The Voice of Freedom

Freedom of Expression For All Ethiopian Peoples , NOW ! ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ለሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝቦች ፣ አሁኑኑ ! Free all Ethiopian Jornalist and Political Prisoners, Stop the Persecution of Independent Press in Ethiopia, We shall prevail! Freedom! Freedom! Freedom! FREEDOM, FREEDOM !!!

Gezahegn Abebe

https://eth-freedom.blogspot.com/
View my complete profile

Monday, December 12, 2016

ወያኔ የመከላከያ ሰራዊቱ ወደ አርበኞች ግንቦት 7 እየተቀላቀሉ መሆኑን አመነ ።

Desember 12,2016
(ዘርይሁን ሹመቴ)
የወያኔን አገዛዝ በመክዳት ወደ ትጥቅ ትግሉ እየተቀላቀሉ የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት ቁጥር እየጨመረ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ። በቅርቡ በሰሜን ጎንደር ለነጻነት እየተዋደቁ ያሉትን ጀግኖች የአማራ ተወላጆችን ለመጨረስ ወያኔ ከላካቸው ወታደሮች አብዛኞቹ ወደ አርበኞች ግንቦት 7 ግንባር መቀላቀላቸው ይታወቃል። በቆራጥነት ቤተሰባቸውን ጥለው በየጫካው የሽምቅ ውጊያ በማድረግ ወያኔን እያርበደበዱ ያሉትን የአማራ ታጋዮችን ትጥቅ ለማስፈታት የሚልካቸው ወታደሮች ከነሙሉ ትጥቃቸው ወያኔን እራሱን ለመውጋት ከህዝቡ ጎን ለመቆም ግንባሩን ተቀላቅለዋል።
አገዛዙ የአርበኞች ግንቦት 7 ሰርጎ ገቦች ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ ያዝከዎቸው ከማለት በስተቀር ከመከላከያ ሰራዊት እየከዱ አርበኞች ግንቦት 7ን ስለሚቀላቀሉ ሰራዊት መግለጫ ሲሰጥ አይሰማም። በብዛት ኤርትራ የሰለጠኑና የሰፈሩ ብሎ ወያኔ የሚፈርጃቸው የአርበኞች ግንቦት 7 ወታደሮች በተቃራኒው በመላ ኢትዮጵያ በተለያየ መልኩ በጥልቀት ገብተው ራስ ምታት እየሆኑበትና የነጻነት ትግሉን እዚያው አገር ውስጥ እያደረጉ እንደሚገኙ ወያኔ ራሱ ለመካድ አዳጋች ደረጃ ላይ ደርሷል። በቅርቡም በሰሜን ጎንደር ህዝቡን በማነሳሳት በማደራጀት እንዲሁም ወታደራዊ እርምጃ ሲወስዱ በቁጥጥር ስር አዋልኩዋቸው ባላቸው የአርበኞች ግንቦት 7 ና የኦነግ አባላት ላይ ክስ መስርቻለው በማለት አገዛዙ በርግጥም የትጥቅ ትግሉ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተደረገ እንደሆነ ማመን ችሏል።
በመከላከያ ሰራዊት ውስጥም ሳይቀር የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት ሰርገው ገብተውብኛል በማለት የተለያዩ ክሶችን አሁን አሁን እያቀረበ የሚገኘው የህውሃት አገዛዛ ከዚህ ቀደም ይህን በይፋ ለማመን ተቸግሮ እንደነበር ይታወቃል። የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በተደጋጋሚ ለመከላከያ ሰራዊቱ የወያኔ መጠቀሚያ ከመሆን የህዝብ አጋርነትን እንዲያሳይና ግንባሩን ተቀላቅሎ በአገዛዙ ላይ አፈ ሙዙን እንዲያዞር ያደረጉት ጥሪ በብዙ ለሚቆጠሩ ወታደሮች መክዳትና ወደ ነጻነት ጉዞው መቀላቀል አስተዋጾ አድርጋል።
አገዛዙ በአቃቢ ህጉ በኩል የአርበኞች ግንቦት 7 የአገር ውስጥ አባላት በተንቀሳቃሽ ስልክና በፌስቡክ በመጠቀም አዳዲስ አባላትን በደብረ ዘይትና በተለያዩ የመከላከያ ሠራዊት እየመለመሉ እንደሚገኙ ደርሸበታለው በማለት ባሳለፍነው አርብ ክስ መስርቷል። ከዚህ በተጨማሪም የአርበኞች ግንቦት 7 የአገር ውስጥ እንቅስቃሴ መረቡን በማስፋት በመረጃና ደኅንነት መስሪያ ቤትም ውስጥም ዘልቆ እንደገባ ክሱ ያመለክታል። በዚሁ እለት በቀረበው ችሎት ወያኔ ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር በመተባበር ሲሰሩ የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላትንም ወደ ክስ አቅርቢያለው ብሏል።በአጠቃላይ ከወያኔ ጋር የሚደረገው ትግል በርግጥም በኤርትራ ምድር ሳይሆን በኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑንና የህዝቡ እምቢተኛነት የነጻነት ታጋዮችን እንቅስቃሴ ወደ ፊት እየመራው እንደሆነ አገዛዙ በአቃቤ ህጉ ያቀረባቸው ክሶች ማመሳከሪያ ሆነዋል።
Posted by https://eth-freedom.blogspot.com/ at 8:29 PM No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Saturday, December 10, 2016

የአውሮጳ ህብረት አባል በሆኑት ክብርት አና ጎመስ ላይ ህወት የተቃውሞ ፊርማ ማሰባሰብ ጀመረ

Desember 10,2016
በምርጫ 97 ወቅት የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድንን በመምራት ኢትዮጵያ ቆይተው ከተመለሱ ወዲህ የህወሃት አገዛዝ በዘጎቹ ላይ የሚፈጽማቸውን የሰባአዊ መብት ጥሰቶች እየተከታተሉ በማጋለጥ  የታወቁትን  የአውሮጳ ህብረት ፓርላማ አባል ክብርት አና ጎመዝ በኢትዮጵያ ጉዳይ የሚያሰሙት ድምጽ እንዲያቆሙ ለመጠየቅ የህወሃት አገዛዝ በቅጥረኝነት ያሰማራቸው አባላቱና ደጋፊዎቹ የተቃውሞ ፊርማ ማሰባሰብ መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሎአል
የህወሃት የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ጋር በቅርበት እንደሚሠራ የሚታወቀው አይጋ ፎረም የተባለው ድረ ገጽ ላይ አባላትና ደጋፊዎች እንዲፈርሙት ተለጥፎ ያለው የተቃውሞ ፊርማ ደብዳቤ ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው  ክብርት አና ጎመስ ባለፈው ወር መጀመሪያ ሳምንት ላይ ብራስልስ በሚገኘው የአውሮጳ ፓርላማ ጽቤት ስብሰባ ላይ ተሳትፈው ወደ አገራቸው ሲመለሱ በህወሃት ደህንነቶች ተይዘው እስር ቤት የተወረወሩት ዶክተር መረራ ጉድናን ለማስፈታት ህብረቱ ጠንካራ አቋም በኢትዮጵያ ላይ እንዲወስድ የሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ አዘጋጀተዋል  ። ክብርት አና ጎመስ የአውሮጳ ህበረት በህወሃት መራሹ አገዛዝ ላይ ጠንካራ እርምጃ እንዲወሰድ ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ከማዘጋጀታቸው በተጨማሪ ለህብረቱ የውጪ ግንኙነት ሃላፊ ለሆኑት ለማዳም ፌደሪካ ሞርጋሪኒ ባለፈው ሳምንት በጻፉት ደብዳቤ ላ፤ ዶ/ር መረራ ጉዲና የታሠሩት በርሳቸው መሪነት የአውሮጳ ህበረት በኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚፈጸመው የሰባዊ መብት ጥሰት ለመስማትና አገራችን ውስጥ እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ እምቢተኝነት ወዴት እንደሚያመራ ለመገምገም  አዘጋጅቶት በነበረው ስብሰባ ላይ መሳተፍቸው እንደወንጀል ተቆጥሮ ነው ማለታቸው ህወሃትን ክፉኛ አስቆጥቶታል። ክብርት አና ጎመስ ባልደረባቸው ለሆኑት ኢጣሊያዊቷ የህብረቱ የውጪ ግንኙነት ሃላፊ በጻፉት ደብዳቤ  ዶ/ር መረራ ጉዲና በህወሃት አገዛዝ ሽብርተኛ ተብሎ ከተፈረጀውና ህብረቱ አዘጋጅቶት በነበረው በዚያ ስብሰባ ላይ ከተገኙት ሌላው እንግዳ የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፈሰር ብርሃኑ ነጋ ጋር ጎን ለጎ ተቀምጦ መታየታቸው ብቻ እንደወንጀለኛ እንዳስቆጠራቸው ይህም ኢትዮጵያ ወስጥ የዜጎች ነጻነትና ሃሳብን የመግለጽ መብት ምን ያህል የከፋ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አመልካች ነው ብለው መግለጻቸው ህወሃትንና ደጋፊዎቹን እጅግ ያናደደና የተቃውሞ ፊርማ እስከማሰባሰብ  ያደረሰ እንደሆነ በተቃውሞ ደብደቤው ላይ ተገልጾአ።
በዚህም የተነሳ ክብርት አና ጎመስ በኢትዮጵያ ጉዳይ ውስጥ እጃቸውን ከማስገባት እንዲቆጠቡ  ለመጠየቅ በህወሃት መሪነት የተጀመረው ፊሪማ የማሰባሰብ ዘመቻ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሚገኝባቸው አገሮች በሙሉ ውስጥ ለውስጥ እየተሰራጨ እንደሚገኝ ሆኖም በርካታ ትኩረት ለማግኘት ያልቻለና በራሱ በህወሃት አባላትና ደጋፊዎች ዘንድ ሳይቀር እንደ ትልቅ ተስፋ መቁረጥ እርምጃ እንደታየ ለዝግጅት ክፍላችን የደረሰ ከደረሰ መረጃ ለማወቅ ተችሎአል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በብድርና በተለያየ መንገድ ከአለም አቀፍ ህብረተሰብ የሚያገኘውን ገንዘብ ለገጽታ ግንባታ አገልግሎት በማዋል በጣም ውድ ገንዘብ በመክፈል ትላልቅ የሎቢ ተቋሞችን ቀጥሮ ሲያሰራ እንደኖረ ይታወቃል። ካለፈው እንድ መት ወዲህ በመላው አገሪቱ በተለይም በኦሮሚያ፤ በኮንሶና  በአማራ ክልሎች ተቃውሞን ለማፈን ሲል እየተወሰደ ባለው የሃይል እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጽሃን ዜጎች በግፍ መጨፍጨፋቸውና በሺዎች የሚቆጠሩት በጅምላ መታሠራቸው የአገዛዙን ፍጹም አምባገነንነትና አውሬነት ባህሪ ለአለም ህዝብ ያጋለጠ በመሆኑ  ተቀጥረው ይሠሩ የነበሩ የሎቢ ተቋሞች ሊያስተባብሉትና ሊሸፋፍኑለት ከሚችሉት በላይ እንደሆነባቸው በአሜሪካና በአውሮጳ ለህወሃት ተቀጥረው ከሚሠሩ እነዚሁ የሎቢ ድርጅቶች አካባቢ የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።
Posted by https://eth-freedom.blogspot.com/ at 10:46 PM No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Thursday, November 24, 2016

የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በወያኔ ጦር ላይ በተለያዩ ቦታዎች በተደጋጋሚ ጥቃት መፈፀሙን በመቀጠል ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ታወቀ፡፡

November 24,2016
November 24, 2016
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)
የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ነበልባል የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ህዳር 10 ቀን 2009 ዓ.ም ለሊት ጎንደር ዳንሻ ከተማ ልዩ ስሙ አዲስ አለም በተባለ ቦታ ሰፍሮ ከሚገኝ የወያኔ መከላከያ ሰራዊት ላይ በፈፀመው ድንገተኛ ማጥቃት ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ አጥቅቶ ተሰውሯል፡፡ በወሰደው ድንገተኛ የማጥቃት እርምጃም 15 የወያኔ ቅጥረኛ ወታደሮችን በመግደል ቁጥራቸው ያልታወቀ ደግሞ ማቁሰሉን አርበኛ ታጋይ ሪፖርተራችን ከስፍራው ባደረሰን ዘገባ አስታውቋል፡፡
የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ጥቃቱን በመቀጠል ህዳር 13 ቀን 2009 ዓ.ም በአብደራፊ ከተማ ዙሪያ በህወሓት መከላከያ ሰራዊት ላይ ተመሳሳይ የደፈጣ ጥቃት የሰነዘረ ሲሆን ባደረገው ሰፊ የማጥቃት እርምጃም 25 በመግደልና 17 በማቁሰል በቅጥረኛው የህወሓት ጦር ላይ ጠንካራ ክንዱን በማሳረፍ የበላይነትን ተጎናፅፎ የህወሓት ቅጥረኛ ወታደሮችን እንቅስቃሴ በመግታት መበታተን እንደቻለ ሪፖረተራችን አክሎ ገልጿል፡፡
ጀግናው የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት እየፈፀመ ያለውን ቆራጥ ተጋድሎ ጥቃቱ በሚፈፀምበት ቦታ ሁሉ ሙሉ በሙሉ የህዝብን ድጋፍ እያገኘ ሲሆን የቆመለትን አላማ ከግብ ለማድረስ ትልቅ ጉልበት እንደሆነው ለማወቅ ተችሏል፡፡ የኢትዮጵያ ትንሳኤ እስኪሆን ድረስም ጀግኖች የአርበኞች ግንቦት 7 ነበልባል ሰራዊት ወደፊት በመግፋት በተግባር የኢትዮጵያ አለኝታነታቸውን እያስመሰከሩ ይገኛሉ፡፡
ag7-nov-2016-1
ag7-nov-2016-2
ag7-nov-2016-3
ag7-nov-2016-4
Posted by https://eth-freedom.blogspot.com/ at 6:54 PM No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Sunday, November 20, 2016

አርበኞች ግንቦት 7 ከመቀሌ ከተላከ ኮማንድ ፖስት ግብረኃይል ጋር ተዋግቶ ድል ተጎናጸፈ

November 20,2016
arebegnoch

















ከ
ዚህ ቀጥሎ እንደወረደ የሚነበበው ዜና አርበኞች ግንቦት 7 ራድዮ ከፎቶግራፍ ጋር አስደግፎ የዘገበው ዘገባ ነው::

የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሰራዊት ህዳር 7 ቀን 2009 ዓ.ም በቃፍቲያ ሁመራ ልዩ ስሙ ማይነብሪ በተባለው ቦታ ከመቀሌ የተላከ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ግብረ ሀይል ጋር ባደረገው ውጊያ ከፍተኛ ድል ተጐናፅፏል።
ይህ ከመቀሌ የተንቀሳቀሰው የወያኔ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖስት ግብረ ሃይል ዋና ተልዕኮ የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊትን እንቅስቃሴ ለመግታት ታስቦ ሲሆን እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት በ56 መኪኖች አጓጉዞ በቃፍቲያ ሁመራ ልዩ ስሙ ማይነብሪ በተባለ ቦታ ቢያሰፍርም ለሀገራቸውና ህዝባቸው ሲሉ ውድ ህይወታቸውን ለመክፈል የማይሰስቱት የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በከፈቱት ድንገተኛ ማጥቃት 92 በመግደልና 65 በማቁሰል አንፀባራቂ ድል ማስመዝገባቸውን ከስፍራው የሚገኘው አርበኛ ታጋይ ሪፖርተራችን ባደረሰን ዘገባ ለማወቅ ተችሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት እንቅስቃሴን ለመግታት የተንቀሳቀሰውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ግብረ ሀይል ኮማንድ ፖስትን ይመሩ ከነበሩ መካከል 5 አዛዦች የተገደሉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል መቶ አለቃ ጣዕመ የሚባል እንደሚገኝበትም ታውቋል።
በተያያዘ ዜና የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሰራዊት ህዳር 8 ቀን 2009 ዓ.ም በቃፍቲያ ሁመራ ሩዋሳ አካባቢ ማይጐነጥ ልዩ ስሙ ማይቆማ በተባለው ቦታ ሰፍሮ ከሚገኘው የ24ኛ ክፍለ ጦር ጋር ባደረገው ውጊያ አንድ ብርጌድ ካምፕ ሙሉ ለሙሉ ከማውደሙም በተጨማሪ በወያኔ መከላከያ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ማድረሱን ከስፍራው የደረሰን የአርበኛ ታጋይ ሪፖርተራችን መረጃ ያመለክታል።
በዚሁ አካባቢ በተደረገው ውጊያ የወያኔው የ24ኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት ከአርበኞች ግንቦት 7 ጀግኖች የሚሰነዘርበትን ጥቃት መቋቋም ተስኖት እንደነበረ ለማወቅ ተችሏል።
በእለቱ በተደረገው ውጊያ 120 የወያኔ መከላከያ ሰራዊትን በመግደልና 80 በማቁሰል በጠላት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን በርካታ ቁጥር ያላቸው ከባድና ቀላል ተተኳሽ መሳሪያዎችን ከነመሰል ጥይቶቻቸው ጋር መማረካቸውንም ሪፖርተራችን ገልጿል።
በውጊያው እለት የቆሰሉ የወያኔ መከላከያ ሰራዊት ብዛት ቁጥር ስፍር የሌለው ከመሆኑ የተነሳ ሁመራ የሚገኘው ሆስፒታል በቁስለኞች መጥለቅለቁንና ከፍተኛ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸውን ደግሞ ወደ ጐንደር ሆስፒታል በመላክ ላይ መሆናቸውም ተገልጿል።
የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ሰራዊት ባደረገው ተከታታይ የማጥቃት ርምጃ የአካባቢው ነዋሪ ህብረተሰብ እጅጉን ከመደሰቱም በተጨማሪ ከትግሉ ጐን ለመሰለፍ ያላቸውን ቁርጠኝነት እየገለፁ እንደሚገኙም ታውቋል።
arebegnoch2
የወያኔ አገዛዝ ባለስልጣናትም በእነዚህ አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎችን አገዛዙን ለመፋለም ከአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ጋር እንዳይገናኙ አካባቢውን በመውረር ህብረተሰቡ ከቤቱ ወጥቶ እንዳይንቀሳቀስ በማድረግ ስራ ላይ ተጠምደው የሚገኙ ሲሆን፤የሞቱ የሰራዊቱ አባሎቻቸውንም ህዝቡ እንዳያይባቸው የራሳቸውን ሰዎች በመመልመል እንዲቀበሩ እያደረጉ መሆናቸውን ሪፖርተራችን አክሎ ገልጿል።
በደረሰባቸው የሰው ህይወትና የንብረት ኪሳራ እጅጉን የተደናገጡት የህወሀት አገዛዝ ባለስልጣናትም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖስት ግብረ ሀይልና በ24ኛ ክፍለ ጦር ላይ ከአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት የሚሰነዘረው ጥቃት ተጠናክሮ በመቀጠሉና ፋታ ሊሰጣቸው ባለመቻሉ በአካባቢው የጦር ሄሊኮፕተሮችን በማሰማራት አሰሳና ቅኝት ሲያደርጉ እንደነበረ ተገልጿል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት እስከአሁን ባደረጋቸው ውጊያዎችና ባስመዘገባቸው ድሎች በመደሰት በአካባቢው የሚገኙ የሚሊሸያ ታጣቂ ሀይሎች ከወንድሞቻችን ጋር ውጊያ አናደርግም በማለት በአገዛዙ ላይ እንዳመጹና ብዛት ያላቸው የሚሊሸያ አባላትም ከአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ጋር መሰለፋቸውን ከስፍራው የደረሰን የአርበኛ ታጋይ ሪፖርተራችን መረጃ ያስረዳል።
Posted by https://eth-freedom.blogspot.com/ at 10:07 AM No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Sunday, October 30, 2016

ኮንትራታቸውን የጨረሱ የወያኔ መከላከያ ሰራዊት አባላት አዲስ ኮንትራት እንዲፈርሙ የቀረበላቸውን ጥያቄ አንቀበልም አሉ።

Oktober 30, 2016

አክሊሉ ታደሰ
የወያኔ ሰራዊት አባላት የሆኑና የሰባት አመት ኮንትራታቸውን የጨረሱ አዲስ የሰባት አመት ኮንትራት እንዲፈርሙ የቀረበላቸውን ጥያቄ በአባላቱ ተቀባይነት ያለማግኘቱ ሲታወቅ በመከላከያም በኩል በወቅቱ ከሚገኝበት ሁኔታ ሳቢያ ሰራዊቱን ማሰናበት ያለመፈለጉ ታውቋል፡፡
የደረሰን መረጃ እንደሚያስረዳው የወያኔ መከላከያ ሰራዊት አባላት የሆኑ በ1999 ዓ/ምና 2001 ዓ/ም የተቀጠሩ የፈረሙት የሰባት አመት የስራ ኮንትራት በመጠናቀቁ ምክንያት ሁለተኛ ዙር የሰባት አመት ኮንትራት እንዲፈርሙ ደብዳቤ ቢደርሳቸውም በአብዛኛው የሰራዊቱ አባላት እስካሁን ለመፈረም ፈቃደኛ ያለመሆናቸው ይልቁንም ወደ የቤተሰባቸው መመለስ እንደሚፈልጉ ለማወቅ ተችሏል፡፡
መረጃው አያይዞም የመከላከያ ሰራዊቱ አመራር አካላት የምንገኘው በፈታኝ ወቅት ላይ ነው በሚል ኮንትራት የጨረሱትን የሰራዊቱ አባላት አዲሱን ኮንትራት እንዲፈርሙ ለማግባባት ቢሞክሩም እስከአሁን ያልተሳካላቸው መሆኑን ሲያስረዳ በአንፃሩም ሰራዊቱም በዚህ ወቅት ማሰናበት እንደማይችሉ ለአባላቱ የገለጹ መሆኑን ያስረዳል፡፡
በተጨማሪ ኮንትራቱን አንፈርምም ያሉት የሰራዊቱ አባላት በቆይታቸው ሊያገኙት የሚችሏቸውን ማንኛውም ጥቅማ ጥቅም በመከልከል አስገድዶ ለማስፈረም የተለመደው ሙከራ መደረጉ የማይቀር መሆኑን መረጃው ሲያስረዳ በአሁኑ ሰአት የወያኔ ስርአት የገጠመውን ፈተና በሰ ራዊት ሀይል ለመቋቋም በመጣር ላይ መሆኑና ተጨማሪ ሰራዊት መመልመል ያለመቻሉ ተጨማሪ ፈተና በሆነበት በአሁኑ ወቅት ኮንትራታቸው ን በጨረሱ የሰራዊቱ አባላትን በግዳጅ በስራ ለማቆየት እየተወሰደ ያለው እርምጃ ሊፈጥር የሚችለው ችግር ምልክቶች ከወዲሁ እየታዩ መሆኑንም ጨምሮ ለማወቅ ተችሏል
Posted by https://eth-freedom.blogspot.com/ at 7:00 PM No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ያደረጉት ጥሪ በመከላከያ ሰራዊቱ ዘንድ ከፍተኛ ተደማጭነትን እያገኘ መምጣቱ ታወቀ!

ናትናኤል ኃይለማርያም
Oktober 30,2016

የአርበኞች ግንቦት ሰባትሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሀኑ  ለመከላከያ ሰራዊት አባላት፣የፌደራለ እና የክልል ፖሊስ አባላት፤ለአጋዚ ልዩ ጦር አባላት እና ለሌሎች ስርአቱ ታጣቂዎች ያደረጉት  ጥሪ  በሰራዊቱ ዉስጥ ከፍተኛ መነጋገሪያ  ከመሆኑም በተጨማሪ ሰራዊቱ ከህዝብ ጋር ለመቆም የመጨረሻ ዉሳኔ ላይ እንዲደርስ ያደረገዉ ጥሪ ነዉ ሲሉ እነዚሁ ምንጮች ጠቅሰዋል።የተደረገዉን ጥሪ መቀበላቸዉን ለማመላከት ሀሳባቸዉን የገለጹት የሰራዊቱ አባላት እንዳሉት “ መከላከያዉ የህዝብ ሳይሆን የህዉሀት ቡድን አገልጋይ እየሆነ መምጣቱን ሙሉ በሙሉ ያወቁበት ደረጃ ላይ መድረሳቸዉን እና ሊቀመንበሩ እንዳሉት ሰራዊቱ የቁም እስረኛ ሲሆን በተለይ ህዝባዊ እምቢተኝነቱ ከተጀመረ ጀምሮ ምን እንደሚያደርግ እና ወዴት እንደሚሄድ የጠራ አቅጣጫ ባለማግኘቱ እና ባለበት ከፍተኛ ጫና የተነሳ አማራጭ በማጣት በሰራዊቱ ዉስጥ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

አክለዉም በአሁኑ ሰአት አዛዦቻቸዉ ድንጋጤ ዉስጥ ከመሆናቸዉ የተነሳ በሰራዊቱ ላይ ያለዉ ቁጥጥር እና ማስጠንቀቂያ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን እንዲሁም ከአንድ ብሄር የሆኑ አባላት ባንድ ላይ ለግዳጅም ሆነ ለስምሪት እንደማይመደቡና በግል ህይወታቸዉ ዉስጥ ስለላን እያካሄዱ ነጻነታቸዉን ፍጹም እንደነጠቋቸዉም ገልጸዋል፡፤በዚህም ምክንያት ከሰራዊቱ መካከል ያሉ አንዳንድ አድር ባይ አባላትን ሳይቀር የሕዉሐት ገደብ ያለፈ ጥርጥር ወደተቃዋሚነት ስለለወጣቸዉ በአሁኑ ሰአት በጥቂት ቁጥር ከሚቆጠሩ የግል ሰዎቻቸዉ በቀር ሰራዊቱ ልቡ ከህዝብ ጎን ሆኗል ብለዋል፡፤  በየጊዜዉ ለግዳጅ ሲወጡ ወደነጻነት ታጋዮች ከነትጥቃቸዉ የሚቀላቀሉ እና በቡድን በመደራጀት በየጫካዉ የሚመሸጉ የሰራዊት አባላት ቁጥር ከቀን ወደቀን እየጨመረ መምጣቱንም አመልክተዋል።

ፕሮፈሰር  ብርሀኑ ነጋ ለሰራዊቱ ያደረጉትን  ጥሪ በርካታ ሰዎች ለዉጥ የሚያመጣ ጥሪ መሆኑን በመግለጽ እነሱን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ መከላከያ ሰራዊቱ ወገኑ ላይ መተኮስ እንዲያቆም እና የመሳሪያ ነጠቃን እና በ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሰበብ የሚደረግባቸዉን የጅምላ አፈሳ እንዲሁም ግድያ በመቃወም ወደጫካ ከገቡ ወጣቶች እና አርሶ አደሮች እንዲቀላቀል ጥሪ አቅርበዉ፤ ከሳምንታት በፊት በፍኖተ ሰላም ከተማ 18 የመከላከያ ሰራዊቶች እና አራት ያጋዚ አባላት ሰራዊቱን ከድተዉ መዉጣታቸዉን አስታዉሰዋል።በተለይ በአማራ ክልል አገዛዙ በስፋት ለማከናወን አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ያለበትን የመሳሪያ  ነጠቃ ሽሽት ወደየጫካዎች በመግባት ላይ ያለዉ ህብረተሰብ እየጨመረ መምጣቱን እና የኮማንድ ፖስት አባላት ወጣቶችን ያለምንም ምክንያት ስለሚያስሩዋቸዉ በፍኖተ ሰላም በከተማዋ ዉስጥ አዛዉንቶች፤ሴቶች እና ህጻናት ብቻ እየቀሩ እንደሆነ ገልጸዋል።

በተያያዘ ዜናም በባህር ዳር ከተማ  ከስድስት ሳምንት በፊት ወቶ የነበረዉና መመዘኛዉ ከ10ኛ ክፍል በላይ የነበረዉ የመከላከያ ምዝገባ ፤ተመዝጋቢ በማጣቱ ምክንያት ማስታወቂያዉ ከወጣ ከሁለት ሳምንት በሗላ መስፈርቱ ወደ 6ተኛ ክፍል ዝቅ ብሎም ባለመሳካቱ በአሁኑ ሰአት ወጣቶች ወደ መከላከያ ቢገቡ ጥቅማጥቅሞችን እንደሚያገኙ ዉስጥ ዉስጡን በቅስቀሳ መልክ እየተወራ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ይህ በእንዲ እንዳለ የክልሉ አየር መንገድ ለአዉሮፕላን አብራሪነት እና ለቴክኒሺያንነት የቅጥር ማስታወቂያ ማዉጣቱን ተከትሎ ምናልባት በስራ አጥነት ሲሰቃይ የከረመዉን ወጣት በዚ መልክ በመመዝገብ ወደመከላከያ ስለጠና ሊወስዱት ይችላሉ የሚል ስጋት እንዳላቸዉም ጠቁመዋል። የህዋት መንግስት ለመከላከያ  እና ለፖሊስ አባላት መላቀቂያም ሆነ ፈቃድ መጠየቅ እንደማይቻል ቢያስተላልፍም እየከዱ እና እየጠፉ በሚለቁ አባላት ምክንያት አለመተማመን የመጣዉን የሰራዊቱን ቁጥር ለመጨመር በሰበብ አስባቡ በቁጥጥር ስር ያዋላቸዉን ወጣቶች በማባባል እና በማስገደድ ወደ ስልጠና ለማስገባት ሙከራ እያረገ ይገኛል ሲሉም ተደማጠዋል።

ከአመት በፊት ጀምሮ ሰራዊቱን እየለቀቁ የሚሄዱ አባላት ቁጥር  በተለይ ህዝባዊ ትግሉ ከተጀመረ በሁዋላ በመጨመሩ፤የህዋት መንግስት  በየክልሉ የመከላከያ  ሰራዊትነት ምዝገባን ለማካሄድ ከጥሩ የደሞዝ ክፍያ ጋር ጥሪ ቢያደርግም የሚመዘገብለት ማጣቱ በሌሎች አስገዳጅ መንገዶች ወጣቶችን በማታለል በግዳጅ ወደ መከላከያ ያስገባበት ሁኔታ መኖሩን ሲዘገብ መቆየቱ ይታወሳል።

Posted by https://eth-freedom.blogspot.com/ at 5:07 PM No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Saturday, October 15, 2016

የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊቶች ከታጣቂው ገበሬ ጋር ጥምረት ፈጥረው የወያኔን ሰራዊት ድባቅ እየመቱት ነው።

Oktober 15,2016
የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊቶች ከታጣቂው ጀግና ገበሬ ጋር ጥምረት ፈጥረው የወያኔን ሰራዊት ግንባር ግንባሩን በማለት መቶ ሰላሳ አምስ ለ 11 እየመሩት ነው ።
___________•••••••••••••___________••••••••••••__________\\\
#ETHIOPIA-revolution : ህውሀት በሰሜን አርማጭሆ የዘር ማጥፋቱን አጠናክሮ ቀጥላል ። በሰሜን ጎንደር አርማጭሆ የሚገኙ ወረዳዎች የጦርነ ቀጠና ሆነዋል ። ጦርነቱ ዛሬም እንደቀጠለ ሲሆን የአማራ ጀግና ገበሬዎች በየአቅጣጫው የህውሀትን ቅጥር ወታደር ትንፋሽ አሳጥተውታል ። ጫካዎች በሙት ወያኔያውያን አስከሬኖች ጠረናቸውን መቀየር ጀምረዋል የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊቶች በታች አርማጭሆ ከገበሬው ጋር በመጣመር እስካፍንጫው የታጠቀውን የወያኔ ጦር መፈናፈኛ አሳጥተው ባልተፈጠርኩ እያሰኙት ነው ። የወያኔ መንግስት አሉ የተባሉትን የሜካናይዝድ ብረት ለበስ ጦሮች ዛሬ በአርማጭሆ ህዝብ ላይ አዝምቶ ከ 40 በላይ ንፁሀን አማራዎችን ሒወት አስቀጥፋል ። 1c71e132-0edb-4537-8304-4dec8194fe06
ይህውሀት ወታደር ያገኙትን ሁሉ በመግደል ላይ ሲሆኑ በታች አርማጭሆ ቆላ ደባ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ውጊያ 11 የአርበኞች ግንቦት 7 እና 9 የአማራ ጀግና ገበሬዎች መስዋእትነት ሲከፍሉ በአንፃሩ ከጠላት የወያኔ ጦር 135 ወታደሮች ሲገደሉ 47 ደሞ ቀላልና ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል ።
በመሆኑም በአሁን ሰአት መስዋእትነት እየከፈሉ የሚገኙት ጀግኖች ወንድሞቻችን ደቡብ ጎንደር ፣ አለፉ ፣ ዳባት ፣ ወገራ ፣ ደባርቅ ፣ ደንቢያ ፣ በለሳ ፣ እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ለሚገኙ ወገኖች ትግሉን በአንድነት እንድትቀላቀሉ ጥሪ አስተላልፈዋል ።
ድል ለአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት እና
ለጭቁኑ የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ
ሞት ለባምዳው ወያኔና ለአቃጣሪ ካድሬዎቹ
Posted by https://eth-freedom.blogspot.com/ at 10:25 AM No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Tuesday, October 11, 2016

የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት እየታደኑ መታሰር ጀመሩ

Oktober 11,2016
አሁን በደረሰን ዜና መሰረት የሰማያዊ ፓርቲ አመራር የሆኑት እንጂነር ይልቃል ጌትነት  ፣ ብሌን መስፍን ፣ወረታው ዋሴ ፣ወይንሸት ሞላ እና ሌሎችም ስም ዝርዝራቸው ያልተጠቅቀሱ አባሎች መታሰራቸውን ምንጮቻችን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መስሪያቤት ከሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ቅርንጫፍ ገልጸዋል ። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የፖሊስ አባላቶች በሌሎችም ዜጎጅ እና የፖለቲካ እንቅስቃሴ በሚያደርጉ ግለሰቦች ላይ እንዲሁም ፣መንግስትን ከሃገርቤት ሆኖ በፌስቡክ እና በሌሎች መገናኛ ብዙሃን የሚኮንኑ ጽሁፎችን የሚያወጡ ወጣቶችን አድኖ ለማሰር ደብዳቤ ከክፍተኛ ባለስልጣናቶች እንደተላከ እና ያንን ተግባራዊ ለማድረግ ከ72 ሰአታት እስከ 315 ሰአታት እንደተሰጣቸው ጠቁመዋል ።yiliqal
ይህንን ለማድረግ የእያንዳንዱን የፖለቲካልም ሆነ የሌሎች አባል የሆኑ ዜጎችን የሚሰሩበትን መስሪያቤትም ሆነ ፣ስራዎቻቸውን አጣርተው ቢጨርሱም ፣እነሱን ለማፈን የሚንቀሳቀሱት አባላቶች ግን የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የፖሊስ ኮሚሽን ታማኝ የሆኑ ሰራዊቶች ብቻ ናቸው ሲኡ አትተዋ።
በተለይም በዛሬው እለት የጀርመኗ ቻንስለር አንጌላ ምራክል በሃገሪቱ ላይ ጉብኝት እሚያደርጉበት ወቅት እንዲህ ማድረጋቸው የአምባገነንታቸው ምልክት ነው ሲሉ ፣የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላቶች ገልጸዋል ። በሃገር ውስጥ በመሆን ብቸኛ የፖለቲካ ትግል የሚያደርገው እና ጠንካራ የፖለቲካ ፓርቲ ተብሎ የተሰየመው እንደዚሁም በወጣት አመራር እና ወጣት ሃይሎች የተሞላው ይሄው የሰማያዊ ፓርቲ ጥቃት በተቃዋሚዎች እና በገዥው ፓርቲ ዱላ ሲሰነዘርበት የቆየ ጠንካራ ፓርቲ ነው ሲሉም አክለው እነዚሁ ፖሊስ አባላቶች ገልጸዋል።
ማለዳ ታይምስ
Posted by https://eth-freedom.blogspot.com/ at 9:03 PM No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

በኢትዮጵያ እስረኞች አጥንትን ቀስ በቀስ በሚያፈርስ መርዝ እየተጠቁ መሆኑን ታውቀ

Oktober 11,2016
“ህወሃት በእስረኞች ላይ አጥንት የሚያመነምን መርዝ ይጠቀማል” እማኝ
"የባዮሎጂካል መሣሪያ ጥቃት ነው፤ ቤተሰብ ለልጆቻችሁ ድረሱ"
bio-bone

ከጥቂት ዓመታት በፊት የግንቦት ሰባት መሪዎች እና አባላት መታሰራቸው ይታወሳል። ብዙዎቹ ቃሊቲ የሚገኘው እስር ቤት ነበሩ። በእስር ቤት እያሉ በደረሰባቸው ያልታወቀ ሕመም ምክኒያት ሕይወታቸውን ያጡ መሪዎችም ነበሩ።ታዲያ አንዴ ከሜክሲኮ ወደ ሃያሁለት በታክሲ ተሳፍሬ ስሔድ በግምት የሃያ ዓመት ዕድሜ ያለው ልጅ ታክሲው ውስጥ ገብቶ አጠገቤ ተቀመጠ።
ታክሲው ሞልቶ መሔድ ሲጀምርም ወንድሜ ይቅርታህን የታክሲ ትከፍልልኛለህ ብሎ ጠየቀኝ። ዞር ብዬ ያየሁት ይህን ሲል ነበር። ድንጋጤ እና መሸማቀቅ ይነበብበት ነበር።ልቤ በጣም አዘነለት። ምን ሆነህ ነው? ከዬት ነው የምትሔደው፤ወዴት ነው የምትሔደው ብዬ ጠየኩት። እርሱም ከቃሊቲ እስርቤት ዛሬ መለቀቄ ነው አለ። ለምን ታሰርክ እንዴትስ ተለቀቅህ ስለው የቦሌ ሁለተኛ ደረጃ  ት/ቤት ተማሪ እንደ ነበረ እና ከመንገድ አፍሰው ወደ እስር ቤት እንደጣሉት ነገረኝ። የግንቦት ሰባት አባል እና ደጋፊ ናችሁ ብለው ቀን ከለሊት ሲገርፉን፤ ሲያስርቡን፤ መዓት መከራ ደርሶብናል፤ እንደምታዬው አእምሮዬ ራሱ ልክ አይደለም። ነገርግን በጣም ጤነኛ ልጅ ነበርኩ ብልህ አታምነኝም፤ ድሮም ትንሽ እብድ ነገር ነበርክ ብለህ ብታስብ አይገርመኝም አለ።
ፍርድቤት የሚባል ነገር አይተን አናውቅም።
መጀመሪያ ላይ ቤተሰብ እንዲጠይቀን ተፈቅዶላቸው ይጠይቁን የነበረ ሲሆን በኋላ ግን ተከለከሉ። ቤተሰቦቼን በአይኔ ካየሁ ሁለት ዓመት ሊሆነኝ ነው አለ። ከዚያም ወዲያው ስለ ራሱ ትቶ ሁላችንም ስለምናውቃቸው እና በግንቦት ሰባት ሰበብ እስርቤት ተጥለው ስለ ነበሩ መሪዎች ይነግረኝ ጀመር። እነ አቶ እከሌ እኛ ጋ ነው ታስረው የነበሩት። እንላላካቸውም ነበር። ምንም እንኳን እነርሱ እንደ እኛ ወደ ውጪ ብዙውን ግዜ እንዲወጡ ባይፈቀድላቸውም ፀሐይ እንዲሞቁ በሚያወጡዋቸው ሰዓት እየተላላክን የሚፈልጉትን እንገዛላቸው ነበር። ከቆይታ በኋላ እነ አቶ እንትናን እና አቶ እንትናን ከሌሎች ለይተው ሌላ ክፍል ውስጥ አሰሯቸው። በኋላም አይናችን እያየ ሰውነታቸው መፈራረስ ጀመረ። አፍንጫቸው፤ ጆሮዋቸው፤ አይናቸው ጣታቸው የስጋ ደዌ እንደያዘው ሰው ይፈራርስ ጀመር። አንድ ቀን ሊልኩኝ ሲጠሩኝ በድፍረት ምን ሆናችሁ ብዬ ስጠይቅእንደ ፍሊት ያለ መርዝ እየረጯቸው መሆኑን ነገሩኝ። መድሃኒቱንም እድሜ ለቻይና እናንተን የማሰናበቻ ቀላል መንገድ ተገኘ እያሉ ይፎክሩብናል፤ ይስቁብናል፤ የውሸታቸውን ሆስፒታል ይወስዱናል። ለቤተሰባችን ታመዋል ብለው ይነግራሉ ብለው ነገሩኝ አለ።
ከዚያስ በኋላ ስለው ቀስ በቀስ መንቀሳቀስ የማይችሉበት ደረጃ ላይ ደረሱ። በሚያስጠላ ሁኔታ ሰውነታቸው እየፈራረሰ ስለነበረ መሸፋፈን ጀመሩ። መጀመሪያ ወደዚያ ክፍል ከገቡት መካከልም እነ አቶ እንትና ሞቱ። ታመው ሞቱ ተብሎ ሲነገር ሰማን አለ።
ቤተሰብ እንዳያያችሁ ለምን ተከለከለ ብዬ ስጠይቀው፤ ምክንያቱን አላወቅንም ነበረ። በኋላ ግን ቤተሰባችን እንዳያዬን ከከለከሉ በኋላ ምግብ ያመጡልን ጀመረ አለ። ምግባቸውን መብላት ስለቀፈፈን የበላን እያስመሰልን እንደፋ ነበረ፤ ወደ ውጪ የመውጣት እድል ስናገኝም የሌሎች እስረኞችን ትራፊ እንበላ ነበር።ከቆይታ በኋላ ግን ምግቡን እንድንበላ አስገድደው እንቢ ስንል የሆነ መርፌ ወጉን። ቀስ በቀስ ሰውነታችን እየደከመ ሔደ፤ ቀስ በቀስ አእምሯችንም እየጨለመ ሲሔድ ይታወቀን ጀመር።
አንዳንዶቹ ልጆች ከሌሎቻችን በበለጠ መልኩ እንደ እብድ የለየላቸው ሆኑ። ታመው ነው እያሉ ሆስፒታል ይወስዷቸዋል። የአእምሮ ጭንቀት ነው እያሉ የስነልቦና ጠበብት መጥተው እንዲጎበኟቸው ያደርጉ ነበር። ከዚያ አውጥተው መንገድ ላይ ይጥሏቸዋል። ስንቶቹን ቤተሰብ እንዳገኛቸው እግዚአብሔር ብቻ ያውቃል አለኝ።
ሰፈሩን ያውቅ እንደሆነ ስጠይቀው በጣም ደስ አለው። አዲሳባ ሃያሁለት ተወልጄ ያደኩ መሆኑን እና ቦሌ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እንደነበርኩ ነግሬህ ቤቴን እንደማውቅ ስትጠይቀኝ ችግሬ በጣም ገብቶሃል ማለት ነው አለኝ። እስከ ቤተሰቡ ቤትም ሸኘሁት። ያ ልጅ ምን ላይ እንደደረሰ አላውቅም። ነገርግን እግዚአብሔር በጥበቡ ካልደረሰለት በስተቀር በሕይወት አለ ብዬ አልገምትም።
ይህ ነገር ወደ አእምሮዬ የመጣው ትላንት የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮን ዜና ስከታተል አንድ ብሔሩ ኦሮሞ የሆነ ኮማንደር በሰበታ የታሰሩ ልጆችን በተመለከተ የአጋዚ አዛዦች ስብሰባ ጠርተውን ለታሰሩት ልጆች ከምግብ ጋር መርዝ እንድንሰጣቸው መመሪያ ተላልፎልናል ብለው በመቆርቆር ሲናገሩ ስሰማ ነው። ከምንምግዜ በላይ አሁን አደጋ ላይ መሆናችን አሳሰበኝ። በየእስርቤት የታጎሩ የኦሮሞ እና የአማራ ልጆች እጣ ፈንታ ይሔው የተባለው መርዝ መሆኑ እረፍት ነሳኝ።
አሁን ሊበሉን ተነሱ ማለት ነው። አሁን ቤተሰብ ለልጆቹ መድረስ ይኖርበታል።ልጆቹ በእጁ እንዲገቡ እስኪያደርግ ድረስ ቤተሰብ መተኛት የለበትም። ይህ እንዲሆን ደግሞ ቤተሰብ ሚስጥሩን መረዳት ይኖርበታል።
ይህ ዜና እንዲሰራጭ ማድረግ አንዱ የመከላከያ መንገድ ሊሆን ስለሚችል እባካችሁ ለዚህ ጉዳይ ትኩረት በመስጠት ዘገባችሁን አጠናክሩ።
ወደ ሕዝቡ ሊደርስ በሚችልበት በማንኛውም መንገድ ይህ ዜና ይሰራጭ። እውነት መሆኑን ማመን ቢያቅታችሁም እንኳን በማሰራጨታችሁ የምትጎዱት ነገር ግን የለም።
(ለደህንነታቸው ስንል ይህንን መረጃ የላኩልን ማንነት ከማውጣት ተቆጥበናል፡፡ ፎቶው ለማሳያነት የተወሰደ ነው)
Posted by https://eth-freedom.blogspot.com/ at 8:57 PM No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

German leader calls for Ethiopia to open up politics after unrest

Oktober 11,2016
ADDIS ABABA, Oct 11 (Reuters) – German Chancellor Angela Merkel told Ethiopia on Tuesday to open up its politics and ensure police do not use heavy-handed tactics against protesters, after more than a year of unrest that rights groups say has led to about 500 deaths.
German Chancellor Angela Merkel told Ethiopia on Tuesday to open up its politics
Merkel, who spoke at a news conference with Prime Minister Hailemariam Desalegn, arrived in Ethiopia after a fresh flare-up near the capital of the clashes that have cast a shadow over a nation with one of Africa’s fastest-growing economies.
The violence prompted the government to declare a nationwide state of emergency on Sunday. It says the death toll cited by rights groups is exaggerated and blames the wave of violence on “armed gangs” backed by foreigners.
Western states, which are among the biggest donors to what is still a poor nation, want their companies to win deals in Ethiopia but have become increasingly concerned by the government’s authoritarian approach to development.
“I made the case that you should have open talks with people who have problems,” Merkel told Hailemariam, adding that police should respond proportionately to protests.
Last week, protesters ransacked or torched about a dozen mostly foreign-owned factories, flower farms and other sites, accusing the government of building on seized land and stifling opposition.
Opponents blamed police for provoking a stampede at a festival in Oromiya that killed at least 55 people on Oct. 2.
“In a democracy there always needs to be an opposition that has a voice – in the best case in parliament,” Merkel added.
Opposition parties failed to win a single seat in parliament in the 2015 election, accusing the government of rigging the vote – charges which it denies. There was just one opposition lawmaker in the previous assembly.
“The government is not using extreme violence. If it happened, we will investigate the units involved,” the prime minister responded.
DEMAND FOR DIALOGUE
Addressing parliament the day before Merkel arrived, Ethiopia’s president called for an amendment to the election law to allow “alternative voices” to be heard – an offer that senior opposition figure Merera Gudina said was “too little, too late”.
Merera, chairman of the Oromo Federalist Congress, from a region where protests have raged, said Merkel should push for the release of political prisoners and a national dialogue.
The government denies it detains people for their politics.
In another show of German discontent, a diplomat said Addis Ababa had proposed that Merkel address parliament, but Berlin refused because it lacked any opposition members.
The diplomat, who asked not to be named, said the message being sent was that there was “no business as usual”.
The international community has praised Ethiopia for its economic achievements and development strategy. Under this, healthcare and other types of social support have spread across a country where most people rely on subsistence farming that has been hit by severe drought in the past two years or more.
A nation still renowned in the West for a devastating 1984 famine exacerbated by the policies of the then Marxist government, Ethiopia has been one of Africa’s fastest-expanding economies for the past 15 years of so. In 2015, growth was 10 percent.
But the lack of public space for criticism has risen up the agenda for Western powers. U.S. President Barack Obama told his Ethiopian hosts in Addis Ababa last year that greater political openness would “strengthen rather than inhibit” development.
The government said at the time it ensured political freedoms but differed over the pace of reforms that Washington wanted.
Till now, Chinese firms and financing have been a major driver of growth, building high-rise towers and a metro system in Addis Abba, and constructing a new railway that links the capital of the land-locked nation to Djibouti port.
Western investors have also secured deals. Britain’s Diageo and Heineken of the Netherlands have bought breweries, Dutch and Belgian firms run flower farms and companies such as Hennes and Mauritz (H&M) are starting to source clothes from Ethiopian plants.
Merkel also visited the headquarters of the African Union, which are in Addis Ababa. She called for the body to try to solve the conflict in Libya and also urged African states to increase efforts to fight Islamist militants.

Posted by https://eth-freedom.blogspot.com/ at 8:16 PM No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Saturday, October 8, 2016

የትግራይ ተወላጆች በሙሉ ከቢሾፍቱ ተጭነው ተወሰዱ

Oktober 8,2016
ክንፉ አሰፋ(ጋዜጠኛ)
በደብረዘይት (ቢሾፍቱ) ይኖሩ የነበሩ የትግራይ ተወላጆች ሙሉ በሙሉ ከተማዋን ለቀው መውጣታቸውን በስልክ ካነጋገርናቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ማረጋገጥ ችለናል።
የትግራይ ተወላጆቹ ከተማዋን ለቅቀው የወጡት በቢሾፍቱ የኢሬቻ በዓል የሰዎች ሕይወት መጥፋቱን ተከትሎ የአካባቢው ሕዝብ ከጫፍ እስከጫፍ ነቅሎ በወውጣት እያካሀደ ባለው ሕዝባዊ አመጽ ሊመጣ ካለው አደጋ ለማምለጥ ነው። ህወሃት በዜጎች ላይ እየፈጸመ ያለውን ግድያ በከተማዋ ያሉ ሁሉ ሲቃወም የትግራይ ተወላጆች ግን ዝም ማለታቸው ሕዝቡን በእጅጉ እንዳስቆጣው ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
የትግራይ ተወላጆቹ ሃብት ንብረታቸውን እየጣሉ ከተማዋን ለቅቀው ወዴት እንደሄዱ የታወቀ ነገር የለም።
ላለፉት አራት ቀናት በደብረዘይት እንደ አብዛኞቹ ከተሞች የንግድ እና የስራ እንቅስቃሴ ቆሟል። ሱቆች ተዘግተዋል፣ ሕዝብም ከቤቱ አይወጣም። አልፎ አልፎ የከባድ መሳርያ ድምጽ የሚሰማ ሲሆን መንግስታዊ ተቋማት እና ከህወሃት/ኦህዴድ ጋር ንክኪ ያላቸው ተቋማት ወድመዋል።
በናዝሬት መግቢያ የምትገኘው ዱላላ ማርያም ወረዳ የህወሃት/ኦህዴድ ንብረቶች እና ጽ/ቤቶች ወድመዋል። ሊበን ጭቆላ ወረዳ አመራሩ ተነስቶ ወረዳው በሕዝብ እየተመራ ይገኛል። ወንጂ የስኳር ፋብሪካው ብቻ ሳይሆን አገዳውም ሙሉ በሙሉ መቃጠሉን ከስፍራው ያነጋገርናቸው እማኞች አረጋግጠዋል።
ከዱከም አንስቶ እስከ አገረማርያም የሚወስደው የጦር ቀጠና በመምሰሉ ምንም አይነት ተሽከርካሪ ላለፉት 6 ቀናት እንዳላዩ እማኞች በስልክ ተናግረዋል። ከደቡብ መስመር አንጻራዊ ሰላም የሚታየው በአዋሳ ከተማ ብቻ ነው።
በዲላ እና ወንዶገነት የህወሃት ባልሰልጣናት መኖርያ ቤቶች አጋይቶባቸዋል። ባለስልጣናቱ እና ከድሬዎቹ በሙሉ ከተማዎቹን እየለቀቁ ወደ አዋሳ ከተማ ገብተዋል።
በዲላ መስጊዶች እና አብያተ-ክርስትያናት በዛሬው እለት ባልታወቀ ሃይል ወድመዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች የህወሃት ካድሬዎች ሆን በለው የሃይማኖት ጸብ ለመቀስቀስ እንዳቃጠሉት ነው የሚናገሩት።
ደምቢዶሎ እና ምእራብ አርሲ የጦር ቀጠና ሆነው መሰንበታቸውን እና በጦርነቱ በርካታ ሰዎች ማለቃቸን የአሜሪካ ድምጽ ራድዮ እማኞችን ጠቅሶ ዘግቧል።
Posted by https://eth-freedom.blogspot.com/ at 9:38 PM No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Tuesday, October 4, 2016

​አዲስ አበቤዎች ዛሬ ጡንቻዎቻቸውን ፈታትሸዋል፤ ይኽ ገና ፍተሻ ነው። ( ዶ/ር ታደሰ ብሩ)

Oktober 4,2016
​​​አዲስ አበቤዎች ዛሬ ጡንቻዎቻቸውን ፈታትሸዋል፤ ይኽ ገና ፍተሻ ነው። ነገ ወደየት እንደሚያመራ መገመት ከባድ ነው። ለማንኛውም የሚከተሉትን ጥቂት ነጥቦች እንዳሰፍር ፍቀዱልኝ። 
1. ከቤት ስትወጡ ወንዶች ኪሳችሁ፣ ሴቶች ቦርሳችሁ ውስጥ ያለው ነገር እወቁ፤ የማታስፈልግ ከሆነ ብጣሽ ወረቀትም ብትሆን አስወግዱ፤

2.ራሳችሁን ለመከላከል የሚረዳችሁ ነገር ብትይዙ መልካም ነው፤

3. ሞባይላችሁን አጽዱ፤ በማትፈልጉበት ሰዓት አጥፉት፤

4. በተለይ ምሽት ላይ ድንገተኛ ፍተሻ  ሊኖር እንደሚችል ገምቹ። ከተቻለ ዋና ዋና መንገዶችን አስወግዳችሁ ውስጥ ውስጡን ሂዱ (እርግጥ ነው ለማጅራት መቺ መጋለጥ ሊኖር  ይችላል ሆኖም መንግሥት ነኝ ባዩ አካል ከማጅራት መቺ በባሰበት አገር ማጅራት መቺ ያነሰ ክፉ ሊሆን ይችላል)፤

5. የወታደር፣ የፓሊስ፣ የመንግሥት መኪና ባገኛችሁትና በተመቻችሁ አጋጣሚ ሁሉ ጎማ ማስተንፈስ፣ መስታወት መስበር፣ ቢቻይልም ማጋየት ተልዕኮዓችሁ አድርጉት፤

6. የህወሓት ሰላዮች ቦንብ ሊያፈነዱ ስለሚችሉ ተጠንቀቁ፤ የማታውቋቸው ሰዎች ሲጠጓችሁ ተጠራጠሩ፤

7. ብልጠት እና ፍጥነት በጣም አስፈላጊ ነገሮች ናቸው። ብልጠት ካለ በቀላል ወጪ ብዙ ጉዳት ማድረስ ይቻላል፤ ፍጥነት ካለ ጉዳት አድርጎ መሰወር ይቻላል።

8. ቶሎ ተሰባብሰው አንዳች ነገር ከከወኑ በኋላ የሚበታተኑ አደረጃጀቶችን ተጠቀሙ፤ ለሥራ የምትፈልጓቸው ቡድኖች ቋሚ አባላት እና ቋሚ መገናኛ አይኑራቸው።

9. የህወሓት ሰላዮችን በማበሳጨት፣ በማደናገር፣ በማሞኘት ተደሰቱ። ትግል የጭንቅላት ጨዋታ ነው፤ የህወሓት ሰላዮች ደግሞ ደደቦች ናቸው።

10. መትቶ መሮጥ (hit and run)፤ ተሰብስቦ መንገድ ዘግቶ፣ በተቃውሞ ድምጽ አበሳጭቶ መበተንን እንልመድ።

11. በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት፣  በጦር ሠራዊቱ፣ በፓሊስ፣ በስለላው፣ በሚኒስት መሥሪያ ቤቶች፣ በፋይናንስ ተቋማትና ሌሎች ድርጅች እንዲሁም በራሱ በኢህአዴድ ጽ/ቤት ውስጥ የምትሠሩ የሕዝብ ወገኖች መሥሪያ ቤቶቻችሁን በሕዝባዊ አሻጥር አሽመድምዱ። በፋሽስት መንግሥት ላይ አሻጥር መሥራት በሰማይ የሚያፀድቅ በምድር የሚያስመሰግን ሰናይ (መልካም) ተግባር ነው።  እኩይ ተግባር ከክፉ አገዛዝ ጋር መተባበር ነው። ህወሓትን የሚረዳ አንዳች ነገር ላለመሥራት ተጠንቀቁ፤ ህሊናችሁ ሲቆረቁረው እንዳይኖር፤ በቢሾፍቱ፣ በጎንደር፣ በባህዳር የወደቁ ወገኖቻችን መንፈስ እንዳይወቅሳችሁ።

12. ዘዴዎችን መቀያየር - ለምሳሌ፣ አደባባይ፣ ቤት፤ ቀን፣ ማታ፤ በሥራ ቀናት፣ በእረፍት ቀናት  -  ከተወሰነ  ጊዜ በኋላ ትግሉ መዳረሻ  (tipping point)  ላይ ይደርሳል፤ ከዚያ መመለሻ አይኖረውም። የአዲስ አበባ ሕዝባዊ እምቢተኝነት የህወሓት አገዛዝ ፍፃሚ አብሳሪ ይሆናል። ያ ደረጃ እስኪደረስ ሊያለፋ እንደሚችል ግን ካሁኑ ግንዛቤ ይወሰድ።

Via - Tadesse Biru Kersmo
Posted by https://eth-freedom.blogspot.com/ at 10:52 PM No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

“አሁን ደም ተቃብተናል፤ ዕርቅ የለም፤ ሌላ ሳይከተል ልቀቁልን”፤ “ከህወሃት ጋር ድርድርና እርቅ ብሎ ነገር የለም”

Oktober 4,2016

ሃይለማርያም ውረድ ተባለ!

hmd1ኦሮሚያ ብቻ ሳትሆን ድፍን አገርን ማቅ ያለበሰው የጅምላ ጭፍጨፋ እያደር አጥንት የሚያደቅ መረጃ እየወጣበት ነው። ህወሃት የእርቅ መንገዶችን በሙሉ አሟጦ የቀበረበት ይህ “ይቅርታ የሌለው ወንጀል” እስካሁን የ678 ንጹሃንን ህይወት አጥፍቷል። የትዳር ጓደኛውን አስከሬን በግል ተሽከርካሪ ጭኖ እያነባ ወደ ቤተሰቡ የወሰደ አለ። ገንዘብ ተዋጥቶለት የሚስቱን አስከሬን ጭኖ ወደ ሱሉልታ የተጓዘ መኖሩ ተሰምቷል። እናትና ልጅ ባንድነት ቀብራቸው ተከናውኗል። በአንድ ቀን ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ወገኖች ከቤተሰባቸው ጎድለዋል። አስከሬን አሁን ድረስ እየተቆፈረ እየወጣ ነው። ሃይቅ ላይ የተንሳፈፉ አስከሬኖች እየተለቀሙ ነው። ህዝብ ቁጣው ገንፍሎ በተለያዩ ስፍራዎች እምቢተኛነቱን እየገለጸ ነው። ህወሃት ግን አሁንም ይዋሻል።
በስፍራው የተገኙ ጋዜጠኞች ስፍራውን ለቅቀው እንዲወጡ በታጣቂዎች እስከታዘዙበት ድረስ የታዘቡትን ለቪኦኤ ሲያስረዱ ሁሉም ነገር ሰላማዊ ነበር። ህዝብ ተቃውሞውን ሲገልጽ የነበረው በሰላማዊ መንገድ ነበር። ምንም ዓይነት ትጥቅ ያልያዙ የኦሮሚያ ፖሊሶች ከህዝቡ ጋር በኦሮሚኛ እየተነጋገሩና ህዝብም “የእኛ” ሲላቸው ይደመጥ ነበር። ታዲያ ሰላማዊ ተቃውሞ ከነበረ ለምን በአየር፣ በታንክና፣ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት ተፈጸመ? የሚለው ጉዳይ መነጋገሪያ ሆኗል።
ከጥቂት ሳምንታት በፊት በሕዝብ ላይ ጦር ሠራዊቱ ጭፍጨፋ እንዲፈጽም ትዕዛዝ የሰጠው ሃይለማርያም ደሳለኝ በህወሃት ቴሌቪዥን ቀርቦ “እስካሁን ባለኝ መረጃ 52 የሚጠጉ ሞተዋል” በማለት ጸቡን ያስነሱትን ህግ ፊት እንደሚያቀርብ ዝቷል። ምንም ዓይነት የጥይት ድምጽ ሳይሰማ ህዝብን በመጠበቅ ከፍተኛ ትጋት ላሳዩት የጦር ሠራዊት አባላት ብሎ ለጠራቸው የአጋዚ ታጣቂዎች ምስጋናውን አሰምቷል። ሃይለማርያም በትዕዛዝ እርቅ በጠየቅ ባጭር ጊዜ ውስጥ ህዝብ ላይ ክተት መታውጁን አብሳሪ ሆኖ “አማራ ክልል” ሰላማዊ ዜጎች እያስጨረሰ ነው። አሁን ደግሞ የህወሃት አንጋቾች ለፈጸሙት የጅምላ ጭፍጨፋ እውቀና መስጠቱ ከሃዘኑ በላይ ህዝብን ያቆሰለ ጉዳይ ሆኖ እያነጋገረ ነው።irreecha75
እልቂቱ በደረሰበት ዕለት ዜና ያነበበችው የቪኦኤዋ አዳነች ፍስሃዬ “በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ” ያለቻቸው፣ “የአማጺ ባንዲራ በመያዝ ነጻነት እንፈልጋለን የሚሉ ነበሩ” ስትል አወላግዳና አሳንሳ ያቀረበችው የተንሸዋረረ መረጃ የሃይለማርያምን ያህል ባይሆንም ትዝብት ውስጥ የሚጥል እንደሆነ አስተያየት የሰጡ አሉ። ወዲያው አዳነች ይህን ብላ ስትጨርስ የተቀበላት ሌላው የቪኦኤ ባልደረባ የኦሮሚያ ክልልን ጠቅሶ እስከ 4 ሚሊዮን ህዝብ በበዓሉ ላይ ተሳታፊ እንደሚሆን አመልክቶ ነበር።
ከዚህ አስዛኝና ዘግናኝ ዜና በኋላ በሟቾችና በቆሰሉ ዜጎች አኻዝ ዙሪያ ለተፈጠረው ሰፊ ክፍተት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ “ህወሃት በቁጥር ማምታታቱ የተለመደ ነው። አይገርምም። የሚደንቀኝ የዓለም ሚዲያዎች እነሱን አምነው የሚዘግቡት ነው” ሲሉ ህወሃት ቀጣፊ እንደሆነ የታሪክ ሪኮርዱ እንደሚመሰክርበት ያመለክታሉ። ምርጫ ሲባል 100 ከ100፣ ኢኮኖሚ ሲባል የድርብ አሃዝ ዕድገት … በማለት የሚጠቀሱት አቶ ኦባንግ “ህወሃት ከግድያ ውጪ ችግርን የሚፈታበት እውቀት የሌለው፣ እምነቱም፣ ፍጥረቱም፣ ዕድገቱም፣ ዕቅዱም ንጹሃንን መግደል ብቻ ነው። የሚጠቅመው ሲሆን ድሮ እንደሚያደርገው ነጻ አወጣችኋለሁ የሚለውን የራሱንም ሰዎች ያጠፋል” ሲሉ ጊዜው የተራራቁ አካላት ተሰባስበው አንድ አካል የሚሆኑበት ጉዳይ ላይ ቅድሚያ የሚሰጥበት እንደሆነ አመልክተዋል። አያይዘውም “ቀደም ብለን አካል ሆነን ቢሆን ኖሮ እየነጣጠሉ አይገሉንም ነበር። ምክንያቱም አካል አንዱ ክፍል ሲጎዳበት ሁለመናውን ያመዋልና” ብለዋል፡፡ በቀናነትና ህዝብን ባስቀደመ መልኩ አንድ አካል መሆን፣ ከዘር ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ መስጠት፣ እንደ ጎሣ ሳይሆን እንደ ሰብዓዊ ፍጡር፣ እንደ ኢትዮጵያዊ ማሰብና መሰባሰብ፣ መታገል ግድ መሆኑን አስመረውበታል።
irreecha77ሃይለማርያም “ጥቂት ጸረ ሰላም ሃይሎች” ሲል አሳዳሪዎቹን ለማስደሰት እንዲህ ባለው መሪር ሃዘን ቢሳለቅም የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ እንዳለውና ኦፌኮ ለቪኦኤ እንዳረጋገጠው በኦሮሚያ ህዝባዊ እምቢተኛነቱ ተፋፈሞ ቀጥሏል። በበርካታ የኦሮሚያ ከተሞች የአገዛዙ መዋቀሮች ላይ ጉዳት ደርሷል። በምዕራብ ሃረርጌ የህወሃት ንብረት የሆኑ የሰላም አውቶቡሶች ወድመዋል። በወለጋ፣ በምስራቅ ሸዋ፣ በምዕራብ ሸዋ፣ በጅማ፣ በጉጂ፣ አርሲና በሌሎችም ስፍራዎች ህዝብ በህወሃት ንብረቶች ላይ የበቀል ርምጃ ተወስዷል። የአምቦ ውሃና የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች ስራ አቁመዋል። እንደ ዜናው የህዝባዊ እምቢተኛነቱ አራማጆች “ቀጣዩ እርምጃ ሕዝብን እያስገደሉና እየገደሉ ያሉትን ግለሰቦችን ያጠቃልላል” ማለታቸውን ይፋ አድርጓል።
ህዝባዊ እምቢተኛነቱ እየከረረ እንደሚሄድ የሚጠበቅ ሲሆን በዛሬው እለት (ሰኞ) በአምቦ 4 ንጹሃን፣ በቢሾፍቱ 2 በአጋዚ ሠራዊት መገደላቸውን የአይን ምስከሮች ለጎልጉል ተናግረዋል። ህዝብ ሃዘኑ ሳያጠግለት ዛሬም ነፍስ ማጥፋት ላይ የተጠመደው ህወሃት ላለፉት 25 ዓመታት የፈጸመውና ያደረሰው በደል አንድ ላይ ተዳምሮ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ሊስማማ የሚችልበት አማራጭ ሁሉ መዘጋቱን ብዙዎች እየተናገሩ ነው።
የኦሮሞና የአማራ ህዝብ ከህወሃት የቀረበላቸውን የእርቅ ጥያቄ አንቀበልም ማለታቸው የዚሁ የቆየው ሰቆቃ ውጤት ስለመሆኑ ብዙዎች ይስማማሉ። ለዚህም ይመስላል ህወሃት በገሃድ እየገደለ በጓሮ የለመነው እርቅ የተዘጋበት። በቤተ እምነት ሰዎች በኩል የእርቅ ጥያቄ የቀረበላቸው እኒህ ሁለት ግንድ ህዝቦች ህወሃት ላለፉት 25 ዓመታት እርቅንና ፍቅርን እንደገደለ አመልክተዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ህወሃት ያደረገውንና እያደረገ ያለውን፣ በተለይም በኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ የፈጸመውን “አረመኔነት የተሞላበት፣ የታቀደና ዝግጅት የተደረገበት” የተባለውን የጅምላ ጭፍጨፋ የተመለከቱ “ህወሃት/ኢህአዴግ ራሱን ለመጨረሻ ጊዜ ገደለ። ምን አልባትም የመጨረሻ እድሉ የሆነውን የባለአደራ መንግስት የማቋቋም ተስፋ የማግኘት ዕድሉም ሊኖረው አይችልም” ሲሉ እየተደመጡ ነው።irreecha78
የኦሮሞ ህዝብ የኢሬቻን በዓል ሲያከናውን ከተፈጸመበት የጅምላ ጭፍጨፋ በፊት ህወሃት በሃይለማርያም ደሳለኝ አማካይነት የተለያዩ ቤተ እምነት ሰዎችን ስለ ዕርቅ ተማጽኖ ነበር። በሃይለማርያም የጥሪ ደብዳቤ መነሻ በተለያዩ ዓለማት የሚገኙ የየእምነቱ የወንጌል አገልጋዮች አዲስ አበባ ተገኝተው ነበር። እነዚሁ ሰዎች ኦሮሚያና አማራ ክልል በመሄድ ህወሃትን ከህዝብ ጋር እንዲያስታርቁ  ተጠይቀዋል። በጥያቄው መሰረት እያንገራገሩ የእምነት አባቶቹ ወደ ትውልድ አካባቢያቸው በመሄድ አግባብ ያላቸውንና ለሕዝብ ቅርብ ከሆኑት ጋር ተወያይተው ተመልሰዋል። ምላሻቸውንም ይዘው ሃይለማርያም ቢሮ በመገኘት ህዝብ የሰጠውን ምላሽ አስረድተዋል። የጎልጉል የአውሮፓ ዘጋቢ በስብሰባው “ተገኝቻለሁ” ካሉ ያገኘውን መረጃ ጠቀሶ እንዳለው የሰዎቹ ምላሽ ሃይለማርያምን አስደንግጦ ነበር።
“በመጀመሪያ በትህትናና በህግ እንዲሁም በልመና ለረዥም ጊዜ ጥያቄ አቅርበናል። ዕርቅ ጠይቀን አልተቀበሉንም። አሁን ደም ተቃብተናል። ሰዎች ሞተዋል። ሌላ ሳይከተል ይልቀቁን ነው የሚሉት” ሲሉ የአማራዎችን አቋም አንደኛው መልዕከተኛ አቀረቡ። “ከህወሃት ጋር ድርድርና እርቅ ብሎ ነገር የለም” ሲሉ ጠቀለል አድርገው ኦሮሞዎች የመለሱት መልስ ምን እንደሆነ ሌላኛው መልዕክተኛ አስረዱ። ይህ በጓሮ ሲደረግ ህወሃት የሚመራው ሚዲያና የህወሃት መሳሪያ የሆኑ ክፍሎች የነጻነት ጥያቄ የሚያቀርቡትን የኅብረተሰብ ክፍሎች አሸባሪ፣ የጥፋት ኃይሎች፣ ተላላኪዎች፣ ጸረ ልማቶች፣ አተራማሾች … ወዘተ እያለ እያወገዙ ነበር፤ አሁንም ነው።
ገና ከጅምሩ ሃይለማርያም “ህዝብ ይሰማችኋልና ዕርቅ አውርዱልን” ብሎ ሲጠይቅ አንድ ትውልዳቸው ከኦሮሞ የሆነ አንጋፋ የወንጌል ሰባኪ “እግዚአብሔር ይህ ‹አገዛዝ› እንደሚወድቅ የተናገረው ከ10 ዓመት በፊት ነው። ልጄ ለምን እዚህ ውስጥ ገባህ? እጅህን አንሳ፣ ውጣ፣ መንግስት ከአንተ እጅ አይደለችም፣ የብዙ ሰዎች ደም በእጅህ አለ። ይህ ቦታህ አይደልም። ልቀቅ…” ብለው ማሳሰቢያ እንደሰጡ ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው የመረጃ ሰው በመናገር የሃይለማርያምን ምላሽ ሳያብራሩ አልፈውታል። ዘጋቢው ማብራሪያ ቢጠይቅም “ቢሰማ ኖሮ ኢሬቻ ሲያከብሩ በነበሩ ወገኖች ላይ አንድም የጥይት ድምጽ አልተሰማም” ብሎ አያወራም ነበር ሲሉ የመጠየፍ ስሜት እየተሰማቸው ተናግረዋል።
ላለፉት እጅግ በርካታ ዓመታት ስለ ዕርቅ መላ ሲቀርብ ሞት እንደ ቡሽ ክዳን ያስፈነጠረው መለስ እያሾፈ ይህ የባልና ሚስት ጠብ አይደለም በማለት ብዙ ሲቀለድ ኖሯል፡፡ በ97ቱ ምርጫ ወቅት ይኸው መለስ ከሰማይ በታች በማንኛውም ጉዳይ ላይ እደራደራለሁ በማለት የሕዝብን ቁጣ እንዲበርድ ካደረገ በኋላ የድርድሩን ምላሽ የተቃዋሚ መሪዎችን ወኅኒ በመወርወር ንቀቱን አሳይቷል፡፡ ከዚያም በተደጋጋሚ የቀረቡ የብዙዎች የዕርቅ ጥያቄዎች የፈሪ ልመና ተደርገው የተወሰዱባቸው ጊዜያት ጥቂት አይደሉም፡፡
ህወሃት/ኢህአዴግ ከዚህ በኋላ የሚያቀርበውም ሆነ የሚቀርብለት የዕርቅ ጥያቄ እንደሌለ በርካታዎች የሚስማሙበት ሃቅ እየሆነ መጥቷል፡፡ ይልቁንም ኢትዮጵያ የወላድ መሃን አለመሆኗ እንደገና የሚታይበት ወቅት ላይ መሆኑ አገር ወዳድ የሆኑና በሕዝብ ዘንድ ታማኝነት የሚጣልባቸው አገርን የማዳን ሥራ የሚሠሩበትና ከተደበቁበት የሚወጡበት ጊዜ ነው፡፡ ጥቃቱ እስከ መቅኔያችን የተሰማን በሙሉ በተለያዩ መጠሪያዎች ሳንከፋፈል በኅብረት የተቃውሞ ድምጽ የምናሰማበት ጊዜ ነው የሚለው አስተሳሰብ የበርካታዎች እየሆነ መጥቷል፡፡ (መግቢያ ፎቶ: Reuters, ሌሎቹ ከማኅበራዊ ገጾች የተገኙ)
በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ


Posted by https://eth-freedom.blogspot.com/ at 3:40 PM No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Sunday, October 2, 2016

Ethiopia: many dead in anti-government protest at religious festival

Oktober 2,2016
Police in Ethiopia’s Oromiya region fired teargas and warning shots to disperse anti-government protesters at a religious festival, triggering a stampede the opposition party said killed at least 170 people.
The government did not give a precise death toll resulting from chaotic scenes on Sunday during the annual festival, where some people chanted slogans against the government and waved a rebel flag. But it said “lives were lost” and that several were injured.
Sporadic protests have erupted in Oromiya in the last two years, initially sparked by a land row but increasingly turning more broadly against the government. Since late 2015, scores of protesters have been killed in clashes with police.
These developments highlight tensions in the country where the government has delivered stellar economic growth rates but faced criticism from opponents and rights group that it has trampled on political freedoms.
screen-shot-2016-10-02-at-8-12-32-am
Thousands of people had gathered for the annual Irreecha festival of thanksgiving in the town of Bishoftu, about 25 miles (40km) south of the capital, Addis Ababa.
Crowds chanted “we need freedom” and “we need justice”, preventing community elders, deemed close to the government, from delivering speeches at the festival. Some protesters waved the red, green and yellow flag of the Oromo Liberation Front, a rebel group branded a terrorist organisation by the government, witnesses said.
When police fired teargas and guns into the air, crowds fled and created a stampede, some of them plunging into a ditch, according to witnesses.
The witnesses said they saw people dragging out a dozen or more victims, showing no obvious sign of life. Half a dozen people, also motionless, were seen being taken by pick-up truck to a hospital, one witness said.
“As a result of the chaos, lives were lost and several of the injured were taken to hospital,” the government communications office said in a statement. “Those responsible will face justice.”
Merera Gudina, the chairman of the opposition Oromo Federalist Congress, told Reuters at least 50 people were killed, saying his group had been talking to families of the victims. He said the government tried to use the event to show Oromiya was calm. “But residents still protested,” he said.
The government blames rebel groups and dissidents abroad for stirring up the protests and provoking violence. It dismisses charges that it clamps down on free speech or its opponents.
Protesters had chanted slogans against Oromo People’s Democratic Organisation, one of the four regional parties that make up the Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front, which has ruled the country for quarter of a century.
In a 2015 parliamentary election, opposition parties failed to win a single seat – down from just one in the previous parliament. Opponents accused the government of rigging the vote, a charge government officials dismissed.
Protests in Oromiya province initially flared in 2014 over a development plan for the capital that would have expanded its boundaries, a move seen as threatening farmland.
Scores of people have been killed since late in 2015 and this year as protests gathered pace, although the government shelved the boundary plan earlier this year.
Posted by https://eth-freedom.blogspot.com/ at 10:53 PM No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Sunday, September 25, 2016

የውሸትና የማስመሰል ጸብ በመቀሌ ተጀምሯል። የነ አባይ ወልዱ አንጃ ከተሸነፈ ሳሞራ ዮኑስ ሊባረሩ ወይም በጡረታ ሊሰናበቱ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ

September 25,2016
ኣዲስ ኣበባው ኣንጃ “ኣቶ ኣባይ ወልዱ ከትግራይ ክልል ኣስተዳዳሪነታቸውና ከህወሓት ሊቀ መንበርነታቸው ማውረድ የሚል ኣላማ ኣንግበው መጥተዋል።

ይህ ማሳካት ማለት “በጥልቀት መታደስ” የሚል ትርጉም ይሰጡታል ይህ እውን ለማድረግ እንደመጡም እያስወሩ ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ የመቐለው ኣንጃ የተፎካካሪው ኔትወርክ ኣፈራርሶ ስልጣኑ የበለጠ ሊያሰፋና ልእልናው ሊያስጠብቅ እየተጣጣረ ነው።

የመቐለው ኣንጃ ኣቶ ኣባይ በስልጣን ማቆየት፣ የኣዲስ ኣበባው ኣንጃ ስልጣን ማዳከም ማሳካት ማለት በጥልቅ መታደስ ነው።
የመቐለው ኣንጃ ዋነጃ ደጋፊ ጀነራል ሳሞራ ከመባረር(የነ ኣባይ ወልዱ ኣንጃ ከተሸነፈ ሳሞራ ዮኑስ ሊባረሩ ወይም በጡረታ ሊሰናበቱ ይችላሉ የሚል ስጋት ኣለ) ማዳን የሚል ግብም ለማሳካት እየታገለ ይገኛል።

የኣዲስ ኣበባው ኣንጃ ኣባይ ሲያወርድ ሊፈጠር የሚችል ግርግርና ኣለመግባባት ለማረጋጋት የሚለምኑና የሚሸመግሉ የድሮ የማእከላይ ኮሚቴ ኣባላት ከያሉበት ኣሰባስበው ኣሳትፈዋል።

የኣዲስ ኣበባው ኣንጃ ወቅታዊ ፕሮፖጋንዳ “ኣዲስ ኣበባው የኢህኣዴግ ግምገማ ኣባይ ወልዱና ገዱ ኣንዳርጋቸው ከስልጣን እንዲወርዱ ተወስነዋል በውሳኔው መሰረት ኣባይ በሌላ ኣመራር መተካት ብቻ ነው” የሚል ወሬ በመንዛት የኣባይ ወልዱ ከስልጣን መውረድ የማይቀር መሆኑ እየገለፁ ይገኛሉ።

የህወሓት በጥልቅ መታደስ ዓላማ ኣቦይ ስብሓት የተነጠቁት የበላይነት ማስመለስ፤ ኣቶ ኣባይ ወልዱ በኣጋጣሚ በእጃቸው የገባው ልዕልና ኣስጠብቆ መውጣት ከሚል ትርጉም የዘለለ ኣይደለም።

በህዝባችን ዓይን የዚህ ጥሎማለፍ (ጥልቅ ተሃድሶ) ውጤቱ “ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ ኣይጣፍጥም” እንደሚባለው ፋይዳ ቢስ ነው።



Posted by https://eth-freedom.blogspot.com/ at 10:35 AM No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Wednesday, September 21, 2016

ጥልቅ ተሃድሶ “በመበስበስ” ጀመረ!

September 21,2016
opdo-new

የኢህአዴግ አካል የሆነው ኦህዴድ “ጥልቅ ተሃድሶውን” “በመበስበስ” መጀመሩን የኢህአዴግ ንብረትና የንግድ ተቋም የሆነው ፋና ብሮድካስቲንግ ያሰራጨው ዜና አመልክቷል፡፡ ዜናውን ተከትሎ “በጥልቀት የመታደሱ” ጉዳይ “በመበስበስ” መጀመሩ አመላካች ነው ተብሏል፡፡ በሌሎች ክልሎችም የመበስበስ መጠናቸው የጠለቀና ለህወሃት ከመታመን ውጪ ተስፋ በሌላቸው ታማኞች በመተካት ሹምሽር እንደሚቀጥል ይጠበቃል፡፡
የኦህዴድ ምክትል ሆነው የተሾሙት ጄኔራል፣ ዶክተር፣ አቶ፣ አሁን ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ብቅ ያሉት የኦሮሞን ብሔር የማይወክሉ የትግራይ ተወላጅ እንዶኑ በስፋት የሚነገርላቸው ሻሸመኔ ያደጉት ወርቅነህ ገበየሁ ናቸው፡፡
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ “ወርቅነህ ገበየሁ ለምን ወደ ትራንስፖርት ሚኒስትርነት?” በሚል ርዕስ (July 6, 2013) ስለ ወርቅነህ ገበየሁ “ነገዎ” መጠነኛ ዘገባ ባቀረበበት ወቅት የሚከተለው ሪፖርት አድርጎ ነበር፤

“የወርቅነህ ገበየሁ “ነገዎ” ሹመት

የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር አቶ ወርቅነህ ገበየሁ የትራንስፖርት ሚኒስትር ስለመደረጋቸው ከሚቀርቡት ምክንያቶች መካከል ቀደም ሲል ለረዥም ዓመታት ከደህንነቱና ከሽብር መከላለከል ግብረ ሃይል ጋር የነበራቸው ቁርኝት ከፍተኛ መሆኑ በግንባር ቀደም ይገለጻል። ለጎልጉል አስተያየት የሰጡ እንደሚሉት ኢህአዴግ የትራንስፖርቱን ዘርፍ በቅርብ መቆጣጠር ይፈልጋል።
በምርጫ 97 ወቅት ለታየው ህዝባዊ መነቃቃት የትራንስፖርቱ ዘርፍ፣ በተለይም የታክሲና የግል ማመላለሻዎች የነበራቸው ሚና ከፍተኛ እንደነበር አስተያየት ሰጪዎቹ ያስታውሳሉ። ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች እስከወዲያኛው እንዳይታሰቡ ለማድረግ ዘርፉን ከደህንነቱ ጋር በቅርብ ማጠላለፍ፣ ኢህአዴግ በከፍተኛ ደረጃ እየገነባሁ ነው የሚላቸውን መንገዶች፣ የስልክና የብሮድ ባንድ መስመሮች፣ የባቡር ትራንስፖርት በቅርብ ለመቆጣጠርና የቁጥጥሩ ሰንሰለት ውስጥ ለማስገባት አቶ ወርቅነህ ሁነኛ ሰው ሆነው መገኘታቸውን እነዚሁ ክፍሎች ይናገራሉ።
አዲሱ ቴሌን ጨምሮ የትራንስፖርት ዘርፉን ከደህንነቱ መዋቅር ጋር በቀላሉ ለማያያዝ ልምዳቸውና የመረቡ አባል ሆነው መቆየታቸው የትራንስፖርት ሚኒስትር ያደረጋቸው አቶ ወርቅነህ፣ የጄኔራልነት ማዕረጋቸው ከሳቸው ጋር ይቆይ ወይም ይነሳ የተገለጸ ነገር እንደሌለ የጠቆሙት ክፍሎች፣ በየትኛውም ደረጃ የሚገኙ የህወሃት አመራሮች አቶ ወርቅነህን በታማኝነት መድበው የተቀበሏቸው ሰው ስለመሆናቸው ጥርጥር የላቸውም።
አቶ ወርቅነህ ታማኝ ስለመሆናቸው፣ በዚሁ ታማኝነታቸው ስልጣናቸውን ሳይጠቀሙ በፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተርነት ለረዥም ጊዜ መቆታቸውን የሚናገሩት አስተያየት ሰጪዎች በበኩላቸው አቶ ወርቅነህ በአገር አቀፍ ደረጃ ከሰባት ሚኒስትር መስሪያቤቶች ተውጣጥቶ በጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚመራው የ”ደህንነት ኮር” ውስጥ አባል እንደነበሩ ይናገራሉ። ይህንን ኮር በአዲስ እየተዋቀረ ስለሆነ አቶ ወርቅነህ ወደ ትራንስፖርት ሚኒስትርነት የተዛወሩት ከደህንነቱ የኮር መዋቅር ውስጥ እንዲወጡ ስለተፈለገ መሆኑን ይገልጻሉ።”
ቀደም ሲል ከተዘረዘሩት የሥልጣን መጠሪያዎች ወርቅነህ ገበየሁ “ነገዎ” አሁን የኦህዴድ ሊቀመንበር ከሆኑት ለማ መገርሳ ጋር በአንድነት በማታው የትምህርት ክፍለጊዜ የዶ/ር መረራ ጉዲና ተማሪዎች ነበሩ፡፡ ከዚህም በላይ ወርቅነህ ገበየሁ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር (የጄኔራል ማዕረግ በህወሃት ተሰጥቷቸው እንደ ሲቪል “አቶ” ተብለው) በሚሠሩበት ወቅት ለማ መገርሣ የኦሮሚያን ደኅንነት በመምራት አብረዋቸው ይሠሩ ነበር፡፡
ከህወሃት የተሰጣቸውን የሚኒስትርነት ሥራ ሳይለቁ፤ ከፓርቲና ደኅንነት ሥራቸውም ሳይነቃነቁ ትምህርት ተምረው “ዶክተር” ለመባል እንደበቁ የሚነገርላቸው ወርቅነህ ገበየሁ “ነገዎ” ተማሩበት በተባለው የትምህርት ተቋም ስማቸው “ወርቅነህ ገበየሁ ወልደኪዳን” ተብሎ ከነፎቷቸው ተመዝግቧል፡፡
ከግራ ወደቀኝ ፓስተር ገመቺስ ቡባ፣ ጌታቸው ረዳ፣ የኦሮሞዎች መገደል ትክክል ነው ያለ አዲሱ ገብረእግዚአብሔር እና ለማ መገርሳ
ከግራ ወደቀኝ ፓስተር ገመቺስ ቡባ፣ ጌታቸው ረዳ፣ የኦሮሞዎች መገደል ትክክል ነው ያለ አዲሱ ገብረእግዚአብሔር እና ለማ መገርሳ
በኢህአዴግ አሠራር የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት የሚሆኑት ዛሬ ፋና ይፋ ያደረጋቸው አዲሱ የኦህዴድ ሊቀመንበር (የኦሮሚያ ምክርቤት አፈጉባዔ) ለማ መገርሣ በደኅንነት ውስጥ ከፍተኛ ታማኝነት ያተረፉና በሚያቋቸው ሰዎችና የሥራ ባልደረቦች “ተንበርካኪ የመቀሌ ልጅ” እየተባሉ የሚጠሩ መሆናቸውን በቅርብ የሚያቋቸው ይመሰክራሉ፡፡
ተሰናባቾቹ ሙክታር ከዲርና አስቴር ማሞ ራሳቸውን ከኃላፊነት አንስተዋል በሚል በሁለቱ የደኅንነት ማሽኖች መተካታቸው ያፈነገጠውን ኦህዴድ ወደ ሃዲዱ ስለመመለሱ ማረጋገጫ አይሰጥም፡፡
በሼህ መሃመድ አላሙዲን ባልደረቦችና ታዛዦች አማካኝነት አባዱላን ገልብጠው የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት የሆኑት ሙክታር ዛሬ ራሳቸውን ከሥልጣን አነሱ ቢባልም ከመሾማቸው ጊዜ ጀምሮ ካድሬው ሙሉ በሙሉ የሚቀበላቸው ሰው አልነበሩም፡፡
በጅማ ንጹሃን በታረዱነበት የህወሃት ወንጀል እጃቸው እንዳለበት በሥፋት የሚነገርላቸው ሙክታር እጅግ ውብ የሆኑት ባለቤታቸው ሚሊዮኔር መሆናቸው የኢህአዴግ ወፍጮ ሊቀረጥፋቸው ታሳቢ ካደረጋቸው መካከል የቅድሚያ ተሰላፊ እንደሚሆኑ ይነገራል፡፡
በባለቤታቸው የህወሃት አባል የሆኑት አስቴር ማሞ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ማሻሻያ ክላስተር አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪስ azeb and asterሚኒስትር የሚል ረጅም ሥልጣን ከተሰጣቸው ጊዜ ጀምሮ ብቃት የላቸውም፣ ዓቅም ያንሳቸዋል፣ ለቦታው አይመጥኑም፣ ወዘተ በሚል ተቃውሞ በግምገማ ላይ ሲቀርብባቸው ህወሃት/ኢህአዴግ “ጥሪ አይቀበልም” ሲል ሰንብቷል፡፡ ይልቁንም ዕድገት እየሰጠ የኦህዴድ መሪ አድረጋቸው፡፡ በሰባራ ጋሪ “ሽምጥ እየጋለብኩኝ” ነው ሲል የነበረው ኦህዴድ ራሱ አንኮታኩቶ ያጠፋውን የመልካም አስተዳደር፤ መሠረታዊ የችግር ቁልፍ አድርጎ በመውሰድ የአስቴር ማሞን ከሥልጣን መውረድ በ11ኛው ሰዓት ላይ ተቀብሎታል፡፡
የአስቴር ማሞን ከኃላፊነት መነሳት የተቀበለው ህወሃት “በጥልቅ ተሃድሶ” ምሎ ጥልቅ ተሃድሶውን በግፍ ከሸተተው መጋዘኑ ውስጥ ታማኞቹ አውጥቶ በመሾም የመታደሱን ቁርጠኝነት አሳይቷል፡፡ በዚህ የሥልጣን ሹም ሽር የቀለዱ አስተያየት ሰጪዎች እንዳሉት የኢህአዴግ የጥልቅ ተሃድሶ “ዳግም መበስበስ” ነው ብለውታል፡፡ አክለውም በመበስበስ የተጀመረው ይህ “ጥልቅ ተሃድሶ” ህወሃትን ወደ ትክክለኛ ጥልቅ ተወርውሮ የሚገባበትን ፍጥነት ቁልቁል የሚያዳልጥ አድርጎ ያፋጥነዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ከጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የተወሰደ
Posted by https://eth-freedom.blogspot.com/ at 6:28 PM No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Ethiopia: The Perennial Cleansing/Painting Strategy of TPLF

September 21,2016
by Dr. Dejenie Alemayehu Lakew
Without making and no intent to change, TPLF cleanses or paints its dirt of utter incompetency using the Ethiopian society on a yearly basis, via a Laundromat or invisibility process named discussions to the future but doing things the same, if not worse, with university, high school communities and others which it thinks may bring danger to its existence. It cleanses periodically by throwing out used socks or worn out boots which are no more useful for protection and replaces them with new hoodlums from other ethnic groups. What TPLF-ites refuse to see and Ethiopians see naked is that, TPLF is making a mockery, its incompetency is its source of pride and the future they envisioned actually is the past where the people lived and what they think of the past is the present, eliminating the future and making Ethiopians stand still on the past for all time.
TPLF leaders Debretsion Gebremichael and Abay Woldu
TPLF leaders Debretsion Gebremichael and Abay Woldu
Ethiopians in the contrary see and troubled by every contradiction TPLF brings on them, on their country and on their future as a people, they see the speed at which they are moving backwards in time while the world is moving forward in every aspect of social development (surprisingly the Tigray region is the one that slowly creeps forward in making buildings to store but there may not be anything to store and the belly of their members is visibly moving forward indeed-one of the achievements of TPLF). It makes universities under its full control and guidance, for fear of the unknown domain of knowledge. It has to make sure they do exactly what it tells them to do, else lose employment – it makes employment, a servitude and a life line for intellectuals than a place of merit, free thinking and creativity to pursue knowledge. It is for this reason that it annually prepares a painting camouflaging discussion forum of invisibility.
The recent such painting forums in some universities is a case in point. At the beginning of these events, TPLF plays a fool or someone who is intellectually incompetent to be aware of what is going on in the country. Ignoring the plights of Ethiopians, current upheavals, tragedies of killings and deaths committed by the TPLF army, the sheer terror, bloodshed and genocide it wages by the direct order of their nominal prime minister Hailemariam Desalegn on the Amhara people and Ethiopians in general, it proceeds by reprinting and forwarding existing manuals of higher education as discussion agendas, which the people already know them for many years and knowing TPLF will not come with something new and of social value but for the annual demand to get paint of camouflage ritual – let us get painted and cheat you so that you keep quite in order they continue with their crimes.
Let me digress a little from here, nature is a sophisticated dwelling place of actions that are results of conscious thinking of higher order or ordinary. We humans utilize our thinking and reasoning capabilities to make decisions hoping best results from our decisions, other creatures do the same. It is those who make the right decisions at the right time that survive better and those who make bad decisions or fail to make the right decisions on the right time perish or always remain underdogs. In such decision making processes, defense comes to be among the several fascinating natural capabilities of creatures that require high degree of precision to act in a right time, either through might, such as lions, dolphins or sharks or by being wise utilizing abilities of invisibility and camouflage in time of dangers. Invisibility by camouflaging or changing appearances by coloration to look alike the surrounding, disguise and disrupt predators is one technique to survive.
The worn out technique TPLF-ites use over and over again is demanding to receive painting coloration of disguises from the society, particularly universities and schools. The strange thing is that TPLF asks the very society it knows, to get a brush paint, so that its ugly works, corruption, culture of thefts of Ethiopian fertile lands, real estates and government resources to enrich themselves, brutality of killings, imprisoning, genocide and mindless acts against the Ethiopian people, its incompetency of governance, all to be invisible from the very victims. Other natural creatures in the contrary do it instantly without consulting the predators, for otherwise they will be consumed, if they are known.
These acts make the Tigray TPLF, the unique bold but inept in every measure, fraud and con-artist social organization ever appeared in the political history of our country. The good thing is the Ethiopian society reached to the lowest point with TPLF and moves further no downwards but upwards living TPLF at the pit. TPLF does not need cleansing deep, deeper or deepest or paint thick, thicker or thickest, it simply has to be removed. Ethiopia is rich in resources and with more than enough far sighted, thoughtful and imaginative children of wisdom and vision to lead her and her children to the promised places of freedom and democracy, equality and happiness and puts her at par with contemporary society.

Posted by https://eth-freedom.blogspot.com/ at 6:14 PM No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest
Newer Posts Older Posts Home
Subscribe to: Posts (Atom)

Ethiopia flag

Ethiopia flag

victims 2005

victims 2005

Blog Archive

  • ▼  2018 (5)
    • ▼  September (2)
      • የነአቶ በቀለ ገርባ መግለጫ አድራሻው ለማን ነው?
      • “የአዲስ አበባ ፓሊስ” ለሉአላዊ ባለቤቱ ይመለስ!
    • ►  March (1)
    • ►  February (2)
  • ►  2017 (17)
    • ►  December (1)
    • ►  November (1)
    • ►  October (1)
    • ►  August (2)
    • ►  July (5)
    • ►  June (1)
    • ►  April (4)
    • ►  February (1)
    • ►  January (1)
  • ►  2016 (109)
    • ►  December (3)
    • ►  November (2)
    • ►  October (10)
    • ►  September (5)
    • ►  August (7)
    • ►  July (22)
    • ►  June (16)
    • ►  May (6)
    • ►  April (6)
    • ►  March (9)
    • ►  February (15)
    • ►  January (8)
  • ►  2015 (332)
    • ►  December (13)
    • ►  November (17)
    • ►  October (20)
    • ►  September (25)
    • ►  August (18)
    • ►  July (36)
    • ►  June (26)
    • ►  May (24)
    • ►  April (36)
    • ►  March (33)
    • ►  February (35)
    • ►  January (49)
  • ►  2014 (1343)
    • ►  December (51)
    • ►  November (60)
    • ►  October (88)
    • ►  September (84)
    • ►  August (96)
    • ►  July (125)
    • ►  June (104)
    • ►  May (121)
    • ►  April (125)
    • ►  March (135)
    • ►  February (146)
    • ►  January (208)
  • ►  2013 (865)
    • ►  December (185)
    • ►  November (65)
    • ►  October (69)
    • ►  September (68)
    • ►  August (99)
    • ►  July (97)
    • ►  June (46)
    • ►  May (44)
    • ►  April (69)
    • ►  March (84)
    • ►  February (33)
    • ►  January (6)
  • ►  2012 (30)
    • ►  December (30)

Popular Posts

  • “የአዲስ አበባ ፓሊስ” ለሉአላዊ ባለቤቱ ይመለስ!
  • Privatizing EFFORT and all Other EPRDF Controlled Companies to Build Abay Dam
  • የህወሃት የደህንነት ተቋም የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚን ስብሰባ መረጃዎችን “እያሾለከ” እያወጣ ነው።
  • ስለ ዳተኛ ምሁራንቸል አንበል
  • የአዲስጉዳይ ፎቶ ጋዜጠኛ አዚዛ መሐመድ ተጨማሪ የ5 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባት
  • 2nd Letter to H.E. Field Marshall Abdu Rabu Mansour Hadi President Republic of Yemen
  • ሚሊዮኖች ድምጽ -ሃብታሙ አያሌው ቶርቸር እየተደረገ ነው !
  • ኢህአዴግ አሣ አስጋሪዎችን ጨፈጨፈ
  • የመንግስትና የፖሊስን መልካም ስም አጥፍተዋል የተባሉ ወጣቶች ተፈረደባቸው
  • በቁም እስር ላይ ያሉት ብጹእ ኣቡነ ማቲያስ ከአሜሪካን መልስ በደህንነት ቢሮ ለ72 ሰአታት ታስረው ነበር::

Popular Posts

  • “ሹገር ማሚዎች” የከተማችንን ጎረምሶች እያጠመዱ ነው Sugar Mommies trap young men in Addis Ababa
  • ወያኔ በባሕርይው ጅብና ውሻ ነው::
  • “የአዲስ አበባ ፓሊስ” ለሉአላዊ ባለቤቱ ይመለስ!
  • በምእራብ ኢትዮጵያ ለኩምሩክ ድንበር አቅራቢያ ጦርነት ተካሄደ።
  • ኢትዮጵያኖቹ በ ISIS ሲገደሉ በግድ እንዲያይ የተደረገው ታዳጊ ህፃን
  • የህወሃት የደህንነት ተቋም የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚን ስብሰባ መረጃዎችን “እያሾለከ” እያወጣ ነው።
  • የፍቅር ትርያንግል አዙሪት(Lovers Triangle)፤ ሼህ መሐመድ አላሙዲ-ከመንግስት ባለስልጣናት-ከልማታዊ አርቲስቶቻችን
  • የሰሜን ግንባር እየታመሰ ነው!
  • የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የግብረሰዶም አራማጆች “የመደራጀት መብታችን ይከበር” የሰጡት አስቂኝ ምላሽ
  • ሰው ለሰው እና አስናቀ ትንቅንቅ ውስጥ ገቡ።አስናቀ በቁጥጥር ስር
Simple theme. Theme images by gaffera. Powered by Blogger.