Friday, May 23, 2014

በሕገ ወጥ መንገድ ፖሊስ ለ7 ሰአት የቆየ ብርበራ አካሄደ

May 23/2014
ያለ በቂ ማስረጃ በሕገ ወጥ መንገድ ከአራት ሳምንት በፌት ከተያዙት ስድስቱ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን በተጨማሪ በአንድ ጦማሪ አባል መኖሪያ ቤት ላይ ፖሊስ ለ7 ሰአት የቆየ ብርበራ አካሄደ፡፡

በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 12 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ በዞን ዘጠኝ ጦማሪና መስራች ሶልያና ሽመልስ ቤተሰብ መኖሪያ ቤት ፖሊስ ብርበራ ያካሄደ ሲሆን የጸረ-ሽብር ሕጉ ይፈቅድልናል የሚል ምክንያት ሰጥተው ያለ ፍርድ ቤት የብረበራ ማዘዣ ከካሜራ ቀራጭ ጋር የተገኙት ሰባት ፖሊሶች በጦማሪዋ ክፍል እና ሌሎች አስፈላጊ ነው ባሉዋቸው ክፍሎች ሲያካሂዱ ነበረውን ብርበራ ጨርሰው ይጠቅመናል ያሉትን የዶ/ር መረራ ጉዲና የመጨረሻ መጽሀፍ እና ሌሎች ወረቀቶች ወስደው ቤት ውስጥ የነበሩትን የጦማሪዋን ወላጅ እናት አስፈርመው ከጠዋቱ 4 ሰአት አካባቢ ቤቱን ለቀው ወጥተው ነበር፡፡ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ተመልሰው በመምጣት ተጨማሪ ፍተሻ በዋናው መኖሪያ ቤት መካሄድ እንፈልጋለን ብለው ሁለተኛ ዙር ብርበራ በምግብ ማብሰያ ክፍል ውስጥ እናካሂዳከን በሚል ሰበብ ትንሹ ክፍል ውስጥ የጦማሪዋን እናት እነዲወጡ በማግለል ከማቀዝቀዛውን አንቀሳቅሰው አፍታም ሳይቆዩ 19 ገጽ የግንቦት ሰባት ፕሮግራም አግኝቻለሁ ሲል አንዱ ፈታሽ ተናግሯል፡።


የጦማሪዋን ወላጅ እናት እነዲፈርሙ ያግባቡ ቢሆንም ወላጅ እናትዋ ከክፍሏ እና ሌላም ቦታ በመፈተሽ ስታገኙ ያየሁት ወረቀት ላይ ፈርሜያለሁ ይህ ግን ምግብ ማብሰያ ክፍል ውስጥ ያልነበረ እና እዚህ ያልተገኘ ሌላ ወረቀት ነው ሲገኝም አላየሁም በማለት አልፈርምም ብለዋቸዋል፡፡ በመሆኑም ፈታሾች ተጨማሪ የሰው ሃይል ደውለው በማስጠራት ለማግባባት ቢሞክሩም ስላልተሳካላቸው ይዘዋቸው የመጡትን የራሳቸውን ሁለት ምስክሮች ብቻ አስፈርመው ባለቤትዋ ለመፈረም ፍቃደኛ አይደሉም ብለው ቤቱን ለቀው ሄደዋል፡፡ ከፓሊስ ጋር የመጡት ምስክሮች አንደኛው አድራሻቸው በብርበራ ምስክርነት ዶክመንቱ ላይ ያልተጻፈ መሆኑንም ለመረዳት ችለናል ፡፡


በብርበራው ወቅት በነበራቸው የ7 ሰአት ቆይታ የጦማሪዋን መጸሃፍት የጉዞ ትኬቶች የስልጠና ማንዋል እና የመሳሰሉትን ጥቃቅን ወረቀቶች የወሰዱ ሲሆን ማብሰያ ክፍል ከፍሪጅ ጀርባ አገኘነው ካሉት ወረቀት ግን ቤት ውስጥ ያልነበረና ፓሊሶች ራሳቸው ያመጡት በመሆኑ እናትዋ ተናግረዋል፡፡
የዞን ዘጠኝ ጦማሪ አባላት ከየትኛውም በፓርላማ በአሸባሪነት ከተፈረጀ የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆኑና ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸው እነዲሁም አነዚህ ድርጅቶች ላይ በተለያየ አጋጣሚ ትችቶቻቸውን ሲያቀርቡና ሲቃወሙ የሚታወቁ ቢሆንም ሲሆን በተያዙት አባሎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው አስገድዶ ለሃሰተኛ መረጃ እንዲፈርሙ የማድረግ ተግባር ሳያንስ ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ለማያያዝ ማስረጃን እንደተገኘ አድርጎ የማቅረቡ ተግባር መንግሰት ይታማበት የነበረውን የፓለቲካ ውንጀላን በሽብር የመቀየር ክስ በተግባር እንድናይ ያስቻለን ነው ፡።
በመሆኑም አሁንም ቢሆነ ጦማሪ ጓደኞቻችን ሃሳባቸውን በነጻነት ከመግለጻቸው ውጪ ምንም አይነት የወንጀልም ሆነ ሽብር ከተፈረጁ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት እንደሌላቸው እያስታወስን መንግስት ያሰራቸውን ጦማርያን እና ጋዜጠኞች አንዲፈታ አሁንም አንጠይቃለን፡፡
#‎FreeZone9bloggers‬‪#‎FreeEdom‬ ‪#‎FreeTesfalem‬ ‪#‎FreeAsemamaw‬ ‪#‎Ethiopia‬
Photo: በሕገ ወጥ መንገድ ፖሊስ ለ7 ሰአት የቆየ ብርበራ አካሄደ፡፡ #FreeZone9bloggers #FreeEdom #FreeTesfalem #FreeAsemamaw #Ethiopia
Minilik Salsawi Via Zone 9
ያለ በቂ ማስረጃ በሕገ ወጥ መንገድ ከአራት ሳምንት በፌት ከተያዙት ስድስቱ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን በተጨማሪ በአንድ ጦማሪ አባል መኖሪያ ቤት ላይ ፖሊስ ለ7 ሰአት የቆየ ብርበራ አካሄደ፡፡
በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 12 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ በዞን ዘጠኝ ጦማሪና መስራች ሶልያና ሽመልስ ቤተሰብ መኖሪያ ቤት ፖሊስ ብርበራ ያካሄደ ሲሆን የጸረ-ሽብር ሕጉ ይፈቅድልናል የሚል ምክንያት ሰጥተው ያለ ፍርድ ቤት የብረበራ ማዘዣ ከካሜራ ቀራጭ ጋር የተገኙት ሰባት ፖሊሶች በጦማሪዋ ክፍል እና ሌሎች አስፈላጊ ነው ባሉዋቸው ክፍሎች ሲያካሂዱ ነበረውን ብርበራ ጨርሰው ይጠቅመናል ያሉትን የዶ/ር መረራ ጉዲና የመጨረሻ መጽሀፍ እና ሌሎች ወረቀቶች ወስደው ቤት ውስጥ የነበሩትን የጦማሪዋን ወላጅ እናት አስፈርመው ከጠዋቱ 4 ሰአት አካባቢ ቤቱን ለቀው ወጥተው ነበር፡፡ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ተመልሰው በመምጣት ተጨማሪ ፍተሻ በዋናው መኖሪያ ቤት መካሄድ እንፈልጋለን ብለው ሁለተኛ ዙር ብርበራ በምግብ ማብሰያ ክፍል ውስጥ እናካሂዳከን በሚል ሰበብ ትንሹ ክፍል ውስጥ የጦማሪዋን እናት እነዲወጡ በማግለል ከማቀዝቀዛውን አንቀሳቅሰው አፍታም ሳይቆዩ 19 ገጽ የግንቦት ሰባት ፕሮግራም አግኝቻለሁ ሲል አንዱ ፈታሽ ተናግሯል፡።
የጦማሪዋን ወላጅ እናት እነዲፈርሙ ያግባቡ ቢሆንም ወላጅ እናትዋ ከክፍሏ እና ሌላም ቦታ በመፈተሽ ስታገኙ ያየሁት ወረቀት ላይ ፈርሜያለሁ ይህ ግን ምግብ ማብሰያ ክፍል ውስጥ ያልነበረ እና እዚህ ያልተገኘ ሌላ ወረቀት ነው ሲገኝም አላየሁም በማለት አልፈርምም ብለዋቸዋል፡፡ በመሆኑም ፈታሾች ተጨማሪ የሰው ሃይል ደውለው በማስጠራት ለማግባባት ቢሞክሩም ስላልተሳካላቸው ይዘዋቸው የመጡትን የራሳቸውን ሁለት ምስክሮች ብቻ አስፈርመው ባለቤትዋ ለመፈረም ፍቃደኛ አይደሉም ብለው ቤቱን ለቀው ሄደዋል፡፡ ከፓሊስ ጋር የመጡት ምስክሮች አንደኛው አድራሻቸው በብርበራ ምስክርነት ዶክመንቱ ላይ ያልተጻፈ መሆኑንም ለመረዳት ችለናል ፡፡
በብርበራው ወቅት በነበራቸው የ7 ሰአት ቆይታ የጦማሪዋን መጸሃፍት የጉዞ ትኬቶች የስልጠና ማንዋል እና የመሳሰሉትን ጥቃቅን ወረቀቶች የወሰዱ ሲሆን ማብሰያ ክፍል ከፍሪጅ ጀርባ አገኘነው ካሉት ወረቀት ግን ቤት ውስጥ ያልነበረና ፓሊሶች ራሳቸው ያመጡት በመሆኑ እናትዋ ተናግረዋል፡፡
የዞን ዘጠኝ ጦማሪ አባላት ከየትኛውም በፓርላማ በአሸባሪነት ከተፈረጀ የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆኑና ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸው እነዲሁም አነዚህ ድርጅቶች ላይ በተለያየ አጋጣሚ ትችቶቻቸውን ሲያቀርቡና ሲቃወሙ የሚታወቁ ቢሆንም ሲሆን በተያዙት አባሎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው አስገድዶ ለሃሰተኛ መረጃ እንዲፈርሙ የማድረግ ተግባር ሳያንስ ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ለማያያዝ ማስረጃን እንደተገኘ አድርጎ የማቅረቡ ተግባር መንግሰት ይታማበት የነበረውን የፓለቲካ ውንጀላን በሽብር የመቀየር ክስ በተግባር እንድናይ ያስቻለን ነው ፡።
በመሆኑም አሁንም ቢሆነ ጦማሪ ጓደኞቻችን ሃሳባቸውን በነጻነት ከመግለጻቸው ውጪ ምንም አይነት የወንጀልም ሆነ ሽብር ከተፈረጁ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት እንደሌላቸው እያስታወስን መንግስት ያሰራቸውን ጦማርያን እና ጋዜጠኞች አንዲፈታ አሁንም አንጠይቃለን፡፡

በአዲስ አበባ ከሚፈርሱ ቤቶች ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ እየተከሰተ ነው

May23/2014
ግንቦት ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን ተጠናክሮ በቀጠለው የቤት ፈረሳ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በድንገት ቤቶቻቸው እየፈረሱባቸው ንብረቶቻቸውን እየተዘረፉ ሜዳ ላይ እየወደቁ ሲሆን፣ ትናንት ሌሊት በድንኳን ተጠልለው ከነበሩት ነዋሪዎች መካከል የ4 ልጆች አባት የሆኑ ግለሰብ በጅብ ተበልተው ዛሬ ከፊል አካላቸው በፖሊሶች መነሳቱን የአካባቢው ሰዎች ለኢሳት ገልጸዋል።

ፖሊሶች መረጃው እንዳይወጣ አካባቢውን ተቆጣጥረው ሰዎች እንዳይንቀሳቀሱ ሲያደርጉ የዋሉ ሲሆን፣ ቀሪው አስከሬን ከተነሳ በሁዋላ ደግሞ በማይክራፎን እየዞሩ በላስቲክ ድንኳን የተጠጉትን ሰዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ እያዘዙዋቸው ነው። ብዙዎቹ ልጆቻቸውን የት እንደሚያስጠጉዋቸው ጨንቋቸው ለኢሳት በመደውል የድረሱልን ጥሪ አቅርበዋል የሟቹን ግልሰብ ስም ለማግኘት ጥረት ብናደርግም እስካሁን አልተሰካላንም።ፖሊስ አስፈላጊውን መረጃ እንዲሰጠን ተደጋጋሚ ሙከራ ብናድርግም አልተሰካላንም።

ቤታቸው የፈረሰባቸው ሰዎች ለኢሳት በጻፉት የጋራ ደብዳቤ ደግሞ ፣ እንደ አዲስ ሰሞኑን የሚፈርሱ ቤቶች በዓለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ተስፋ በተደረገ ፈንድ ለሚገነባው የኦሎምፒክ መንደር ፕሮጀክት ቦታ ለማዘጋጀት ሲባል በመሆኑ ኦሎምፒክ ኮሚቴው የህዝቡን ስቃይ አይቶ፣ ድጋፉን እንዲያዘገይ ጠይቀዋል።

ነዋሪዎቹ በደብዳቤያቸው “የኢትዮጵያ መንግስትና የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ከዓለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ 2 ሚሊዩን የኢትዮጵያ ብር እንደሚሰጣቸው” ገልጸዋል።

“በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በሦስት ቀናት ውስጥ መኖሪያቸውን ነቅለው ከአካባቢው እንዲወጡ ጥብቅ ትዕዛዝ የተላለፈው ከዚህ ፕሮጅክት ጋር በተያያዘ መሆኑን ነዋሪዎች በደብዳቤያቸው ጠቁመዋል።

ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ” የተሰጣቸው ማስጠንቀቂያ ከዚህ በፊት ቤታቸውን ነቅለው አካባቢውን እንዲለቁ በተደጋጋሚ እንደ ተገለጸላቸው የሚጠቁም  ቢሆንም ፣  ከዚህ በፊት ቤት ግን አንድም ቀን ነዋሪዎቹ ነቅለው እንዲነሡ እንዳልተነገራቸውና ደብዳቤም ተጽፎላቸው እንደማያውቅ” ጠቅሰዋል፡፡

በሦስት ቀናት ውስጥ ቤቶች እንዲፈርሱ የታዘዘበት ምክንያት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቋማት ሁሌም እንደ ሚያደርጉት የኗሪዎችን ቤት ነቅለው በመወሰድ እንጨቶችን፣ ቆርቆሮዎችን፣ በሮችንና መስኮቶችን በወረዳ አሰተዳደር ቅጥር ግቢ እያጫረቱ በመሸጥ ቤት አፍራሾቹና አመራሩ እንዲካፈሉት ለማድረግ መሆኑን ነዋሪዎች ይገልጻሉ።

“የወረዳው ዋና ሥራ አስፈጻሚ  ከክፈለከተማው አስተዳደር የመጣ ትእዛዝ ነው ምንም ማድረግ አልችልም የሚል መልስ ለአቤቱታ አቅራቢዎች ሲሰጡ፣ የክፍለ ከተማው አስተዳዳሪ አቶ ደስታ ደግሞ አቤቱታ አቅራቢዎች ከቢሯቸው እንዲባረሩ ማስደረጋቸውን ነዋሪዎች በጽፋቸው አስፍረዋል።

ኗሪዎች በንብረታቸው ላይ ሊካሄድ የታቀደውን ዝርፍያ በመፍራት የቤቶቻቸውን ጣራና በር አንስተው ዘመድ ያለው ከዘመድ የሌላቸው ደግሞ ላስትክ ዘርግተው በተጠለሉበት ቅዳሜና እሁድ ባለማቋረጥ የዘነበውን ዝናብ በላያቸው ማሳለፋቸውን፣ አራስ እናቶች እና አዲስ የተወለዱ ሕጻናት፣  ነፍሰጡር ሴቶች  በበሽታ ላይ መውደቃቸውንም አመልከተዋል።

የኢህአደግ መንግስት በሕይወት እያለን ገድሎን በድኖቻችንን በሜዳ ላይ በትኗል የሚሉት ነዋሪዎቹ፣  በካሬ እስከ ሠላሳ ሺ ብር ድረስ የሚያጫርቱትን የአዲስ አበባ መሬት 18 ብር ብቻ ተቀብለው እንዲለቁ የታዘዙ በዙሪያችን ያሉ የኦሮሚያ አርሶ አደሮች እያለቀሱ እንደሚገኙም ገልጸዋል።

ነዋሪዎቹ በደብዳቤያቸው መጨረሻ ” የኦለምፒክ ፌዴሬሽን በዓላማውና ባለው እሴት ሰብዓዊ መብትን ከሚጋፋ ተግባር ጋር የማይተባበር ተቋም ቢሆንም በጭካኔ ከሚታወቀው የኢትዮጵያ መንግስት መተባባሩን ኮንነዋል።

” በኢትዮጵያውያን ላይ በኦሎምፒክ ኮሚቴ ስም እያረፈ ያለውን ሊረሳ የማይችል ጠባሳ በተመለከተ  በማስገንዘብ በእኛ ላይ ለሚፈጸመው ግፍ ከዓለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የሚያገኘውን ፈንድ እንዲቆምላቸው” ጠይቀዋል።

ከአለማቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴው ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎችም ጉዳዩን እንዲያደርሱላቸው ተማጽነዋል።
ደብዳቤውን የጻፉትን ሰዎች በስልክ አነጋግረን እንደተረዳነው፣ ደብዳቤያቸውን ከጻፉ 2 ሳምንታት ያለፈው ሲሆን፣ መንግስት የሚወሰድውን እርምጃ በመፍራት እስካሁን ይፋ ለማድረግ ሳይፈልጉ ቀርተዋል።

በኮልፌ ቤቱ የፈረሰበት አባወራ በጅብ ሲበላ አንዲት ወላድ በድንጋጤ ህይወቷ አለፈ

May23/2014
‹ቪዛ ይሰጠንና ወደ ሱማሌያ ቢሆንም እንሂድ›› ቤታቸው የፈረሰባቸው>>
ዳዊት ሰለሞን 
በኮልፌ ቀራኒዮ አለም ባንክ አካባቢ ህገ ወጥ የመሬት ወረራ በማድረግ ቤቶችን ሰርታችኋል የተባሉ ዜጎች ቤቶቻቸው በላያቸው ላይ በሀይል ፈርሶ ንብረታቸው መወረሱን አመለከቱ፡፡ ከ15.000 የሚልቁ ነዋሪዎች በሚገኙበት አለም ባንክ አካባቢ ሰዎቹ አነስተኛ መጠለያ ያረፉባቸውን ቤቶች ከገበሬዎች ላይ በመግዛት መኖር ከጀመሩ አመታት መቆጠሩን ያስረዳሉ፡፡ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት ልከውና ወደ ስራ በተሰማሩበት ቅጽበት ከጸጥታ ሰራተኞች ጋር አካባቢውን የወረሩት አፍራሽ ግብረ ሃይሎች መኖሪያ ቤቶቹን ማፍረሳቸውን በሀዘን ተውጠው ገልጸዋል፡፡ ቤቶቹ በድንገት መፍረሳቸውን በመቃወም ድምጻቸውን ያሰሙ የአካባቢው ነዋሪዎች በፖሊሶች ክፉኛ መደብደባቸውንና መወሰዳቸውን የአይን እማኞች አስረድተዋል፡፡ቤቷ ሲፈርስ የደነገጠች እመጫት ወዲያኑ ህይወቷ ሲያልፍ ቤቱ በመፍረሱ መሄጃ ያጣ አባወራ ላስቲክ ዘርግቶ በተኛበት ጅብ ጎትቶት ወስዶት በልቶታል፡፡በጅብ የተበላው አባወራ ስርዓተ ቀብርም ዛሬ መፈጸሙ ታውቋል፡፡ ቤታቸው ፈርሶ ለጎዳና እንደተዳረጉ የሚናገሩ ሰዎች‹‹ኢትዮጵያዊነታችን ተሰርዟል፣ቪዛ ይሰጠንና ሌላው ቢቀር ወደ ሶማሊያ እንድንሄድ ይደረግ ›› ብለዋል፡፡

አረና አመራሮች በሐውዜን ከተማ አዳራሽ ውስጥ ታግተዋል

May23/2014

ፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ በሰበር ዜናው እንደገለጸው አረና ትግራይ ለሉአላዊነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ በዛሬው ዕለት በሀውዜን ከተማ ከ3፡00 ሰዓት ጀምሮ ሕዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ በዝግጅት ላይ እንዳለ ከመቀሌ የመጡ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ደርሰው እኛ ሰላማዊ ሰልፍ ስለምናደርግ ስብሰባ የሚባል ነገር የለም በማለት ወደ አዳራሹ የሚመጣውን ሰው ድንጋይ በመወርወር ስብሰባው እንዳይካሄድ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ስብሰባውን እንዲታደም ሲቀሰቅሱ የነበሩ አንድ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና ሁለት አባላት ታርጋ በሌላቸው ሞተር ሳይክሎች በመግጨት አደጋ አድርሰውባቸዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት አዳራሹ ውስጥ ተዘግቶብን ዙሪያውን ተከበናል ፖሊስ መቆጣጠር ስላልቻለ ተጨማሪ ኃይል ጠይቋል ሲሉ የአረና አመራር ለፍኖተ ነፃነት ገልጸዋል፡፡

ከአሁን ቀደም በአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የትውልድ ስፍራ ወላይታ ከተማ በተደራጁ ሰዎች ዝርፊያና ታርጋ በሌላቸው ሞተር ሳይክሎች አደጋ ለማድረስ መሞከራቸውን ፍኖተ ነፃነት መዘገቧ የሚታወስ ነው፡፡

ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ዙሪያ መረጃ እንዳያቀርብ ታገደ

May23/2014


በሳውዲ አረቢያ እና በመካከለኘው ምስራቅ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በደል እና ስቃይ በማለዳ ወጎቹ ዘገባው የሚታወቀው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ በመረጃ ቅበላው ባልተደስቱ ወገኖች ለእስር መዳረጉ ይታወሳል። ነብዩ ሲራክ ላለፉት ሁለት አስርት አመታት ከኖረባት ሳውዲ አረቢያ «ጅዳ» ከተማ በስሙ በከፈተው ሶሻል ሚዲያ እና ከቅርብ ግዜ ወዲህ የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ወኪል በመሆን በአረቡ አለም የሚገኙ ወገኖች የሚያሰሙትን እሮሮ በማስተጋባት በህዝብ ዘንድ ክብር እና አድናቆትን ያተረፈ ጋዜጠኛ ነው።

ይህ ጋዜጠኛ እንደማንኛውም ሰው የስደት አለም ህይወቱን ለመግፋት በግል ተቀጥሮ ከሚሰራበት መ/ቤት የስራ ሰዓት ውጭ የእረፍት ግዜውን መስዋት በማድረግ ሰለቸኝ፡ ደከመኝ ሳይል «ሳይማር ያስተማረውን ወገኑን» በሙያው ሲያገለግል የኖረ ጋዜጠኛ መሆኑ በአብዛኛው ኢትዮጵያውያን ዘንድ ይነገራል። ነብዩ ሲራክ በሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈፀሙ ቅጥ ያጡ ግፍ እና በደሎች መቋጫ ይበጅላቸው ዘንድ በሚያቀርባቸው ተከታታይ ዘገባዎቹ በስልክ እና በጽሑፍ ይሰነዘሩበት ለነበሩ ስድብ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ቅንጣት ያህል ሳይሸበር ወህኒ እስከገባበት ዕለት የወገኑን ህይወት ለመታደግ ከማለዳ ወግ የመረጃ ቅበላው ባሻገር በስው ሃገር በወረበሎች የታገቱ እህቶቻችንን ነጻ ለማውጣት ከህግ አስከባሪዎች ጎን ቆሞ የአጋች እና ታጋች ድራማ በሠላም እንዲጠናቀቅ ያደረገ ከህዝብ የወጣ ለህዝብ የኖረ ኢትዮጵያዊ ነው።
ከዚህ ባሻገር ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ የሳውዲ አረቢያ መንግስት ለውጭ ሃገር ዜጎች ያወጣውን የ 6 ወር እና የ 3 ወር የግዜ ገደብ መጠናቀቅ ተከትሎ ሰነዶቻቸውን ለማስተካከል ጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት አይን ያልገልጹ ህጻናት ልጆቻቸውን ታቀፈው በጠራራ ጸሃይ ሲነፍሩ ለነበሩ እናቶች እና በስደት አለም ግራ ተጋብተው በተስፋ ቆንስላ ጽ/ቤት በር ላይ ድንጋይ ተንተርሰው ጸሃይ እና ነፋስ ሲፈራረቅባቸው ለነበሩ ዜጎች ቀዝቃዛ ውሃ በማደል ከሰው ምስጋናንን ከፈጣሪ ጽድቅን ያገኘ ሩሩሁ እና ለወገን አዛኝ መሆኑ ይታወቃል።
በሰው ሃገር ተስፋ ሰንቀው ግፍ በደሉ የስደት አለም ኖሮቸውን መቅኔ ላሳጣው ወገኖች ድምጽ በመሆን የሚታወቀው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በቆንስላው ጽ/ቤት በአግባቡ መስተናገድ እና ፈጣን የሆኑ አገልግሎቶችን ማግኘት እንደሚገባው ባቀረበው የመፍትሄ ሃስብ በተበሳጩ አንዳንድ የጽ/ቤት ሹማምንቶች ቂም ተይዞበት ጉድጓድ ሲማስለት መሰንበቱ ይታወሳል። ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ እንደ ዜጋ በጅዳ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ስር የሚገኙ ንብረቶችን ለማስተዳደር በት/ቤት የወላጆች ኮሚቴ እና በተለያዩ የኮሚኒቲው መዋቅሮች የሃላፊነት ቦታዎች እንዲያገለግል በማህበረሰቡ ተመርጦ የመረጠውን ህዝብ በቅንነት እና በታማኝነት ለማገልገል በነበረው ሂደት ውስጥ ህሊናው የማይቀበላቸውን አያሌ ሚስጥራዊ አሰራሮች በመቃወሙ ብቻ ከነበረበት የሃላፊነት ቦታ እንዲነሳ ከማድረጉም በላይ ላልተወሰነ ግዜ ቆንስላ ጽ/ቤት አካባቢ እንዳይደርስ ህገወጥ ውስኔ ተላልፎበት እንደነበር የሚያስታውሱ ወገኖች ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ከወህኒ ነጻ ከወጣም በኃላም ስለወገኑ ስቃይ እና በደል እንዳይጽፍ እና እንዳይናገር የተጣለበት የህሊና ነጻነት ገደብ ከዚህ በላይ በተገለጹ መስረታዊ ጉዳዩች ህዝብ መረጃ የማግኘት መብቱን ለመቀልበስ በእጅ አዙር የተውሰደ እርምጃ ሊሆን እንደሚችል ይነገራል።
ከሁለት ወራት ወህኒ ቆይታ በሃላ በቀርብ ቀን ነጻ የወጣው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ በአሁኑ ሰአት በመልካም ጤንነት ላይ መሆኑን ቢታወቀም ጋዜጠኛው ከእንግዲህ በስደተኞች ዙሪያ ምንም አይነት መረጃዎችን በሶሻል ሚዲያ ሆነ በጀርመንድ ድምጽ እንዳይዘግብ ከባድ ማስጠንቀቂያ የተላለፈበት መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል ። የጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ የህሊና እስረኛ መሆንን ተከትሎ አንዳንድ ወገኖች በመካከለኛው ምስራቅ ግፍ እና በደል የሚፈጸምባቸውን በሚልዮን የሚቆጠሩ ድምጽ አልባ ኢትዮጵያውያን ህይወት የከፋ ሊያደርገው እንደሚችል ስጋታቸውን ይገልጻሉ።
Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ

የኢትዮጵያ መንግስት በጎረቤት ኤርትራ በኩል እየጠነከረ የመጣውን የነጻነት ሃይሎች እንቅስቃሴ ለመግታት ሲል ኤርትራውያን ስደተኞችን መስታጠቅ ሊጀምር ነው።

May 23/2014
(አባይ ሚዲያ)፡ የኢትዮጵያ መንግስት በጎረቤት ኤርትራ በኩል እየጠነከረ የመጣውን የነጻነት ሃይሎች እንቅስቃሴ ለመግታት ሲል ኤርትራውያን ስደተኞችን መስታጠቅ ሊጀምር ነው።
የኢትዮጵያ መንግስት በጎረቤት ኤርትራ በኩል እየጠነከረ የመጣውን የነጻነት ሃይሎች እንቅስቃሴ ለመግታት ሲል ኤርትራውያን ስደተኞችን መስታጠቅ ሊጀምር ነው።
የኢትዮጵያ መንግስት በጎረቤት ኤርትራ በኩል እየጠነከረ የመጣውን የኢትዮጵያውያን የነጻነት ሃይሎች እንቅስቃሴ ለመግታት ያስችለው ዘንድ በኢትዮጵያ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞችን በማሰባሰብ የአስመራን መንግስት በሃይል በመገልበጥ ዴሞክራሲ በኤርትራ መፈንጠቅ አለበት የሚል አዲስ ዘዴ መጀመሩን ከአካባቢው ለመረዳት ችለናል።
አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ወጣት ኤርትራዊ ሲገልጽ፡- አካባቢው የእርስ በርስ የጦርነት ቀጠና መሆኑ ለወያኔ የትኩረት አቅጣጫን በኤርትራኖች የእርስ በርስ ጦርነት በመለወጥ በአካባቢው እየጠነከረ የመጣበትን ሃይል ወደ ህዝቡ እንዳይዳረስ ለማድረግ ለራሱ ጥቅም የጀመረው ሴራ እንጂ ለእኛ የኤርትራውያን ተቃዋሚዎች አስቦ በኤርትራ ዴሞክራሲ ይፈጠር በሚል ትላንት በድንገት ወደ ትግሉ ግቡ ሊለን አይችልም ሲል መረጃውን ሰጥቶናል።
በትላንታናው እለት የኤርትራውያን ስደተኞች 23ኛ የነጻነት አመታቸውን በሚያከብሩበት የስደተኞች መጠለያ የወያኔ ባለስልጣኖች ተገኝተው ስደተኞችን ወደ ተቃዋሚው ጎራ ገብተው እንዲታገሉና የኢሳያስን መንግስት እንዲገለብጡ በጥብቅ ያሳሰቡ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ይህን ተከትሎም ለተለያዩ የመገናኛ ብዙሃኖች “ በኢትዮጵያ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ትጥቅ አንስተው ለመታገል ተቃዋሚ ሃይሎችን ሊቀላቀሉ ነው” የሚል ዜና መላኩን ሱዳን ትሪቢውት የተባለው ድህረ ገጽ አስፍሮታል።
በአለፈው ሳምንት የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል 4ኛ ዙር በርካታ የነጻነት ታጋይ ወታደሮችን ማስመረቁን መዘገባችን ይታወሳል።
አባይ ሚዲያ

ወጣቱና ለነጻነት የሚያደርገው የትግል መስዕዋትነት (ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ ሌና)

  May24/2014
By Gezahegn Abebe (Norway Lena )

የአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ህልውና የሚወሰነው ወጣቶች ባላቸው ሚና ላይ ሲሆን በብዙ ሀገራት እንዳየነው እና እንደተመለከትነው ወጣቶች ስለ ነፃነታቸው ፊት ለፊት መንግስታትን በመጋፈጥ ለመብታቸው ታግለዋል መስዋህትነትምበመክፈል የፈለጉትን አለማና ግብ አሳክተዋል::ለዚህም የሰሜን አፍሪካ አገሮችንና የመካከለኛው ምሥራቅን የለውጥ አብዮት ያቀጣጠሉትን ወጣቶች ዞር ብሎ መመልከት ያሻል:: የአንባ ገነኖች የስልጣን አገዛዝ አልዋጥላቸው ያላቸው እነዚህ የሰሜን አፍሪካ አገሮች እንደነ ግብጽ ፣ ቱኒዚያ እና ሊቢያ ያሉ ሀገሮች የሚኖሩ ወጣቶች በጊዜው ለናፈቁት እናለተመኙለት ነጻነት ብዙ መስዋትነትን በመክፈል ዓላማቸውን አሳክተዋል:: በወቅቱ የነበረው የዓረብ የፖለቲካ ትኩሳትመነቃቃት ለብዙ ሀገራት ወጣቶች ትምህርት ሰጥቶ ያለፈ ታሪክ ነው::

ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ ስንመለስ የኢትዮጵያን የፖለቲካ አካሄድ ወደ ኋላ ዞር ብለን በምናይበት ጊዜ በኢትዮጵያ ሲደረግ በነበረው የፓለቲካ እንቅስቃሴ ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ትልቁን ሚና ይጫወት እንደነበር ከታሪክ መረዳት እንችላለን::እነሆ በኢትዮጵያ ረዥም ታሪክ ውስጥ እያንዳንዱ ትውልድ በተለያየ ጊዜና ወቅት የራሱን አሻራ ጥሎ አልፏል፡:

በተለይ በንጉሡ ጊዜ የመሬት ላራሹንና ሌሎችንም የፖለቲካዊ ጥያቄዎች አንግቦ ሲንቀሳቀስ የነበረው የተማሪ ንቅናቄ ዛሬ ላይ በኢትዮጵያ የፖለቲካ የታሪክ ጉዞ ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ሲሆን በዚያን ጊዜው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የነበሩትና ግንባር ቀደሞቹ ዋለልኝ መኮንንና ጥላሁን ግዛው በድንገት በወታደራዊው ኃይል ቁጥጥር ሥር ለወደቀው የተማሪው አብዮት ተጠቃሾች ሲሆኑ፣ በዘመኑ ለነበረው ሃይለኛ እና ወኔን የታጠቀ ትውልድም መታወቂያ ሆነው ማለፋቸውን የታሪክና የፖለቲካ ተንታኞች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የሚያወሱት የታሪክ ትውስታ ነው፡፡

ከቅርብ አመታት በፊትም ማለትም በ97 ምርጫ ሁሉም ሰው እንደሚያስታውሰው ይህ ወቅት ወያኔ ወጣቶችን ሙሉ በሙሉ የገፋበት ወቅት ጊዜ እንደነበር እና መንግስት ስራ አጥተው የሚንከራተቱ ወጣቶችን “አደገኛ ቦዘኔ” የሚል ታፔላ በመስጠት የተለያዩ እስሮችና የማንገላታት እርምጃዎችን የወሰደበት እና የፈፀመበት ወቅት እንደነበር በብዙዎች ዘንድ ይታመናል፡፡ ይህ አይነቱ የመንግስት ግብታዊ እርምጃ ወጣቱን ወደ ተቃውሞ ጐራ እንዲያዘነብል አድርጐታል፡፡ ለዚህም ይመስላል በወቅቱ በምርጫ 97 ዋዜማ ወያኔ ትግሬ ያቀረባቸውን የተለያዩ ማባበያዎች “አደገኛ ቦዘኔ ራሱ ወያኔ” የሚል ዜማ በማቀንቀን ለተቃዋሚዎች ድጋፍ የሰጠው፡፡ ወያኔ በምርጫ 97 የደረሰበትን አስደንጋጭ ሽንፈት ተከትሎ በተፈጠረው ውዝግብ ቀዳሚ ተጠቂ የሆነውም ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል እንደነበር እናስታውሳለን፡:ለዚህም ነው ምርጫ 97 ተከትሎ በጊዜው የወያኔው መለስ መንግስት ከሃያ ሺ በላይ ወጣቶች በእስር ቤቶችና በወታደራዊ ካምፖች ታሰረው የተሰቃዩት እና ከ200 በላይ የሆኑ ባብዛኛው ወጣት የሆኑ ንፁሀን ዜጐች በግፍ በአደባባይ የተገደሉት::ይህንን ለነጻነት ትግል የተደረገን የወጣቶች የህይወት መስዋትነት ሁል ጊዜ ስናስታውሰው የምንኖረው ነው::

እንደሚታወቀው በአሁን ወቅት በሀገራችን ኢትዮጵያ ከሚኖረው ህዝብ ከፍተኛውን ቁጥር ይዞ የሚገኘው ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል መሆኑ ይታወቃል:: ይህንንም ተከትሎ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከወጣቶች ብዙ የምትጠብቀው ነገር መኖሩ የማያጠያይቅ እውነታ ነው;; ምክንያቱም የኢትዮጵያ ሀገራችን የወደፊት ሁለንተናዊ ህልውናዋ ያለው እና የሚወሰነውም በእነዚሁ በዛሬዎቹ የኢትዮጵያ ወጣቶች ስለሆነ :: ከላይ እንደገለጽኩት በሀገራችን ኢትዮጵያ ከሚኖረው ሕዝብ አብዛኛውን ቁጥር የያዘው ወጣቱ እንደመሆኑ ይሄ ወጣት የህብረተሰብ ክፍል በስልጣን ላይ ባለው ስርዓት ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ፍላጐቱ ሊሞላለት አልቻለም:: ከዚያም ባለፈ ወጣቶች የነጻነትም ሆነ የመብት ጥያቄያቸውን ወይም ፍላጐታቸውን መግለጥ እና መናገር የሚችሉበት አግባብ የተዳፈነ በመሆኑ፣ በአለም ላይ ኢትዮጵያን የተገፉ ወጣቶች የበረከቱባት ሀገር እና ሀገራቸውን እየጣሉ ከሚሰደዱ ወጣቶች መካከል ቅድሚያውን እንድትይዝ አድርጓታል፡፡

የወያኔ መንግስት በስልጣን በቆየባቸው ባለፉት 23 አመታቶች እየበደለ እና እያሰቃየ ያለው በመላ ሀገሪቱ ላይ የሚኖረውን ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ቢሆንም ይበልጥኑ በወያኔ ራዳር ውስጥ በመግባት በአገዛዙ ጭቆናና ግፍእየደረሰበት ያለው በሀገራችን የሚኖረው ወጣቱ ዜጋ መሆኑ የታወቀ ነው:: ዛሬ የአማራው፣ የጋምቤላው፣ የኦሮሞው ፣የደቡቡ፣ የአፋሩ መላው የኢትዮጵያ ወጣት ዜጋ ለነጻነቱ በሚያደርገው ትግል በወያኔ ጨካኝ መንግስት እያተደበደበ፣እየታሰረና እየተገደለ ለነጻነቱ መስዕዋትነትን በመክፈል ላይ ይገኛል :: ለዚህ ማሳያ የሚሆነን በሀገራቸው ፖለቲካበመሳተፍ የተቃዋሚዎችን ጐራ የተቀላቀሉ እንደነ አንዱ አለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንን እና ኦልባና ሌሊሳ የመሳሰሉወጣት ፖለቲከኞች እንዲሁም እንደነ እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ እና ርዮት አለሙን የመሳሰሉ የወደፊቷ ኢትዮጵያተስፈኞች ብዙ የምትጠብቅባቸው ወጣት ጋዜጠኞች እንዲሁም በቅርቡ ህገ መንግስቱ ይከበር በማለት ሀሳባቸውን በብህራቸው የገለጡ የዞን9 ጦማሪዎች የወያኔ መንግስት እያራመደ ካለው የዘረኝነት ፖለቲካ የተለየ አቋም በመያዛቸው እና በተለያዩ ጋዜጦች ላይ ሀሳባቸውን በመግለፃቸው ብቻ በአሸባሪነት ተከሰው ወደ እስር ቤት በግፍ መወርወራቸው የኢትዮጵያ ወጣቶች በገዥው  ስርዓት ምን ያህል መብታቸው እየተረገጠ እና ነጻነታቸው እየታፈነ በወያኔ የግፍ አለንጋ እየተገረፉ እንደሚኖሩ አመላካች ነው፡፡

የወያኔ መንግስት በወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል እየወሰዳቸው ያnለው እነዚህ በግፍ የተሞሉ እርምጃዎች ወጣቶች እጃቸውን አጣጥፈው እንዲቀመጡ አላደረገም፡፡ ይባሱኑ ወጣቱ ሀይሉን እያጠናከረ እና ወደ ተቃዋሚ ጎራ በመግባት ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለወያኔ መንግስት የእግር እሳት እየሆነበት ይገኛል::ከተለያዩ አካባቢዎች በአሁን ሰአት እንደማገኛው  መረጃዎ በኢትዮጵያ የሚገኙ ወጣቶች የወያኔን መንግስት ለመጣል በሚደረጉ ማንኛውም አይነት ትግል መስዋህት ለመሆን ከመቼውም ጊዜ ቆርጠው መነሳታቸውን በብዙ መንገድ እያስመሰከሩ ይገኛሉ ::በመሆኑም ይህ በወያኔዎች የግፍ አለንጋ እየተገረፈ ለነፃነቱ መስዕዋት እየከፈለ ያለ ወጣት የወያኔን ዘረኛ መንግስት ወደ መቃብር እንደሚያስገባው ምንም ጥርጥር የለኝም::

   ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Thursday, May 22, 2014

በባሌ ዩንቨርስቲ አንዲት የአማራ ብሄር ተወላጅ ተማሪ በአክራሪ ሙስሊም ኦሮሞዎች ከፎቅ ላይ ተገፍታ ኮንክሪት ላይ በመውድቅዋ በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወትዋአልፍዋል::

MaY22/2014
ሰሞኑን ከአዲስ አበባ መስፋፋት ጋር በተያያዘ በተስፋፋው አመጽ ምክንያትነቱ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ይሁን እንጂ አላማው በክልሉ ለረጅም ጊዜ በኖሩት አማራዎች ላይ መሆኑ ከቀን ወደ ቀንእየታየ ያለ ሀቅ ነው:: የአማራ ቢዝነሶች ይቃጠላሉ የዓማራ ተወላጆች ከፍተኛ የሆነ የአካልና የስነ ልቦና ጥቃት እንዲሁም የግድያ እርምጃ እየተወሰደባቸው ነው:: በባሌ ዩንቨርስቲ የ 3 ኛ አመትተማሪ የነበረችና ከአማራ ክልል የሄደች ተማሪ ከ ፎቅ ላይ ተገፍታ ኮንክሪት ላይ በመ...ውደቛ ሰውነትዋ ና ጭንቅላትዋ ተፈጥፍቶ ህይወትዋ ወዲያው ሊያልፍ ችልዋል:: ኢሳትን ጨምሮ ሌሎችሚዲያዎች ይህንን በዘር ላይ ያተኮረ ጥቃት ከማጋለጥ ይልቅ ዝምታን መርጠዋል::

 በኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ , አብዲ ፈቲና ጃዋር የሚመራው በአክራሪ የኦሮሞ እስላማዊ ቡድን በየ ዩንቨርስቲውስር የሰደደ መረብ ያለው ሲሆን በአሁኑ ሰአት የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን መሰረት አድርጎ የተነሳውን ተቃዎሞ ወደ ጸረ አማራ ና ክርስቲያን ለመለወጥ ተግቶ እየሰራ ነው :: በዚህም የተሳካ መረብአማካኝነት በክልሉ በሚኖሩና ለትምህርት ወደዚያው ባመሩት የአማራ ክልል ተወላጆችና ተማሪዎች ላይ ጥቃቱ ቀጥልዋል :: አዲስ አበባ ማስተር ፕላን ይሁን ሌላ ነገር ጋር ምንም ግንኙነትየሌላቸውን ደሀ ዜጎች ላይ ጥቃት እንዲዘር በጃዋር መሀመድ, አብዲ ፈቲ, መሀመድ አዴሞ ,ትግስት ገሜ ና ሌሎችም በከፍተኛ ሁኔታ ኦሮሞ ፈርስት በሚባለው እንቅስቃሴ ሲሰራበት የቆየ በመሆኑዛሬ ውጤት አምጥቶ ምስኪን ዜጎች ዋጋ እየከፈሉበት ይገኛሉ:: የኢትዮጵያ የሚባሉ ሚዲያዎች ለምን ዝምታን እንደመረጡ ለብዙዎች አነጋጋሪ ሆንዋል::

የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ስራ አስፈጻሚ በድንጋይ ተፈነከተ

May222/2014
ዳዊት ሰለሞን
የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ስራ አስፈጻሚ አባልና የወጣቶች ጉዳይ ሰብሳቢ አቶ ስንታየሁ ቸኮል ትናንት ለምሳ ወደ መኖሪያ ቤቱ ሲያቀና ማንነታቸውን ባልለያቸው ሰዎች በድንጋይ መፈንከቱ ታውቋል፡፡ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ኳስ ሜዳ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ከቀኑ 8፡00 እንደደረሰ ሁለት ሰዎች ወደ እርሱ በመቅረብ ምንም ሳያነጋግሩት በድንጋይ ፈንክተውት መሰወራቸውን አቶ ስንታየሁ ለፍኖተ ነፃነት አስረድቷል፡፡በድንጋይ ከተፈነከተ በኋላ ለደቂቃዎች ራሱን ስቶ የወደቀው አቶ ስንታየሁ በሰዎች እገዛ ህክምና አግኝቶ በአሁኑ ሰዓት በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛል፡፡ አንድነት ፓርቲ ‹‹የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት››የሚለውን ህዝባዊ ንቅናቄ መጀመሩን ተከትሎ አቶ ስንታየሁ ታላቅ አስተዋጽኦ ሲያበረክት ቆይቷል፡፡ፓርቲው በመስከረም 19 እና ሚያዚያ 26/2006 አዲስ አበባ ላይ ባደረጋቸው ሰላማዊ ሰልፎች ስንታየሁ እጆቹን በካቴና አስሮ በእስር ቤት የሚገኙትን የህሊና እና የፖለቲካ እስረኞች ትኩረት እንዲያገኙ ማድረጉ አይዘነጋም፡፡ በቅርቡ አንድነት ላደረገው ሰላማዊ ሰልፍ የቅስቀሳ ስራ ለመስራት ስንታየሁ ከሌሎች የፓርቲው አባላት ጋር ሲንቀሳቀስ በፖሊስ ተይዞ በህገ ወጥ መንገድ ታስሮ መለቀቁም አይዘነጋም፡፡
ፍኖተ ነፃነት

ፍትህ በምዕራብ ወለጋ እንጨት ለቀማ ወጥቶ በወታደሮች ጥይት ሕይወቱ ላለፈው ገመቺስ

May 22/2014
ከዳዊት ሰለሞን
ፍትህ ለገመቺስና ለመሰሎቹ
በምዕራብ ወለጋ የጊምቢ አጎራባች በሆነችው ዋሎ የሱስ መንደር ነዋሪ የነበረው ገመቺስ ደበላ ከእንጨት ከሰል እያመረተ
ቤተሰቦቹን በመደጎም ህይወትን ሲጋፈጥ ቆይቷል፡፡የ16ዓመቱ ገመቺስ በ02/09/2006 እንደተለመደው ማለዳ ተነስቶ
ለከሰል የሚሆነውን እንጨት ፍለጋ ወደ ጊምቢ እያቀና ነበር በወታደሮች በተተኮሰበት ጥይት እግሩ ላይ የተመታው፡፡የዘጠነኝክፍል ተማሪ የነበረውን ገመቺስን በጊምቢ የሚገኘው የአድቪንቲስት ሆስፒታል ህክምና ሲሰጠው ቢቆይም በ12/09/2006ይህችን አለም በግፍ ተሰናብቷል፡፡

Ethiopia crackdown on student protests taints higher education success

May22/2014
Western backers of the Ethiopian education system should not ignore reports of violent clashes on university campuses
MDG : Ethiopi : Student protest in Ambo
Oromia, Ethiopia, where at least three dozen people were reportedly shot dead by security forces during student protests
Over the past 15 years, Ethiopia has become home to one of the world’s fastest-growing higher education systems. Increasing the number of graduates in the country is a key component of the government’s industrialisation strategy and part of its ambitious plan to become a middle-income country by 2025. Since the 1990s, when there were just two public universities, almost 30 new institutions have sprung up.
On the face of it, this is good news for ordinary Ethiopians. But dig a little deeper and tales abound of students required to join one of the three government parties, with reports of restricted curricula, classroom spies and crackdowns on student protests commonplace at universities.
Nowhere has this been more evident than in Ambo in Oromia state. On 25 April, protests against government plans to bring parts the town under the administrative jurisdiction of the capital, Addis Ababa, began at Ambo University. By the following Tuesday, as protests spread to the town and other areas of Oromia, dozens of demonstrators had been killed in clashes with government forces, according to witnesses.
As Ethiopia experiences rapid economic expansion, its government plans to grow the capital out rather than up, and this involves annexing parts of the surrounding Oromia state. An official communique from the government absolved it of all responsibility for the clashes, claiming that just eight people had been killed and alleging that the violence had been coordinated by a few rogue anti-peace forces. The government maintains that it is attempting to extend Addis Ababa’s services to Oromia through its expansion of the city limits.
However, Oromia opposition figures tell a different story. On 2 May, the nationalist organisation the Oromo Liberation Front (OLF) issued a press release that condemned the “barbaric and egregious killing of innocent Oromo university students who have peacefully demanded the regime to halt the displacement of Oromo farmers from their ancestral land, and the inclusion of Oromo cities and surrounding localities under Finfinnee [Addis Ababa] administration under the pretext of development”. The Addis Ababa regime dismisses the OLA as a terrorist organisation.
While news of the killing of unarmed protesters has caused great concern among many Ethiopians, there has been little coverage overseas. The government maintains strict control over the domestic media; indeed, it frequently ranks as one of the world’s chief jailers of journalists, and it is not easy to come by independent reporting of events in the country.
Nevertheless, the government’s communique does run contrary to reports by the few international media that did cover the attacks in Ambo, which placed the blame firmly on government forces.
The BBC reported that a witness in Ambo saw more than 20 bodies on the street, while Voice of America (VOA) reported that at least 17 protesters were killed by “elite security forces” on three campuses in Oromia. Local residents maintain that the figure [of those killed] was much higher.
These reports, while difficult to corroborate, have been backed up by Human Rights Watch, which issued a statement saying that “security forces have responded [to the protests] by shooting at and beating peaceful protesters in Ambo, Nekemte, Jimma, and other towns with unconfirmed reports from witnesses of dozens of casualties”. One university lecturer said he had been “rescued from the live ammunition”, and that it was the “vampires – the so-called federal police” who fired on the crowds.
The Ethiopian government likes to trumpet its higher education system to its western aid backers as a crowning success of its development policy. As billions in foreign aid are spent annually on Ethiopia, the west must be more cognisant of the fact that this money helps reinforce a government which cuts down those who dare to speak out against it.
Inevitably, continued support for such an oppressive regime justifies its brutal silencing of dissent. Yes, the higher education system has grown exponentially over the past 15 years but the oppression and killing of innocent students cannot be considered an achievement. Any system which crushes its brightest should not be considered a success.
Paul O’Keeffe is a doctoral fellow at La Sapienza University of Rome, where he focuses on the higher education system in Ethiopia.

መድረክ የጠራው ሰልፍ ተከለከለ

May 22/2014

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ህዳር 29 ቀን 2006 ዓ.ም ለማድረግ ያሳወቀው ሰልፍ ተከለከለ፡፡ መድረክ
ሰልፉን ለመጥራት በሀገራችን መሰረታዊና ወቅታዊ የሆኑ ችግሮችን እንዲሁም በሳውዲና በአለም ዙሪያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰያለው ሰቆቃ መሰረቱ የስደት መንስኤው ላይ በመሆኑ፣ መንግስትን በሰላማዊ ሰልፍ ለመጠየቅ እንደነበር ለማወቅ ችለናል፡፡
ሰልፉን ለማድረግ የታቀደው ስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ አምስተኛ በር ፊት ለፊት ከሚገኘው የመድረክ ቢሮ በመነሳት በአምስት
ኪሎና ስድስት ኪሎ አድርጎ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ድረስ ለመጓዝ ነበር፡፡ ነገር ግን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባፅ/ቤት “ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እውቅና የጠየቃችሁበት ስፍራ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስብሰባና የሰላማዊ ሰልፍ አሰራር ስነ-ስርዓት አንቀፅ አምስት ሀ እና መ የሰላማዊ ሰልፍ የማይካሄድባቸው ቦታዎች ተብለው የተጠቀሱ በመሆናቸው የተጠየቀው የሰላማዊ ሰልፍእውቅና መስጠት የማንችል መሆናችንን እንገልፃለን” ሲል መልስ ሰጥቷል፡፡
በጉዳዩ ላይ አስተያት እንዲሰጡ የጠየቅናቸው የመድረክ ስራ አስፈፃሚና የአንድነት ፓርቲ ዋና ፀሀፊ አቶ አስራት ጣሴ “መልሱ
የመድብለ ፓርቲ ቅልበሳ ከመሆን አይዘልም” ይላሉ፡፡ አስተዳደሩ እውቅና ለመንፈግ የተጠቀመበት ደንብ ማንም የማያውቀው መሆኑንየተናገሩት አቶ አስራት በማያውቁት ህግ እንደማይዳኙ ገልፀውልናል፡፡
በ1983 ዓ.ም የወጣው የሰላማዊ ሰልፍና ህዝባዊ ስብሰባ አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 3/1983) የተከለከሉ ብሎ የሚጠቅሳቸው ቦታዎች
እንደሌሉና ከኤምባሲዎች፣ ት/ቤቶች፣ ሆስፒታሎች፣ የሀይማኖት አምልኮ ስፍራዎች፣ በገበያ ቀን (ከገበያ ስፍራ) መቶ ሜትር መራቅእንዳለበት ማዘዙን አቶ አስራት ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ከጦር ካምፕና የደህንነት ተቋማት 500 ሜትር መራቅ እንዳለበት አዋጁማስገደዱን ያስረዱት አቶ አስራት ከዚህ ቀደም አንድነት መስከረም 19 ቀን 2006 ዓ.ም በጠራው ሰልፍ ይህንን አዋጅ በመሻር በጦርካምፕና በደህንነት መስሪያቤቶች በተከበበው ጀንሜዳ እንድንወጣ ነግረውናል ብለዋል፡፡
በተሰጠው መልስ ላይ አቋም ለመያዝ የመድረክ አመራር እንደሚሰበሰብ ከአቶ አስራት ጣሴ ለማወቅ ችለናል፡፡
መድረክ ህዳር 5 ቀን 2006 ዓ.ም መድረክ ለጠራው ሰልፍ አስተዳደሩ ከተደራራበ የስብሰባ ጫና የተነሳ የፖሊስ ሀይል ስለሌለኝ
ጥበቃ ላደደርግለት አልችልም በሚል እውቅና መንፈጉ ይታወቃል፡፡

Ethiopia: Bloggers of the World, Unite!

May 22, 2014
Zone 9 Bloggers in Ethiopia Jail
Today is the 25th day in jail for Zone 9 Bloggers in Ethiopia. They have not been charged; in fact, the government could not come up with reasonable cause for detaining the 6 bloggers and 3 journalists. It has now come to our attention that two have been tortured. All they did was blog about conditions in their own country. Corruption has gone out of control; in a decade beginning in 2001 $16.5 billions have been illicitly transferred to foreign banks [according to Washington, DC-based Global Financial Integrity]. There are chronic water, power and food shortages. The state security literally eavesdrops on telephone conversations and controls Internet connectivity making Ethiopia the least served in Africa. The ruling party took office through the barrel of the gun and divided the country arbitrarily along ethnic lines [and later orchestrated a sham elections that it won]. This is 22 years ago. It has made it clear that it will not hand over or share power through the ballot box. It refused to abide by results of the 2005 elections when it was dealt a humiliating defeat. A year later, it abolished all opposition on the pretext of terrorism which the US and UK governments wholly endorsed and financed. All grassroots organizations that the ruling party did not like were de-registered. Ethiopia now leads the world in the number of journalists jailed or exiled and in human rights abuses.
If you are a blogger you can be part of a global effort to give voice to those denied and to help free those in jail for demanding their constitutional and unalienable rights. Please send a note to Obama and Cameron Administrations, to European Parliament, etc or simply to friends. We can change conditions both locally and globally if we come together. We refuse to bend to those who seek to divide our humanity in order to remain in power! Freedom! Freedom! Freedom!

Wednesday, May 21, 2014

በቀጣይ ዓመት የሚጠናቀቀው የኢትዮጵያ መንግሥት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በአብዛኛዎቹ ዘርፎች እንደማይሳካ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ጠቆመ፡፡

May 21/2014
ግንቦት ፲፫ (አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ2003 እስከ 2007 ዓ.ም ሊከናወን የታቀደው የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ከፋይናንስ አቅም ፣ከሰለጠነ የሰው ኃይል እና ከመሠረተ ልማት አለመሟላትና ከመሳሰሉ ጉዳዮች  ጋር በተያያዘ ፈተናዎች ገጥመውታል፡፡

በዕቅዱ ዓመታት  11 በመቶና ከዚያ በላይ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ የታሰበ ቢሆንም ባለፉት ሶስት የዕቅዱ ዓመታት የተመዘገበው እድገት 10 በመቶ ብቻ ነው፡፡ ከኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ አንጻር በሚጠበቀው አቅጣጫ እና በጎላ መልኩ ለውጥ ማምጣት አለመቻሉን መረጃው ይጠቅሳል፡፡

በተለይ ባለፉት ሶስት ኣመታት ካጋጠሙ ፈተናዎች መካከል በመጀመሪያዎቹ ሁለት ዓመታት የተከሰተው የዋጋ ንረት፣ የግብርና ዘርፍ ምርታማነት ዕድገት አርኪ አለመሆን፣ ኤክስፖርት የገቢ ድርሻ ማሽቆልቆል ፣ የኢምፖርት ድርሻ በከፍተኛ ደረጃ ማደግ፣ የግብርና ዘርፍ የምርታማነት ዕድገት የተፈለገውን ያህል አለመሆን፣ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ከመነሻው መሠረተ ጠባብ መሆን፣ የግል ባለሃብቱ ተሳትፎ ማሽቆልቆል ፣ ከምንም በላይ የማስፈጸም አቅም ማነስ እና በየደረጃው የሙስናና ብልሹ አሰራር ፣የመልካም አስተዳደር ችግሮች መንሰራፋት ይጠቀሳሉ፡፡

የመካከለኛና ትልልቅ ኢንዱስትሪዎች ልማት በውጪ ንግድ የሚመራ፣ የውጪ ምንዛሪ እጥረትን የመቅረፍና ለግብርና ልማት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ከተቀመጡ ኣላማዎች አኳያ ባለፉት ሶስት የዕድገትና የትራንስፎርሜሸን ዕቅድ የትግበራ ዓመታት ክንውን ወደኃላ የቀረ መሆኑን የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር መረጃ ይጠቅሳል፡፡

በፕሮጀክቶችም ደረጃ የታላቁ ህዳሴ ግድብ በአሁኑ ወቅት በመንግሥት መረጃ መጠናቀቅ የቻለው 30 በመቶ ያህል ብቻ ሲሆን በባቡር ፤ በስኳር፣ በማዳበሪያ ፋብሪካዎች ግንባታ የተያዙ ዕቅዶች ቀጣዩ የእቅዱ መጨረሻ ኣመት ድረስ የሚሳኩ አይደሉም፡፡

በዚህም ምክንያት ለመጪው ዓመት ምርጫ ድረስ የአዲስአበባ ቀላል ባቡርን ስራ ለማስጀመር ኢህአዴግ መራሹ መንግሥት የቻይና ኩባንያዎችን ጥብቅ መመሪያ የሰጠ ሲሆን ይህ ዓይነቱ የጥድፊያ አካሄድ በግንባታው ጥራት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ባለሙያዎች ከወዲሁ አስተያየታቸውን እየሰጡ ነው፡፡

የአዲስአበባ ቀላል ባቡር ግንባታ በዕድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅዱ ውስጥ የሌለና በእነአቶ መለስ ዜናዊ ደንገተኛ ውሳኔ የተጸነሰ ዕቅድ ሲሆን ግንባታው ከፍተኛ ወጪ የወጣባቸውን የመንገድ መሰረተ ልማቶች፣ ሕንጻዎች እያፈራረስ ከመምጣቱም ባሻገር የባቡሩ መስመር ዝርጋታ ለእግረኞችና ለተሸከርካሪዎች ማቋረጫ ግምት ውስጥ ባላስገባ መልኩ እየተከናወነ መሆኑ በባለሙያዎች ጭምር ጠንካራ ትችትን አስከትሎአል፡፡

የመንግሥት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ እጅግ የተለጠጠ እና በፋይናንስና በሰውኃይል አቅም ሊተገበር እንደማይችል በተለይ በአገር ውስጥ በሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቶዎችና በውጪ አገር በሚገኙ ኢትጽያዊያን ባለሙያዎች በሰፊው ሲተች የቆየ ቢሆንም ኢህአዴግ መራሹ መንግሥት ይህ የኒዮሊበራሊስቶች አፍራሽ አስተሳሰብ ነው በሚል ሲያጣጥለው ከመቆየቱም በላይ የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር በፓርላማ ተቃዋሚዎችን በኃላ ዕቅዱ ሲሳካ እንዳታፍሩ እስከማለት መድረሳቸው የሚዘነጋ አይደለም፡፡

በኦሮሚያ ለተቃውሞ የወጡ ሠላማዊ ሰዎች ሲገደሉ ይህ የመጀመሪያ አይደለም

 May 21/2014 12:27
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የቀድሞ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የቀድሞ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት እንዲሁም የኦህዴድ ሥራ አስፈፃሚ አባል ነበሩ። ከመንግሥታዊ ሥልጣናቸው ከለቀቁ በኋላም በግል ተወዳድረው ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተመርጠዋል። በግል የተቃውሞ እንቅስቃሴም ተሳትፈዋል። የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን በሊቀመንበርነት መርተዋል። ከአራት ወራት በፊት ግን ከፖለቲካ አባልነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው ለቅቀዋል። ሰሞኑን ከአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ልዩ ዞን ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ የተነሱ ተቃውሞዎችን አስመልክቶ አነጋግረናቸዋል።
ሰንደቅ፡- ከአዲስ አበባና ኦሮሚያ የተቀናጀ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ አንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች በተነሳ ሰሞኑን ተቃውሞ ሰዎች ለሞት እና ለጉዳት ተዳርገዋል፤ ንብረቶች ወድመዋል ይህን ጉዳይ እንዴት ተከታተሉት?
ዶ/ር ነጋሶ፡- ይህ ክስተት በጣም ያዘንኩበትና የደነገጥኩበት ነው። ምክንያቱም ተማሪዎችና ሌሎች ዜጎች የሞትና የአካል ጉዳት መድረሱ ብቻ አይደለም፣ በዚህ ጊዜ ከተከሰቱ ጉዳዮች አንዳንዶቹ በጣም መጥፎና አሰቃቂ መሆናቸው ነው። ሰብዓዊ ፍጡር አያያዝ በተመለከተ መጥፎ ሁኔታዎችን እስማ ነበር። ጭካኔዎች የታዩበት ክስተት ነው። አልፎ ተርፎም ጉዳዩ ወደአልተፈለገ የብሄር ጥላቻ የወረደበትን ሁኔታ በአንዳንድ ቦታዎች ተፈጥሮ ነበር። በተለይ በአምቦ የተከሰተው ተቃውሞ ሰዎች ሲጎዱ አሁን ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ከዚህ በፊት አቶ ጁነዲን በነበረ ጊዜ በአዲስ አበባ (ፊንፊኔ) (1995 ወይም በ1996 ዓ.ም ይመስለኛል) ረብሻ ተነስቶ በጥይት ሰዎች ሞተዋል። ያን ጊዜ በጣም የተቸነውና የገመገምነው እንዴት ለሰላማዊ ተቃውሞ ጥይት ትጠቀማላችሁ በሚል ነበር። በወቅቱ ለዚህ ጥያቄ የተሰጠው መልስ እኛ ለልማቱ በቂ ገንዘብ የለንም፣ ስለዚህ ረብሻ ሲነሳ የምናቆምበት ሌላ መንገድ የለም የሚል ነበር። አሁንም ያንኑ ነው የደገሙት። ያ ጊዜ ካለፈ 10 ዓመት ይሆነዋል፣ ከዚያ ወዲህ ፖሊስን አስታጥቀው፣ አሰልጥነው፣ ሰላማዊ ሰልፍን በሠላማዊ መንገድ የመቆጣጠሪያ መንገዶች ተግባራዊ ማድረግ ይቻል ነበር። ነገር ግን አሁንም ችግሩን ለማርገብ ጥይት መመረጡ አሁንም ገና ኋላቀር ነን ወይ የሚል ነገር በውስጤ ፈጥሯል። ባለፈው ሳምንት ደምቢዶሎ አካባቢ ተማሪዎች ረብሸው ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁት ፖሊስ አስለቃሽ ጢስ ተጠቅሞ ተቃውሞውን መቆጣጠር ችሏል። አንዳንድ ቦታ የዚህ ዓይነት የመሰልጠን ምልክቶች መታየታቸው ጥሩ ነው። ግን በአጠቃላይ ሁከትን በሠላማዊ መንገድ የመቆጣጠር ጉዳይ ገና ኋላቀር ደረጃ ላይ ነን የሚል ስሜት ነው የተሰማኝ።
በሌላ በኩል በጉዳዩ ላይ ሰዎች ስሜታዊ እና ግብታዊ የመሆን ጉዳይም መኖሩን ታዝቤአለሁ። አንድ ነገር ሲከሰት ተናድዶ ወደተቃውሞ የመሄድ ነገር አለ። በተቃውሞ ጊዜ ሳትዘጋጅ፣ ሳትደራጅ፣ ተቃውሞ ሲወጣ ምንድነው መፈክር ይዘን የምንወጣው፣ እነማን ይሳተፋሉ፣ በመካከል ችግር ቢፈጠር እንዴት እንቆጣጠረዋለን ተብሎ መታሰብ ነበረበት። ምክንያቱም በተፈጠረው አጋጣሚ ሰልፈኛውን የሚጎዳ ድርጊት ሊፈፀም ይችላልና። ወይንም በሰልፈኞች መካከል ሆነው በንብረት እና በሰዎች ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉና አስቀድሞ እነዚህ ጉዳዮች ሊታሰብባቸው ይገባ ነበር።
ሰንደቅ፡- ምን ተሰማዎት ሁኔታውን ሲሰሙ?
ዶ/ር ነጋሶ፡- እጅግ በጣም ነው ያዘንኩት። የማስተርፕላኑ ጉዳይ ሲመጣ የሚያናድዱ ጉዳዮች ሊኖሩ ይችላሉ። ተናደህ በምትወጣበት ጊዜ እንደዚህ አይነት ችግሮች ሊፈጠሩ ይችላሉ። በዚህ መልኩ በስሜት ሰዎች አደባባይ ሲወጡ እንዴት ነው የምንቆጣጠረው የሚለው በመንግስት በኩል ዝግጅት ያለመኖር ነገር አይቼበታለሁ።
ሰንደቅ፡- ማስተር ፕላኑን በሚመለከት በተደጋጋሚ ከመንግስት የተሰጠው መግለጫ ሁለቱንም ክልሎች የሚጠቅም እንጂ የአንዱን መሬት ቆርሶ ወደሌላ የሚያስተላልፍ አይደለም የሚል ነው፣ የእርስዎ አስተያየት ምንድነው?
ዶ/ር ነጋሶ፡- የአዲስ አበባ አስተዳደር ይህን ቢልም፣ ባይልም ያለነው 21ኛው ክፍለ ዘመን ውስጥ ነው። እድገት፣ ልማት ይመጣል እና ዘመናዊ የመሆን ሁኔታ ይከሰታል፣ ይሄ የማይካድ ነው።
ሰንደቅ፡- ማስተር ፕላኑ ቢኖርም፣ ባይኖርም ማለትዎ ነው?
ዶ/ር ነጋሶ፡- አዎ! ይከሰታል። አብዛኛው ሕዝብ በአርሶአደርነት መተዳደሩን ትቶ ወደከተማ ይወጣል። ጥቂት አርሶአደሮች ይቀሩና በዘመናዊ አስተራረስ ብዙ ያመርታሉ። ትንሽ አርሶ አደሮች ብዙ አምርተው ከተማውን ይመግባሉ። አሁን አሜሪካ የእርዳታ እህል የሚሰጡን ጥቂት አርሶአደሮች ትርፍ እህል ጭምር ማምረት በመቻላቸው ነው። ይሄ የማይቀር ነው። ለምሳሌ እስከአዳማ ድረስ ይሄ ፈጣን የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ቢዘረጋ ጥሩ ነበር። ሠራተኛ ከዚያ ወደዚህ ተመላልሶ መስራት ይችላል። ወደአምቦ ባቡር ቢገባ በጥቂት ደቂቃዎች አገልግሎት መስጠት ይቻላል። ይሄ ዓይነት የልማት መቀናጀት ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም። በሒደት በትራንስፖትና በሌሎች መሠረተ ልማቶች ትስስሩ መጥበቁ አይቀርም። ለምሳሌ የኤሌክትሪክ ኃይል ከኦሮሚያ አካባቢዎች ይገኛል። ቆቃ፣ ግልገልጊቤ፣ መልካሳ፣ ባሌ ከመሳሰሉት ከወንዞች የሚገኝ ኃይል ወደሌሎች ክፍሎች ይሰራጫል። ህዝቡ ግን አያገኝም፣ የተወሰኑ ከተሞች ብቻ ናቸው እየተጠቀሙ ያሉት። እናም ከልማት አኳያ ከሆነ ነገሩ ጥሩነው። ይህንን የሚጠላ ሰው ያለ አይመስለኝም።
ሰንደቅ፡- ለተቃውሞው መነሻ ታዲያ ምንድነው ይላሉ? መንግስት እንደሚለው ሁኔታውን አለመረዳት ወይንም የውጪ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት ነው?
ዶ/ር ነጋሶ፡- የውጪ ኃይሎች በሁኔታው ሊጠቀሙ ይችሉ ይሆናል። በኢትዮጵያ ውስጥም ቢሆን ወደድንም፣ ጠላንም ገና ያልተፈታ ጥያቄ አለ። የብሔርተኝነት ጥያቄ አለ። አንዳንዱ የኢትዮጵያ አንድነት ይላል፣ ሌላው የለም፣ በተቃራኒው የአንድ ብሄር ጉዳይ ማቀንቀን ብቻ ሳይሆን ከኢትዮጵያ መነጠል አለብን የሚሉ ኃይሎች አሉ። ሁለቱም ብሄርተኞች ናቸው። ለምሳሌ አንድ ጃዋር መሀመድ የሚባል ሰው በአልጀዚራ ቴሌቭዥን ቀርቦ ሲጠየቅ መጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ ከዚያ ነው ኢትዮጵያዊነቴ የሚመጣው ብሎ ተናግሮ ነበረ። እነኚህ የኢትዮጵያ ብሔርተኛ ደግሞ እንዴት ኦሮሞ ነኝ ይላል ብለው በጣም ተቃወሙት። ሁለተኛ የሚኒሊክ መሞት 100ኛ ዓመት መጣ። በዚያ ላይ ኢትዮጵያዊነት የሚያቀነቅኑ ቡድኖች ኢትዮጵያን አንድ ያደረጉ፣ ዘመናዊነትን ያመጡ እያሉ ያሞግሱ ነበር። በሌላ በኩል በሚኒሊክ ወረራ ጊዜ ግን የተፈፀሙ ችግሮች ግን ነበሩ። ፈለግንም፣ አልፈለግንም፤ አመንም፣ አላመንም የዛሬዋ ኢትዮጵያ የተመሰረተችው በአፄ ሚኒሊክ ጊዜ ነው። ያ የሆነው በወረራ ነው። አዲስአበባ የተቆረቆረችው በ1879 ዓ.ም ነው። በወረራ ስለሆነ ያንን የሚያስታውሱ ደግሞ በብሔር እና በማንነት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ የሚያራምዱ ሰዎች ደግሞ የአፄ ሚኒልክ ሐውልት ከአዲስ አበባ መነቀል አለበት የሚለውን አስተሳሰብ ያራምዳሉ። ቴዲ አፍሮ የተባለው ድምፃዊ የሚኒሊክ ጦርነት ቅዱስ ጦርነት ነው ብሏል በሚል እነዚህ በብሔር ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ የሚያራምዱ ኃይሎች በመቃወማቸው ልጁ በበደሌ ቢራ ስፖንሰርነት ሊያካሂድ የነበረው ኮንሰርት እስከመሰረዝ መደረሱን እናስታውሳለን። ይህ ከሆነ በኋላ የኦኖሌ ሃውልት ጉዳይ መጣ። ብዙ ብሔር ብሔረሰቦች በፅሁፍ የሠፈረ ታሪክ የላቸውም። የሚያስታውሱት ከአባት፣ ከአያት የተላለፈ አፈ ታሪክ ነው። ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚያልፉ ታሪኮች አሉ። ሚኒሊክ በ1874 እስከ 1879 ድረስ ሌሎች የኦሮሞ አካባቢዎችን ከወረሩ በኋላ አርሲን መውረር አልቻሉም ነበር። እንዲያውም አርሲዎች በጦርነት ገጥመዋቸው በማሸነፍ አፄ ሚኒልክን አባረዋል። በመጨረሻ ብዙ ኃይል ካከማቹ በኋላ ነው ከአራት ዓመት በኋላ ተንቀሳቅሰው አርሲን ማስገበር የቻሉት። በወቅቱ በ1879 መስከረም ወር በተካሄደው ጦርነት በአጎታቸው ራስ ዳምጠው መሪነት ወደ 12ሺ ሰዎች መጨፍጨፋቸው ይነገራል። በዚያን ጊዜ ወታደሮቹ መጥፎ ነገሮች ማለትም ጡት መቁረጥ፣ እጅ መቁረጥ የመሳሰሉ ግፎችን ፈፅመው ነበር ይባላል። ያንን ለማስታወስ ሐውልት ቢያቆሙ እንዴት የዚህ አይነት ሐውልት ያቆማሉ፣ ይሄ ቂምና በቀልን ማስፋፋት ነው ተብሎ ተተችቷል። ይሄ ከሆነ በኋላ በቅርቡ በባህርዳር ላይ በተካሄደ ስፖርታዊ ውድድር ላይ የታየው ዘረኝነት በጣም መጥፎ እንደነበር ነው የሰማሁት። ፕሬዚዳንቱ ወደስታዲየሙ ሲገቡ የተቃውሞ ጩኸት ሁሉ ነበር ነው የተባለው። እዚያ የተነገረውን መጥፎ ነገር ሌሎች የኦሮሚያ አካባቢዎች ሰምተዋል። ይህ ቁጣ ቀስቅሷል። ይሄ ሁሉ እያለ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጉዳይ ይመጣል። ይህ ማስተር ፕላን በቅርቡ አዳማ ላይ ውይይት ተካሂዶበታል አሉ። የተሳተፉት የአዲስአበባና የኦሮሚያ ሰዎች ናቸው። ያን ጊዜ ተቃውሞ ነበር። ኤክስፐርቶቹ ተቃውሞውን በማውገዝ ይሄ ጠባብነት ነው፣ ብትፈልጉም፣ ባትፈልጉም ማስተር ፕላኑ ተግባራዊ ይሆናል የሚል አስተያየት ሰጡ መባሉንም ሰምተናል። 
ሰንደቅ፡- ከማስተር ፕላኑ ትግበራ በፊት ግን ኦሮሚያ ከአዲስአበባ ማግኘት ያለባት ጥቅም ጉዳይ መመለስ አልነበረበትም?
ዶ/ር ነጋሶ፡- በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 49 ንዑስ አንቀፅ 5 ላይ ኦሮሚያ ከአዲስ አበባ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም በተመለከተ ሰፍሯል፣ ለዚህም ሕግ ይወጣል ይላል። እንግዲህ ተመልከት፤ ሕገመንግስቱ ከወጣበት ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ ሲቆጠር 19 ዓመት ነው። 19 ዓመት ሙሉ ይሄ ሕግ አልወጣም። እንዲያውም በ1998 ዓ.ም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ለፌዴሬሽን ም/ቤት ስለዚህ ጉዳይ በደብዳቤ ጠይቆ ፅፎ ነበር። በሕገመንግስቱ ላይ የኦሮሚያ ጥቅምን በሚመለከት ሕግ ይወጣል የሚለው ምን ማለት እንደሆነ እንዲተረጎምና ሕጉ እንዲወጣ ብሎ ጠይቆ ነበር። ያውም ይህ ጥያቄ የቀረበው ሕገመንግሥቱ ከወጣ ከ10 ዓመት በኋላ ነው። መልስ ግን አልተሰጠውም።
ሰንደቅ፡- ሕገመንግሥቱን ካረቀቁ ኢትዮጵያዊያንም አንዱ እንደመሆንዎ መጠን በሕገመንግሥቱ አንቀፅ 49 ንዑስ አንቀፅ 5 ላይ ኦሮሚያ በአዲስአበባ የሚኖረውን አስተዳደራዊ ጉዳዮች በተመለከተ ልዩ ጥቅም እንደሚጠበቅለትና ዝርዝሩም በሕግ እንደሚወሰን ደንግጓል። በወቅቱ ሕገ መንግሥቱ ሲረቀቅ ታሳቢ ያደረገው ምንድነው?
ዶ/ር ነጋሶ፡- ይህንን በተመለከተ ነገሩን እንደገና ለማስታወስ፣ የሕገመንግሥቱ ቃለጉባኤ አንብቤአለሁ። ልዩ ጥቅም ሲባል የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ቢሮዎችን ለመስራት ቢፈልግ መሬት በነፃ የማግኘት ጉዳይ፣ ህንጻዎች ካሉ በነፃ የማግኘት ጉዳይ ይመለከታል።
ሰንደቅ፡- ግብርን ይመለከታል?
ዶ/ር ነጋሶ፡- ግብርን አይመለከትም። ያን ጊዜም ይሄ ጉዳይ ተነስቶ በግልፅ ግብርን እንደማይመለከት መልስ ተሰጥቶበታል።
ሰንደቅ፡- የኦህዴድ ከፍተኛ አመራር ሆነው በአንድ ወቅት እንደመስራትዎ፣ በተለይ ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ያላትን ልዩ ጥቅም በሚመለከት ከፍተኛ አመራሩ በግልፅ የሚወያይበት፣ ጥቅሙን ለማስከበር የሚሞክርበት እድል ነበረው?
ዶ/ር ነጋሶ፡- የአገሪቱ ፕሬዚዳንት በነበርኩበት ወቅት የኦህዴድ የሥራ አስፈፃሚ አባል ነበርኩ። በዚያ ላይ በአዲስ አበባ ጉዳይ ይሄ ሕግ እንዲወጣ ጠይቀናል። ጉዳዩም ያስጨንቀን ነበር። በወቅቱ እኔ የካቢኔ አባል ስላልነበርኩኝ፣ በመንግሥት ጉዳይ ስለማልገባ በምሳተፍባቸው የኦህዴድ እና የኢህአዴግ መድረኮች ላይ ጉዳዩ በተደጋጋሚ ተነስቷል። ይሄ ብቻ አይደለም፤ አቶ ዓሊ አብዶ የአዲስ አበባ ከንቲባ ነበሩ። ያን ጊዜም የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ ድንበር መካለል አለበት፣ አሁን ካልተካለለ ኋላ ችግር ያመጣል ብለን እንሞግት ነበር። በዚህ ጉዳይ ላይ አቶ ዓሊ አብዶ እና አቶ ሐሰን ዓሊ ቶሎ ብለው ኮሚቴ አቋቁመው እንዲያስፈፅሙ በኦህዴድ ደረጃ ተወስኖ ነበር።
የደርግ ማስተር ፕላን የትናየት ይደርስ ነበር። አሰላ፣ አምቦ፣ ፍቼ፣ ደብረብርሃን ይደርስ ነበር። በሽግግር ጊዜ የማስተር ፕላን ክለሳ ጉዳይ መጣ። በአፄ ኃይለስላሴ ጊዜ አዲስ አበባ በጣም ትንሽ ነበረች። ይህም አይሆንም ቢያንስ እስከ ለገጣፎ፣ በዚህኛው እስከአቃቂ፣ በሌላ በኩል እስከ ቡራዩ እንዲወሰን አስተዋፅኦ አድርገናል።
ሰንደቅ፡- ሕገመንግሥቱ ላይ የተቀመጠው ድንጋጌ አለመከበር ወይንም ዝም መባሉ አሁን ለተፈጠረው ችግር እንደአንድ መንስኤ መውሰድ ይቻላል?
ዶ/ር ነጋሶ፡- በትክክል። 19 ዓመት ሙሉ አንተ ባለቤቱ ካላስታወሰ ማነው የሚያስታውሰው? የኦሮሚያ ክልል ሕገመንግሥቱ ከወጣ ከ10 ዓመት በኋላ በደብዳቤ ጠይቆ ምላሽ አላገኘም። ከዚያ ወዲህ በተግባር ያየነው ነገር የለም።
ሰንደቅ፡- ለዚህ ችግር ኃላፊነት የሚወስደው ማነው?
ዶ/ር ነጋሶ፡- ክልሉን የሚመራው ኢህዴድ ራሱ ነው። የልዩ ጥቅም ማግኘት ብቻ አይደለም። ጉዳዩ በሕገመንግሥቱ ውይይት ጊዜ ተነስቷል። አዲስ አበባ የኦሮሚያም ዋና ከተማ ናት ሲባል የተቃወመ ሰው አልነበረም። ይሄ በኦሮሚያ ሕገመንግሥት ውስጥ ሰፍሯል። እና ባልሳሳት በ1995 ወይም በ1996 ዓ.ም ይመስለኛል የኦሮሚያ ዋና ከተማ ወደአዳማ እንዲዛወር ተደረገ። ያኔ እነአቶ ቡልቻ ሁሉ መስቀል አደባባይ ለተቃውሞ ወጥተው ተደብድበዋል። በወቅቱ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ተቃውሞ ተነስቶ ጉዳት ደርሷል። ወደ 300 የሚሆኑ ተማሪዎች ለአንድ ዓመት ከትምህርት ገበታቸው ተባረዋል፣ አንዱ የወንድሜ ልጅ ነበር። ያንን ካደረጉ በኋላ ቅንጅት ሲያሸንፍ ኦሮሚያን ህዝብ ለማጓጓት ተብሎ መቀመጫው ወደአዲስ አበባ እንዲመለስ ተደረገ። ይህ ብቻ አይደለም፤ የተገቡ ቃሎችም ነበሩ። በአዲስ አበባ ለኦሮሞዎች የባህል ማዕከል እንዲሰራ፣ (አሁን ስታዲያም አካባቢ እየተሰራ ያለው ነው)፣ በተመሳሳይ በየክፍለ ከተማው የባህል ማዕከል እንደሚሰራ፣ ለሥራ ወደ አዲስ አበባ የሚመጡና ሌሎችም ልጆቻቸው በኦሮምኛ ቋንቋ ማስተማር ለሚፈልጉ በየአስሩ ክ/ከተሞች አንድ፣ አንድ ት/ቤቶች ይሠራሉ ተብሎ ተወስኖ ነበር። ያ እስከአሁን አልተደረገም። የባህል ማዕከሉም ዘንድሮ ዘጠነኛ ዓመቱ ነው፣ አልተጠናቀቀም። በየክፍለከተማው ይሠራሉ የተባሉትም አልተሠሩም። ይህንን ተከታትሎ የኦሮሚያ ጥቅም እንዲከበር አለመደረጉን በተመለከተ ክልሉን የሚመራው ኦህዴድ ኃላፊነቱን መውሰድ ይኖርበታል።

አቶ ስብሐት ነጋ ተቃዋሚዎችን እና ኢሕአዴግ እንዲወያዩ ኢኒሼቲቭ እወስዳለሁ አሉ

May 21/2014

የጀርመን ድምጽ ራዲዮ በእንወያይ መድረኩ፣ የሕወሃት አባት ተብለው የሚታወቁት አቶ ስብሐት ነጋ፣ የመኢአድ ሊቀመንበር አቶ አበባዉ መሐሪ፣ ብቸኛ የተቃዋሚ ፓርቲ የፓርላማ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉና፣ በቅርቡ አንድነት ፓርቲን የተቀላቀሉት ደራሲና አክቲቪስት አቶ አስራት አብራሃ፣ በግንቦት ሃይ ዙሪያ ዉይይቶች በማድረግ ላለፉት 23 አመታት የነበረዉን ሁኔታ የቃኘ ሲሆን፣ በዉይይቱ ማብቂያ ላይ ኢሕአዴግን እና ተቃዋሚዎች ለአገር ጥቅም ሲባል ተቀራረበው መነጋገር እንዳለባቸው ተግባብተዋል።
አቶ ስብሐት ነጋ መንግስትም ድክመቶቹን ማረም አለበት ፣ 1፣ 2፣ 3 እያለን መነጋገር አለብን ያሉ ሲሆን፣ ተቃዋሚዎችን እና ኢሕአዴግ የሚነጋገሩብት መድረክ ማን ያዘጋጅ የሚል ጥያቄ ሲቀርብላቸው «እኔ ኢኒሼቲቩን እወስዳለሁ» ሲሉ በአጭር ጊዜ ዉስጥ መድረኩን እንደሚያዘጋጁ ቃል ገብተዋል።
አቶ ግርማ ሰይፉ ና አቶ አበባዉ መሃሪ በበኩላቸው፣ የአቶ ሰብሐትን ኢኒቼቲቭ እንደሚደግፉና በሚደረጉ ዉይይቶች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለመከፈል ዝግጁ እንደሆነ የገለጹ ሲሆን፣ አቶ ስብሐትን ለወሰዱት ኢኒቼቲቭ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። አቶ አስራት በበኩላቸው እኛ ኢትዮጵያዊያን ድሃ የሆንበት ነገር ቢኖር አንዱ ተቀራረቦ መወያያይ አለመቻላችን መሆኑን አስረድተው፣ በአገር ጉዳዩ ዙሪያ ተቀራረቦ መነጋገሩ ተገቢ እንደሆነ አስረድተዋል።
አቶ አበባው የኢትዮጵያ ምሁራን፣ እንዲሁም ኢትዮጵያዊያን የአቶ ስብሐትን ኢኒቼቲቭ እንዲደግፉ ጥሩ አቅርበዋል።