Wednesday, November 27, 2013

ከኢትዮጵያ እሳት ወደ ሳውዲ አረቢያ እረመጥ፣ ከድጡ ወደ ማጡ

November 27, 2013
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሀገሬ
What “foreign minister” Adhanom said and did not even know he said it
Tedros Adhanom, the malaria researcher-turned-instant-foreign-minster
ባለፉት አስርት ዓመታት በመቶሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች በአገራቸው ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አህጉር በተለየ መልኩ ተንሰራፍቶ እየተፈጸመ ካለው ጭካኔና ርህራሄ የጎደለው አምባገነናዊ ስርዓት ለማምለጥ ሲሉ እግራቸው ወዳመራቸው አገር በመሰደድ ላይ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ “ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር” እንደዘገበው ከሆነ እ.ኤ.አ በ2012 በግምት 200,000 ኢትዮጵያውያት ሴቶች በውጭ አገር በአብዛኛውም በመካከለኛው ምስራቅ አገሮች የውጭ የስራ ዕድል ለመፈለግ ተገደዋል፡፡ ከእነዚህ ኢትዮጵያውያት ሰራተኞች አብዛኞቹ በኢትዮጵያ ተንሰራፍቶ ከሚገኘው አምባገነናዊ የእሳት ነበልባል አመለጥኩ የሚል እምነት ነበራቸው፣ ሆኖም ግን ወደ ሳውዲ አረቢያው የእሳት እረመጥ ተወርውረው እራሳቸውን አገኙት፡፡
በኢትዮጵያውያን ስደተኛ ሰራተኞችና በሌሎች በሳውዲ አረቢያ ጥገኝነት በጠየቁ ዜጎች ላይ ገደብ የለሽ አደን እየተካሄደ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ በዚህ ወር በየዕለቱ በሚባል መልኩ የሳውዲ አረቢያ ፖሊሶች፣ የደህንነት ኃላፊዎች፣ ወሮበሎች እና ህገወጦች ኢትዮጵያውያንን/ትን ሁሉ በየመንገዱ እያደኑ ይደበድባሉ፣ ያሰቃያሉ፣ አንዳንድ ጊዜም ይገድላሉ፡፡ የሳውዲ አረቢያ ፖሊሶች ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎችን ሲደበድቡ የሚያሳየውን የዩቱቤ የቪዲዮ ምስል መመልከት ለህሊና የሚሰቀጥጥ ነገር ነው፡፡ የሳውዲ አረቢያ ወሮበሎችና ህገወጦች ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎችን በየመንገዶች ሲያሳድዱ፣ ሲያጠቁና ሲገድሉ የሚያሳየው የቪዲዮ ምስል ለኩነቶቹ እውንነት ምንም ዓይነት ማብራሪያ አላስፈለገውም፡፡ በአሁኑ ጊዜ የሳውዲ አረቢያ ወሮበሎችና ጋጠወጦች በኢዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ እየፈጸሙት ያለው በቪዲዮ ማስረጃነት ተደግፎ የቀረበው የሰብአዊነት መብት ረገጣ ወንጀል በጣም የሚዘገንንና በሰለጠነ የሰው ልጅ ህሊና ሊታሰብ የማይችል ነገር ነው፡፡
ኢትዮጵያና ሳውዲ አረቢያ፡ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች፣
ኢትዮጵያና ሳውዲ አረቢያ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው፡፡ የሳውዲ አረቢያና የኢትዮጵያ ገዥዎች ከአንድ ጥለት የተቆረጡ ናቸው፡፡ የሳውዲ አረቢያ መንግስት በሰብአዊ መብት አያያዝ መዝገቡ በመጥፎ ተምሳሌነቱ ይታወቃል:: በተመሳሳይ መልኩ የኢትዮጵያ መንግስት በሰብአዊ መብት አያያዝ እንደ ሳውዲ አረቢያ ሁሉ ያስጠይፋል፡፡ የሳውዲ አረቢያው ገዥ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎችን በጣም ሰብአዊነት በጎደለው መንገድ ከግዛቱ በኃይል እንዲጋዙ/እንዲባረሩ የሚያደርግ መርህን ተከትሏል፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ መደብም በተመሳሳይ መልኩ በሀገሩ ግዛት ውስጥ ኢትዮጵያውያንን/ትን ከሚኖሩበት ቀያቸው በግዳጅ ወደሌላ አካባቢ በማጋዝ አስደንጋጭ የሆነ የሀገር ውስጥ የማጋዝ (ሰፈራ) መርህን ተከትሏል፡፡ የሳውዲ ገዥ አናሳ የእምነት ተከታዮችን አሰቃይቷል፣ የኢትዮጵያ ገዥ መደብም እንደዚሁ አድርጓል፡፡ በሳውዲ ያለው ገዥ መደብ ዜጎችን በስፋት በዘፈቀደ በቁጥጥር ስር ያውላል፣ በእስር ቤት ያጉራል፣ ያሰቃያል፣ እንዲሁም በህግ ከለላ ጥላ ስር በሚገኙት ዜጎች ላይ ህገወጥ የእስር ቤት አያያዝን ያራምዳል፡፡ የኢትዮጵያ ገዥ መደብም በተመሳሳይ መልኩ የሳውዲ ገዥ የሚፈጽማቸውን የአፈና ድርጊቶች ሙሉ በሙሉ ይፈጽማል፡፡ የሳውዲ ገዥ የባሪያ ንግድን እ.ኤ.አ በ1962 በአዋጅ ካስቆመ በኋላ “ከፋላ” “kafala” (ተያዥ ያላቸው ስደተኛ ሰራተኞች፣ ሆኖም ግን በባሪያ ንግድ የአሰራር ሁኔታ የሚሰሩ) የሚል ቅጥያ በመስጠት ብዝበዛውን ቀጥሎበታል፡፡ እ.ኤ.አ በ2009 የባህሬን የሰራተኛ ሚኒስትር ማጅድ አል አላዊ ሲናገር ከፋላ የሚለውን የማደናገሪያ ቅጥያ ከባሪያ ንግድ ጋር አመሳስሎታል፡፡ እ.ኤ.አ የ2013 ዓለም አቀፍ የባርነት አመላካች አሀዝ/Index እንዳመለከተው 651,000 የሚሆኑ በባርነት ተይዘው ህይወትን በመግፋት ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ዜጎች ሲኖሩ ከእነዚህም የዓለምን ሶስት አራተኛ ከሚይዙት ከመጀመሪያዎቹ አስር አገሮች ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን በግልጽ አስቀምጧል፡፡
ሂዩማን ራይትስ ዎች/Human Rights Watch እ.ኤ.አ በ2013 ባቀረበው ዓለም አቀፋዊ ዘገባው የኢትዮጵያንና የሳውዲ አረቢያን የሰብአዊ መብት አያያዝ ሬከርድ በሚመሳሰል መልኩ እንደሚከተለው አቅርቦታል፤
በ2012… የኢትዮጵያ ባለስልጣኖች ሀሳብን በነጻ የመግለጽ፣ የመደራጀትና የመሰብሰብ መሰረታዊ መብቶችን መገደብን በስፋት ቀጥለውበታል፡፡ ሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባውን በመቀጠል በአዲስ አበባ ማዕከላዊ እየተባለ በሚጠራው የፌዴራል ፖሊስ የምርመራ ማዕከል ፣ እንዲሁም በሶማሊ፣ በኦሮሚያ እና በጋምቤላ ክልሎች እስር ቤቶችና በወታደራዊ ማዕከሎች የሚፈጸሙትን የማሰቃየት ድርጊቶች ዝርዝር ዘገባ አቅርቧል፡፡
የሙስሊሙን ህብረተሰብ አመጽ ተከትሎ በኦሮሚያና የአገሪቱ መናገሻ በሆነችው በአዲስ አበባ ከተማ አመጹን ለመግታት በሚል ሰበብ የደህንነት ኃይሎች ሰላማዊ ሰዎችን ከህግ አግባብ ውጭ በቁጥጥር ስር በማዋል፣ እስራትና ድብደባዎችን ፈጽመዋል፡፡ የፌዴራል ፖሊስ ድብደባን ጨምሮ በአገሪቱ ከፍተኛ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ላይ መንግስት ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆም የሚጠይቀውን የሙስሊሙን ህብረተሰብ ሰላማዊ ተቃውሞ ለመግታት ሲል መንግስት ከልክ ያለፈ ኃይልን ተጠቅሟል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ ለማድረስ በሚል ሰበብ የመንደር ማሰባሰብ ተግባሩን እውን ለማድረግ በአምስት የአገሪቱ ክልሎች 1.5 ሚሊዮን የገጠር ሰፋሪዎችን የማሰባሰብ ስራ ቀጥሏል፡፡ በጋምቤላ ክልል ብዙ ሰፋሪዎች ከሚኖሩበት ቀዬ በኃይል ተፈናቅለው ብዙ መከራ ደርሶባቸዋል… በመንግስት ጥረት የሚከናወን የሸንኮራ አገዳ ልማትን ለማፋጠን ሲባል በኢትዮጵያ የታችኛው ኦሞ ሸለቆ የሚኖሩትን ኗሪ የፓስቶራል ህዝቦች መንግስት በኃይል አፈናቅሏል:: በደቡብ ኦሞ ዞን ወደ 200 ሺ የሚሆኑ የአካባቢው ኗሪ ህዝቦች መሬታቸውን ለሸንኮራ አገዳ ልማት ይፈለጋል በሚል ሰበብ መንግስት መሬታቸውን በመንጠቅ ወደ ሌላ ቦታ እንዲሰደዱ አድርጓል፡፡
ሳውዲ አረቢያን በሚመለከት ሂዩማን ራይትስ ዎች የሚከተለውን ዘገባ አቅርቧል፣
እ.ኤ.አ በ2012 ከህግ አግባብ ውጭ የሚከናወኑትን እስራቶችና ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን የማዋከቡ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ ዜጎች ሰላማዊ ሰልፍ በማድረጋቸው ምክንያት የሳውዲ አረቢያ መንግስት የኃይል እርምጃን ተጠቅሟል… እንዳለፉት ዓመታት ሁሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ፍትሀዊ ያልሆነ ፍርድን ተቀብለዋል፣ ወይም ደግሞ ከህግ አግባብ ውጭ ለእስራት ተዳርገዋል… እስረኞች ህጻናትን ጨምሮ ስልታዊ የህግ የበላይነት ጥሰት እና ፍትሃዊ ህግ የማግኘት መብት የመነፈግ፣ ከህግ አግባብ ውጭ እስራትና ማሰቃየት እንዲሁም ህገወጥ የእስር ቤት አያያዝ ደባ ይፈጸምባቸዋል… ባለስልጣኖች የ9 ሚሊዮን የውጭ ሰራተኞችንና የ9 ሚሊዮን የሳውዲ ሴቶችና ልጃገረዶች መብት ማስከበር አልቻሉም ወይም ጭቆናውን ቀጥለውበታል…
ወደ 1.5 ሚሊዮን የሚሆኑ የአገር ውስጥ ስደተኛ ሰራተኞች ከ2005 የሰራተኞች ህግ ውጭ ተደርገዋል… ባለፉት ዓመታት የኤሲያ ኤምባሲዎች ዘገባ እንደሚያመለክተው ከሀገር ውስጥ ሰራተኞች ቅሬታ እንደሚያሳየው በቀን ከ15 እስከ 20 ሰዓታት፣ በሳምንት ደግሞ 7 ቀናት እንዲሰሩ ከመገደዳቸውም በላይ ደመወዛቸውን ያለመክፈል ሁኔታም ተንጸባርቋል፡፡ የሀገር ውስጥ ሰራተኞች በአብዛኛውም ሴቶች በተደጋጋሚ ጊዜ ተገደው እንዲወልዱ ይደረጋል፣ ምግብ የማግኘት መብታቸውን ያጣሉ፣ እንዲሁም የጾታ ትንኮሳ፣ የአካልና የስነልቦና ጫናዎች ይደረጉባቸዋል፡፡
ሳውዲ አረቢያ ከእስልምና አስተህምሮ ውጭ የሌሎችን እምነቶች አስተምህሮዎችን ለመቀበል ትዕግስቱ የላትም፡፡ ባለፈው መጋቢት ወር ልዩ ልብስ ለባሹ ሸክ በአረቢያ ፔንሱላ የሚገኙ ማናቸውም ቤተክርስቲያኖች በሙሉ እንዲወድሙ ጥሪ አስተላልፎ ነበር…
“የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር” ቴዎድሮስ አድሃኖም ምን እንዳሉና ያሉትንም እንዳላወቁ፣
በኢትዮጵያ ያለው ገዥው አካል በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ በአሁኑ ጊዜ እየደረሰ ያለውን አስፈሪ ሁኔታ በማስመልከት የሚሰጠው ምላሽ ጭንቅላትን ይበጠብጣል፡፡ የወባ ትንኝ ተመራማሪውና ከመቅጽበት ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት የተቀየሩት ቴዎድሮስ አድሃኖም እንዲሁም እ.ኤ.አ ከ2015 ሀገራዊ ምርጫ በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ይረከባሉ ተብለው የሚጠበቁት ባለስልጣን ስለሳውዲ አረቢያው የኢትዮጵያውያን/ት ሁኔታ አስመልክቶ በኖቬምበር አጋማሽ በአዲስ አበባ ላይ በተካሄደው በ3ኛው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ዕቅድ ምጣኔ ጉባኤ ላይ ሲናገሩ ግራ ተጋብተዋል፣ እዚህና እዚያ የሚዋዥቅ ንግግርም አሰምተዋል፡፡ ቅንነት የጎደለው እርግጠኝነትና በባዶ ተስፋ የተሞሉ ቃልኪዳኖችን አነብንበዋል፡፡ ወገኖቻችን ወደ ትውልድ አገራቸው እንዲመጡ በደስታ ለመቀበልና ዓለም ቀፋዊ ተብብርን ማጠናከር አስፈላጊ እንደሆነ በየኋህነት/ሞኝነት አገላለጽ አስቀምጠውታል፡፡
እንደምታውቁት፣ ከሳውዲ አረቢያ እንደምታውቁት ኢትዮጵያውያንን ብቻ ቢያግዙም/ቢያባርሩም ቅሉ ሌሎችን ዜጎችም እንዳባረሩ እንረዳለን… ባለፉት አስርት ቀናት እንዳየሁትም፣ ምክንያቱም በቤተሰብ ምጣኔ ዕቅድ እንደምንለው ለልጃገረዶችና ለሴቶች ክብካቤ እናደርጋለን፣ ከጣቢያዎች እርዳታ በመፈለግ ከሚጮሁ ሴቶች በቀጥታ ጥሪዎች ደርሰውኛል… በመቶዎቸ የሚቆጠሩትን በእርግጠኝነት ተቀብለናል፣ በሺዎችና በአስር ሺዎች የሚቆጠሩትን እንቀበላለን ብለን እንጠብቃለን፣ በእርግጠኝነት ለመናገር የምፈልገው ዜጎቻችንን ወደ አገራቸው እንዲመጡ ለመቀበል ሙሉ በሙሉ ዝግጁ ነን፡፡
በጣም አዝኛለሁ፣ ስሜቴም ተጎድቷል፡፡ ለዚህም ነው ይህ ሁኔታ ከተጀመረ ወዲህ ባለው የጊዜ መደበላለቅ ምክንያት ወደዚህ ላለመምጣት ዶ/ር ተከስተን ጠይቄ የነበረው፡፡ ሆኖም ግን በዓለምአቀፋዊነት ትብብር መሰረት ህገወጦችን ማባረር/ከአገር ማስወጣት የምንችል ቢሆንም ይህንን ጉዳይ በሰከነና በሰለጠነ መልክ እናደርገዋለን፣ ምክንያቱም ይህ ድርጊት የጦርነት ሁኔታ አይደለምና፡፡ እንደዚህ ያለው ሁኔታ ተቀባይነት ሊኖረው የሚችለው አገሮች በጦርነት  ላይ ሲሆኑ ብቻ ነው፣ ህዝብም በፈጠነ መልኩ ነገሩን ሊረዳው ይችላል፣ ነገር ግን በሰላማዊ ሁኔታ ሊሆን አይችልም፡፡
…በመሆኑም በዚህ መልክ በመጀመሬ አዝናለሁ፣ ይህ ሁኔታ እስከ አሁን ድረስ እየቆጠቆጠኝ የቆየ ጉዳይ ስለሆነ ነው፡፡
በእርግጥ በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ የአጭርና የረዥም ጊዜ መፍትሄ በማስቀመጥ ችግሮቹን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት ጥረት ስናደርግ ቆይተናል፣ ምክንያቱም ችግሮቹ ስር የሰደዱና ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መወገድ ያለባቸው በመሆናቸው ነው፡፡ እንደምታውቁት ኢትዮጵያ እያደገችና ባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ እድገት ምጣኔ እያስመዘገበች ነው፣ በዚህም አካሄድ ከጨለማው ዋሻ የውስጥ ጉዞ በኋላ ከጫፍ ላይ ብርሀን ይታየኛል፣ እና ይህንን ያለጥርጥር ተግባራዊ እናደርገዋለን፣ በዚህም ጥረታችን ድህነትን ተረት እናደርጋለን፡፡ በትክክለኛው መንገድ ላይ ነን፣ ሆኖም ግን ዓለም አቀፋዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ እምነቴ የጸና ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ይሳካል ብለን አንጠብቅም፡፡
ነገሩን ለማታውቁት አንድ ነገር ላካፍላችሁ እፈልጋለሁ፡፡ ነብዩ መሀመድ ታላቁን የእስልምና እምነት አስተምህሮቱን ሀ ብሎ ሲጀምር በደረሰበት መሳደድ ምክንያት ደቀመዝሙሮቹን/ተከታዮቹን ወደ ኢትዮጵያ ነበር የላከው… ስለዚህ አዝናለሁ፣ ንግግሬንም እዚህ ላይ አቆማለሁ…ሆኖም ግን የሚሰማኝን ስሜት ሁሉ በዝርዝር በመግለጼ፣ ያለፉት 10 ቀናት በህይወቴ ካየኋቸው ነገሮች ሁሉ እንዴት መራር እንደነበሩና ይከሰታሉ ብለን የማንጠብቃቸው አስገራሚ ነገሮች እየሆኑ በማየቴ እዚህ በመካከላችሁ በመገኘት ለእናንተ ሀሳቤን በማካፈሌ ደስታ ይሰማኛል…::
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ በሳውዲ አረቢያ መንግስት አየተፈጸመ ያለውን አስደንጋጭ የሰብአዊ መብት ረገጣ ወንጀል በማስመልከት የኢትዮጵያ “ቁንጮ የዲፕሎማት ሰው” እንደዚህ ያለ ተያያዥነት የሌለው፣ የተበታተነ፣ ዝብርቅርቅ ያለ እና እጅ እግር የሌለው ትንታኔ እና ገለጻ ሲያቀርቡ ስሰማ እጅጉን ነው ያዘንኩት፡፡ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ከወባ ትንኝ ተመራማሪነትና ከመቅጽበት ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት በተቀየሩ ግለሰብ የአፍ ካራቴ ዥዋዥዌ ልምምድ መቀለጃ ሆነ! ማንም ሊያደርገው እንደሚችለው የአድሃኖምን ቅጥ አምባሩ የጠፋ ንግግር መሰረት በማድረግ የሚከተሉትን ጭብጦች መመርመር ተገቢ ይሆናል፡፡
1. አድሃኖም እንዲህ አሉ “…በቃላት ሊገለጽ በማይችል መልኩ በኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ የሳውዲ አረቢያ መንግስት ያደረሰውን ሰቆቃ ሲያስታውሱ “እስከ አሁን ድረስ ነገሩ እየቆጠቆጣቸው“ እና አሁንም ድረስ “እንዳዘኑ“ እና የሳውዲ አረቢያ መንግስት በኢትዮጵያውያት ሴቶች ላይ በሚፈጽመው ደባ ምክንያት ሰብአዊ መብታቸው እየተረገጠ ያሉ ሴቶች እገዛ ለማግኘት በሚያሰሙት ጩኸት “ስሜታቸው እንደተጎዳ“ ተናግረዋል፡፡ ይኸ “ታላቁ የዘመኑ ውሸት!“ ሊባል ይችላል፡፡
ምናልባትም አድሃኖም በእንግሊዝኛ ቃላት መካከል ያለውን ጥቃቅን ልዩነት ማስተዋል ባለመቻላቸው በተለይም ቀጥተኛ ያልሆነውን የአነጋገር ዘየ/colloquialism ተከትለው ይሆናል በማለት አስተያየት መስጠት ይቻል ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን እንደ ቁንጮ የዲፕሎማት ሰውነታቸው ለአላዋቂነት የቃላት አጠቃቀሞቻቸው ይቅርታ ሊደረግላቸው አይገባም (በእርግጥ የቃላት እና የሀረጎች አመራረጣቸው አመለካከታቸውንና ስሜታቸውን የሚገልጹ ቢሆንም)፡፡ በኢትዮጵያውያን/ት ላይ በሳውዲ አረቢያ መንግስት እየተደረገ ያለው ግፍ “እስከ አሁን ድረስ ነገሩ እየቆጠቆጣቸው“ እንደሆነ የሚገልጸው አባባል ተጎጂ ኢትዮጵያውያን/ት በሳውዲ አረቢያ ያሉበት ሁኔታ የንዴት ምንጭ እንደሆናቸውና ጥቂት እንዳሳሰባቸውም ጠቋሚ ነው፡፡ ይህ ትልቅ ጉዳይ አይደለም እንደማለት አነጋገር ነው ፡፡ በዓለም ላይ የየትኛውም አገር የዲፕሎማሲ ቁንጮ የሆነ ሰው በዜጎቹ ላይ ኢሰብአዊና ኃላፊነት የጎደለው አያያዝ መደረጉን አስመልከቶ “እስከ አሁን ድረስ ነገሩ እየቆጠቆጠው” መሆኑን ለሌላ አገር ሰው ሲናገር አልተሰማም፣ አልታየምም፡፡
አድሃኖም በውል ያላጤኑት ቢሆንም ቃላት በዓለም አቀፍ የዲፖሎማሲው ቋንቋ ትልቅ ትርጉም አላቸው፣ ቃላት የዲፕሎማቶች ዓላማ ማስፈጸሚያ መሰረታዊ ሀብቶች ናቸው፡፡ የዲፕሎማቲክ ሰዎች እነርሱ በመረጧቸው ቃላትና የቃላት አጠቃቀም ዓለም እንዲቆምና እንዲሄድ የማድረግ ወይም አንዳንድ ጊዜም ሆን ብለው ለትርጉም ልቅ የሆኑ ወይም ደግሞ ውሱን የሆኑ ቃላትን በመጠቀም ዓላማቸውን ለማሳካት የሚሄዱበት ዘዴ ነው፡፡ የዲፕሎማቶች ቃላት ግልጽና ድብቅ ትርጉም ባላቸው መልዕክቶች የተሽሞነሞኑ እና ድብቅ ዓላማን ለማሳካት የተዘየዱ ማስፈጸሚያ መሳሪያዎች ናቸው፡፡ በሰዋስዋዊው የቃላት አመሰራረትና በሚሰጡት ትርጉም ጥንቁቅነት በዲፕሎማሲው ቋንቋ ቃላት ሰላምን ያሰፍናሉ፣ ጦርነትን ያውጃሉ፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ የዲፕሎማቶች ቃላት የዲፕሎማቶችን ግላዊ የሀዘን ስሜትና የስሜታቸውን መጎዳት ብቻ የሚገልጹ ሳይሆን ከዚህ በተጨማሪ የዲፕሎማቶቹን የሞራል ስብእና፣ የስቅይቱን ጥልቀትና የሀገራቸውን ህዝቦች ስሜት ሊያንጸባርቅ ይገባል፡፡
አድሃኖም በሳውዲ አረቢያ ያሉ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ሁኔታ “እስከ አሁን ድረስ ነገሩ እየቆጠቆጣቸው“ እንደሆነ ሲገልጹ ለሳውዲ አረቢያ መንግስት አደገኛ የሆነ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ እንዲህም ብለው እየነገሯቸው ነው፣ አዲሱ የይስሙላው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ የዓለም አቀፉን የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ለማውገዝ በአፍሪካ ህብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተገኝተው የተናገሩትን በመዋስ “የዘር አደን“ በኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሰራተኛ ዜጎች ላይ በሳውዲ አረቢያ ፖሊሶችና ጋጠወጦች በየመንገዱ እየተደረገ ያለውን ሁከትና ትርምስ አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡ ተገቢ የዲፕሎማሲ ንግግር ከተደረገ ይህንን አደገኛ ሁኔታ  እንዲቀንስ ያደርገዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በሳውዲ አረቢያ እየተካሄደ ያለው ኢትዮጵያውያንን/ትን የማዋረድና ኢሰብአዊ የሆነ ድርጊት የመፈጸም ሁኔታ ትልቅና በጣም ትልቅ የሆነ አገራዊ ጉዳይ ነው፡፡ በግሌ ለምሳሌ በዋና የስራ ሰዓት ጊዜ የሚይዝ የትራፊክ መኪና መጨናነቅ የንዴት ደረጃየን ከፍ ያደርገዋል፣ የተሰጣቸውን የቤት ስራ ሳይሰሩ በሚመጡ ተማሪዎቼ ላይ የሚኖረኝ ንዴት ከልኩ ያለፈ ነው:: ሳውዲዎች በኢትዮጵያውያን/ት ላይ እየፈጸሙት ያለው ግፍ ግን እንድናደድ ብቻ አላደረገኝም፣ ደሜ እንዲፈላ ጭምር አደረገኝ እንጅ፡፡ የሳውዲ አረቢያ ፖሊሶች በኢትዮጵየውያን/ት ላይ ሲፈጽሙት የነበረውን አረመኒያዊና ኢሰብአዊ የሆነ ድርጊት ስመለከት እሳት ነበልባል ሆኛለሁ፡፡ የሳውዲ አረቢያ ወሮበሎችና ጋጠወጦች በኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ ሲፈጽሙት የነበረውን አረመኒያዊና ጭካኔ የተሞላበት የሰብአዊ መብት ረገጣ ስመለከት በንዴት ድብን ብዬ አራሴን አስከ መሳት ደርሼ ነበር፡፡ በኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሰራተኞች ላይ በሳውዲ አረቢያ ወሮብሎችና ጋጠወጦች እየተደረገ ያለውን ኢሰብአዊና ከህግ አግባብ ውጭ እየተደረገ ያለውን ጀብደኝነት የሳውዲ ገዥው አካል እያየ ጆሮዳባ ማለቱ የበለጠ እንድበሳጭና እራሴን እንድስት አድርጎኛል፡፡ የሳውዲ መንግስት ዓለም አቀፍ ሕግን በጠበቀ መልኩ በኢትዮጵያውያን ስደተኛ ሰራተኛ ዜጎች መብት አያያዝ ላይ ምንም ነገር ባለማድረጉ በጣም ተበሳጭቻለሁ፣ አማርሪያለሁም፡፡ ኢትዮጵያውያን/ት በሳውዲ አረቢያ እየተፈጸመባቸው ያለው ግፍና መከራ አድሃኖምን ብዙም ያሳሰባቸውና ያስጨነቃቸው አይመስልም፡፡
በዓለም አቀፋዊ የዲፕሎማሲ ቋንቋ መርህ መሰረት ጠንካራና ፊትለፊት በመግጠም የሚደረግ እና አስታራቂና ዲፕሎማሲያዊ በሆነ ለስለስ ባለ ቋንቋ ለመጠቀም የራሱ ጊዜ አለው፡፡ በእውነቱ ይህ ታላቅ ሀገራዊ ውድቀት ነው፣ አድሃኖም በሁለቱ መካከል ያለውን ልዩነት በውል የተገነዘቡት አይመስለኝም፡፡
2. ሳውዲ አረቢያዎች በኢትዮጵያውያን/ት ላይ እንዲህ በፈጣን መልኩ እየፈጸሙ ያሉት ከአገር የማባረርና የማስወጣት ሁኔታ “አንድ አገር በጦርነት በወደቀችበት ጊዜ የተደረገ ቢሆን ኖር ተቀባይነት ሊኖረው ህዝብም ሊረዳው ይችል ነበር” ብለዋል አድሃኖም፡፡ ከዚህ አንጻር አድሃኖም ያልተገነዘቧቸው በርካታ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች፣ በጣም መሰረታዊ የሆኑ መርሆዎችና ህጎች መኖራቸውን ያሳያል፡፡ ከጦርነት ጋር በተያያዘ መልኩ ዜጎችን ከሀገር የማባረሩ ሁኔታን አስመልክቶ ያሉትን ህጎችና ልምዶች አንዳንድ ጊዜም የዘር ማጽዳት ድርጊቶች እንደሚፈጸሙ አድሃኖም የተገነዘቡ አለመሆኑን ይህ ሁኔታ በግልጽ ያመላክታል፡፡ እ.ኤ.አ 1990ዎቹ የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ገደማ በሄርዞጎቪና እና ቦሲኒያ መካከል በተደረገው ጦርነት በርካታ የቦሲኒያ እስልምና እምነት ተከታዮች፣ ክሮሽያዎች፣ ሰርቦችና ቦሲኒያዎች ከትውልድ ቦታቸው የተቀነባበረ የማባረር/የማስወጣት ስልት በመጠቀም ተግባራዊ ተደርጎባቸዋል፡፡ ያ የጦር ወንጀለኝነት ነው፡፡ ይኸ እንዲሁ “ህዝብ በቀላሉ ሊረዳው የሚችል” ጉዳይ አይደለም አድሃኖም አንዳሉት፡፡ በጦርነት ጊዜ በኃይልና በማስገድደ ከአገር የማስወጣት አስፈላጊነት ለህዝቡ ደህንነት ሲባል በሚጠበቁ ሰዎች ወይም በጦር መሪዎች ላይ የሚፈጸም መሆኑን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በ1949 የጸደቀው ስምምነት (IV) በጦርነት ጊዜ የሲቪል ሰዎችን ለመከላከል የተዘጋጀው ሰነድ በግልጽ ያሳያል፡፡ የስደተኞችን ጉዳይ አስመልክቶ በ1951 ስምምነት መሰረት በ1967 የስደተኞችን ሁኔታ አስመልክቶ የተዘጋጀው ፕሮቶከል እንዲሁም በአንቀጽ 3 በ1984 ማሰቃየትን በተመለከተ የተዘጋጀውን ስምምነት መሰረት በማድረግ ኢትዮጵያውያን/ት ስደተኞች ከማንኛውም ህገወጥ ማባረር/ማስወጣት ድርጊት መጠበቅ እንዳለባቸው በግልጽ ያሳያሉ፡፡ በጣም መሰረታዊ በሚባሉ የዓለም አቀፍ ህጎች፣ ደንቦችና መርሆዎች አንጻር አድሃኖም ያላቸው ግንዛቤ ሲመዘን በጣም አናሳ ሆኖ መገኘቱን ስናጤን እንደ ሀገር አሳሳቢ ሀገራዊ ኪሳራ መሆኑን ያሳያል፡፡
3. በአሁኑ ጊዜ በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ ለሚፈጸመው ሰቆቃና አንገብጋቢ ችግር መፍትሄው ዜጎቹ ከዚያ ሀገር የሚወጡበትን ስራ ማፋጠን እንደሆነ አድሃኖም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን/ት ስደተኞች ላይ የሚፈጸመውን የኃይል እርምጃ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ግድያና ማሰቃየት ማስቆም ጊዜ የማይሰጠው አጣዳፊ፣ ወሳኝ፣ አንገብጋቢ እና ክብደት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ በእርግጥ አድሃኖም ይህንን ጉዳይ በሚመለከት እንደሚከተለው አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ “በእርግጥ ችግሩን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት የረዥምና የአጭር ጊዜ መፍትሄዎችን በመንደፍ ጥረት ስናደርግ ቆይተናል፣ ምክንያቱም እነዚህ ችግሮች ለብዙ ጊዜ የቆዩና ስር የሰደዱ በመሆናቸው ነው“ በማለት አስተያየታቸውን ቋጭተዋል፡፡ እርግጥ ነው የረዥምና የአጭር ጊዜ መፍትሄዎች ሊቆዩ ወይም ጊዜ ሊወስዱ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በሳውዲ አረቢያ ፖሊሶች፣ ወሮበሎች እና ህገወጦች በየዕለቱ እየተፈጸሙ ያሉ የውርደት ሰራዎች፣ ህገወጥ አያያዞች፣ ፍትህአልባነት እና ወንጀሎች በእንዲህ ያለ ሁኔታ ሊቆዩ በፍፁም አይችሉም፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ እየተፈጸመ ያለው መጠነሰፊ ኪሳራ ነው፡፡ ስቅይቱን በፍጥነት ለማስቆም አድሃኖም ምንም ዓይነት ሀሳብ የሌላቸው እና መፍትሄዎችን ያላመላከቱ በመሆኑ ይህ አንገብጋቢ አገራዊ ኪሳራ ነው፡፡
አድሃኖም እንዲህ ይላሉ፣ በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ትዮጵያውያን/ት ስደተኞች ላይ “እንዲህ ያለ ድርጊት ይፈጸማል ብለን በምንም ታምር አልጠበቅንም“፣ እንዲህም ይላሉ ለእራሳቸው፣ “ሁሉም ነገር የሚያስደንቅ ነው“፣ በመቀጠልም እንዲህ ይላሉ፣ “የረዥምና የአጭር ጊዜ መፍትሄዎችን ለማምጣት ለብዙ ጊዜ ጥረት አድርገናል“፡፡ ይህ የተምታታ እና የተዘበራረቀ አባባል እርስ በእራሱ የሚጣረስ ብቻ አይደለም፣  ሊታመን በማይችል መልኩ አሳሳች መግለጫ እና የአድሃኖምን የዋህነትና የዲፕሎማሲ  እውቀት እጥረትና ችሎታ ማጣት የሚያሳይ መገለጫ እንጅ፣ በሳውዲ አረቢያ የኢትዮያውያንን/ትን ሁኔታ በሚመለከት “ሁሉም ነገር የሚያስደንቅ ነው“ የሚለው የአድሃኖም አባባል ተቀባይነት የሌለው ነገር ነው፡፡ ምክንያቱም እ.ኤ.አ በኤፕሪል 2013 አድሃኖምና የእርሳቸው ገዥው አካል  የሳውዲ አረቢያ ገዥ በሀገሩ ውስጥ በህገወጥ መንገድ ገብተው ምንም ዓይነት ህጋዊ ሰነድ ሳይኖራቸው በሀገሩ የግዛት ክልል ውስጥ የሚገኙ የውጭ አገር ሰራተኞችን ህጋዊ ለማድረግ ወይም ደግሞ ወደየመጡባቸው አገሮች እንዲመለሱ እና ህገወጥ ማባረር፣ እስራትና ስቅይትን ለማስቀረት በማለት ያስተላለፈውን ትዕዛዝ በሚገባ ያውቃሉ፡፡ የአድሃኖም ገዥው አካልም በተመሳሳይ መልኩ በሳውዲ አረቢያ ውስጥ ምንም ዓይነት ህጋዊነት  ሳይኖራቸው የሚሰሩና የሚኖሩ በርካታ ህገወጥ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን/ት እንዳሉ ከማመናቸውም በላይ አሳምረው ያውቃሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የሳውዲ ገዥ እ.ኤ.አ በጁላይ 2013 በሀገሩ ውስጥ የሚገኙትን ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸውና ምንም ሰነድ የሌላቸውን የውጭ አገር ዜጎች በማስመልከት ህጋዊ እንዲሆኑ ወይም ሀገር ለቀው እንዲወጡ አጽንኦ በመስጠት እ.ኤ.አ እስከ ኖቬምበር 2013 ድረስ ቀነ ገደብ መስጠቱን አድሃኖምና ገዥው አካላቸው በሚገባ ያውቁታል፡፡ ግና የአድሃኖም ገዥ አካል ከመስማት ባለፈ የአዋጁን እንደምታና ወደፊት በስደተኛ ዜጎቹ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን በአዎንታዊም ሆነ በአሉታዊ ጉኑ ሊያየው ስላልፈለገ የወደፊቱን ማቀድም አልቻለም፣ በቀጣይነት በገፍ ወደ ሳውዲ አረቢያ በሚጓዙ ዜጎች ላይ እንዲሁም በሳውዲ አረቢያ ፖሊስና ወሮበሎች በቀጣይነት ስለሚደረገው ጥቃት የሚሉት ነገር አልነበራቸውም፡፡ በአጭሩ ምንም ነገር ሳያደርጉ እጃቸውን አጣጥፈው በመቀመጥ ሲመለከቱ በከንቱ ሳይጠቀሙበት ጊዚያቸውን አባክነዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ እ.ኤ.አ በኖቬምበር 2013 በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ዜጎች ላይ ማህበራዊ ቀውስ ይደርሳል የሚለውን ሁኔታ እንዴት አድሃኖም በእርግጠኝነት መተንበይ አልቻሉም ይቻላል?
አድሃኖም ፈጣን የፖሊሲ እርምጃ ለመውሰድ ብቃት የሌላቸው ሰው መሆናቸውን የድርጊቶች ኩነት በተጨባጭ ያሳያል፡፡ እንደ “ቁንጮ የዲፕሎማሲ ሰው” ብዙ መማር ይጠበቅባቸዋል፣ እንዲሁም ወደፊት ሊከሰቱ በሚችሉ ነገሮች ላይ ትኩረት በመስጠት የነገሮችን የአመጣጥ ሁኔታና ችግሮችን አስቀድሞ በማየት ተጨባጭ መፍትሄ ለማምጣትና ወደተግባር ለመፈጸም የሚያስችል ብቃትን ሊጎናጸፉ ይገባል፡፡ ፈላስፋው ጎቴ የሚከተለውን ሲል እውነትም ትክክል ነበር፣ “ምንም  ድንቁርናን በተግባር ከማየት የበለጠ አስደንጋጭ ነገር የለም ብሏል።
አድሃኖም ያልተናገሩት ወይም ያላደረጉት፤
በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን የኃይል እርምጃ ለማስቆም የኢትዮጵያ ገዥው አካል ስላደረገው ሁኔታ አድሃኖም አንድም ያሉት ነገር የለም፣ ሆኖም ግን አገዛዙ ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ዘለቄታዊ መፍትሄ ለመስጠት የረዥም እና የአጭር ጊዜ መፍትሄዎችን ለማምጣት ብዙ ርቀት የተጓዘ መሆኑን ከመግለጽ ውጭ ተጨባጭነት ያለው እርምጃ አልታየም፡፡ በተጨባጭ እየሆነ ያለው ግን አድሃኖም እና ገዥው አካላቸው አትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ዜጎቻቸው በሳውዲ አረቢያ መንገዶች እንደ አውሬ እየታደኑ ኢሰብአዊ ድርጊት ሲፈጸምባቸው ከዳር ቆመው ጣቶቻቸውን በመቀሰር፣ ጭንቅላቶቻቸውን በመነቅነቅ ከመታዘብ ውጭ ሌላ መገለጫ የለውም፡፡ አድሃኖም በዜጎቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለውን የኃይል እርምጃ ለማስቆም ምንም  ጥረት አለማድረጋቸው ብቻ ሳይሆን ትንሿን ነገር ለዓም አቀፉ ማህብረሰብ በማሳወቅ በሳወዲ አረቢያ መንግስት ላይ ጫና እንዲደረግ እንኳን ሙከራ አላደረጉም፡፡ አድሃኖም ካልተናገሯቸው ወይም ካልፈጸሟቸው ጉዳዮች ውስጥ ከብዙ በጥቂቱ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡
በጠንካራ ቃላት የተዘጋጀ የውግዘት መግለጫ፤ አድሃኖም እንዲህ ብለዋል፣ “ገዥው አካል የሳውዲ አረቢያ መንግስት በግዛት ክልሉ ውስጥ ባሉ ስደተኛ ሰራተኛ ዜጎቻችን ላይ ያደረሰውን ጭካኔ የተሞላበት የኃይል እርምጃ እናወግዛለን፣ ይህ በምንም ዓይነት መልኩ ተቀባይነት የለውም፣ የሳውዲ መንግስት ለጉዳዩ አጽንኦ በመስጠት ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ እናደርጋለን፣ ዜጎቻችን ባሉበት በክብርና በመልካም ሁኔታ እንዲያዙ ሆኖ ዜጎቻችንን ወደ ሀገራቸው የምንወስድ መሆኑን እናሳውቃለን“ የሚል ነበር፡፡ “ተቀባይነት የለውም“ የሚለው ቋንቋ በሳውዲ አረቢያ ገዥ አካል፣ በፖሊስ ኃይሉ እና በወሮበሎች እየተፈጸመ ያለውን ዘገናኝ ጭካኔ፣ ለመናገር የሚዘገንን አረመኔነት፣ አስደንጋጭ ስቅይትና ወንጀለኝነት ለመግለጽ የሚጠቀሙበት የውግዘት ቃል ነው፡፡ እንደ አድሃኖም ግንዛቤ “ምርመራ“ ማለት የሳውዲ ገዥ ክፍል ከዚህ ከተፈጸመው ዘግናኝ ወንጀል አንጻር ጠንካራ እርምጃ ተወስዶ ማየት ነው፡፡
አድሃኖም “ተቀባይነት የለውም“ የሚለውን ቋንቋ በውል የተገነዘቡት አይመስልም፡፡ ይህ አባባል በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ የዲፕሎማሲ ሰዎች ምንም ነገር ሳይሉ አንድ ነገር እንዳሉ በማስመሰል የሚጠቀሙበት ባዶና መሰረት የለሽ ቃል ነው፡፡ ሁሉንም ነገር የሚል ትርጉም የያዘ ቃልም ነው…”ምንም ዓይነት ጠንቅ የለዉም አይኖረዉም ማለትም  ነው”:: እንደዚህ ነው እንግዲህ የዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ  ባህሪያት፡፡ አንድ መስመር ዓረፍተ ነገር ሁለት የማይገናኙ ዓላማዎችን ሊያስተላልፍ የሚችል መልዕክት ሊኖረው ይችላል፡፡ በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ አትዮጵያውያን/ት ላይ እየተፈጸመ ያለው ድርጊት “ተቀባይነት የለውም” የሚል መልዕክት ለሳውዲ አረቢያ አምባሳደር በማስተላለፍ አድሃኖም በጉዳዩ ላይ የይስሙላ ስራን በመስራት ጉዳዩ አስኪረጋጋ ድረስ መጠቀሚያ ያደርጉታል፣ ከዚያ በኋላ ግን ሁሉቱም ወገኖች ወደነበሩበት ግንኙነት ተመልሰው የመሞዳሞ ስራቸውን ይቀጥላሉ፡፡ ቃሉን በትክክል ለመግለጽ “ተቀባይነት የለውም” የሚለው ቃል ብልህነት የጎዳላቸው ፉከራና ባዶ ኳኳታ በሚያሰሙ ምንም ነገር እና አንድም ነገር የማያደርጉ ሰዎች መገለጫ ነው፡፡
የጥገኛውን ሀገር አምባሳደር በመክሰስ የብጥብጡን ሁኔታ እንዲረዳና በፖሊስና በህገወጦች የሚፈጸመውን ህገወጥ ድርጊት በአስቸኳይ እንዲያስቆም ማድረግ፡ አድሃኖም የሳውዲ አረቢያ አምባሳደርን በመክሰስ እንዲህ ብለዋቸዋል፣ “የሳውዲ አረቢያ መንግስት ህገወጥ ስደተኞችን ለማስወጣት የተከተለውን መርህና የሳውዲ አረቢያ ባለስልጣኖች በህገወጥ ስደተኞች ላይ የወሰዷቸውን እርምጃዎች በተመለከተ ኢትዮጵያ ታላቅ አክብሮት አላት፡፡ እንዲሁም በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ዜጎቻችን ላይ የተወሰደውን ህገወጥ አያያዝና ግድያ ታወግዛለች“ ይላል፡፡ ግን ሰው  ምን ዓይነት አሽከርነትና ጫማ ላሽነት ውሰጥ ይዘፈቃል?! ለዜጎቹ የሚቆረቆር በምድር ላይ የሚኖር ማንም አገር ቢሆን የራሱን ዜጎች የስቃይ ሰለባ ላደረገ ሌላ አገር በምንም ዓይነት መልኩ ቢሆን “ክብር አለው” የሚል ቃል አይተነፍስም፡፡ አድሃኖም በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ግንዛቤ ያላቸው አይመስልም፣ ምክንቱም ጉዳዩ ስለሳውዲ አረቢያ የግዛት ሉዓላዊነት ወይም ስለስደተኞች ፖሊሲ ጉዳይ አይደለም፣ ጉዳዩ የሳውዲ አረቢያ ገዥ አካል በኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሰራተኛ ዜጎች ላይ እየፈጸመ ስላለው የሰብአዊ መብት ረገጣ ተገቢውን እርምጃ የመውሰድና ያለመውሰድ ጉዳይ ነው፡፡
ከዚህም በላይ አደሃኖምም ሆነ ወይም ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው ከሳውዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር የሚኖርን ተቃውሞ በይፋ ለህዝብ አላሳወቁም፡፡ “የተቃውሞ ደብዳቤ” ወይም “የዲፕሎማቲክ ማስታወሻ” የአንድ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሌላው ጥፋት ለፈጸመው መንግስት ይቅርታ የማይደረግለትን የማይናወጥ አቋም በመግለጽ በይፋ ያሳውቃል፡፡ የተቃውሞ ደብዳቤው በምንም ዓይነት መልኩ ቢሆን “ተቀባይነት የለውም” የሚል ቃል አይጠቀምም፡፡ በጥቂቱም ቢሆን ስለ “”አሳሳቢ ጉዳዮች” እና ነገሮች መሻሻል ካላሳዩ ወደፊት “ጉዳት ሊያመጡ” የሚችሉ ጉዳዮችን በመጥቀስ ሊያሳውቅ ይችላል፡፡ አድሃኖም እንዳደረጉት እንቁጠረውና የተቃውሞ ደብዳቤ ለሳውዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጻፉ መሆኑን ለህዝብ ይፋ ሊያደርጉ ይገባል፡፡
በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ የተፈጸመውን የሰብአዊ መብት ረገጣ በሚመለከት የአፍሪካ ህብረት የውግዘት መግለጫ እንዲያወጣ ማድረግ፤ እ.ኤ.አ በ2015 አስከሚደረገው አገር አቀፍ ምርጫ ድረስ የአድሃኖምን ወንበር እያሟሟቁ የሚገኙት የይስሙላው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያ ደሳለኝ የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት የዝውውር ሊቀመንበር ናቸው፡፡ ኃይለማርያም ደሳለኝ የተባበሩት መንግስታት የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በአፍሪካ መሪዎች ላይ የዘር አደን ይፈጽማል በማለት የዘር አደናውን ለማስቆም የአፍሪካ መሪዎችን በማሰባሰብና በማስተባበር ቆላ ደጋ በማለት ጥረት ሲያደርጉ የቆዩ እና እንዲያውም የህብረቱ አባል አገራት የሮማ ስምምነተን በመጣስ ከአይሲሲ አባልነት እንዲወጡ በመሃንዲስነት ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸወ የሚታወስ ነው፡፡ ነገር ግን በመቶዎችና በሺዎች የሚቆጠሩ የአገራቸው ዜጎች በሳውዲ አረቢያ መንገዶች በፖሊሶች፣ በወሮበሎችና በህገወጦች “የዘር አደና” ጥቃት ሲፈጸምባቸው ትንፍሽ አላሉም፣ የጎመንዘር ቅንጣት የምታክል ድርጊት አልፈጸሙም፡፡ (በነገራችን ላይ ይህ ሁሉ ስቃይ በኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ ሲፈጸም የይስሙላው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በአገር ውስጥ ነበሩን? ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ “የዘር አደን” እየተፈጸመባቸው መሆኑን አስመልክቶ ቃል ትንፍሽ ሲሉ የሰማ ይኖራልን?)
አስቸኳይ ምርመር እንዲካሄድ ለተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) ኮሚሽነር ማሳወቅ፣ ዩኤንኤችሲአር/UNHCR በተባበሩት መንግስታት በተሰጠው ኃላፊነት መሰረት “ዓለም አቀፍ የስደተኞችን ጥበቃ ማድረግና በስደተኞች ችግር ላይ ውሳኔ የመስጠት እንዲሁም ስደተኞችን የመምራትና የማስተባበር ስራ” ያከናውናል፡፡ ስደተኞች አግባብ ባልሆነ መልክ ሲያዙና የሰብአዊ መብት ጥሰት ካለ የመመርመር ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡ አድሃኖም UNHCR ጉዳዩን እንዲመረምረው መጠየቃቸውን የገለጹበት ሁኔታ የለም፡፡ ምናልባትም ጥያቄ አቅርበው ከሆነ መጠየቃቸውን የሚገልጽ መረጃ አልቀረበም፡፡
እንዲህም ሆኖ UNHCR ስደተኛ ሰራተኞችን ግጭት ከተከሰተበት ቦታ ወደ ሌላ ለማዘዋወር የሎጅሰቲክስ እርዳታ ብቃት አለው፡፡ ለምሳሌ ያህል እ.ኤ.አ በ2011 በሊቢያ ጸረ መንግስት አመጽ በተቀሰቀሰ ጊዜ UNHCR በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኛ ሰራተኞችን ከሊቢያ ወደ ጎረቤት አገሮች በማመላለስ የተቀላጠፈ ስራ ሰርቷል፡፡
ጉዳዩ በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ኮሚሽነር/UNHCR እና በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ጽ/ቤት/OHCHR ቀርቦ እንዲጣራ ቅሬታን ማስመዝገብ፤ ከOHCHR ዋና ዋና ተግባራት መካከል “የከፋ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ማጣራት” እና “የሰብአዊ መብት ጥበቃ ስራዎችን ማከናወን” ናቸው፡፡ የማጣራት ስራውን እንዲሰራ የሳውዲ ገዥ አካልን ከመጠየቅ ይልቅ አድሃኖም እንዲያጣሩትና ጣልቃ እንዲገቡ UNHCR እና OHCHRን መጠየቅ ነበረባቸው፡፡
የኢትዮጵያ ዜጎች ከሳውዲ አረቢያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ እንዲያደርጉ መፍቀድ፤ ኢትዮጵያውያን/ት በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ላይ በተፈጸሙባቸው እና እየተፈጸሙባቸው ባሉት የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ምክንያት ተዋርደዋል፣ ሀፍረትም ደርሶባቸዋል፡፡ አድሃኖም በኢትዮጵያ ጥገኝነት እንዲጠይቁ ነብዩ መሀመድ ተከታዮቹን ወደ ኢትዮጵያ ልኮ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ በአንድ ወቅት ጥገኘነት የሚጠየቅባት ምቾትና እርዳታ የሚደረግባት ቅዱስ ቦታ ነበረች፡፡ ኒልሰን ማንዴላና ሌሎች የአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ ፓርቲ አመራሮች እ.ኤ.አ በ1962 ስልጠና ለመውሰድ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ነበር፡፡ በአጼ ኃይለ ስላሴ ልዩ ትዕዛዝ መሰረት ኒልሰን ማንዴላ የኢትዮጵያ ፓስፖርት እንዲሰጣቸው ተደርጎ ያለምንም ችግር ዓለምን ሲዞሩ ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ኢትዮጵያውያን/ት በዓለም ላይ የሚከበሩና የሚሞገሱ ነበሩ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ደካሞችና በባርነት የሚገዙ ሆነዋል፡፡ ያሰቡትን በመናገራቸው ይደበደባሉ፣ ይታሰራሉ፡፡ አዲስ አበባ በሚገኘው የሳውዲ አረቢያ አምባሳደር ፊት ለፊት በመገኘት ተቃውሟቸውን በሰላማዊ መንገድ ለማሰማት ሲሞክሩ የሳውዲ አረቢያ ፖሊስ በሀገሩ ኢትዮጵያውያንን/ትን ባስተናገደበት መጥፎ አያያዝ ሞዴልነት በተመሳሳይ መልኩም በአዲስ አበባ እንዲደረግ ሆኗል፡፡ ተዋርደዋል፣ ርህራሄ በጎደለው መልኩ ተደብድበዋል፣ በቁጥጥር ስርም ውለዋል፡፡ የገዥው አካል አፈቀላጤ የሆነው ሽመልስ ከማል ገዥው አካል በሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፈኞች ላይ እርምጃ መውሰድ ይገባዋል ብሏል፣ ምክንያቱም ይላል፣ “አብዛኞቹ ሰላማዊ ሰልፍ አድራጊዎች በኢትዮጵያና በሳውዲ አረቢያ መካከል ጸንቶ የቆየውን ጠንካራ ግንኙነት የሚያበላሽና ጸረ አረብ የሆኑ መልዕክቶችን የያዙ በመሀናቸው ነው::
“ማንም ቢሆን ከሚቀርበው ጓደኛው ጋር የመስታወት ላይ ጠብ ያደርጋል የሚል ግምት የለኝም፡፡ አድሃኖምና ገዥው አካል እንዲያስታውሱት የምፈልገው ነገር…”ለመበሳጨት ዘገምተኛ የሆነውን እሱን ተጠንቀቁ፣ ለመምጣት ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ፣ ከመጣ ደግሞ ኃይለኛው እርሱ እንደሆነ እና ለብዙ ጊዜ የሚቆይ ነው፡፡ የተዋረደ ትዕግስተኝነት ወደ ቁጣ ይቀየራል::”
የአጣዳፊ ሁኔታውን ለመስራት ልዩ ግብረ ኃይል አያስፈልግምን? ኢትዮጵያ በሳውዲ አረቢያው እንደደረሰባት ዓይነት ኪሳራ በሚደርስባት ጊዜ ለዜጎቹ የሚያስብ ገዥ አካል ተገቢውን ምላሽ ለመስጠትና ለማስተባበር የአስቸኳይ ጊዜ ማስፈጸሚያ ግብረ ኃይል ያቋቁማል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ቡድኖች ተመላሽ ስደተኛ ወገናቸውን ለማገዝ  እንቅስቃሴ ያደርጋሉ፡፡ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች እገዛ እንዲያደርጉ ይጠየቃሉ፡፡ አነዚህ አልተደረጉም:: በሳውዲ አረቢያ ያለው የኢትዮጵያውያን/ት ሁኔታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያልፋል፣ ስለዚህም ብዙ ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለሳውዲ አረቢያ ኢንቨስተሮች በመስጠት የተለመደው ቢዝነስ በተለመደው ሁኔታ ይቀጥላል የሚል ስሌት በአድሃኖምና በገዥው አካል አቅዋም የተያዘ መሆኑም ይገልጣል፡፡
አድሃኖም ወደፊት አንደሚሉ ፤
አድሃኖምና ገዥው አካል ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ለሚመለሱትና ለሚቋቋሙበት የተመደበውን 50 ሚሊዮን ብር ተመድቧል ብለዋል:: ይህ ከባልዲ ውኃ አንዷ ጠብታ ናት፡፡ ይህም ገንዘብ ወደ 2 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ይሆናል፡፡ በዚህች በጣም ትንሽ በሆነች 2 ሚሊዮን ዶላር 200 ሺ ወይም ከዚያ በላይ የሚሆኑ ከስደት ተመላሾችን ለማስፈር፣ ለማዘዋወርና ለማጓጓዝ የሚያስችል አይደለም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ገዥው አካል ይህን ያህል ገንዘብ ለእነዚህ ተግባራት ተብሎ የተያዘ ለመሆኑ ማረጋገጫ የለም፡፡ እ.ኤ.አ ጁላይ 2013 የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ባለሙያዎች ተልዕኮ መግለጫ መሰረት ኢትዮጵያ ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ ለምታስገባቸው ሸቀጦችና አገልግሎቶች ለሶስት ወራት ብቻ ሊያቆይ የሚያስችል የውጭ ምንዛሬ ክምችት እንዳላት ይፋ አድርጓል፡፡
አድሃኖምና ገዥው አካል ብዙም ሳይቆዩ ተመላሽ ዜጎቸን ለማጓጓዝና ለማቋቋም የልመና ኮሮጃቸዉን አንጠልጥለው ወደ ዓለም አቀፉ የመንገድ ልመና መውጣቸው የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡ በእርግጥ የሚገኘውን እርዳታ ለመቀራመት የሚችሉ የራሳቸውን አትራፊ ያልሆኑ ድርጅቶችን አስቀድመው ያቋቁማሉ፡፡ አድሃኖም ይለምናሉ፣ እንዲህ በማለት፣ “ከሳውዲ አረቢያ ለሚመለሱ ስደተኛ ዜጎች ገንዘብ በጣም ብዙ ገንዘብ እንፈልጋለን፡፡“ ጋሻጃግሪዎቻቸው በህዳሴው ግድብ ወይም በሌላ መልክ እንደሚጠሩት እንዳደረጉት ሁሉ በዓለም ዙሪያ በመሰማራት ኑስ ሳንቲም ሳይቀር ልመናቸውን ያጧጡፋሉ፡፡ ለገዥው አካል መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጀቶች ይህ ሁኔታ ንፋስ አመጣሽ ዘረፋ ነው፡፡ በልመናው በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር እንደሚገኝ በመገመት እነዚህ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እጃቸውን በማሻሸት እና ለሀጫቸዉን በማንጠባጠብ ሰፍ ብለው ይጠባበቃሉ፡፡ ግን በልመና ብዙ ዕርዳታ ላያገኙ ይችላሉ፡፡ ለዚህም ነው በሳውዲ አረቢያ መንገዶች ላይ እጃቸውን በመዘርጋት ምጽዋት፣ ቢለምኑ አልደነቅም ያልኩት፡፡
ለኢትዮያችን አለቅሳለሁ፣ ለውዲቷ አገሬ! ግን “ከዋሻው መጨረሻ ብርሃን አለ“
አድሃኖም እንዲህ አሉ፣ “ከዋሻው መጨረሻ ብርሃን አለ፣ እና ይህን እውን እንደምናደርገው እናውቃለን፣ እና ድህነትን ተረት እንደምናደርገው ጥርጥር የለንም”፡፡ እኔ ደግሞ እላለሁ በኢትዮጵያ ምድር ውስጥ ከዘውዳዊነትና ከአምባገነንነት ዋሻ መጨረሻ ብርሃን አለ፡፡ ከአድማስ ባሻገር አዲስ ቀን አለ፡፡ መደጋገፍ አለብን፣ እጅ ለእጅ ተያይዘን ሁለት አስርት ዓመታት እና ከዚያ በላይ ከዘለቀው የጭቆና እና የመሰረታዊ የሰብአዊ መብቶች እጦት ዋሻ ውስጥ ተጉዘን በድል አድራጊነት መውጣት አለብን፡፡
በሳውዲ አረቢያ ያሉ ኢትዮጵያውያን/ት ያሉበትን አስከፊ ሁኔታ አስመልክቶ የተዘጋጁትን የእኔን ትንታኔዎች ያነበበ ሁሉ እኔ በጣም ህግ አጥባቂና ሲበዛ ትንታኔ ሰጭ እንደሆንኩ ሊናገር ይችላል፡፡ እንዲያውም ታላቁን የሰው ልጅ ሰቆቃ “ለመፈላሰፊያ ትምህርታዊ ክህሎት” አውሎታል ብለው ሊከሱኝ ይችላሉ፡፡ ይህን ሊሉ ይችላሉ ምክንያቱም ለዚህች ተወዳጅ አገሬ ምን ያህል እንዳለቀስኩና ምን ያህል ተስፋ እንደቆረጥኩ ስለማያውቁ ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ1948 በዚሁ ዓመት አፓርታይድ በአፍሪካ ህግ ሆነ፣ አላን ፓቶን እንዲህ ሲል ጻፈ…”ውዷ ሀገሬ አልቅሽ“… እና በደቡብ አፍሪካ ዕጣ ፈንታ ላይ ያለውን የታሟጠጠ ተስፋ ገለጸ፡፡ የእኔም በኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ላይ ያለኝ ተስፋ ፓቶን ካለው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ፓቶን ሲጽፍ፣
ለተገነጣጠለው ጎሳ፣ ለወደቀው ባህልና ህግ አልቅስ! አዎ! ለሞተው ሰውዬ ድምጽህን ከፍ በማድረግ አልቅስ፣ ፍቅሩን ላጣችው ሴትና ለልጆቹ አልቅስ፡፡ ለውድ ሀገርህ አልቅስ፣ እነዚህ ነገሮች በእራሳቸው የመጨረሻ አይደሉም፡፡ ፀሐይ በመሬት ላይ ብርሀኗን ትፈነጥቃለች፣ በተወዳጁ መሬት ሰው ባልተደሰተበት ላይ፡፡ የልቡን ፍርሃት ብቻ ያውቃል፡፡
አኔም በኢትዮጵያ “ለተበጣጠሰው ጎሳ” አለቅሳለሁ፡፡ ከሰውነት በታች ሆነው በሳውዲ አረቢያ ለሚሰቃዩት ወንድሞቸና እህቶቸ በዝምታ አለቅሳለሁ፡፡ በመካከለኛው ምስራቅ ለሚደፈሩት፣ ለሚደበደቡት እና በመስኮት ለሚወረወሩት፣ ከጣራ እና ከዛፍ ላይ ተሰቅለው ለሚሞቱትና በፈላ ውኃ ሰውነታቸውን ለሚጠበሱት እህቶቸ አለቅሳለሁ፡፡ በሳውዲ ሌባ ጭንቅላቱን ለሚበረቅሰው ወጣት አለቅሳለሁ፡፡ ነጻነት በማጣታቸው እና በሀገራቸው መብት እንደሌላቸው በመቆጠራቸው ምክንያት ሀገር ጥለው ለመሰደድ ለሚገደዱት ወጣት ወንዶች እና ሴቶች አለቅሳለሁ፡፡ ህይወታቸውን ለማሻሻል በማሰብ የየመንንና የሳውዲ አረቢያን በረሀዎች ሲያቋርጡ በሞት ለተለዩ ኢትዮጵያውያን አለቅሳለሁ፡፡ በየዕለቱ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሲኦሉ ሳውዲ አረቢያ ለሚበሩ ወጣት ኢትዮጵያውያት ቆነጃጅት አለቅሳለሁ፡፡
የ2005 ሀገራዊ ምርጫን ተከትሎ በኢትዮጵያ በየጎዳናው በግፍ ለተገደሉት ወጣት ወንዶችና ሴቶች፣ እንዲሁም አባቶች እና እናቶች አለቅሳለሁ፡፡ ለእህቴ ለርዕዮት ዓለሙ እና ለወንድሞች ለእስክንድር ነጋ፣ አንዷለም አራጌ፣ ውብሸት ታዬ፣ በቀለ ገርባ፣ አቡበከር አህመድ፣ እና በብዙ ሺዎች ለሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞች አለቅሳለሁ፡፡ መሪ በመምሰል በባዶ ልብስ ለተጀቦኑትና በሙሰኛ ሌቦች መዳፍ ስር ለወደቁት ኢትዮጵያውያን/ት አለቅሳለሁ፡፡
አዎ አለቅሳለሁ እናም አለቅሳለሁ፣ “ልቅሶዎቸ ያልተሳኩ ቢሆንም“ ለውዲቷ አገራችን አለቅሳለሁ፣ ግን እኮ ጩኸታችን ይሰማል፣ ደቡብ አፍሪካ ከአፓርታይድ የአምባገነንነት ዋሻ ወጥቷል፣ ኒልሰን ማንዴላም ቃል ገብተዋል…”በፍጹም በፍጹም እና በፍጹም ይህች የተዋበች መሬት ተመልሳ የአንዱ በአንዱ ላይ መጨቆኛ አትሆንም፣ ክብር የታጣባት የተዋረደች ዓለም አትሆንም“::
ኢትዮጵያውያን/ት እንደገና ክብራቸውን ይቀዳጃሉ፣ እና በአገር ውሰጥም ሆነ በውጭ የተከበሩ ይሆናሉ፡፡ “የዓለም ተዋራጂ” ሆነው አይቀጥሉም፡፡ እና በጥልቅ ከልብ አምናለሁ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች፣ እንደገና አናለቅስም፣ ሀሴትንም እናደርጋለን፡፡

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ 3ኛ ዓመት ተማሪዎች ሲጮኹ ዋሉ፤ ዲኑ ተማሪዎቹን “በዩኒቨርሲቲው በቀን ሦስቴ እየበላችሁ ጠገባችሁ” አሉ

November 27/2013

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ 3ኛ ዓመት ተማሪዎች ሲጮኹ ዋሉ፤ ዲኑ ተማሪዎቹን “በዩኒቨርሲቲው በቀን ሦስቴ እየበላችሁ ጠገባችሁ” አሉ
በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ 3ኛ ዓመት ተማሪ የሆኑ ተማሪዎች ከውጤት አሰጣጥ ጋር ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር በፈጠሩት አለመግባባት ሲጮኹ መዋላቸውን የዘ-ሐበሻ የባህርዳር ዘጋቢዎች ከስፍራው ዘግበዋል። እንደ ዘጋቢዎቻችን ገለጻ የ3ኛ ዓመት ተማሪዎቹ ጩኸታቸውን ሲያሰሙ ከዋሉ በኋላ የዩኒቨሲቲው ዲን ዶ/ር ባየልኝ ዳምጤ ሰብስበው ያነጋግሯቸው ቢሆንም፤ ዶ/ሩ ችግሩን ከማብረድ ይልቅ እሳት ለኩሰውበት ሄደዋል ሲሉ ተማሪዎቹ ለዘ-ሐበሻ ዘጋቢ ነግረውታል።

ዩኒቨርሲቲው አዲስ ባወጣው መመሪያ መሠረት በተማሪዎች ማርክ አሰጣጥ ላይ ከዚህ ቀደም 85 የነበረው ወደ 95 ያድጋል ባለው መሠረት ተማሪዎቹ ልክ እንደ 1ኛ እና 2ኛ ዓመት ተማሪዎች ማርክ ሊያዝልን ይገባል በሚል የዛሬው የባህርዳር ዩኒቨሲቱ ሁከት መፈጠሩን የገለጹት ዘጋቢዎቻችን፤ ይህን ተከትሎም በሃገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ፖለቲካ የሚመለከቱ መፈክሮችን ተማሪዎቹ ሲያሰሙና ሲጮኹ ከዋሉ በኋላ ዶ/ር ባየልኝ ዳምጠው ጠርተው አንጋግረዋቸዋል። ተማሪው ዶ/ር ባየልኝ ወደ ጠሩት ስብሰባ ሲገባ የተለያዩ መፈክሮችን እያሰማ ሲጮህ ነበር ያሉት ዘጋቢዎቻችን ዲኑ ስብሰባውን ሲመሩ የነበረው እንደተማረ ሰው አልነበረም የሚሉ አስተያየቶች ከ3ኛ ዓመት ተማሪዎቹ ተሰምቷል።

ዶ/ር ባየልኝ ተማሪውን ሰብስበው “በቤታችሁ በነበራችሁበት ጊዜ በቀን 2 ጊዜ የምትበሉ ተማሪዎች እዚህ ዩኒቨሲቲ ውስጥ በቀን 3 ጊዜ እየበላችሁ ጠገባችሁ፤ ይሄ ጥጋብ ነው ስለማርክ አሰጣጥ ጥያቄ ያስነሳችሁ” የሚል አንባገነናዊ ንግግር በመናገራቸው ተማሪው ቁጣውን እንዳሰማ የገለጹት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች “እኛ በችግረኛ ሃገር ላይ ሆነንና የትምህርት ጥራት በሌለበት መልኩ ያደጉ ሃገራት የትምህርት ፖሊሲ መሞከሪያ አንሆንም” በሚል የ3ኛ ዓመት ተማሪዎቹ ቁጣቸውን ገልጸዋል ብለዋል። ይህን ተከትሎም ጉዳዩ እኛንም ይመለከተናል በሚል የባርዳር ዩኒቨርሲቲ 1ኛ እና 2ኛ ዓመት ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት ተማሪዎቹን ጥያቄ መቀላቀላቸው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ዘ-ሐበሻ ወደ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ዲን ቢሮ ደውላ የነበረ ቢሆንም ዶ/ር ባየልኝ ዳምጤን ማግኘት አልቻለችም። በዩኒቨርሲቲው ውስጥ አሁንም ውጥረቱ እንዳለ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ገልጸዋል።

የግንቦት7 እና አክራሪ የእስልምና ሀይሎች በኢህአዴግ አባላት ስም ፓርላማውን በመቆጣጠር ኢህአዴግን ሊጎዱት ይችላል ሲሉ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ተናገሩ

November 26/2013
ህዳር ፲፯(አስ ሰባት )ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም ይህን የተናገሩት ” በክርስትና እና በእስልምና ሃይማኖት ሽፋን የሚካሄደው የፖለቲካ እንቅስቃሴ የመንግስት ቀጣዩ የምርጫ ፈተና” በሚል ርእስ ለኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ባቀረቡት ጽሁፍ ነው።
ኢሳት የሚኒስትሩን  ሙሉ ንግግር የያዘ ሰነድ የደረሰው ሲሆን፣ በሰነዱ ግርጌ ላይ ” ለመደበኛ አባላት የማይነገር፣ ለከፍተኛ አመራሮች ብቻ” የሚል ተጽፎበት ይታያል።  በዚህ ርእስ ስር ደግሞ ” ቀጣዩ የምክር ቤት አባላት ምርጫ የግንቦት ሰባት እና አክራሪ እስልምና ሀይሎችን የሚያስቀጥሉ አባላት ወንበሩ በኢህአዴግ አባላት ስም ሊነጠቅ ይችላል። ” ብሎአል። ሚኒስትሩ ለዚህ አስተሳሰባቸው የምርጫ 97ትን ሁኔታ እንደማጠቃሻ ተጠቅመዋል። ” የ97 የቅንጅት አሸናፊት አካሄድ ስልት ማለትም የተቃዋሚ አባላት ሁነው በህቡእ ተደራጅተው በኢህአዴግ የአባላትን ካርድ ሙሉ በሙሉ ፓርቲውን ሊጎዱት ይችላሉ” ሲሉ ሚኒስትሩ ጽፈዋል።
ሚኒስትሩ በዚህ ጽሁፋቸው፣ ቅንጅት በ97 ምርጫ ማሸነፉን እንዲሁም የኢህአዴግ አባላት ሆነው ለቅንጅት በውስጥ ይሰሩ የነበሩ ሰዎች እንደነበሩ ጠቅሰዋል። በክርስትና እና በእስልምና ሀይማኖት ሽፋን የሚካሄደውን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ሚኒሰትሩ በዝርዝር አቅርበዋል።
በክርስትና ሀይማኖት በኩል ” መንግስት በሃይማኖት አባቶች ሹመት ላይ እጁን ያስገባል፤ የዋልድባ ገዳም ተደፈረ፤ አልፎ አልፎ በአጋጣሚ ቤተክርስታያን ባለበት አካባቢ ከድርቅ ጋር ተያይዞ በሚነሳ ቃጠሎ ሆነ ተብሎ እንደተደረገ ማስወራት፤ ይህን የሚያግዝ የውጭ ሚዲያ መኖር ኢሳት በቀዳሚኒት ፣ የደርግ ስርዓት ደጋፊዎች የሆኑት ቪኦኤ በቀጣይነተወ የሚያራግቡት አካሄደ ጉዳዩን ትኩረት እንዲያገኝ ” ማድረጉን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
የሙስሊሙ እንቅስቃሴንም በተመለከተ ሚኒሰትሩ ሲገልጹ”  ከቅንጅት እስከ ህብረት፣ ከቪኦኤ እስከ ቲቪ አፍሪካ፣ ከጀርመን ድምጽ እስከ ቢላል ሬዲዮ፣ ከጅሃዳዊ ሀረካት እስከ ግንቦት ሰባት፣ ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች ዓለም አቀፍ እስከ መድረክ እስከ ስደተኛው ሲኖዶስ ያሉ ሀይሎች በተናጠልና በህብረት” ተሳትፈውበታል ብለዋል።
የሙስሊሙ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ፍጥነት በመዳከም ሂደት ውስጥ የገባው በቡድኑ ቀንደኛ መሪዎች ላይ ህጋዊ ስርአቱን ተከትሎ የእስራት እርምጃ ከተወሰደ በሁዋላ ነው ብለዋል።
በሃይማኖት ሽፋን የሚካሄዱ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ውለው አድረው እየተጋለጡና እየተዳከሙ መሄዳቸው ባይቀርም ባለፉት ሁለት ዓመታት ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን በሀይል ለመፈታተን ከሞከሩት የሁከት ሀይሎች ዋነኞቹ ነበሩ ማለት ይቻላል ብለዋል ሚኒሰትሩ።
“በሃይማኖት ስም የሚካሄደውን ንግድ ውጤታማ እንዲሆን በማድረግ ረገድ  የድህነት መንሰራፋትና የመልካም አስተዳደር  እጦት ወይም ጉድለት ተጠቃሽ ናቸው” የሚሉት ዶ/ር ሽፈራው በተለይ ከድህነትና ኋላቀርነት መውጫውን ትክክለኛ መንገድ የሚያመላክት መሪ ድርጅት በሌለበት ፣ በሃይማኖት ሽፋን የሚነግዱ የፖለቲካ ሀይሎች አንዱን በሌላው ላይ ማነሳሳት የፅድቅ መንገድ እንደሆነ አስመስለው በማቅረብ ዜጐችን ወደጥፋት ይመራሉ” ብለዋል።
መሪ ድርጅቱም ኖሮ በአመራርም ሆነ በአባላት ደረጃ በአንድ በኩል ከፀረ ድህነትና ኋላቀርነት ትግሉ ላይ ጽናትና ብቃት ያለው አመራር መስጠት ካልተቻለ፣ በሌላ በኩል ደግም የፓርቲና የመንግስት መሪዎች ስራቸውን ከየትኛውም ሃይማኖት ገለልተኛ በሆነ መንገድና ሁሉን ሃይማኖቶች እኩል በሚያስተናግድ አግባብ ካልፈፀሙ ይኸው ችግር ተባብሶ መቀጠሉ አይቀርም ሲሉ ዶ/ር ሽፈራው አስጠንቅቀዋል።
አሁንም ድህነትና ኋላቀርነት በመኖሩ፣ በፓርቲና በመንግስት አመራራችን የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ጉድለቶች በመኖራቸውና የእምነት ጉዳይ ለሚዛናዊ አስተሳሰብ ያለው ተጋላጭነት ዝቅተኛ በመሆኑ አልፎ አልፎ የተካረረ ፍጥጫ እያጋጠመ መሆኑንም ሚኒስተሩ በጽሁፋቸው አብራርተዋል።
ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም ለኢህአዴግ ባለስልጣናት ያቀረቡትን ሙሉ ጽሁፍ በድረገጻችን መመልከት የምትችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።
በክርስትና እና በእስልምና ሃይማኖት ሽፋን የሚካሄደው የፖለቲካ እንቅስቃሴ የመንግስት ቀጣዩ የምርጫ ፈተና
ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም
ህዳር 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባ
1. በክርስትና ሃይማኖት ሽፋን የሚካሄደው የፖለቲካ እንቅስቃሴና ቀጣይ አዝማሚያዎቹ፣
  በክርስትና ሃይማኖት ሽፋን የሚካሄደው እንቅስቃሴ በዋነኛነት ኢትዮጵያ የክርስትና ሃይማኖት የበላይነት ሊኖርባት ይገባል በሚል ኋላቀርና ዘመን የሻረው አስተሳሰብና ሀይል የሚመራ ነው፡፡
  በዚህ መሠረት ይህ ኋላቀር ሀይል መነሻና መድረሻውን የክርስትና ሃይማይማኖትን  የበላይነት አድርጐ ይህን ሊያረጋግጡልኝ ይችላሉ የሚላቸውን መፈክሮች ጐላ አድርጐ ያሰማል፡፡
  በዚህ ረገድ “ኢትዮጵያ የክርስትና ደሴት ነች”፣ “አንድ አገር አንድ ሃይማኖት” የሚሉ መፈክሮቹ የአስተሳሰቡን ጭብጥ የሚያሳዩ ናቸው፡፡
 በዚህ ሀይል አስተሳሰብ መሠረት አገራችን በርካታ ሃይማኖቶችን ያስተናገደችና በማስተናገድ ላይ የምትገኝ አገር መሆኗ ቀርቶ የክርስቲያን ደሴት ብቻ ተደርጋ ትቀርባለች፡፡
  እራሱ አንድ አገር አንድ ሃይማኖት የሚለው አስተሳሰብም በተመሳሳይ መልኩ በኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ሃይማኖት ብቻ እንዳለ ወይም ሊኖር እንደሚገባ የሚሰብክ ኋላቀር የፀረ እኩልነት አስተሳሰብ ነው፡፡
  እነዚህ ሀይሎች አንደንዶቹ የሃይማኖት ጉዳይ ህብረተሰቡን በቀላሉ ሊያደናግርልን ይችላል ብለው የሚያምኑ ተቃዋሚ የፖለቲካ ሀይሎች ሲሆኑ
  ከፊሎቹ ደግሞ ከሃይማኖት አኳያ የኦርቶዶክስ እምነት መንግስታዊ ሃይማኖት መሆኑ ቀርቶ ከሌሎች ሃይማኖቶች በእኩልነት የሚታይና የሚከበር መሆኑን ያልተቀበሉ በትላንቱ ዓለም የሚኖሩ ሀይሎች ናቸው፡፡
  የፖለቲካ ሀይሎቹ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የክርስትና ሀይማኖትን መጠለያ በማድረግ የተለያዩ ቀስቃሽና ስሜትን የሚኮረኩሩ የፈጠራ አጀንዳዎችን ለማራገብ የሚሞክሩ ናቸው፡፡
ለምሳሌ፡- መንግስት በሃይማኖት አባቶች ሹመት ላይ እጁን ያስገባል፤ የዋልድባ ገዳም ተደፈረ፤ አልፎ አልፎ በአጋጣሚ ቤተክርስታያን ባለበት አካባቢ ከድርቅ ጋር ተያይዞ በሚነሳ ቃጠሎ ሆነ ተብሎ እንደተደረገ ማስወራት፤ ይህን የሚያግዝ የውጭ ሚዲያ መኖር ኢሳት በቀዳሚኒት እና ቪኦኤ /የደርግ ስርዓት ደጋፊዎች/ የሚያራግቡት አካሄደ ጉዳዩን ትኩረት እንዲያገኝ አድርግውታል፡፡ ፤
  በራሳቸው ፖለቲካዊ መስፈርት የቤተ ክርስቲያኒቱን መሪዎችና ሀላፊዎች መሾምና መሻር የሚፈልጉ ተቃዋሚ ሀይሎች በተለይም ደግሞ በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚ ሀይሎች የራሳቸውን ሰው አዘጋጅተው ለማስመረጥ ብዙ ጥረት አድርገዋል፡፡
  በዛሬማ ሸለቆ አካባቢ የስኳር ልማቱ የሚካሄደው በጣም ዝቅተኛና ቆላ ላይ ሲሆን፤ የዋልድባ ገዳም መሬት ደግም በደጋና ወይናደጋ ቦታዎች ላይ የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሃቁ ይህ ሆኖ ሳለ በገዳሙና በስኳር ማሳው መካከል ያለውን ከፍተኛ የመልክዓምድር ልዩነት በቅርቡ ለማያውቁ የክርስትና ምዕመናን ሁሉ ገዳሙ ተደፈረ የሚለው ቃል እልህና የቁጣ ስሜት ይፈጥርባቸዋል ብሎ በማመን ሰፊ ዘመቻ ሲካሄድበት ከርሟል፡፡
  የዚህ ዘመቻ ፊታውራሪዎች በአሜሪካን ድምጽ ሬዲዮ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ የቀድሞ የኢህአፓዎችና የቅንጅት ትርፍራፊዎች ናቸው፡፡
 በአንድ ወቅት በምዕራብ ኢትዮጵያ ጅማ አካባቢ በኻዋርጃ ስም የሚታወቁ አክራሪዎች በክርስቲያኖች ላይ ያደረሱትን ግድያ መጠጊያ በማድረግ “ክርስቲያኖች እየተጨፈጨፉ ነው ስለዚህም አፀፋው ሊመለስ ይገባዋል” በሚል ቅኝት መንቀሳቀስ ጀምረው ነበር፡፡
 አልፎ አልፎ እንደምናየውም ከድርቅ ጋር በተያያዘ ምክንያት በሚነሳ ቃጠሎ አንድ ቤተ ክርስትያን ወይም ገዳም ባለበት አካባቢ በአጋጣሚ ቃጠሎ ከተነሳ ይህንኑ ሆን ተብሎና በክርስትና ላይ ጥቃት ለመፈፀም ሲባል እንደተደረገ አስመስሎ የማቅረብ፣
  እንዲሁም ለቤተ ክርስትያን መስሪያ ተብሎ ባልተሰጠ ቦታ የቤተክርስትያን ግንባታ መጀመርና ህገ ወጥ ግንባታ እንዲቆም ሲጠየቅ በክርስትና ሃይማኖት ላይ ተዘመተ ብሎ የእኩልነት ጥያቄ ማንሳት አዘውትረው የሚጠቀሙባቸው ስልቶች ናቸው፡፡
 ከመንግስትና ድርጅት ሀላፊዎች ውጭ ባሉ የተሳሳተ አስተሳሰብ ባላቸው ዜጐች የሚራመዱት እነዚህ ኋላቀርና ፀረ እኩልነት አስተሳሰቦች እንደተጠበቁ ሆኖ ሃይማኖታዊ አዝማሚያ ባልተለያቸውና በመንግስታዊ ሀፊነትና በእምነታቸው መካከል ያለውን ልዩነት በውል መገንዘብ የተሳናቸው ሀላፊዎች ደግሞ የየራሳቸውን ስህተት ሲሰሩ ማስተዋል የተለመደ ነው፡፡
 በአጠቃላይ ሲታይ ወቅታዊና ለፖለቲካ ንግድ የሚያመች እንዲህ አይነት አጀንዳ ሲፈጠር አጋጣሚውን ለመጠቀም ምን ጊዜም ወደ ኋላ አይሉም፡፡
 በክርስትና ስምና ሽፋን የሚነግዱ ፖለቲከኞች አነዚህን የመሳሰሉ መሠረተ ቢስ አጀንዳዎችን በመቅረጽና በማራገብ ክርስትና ሃይማኖት ተከብሮና ተቻችሎ በሚኖርባት አዲሲቷ ኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ክብርና ሞገሱን የተገፈፈ አስመስለው ያቀርባሉ፡፡
  ለእምነቱ ክብርና ሞገስ የሌላቸው ራሳቸው በሃይማኖቱ ሽፋን የፖለቲካ ንግድ የሚያካሂዱት
  ሀይሎች መሆናቸውን ደብቀው መንግስትና ስርዓቱን በመሰረተ ቢስ ወንጀል ይከሳሉ፡፡
2. በእስልምና ሀይማኖት ሽፋን የሚካሄደው የፖለቲካ እንቅስቃሴና ቀጣይ አዝማሚያዎቹ፤ 
በክርስትና ሀይማኖት ሽፋን ከሚካሄደው እንቅስቃሴ ባልተናነሰ ይልቁንም አልፎ አልፎ በራሱ ባህሪ ከዚያም በከፋ ሁኔታ በእስልምና ሀይማኖት ስም ሚካሄድ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የሚታይ መሆኑ ይታወቃል፡፡
  እንቅስቃሴው ውስጥ ውስጡን ሲካሄድ ቆይቶ ከቅርብ አመታት ወዲህ አክራሪነትን ለመታገል እንቅስቃሴ ሲጀመር ነው በግልጽ ፀረ ህገመንግስታዊ መልክ ይዞ መታየት የጀመረው፡፡
  ከ20 ዓመታት በፊት በጨቋኙ ስርዓት ይደርስባቸው ከነበረው ግፍና በደል በዲሞክራሲያዊ ትግል ተላቀው የሃይማኖታቸውን እኩልነት ባስከበሩባት አዲሲቷ ኢትዮጵያ የሃይማኖት የበላይነትን በማስፈን ቅኝትና ከሌሎች ሃይማኖት ተከታይ ወንድሞቻቸው ጋር በመቻቻልና በእኩልነት የመኖር እድልን በሚዘጋ ሁኔታ የሚንቀሳቀሱ አክራሪ ዝንባሌዎች መታየት ጀምረዋል፡፡
  እነዚህ አክራሪ እንቅስቃሴዎች በዋኛነት ከሰሜን አፍሪካና ከመካከለኛው ምስራቅ አገሮች አክራሪ ሀይሎች የመነጩ፤ በአንድ በኩል የእስልምናን የበላይነት በአካባያችን ለማስፈን የሚካሄደው እቅድ ማስፈጸሚያ፤ በሌላ በኩል በሃይማኖቱ በሚነግዱ ግለሰቦችና ቡድኖች በሃገሪቱ የተፈጠረውን የእኩልነት ስርዓት በመፃረር የበላይነትን ለማሰፈን የሚካሄደው እንቅስቃሴ መገለጫዎች ናቸው፡፡
  በእነዚህ  አክራሪ አስተሳሰቦች የሚመሩ ጽንፈኞች መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ እንደማይገባ በመገንዘብ በሀይማኖት ሽፋን የዜጐችን ሰብዓዊ መብቶች የሚረግጡ በርካታ አስነዋሪ ተግባራትን ፈጽመዋል፡፡ ነባር መስጊዶችን አቃጥለዋል፣ ነባርና ኢትዮጵያዊ መሠረት አላቸው የሚሏቸውን የሃይማኖት መጽሃፍት አቃጥለዋል፡፡
  ይህን በመቃወም ለማስቆም የሞከሩ ዜጐችና የሃይማኖት ትምህርት ቤቶችንና መስጊዶችን የአመራር ቦታዎች በጉልበት ነጥቀዋል፣ ይህን የተቃወሙ ዜጐችን ሁሉ ከቤት ንብረታቸው አፈናቅለዋል፡፡ ይህ ከሞላ ጐደል አክራሪዎቹ በደረሱባቸው ቦታዎች ሁሉ የተካሄደ ነው፡፡
  የመጀመሪያው ሙከራ ያነጣጠረው በኢትዮጵያ ያሉ ብዙዎቹ ነባር ሃይማኖቶች ሁሉ መሠረታቸው መካከለኛው ምስራቅ መሆኑ እየታወቀ መንግስት አህባሽ የሚባል ሃይማኖት ከውጭ አመጣብን የሚለው መከራከሪያ ውሃ የማይቋጥር ቢሆንም መንግስት ይህኛውን ወይም ያኛውን ሃይማኖት ከዚህኛው ወይም ከዚያኛው አገር በብድር የሚያመጣበት ምክንያትም ሆነ ሎጂክ አልነበረውም፣ የለውምም፡፡ ሃቁ ይህ ሆኖ ሳለ በውጭ ገንዘብ ድጐማ የሚንቀሳቀሱት እነዚህ ሀይሎች ባላቸው አቅመ ሁሉ በመታገዝ
  መንግስት አህባሽ የሚባል የውጭ እምነት አምጥቶ /በሃጂ አብዲላሂ መምህርነት የተስፋፋውን/ ሙስሊሙን ህብረተሰብ ሊጭንበት እየተንቀሳቀሰ ነው የሚል መሠረተ ቢስ ጉዳዮችን እያመጡ መንግስት በሃይማኖታችን ጉዳይ ጣልቃ ገባ ብለው ሲከሱ ሰንብተዋል፡፡ ቀላል ያልሆነ የህብረተሰብ ክፍል በተለይም ወጣት አደናግረዋል፡፡
 የአስተምህሮ መሰረታቸው ብቻ ሳይሆን የየፋይናንስ ምንጫቸውም የውጭ ሀይል ለዚያውም በጣም በቅርቡ የምናውቀው መካከለኛው ምስራቅ በሆነበት ሁኔታ መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ ገብነት ለመክሰስ የሚያስችላቸው ሞራላዊ ብቃት እንዴት ሊጐናፀፉ ቻሉ?
  ገንዘብን በመጠቀም ነባሩን የሱፊ እምነት ለመገለባበጥ ያደረጉት ጥረትና በተወሰነ ደረጃ ያገኙት ውጤት የልብ ልብ ስለሰጣቸው ብቻ ራሳቸውን ምሉዕ በኩልሄ አገር በቀል ሌላውን ደግሞ መጤ ለማስመሰል እስከመሞከር ደርሰዋል፡፡
 ደግነቱ በዚህች ዴሞክራሲያዊት ምድር አገር በቀል መሆን ወይም አለመሆን እምነትን ለማስተማር ቦታ የሌለው መሆኑ እንጅ አገር በቀል ያልሆነ እምነት ሁሉ ኢትዮጵያ ውስጥ ቦታ ሊኖረው አይገባም ቢባል ማን ይቀራል፤
  ነገር ግን አዲሱቱ ኢትዮጵያ የሃይማኖት መለኪያዋ የዜጐች ምርጫ መሆን አለመሆኑ ነው፡፡ መሠረቱ ኢትዮጵያዊ፣ አፍሪካዊ ወይም የሌላ ዓለም መሆን አለመሆኑ አይደለምና ከመካከለኛው ምስራቅ አንዳንድ አገሮች በቅርቡ የገቡትን ሌሎች አስተምህሮዎች ያልከለከለችውን ያክል አህባሽም ሆነ ሌላ አስተምህሮ የዜጐች ምርጫ እስከሆነ ድረስ እንዳይገባ የምትከለክልበት አንዳችም ምክንያት አልነበረም፡፡
 በዚህ ጉዳይ ላይ መንግስት ጉዳዩን አቃሎ በመመልከት ሰፊና አጥጋቢ ማብራሪያ ባለመስጠቱ ግን አክራሪዎቹ ፈቃጅና ከልካይ ሆነው አህባሽ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት የለበትም የሚል አስተምህሯቸው የብዙዎቹን ወጣት ሙስሊሞች አዕምሮ እንዲበርዝ እድል አገኘ፡፡
  ሌላው መጠቀሚያ ሊያደርጉት የሞከሩት                                                                                                                                                                                                                                                                                                         እና የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምርጫ ነበር፡፡
 መንግስት ከት/ቤቱ የፈለገው ሃይማኖትና ፖለቲካ የተነጣጠሉ መሆናቸውን በመቀበል ከማናቸውም አይነት የፖለቲካ አስተምህሮ በፀዳ አኳኋን ተግባሩን እንዲፈጽም ብቻ ነው፡፡
  ተቋሙ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን አክብሮ ከመንቀሳቀስ ይልቅ ለማንም ተጠያቂነት በሌላቸው ወገኖች እየተመራ ከሃይማኖታዊ ጉዳዮች በራቁና ለአክራሪዎች በተመቹ አጀንዳዎች ተጠምዶ ጊዜውን ሲያሳልፍ ቆይቷል፡፡ በመሆኑም ይህንኑ መነሻ በማድረግ ድርጅቱ በእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሚመራና ተጠያቂነት ያለበት ተቋም እንዲሆን ተደርጓል፡፡
 የሙስሊሙ ማህበረሰብ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤቶችን እንደ አዲስ መርጦ ማደራጀት እንደሚፈልግ ግልጽ ነበር – ከየአቅጣጫው በሚነሱ ጥያቄዎች፡፡ በዚህመ ሠረት ምክር ቤቶቹ በአፋጣኝ በሚካሄድ ምርጫ እንዲዋቀሩ ጥያቄ አቅርቦ ነበር፡፡ ይህ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ህገ መንግስታዊ መብት በመሆኑ መንግስት ይህንኑ ተቀብሎ፤ ምክር ቤቶቹ ለዚህ የህዝብ ጥያቄ አወንታዊ ምላሽ እንዲሰጡ ከእርሱ የሚጠበቀውን ምክር ለግሷል፡፡ ምክር ቤቶቹ በአፋጣኝ በሚካሄድ ምርጫ እንዲዋቀሩ የማድረጉን ዴሞክራሲይዊ አሰራርም ደግፏል፡፡
  ልክ መንግስት ጣልቃ እንደገባና ያለሙስሊሙ ህዝብ ፍላጐት  መራጮች በላዩ ላይ እንደተጫኑበት በማስመሰል ሲቀሰቅሱ ከቆዩ በኋላ ከዚህ ታላቅ የዴሞክራሲ ተግባር አቋርጠው ወጡ፡፡
በውጤቱም ህዝቡ ከአክራሪነት የፀዱ የሚላቸውን ሰዎች መምረጡን አረጋግጧል፡፡ ነገር ግን ይህ ምርጫ ዴሞክራሲያዊና ሰላማዊ ሆኖ መካሄዱ ያንገሸገሻቸው አክራሪ ሀይሎች ገና ከምርጫው ዋዜማ ጀምሮ ይህንኑ ለመቃወም ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል፡፡
  ድምፃችን ይሰማ በማለት አርብ አርብ በአንዋር መስጊድና አልፎ አልፎም በሌሎች መስጊዶች ከመንግስት ጋር በከፍተኛ ደረጃ ሲፋጠጡ ከርመዋል፡፡
  ከውጭ ሚዲያዎች ጋር በተቀናጀ አኳኋን በእስልምና ሃይማኖት ላይ ጥቃት የደረሰ በማስመሰል ለማነሳሳት ብዙ ጥረት አድርገዋል፡፡
  በፖሊስና ፀጥታ አስከባሪ ሀይሎች ትዕግስት ወደ መካረርና ግጭት እንዳይመራ ተደረገ እንጂ ከሞላ ጐደል ለአንድ ዓመት ተኩል ያክል አክራሪዎቹ መንግስትን ወደ ግጭትና ደም መፋሰስ ለማስገባት ያላደረጉት ጥረት አልነበረም፡፡
  በአፍሪካ ህብረት ዓመታዊ ስብሰባ ወቅት ያልተፈቀደ የሚሊዮን ሰዎች ሰልፍ ለማድረግና የአዲስ አበባን መንገዶች በመዘጋጋት አደጋ ለመፍጠር ሙከራ አድርገው ነበር፡፡ እንደዚሁም ባለፈው ክረምት አንድ ሌሊት ላይ ከቢላል መስጊድ በመነሳት አዲስ አበባ ከተማን ለማተራመስ ሞክረው ነበር፡፡
  እራሱን ጀሃዳዊ ሃረካት በሚል ስያሜ ለማስተዋወቅ ጥረት ያደረግ ከነበረ የአሸባሪዎች ድርጅት ጋር በመቀናት የአንዋር መስጊዱንም ሆነ ሌሎች መሰል የነውጥ ሙከራዎች በሽፋንነት መጠቀም መርጠው ነበር፡፡
  ይህም ሆኖ መንግስት ረጀም ጊዜ ወስዶ ባካሄደው ጥናትና በሰበሰባቸው ማስረጃዎች ላይ በመመስረት በቡድኑ ቀንደኛ መሪዎች ላይ ህጋዊ ስርዓቱን ተከትሎ የእስራት እርምጃ ወስዷል፡፡
  ከዚህ ጊዜ በኋላ ነው ንቅናቄው በከፍተኛ ፍጥነት በመዳከም ሂደት ውስጥ የገባው፡፡
  በሌላ በኩል ደግም ሃይማኖትን በሽፋንነት ለመጠቀም የሞከረው ይኸው ሀይል በተለይ በውጭ ከሚገኙ ደጋፊዎቹ ጋር በመቀናጀት አሉ የተባሉትን ፀረ ኢትዮጵያ ሚዲያዎች ከመጠቀሙም ባሻገር ከግንቦት 7 እስክ ስደተኛው ሲኖዶስ ባለ የትምክህት ሀይሎች ለመደገፍና ብርቱ ጥረት አድርጓል፡፡ የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው በሚል ፈሊጥ እርስ በእርስ ተሳስረውና ተደጋግፈው ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል፡፡
  በማጠቃለል ሲታይ በሃይማኖት ሽፋን የሚካሄዱ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ውለው አድረው እየተጋለጡና እየተዳከሙ መሄዳቸው ባይቀርም ባለፉት ሁለት ዓመታት ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን በሀይል ለመፈታተን ከሞከሩት የሁከት ሀይሎች ዋነኞቹ ነበሩ ማለት ይቻላል፡፡
  በሀይማኖት ሽፋን የሚካሄደው እንቅስቃሴ በጽንፈኛ የፖለቲካ ፓርቲዎች በቀጥታ ከተደረገው የነውጥ ማነሳሰት በእጅጉ የላቀ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
  ምንም እንኳን ነውጠኛ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከ97 ውድቀታቸው በኋላ በተመሳሳይ ደረጃ ወደሚገለጽ የጐዳና ላይ ነውጥ ለማምራት በከፍተኛ ደረጃ እየተቸገሩ ቢሆኑም በሃይማኖት ሽፋን የሚካሄደውን እንቅስቃሴ በመደገፍና ነዳጅ በማርከፍከፍ ለማቀጣጠል ያደረጉትን ጥረት ጨምሮ የወቅቱ ፀረ ህገ መንግስታዊ ንቅናቄ መገለጫ የሃይማኖት ልባስ ይዞ የሚካሄደው እንቅስቃሴ ነው ማለት ይቻላል፡፡
  በሃይማኖት ሽፋን ለመንቀሳቀስ የተመረጠበትን ዋነኛና ደጋፊ ምክንያቶች መለየትና ከዚህም አኳያ መሠረታዊ መፍትሄ ማበጀት ይገባል፡፡
3. ሃይማኖትን በሽፋንነት ለመጠቀም የተመረጠባቸው ምክንያቶች፣
  ሃይማኖትን በሽፋንነት በመጠቀም የፖለቲካ እንቅስቃሴውን ማካሄድ የመረጡት ሀይሎች የተለያየ መጠሪያ ያላቸው ነገር ግን በመሰረቱ የትምክህት ወይም የጠባብነት መፈክሮችን አንግበው ለመፋለም የሞከሩ የፖለቲካ ሀይሎች እንደሆኑ ይታወቃል፡፡
  ከቅንጅት እስከ ህብረት፣ ከቪኦኤ እስከ ቲቪ አፍሪካ፣ ከጀርመን ድምጽ እስከ ቢላል ሬዲዮ፣ ከጀሃዳዊ ሃረካት እስከ ግንቦት ሰባት፣ ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች ዓለም አቀፍ እስከ መድረክ እስከ ስደተኛው ሲኖዶስ ወዘተ ያሉ ሀይሎች በተናጠልና በህብረት የተሳተፉበት ነው፡፡
  ሁሉም ያነገቡትን ዓላማ በተለያዩ ፀረ ህገ መንግስታዊ ስልቶች በመታገዝ ለማስፈፀም ሞክረው የከሸፈባቸው ሀይሎች ናቸው፡፡
  እነዚህ አላማቸውን በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ በማራመድ ለስኬት መብቃት ያቃታቸው ድርጅቶችና ሀይሎች ከፍ ሲል እንደተመለከትነው የፖለቲካ ዓላማቸውን በሃይማኖት ሽፋን ማራመድ የመረጡት ይህ ስልት ምን ዓይነት እድል ቢሰጣቸው ነው ብሎ ጥያቄ ማንሳትና ጉዳዩን መመርመር በዚሁ ዙሪያ በቀጣይነት መካሄድ ያለበትን ትግል በትክክል ለመወሰን አስፈላጊ ነው፡፡
  በድሃና ኋላቀር ህብረተሰብ ውስጥ በእምነት ጉዳይ ዜጐችን ብዥታ ውሰጥ መክተት ይህን ስልት ለመረጡ ወገኖች በቀላሉ ያለመጋለጥ እድል ያጐናጽፈናል፡፡ ከዚህም አለፍ ሲል ለድል ያበቃናል ብለው ማመናቸው ነው፡፡
  የእምነት ጉዳይ ለሚዛናዊ አስተሳሰብ ያለው ተጋላጭነት በተነፃፃሪ አነስተኛ ከመሆኑ ጋር የተያያዘ ነው፡፡
  በሃይማኖት ለሚመራ ሰው ወደ ማንኛውም ድርጊት ለማምራት ማመን ብቻውን በቂ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡
  “በእምነትህ የመጣ ነው” ተብሎ የቀረበለትን ጉዳይ ያለማንገራገር ተቀብሎ ወደ ድርጊት ማምራት በብዙ የሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ የሚታይ ክስተት ነው፡፡
  ስለሆነም ይህ አካሄድ በሃይማኖታቸው ቀናዒ የሆኑ ሰዎች በሃይማኖት ሽፋን የሚራመዱ የፖለቲካ አጀንዳዎች ሰለባ ለማድረግ የተሻለ እድል ይፈጥርልናል በማለት ነው፡፡
  በበለፀገው ዓለምም በአሸባሪነትም ሆነ በፀረ አሸባሪነት ጐራ ተሰልፈው የሚፋለሙ ሀይሎች ሃይማኖታዊ ጥሪ በማስተላለፍ የፖለቲካ ዓላማቸውን በሃይማኖት ግጭት መልክ ሲያስኬዱ ማየት የተለመደ ነው፡፡
  የትኛውንም ጎራ በመሠረተ ቢስ እምነት ነክ ውንጀላዎች በቀላሉ በስሜት በማነሳሳት ሌላውን እንዲገጥሙ ማድረግ ይቻላል ተብሎ ይታመናል፡፡
በመሆኑም የከሰሩ ፖለቲከኞች ሁሉ ሃይማኖትን በሽፋንነት በመጠቀም መንቀሳቀሳቸው የእምነት ጉዳይ ለሚዛናዊ አስተሳሰብ ያለው ተጋላጭነት በተነፃፃሪ አነስተኛ ከመሆኑ ጋር የተያያዘ ነው፡፡
  በሃይማኖት ስም የሚካሄደውን ንግድ ውጤታማ እንዲሆን በማድረግ ረገድ አጋዥ ሚና የሚጫወቱ ችግሮች ደግሞ ይኖራሉ፡፡ በዚህ ረገድ የድህነት መንሰራፋትና የመልካም አስተዳደር  እጦት ወይም ጉድለት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
  በተጨባጭ እንደሚታየው በበለፀገና ሰርቶ የመጠቀም እድል በሰፋበት ማህበረሰብ ውስጥ ለጽንፈኝነት መሠረት የሚሆን ተስፋ መቁረጥ አይገኝም፡፡ ሰርቶ መክበርና ማደግ ስለሚቻል ለተስፋ መቁረጥ ምክንያት የሚሆን ችግር አይኖርም፡፡
  መልካም አስተዳደር በሰፈነበት ሁኔታ ዜጐችና ህዝቦች በደስታና በስምምነት ይኖራሉ፡፡ በአንፃሩ ድህነትና ኋላቀርነት በተስፋፋበት ህብረተሰብ ውስጥ ተስፋ መቁረጥ ያይላል፡፡ ዜጐች የምድራዊ ኑሯቸውን ከሲኦል ያልተለየ አድርገው በመውሰድ በሃይማኖት ስም ለሚቀርቧቸው ሃሳዊ መሲሆች ሁሉ አመኔታቸውን ሊሰጡ ይገደዳሉ፡፡ ኢትዩጵያ በመጭው ምርጫ ፈተና ይሆንብናል፡፡
  በተለይ ከድህነትና ኋላቀርነት መውጫውን ትክክለኛ መንገድ የሚያመላክት መሪ ድርጅት በሌለበት በሃይማኖት ሽፋን የሚነግዱ የፖለቲካ ሀይሎች አንዱን በሌላው ላይ ማነሳሳት የፅድቅ መንገድ እንደሆነ አስመስለው በማቅረብ ዜጐችን ወደጥፋት ይመራሉ፡፡
  መሪ ድርጅቱም ኖሮ በአመራርም ሆነ በአባላት ደረጃ በአንድ በኩል ከፀረ ድህነትና ኋላቀርነት ትግሉ ላይ ጽናትና ብቃት ያለው አመራር መስጠት ካልተቻለ፣ በሌላ በኩል ደግም የፓርቲና የመንግስት መሪዎች ስራቸውን ከየትኛውም ሃይማኖት ገለልተኛ በሆነ መንገድና ሁሉን ሃይማኖቶች እኩል በሚያስተናግድ አግባብ ካልፈፀሙ ይኸው ችግር ተባብሶ መቀጠሉ አይቀርም፡፡
  ከዚህ አኳያ ሲታይ ድህነትና ኋላቀርነነት እንዲሁም እነዚህን ለማስወገድ የሚያስችል ብቃት ያለው አመራር እጦት የፖለቲካ ጽንፈኝነትና የሃይማኖት አክራሪነት የሚስፋፋባቸው ለም አፈሮች ብቻ ሳይሆኑ በሃይማኖት ሽፋን የሚነግዱ ፖለቲከኞችም እንደመልካም አጋጣሚ የሚመለከቷቸው ናቸው፡፡
  በመሆኑም እነዚህን ችግሮች በመፍታት በሃይማኖት ሽፋን ለሚነግዱ ፖለቲከኞች መንቀሳቀሻ አድማሱን ማጥበብ እጅግ ተፈላጊ ሆኖ ይገኛል፡
IV. በሃይማኖት ሽፋን የሚካሄደውን የፖለቲካ ንግድ በአስተማማኝ ደረጃ ለማሸነፍ ምን እንስራ?
  ከፍ ሲል እንደገለጽነው ፈጣንና ህዝብ የሢቀምበት ለውጥና ብዝሃነነትን በአግባባ የማስተናገድ ችሎታተ የያለው ህብረተሰብ በመፈጠሩሪ ምክንያት በሀይማኖት ሽፋንም ሆነ በግላጭ ሲካሄድ የቆየው ጽንፈኛ እንቅስቃሴ የህዝብ ይሁንታን ሊያገኘ ባለመቻሉ ትርጉም ያለው ሁከትና ብጥብጥን ለመቀስቀስ ሳይቻለው ቆይቷል፡፡
 ይህ መሠረታዊ ሃቅ አንደተጠበቀ ሆኖ አሁንም ድህነትና ኋላቀርነት በመኖሩ፣ በፓርቲና በመንግስት አመራራችን የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ጉድለቶች በመኖራቸውና የእምነት ጉዳይ ለሚዛናዊ አስተሳሰብ ያለው ተጋላጭነት ዝቅተኛ በመሆኑ አልፎ አልፎ የተካረረ ፍጥጫ የሚያጋጥመን ሆኖ ቆይቷል፡፡
 ይህ ፍጥጫ በተለይ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከሞላ ጐደል ሁሉንም ተፋላሚ ሀይሎች በሁለት ጐራ ከፍሎ ያፋጠጠ ሆኖ ከርሟል፡፡
  ምንም እንኳን ችግሩ ለጊዜውም ቢሆን በመንግስት ታጋሽነትና አርቆ አስተዋይነት እንዲሁም በሰላም ወዳዱ ህዝብ ብርቱ ትግል የከሸፈም ቢሆን ለችግሩ መቀስቀስ ምክንያት የሆኑት ጉዳዮች በሙሉ ዛሬም በተጨባጭ ይገኛሉና ይህንን ታሳቢ ያደረገ የመፍትሄ ሃሳብ ማመላከት ተገቢ ይሆናል፡፡
1. ፀረ- ድህነትና ፀረ-ኋላቀርነት ትግላችንን እናፋፍም፣
  በድህነት የተጐዳ ህብረተሰብ ሁሌም በምሬት ውስጥ የሚኖርና ከዚህ ችግር የሚያላቅቀው ትክክለኛ አማራጭ ካልቀረበለት በስተቀር በሌሎች ጽንፈኛና መሰረተ ቢስ አማራጮች ሊማለል የሚችል ነው፡፡
  በተለይ ደግም በምድራዊው ህይወቱ ያላለፈለትን ህዝብ በሰማይ ቤት ያልፍልሃልና ማንኛውንም ጽንፈኛ አቋም ተግባራዊ አድርግ ለሚሉ አይነት ቅስቀሳዎች ተጋላጭ ይሆናል፡፡
 ኋላቀርነትም እንደዚሁ አንድን ህብረተሰብ የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር እድል በመንፈግ ለተስፋ መቁረጥና ጽንፈኝነት ሊዳርገው ይችላል፡፡
  ምሬቱ የከፋና ተስፍ የቆረጠ ህዝብ ባለበት ሁሉ ጽንፈኝነት ሲስፋፋ የምንመለከተው በዚህ ምክንያት ነው፡፡
  ይህ አዲስ ግኝት ሳይሆን ድርጅታችን ቀደም ሲል ጀምሮ የተገነዘብነውና ለመፍትሄውም የታገለለት ጉዳይ ነው፡፡
 ድርጅታችንና በርሱም የሚመራው ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ድህነትና ኋላቀርነት ጽንፈኝነትንና፣ ፀረ እኩልነት የሆኑ የትምክህትና ጠባብነት አዝማሚያዎችን ወዘተ ሊሸከም የሚችል ለም አፈር መሆኑን ታሳቢ በማድረግ በድህነትና ኋላቀርነት ላይ ጦርነት ካወጀ ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡
 ፈጣንና ብዙሃኑ ህዝቦች የሚቀጠሙበትን ልማት አስፋፍቷል፡፡
  መሠረተ ሰፊና አሳታፊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ገንብቷል፡፡ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ቀጣይ ትግል አካሂዶ በመስኩ ከፍተኛ ድሎችን አስመዝግቧል፡፡
  ይህም በመሆኑ ዛሬ አገራችን ከመቼውም ጊዜ በተለየ ሁኔታ በፈጣንና ህዝብ በሚጠቀምበት ዴሞክራሲያዊ የእድገት አቅጣጫ እየገሰገሰች ትገኛለት፡፡
  እድገታችን ፈጣንና መሰረተ ሰፊ በመሆኑም የህዝቡን ተስፋ አለምልሟል፡፡
  ዴሞክራሲያችን ብዝሃነትን በማወቅና በማክበር ላይ የተመሰረተ በመሆኑ በህዝቦች መካከል ፍቅርን መከባበርና መቻቻልን አጐልብቷል፡፡
  የእርስ በርስ መናቆርና ከዚህም ጋር ተያይዞ ሊመጣ የሚችል ተስፋ መቁረጥ መሰረት ተንዷል፡፡ ብዙ አገሮች በቀለም አብዮቶች ሲናጡና ከቀውስ ወደ ቀውስ ሲረማመዱ በአገራችን ሰላምና መረጋጋት እንደሰፈነ የቀጠለው በዚህ ምክንያት ነው፡፡
2. ወጣቱን ከስራ አጥነትና ተስፋ መቁረጥ እንታደግ?
 አብዛኛውን ጊዜ በስሜት የሚያነሳሱ ጉዳዮች በቀላሉ ተጽዕኖ የሚያሳርፉት በወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ላይ ነው፡፡
  በተለይ ወጣቱ ለስራ አጥነት፣ ጥራት ለሌለው ትምህርት፣ ከተደራጀ ፖለቲካዊ ተሳትፎ መገለልና ለመልከም አስተዳደር የሚያመች ሁኔታ ባልገጠመው ወቅት ስሜት ቀስቃሽ የሆኑ አቀራረቦች በደካማ ጐኑ ለመግባት የተሻለ እድል ያገኛሉ፡፡
  በአገራችን በተለይ ከ97 ዓ/ም ድህረ ምርጫ ቀውስ በመማር የወጣቱን የልማትና የተጠቃሚነት፣ የመልካም አስተዳደርና የተሳትፎ ጥያቄዎች ለመመለስ ጥረት ያደረግነውና የተሳካ ውጤት ያገኘነውም በመሰረቱ ለስራ አጥነትና ለተስፋ መቁረጥ የተጋለጠ ወጣት ሊኖርበት የሚችለውን ተጋላጭነት በማስወገድ ንቁ የአገር ገንቢ ለማድረግ ነው፡፡
  ወጣቱ ያለበትን የመነሻ ካፒታል ችግር በከፊልና የራሱን ተሳትፎ ባረጋገጠ አኳኋን ልንቀርፍለት፣ የመስሪያና የመሸጫ ቦታዎችን ገንብተን በማቅረብ ለልማታዊ ጥረቱ የተሻለ ሁኔታ ልናመቻችለት ይገባናል፡፡
  በገጠርም በግብርናና ከግብርና ውጭ በሚካሄዱ ልማታዊ ሰራዎች ተሳትፎውንና ተጠቃሚነቱን ማረጋገጥ ይገባናል፡፡
  ከዚህ ጐን ለጐን ወጣቱ ትውልድ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን በሚካሄደው ትግል ዋነኛ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ ተጠናከሮ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡
 ይህ ሲሆን ብቻ ነው ወጣቱ ሚዛናዊ አስተሳሰብ እንዲይዝ ለማድረግ የምናደርገውን አስተምህሮ በቅን ልቦና ተመልክቶ ሊቀበል የሚችለው፡፡
3. የመንግስትና ፓርቲ አመራርን ሃይማኖታዊ ገለልተኝነት እናጠናክር፣
  ህዝቡ ለመብቱና ለጥቅሙ የሚያደርገውን ትግል በትክክለኛ መስመር ለመምራት የተነሳው ድርጅታችንም ሆነ ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስታችን የብሄርና የሃይማኖት ልዩነት ሳያደርግ አላማውን የተቀበሉና መንግስታዊ ተልዕኮን ለመፈፀም ዝግጁ የሆኑ ታጋዮችንም ያሰባስባል፡፡
  ይህም በመሆኑ ድርጅታችንም ሆነ ልማታዊ መንግስታችን የተለያዩ እምነቶች ተከታዮች የሚሳተፉባቸው ተቋማት እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፡፡
  ይህ መሠረታዊ የግል እምነትን የማክበርና የማስከበር ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ ድርጅታዊ አመራርን የማረጋገጥም ሆነ መንግስታዊ አገልግሎትን የመስጠት ጉዳይ ከሃይማኖት /ከራስህም እምነት ጭምር/ ገለልተኛ በሆነ መንገድ መካሄዱን ማረጋገጥ ይገባል፡፡
 ዜጐችና የተለያዩ እምነት ተከታዮች ከድርጅት የሚያገኙት አመራርና ከመንግስት የሚያገኙት አገልግሎት በእኩልነት ከሀይማኖት ገለልተኛ በሆነ መንገድ ሊፈፀም ይገባዋል፡፡
  በየደረጃው የሚገኙ ሀላፊዎች ከዚህ አኳያ በተጨባጭ ከሚፈፀሙ ገለልተኝነትን ለድርድር ከሚያቀርቡ ስህተቶች መጽዳታቸውን ማረጋገጥ ይገባል፡፡
4. የህገ መንግስታዊና ሚዛናዊ አስተሳሰብ ትምህርትን ማስፋፋት፣
 ሆን ብለውና እያወቁ በሀይማኖት ሽፋን የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ጥረት የሚያደርጉ ወገኖችን ከተሳሳተ አቅጣጫቸው በትምህርት መመለስ አይቻልም፡፡
  እነዚህ ጥቅማቸውን በጥገኛ ወይም የኪራይ ሰብሳቢ መንገድ ለማሳካት የሚንቀሳቀሱና ለዚህም የቆረጡ ናቸው፡፡
  ስለሆነም ተጋልጠው የፖለቲካ ተፅዕኖ የማሳረፍ አቅማቸው እንዲዳከምና የማታ ማታ ደግሞ ተነጥለው ወደ ዳርቻ እንዲገፉ /marginalized/ ማድረግ ብቻ የሚጠይቁ ወይም የሚፈልጉ ናቸው፡፡ ስለሆነም ስለህገ መንግስታዊና ሚዛናዊ አስተሳሰብ አስተምህሮ ስናነሳ ለእነዚህ እንደማይሆን በመገንዘብ ጭምር ነው፡፡
  ህገ መንግስታዊና የሚዛናዊ አስተሳሰብ ትምህርት ከማንም በላይ የሚያስፈልገውና የሚጠቅመው ከልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ሂደቱ ተጠቃሚ ለሆኑት ብዙሃን ህዝቦች ነው፡፡
  ስለሆነም ለራሳችን ማህበራዊ መሰረቶች በህገ መንግስታዊ ስርዓታችን ላይ ግልጽነት፣ እምነትና ስርዓቱን ከአደጋ የመጠበቅ ቁርጠኝነት እንዲያዳብሩ የሚያግዝ ትምህርት ልንሰጥ ይገባናል፡፡
  እያንዳንዱ ዜጋ በማንኛውም ጉዳይ ላይ አቋም ከመውሰዱ በፊት ለምን? ለማንና መቼ? እንዴትና የት? ወዘተ የሚሉ መሠረታዊ ጥያቄዎችን በማንሳት መመርምር እንደሚገባው ማስተማር ይገባናል፡፡
  እነዚህን ጥያቄዎች በማንሳት የህዝብንና የአገርን ጥቅም የሚጐዳን ማናቸውም ጉዳይ መቃወም፣ የሚጠቅመን ጉዳይ ደግሞ መደገፈ እንዳሚገባ ማስተማር ይገባል፡፡
  ሌላው ሰው አድርጐታል በማለትና በመንጋ ቅኝት በመመራት አቋም መውሰድ እንደማይገባ ይልቁንም አያንዳንዱ ሰው ራሱን ችሎና በህሊናው አመዛዝኖ አቋም መውሰድ እንዳለበት ማስተማር ይገባናል፡፡
 በአንድ በኩል ከእያንዳንዱ ሚዛናዊ አቋምና ተግባር በሌላ በኩል ደግሞ ከእያንዲንዱ ሚዛናዊነት የጐደለው አስተሳሰብና ተግባር ተፈላጊውን ትምህርት መስጠትና የሚዛናዊ አስተሳሰብን የበላይነት ማረጋገጥ ይገባናል፡፡
5. በሃይማኖት ሽፋን የሚነግዱትን ሀይሎች በቀጣይነት ማጋለጥና መሰረት ማሳጣት፣
ü እነዚህ ተግባራት በትክክል ከተፈፀሙ አክራሪነትንና ጽንፈኝንት ከማሸነፍ አኳያ ረጅም ርቀት እንደሚወስዱን አያጠያይቅም፡፡ ይህም ሆኖ ብቻቸውን በቂ ናቸው ሊባሉ የሚችሉ አይደሉም፡፡ በሃይማኖት ሽፋን የሚነግዱ ጽንፈኞችን ሁሉ በማጋለጥ ትግል ሊደገፉ የሚገባቸው ናቸው፡፡ ከዚህ ትግል ውጭ የምናገኛቸው ውጤት ምሉዕነት ሊኖረው የሚችል አይደለም፡፡
  ህዝቡ ህይወቱን በሚመለከቱ መሠረታዊ ጉዳያች ላይ ሁሉ ብቁ፣ ዝርዝርና ወቅታዊ መረጃ እንዲኖረው ማድረግ ነው፡፡
  የመንግስትን እቅዶችና አፈፃፀም እንዲሁም በአፈፃፀም ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችና መልካም አጋጣሚዎችን የሚመለከት መረጃ ለህዝቡ በፍጥነትና በግልጽ ማቅረብ ይገባናል፡፡
  ከዚህ አኳያ በየመስሪያ ቤቱና በየድርጅት ጽ/ቤቱ ያሉትን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊዎች አደረጃጀቶች በብቃት ማንቀሳቀስ ይጠበቅብናል፡፡
  ይህን የማጋለጥና መሠረታቸውን የመናድ ስራ እየሰራን አስፈላጊ ሆኖ በተገኘበት ደረጃና መጠን ደግም ህጋዊ እርምጃ መውሰድ ይገባናል፡፡
  እነዚህን በተናጠልና በድምር በመፈፀም በሃይማኖት ሽፋን የሚካሄዱ አፍራሽና አክራሪ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን በተሟላ አኳኋን አይሳነንም፡፡
ለመደበኛ አባላት የማይነገር ፤ ለከፍተኛ አመራሮች ብቻ
ቀጣዩ የምክር ቤት አባላት ምርጫ የግንቦት ሰባት አና አክራሪ እስልምና ሃይሎችን የሚያስቀጥሉ አባላት ወንብሩ በኢህአዴግ አባላት ስም ሊነጠቅ ይችላል፡፡
  የ97 የቅንጅት አሸናፊነት አካሄድ ስልት ማለትም የተቃዋሚ አባለት ሁነው በህቡእ ተደረጅተው በኢህአዴግ የአባላትንት ካርድ ሙሉ በሙሉ ፓርቲው ሊጎዱት ይችላሉ፡፡ 

Tuesday, November 26, 2013

EU Member of Parliament Ana Gomes in Addis Ababa

November 26, 2013
Ana Gomes, known for publicly criticising Ethiopia following the 2005 government crackdown
Serious talk! EU Member of Parliament Ana Gomes, known for publicly criticising Ethiopia following the 2005 government crackdown, which claimed over 200 lives, in a seemingly serious discussion during lunch break with Ethiopian MP and Speaker of the House Abadulla Gemeda in Addis Ababa, November 25, 2013. ANDUALEM SISAY | NATION MEDIA GROUP
The 26th European Union (EU) and African Caribbean Pacific (ACP) Joint Parliamentary Assembly (JPA) opened in Addis Ababa, Ethiopia Monday morning.
The assembly is expected to debate several issues, ranging from use of natural resources to fiscal reform and redistribution of wealth and decentralised cooperation.
The gathering is also expected to discuss respect for the rule of law and the role of an impartial and independent judiciary and South-South and triangular cooperation.
The assembly that will be concluded on Wednesday, has no decision-making powers.
However, it allows elected representatives of ACP countries to address their concerns directly to the EU Commission and be updated on the negotiations on trade deal, such as the Cotonou Agreement.
“There is an ample room for more enhanced partnership in many areas of interest to both sides,” said Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn, while opening the assembly.
“But in a large sense, this relationship should not in any way be based on the rather obsolete assumption that one side is the ultimate provider and the other perennial receiver of resources whatever the object of the relationship might be – economic or political.”
JPA comprises 78 members of parliament and 12 vice-presidents from both sides (EU and ACP).
The assembly is expected to be concluded after discussing social and environmental impacts of pastoralism on ACP countries on the last day.
JPA meets twice a year, once in the EU, traditionally in the country holding the presidency of the Council of the EU and once in an ACP country, determined by the group of ACP countries.
Source: AFRICA REVIEW

Monday, November 25, 2013

“ኦሮሞዎች ኢትዮጵያውያን አይደለንም”የሚለውን መፈክር ማሰማት- ምን ማለት ነው?

November 25/2013

እኛ ኦሮሞዎች ኢትዮጵያውያን አይደለንም”የሚሉ ኦሮሞዎች እንዳሉ አውቃለሁ። ይህን አቋም የሚያራምዱት ከአጠቃላይ የኦሮሞ ህዝብ ውስጥ ምን ያህል ፐርሰንቱን እንደሚወክሉ ግን መረጃው የለኝም። በፖለቲካ ፓርቲ ደረጃ አንድኛው የኦነግ ክንፍ ከኢትዮጵያ የተለየችን ኦሮሚያ የመፍጠር ዓለማ ሰንቆ ሲንቀሳቀስ፤ ሌለኛው ደግሞ “መፍትሔው ሁላችንም በእኩልነትና በፍትህ የምንኖርባትን ኢትዮጵያ እውን ማድረግ ነው” ብሎ ማወጁን ከሁለት ዓመት በፊት ሰምቻለሁ። ይህ ብቻ ሳይሆን በነ ፕሮፌሰር መረራ የሚመራው ኦብኮ( ልብ በሉ ኦብኮ በ 1997ቱ ምርጫ ወቅት ከቅንጂት ቀጥሎ በተናጠል በርካታ የፓርላማ መቀመጫዎችን ያሸነፈና በኦሮሞ ህዝብ ንድ ተቀባይነቱን ያስመሰከረ ፓርቲ ነው) ፣ በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ የተመሰረተው ኦፌዲንና ሌሎችም የኦሮሞ ፓርቲዎች- ከነባሩ ኦነግ የተለየ አቋም እንደሚያራምዱ እና ዲሞክራሲ፣ ፍትህና እኩልነት በሰፈነባት ኢትዮጵያ ውስጥ የ ኦሮሞን ህዝብ መብትና ጥቅም ከማረጋገጥ ውጪ ሌላ የተሻለ አማራጭ እንደሌለ አውጀው እየተንቀሳቀሱ ነው። በ ያ ላይ ጥርስ የሌለው አንበሳ የሆነው የኢህአዴጉ- ኦህዴድም አለ። በኢትዮጵያ ጉዳይ ከ ኦነግ የተለየ አቋም የሚያራምዱት እኚህ ሁሉ ፓርቲዎች ይነስም ይብሳም የየራሳቸው ደጋፊዎች አሏቸው።

ከዚህ አንፃር ከታች በቪዲዮው የሚታዩት ሰልፈኞች እንደ ኦነግነታቸው፦”ሳዑዲ ዐረቢያ የኦሮሞ ህዝብን መግደል አቁሚ!”የሚል መፈክር ማሰማት መብታቸው ነው። “ኦሮሞዎችኢትዮጵያውያን አይደለንም!” የሚለው ግን የተሣሳተ እንዲሁም ከሞራልን ከህሊና አኳያ ተገቢ ያልሆነ ነው።

አዎ! ሰልፈኞቹ፦”እኛ ኢትዮጵያውያን አይደለንም” ማለት ይችላሉ። በነፕሮፌሰር መረራ ፣ በነ ኦቦ ቡልቻ ደመቅሳ እና በሌሎችም በርካታ ኦሮሞዎች ጉዳይ ግን ህዝበ ውሳኔ ማሳለፍ አይችሉም። በየትኛው ውክልናቸው ነው ስለ አጠቃላዩ የ ኦሮሞ ህዝብ ውሳኔ የሚያሳልፉት በኢትዮጵያዊነታቸው የማይደራደሩ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊነታቸውን ጥያቄ ምልክት ውስጥ የማያስገቡ እልፍ ኦሮሞዎችን ባቀፈች አገር ላይ ፦”ኦሮሞዎች ኢትዮጵያውያን አይደለንም!” ብሎ ያለ ውክልና ማወጅ አይቻልም። “እኛ የኦነግ አባላት ኢትዮጵያዊ አይደለንም!”ማለት ግን መብት ነው። ይቻላል።

ሌላው ያሳነኝ ነገር የዚህ ሰልፍ ዓላማ በሳዑዲ በስደተኞች ላይ እየተፈፀመ ያለው ስቃይና ግድያ እንዲቆም ለመጠየቅ ነው። ይህ ከሆነ እንደ ኦነግ አስተሣሰብስ ቢሆን ፦“ሳዑዲ ዐረቢያ የኦሮሞ ህዝብን መግደል አቁሚ!” የሚለው አይበቃም ነበር ወይ? “ በዝህ አስከፊ ሁኔታና ሁሉም ስለሁሉም እየጮኸ ባለበት ወቅት “ኦሮሞዎች ኢትዮጵያውያን አይደለንም”የሚለውን መፈክር ማሰማት- ምን ማለት ነው? ‘ሳዑዲ ኢትዮጵያውያንን መምታት ትችየለሽ’ ማለት አይመስልም ወይ? አረ እየተስተዋለ!
Dereje Habtewold

ተዋርደን አንቀርም!!!

November 25/201
ሳውዲ አረቢያ በዜጎቻችን ላይ እያደረሰች ያለውን ግፍና በደል በሰላማዊ ሰልፍ ለመቃወም ፓርቲያችን በወሰነው መሰረት ለሚመለከተው ክፍል አሳውቀን ነበር፡፡መቸም ህዝባችን በጭቆና ውስጥ ስለኖረ በመብቱና በግዴታው መሀል ያለውን ድንበር በውል ካለመረዳቱ የተነሳ ሰልፉ እንዲደረግ ስለመፈቀዱ በተደጋጋሚ ስንጠየቅ ነበር፡፡ህጉ የሚለው ግን ማስፈቀድ ሳይሆን ማሳወቅ ብቻ ነው፡፡በተቃራኒው መንግስት በተለያዩ ጉዳዮች ሳቢያ በእለቱ ለሰላማዊ ሰልፉ የደህንነት ከለላ መስጠት የማይችልበት ሁኔታ ከገጠመው ሰልፉን ለጠራው አካል ችግሩን ገልጾ ቀኑ እንዲተላለፍለት ይጠይቃል፡፡

በመሆኑም ይህን መሰል ጥያቄ ከሚመለከተው መስሪያ ቤት ለፓርቲያችን ባለመቅረቡ በሙሉ ልብ ቅድመ-ዝግጅት ማድረጉን ተያያዝን፡፡
ሁሌም ቢሆን መንግስት ሰበብ ፈልጎ ሊወነጅለንና ከመስመር ሊያስወጣን እንደሚፈልግ በሚገባ እናውቃለንና በጥቃቅን ጉዳዮች ላይ ሳይቀር ጥንቃቄ እናደርጋለን፡፡ለሚመለከተው መስሪያ ቤት ባሳወቅን በአስራ ሁለት ሰአታት ውስጥ ምላሽ ስላልመጣ ሙሉ በሙሉ ህጋዊነታችንን አረጋግጠናል ማለት ነው፣እነሱ ደግሞ ጠብ-መንጃ በእጃቸው አለና የፈለጉትን ሁሉ ማድረግ ይችላል፡፡
አቶ ሽመልስ ከማል ለሚዲያወች የሰጡትን ፍጹም ከእውነት የራቀ ውንጀላና ሰበብ አዳምጨዋለው፡፡ “ሰላማዊ ሰልፉን ያገድንበት ምክንያት ጸረ-አረብ መፈክሮች ስለነበሩ ነው“ብለዋል፡፡መጀመሪያ ደረጃ ሰልፉ ገና ከግቢው ፈቅ ሳይል ነው ያፈኑት፣ሆኖም የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም አንድ በአንድ እየሆንን ወደ ሰላማዊ ሰልፉ መዳረሻ ለመሄድ ስንሞክር የተወሰኑ አመራሮችን አራት ኪሎ አካባቢ ያዙን፣እነሱ ቀድሞውኑ ሰልፉ እንዳይካሄድ ስለወሰኑ ነው እንጅ ትንሽ እንኳ ተንቀሳቅሶ የሰልፉን ባህሪ ለመገምገም ምንም እድል አልሰጡንም፡፡
ለምሳሌ ሰልፉን እንደምናደርግ ይፋ ባደረግን ማግስት ከራዲዮ ፋና ተደውሎ አንዳንድ ጥያቄዎች ተጠይቄ ነበር፡፡በቃለ-መጠይቁ ሰላማው ሰልፉ በዜጎቻችን ላይ የሚደርሰውን በደል በመቃወም እንደምናደርግ ተናግረናል፡፡ጋዜጠኛው ለሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች መልዕክት ካለ ብሎ በጠየቀኝ ወቅት የሳውዲ አረቢያ ሰንደቅ አላማ ላይ ያለው ምልክትና ጽሁፍ ሀይማኖትን የሚመለከት በመሆኑ ዜጎች በስሜታዊነት ባንዲራ እንዳያቃጥሉ፣እነሱ ቢያዋርዱንም እኛ ግን ክብር ያለን ዜጎች ስለሆንን ተቃውሟችንን ጨዋነት በተሞላበት ሁኔታ ማካሄድ እንዳለብን ተናግሬ ነበር፡፡ከሰላማዊ ሰልፉ በፊት በዚህና በተለያየ መንገድ በማያሻማ ሁኔታ መልዕክት ባስተላልፍም እነሱ ግን ይህን በመቁረጥ አላስተላለፉትም፡፡እነዚህና ሌሎች ምክንያቶች ሲደመሩ የአቶ ሽመልስ ከማል ንግግር ነጭ ውሸት መሆኑን ያስገነዝባል፡፡
ሁለተኛ የአንድ ሀገር መንግስት ዜጎቹ እየተደፈሩ፣በማጎሪያ ካምፕ በረሀብና በውሃ ጥም፣ሌላው ቢቀር መጸዳጃ ቤት እንኳ ተከልክለው ፍጹም ከሰውነት ክብራቸው ወርደው እየተበደሉ፣እየተገደሉ ባለበት ወቅት ገና ለገና ተቃዋሚ ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ በሚንጸባረቅ ጥላቻና ተቃውሞ የዲፕሎማሲ ግንኙነቴ ይበላሽብኛል ብለን መናገር እንችላለን?ሌላው ይቅር አንድ ክፉና ደጉን የለየ ሰው የሚያስበው ጤነኛ ሃሳብ ነው ማለትስ ይቻላል?
ከእገዳው ባሻገር የሚደንቀው ነገር ደግሞ በፓርቲያችን አመራሮችና አባላት ላይ የተደረገው ድብደባ ነው፣የሆነ ማስተላለፍ የፈለጉት ነገር ያለ ይመስላል፡፡የጭካኔያቸውን መጠን እንድናውቅ የሚደበድቡት አቅመ-ደካሞችን፣ሽማግሌወችንና ሴቶችን እየመረጡ በፍጹም አረመኔነት ነበር፡፡ይህን ተግባራቸውን ስመለከት የደረሱበትን የዝቅጠት ደረጃ መታዘብ ችያለው፡፡ከፖለቲካ ልዩነትም፣ከአምባገነንነትም በላይ ሰወቹ እንደታመሙ ነው ለመረዳት የቻልኩት፣ስር የሰደደ የቁስ ሰቀቀንና የስልጣን ጥም የተጣባቸው፣ለዚያ ሲሉም የትኛውንም አይነት ውርደት ለመቀበል የቆረጡና የሞራል ልዕልናቸውን ሙሉ በሙሉ ያጡ ሰዎች ናቸው፡፡ስነ-ልቦናቸው ክፉኛ ተቃውሷል እንጂ ሀገር እመራለው የሚል ቡድን እንዲህ ያለ ተግባር ይፈጽማል ለማለት እቸገራለው፡፡በአባላቶቻችን ላይ ክፍኛ ድብደባ ተፈጽሟል፣እስከዛሬም እግሮቻቸው መራመድ የማያስችላቸው፣የሚያነክሱ ሰዎች አሉ፡፡እውነት ለመናገር ይሄ እብደት ነው፡፡አንዲት እራሷን መከላከል የማትችል ሴትን ለሶስት መደብደብን ከዚህ በተሸለ ልገልጸው አልችልም፡፡
አንድ ማስገንዘብ የምፈልገው ነገር ለኛ ዋነው ጉዳይ የዜጎቹ ህጋዊነት ወይም ህጋዊ ያለመሆን ጉዳይ አይደለም፡፡በምንም አይነት መንገድ ሴቶች እየተደፈሩ፣ወንዶች በየስርቻው እንደ ውሻ ተቀጥቅጠው እየተገደሉ እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች ታጉረው ይህን ሁሉ መከራ መቀበላቸውን ልንታገሰው፣ወይም ከህጋዊነት አንጻር እየተራቀቅን ልንመለከተው አንችልም፣ስለ ህግም ከተወራ የሳውዲ አረቢያ መንግስት ጭፍጨፋው ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ባላቸው ላይ ጭምር ሲፈጸም እንደነበር አምኗል፡፡
ባለንበት የግሎባላይዜሽን ዘመን የአንዱ ሀገር ዜጋ ካለ ሀገሩ መገኘት አገር ይያዝ የሚያስብል አይደለም፡፡መውጣት ካለባቸው ጊዜ በመስጠት፣ከመንግስታቸው ጋር በመነጋገር በዘዴ ነገሩን መከዎን እየተቻለ አንድ ሀገርና መንግስት በሰዎች ላይ እንዲህ የጭካኔ ጥግ የሆነን አቋም ይዘው መንቀሳቀሳቸው ፍጹም ኢ-ሰብአዊነት ነው፡፡
ለኢትዮጵያውያን እንዲህ ያለ አስከፊ ጊዜ የለም፣እውነቱን ለመናገር ለአገዛዙ ሰዎች የነበረኝ ጭላንጭል ተስፋም አፈር ተደፍቶባታል፣እንዲህ ግልጽ የሆነ ጭፍጨፋ እየደረሰብን እንኳ በድፍረት ለመናገር አልፈለጉም፡፡ስለ ኢትዮጵያውያን መገደል ለማውራት ሲፈልጉ ሌላ ሀገር ይጠቅሱና እነሱም እኮ እየተገደሉ ነው ይላሉ፣ወገን ከምንለው የማህበረሰባችን አካል ይሄን መስማቱ ከጥቃቱ ይበልጥ ያማል፡፡
ለምሳሌ ኢቲቪ ስጉዳዩ ሲያወራ ህገ ውጥ ሊባል የሚችል ድርጊት ተፈጽሟል በማለት ነው፡፡ተመልከቱ! እንዴት ያለ ባዕድነት ነው?ኢትዮጵያውያን በድህነትም ውስጥ እንኳ ለክብራችን የመሞት ባህሪ አለን፣ይሄ ከቀደሙት አንጡራ ኢትዮጵያውያን የወረስነውና ዛሬም ያለን ሀብታችን ነው፡፡
ትናንት ፍየል ጠባቂ የነበረ በረኸኛ ይህን ክብራችንን ገፍፎ እንደውሻ ቀጥቅጦ ስርቻ ሲጥለን ያልተቆጣ መንግስት ኢትዮጵያዊ ነው?ከዜጎቹ የወጣና ለህዝቡ የቆመ እውነተኛ መንግስት ከዚህ የበለጠ የሚቆጣበት ጉዳይ ከወዴት ይመጣል?
እውነተኛ መንግስት ቢሆን ኖሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የሳውዲ ካምፓኒዎችን በሰአታት ውስጥ ማባረር፣ኢምባሲውን ዘግቶ አምባሳደሩን ማሰናበትን የመሳሰሉ ውሳኔዎችን ያሳልፉ ነበር፡፡የሆነው ግን በተቃራኒው ነው፣የድፕሎማሲ ግንኙነቴ ሊበላሽ ይችላል ብሎ እኛ ድምጻችን እንዳናሰማ ደበደበን፣አፈነን፡፡በግልጽ እንደሚታየው የጥቅም ትስስሩ ነው አፋቸውን ያዘጋቸው፣ይህች ጥቅማቸው እንዳትቋረጥ በዜጎች ህይዎት መደራደርን መርጠዋል፡፡
ስነ ልቦናቸው የተቃወሰ በመሆኑና ተራ ስስታሞች በመሆናቸው እንጂ ኢንቨስትመንትም ሆነ ዲፕሎማሲ ግብአትነታቸው ለሰው ልጅ ነው፣እንደ አህያ ሲያፈጋ ከርሞ ሬሳቸውን ለላከ መንግስት እንዴት ተመጣጣኝ ምላሽ ለመመለስ ይገዳል?እንዴት እንደ ኢትዮጵያ ያለች ታሪካዊትና ለአፍሪካ የነጻነትና የኩራት ተምሳሌት የሆነች ሀገርን እየመሩ እንዴት ትናንት የነዳጅ ዘይት ባቆማቸው እረኞች ስትዋረድ ዝም ይላሉ?!::
እንዴት!
በዜጎች ህይወት የተደራደረው አገዛዝ ማለፉ አይቀርም፣ለዚህ ጥርጥር የለኝም፡፡ታሪክ ለመጥቀስ ብዙ ርቀት መሄድ አያስፈልግኝም፡፡የቅርብ የሰሜን አፍሪካ አምባገነኖች የከፋ ፍጻሜ አለና፡፡ኢትዮጵያውያን ፍቅርም ጸብም እናውቃለን፣ሳውዲወችም የፈጸሙትን ግፍ ማወራረዳቸው አይቀርም፡፡በዚህ ክፉ ጊዜ ስለስብአዊ መብት ቆመናል የሚሉ አለም አቀፍ ተቋማት ዝምታን መምረጣቸው እውነተኝነታቸውን ለመመርመር ጥሩ እድል ይሰጠናል፡፡
መንግስት ቢኖረን ኖሮ ይሄ ሁሉ ውርደት ይፈጸምብን ነበር ብየ አላስብም፡፡በዚህ ሰአት ርዕሰ-መንግስት ብሆን ኖሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትልቅ ድርጅት እንደመሆኑ፣ወደየትኛውም ሀገር የሚደረገውን ጉዞ አቋርጨ ዜጎቸን ማስወጣትን አስቀድም ነበር፡፡ያሄ ጥቂት ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ ሊያመጣብን ቢችልም ከከፋው የዜጎች ስቃይ ጋር ግን በአንድ ሚዛን ላይ አይቀመጥም፡፡የአደጋ መከላከያና ዝግጁነት ኮሚሽን የሚባል ድርጅት አለ፡፡በዜጎቻችን ላይ ጎርፍና ድርቅ ሲመጣ ብቻ ነው የሚንቀሳቀሰው? ይሄም ሰው ሰራሽ አደጋ ነው ሙሉ ሀይሉን ወደዚህ አዙሮ ሊንቀሳቀስ ይገባው ነበር፡፡
እርግጥ ነው ባቀድነው መሰረት ሰላማዊ ሰልፉ ሙሉ በሙሉ ስኬታማ እንዳይሆን አድርገውታል፡፡ጩኸቱ ግን ይቀጥላል……ባለን አቅም ሁሉ አፈናውንም፣ወከባውንም ተቋቁመን ለዜጎቻችንና ለኢትዮጵያዊነት እንታገላለን፡፡
አገዛዙ ይሄን ሰላማዊ ሰልፍ ሲያፍን ለኢትዮጵያ ህዝብ እንድ መልእክት አስተላልፏል፣ይህን መልእክት እንዲያስትላልፍ ማስገደዳችንም ለኛ ትልቅ ስኬት ነው፡፡የሳውዲ መንግስት ያሻውን ያደርግ ዘንድ የፈቀድኩት እኔ ነኝ፣በመሆኑም እሱን በመቃወም ግንኙነቴን አታበላሹ ብሎ እርምጃ በመውሰዱ ህዝቡ የነገሩ ቁልፍ የት እንዳለ፣የአጥቂወቹ በራስ መተማመን ምን ላይ እንደቆመ በጠራ ሁኔታ ለመመልከት እንዲችል ሆኗል፡፡
ይሄ ሁሉ ነገር እየተፈጸመ የተስተዋለ አንድ ነገር አለ፡፡የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዝምታ እውነተኛ ማንነታቸው፣እውነተኛ በአገዛዙ ውስጥ ያላቸውን ቦታ ያሳየን ክስተት ነው፡፡እንደሚታወቀው እሳቸው በኢህአዲግ እንጂ በኢትዮጵያ ህዝብ የተመረጡ አይደሉም፡፡ኢህአዲግ የሚናገረው ከሌለ እርሳቸው የሚሉት አይኖርም፡፡እንደ አንድ ሀገርና ህዝብ መሪ ግን የመኮነንም ሆነ የማጽናናት ቃል ይጠበቅባቸው ነበር፡፡
ባሉበት ቦታ ያስቀመጣቸው ህወሀት ነው፤ድርጅቱ ደግሞ ይሄን አቋም አልወሰደም፡፡ስለዚህ እንደሚቆጣቸው ስለሚያውቁ ዝምታን መረጡ፣ቸልታንም አስበለጡ፡፡በሀገርም ሆነ በግለሰብ ደረጃ ከዚህ በላይ ሽንፈት ያለ አይመስለኝም፡፡
(ይህ ጽሁፍ በፋክት መጽሄት ተስተናግዷል፣ነገር ግን መጽሄቱ ላልደረሳቸው ሰዎች ይደርስ ዘንድ እዚህ ለማስተናገድ ወደድኩ፡፡)