የጠቅላላው ጉባኤ የዴሴምበር 16/2005 ጉባኤ ውሳኔ ቁጥር 60/147) እንደሚገልጸው መንግስታት በሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ወንጀል ፈጽመዋል በሚል የተጠረጠሩትን እና ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶችን ጥሰዋል የሚባሉትን መብት ደፍጣጮች የመዳኘት ኃላፊነት እንዳለባቸው በግልጽ ተደንግጓል፡፡“
በሰው ልጆች ላይ ወንጀልን ፈጽመው በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ተደብቀውበሚገኙ የኢትዮጵያ ወንጀለኞች ላይ ጥቆማ እንዲደረግ የቀረበ ጥሪ፣
እ.ኤ.አ ጃንዋሪ 2012 “የአፍሪካ አምባገነኖች፡ የትም ሮጠው ሊያመልጡ አይችሉም፣ የትም ተደብቀው ሊያመልጡ አይችሉም!“ በሚል ያቀረብኩት ፅሁፍ  በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶችን ደፍጥጠው ወደ ውጭ በመኮብለል በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ እየኖሩ የሚገኙትን መብት ደፍጣጮች አሳድዶ በማደን ስማቸውን እና ያሉበትን ልዩ ቦታ ለአሜሪካ ባለስልጣኖች ጥቆማ በመስጠት የዜግነት ግዴታዎቻችሁን እንድትወጡ እና የወገኖቻችሁ ደም ደመከልብ ሆኖ እንዳይቀር የሚል ጥሪ አስተላልፌ ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ እየተጠናከሩ በመጡት ምርመራዎች እና የሰብአዊ መብቶችን በመደፍጠጥ ወደ አሜሪካ በማታለል እና በህገወጥ መልክ የገቡትን ወንጀለኞች አሳድዶ በመያዝ በተለይም ለአሜሪካ ባለስልጣኖች ለህግ ማቅረብ በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡ እነዚህን የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ለዜግነት እና ለጉምሩክ አስፋጻሚ ፣ ለአገር ውስጥ ደህንነት ጉዳይ ፣ ለሰብአዊ መብት ደፍጣጮች እና ለጦር ወንጀለኞች ቡድኖች እና ለብሄራዊ ደህንነት የምርመራ ክፍል  መ/ቤቶች መጠቆም ትችላላችሁ፡፡ ያሜሪካ መንግስት የጦር ወንጀለኞች፣ የዘር ማጥፋት ወንጀለኞች፣ የአሰቃዮች እና ሌሎች በዓለም ላይ ግጭትን ሊያመጡ የሚችሉ የሰብአዊ መብቶች  ደፍጣጮች ኮሚሽን መደበቂያ ገነት እንዳትሆን ለመከላከል ጠንካራ ምርመራዎችን ያደርጋል፡፡ የውጭ ተጠርጣሪ የጦር ወንጀለኞች፣ አሰቃዮች እና የሰብአዊ መብት ድፍጣጮች ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የግዛት ክልል ውስጥ መኖራቸው በሚታወቅበት ጊዜ  የምርመራ ቡድን ሙሉ የህግ ኃይሉን እና ስልጣኑን በመጠቀም ለማጣራት፣ ለመዳኘት እና በሚቻልት ሁኔታ ሁሉ እንደዚህ ያሉ ሰብአዊ መብት ደፍጣጮችን ከአሜሪካ ለማስወገድ ጥረት ያደርጋል፡፡
ባለፉት አስርት ዓመታት ያሜሪካ መንግስት በመቶዎች በሚቆጠሩ ከሰብአዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ መልኩ በወንጀለኛ እና/ወይም ስደተኞች ምርመራ ላይ ስኬታማ ሆኗል፡፡ የዚህ ቡድን የዳታ መሰረት በርካታ የታወቁ ተጠርጣሪ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮችን ስም ዝርዝር አካትቶ ይዟል፡፡ የዳታ ቋቱ የታወቁ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ለማድረግ ጠቃሚ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ዜጉአ ወደ100 አካባቢ ከሚሆኑ ከተለያዩ አገሮች የመጡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ላይ ክትትል በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ባለፉት ስምንት ዓመታት በመቶዎች የሚቆጠሩ ከሰብአዊ መብት ድፍጣጮች እና ከተለያዩ የወንጀለኛ እና/ወይም ከስደተኝነት ጋር በተያያዘ መልኩ በቁጥጥር ስር አውሎ ሌሎች በመቶዎች የሚቆጠሩትን ታዋቂ ወይም ተጠርጣሪ ግለሰቦችን ደግሞ ከዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በማስወጣት ወደ አገራቸው እንዲጋዙ አድርጓል፡፡
በሰው ልጆች ላይ ወንጀልን የፈጸሙ እና በአሜሪካ እየኖሩ ያሉ የኢትዮጵያወንጀለኞች ለምርመራ ለዜጉአ ሰመደጦወቡ ጥቆማ መቅረብ ይኖርባቸዋል፣
በኢትዮጵያ በሰው ልጆች ላይ የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣዎች እና የጦር ወንጀሎች መረጃዎች በተሟላ ሁኔታ ተተንትነው እና ተጠቃለው ተዘጋጅተው ተይዘዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2007 በኢትዮጵያ ያለው የህወሐት ገዥ አካል አጣሪ ኮሚሽን ባቀረበው ዘገባ መሰረት የ2005 ድህረ ምርጫ ውዝግብን ተከትሎ በአገሪቱ ውስጥ ከህግ አግባብ ውጭ በዘፈቀደ 193 ሰላማዊ ዜጎች የተገደሉ፣ ሌሎች 763 ሰዎች ቁስለኛ እና ሌሎች ወደ 30 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ከህግ አግባብ ውጭ ለዘፈቀደ እስራት የተዳረጉ መሆናቸውን በተጨባጭ መረጃ አስደግፎ አቅርቧል፡፡ በዚህ የወንጀል ድርጊት ውስጥ ተዋንያን የነበሩ 237 ግለሰቦች ታውቀዋል፣ እንዲሁም ከዚሁ ጋር ንክኪ ያላቸው ተጠርጣሪዎች ተለይተዋል፡፡ እ.ኤ.አ ዴሴምበር 2003 በኢትዮጵያ በጋምቤላ 424 ንጹሀን ዜጎች ከህግ አግባብ ውጭ በዘፈቀደ ለህወሐት ታማኝ በሆኑ የደህንነት ኃይሎች ተገድለዋል፡፡ በኦጋዴን ላይ በሚደረገው ጭቆና እ.ኤ.አ በ2008 ሂዩማን ራይትስ ዎች ባወጣው ዘገባ መሰረት “150 የተገደሉ ግለሰቦች“ እና ሌሎች 37 ተጨማሪ ሰላማዊ ዜጎች በጦር ወንጀለኝነት ተጠያቂ በሚሆኑ በኢትዮጵያ ወታደሮች ትዕዛዝ እና ተሳታፊነት  በተደረገ ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ስም ዝርዝር ተመዝግቦ ተይዟል፡፡ ይህንን የጦር ወንጀል የሚያወቁት ወይም ደግሞ እንደዚህ ያለ ወንጀል እንደሚፈጸም ማወቅ ያለባቸው ሆኖም ግን ምንም ዓይነት እርምጃ ያልወሰዱ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እና የሲቪል ባለስልጣኖች እንደ ትዕዛዝ ሰጭነታቸው በወንጀሉ ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ የተስፋፋው እና ስልታዊ በሆነ መልክ በሶማሊ ክልል በእያንዳንዱ መንደር ላይ እየተካሄደ ያለው ከህግ አግባብ ውጭ በዘፈቀደ የሚደረገው ግድያ፣ ማሰቃየት፣ አስገድዶ መድፈር፣ እና አፍኖ መሰወር በስልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ ገዥ አካል የመጨረሻውን ተጠያቂነት ሊወስድ የሚችልባቸው እና ሊጠየቅባቸው የሚችሉ በሰው ልጆች ላይ እየፈጸማቸው ያሉ ወንጀሎች ጠንካራ ማስረጃዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ከብዙው በጥቂቱ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ተደብቀው በሚገኙ የኢትዮጵያ ወንጀለኞች ላይጥቆማ ለማድረግ ለምን ተነሳሽነት ማሳየት እንዳለብን፣
ምናልባትም ባለፉት በርካታ ዓመታት በኢትዮጵያውያን/ት ዘንድ በተደጋጋሚነት ሲቀርቡልኝ ከነበሩት ጥያቄዎች ውስጥ “እኔ እንደ ግለሰብ በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ መብት ለማሻሻል ምን ማድረግ እችላለሁ?“ የሚሉ ነበሩ፡፡
በርካታ ኢትዮጵያውያን/ት በተለይም የዲያስፖራው ማህበረሰብ በግለሰቦች አቅመቢስነት ተስፋ እየቆረጡ የመጡ ይመስላል፡፡ በተቃዋሚ የፖለቲካ ቡድኖች መካካል የሚታዩትን የአንድነት መላላት በመመልከት እና መቋጫ በሌለው መልኩ እየተሰነጣጠቁ ሲፈረካከሱ በማየታቸው በሀዘን በመሞላት ከዳር ቆመው በመመልከት ላይ ይገኛሉ፡፡
ባለፈው ሳምንት በኮካ ኮላ ኩባንያ እና በሚያመርታቸው 114 ምርቶቹ ላይእንዳንጠቀም የሚቀሰቅስ ጥሪ አቅርቤ ነበር፡፡ ኮካ ኮላ 32 የዓለም ለዓለም እግርኳስ የመክፈቻ ስነስርዓት ማድመቂያ የሚሆን ምርጥ አገራዊ ሙዚቃቸውንእንዲያቀርብ 32 ታዋቂ ሙዚቀኞች ጋብዞ ከእነዚህ ውስጥ 31ዱን በመምረጥ ሲለቅቅ አንዱን ብቻ ነጥሎ በማውጣት የኢትዮጵያውን ወደ ጎን አሽቀንጥሮበመጣሉ ኮካ ኮላን ገሀነብ ግባ!!!” በማለት እቅጩን ነግሬዋለሁ፡፡ በምንምዓይነት መልኩ የኮካ ኮላን ምርት አልገዛም፣ በፍጹም አልጠቀምም፣ እንዲሁምሌሎች የኮካ ኮላን ምርት እንዲገዙ ወይም እንዲጠቀሙ አላበረታታም፡፡ግለሰቦች በተናጠል እና እንዲሁም በጋራ በሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎችያለምንም ጥርጥር ለውጥ ያመጣሉ፡፡ ኮካ በጭራሽ በፊቴ አይዞርም!
ባለፈው ሳምንት በኮካ ኮላ ምርት ላይ ላለመጠቀም የሚቀሰቅሰው ጥሪ መተላለፉን ተከትሎ በእስፔን አገር ከፍተኛ የሆነ የኮካ ኮላ ምርት ሽያጭ ቅነሳ ተስተውሏል፡፡ በእስፔን የኮካ ኮላ ምርት ሽያጭ በግማሽ ቀንሷል ምክንያቱም የእስፔን ህዝብ የኮካ ኮላ ኩባንያን ገሀነም እንዲገባ ስለነገረው ነው!!!
(በኢትዮጵያ ኮካ ኮላን ባለመጠቀም ጸጥ በማለት ውጤታማ እንቅስቃሴዎች እየታዩ መሆኑን ተጨባጭ መረጃዎች ያመላክታሉ)፡፡
እስፔኖች ኮካ ኮላን  አሽቀንጥረው  ከጣሉት  ኢትዮጵያውን/ትስ  ምን ይሳናቸዋል?
ኢትዮጵያውያን/ት የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ለአሜሪካ የዜጎች እና ጉምሩክ አስፈጻሚ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች እና የጦር ወንጀለኞች ቡድን ለምን መጠቆም እንዳለባቸው በማስረጃ እና በመረጃ የተደገፉ በርካታ ምክንቶች አሉ፡፡
1ኛ) በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ወንጀል ሰርተው በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ሄደው ተደብቀው የሚኖሩትን መጠቆም በምንም ዓይነት ሊታለፍ የማይችል በቀጥታ የጥቃቱ ሰለባ የሆነው የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ/ት ወይም ደግሞ በሌሎች ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመ ለመሆኑ እውቀቱ ያለው የሞራል ሰብዕና ተግባር በመሆኑ ነው፡፡ በሰው ልጆች ላይ እንደዚህ ያለ ወንጅልን የሚፈጽሙ ወንጀለኞች መጋለጥ እና ከአሜሪካ ህብረተሰብ መካከል መወገድ ይኖርባቸዋል፡፡
2ኛ) በእነዚህ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ላይ ጥቆማ ማካሄድ በኢትዮጵያ በስልጣን ወንበር ላይ ተጣብቀው ላሉት ባለስልጣኖች አሜሪካ የሰብአዊ መብትን እየደፈጠጡ ለሚመጡ ወሮበላ ወንጀለኞች የሀሰት እና የተጭበረበረ የጥገኝነት ቪዛ እያመጡ በሰላም ለመኖር አሜሪካ በተጨባጭ መደበቂያ ገነት የማትሆን መሆኗን የሚገልጽ ጠንካራ መልዕክት ያስተላልፋል፡፡ እነዚህ ወንጀለኞች አሜሪካ ቢገቡ እንኳ ወደ እስር ቤት እንደሚጋዙ ዝግጅት ማድረግ አለባቸው ምክንያቱም ለፖሊስ ጥቆማ በማቅረብ ለፍትህ ይቀርባሉ፡፡
3ኛ) በዚህ ጥቆማ ላይ የሚደረግ ሰፊ የሆነ ተሳትፎ ኢትዮዮጵያ በስልጣን ላይ ላሉት የገዥው አካል አባላት አስቀያሚ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈጽመው ወደ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በመሄድ አሜሪካንን የሚረግጡ ከሆነ በአሜሪካ ባንኮች የደለበውን የባንክ ሂሳቦቻቸውን ብቻ አይደለም የሚያጡት፣ ሆኖም ግን የእራሳቸውን ነጻነትም እንደሚያጡ ጠንካራ የሆነ መልዕክት ያስተላልፋል፡፡ የመጨረሻዎቹን ቀናት በአሜሪካ እስር ቤቶች ሊያሳልፉ እንደሚችሉ ዝግጅት ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
4ኛ) የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች አሜሪካ የእነርሱ መደበቂያ ገነት ዋሻ እንደማትሆን እሰካመኑ ድረስ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሰብአዊ መብቶችን ጥሰት ከመፈጸም እኩይ ተግባራት ይታቀባሉ፡፡ ሁሉም የገዥው አካል አመራር አባላት በሚባል መልኩ እና የእነርሱ ታማኝ ሎሌዎች በአሁኑ ጊዜ ነገሮች በዚህ ሁኔታ የሚቀጥሉ ከሆነ እና በኢትዮጵያ ለውጥ ከመጣ ወደ አሜሪካ የሚያደርጉትን የፍርጠጣ ጉዞ በመሰረዝ ወደ ሌላ አዲስ ቦታ ጉዞ እንደሚያርጉ ይታመናል፡፡ እንደገና ቢያስቡ የተሻለ ይሆናል!
በኢትዮጵያ ወንጀል ፈጽመው ወደ አሜሪካ በመሄድ ተደብቀው የሚኖሩወንጀለኞች እንዳሉ እያወቁ አለመጠቆም እና ለፍትህ እንዲቀርቡ አለማድረግእና እንዲኖሩም መፍቀድ በእራሱ ወንጀል ነው፡፡ ወንጀል ከተሰራ በኋላለወንጀለኞች ተባባሪ መሆን ወንጀል ከመስራት ጋር እኩል ነው፡፡ እነዚህ በሰው ልጆች ላይ ወንጀልን ፈጽመው በአሜሪካን አገር ተደብቀው የሚገኙ ወንጀለኞች ፍትህ እንደዘገዬ ባቡር መሆኑን ሊገነዘቡ ይገባል፡፡
የጥቃት ሰለባዎች ለጥቂት ጊዜ መታገስ ይኖርባቸዋል፣ ሆኖም ግን በመጨረሻው ሰዓት ፍትህ በሙሉ ኃይሉ ታጅቦ ይመጣል፡፡ እ.ኤ.አ ሜይ 23/2014 ከፈለኝ ዓለሙ ወርቁ የተማረው ይህንን ሀቅ ነው፡፡ ያ በአሜሪካ ግልጽ ተደብቆ እየኖረ ያለው እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ/ት የሰብአዊ መብት ደፍጣጭ በየዕለቱ ሊማርበት የሚገባ አብይ ትምህርት ነው፡፡ ያ ሁኔታ አሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብትን እየደፈጠጡ ያሉ እና አሜሪካ ሄዶ ከመደበቅ ይልቅ ወደ ሌላ አዲስ ቦታ ለመሸሽ ዕቅድ የሚያወጡት ወንጀለኞች ሊማሩበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡
ለሁሉም  ኢትዮጵያውያን/  የሚሆን  ፍትህ  ትምሀርት
ባለፈው ሳምንት በፊላደልፊያ ግዛት ለ65 ዓመታት ከኖረ በኋላ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የናዚ የእስር  ቤት  ጥበቃ አባል በመሆን በታዋቂው አውሽውዝ   እየተባለ ይጠራ በነበረው የጦር ካምፕ እና በሌሎች ቦታዎች ላይ በሰራው ወንጀል በጦር ወንጀለኛነት በመጠርጠር ጆሀን ብሪየር የተባለው የ89 ዓመት አዛውንት ወንጀለኛ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡  ብሪየር እ.ኤ.አ 1952 ወደ አሜሪካ በመሄድ ተፈናቃይነት በሚል ምክንያት ዜግነትን ጠይቋል፡፡ ይህ ወንጀለኛ 1.1 ሚሊዮን ወንዶች፣ ሴቶች እና ልጆች ያለቁበትን ወንጀል ተሳታፊ ነበር ፡፡ የጀርመን ባለስልጣኖች ከ216, 000 በላይ የሚሆኑ የአውሮፓ አይሆዶችን በመግደል በሚል በጥፋተኝነት በመንጀል በሪየር ላይ ክስ መስርተዋል፡፡
ከፈለኝ ዓለሙ ወርቁ የናዚ እስር ቤት የጥበቃ አባል የነበረው ጆሀን ሪየር ከሰራው ወንጀል በምንም ዓይነት መንገድ አይለይም፡፡ ከፈለኝ ዓለሙ ወርቁ የደርግ ወታደራዊ አምባገነን መንግስት የእስር ቤት ጥበቃ አባል ነበር፡፡ እንደ ብሪየር ሁሉ ወርቁም የሰብአዊ መብት እልቂትን ፈጽሟል ወይም ደግሞ ያልተነገረ የሰብአዊ መብት ደፍጣጭ ነው፡፡ በማሰቃየት እና በመግደል በርካታዎቹን የግፍ ሰለባ አድርጓል፡፡  እንደ ሪየር ሁሉ ወርቁ በዩናይትድ ስቴትስ ጥገኝነት በጠየቀበት ጊዜ የእራሱን ማንነት እና ጥፋተኝነት ለመደበቅ እንዲሁም በቀይ ሽብር በተካሄደው እልቂት የእራሱን ሚና አሳንሶ ለማቅረብ ጥረት አድርጓል፡፡ ወርቁ እንደ ሪየር ሁሉ ከፍትህ ለማምለጥ ሙከራ አድርጓል፣ ሆኖም ግን እንደ ሪየር ሳይሆን ፍትህ በ10 ዓመታት የጊዜ ገደብ ውስጥ አሳድዳ ያዘችው፡፡
እውነታው ሲገመገም ግን በአሜሪካ የሚኖሩት የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች በደርግ ወታደራዊ አምባገነን መንግስት የቆሸሸ ስራ የሰሩት ብቻ አይደሉም፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ሌሎች በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል የህወሐት ወይም ተባባሪዎቻቸው በርካቶች አባላት ተመሳሳይ የሰብአዊ መብት ደፍጠጣ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡ ሁሉም በተጠናከረ ጥቆማ እና ምርመራ እየተለቀሙ ለፍርድ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
የስድስት ዓመትም ይሁን የስድሳ አምስት ዓመታት እነዚህ የህወሐትም ይሁኑየደርግ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ለፍትህ መቅረብ አለባቸው፡፡
በፍትህ ላይ የሚሰናሰል ምንም ዓይነት ነገር እንደሌለ ሊገነዘቡ ይገባል! በእነዚህ በመሀከላችን በነጻነት በሚኖሩ ወንጀለኞች ላይ የሚደረግ ልዩነት ማብቃት አለበት!
ሁሉንም ኢትዮጵያውያንን እና ኢትዮጵያውያትን አንድ ቀላል የሆነ ጥያቄ ላቀርብላቸው እወዳለሁ፡፡ ይህም የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የፍትህ መምሪያ በሰው ልጆች ላይ ወንጀልን ሰርተው በአሜሪካ አገር እራሳቸውን ደብቀው የሚኖሩ ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን ለህግ ለማቅረብ ጥረት እያደረገ ባለበት ሁኔታ ኢትዮጵያውያን/ት እነዚህን በደም የተጨማለቁ ወንጀለኞች ከእያሉበት በመጠቆም ለምርመራ መምሪያው ተባባሪ መሆን ሊበዛብን ይችላልን?
እራሳቸውን በአሜካ ደብቀው የሚኖሩ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮችን እየጠቆሙ ማሳወቅ ቀላል ነገር ነው፣ ጥቆማ በምታደርጉበት ጊዜ ስማችሁን መስጠትአይጠበቅባችሁም፡፡
በሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ወይም በሰብአዊ መብት ረገጣ ወይም በጦር ወንጀለኝነት በሚጠረጠሩ በውጭ ዜጎች ላይ ማስረጃ ወይም መረጃ ካላችሁ ICE HISየስልክ ቁጥር 1-866- 347- 2423 በመጠቀም እና online tip form ያጠናቅቁ፡፡
ጥቆማ በምታካሂዱበት ጊዜ ስም መስጠት አስፋለጊ አይደለም!
በሰብአዊ መብት ደፍጣጮች እና የጦር ወንጀለኞች ቡድን ያላችሁን ማስረጃ እና መረጃ በኢሜል አድራሻ VRV.ICE@ice.dhs,gov ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡
ለሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ሰለባዎች እገዛ አለ፡፡ ለICE confidential victim/witness hotline toll free number at 1-866- 872- 4973 ጥሪ ያድርጉ፡፡
“ዩናይትድ ስቴትስ የእራሷን ሰላማዊ የዜግነት መብት ህጎቿ አታላዮች እና አጭበርባሪዎች ተበውዘው ከውጭ የሚመጡ ገዳዮች እና አሰቃዮች መደበቂያ ዋሻ አትሆንም“ (የዩናይትድ  ስቴትስ  ፌደራል  ጠበቃ ጆን ዋልሽ)
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ሰኔ 17 ቀን 2006 ዓ.ም