Thursday, February 28, 2013

የሳጅን ዘመድኩን ዛቻ እና ትርጉሙ

የሳጅን ዘመድኩን ዛቻ እና ትርጉሙ
February 28, 2013 | Filed underG7 Editorial,Slider Post | Posted by admin
ባለፉት ሳምንታት በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ክፈለ ከተማዎች የወያኔ መንግስት ፓሊሶችና ደህንነቶች በሙስሊሙ ወገኖቻችን መኖሪያ ቤቶች በመዘዋወር ዝርፊያ የተቀላቀለበት አሸባሪ ብርበራና ፍተሻ ሲያካሄዱ ሰንብተዋል። ይህ ብርበራ በአይነቱ ፍጹም ከሆነ የወሮባላ ተግባር የተለየ እንዳልሆነ የደረሰባቸው፣ ያዩና የሰሙ ሁሉ የሚመሰክሩት ነው።

የፍርድ ቤት ትእዛዝ ለይስሙላ እንኳን ያልያዙ ጭንብል ያጠለቁ ፓሊሶችና ደህነነቶች ጨለማን ተገን በማድረግ በር እየበረገዱ በመግባት ቅዱሳን መጸሃፍትን፣ ሞባይልን፣ ቴሌፎኖን እና ወርቅ በግፍ መዘረፋቸውን ሰለባዎቹ አረጋግጠዋል። ይህ በእነዚህ ንጹሃን ሙስሊም ወገኖች ላይ ከተፈጸመው ድብደባ፣ ማስፈራሪያና ማስደንገጫ ተጨማሪ መሆኑ ነው።
...
የእነዚህን አሳዛኝ ግፈኛ ተግባር የሰማው የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ዜናውን በየካቲት 14 ቀን 2005 አ.ም ምሽት ዘግቦ ነበር። በዚህ ዘገባ ላይ የቪ.ኦ.ኤው ጋዜጠኛ የሰለባዎቹን ምስክርነትና አስተያየት ብቻ ማቅረብ ተገቢ ያልመሰለው ፕሮፌሽናሉ ጋዜጠኛ፣ ሚዛናዊ ዘገባ ለማቅረብ ድርጊቱ ተፈጸመባቸው ወደተባሉት ክፍለ ከተማዎች የፓሊስ አዛዦች መደወል ነበረበት። ይኼኔ ነበር ጋዜጠኛው ሳጅን ዘመድኩንን ያገኘው። ይህን የመንግስት ወንጀል እንዲያስተባብሉ እድል የተሰጣቸው ሳጅን ዘመድኩን የሰጡት መልስ ሰዋዊ ሳይሆን አውሬያአዊ ነው ማለት ይቻላል።

የተሰራውን ግፍ መዘገቡ ያናደዳቸው የፖሊስ አዛዦች ጭራሹኑ ጋዜጠኛውን ራሱን አሁን መጥቼ አስርሃለሁ የሚል መልስ ነበር የሰጡት። እብሪተኛው ሳጅን ጋዜጠኛው እንኳን ዋሽንግተን መንግስተ ሰማያትም ገብቶ እንደማያመልጠው ካዛቱ በኋላ ቃለ ምልልሱ አለቀ።

ይህን ቃለ ምልልስና የሳጅን ዘመድኩን ዛቻ ስንሰማ ቅጽበታዊ ምላሻችን ሳቅና መገረም ሊሆን ይችላል። ከዚህ የደንቆሮ ሃሳብ ከሚመስል አስቂኝና አስገራሚ አነጋገር በስተጀርባ ግን በእጅጉ የሚያሳዝን፣ የሚያስለቅስና የሚያስቆጭ ትርጉም አለው። የሳጅን ዘመድኩን ጥያቄ አመላለስ የልዩ አጋጣሚ ጉዳይ (Isolated Event) አይደለም። እንደዚያ ከመሰለን ክፉኛ ተሳስተናል። በሳጅን አንደበት የሰማነው አውሬ ወይም የህወሃት ድምጽ ህዝባችን በእየለቱ ቁም ስቅሉን የሚያሳየውን የወያኔ የየእለቱን ዘረኛ ቋንቋ እና ተግባር ነው። ሳጅን ዘመድኩን የተናገረው የሰለጠነበትንና ወያኔ የወሰነውን ነው በእሱ ልሳን የሚናገረው።

ወያኔዎች የፈለገንን አድርገን አዋርደን እንገዛችኋለን፤ ምን አባታችሁ ትሆናላችሁ ነው የሚሉን በወያኔኛ ቋንቋ። ሳጅን ዘመድኩን እንደምንገምተው ደንቆሮ አይደለም። ወያኔ ውስጥ ያደገ ወያኔኛ የተማረና የሰለጠነ፣ ሁሉንም ጣቢያዎች ከሚያዙት ሰዎች አንዱ ነው። ትእዛዝ ፈጻሚ ወያኔ ነው። ህዝብ ደሞዝ የሚከፍለው የህዝብ ተቀጣሪ ነኝ ብሎ አያምንም። እንደሁሉም ወያኔዎች እየዘረፈ የሚኖር ሽፍታ ነው። ህግና ህገ-መንግስት ለጌጥ የተቀመጠ መሆኑን ወያኔዎች ሁሉ ያውቃሉ። ተናግረውታልም።

በሳጅን ዘመድኩን አራዊታዊ አነጋገር ስቀን ከሆነ የሳቅነው በራሳችንና በህዝባችን ሰቆቃ ነው። በራሳችን ውርደት ለመሳለቅ አይተናነስም።ሀገራችን በእንደ እነ ሳጅን ዘመድኩን ያሉ ሰዎች ነው የምትመራው። ትልቅ ውርደት ላይ ነን። ሀገራችን ከውረደት፣ ህዝባችንን ከሰቆቃ የማዳን ግዜው አሁን ነው።

የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ፡- ምርጫችን ሁለት ነው። ወይ “ኑሮ ካሉት መቃብርም ይሞቃል እያልን የቁም ሞት ኑሮአችንን መኖር” አሊያም ወያኔን አስገድደንም ሆነ አስወግደን የሚገባንን የኩሩ ህዝብና ሀገር ስብእናችንን ማስመለስ እና ሀገርን ከማዳን ከሞራላዊ ግዴታ ተጠያቂነት ነጻ የመሆን።

እንዳንሳሳት! የሳጅን ዘመድኩን አራዊታዊና እብሪታዊ ቋንቋ ወያኔያው የእለት ተእለት ዘይቤ ነው። ስለዚህ ጀንበር ቁልቁል ሳትጠልቅብን ወያኔን አስገድዶ ለመጣል ከሚንቀሳቀሰው ህዝባዊ ሃይል ጋር በመሆን የመታገያ ጊዜው አሁን ነው።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

ጅሃዳዊ ሃራካት’’ ዘጋቢ ፊልም ጋር በተያያዘ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ከፍተኛ የሀገሪቱ የመንግስት ባለስልጣናት ሊከሰሱ ነው::


Hailemariam_Desalegn_Ethiopiaጠ/ሚ ኃ/ማርያምን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት
ባለስልጣናት ሊከሰሱ ነው
*ኢቴቪና ፌዴራል ፖሊስም ይከሰሳሉ
በዘሪሁን ሙሉጌታ ሰንደቅ ጋዜጣ


በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በቅርቡ ከተላለፈው ‘‘ጅሃዳዊ ሃራካት’’ ዘጋቢ ፊልም ጋር በተያያዘ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ከፍተኛ የሀገሪቱ የመንግስት ባለስልጣናት ላይ የወንጀልና የፍትሃብሔር ክስ ሊመሰረት ነው። ከመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ባሻገር በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት (ኢሬቴድ) እና በፌዴራል ፖሊስ ተመሳሳይ ክስ ይመሰረትባቸዋል።
ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናቱ እና የተጠቀሱት ተቋማት ላይ ክስ የሚመሰረተው ሰሞኑን ‘‘ጃሃዳዊ ሃራካት’’ በሚል በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ደርጅት የቀረበው ዘጋቢ ፊልም በሽብርተኝነት ተጠርጥረው በሕግ ጥላ ስር ያሉትን ተጠርጣሪዎች መብት ሲጣስ መከላከል ባለመቻላቸው፣ ስልጣናቸውን ያለአግባብ በመጠቀማቸው፣ በሕዝብ ሐብት ያለአግባብ በመገልገላቸው፣ የተሰጣቸውን የሕዝብ አደራ ባለመወጣታቸውና በሃይማኖት ጣልቃ በመግባታቸው የወንጀልና የፍትሐብሔር ክስ ይመሰረትባቸዋል። ክሱን የሚመሰርቱት በአሁኑ ወቅት በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ጉዳያቸው በሕግ እየታየ ባሉት ተጠርጣሪዎች ጠበቆች አማካኝነት ሲሆን ክሱም በሁለት ደረጃ ተከፍሎ እንደሚቀርብ ለማወቅ ተችሏል።
ክሱን እያዘጋጁ ከሚገኙት ጠበቆች አንዱ የሆኑት ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ክሱን በማስመልከት በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ በመንግስት ባለስልጣናት ላይ የሚመሰረተው ክስ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይቀርባል ብለዋል። በኢቲቪ ላይ የሚመሰረተው የፕሬስ ክስ ቀጥታ በከፍተኛው ፍርድ ቤት የሚቀርብ ሲሆን ክሱም ከሞራል ጉዳት ጋር እንደሚያያዝ ጠበቃው አስታውቀዋል።
‘‘መጀመሪያ ክርክራችን ዘጋቢ ፊልሙ እንዳይተላለፍ ነበር። ከተላለፈ በኋላ ግን ይግባኝ ማለት ሳይጠበቅብን ይሄንን ጉዳት ባደረሱ አካላት ማለትም ፊልሙን በሰሩት፣ ፖሊስና የደህንነት ኃይሎች ጨማምረን ክሱ እንመሰርታለን’’ ያሉት ጠበቃ ተማም በፕሬስ ህጉ መሰረትም ዘጋቢ ፊልሙ በተላለፈ በሦስት ወራት ውስጥ ክስ መመስረት እንደሚያስችልም አያይዘው ገልፀዋል።
በኢቲቪ በተላለፈው ዘጋቢ ፊልም ላይ በሚመሰረተው ክስ እስከ 100ሺህ ብር የሞራል ካሳ እንደሚጠየቅ በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ክስ ደግሞ በሌላ መዝገብ በፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በሚመሰረተው ክስ ለደንበኞቻችን የሞራል ካሳ እንዲካሱ፣ ደንበኞቻችን ይቅርታ እንዲጠየቁ፣ በተመሳሳይ የአየር ጊዜ ተሰጥቷቸው ደንበኞቻችን የራሳቸውን ኀሳብ እንዲሰጡ፣ በሃይማኖት ውስጥ በተደረገ ጣልቃ ገብነት ለደረሰው ጉዳት ኃላፊነት እንዲወስዱ የሚያደርግ ክስ ነው ብለዋል።
‘‘ክሱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን የማያካትትበት ምክንያት የለም። የሀገሪቱ መሪ እሳቸው ናቸው። ፖሊስም እያደረገ ላለው ነገር ለምሳሌ ተጠርጣሪዎችን ቶርች በማድረግ ጭምር እንከሳለን። የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ዘጋቢ ፊልሙ ያግዱ፣ አያግዱ የሚለውን አጣርተን የሚመለከታቸውን አካላት ለይተን ክሱን ለመመስረት ተዘጋጅተናል። ክሱን ለማዘጋጀት አስፈላጊ መረጃዎችን እየሰበሰብን ነው። በቅርቡም ክሱን እንመሰርታለን’’ ሲሉ ጠበቃ ተማም ጨምረው ገልፀዋል።
ደንበኞቻችን እራሳቸውን በማይከላከሉበት ሁኔታ ታስረው፣ መልስ እንዲሰጡ ባልተደረገበት ሁኔታ ስማቸው እንዲጠፋ መደረጉ አግባብ አለመሆኑን የጠቀሱት ጠበቃው ዘጋቢ ፊልሙ የደንበኞቻችንን መልካም ባህሪ የገደለ (Character assination) ነው ብለዋል።
መንግስት በሽብርተኝነትና ከህገ-መንግስቱ በተቃራኒ ሃይማኖታዊ መንግስት ለማቋቋም ሲያሴሩ አግኝቻቸዋለሁ፤ በሶማሊያ ከሚንቀሳቀሰውና ከአለም አቀፍ አሸባሪ ቡድን አልቃይዳ ጋር ከሚንቀሳቀሰው አል-ሻባብ ጋር ተመሳጥረው ሲሰሩ አግኝቻቸዋለሁ ባላቸው ተጠርጣሪዎች ላይ ዘጋቢ ፊልም ማቅረቡ ይታወሳል።
ፊልሙ ከመተላለፉ በፊት የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት የእግድ ትእዛዝ ቢያስተላልፍም ፊልሙ ለሕዝብ አይታ መቅረቡ አይዘነጋም፤ ፊልሙ ለተመልካቾች ከቀረበ በኋላም አነጋጋሪ ሁኔታ መፈጠሩም ይታወቃል።n
ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ

Wednesday, February 27, 2013

ጀርመን ራዲዮ እና የወያኔ ሴራ በፈስ ቡክ ኢትዮጵያውያን ላይ

 



ጀርመን ራዲዮ እና የወያኔ ሴራ በፈስ ቡክ ኢትዮጵያውያን ላይ


በሃገራችን ታሪክ ታይቶ እና ተከስቶ የማያውቅ የሽፍቶች አሸባሪ መንግስት በተለያየ ስልት ኢትዮጵያውያንን መከራቸውን እያሳየ ይገኛል:: ይህ ወንበዴ መንግስት ማፊያዊ ስልቶችን በመጠቀም የተለያዩ ሽብሮችን እየፈጸመ ነው:; መውደቂያው የደረሰው እና በቋፍ ላይ ያለው ይህ መንግስት ስለ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን የሚያስቡ ሰዎችን የሚዋጋበት ስልቱ የህዝብ ንብረት እና ገንዘብ በመጠቀም ስልጣኑን ላለማጣት እየተራወጠ ይገኛል::ይህንንም ለመዋጋት ድፍን ኢትዮጵያዊ ዘር ሃይማኖት ቀለም ወ.ዘ.ተ. ሳይለይ በአሁን ሰአት በጋር ድምጻችን ይሰማ እያለ ለመብቱ እና ለነጻነቱ እየታገለ ነው:: ይህንን ትግል ለማኮላሸት ሴራ ከሸረቡት አንዱ ከዚህ አሸባሪ መንግስት ጋር በማበር እየሰራ የሚገኘው የጀርመን ድምጽ አንዱ ነው ::

ይህ የራዲዮ ጣቢያ ከቀድሞው ጀምሮ ከወያኔ ጋር በመመሳጠር በኢትዮጵያ እና በዜጎችዋ ላይ የምእራባውያኑን ጥቅም ሲያራምድ ቆይቷል:: ምእራብያውያኑ በተለይ ጀርመን አጋርዋ የሆነው አሸባሪ የማፊያ ቡድን እንዳይቐየማት እና አስልፎ የሚሸጥላት የኢትዮጵያውያንን ጥቅም በማግበስበስ ለብሄራዊ ጥቅሟ ስትል የሃገሪቱ ህዝቦች ድምጽ እንዳይሰማ የህን የራዲዮ ጣቢያ እየተጠቀመች ነው::

ከዚህ በዘለለ በኢትዮጵያ አንጡረ ሃብት የተማሩ ያደጉ የት እንደደረሱ እንኩዋን ራሳቸውን የላዩ የራዲዮው ጋዜጠኞች የእናት ጡት ነካሾች ኢትዮጵያዊ የሚል ዜግነታቸውን አስረክበው ጀርመን የሚል ዜግነትን በመጎናጸፍ/ለነሱ ይመስላቸዋል/ በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያውያን ላይ እጅ አዙር ወያኔያዊ ዘመቻ ከፍተዋል::

ይህንን ዘመቻቸውን የከፈቱት በሃገራቸው መኖር መናገር መስራት በተከለከሉ ዜጎች ላይ ነው:: ይህ ደሞ እጅግ አስቀያሚ ምግባር እና ወያኔያዊ ሃራካት መሆኑን እንገነዘባለን::ወያኔ በምትሰጣቸው ጉርሻ የሚፎልሉብን እነማሙሽ ስብሃቱ ዛሬም ወሬያቸውን ይዘው እንደውሻ መጮህ ጀምረዋል::
በዚህም መሰረት አድርገው የወያኔ ተሊኮዋቸን በማማሰል ፌስቡክ በአሸባሪ እና በወንጀለኛ የተሞላ ነው እያሉን ነው ይህን እኛ ኢትዮጵያውያን በነዚህ ሰዎች ላይ ዘመቻ እንድናደርግ አስገድዶናል:: እንደዚህ አይነት ጩኸታቸውን የጀመሩት ወያኔ ከተዋረደበት የሳኡዲ አረቢያ የቦንድ ስብሰባ ጊዝይ በሁዋላ ነው ::ከዛ ቀደም ብሎ የሚሰሩትም ስራ ለማንም ኢትዮጵያዊ አይጥመውም የቦንድ ሽያጭ ስብሰባ የኢትዮጵያውያን ተቃውሞ በራዲዮናቸው ላለመናገር ሲዘባበቱ ነር ይባስ ብለው ወኪላቻው በዛ ምሽት ከወያኔ ዲፕሎማቶች ጋር ሲያሽካካ እንደነበር በሳኡዲ የሚገኘው የወጣቶች ማህበር ጠቁሟል:; ዛረ ይህንኑ የተመሸጉበት የወያኔ ምሽግ ለምን ተደፈረ ሊናድ ነውን ባማለት ፌስቡክ ላይ ያሉት ኢትዮጵያውያን ኢላማ አድርገው ተነስተዋል::

በፈስ ቡክ ያሉ እትዮጵያውያንን ለመታገል እነዚህ የወያኔ ጀሌዎች እኛ ታዋቂ ነን የእከሌ ወንድም ነን እኛ ኦዲየንስ አለን በሚሉ...አነጋገሮች በመኮፈስ የተለያዩ መላምቶችን በመሰንዘር እየተራወጡ ሲገኙ የተለያዩ የፈስቡክ አካውንቶችን ለማዘጋት ሪፖርት እያደርጉ ነው ለዚህም የሚጠቀሙበት አሸባሪ እና ወንጀለኛ የሚል የወያኔ ቋንቋ ነው::አሸባሪነትን ለመከላከል እየሰራን ነው የሚል ፕሮፖዛል ለነጭ አለቆቻቸው እስከማቅረብ ደርሰዋል::

እለት እለት እየተጠናከረ በመጣው አፈና ምክንያት ፌስቡክን እንደመተንፈሻ እና መንግስትን ለመታገል እንደዋነኛ መደራጃ እያገለገለ እንደሚገኝ ግልፅ ነው ታዲያ ሁሉንም ነገር ካላፈኑ እንቅልፍ የማይወስዳቸው ወያኔዎች የፌስቡክ ነገር ከቁጥጥራቸው እንደወጣ ስለተገነዘቡ ፌስቡክ የሚፈጠሩ ግሩፖቹን፥ገፆችንና የግለሰብ ፕሮፋየሎችን እየተከታተሉ ከመዝጋት ባሻገር ፀረ-ፌስቡክ የሆነ ዘመቻ ከጀመሩ ውለው አድረዋል እስከአሁን ፀረ-ፌስቡክ የሆኑ
የፕሮፓጋንዳ ስራዎች በኢቲቪ፥ በሪፓርተር እና በዛሚ ኤ.ኤፍ.ኤም ጀርመን ራዲዮ ቀርበዋል።ከሆድ አሳዳሪዎቹ ጋር እንዘጭ እንዘጭ ያበዛው የጀርመን ራዲዮው ማንተጋፍቶት ስለሺ (ማሙሽ ስብሃቱ) በወያኔ እየተካሄደ ያለው ፀረ-ፌስቡክ ዘመቻ እራሱን አካል ስለአደረገ ይመስለኛል ከመስመር በወጣ መልኩ ፌስቡክና ፌስቡካውያንን በአንድ ከረጢት አጭቆ የዘለፈው።

ሶስተኛው ዙር የአፈና እና የስለላ መምሪያ ንድፍ/እቅድ

 





በፈረንጆቹ አዲስ አመት ተከትሎ ወያኔ ያቋቋመው የአፈና እና የስለላ መዋቅር በደረረሰን መረጃ መሰረት ባለሃብት ናቸው የሚባሉ ሙስሊሞችን ለመጉዳት...የቤት ለቤት አሰሳ እና ፍተሻ እንደሚያካሂድ እንዲሁም ወደ ኢንተርኔት ካፌዎች ሊዘምት እቅድ እንደነደፈ የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች መረጃ መስጠታቸውን ተከትሎ ይኅን ጉዳይ ብሎግ ያደረግንበት ድህረገጻችን እትዮጵያ ዉስጥ ለ2ኛ ጊዜ ታግዶ ይገኛል::

የውስጥ አዋቂ ምንጮች ለምኒሊክ ሳልሳዊ ባደረሱት መረጃ መሰረት የስለላ እና የአፈና መምሪያው ከብሄራዊ መረጀ እና ደህንነት መምሪያ ጋር በመሆን አዲስ ሚስጥራዊ ያሉትን የአፈና ስልት ነድፈው በይፋ ለመጀመር ቅድመዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ተደርሶበታል::
በዚሁ መሰረት 3ኛው ዙር የአፈና እና የስለላ እቅድ የሞባይል ጠለፋ እና ሰበብ በመፍተር ሙስሊም ወጣቶችን ከመንገድ ላይ አፍኖ የመውሰድ ሴራ ነድፈዋል:: ያሉት የምኒሊክ ሳልሳዊ ምንጮች ይህንን እቅድ ተከትሎ በሙስሊም ስሞች ተመዝግበው የሚገኙ ሲም ካርዶችን የባለቤቶቹን ስም እና አድራሻ በዝርዝር እንዲሰጠው በአቶ ደብረጺሆን በኩል ለቴሌ ምስጢራዊ ያሉት እነሱ ትእዛዝ የተላለፈ ሲሆን እያንዳንዱ የስልክ ግንኙነት እንዲመረመር ሲነገራቸው እንዲሁም የተቃዋሚ ሃይሎች እና ለቤተክርስቲያን ቅርብ ናቸው ተብለው በተቃዋሚነት የተፈረጁ ግለሰቦች የዚህ አፈና ኢላማ ናቸው::

ሌላኛው በንኡስ አንቀጽ የተቀመጠው በትምህርት በስለዋል የሚባሉ ሙስሊም ወጣቶችን እና የማህበረቅዱሳን `አማፂ` የተባሉ እንዲሁን የራእይ ወጣቶች ማህበር አባላትን ኢላማ አድርጎ ከመንገድ በሰባብ አስባቡ አፍኖ መውሰድ ሲሆን ይህም በብዛት የሚአተኩረው ፈረንሳይ ለጋሲዎንን መነሻ አድርጎ እስከ ጉለሌ እና ላፍቶ ድረስ ሊሰራ የታሰበ ሲሆን በመሃል ከተማ አከባቢ ጨለማን ተገን በማድረግ ተፈጻሚ ይሆናል::ሲሉ የምኒሊክ ሳልሳዊ ምንጮች ተናግረዋል::
ስለዚህ በሰፊው ማብራሪያው ደርሶን መርጃውን እስከምንሰጣቹህ ድረስ ይህንን መሰረታዊ መረጃ ተመርኩዛችሁ ቤያንዳንዱ እንቅስቃሴያችሁ ላይ ከ ፈጣሪ ጋር ተጠንቅቃችሁ እንድትታገሉ ምክር እየሰጠን ለሁላችንም ፈጣሪ ይረዳን ዘንድ በፆም እና በጸሎት እንድንተጋ መልእክታችንን እናስተላልፋለን::

ወያኔ ቅዠት እንጂ ራዕይ የለውም!


ትላንት የተናገሩትን ዛሬ፤ ዛሬ የተናገሩትን ነገ የማይደግሙ ከሀዲ አንባገነን እና ዘረኛ ቡድኖች የስልጣን ኮረቻ በሀይል ከተፈናጠቱበት እለት ጀምሮ የተለያዩ የማወናበጃ ዘዴዎችን እየተጠቀሙ የበርካታ ንጹሀን ዜጎችን ህይወት ቀጥፈዋል አስቀጥፈዋል፡፡እንኳን እንደጠላት የሚቆጥሩትንና በመርሃ ግብራቸው ነድፈው መጥፋት አለበት ብለው የፈረጁትን ህዝብ ቀርቶ አርነት እናወጣሀለን እያሉ ክእናንተ በመፈጠራችን ኮራንባችሁ የሚሏቸውን የትግራይን ንጹሀን ዜጎች ሳይቀር የራሳቸውን የስልጣን ዕድሜ ለማራዘም ውድ ህይወታቸውን እንዲገብሩ አድርገዋል፡፡ የሀውዚንን ጭፍጨፋ አቀናብረዋል፣በ1991ዓ.ም በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል በተደረገው ጦርነት ከ70000 በላይ የጠርነቱ ሰለባ ሁነዋል፡፡አልሻባብን ለመደምስስ በሚል በሶማሊያ በረሃ የረገፉትን ወታደሮች ቤት ይቁጠራቸው፡፡ስልጣን ለወያኔ ከምንም ነገር በላይ ነው፡፡ ስልጣን ከሉአላዊነት፣ከባህር በር ፣ከሀገርና ከህዝብ እንደሚበልጥባቸው ከመጀመሪያው ጀምሮ የወሰዷቸው እርምጃዎች ማሳያ ናቸው፡፡የገንዛ ሀገሩን ቆርሶ ለሱዳን የሚሰጥ፣የባህርበር አያስፈልገኝም የአሰብን ወደብ ውሰዱት፣ኤርትራ እንድትገነጠል ፈቅጃለሁና እውቅና ስጡልኝ እባካችሁ እያለ የአለም መንግትታትን የተማጸነ፣የገንዛ ዞጎቹን አፈናቅሎ ለውጭ ባለ ሀብቶች መሬታቸውን የሚሰጥ፤የሀገሪቱን ሀብት ለተደራጁ ወንበዴወች የሚያስዘርፍና የሚዘርፍ፤ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦችን አጥፍቼ ታላቋን ትግራይን እመሰርታለሁ ብሎ የሚንቀሳቀስ አንባገነን እንዴት ያለ ሀገራዊ ራዕይ ነው የሚኖረው፡፡

ዘረኛው መንግስት በተለያዩ ጊዜያት እንዱን ብሄር በሌላው ብሄር ላይ በማነሳሳት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩት ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው ሀብትና ንብረታቸውን ተዘርፈው ለከፍተኛ ችግር ሲዳረጉ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ለእልፈት ተዳርገዋል፡፡የፖለቲካ ፓርቲዎችና ጋዜጠኞችን በሽብር ስም እያሰረ ንጹሀንን ሲያሸብር ቆይቷል፡፡በርካታ ፓርቲዎች በሰርጎ ገብ ሰላዮች የተነሳ ይዘውት የተነሱትን አላማ እና የህዝብ አደራ እዳር ሳያደርሱ በጅምር ቀርተዋል፡፡በወያኔ መሰሪ ተንኮል በተቀነባበረ ሴራ ጦርነት ውስጥ ያልገባ ክልልና ብሄር ባይገኝም ውጤቱ እንደሚፈልጉት ስላልሆነላቸው እና የኢትዮጵያ ህዝቦችም ባላቸው አርቆ አስተዋይነትና ረጅም ጊዜ በሰላም አብሮ የመኖር ባህሉ በመታገዝ የፕሮፖጋንዳቸው ሰለባ ባለመሆናቸው ለወያኔዎች ትልቅ ራስ ምታት ጥሮባቸዋል፡፡እስካሁን ሲጫወትበት የነበረውን ካርድም እንዲቀይርም ተገዷል፡፡ አዲሱ የመጫወቻ ካርድም ከብሄር ግጭት ወደ ሐይማኖታዊ ግጭት ለማሸጋገርም የሚያስችለውን “ጀሀዳዊ ሀረካት”የተሰኘ ዘጋቢ ፊልም በመስራት ከ1500 አመት በላይ አብረው የኖሩትን ሁለቱን ታላላቅ እምነቶች ማለቂያ ወደሌለው ጦረነት በመማገድ የስልጣን ጊዜውን ለማራዘም ቢምክርም እናንተ ከመጣችሁት ገና 21 ዓመታችሁ ነው እኛ ደግም ለረጅም ጊዜ በፍቅር አብረን ኑረናል፤ የጋራ ጠላታችን ዘረኛው ወያኔ ነው፡፡እኛ ከእነሱ እንሻላለን አንለያይም እያሉ በየአደባባዮ አንገት ላንገት ተቃቅፈው እየተላቀሱ ቁጭታቸውን ሲገልጹ መመልከት የተለመደ ተግባር ነው፡፡ሰሞኑን ለኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕርግራም ሙኒክ ላይ የታየውም ህብረት የዚሁ አካል ነው፡፡
እንዴት እንደ ኢትዮጵያ ያለች ታላቅ ሀገር እና እንደ ኢትዮጵያውያን ያሉ ቀደምት ህዝቦች እንደ ወያኔ ባሉ ትንሽ ሰዎች ይገዛሉ?እንዴት የአለም ማህበረሰብ በሀሰት የወያኔ ፕሮፖጋንዳ ሲታለል ይኖራል?እስከመቼ ብቻቸውን በምርጫ ተወዳድረው አሸነፍን እያሉ ሲያላግጡ ይኖራሉ? ወያኔዎችስ በቀጣይ ምን የማደናገሪያ ስልት ያመጡ ይሆን? እኔ በበኩሌ በቃ ብያለሁ፡፡ ወያኔ ራዕይ የለውም ኑሮትም አያውቅም፤ ወደፊትም አይኖረውም፡፡የወያኔ ሀገር እና ህዝብ የማውደም ቅዠት እንጂ ሀገራዊ ራዕይ ብሎ ነገር አያውቅም፡፡በጋራ ጠላታችን ላይ በጋራ እንነሳ!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!



 

Tuesday, February 26, 2013

በሽብርተኝነት ተከሰው በወህኒ ቤት የሚገኙ በጣም በርካታ እስረኞች የይቅርታ ፎርም እንዲሞሉ እየተደረገ ነው

     

በሽብርተኝነት ተከሰው በወህኒ ቤት የሚገኙ በጣም በርካታ እስረኞች የይቅርታ ፎርም እንዲሞሉ እየተደረገ ነው (ምንአልባት የሀይለማርያም መንግስት ሪፎርም /ማሻሻያ/ የማድርግ ዕቅድ ካለው በዚሁ ሊጀምር አስቦ ሊሆን ይችላል፤ አሊያም እንደተለመደው እስረኛ በመልቀቅ የፖለቲካ ማሻሻያ እንደተደረገ ለማስመሰል ይሆናል)፡፡ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እና ዘሪሁን ገ/እግዚአብሄርም በብዛት ከሚለቀቁት እስረኞች ጋር አብረው እንደሚፈቱ ምንጮቼ አረጋግጠውልኛል፡፡
አጀንዳችን…
ዛሬ በከፍተኛው ፍርድ ቤት የእነእስክንድር ነጋን ንብረት ለመውረስ ፍትህ ሚንስቴር የመሰረተው ክስ ሲታይ ውሎአል፡፡
እስክንድር ከዚህ ቀደም ‹‹የታሰርኩት በግፍ ስለሆነ ንብረቴን አትውረሱ ብዬ አልከራከርም፤ ዛሬውኑ ልትወስዱት ትችላላችሁ›› በማለት ያልተከራከረ ሲሆን፣ የአበበ በለውን ንብረት በሚመለከት በሌለበት ታይቷል፡፡ የአንዱአለም አራጌ ባለቤት ደግሞ በስሟ የተመዘገበው መኪና መወረሱ አግባብ እንዳልሆነ በጠበቃዋ አቶ ደርበው ተመስገን አማካኝነት ተከራክራለች፡፡ ፍርድ ቤቱም ለውሳኔ የፊታችን ሚያዚያ አስር ቀን ቀጠሮ ሰጥቷል (በእኔ ግምት ቀጠሮው እንዲህ የራቀው መጋቢት አስራ ስምንት ቀን እነእስክንድር የጠየቁት ይግባኝ የመጨረሻ ውሳኔ ስለሚሰጥበት ከዛ በኋላ የንብረቱን ጉዳይ ለመጨረስ ይመስለኛል)
የሆነ ሆኖ ዓቃቢ ህግ የእስክንድር ንብረት ተብለው ከቀረቡት ባለሁለት ፎቅ ዘመናዊ መኖሪያ ቤት፣ በባለቤቱ ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል ስም የተመዘገበ የቤት መኪና፣ እንዲሁም የእስክንድር እናት ንብረት የሆነ በአንድ ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ መኖሪያ ቤትን ለመውረስ ጥያቄ ያቀረበ ቢሆንም፣ በዛሬው ዕለት በእናቱ ስም የተመዘገበውን ቤት እንደተወው ገልጿል (አዲስ ታይምስ መፅሄት የእናቱ ቤት ዝርዝር ውስጥ መግባቱ ተገቢ አለመሆኑን ደጋግማ መግለጿ የሚታወስ ነው)፡፡
ይህንና ዓቃቢ ህግ በእስክንድር እናት ስም የተመዘገበውን መኖሪያ ቤት ከሚወርሳቸው ዝርዝር ውስጥ በማውጣቱ ምንም አይነት ምስጋና የለኝም፡፡ ምክንያቱም እንኳን ንብረታቸው ተከሳሾቹም ምንም ጥፋት ያላጠፉ ንፁሀን ናቸው ብዬ ስለማምን፡፡ ስለዚህም አሁንም እንዲህ እላለሁ፡- ዓቃቢ ህግ ዕዳ አለብህ! አዎ እዳ አለብህ!! ንፁሀን ወንድሞቻችንን ይቅርታ ጠይቀህ እስክትለቅልን ድረስ!!!

የመናገር ነጻነት ዘመቻው ለህወሃት መራሹ መንግስት ምኑ ነው?

የመናገር ነጻነት ዘመቻው ለህወሃት መራሹ መንግስት ምኑ ነው?

ሰሞኑን የዞን 9 አባላት የብሎጋቸውን በኢትዮጵያ መከልከል ተከትሎ ከክፈቱልን ያለፈ ፤ መሰረታዊ ሊባል የሚችል ዘመቻ በማህበራዊ ድህረ ገጾች ጀምረዋል፡፡ በዚህ ደረጃ ምላሽ መስጠቱ እና መጠቀም የሚቻለውን መድረክ ተጠቅሞ የችግሩን ጥልቀት ለማመላከት መሞከር ጥሩ ነው። ነገር ግን የመጻፍ እና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እየተጠየቁ ያሉትን ቡድኖች(‘ፎርማሊ’ ካወራን መንግስት ናቸው -ያውም ፈላጭ ቆራጪ) ባህሪ ግምት ውስጥ በማስገባት፤ ዘመቻው እነዚሁ ቡድኖች አምነትውበት በማናለብኝነት የወሰዱትን ርምጃ ከማስቀየር ይልቅ በስነ ልቦናቸው ለተቀረጸው የትምክህት እና የበላይነት አስተሳሰብ ሃሴት የሚሰጥ ሆኖ ስለተሰማኝ ለነሱ ትምክህት ሃሴት ላለማዋጣት ስል በዚህ በዘመቻ አልተሳተፉኩም።
እንኳንስ የመናገር ነጻነት አይደለም ለእምነት ነጻነት ጀርባቸውን ሰጥተው የክስርቲያኑን የእምነት ተቋማት በቁጥጥር ስር አድርገው ሙስሊሙንም እንዲሁ እምነቱን ለመንጠቅ ቤት ለቤት ጭምር አሰሳ የገቡ ሰዎች ናቸው፡፡ የመናገር እና ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት ጋር በእጂጉ የተቆራኘ የጋዜጣ ህትመት ማስቆም ሳያንሳቸው ዜጎችን –ያውም ኩሩ ሀገር ወዳድ ዜጎችን በሽብረተኛነት በመክሰስ ፣ብዙ እንግልት በማድረስ እና ክብራቸውን ጭምር ለማዋረድ በመሞከር ሌሌች ዜጎች የዜግነት ክብር እና ነጻነት ጥያቄ ቅብጠት እና በህይወት መቀለድ እንዲመስላቸው በማድረግ የባርነትን እስተሳሰብ በደህንነት ተቋማት ፣በህግ ተቋማት እንዲሁም የማህበራዊ ድንዝዝነት በሚያስፋፉ ሌሎች ልማዶች የሚስፋፉበትን መንገድ በስውርም በግልጽም በማበረታታት የባርነትን መስረት ለማጽናት ሌት ከቀን የሚሰሩ ለመሆናቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁኔታ ያለ ብዙ ምርምር ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
የህገ-መንግስት ጉዳይ እና የዜጎች መብት ፋይዳ ሳይገባቸው ቀርቶ ነው እንዳይባል፤ ትግል ጀመርንም ጨረስንም የሚሉባቸውን ቀናቶች በብሔራዊ ደረጃ ጭምር እንዲከበርላቸው የሚፈልጉ ናቸው። እንዲያውም ያለባቸውን የስነ-ልቦና ችግር ከሚያመላክቱ ነገሮች እንደኛው ይሄው ነው። ህወሃት ስልሳ ሺህ ሰው ሰዋበት የሚሉትን በዓላቸውን የሚያዳንቁትን እና ሰው እንዲያዳንቅላቸው የሚፈልጉትን ያህል ለኢትዮጵያ ነጻነት ከጎጠኝነት በጸዳ በንጹህ የሃገር ፍቅር ስሜት የወደቁ በሚሊየን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያኖች ጉዳይ እንዲነሳም እንዲታወስም እይፈልጉም። ታሪኩ ሲነገር ያሳንሳቸዋላ!የሃሳብ ነጻነት ወደሚያፈኑበት ጉዳይ ስመለስ -የሚያፍኑበት እና ሃሳብ እንደጦር የሚፈሩበት ጉዳይ ምንድን ነው የተባለ እንደሆነ መሳሪያ እንቆ የተኮፈሰ የፓለቲካ ስብዕናቸውን የሚያኮስስ ስለሚመስላቸው። እደፊኛ የሚነፉትን ፕሮፓጋንዳ የሚያስተነፍስ ስለሚመስላቸው። የሃሳብ ልውውጥ ላይ ያለ ስለት ስለሚያስፈራቸው። አንግበው ለተነሱት የትምክህት እና የበላይነት ግንባታ ዓላማ እንቅፋት እንደሆነ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ይመስለኛል። የእምነት ነጻነትም እስከመንጠቅ የሄዱበት ምክንያት ከፍራቻ ውጭ ሌላ ሊሆን አይችልም። የፍርሃት ገጹ ይለያያል። የህወሃት መራሹ መንግስት ፍርሃት በአንድ በኩል በጥጋብ እና በማናለብኝነት የተከናነበ ይመስላል በሌላ በኩል ደሞ በልማት ዲስኩር ተከልሎ ከዲስኩሩ በስከጀርባ በምናቡ የሚስላቸውን “ጸረ-ልማት ሃይሎች” (ኢትዮጵያውያኖች እኮ ናቸው የኢትዮጵያ ልማት ጠላቶች?) እንደምክንያት እየተጠቀመ የአፈና የሚጧጡፍበት የሞራል ፈቃድ አብረውት ክሚሰሩት “እህት ድርጂቶች” ይወስዳል፡፡ በህወሃት “የማይበገር ጀግንነት” ውስጥ ያለው እውነታ (‘ሪያሊቲ’) ሃሳብን በነጻነት የመግልጽ መብትን እስከመፍራት የሚያደርስ ፍርሃት ነው። የደህንነት ተቋማቱም እወቃቀር የሚሰማቸውን የፍርሃት ደረጃ ግምት ውስጥ ያስገባ ይመስላል።ስለ ህወሃቶች እና ስለገነቡት የማፈኛ ተቋም የራሴም የሰዎችም ተሞክሮ አለኝ። ገና በልጂነት ባደኩባት የደሴ ከተማ ፓሊስ(ህወሃት ለአፈና ተግባር ካሰለጠናቸው ውስጥ ነበር) አንዱን ያለ እግባብ እያንገላታ ለማሰር ዱብ እንቅ ሲል (እንደዛ ይደረግ የነበረው ደሞ ለሃገሩ በብሄራዊ ውትድርና ዘምቶ የመጣ ዜጋ ነው-የገባው የሚመስለው የፖለቲካ ሁኔታ እንገቱን ባያስደፋው ኖሮ የዛን ለፍዳዳ ፖሊስ ጥርሱን የሚያራግፍ ጎበዝ ነበር። አውቀዋለሁ ) ነገሩ ከንክኖኝ ከፖሊሱ ጋር “የምን እደረገህ” ያደረገውም ነገር ካለ በስነ-ስርዐት ውሰደው የሚል ሙግት ውስጥ ገባሁ። ከዚያ በኋላ ፖሊሱ ልጁን ትቶ ወደኔ ዞረ። ዱላም ጀመረ። ታሳሪው እኔ ሆንኩ፡፡ እና ሂድ እልሄድም ውዝግብ ተጀመረ። ጓደኛየ ታደሰ ባየ( ፌስ ቡክ ላይ አለ) በዛ በዝናብ ተንበርክኮ ሁሉ ለመነው ፓሊሱን፡፡ እኔ ደሞ እንኳን ልለምነው እንዴት ድንጋይ እንደሆነ በተጋጋሚ እነግረዋለሁ። የመምታት አቅሙን ተጠቅሞ ያ ሁሉ የፖሊስ ዱላ ወረደብኝ። በመጨረሻ ላለመታሰር ጨለማውን ምክንያት እድርገን ሁለታችንም አመለጥነው። የተመታሁት ብዙ እንደነበረ የገባኝ ግን በነገታው መሄድ እቅቶኝ ቀኑን አልጋ ላይ ሳሳልፍ ነው። ያኔ ተናድጄ ስለነበር ምንም አልተሰማኝም። ሶስት ቀን ያህል ሳያስነክሰኝ አልቀረም።
Eskinderኮተቤ እያለሁ ደሞ ሮብ ሮብ መብራት ይጠፋ ነበር። በዚያ ምክንያት ረቡዕ ማታ አካባቢ ጥናት የለም ። ወክ ነው የምናደርገው። ወደ ገደራ እየሄድን ስናወራ የነበረውን ከኋላ ይሰማ የነበረ አስቁሞን መታወቂያችንን ከጠየቀ በኋላ እዚያው እካባቢ ወደ ነበረ ፓሊስ ጣቢያ ተወስደን ተመዝግበን የሚጠይቁትን ጠይቀው ተመልሰናል። ሌላ ጊዜ እንዲሁ አራት ኪሎ ላይ የከተማ አውቶብስ ይዞ የነበረ የትግሪኛ ተናጋሪ ሾፌር በራሱ ስህተት እና ትክምህት ምክንያት ተሳፋሪውን ከአራት ኪሎ ይዞ ሚኒሊክ እካባቢ ወደነበረው ፓሊስ ጣቢያ ወሰደን። በትግሪኛ አወራ ከሰዎቹ ጋር። እኛ “ጥፋተኞች ሆንን።” የተማሪዎች ዲን ነው ጣልቃ ገብቶ ነገሩ ያለቀው።የሌሎችን ተሞክሮ በሚመለከት እዚያው ያደኩባት ደሴ ከተማ ላይ በጠራራ ጸሃይ አፉን በደንብ ያልፈታ የህወሃት ታጣቂ እንድ ባዶ እጁን የነበረ ወጣት አሯሩጦ ከደረሰበት በኋላ ሰው እየተጯጯኽ የክላሹን አፈሙዝ ደረቱ ላይ አድርጎ ተኩሶ ከገደለው በኋላ ክላሹን እንቆ እንደያዘ ሲሄድ ያስቆመው ፓሊስ አልነበረም። ሌሎች ታጣቂዎችም ያሉት ነገር የለም። (በነገራችን ላይ ያኔ እስከማውቀው ድረስ የልጁ ገዳይ ለፍርድ እልቀረበም)እንደዛ እይነቱ የህወሃት ጭራቅነት በርሃ ባልነበሩት ዘመድ እዝማዶቻቸው ላይ ተጋብቶ “ምክንያታዊ” በሚመስል ሁኔታ ስለፍትህ በሚጮሁ ኢትዮጵያውያን የሚያሳዩትን ቅጥ ያጣ ንቀት ማየት እሁን የተጀመረው እይነት ዘመቻ በበታችነት ስሜት በሚናጥ ስብናቸው እና እስተሳሰባችው ላይ የበላይነት እና የገዠነት ካባ ከሚደርብላቸው በስተቀር ትርጉም ያለው ጩኽት ይሆናል የሚል እምነት የለኝም። የማስጮህ ስሜት እንዲሰማቸው አልፈልግም። ዛሬ ፌስ ብክ ላይ እንዲህ ያለ ዘመቻ ባለበት ሰዐት እዚሁ ፌስ ቡክ ላይ እስክንድር ነጋን በሚመለክት የነዚሁ የህወሃት ወገን የሚመስሉ ሰዎች ያደረጉትን ምልልስ ለአብነት እንዲሆን ያህል ከ’ሆም ፔጂ ላይ ስክሪን ሾት’ ወስጃለሁ፡፡
ከዚያ ውጭ የህግ ስርኦት ያለበት ሃገር ቢሆን ኖሮ እንደ ዳንኤል ብርሃነ ያሉ የህወሃት ደጋፊዎች ሃገር ውስጥ ያለው የሃሳብ ሙግት በጸጥታ ሃይል እና በ”ፍትህ አካላት” እየታፈነ ባዶ ሆኖ ሙግታቸውን እና የሃሳብ ክርክራቸውን ከውጭ ሃገራት ሰዎች ጋር ሲያደርጉ ማየት የህወሃት ደጋፊዎች እና ዘመዶች ባይሆኑ ኖሮ ሊያስገርም ይችል ነበር። ከታች በሊንክ ባስቀመጥኩት የዳንኤል ጽሁፍ የሂውማን ራይቱ ቤን ራውለንስ የእንግሊዝ መንግስት የዕርዳታ እሰጣጥ የሚተች የመጽሃፍ ሪቪው አወጣ ብሎ የእንግሊዝ መንግስት ትችት ሳይሆን ምስጋና ነው የሚገባው የሚል ጽህፍ አውጥቶ ብሎጉም ላይ ጭምር ለጥፎታል። የጽሁፉ ዓላማ ምን ነበር የሚለው ሌላ ጥያቄ ሆኖ መነሳት ያለበት መሰረታዊ ጥያቄ እንደ ዳንኤል ያለው የህወሃት ፖለቲካ ደጋፊ ስለሆነ ብቻ ሃገር ቤት በሚታተሙም ራሱ በፈጠረውም ብሎግ ላይ የመጻፍ ነጻነት ሲሰጠው ሌሎች ዜጎች (ለምሳሌ የዞን ዘጠኝ ብሎገር አባላት) የሚታፈኑበት ምክንያት ከላይ የገለጽኩት ነው። እፈናውን ተቃውሞ የሚደረገውን ተቃውሞ ያልተቀላቀልኩበት ምክንያት የሚጨምርላቸውን -ተዋጋን እያሉ ለሚያወሩት ብቻ ሳይሆን ያኔ ልጆች ለነበሩት እና የደም ትስስር በሚመስል ምክንያት ብቻ እፈናን በምክንያታዊነት ለማስተባባል እና ተቀባይነት እንዲኖረው ለማድረግ ለሚሞክሩትም ጭምር- ለትምክህታቸው የሚጨምረላቸውን ሃሴት ላለመስጠት ነው። የዳኤል ፓስት
ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አምባገነናዊነት ሌላ ዓለም ከሚስተዋለው በመሰረታዊነት የሚለይ እንደሆነ እምኖ ተቀብሎ የሚደረገው ተቃውሞ የህወህትን እምባገነናዊ ባህሪ ግምት ውስጥ ያስገባ እና ህወሃቶች በመንፈስም በፖለቲካም የማይጠቀሙበት እና ትምክህት የማይጨምርላቸው መሆነ አለበት ብየ ስለማምን ነው፡፡ በሌላ አንጻር ደሞ የሚደረገው ዘመቻ መሬት ላይ ያለ እና ለህዝቡ ስነ-ልቦና እና አስተሳሰብ ቅርበት ያለው ፣ በቀላሉ የሚገባ ቢሆንም ጥሩ ነው። ምን ያህል ኢትዮጵያዊ ነው በፌስ ቡክ እና ትዊተር ላይ ያለው? ፌስ ቡክ ላይ ካለውስ የህወሃት ደጋፊ ከሆነው ውጭ ስለ ህወሃት መራሹ መንግስት አፈና እና ቅጥ ያጣ እምባገነናዊነት የማያውቀም ምን ያህሉ ነው? ለ “ዓለማቀፉ” ማህበረሰብ ነው እንዳይባል ለዚሁ አፈና ለሚያደርሰው መንግስት ትብብር እና ርዳታ የሚሰጡት እነዚሁ ወገኖች ናቸው። ዳንኤል የእንግሊዝን የእርዳታ አሰጣጥ በመደገፍ የእንግሊዝን መንግስት የሚከላከል ጽሁፍ መጻፍ ደረጃ ላይ የደረሰበት ”የዲፕሎማሲ” ልምምድ ሳይሆን የፖለቲካ ትስስርንም ጭምር የሚያመላክት ይመስለኛል። ለሃወሃት የጥጸጥታ ሃይሎች ስልጠና እና ሎጂስቲክ የሚያቀርበው ማን ነው? ብዙዎቹ የህወሃት ፖሊሲዎች በርግጥ ከህወህት ብቻ የመነጩ ናቸው? “የመለስ” ራዕይን ጨምሮ?

Monday, February 25, 2013

መንግስት ሕገ መንግስቱን ንዶ እየጨረሰው ነው!
ድምፃችን ይሰማ
‹‹የያዛቸው የፖሊስ መኮንን ወይም የሕግ አስከባሪ በጊዜው ገደብ ፍርድ ቤት በማቅረብ የተያዙበትን ምክንያት ካላስረዳ፣ ፍርድ ቤቱ የአካል ነጻነታቸውን እንዲያስከብርላቸው የመጠየቅ ሊጣስ የማይችል መብት አላቸው፡፡››
ሕገ መንግስት አንቀጽ አንቀጽ 19መንግስት ሕገ መንግስቱን ንዶ እየጨረሰው ነው!
ለ200 ቀናት ያለ ክስ የታሰሩ ሙስሊሞች በኢትዮጵያ ምድር
የዜጎችን ዴሞክራሲያዊ መብት ያስከብራል ብለን ተስፋ የጣልንበት ሕገ መንግስት በመንግስት አስፈጻሚዎች እየተጣሰ መብታችንም ፈጽሞ በማይነጻጸር መልኩ እየተመዘበረ ነው፡፡ የእምነት ነጻነታችን፣ የአምልኮ መብታችን፣ ሃይማኖታችንን በነጻናት የመተግበር ተፈጥሮአዊ መብታችን፣ የእምነት ተቋማትን የማቋቋም መብታችን፣ የሃይማት መሪዎችን በነጻነት የመምረጥ መብታችንና መሰል መብቶች ሕገ መንግስታዊ እውቅና የተሰጣቸው ነገር ግን በመንግስት ባለፉት አመታት እንደዘበት እየተወረሱብን የሄዱ መብቶቻችን ናቸው፡፡ ለእነዚህ ሕገ መንግስታዊ መርሆች መከበር ሁለመናችንን አሳልፈን ሰጥተን ሰላማዊ ትግል እያደረግን ነው፡፡
ሆኖም የመንግስት የህገ መንግስት እና የመብት ጥሰት ድንበር የለሽ እየሆነ መጥቷል፡፡ መንግስት ሕገ መንግስቱን አስጠብቃለሁ በሚል የለበጣ ምክንያት ሕገ መንግስቱን እየናደው ነው፡፡ የዜግነት ሕገ መንግስታዊ መብቶቻችን ሁሉ ውሃ እየበላቸው ነው፡፡ ከቀናት በፊት ገልጸነው እንደነበረው መንግስት የህግ ጥሰቱን ለመደበቅ እንኳ የማይጨነቅበት ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡ በአገሪቱ በሁሉም አቅጣጫዎች የመብት ጥሰቱ ያለ መስፈሪያ.. ያለ ከልካይ እየተሳለጠ ነው፡፡ ሕገ መንግስቱን ማስጠበቅ የሚገባቸው አካላት ዝምታን መርጠዋል፤ እንዲያውም በሌላ አቅጣጫ የመብት ጥሰቱ አቢይ ተዋናይ እየሆኑ ነው፡፡
ፍ/ቤቶችን ተመልከቷቸው – ሕግ ከማስከበር ይልክ ከጸጥታ አስከባሪዎች ጋር በመተባበር የዜጎችን መብት እየጣሱ ነው፡፡ ሕገ መንግስቱ በአንቀጽ 19 የተያዙ ሰዎች መብት በሚል ርእስ በሁለቱ የመጀመሪያ አንቀጾች የታሰሩ ሰዎች ያላቸውን መብቶች ይጠቅሳል፡፡ ‹‹የተያዙ ሰዎች በአርባ ስምንት ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት የመቅረብ መብት አላቸው፡፡ ይህም ጊዜ ሰዎቹ ከተያዙበት ቦታ ወደ ፍርድ ቤት ለመምጣት አግባብ ባለው ግምት የሚጠይቀውን ጊዜ አይጨምርም፡፡ ወዲያውኑ ፍርድ ቤት እንደቀረቡ በተጠረጠሩበት ወንጀል ለመታሰር የሚያበቃ ምክንያት ያለ መሆኑ ተለይቶ አንዲገለጽላቸው መብት አላቸው፡፡›› እንዲሁም ሌላኛው ንኡስ አንቀጽ ‹‹የያዛቸው የፖሊስ መኮንን ወይም የሕግ አስከባሪ በጊዜው ገደብ ፍርድ ቤት በማቅረብ የተያዙበትን ምክንያት ካላስረዳ፣ ፍርድ ቤቱ የአካል ነጻነታቸውን እንዲያስከብርላቸው የመጠየቅ ሊጣስ የማይችል መብት አላቸው፡፡›› ይላል ሕገ መንግስቱ፡፡ መሬት ላይ ያለው ግን ከዚህ በተቃራኒው ነው፡፡
ዛሬ ግን በኢትዮጵያ ምድር ከ190 በላይ ቀናት ያለ ክስ በእስር ላይ የሚገኙና የሚንገላቱ ዜጎች አሉ፡፡ በተለይም በአማራ ክልል ጥቂት በማይባሉ ከተሞች ኢማሞች፣ የሃይማኖት አዋቂዎች፣ አረጋውያንና ወጣቶች ያለ ክስ ከ6 ወራት በላይ በእስር ላይገኛሉ፡፡ ከሕገ መንግስቱ ይጋጫል የተባለው የጸረ ሽብር ሕጉ አንኳ በ4 ወራት ውስጥ ክስ እንዲመሰረት ያዛል – ያ ካልሆነ ታሳሪዎቹ እንዲለቀቁ ያዛል፡፡ ነሀሴ አራት በደሴ ፖሊስ ባስነሳው ግርግር የተያዙት ሸኽ ሀሰን ሀሚዲን፣ ሸኽ ጀማል እና ኡስታዝ ባህረዲን 195 ቀናት ያለምንም ክስ በወህኒ ይገኛሉ፡፡ በሰሜን ወሎ መርሳ ከተማ ያለው ደግሞ ከዚህ እጅግ የከፋ ነው፡፡ ከረመዳን ወር ጀምሮ ማለትም ከባለፈው ሐምሌ ወር 2004 ጀምሮ ያለ ክስ በእስር ላይ የሚገኙ በርካታ ሙስሊሞች አሉ፡፡ የመርሳው ታሳሪዎች ከ200 በላይ ቀናት በእስር ቤት ያለ ምንም ክስ ታጉረዋል፡፡ በወልዲያ፣ በኮምቦልቻ፣ በከሚሴ እና በሌሎችም አቅራቢያ ከተሞች በርካታ ሙስሊሞች ያለ ክስ ያለ ፍርድ በወህኒ ይገኛሉ፡፡ እነዚህን ዜጎች ዳኞች በነጻ ሊያሰናብቷቸው ቢገባም ይህ አልሆነም፡፡ እነዚህ ዜጎች የተከሰሱበት የተጠረጠሩበት ወንጀል አልተነገራቸውም – ፖሊስ ይህን እንዲያደርግ ሕጉ ቢያስገድደውም አላደረገውም፡፡ ሌላዉ ቢቀር መንግስት በራሱ ፍ/ቤቶች እንኳ አስቀርቦ ሊያቀርብባቸው የሚችለው ክስ የለውም፡፡ ንጹሀን ዜጎች ሙስሊም በመሆናቸው ብቻ፣ በሃይማኖታቸው ምክንያት ብቻ በእስር እና ስቃይ ውስጥ ይገኛሉ፡፡
ይህ ሁለ ሲደረግ የፍትህ አካላት፣ ለሕገ መንግስቱ ዘብ ነን የሚሉ ዜጎች እና ተቋማት፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ ስለ ሕግ የበላይነት የሚጨነቁ ዜጎች የት ናቸው? ሕገ መንግስቱ ጠባቂ እና አስከባሪ አጣ እኮ፡፡ ዜጎች ሕገ መንግስታዊ መብታቸው ተደፈጠጠ እኮ፡፡ ሕገ መንግስታዊ ዋስትናችን ተገሰሰ እኮ!
መንግስት ሕገ መንግስቱን ንዶ እየጨረሰው ነው! ክፍል ሁለት ይቀጥላል…
አላሁ አክበር!

Sunday, February 24, 2013

Ethiopia’s high profile official, Junedin Sado defects to Kenya

Ethiopia’s high profile official, Junedin Sado defects to Kenya


Awramba Times (Addis Ababa) – Junedin Sado, Ethiopia’s high profile official and former Minister of Civil Service has defected.
According to Ethiochanel, a pro-government private newspaper based in Addis Ababa, Junedin Sado is seeking asylum in neighboring Kenya.
Ethiopian authorities have charged Junedin Sado’s wife, Habiba Mohamed, with terrorism for using money from the Saudi Arabian Embassy to pay for Islamic protests against the government.
Junedin Sado

In the aftermath of Habiba’s arrest, Junedin published a letter on Ethiochannel newspaper defending his wife and criticizing the federal prosecutor’s charges. Last December, Awramba Times has reported about the Ethiopian parliament’s plan to waive the immunity of Junedin Sado.
Since 2001, Jundein Sado has served on various key positions of the government including as president of the Oromia Region , Minister of Transport and Communication and Minister of Civil Service.

Saturday, February 23, 2013

የካቲትን የምንዘክረው ከሀገር በቀል ወራሪው ህወሃት ጋር በመፋለም ነው!!

የካቲትን የምንዘክረው ከሀገር በቀል ወራሪው ህወሃት ጋር በመፋለም ነው!!

ቀደምቶቻችንን የምናስታውስበት፣ ሀገራችንን ከጠላት ወራሪ እና አንድነቷን ለማስጠበቅ ያደረጉትን ተጋድሎ ከምንዘክርበት እለት አንዱ የካቲት 12 ነው። በዚህ ግዜ ይህንን ታሪክ ገልብጦ ለማበላሸትና ለመጻፍ የሚጥረውን፣ የአሁኑን የግራዚያኒ ትንሽ ወንድም ሀገር በቀል ዘረኛ መንግስት የሆነውን ህወሃት/ኢህአዴግን ሀይማኖት፣ ዘርና ጾታ ሳይለየን የምንታገልበት ሁነኛ ወቅት ላይ እንገኛለን።
የቀድሞዋ የአፍሪካ ሀገራት የነጻነት ተምሳሌት የሆነችው እማማ ኢትዮጵያ፤ ዛሬ ሀገር በቀል በሆኑ የዘረኛ መዥገሮች ስብስብ ተጣብቃ የአበው መሰዋእትነት ከንቱ ይሆን ዘንድ ወያኔዎች እየሰሩ ነው። ጥንታዊ ታሪክን በመፋቅ፣ ባልተደረገና ባልተፈጸመ ታሪክ ለመተካት ወያኔ/ኢህአዴግ እያንዳንዱን የአበውን የታሪክ ማህደር በማጥፋት፣ እንደ አቡነ ጴጥሮስ የመሳሰሉ የጀግኖችን ሀውልት አሻራ በማፍራረስ ርካሽ የሆነ ግዚያዊ የፖለቲካ ጥቅም ማስገኛ ስራ ላይ በመሰማራት ሀገራችንን ወደኋለዮሽ እድገት እየጎተቷት ይገኛሉ።
ሁለቱን ገዳዮች የሚያገናኛቸው፤ የግራዚያኒ ወታደር አበው ለነጻነታቸው ለአንድነታቸው ሲያደርጉት የነበረውን ተጋድሎ ለማስቆም፤ የህዝቡን የትግል ሞራል ለመግደል የአዲስ አበባን ነዋሪ ቁጥሩ 30ሺ የሚሆን ንጹሃን ዜጎችን በመጨፍጨፍ ፋሽስትነቱን ለማሳየት ያደረገው ያልተሳካ ሙከራ ነው፡፡ ይሁን እንጅ ኢትዮጵያውያን ለነጻነታቸው የሚያደርጉትን ትግል ይህ አልገታቸውም። በተመሳሳይ ደግሞ ዘመን አመጣሹ የየካቲት አስራ አንዱ ወያኔም፤ እንደፋሽስቱ ሁሉ በንጹሃን ህዝባችን ላይ በጎንደር ስላሴ፣ በምርጫ 97፣ በጋምቤላ፣ በአዲስ አበባ፣ በኦሮምያ፣ በአዋሳ፣ በሀረር አሁን ደግሞ በሙስሊሙ ወገናችን ያደረሰው ጭፍጨፋ፣ እስርና ግድያ ከግራዚያኒ ጋር ያመሳስለዋል። ልዩነታቸው ይሄኛው ሀገር በቀል ወራሪ መሆኑ ነው። ምን አልባትም ወያኔ ልደቴ ብሎ የሚጨፍርበት የካቲት 11 ለሱ የድል ቀን ሲሆን፤ ለእኛ ደግሞ አባቶቻችን የምናስታውስበት የመከራ ቀን ነው።
በየካቲት12 የኢትዮጵያ ህዝብ ለነጻነቱ፣ ለአንድነቱ፣ ለሀገሪቱ ከብር የፋሽስቱን ወራሪ ሃይል በመመከት፤ ልጅ አዋቂ ሳይለይ ከሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫዎች በመጉረፍ ጠላትን በማስጨነቅ እየሞቱም አልበገርነታቸውን ያስመሰከሩበት ልዩ ቀን ነው። ኢትዮጵያ ብቸኛዋ የአፍሪካ የነጻነት ተምሳሌት ሀገር እንድትሆንም በማድረግ፤ ወርሃ የካቲት ታሪካዊ ወርና በድል አጥቢያነት በሀገራችን እንዲሁም በአሁጉራችን አፍሪካ ዘለአለም እንዲታወስና እንዲዘከር አድርገው አበው አልፈዋል። ይህን የማስጠበቅ ታሪካዊ የሞራል ግዴታ የማን ነው?
አበው የፋሽስቱን የግራዚያኒ ወራሪ ጦር ድባቅ በመምታት አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ሀገራችንን ከጠላት ወራሪ አድነው አስረክበውናል። በዚህ ታሪካዊ ገድል በሆነው በወርሃ የካቲት የተሰዉት ጀግኖች፣ የኢትዮጵያ ልጆች አጥንትና ደም መሰዋእትነት ከቶ ከታሪክ ማህደር የማይጠፋ ስማቸው ከመቃብር በላይ ሆኖ ሲዘከር ይኖራል። ይህ ትውልድ ይህን የማስጠበቅ የታሪክ ባለተራ ነው እንላለን።
ግንቦት 7፣ የአባቶቻችንን ጀግንነትና ወደር የሌለውን የሀገር ፍቅር፣ የሀገር ክብር፣ የቁርጠኝነት መንፈስና የአደረጉት መሰዋእትነት ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ይታገላል። በቁርጥ ቀን ልጆች በቁርጥ ቀን ሰዓትም ለመድረስ፤ እስከመጨረሻው በመታገል ታሪካዊ ግዴታውን ለመወጣትና ይህን ድል ለማስመለስ፤ አስመልሶ ለትውልድ ለማስረከብ፣ ለማስጠበቅ እያንዳንዷን ደቂቃ ሊጠቀምባት ቆርቶ ተነስቷል።እርሰዎስ?
የሀገራችን ህዝብ ሆይ፡- የኢትዮጵያ ጀግኖች እነ አጼ ሚኒሊክ፣ የበላይ ዘለቀ፣ እነ አብዲሳጋ፣ እነ ዘራይደረስ፣ እነ አቡነ ጴጥሮስ፣ እነ አፄ ዮሃንስ፣ እንደ ቋራው ካሳ እና ሌሎችም በበቀሉበት፣ በተፈጠሩበት በጥቁር አፈር ምድር፤ ፀረ-ኢትዮጵያ ሀገር በቀል ዘረኛ ሃይሎች መፈጠራቸው አሳዛኝ ታሪክ መሆኑን እኛም እንመሰክራልን። ይሁን እንጅ፣ ቅሉ ይህንን በሁለት ትውልድ መካከል የተፈጠረውን የሰማይና የምድር ልዩነት ቁጭ ብለን በማየት ከንፈራችንን እየመጠጥን የምንቀመጥበት ሰአት ላይ አይደለንም። ጥሪ ከወዲያ ማዶ እየተበራከተ ነው። የድረሱልን ጥሪ!
ስለዚህም መላው የሀገራችን ህዝብ ወያኔን ለማስገደድ አሊያም ለማስወገድ አቅሙ በፈቀደ ሁሉ በገንዘብ፣ በእውቀት በጊዜና ጉልበቱ በመርዳት ታግለን የካቲትን የመሰዋእትነት መንፈስ እያስታወስን፣ ግንቦት 7ን የህዝብ ድምጽ ለማስከበር ይህ ትውልድ ሞራላዊ ግዴታ አለበት እና እንነሳ! እንሂድ።
በአንጻሩ በወያኔ መንደር በአጋጣሚም ሆነ በጥቅም ምክንያት ያላችሁ፡- እንደ ጠዋት ጤዛ ብን ብለው ከሚጠፉ አምባገነኖች ጋር በመለጠፍ ህዝባችንና ሀገራችንን መበድልና ማሰቃየት ለታሪክ ተጠያቂነት ይደርጋል። በወንጀል ተባባሪነት ስለሚያስጠይቅ ከወዲሁ መንገድን በማስተካከል እምቢ ለህወሃት፣ በቃኝ ባርነት፤ በሚል የህዝብ አጋርነትና ድጋፍ ወደ አለው የነጻነት ትግል በመቀላቀል ከማይሻር፣ ከማይጠፋ የታሪክ ማህደር ውስጥ ራስዎትን ያስገቡ ዘንድ የካቲት ጥሩ አጋጣሚ ነው።
በተለይም ኢትዮጵያውያን አርበኞች በጠላት ላይ የወሰዱት የማያዳግም እርምጃ ለመድገም እና ኢትዮጵያን ከሀገር ውስጥ ጠላት ከሆነው ህወሃት ለመታደግ፤ ነፃነታችንን አሳልፎ ላለመስጠት፣ ብርቱ ክንዳቸውን በአኩሪ መሰዋእትነት ለማሳረፍ እና ሕያው ምስክር ለመሆን ከተነሱት ከግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ጋር ሆነን በጋራ በተባበረ ሃይል የምንታገልበት ጊዜ ዛሬ ነው።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

ጊዮን ሆቴል የተጠናቀቀው የኦህዴድ ድራማ!!

ጊዮን ሆቴል የተጠናቀቀው የኦህዴድ ድራማ!!

ግለሰብ የሚጠመዝዘው “የህዝብ” ወኪል
opdo1
የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ወገኛ ድርጅት ነው። “ሲያደርጉ አይታ” እንደሚባለው እንደ ኤፈርት አይነት ታላቅ የንግድ ኢምፓየር ከፈተ። ስሙንም ቱምሳ ኢንዶውመንት አለው። ቱምሳ የድርጅት ቅርጽና መልክ ተበጅቶለት ስራ ጀመረ። በበረሃ ትግል ወቅት በነበረን ሃብት መሰረትነው ለማለት ቀዳሚዎቹ የኦህዴድ ምልምሎች ሳንቲም አዋጡና ወደ ተግባር ገቡ።
ቱምሳ በስሩ ዲንሾ ትሬዲንግ፣ ዲንሾ ትራንስፖርት፣ አግሮ ኢንዱስትሪና የንግስ ድርጅቱ የጀርባ አጥንት የሆነውን ቢፍቱ ገነማ የሚባል የጫት ንግድ አቋቋመ። የትራንስፖርት ዘርፉን ይመሩ የነበሩት የአቶ ኩማ ደመቅሳ ወንድም እንክት አድርገው በሉትና ከሰረ። ዲንሾ ንግድ ማዳበሪያ እነግዳለሁ ብሎ ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ከንግድ ባንክ ተበደረና ታሪኩን በኪሳራ ደመደመው። ዲንሾ አግሮም ከእህት ኩባንያዎቹ እንደተማረው ኪሳራ ተከናንቦ መሬት ብቻ አንቆ ቀረ። መጨረሻ ላይ በገፍ የሰበሰበውን መሬት በሽርክና ስም ለሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ አስረክቦ እጁን ታጠበ።
ማዳበሪያ ንግድ ሲገባ ለመወዳደር ያሰበው ከጉና ንግድና አምባሰል ከሚባለው የህወሃት ማዳበሪያ አቅራቢ ጉልበተኛ ድርጅት ጋር ነበርና ገበያ ለመሳብ በሚል ማዳበሪያ በዱቤ አደለ። መጨረሻ ላይ “የበተነውን ብር መሰብሰብ አልቻለም” ተባለና ከማዳበሪያ ንግድ ተገለለ። ባንክ ተጨማሪ ብር እንዲሰጠው ቢጠይቅም ተከለከለ። ኤፈርት በላይ በላይ እንደሚፈቀድለት ብድር ቱምሳ ቢጠይቅም ባንክ አልሆነለትም። በክልሉ ማዳበሪያ እንኳ የመነገድ መብቱን አሳልፎ ተመልካች ለመሆን ተስማማ። ከፍተኛ የአክሲዮን ባለቤት ከሆነበት ወጋገን ባንክ እንኳ ብር ወስዶ ንግዱን ማስቀጠል ባለመቻሉ ዲንሾ ትሬዲንግ ሰመጠ። ከሙስናው ጋር ተዳምሮ ስውር ደባና ድንቁርና ገደለው። አሁን የአረም መድሃኒት ይቸረችራል።
(የምስሉ ባለቤት: ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ)
የማዳበሪያ ንግዱ እንዳከተመለት ኦህዴድ “ብልሃት አድርጎ” የወሰደውን አዲስ የንግድ ስልት ቀየሰ። ገጠር በመዝለቅ ኮንጎ /ላስቲክ/ ጫማ ለመነገድ ተስማማ። በገፍ በኮንቴነር አስገባ። አገር የሚመራው ኦህዴድ ኮንጎ ቸርችሮ ሊያተርፍ የንግድ “ፋኖ ተሰማራ” አለ። ብዙም ሳይቆይ ያስመጣውን ኮንጎ ይዞ እጁን አጣጥፎ ተቀመጠ። ድርብ ኪሳራ። አቻ ድርጅቶች መኪና መገጣጠሚያ ሲከፍቱ፣ ሲሚንቶ ማምረት ሲጀምሩ፣ ማዳበሪያ ለማምረት ሲነሱ፣ ትርፋቸውን እያሰቡ ወርቅና ማዕድን ቆፍረው ለማውጣት ሲሰማሩ፣ በትራንስፖርትና በሸቀጥ ንግድ ከብረው ትርፋቸውን በዶላር ሲያሰሉ ኦህዴድ ኮንጎ ጫማ ለመነገድ እቅድ አውጥቶ፤ እሱም ከሽፎበት ይደናበር ነበር።
እንጂ ቀደም ሲል ሽፈራው ጃርሶ፣ ከዚያም ግርማ ብሩ ሲመሩት የነበረው ቱምሳ ኢንዶውመንት እንዳይከስም ተሸክሞ የያዘው የጫት ንግዱ ስለነበር አዲስ ስልት ዘርግቶ ለመክበር ያወጣው እቅድና የበረሃ ላይ ስቃዩ ጊዮን ሆቴል እንዴት እንደተቋጨ የሚለው ጥያቄ ምላሽ የሚያስፈልገው ነው።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ “ቱጃሯ ሱራና ኦህዴድ – ከጫት ንግድ በስተጀርባ ያለው ቁማር” በሚል ርዕስ አንድ ዘገባ ማስነበባችን ይታወሳል፡፡ በዚያው ዘገባ ላይ ኦህዴድ ሶማሌ ጫት ንግድ ውስጥ ገብቶ እንዳልተሳካለት እናስከትላለን ባልነው መሠረት በተወሰነ መልኩ ከዚህ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡
ግመሉ ኦህዴድና የጊዮን ሆቴሉ ድራማ
ዋና ጽህፈት ቤቱን ድሬዳዋ ያደረገው ቢፍቱ ገነማ የጫት ንግድ አትራፊነቱ ከግለሰቦች ባይበልጥም ከፍተኛ የሚባል ነው። በዚሁ አትራፊነቱ የተነሳ “ኢገ ኬኛ” ደማችን ይሉታል። የባለስልጣኖችን ከርስ፣ የተለያዩ ሃላፊዎችንና የበታች ሰራተኞችን ቅርምት ተቋቁሞ አዲስ አበባ ኮሜርስ ፊት ለፊት ህንጻ ለመስራት ችሏል። ብቸኛው የቱምሳ ስኬት መሆኑ ነው።
በጫት ንግድ ውስጥ ያለው የገንዘብ ዝውውርና ትርፉ ያጓጓው ቱምሳ ኢንዶውመንት አዲስ ስራ አስኪያጅ ከመደበ በኋላ ወደ ሶማሌ የሚላከውን ጫት ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር እቅድ ዘረጋ። ወይዘሮ ሱሁራ እስማኤል በብቸኛነት ወይም በከፍተኛ ደረጃ የተቈጣጠሩትን የሶማሌ የጫት ንግድ ለማምከን ኦህዴድ ባሉት ከፍተኛ የፖለቲካ ሃላፊዎች አማካይነት ጡንቻውን ለማሳየት ሞከረ። ወይዘሮ ሱራ ባላቸው ከብረት የጠነከረ ሃይልና ጉንጉኑ ሊበተን የማይችል ሰንሰለት ኦህዴድ የመጀመሪያ ሃሳቡ ቅዠት ሆነ። ከሸፈ!!
የመከላከያ ድጋፍ
ሱሁራ ኢስማኤል (ፎቶ: Philipp Hedemann)
ሁለተኛው አካሄድ ወይዘሮዋ ሃርጌሳን ስለተቆጣጠሩት ሃርጌሳ ላይ ተወዳዳሪ ለመሆን ዋጋ በመቀነስ ጫት ማቅረብ ነበር። ሆኖም ኦህዴድ ጫት ወደ ሃርጌሳ የላከ ቀን ሃርጌሳ ጫት በነጻ ታደለ። ኦህዴድ የላከውን ጫት የሚገዛው ታጣ። ጫት በባህሪው ቶሎ ስለሚበላሽ “ተቃጠለ” አስቀድሞ መረጃ የደራሳቸው ሞኖፖሎች ኦህዴድን “አርፈህ ተቀመጥ” በማለት “አይቼሽ ነው ባይኔ ወይስ በቴሌቪዥን” የሚለውን ዘፈን ጋበዙት።
ሶስተኛው መንገድ ተቀየሰ። “ተነሳ ተራመድ፣ ክንድህን አበርታ …” ተዘመረ። በእቅዱ መሰረት ኦህዴድ የጫት አበባ ይዞ ጉዞውን ወደ ፑንት ላንድ አቀና። የፑንት ላንድ ጉዞና የንግድ አላማ በሚስጥር እንዲሆን ተወሰነ። የቱምሳ አመራሮች ስንቅና አገልግል ቋጥረው የኦጋዴንን በረሃ በመኪና ለማቋረጥና ፑንት ላንድ ለመግባት ወሰኑ። በረሃው ለህይወትም አስጊ ስለሆነ የመከላከያ ትብብር አስፈለገ።
ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ እንደሚመሰክሩት የኦህዴድ ሰዎች ፑንት ላንድ ለመግባት በበረሃ የተንከራተቱት አንዴ አይደለም። በተደጋጋሚ ፈታኝ ሁኔታዎች አጋጥሟቸዋል። የመጀመሪያውን ጉዞ አከናውነው ሲመለሱ በረሃው በልቶ ጨርሷቸው ከሰል መስለው ነበር። ከበርካታ ምልልስ በኋላ የፑንት ላንድ አስተዳደር ቀና ምላሽ ሰጠ። በውሳኔው መሰረት የፑንት ላንድ “የፓርላማ አባላት” አዲስ አበባ ተገኝተው በኦፊሴል የንግድ ውል ለመዋዋል ቀጠሮ ያዙ።
በቀጠሮው መሰረት የፑንት ላንድ ወኪሎች አዲስ አበባ ገቡ። በቱምሳ ወጪ ግዮን ሆቴል አረፉ። ምርጥ የአወዳይ ጫት ሆቴል ድረስ እየተላከላቸው “ቃሙት”። ተዝናኑ። ለቀናት ውሎ አበልና ሙሉ ወጪያቸው እየተቻለ ተምነሸነሹ። አዲስ አበባ ያሉ ጓደኞቻቸውንና ወዳጆቻቸውን በመጋበዝ ኦህዴድ የሚያቀርበውን ጫት “በሉት”። “አገር መሪ ነኝ የሚለው” ኦህዴድም የታዘዘውን እያቀረበ ጋበዘ። የቢዝነስ ማባበያ መሆኑ ነው። ይህ ሁሉ ሲደረግ የጫቱን ንግድ የተቆጣጠሩትና ከጀርባ ሆነው ከለላ የሚሰጡት ራዳራቸውን አስተካክለው ይቀርጻሉ።
ጋዜጣዊ መግለጫ
የፑንት ላንድ የፓርላማ ወኪል ናቸው የተባሉት ክፍሎች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ። ታላቅ የንግድ ስራ ለመስራት ይህ የመጀመሪያ እንደሆነና ወደፊት “ዘርፈ ብዙ” ስራ በጋራ ለመስራት እቅድ እንዳለ ተናገሩ። መርቅነው መግለጫውን አደመቁት። ኦህዴድም ፈነጠዘ። በጫት ንግድ ፑንት ላንድን ሲቆጣጠር ታየው። ዶላር ለመሰብሰብ ጎመጀ። ታላቅ የንግድ ኢምፓየር ዘርግቶ ኢኮኖሚውን ሲዘውር ተመለከተ። የማዳበሪያ ቁጭቱን ሲወጣና ሲረካ ተሰማው። ሁሉም ነገር ከንቱ መሆኑ የታወቀው ግን ሰዎቹ አዲስ አበባ በገቡ በበነጋው እንደነበርና ጉዳዩ ገብቷቸው እናባራቸው ያሉም ነበሩ።
ውለታ ለመፈጸም መጥተው ከዛሬ ነገ እያሉ ከሳምንት በላይ በድሎት ጊዮን ሆቴል ተኝተው ሙሉ እንክብካቤ የተደረገላቸው እንግዶች መግለጫውን አስቀድመው ከሰጡና ውሉን ከፈጸሙ ወደ አገራቸው ስለሚመለሱ ጉዳዩን በማዘግየት ኦህዴድን ያልቡት ነበር። ከነሱ መካከል በጓሮ ከሌሎች ጋር የሚነጋገሩም ነበሩ። እንደምንም ተብሎ መግለጫ ከተሰጠ በኋላ መጽሃፉም ዝም ቄሱም ዝም ሆነ። ኦህዴድ ከፍ ዝቅ ብሎ ያስተናገዳቸው ሰዎች ደብዛቸው ጠፋ። የሞራልና የስሌት ኪሳራ ተከተለ። መንግስት ሆነው እንደ ሌባ በጓሮ ሲርመጠመጡና ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ሲልከሰከሱ ተታለሉ። በግልጽ የሂሳብ ሰነድ ያልተወራረደ ከፍተኛ ገንዘብ በወቅቱ በጉርሻ ስም መሰጠቱን፣ የሽኝት ቀን የኢትዮጵያ ባህል እቃዎች ስጦታ መቅረባቸውም የአደባባይ ምስጢር ነው። የኦህዴድ “ግመሉ” የበረሃ ታሪክ ይኸው ነው። ሰዎቹ ድምጻቸውን አጠፉ። ኦህዴድም “ግመሉ” የሚለውን ስም ይዞ ቀረ።
ፉከራው
የፑንት ላንድ ጉዞ ከድግግሞሽ በኋላ መሳካቱ ሲታወቅ የቱምሳ አመራሮች “ገድላቸውን” በገሃድ ቢሮ መናገር ጀመሩ። ኦጋዴን በረሃ ውስጥ ያጋጠማቸውን መከራና ድካም እንዴት እንደተቋቋሙ በኩራት መተረክ ተያያዙ። በተለይ አዲሱ ሃላፊ የዘመቻው መሪ መሆናቸውን ለማሳየት እጅጌያቸውን ይሰበስቡ ጀመር። ወደ ቢሮ ሲገቡ አረማመዳቸውና አስተያየታቸው ተቀየረ። ሰራተኞችን ሲያዙ “የበረሃ ተሞክሮዬ” ማለት ጀመሩ። ስለቁርጠኝነትና ዓላማ መስበክ አበዙ። “ግመል” በስብሰባ ላይ ቋሚ ምሳሌያቸው ሆነ። አስተዳደሮቹን የሚከቡዋቸው በኩራት ታበዩ። ተወጣጠሩ። ቱምሳ ከክስረቱ አገግሞ በትርፍ የሚተኮስበትን አቅጣጫ ያገኙ ያህል በየቀኑ ይዘሉ ነበር። ወሬያቸውም ሁሉ “ፑንት ላንድ ተኮር” ሆነ። ፑንት ላንድ ለመመደብ ዝግጅት የጀመሩና ትርፋቸውን የሚያሰሉት ባልደረቦቻችን ድርጊታቸው ሁሉ ያሳፍር ነበር።
አገር የሚመራ ድርጅት፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ “ወኪል” ነኝ የሚል ድርጅት ክብሩን ጠብቆ ስራውን መስራት እየቻለ፣ እንደ ኮንትሮባንድ ነጋዴ በረሃ ለበረሃ ሲቀበዘበዝ ማየት ያሳፍራል። ከሁሉም በላይ ደግሞ የኦህዴድ ከፍተኛ አመራሮች ሆነው ለጥቅም ሲሉ ግለሰብ አንግበው ሲነጉዱ ማየት ያሳዝናል። ከሁሉም በላይ ደግሞ የኦሮሞ ገበሬዎች በራሳቸው መሬት ላይ የተከሉትን ጫት ለፈለጉት እንዳይሸጡ በሞኖፖል ገበያ ተወጥረው እንዲያዙ ሲደረግ ተከራካሪ ማጣታቸው አንገት ያስደፋል። የጫት ኬላ ተነስቶ ክልሉ ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢውን ማጅራቱን ሲመታ አቋም የሚይዝ መጥፋቱ በባርነት የመያዝ ያህል ዘግናኝ ነው።
ከሁሉም በላይ አሳፋሪው ደግሞ የክልሉ ገቢና ጥቅም ወደ ግለሰቦች ኪስ እንዲገባ በፊርማቸው ያዘዙት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ይህንን ውሳኔ የወሰኑበት ምክንያት እየታወቀ የኦሮሞን ህዝብ ለቅሶ ተቀመጥ ማለታቸው ነው። በቱምሳ ቢሮ ውስጥ “ባለራዕዩ መሪያችን ተለየኸን” ተብሎ መለጠፉ በራሱ የውርደቱ ድምር ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም።

The former Oromia region president and Minster of Civil Service , Junedin Sado, is seeking an asylum in Kenya

The former Oromia region president and Minster of Civil Service , Junedin Sado, is seeking an asylum in Kenya. He was president of the Oromia Region from 28 October 2001 until 6 October 2005 when he was replaced by Abadula Gemeda. He subseq...uently was appointed Transport and Communication Minister, which is the office he was holding when Prime Minister Meles Zenawi moved him to the Science and Technology Ministry October 2008. Following the 2010 general election, Junedin was appointed Minister of Civil Service.

He has been at odds with the TPLF leadership at different times but his rift with the administration came in to light even more when his wife ,Habiba Mohammed, was listed among 29 Muslim activists accused of criminal conspiracy to commit unspecified acts of terrorism — charges that could attract the death penalty in October 2012

የቡድን አንቅስቃሴ ያደርጋሉ የተባሉ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው !!!

Thursday, February 21, 2013

የቡድን አንቅስቃሴ ያደርጋሉ የተባሉ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው !!!

ማስጠንቀቂያው የተሰጣቸውብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት
በምርጫው እንቅስቃሴ ዙሪያ መንግሥት ለሦስት አባቶች ማስጠንቀቂያ ሰጠ
• በስመ ደኅንነት ያጭበረበሩ 40 ግለሰቦች ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው
• እነንቡረ እድ ኤልያስ የመራጮች ዝርዝር እንዲሰጣቸው ጫና እየፈጠሩ ነው
ለስድስተኛው ፓትርያሪክ ምርጫ እየተደረገ በሚገኘው ቅድመ ዝግጅት፣ የየራሳቸውን ‹ምርጥ› ይዘው የቡድን እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ያሉ አካላትን ያስተባብራሉ ለተባሉ ሦስት ሊቃነ ጳጳሳት መንግሥት ጥብቅ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ተሰማ፡፡ ማስጠንቀቂያው የተሰጣቸው ሦስቱ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት÷ የአስመራጭ ኮሚቴው ሰብሳቢ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ እና የምሥራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ናቸው፡፡

ለሐራዊ ምንጮች የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ለሦስቱ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ማስጠንቀቂያው የተሰጣቸው ሰኞ፣ የካቲት 11 ቀን 2005 ዓ.ም በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ተጠርተው ሲኾን፣ ያነጋገሯቸውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ኀይለ ማርያም ደሳለኝና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አማካሪ አቶ ጸጋዬ በርሄ ናቸው፡፡ ባለሥልጣናቱ÷ የፓትርያሪክ ምርጫው ቤተ ክርስቲያኒቱ ባጸደቀችው የፓትርያሪክ ምርጫ ሕገ ደንብ መሠረት ብቻ መፈጸም እንደሚገባው መናገራቸው ተዘግቧል፡፡ ‹‹የራሳችኹን ሕገ ደንብ አክብራችኹ መሥራት ሲያቅታኹ በመንግሥት ላይ የሚቀርበውን ሰበብ ማስቆም አለባችኹ፤ በየካፌው፣ በየሬስቶራንቱ፣ በየሆቴሉና በየልኳንዳ ቤቱ እየተሰበሰቡ የሚመክሩትንና የምታስተባብሯቸውን ቡድኖችም መግታትና መቆጣጠር አለባችኹ፤›› የሚል ማሳሰቢያ መስጠታቸው ተነግሯል፡፡
ሦስቱ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በምርጫው ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ቡድኖች ስለመኖራቸው በማመን አስተያየት መስጠታቸው ተመልክቷል፡፡ የተለያዩ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን በቢሯቸውና በማረፊያቸው ሲያነጋግሩ የተለያየ ስምና መታወቂያ ይጠቀማሉ ስለሚባሉት የቡድኖቹ መሪዎችም ሊቃነ ጳጳሳቱ ሲያብራሩ፣ ‹‹የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት መታወቂያ የሚያሳዩና ከመንግሥት እንደተላኩ የሚናገሩ፣ መንግሥት እንዲመረጥ የሚፈልገው አቡነ እገሌን ነው፤ አቡነ እገሌን መምረጥ አለባችኹ፤ አቡነ እገሌን ካልመረጣችኹ የእገሌ ተቃዋሚ አባል ናችኹ ማለት ነው፣ እናሰራችኋለን፤ ከሥራ እናባርራችኋለን፤›› የሚሉ በመኾናቸውና ይህም በየዕለቱ የሚታዘቡት ጉዳይ በመኾኑ በመንግሥት ወደማማረር መድረሳቸውን አስረድተዋል ተብሏል፡፡
በዚህ ሳምንት ሰኞ ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ጋራ የተደረገውን ውይይት ተከትሎ የመንግሥት ስቭል፣ ፖሊስና ወታደራዊ ደኅንነት ጥምር ግብረ ኀይል በመንበረ ፓትርያሪኩ ቅጽር ውስጥ ለሁለት ቀናት ባካሄደው ክትትልና አሠሣ፣ በስመ ደኅንነት ሲንቀሳቀሱ ነበር የተባሉ 40 ግለሰቦችን በትናትናው ዕለት በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ተዘግቧል፡፡ አሠሣው እኒህ ስመ ደኅንነቶች በየፊናቸው ከሚመሯቸው ቡድኖች (የተለያዩ ሊቃነ ጳጳሳትን ለፕትርክና በማጨት የተስማሙ የመነኰሳትና ካህናት ስብስቦች ናቸው) ጋራ ያዘወትሯቸዋል በሚባሉ ካፌዎች፣ ሬስቶራንቶች፣ ሆቴሎችና ልኳንዳ ቤቶች ተጠናክሮ ቡድኖቹን የመበተንና የማስጠንቀቅ ሥራ ሲሠራ መዋሉ ተነግሯል፡፡
በመንበረ ፓትርያሪኩ ቅጽርና ዙሪያ ሲንቀሳቀሱ በጥምር የደኅንነት ኀይሉ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት 40 ግለሰቦች መካከል 35ቱ ተይዘው ማንነታቸውን ሲጠይቁ ያሳዩት መታወቂያ ሐሰተኛ ኾኖ ተገኝቷል፤ የአምስቱ መታወቂያ ደግሞ ትክክለኛ ቢኾንም ከሚመለከተው አካል ትእዛዝ ሳይሰጣቸው ራሳቸውን ለቡድናዊ ጥቅም አሰማርተው መገኘታቸው ተረጋግጧል ተብሏል፤ አብዛኞቹ ከክልሎች የመጡ፣ በአንድ ወገን የተሰጣቸውን ቡድናዊ ተልእኮ ለማስፈጸም የሚላላኩ እንጂ የመንበረ ፓትርያሪኩን መግቢያና መውጫ በሮች እንኳ በቅጡ የማያውቁ መኾናቸው በቁጥጥር ሥር ሲውሉ በታየባቸው መርበትበትና ድንጋጤ ይበልጥ ራሳቸውን ያጋለጡ መኾኑ ተገልጧል፡፡
በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ ወገኖች መንግሥት ‹‹ተጽዕኖ አላደረግኹም፤ ጣልቃ አልገባኹም›› ለማለት ያህል የወሰደው ርምጃ ሊኾን ይችላል በሚል መረጃውን በጥርጣሬ ይመለከቱታል፤ በአንጻሩ የምርጫው እንቅስቃሴ ከመንግሥት ቀጥተኛ እይታና ቁጥጥር ውጭ ሊኾን እንደማይችል ይከራከራሉ፡፡ ሌሎች ወገኖች ደግሞ መንግሥት በጥምር የደኅንነት ኀይሉ እያካሄደው ስለ መኾኑ የተዘገበው የቁጥጥር እንቀስቃሴ የየራሳቸውን ፓትርያሪክ አጭተው በመንበረ ፓትርያሪኩ የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች÷ በአንድ በኩል የመንግሥትን የጸጥታ፣ የደኅንነትና የመከላከያ መዋቅሮች ለሚሹት ዓላማ ለመጠቀም የሄዱበትን ርቀት (በመንግሥት ቋንቋ የኪራይ ሰብሳቢዎችን ትስስር) የሚያሳይ ሲኾን በሌላ በኩል ደግሞ ቤተ ክርስቲያን ተቋማዊ ክብሯን ለማስጠበቅ ካለመቻሏ የተነሣ የምትገኝበትን አስከፊ ተቋማዊ ውርደት/ዝቅጠት እንደሚያሳይ ተመልክቷል፡፡
በዚህ ዜና ርእሰ ጉዳይ እንደሰማነው ከቀድሞውም እንደሚታወቀው ሁሉ፣ የዚህ ተቋማዊ ውርደት መነሻዎች የእኛው ሊቃነ ጳጳሳት እንደኾኑ መጠቀሱ በእጅጉ የሚያሳፍር ነው፡፡ ቡድኖቹን በማንቀሳቀስ ረገድ÷ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ለብፁዕ አቡነ ማቲያስ፣ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ‹‹ቀጣዩ ፓትርያሪክ ከወሎ መመረጥ አለበት፤ ጊዜው የወሎ ነው›› የሚለውን ቡድን (w – group) በመደገፍ ብፁዕ አቡነ ገብርኤልን ወይም ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ዘካናዳን፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ደግሞ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልን በመደገፍ ስማቸው ይነሣል፡፡ የድጋፉ ስለምንነት በተለይ ለመጀመሪያዎቹ ሁለቱ በዋናነት ከጎጠኝነት ጋራ የተያያዘ ቢኾንም ሁሉም በቀጣይ ስለሚያገኘው ሹመት፣ ሥራ ወይም የኾነ ዐይነት ግላዊና ቡድናዊ ጥቅም ወይም አንዱ ሌላው ላይ ስላለው ቂምና ጥላቻ መኾኑ ደግሞ በእጅጉ ከማሳፈርም አልፎ በእጅጉ ያሳዝናል፡፡
ሹመትና ሥራ ወይም የኾነ ዐይነት ሌላ ጥቅም ፈልጎ አሉታዊ የምርጫ ድጋፍ ማድረጉ፣ በቂምና ጥላቻ መነዳቱ በውጤቱ የሚገኘውን ሹመት መንፈሳዊ ወይም ከመንፈስ ቅዱስ ነው እንደማያሰኘው ግልጽ ነው፡፡ እስኪ ይህም ይኹን ብንል እንኳ፣ የየራሳቸውን ፓትርያሪክ አጭተው በየካፌው፣ በየሬስቶራንቱ፣ በየሆቴሉና በየልኳንዳው ተሰብስበው የሚዶልቱት የ‹መነኰሳት›፣ ‹ካህናት›ና ወይዛዝርት ስብስቦች ለሹመቱም ለሥራውም የሚታመኑ፣ የሚበቁም እንዳልኾኑ ባለፉት ዓመታት በሚገባ የምናውቃቸው ናቸው፡፡
‹‹አቡነ ማቲያስን ለማስመረጥ ቤቴንም ቢኾን እሸጣለኹ›› የሚሉት ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ
ለአብነት ያህል÷ ‹‹መንግሥት የሚፈልገው አቡነ ማቲያስን ነው፤ አቡነ ማቲያስን መምረጥ አለባችኹ፤ አቡነ ማቲያስን ካልመረጣችኹ እናስራችኋለን፤ እናባርራችኋለን›› በሚል እየተንቀሳቀሱ ያሉት እነ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ፣ መጋቤ ካህናቱ ኀይለ ሥላሴ ዘማርያም እና ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ ምን እያደረጉ ነው? ቡድናዊና ግላዊ ጥቅም፣ ቂምና ጥላቻ የሚገፋቸው እኒህ ግለሰቦች፣ ለፕትርክና ሊመረጡ ይችላሉ ያሏቸውን ሌሎች ብፁዓን አባቶች ስም በየሚዲያው የማጥፋት ዘመቻ ይዘዋል፤ ሚዲያውም ያለአንዳች ሚዛናዊነት የእነርሱን ክሥ ያስተጋባል (የዛሬው ሰንደቅ ጋዜጣ አንዱ ነው፤ በዛሬው ዕለትም እኚህ ሴትዮ በአድልዎና በሕገ ወጥ መንገድ ከያዟቸው የቤተ ክህነት ቤቶች መካከል አንዱ የኾነውንና በአራት ኪሎ የሚገኘውን ቀራንዮ የጉዞ ወኪል የከፈቱበትን ቢሮ የሰንደቅ ጋዜጣ ማከፋፈያ አስመስለውት ውለዋል)፡፡ በስመ ደኅንነት የሚንቀሳቀሱ ነገር ግን የጸጥታና ደኅንነት ባልደረቦች የሚመስሉ በርካታ በገንዘብ የተገዙ ግለሰቦች መንበረ ፓትርያሪኩን እንዲያጥለቀልቁ ያደረጉት በቀዳሚነት እነእጅጋየሁ ናቸው፡፡
እነንቡረ እድ ኤልያስ በአዲስ አበባ አራቱ አህጉረ ስብከት፣ በባሕር ዳር፣ በደሴ፣ በሐዋሳ፣ በድሬዳዋ፣ በአሰበ
ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ
ተፈሪና በጅጅጋ አህጉረ ስብከት ስልክ እየደወሉ ከጠቅላላው መራጭ ከ600 በላይ የሚኾኑ መራጮችን ስም ዝርዝር አሳውቁን እያሉ ጸሐፊዎችንና ሥራ አስኪያጆችን እያስገደዱና እያስፈራሩ ነው፡፡ በተወሰኑ አህጉረ ስብከትም ሥራ አስኪያጆቹ የካህናት፣ ገዳማትና አድባራት አበ ምኔቶችና እመ ምኔቶች እንዲሁም የምእመናን ተወካዮችን ሰብስበው ድምፅ መስጠት ያለባቸው ለአቡነ ማቲያስ መኾን እንደሚገባው በማሳሰቡ ረገድ ተሳክቶላቸዋል፡፡ ጉዳዩን በተመለከተ የአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሁለት ጸሐፊዎችና ሥራ አስኪያጆች ለየሊቃነ ጳጳሳቱ ሪፖርት ያደረጉ ሲኾን ሊቃነ ጳጳሳቱ ብፁዕ አቡነ ዳንኤልና ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ለእነ ንቡረ እድ ኤልያስና ለተላላኪዎቻቸው ስመ ደኅንነቶች ጠንከር ካለ ማሳሰቢያ ጋራ ምላሽ መስጠታቸው ታውቋል፡፡
የእነእጅጋየሁ ድፍረት በዚህ ብቻ የሚያበቃ ሳይኾን አስመራጮችን በግልጽ እስከማጨናነቅም የደረሰ መኾኑም ታውቋል፡፡ ለአስመራጭ ኮሚቴው ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደሚያስረዱት የሴትዮዋ ድፍረት፣ ‹‹አቡነ እገሌ በዕጩነት መካተት ወይም መመረጥ እንደማይገባቸው የሚያስረዱ መጣጥፎችን በኮሚቴው ስብሰባዎች ላይ ለማስነበብ እስከ መሞከር የደረሰ ነው፤›› ይላሉ፡፡ የመረጃ ምንጮቹ የአንባቢውን ማንነት ባይገልጡ ም ሙከራው የአስመራጭ ኮሚቴውን ሰብሳቢ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን አስደንግጧል፤ በተለይም የታዋቂ ምእመናን ተወካዮቹን እነ ቀኝ አዝማች ኀይሉ ቃለ ወልድንና አቶ ዓለማየሁ ተስፋዬን ክፉኛ አስቆጥቷል፡፡ ‹‹በስመ ደኅንነቶቹ ላይ የተወሰደው ርምጃ አስመራጭ ኮሚቴውን ሳያነቃቃው አልቀረም፤›› ይላሉ የዜናው ምንጮች፡፡
የኾነው ኾኖ ነገ፣ የካቲት 14 ቀን 2005 ዓ.ም የስድስተኛው ፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ አጣርቶ የመረጣቸውን አባቶች ለቋሚ ቅ/ሲኖዶሱ የሚያቀርብበት ዕለት ነው፡፡ እስከ ትላንት ምሽት በነበረን መረጃ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል፣ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል እና ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ከካህናትና ምእመናን በተሰበሰቡ ጥቆማዎች ብዛት ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ያለውን ደረጃ መያዛቸው ታውቋል፡፡
ቀደም ባስነበብነው ዘገባ እንዳስረገጥነው፣ በብዙ ዕጩዎች መጠቆም ለፓትርያሪክነት መታጨትን ወይም ለፓትርያሪክነት መመረጥን አያረጋግጥም፡፡ የአስመራጭ ኮሚቴው መግለጫ ደጋግሞ እንደሚያሳስበው የጥቆማው መረጃዎች ለዕጩዎች መለያ እንደ ግብአት ብቻ የሚያገለግል ነው፤ ዕጩዎቹ እነማን እንደሚኾኑ የሚታወቁት ቅ/ሲኖዶስ በነገው ዕለት ከኮሚቴው ተለይተው በሚቀርቡለት አባቶች ላይ ተወያይቶ ስማቸውን በብዙኀን መገናኛ ይፋ ሲያደርግ ብቻ ነው፤ ፓትርያሪኩም የሚታወቀው የካቲት 21 ቀን በሚሰጠው የመራጮች ድምፅ ብቻ ነው፡፡

Friday, February 22, 2013

እስከመቼ ተጨቁነን!?? ሃሳባችንን የመግለጽ መብታችንን እናስከብር!!!

እስከመቼ ተጨቁነን!?? ሃሳባችንን የመግለጽ መብታችንን እናስከብር!!!



እስከመቼ ተጨቁነን!?? ሃሳባችንን የመግለጽ መብታችንን እናስከብር!!!
‹‹ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ለሁሉም፣ አሁኑኑ!››
‹‹ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ለሁሉም፣ አሁኑኑ!››
‹‹ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ለሁሉም፣ አሁኑኑ!››
‹‹ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ለሁሉም፣ አሁኑኑ!›› የሚለውን ዘመቻ የምደግፈው የዚህኛው ወይም የዚያኛው ርዕዮተዓለም ደጋፊ ስለሆንኩ አይደለም፡፡ በዚህ ዘመቻ ላይ የሐሳብ ነጻነት (Freedom of Expression) ደጋፊ ነኝ፡፡ ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ተፈጥሮ የሰጠን ነጻነት ነው፡፡ ሰው ሁሉ ሐሳብ አለው፤ ሐሳብ ያለው ሁሉ የመናገር ተፈጥሯዊ ተሰጥኦ አለው፤ በሕገ-መንግሥቱ እስከተፈቀደልኝ ድረስ ይህንን ተፈጥሯዊ ስጦታዬን መጠቀሜ እና የሌሎችን ማክበሬ ለማንም ወገንተኛ ብሆንም ባልሆንም የማምንለት እና የምከራከርለት ነው፡፡ ይህንን ነጻነቴን ስጠቀም እና ሳደርግ በእራሴ ማሰብ እና ማድረግ የማልችል ይመስል ‹‹ከጀርባው ማን አለ?›› መባል ሰልችቶኛል፡፡ አገሬን እወዳለሁ፤ የገዛ አገሬን እና ሕዝቤን የሚጎዳ ሐሳብ እና ድርጊት ማፍለቅ አልፈልግም፤ ታዲያ ለምን ሐሳቤ እና ሐሳቤን የመግለጽ ነጻነቴ ይገደባል? የኔ ሐሳብ ከንቱ መሆን አለመሆኑን ገምግሞ የማጽደቅ ችሎታ ያለውስ ማነው? የኢትዮጵያ ሕዝብስ ሰምቶ ሲያበቃ ክፉ እና ደጉን መለየት አይችልምን? ‹‹ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ለሁሉም፣ አሁኑኑ!››
እያንዳንዳችን በየትኛውም አለም ያለን ኢትዮጵያውያን ሃገር ቤት ያለውን ጨምሮ የማህበራዊ ንቃተ ህሊናችን ከማንኛውም አለም የተሻለ መሆኑ ማንም የሚመሰክረው ነው :: ሆኖም ልንጠቀምበት አለመቻላችን ራሳችንን ለግዞት እንድንዳርግ መንገድ ለአምባገነኖች አመቻችተናል::ያለንን እምቅ ሃሳብ ሳንገልጠው ይዘነው መሞት መሰደድ እንደሌለብን የማወቅ ግደታ አለብን :: ስለዚህ እያንዳንዳችን የሃገራችን ጉዳይ ይመለከተናል:: ስለዚህ እያንዳንዳችን ሃሳባችንን በነጻነት እንገልጽ ዘንዳ ወዳፈኑን ሰዎች መጮህ አለብን:: እስከመች ተጨቁነን!!??

ዘመኑ በቴክኖሎጂ በገሰገሰበት እና በሰለጠነበት ግዜ እኛ ግን ተኮራምተን የምንፈልገውን ነገር እንዳናገኝ በጥቂት አምባገነኖች ተቆልፎብን እንገኛለን :: ከዚህ ጭቆና ነጻ ለመውጣት መጮህ ብቻ ሳይሆን ከድምጽም አልፎ በአምባገነኖች ላይ አስፈላጊውን ግፊት ማድረግ አለብን:: እኛ እስከመቼ በተጭበረበረ ፖለቲካ በተገነባ ኢኮኖሚ መጨቆናችን ሳያንስ እርስ በእርስ እንክኡዋን ሃሳባችንን እንዳንካፈል እንዳናነብ እንዳንጦምር እየተደረግን ነው:: ወገን ታዲያ ምን እንጠብቃለን??

በኑሮ የተጎዳሀው ሳያንስህ መረጃ ማግኘት የተገፈፍከው ህዝብ ሆይ!!!

በህግ የማይከለከሉ ሰብኣዊ መብቶችህ ተግደው እና ተሸራርፈው በተራ ወንበር ላይ ሲወሰንባቸው ፍትህ የማግኘት መብትህ ሲገሰስ ማድረግ የምትፈልገው ህጋዊ ሁነቶን እንዳታደርግ እንዳታይ የዲሞክራሲ እስቲንፋስ በቀጭኑ እንዳትተነፍስ ተደርገሃል:: ማንንም የማትጎዳ ህዝብ መሆንህ እየታወቀ ሃሳብህ ተገድቦ ባላዋጣሀው ህግ እየተገዛህ ትገኛለህ :: አንተና ልጆችህ እስከመች ተጭበርብራቹህ ትኖራላችሁ???

ህገ መንግስቱ አጎናጽፎሃል የተባለውን መብት እውን ተጠቅመህበታልን?? ሃይማኖትህን በነጻነት እየመራህ ነውን? በነጻነት እየኖርክ ነው?? ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያላቸውንጥያቄዎች ራስህን ጠይቀው:: በአሁኑ ሰአት ካለገደብ በነጻነት ሃሳብህን መግለጥ ትችላለህ?? የህን ብታድርግ ግን ከ አሸባሪዎች ጋር ተባባሪ...ወንጀለኞን ያዘለ...ጸረ ህዝብ...ወዘት ታፔላ ተለጥፎልህ ወደ ወያኔያዊ ካንጋሮ ፍርድ ቤት ትሄዳለህ ወደ እስር ቤትም ትወረወራልህ :: ስለዚህ ማንነትህን ሳታስነካ ኢትዮጵያዊ ኩራትህን እንደለበስክ ላንተ እና ለመጪው ትውልድ መስዋእት መሆን ይጠበቅብሃል እኔም እንዳተው:: አውቄ ማሳወቕ ታግየ ማታገል እስከመሰዋትነት ይጠበቅብኛል::

ስለሃገርህ መቼ እና እንዴት በይፋ ማውራት እንዳለብህ ሊነግሩህ የሚፈልጉትን ሰዎች ማስወገድ የሁላችንም ድርሻ ነው :: አንተ ነህ የመረጥከኝ እስካሉ ድረስ ሃስባችንን በገህድ የተሰማንን በይፋ ልንናገር ሌላውም ጋር የለውን መረጃ ልንቀበል ግድ ይለናል ..ይህ ግን ለኔ እና ላንተ ላንቺ አልተፈቀደም ስለዚህ ድምጻችንን ማሰማት አለብን እንዲ ብለን......
‹‹ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ለሁሉም፣ አሁኑኑ!››
‹‹ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ለሁሉም፣ አሁኑኑ!››
‹‹ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ለሁሉም፣ አሁኑኑ!››
‹‹ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ለሁሉም፣ አሁኑኑ!››
አሁኑኑ አሁኑኑ አሁኑኑ አሁኑኑ አሁኑኑ
አንተ እና እኔ አንቺ እና እናንተ በዉነት ሃሳባችን ገደል ነውን ? የሰፊው ህዝብ ማንነት እየተደፈጠጠ ባለበት በዚህ ወቅት ሃሳባችንን እንድጥ ማሰማት አለብን ሁላችንም በ‹‹ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ለሁሉም፣ አሁኑኑ!›› በሚለው ዘመቻ የምንሳተፍ ሰዎች መረጃው ላልደረሳቸው የማድረስ ግዴታ አለብን:: በሃገር ቤት ያለ ኢትዮጵያዊ ሁሉ መረጃ ይፈልጋል የተማረውም ያልተማረውም ህብረተሰብ ንቃተ ህሊናው ሰፊ በመሆኑ እያንዳንዱን ነገር ማወቅ ይፈልጋል :: ለዚህ ዘመቻ ስኬት ደሞ ጠንክረን መስራት እና ያምባገነኖችን ጆሮ መስበር አለብን::

ለመጨረሻ ይህንን አባባል ደጋግመን እናንብበው ...ላላነበቡም እናንብብላቸው...
የመንግሥትን አመለካከት ለማንፀባረቅ ፓርላማ፣ የመንግሥት ብዙኃን መገናኛ እና ብዙ መንገዶች አሉ፤ የእኔን ሐሳብ ግን የማቀርብበት መንገድ የለኝም፡፡ የፕሬስ ነጻነት ይከበር፣ የኢንተርኔት ገደብ ይቁም፣ ዙሪያ ገባውን በፍርሐትና በጥርጣሬ ሳልመለከት ሐሳቤን የመግለጽ ነጻነቴ ይከበርልኝ፡፡ ይህ የሚሆነው የታገዱ የሕትመት ውጤቶች እና የኢንተርኔት ብዙኃን መገናኛዎች ሲለቀቁ፣ ሐሳባቸውን በመግለጻቸው የተፈረደባቸው የኅሊና እስረኞች ሲፈቱ፣ የተሰደዱ ጋዜጠኞች ወደአገር ቤት ሲመለሱ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የሁላችንም ነች፤ እኔም ለአገሬ የማዋጣው ሐሳብ አለኝ፤ እንድናገረው ይፈቀድልኝ፡፡

ድል ሃሳባችንን በነጻነት መግለጥ እና መረጃ ለማወቅ ለምንሻ ሕዝቦች!!!

Saudi religious police arrest Ethiopian workers for practicing Christianity


Saudi religious police arrest Ethiopian workers for practicing Christianity


By

Published February 21, 2013
FoxNews.com
Saudi Arabia’s notorious religious police, known as the mutawa, swooped in on a private gathering of at least 53 Ethiopian Christians this month, shutting down their private prayer, and arresting the peaceful group of foreign workers for merely practicing their faith, FoxNews.com has learned.
The mixed group of men and women was seized in a private residence in the city of Dammam, the capital of the wealthy oil province in Eastern Arabia, and Saudi authorities charged three Christian leaders with seeking to convert Muslims to Christianity. The latest crackdown on Christianity in the ultra-fundamental Islamic country comes on the heels of a brutal 2011/2012 incarceration and torture of 36 Ethiopian Christians, and drew a sharp rebuke from a U.S. lawmaker.
“Nations that wish to be a part of the responsible nations of the world must see the protection of religious freedom and the principles of reason as an essential part of the duty of the state,” Rep. Jeff Fortenberry, R-Neb., who sits on the Caucus on Religious Minorities in the Middle East, told FoxNews.com.

“The U.S. … should demand that any expatriate worker detained and held without charge for private religious activity in the Kingdom should be released immediately.”
- Dwight Bashir, U.S. Commission on International Religious Freedom
During Advent in 2011, Saudi authorities stormed a prayer meeting at the private home of one of the Ethiopian workers in the Red Sea city of Jeddah. The Saudi mutawa imprisoned 29 women and six men for more than seven months in barbaric prison conditions, where the men faced severe beatings and the women were subjected to sexually intrusive torture methods. After Christian organizations and human rights groups, as well as the United States government, complained, the Saudis deported the 35 Christian Ethiopian workers in August 2012.
Last March, Abdulaziz ibn Abdullah Al al-Sheikh, the grand mufti of the Kingdom of Saudi Arabia, declared it is “necessary to destroy all the churches in the Arabian Peninsula.”
Still, Saudi officials claim to tolerate other faiths even as the mutawa, or Commission to Promote Virtue and Prevent Vice, mount their crackdowns, said Dwight Bashir, deputy director for policy at the U.S. Commission on International Religious Freedom.
“During an official USCIRF visit to the Kingdom earlier this month, Saudi officials reiterated the government’s long-standing policy that members of the Commission to Promote Virtue and Prevent Vice, also known as the religious police, should not interfere in private worship,” Bashir said. “However, the past year has seen an uptick of reports that private religious gatherings have been raided resulting in arrests, harassment and deportations of foreign expatriate workers.
“The U.S. government and international community should demand that any expatriate worker detained and held without charge for private religious activity in the Kingdom should be released immediately,” Bashir added.
A spokeswoman for the Saudi Embassy in Washington said she “is not allowed” to give her name and referred a FoxNews.com query to Nail al-Jubeir, a spokesman for the Saudi Embassy in Washington. He did not immediately return FoxNews.com telephone and email requests. Diplomats from Ethiopia’s embassy in Washington told FoxNews.com they are looking into preparing a statement about the arrests.
Nina Shea, the director of the Washington-based Hudson Institute’s Center for Religious Freedom, told FoxNews.com that the arrests in Dammam are “part of Saudi Arabia’s policy to ban non-Muslim houses of worship and actually hunt down Christians in private homes.”
Shea, who was in the Saudi capital Riyadh as part of a U.S delegation two years ago, sharply criticized the Saudis for breaking their 2006 pledge to the U.S. government to not disrupt non-Islamic religious practices. The U.S. Commission on International Religious Freedom termed in its 2012 report Saudi Arabia a “country of particular concern”– along with other authoritarian states such as the Islamic Republic of Iran, North Korea, China and Sudan– for repression of religious freedom.
The Saudi government adheres to a strict form of Sunni Islam called Wahhabism that has animated many followers to engage in terrorism across the globe. The 9/11 terrorists, 19 of whom were Saudis, followed the Wahhabi school of militant Islamic ideology.
Shea said “the U.S. government does not raise its voice in protest” as part of the U.S.-Saudi strategic partnership. She added the failure to push the Saudis to change their intolerant behavior “has taken the backseat to oil and the war on terror. The Saudis are playing a double game — cooperating with the war on terror and working against the war on terror campaign.” A telling example, she stressed, involves the Saudi government sending text books around the world that contain extreme forms of Islam.
Benjamin Weinthal is a journalist who reports on Christians in the Middle East and is a fellow at the Foundation for Defense of Democracies. Follow Benjamin on Twitter: @BenWeinthal.
Read more: http://www.foxnews.com/world/2013/02/21/saudi-religious-police-arrest-ethiopian-workers-for-practicing-christianity/#ixzz2LcSULySV

Thursday, February 21, 2013

ESAT Daliy News Amsterdam Feb 21, 2013 Ethiopia

ESAT Daliy News Amsterdam Feb 21, 2013 Ethiopia

www.youtube.com
www.ethsat.com - Ethiopian Satellite Television (ESAT) ESAT is the first independent Ethiopian Satellite Television service and Radio Station who broadcast to Ethiopia and the rest of the world

የዝንጀሮ መንገድ ቢከተሉት መጨረሻው ገደል ነው እንዲሉ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ – የህወሓት ታሪክ ዞሮ ዞሮ የእርስ በርስ መበላላትና የመናቆር ታሪክ ነው።

የህወሀት ጉዞ የርስበርስ መበላላት ታሪክ ነው
ከትእዝብት አድማሱ
የዝንጀሮ መንገድ ቢከተሉት መጨረሻው ገደል ነው እንዲሉ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ – የህወሓት ታሪክ ዞሮ ዞሮ የእርስ በርስ መበላላትና የመናቆር ታሪክ ነው። በገዛ ወንድሙ ላይ መጨከን፣ የገዛ ወንድሙንtplf rotten apple ገድሎ አካኪ ዛረፍ ማለት፣ የገዛ ወንድሙን ገድሎ ጀግና ነኝ ማለት፣ በገዛ ወንድሙ ላይ በሐሰት መስክሮ ለጥቕምና ለስልጣን ሲባል አሳልፎ መስጠት፣
በንፁኃን ደም እየነገዱ የግል ስልጣንን ማደላደል የመሳሰሉትን አስነዋሪ ተግባራት ዛሬ ከአቶ መለስ ዜናዊ አገዛዝና አመራር የወረስናቸው ሰይጣናዊ አስተሳሰቦችና ፓሊሲዎች ናቸው። የሚገርመውና የሚያሳዝነው ደግሞ የህወሓት አረሜናዊ ባህርይ እንደ ኤይድስ በሽታ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እየተዛመተ መምጣቱ ነው።
አቶ መለስና አቶ ስብሓት ነጋ በህወሓት የጥሎ ማለፍ ጉዞ እስካሁን ድረስ እነማን እያስወገዱ ስልጣናቸውን እንዴት እየገነቡ እንደመጡ ጥቂት ልበል፡-
በመጀመሪያዎቹ አካባቢ በድርጅቱ ውስጥ አውራጃዊነት (ሕንፍሽፍሽ) ተፈጥሯል በሚል ሰበብ “አሽዓ” (አክሱም ሽሬ ዓድዋ) ተብሎ የሚጠራ በነ አቶ ስብሓት ነጋ የሚመራ ጠባብ ቡድን አብዛኞዎቹ ከሌላ የትግራይ አውራጃዎች ማለት ከእንደርታ፣ ከራያ አዘቦ፣ ከአጋሜና ከተምቤን አካባቢ የመጡትን ታጋይ ወጣቶች እንደመቱዋቸው ታሪክ ይናገራል።
በፈረንጆች አቆጣጠር በ1985ዓ/ም በነ አቶ ግደይ ዘርኣፅዮንና ዶክተር አረጋዊ በርሄ ላይ የተወሰደው እርምጃም ተመሳሳይ ነው። በተለይም አቶ መለስ ሌሎች አስጊ ናቸው የሚላቸውን ሰዎች አፅድቶ ካጠናቀቀ በኋላ በሁለተኛው ምዕራፍ ላይ ጣቱን የቀሰረው በነ አቶ ግደይ ዘርአፅዮን ላይ ነበር። የድራማው ዋና ተዋናይም አቶ ስብሃት ነበር። የክሱ ይዘትም “አረጋዊ በርሄ መለስን ለመግደል አሲሮ ነበር” የሚል በአቶ ስብሓት ነጋ የቀረበ የምስክርነት ቃል መነሻ ያደረገ እንደ ነበር ይታወሳል።
ማርክሰ ለኒን ሊግ ትግራይ (ማሌሊት) ከተመሰረተ ማግስትም “የቻለ ይሩጥ፣ ያልቻለ ያዝግም፣ ያበቃለት ይለይለት” በሚል መሪ መፈክር ፀረ ኮሚኒዝም እየተባለ የተባረረ፣ የተመታ፣ የተሰወረና የታሰረ ታጋይ ቁጥሩ ብዙ ነው። ከዚያው ከትግራይ ሳንወጣ የድርጅቱ ማእከላይ ኮሚቴ አባል የነበረው በአቶ ተኩሉ ሃዋዝ ላይ የተወሰደው የግዲያ እርምጃም ፀረ ህወሓት/ማሌሊት አመለካከት ታራምዳለህ በሚል እንደነበር ብዙዎቹ ይስማማሉ።

የመንግስት ስልጣን ከያዙ በኋላስ

የህወሓት መሪዎች አዲስ አበባ ገብተው የመንግስት ስልጣን ከያዙ በኋላም በበረሃ የትጥቅ ትግል ዘመን ድብቅ አጀንዳ ሆነው ውስጥ ለውስጥ ይሰራባቸው የነበሩት ሶስት ነገሮች ጋሃድ እየወጡ መሄድ ጀመሩ። አንደኛ በኤርትራ ጉዳይ ላይ ግልፅ የሆነ ልዩነት መታየት ጀመረ። ሁለተኛ በድርጅታዊና በመንግስታዊ መዋቅሮች በሚሰሩ ሰዎች መካከል የጥቅም ግጭትና የአመለካከት ክፍተት እየተፈጠረ ሄደ። ሶስተኛ በህወሓትና በሌሎች የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች መካከል የሎሌና የጌታ (የሞግዚትነት) ግንኙነት እየተፈጠረ መጣ። እስካሁን ድረስ በህወሓት መሪዎች መካከል እየተካሄደ ያለው የፍጥጫና የርስ በርስ መበላላት ሂደትም በነዚህ ሶስት ነገሮች ላይ የተመሰረቱ ናቸው።
1. በኤርትራ ጉዳይ ላይ በግልፅ በአጀንዳ ተይዞ መነጋገር የተጀመረው ገና ከደርግ ውደቀት ማግስት ነው። አንዴ ሞጎደኞች ሌላ ጊዜ ደግሞ እሳት ጫሪዎች፣ ጦርነት ናፋቂዎች፣ ወዘተ እየተባሉ በተለያየ ስም ሲጠሩ የነበሩት እነአቶ ገብሩ አስራት ከኤርትራ ጋር ያለንን ግንኙነት ገደብ ይኑረው የሚል አመለካከት ቢኖራቸውም አቶ መለስ ደግሞ እሳትን አንንካ
በማለት ሾላ በድፍን የሆነ አካሄድ ይከተሉ እንደነበር እሙን ነው። በዚሁ ልዩነት እንዳሉ ሻዕቢያ በኢትዮጵያ ላይ ወረራ ለማካሄድ ምቹ ሁኔታ ተፈጠረለት። ከወረራ በኋላም ልዩነቱ እየሰፋ መጣ። በመጨረሻም 13 ከፍተኛ የህወሓት ማ/ኮሚቴ አመራር አባላት ድርጅቱን ጥለው ወጡ። 5 ጀነራሎችን ጨምሮ ብዙ ኰለኔሎችና ነባር የህወሓት ታጋዮች
ድርጅቱን ጥለው ሲወጡ ብዙዎቹም ታሰሩ።
በዚህ ምክንያት እነአቶ መለስና እነ አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ምኞታቸውን ስለተሳካ የልብ ልብ ተሰማቸው። የትግራይ ብሄረተኝነት ጭንቅላቱን ተመታ ተባለ። ህወሓትም ከድርጅትነት ወደ ቤተሰባዊ የግል ኩባንያነት ተለወጠ። መለስም ነባሩ የህወሓት ታጋይ እያፀዳ ቁልፍ የሆኑ ቦታዎችን በታማኞቹ በኤርትራውያን እንዲያዙ አድርጓል። አቶ በረከት ስምዖንና ቴድሮስ ሐጎስ ሙሉ በሙሉ ኤርትራውያን ቢሆኑም ከመለስ ቀጥለው ስልጣን ያላቸው እነሱ ናቸው። የህወሓት ማ/ኮሚቴና በሚኒስትር ማዕረግ የመለስ አማካሪ ሆኖ ሲሰራ የቆየው ሃለቃ ፀጋይ በርሄ ግማሽ ጎኑ ኤርትራዊ ነው። ሌላው በሚኒስትር ማዕረግ የመለስ አማካሪ ሆኖ ሲሰራ የነበረው ሂያብ ሱራፌኤልም ሙሉ በሙሉ ኤርትራዊ ነው። የትግራይ ፕረዚዳንት የአባይ ወሉ ሚስት ወ/ሮ ትርፉ የህወሓት ማ/ኮሚቴ አባል ትውልድዋ ሙሉ በሙሉ ኤርትራዊት ናት። የህወሓት ማ/ኮሚቴ የአቶ አባዲ ዘሞ ሚስት ወ/ሮ ሂሪቲ ሱራፌኤል የትግራይ የዳኝነት ሃላፊ ሙሉ በሙሉ ኤርትራዊት ናት።
2. ሌላው በህወሓትና በሌሎች የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች መካከል ያለው የስልጣን ክፍፍል አለመመጣጠን ነው። መለስ እነ ስየና እነ ገብሩ ለመምታት የብሄረ አማራ ድርጅት – ብአዴንን እንደ መሳሪያ ተጠቅሞበታል። የህወሓት ለሁለት መሰንጠቅና መከፋፈል ከማንም በላይ ያስደሰተው እነ አዲሱ ለገሰንና በረከት ስምዖንን ነው። መለስ ከማንም በላይ እንደ ትልቅ አደጋ ሲያይ የነበረው የፓለቲካ ተቃዋሚ ድርጅቶች ሳይሆን በህወሓትና በሌሎች የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች ያለው ውስጣዊ ሽኩቻ ነው። ህወሓት በስልጣንም፣ በሀብት ክፍፍልም ሆነ በመከላኪያ አካባቢ የአንበሳ ድርሻ ይዟል የሚል ለረጅም ጊዜ ውስጥ ለውስጥ ሲብላላ የቆየ አመለካከት እንዳላቸው ማንም ያውቃል። መለስም ይህን አደጋ በማጤን የየድርጅቶቹን መሪዎችና ካድሬዎች ያጠመዳቸውና የተቆጣጠራቸው በስኳር (በሙስና) ነው። እያንዳንዱ የህወሓት/ኢሕአዴግ አመራር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በሙሱና የተዘፈቀ ስለሆነ አፉን ሞልቶ መቃወም አይችልም።

ከመለስ ህልፈት በኋላስ

ከመለስ ህልፈት በኋላ በህወሓት/ኢሕአዴግ አካባቢ አስደንጋጭ ክስተቶች ተፈጠሯል። አንድኛ የመንግስት ስልጣን ክፍተት ነው። በእውነት በአሁኑ ጊዜ አገሪትዋን እየመራ ያለው ማን ነው? የሚለው በትክክል የተመለሰ አይደለም። በአንድ በኩል የመለስ ራእይ ወራሾች ነን የሚሉ በበረከት ስምዖንና በወ/ሮ አዜብ የሚመራ ቡድን እንዳለ ይታየኛል። በሌላ በኩል ደግሞ የሁሉም ጥበብ፣ የዕድገት ምንጭና የትኩረት ማዕከል ተደርጎ እየተወሰደ ያለው መከላኪያም በመንግስታዊ አመራሩ ውስጥ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ቁልጭ ብሎ እየታየ ነው። በሶስተኛው ረድፍ ደግሞ አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መቅረባቸው ምን ያህል መፍትሄ ሊያመጣ ይችላል? የሚለው ነው። ይህ ሁሉ ሁኔታ ተደማምሮ ወዴት ሊወስደን ይችላል? ብሎ መጠየቅም የግድ ይላል።
ከመለስ ህልፈት በኋላ የተፈጠረው ሌላው ክስተት መደናገጥን ነው። በአቶ መለስ ሞት ከማንም አባል ድርጅቶች በላይ መደናገጥና አጣብቅኝ ውስጥ የገባው ህወሓት ነው። ምክንያቱም ህወሓት እንደ ድርጅት ሳይሆን እንደ ግል ኩባንያ ተይዞ ፓለቲካዊ ካፒታሉ በልቶ የጨረሰ፣ ዘመን የጣለውና በቁሙ የሞተ ድርጅት ሆኖ ስለተገኘ ነው። ስለሆነም የመለስን ቦታ ለመተካት ቀርቶ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ደረጃም ቢሆን ብቁ ሰው ለማቅረብ አልቻለም ነበር። አሁንም ገና ያልተረጋጋና በሽኩቻ ላይ ያለ ድርጅት ነው።
ሰሞኑን እንደሚወራው ህወሓት አሁንም ለሁለት ቡድን ተሰንጥቀዋል ይባላል። አንደኛው ቡድን በነበረከት፣ አዜብ፣ እነ አባይ ወሉና ሌሎች ያካተተ ሲሆን ሁለተኛው ቡድን ደግሞ በነአቶ ስብሃት ነጋ የሚመራ ነው። አቶ ስብሃት ነጋ “ህወሓትን እናጠናክር” የሚል መፈክር የያዘ ቢሆንም ግልፅ ራዕይና ፓለቲካዊ መስመር የሌለው የጎበዝ አለቃ እንቅስቃሴ እስከሆነ ድረስ ሩቅ የሚሄድ አይሆንም። በኤርትራ ጉዳይ ላይ ያለው አመለካከትም ከነበረከት ስምዖን የተለየ አይደለም። አቶ ስብሃት ቀደም ሲል ከነ አዜብ ጋር በነበረው የግል ቅራኔ ምክንያት ከህወሓት ጋር አብሮ የተጣለ ብቻ ሳይሆን በታሪኩም ሆነ በፓለቲካዊ አመለካከቱ ኢፍትሃዊና ኢዲሞክራሲያዊ ሰው ነው። ስብሃት ህወሓትን ከአዜብና ከበረከት እጅ ፈልቅቆ ለማውጣት ቀርቶ ለራሱም መከላከል የማይችል ጥርስ እንደሌለው ጅብ ሜዳ ላይ የወደቀ ሰው ነው። ስብሓት በትግራይ
ዘንድ የሚታወቀው እንደ ነፃ አውጪ ሳይሆን ነገር አመንጪ፣ ቂመኛ፣ አውራጃዊ፣ ስነ ምግባርና ሃላፊነት የጎደለው አውቆ አበደ ሽማግሌ እየተባለ ይጠራል። ስብሓትን በማየት ህወሓት ምን ዓይነት ድርጅት መሆኑን መገንዘብ ይችላሉ የሚል አባባልም አለ። ስለዚህ ሌላ ዓይነት መንገድ ካልመጣ በስተቀር ህወሓት/ኢሕአዴግ ከበረከት፣ ከአዜብና ከቴድሮ ሓጎስ እጅ ይወጣል ብሎ ማሰብ አይቻልም።

ላንዲት አገር መሰረታዊ እድገት ሃይል ያላት የተፈጥሮ ሃብትና የሕዝቦቿ ሁለንተናዊ ብቃት ናቸው

ድንቄም ምርጫ!
ከይኸነው አንተሁነኝ
feb 21 2013

ላንዲት ሀገር መሰረታዊ የእድገት ሃይል ያላት የተፈጥሮ ሃብትና የሕዝቦቿ ሁለንተናዊ ብቃት ናቸው። የሕዝቦቿን ሁለንተናዊ ብቃት ለመገንባት ደግሞ ካሏት የትምህርት ተቋማትና
Ethiopian election 2013 የትምህርቱ ስርአት በተጨማሪ በሕዝቦቿ መካከል ያለው የባህል፣ የሃይማኖትና የአኗኗር መስተጋብር የሚያበረክቱት አስተዋጽኦና በዚሁ ሳቢያም የሚገኘው ቀጥተኛ ያልሆነ የእውቀትና የልምድ አቅምና ዝውውሩ የሚናቅ አይሆንም። የተረጋጋና በመከባበር የሚመራ የሃይማኖት ስርአት፣ የአንደኛው እንቅስቃሴ ሌላኛውን በመደገፍ ላይ የተመሰረተ ማህበራዊ እንቅስቃሴ፣ ጎጂ የሆኑ ብህሎችን በማስቀረት ላይ ያተኮረና የሁሉም ብህላዊ ዕሴቶቻችን አስፈላጊነት ላይ ጥያቄ የማያነሳ ማሕበረሰብ ከሁሉም በላይ ለአንዲት ሀገር እድገት አስፈላጊዎች ናቸው።
በሌላ በኩል ደግሞ ምንም እንኳ የተፈጥሮ ሃብትና ብቃት ያለው የሰው ህይል የእድገት መሰረቶች ናቸው ቢባልም እነዚህን ሃብቶች ስርአት ባለው መልክ አቀናጅቶና አስተባብሮ መምራት የሚችል የሕዝብ አስተዳደርም ወሳኝ መሆኑ አሌ ልባል አይገባም። ያሉንን ሃብቶች ወደ ውጤት የመቀየሩ ሂደት ሳይደናቀፍ እንዲቀጥል ደግሞ ሀገሪቱ የህግን የበላይነት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የሚቀበል ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርና የሕዝብን የበላይነት የሚያምን ዴሞክራሲያዊ ስርአት ሊኖራት ይገባል። ይህም ሲጠቃለል ለአንዲት ሀገር ሁለንተናዊ እድገት ቀጣይነት ዴሞክራሲና ዴሞክራሲአዊ ስርአት ወሳኝ ግብአት ነቸው ማለት ነው።
አንዳንድ ሰዎች ከዴሞክራሲ ውጭ እድገት ሊመጣ እንደሚችል አንዳንድ ሀገሮችን እየጠቀሱ ቢሞግቱም በቅርብ ጊዜያት እየወጡ ያሉ ስለ እድገት የሚያወሩ ከሂዎት ልምድ የተገኙ ተሞክሮዎችና ትንተናዎች ግን የእድገት መሰረት የሆነው ማሕበረሰብ ነፃነትና ሁሉንም ያማከለ የሃብት ክፍፍል ወሳኝ እንደሆኑ ያረጋግጣሉ። ነጻነትና የተማከለ የሃብት ክፍፍል ደግሞ ከዴሞክራሲ ፍሬዎች ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውን ልብ ይሏል።
በሀገራችን ኢትዮጵያም ለእድገት ዋና ግብአት የሆነውን ዴሞክራሲን በወረቀት ላይ ለተመልካች እንዲመች በማስቀመጥና የነጻነትን አስፈላጊነትም በሚዲያ በመልፈፍ ወያኔ ተወዳዳሪ አልተገኘለትም። የዴሞክራሲ ውጤት የሆነው ነፃ ምርጫም ለወያኔ የፕሮፓጋንዳ አንዱ ጭራ እንጅ የህግ የበላይነት የሚታይበት፣ የሕዝብ አሸናፊነት የሚታወጅበት፣ የምርጫ ቦርድ ገለልተኛነት የሚገለጽበትና የምርጫ ታዛቢዎች ሳይሸማቀቁ ያዩትን የህሊና ፍርድ የሚሰጡበት መድረክ አይደለም። ይልቅስ ወያኔ ሲመቸው እየታገለ ሳይመቸው እያጭበረበረ የሚጋልብበት ነጻ የግሉ ሜዳ እንጅ።
የወያኔ ምርጫ ተሳታፊዎች የተወሰኑት ከምርጫ በፊት በሰበብ አስባቡ የሚገፉ ውድድር ተብየው ውስጥ የገቡትም ቢሆኑ ወያኔ የፈቀደውን ያህል የምርጫ ድምጽ የሚሰጡ እንጅ የሕዝባቸውን እውነተኛ ድምጽ የሚያገኙ እይደሉም አልነበሩምም። ይህን ለማረጋገጥ ሩቅ መሄድ አያስፈልገንም በቅርቡ የወያኔው አፈ ቀላጤ የምርጫ ህጉ ይከበር ብለው ጥያቄ ስላነሱት 33 ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተናገረውን ብቻ መጥቀስ በቂ ይሆናልና።
ሰላሳ ሶስቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች (በሗላ ላይ ቁጥራቸው በሶስት ወይም ባራት ቀንሷል) ባነሱት የምርጫ ህግ ይከበር ጥያቄ ላይ ተንተርሶ የተናገረው የወያኔው አፈ ቀላጤ “ተቃዋሚዎች ኖሩም አልኖሩም በምርጫው ላይ ብዙ ለውጥ አይኖርም” ነበር አለው። ይህን በብዙ መልኩ መተንተን ይቻል ይሆናል ባጭሩ ግን መልክቱ ተቃዋሚዎች ኖሩም አልኖሩም ምራጫውን በምንፈልገው መልኩ የምናስኬደው እኛ ወያኔዎች ነን፣ ተቃዋሚዎች ኖራችሁም አልኖራችሁም ውጤቱ ታውቋል፣ ተቃዋሚዎችን የምንፈልጋችሁ ላሯሯጭነት ብቻ ነውና ሌሎችንም ማለት እንደሆነ መገመት ከወያኔና አገዛዙ ጋር ከለሁለት አስርት ዓመታት በላይ ለቆየ ማንኛውም ዜጋ የሚያስገርም አይሆንም።
ባለፉት የወያኔ ምርጫዎች መታዘብ እንደተቻለው በእንደዚህ ያሉ ኩነቶች ወቅት ወያኔ የሚገርሙ ድርጊቶችን ባጋጣሚ ሳይሆን ሆን ብሎ፣ በማንአለብኝነት ሲተገብር ቆይቷል እየተገበረም ነው። ከዚህ በፊት ወያኔን ወክለው በይስሙላ ምርጫው ላይ ተሳትፈው የነበሩ ዜጎችን ያለ ምንም ጭንቀት ሕዝብን በመናቅ ገለልተኛ ነኝ እያለ እራሱን በሚያታልለው የወያኔ ምርጫ ቦርድ ውስጥ እንዲሰገሰጉ በማድረግ የወያኔን አሸናፊነት ህጋዊ ሽፋን እንዲሰጡ ሲያደርግ መቆየቱና እያደረገም መሆኑ በማስረጃ ተረጋግጧል።
ከዚህም በተጨማሪ ወያኔ የሚተማመንበትና ኩኩ ብሎ የሚታዘዝ ለማግኘት እርግጠኛ ሳይሆን ሲቀር ከዚህ በፊት የሚያውቃቸውን መልካም ታዛዦቹን ከከፍተኛ ወታደራዊ ስልጣን ሳይቀር አውርዶ በእንደዚህ አይነቶቹ የቀልድ ምርጫዎች ላይ ተሳትፈው አሸነፋችሁ እንዲባሉ ሲያደርግ መቆየቱ ያደባባይ ሚስጥር ነው። ከዚህ እጅግ የከፋውና ቀልድ ለማለትም የሚያስቸግረው ደግሞ ወያኔ ሰሞኑን ለወረዳና አካባቢ ምርጫ እያደረገው ነው የተባለው ነው። ባደባባይ ከአምስት ሚሊዮን በላይ አባላት እንዳሉት የሚለፈው ወያኔ በተለይ በአዲስ አበባ ለምርጫ የሚያቀርበው በመቸገሩ የተለያዩ መስሪያ ቤቶች ሃላፊዎችን ለምርጫ ለማቅረብ ወስኖ ማስመዝገቡ እየተወራ ይገኛል። ይህ ማለት ደግሞ ሁሉም የሕዝብ አገልግሎት የሚሰጥባቸው ተቋማት ሙሉ በሙሉ በወያኔ ቁጥጥር ስር መሆናቸውን ያረጋግጣል ማለት ነው።
ከዚህ በፊት አንዳንድ መስሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወይም እጅግ በጣም የሚበዛው የስልጣን ቦታቸው በህወሃትና ወያኔዎች መወረሩ በጥናት መረጋገጡና መገለጹ የሚታወቅ ሲሆን በሰሞኑም ወያኔ ለይስሙላ ምርጫው በሚያደርገው እንቅስቃሴ ሌሎች ቀሪ የሕዝበ አገልግሎት ተቋማትም ቢሆኑ ሙሉ በሙሉ በራሱ ቁጥጥር ስር መሆናቸውን እንደከዚህ ቀደሙ ጥናት ሳያስፈልግ ወይም ማንም ሳይጠይቀው በራሱ መንገድ ወያኔ አረጋግጧል። ይህም ማለት ወያኔ በሁሉም መስሪያ ቤቶች ሰርጎ ገብቶ የወያኔውን ምርጫ ቦርድን ሳይቀር በራሱ ሰዎች መቶ በመቶ ተቆጣጥሮ የፈለገውን እየገፋ ያሻውን እያወጣ ቀጥሏል። ስለዚህም ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሕዝብን እንወክላለን እስካሉ ድረስ እንደዚህ ካሉ ቀድመው ከተጠናቀቁ የይስሙላ ምርጫዎች ይልቅ ሕዝባዊ እምቢተኝነትን በማጠናከር ሕዝቡ ለመብቱ እንዲነሳና ነፃነቱን ራሱ እንዲያስከብር ለማድረግ የበኩላቸውን መወጣት ከሕዝባዊ ተወካይነታቸው በተጨማሪ የዜግነት ግዴታቸው ነው። አበቃሁ።

የታማኝ ጥሪ ለተቃዋሚ ኃይል መሪዎች – ታማኝነት ያፈራውን ህዝባዊ ፍቅር ተረከቡኝ ነው

የታማኝ ጥሪ ለተቃዋሚ ኃይል መሪዎች – ታማኝነት ያፈራውን ህዝባዊ ፍቅር ተረከቡኝ ነው
“ህዝቡ መሪዎችን ተጣራ! … ሳትሰሙ ብትቀሩ ግን ግፍ ይሆናል! … እኔ ተራው ሰው ይህንን የህዝብ ጥያቄ የመሸከም አቅሙም ብቃቱም የለኝም! የመነጋገሪያና የመደማመጫ ጊዜያችሁ አሁን ነው! እባካችሁን?!” በማለት የተቃዋሚ ኃይሎችን እንደ ድርጅት የህዝብን ፍላጎት እንዲረከቡና እንዲመሩ ከሰበዕዊ መብት ተሟጋቹ ከአርቲስት ታማኝ በዬነ ጋር በተደረገው ቃለ ምልለስ ከኢሳት Feb 18, 2013 ከዕለታዊ ዜና ጋር አዛምዶ ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም ካቀረበው የተወሰደ።
“ህዝብ መሪዎችን ተጣራ!” መንገድ ጠራጊው ለአዲስ ምዕራፍ – ብሄራዊ የፍቅር ጥሪ አቀረበ!
ሥርጉተ ሥላሴ 19.02.2013
ወይ ጉዴ ዛሬ ደግሞ እንዴትና እንዴት አድርጌ ነው ላቀርበው ያሰብኩት ይሆን … እም! ስገርም
የሰብዕዊ መብት ተሟጋቹ አርቲስት ታማኝ በዬነ ከእኛም ሲዊዘርላንድ መጥቶ በነበረበት ጊዜ የተናገረው አንድ ኃይለ ቃል ነበር። „ …ሰው ጠፋና እኔ ሰው ሆኜ ለእኔ እንዲህArtist Tamagne Beyene on ESAT News ትወድቃላችሁ ትነሳላችሁ …“ እኔ ይህን ሲል … እኔን! አፍር ልብላልህ አልኩኝ። እራሴ ሥርዓቱን በቪዲዮም እዬቀረጽኩት፤ በተጨማሪም በድምጽ መቅረጫም እዬቀዳሁት መሆኔን ዘንግቼ። ትናንትና ሳዳምጠው የእኔንም ድምጽም ቀድቶታል። የቀደሙት ሐዋርያትና ሰማዕታት „እኔ ትቢያ እኔ ታናሽ ስሆን ይሉ ነበር።“ ላቅ ያለ አብነት ነው። እንዲህ ዝቅ ማለት። እራስን ማዋራድ ~ ጸጋ ነው። እራስን ዝቅ ሲያደርጉ ህዝቡ የአንተ ሥፍራ ይህ አይደለም ብሎ፤ ቦታውን አደላድሎ፤ ወዶና ፈቅዶ የመረጠውን ከፍቅሩ ማህደር ያስቀምጣል። ለአርቲስት ታማኝ በዬነ ቦታውን የመደበለት፤ የደለደለለት ህዝቡ እራሱ ነው። በፈቃዱ ወዶና ደስ ብሎት ነው የሰጠው።
ስለዚህ ወንድሜ ታማኝ በዬነ በዚህ ሊሸማቀቅበት አይገባውም ባይ ነኝ። ከዚህች ቃል ኪዳናዊ ስጦታ ፈቀቅ ያለ ዕለት ግን ያን ጊዜ ቢከብደው፤ ቢሳነው ይገባል እንጂ አሁንማ … ደስ ብሎት በሐሤት ሊቀበለው ይገባል። አክብሮ በተግባር ሊከበክበው ይገባል። የህዝብን ልዩ ሥጦታ ሊያስመቸውም ይገባል። አርቲስት ታማኝ በዬነ ግበረ – ሰላም አስገብቶ፤ ሊጋባ አሰልፎ፤ ወይንም ሽልንጓን ዘርዘር – መንዘር አድርጎ በነፍስ ወከፍ ስለአደለ አይደለም የህዝብን ፍቅር ተንበርክኮ እንዲህ የሚዘቀው፤ በነጠረ ድርጊቱ ብቻ ነው። ያገኘውን ህዝባዊ ፍቅርን በቅጡ ማስተዳደር የመቻል አቅሙ ሥልጡን በመሆኑ ነው። የሚታይ የሚጨበጥ ዕውነት አንጡራ ንብረቱ በመሆኑ ነው። ለህዝብ ዕንባ ታማኝና ቋሚ አገልጋይ በመሆኑ ነው።
እጅግ የማከብራችሁ የጹሑፌ ታዳሚዎች … ወደ እርእስ ጉዳዬ ከመግባቴ በፊት ግን ስለ አዬሁት ነገር ትንሽ ምስክርነት ቢጤ ብሰጥ መልካም ነው። ሙንሽን ውስጥ እንዲህ ቅልጥ ያለ የኢትዮጵውያን ህዝባዊ ስብሰባ ሲካሄድ ይህ የመጀመሪያው ነው። የእስልምና እህቶቻችንም እንዲህ በብዛት ወጥተው ትግሉን ሲቀላቀሉ ሳይም ይህ የመጀመሪያ ጊዜ ነው። በተረፈ ሙንሽን የታደለ ነው። ዓላማቸውን ጠንቅቅው የሚያውቁ፤ ከፍላጎታችው ጋር ያልተላለፉ፤ ፍላጎታቸውን ጽላታቸው ያደረጉ፤ የህዝብን መዋዕለ ሃብት ሆነ መክሊት በአግባቡ የሚመሩና የሚያስተዳደሩ ብቻ ሳይሆን ብቃትን በአግባቡ ጥቅም ላይ በመዋል ረገድ አንቱዎች ያሉበት ከተማ ነው። እኔ በዓይኔ አይቻለሁ – መስክሬያለሁም። ሙንሽን የተግባር ጀግኖች ያሉበት ቦታ ስለሆነ ውጤቱ እንደ ሰማችሁትና እንዳያችሁት ሆኗል። ነገም …
አሁን ወደ የምወዳት ከተማ ወደ ፍራንክፈርት አማይን አብረን እንጓጓዝ። የትኬት አትጠየቁም። እሺ! አንድ ሚስጢር ላውጣ መሰል … ፍራንክፈርቶች ቀናተኞች ናቸው። ወንድሞቻችን ከሙንሽን እዬሄዱ ትግሉን ሲመሩ፤ ሲያስተባብሩና ሰያግዙ እኛ እያለን ስለምን? ሲሉ ከትግሉ ተቆርቋሪዎች አድምጫለሁ። ለምን ተበለጥን? ማለት ለመስዋዕትንት ከሆነ በጣም አዎንታዊ ነው። በተረፈ ቀደም ባለው ጊዜ ፍራንክፈርት አማይን የኢትዮጵያ ኮምኒቲው እራሱ ስንት በተግባር የተባ ክንውን ፈጽሟል መሰላችሁ። በአጎራባች ሀገሮች እዬተጠራ የልምድ ልውውጥም ያደርግ ነበር የፍራንክፈርቱ አማይን ዬኢትዮጵያ ኮሚኒቲ።
ፍራንክፈረት አማይን በ90ዎቹ አጋማሽ ለመጀመሪያ ጊዜ ከኦነግ በስተቀር የተቃዋሚ ኃይሎችን በአንድ መድረክ አገናኝቶ ያነጋገረ፤ በአማራጭ ኃይሎች፤ በኢተፖድህ፤ በመህአድ፤ በመድህን፤ በአርበኞች ግንባር … ምሰረታ ሆነ የድጋፍ ኮሚቴ በማደራጀትና በመምራት ወግ ያለው ተግባራትን ሲከውንብት የቆዬ ነው። በዘመነ ቅንጅትም – ትንሳኤ ራዲዮ ፕሮግራምን ጨምሮ የበቃ ተሳትፎ እድርጓል። በኋላም ቢሆን የግንቦት ሰባት የተሳኩ ስብሰባዎችን በውጤት ለናሙናነት የበቃበት ከተማ ነው ፍራንክፈርት አማይን። የሚገርመው በማናቸውም ጊዜ ጀርመን ውስጥ የሚኖሩ የወያኔ አባላትና ደጋፊዎቻቸው በህዝባዊ ስብሳባ በመገኘት „እኛ ወያኔ ነን“ በማለት ሲያፋጥጡም ፊት ለፊት በመፋለም አሳፍረው፤ አሸማቀው ይልኳቸው ነበር። ይህም ብቻ አይደለም ልክ አሜሪካን ሀገር ኮለንቮስ ኦሃዩ ባለው መልክ የእናት ልጆች ተለያይተው የነፃነት ትግሉን በመደገፍና በመቃወም አጋ ለይተው የሚፋለሙበት ከተማ ነው ፍራንክፈረት አማይንና አካባቢው።
ስለሆነም ፍራንክፈርት አማይን እጅግ ድንቅ፤ አንጋፋ፤ ሰፊ የተግባር ልምድ ያካበቱ ወገኖች የሚገኙበት ነው። እራሱ 25ኛው የብር እዮቤል የኢህአፓ በዓል የተከበረው እዛው ፍራንክፈርት አማይን ላይ ነበር። የኢተፖድህ ሁለተኛ ዓለም ዓቀፍ ጉባኤንም ያስተናገድ ፍራንክ ፈርት አማይን ነበር። በሱዳን የነበሩ ኢትዮጵውያን ወገኖቻችን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ኤን. ሲ. ኤች አር ሲበይን እስከ ተባበሩት መንግስታታ ጽ/ቤት ድረስ የተፋለሙት ትንታጎች ደመላሽ ይመራው የነበረው የድርሻችን እንወጣ የወጣቶች ማህበር ነበር። የሟቹ የአባ ጳውሎስ የተቃውሞ ቦንብ የፈነዳውም ፍራንክፈርት ቅድስተ ማርያም ላይ ነበር ….
የመጀመሪያው የአውሮፓ እግር ኳስ ጥንስስ ጨዋታ የተካሄደው ፍራንክፈርት አማይን ውስጥ ነበር። አውሮፓ አቀፍ „ „ራዕይ“ መጽሄት ዝግጅትና ስርጭት ፍራንክፈርት ላይ ነበር … እንዲያውም „ራዕይ“ መጽሔት አንደኛ ዓመቱን ሲያከብር አውሮፓ አቀፍ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ተካሂዶ የነበረው ወርክ ሾፕና ፓናል ዲስከሽን ለዘመኑ ልዩ ጌጥ ነበር። እና ለፍራንከፈርት አማይን ልጆች ለኢሰአት ባይታወር ሲሆኑ እንደ ልብ አምላኩ ንጉሥ ዳዊት „የቤትህ ቅናት በላኝ“ ብለው መነሳታቸው ወሸኔ ነው። ማለፊያም ነው። ወንድሜ ታማኝ ከዕቅዱ ውስጥ ያልነበረውን ፍራንክፈርት አማይን እንዲሳተፍና በቦታውም ተገኝቶ ሰብሉን ለመሰብሰብ መወሰኑ የተገባ ብይን ነው። „አያሰፍሩኝም!“ ብሏል። እኔም እደግመዋለሁ። አዎን! ፍራንክፈርትና አካባቢዊው ፈጽሞ አያሰፈሩህም። ለነፃነት ትግሉ ሲሉ የአንድ እትብት በሥጋም የሚገናኙ ልጆች ተፋተው የሚኖሩበት ከተማ ነውና …. በሃዘን በደስታ ጨርሶ አይገናኙም።
እኔ እንደማስበው ብቻም ሳይሆን በጣም በእርግጠኝነት ልናገር የምፈልገው ፍራንክፈረት አማይን ውጤቱም ቢበልጥ እንጂ አያንስም። ሃይድልበርግ፤ ማንሃይም፤ ካልስሮ ምን አልባትም ሽቶትጋርዶች ወደ ሙንሽን ካልሄዱ፤ እንዲሁም ከፈረንሳይ ከኢጣሊያን ያሉ ወገኖችም ወደ ዛ ሊያመሩ ይችላሉ ብዬ አስባለሁና …
እራሱ ፍራንከፈርት አማይን አንዱ መንደር ብቻ እንኳን ሲሰላ የትዬለሌ ነው። እንኳንስ ኩታ-ገጠም ሁነቶች ሲዳሰሱ። እንደ እኔ እጅግ ተቆርቋሪ ወንድምና እህቶች ያሉበት አካባቢ ስለሆነ ውጤቱ ዝቀሽ ነው። ለአሁን ለአርቲስት ታማኝ በዬነ ጉዞና ተልዕኮም ብቻ ሳይሆን ሃብትን በቋሚነት በማነጽ ረገድም ይህ የአሁኑ መጠነ ሰፊ ህዝባዊ ስብሰባ ትግሉን ሊያግዙ የሚችሉ የበቁ ተግባራት ይከውንበታል ብዬም አስባለሁ። ሰፊ መሰረት ሊያስጥል የሚችል ይሆናል ብዬም እገምታለሁ።
አሁን ደግሞ ወደ አምሰተረዳም ልውሰዳችሁ ዬት እንደ ደረሱ አላውቅም። ብቻ በማናቸውም አውሮፓ አቀፍ ስብሰባዎች በራሳቸው ወጪ፤ በተሟላ ካሜራ ለታሪክ ዶክመንቴሽን ይሰሩ የነበሩ የአእምሮ ጋዜጣ አዘጋጆች ከሀገር ከወጡም በኋላ መልካም ተግባር ሲከውኑ ነበር። እና ስለ አምስተረዳም ሲነሳ እነሱ ሁልጊዜ ትዝ ይሉኛል … ማለት ተሳትፎው በሁሉም ዘርፍ ከዬአካባቢው ነበር። ነፍሱን ይማረውና የኢቶጲሱ ያ ጀግና ጋዜጠኛ ሟቹ ተፈራ አስማረም ነፍሱን ይማረውና ወደ ለንድን ከማቅናቱ በፊት በርካታ ተግባራትን ከውኖበታል። እንዲሁም ሌሎቹም … ዬሲዊዲን ተሳታፊዎች ነበሩት … ራዲዮኑም በዬስብሰባዎች እዬተገኘ ይዘግብ እንደ ነበር አስታውሳለሁ።
ያው ሰብሰብ ያለው፤ ከወን ያለው ነዶ የሚበተነው በተቃዋሚ ኃይሎች የውስጥና የውጭ የቅራኔ አያያዝ ድክመት ምክንያት፤ ኃይሉ በዬጊዜው ካለአግባብ ይባክናል እንጂ። እርግጥ ነው አሁን አሰባሳቢው የፖለቲካ ድርጅት ሳይሆን ነፃው ሚዲያ ኢሰአት ነውና መሰንበትን ለማሰብ የሚቻል ይመስለኛል። በተረፈ ኩታ ገጠም ሀገሮች በተለይ ጀርመን፤ ሆላንድና ሲዊድን እጅግ የተቀራራበ፤ የተዋህደ ተግባር ሲከውኑ የቆዩ ብቻም ሳይሆን የጋራም ታሪክ ያላቸው ናቸው። እርግጥ በዬወቅቱ አናቱና ዓውራው ጀርመን ነበር። በዚህ ሁሉ ጊዜ ግን ከእስልምና እህቶች አንዲት ነፍስ ከባላቤቷ ጋር አብራ ሙሉዑ ተሳትፎ ታደርግ ነበር። ዛሬ ግን ሙንሽን ላይ ያዬሁት የእስልምና እምነት ተከታይ እህቶቻችን በመጠን ላቅ ብለው መገኘት እፁብ ድንቅ የሆነ የሰማይ ታምር ነው። ዋው! እንዴት ደስ እንዳለኝ አትጠይቁኝ። ብርቅ ስለሆኑብኝ በተደጋጋሚ ነበር ያዬሁት።
ወደ ቀደመው ይላሉ አባቶቻችን … ከኢሰአት ትርፋማ ጉዞ የተገኘው ዕንቁ ጉዳይ የታማኝ ሀገራዊ ጥሪ ነው„ታማኝነትንና ህዝባዊ ፍቅርን ተረከቡ ነው።“ ይገርማል። አሁን ማን ይሙት? የትኛው ሰው ነው መዳፌ ውስጥ ላይ የሚገኘውን መጠነ ሰፊ የለማና የፋፋውን ህዝባዊ ፍቅርን ተረከቡኝ የሚለው? ፍልሚያው ያለው እኮ ከዛ ላይ ነው። እውነት ከዚህ ላይ ያለው የአርቲስት ታማኝ ፍጹም ታማኝነት ደግሞ ከዘመኑ ያፈነገጠ ሆነብኝ። „ህዝብ ለእኔ የሰጠኝን ፍቅር ተረከቡኝና ከዕንባ ታደጉን ነው“ የሚለው። እንዴት ውብ ነገር ነው?! እንዴትስ ለዘመናት የሚቀር ትውፊት ነው እያሰተማረን ያለው?! እንዴትስ ያለ የበቃ የሐዋርያነት ተግባር ነው? ይገርማል። ይደንቃል። ያሰተምራል። ይመረምራል። ይፈውሳል። ያለማጋነን መድህንነት ነው። ታማኝ በታማኝነት የቆረበ አይደለ – ለዛውም በዚህ ዘመን ለኮፒራይት ልባችን ድብን በሚልበት፤ የግለኝነት ሞተር መንፈሳችን አንጠልጥሎ እንደ አሻው በሚዘውርበት ዘመን … …“ ህዝባዊውን ፍቅርተረከቡኝ!“ አለ። ዋው! ታማኝና ዕሴቱ ልዩ ሥጦታችን ናቸው። ቀለማም፣ ቅዱስ፣ ቅናዊ መንፈስ … ም!
አርቲስት ታማኝ በዬነ ደቡብ አፍሪካ ላይ የነበረውን ሁኔታ አስመልከቶም ኢሰአት ላቀረበለት ጥያቄ እንዲህ ሲል ነበር የመለሰው “እኔ መንገድ ጠራጊ፤ ደልዳይ ነኝ“ ሲል ተደምጦ ነበር። አሁን ደግሞ „እኔ መሸከም አልቻልኩም! ይህ ህዝብ ቆሞም ተንበርክኮም እዬለመናችሁ ነውና እባካችሁ ተደማመጡ! ኃብታችሁንም ተረከቡ አለ። ለዛውም የከበረውና የበቃውን የሥነ ምግባር ልዑልን ፍቅርን ተረከቡኝ!“ ነው የሚላቸው የተቃዋሚ ኃይሎችን መሪዎችን። እስኪ ይህን አብነትነትህን፤ አደራህን ለመወጣት ሁሉም ደጋፊህ፤ አድናቂህ በተግባር እንዲሆንበት አምላክ ይርዳን። አሜን!
እኔ እንደማስበው በፖለቲካ ድርጅቶች አንድነትና ውህደት መሰባሰብ፤ ልዩነትና መፈራቀቅ፤ እንዲሁም መለያዬት የተፈጠረው ጦርነት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ያለነሰ ነው። ጠቅልለው ወደ ወያኔ የገቡት መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ እንበላቸውና … የኛ በምንላቸው እነሱም አለን ለሚሉት ግን ይህ ቅንነትን ስንቅ ያደረግ የህዝባዊ ፍቅር ርክክብ ዓዋጅ አዲስ ምዕራፍ ከፋች ማዕልት ሁላችነንም ናፍቆናል። አዎን! የአርቲስት ታማኝ በዬነ ብሄራዊ ጥሪ እንደ ባላንጣ መተያዬት በነበር … ነበር … ብቻ እንዲዘለል ነው ፍላጎቱ ….
ነበርን እንደ ነበር ለታሪክ ትቶ፤ አሁን ግን በግል እንኳን እዬተገናኙ የፖለቲካ መሪዎች፤ አባላቶቻቸውም ሆነ አካላቶቻቸው ይህን የህዝብ ጥሪ በጸጋ ተቀብለው በሥርዓት መምራትና ማስተዳደር ይኖርባቸዋል። በኢሰአት ስብሰባዎች ላይ የሚታደመው ወገን አብዛኞቹ በትግሉ ውስጥ የቆዩ ናቸው። አስተባበሪዎቹ ደግሞ የአንደኛው ወገን የነበሩ ሊሆኑ ይችላሉ፤ ወይንም ተቀላቅለው፤ ወይንም ተዋህደው ሊሆንም ይችላል። የሆነ ሆኖ ተሳታፊው ኢሰአትን ፈልጎ ሲሄድ፤ ግልምጫ – መገለል – ፊት መነሳት – ባይታዋርነት ሊደርስበት እንደሚችል አምናለሁ ያዬሁት ነውና።
ግን ነገር ግን ተሳታፊው ፊት ለፊቱ የተጋረደውን የልዩነት ጋራ ንዶና አሽንፎ፤ ህሊናውንም አባብሎና አሳምኖ ለመሰዋእትነቴ የማንም ፈቃድ አያስፈልግኝም፤ እኔ ለሀገሬ አንባሳደር ነኝ፤ ብሎ እንዲህ ተሞ ሲሄድ፤ መሄድ ብቻ ሳይሆን ልዩ ታሪክ ፈጽሞ፤ ልዩ ታሪክ ሲሰራ ከላይ ያሉት የፖለቲካ መሪዎችም ከታችኛው ክፍል በመማር እራሳቸውን ቆንጠጥ እድርገው፤ ቢያስፈልግም ገስጸው የትግሉን ባህሪ ለውጥ እድርገው ለአዲሱ ዘመን የሚስማማ በሙሉ ሥነ ምግባር ፍቅርን ማወጅ አለባቸው። በሰነድ ለምደነዋል – በመሆን ይጋቡ …
ይህን ቢያደርጉ ወያኔ እያለ የሌለ ነውና ዘነዘናውን ይቀራል። የሚበጀው ነገር ወደ ኋላ በሚስቡ፤ በሚጎትቱ ጉዳዮች ላይ ጊዜን ከማባከን፤ አዕምሮን ከማቁሰል ወደ ፊት በማዬት የህዝብን ፍዳን፣ ስቃይን፣ መከራን፣ ስደትን፤ ሞትን፤ እስራትን፤ ራህብን በማሰብ ለዚህ ሲባል እራስን ዝቅ አድረጎ ወደ ዬሚያስማማ መስመር መጥቶ ትግሉን መምራት መቻል ብልህንት ይመስለኛል። ብልጥነትም ነው። ትርፋማነትም ነው። እስኪ ዛሬስ ይሁንባቸውና ወያኔን በብልጠትና በብልህነት ይብለጡት።
የኢትዮጵያ እስልምና እምነት ተከታዮችና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች ወያኔን እኮ ቅስሙን እንኩት አድርገው ሰባባሩት። ደራጎን አፈረ ከሰረ … ተከሰከሰ። ይህ አስተምህሮት ለተቃዋሚ የፓለቲካ ድርጅቶችም ቢሰራ እንዴት ባማረብን ነበር። መንገዱም እኮ … እንደ እኔ የሰለጠነ ነው። ጠላት የማይፈልገውን አድኖ መፈጸም፤ … ጠላትን ካለ ባሩድ ማንደድ ነው። እያገላባጡም በጥቃት መንገርገብ ነው። ለድልም ያበቃል።
እርግጥ ነው ከቅንጅት መራራ ስንብት በኋላ አንድነትና ግንቦት ሰባት በተቻላቸው ተንቀሳቅሰው ትግሉን አሟሙቀውት ነበር። የዬሀገሮች የኮሚኒቲ ራዲዮ ጣቢያዎች፤ ድህረ ገጾች፤ የመወያያ መድረኮችም፤ ሀገር ድረስ መሰማት የሚችሉ ራዲዮኖችም ጭምር የበኩላቸውን አስተዋፆም አድርገውበታል። በዚህ ዙሪያም ያለው ኃይል፤ የሚፈስው አንጡራ ኃብት፤ ቀላል አይደለም …
የሆነ ሁኖ ግን ሚዲያ እንደ አንድ የፖለቲካ ድርጅት ፓርቲ ሊያታግልና የነፃነት ትግሉን ሊመራ ፈጽሞ አይችልም። የሚዲያ ሚና፤ ኃላፊነቱና ተግባሩ የነቃውን የህሊና ክፍል መንፈስን አለስልሶ በገዢው ፓርቲ ላይ ሙሉ በሙሉ መንፈስን ማሸፈት ብቻ ነው። በመረጃ የተደገፉ እውነቶችን ህዝቡ እንዲያውቅ በማድረግ የህዝብን የመረጃ የማግኘት ሙሉ መብት በተግባር ማረጋገጥ ነው። ሃቅን መነሻውና መድረሻው ላደረገ መረጃ ከወያኔ ደጅ የዕብለት መረጃ ፍርፈሪ ህዝብ ቆሞ እንዳይለምን የህዝብን የመረጃ ባለቤትነት መብቱን እቤቱ፤ እደጁ ድረስ በመገኘት በተግባር ማስጌጥ ነው። ወያኔ የሚፈጥራቸው አፈናዎችና የነፃነት እግርብረቶችን በብዕር ሰይፍ ብትንትናቸውን ማውጣት ነው። ኢ ሰ አ ት ይህን መጠነ ሰፊ ኃላፊነት በብቃት ይወጣ ዘንድ ነው የሰብዕዊ መብት ተሟጋቹ የአርቲስት ታማኝ በዬነ ጉዞና ድካም። ይህ የሰላ፤ የለሰለሰ መንገድ ደግሞ የበቃኝን፤ የእንቢተኝነትን የፋሙ ፍላጎቶችን ይፈጥራል – ያነጥራል። ግን እንቢታና በቃኝ መሪ ያስፈልጋቸዋል … „ተደማመጡ! ጊዜው አሁን ነው። ግፍ ይሆናል። ተደራጁና ምሩኝ ይላል ወገናችሁ። እባካችሁን?“ ብሏል መንገድ ጠራጊው „ፈረስ ያደርሳል እንጂ …“ ጨርሱት እኔም ጨረስኩ።
አራት ዓይናማው መንገዳችን ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው!
እልፍ ነና እልፍነታችን እልፍ እናድርገው!
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።