Thursday, January 16, 2014

ኡስታዝ አቡበክር አህመድ በመኪና ሰው ገጭተህ አምልጠሃል በሚል በሃሰት ክስ ተመሰረተባቸው

January15/2013

ሳዲቅ አህመድ እንደዘገበው

የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ላይ ፖሊስ በሃሰተኛ ወንጀል አዲስ ክስ እንደመሰረተባቸው ምንጮች አስታወቁ፡፡

ኡስታዝ አቡበከር አህመድ የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ዛሬ ረቡዕ እንዲቀርቡ የተደረገ ሲሆን በ 2004 በመኪና ሰው ገጭተው አምልጠዋል በሚል ክስ እንደተመሰረተባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ፍርድ ቤት ከቀረቡ ቡሃላ አቃቤ ህጉ ክሱን ለፍርድ ቤቱ በንባብ ያሰማ ሲሆን ሀምሌ 8 2004 ላይ በተለምዶ ሶማሌ ተራ በሚባለው አካባቢ ላይ በንብረት እና በሰው ሂወት ላይ አደጋ ሊያስከትል በሚችል መልኩ ከተገቢው ፍጥነት በላይ አሽከርካሪውን በማሽከርከር በአንድ ሰው የእጁ አውራ ጣት ላይ የስብራት አደጋ አድርሰው ጥለውት ሄደዋል የሚል ክስ እንዳቀረበባቸው ተዘግቧል፡፡

ይህም ድርጊት ተፈፀመ የተባለው ሃምሌ 8 ቀን የደህንንንት ሃይሎች የኮሚቴውን አመራሮች ከመንገድ ላይ በማገት ወደ ሚፈልጉት ቦታ የብልግና ስድብ እየሰደቡ ይዘዋቸው በሚወስዱበት ሰአት መሆኑ ታውቋል፡፡ በዚህ ቀን መታቂያቸውን አናሳይም ያሉት ደህንነቶች ጋጠወጥ በሆነ መልኩ ብልግና እየተሳደቡ ለማገት ያደረጉትን ሙከራ በማክሸፍ ወደ ታላቁ አንዋር መስጂድ አምልጠው መግባታቸው ይታወሳል፡፡ በዚህ ወቅት ነው ሰው ገጭታችሁ አምልጠሃል በሚል በሃሰት ወንጀል የቀረረበባቸው፡፡

ኡስታዝ አበቡበከር አህመድ ከዚህ ቀደም በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የወንጀል መርማሪ ፖሊሶች ወደሳቸው በመሄድ ይህን ወንጀል ፈፅመዋል በሚል ቃላቸውን እንዲሰጡ ተጠይቀው የነበረ ሲሆን ኡስታዝ አቡበከርም የተባለውን ድርጊት አለመፈፀማቸውን በወቅቱ መኪና ሲያሽከረክሩ እንዳልነበር፣መኪናውም የሌላ ሰው እንደነበር እና በሹፌር ሲሄዱ እንደነበር ብሎም ከፊት ለፊት በነበረው የመኪና መቀመጫ ላይም ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ተቀምጠው እንዳልነበር እና በደህንነቶች ጋጠ ወጥ በሆነ መንገድ የእገታ ወንጀል ሲፈፅምባቸው ከወንጀል ድርጊቱ ማምለጣቸውን በዝርዝር ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡

ይህንንም በማስመለከት ዛሬ ፍርድ ቤት በቀረቡበት ሰአት ፍርድ ቤቱ ቃላቸውን ሰጥተው እንደሆነ ለማረጋገጥ የጠየቃቸው ሲሆን ኡስታዝ አቡበከር አህመድም ቃላቸውን መስጠታቸውን እና የዚህ አይነት ድርጊት በወቅቱ አለመፈፀሙን ብሎም የሚያውቁት ጉዳይ እንደሌለ አስረድተዋል፡፡
ፍርድ ቤቱም ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የሚባሉ አካላት ፍርድ ቤት መቅረባቸውን የጠየቀ ቢሆንም አለመገኘታቸው የተገለፀ ሲሆን ምስክር የተባለ አንድ ግለሰብ ብቻ ግን ችሎት የቀረበ ሲሆን ሁሉም ተሟልተው እንዲቀርቡ ለጥር 28 ቀነ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
ይህ ክስ ሆን ተብሎ የኡስታዝ አቡበከር አህመድን ፅናት ለመፈታተን እና ተስፋ ለማስቆረጥ ሆን ተብሎ የተደረገ ተግባር ሲሆን በተጨማሪም ኮሚቴው በእስር ላይ ሆነው ባወጡት መግለጫ በመበሳጨታቸው እና የተፈጠረው መነቃቃት ወደሌላ አቅጣጫ ሆን ተብሎ ለማስቀየስ መሆኑን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

ለትውስታ ኢቲቪ በአቡበከር ላይ ሃሰተኛ ቪድዮ ሰርቶ ከለቀቀ በኋላ በስህተት ኤዲት ያልተደረገውን ቪድዮ ለቆት እንደነበር ይታወሳል፤ በድጋሚ ይመልከቱት



ዘ -ሐበሻ

ኡስታዝ አቡበክር አህመድ በመኪና ሰው ገጭተህ አምልጠሃል በሚል በሃሰት ክስ ተመሰረተባቸው

January15/2013

ሳዲቅ አህመድ እንደዘገበው
የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ላይ ፖሊስ በሃሰተኛ ወንጀል አዲስ ክስ እንደመሰረተባቸው ምንጮች አስታወቁ፡፡
ኡስታዝ አቡበከር አህመድ የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ዛሬ ረቡዕ እንዲቀርቡ የተደረገ ሲሆን በ 2004 በመኪና ሰው ገጭተው አምልጠዋል በሚል ክስ እንደተመሰረተባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡
ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ፍርድ ቤት ከቀረቡ ቡሃላ አቃቤ ህጉ ክሱን ለፍርድ ቤቱ በንባብ ያሰማ ሲሆን ሀምሌ 8 2004 ላይ በተለምዶ ሶማሌ ተራ በሚባለው አካባቢ ላይ በንብረት እና በሰው ሂወት ላይ አደጋ ሊያስከትል በሚችል መልኩ ከተገቢው ፍጥነት በላይ አሽከርካሪውን በማሽከርከር በአንድ ሰው የእጁ አውራ ጣት ላይ የስብራት አደጋ አድርሰው ጥለውት ሄደዋል የሚል ክስ እንዳቀረበባቸው ተዘግቧል፡፡
ይህም ድርጊት ተፈፀመ የተባለው ሃምሌ 8 ቀን የደህንንንት ሃይሎች የኮሚቴውን አመራሮች ከመንገድ ላይ በማገት ወደ ሚፈልጉት ቦታ የብልግና ስድብ እየሰደቡ ይዘዋቸው በሚወስዱበት ሰአት መሆኑ ታውቋል፡፡ በዚህ ቀን መታቂያቸውን አናሳይም ያሉት ደህንነቶች ጋጠወጥ በሆነ መልኩ ብልግና እየተሳደቡ ለማገት ያደረጉትን ሙከራ በማክሸፍ ወደ ታላቁ አንዋር መስጂድ አምልጠው መግባታቸው ይታወሳል፡፡ በዚህ ወቅት ነው ሰው ገጭታችሁ አምልጠሃል በሚል በሃሰት ወንጀል የቀረረበባቸው፡፡
ኡስታዝ አበቡበከር አህመድ ከዚህ ቀደም በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የወንጀል መርማሪ ፖሊሶች ወደሳቸው በመሄድ ይህን ወንጀል ፈፅመዋል በሚል ቃላቸውን እንዲሰጡ ተጠይቀው የነበረ ሲሆን ኡስታዝ አቡበከርም የተባለውን ድርጊት አለመፈፀማቸውን በወቅቱ መኪና ሲያሽከረክሩ እንዳልነበር፣መኪናውም የሌላ ሰው እንደነበር እና በሹፌር ሲሄዱ እንደነበር ብሎም ከፊት ለፊት በነበረው የመኪና መቀመጫ ላይም ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ተቀምጠው እንዳልነበር እና በደህንነቶች ጋጠ ወጥ በሆነ መንገድ የእገታ ወንጀል ሲፈፅምባቸው ከወንጀል ድርጊቱ ማምለጣቸውን በዝርዝር ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡
ይህንንም በማስመለከት ዛሬ ፍርድ ቤት በቀረቡበት ሰአት ፍርድ ቤቱ ቃላቸውን ሰጥተው እንደሆነ ለማረጋገጥ የጠየቃቸው ሲሆን ኡስታዝ አቡበከር አህመድም ቃላቸውን መስጠታቸውን እና የዚህ አይነት ድርጊት በወቅቱ አለመፈፀሙን ብሎም የሚያውቁት ጉዳይ እንደሌለ አስረድተዋል፡፡
ፍርድ ቤቱም ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የሚባሉ አካላት ፍርድ ቤት መቅረባቸውን የጠየቀ ቢሆንም አለመገኘታቸው የተገለፀ ሲሆን ምስክር የተባለ አንድ ግለሰብ ብቻ ግን ችሎት የቀረበ ሲሆን ሁሉም ተሟልተው እንዲቀርቡ ለጥር 28 ቀነ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
ይህ ክስ ሆን ተብሎ የኡስታዝ አቡበከር አህመድን ፅናት ለመፈታተን እና ተስፋ ለማስቆረጥ ሆን ተብሎ የተደረገ ተግባር ሲሆን በተጨማሪም ኮሚቴው በእስር ላይ ሆነው ባወጡት መግለጫ በመበሳጨታቸው እና የተፈጠረው መነቃቃት ወደሌላ አቅጣጫ ሆን ተብሎ ለማስቀየስ መሆኑን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
ለትውስታ
ኢቲቪ በአቡበከር ላይ ሃሰተኛ ቪድዮ ሰርቶ ከለቀቀ በኋላ በስህተት ኤዲት ያልተደረገውን ቪድዮ ለቆት እንደነበር ይታወሳል፤ በድጋሚ ይመልከቱት


Wednesday, January 15, 2014

EPRDF abandons Revolutionary Democracy: Bereket

ESAT News
January 15, 2014
The former Minister of Communications and now the advisor of Prime Minister Hailemariam Dessalegn, Bereket Simon, said at a recent meeting and evaluation with ministers and top leadership of the Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) “as theories used to lead the people could rust unless updated, it has become necessary to replace Revolutionary Democracy with Developmental Democracy”.  EPRDF’s is better described through the latter, he said.
He said before we replaced Revolutionary Democracy with Developmental Democracy, the Front has been divided into three groups. Bereket said one group of the leadership had argued that our problem was internal and that we need to first check that while the other group held that our problem was Shabia/Eritrea and that we need to fight them first but the third position which said that after fighting Shabia/Eritrea, we should then look at our internal problems had becoming the winning idea.
Bereket said the main force of riot during the 2005 post election violence had been the youth and unless job opportunities are created for the youth, they can rebel against the regime and the country. It is to be recalled that the government had been accusing oppositions for instigating the post election violence of 2005.
EPRDF wants to establish a government that is independent of investors or the private sector as “it is the farmer and the poor urbanite that brings us to power” Bereket added. He said the government is not administered by the finance of the private sector and if it wanted money, it could get it from them in the name of taxation. This government has its own sources of income for the sake of its own survival such as Airlines, Banks and Electric Corporation, he added.
A senior member of the Front said that attendants were surprised at Bereket’s statements which remarked that the EPRDF can win the upcoming election without the support of investors and saying that the government has sufficient finance. He said Bereket’s statements tell that the EPRDF will take money from the government to conduct the election.
Unless the government has its own sources of income, it will be like Western African countries such as Coted D’ivore’s government which gets its payments from the French embassy in the Country.  He said the case is similar in Kenya.
EPRDF obtained over 100 million birr from private investors during the 2010 election.

Due to the light train, road construction and digging and lack of transport, it has become so unpleasant to live in Addis Abeba but most residents accept it as ‘development’.

የአንድነት ከፍተኛ አመራሮች ከአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያዩ

January15/2014
የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ለአንድነት ፓርቲ ባቀረበው ጥሪ መሰረት የፓርቲው ስራ አስፈፃሚዎችና ከ22 ከሚበልጡ የህብረቱ ሀገራት ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን የአንድነት ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ክፍል አስታወቀ፡፡ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ለፍኖተነፃነት እንዳስታወቁት ትላንት ጥር 6 ቀን 2006 ዓ.ም በተደረገው በዚህ ውይይት የአንድነት ፕሬዝዳንት ፣የህዝብ ግንኙነትና የውጪ ግንኙነት ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

  በውይይቱ ወቅት የተለያዩ ሀገራትን የወከሉት የህብረቱ ዲፕሎማቶች አሁን ስለሳለው አጠቃላይ የሀገራችን የፖለቲካ ሁኔታ፣አንድነት እንደ ፓርቲ ያለበትን ሁኔታ በዝርዝር ለማወቅ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት የፓርቲው ፕሬዝደንት በፕሮጀክተር የታገዘ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አንድነት ከግንኙነት ስትራቴጂ አንፃር በሀገር ውስጥ እንዲሁም በውጪ ማለትም ከኢትዮጵያ ዳያስፖራና ከአለም አቀፉ ህብረተሰብ ጋር ስለሚኖረው ግንኙነት የተብራራ ምላሽ ተሰጥቷቻዋል፡፡ ኢንጅነት ግዛቸው አንድነት በሚመለከት ባቀረቡት ገለፃ የፓርቲውን ርዕይ፣ተልዕኮና አላማ በሰፊው    አብራርተዋል፡፡በመቀጠልም ስለአንድነት ፖሊሲዎችና መርሆዎች ጥልቅ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

 አክለውም የአንድነት ፓርቲን ተቋማዊ አደረጃጀት በሚመለከት ገለፃ ሰጥተዋል፡፡ የሀገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ በሚመለከትም የኢህአዴግ መንግስት ባለፉት አመታት አንዳችም አይነት የለውጥ አዝማሚያ እንዳላሳየ ይልቁኑም ተቋማዊ የአፈና ስርአትን እያጠናከረ እንደሚገኝ ፕሬዝዳቱ ማሳያዎችን በመጥቀስ አብራርተዋል፡፡

የኢህአዴግ መንግስት የተዘፈቀበትን ሙስና ግዝፈት የዘረዘሩት ኢንጅነር ግዛቸው የፀረሽብር ህጉ ከመንግስት የተለየ የፖለቲካ አቋም ያላቸውን ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ለማጥቃት የተቀመጠ መሆኑን በአንድነት አመራሮችና በሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችም ላይ የደረሰውን እስርና እንግልት በማሳያነት አስረድተዋል፡፡ አንድነት ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት ጋር መልካም ግንኙነት እንዳለውና በበርካታ ሀገራትም የተቋቋሙ የአንድነት ድጋፍ ሰጪ ቻፕተሮች እንዳሉ ጠቁመዋል፡፡

 ወደፊትም በተጠናከረ ደረጃ በሀገራቸው ፖለቲካ ላይ በቀጥታ የሚሳተፉበትን መንገድ እንደተቀየሰና የዲያስፖራው አባላትን በአባልነትና በድጋፍሰጪነት በንቃት ለማሳተፍ መታቀዱን ፕሬዝደንቱ ተናግረዋል፡፡ በውይይቱ ላይ ከፓርቲው ፕሬዝደንት ከኢንጅነር ግዛቸው ሽፈራው ጋር የተገኙት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ሀብታሙ አያሌውና የውጪ ግንኙነት ሀላፊው ኢ/ር ዘለቀ ረዲ ተጨማሪ ማብራሪያ መስጠታቸውም ታውቋል፡፡

“የህዝባዊ አንድነትና ኃይል የወያኔ ሕወሐት ማጥፊያ መድሃኒት”

January15/2014

ከሮባ ጳዉሎስ

ካለመታደል ሀገራችን ዛሬም ሰላም ፍትህና ዲሞክራሲ የሰፈነባት በልማትና በእድገት ጎዳና የምትራመድ ሀገር አልሆነችም። ለዚህም በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም እንደ ዓቢይ ምክንያት ተደርጎ የሚቀርበው የህዝብን ይሁንታን ያገኘ፡ ህዝብን በእኩልነት የሚዳኝ፡ ህዝባዊና ዲሞክራሲያዊ የሆነ መንግሥት አለመመስረቱ፡ አገርና ህዝብ የሚተዳደሩበት ዲሞክራሲያዊ ህገ መንግሥት አለመኖሩ ነው። እስከዛሬ በተጨባጭ እንደታየው በ ኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ የተፈራረቁበት ገዥዎቹ በየበኩላቸው አንዱ ከሌላው የሚለዩባቸው ባህርያት ቢኖራቸውም ሁሉንም ግን አንድ የሚያስመስሏቸው ባህርያትም አሏቸው። እነሱም ሁሉም በኃይል ሥልጣን መያዛቸው፡ አምባገነንነታቸው፡ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ማራመዳቸው፡ በህዝብ መካከል የጋራ መተማመንና ከበሬታን ለመፍጠር፡ ሁሉም ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን በሀገሪቱ ለማስፈን አለመቻላቸው ደግሞ ዛሬ ለሁሉም በግልጥ እየታየ ያለ ነው። በዚህም የተነሳ በሀገራችን ለብሔራዊ ክብርና ነፃነት፡ ለዲሞክራሲ፡ ለማህበራዊ ፍትህ፡ ለሰላምና ለእኩልነት የሚታገሉ ኃይሎች የሰላማዊ ለውጥ በሮች ስለተዘጉባቸው የአ መፅን ጎዳና እንዲከተሉ የሚጋብዝ በር ተቀዶ ይገኛል።


በሌላ በኩል ደግሞ በሀገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ መረጋጋት ንእዲፈጠር፡ ሕዝቡም አስተማማኝ ሰላምና ፀጥታ አግኝቶ ያለስጋት ለመኖር እንዲችል፡ የዳኝነት ተቋሞች ነፃ ሆነው የሚሠሩበት፡ የህግ የበላይነት የተረጋገጠበት ሁኔታ እንዲፈጠርና፡ ህዝቡም በህግና ሥርዓት መኖር ላይ እምነት እንዲያድርበት ለማድረግ እንዲቻል፡ ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊ ተቃዋሚ ኃይሎች በተናጠልም ሆነ በኅብረት በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል። ሆኖም እስከዛሬ የተደረጉት ጥረቶችን ሁሉ በማምከን ወያኔ የሰላምና የእርቅ መሰናከል ከመሆኑም ባሻገር በንፁሃን ዜጎች ደም ሰላምን አጠልሽቶታል። ወያኔ ስለ ሰላምና እርቅ ሊሰማም ሊነጋገርም እማይችልበት የደም ስካር ላይ ደርሷል።

ብአዴን ቢመጣ ኦህዴድ ቢመጣ ደህዴን ቢመጣ የሚለወጥ ነገር አይኖርም። ጠንከር ያለ ለለውጥ የተዘጋጀ – አስከ ሞት የቆረጠ -ጠቅላይ ሚኒስተር ስልጣን አገኘ ማለት የህወሃት የበላይነት እና ፈላጭ ቆራጭነት ፍላጎት ፈተና ይገጥመዋል ማለት ስለሆነ! ህወህት የበላይነቱን ለማሰጠበቅ የፈጠራቸው የመንግስት ስልጣን አደረጃጀት አና ተቋማት ዛሬም በሙሉ ሃይላቸው አሉ። የህወሃት ፈላጭ ቆራጭነት ሳይዳከም ለውጥ አይመጣም። የህወሃት ፈላጭ ቆራጭነት መሰረቱ ደሞ ከምንም በላይ ወታደራዊ ሃይሉ ላይ የተመሰረተ አንደሆነ የአደባባይ ሚስጥር ነው። በደህነንት ቢሮ ያሉትን የህወሃት አመራሮች ከታች ያሉት ማዳክም የሚችሉበትን አጋጣሚ አና ሁኔታ ተጠቅመው አስካላዳከሙት ደረስ የህወሃት የስልጣን የበላይነት ትርጉም ባለው ሁኔታ እክል ሊገጥመው አይችልም።

ሌላ ሌላውን ትተን መሰረታዊ የሆነ ህገ-መንግስታዊ ማሻሻያ ያስፈልጋል፣ የፍትህ ስርዕቱ የፍትህ ስርእት መመስልም መሆንም አለበት፣ የነጻው ፕሬስና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ህዳሴ አንመራለን አየተባለ በመካከለኛው ዘመን አና ከዛ በፊት ከነበረው አንደነበረው በሰይፍ አና በሰደፍ መያዝ የለበትም። አነኚህ ወሳኝ ርምጃዎች በአዝጋሚ ለውጥ ይመጣሉ ብየ አላስብም። የአዝጋሚ ለውጥ ዲስኩር (ፍላጎት ካለ ፍላጎትም) ጭራሽ ወደማይቀልበስ የባርነት ዓለም አና ዘመን የመውሰጃ ከፓለቲካ ዘዴ ሊሆን ይችላል። ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ ፓለቲካ መሪዎች ዘብጥያ ሲጣሉ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የፈጠሩትን ዓይነት ጫና መፍጠር ስላልተቻለ አንኳን መሰረታዊ የፕሬስ ነጻነት አና በነጻነት ያለገደብ የመደራጀት መብት የሚከበርበት ፍንጭ ሊገኝ ቀርቶ የታሰሩትን ጋዜጠኞች አና የፓለቲካ መሪዎች ማስፈታት አንኳን አልተቻለም። ጭራሽ መብታቸው ተረግጦ ያላግባብ አስር ቤት የተጣሉ ኢትዮጵያውያን ዛሬ ድረስ “አሸባሪ” አየተባሉ አየተፌዘባቸው ነው ያለው። አቶ ኃይለማርያምም ፌዙን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ አያስተጋቡት ነው።

ከበቀለበት የተጋጋበት አንዲሉ የ”በሳሉ መሪ ራዕይ” ዜማ ከህወሃት አባላት በእህት ድርጂቶች የፓለቲካ አላዋቂዎች አና መሪዎች ይበልጥ ተዜመ! በአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝም ተሰማ። ችግሩ የለውጥ ጥያቄ ማድበስበሻ ሆኖ ለረዢም ጊዜ ሊቆይ አይችልም። በውሽት ላይ የተመሰረተ ፐሮፓጋንዳ ስር ሊይዝ አይችልም።አንዴት ይሄን ማየት አቃታቸው?!የሕዝባችን መከራና ሰቆቃ እየከፋ ሄደ። የተጨቆነዉ ሕዝብ ተነሳስቶ ለመብቱ ሲታገል ጨቋኝ መንግሥታት ለዉጥ እንዲያደርጉ ይገደዳሉ፤ ካለዚያ በተባበረዉ የሕዝብ ኃይል ተንኮታኩተዉ ይወድቃሉ። የታገለዉ ለዉጥ ያመጣል፤ ያልታገለዉ ቁጭ ብሎ በባርነት ሲገዛ ይኖራል፤ ቁጭም ባለበት ይሞታል ማለት ነው። የለዉጥ ባለቤት ሁሌ ሕዝብ መሆን አለበት። ህዝቡ ትግሉን በሚገባ እንዲያቀናጅ የትግል መሪ ይፈልጋል። ስለዚህ የተቃዋሚ የፖሊቲካ መሪዎች ታላቅ ኃላፊነት ይጠበቅባቸዋል። ያገራችንን ጭብጥ ሁኔታ ስንመረምር ግን በሁለቱም በኩል ታላላቅና ተደጋጋሚ ድክመቶች ታይተዋል። አምባገነን መንግሥታት ለዘለዓለም ካልገዛን ሲሉ የተቃዋሚ ድርጅቶች ኅብረታቸዉን ማጠናከር ስላልቻሉ የጨቋኝ መንግሥታትን ዘመናት ሲያራዝሙ ቆይተዋል።ወያኔ/ኢሕአደግ ለዘለዓለም ሊገዛ አይችልም፤ ለሁሉም ጊዜ አለዉና።ትግሉ ይበልጥ መፋፋም፡ ይበልጥ መጨስ፡ መጋጋም፡ መንደድ ይጠበቅበታል። ትግሉን ለማፈንና አቅጣጫውን ለማሳት የወያኔ መንጋ እየተሯሯጠ ነው።

 በውጭ ያለውንም የሕዝብና የድርጅቶችን ተቃውሞ ቢቻለው ለማዳፈን፡ ካልሆነለት ደግሞ ለማዳከም፡ በአሁኑ ወቅት የወያኔ ከፋፋይ ቡድን በየቦታው በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ እያየን ነው። ይህ ቡድንም፡ ምሁር ነን፡ አስታራቂ ነን፡ ሽማግሌ ነን ወይም ታጋይ ነን በሚሉ መሰሪዎችም እየተደገፈ ነው። የሕዝብ ክንድ ይላላ፡ ይደክም ዘንድ፡ በከፋፋይ ሴራ የተሰማሩትን ነቅቶ መጠበቅ፡ ትግሉን መከላከል ብቻ ሳይሆን ወያኔ ለባሾችን፡ ሰላዮችን ሳንፈራ እየመነጠርን ማጋለጥ ይኖርብናል። ዘረኛው ቡድንና ጭፍሮቹ የሕዝቡን ትግል ለመከፋፈል ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እየጣሩ ናቸውና። ሕዝብ አንድነቱን ጠብቆ፡ የወያኔን ቡድን ለአንዴም ለሁሌም ለማስወገድ አስፈላጊውን መስዋእ ትነት እየከፈለ ባለበት ወቅት የፖለቲካ ድርጅቶችን እገዛና አመራር ይጠይቃል። የሕዝብ አሸናፊነት አጠራጣሪ ባይሆንም፡ አሸናፊ ለመሆን ግን መታገል መቅደም እንዳለበት ምን ጊዜም መረሳት የለበትም። ለዚህ መሠረቱ ግን ከራስ ጋር እየታረቁ፡ ከወገን ጋር እየተስማሙ በጋራ ዓላማና ብሔራዊ እጅንዳ ዙሪያ ተሰባስቦ በጋራ መታገል ብቻ ነው። በዓለም ታላቅ ዝና ያተረፉት የግ/ቀ/ኃ/ሥና በአፍሪቃ አህጉር መሬትን ያንቀጠቀጠዉ የደርግ መንግሥት ቀናቸዉ ሲደርስ እንዴት እንደመነመኑና እንደከሰሙ መዘርዘር አይኖርብኝም፤ በታሪክ ፊት ተቀምጧልና። በሩቁም በእነ አሜሪካ ለረዥም ዓመታት ሲረዱና ሲደገፉ በነበሩት በእነ ሞቡቱ፤ የሻህ ንጉሥ፤ ሆስኒ ሙባረክ፤ ወዘተ ላይ በመጨረሻ የደረሰዉን ዉርደት መገንዘብ ያስፈልጋል። ተቃዋሚ የፖሊቲካ ድርጅቶች ነን የሚሉትና በተግባር ግን የጭቆናን ዘመን የሚያራዝሙ በሙሉ ካለፉት ስህተቶች ገና ሊማሩ አልቻሉም፤ ・ድር ቢያብር እንበሳ ያስር・ የተባለዉን ቅዱስ አሳብ ደጋግመዉ መናቃቸዉ ያስተዛዝባል። ቁርጥ ያለ አቋም ያስፈልጋል፤ ከዛፍ ዛፍ መዝለል ዬትም አያደርስም። ለጊዜያዊ ጥቅማ ጥቅሞች በርካሽ መገዛትና አገርን መሸጥ በሰማይም በምድርም ያስጠይቃል። ቀኑ ሲደርስ ራቆታችንን ወደምድር እነደመጣን ሁሉ ራቆታችንን ወደዚያዉ እነደምንመለስ አንርሳ!!!

ነገርግን በህብረት ለሀገር ታሪክ ሰርቶ ማለፍ ዘላለማዊ የትዉልድና የሀገር ክብር ነዉ!!!

ዘ-ሐበሻ

አቶ ሌንጮ ለታ “ሃገር ቤት ገብተን በመታገል አዲስ ታሪክ እንሰራለን” አሉ

january15/2013

(ዘ-ሐበሻ) ባለፈው ሳምንት ዘ-ሐበሻ በሰበር ዜና እወጃዋ “እነ ሌንጮ ለታ ኢትዮጵያ ሊገቡ ነው” ስትል መዘገቧ ይታወሳል። የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግምባር ሊቀመበር የሆኑት አቶ ሌንጮ ለታ ጀርመን ድምጽ ራድዮ ላይ ቀርበው “አዎ እውነት ነው ሃገር ቤት ገብተን ልንታገል” ነው ሲሉ አረጋግጠዋል። “ባለፉት 20 ዓመታት ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ ይህ ወሬ ይወራ ነበር ያሉት አቶ ሌንጮ በቃለምልልሳቸው “ኖርዌይ ተቀምጬ ምን አደርጋለሁ፤ እዚህ የሚደረግ ትግል የለም ስለዚህ ሃገር ቤት ገብተን ነው የምንታገለው” ብለዋል።

“ለኢትዮጵያ ህዝቦች አዲስ ራዕይ አለኝ” በሚል የተመሰረተው የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ህጋዊ መሰረት ያለው አገራዊ አንድነትን ለመመስረትና ለሁሉም የምትሆን ኢትዮጵያን ለማቅናት ሃገር ቤት በመግባት እንደሚታገል ይፋ አድርጓል።

አቶ ሌንጮ ለታ ከጀርመን ድምጽ ራድዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “ከመንግስትም ሆነ ከተቃዋሚዎች ጋር ድርድር እንፈልጋለን” ያሉበትን ቃለ ምልልስ ያድምጡት፦



ዘ-ሐበሻ

የመረጃዎች እውነት ፣ ና የውሸት ፍልሚያ ጅማሮ !

January 15/2014

የማለዳ ወግ ...

የተመላሾች ጉዳይ ..

በርካታ ከሳውዲ ወደ ሃገር ቤት የተመለሱ ዜጎችን በሚመለከት የጀርመንና የአሜሪካ ራዲዮን ጨምሮ በርካታ የመገናኛ ብዙሃን አንድ አይነት የሚመስል መረጃ  ግፉአን ተመላሾችን እማኝ እያደረጉ መረጃ አቀብለውናል ::
http://www.rappler.com/world/regions/africa/45783-ethiopia-s-colossal-human-airlift-from-saudi-arabia
 " ራፕለር " በያዝነው ሳምንት ባቀበለን መረጃ ሻንጣቸው ጠፍቷቸው በአንድ የሻንጣ ማጠራቀሚያ ግቢ ሻንጣቸውን ሲፈትሹ የሚያሳየውን ፎቶ አስደግፎ የተመላሾችን አስተያየት አካቶበታል። ዜጎች ወደ ሳውዲ ሲሰደዱ ከቤተሰብ ፣ ከዘመድ አዘመድ አዝማድና ከተለያዩ ቦታወች የወሰዱትን የብድር ገንዘብ ስላልመለሱ ኑሯቸው የሰመረ እንዳልሆነ እየተናገሩ ነው ።  ሃገር ቤት ገብተው የስራ ማጣት እና እሳት የሆነው  የኑሮ ውድነት ግራ ያጋባቸው  በርካቶችም አሁንም መልሰው ለስደት እንደቋመጡ እኛ የምንቀርበው መረጃ ባይስማማ የፈረንጆቹ መገናኛ ብዙሃን የሚያቀርቡት የገሃዱን እውነት አንድምታ ያሳያል ።

በግል ሃገር ግብተው  የማገኛቸውን  በርካቶች ሃገር ቤት ተመልሰው የጋጠማቸው የኑሮ ውድነት አማሯቸዋል።  መልሶ 
ማቋቋሙ ደግሞ ከወሬ ባለፈ አለመጀመሩን እየሰማን ነው ። ባሳለፍነው እሁድ በጀርመን ራዲዮ እንዎያይ ፕሮግራም የቀረበው ተመላሽ ወንድምም ተመላሾችን በማደራጀቱና መልሶ በማቋቋሙ ረገድ የተጀመረ ነገር እንደ ሌለ መረጃውን አካፍሎናል። በአንጻሩ በመንግስት ኢቲቪና የቀሩት በስሩ የሚተዳደሩት መገናኛ ብዙሃን የሚናገሩት የሚታመን ከሆነ "ተመላሾቹ በየክልሉ ተደራጅተው እራሳቸውን የሚያቋቁሙበት ስራ ተጀመሯል!" የሚል መልካም መረጃ እያስተላለፉ ይገኛሉ ...ከዚህ ጋር ያያዝኩት አዲስ ዘመን ጋዜጣ " ከስደት ተመላሾች ሥልጠና ጀምረዋል !" በሚል ሁላችንም ሳውዲን ለቀን ወደ ሃገር እንገባ ዘንድ የሚያበረታታ መልካም የብስራት ዜና አሰራጭቷል። ...  እውነት ከሆነ ማለቴ ነው  !  ይህንን አሻግሮ ተቀምጦ "እውንት እውሸት "ማለት አይቻልምና ሊናገሩ የሚገባቸው ባለቤቶቹ ብቻ ናቸው ። ተመላሾች ሆይ ምን ትላላችሁ ?
 http://www.ethpress.gov.et/addiszemen/index.php/addiszemen/news/7374-2014-01-13-08-07-09
     አለም አቀፉ የስደተኞች ተጠሪ IOM መስሪያ ቤት ተመላሾችን መልሶ ለማቋቋም  $13.1 ሚሊዮን ዶላር ወይም 9.5 ዩሮ እንደሚያስፈልግ ይፋ አድርጓል ።  የስደተኞች ንብረት በተለይ የሻንጣ ጌጣጌጡን መጥፋት  ጉዳይ አሳሳቢነት ግን ከፍተኛ ሃላፊዎችን ሳይቀር ያስደመመ እንደሆነ በሚሰራጩት መረጃዎች ለመረዳት አልገደደንም ።
















"ወደ ሃገር  ግቡ አንገባም ፣ እንግባ አትገቡም ..."

ከአሰሪያቸው ጋር የማይሰሩና በህገ ወጥነት የተፈረጁ ዜጎች  ወደ ሃገር እንዲመለሱ የሚጠይቀው የሳውዲ መንግስትን ጨምሮ የኢትዮጵያ ኢንባሲና የቆንስል መስሪያ ቤቶች ጥሪ ነው ። ጥሪው በቀጥታ የሚመለከታቸው ሰነዳቸውን ያላሟሉ የሚባሉት በባህር በኡምራና ሃጅ ብቻ ሳይሆን በስራ ኮንትራት መጥተው ከአሰሪዎቻቸው ጋር የማይሰሩ "ህገ ወጥ " የተባሉ ዜጎች ግን "ሳውዲን ለቃችሁ ውጡ! " የሚለውን ጥሪ ችላ በማለት ዘና ብለው የተለመደ ኑሯቸውን መኖር ጀምረዋል።  ፍርሃትና  ጭንቀቱ የት እንደገባ ባይታወቅም የሳውዲ መንግስት ባሳለፍነው ሳምንት ጉዳያቸውን ጀምረው ላልጨረሱ የሰጠው የሁለት ወር ማስተካከያ ጊዜ ገደብ ነዋሪውን ያዘናጋው ይመስላል።  ያን ሰሞን በስጋት እቃቸውን ሲጠራርፉ  የነበሩት ዛሬ እቃቸውን ወደ ነበረበት መልሰው የለመዱትን የመዘናጋት ኑሮ መግፋት ይዘዋል። አንዳንዶቹን ጠይቄያቸው "ዛሬም የሳውዲ መንግስት አይጨክንም ህጉን ያሻሽለዋል !" በማለት ሲመልሱልኝ አንዳንዶቹ ደግሞ "ሃገር ቤት የሄዱት የኑሮ ውድነት እያማረራቸው እየሰማን መሄዱ ማበድ ነው "ሲሉ መልሰውልኛል ። እስርና ቅጣቱስ አልኳቸው እንዴት ትቋቋሙት አላችሁ?  አልኳቸው " የፈለገው ቢሆን እዚሁ ሁኔ መቋቋም እና መቀበሉ ይቀላል !" ሲሉ ክችም ያለ መልስ ሰጥተውኛል  ! እኒህ ለእኔ ቀቢጸ ተስፈኞች ናቸው ..

  የሳውዲን መንግስት ወደፊት ጠንከር ብሎ ይወስደዋል ተብሎ የሚጠበቀውን  እርምጃ  የፈሩ ጥቂቶች አሁንም ወደ መጠለያ በመግባት እና ለመግባት በዝግጅት ላይ ናቸው።  ያም ሆኖ በጅዳ የሽሜሲ መጠለያ ሰነዳቸው ይሰራላቸው ዘንድ በመጠባበቅ ላይ እንዳሉ በስልክ እየደወሉ  "ተቸገርን! ።የምግቡ ችግር ቢቻልም ፣ በመጓጓዙ ላይ ዘገየን፣ መላ ወደሚገኝበት ቦታ ጩኸልን !" እያሉ ተማጽነውኛል ።  ትናንት ሰኞ ከቀትር በኋላ ጀምሮ እስከ እኩለ ሌሊት መረጃ ያቀበሉኝ "ከመዲናና ከጅዳና ከተለያዩ ቦታወች ከቀናትና ከሳምንታት እና ከወር በፊት ወደ ሽሜሲ ገባን!" ያሉኝ ወገኖች " ጉዟችን ለማፋጠን በቆንስላችን ክትትልና ትብብር ስለማይደረግልን  እየተጉላላን ነው !" ሲሉ ጭንቀታቸውን ገልጸውልኛል። በኮንትራት ስራ የመጡትን ወደ ሃገር ቤት ለመመለስ ችግሩ መቋጫ አግኝቷል ቢባልም አሁን ድረስ ችግሩ አለመፈቱን ነዋሪዎች ከሽሜሲ መጠለያ  በምሬት ገልጸውልኛል ። "ካለፉት ሶስት ቀናት ወዲህ ወደ መጠለያ ለመግባት ፈልገን ወደ መጠለያ የሚወስደን የሚቀበልን አጣን! ውጡ ብለውን እንውጣ ስንል የሚያስወጣን አጣን  !" ያሉኝ በርካቶችም በጅዳ ሸረፍያ እንደሚገኙ አጫውተውኛል ። ህግን ተጋፍተው በሳውዲ ለመኖር ተስፋቸው የተሟጠጠ እንህኞች የሚደግፋቸው ይሻሉ ... !

የጀዛን ...እውነት

        በጅዛን በተደጋጋሚ የሚደርሰኝ መረጃ በማቅረቤ ያን ሰሞን የወገን ለወገን ደራሽ ኮሚቴን የጠለፉት የመንግስት ፖለቲካ ድርጅት አንዳንድ ካድሬዎች እዚህ ጅዳ ከጎኔ ተቀምጠው አዲስ የማጥላላት ዘመቻ ጀምረዋል። የወገንን ሳይሆን ለመንግስት ሃላፊዎች በማደገግደግ  እንደፈለጉ በሚፈነጩበት የህዘብ ግንኙነት የፊስ ቡክ ገጽ " እውነቱ  ይሄ ነው " በሚል ባስነበቡን መረጃ የእኔን ሳይሆን የተበዳዮችን እውንት ጥላሸት ሊቀቡት ከጅለው ሳይ አዝኛለሁ። "በሉ !" ትዕዛዙን ይፈጽሙ ዘንድ አንደተባሉት በማስተጋባት እውነቱን " ውሸት !"  ብለውታል። ሳያፍሩ  ፣ ሳይፈሩ !

       የተሳሳተ መረጃ ደረወሶኝ ይሆን ስል አጠራጠሩኝ ። ግን እንዲያ አልነበረም ። መረጃውን ለማጣራት ጅዛኖችን ደጋግሜ  "ሃሎ" ብያቸው ነበር ...  ያገኘኋቸው አስገራሚና አሳዛኝ መረጃዎች  " አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል !" አስብሎኛል ። ከህግ ታሳሪዎቹ ጋር በነበረኝ ቆይታ "የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች የእናንተን ጉዳይ  እየሰሩ እንደሆነ  ተነግሮኛል ፣ እውነት ነውን?   !"ያልኳቸው ወንድሞች የተባለው መረጃ ትክክል አለመሆን ተበሳጭተው የሚጠይቅላቸው ስላጡትነና በሚሰራው ስራ ዙሪያ  ብዙ አጫውተውኛል ። በአሳዛኝ እና በአስገራሚው የስደት ህይወት እጁ የተቆረጠውን ወንድም ፣ ታናሽ ወንድሙን  እና እሱ በርሃ ላይ ሲጓዙ ተይዘው ዛፍ ላይ ታስረው ተንጠልጥለው ሲውሉ አቅም አንሶት ከፊቱ ላይ ደክሞ ተዝለፍልፎ የሞተ ታናሽ ወንድሙን ታሪክ ወንድሙ ራሱ ይነግረናል ... ይህ ወንድሙን በበርሃ ላይ ያጣ ወንድም ስድስት ወር እንዲታሰር ቢፈረድበትም ከአመት በላይ ጠያቂ አጥቶ መንገላታቱን መስማት ያማል ! ይህንንም በድምጽ ይዠዋለሁ ! ትሰሙታላችሁ ...  እናም በጀዛን ፍርዳቸውን የጨረሱ የህግ ታራሚዎች ድምጽ  "ወደ ሃገር እንድንገባ ድጋፍ የሚያደርግልን የመንግስታችን ሃላፊዎችን አጣን ! " የሚል ነው ! የጅዛን እውነቱ ይህ ነው  !

መንግስት ሆይ ስማን ... ወገን ሆይ ስማን  !

      ሰነድ የሌላቸው ዜጎች " ህግን ተላልፋችኋል !" ተብለው " ከሃገር ይውጡ !" ተብሏል  !  ዜጎች ከሃገር ውጡ ሲባሉ መንገዱን በማመቻቸቱ ረገድ ከኢትዮጵያ መንግስት የኢንባሲና ቆንስል መስሪያ ቤቶች ከመረጃ ጀምሮ ብዙ ይጠበቃል  !  ቢያንስ ሁሌ እንደምለው "መውጣት አልፈልግም !" የሚለውን ዜጋ ምክንያት ሊሰማበሊደመጥ ይገባልና ፣ ስሙት ! " እንውጣ !"ሲል እንግልት የሚገጥመውን ዜጋ ታደጉት !  በአረብ አሰሪዎች ቤት ሆነው "ወደ ሃገራችን እንግባ ድረሱልን!"  የሚሉ የኮንትራት ሰራተኞችን ያላባራ ጩኸት ይሰማል ።  የሰማነውን ለሃላፊዎች ብናሰማም መፍትሔ የሚሰጥ ጠፍቷል  !  ይሀወ አሁንመወ ያሳስባል !  "ድረሱልን! " ሲሉ ደራሽ ያጡትን የኮንትራት ሰራተኞች  ፈጥናችሁ ድረሱላቸው  !  መውጣት ያለበት "ህገ ወጥ " የተባለ ሁሉ ዜጋ ይውጣ  !  አስከፊውን የስደት እንግልትና መከራን ማየቱ ይብቃን !

   ሰው ተጨንቆ ተጠቦ ፣ የመረጃዎችን እውነት እውሸት የሙግት ጅማሮ  ቀልቤን ባይስበውና መነታረኩን ባልፈልገውም ለሚወረወረው አሳሳች መረጃ እውነቱ ለማስጨበጥ ስድቡን ባልገባበትም ትክክለኛውን መረጃ ከምንጩ ለማቅረብ ወደ ኋላ የምል አይደለሁም!  ይህም በመሆኑ ይህንና ያንን በሰፊው እስክመለስበት ሰላም  !

አስኪ ቸር ያሰማን  !

ነቢዩ ሲራክ

Emerging Political differences between Oromo Organisations

January 15, 2014
by Dr Biri Yaya

SBS Amharic Radio

00:00
00:00

1. OLF that is led by Ato Daud Ibsa
The spokes-person for this group, more or less, repeated the long standing political stance of the OLF that the organisation’s objective is for the ‘freedom’ of the Oromo people through a self-determination with all options under consideration(autonomy to independence).
2. Oromo Democratic Front,ODF (Re: Lencho Leta, Dr Dima Negewo)
This group is yet to establish itself as a political party. Dr Dima Negewo is a seasoned and articulate politician.
In the interview with the Australian radio, Dima repeated what the group’s most articulate spokes-person, Lencho Bati, stated sometime ago. The group is keen to find a mid-point to re-engage and energise a discourse on the resolution of the conflict by some sort of negotiation with the current ruling clique in Ethiopia.
They would like to join in hands wih Ethiopian opposition groups for the ‘proper implementation’ of the provisions of the current federal constitution that the TPLf/Eprdf uses as a device to mislead the nation.
The ODF sees Oromos as a subject people of the empire while accepting the prospect of a democratic Ethiopian state when and if one emerges in the future.
3. OLF that General Kemal Gelchu is a chairman of
This group’s stance is the most clear:
* Full acceptance that Oromos are Ethiopians who are, nevertheless, being denied of their full citizenship rights due to the undemocratic nature of previous and current regimes in Ethiopia.
General Kemal has dismissed the other Oromo groups’ political stance which sees Oromos as non-Ethiopian. He ridiculed the assumption that oromos are not Ethiopians as a shallow thinking that was accidentally borrowed from comparisons with the status of the American slaves. He is right in that!
The crucial lines of emphasis and differences in this group to notice are:
* Oromos are not colonial subjects
* The Group does not believe that there is any mileage in trying to join the tested and failed attempt of working as a ‘legal’ opposition within the constraints of the TPPLF/EPLF’s domination.
However, what is common to all the three strands of the Oromo groupings is the realization that Oromos’ rights cannot be attained without some level of cooperation with other stakeholders in Ethiopia.

Tuesday, January 14, 2014

አፈንዲ፣ ጃዋር መሐመድ እና የቴዲ አፍሮ ጉዳይ

January 14/2014

teddy and jawar



የሰሞኑ የነ ጃዋር ሲራጅ ግርግር ለኛም ስም አትርፏል፡፡ እንደፈቀደው ይሁን፡፡ እኛ ጉዳያችን ሞልቶልናል፡፡ የታቀደው የቴዲ ኮንሰርት በመሰረዙ በጣም ደስተኞች ነን፡፡ በኮንሰርቱ ታክኮ ሊከሰት የሚችለው የህዝብ መተላለቅ በመቅረቱ እሰየው ነው፡፡ ብርና ዝና ብቻ እያሰቡ የህዝብ መጨራረስን ሊጋብዙ የነበሩ ሰዎች ተንኮላቸው ስለከሸፈባቸው አላህን በጣም ነው የምናመሰግነው፡፡
ታዲያ ያስገረመኝ ነገር ስሜት እውነትን ለመሸፈን ምን ያህል ጉልበት እንዳለው መረዳቴ ነው፡፡ አጃኢብ ነው! ግጭትና ትርምስ ሲሰበክ የነበረው በውሸት የተፈጠረውን ወሬ እንደ ሰበብ በማድረግ ነው፡፡ ውሸቱን ለማዳመቅ በግርግሩ ውስጥ የገቡ ሀይሎች አበዛዝም ያስገርማል፡፡ ከአሜሪካ እስከ ኖርዌይ፣ ከለንደን እስከ ሸገር እየተጠራሩ ሽብሩን ለማጋጋል የተደረገው ጥረት አስደናቂ ነበር፡፡ ለወትሮው በአንድ ብሄር ላይ የሚደረግ ዘረኛ ቅስቀሳን እንቃወማለን ሲሉ የነበሩ አንዳንድ ምሁራን ደግሞ ከኛ ጋር ተባብረው ግጭት እንዳይከሰት ጥረት ያደርጋሉ ብለን ስንጠብቅ የኛ ተቃራኒ መሆናቸው አስገርሞናል፡፡ ለምሳሌ እነ ዳንኤል ብርሃኔ “ቀኝ አክራሪዎች እንዲህ አደረጉ” እያሉ ሲጽፉት የነበረው ነገር በእጅጉ የሚያሳዝን ነው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ሰዎች ነገሮችን በስሜት በመቀበል እውነትን ከውሸት ለመለየት ጥረት አለማድረጋቸው አስቂኝ ብቻ ሳይሆን አሳፋሪ ሆኖ ነው ያለፈው፡፡ ለምሳሌ በግርግሩ መጀመሪያ ሰሞን “መጽሔቱ ቃለ-ምልልሱን አትሞ አውጥቶታል” ሲባል ከርሞ “ሁለት ዓይነት መጽሔት ነው የታተመው” የሚል ነጠላ ዜማ ተለቀቀ፡፡ ከዚያ ለጥቆም “መጽሔቱ አከራካሪውን ቃለ-ምልልስ ቆርጦ አስቀርቶታል” ተብሎ ተወራ፡፡ “የተቆረጠው ክፍልም ይኸውላችሁ” ተብሎ በአንዳንድ ዌብሳይቶች ላይ ተለጠፈ፡፡ በመጨረሻው ላይ ጭራሽ የቴዲ አፍሮ ቃለ-ምልልስ በኦዲዮ ተቀርጾ በእጃችን ገብቷል የሚል ማስመሰያ ተፈጠረ፡፡ ይህ ሁሉ የውሸት ወሬ ነው፡፡ በግርግሩ የተሳተፉት ግን አንዱንም ለማጣራት አልሞከሩም፡፡ “ጀዋር የተናገረው ነገር ምንጊዜም እውነት ነው” የሚል መመሪያ ያላቸው ነው የሚመስለው፡፡ (ያሳቀኝ ነገር ቴዲ አፍሮ ራሱ መጽሔቱ “ቅዱስ ጦርነት” በሚለው ርዕስ አለመታተሙን ያላወቀ መሆኑ ነው፤ እንደዚያ ዓይነት ርዕስ ያለው መጽሔት በጭራሽ አልታተመም)፡፡
እኛ ለቴዲ አፍሮ አልነበረም የተከራከርነው፡፡ ቴዲ ተናገረ የተባለው ቃል ትክክል ነው ያለ ሰው የለም፡፡ በደሌ መጠጣትን አቁሙ መባሉንም የተቃወመ ሰው የለም (እኛ እንዲያውም አስካሪ መጠጥ የተባለ በሙሉ ቢወገድ ነው የምንፈልገው)፡፡ እኛ ያልነው በሀሰተኛ ወሬ ሰውን ለማጨራረስ አትሞክሩ ነው፡፡ ይህንን ሀሰተኛ ወሬ የሚያራግቡ ሀይሎች ድብቅ አጀንዳ አላቸው ነው ያልነው፡፡ ይኸው ነው መልዕክታችን፡፡
ከዚህ በፊት እንደገለጽኩት ቴዲ አፍሮ በትክክል “ቅዱስ ጦርነት” የሚለውን ቃል ተናግሮ ቢሆን እንኳ መደረግ የነበረበት በፍትሕ መንገድ መፋረድ ነው፡፡ ሆኖም የግርግሩ አድማቂዎች በቀጥታ ወደ ዘረኝነት ቅሰቀሳ ነው የገቡት፡፡ ያሳዝናል! የኦሮሞ ህዝብ ባህልና ወግ ይህ አልነበረም፡፡ የህዝቡ ትግልም ከስርዓቶች ጋር ነው እንጂ ከሰፊው የአማራ ህዝብ ጋር አይደለም፡፡
በኔ በኩል የምችለውን አድርጌአለሁ፡፡ በአላህ እርዳታ የምፈልገውን ውጤት አግኝቼበታለሁ፡፡ ህዝቦቻችን አልተገዳደሉም፡፡ አልተፋጁም፡፡ እነርሱ እንደተመኙት አልተጨራረሱም፡፡ ስለዚህ ባደረግኩት ነገር ደስተኛ ነኝ፡፡ በዚህ ጉዳይ ቅንጣት ታክል ጸጸት አይሰማኝም፡፡ ወደፊትም እንዲሁ ማድረጌን እቀጥላለሁ፡፡
===መነሻው===
ይህንን ሁሉ ትርምስምስ በአጋፋሪነት የመሩትን እናውቃቸዋለን፡፡ ሁሉም በውጪ ሀገር ተቀማጭ ሆነው ነበር እሳቱን ሲያጋግሉት የነበረው፡፡ ዓላማቸው ሰሞኑን የፈጠሩት የሰንበቴ ማህበር ግዙፍ ስኬት እያስመዘገበ እንደሆነ እንደ መጠቆሚያ አድርጎ መጠቀም ነው፡፡ ህዝብ ቢጨራረስ ባይጨራረስ ጉዳያቸው አይደለም፡፡
የግርግሩ ዋና አቀናባሪ ማን እንደሆነ አላውቅም፡፡ እንደ ቃል አቀባይ ሆኖ ሲያገለግል የነበረው ግን ጀዋር መሐመድ ነው፡፡ ጀዋር በቅድሚያ ስለጉዳዩ በኔ ኢንቦክስ ሲነግረኝ “የእንቁ መጽሔት ባለቤቶች ጎል ሊያስገቡን የውሸት ሽፋን በፎቶሾፕ ሰርተው በትነዋል” ነው ያለኝ፡፡ እናም “ይህንን መጽሔት መበቀል አለብን” በማለት ሊቀሰቅሰኝ ሞከረ፡፡ “እንቁ ማለት የማይታወቅ መጽሔት ነው፤ ነገሩን ባናጋግለው ይሻላል” አልኩት፡፡ እርሱ ግን “አይደለም! በጣም ግዙፍ የሆኑ ነፍጠኞች ናቸው በገንዘብ የሚደጉሙት” ብሎ ሊያነሳሳኝ ሞከረ፡፡ እኔ በበኩሌ የሰውዬው አጉል ብልጠት ስለሚደብረኝ ግድ አልሰጠሁትም (እርሱ የሚያወራውን ነገር ሁልጊዜ በጥርጣሬ ነው የማየው)፡፡ ከዚያ በኋላ እርሱን ላለመገናኘት ስሸሸው ቆየሁ፡፡ በዚህ መሀል ቴዲ ሰጠ ስለተባለው ቃለ-ምልልስ ሐቁን ለማወቅ ጥረት አድርጌ ነበር፡፡ እናም ውሸት መሆኑን አረጋገጥኩ፡፡
ታህሳስ 14/2006 ከጀዋር ጋር በሌላ ጉዳይ ስንገናኝ ግን ቀደም ሲል ውሸት ነው ሲለው የነበረውን ነገር “እውነት ነው! የኦዲዮ ማስረጃ ጭምር አለን፤ የመጽሔቱ አዘጋጅ ማረጋገጫ ሰጥቶኛል” የሚል ማሻሻያ ሰጥቶት ከርሱ ጋር እንድሳተፍበት ይጨቀጭቀኝ ጀመር፡፡ ነገሩ ውሸት ነው ሳልለው “ይህንን ነገር ከማጋጋል መቆጠቡ ይመረጣል” ብዬ ላቀዘቅዝ ሞከርኩ፡፡ እርሱ ግን “እምቢ! ቴዲን አፈር አባቱን ሳናበላው አንተወውም፤ አንተ ደስ ካለህ እንደ ፈለግክ ሁን” እያለ ይፎክርብኝ ገባ፡፡ ለፉከራው ግድ ባይኖረኝም ለራሱ ዝና ሲል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኦሮሞ ወጣቶች ዘንድ ያገኘውን ተቀባይነት በመጠቀም ስለሜንጫው የፎከረውን ቃል ተግባራዊ ሊያደርግ ይችላል ብዬ ፈራሁ፡፡ እና የርሱን እንቅስቃሴ የሚያኮላሽ እርምጃ መውሰድ አለብኝ በማለት ወሰንኩኝ (በወቅቱ እኔም እንደርሱ በቢራ የምንቦጫረቅ መስሎት “በደሌ መጠጣት አቁም” ሲለኝ ለጥቂት ነበር ከመሳደብ ራሴን የተቆጣጠርኩት!)፡፡
***** ***** *****
ይህ ሰው በጣም አጭበርባሪ ነው፡፡ የውሸት ወሬ መፈብረክ ይችልበታል፡፡ ደግነቱ የሚፈበርካቸውን ወሬዎች ሀሠትነት ለማረጋገጥ ረጅም ጊዜ አይፈጅም፡፡ የዚህ ሰው ሌላኛው ባህሪ ደግሞ ለሁሉም የፖለቲካ ቡድኖችና ፓርቲዎች የሚሰራ መሆኑ ነው፡፡ ሰውዬው ከላይ ሲታይ የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ ይመስላል፡፡ ሆኖም አብዛኛው ሰው እንደሚያውቀው ከኦፒዲኦ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋርም የጠበቀ ግንኙነት አለው፡፡ አንድ ቀን ሳያስበው ይህንን ግንኙነቱን ግልጽ ያደረገበትን ጥያቄ ጠየቀኝ፡፡ እኔ በሰጠሁት ምላሽ ሳስደነግጠው ትንሽ እንደማፈር ብሎ ዘጋው (በወቅቱ የጠየቀኝን ጥያቄ ሌላ ጊዜ ብነግራችሁ ይሻላል)፡፡ በርሱ ቤት ነገሩን የማላውቅ መስሎታል፡፡ ይሁንና በፌስቡክም ጭምር በሰፊው ሲባል የነበረ ነገር በመሆኑ ብዙም አልደነቀኝም፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ይህ ሰው ከኦነግ-ቀመስ ቡድኖችም ጋር በትክክል እንደሚሰራ መረጃው አለን፡፡ ከሻዕቢያ ጋር እንደሚሰራም ውስጥ ውስጡን ይወራል፡፡ እነዚህ ግንኙነቶቹ ቀደም ብዬ የሰማኋቸው በመሆኑ ብዙም አላስገረሙኝም፡፡ በጣም የተደነቅኩት ግን “ነፍጠኛ” እያለ ቀን ከሌሊት ከሚሰድባቸው ቡድኖችም ጋር የሚሰራ መሆኑን እራሱ በነገረኝ ጊዜ ነው፡፡ የዚያን ቀን በጣም ነበር የደነገጥኩት (ዕለቱ ህዳር 7/2006 ነው)፡፡ “ይህ ሰው ጥቅም ካገኘ ለሰይጣንም ይሰራል ማለት ነው ለካ!” በማለት ተደመምኩበት፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከዚህ ሰው ጋር የማደርገውን የመልዕክት ግንኙነት ገታ ማድረግ ጀመርኩ (እንግዲህ ለዚህ ሁሉ ማስረጃው በእጄ ነው ያለው)፡፡
ሰውዬው ከነዚህ ሁሉ ቡድኖች ጋር የሚሰራበት ዓላማ ገንዘብና ዝና ማግኘት ይመስለኛል፡፡ በየሀገሩ እየዞረ ብር እንደሚለቅምም ይታወቃል፡፡ እኔ በበኩሌ በግርግሩና በጉዞው ብር ቢያገኝበት ጉዳይ የለኝም፡፡ ብር አገኝበታለሁ ብሎ የማይገባ ድራማ ሲጫወት ግን ዝም ብዬ ላልፈው አልፈቀድኩም፡፡ የጸረ-በደሌውን ዘመቻ በጎን በኩል የተጋፈጥኩት በዚሁ ምክንያት ነው፡፡ አስቡት እስቲ! የቴዲ አፍሮን ኮንሰርት ለመታደም ድሬዳዋ ስቴድየም በተገኘው ህዝብና እርሱን በሚቃወመው ህዝብ መካከል ግጭት ቢፈጠር ውጤቱ ምን ሊሆን ነው? በዚያ ውጤትስ ተጠቃሚ የሚሆነው ማን ነው? አማራው ነው? ኦሮሞው ነው? ወይንስ ማን ነው? እስኪ እናንተው መልሱት፡፡ … የጃዋር የፖለቲካ ተንታኝነት ይህ ነው እንግዲህ!…(እንኳንም ኮንሰርቱ ቀረ! እሰይ!)
ከዚህ ሰው ጋር የተዋወቅኩት በኢንተርኔት ነው፡፡ የምጽፋቸውን ጽሑፎች በዌብሳይቱ ለመጠቀም በፈለገበት ጊዜ ሲያነጋግረኝ ነው ያወቅኩት፡፡ ከዚያ ውጪ ሌላ ትውውቅ የለንም፡፡ ለአንድም ቀን አይቼው አላውቅም፡፡ እኔ የጻፍኳቸውን ጽሑፎች ከኔ የፌስቡክ ፔጅ ላይ እየወሰደ ዌብሳይቱ ላይ ይለጥፋል፡፡ በቃ ይኸው ነው፡፡ ባለፈው ክረምት ደግሞ “ያንተን መጽሐፍ እናሳትማለን” የሚል ቃል ሰጠኝ፡፡ በጥቅምት ወር መጨረሻ ገደማ ግን የመጽሐፉ ጉዳይ ቀረና መጽሔት እንጀምራለን ብሎ መጣ፡፡ የመጽሐፉ ጉዳይ መቅረቱ ሆዴን እየበላኝ ብቸገርም እስቲ ትንሽ ልመርምረው ብዬ አብሬው ሰነበትኩ፡፡ ይሁንና ከህዳር ወር 10/2006 ወዲህ የመጽሔቱም ነገር የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ፡፡ (የማያደርገውን ነገር በስሜት የሚያወራው እንዲህ ዓይነቱ ቀጣፊ ሰው በድሬዳዋ ልጆች ቋንቋ “ሐጂ ቅደደው” ወይንም “ሐጂ ቦንባ” ነው የሚባለው)፡፡
የሆነ ሆኖ የአሁኑ ግርግር ከዚህ ጉዳይ ጋር አይገናኝም፡፡ መጽሔት እናዘጋጃለን ብዬ የለፋሁበትን ድካም መና ስላስቀረብኝ ቂም ቋጥሬ አይደለም ልጋፈጠው የወሰንኩት፡፡ እርሱ ያመጣው ሎጂክ እጅግ አደገኛና ህዝቦችን የሚያጨራርስ በመሆኑ ነው ዝም ማለቱን ትቼ በቀጥታ የገባሁበት (መጽሔቱን በራሴ ወጪ ይፋ አደርገዋለሁ)፡፡
===ታሪክ ====
እኔ የታሪክ ምሁር አይደለሁም፡፡ ግን ስለታሪክ አንብቤአለሁ፡፡ በተለይ ስለ20ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክ በደንብ ነው ያነበብኩት፡፡ ከሰሞኑ ግርግር ጋር ተያይዞ የሚነሳውን የአጼ ምኒልክንም ታሪክ አንብቤአለሁ፡፡ ነገር ግን ግርግሩ በተጋጋለበት ወቅት ስለርሱ ትንፍሽ አላልኩም፡፡ ወደፊትም እንዲህ አይነት አደገኛ አሻጥር የተመላበት ሁኔታ በሚፈጠርበት ወቅት ግጭትን የሚያጋግሉ ታሪኮችን አልቆሰቁስም፡፡ ግጭት ሲቀሰቀስ ተጠቃሚው ህዝብ ሳይሆን የህዝብ ጠላት ነው፡፡
አጼ ምኒልክ ደቡብና ምስራቅ ኢትዮጵያን ከግዛተ መንግሥታቸው ጋር ለመቀላቀል ያደረጉት ጦርነት ከፍተኛ እልቂትና ፍጅት የተፈጸመበት ነው፡፡ በዚህ ዘመን ሊታሰቡ የማይገባቸው አጸያፊ ድርጊቶች ተፈጽመዋል፡፡ ህዝቦች የገዛ መሬታቸውን ተነጥቀው በትውልድ ቀዬአቸው ጭሰኛ ለመሆን ተገደዋል፡፡ ይህንን ታሪክ የምኒልክ ጸሐፊ ከነበሩት ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረ-ሥላሴ ጀምሮ በርካቶች በድርሳናቸው ጽፈውታል፡፡
ታዲያ የአጼ ምኒልክ ጦር ያኔ ለፈጸመው ጥፋት የአሁኑ ትውልድ ዕዳ ከፋይ የሚሆንበት ምክንያት የለም፡፡ በዚህ ዘመን ያለው ትውልድ ያለበት ሃላፊነት ከታሪክ ተምሮ የያኔው ጥፋት እንዳይደገም መከላከልና የህዝቦች የመብት ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ እንዲያገኝ አብሮ መታገል ነው፡፡ ታሪክን የፕሮፓጋንዳ መጠቀሚያ እያደረጉ እልቂትና ሁከትን መቀስቀስ የህዝቦችን ትግል ወደኋላ ማስቀረት እንጂ ለህዝቦች የመብት ጥያቄ አንዳች መፍትሄ አያመጣም፡፡
የዛሬ ሶስት ሳምንት ገደማ ስለ አጼ ምኒልክ አልጽፍም ያልኩት አንደኛ ወቅቱን ያልጠበቀ በመሆኑ ነው፡፡ ስውር ዓላማ ያነገቡ ግለሰቦችና ቡድኖች ህዝቦችን ለማጨራረስ ስለአጼ ምኒልክ በሚነዘንዙበት በዚህ ወቅት እንዲህ ዓይነት ታሪኮችን መጻፍ እነርሱ በሚፈልጉት ወጥመድ ውስጥ ራስን ማስገባት ነው፡፡ ሁለተኛ እንዲህ ዓይነት ታሪኮች በአብዛኛው የሚያወዛግቡን በመሆናቸው ታሪኮቹን በሶሻል ሚዲያ ላይ እያመጡ መለጠፍ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ የአዲስ ነገር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረው ታምራት ነገራ እንደጻፈው እንዲህ ዓይነት የሚያነታርኩ ታሪኮችን በፌስቡክ ላይ መለጠፍ ሌሎች ታላላቅ ህዝባዊ አጀንዳዎች እንዲረሱ መንገድ መክፈት ነው፡፡ ታሪኩን ማወቅ የሚፈልግ ሰው በታሪክ ምሁራን የተጻፉ ድርሳኖችን ቢያገላብጥ ነው የሚሻለው፡፡ ሶስተኛ ደግሞ እንዲህ ዓይነት ታሪኮችን መጻፍ እኔ ፌስቡክን ከምጠቀምበት ዓላማ ጋር በጭራሽ የማይሄድልኝ በመሆኑ ነው፡፡
===ትምህርት===
ይህ ግርግር ከተጀመረ ወዲህ ብዙ ተብዬአለሁ፡፡ በወረዱ ቃላት ተሰድቤአለሁ፡፡ አብዛኛው ተሳዳቢ የማያውቀኝ ስለሆነ ምንም አልተሰማኝም፡፡ አንዳንድ ሰዎች የሚንጫጩበት ግለት ግን በጣም አስደንቆኛል፡፡ ይገርማል! አንድ ነገር ልንገራችሁ፡፡
ወላጅ አባቴ ለኦሮሞ ህዝብ በተደጋጋሚ ጊዜአት ታስሮ፣ ተደብድቦ፣ በሚሊዮን የሚቆጠር ንብረቱን አጥቷል፡፡ ትግሉ ሲጀመር ጳጉሜ 5/1966 ቀን የመጀመሪያ ሰማዕት ሆኖ የወደቀውና ሬሳው ረጅም ርቀት የተጎተተው ሰው አሕመድ ተቂ (ሁንዴ) የተሰኘው አጎቴ ነው (ጓደኛው ኤለሞ ቂልጡ በዚያው ቀን ነው የሞተው፤ ሆኖም በወቅቱ የአካባቢው ጸጥታ ሀይሎች ስላላወቁት እዚያው የወደቀበት ቦታ ላይ ትተውት ሄደዋል፤ እስከዛሬ ድረስ ያንን የመሰለ ጀግና ገበሬዎች በአንድ ገደል ጥግ በቆፈሩት ጉድጓድ ውስጥ ራቅ ብሎ ተኝቷል፤ እነ ጀዋርን የመሳሰሉ ሰዎች ግን ሬሳውን እንኳ ደህና ቦታ ስለመቅበር ጉዳይ ላይ ሳይመካከሩ በየስርቻውና በየፓርቲው “ኤለሞ” እያሉ ቱሪናፋ ይነዛሉ… ሐፍረተ ቢስ! አዳማ ውስጥ ደግሞ በርሱ ስም ትልቅ ግንብ አቁመዋል፤ ሬሳውን እንቅበር ብሎ የጠየቀ ሰው ግን እስከ አሁን ድረስ የለም፤ እኛ ከጠየቅን “ሌላ ተልዕኮ አላችሁ” እንባላለን፤ ጉድ እኮ ነው)፡፡
አባቴ የታናሽ ወንድሙን ሬሳ ካየበት ደቂቃ ጀምሮ አዕምሮው ተነክቷል፡፡ ኑሮው የቀን ጭለማ ሆኖበት ከሰው ተለይቶ በራሱ መንገድ ለብቻው ነው የኖረው፡፡ ደርግ ሲወድቅ ያለ አዋጅ የተወረሰበትን አንድ ክፍል ቤቱን እንዲመልሱለት ጥረት አድርጎ ተከልክሏል፡፡ በዚያው ከተማ ውስጥ ግን እስከ አምስት ክፍል ቤት ያላቸው ሰዎች (ለዚያውም በአዋጅ የተወረሱ) ተመልሶላቸዋል፡፡ በዚህ ረጅም ዓመታት ውስጥ አባቴን የት ነህ ብሎ የጠየቀው ሰው የለም፡፡ ከርሱ ጋር የምንቸገረው እኛ ልጆቹ ነን፡፡ አሁንም የድሮው ግርፋት አገርሽቶ እግሩን ፓራላይዝ አድርጎት ሲያስቀምጠው ከርሱ ጋር እየተቸገሩ ያሉት ልጆቹ (በተለይ ሴት ልጁ) ብቻ ናቸው፡፡ እነዚህ “እናውቅሃለን፤ ዘመድህ ነን” ባይ ወገኖች “አባትህ የት ደረሰ” ብለው ጠይቀውኝ እንኳ አያውቁም፡፡ እኔም ነገ ብቸገር የሚገጥመኝ ዕድል ይኸው ነው፡፡ እነዚህ ቱሪናፋ የሚነፉት ወሽከሬዎች ጉዳይ ኖሮኝ እገዛ ብጠይቃቸው አካውንት ዲአክቲቬት እስከማድረግ ይደርሳሉ፡፡ በተለይ ዘላለም ወዬሳ የሚባለው የኦነግን ማሊያ የለበሰ የኦፒዲኦ አገልጋይ “በኦሮሞ እጅ አድገህ፣ የኦሮሞን እንጀራ በልተህ፣ የኦሮሞን ልብስ ለብሰህ፤ ዛሬ ኦሮሞን ከዳህ”… እያለ ሲዘባርቅ ከቤታቸው ኩሽና በየቀኑ እንጀራ በወጥ ሲያቀብለኝ የኖረ ነበር የሚመስለው፡፡
ምሁራን ነን ተብዬዎቹም ኤለሞ ቂልጡን ሲያወድሱት ሳት ብሎአቸው እንኳ በዚያው ቀን በዚያው ሜዳ ላይ ከኤሌሞ ቀድሞ የሞተውንና በርሱ ሰበብ መላው የሀረርጌ ክፍለ ሀገር የታመሰበትን የሰማዕት አጎቴን ታሪክ በአንድም መጽሔትና መጽሐፍት ሲያነሱት አይቼ አላውቅም (እርግጥ አንድ ጊዜ የድሮው የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ገላሳ ዲልቦ ገለምሶ ከተማ መጥተው የአጎቴን ስም ሲያነሱት ሰምቻለሁ፤ ”ግዝትና ግዞት” በተሰኘው መጽሐፍ ውስጥም ስሙን አይቼዋለሁ፤ ቴዎድሮስ ሙላቱ በጻፈው አኬል ዳማ ውስጥም ታሪኩ በጥቂቱ ተጠቅሷል፤ ፕሮፌሰር ሙሐመድ ሐሰንም በኢንሳይክሎፒዲያ ኢትዮፒካ ውስጥ አንዴ ስሙን የጠቀሰው ይመስለኛል፤ እነዚህን አራቱን ብቻ በቤተሰቤ ስም አመሰግናቸዋለሁ፤ ከዚህ የተቀረው ሁሉ አስመሳይ ነው)፡፡
ለረጅም ገዜ የዚህ አጎቴ ታሪክ መረሳት በጣም ያንገበግበኝ ነበር፡፡ እናም ታሪኩ መጻፍ አለበት ብዬ ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ መለስተኛ ጽሑፍ በዊኪፒዲያ ውስጥ ያስቀመጥኩት እኔ ነኝ፡፡ ከዚያ በኋላ ነው እርሱን ለማወቅ በሚል መጠነኛ ግርግር የተጀመረው፡፡ ከማንም በፊት አጎቴን ያስታወሰው ግን ዓሊ ቢራ ነው፡፡ ገጣሚው አቡበከር ሙሳ እና ዓሊ ቢራ በጋራ ምስጋና ሊደርሳቸው ይገባል፡፡ “ያ ሁንዴ በሬዳ” የተሰኘው ዜማ የተጻፈው ለአጎቴ ለአሕመድ ተቂ ሼኽ ሙሐመድ-ረሺድ ነው (በነገራችን ላይ ዓሊ ቢራንም ለመጀመሪያ ጊዜ በዊኪፒዲያ ያስገባሁት እኔ ነኝ፤ ዓሊ ቢራ ለአጎቴ ማስታወሻ የሰራውን ስራ ለማክበር ይሆን ዘንድ ነው ታሪኩን በዊኪፒዲያ የጻፍኩት)፡፡
ታዲያ የአጎቴ ስም አለመነሳቱ አንዳንዴ ለበጎ ነው ያሰኘኛል፡፡ በርሱ ጦስ የአባታችን ህሊና ተቃውሶ የአባት ፍቅር በደንብ ሳይገባን ነው ያደግነው፡፡ አባቴ በ1975 ከእስራት ወጥቶ ከዝርፊያ የተረፈውን ገንዘብ ዝም ብሎ ሲበትን ጸባዩን ማስተው ያቃታት እናቴ እኛን ለማሳደግ ያሳለፈችው ስቃይ እስከ አሁን ድረስ ውስጤን ያነደኛል፡፡ በተገደለው አጎቴ ሰበብ ሌላኛው አጎቴም (ኢስራፊል ይባላል) አዕምሮው ተነክቷል፡፡ ሟች እናታቸው መርየም “ልጄ አህመድ ተቂ” እንዳለች ነው ህይወቷ ያለፈው፡፡ ወላጅ አባቱ ሼኽ ሙሐመድ ረሺድ ግን የአላህ ሰው ስለሆኑ ትዕግስቱ ነበራቸው፡፡ የአጎቴ ጓደኞች የነበሩት እነ ነጃሽ ዒስማኢል፣ ሙሐመድ በከር፣ ዒስማኢል አሕመዩ፣ ሙሐመድ አብዶ (ሉንጎ) የመሳሰሉት ድንቅ ነጋዴዎች ፣ በግርፋትና ቶርች ብዛት ናላቸው ዞሮ ያለ ጊዜአቸው ከስራው ዓለም ተሰናብተው የሰው ጡረተኛ ለመሆን ተገደዋል (ሉንጎ ከድብደባ ብዛት ዐይኑን አጥቷል)፡፡ የአጎቴን ታሪክ ማንሳት የሚችሉት በርሱ ሰበብ እውነተኛውን ስቃይ ያዩት እነዚህ ሰለባዎችና ቤተሰቦቻቸው ናቸው፡፡ ምድረ አጭበርባሪ መንገደኛ ሁሉ ስሙን እየጠራ መነገጃ እንዲያደርገው አንፈቅድም፡፡
የኔ አጎት የሞተው ለኦሮሞ መብትና ነጻነት ሲል ነው፡፡ አጎቴ አማራን ለመጨፍጨፍ አይደለም ጫካ የገባው፡፡ ከአማራዎች ጋር በጉርብትና ሲኖርና በጋራ ሲሰራ የነበረ ሰው ነው፡፡ እርሱ የታገለው ጨቋኙን ስርዓት ነው እንጂ የአማራ ተወላጆችን አይደለም፡፡ የርሱን ታሪክ ከበደሌ ቢራ ጋር እያገናኛችሁ ማስጠንቀቂያ ልትሰጡኝ የምትሞክሩት ሀይሎች ህልመኞች መሆናችሁን እወቁ፡፡ ለራሳችሁ ሰው የመጨፍጨፍ ዓላማ ካላችሁ በግልጽ አሳውቁን፡፡ የአጎቴን ስም ግን አለቦታው አታንሱት፡፡ እዚያው መቃብሩ ውስጥ በሰላም ይተኛበት፡፡
*****
እንግዲህ አፈንዲ ማለት ይህንን ሁሉ ታግሶ ዝም ያለ ሰው ነው፡፡ ዛሬ “አፈንዲ ጉራጌ ነው፣ አደሬ ነው፣ ጎበና ነው ጂንኒ ጀቡቲ” እያሉ የሚጯጯኹት ታሪክን መሸጥ የለመዱ አስመሳዮች ናቸው፡፡ “ህዝብን ማጋጨት አቁሙ” ማለት ጎበና ከሆነ በእርግጥም ጎበና ነኝ (አንዳንዶች ጭራሽ የጻፍኩትን ሳያገናዝቡት “አባት ማር ስለበላ የልጅ አፍ ጣፋጭ አይሆንም” እያሉ ሊተርቱ ይፈልጋሉ)፡፡
ሰማችሁ ወይ! እኔ ልረዳችሁ ብዬ ነው እንጂ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል፡፡ አንድም ነገር የመጻፍ ግዴታ የለብኝም፡፡ በአባቴ ላይ የደረሰውን ስቃይ እያየሁ ያደግኩ በመሆኔ ከርሱ ህይወት በቂ ትምህርት ወስጄአለሁ፡፡ የሚያሳዝነኝ እንዲህ የሚነገድበት ህዝብ ለሁሉም ነገር ባይተዋር መሆኑ ነው፡፡ ለሁሉም ትምህርት ወስጄበታለሁ፡፡
===የኔ ዓላማ===
ከዚህ ቀደም እንደጻፍኩት እኔ የፖለቲካ ዓላማ የለኝም፡፡ የኔ ጉዳይ ያለው ከህዝብ ዘንድ ነው፡፡ የማንኛውም ህዝብ መብትና ነጻነት እንዲከበር ጽኑ ፍላጎቴ ነው፡፡ የአንዱን ህዝብ መብት ለማስከበር ሌላውን መንካት ትክክለኛ ነገር አይደለም፡፡ እኔ የወጣሁበት የኦሮሞ ህዝብ መብት የሚከበረው የአማራን ህዝብ በመጨቆን አይደለም፡፡ የአማራውንም መብት ማስከበር የሚቻለው ኦሮሞን በመጨቆን አይደለም፡፡ የጭቆናው ደረጃና ስልት ቢለያይም ሁሉም ህዝብ መብቱን ፈላጊ ነው፡፡ ስለዚህ ለህዝቦች መብት የሚታገሉ ወገኖችና ቡድኖች ይኑሩ፡፡ እኛ ደግሞ ይህ የመብት ትግልና በርሱ ምክንያት ከሌላ አቅጣጫ የሚሰነዘረው ግብረ-መልስ ውላቸውን ስተው ሌላ አቧራ እንዳይቀሰቅሱ የመከላከሉን ስራ እንስራ፡፡ በህዝቦች መካከል ፍቅርና ወንድማማችነትን እናጎልብት፡፡
የኔ የምንጊዜም ፍላጎትና ዓላማ ይህ ነው፡፡ ከተወለድኩበት የኦሮሞ ህዝብ በፊት በሀረሪ ህዝብ ላይ ያተኮረ መጽሐፍ የጻፍኩት በዚህ መንፈስ ነው፡፡ ከገለምሶ የተገኙትን የመምሬ ሙላቱ እና የሼኽ ዑመር ገለምሲይ አስደሳች ታሪኮችን ጽፌ በፌስቡክ እና በድረ-ገጾች ላይ የለጠፍኩት ለዓላማችን መሳካት ያግዘናል በሚል ነው፡፡ ሰዎች የፖለቲካ ታጋይ መስዬአቸው በተሳሳተ መንገድ እንዳይረዱኝ በሚል ልዩ ልዩ ማስታወሻዎችን ለጥፌ ያስነበብኩት “ፖለቲካው አይመለከተኝም” ብዬ ሳይሆን በዚህ ገጽ ላይ ፖለቲካ እንደማላካሄድ ለማሳወቅ በሚል ነው፡፡
አፈንዲ ሙተቂ
አፈንዲ ሙተቂ
ወደፊት በዚህ ገጽ ከኔ ጋር መማማር የሚፈልግ ሰው በዚሁ መንገድ ከኔ ጋር ሊቀጥል ይችላል፡፡ ለኔ የሚከፍል ይመስል እየተሳደበ፣ ቡራ ከረዩ እያለ፤ እየተራገመ ወደርሱ መንገድ እንድገባለት የሚሻ ሰው ካለ ግን በሰላም ወደመጣበት ቢሄድልን እንመርጣለን፡፡ እኛ ለፈጣሪ እንጂ ለሌላ ሀይል አጎብድደን የማናውቅ ሰዎች ነው፡፡ ህሊናችንንም ለገንዘብ ቸብችበን አናድርም፡፡
===ያክብርልኝ===
በዚህ ጉዳይ ዙሪያ በገጠምኩት ሙግት ብዙዎች (65 %) የሚሆኑት ከኔ ሃሳብ ጋር ተግባብተዋል፡፡ ሁሉንም አመሰግናለሁ፡፡ በተለይ ግን መንሱር አሊዩ፣ ጃዕፈር ሰይፊ (ጃፈር አሕመድ)፣ ፊርዶስ ሐሶ፣ ዑስማን አሕመድ፣ ያሕያ ሙሐመድ፣ ጀሚል ይርጋ፣ ፍጹም ታዬ፣ ታጠቅ ወንድሙ፣ ተካበ መኮንን፣ የሚባሉ ጓደኞቼን በጣም አመሰግናቸዋለሁ (ምክንያቱን ወደፊት ብነግራችሁ ይሻላል)፡፡
——–
ሰላም
አፈንዲ ሙተቂ
ታሕሳስ 26/ 2006
Afendi Muteki is a researcher and author of ethnography, history and art with special focus on Eastern Ethiopia.

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ 

New report calls on Ethiopia to reform repressive anti-terror law

IPI and partners also call for immediate release of five imprisoned journalists

VIENNA, Jan 14, 2014 – Ethiopia’s use of sweeping anti-terrorism law to imprison journalists and other legislative restrictions are hindering the development of free and independent media in Africa’s second largest country, according to a report published today by the International Press Institute (IPI).
Dozens of journalists and political activists have been arrested or sentenced under the Anti-Terrorism Proclamation of 2009, including five journalists who are serving prison sentences and who at times have been denied access to visitors and legal counsel. The report, “Press Freedom in Ethiopia”, is based on a mission to the country carried out in November by IPI and the World Association of Newspapers and News Publishers (WAN-IFRA).










“Despite a strong constitutional basis for press freedom and freedom of information, the Ethiopian government has systematically used the anti-terrorism law to prosecute and frighten journalists, which has put a straight-jacket on the media,” IPI Executive Director Alison Bethel McKenzie said. “Our joint mission also found a disturbing pattern of using other measures to control the press and restrict independent journalism, including restrictions on foreign media ownership and the absence of an independent public broadcaster.”

The report urges the Ethiopian government to free journalists convicted under the sedition provisions of the 2009 measure. These journalists include Solomon Kebede, Wubset Taye, Reyot Alemu, Eskinder Nega and Yusuf Getachew. Mission delegates were barred access to the journalists, who are being held at Kaliti Prison near the capital Addis Ababa.
The report urges the 547-member lower house of parliament to revamp the anti-terror law to ensure that it does not trample on the rights of freedom of speech and assembly provided under Article 29 of the Ethiopian Constitution and further guaranteed under the African Charter on Human and People’s Rights and the U.N. Human Rights Covenant, which Ethiopia has ratified.
In addition, the report:
  • Recommends that Ethiopian lawmakers review laws that bar foreign investment in media, measures that inhibit the development of an economically viable and diversified market.
  • Urges the courts to ensure that rulings restrict press freedom only in cases of intentional incitement or clear participation in acts of terrorism, and that judges act independently to protect the public’s right to be informed about political dissent and acts of terrorism.
  • Urges Ethiopia’s journalists and media owners to step up cooperation to improve professionalism and independence, and to form a unified front to defend press freedom.
The joint IPI/WAN-IFRA mission was carried from Nov. 3 to 6, just ahead of the African Media Leaders Forum (AMLF) in Addis Ababa. The organisations’ representatives met with more than 30 editors, journalists, lawyers, politicians and bloggers, as well as associates of the imprisoned journalists. The delegation also held meetings with the ambassadors of Austria and the United States, a senior African Union official, an Ethiopian lawmaker and government spokesman Redwan Hussien.
The organisations urged Prime Minister Hailemariam Desalegn to free the imprisoned journalists, some of whom are suffering from deteriorating health. In a joint statement issued immediately following the mission, IPI and WAN-IFRA also expressed their commitment to helping improve the professionalism, quality and independence of journalism in Ethiopia.
While the report highlights a long history of press freedom violations in Ethiopia, including a crackdown on journalists and opposition politicians following the country’s 2005 national elections, it notes that the 2009 anti-terrorism law has given the government expansive powers.
“The 2009 anti-terrorism law gave new powers to the government to arrest those deemed seditious, including journalists who step beyond the bounds of politically acceptable reporting or commentary,” the report says. “Armed with statutory authority, the government has not shied from using the laws to bludgeon opposition figures and journalists. Dozens of journalists have been imprisoned or accused of sedition or fomenting unrest, forcing many to flee the country.”
The report notes other forms of pressure by the government. Independent journalists recalled being the target of smear campaigns by state-run media, while editors recounted that managers of the government-run printing press refused to print editions of newspapers containing controversial articles.
The report does note positive developments, such as the growth in advertising and readership for some of the country’s leading independent newspapers. Journalists and newspaper publishers also expressed a desire to improve professionalism, quality and solidarity; although they added that government pressure and laws continue to create hurdles to self-regulation and cooperation.
“We came away from Ethiopia recognising the tremendous potential for a highly competitive, professional and successful media market in Ethiopia,” Bethel McKenzie said. “But to make this happen, the Ethiopian government must remove the roadblocks, starting with the release of imprisoned journalists and then conduct a thorough review of the laws to ensure that reporting on legitimate criticism or dissent is not grounds for prosecution.”
For more information, contact Timothy Spence, senior IPI press freedom advisor for the Middle East and Africa, at +43 (1) 512 9011 or email tspence[@]freemedia.at.

መንግስት መጪውን ሀገራዊ ምርጫ አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን የማግባባት መጠነ ሰፊ ዘመቻ ሊጀምር እንደሆነ ተደረሰበት።

January 14/2014

መንግስት መጪውን ሀገራዊ ምርጫ አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን የማግባባት መጠነ ሰፊ ዘመቻ ሊጀምር እንደሆነ ተደረሰበት። የመጀመሪያው ሙከራም በደሴ እንደሚጀመር ተረጋግጧል። በመንግስት ሚዲያዎች አማካኝነት ተቃዋሚዎችን ጥላሸት የመቀባት ዘመቻም በእቅዱ አብሮ ተካቷል። ከረቡእ ታህሳስ 17 እስከ አርብ ታህሳስ 19\2006 ድረስ ለከፍተኛ የአዲስ አበባና የክልል ስራ ሃላዎች በተካሄደ ዝግ ስብሰባ ላይ ሙስሊሙን አስመልክቶ ሰፊ የዘመቻ እቅድ ነው ይፋ የሆነው ፡፡ መንግስት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ በከፍተኛ ባጀት ጭምር በመታገዝ አዲሱን እቅድ ለመጀመር የተገደደው ምርጫው ላይ ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ከፍተኛ የሆነ ሽንፈት ይደርስብኛል በሚል ስጋት እንደሆነ ገለፃ ተደርጎበታል።

ይህ እቅድ ተግባራዊ እንዲሆን ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለስልጣናትና የታወቁ አምባሳደሮች ጭምር እቅዱን በማዘጋጀት ደረጃ እንደሚሳተፉ የተገለፀ ሲሆን ለእቅዱ የሚሆን መሪ ሃሳቦችም በባለስልጣናቱ ይፋ ተደርጓል። በአሁኑ ወቅት በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ሙስሊሞች በግልፅ በሚታይ መልኩ በመንግስት ላየ ከፍተኛ ጥላቻ እንዳላቸው ለስራ ሃላፊዎቹ የተገለፀላቸው ሲሆን ምርጫውን ለማሸነፍ ሲባል ውስብስብ የሆኑ ዘመቻዎችን ተግባራዊ በማድረግ ህዝቡ ወዶ ሳይሆን ተገዶም ጭምር እንዲመርጥ የማድረግ ስትራቴጂ መንደፍ እንዳለባቸው ከስምምነት ላይ ደርሰዋል ፡፡ ምንም እንኳ ሁሉም ሙስሊም ሊባል በሚችል መልኩ መንግስት ላይ ጥላቻ እንዳለባቸው ቢረጋገጥም ቀላል ቁጥር የሌላቸው ሙስሊም ያልሆኑ ዜጎችም የኢህአዴግ መንግስት ላይ ጥላቻ እንዳላቸው መረጋገጡን ባለስልጣናቱ በስብሰባው ላይ ስጋታቸውን አስቀምጠዋል። በዚህም መሰረት የእነዚህን ህብረተሰብ ክፍሎች ድምፅ ለማግኘት ይህ እቅድ በዘመቻ መልክ መሰራቱ ወሳኝ መሆኑ የማያጠራጥር እንደሆነ የገለፁት ባለስልጣናቱ እቅዱን በሶስት እርከን ከፍሎ ለመስራት አቅደዋል ፡፡

ይሄውም እጅግ በጣም ደሃ የሚባሉትን የህብረተሰብ ክፍሎች ኖረም አልኖረ በአነስተኛ ጥቃቅን በማታለልና በመያዝ ኢህአዴግን በውድም ሆነ በግድ እንዲመርጡ ማድረግ የመጀመሪያው እርከን ሲሆን በሁለተኛው እርከን የሚገኙት ደግሞ ሃብታም የሚባሉ ክፍሎች እንደሀኑ ተገልፇል። እነዚህን ክፍሎች ኢህአዴግን እንዲመርጡ ለማድረግ ቀላል እንደሆነ የገለፁት የስብሰባው ተሳታፊዎች በሀብታቸው ላይ በመምጣት ከነሙሉ ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው ጭምር ኢህአዴግን እንዲመርጡ በማድረግ ተፈላጊውን ድምፅ ማግኘት እንደሚቻል ተገልፇል። ለኢህሃዴግ ሃላፊዎች ፈታኝ ሊሆኑ የሚችሉት በሶስተኛው እርከን ላይ የተገለፁት ክፍሎች ሲሆኑ እነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከለኛ ገቢ እንዳላቸው የታመነባቸውና ተማሪዎች እንደሆኑ ተገልፇል። ኢህአዴግ እነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎች በውድም ሆነ በግድ እንዲመርጡት ለማድረግ እንደሚቸገር ገልፀው በነዚህ ክፍሎች ላይ ዘመቻው ከፍተኛ የሆነ እንቅስቃሴ እንደሚያደርግባቸው ይፋ ሆኗል።

ዘመቻውን በሚፈለገው ደረጃ ተፈፃሚ ለማድረግ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትልቅ ፈተና ሊሆኑ እንደሚችሉ እንደ ስጋት የተቀመጠ ሲሆን ይህን ለመከላከል በቀጣይ ጊዚያቶች የመንግስት ሚዲያዎች በተቃዋሚዎች ላይ ሰፊ የማጥላላት አመቻ እንዲከፍቱ እንደሚደረግ ታውቋል። ይህ እቅድ እንዲጎለብትና ወደ ስራ በአፋጣኝ ለመግባት እንዲቻል ከፍተኛ የመንግስት ኤክስፐርቶችና አምባሳደሮች ጭምር የሚከታተሉት ኮሚቴ ተቋቁሞ እቅዱ እየተሰራ ሲሆን በሁለት ሳምንት ጊዜውስጥ የመጀመሪያው ዘመቻ ለኢህአዴግ ከፍተኛ ጥላቻ እንዳላቸው በሚታመኑት በደሴ ከተማ ነዋሪዎች እንደሚጀመር የመንግስት ባለስልጣናቱ ይፋ ማደረጋቸውን የፍትህ የውስጥ ምንጮች አጋልጠዋል።

የመከላከያ መኮንኖች በአዲስ አበባ ፖሊስ የመምሪያ ሃላፊ ተደርገው ተመደቡ:: ‪‬

January14/2014
"የአዲስ አበባ ፖሊስ ከጨዋታ ውጭ እንደሚደረግ ምንም ጥርጥር የለውም "::
በአዲስ አበባ ለጤና አገልግሎት የተሰሩ ክሊኒኮች ወደ እስር ቤትነት ተቀየሩ :: በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስሩ ክፍለ ከተሞች የመከላከያ መኮንኖች ተዛውረው መመደባቸውን ታማኝ የቅርብ ምንጮች ገለፁ። የሕወሐት አባላት የሆኑትና ከመቶ አለቃ እስከ ሻለቃ ደረጃ ያላቸው የመከላከያ መኮንኖች የአዲስ አበባን ፖሊስ በበላይነት እንዲቆጣጠሩ በአስሩም ክፍለ ከቶሞች የመምሪያ ሃላፊ ተደርገው መሾማቸውን ምንጮቹ አስታውቀዋል።ከዚሁ ጎን ለጎን በአዲስ አበባ በሚገኙ ወረዳዎች “ኮሚኒቲ ፖሊስ” በሚል አዳዲስ የፌደራል ፖሊሶች እንደመተደቡ ምንጮቹ አያይዘው ገለፀዋል።
 በአዲስ አበባ ፖሊስ ሃይል እምነት ያጣው ገዢው ፓርቲ ሕወሐት/ኢህአዴግ ታማኝ በሚላቸው መኮንኖችና የፌደራል ፖሊሶች እየተካና አፈናውን እያጠናከረ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም አሁን በተጀመረው የክልሉን ፖሊስ የማፍረስ ተግባር በቅርብ ጊዜ የአዲስ አበባ ፖሊስ ከጨዋታ ውጭ እንደሚደረግ ምንም ጥርጥር የለውም ብለዋል። 
ገዢው ፓርቲ ራሱ በደነገገው ሕገ-መንግስት ላይ ፖሊስ ፀጥታውን እንደሚቆጣጠር እንዲሁም መከላከያ ገለልተኛ ሆኖ የአገሩን ሉአላዊነት እንደሚጠብቅና ከማንኛውም ፖለቲካ ድርጅት ነፃ ሆኖ እንደሚቆም አዋጁ የሚገልፅ ቢሆንም ነገር ግን ራሱ ላወጣው ሕገ መንግስት ተገዢ መሆን እንዳልቻለ የሕወሐት መኮንኖች ከመከላከያ ተዛውረው የአዲስ አበባን ፖሊስ በበላይነት እንዲመሩና እንዲቆጣጠሩ መመደባቸው የህግ ጥሰት እያካሄደ እንደሆነ በቂ ማስረጃ ነው ብለዋል ምንጮቹ። ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲስ አበባ ለጤና አገልግሎት የተሰሩ ክሊኒኮች ወደ እስር ቤትነት እየተቀየሩ መሆኑን ምንጮች አጋልጠዋል። በአዲስ አበባ የካና አራዳ ክፍለ ከተሞች “ኬርና ፕላን” በተባሉ ግብረሰናይ ድርጅቶች የተሰሩት ጤና ጣቢያዎች ወደ ፖሊስ ጣቢያነት ተቀይረው እስረኞች እየታሰሩባቸው መሆኑን አረጋግጠዋል። በየካ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 06/07 ቤላ፣ ፈረንሳይ ለጋሲዮን ቀበሌ 11 እንዲሁም ጃንሜዳ ቀበሌ 05 የሚገኙ ጤና ጣቢያዎች በከፊል እንደሚጠቀሱ ያስታወቁት ምንጮቹ በተጠቀሱት ቦታዎች እስረኞች በብዛት ታስረው እንደሚገኙ አያይዘው ገልፀዋል።

ይህን አንብባችሁ ዝም አትበሉ ይህን መልዕክት ለሌላው በማስተላለፍ ተባበሩ:: !

January14/2014

ይህን አንብባችሁ ዝም አትበሉ ይህን መልዕክት ለሌላው በማስተላለፍ ተባበሩ !

3ኛ ወንጀል ችሎት በእኔ ላይ ፍርድ ሲሰጥ የተሰማኝን ሃዘንና ባዶነት የትኛውም ኢትዮጵያዊ ድጋሚ እንዲሰማው አልሻም ::በፈጣሪ እርዳታ ከእድሜም ልክ በላይ ምት ቢፈርዱብኝም ለምቀበል ተዘጋጅቼ ነበር :: ይሁንና ይኼን ያህል የሚያስፈርድ ወንጅል ቀርቶ አንድ ምሽት ወህኒ የሚያሳድር ወንጀል ባለመስራቴ ህሊናዬ ፍፁም እረፍት ይስማዋል ::እንዲህ አይነት ” የፍትህ ስርዓት ” ያለባት ሃገር ልጅ መሆኔ ግን የሃፍረት ማቅ አከናንቦኛል:: ዳኞቹ አሳዘኑኝም ፤ አሳፈሩኝም::

ያም ሆነ ይህ እኔና እኔን መሰል ስዎች ያልሆነውን ሆናችሁ ተብለን የምንገፍው የመከራ ህይወት በኢትዮጵያችን የነፃነት ቀን እንዲጠባ የሚረዳ ክሆነ ፤ የሚከፈለው መስዋዕትነት ቢያንስ እንጂ ፈጽሞ አይበዛም:: በትውልድና በታሪክ ፊት ለከበረ ነፃነት ሲባል ዋጋ መክፈል ተመርቆ መፈጠር እንጂ ከቶም አለመታደል አይሆንም:: የልጆቻችንና የሚስቶቻችንም ስብራት ሁላችንም የምንኮራባት ሀገር ስትኖረን ያን ግዜ ይጠግን ይሆናል ::

ዛሬ ግን በዚች ሀገር የፍትህ ስርዓት አለን ብለን መናገር ፈጽሞ የማንችልበት ደረጃ ላይ እንገኛለን :: እንደዚህ ዘመን ፍትህ መሬት ላይ ተጥሎ የተዘበተበት ዘመን ይኖር ይሆን ? ፍርድ ቤቶቻችን የፍትህ መባ የሚፈታባቸው ምኩራቦች እስኪሆኑ ድረስ አበክረን ልንታገል ይገባል:: ይኽንን የነፃነት ብርሃን የሚናፍቅ ህዝብ በልበ ሙሉነትም የሚታገል ትውልድ የነፃነቱ ባለቤት ይሆናል::

ለመታግል ገዠዎችን መፍራት አያስፈልግም:: በተላይ ወጣቱ ለነገዋ ሀገሩ ዛሬ በእውነትና በልበ ሙሉነት ይቁምላት :: የኢትዮጵያን ህዝብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ከልብ የማይሰራ የኢህአዴግ አመራር ከፕለቲካ ሜዳው በአስቸኳይ ሊወጣ ይገባዋል፤ በተቃዋሚ ጎራውም ይኽን መሰል አስተሳሰብ ያለው ወገን ካለ መንገዱን ይልቀቅ:: ከዚህ በላይ ኢ-ፍትሐዊነትንና ኢ-ሰብአዊነትን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እያሰፈኑ ሊቀጥሉ አይችሉም፤ ለፍትህ ለወንድማማችነትና ለነፃነት መንገዱን መልቀቅ አለባቸው:: በእኔ እይታ ሁሉንም የድርድር በሮች ዘግቶ የምላችሁን ብቻ ተቀበሉ ለሚል ጠቅላይ አገዛዝ መታዘዝ በሽታው እንዲብስበት ማድረግ ብቻ ነው :: ዘላቂ መፍትሄው ደግሞ በየግዜው የሚከፈለውን ዋጋ እየከፈሉ ከእውነትና ነፃነት ጋር መቆም ብቻ ነው::

በቃልቲ እስር ቤት የሚገኘው አቶ አንዱዓለም አራጌ ዋለ ” ያልተሄደበት መንገድ ” መጽሐፍ የተወሰደ
Image

አንዱዋለም ግንቦት ሰባት ከተባለ እኔም ግንቦት ሰባት ነኝ – ግርማ ካሳ

January 14/2014

«በሕገ መንግስቱ የመደራጀት መብታቸው የተጠበቀላቸው ፓርቲዎችን አልከሰስንም።ፓርቲዎችን ግን ሽፋን አድርገዉ ስርዓቱን ወይንም ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ እንቀሳቀሳለን የሚሉ ኃይሎችን ግን ዛሬም ፣ ነገም ፣ ሕጉን የማስከበር ግዴታና ሃላፊነት ስላለብን ከመከሰስ አያመልጡም ማለት ነዉ።»

ኢቲቪ በቅርቡ በ«ሽብርተኝነት» ላይ፣ በቅርቡ ባቀረበዉ አሳዛኝ ዶኩሜንተሪ ላይ ፣ የፌደራል መንግስት አቃቤ ሕግ፣ አቶ ብርሃኑ ወንድማገኝ የተናገሩት ነበር።
እኝህ የሕግ ባለሞያ እየደጋገሙ ሕግን ስለማክበርና ስለ ሕገ መንግስቱ ነግረዉናል። ስለሕገ መንግስት ካነሳን አይቀር አንድ ነገር ጣል ላድርግ። የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 29 ንኡስ አንቀጽ 4 «በመንግስት ገንዘብ የሚካሄድ ወይንም በመንግስት ቁጥጥር ሥር ያለ መገናኛ ብዙሃን የተለያዩ አስተያየቶችን ለማስተናገድ በሚያስችለው ሁኔታ እንዲመራ ይደረጋል» የሚል ድንጋጌ ያካትታል። ኢቲቪ በሕዝብ ገንዘብ የሚተዳደር እንደመሆኑ ይህ የሕገ መንግስት አንቀጽ ይመለከተዋል። ነገር ግን ኢቲቪ በቀጥታ፣ ሕግ መንግስቱን ሲንድ፣ ገለልተኛነት በጎደለው መልኩ የአንድ ድርጅትን የፖለቲክ ፕሮፖጋንዳ መጠቀሚያ ሲሆን ነው እያየን ያለነዉ። እነ አንዱዋለም አራጌ ላይ፣ ኢቲቪ የአንድ ወገንን አቋም የያዘ፣ የስም ማጥፋት ዘመቻ ሲያዥጎደጉድ፣ ቢያንስ ቢያንስ ጥቂት ሰኮንዶች፣ የአንዷለምን ጠበቃዎች፣ ወይንም ቤተሰብ፣ አሊያም የትግል አጋሮቹ የሆኑት የአንድነት አመራር አባላትን ለማነጋገር አልተሞከረም። እንግዲህ ከዚህ የምንረዳዉ፣ ሕግን በማክበር አኳያ፣ ሕወሃት/ኢሕአዴጎችና ኢቲቪ፣ አንድ ጣታቸዉን ወደሌሎች ሲጠቁሙ፣ አራቱ ጣቶቻቸው ወደ እነርሱ መዞራቸውን፣ ሕገ መንግስቱን እየጣሱ ያሉ እነርሱ መሆናቸውን ነዉ።
«አንዱዋለም አራጌን በተመለከተ፣ የግንቦት ሰባትን ተእልኮ ለማስፈጸም አገር ዉስጥ በሕቡእ (ስዉር) ይንቀሳቀሳል በሰላማዊ ትግል እንታገላለን የሚሉ የፓርቲዎችን ሽፋን አድርጎ ሲንቀሳቀስ የነበረ በመሆኑ በቂ ማስረጃ አቅርበናል» ሲሉ ነበር የፌደራል አቃቤ ሕጉ ለኢቲቪ አክለው የገለጹት። ምን አይነት መረጃ እንዳቀረቡ ግን አልነገሩንም። ለምን ቢባል ምንም ስለሌለ።
አንዱዋለም ያደርጋቸው የነበሩ እንቅስቃሴዎች በሙሉ ሲያደርግ የነበረው በግልጽና በገሃድ ነዉ። ለተለያዩ ፓልቶክ ክፍሎች፣ አገር ዉስጥና በዉጭ ለሚገኙ ሜዲያዎች በርካታ ቃለ መጠይቆችን ሰጥቷል። በአገር ቤት፣ በአንድነት ፓርቲ ዉስጥ ሆነ በተለያዩ ቦታዎች በተደረጉ ዉይይቶችና ስብሰባዎች ያቀረባቸው ንግግሮች በሙሉ የተደበቁ አይደሉም። ዉጭ ካሉ ኢትዮጵያዊያን ጋር (አንዱም እኔው ነበርኩ) ፣ ብዙ ጊዜ በስልክ ሃሳቦችን ተለዋዉጧል። በስልክ ያደረጋቸው ንግግሮችም፣ 24 ሰዓት የሰላማዊ ተቃዋሚ መሪዎችን ስልክ በሚጠልፈው ቴሌ ዘንድ የተሰሙ ናቸው። ቤቱና ቢሮዉ ከላይ እስከ ታች ተበርብረዉ ፣ የሚስጥራዊ የኮሚኒኬሽን መሳሪያዎች፣ ቦምቦች፣ ፈንጂዎች፣ ሚስጥራዊ ሰነዶች አልተገኙም። ኤሜሎቹ በሙሉ ተነበዋል። አንዱዋለምን ከግንቦት ሰባት ጋር የሚያገናኝ፣ በሕቡእ እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሆነ የሚያመለክት አንዳች መረጃ አቃቤ ሕግ አላቀረበም። መረጃዎች ቢኖሩ ኖሮ፣ «እንኳን ዘንቦብሽ ድሮም ጤዛ ነሽ» እንደተባለ፣ ዜጎችን በማዋረድና በማሳነስ የሚታወቀዉ ኢቲቪ፣ ይሄን ጊዜ በስፋት ያወራልን ነበር።
ኢቲቪ ግን አንዱዋለምን ለመክሰስ ያቀረበው፣ አንድ የአንድነት አባል የነበሩ፣ ተስፋሁን አናጋዉ የተባሉ ሰው የተናገሩትን ነዉ። አንዱዋለም ከታሰረ በኋላ አቃቤ ሕጎች መረጃ ማቅረብ ባለመቻላቸው፣ የዉሸት መረጃዎች ማሰባሰቡ የግድ ሆነባቸው። የታሰሩ ሌሎች የአንድነት አባላትን ማግባባት ጀመሩ። «በአንዱዋለም ላይ እኛ ተናገሩ የምንላችሁን ከተናጋራችሁ እንፈታቹሃለን» ብለው እጆቻቸዉን ጠመዘዙ። ብዙዎች በአንዱዋለም ላይ የዉሸት መረጃ ማቅረቡ ሕሊናቸውን ስለከበደው ፍቃደኛ አልሆኑም። ነገር ግን እንደ ተስፋሁን አናጋው፣ የሚባሉ ደካማ ሰዎች ተገኙና የዉሸት ምስክርነት ቀረበ። እንግዲህ በአገዛዙ ካድሬዎች ተቀናብረው ከቀረቡ የዉሽት ምስክርነቶች ዉጭ፣ ቅንጣት የምታክል፣ አንዱዋለምን ሽብርተኛ ወይንም ከግንቦት ስባት ጋር የሚሰራ መሆኑን የሚያሳይ መረጃ አልቀረበም።
«ግንቦት ሰባት ፣ ግንቦት ሰባት ……» እንባላለን። ከጅምሩ በግንቦት ሰባት ላይ ጠንካራ ተቃዉሞ ያለኝ ሰው ነኝ። የግንቦት ሰባት ፖለቲካ አይመቸኝም፣ ለአገርም ይጠቅማል ብዬ አላስብም። ግንቦት ሰባቶች ከያዙት የተሳሳተ መንገድ እንዲመለሱ፣ በሻእቢያ ድጋፍ ሳይሆን፣ በሕዝብ ጉልበት በመተማመን ወደ ሰላሙ መንገድ እንዲመጡ መክሪያለሁ። በተለያዩ ጊዜያት ለአንባቢያን ያቀረብኳቸውን ጽሆፍችን መመልከት ይቻላል።
ከቅንጅት ጊዜ ጀምሮ በአገር ዉስጥ በሰላም ለዉጥ ለማምጣት የሚሰሩ ድርጅቶችን ደግፊያለሁ። በተለይም የአንድነት ፓርቲ በጣም የሚመቸኝ ፓርቲ እንደመሆኑ፣ አንዱዋለም አራጌን ጨምሮ፣ ከፓርቲዉ አመራር አባላት ጋር ሃሳብ የተለዋወጥኩባቸው በርካታ ጊዜያት ነበሩ። አንዱዋለም አራጌ፣ እግዚአብሄርን የሚፈራ፣ የልጆች አባት፣ የሰላማዊ ትግል አርበኛ ነዉ። አንዱዋለም ስለ ትጥቅ ትግል ያለዉን አመለካከት አውቃለሁ። በየትኛዉም መድረክና ፍርድ ቤት፣ መጽህፍ ቅዱስ ላይ እጄን ጭኜ የምመሰክረዉ ነዉ። አንዱዋለም አራጌ የግንቦት ስባት አባል ወይንም ሽብርተኛ ነው የሚለውን፣ በምን መስፈርትና መልኩ ልቀበለው አልችልም። በርግጥ አንዱዋለም የግንቦት ሰባት አባል ከተባለ፣ እኔም የግንቦት ሰባት አባል ነኝ እንደ ማለት ነዉ።
በጣም ያሳዝናል። እንደ አንዱዋለም አራጌ አይነት አገር ወዳድ ዜጎች፣ አገራቸዉን በመዉደዳቸው፣ የሕዝብ መብት ይከበር በማለታቸው፣ «ሽብርተኞች» በሚል አሳዛኝ ክስ ሲታሰሩ ማየት፣ አገራችን ኢትዮጵያ ዜጎች ቀና ብለው የሚራመዱባት ሳይሆን ፣ አሳፋሪ ድራማ የሚካሄድባት፣ ሕግ መቀለጃ የሆነባት አገር መሆኗ፣ በርግጥ ልብን የሚያደማ ነው።
እንግዲህ፣ ሁሌ እንደማደርገዉ፣ ጥሪ ለኢሕአዴጎች አስተላልፋለሁ። ኢሕአዴግ ዉስጥ፣ ለአገርና ለሕዝብ የሚያስቡ ካሉ፣ በድርጅታቸው ዉስጥ እየተደረገ ያለውን አፈናና ግፍ በቃ የማለት አቅምና ጉልበት ሊኖራቸው ይገባል ባይ ነኝ። ድርጅታቸው ዉስጥ ያሉ ጥቂቶች ድርጅታቸውን ይዘው ገደል እንዲወስዱ ሊፈቀድላቸው አይገባም። እነ አንዱዋለምን በማሰር ኢሕአዴግ ምንም የሚጠቀመው ነገር የለም። እነ አንዱዋለምን በዉሸት ክስ ከሶ፣ በቴለቭዥኝ ደግሞ ስማቸውን ማጉደፍ፣ ነዉር ነዉ። ኢሕአዴግ የበለጠ እንዲጠላ የሚያደርግ ነዉ። የአረና ትግራይ አመራር አባል አብርሃ ደስታ አንዴ ሲጽፍ፣ የሕወሃት እምብርት በነበረችው የትግራይ ክልል፣ አንዱዋለም አራጌ በጣም ተወዳጅ ፖለቲከኛ እንደሆነ ገልጾ ነበር። አንዱዋለም አራጌ፣ በክልሎች ሁሉ ሕዝብ የሚያውቀዉ ጀግና መሪ ነዉ። በርሱ ላይ እየተደረገ ያለው ዘመቻ፣ የበለጠ አንዱዋለምን ከፍ የሚያደርግ፣ ኢሕአዴግን ደግሞ የሚያሳንስ ነዉ። አንዱዋለምን እና ሌሎች የሕሊና እስረኞች፣ አለመፍታት በቀጥታ ከሕዝቡ ጋር እንደመላተም ነው። አይጠቅምም። ጉዳት አለው።
ለኢሕአዴጎች ጥሪ ባቀርብም፣ የነአንዱዋለም ጉዳይ፣ የኢሕአዴጎች ጉዳይ ብቻ ግን አደለም። ኢሕአዴጎች ወደ ሕሊናቸው ተመልሰው መልካም ነገር ያደርጉ ዘንድ እነርሱን ማነጋገርና ለማሳመን መሞከር፣ ማበረታታት ተገቢ ነዉ የሚል እምነት ቢኖረኝም፣ ሁሉንም ነገር ከነርሱ ጠብቆ ቁጭ ማለቱ ግን፣ እጅግ በጣም ትልቅ ስህተት ነው። እነርሱ ቢሰሙ መልካም ነዉ፤ ካልሆነ ግን እያንዳንዳችን መብታችንን የማስከበር ሃላፊነት ያለብን ይመስለኛል። ዛሬ እነ አንዱዋለም ናቸው። ነገ እያንዳንዳችን ቤት ይንኳኳል ። ዛሬ ሊመቸን ይችላል። ነገር ግን ለሕይወታችን ምንም ዋስትና አይኖረንም። አንድ የመንግስት ባለስልጣን ፊታችንን አይቶ ከጠላን፣ በቀላሉ ወደ ወህኒ ሊወረወረን የሚችልበት ሁኔታ እንዳለ ማወቅ አለብን። አለን የምንለውን ቢዝነስ አንዱ ከፈለገዉ፣ «ያለ የሌለዉን እያመጡ፣ ይሄን ያህል ግብር ክፈል» ተብለን ከጨዋታ ዉጭ በቀላሉ ልንሆን የምንችልበት አገር ነዉ ያለችን። አቤት የምንልበት የሕግ ስርዓት የለም። አብዛኞቹ ዳኞች በመመሪያ የሚፈርዱ ካድሬዎች ናቸው። በመሆኑም፣ ኢትዮጵያ፣ ሕግ የበላይ የሆነባት፣ ለሁሉ ዜጎቸ እኩል የሆነች፣ ኢትዮጵያዊያን ሳይፈሩና ሳይሸማቀቁ ሃሳባቸውን በነጻነት መግለጽ የሚችሉባት፣ መቀባባል፣ ይቅርታ፣ ፍቅር፣ ሰላም ፣ ፍትህና ወንድማማችነት የሰፈነባት፣ የበለጸገች አገር እንድትሆን፣ እያንዳንዳችን የድርሻችንን መወጣት አለብን። ዳር ሆኖ ተቀመጦ ማውራት ይብቃ። ሌሎች ለምን እንዲህ አላደረጉም ብሎ መክሰስ ይብቃ። ሌሎች ሞተው በነርሱ አስክሬን ላይ ተረማመደን ለመሻሻል መሞከር ይብቃ። አገራችን የእስክንደር፣ ወይንም የአንዱዋለም፣ ወይንም የበቀለ ገርባ፣ ወይንም የርዮት አለሙ ብቻ ሳትሆን የሁላችንም ናት፣ ሁላችንም ተስፋ ሳንቆርጥ፣ ሌሎች ነጻ እንዲያወጡን ሳንጠብቅ፣ የድርሻችንን እንወጣ።