Wednesday, June 11, 2014

የፌስ ቡክ ላይ ተሳዳቢዎች (ናይ ፌስቡክ ተፃረፍቲ)

June 11/2014
በታደሰ ብሩ
መንደርደሪያ
ፌስ ቡክ ላይ ህወሓትን (ወያኔን) የሚተች ጽሁፍ ሲወጣ ስድቦችን “በብርሃን ፍጥነት” የሚያዥጎደጉዱ ሃያ ያህል ሠራተኞች ሬድዋን ሁሴን  ቢሮ ውስጥ መኖራቸውን ሰምቼ ነበር። ይህ ራሱ እየደነቀኝ እያለ ሰሞኑን ሌሎች ዜናዎች ተከታትለው መጡ።
Facebook Tplf
በፌስ ቡክና መሰል ማኅበራዊ ሚዲያዎች ለሚቀርቡበት ትችቶች ፈጣን የስድብ ምላሽ የሚሰጡለት 235 “ባለሙያ ተሳዳቢዎችን” ኢህአዴግ አሠልጥኖ ማስመረቁ ከግንቦት 27 ቀን 2006 ዓም የኢሳት ዜና ሰማሁ።  ዜናው እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ኢሳት በነበረው መረጃ  ሰልጣኞቹ 2, 350 የፊስ ቡክ፣ የቲውተር እና የብሎግ አካውንቶችን ከፍተዋል።
የኢሳት ዜና ከተሰማ ጥቂት ቀናት ቆይታ በኋላ ደግሞ 300 ብሎገሮች ለተመሳሳይ ተግባር  በባህር ዳር ሠልጥነው የመመረቃቸውን ዜና ሴቭ አዲና የተባለው የፌስ ቡክ ባልደረባዬ አጋራን።  እሱ ባለው መረጃ መሠረት ደግሞ  ሠልጣኞች 3 000 የፌስ ቡክ አካውንቶች ከፍተዋል።
ህወሓት ይህን ልምድ ከየት አመጣው? ይህ ነገር የት ያደርሰናል? ለዚህ ምላሻችን ምን መሆን ይኖርበታል? ይህ አጭር ጽሁፍ እነዚህ ጥያቄዎች ለመመለስ የሚያገለግሉ ውይይቶችን ለመቀስቀሻነት የሚረዱ ሀሳቦችን ይወረውራል።
 የቻይና 50 ሣንቲም ፓርቲ
china
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በኦክቶበር 2004 አንድ የቻይና የክልል የሕዝብ አስተዳደር ቢሮ በማኅበራዊ ሚዲያ የደረሰበት ወቀሳ ለመቋቋም ከመንግሥት ጎን ወግነው የአፀፋ አስተያየቶችን የሚጽፉ ሠራተኞችን ቀጠረ። ይህም የተቀጣሪ የማኅበራዊ ሚዲያ ተሳዳቢዎች ጅማሮ ሆነ። በአስተዳደሩ ላይ ወቀሳ ያቀርቡ የነበሩ ሰዎች በተራ ስድቦች ተሸማቀው ዝም ማለታቸውን የተመለከቱ ሌሎች የአስተዳደር ቢሮዎችን ይህ ልምድ ለእነሱም እንደሚጠቅም አስተዋሉ።
በ2005 (በእኛ አቆጣጠር 1997) የቻይና የትምህርት ሚኒስትር የኮሌጅ ጋዜጦችን ስልታዊ በሆነ መንገድ እንዲዘጉ አደረገ። ለምሳሌ ናንጅንግ ዩኒቨርስቲ ያትመው የነበረውን “Little Lily” የተባለው ተወዳጅ ጋዜጣ ታገደ። ተማሪዎች ተቃውሟቸውን በማኅበራዊ ሚዲያዎች መግለጽ ጀመሩ። የዩኒቨርስቲዎች አስተዳዳሪዎች ካድሬ ተማሪዎችን እየፈለጉ አልያም ለገንዘብ ሲሉ የታዘዙትን ለመፈፀም ፈቃደኛ የሆኑ ተማሪዎችን እየመለመሉ በትርፍ ጊዜ ሠራተኝነት ቀጥሯቸው። የእነዚህ ቅጠረኞች ሥራ በማኅበራዊ ሚዲያ ዩኒቨስቲውን በመደገፍ ነፃ ህሊና ያላቸው ተማሪዎችን መፋለም ሆነ። እዚህም በስድቦችና ማስፈራሪያዎች ብዛት የተቃውሞ ድምጾችን ማዳከም ቻሉ።  ከዚህ “ድል” በኋላ እያዳንዱ የትምህርት ተቋም የየራሱን ተሳዳቢ ቡድን ማደራጀት ጀመረ። የተቋም ስምን በተሳዳቢዎች መጠበቅ ራሱን የቻለ የሥራ  ዘርፍ ሆነ።
በጃንዋሪ 2007 የቻይናው መሪ ሁ ጂንታኦ የቻንናን መልካም ገጽታ ለመገንባት “ጥራት ያላቸው በየድረገጹ አስተያየት ሰጭ ጓዶች” የመኖራቸው አስፈላጊነት ከተናገሩ በኋላ ይኸ “ሥራ” አገር አቀፍ እውቅና አገኘ። ከዚያ ወዲህ የቻይና የባህል ሚኒስትር የማኅበራዊ ሚዲያ “ኮሜንት” አድራጊዎችን በቋሚነት ማሰልጠንና ማሠማራት ጀመረ። በአሁኑ ሰዓት 300 000 የሚሆኑ “ኮሜንት አድራጊዎች” በቻይና የባህል ሚኒስትር  ሥር እየሠሩ ይገኛሉ።
ከጥቂት “ከፍተኛ ካድሬ ተሳዳቢዎች” በስተቀር አብዛኛዎቹ ተቀጣሪዎች የሚከፈላቸው በሥራቸው መጠን ነው – ማለትም በፃፉት አሸማቃቂ ኮመንት ብዛት ነው። ታሪፉም ለአንድ ኮሜንት ግማሽ የን ነው። በዚህም ምክንያት ተረበኛው ሕዝብ የ50 ሳንቲም ፓርቲ (The 50 Cent Party) የሚል የወል መጠሪያ ሰጣቸው።
የቻይና የስድብ እድገት መዘዝ
አብዛኛዎቹ የ50 ሣንቲም ፓርቲ አባላት ክፍያቸው የሚታሰበው በኮመንት ብዛት ነው። በዚህም ምክንያት መንግሥትን የሚተቹ ጽሁፎች እንደወጡ በፍጥነት ይረባረባሉ። በአጭር ጊዜ ብዙ 50 ሳንቲሞን “ለመሸቀል” እንዲያመቻቸው አጫጭር አሸማቃቂ ስብዶችን ዘርዝረው ይዘው እንዳመጣላቸው ኮፒ ፔስት ማድረግ ልማዳቸው ሆነ። በዚህም ምክንያት አብዛኛውን ግዜ በጽሁፉ ይዘት እና በባላ 50 ሣንቲሙ ኮሜንት መካከል ምንም ዝምድና የለም። ስድቦቻቸውም የተለመዱ ናቸው “ባለጌ”፣ “ከሃዲ”፣ “የታይዋን አሽከር”፣ “የታይዋን ተላላኪ” የታይዋን ሰላይ” የሚሉ እና የመሳሰሉ ስድቦች የተለመዱ ሆኑ።  ባለ50 ሣንቲሞች የቻይናን ማኅበራዊ ሚዲያ አቆሸሹት።
ይህ ደግሞ በበርካታ ምክንያቶች እንደገና መንግሥትን የሚያሳስብ ጉዳይ ሆነ።
ሀ)    “የ50 ሣንቲም ፓርቲ” የሚለው መጠሪያ በሰፊው ከተሰራጨ በኋላ ኮሜንቶቹ ማሸማቀቃቸው ቀረ። እንዲያውም የሶሻል ሚዲያ ፀሀፊዎች መሸማቀቃቸው ቀርቶ  በ50 ሣንቲሞች ስድቦች መዝናናት  ጀመሩ፣
ለ)    “የ50 ሣንቲም ፓርቲ አባል” መሆን ራሱ የሚያሸማቅቅ ነገር ሆነ፣
ሐ)   የታይዋን ስም በመጥፎም ቢሆን ደጋግሞ በተነሳ ቁጥር ታይዋንን የሚያስተዋወቅ፣ ቻይናዊያን የታይዋን ሥርዓት ናፋቂዎች እንዲሆኑ የሚያደርግ ነገር ሆነ፣
መ)   የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ከቻይና የልማት አቅጣጫዎች አንዱ ሆኖ እያለ የድረገጾችና የማኅበራዊ ሚዲያዎች መንግሥት በከፈለባቸው ስድቦች መቆሸሻቸው በረዥም ጊዜ የቻይናን ቢዝነስ እንደሚጎዳ ተረዱ።
በዚህም ምክንያት ለ50 ሣንቲም ፓርቲ አባላት ተግባር የሥነምግባር ደንብ ይውጣለት ተብሎ የሚከተሉትን ነጥቦች የያዘ ደንብ ወጣ። ይህ የስልጠና ሰነድ አፈልትልኮ ወጥቶ ተሰራጭቷል። ይዘቱም በአጭሩ የሚከተለው ነው።
(1)    ትኩረታችሁ አሜሪካ ላይ ይሁን፤ ታይዋንን ናቋት፣ እንደሌለች ቁጠሯት፣
(2)   የዲሞክራሲ ሃሳቦችን በቀጥታ አትቃወሙ፤ ይልቁንም “የቱ ዲሞክራሲ? ምን ዓይነት ዲሞክራሲ? የት አገር በተግባር ስለታየው ዲሞክራሲ ነው የምታወራው? … ወዘተ እያላችሁ አዋክቡ፣
(3)   በዲሞክራሲ ስም ስለተነሱ ረብሻዎች፥ ስለሞቱ ሰዎች፣ ስለተፈናቀሉ ማኅበረሰቦች ማስረጃ በመዘርዘር ዲሞክራሲና ልማት አብረው እንደማይሄዱ የቅርብ ጊዜ ማስረጃዎችን በማንሳት አስረዱ፣
(4)   አሜሪካና አውሮፓ በዓለም ዙሪያ ነውጦችን እያስነሱ የድሃ አገር ሕዝቦችን እርስ በርስ እንደሚያፋጁ ምሳሌ እየጠራችሁ ተከራከሩ፣
(5)   ደም አፋሳሽ አብዮቶችን እያስታወሳችሁ፤ ምስሎችንም እየለጠፋችሁ ቻይና ውስጥ ነውጥ ቢነሳ የሚደርሰውን ውድመት በአንባቢያን አዕምሮ  እንዲቀረጽ አድርጉ፣ እና
(6)  የቻይናን ስኬቶች አወድሱ፤ ፈጣን ልማቷና ሰላሟን አድንቁ።  የዓለም ኃያል አገር የመሆን ሕልሟን አጋሩ
እኔ እስከማውቀው ይህ አሁን ቻይና ያለችበት ሁኔታ ነው። የተሻለ መረጃ  ያላቸው ወገኖቻችን ደግሞ የሚያውቁትን ያጋሩናል ብዬ ተስፋ  አደርጋለሁ። የቻይናን የውስጥ ፓለቲካ መከታተል ለአገራችን ጠቃሚ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ማስታወስ እወዳለሁ።  ስለዚህ ጉዳይ ተጨማሪ ለማንበብ ለሚፈለግ ለምሳሌ ያህል በዚህ ዓረፍተ ነገር ያሉ ሊንኮችን ይጫን
ናይ ፌስ ቡክ ተፃረፍቲ
እነሆ ከቻይና ልምድ በመቅሰም ህወሓትም የፌስቡስ ተሰዳቢዎችን ቀጥሮልናል። አዲስ ክፍት የሥራ መደብ በመሆኑ በሚቀጥለው ጥቂት ወራት ውስጥ የእነዚህ ተሰዳቢዎች ቁጥር በከፍተኛ መጠን የሚጨምር ይመስለኛል። እኛም የስነልቦና ዝግጅት አድርገን ልንጠብቃቸው ግድ ይለናል።
እስካሁን ባለው ልምድ የኛዎቹ ናይ ፌስ ቡክ ተፃረፍቲ የቻይናዎቹ “አቻዎቻቸው” ሲነሱ በነበሩት ሁኔታ ነው ያሉት። እነዚህን ሰዎች “ኮተታሞች”፣ “ዝተታሞች” ብለው የሚጠሯቸው ባልደረቦች አሉኝ። የአዕምሮ ዝግመት ያለባቸው ስለሚመስል አባባላቸው እውነት አለው። የተለመዱ ስድቦችን ማዥጎድጎች እንጂ ደርዝ ይዘው መከራከር አይችሉም። ስድቦቻቸውም ያረጁና የተሰለቹ ናቸው። “ደደብ”፣ “አህያ”፣ “ጠባብ”፣ “ዘረኛ”፣ “ሻዕቢያ”፣ “የሻቢያ ቅጥረኛ” “የሻብያ ተላላኪ”፣ “አክራሪ”፣ እና በርካታ እዚህ ለመፃፍ የማይመቹ ቃላት ናቸው። በቆሻሻ ቃላት ማኅበራዊ ሚዲያውን በማቆሸሻቸው የፊስ ቡክ አካውንታቸውን የዘጉ ልባም ሰዎች መኖራቸውን አውቃለሁ። አብዛኛው ተጠቃሚ ግን ንቆ ትቷቸዋል።
ወደፊት ግን እንዲህ አይቀጥልም።
የሰለጠኑት ናይ ፌስ ቡክ ተፃረፍቲ ወደ “ፍልሚያ ሜዳ” የሚገቡት ከተሻሻለ ስትራቴጂ ጋር ይሆናል ብዬ እገምታለሁ። አሁንም ከቻይና ልምድ በመነሳት ምን ዓይነት ስትራቴጄ ይዘው እንደሚገቡ አስቀድመን መገመት እንችላለን። የራሳችን ግምት ለመስጠት  ወያኔ በእርግጥ የሚፈራቸውን ነገሮች ማወቅ ይኖርብናል።  እኔ እራሴን በደብረ ጽዮን ጭንቅላት ውስጥ አስገብቼ ሳስብ ያገኘሁት የሚከተለውን ነው።
  1. በአገር ውስጥ
    1. ከአገር በቀል ኃይሎች የወያኔ ቀዳሚ ሥጋት ያረፈው ግንቦት 7 ላይ ነው። ወያኔ ግንቦት 7 የድርጅት መዋቅሬን ሰርጎ ገብቷል ብሎ ያምናል። ስለግንቦት 7 ያለው ጥቂቱ መረጃ አስልቶና አሰላስሎ የሚራመድ ድርጅት እንደሆነ ይነግረዋል፤ ይህ ደግሞ ይበልጥ ያስፈራዋል። ትምህርትና ቴክኖሎጂ ባለበት ቦታ ሁሉ ግንቦት 7 አለ ብሎ ያምናል። በዚህ ፍርሃት ምክንያትም በልበሙሉነት የሚንቀሳቀሱ ኢትዮጵያዊያንን ሁሉ በግንቦት 7 አባልነት ይጠረጥራል።
    2. በሁለተኛ ደረጃ የሚፈራው ኃይል ኦብነግን ነው። ኦጋዴን የሚንቀሳቀሰው ለቁጥጥር በማያመች ቦታ ነው። የሶማሊያ ሁኔታም ለአብነግ አመቺ ነው። ኦብነግ ድርጅታዊ ጥንካሬውን ካጎለበተ ፈታኝ ኃይል  ሊሆን  እንደሚችል ይገባዋል።
    3. በሶስተኛ ደረጃ የሚመጣው የሙስሊሞች እንቅስቃሴን ነው። የሙስሊሞች እንቅስቃሴ ከቁጥጥሬ ሊወጣ ይችላል ኢህአዴግንም ሊከፋፍለው ይችላል ብሎ ይሰጋል። የሙስሊም አክቲቪስቶች የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እውቀት ከፍተኛነት ስጋቱን አባብሶታል።
    4. በአራተኛ ደረጃ የሚመጣው በህጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ናቸው።  It’s the economy stupid እንዲሉ የድንጋይ ካቦችም ሆኑ “የተቀቀሉ” ቁጥሮች የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ያለበትን አሳዛኝ ሁኔታ መደበቅ አልቻሉም። ህጋዊ ፓርቲዎች እመዳፉ ውስጥ እንዳሉ ቢያውቅም በየቦታው የሚታዩ የሥርዓቱ መበስበሶችን ተጠቅመው ድንገት ሊያፈተልኩብኝ ይችሉ ይሆናል ብሎ ይሰጋል።
    5. አምስተኛ ደረጃ የወያኔ ስጋት ኢህአዴግ ነው። የተማከለ አመራር እጦትና መረን የለቀቀው ሙስና የኢህአዴግ ድርጅቶችን እንዳይበታትናቸው ወያኔ ይሰጋል። የኦነግ መንፈስ በኦህዴድ ውስጥ አለ የሚለው ስጋት ወያኔን ምቾት የሚነሳ  ነገር ነው።
  1. በውጭ ግኑኝነት
    1. ወያኔ ከሁሉም በላይ የሚፈራው የውጭ ጠላት ሻዕቢያን ነው፤ ሻዕቢያን በጦር ኃይል ማሸነፍ እንደማይችል ያውቀዋል።
    2. ሁለተኛው አቢይ የወያኔ የውጭ ስጋት አልሸባብ ነው። መለስ በግብተኛነት የገባበት ድጥ፣ ማጥ ሆኖበታል።
    3. ሶስተኛው ስጋት ያለው ደቡብ ሱዳን ነው። ይህ ገና በግልጽ ያለየለት ቢሆንም እረፍት የሚነሳ ነገር ነው፡
    4. አራተኛውና የመጨረሻው ስጋት ግብጽ ነው። አባይ ለብዙ ሺህ ዓመታት ለኢትዮጵያ ነገሥታት “ረዥም ጦር ባይወጉበት ያስፈራሩበት” ዓይነት ነበር። አቅም ባይኖርም “አባይን እገድባለሁ” ለኢትዮጵያ መሪዎች ማስፈራሪያ ነበር። ያ የዘመናት ማስፈራሪያ ባላዋቂ እጅ ተነካና ግብጽ ሥጋት ሆነች። ለጊዜው ሁለቱም አገሮች ከዛቻ የማያልፉ በመሆኑ ግልጽ ስጋት የለም። ወደፊት ግን ግብጽ ብቻ ሳትሆን ግድቡ ራሱ የስጋት ምንጭ ሊሆን ይችላል።
የተመራቂ ናይ ፌስ ቡክ ተፃረፍቲ ስትራቴጂዎች

አሁን አንባቢዎቼ የተመራቂ “ናይ ፌስ ቡክ ተፃረፍቲ” ስትራቴጂዎች ምን ሊሆኑ እንደሚችል መገመት ይችላሉ ብዬ አምናሉ። ተራ ስድቦችን ቀንሰው ተቀርቋሪና ሩቅ አሳቢ መስለው ለመቅረብ ይሞክራሉ። ግን የፈለገውን ያህል ቢጥሩ ተፈጥሯቸው ስለማይፈቅድላቸው እጅግም መለወጥ አይችሉም። እነሱ ሳይሳደቡ ማውራትም ሆነ መፃፍ አይችሉበትም፤  እኛም እነሱን ለይተን ለማወቅ ጊዜ አይፈጅብንም። በስጋት ደረጃቸው ቅደም ተከተል ከላይ የቀረበውን ዝርዝር ገልጠው፤ የላዩን ታች የታቹን ላይ አድርገው ነው “ሜዳ” የሚገቡት። ዋና ዋናዎቹን ስትራቴጂዎችን ብቻ  ላንሳ።
(1)    አዳዲሶቹ ናይ ፌስ ቡክ ተፃረፍቲ ስለሻዕቢያ ብዙ እንዳይጽፉ መመሪያ ይሰጣቸዋል። ሆኖም አንዳንዴ – በነገር መሃል – ሻዕቢያን አናንቀው በፈለጉበት ቀንና ሰዓት ከአዲግራትና ዛላንበሳ በሚልኩት ፓሊስና ሚሊሽያ ሊያሸንፉት የሚችሉ ደካማ ኃይል አስመስለው ያቀርቡታል።
(2)   የአዳዲሶቹ ተፃረፍቲ “ታርጌት” ጠላት አገር ግብጽ ይሆናል። በሽፍንፍንም በአጠቃላይ አረቦች ተነስተውብናል የሚል ስውር  መልዕክት ለማስተላለፍ መጣራቸው አይቀርም። ግልጽ ስጋት ባይኖርም ግብጽ ላይ ያቅራራሉ፣ ይፎክራሉ።
(3)   ግንቦት 7፣ ኢሳት፣ ሻዕቢያንና ግብጽን አሳክረው ያቀርባሉ።
(4)   የሚቀጥለው ዓመት ምርጫ ትልቅ ስጋት ይዞ እንደሚመጣ አድርገው ማውራታቸው አይቀርም።
(5)   ስለ ኢትዮጵያ ሙስሊም ማኅበረሰብ ሲያነሱ ሆነ ብለው ከአልሸባብ፣ አልቃይዳ እና ቦኮ ሃራም ጋር እያያዘው ይሆናል።
(6)  አሁኑ ኢቲቪ በርትቶ እየሠራባቸው ያሉት “በአብዮቶች የማስፈራራት ስልት” ተጠናክሮ  ይቀጥላል።  ሊቢያ፣ ግብጽ፣ ሶሪያ፣ ዩክሬን በማስፈራሪያነት የሚነሱ አገሮች ይሆናሉ።
(7)   በምግብ ራሳችን ችለናል፤ መካከለኛ ገቢ አላቸው አገሮች ምድብ ደርሰናል፤ አድገናል፤ አምሮብናል … የሚሉ ጉራዎች ተፋፍመው ይቀጥላሉ።
አዳዲስ ተመራቂዎችን እንዴት እንቀበላቸው
facebook
ይህ ጽሁፍ ከአቀባበል ዝግጅቶቻችን አንዱ ነው። ከመምጣታቸው በፊት ምን ይዘው ለመጣት እንደተዘጋጁ፤ ምን ዓይነቱ ስልጠና  እንደተሰጣቸው የምናውቅ መሆኑ ማወቃቸው አዲሱ ሥራቸውን በመሸማቀቅ እንጂምሩት ያደርጋቸዋል። እንደሁኔታው የሚለዋወጥ ሁኖ ሶሻል ሚዲያ (በተለይም ፌስ ቡክ) የምንጠቀም ሰዎች የሚከተሉትን መርሆዎች በሥራ ላይ ብናውል ይበጃል ብዬ አምናለሁ።
  1. ሶሻል ሚዲያን በተለይም ፌስቡክን ለእነሱ አለመቀቅ፤ በሚሰጧቸው አስተያየቶች በመሳቀቅ ፋንታ መዝናናት።
  2. ናይ ፌስ ቡክ ተፃረፍቲዎችን ማስነወር፤ “ሥራቸው” ምን ያህል አዋራጅ እንደሆነ መንገር፤ እነሱን በማብሸቅ መዝናናት።
  3. ከእነሱም መካከል ልባሞች አይጠፉምና ምስጥራዊ ግኑኝነት መመሥረት ሆኖም በቀላሉ አለማመን።
  4. የሚታወቁበትን መንገድ፣ ዘይቤዎቻቸውን፣ ስልቶቻቸውን እየተከታተሉ ማጋለጥ።
  5. የሚተማመኑ ወዳጆች የውስጥ ክበብ እና ለእውነት የቀረበው እውነታ (Virtual reality) እውነት እንዲሆን መጣር፤ ለምሳሌ በፌስ ቡክ የተዋወቁና በተወሰኑ መጠንም ቢሆን የሚተማመኑ ወዳጆች ከፌስ ቡክ ውጭ በሌሎች ሚዲያዎች የሚገናኙበት መንገድ መፍጠር።
  6. በነፃነት ማሰብ የጀመሩ ወጣቶች የፈጠራ አቅም አስገራሚ ነው፤ ናይ ፌስ ቡክ ተፃረፍቲዎች ላይ መሳለቂያ የፈጠራ ዘዴዎችን መጠቀም።
  7. በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነው ወያኔን የሚተቹ ጽሁፎን የሚጽፉ ወገኖቻችን ለዚህ ተግባር በስማቸው በተከፈቱ አካውንቶች ፈጽሞ  አለመጠቀም ። ይህ በብዙዎች የሚታወቅ ቢሆንም ማንሳቱ ይጠቅማል።
 እንደማሳረጊያ
እኔ፣ እንኳንስ በሳይበር ትግል ውስብስብ የሆኑ የሰላማዊ ትግል ስልቶችን ተጠቅመንም ቢሆን በሰላማዊ መንገድ ብቻ ኢትዮጵያ  ውስጥ የሥርዓት ለውጥ ሊመጣ ይችላል ብዬ አላስብም። ኢትዮጵያ ውስጥ የሥርዓት ለውጥ እንዲመጣ ጉልበት መጠቀም የማይቀር እዳ ነው ብዬ አምናለሁ። ያም ሆኖ ግን ሁሉም ሰው በጉልበቱ መስክ አይሳተፍምና እያንዳንዱ እንደፍላጎቱና አቅሙ ለትግሉ የሚያበረክተው ነገር አለ። ትግሉ የሚካሄደው በሁሉም ቦታዎች ነው።
በተለያዩ መስኮች በሚደረጉ ትግሎች መካከል ያሉ ግኑኝነቶች ለጊዜው በግልጽ ላይታይ ይችላሉ። በመካከላቸው ያለው ከፍተኛ  መደጋገፍ ግን በግልጽ የሚታይበት ጊዜ ይመጣል። በየተየሰለፍንበት ሜዳ ወያኔን ማሸነፍ ዓላማችን አድረገን መነሳት ይኖርብናል። ናይ ፌስ ቡክ ተፃረፍቲዎች ዝም ሊያሰኙን በፍጹም አይገባም።
አስተያየት  ካለዎት tkersmo@gmail.com

ኦባንግ “ከምርጫው” በፊት ለተቃዋሚዎች “ምርጫ” አቀረቡ

June 11/2014
ometho


ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ በአገር ውስጥ ለሚገኙ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችና አግባብ አላቸው ለሚሏቸው አካላት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ተቀምጠው እንዲመክሩ ማሳሰቢያ ሰጡ፡፡ ኢህአዴግ በውስጥ ችግሩ፣ በውጭ ተጽዕኖ ወይም በፖለቲካው የተፈጥሮ ባህርይ የሚከስምበት ደረጃ መድረሱን ያሳሰበው በ”ጥቁሩ ሰው” ኦባንግ ስምና ፊርማ የተበተነው የአኢጋን ደብዳቤ፤ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ልዩነታቸውን አጥብበው እንዲሠሩ ጠይቋል፡፡ ይህንን ለኢትዮጵያና ለሕዝባቸው ሲሉ መሥራት የማይችሉ ከሆነ ከኢህአዴግ በላይ ተጠያቂ ሊሆኑ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል፡፡
የፖለቲካ ዕርቅ በመጀመሪያ በተቃዋሚዎች ደጅ ሊተገበር እንደሚገባው ያሳሰበው አኢጋን፤ ይህንኑ ዕርቅ መሠረት በማድረግ ወደ ኅብረት እንዲመጡ በደብዳቤው ገልጾዋል፡፡ ወደ ኅብረት ሲመጡ የፖለቲካ ሥልጣን የመጨበጥ ዓላማቸውን ወደ ጎን መተው እንዳለባቸውና ኢትዮጵያን በማዳን ተግባር ላይ እንዲያተኩሩ በጥብቅ አሳስቧል፡፡
መግለጫው ሲቀጥልም “የጋራ ንቅናቄያችን ከበርካታ ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶችና ታዋቂ ግለሰቦች ጋር ካለው ግንኙነት አኳያ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ መረጃ ይሰበስባል፡፡ በቅርቡ አንድ ታዋቂ የምዕራቡ ዓለም የፖሊሲ አውጪ ሲናገሩ ኢትዮጵያውያን የምዕራቡ ዓለም ነጻ ያወጣናል ብለውበጭራሽ ማመን የለባቸውም፡፡ ከውጭ የሚላከውን ዕርዳታና ድጋፍ ብናቆም እንኳን ይህ የሚሆን አይደለም፡፡ የለውጥ አራማጅና መሪመሆን ያለባቸው ኢትዮጵያውያን ራሳቸው ናቸው እንጂ ለጋሽ መንግሥታት አይደሉም፡፡ ኢትዮጵያውያን ይህንን ሊረዱ ይገባል፡፡ኢትዮጵያውያን ራሳቸው ከህወሃት/ኢህአዴግ የተሻለ አማራጭ በሚፈጥሩበት ጊዜ እኛ የግድ እንድንደግፋቸው ያደርጉናል በማለት ለጋራ ንቅናቄያችን ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል” በማለት በመረጃ ላይ የተደገፈ ጭብጥ አቅርቧል፡፡
ሰሞኑን የዚህ ዓመት የSEED ተሸላሚ የሆኑት ይህ የአቶ ኦባንግ የምርጫ አማራጭ ግልጽ ደብዳቤ መጪውን ሁኔታ በሚከተለው ሁኔታ ገልጾታል፤ “አገራችን በበርካታ ድሎች ያንጸባረቀ ታሪክ ያላት ነች፡፡ ከሁሉ በበላይ የሚጠቀሰው የዓድዋ ድል በድጋሚ የሚፈጸምበት ጊዜቢኖር አሁን ነው፡፡ የዓድዋን የጦር ድል በፖለቲካው መድረክ እንድገመው፡፡ መጪውን ምርጫ ፖለቲካዊ የዓድዋ ድልየምንጎናጸፍበት እናድርገው፡፡ ነጻነታችን እንደ ዕርዳታ እህል ከምዕራባውያን የሚለገሰን አይደለም፡፡ ስለዚህ እኛው ራሳችን እንደአድዋ ድል አንድ ሕዝብ ሆነን በመውጣት የራሳችን የምናደርገበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ ቅንነት ካለ የጦር ሜዳውን አድዋ በፖለቲካውሜዳ ላይ መድገም ይቻላል፡፡ አንድ ሊያደርጉንና ሊያስተባብሩን የሚችሉ “ምኒልኮችን” ለመጠቀም ፈቃደኛና ቅን እንሁን፡፡
በአኢጋን አድራሻና በዋና ዳይሬክተሩ አቶ ኦባንግ ሜቶ ስምና ፊርማ የተሰራጨው ይህ የማሳሰቢያ ግልጽ ደብዳቤ አኢጋን በተለይ በዕርቅ ዙሪያ የሚጠየቀውን ማንኛውንም ጥያቄ ድጋፍ እንደሚሰጥ ያረጋገጠ ነው፡፡ የደብዳቤው ሙሉ ቃል ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

“ነጻነትነታችን እንደ ዕርዳታ እህል ከምዕራባውያን የሚለገሰን አይደለም!”
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የፖለቲካ መሪዎች ያስተላለፈው ግልጽ መልዕክት
የተወደዳችሁ በኢትዮጵያ የምትገኙ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፤
በቅድሚያ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) የአክብሮት ሰላምታ በማቅረብ በትግሉ መስክ የምትከፍሉትን መስዋዕትነት የሚያደንቅ መሆኑን ይገልጻል፡፡ በተለይ በአሁኑ ጊዜ የፖለቲካ ምህዳሩ እጅግ ጠብቦ የለም የሚባልበት ደረጃ በደረሰበት ወቅት በምታገኙት ስንጥቅ ሁሉ እየተጠቀማችሁ ለህዝባችሁ የብርሃን ጭላንጭል ስለምትፈነጥቁ አኢጋን ሥራችሁን ያደንቃል፤ ያከብራል፡፡ እኛ በሥራችሁ ስኬት የምንመኘው ለቆማችሁለት የፖለቲካ ዓላማ ብቻ ሳይሆን ከህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ራሳቸውን ነጻ ለማውጣት አቅቷቸው መፈናፈኛ ላጡትም የመወሰን ኃይል እንደምትሰጧቸው በማመን ነው፡፡
አገራችን ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አኳያ የበርካታዎች ጥያቄ “ህወሃት/ኢህአዴግን በምን ዓይነት የተሻለ አስተዳደር እንዴት መለወጥ ይቻላል የሚለው ነው?” ይህ ጥያቄ “እኛ ኢትዮጵያውያን የዘርና የጎሣ ትንንሽ አጥሮቻንን አፍርሰን ሁሉን አቀፍ ትግል ለማድረግ ተዘጋጅተናል ወይ?” ብለን ራሳችንን መልሰን አንድንጠይቅ የሚያደርገን ነው፡፡ እንዲሁም ከጎሣ ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ በመስጠትሁሉም ነጻ ሳይወጣ ራሳችንን ነጻ ለማውጣት እንችላለን ወይ? ብለንም እንድንጠይቅ የሚያስገድደን ነው፡፡
ህወሃት/ኢህአዴግ ከኢትዮጵያ አልፎ ለቀጣናው እንዲሁም ለመላው አፍሪካ “የሚተርፍ” እኩይ የዘርና የጎሣ ፖለቲካ በማስፋፋት አገራችንን እንደዚህ ባለ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በጣለበት በአሁኑ ወቅት የብዙዎች ጭንቀት አገራችን ወደ ምን ዓይነት አዘቀት ውስጥ እየገባች ይሆን የሚለው ከሆነ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ነገር ግን ይህንን ፍርሃት ወደ ተስፋ የሚቀይር አማራጭ እስካሁን ተግባራዊ መሆን ባለመቻሉ አማራጭ የጠፋ ይመስል ህወሃት/ኢህአዴግም “እኔ ከሌለሁ …” እያለ ያስፈራራል፤ ተቃዋሚዎችም በእርስበርስ ሽኩቻ የህዝብ አመኔታ በማጣት ወደ አለመታመን ከመሄዳቸው የተነሳ መልሶ ተዓማኒነትን ለማግኘት ጥረት እያደረጉ ቢሆንም ገና ብዙ የሚቀር አለ፡፡ ይህም ሆኖ ግን ለኢትዮጵያ ሕጋዊ አማራጭ በመሆን ለሕዝባችን መፍትሔ የምታመጡበት ወሳኝ ጊዜ አሁን መሆኑን የጋራ ንቅናቄያችን ያምናል፡፡
እንደምታውቁት የዛሬ ዓመት ምርጫ የሚካሄድበት ጊዜ ነው፡፡ ምርጫውንና አመራረጡን ከሥሩ ጀምሮ የተቆጣጠረው ህወሃት/ኢህአዴግ ሆኖ ሳለ በኢትዮጵያ ውስጥ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ይካሄዳል ብለን አናምንም፡፡ ሆኖም ከተቃዋሚ ፓርቲዎች በኩል የሚፈለገው ተግባር ከተከናወነ በአገራችን እውነተኛ ለውጥ ይመጣል ብለን እናምናለን፡፡ ዓመኔታ የሚጣልበት አማራጭ ከተገኘ ዓለምአቀፉ ኅብረተሰብ ህወሃት/ኢህአዴግን አንቅሮ ለመትፋት ከምንጊዜውም ይልቅ ዝግጁ ነው፡፡ ይህንንም የምንለው ከምንም ተነስተን ሳይሆን ድርጅታችን በአውሮጳ፣ በሰሜን አሜሪካ እና በሌሎች የዓለም ክፍሎች ባለው የግንኙነት መስመር ከሚያገኘው ተጨባጭና ተዓማኒ መረጃ በመነሳት ነው፡፡ በምዕራቡ ዓለም ዘንድ ህወሃት/ኢህአዴግ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚያራምደው የዘር ፖለቲካ፣ የሚከተለው እጅግ ጭቋኝ ፖሊሲ፣ በየጊዜው በሚያወጣቸው አረመኔያዊ ህግጋት፣ ወዘተ ኢትዮጵያን ለከፍተኛ አደጋ የጣለና ለአህጉሩ መጥፎ ምሳሌ እየሆነ በመምጣቱ በኢትዮጵያ የሥርዓት ለውጥ የመከሰቱ ጉዳይ ከምንጊዜውም በላይ አሳማኝ የሆነበት ጊዜ ላይ ይገኛሉ፡፡ አሁንም ጥያቄው “ህወሃት/ኢህአዴግን ማን ይተካዋል?” የሚለው ነው፡፡ይህንን የመመለሱ ኃላፊነት በሁሉም ኢትዮጵያውያን ላይ የወደቀ ቢሆንም በተለይ አገር ውስጥ ያላችሁት የፖለቲካ ፓርቲዎች በቅድሚያ ልትመልሱት የሚገባ ጥያቄ ነው፡፡ አመኔታ የሚጣልበት አማራጭ ሆናችሁ የመቅረባችሁ ሁኔታ ስለምርጫው ነጻና ፍትሃዊነት ከመጠየቅ ባልተናነሰ መልኩ ተጠይቆ መልስ ሊሰጠው የሚገባ ነው፡፡
አገራችን ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ለእናንተ ማስረዳት የሚያስፈልግ አይመስለንም፡፡ በየቀኑ የሚፈጸመውን በደልና ግፍ መከታተል ብቻ ኢትዮጵያ ወዴት እየሄደች እንደሆነ በበቂ ሁኔታ የሚያመላክት ነው፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግ እንደ ተቀጣጣይ (ክላስተር) ቦምብ በየቦታው የበተነው የጎሣ ፖለቲካ ፈንጂ ከፋፍሎ በመግዛት ለራሱ የሥልጣን ማቆያ ቢጠቀምበትም በአሁኑ ጊዜ አገራችንን ከላይና ከታች እያነደዳት ይገኛል፡፡ ከዚህ አኳያ በአገራችን ላይ ሊፈነዳ የሚችለው ነገር ሁሉንም የሚያሳስብ እንደሆነ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግ ራሱ በፈጠረው ችግርና በበተነው መርዝ ራሱን በራሱ ሊያጠፋው እንደሚችል ከድርጅቱ ውስጥ የሚታዩት የሥልጣን ሽኩቻዎች ሁሉም “ሳይቀድሙኝ ልቅደም” በሚል አስተሳሰብ እንደተወጠረ የሚያመለክት ነው፡፡ አገራችን ነጻነቷን ከመጎናጸፏ በፊት ይህንን ዓይነቱ የህወሃት/ኢህአዴግ እርስበርስ መበላላት የሚያሳስባቸው ኢትዮጵያውያን እጅግ በርካቶች ናቸው፡፡ ከሁሉ በላይ ደግሞ እናንተ ባላችሁ ኃላፊነት ይህንን በውል የምታጤኑት እንደሆነ የጋራ ንቅናቄያችን ያምናል፡፡
ህወሃት/ኢህአዴግ ከውስጥ በሚነሳበት ግፊትና የመበላላት ስጋት፤ ከውጪ በሚመጣበት ተጽዕኖ ወይም በሁለቱ ጥምረት ከሥልጣን መወገዱ የማይቀር ነው፡፡ ይህንን የሚቀበል ካልሆነም ሥርነቀል ተሃድሶ ማድረጉ እየጎመዘዘው የሚጠጣው ሐቅ ነው፡፡ በየትኛውም መልኩ የሚከሰተው ለውጥ አገራችንን መልሶ መልኩን ለቀየረ በዘር ላይ ለተመሠረተ አገዛዝ አሳልፎ የሚሰጣት መሆን የለበትም፡፡ ይልቁንም የሚመጣው ለውጥ ሕዝባችንን እውነተኛ ነጻነት የሚያጎናጽፍ፣ ፍትሕ የሚሰጥና ወደ ዕርቅ የሚመራ መሆን ይገባዋል፡፡ አገራችን በዚህ ጎዳና ላይ እንድትጓዝ የማድረጉ ኃላፊነት የእናንተ እንደሆነ የጋራ ንቅናቄያችን ያሳስባል፡፡
ይህ ደግሞ ሥልጣን ከመጨበጥ ባለፈ ምኞት ላይ የተመሠረተና እያንዳንዱ ነጠላ ፓርቲ ከሌሎች ጋር በኅብረት በመሥራት ተግባራዊ ሊያደርግ የሚገባው መሠረታዊ ዓላማ ነው፡፡ አገራችን ካለችበት ታላቅ ችግር አኳያ የፓርቲዎች መተባበርና ከተቻለም መዋሃድ ወደ መፍትሔ በሚወስደው መንገድ ላይ የመጀመሪያው ስኬት ነው፡፡ ይህ ግን በቀላሉ አይገኝም፤ ሆደ ሰፊ መሆንን፣ ከራስ ይልቅ ለአገርና ለሕዝብ እንዲሁም ለመጪው ትውልድ ማሰብን፣ ከሁሉ በላይ ደግሞ ከፍተኛ የመንፈስ ልዕልናን የሚጠይቅ ነው፡፡ ሥልጣንን፣ የራስን ክብር፣ የበላይነትን፣ “እኔ ከሌላው የተሻልኩ ነኝ” ማለትን፣ ወዘተ እያውጠነጠኑ ለአገር አስባለሁ ማለት በእጅጉ አስቸጋሪ ነው፡፡ “ከጠላት” የላቀ የመንፈስ ልዕልና ከሁሉም ይጠበቃል፡፡
በመጪው ምርጫ ከምንጊዜውም በበለጠ በመጽናት ለለውጥና ለነጻነታችን የምንታገልበት ሊሆን ይገባል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ የናፈቀውን ነጻነት ሊጎናጸፍ የሚችልበት አማራጭ ሊፈጠር እንደሚችል አኢጋን ያምናል፡፡ ይህ ሊከሰት የሚችለው በአገር ውስጥ ያላችሁት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥቃቅን ልዩነታችሁን አስወግዳችሁ አጀንዳችሁን ሕዝባዊ በማድረግ በኅብረት ለመሥራት ስትወስኑ ነው፡፡ የጋራ ንቅናቄያችን ባደረገው ጥናት አብዛኞቻችሁ ያላችሁ ልዩነት መሠረታዊ እንዳልሆነ ለመረዳት ችሏል፡፡ ይህም የሚያሳየው እርስበርስ ከሚያለያያችሁ ነገሮች ይልቅ ሊያስማሟችሁ የሚችሉት በርካታዎች እንደሆኑ ነው፡፡ በተለይ በአመራር ላይ ያላችሁ በተለያየ ጊዜ ከሌሎች ጋር የተከሰቱ ልዩነቶችና ግጭቶች እንዲሰፉ ምክንያት ከመሆን ይልቅ ለአገርና ሕዝብ በማሰብ ኢትዮጵያን የመታደግ ኃላፊነት ወድቆባችኋል፡፡ አገር ከሌለ ምንም ሊኖር አይችልም፤ እንደ ትልቅ የያዛችሁት ልዩነትና ችግርም ከንቱ ይሆናል፤ አብሮ ይከስማል፡፡
በተደጋጋሚ የሚሰማው ነጠላ ዜማ “በኢትዮጵያዊ ውስጥ ተስፋ የሚጣልበት ተቃዋሚ ፓርቲ የለም” የሚል ነው፡፡ በእርግጥ ለዚህ ጥያቄ ዋንኛ ተጠያቂው ኢህአዴግ ነው፡፡ ምክንያቱም በአስመሳይ ዲሞክራሲና ተግባራዊ ባልሆነ ሕገመንግሥት ሕዝባችንን ከመጠርነፍ አልፎ የፖለቲካ ፓርቲዎችንም በተመሳሳይ ሁኔታ ሸብቧቸዋል፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግ የሚከተለው ፕሮግራም በኢትዮጵያ ውስጥ ጠንካራ የፖለቲካ ፓርቲ እንዳይኖር ያደረገ ለመሆኑ ማንም የሚክደው አይደለም፡፡ ሆኖም ግን በኢህአዴግ ብቻ እያመካኙ መኖር ተቀባይነት የሌለው አካሄድ ነው፡፡እያንዳንዱ የተቀናቃኝ ፖለቲካ ፓርቲ ዓላማው የኢህአዴግን መሰሪነትና አፋኝነት ለመስበክ ሳይሆን ሕዝብን ለነጻነት ማብቃት ነው፡፡ እታገለዋለሁ ከሚለው አካል መላቅ ካልቻለ ለትግል ብቁ ነው ለማለት ያስቸግራል፡፡
ሽንፈት ላይ እያተኮሩና የጠላትን ኃይለኛነት እየሰበኩ ድል አይገኝም፡፡ ልዩነትን እያራመዱ ኅብረትና አንድነት ተግባራዊ መሆን አይችልም፡፡ለአገራዊ ዕርቅ እንሰራለን እያሉ በፓርቲ መካከል ከዚያም በታች በግለሰብ ደረጃ መተራረቅ ካልተቻለ ብሔራዊ ዕርቅ ከቀን ቅዠት አያልፍም፡፡ እያንዳንዳችሁ የፖለቲካ ፓርቲዎች መድረክ፣ መኢአድ፣ አንድነት፣ ሰማያዊ፣ ኦህኮ፣ አረና፣ እና ሌሎች እጅግ በርካታ ፓርቲዎች የተቋቋማችሁትና ዓላማ ያደረጋችሁት ኢህአዴግን እየተቃወማችሁ ለመኖር እንዳልሆነ የፓርቲ ፕሮግራማችሁ ይመሰክራል፡፡ ወይም ዓላማችሁ የራሳችሁን የፓርቲ ምርጫ የማድረግና ፕሬዚዳንት (ሊቀመንበር)፣ ምክትል፣ ሥራ አስፈጻሚ፣ … በመምረጥ አዙሪት ውስጥ ራሳችሁን ላለማሽከርከር እንደሆነ ከማንም በላይ ራሳችሁ ታውቁታላችሁ፡፡ ከዚህ አንጻር በጥንቃቄና በብዙ ጥናት የተቀመጠው የፓርቲያችሁ ፕሮግራምና ዓላማ ለአገራችን አንዳች ለውጥ ሳያመጣ እንደዚሁ እንዳማረበት ቢቀመጥ ለሕዝብ የሚያመጣው ትርፍ ምንድርነው? እናንተንስ ለመቃወም ብቻ የምትሰሩ አያደርጋችሁምን? ለኢህአዴግና ወዳጆቹስ ጣት የሚጠቁሙበትን ዕድል እየሰጣችሁ እስከመቼ ትኖራላችሁ? ስለዚህ የእስካሁኑ በነጠላ የመጓዙ ጉዳይ ካልሰራ በኅብረት የመሥራቱ ጉዳይ የግድ ይሆናል፡፡ ይህ ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነ አኢጋን ያምናል፡፡
የጋራ ንቅናቄያችን ከበርካታ ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶችና ታዋቂ ግለሰቦች ጋር ካለው ግንኙነት አኳያ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ መረጃ ይሰበስባል፡፡ በቅርቡ አንድ ታዋቂ የምዕራቡ ዓለም የፖሊሲ አውጪ ሲናገሩ “ኢትዮጵያውያን የምዕራቡ ዓለም ነጻ ያወጣናል ብለው በጭራሽ ማመን የለባቸውም፡፡ ከውጭ የሚላከውን ዕርዳታና ድጋፍ ብናቆም እንኳን ይህ የሚሆን አይደለም፡፡ የለውጥ አራማጅና መሪ መሆን ያለባቸው ኢትዮጵያውያን ራሳቸው ናቸው እንጂ ለጋሽ መንግሥታት አይደሉም፡፡ ኢትዮጵያውያን ይህንን ሊረዱ ይገባል፡፡ ኢትዮጵያውያን ራሳቸው ከህወሃት/ኢህአዴግ የተሻለ አማራጭ በሚፈጥሩበት ጊዜ እኛ የግድ እንድንደግፋቸው ያደርጉናል” በማለት ለጋራ ንቅናቄያችን ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ይህ ንግግር በአገር ውስጥ ለምትገኙት ብቻ ሳይሆን በዳያስፖራ ለምንገኘውም ልንገነዘብ የሚገባው ሐቅ ነው፡፡ ነጻነት ከምዕራቡ ዓለም ብቻ ሳይሆን በዳያስፖራ ከሚገኙት ኢትዮጵያውያንም ሊመጣ አይችልም፡፡ የነጻነታችንን ጥያቄ ተግባራዊ የሚሆነው እናንተ በአገር ውስጥ የምትገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች በኅብረት በመሥራት ሕዝባችንን ለለውጥ ስታስተባብሩት ብቻ ነው፡፡ እኛ ይህንን ከራሳችን ትከሻ ላይ ለማውረድና እናንተን በኃላፊነት ለመጠየቅ የምንጭነው ሳይሆን አገር ውስጥና ውጭ መሆናችን በታሪክም ይሁን በሌላ ምክንያት የተከሰተ በመሆኑ በቅንነትና በሐቅ የምንናገረው እውነታ ነው፡፡ እኛም ከአገር ውጭ ነን በማለት እጃችንን አጣጥፈን የምንቀመጥ ሳይሆን በአገር ውስጥ የሚካሄደውን ትግል የመደገፍ፣ የማገዝ፣ የምዕራባውያንን አመለካከት የማስቀየር፣ በአገር ውስጥ የሚካሄደውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ የማሳወቅ፣ … ኃላፊነት እንዳለብን በመገንዘብ ነው፡፡ አኢጋን ይህንን ዓይነቱን ተግባር ሲያካሂድ የቆየ አሁንም ከአገር ውስጥ የሚመጣውን ጥያቄ ለመመለስና በሚችለው ሁሉ ለማገዝ ሙሉ ዝግጁ መሆኑን ለመግለጽ ይወዳል፡፡
ከዚህ በፊት በተካሄዱት ምርጫዎች እንደታየውና በፓርቲያችሁ ፕሮግራም ላይ እንደሰፈረው እንደ ፖለቲካ ፓርቲ በምርጫ ተወዳድራችሁ ሥልጣን የመያዝ ዓላማ እንዳላችሁ ግልጽ ነው፡፡ ሆኖም ግን ማናችሁም ብትሆኑ በነጠላ ፓርቲነት ተወዳድራችሁ ሥልጣን በመያዝ ለውጥ እንደማታመጡ በግልጽ ልንነግራችሁ እንወዳለን፡፡ በምርጫ አሸነፋችሁ ቢባል እንኳን ሥልጣን የሌለው ቢሮ ከመያዝና የህወሃት/ኢህአዴግ አሻንጉሊት ከመሆን እንደማታመልጡ እሙን ነው፡፡ ይልቁንም ይህ ዓይነቱ አካሄድ ህወሃት/ኢህአዴግ በተለይም ለምዕራቡ ዓለም ለሚደሰኩረው የይስሙላ ዴሞክራሲ ማረጋገጫ ሆኖ በማቅረብ የኢህአዴግ ዕድሜ መቀጠያ መድሃኒት ነው የምትሆኑለት፡፡ ስለዚህ ከመጪው ምርጫ አኳያ ትግሉ የተናጠል ሳይሆን ፓርቲዎች በኅብረት በመሆን ኢህአዴግን በእርግጠኝነት ሊተኩ የሚችሉበት አማራጭ ሊሆን ይገባዋል፡፡
በበርካታ አገሮች እንደሚታየው እናንተም በኅብረት በመሆን ኃይላችሁን አስተባብራችሁ ለሕዝባችሁ ስትሉ እርስ በርስ መጠላለፍ፣ መነቋቆር፣ መካሰስ፣ ወዘተ አሁኑኑ ማቆም ይገባችኋል፡፡ በእስራኤል፣ ብሪታኒያ፣ ጀርመን፣ … በተለያዩ ጊዜያት እንደታየው ፓርቲዎች ጥምር መንግሥት በመመሥረት ሕዝባቸውን ታድገዋል፣ አገልግለዋል፡፡ በኢትዮጵያስ ይህ ሊሆን የማይቻልበት ምክንያት ምንድርነው? መልሱን መመለስ የሚገባችሁ እያንዳንዳችሁ የፓርቲ አመራሮች ናችሁ፡፡
ይህ ሳይሆን የሚቀር ከሆነ በቅርቡ የፖለቲካ ታሪካችን እንደታየው በዚህም ዘመን በተመሳሳይ መልኩ ይደገማል፡፡ በዘመነ አጼ ኃይለሥላሴ የተነሳው የህዝብ ብሶት ዳር ሳይደርስ ደርግ ለራሱ አስቀረው፡፡ በደርግ ዘመን መከራውንና ስቃዩን ያየው ሕዝብ ህወሃት/ኢህአዴግ “የሕዝብ ብሶት” የወለደኝ ነው ብሎ ሲመጣ የመከራው ዘመን ማብቂያው የደረሰ መስሎት ተስፋ አደረገ፡፡ “ብሶት” ወለደኝ ያለው ኢህአዴግ ኢትዮጵያን ታይቶ በማይታወቅ የዘር “ድንበር” ከፋፍሎ የሕዝባችንን ብሶት ለ23ዓመታት በየቀኑ እያበዛው ይገኛል፡፡ አሁንም ጥንቃቄ ወስዳችሁ ሁላችሁም ለሕዝባችን የሚሆን መፍትሔ የማታመጡ ከሆነ የሕዝባችን ብሶት እንዲቀጥል የምታደርጉ ብቻ ሳይሆን በመጪው ትውልድም ከመጠየቅ አታመልጡም፡፡
በቅንጅት ጊዜ ሕዝብ እጅግ ተስፋ አድርጎ ውጤት ሲጠብቅ ቅንጅቶች “መቀናጀት” አቅቷቸው ጫፍ ላይ ደርሶ የነበረው የሕዝባችን ድል ገደል ገባ፤ በራሱ ተቀናጅቶ የነበረው ሕዝብ የህወሃት/ኢህአዴግ የበቀል እርምጃ ሰለባ ሆነ፡፡ የጋራ ንቅናቄያችን ከበርካታ ወገኖች ጋር ባለው ግንኙነት አሁንም ተመሳሳይ ችግር ይፈጠራል እያሉ ስጋታቸውን የሚገልጹልን ቁጥራቸው በርካታ ነው፡፡ በአገራችን ላይ በርካታ ችግሮች የተጋፈጥን ቢሆንም ከፈጣሪ በኩል ግን ሁልጊዜ መፍትሔና የተበላሸውን የማስተካከል ዕድል አለ፡፡ ይህም ዕድል አሁን እንደሆነ አኢጋን ያምናል፡፡ ከዚህ አንጻር ጥቂት ሃሳቦችን ለማካፈል እንወዳለን፤
  1. በምንም መልኩ በኢትዮጵያ አማራጭ ፓርቲ የለም የሚለውን ተስፋ አስቆራጭ ንግግር አትቀበሉ፡፡
  2. ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር አብራችሁ ልትሰሩ የሚያስችላችሁን ነጥቦች ዘርዝሮ በማውጣት በሚያስማማችሁ ጉዳዮች ላይ የጋራ አስተሳሰብ ልትወስዱ የምትችሉበትን መንገድ አመቻቹ፡፡
  3. በዕቅዳችሁና ከሌሎች ጋር በጥምረት በመሆን ምንም እንኳን አስቸጋሪ ቢሆን በዋንኛነት በአገራችን የፖለቲካ ምህዳር የሚሰፋበትንና ዕርቅ የሚመጣበትን መንገድ ከመቀየስ ተስፋ አትቁረጡ፡፡
  4. የፓርቲ ፕሮግራምና ማኒፌስቶ ከሰማይ የወረደ፣ የማይገሰስ፣ የማይሻርና የማይለወጥ የፈጣሪ ቃል አይደለም፡፡ ስለዚህ ወደ ውኅደት በሚደረገው ጉዞ መሻሻል፣ መለወጥ፣ መስተካከል፣ የሚገባው የፕሮግራም አንቀጽ የፓርቲያችሁን ኅልውና አደጋ ላይ እስካልጣለ ድረስ ተፈጻሚ ለማድረግ ሆደሰፊ ሁኑ፡፡
  5. ከመሪዎች ጀምሮ በፓርቲያችሁ ውስጥ ውህደትን፣ ጥምረትን፣ … ተግባራዊ ለማድረግና በጋራ ለመሥራት ዕንቅፋት የሚሆኑ ግለሰቦችን በግልጽ መውቀስና እንዲታረሙ ወዲያውኑ ማድረግ ወሳኝነት ያለው ተግባር ነው፡፡ “እገሌን እንዴት እወቅሰዋለሁ” ወይም “አቶ እገሌ የፓርቲያችን የጀርባ አጥንት ነው እንዴት ተሳስተሃል እላልሁ” በሚሉ የይሉኝታ አስተሳሰቦች ለአንድ ሰው ሲባል አገርና ሕዝብ መከራና ስቃይ እንዲቀጥል መደረግ የለበትም፡፡ አገር ለመምራት ፓርቲ መሥርታችሁ ሕዝብን በይሉኝታ መንግሥት ማስተዳደር ፈጽሞ አይቻልም፡፡ ለይሉኝታ በራችሁን ዝግ ይሁን፡፡
  6. ሁልጊዜ ለመምራት ሳይሆን ለመመራት ተዘጋጁ፡፡ የሰላማዊ ትግል መሪ መመሪያ ይኸው ነው፡፡ ለመመራት የተዘጋጀ መሪ ለመሆን ምንም አይቸግረውም፡፡ ከሥልጣንህም ተነሳ ሲባል ፓርቲውን አይገነጥልም ወይም “እኔ ከሞትኩ …” በሚል ጭፍን አስተሳሰብ በሕዝብ ላይ የውድመት ተግባር አይፈጽምም፡፡ ይህ ምንም የምንደባበቅበት ነገር አይደለም በተግባር ሲፈጸም የኖረ ነው፤ መስተካከልና መሻሻል የሚያስፈልገው ነው፡፡ ከመገልገል ይልቅ ለማገልገል ትሁት ሁኑ፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈልገው ትክክለኛ አስተዳደር ነው እንጂ ህወሃት/ኢህአዴግን በሌላ መተካት አይደለም፡፡ ሕዝባችን ይህ ያንሰዋል እንጂ አይበዛበትም፡፡ ስለሆነም “ኢህአዴግ ይነሳ እንጂ” የሚለው ጠባብና ሰንካላ ሃሳብ የእውነተኛ ለውጥ መርህ ስላልሆነ በጭራሽ ለሕዝባችን አትመኙለት፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከእንግዲህ ወዲህ የሚያስፈልገው “ከጎሣና ዘረኝነት ይልቅ ሰብዓዊነት”የሚያብብባትና “አንዱ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ነጻ የወጣባትን”፤ ፍትህ፣ ሰላምና ዕርቅ የሰፈነባትን አዲሲቷን ኢትዮጵያን ነው፡፡ ከዚህ ያነሰ ለውጥ በለውጥ ደረጃ ሊታሰብም ሆነ ሊታቀድ አይገባውም፡፡
እናንተ አገር ውስጥ ሆናችሁ በየጊዜው በምታደርጉት የመስዋዕትነት ተግባር የጋራ ንቅናቄያችን ከጎናችሁ ይቆማል፡፡ ሥራችሁንም በታላቅ አክብሮት ይከታተላል፡፡ የመስዋዕትነታችሁ ውጤት ፍሬ እንዲያፈራ የሚቻለውን ሁሉ ያደርጋል፡፡ በውጭ ከበርካታ ወገኖች ጋር ባለን ግንኙነት ለምትፈልጉን ሥራ በምንችለው ሁሉ ለመተባበር ፈቃደኛ መሆናችን እንገልጻለን፡፡ በተለይ በዕርቅ መንገድ ላይ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የሚጠየቀውን ሁሉ ለማድረግ ፈቃደኝነቱን ይገልጻል፡፡ ይህ ጉዳይ በዚህ ደብዳቤ ላይ ለፕሮቶኮል ብለን የምንናገረው እንዳልሆነ እንድትረዱልን እንፈልጋለን፡፡
አገራችን በበርካታ ድሎች ያንጸባረቀ ታሪክ ያላት ነች፡፡ ከሁሉ በበላይ የሚጠቀሰው የዓድዋ ድል በድጋሚ የሚፈጸምበት ጊዜ ቢኖር አሁን ነው፡፡ የዓድዋን የጦር ድል በፖለቲካው መድረክ እንድገመው፡፡ መጪውን ምርጫ ፖለቲካዊ የዓድዋ ድል የምንጎናጸፍበት እናድርገው፡፡ ነጻነታችን እንደ ዕርዳታ እህል ከምዕራባውያን የሚለገሰን አይደለም፡፡ ስለዚህ እኛው ራሳችን እንደ አድዋ ድል አንድ ሕዝብ ሆነን በመውጣት የራሳችን የምናደርገበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ ቅንነት ካለ የጦር ሜዳውን አድዋ በፖለቲካው ሜዳ ላይ መድገም ይቻላል፡፡ አንድ ሊያደርጉንና ሊያስተባብሩን የሚችሉ “ምኒልኮችን” ለመጠቀም ፈቃደኛና ቅን እንሁን፡፡
እርስበርሳችን እንደ ወንድምና እህት ለመተያየትና ለመግባባት ፈጣሪ ቅን ልብ ይስጠን፡፡ እናንተንም ለፍትሕ፣ ለነጻነት፣ ለሰብዓዊነት፣ ለፍቅርና ዕርቅ ስትታገሉ ማስተዋልንና ጥበብን ይስጣችሁ፡፡
ከአክብሮት ጋር ለአገራችን ፈውስ እንዲመጣ የትግል አጋራችሁ፤
ኦባንግ ሜቶ
ዋና ዳይሬክተር፤
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን)

Tuesday, June 10, 2014

በሃረር በጅምላ የተቀበሩ ሰዎች መቃብር መገኘቱን ተከትሎ ግጭት ተነሳ

June 10/2014


ሰኔ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቀበሌ 19 ልዩ ስሙ ሃመሬሳ ወይም መድፈኛ ጀርባ በሚባለው አካባቢ ሰኔ 2 ቀን 2006 ዓም በቁፋሮ ላይ የነበረ አንድ የግሪደር ሹፌር የተከማቹ አስከሬኖችን አግኝቷል።

የ2ቱ አስከሬን ምንም አይነት የመበስበስ ምልክት አለማሳየቱን የገለጸው ወኪላችን፣ ግለሰቦቹ በቅርቡ የተገደሉ መሆናቸውን ያሳያል ብሎአል። አንደኛው ሟች እጆጁን ወደ ሁዋላ ለፊጥኝ ታስሮ የተገኘ ሲሆን ሌላው ደግሞ አይኖቹ በጨርቅ ተሸፍነዋል።

የአራት አስከሬኖች አጽምም እንዲሁ አብሮ መገኘቱን የገለጸው ወኪላችን ፣ ቀደም ብለው የተገደሉ መሆናቸውን መረዳት እንደሚቻል ገልጿል።

ህዝቡ አስከሬኖቹ እንዳይነሱ እና ምርመራ እንዲካሄድባቸው ጥያቄ ቢያቀርብም፣ ፖሊስ ፈቃደኛ ባለመሆኑ አስከሬኖቹን በማንሳት ከዋናው ቦታ በቅርብ ርቀት በሚገኝ ቦታ ላይ እንዲቀበሩ አድርጓል። በቅርቡ የተገደሉትን የሁለቱን አስከሬኖች ማንነት ለማወቅ አልተቻለም።

የግሪደሩ ሾፌር አስከሬኖቹን እንዳየ ራሱን በመሳቱ ወዲያውኑ ወደ ሆስፒታል ተወስዷል።

ኢሳት  በሃረር ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የነበሩ ሁለት ወጣቶች አድራሻቸው መጥፋቱን መዘገቡ ይታወሳል።

ስቱዲዮ ከመግባታችን በፊት ደግሞ የአወዳይ ህዝብ ዛሬ  ሰኔ 3 ወደ አካባቢው በመኪና ተጉዞ ከደረሰ በሁዋላ ተቃውሞ አሰምቷል። የፌደራል ፖሊስ እና የክልሉ ፖሊስ በጋራ በአስለቃሽ ጭስ እና በተኩስ ተቃውሞውን የተቆጣጠሩት ሲሆን፣ ህዝቡ በወሰደው እርምጃ በርካታ ፖሊሶች ቆስለዋል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የልዩ ሃይል ዋና አዛዥ የሆኑት ኮማንደር ሳላሃዲን ግራ አይኑ አካባቢ በድንጋይ ተመትቶ ከባድ ጉዳት ደርሶበት ወደ ሆስፒታል ተወስዷል።

አካባቢው በክልሉ የኢንዱስትሪ መንደር የሚል ስያሜ ተሰጥቶት በአነስተኛ እና ጥቃቅን ስም ለተደራጁ የባለስልጣናት ዘመዶች መሰጠቱን የዘገበው ወኪላችን፣ ለግንባታ የሚውሉ እቃዎች የተጠራቀሙበት መጋዘን በህዝቡ እንዲቃጠል ተደርጓል።

የህዝቡ ጥያቄ “አስከሬን እንዴት የትም ይጣላል፣ ትክክለኛ ቦታ ተፈልጎ በክብር ሊያርፍ ይገባል” የሚል መሆኑን ዘጋቢያችን ገልጿል።

የኦሮምያ ክልል ባለስልጣናት ወደ አካባቢው ተጉዘው ለማረጋጋት ሙከራ አድርገው ባለመሳካቱ ፖሊሶች ህዝቡን በሃይል ለመበተን መገደዳቸውን ወኪላችን አክሎ ገልጿል።

ሀመሪሳ ከአወዳይ ወደ ሃረር መግቢያ ሲሆን አካባቢው ጫካ እና ሜዳ ነው።

በጉዳዩ ዙሪያ የክልሉን ፖሊስ ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።

The moving message of Swedish journalist Martin Schibbye about Eskinder Nega

June 10/2014

Swedish journalist Martin Schibbye accepts the award on behalf of Eskinder Nega

“This Golden Pen is more important than food, medicine and water. It materializes the support and shows that he is not forgotten. That he is one of us. That an attack on one journalist is an attack on us all and that jailing a journalist is a crime against humanity,” Swedish journalist Martin Schibbye said, accepting the 2014 Golden Pen of Freedom, the annual press freedom prize of the World Association of Newspapers and News Publishers (WAN-IFRA), on behalf of imprisoned Ethiopian publisher, journalist and blogger Eskinder Nega.

The honour was formally bestowed on Nega in a ceremony at the 66th World Newspaper Congress, under way in the Italian city of Torino this week, where more than 1,000 media industry representatives have gathered.

Nega is serving an 18-year jail sentence in Addis Ababa’s notorious Kaliti prison, convicted on trumped-up terrorism charges after daring to wonder in print whether the Arab Spring could reach Ethiopia, and for criticising the very anti-terrorism legislation under which he was charged. Arrested in 2011, he was sentenced on 23 January 2012, and denounced as belonging to a terrorist organisation.

Imprisoned at least seven times in the past decade for committing fearless acts of journalism, Nega is a celebrated intellectual and a relentless fighter for freedom of expression. “Eskinder Nega has become an emblem of Ethiopia’s recent struggle for democracy,” World Editors Forum President Erik Bjerager said, delivering the Golden Pen during the opening ceremony of the World Newspaper Congress and the World Editors Forum in Torino. “No stranger to prison, he is also an unforgettable warning to every working Ethiopian journalist and editor that the quest to create a just, free society comes with a heavy price,” Bjerager said.

Nega’s former prisonmate, Swedish journalist Martin Schibbye, accepted the award on the jailed journalist’s behalf, at the invitation of Nega’s family. He painted a dark picture of life inside Kaliti Prison. “The rooms are more like barns with concrete floors, and it is so crowded that you have to sleep on your side,” he said. “Prisoners are packed likes slaves on a slaveship. Once a month an inmate leaves with his feet first.”

But disease and torture are not the hardest part of life inside Kaliti, according to Schibbye. “It (is) the fear of speaking. It’s not the guard towers with machine guns that keep the prison population calm. It is the geography of fear. People who speak politics are taken away. They disappear.” Schibbye is a freelance journalist who was jailed for 14 months in Kaliti Prison, along with his photographer Johan Persson. They were pardoned and released in September 2012.

“In (Kaliti), fearless people like Eskinder Nega helped the whole prison population to keep their dignity. By still writing. Protesting. Not giving up. He helped us all maintain our humanity. But there is one thing I know that even Eskinder fears. That is to be forgotten,” Schibbye says.

“When you’re locked up as a prisoner of conscience, this is the greatest fear, and the support from the outside is what keeps you going. This Golden Pen Award will not set him free tomorrow, but it will ease his day today. He will go with his head high knowing that he is there for a good cause. That the pain and suffering has a meaning.”

WEF President Erik Bjerager told the ceremony that the world needs to watch the creeping threat of anti-terrorism legislation being used to target journalists. “Ethiopia continues to resort to anti-terrorism legislation to silence opposition and shackle the press. Alarmingly, beyond Ethiopia, countless states around the world are misusing anti-terrorism legislation to muzzle journalists, bloggers and freedom of expression advocates,” Bjerager said. “Research suggests that over half of the more than 200 journalists in jail last year were being held on ‘anti-state’ charges. Let me be clear: Journalism is not terrorism. Politicians should not abuse the notion of national security to protect the government, powerful interests or particular ideologies, or to prevent the exposure of wrongdoing or incompetence.”

Schibbye concluded his acceptance speech, reading from a moving letter penned by Nega to his eight-year-old son. It was smuggled out of Kaliti prison: “The pain is almost physical. But in this plight of our family is embedded hope of a long suffering people. There is no greater honour. We must bear any pain, travel any distance, climb any mountain, cross any ocean to complete this journey to freedom. Anything less is impoverishment of our soul. God bless you, my son. You will always be in my prayers.”

Schibbye told a tearful audience: “When I read these words by Eskinder I know that they will never break him. Because he is in peace with himself. He knows that even though he is chained, robbed of his physical freedom, the freedom to talk or to be silent, the freedom to drink or eat, and even to shit. He knows, as do all prisoners of conscience, that you have it in you to keep the most valuable, the freedom that nobody can take from you, the freedom to determine who you want to be. Eskinder is a journalist. And every day he wakes up in the Kaliti prison is just another day at the office.”

Nine more journalists were jailed in the past month in Ethiopia, as the election campaign started ahead of next year’s poll. “The crackdown was a flashing alarm to the world that no one is safe. That there is a hunting season for journalists in Addis Abeba. But despite this difficult situation, there is light,” Schibbye said.

“Eskinder Nega’s courage has turned out to be contagious; a new generation is stepping up. A generation of young cheetahs have been taking enormous risks writing, tweeting and speaking truth to power, demanding the jailed to be released. It is hopeful. It shows that they can jail journalists but they can never succeed in jailing journalism. Words led Eskinder Nega to the Kaliti prison. And in the end it must also be words that set him free,” Schibbye told a clearly emotional audience.

“When I see this Golden Pen of his, I look back, and think of Eskinder who is left behind in the chaos, on the concrete floor, between walls of corrugated steel I feel sick to the stomach. But then I remember his smile and his strength and I think that at the end of the day, it’s not us that are fighting for his freedom – but rather he who is fighting for ours. Ayzoh Eskinder! Ayzoh! (translation: be strong, chin up).”

አራስ እናት በካድሬዎች አበደች!

June 10/2014
አብርሃ ደስታ
በራያ ዓዘቦ ወረዳ ወራባዮ ቀበሌ ፈድሻ በተባለ መንደር ነው። ያከባቢው ኗሪዎች እንደማንኛውም የሌላ ወረዳ ኗሪዎች በሴፍቲኔትና አስቸኳይ እንደርታ (ህፁፅ ሓገዝ) ይተዳደራሉ። የሴፍቲኔት እርዳታ በሥራ የሚሰጥ ነው። መስራት የሚችሉ ጉልበት ያላቸው ግን ድሃ ገበሬዎች በሴፍቲኔት ታቅፈው ያለማሉ። ከዛ ለሰሩት ሥራ ይከፈላቸዋል። ክፍያው የሴፍቲኔት እርዳታ ነው። የሴፍቲኔት እርዳታ ለድሆች በነፃ ሊሰጣቸው የሚገባ ቢሆንም (ምክንያቱም እርዳታ ነው) በስራ ነው የሚሰጣቸው። ለልማት እስከሆነ ድረስ በሥራ መሆኑ ችግር የለውም።
ድሃ ሁነው የጉልበት ስራ መስራት ለማይችሉ የሚሰጥ እርዳታም አለ። "አስቸኳይ እርዳታ" (ህፁፅ ሓገዝ) ይሉታል። የሚቀመስ የሌላቸው በእርጅናም በሌላ ችግርም መስራት ለማይችሉ የሚሰጥ እርዳታ ነው።
አሁን በተለያዩ የትግራይ አከባቢዎች ያሉ በእርዳታ የሚተዳደሩ ድሆች በማልቀስ ላይ ይገኛሉ። ለምን? የህወሓት መሪዎች ድሆች እርዳታ የሚሰጣቸው ማዳበርያ መግዛት ሲችሉ ብቻ ነው ብለው ወሰኑ። የሴፍቲኔት እርዳታ ለመውሰድ የግድ የ1400.00 ብር ማዳበርያ ከፍለው መወሰድ አለባቸው። ግን የሴፍቲኔት እርዳታ በነፃ መሆን ሲገባው በሥራ ነው። በስራ መሆኑ አይደለም ችግሩ። ሰዎች የሴፍቲኔት እርዳታ ለማግኘት ጉልበታቸው ያፈሰሱ ቢሆንም የሥራቸው ለመውሰድ የግድ ማዳበርያ መግዛት አለባቸው። ማዳበርያ ካልገዙ የሰሩትን የሴፍቲኔት እርዳታ መውሰድ አይችሉም። የስራቸውን ዋጋ የከለከላቸው የግል ድርጅት ቢሆን መክሰስ ይቻል ነበር። ችግር እየፈፀመ ያለው መንግስት ሲሆንስ ለማን ይከሰሳል? ይሄ ነገር በትግራይ ሙሉ ያለ ችግር ነው። ማዳበርያ ሳትገዙ እርዳታ የለም ይባላሉ።
የማዳበርያ ዋስ የሆነው ለባለጉልበት ድሆች የሚሰጠውን የሴፍቲኔት እርዳታ ብቻ አይደለም። መስራት ለማይችሉ (አዛውንቶችና አካላቸው ለጎደሉ) የሚቀመስ የሌላቸው ድሆች የሚሰጠው የአስቸኳይ እርዳታ (ህፁፅ ሓገዝ) ጭምር ነው የማዳበርያ ዋስ የሆነው።
በጣም ድሃ ለሆኑና መስራት ለማይችሉ የሚሰጠው አስቸኳይ እርዳታ ለመውሰድ የማዳበርያ ገንዘብ መክፈል አለባቸው። እነኚህ ድሆች የሚበላ ስለሌላቸው አስቸኳይ እርዳታ አስፈለጋቸው። የህወሓት ሰዎች ግን አስቸኳዩ እርዳታ ለመውሰድ የማዳበርያ ብር 1400.00 መክፈል እንዳለባቸው ይነግሯቸዋል። ቆይ ግን እንዚህ የአስቸኳይ እርዳታ ተጠቃሚዎች የሆኑት ምንም ሃብት ስለሌላቸው አይደለምንዴ??? ለማዳበርያ መግዣ ብር 1400.00 (1600.00 ከነወለዱ) ቢኖራቸውማ መቼ ህፁፅ ሓገዝ (አስቸኳይ እርዳታ) የሚያስፈልጋቸው ተብለው ይለዩ ነበረ?
ምንም ሃብት የሌላቸው በሴፍቲኔትና ህፁፅ ሓገዝ (አስቸኳይ እርዳታ) የሚተዳደሩ አርሶአደሮች የማዳበርያ ገንዘብ ሳትከፍሉ አይሰጣችሁም ስለተባሉ ተጨናንቀዋል። ምክንያቱም የማዳበርያ ዋጋ መክፈል አይችሉም። ምክንያቱም ድሆች ናቸው፤ ምንም ገንዘብ የላቸውም። ገንዘብ ስለሌላቸውም ነው እርዳታ ያስፈለጋቸው። የማዳበርያ ገንዘብ ካልከፈሉ ደግሞ እርዳታው አይሰጣቸውም። በግዜው ስላልተረዱ ደግሞ በረሃብ ችግር እየተሰቃዩ ነው። አቤት ብለው የሚሰማቸው የለም።
በራያ ዓዘቦ ወረዳ ወራባዩ ቀበሌ ማህበር የሚገኙ 25 አዛውንቶች እርዳታው ስለተከለከሉ የሚበሉት አጥተው እየተሰቃዩ ነው። አሁን ልመና ጀምረዋል። እያለቀሱ ነው የሚውሉት። ለነሱ ተብሎ የተለመነ የእርዳታ እህል ግን ለማዳበርያ መግዣ ተብሎ በካድሬዎች ተይዞ ታሽጎ ይገኛል። በነሱ ስም ይለመናል ከዛ ለፖለቲካ ፍጆታ ይውላል።
በተያያዘ ዜና በ"ፈድሻ" ሰፈር (ራያ ዓዘቦ ወረዳ ወራባዩ ቀበሌ) የምትገኝ አንዲት ድሃ ነፍሰጡር እናት የሴፍቲኔት እርዳታ ይሰጠኛል ብላ ሲትጠባበቅ ለመዳበርያ ተብሎ ስለተያዘ በምግብ እጦት ስትሰቃይ ቆይታ በቂ ምግብ ሳታገኝ ወልዳለች። ከወለደች በኋላም ምግብ ፈለገች። እርዳታው እንዲሰጣት ጠየቀች። የማዳበርያ ገንዘብ መክፈል እንዳለባት ተነገራት። ገንዘብ የላትም። እርዳታውም አላገኘችም። አሁን የሚበላ አጥታ በረሃብ ምክንያት አብዳለች። ያሳዝናል። ካድሬዎቹ ግን የማዳበርያ ገንዘብ ለመሰብሰብ ህዝብ አስረው ሲያሰቃዩ ይውላሉ!
ከመቼ ጀምሮ ነው ማዳበርያ አለመውሰድ የሚያሳስር ወንጀል የሆነው? ከመቼ ጀምሮ ነው እርዳታ የሚያስከለክል ጥፋት የሆነው? መዳበርያ መግዛት'ኮ መብት እንጂ ግዴታ አይደለም። እናቶች እስካሁን ድረስ እያነቡ ነው። የሚደርስላቸው ይሻሉ።
It is so!!!

ሰማዕታትን እንዘክር፤ እራሳችንንም እንጠይቅ!

June 10/2014
ሰኔ 1997 በዘረኝነት፣ በአፍቅሮተ ንዋይና አፍቅሮተ ሥልጣን የተለከፉ የትግራይ ገዢ ጉጅሌ አባላት ጭካኔ በይፋ የታየበት ወቅት ነው። ለዓመታት በማስመሰያ ጭንብል ተሸፋፍኖ የቆየው የህወሓት እውነተኛ ባህርይ የዛሬ ዘጠኝ ዓመት በወርሃ ሰኔ አደባባይ ወጣ። በሀውዜን ላይ የደረሰውን የግፍ ጭፍጨፋ ሲያወግዝ የቆየው ቡድን ሌላ ሀውዜን አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ፈጠረ። ይኸኛው ሀውዜን ግን በአንድ ቦታ ተወስኖ የቀረ አልነበረም። ጭፍጨፋው በአዲስ አበባ ተጀምሮ ወደ አዳማ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ አዋሳ፣ ሃረር፣ ድሬዳዋ እና ሌሎች ከተሞችና ገጠሮች ተዛመተ። “አግዓዚ” የተሰኘው ገዳይ ሠራዊት በሰላማዊ እናቶችና አባቶች፤ ወጣቶችና ህፃናት ላይ ዘመተ። ደብተርና እርሳሶቻቸውን እንደያዙ ከትምህርት ቤት የሚመለሱ እምቦቃቅላ ህፃናትን ሳይቀር በጥይት ግንባርና ደረታቸውን እየመታ ጣለ።
በ1997ቱ ሚያዝያ መጨረሻና ግንቦት መጀመሪያ ላይ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ በደስታና ተስፋ ተሞልቶ ነበር። የሚያዝያ 30 ታላቅ ሕዝባዊ ሰልፍ እና የግንቦት 7 ጨዋነት የተላበለው ምርጫ የፈጠሩት ተስፋ ቃላት ሊገልጹት በሚችሉት በላይ ነበር። ሆኖም በህወሓት የተመራው የሰኔው ጭፍጨፋ ያንን ሠናይ ስሜት አደፈረሰው፤ አጨለመው።
በዘረኝነት፣ በአፍቅሮተ ንዋይና አፍቅሮተ ሥልጣን የታወረው ወያኔ ከራሱ አባላት ሌላ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰው መኖሩ አይታየውም። በህወሓት ጎጠኞች እሳቤ መሠረት ወጣት ሽብሬ፣ ህፃን ነቢዩ፣ ወ/ሮ እቴነሽ፣ ሌሎች እናቶችና አባቶች ሰዎች አይደሉም። ስለሆነም ያለአንዳች ምክንያት ተገደሉ። እስከዛሬ ድረስም ከገዳዮች መካከል አንዱ እንኳን ተጠያቂ አልሆነም። በግልባጩ ገዳዮች በመግደላቸው ተሾሙ፤ ተሸለሙ። ይህ ሁሉ ያሳምማል።
የሰኔ 1997 ሰማዕታትን የምናስባቸው በጥልቅ ሃዘን ብቻ ሳይሆን በቁጭትና እልህ ጭምርም ነው። ወገኖቻችን እንደሰው ባለመቆጠራቸው ተገደሉ። አሁንም እንደሰው የማይቆጠሩ በመሆኑ ሙት ዓመታቸውን መዘከር ወንጀል ነው። መቸ ነው ይህ ውርደት የሚያበቃው?
ሰማዕታት ወገኖቻችን የሕይወት ዋጋ ከፍለው ዘረኝነትን የማስወገድ ሸክም እኛ ላይ ጥለዋል። እኛስ ይህንን ኃላፊነት ለመሸከም ብቁዎች ነንን? እያንዳንዳችን የገዛ ራሳችንን እንጠይቅ።
ዘላለማዊ ክብር ለሰማዕቶቻችን !!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!

የትግራይ ህዝብ የወያኔ ስርአት ተጠቃሚነው!

June 9, 2014
ከአንዷለም አስራት 
ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ በቅርቡ የማከብራቸውና የሶስት አፋኝ መንግስታትን ጭቆና ከህዝብ ጫንቃ ላይ ለማንሳት እየታገሉ ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም እና የአረና ትግራይ አባል የሆነው አብርሃ ደስታ የትግራይ ህዝብ የወያኔ አገዛዝ ተጠቃሚ እንዳልሆነ ለማስረዳት የሞከሩት ስህተት መሆኑን ለመግለጽ ነው፡፡The Tigray region of Ethiopia
የትግራይ ህዝብ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ አገልግሎት፣ በመሰረተ ልማትና በልማት ባለፉት 23 አመታት በአንጻራዊነት ከሌሎች ክልሎች በተሻለ ሁኔታ ተጠቃሚ እንደሆነ ለማስረዳት እሞክራለሁ። ይህን ስል የትግራይ ህዝብ አልፎለታል ፤ በልጽጓል፤ ከድህነት ወጥቷል እያልኩ ሳይሆን ህዋሃት በሚያደርገው በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ አድልኦ ምክንያት ከሌሎች ክልሎች የተሻለ የስራ እድል ተፈጥሯል ፤ የተሻሉ የአገልግሎት ተቋማት አሉ፤ እንዲሁም ከፍ ያለ የገንዘብ ፍሰት አለ ይህም የሆነው የሌሎችን ክልሎች ጥቅም በሚጎዳ መልኩ ነው የሚለውን ለማስረዳት ነው። ከመጀመሪያው ማስረገጥ የምፈልገው ግን ለወያኔ ወንጀሎች የትግራይ ህዝብ ተጠያቂ ሊሆን አይችልም።
1. በፖለቲካ
ወያኔ በትግራይ ውስጥ ከፍተኛ ተቀባይነት አለው ፣ የወያኔን ዓላማ የማይደግፍ ትግረኛ ተናጋሪ በጣም ጥቂት እንደሆኑ ይታዎቃል፡፡ አብዛኛዎቹ ትግርኛ ተናጋሪ የህዋሃት ተቃዋሚዎች አላማውን ሳይሆን ግለሰቦቹን የሚጠሉ መሆናቸው የታዎቀ ነው፡፡ እነ ገብሩ አስራት ፣ ስየ አብርሃ ፣አረጋዊ በርሄ የመሳሰሉት ከወያኔ የተለዩት አላማውን ጠልተው ሳይሆን መለስ ዜናዊና መሰል አምባገነኖችን በመጥላት እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ አንጋፋው ገብረ መድህን አርአያ ግን የወያኔን አላማ የማይቀበል እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ሁኖም የሁሉንም ትግርኛ ተናጋሪዎች የፖለቲካ አቋም አውቃለሁ ብየ አልታበይም ሌሎችም የወያኔን እኩይ ተግባር የማይደግፉ ይኖሩ ይሆናል ግን አብዛኛው ደጋፊ መሆኑ አሊ አይባልም።
ስለዚህም ወያኔ የትግርኛ ተናጋሪ ምሁራንን ሙሉ አቅም በሁሉም የስራ መስኮች ይጠቀማል፣ ኢትዮጵያ እንደ አዲስ በክልል ከተዋቀረችበት ጊዜ ጀምሮ የትግራይ የተለያዩ ቢሮዎች በአንጋፋና የረጅም ጊዜ ልምድ ባላቸው የቢሮ ሃላፊዎች ሲመሩ ቆይተዋል፡፡ እነዚሁ ምሁራንም የውስጥ ነጻነታቸው የተጠበቀ በመሆኑ በሙሉ አቅም ይሰራሉ፡፡ በተቃራኒው የሌሎች ክልሎች ተዎላጅ የሆኑ አብዛኛዎቹ ምሁራን የወያኔን አላማ ከመጀመሪያው የተጸየፉ በመሆናቸውና ወያኔም ገና ከጅምሩ በጣላቻና በጥርጣሬ ስላያቼውና እንዲጠጉ ስላልፈለገ በተለጣፊ ድርጅቶች መዋቅሮቹ ውስጥ አልተካተቱም፡፡ በዚህም ምክንያት በሌሎች ክልሎች ከክልል አስተዳዳሪዎች ጀምሮ ትምህርትም ፣ብቃትም፣ ልምድም የሌላቼውና ጠርናፊ ወያኔዎች ሲጠሩዋቸው አቤት ሲልኳቸው ወዴት የሚሉ ፣ ታማኝነታቼውንም ለማሳየት የተሻለ ነገር ከመስራት ይልቅ በሚገዙት ህዝብ ላይ ቀንበር የሚያጠቡ ደካሞች ክዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ስልጣን ተሰግስገውበታል፡፡ ለዚህ አለምነው መኮንን አይነቶችን እንደምሳሌ ማየት ይቻላል፣ አለምነው መኮንን መለስ ዜናዊን ያመልክ እንደነበር ይነገራል ፣አለቆቹ የመለስን ራእይ ማስቀጠል ሲሉ ሰምቶ እሱም ራሱን ጭምር አይሰድቡ ስድብ ሰደበ፡፡
ስለዚህም ትግራይ የተሻለ ትምህርት፣ ልምድ፣ ብቃት፣ ዝግጁነት እና ሙሉ ስልጣን ባላቸው ሰዎች የሚተዳደር ክልል እና ህዝብ በመሆኑ ተጠቃሚ ነው፡፡
በአንጻራዊነት መልካም አስተዳደርም አለ ማለት ይቻላል፤ ፖለቲካውን እስካልነካ ድረስ ማንኛውም ትግራዊ በትግራይ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ክልሎችም አቅሙ የፈቀደውን ይሰራል። አሁን ያለው የፖለቲካ ስርአት ቢቀየር የትግራይ ህዝብ አሁን በስልጣን ላይ ያሉት ሰዎች ምናልባት አምልካከታቸውን ቀይረው ዲሞክራቶች ይሆናሉ ብለን እናስብ እንደሆነ እንጅ የተለዩ ሰዎች ያገኛል ብየ አላስብም ፤ ምክንያቱም የአረናና የህዋሃት ልዩነት የግለስቦች ጸብ ብቻ ነው ብየ አስባለሁ።
በኢኮኖሚ
ሀ. በኢትዮጵያ በጣም ሀብታሙ ድርጅት ኢፈርት ነው፣ ኢፈርትም ትግራይ ውስጥ ከሃያ በላይ ግዙፍ ድርጅቶች አሉት፣ የነዚህ ድርጅቶች ክፍተኛ ገቢ የት እንደሚገባ መረጃው ባይኖረኝም እነዚህ ድርጅቶች ግን በጣም ብዙ የስራ እድል ትግራይ ውስጥ ከፍተዋል፣ ብዙ የትግራይ ወጣቶች በትግራይ ውስጥም ሆነ ከትግራይ ውጭ የዚህ ህገውጥ ድርጅት ተቀጣሪ በመሆን የሌሎች ክልሎች ወጣቶች ያላገኙትን እድል አግኝተዋል፡፡ በነገራችን ላይ የኢፈርት የገንዘብ ምንጭ በጦርነቱ ወቅት ከወሎ፣ ከጎንደር፣ ከጎጃምና ከወለጋ አካባቢዎች የተዘረፈ ገንዘብና እንዲሁም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ልማት ባንክ በትእዛዝ የተወሰደና ከጊዜ በኋላ እንዲሰረዝ የተደረገ ብድር ነው፡፡ በሌሎች ክልሎች የሌሉ በርካታና ብዙ ቢሊዮን ብር ኢንቭስት ያደረጉ ድርጅቶች የስራ እድል ሲፈጥሩ የክልሉ ህዝብ አልተጠቀመም ማለት አይቻልም።
ለ. ህወሃት በጠባብ አላማው ከጎንደርና ከወሎ በጣም ሰፊ ለም የእርሻ መሬት ዘርፏል፣ ይህንንም የእርሻ መሬት ለአባላቱና ሌሎችም የትግራይ ተዎላጆች ብቻ አከፋፍሏል፣ እንዲሁም በርካታ የትግራይ ገበሬዎች በነዚህ ለም መሬቶች ሰፍረዋል፣ እነዚህ መሬቶች ቀደም ሲል በሌሎች ሰዎች የተያዙና የሁመራ አካባቢ ደግሞ የመንግስት እርሻ የነበረ ነው፡፡ ይህንኑ የዘረፈውን መሬት ህጋዊነት ለማረጋገጥ ይመስላል ወያኔ በተለይ በወልቃይት አካባቢ የዘር ማጥፋት ዘመቻ አካሂዷል፣ በርካታ ሰዎች ተገድለዋል፣ ታፍነው ተወስደው የደረሱበት አይታዎቅም፡፡ በነዚህ መሬቶች መወሰድ ምክንያት በርካታ የጎንደር ስዎች ተፈናቅለዋል፤ ተጎድተዋል፡ የትግራይ ሰዎች ደግሞ በከፍተኛ ደረጃ ተጠቅመዋል።
ከዚህ ጋር የተያያዙ በተለይ በሁመራ አካባቢ የተደረጉ ሶስት ነገሮችን ልጥቀስ፤
በተፈጥሮ በተራቆቱ የጎንደርና የወሎ አካባቢዎች የሚኖሩ ገበሬዎች በቂ የእርሻ መሬት ስለሌላቸውና በለም አካባቢዎችም መስፈር ስለማይፈቀደላቸው ወደሁመራ አካባቢ እየሄዱ በቀን ሰራተኛነት ህወሃትን ያገለግላሉ፣ እነዚሁ ድሆች ከደጋው አካባቢ የመጡ፡በመሆናቸው ለወባና ሌሎችም ተላላፊ በሽታዎች በቀላሉ ይጋለጣሉ፣ መጀመሪያም እንደሰው የማይቆጥሯቸው የትግራይ ባለሃብቶችም ሲታመሙ አውጥተው ይዎረውሯቸዋል በርካቶችም በዚህ ሁኔታ ይሞታሉ፡፡ ይህን ሪፖርት ያደረገው በጊዜው በቦታው እርዳታ ይሰጥ የነበር የ MSF ሰራተኛ ፈረንጅ ነው። በጊዜው ሰው እንዴት በሰው ላይ እንደዚያ እንደሚጨክን በግርምት ያውራ ነበር። እንደዚህ አይነት ሰዎች ወደሁመራ ለስራ መሄድ በደርግ ጊዜም የነበረ ሲሆን በዚያን ጊዜ ግን በቂም ባይሆን እንደሰው ህክምና የማግኘት እድል ነበራቸው፡፡
ሌላው ባለፈው አመት በሚድያ እንደተነገረው በህዋሃት ካድሬዎች ደባ የቀን ሰራተኞቹ የወሎና የጎንደር በሚል በቡድን ተከፋፍለው ለሳምንታት ሲጨራረሱ የአካባቢው ፖሊስም ሆነ የወያኔ የመከላከያ ሰራዊት ግጭቱን ለማስቆም አጥጋቢ እርምጃ አልወሰዱም፡፡
ሶስተኛውና ከአመት በፊት ከስፍራው ከመጣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በነበረ ወጣት የተገለጸው የቀን ሰራተኞቹ የሰሩበት ደመዎዝ ተከፍሏቸው ከወያኔ እርሻዎች ሲወጡ በቅርብ ርቀት በሽፍቶች በተደጋጋሚ መዘረፋቸው ነው፣ በኋላ የቀን ሰራተኛ የነበረው ይህ ወጣት ያረጋገጠው ነገር ቢኖር ግን በሽፍታ መልክ መልሰው የሚዘርፉትም ቀደም ሲል ደመወዝ ከፋይ የነበሩት የእርሻዎቹ ባለቤቶች የሆኑት የህዋሃት ካድሬዎች ናቸው፡፡
በሶስቱም መንገድ የህዋሃት ካድሬዎች በነጻ ጉልበት ስራቸውን ያሰራሉ፡፡ ድሆቹ ገበሬዎች ደግሞ ወደቤተሰባቸው የመመለስ እድላቸው ዝቅተኛ ነው፡፡ ብዙዎቹ በበሽታና በእርስ በርስ ድብድብ ያልቃሉ ቀሪዎቹም በተደጋጋሚ የሰሩበት በቀጣሪዎቹ ስለሚዘረፍ ወያኔ ያዘጋጀላቸውን የባርነት ኑሮ ይቅጥላሉ።
ሐ. በኢትዮጵያ የወታደራዊ (90% በላይ የኢትዮጵያ ጀኔራሎቹ ትግርኛ ተናጋሪዎች ናቸው)፣ የደህንነት፣ የጉምሩክ፣ የኢምባሲ፣ የቴሌ፣ የመብራት ሃይል፣ የአዲስ አበባ መስተዳድር በተለይ በክፍለ ከተማና በወረዳ (አብዛኛዎቹ የአዲስ አበባ ወረዳ አስተዳዳሪዎች ትግርኛ ተናጋሪዎች ናቸው) ፣የአየር መንገድ፣ የፖስታ ቤት፣ የስኳር ፋብሪካዎችና ሌሎችም በፌደራል መንግስት ስር የሚተዳደሩ መስሪያ ቤቶች ቁልፍ ቦታዎች በአብዛኛው የተያዙት በትግርኛ ተናጋሪዎች ነው፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የእርዳታ ድርጅቶች የተባበሩት መንግስታትን ጨምሮ ትግርኛ ተናጋሪዎችን በብዛት እንዲቀጥሩ እየተደረገ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ሰዎች የሚመጡት ከትግራይ ነው ስለዚህም ትግርኛ ተናጋሪዎች ከሌላው ክልል ተወላጆች የበለጠ የስራእድል አላቸው ማለት ነው፡፡ እነዚህ አዲስ አበባን የሰማይ ጠቀስ ፎቆች ባለቤት ያደረጓት ጀኔራሎች ትግራይ ውስጥ ምንም ኢንቭስት አያደርጉም አይባልም፡፡ የየመስሪያቤቶቹን ቁንጮ ስልጣን የያዙት ትግረኛ ተናጋሪዎች በክልላቸው ኢንቨስት አያደርጉም ማለት ዘበት ነው። በአንድ ወቅት “አዲ በግዲ” ተብሎ ሁሉም ከትግራይ ውጭ የሚኖር የክልሉ ተዎላጅ በትግራይ ከተሞች ቤት እንዲሰራ ተደርጎ እና በርካታ ቤቶች ተሰርተው ተከራይ ጠፍቶ እንደነበር ይታዎሳል።
መ. የትግራይ ተወላጆች በፈደራል መንግስትና በሌሎችም ቦታዎች ባላቸው ስልጣን ተጽኖ በማድረግ በርካታ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ትግራይ ውስጥ ፕሮጄክት እንዲኖራቸው ይታዘዛሉ አንዳንዶችም ፕሮጄክቶቻቼው በቀና መንገድ እንዲሄዱላችው ቀድመው ትግራይን ይመርጣሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ትግራይ ውስጥ ቅርንጫፍ የሌለው፡የውጭም፡ሆነ የአገር በቀል ድርጅት ጥቂት ነው ብል ማጋነን አይሆንም፡፡ ትግራይ ውስጥ ደግሞ ማንም የውጭ ሆነ የአገር ውስጥ ድርጅት የሌላ ክልል ተወላጅ መቅጠር አይታሰብም ቋንቋ እንደምክንያት ይቆጠራል፤ በተቃራኒው የትግራይ ተዎላጆች በሌሎች ክልሎች ውስጥ በብዛት ይሰራሉ።
2. በማህበራዊ አገልግሎት
የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ክልሎች ጋር ሲወዳደር የተሻለ የትምህርትና የጤና አገልግሎት ያገኛል፣ በምሳሌ ላስረዳ ወያኔ ብዙ ያዎራለትን የጤና አገልግሎት ብናይ በ2000 አ. ም እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሪፖርት በትግራይ ለሚኖር 4.5 ሚሊዮን ህዝብ 15 ሆስፒታሎችና 123 ጤና ጣቢያዎች ይህም ለ304333 ህዝብ አንድ ሆስፒታልና ለ37113 ህዝብ አንድ ጤና ጣቢያ ሲሆን በአማራ ደግሞ ለ20.1ሚሊዮን ህዝብ 20 ሆሰፒታሎችና 183 ጤና ጣቢያዎች ይገኛሉ፡ ይሕም አንድ ሆስፒታል ለ1ሚሊዮን ህዝብ እና አንድ ጤና ጣቢያ ለ110636 ህዝብ ይደርሳል፡፡ ይህ ቁጥርን በሚመለከት ሲሆን በአማራ ክልል ያሉት ሆሲፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች በመስፈርቱ መሰረት የተሟላ አገልግሎት የሚሰጡ ሳይሆኑ የተሾሙ ናቸው [የተሾሙ ማለትም በወያኔ ሹመት ብቃት ስለማይጠይቅ ያለብቃታቸው ለፖለቲካ ጠቀሜታ የተሰየሙት ጤና ድርጅቶችና ትምህርት ቤቶች የተሾሙ ይባላሉ]በዚህ በወያኔ ዘመን የሚአርጉ ድርጅቶችም እንዳሉ ስነግራችሁ የቀልድ ይመስላችሁ ይሆናል፣ የአረጉ ማለት ያልተሰሩ ግን እንደተሰሩ ተደርገው ሪፖርት የሚደረጉና እንደተሰሩ ተደርጎ የወጣው ገንዘብም በየደረጃው የሚወራረድ ማለት ነው፡፡ ከጥቅሙ ተካፋይ ያልነበረ ተቆጣጣሪ ሲመጣ ድርጅቱ ማረጉ ይነገረዋል፡፡
3. በመሰረተ ልማት
ትግራይ በመሰረተ ልማት ማለትም በመንገድ ፣ በቴሌኮሙኔኬሽን ፣ በመብራት ከሌሎቹ ክልሎች በተሻለ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ በቅርቡ ሪፖርተር የሚገርም ዜና አውጥቷል አንድ ትግራይ ውስጥ ለሚሰራ መንገድ ሱር ኮንስትራክሽን የ2ቢሊዮን ብር ውል ፈረመ የመንገዱ ርዝመት 53ኪሚር ሲሆን ለአንድ ኪሎ ሜትር 40ሚሊዮን ብር ይከፈለዋል፡፡ እስካሁን በአገሪቱ ለኮንትራክተር የተሰጡ መንገዶች በኪሎሜትር ከ20ሚሊዮን አይበልጥም ነበር ይላል፡፡
4. በልማት
ባለፉት 23 አመታት ትግራይ ውስጥ በአድዋ፣ አዲግራት ፣ መቀሌ ፣ ማይጨው በርካታ ፋብሪካዎችና የአገልግሎት ሰጭ ትቋማት ተሰርተዋል እነዚህም ድርጅቶች ለብዙ ሰዎች የስራ እድል ፈጥረዋል፡፡
ከዚህ በላይ የቀረቡት መረጃዎች የሚያሳዩት ትግራይ ውስጥ የተሻለ መሰረተ ልማት ፣ ማህበራዊ አገልግሎትና በጣም የተሻለ የሰራ እድል መኖሩን ነው፡፡ ወያኔ ማእከላዊ መንግስቱን በመቆጣጠሩ ለወጣበት ክልል ልጆች የስራ እድል ፈጥሯል፡፡ ወያኔ ለትግራይ ወጣቶች ያመጣላቼው ግን የተሻለ የስራ እድልና ገንዘብ ብቻ አይደለም፤ በየሄዱበት በጥርጣሬ መታየትን በአንዳንድ ቦታም መጠላትን ጭምር እንጅ።
ይህ የወያኔ አንድን ክልል ለብቻው ሌሎችን ክልሎች በሚጎዳ መልኩ ለማሳደግ የሚደረግ ጥረት ፍሬ እያፈራ ነውን? የሚል ጥያቄ መጠይቃችን አይቀርም። መልሱ አዎ የትግራይ ህዝብ የተሻለ የትምህርት ደረጃ ፤ ዝቅተኛ የስራ አጥ ቁጥርና በተለይ በህጻናት ሞት ዝቅተኛ መጠን አስመዝግቧል።
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2011 በአሜሪካ የእርዳታ ድርጅትና በማእከላዊ ስታቲስቲክስ ድርጅት በተደረገ የህዝብና የጤና ጥናት (Demographic and health survey) መሰረት ክጥናቱ በፊት ባሉት 12 ወራት ውስጥ ምንም ስራ ያልሰሩ ወይም ያልተቀጠሩ ሴቶች በመቶ ሲለካ በትግራይ 24.8%፣ በአማራ 38.4%፤ በኦሮሚያ 43.9% ና በደቡብ ህዝቦች 44.8% ነበር። በተመሳሳይ ጥናት መሰረት በእርግዝናቸው ጊዜ በሰለጠነ ባለሙያ ምርመራ የተደረገላቸው እርጉዞች በመቶ የሚከተለውን ይመስል ነበር፤ ትግራይ 50.1% ፤ አማራ 33.6% ፤ ኦሮሚያ 31.5% ፤ የደቡብ ህዝቦች 27%. ከዚህ ላይ የትግራይም ሽፋን ቢሆን በቂ ነው ማለት አይደለም ግን ከሌሎች ክልሎች ጋር ሲውዳደር ከፍተኛ ነው።
በተመሳሳይ ጥናት መሰረት ክትባት የተከተቡ ህጻናት በመቶ ትግራይ 73.4%፤ አማራ 38.4%፤ ኦሮሚያ 26.8% ና ድቡብ ህዝቦች 38.1% ነበር።
በዚሁ ጥናት መሰረት ከአንድ አመት በታች የሆኑ ህጻናት ሞትና (IMR) ከአምስት አመታት በታች ባሉ ህጻናት የሞት መጠን በሚቀጥለው ሰነጠረዥ ቀርቧል
Tigray region got better
ከዚህ በላይ እንደሚታየው ትግራይ በሁሉም መለኪያዎች የተሻለ ደረጃ ላይ ይገኛል። ትግራይ በ 2005 የደረሰበት ደረጃ ሌሎቹ ክልሎች በ2011 ማለትም ከ5 አመታት በኋላም አልደረሱም ፤ በሌላ አነጋገር ሌሎቹ ክልሎች ትግራይ የደረሰበት ደረጃ ለመድረስ ከ7-8 አመታት ያስፈልጋቸዋል ማለት ነው።
በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ ውስጥ አንድ ቀልድ አለ እሱም ቀደም ሲል አንድ ወጣት ስታድግ ምን መሆን ትፈልጋለህ? ሲባል ፓይለት ፤ ዶክተር ማለት የተለምደ ነበር፤ ያሁኑ ወጣቶች ግን ምን መሆን ትፈልጋለህ ሲባሉ ቶሎ ብለው “ትግሬ” ይላሉ። አሁን ባቋራጭ ሀብታም የሚያደርገው ፓይለትነት ወይም ዶክተር መሆን ሳይሆን ከገዥ ጎሳ መወለድ በመሆኑ ነው።
ለማጠቃለል ያህል በሁሉም መስፈርቶች የትግራይ ክልልም ሆነ ግለሰብ ትግርኛ ተናጋሪዎች የወያኔ ከፋፍለህ ግዛ ስርአት ተጠቃሚዎች እየሆኑ ነው ይህም እንዲቀጥል ወያኔ ሌሎች ክልሎች ብቃት ባላቸው ሰዎች እንዳይተዳደሩና ለእድገት ጥረት እንዳያደርጉ ሌሊት ከቀን ተግቶ ይሰራል። የክልል ፕሬዘዳንቶችን ይሽራል፤ ይሾማል፤ ይቆጣጠራል። ህዝብን ከህዝብ ያጋጫል ፤ ያፈናቅላል። ሲፈልግ አመጽ ያስነሳል፤ አመጹን ልቆጣጠር በማለት ይገድላል ፤ ያስራል፤ ከስራም ያፈናቅላል።
የዚህ ሁሉ ግፍ ቁናው ሞልቶ ዶክተር መረራ በተደጋጋሚ እንደሚሉት የሚበላው ያጣ ህዝብ መሪዎቹን ሳይበላ ሊታሰበብት ይጋባል እላለሁ።
ቸር ይግጠመን።Andasr1983@gmail.com

Monday, June 9, 2014

2014 Golden Pen of Freedom Awarded to Eskinder Nega of Ethiopia

June 9, 2014
(WAN-IFRA) – “This Golden Pen is more important than food, medicine and water. It materializes the support and shows that he is not forgotten. That he is one of us. That an attack on one journalist is an attack on us all and that jailing a journalist is a crime against humanity,” Swedish journalist Martin Schibbye says, accepting the 2014 Golden Pen of Freedom, the annual press freedom prize of the World Association of Newspapers and News Publishers (WAN-IFRA), on behalf of imprisoned Ethiopian publisher, journalist and blogger Eskinder Nega.
The honour is formally bestowed on Nega in a ceremony at the 66th World Newspaper Congress, under way in the Italian city of Torino this week, where more than 1,000 media industry representatives have gathered.
Nega is serving an 18-year jail sentence in Addis Ababa’s notorious Kaliti prison, convicted on trumped-up terrorism charges after daring to wonder in print whether the Arab Spring could reach Ethiopia, and for criticising the very anti-terrorism legislation under which he was charged. Arrested in 2011, he was sentenced on 23 January 2012 and denounced as belonging to a terrorist organisation.
Imprisoned at least seven times in the past decade for committing fearless acts of journalism, Nega is a celebrated intellectual and a relentless fighter for freedom of expression. “Eskinder Nega has become an emblem of Ethiopia’s recent struggle for democracy,” World Editors Forum President Eric Bjerager says, delivering the Golden Penduring the opening ceremony of the World Newspaper Congress and the World Editors Forum in Torino. “No stranger to prison, he is also an unforgettable warning to every working Ethiopian journalist and editor that the quest to create a just, free society comes with a heavy price,” Bjerager says.The honour is formally bestowed on Nega in a ceremony at the 66th World Newspaper Congress
Nega’s former prisonmate, Swedish journalist Martin Schibbye, accepts the award on the jailed journalist’s behalf, at the invitation of Nega’s family. He paints a dark picture of life inside Kaliti Prison. “The rooms are more like barns with concrete floors, and it is so crowded that you have to sleep on your side,” he says. “Prisoners are packed likes slaves on a slaveship. Once a month an inmate leaves with his feet first.”
But disease and torture are not the hardest part of life inside Kaliti, according to Schibbye. “It (is) the fear of speaking. It’s not the guard towers with machine guns that keep the prison population calm. It is the geography of fear. People who speak politics are taken away. They disappear.” Schibbye is a freelance journalist who was jailed for 14 months in Kaliti Prison, along with his photographer Johan Persson. They were pardoned and released in September 2012.
“In (Kaliti), fearless people like Eskinder Nega helped the whole prison population to keep their dignity. By still writing. Protesting. Not giving up. He helped us all maintain our humanity. But there is one thing I know that even Eskinder fears. That is to be forgotten,” Schibbye says.
“When you’re locked up as a prisoner of conscience, this is the greatest fear, and the support from the outside is what keeps you going. This Golden Pen Award will not set him free tomorrow, but it will ease his day today. He will go with his head high knowing that he is there for a good cause. That the pain and suffering has a meaning.”
WEF President Erik Bjerager tells the ceremony that the world needs to watch the creeping threat of anti-terrorism legislation being used to target journalists. “Ethiopia continues to resort to anti-terrorism legislation to silence opposition and shackle the press. Alarmingly, beyond Ethiopia, countless states around the world are misusing anti-terrorism legislation to muzzle journalists, bloggers and freedom of expression advocates,” Bjerager says. “Research suggests that over half of the more than 200 journalists in jail last year were being held on ‘anti-state’ charges. Let me be clear: Journalism is not terrorism. Politicians should not abuse the notion of national security to protect the government, powerful interests or particular ideologies, or to prevent the exposure of wrongdoing or incompetence.”
Schibbye concludes his acceptance speech, reading from a moving letter penned by Nega to his eight-year-old son. It was smuggled out of Kaliti prison: “The pain is almost physical. But in this plight of our family is embedded hope of a long suffering people. There is no greater honour. We must bear any pain, travel any distance, climb any mountain, cross any ocean to complete this journey to freedom. Anything less is impoverishment of our soul. God bless you, my son. You will always be in my prayers.”
Schibbye tells a tearful audience: “When I read these words by Eskinder I know that they will never break him. Because he is in peace with himself. He knows that even though he is chained, robbed of his physical freedom, the freedom to talk or to be silent, the freedom to drink or eat, and even to shit. He knows, as do all prisoners of conscience, that you have it in you to keep the most valuable, the freedom that nobody can take from you, the freedom to determine who you want to be. Eskinder is a journalist. And every day he wakes up in the Kaliti prison is just another day at the office.”
Nine more journalists were jailed in the past month in Ethiopia, as the election campaign started. “The crackdown was a flashing alarm to the world that no one is safe. That there is a hunting season for journalists in Addis Abeba. But despite this difficult situation there is light,” Schibbye says.
“Eskinder Nega’s courage has turned out to be contagious; a new generation is stepping up. A generation of young cheetahs have been taking enormous risks writing, tweeting and speaking truth to power, demanding the jailed to be released. It is hopeful. It shows that they can jail journalists but they can newer succeed in jailing journalism. Words led Eskinder Nega to the Kaliti prison. And in the end it must also be words that set him free,” Schibbye tells a clearly emotional audience.
“When I see this Golden Pen of his, I look back, and think of Eskinder who is left behind in the chaos, on the concrete floor, between walls of corrugated steel I feel sick to the stomach. But then I remember his smile and his strength and I think that at the end of the day, it’s not us that are fighting for his freedom – but rather he who is fighting for ours. AyzohEskinder! Ayzoh! (translation: be strong, chin up).”
Note: The Golden Pen of Freedom is an annual award made by WAN-IFRA to recognise the outstanding action, in writing or deed, of an individual, a group or an institution in the cause of press freedom. Established in 1961, the Golden Pen of Freedom is presented annually and is amongst the most prestigious awards of its kind throughout the world. Behind the names of the laureates lie stories of extraordinary personal courage and self-sacrifice, stories of jail, beatings, bombings, censorship, exile and murder. One of the objectives of the Golden Pen is to turn the spotlight of public attention on repressive governments and journalists who fight them. Often, the laureate is still engaged in the struggle for freedom of expression and the Pen has, on several occasions, secured the release of a publisher or journalist from jail or afforded him or her a degree of protection against further persecution.

የየመን መገናኛዎች ካሉት….. የኢትዮጵያዊውን ሬሳ አውጥተው የራሳቸውን ቀበሩ… 100 ኤርትራዊያን ባህር ላይ ሰመጡ

June 9/2014
በግሩም ተ/ሀይማኖት

ወደ የመን የሚገባው ሰደተኛ ቁጥር ከዕለት ዕለት እየጨመረ ነው፡፡ አሁን አሁን የኤርትራዊያኑም ስደተኞች ቁጥር እንዲሁ እየጨመረ ነው፡፡ በትላንትናው እለት ከኤርትራ ተነስቶ ወደ የመን እየተጓዘ የነበረ 60 ኤርትራዊያንን የጫነ ጀልባ ባብል መንደብ የሚባለው የየመን ድንበር አካባቢ ሰመጠ፡፡ የተጫኑት በሙሉ ማለቃቸውን የዛሬ ጋዜጦች ዘግበዋል፡፡ ከሶስት ቀን በፊትም በተመሳሳይ ሁኔታ ከኤርትራ የተነሳ እና ኤርትራዊያንን የጫነ ጀልባ ሰምጦ 40 ሰዎች መሞታቸውን ጋዜጦች ዘግበዋል፡፡ በአጠቃላይ ከ100 በላይ ኤርትራዊያ በጀልባ መስመጥ ምክንያት በሶስት ቀን መሞታቸውን የተለያዩ ጋዜጦች ዘግበዋል፡፡

አልዮም የመን Yemen Today የተባለው ዕለታዊ ጋዜጣ ባለፈው ሳምንት በሁለት እትሙ ስለ ኢትዮጵያዊያን ስቃይ አስፍሯል፡፡ ሰሞኑን በነበረብኝ የልጄ መታፈን ችግር ምክንያት በሰዓቱ ተርጉሜ ለማቅረብ አልቻልኩም ነበር፡፡ ባብል መንደብ የሚባለው አካባቢ የመናዊያኖቹ የአንድ ኢትዮጵያዊ ሬሳ አውጥተው የራሳቸውን ሬሳ መቅበራቸውን ይፋ አውጥቷል፡፡ ይህንንም ሁኔታ በአካባቢው ያሉ ድርጊቱ ያሳዘናቸው የመናዊያኖች ማጋለጣቸውን ጭምር አስፍሯል፡፡ እዚሁ ባብል መንደብ አካባቢ በአንድ ወቅት ስሄድ ከ500 ሜትር ርዝመት በላይ ያለ ቦታ ላይ በየመንገዱ የሞቱ የኢትዮጵያዊያን ሬሳ ተቀብሮ ለማየት ችያለሁ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ከሶማሊያዋ አነስተኛ ወደብ ቦሳሶ ተነስተው ወደ የመን ከገቡ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ውስጥ 50 የሚሆኑትን ባለፈው ሳምንት በፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል፡፡ ምክንያትም ሲሰጡ የአል-ቃይዳ ግሩፖች ይንቀሳቀሱብታል በሚባለው እና ዋና ቤዛቸው አቅራቢያ ስላገኙዋቸው መሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡ በእርግጥም ሶማሊያዊያኑ ህገ-ወጥ አጓጓዦች በጣም ችግር ባለበት ሸቡዋ በሚባለው ቦታ ነው ያወረዷቸው፡፡ የUNHCR ቢሮ ሰራተኞች ለስደተኞቹ ወደ ከተማ እንዲገቡ ለ20 ቀን የሚያገለግል የይለፍ ወረቀት የሰጧቸው ሲሆን ይህን ወረቀት ፖሊሶቹ ቀደው ስደተኞቹን እንዳሰሩ ነው ጋዜጣው የዘገበው፡፡ የመን አልዮም ጋዜጣ በዘገባውም ሲያክል የይለፍ ወረቀቱን የቀደዱት እና እነሱን በቁጥጥር ስር ያዋሉት ቦታው በጣም አስቸጋሪ በመሆኑ አሸባሪዎቹ የአል-ቃይዳ ቡድኖች አፍነው ወደ እነሱ እንዳያስገቡዋቸው ሲሉ መሆኑን የሸቡዋ የፖሊስ ጣቢያ አዛዥ መግለጻቸውንም ጨምሮ አስፍሯል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ከሶማሊያ የሚነሱት ስደተኞች የሚወርዱበት የየመን ድንበር ሸቡዋ የሚባለው በአል-ቃይዳ ሀይሎች ቁጥጥር ስር ስለሆነ ከዚህ ቀድሞ ችግር የገጠማቸው እንኳን መኖራቸው ባይሰማ ከዚህ በኋላ ችግር ሊገጥማቸው እንደሚችል ማሰቡ አይከብድም፡፡ እባካችሁ…..