Tuesday, December 4, 2012

የሙስሊም ወገኖቻችንን የመብት ጥያቄ ጥላሸት መቀባት በእሳት መጫወት ነው ።


በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ
ሕዳር 24, 2005 ዓ.ም
የሙስሊም ወገኖቻችንን የመብት ጥያቄ ጥላሸት መቀባት በእሳት መጫወት ነው ።
“ይሉሽን በሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ” እንዲሉ ወያኔ/ኢሕአዴግ በመንግስት ስም ሥልጣን ላይ ተቀምጦ በድርጅትም በግልም ነፃነቴ ይከበር ፣ ነፃነቴ አይደፈር ፣ ንብረቴ አይዘረፍ ፣ እትብቴ የተቀበረበት መሬት ለባዕድ አገር ከበርቴ አይሸጥብኝ፣ የዕምነቴን ሥርዓት በነፃነት ላከናውን….ወዘተርፈ የሚለውን ሁሉ ሽብርተኛ በሚል የሀሰት ውንጀላ ለስቃይና ለመከራ ሲዳርግ ቆይቷል። አሁንም ቀጥሎበታል። የኢትዮጵያ መምህራንና ማህበራቸው ኢመማ ይሕን ለመሰለው የወያኔ የሀሰት ክስና ውንጀላ ሥርዓት ፣የአዳፍኔ (የአባይ) ምስክርነት፣ የፍርደገምድል ዳኝነት፣ ከዚሁ ጋር ተያይዞም እስራትና ግድያም ሰለባ የሆኑት ገና በጧቱ ነበር። ያኔ ሕብረተሰቡ ውዥንብርና መጠራጠር ውስጥ ሊገባ የተገደደ መስሏል። ውሎ እያደረ ግን የወያኔ/ ኢሕአዲግ ማንነትና ምንነት በሂደት ቁልጭ ብሎ ታይቷል። የዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችንም ሆነ ራሱ በተግባር ለማዋል በሰነድነት ይዤዋለው የሚለውን ሕገ መንግሥት ተብዬ ሰነዱን ጎዝጉዞ ተቀምጦበታል። በአንዳንድ ወገኖቻችን እንደተጠቀሰው ሕገ መንግሥት ተብዬው የውሽት ሰነድ “ሕገ አራዊት” መሆኑ ማረጋገጫው ይህ ቡድን ለመብቴ እቆማለሁ ያሉትን ሰዎች እያደነ ማሰሩ፣ ማሰቃየቱ፣ ንብረት መዝረፉና ከዚያም በላይ ግድያ መፈጸሙ ነው።
የሩቁን ትተን በቅርቡ ያየነውና የሰማነው ለነፃ ሚዲያና ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት የቆሙ ጋዜጠኞች፣ ሕዝባዊ አስተዳደር እንዲሰፍን በሚታገሉ የፖለቲካ መሪዎች ላይ በኢ-አቃቤ ሕግ የተተወነው የአኬልዳማ ድራማና የሽብርተኝነት ክስ ካለፉት ዓመታት ተከታታይ የተውኔት ገቢር ከመሆኑ ሌላ እንግዳ ነገር አይደለም። ወያኔ/ኢሕአዴግ በአገር አማን ከመሬት ተነስቶ የሽብርተኝነት ሕግ አውጥቶ በይሰሙላ ፓርላማው ሲያስጸድቅ ራሱ የሽብሩ ተዋናይ ሆኖ እንደሚሠራው ሕዝቡ ከመነሻው በውል ተረድቷል። ይህን አፋኝ ሕግ ብዕራቸውን አንስተው የነቀፉትንና በአደባባይ የተቃወሙትን እንደተጠበቀው “ሽብርተኞች“ ብሎ ወህኒ አወረዳቸው። የመብት ጥያቄ ማቅረብና የወያኔን ሕገወጥነት መቃወም በሽብርተኝነት የሚያስፈርጅ ከኛ አገር ሌላ መኖሩ ያጠራጥራል። መምህራን ለችግራቸው ማስታገሻ የደመወዝ ጭማሪ እንዲደረግላቸው ቢጠይቁ ሰሚ በማጣታቸው በመጨረሻ በመጋቢት ወር 2004 ዓ.ም የሥራ ማቆም አድማ መትተው የመብት ጥያቄ በማቅረባቸው ከሽብርተኞች ጋር ያበሩ ተብለው በውርደት፣ በዘለፋ፣ በዘረፋ፣ በዘረኛው “ባለራዕዩ” ሰውዬ መሰደባቸውና እስካሁንም የሚደርስባቸው ዙሪያ ገብ ስቃይ አሸባሪው ማን እንደሆነ ለማወቅ አይከብድም።
በአሁኑ ወቅት የዙር ተራ የደረሰው በኢትዮጵያውያን ሙስሊም ወገኖቻችን ላይ ነው። ይህ ወንጃለኛ አምባገነን ቡድን በኃይማኖት ላይ መዝመት የጀመረው ቀደም ብሎ ነው።በአንዋር መስጊድና በአደባባይ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን የፈፀመው በቂ መረጃ ነው። በተለይ በአንዋር መስጊድ ያካሄደው ግድያና በዚያ ሳቢያ የመጅሊሱን አመራር በካድሬዎቹ ለማስያዝ እንደስልት ተጠቅሞ በምዕምናኑ ተቀባይነት ያላቸውን ግለሰቦች ወንጅሎ ወህኒ ወረወራቸው።ለሦሥት ዓመታት በእስራት አንዲንገላቱ ካደረገ በኋላ በነፃ ተለቀቁ። ከዚህ ጎን ለጎን የመጅሊሱን አመራር
2
ያለዕምነቱ ተከታዮች ይሁንታ ምርኮኛ አድርጎ ሲጓዝ የሙስሊሙ ማሕበረሰብ ሁኔታዎችን በጥሞናና በትዕግሥት በመከታተል ይህን ሕገወጥ የወያኔ እርምጃ ለመለወጥ ሲታገሉ እንደቆዩ ከዕምነቱ ተከታዮች አንደበት ተሰምቷል። የኢትዮጵያ ሕዝብም የሚያውቀው ሐቅ ነው።
ይህ በእንዲህ እያለ የወያኔ/ኢሕአዴግ ባለሥልጣናት “አህባሽ” የሚል ባዕድ አምልኮና አስተምህሮት በሙስሊሞች ላይ እንዲጫን መሪውን ከሊባኖስ አምጥተው በማሰማራታቸው ሁኔታዎች በቅጽበት እንዲለዋወጡ አደረገ። ወያኔ በባህርዩ ከራሱ ቁጥጥርና አጀንዳ ውጪ የሙያ ማህበራትና ድርጅቶች ማለትም የመምህራን፣ የሠራተኛ፣ የሴቶች፣ የጋዜጠኞች፣ የተማሪዎች---ወዘተርፈ ማህበራት ነፃ ሆነው የሚንቀሳቀሱ ከሆነ ለህልውናዬ ያሰጉኛል የሚል መጥፎ አባዜ ስለተጠናወተው በኦርቶዶክስ ኃይማኖትም ሆነ በሙስሊሞች ለፈጸመውና እየፈጸመ ላለው ደባ መንስሔው ይሔው ነው። ያሁኑ የሙስሊም ወገኖቻችን ጥያቄ መሠረቱ የዕምነት ተቋማችን የሆነው መጅሊስ አማኞች በሚመርጧቸው ሰዎች ይመራ የሚለው መነሻ ሆኖ የአህባሽ አስተምህሮም በመንግሥት አጋፋሪነት በአማኞች ላይ ሊጫን ሕገ መንግሥታዊም ሆነ ዕምነታዊ (መለኮታዊ) ፈለግ አይደለም ነው የሚሉት።ይህ ደግም ጥርት ያለ ሐቅ ነው። ይህን ሐቅ ይዘውም አካሄዳቸው እጅግ ሰላማዊና ሕጋዊ መሆኑ ዓለምን ያስደመመ ታሪካዊ ገድል ሆኗል።
አንድ ዓመት ባስቆጠረው የሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ማጠንጠኛ ማዕከል የሆነው የዕምነት ድርጅታችንን (መጅሊስ) እንዲመሩ የምንመርጥ እኛው ነን፣ የምርጫው ማዕከል የሚሆኑትም መስጂዶች ናቸው የሚል ሲሆን ወያኔ ደግሞ በራሱ የአስተዳደር አካላት በሆኑት ቀበሌዎች በካድሬዎች አማካይነት እንዲከናወን መፈለጉ ሂደቱን በማይገናኙ ትይዩ መስመሮች (Parallel lines) ላይ እንዲቆም ያደረገ አምባገነናዊ ተግባር እንደሆነ ያሳያል። ይህን በመንግሥት ስም የሚካሄድ ሕገወጥ አሠራር ማስተካከል እንዲቻል በማሰብ ሙስሊም ምዕመናን “መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ” አቋቁመው ከወያኔ/ኢሕአዴግ ጋር ተቀራርቦ በመወያየት እልባት እንዲገኝ አመቻችተዋል። በሰላማዊ መንገድ ተወያይቶ መፍትሔ በመፈለጉ ረገድ በመንግሥት ስም ከተቀመጠው ቡድን ሙስሊም ምዕመናንና ወኪሎቻቸው በልጠው ታይተዋል። “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ” እንዲሉ ሆኖበት ወያኔ ይህ የሠለጠነ አካሄድ አያምርብኝም ብሎ ባደገበትና በተካነበት አሠራር በአርሲ አሣሣ መስጊድ ግድያ ጀመረ፣ በአወልያ ት/ቤትም አማኞችን በጭካኔ ደበደበ ዘረፋም አካሄደ፤ ወሎም ዘልቆ በደጋንና አካባቢዋ ነዋሪዎች ላይ ጦሪነት አውጆ አማኞችን በአሰቃቂ ሁኔታ ጭዳ አደረጋቸው፣ ብዙዎችን አቆሰለ ፣ በሆስፒታል የሕክምና ዕርዳታ እንዳያገኙ አደረገ። በተመሳሳይ እርድ የሚጣሉ ፍለጋ ወልዲያ አካባቢ መስጊድ አቃጥሎ በትንኮሳው የተበሳጩ ሙስሊሞችን ለማጥመድ አቅዶ ከሸፈበት። ይባስ ብሎ አሸባሪዉ የወያኔ መንግሥት ሰላማዊ የሆኑትን የሙስሊም ማህበረሰብ መሪዎችን “አሸባሪዎች” ብሎ ቅራቅንቦ የሀሰት ማስረጃ ተብትቦ በመክሰስ ቃሊቲ ወህኒ ጥሏቸዋል። የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሚያውቀውና በዚህ ጽሑፍ በመጠኑም ቀንጨብ ተደርጎ እንደቀረበው የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ጥያቄና በአንድ ዓመት የተቃውሞ እንቅስቃሴም እንደታየው የሽብርተኝነት መንፈስ አለመኖሩን ነው።በአንፃሩ ግን ገሃድ የወጣውና አስከፊ ደረጃ ላይ የደረሰው የወያኔ መንግሥታዊ አሸባሪነት ነው።
የሙስሊም ወገኖቻችን ጥያቄ የመብት ጥያቄ ነው። የሠራተኛው፣ የመምህራን፣ የሴቶች፣ የገበሬዎች፣ የጋዜጠኞች፣ የተማሪዎች ---- የሌሎች የሕብረተሰብ ክፍል የመብት ጥያቄ አካል ነው። በነፃ የመደራጀት ጥያቄ ነው። የሙስሊም ወገኖቻችንን ጥያቄ ልዩ የሚያደርገው ነገር አለ ቢባል እየተገደሉ፣ እየታሠሩ፣ እየተገረፉና እየተዘረፉ በጽናትና በአንድነት ቆመው ባይበገሬነት ወደፊት መራመዳቸው ነው።ይህን የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ትግል መደገፍ የሚገባን ያለምክንያት በስሜታዊነትና ግብታዊ በሆነ አካሄድ አይደለም።የወገኖቻችን ትግል የመደራጀት ጉዳይ፣
3
የዕምነት ነፃነት ጉዳይ፣ የርትዕና ፍትሕ፣ ሕግና ሕጋዊነት፣ ባጠቃላይ የሰብአዊ መብቶች መከበር ጥያቄ ላይ ተመስርቶ የሚካሄድ ነው።ይህን የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን የመብት ጥያቄ በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ ይደግፋል። መምህራንና ሌላውም የሕብረተሰብ ክፍል መደገፍ ይጠበቅባቸዋል።
ከሙስሊሙ ወገኖቻችን ጥያቄ በመነሳት በኦርቶዶክስ ዕምነት ተከታዮች የገዳማት ይዞታ የሆኑ መሬቶች በሕገወጥነት መነጠቅ ፣ አድባራት መዘረፋቸው፣ ሆን ተብሎ በወያኔ በተሎከስ ሰደድ እሳት በንብረትና በአገር ቅርስ ጥፋት መድረሱ፣ የቤተ ክርስቲያኑዋ ቀኖና መጣሱ፣ በክርስቲያኑም በሙስሊሙም ከመንግሥት የተቃጣው ጥቃት በጋራ ቆመው እንዲታገሉ ነባራዊ ሁኔታዎች ተሟልተዋል። በመምህራንም ላይ እየደረሰ ያለው የማያባራ እንግልት፣ የሥራ ዋስትና ማጣት፣ በነፃ የመደራጀት መብት መገፈፍ፣ ---- ትግላቸውን ከሌሎች ተመሳሳይ ጭቆናና አፈና ከሚደርሰባቸው ክፍሎች ጋር ማቀናጀት የሚጠበቅባቸው የትግል ስልት ለመሆኑ ግልጽ ሆኗል። እንዲያውም ባላቸው የትግል ተመክሮ መምህራን የሙስሊም ዕምነት ተከታዮች ጥያቄዎችን ሆነ የኦርቶዶክስ ዕምነት ተከታዮች የመብት ጥያቄዎችን ማገዝ ይጠበቅባቸዋል። እንዲሁም በዘር ምንጫቸውና በቋንቋቸው ተነቅሰው ይኖሩበት ከነበረው የእርሻ መሬት ላይ መፈናቀል የደረሰባቸውን ገበሬዎች፣ ቤት ሠርተው ንብረት አፍርተው ይኖሩ የነበሩትን የከተማ ነዋሪዎች ቤትና ንብረታቸው በቡልዶዘር እየደረመሰ አውላላ ሜዳ ላይ ከነቤተሰቦቻቸው የጣላቸውን ዜጎች ሁሉ ማሰባሰብ የዚህን ግፈኛ ሥርዓት ቀበጥ ባለሥልጣናት አስወግዶ የሕዝብ የበላይነት፣ ተጠሪነትና ተጠያቂነት ያለው ሥርዓት እንዲመሰረት በጋራ መነሳትና ለመሰዋዕትነትም ዝግጁ መሆን ያሰፈልጋል።
በዚህ በኩል መምህራን የማስተባባር፣ የማደራጀትና የመምራት ብቃታቸውን መጠቀም ይኖርባቸዋል። በዚህ አኳያ እንኳንስ ሕዝባዊ አመጽ የመምህር የኔሰው ገብሬ በግሉ የከፈለው መስዋዕትነት መና አልቀረም። ይሄውና የሙት ዓመቱን የሚዘክሩለት ታይተዋል።የዚህ ጀግና መምህር መስዋዕትነት በሙያ ጓዶቹ በመምህራን እንዲታወስና እንዲወሳ ሁኔታዎች ባለመፍቀዳቸው እናዝነለን።ይህ እንዲሳካ የዘረኛው ሥርዓት ዕድሜ እንዲያጥር ሁላችንም የበኩላችንን እንድናበረክት ይጠበቃል። በስልት መደራጀት በስልት ማደራጀት ምን ጊዜም ትኩረት የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው።
በመጨረሻም የኢትዮጵያ ሙስሊም ወገኖቻችን የጀመሩት ትግል ከዳር እንዲደርስ የመምህራን የትግል አጋርነት አስፈላጊ ነው። ሌላዉ የሕብረተሰብ ክፍልም ሊተባባር ያስፈልጋል። ስንት ጊዜ የጋራችን ጠላት የሆነው የወያኔ ቡድን በግል ያጠቃናል? በተለያዩ ወቅቶች አንድ ላይ ሆነን ባለመነሳታችን የከሸፉትን የትግል እንቅስቃሴዎችን እናስብ። ወያኔ/ኢሕአዴግ እንዳለፈው ሁሉ በሐሰት ውንጀላ የሕዝብን ጥያቄ አፍናለሁ የሚልበት ነፍጥ ቀለሃው ብቻቀርቷል። ባሩዱ ያለው በሕዝብ እጅ ስለሆነ የወያኔ አጉል መራወጥ በእሳት መጫወት ይሆናል፤ በጣዕር ላይ ያለ ሥርዓት ደግሞ በስተመጨረሻው እንዲህ በጥፋት የሚጠመድ መሆኑ በታሪክ የተመዘገበ ነው። የአምባገነኖች መገለጫም ነው። ሕዝብ አሸናፊ ነው፤ ቆርጠን እንታገል።
ከሙስሊም ወገኖቻችን ጋር እናብር!!
የሙስሊም መሪዎችን የሚሰይም አማኙ ነው!!
መጅሊስ የዕምነት ማራመጃ እንጂ የፖለቲካ ማስተናገጃ አይደለም!!
መንግስታዊ አሸባሪነት ይሰበር!!

The ICC’s Africa circus continues…
The Horn Times opinion box, Dec 3, 2012
*Who should have been prosecuted first, the kind- hearted Madame Simone Gbagbo or the ferocious Senorita Azeb Mesfin?
by Getahune Bekele
The international criminal court has become a laughing stock in Africa
Simone
Is the ICC starting to pick soft targets?
Azeb Mesfin

The international criminal court has become a laughing stock in Africa, once again, when it bizarrely indicted the wife of former Ivory Coast president Laurent Gbagbo, Madame Simone Ehivert Gbagbo, 63, on four counts of crimes against humanity.
In a charge widely denounced across Africa as flawed, unjust and French fabricated, the ICC accused the former first lady of being her husbands’ alter ego in orchestrating a campaign of election violence where more than 3000 people lost their lives.
Madame Gbagbo has been in prison for the past 18 months in Odienne town, north west Ivory Coast, on charges of genocide and embezzlement.
Is the ICC starting to pick soft targets? Frustrated by lack of co-operation to go after the continent’s notorious war criminals; is the ICC targeting the weak, the meek and the down trodden?
After Lewis Moreno Ocampo exited the ICC, Africa expected more from the newly appointed chief prosecutor Fatou Bensouda in pursuing unresolved major cases such as going after Joseph Kony, and in dealing with hordes of jittery genocidal Tigre warlords in Ethiopia, who are left exposed by the sudden death of the fuehrer, Meles Zenawi.
Furthermore, the arrest warrant issued for Simone Gbagbo who didn’t held political office, while Ethiopia’s ferocious former first lady, the mastermind of the 2005 election massacre walks free, is regarded as implementing the one sided victor’s justice.
Dubbed the mother of corruption, Azeb Mesfin worked as second-in-command of her late husband’s ethnocentric regime, leading the 21 years ethnic cleansing campaign of western Gonder with no fear of prosecution, and she is yet to be held to account.
When her late husband lost elections, gave up the fight and fled to South Africa with his three kids in 2005, Azeb Mesfin who held political office with the power to make state decisions stayed behind alongside the inner circle of the clannish junta, with whom she met frequently to discuss the implementation and co-ordination of her evil plans, and was repeatedly filmed directing military operations in Addis Ababa, where more than 250 protesters were brutally killed by her dead husband’s private militia known as the Agazit brigade.
Together with her Hench men they targeted civilians and ethnic Amharics in particular, whom they perceived as their mortal enemy.
On Zenawi’s so called triumphant return on November 2005, during a victory parade in the compound of the palace, Azeb appeared before a crowd of jubilant warlords and praised herself, former Addis Ababa Meyer Arkebe ouqubay, former security chief Kinfe Gebre Medhin, Gen Samora Younis and the aging retard Sibehat Nega (all ethnic Tigres) as heroes of the “people’s revolution.”
Besides getting involved in flagrant human rights violations the former iron lady who until recently refused to vacate the official residence of the PM, showing her middle finger to the confused warlords, has also been accused of acquiring vast wealth through corrupt practices.
How on earth is then the ICC turning a blind eye to such crimes, leaving millions of victims in search of justice?
How long is going to take for the ICC to deliver an evenhanded justice to the people of Africa?
Only time will tale.

Monday, December 3, 2012


 
ሰማያዊ ፓርቲ የአቡነ ጴጥሮስን ሀውልት መፍረስ ተቃወመ

ህዳር ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ፓርቲው ባወጣው መግለጫ ማንኛውም ልማት ወጪን ቆጣቢ ሆኖ መሰራት እንዳለበት የሚታመን ቢሆንም በዋጋ ሊተመኑ የማኢችሉ ቅርሶችን በማጥፋት ግን ወጪን ለመቀነስ ማሰብ የእብደት አስተሳሰብ ነው ብሎአል።
 የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌታሁን ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ኢህአዴግ ከፍ ብሎ ለመታየት ባለው ፍላጎት የተነሳ ከዚህ በፊት የተሰሩትን ስራዎች ሁሉ ለማሳነስ እንደሚሞክር ገልጠው፣ የአቡነ ጴጥሮስን ሀውልት ለማፍረስ ቀድሞውን ነገር መታሰብ አልነበረበትም ብለዋል::
 የመንግስት ባለስልጣናት የአቡነ ጴጥሮስን ሀውልት ለማፍረስ ሲወስኑ አጥር እንደማፍረስ አድረገው እንደቆጠሩት የተናገሩት አቶ ይልቃል ፣ ህዝብ ባይጮህ ኖሮ መልስ ለመስጠትም አይፈልጉም ነበር ብለዋል
 የግራዚያኒ ሀውልት ጣሊያን ውስት ሲሰራ በዛው ሳምንት የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት መፍረሱ የታሪክ ምጸት ነው በማለት የመንግስትን የታሪክ አረዳድ አቶ ይልቃል ተችተዋል
 ይህ በእንዲህ እንዳለ ሉሲ በመጪው የፈረንጆች አመት አጋማሽ ላይ ወደ ኢትዮጵያ እንደምትመለስ መንግስት አስታውቋል።
 የህወሀት/ኢህአዴግ ንብረት የሆነው ፋና ብሮድካስቲንግ እንደዘገበው የ5 ዓመታት ቆይታ ለማድረግ ወደ አሜሪካ ያመራው የሉሲ ቅሪተ አካል በመጪው የፈረንጆች ዓመት አጋማሽ ላይ ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳል።
 ቅሪተ አካሉ ከመመለሱ በፊት የመጨረሻ ኤግዚቪሽኑን በካሊፎርኒያ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ራዲዮው ዘግቧል።
 በመጪው የ2013 የፈረንጆች አመት አጋማሽ ላይ ከሉሲ ጋር አብረው የሄዱትን ፥ ሌሎች 149 ቅርሶች በተሸኙበት መልኩ በጥሩ ሁኔታ ለመቀበል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ደስታን ዋቢ አድርጎ ራዲዮው ዘግቧል::
 ከሉሲ ጉብኝት የሚገኘው ገንዘብ በፕሮጀክቱ ስም በተከፈተው አካውንት ገቢ በመደረግ ላይ መሆኑንና ፥ ፕሮጀክቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ሙዚየሞችን ለማሳደግና ለማስፋፋት እንደሚውል ራዲዮው ዘግቧል።
 ይሁን እንጅ የሉሲ አጽም ትክክለኛው ይመለስ ቅጅው አይታወቀም። በሉሲ አማካኝነት ስለተገኘው ገንዘብ ዝርዝር ማብራሪያም አልተሰጠም። ራዲዮው በሚቀጥለው የፈረንጆች አመት አጋማሽ ላይ አለ እንጅ በየትኛው ወርና ቀን ሉሲ ወደ አገሯ እንደምትመለስ አልተገለጸም።

ወያኔ ታሪክን የማፍረስ ዘመቻውን ቀጥሏል!!


ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ ገና ከጫካ ሳይወጣ በስትራቴጂ ደረጃ የነደፈዉን ኢትዮጵያንና ታሪኳን የማጥፋት ዘመቻውን አሁንም እንደቀጠለ ነው። የወያኔ ዘረኞች የኢትዮጵያ ህዝብ የትግልና የመስዋዕትነት ምልክት የሆኑትን ጅግኖች ታሪክና የወያኔ አስራ ሰባት አመት የጫካ ትግል አሻራ ያላረፈባቸዉን ሰማዕታቶቻችንን የገድል ታሪክና ሀዉልት እያጠፋ በምትኩ የኔ ናቸዉ የሚላቸዉን የእነ አባ ጳውሎስን ዝከረ ሀውልትና የእነ መለስ ዜናዊን ምስሎች ብቻ በመዲናችን በአዲስ አበባ በማስቀረት፤ አዲስ አበባን የሀዝብ ሳይሆን የወያኔ ታሪክ ማስታወሻ እያደረጋት ነዉ። ወያኔ በላፈዉ አመት አጋማሽ ላይ በልማት ስም በታሪካዊዉ ዋልድባ ገዳም ላይ የጀመረዉን የአገር ታሪክና ቅርስ የማጥፋት ዘመቻ አሁን ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ አልበገረም ባይነት ታሪክ ተምሳሌት የሆኑትን የሰማዕቱን የአቡነ ጴጥሮስን ሀዉልት የባቡር ሀዲድ እሰራለሁ በሚል ሰበብ ለማፍረስ በዝግጅት ላይ ነዉ። ይህ የወያኔ የጥፋት ዘመቻ ደግሞ እኛ ካላቆምነዉ በቀር የማንነታችን መገኛ አረአያ የሆኑትንና የአበውን ጀግንነት፤ አልበገርም ባይነትና እምቢተኝነት የሚስታውሱን ግዙፍ የታሪክ ማስታወሻዎቻችን የወያኔ ቡልዶዘሮች ሰለባ የሚሆኑበት ቀን ሩቅ አይደለም። ይህን ዘረኛ አገዛዝ በቶሎ ማሰወገድ አለብን ሰንል ግባችን እድገትና ዲሞክራሲ ብቻ ሳይሆን በወያኔ እየላላ ያለዉን አንድነታችንን ማጥበቅና ወያኔ በየቀኑ እያወደመ ያለዉን የታሪክ ቅርሶቻችንን በፍጥነት ማዳንና መጠበቅ ጭምር ነዉ።

የጣሊያን ፋሺስቶች አቡነ ጴጥሮስን “አርበኞች የሀዝብና የአገር ጠላት” ናቸዉ ብለዉ የሚያስተምሩ ከሆነ ዛሬዉኑ ከእስር ይፈታሉ ሲሏቸዉ አምላኬ ይህንን አላስተማረኝም ብለዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላቶች እነዚህ ፊት ለፊታችን የቆሙትና ከሩቅ አገር የመጡት ፋሺስቶች ናቸዉና የኢትዮጵያ ህዝብና መሬት ከእነዚህ ሀገር ቀሚዎች ስጦታ እንዳይቀበል” ብለዉ በህዝብ ፊት በጥይት ተደብድበዉ የሞቱ ጅግና ናቸዉ። ወያኔ የእኚህን ጀግና ሰዉ ታሪክ ሰበብ እየፈጠረ የሚያፈርሰዉ እንደም የእሱ አሻራ ስላላረፈበት በሌላ በኩል ደግሞ ህዝብ ይህንን ሀዉልት በተመለከተ ቁጥር የሚማረዉ አልበገርም ባይነትንና አልገዛም የሚል እምቢተኝነትን ስለሆነ ነዉ። ለዚህ ነዉ ወያኔ እንኳን በቁም ላሉት ሞተዉ ላንቀላፉት ጀግኖቻችንም የማይተኛዉ። ወያኔን የመሰለ አገር በቀል ወራሪ ሀይልን ለአንዴና ለመጨረሻ እናጥፋ ሰንል እንደዚህ አይነቱን በማንነታችንና በታሪካችን ላይ የሚፈጸመዉን በደል ስር ከመስደዱና ትውልድን ከማጥፋቱ በፊት ለማስቆም ነዉ።
ወያኔ በተለመደ ቅጥፈቱ ሀውልቱ ተመልሶ ይመጣል እያለ የሚናገረው ህዝብን ለማዘናጋት እንጂ ከቶዉንም እውነቱን አይደለም፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ እንደዚህ አይነቱን አይን ያወጣ ቅጥፍት ሃያ አንድ አመት ሙሉ አይቷል። ስለዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን ቅጥፈታቸውን ተረድቶ በምንም ነገር ሳይታለል አባቶቹ አስቀምጠውለት የሄዱትን የታሪክ አሻራዎች የመጠበቅ ግዴታ አለበት። የነጻነት ታሪክ አሻራና ቅርስን እያፈረሱ የሚሰሩት ልማት ከቶ ጥፋት እንጂ ልማት አይደለም። ትላልቅና አጅግ ዉስብስብ ለሆኑ ችገሮች መፍትሄ ያለዉ የምህንድስና ሙያ አዲስ አበባን ያክል ትልቅ ከተማ ዉስጥ አንድ ሳይሆን በብዙ ሺ የሚቆጠሩ መንገዶችንና የባቡር ሀዲዶችን የታሪክ ቅርሶቻችንን በማይነካ መንግድ እንዲሰሩ ማድረግ ይችላል። የአቡነ ጴጥሮስ ሀዉልት የቆመዉ አቡኑ ያንን ታሪካዊ ንግግር ባደረጉበትና ፋሽስቶች በጥይት በደበደቧቸዉ ቦታ ላይ ነዉና የኢትዮጵያ ህዝብ በእሳቸዉ ሀዉልት ላይ የተነጣጠረዉን የወያኔ ጠመንጃ ማክሸፍ ግዴታ አለበት።
ህወአት/ወያኔ ውብ ታሪካዊ ቦታዎችን፣ መታሰቢያ ቅርሶቻችንን ከኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ ጋር የተያያዙ ናቸዉ ያላቸዉን ቦታዎች ሁሉ ከኢትዮጵያ ካርታ ላይ እየፋቀ የአምባገነኑን የመለስ ፎቶ፤ የአባ ጳዉሎስ ሀዉልትና የከሀዲ ጄኔራሎችን ምስል እያስቀመጠ ነዉ። በአጠቃላይ የወያኔ ዘረኞች እዉነተኛዉን የኢትዮጵያ ታሪክ በእነሱ የዉሸትና የፈጠራ ታሪክ እየተኩ ነዉ። ይህ የጥፋት ዘመቻቸዉ ስር ከሰደደና መጪዉን ትዉልድ በዚህ ጥፋታቸዉ እየበከሉ የሚያሰተምሩ ከሆነ ጥፋቱን ማረም እጅግ በጣም ይከብዳልና የኢትዮጵያ ህዝብ ነገ ዛሬ ሳይል ወያኔ በያዘው የጥፋት ዘመቻ ላይ ሆ! ብሎ በመዝመት ታሪካችንን ና ሀገራችንን ከወያኔ አምባገነኖች መንጋጋ ማስለቀቅ ወቅቱ የሚፈልገው ግድ ነው። ይህን ባለማድረጋችን ደግሞ የታሪክ ተጠያቂዎች ያደርገናል።
በመጨረሻም ወያኔዎች ሊረዱት የሚገባቸዉ አንድ ሀቅ ቢኖር ግዜና ትውልድ እንደሚፋረደቸውና የጀግናውና የታጋዩ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት በማፍረስ ሀውልቱን እንጂ እሳቸዉ የተሰዉለትንትን አላማ ከቶ ሊያፈርሱት እንደማይችሉ ነው። ይህ የሚያሳየን ገድለ-ታሪክ ታሪክን አምጦ ወልዶ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ በጀግነነት ገድል ተጽፎ፣ ተቀልሞና ተከትቦ መቀመጡን ነው፤ ከዚህ በተጨማሪ ወያኔዎች ኢትዮጵያ ዉስጥ ብቻ ሳይሆን በመላው አፍሪካ ለዘላለም ሲከበር የሚኖርን ትልቅ የጀግንነት ስራ፤ ሀውልትን በማፍረስ ማጥፋት አንደማይችሉ ሊረዱ ያገባል እንላለን። ይልቁኑ ሃውልቱን ለማጥፋት የሚቆፈረው ጉድጓድ የወያኔ ማንነት የመጨረሻ መቀበሪያ የሚሆንበት ግዜ ሩቅ አለመሆኑን እያንድንዱ የወያኔ አባልና ደጋፊ አበክሮ ሊገነዘበዉ ይገባል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

Ethiopian authorities continued to severely restrict basic rights of freedom of expression, association, and assembly. Hundreds of Ethiopians in 2011 were arbitrarily arrested and detained and remain at risk of torture and ill-treatment.
Attacks on political opposition and dissent persisted throughout 2011, with mass arrests of ethnic Oromo, including members of the Oromo political opposition in March, and a wider crackdown with arrests of journalists and opposition politicians from June to September 2011.
The restrictive Anti-Terrorism Proclamation (adopted in 2009) has been used to justify arrests of both journalists and members of the political opposition. In June 2011 the Ethiopian House of Federations officially proscribed two armed groups—the Ogaden National Liberation Front (ONLF) and the Oromo Liberation Front (OLF) and one opposition party, Ginbot 7—labeling them terrorist organizations.
Political Repression, Pretrial Detention, and Torture
In March 2011, authorities arrested more than 200 members and supporters of registered Oromo opposition parties—the Oromo Federal Democratic Movement (OFDM) and the Oromo People’s Congress (OPC)—during mass roundups. Those arbitrarily arrested and detained included former members of parliament, long-serving party officials, and candidates in the 2010 regional and parliamentary elections. They were publicly accused of being involved with the banned OLF; at least 89 have been charged with a variety of offenses, some relating to terrorism.
On August 27 Bekele Gerba, deputy chairman of OFDM; Olbana Lelisa, a spokesman for OPC; and seven other opposition party members were arrested on charges of involvement with the OLF. They were held in pre-trial detention at the Federal Police Crime Investigation Department, also known as Maekelawi, where torture is reportedly common. At least 20 other ethnic Oromo were arrested in this same sweep.
On September 8 popular actor Debebe Eshetu was arrested and accused of belonging to the banned opposition party Ginbot 7. The following week, on September 14, Andualem Aragie, vice-chairman of the opposition party Unity for Democracy and Justice (UDJ), two other active members of UDJ, and the general secretary of another opposition party, the Ethiopian National Democratic Party (ENDF), were arrested in Addis Ababa, the capital, on similar accusations.
Human Rights Watch continues to receive credible reports of arbitrary detention and serious abuses of civilians alleged to be members or supporters of ONLF. These civilians were being held in detention facilities in Ethiopia’s Somali region.
Long-term pre-trial detention without charge, often without access to counsel, is common, notably under the Anti-Terror law, which allows police to request additional investigation periods of 28 days each from a court before filing charges, for up to four months. Human Rights Watch is aware of at least 29 opposition party members, journalists, and an actor who at this writing were currently held in remand detention under the Anti-Terror law.
No independent domestic or international organization has access to all of Ethiopia's detention facilities; it is impossible to determine the number of political prisoners and others arbitrarily detained or their condition.
Freedom of Expression and Association
What little remains of the private independent media and foreign media faced further attacks and restrictions during 2011. Self-censorship is rampant. Journalists working for the few remaining “independent” domestic newspapers have faced regular harassment and threats. Several journalists were arbitrarily arrested and detained in 2011.
On June 19 and 21 respectively Woubshet Taye of Awramba Times and Reeyot Alemu of Feteh, journalists for two newspapers often critical of the government, were arrested, along with seven other individuals, including two ENDP members, and accused of conspiring to commit terrorist acts. After almost three months of detention, without access to their lawyers, the two were charged on September 6 of several counts of terrorism. Charges were also leveled against Elias Kifle, editor of the online Ethiopian Review, in absentia. One ENDP member, Zerihun Gebre-Egzabiher, was also charged.
On September 14, 2011, veteran journalist Eskinder Nega was arrested on charges of involvement with Ginbot 7. Eskinder, like Elias Kifle, was among the 121 opposition party members, journalists, and human rights activists arrested following the 2005 elections, and accused of treason and other related crimes, and among the 76 who were later convicted. He has faced ongoing harassment since his release and has been repeatedly denied a license to practice journalism.
Journalists working for foreign media have not been spared from these attacks. In September 2011 the Ethiopian correspondent of the Kenyan Daily Nation, Argaw Ashine, was forced to flee the country after he was named in an unedited WikiLeaks United States diplomatic cable regarding planned attacks, by the governmental Communication Affairs Office (GCAO), on journalists from the Addis Neger newspaper. The GCAO and Federal Police summoned Argaw for questioning regarding his sources within the GCAO. Addis Neger editors and journalists were forced to close their newspaper and flee the country in November 2009 after threats of arrest under the Anti-Terror law.
Independent reporting on the conflict-affected areas of the Somali region remains severely restricted. On July 1, 2011, two Swedish journalists who had entered Ethiopia in order to report on the situation were arrested. They were held without charge for two months in Jijiga and Addis Ababa before being charged on September 6 with terrorism. Their trial continued at this writing.

Restrictions on Human Rights Reporting
The restrictive Charities and Societies Proclamation, adopted in 2009, which prohibits organizations receiving more than 10 percent of their funding from abroad from carrying out human rights and governance work, continues to severely hamper basic rights monitoring and reporting activities. Two former leading rights organizations, the Ethiopian Women’s Lawyers Association (EWLA) and the Human Rights Council (HRCO, formerly EHRCO), have had to slash their budgets, staff, and operations. Their bank accounts, which the government arbitrarily froze in December 2009, remain frozen.
The government-affiliated Ethiopian Human Rights Commission lacks independence and is not yet compliant with the Paris Principles, which the United Nations General Assembly adopted in 1993 and which promote the independence of national human rights institutions.
On August 27, 2011, an Amnesty International delegation to Ethiopia was ordered to leave the country following a series of meetings with members of the political opposition; two of these members were arrested after their meeting with Amnesty International.
Discrimination in Government Services
In October 2010 Human Rights Watch published Development without Freedom: How Aid Underwrites Repression in Ethiopia, a report which documented discrimination in the administration of foreign donor-funded government services, including agricultural assistance, food-for-work programs, educational training opportunities, and civil-service reform programs. The report also showed how donor-funded facilities, such as schools and teacher training colleges, underwrite the indoctrination of civil servants and school children in political propaganda. Human Rights Watch’s research suggested that donors in the Development Assistance Group (DAG), including the US, Canada, the United Kingdom, and the European Union, were aware of such allegations, but were taking insufficient steps to investigate the misuse of their aid money.
DAG denied that aid was politicized, citing as evidence a UK Department for International Development-led report, “The Aid Management and Utilization Study,” which concluded that existing monitoring mechanisms would not detect politicization if it were occurring. That report also promised a second phase, a field investigation, which it said was crucial to establishing whether or not politicization was occurring on a broad scale. In April 2011 DAG told Human Rights Watch that this second phase, the field investigation, had been cancelled. A 2009 US diplomatic cable released by WikiLeaks said that the US embassy in Ethiopia was “keenly aware that foreign assistance … is vulnerable to politicization,” but that monitoring the problem, “risks putting the assistance programs themselves in jeopardy from a ruling party that has become confident that its vast patronage system is largely invulnerable.”
Key International Actors
International donor assistance continues to pour into Ethiopia, one of the world’s largest recipients of aid, but this has not resulted in greater international influence in ensuring government compliance with its human rights obligations. Conversely, donors appear to be reluctant to criticize the Ethiopian government’s human rights record so as not to endanger the continuity of their assistance programs.
Nonetheless, government spending remains hugely reliant (between 30 and 40 percent) on foreign assistance, and donors retain significant leverage that they could use to greater effect to insist on basic measures, such as the repeal or amendment of the Charities and Societies Proclamation and the Anti-Terrorism Proclamation, admission of UN special rapporteurs on human rights, the release of political prisoners, and better monitoring of foreign-funded programs to make sure they are not being used to bolster the ruling party.

Sunday, December 2, 2012


ኃላፊነቴን ከህዝቡ ጋር በአግባቡ እወጣለሁ – ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ሹመቱ ኢህአዴግ ያለበትን የፖለቲካ ሽኩቻ ለማስታገስ ያደረገው ነው የተሰጠው ሹመት በብቃት ላይ የተመሰረተ አይደለም ሹመቱ የቀድሞ ጠቅላይ ሚ/ር አሻራ አለበት (ተቃዋሚዎች) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከትናንት በስቲያ ያፀደቀውን የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት፣ የንግድ ሚኒስትርነት፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስትርነትና ሌሎች ሹመቶችን አስመልክቶ ሹመቱ በአግባቡና በሥርዓት ያልተሰጠና ህጋዊ ሥርዓት የሚጐድለው ነው ሲሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተናገሩ፡፡ ሹመቱ ህገመንግስቱን የሚጋፋና ከህግና ሥርዓት ውጪ የተሰጠ ነው ሲሉም ተችተውታል፡፡

በአንድ ድምፀ ተአቅቦና በሙሉ ድምጽ ድጋፍ በፀደቀው ሹመት መሠረት ሁለት ተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስትሮችም ተሹመዋል፡፡ ከትናንት በስቲያ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተከናወነው ሥነሥርዓት ሹመታቸው የፀደቀላቸው አቶ ሙክታር ከድር በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር እና ሪፎርም ክላስተር አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በምክትል ጠቅላይ ሚ/ር ማዕረግ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ አቶ ታደለ ጫኔ የንግድ ሚኒስቴር ሚኒስትር እና ዶ/ር ከስተብርሃን አድማሱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡ ብቸኛው የመድረክ ተወካይና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ በሹመቱ ወቅት ድምፀ ተአቅቦ አድርገዋል፡፡ አቶ ግርማ ድምፀ ተአቅቦ ያደረጉበትን ምክንያት ሲናገሩም፤ ሹመቱ ከመሰጠቱ በፊት ስለተሿሚዎቹ ለምክር ቤቱ አባላት መረጃ እንዳልደረሳቸው አመልክተው፤ ሹመቱ የተሰጠበት አሠራር ቀደም ሲል ተቃውሞአቸውን ሲያሰሙ በቆዩበት ህግ መሠረት በመሆኑና መዋቅሩ አስቀድሞ መጽደቅ ቢገባውም ባለመጽደቁ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

ፓርቲያቸው ምክር ቤቱ የሰጠው ሹመት ትክክል ነው ብሎ እንደማያምን የገለፁት አቶ ግርማ፤ በተለይ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ የተሰጠው ሹመት ህግና አሠራርን የተከተለና አግባብ የሆነ ነው ብሎ መቀበል እንደሚቸገሩ ተናግረዋል፡፡ ሹመቱ ኢህአዴግ ያለበትን የፖለቲካ ሽኩቻ ለማስታገስ ያቀረበው መፍትሄ ነው ያሉት አቶ ግርማ፤ ህጋዊ አሠራርን ያልተከተለና በብቃት ላይ ያልተመሰረተ ሹመት ነው ሲሉ ገልፀውታል፡፡ የኢዴፓ ሊቀመንበር አቶ ሙሼ ሰሙ በበኩላቸው፤ ፓርቲው እንደ ፓርቲ አቋም ለመያዝና መግለጫ ለማውጣት ገና አለመገናኘቱን ጠቁመው እንደግለሰብ ግን ሹመቱ ህጋዊ አሠራርን የተከተለ ነው ብሎ ማመን እንደማይችሉ ተናግረዋል፡፡ ይህ ሹመት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አሻራ ያለበትና ከዚህ ቀደም ይወራ የነበረውን ጉዳይ በይፋ ያረጋገጠ ሹመት ሆኖ እንደሚሰማቸውም ተናግረዋል፡፡ ሹመቱ የተሰጠበት አግባብ ህገመንግስታዊ ሥርዓቱን የተጋፋ ነው ያሉት አቶ ሙሼ፤ ይህንን ለማድረግ ከፈለጉም በቅድሚያ ህገመንግስቱን ማረም ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ኢህአዴግ ቀደም ሲል የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በሚሰሩት ደረጃ ለመሥራት አቅም የለንም የሚለውን ሃሳብ የሚያጠናክርና በራሳቸው አቅም ማስቀጠል አለመቻላቸውን አመላካች ነው ሲሉም አክለዋል፡፡ “በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥር በርካታ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮችን በመሾም የጠቅላይ ሚኒስትሩን ስልጣኖች ቀንሰው ለሌሎች ኃላፊነት መስጠት ምን ማለት እንደሆነ ግልጽ አይደለም፡፡ በሹመቱ ላይ ያለው ሁኔታ ግን ቀደም ሲል ሲወራ የቆየውን ጉዳይ ተግባራዊ ማድረግ ነው፤ ምንም አዲስ ነገር የለውም” ሲሉ ተናግረዋል – አቶ ሙሼ፡፡ በውጪ ጉዳይ ሚኒስትርነት የተሾሙት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ሹመቱን አስመልክቶ በስልክ በሰጡን አስተያየት፤ የተጣለባቸው ሃላፊነት እጅግ ከፍ ያለ መሆኑን ጠቁመው፤ ህዝብ እምነት አሳድሮ እስከመረጠኝ ድረስ ሃላፊነቴን በአግባቡ ለመወጣት ዝግጁ ነኝ ብለዋል፡፡ ለአመታት የሰሩበትን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መ/ቤትን አስመልክተው ሲናገሩም፤ ቀደም ሲል በተዘጋጁ መስመሮች በመጓዝ ህዝቡን በሚያሳትፍ መልኩ ሥራዎችን መሥራት ከተተኪው ሚኒስትር የሚጠበቅ ተግባር መሆኑንም ዶ/ር ቴዎድሮስ ጠቁመዋል