Wednesday, September 4, 2013

የወያኔ ጁንታ ለሚወርደው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በወር የአምስት መቶ ሺህ ብር መኖርያ ቤት ተከራየ::

September 04, 2013
by Minelik S

አገር በኢኮኖሚ እየደቀቅች ለግል ምቾት ገንዘብ ይዘረገፋል:: የወያኔ ጁንታ ለሚወርደው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በወር የአምስት መቶ ሺህ ብር መኖርያ ቤት ተከራየ:: አዲስ አበባ የሚገኘው የፕሬዚዳንቱ ቢሮ እንዳሳወቀው የወያነ ጁንታ በቅርቡ ለሚወርዱት ሹመኛው ፕሬዚዳንት የ500.000 ሺህ ብር መኖሪያ ቤት መከራየቱን ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል::ታምኝ ምንጮች ለጋዜጣው እንዳሉት የመኖሪአይ ቤቱ የኪራይ ውል ስምምነት ሰነድ ከአቶ ኤሊያስ አራጌ   የመኖሪያ ቤቱ ባለቤት ጋር ተፈርሞ ሙሉ ለሙሉ በውል እና ማስረጃ ክፍል ጸድቆ የተጠናቀቀ ሲሆን መኖሪያ ቤቱ ከነሙሉ ኢቃዎቹ እና የምቾት አቅርቦቶች ጋር ማንኛውንም ነገር ያሟላ ነው::

ምንጮቹ ቤቱ የሚገኝበትን አከባቢ ባይጠቅሱም እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ እንደሆነ ጠቁመው ይህ ውል የተፈጸመው የወያኔን አዋጅ ቁጥር 255/2001 እና በመስከረም 2009 የተሻሻለውን ተመርኩዞ ሲሆን በኢኮኖሚ እየደቀቀች ባለች አገር ላይ የህን ያህል ምቾት ለባለስልጣናት ከመስጠት በአመት የሚወጣው ውጪ አስፈላጊ የአገልግሎት መስጫዎችን ሊገነባ እንደሚችል ተቺዎች ይናገራሉ::

ዝርዝሩን እዚህ ላይ ያገኙታል:- http://www.ethiopianreview.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=60420&p=366853#p366853


People left for abuse, a regime bankrolled to abuse

For Immediate Release
  September 4 2013

 People left for abuse, a regime bankrolled to abuse

On Saturday August 31, 2013, the Ethiopian capital once again turned into a hell where heavily armed TPLF commando forces besieged the Blue Party headquarters, looted the entire office material, and assaulted young men and women who at the time were on their last minute preparation for a peaceful demonstration planned for the following day. According to eye witnesses, leaders, members and supporters of Blue party were handcuffed; frog marched and badly beaten by heavily armed Special Forces. The assault and humiliation on young female members of the party was even worse and strange to the Ethiopian culture that treats all women as mothers. Many female members of the party were taken to police stations and army barracks, ordered to take out their clothes, and forced to roll in stinking sewage sludge.
Just like the absolute majority of the over 90 million Ethiopians, the dream of young men and women of Blue party is to see the important values of justice, liberty, and democracy prevail in their country. The only weapons they carry are pen and paper, their sole goal is peace and prosperity, and their slogan is “Let our voices be heard”. However, last Saturday; the response from an excessively brutal regime that knows only violence was to use an overwhelming force to silence the voices of freedom. This past Saturday, as it usually does; the TPLF regime took the constitutional right of the people and by doing so; the brutal regime has once again demonstrated its utter intolerance to multi-party politics and any kind dissent in Ethiopia.
Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy denounces the savage and heartless acts of the TPLF regime in its strongest sense and holds the regime accountable for all of its actions. Ginbot 7 understands that no words can comfort those who endured last Saturday’s horrendous assault and humiliation at the Blue party headquarters. However, we at Ginbot 7 want the courageous Blue Party leaders and members to know that we are thinking of you and sharing your pain at this difficult time. Most importantly, we want to reassure you that regardless of what the brutal regime does, no one can close the opened gates of liberty, and we shall overcome.
After 22 years of brutal killing, complete neglect for human right, utter intolerance for dissent, ever shrinking democratic space and unprecedented corruption; Ethiopia is left completely shattered and is now a failed State. At this historic juncture, Ginbot 7 wants to ask donor nations and other enablers of Ethiopia’s brutal dictators a very important question: Are you for the Ethiopian people or against the Ethiopian people? Are you financing dictatorship or development?
At the meantime, Ginbot 7 makes a call for all democratic forces of Ethiopia inside and outside the country to set aside their minor differences and stand firm for a nation that has been bleeding for so long. The question of how to fight the TPLF regime has already been answered by the continued and unabated brutal actions of the regime. We as a nation have been pushed to the limit and there is no more space to be pushed. We either fight collectively and declare our freedom or perish collectively. The nation has called us, let us answer the call.
We shall overcome!
pr@ginbot7.org | +44 208 133 5670

ወያኔ የሚገነፍል ድስት ነዉ

September 4, 2013
ኤፍሬም ማዴቦ

ስፖርት በጣም እወዳለሁ፤ ወቅታዊ ዜናና ጥናታዊ ፊልምም አዘወትራለሁ። ከሁለቱ ዉጭ ግን ኢትዮጵያ እያለሁም ሆነ ዛሬ በስደት ኑሮዬ ከቴሌቪዥን ጋር ብዙም አልዋደድም . . .  ግን አንዳንዴ እበድ ሲለኝ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም ቴሌቪዥን ሆኖ ከመተኛቴ በፊት ኢቲቪ እየከፈትኩ አብዳለሁ።  አዎ . . . አብዳለሁ። ሆዴ ያመቀዉ ቁጣና ልቤ የተሸከመዉ የ22 አመት በደል ቀለል የሚለኝ ሳብድ ነዉና ኢቲቪ እየከፈትኩ አብዳለሁ። ምን ላድርግ ተሰድጄ ልበድ እንጂ በወያኔዋ ኢትዮጵያማ እነ በረከት ካልፈቀዱ ማበድም አይቻልምኮ!   አደራ እንግዲህ እንደኔ ጠንካራ ቆዳ የሌላችሁና በትንሹም በትልቁም እየተበሳጫችሁ ዕቃ የምትወረዉሩ ሰዎች ኢቲቪን ከመክፈታችሁ በፊት ባንካችሁ ዉስጥ ቴሌቪዥን መግዢያ ትርፍ ገንዘብ መኖሩን አረጋግጡ፤ አለዚያ እዉነትም ማበዳችሁ ነዉ።

ባለፉት ሃያ ሁለት አመታት የወያኔን ፀባይ በተከታታይ እንዳየሁት የወያኔ ፀባይ ከበቅሎ፤ ከድስት ወይም ከሁለቱም ጋር ተመሳስሎብኛል። በቅሎ የታሰረችበትን ገመድ በጠሰች ቢሉት “በራሷ አሳጠረች” ብሎ መለስ አሉ የበቅሎዋ ጌታ። በቅሎ መታሰሪያዋን በበጠሰች ቁጥር የምትጎዳዉ እራሷን ነዉ፤ ግን በቅሎ በጭራሽ ከስህተቷ አትማርምና ሁሌም ገመዷን እንደበጠሰች ነዉ። አምባገነኑ ወያኔም እንደዚሁ ነዉ።  ድስት ሁሉም ባይሆንም አንዳንዱ በጣዱት ቁጥር ይገነፍላል፤ የሚገነፍል ድስት ደግሞ የሚያበላሸዉ እራሱን ነዉ። ወያኔ ድስትም በቅሎም የሚሆነዉ ዕድሜዉን ለማራዘም ነዉ፤ ሆኖም ሲገነፍልም ሆነ ገመዱን ሲበጥስ እድሜዉ ያጥራል እንጂ አይረዝምም።

ከሰሞኑ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሐይማኖቶች ጉባኤ ይካሄዳል ሲባል ሰምቼ ባለፉት ሁለት አመታት ካልጠፋ ነገር አገራችን የምትታመሰዉ በሐይማኖት ጉዳዮች ነዉና እስኪ ዜናዉን ከምንጩ ልስማ ብዬ ኢቲቪ ላይ አፈጠጥኩ። መቼም ኢቲቪ በብዙ ነገሮች ሊያበሳጫችሁ ይችላል ግን  ዛቻ፤ ዉሸትና፤ ዘራፊ ባለስልጣኖች ሲሞገሱ መስማት ከፈለጋችሁ ግን ሌላ ዬትም ቦታ መሄድ አያስፈልጋችሁም በዚህ ኢቲቪ የልባችሁን ያደርስላችኋል።

ወያኔ ስልጣን ይዞ በቆየባቸዉ አመታት ሁሉ ዛሬም ድረስ ኢትዮጵያ ጨንቋት ያላማጠችበትና ግራ ግብቷት ድረሱልኝ ያላለችበት አንድም ግዜ የለም። ወያኔ ባለፉት ሃያ አመታት ዉስጥ አገራችን ኢትዮጵያን እንዳልነበረች ለማድረግ ያልቆፈረዉ ጉድጓድና ያልሸረበዉ ደባ ባይኖርም ባለፉት ሁለት አመታት ይዞብን የመጣዉ ሸርና ተንኮል ግን የክርስቲያኑንና የሙስሊሙን ማህብረሰብ የአንድ ሺ አራት መቶ አመታት በሰላም አብሮ የመኖር ባህል የሚያደፈርስና አገራችንን አስከፊ የሐይማኖቶች ግጭት ዉስጥ የሚከት አደገኛ ሴራ ነዉ። ለወትሮዉ ፖለቲካዉን በዘር፤በቋንቋና በክልል ቋጥሮ ማዶ ለማዶ የለያየን ወያኔ ዘንድሮማ ጭራሽ የፓርቲ አባልነታችንን ብቻ ሳይሆን የምናመልክበትን የእምነት ቦታና አለም በቃኝ ብለን የምንመንንበትን ገዳም ጭምር አኔ ነኝ መርጬ የማድላችሁ ማለት ጀምሯል። በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ ጳጳስ አዉርዶ ጳጳስ ሾሞባቸዋል፤ የወንጌላዉያን ቤ/ክርሲቲያኖችን ፓስተር አንዴ አስታራቂ አንዴ አማላጅ እያደረገ ቤ/መንግሰትና ቃሊቲ መሃል ተላላኪ አድርጎታል፤አሁን በቅርቡ ደግሞ ፊቱን ወደ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በማዞር የራሱን መጅሊስ ሾሞባቸዋል።

ወያኔ ጥንታዊቷን የኦርቶዶክስ ቤ/ክርሰቲያናችንን የአገር ዉስጥና የአገር ዉጭ ሲኖዶስ በሚል በመከፋፈል ወንጌላዉያኑን አብያተ ክርስቲያናት ደግሞ እኔ ነኝ የማምለክ ነጻነት የሰጠኋችሁ እያለ በማስፈራራት የክርስቲያኑን ህብረተሰብ ለግዜዉም ቢሆን ጭጭ አሰኝቶ እንዳሰኘዉ መቆጣጠር ችሏል። በድርጅታዊ ጥንካሬዉ፤ በምዕመኑ መካከል በገነባቸዉ የግንኙነት መስመሮችና  በእምነት ቀናኢነቱ ከክርስቲያኑ እጅግ በጣም በተሻለ ደረጃ ላይ የሚገኘዉ የሙስሊሙ ህብረተሰብ ግን  የወያኔን ፈላጭ ቆራጭነት አልቀበልም ብሎ ወያኔንና ዘረኝነቱን ፊለፊት በመጋፈጥ ላይ ይገኛል። ሰለሆነም ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያ  ሐይማኖቴን አትንካብኝ በሚለዉ በሙስሊሙ ህብረተሰብና አጎንብሰህ ተገዛ በሚለዉ ወያኔ መካከል በተፈጠረዉ የፖለቲካ አለመረጋጋት በመታመስ ላይ ትገኛለች። እኔም ሞኝ ይመስል ኢቲቪ ላይ ያፈጠጥኩት ይካሄዳል የተባለዉ የሐይማኖት ጉባኤ ይህንን አገራችን ላይ የተደቀነዉን አደጋ ተመልክቶ የመፍትሄ ሃሳብ ያቀርባል ብዬ ነበር። ግን የወያኔ ነገር ሁሌም ታጥቦ ጭቃ ነዉና የሐይማኖት ጉባኤ ተብሎ የቀረበዉ ጉድ እንደ አኬልዳማና ጂሃዳዊ ሐረካት ሆን ተብሎ  ህዝብን ለማደናገር የተሰራ ድራማ ነዉ እንጂ በችግሮች ላይ ተወያይቶ የመፍትሄ ሃሳብ የሚያቀርብ ጉባኤ አይደለም። በአኬልዳማ ድራማና ሰሞኑን በተካሄደዉ የሐይማኖቶች ጉባኤ መካከል ልዩነት ቢኖር አንዱ የቴሌቪዥን ድራማ ሌላዉ ደግሞ የመድረክ ላይ ድራማ መሆናቸዉ ብቻ ነዉ።

በዚህ የሐይማኖቶች ጉባኤ ተብዬዉ የአዳራሽ ውስጥ ድራማ ላይ የተገኙት አብዛኛዎቹ ተዋንያን የዚያ “የድንጋይ ማምረቻ” ተቋም ዉጤቶች የሆኑ የወያኔ ካድሬዎች፤ የወያኔ ባለስልጣኖችና ኤሳዉ ታላቅነቱን ለምግብ እንደሸጠ የሐይማኖት አባትነታቸዉን ለጥቅም የሸጡ ካህናት ለመሆናቸዉ ምስክር የሚያሻ አይመስለኝም፤ ቴሌቪዥኑ መስኮት ዉስጥ አንደተከበበ አዉሬ የሚቁለጨለጨዉ አይናቸዉ ምስክር ነዉ።  ድራማዉን በኢቲቪ ስመለከት ተጠያቂነት የሚባል ነገር የማያዉቁ የወያኔ ባለስልጣኖች እንዳሰኛቸዉ እንደሚናገሩ ስለማዉቅ እነሱ ተናገሩም አልተናሩ ከነሱ ብዙም የምጠብቀዉ ነገር አልነበርም። ይልቁን ጉባኤዉን ስከታተል እጅግ በጣም የገረመኝና የራሴኑ ጆሮ ማመን ያቃተኝ አንድ በሰማይም በምድርም ተጠያቂነት ያለባቸዉ የሐይማኖት አባትና በዋሸ ቁጥር ኩራት የሚሰማዉ በረከት ስምኦን ያደረጉት እንደ ብርሀንና ጨለማ የተቃረነ ንግግር ነዉ። መቼም እርግጠኛ ነኝ የበረከትንና የአባዉን   ፊት ሳያይ ንግግራቸዉን ብቻ ያዳመጠ ሰዉ የቱ ነዉ በረከት የትኛዉ ናቸዉ የሀይማኖት አበት ብሎ መጠየቁ አይቀርም።

ለሁሉም እኚያ የሐይማኖት አባትና በረከት እንዲህ ነበር ያሉት

የሐይማኖት አባት                        መንግስት ትዕግስቱን አብዝቶታል  . . . . እርምጃ ይዉስድ

በረከት ስምኦን                መንግስት ኃይሉ አለዉ ግን መታገሱ ጠቃሚ ነዉ

መቼም አንደህ አይነቱን ጉድ ከጉድም ጉድ የሚያዳምጡ ሰዎች ጆሯቸዉን ሲያማቸዉ፤ ሲበሳጩና አንጀታቸዉ ሲቃጠል ይታየኛል . . ደግሞስ ለምን አይበሳጩ ለምንስ አንጀታቸዉ አይረር?  ትዕግስት ምን አንደሆነች የማያዉቃት ወያኔ ለዛዉም በበረከት ስምኦን አፍ መታገሱ ጠቃሚ ነዉ ነዉ ብሎ ሲናገር የትዕግስት አባት የሆነዉን እግዚአብሄርን አገለግላለሁ ባዩ ቄስ “ትዕግስት በዛ እርምጃ ይወሰድ” ብለዉ መንግስትን የሚማጸኑበት ግዜ መጣ . . . ያዉም ስራዉ ዜጎችን መግደል የሆነዉን መንግስት!  እግዚኦ!  ለመሆኑ አንደ አገርና እንደ ህዝብ ስነምግባራችንና ሀይማኖታዊ እሴታችን እንደዚህ የዘቀጠበት ግዜ ኖሮን ያዉቃል? የወደፊቱን አገር ተረካቢ ትዉልድ በስነምግብርና በግብረገብ አንጾ የማሳደግ ኃላፊነት ያለባቸዉ የሐይማኖት አባት መንግስትን አሁንስ አበዛኸዉ ሂድና ግደል እንጂ የሚሉ ከሆነ ይህ እዉነት ሳይሰማ ያደገ ትዉልድ ስራዉ መግደል ብቻ ሊሆን ነዉኮ . . .   አረ እግዚኦ ማረን!  እባክህ ማረን!

ልጅ እያለሁ አንድ በኃይሉ እሼቴ የሚባል “መሆኑ ይገርማል የተገላበጦሽ አህያ ወደሊጥ ዉሻ ወደ ግጦሽ” ብሎ የዘፈነ አለግዜዉ የተፈጠረ ዘፋኝ ነበር  . . ያኔ የማይመስል አባባል ይመስለኝ ነበር፤  ይሄዉና ዘመን ቆጥሮ ደረሰ። በረከት ስምኦንን በተመለከተ ያንን ንግግር ከልቡ ይናገረዉ ወይ ለማሽሟጠጥ አላዉቅም ሆኖም በረከት ያዉ በረከት ነዉና ስለሱ ምንም የምለዉ የለኝም። እኚያ የሐይማኖት አባት ግን ይህንን አሳፋሪ ንግግር የተናገሩት ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ ያንን ለትዉልድ ሁሉ ኩራት የሆነዉን ታሪካዊ ንግግር በተናገሩበት ከተማ ዉስጥ ነዉና አሳቸዉ ያለ እፍረት አፋቸዉን እንደከፈቱ እኔም በድፍረት አፌን አከፍትባቸዋለሁ . . . ምን ላድርግ 1ኛ ሳሙኤል 2፡1 ላይ  “አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ” ይላልኮ አባ እራሳቸዉ ያስተማሩኝ ቅዱስ መጽሐፍ።  ለሁሉም “እናቷን ምጥ አስተማረች” እንዳይሆንብኝ እንጂ  እኚያ ወያኔን “ምነዉ መንግስት ትዕግስት አበዛ” ብለዉ ያወገዙት አባት ተሸክመዉ የሚዞሩትን መ/ቅዱስ አንብበዉት ከሆነ እዚያ ቅዱስ መጽሐፍ ዉስጥ ትዕግስት የሚለዉ ቃል 33 ግዜ ተጠቅሷል። “አትግደል” የሚለዉ ትዕዛዝ ደግሞ ከአስርቱ ትዕዛዛት አንዱ ሲሆን ቅዱስ ታቦቱ ላይም የሰፈረ ቃል ነዉ። መጽሐፍ ቅዱስ ትዕግስትን አስመልክቶ  መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ 25፤15 ላይ “በትዕግስት ማግባባት ታላቅ ተቃወሞን ያበርዳል፤መሪዎችን ሳይቀር በሃሳብ እንዲስማሙ ያደርጋል” ይላልኮ! ለመሆኑ ትዕግስቱን ተትህ ግደል እንጂ ብለዉ ወያኔን የተማፀኑት የሐይማኖት አባት የኦርቶዶክስ አባ ናቸዉ፤ የካቶሊክ ካርዲናል፤ የፕሮቴስታንት ፓስተር ወይስ በሐይማኖት ስም የመጡ የወያኔ ካድሬ? ማናቸዉ እኚህ ታገሱ ፤ ትዕግስትን ገንዘባችሁ አድርጉ፤“መግደል” ኃጢያት ነዉና ሰዉ አትግደሉ ብለዉ ማስተማር ሲገባቸዉ የተገላቢጦሽ “ግደል” እያሉ የሚማጸኑ የሐይማኖት ሰዉ?

ኢትዮጵያዉያን የእስልምና እምነት ተከታዮች ያነሱትን የመብትና የነጻነት ጥያቄ በተመለከተ ፖለቲካና ሐይማኖት፤ካድሬነትና ቅስና ተቀላቅሎባቸዉ ግራ ተጋብተዉ ህዝብን ግራ ከሚያጋቡ ሰዎች አንዱ ጠ/ሚ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ነዉ። ኃ/ማሪያም ደሳለኝ እንደ መለስ ዜናዊ ምላስ እንቆርጣለን ብሎ እንዳይዝት እንኳን ምላስ ለመቁረጥ ቤ/መንግስት ከመግባቱ በፊት በነጻነት ያመልከዉ የነበረዉን አምላኩን ለማምለክም የወያኔ ፈቃድ ያስፈልገዋል። ደሞ ምንም ቢሆን ሰዉዬዉ የአገር መሪ ነዉና ችግሮችን እፈታለሁ በሚል ሚዛናዊ እርምጃ ልዉስድ ቢል እሱ እራሱ በስልክ እየታዘዘ የሚሰራ ሰዉ ነዉ። መቼም በወያኔዋ ኢትዮጵያ እንዲህ አይነቱ ነገር አይታሰብም እንጂ ኃ/ማሪያም ዳሳለኝ የሙስሊሙ ህብረተሰብ ያነሳዉን ጥያቄ ከሐይማኖት፤ከባህልና ከስነምግባር አንጻር አይቶ ትክክለኛ ጥያቄ ነዉ ብሎ ጥያቄዉን ለመመለስ ቢሞክር እንኳን ብዙም ሳይቆይ “እንደወጣች ቀረች” ተብሎ ይተረትበታል አንጂ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ህዝባዊ ጥያቄዎችን መመለስ ቀርቶ እሱ እራሱ ያሻዉን ጥያቄ መጠየቅም አይችልም ። እንግዲህ ይህ እራሱን መሆን የተሳነዉና ሦስት ቅርቃሮች ዉስጥ ገብቶ የተቀረቀረዉ ኃ/ማሪያም ነዉ አንዴ ተጨማሪ የኃይል እርምጃ እንወስዳለን፤ አንዴ የሙስሊሙ ጥያቄ የሸሪአ ጥያቄ ነዉ፤ ይባስ ሲለዉ ደግሞ ከሙስሊሙ ትግል ጋር የተባበረ ሁሉ ሽብርተኛ ነዉ እያለ ያልተጻፈ መጽሐፍ የሚያነብበዉ። ለመሆኑ ይህ ጧትና ማታ የጓድ መለስን ራዕይ ተግባራዊ እናደርገለን እያለ የሚዘምረዉ ኃ/ማሪያም  “ተጨማሪ የኃይል እርምጃ እንወስዳለን” ሲል የጌታዉን ራዕይ ተግባራዊ ማድረጉ ይሆን?

ባለፉት ሦስት ሳምንታት በተለይ ባለፈዉ ቅዳሜ በወያኔ ጌቶቹ እየተመራ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ የወሰዳቸዉ ፀረ ህዝብና ፀረ አገር እርምጃዎች ለኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ ኢትዮጵያ ዉስጥ በመካሄድ ላይ ያለዉን ህዝባዊ እንቅስቃሴ ለሚከታተሉ አገሮች ያረጋገጠዉ ነገር ቢኖር የኢትዮጵያ ህዝብ የወያኔን ዘረኛ ስርዐት ለማስወገድ የሚከተለዉን እስትራቴጂ በጥልቀትና በስፋት መመርመር እንዳለበት ነዉ። እስካዛሬ እንዳየነዉ ወያኔ በልመናም፤ በሰላማዊ ትግልም፤ በአመጽም ሆነ በሌላ በምንም አይነት መንገድ እንድንታገለዉ የማይፈልግና እኔ ብቻ ዝንተ አለም እንደገዛኋችሁ ልኑር የሚል ልቡ ያበጠ አምባገነን ነዉ። ህዝባዊ ተሳትፎን በተመለከተ የወያኔ ፍላጎት አንድ ብቻ ነዉ፤ እሱም በዚያ እሱ እንደ ቤቱ ጓዳ በሚቆጣጠረዉና በየአምስት አመቱ በሚደረገዉ ምርጫ እንድናጅበዉ ብቻ ነዉ። ከዚህ ዉጭ ዲሞክራሲና መብት የሚባል ቃል ስሙን ያነሳ ሰዉ ወይ ይታሰራል፤ ይደበደባል፤ከአገር ይሰደዳል አለዚያም ይገደላል። የወያኔና የእኛ ሠላማዊ ትግል በይዘትም በቅርጽም እጅግ በጣም የሚለያይ ይመስለኛል። የወያኔ ሠላማዊ ትግል እኔን ብቻ ስሙኝ ወይም በየአምስት አመቱ በምርጫ አጅቡኝ ነዉ። እኛ ሠላማዊ ትግል የምንለዉ ደግሞ መብታችን ይከበር ብለን ባሰኘን ግዜና ቦታ የተቃዉሞ ሠልፍ ማድረግ፤ የስራ ማቆም አድማ ማድረግና ወያኔ ህገመንግስቱን የሚጻረር መመሪያና ህግ ሲያወጣ በፍጹም አንቀበልም ብለን በህዝባዊ እምቢተኝነት ማመጽ ነዉ። ይህንን አድርገን ቢሆን ኖሮ ዛሬ እስክንድርን፤ አንዱአለምን፤ ርዕዮትንና ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ሠላማዊ ዜጎችን ቃሊቲ የወረወረዉ ህግ አይኖርም ነበር።

ሠላማዊ ትግል የሚባለዉ እንደዚህ አይነቱ ትግል ነዉና ወያኔን ማፋጠጥ ያለብን በዚህ አይነቱ ትግል ነዉ፤ ካለዚያ የትግላችንን እስትራቴጅ ፈትሸን ለግዜዉ የወያኔን ጥቃት ባይመጥንም ወያኔ ጥቃት ከመሰንዘሩ በፊት ሁለቴ እንዲያስብ የሚያደርግ የትግል እስትራቴጅ መንደፍ አለብን። ከዚህ በተጨማሪ ወያኔን በመሳሪያ ለመፋለም የቆረጡ ኃይሎችን ቢቻል መደገፍ አለዚያም ጣታችንን እነሱ ላይ መጠንቆሉን ማቆም አለብን።

ከሰዐት በኋላ ረፋዱ ላይ ከስራ ወጥቼ ቴሌቪዥኑ ፊት ስደቀን የአገሬ የኢትዮጵያ ነገር አይኔ ላይ ይመጣና አንዳንዴ ግርም ይለኛል፤ አንዳንዴ ይጨንቀኛል፤ አንዳንዴም ይነድደኛል። የከሰሞኑ ግን አታምጣ ነዉ።  አግራሞቱም፤ ጭንቀቱም፤ ንዴቱም እንደ ክፉ መንፈስ በአንዴ ተከመሩብኝ። መቼም የኢትዮጵያ ነገር የማይገርመዉ ኢትዮጵያዊም ሆነ የዉጭ አገር ሰዉ ያለ አይመስለኝም፤ ደግሞስ የኢትዮጵያ ነገር ለምን አይገርምም?  መንግስት ተብዬዉና አገር እመራለሁ ባዩ ወያኔ የምትወደዉ እንድዬ ልጇ እንደሞተባት አሮጊት አመት ጠብቆ ተዝካር ሲያወጣ . . . .  ጎበዝ ለመሆኑ ተዝካር የሚያወጣ መንግስት አይታችሁ ወይም ሰምታችሁ ታዉቃላችሁ? አኔ እንኳን መስማት አስቤዉም አላዉቅም። የሚገርመዉ ወያኔ ያንን የፈረደበትንና የዛሬ አመት እያስፈራራ በጉልበት ያስለቀሰዉን ህዝብ ብቻ ሰብስቦ የጌታዬን ተዝካር አዉጡልኝ ቢል ኖሮ ነገሩ እኛዉ በእኛ ነዉና ስቀን ዝም እንል ነበር፤ ግን ጉደኛዉ ወያኔ ተዝካር ድረሱልኝ ብሎ የጠራዉኮ የጎረቤት አገር መሪዎችን ጭምር ነዉ። የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ነኝና ተዝካር ለሟቹም ለቋሚዉም አይጠቅምም ብዬ አምናለሁ፤ ሆኖም ተዝካር ትክክለኛ ነገር ነዉና መዘከር አለበት የሚሉ ወገኖች ተዝካር የማዉጣት መብታቸዉ እንዲከበር ሽንጤን ገትሬ የምታገል ሰዉ ነኝ። ግን የኢትዮጵያ መንግስት ሲባል የኦርቶዶክሱ፤ የሙስሊሙ፤ የጴንጤዉ፤ የካቶሊኩና የሌሎቹም የዬትኛዉም አይነት እምነት ተከታዮችና ስለሐይማኖት ግድ የሌላቸዉም ሰዎች መንግስት ስለሆነ ተዝካር ማዉጣጥ ቀርቶ ስለተዝካር መልካምነትም ሆነ መጥፎነት መናገርም የለበትም የሚል የፀና እምነት አለኝ። በረከት ስምኦንና ሽመልስ ከማል አይገባቸዉም አንጂ የሚገባቸዉ ቢሆን ኖሮ ሐይማኖትና መንግስት ተቀላቀሉ የሚባለዉ እንደዚህ መንግስት በአገር አቀፍ ደረጃ ተዝካር ሲያወጣ ነዉ አንጂ ሐይማኖትና ፖለቲካ ሲነካኩ አይደለም፤ እነሱማ መነካካት አለባቸዉ፤ የአገሪቱ ህገመንግስትም ይህንን አይከለክልም።

ሌላዉ ከሰሞኑ ያየሁት የወያኔ ጉድ  . . . ማንን እንደሚቃወም ባላዉቅም ወያኔ ሠላማዊ ሠልፍ የሚወጣ ብቸኛዉ የአለማችን መንግስት  ነዉ። ወገኖቼ ይህ ጉድ ካልገረመን፤ ካልጨነቀንና ካልነደደን ሌላ ምን. . . ምን . . . .  ምን! ደግሞኮ የ39 አመቱ ጎልማሳ ወያኔ ሠላማዊ ሠልፍ የጠራዉ ገና በእግሩ መሄድ ካልጀመረዉ ከሠማያዊ ፓርቲ ገር ሽሚያ ገብቶ ነዉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ መንግስት በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ለአገሪቱ ደህንነት ሲባል ካላገደ በቀር ሠላማዊ ሠልፍ ማድረግ ህገመንግስታዊ መብት ነዉ፤ወይም  ዜጎች ሠላማዊ ሠልፍ ለመዉጣት ማሳወቅ እንጂ ፈቃድ መጠየቅ አያሻቸዉም። ወያኔ ሠማያዊ ፓርቲ የጠራዉን ሠልፍ ለጸጥታ ወይም ለሌላም ጉዳይ ብሎ እንዳይካሄድ ቢፈልግ ኖሮ ብቸኛዉ አማራጭ ወይ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር መደራደር አለዚያም ፍርድ ቤቶች የራሱ ንበረቶች ቢሆኑም ለይስሙላም ቢሆን እዚያ መሄድና ፍርድ ቤቱን ማሳመን ነበረበት እንጂ ልቡ እንዳበጠ የመንደር ዉስጥ ወጠጤ በተራ ዝርፊያና ድብደባ ላይ አይሰማራም። መንግስት ማለት ያሰኘዉን ነገር ሁሉ የሚያደርግ ተቋም አለመሆኑን ወያኔም ሆነ ወያኔ በተተቸ ቁጥር ምጣድ ላይ እንደቆየ ተልባ የሚንጣጡት ደጋፊዎቹ ሊረዱት ይገባል።

ባለፈዉ ቅዳሜ ወያኔ ከሠማያዊ ፓርቲ ጋር ሠልፍ ልዉጣ አትወጣም በሚል በገባዉ እሰጥ አገባ በህግም በሃሳብም በሠማያዊ ፓርቲ በመሸነፉ የተሸናፊዎች ብቸኛ መሳሪያ የሆነዉን ጉልበትና በህግ ያልተገደበ ኃይል በመጠቀም የሠማያዊ ፓርቲ መሪዎችን በቆመጥና በሰደፍ ሲደበድብ ዉሏል፤ የፓርቲዉን ጽ/ቤት ሰብሮ በመግባት ንብረት ሰርቋል እንዱሁም ፓርቲዉ በህጋዊ መንገድ የተከራየዉን ጽ/ቤት ከብቦ አካባቢዉን የጦርነት ወረዳ አስመስሎታል። መስበር፤ መዝረፍ፤ ሠላማዊ ዜጎችን መደብደብና የአካባቢን ጸጥታ መንሳት . . . . ለመሆኑ ማነዉ ሽብርተኛዉ?  አገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ አለማችን ብዙ አምባገነን መሪዎችን አስተናግዳለች፤ እንደ ወያኔ አይነቱ ተራ ዱሪዬና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ንፍጣቸዉን የተናፈጡበትን መሀረብ ጭምር የሚሰርቅ ተራ ሌባ የሆነ ስርዐት ግን ዬትም አገር ዉስጥ ታይቶ አይታወቅም። ይህ ስርዐተ አልበኛ የሆነ የወንበዴ አገዛዝ ከአሁን በኋላ የሚወስደዉ እርምጃ ለሁላችንም ግልጽ የሆነ ይመስለኛል፤ ትናንት በአንዱ አለም አራጌ፤ በእስክንድር ነጋ፤ በበቀለ ገርባና ኦብላና ሌሊሳ ላይ የተመሰረተዉ የግፍ ከስ ዛሬ በሠላማዊ ፓርቲ መሪዎች ላይ መመስረቱ አይቀርም፤ የሚያሳዝነዉ በሠማያዊ ፓርቲ መሪዎች ላይ መረጃ ሆነዉ የሚቀርቡት እነዚሁ ባለፈዉ ቅዳሜ ከፓርቲዉ ጽ/ቤት የተዘረፉት የፓርቲዉ ህጋዊ ሰነዶች ናቸዉ። እንገዲህ ያታያችሁ . . .  ከሳሾቹ ሌቦች፤ ዳኞቹ ሌቦች ምስክሮቹ ሌቦች፤ ማስረጃዉም በሌብነት የተሰበሰበ ማስረጃ ነዉ . . .  “እዛዉ ሞላ እዛዉ ፈላ”  . . .  እንደዚህ ነዉ የወያኔ ነገር … ሁሉም ነገር በሌብነት!

ባለፈዉ ቅዳሜ ወያኔ ከብዕርና ከመጽሐፍ ዉጭ እጃቸዉ ሌላ ምንም ነገር ጨብጦ የማያዉቀዉን ነፃነትና ፍትህ ናፋቂ ወጣቶች ወራሪ ጠላትን ለማጥቃት በሰለጠኑ የልዩ ኮማንዶ ኃይሎች ሲደብድብ ዉሏል። ሴቶች እህቶቻችንን ባዕዳን አረቦች ከሚያድርሱባቸዉ የአካልና የሂሊና ጉዳት እጅግ በጣም በከፋ መልኩ ተድብድበዋል፤ ክብራቸዉንና ሰብእናቸዉን በሚያንቋሽሽ ስድብ ተሰድበዋል። ከሁሉም የሚያሳዝነዉ ወጣት ሴቶቻችን ልብሳቸዉን እንዲያወልቁ ተደርገዉ በዉስጥ ሱሪያቸዉ ብቻ ጭቃ ዉስጥ እንዲንከባሉ ተደርገዋል። በቀጥታ ከዲስ አበባ በደረሰኝ መረጃ መሠረት የወያኔ ደነዝ አግአዚ ቅልቦች በ1997ቱ ምርጫ ማግስት በግልጽ የነገሩንን ቃል አሁንም በማያሻማ መልኩ አስረዉ እየደበደቡ በሚያሰቃዩዋቸዉ የሠማያዊ ፓርቲ አባላት ፊት አንደዚህ ሲሉ ደግመዉታል -

እንገዛችኋለን . . .  መግዛት ብቻ ሳይሆን እንረግጣችኋለን!! ደማችንን አፍስሰንና አጥንታችንን ከስክሰን የያዝነዉን ስልጣን አሁንም እንሞትለታለን እንጂ በፍጹም አንለቅም። በሠላማዊ ትግል ስልጣን መያዝ ቀርቶ ከዛሬ በኋላ እኛ ሳንፈቅድላችሁ ከቤታችሁም አትወጡም። ስለህግ አታዉሩ ህግ ማለት እኛ ነን።

ዉድ ኢትዮጵያዉያን ለወያኔ ጅላጅሎችና ጋጠወጦች የማንገዛና የማንረገጥ መሆናችንን ብቻ ሳይሆን ታቦት ተሸክመዉ እባካችሁ ማሩን ብለዉ እስኪለምኑን ድረስ መርገጥ ማለት ምን ማለት መሆኑን ማሳየት የምንችል መሆናችንን በተግባር ማሳየት አለብን። ለአገራቸን ግድ ከሌላቸዉ፤ ታሪካችንን ከናቁና ለሰብዕናችንና በተለይም ለሴት እህቶቻችን ክብር ከሌላቸዉ እኛስ እነዚህን አዉሬዎች ለምን መታገስ አለብን፤ ለምን መሸከም አለብን ለምንስ እነሱ አድርጉ የሚሉንን ማድረግ አለብን? የታለ ያ ባርነትን የሚጸየፈዉ ኢትዮጵያዊታችን? የታለ ያ ጥቃትን በፍጹም የማይቀበለዉ ኢትዮጵያዊ ወኔያችን? የታለ ያ “እታለም” ስትደፈር ዱር ቤቴ ብሎ የሚሰደደዉ ኢትዮጵያዊ ማንነታችን? የታለ ያ በ1970ዎቹ የትግል ጓዱ በደርግ ባንዳዎች እጅ እንዳይወድቅ ሲል ብቻ ፖታሲየም ሳይናይድ እየቃመ የሞትን ፅዋ የጨለጠዉ ኢትዮጵያዊ ጅግንነታችን. . .  የታለ?  . . .የታለ? . . .የታለ?  የወያኔ ዘረኞች ረግጠዉ ሊገዙን ሞተዋል፤ ዛሬም ይህ ረጋጭ ስርአታቸዉ እንዲቀጥል ለመሞት ቆርጠዋል? እኛስ ምነዉ ላለመረገጥ፤ ላለመገዛትና እህቶቻችንና ወንድሞቻችን በዘረኞች እንዳይገደሉ ስንል የማንሞተዉ ለምንድነዉ? ጎበዝ እኔ አልሞትም ብንልም በቁማችን ሞተናልኮ፤ አንዱኑ በክብር እንሙትና ለወገኖቻችንና ለአገራችን ቤዛ እንሁን አንጂ!

የኢትዮጵያ ህዝብ ህግ አክባሪ ህዝብ ነዉ፤ ሆኖም ወያኔ የራሱን ህገመንግስት ጥሶ በህግ ያልተገደበ ኃይል ሲጠቀም ወይም ህጉን የጻፈዉ አካል እራሱ ያላከበረዉን ህግ ማክበር ሞኝነትና እራስን ለጥቃት ማጋላጥ እንጂ ህግ አክባሪነት አይደለም። እኛ ኢትዮጵያዉያን ከበስተጀርባዉ የማስፈጸሚያ ኃይል የሌለዉ ህግ እንደማይጠቅመን ሁሉ ህግ የማይገዛዉ ልቅ የሆነ ኃይልም ይጎዳናል እንጂ በፍጹም አይጠቅመንም። ስለዚህ እንደ አገርና እንደ ህዝብ መቀጠል ከፈለግን በህግ ያልተገደበ ኃይል የጨበጡ የወያኔ ዘረኞችን ወይ ህግ እንዲገዛቸዉ ማስገደድ አለዚያም ማስወገድ አለብን። በህግ አክባሪነትና በስርአተልበኝነት መካከል ምንም አይነት ማመቻመች ወይም ድርድር ሊኖር አይገባም።

ከዉጭ ራቅ ብሎ ለተመለከተዉ የወያኔ አገዛዝ ሽብርተኝንትን ለማጥፋት ወይም ለመቆጣጠር ከአቅሙ በላይ ሽር ጉድ ሲል ይታያል፤ ነገሩ “ላም ባልዋለችበት ኩበት ለቀማ” ሆነ እንጂ ወያኔ ሽብርተኝነት ከኢትዮጵያ መጥፋቱን ለማረጋገጥ ከፈለገ ማድረግ ያለበት ነገር አንድ ብቻ ነዉ፤ እሱም ሳይዉል ሳይድር ዛሬዉኑ የኢትዮጵያን ህዝብ ማሸበሩን ማቆም ነዉ። ሽብር እየፈጠሩ የአገርን ሠላምና ጸጥታ አስከብራሁ ማለት የለየለት ምግባረብልሹነት የመሆኑን ያክል ህዝብን በመግደል የተካነ መንግስትን ምነዉ ዝም አልክ ግደል እንጂ ብሎ መማጸንም ምግባረብልሹነት ብቻ ሳይሆን አማኑኤል የሚያስኬድ የዕምሮ በሽታ ነዉ። በዚህ አጋጣሚ የሠማያዊ ፓርቲ መሪዎችን፤ አባላትንና ደጋፊዎችን ትክክለኛዉን ሠላማዊ ትግል አሳይታችሁኛልና ባርኔጣዬን አንስቼ ለእናንተ ያለኘን አድናቆት መግለጽ እወዳለሁ። የቆማችሁለትን የፍትህ፤ የነጻነት፤ የዲሞክራሲና የእኩልነት እሴቶች እንደ ጦር የሚፈሩ ጉግማንጉጎች በሚወስዱት የቀቢፀ ተስፋ እርምጃ ተደናግጣችሁ ከቆማችሁለት ትክክለኛ አላማ ወደ ኋላ እንደማትሉ እርግጠኛ ነኝ። እዉነትና የእትዮጳያ ህዝብ ከእናንተ ጋር ነዉና ማሸነፋችን የተረጋጋጠ ነዉ . . .  ኑ ተነሱ የወያኔን ሽብርተኝነት አብረን እንዋጋ!

ebini23@yahoo.com

http://ecadforum.com/Amharic/archives/9660/

An Armed Force that comes out from Oppression

September 4, 2013

As all know Tigray People’s Liberation Front (TPLF) has been in power for more than 22 years in Ethiopia. TPLF took power with force and it rules the country with force applying draconian laws that deny basic human rights and the right of the people to elect its own government. Anyone who expresses its firm opposition to the TPLF regime in Ethiopia is convicted for terrorist act, citing the controversial ‘terrorist proclamation’ adopted by the regime to crush the opposition. Since TPLF took power, there is no free media, and the country became one of the countries with lots of exiled and jailed journalists.


The so called Ethnic federalism introduced into the country by TPLF turns to be ethnic racism, that threaten the sovereignty of the country. The Ethiopian ethnic federalism is a tool used to implement the dangerous divide and rule principle of TPLF. The current ‘Ethnic federalism’ in Ethiopia is properly designed to create hatred and suspicion among ethnic groups in the country. As a result there were lots of incidents where thousands were massacred after different ethnic groups are turned to each other.

Election is becoming a joke in Ethiopia. The election in 2005 was the first and the last resembling more or less democratic at its initial phase. The result was however stolen by TPLF and the woyane junta declared victory. During the 2010 election, TPLF declared a 96.9% victory which no one on earth can believe it is a democratic election. In the current Ethiopia, peaceful demonstrators get killed on streets and arrested with no conviction. Muslim brothers and sisters are the living examples who have faced this punishment every day at this time.

From a country with the described suffocating political atmosphere, Ginbot7 Popular Force (GPF) came out saying ‘enough is enough’ and calls all Ethiopians to stand by its side and fight for rule of law and justice in the country.

Ginbot7 popular Force has a vision of a vibrant and democratic Ethiopia, wherein the sovereign will of the Ethiopian people becomes the source of all political power, the full range of people’s rights are respected and the national unity, security and welfare of the country is adequately defended.
Ginbot7 Popular Force’s mission is forceful removal of the dictatorial regime of TPLF, usher the condition for peaceful and democratic transition, play a part in the creation of a strong and capable national defense, security and police forces whose only allegiance is to the constitution of the country, thereby, bringing an end to the existing affiliation of these institutions to the political forces in the country. It is therefore we give a positive response to this very timely call and support GPF.
In order you know more about GPF and can support it, a grand Fundraising Event is organized for the force in Oslo Norway on September 28, 2013.

Come and support G7PF!
Supporting GPF will shorten TPLF’s rule in Ethiopia!
Organized by Ginbot7 popular force fundraising task force

መብራት ኃይል ከ5ሺ የሚልቁ ሰራተኞቹን ሊቀንስ መሆኑን ምንጮች ጠቆሙ

ከቅነሳው ጀርባ የዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል እጅ እንዳለበትም እየተነገረ ነው “ሰራተኛ ሊቀነስ ነው የተባለው ግን የውሸት ውሸት ነው” አቶ መስክር ነጋሽ የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ኮርፖሬሽን ከ5ሺ የሚልቁ ሰራተኞቹን ሊቀንስ መሆኑን የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ምንጮች ጠቆሙ፡፡ ዶ/ር ደብረፂዮን ነገ ከኮርፖሬሽኑ ሰራተኞች ጋር በሚያደርጉት የፕላዝማ ውይይት ስለሚቀነሱት ሰራተኞች ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡ ምንጮቻችን እንደጠቆሙት መስሪያቤቱ ይህንን ያክል ሰራተኛ ከስራ ከስራ ውጪ ለማድረግ የተዘጋጀው መንግስት ኮርፖሬሽኑን ለፓውርና ማኔጅመንት በሚል ከሁለተ ከፍሎ አንድ የህንድ ኩባንያ እንዲያስተዳድረው በመወሰኑ ነው፡፡
 
የፍኖተ ነፃነት የዜና ምንጮች ጨምረው እንደገለፁት መብራት ኃይል ከመከላከያ ኢንጅነሪንግ ጥራታቸውን ያልጠበቁ ትራንስፎርመሮችን እንዲገዛ መደረጉ መስሪያ ቤቱን ለከፍተኛ ወጪ ሲዳርግ የኮርፖሬሽኑ ደንበኞቸም ለተደጋጋሚ የኃይል መቆራረጥ ተጠቂ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ “አሁንም መስራቤታችን ለህንድ ካምፓኒ እንዲሰጥ መደረጉ ከፍተኛ ጦስ ሊያመጣ እንደሚችል እንጠብቃለን” የሚሉት ምንጮቻችን “ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል የቴሌን ሰራተኞች እንደበተኑት ዛሬም ኤልፓን ሊያንኮታኩቱት ነው” ብለዋል፡፡
 
ፍኖተ ነፃነት ስለጉዳዩ ለማጣራት ወደ ኮርፖሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መስክር ነጋሽ በመደወል የመስሪያቤቱን ምላሽ አግኝታለች፡፡ አቶ ምስክር “ነገ ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠና አለን፤ ሰራተኛ ሊቀነስ ነው የተባለው ግን የውሸት ውሸት ነው” የሚል ምላሸ ሰጥተዋል፡፡ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ኮርፖሬሽን ለህንድ ካምፓኒ ሊሰጥነው የተባለው ገና ሂደት ላይ ያለ ነው ብለዋል፡፡

Tuesday, September 3, 2013

ላለፉት 2 አመታት ስርአቱን በሀይል ለመፈታተን ከሞከሩት ሁሉ የሀይማኖት እንቅስቃሴዎች ዋነኞቹ እንደነበሩ ኢህአዴግ አስታወቀ

ነሃሴ ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው አዲስ ራእይ በሚባለው ልሳኑ ” ፣ በሀይማኖት ሽፋን የሚካሄዱ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች እየተዳከሙና እየተጋለጡ መሄዳቸው ባይቀርም ባለፉት ሁለት አመታት ልማታዊና ዲሞክራሲያዊ ስርአቱን በሐይል ለመፈታተን ከመከሩት የሁከት ሀይሎች ዋነኞቹ ነበሩ ማለት ይቻላል” ብሎአል።

ኢህአዴግ ከአክራሪዎች ጎን በመቆም አመጽ ለማነሳሳት ሞክረዋል ካላቸው ድርጅቶች መካከል ድምጻችን ይሰማ፣ ግንቦት 7 አሜሪካ ድምጽ ሬዲዮና ቢላል ሬዲዮ በዋናነት ተጠቅሰዋል።

በውስጡ ያሉ አንዳንድ የኢህአዴግ አመራሮችም እንዲሁ በሀማኖት ጉዳይ ጣልቃ እየገቡ ችግሩን እያባባሱ በመሆኑ፣ እነዚሁ ባለስልጣናት የመንግስትን ስልጣን አስረክበው ወደ ሰባኪነታቸው እንዲያመሩ እንመክራለን ብሎአል።

መጽሄቱ በኢትዮጵያ ውስጥ በክርስትና እና በእስልምና ሀይማኖቶች ውስጥ እየታየ ያለውን የአክራሪነት አዝማሚያና ይህን ተጠቅሞ የሚካሄደውን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ለመግታት መንግስት በየትምህርት ተቋማት ትምህርቶችን መስጠት፣ ለወጣቶች ተገቢውን ስራ በመስጠትና አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ መውሰድ እንደላበት ጠቁሟል።

ኢህአዴግ አሁን የሚታየው የሙስሊሙ እንቅስቃሴ እየተዳከመ ቢመጣም ተመልሶ ስርአቱን ሊገዳደር የሚችልበት ምልክት እየታየ መሆኑን ጠቁሟል።

በሌላ ዜና ደግሞ ኢህአዴግ የሚዲያ አደረጃጀቱን በአዲስ መልክ ማዋቀሩ ታውቋል። የፌደራል እና የክልል የመገናኛ ብዙሀንም ከእንግዲህ ወዲህ የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች በሚሰጡዋቸው አቅጣጫ ፕሮግራሞቻቸውን እንደሚያዘጋጁ ታውቋል። በደቡብ ክልል አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ በአማራ ክልል አቶ አለምነው መኮንን፣ በኦሮምአ አቶ አለማየሁ አቶምሳ በየወሩ ከጋዜጠኞች እና ዋና አዘጋጆች ጋር በመተባበር የዜና ዘገባ አቅጣጫዎችን ይሰጣሉ።
ማንኛውም ጋዜጠኛ ስራውን የሚሰራው እነዚህ የኢህአዴግ አመራሮች በሚሰጡት የትኩረት አቅጣጫ መሰረት እንደሚሆን ከግንባሩ የቅርብ ሰዎች ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።

የሙስናው ጉዳይ ክንፉ አሰፋ

September 3, 2013

በተንጣለለ ቪላ ውስጥ ከበድ ያሉ እንግዶች “ጸዳ” ባሉ ምግብና መጠጦች እየተስተናገዱ ነው። ታዋቂ ግለሰቦች፤ ባለስልጣናት እና አርቲስቶች የቀረበላቸውን ብፌ በልማታዊ ወጋቸው እያወራረዱ ሳሉ አንድ እንግዳ ነገር በመሃላቸው ተከሰተ። ሞቅ ባለው የአይቴ ነጋ ገብረእግዚአብሄር ድግስ ላይ ያልተጋበዙ ሁለት ሰዎች ዘው ብለው ከግብዣው ክፍል ገቡ። የፌዴራል ፖሊስ አባላት ነበሩ። በዚህ ያልተለመደ  ክስተት የአቶ ነጋ እንግዶች አልተደናገጡም ነበር። ይልቁንም  የፌዴራል ፖሊሶቹ ለተጨማሪ ጥበቃ የመጡ ነበር የመሰላቸው። አንድ ብርጌድ ያህል ጦር አስከትለው የመጡት ፖሊሶች ግን አቶ ነጋ ገብረእግዚአብሄርን አስጠሯቸው።  አቶ ነጋም ለጥሪው እንደወትሮው በመወጣጠርና ፍጹም ትእቢት በተሞላበት አነጋገር ምላሽ ሰጡ። በፖሊስ አባላቱ እና በአቶ ነጋ መካከል የሃይለ-ቃል ልውውጥ ተጀመረ። እሰጥ እገባው  አንድ፣ ሁለት እያለ ሄደና በመጨረሻ ተካረረ። በዚህ ሰዓት አቶ ነጋ ስልክ መደዋወል ያዙ። ከፍተኛ የሚባሉ ባለስልጣናትና ምኒስትሮች ጋ ደወሉ።  ከዚያም በመቀጠል፣ ጀነራሎች ጋ ደወሉ... የጦር መኮንኖች፣ የፓርቲ ባለስልጣናት... ሁሉም ጋ ተደወለ። የባለስልጣናቱ ምላሽ ግን ጥሩ እንዳልነበር ከአቶ ነጋ ፊት ላይ ይነበብ ነበር። ወዳጆቻቸው ሁሉ እንደ ቱኒዚያው ቤን አሊ በአንድ ጊዜ ከዷቸው።
"በል - ና - ውጣ!" አለ አንደኛው የፖሊስ አባል፣ የስልኩን ሽርጉድ በጥሞና ከተከታተለ በኋላ።
"ምን ማለትህ ነው? እኔኮ ነጋ ነኝ። ነጋ ታሪኩ!" አሉ። አነጋገራቸው የጀምስ ቦንድን ይመስል ነበር። በዚህ ጊዜ ታዲያ እጃቸውም አላረፈም። ከጎን ያሸጎጡትን መሳርያ ለማውጣትም ዳዳቸው።
በቅጽበት ግን ፌዴራል ፖሊሱ ቀደማቸው። በድንገት "ጯ!" የሚል ድምጽ አዳራሹን አናጋው። የፖሊሱ አይበሉባ የግራ መንጋጭላቸው ላይ ሲያርፍባቸው ጊዜ፤ አይቴ ነጋ ነገር አለሙ ተደበላለቀባቸውና እጅ መስጠትን መረጡ። ግብር ሊያበሉ በጠሯቸው የክብር እንግዶቻቸው ፊት፣ ከዚህ በላይ መዋረድ አልፈቀዱም።   ሁለት እጃቸውንም ወደ ፖሊሱ በመዘርጋት ለብረት ማሰርያው ራሳቸውን አመቻቹ። እጃቸው የኋሊት ከተጠፈረ በኋላም አቶ ነጋ እንዲህ አሉ። "በቃ! ህወሃት አበቃለት!"
"ባለሃብቱ" በዚህ ሁኔታ በፖሊስ መኪና ተጭነው ወደ እስር ቤት ሲሄዱ፣ ተጋባዥ እንግዶቹም እግሬ-አውጭኝ እያሉ ከስፍራው አፈተለኩ።  ይህ ታሪክ ድራማ ሊመስል ይችላል። ግን በእውን የተፈጸመ ሃቅ ነው። ታሪኩን ያጫወተኝ ሰውም እዚያ ግብዣ ላይ ግብር ሊበላ ተገኝቶ ነበር። እንደ አግራሞቱም  "ይህ መቼም የፈጣሪ ስራ ነው።" ከማለት ውጪ ስለ ጉዳዩ እንድምታ የሰጠው ማብራሪያ የለም።
ነጋ ገብረእግዚአብሄር የነፃ ትሬዲግ ኃላፊነቱ የተወሰነ (ሰዎች ያልተወሰነ ይሉታል) የግል ማህበር ባለቤት ነበሩ። ድርጅታቸውም እንደስሙ ከሁሉም ነገር ነጻ ነበር። ከግብር ነጻ፤ ከቁጥጥጥር ነጻ፤  ከፍተሻም ነጻ። በመቶዎች የሚቆጠሩ የጭነት መኪናዎች እቃ ጭነው በየኬላው ሳይፈተሹ እንዲያልፉ የተሰጠ ልዩ መብት ሁሉ እንደነበራቸው ይነገራል።  ዛሬ ፈጣሪ ሲፈርድባቸው በኢፍትሃዊ መንገድ ቢልየነር ያደረጋቸው ስርዓት፤ ያው ስርዓት ሰለባ አደረጋቸው... ነጋ ገብረእግዚአብሄር ለአቶ መለስ ዜናዊ እና ለባለቤታቸው ለወ/ሮ አዜብ መስፍን ቅርብ - በጣም ቅርብ ነበሩ። ለጉምቱ ባለስልጣናት ይሰጡት የነበረው እጅ መንሻ ከዚህ አይነት ውርደት እና እስራት ሊያድናቸው አልቻለም። በትግራይ ውስጥ ከ40 ሚሊየን ብር በላይ አውጥተው በስማቸው ያሰሩት የቴክኒክ ኮሌጅም እንደ ውለታ አልተቆጠረላቸውም።...
ይህችን  አጭር መጣጥፍ ለመጫር እንደተቀመጥኩ አንድ ዜና በኢሜይል ደረሰኝ።  የዜናው ርእስ "ጀነራል ባጫ ደበሌ የአዋሽ ባንክ ሰራተኞችን ከሥራ እንዲባረሩ አደረጉ!" ይላል። ባጫ ደበሌ የባንክ ሰራተኞቹን ያባረሩዋቸው ‘’እኔ ጀነራል ባጫ ደበሌን እንዴት አታውቁኝም?’’ በሚል በሰራተኞቹ አለመታወቃቸው አበሳጭቷቸው ነበር።  ወደ ፌስ ቡክ ጎራ ስልም አንዳንዶች በዜናው ላይ ሲወያዩ አስተዋልኩ። ይህ እኮ አዲስ ክስተት አይደለም። ለብዙ ጊዜ የሚደጋገም እና የተለመድ ነገር ዜና ሊሆን አይችልም። ውሻ ሰውን ሲነክስ ዜና አይሆንም። በተቃራኒው ግን ሰው ውሻን ከነከሰ ዜና ይሆናል። እንዲህ አይነቱ ክስተት ስር የሰደደ የስርዓቱ ባህርይ ነው። ባጫ ደበሌ እነዚያን ሰዎች ማስገደል የሚያስችልም ስልጣን እና መብት ያላቸው የአዜብ ሰው መሆናቸውን አንዘንጋ።  ጀነራል ባጫ  በተልእኮ ትምህርት ከአንድም ሁለተኛ ዲግሪ እንዲገዛላቸው ካደረጉ በኋላ፣ ለምርቃታቸው ስነ-ስርዓት፣ ሰንጋዎች ጥለው፣ የሙዚቃ ባንድም አስመጥተው፣  መንገድ ሁሉ እንዲዘጋ አድርገው ሲያበቁ፤ በተለመደው ብሬክ ዳንሳቸው መንደሩን የቀወጡ ሰው ናቸው።  በብርሃን ፍጥነት ከኪነት ጓድነት ወደ ጀነራል የተሸጋገሩት ባጫ ደበሌ በመደበኛ የስራ ጊዜያቸው ጫት ይነግዳሉ። በትርፍ ጊዜያቸው ደግሞ በዜጋው ላይ እንዲሁ እንደዋዛ እየቀለዱ እስካሁን አሉ። የነገውን አንድዬ ብቻ ነው የሚያውቀው።  የፍትህ ሳይሆን የግለሰቦች የበላይነት የሰፈነበት ሃገር ስልጣንን ያላግባብ መጠቀም ሙስና ሊደንቀን አይገባም።  የፍትሃዊ ስርዓት መጥፋት ነው ሙስና።
ፕሮፌሰር አል ማርያም ባለፈው መጣጥፉ ስለሙስና ሲጽፍ  ከሙስና ሁሉ በላይ ሙስና የሚሆነው የፍትህ መጓደል እንደሆነ አስነብቦናል። የፍትህ መጥፋት ስብእናን፣ ነጻነትንና ንብረት ማጣትን ያስከትላልና። In my view, denial of due process (fair trial) is the highest form of corruption imaginable in the “justice sector” because it results in the arbitrary deprivation of a person’s life, liberty and property.  (Al Mariam)
ከሰሞኑ ደግሞ ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም ምንጩ ያልታወቀ ሃብት አፍርተሃል በመባል ተወንጅሎ ወህኒ የወረደው የወልደስላሴ ወልደሚካኤልም ዜና በስፋት እየተሰራጨ ነው። ወልደስላሴ  ሌላኛው የአዜብ መስፍን የቅርብ ሰው ነበር። በዚህ ጉዳይ ላይ ዳዊት ከበደ በስፋት ትንታኔ ስለሰጠበት እዚህ ላይ አልደግመውም። ወልደስላሴ ግን ከህወሃት የጫካ ትግል ጀምሮ ቀልፍ ቦታዎች ላይ ተመድቦ የሰራና - የመለስ ቀኝ እጅ የነበረ ሰው ነው። ታማኝ አገልጋይም ስለነበረ በህወሃት ውስጥ ወሳኝ ቦታ ነበረው።
ከወልደስላሴ እስር በኋላ ብዙዎች በህወሃት ውስጥ ውጥረት እንዳለ መናገር ጀምረዋል። ውስጥ ለውስ እየተንከባለለ ያለው ውጥረትማ ከከረረ ትንሽ ዘግየት ያለ ይመስላል። በውጥረቱ የተነሳም በባለስልጣናቱ መካከል እርስ በርስ መተማመን ከጠፋ ቆየ። አንድ ውስጥ አዋቂ ስለዚህ ሁኔታ ሲያጫውተኝ አባላቱ በምሽት ሲወጡ እንደ ጅብ ጎን ለጎን ነው የሚሄዱት። ጅብ ስለሚፈራ ብቻውን አይሄድም። ሁሌም ተጠራርቶ በቡድን ይሄዳል። ከባልንጀራው ጋር አብሮ ሲሄድ ደግሞ ጎን ለጎን መሆን አለበት።  ፊትና ኋላ ከሆኑ እርስበርስ ይበላላሉ።
በአሁኑ የህወሃት አሰላለፍ ግን አንደኛው ወገን ከኋሊት መጥቶ የቀደመ ይመስላል። ከፊት ያለው የኋላውን መብላት ጀምሯል። ተገላቢጦሽ የሆነው ይህ አስገራሚ ክስተት ነው ውጥረቱን ይበልጥ ያከረረው። የአዜብን ቡድን የማጥፋቱ ሂደት ላይ ግን ከፍተኛ ጥናት ሳይደረግ አልቀረም።  የፖለቲካ ሃይል አሰላለፉ ላይ ሚዛን የደፋው አንደኛው ቡድን ከደሙ ንጹ ባይሆንም የሙስናውን ወንጀል ለብቀላ መጠቀምያ ማድረጉ የአደባባይ ምስጢር ነው።
አንዳንድ የዋሆች ታዲያ ይህ የጸረ-ሙስና ዘመቻ አቶ መለስን ለማሳጣት እየተደረገ ያለ ድራማ እንደሆነ ይናገራሉ። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝንም የሚያመሰግኑም አልጠፉም። አቶ ሃይለማርያም ብዙውን ክስተት እንደ ተራው ሰው በዜና እንደሚሰሙ የሚያውቁት በቅርብ ያሉት ሰዎች ብቻ ናቸው። ለነገሩ እሳቸውም አስቀድመው "የእኔ ስራ ከፊትም ሆነ ከኋላ የሚሰጠኝን ትእዛዝ እየተቀበሉ ማስፈጸም ብቻ ነው።" ብለዋል። ከፊትና ከኋላ ብቻ ሳይሆን ከላይና ከታችም መመርያ እየተቀበሉ ያስፈጽማሉ። በሙስናው ስም የሚካሄደው ጨዋታ ከሳቸው ራዳር ውጭ ያለ መሆኑን ለመረዳት የፖለቲካ ጥበብን አይጠይቅም።
አቦይ ስብሃት በአንድ ቃለ-መጠይቅ ላይ ስለዚህ ጨዋታ ሲናገሩ የ10 ሚሊዮኑ ዘራፊ ቁጭ ብሎ የ10 ሺው መታሰር የለበትም ብለው ነበር። አቦይ ስብሃት እውነት ብለዋል። ከሌላው ጋር ሲነጻጸር ከአቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ ቤት ተገኘች ተብላ በኢቲቪ ጭምር ስትታይ የነበረችው 26 ሺ ኢሮ ኢምንት ናት። Global Financial Integrity (GFI) በመባል የሚታወቀው አለማቀፍ የገንዘብ ግልጸኝነት ተቋም ከ 2001 እስከ 2010 ብቻ ከኢትዮጵያ ተዘርፎ ወደውጭ የወጣው ገንዘብ 16.5 (አስራ ስድስት ነጥብ አምስት) ቢሊየን ዶላር ነው ሲል መረጃውን ከነማስረጃው ይፋ አድርጓል። ይህ ድርጊት ደግሞ በሙስና ከዘቀጡ ሃገራት ኢትዮጵያን በመጀመሪያው ደረጃ ላይ አስቀምጧታል። ልብ በሉ! 16.5 ቢሊየን ዶላር ከአራት በላይ የ"ህዳሴ" ግድቦችን ያሰራል። ከሁለተኛው አለም ጦርነት በኋላ መላው አውሮፓን ከውድቀት ያስነሳው የማርሻል ፕላን በጀት 20 ቢሊየን ዶላር ነበር። ከኢትዮጵያ በስምንት አመታት ጊዜ ውስጥ ብቻ የወጣው 16 ቢሊየን ዶላር ደግሞ አፍሪካ ካለችበት ውድቀት ሊያስነሳት የሚችል ገንዘብ እንደሆነ የኢኮኖሚ ጠበብት ይናገራሉ።
ኤ.ቢ.ሲ ኢንተርናሽናል የተባለው የማድሪድ ጋዜጣ ወ/ሮ አዜብ መስፍን በአንድ ቀን ግብይት ብቻ ለልብሷ 1.5 ሚሊዮን ዶላር እንዳወጣች ዘግቧል። አዜብ መስፍን ባለፈው የህወሃት ስብሰባ ላይ ተገኝታ ስትናገር ግን የአቶ መለስ የወር ደሞዝ 250 ዶላር እንደሆነ ነበር የተናገረችው። አዜብ የ1.5 ሚሊዮን ዶላር ልብስ በአንዲት ምሽት ስትሸምት መንግስት ድጎማ አድርጎላት ከሆነ ይኸው በይፋ ይነገር። በ250 ዶላር የወር ገቢ በሚሊዮን ዶላር ወጪ ማድረግ የሚቻልበት ሚስጥር የአባባ ታምራት ገለቴ ምትሃት ካልሆነ ታዲያ ምን ሊሆን ይችላል?  ይህንን መራራ ሃቅ የጸረ-ሙስናው ኮሚሽንን የሚነዳው ቡድን እንዴት ችላ ሊለው ቻለ? በዚህ ጉዳይ ላይ በርካታ ታዛቢዎች የሚሰጡት አስተያየት የሚያስኬድ ይመስላል።  ቡድኑ በቅድሚያ ወደ እነ አዜብ ሰፈር የሚወስደው መንገድ ላይ ያሉ ከእንቅፋቶችን ሁሉ ማጥራት አለበት።
በዛሬይቱ ኢትዮጵያ  እንደ ቀልድ የሚነገሩ አንዳንድ እውነታዎች ለማመን የሚከብዱ ናቸው።  አንዱ 'ልማታዊ ባለሃብት' በሪል ስቴት ስም የተመራው ቦታ ሲሰላ ከጅቡቲ የቆዳ ስፋት በልጦ ተገኘ። ይህ ሰው ትንሽ ቆይቶ ህገ-መንግስታዊ መብቱን በመጠቀም የመገንጠል ጥያቄም ሊያነሳ ይችላል እያሉ ያወሩ ነበር - በዚያ የቀኑት ባልንጀራዎቹ። በመጨረሻ ግን "ባለሃብቱ" በሙስና ታሰረና ይዞት የነበረው መሬት ለነ ቱሬ ዘመዶች በሄክታር ሁለት ብር ሂሳብ ተቸበቸበ።   ለነገሩ 3.5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ከዜጋው እየተቀማ ለውጭ ዜጎች በተቸበቸባት ሃገር ይህ ምንም ላይደንቀን ይችላል።
የሙስና ሰለባ የሆነው የሌላኛው ባለስልጣን ቤት ሲበረበር ደግሞ ብሄራዊ ባንክ ይመስል ነበር። እዚያ ቤት ውስጥም የአለም መገበያያ ገንዘብ ተገኘ። ዶላር፣ ኢሮ፣ ድራም፣ የን፣ ፓውንድ፤ ክሮን፤ ፍራንክ፣ ዲናር፣ ረንቢኒ ... እንዲያውም የኤርትራ ናቅፋ በገፍ ነበር። ከአቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ 26 ሺ ዶላር ተጋንና በቲቪ ስትቀርብ የዚህኛው ንግድ ፈቃድ የሌለው ባንክ በግል እጅ ሲገኝ ሜዲያም ዝም ማለትን መረጠ።  በዚህ ጊዜ ነበር የአሳሪው ቡደን ሃላፊ የኮሎኔል መንግስቱን ንግግር የተጠቀመው። "ደፍረውናል፣ ንቀውናል።.. ብታምኑም ባታምኑም በቁም ሞተናል።"
አነጋገሩ ለምን ሃገር ተዘረፈ ሳይሆን እኛ ታግለን ለዚህ የደረስን የቁርጥ ቀን ታጋዮች ቁጭ ብለን እንዴት ከኋላ የመጣው ሊበልጠን ቻለ ለማለት ነበር። የሙስናው ዘመቻ ድ
የሙስናው ጉዳይ
ክንፉ አሰፋ
          በተንጣለለ ቪላ ውስጥ ከበድ ያሉ እንግዶች "ጸዳ" ባሉ ምግብና መጠጦች እየተስተናገዱ ነው። ታዋቂ ግለሰቦች፤ ባለስልጣናት እና አርቲስቶች የቀረበላቸውን ብፌ በልማታዊ ወጋቸው እያወራረዱ ሳሉ አንድ እንግዳ ነገር በመሃላቸው ተከሰተ።  ሞቅ ባለው የአይቴ ነጋ ገብረእግዚአብሄር ድግስ ላይ ያልተጋበዙ ሁለት ሰዎች ዘው ብለው ከግብዣው ክፍል ገቡ።  የፌዴራል ፖሊስ አባላት ነበሩ።
በዚህ ያልተለመደ ክስተት የአቶ ነጋ እንግዶች አልተደናገጡም ነበር። ይልቁንም  የፌዴራል ፖሊሶቹ ለተጨማሪ ጥበቃ የመጡ ነበር የመሰላቸው። አንድ ብርጌድ ያህል ጦር አስከትለው የመጡት ፖሊሶች ግን አቶ ነጋ ገብረእግዚአብሄርን አስጠሯቸው።  አቶ ነጋም ለጥሪው እንደወትሮው በመወጣጠርና ፍጹም ትእቢት በተሞላበት አነጋገር ምላሽ ሰጡ። በፖሊስ አባላቱ እና በአቶ ነጋ መካከል የሃይለ-ቃል ልውውጥ ተጀመረ። እሰጥ እገባው  አንድ፣ ሁለት እያለ ሄደና በመጨረሻ ተካረረ። በዚህ ሰዓት አቶ ነጋ ስልክ መደዋወል ያዙ። ከፍተኛ የሚባሉ ባለስልጣናትና ምኒስትሮች ጋ ደወሉ።  ከዚያም በመቀጠል፣ ጀነራሎች ጋ ደወሉ... የጦር መኮንኖች፣ የፓርቲ ባለስልጣናት... ሁሉም ጋ ተደወለ። የባለስልጣናቱ ምላሽ ግን ጥሩ እንዳልነበር ከአቶ ነጋ ፊት ላይ ይነበብ ነበር። ወዳጆቻቸው ሁሉ እንደ ቱኒዚያው ቤን አሊ በአንድ ጊዜ ከዷቸው።
"በል - ና - ውጣ!" አለ አንደኛው የፖሊስ አባል፣ የስልኩን ሽርጉድ በጥሞና ከተከታተለ በኋላ።
"ምን ማለትህ ነው? እኔኮ ነጋ ነኝ። ነጋ ታሪኩ!" አሉ። አነጋገራቸው የጀምስ ቦንድን ይመስል ነበር። በዚህ ጊዜ ታዲያ እጃቸውም አላረፈም። ከጎን ያሸጎጡትን መሳርያ ለማውጣትም ዳዳቸው።
በቅጽበት ግን ፌዴራል ፖሊሱ ቀደማቸው። በድንገት "ጯ!" የሚል ድምጽ አዳራሹን አናጋው። የፖሊሱ አይበሉባ የግራ መንጋጭላቸው ላይ ሲያርፍባቸው ጊዜ፤ አይቴ ነጋ ነገር አለሙ ተደበላለቀባቸውና እጅ መስጠትን መረጡ። ግብር ሊያበሉ በጠሯቸው የክብር እንግዶቻቸው ፊት፣ ከዚህ በላይ መዋረድ አልፈቀዱም።   ሁለት እጃቸውንም ወደ ፖሊሱ በመዘርጋት ለብረት ማሰርያው ራሳቸውን አመቻቹ። እጃቸው የኋሊት ከተጠፈረ በኋላም አቶ ነጋ እንዲህ አሉ። "በቃ! ህወሃት አበቃለት!"
"ባለሃብቱ" በዚህ ሁኔታ በፖሊስ መኪና ተጭነው ወደ እስር ቤት ሲሄዱ፣ ተጋባዥ እንግዶቹም እግሬ-አውጭኝ እያሉ ከስፍራው አፈተለኩ።  ይህ ታሪክ ድራማ ሊመስል ይችላል። ግን በእውን የተፈጸመ ሃቅ ነው። ታሪኩን ያጫወተኝ ሰውም እዚያ ግብዣ ላይ ግብር ሊበላ ተገኝቶ ነበር። እንደ አግራሞቱም  "ይህ መቼም የፈጣሪ ስራ ነው።" ከማለት ውጪ ስለ ጉዳዩ እንድምታ የሰጠው ማብራሪያ የለም።
ነጋ ገብረእግዚአብሄር የነፃ ትሬዲግ ኃላፊነቱ የተወሰነ (ሰዎች ያልተወሰነ ይሉታል) የግል ማህበር ባለቤት ነበሩ። ድርጅታቸውም እንደስሙ ከሁሉም ነገር ነጻ ነበር። ከግብር ነጻ፤ ከቁጥጥጥር ነጻ፤  ከፍተሻም ነጻ። በመቶዎች የሚቆጠሩ የጭነት መኪናዎች እቃ ጭነው በየኬላው ሳይፈተሹ እንዲያልፉ የተሰጠ ልዩ መብት ሁሉ እንደነበራቸው ይነገራል።  ዛሬ ፈጣሪ ሲፈርድባቸው በኢፍትሃዊ መንገድ ቢልየነር ያደረጋቸው ስርዓት፤ ያው ስርዓት ሰለባ አደረጋቸው... ነጋ ገብረእግዚአብሄር ለአቶ መለስ ዜናዊ እና ለባለቤታቸው ለወ/ሮ አዜብ መስፍን ቅርብ - በጣም ቅርብ ነበሩ። ለጉምቱ ባለስልጣናት ይሰጡት የነበረው እጅ መንሻ ከዚህ አይነት ውርደት እና እስራት ሊያድናቸው አልቻለም። በትግራይ ውስጥ ከ40 ሚሊየን ብር በላይ አውጥተው በስማቸው ያሰሩት የቴክኒክ ኮሌጅም እንደ ውለታ አልተቆጠረላቸውም።...
ይህችን  አጭር መጣጥፍ ለመጫር እንደተቀመጥኩ አንድ ዜና በኢሜይል ደረሰኝ።  የዜናው ርእስ "ጀነራል ባጫ ደበሌ የአዋሽ ባንክ ሰራተኞችን ከሥራ እንዲባረሩ አደረጉ!" ይላል። ባጫ ደበሌ የባንክ ሰራተኞቹን ያባረሩዋቸው ‘’እኔ ጀነራል ባጫ ደበሌን እንዴት አታውቁኝም?’’ በሚል በሰራተኞቹ አለመታወቃቸው አበሳጭቷቸው ነበር።  ወደ ፌስ ቡክ ጎራ ስልም አንዳንዶች በዜናው ላይ ሲወያዩ አስተዋልኩ። ይህ እኮ አዲስ ክስተት አይደለም። ለብዙ ጊዜ የሚደጋገም እና የተለመድ ነገር ዜና ሊሆን አይችልም። ውሻ ሰውን ሲነክስ ዜና አይሆንም። በተቃራኒው ግን ሰው ውሻን ከነከሰ ዜና ይሆናል። እንዲህ አይነቱ ክስተት ስር የሰደደ የስርዓቱ ባህርይ ነው። ባጫ ደበሌ እነዚያን ሰዎች ማስገደል የሚያስችልም ስልጣን እና መብት ያላቸው የአዜብ ሰው መሆናቸውን አንዘንጋ።  ጀነራል ባጫ  በተልእኮ ትምህርት ከአንድም ሁለተኛ ዲግሪ እንዲገዛላቸው ካደረጉ በኋላ፣ ለምርቃታቸው ስነ-ስርዓት፣ ሰንጋዎች ጥለው፣ የሙዚቃ ባንድም አስመጥተው፣  መንገድ ሁሉ እንዲዘጋ አድርገው ሲያበቁ፤ በተለመደው ብሬክ ዳንሳቸው መንደሩን የቀወጡ ሰው ናቸው።  በብርሃን ፍጥነት ከኪነት ጓድነት ወደ ጀነራል የተሸጋገሩት ባጫ ደበሌ በመደበኛ የስራ ጊዜያቸው ጫት ይነግዳሉ። በትርፍ ጊዜያቸው ደግሞ በዜጋው ላይ እንዲሁ እንደዋዛ እየቀለዱ እስካሁን አሉ። የነገውን አንድዬ ብቻ ነው የሚያውቀው።  የፍትህ ሳይሆን የግለሰቦች የበላይነት የሰፈነበት ሃገር ስልጣንን ያላግባብ መጠቀም ሙስና ሊደንቀን አይገባም።  የፍትሃዊ ስርዓት መጥፋት ነው ሙስና።
ፕሮፌሰር አል ማርያም ባለፈው መጣጥፉ ስለሙስና ሲጽፍ  ከሙስና ሁሉ በላይ ሙስና የሚሆነው የፍትህ መጓደል እንደሆነ አስነብቦናል። የፍትህ መጥፋት ስብእናን፣ ነጻነትንና ንብረት ማጣትን ያስከትላልና። In my view, denial of due process (fair trial) is the highest form of corruption imaginable in the “justice sector” because it results in the arbitrary deprivation of a person’s life, liberty and property.  (Al Mariam)
ከሰሞኑ ደግሞ ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም ምንጩ ያልታወቀ ሃብት አፍርተሃል በመባል ተወንጅሎ ወህኒ የወረደው የወልደስላሴ ወልደሚካኤልም ዜና በስፋት እየተሰራጨ ነው። ወልደስላሴ  ሌላኛው የአዜብ መስፍን የቅርብ ሰው ነበር። በዚህ ጉዳይ ላይ ዳዊት ከበደ በስፋት ትንታኔ ስለሰጠበት እዚህ ላይ አልደግመውም። ወልደስላሴ ግን ከህወሃት የጫካ ትግል ጀምሮ ቀልፍ ቦታዎች ላይ ተመድቦ የሰራና - የመለስ ቀኝ እጅ የነበረ ሰው ነው። ታማኝ አገልጋይም ስለነበረ በህወሃት ውስጥ ወሳኝ ቦታ ነበረው።
ከወልደስላሴ እስር በኋላ ብዙዎች በህወሃት ውስጥ ውጥረት እንዳለ መናገር ጀምረዋል። ውስጥ ለውስ እየተንከባለለ ያለው ውጥረትማ ከከረረ ትንሽ ዘግየት ያለ ይመስላል። በውጥረቱ የተነሳም በባለስልጣናቱ መካከል እርስ በርስ መተማመን ከጠፋ ቆየ። አንድ ውስጥ አዋቂ ስለዚህ ሁኔታ ሲያጫውተኝ አባላቱ በምሽት ሲወጡ እንደ ጅብ ጎን ለጎን ነው የሚሄዱት። ጅብ ስለሚፈራ ብቻውን አይሄድም። ሁሌም ተጠራርቶ በቡድን ይሄዳል። ከባልንጀራው ጋር አብሮ ሲሄድ ደግሞ ጎን ለጎን መሆን አለበት።  ፊትና ኋላ ከሆኑ እርስበርስ ይበላላሉ።
በአሁኑ የህወሃት አሰላለፍ ግን አንደኛው ወገን ከኋሊት መጥቶ የቀደመ ይመስላል። ከፊት ያለው የኋላውን መብላት ጀምሯል። ተገላቢጦሽ የሆነው ይህ አስገራሚ ክስተት ነው ውጥረቱን ይበልጥ ያከረረው። የአዜብን ቡድን የማጥፋቱ ሂደት ላይ ግን ከፍተኛ ጥናት ሳይደረግ አልቀረም።  የፖለቲካ ሃይል አሰላለፉ ላይ ሚዛን የደፋው አንደኛው ቡድን ከደሙ ንጹ ባይሆንም የሙስናውን ወንጀል ለብቀላ መጠቀምያ ማድረጉ የአደባባይ ምስጢር ነው።
አንዳንድ የዋሆች ታዲያ ይህ የጸረ-ሙስና ዘመቻ አቶ መለስን ለማሳጣት እየተደረገ ያለ ድራማ እንደሆነ ይናገራሉ። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝንም የሚያመሰግኑም አልጠፉም። አቶ ሃይለማርያም ብዙውን ክስተት እንደ ተራው ሰው በዜና እንደሚሰሙ የሚያውቁት በቅርብ ያሉት ሰዎች ብቻ ናቸው። ለነገሩ እሳቸውም አስቀድመው "የእኔ ስራ ከፊትም ሆነ ከኋላ የሚሰጠኝን ትእዛዝ እየተቀበሉ ማስፈጸም ብቻ ነው።" ብለዋል። ከፊትና ከኋላ ብቻ ሳይሆን ከላይና ከታችም መመርያ እየተቀበሉ ያስፈጽማሉ። በሙስናው ስም የሚካሄደው ጨዋታ ከሳቸው ራዳር ውጭ ያለ መሆኑን ለመረዳት የፖለቲካ ጥበብን አይጠይቅም።
አቦይ ስብሃት በአንድ ቃለ-መጠይቅ ላይ ስለዚህ ጨዋታ ሲናገሩ የ10 ሚሊዮኑ ዘራፊ ቁጭ ብሎ የ10 ሺው መታሰር የለበትም ብለው ነበር። አቦይ ስብሃት እውነት ብለዋል። ከሌላው ጋር ሲነጻጸር ከአቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ ቤት ተገኘች ተብላ በኢቲቪ ጭምር ስትታይ የነበረችው 26 ሺ ኢሮ ኢምንት ናት። Global Financial Integrity (GFI) በመባል የሚታወቀው አለማቀፍ የገንዘብ ግልጸኝነት ተቋም ከ 2001 እስከ 2010 ብቻ ከኢትዮጵያ ተዘርፎ ወደውጭ የወጣው ገንዘብ 16.5 (አስራ ስድስት ነጥብ አምስት) ቢሊየን ዶላር ነው ሲል መረጃውን ከነማስረጃው ይፋ አድርጓል። ይህ ድርጊት ደግሞ በሙስና ከዘቀጡ ሃገራት ኢትዮጵያን በመጀመሪያው ደረጃ ላይ አስቀምጧታል። ልብ በሉ! 16.5 ቢሊየን ዶላር ከአራት በላይ የ"ህዳሴ" ግድቦችን ያሰራል። ከሁለተኛው አለም ጦርነት በኋላ መላው አውሮፓን ከውድቀት ያስነሳው የማርሻል ፕላን በጀት 20 ቢሊየን ዶላር ነበር። ከኢትዮጵያ በስምንት አመታት ጊዜ ውስጥ ብቻ የወጣው 16 ቢሊየን ዶላር ደግሞ አፍሪካ ካለችበት ውድቀት ሊያስነሳት የሚችል ገንዘብ እንደሆነ የኢኮኖሚ ጠበብት ይናገራሉ።
ኤ.ቢ.ሲ ኢንተርናሽናል የተባለው የማድሪድ ጋዜጣ ወ/ሮ አዜብ መስፍን በአንድ ቀን ግብይት ብቻ ለልብሷ 1.5 ሚሊዮን ዶላር እንዳወጣች ዘግቧል። አዜብ መስፍን ባለፈው የህወሃት ስብሰባ ላይ ተገኝታ ስትናገር ግን የአቶ መለስ የወር ደሞዝ 250 ዶላር እንደሆነ ነበር የተናገረችው። አዜብ የ1.5 ሚሊዮን ዶላር ልብስ በአንዲት ምሽት ስትሸምት መንግስት ድጎማ አድርጎላት ከሆነ ይኸው በይፋ ይነገር። በ250 ዶላር የወር ገቢ በሚሊዮን ዶላር ወጪ ማድረግ የሚቻልበት ሚስጥር የአባባ ታምራት ገለቴ ምትሃት ካልሆነ ታዲያ ምን ሊሆን ይችላል?  ይህንን መራራ ሃቅ የጸረ-ሙስናው ኮሚሽንን የሚነዳው ቡድን እንዴት ችላ ሊለው ቻለ? በዚህ ጉዳይ ላይ በርካታ ታዛቢዎች የሚሰጡት አስተያየት የሚያስኬድ ይመስላል።  ቡድኑ በቅድሚያ ወደ እነ አዜብ ሰፈር የሚወስደው መንገድ ላይ ያሉ ከእንቅፋቶችን ሁሉ ማጥራት አለበት።
በዛሬይቱ ኢትዮጵያ  እንደ ቀልድ የሚነገሩ አንዳንድ እውነታዎች ለማመን የሚከብዱ ናቸው።  አንዱ 'ልማታዊ ባለሃብት' በሪል ስቴት ስም የተመራው ቦታ ሲሰላ ከጅቡቲ የቆዳ ስፋት በልጦ ተገኘ። ይህ ሰው ትንሽ ቆይቶ ህገ-መንግስታዊ መብቱን በመጠቀም የመገንጠል ጥያቄም ሊያነሳ ይችላል እያሉ ያወሩ ነበር - በዚያ የቀኑት ባልንጀራዎቹ። በመጨረሻ ግን "ባለሃብቱ" በሙስና ታሰረና ይዞት የነበረው መሬት ለነ ቱሬ ዘመዶች በሄክታር ሁለት ብር ሂሳብ ተቸበቸበ።   ለነገሩ 3.5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ከዜጋው እየተቀማ ለውጭ ዜጎች በተቸበቸባት ሃገር ይህ ምንም ላይደንቀን ይችላል።
የሙስና ሰለባ የሆነው የሌላኛው ባለስልጣን ቤት ሲበረበር ደግሞ ብሄራዊ ባንክ ይመስል ነበር። እዚያ ቤት ውስጥም የአለም መገበያያ ገንዘብ ተገኘ። ዶላር፣ ኢሮ፣ ድራም፣ የን፣ ፓውንድ፤ ክሮን፤ ፍራንክ፣ ዲናር፣ ረንቢኒ ... እንዲያውም የኤርትራ ናቅፋ በገፍ ነበር። ከአቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ 26 ሺ ዶላር ተጋንና በቲቪ ስትቀርብ የዚህኛው ንግድ ፈቃድ የሌለው ባንክ በግል እጅ ሲገኝ ሜዲያም ዝም ማለትን መረጠ።  በዚህ ጊዜ ነበር የአሳሪው ቡደን ሃላፊ የኮሎኔል መንግስቱን ንግግር የተጠቀመው። "ደፍረውናል፣ ንቀውናል።.. ብታምኑም ባታምኑም በቁም ሞተናል።"
አነጋገሩ ለምን ሃገር ተዘረፈ ሳይሆን እኛ ታግለን ለዚህ የደረስን የቁርጥ ቀን ታጋዮች ቁጭ ብለን እንዴት ከኋላ የመጣው ሊበልጠን ቻለ ለማለት ነበር። የሙስናው ዘመቻ ድራማ ቁልፍ እዚህ ላይ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ወደፊት በሰፊው እሄድበታለሁ። ለአሁን ግን  በአቶ ኤርምያስ አመልጋ የሚደነቅ ታሪክ ጽሁፌን ልቋጭ።
በዚያ ሰሞን የአክሰስ ሪል ስቴት ሥራ አስኪያጅና የቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት አቶ ኤርምያስ ጠቅል አመልጋ፣ በተለይ በውጪ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለመኖሪያ ቤት ግንባታ ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ ከሰበሰቡ በኋላ፣ ከሃገር መጥፋታቸው ተዘግቦ ነበር።  ታዲያ አቶ ኤርምያስን የሚረግሙ ጌጃ ዲያስፖራዎች እንዳሉ ሁሉ እሳቸውን የሚያደንቁም አልጠፉም። ስለአቶ ኤርምያስ በቀልድ እየተመሰለ ብዙ ነገር ይወራል።  የተከበሩ ሎሬት አፈወርቅ ተክሌን እና አቶ ኤርምያስን የሚያመሳስላቸው ነገር ቢኖር ሁለቱም የተዋጣላቸው ሰአሊያን መሆናቸው ነው ተብሏል። ለላሜ ቦራው ዲያስፖራ እንዲሰሩ ገንዘብ የተከፈለባቸው ቤቶች ሁሉ ባማሩ ስዕሎች በወረቀት ላይ ዱቅ ብለዋል።  በንዴት ገንዘቡን ሊያስመልስ የሚሄደው ሁሉ በስእሎቹ እና በአቶ ኤርምያስ ምትሃታዊ ንግግር እየተማረከ እንዲያውም ለሁለተኛና ሶስተኛ ቤት የከፈለው ዲያስፖራ ቁጥር ትንሽ አይደለም።  አቶ ኤርምያስ በአንድ በኩል በሙስና ክስ እየተፈለጉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ከሃገር በቦሌ አድርገው እንዲወጡ የተደረጉ "ጀግና" ባለሃብት ናቸው።
ለፖለቲካው እንግዳ ለሆኑ ሰዎች፤ እነዚህ ሁሉ ፈጠራ ሊመስሉ ይችላሉ። ግን የኢትዮጵያ ህዝብ የእለት ተለት ገጠመኞች ውስጥ አንድ እጅ እንኳን የማይሞሉ እውነታዎች ናቸው።
ራማ ቁልፍ እዚህ ላይ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ወደፊት በሰፊው እሄድበታለሁ። ለአሁን ግን  በአቶ ኤርምያስ አመልጋ የሚደነቅ ታሪክ ጽሁፌን ልቋጭ።
በዚያ ሰሞን የአክሰስ ሪል ስቴት ሥራ አስኪያጅና የቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት አቶ ኤርምያስ ጠቅል አመልጋ፣ በተለይ በውጪ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለመኖሪያ ቤት ግንባታ ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ ከሰበሰቡ በኋላ፣ ከሃገር መጥፋታቸው ተዘግቦ ነበር።  ታዲያ አቶ ኤርምያስን የሚረግሙ ጌጃ ዲያስፖራዎች እንዳሉ ሁሉ እሳቸውን የሚያደንቁም አልጠፉም። ስለአቶ ኤርምያስ በቀልድ እየተመሰለ ብዙ ነገር ይወራል።  የተከበሩ ሎሬት አፈወርቅ ተክሌን እና አቶ ኤርምያስን የሚያመሳስላቸው ነገር ቢኖር ሁለቱም የተዋጣላቸው ሰአሊያን መሆናቸው ነው ተብሏል። ለላሜ ቦራው ዲያስፖራ እንዲሰሩ ገንዘብ የተከፈለባቸው ቤቶች ሁሉ ባማሩ ስዕሎች በወረቀት ላይ ዱቅ ብለዋል።  በንዴት ገንዘቡን ሊያስመልስ የሚሄደው ሁሉ በስእሎቹ እና በአቶ ኤርምያስ ምትሃታዊ ንግግር እየተማረከ እንዲያውም ለሁለተኛና ሶስተኛ ቤት የከፈለው ዲያስፖራ ቁጥር ትንሽ አይደለም።  አቶ ኤርምያስ በአንድ በኩል በሙስና ክስ እየተፈለጉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ከሃገር በቦሌ አድርገው እንዲወጡ የተደረጉ "ጀግና" ባለሃብት ናቸው።
ለፖለቲካው እንግዳ ለሆኑ ሰዎች፤ እነዚህ ሁሉ ፈጠራ ሊመስሉ ይችላሉ። ግን የኢትዮጵያ ህዝብ የእለት ተለት ገጠመኞች ውስጥ አንድ እጅ እንኳን የማይሞሉ እውነታዎች ናቸው።

አዜብ መስፍን ይታሰራሉ?

 
"አዜብን ማሰር፣ መለስን ከሞት ቀስቅሶ ለፍርድ ማቆም ነው"
 
                     መለስ ዜናዊ ሆን ብለው ለፖለቲካ ሚዛን መጠበቂያ ሲገለገሉበት በነበረው “የሙስና ባህር” ያልተነከረበት የለም። ባህሩ ውስጥ ያልዋኘ የለም። ከባህሩ ራሳቸውን ያገለሉ ጥቂቶች ቢኖሩም ወ/ሮ አዜብ መስፍን ግን የባህሩ ዋናው አጥማቂና የውሃው ባለቤት እንደሆኑ በርካታ ምስክሮች አሉ።
 
azeb-mesfin-e
አቶ መለስ “ውርሳቸውን/ሌጋሲያቸውን” ትተው ካለፉ በኋላ አገሩን አከርፍቶት የነበረው የሙስና ባህር በስንጥር መነካካት ተጀመረና አሁን ቁንጮዎቹ ግድም ደርሶ እያሸበረ ነው። ይህንኑ የሙስና ማዕበል ተከትሎ የባለቤታቸውን ውርስ ታኮ ያደረጉት ወ/ሮ አዜብና በተሸናፊው የፖለቲካ መስመር ያሉ ሁሉ ተሸብረዋል። አንዳንድ ጥቆማዎችና የህዝብ አስተያየቶች እንደሚያመለክቱት ወ/ሮ አዜብ ታውከዋል።
 
ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሃላፊዎችና ከነሱ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ከዋሉት “ባለሃብቶች” መካከል ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር እንደሚነግዱ የሚታወቁ በቁጥጥር ስር መዋላቸው የስጋታቸው መነሻና እምብርት ስለመሆኑ አብዛኞች ይስማማሉ። ከዚህም በተጨማሪ ያለታክስ በሚገቡ ምርቶች፣ ተሽከርካሪዎች፣ በቴሌ የህገወጥ ማስደወል ወንጀል፣ በጫት ኤክስፖርትና በኮንስትራክሽን ዘርፍ በስፋት ቢዝነስ እንደሚያጫውቱ የሚታወቁት ወ/ሮ አዜብ በገንዘብ የከበሩትን ያህል በርካታ ጠላት እንዳፈሩም የሚቀርቧቸው ይናገራሉ።
 
azeb 2
 
ኤፈርትን ለወ/ሮ አዜብ ያስረከቡት አቶ ስብሃት ነጋ በተደጋጋሚ ስለሙስና መናገር የጀመሩት አቶ መለስ አፈር ሳይቀምሱ ነበር። ወ/ሮ አዜብ የባለቤታቸውን ጡንቻና በዘመቻ በጀት ተመድቦለት “ባለራዕይ፣ ታላቁ መሪ” በሚል የተሰጣቸውን የሸቀጥ ስም ተገን አድርገው ሙስና ውስጥ መነከራቸውን የሚያውቁት አቶ ስብሃት ስም አይጥቀሱ እንጂ ነገራቸው ሁሉ ከወ/ሮ አዜብ ደጅ እንደነበር ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የሚናገሩት የአደባባይ ምስጢር ነው።
 
አቶ ስብሃት ነጋ ከመለስ ሞት በኋላ ይህንኑ አቋማቸውን አጠንክረው የገፉበት ቢሆንም በፖለቲካ አሰላለፋቸው ተሸናፊ በመሆናቸው ለማፈግፈግ ተገደው እንደነበር የሚናገሩ አሉ። ከውስጥ አዋቂዎች እንደሚሰማውና በተባራሪ እንደሚነገረው አቶ ስብሃት ዳግም አሸናፊውን ቡድን ተመልሰው ተቀላቅለዋል። ለዚህም ይመስላል እሳቸው ምን ያህል የጸዱ ስለመሆናቸው መረጃ ባይኖርም አሁን ከተጀመረው የሙስና ዘመቻ ጀርባ እንዳሉበት የሚጠቆመው። አንዳንዶች እንደሚሉት ህወሃት በትከፋፈለ ጊዜ (ዘመነ ህንፍሽፍሽ) አቶ አባይ ጸሐዬ ውህዳኑን ተቀላቅለው መረጃ ከሰበሰቡ በኋላ አቶ መለስን በመቀላቀል የተጫወቱትን የ”መንታ”/ደብል/ ስልት፣ የመለስ ሞትን ተከትሎ ለተነሳው የሃይል ሰልፍ ትንቅንቅ አቶ ስብሃት ነጋም ተጠቅመውበታል። በዚሁ ስልታዊ አካሄድም የእነ ዶ/ር ደብረጽዮን ክንፍ አሸናፊ ሆኖ እንዲወጣ አስችለዋል።

አዜብ መስፍን ለምን አይታሰሩም?

ከሙስና ጋር ስማቸው በስፋት የሚነሳው ወ/ሮ አዜብ፤ በባለቤታቸው እንደ ቪኖ ቡሽ ድንገት ሲፈተለኩ በሃዘን ድባብ ውስጥ ሆነው የጀመሩት ዘመቻ የቀልድ መሃላ ይዘት ያለው ነው። በ”ፖለቲካ ቁጭ በሉ” እንዲመለኩ የተደረጉትን አቶ መለስን ደጋግሞ በመጥራት አዜብ መስፍን “የመለስ ራዕይ ካልተቀየረና ሌጋሲው እስካልተበረዘ ድረስ …” እያሉ ካድሬውንና ቀሪውን የህወሃት ሰዎች መማጸን ላይ አተኩረው ነበር። በሄዱበትና ባገደሙበት የባለቤታቸው ስምና ዝና ላፍታም ካንደበታቸው የማይለያቸው ወ/ሮ አዜብ ጀርባቸውን ስለሚያውቁት የመለስን ስም የሚያንጠለጥሉት ራሳቸውን ለመከላከል እንደሆነም ከታች እስከ ላይ ስምምነት አለ።
ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ከደረሱት አስተያየቶች መካከል “ካድሬው ባብዛኛው፣ የበላይ አመራሩ በከፊል አዜብስ?” በማለት ለምን በቁጥጥር ስር እንደማይውሉ የሚጠይቁትና የሚነጋገሩት በገሃድ ነው። ይሁን እንጂ አዜብ ለምን እንዲታሰሩ የፍርድቤት ትዕዛዝ (ዋራንት) አይቆረጥባቸውም? ለሚለው የሚሰጠው መልስ “የመለስ ሌጋሲ እንዳይወድም፣ እንዳይቆሽሽ፣ የተሰራው የረከሰና የሸቀጥ ያህል በፖለቲካ ውዳሴ የተገነባው ከንቱ ዝና እንዳይቆሽሽ፣ ብሎም ሌላ ጥያቄ እንዳያስነሳ ነው” የሚል ነው።
 
azeb 1
 
አቶ ስብሃት ሲመሩት የነበረው ኤፈርትን በሳቸው አዲስ አመራርና በመለስ ልዩ አመራር ሰጪነት በሺህ ለሚቆጠሩ የትግራይ ልጆች የስራ እድል ማዘጋጀቱን፣ ትግራይ ውስጥ በርካታ ፋብሪካዎች እንደሚከፈቱና ሲደበቅ የነበረው በጀት በዶላር ተሰልቶ ለህዝብ ይፋ እንዲሆን በማድረግ ስብሃት ነጋን የማሳጣት እጅ አዙር ዘመቻቸውን አጣድፈው የጀመሩት ወ/ሮ አዜብ የትግራይን ህዝብ ልብ ለማግኘትና አቶ ስብሃት የሚከፍቱባቸውን ዘመቻ አስቀድሞ ለመቋቋም በማሰብ ነበር።
 
ህወሃት የክልሎችን በጀት እልብ አድርጎ የሚጠባበት የብር ማሽኑ የሆነውን ሜጋ ኢንትርፕራይዝን ይመሩ የነበሩት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከምርጫ1997 በኋላ በድርጅት አቋም፣ በአቶ መለስ ፊርማና ውሳኔ እንዲነሱ መደረጉን፤ ከሃላፊነት የተነሱበት ደብዳቤ እንደደረሳቸው አኩርፈው ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሄደው “በሽማግሌ” ከባለቤታቸው ጋር እንደታረቁ፣ ሽምግልናውን ባከናወኑት ሰው አማካይነት ወ/ሮ አዜብ የተነጠቁት ሹመት እንዲመለስላቸው መደረጉን እንደሚያውቁ የሚናገሩ ክፍሎች “ኢትዮጵያ ውስጥ ህግና ፍትህ ለሰከንድ ቢተገበር ህገወጥ ስልክ በማስደወል የሜጋን ቢሮ ለዋና ማቀናበሪያና የተጠቀሙበት ወ/ሮ አዜብ የመጀመሪያዋ ተጠያቂ ሊሆኑ በተገባ ነበር። የመለስ ሌጋሲ እንግዲህ ይህን ነው” በማለት ይጠይቃሉ።
 
እነዚህ ክፍሎችም ሆኑ ሌሎች ወገኖች አዜብ መስፍን የፖለቲካ ሃይላቸው የተቦረቦረ፣ ከበዋቸው የነበሩት ሃይሎች የተመናመኑ፣ እንደ ተርብ የሚናደፈው አንደበታቸውና ባህሪያቸው እንደበረዶ የቀዘቀዘበት ወቅት ላይ እንደሚገኙ እየተገለጸ ነው። በጸለመ ልብስ የሚታዩትና የሃዘን ጥቁር ልብሳቸውን ለመቀየር ፈቃደኛ ያልሆኑት ወ/ሮ አዜብ ተቅለስላሽ ሰው ሆነው መታየታቸው ስጋታቸው ማየሉን የሚያሳይ እንደሆነ የሚመሰክሩት ክፍሎች “አዜብ መስፍን ወዳጅ እንደሌላቸውና በተለይም በህወሃት ሰዎችና ካድሬዎች
 
azeb-mesfin
 
 ዘንድ ስለማይወደዱ ዙሪያቸውን ከሚዞራቸው የሙስና ደወል ማምለጥ ስለሚችሉበት ሁኔታ ሊያስቡ እንደሚችሉ እንገምታለን” ይላሉ። ለአብነትም ሲያኮርፉ ወደ ሳዑዲ እንደሚሄዱና በዱባይ ሪል ስቴት እንዳላቸው ስለሚታሙ ጓዛቸውን ጠቅልለው ወደዚያው ሊያመሩ እንደሚችሉ ምልክት እንዳለ ይጠቁማሉ። በዱባይ አላቸው ስለሚባለውና በሌሎች ተቋራጭ ድርጅቶች ስም ስለተገነቡት ቤቶችና ንብረቶቻቸው እነዚህ ክፍሎች ለጊዜው ዝርዝር አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።
 
በሌላ ወገን ግን አሁን የባለቤታቸውን የፋውንዴሽን ስራ እንዲሰሩ የተመደቡት ወ/ሮ አዜብ የእነ በረከት ስምዖን ቡድን በመሆናቸው፣ ለዚሁ ቡድን ቀኝ እጅ የሆኑት የደህንነቱ አውራ አቶ አሰፋና ሸራተን ያሉት ባለሃብት እጅግ ወዳጃቸው በመሆናቸው ቀስ በቀስ እንዲከስሙ ይደረጋል እንጂ አይታሰሩም ሲሉ በድፍረት ይናገራሉ። ወ/ሮ አዜብን ማሰር ማለት አቶ መለስን ከመቃብር አውጥቶ እንደገና ፍርድ አደባባይ የማቅረብ ያህል እንደሆነ የሚናገሩት እነዚህ ክፍሎች “ታላቁ፣ ባለራዕዩ፣ አስተዋዩ፣ አርቆ አሳቢው፣ የደሆች አባት፣ ራሱን ‘ለኢትዮጵያ’ አንድዶ የሞተ፣ አንዲት ሃሳብ ይዞ ወደ (ኢትዮጵያ) ምድር የመጣው አዳኝ፣ እረፍት የማያውቀው፣ ዜጎቹን በቀን ሶስቴ እንዲበሉ ያስደረገው፣ የአፍሪካ አንደበት፣ የዓለም ቅርስ፣ የወደፊቱ ኢትዮጵያ ተምሳሌት፣ የታሪክ አውራ፣ እርምና ወንጀል የሌለበት … በማለት ህወሃት ሆን ብሎ የገነባውን ስም አዜብን በማሰር አፈር አይከተውም” በማለት አዜብ ሊታሰሩ የማይችሉበትን ምክንያት ያመላክታሉ።

የመጨረሻው መጀመሪያ

birhane
ብርሃነ ኪዳነማርያም
ወ/ሮ አዜብ የመጨረሻው መጀመሪያ ላይ ስለመሆናቸው ምልክቶች እንዳሉ የሚጠቅሱ አሉ። ያለ ከልካይ ሲመሩትና ሲነዱት ከነበረው ግዙፉ የህወሃት የገንዘብ ቋት ኤፈርት ተሰናብተዋል። ወንበራቸውን እንዲቀሟቸው የተደረጉት የዋልታ ኢንፎርሜሽን ዋና ስራ አስኪያጅና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት የሆኑት ብርሃነ ኪዳነማርያም (ብርሃነ-ማረት) የቀድሞው የፍቅር ወዳጃቸው ናቸው። በደህንነት ውስጥ አድራጊና ፈጣሪ የነበሩት የቅርብ የንግድ ሸሪካቸው አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የሚጠየፉትን ወህኒ ገብተውበታል። በከፍተኛ የንግድ ቅርርብና ሽርክና የሚወዳጇቸው አቶ ነጋ ገብረ እግዚአብሔር ከታሰሩ ወራት ተቆጥሯል። የገቢዎችና ጉምሩክ ምክትል ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ገብረዋህድ ከቀረጥ ነጻ በመፍቀድ አብረዋቸው በኤፈርት ታርጋ ገንዘብ ሲያልቡ ኖረው አሁን ወደ እስር ቤት ተወርውረዋል። የቴሌ የሙስና ቅሌትና በኦሮሚያ የመሬት ንግድ አብረዋቸው ሲሳተፉ የነበሩ ሁሉ ዋራንቲ ተቆርጦባቸው እስር ቤት ገብተዋል። እንግዲህ በዚህ ሁሉ መዓት ውስጥ ያልተነኩት ወ/ሮ አዜብ ብቻ ናቸው።
 
ለፌደራል የጸረ ሙስና ኮሚሽን ቅርብ የሆኑ ምንጮች እንደሚሉት ተጠርጣሪዎቹ በምርመራ ወቅት ወ/ሮ አዜብን በትዕዛዝ ሰጪነትና በንግድ አጋርነት ዋና ተባባሪ መሆናቸውን በማመልከት መስክረዋል። ከዚህም በላይ በርካታ ጥቆማ አለ። በነዚህና በበርካታ ምክንያቶች ጣት የተቀሰረባቸው ወ/ሮ አዜብ አሁን የቀብርና የተስካር፣ ሙት ዓመት ዘካሪና የማስታወሻ ግንባታ ኮሚቴ ሃላፊ ሆነው ተቀምጠዋል። የመጀመሪያው መጨረሻ “መገለል” እንደሆነ፣ ከዚያም እውነተኛው መጨረሻ ሊገጥማቸው እንደሚችል ግምታቸውን የሚሰጡ ተበራክተዋል። “ከቶውንም አይታሰሩም። ለመለስ ሲባል “የሚሉት ደግሞ መጨረሻቸው ከኢህአዴግና አሁን ካለው የቡድን ፍትጊያ ጋር እንደሚሆን ይናገራሉ።
 

በሰማያዊ ፓርቲ አባላት በደረሰው ወያኔያዊ ጥቃት ተቆጭተናል!!! ወጣቶች መንገዳችሁን እንድትመርምሩ እንመክራለን!!!



       
ነሐሴ 25 ና 26 ቀን 2005 ዓ. ም. ወያኔ በአብዛኛው በወጣቶች በተገነባው ሰማያዊ ፓርቲ መሪዎች እና አባላት ላይ ያደረሰው ወንበዴያዊ የመብት ጥሰት አሳዝኖናል፤ አስቆጭቶናልም። ይህንን ጥቃት አጥብቀን እንቃወማለን። ከወራት በፊት በይፋ አስታውቀውና ደጋፊዎቻቸውን በይፋ ጠርተው ለሰላማዊ ተቃውሞ በዝግጅት ላይ የነበሩ ወጣቶችን በቅልብ ኮማንዶዎች ማስደብደብ ተራ የመንደር ወንበዴ እንኳን የማይፈጽመው ወራዳ ተግባር ነው፤ ወያኔ ግን አድርጎታል።

የመፈክር መፃፊያ ቡርሾችና ማርከሮች ካልሆነ በስተቀር ራሳቸውን መከላከያ ዱላ እንኳን ያልያዙ ወጣቶችን በጠመንጃዎች ሰደፍ፣ በጁዶና በካራቴ ተደብድበዋል። ልጃገረዶች
ጤንነታቸውን ብቻ ሳይሆን ክብራቸውን በሚነካ መንገድ እተሰደቡና እየተደበደቡ ጭቃ ውስጥ እንዲከባለሉ ተደርገዋል። ጋጠወጦቹ የወያኔ ቅልብ ወታደሮች ከወያኔ ሹማምንት ለሰማያዊ ፓርቲ አባላት የተላከውን መልዕክት በቃልም በተግባርም አድርሰዋል።

የመልዕክቱ ይዘት ባጭሩ የሚከተለው ነው።

ሞተን አጥንታችንን ከስክሰን ያገኘነው ሥልጣን ትንፋሻችን እያለ ከእጃችን አይወጣም። እንኳንስ በሰላማዊ ትግል የመንግሥት ሥልጣንን ልትይዙ ቀርቶ፤ እኛ ሳንፈቅድላችሁ እደጅም አትወጡም። እንገዛችኋለን!!! እንረግጣችኋለን!!! ሕግ አያግደንም። እኛ ራሳችን ሕግ ነን። ምን ታመጣላችሁ? ምን አቅም አላችሁ?
 
ይህ መልዕክት ለሰማያዊ ፓርቲ መሪዎችና አባላት በዱላና እርግጫ ታጅቦ ቃል በቃል ተነግሯቸዋል።

ወጣቶች ምን ትላላችሁ? ጥንካሬያችሁን እናደንቃለን፤ ሆኖም የያዛችሁት መንገድ የባላንጣችንን ባህሪይ እግምት ውስጥ ያስገባ ስለመሆኑ ጥርጣሬ አለን። ዛሬ ጥያቄው ከመቼውም በላይ አፍጦ መጥቷል። ባርነትን ትቀበላላችሁ ወይስ አማራጭ የትግል ስልቶችን ለመመርመር ትደፍራላችሁ? ባዶ እጆቻችሁን እያሳያችሁት እየረገጠና እያዋረደ “መንግሥት” ነኝ ብሎ የሚኮፈስ እኩይ ጋጠወጥ ጋር ሰላማዊ ትግል ያዋጣል ትላላችሁ? ፍርዱን ለእናነተ እንተዋለን።

ወያኔ ለሰማያዊ ፓርቲ አባላት የላከው መልክት ለፓርቲው አባላት ብቻ የተላከ አይደለም። መልዕክቱ ለኢትዮጵያዊያን በሙሉ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! ምላሽህ ምንድነው? እስከ መቼ የወያኔን እብሪት እንታገሳለን? ያለን ምርጫ ሰላማዊ ትግል ብቻ ነው ሲል የደነገገልን ማነው?

ግንቦት 7፤ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ሁለገብ የትግል ስልትን ሲመርጥ የሰላማዊ ትግል አስፈላጊነት በማመን ሆኖም ግን ብቻውን የትም እንደማያደርሰን በመገንዘብ ነው። ስለዚህም ሁለቱም የትግል ስልቶች ተደጋግፈው መሄድ አለባቸው ይላል። ግንቦት 7 ይህንን የትግል ስልት የቀየሰው በወያኔ ባህሪ ላይ ተመሥርቶ ነው። የወያኔ ዓይነቱ እብሪተኛ ሥልጣን በያዘበት አገር ሰላማዊ ትግል ከአመጽ ትግል በላይ ዋጋ የሚያስከፍል ሊሆን ይችላል። ከዚህም በላይ ከፍተኛ ዋጋ አስከፍሎም ቢሆን ሰላማዊ ትግል ብቻውን ድል ማቀዳጀት የሚችል ስለመሆኑ ማረጋገጫ የለም። ሰላማዊ ትግልና የአመጽ ትግል ውሃና ዘይት ወይም እሳትና ጭድ አይደሉም። እንዲያውም በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ እና ወያኔ በሥልጣን ላይ እስካለ ድረስ አንዱ ያለሌላኛው ዋጋ የለውም።

ስለሆነም ከደረሰባችሁ ወንበዴያዊ ጥቃት ትምህርት በመውሰድ፤ ወደፊት ደግሞ ከዚህ የባሰ ሊመጣ እንደሚችል በመገንዘብ፤ ሁኔታዎችን መርምራችሁ በግል የስትራቴጂ ለውጥ ለማድረግ የወሰናችሁ ወጣቶች ግንቦት 7ን ማግኘት አይቸግራችሁም። ሆኖም ጊዜ የለም። በወያኔ ዓይን እና በወያኔ ፍርድ ቤት እይታ መብቱን የጠየቀ ሁሉ የግንቦት 7 አባል ነውና የምታጡት ነገር የለም። ዛሬውኑ ወስኑ!!!!

ግንቦት 7፤ በዚሁ እለት ክርስቲያኑንና ሙስሊሙን ኢትዮጵያዊያንን ለማቃቃር ወያኔ የጠራውን ሰልፍ ጥበብ በተሞላበት ስልት ላከሸፈው “የድምፃችን ይሰማ” አመራርና አባላት ያለውን አድናቆት በዚህ አጋጣሚ ይገልፃል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

BBC – Ethiopia denies crackdown on Semayawi party

September 2, 2013
BBC – Some 100 members of Ethiopia’s opposition Semayawi (Blue) party were arrested and some badly beaten over the weekend, the party says.
Party chairman Yilekal Getachew said equipment such as sound systems were confiscated ahead of a rally on Sunday which was banned.
Some 1,500 people attended the pro-government rally against extremism
Some 1,500 people attended the pro-government rally against extremism
Communication Minister Shimeles Kemal denied there had been a crackdown.
The government said the venue had already been booked by a pro-government group condemning religious extremism.
The governing EPRDF maintains strict control over public life in Ethiopia.
The public protest Semayawi organised in June was the first major demonstration on the streets of Addis Ababa since 2005 when hundreds of protesters were killed in violence.
It was called to demand the release of jailed journalists and activists.
The rally planned for Sunday was to call for political reforms.
Mr Shimeles said that any group which wanted to organise a public protest had to seek a permit.
He said the authorities could not refuse to grant a permit but could insist that the event be held at a different time or place to that requested.
Hailemariam Desalegn took office as prime minister a year ago, following the death of long-time leader Meles Zenawi.
Ethiopia is a US ally against Islamist militants in the region.
ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
Blue 1


ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም. ባካሄደው ታላቅ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለመንግሥት ያቀረባቸው ጥያቄዎች አስፈላጊው ምላሽ እንዲሰጣቸው በመጠየቅ ይህ ካልሆነ ግን ከሦስት ወር በኋላ ተቃዉሞውን ከፍ ባለ ደረጃ እንደሚያቀርብ በመጋለፅ ሰልፉን አጠናቋል፡፡ ለተነሱት ጥያቄዎች የተገኘ ምላሽ ባለመኖሩ ፓርቲው ለሕዝብ በገባዉ ቃል መሠረት ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም. ታላቅ የተቃዉም ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሔድ በመወሰን በሕግም ሆነ በሥራ የሚያስፈልጉ ነገሮችን በማጠናቀቅ እለቱን በመጠበቅ ላይ እያለ ምንም አይነት መለዮ ባልለበሱ ግለሰቦች የሚመራ የፖሊስ መለዮ ለባሽ ታጣቂዎች ከሕግ ውጭ ነሐሴ 25 ቀን 2005 ዓ.ም. ከምሽቱ 12 ሰዓት አካባቢ የፓርቲውን ቢሮ ጥሰው በመግባት ፓርቲው ይጠቀምባቸው የነበሩ የቅስቀሳ ቁሳቁሶችና ሌሎች የፓርቲውን ንብረቶች ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወርሰዋል፡፡ በፓርቲው ፅ/ቤት የነበሩ አባላትን እና መሪዎችን በጠመንጃ በማስገደድ ወደተለያዩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያዎች ከፋፍሎ በመውሰድ አስረዋል፣ ዘልፈዋል፣ አስፈራርተዋል እንዲሁም አረመኔያዊ በሆነ መንገድ ደብድበዋል፡፡
አንዳንዶችን በጭቃ ላይ ጭምር አንከባለዋል፡፡ ይህ ሁሉ ሕገ ወጥና አረመኔያዊ ድርጊት ሕገ መንግስታዊ የሆነውን መብታቸውን በሚጠቀሙ ዜጎች ላይ ሲፈፀምና በሕግ ማስከበር ስም በቁጥጥር ሥር በዋሉ ዜጎች ላይ የግል ጥላቻን መወጣጫ እስኪመስል ድረስ ማንኛዉንም የማንአለብኝነት ድርጊት ሲፈፅሙ ማየት ያልታጠቁ ዜጎችን አቅመ ቢስነትና የሕግ ከለላ ማጣትን ገሃድ አድርጎታል፡፡ ይሕ አይነቱ የጡንቻ ሥራ በአንድ በኩል ልብን በሐዘን የሚሰብር ድርጊት ሲሆን በሌላ በኩል ለነፃነትና ለፍትህ የሚደረገው ትግል እጅግ ትክክለኛና ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ሰማያዊ ፓርቲ የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ሕጋዊ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ሁሉ አድርጓል፡፡ የአስፈፃሚው አካላት በሕግ ከተሰጣቸው ስልጣንና ተግባር በመውጣት የፈለጉትን ለማድረግ መብት እንደሌላቸው ማሳዬት ፓርቲያችን ከተመሰረተባቸው አብይ መርሆች አንዱ በመሆኑ፤
1ኛ. በአዲስ አበባ ከተማ ከቤት ውጭ የሚደረጉ ስብሰባንና ሰላማዊ ሰልፍን አስመልክቶ ጥያቄዎችን ተቀብሎ በሕግ በተወሰነው መሰረት አስፈላጊውን ሁሉ ማከናወን የሚገባው በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የሕዝባዊ ስብሰባና የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ኃላፊነቱን ባለመወጣቱ በፓርቲው ላይ ለደረሰው የአካል፣ የንብረትና የሞራል ጉዳት ምክንያት በመሆኑ በሕግ እንጠይቃለን፤
2ኛ. የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የፓርቲ መሪዎችን በማስፈራራት ከሰልፍ ለማስቀረት የሚያደርገው ድርጊት ከህግ ውጭ በመሆኑና በፖሊስ መለዮ ለባሾች ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የፓርቲውን ቢሮ በመውረር ለፈፀሙት የንብረት ዘረፋና ውድመት እንዲሁም ፓርቲው ባቀደውና በተዘጋጀበት ጊዜ የተቃውሞ ሰልፉን እንዳያካሂድ በማደናቀፉ በሕግ እንጠይቃለን፤
3ኛ. በሐገራችን ፓርቲዎችን እንዲያስተዳድርና እንዲከታተል ስልጣን የተሰጠው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና ሰጥቷቸው በሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ላይ እንዲህ አይነት ሕገ ወጥ ድርጊት እየተፈፀመባቸው መሆኑን እንዲያውቀው እናደርጋለን፤
4ኛ. የፖለቲካ ትግላችንን በመቀጠል ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብታችንን የትኛውም የአስፈፃሚ አካል የመከልከል መብት ስለሌለው የተቃውሞ ሰልፈችንን ቅዳሜ ጳጉሜ 2 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እንደምናከናውን ለአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የሕዝባዊ ስብሰባና የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል በዛሬው ዕለት አሳውቀናል፡፡
በመሆኑም ከዚህ ቀደም ለመንግስት ያቀረብናቸው ጥያቄዎች እንደተጠበቁ ሆነው በተደጋጋሚ እንዳስተዋልነው በዚህች ታሪካዊት ሐገር የሕግ የበላይነት ግብዓተ መሬት ከመፈፀሙ በፊት እንድንደርስላት ለዘመቻ የሕግ የበላይነት ትግላችን የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማሕበራትና ዜጎች በአጠቃላይ ከጎናችን እንዲሰለፉ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
Blue 2በመንግስታዊ ውንብድና ትግላችን አይገታም!!!!
ነሐሴ 27 ቀን 2005 ዓ.ም.
አዲስ አበባ

A Blocker of Internet as a Clean Reformist?

September 2, 2013
Tedla Asfaw
Dear Ethiomedia Editor,
After the brutal beating of Semayawi Party members and supporters this past Saturday reading about Woyane “Reformist” in your editorial note today http://www.ethiomedia.com/2013report/4660.html
is a big insult to many Ethiopians. It seems to me a preemptive action not to condemn Woyane because there are “reformists” like Debretsion, the enemy of free speech known for blocking Internet in Ethiopia.Debretsion Gebremichael is the current minister of communication and information technology
Debretsion and even those who are telling us they opposed Woyane the likes of Seye, Asgede etc still believe that Woyane should be “reformed” with the help of the reformists not be replaced by an elected representative of the Ethiopian people.
Talk of “split” within TPLF and statement the one you made today are used by the regime as distraction from the popular upheaval brewing under. Debretsion and all his buddies are worried about their power and stolen wealth.
I still remember Seye a year ago on BBC after the death of Meles saying that “They need to keep the development made on the last two decades”. Whose development ? Weyane connected within and out posing themselves as “opponents of Woyane” do not want popular change at all.
Debretsion a “clean” man you suggested has benefited from EFFORT so does Seye Abraha. That is why they want to keep this loot for future bargaining.
There are no so called reformists within or out of TPLF. Once you are Woyane you will live 

Sunday, September 1, 2013

Semayawi attacked, beaten up and ransacked

sunday, September 1, 2013 @ 03:09 AM ed

(AV) In the evening of Saturday August 31, Semayawi Party headquarters around Ginfle, Addis Ababa, was buzzing like a bee hive as nearly one hundred party activists and organizers were busy making posters, writing slogans, stacking flags and other paraphernalia needed for a colorful rally. They were making the final push for a peaceful demonstration they had planned to hold the next morning with their supporters.
These peaceful and law-abiding citizens were doing what true political activists were supposed to do. They wanted to demand justice and freedom. They wanted to petition their rulers to respects the rights of citizens who are being routinely abused, tortured and killed in broad daylight. They only wanted to ask the thuggish TPLF regime to free all prisoners of conscience jailed on trumped-up terrorism and treason charges. They wanted to demand the TPLF to respect its own constitution. They were not preparing to commit acts of terrorism or bank robbery.
Suddenly there was a blackout. Electricity to Semayawi’s headquarters was cut off. Apparently hundreds of heavily armed ‘federal police’ officers had already besieged the office like terrorists.
Yidenekachew Kebede, the party’s legal affairs head and coordinator of the rally was heading to his office. ESAT reached him in good time on his cell phone. He was describing the situation in detail. He was very upset that such a criminality happens with impunity. He was outraged that the TPLF is treating Ethiopians worse than prisoners of war in their own country.
The young lawyer was outraged that the constitution, which the TPLF never respected, was being violated by armed thugs and criminals again. It was another evidence of lawlessness and tyranny that the TPLF has imposed on the people of Ethiopia. Those who were eager to demand freedom and justice for their people became victims of criminality. While he was telling ESAT that his colleagues and friends were under siege, a federal police officer snatched his phone and the line was cut off. Apparently he was detained.
TPLF federal squad broke into the office and ransacked and beat Semayawi’s leaders and members. The party’s chairman Eng. Yilkal Getnet was also arrested and taken to a police station around Gedam Sefer. The thugs reportedly targeted everyone and even savagely attacked and kicked women. They detained all of Semayawi’s operatives found on the party’s premises for hours, kicked and tortured them. Scores of people were even made to roll over mud and dung in a bid to humiliate and degrade them. They were stat at and insulted by TPLF’s thugs.
According to Eng. Yilkal, he was released after a few hours. Other members who were also said to have been roughed up, beaten up and tortured were also freed. But the headquarters has reportedly been trashed. Documents, equipment, and all the materials prepared for the rally were taken away by the federal squad.
Ethiopians in the Diaspora has been expressing outrage on Facebook and Paltalk rooms. What has been the focus of angry discussion is how long the state-sponsored terrorism can go on. The decision to launch an illegal attack against a political party operating legally is another affront to law and order. TPLF’s thuggery and lawlessness has posed serious challenges to every law-abiding citizen. People are abused and tortured without any ground.
Semayawi is a relatively budding political party that should have been accorded protection. But TPLF’s paranoid has reached a critical and dangerous point. The more cornered it is, the more dangerous it is becoming. The attack against Semawi only reveals the level of fear gripping the TPLF and its cronies.
In a press release it issued, Semayawi has vowed to press for justice and rule of law. It emphasized that nothing will distract it from making demands and voicing the concerns of the people of Ethiopia.
In the meantime, Muslim Ethiopians are also being hunted down across the country. TPLF organized a rally in the metropolis on the day and at the venue where Semayawi had planned to stage a protest demonstration. The worst part is that TPLF is trying to create religious conflict among Christians and Muslims. The two religions have co-existed harmoniously for over a millennium. The futile efforts only reveal the fact that TPLF is desperate to survive.No matter what the TPLF does, the struggle for equality, dignity, justice and freedom continues….















Jailed: top TPLF warlord Woldesilassie’s kingdom of death and deceit crumbles

September 1, 2013
by Getahune Bekele-South Africa
The Horn Times Newsletter
A face tinged with cruelty, wealthy warlord Woldesilssie W.Micael
A face tinged with cruelty, wealthy warlord Woldesilssie W.Micael
He was the dead tyrant Meles Zenawi’s alter ego and docile horse for 21 years and the most feared man in the complex TPLF security cluster. He amassed millions through corrupt practices and managed to build his own kingdom in partnership with equally corrupt former first lady Azeb Mesfin and her daughter Semhal Meles, the two queens of his vast empire.
The malevolent warlord was well protected by the Zenawi family for 21 years and well placed in the inner circle of the ruling elite where lack of maturity among the junta often led to political upheavals, quarrelling, divisions, and susceptibility to large-scale thieving.
However, exactly one year after Zenawi’s death, a TPLF splinter group led by the ‘retired’ old codger Sebehat Nega, convinced chief spy Getachew Assefa to capture the vulnerable Woldselassie Woldemicael and throw him into the dark cells of central intelligence prison in Addis Ababa.
He was caught while enjoying the transcendental beauty of one of his flower farms outside Addis Ababa, near Holeta Genet town.
The most violent man who allegedly killed Zenawi’s ideological rival, former minister of communications Ato Ayenew in front of his wife and children and gained more notoriety when he pulled out a machete and barbarically chopped off the head of former palace security boss Tegadalay Zerhu, is now awaiting his fate after being arrested on corruption charges last week.
“Today I reaped a great harvest for the great leader.” The condemned warlord nicknamed by the ruling Tigre coterie “the red Khmer Rouge” reportedly told his commander whose name is known to the Horn Times after the gruesome killing of tegadaly Zerhu.
According to our sources inside the TPLF hierarchy, tegadaly Zerhu sympathizers who were longing for justice since Zenawi’s death are currently preparing to bring additional charges of murder against the jailed super-rich warlord.
“His fatal strategic error was that he remained loyal to Zenawi’s wife even after the tyrant’s death while others quickly switched side and joined the powerful Sibehat Nega clique. The ill-educated Woldesilassie played the loyalty game badly and ended up in jail. I doubt if he ever walks out of that prison alive. The desire to enjoy his corruptly accumulated wealth undisturbed has been lost because of his own terrible miscalculation of circumstances.” A political analyst based in Addis Ababa told the Horn Times.
“No one in the rival camp is safe or able to remain unruffled in the face of such onslaught disguised as anti-corruption drive. Tigray republic president Abbay Woldu, adviser to the Prime Minister Berket Simeon and, more important, mother of corruption Azeb Mesfin are deeply disturbed by the arrest of Woldesilassie whom they regard as their son. The cornered widow of the late ruler even let loose a torrent of swear-words directed at spy boss Getachew Assefa, but mark my words, she is next.” The analyst added.
Moreover, according to other credible reports obtained by the Horn Times, since her removal as CEO of EFFORT few days ago, Azeb Mesfin has been barred from leaving the country until the ongoing investigations into misappropriation of funds; tax evasion, money laundering, and alleged corruption are completed.

የደህንነት ኃይሎች ጋዜጠኞችን ማዋከብና ማስፈራራት አጠናክረው ቀጥለዋል

September 1, 2013

ከበትረ ያዕቆብ
ለረጅም ጊዜ የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ አዘጋጅ ሆኖ ያገለገለዉና የጋዜጣዉ ህትመት ከተቋረጠበት ጊዜ ጀምሮ የኢቦኒ መፅሔት ዋና አዘጋጅ ሆኖ በመስራት ላይ የሚገኘዉ ጋዜጠኛና ብሎገር ብስራት ወልደ ሚካኤል ሰሞኑን በ4 የደህንነት ኃይሎች ታግቶ ዛቻ እና ማስፈራሪያ እንደተፈፀመበት ተናገረ ፡፡ ድርጊቱ የተፈፀመዉ ባሳለፍነዉ ሰኞ (ነሐሴ 20 – 2005ዓ.ም) ከምሽቱ 2፡35 ላይ ከስራ ወደ ቤቱ በጉዞ ላይ እያለ ነበር፡፡
ብስራት ወልደ ሚካኤል እንደገለፀዉ ግለሰቦቹ ለ50 ደቂቃ ያህል ያገቱት ሲሆን ፤ ከአሁን በኋላ በየትኛውም ጋዜጣ ፣ መፅሔትም እንዲሆም ብሎግ ላይ ብትፅፍ በህይወትህ ላይ ፈርደህ ነዉ ሲሉ ዝተዉበታል፡፡ በመጨረሻም በጥፊ መተዉታል፡፡ ብስራት እንደገለፀዉ ከሰዎቹ መካከል አንዱ ሽጉጡን እየደጋገመ በማሳየት ሊያስፈራራዉ ሙከራ ያደረገ ሲሆን ፤ ሌላኛዉ ደግሞ እንዳይንቀሳቀስ ሴንጢ በሆዱ ላይ ደግኖበት ነበር፡፡ ጋዜጠኛ ብስራት አያይዞም “አቶ መለስ ዜናዊ አለዉ ከተባለዉ 3 ቢሊዮን ዶላር እና ልጁ ከታማችበት 5 ቢሊዮን ዶላር እንዲሁም የፀረ ሽብርተኝነት ህጉን በሚመለከት የፃፋኳቸዉ ፅሑፎች እንዳናደዷቸውና እንዳበሳጯቸው በንግግራቸው ይጠቃቅሱልኝ ነበር” ሲል ተናግሯል፡፡
“ይህን የጋዜጠኝነት ሙያየ ወድጄና ፈልጌ በመማር የገባሁበት እንጂ ተገድጄና ተመድቤበት የምሰራው አይደለም ፤ ከዚህም ሙያ ልወጣ አልችልም ” የሚል ምላሽ ሰጠኋቸዉ ሲል የተናገረዉ ጋዜጠኛ ብስራት ፤ አያይዞም ፀያፍ ስድብ እንደሰደቡትና ከወላጅ አባቱ ጋር በተያያዘ የተናገሩት አሳዛኝ ነገር እንደነበረ ጠቁሟል፡፡ አያይዞም “ከግለሰቦቹ መካከል አንዱን ልደታ ፍርድ ቤት በተለይም በሽብርተኝነት የተከሰሱትን የእነ አንዱዓለምንና እስክንድርን ጉዳይ ልዘግብ ስሄድ ሁሌም እዚያ የማላጣው ሰዉ ነበር” ብሏል፡፡
“ይህንን ሁሉ ወዲያው ሳሪስ ለሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ሄጄ ያሳወቅሁ ሲሆን ፤ ያኔ ተረኛ መርማሪ ፖሊስ የነበረው ኮንስታብል ጥላሁን ታዴ የተባለ ሰዉ ያንተ ጉዳይ ከበድ ስለሚል የጣቢያው ዋና ኢንስፔክተር አበበ አያሌው ሲመጣ ጠዋት ንገረው አለኝ፡፡ በሰዓቱ የሚተባበረኝ ፖሊስ ቢኖር ግን የገቡበትን አቅጣጫ ስላየሁ አጋቾቹን እናገኛቸው ነበር ፤ ግን በሰዓቱ ለሚቀጥለዉ ቀን ከመቅጠር በቀር የተባበረኝ አልነበረም፡፡” በማለት ጋዜጠኛ ብስራት ተናግሯል፡፡ አያይዞም “በነጋታው ማክሰኞ ጠዋት ነሐሴ 21 ቀን ዋና ኢንስፔክተር አበበን ለማናገር ወደ ጣቢያው ብሄድም አሁን የሉም ፣ ለስብሰባ ወጥተዋል ተብዬ ከሰዓት እንድመለስ ተነገረኝ፡፡ ከሰዓትም ስሄድ ተመሳሳይ መልስ ከተሰጠኝ በኋላ ለረቡዕ ነሐሴ 22 ቀን ጣዋት እንድሄድ ተነገረኝ፡፡” ሲል የገጠመዉን ዉጣ ዉረድ አስረድቷል፡፡
እንደሚታወቀዉ ሰሞኑን እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት አምባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት በጋዜጠኞች ላይ መጠነ ሰፊ ዛቻና ማስፈራሪያ እየፈፀመ ይገኛል፡፡