Friday, October 25, 2013

የኢህአዴግ መንግስት መለያ ባህሪያት

October25/2013

ከአቶ አስገደ ገብረስላሴ (የህወሓት መስራች የነበሩ ከመቀሌ)

1. ህግ የማያከብር መንግስት

የኢህአዴግ መንግስት የፍትህ የዳኝነትና የፖሊስ አካላት እንዲቋቋሙ አድርጓል፡፡ እነዚህ የፍትህ አካላት አንዳንድ የሚወስዱትን ህገ-ወጥ እርምጃ ሳይ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ሳይሆን የኢህአዴግን መንግስት ለሚቃወሙ ግለሰቦች፣ ቡድኖች፣ የፖለቲካ ድርጅቶች በአጠቃላይ የተለየ ሐሳብ የሚያራምዱ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመጫን የተመሰረቱ ይመስሉኛል፡፡ በማንኛውም ወንጀል የተጠረጠረን ግለሰብ ፖሊስ መጀመርያ ግለሰቡን ..ከኢህአዴግ የፖለቲካ ታማኞች.. አንዱ መሆኑን እና አለመሆኑን ከኢህአዴግ ባለስልጣናት ይሁንታ ካላገኘ የማሰር አቅም አይኖረውም፡፡ የፍትህ አካላትም ክስ የሚመሰረቱበትን የግለሰቡን ማንነት አስቀድመው ከኢህአዴግ የፖለቲካ ታማኞች ውጭ መሆኑን ማረጋገጥ የግድ ይላቸዋል፡፡ ዳኞችም እንግዲህ በአንፃሩ ከኢህአዴግ መንግስት በአመለካከት ያልተለዩ ከሆኑ ወንጀል ቢፈፅምም ተጠርጣሪ ጠያቂ አለበት ማለት ይከብዳል፡፡ የፖለቲካ ታማኝነቱ ሳይታወቅ የተከሰሰ ..አባል.. እንኳ በችሎት ላይ እያለም ክሱ እንዲሰረዝለት የሚደረግበት አጋጣሚ አለ፡፡

የኢህአዴግ መንግስት ሁሉም ዜጋ በህግ ፊት እኩል ነው እያለ ሲፅፍና ሲናገር እንሰማለን፡፡ ኢህአዴግ ይህንን ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ በአመለካከት ከኔ እስካልተለያየህ ድረስ ማለቱ እንደሆነ እንረዳለን፡፡ በአስተሳሰብ የተለየ እስካልሆንክ ሰው ብትገድል እንኳ በእርቅ ነፃ መውጣት ትችላለህ፡፡ ስልጣንህን ተገን በማድረግ የህዝብ ንብረትና ገንዘብ ብትዘርፍ ዘመነኛ ተብለህ ልትሸለማለህ ትችል እንደሆነ እንጂ ሙሰኛ አያሰኝህም፡፡

2.ፀረ ዴሞክራሲያዊ መንግስት

የህግ የበላይነት ባልተከበረበት ሀገር ስለዴሞክራሲያዊ መብቶች ማንሳት ተገቢ አይደለም፡፡ ሁለቱን ለብቻቸው ነጥሎ ማየት ሁኔታውን ጎልቶ እንዲታይ ያደርገዋል፡፡ የኢህአዴግ መንግስት ዴሞክራሲ እየገነባ እንደሆነ በየቀኑ ከመቶ ጊዜ በላይ ራሱ በሞኖፖል ይዞ በሚቆጣጠራቸው የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን እየነገረን ነው፡፡ ..ማን ይናገር የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ.. ነው በሚለው ብሂል ሄደን እኔ የምኖርበትን ትግራይ ያለውን ሃቁን ብናይ እንኳን ፍፁም ፀረ-ዴሞክራሲያዊ ተግባራት በላዩ ላይ ተንሰራፍቶበት ይገኛል፡፡ ተቃዋሚዎች መዘጋጃ ቤት ላይ ስብሰባ ህዝቡን ሲጠሩት አስቀድሞ ፖሊሲ በመላክና በማስፈራራት እንዲበተኑ ያደርጋል፡፡ የመንግስት ሰራተኛ ከሆነ በነጋታው ግምገማ እንቀመጥ ተብሎ በተቃዋሚዎች ስብሰባ የተገኘበትን እንደ ምክንያት በመፈለግ እንዲቀጣ ነጋዴ ከሆነ ደግሞ ግብር እንዲጨመርበት ይደረጋል፡፡ በዚህ ምክንያት ሃሳብን በነፃ እንዳይገልፅ ታፍኖ እየኖረ ነው፡፡

ሌላው ይቅርና በየቀኑ ለሚገጥመው ችግር እንኳ አቤት ማለት አይችልም፡፡ በመቀሌ ከተማ ካሉት ችግሮች አንዱ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ነው፡፡ በወር ሁለት ጊዜ ብቻ ውሃ የሚያገኝ ቀበሌ አለ፡፡ ህዝቡ ለእንደዚህ አይነት ችግሮች ለባለስልጣናት አቤት ማለት ሳይፈታ ሲቀርም በሰላማዊ ሰልፍ ችግሩን ለመግለፅ አይፈቀድለትም፡፡ በኑሮ ውድነት አብዛኛው የመቀሌ ህዝብ እየተሰቃየ ባለበት ወቅት ህወሓት/ኢህአዴግ እኛ ከሌለን ትግራይ/ኢትዮጵያ ተበታተናለች፤ ህዝቡም ይጠፋል የሚል መዝሙር እንዲዘመር ያደርጋል፡፡

የመንግስት ሰራተኛው፤ ባለስልጣናት የሚፈፅሙትን የሙስና ቅሌት እያዩ ለማጋለጥ አይችሉም፡፡ በወገን፣ በአድልዎ፣ በዘመድ አዝማድ የማይገባቸውን ጥቅም ሊያገኙ እያዩ እንዳላዩ፣ እየሰሙ እንዳልሰሙ ሆነው ቀኑን እየቆጠሩ ይገኛሉ፡፡

የመንግስት ሰራተኛ የህወሓት/ኢህአዴግ አባል ካልሆነ የተለየ አመለካከት አለው በሚልና ይህ አመለካከት ደግሞ ኢትዮጵያን የሚበታትን፣ የትግራይ /ኢትዮጵያ ህዝብ እንዳይኖር ስለሚያደርግ ግለሂስ አድርግ እየተባለ እየተገደደ ይገኛል፡፡ ይህ ሁሉ ታዲያ ፍፁም ፀረ-ዴሞክራሲ ተግባር አይደለም ትላላችሁ?

3. ወጣቱንና ምሁራኑን የመንግስት ጥገኞች ያደረገ መንግስት

የኢህአዴግ መንግስት የትምህርት ጥራት ዜሮ እንዲሆን በማድረግ ወጣቱ ተወዳዳሪ የሚያደርገውን እውቀትና ክህሎት እንዳይገበይ በማድረግ በራሱ የሚተማመን፣ እሱነቱን የሚያውቅ፣ ለማንም እጅ የማይነሳ የተማረ የሰው ኃይል እንዳይፈራ በማድረግ የወጣቱና የምሁሩ ክፍል ለኢህአዴግ ፓርቲና መንግስት እንዲያጎበድድ በተጨማሪም ጥገኛ እንዲሆን ያደረገው ያላሰለሰ ጥረት ተሳክቶለታል፡፡ በጣም ብዙ ወጣቶች በኮሌጆችና በዩኒቨርስቲዎች ..እንዲያልፉ.. እና ..ምሩቃን..ን ብቻ በማፍራት ከእውቀት ይልቅ ወረቀትን በመስጠት የኢህአዴግ ድርጅት ..ትእዛዝ.. ተጠባባቂ እንዲሆኑ በማድረግ ጥገኛ ኃይል (ጥገኛ ልማታዊ ሰራዊት) እንዲፈጠር እያደረገ ይገኛል፡፡ የኢህአዴግ መንግስት በተለያየ መንገድ ገንዘብ በመሰብሰብ ብድር የሚሰጠው፣ ወለድ የሚሰበስበው ወጣቱን ..አደራጅቶ.. ስራ የሚሰጠው፣ መንገድ ላይ ቆሞ ታክሲዎች ወደ ሰሜን ሂዱ ደቡብ ሂዱ እያለ ትእዛዝ የሚያስተላልፍ፣ ራሱ በሆነበት በአሁኑ ወቅት ወጣቱና ምሁሩ ከመንግስት ..ረጅም እጅ.. ሊያመልጡ በፍፁም አይችሉም፡፡ ለጊዜውም ቢሆን ለኢህአዴግ ታማኝ ካልሆነ ወጣቱ የሚያገኘው ነገር አይኖርም፡፡ በእውቀቱና በችሎታው የሚተማመን ወጣት እንዳይሆን አስቀድሞ ሰርቶታል፡፡

4. ርስተ ጉልት ተመልሶ እንዲመጣ ያደረገ መንግስት

በፊውዳል ስርዓት ጊዜ ፊውዳሎች መሬትን በራሳቸው ቁጥጥር ስር በማዋል የገበሬ ጉልበት ተጠቅመው የዓመት ምግባቸውን ይሰበስቡ ነበር፡፡ ፊውዳሉ ለአንድ ዓመት የሚሸፍን ምግብ ካገኙ ለዘር ማንዘራቸው ብለው የሚሰበስቡት ሃብት አልነበረም፡፡
የኢህአደግ መንግስት ከፊውዳል ስርዓት የሚለየው ከመሬት በሚያገኘው ጥቅም ብቻ ሳይሆን ለዘር ማንዘሩም ጭምር ብሎ ለብዙ ዓመታት የሚሆን የሚሰበስበው ሃብት መኖሩ ነው፡፡ ..መሬት.. የመንግስትና የህዝብ ነው በማለት መሬት ከገበሬዎች እየነጠቀ ቢፈልግ ለራሱ ህንፃ፣ ቢፈልግ ለሃብታሞች በመስጠት፣ የጥቅም ተካፋይ በመሆን፣ ቢፈልግ ለውጭ ዜጐች በመሸጥ በድሃው ህዝብ ሃብታም መንግስት ሊሆን ችሏል፡፡

5. በሉዓላዊነት የማይታመን መንግስት

ኃ/ስላሴ እና የደርግ መንግስታት በሌላ ችግር ካልሆነ በቀር በሀገርና በሉዓላዊነት ጥያቄ ዙሪያ የሚታሙ አልነበሩም፡፡ የኢህአዴግ መንግስት በዚህ ጉዳይ የማይታመን መንግስት ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ኢትዮጵያ በኤርትራ መንግስት ሉአላዊነቷ እንዲደፈርና ባድመን ለሻዕብያ መርቆ የሰጠ መንግስት ነው፡፡ ሻዕብያ ተዳክሞ ለኢትዮጵያ ሰላም አስጊ የማይሆንበት ደረጃ እንዲደርስ አይፈቅድም፡፡ በመሆኑም ኤርትራን የሚያዋስኑ የትግራይና ዐፋር አካባቢዎች በትልቅ ችግር ላይ ወድቀው ይገኛሉ፡፡

6. የግለሰብ ፈላጭቆራጭ የተረጋገጠበት መንግስት

በደርግ ጊዜ መንግስቱ ኃ/ማርያም ብዙ ስልጣን ጠቅልሎ በመያዝ በመዳፉ ስር አስገብቶ ነበር፡፡ ..ከቆራጡ መሪ መንግስቱ ኃ/ማርያም አመራር ጋር ወደፊት..፣ ..ያለጓድ መንግስቱ ኃ/ማርያም ቆራጥ አመራር አብዮቱ ግቡን አይመታም.. ይባል ነበር፡፡ የመንግስቱ ኃ/ማርያም ፎቶ ግራፍ በየመ/ቤቱና አደባባዩ መለጠፍ አንዱ የስርዓቱ መገለጫ ነበር፡፡ አሁን ..ያለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቆራጥ አመራር ኢህአዴግ ሊኖር አይችልም..፣ ..ኢትዮጵያ ትበታተናለች.. እየተባለ እየሰማን ነው፡፡ ኢትዮጵያ ባለሁለት አሃዝ እድገት ለማረጋገጥ የግድ የእርሳቸው አመራር ያስፈልገናል እየተባለ የጠቅላይ ሚኒስቴር ፎቶ ግራፎች በየመ/ቤቱ በየአደባባዩ ይለጠፋል፡፡ በትጥቅ ትግል ጊዜ እንኳን እንደዚህ አይነት የግለሰብ ፈላጭ ቆራጭ አካሄድ ሊኖር ቀርቶ በጊዜው ይታተሙ የነበሩ መጽሐፍት እንኳ ማን እንደፃፋቸው የሚታወቅበት ሁኔታ አልነበረም፡፡ በትጥቅ ትግል ጊዜ በባለስልጣናት መካከል ያለው ግንኙነት እንኳን ብንመለከት የአስተማሪና የተማሪ ዓይነት ነበር፡፡

ጠ/ሚኒስትሩ የኢህአዴግ ም/ቤት ስብሰባን ሲመሩ የስራ ሪፖርት ሲያቀርቡ፣ ግንኙነቱ የጠያቂና የተጠያቂ ሳይሆን እሳቸው እንዳስተማሪ የተቀረው የም/ቤት አባል እንደተማሪ ቁጭ ብሎ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሪፖርት ደብተርና እስክርቢቶ ይዞ መገልበጥ ብቻ ነው፡፡ የሚነሳ ጥያቄ ካለም የቃላትና የፊደል ግድፈቶችን በሚመለከት ብቻ ነው፡፡ ለወደፊትማ ደበተሩ ላይ በደንብ ያልገለበጠ፣ የኢህአዴግ ም/ቤት አባል በማብዛት በምርጫ ጊዜ አባል ያልሆነን እንዴት መቆጣጠር እንዳለባቸው ዝርዝር ስልት በመንደፍ የሚቆጣጠሩት ነው የሚመስለኝ፡፡ የአለፈውን ምርጫ እንኳ ብናይ በየአንዳንዱ ቤት የኢህአዴግን አባል በመመደብ አስቀድመው ማንን ለመምረጥ እንደተዘጋጁ እንዲያስታውቅ አድርገዋል፡፡ መምረጥ የፈለጉትን መናገር ያልፈቀዱ ግለሰቦችን እንደ ተቃዋሚ በመፈረጅ የተለያየ የማስፈራራት እርምጃዎች ፈጽመውባቸዋል፡፡ ከምርጫ በኋላም እንደ ጠላት በመፈረጅ ብዙ ግፍ እያደረሰባቸው ይገኛል፡፡
'
ኢህአዴግ ከሁሉም በላይ የሚጠላው የሓሳብ ልዩነት የሚይዝና የሚያራምድ ህዝብ፣ ግለሰብ፣ ቡድን፣ ፖለቲካዊ ድርጅትን፣ ነው፡፡ ልዩነት የሚያስፈራው የተለየ መንግስት ኢህአዴግ ብቻ ነው፡፡ የሚገርመው ጥይትና መድፍ ሰው ይገድላል ቢባል እንኳን የተለየ ሓሳብ የሚገድለው ፍጡር በሌለበት ምድር ሀሳብን እንደ አጥፊ ማሳሪያ መቁጠር ተገቢ አይደለም፡፡ የኢህአዴግን መንግስት የሚገድለው ከጥይት ይልቅ በሀሳብ ልዩነት መሆኑ ነው፡፡ ኢህአዴግ የሃሳብ ልዩነትን ለመፍራት ምክንያታዊ ነው ባይ ነኝ፡፡ ምክንያቱም ግልጽ ሀሳብና መድረክ ከህዝቡ ከከፈተ ህዝቡ ተቆጥሮ የማያልቅ የኢህአደግን ችግር ያነሳል፡፡ የፍትህ እጦት፣ የሃብትና ገንዘብ ዝርፊያ፣ የመሬት ዝርፊያ፣ አድልዎና ጉበኝነት ወዘተ በማንሳትና ኢህአዴግ ከነዚህ ችግሮች ከባህሪው ስለሚያያዙና ሊመልሳቸው ስለማይችል ለግድያው (ለሞቱ) ምክንያት ስለሚሆኑ ነፃ ሀሳብን ማፈን ይመርጣል፡፡

7. ክህደት በመፈጸም የሚታወቅ መንግስት

በትጥቅ ትግል ጊዜ አንድ አንድ ሰዎች የህወሓትን ስብስብ ..የሰዎች ብስብስ ነው ወይስ ሰዎች መስለው መላእክት ናቸው የተሰባሰቡበት.. የሚል ጥርጣሬ ውስጥ እሁ እስከመግባት ደርሰው እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ እንደ ዛሬ አያድርገውና በጊዜው የህዝብን ችግር ለመፍታት ህወሓት መስዋእትነት ለመክፈል ተወዳዳሪ አልነበረውም፡፡ የህወሓት መሪዎች ታጋዩ ለመስዋእትነት እንደተፈጠረና የሱ መስዋእትነት ሰላም፣ ብልጽግና፣ ለሁሉም ዜጋ እኩል የስራ እድል፣ ትምህርት እንደሚያገኝ፣ በህግ ፊት ሁሉም ዜጋ እኩል እንደሚሆን በማስተማርና በማሳመን ፈንጅ እንዲረግጥ አድርገውታል፡፡ የዚያ ዘመን ትውልድ የመስዋእት ትውልድ እንደሆነ ተቀብሎና አምኖ ታሪክ ሰርቶ አልፎዋል፡፡

አንድ ግዳጅ አለና ቅድሚያ መስዋእት ለመክፈል ዝግጁ የሆነ ማን ነው ተብሎ በሚጠየቅበት ጊዜ ልክ ተማሪዎች ክፍል ውስጥ ጥያቄ ሲቀርብላቸው ለመመለስ እኔ እኔ እያሉ እንደሚሽቀዳደሙ ሁሉ ታጋዩ ለአንዴና ለመጨረሻ ህይወቱን ለመክፈል ይሽቀዳደም ነበር፡፡ አሁን ያለው ሁኔታ ይመጣል ብሎ አልገመተማ፡፡ በዚሁ ጊዜ አድልዎ ተፈጸመ ሊባል የሚችለው ለመስዋእትነት ቅድሚያ አልሰጠም በማለት ታጋዩ ለበላይ አለቃው (ጠርናፊው) ሂስ ማቅረብ ነበር፡፡ እንደ ዛሬ የህዝብና የመንግስት ሃብት መውረር የሚባለ ነገር አልነበረም፡፡

ታጋዩ ለመስዋእትነት ..እኔ ልቅደም.. እና ..የለም እኔ ነኝ መቅደም ያለብኝ.. ሲል ግን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ህይወቱን እያጣ መሆኑን ዘንግቶት አልነበረም፡፡ ዳግም ተመልሶ በሱ መስዋእትነት የተገኘውን ድል እንደማያየው አስረግጦ ያውቅ ነበር፡፡ በእኔ መስዋእትነት ጥቂቶች ያውም ፈንጅ እርገጥ ብለው ትእዛዝ በመስጠት የህዝብ መስዋእትነት ከንቱ ነገር ያተርፉበታል የሚል እምነት አልነበረውም፡፡ መስዋእትነቱን ከድተው በስልጣን ይጨማለቃሉ ብሎ አልገመተም ነበር፡፡ ጀግናው አሞራው በደርግ ቁጥጥር ስር ወድቆ ለምንድን ነው በረሃ የሄድከው ሲሉት እንደሚገድሉት እያወቀ ስልጣኑን በህዝብ ለሚመረጥ መንግስት ለማስረከብ ነው አለ፡፡ ለዚህም መስዋእትነት የግድ እንደሚልና ለመስዋእትነት ዝግጁ እንደሆነ በጠላቶቹ ፊት ሆኖ የመለሰው የውስጡን እምነት ደብቆ ጠላት ወይም ደርግ የሚፈልገውን ሃሳብ ተናግሮ ህይወቱን ማትረፍ አቅቶት አልነበረም፡፡ ወይም ደርግ እንደሚረሽነው ዘንግቶትም አይደለም፡፡ ነገር ግን በእሱ መስዋእትነት ህዝቡ ሰላምና ብልጽግና ያገኛል፤ ሁሉም ዜጋ በነፃ የሚኖርባት ኢትዮጵያ ትመጣለች በሚል ቅንነት ነበር፡፡ ህዝብ የመረጠው መንግስት ይመሰረታል፤ ህዝብ የሚቆጣጠረው መንግስት እንጂ መንግስት ህዝብን የሚቆጣጠርበት እና የሚያስፈራራበት አመራር በእኔ መስዋእትነት ይወገዳል የሚል እምነትም ስለነበረው ነው፡፡ በሱ መስዋእትነት፣ በታጋዮች ቤተሰብ እና በጭቁኑ ህዝብ የተመረጠው መንግስት ህዝብ የሚቆጣጠረው ይሆናል ብሎ ነበር፡፡ በተገላቢጦሽ በዚሁ ጊዜ በጠላትነት ተሰልፈው ይዋጉት የነበሩና አሁን ከመስዋእትነት ከተረፉ በስልጣን ላይ ያሉ ታጋዮች የታጋዩን እናት አባትና ልጆች እንደ ጠላት ፈርጀው ያሰቃዩታል የሚል እምነት አልነበረውም፡፡ ፈንጅ እርገጥ እያሉ መስዋእትነት እንድንከፍል ትእዛዝ ይሰጡን የነበሩ ሰዎች በወላጆቻችንና ልጆቻችን ላይ ክህደት ይፈጽማሉ ብሎ ማን ይገምታል፡፡ ግን በተግባር ክህደት ተፈጸመ፡፡

የታጋዩ እናት ..ልጅሽ በረሃ የገባው ተርቦ ነው እንጂ፤ ለኛ ብሎ አልወጣም.. እየተባለች እያለቀሰች ትገኛለች ፡፡ እነኛ ፈንጅ እርገጥ ካንተ መስዋእትነት በስተጀርባ ድል አለ፤ ብልጽግና አለ ይሉት የነበሩ መሪዎች አሁን በስልጣን ኮርቻቸው ላይ ተፈናጠው ፍጹም ጸረ-ዴሞክራሲና ሙሰኞች ሆነው ይገኛሉ፡፡ ተወዳዳሪ የማይገኝላቸው ጉበኞች ፣ የመሬት ሻጮች ፣ አገር ሻጮች ሆነው አርፈውታል፡፡ ክህደት የፈፀመ ልዩ መንግስት የተባለበትም ለዚሁ ነው፡፡
.

Gov’t bans the travel of citizens overseas for employment (walta info)

October24/2013

Addis Ababa, (WIC) - The government of Ethiopia has temporarily banned the travel of citizens overseas for employment.

It has also provisionally barred the work permit of agencies facilitating such travels.
According to a statement from the Ministry of Foreign Affairs, countless Ethiopians have lost their dear lives and undergone untold physical and psychological traumas due to illegal human trafficking.
And the government has taken various measures to curb the loss incurred due to the problem.
It set up a national council and a taskforce meant to educate the public and caution illegal human traffickers.
The measures taken so far could not help address the problem effectively, the statement said.
Hence, the government has temporarily banned the travel of citizens for employment overseas.
It has also provisionally barred the work permit of agencies facilitating such travels.
The decision is meant to safeguard the wellbeing of citizens and is effective until a lasting solution is sought for the problem.
 

Thursday, October 24, 2013

መላኩ ፈንታ ሥልጣናቸውን መከታ በማድረግ የሶስት ልጆች እናትን ከትዳሯ አፋተው አግብተዋል’’ ዐቃቤ ሕግ

October 24/2013

‘‘መላኩ ፈንታ ሥልጣናቸውን መከታ በማድረግ የሶስት ልጆች እናትን ከትዳሯ አፋተው አግብተዋል’’ ዐቃቤ ሕግ

 የፌዴራሉ የሥነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዐቃቤ ህግ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣናት እና ግብረ አበር ባለሀብቶች ላይ የመሰረተውን ክስ በፍርድ ቤት ማሰማት ጀምሯል። የኮሚሽኑ ዐቃቤ ህግ በተለይም በአንደኛው ተከሳሽ በአቶ መላኩ ፈንታ ላይ መዝገብ ቁጥር 14356 ስር ባለው 11ኛ ክስ ውስጥ ተከሳሹ በትዳር ያለችን ሴት አስኮብልለዋል የሚል ክስ መስርቶባቸዋል።

ትናንት በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ክሱ ሲነበብ፤ 1ኛው ተከሳሽ አቶ መላኩ ፈንታ የስራ ኃላፊነታቸውን በመጠቀም ለስራ ጉዳይ የመጣችን ሴት፤ ትዳሯን ፈታና በትዳር ውስጥ ያፈራቻቸውን ሦስት ልጆች በትና አብራቸው እንድትሆን አድርገዋል ሲል ስልጣንን ያለአግባብ የመጠቀም የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል ሲል ከሷቸዋል።

ወ/ሮ መቅደስ ለማ የተባሉት እኚሁ ሴት የቀድሞ ባለቤታቸውን ንብረት የሆነውን ሳንክቸሪ ኢንተርናሽናል ኃ/የተወሰነ የግል ማህበር በ2001 ዓ.ም የስራ ግብር ለመክፈል ወደገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሲሄዱ 144 ሺህ ብር እንዲከፍሉ በመጠየቃቸውና በዚህም ምክንያት አቤቱታ ለማቅረብ ወደ ምስራቅ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ለአንድ አመት ከ4 ወር መጉላላታቸውን ለማስረዳትና መፍትሄ ለማግኘት ወ/ሮ መቅደስ ለማ የአቤቱታ ደብዳቤ ይዘው ወደተከሳሹ ዘንድ በቀረቡበት ወቅት የፍቅር ግንኙነት መጀመራቸውን በክስ መዝገቡ ያትታል።

በዚህም መሠረት ተከሳሽ የነበረውን ስልጣን መከታ በማድረግ ባለጉዳዩዋ ቀደም ሲል ከከፈሉት ብር ውስጥ አንድ መቶ ሺህ ብር ተመላሽ እንዲሆን አድርጓል፤ በትዳር ውስጥ ያለችን ሴትም አማግጧል ሲል የሙስና ክስ መስርቷል።

ዐቃቤ ህግ በዚህ ክስ ዝርዝር ውስጥ በተጨማሪነትም ተከሳሽ በጋብቻ ውስጥ ያለችን ሴት በመንግስት ተሽከርካሪና ነዳጅ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ክብረ በዓል ላይ እንድትገኝ ከማድረጉም በላይ ቀኑ በውል ባልታወቀበት ዕለትም፤ በጋብቻ ውስጥ የነበረችው መቅደስ ለማን በግል ሾፌሩ አማካኝነት ወደ ባህርዳር ከተማ እንድትሄድ በማድረግ ሰመርላንድ ሆቴል ለአንድ ሳምንት አብረው እያደሩ እና በሾፌሩ አማካኝነት ከተማ ውስጥ ተዝናንታለች ሲል፤ የተፈፀመው ወንጀል መንግስትና ህዝብ የጣለበትን አደራ ያለአግባብ የመጠቀም ሙስና ሰርቷል ይላል። (በእነ መላኩ ፈንታ መዝገብ ሥር ያሉትን 24 ተከሳሾች የክስ ሙሉውን ጭብጥ

  (በእነ መላኩ ፈንታ መዝገብ ሥር ያሉትን 24 ተከሳሾች የክስ ሙሉውን ጭብጥ እነሆ)

ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት
አዲስ አበባ
የፌ/ሥ/ፀ/ሙ/ኮ/መ/ቁ.
የዐ/ህ/መ/ቁ.
የከ/ፍ/ቤ/ወ/መ/ቁ/ 141352
ከሣሽ ………….. የፌደራል የሥነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮማሽን ዐቃቤ ሕግ
ተከሣሾች ……… 1ኛ/ አቶ መላኩ ፈንታ ቻይ
ሥራ፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋ/ዳይሬክተር
2ኛ. አቶ ገ/ዋህድ ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል
ሥራ፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የሕግ ማስከበር ዘርፍ ም/ዋ/ዳይሬክተር
3ኛ. አቶ በላቸው በየነ ገ/ጊዮርጊስ
ሥራ፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
4ኛ. አቶ ማርክነህ አለማየሁ ወዴቦ
ሥራ፡- ም/ዋና ዐ/ሕግ
5ኛ. አቶ እሸቱ ግረፍ አስታክል
ሥራ፡- ገ/ጉ/ባለሥልጣን አ.አ ቃሊቲ ቅርንጫፍ የሕግ ማስከበር ኃላፊ
6ኛ. አቶ አስፋው ስዩም ተፈራ
ሥራ፡- ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት የጣቢያ አስተባባሪ
7ኛ. አቶ ያዴሳ ሚዴቅሳ ዲባባ
ሥራ፡- የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አዳማ ቅ/ፅ/ቤት ሥራ አስኪያጅ
8ኛ. አቶ አስመላሽ ወ/ማርያም ገብሬ
ሥራ- የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት አፈፃፀም የሥራ ሂደት መሪ የነበረ
9ኛ. አቶ ነጋ ገ/እግዚአብሔር ደበበ
ሥራ፡- ነጋዴ
10ኛ. አቶ ከተማ ከበደ አስገልጥ
ሥራ፡- የግል ባለሀብት
11ኛ. አቶ ስማቸው ከበደ ካሳ
ሥራ፡- ነጋዴ
12ኛ. ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ ወርዶፋ
ሥራ፡- ሐኪም
13ኛ. ኮ/ል ኃይማኖት ተስፋዬ ገ/ስላሴ
ሥራ፡- የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ፌዴሬሽን ም/ስራ አስኪያጅ
14ኛ. አቶ ዳንኤል ገ/ኪዳን (ያልተያዘ)
ሥራ፡- የግብር አውሳሰንና ምርመራ ኦዲተር
15ኛ. አቶ አውግቸው ክብረት
ሥራ፡- ዐቃቤ ሕግ
16ኛ. አቶ ጌቱ ገለቴ (ያልተያዘ)
ሥራ፡- ነጋዴ
17ኛ. አቶ ገ/ስላሴ ገብረ ኃ/ማርያም
ሥራ፡- ነጋዴ
18ኛ. ኬኬ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
ሥራ፡- ጄ.ኤች.ሲሜክስ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
19ኛ. ጄ.ኤች ሲሜክስ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
20ኛ. ነፃ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
21ኛ. ጌታስ ኃ/የተ/የግ ማኅበር
22ኛ. ኮሜት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
23ኛ. አቶ ፍፁም ገብረመድህን አብርሃ

ሥራ፡- ነጋዴ

24ኛ. አቶ ወልደስላሴ ወ/ሚካኤል
ሥራ፡- የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አማካሪ

1ኛ ክስ

በ1ኛ፣ 2ኛ እና 10ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ

ወንጀሉ

በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)፣ 33፣ 411(1) (ሐ) እና 2 ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣

የወንጀሉ ዝርዝር

1ኛ እና 2ኛ ተከሣሾች እንደ ቅደም ተከተላቸው በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር እና ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ ሲሆኑ፤ ስልጣንና ኃላፊነታቸውን በመጠቀም የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት በማሰብ፣ 10ኛ ተከሳሽም በመንግስት ሰራተኞች ብቻ በሚፈፀም የሙስና ወንጀል ልዩ ተካፋይ በመሆን፣

- 1ኛና 2ኛ ተከሳሾች በ2001 ዓ.ም በተካሄደው አራጣ አበዳሪዎችን ለሕግ የማቅረብ ተግባር በተጀመረበት ወቅት ለተከሳሹ በጥቆማ መልክ ከቀረቡት ዘጠኝ አራጣ አበዳሪዎች ስም ዝርዝር መካከል 10ኛ ተከሣሽ አራጣ አበዳሪ መሆኑን የሚያስረዱ ማስረጃዎች ቀርበውለት እያለ የተከሳሹ ጉዳይ በምርመራ ተጣርቶ ለሕግ እንዲቀርብ ማድረግ ሲገባው ከዚህ በተቃራኒው ከተከሣሹ ጋር በፈጠሩት ሥውር የጥቅም ግንኙነት ሌሎች አራጣ አበዳሪዎች ምርመራ ተጣርቶባቸው ለሕግ ሲቀርቡ ያለምንም ሕጋዊ ምክንያት 10ኛ ተከሳሽ ላይ ምርመራ እንዳይጣራና ሕግ ፊት ቀርቦ እንዳይጠየቅ በማድረጋቸው፣

- 10ኛ ተከሳሽ በበኩሉ ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ አራጣ አበዳሪነቱን የሚያስረዱ ማስረጃዎች ቀርቦበት እያለና ሌሎች አራጣ አበዳሪዎች ሕግ ፊት ቀርበው ሲከሰሱ ከ1ኛ እና 2ኛ ተከሣሾች ጋር በስውር በፈጠረው ሚስጥራዊ የጥቅም ግንኙት በአራጣ አበዳሪነቱ ምርመራ እንዳይጣራበትና ሕግ ፊት ቀርቦ እንዳይጠየቅ የ1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾችን ሽፋን አግኝቶ ሕገወጥ ተጠቃሚ በመሆኑ፣

በአጠቃላይ ሁሉም ተከሳሾች በሙሉ ፈቃዳቸውና ዕወቀታቸው የወንጀሉ ሙሉ ተካፋይ በመሆን በተሰጣቸው የመንግሥት ኃላፊነት ሊጠብቁትና ሊከላከሉት የሚገባውን የመንግስትና የሕዝብ ጥቅም በሚጎዳ አኳኃን በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት የመንግስት ስራን በማያመች አኳኃን መምራት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።

2ኛ ክስ

በ1ኛ፣ 2ኛ፣ 3ኛ እና 11ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ

ወንጀሉ

በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)፣ 33፣ 411(1) (ሐ) እና 2 ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣

የወንጀሉ ዝርዝር

1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ ተከሣሾች እንደ ቅደም ተከተላቸው በኢትዮጰያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ እና የኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሲሆኑ፣ ስልጣንና ኃላፊነታቸውን በመጠቀም የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት በማሰብ፣ 11ኛ ተከሳሽም በመንግስት ሰራተኞች ብቻ በሚፈፀም የሙስና ወንጀል ልዩ ተካፋይ በመሆን፣

- 1ኛ ተከሣሽ በ2003 ዓ.ም ለሆቴል አገለግሎት የሚውሉ እቃዎችን ከቀረጥ ነፃ ያስገቡ ሆቴሎች ከቀረጥ ነፃ ያስገቡትን ዕቃ ከታለመለት ዓላማ ውጭ እየተገለገሉበት ስለመሆኑ መረጃ ደርሶት ጉዳዩ በባለሥልጣኑ የኢንተለጀንስ ክፍል ጥናት እንዲደረግ ተወስኖ ጥናትና የኦዲት ክትትል ከተደረገ በኋላ ጥናት ከተደረገባቸው ሆቴሎች መካከል አንዱ ጄ.ኤች ሲሜክስ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር (ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል) ሲሆን በተካሄደው ጥናትና የኦዲት ክትትል መሠረት ወንጀል መፈፀሙን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች ቀርቦ እያለና ሌሎች ተመሣሣይ ድርጊት የፈፀሙ ሆቴሎች ምርመራ እንዲጣራባቸው ሲደረግ የ11ኛ ተከሣሽ ሆቴል ከቀረጥ ነፃ ያስገባቸውን ዕቃዎች ለተፈለገው ዓላማ አለማዋሉን በ26/11/2002 እና በ19/16/03 ዓ.ም በተደረገው ቆጠራ በማስረጃ ተረጋግጦ እያለ ከ11ኛ ተከሣሽ ጋር በስውር በመመሣጠር የተፈፀመው ሕገወጥ ድርጊት ምርመራው እንዳይጀመርና ተከሳሹ ለሕግ እንዳይቀርብ በማድረጉ፣

- 2ኛ ተከሣሽ በበኩሉ ከላይ በተ.ቁ. 1 በተጠቀሰው ጊዜና አኳሃን የ11ኛ ተከሣሽ ሆቴል ከቀረጥ ነፃ ያስገባቸውን ዕቃዎች ለተፈለገው ዓላማ አለማዋሉን በተካሄደው ቆጠራ ተረጋግጦና ሌሎች ተመሣሣይ ድርጊት የፈፀሙ ሆቴሎች ምርመራ እንዲጣራባቸው ሲያደርግ ከ11ኛ ተከሳሽ ጋር በስውር በመመሳጠር ከላይ በተጠቀሰው ሆቴል ላይ ምርመራው እንዳይጀመርና ለሕግ እንዳይቀርብ በማድረጉ፣

- 3ኛ ተከሣሽ በበኩሉ ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና አኳኃን የ11ኛ ተከሣሽ ሆቴል ከቀረጥ ነፃ ያስገባቸውን ዕቃዎች ለተፈለገው ዓላማ ማዋል አለማዋሉን ለማረጋገጥ ቡድን አቋቁሞ ወደ ሆቴሉ በመላክ በተደረገው ቆጠራ ብር 9‚981‚651.83 (ዘጠኝ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሰማንያ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ አንድ ብር ከ83/100) ከቀረጥ ነፃ ያስገባቸውን ዕቃዎች ለተፈለገው ዓላማ አለማዋሉን በቡድኑ ተረጋግጦ እያለ ተከሣሹ አቤቱታ እንዲያቀርብና ድጋሚ ቆጠራ እንዲደረግ ከማድረጉም በላይ በድጋሚ ቆጠራውም ብር 8‚716‚012.84 (ስምንት ሚሊዮን ሰባት መቶ አስራ ስድስት ሺህ አስራ ሁለት ብር ከ84 ሳንቲም) እንዲከፍል በመወሰን ድርጅቱ ምርመራ እንዳይጣራበትና በወንጀል እንዳይከሰስ ሁኔታዎችን በማመቻቸቱ፣

- 11ኛ ተከሳሽ በበኩሉ ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና አኳኃን ለድርጅቱ መገልገያ የሚሆኑ የሆቴል ዕቃዎች ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገባ ተፈቅዶለት አስገብቶ ለተፈቀደለት ዓላማ ማዋል ሲገባው ከተፈቀደለት ዓላማ ውጭ መጠቀሙን በገ/ጉ/ባለሥልጣን ባለሙያዎች ተረጋግጦ እያለ በፈፀመው ድርጊት በወንጀል መጠየቅ ሲገባው ከ1ኛ-3ኛ ከተጠቀሱት ተከሣሾች ጋር በጥቅም በመመሣጠር ከ1ኛ እስከ 3ኛ የተጠቀሱት ተከሳሾችን ሽፋን አግኝቶ በወንጀል እንዳይጠየቅ በማድረግ ሕገወጥ ተጠቃሚ በመሆኑ፣
በአጠቃላይ ሁሉም ተከሳሾች በሙሉ ፈቃደቸውና ዕውቀታቸው የወንጀሉ ሙሉ ተከፋይ በመሆን በተሰጣቸው የመንግሥት ኃለፊነት ሊጠብቁትና ሊከላከሉት የሚገባውን የመንግስትና የሕዝብ ጥቅም በሚጎዳ አኳኃን በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት የመንግስት ስራን በማያመች አኳሃን መምራት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
3ኛ ክስ

በ1ኛ፣ 2ኛ፣ እና 12ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ

ወንጀሉ

በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)፣ 33፣ 411(1) (ሐ) እና 2 ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣

የወንጀሉ ዝርዝር

1ኛ እና 2ኛ ተከሣሾች እንደ ቅደም ተከተላቸው በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር እና ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ ሲሆኑ፤ ስልጣንና ኃላፊነታቸውን በመጠቀም የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት በማሰብ፣ 12ኛ ተከሳሽም በመንግስት ሰራተኞች ብቻ በሚፈፀም የሙስና ወንጀል ልዩ ተካፋይ በመሆን፣

- 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች 12ኛ ተከሳሽ ጥቅምት 20 ቀን 2003 ዓ.ም በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ከስዊድን ሀገር ወደ ኢትዮጵያ ምንም ዓይነት የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ያልተፈፀመባቸውንና ገደብና ቁጥጥር የሚደረግባቸውን 32 ዓየነት የተለያዩ ብዛት ያላቸው የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎችን በአራት ሻንጣ ሲያስገባ ተይዞ 5% ቀረጥና ታክስ ከፍሎ ወደ መጣበት ሀገር እንዲመልስ ተወስኖ ሕዳር 1 ቀን 2003 ዓ.ም ታግ ተለጥፎበት ቤልት ላይ ከገባ በኋላ ከሀገር እንዲወጣ የተባለውን ዕቃ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ደብቆ መልሶ ወደ ሀገር ውስጥ ሊያስገባ ሲል ተይዞ በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 9/1/ የተመለከተውን በመተላለፍ በፈፀመው የኮንትሮባንድ ወንጀል በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተከሶ ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን ማስረጃ ሰምቶ ካጠናቀቀ በኋላ ለፍርድ ተቀጥሮ ባለበት ሁኔታ ከተከሳሹ ጋር በፈጠሩት ሕግ ወጥ የጥቅም ግንኙነት እንዳይቀጣ በማሰብ ለፍርድ የተቀጠረውን ክስ ያለ ሕጋዊ ምክንያት እንዲነሳ በማድረጋቸው፣

- 12ኛ ተከሣሽም በፈፀመው ወንጀል ተከሶ የነበረ ቢሆንም ከ1ኛ እና የ2ኛ ተከሳሾች ጋር በፈጠረው የጥቅም ግንኙነት የተከሳሾችን ሽፋን አግኝቶ ክሱን በማስነሳት ሕገወጥ ተጠቃሚ በመሆኑ፣

በአጠቃላይ ሁሉም ተከሣሾች በሙሉ ፈቃዳቸውና ዕውቀታቸው የወንጀሉ ሙሉ ተካፋይ በመሆን በተሰጣቸው የመንግሥት ኃላፊነት ሊጠብቁትና ሊከላከሉት የሚገባውን የመንግስትና የህዝብ ጥቅም በሚጎዳ አኳኃን በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት የመንግስት ስራን በማያመች አኳኃን መምራት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።

4ኛ ክስ

በ1ኛ፣ 2ኛ፣ 8ኛ፣ 9ኛ፣ 16ኛ፣ 17ኛ እና 24ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ

ወንጀሉ

በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)፣ 33፣ 411(1) (ሐ) እና 2 ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣

የወንጀሉ ዝርዝር

1ኛ፣ 2ኛ፣ 8ኛ እና 24ኛ ተከሣሾች እንደ ቅደም ተከተላቸው በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ፤ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት አፈፃፀም የሥራ ሂደት መሪ እና 24ኛ ተከሳሽ ደግሞ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አማካሪ ሲሆኑ፣ ስልጣንና ኃለፊነታቸውን በመጠቀም የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት በማሰብ፣ 9ኛ፣ 16ኛ እና 17ኛ ተከሳሾችም በመንግስት ሰራተኞች ብቻ በሚፈፀም የሙስና ወንጀል ልዩ ተካፋይ በመሆን፣

ከ1999 ዓ.ም እስከ 2000 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት በሀገሪቱ ተከስቶ የነበረውን የሲሚንቶ እጥረትና ዋጋውን ለማረጋጋት ከውጪ አገር ያለ ውጪ ምንዛሪ ክፍያ ከቀረጥ ነፃ ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ለሀገራዊ የቤቶች ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ ላይ ለማዋል ታሰቦ የገባው ሲሚንቶ ከታለመለት ዓላማ ውጪ ለ3ኛ ወገን በመተላለፉ ቀኑና ወሩ ለጊዜው ባልታወቀበት 2002 ዓ.ም ለ2ኛ ተከሳሽ እና እሱ ለሚመራው የሕግ ማስከበር ዘርፍ ጥቆማ ተደርጎ የብር 21‚602‚608.64 /ሃያ አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ስምንት ብር ከ64/100/ ቀረጥና ታክስ ባለመከፈሉ በመንግስት ላይ ጉዳት መድረሱ በመረጋገጡ ውሉን የተዋዋለው አቅራቢው ድርጅት፣ ትራንዚተሮች፣ ሲሚንቶውን በትራንስፖርት አስገብተው ለ3ኛ ወገን አሳልፈው የሰጡ አጓጓዥ ድርጅቶች እና ስራ አስኪያጆቻቸው ወይም ባለንብረቶቻቸው እንዲሁም ቁጥጥርና ክትትል ያላደረጉት የጉምሩክ ሰራተኞች ጭምር ተጠያቂ መሆናቸው በኣዲት ተረጋግጦ ቀርቦ እያለ ይህንኑ መነሻ በማድረግ ምርመራ በማጣራት አጥፊዎችን ለሕግ እንዲቀርቡ ማድረግ ሲገባቸው ከዚህ በተቃራኒው በመስራት ሕገወጥ ተጠቃሚ ለመሆን በማሰብ፣

- 1ኛ ተከሳሽ የመ/ቤቱ የበላይ ኃላፊ እንደመሆኑ የመ/ቤቱ ሰራተኛ የሆነው 8ኛ ተከሳሽ በደንብ ቁጥር 155/2000 መሰረት በፈፀመው ድርጊት በወንጀል እና በዲሲፒሊን እንዲጠየቅ ማስደረግ ሲገባው በፈፀመው ድርጊት እንዳይጠየቅ ከማድረጉም በተጨማሪ በዐቃቤ ሕግ በኩል ክሱ ሲቀርብበትም ተከሳሹን ለሕግ ማቅረብ ሲገባው ስራውን እንዲለቅ ማመልከቻ እንዱያቀርብ ሁኔታዎችን በማመቻቸቱና ሊጠየቁ በሚገባቸውም ሲሚንቶውን ባስገቡትና ባጓጓዙት በሁሉም የትራንስፖርት ድርጅቶች ላይ ክስ እንዲቀርብ ባለማስደረጉ፤

- 2ኛው ተከሳሽ በበላይነት በሚመራው የስራ ዘርፍ ምርመራው ሲጣራና ክሱ ሲቀርብ የባለስልጣኑ መ/ቤት ሰራተኛ የሆነው 8ኛ ተከሳሽ ቃሉን እንዳይሰጥ በማስደረግ፣ ደመወዝ እየተከፈለው ስራ ላይ ያለ ሰራተኛ መሆኑን እያወቀ ያለአግባብ በጋዜጣ ሲጠራም በዝምታ በማለፍ በመጨረሻም ከ1ኛው ተከሳሽ ጋር ተመካክሮ ተከሳሹ ስራውን እንዲለቅ በማስደረጉ እንዲሁም ሊከሰሱ ከሚገባቸው የትራንስፖርት ድርጅቶችና ባለንብረቶች ጋር ባለው ስውር የጥቅም ግንኙነት ምክንያት የራሱና የሌሎችን ጥቅም በሕገወጥ መንገድ ለማራመድ በማሰብ ጉዳዩን እንዲያጣራ ምንም ኃለፊነት ካልተሰጠው የደህንነት መ/ቤት ከፍተኛ አመራር ከሆነው 24ኛ ተከሳሽ ጋር በመሆን ጉዳዩን የሚያውቁ ሰዎችን እያስቀረበ ከመረመረ በኋላ ወንጀል የተፈፀመበት ሲሚንቶ የሌላ ሰው ነው ብላችሁ መስክሩ በማለት የጉዳዩን አቅጣጫ እሱ በሚፈልገው መንገድ እንዲሄድ ከመገፋፋቱም በላይ ኤ ኤንድ ጂ ድርጅት፣ ኃይሌ አሰፋ እና ሸሚዛል በተባሉት 3 ድርጅቶች ላይ ብቻ ምርመራው ተጣርቶ ክሱ እንዲቀርብ ሲያስደርግ ከእሱ ከ24ኛ ተከሳሽ ጋር የጥቅም ግንኙነት ባላቸው 1ኛ. ነፃ ትራንስፖርት ድርጅት እና የድርጅቱ ባለቤት የሆነው 9ኛ ተከሳሽ፣ 2ኛ. ጌታስ የተባለው ድርጅት እና የድርጅቱ ባለቤት የሆነው 16ኛ ተከሳሽ እና 3ኛ. ኮሜት ትራንስፖርት ድርጅት እና የድርጅቱ ባለቤት የሆነው 17ኛ ተከሳሽ ላይ ተነጥሎ ምርመራ እንዳየጣራባቸው በማስደረጉ፤- 24ኛ ተከሳሽም በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መ/ቤት ውስጥ ከፍተኛ መዋቅር ላይ ተመድቦ ሲሰራ ይህን ስልጣንና ኃላፊነቱን አለአግባብ መከታ በማድረግ ከቀረጥ ነፃ የገበያ ሲሚንቶ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ለገቢዎችና ጉምረክ ባለስልጣን የቀረበውን ጥቆማና ምርመራ እንዲከታተል ከመ/ቤቱ ባልተወከለበት ሁኔታ የራሱና የሌሎችን ጥቅም በሕገወጥ መንገድ ለማራመድ በማሰብ በተለያዩ ቅናት 2ኛ ተከሣሽቢሮ ድረስ በመሄድ ጉዳዩን የሚያውቁ ሰዎችን እያስቀረበ ከመረመረ በኋላ ወንጀል የተፈፀመበት ሲሚንቶ የሌላ ሰው ነው ብላችሁ መስክሩ በማለት የጉዳዩን አቅጣጫ እሱ በሚፈልገው መንገድ እንዲሄድ ሙከራ ከማድረጉም በላይ ኤ ኤንድ ጂ ድርጅት፣ ኃይሌ አሰፋ እና ሸሚዛል በተባሉት 3 ድርጅቶች ላይ ብቻ ምርመራው ተጣርቶ ክሱ እንዲቀርብ ሲያስደርግ ከእሱና ከ2ኛ ተከሳሽ ጋር የጥቅም ግንኙነት ባላቸው 1ኛ. ነፃ ትራንስፖርት ድርጅት እና የድርጅቱ ባለቤት የሆነው 9ኛ ተከሳሽ፣ 2ኛ. ጌታስ የተባለው ድርጅት እና የድርጅቱ ባለቤት የሆነው 1ኛ ተከሳሽ እና 3ኛ. ኮሜት ትራንስፖርት ድርጅት እና የድርጅቱ ባለቤት የሆነው 17ኛ ተከሳሽ ላይ ተነጥሎ ምርመራ እንዳይጣራባቸው በማስደረጉ፤

- 8ኛ ተከሳሽ በዚህ ጉዳይ ተከሶ ፍ/ቤት እንዲቀርብ የታዘዘ ቢሆንም ከ1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ጋር ባለው የጥቅም ትስስር እና የነሱን ሽፋን ተጠቅሞ ፍ/ቤት ቀርቦ እንዳይጠየቅ በማስደረጉ፣

- 9ኛ፣ 16ኛ እና 17ኛ ተከሳሾችም ከቀረጥ ነፃ የገባ ሲሚንቶ አጓጉዘው ከታለመለት ዓላማ ውጪ ለ3ኛ ወገን ለመሸጣቸው ተረጋግጦ እያለ ከ2ኛ ተከሳሽ ጋር ባላቸው የጥቅም ትስስር ምክንያት በምርመራው እንደይካተቱ የ2ኛ ተከሳሽን ሽፋን አግኝተው በሕግ እንዳይጠየቁ በማስደረጋቸው፣ ሁሉም ተከሳሾች ሊጠብቁትና ሊከላከሉት የሚገባውን የመንግስትና የህዝብ ጥቅም በሚጎዳ አኳሃን በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈፀሙት የመንግስት ስራን በማያመች አኳሃን መምራት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።

5ኛ ክስ

በ1ኛ፣ እና 2ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ

ወንጀሉ

በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)፣ 33፣ 411(1) (ሐ) እና 2 ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣

የወንጀሉ ዝርዝር

ተከሣሾች እንደ ቅደም ተከተላቸው በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር እና ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ ሲሆኑ፤ ስልጣንና ኃላፊነታቸውን በመጠቀም የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት በማሰብ፣

- 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ኢኖቫ ፓኬጂንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር እ.ኤ.አ በ2009 ለመንግስት መከፈል የነበረበትን ገቢ ግብር ብር 2‚088‚328.72 (ሁለት ሚሊየን ሰማንያ ስምንት ሺህ ሦስት መቶ ሃያ ስምንት ብር ከሰባ ሁለት ሳንቲም) ግብርን አሳውቆ ባለመክፈሉ እና ዓመታዊ ትርፉ 11‚448‚939.30 (አሥራ አንድ ሚሊዮን አራት መቶ አርባ ስምንት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ዘጠኝ ብር ከሰላሳ ሳንቲም) ሆኖ እያለ በበጀት ዓመቱ ያሳወቀው ግብር ብር 9‚569‚671.05 (ዘጠኝ ሚሊዮን አምስት መቶ ስልሣ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ ሰባ አንድ ብር ከዜሮ አምስት ሣንቲም) ነው ብሎ አሳሳች ማስረጃ በማቅረቡ በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 96፣ 102፣ 97/1/ እና 3(ለ) የተመለከተውን ተላልፎ ሕግን በመጣስ ግብር አለመክፈልና አሳሳች መረጃ ማቅረብ ተደራራቢ ወንጀል ፈፅሟል ተብሎ በድርጅቱና በድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ላይ በፌ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ክስ ተመስርቶ እያለ ድርጅቱና የድርጅቱ ስራ አስኪያጅን ከወንጀል ተጠያቂነት ለማዳን በማሰብ 2ኛ ተከሳሽ ክሱ እንዲነሳ ለ1ኛ ተከሳሽ በ7/2/2005 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ የውሳኔ ሀሳብ አቅርቦ 1ኛ ተከሳሽ አፅድቆ ያለምንም ሕጋዊ ምክንያት ክሱን እንዲነሳ በማድረጋቸው፣ ሁለቱም ተከሣሶች በሙሉ ፈቃደቸውና ዕውቀታቸው የወንጀሉ ሙሉ ተካፋይ በመሆን በተሰጣቸው የመንግሥት ኃላፊነት ሊጠብቁትና ሊከላከሉት የሚገባውን የመንግሰትና የሕዝብ ጥቅም በሚጎዳ አኳሃን በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት የመንግስት ስራን በማያመች አኳሃን መምራት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።

6ኛ ክስ

በ2ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ

ወንጀሉ

በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)፣ 33፣ 411(1) (ሐ) እና 2 ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣

የወንጀሉ ዝርዝር

ተከሳሹ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ ሲሆን፤ ስልጣንና ኃለፊነቱን በመጠቀም የማይገባ ጥቅም ለራሱ ለማግኘት ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት በማሰብ፣

- 2ኛ ተከሣሽ በ26/07/2001 ዓ.ም ጐላጐል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር የተባለ ድርጅት ያለቫት ደረሰኝ ግብይት እንደሚፈፅም ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ጥቆማ ቀርቦ እውነተኛነቱን ለማረጋገጥ የባለሥልጣኑ ሠራተኞች ተልከው እንደጥቆማው አቀራረብ እንደሚፈፅም በወቅቱ በተላኩት ሠራተኞች ከተረጋገጠና ተጠርጣሪዎችም ከተለዩና ምርመራ መዝገቡ ተደራጅቶ እንደሚያስከስስ ከተረጋገጠ በኋላ ተከሣሹ የባለሥልጣኑ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የድርጅቱ ባለቤት አቤቱታ ስላቀረበ ጉዳዩ በድጋሚ መታየት አለበት በሚል ሽፋን ምርመራው እንደገና እንዲጣራ በማድረግ ቀደም ሲል በጉዳዩ ዙርያ ከተሰጠው የምስክርነት ቃል በተለየ ጉዳዩን ሊያዳክም የሚችል አዲስ ተጨማሪ ቃል እንዲቀርብ በማድረግ መዝገቡ ውጤት እንዳይኖረው ካመቻቸ በኋላ ምርመራ መዝገቡ እንዲዘጋ በማስደረጉ፣ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈፀመው የመንግስት ሥራን በማያመች አኳሃን መምራት የሙስና ወንጀል ተከሷል።

7ኛ ክስ

በ2ኛ፣ እና 7ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ

ወንጀሉ

በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)፣ 33፣ 411(1) (ሐ) እና 2 ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣

የወንጀሉ ዝርዝር

ተከሣሾች እንደ ቅደም ተከተላቸው በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ እና የአዳማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ ሲሆኑ፤ ስልጣንና ኃለፊነታቸውን በመጠቀም የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት በማሰብ፤

- ገላን ታነሪ ኃ/የተ/የግ ማኅበር የተባለው ድርጅት በዲክላራሲዮን ቁጥር E-3248/1 ወደ ውጭ ለመላክ ዲክሌር ያደረገው የቆዳ ብዛት 33‚600.00 (ሰላሳ ሦስት ሺህ ስድስት መቶ) ሆኖ በአዳማ ገቢዎችና ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ11/03/04 ፍተሻ በሚደረግበት ጊዜ ብዛቱ 42‚360 (አርባ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ስልሳ) ሆኖ በመገኘቱ ምክንያት በልዩነት ለተገኘውና ግምቱ ብር 423‚189.94 (አራት መቶ ሃያ ሦስት ሺህ አንድ መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ከ94/100) ለሆነው 8‚760 (ስምንት ሺህ ሰባት መቶ ስልሳ) ቀዳ በድርጅቱ እና በድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ አህመድ ኑር ሐሰን ላይ የወንጀል ምርመራ ተጣርቶ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዐቃቤ ሕግ በቁጥር 8-54593/04 በ26/08/2004 የተዘጋጀ ክስ አቅርቦባቸው እያለ፤

7ኛ ተከሳሽ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በነበረው ኃላፊነት ባለሀብቱ ወደ ውጪ ለመላክ ባቀረበው ቆዳ ላይ ፍተሻ በሚደረግበት ወቅት ቆዳ በትርፍነት የተገኘበትና ምርመራም የተጣራበት መሆኑን እያወቀ ባለሀብቱንና ድርጅቱን ከተጠያቂነት ለማዳን አስቀድሞ በቁ.8.0/0/1048 በ12/06/04 ለድርጅቱ በፃፈው ደብዳቤ ጉዳዩን ለዐቃቤ ሕግ እንደማይልክ ከመግለፁም በተጨማሪ በባለሀብቱ ላይ የቀረበው ክስ እንዲነሳ የሚጠይቅ የውሳኔ ሀሳብ በ15/09/04 በተፃፈ ቃለ ጉባኤ ለ2ኛ ተከሳሽ በማቅረቡ፣ 2ኛ ተከሳሽ በበኩሉ ባለሀብቱ የማታለል ድርጊት በመፈፀም ቆዳ በትርፍነት ለመላክ ሲሞክር መያዙን እያወቀ በባለሀብቱ ላይ የተመሰረተው ክስ የሚነሳበት ሕጋዊ ምክንያት በሌለበት ሁኔታ ከባለሀብቱ ጋር በጥቅም በመመሳጠር በባለሀብቱ ላይ የቀረበው ክስ እንዲቋረጥ በ24/09/04 ትዕዛዝ በመስጠት ክሱ እንዲነሳ በማድረጉ፣ ሁለቱም ተከሳሾች ባለሀብቱ በሕግ እንዳይጠየቅና በትርፍነት የተገኘው ቆዳ ላይም እርምጃ እንዳይወሰድ በማድረጋቸው፣ በተሰጣቸው የመንግሠት ኃላፊነት ሊጠብቁትና ሊከላከሉት የሚገባውን የመንግስትና የሕዝብ ጥቅም በሚጎዳ አኳሃን በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት የመንግስት ስራን በማያመች አኳሃን መምራት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።

8ኛ ክስ

በ2ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ

ወንጀሉ

በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)፣ 33፣ 411(1) (ሐ) እና 2 ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣

የወንጀሉ ዝርዝር

ተከሳሹ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ ሲሆን፤ ስልጣንና ኃላፊነቱን በመጠቀም የማይገባ ጥቅም ለራሱ ለማግኘት ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት በማሰብ፣

- 2ኛ ተከሣሽ አቢ ብርሃኑ የተባለ ግለሰብ ተገቢው ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸውን የሰሌዳ ቁ.ኮድ 3-48863 አ.አ. እና ተላላፊ ሰሌዳ ቁ.545 አ.አ. የሆኑ ሁለት ተሽከርካሪዎች ይዞ በ30/01/2001 ዓ.ም በመገኘቱ ምክንያት ከሌላ ግብረአበሩ ጋር ምርመራ ተጣርቶበት መዝገቡ ለሚመለከተው ዐቃቤ ሕግ ከተላለፈ በኋላ ተከሳሹ ሥልጣኑን በመጠቀም በመዝገቡ ውስጥ 1ኛ ተጠርጣሪ ከሆነው አቢ ብርሃኑ ከተባለው ተጠርጣሪ አባት አቶ ብርሃኑ ብሩ ጋር ባለው የጥቅም ትስስር ጉዳዩ ወደ ፍ/ቤት እንዳይሄድና መኪናውም እንዲለቀቅ ለማድረግ ከተያዙት ሁለት መኪኖች ውስጥ ኮድ 3-48863 አ.አ የሆነው መኪና በአዋጅ ቁ. 60/89 አንቀፅ 74 መሠረት መወረስ እየተገባው ቀረጥና ታክሱ ተከፍሎ እንዲለቀቅ በማድረግ በዚህም መነሻነት የወንጀል መዝገቡ እንዲዘጋ በማድረጉና ለዚህም ውለታው በአሁኑ አጠራር ለገጣፎ ለገዳዲ በቀድሞ ስሙ ወልገወ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ሊቀመንበር በነበረው አቶ ብርሃኑ ብሩ አማካኝነት በአሁኑ ሰዓት ሊገኝ ያልቻለ ሕገ ወጥ የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያ በመስጠትና በዚህም መታወቂያ መነሻነት በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ 500 ካ.ሜ ቦታ በሕገወጥ መንገድ በመውሰዱ፣ በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀመው የመንግስት ሥራን በማያመች አኳሃን መምራት የሙስና ወንጀል ተከሷል።

9ኛ ክስ

በ2ኛ፣ 4ኛ፣ 5ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ

ወንጀሉ

በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)፣ 33፣ 411(1) (ሐ) እና 2 ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣

የወንጀሉ ዝርዝር

ተከሣሶች እንደ ቅደም ተከተላቸው በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ፣ ምክትል ዋና ዐቃቤ ሕግ፣ በዐቃቤ ቃሊቲ ቅ/ፅ/ቤት የሕግ ማስከበር ኃላፊ እና የድሬ ዳዋ ቅ/ፅ/ቤት የጣቢያ አስተባባሪ ሲሆኑ፤ ስልጣንና ኃለፊነታቸውን በመጠቀም የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት በማሰብ፣
6ኛ ተከሳሽ በ8/8/2002 ዓ.ም በባለሥልጣኑ አዋሽ መቅረጫ ጣቢያ ማንነቷ ለጊዜው ካልታወቀች ግለሰብ ላይ በፍተሻ ከተያዙ ኮንትሮባንድ ካሜራዎች ውስጥ ሦሰት ሶኒ ጂጅታል ካሜራዎችን ወስዶ ለግል ጥቅሙ ማዋሉ ታውቆ ምርመራ መጣራት ሲጀመርበት፡-

- 5ኛ ተከሣሽ የባለስልጣኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዐቃቤ ሕግ የሆኑትን አቶ ምንይችል ተኮላ ጋር ስልክ ደውሎ “6ኛ ተከሳሽ ለምን ታሰረ? እንዲፈታ!” ብሎ በቃል ትዕዛዝ ከማስተላለፉም በላይ በአካል ከሥፍራው ድረስ በመሄድ ምርመራው እንዳይጣራ ለፍ/ቤት በቃል አመልክቶ እንዲፈታ በማስደረጉ፣

- 4ኛ ተከሣሽ ምርመራ እንዲጣራ ትዕዛዝ ሰጥተው ለነበሩት ዐቃቤ ሕግ አቶ አምደሚካኤል ጌታቸው የስልክ ትዕዛዝ በመስጠት በ6ኛ ተከሣሽ ላይ ምርመራ እንዳይጀመር በማድረጉ፣- 2ኛ ተከሳሽ 6ኛ ተከሣሽ በተጠረጠረበት ብልሹ አሰራርና የሙስና ወንጀል በባለሥልጣኑ ደንብ ቁጥር 155/2000 አንቀጽ 37/1/ መሠረት የዲሲፒሊን እርምጃ እንድወሰድና ለሕግም እንዲቀርብ ማስደረግ ሲገባው በስራው ላይ እንዲቆይና በሕግም እንዳይጠየቅ በማድረጉ፤

- 6ኛ ተከሳሽ በዚህ ጉዳይ ታስሮ ምርመራው የተጀመረበት ቢሆንም ከ2ኛ፣ 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች ጋር ባለው የጥቅም ትስስር ምክንያት የነሱን ሽፋን ተጠቅሞ ምርመራው እንዲቋረጥለት በማስደረግ ሕገወጥ ተጠቃሚ በመሆኑ፣

በአጠቃላይ ሁሉም ተከሣሾች በሙሉ ፈቃዳቸውና ዕውቀታቸው የወንጀሉ ሙሉ ተካፋይ በመሆን በተሰጣቸው የመንግሥት ኃላፊነት ሊጠብቁትና ሊከላከሉት የሚገባውን የመንግስትና የህዝብ ጥቅም በሚጎዳ አኳሃን በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈፀሙት የመንግስት ስራን በማያመች አኳሃን መምራት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።

10ኛ ክስ

በ6ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ

ወንጀሉ

በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 413/1/ሀ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣

የወንጀሉ ዝርዝር

ተከሣሹ በኢት/ገ/ጉ/ባለሥልጣን የአዋሽ መቅረጫ ጣቢያ አስተባባሪ ሆኖ ሲሰራ የማይገባ ቁሳዊ ጥቅም ለራሱ ለማግኘትና ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት አስቦ በ8/8/2002 ዓ.ም ስሟ ለጊዜው ያልታወቀች ኮንትሮባንዲስት ከጅጅጋ ወደ አዲስ አበባ በሚጓዝ ተሽከርካሪ ተሳፍራ ስትመጣ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን አዋሽ መቅረጫ ጣቢያ ላይ በተደረገባት ፍተሻ ሦስት ሶኒ ዲጅታል ካሜራ ተይዞባት በደረሰኝ ቁጥር 849781 ተመዝግቦ የነበረውን ደረሰኝ እንዲሰረዝ (void እንዲሆን) በማድረግና በማስደረግ ወስዶ ለግል ጥቅሙ በማዋሉ በፈፀመው በሥራ ተግባር ላይ የሚፈፀም የመውሰድና የመሰወር የሙስና ወንጀል ተከሷል።

11ኛ ክስ

በ6ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ

ወንጀሉ'

በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 408(1) ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣

የወንጀሉ ዝርዝር

ተከሳሹ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት የላጋር መቅረጫ ጣቢያ አስተባባሪ ሆኖ ሲሰራ በኃላፊነቱ እና በሥራ ግዴታው ማድረግ የማይገባውን በማድረግ ሕገወጥ ጥቅም ለማግኘት አስቦ፤
- ቀኑ በውለ ተለይቶ ባልታወቀበት ጥር ወር 2005 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ ድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 03 ፖሊስ መምሪያ አካባቢ ወደ ኮንደሚኒየም በሚወስደው መንገድ ላይ ኤምዲ (MD Transit) የተባለ ድርጅት አስተላላፊ ሥራ አስኪያጅ ከሆኑት አቶ ታደሰ ገ/ዮሐንስ ላይ ከጅቡቲ ተጓጉዞ ድሬዳዋ ጉምሩክ የገባ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች በሠነድ ከተዘረዘሩት በላይ (ትርፍ) በመገኘቱ ዕቃው በመያዙ ዕቃውን ለመልቀቅ ብር 10‚000 (አሥር ሺ ብር) ተቀብሎ በመውሰዱ፤

- ቀኖቹ በውል ተለይተው ባለታወቁበት በሚያዝያ ወር 2005 ዓ.ም በተለያዩ ሁለት ቀናት ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ሲሆን፤ በድሬዳዋ ከተማ 03 ቀበሌ ማርያም ሰፈር ዲፖ አካባቢ የንግድ ረዳት ሆነው ይሰሩ ከነበሩት አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው ከጅቡቲ ተጓጉዘው ድሬዳዋ ጉምሩክ የገቡ አምፖሎች ተፈትሸው ከተጠናቀቁ በኋላ ተከሳሹ ገንዘብ ካልሰጠኸኝ እቃዎቹ አይወጡም ብሎ በመደራደር ለመጀመሪያዎቹ ብር 15‚000 (አስራ አምስት ሺህ)፣ ለሁለተኛዎቹ ብር 20‚000 (ሃያ ሺህ) በድምሩ ብር 35‚000 (ሰላሳ አምስት ሺህ ብር) ተቀብሎ በመውሰዱ፤ በፈፀመው ጉቦ መቀበል የሙስና ወንጀል ተከሷል።

12ኛ ክስ

በ2ኛ፣ 4ኛ እና 9ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ''

ወንጀሉ

በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)(ለ)፣ 33፣ እና 408(1) እና (2) ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣

የወንጀሉ ዝርዝር

2ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች እንደቅደም ተከተላቸው በኢትዮጰያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ እና ምክትል ዋና ዐቃቤ ሕግ ሆነው ሲሰሩ፣ በስራ ኃላፊነታቸው ማድረግ የማይገባቸውን በማድረግ ሕገወጥ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ፣ 9ኛ ተከሳሽ በበኩሉ የመንግስት ሰራተኞች ብቻ በሚፈፀም የሙስና ወንጀል ልዩ አካፋይ በመሆን፤
- 2ኛ ተከሣሽ ብሥራት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር የተባለ ድርጅት ያለ ቫት ደረሰኝ ግብይት ሲፈፅም ተከሣሹ ለሚሰራበት መ/ቤት ጥቆማ ቀርቦ እንደ ጥቆማው አቀራረብ ለማረጋገጥ የድርጅቱ ሠራተኞች መጋቢት 29 ቀን 2001 ዓ.ም ወደ ድርጅቱ በመሄድ ኦፕሬሽን ሲካሄድ ያለደረሰኝ ግብይት እያከናወነ መሆኑ በመረጋገጡ በድርጅቱ፤ በድርጅቱ ባለቤትና ሌሎች ሁለት የድርጅቱ ሠራተኞች ላይ ምርመራ ተጣርቶ ክስ ቀርቦባቸው በክርክር ላይ እያለ ተከሣሹ ለብሥራት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ባለቤት አቶ ባህሩ አብርሃ በቀጥታ መስመር ስልካቸው ላይ በመደወል “አንተ ከማን ትበልጣለህ ወደ መደበኛ ፍ/ቤት ክስህን አቅርበን ከፍተኛውን ቅጣት አንደምናስቀጣህ እወቅ” በማለት ግለሰቡን በማስፈራራትና በማስጨነቅ በተከሳሹ የቅርብ አገናኝ በነበረው 9ኛ ተከሳሽ አማካኝነት ቀጠሮ በማስያዝ ከላይ የተጠቀሰውን ባለሀብት ቢሮው በተደጋጋሚ እንዲገኝ በማድረግ ከላይ በተጠቀሰው የማስፈራሪያ ቃል በማስፈራራት “ሌሎች ልጆች ከእኔ ጋር ስላሉ በደንብ ተዘጋጅተህ ና” በማለት የራሱን ስልክ ቁጥር በመስጠት የስልክ ግንኙነት በማድረግ ቀኑና ወሩን በትክክል በማይታወቅበት 2004 ዓ.ም መጀመሪያ አካባቢ ዮርዳኖስ ሆቴል አካባቢ ከምሽቱ 1፡45 ሰዓት በመቅጠር ብር 250‚000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ከባለሀብቱ ከተቀበለ በኋላ ባሀብቱ አድርጐት የነበረውን ብራስሌት እጁ ላይ ከተመለከተ በኋላ “የእሱ ዓይነት ግዛልኝ” በማለት ግለሰቡ በብር 30‚000 (ሠላሳ ሺህ ብር) የተገዛ ብራስሌት በማግስቱ ኢንተርኮንቴኔታል ሆቴል አካባቢ ድረስ ይዞ በመሄድ ከምሽቱ 1፡30 ሰዓት አካባቢ ተከሳሹ በእራሱ መኪና ውስጥ ሆኖ ተቀብሎ ጉዳዩ እንዲጨርስለት ለ4ኛ ተከሣሽ ነግሮ ጉዳዩ እንዲያልቅ በማድረጉ፤

- 4ኛ ተከሣሽ በበኩሉ ቀኑና ወሩን በውል በማይታወቅበት በ2004 ዓ.ም መጀመሪያ አካባቢ ፒያሣ ግራር ሆቴል እየተባለ ከሚጠራ ሆቴል ውስጥ በግምት ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት አካባቢ ከላይ ከተጠቀሰው ድርጅት ባለቤት (አቶ ባህሩ አብርሃ) ብር 50‚000 (ሃምሳ ሺህ ብር)፤ ከላይ በተጠቀሰው ቀኑና ወሩ በውል በማይታወቅበት ጊዜ ባለሀብቱን እቤቱ ድረስ በመጥራት ብር 30‚000 (ሠላሳ ሺህ ብር) እና ብር 20‚000 (ሃያ ሺህ ብር) በአጠቃላይ ብር 100‚000 (መቶ ሺህ ብር) በመቀበሉ እና ከባለሀብቱ ከላይ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ተቀብሎ በባለሀብቱ ላይ የተመሠረተውን ክስ በፍ/ቤት በነፃ ከተሰናበተ በኋላ ይግባኝ እንይጠየቅ በማድረጉ፤
- 9ኛ ተከሣሽ በበኩሉ ቀኑና ወሩ በማይታወቅ በ2004 ዓ.ም ባህሩ አብርሃ የተባሉ የብሥራት ኃ/የተ/ማኅበር ባለቤት በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የተመሰረተባቸውን ክስ እንዲዘጋ ከ2ኛ ተከሣሽ ጋር በማገናኘት ብር 250‚000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) እና ብር 30‚000 (ሠላሳ ሺህ ብር) የሚያወጣ ብራስሌት 2ኛ ተከሣሽ በሕገ ወጥ መንገድ እንዲያገኝ በማድረጉ፤

በአጠቃላይ ተከሣሾች በመላ ሀሳባቸውና አድራጐታቸው በወንጀሉ ድርጊትና በሚሰጠው ውጤት ሙሉ ተከፋይ በመሆን በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት ጉቦ መቀበል የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።

13ኛ ክስ

በ2ኛ፣ እና 13ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ

ወንጀሉ

በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 419(1) (ሀ) እና ለ ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣

የወንጀሉ ዝርዝር

2ኛ ተከሳሽ በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከ1978 ዓ.ም ጀምሮ እጁ እስከተያዘበት 2005 ዓ.ም ተቀጥሮና ተሹሞ ሲሰራ ከብር 247 (ሁለት መቶ አርባ ሰባት) እስከ ብር 5‚700 (አምስት ሺህ ሰባት መቶ) ያልተጣራ ወርሃዊ ደመወዝ ይከፈለው እንደነበረ እና 13ኛ ተከሣሽ ደግሞ በአገር መከላከያ ሚኒስቴር ከ01/11/1989 ዓ.ም እስከ 30/01/2000 ዓ.ም ተቀጥራ ስትሰራ ከብር 790 (ሰባት መቶ ዘጠና ብር) እስከ ብር 2‚145 (ሁለት ሺህ አንድ መቶ አርባ አምስት) ያልተጣራ ወርሃዊ ደመወዝ ይከፈላት የነበረ ሲሆን ተከሳሾቹ ያገኙት ከነበረው ደመወዝና ገቢ ጋር የማይመጣጠን፤

1ኛ. በወጋገን ባንክ ካዛንቺስ አካባቢ በሂሣብ ቁጥር 302993 ብር 96‚477.79 (ዘጠና ስድስት ሺ አራት መቶ ሰባ ሰባት ከሰባ ዘጠኝ ሣንቲም) በ13ኛ ተከሳሽ ስም
2ኛ. በእናት ባንክ እቴጌ ጣይቱ አብይ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር R/S746 ብር 4‚000 (አራት ሺህ) በ13ኛ ተከሳሽ ስም፤
3ኛ. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፊንፊኔ ቅርንጫፍ በሂሣብ ቁጥር 1000001730766 ብር 1‚427.59 (አንድ ሺ አራት መቶ ሃያ ሰባት ከሃምሳ ዘጠኝ ሳንቲም) በ13ኛ ተከሳሽ ስም፤
4ኛ. በኢትዮጰያ ልማት ባንክ በሂሣብ ቁጥር 1258hA, 40612HC, 35933HD, 41304HE, 2636HG, ብር 3‚925 (ሦስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ አምስት) በ13ኛ ተከሳሽ ስም፤
5ኛ. የካ ክ/ከተማ ቀበሌ 11/12 የቤ.ቁ. 634 የካርታ ቁጥር 29870 የቦታው ስፋት 4‚000 ካ.ሜ የሆነ ቦታ ተከሣሽን ጨምሮ 7 ሰዎች በብር 4‚200‚000 (አራት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ ብር) የተገዛ ቦታ (የተከሳሽ ድርሻ ብር 600‚000 (ስድስት መቶ ሺህ ብር)፤
6ኛ. የሠሌዳ ቁጥር 3-02725 ትግ የሆነ አውቶቡስ ተሽከርካሪ (ለጊዜው ግምቱ ያልታወቀ) በ13ኛ ተከሳሽ ስም፤
7ኛ. የሠሌዳ ቁጥር 3-49614 አ.አ የሆነ የንግድ መኪና (ለጊዜው ግምቱ ያልታወቀ) በ13ኛ ተከሳሽ ስም፤
8ኛ. የካረታ ቁጥር 2713/22/93 መቀሌ ከተማ ቀበሌ 11 የሚገኝ መኖሪያ ቤት በ13ኛ ተከሳሽ ስም፤
9ኛ. በ2ኛ ተከሳሽ ስም ዳሸን ባንክ መቀሌ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር 5013022467001 ብር 42244.62፣
10ኛ. በ2ኛ ተከሳሽ ስም አንበሳ ባንክ የካ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር 00300000799-97 ብር 387.65
11ኛ. በ2ኛ ተከሳሽ ስም ወጋገን ባንክ መስቀል ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር 23444/501/03024 ብር 102‚553.50 (አንድ መቶ ሁለት ሺ አምስት መቶ ሃምሳ ሦስት ከ50/100)
12ኛ. በፀረ ብርሃን ገ/ዋህድ ስም (ልጅ) ካሳንቺስ ቅርንጫፈ በሂሳብ ቁጥር 262179 ብር 18‚142.04፣
13ኛ. በፀረ ብርሃን ገ/ዋህድ ስም (ልጅ) ካሳንቺስ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር 262180 ብር 1‚015.07፣
14ኛ. በፀረ ብርሃን ገ/ዋህድ ስም (ልጅ) በኢትዮጰያ ንግድ ባንክ ሀዋሳ ቅርንጫፈ በሂሳብ ቁጥር 1000013401587 ብር 1‚753.77፣
15ኛ. በፀረ ብርሃን ገ/ዋህድ ስም (ልጅ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፊንፊኔ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር 0173007267000 ብር 203424.99 (ሁለት መቶ ሦስት ሺ አራት መቶ ሃያ አራት ከ99/100)፤
16ኛ. በ2ኛ ተከሳሽ ስም በአንበሳ ባንክ የብር 34‚275.25 (ሰላሳ አራት ሺ ሁለት መቶ ሰባ አምስት ከ25/100) አክስዮን፤
17ኛ. በሳሙኤል ገ/ዋህድስም (ልጅ) የብር 10‚000 (አሰር ሺ) አክስዮን፤
18ኛ. ከተከሳሾች መኖሪያ ቤት የተገኘ፡-
18.1. የኢትዮጵያ ብር 200‚000 (ሁለት መቶ ሺ)
18.2. EURO 19435 (አስራ ዘጠኝ ሺ አራት መቶ ሰላሳ አምስት)
18.3. USD 26300(ሃያ ስድስት ሺ ሶስት መቶ)
18.4. POUND 560 (አምስት መቶ ስድሳ)
18.5. TAILAND 210 (ሁለት መቶ አስር)
19ኛ/ በካርታ ቁጥር L/X/L/D/3139100 ግምቱ ብር 596868፣24 የሆነ 500 ካ.ሜ
20ኛ/ 6 የተለያዩ ላፕቶፖች፤

በአጠቃላይ ተከሳሾች የኑሮ ደረጃቸው አሁን ባለበትም ሆነ አስቀድሞ በነበሩት የመንግሥት ሥራ ከሚያገኙት ህጋዊ ገቢ ጋር የማይመጣጠን ብር 1,451,941.609 (አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ሃምሳ አንድ ሺ ዘጠኝ መቶ አርባ አንድ ከ60/00)፣ ከላይ ከተራ ቁጥር 18.2 – 18.5 ድረስ የተጠቀሱትን የውጭ አገር ገንዘቦችና እና እንዲሁም የተለያዩ ንብረቶች ይዘው በመገኘታቸው በፈፀሙት ምንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ ይዞ መገኘት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
14ኛ ክስ

በ2ኛ እና 13ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ

ወንጀሉ

በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 684(1) እና (2) ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር

ተከሳሾች ከላይ በ13ኛው ክስ በተገለፀው ጊዜና አኳኋን በፈፀሙት የሙስና ወንጀል ያገኙትን ገንዘብና ንብረት ህገወጥ አመጣጡን በመሰወር ህጋዊ ለማድረግ በማሰብ መሬት እና መኪና በመግዛት፣ በተለያዩ ባንኮች በእራሳቸውና በልጆቻቸው ስም እንዲሁም መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ገንዘቦችን በማስቀመጥ በፈፀሙት በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብና ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብና በወንጀሉ መርዳት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።

15ኛ ክስ

በ13ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ

ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 40፣419 እና 684 ላይ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች በመተላለፏ፣

የወንጀሉ ዝርዝር

ተከሳሿ ባለቤቷ የሆነው 2ኛ ተከሳሽ ግንቦት 2 ቀን 2005 ዓ.ም በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ ተጠርጣሪው የተጠረጠረበትን የወንጀል ፍሬ መሆናቸውን እያወቀች ባለቤቷ በፈፀመው የወንጀል ድርጊት ከመከሰስና ከመቀጣት እንዲያመልጥ ለመርዳት፡-

1. በአቶ ገ/ዋህድ ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል ስም ተመዘገበ የባንክ ደብተር ቁጥር 0123586 የሆነ ብር 10000 (አስር ሺ) ተቀማጭ ያለው፤

2. ካርታ ቁጥር L/X/L/D/3139/00/06/01 ከለገጣፎ ለገዳዲ አስተዳደር ለገ/ዋህድ ወ/ጊዮርጊስ የተሰጠ፤

3. በአቶ ገ/ዋህድ ወ/ጊዮርጊስ እና በወ/ሮ ሀይማኖት ተስፋዬ ስም ለኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ብር 820,000 (ስምንት መቶ ሃያ ሺ ብር) ብድር ለመጠየቅ የተሞላ ቅፅ፤

4. በአቶ ገ/ዋህድ ወ/ጊዮርጊስ እና በኮ/ል ሃይማኖት ተስፋዬ ስም ለኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ብር 1,000,000 (አንድ ሚሊዮን ብር) የባንክ ሼር ለመግዛት የጠየቁበት ሰነድና የተለያዩ የቤት ፕላኖችን ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ እህቷ ለሆነችው  ወ/ሮ ንግስቲ ተስፋ ገ/ስላስ እና አቶ ሀብቶም ገ/መድህን ገ/የስ ለተባሉ ግለሰቦች አሳልፋ በመስጠትዋ በፈፀመችው ወንጀል ከተፈፀመ በኋላ ወንጀል አድራጊውን መርዳት ወንጀል ተከሳለች።

16ኛ ክስ

በ2ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ

ወንጀሉ

በ1996 ዓ.ም የወጣውን ኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀፅ 808(ሀ) ላይ የተደነገገውን በመተላለፉ፣

የወንጀሉ ዝርዝር

ተከሳሹ የጦር መሳሪያ አያያዝና አጠቃቀም ደንብ ተከትሎ ፈቃድ ከሚሰጥ አካል አስፈቅዶ መያዝና መጠቀም ሲገባው ከሚመለከተው ፈቃድ ሰጪ አካል ሳያስፈቅድ የመኖሪያ ቤቱ በ02/09/05 ዓ.ም በፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ብርበራ በተካሄደበት ወቅት፡-

1. የውግ ቁጥር 1529 የሆነ ባለ አንድ እግር ታጣፊ ክላሽ፣
2. የውግ ቁጥር 0624 የሆነ ባለ አንድ እግር ታጣፊ ክላሽ፣
3. የውግ ቁጥር ሠበ0402 የሆነ ማክሮቭ ሽጉጥ
4. የውግ ቁጥር የሌለው ማካሮቭ ሽጉጥ፣
5. የውግ ቁጥር የሌለው ኮልት ሽጉጥ፣
6. የውግ ቁጥር 47391 ኮልት ሽጉጥ፣
7. የውግ ቁጥር NK252926 ማካሮቭ ሽጉጥ፣
8. የውግ ቁጥር የሌለው ማካሮቭ ሽጉጥ
9. የውግ ቁጥር 2235 ስታር ሽጉጥ እና
10. የተለያዩ ጥይቶችን ይዞ በመገኘቱ

በፈፀመው እንዲይዝ ያልተፈቀደለትና ፈቃድ የሌለው የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት ወንጀል ተከሷል።

17ኛ ክስ

በ8ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ

ወንጀሉ

በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀፅ 419(1)(ለ) ላይ የተደነገገውን በመተላለፉ፣

የወንጀሉ ዝርዝር

ተከሳሹ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የመንግስት ሰራተኛ ሆኖ በሰራበት ከ22/11/87 ዓ.ም እስከ 30/7/2004 ዓ.ም ድረስ ባሉት ጊዜያት ተቀጥሮ ሲሰራ በወር ይከፈለው የነበረው ያልተጣራ ደሞዝ ከብር 445 (አራትመቶ አርባ አምስት) እስከ ብር 8,651 (ስምንት ሺ ስድስትመቶ ሃምሳ አንድ ሺህ) ሲሆን በመንግስት ስራ ላይ እያለ ያገኝ ከነበረው ከህጋዊ ገቢው ጋር የማይመጣጠን፡-

1ኛ/ ግንቦት 2 ቀን 2005 ዓ.ም በመኖሪያ ቤቱ ብርበራ ተደርጎ የተገኘ ብር 1,947,676.10 /አንድ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አርባ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ሰባ ስድስት ብር ከአስር ሳንቲም/፣

2ኛ/ በተለያዩ ባንኮች እና የአክሲዮን ማህበራት በተከሳሽ ስም የተቀመጠ በድምሩ ብር 2,090,880.03 /ሁለት ሚሊዮን ዘጠኛ ሺ ስምንተ መቶ ሰማንያ ብር ከአስር ሳንቲም/

3ኛ/ በተከሳሽ ስም ቦንድ የተገዛበት ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/

4ኛ/ በአዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ ፣ ወረዳ 24፣ ቀበሌ 02/03 በተከሳሽ ደሞዝ በምትተዳደረው ባለቤቱ ወ/ሮ ሀዲስ ሙሉ ስም ተመዘግቦ የሚገኝ 74.56 ካ/ሜ ስፋት ላይ የተሰራና ግምቱ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ የሆነ ባለ ሁለት መኝታ ኮንደምኒየም ቤት፣

5ኛ/ በተከሳሽ ደሞዝ በምትተዳደረው ባለቤቱ ወ/ሮ ሀዲስ ሙሉ ስም በተለያዩ ባንኮች የተቀመጠ በድምሩ ብር 185,641.19 (አንድ መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ስድስት መቶ አርባ አንድ ብር ከአስራ ዘጠኝ ሳንቲም/
6ኛ/ በተከሳሽ ደሞዝ በምትተዳደረው ባለቤቱ ወ/ሮ ሀዲስ ሙሉ ስም አክሲዮን የተገዛበት ብር 5,000፣ አምስት ሺህብር/፣
7ኛ/ በተከሳሽ ደሞዝ በምትተዳደረው ባለቤቱ ወ/ሮ ሀዲስ ሙሉ ስም ቦንድ የተገዛበት ብር 10,000 /አስ 

በሁለት የቀድሞ የህወሀት ባለስልጣናት ቤቶች በርካታ የጦር መሳሪያዎች መገኘታቸውን አቃቢ ህግ ገለጸ

ጥቅምት ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ህግ አንድ ግለሰብ ከመንግስት በማስፈቀድ አንድ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ እንዲይዝ ቢፈቀደልትም ፣ በተግባር ግን አብዛኛው ህዝብ በመሳሪያ አሰሳ ስም የግል መሳሪያውን መቀማቱን በተለያዩ የመገናኛ ብሀን ሲዘገብ ቆይቷል።

በ1997 ምርጫ ወቅት የአንድ ብሄር አባላት በገዢው ፓርቲ ህወሀት  ራስን የመጠበቂያ መሳሪያ እንዲታደላቸው መደረጉ በስፋት መዘገቡ ይታወቃል።

የፌደራል አቃቢ ህግ በቀድሞው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋ/ዳይሬክተር መላኩ ፋንታ መዝገብ ላይ ባቀረበው ክስ፣ በህወሀቱ አባል ምክትል ዳይሬክተሩር አቶ ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ መኖሪያ ቤት ውስጥ 2 ታጣፊና ባለእግር ክላሾች፣ 4 ማካሮቭ ሽጉጦች፣ 2 ኮልት ሽጉጦች፣እና አንድ ስታር ሽጉጥ በድምሩ 9 የጦር መሳሪያዎች መገኘቱን ጠቅሷል።በሌላው የህወሀት አባል በ24ኛው ተከሳሽ በቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አማካሪ በነበሩት በአቶ ወልደስላሴ /ሚካኤል ቤት ደግሞ 2 ባለሰደፍና ታጣፊ ጠመንጃዎች፣ አንድ ኡዚ ጠመንጃ፣ አንድ እስታር ሽጉጥ፣ አንድ የጭስ ቦንብ እና የተለያዩ ጥይቶችን ይዞ መገኘቱ ተገልጿል።

ግለሰቡ ከቀድሞው ጠ/ሚ አቶ መለስ ዜናዊ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር የጠበቀ ቁርኝት እንዳላቸው  በተቃራኒው ደግሞ ከደህንነት ሚኒስትሩ ከአቶ ጌታቸው አሰፋ ጋር በተፈጠረው አለመግባባት ለእስር መዳረጋቸው በተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን ሲዘግብ ቆይተዋል።

 በተመሳሳይ ሴና ዋና ዳይሬክተሩ አቶ መላኩ ፋንታ ባለትዳር በማማገጥ ወንጀል አቃቢ ህግ ክስ እንደመሰረተባቸው ሰንደቅ ጋዜጣ ዘግባል። ዐቃቤ ህግ  አቶ መላኩ የስራ ኃላፊነታቸውን በመጠቀም ለስራ ጉዳይ የመጣችን ሴት፤ ትዳሯን ፈታና በትዳር ውስጥ ያፈራቻቸውን ሦስት ልጆች በትና አብራቸው እንድትሆን አድርገዋል ሲል ስልጣንን ያለአግባብ የመጠቀም የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል ብሎአል።  ሰንደቅ አቃቢ ህግን ጠቅሶ እንደዘገበው ” ወ/ሮ መቅደስ ለማ የተባሉት እኚሁ ሴት የቀድሞ ባለቤታቸውን ንብረት የሆነውን ሳንክቸሪ ኢንተርናሽናል ኃ/የተወሰነ የግል ማህበር በ2001 ዓ.ም የስራ ግብር ለመክፈል ወደገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሲሄዱ 144 ሺህ ብር እንዲከፍሉ በመጠየቃቸውና በዚህም ምክንያት አቤቱታ ለማቅረብ ወደ ምስራቅ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ለአንድ አመት ከ4 ወር መጉላላታቸውን ለማስረዳትና መፍትሄ ለማግኘት ወ/ሮ መቅደስ ለማ የአቤቱታ ደብዳቤ ይዘው ወደተከሳሹ ዘንድ በቀረቡበት ወቅት የፍቅር ግንኙነት” ጀምረዋል።  ተከሳሽ የነበረውን ስልጣን መከታ በማድረግ ባለጉዳዩዋ ቀደም ሲል ከከፈሉት ብር ውስጥ አንድ መቶ ሺህ ብር ተመላሽ እንዲሆን አድርጓል፤ በትዳር ውስጥ ያለችን ሴትም አማግጧል ሲል አቃቢ ህግ ክስ አሰምቷል።

ዐቃቤ ህግ ተከሳሽ “በጋብቻ ውስጥ ያለችን ሴት በመንግስት ተሽከርካሪና ነዳጅ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ክብረ በዓል ላይ እንድትገኝ ከማድረጉም በላይ ቀኑ በውል ባልታወቀበት ዕለትም፤ በጋብቻ ውስጥ የነበረችው መቅደስ ለማን በግል ሾፌሩ አማካኝነት ወደ ባህርዳር ከተማ እንድትሄድ በማድረግ ሰመርላንድ ሆቴል ለአንድ ሳምንት አብረው እያደሩ እና በሾፌሩ አማካኝነት ከተማ ውስጥ እንድትዝናና ” አድርጋል ብሎአል።

አቃቢ ህግ ባቀረባቸው በርካታ የወንጀል ዝርዝሮች ውስጥ የሼክ ሙሀመድ ሁሴን አላሙዲንና በጄኔራል ክንፈ ዳኘው የሚመራው በመከላከያ ውስጥ የሚገኘው የብረታ ብረት ኮርፖሬሽን እቃዎች ያለቀረጥ እንዲገባላቸው ቢደረግም፣ ሌሎች ኩባንያዎች ሲከሰሱ ሁለቱ ድርጅቶች እና የኩባንያው መሪዎች አልተከሰሱም። አቃቢ ህግ እነዚህ ሁለት ግዙፍ ኩባንያዎች በሙስናው ውስጥ እንዳሉበት መረጃ ቢኖረውም ለመክሰስ ለምን ፈቃደኛ እንዳልሆነ አልታወቀም።

ጠ/ሚ ኃይለማርያም ከማስረጃ አልባ ፍረጃ እንዲላቀቁ አንድነት አሳሰበ

October 23/2013

 አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ ካለፈው ስህተታቸው በመማር ከአጉልና ማስረጃ አልባ ፍረጃ እንዲላቀቁ አሳሰበ። ፓርቲው ከትናንት በስትያ ባወጣው መግለጫ እንደገለፀው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ባለፈው ሳምንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በመሪ ደረጃ በማይጠበቅ መልኩ የአንድነትን እንቅስቃሴ ስም ለማጥፋት በመሞከራቸው ከዚህ ድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል ብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የራሳቸው አጀንዳ የላቸውም፣የሻዕቢያ መልእክት አድራሾች ናቸው ያሉት የራሳችን አጀንዳ እንዳለን ጠፍቷቸው ሳይሆን ሆን ብለውና አቅደው ስም ለማጥፋት እንዲሁም ህዝቡ ውስጥ ጥርጣሬ ለመጫር በመፈለግ ነው ብሏል።

ፓርቲው ተላላኪነቱ ለኢትዮጵያ ህዝብና ይጠቅማል ብሎ ለቀረፃቸው የፖለቲካ ፕሮግራም ብቻ መሆኑን የገለፁ ሲሆን፤ እንዲህ አይነቱን ስም ማጉደፍም በቸልታ እንደማያልፈው ገልጿል። በተጨማሪም የሙስሊም ወገኖችን ጥያቄ በተመለከተ ፓርቲው በሰላማዊና በህጋዊ መንገድ ይመለስ፣ ዜጎች የመብት ጥያቄ ሲያነሱ መፈረጁ ይቁም እንዲሁም ካለአግባብ የሃይማኖት ነፃነት ጥያቄ በማንሳታቸው ወደ እስር ቤት የተወረወሩ ዜጎች በአስቸኳይ ይፈቱ የሚል ጥያቄ ማንገቡን ፓርቲው ገልጿል። በመሆኑም ፓርቲው ከኢፍትሃዊት ጋር እንደማይደራደር እና እንደማይቀበለው አመልክቶ፣ ፓርቲውን ከሙስሊም ወገኖች ጥያቄ ጋር በማያያዝ ትርፍ ፍለጋ መሯሯጥ ወንጀል ነው ብሏል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሰላማዊ ሰልፍን በተመለከተ የተናገሩት በህገ መንግስቱ የተቀመጠውን መብት በአደባባይ የጨፈለቀ ነው ብሏል ፓርቲው። ሰላማዊ ሰልፍ ለሚያደርጉ በቂ ጥበቃ የለንም በሚል ተልካሻ ሰበብ የዜጎችን መብት መንጠቅ እንደማይቻል የገለፀው ፓርቲው፤ ጥበቃ ማድረግ ያልቻለ መንግስትም ስልጣኑን ለህዝብ በማስረከብ ይቅርታ ጠይቆ መሄድ እንጂ ከአሁን በኋላ መብታችሁን አታገኟትም ብሎ መዛት ትዝብት ላይ ይጥላል ብሏል።
 
ፓርቲው አያይዞም የአፍሪካ መሪዎች ተሰብስበው አይ ሲሲ ሊከሰን አይገባም ሳይሆን ማለት ያለባቸው፣ የዜጎቻቸውን እንባ ማበስ እና ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲረጋገጡ መጣር ነው ብሏል። መሪዎች በርካታ መፍትሄ ፈላጊ ችግሮች ባሉባት አፍሪካ ተሰብስበው እንግደል፣ እንሰር፣ እንጨፍጭፍ፣ ዘር እናጥፋ፣ ዜጎቻችንን እናሰቃይ ግን መታሰርም፣ መከሰስም የለብንም የሚለው አቋም አሳፋሪ በመሆኑ ፓርቲው እንደማይቀበለው ገልጿል። በመሆኑም ዜጎች ላይ ግፍና ስቃይ የሚፈፅሙ ሁሉ ሳይውል ሳያድር ወደ ፍርድ መቅረብ አለባቸው በማለት፤ አንዳንድ የአፍሪካ መሪዎች አይሲሲን በተመለከተ የሚያራምዱትን የአትክሰሱን አቋም ፓርቲው እንደማይቀበለውም ገልጿል።

Wednesday, October 23, 2013

የመከላከያው ሹመትና መዘዙ

October 23/2013

 የሰሞኑና የቀደሙት የመከላከያ አድሎአዊ ሹመቶች ከማሳሰብ በላይ እየሆኑ ነው:: ይህ ተደጋጋሚ ተግባር የህገ መንግስቱን አንቀጽ 12:1 ፣62:4፣87:1ና5 እንደዚሁም አንቀጽ 88:2ን በጽኑ ይጥሳል:: በተለይም በአንቀጽ 87:1 ላይ የተቀመጠውንና በመከላከያ ሰራዊቱ ተዋጽኦ ላይ ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖር የሚጠይቀውን ግብ ሙሉ በሙሉ ይሽራል:: አጠቃላይ የማንኛውም ህገ መንግስት መንፈስ የሆነውን ፍትሀዊና በአንድ ማህበረሰብ ሊኖር የሚገባውን የነጻነት፣ እኩልነትና ወንድማማችነትን የማስፈንና የማበረታታት ተግባርን ያኮላሻል:: በህሊና ተጠያቂነትም ላይ ይሳለቃል::
ትልቁና ስልታዊ (ስስተሚክ) ሙስና ይህ ነው:: 400,000 ብር የቤት ኪራይ ለግርማ ወ/ጊዮርጊስ ቤት ተከፋለ አልተከፈለ ኢትዮጵያ በርካታ ጉድ ችላለች:: ትችላለችም! በተደጋጋሚ የምንሰማው በመካላከያ ሹመት ግን ከህወሐት አይን አውጣነት ያለፈ ነው::የምርም ስድብ ነው:: ንቀት ነው:: እንዲህ ያሉ አብሮ መኖርን የሚጋፉና ኢፍትሀዊ አሰራሮች መቆም አለባቸው:: ማንኛውም ለትክክለኛ ሰላም፣ አብሮ መኖርና ፍትህ የሚያስጨንቀው ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ይህ ይመለከተዋል:: ጥቂቶች ይጠቀሙ ዘንድ እንዲህ አይነት ግፍ ሲፈጸም እያዩ ዝም ማለት ተገቢ አይደለም:: አይሆንም::
የሀገሪቱ መከላከያ እንደግብ የተቀመጠለትን የብሔር ብሔረሰብ ተዋጽኦነት በአስቸኳይ ሊፈጽም የግድ ነው:: አለያ ይህ ሀገር ቅኝ ግዛት እየሆነ ነው:: በቅኝ ግዛት ያለ ህዝብ ነጻ መውጣቱ ግድ ይላል! የሕወሀት ሰዎች መሾም የለባቸውም የሚል የለም:: ህወሐት ከአንድ ብሔር የመጡ ሰዎች የመሰረቱት ድርጅት ነው::ድርጅቱ የኢህኣዴግ ባለውለታ ነው:: የሀገሪቱ ባለውለታነት ከነበረውም ጨርሶታል:: ቀሪ ሂሳቦዎ እየተባለ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው:: ያም ሆኖ እንደ አንድ አባል መሳተፍ እንጂ ከሁሉ ብሄር እንደሆነ ሁሉ ሁሉንም የተቋሙን የስልጣን እርከኖች ሹመቶች መቆጣጣር አይበጅም::
ይህ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ነው:: ኢትዮጵያም መከላከያ ሰራዊቱም የብዙ ብሔሮችና ብሔረሰቦች ሀገርና ተቋም ናቸው:: ስለሆነም ብዙ ጊዜ በምክንያትነት የሚቀርበው የልምድ: የዕውቀት ማነስ ወዘተ እንኳን ከ22 ዓመት በኋላ ቀድሞም ምክንያትነቱ አይታመንምና ማብቃት አለበት:: እስካሁንም ይህን ለማድረግ እውነተኛ ጥረት አልተደረገም ምናልባት በተቃራኒው እንጂ::
ይህ አድሎአዊ አሰራር አሁን ባለው ሁኔታ ከልክ አልፏል:: በአስቸኳይም ሊገታና ማስተካከያ መወጠን አለበት:: ይህ ካልሆነ አገሪቱን ይጠብቃል ተብሎ የተዋቀረ ተቛም በአወቃቀሩ ኢፍትሃዊነትና በህወሐት ማን-አለብኝነት ምክንያት አገሪቱን ለማፍረስ የተጋረጠ አደጋ ሆኖ ይቀጥላል:: ስለዚህ የህወሐትና የማዕከላዊው መንግስት ባለስልጣናት በተለይ በመከላከያው ተቋም የብሔር ተዋጽኦ ላይ ጠንካራ የሆነ ክለሳ ተደርጎ በሚቀጥሉት አምስት አመታት የሚቆይ ፕሮግራም ካልነደፉና በአስቸኳይ በስራ ላይ ካላዋሉ ሀገሪቱን ወደ ከፋ አደጋ በማዝቀጥ እንደሚያፈራርሷት ግልጽ ነው::
ፖለቲካ የማህበረሰቡ ስልጣንና ሀብት በትክክል እንዲከፋፈል ፍትሃዊ መፍትሔ ማምጣት ነው ግቡ:: በየጊዜው የምናየው የሀገራችን ፖለቲካ ግን በፍጥነት አድሎአዊነቱ እየጨመረና በርካታ የተወከሉ የመሰላቸውን ብሄሮችንና ግለሰቦችን በማግለል ስራው ተጠምዷል::ይህ ከሶማሊያም የባሰ አደጋ አለው ነው መልክቴ! መንገዳችሁ ለእኛም ለናንተም አይበጅምና ህሊና ያላችሁና የኢትዮጵያ መኖር የሚጠቅማችሁ የህወሐት አባላት እንድትሰሙ እመክራለሁ::

Tuesday, October 22, 2013

ዶ/ር መረራ የፍንዳታውን ዜና “እንጠራጠረዋለን” አሉ

bole 1October 22, 2013 06:39 am 
በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ሩዋንዳ ሰፈር የደረሰውን ፍንዳታ አስመልክቶ ኢህአዴግ ያሰራጨውን ዜና የሚቃረኑ መረጃዎችና አስተያየቶች ቀረቡ። ለኢህአዴግ ቅርበት ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች የድጋፍ አስተያየት ሲሰጡ ዶ/ር መረራ “አትፍቶ ጠፊ አጥፍቶ ይጠፋል እንጂ በሜዳ ዝም ብሎ አያጠፋም” ሲሉ ጥርጣሬ እንዳላቸው ተናግረዋል። የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/ በፍንዳታው የሞቱት ኢትዮጵያውያን ናቸው ሲል ስም ገልጾ የኢህአዴግን ዜና አጠጥሎታል።
በፓርላማ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ የጠየቁት ከኢህአዴግ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የሚታሙ ፓርቲዎች “የጸረ ሽብርተኞች አዋጅ ሊጠናከርና ሊጠብቅ ይገባል” ሲሉ ተደምጠዋል። የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ያነጋገራቸው የኢራፓ፣ የኢሴዳፓ፣ ቅንጅትና አዲአን ተወካዮች በየተራ የኢህአዴግን ዜና የሚቃወሙና በጥርጣሬ የሚመለከቱትን አውግዘዋል። በወቅቱ የቴሌቪዥን ጣቢያውም አንድነትና የሰማያዊ ፓርቲ ጠርተውት በነበረው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ “የጸረ ሽብርተኛነት አዋጅ ለሌላ ተግባር መዋሉን እንቃወማለን” በማለት የተቃውሞ ድምጻቸውን ሲያሰሙ በማሳየት ዜናውን ለማጀቢያነት ተጠቅሞበት ነበር።
በግል አስተያየታቸውን የተጠየቁት ዶ/ር መረራ ጉዲና በቴሌቪዥን መስኮት ቀርበው “ብዙዎች፣ እኔም ጓደኞቼም በጥርጣሬ ነው ያየነው” ሲሉ ከተቆረጠው ንግግራቸው ተደምጧል። ዶ/ር መረራ “አጥፍቶ ጠፊ አጥፍቶ ይጠፋል እንጂ በሜዳ ዝም ብሎ ራሱን አያጠፋም” ካሉ በኋላ “ስለዚህ እውነት ተደርጓል?” የሚለው ትልቁ ችግርና የጥርጣሬው መነሻ እንደሆነ አመልክተዋል። ስለዚህ በሚል ድምዳሜ “ሰው አንዳንድ ጊዜ የኢትዮጵያ መንግስት ለራሱ ፖለቲካ ብሎ የሚያደርገው ያው የለመደው ስራ ነው” እንደሚል ዶ/ር መረራ በተቀነጨበው አስተያየታቸው ሲናገሩ ተሰምቷል። በተቃራኒ ከላይ በስም የተዘረዘሩት የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ ኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት ኢላማና የአልሸባብ ስጋት ላይ ያለች አገር በመሆኗ ኢህአዴግ ህዝብን የመጠበቅና ደህንነትን የማስጠበቅ አደራ ስላለበት እነሱን ጨምሮ እንዲጠብቃቸው ጥሪ አቅርበዋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስሙ የሚነሳውና በታጣቂ ሃይሉ ፈርጣማነት የሚታወቀው የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ  /ትህዴን/ በቦሌ ክፍለ ከተማ በቤት ውስጥ ፈነዳ በተባለው ፈንጂ ህይወታቸው እንዳለፈ የተገለጸው ሁለት የሶማሌ ዜጎች አይደሉም ሲል ከሁሉም ወገን የተሰራጨውን ዜና በዜሮ አጣፍቶታ። በፈንጂው የሞቱት ሁለት ሰዎች ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ስማቸውም “ምክትል ኢንስፔክተር ሞላ መላኩ የተባሉ የፖሊስ አባልና አቶ ሞገስ አስቻለው የተባሉ ሲቪል ናቸው” ሲል የገለጸው ትህዴን የሟቾቹ ስም በመታወቂያ መረጋገጡን አመልክቷል።የመታወቂያውን ቅጂ ግን በገጹ አላተመም። ከአደጋው ጋር በተያያዘ በስፍራው ታይታችኋል በሚል በርካታ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት መታሰራቸውን በመግለጽ የሶስት እስረኞችን ስም ይፋ ያደረገው ኦክቶበር 19 ቀን 2013 በራሱ ኦፊሳላዊ ድረገጽ ላይ ነው። ኢህአዴግም ቢሆን ሞቱ የተባሉትን ሰዎች ይህ ዜና እስከተጻፈበት ቀን ድረስ በሰነድ አስደግፎ አላቀረባቸውም።
በሌላ በኩል ኦክቶበር16 ለንባብ የበቃው ሪፖርተር ጋዜጣ ጥቅምት 3ቀን 2006ዓ.ም. በቦሌ ክፍለ ከተማ ሩዋንዳ ማዞሪያና ቦሌ ሚካኤል መግቢያ አካባቢ በቦምብ ፍንዳታ ሕይወታቸው ያለፈው ሁለት ሶማሊያውያን ሽብርተኞች መሆናቸውን ማረጋገጡን፣ የፌዴራል ፖሊስ የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል ማስታወቁን ዘግቧል።
Bomb-Blast-Addisየአንድ ግለሰብ ሰርቪስ ቤት ተከራይተው ከነበሩት ሶማሊያውያኑ መካከል፣ አንደኛው ከ20ቀናት በላይ የቆየ ሲሆን፣ ሌላኛው ፍንዳታው ከመድረሱ ከሁለት ሰዓታት በፊት የደረሰ መሆኑን ግብረ ኃይሉ ማረጋገጡን ያመለከተው ሪፖርተር ሽብርተኛ የተባሉት ሶማሊያውያኑ ካፈነዱት ቦምብ በተጨማሪ መጠናቸው ያልተገለጸ ቦምቦችና አንድ ሽጉጥ ከሁለት ካርታ ጥይት ጋር መገኘቱን፣ የፈንጂ ማቀጣጠያና የአደጋ መከላከያ ጃኬቶች፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማሊያና ቀበቶዎች መገኘታቸውም ጠቁሟል፡፡ ከሶማሊያውያኑ ጋር ቀጥታ ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሦስት ተጠርጣሪዎችና የቤቱ አከራይ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተካሄባቸው መሆኑንም ግብረ ኃይሉ አክሏል በማለት ሪፖርተር ዘግቧል። አዲስ አድማስ በበኩሉ አልሸባብ ለጥቃቱ ሃላፊነት መውሰዱን አድራሻው አልተመዘገበ የትዊተር ማረጋገጫ በማመላከት ከዚህ በታች ያለውን ዜና አስነብቧል።
ባለፈው እሁድ በቦሌ ሚካኤል አካባቢ ከደረሰው ፍንዳታ ጋር ተያይዞ ሁለት ተጨማሪ የፍንዳታ ጥቃት ለማድረስ አልሸባብ የተሰኘው የሶማሊያ ቡድን እንደዛተ የገለፀው የአሜሪካ ኤምባሲ፤ የዛቻው ተአማኒነት ባይረጋገጥም በኢትዮጵያ የሚገኙ አሜሪካዊያን ጥንቃቄ እንዳይለያቸው ሁኔታው አሳሳቢ እንደሆነ በመግለጽ ዜናውን የከፈተው አዲስ አድማስ፣ “የኢትዮጵያና የናይጄሪያ ቡድኖች ግጥሚያ በሚካሄድበት ሰዓት ጥቃት ለመፈፀም ሲዘጋጁ የነበሩ ሁለት ሰዎች መሞታቸው የሚታወስ ሲሆን በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት በማወጅና ሽብር ለመፈፀም በመዛት የሚታወቀው አልሸባብ “ድርጊቱ በኔ አባላት የተፈፀመ ነው” ብሏል በማለት አልሸባብ በቦሌ ሚካኤል ለተከሰተው ፍንዳታ ሃላፊነት እንደሚወስድ በትዊተር እንዳስታወቀ ማሰራጨቱን፤ በፒያሳና በቸርችል ጐዳና አካባቢ የፍንዳታ ጥቃት ለመፈፀም እንደዛተም ገልጿል፡፡
በቦሌ ሚካኤል በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ በተከሰተው ፍንዳታ ሁለት የሶማሊያ ተወላጆች መሞታቸውን የገለፀው ፖሊስ፤ ከሟቾቹ አንዱ የኢትዮጵያ ማሊያ በመልበስ ከኳስ ተመልካቾች መሃል የፍንዳታ ጥቃት ለመፈፀም እየተዘጋጀ እንደነበር መጠቆሙን አዲስ አድማስ በዜናው አውጇል። አዲስ አድማስም ሆኑ ሪፖርተር ፖሊስ የነገራቸውን ከመዘገብ ውጪ ከሌሎች ሚዲያዎች፣ በተለያዩ ማህበረ ገጾችና በቅርበት ከህብረተሰቡ የሚሰጡትን አስተያየቶች አስመለክቶ ዜናውን ላቀበላቸው ክፍል አላቀረቡም።
የኢህአዴግ አንደበትና የንግድ ድርጅት የሆነው ፋና ብሮድካስቲንግ በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ የደረሰው የፈንጂ ፍንዳታ በሁለት ሶማሊያውያን አሸባሪዎች የተፈፀመ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል አሰፋ አብዩን ጠቅሶ አስታውቋል። ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳለው ፍንዳታው የደረሰው በክፍለ ከተማው ወረዳ 01 ቀበሌ 01 በተለምዶ ሩዋንዳ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በአንድ የመኖሪያ ቤት ውስጥ ነው። ፖሊስ ፍንዳታው ፈንጂ መሆኑንና በጥቅም ላይ የዋለው ቲ ኤም ቲ የተባለ የፈንጂ ዓይነት መሆኑን እንደደረሰበት አረጋግጧል። ፍንዳታውንም ሁለት ሶማሊያውያን ማቀነባበራቸውን ፖሊስ እንዳረጋገጠና ግለሰቦቹ የአሸባሪ ቡድኑ አልሸባብ አባል መሆናቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች መገኘታቸውን ጄኔራል አሰፋ አብዩ መናገራቸውን የጠቆመው ፋና ከሁለቱ አሸባሪዎች መካከል አንደኛው ወገቡ ላይ የታጠቀና ለአጥፍቶ ጠፊ ተግባር የተዘጋጀ መሆኑን ያመላክታል ብሏል።
ሌላኛው አሸባሪ በሻንጣ ፈንጂ የያዘ ሲሆን፥ የፈነዳውም ፈንጂ በሻንጣው ውስጥ የነበረ መሆኑን ነው ጀነራል አሰፋ ያስረዱት። ለአጥፍቶ ጠፊ ተግባር ሲዘጋጅ የነበረው ግለሰብ የታጠቀው ፈንጂ ግን እንዳልፈነዳ አመልክተዋል። አሸባሪዎቹ በአጠቃላይ ሶስት ፈንጂዎችንም ይዘው ነበር። አሸባሪዎቹ ህዝብ ባለበት ስፍራ አደጋ ለማድረስ ተከራይተው በነበሩበት ቤት ውስጥ ሲዘጋጁ ፍንዳታው ደርሷል ብሎ ፖሊስ እንደሚጠረጥር ነው የጠቆሙት። ከአሸባሪዎቹ ጋር ፖሊስ የእጅ ቦምቦችንና ሽጉጥ ከነጥይቱ አግኝቷል።
የፋናን ዜና ተንተርሶ የተሰነዘሩ አስተያየቶች እንደሚያመለክቱት ሪፖርተር በፈነዳው ፈንጂ ህይወቱ ያለፈው አንደኛው ሰው ሰውነቱ መበታተኑና የአይን እማኞችን ገልጾ መዘገቡን ያስታውሳሉሉ። ፈነዳ የተባለው ፈንጂ ከፈነዳ በሁዋላ አጥፍቶ ለመጥፋት የተዘጋጀው ሰው የታጠቀው ፈንጂ አለመፈንዳቱ መገለጹ ከሙያ አንጻር ጥያቄ የሚያስነሳ እንደሆነ፣ ከዚህም በላይ ድርጊቱን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታ ጋር ለማገናኘት የብሔራዊ ቡድን መለያ ሹራብ ተገኘ መባሉ ድርጊቱን ድራማ ያስመስለዋል ባይ ናቸው። (ፎቶ: ሪፖርተር)

መለስ የሚባል ራእይ የለም ሲሉ አቶ ስብሀት ነጋ ተናገሩ

October 21/2013

ጥቅምት (አስር)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-በህዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ(ህወሀት) ውስጥ የተካረረ አለመግባባት እንደተፈጠረ በስፋት በሚነገርበት በዚህ ወቅት አቶ ስብሀት ነጋ ፣ የኢህአዴግ እንጂ የመለስ የሚባል ራእይ የለም ብለዋል።

የህወሀት መስራች የሆኑት አቶ ስብሀት ነጋ ይህን ያሉት ከጋዜጠኛ ደረጀ ደስታ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ነው።

አቶ ስብሀት ፦” መለስ የ ኢህአዴግን ራዕይ ለማስፈፀም ከፊት ሆኖ ብዙ ሥራ ሠራ እንጂ ራዕዩ የመለስ አይደለም። ራይዩ የድርጅቱ ነው”ብለዋል።

በዚሁ ቃለ-ምልልስ ከሟች ጠቅላይ ሚኒስትር ባለቤት ከወይዘሮ አዘዜብ መስፍን ጋር አለመግባባት ውስጥ ገብተው እንደነበርም አቶ ስብሀት በግልጽ ተናግረዋል።

አቶ ስብሀት በዚሁ አስገራሚ መልሶችን በሰጡበት ቃለ-ምልልስ የአቶ መለስን ሞት ተከትሎ ስለተሾሙት  33 ጀነራሎች ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለም ተናግረዋል።

አቶ መለስ ማረፋቸውን ተከትሎ ከ አራቱ የ ኢህአዴግ ድርጅቶች በተውጣጡ  አራት ምክትል ጠ/ሚ/ሮች  እየተመራች ያለችው ኢትዮጵያ፤ያም አልበቃ ብሎ  ከአራቱም ድርጅቶች የተውጣጡ አራት ከፍተኛ ካድሬዎች  አማካሪዎች ተብለው አቶ ሀይለማርያም አጠገብ እንዲሆኑ መደረጋቸው ይታወሳል።

አቶ ሀ ይለማርያም ደሳለኝም አመራራቸውን አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ፦በጋራ፣በኮሚቴ እየመራን ነው ማለታቸው አይዘነጋም።

በቂ ጥበቃ ማድረግ ያልቻለ መንግስት ስልጣን ለህዝብ ማስረከብ አለበት” ሲል አንድነት ፓርቲ ገለጸ

October 21/2013


ጥቅምት (አስር)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-ፓርቲው ይህን የገለጸው ጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ ” በቂ ጥበቃ የለንም በሚል ሰላማዊ ሰልፍን እንደሚከለክሉ” መናገራቸውን ተከትሎ በሰጠው መልስ ነው። ” በቂ ጥበቃ ማድረግ ያልቻለ መንግስት ስልጣኑን ለህዝብ በማስረከብ ይቅርታ ጠይቆ መሄድ እንጅ ከአሁን በኋላ መብታችሁን አታገኟትም ” በማለት መዛት ትዝብት ውስጥ የሚጥል ድርጊት ነው ብሎአል አንድነት በመግለጫው፡፡

አንድነት  ” ተገዥነቱን ለህዝቡና ለህግ አድርጎ በአምባገነኖች ዛቻ ሳይበረግግ፤ ዘር፣ ፆታ፣ ሀይማኖት፣ ቀለም ሳይለይ ዜጎች የሚያነሱት ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች እንዲመለሱ፤ የመንግስት በሐይማኖት ጣልቃ ገብነትም እንዲቆም ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ያረጋግጣል”  ብሎአል።

ፓርቲው እንደ ኢትዮጵያ አሉ አንዳንድ የአፍሪካ መሪዎች በአለማቀፍ ፍርድ ቤት ላይ የያዙትን አቋምም ተችቷል።  ” የአፍሪካ መሪዎች ተሰብስበው እንግደል፣ እንሰር፣ እንጨፍጭፍ፣ ዘር እናጥፋ፣ ዜጎቻችንን እናሰቃይ ግን መታሰርም መከሰስም የለብንም በሚል የያዙት አቋም አሳፋሪና ተቀባይነት የሌለው ነው፣ የሚለው አንድነት፣ ሕግ እየጣሱ በህግ አለመጠየቅ አይቻልም፡፡ ዘር እያጠፉ ያለመታሰር መብት አይኖርም፡፡ ማንም ሰው ከህግ በላይ የመሆን መብት የለውም፡፡” ሲል አክሏል።

የአፍሪካ መሪዎች ተሰብስበው ማለት ያለባቸው አይሲሲ ሊከሰን አይገባም ሳይሆን የዜጎቻቸውን እንባ ማበስ ነው የሚለው አንድነት፣  አሁንም ሆነ ወደፊት በዜጎቻቸው ላይ ግፍና ሰቆቃ የሚፈፅሙ ሁሉ ሳይውል ሳያድር ወደ ፍርድ መቅረብ አለባቸው ብሎ ያምናል ሲል አቋሙን ግልጽ አድርጓል፡፡

Monday, October 21, 2013

ONLF fighters attacked Ethiopian Officials at Kebridahar Airport: several Ethiopian Troops KILLED at the airport and destroyed two vehicles.



ONLF fighters attacked at Kebridahar Airport: ONLF official

Photo: Deputy Prime Minister of Ethiopia Demeke Mekonnen and his delegation landing on the Godey Airport

By Mohamed Faarah

October 21, 2013

(Ogadentoday Press)- Ogaden National Liberation Front “ONLF,” official have claimed that their fighters attacked on Kebridahar town Airport on last week.

Our aim for this attack was to disrupt the visiting delegation in Ogaden and send a clear message to the puppet administration that serves only the colonial agendas in our people and land. The official said to Ogadentoday Press on the phone.

Speaking on the attack the official said that they have killed several Ethiopian Troops at the airport and destroyed two vehicles.

This was a co-ordinated attack and went successfully, the official said.

The puppet administration was hiding the attack but the military leaders informed the delegation, said the official citing their intelligence in the Ogaden.

I can confirm to you that, it was midnight and they have been waiting to welcome the federal delegation in the morning.

There is no comment from Ethiopia government.

The Deputy Prime Minister of Ethiopia Demeke Mekonnen, nine regional leaders, domestic and foreign investors were visiting Ogaden Region last week.

According to Ethiopian government, the domestic investors are interesting to invest the agricultural sector in Ogaden.

Ogaden National Liberation Front, a secessionist group fighting for the independence of Ogaden warns the foreign oil companies in Ogaden, and attacked in 2007 a Chinese oil field in Ogaden.

According to the source, ONLF were watching closely the visit and Pro- ONLF site "Ogaden News Agency (ONA) published that, ONLF fighters are on the high alert.

The arid Somali (or Ogaden) region of Ethiopia, home to some 7-8 million ethnic Somalis has been isolated from the world since 2005, when the government imposed a ban on all international media and most humanitarian groups from operating in the area.

Ogadentoday Press

የኢህአዴግ ቀጣይ የፖለቲካ ሴራዎች – (ተመስገ ደሳለኝ)

October 21/10/20

ከ ተመስገ ደሳለኝ 

አዲስ አበባ

የሁለት ሺህ ስድስት ዓመተ-ምህረት የመጀመሪያ ወር ተጠናቅቋል፤ አዳዲስ ክስተቶችም ታይተዋል፤ ያለፉት አስራ ሁለት ዓመታትንበጃንሆይ ቤተ-መንግስት ያሳለፉት ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ፣ በኦህዴዱ ሙላቱ ተሾመ መተካታቸው አንዱ ነው፡፡ አባይ ፀሀዬና ዶ/ር ካሱ ኢላላም ከበረከት ስምዖንና ኩማ ደመቅሳ በተጨማሪ በሚኒስትር ማዕረግ የኃ/ማሪያም ደሳለኝ ‹‹የፖሊሲና ጥናት ምርምር›› አማካሪ ሆነው መሾማቸው ሌላው ነው (በነገራችን ላይ ሹመቱን እንደተለመደው አይቶ ችላ ብሎ ለማለፍ የማያስችሉ ሶስት ምክንያቶች አሉ፤ የመጀመሪያው በሀገሪቱ ለአንድ የሥራ መደብ አራት ሚንስትር ተሹሞ አለማወቁ ሲሆን፤ ሌላው ተሿሚዎቹ፣ ኢህአዴግን ከመሰረቱት አራት ፓርቲዎች በኮታ የተወጣጡ መሆናቸው ነው፡፡ ሳልሳዊውና አስገራሚው ደግሞ ሰዎቹ ፖለቲከኞች እንጂ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ጥናትና ምርምር ያካሄዱ ምሁራን አለመሆናቸው ነው)
እነዚህ ሁሉ በግልፅ የሚታወቁ የዓመቱ መጀመሪያ ክስተቶች ናቸው፡፡ ለስርዓቱ ቅርበት ካላቸው ምንጮቼ ባገኘሁት መረጃ መሠረት፣ በቅርቡ ‹ሚዲያ›ን እና ‹የይቅርታ ስነስርዓት›ን የተመለከቱ አዳዲስ አዋጆች በተወካዮች ም/ቤት ለመፅደቅ ተዘጋጅተዋል፡፡ በተለይም ‹ሚዲያው›ን የሚመለከተው አዲሱ ህግ፣ ከአምስት ዓመት በፊት ተግባር ላይ የዋለውን የ‹‹ፕሬስ አዋጁ››ን የአፋና ጉልበት ይበልጥ የሚያጠናክር በመሆኑ፣ የነበረው አንፃራዊ ጭላንጭል ጭራሽ ሊዳፈን እንደሚችል መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ‹‹የይቅርታ አዋጁ››ም ቢሆን ጥቂት የአገዛዙ ጉምቱ ባለስልጣናት ‹‹የተቃዋሚ ፓርቲ የአመራር አባላትና አንዳንድ የግል ጋዜጠኞች ብንታሰርም በይቅርታ እንፈታለን በሚል ግንባሩን እየተፈታተኑ ነው›› ሲሉ ደጋግመው መደመጣቸውን፣ ከአዲሱ ‹‹የይቅርታ አሰጣጥ እና አፈፃፀም ሥነ-ሥርአት አዋጅ›› ጋር ካያያዝነው፣ አንቀፆቹ ሊኖራቸው የሚችለውን አንድምታ መገመቱ ብዙ ከባድ አይሆንም፡፡

ለማንኛውም ኢህአዴግ ከመቼውም ጊዜ በላይ ጉልበታም በመሆን ቀጣዩን ምርጫ በስኬት ለማለፍ፣ በያዝነው ዓመት የተለያዩ አፋኝ ህጎችን በማውጣት ፓርቲዎቹን የማዳከም ስራ ለመስራት በተለየ መልኩ መዘጋጀቱ ተሰምቷል፡፡ በአናቱም ኃ/ማርያም ደሳለኝ-ከመንግስት፣ ከፓርቲውና ከውስን የግል ጋዜጠኞች፤ ደመቀ መኮንን-ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ፤ ሽመልስ ከማል -ከኢዜአ ጋር ያደረጓቸው ቃለ-መጠይቆችም ይህንን መረጃ የሚያጠናክር ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ የዚህ ፅሁፍ ተጠየቅም አገዛዙ በቀጣይ ሊኖረው የሚችለውን ባህሪ እና ‹አምስተኛው ዙር ሀገር አቀፍ ምርጫ›ን አስቀድሞ ለማሸነፍ እየቀመረ ያለውን ሴራ መጠቆም ነው፡፡

የባለስልጣናቱ አንደበት

ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያምና ምክትሉ ደመቀ ሰሞኑን ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃለ-መጠይቅ ላይ፣ በስሱም ቢሆን ከጀርባቸው ያደፈጡትን አንጋፋ ታጋዮች ቀጣይ ‹‹የፖለቲካ ሴራ›› (Political Conspiracy) አርድተውናል ብዬ አስባለሁ፡፡

ሁለቱ መሪዎች በዋናነት እንዲያተኩሩ የተደረገው በአራት ጉዳዮች ላይ ነው፡፡ በግንባሩ ውስጥ ክፍፍል መፈጠሩን መካድ፣ አመቱን ሙሉ ‹የመለስ ራዕይ› እየተባለ የተዘመረለትን ‹እሳት ማጥፊያ› ፕሮፓጋንዳ ማስተባበል፣ የሙስና ክሱን ሂደትና ውጤት መሸፋፈን እንዲሁም ተቀናቃኝ ፓርቲዎችን ማስፈራራት የሚሉ ናቸው፡፡ በአዲስ መስመርም እነዚህን አራት አጀንዳዎች ነጣጥለን ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡

ክፍፍሉን በተመለከተ

ከመለስ ህልፈት ማግስት አንስቶ በግንባሩ ግልፅ ክፍፍል መከሰቱ የአደባባይ ሀቅ ቢሆንም፣ ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማሪያም ‹‹ፓርቲዎ ውስጥ ክፍፍል አለ ይባላል፤ የኃይል አሰላለፍ እየተጠበቀ ነው የሚኬደው የሚባሉ አሉባልታዎች ይሰማሉ፣ የፓርቲዎ ጤናስ እንዴት ነው?›› የሚል ጥያቄ ሲቀርብለት፡-

‹‹በፓርቲዬ ውስጥ ክፍፍል አለ የሚለው ጥያቄ የምኞት ነው፤ ብዙ ምኞቶች ሲሰሙ ነበር፤ ምኞት አይከለከልም፡፡ ስለዚህም ምኞት ይኖራል የሚል ሃሳብ ከማቅረብ በዘለለ እውነት ስለሌለው ምኞት ነው ብሎ ማለፍ ነው›› በማለት አስተባብሎ ሲያበቃ፤ ከደቂቃዎች በኋላ ደግሞ ተገልብጦ ‹‹አሁን በቅርቡ እንደደረስንበት አንዳንድ ጊዜ በየቦታው ደባ የሚሰሩ ጥቂት የመሥሪያ ቤት ሰራተኞች አሉ›› ብሎ የራሱ ሰዎች በመንግስቱ ላይ እያሴሩበት እንደሆነ በመግለፅ ከላይኛው ንግግሩ ጋር መጣረሱ፣ በርግጥም የተጠቀሰው ችግር መኖሩን ለመረዳት አያዳግትም፡፡

ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተም ‹‹አዲስ ዘመን›› ጋዜጣ ምክትል ጠ/ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መልኩ አጠንክሮ ጠይቆት ያስተባበለበት መንፈስም ለመሸሸግ የፈለገው ጉዳይ እንዳለ የሚያሳብቅ ይመስላል፡፡
‹‹አንድ ግልፅ መሆን ያለበት እንደ አቶ መለስ ያለ ታላቅ መሪ፣ ታግሎ የሚታገል ጠንካራ መሪን ማጣት ትልቅ ጉድለት ነው፡፡ ጉድለቱ እንዲሁ ዝም ተብሎ እዚያና እዚህ በዘመቻ የሚሞላ ጉዳይ አይደለም፡፡ …ስለዚህም ሁለት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደረጃ ኃላፊዎችን በመሰየም ክላስተር እንዲያስተባብሩ ማድረግ ያለመተማመን መገለጫ አይደለም፡፡››
የሁለቱ ሚኒስትሮችን ያልተጠበቀ ቃለ-መጠየቅ መግፍኤ ለመረዳት በተለይ ደመቀ መኮንን ለቀረቡለት ጥያቄዎች የሰጠውን ምላሾች በጥልቅ መፈተሽ አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም ተከስቶ የነበረውን መከፋፈልም ሆነ ‹ፓርቲው በጥቂት የህወሓትና የብአዴን ታጋዮች ነው

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

የሚሽከረከረው› መባሉን ለማስተባበል የሄደበት መንገድ፣ ከዚህ ቀደም ኢህአዴግ የሚከራከርባቸውን እምነቶቹን ጭምር እስከመናድ የደረሰ ነውና፡፡ ወይም እንዲንድ ታዝዟል ያስብላል (በነገራችን ላይ ከምንጮቼ ባገኘሁት መረጃ እነአባይ ፀሀዬና በረከት ስምዖንም ከመጋረጃው ጀርባ የሚሰራ ኃይል መኖሩን ማስተባበል ይፈልጋሉ፡፡ በተለይም ‹‹በነፃነት እንዲሰሩ አመቻቹላቸው›› እያሉ የሚወተውቷቸውን ምዕራባውያን ዲፕሎማቶች ማሳመኑ ከባድ ሥራ እንደሆነባቸው ሰምቻለሁ፡፡

የሰሞኑ የቃለ-መጠይቅ ጋጋታም ይህንኑ የሚያጠናክር ይመስላል፡፡ ‹‹አዲስ ዘመን›› ጋዜጣም ለደመቀ መኮንን ያቀረባቸው ጥያቄዎች ከቀደመው ታሪኩ አኳያ ሲመዘን የግል እምነቱ አለመሆኑን መረዳት አያዳግትም፡፡ ‹‹ጋዜጣው እስከአሁን ያልነበረውን ‹የኤዲቶሪያል ነፃነት› ዛሬ አግኝቶ ነው ሰውየውን እንዲህ ያፋጠጠው›› የሚል ተከራካሪ ካልቀረበ ማለቴ ነው፡፡ ምናልባትም ጉዳዩን በሌላ አውድ እንየው ከተባለ ደግሞ የሚያያዘው፣ የድርጅቱ አመራሮች አልፎ አልፎ ህዝብ ዘንድ የደረሱ እውነታዎችን፣ በራሳቸው ጋዜጠኞች እንዲጠየቁ በማድረግ ለማስተባበል ከሚሞክሩበት የቆየ ልማዳቸው ጋር ብቻ ነው፡፡ በመስከረም 22፣ 23 እና 24 ቀን 2006 ዓ.ም በታተመው የ‹‹አዲስ ዘመን›› ጋዜጣ በተስተናገደው የደመቀ መኮንን ቃለ-መጠይቅ ላይ የተነሱትን ጥያቄዎች ብንመለከት ይህንኑ ያረጋግጡልናል፡፡ ‹‹ፓርቲው በጥቂት ሰዎች ስር ስለመውደቁ፣ ከመንግስት ኃላፊነት የተነሱ ባለስልጣናት በፓርቲው ውስጥ ስራ-አስፈፃሚ ሆነው ስለመቀጠላቸው፣ መተካካቱ የቦታ መቀያየር ብቻ ስለመሆኑ፣ ሥራ የማይሰሩ ደካማ መሆናቸውን በተወካዮች ም/ቤት ጭምር የተረጋገጠባቸው ከፍተኛ አመራሮች ዛሬም በኃላፊነት ቦታ ላይ ስለመቀመጣቸው፣ በብልሹ አሰራር /በሙስና/ የተጠየቁ ባለስልጣናት ጥቂት ብቻ መሆናቸው፣ በአቅም ማነስ የሚነሱ ኃላፊዎች ወይ ከነበሩበት የተሻለ አሊያም ተመጣጣኝ በሆነ ደረጃ ስለመመደባቸው፣ አንድ ጊዜ የላይኛውን የስልጣን እርከን የተቆናጠጠ ባለስልጣን ከፓርቲው ቁልፍ አመራሮች ጋር ካልተጋጨ በቀር አቅም ባይኖረውም እንደማይሻር፣ ለፓርቲው መስራቾችና እስከአሁንም ወሳኝ ለሆኑት አመራሮች ታማኝ የሆነ ኃላፊ ምንም አይነት ድክመትና ወንጀል ቢፈፅምም በስልጣን መቆየት መቻሉን፣ የሁለቱ ተጨማሪ ምክትል ጠ/ሚኒስትሮች ሹመት በአራቱ የብሔር ድርጅቶች መካከል ያለውን አለመተማመን ስለማሳየቱ፣ ሁሉም ፓርቲዎች እኩል አለመሆናቸውን፣ መለስ በሃያ ሁለት የሥልጣን ዓመታቱ ተተኪ ማፍራት አለመቻሉን፣ ‹የመለስ ራዕይ› የሚባል ነገር አለመኖሩን…›› እና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ባልተለመደ ድፍረት የጠየቀው መንግስታዊው ዕድሜ ጠገብ ‹‹አዲስ ዘመን›› ጋዜጣ ነው)

ቃለ-መጠየቁ ከእነዚህ በተጨማሪም ቀጣዩን የኢህአዴግ አቅጣጫ አመላክቷል፡፡ የሆነው ሆኖ ክፍፍሉንና ከጀርባ ሆነው ያሽከረክራሉ የሚባሉትን አንጋፋ የአመራር አባላት አስመልክቶ ለቀረበለት ጥያቄ ከሰጠው ምላሽ ውስጥ እንዲህ የሚል ይገኝበታል፡-

‹‹ፓርቲው አንድ ሰው፣ ሁለት ሰው፣ ሶስት ሰው እጅ ጠምዝዞ ‹ይሄን አድርጉ› በሚል አንዳችም ጉዳይ የሚያስፈፅምበት አይደለም፡፡ …ኢህአዴግ በጥቂቶች የሚመራ ድርጅት አይደለም፡፡ …ጥቂት ግለሰቦችን በተለየ ሁኔታ የሚያይ፣ በእነርሱም ስር የሚሆን አይደለም፡፡ የጥቂቶች ነው የሚለው ከእውነት የራቀ ነው፡፡ …ማንም በራሱ ተቆጥሮ በተሠጠው ሥራ ሊወስን፣ ሊመራና ሊንቀሳቀስ ይችላል፡፡ በድርጅታዊ ዲሲፒሊንና አሰራር፣ የግልና የጋራ አሰራር በሚዛን ተቀምጦ በንቅናቄ የሚመራ እንጂ በግለሰቦች አይደለም የሚለው ቢሰመርበት ጥሩ ነው፡፡››

በርግጥ ይህንን ያነበበ ‹‹ሰውየው ስለየትኛው ኢህአዴግ ነው የሚያወራው?›› ቢል ላይፈረድበት ይችላል፡፡ ምክንያቱም የድርጅቱ የታሪክ ንባብም ሆነ የቀድሞዎቹ ስዬ አብርሃ፣ አለምሰገድ ገ/አምላክ፣ አውዓሎም ወልዱ፣ ገብሩ አስራት፣ አረጋሽ አዳነ፣ ነጋሶ ጊዳዳ፣ ሀሰን አሊ፣ አልማዝ መኩን የመሳሰሉት የአመራር አባላት የነገሩን ‹ድርጅቱ በጣት በሚቆጠሩ ሰዎች ፍቃድ የሚያድር› መሆኑን ነው፡፡ ለነገሩ ራሱ ደመቀም ቢሆን ከኤርትራ ጋር ወደ ጦርነት ለመግባት ህወሓት በር ዘግቶ ብቻውን መምከሩንም ሆነ የግንባሩን አባል ድርጅቶች ነፃነት እንዳሻው መጋፋቱን አምኖ መቀበል ባይፈልግ እንኳን፣ በ1999 ዓ.ም መጨረሻ ከሱዳን ጋር የሚዋሰነው የጎንደር መሬት ላይ የተላለፈው ውሳኔ በምን መልኩ እንደነበረ ሊክደው አይችልም (በነገራችን ላይ በወቅቱ የአማራ ክልል አስተዳዳሪው አያሌው ጎበዜ ምክትል የነበረ በመሆኑ፣ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ጎንደርና ትግራይ አካባቢ፣ የሚወራበትን ውንጀል በሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ)

የሰውየው መከራከሪያ ግን እውነት አለመሆኑን ‹ፍትህ›ና ‹ልዕልና› ጋዜጦች፤ ‹አዲስ ታይምስ›ና ‹ፋክት› መፅሄትን ጨምሮ የምዕራብ ሀገራት ብዙሃን መገናኛ እና ድርጅቱን በቅርብ የተከታተሉ ምሁራን በተለያየ ጊዜ ማስረጃ በማጣቀስ ደጋግመው ስላቀረቡ ተጨማሪ ማብራሪያ ያስፈልገዋል ብዬ አላስብምና ወደ ቀጣዩ ጉዳያችን አልፋለሁ፡፡

‹‹መተካካት›› ሲባል…

በአንድ ወቅት አቶ መለስ ብዙ ብሎለት የነበረው የመተካካት ዕቅድ ‹‹ቦታ ከመቀያየር ያለፈ አዲስ ፊት አላመጣም›› መባሉን በተመለከተ፣ ደመቀ መኮንን የሰጠውን ምላሽ፣ ከተለያየ አውድ ካየነው ከላይ የተጠቀሰውን ክፍፍል በሌላ በኩል ይነግረናል፡፡ ምክንያቱም መለስ በህይወት በነበረበት ዘመን ጉዳዩን አስመልክቶ የነገረን ‹መተካካቱ ከላይ ያሉትን ነባር የአመራር አባላት፣ በየተራ በጡረታ በማሰናበት አዲሱን ትውልድ (አዲስ ፊት) ወደመሪነት ማምጣት ነው› የሚል እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ደመቀ መኮንን ደግሞ በግልባጩ እንዲህ ይላል፡-

‹‹አዲስ ፊት ሲባል የማናውቀው ሰው ከጨረቃ ይምጣ? የሚመራው እኮ አገር ነው፡፡ አንድ ሰው አንድ ቦታ ላይ ሆኖ ሥራውን እየተወጣ፣ ሌላውንም እያበቃ ሥርዓቱ መቀጠል አለበት፡፡ በጣም የሚታወቅ ህዝባዊ አገልግሎት ላይ ያለ ሰው፣ ከያዘው ኃላፊነት ሌላ፣ በሌላ ጊዜ ሌላ ተክቶ ሊቀርብ ይችላል፡፡ አዲስ ፊት የለም፤ የማናውቃቸው ሰዎች ይምጡ ማለት፣ ሀገር የሙከራ ቦታ ይሁን ማለት ነው፡፡››

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲህ የሚደክመው በረከት ስምዖን፣ አባይ ፀሀዬ፣ ኩማ ደመቅሳ፣ ሽፈራው ጃርሶ፣ ካሱ ኢላላ፣ ሙላቱ ተሾመን… የመሳሰሉ አንጋፋ መሪዎች ከዚህ ቀደም ለአባላቶቻቸው የገቡትን ቃል ጠብቀው በክብር ከመሰናበት ይልቅ ስልጣን መቀያየራቸውን ለማስተባበል ይመስለኛል፤ በርግጥ ጉዳዩን ከለጠጥነው ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ከአንጋፋዎቹ መካከልም ሊሆን ይችላል እያለን ይሆናል፡፡ ይሁንና ሰውየው ያስተባበለበት መንገድ ግን በውስጡ ካለው እውነታ ጋር የተቃረነ በሚመስል መልኩ
የመተካካቱ አንድምታ የተቀየረው በመካከል የተፈጠረውን የኃይል ልዩነት አርግቦ፣ ስርዓቱ ከገጠመው መንገራገጭ ወጥቶ በሁለት እግሩ ቀጥ ብሎ ቆሞ እንዲቀጥል ለማስቻል መሆኑን ፍንጭ ይሰጣል፡፡

‹‹መተካካት ግለሰብን አይደለም የሚተካው፤ የስርዓት ቀጣይነትን ማረጋገጥ ነው!››

ይህ ሁናቴ በደንብ የሚፍታታው አቦይ ስብሃት ነጋ በተለይ ህወሓት ውስጥ የተካሄደው መተካካት ከተፈጠረው ልዩነት ጋር ተያይዞ መሆኑን ለ‹‹ውራይና›› መፅሄት የሰጡትን ቃለ-መጠየቅ ስናነብ ነው፡-

‹‹ጉባኤው ከማዕከላዊ ኮሚቴ ለተሰናበቱ ሰዎች ከዚህ ቀደም እንደሚያደርገው፣ አሰራር ለምን እነሱን በሌሎች መተካት እንዳስፈለገ፣ ተራ በተራ እየጠቀሰ አስተያየት (ማብራሪያ) መስጠት ነበረበት፡፡ ይህ ተደርጎ ቢሆን ኖሮ ከተሰናባቾቹ መካከል ማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ መቆየት (መቀጠል) የሚገባቸው በተገኙ ነበር፡፡ ከተመረጡት ውስጥ ደግሞ መሰናበት (በሌላ መተካት) የሚኖርባቸው ሊገኙ ይችሉ ነበር፡፡ ስለዚህ አካሄዱ ስህተት ስለሆነ ውጤቱም እንደዚያው ሊሆን ችሏል፡፡ እነማን መሰናበት፣ እነማን መቆየት እንደነበረባቸው በዝርዝር ስም ጠርቼ መናገር እችል ነበር፡፡ ግን ምንም ለውጥ ስለማያመጣ ስም መዘርዘሩ አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡››

የ‹‹ራዕዩ›› ጉዳይ…

በፋክት መፅሄት ቁጥር 5 ላይ ኢህአዴግ ‹የመለስ ራዕይ› እያለ ይደሰኩርለት የነበረውን አጀንዳ በወራት ጊዜ ውስጥ ገልብጦ በማጠቋቆር ሊቀየረው መዘጋጀቱ ተጠቅሶ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ በደመቀ መኮንን ቃለ-መጠይቅ ላይም፣ መለስ ሥልጣን ላይ በነበረበት ዘመን ተገምግሞ መንግስታዊ ተቋማትንና የልማት ዕቅዶችን በአግባቡ መከታተልና መቆጣጠር አለመቻሉ ተገልጿል፡፡

‹‹ያለፉት ዓመታት ሥራዎቻችንን ስንገመግም ጠቅላይ ሚኒስትራችን ብዙ ሥራ ተሸክመው ይሰሩ በነበረበት ዋና ዋና የልማት ሥራዎቻችን ላይ በማተኮር አንዳንድ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና የልማት መስኮችን በሚፈለገው ደረጃ ያለመፈተሽ፣ በዝርዝር ዕቅድ ግምገማና ድጋፍ ያለማድረግ ክፍተቶች እንደነበሩ እንደ ችግር በጋራ ያገኘናቸው ነጥቦች አሉ፡፡››

እንዲያ ሀገር-ምድሩ ‹ካልዘመረለት ተደፍረናል!› ሲሉለት የነበረው ‹‹የመለስ ራዕይ››ም ቢሆን የኢህአዴግ እንጂ የመለስ አለመሆኑን እየነገሩን ነው፡፡ አቶ ደመቀም፣ መለስ የነበረው ‹‹ራዕይ›› ሳይሆን ኃላፊነት ነው ወደ ማለቱ አዘንብሏል፡፡
‹‹ይሄን የዕድገት መንገድ ከኢህአዴግ አባላትና ከመሪዎቹ ጋር በመሆን በግንባር ቀደምነት የመሪነት ቁልፍ ሚና የተጫወቱ መሪ ናቸው፡፡››

በጥቅሉ በወቅታዊው የድርጅቱ ፖለቲካዊ አተያይ ‹‹የመለስ ራዕይ›› የሚለው ሀረግ ከየት እንደመጣ የተተነተነበትን አውድ ለመረዳት ከጋዜጣው ላይ አንድ ተጨማሪ ጥያቄና መልስ እንደወረደ ልጥቀስ፡-

‹‹አዲስ ዘመን፡- በየዘርፉ ራዕያቸው ተብለው የሚነገሩት መልእክቶችና መሪ ቃሎች ጋር በተያያዘ የተለጠፈባቸው ራዕይ እንዳለ ነው የሚነገረው፤ አገሪቱን ከመሩበት 22 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ምናልባት አንድ ጊዜ በንግግር መሀል የተናገሯት ወይም ለጋዜጠኞች የሰጡት ምላሽ ራዕይ ተደርጎ እየቀረበ ነው ስለሚባለውስ?

‹‹አቶ ደመቀ፡- እነዚያ መልዕክቶች ያንን ራዕይ የሚገልፁ፣ የሚያስታውሱ ምልዕክቶች ናቸው፡፡ ከማንኛውም ጉዳይ ጋር የተያያዙ መልዕክቶች ይኖራሉ፡፡ እነዚያ ያንን ትልቁን ራዕይ የሚመግቡ መልዕክቶች እንደሆኑ አድርጎ መመልከት ይቻላል፡፡››
ይኸው ነው፤ በቃ፡፡ መለስ ራዕዩን በጥሩ ቋንቋ ከመግለፅ ባለፈ የብቻው የሆነ ነገር የለውም፡፡ በክፍፍሉ ወቅት ከ‹አዲስ አበባው-ህወሓት› ጎን የተሰለፉት አቦይ ስብሃት ነጋ በጉባኤ፣ በተለያዩ ጋዜጦችና መፅሄቶች እንዲሁም አርከበ እቁባይ በህወሓት ጉባኤ ላይ የመለስ ‹ራዕይ› የሚባል ነገር አለመኖሩን በመግለፅ፣ በወቅቱ በአሰላለፍ የተመሳሰሉት ‹የመቀሌው-ህወሓት› እና ብአዴን በ‹ራዕይ› ስም ኃይል የማጠናከር እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን ለመተቸትና ለማደናቀፍ መሞከራቸው ይታወሳል፡፡ ይህ ሁናቴም ልዩነቱ ከተገለፀባቸው ምልክቶች አንዱ ተደርጎ ተወስዷል፡፡ ሌላው እዚህ ጋ መነሳት ያለበት ጉዳይ በዚህ ዓመት በዚሁ መፅሄት ላይ ‹‹አዲሱ የኢህአዴግ አሰላለፍ›› በሚል ርዕስ የቀረበው ፅሁፍም ‹‹የመለስ ራዕይ››ን የማይቀበለው ቡድን እያሸነፈ በመምጣቱ፣ የእነ አዜብ-አባይ ወልዱ ህወሓትን አዳክሞ፣ የእነ በረከት-ብአዴንን ከጎኑ ማሰለፍ መቻሉን የተተነተነበትን ጉዳይ የሚያጠናክር መሆኑን ነው፡፡

የሆነው ሆኖ አሁን መለስን የሚያመልኩት ሄደዋል፤ በቦታውም እርሱ የሚያርቃቸው፣ እነርሱም ይፈሩት የነበረ ተተክተዋል፡፡ እናም በህልፈቱ ማግስት ድጋፍ ማሰባሰቢያ እና ኃይል ማጠናከሪያ ከመሆን አልፎ ሀገሪቱን ወደ ብልፅግና ሰማይ የሚያከንፍ፣ መና የሚያዘንብ ተደርጎ የነበረውን ‹‹የመለስ ራዕይ›› ታሪክ በማድረጋቸው፣ አርቀው መስቀል ይፈልጋሉ፡፡ በሌላ አነጋገር በፋውንዴሽኑ አጥር ክልል ተወስኖ ይቀመጥ ዘንድ በይነዋል (በነገራችን ላይ ይህን ጉዳይ በዚህ ደረጃ ያነሳሁት የስርዓቱ መሪዎች ‹‹እንመራዋለን›› የሚሉትን ህዝብ በአደባባይ ሲዋሹ ቅንጣት ያህል ሀፍረት እንደማይሰማቸው ለማሳየት እንጂ፣ በግሌ መለስም ሆነ ጓደኞቹ ለስልጣናቸው ካልሆነ በቀር ሀገር የሚጠቅም ራዕይ አላቸው ብዬ አላምንም)

የ‹‹ሙስና››ውን ክስ ሂደት መሸፋፈን

የእነ መላኩ ፈንቴን እስር ተከትሎ ‹‹ሙስና›› ዋነኛ አነጋጋሪ አጀንዳ ሆኖ ነበር፡፡ በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማሪያምም ‹ጉዳዩን ራሴ እከታተለዋለሁ› የምትል ፉከራ ብጤም ሞካክራው ነበር (ቀደም ሲል በዚሁ መፅሄት የ‹ሙስና›ው ክስ በፖለቲካው የኃይል አሰላለፍ ላይ የበላይነትን ለመጨበጥ በአዲስ አበባው ህወሓት የተመዘዘ ‹‹ካርድ›› እንደሆነ መገለፁ ይታወሳል)
ባለሥልጣናቱ የታሰሩ ሰሞን ‹‹የመለስ ራዕይ›› ገና አልከሸፈም ነበርና ‹‹የፀረ-ሙስና ኮሚሽን›› ኮሚሽነር አሊ ሱለይማንም ጉዳዩን አቶ መለስ ራሱ ጀምሮት ለሁለት ዓመት ያህል ሲከታተለው ከቆየ በኋላ፣ በመጨረሻ ህይወቱ እንዳለፈ እያለቃቀሰ ነግሮን ነበር፡፡ 
ይሁንና
ከእስራ አምስት ቀን በፊት ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ባደረገው ቃለ-መጠይቅ፣ የታሰሩትን ሰዎች አስመልክቶ ከጊዜ ቀጠሮ ያለፈ ቁርጥ ያለ ነገር አለመኖሩ፣ በሌሎች ላይ ስጋት ስለመፍጠሩ ተጠይቆ በሰጠው ምላሽ ‹ገድሉ›ን ከመለስ ወደራሱ (ከኋላው ወደአሉ ሰዎች) መልሶታል፡፡

‹‹በቅርቡ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አካባቢ የተፈጠረውን ችግር ለማቃለል በሙስና የተጠረጠሩ የባለሥልጣኑ ኃላፊዎችና በሙስና ተግባሩ ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች ተጠያቂ የሚሆኑበት ስርዓት ተዘርግቶ የመንግስት አካል የሆነው የፌደራል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ክስ መስርቷል፡፡››

ጥያቄውም ይህ ነው፡፡ ‹‹የአሊ ሱሊማንን ‹መለስ የጀመረው…› መግለጫንስ ምን እናድርገው?››

…ደመቀ መኮንንም ‹‹እዚያም እዚያም ከኃላፊነት የማውረድ፣ በሕግ የመጠየቅና ሕጋዊ እርምጃዎች ደረጃቸውን ጠብቀው ይቀጥላሉ›› ቢልም በመሬት ያለው ተጨባጭ እውነታ ግን የሚያሳየው ሙስና የተዘጋ አጀንዳ መሆኑን ነው፡፡ የ‹‹አዲስ ዘመን›› ጋዜጣ የፊት ገፆችም ‹‹ሚኒስትር እገሌ…››፣ ‹‹ዳይሬክተር እገሌ… በሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ›› ከሚል ዜና በብርሃን ፍጥነት ‹‹በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 10 የዲዛይንና ግንባታ ፍቃድ ጽ/ቤት፣ የግንባታና ዕድሳት ባለሙያ የነበረችው ግለሰብ መስከረም 21 ቀን 2006 ዓ.ም አራት ሺ ብር ጉቦ ስትቀበል በፌደራል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሠራተኞች እጅ ከፍንጅ ተያዘች›› ወደሚል ቧልት ተቀይረዋል፡፡

አቦይ ስብሃት ነጋ ከላይ በጠቀስኩት መፅሄት የሙስናውን ጨዋታ የገለፁት እንዲህ በማለት ነበር፡-
‹‹አሁንም ድረስ ያልተፈቱ የአካሄድ (የአሰራር) ችግሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ ‹ሙስና አለ› ብትል፣ ሙስና በስርዓቱ ላይ በሚያደርሰው አደጋ ላይ ከማተኮር ይልቅ ‹አንተስ ከሙሰኛነት ነፃ ነህ ወይ?› በማለት ዋናው ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ቀዝቃዛ ውሃ የሚቸልሱ ሰዎች ጥቂት አይደሉም፡፡ አሁንም ቢሆን ይህንን የከፋ ድርጅታዊ ጉዳይ (ችግር) በመጋረጃ ሸፋፍኖ ለማለፍ ‹ስብሃት ለምን በጊዜው ጉባኤው ላይ አላቀረበውም ነበር› የሚሉ አይጠፉም የሚል ግምት አለኝ፡፡ በበኩሌ ይህ ነገር በሌላ ላይ ጊዜው ሲደርስ የሚነሳ ይሆናል ነው የምለው:፡››

በርግጥ የአቦይ ወቀሳ እውነት ነው፡፡ ይሁንና ጉዳዩን በጉባኤው ላይ ያላነሱበት ምክንያት ‹‹በሌላ ላይ ጊዜው ሲደርስ የሚነሳ ይሆናል›› በሚል እንደሆነ ለመናገር መሞከራቸው ግን የክፍለ ዘመኑ አስቂኝ ቀልድ ከመሆን የዘለለ ፋይዳ የለውም፤ ባይሆን ‹‹አንተስ ከሙሰኛነት ነፃ ነህ ወይ?› ይሉኛል ብዬ ተውኩት›› ቢሉን፣ ቢያንስ ለግልፅነታቸው ባርኔጣ እናነሳ ነበር፡፡ ምክንያቱም በኢትዮጵያ ሰማይ ስር የኢህአዴግ ሰዎችን የሙስና ወንጀል በህግ የሚያስጠይቅ ከሆነ አቦይ ስብሃት ከፊት መስመር መሰለፋቸው አይቀርምና፡፡ ሌላው ቀርቶ አርከበ እቁባይ ለጊዜው ገለል እንዲል (ከሀገር እንዲወጣ) የተደረገው ከዚሁ ጋር በተያያዘ እንደሆነ የመረጃ ምንጮቼ ነግረውኛል፡፡ አርከብ፣ አቦይን ጨምሮ ከታሰሩት ባለሀብቶች ውስጥ ጥቂቶቹ በስጋ ዝምድናና በጋብቻ የተሳሰሩት የመሆኑ ጉዳይ ይመስለኛል ‹ማዕበሉ እስኪረጋ› ከዕይታ እንዲርቅ የተደረገበት ምስጥር፡፡ በተቀረ አርከበ ሀገር ጥሎ ኮበለለ፣ ኢህአዴግን ከዳ… ጂኒ ቁልቋል የሚሉት የፒያሳ ወሬዎች፣ አንድም ወቅታዊውን የኢህአዴግ አሰላለፍ ካለመረዳት ሊሆን ይችላል፤ አሊያም የጉዳዩ ባለቤቶች ስራዬ ብለው የተሳሳተ መረጃ በሚያስተላልፉበት በተለመደው ሰርጥ ያሰራጩት ማስቀየሻ ነው የሚሆነው፤ አርከበ የሄደው አቦይ እንዳሉት ‹‹አንተስ ከሙስና ነፃ ነህን?›› የማለቱ አቅም ያላቸውን አጉረምራሚ ሰዎችን ለማለዘብ ነው፡፡ ምናልባት የመቀሌው ህወሓት አሸንፎ ቢሆን ኖሮ እውነትም አርከበ ከቃሊቲ ይልቅ አሜሪካ ይሻለዋል ማለታችን አይቀርም ነበር፡፡ እነርሱም ቢሆኑ በእጁ ላይ ካቴና ለማጥለቅ አያመነቱም፡፡ ግና! የሆነው በተገላቢጦሹ ነው፡፡ …ማን ነበር ‹‹አባቱ ዳኛ…›› ያለው? (በነገራችን ላይ ኢህአዴግ የሙስና አዋጁንም በዚሁ ዓመት የማሻሻል ዕቅድ አለው፡፡)

የአፈናው ዝግጅት

ስርዓቱ በሚቀጥለው ዓመት የሚደረገው አምስተኛ ዙር ሀገር አቀፍ ምርጫን ከወዲሁ ‹የቤት ስራን በማጠናቀቅ› ካልተዘጋጀንበት፣ ያልተጠበቀ አደጋ ሊያመጣብን ይችላል ወደሚል ጠርዝ የተገፋው አንድነት እና ሰማያዊ ፓርቲ በተለያየ ጊዜ በጠሩት የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተገኘው ህዝብ ቁጥር አሳስቦት ብቻ አይመስለኝም፡፡ ይልቁንም ኢህአዴግ ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ ያለ መለስ ዜናዊ የሚጋፈጠው የመጀመሪያው ምርጫ በመሆኑም ጭምር ነው፡፡ እንደሚታወሰው አቶ መለስ ሁሉንም የሥልጣን ምንጮች ጠቅልሎ የያዘ ‹ጠንካራ ሰው› (Strong Man) በመሆኑ፣ በእንዲህ አይነት ወቅት የሚመጡ ድንገቴ አደጋዎችን ለመቋቋም ብዙም ሲቸገር አይስተዋልም ነበር፡፡ ይሁንና በቀጣዩ ምርጫ አንድም በድርጅቱ ውስጥ የእርሱ አይነት ተተኪ ሰው አለመኖሩ፣ ሁለትም ምንም እንኳ ከህልፈቱ በኋላ የተፈጠረው ልዩነት በአንፃራዊነት የተረጋጋ ቢመስልም፣ ለሌላ ዙር የክፍፍል አደጋ አለመጋለጡ አስተማማኝ ባለመሆኑ ስጋት መፍጠሩ የሚጠበቅ ነው፡፡ በአናቱም ከእስልምና እምነት ተከታዮች ጋር የተከሰተው አለመግባት እና በማህበረ ቅዱሳን ላይ ተፅእኖ ለማድረግ የመሞከሩ ጨዋታም ለተቀናቃኞች ያልተጠበቀ ኃይል ሊሆን የሚችልበት ዕድል ቢፈጥርስ የሚል ስጋት አለ፡፡

የባለሥልጣናቱ በአደባባይ የማስፈራራት መግፍኤም ይኸው ነው፡፡ ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማሪያም በቃለ-መጠይቁ ላይ ተቃዋሚዎችን (አንድነትና ሰማያዊን) እና የሀይማኖት ማህበራትን ለማስፈራራት ከሰባት ጊዜ በላይ የመለስን ‹‹ቀይ መስመር›› አገላለፅ ተጠቅሞበታል፡፡ በተለይም ሁለቱ ፓርቲዎች የያዙት በሠላማዊ ሠልፍ ተፅዕኖ የመፍጠር መንገድ ተከታዮቻቸውን እያበዛ እና የፈዘዘውን የፖለቲካ ተሳትፎ እያነቃቃው መሆኑን ግንባሩ ጠንቅቆ የተረዳው ይመስለኛል፡፡ በኃ/ማሪያምም በኩል ያስተላለፈው መልዕክትም ቀጣዩን የፖለቲካ ሴራ አመላካች ነው፡-

‹‹መታወቅ ያለበት አንድ ጥያቄ በተደጋጋሚ የሚጠየቅ ከሆነ፣ እኛም አንድ ቦታ ስንደርስ ‹ለዚህ ጥያቄ ብዙ ጊዜ መልስ ሰጥተናል፤ ጥያቄው ይህ ከሆነ የሠልፍ ትርጉም ምንድነው?› ብለን የምናቆምበት ደረጃ እንደርሳለን፡፡ ምክንያቱም ሠልፍ ለዘላለም የሚካሄድበት ሀገር ያለ አይመስለኝም፡፡››

በተመሳሳይ መልኩ የሃይማኖት ማህበራት የሚያነሱትን የመብት ጥያቄም ወዴት ሊገፋው እንደሚችል ጥቁምታ ሰጥቷል፡-
‹‹የሀይማኖት ግብንም አክራሪዎች በምድር ላይ ሊሰሩ የሚፈልጉትን ግብ ሁለቱን የሚያምታቱ ሰዎች አሉ፤ የሌላውን ግብ በምድራዊ ዓለማዊ ማሳካት ስለማይቻል፣ እነዚህ ፖለቲከኞች ይዘዋቸው እንዳይነጉዱ፣ ከህዝብ እንዲነጠሉ ምክር ማስተላለፍ እፈልጋለሁ፡፡ የሚታወቁ ስላሉ፡፡ በተለይ ወጣቶች፣ ከወጣቶችም ወጣት ሴቶች በአሁኑ ወቅት በዚህ ውስጥ ተሳትፈው የሚጓዙ እንዳሉ በግልፅ ይታወቃሉ፡፡ መንግስት በዚህ ደረጃ ለእነዚህ አካላት መልዕክት ማስተላለፉ ጠቃሚ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡››
የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤትን በሚንስትር ዴኤታ ማዕረግ የሚመራው ሽመልስ ከማልም ከ‹‹ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ)›› ጋር ያደረገውና ጥቅምት 3 ቀን 2006 ዓ.ም በታተመው ‹‹አዲስ ዘመን›› ጋዜጣ ላይ በወጣው ቃለ-ምልልስ እንደተለመደው ጉዳዩን በተመለከተ ጠንከር ያለ ማስፈራሪያና ማስጠንቀቂያ ለማስተላለፍ የፈለገ (የታዘዘ) መስሎ አግኝቸዋለሁ፡-
‹‹አንዳንድ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሕጉን እናሰርዛለን፣ ሕጉ ሰብዓዊ መብት የሚጥስ ነው ብለው በአደባባይ የቅጥፈት ፕሮፓጋንዳ ሲያሰሙ የሚታዩና በተዘዋዋሪ መንገድ ከሽብርተኞች ጋር ለሽብርተኞች የሞራል ድጋፍ ሲሰጡና ሲቸሩ የምናያቸው አንዳንድ ወገኖች ሳያውቁ፣ ግንዛቤ ሳይኖራቸው በቀና መንገድ ተሳስተው ነው የሚል ግምት ሊኖር የሚገባው አይመስለኝም፡፡ 

እነዚህ ወገኖች አውቀው ነው ይህንን ሥራ የሚሰሩት፤ በስሌት ነው ይህን የሚከናውኑት፡፡››

በእርግጥም የስርዓቱ የሴራ ቀማሪዎች ‹‹አንድነት እና ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ የፈጠሩት መነቃቃት፣ በጊዜ ካልተቋጨ በሚቀጥለው ዓመት በሚደረገው ምርጫ ‹ባልታወቀ ስፍራ የተኛ ሰይጣን ቀስቅሶ፣ ድንገቴ ማዕበል ሊያስነሳ ይችላል›› የሚለው ትንተናቸው ይመስለኛል ቀድሞም የጠበበውን ምህዳር ይበልጥ ለማጥበብ (ለመድፈን) ከወዲሁ እላይ-ታች እንዲሉ ያስገደዳቸው፡፡

እንደ መውጫ

ስርዓቱ በብዙ መልኩ ያለ ስኬት ከሃያ ሁለት ዓመታት በላይ መጓዙ እርግጥ ነው፡፡ በተቃውሞ ሰፈርም ይህንን ሁናቴ ለመለወጥ አብዛኛውን ዓመታት የበረዶ ያህል ቢቀዘቅዝም፣ አልፎ አልፎ እየጋመ ለውጥ ለማምጣት ያደረገው ሙከራ፣ አገዛዙ ካከማቸው ኃይል ጋር ባለመስተካከሉ ደጋግሞ መምከን አሳዛኝ ዕድል ፈንታ ሆኖ ቆይቷል፡፡ በዚህ ዓመት የተያዘው ዕቅድም ከቀድሞ በባሰ መልኩ፣ ለመደራጀት የሚውተረተረውን ኃይልም ሆነ ተበታትኖና ተከፋፍሎም ቢሆን ለውጥ የሚጠይቀውን ህዝብ በተለያየ መንገድ ማቀዝቀዝ ላይ የሚያተኩር ነው፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ጉዳዩን በደንታቢስነት ማየቱ ይህ እውን ሆኖ የ2002ቱ የምርጫ ድል፣ በ2007 ዓ.ምም ይደግም ዘንድ ፍቃድ የመስጠት ያህል ነው የምለው፡፡

አሁንም አረፈደም፡፡ ነገር ግን ፈረንጅኛው እንደሚለው ‹‹እውነቱ ግድግዳው ላይ ተፅፏል›› የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራት፣ ለውጥ ፈላጊ ዜጎች… ስርዓቱ ለህዝብ ፍላጎት ይገዛ ዘንድ ከዚህ ቀደም ያልተሞከሩ (በሰላማዊ ትግል ማዕቀፍ ውስጥ ያሉ) አማራጮችን ከመተግበር ውጪ ጠረጴዛው ላይ የተቀመጠ ተጨማሪ ‹የዕድል ቁጥር› አለመኖሩን መቀበል ይኖርባቸዋል፡፡

በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ውጥረት አይሏል::

ethiopian_troops_pickupOctober 21/2013


ሌ/ጄ ሳሞራ የኑስ በሜ/ጄ ዮሃንስ ገብረመስቀል ለመተካት የሚደረገው ሩጫ ተቃውሞ ገጥሞታል::
ከፍተኛ ጄኔራሎች ምስጢራዊ ስብሰባዎችን አብዝተዋል::የምስጢራዊ ስብሰባ ቃለ ጉባዬ የምትይዝ የሆነችው የአንድ ከፍተኛ ጄነራል ጸሃፊ ትክዳ ወይም ትገደል አልታወቀም::ለሜ/ጄ ዮሃንስ ገብረመስቀል የተሰጠው የሌ/ጄ ማእረግ የታሰበው ሌ/ጄ ሳሞራን ይተካሉ ተብለው ለነበሩት ለሜ/ጄ አበባው ታደሰ የነበረ ቢሆንም በምን ምክንያት እንደተዘዋወረ አልታወቀም::

በሰሜን እዝ እና በምስራቅ እዝ የተከሰተው የሰራዊቱ ህገመንግስታዊ ጥያቄ እና የጥቅማ ጥቅም አቤቱታ በመላው ሃገሪቱ ተስፋፍቶ በከተማ እና በሌሎች የእዝ መምሪያዎችም መቀጠሉን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቁመዋል::በተለያዩ ጊዜያት እየተንከባለለ የመጣው ይህ የሰራዊቱ አቤቱታ እጅግ አደገኛ አዝማሚያ እያሳየ ሲሆን በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ አስተዳደር እንዲወገድ እና ህገመንግስታዊ መብቶች እንዲከበሩ ጥያቄዎች ገፍተው መምጣታቸው ሲታወቅ ከፍተኛ የሕወሓት ጄኔራሎች በየቀኑ ካለማቋረጥ ምስጢራዊ ስብሰባዎችን እያደረጉ ከመሆኑም በላይ ከየእዙ የሚመጣላቸው ሪፖርት መፍታት የሚቻልበትን ጉዳይ እየተወያየኡ መሆኑ ተጠቁሟል::

ሰራዊቱ በኑሮ ውድነት እና በተቃዋሚዎች ህገመንግስታዊ መብቶች ላይ ያነሳው ጥያቄ አዛዦቹን ያስደነገጠ ከመሆኑም በላይ በአንድ ብሄር ላይ የተመሰረተ አስተዳደር እስከመቼ የሚለውም ጥያቄ መመለስ አለበት በሚል የእግር እሳት እየሆነባቸው ነው:: በቅርቡ ከስልጣን ይነሳል የሚባለው ሌ/ጄ ሳሞራ የኑስን በሜ/ጄ ዮሃንስ ገብረመስቀል ለመተካት የሚደረገውን ጥረት የብኣዴን ታጋይ መኮንኖች የተቃወሙት ሲሆን እኛም ከማንም ያላነሰ የታገልን ስለሆነ ለቦታው ብቁ የሆነ ሰው ብኣዴን እያለው ለምን እንዲህ ይደረጋል የሚል ጥያቄ አንስተዋል::

ከፓርቲ አጣብቂኝ ያልተላቀቀው የመከላከያ ሰራዊቱ የበላይ አመራር ህገመንግስታዊ መዋቅር እንዲይዝ ለማድረግ ምንም አይነት ስራ አለመሰራቱ በሰራዊቱ አዳዲስ መኮንኖች ዘንድ አቤቱታ ቢያስነሳም ጄኔራሎቹ የሚያደርጉት ምስጢራዊ ስብሰባ እንዴት መፍታት ሳይሆን ማክሸፍ እንደሚቻላቸው እየመከሩ ሲሆን አዳዲስ ወታደራዊ ደህንነቶችን በየእዙ አስርጎ በማስገባት እንዲሁም የሰራዊቱን አቤቱታ ያስተባብራሉ የሚባሉትን በስራ ምክንያት በየማእዘኑ በመበተን ለመስራት የታቀደ ሲሆን የአበታተኑን ሁኔታ በማስጠናት ላይ መሆናቸው ታውቋል:: በተጨማሪ የሚደርስባቸውን ጥቃት ለመከላከል ይረዳቸው ዘንድ ኮማንዶዎችን እና ንቁ የደህንነት ጠባቂዎችን ለራሳቸው እና ለቤተሰቦቻቸው ለመመደብ ተነጋግረዋል::

መከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ ምዽር ጦር መምሪያ እንዲሁም ደብረዘይት እና አስፈላጊም ሲሆን በመኖሪአ ቤቶቻቸው የሚያደርጉትን ስብሰባ ቃለጉባዬ የምትይዘው የአንድ ጄኔራል ጸሃፊ ከድታ ይሁን ተገድላ ሳይታወቅ ካለፈው ሳምንት ጀምራ በስራ ገበታዋ ላይ ያልተገኘች እና የት እንዳለች የማይታወቅ ሲሆን ስልኳም መዘጋቱን ምንጮቹ አያይዘው ጠቁመዋል::

ምንሊክ ሳልሳዊ

Systematisk tortur av politiske fanger i Etiopia


  • October 20/2013

    Etiopisk opprørspoliti slo hardt ned på opptøyene i landet i 2005. Siden den gang av menneskerettighetssituasjonen i landet forverret seg kraftig, ifølge Human Rights Watch.
    FOTO: ANDREW HEAVENS, REUTERS

Systematisk tortur av politiske fanger i Etiopia

Opposisjonspolitikere, journalister og regimekritikere blir utsatt for systematisk tortur på en politistasjon i Addis Abeba, viser ny rapport
Torturmetodene som brukes er blant annet slag mot kroppen med harde gjenstander og pisking. Fanger blir også hengt fra taket i svært smertefulle posisjoner.

Human Rights Watch-rapporten, som presenteres i dag, gir et detaljert bilde av mishandlingen som foregår i landets beryktede Federal Police Crime Investigation Sector. Politistasjonen, som er kjent under navnet Maekelawi, ligger i hjertet av hovedstaden Addis Abbeba.

Flere menneskerettighetsaktivister har tidligere meldt om grufulle forhold ved Maekelawi. Denne ferske rapporten har gått systematisk til verks og intervjuet 35 tidligere innsatte ved Maekelawi og deres familiemedlemmer.

- Sparket meg i munnen med støvelen

En tidligere innsatt har fortsatt arr etter torturen.
- De sparket meg i munnen med støvelen, og da mistet jeg fire tenner, sier han.

En annen beskriver hvordan han ble holdt i en smertefull posisjon og så slått.
 
- De tok av skoene og sokkene mine og plasserte en pinne bak knærne mine. Så rullet de meg rundt og slo mot fotsålene mine, sier han.


Les også



– Svenske journalister i Etiopia holdt på å bli skutt

De to svenske journalistene som ble tatt til fange i Etiopia, skal nesten ha blitt skutt av soldater, ifølge Sveriges ambassadør til landet.

Flere beskriver å ha blitt dynket med iskaldt vann og hengt med hendene i taket slik at kun tåspissene nådde gulvet. Human Rights Watch og andre menneskerettighetsorganisasjoner har ikke tilgang til fengselet, men har sjekket de innsattes historier opp mot hverandre for verifisering.

Politisk styrt rettsvesen

Etiopias regjeringsparti – Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) – har styrt landet i over 20 år. Etter det omstridte valget i 2005, har myndighetene slått knallhardt ned på opposisjon og dissens.
Anti-terrorlovene fra 2009 er blitt brukt til å fengsle både journalister og opposisjonelle.
Samtidig som menneskerettighetssituasjonen i landet er blitt vanskeligere de siste årene, har landet hatt en stabil, økonomisk vekst i mange år.

Landets nå avdøde statsminister Meles Zenawi hadde et godt forhold til vestlige ledere, blant annet den norske regjeringen. Etiopia fikk i 2012 228 millioner kroner i bistand fra Norge.

Den siste rapporten forholdene på politistasjonen i Addis Abeba står i grell kontrast til beskrivelser av Etiopia som løfter millioner ut av fattigdom. Etiopias rettssystem er ikke uavhengig av regjeringspartiet, noe som blir ekstra tydelig i behandlingen av politiske fanger.

Torturen har ofte til hensikt å få fanger til å signere forklaringer og falske tilståelser. Blant fangene som ble bedt om å signere slike papirer var de svenske journalistene Johan Persson og Martin Schibbye som satt fengslet i det beryktede fengselet i 2011.

source,,,http://www.aftenposten.no/nyheter/uriks/Systematisk-tortur-av-politiske-fanger-i-Etiopia-7343315.html#.UmS9qHAWL_Y