Monday, August 26, 2013

Corruption in the Ethiopian JUST US Sector

by Alemayehu G. Mariam

For the past several months, I have been commenting on the findings of the World Bank’s “Diagnosing Corruption in Ethiopia”, a 448-page report covering eight sectors (health, education, rural water supply, justice, construction, land, telecommunications and mining). In this my sixth commentary, I focus on “corruption in the justice sector”. The other five commentaries are available at my blog site.

A glossy “diagnosis” of corruption in the Ethiopian justice sectorTalking about corruption in the Ethiopian “justice sector” is like talking about truth in Orwell’s 1984 Ministry of Truth (“Minitrue”).  The purpose of Minitrue is to create and maintain the illusion that the Party is absolute, all knowing, all-powerful and infallible. The purpose of the Ministry of Justice in Ethiopia is to create the illusion that the ruling regime under the command and control of the Tigrean People’s Liberation Front (TPLF) masquerading as the Ethiopian People’s Democratic Front (EPDRF) is absolute, all knowing, all-powerful and infallible.

I have long caricatured the “justice sector” of the TPLF/EPDRF as a kangaroo justice system founded on a sham, corrupt and whimsical legal process. What passes off as a “justice system” in Ethiopia is little more than a marketplace where “justice” is bought and sold in a monopoly controlled by one man supported by a few nameless, faceless and clueless men who skulk in the shadows of power. It is a justice system in which universal principles of law and justice are disregarded, subverted, perverted and mocked. It is a system where the poor, the marginalized, the audacious journalists, dissidents, opposition and civic society leaders are legally lynched despite the criticism and bootless cries of the international community. It is a system in which regime leaders, their families, friends and cronies are above the law and spell justice “JUST US”.

My first critique of the TPLF/EPDRF “justice system” appeared in 2006 when I wrote a 32-page analysis titled, “Keystone Cops, Prosecutors and Judges in a Police State.” It was written in the first year of what has become my long day’s journey into the dark night of advocacy against human rights violations in Ethiopia and Africa. The piece was intended to be a critical analysis of the trial of the so-called Kality defendants consisting of some 130 or so major opposition leaders, human rights advocates, civic society activists, journalists and others in the aftermath of the 2005 election. I tried to demonstrate that the show trial of those defendants was little more than a third-rate theatrical production staged to dupe the international community. I also tried to show how a dysfunctional and bankrupt judicial system was used to destroy political opposition and dissent. I described the “judicial proceedings” of the Kality defendants as “an elaborate hoax, a make-believe tribunal complete with hand-picked judges, trumped up charges, witless prosecutors, no procedures and predetermined outcomes set up to produce only one thing: a  monumental miscarriage of justice.”

A glossy “diagnosis” of corruption in the Ethiopian justice sector

The WB’s “diagnosis” of corruption in “Ethiopia’s justice sector” is based on “interviews of 60 individuals” including “federal judges and prosecutors”, police, private attorneys, etc. in the capital and at another location. No ordinary citizens were included in the interview panel or the smaller focus groups. The study is intended to “explore the incidence of corruption in Ethiopia’s justice sector (including not only the courts but also several other organizations).” The “justice sector” includes, among others, “courts, police, prosecutors, administrative agencies with quasi-judicial powers, and public and private attorneys, prisons, and those in the executive and legislative branches responsible for enacting the laws and regulations governing their operations”.

The report begins with unusual disclaimers and apologia. The author proclaims that “this report begins from an agnostic standpoint—attempting only to document reality in Ethiopia’s justice sector and to compare it… with the situation elsewhere in African and other countries…” It is not clear what she means by “an agnostic standpoint”, but her analysis is frontloaded with servilely apologetic language manifestly intended not to offend or appear to point an accusatory finger at the ruling regime in Ethiopia. The report appears to have been written with some trepidation; perhaps the author was afraid of a backlash (tongue-lash) from the regime. The author timorously tiptoes around well-established and notorious facts about corruption in the regime’s justice sector. In light of the many disclaimers, reservations and contingencies in the report, it is obvious that the author does not want to call a spade a spade, so she calls the spade a bucket. But corruption by any disclaimer is still corruption; and Ethiopia’s justice sectors reeks of corruption.

The author claims an examination of  “corruption in the justice sector is important because it undermines the peaceful resolution of conflicts, the control of corruption in other sectors, the strengthening of the normative framework underlying private and public actions (the rule of law), and the creation of a predictable environment for public and private transactions.” According to the study,

 corruption in the Ethiopian justice sector “takes one of two forms: (a) political interference with the independent actions of courts or other sector agencies, or (b) payment or solicitation of bribes or other considerations to alter a decision or action.” The study claims the “most common form of corruption involves bribes solicited by or offered to police to ignore a criminal offense, not make an arrest, or not bring witnesses or suspects to court (which can cause a provisional adjournment of the case). Traffic police are the worst offenders.” Another “common form of corruption” involves “payment of court staff to misplace case files or evidence” (a practice that has nearly disappeared because of new judicial policies on archive management introduced under a Canadian International Development Agency program”.

The author provides a catalogue of corrupt practices which she claims are disputed by various respondents in her study but include “(a) sales of judgments or other judicial actions in civil disputes; (b) lawyers’ solicitation of “bribes” that never reached the bench; (c) prosecutors’ misuse of their own powers, in response to bribes or political directives, to advance or paralyze a case; and (d) the corrupt actions of various officials entrusted with enforcement of judgments, especially in civil cases.” She attributes the divergence in viewpoints to a “likely gap between perceptions and reality [which] are partly a function of the persistent lack of transparency in personnel policies.”

What is remarkable about the WB “justice sector” study is the fact that the author, by focusing on the “most common form of corruption” (i.e. petty police, particularly traffic police, corruption), fails to critically probe grand corruption involving party officials and regime leaders and their cronies who routinely subvert the justice system through political interference and pressure to protect their political and economic interests. She circumvents serious inquiry into grand corruption in the “justice sector” by providing catalogues of “potential forms of criminal and civil corruption” and “corruption risks”. She appears averse to investigating high-level corruption that occurs in the process of judicial appointment of handpicked party loyalists and hacks, laws written to aid certain elites in society, or in the debasement and corruption of the integrity and independence of the judiciary. She ignores the type of justice corruption that occurs in “state capture” where economic elites develop cozy relationships with political and judicial officials through whom they obtain favorable judicial decisions to advance their own advantage. For instance, on the issue of political interference in the judicial process, the author demonstrates her “agnosticism” by reporting that “the one who came closest eventually admitted that ‘there was some [political interference], but it was very rare.’” Other responses ranged from ‘a moderate amount’ (limited to the bad apples) to the extreme of holding that ‘every civil judgment is sold.’”

Curiously, the author points an accusatory finger at petty corruption as the “most common form of corruption” distracting attention from the systemic and structural corruption in the justice sector. The importance of petty corruption must not be understated because of the serious impact it has on the lives and livelihoods of ordinary citizens interacting with police, prosecutorial and other petty judicial officials. There is ample anecdotal evidence of petty corruption in which ordinary Ethiopian citizens and businesspersons are “shaken down” by traffic cops or minor functionaries in the judicial or state bureaucracy seeking small bribes. However, though petty corruption may be easier to detect, the real focus should be on grand corruption which is systemic, structural and difficult to detect and nearly impossible to punish. Structural and systemic corruption in the legal institutions, rules, and norms and those who are practitioners in the system create, maintain and sustain a culture of corruption in the justice sector, which the author appears to overlook.

Justice corruption is primarily a systemic failure of judicial institutions, lack of political will and capacity to manage judicial resources, maintain integrity of institutions. The author makes abstract references to the usual catalogue of corruption variables but does not seek to gather data to illuminate the scope, breadth and gravity of the problem of political interference and lack of accountability in the justice system. Grand corruption in the justice sector stems from the fact that political officials have wide authority over judicial officials (from appointment to management of judicial functions); and political officials have little accountability and incentive to maintain the integrity of the justice sector. There are few functional formal systems of control in the relationship between the judicial and political processes in Ethiopia. If there ever were control systems, they have been broken for a long time making it nearly impossible to administer fairly the laws while maintaining accountability in the form of a robust reporting system and transparency in the form of robust management practices. Such institutional decay has promoted the growth of a culture of corruption in the justice sector and continues to undermine not only the broad adjudicatory role of justice sector institutions but also public confidence in the integrity of the justice system itself.

Justice sector in a police state?

Justice in a dictatorship is to justice as military music is to music. No reasonable person would consider martial law (military rule) to produce justice.  By definition dictatorship — a form of government in which absolute power is concentrated in the hands of a dictator or a small clique — is the quintessential definition of injustice. Any form of government that operates in flagrant disregard of the rule of law is inherently corrupt.

I have on previous occasions tried to expose such corruption in Ethiopia’s “justice sector” with anecdotal evidence of arbitrary administration of justice or denial of fair trial to those accused of  “terrorism”, “treason” and even “corruption”, opposition leaders, human rights advocates, journalists, etc. In the kinder and gentler police state that Ethiopia has become, any petty “law enforcement” official of the regime has the power to arrest and jail an innocent citizen. As I argued in my February 2012 commentary, “The Prototype African Police State”, a local police chief in Addis Ababa felt so arrogantly secure in his arbitrary powers that he threatened to arrest a Voice of America reporter stationed in Washington, D.C. simply because that reporter asked him for his full name during a telephone interview.  “I don’t care if you live in Washington or in Heaven. I don’t give a damn! But I will arrest you and take you. You should know that!!”, barked the impudent police chief Zemedkun. If a flaky policeman can exercise such absolute power, is it unreasonable to imagine those at the apex of power have the power to do anything they want with impunity. The regime in Ethiopia is the petri dish of corruption and living proof  that power corrupts and an absolute power corrupts absolutely.

In my view, denial of due process (fair trial) is the highest form of corruption imaginable in the “justice sector” because it results in the arbitrary deprivation of a person’s life, liberty and property. Could anyone (other than those politically connected) really expect to get a fair trial in the regime’s kangaroo courts or fair treatment in the pre-trial process?

The systemic corruption in the “justice sector” is that the law of the land is ignored, disregarded and perverted at the whim and fancy of those in power. For instance, the presumption of innocence (Eth. Const. Art. 20(3)) is openly flouted. The late leader of the regime used to routinely and publicly talk about the guilt of opposition leaders, journalists and others standing trial without so much of an awareness of the suspects’ right to a presumption of innocence or appreciation of the risk of prejudicial pretrial publicity emanating from such inflammatory statements which are prohibited under the Constitution and other international human rights regimes (e.g. Article 11 of the Universal Declaration of Human Rights, Article 14(2) of the International Covenant on Civil and Political Rights (ICCPR) and Article 7(b) of the  African Charter on Human and People’s Rights (ACHPR)). In 2011, the late leader of the regime proclaimed the guilt of freelance Swedish journalists Johan Persson and Martin Schibbye on charges of “terrorism” while they were being tried and he was visiting Norway. He emphatically declared the duo “are, at the very least, messenger boys of a terrorist organization. They are not journalists.” Persson and Schibbye were “convicted” and sentenced to long prison terms.

Show trials by publicity and demonization are another hallmark of the regime’s justice system. Following the 2005 election, the late leader of the regime publicly declared that “The CUD (Kinijit) opposition leaders are engaged in insurrection — that is an act of treason under Ethiopian law. They will be charged and they will appear in court.” They were charged, appeared in “court” and were convicted. In December 2008, the late leader railroaded Birtukan Midekssa, the first female political party leader in Ethiopian history, without so much as a hearing let alone a trial. He sent her straight from the street into solitary confinement and later declared: “There will never be an agreement with anybody to release Birtukan. Ever. Full stop. That’s a dead issue.” In making this statement, the late leader proclaimed to the world that he is the law and the ultimate source of justice in Ethiopia. His words trump the country’s Constitution!

In 2009, one of the top leaders of the regime labeled 40 defendants awaiting trial as “desperadoes” who planned to “assassinate high ranking government officials and destroying telecommunication services and electricity utilities and create conducive conditions for large scale chaos and havoc.” They were all “convicted” and given long prison sentences.

Violations of the constitutional rights of those accused of crimes by the regime are rampant. Article 20 (2) provides, “Any person in custody or a convicted prisoner shall have the right to communicate with and be visited by spouse(s), close relatives and friends, medical attendants, religious and legal counselors.” Internationally celebrated Ethiopian journalists including Reeyot Alemu, Woubshet Taye and many others were denied access to legal counsel for months. Ethiopian Muslim activists who demanded an end to religious interference were jailed on “terrorism” charges were also denied access to counsel.  They were mistreated and abused in pretrial detention. Scores of journalists, opposition members and activists arrested and prosecuted (persecuted) under the so-called anti-terrorism proclamation were also denied counsel and speedy trials and have languished in prison for long periods. Suspects are interrogated without the presence of counsel and coerced confessions extracted. Yet, Article 19 (5) provides, “Everyone shall have the right not to be forced to make any confessions or admissions of any evidence that may be brought against him during the trial.”

Article 19 (1) provides, “Anyone arrested on criminal charges shall have the right to be informed promptly and in detail… the nature and cause of the charge against him… Article 20 (2) provides, “Everyone charged with an offence shall be adequately informed in writing of the charges brought against him. Recently, the regime arrested members of its officialdom and their cronies on suspicion of corruption and kept the suspects in detention for months without informing them “promptly and in detail the charges against them”. Although the regime’s “top anti-corruption official” claimed that the corruption “suspects have been under surveillance for two years”, on their first court appearance, the prosecutors requested a 14-day continuance to gather more evidence! There is no judicial system in the world where suspects are arrested of committing crimes after being investigated for 2 years and then the prosecution asks for endless continuances to gather additional evidence.

Injustice impersonating justice

The 2012  U.S. State Department Human Rights report concluded, “The law provides for an independent judiciary. Although the civil courts operated with a large degree of independence, the criminal courts remained weak, overburdened, and subject to political influence.”  The WB could have done a much better job of “diagnosing corruption” in Ethiopia’s “justice sector”. Candidly speaking, any deficiency in the report should not reflect exclusively on the World Bank or its consultants but on Ethiopians, particularly the Ethiopian intelligentsia, who do not seem find it worth their time or effort to read, challenge and supplement such reports. It seems few, very few, Ethiopian scholars and analysts take the time and effort to locate, study and critically analyze such important studies done by international institutions and other private research institutions.

I doubt the WB justice sector study will be of much value to policy makers, scholars or the casual reader. Having said that, the burden is on Ethiopian scholars in Ethiopia and abroad to work collaboratively and carefully document corruption in Ethiopia’s justice and other sectors. No study of Ethiopia’s justice sector is worthy of the title if it does not rigorously evaluate the factors that are at the core of corruption in the “justice sector” – absence of the rule of law, lack of independence of the judiciary,  absence of due process, lack of impartiality and neutrality in the judicial process, the culture of corruption and impunity and the lack of accountability, transparency and confidence in the legal system. Such a study is the principal responsibility of Ethiopians, not the World Bank or its consultants. On the other hand, when the sword of justice is beaten into a sledgehammer of injustice, it is the supreme duty of ordinary citizens to expose it!

Sunday, August 25, 2013

ሰንደቅ አላማውን ያዋረደው ማን ነው?

August 25, 2013

ጌታቸው ሺፈራው
ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ ‹‹መንግስት በእምነታችን ጣልቃ እየገባ ነው!›› በሚል ከአንድ አመት በላይ እየተቃወሙ የቀጠሉት የእስልምና እምነት ተከታዮች ሀምሌ 19/2005 ዓ/ም ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ ኢህአዴግ ‹‹ሰልፈኞቹ የሰንደቅ አላማውን ክብር አዋርደዋል?›› የሚል ክስ ማቅረቡ ነው፡፡ እኔ በበኩሌ የተበጣጠሰውን ሰንደቅ አላማው የያዙት ሰልፈኞቹን የሚኮንን መንግስት ቅጥረኞችም ይሁን ሰልፈኞቹ ትክክል ነው ብዬ አላምንም፡፡ ምንም እንኳ ህግ የማስከበር ሀላፊነት የነበረበት ቢሆንም ኢህአዴግ ጉዳዩን ያነሳው በእርግጥም በሰንደቅ አላማ ክብር ስለሚያምን አይደለም፡፡ የዚህ ጽሁፍ አላማም ሀምሌ 19/2005 ዓ/ም የተፈጠረው ስህተትን ማስተባበል አሊያም መክሰስ ሳይሆን በተፈጠረው ክስተት ‹‹ሌሎችን›› የሚከሰው ኢህአዴግ ራሱ ሰንደቅ አላማውን እያዋረደ መቀጠሉን  የተለያዩ ክስተቶችንና የራሴን ገጠመኝ በመቃኘት ማሳየት ነው፡፡Ethiopian national flag
ሰንደቅ አላማ የአንድ አገር ዋነኛ ምልክት በመሆን ያገለግላል፡፡ ለቅኝ ግዛት እጇን ያልሰጠችው የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ደግሞ ከዚህም በላይ ክብር አግኝቷል፡፡ በተለይ በጸረ ቅኝ ግዛት ዘመን አፍሪካውያንና በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ጭቁን ጥቁሮች የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ የነጻነት አርማ አድርገው ተጠቅመውበታል፡፡ የአፍሪካ፣ የካሪቢያንና የደቡብ አሜሪካ አገራትም ይህን የነጻነት አርማ ቅርጽና አቀማመጡን ብቻ በመቀያየር ለአገራቸው መለያነት እየተጠቀሙበት ይገኛሉ፡፡ ከ6 ሚሊዮን በላይ ራስ ተፈሪያን ህዝቦችም የነጻዋን ኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ከአምላክ የተላከ አንዳች ምልክት አድርገው እስከ ማምለክ ደርሰዋል፡፡ ይህም የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በዓለም ለበርካታ አገራትና ኢትዮጵያዊ ባልሆኑ ህዝቦች መለያነት ያገለገለ ብቸኛውና ተወዳጅ ሰንደቅ ያደርገዋል፡፡
በሌላ በኩል ይህ ዓለም አቀፍ ክብር ያለው ሰንደቅ አላማ በተለያዩ ጊዜያት አገር ውስጥ ክብሩ ተዋርዶ ተስተውሏል፡፡ የመጀመሪያው ለሰንደቁ ክብር መሰረት በሆነው አድዋ በኢትዮጵያውያን የተሸነፉት ፋሽስቶች ኢትዮጵያን ዳግመኛ ሲወሩ የፈጸሙት ነው፡፡ ጣሊያን ለአምስት አመት ኢትዮጵያ ውስጥ በነበረችበት ወቅት የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ በሌሎች አፍሪካውያንና በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በሚገኙ ጥቁሮች ዘንድ በስፋት በመለያነት ላይ የዋለ ቢሆንም ኢትዮጵያ ውስጥ ግን በጣሊያን ሰንደቅ አላማ ተቀይሯል፡፡ ይህ ከአንድ ‹‹ያልሰለጠነ›› በሚሉት ጥቁር ህዝብ ሽንፈትን ከተከናነበ የአውሮፓዊ ሀይል የሚጠበቅ ነው፡፡ ከዚህ ይልቅ የሚያሳዝነው ግን ጣሊያን ተባራ እንደገና ክብሩን ያገኘው ሰንደቅ በኢትዮጵያውያን ያውም የመንግስትን ስልጣን በያዘው ኢህአዴግ የደረሰበት ውርደት ነው፡፡ ለእኔ ሰንደቁን አውርደው የራሳቸውን ከሰቀሉት ጣሊያኖች በላይ ሰንደቁን ሰቅለው ‹‹ጨርቅ›› ያሉት የኢትዮጵያው አቶ መለስ ዜናዊና ኢህአዴግ ናቸው ሰንደቁን ያዋረዱት፡፡
ፋሽስት ከኢትዮጵያ ምድር ከወጣ 50 አመት በኋላ ስልጣን ላይ የወጣው ኢህአዴግ መሪ አቶ መለስ ዜናዊ ሰንደቁን ‹‹ጨርቅ›› ብለው ባዋረዱበት ወቅት እነ ጋና፣ ጊኒ፣ ማሊ ሌሎች ከ10 በላይ አገራት የእኛውን ሰንደቅ አላማ ወስደው ያደመቁበት ዘመን ነው፡፡ አሁንም ከእኛው ይልቅ ከእኛ የወሰዱት አገራት ሰንደቁን ትልቅ ክብር ሰጥተውታል፡፡ በወቅቱ አቶ መለስ ዜናዊ ይህን ክብረ ነክ ተግባር ሲፈጽሙ ከተቃዋሚዎች፣ ከነጻው ሚዲያ እንዲሁም ከህዝብ ውጭ ከፓርቲያቸው ምንም አይነት ግፊት አልተደረገባቸውም፡፡ በመሆኑም ለዚህ አሳፋሪ ተግባር እርሳቸውም ሆነ ፓርቲው ህዝብን ይቅርታ ሳይጠይቁ በዚሁ ሰንደቅ ስም ሲገዙ ቆይተዋል፡፡
ኢህአዴግ በ2001 ዓ/ም የሰንደቅ አላማ አዋጅን አውጥቶ ‹‹የሰንደቅ አላማ ቀን›› ማክበር ሲጀመር በርካቶች ‹‹ሰንደቁ ወድቆ ተነሳ!›› በማለት ኢህአዴግ ለሰንደቅ አላማው ክብር በመስጠት ከስህተቱ መማር እንደጀመረ እምነት ጥለው ነበር፡፡ ሆኖም ሰንደቅ አላማው አሁንም ክብር አልተሰጠውም፡፡ የሰንደቅ አላማ አዋጅም ሆነ በስሙ ‹‹የሚከበርለት በዓል›› ኢህአዴግ ሰንደቁን እንዳላዋረደ ለማሳየት እንጅ ክብሩን የሚገልጽበት አይደለም፡፡ ኢህአዴግና የቀድሞው መሪ ‹‹ጨርቅ›› ብለው ለጠሩት ሰንደቅ አላማ አዋጅ ሲያወጡም ሆነ ‹‹በዓል›› ሲያከብሩ ለቀደመው ጥፋታቸው ህዝብን ይቅርታ አልጠየቁም፡፡ የሰንደቅ አላማ አዋጅ ያወጣውና በዓል እያከበርኩ ነው የሚለው ኢህአዴግ አሁንም ቢሆን ለሰንደቁ የሚሰጠው ክብር የይስሙላህ ነው፡፡
ከመለስና ከሰንደቁ ማን ክብር አለው?
ሰንደቅ አላማውን ‹‹እራፊ›› ያሉት አቶ መለስ ከህዝብና ከተቃዋሚዎች ከደረሰባቸው ትችት ባለፈ በፓርቲያቸው ምንም አይነት ግፊት አለመደረጉ ኢህአዴግ ከሰንደቁ ይልቅ ስልጣን ሊነጥቁ፣ ሊሰጡ፣ ‹‹ሊያራግፉ›› አሊያም ሊያስሩ ለሚችሉት አቶ መለስ ክብር ሰጥቷል ማለት ነው፡፡ በእርግጥ በብሄር ስም የተደራጁት የኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች ከአገሪቱ ሰንደቅ አላማ ይልቅ ለየክልሉ ‹‹ባንዲራ›› ክብር የሚሰጡ ናቸው፡ ለዚህ ደግሞ የካሪቢያንና ሌሎች የአፍሪካ አገራት የኢትዮጵያን የሰንደቅ አላማ ቀለማት ሲወስዱ አብዛኛዎቹ የኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች ለክልሎቻቸው ከእኛዎቹ ቀለማት ይልቅ ቀይ ባህር፣ ሜዲትራኒያንና አትላንቲክን ተሸግረው የአረብና የምዕራባዊያንን የሰንደቅ አላማ ቀለማት መዋሳቸው ነው፡፡ የሰንደቅ አላማ አዋጅና በዓል መከበር ከተጀመረ በኋላም ቢሆን ኢህአዴግ እነዚህ ራሱ ያጸደቃቸውን ህጎች ጥሶ ከሰንደቅ አላማው የአቶ መለስን ክብር አስበልጧል፡፡ ጥቂት ክስተቶችን እንመልከት፡፡
በ2004 ዓ/ም መጋቢት አጋማሽ አካባቢ ሰንደቅ አላማውን ‹‹እራፊ›› ያሉት አቶ መለስ ከኬንያና ደቡብ ሱዳን ጋር እንደ ሰንደቁ ሁሉ ‹‹ሸቀጥ›› ብለው የሚያጣጥሉት ወደብ ላይ አንድ ስምምነት አድርገው ነበር፡፡ በዚህ የለሙ ወደብን በአማራጭ ወደብነት ለመጠቀም ባደረጉት ስምምነት ድሮም የማይወዱትን ሰንደቅ አላማ ገልብጠውት ታይተዋል፡፡ በአቶ መለስና ኢህአዴግ የበላይነት የጸደቀው የኢፌደሪ ህገ መንግስት በአንቀጽ 3(1) እንዲሁም በ2001 ዓ/ም የወጣው አዋጅ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ቀለሞች አቀማመጥ ከላይ ወደ ታች አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ መሆኑን ያስቀምጣል፡፡ በተለይ በሰንደቅ አላማው አዋጅ አንቀጽ 17 መሰረት ‹‹(ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይቅርና) ማንኛውም ዜጋ ለሰንደቅ አላማው የሚገባውን ክብር የመስጠት ሀላፊነትና ግዴታ›› አለበት በሚል ደንግጓል፡፡ በአዋጁ አንቀጽ 23(6) ላይ ደግሞ የሰንደቅ አላማውን ቀለማት ቅደም ተከተል ሳይጠብቅ ማውለብለብ የተከለከለ መሆኑን ይደነግጋል፡፡ በአንቀጽ 24(1) ላይ ይህን ህግ የተላለፈ ግለሰብ ከ3000 ሺህ ብር መዋጮና እስከ አንድ አመት ጽኑ እስራት እንደሚፈረድበት በግልጽ አስቀምጧል፡፡ ኢህአዴግ በቅርቡ የሙስሊም ሰልፈኞቹን ‹‹ጥፋተኛ›› ብሎ የፈረጀው በዚህ አዋጅ ላይ ያሉትን ህጎች መዞ ነው፡፡ አቶ መለስ ላይ ግን ይህ ህግ አልሰራም፡፡
አቶ መለስ የገለበጡት አውቀው ነው በስህተት የሚል ጉንጭ አልፋ ክርክር ውስጥ መግባት አያስፈልግም፡፡ በህጉም መሰረትም ቢሆን አለማወቅ በራሱ ከጥፋተኝነት ሊያድን አይችልም፡፡ ዳግመኛ እንዲያውም በራሳቸው ትዕዛዝ የወጣውን አዋጅ ጥሰው ሰንደቁን ያዋረዱት አቶ መለስ ግን 3000 ብርና የአንድ አመት እስር ይቅርና ይቅርታ አልጠዩቁም፡፡ ኢህአዴግም እርሳቸውን ወክሎ ይቅርታ አይጠየቀም፡፡ እንዲያውም አቶ መለስ ሰንደቅ አላማውን መገልበጣቸው ስህተት መሆኑን የገለጹ ኢትዮጵያውያን ላይ ‹‹ምን አገባችሁ!›› ተብለው እርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ እኔው ራሴ ቋሚ ምስክር ነኝ፡፡
በወቅቱ ለአቶ መለስ ተጠሪ በሆነ ‹‹ኢንሳ›› በተባለ መስሪያ ቤት ውስጥ ተቀጥሬ እሰራ ነበር፡፡ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ አቶ መለስ በፈጸሙት ነገር ተቃውሞ ማሰማት ነበረብኝና በፌስ ቡክ ገጼ ትክክል አለመሆኑን ፎቶውን አስደግፌ ሀሳቤን ገለጽኩ፡፡ ታዲያ ከሰንደቅ አላማው ይልቅ ለአቶ መለስ ክብር የሚሰጡት የመስሪያ ቤቱ አመራሮች (ኢህአዴጎች ናቸው) ጠቅላይ ሚኒስትሩ እስከሆኑ ድረስ ሰንደቅ አላማውን መዘቅዘቃቸው ስህተት መስሎ አይታያቸውም፡፡ በተቃራኒው እኔ ‹‹አቶ መለስ ለምን ሰንደቅ አላማውን ዘቀዘቁት?›› ብዩ መጠየቄን በህገ ወጥነት ፈረጁት፡፡ ሰንደቅ አላማውን ‹‹ጨርቅ›› ሲሉም ሆነ ሲዘቀዝቁ ምንም ያልተባሉት አቶ መለስ ላይ ጥያቄ በማንሳቴ ‹‹የጠቅላይ ሚኒስትሩን ክብር አዋርደሃል!›› በሚል ‹‹ወንጀል›› ተከስሼ ከመስሪያ ቤት ታገድኩ፡፡ ህገ መንግስቱም ሆነ አዋጁ ስለ ሰንደቅ አላማ ክብር ያስቀመጠውን ጠቅሼ መከራከሬ ‹‹በከፍተኛ ወንጀል›› ከመስሪያ ቤቱ ከመባረር አላዳነኝም፡፡
ከሟቹ መለስም ያነሰው ሰንደቅ አላማ
ለሰንደቅ አላማው ጥላቻ ያላቸው አቶ መለስ ብቻ ቢሆኑ ኖሮ አቶ መለስ ከሞቱ በኋላ ኢህአዴግ ለሰንደቅ አላማው ከድሮው የተለየ ክብር በሰጠ ነበር፡፡ ሰንደቅ አላማ ከተዘቀዘቀ ከወራት በኋላ በስልጣን ዘመናቸው ሰንደቅ አላማውን ሲያዋርዱ የኖሩትና በኢህአዴግ ዘንድም ከሰንደቅ አላማው በላይ የሚከበሩት አቶ መለስ ከዚህ ዓለም በሞት ይለያሉ፡፡ ከአቶ መለስ ሞት በኋላ ረዥም የሀዘን ቀን መታወጁ ይታወሳል፡፡ ለዚህ ሀዘን ሲባል ደግሞ አገራዊ ቀናትም ተራዝመዋል፡፡ አሊያም ተሰርዘዋል፡፡ በአዋጅ የተወሰነው የሰንደቅ አላማ ቀን ከተራዘሙት መካከል አንዱ ነው፡፡
በአዋጅ 654/2001 መሰረት የሰንደቅ አላማ በዓል በየ አመቱ መስከረም ሁለተኛ ሳምንት ላይ በአገር ደረጃ እንዲከበር ቢደነገግም ኢህአዴጎች ‹‹አይሞትም!›› ለሚሏቸው አቶ መለስ ሀዘን ሲባል ለጥቅምት ሶስተኛ ሳምንት (ሰኞ ጥቅምት 19) ተራዝሞ ‹‹ተከብሯል››፡፡ በዚህ ቀንም ቢሆን ከሰንደቅ አላማው ይልቅ ህወሓት ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ያለው የአቶ መለስ 38 አመት ታሪክ በሚዘክር መልኩ ተከብሮ ውሏል፡፡ እናም ከሰንደቅ አላማው ይልቅ ተከብረው የዋሉት አቶ መለስ ነበሩ፡፡
በኢህአዴግና ሰንደቅ አላማው መካከል ያለውን ተቃርኖ ተከትሎ የሚመጣው መዘዝ ደግሞ እኔን አልለቀቀኝም፡፡ በወቅቱ ሰንደቅ አላማውን አዋርደው ምንም ያልተባሉትን አቶ መለስን ‹‹አዋርደሃል!›› በሚል ተባርሬ መሰናዘሪያ ጋዜጣ ላይ እየሰራሁ ነበር፡፡ በአቶ መለስ ሀዘን ምክንያት ተራዝሞ ሲወደሱበት ከዋሉት ‹‹የሰንደቅ አላማ ቀን›› ማግስት ማክሰኞ ጥቅምት 20/ 2005 ዓ/ም ሳምንታዊ መሰናዘሪያ ጋዜጣ ላይ ‹‹እውን ኢህአዴግ ሰንደቅ አላማውን ያከብረዋልን?›› የሚል ጽሁፍ ጽፌ ነበር፡፡ እኔ ከመስሪያ ቤት የተባረርኩበት የሰንደቅ አላማው ጉዳይ አሁን ወደ መሰናዘሪያ ዞረ፡፡ ከሰንደቅ አላማው ይልቅ ለአቶ መለስ ክብር የሚሰጠው ኢህአዴግ መሰናዘሪያ ዳግመኛ እንዳትታተም በማተሚያ ቤቶች ላይ ጫና አደረገ፡፡ እኔን ከመስሪያ ቤት ያባረረኝ ኢህአዴጋዊ የአቶ መለስ ክብር መሰናዘሪያን አሳገዳት፡፡ ይህም ከአንድም በሁለት ሶስት ህግ ስለ ሰንደቅ አላማው አስፍሮ፣ ወጭ አውጥቶና ቀን ቆርጦ ለሰንደቅ አላማው ቀን ‹‹እያከበረ›› የሚገኘው ኢህአዴግ በእውኑ ለሰንደቅ አላማው ክብር እንደማይሰጥ ያሳያል፡፡ ይህ እርምጃ ግን የተወሰደው በእኔ ብቻ አይደለም፡፡ የሰንደቅ አላማ ቀን መከበሩን ተከትሎ ኢህአዴግ በግዳጅ ‹‹በዓል አክብሩ›› ያላቸው በርካታ ወጣቶች ሰንደቅ አላማው ‹‹ጨርቅ›› መባሉን በመከራከሪያነት በማቅረባቸው መባረራቸውን ሰምቻለሁ፡፡ ኢህአዴግ ጥፋቱን አምኖ ለሰንደቅ አላማው ክብር እስካልሰጠ ድረስ በቀጣይነትም ጥያቄ ያነሱ ኢትዮጵያውያን ይባረራሉ፡፡ ተቋማትም ይዘጋሉ፡፡
ኢህአዴግ ያኔ አቶ መለስ ሰንደቁን ‹‹እራፊ›› ሲሉም ሆነ ሲዘቀዝቁት ይቅርታ አልጠየቀም፡፡ ለአቶ መለስ ሲል በአዋጅ የጸደቀውን የሰንደቅ አላማ ቀን እንደፈለገው ሲያራዝም ጥፋት መስሎ አልታየውም፡፡ ታዲያ በሰንደቅ አላማው ላይ ይህን ሁሉ ጥፋት የፈጸመው ኢህአዴግ ሰንደቅ አላማው ላይ ጥፋት ፈጽመዋል በሚል በሌሎች ላይ ክስ ለመመስረት ሞራል ከየት አገኘ? ካልሆነ ህገ መንግስቱና አዋጁ ከኢህአዴግ ውጭ ለሚገኙት ኢትዮጵያውያን ነው የሚሰራው እንደማለት ነው፡፡
እስካሁን በዓለም የራሱን ሰንደቅ አላማ የተሳደበ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ፕሬዝዳንት አሊያም ፓርቲ ተሰምቶ አይታወቅም፡፡ ይህ የኢህአዴግ ብቸኛ መገለጫ ነው፡፡ በተቃራኒው ሰንደቅ አላማውን ያከበረ የሚያስመስልባቸው ህጎችና አዋጆች ሰንደቅ አላማቸውን ከልብ ከሚወዱ ስርዓቶች ‹‹በመልካም ተሞክሮነት›› ቃል በቃል የተገለበጡ ናቸው፡፡ ለአብነት ያህል የብሪታኒያ ፓርቲዎች ለሰንደቃቸው ትልቅ ክብር ከሚሰጡት መካከል ይመደባሉ፡፡ ኢህአዴግ አጽድቆ የሚጥሰው ‹‹የሰንደቅ አላማ ቀን››ም ሆነ ‹‹አዋጅ›› ከብሪታኒያ ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡ ሆኖም ብሪታኒያውያን ለራሳቸው ሰንደቅ አላማ ይቅርና ለሌሎቹም ክብር ይሰጣሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል ባለፈው የለንደን ኦሎምፒክ ከሰንደቅ አላማ ጋር በተያያዘ አንድ ስህተት ተፈጽሞ ነበር፡፡  በኦሎምፒኩ ወቅት የሰሜን ኮሪያ የሴቶች የእግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን እየተዋወቀ እያለ ቴሊቪዥን ላይ ይታይ የነበረው ሰንደቅ አላማ የደቡብ ኮሪያ ነበር፡፡ ለዚህ ስህተትም በተለይ በሰሜን ኮሪያውያን ዘንድ የኦሎምፒኮ አዘጋጆች ብቻ ሳይሆኑ ብሪታኒያ ራሷም ተወቅሳለች፡፡ ብሪታኒያውያን ይህንን ወቀሳ የኦሎምፒኩን አዘጋጆች፣ የብሪታኒያ መሪዎች አሊያም ብሪታኒያን ‹‹ክብር አዋረደ›› ብለው መስል አልሰጡም፤ እርምጃ አልወሰዱም፡፡ ይልቁንስ የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ለተፈጠረው ስህተት በዓለም አቀፍ ደረጃ ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ ስህተቱን የፈጸሙት የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር አልነበሩም፡፡ ሆኖም ለሌላ አገር ሰንደቅም ያላቸውን አክብሮትና የተፈጸመውን ጥፋት በይቅርታቸው አምነዋል፡፡ የብሪታኒያ ገዥዎች በራሳቸው ላይ ብቻ ሳይሆን በሌላ አገር ሰንደቅ አላማ የሚፈጸም ስህተት ላይ የመክሰስ፣ የመቃወምና የመተቸት የሞራል ልዕልና ይኖራቸዋል፡፡ ሙስሊሞቹ ሲያውለበልቡት ነበር ያለውን የተበጣጠሰ ሰንደቅ አላማንም በሰንደቅ አላማ የማያምንበት ኢህአዴግ እንዴት  ጥብቅና ለመቆም ይቻለዋል?
ኢህአዴግ የሚያደርገው ከዚህም በተቃራኒ ነው፡፡ ራሱ ህግ አውጥቶ፣ አዋጅ አጸድቆ፣ በዓል ‹‹እያከበርኩ ነው›› እያለ፣ እራሱ የቀየረውን ሰንደቅ አላማ አሁንም እያወረደው ነው፡፡ ከጣሊያን ቀጥሎ ደግሞ ለረዥም አመት የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ እያዋረደ ይገኛል፡፡ በመሆኑም እስካሁን በተፈጸሙት ላይ ህዝብን ይቅርታ ሳይል ሌሎች ሰንደቅ አላማውን እንደማየከብሩት ለማሳጣት መሞከሩ አሁንም ከራሱ ጠባብ ቡድናዊ ጥቅም የዘለለ ነው ለማለት ያስቸግራል፡፡ ሰንደቅ አላማው ከኢትዮጵያውያን አልፎ በዓለም ህዝቦች ዘንድ ዝና እና ተቀባይነትን ያተረፈው ህገ መንግስትም ሆነ አዋጅ ሳይወጣለት ነው፡፡ ኢህአዴግ ደግሞ ስፍር ቁጥር የሌለው ህግ አውጥቶ እራሱ እየጣሰ ሌሎችን ለመክሰሻነት ብቻ እየተጠቀመበት ነው፡፡ መቼም ከአሁን በኋላ ሰንደቁን የሚያዋርድ የውጭ ሀይል ይበጣል ተብሎ አይገመትም፡፡ ኢህአዴግ እስካለ ድረስ ግን ሰንደቁ እንደተዋረደ የሚቀጥል ይመስላል፡፡ ከኢህአዴግ ውጭ ያሉት እንኳን ሰንደቁን ቢያዋርዱት ያዩት ከእሱው ነው፡፡ ‹‹መንግስት››ን ያህል ነገር የተቆጣጠረ ፓርቲ፣ የጠቅላይ ሚኒስትርነትን መንበር የተቆናጠጠ አካል ሰንደቁን ሳያከብር ማን ሊያከብረው ይችላል? ህጉን ለማጥቂያነት ብቻ የሚጠቀምበት ኢህአዴግ ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ‹‹ለሰንደቁ ክብር የላቸውም›› የሚል ፕሮፖጋንዳውን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በእርግጥ ይህ የተጀመረው በሙስሊሞቹ ብቻ አይደለም፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ባዘጋጀው ሰልፍ ላይም ሰልፈኞቹ ‹‹ሰንደቅ አላማውን አዋርደዋል›› ተብለው ተከሰዋል፡፡ ሰንደቅ አላማ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ምን ያህል ቦታ እንዳለው የሚያውቀው የኢህአዴግ ‹‹መንግስት›› ሰንደቁን ከማክበር ይልቅ ሌሎቹ እንደማያከብሩት በመምቻነት በስፋት እየተጠቀመበት መሆኑ ያሳየናል፡፡
ይህን ጽሁፍ ዳግመኛ ስጽፍም ሆነ ስለ ሰንደቁ ለሶስተኛ ጊዜ ሳነሳ ከሰንደቁ ይልቅ ለአቶ መለስ ክብር የሚሰጠው ኢህአዴግ የሚወስደው እርምጃ አላሳሰበኝም፡፡ በአባቶታችን ደም የተቀለመው ይህ ሰንደቅ አላማ ከስራ ከመባረርና ከመሳሰሉት ‹‹ጥቃቅን›› እንቅፋቶች በላይ በርካታ መስዋትነት ተከፍሎበታልና!

ሕወሐት በአዜብ ጉዳይ ተወጥሯል (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

azeb Mrs. corruption
ለስድስት አመት ኤፈርትን ሲመሩ የቆዩት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከሃላፊነት መነሳት ተከትሎ በሕወሐት ውስጥ ውጥረት መንገሱን ምንጮች አመለከቱ። የኤፈርት ቦርድ ሰብሳቢ በነበሩት ባለቤታቸው አቶ መለስ አማካይነት ዳይሬክተር ተደርገው አዜብ መሾማቸውን ያስታወሱት ምንጮች፣ ከመለስ ሕልፈት በኋላ ቦታውን የተረከቡት ኤርትራዊው ቴዎድሮስ ሃጎስ መሆናቸውን፣ እንዲሁም ዳይሬክተር የመሾምና የመሻር ስልጣኑ የቦርዱ መሆኑን ያስረዳሉ።

 አዜብ ከኤፈርት እንዲወገዱ የተደረገው ግን በነቴዎድሮስ ሃጎስ ሳይሆን ስብሃት ነጋ ባቀነባበሩት ጣልቃ ገብ ውሳኔ መሆኑን ምንጮቹ ገልፀዋል። በኤፈርት የተለያዩ ተቋማት የሚሰሩ ሰራተኞች አዜብ በመባረራቸው ደስታቸውን እየገለፁ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮች፣ አያይዘውም ደስታቸውን በስብሰባ ጭምር ከመግለፅ ባለፈ፥ « አዜብ ከኤፈርት ጀምሮ ለፈፀሟቸው የሙስና ወንጀሎች በሕግ መጠየቅ አለባቸው» በማለት አቋም እስከ መያዝ መድረሳቸውን አስታውቀዋል። ከዚህ በስተጀርባ በበቀለኝነታቸውና የጥፋት ሴራ በማቀነባበር የሚታወቁት ስብሃት ነጋ እንዳሉበትና ከኤፈርት ስልጣናቸው ያስነሷቸውን አዜብ ከጨዋታ ውጭ ከማድረግ ባለፈ በሙስና እንዲጠየቁ በየአቅጣጫው ጫና እያሳደሩ መሆኑን ምንጮቹ አስረድተዋል።

 በአዜብ ተፈፀሙ ተብለው ከተነሱት የሙስና ወንጀሎች በኤፈርት ስም 200 ከባድ ተሽከርካሪዎች አቶ ነጋ ገ/እግዚያብሄር ቀረጥ ሳይከፍሉ እንዲያስገቡ ማድረጋቸውን፣ በሚሊዮን የሚገመት ቀረጥ ሊከፈልባቸው የሚገቡ የተለያዩ የሕክምና መሳሪያዎች፣ በኤፈርት ገንዘብ ሶስት መርከብ ስሚንቶ የፍራንኮ ቫሉታን ሕግ በመተላለፍ ቀረጥ ሳይከፈልበት አገር ውስጥ መግባቱ፣ ክሶች እንዲቋረጡ ትእዛዝ በመስጠት..የሚሉት በዋነኛነት መነሳታቸውን ምንጮቹ አመልክተዋል። ( አዜብ ከኤፈርት እንደሚነሱ ከዚህ ቀደም በወጡ ዘገባዎች ምንጮችን በመንተራስ መገለፁ ይታወሳል)
 ይህ በእንዲህ እንዳለ – በአዜብ ቦታ የተተኩት ብርሃነ ኪ/ማርያም (በቅፅል ስማቸው ብርሃነ “ማረት”) ሲሆኑ፣ ከመለስ በፊት የአዜብ ፍቅረኛ የነበሩና ከሱዳን ተያይዘው በመምጣት ሕወሐትን እንደተቀላቀሉ ምንጮች አስታውሰዋል። ድርጅቱን ከተቀላቀሉ ከጥቂት ወራት በኋላ ሁለቱ (አዜብና ብርሃነ) የፍቅር ግንኙነታቸውን እንዲያቋርጡ ከበላይ አመራር መወሰኑን፣ አዜብ ከመለስ ጋር ግንኙነት መቀጠላቸውን ይገልፃሉ። ፓርቲው ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ብርሃነ በመቀሌ ማዘጋጃ ቤት ተመድበው ሲሰሩ «ለመንገድ ስራ ከተመደበ ገንዘብ አምስት ሚሊዮን ብር ተዘርፏል» በሚል በሙስና እንዲባረሩ መደረጉን ምንጮች ጠቁመዋል።
 
 አዲስ አበባ የመጡት ብርሃነ ብዙ ጥረት አድርገው አዜብ ዘንድ (ቤተ መንግስት) የመግባት አጋጣሚ ያገኛሉ። ባቀረቡት አቤቱታና ተማፅኖ መሰረት ሲቪል ሰርቪስ እንዲገቡ አዜብ ትእዛዝ ያስተላልፋሉ። ከኰሌጁ እንደወጡ የማ.ረ.ት. ሃላፊ ተደርገው በመለስ የተሾሙት ብርሃነ፣ በተለይ ከ1993ዓ.ም በኋላ የመለስ ቀኝ እጅ በመሆን በአውሮፓና አሜሪካ ያለውን የፓርቲውን መዋቅርና ስለላ በመምራት፣ አምባሳደሮችን በማስፈራራት፣ በማዘዝና ፈላጭ ቆራጭ ውሳኔ በማሳለፍ ታማኝ አገልጋይ ሆነው እንደቆዩ ያስታወሱት ምንጮች፣ ከመለስ ሞት በኋላ ግን የስብሃት ነጋ ተከታይና አስፈፃሚ በመሆን አሰላለፋቸውን ቀይረው እንደቀጠሉ አያይዘው ገልፀዋል። ስብሃትና ብርሃነ ዝምድና እንዳላቸው የጠቆሙት ምንጮች፣ አዜብን በማስነሳት ብርሃነ እንዲቀመጡ ያደረጉት ስብሃት መሆናቸውን አመልክተዋል።

Saturday, August 24, 2013

የግብፅና ኢትዮጵያ መጪው ዘመን ምን ሊመስል ይችል ይሆን?


ግብፅ (ምስር) እንደሃገር ከምትታውቅበት ማለትም ከፈሮኦኖች ዘመን ጀምሮ ፤ የታሪኳም ሆነ የህልውናዋ መሰረት አባይ ነው። አባይ ባይኖር የግብፅ የቆየና ጥንታዊ ታሪኳ የለም ፤ የፈርኦኖች ታሪክ የለም፤ አባይ ባይኖር የክሊዮፓትራ ታሪክ የለም ። ባጠቃላይ አባይ ባይኖር ግብፅም ታሪኳም፤ጥንታዊ ስልጣኔዋም፤ የአለማችንን እውቅ የታሪክ ምርምር መፃህፍት ገፆች ባላጣበቡ ነበር ። ታላቁ የግሪክ የታሪክ ሰው ሄሮዶቱስ ግብፅ የአባይ ስጦታ ነች ያለውም ለዚህ ነበር ። ታላቁ አሌክሳንድር ከግሪክ ተነስቶ መካከለኛው እስያ የሚባለውን ምድር ወርሮ ወረራውን በጊዜው ታላቅ አገርና አስፈሪ ጦር የነበረውን ፐርሽያን በዛሬው አጠራር ኢራንን ድል አድርጎ ወደ ህንድ ድንበር ከተጠጋ
በሁዋላ በድንገት አረፈ ።

 ከታላቁ አሌክሳንደር ሞት በኋላ ጀነራሎቹ የአሌክሳንደርን ግዛት ለአራት ከፍለው እጣ ተጣጥለው ፤ ግብፅ ፕቶሎሚ ለተባለው የጦር ጀነራል ደረሰችው ። የሮማውያንን ታሪክ የለወጠችው ክሊዎፓትራ ይሕ ግሪካዊው ጀነራል የመሰረተው ፕቶሎሚያዊ ስረወ- መንግስት
የመጨረሻዋ ወይም 11ኛዋ ልጅና ገዢ ነበ ረች ፤ በ ሷ ዘመን ደግሞ ሌላ ሃያል አገዛዝ ከሮም ተነስቶ ግብጽን ይወርራል ። በፍቅሯ ከወደቀው ከመጀመሪያው የሮማ ቄሳራዊ ዲክታተር ጁሊየስ ቄሳርም ልጆች ትወልዳለች አንዱን ልጇንም ለሮማ ገዢነት እሷም ሆነች አባቱ ጁሊየስ ቄሳር ያዘጋጁት ነበ ር ። ጁሊየስ ቄሳር በሮም ከተገደለ በኋላ ፤ የሮማ ጀነራሎች የሮማን ግዛት ለሶስት ከፍለው ግብፅ ለማርክ አንቶኒ ደረሰችው ። ማርክ አንቶኒ በክሊዎፓትራ ፍቅር ወድቆላት እዚያው ከግብፅ መንቀሳቀስ ያቅተዋል ። እሷና አዲሱ ሮማዊ ወዳጇ ፤ በአውግስጦስ ቄሳር ጦር ድል ሲሆኑ ፤ ክሊዎፓትራ ብዙ ገንዘብ አስይዛ ከቄሳር የወለደችውን ልጇን የላከችው ወደ ኢትዮጵያ እንዲሸሽ ነበር ። ክሊዎፓትራ እንዳሰበችው ልጇ ኢትዮጵያ ሳይደርስ በጠላቶቹ ተይዞ በ17 አመት እድሜው ታንቆ ተገደለ።

 ግብፅ በታሪክ የምትታወቅባቸው ሁለት ስሞች አሏት ። በመፅህፍ ቅዱስ ምስሪያም ይላታል ፤ በኛ “ ” “ ” ምስር ( “ስ አይጠብቅም ” ) ሌላው ደግሞ ከግሪክ የተወረሰው ኤጊፕቶስ የሚለው መጠሪያ ስም “ ” ራሱ ከአባይ ጋር የተያያዞ የወጣላት ስም ነው ፤ ጥቁር አፈር ማለት ነው። የግብፅ ምድር
በተፈጥሮው አሸዋና የምድሩም ቀለም ሽሯማ ነው ። አባይ ወንዝ ግብፅ ደርሶ ግራና ቀኝ ሞልቶ ሲፈስና ዳርቻዎቹ ከኢትዮጵያ በመጣው ደለል ሲሞሉ መሬቱ ይጠቁራል ። በዚህ ምክንያት ነው “ ” ኤጊፕቶስ የሚለውን ግሪካዊ መጠሪያ ያገኘችው ግብጽ ። ይህ ጥቁር መሬቷ በየአመቱ በደለል ተሞልቶ ለዘር ስለሚዘጋጅ ፤ ለጥንታዊት ግብፅ ፤ የፈርኦኖቹ መለኮታዊነትም ምስጢር መገለጫም ነበ ር። ስለዚህም አባይ ለግብፅ የህልውናዋም ፤ የአንፀባራቂ ታሪኳም ፤ ያለፈውም ሆነ መፃኢ ህልውናዋ መሰረት ነው።

 የግብፅ ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ታሪኳ ፤ ከፈሮኖች የ 4500 አመታት ግዛት በኋላ በግሪኮች ወደ3 መቶ አመታት ፤ ቀጥሎም በሮማውያን ለ3መቶ አመታት ፤ ከዚያም በቢዛንቲያ ለ3መቶ አመታት ፤ በ መቀጠልም ለ1100 አመታት አረቦችና ማምሉኮች በፍርርቅ ፤ ቀጥሎም የትውልደ-አልባኒያዊው የሞሀምድ አሊ ስርወ-መንግስት በቀጥታ ወደ ሰማኒያ አመታት ከገዟት በኋላ ፤ ቀሪዎቹ የመሃመድ
አሊ ልጆች የእንግሊዝን ቅኝ ገዢነት ተቀብለው እስከ 1922 ድረስ ቀጥሎም የእንግሊዝ ከባድ እጅ ቢኖርበትም የመሃመድ አሊ ልጆች እስከ 1952 ድረስ በንጉስነት ገዝተዋታል ። በዚህ አይነት ግብፅ ከፈሮኖች በኋላ ፤ ወደ 2500 አመታት ገደማ ግብፃዊ ባልሆኑ ባዕዳን ተገዝታለች ። ከዚህ የባእዳን ግዛት በኋላ ግብፅ የመጀመሪያውን ግብፃዊ መሪ ፤ በወታደራዊ መፈንቅለ-መንግስት አገኘች ። የሪፐብሊክ ዘመን የሚል መጠሪያ ስም በ መስጠት ” ” 3 ወታደሮች ፤ 1ኛ ጀማል አብደል ናስር ፤ 2ኛ አንዋር ሳዳትና 3ኛው ሆስኒ ሙባረክ ለ60 አመታት እስከ 2012 ድረስ በይስሙላ ምርጫ ገዝተዋታል ። ከሶስቱ ወታደራዊ መሪዎች ዘመን ከግማሽ በላይ የሚሆነውን የሆስኒ ሞባረክ አገዛዝ
ነው የፈጀው። ይህን ከላይ ለማስገንዘብ የወደድኩበት ዋናው ምክንያት ለዘመናት በበእዳንና በአምባገነኖች ሲገዛ የኖረው የግብፅ ህዝብ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በዲሞክራሲያዊ ምርጫ የመጀመሪያውን መሪ መርጦ ነበር ።

 በግልፅና በዲሞክራሲያዊ መንገድ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመረጡት መሃመድ ሞርሲ ለአንድ አመት ሃገሪቱን ካስተዳደሩ በኋላ በወታደራዊ መፈቅለ-መንግስት ከስልጣናቸው ተውግደዋል ። በምንም መለኪያ ይሁን ፤ ባለፈው አመት ለግብፅ ፈንጥቆ የነበረው ዲሞክራሲያዊ ብርሃን ዛሬ ጨልሟል ።

 ወታደሮች በፈለጉት ሰዓትና ጊዜ ምክንያት ፈጥረው የግብፅ ህገ-መንግስት ከሚያዘው ውጪ የግልበጣ እርምጃ ወስደዋል ። ይህ እርምጃ ግብፅን ቀጣይ ወደሆነ የመንግስታዊ አስተዳደር ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት አዙሪት ውስጥ ለወደፊትም የሚከታት ይሆናል ።
በአለማችን ዘመናዊ የመንስታት ግልበጣ ታሪክ እንደሚታየው መጀመሪያ አንድ ጀነራል ወይም የጦር መኮንን መንግስት ይገለብጥና የሃገሪቱን መሪ ያስራል ፤ ህገ-መንግስቱን ይሽራል ፤ ፓርላማውንም ይበትናል ፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም ያውጃል ፤ ህዝብ የሚቃወም ከሆነ በደም
ህገሪቱን ያጥለቀልቃታል ። ግብፅም ከዚህ አላመለጠችም ። ጀነራል አብዱል ፋታህ አልሲሲ በውሻ ገመድ አስሮ እንደፈለገ ከኋላ ሆኖ የሚሽከረክረው ሲቪል መሰል ጊዜያዊ መንግስት አቋቁሟል ።

 ይህ መንግስትም እስካሁን የተገደሉት ግብፃውያን ቁጥር ከስምንት መቶ አይበልጥም እያለ ነው ፤ መረጃዎች የሚያሳዩት ግን ከዚያ በላይ ነው ። ገለልተኛ አቋም አለው ይባል የነበረው የግብፅ ሴኩላር ህብረተሰብና እስላማዊ ፓርቲዎች መካከል ተፈጥሮ ነበር የሚባለው የፖለቲካና የአይዲዎሎጂ ግብግብ ዛሬ መልኩን ቀይሮ ፤ የሙባረክ ዘመን ሰዎች ወደስልጣን የተመለሱበት ትያትር ሆኗል ።

 የሴኩላሩ ህብረተሰብ ቁንጮ ይባል የነበረውም ሞሃመድ አል ባራዳይ ፤ በህዝቡ ላይ በደረሰው ጭፍጨፋ ምክንያት የጊዜያዊው መንግስት ምክትል ፕሬዝደንትነቱን በፈቃዱ ለቅቆ ከግብፅ ውጥቶ ስዊዘርላንድ ገብቷል ። በዚህ አይነት ሴኩላሩ ህብረተሰብ በሙባረክ ሰዎችና በጀነራል አልሲሲ ተሸውዷል ። ሃገሪቱን ለ32 አመታት በፈላጭ ቆራጭነት ያስተዳደረው ሙባረክም ከወንጀሎቹ ሁሉ ነፃ ሆኖ ከእስር ተፈትቷል ። የሚገርመው ሙባረክ ሃገሪቱን ባስተዳደረባቸው 32 አመታት ጥሎት የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከስልጣን እስኪወርድ ድረስ ተነስቶ አያውቅም ነበር ። አሁንም ጀነራል አልሲሲ ሞርሲን ከገለበጠ በኋላ መጀመሪያ ያደረገው ይህንኑ አዋጅ መመለስ ነበር።

 የእስላማዊ ወንድማማችነት ፓርቲ በሞሃመድ ሞርሲ አማካይነት ወደስልጣን ከመጣ ጀምሮ ተከታታይ የፖለቲካ ስህተቶች ሰርቷል ። ከ70 አመታት በላይ እድሜ ያስቆጠረው እስላማዊ ወንድማማችነት ፓርቲ ፤ ብዙ የግብፅ ምሁራንን ከተለያዩ የሙያ መስኮች ያካተተ ድርጅት ቢሆንም ፤ የመንግስት አስተዳደራዊ መዘውር ላይ ባለፈው አንድ አመት ተሞክሮው ደካማነቱ ተጋልጣል ።

 ያም ሆኖ ግን ተቃዋሚዎቹ እንደሰለጠነው አለም የምርጫውን ጊዜ ጠብቀው በምርጫ ቢጥሉት ኖሮ ፤ ለራሳቸውም መፃኢ እድል ይበጃቸው ነበር ። አሁን ያለው የግብፅ ሁኔታ እንደሚያሳየው ግብፃውያን ተከፋፍለዋል ። የጨሰው አቧራ ሲረጋና ጭጋጉ ሲገፈፍ የግብፅን ህዝብ እንደገና ለአንድነቱ መስራቱ አይቀሬ ነው የሃገር ጉዳይ ነውና ።

 መጪው የግብፅ መንግስት ወታደራዊም ሆነ ወይም በወታደሮቹ ከኋላው የሚገፋ ጋሪ ፤በ አምባገነኖች እንደተለመደው ፤ የህዝቡን ትኩረት አቅጣጫ ማስለወጫ አንድ ዘዴ መፍጠር ይኖርበታል ። ይህ ዘዴ ደግሞ የቆየ ታሪካዊ መሰረት ያለውና የአገሪቱ ቁስል መሆን ይኖርበታል ።

 ለማንም የፖለቲካ ታዛቢ በግልፅ እንደሚታየው የመጀመሪያውን ትኩረት የሚስበው ፤ ግብፅ ከእስራኤል ጋር ያላትን የቆየ አረባዊ ችግርን በመቆስቆስ የህዝቡን እኩረት አቅጣጫ ማስለውጥ ይሞከር ይሆናል ፤ ሆኖም ግን በወታደራዊ አቅሟም ሆነ ባሏት ጡንቸኛ ወዳጆችና ምክንያት እስራኤልን ለዚህ አላማ ለማዋል መሞከር የሚያስከፍለው ዋጋ ከፈተኛ ሊሆን ስለሚችል የማይሞከር ይሆናል ።
ሁለተኛውና ቀጣዩ የአቅጣጫ ማስለወጫ የቆየና ታሪካዊ የግብፅ ቁስል አባይና ኢትዮጵያ ይሆናሉ ። ከላይ እንደገለፅኩት አምባገነኖች የሚጠቀሙበት ዘዴ ነውና ፤ በኢትዮጵያም የአካባቢው አገሮች ህዝባዊ አመፅ ጣራ በነካበት ጊዜ ሟቹ አምባገነን የኢትዮጵያን ህዝብ ትኩረት የሳበውና ሊመጣ ይችል የነበረውን የህዝባዊ አመፅ ሰልፍ ወደአባይ ግድብ ግንባታ የድጋፍ ሰልፍ የቀየረው በዚሁ አይነት ዘዴ ነበር ። አሁን ደግሞ በተራቸው የግብፅ አምባገነኖች ይህን ዘዴ የማይጠቀሙበት ምክንያት አይኖርም ።
ለዚህም አራት ምክንያቶችን መጥቀስ ይቻላል ።
1ኛ- አባይ ለግብፅ ህይወቷም ህልውናዋም ነው ። ህዝቧንም በቀላሉ ወደአንድ የሰልፍ መስመር ሊያመጣ የሚችል ጉዳይም ነው ። ሌላው ቀርቶ ብዙ መከራ እየተቀበሉ ያሉት የግብፅ ክርስቲያኖች ዛሬ ወታደራዊውን መፈንቅለ መንግስት ደግፈው ይገኛሉ ፤ እንዲያውም ባለፈው አርብ የኦርቶዶክሱ ፅ/ቤት ሙሉ ድጋፉን የገለፀበትን መግለጫ አውጥቷል ። እነሱም ቢሆኑ ግብፃዊ ናቸውና ወደሰልፉ መቀላቀላቸው አይቀርም ። በአባይ ጉዳይ ላይ ሊይዙት የሚችሉት አቋም ከሙስሊሙ ግብጻዊ አይለይም ። ለማሳያ ያህል ክርስቲያን የሆነውና የቀድሞው የግብፅ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር (በኋላ ላይ የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሁፊ ሆኖ ያገለገለው) ቡትሩስ ቡትሩስ ጋሊ ፤ የአካባቢያችን ቀጣዩ “
ጦርነት የሚደረገው በፖለትካ ሳይሆን በአባይ ምክንያት ነው ፤ ወደዚያ ደረጃ ከተደረሰ ደግሞ ጄቶቻችንን ልከን ግድቡን በአንድ ቀን እናፈነዳውና ወዲያው እንመለሳለን ፤ ጉዳዩ ይህን ያህል ቀላል ነው ፤ ሲል የተናገረው የሚረሳ አይደለም ።
2ኛ- የግብፅ ወታደራዊ ሃይል ከኢትዮጵያ ጋር ሲወዳደር ጠንካራ ነው በተለይ የአየር ሃይሉ። የግብፅ አየር ሃይል በአሁኑ ጊዜ 240 ተዋጊ አውሮፕላኖች አሉት ፤ ከነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ አሜሪካን ሰር F16 የተለያዩ ሞዴሎች ሲሆኑ በቅርቡም እጅግ ዘመናዊ የሆኑትን ተዋጊዎች ከአሜሪካ አግኝቷል ።
 የምእራቡ አለምም የሚቆመው ለጥቅሙ ነውና ከኢትዮጵያ ይልቅ ግብፅ ላይ የበለጠ ጥቅም ስላለው ከግብፅ ጋር መቆሙ አይቀሬ ነው ።
3ኛ- የኢትዮጵያ ጎረቤቶችም ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸው ግንኙነት አስተማማኝ አይደለም ። በዚሁ የፈረንጆች አመት ኤፕሪል ላይ ፤ ኤርትራ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯን እና የኢሲያስ አፈውርቂን የፖለቲካ አማካሪ የማነ ገብረ-አብን ካይሮ ድረስ በ መላክ ፤ የግብጽን የቅኝ-ገዢነት ዘመን የአባይ ውሃ ስምምነት እንደምትደግፍ ፤ ከስልጣን ለተወገዱት ሞሃመድ ሞርሲ አሳውቃ ነበር ። ሰሜን ሱዳንም
በተለዋዋጩ የፖለቲካ ባህሪዋና አረባዊ ተባባሪነቷ የተነሳ በተለይ ደግሞ ካላት የአባይ ጥቅም ጋር ተደማምሮ ፤ የገልፍ አረብ አገሮችም ተጨማሪ ግፊት ካደረጉባት ባልተጠበቀ ጊዜ ግልብጥ የምትል ሃገር ናት ። በተለይ ደግሞ የሳውዲው ልዑል በአረቦች የውሃ ሚኒስቲሮች ስብሰባ ላይ የሰነዘረውን አይነት ፤ ማለትም ጥቃቱ ሁሉ በመላው አረቦች ላይ እየተሰነዘረ ነው የሚለውን ሃሳብ ፤ ከተለያዩ አረብ ሃገራት ከተደረገባት አሁን የለበሰችውን ቆዳ ቀለም በቀላሉ የማትቀይርበት ምክንያት የለም ።
4ኛ- ግድቡ እየተሰራ ያለበትም ስፍራ በቀላሉ ለአደጋ የተጋለጠ ያደርገዋል ፤ በተለይ ለአየር ሃይል ድብደባ ። ከኢትዮጵያ ድንበ ር በ 40 ኪ.ሜ ወይም በ 25 ማይል ርቀት ላይ ነው ግድቡ የሚገኘው ።
 በቀላሉ የሰሜን ሱዳንን አየር ክልል አቋርጦ ወደግራ እጥፍ ያለ F 16 ተዋጊ አውሮፕላን በደቂቃዎች ውስጥ የአየር ድብደባውን አከናውኖ ሊሄድ ይችላል ። ኢትዮጵያስ የአየር መከላከያ አቅሟ ምን ያህል ነው? አጸፋውን ለመመለስ የሚያስችል ብቃትስ አላት ወይ ? ከስልጣን የተወገዱት ሞሃመድ ሞርሲ እንኳን ከመገልበጣቸው 10 ሳምንታት በፊት የአባይን ውሃ እያንዳንዷን ጠብታ በደማችን “ እንከላከላለን ሲሉ ተናግረው ነበር ” :: እስከ አለፈው አመት ድረስ የግብፅ የውሃና የመስኖ ሚኒስትር የነበረው ሞሃመድ ናስር ኤል አላም ሚሊዎኖች እንራባለን ፤ የውሃ እጥረት በየቦታው ይከሰታል “ ፤አደጋውም ከፍተኛ ይሆናል ብሎ ነበር ። አሁን ደግሞ ወደ ስልጣን እየተመለሱ ያሉት የቀድሞዎቹ ”
የሙባረክ ዘመን ሰዎች ናቸው ። የሁለቱ ተቃራኒ የፖለቲካ ቡድኖች ሰዎች አባባል የሚያመለክተን አባይ ላይ የሚያስማማ ነጥብ ያላቸው መሆኑን ነው ። እናም ይህን በተመለከት እትዮጵያዊው ህብረተሰብ ምን እየሰራ ይገኛል ? ግብፃውያኑን የማስተባበሩ ተግባር በመጪው የግብፅ መንግስት በኩል ሲጠናቀቅ በኛስ በኩል ምን መደረግ አለበት ?  ጦርነት አይቀሬ የሚሆንበት ሁኔታዎችም ሊመጡ ይችላሉ ። እንደዜጎች እያንዳንዳችን ልናስብበት አይገባም ወይ ? ወይስ የፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያምን የቅርብ ጊዜ የፅሁፋቸውን አባባል
ልዋስና በግብፅና በኢትዮጵያ ውዝግብ የሚያሸንፈው አሜሪካ መሆኑን የሚጠራጠር ይኖር ይሆን “ ?” ስለዚህ አሜሪካ ለሚያሸንፈው ጦርነት እኛ ለምን እንለፋለን ብለን እጃችንን አጣጥፈን እንቀመጥ?  በእኔ በኩል ፅሁፌን አበቃሁ ።
gmgbelete@gmail.com
ተጨማሪ
 ትንሽ ለዲያስፖራው ትግል ማሳሰቢያ !
ቀጥሎ የምገልፀው የቅርብ ጊዜ ትዝታየን ነው ። በተለይ እንዲህ አይነት ሁኔታዎች ሲፈጠሩ በቋፍ ያለው የዲያስፖራ ትግል መሰንጥቅ ይጀምራል ። በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት የደረሰውን ማስታወሱ በ ቂ ማስረጃ ይሆነናል ። ዛሬ የውጪውን ትግል ክፉኛ የሚታገሉት እዚሁ ከኛው ጋር አብረውን የነበሩና በኤርትራ-ወያኔ ጦርነት ወቅት ወደ ባንዳነት የተቀየሩ የዲያስፖራው ሰዎች ናቸው ። ምሳሌዎችን ማንሳት ይቻላል ። ዛሬ በየአቅጣጫው የዲያስፖራው ትግል ተቀናቃኝ ሚዲያዎች በዲያስፖራው ድጋፍ እግራቸውን የተከሉና በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በኩል አገራችን “  ስትደፈርማ ቁጭ ብለን አናይም በሚል ምክንያት እጃቸውን የሰጡ ናቸው ። የሰሜን አሜሪካ ”
አመታዊ የእስፖርት ፈደሬሽንን ለመገንጠል ያሰቡትና በተመሳሳይ ጊዜም ለሁለተኛ ጊዜ ውድድር በተደራቢ ያዘጋጁት ወገኖች ፤ እንዴ !! አገራችን ተወራለች እንዴት ነው ነገሩ ብለው ፤ ተዉ ሲባሉ ፡ እኛ ደሞ ከወያኔ ጋር ልንሰራ ! አብዳችኋል እንዴ ! እያሉን ገብተው ፡ ቀልጠው የቀሩ ወገኖች ናቸው ። እናም በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል ሊነሱ የሚችሉ ሁኔታዎችን ተጠቅመው ለመግባት የሚንደረደሩ አይጠፉምና ጠንቀቅ ማለት ይገባል ። መግባቱን ሊገቡ ይችላሉ አትግቡም ብንላቸው አይቀሩም ፤ ሆኖም ግን እንደተላከ ውሻ ጩሀታቸውን መጥተው እንዳይለቁብን በማለት ነው ይህን ማሳሰቤ ለሁሉም መዘጋጀቱ ተገቢ ይመስለኛልና ፡፤

የአቶ መለስ ሞት እና ጥቅማጥቅሞቹ፤ ስላቅ እና ሀቅ



የአቶ መለስ ሞት እና ጥቅማጥቅሞቹ፤ ስላቅ እና ሀቅ

2012-03-02t171851z_319859376_gm1e83303nh01_rtrmadp_3_kenyaሰላም ወዳጄ… ተጠፋፍተናል ግዴለም እቅ….ፍ አድርጌ ሰላም ልበልዎት… እንዴት አሉልኝ.. እኔ የምለው አቶ መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከሞቱ እንደዋዛ አንድ አመት ሞላቸው አይደለም እንዴ… ወይ ጉድ ጊዜው እንዴት ይሮጣል ጃል… ምን እንደሚያመጣልን እንጃለቱ፤ አሯሯጡ ግን ወርቅ በወርቅ እንደሚያንበሻብሽ አትሌት ነው፡፡ ይሁና እኛ እንደሆነ “በርታ ግፋ” እያልን ከመደገፍ ወደ ኋላ አንልም… አረ እንደውም ጊዜ ሆይ፤ …ሩጥልኝ ልጄ አምልጠልኝ ልጄ ቁጭ ብሎ መጠበቅ ለኔውም አልበጄ… ብለን እንደ ዶክተር ፈቃደ አዘዘ እንቀኛለን፤

እናልዎ ወዳጄ ዛሬ የመጣው ይምጣ ብዬ ሙት ወቃሽ አታድርገኝም ሳልል የአቶ መለስ መሞት ለሰፊው ህዝብም፣ ሰፊ መሆን ለተሳነው ኢህአዴግም፣ መጠን አልባ ለሆኑት ተቃዋሚዎችም በጣም ስንሳለቅ ደግሞ ለወይዘሮ ሀዜብ ሳይቀር በርካታ ጥቅማጥቅሞች አሉት ብዬ ልሟገትልዎ ነው…!

በ22 ዓመት ውስጥ ያየናቸው አቶ መለስ እንደው ዝም ብለው የእነ ስምሃል አባት እንደው ዝም ብለው የነ ወይዘሮ አዜብ ባለቤት እንደው ዝም ብለው የአቶ ዜናዊ አስረስ ልጅ ብቻ አልነበሩም፡፡ አቶ መለስ ሀገሪቱን እያስተዳደረ ያለው ኢህአዴግ ሊቀመንበር ከዛም ውስጥ ደግሞ እጅግ አደገኛ የሚባለው ህውሃት አባወራ የሀገሪቱ ጦር ሃይሎቹ አዛዥ (አሃ ለካስ ጦር ሃይሎች የድሮው ነው… እንደው የድሮ ስርዓት ናፋቂ የሆንኩ ሰውዬ… አሁን መከላከያ ነው ማለት ያለብን… በመከላከያው ውስጥ ጦር አለ ከተባለ እንኳ ጦሩ አቶ መለስ ነበሩ… ስለዚህ የጦር ሃይሎች አዛዥ ሳይሆኑ በመከላከያ ውስጥ ጦር የሆኑ ሰውዬ ነበሩ ብሎ አለመመስከር ጡር ነው… ) በጥቅሉ ሰውዬው የመላዋ ኢትዮጵያ ፈላጭ ቆራጭ ነበሩ፡፡

አሁን እኒህ ሰውዬ ሞተዋል… እስቲ ከተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ጋር አያይዘን የሞታቸውን ጥቅማ ጥቅሞች እንዘርዝር…
ለአባይ ግድብ ሲሉ አቶ መለስ እንኳን ሞቱ!

አባይን አቶ መለስ እንዴት እንዴት ይገደብ ብለ
ው እንደጀመሩት ተነጋግረን ተነጋግረን መቼም ከስምምነት ላይ የደረስን መስለኛል፡፡ አባይዬ ድንገት ያለ ዕቅድ… ያቺ እነ ሙባረክን እንደ ሾላ ፍሬ ርግፍ ርግፍ ያደረገች አብዮት ወደ እኛም ትመጣ ይሆናል… በሚል ስጋት ነው ለማስቀየሻ ተብላ ነው የተጀመረችው፡፡

ለዚህ ዋና ማስረጃ በአምስት አመቱ ትራስፎርሜሽን እቅድ ውስጥ አለመፃፏ ሲሆን ሌላው ደግሞ የፕሮጀክቷ ስም አሁንም አሁንም መቀያየሩ ድሮውንም ቃሚዎች “በምርቃና” እንደሚሉት አይነት የታሰበች ድንገቴ ስራ መሆኗን ያሳብቃል፡፡ በነገራችን ላይ አሁንም ጭምር በተለይ ውጪ ሀገር የሚኖሩ “የኢህአዴግ ወጣት ክንፎች” የአባይን ግድብ “ሚሊንየም ዳም” ነው የሚሏት…! ህዳሴ መባሏን ከነጭርሹም አለሰሙም!

የሆነው ሆኖ አባይን አቶ መለስ ድንገት እንደጀመሯት ሁሉ ድነገት ያቋርጧታል የሚል ስጋት ሰቅዞ የያዛቸው ብዙዎች ነበሩ… (ብዙዎች ያልኩት አካብዶ ለማውራት እንዲመቸኝ ብዬ እንጂ… እንዲህ የሚያስቡት ምን ያህል ብዙ እንደሆኑ ስታስቲክስ አልሰራሁም፡፡ ነገር ግን ያናገርኳቸው ሁሉ የሰጡኝ ማብራሪያ አሳማኝ ነበር፡፡)  እንደሚታወቀው አባይን ለመገደብ የሚጠይቀው የገንዘብ አቅም ቀላል አይደለም፡፡ በየመስሪያቤቱ በጥፊም በርግጫም የሚደረገው መዋጮ አስከምን ድረስ እንደሚያስኬድ የሚያውቁት እርሳቸው ብቻ ነበሩ… እናም የሆነ ቀን የሆነ ቀን ማጣፊያው ያጠራቸው ቀን መለኛው መሌ በሆነ መላ ግንባታው እንዲቋረጥ ያደርጉ ነበር የሚለው ነገር ውሃ የሚያነሳ ሆኖ አግኝቼዋለሁ… ይህንን እያንሰላሰልን ታድያ ምን ይበጃል እያልን ስንጨነቅ አቶ መለስ ሞቱ… ለአባይ ሲባልስ እንኳን ሞቱ! ልክ እርሳቸው ሲሞቱ ሌጋሲን ማስቀጠል በሚለው መርህ ከዋናዎቹ አንዱ አባይ ግድብ አይቋረጥም የሚለው ሆነ፡፡ እሰይ እንኳንም አልተቋረጠ፡፡ እንኳንም ሞቱልን…!
ለተቃዋሚዎች ሲባል አቶ መለስ እንኳን ሞቱ!

ተቃዋሚዎች በተለያየ ጊዜ ኢህአዴግን ሲቃወሙ ከሁሉ በላይ የሚበረታባቸው የአቶ መለስ ግልምጫ ሽሙጥ እና እርምጃ ነበር፡፡ ሲያሻቸው ጣት እንቆርጣለን እያሉ ሲያሰኛቸው ሰብስበው እስርቤት እየላኩ አቶ መለስ ተቃዋሚዎች ላይ እንደሚጨክኑት ኢህአዴግ አይጨክንባቸውም፡፡ እውነቱን እንበለው ካልን ደግሞ መጨከን ብቻም ሳይሆን በፖለቲካው ቼዝም አቶ መለስን ተቃዋሚዎቹ አይችሏቸውም ነበር፡፡ ተቃዋሚዎቹ ፈረሳቸውን ቆስቁሰው ገና “ቼ…” ብለው ሮጥ ሮጥ ማለት ሲጀምሩ መለስ በወታደሮቻቸው ፈረሶቻቸውን እየሰነከሉ፤ ንግስታቸውን “ቼዝ” እያሉ ተቃዋሚዎቹን መላወሻ አሳጥተዋቸው ነበር፡፡
አሁን አቶ መለስ ሞተውላቸዋል፡፡ ተቃዋሚዎች መቼም ጨካኞች እንዳይባሉ ሰግተው በአቶ መለስ ሞት ሀዘናቸውን ሲገልፁ ቢሰማም ውስጥ ውስጡን ግን እሰይ ግልግል እንደሚሉ ማወቅ አያቅተንም፡፡ በአሁኑ ጊዜ ተቃዋሚዎቹ ትንሽ ጠንከር ካሉ ኢህአዴግ ውስጥ ክፉኛ የሚገዳደራቸው አለ ብሎ ማመን ይቸግራል፡፡ ስለዚህም ለተቃዋሚዎች ሲባል አቶ መለስ እንኳን ሞቱ!
ለራሱ ለኢህአዴግ ሲባል አቶ መለስ እንኳን ሞቱ!

በተለይ ከሆነ ጊዜ በኋላ ይመስለኛል ህውሃት ለሁለት ቃቃቃ…ቃ ብሎ ከተሰነጠቀ ጊዜ በኋላ የኢህአዴግ ስብዕና ኮስምኖ የአቶ መለስ ዜናዊ ስብዕና ደግሞ እጅግ በጣም የጎላበት ወቅት ነበር፡፡ አረ ከነጭርሹ መለስ ከልለውን ኢህአዴግን ማየት ተስኖን ነበር…! በዛ አያያዙ ጥቂት አመታት ቢገፉ ኖሮ ኢህአዴግዬ መለስ በተባለ ቅብ ተሸፍና እሰከመፈጠሯም እንረሳት ነበር፡፡
አሁን ግን መለስ ሞቱ ኢህአዴግ የሚባል ፓርቲም ምን አይነት ቅርጽ እና መልክ እንዳለው ሊታወቅ በቃ፡፡ ታድያ ለኢህአዴግ ሲባል ቅርፀ ግንባሯ እንዲታይ ሲባል፤ ያለ መለስ መኖር እንደምትችል ለማሳየት ሲባል፣ እንኳን መለስ ሞቱላት ብንል ምን ግፍ ተናገርን ይባላል፡፡
ወላ ለወይዘሮ አዜብ ሲባል አቶ መለስ እንኳን ሞቱ!

መጣች ስላቋ… ወይዘሮ አዜብ ቀላል ክብሮ ሆኑ እንዴ…! ክብሮ ማለት አራዶቹ ከበረ ከሚለው አማርኛ ቃል የወሰዷት ስትሆን የተከበረ ለሚባል ሰው የሚሰጥ ማዕረግ ነው፡፡ አዎ ወሮ አዜብ ክብሮ ሆነዋል፡፡ የመለስ ፋውንዴሽን ፕረዘዳንትነት አቶ  መለስ ባይሞቱ ኖሮ ከየት ይመጣ ነበር… አረ እንኳን ሞቱላቸው… (እዝችጋ እንኳ ጨክኛለሁ ይቅር ይበለኝ!) የምር ግን ወይዘሮ አዜብ እንደልቸው መልካም ገፅታቸውን እንዲገነቡ የአቶ መለስ ሞት ትልቅ እድል ሰጥቷቸዋል ብዬ አምናለሁ… ዝም ብለን ከመረመርን ወይዘሮ አዜብ በአቶ መለስ ሞት ጉዳት እንደገጠማቸው ሁላ በርካታ ትቅማጥቅሞችንም እንዳገኙ ግን መጠርጠር አያቅተንም!
ለችግኝ ተከላ ሲባል አቶ መለስ እንኳን ሞቱ!

አቶ መለስ ዜናዊ በህይወት ዘመናቸው እና በበትረ ስልጣናቸው ጊዜ ሰዎች አጥብቀው የሚያማርሯቸው በችግር ተከላ ነበር፡፡ አሁን ግን ሞቱ፣ አመትም ሞላቸው በስማቸውም በርካታ ችግኞች እየተተከሉላቸው ነው፡፡ በእውኑ ለእነዚህ ችግኞች ሲባል አቶ መለስ እንኳን ሞቱ ብንል ማነው እርኩስ የሚለን…! ማንም!

http://www.abetokichaw.com/
 

Friday, August 23, 2013

ከአዲስ አበባ ወደ ወልዲያ ሲጓዝ የነበረ አውቶቡስ ተገልብጦ በርካታ ሰዎች ሞቱ

ነሃሴ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአዲስ አበባ ወደ ወልድያ ሲጓዝ የነበረ ሚኒባስ አውቶቡስ ደሴ አካባቢ ሲደርስ በመገልበጡ የ21 ሰዎች ህይወት ጠፋ፣ የዛሬውን ጨምሮ በአንድ ሳምንት ውስጥ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 66 ደርሶአል።
የአደጋው  መንስኤ ጥራት የሌለው የአስፓልት መንገድ በጎርፍ በመቆረጡ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። የወልድያ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ለኢሳት እንደገለጸው ደግሞ የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ባሙያዎች ከደሴ በመላካቸው መረጃው ተጣርቶ እስከሚቀርብ ድረስ አስተያየት ለመስጠት አይቻልም ብሎአል።
ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ሾፌሩን ጨምሮ የ3 ሰዎች አስከሬን በጎርፍ በመወሰዱ ለማግኘት አልተቻለም። የተወሰኑ አስከሬኖች ወደ ቀወጃ፣ ቆቦ፣ ወልድያና ሳንቃ ተልከው የቀብር ስነስርአታቸው ተፈጽሟል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአካባቢው የሚጥለው ዝናም የአስፓልት መንገዶችን እየጎመደ ጉዳት ማድረሱን  ነዋሪዎች ይናገራሉ። መንገዶቹ የውሀ ፍሳሽ የሌላቸው በመሆኑ በቀላሉ ለአደጋ እንደሚዳረጉ እነዚሁ ነዋሪዎች ይገልጻሉ።
ከሁለት ቀናት በፊት በአምባሰል ወረዳ አንድ ሚኒባስ ተሽከርካሪ በጎርፍ በመወሰዷ የ15 ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወቃል። በጉዳዩ ዙሪያ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣንን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

በአንዋር መስጂድ ፖሊስ ሙስሊም ሴቶች ላይ ከፍተኛ ድብደባ ፈጸመ! ጁምአ

August 23, 2013
ድምፃችን ይሰማ

ጭንቅላታቸው የተፈነከተና ደም ይፈሳቸው የነበሩ ሴቶች ታይተዋል!

Ethiopian Musilms
ጥቂት የማይባሉ እናቶችና እህቶች ሰላታቸውን ሳይሰግዱ ወደ ቤታቸው ለመመለስ ተገደዋል!
ዛሬ የጅምአን ሰላት ለመስገድ በተገኙ እናቶች ላይ ፖሊስ ድብደባ መፈጸሙ ታወቀ፡፡ በመርካቶ አንዋር መስጂድ የዛሬውን የጁምአ ሰላት ለመፈጸም የተገኙ በርካታ እናቶችና እህቶች በፖሊስ አባላት ከፍተኛ ድብደባ ተፈጸመባቸው፡፡ እነዚሁ ለጸሎት የተሰባሰቡ እናቶች ድብደባ የተፈጸመባቸው ከመስጂዱ ግቢ ውጪ አንጥፋችሁ መስገድ አትችሉም በሚል ነው፡፡

ታላቁ አንዋር መስጂድና ሌሎችም መስጂዶች በጁምአ እለት የሚመጣውን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ማስተናገድ ስለሚሳናቸውና ስለሚሞሉ ህብረተሰቡ ውጪ አንጥፎ መስገዱ ባለፉት 15 ዓመታት የተለመደና የሚታወቅ ሀቅ ቢሆንም በሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ ብሄራዊ ጭቆናን እያሰፈነ ያለው መንግስት ሙስሊሞችን በሁሉም አቅጣጫ ለማጥቃት በማለም የተለያዩ ምክንያቶችን በመደርደር በተለይም ሴቶች ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ቀጥሎበታል፡፡

በዛሬው ድብደባ ጭንቅላታቸው የተፈነከተና ደም ይፈሳቸው የነበሩ ሴቶች እንደነበሩ የታወቀ ሲሆን ጥቂት የማይባሉ እናቶችና እህቶች ሰላታቸውን ሳይሰግዱ ወደ ቤታቸው ለመመለስ ተገደዋል፡፡ መንግስት የሃይማኖት አክራሪነትን እታገላለሁ በሚል ስም በሙስሊሙ ላይ ብሔራዊ ጭቆና በማስፈን ላይ ይገኛል፡፡ የዚህ ጭቆና ዒላዎችም ልክ ዛሬ እንደታየው አረጋውያን እናቶችና እህቶች ሆነዋል፡፡

የእምነት ነጻነትን አክብሪያለሁ እያለ ደጋግሞ በሚዲያ የሚናገረው መንግስት በሕገ መንግስቱ የተቀመጡትን የእምነት ነጻነት መብቶች በመጣስ ሙስሊሙ ላይ ከፍተኛ በደል በማድረስ ላይ ይገኛል፡፡ ሙስሊሙ ህብረተሰብ የራሱ የእምት ተቋም እንዳይኖረው ከማድረግ አንስቶ አዲስ እምነት በሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ በኃይል መጫን፣ የሙስሊሙን ማህበረሰብ መሪዎች ማሰርና ማሰቃየት፣ የመብት ጥያቄ ያነሱ ሰላማዊና ያልታጠቁ ዜጎችን መግደል፣ መስጂዶችን ማሸግ፣ ኢማሞችን ያለ ሕዝቡ ፍላጎት ከስራቸው ማፈናቀልና በራሱ ፍላጎት መንግስታዊ ኢማሞችን መተካት እና ሌሎችም በ21ኛው ክፍለ ዘመን ሊፈጸሙ የማይችሉ ተግባራትን መንግስት ያለ ምንም ሀፍረት ሲፈጽም ቆይቷል፡፡

አሁን ደግሞ በክልሎች ሲካሄድ እንደነበረው ሁሉ ሙስሊሙን ሕብረተሰብ ከሰላት ለማቀብና ለማሸማቀቅ ለመስገድ ወደ መስጂድ የሄዱ ሙስሊሞችን ለጸሎት በተቀመጡበት ድብደባ ሲፈጸምባቸው እየተመለከትን ነው፡፡ የዚህ አይነቱ ተግባር በኢትዮጵያ ታሪክ ቢያንስ ባለፉት 90 ዓመታት እንኳ ያልታየ ድርጊት የእምነት ነጻነት በሕገ መንግስት ደረጃ በተደነገበት በዚህ ወቅት እየተፈጸመ መሆኑ ሙስሊሙ ህብረተሰብ የመንግስትን አላማና ግብ በአንክሮ አንዲያጤነው የሚጋብዝ ነው፡፡ ባለፈው ዓመት በደሴ ሸዋ በር መስጂድ መስጂድ የሞላባቸው የከተማው ሙስሊሞች ውጪ አንጥፋችሁ ሰግዳቹሀል በሚል ፖሊስ ከፍተኛ ጥቃት ሰንዝሮ በርካቶችን ለእስርና አሰቃቂ ድብዳባ መዳረጉ ይታወሳል፡፡

መንግስት መሰል ሁኔታዎችን ኹከት ለመፍጠር የሚጠቀምባቸው በመሆኑ ሁኔታዎችን በትእግስት ከማሳለፍ በዘለለ ድርጊቱ ሲፈጸም ፎቶ ግራፍና ቪዲዮ ማንሳት ሊዘነጋ የማይገባ ተግባር መሆኑን ማስታወስ ያሻል፡፡

Top UDJP Official Nebiyou Bazezew in critical condition after assault

August 23, 2013
The Horn Times Newsletter August 22, 2013
by Getahune Berkeley-South Africa


UDJP tour bus mobbed by its diehard supporters in Fiche. (Pic minilik Salsawi)

UDJP tour bus mobbed by its diehard supporters in Fiche. (Pic minilik Salsawi)
Drunk with ethnocentric tyranny, the Ethiopian ruling minority junta under the leadership of Prime Minister Hailemariam Desalegn is continuing its crack down on opposition groups with devastating cruelty and mercilessness.

Currently, the inept and abusive regime and its cadres are focusing on the opposition party UDJP’s nationwide campaign for change under the banner of “millions of voices for change.”

According to Finotenetsanet weekly Amharic tabloid, as part of the naked assault on freedom of association, UDJP Addis Ababa zone executive committee member Nebiyou Bazezew Wubalem, 42, and colleague Messay Teke were severely assaulted and robbed by more than sixteen TPLF cadres in the town of Fiche; about 45 km north of the capital while on campaign to mobilize the local youth for Saturday 25 August 2013 peaceful march.

The incident took place yesterday 21 August 2013 at 9pm local time.
The injured duo have arrived in Addis Ababa this morning, 22 August for further medical attention and UDJP acted swiftly and decisively by sending another strong team to the town of Fiche.
The town’s deputy security chief, Haileeyesus Beyene, spearheaded yesterday’s well-coordinated attack and robbery on UDJP members.

“Nebioyu Bazezew Woubalem became a target before even going to the town of Fiche after his recent interview with you guys (the free media in exile). I spoke to him today at 12 o’clock and despite the ordeal he is in good spirit and raring to go. His injuries are not life threatening but he was in critical condition earlier. We all hope and pray that he will be back to work soon.” A close friend of the brutally mauled UDJP stalwart Ato Nebiyou Bazezew who requested anonymity told the Horn Times from Addis Ababa.

infohorntimes@gmail.com

የፍራቻ ፖለቲካ እና የፖለቲካ ፍራቻ -እውነቱ እና ፍርሃቱ

by Minelik S
የፍራቻ ፖለቲካ እና የፖለቲካ ፍራቻ -እውነቱ እና ፍርሃቱ በፍቃዱ ዘ ሃይሉ
የፍራቻ ፖለቲካ እና የፖለቲካ ፍራቻ - ጥንድ በኢትዮጵያ መሪዎችና ሕዝቦች መሀል የተጋረጡ የጦር መሳሪያዎች ናቸው፡፡ ሕዝቡ ካልፈራ ፖለቲከኞቹ የፍራቻ ፖለቲካ ይጫወታሉ፣ ፖለቲከኞቹ የፍራቻ ፖለቲካ ካልተጫወቱ ሕዝቡ ፖለቲካን ይፈራል፡፡ የሁለቱም ውጤት አንድ ነው፤ ውጤቱም ሕዝቡ መሪዎቹን የሚያስከፋ ነገር መናገርም ሆነ መተግበር ይፈራል፡፡

የፍራቻ ፖለቲካ፤ በገዢው እና ተቃዋሚዎቹ
ጥንት፣ ወትሮም ንጉሥ የማይከሰስ በመሆኑ መንግስታት ሕዝቦቻቸውን ማስፈራራታቸው የደንብ ያህል ነበር፡፡ ‹‹የተማረ ይምራን›› መባል ከተጀመረበት እና ደርግ የንጉሡን መንበር ከተረከበበት ጊዜ ወዲህም ግን ‹‹ደንቡ›› አልቆመም፡፡ ደርግ ‹‹አብዮቱን›› ሊቀለብሱ የሚንቀሳቀሱትን በሙሉ እንደማይምራቸው በሕዝብ ፊት ምሎ ዘመተባቸው፡፡ አብዮቱን ከሚቀለብሱት እንዳንዱ ላለመሆን የፈራ በሙሉ የኢሠፓ አባል ሆኖ በወንድሙ ላይ ዘመተ፡፡ ቀሪው ‹‹መሀል መስፈር›› የፈለገውም፣ ከፍራቻው’ጋ እንደተሟገተ 17 ዓመታት ኖረ፡፡
ኢሕአዴግ ቀርቶ የፍራቻ ፖለቲካ የቀረ ከመሰለ በኋላ ግን መልኩን ቀይሮ መጣ፡፡ አብዮቱን መቀልበስ፣ ሕገመንግስቱን መቀልበስ በሚል ተተካ፡፡ መንግስት የተቃወመውን ሁሉ በሆነ ስም በመፈረጅ ስለሚወነጅል፣ ላለመፈረጅ የሚሰጋው ሁሉ ወደወጣበት ምሽግ ተመልሶ ገባ፡፡ ‹‹ፖለቲካ እና ኮረንቲ›› የሚለው አባባል የተፈጠረው ያኔ ነው፡፡
የፍራቻ ፖለቲካን፣ ኢሕአዴግ በሌላም አካሔድ ይጫወትበታል፡፡ እንደገዢው ፓርቲ ዲስኩር ከሆነ፣ ኢሕአዴግ ከወረደ ወይም ተቃዋሚዎች ወደስልጣን ከወጡ የብሔር ብሔረሰቦች ጥያቄ/ነፃነት ተዳፍኖ ይቀራል፣ የሃይማኖቶች እኩልነት አደጋ ላይ ይወድቃል፣ ልማቱ ይደናቀፋል… ወዘተ፣ ወዘተ፡፡
የዚህኑ ግልባጭ ተቃዋሚዎችም ይጠቀሙበታል፡፡ ኢሕአዴግ ካልወረደ ብሔር ብሔረሰቦች እርስ በእርሳቸው ይባላሉ፣ የኢትዮጵያ አንድነት እመቃብር ይወርዳል፣ ሃይማኖተኞች ጽንፈኛ ይሆናሉ፣ ኢኮኖሚው ተጣምሞ ይቀራል… ወዘተ፣ ወዘተ፡፡ ሙግቶቹ እውነትነት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ነገር ግን የፖለቲካዊ ጫወታም ሆነ የምጣኔ ሃብታዊ ትንታኔ እና ትንቢት ለማይገባው ምስኪን ግን ያኛው ከመጣ፣ ይሄኛው ከወረደ ወይም ያኛው ካልመጣ ይሄኛው ከሰነበተ ነገሩ ሁሉ ምስቅልቅሉ ወጥቶ፣ ሕዝቦች ሁሉ አደጋ ላይ ወድቀው…በሚል ፍርሃት ሙሉ ራዕይ ታቅፎ ይቀራል፡፡ ለሁሉም እንደመፍትሄ የሚቆጥረው ደግሞ ሽሽት /ስደትን/ ነው፡፡
የፖለቲካ ፍራቻ፤ በተመልካቹ ሕዝብ
የ2011 Legatum Prosperity Index፤ ኢትዮጵያን ከ110 አገሮች ጋር አወዳድሮ በብልፅግናዋ 108ኛ ባስቀመጠበት ሪፖርቱ Safety & Security ንዑስ ዘርፍም 106ተኛ ይበቃሻል ለማለት ያበቃውን ምክንያት ሲዘረዝር፣ “The Ethiopian government has been known to engage in political violence and, globally, Ethiopia is the country where expression of political views is perceived by the population to be most restricted. This may be contributing to the rate of flight of professionals, intellectuals, and political dissidents, which is among the 20 highest rates in the world.” (‹‹የኢትዮጵያ መንግስት በፖለቲካዊ አመጾች ላይ እጁን በማስገባት ይታወቃል፣ በዓለምአቀፍ ደረጃም ኢትዮጵያ ፖለቲካዊ አመለካከትን ማንፀባረቅ በጣም የተገደበባት አገር ተደርጋ በዜጎቿ ትታሰባለች፤ ይህ ምናልባትም፣ ከዓለማችን ችግሩ የከፋባቸው 20 አገራት መካከል ኢትዮጵያን ላሰለፋት፥ የባለሙያዎች፣ ምሁራን እና ፖለቲከኞች ስደት መንስኤ ሳይሆን አይቀርም፡፡››) ብሏል፡፡
Personal Freedom ብሎ በሰየመው ንዑስ ዘርፍም ኢትዮጵያ ውራ (110ኛ) ሆናለች፡፡ ሲዘረዝረውም እንዲህ ብሎ ነው፤ “Ethiopia ranks among the bottom 10 countries for citizens’ freedoms in expression, belief, association, and personal autonomy.” (‹‹ኢትዮጵያ ለዜጎቿ ሐሳብን፣ እምነትን፣ ማሕበርን፣ እና የመግለፅ ነፃነት፣ እና የግል አቋምን ለማንፀባረቅ ከማይመቹ የዓለማችን 10 አገሮች ተርታ ትሰለፋለች፡፡››)
ሐሳብን ለመግለፅ ካለመቻል ጀርባ ብዙ ምክንያቶች አሉ፡፡ ኢትዮጵያውያን የማይገልፁት/ለመግለጽ የሚፈሩት ፖለቲካዊ አመለካከታቸውን ብቻ አይደለም ሃይማኖታዊ፣ ፆታዊ ጉዳዮቻቸውንም ጭምር ነው፡፡ ለዚህ አንዱ አስተዋፅዖ አዋጪ ‹‹የመቻቻል ምሳሌ›› የሚባለው ነገር ግን ‹‹መቻቻልን›› በጥያቄ ምልክት ውስጥ ያስቀመጠው ባሕላችን ነው፡፡ ‹‹መቻቻል›› በአገራችን አናሳው ብዙሐኑን ሲችል በሚል እሳቤ ተውጦ መክረሙ አጨቃጫቂ አይደለም፡፡ ስለዚህ አፈንጋጭ አመለካከቶች እውነታ ቢኖራቸውም እንኳን ተቀባይነት አይኖራቸውም፣ ሌላው ቀርቶ አፈንጋጭ አሳቢው ከሐሳቡ’ጋ ተግባብቶ እንዳይኖር ዱላ ይበዛበታል፡፡ ይህ ባሕል የወለደው ፍራቻ ፖለቲካዊ አስተሳሰብን የማንፀባረቅ፣ አንፀባርቆ ተቀባይነት የማጣት ፍራቻን ይወልዳል፡፡
ሕዝባችን ይፈራል፣ እንዲፈራም ታሪኩ ያስገድደዋል፤ ነገር ግን የሚፈራው በብትር የሚቀጣውን መንግስት ብቻ ሳይሆን በቃላት እና በማግለል የሚቀጣውን የራሱን ማኅበረሰብም ጭምር ነው፡፡ በዚህም የራሱን ሐሳብ ለራሱ አፍኖ በማለፍ ለአገሪቱ ለውጥ የሚበጁ በርካታ አማራጭ ሐሳቦችን አፍኖ ገድሏል፡፡ ይህንን ዓይነቱን ሕዝባዊ ፍራቻ አምባገነን መንግስታት ይፈልጉታል፣ እንዲለመልም እንጂ እንዲኮሰምን አያደርጉም፡፡ ለአምባገነን መንግስታት፣ ፍርሃት ከሰራዊቱ ይልቅ ሕዝቡን ከተቃውሞ ያቅብላቸዋል፡፡
በአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ደፋር ጋዜጠኞች፣ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች እና አፈንጋጭ ሃይማኖተኞች ሲገደሉ ነበር፣ እየታሰሩ እና እየተሳደዱ ነው፡፡ ይህ እውነታ ግን ከሕዝባዊው የፍራቻ አድማስ የበለጠ አይደለም፡፡ በግሌ የኢሕአዴግ መንግስትን ካጠነከሩት ጉዳዮች መካከል የሕዝቡ ፍራቻውን ከእውነተኛው ስጋት (risk) በላይ ማግነን እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ ለዚህም ነው ይህንን መጻፌ!
"መፍራት ያለብን ብቸኛው ነገር ፍርሃትን እራሱን ነው" እንዲሉ ፍራንክሊን ዲ. ሩዝቬልት፣ ፍርሃታችንን እንፍራው፡፡

ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ ወደ ሃገሯ ለመመለስ በተዘጋጀችበት ወቅት እራሷን በገመድ አንቃ ገደለች

በትላንትናው እለት በሳኡዲ አረቢያ አስደንጋጭ የሆነ ትእይንት ተፈጥሮአል ፡ይሄውም በቤት ሰራተኝነት ለሁለት አመት አገልግሎት ወደ ሳኡዲ አረቢያ ሄዳ ሁለት አመቷን አጠናቃ ወደ ሃገሯ ለመመለስ ጊዜዋን በጨረሰችበት ወቅት እና እንዲሁም አሰሪዎቿ የሰራተኝነት ቪዛዋን ፣የጊዜ ገደቡን እንዲጨርስ አድርገው ጨርሰውላት ለመሄድ በተዘጋጀችበት ወቅት እራሷን ለማጥፋት በመወሰን በመኝታ ቤቷ በመግባት በገመድ እርሳሷን አጥፍታለች ሲሉ አሰሪዎቿ ለመገናና ብዙሃኖች ተናግረዋል ::
 
ምን እንደነካት አናውቅም እኛንም አስገርሞናል አስደንግጦናል ለሁለት አመታት ከእኛ ጋር ስትሰራ ምንም ችግር የለባትም ያለ ጊዜ ገደቡ የቪዛዋን ጉዳይ ጨርሰን በጠየቀችን መሰረት ልንሸኛት ሁላችንም በተዘጋጀንበት ሰአት እርሷን አጥፍታለች ያሉት አሰሪዋ ከሚኖሩበት ደቡባዊ ሳኡዲ አረቢያ ከሃሚስት ሙሽህቲ ከተማ አካባቢ ነው ።እስካሁን የማንነቷ ጉዳይ አልታወቀም !

Thursday, August 22, 2013

Anti-terrorism decree: Born from power thirst

by Reeyot Alemu, Ethiopia

The article has been translated from the Amharic original for the International Women Media Foundation. The author,

a columnist for the now-defunct Ethiopian newspaper Feteh, is currently serving a 5-year prison sentence in Addis Ababa on bogus terrorism charges. The International Women’s Media Foundation honored Alemu with its 2012 Courage in Journalism Award last year, and in May 2013, the UNESCO recognized her “commitment to freedom of expression” with its Guillermo Cano World Press Freedom Prize.

Many questions cross my mind when I look at the “‘Anti-Terrorism Decree” and its application. Why does this decree have paragraphs that violate human rights? Why does it prosecute innocent citizens who have no ties to terrorism or terrorist organizations? I ask myself. In order to answer these questions one needs to look at the reasons behind the creation of such a decree, and so I did.

Why was the anti-terrorism decree written? One needn’t look too far to realize that the ruling party, EPRDF, didn’t create these anti-terrorism laws because it faced a real threat. You only need to look at the individuals who are either facing such charges, or have already been found guilty under this decree. Members of the opposition party who have denounced human rights violations and have peacefully called for the replacement of the current regime by a more democratic one,

freethinkers who dared ask stern questions to officials at locally organized discussion forums, leaders of the Muslim community who refused to dilute and redraft their religious beliefs to appease the government’s stance on religion, and ourselves, members of the free press who performed their duty as voices of the people have been the main victims of this anti-terrorist decree.

This proves that the real purpose of this decree is to enable the current regime to comfortably rule without any criticism, opposition, or competition. These actions are not creations of the EPRDF, instead they are old tried and true methods copied from other brutal regimes. It is very well known that colonial regimes of the past found it convenient to label the freedom fighters that refused to kneel as “terrorists.” And today, the EPRDF travels this same colonial path by stuffing its prisons with its own citizens and punishing those of us who have refused to give up our human and citizenship dignity.

What is to be done? Stopping the gross human rights violations that the EPRDF is committing under the guise of the anti-terrorism decree requires a lot of work. The current anti-terrorism decree will have to be replaced by a more appropriate one. Even with such changes, as long as the judicial system leans in favor of the EPRDF such arrests will continue. For, those of us who are currently imprisoned would have been found “not guilty” had we been judged fairly, even under the current anti-terrorism decree. As such, demonstrations and movements aimed at this decree, and more importantly at the ruling EPRDF who seeks to illegally use it, shall be strengthened and continued.

The reason I strongly believe that these protests should primarily be aimed at the ruling party is because it is the source of the wrongful application of this law and other innumerable Ethiopian problems. We have observed with disgust the length this regime will travel to protect its grip on power, and its rule. In other words, the actions of the EPRDF are based on motives that are tied to ethnicity, power hunger, and unjust prosperity among others. In Arthur Gordon’s words “If one’s motives are wrong, nothing can be right.” Because of this, nothing good can be expected from the EPRDF.

Therefore our only option for change remains a modern and peaceful struggle wherein we should be prepared to provide the needed sacrifices. As we embark on this journey to transform the system, there are many related issues that we should consider. We should deeply consider all the challenges set forth by the ruling party whether they are the ethnic, religious, ideological, or the interest based divisive elements it nourishes. We shall learn how to unite our many fronts of struggle into one.

Looking forward, it is the role of any responsible citizen, and especially that of the opposition parties and related groups, to think of and discuss  the nature of the system that shall proceed the current one. For as long as we accomplish these required duties, and stay  firm in our convictions, a Bright Day will not be too far.

ለእምነት ነፃነት የምናደርገውን ትግል ለሰብዓዊ መብቶች መከበር፣ ለዜግነት ክብር እና ለሀገር ነፃነት ከምናደርገው ትግል ጋር እናቀናጅ!!!


       
ትንሽነቱ በፈጠረበት ስጋት ምክንያት ሁሉንም ነገር ካልተቆጣጠረ በጉልበት የያዘውን ሥልጣን የሚያጣ የሚመስለው እና በዚህም ሳቢያ ሁሉም ነገር ውስጥ እጁን የሚነክረው ወያኔ ራሱን በገዢነት ከሾመበት እለት ጀምሮ የሃይማኖት ተቋማትን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር እንደተጋ ነው። በእኛ በኢትዮጵያዊነት ዳተኝነት ታግዞም ትጋቱ ውጤት እያስገኘለት ነው።

ወያኔ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክህነትን ከፓትሪያርክ ጀምሮ እስከ ደብር አለቆች ድረስ ያለው መንፈሳዊ ሹመት ተቆጣጥሯል። አሁን የቀየረው የቤተክርስቲያኒቷን ሃይማኖታዊ ቀኖናን መቀየር ነው። ወያኔ በሥልጣን ላይ ከቆየ ይህንንም ከማድረግ የማይመለስ መሆኑን በእስልምና እምነት ላይ ተግባራዊ እያደረገ ካለው መገንዘብ ይቻላል።

ልክ እንደ ክርስትናው ሁሉ ወያኔ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን (መጅሊስ) በራሱ ካድሬዎች ሞልቶት ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮታል። እስልምና ላይ ግን የሃይማኖት ተቋማትን ከመቆጣጠር አልፎ በቀኖና ጉዳይ በመግባት የራሱን “ምርጥ እስልምና” እያስተዋወቀ ነው። ዛሬ በሙስሊሞች ላይ የመጣው ነገ በክርስቲያኖችም ላይ የሚመጣውን አመላካች ነው።

እርግጥ ነው ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች የወያኔን ጥቃት በፀጋ አልተቀበሉትም። ሁሉም በየራሳቸው መንገድ የወያኔን ሁሉን-ጠቅላይ አገዛዝ እየተቃወሙትና እየታገሉት ነው። ዛሬ የወያኔ ጥቃት የደረሰበት ደረጃ ግን የሁለቱን ሃይማኖቶች አማኖችን ኅብረት የሚጠይቅ ሆኗል። ወያኔ ደግሞ በበኩሉ ይህ መከባበርና መተባበር እንዳይኖር ጥረት እያደረገ ነው።

የሁለቱም ትላልቅ ሃይማኖቶች ምዕመናን ለእምነታቸውና ለእምነት ተቋሞቻቸው ነፃነት በሚታገሉበት በአሁኑ ሰዓት “ጅራፍ እራሱ ገርፎ ራሱ ይጮህ” እንዲሉ ወያኔ ድምፃቸውን ቀምቶ በደሉን ለማጠናከር እየተጠቀመበት ነው። እፍረት ያልፈጠረባቸው የወያኔ ሹማምንት “መንግሥት በእምነታችን ጉዳይ ጣልቃ አይግባብን” እያሉ አቤት የሚሉትን ምዕመናንን “በፓለቲካ ጉዳይ ጣልቃ ገባችሁ፤ ይህ ደግሞ በኛ ሕግ ክልክል ነው” እያለ ይከሳቸዋል።

“ሃይማኖት በመንግሥት፤ መንግሥትም በሃይማኖት ጉዳዮች ጣልቃ አይገቡም” የሚለውን ሰፊ ተቀባይነት ያለው መርህ ወያኔ መሠሪ በሆነ ተንኮሉ “ሃይማኖት በፓለቲካ፤ ፓለቲካም በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገቡም” ወደሚል እጅግ አደገኛ መርህ እየቀየረው ነው።

“በሃይማኖትና መንግሥት” እና “በሃይማኖትና ፓለቲካ” መካከል ያለው ግዙፍ ልዩነት ለአብዛኛው ምዕመን ግልጽ አይደለም በሚል ግብዝነት ነገሮችን በማጣመም ምዕመናንን በማደናገር ለፍረጃ ያመቻቻቸዋል።

አዎ ሃይማኖትና መንግሥት መለያየት አለባቸው። ኢትዮጵያዊ ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች እየጠየቁ ያለውም ወያኔ ይህንን መርህ እንዲያከብር ነው። “ወያኔ ሆይ!!! በሃይማኖታችን ጉዳይ ጣልቃ አትግባብን!” እያሉት ነው።

ሃይማኖትና ፓለቲካ ግን በብዙ ክሮች የተቆላለፉ ነገሮች ናቸው። ለሃይማኖት ነፃነት መከራከር ራሱ ፓለቲካ ነው። ለሰብዓዊ መብቶች መከበር መከራከርም ትልቅ ፓለቲካ ነው። የሁለቱ ሃይማኖቶች አማኞች ይከባበሩ፤ ይተባበሩ ማለትም ፓለቲካ ነው። ይህ እንዳይፈጠር ነው ወያኔ ሃይማኖትና ፓለቲካ እሳትና ጭድ አድርጎ ሊስላቸው የሚዳዳው።

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ኢትዮጵያዊያን ምዕመናን በሃይማኖትና ፓለቲካ አንድነትና ልዩነት ላይ የጠራ አቋም መያዛቸው ትግላችን ያግዛል ብሎ ያምናል።

ሃይማኖትና መንግሥት መለያየታቸው ተገቢ ነው። ሃይማኖትና ፓለቲካ ግን አንድ ባይሆኑም በብዙ መንገዶች የሚደጋገፉ ናቸው። ሃይማኖቶች ለእምነት ነፃነት፣ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር፣ ለዜግነት ክብር፣ ለሀገር ነፃነት እና መሰል ጉዳዮች በግንባር ቀደም መታገል ይኖርባቸዋል። በታሪካችን ውስጥ ታቦቶች ጦር ሜዳዎች ዘምተው አርበኞችን አበረታተዋል። ይህ ዛሬም ሊደረግ የሚገባው የተቀደሰ ተግባር ነው።

በዛሬ የአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ሃይማኖትና የሃይማኖት ተቋማትን ከወያኔ መዳፍ ማውጣት ሀገርን ከወያኔ መዳፍ ከማዳን ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ጉዳይ ሆኗል። ስለሆነም ለሃይማኖት ነፃነት የምናደርገው ትግል ለሀገራችንም የምናደርገው ትግል አካል ነው።
ወያኔ በሃይማኖቶቻችን፣ በሀገራችን ብሎ በራሳችን ላይ የመጣ እኩይ ኃይል ነው።

ስለሆነም፣ ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ለሃይማኖት ነፃነት የምናደርገውን ትግል ለሰብዓዊ መብቶች መከበር፣ ለዜግነት ክብር እና ለሀገር ነፃነት ከምናደርገው ትግል ጋር እንድናቀናጅ ወገናዊ ጥሪ ያደርጋል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

ሰላሳ ሶስቱ ፓርቲዎች -ሰማያዊ ፓርቲን ከፓርቲዎች የትብብር መድረክ አሰናበቱ።

ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የ33ቱ ፓርቲዎች የትብብር መድረክ -ሰማያዊ ፓርቲን ያሰናበተው፤የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ሰሞኑን ለ ሰንደቅ ጋዜጣ የሰጡት ቃለምልልስ የሌሎች ፓርቲዎችን ክብር የነፈገ ነው በሚል ነው።

በዚህም መሰረት ፓርቲዎቹ ባደረጉት ስብሰባ ሰማያዊ ፓርቲ ከስብስቡ እንዲወጣ መወሰናቸውን የቪኦኤ ዘገባ ያስረዳል።
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ፀሀፊ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ ውሳኔው የተላለፈው ባለፈው እሁድ በተካሄደ አስቸኳይ ስብሰባ እንደሆነ  ገልጸዋል።

አቶ ይልቃል ለሰንደቅ በሰጡት ቃለ ምልልስ በዚህች አገር ከሰማያዊ ፓርቲ ውጪ ሌላ ተቃዋሚ ፓርቲ አለ ብለው እንደማያምኑ መገለፃቸው ይታወሳል።

“ገዥው ፓርቲና ምርጫ ቦርድ የሰጡንን ዕውቅና ሳይቀር አቶ ይልቃል ነስተውናል”ያሉት የመኢአድ ፀሀፊ፤ህዝቡ በፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ እምነት እንዳያድርበት ደባ ስለፈጸሙ፤ ድርጊታቸውን እንዲያርም ጊዜ ቢሰጣቸውም ሊያርሙ ስላለረቻሉ፤ ይባስ ብለውም ያንኑ ሃሳባቸውን ፡”የኛ ፕሬስ”በተሰኘ ጋዜጣ ላይ በማንፀባረቃቸው እና አቋሙ የ እርሳቸው ብቻ ሳይሆን የፓርቲያቸው ጭምር እንደሆነ በመረጋገጡ ከስብስቡ እንዲሰናበቱ ወስነናል ብለዋል።

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ይልቃል በበኩላቸው “የሰጠሁት አስተያየትና ያንፀባረቅኩት ሃሳብ አዲስ አይደለም፤ እውነትም    ነው”ብለዋል።

እስካሁን ሌሎች ፓርቲዎች የከፈሉትን መስዋዕትነት እርሳቸውና ፓርቲያቸው እንደሚያደንቁ ለቪኦኤ የተናገሩት አቶ ይልቃል፤ይሁንና ተቃዋሚዎች በአሁኑ ጊዜ የህዝብን የለውጥ ጥያቄ ለመመለስ በሚያስችል ጥንካሬና አቋም ላይ አለመሆናቸውን ገልጸዋል።
“እኔ ስህተተኛ ብሆን ደስታዬ ነበር”ያሉት አቶ ይልቃል፤”እነዚህ ፓርቲዎች ነን እንደሚሉት ቢሆኑ እኔና ጓደኞቼ ሰማያዊ ፓርቲን አፍርሰን ወደየሌሎች ፓርቲዎች እንገባለን፤ወይም ወደየቤታችን እንሄዳለን”ብለዋል።

“ግን እውነቱ ሌላ ነው። የኢትዮጵያን ችግር መጋፈጥ አለብን ካልን እውነቱን ማድበስበስ የለብንም” በማለት ቀደም ሲል በሰጡት አስተያዬት እንደሚያምኑ በድጋሚ አረጋግጠዋል።

32 suspected of organizing protests in Kucha fired

ESAT News  August 22, 2013

Thirty-two people that were suspected of organizing the opposition and protests in Kucha Woreda, Selam Ber town, Gamogofa Zone of Southern Ethiopia, have been fired from their jobs. Among whom are 2 prosecutors, 2 judges, 1 court registrar and a police officer. Eight others have left their jobs and fled to other regions. Sixteen more people have been arrested in the past weeks alone.

Over 40 people, who include people that were detained since last month, had appeared in Court yesterday and were given another appointment to August 30, 2013. Worried that the tensions might turn into violence, 60 elders of the Woreda have travelled to Addis Abeba to speak to Federal government officials yesterday. A month ago, some elders that had travelled to Addis Abeba on a similar mission have been detained. Masebo Madalcho, investor and prominent elder of the area, has been detained three days ago.

Over 160 Bajaj motorcycles, suspected of serving as information conduits between the districts, are still seized by the police. ESAT has learnt that the elders that travelled to Addis Abeba will warn the Federal government officials that the local community will take its own measures unless the government stops evicting civil servants and detaining people, which the government will be responsible for.

The Unity for Democracy and Justice Party (UDJ) had called on the government to immediately find solutions to the “rights and identity” questions of the residents of Kucha Woreda.

ESAT’s attempt to speak to Ethiopian government officials on the issue was unsuccessful.

አሳ ጐርጓሪ ዘንዶ ያወጣል (ክፍል ፭)

ugust 22, 2013

ናደዉ፦ከዋሽንግተን ዲሲ
የወያኔ ጉጅሌዎችን ስዉር አጀንዳ ፅሁፍ ከዚህ ሆድ አደር ተላላኪ ታሪክ በኋላ ወደ ሌሎቹ እዘምታለሁ፤በማህበር ተጠርንፈዉ እስከሚመጡልኝ ወይም እስከሚመጡብኝ ድረስ ማጋለጤ በሰፊዉ ይቀጥላል፧ለጠላቴ አልተኛም እንደ በትናቸዉ/ፍርሻው ስንሻዉ የታች አርማጭሆ ልጅ መሆኔ ቀረ?!
ምርጫዉ ስንሻዉ ወይም ብዙዎች የዲሲና አካባቢዉ ነዋሪዎች እንደሚጠሩት በትናቸዉ/ፍርሻው ስንሻዉ ባለፈዉ እሁድ ደግሞ አዲስ የጥላቻና የጋጠወጥ ስድብ ከረጢቱን ዘረገፈዉ፣ አዎ በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ በሚገኙት በሙስሊሙ ሕብረተሰብ መሪ በፈርስቲ ኢጂራ ፕሬዘዳንት በሼክ ነጂብ ላይ፧ በወያኔ ጉጅሌ በጀት በሚተዳደረዉ ወናፍ መንደርተኛ ራዲዮኑ እሳቸዉን ብቻ ሳይሆን ባለቤታቸዉንና የሙስሊሙን ሕብረተሰብ የድምፃችን ይሰማ እንቅስቃሴም ጭምር፥እንደወያኔ አስተዳዳሪዎቹ ሁሉ እሱም ሲሳደብ ዉሎ አደረ ፧ተወካያቸዉ መሆኑም አይደል?!መሽቶ ነጋ በቅዳሜ ማታና በእሁድ ቀን ፕሮግራሞቹ፤እኔም በዚህ ባንዳ ዙርያ በተከታታይ ለማወጣቸዉ ፅሁፎቼ ስል አለፍ አለፍ አድርጌ መቅረፀ ድምፄን ይዤ መከታተሌ አልቀረም፧ሚስቴና ልጆቼን ተደብቄ በሌሉበት መሆኑ ይታወቅልኝ !ምክንያት፥የዚህን ተሳዳቢ ሰዉዬ ቱማታ ላለመስማት ቤቱን ጥለንልህ እንዉጣ የሚለዉ ብስጭታቸዉ ስላሳሰበኝ ብቻ !!
ለእለቱ ለስድብ ኢላማነት የተመረጡትን እኝህን የሀይማኖት መሪ እንዲህ አለ፦ በአክብሮት ዘለፋዬን እርስዎም ባለቤትዎም የሀይማኖትዎም ተከታዮች በጥሞና ያዳምጡኝ ብሎ የራዲዮን ፕሮግራሙን ጀመረ፣የተለመደዉን የጥላቻ ስድብ ዉርጅብኝ በይሉኝታ ቢስና ፀያፍ ቃላቶቹ ለቀቀዉ አዎ እሱ ማንን ፈርቶ?!
ዛሬ ገና ለዚህ ተከታታይ ፅሁፌ ተገቢና ትክክለኛ ርእስ መስጠቴን አረጋገጥኩ። አሳ ጐርጓሪ ዘንዶ ያወጣል። ያልኩትን፧ በትምህርተ ጥቅስ አስቀመጥኩት፤ ለምን እንዲህ አልክ ብትሉኝ መልሴ እንደሚከተለዉ ይሆናል፧! እኚህ ሰዉ ስለዚህ መሰሪ የደርግ ካድሬ ብዙ ምስጢር እንደሚያዉቁ ስለማዉቅ ብቻ ሳይሆን ዛሬ የሚያዉቁት ነገር ምናልባትም ላለፉት አስርተ አመታት ለዋሽንግተን ነዋሪ ኢትዮጵያዉያን ያልተናገሩትን የደራሽ ግብረሃይል ምስጢር የሚያጋልጡበት ወቅት አሁን በመሆኑ ነዉ። ሳይቸግረዉ የነካካቸዉ ይመስለኛል፧ያዉም የሞራል ህልዉናን በሚፈታተን መልኩ፥ለዚህ ወስላታ የመልስ ምት አያስፈልገዉ ብለዉ ነዉ ሃጂ?! ነገሩ እንዲህ ነዉ በክፍል አንድና ሁለት ላይ በግልፅ እንዳሠፈርኩት የዛሬ አስር አመት አካባቢ አገራችን ኢትዮጵያ በከፍተኛ ረሀብና ድርቅ በተጠቃችበትና አላፊነት የጎደለዉ የህወሀት ዘረኛ አምባገነን አገዛዝም ሁኔታዉን ለመደበቅ በሚድበሰበስበት በዚያን ወቅት የዓለም አቀፍ የዜና ማሰራጫዎች ሁኔታዉን ገሀድ ማዉጣታቸዉ እርግጥ ነዉ። በወገኖቻችን ላይ ደርሶ የነበረዉ አስከፊ ሁኔታ ወያኔን ከመታገል ጎን ለጎን ለተጎዱት ወገኖች በአፋጣኝ መድረስ ጊዜዉ ግድ ይል ነበር። በዚህም መሰረት በዳያስፓራ የሚገኙት አገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያን ትልቅ ድርሻ አበርክተዋል በዋሽንግተንና አካባቢዉም በተመሳሳይ መልኩ ከተጎጂ ወገኖቻቸዉ ጎን ለመቆም መንቀሳቀሳቸዉ አልቀረም። ይህንኑ የወገን ጥሪ ምላሽ ለመስጠት ሲባል በተቋቋመዉ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ግብረሃይል ዉስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ በማድረግ ከሁለት መቶ ሽህ ዶላር በላይ ተሰበሰበ የተሰበሰበዉንም ገንዘብ ደራሽ ግብረሃይል የሚል ስያሜ ለተሰጠዉ ኮሚቴ በአደራ በአደራ አስረከበና ዉጤቱን መጠባበቅ ጀመረ። በጊዜዉ ከኮሚቴዉ አባላት ዉስጥ በግምባር ቀደምትነት የሚጠቀሱት የኢትዮጵያዊነት ራዲዮኑ ጓድ ምርጫዉ ስንሻዉ፤የሀገር ፍቅር ራዲዮኑ ባንዳዉ ንጉሴ ወልደማርያም፤የፈርስቲ ኢጅራዉ ፕሬዘዳንት ሃጂ ነጂብና ሲስተር እማዋይሽ ነበሩ። ተወካዮቹ በአካል ተገኝተዉ ለተጎጂ ወገኖቻችን አስፈላጊዉን ቁሳቁስ ገዝተዉ አንዲሰጡ የሕዝብ አደራ ተቀበሉ ፧አደራዉን ግን በሉት።
እንዲህ ሆነላችሁ የተከበራችሁ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቼ፧ የኮሚቴዉ ተወካዮች አዲስ አበባ ቦሌ አለምአቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ እንደደረሱ በወያኔ ካድሬዎችና ሰላዮች ታጅበዉ ወደተዘጋጀላቸዉ ሸራተን ሆቴል አመሩ፧ ከተለያዩ ባለስልጣኖችም የምስጋናና የእንኳን ደህና መጣችሁ ስልኮች አቃጨሉላቸዉ የኰሚቴዉ መሪ የነበረዉ ሆድ አደር ተላላኪዉ ንጉሤ ወልደማርያም ከመመሪያ ጋር በእለቱ በሆቴል ክፍሉ ዉስጥ የወያኔ አባልነት ፎርም መሙላቱን የከብት ሕክምና ባለሙያዋ ባለቤቱ ታወራለች። በተያዘላቸዉ ምርጥ ክፍል አርፈዉ ለጥቂት ቀናት በከተመዉ ዉስጥ ከተዝናኑ በኋላ ፧ከየአቅጣጫዉ ከአገር ዉስጥም ሆነ ከዉጭ አገር በተጎጂዎች ስም በሚጎርፍለት ገንዘብ የሰከረዉ ወያኔ መልእክተኞቹን በቴሌቪዥን መስታወት ለጥቂት ደቂቃዎች ከሌሎች ለጋሾች ጋር ቀርበዉ ሁለት መቶ ሽህ የኢትዮጵያ ብር በጊዜዉ የወያኔ የአደጋ መከላከል ኰሚሽን ኮሚሽነር ለነበሩት ለአቶ ስምኦን መቻሌ ያስረክቡና በሌላ የክህደት ፕሮግራም ለመገናኘት ተማምለዉ ይለያያሉ። ከመሐል አንድ እህታችን ብቻ በነገሩ ግራ በመጋባት ይህንን የህዝብ አደራ በልነትን ታወግዛለች ወደ አሜሪካ ስትመለስ ለማጋለጥም ለራሷ ቃል ትገባና ዋሽንግተን በገቡ ማግስት ጀምሮ በተለያዩ ራዲዮኖች እየቀረበች ወገኖቼ የረሀብተኛዉ የእርዳታ ገንዘብ ተበላ እያለች መጮህዋን ትቀጥላለች ፧ቀሪ የኰሚቴ አባላትን ጨምሮ በአማላጅ ሁኔታዉ ይፋ እንዲወጣ ታስጠይቃለች ነገር ግን የሚሰማት ጠፋ ። አንድ እለት ብቻ ጓድ በትናቸዉ ስንሻዉ ከሕብረተሰቡ ዛቻና ማስፈራርያ ሲበዛበት በራሱ ራዲዮ ላይ ወጥቶ ሃምሣ ሽህ ዶላር ብቻ መቅረቱንና ይህም ገንዘብ ወደፊት የሕዝብ ዉሳኔ ያገኛል ብሎ ለፈፈ፤ከዚያ ቀናት ሳምንታትን ሳምንታት ወራትን ወራት አመታትን አስቆጠሩ እነሆ ዛሬ አስርተ አመቱ ተቆጠረ ነገሩ የተረሳ ከሀዲ ቀማኞቹም ለይቶላቸዉ ወያኔ በፍርፋሪ ከጎኑ በግልፅና በስዉር አሰልፏቸዉ በሚመፀወቱት የራዲዮን የአየር ሰአት እንደገና ይሰድቡናል ያላግጡብናል፣ ገንዘቡንና ጊዜዉን የተበላዉ ነዋሪም አፈር ብላ ብሎ ተራግሞ ወደ ቤቱ ገባ ብዙዎች ግን በተለያዩ ቦታዎች የነዚህን ከሀዲዎች ፀያፍ ተግባር ዛሬም ያስታዉሳሉ። ይህ የህዝብ ገንዘብ ነዉ ያለንበት አገር ደግሞ የህግ የበላይነት ይከበራል የተበላዉ በረሀብ ለተጎዱ ወገኖች የተዋጣ ገንዘብ ነዉ የፈለገዉ ያህል ጊዜ ቢቆይም ጉዳዩን በሕግ ፊት ማቅረብ ይቻላልና የህግ ባለሞያ ኢትዮጵያዉያንን ነገሩን እንዲመረምሩት በዚህ አጋጣሚ አሳስባለሁ!
አሁንም በቅርቡ በዚያ በዘራፊዎቹ ንኡስ ኰሚቴ ዉስጥ የነበሩ አዛዉንትን አግኝቼ ሳነሳባቸዉ ነገሩ እንደዉስጥ እግር እሳት ያንገበግበኛል አሉ ወንጀለኞቹን እነ በትናቸዉ ስንሻዉን ዛሬም ምርር ብለዉ በፊቴ ተራገሙ በተጨማሪም እንዲህ አሉኝ በዚያን ወቅት ተጨንቄ ሃጂ ነጂብም ዘንድ ሄጄ እዉነቱን ለሕዝቡ ንገሩ ብዬ ብጠይቀዉ ዳግም አጠገቡ እንዳልደርስ አባረረኝ አሉና ሁኔታዉን ጊዜ እንዳመቻቸዉ የሚያዉቁትን ሁሉ በተገኘዉ ሚዲያ ገሃድ እንደሚያደርጉት ገለፁልኝና ተሰነባበትን።
በመጨረሻ ማሳሰብ የምወደዉ ሃጂ ነጅብ የሚያዉቁትን ይንገሩንና እርስዎም ከሕሊና ወቀሳ ይገላገሉ፣በብዙ ሀይማኖቶች ሲነገር የምንሰማዉ፦ ሌባና ሌባ ሲሰረቅ አይቶ እንዳላየ የሆነ ፧የሁለቱም ወንጀል አንድ ነዉ ይባል የለ?!እና እነዚህ ወሮበሎች ስለዘረፉት ገንዘብ የሚያውቁትን ይንገሩን እግረመንገድዎንም ከሃሜቱ ነፃ ይዉጡ እያልኩ ነዉ። ወቅቱም አሁን ነዉና!!!
የጓድ በትናቸዉ ስንሻዉ ጉድ መቸም ቢጎለጎል አያልቅም እኔም አንዴ ጀምሬዋለሁና የማዉቃቸዉንና የሚደርሱኝን መረጃዎች በሙሉ እሄድባቸዋለሁ አዲስ አበባ አፍንጮ በር አካባቢ ለምትኖረዉ የድሮ ጓደኛዪ ምሥራቅ ስንሻዉ ከባለቤትዋ ከታጋይ ተክሌ አጋበዝ ጋር ሆና የወንድምዋን ጉድ እንድታየዉና ይህንን ፅሁፍ እንድትፈትሸዉ ሰሞኑን ሳልደዉልላት አልቀርም።
ይህን ማስታወሻ ስፅፍ ዶክተር ታዬ ወልደሰማያትና አቶ ብርሃነ መዋ ትዝ አይሉኝ መሰላችሁ!?በነገራችን ላይ ሁለቱንም ወንድሞቼን እጅግ አድርጌ አከብራቸዋለሁ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዉስጥ ቀላል የማይባል አስተዋፅዖ ማበርከታቸዉ እውነት ነው። ዛሬ ግን ወደ ፓለቲካዉ መድረክ ዳግም ላይመለሱ ከአንደበታቸዉ ብዙዎቻችን ሰማን። የሚገርማችሁ ደግሞ ሁለቱም በአንድ ወቅት በቅንጅት መፍረስ ማግስት መሆኑ ነዉ፧ ለዚህ ትልቁና ዋናዉ ተከሳሽ ጓድ በትናቸዉ ስንሻዉ መሆኑ አይደንቅም። የቅንጅት አመራሮች በእስር ላይ በነበሩበት ግዜ እዚህ የነበሩት የቅንጅት የድጋፍ ኮሚቴ አባላት መከፋፈል ጀመሩ የኰሚቴው ሰብሳቢ የነበሩት ሻለቃ ዮሴፍ በእስር ላይ ከሚገኙት የቅንጅት ፕሬዘዳንት ከኢንጅነር ሃይሉ ሻወል የኰሚቴ አባላቶች ሹም ሽር በፊርማቸዉ አረጋግጠዉ ላኩ ተባለ አሰራሩ ማእከላዊነት ያልጠበቀ ነዉ ይሄ የንጉሣዊ ሹመት አይነት ነዉና አንቀበልም የሚል አካል ተፈጠረ የነብርሃነ መዋ ቡድን፧ ከስር ቤት ሾልኮ መጣ በተባለዉ የሹመት ዝርዝር ዉስጥ በዚያ የፓርቲ ስብስብ ዉስጥ ያልነበሩት የዶክተር ታየ ወልደሰማያት ስም የመሪነቱን ቦታ ይዞ ቀረበ ይህንን ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ እንዲያራግቡት ሃላፊነቱን በበላይነት አንዲመራዉ ደጎስ ካለ የገንዘብ ጉርሻ ጋር ጓድ ምርጫዉ ስንሻዉ ተረከበ ረዳት ሆድአደር አፍራሾችም ተመደቡለት ረዳቶቹ ደግሞ ከኛ ወዲያ ትግል ላሳር የሚሉ የትግል ዘመናቸዉን ሻማ በማብራት ብቻ የሚደክሙ የዲሲ ፋኖዎችና በታኞች ተሳካላቸዉ በአጭር ጊዜ የአገሪቱን ሕዝብ አንድ አድርጎ ወያኔን ያርበደበደዉን ብዙ ዜጎች በጠራራ ፀሐይ ዉድና ተተኪ የማይገኝለትን ዉድ ሕይወታቸዉን የገበሩለትን የፓለቲካ ንቅናቄ ጠልፈዉ ጣሉት አሽመደመዱት። አዎ ምርጫዉ ስንሻዉ፧እነ ሻለቃ ዮሴፍንና ታዋቂዉን ስመ ጥር የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ማኖ አስነካቸዉ ሸወዳቸዉ በግርግርም ከፍተኛ ገንዘብ ተበላ ቅንጅትም ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ከጨዋታ ዉጪ ሆነ ተበተነ የበትናቸዉ ስንሻዉ አለቆች ከበሮአቸዉን ደለቁ ከሕዝባዊዉ ማእበል ተጠራርጎ ከመጥፋት ዳኑ፧ ያን ሁሉ ወንጀል ፈፅመዉ ዛሬም እነምርጫዉ አሉ!አሁንም ኢንጅነር ሐይሉን እነ ብርሃነ መዋንም ጨምሮ ሁሉንም ባልተገራዉ ግልብ ንግግሩ ሙልጭ አድርጎ እያወረዳቸዉ ነዉ።ዛሬ በዚህ ባንዳ ምክንያት ብዙ ጠንካራ ሰዎችን አጥተናል አሁንም ዘለፋዉን ቀጥሏል።
መቸም በበትናቸዉ ስንሻዉ ዘለፋና ዝርፊያ ቆሽቱ ያልተቃጠለ አንጀቱ ያላረረ የለምና የዚህ ካድሬ ተጠቂዎች ለዚህ ፅሁፍ አቅራቢ ብዙ መረጃዎች አደርሰዉታል፧ብዙዎቹ ይበሳጫሉ እንዲህ ያለ ኢትዮጵያዊ የለም ያስብላሉ ተግባራቶቹ ግን እዉነቶች ናቸዉ። እና አኔ እያልኩ ያለሁት ስም ለማጥፋት ለመጠፋፋት ሳይሆን አካሄድህ አስነዋሪ ነዉ ብሎ እሱነቱንና ወልጋዳ አካሄዱን ለራሱ እንደመስታወት አሳይቶ ወደወገኖቹ ለመመለስ ነዉ እንጂ ከተላላኪ ሆድ አደሮች ጋር ይሄን ያህል ግዜ ማባከን ባላስፈለገም ነበር ምናልባት ወደቀልቢያዉ ቢመለስ ብዬ እንጂ!!
ትናንት አንድ ወዳጄ አንድ አባት በዚህ አጉራ ዘለል ካድሬ የሆኑትን ልንገራችሁና የዛሬዉን ፅሁፊን ላብቃ በአንድ ወቅት ለከፈተዉ ቤተክርስትያን በደመወዝ እንዲያገለግሉት አንድ አባት ከምስጢራተ ቤተክርስትያንና ቅዱሳን መጽሐፍቶች ጋር ከአገር ቤት ያስመጣቸዋል በሚኖርበት አካባቢ ነዋሪዎች ቪላ ዉስጥ የምትገኝ አንድ ጠባብ ክፍል ይከራይላቸውና ይገባሉ ቄሱም በየወሩ ከሚሰጣቸዉ ደመወዝ ለቤቱ ኪራይ እየቀነሰ ቀሪዉን ሲሰጣቸዉ ይከርማል የሰዉየዉ ግልብ ባህርይ ባይመቻቸዉም ሌላ መጠጊያ ስለሌላቸዉ ረዘም ላለ ጊዜ እንደተቀመጡ እንባ እየተናነቃቸዉ ይናገራሉ አነጋገራቸዉ ሁኔታቸዉ በዚህ በመጦርያ እድሜያቸዉ ስደተኝነታቸዉና ሁኔታቸዉ እጅግ አሳዝኖኝ መንፈሴ እየተሸበረ ስላስቸገረኝ ንግግራቸዉን ቶሎ እንዲጨርሱ በመመኘት ከዚያ በኋላስ አልኳቸዉ ከዚያ በኋላማ ልጄ አሉ አንገታቸዉን አቀርቅረዉ መሬቱን በያዙት ረጅም ጃንጥላ ጫፍ እየቆረቆሩ ፦አንድ ቀን ትንሽ አመም አርጎኝ እቤት ዋልኩ ያለወትሮየ ቤት መዋሌን የተመለከቱት የቤቱ ባለቤቶች ሊጠይቁኝ መጡ እህል ዉሃም ሰጡኝና በደንብ ሳይሻለኝ እንዳልነሳ ሲመክሩኝ አይ እዚህ አገር ወጪዉ መች ያስተኛል አልኳቸዉ ሴትየዋም ሳቅ ብለዉ አይ አባ እርስዎ ደግሞ ምን ወጪ አለብዎት ለምግቡም ቢሆን አያስቡ አሉኝ እኔም ለሆዴ እንኳ ግድ የለኝም የቤት ኪራዩን ማን ይከፍልልኛል ስላቸዉ የምን የቤት ኪራይ ነዉ የሚያወሩት እኛ ሁኔታዎን አይተን ምርቃትዎ ይበቃናል ብለን ገንዘብ ተቀብለዉ አናዉቅም አሉኝ እኔም በየወሩ ከደመዜ ላይ እንደሚቆርጥብኝ ነገርኳቸዉና ከዚያን አለት ጀምሮ አይኑን አያሳየኝ ብዬ ለአምላኬ አልቅሼ ቀረሁ አሉኝ። አይገርምም ወገኖቼ?!
እነዚህን የመሳሰሉ አሳፋሪ ብዙ ተግባሮቹን ብዙ ትሰማላችሁ እዚህ አካባቢ ጎራ ብትሉ፤ከዚህ ነዉረኛ የወያኔ ተላላኪ የምንረዳው አንድ ነገር አለ ይኸዉም አምባገነኑና ጨካኑ የህወሀት ስርአት በዙርያው የሚኮለኩላቸዉ ፍርፋሪ ለቃቃሚዎች ምንአይነት ከርሳሞችና ምግባረ ብልሹዎች እንደሆኑ ነዉ።
ክፍል ፮ ይቀጥላል

Wednesday, August 21, 2013

Ethiopia’s Muslim Activists Pave a Path for Nonviolent Political Activism

August 21, 2013
by Terrence Lyons, Briefing
 World Politics Review


The embarrassing Interview of Deputy PM Haile Mariam DesalegnA year after Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn came to power following the death of longtime leader Meles Zenawi in August 2012, the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) remains firmly in control. It has continued to govern through a collective leadership that includes three deputy prime ministers from the Amhara, Tigray and Oromo wings of the coalition; Hailemariam hails from the Southern People’s Party. Party discipline and coherence has held, although the lead-up to elections in 2015 may reveal destabilizing fissures. But while older opposition parties and armed movements have been marginalized, a social movement of Ethiopian Muslims is an important new development.

Rapid economic growth has been key to Ethiopia’s stability. The economy grew by more than 10 percent annually over the past decade, and while growth has slowed down it remains higher than the African average. Recent data, however, suggest that earnings from coffee and gold, Ethiopia’s two largest sources of export revenues, have declined. The World Bank also raised concerns that Ethiopia’s boom has relied too heavily upon public investment and that sustained growth will require a significant increase in private investment.

The political opposition to the EPRDF—currently divided into camps based on whether they subscribe to ethno-national or pan-Ethiopian goals and whether they operate in exile or have remained in the country—has struggled to find channels to influence Ethiopian politics. After competitive elections in 2005 and the subsequent crisis that led to the arrest of much of the opposition leadership and the collapse of the main opposition coalitions, the regime effectively criminalized dissent. Restrictions on independent media and civil society limit the ability of Ethiopians to mobilize outside of the structures of the ruling party. The EPRDF’s dominance was evident in local elections this year, in which it and its affiliated parties won all but one seat nationwide.

As a result, opposition political parties that challenged the regime in 2005 now play virtually no role in national politics. The Semayawi, or Blue, party organized a notable demonstration in June and has some following among the youth, but its potential to challenge the regime is limited. Berhanu Nega, a politician who had considerable influence in 2005, is now operating in exile without a significant presence in the country. Repression and the use of anti-terrorism laws, as well as weak structures and leadership, limit the opposition’s ability to operate within Ethiopia.

Meanwhile, several groups, notably the Oromo Liberation Front (OLF) and the Ogaden National Liberation Front (ONLF), remain engaged in protracted armed struggles, but Addis Ababa has effectively managed these military challenges. Oromo nationalism remains potent, but the OLF leadership is divided and discredited. Promising talks between the ONLF and Addis Ababa collapsed in October 2012, but there are officials on both sides that see advantages from a negotiated settlement. The government would like to end the war in order to concentrate on development of the region’s natural gas and other resources. Some Ogadenis recognize that they are unlikely to win the military contest and wish to end the ferocious counterinsurgency campaign in the region. But reaching a durable agreement, a recent International Crisis Group report accurately notes, will require “unprecedented concessions from both sides.”

Finally, the ongoing demonstrations by Ethiopian Muslims, who make up approximately 40 percent of the country, provide an important model of politics outside of the ruling party that relies upon neither armed struggle nor the strategies of electoral competition on a hopelessly lopsided playing field. The demonstrations began 18 months ago to protest government interference in Islamic affairs and the regime’s links to the Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council. The movement has been extraordinarily disciplined and nonviolent and has succeeded in part by focusing on a specific set of issues. Demonstrations have been held after Friday prayers in Addis Ababa but also notably in other towns across Ethiopia.

Muslim activists emphasize that they are operating within the framework of the Ethiopian constitution and that they are not seeking to overthrow the regime. The Ethiopian government, in contrast, has consistently claimed that the protests were organized by extremists bankrolled from overseas and seeking to establish an Islamist state. More recently Addis Ababa has identified neighboring Eritrea as the source of this alleged external support. The movement’s leadership was arrested July 2012 and charged with terrorism in October.

Earlier this month there were clashes between Ethiopian security forces and Muslims reportedly following the arrests of three local imams in Kofele, a town in the Oromo region. A heavy police presence and arrests in Addis Ababa following the Eid al-Fitr ceremonies celebrating the end of Ramadan on Aug. 8 further raised the temperature and tensions. Government spokesman Shimeles Kemal alleged that the arrests were of “Salafist elements who tried to create disturbances.”
Despite the government’s arrests and condemnations, the Ethiopian Muslim demonstrators have shown that sustained, nonviolent political activism is possible in Ethiopia. What is not clear,

however, is the movement’s future. Many leaders in the older ethno-nationalist movements, including those with large Muslim constituencies, such as the Oromo and Somali, view the multiethnic nature of the movement with trepidation. Others, including leaders in the Semayawi party, view it as a vehicle to advance pan-Ethiopian political ideas. Some Muslim activists propose a strategy of sustained low-level protest that avoids confrontation and recognize that a quick victory is impossible.

 To move more assertively would spark a military crackdown, and the movement’s leadership is likely to lose control if there is violence. The key dynamics to watch in the lead-up to elections in 2015 are therefore competition within the ruling party and the potential for the Ethiopian Muslim movement to create new space for political activism.

Terrence Lyons is associate professor of Conflict Analysis and Resolution and co-director of the Center for Global Studies, George Mason University.

‘እኔ ከሞትሁ ሰርዶ አይብቀል’ – ልንዋጋው የሚገባ አህያዊ ብሂል! – By Nasrudin Ousman

በኢሕአዴግ የሚመራው መንግሥት በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እና ክርስቲያኖች መካከል የእርስ በርስ ጥርጣሬና ጥላቻ ለመፍጠር፣ ከተሳካም የሃይማኖት ግጭት ለመቀስቀስ በተለያዩ አቅጣጫዎች በጣም አደገኛና መርዘኛ የሆነ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ከፍቷል፡፡ “እኔ ከሞትሁ ሰርዶ አይብቀል” በሚል አህያዊ ብሂል ላይ የተመሠረተውን ይህንን እርኩስ ዘመቻ፣ ለዚህች አገር ህዝቦች ሰላምና ፍቅርን የሚመኝ ኢትዮጵያዊ በሙሉ አጥብቆ ሊዋጋው ይገባል፡፡ …
እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ያነሳናቸውና ተገቢ ምላሽ ያገኙ ዘንድ በሰላማዊ መንገድ የምንታገልላቸው ጥያቄዎች፣ መንግሥት በሃይማኖታችን ላይ የቃጣውን ዓይን ያወጣ ጣልቃ ገብነት መነሻ አድርገው የተነሱ እንጂ ድንገት ከመሬት ላይ የበቀሉ አይደሉም፡፡ [ከቶውኑ ድንገት ከመሬት ላይ የበቀሉ ጥያቄዎች የድፍን አገሪቱን ሙስሊሞች በአንድ መንፈስ በጋራ ሊያነቃንቁ ይቻላቸዋልን? ይህ የማይመስል ነገር ነው፡፡]
… መንግሥት ከ1987 አጋማሽ አንስቶ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) ላይ ያሻውን ሰው ሲሾም እና ተቋሙን በካድሬዎቹ ሲያሽከረከር እየታዘብን በዝምታ አሳልፈናል፡፡ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለህዝበ ሙስሊሙ ምንም የረባ መንፈሳዊም ሆነ ማኅበራዊ አገልግሎት የመስጠት ብቃት እንደሌለው፣ በህዝበ ሙስሊሙ ስም በተቋሙ የሚንቀሳቀስ የህዝብ እና የአገር ሀብት በአሳፋሪ ሁኔታ በግለሰቦች ሲመዘበር፣ በሐጅና ዑምራ ጉዞ በህዝበ ሙስሊሙ ላይ ከፍተኛ ብዝበዛ (ዝርፊያ) ሲፈፀም፣ የአርባ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ተቋም የሠፈር ዕድር እንኳ ለመምራት በማይበቁ መደዴ ግለሰቦች ሲመራ … ልባችን በሐዘን እየደማም ብዙ ዓመታትን በዝምታ አሳልፈናል፡፡ ይህ ሁሉ ሲኾን፣ ከዚህ የተቋማችን አሳዛኝ ገፅታ ጀርባ የኢሕአዴግ እጅ እንዳለ ሳናውቅ ቀርተን አልነበረም፡፡ … መንግሥትን “በቃህ!” ለማለት የተገደድንበት ሁኔታ የተከሰተው ኢሕአዴግ ይህንኑ ተቋማችንን መሣርያ በማድረግ በአዲስ አስተምህሮ ሊያጠምቀን መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ ማድረግ ከጀመረበት ከሐምሌ 2003 ወዲህ ነው፡፡ [… ይህ በስፋት የሚታወቅ በመሆኑ እዚያ ላይ ሀተታ አላበዛም፡፡]
የሰላም ዘቦች እሥር እና ግልብ “ፀረ-አክራሪነት”
እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ባይኖረን ኖሮ፣ እንደ ተቋም አልባነታችን ከዓመታት በፊት ወደ አስከፊ የጥፋት መንገዶች ለመነዳት በተዳረግን ነበር፡፡ በእርግጥም ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መሪ አልባ ሁነው በቆዩባቸው ባለፉት አሥራ ዘጠኝ ዓመታት የሃይማኖት ጽንፈኝነት እና ነውጠኝነት ሊስፋፉ የሚችሉባቸው ብዙ ክፍተቶች ነበሩ፡፡ እነዚህን ክፍተቶች የደፈናቸው የነቀዘው መጅሊስ ሳይሆን፣ ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ ውስጥ የበቀሉ በሳል አንጋፋና ወጣት የሃይማኖቱ ምሁራን ናቸው፡፡ በተለያዩ መድረኮች፣ እንዲሁም የትምህርትና መረጃ ማሰራጫ አውታሮች (መጻሕፍት፣ መጽሔት፣ ሲዲ፣ ወዘተ.) በሃይማኖት መቻቻልና ከሌሎች ሃይማኖት ተከታዮች ጋር አብሮ በመኗኗር፣ የጎረቤትን ሐቅ (መብት) በመጠበቅ አስፈላጊነት፣ የጽንፈኛ አስተምህሮቶችን ጉድፍ እና አሉታዊ ገፅታ በማጋለጥ እነዚህ ወጣት እና አንጋፋ ምሁራን ሙስሊሙን ማኅበረሰብ በትጋት አስተምረዋል፡፡ እነዚህ አንጋፋና ወጣት የሃይማኖቱ ምሁራን በሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 27 የተደነገገውን “የሃይማኖት፣ የእምነትና የአስተሳሰብ ነፃነት” በመጠቀም ለኢትዮጵያ ሙስሊም ማኅበረሰብ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ህይወት መበልፀግ፣ እንዲሁም ህዝበ ሙስሊሙ ከሌሎች ሃይማኖት ተከታዮች ጋር በሰላም፣ በፍቅር እና በመከባበር የመኖር እሴትን በጥልቀት ተገንዝቦ ይህን እሴቱን እንዲንከባከብ በማስተማር ባይተጉ ኖሮ ኢትዮጵያዊው ሙስሊም በተለያዩ ኃይሎች ተፅዕኖ ውሉ በማይታወቅ አቅጣጫ የዕውር ድንብር በተጓዘና በተጋለበ ነበር፡፡ በእርግጥም የኢሕአዴግ መንግሥት ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ በኩል የሃይማኖት ጽንፈኝነት የሚያሰጋው ቢሆን ኖሮ፣ በኢትዮጵያዊው ሙስሊም ማኅበረሰብ ውስጥ የሰላምንና የአብሮ መኖር እሴቶችን ያሰረፁትን እነዚህን ድንቅ የማኅበረሰቡ አባላት (የሃይማኖት ምሁራን) በአጋርነት በማሰለፍ ስጋቱን በአስተማማኝ ሁኔታ የሚያስወግድ ውጤታማ ሥራ መሥራት በቻለ ነበር፡፡
የሁከት ናፍቆት
እጅግ የሚያሳዝነውና በአሁኑ ወቅት በገሃድ የሚታየው ግን፣ የኢሕአዴግ መንግሥት ፍላጎት በአገሪቱ ላይ ሰላምንና የህዝቦች አንድነትን ማስፈን አለመሆኑ ነው፡፡ ኢሕአዴግ የአገር ሰላምን እና የህዝቦችን በሰላም አብሮ የመኖር ትሩፋት በጽናት ሲሰብኩ የኖሩ የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ወጣትና አንጋፋ የሃይማኖት ምሁራንን ዘብጥያ የወረወረው ከሰላም ፍፁም ተቃራኒ የሆነ እኩይ አጀንዳ በማንገቡ መሆኑ አሁን ግልፅ ሆኗል፡፡ ፍላጎቱ ሰላም ባለመሆኑም ነው፣ አልሳካልህ ያለውን ጽንፈኝነት ለመፈብረክ ነጋ ጠባ የሚደክመው፡፡ የህዝቦች ተፈቃቅሮ እና ተከባብሮ መኖር አልዋጥልህ ቢለው ነው ጽንፈኝነትን እና ሽብርን በዶኩመንታሪ ፊልም ለማቀናበር አለቅጥ ደፋ ቀና የሚለው፡፡ … የህዝቦች በሰላም መኖር፣ ሰላም ቢነሳው ነው በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እና ክርስቲያኖች መካከል ጥላቻን ለመዝራት፣ ሁከትና የእርስ በርስ ግጭትን ለመጋበዝ ያለ አንዳች ኃፍረት በዘመቻ መልክ መንቀሳቀስ የጀመረው፡፡ …
… ዛሬ አመሻሽ ላይ አንድ ወንድሜ “ኢትዮጵያን ዳያስፖራ” የተሰኘ አሜሪካ ውስጥ የሚሰራጭ የራዲዮ ጣቢያ በቅርቡ ካሰራጫቸው ዝግጅቶች የቀዳቸውን የተወሰኑ ድምፆች ልኮልኝ ሳደምጥ የተረዳሁት ይህንን እና ይህንን ሐቅ ብቻ ነው፡፡ የኢሕአዴግ መንግሥት እና አጫፋሪዎቹ ለዚህች አገር እና ለህዝቧ ምን እየደገሱለት እንደሆነ ማሰብ በጣም ይዘገንናል፡፡ ምን ያህል አቅላቸውን ቢስቱ ይህንን ለማድረግ እንደወሰኑ ለእኔ ፈጽሞ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ ምን ያህል አዕምሯቸው ማሰብ ቢሳነው ነው የዚህ ተግባራቸውን ውጤት አስከፊነት ለመገመት ያልቻሉት ለሚለው ጥያቄዬ ፈጽሞ መልስ ላገኝለት አልቻልኩም፡፡ ሃይማኖትን በመሰለ ለሰዎች ስሜት እጅግ ቅርብ በሆነ ጉዳይ ላይ እንዲህ ያለ መርዘኛ የጥላቻ እና የግጭት ቅስቀሳ ያውም በራዲዮና በድረ ገፅ ማሰራጨት እንደምን ለአገር ሰላም አሳቢ ሊያሰኝ እንደሚችል አላውቅም፡፡ ከዓመታት በፊት በአንድ የአገሪቱ አካባቢ በተፈጠረ ሃይማኖት ነክ ሁከት ላይ ‹‹እንዲህ እና እንዲያ አደረጉን›› የሚሉ የሰዎችን ስሜት በመጥፎ መልኩ የሚኮረኩሩ መልዕክቶችን ማሰራጨት እውን ለአገር ሰላም ከማሰብ የመነጨ ነውን? … የመንግሥት ሥልጣን ከስኳር እንደሚጥም ቢያንስ መገመት አያቅተኝም፡፡ ፖለቲከኞች ከጠላት ጋር የሚደረግ ጦርነትን ለሥልጣን ዕድሜ ማራዘሚያነት እንደሚጠቀሙባትም አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን በሥልጣን ላይ ለመቆየት ሲባል ለረዥም ጊዜ ሊገዙት የሚሹትን የራስን አገር ህዝብ በሃይማኖት ለማጋጨት ታጥቆ መነሳት፣ ፖለቲካዊ ጥበብ ሳይሆን “እኔ ከሞትሁ ሰርዶ አይብቀል” ያለችውን አህያን መሆን ይመስለኛል፡፡ አላህ ከአህያነት ይጠብቀን!!
ኢሕአዴግ ህዝበ ክርስቲያኑን ከሙስሊሙ ጋር ለማጋጨት ታጥቆ በተነሳበት በአሁኑ ወቅት ከወደ አሜሪካ እንዲህ ያለ መርዘኛ ፕሮፖጋንዳ በራዲዮና በድረ ገፅ መሰራጨቱ፣ አገራችን እና ህዝቧ ምን ያህል ከባድ አደጋ እንደተደቀነባቸው በግልፅ ያሳያል፡፡ ምንም እንኳ እንዲከሰት የሚናፍቁት የህዝቦች የእርስ በርስ ግጭት ቢከሰት (በአክራሪ እና በጽንፈኛ ዲስኩራቸው) ሙስሊሙን ተጠያቂ ለማድረግ እንደሚንደረደሩ ግልፅ ቢሆንም፣ አደጋው ግን በሙስሊሙ ላይ ብቻ የተደቀነ አለመሆኑን መላው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ክርስቲያኑም ጭምር በውል ሊገነዘበው ይገባል፡፡ በዚህ ግንዛቤ ላይ በመመሥረትም፣ ይህን በእኛ በኢትዮጵያውያን ላይ የተደቀነ ወቅታዊ አደጋ ወይም ፈተና፣ የረዥም ዘመናት አብሮ መኖር ባስተማረን ትዕግስት፣ ብልሀትና ጥበብ በአሸናፊነት ለመወጣት የየድርሻችንን ኃላፊነት እንወጣ እላለሁ፡፡ ይህንንም ለማድረግ የኃያሉን ፈጣሪያችንን እገዛ እማፀናለሁ፡፡ …
ላለፉት ሁለት ዓመታት እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም፣ በሚሊዮኖች ከሚቆጠሩ የእምነት ወንድምና እህቶቼ ጋር ለሃይማኖት ነፃነቴ መከበር በሰላማዊ መንገድ እየታገልኩኝ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ነገር ግን የሃይማኖት ነፃነቴ መከበር ከሚያስጨንቀኝ ባላነሰ፣ ምናልባትም በበለጠ የኢሕአዴግ መንግሥት ህዝበ ክርስቲያኑን ከሙስሊሙ የማጋጨት ዕኩይ ሤራ ያስጨንቀኛል፡፡ እናም በአላህ ፈቃድ እና እገዛ ይህንን ዕኩይ ሤራ እስከ መጨረሻው አምርሬ እታገላለሁ፡፡ ለእኔ ከዚህ በላይ ኢትዮጵያዊነት የለም፡፡
… ቅኑን መንገድ በተከተሉ ሁሉ ላይ ሰላም ይስፈን፡፡ የዓለማት ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ከክፋት ኃይሎች ክፋት ይጠብቅልን፡፡ አሚን፡፡
_______________________
*መልዕክቴን ከተጋራችሁት፣ በሰሌዳችሁ ላይ ለሌሎች ብታጋሩት ደስ ይለኛል፡፡ አመሰግናለሁ፡፡