Thursday, May 22, 2014

መድረክ የጠራው ሰልፍ ተከለከለ

May 22/2014

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ህዳር 29 ቀን 2006 ዓ.ም ለማድረግ ያሳወቀው ሰልፍ ተከለከለ፡፡ መድረክ
ሰልፉን ለመጥራት በሀገራችን መሰረታዊና ወቅታዊ የሆኑ ችግሮችን እንዲሁም በሳውዲና በአለም ዙሪያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰያለው ሰቆቃ መሰረቱ የስደት መንስኤው ላይ በመሆኑ፣ መንግስትን በሰላማዊ ሰልፍ ለመጠየቅ እንደነበር ለማወቅ ችለናል፡፡
ሰልፉን ለማድረግ የታቀደው ስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ አምስተኛ በር ፊት ለፊት ከሚገኘው የመድረክ ቢሮ በመነሳት በአምስት
ኪሎና ስድስት ኪሎ አድርጎ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ድረስ ለመጓዝ ነበር፡፡ ነገር ግን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባፅ/ቤት “ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እውቅና የጠየቃችሁበት ስፍራ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስብሰባና የሰላማዊ ሰልፍ አሰራር ስነ-ስርዓት አንቀፅ አምስት ሀ እና መ የሰላማዊ ሰልፍ የማይካሄድባቸው ቦታዎች ተብለው የተጠቀሱ በመሆናቸው የተጠየቀው የሰላማዊ ሰልፍእውቅና መስጠት የማንችል መሆናችንን እንገልፃለን” ሲል መልስ ሰጥቷል፡፡
በጉዳዩ ላይ አስተያት እንዲሰጡ የጠየቅናቸው የመድረክ ስራ አስፈፃሚና የአንድነት ፓርቲ ዋና ፀሀፊ አቶ አስራት ጣሴ “መልሱ
የመድብለ ፓርቲ ቅልበሳ ከመሆን አይዘልም” ይላሉ፡፡ አስተዳደሩ እውቅና ለመንፈግ የተጠቀመበት ደንብ ማንም የማያውቀው መሆኑንየተናገሩት አቶ አስራት በማያውቁት ህግ እንደማይዳኙ ገልፀውልናል፡፡
በ1983 ዓ.ም የወጣው የሰላማዊ ሰልፍና ህዝባዊ ስብሰባ አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 3/1983) የተከለከሉ ብሎ የሚጠቅሳቸው ቦታዎች
እንደሌሉና ከኤምባሲዎች፣ ት/ቤቶች፣ ሆስፒታሎች፣ የሀይማኖት አምልኮ ስፍራዎች፣ በገበያ ቀን (ከገበያ ስፍራ) መቶ ሜትር መራቅእንዳለበት ማዘዙን አቶ አስራት ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ከጦር ካምፕና የደህንነት ተቋማት 500 ሜትር መራቅ እንዳለበት አዋጁማስገደዱን ያስረዱት አቶ አስራት ከዚህ ቀደም አንድነት መስከረም 19 ቀን 2006 ዓ.ም በጠራው ሰልፍ ይህንን አዋጅ በመሻር በጦርካምፕና በደህንነት መስሪያቤቶች በተከበበው ጀንሜዳ እንድንወጣ ነግረውናል ብለዋል፡፡
በተሰጠው መልስ ላይ አቋም ለመያዝ የመድረክ አመራር እንደሚሰበሰብ ከአቶ አስራት ጣሴ ለማወቅ ችለናል፡፡
መድረክ ህዳር 5 ቀን 2006 ዓ.ም መድረክ ለጠራው ሰልፍ አስተዳደሩ ከተደራራበ የስብሰባ ጫና የተነሳ የፖሊስ ሀይል ስለሌለኝ
ጥበቃ ላደደርግለት አልችልም በሚል እውቅና መንፈጉ ይታወቃል፡፡

Ethiopia: Bloggers of the World, Unite!

May 22, 2014
Zone 9 Bloggers in Ethiopia Jail
Today is the 25th day in jail for Zone 9 Bloggers in Ethiopia. They have not been charged; in fact, the government could not come up with reasonable cause for detaining the 6 bloggers and 3 journalists. It has now come to our attention that two have been tortured. All they did was blog about conditions in their own country. Corruption has gone out of control; in a decade beginning in 2001 $16.5 billions have been illicitly transferred to foreign banks [according to Washington, DC-based Global Financial Integrity]. There are chronic water, power and food shortages. The state security literally eavesdrops on telephone conversations and controls Internet connectivity making Ethiopia the least served in Africa. The ruling party took office through the barrel of the gun and divided the country arbitrarily along ethnic lines [and later orchestrated a sham elections that it won]. This is 22 years ago. It has made it clear that it will not hand over or share power through the ballot box. It refused to abide by results of the 2005 elections when it was dealt a humiliating defeat. A year later, it abolished all opposition on the pretext of terrorism which the US and UK governments wholly endorsed and financed. All grassroots organizations that the ruling party did not like were de-registered. Ethiopia now leads the world in the number of journalists jailed or exiled and in human rights abuses.
If you are a blogger you can be part of a global effort to give voice to those denied and to help free those in jail for demanding their constitutional and unalienable rights. Please send a note to Obama and Cameron Administrations, to European Parliament, etc or simply to friends. We can change conditions both locally and globally if we come together. We refuse to bend to those who seek to divide our humanity in order to remain in power! Freedom! Freedom! Freedom!

Wednesday, May 21, 2014

በቀጣይ ዓመት የሚጠናቀቀው የኢትዮጵያ መንግሥት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በአብዛኛዎቹ ዘርፎች እንደማይሳካ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ጠቆመ፡፡

May 21/2014
ግንቦት ፲፫ (አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ2003 እስከ 2007 ዓ.ም ሊከናወን የታቀደው የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ከፋይናንስ አቅም ፣ከሰለጠነ የሰው ኃይል እና ከመሠረተ ልማት አለመሟላትና ከመሳሰሉ ጉዳዮች  ጋር በተያያዘ ፈተናዎች ገጥመውታል፡፡

በዕቅዱ ዓመታት  11 በመቶና ከዚያ በላይ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ የታሰበ ቢሆንም ባለፉት ሶስት የዕቅዱ ዓመታት የተመዘገበው እድገት 10 በመቶ ብቻ ነው፡፡ ከኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ አንጻር በሚጠበቀው አቅጣጫ እና በጎላ መልኩ ለውጥ ማምጣት አለመቻሉን መረጃው ይጠቅሳል፡፡

በተለይ ባለፉት ሶስት ኣመታት ካጋጠሙ ፈተናዎች መካከል በመጀመሪያዎቹ ሁለት ዓመታት የተከሰተው የዋጋ ንረት፣ የግብርና ዘርፍ ምርታማነት ዕድገት አርኪ አለመሆን፣ ኤክስፖርት የገቢ ድርሻ ማሽቆልቆል ፣ የኢምፖርት ድርሻ በከፍተኛ ደረጃ ማደግ፣ የግብርና ዘርፍ የምርታማነት ዕድገት የተፈለገውን ያህል አለመሆን፣ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ከመነሻው መሠረተ ጠባብ መሆን፣ የግል ባለሃብቱ ተሳትፎ ማሽቆልቆል ፣ ከምንም በላይ የማስፈጸም አቅም ማነስ እና በየደረጃው የሙስናና ብልሹ አሰራር ፣የመልካም አስተዳደር ችግሮች መንሰራፋት ይጠቀሳሉ፡፡

የመካከለኛና ትልልቅ ኢንዱስትሪዎች ልማት በውጪ ንግድ የሚመራ፣ የውጪ ምንዛሪ እጥረትን የመቅረፍና ለግብርና ልማት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ከተቀመጡ ኣላማዎች አኳያ ባለፉት ሶስት የዕድገትና የትራንስፎርሜሸን ዕቅድ የትግበራ ዓመታት ክንውን ወደኃላ የቀረ መሆኑን የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር መረጃ ይጠቅሳል፡፡

በፕሮጀክቶችም ደረጃ የታላቁ ህዳሴ ግድብ በአሁኑ ወቅት በመንግሥት መረጃ መጠናቀቅ የቻለው 30 በመቶ ያህል ብቻ ሲሆን በባቡር ፤ በስኳር፣ በማዳበሪያ ፋብሪካዎች ግንባታ የተያዙ ዕቅዶች ቀጣዩ የእቅዱ መጨረሻ ኣመት ድረስ የሚሳኩ አይደሉም፡፡

በዚህም ምክንያት ለመጪው ዓመት ምርጫ ድረስ የአዲስአበባ ቀላል ባቡርን ስራ ለማስጀመር ኢህአዴግ መራሹ መንግሥት የቻይና ኩባንያዎችን ጥብቅ መመሪያ የሰጠ ሲሆን ይህ ዓይነቱ የጥድፊያ አካሄድ በግንባታው ጥራት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ባለሙያዎች ከወዲሁ አስተያየታቸውን እየሰጡ ነው፡፡

የአዲስአበባ ቀላል ባቡር ግንባታ በዕድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅዱ ውስጥ የሌለና በእነአቶ መለስ ዜናዊ ደንገተኛ ውሳኔ የተጸነሰ ዕቅድ ሲሆን ግንባታው ከፍተኛ ወጪ የወጣባቸውን የመንገድ መሰረተ ልማቶች፣ ሕንጻዎች እያፈራረስ ከመምጣቱም ባሻገር የባቡሩ መስመር ዝርጋታ ለእግረኞችና ለተሸከርካሪዎች ማቋረጫ ግምት ውስጥ ባላስገባ መልኩ እየተከናወነ መሆኑ በባለሙያዎች ጭምር ጠንካራ ትችትን አስከትሎአል፡፡

የመንግሥት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ እጅግ የተለጠጠ እና በፋይናንስና በሰውኃይል አቅም ሊተገበር እንደማይችል በተለይ በአገር ውስጥ በሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቶዎችና በውጪ አገር በሚገኙ ኢትጽያዊያን ባለሙያዎች በሰፊው ሲተች የቆየ ቢሆንም ኢህአዴግ መራሹ መንግሥት ይህ የኒዮሊበራሊስቶች አፍራሽ አስተሳሰብ ነው በሚል ሲያጣጥለው ከመቆየቱም በላይ የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር በፓርላማ ተቃዋሚዎችን በኃላ ዕቅዱ ሲሳካ እንዳታፍሩ እስከማለት መድረሳቸው የሚዘነጋ አይደለም፡፡

በኦሮሚያ ለተቃውሞ የወጡ ሠላማዊ ሰዎች ሲገደሉ ይህ የመጀመሪያ አይደለም

 May 21/2014 12:27
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የቀድሞ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የቀድሞ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት እንዲሁም የኦህዴድ ሥራ አስፈፃሚ አባል ነበሩ። ከመንግሥታዊ ሥልጣናቸው ከለቀቁ በኋላም በግል ተወዳድረው ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተመርጠዋል። በግል የተቃውሞ እንቅስቃሴም ተሳትፈዋል። የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን በሊቀመንበርነት መርተዋል። ከአራት ወራት በፊት ግን ከፖለቲካ አባልነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው ለቅቀዋል። ሰሞኑን ከአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ልዩ ዞን ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ የተነሱ ተቃውሞዎችን አስመልክቶ አነጋግረናቸዋል።
ሰንደቅ፡- ከአዲስ አበባና ኦሮሚያ የተቀናጀ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ አንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች በተነሳ ሰሞኑን ተቃውሞ ሰዎች ለሞት እና ለጉዳት ተዳርገዋል፤ ንብረቶች ወድመዋል ይህን ጉዳይ እንዴት ተከታተሉት?
ዶ/ር ነጋሶ፡- ይህ ክስተት በጣም ያዘንኩበትና የደነገጥኩበት ነው። ምክንያቱም ተማሪዎችና ሌሎች ዜጎች የሞትና የአካል ጉዳት መድረሱ ብቻ አይደለም፣ በዚህ ጊዜ ከተከሰቱ ጉዳዮች አንዳንዶቹ በጣም መጥፎና አሰቃቂ መሆናቸው ነው። ሰብዓዊ ፍጡር አያያዝ በተመለከተ መጥፎ ሁኔታዎችን እስማ ነበር። ጭካኔዎች የታዩበት ክስተት ነው። አልፎ ተርፎም ጉዳዩ ወደአልተፈለገ የብሄር ጥላቻ የወረደበትን ሁኔታ በአንዳንድ ቦታዎች ተፈጥሮ ነበር። በተለይ በአምቦ የተከሰተው ተቃውሞ ሰዎች ሲጎዱ አሁን ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ከዚህ በፊት አቶ ጁነዲን በነበረ ጊዜ በአዲስ አበባ (ፊንፊኔ) (1995 ወይም በ1996 ዓ.ም ይመስለኛል) ረብሻ ተነስቶ በጥይት ሰዎች ሞተዋል። ያን ጊዜ በጣም የተቸነውና የገመገምነው እንዴት ለሰላማዊ ተቃውሞ ጥይት ትጠቀማላችሁ በሚል ነበር። በወቅቱ ለዚህ ጥያቄ የተሰጠው መልስ እኛ ለልማቱ በቂ ገንዘብ የለንም፣ ስለዚህ ረብሻ ሲነሳ የምናቆምበት ሌላ መንገድ የለም የሚል ነበር። አሁንም ያንኑ ነው የደገሙት። ያ ጊዜ ካለፈ 10 ዓመት ይሆነዋል፣ ከዚያ ወዲህ ፖሊስን አስታጥቀው፣ አሰልጥነው፣ ሰላማዊ ሰልፍን በሠላማዊ መንገድ የመቆጣጠሪያ መንገዶች ተግባራዊ ማድረግ ይቻል ነበር። ነገር ግን አሁንም ችግሩን ለማርገብ ጥይት መመረጡ አሁንም ገና ኋላቀር ነን ወይ የሚል ነገር በውስጤ ፈጥሯል። ባለፈው ሳምንት ደምቢዶሎ አካባቢ ተማሪዎች ረብሸው ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁት ፖሊስ አስለቃሽ ጢስ ተጠቅሞ ተቃውሞውን መቆጣጠር ችሏል። አንዳንድ ቦታ የዚህ ዓይነት የመሰልጠን ምልክቶች መታየታቸው ጥሩ ነው። ግን በአጠቃላይ ሁከትን በሠላማዊ መንገድ የመቆጣጠር ጉዳይ ገና ኋላቀር ደረጃ ላይ ነን የሚል ስሜት ነው የተሰማኝ።
በሌላ በኩል በጉዳዩ ላይ ሰዎች ስሜታዊ እና ግብታዊ የመሆን ጉዳይም መኖሩን ታዝቤአለሁ። አንድ ነገር ሲከሰት ተናድዶ ወደተቃውሞ የመሄድ ነገር አለ። በተቃውሞ ጊዜ ሳትዘጋጅ፣ ሳትደራጅ፣ ተቃውሞ ሲወጣ ምንድነው መፈክር ይዘን የምንወጣው፣ እነማን ይሳተፋሉ፣ በመካከል ችግር ቢፈጠር እንዴት እንቆጣጠረዋለን ተብሎ መታሰብ ነበረበት። ምክንያቱም በተፈጠረው አጋጣሚ ሰልፈኛውን የሚጎዳ ድርጊት ሊፈፀም ይችላልና። ወይንም በሰልፈኞች መካከል ሆነው በንብረት እና በሰዎች ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉና አስቀድሞ እነዚህ ጉዳዮች ሊታሰብባቸው ይገባ ነበር።
ሰንደቅ፡- ምን ተሰማዎት ሁኔታውን ሲሰሙ?
ዶ/ር ነጋሶ፡- እጅግ በጣም ነው ያዘንኩት። የማስተርፕላኑ ጉዳይ ሲመጣ የሚያናድዱ ጉዳዮች ሊኖሩ ይችላሉ። ተናደህ በምትወጣበት ጊዜ እንደዚህ አይነት ችግሮች ሊፈጠሩ ይችላሉ። በዚህ መልኩ በስሜት ሰዎች አደባባይ ሲወጡ እንዴት ነው የምንቆጣጠረው የሚለው በመንግስት በኩል ዝግጅት ያለመኖር ነገር አይቼበታለሁ።
ሰንደቅ፡- ማስተር ፕላኑን በሚመለከት በተደጋጋሚ ከመንግስት የተሰጠው መግለጫ ሁለቱንም ክልሎች የሚጠቅም እንጂ የአንዱን መሬት ቆርሶ ወደሌላ የሚያስተላልፍ አይደለም የሚል ነው፣ የእርስዎ አስተያየት ምንድነው?
ዶ/ር ነጋሶ፡- የአዲስ አበባ አስተዳደር ይህን ቢልም፣ ባይልም ያለነው 21ኛው ክፍለ ዘመን ውስጥ ነው። እድገት፣ ልማት ይመጣል እና ዘመናዊ የመሆን ሁኔታ ይከሰታል፣ ይሄ የማይካድ ነው።
ሰንደቅ፡- ማስተር ፕላኑ ቢኖርም፣ ባይኖርም ማለትዎ ነው?
ዶ/ር ነጋሶ፡- አዎ! ይከሰታል። አብዛኛው ሕዝብ በአርሶአደርነት መተዳደሩን ትቶ ወደከተማ ይወጣል። ጥቂት አርሶአደሮች ይቀሩና በዘመናዊ አስተራረስ ብዙ ያመርታሉ። ትንሽ አርሶ አደሮች ብዙ አምርተው ከተማውን ይመግባሉ። አሁን አሜሪካ የእርዳታ እህል የሚሰጡን ጥቂት አርሶአደሮች ትርፍ እህል ጭምር ማምረት በመቻላቸው ነው። ይሄ የማይቀር ነው። ለምሳሌ እስከአዳማ ድረስ ይሄ ፈጣን የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ቢዘረጋ ጥሩ ነበር። ሠራተኛ ከዚያ ወደዚህ ተመላልሶ መስራት ይችላል። ወደአምቦ ባቡር ቢገባ በጥቂት ደቂቃዎች አገልግሎት መስጠት ይቻላል። ይሄ ዓይነት የልማት መቀናጀት ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም። በሒደት በትራንስፖትና በሌሎች መሠረተ ልማቶች ትስስሩ መጥበቁ አይቀርም። ለምሳሌ የኤሌክትሪክ ኃይል ከኦሮሚያ አካባቢዎች ይገኛል። ቆቃ፣ ግልገልጊቤ፣ መልካሳ፣ ባሌ ከመሳሰሉት ከወንዞች የሚገኝ ኃይል ወደሌሎች ክፍሎች ይሰራጫል። ህዝቡ ግን አያገኝም፣ የተወሰኑ ከተሞች ብቻ ናቸው እየተጠቀሙ ያሉት። እናም ከልማት አኳያ ከሆነ ነገሩ ጥሩነው። ይህንን የሚጠላ ሰው ያለ አይመስለኝም።
ሰንደቅ፡- ለተቃውሞው መነሻ ታዲያ ምንድነው ይላሉ? መንግስት እንደሚለው ሁኔታውን አለመረዳት ወይንም የውጪ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት ነው?
ዶ/ር ነጋሶ፡- የውጪ ኃይሎች በሁኔታው ሊጠቀሙ ይችሉ ይሆናል። በኢትዮጵያ ውስጥም ቢሆን ወደድንም፣ ጠላንም ገና ያልተፈታ ጥያቄ አለ። የብሔርተኝነት ጥያቄ አለ። አንዳንዱ የኢትዮጵያ አንድነት ይላል፣ ሌላው የለም፣ በተቃራኒው የአንድ ብሄር ጉዳይ ማቀንቀን ብቻ ሳይሆን ከኢትዮጵያ መነጠል አለብን የሚሉ ኃይሎች አሉ። ሁለቱም ብሄርተኞች ናቸው። ለምሳሌ አንድ ጃዋር መሀመድ የሚባል ሰው በአልጀዚራ ቴሌቭዥን ቀርቦ ሲጠየቅ መጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ ከዚያ ነው ኢትዮጵያዊነቴ የሚመጣው ብሎ ተናግሮ ነበረ። እነኚህ የኢትዮጵያ ብሔርተኛ ደግሞ እንዴት ኦሮሞ ነኝ ይላል ብለው በጣም ተቃወሙት። ሁለተኛ የሚኒሊክ መሞት 100ኛ ዓመት መጣ። በዚያ ላይ ኢትዮጵያዊነት የሚያቀነቅኑ ቡድኖች ኢትዮጵያን አንድ ያደረጉ፣ ዘመናዊነትን ያመጡ እያሉ ያሞግሱ ነበር። በሌላ በኩል በሚኒሊክ ወረራ ጊዜ ግን የተፈፀሙ ችግሮች ግን ነበሩ። ፈለግንም፣ አልፈለግንም፤ አመንም፣ አላመንም የዛሬዋ ኢትዮጵያ የተመሰረተችው በአፄ ሚኒሊክ ጊዜ ነው። ያ የሆነው በወረራ ነው። አዲስአበባ የተቆረቆረችው በ1879 ዓ.ም ነው። በወረራ ስለሆነ ያንን የሚያስታውሱ ደግሞ በብሔር እና በማንነት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ የሚያራምዱ ሰዎች ደግሞ የአፄ ሚኒልክ ሐውልት ከአዲስ አበባ መነቀል አለበት የሚለውን አስተሳሰብ ያራምዳሉ። ቴዲ አፍሮ የተባለው ድምፃዊ የሚኒሊክ ጦርነት ቅዱስ ጦርነት ነው ብሏል በሚል እነዚህ በብሔር ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ የሚያራምዱ ኃይሎች በመቃወማቸው ልጁ በበደሌ ቢራ ስፖንሰርነት ሊያካሂድ የነበረው ኮንሰርት እስከመሰረዝ መደረሱን እናስታውሳለን። ይህ ከሆነ በኋላ የኦኖሌ ሃውልት ጉዳይ መጣ። ብዙ ብሔር ብሔረሰቦች በፅሁፍ የሠፈረ ታሪክ የላቸውም። የሚያስታውሱት ከአባት፣ ከአያት የተላለፈ አፈ ታሪክ ነው። ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚያልፉ ታሪኮች አሉ። ሚኒሊክ በ1874 እስከ 1879 ድረስ ሌሎች የኦሮሞ አካባቢዎችን ከወረሩ በኋላ አርሲን መውረር አልቻሉም ነበር። እንዲያውም አርሲዎች በጦርነት ገጥመዋቸው በማሸነፍ አፄ ሚኒልክን አባረዋል። በመጨረሻ ብዙ ኃይል ካከማቹ በኋላ ነው ከአራት ዓመት በኋላ ተንቀሳቅሰው አርሲን ማስገበር የቻሉት። በወቅቱ በ1879 መስከረም ወር በተካሄደው ጦርነት በአጎታቸው ራስ ዳምጠው መሪነት ወደ 12ሺ ሰዎች መጨፍጨፋቸው ይነገራል። በዚያን ጊዜ ወታደሮቹ መጥፎ ነገሮች ማለትም ጡት መቁረጥ፣ እጅ መቁረጥ የመሳሰሉ ግፎችን ፈፅመው ነበር ይባላል። ያንን ለማስታወስ ሐውልት ቢያቆሙ እንዴት የዚህ አይነት ሐውልት ያቆማሉ፣ ይሄ ቂምና በቀልን ማስፋፋት ነው ተብሎ ተተችቷል። ይሄ ከሆነ በኋላ በቅርቡ በባህርዳር ላይ በተካሄደ ስፖርታዊ ውድድር ላይ የታየው ዘረኝነት በጣም መጥፎ እንደነበር ነው የሰማሁት። ፕሬዚዳንቱ ወደስታዲየሙ ሲገቡ የተቃውሞ ጩኸት ሁሉ ነበር ነው የተባለው። እዚያ የተነገረውን መጥፎ ነገር ሌሎች የኦሮሚያ አካባቢዎች ሰምተዋል። ይህ ቁጣ ቀስቅሷል። ይሄ ሁሉ እያለ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጉዳይ ይመጣል። ይህ ማስተር ፕላን በቅርቡ አዳማ ላይ ውይይት ተካሂዶበታል አሉ። የተሳተፉት የአዲስአበባና የኦሮሚያ ሰዎች ናቸው። ያን ጊዜ ተቃውሞ ነበር። ኤክስፐርቶቹ ተቃውሞውን በማውገዝ ይሄ ጠባብነት ነው፣ ብትፈልጉም፣ ባትፈልጉም ማስተር ፕላኑ ተግባራዊ ይሆናል የሚል አስተያየት ሰጡ መባሉንም ሰምተናል። 
ሰንደቅ፡- ከማስተር ፕላኑ ትግበራ በፊት ግን ኦሮሚያ ከአዲስአበባ ማግኘት ያለባት ጥቅም ጉዳይ መመለስ አልነበረበትም?
ዶ/ር ነጋሶ፡- በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 49 ንዑስ አንቀፅ 5 ላይ ኦሮሚያ ከአዲስ አበባ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም በተመለከተ ሰፍሯል፣ ለዚህም ሕግ ይወጣል ይላል። እንግዲህ ተመልከት፤ ሕገመንግስቱ ከወጣበት ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ ሲቆጠር 19 ዓመት ነው። 19 ዓመት ሙሉ ይሄ ሕግ አልወጣም። እንዲያውም በ1998 ዓ.ም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ለፌዴሬሽን ም/ቤት ስለዚህ ጉዳይ በደብዳቤ ጠይቆ ፅፎ ነበር። በሕገመንግስቱ ላይ የኦሮሚያ ጥቅምን በሚመለከት ሕግ ይወጣል የሚለው ምን ማለት እንደሆነ እንዲተረጎምና ሕጉ እንዲወጣ ብሎ ጠይቆ ነበር። ያውም ይህ ጥያቄ የቀረበው ሕገመንግሥቱ ከወጣ ከ10 ዓመት በኋላ ነው። መልስ ግን አልተሰጠውም።
ሰንደቅ፡- ሕገመንግሥቱን ካረቀቁ ኢትዮጵያዊያንም አንዱ እንደመሆንዎ መጠን በሕገመንግሥቱ አንቀፅ 49 ንዑስ አንቀፅ 5 ላይ ኦሮሚያ በአዲስአበባ የሚኖረውን አስተዳደራዊ ጉዳዮች በተመለከተ ልዩ ጥቅም እንደሚጠበቅለትና ዝርዝሩም በሕግ እንደሚወሰን ደንግጓል። በወቅቱ ሕገ መንግሥቱ ሲረቀቅ ታሳቢ ያደረገው ምንድነው?
ዶ/ር ነጋሶ፡- ይህንን በተመለከተ ነገሩን እንደገና ለማስታወስ፣ የሕገመንግሥቱ ቃለጉባኤ አንብቤአለሁ። ልዩ ጥቅም ሲባል የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ቢሮዎችን ለመስራት ቢፈልግ መሬት በነፃ የማግኘት ጉዳይ፣ ህንጻዎች ካሉ በነፃ የማግኘት ጉዳይ ይመለከታል።
ሰንደቅ፡- ግብርን ይመለከታል?
ዶ/ር ነጋሶ፡- ግብርን አይመለከትም። ያን ጊዜም ይሄ ጉዳይ ተነስቶ በግልፅ ግብርን እንደማይመለከት መልስ ተሰጥቶበታል።
ሰንደቅ፡- የኦህዴድ ከፍተኛ አመራር ሆነው በአንድ ወቅት እንደመስራትዎ፣ በተለይ ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ያላትን ልዩ ጥቅም በሚመለከት ከፍተኛ አመራሩ በግልፅ የሚወያይበት፣ ጥቅሙን ለማስከበር የሚሞክርበት እድል ነበረው?
ዶ/ር ነጋሶ፡- የአገሪቱ ፕሬዚዳንት በነበርኩበት ወቅት የኦህዴድ የሥራ አስፈፃሚ አባል ነበርኩ። በዚያ ላይ በአዲስ አበባ ጉዳይ ይሄ ሕግ እንዲወጣ ጠይቀናል። ጉዳዩም ያስጨንቀን ነበር። በወቅቱ እኔ የካቢኔ አባል ስላልነበርኩኝ፣ በመንግሥት ጉዳይ ስለማልገባ በምሳተፍባቸው የኦህዴድ እና የኢህአዴግ መድረኮች ላይ ጉዳዩ በተደጋጋሚ ተነስቷል። ይሄ ብቻ አይደለም፤ አቶ ዓሊ አብዶ የአዲስ አበባ ከንቲባ ነበሩ። ያን ጊዜም የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ ድንበር መካለል አለበት፣ አሁን ካልተካለለ ኋላ ችግር ያመጣል ብለን እንሞግት ነበር። በዚህ ጉዳይ ላይ አቶ ዓሊ አብዶ እና አቶ ሐሰን ዓሊ ቶሎ ብለው ኮሚቴ አቋቁመው እንዲያስፈፅሙ በኦህዴድ ደረጃ ተወስኖ ነበር።
የደርግ ማስተር ፕላን የትናየት ይደርስ ነበር። አሰላ፣ አምቦ፣ ፍቼ፣ ደብረብርሃን ይደርስ ነበር። በሽግግር ጊዜ የማስተር ፕላን ክለሳ ጉዳይ መጣ። በአፄ ኃይለስላሴ ጊዜ አዲስ አበባ በጣም ትንሽ ነበረች። ይህም አይሆንም ቢያንስ እስከ ለገጣፎ፣ በዚህኛው እስከአቃቂ፣ በሌላ በኩል እስከ ቡራዩ እንዲወሰን አስተዋፅኦ አድርገናል።
ሰንደቅ፡- ሕገመንግሥቱ ላይ የተቀመጠው ድንጋጌ አለመከበር ወይንም ዝም መባሉ አሁን ለተፈጠረው ችግር እንደአንድ መንስኤ መውሰድ ይቻላል?
ዶ/ር ነጋሶ፡- በትክክል። 19 ዓመት ሙሉ አንተ ባለቤቱ ካላስታወሰ ማነው የሚያስታውሰው? የኦሮሚያ ክልል ሕገመንግሥቱ ከወጣ ከ10 ዓመት በኋላ በደብዳቤ ጠይቆ ምላሽ አላገኘም። ከዚያ ወዲህ በተግባር ያየነው ነገር የለም።
ሰንደቅ፡- ለዚህ ችግር ኃላፊነት የሚወስደው ማነው?
ዶ/ር ነጋሶ፡- ክልሉን የሚመራው ኢህዴድ ራሱ ነው። የልዩ ጥቅም ማግኘት ብቻ አይደለም። ጉዳዩ በሕገመንግሥቱ ውይይት ጊዜ ተነስቷል። አዲስ አበባ የኦሮሚያም ዋና ከተማ ናት ሲባል የተቃወመ ሰው አልነበረም። ይሄ በኦሮሚያ ሕገመንግሥት ውስጥ ሰፍሯል። እና ባልሳሳት በ1995 ወይም በ1996 ዓ.ም ይመስለኛል የኦሮሚያ ዋና ከተማ ወደአዳማ እንዲዛወር ተደረገ። ያኔ እነአቶ ቡልቻ ሁሉ መስቀል አደባባይ ለተቃውሞ ወጥተው ተደብድበዋል። በወቅቱ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ተቃውሞ ተነስቶ ጉዳት ደርሷል። ወደ 300 የሚሆኑ ተማሪዎች ለአንድ ዓመት ከትምህርት ገበታቸው ተባረዋል፣ አንዱ የወንድሜ ልጅ ነበር። ያንን ካደረጉ በኋላ ቅንጅት ሲያሸንፍ ኦሮሚያን ህዝብ ለማጓጓት ተብሎ መቀመጫው ወደአዲስ አበባ እንዲመለስ ተደረገ። ይህ ብቻ አይደለም፤ የተገቡ ቃሎችም ነበሩ። በአዲስ አበባ ለኦሮሞዎች የባህል ማዕከል እንዲሰራ፣ (አሁን ስታዲያም አካባቢ እየተሰራ ያለው ነው)፣ በተመሳሳይ በየክፍለ ከተማው የባህል ማዕከል እንደሚሰራ፣ ለሥራ ወደ አዲስ አበባ የሚመጡና ሌሎችም ልጆቻቸው በኦሮምኛ ቋንቋ ማስተማር ለሚፈልጉ በየአስሩ ክ/ከተሞች አንድ፣ አንድ ት/ቤቶች ይሠራሉ ተብሎ ተወስኖ ነበር። ያ እስከአሁን አልተደረገም። የባህል ማዕከሉም ዘንድሮ ዘጠነኛ ዓመቱ ነው፣ አልተጠናቀቀም። በየክፍለከተማው ይሠራሉ የተባሉትም አልተሠሩም። ይህንን ተከታትሎ የኦሮሚያ ጥቅም እንዲከበር አለመደረጉን በተመለከተ ክልሉን የሚመራው ኦህዴድ ኃላፊነቱን መውሰድ ይኖርበታል።

አቶ ስብሐት ነጋ ተቃዋሚዎችን እና ኢሕአዴግ እንዲወያዩ ኢኒሼቲቭ እወስዳለሁ አሉ

May 21/2014

የጀርመን ድምጽ ራዲዮ በእንወያይ መድረኩ፣ የሕወሃት አባት ተብለው የሚታወቁት አቶ ስብሐት ነጋ፣ የመኢአድ ሊቀመንበር አቶ አበባዉ መሐሪ፣ ብቸኛ የተቃዋሚ ፓርቲ የፓርላማ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉና፣ በቅርቡ አንድነት ፓርቲን የተቀላቀሉት ደራሲና አክቲቪስት አቶ አስራት አብራሃ፣ በግንቦት ሃይ ዙሪያ ዉይይቶች በማድረግ ላለፉት 23 አመታት የነበረዉን ሁኔታ የቃኘ ሲሆን፣ በዉይይቱ ማብቂያ ላይ ኢሕአዴግን እና ተቃዋሚዎች ለአገር ጥቅም ሲባል ተቀራረበው መነጋገር እንዳለባቸው ተግባብተዋል።
አቶ ስብሐት ነጋ መንግስትም ድክመቶቹን ማረም አለበት ፣ 1፣ 2፣ 3 እያለን መነጋገር አለብን ያሉ ሲሆን፣ ተቃዋሚዎችን እና ኢሕአዴግ የሚነጋገሩብት መድረክ ማን ያዘጋጅ የሚል ጥያቄ ሲቀርብላቸው «እኔ ኢኒሼቲቩን እወስዳለሁ» ሲሉ በአጭር ጊዜ ዉስጥ መድረኩን እንደሚያዘጋጁ ቃል ገብተዋል።
አቶ ግርማ ሰይፉ ና አቶ አበባዉ መሃሪ በበኩላቸው፣ የአቶ ሰብሐትን ኢኒቼቲቭ እንደሚደግፉና በሚደረጉ ዉይይቶች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለመከፈል ዝግጁ እንደሆነ የገለጹ ሲሆን፣ አቶ ስብሐትን ለወሰዱት ኢኒቼቲቭ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። አቶ አስራት በበኩላቸው እኛ ኢትዮጵያዊያን ድሃ የሆንበት ነገር ቢኖር አንዱ ተቀራረቦ መወያያይ አለመቻላችን መሆኑን አስረድተው፣ በአገር ጉዳዩ ዙሪያ ተቀራረቦ መነጋገሩ ተገቢ እንደሆነ አስረድተዋል።
አቶ አበባው የኢትዮጵያ ምሁራን፣ እንዲሁም ኢትዮጵያዊያን የአቶ ስብሐትን ኢኒቼቲቭ እንዲደግፉ ጥሩ አቅርበዋል።

በጋዜጠኞቹ እና በጦማሪያኑ ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተሰጠ

May 21/2014 
ሰበር ዜና፡- ፍርድ ቤቱ በተጠረጠሩት ጋዜጠኞችና ጦማሪያን ላይ የ10 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ፈቀደ
-    “ከአሸባሪ ድርጅቶች ጋር ስልጠና ወስደዋል፤ ብርም ተቀብለዋል” ፖሊስ
-    “ስልጠና የወሰዱት ‘አርቲክል 19’ እና ‘ፍሪደም ሀውስ’ ከተሰኙ በአሜሪካና በእንግሊዝ መንግሥታት ዕውቅና ከተሰጣቸው ዓለም አቀፍ ህጋዊ ድርጅቶች ነው” ጠበቆች
-    “ከአሸባሪ ድርጅቶች ጋር ስልጠና ወስደዋል፤ ብርም ተቀብለዋል” ፖሊስ
-    “ስልጠና የወሰዱት ‘አርቲክል 19’ እና ‘ፍሪደም ሀውስ’ ከተሰኙ በአሜሪካና በእንግሊዝ መንግሥታት ዕውቅና ከተሰጣቸው ዓለም አቀፍ ህጋዊ ድርጅቶች ነው” ጠበቆች

ምስጢራዊ በሆነ መንገድ በህቡዕ በመድራጀት፣ በህጋዊ መንገድ ስልጣን የያዘውን መንግስት በህገወጥ መንገድ ከስልጣን ለማውረድ በማሰብ፣ ውጪ ሀገር ከሚገኙ አሸባሪ ድርጅቶች ጋር በመስማማትና ሀገሪቱን ለማተራመስ ትዕዛዝ በመቀበል የገንዘብና የስልጠና ድጋፍ በመውሰድ፤ በአገሪቱ ላይ ብጥብጥ ለማስነሳትና ብጥብጡንም ለመምራት በመንቀሳቀስ የሽብር ተግባር ፈፅመዋል ሲል የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን በሶስት መዝገቦች ከፋፍሎ እየመረመራቸው የሚገኙት ጋዜጠኞችና ጦማሪያን የ28 እና የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባቸው።
ቅዳሜ ግንቦት 10 ቀን 2006 ዓ.ም በፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አንደኛ አራዳ ምድብ ችሎት በቅድሚያ የቀረቡት በእነ አጥናፍ መዝገብ ስር የሚገኙት ጦማሪያኑ አጥናፍ ብርሃነ፣ ናትናኤል ፈለቀ እና ጋዜጠኛ ኤደም ካሳዬ ናቸው።
በተመሳሳይም በእነዘላለም መዝገብ ስር የዞን ዘጠኝ ጦማሪውና የህግ መምህሩ ዘላለም ክብረት፣ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስና ጋዜጠኛ አስማማው ወ/ጊዮርጊስ እንዲቀርቡ ተደርጓል።
ሁለቱ መዝገቦች ተለያይተው ቢቀርቡም የምርመራ ቡድኑ በሁሉም መዝገቦች ላይ ተመሳሳይ ሀሳብ ያቀረበ ሲሆን በክርክር ይዘትም ሲታይ የሶስቱም ተመሳሳይነት የሚታይበት ነው።
ተጠራጠሪዎቹ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ችሎት ቀርበው ፖሊስ በጠየቀው እና ፍርድ ቤቱም በፈቀደው የ10 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ውስጥ ፖሊስ ያከናወናቸውን ተግባራት ዳኛው በመጠየቅ የተጀመረው ይህ ችሎት ከፖሊስ የተገኘው ምላሽ፣ “ተጠርጣሪዎቹ የተፃፋፏቸውን ፅሁፎች ለማስተርጎም በሂደት ላይ መሆናቸውን፤ የምስክሮችን ቃል ለመቀበል የማስፈራራት ሁኔታ በመግጠሙ አዳጋች መሆኑን፤ ቀሪ ግብረአበሮችን በአድራሻ መለዋወጥ ምክንያት አለመያዛቸው በመጥቀስ ለዚህም ድርጊቱ በቡድንና በህቡዕ የሚከናወን መሆኑን ለፍርድ ቤቱ አስረድቶ ሊፈፀም የታቀደው የሽብር ተግባር ነው ሲል ተጨማሪ 28 ቀናት የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።
በተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች በኩልም፤ ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ካዋለ 23 ቀናት ቢልፉም ምንም አዲስ ነገር አለመፈፀሙን በመጠቆም፤ ሲጀመር ለጥርጣሬው ዋና ምክንያት አድርጎ ያቀረበውን በማህበራዊ ድረ-ገፅ ላይ መፃፍ የሚል ሃሳብ ቀይሮ የሽብር ተግበራ ፈፅመዋል ማለቱ አዲስ እንደሆነባቸው፤ ለዚህም ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ከመዝገቡ መርምሮ በመደበኛ የወንጀል ህግ ጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጥ አሳስበዋል። አያይዘውም መርማሪ ቡድኑ በመዝገቡ በይፋ የጠቀሰው ኢትዮጵያም ሆነ አለማቀፋዊ የሽብር ድርጅት አለመኖሩን በማስታወስ ተጠርጣሪዎቹ ስልጠና ወስደዋል ከተባለም የአሜሪካና የእንግሊዝ መንግስታት እውቅና ከሰጧቸው “አርቲክል 19” እና “ፍሪደም ሀውስ” ከተባሉ ድርጅቶች እንደሆነ፣ እነዚህም በአለም አቀፍ ደረጃ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ላይ የሚሰሩ ሕጋዊ ተቋማት ናቸው ሲሉ አስታውሰዋል።
ፖሊስም በሰጠው ምላሽ፤ ድርጊቱ በቡድንና በህቡዕ የተፈፀመ መሆኑን፤ ምስክሮች ቃላቸውን እንዳይሰጡ በተጠርጣሪዎቹ ግብአበሮች ዛቻና ማስፈራሪያ እየተፈፀመባቸውና አድራሻቸውን እንዲቀይሩ መደረጋቸው ቃላቸውን ለመቀበል አዳጋች እየሆነበት መምጣቱን፤ ከተጠርጣሪዎቹ ኢሜይሎች የተገኙት ማስረጃዎች አስተርጉሞ ለማቅረብ በሂደት ላይ መሆኑን እና በዳታ ክፍሉ ውስጥ ፖሊስ ያለው ኮምፒዩተር አንድ ብቻ በመሆኑ በኢሜይል የቀረቡትን ፅሁፎች መርምሮ ለመጨረስ እንቅፋት እንደሆነበት ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።
የግራ ቀኙን ሀሳብ የመረመረው ፍርድ ቤቱም ፖሊስ ባለፈው የተሰጠውን የ10 ቀናት የምርመራ ጊዜ ቀጠሮን በሚገባ እንዳልተጠቀመበት አስታውሶ፤ ነገር ግን መዝገቡ ከሽብር ድርጊት ጋር የተያያዘ ለጥርጣሬ የሚያበቃ በቂ ምክንያት አለኝ ካለ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሊሰጠው ይገባል በሚሉት በሁለቱም መዝገቦች ላይ የ28 ቀናትን የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል። በመሆኑም ተጠርጣሪዎቹ ሰኔ 7 ቀን በ2006ዓ.ም እንዲቀርቡ ታዟል።
በተያያዘም በማግስቱ እሁድ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው ሶስተኛ መዝገብ በጦማሪያኑ አቤል ዋበላ፣ በፍቃዱ ኃይሉና ማህሌት ፋንታሁን የቀረቡ ሲሆን በችሎቱ የተሰየሙት ዳኛ ከመቀየራቸው ውጪ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን አባላቱ ከቅዳሜው መዝገብ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ሃሳብ የያዘ ደብዳቤ በማቅረብ ጉዳዩን ለመመርመር ተጨማሪ የ28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ፍ/ቤቱን ጠይቋል።
ፖሊስ በተሰጠው የጊዜ ቀጠሮ ውስጥ ስላከናወናቸው ተግባራት በፍርድ ቤቱ ሲጠየቅ፤ “ፖሊስ ወረዳቸውን ተቀብሎ ኢሜይላቸውን ፈትሸናል። ከዚያም ውስጥ ከሽብርተኛ ድርጅት ጋር የተፃፃፉትን መልዕክት አግኝተናል” የሚል ምላሽ ሰጥቷል። ያም ሆኖ ይህ አገኘነው የሚሉትና የተላኩትን መልዕክት ከመዝገቡ ጋር መያያዝ አስመልክቶ ፍርድ ቤቱ ላቀረበው ጥያቄ ፖሊስ፤ አለማያያዙን ተናግሯል። ይህን ተከትሎም ዳኛዋ፣ “መዝገቡ እንደሚያሳየው መጀመሪያ ሲከፈት ከተከፈተበት የጥርጣሬ ምክንያት በተለየ የጠቀሳችሁ አዲስ ነገር የለም” በሚል በፖሊስ ከሽብር ሕጉ ጋር በማገናኘት የጠየቀውን የ28 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ ውድቅ በማድረግ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ በመፍቀድ ለግንቦት 24 ቀን 2006 ዓ.ም ቀጥሯል።
በሁለቱም ቀናት በፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ በርከት ያሉ የተጠርጣሪዎቹ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመድ፣ የአገር ውስጥና የውጪ ጋዜጠኞች እንዲሁም አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ተገኝተው ነበር።
ምስጢራዊ በሆነ መንገድ በህቡዕ በመድራጀት፣ በህጋዊ መንገድ ስልጣን የያዘውን መንግስት በህገወጥ መንገድ ከስልጣን ለማውረድ በማሰብ፣ ውጪ ሀገር ከሚገኙ አሸባሪ ድርጅቶች ጋር በመስማማትና ሀገሪቱን ለማተራመስ ትዕዛዝ በመቀበል የገንዘብና የስልጠና ድጋፍ በመውሰድ፤ በአገሪቱ ላይ ብጥብጥ ለማስነሳትና ብጥብጡንም ለመምራት በመንቀሳቀስ የሽብር ተግባር ፈፅመዋል ሲል የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን በሶስት መዝገቦች ከፋፍሎ እየመረመራቸው የሚገኙት ጋዜጠኞችና ጦማሪያን የ28 እና የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባቸው።
ቅዳሜ ግንቦት 10 ቀን 2006 ዓ.ም በፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አንደኛ አራዳ ምድብ ችሎት በቅድሚያ የቀረቡት በእነ አጥናፍ መዝገብ ስር የሚገኙት ጦማሪያኑ አጥናፍ ብርሃነ፣ ናትናኤል ፈለቀ እና ጋዜጠኛ ኤደም ካሳዬ ናቸው።
በተመሳሳይም በእነዘላለም መዝገብ ስር የዞን ዘጠኝ ጦማሪውና የህግ መምህሩ ዘላለም ክብረት፣ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስና ጋዜጠኛ አስማማው ወ/ጊዮርጊስ እንዲቀርቡ ተደርጓል።
ሁለቱ መዝገቦች ተለያይተው ቢቀርቡም የምርመራ ቡድኑ በሁሉም መዝገቦች ላይ ተመሳሳይ ሀሳብ ያቀረበ ሲሆን በክርክር ይዘትም ሲታይ የሶስቱም ተመሳሳይነት የሚታይበት ነው።
ተጠራጠሪዎቹ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ችሎት ቀርበው ፖሊስ በጠየቀው እና ፍርድ ቤቱም በፈቀደው የ10 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ውስጥ ፖሊስ ያከናወናቸውን ተግባራት ዳኛው በመጠየቅ የተጀመረው ይህ ችሎት ከፖሊስ የተገኘው ምላሽ፣ “ተጠርጣሪዎቹ የተፃፋፏቸውን ፅሁፎች ለማስተርጎም በሂደት ላይ መሆናቸውን፤ የምስክሮችን ቃል ለመቀበል የማስፈራራት ሁኔታ በመግጠሙ አዳጋች መሆኑን፤ ቀሪ ግብረአበሮችን በአድራሻ መለዋወጥ ምክንያት አለመያዛቸው በመጥቀስ ለዚህም ድርጊቱ በቡድንና በህቡዕ የሚከናወን መሆኑን ለፍርድ ቤቱ አስረድቶ ሊፈፀም የታቀደው የሽብር ተግባር ነው ሲል ተጨማሪ 28 ቀናት የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።
በተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች በኩልም፤ ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ካዋለ 23 ቀናት ቢልፉም ምንም አዲስ ነገር አለመፈፀሙን በመጠቆም፤ ሲጀመር ለጥርጣሬው ዋና ምክንያት አድርጎ ያቀረበውን በማህበራዊ ድረ-ገፅ ላይ መፃፍ የሚል ሃሳብ ቀይሮ የሽብር ተግበራ ፈፅመዋል ማለቱ አዲስ እንደሆነባቸው፤ ለዚህም ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ከመዝገቡ መርምሮ በመደበኛ የወንጀል ህግ ጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጥ አሳስበዋል። አያይዘውም መርማሪ ቡድኑ በመዝገቡ በይፋ የጠቀሰው ኢትዮጵያም ሆነ አለማቀፋዊ የሽብር ድርጅት አለመኖሩን በማስታወስ ተጠርጣሪዎቹ ስልጠና ወስደዋል ከተባለም የአሜሪካና የእንግሊዝ መንግስታት እውቅና ከሰጧቸው “አርቲክል 19” እና “ፍሪደም ሀውስ” ከተባሉ ድርጅቶች እንደሆነ፣ እነዚህም በአለም አቀፍ ደረጃ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ላይ የሚሰሩ ሕጋዊ ተቋማት ናቸው ሲሉ አስታውሰዋል።
ፖሊስም በሰጠው ምላሽ፤ ድርጊቱ በቡድንና በህቡዕ የተፈፀመ መሆኑን፤ ምስክሮች ቃላቸውን እንዳይሰጡ በተጠርጣሪዎቹ ግብአበሮች ዛቻና ማስፈራሪያ እየተፈፀመባቸውና አድራሻቸውን እንዲቀይሩ መደረጋቸው ቃላቸውን ለመቀበል አዳጋች እየሆነበት መምጣቱን፤ ከተጠርጣሪዎቹ ኢሜይሎች የተገኙት ማስረጃዎች አስተርጉሞ ለማቅረብ በሂደት ላይ መሆኑን እና በዳታ ክፍሉ ውስጥ ፖሊስ ያለው ኮምፒዩተር አንድ ብቻ በመሆኑ በኢሜይል የቀረቡትን ፅሁፎች መርምሮ ለመጨረስ እንቅፋት እንደሆነበት ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።
የግራ ቀኙን ሀሳብ የመረመረው ፍርድ ቤቱም ፖሊስ ባለፈው የተሰጠውን የ10 ቀናት የምርመራ ጊዜ ቀጠሮን በሚገባ እንዳልተጠቀመበት አስታውሶ፤ ነገር ግን መዝገቡ ከሽብር ድርጊት ጋር የተያያዘ ለጥርጣሬ የሚያበቃ በቂ ምክንያት አለኝ ካለ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሊሰጠው ይገባል በሚሉት በሁለቱም መዝገቦች ላይ የ28 ቀናትን የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል። በመሆኑም ተጠርጣሪዎቹ ሰኔ 7 ቀን በ2006ዓ.ም እንዲቀርቡ ታዟል።
በተያያዘም በማግስቱ እሁድ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው ሶስተኛ መዝገብ በጦማሪያኑ አቤል ዋበላ፣ በፍቃዱ ኃይሉና ማህሌት ፋንታሁን የቀረቡ ሲሆን በችሎቱ የተሰየሙት ዳኛ ከመቀየራቸው ውጪ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን አባላቱ ከቅዳሜው መዝገብ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ሃሳብ የያዘ ደብዳቤ በማቅረብ ጉዳዩን ለመመርመር ተጨማሪ የ28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ፍ/ቤቱን ጠይቋል።
ፖሊስ በተሰጠው የጊዜ ቀጠሮ ውስጥ ስላከናወናቸው ተግባራት በፍርድ ቤቱ ሲጠየቅ፤ “ፖሊስ ወረዳቸውን ተቀብሎ ኢሜይላቸውን ፈትሸናል። ከዚያም ውስጥ ከሽብርተኛ ድርጅት ጋር የተፃፃፉትን መልዕክት አግኝተናል” የሚል ምላሽ ሰጥቷል። ያም ሆኖ ይህ አገኘነው የሚሉትና የተላኩትን መልዕክት ከመዝገቡ ጋር መያያዝ አስመልክቶ ፍርድ ቤቱ ላቀረበው ጥያቄ ፖሊስ፤ አለማያያዙን ተናግሯል። ይህን ተከትሎም ዳኛዋ፣ “መዝገቡ እንደሚያሳየው መጀመሪያ ሲከፈት ከተከፈተበት የጥርጣሬ ምክንያት በተለየ የጠቀሳችሁ አዲስ ነገር የለም” በሚል በፖሊስ ከሽብር ሕጉ ጋር በማገናኘት የጠየቀውን የ28 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ ውድቅ በማድረግ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ በመፍቀድ ለግንቦት 24 ቀን 2006 ዓ.ም ቀጥሯል።
በሁለቱም ቀናት በፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ በርከት ያሉ የተጠርጣሪዎቹ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመድ፣ የአገር ውስጥና የውጪ ጋዜጠኞች እንዲሁም አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ተገኝተው ነበር።

የስደተኞች ዋይታ በሱዳን

May20/2014
አንድ የሱዳን ፍርድ ቤት፣ በአንዲት የ 27 ዓመት ሴት፣ ከልጅነቷ አንስቶ የ ወላጅ እናቷን ሃይማኖት ስተከተል መኖሯን በይፋ ብትገልጸም ፣ ያላሳደጋትን ሙስሊም አባቷን ሃይማኖት እንደለወጠች በመቁጠር ሙት-በቃ በመፍረዱ፣ በዛ ያሉ ምዕራባውያን መንግሥታትና የሰብአዊ መብት ድርጅቶች፣
Konflikt im Südsudan Flüchtlinge 16.01.2014
ሱዳን የሃይማኖት ነጸነትን እንድታከብር መጠየቃቸው ይታወሳል። በዚያ የሚኖሩ ስደተኞች ደረሰብን ስለሚሉት ወከባ፤ እንግልት ፣ እሥራት፤ የንብረት መቀማትና የመሳሰለው ግን ያን ያህል ትኩረት ያገኘ አይመስልም። ከተለያዩ ምንጮች እንደምንሰማውና በቀጥታም ዶቸ ቨለም ከሚደርሰው መልእክት መረዳት እንደቻልነው ፤ ባለፉት 3 ወራት በተለይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወከባው ያየለባቸው ሲሆን ፤ እየታደኑ እንደሚያዙ፣ እንደሚታሠሩ ንብረታቸው እንደሚዘረፍ በምሬት ይገልጻሉ ተክሌ የኋላ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።
ተክሌ የኋላ
አርያም ተክሌ

AUDIOS AND VIDEOS ON THE TOPIC


Tuesday, May 20, 2014

ዘላለም ስንት ነው? በአቶ ግርማ ሰይፉ ማሩ

May 20/2014

አውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ሰርዓት ሲኖር ተጠቃሚ የሚሆኑት ለዚህ ሲሉ ክቡር ህየይወታቸውን ለመሰዋዕትነት ያዘጋጁትና ይህንን መራራ ፅዋ በክብር የከፈሉት ብቻ አይደሉም፡፡ ይልቁንም የነፃነት፣ የዲሞክራሲ፣ የፍትህ ሰርዓት መሰፈን ደስ የሚያሰኘው የተጠቃሚ ምርጫ ለመሰዋዕትነት በመዘጋጀት እና በመክፈል አድልዖ ያለማድረጉ ነው፡፡ ከዚህ ዓይነት ሰርዓት የሚጠቀሙትም እነዚህን መሰረታዊ የሰው ልጅ መብቶችን ለማስከበር በሚደረግ ትግል ወቅት እራሳቸውን በፍርሃት ውስጥ ያኖሩትን ብሎም እራሳቸው ጨቋኞቹን ጭምር መሆኑ ነው፡፡ ለመሰዋዕትነት እራሳቸውን ያዘጋጁ ዜጎች ለምን እንዲህ ሆነ ብለው የሚቆጩበት ጊዜ የላቸውም፡፡ የዲሞክራሲ ስርዓት በሌለበት በመንግሰት የሚመራ ቁሳዊ ዕድገት አስተማማኝ እንዳልሆነ በተደጋጋሚ የተገለፀ ሀቅ ነው፡፡ በሀገራችን ዕድገት አለ የለም ክርክር ጉንጭ አልፋ ከሆነም ቆይቶዋል፡፡ በሀገራችን ቁሳዊ ዕድገት እንዳለ ምንም ጥርጥር የለም፡፡ የዚህ ዕድገት ተቋዳሾችም ጥቂቶች እንደሆኑ ማመን የግድ ይላል፡፡ እነዚህ ደልቃቆች ውኃ ስለማይጠጡ የውሃ ችግር ችግራቸው አይደለም፤ መብራት ቢጠፋ ጄኔሬተር ያስነሳሉ፣ ሞባይልም ቢሆን ባለ ሳተላይት ይኖራቸዋል (እነዚህ ብዙ አይደሉም)፣ ሌላም ሌላም ልንዘረዝር እንችላለን፡፡ እነዚህ ኪሳቸውን በገንዘብ ሞልተው፤ ነፃነታቸውን በፍርሃት በኢህአዴግ ቁጥጥር ስር ያደረጉ ሰዎች ሌሎች በሚከፍሉት መስዋዕትነት ነፃ የሚወጡ ናቸው፡፡ ለዚህ ፅሁፍ ገፊ የሆነው ምክንያት የሆነው ግን እነዚህ በፍርሃት ቆፈን ውስጥ ያሉ ሰዎች ፍርሃትን አበደባባይ ሲሰብኩት መስማቴ ነው፡፡
ይህ ቀን እስኪያልፍ ድረስ ተዉኝ ልኑርበት እየተባለ በድፍረት መፎከር ተጀምሮዋል፡፡ ድሮ በድብቅ ይፈራል ሲባል ነው የምናውቀው አሁን በድፍረት ስለ ፍርሃት የሚወራበት ዘመን ደረስናል፡፡ ይህን የሰማሁት ባለቤቴ ክሊኒክ ወረፋ ሆና ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ ድንገት እግር ጥሎኝ አልፎ አልፎ ጎራ ከምልበት “መዝናኛ” ቤት እንደተቀመጥኩ ነው፡፡ መቁሰያ ቢባል ይሻላል፡፡ አንድ ወደ ጎልምሳና የተጠጋ የሰላሣ ሰምንት ዓመት ሰው ስድስተኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ የማውቀው
ብሎ እንዲህ ብሎ ፎከረ፤
“ፈሪና ተራራ ዘላለም ይኖራል፤
ብርሌና ደፋር ቶሎ ይሰበራል፡፡”
ስለዚህ ተዉኝ ልኑርበት ብሎ የሱን ፍርሃት እንደ ተራራ ሲያገዝፈው፡፡ ለነፃነታቸው ቀናዔ የሆኑትን እና በተፈጥሮ ያገኙትን ነፃነት አናሰነካም የሚሉትን ደግሞ ከተራ ድፍረትና ብርሌ ጋር አነፃፅሮ ለፍርሃቱ ማወራረጃ ውሲኪውን ተጎነጨበትም፡፡ ይኼኔ ነው የቆሰልኩት እና ይህን ለመክተብ ማሰታወሻ የያዝኩት፡፡
እንግዲህ የሳላሣ ስምንት ዓመት ጎልማሳው በከተሜነት ዕድሜው ስሌት በአስራ ሁለት ዓመቱ ሰለፈሪነት ገብቶት እሰከ ዛሬ ለሃያ ስድስት ዓመት አብዛኛውን ደግሞ በኢህአደግ የአገዛዝ ዘመን አንገቱን ደፍቶ እየኖረ ነው፡፡ ለዘላለምም ከነፍርሃቱ ይኖራል፡፡ ፍርሃትም ተራራም ዘላለም ሊኖሩ ይችላሉ ይህ ወንድማችን ግን ከአሁን በኋላ ስንት ሊኖር ብሎ ነው የፍርሃት ፉከራ የሚያወርደው? የሚል ጥያቄ ጫረብኝ፡፡ ዘላለም ለእንዲህ ዓይነት ፈረዎች ስንት ነው? ሰዎች በምድር ላይ በፍርሃት ተውጠው በተጎለቱበት አይደለም ዘላለማዊ የሚሆኑት፡፡ ብዙ ቁም ነገር የሰሩ ጀግኖች የሚዘከሩት በሰሩት ቁም ነገር ነው፡፡ ማርቲን ሉተር ኪንግ፣ ጆኔፍ ኬኔዲ፤ ወዘተ ከሀገራቸው አልፈው እኛ እንደመደበኛ እውቀት የምናውቃቸው ሰዎች በለጋ ዕድሜያቸው ይህችን አለም ተሰናብተዋል ነገር ግን ለዘላለም ሲታወሱ ይኖራሉ፡፡ በላይ ዘለቀ ስቅላት ሲፈረድበት አርባ ዓመት ያልሞላው ጎልማሳ ነበር እንቢኝ ውርደት ብሎ የሞትን ፅዋ ተጎነጨ ነገር ግን በላይ ዘለቀ “የበላይ ናት እሷስ” እየተባለ በዘፈን ይወደሳል፣ ቅኔ ይቀኙለታል፡፡ ዘላለም ስንት ነው ያልኩትም ለዚህ ነው፡፡ በፍርሃት አንገት ደፍቶ በቁም ሞቶ እድሜ መቁጠር? ወይስ በድፍረት አንገት ቀና አድርጎ መኖር?
ተማም አባቡልጎ የሚባል የህግ አማካሪኛ ጠበቃ መቼም የማያውቅ ያለ አይመስለኝም፡፡ በአንድ አጋጣሚ በፍርድ ቤት ቅጥር ጊቢ ሆነን ስንጫወት እንዲህ አለኝ “እሰር ቤት ስለ መግባት እና ሰለመገደል ማሰብ የእኛ ስራ መሆን የለበትም፡፡ የእኛ ተግባር መሆን ያለበት በድፍረት፣ በስርዓት፣ በነፃነት አንገት ቀና አድርጎ መኖር ነው አለኝ፡፡” እውነቱን ነው አሳሪና ገዳዮች እንዴት፣ መቼ እና በምን ሁኔታ እንደሚያደርጉት ያስቡበት እንጂ እኛ ምን በወጣን ሰለ እሰርና ሞት እናስባለን፡፡ በተቃራኒው ግን ፈሪ ሁልጊዜ በትክክል መፍራቱን እያረጋገጠ መኖር አለበት፤ ያለበለዚያ ሰው መሆኑ በሚፈጥርበት የነፃነት ስሜት ተነሳስቶ ደፋር ሆኖ ገዢዎችን እንዳያሰቀይም መጠንቀቅ ይኖርበታል፡፡ ፍርሃቱን በትክክል መፍራቱን ማረጋገጥ የፈሪ ሃላፊነት ነው፡፡ ያለበለዚያም እንዴት ዘላለም ይኖራል፡፡ ድንገት ድፍረት ይመጣና እንደ ብርሌ መሰበር ይመጣል፡፡ አንባቢዎች ፍረዱኝ ፈሪ ነው ወይስ ከፍርሃት ውጭ ያለ በሰጋት የሚኖር?
የሀገራችን ሁኔታ ጉራማይሌ መሆኑን ማሳያው ይህን የፍርሃት ቀረርቶ የሰማሁት ሚያዚያ 26/2006 ካደረግነው ሰልፍ በተመለስን ሶስት ቀን ሳይሞላው መሆኑ ነው፡፡ ፍርሃትን እንቢ ብለው “እመነኝ አልፈራም” ሲሉ የነበሩ ወጣቶች ድምፅ በተለይ የወጣት ሀብታሙ አያሌው ድምፅ ጆሮዬ ላይ እያቃጨለ በነበረበት ወቅት ነው፡፡ “መብትን መጠየቅ አሸባሪነት አይደለም”፣ “ማዕከላዊ ይዘጋ፣ ማዕከላዊ ጓንታናሞ”፣ ወዘተ. የሚሉ መፈክሮች በሰማሁበት ጆሮ መሆኑ ነው፡፡ “አንገድለም ግደሉን” እየተባለ በአደባባይ ሲፈክር ከነበረ ብዙ ሺ ህዝብ በተለየ በአንድ “መዝናኛ” በተባለች ጠባብ ክፍል ውስጥ የፍርሃት ፉከራ ምን የሚሉት እነደሆነ ለእኔ ግልፅ አይደለም፡፡ ፍረዱኝ የቱ ነው ለመኖር ጣዕም የሚሰጠው? ተዉኝ ልኑርበት ብሎ በፍርሃት ቆፈን ውስጥ ሆኖ ቀንና ምሽት ሳይለዩ በአልኮል ውስጥ፣ ግራና ቀኝ ያለን ሁሉ እየፈሩና እየተጠራጠሩ የእነ ማቱሳላህ ዕድሜ ቢገኝ እንኳን ዘላለም መኖርን ያስመኛል?
የዚህ ፅሁፍ ዋና ዓለማው ፈሪን መውቀስ አይደለም ይልቁንም ፍርሃትን ስለመፍራት እንድንወያይ እና ከዚህም የሚገኘውን የተሻለ የዘላለም ትርጉም የሚገኝበትን መንገድ መሻት ነው፡፡ በድፍረት ውስጥ ስለ አለ የነፃነት ጣዕምን ሰዎች እንዲያጣጥሙት ማሳየት ያለብኝ ስለመሰለኝ ነው፡፡ ድፍረት ሲባል በፍፁም ከጀብደኝነት ጋር ተገናኝቶ አላስፈላጊ ትርጉም እንዲሰጠው አልፈልግም፡፡ ውሃ ዋና የማይችል ሰው፣ ደፋር ነኝ ብሎ ቢዋኝ እንደሚሰምጥ ማወቅ አለበት፡፡ ሁሉም እርግጠኛ መሆን ያለበት ፈንጂ ላይ የመረማመድ ድፍረት እየሰበኩ አይደለም፡፡ ተፈጥሮዋዊ መብታችንን ላለማስናካት የሚያስፈልገውን ወኔ በአሰፈላጊ ጊዜ መጠቀም ይኖርብናል የሚል ሃሳቤን ለማጋራት ነው፡፡ እንደዚህም ሆኖ ግን መፍራትም፣ ከፍርሃት ጋር ተዋዶ መኖርም ምርጫ ነው፡፡ የሰውን ልጅ ምርጫ እናከብራለን የምንል ከሆነ ደግሞ የተሳሳተ ምርጫም ቢሆን ምርጫውን ማክበር የግድ ይላል፡፡ ሰው ከሆነ ግን ምርጫው ልክ እንዳልሆነ ሲረዳ ምርጫውን ያስተካክላል፡፡ ሰው የመሆን ጥቅሙ ይህ ነው፡፡ ነፃነት ለእኔ ከእግዜር የተሰጠኝ መክሊት እንጂ በማንም የተቸርኩት አይደለም፡፡ ይህን መክሊቴን ቀብሬ መኖር አብዝቼ መጠቀም የእኔ ድርሻ ነው፡፡ በተሰጠን መክሊት ልክ እንጠየቃለን፡፡
ከላይ ሰለ ሚያዚያ 26 ሰልፍ ካነሳሁ አይቀር ሁለት ትዝብቶኝ ማሰፈር ይገባኛል ብዬ አመንኩ፡፡ በሰልፉ ላይ ሆኜ የታዘብኩት አንድ የወታደሮችን መኖሪያ የሚጠብቅ ዘብ ያሳየውን የተለየ ባህሪ ነው፡፡ ጠብ መንጃውን የታጠቀው ዘብ መቼ እንደሚተኩስ እና እንደሚገድል አይታወቅም ወይ? ለህውቀት እንዲረዳኝ መሳሪያ የያዘ ወታደር በፈለገ ሰዓት መሳሪያውን የመጠቀም መብት አለው ወይ? ይህን ጥያቄ እንዳነሳ የገፋፋኝ በወታደሮች መኖሪያ ቅጥር ጊቢ መግቢያ ላይ በስሜት የተነሱ ሰዎችን ከመግቢያው በር እንዲርቁ እየተከላከልን እያለ አንድ መሣሪያ የታጠቀ ዘብ ጠጋ ብሎን “አልሄድም ነው የሚሉት!!” ብሎ መሳሪያውን ከቃታው ላይ ሲያደርግ ተመልክቼ እንዴት አንደዘገነነኝ ማሰረዳት ስለምቸገር ነው፡፡
ለምሣሌ መዝገብ ቤት ያለ ሰራተኛ ማህተም ሳይፈቀድ እንደማያደርገው፣ ገንዘብ ቤት ያለ ገንዘብ ያዥ ሳይታዘዝ እንደማይከፍለው ሁሉ ጠመንጃ የያዘ ወታደር ሆነ ፖሊስ ተራ ግርግር ተፈጠረ ብሎ መተኮስ፣ ሲተኩስም አንገት ላይ ተኩሶ መገድል ይችላል ወይ? ለወታደርና ፖሊስ አሰገዳጅ የሚባሉ ሁኔታዎች እንዳሉ እረዳለሁ፡፡ የሰለፉ ዕለት የተመለከትኩት የዘብ ሰሜት እጅግ ያስደነገጠኝ ነገር ሰለሆነ ነው፡፡ እግረ መንገዱን በሲግናል በኩል ስናልፍ አንድ አንድ ሰልፈኞች ያሳዩት ያልተገባ ድርጊት በግሌ ይቅርታ መጠየቅ ይኖርብኛል፡፡ በህንፃ ላይ ሆነው የድጋፍ እንዲሁም የሰድብም ምልክቶች ይተላለፉ ነበር እነዚህን ሁሉ በትዕግሰት እና በፍቅር መመለስ ነበረባቸው፡፡ “መከላከያ የኛ!!” የሚል መፈክር መኖር ነበረበት በእርግጥም መከላከያ የእኛ ነው፡፡ ጥቂቶች መጠቀሚያ ስላደረጉት የእኛ መሆኑን መካድ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያማዝናል፡፡ ኢህአዴግ ለስልጣን እየቀረበ ሲመጣ “የጭቁን መኮንኖች እና ጭቁን ወታደሮች” ማህበር መመስረቱ የማይረሳ ነው፡፡ በመጨረሻው ግን ሁሉንም መበተን ነበር የወሰነው፡፡ ኢህዴግ የደርግን መንግሰት ካስወገደ በኋላ ከሰራቸው ትልቅ ሰህተቶች አንዱ የኢትዮጵያን መከላከያ ሀይል የደርግ ሰራዊት ብሎ መበተኑ ነው፡፡ ይህ የማይታረም ስህተት ከአሁን በኋላ መደገም ያለበት አይደለም፡፡ ከሌላው ሰህተት መማር መቻል ይኖርብናል፡፡
በመጨረሻም “ማዕከላዊ ይፍረስ፣ ጓንታናሞ ነው!!” ሲባል የነበረውን የሚያዚያ 26 መፈክር ድጋሚ ብቻዬን ማለት አማራኝ፡፡ ምክንያቱም “ዞን 9” በመባል የሚታወቁትን ወጣት ጦማሪዎች በፍርድ ቤት ቀርበው ግርፋትና ድብደባ ደርሶብናል ብለው አቤት ማለታቸውን ሰምቼ ነው፡፡ የፀረ ሽብር ህግ ለመርማሪዎች ከገደብ በላይ በሚስጥር የመመርመር እና መረጃ የመሰብሰብ ስልጣን የሰጣቸው (የወሰዱት) መረጃን በበቂ አሰባሰበው ወንጀለኛ ለመያዝ ነው ቢባልም ይህን ከመጠቀምና መረጃ ለፍርድ ቤት ከማቅረብ ይልቅ የመረጡት መንገድ በአሰራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን የሚሰራበትን የግፍ ምርመራ ዘዴ ነው፡፡ተጠርጣሪን አጣርተው መያዝ ሲገባቸው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመጠየቅ ተጠርጣሪንም ቤተሰብንም ማንገላታት ነው፡፡ ይህ የሚያሳየው መንግሰት በተደራጀ መልክ መረጃ አሰባሰበው ክስ መመስረት እንደማይችል፤ ይልቁንም በጉልበት በመጠቀም ማሰፈራራትን መምረጡን ነው፡፡ ተፈጥሮዋዊ ነፃነታቸውን በህውቀታቸውና በልምዳቸው መሰረት ህዝብ እንዲያውቅ ሲተጉ ከነበረ ወጣቶችና በባንኮኒ ውስጥ ተዉኝ ልኑርበት ከሚለው ማን ክብር አለው? ምርጫው የግል ነው፡፡

ቸር ይግጠመን!!!!

Silencing the Zone9 by hook or crook

May 20, 2014
by Hindessa Abdul
It has been over three weeks since close to a dozen journalists and bloggers were arrested, most of whom members of the blogging collective known as Zone 9. Their site, hosted in Google’s Blogger platform, was launched two years ago with a catching motto “We blog because we care.” They coined the name after a visit to the Zone 8 of the Kaliti prison, where a fellow journalist, Reeyot Alemu, is serving a five year sentence. Zone 9 is a metaphor to say the rest of the populace is also in jail but in a different cell block. No surprises, their page was blocked within weeks of its launch.An Ethiopian court granted police 10 more days to investigate six bloggers and journalists
Abel Wabela, Asmamaw W/Giorigis, Atnaf Berhane, Befekadu Hailu, Edom Kassaye, Mahlet Fantahun, Natnael Feleke, Tesfalem Weldyes, Zelalem Kebret have been locked up in the notorious Maekelawi in the north of Addis, where the tradition of torture is well alive and kicking.The bloggers were public servants,university professors,information technology professionals, full time journalists so on and so forth.
As it has become absurdly the norm, police had detained then started to investigate the alleged crimes, dashing the hopes of a speedy trial. So far the broad allegations are: working with a foreign organization that claim to be human rights group; conspiring to incite violence via the social media. An advisor to the Prime Minister put it as “criminal activities” without delving into specifics. Police have requested more time to investigate. The courts have no problem granting the wishes of the police at the expense of the detainees.
Some papers that came out in the last couple of days said, weeks after the arrest nobody knows the reason for their detention. However piecing together the words of police and close associates of the ruling party , there are clues to indicate where this thing is going to end up.
The dots
At the beginning of April, security officials detained Patrick Mutahi, a Kenyan national and a staff of Article 19 – a London based rights group working for the defense of freedom of expression — at the Bole International Airport. His earlier visits to the country (said to be five times) have been closely monitored.
Ironically Patrick’s travel to Ethiopia was related to a training on security and safety. Talking of safety, media watchdog groups train journalists in various skills. In recent years, with governments filtering the web, the subject of circumnavigating censorship; concealing the location from where blogs are posted have gained traction. Back in the early days of Internet filtering, the Paris based Reporters without Borders produced a famous manual called Handbook for Bloggers and Cyber-dissidents to help protect journalists in otherwise unfriendly political systems.
While Patrick was deported back to his country after a day in custody, his cell phone was confiscated, leaving behind a trove of information.
Enter HRW
In March of this year Human Rights Watch published a report on the state of surveillance in Ethiopia. The 100 page report entitled: ‘They Know Everything We Do: Telecom and Internet Surveillance in Ethiopia’ explains how security officials willy-nilly eavesdrop on the phone conversation of citizens. Here is a witness telling his encounter in the report:
“After some time I got arrested and detained. They had a list of people I had spoken with. They said to me, “You called person x and you spoke about y.” They showed me the list—there were three pages of contacts—it had the time and date, phone number, my name, and the name of the person I was talking with. “All your activities are monitored with government. We even record your voice so you cannot deny. We even know you sent an email to an OLF [Oromo Liberation Front] member.” I said nothing.”
Hence, the call log in Patrick’s phone will reveal all the individuals he had contacted. No matter what the conversations, it would be construed in a way that justifies the government’s paranoia.
TPLF insiders
A day after the detention of most of the suspects, Mimi Sebhatu, a close confidant of the Meles-Azeb family went on to her radio station and said the suspects had contact with Article 19. Mimi may have an inside knowledge not least because of her association with the inner circle as to her family’s history in the lucrative security business in the country.
In the closed court appearance police told the judges that some of the suspects travelled to Kenya and have received money and training from a human rights group. Police stopped short of mentioning who the rights group was.
TPLF run online media in North America are having a field day attacking Article 19 and the bloggers. They call the group “a neo-liberal extremist organization for hire, created for the sole reason of overthrowing democratically elected governments.” And the bloggers are guilty even before they are formally charged. “It’s a criminal act to make Addis Ababa turn into Ukraine’s Kiev for the sake of money, by working with the likes of ‘Article 19’ Eritrea and Egypt,” opined one.
So there should be no doubt as to what the charges will be associated with. The insiders have told us in no uncertain terms that it is all about Article 19. We, surly, will stay tuned.

በጅዳ የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ጣቢያ ዘጋቢ ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ የህሊና እስረኛ መሆኑ ተገለፀ !

May19/2014
በጅዳ የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ጣቢያ ዘጋቢ ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ የህሊና እስረኛ መሆኑ ተገለፀ !

በሳውዲ አረቢያ እና በመካከለኘው ምስራቅ  የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በደል እና ስቃይ  በማለዳ ወግ ዘገባው የሚታወቀው  ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ  በመረጃ ቅበላው ባልተደስቱ ወገኖች  ለእስር መዳረጉ ይታወሳል።  ነብዩ ሲራክ ላለፉት ሁለት አስርት አመታት ከኖረባት ሳውዲ አረቢያ «ጅዳ » ከተማ  በስሙ  በከፈተው ሶሻል ሚዲያ እና ከቅርብ ግዜ ወዲህ የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ወኪል በመሆን በአረቡ አለም የሚገኙ ወገኖች የሚያሰሙትን እሮሮ  በማስተጋባት በህዝብ ዘንድ ክብር እና አድናቆትን ያተረፈ ጋዜጠኛ ነው ። ይህ ጋዜጠኛ  እንደማንኛውም ሰው  የስደት አለም ህይወቱን ለመግፋት በግል ተቀጥሮ ከሚሰራበት መ/ቤት የስራ ሰዓት ውጭ የእረፍት ግዜውን መስዋት በማድረግ ሰለቸኝ፡ደከመኝ ሳይል «ሳይማር ያስተማረውን  ወገኑን» በሙያው ሲያገለግል የኖረ  ጋዜጠኛ መሆኑ በአብዛኛው  ኢትዮጵያውያን  ዘንድ ይነገራል ። ነብዩ ሲራክ  በሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈፀሙ  ቅጥ ያጡ ግፍ እና በደሎች መቋጫ ይበጅላቸው ዘንድ  በሚያቀርባቸው ተከታታይ ዘገባዎቹ  በስልክ እና በጽሑፍ ይሰነዘሩበት  ለነበሩ ስድብ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ቅንጣት ያህል ሳይሸበር ወህኒ እስከገባበት ዕለት የወገኑን ህይወት ለመታደግ ከማለዳ ወግ የመረጃ ቅበላው ባሻገር በስው ሃገር በወረበሎች የታገቱ እህቶቻችንን ነጻ ለማውጣት ከህግ አስከባሪዎች ጎን ቆሞ የአጋች እና ታጋች ድራማ በሠላም እንዲጠናቀቅ ያደረገ ከህዝብ የወጣ ለህዝብ የኖረ ኢትዮጵያዊ ነው  ። 

ከዚህ ባሻገር ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ የሳውዲ አረቢያ መንግስት ለውጭ ሃገር ዜጎች  ያወጣውን የ 6 ወር እና የ 3 ወር የግዜ ገደብ መጠናቀቅ  ተከትሎ ሰነዶቻቸውን ለማስተካከል ጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት  አይን ያልገልጹ ህጻናት ልጆቻቸውን ታቀፈው በጠራራ ጸሃይ  ሲነፍሩ ለነበሩ እናቶች እና በስደት አለም ግራ ተጋብተው በተስፋ ቆንስላ ጽ/ቤት በር ላይ ድንጋይ ተንተርሰው ጸሃይ እና ነፋስ ሲፈራረቅባቸው ለነበሩ ዜጎች  ቀዝቃዛ ውሃ በማደል  ከሰው ምስጋናንን ከፈጣሪ  ጽድቅን ያገኘ ሩሩሁ እና ለወገን አዛኝ መሆኑ ይታወቃል። 

በሰው ሃገር ተስፋ ሰንቀው ግፍ በደሉ የስደት አለም ኖሮቸውን መቅኔ ላሳጣው ወገኖች ድምጽ በመሆን  የሚታወቀው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ   ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በቆንስላው ጽ/ቤት በአግባቡ መስተናገድ እና ፈጣን የሆኑ አገልግሎቶችን ማግኘት እንደሚገባው ባቀረበው የመፍትሄ ሃስብ  በተበሳጩ  አንዳንድ የጽ/ቤት ሹማምንቶች  ቂም ተይዞበት ጉድጓድ ሲማስለት መሰንበቱ ይታወሳል።  ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ እንደ ዜጋ  በጅዳ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ስር የሚገኙ ንብረቶችን  ለማስተዳደር በት/ቤት የወላጆች ኮሚቴ እና በተለያዩ የኮሚኒቲው መዋቅሮች  የሃላፊነት ቦታዎች  እንዲያገለግል በማህበረሰቡ  ተመርጦ የመረጠውን ህዝብ በቅንነት እና በታማኝነት ለማገልገል በነበረው ሂደት ውስጥ ህሊናው የማይቀበላቸውን አያሌ ሚስጥራዊ አሰራሮች በመቃወሙ ብቻ ከነበረበት የሃላፊነት ቦታ እንዲነሳ ከማድረጉም በላይ  ላልተወሰነ ግዜ ቆንስላ ጽ/ቤት አካባቢ እንዳይደርስ  ህገወጥ ውስኔ  ተላልፎበት እንደነበር የሚያስታውሱ ወገኖች ጋዜጠኛ  ነብዩ ሲራክ  ከወህኒ ነጻ ከወጣም በኃላም ስለወገኑ ስቃይ እና በደል   እንዳይጽፍ እና እንዳይናገር  የተጣለበት የህሊና ነጻነት ገደብ ከዚህ በላይ በተገለጹ መስረታዊ ጉዳዩች ህዝብ መረጃ  የማግኘት  መብቱን  ለመቀልበስ በእጅ አዙር   የተውሰደ እርምጃ ሊሆን እንደሚችል ይነገራል  ። 

ከሁለት ወራት ወህኒ ቆይታ በሃላ በቀርብ ቀን ነጻ የወጣው ጋዜጠኛ  ነብዩ ሲራክ በአሁኑ ሰአት በመልካም ጤንነት ላይ መሆኑን ቢታወቀም  ጋዜጠኛው  ከእንግዲህ በስደተኞች ዙሪያ ምንም አይነት መረጃዎችን በሶሻል ሚዲያ ሆነ በጀርመንድ ድምጽ እንዳይዘግብ  ከባድ ማስጠንቀቂያ የተላለፈበት መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል ።  የጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ  የህሊና እስረኛ መሆንን ተከትሎ አንዳንድ ወገኖች  በመካከለኛው ምስራቅ  ግፍ እና በደል የሚፈጸምባቸውን በሚልዮን የሚቆጠሩ ድምጽ አልባ  ኢትዮጵያውያን  ህይወት የከፋ ሊያደርገው እንደሚችል ስጋታቸውን ይገልጻሉ ። 
Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ
በሳውዲ አረቢያ እና በመካከለኘው ምስራቅ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በደል እና ስቃይ በማለዳ ወግ ዘገባው የሚታወቀው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ በመረጃ ቅበላው ባልተደስቱ ወገኖች ለእስር መዳረጉ ይታወሳል። ነብዩ ሲራክ ላለፉት ሁለት አስርት አመታት ከኖረባት ሳውዲ አረቢያ «ጅዳ » ከተማ በስሙ በከፈተው ሶሻል ሚዲያ እና ከቅርብ ግዜ ወዲህ የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ወኪል በመሆን በአረቡ አለም የሚገኙ ወገኖች የሚያሰሙትን እሮሮ በማስተጋባት በህዝብ ዘንድ ክብር እና አድናቆትን ያተረፈ ጋዜጠኛ ነው ። ይህ ጋዜጠኛ እንደማንኛውም ሰው የስደት አለም ህይወቱን ለመግፋት በግል ተቀጥሮ ከሚሰራበት መ/ቤት የስራ ሰዓት ውጭ የእረፍት ግዜውን መስዋት በማድረግ ሰለቸኝ፡ደ...ከመኝ ሳይል «ሳይማር ያስተማረውን ወገኑን» በሙያው ሲያገለግል የኖረ ጋዜጠኛ መሆኑ በአብዛኛው ኢትዮጵያውያን ዘንድ ይነገራል ። ነብዩ ሲራክ በሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈፀሙ ቅጥ ያጡ ግፍ እና በደሎች መቋጫ ይበጅላቸው ዘንድ በሚያቀርባቸው ተከታታይ ዘገባዎቹ በስልክ እና በጽሑፍ ይሰነዘሩበት ለነበሩ ስድብ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ቅንጣት ያህል ሳይሸበር ወህኒ እስከገባበት ዕለት የወገኑን ህይወት ለመታደግ ከማለዳ ወግ የመረጃ ቅበላው ባሻገር በስው ሃገር በወረበሎች የታገቱ እህቶቻችንን ነጻ ለማውጣት ከህግ አስከባሪዎች ጎን ቆሞ የአጋች እና ታጋች ድራማ በሠላም እንዲጠናቀቅ ያደረገ ከህዝብ የወጣ ለህዝብ የኖረ ኢትዮጵያዊ ነው ። 

ከዚህ ባሻገር ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ የሳውዲ አረቢያ መንግስት ለውጭ ሃገር ዜጎች ያወጣውን የ 6 ወር እና የ 3 ወር የግዜ ገደብ መጠናቀቅ ተከትሎ ሰነዶቻቸውን ለማስተካከል ጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት አይን ያልገልጹ ህጻናት ልጆቻቸውን ታቀፈው በጠራራ ጸሃይ ሲነፍሩ ለነበሩ እናቶች እና በስደት አለም ግራ ተጋብተው በተስፋ ቆንስላ ጽ/ቤት በር ላይ ድንጋይ ተንተርሰው ጸሃይ እና ነፋስ ሲፈራረቅባቸው ለነበሩ ዜጎች ቀዝቃዛ ውሃ በማደል ከሰው ምስጋናንን ከፈጣሪ ጽድቅን ያገኘ ሩሩሁ እና ለወገን አዛኝ መሆኑ ይታወቃል። 

በሰው ሃገር ተስፋ ሰንቀው ግፍ በደሉ የስደት አለም ኖሮቸውን መቅኔ ላሳጣው ወገኖች ድምጽ በመሆን የሚታወቀው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በቆንስላው ጽ/ቤት በአግባቡ መስተናገድ እና ፈጣን የሆኑ አገልግሎቶችን ማግኘት እንደሚገባው ባቀረበው የመፍትሄ ሃስብ በተበሳጩ አንዳንድ የጽ/ቤት ሹማምንቶች ቂም ተይዞበት ጉድጓድ ሲማስለት መሰንበቱ ይታወሳል። ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ እንደ ዜጋ በጅዳ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ስር የሚገኙ ንብረቶችን ለማስተዳደር በት/ቤት የወላጆች ኮሚቴ እና በተለያዩ የኮሚኒቲው መዋቅሮች የሃላፊነት ቦታዎች እንዲያገለግል በማህበረሰቡ ተመርጦ የመረጠውን ህዝብ በቅንነት እና በታማኝነት ለማገልገል በነበረው ሂደት ውስጥ ህሊናው የማይቀበላቸውን አያሌ ሚስጥራዊ አሰራሮች በመቃወሙ ብቻ ከነበረበት የሃላፊነት ቦታ እንዲነሳ ከማድረጉም በላይ ላልተወሰነ ግዜ ቆንስላ ጽ/ቤት አካባቢ እንዳይደርስ ህገወጥ ውስኔ ተላልፎበት እንደነበር የሚያስታውሱ ወገኖች ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ከወህኒ ነጻ ከወጣም በኃላም ስለወገኑ ስቃይ እና በደል እንዳይጽፍ እና እንዳይናገር የተጣለበት የህሊና ነጻነት ገደብ ከዚህ በላይ በተገለጹ መስረታዊ ጉዳዩች ህዝብ መረጃ የማግኘት መብቱን ለመቀልበስ በእጅ አዙር የተውሰደ እርምጃ ሊሆን እንደሚችል ይነገራል ። 

ከሁለት ወራት ወህኒ ቆይታ በሃላ በቀርብ ቀን ነጻ የወጣው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ በአሁኑ ሰአት በመልካም ጤንነት ላይ መሆኑን ቢታወቀም ጋዜጠኛው ከእንግዲህ በስደተኞች ዙሪያ ምንም አይነት መረጃዎችን በሶሻል ሚዲያ ሆነ በጀርመንድ ድምጽ እንዳይዘግብ ከባድ ማስጠንቀቂያ የተላለፈበት መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል ። የጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ የህሊና እስረኛ መሆንን ተከትሎ አንዳንድ ወገኖች በመካከለኛው ምስራቅ ግፍ እና በደል የሚፈጸምባቸውን በሚልዮን የሚቆጠሩ ድምጽ አልባ ኢትዮጵያውያን ህይወት የከፋ ሊያደርገው እንደሚችል ስጋታቸውን ይገልጻሉ ።
Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ

Monday, May 19, 2014

President Obama and Ethiopia’s Call for Freedom (Video)

May19/2014



On May 8, 2014, Ethiopian journalist and freedom activist Abebe Gellaw interrupted

President Barack Obama at a Democratic National Committee Fundraiser. He called onPresident Obama to support freedom for Ethiopia and stand with the oppressed people ofEthiopia. The U.S. has been funding the tyrannical regime in Ethiopia, which is routinelyaccused of committing gross human rights violations including extrajudicial killings, torture,

Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statementsof various information and content providers. The Website neitherrepresents nor endorses the accuracy of information or endorsesthe contents provided by external sources. All blog posts andcomments are the opinion of the author