The Voice of Freedom

Freedom of Expression For All Ethiopian Peoples , NOW ! ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ለሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝቦች ፣ አሁኑኑ ! Free all Ethiopian Jornalist and Political Prisoners, Stop the Persecution of Independent Press in Ethiopia, We shall prevail! Freedom! Freedom! Freedom! FREEDOM, FREEDOM !!!

Gezahegn Abebe

https://eth-freedom.blogspot.com/
View my complete profile

Sunday, October 30, 2016

ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ያደረጉት ጥሪ በመከላከያ ሰራዊቱ ዘንድ ከፍተኛ ተደማጭነትን እያገኘ መምጣቱ ታወቀ!

ናትናኤል ኃይለማርያም
Oktober 30,2016

የአርበኞች ግንቦት ሰባትሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሀኑ  ለመከላከያ ሰራዊት አባላት፣የፌደራለ እና የክልል ፖሊስ አባላት፤ለአጋዚ ልዩ ጦር አባላት እና ለሌሎች ስርአቱ ታጣቂዎች ያደረጉት  ጥሪ  በሰራዊቱ ዉስጥ ከፍተኛ መነጋገሪያ  ከመሆኑም በተጨማሪ ሰራዊቱ ከህዝብ ጋር ለመቆም የመጨረሻ ዉሳኔ ላይ እንዲደርስ ያደረገዉ ጥሪ ነዉ ሲሉ እነዚሁ ምንጮች ጠቅሰዋል።የተደረገዉን ጥሪ መቀበላቸዉን ለማመላከት ሀሳባቸዉን የገለጹት የሰራዊቱ አባላት እንዳሉት “ መከላከያዉ የህዝብ ሳይሆን የህዉሀት ቡድን አገልጋይ እየሆነ መምጣቱን ሙሉ በሙሉ ያወቁበት ደረጃ ላይ መድረሳቸዉን እና ሊቀመንበሩ እንዳሉት ሰራዊቱ የቁም እስረኛ ሲሆን በተለይ ህዝባዊ እምቢተኝነቱ ከተጀመረ ጀምሮ ምን እንደሚያደርግ እና ወዴት እንደሚሄድ የጠራ አቅጣጫ ባለማግኘቱ እና ባለበት ከፍተኛ ጫና የተነሳ አማራጭ በማጣት በሰራዊቱ ዉስጥ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

አክለዉም በአሁኑ ሰአት አዛዦቻቸዉ ድንጋጤ ዉስጥ ከመሆናቸዉ የተነሳ በሰራዊቱ ላይ ያለዉ ቁጥጥር እና ማስጠንቀቂያ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን እንዲሁም ከአንድ ብሄር የሆኑ አባላት ባንድ ላይ ለግዳጅም ሆነ ለስምሪት እንደማይመደቡና በግል ህይወታቸዉ ዉስጥ ስለላን እያካሄዱ ነጻነታቸዉን ፍጹም እንደነጠቋቸዉም ገልጸዋል፡፤በዚህም ምክንያት ከሰራዊቱ መካከል ያሉ አንዳንድ አድር ባይ አባላትን ሳይቀር የሕዉሐት ገደብ ያለፈ ጥርጥር ወደተቃዋሚነት ስለለወጣቸዉ በአሁኑ ሰአት በጥቂት ቁጥር ከሚቆጠሩ የግል ሰዎቻቸዉ በቀር ሰራዊቱ ልቡ ከህዝብ ጎን ሆኗል ብለዋል፡፤  በየጊዜዉ ለግዳጅ ሲወጡ ወደነጻነት ታጋዮች ከነትጥቃቸዉ የሚቀላቀሉ እና በቡድን በመደራጀት በየጫካዉ የሚመሸጉ የሰራዊት አባላት ቁጥር ከቀን ወደቀን እየጨመረ መምጣቱንም አመልክተዋል።

ፕሮፈሰር  ብርሀኑ ነጋ ለሰራዊቱ ያደረጉትን  ጥሪ በርካታ ሰዎች ለዉጥ የሚያመጣ ጥሪ መሆኑን በመግለጽ እነሱን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ መከላከያ ሰራዊቱ ወገኑ ላይ መተኮስ እንዲያቆም እና የመሳሪያ ነጠቃን እና በ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሰበብ የሚደረግባቸዉን የጅምላ አፈሳ እንዲሁም ግድያ በመቃወም ወደጫካ ከገቡ ወጣቶች እና አርሶ አደሮች እንዲቀላቀል ጥሪ አቅርበዉ፤ ከሳምንታት በፊት በፍኖተ ሰላም ከተማ 18 የመከላከያ ሰራዊቶች እና አራት ያጋዚ አባላት ሰራዊቱን ከድተዉ መዉጣታቸዉን አስታዉሰዋል።በተለይ በአማራ ክልል አገዛዙ በስፋት ለማከናወን አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ያለበትን የመሳሪያ  ነጠቃ ሽሽት ወደየጫካዎች በመግባት ላይ ያለዉ ህብረተሰብ እየጨመረ መምጣቱን እና የኮማንድ ፖስት አባላት ወጣቶችን ያለምንም ምክንያት ስለሚያስሩዋቸዉ በፍኖተ ሰላም በከተማዋ ዉስጥ አዛዉንቶች፤ሴቶች እና ህጻናት ብቻ እየቀሩ እንደሆነ ገልጸዋል።

በተያያዘ ዜናም በባህር ዳር ከተማ  ከስድስት ሳምንት በፊት ወቶ የነበረዉና መመዘኛዉ ከ10ኛ ክፍል በላይ የነበረዉ የመከላከያ ምዝገባ ፤ተመዝጋቢ በማጣቱ ምክንያት ማስታወቂያዉ ከወጣ ከሁለት ሳምንት በሗላ መስፈርቱ ወደ 6ተኛ ክፍል ዝቅ ብሎም ባለመሳካቱ በአሁኑ ሰአት ወጣቶች ወደ መከላከያ ቢገቡ ጥቅማጥቅሞችን እንደሚያገኙ ዉስጥ ዉስጡን በቅስቀሳ መልክ እየተወራ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ይህ በእንዲ እንዳለ የክልሉ አየር መንገድ ለአዉሮፕላን አብራሪነት እና ለቴክኒሺያንነት የቅጥር ማስታወቂያ ማዉጣቱን ተከትሎ ምናልባት በስራ አጥነት ሲሰቃይ የከረመዉን ወጣት በዚ መልክ በመመዝገብ ወደመከላከያ ስለጠና ሊወስዱት ይችላሉ የሚል ስጋት እንዳላቸዉም ጠቁመዋል። የህዋት መንግስት ለመከላከያ  እና ለፖሊስ አባላት መላቀቂያም ሆነ ፈቃድ መጠየቅ እንደማይቻል ቢያስተላልፍም እየከዱ እና እየጠፉ በሚለቁ አባላት ምክንያት አለመተማመን የመጣዉን የሰራዊቱን ቁጥር ለመጨመር በሰበብ አስባቡ በቁጥጥር ስር ያዋላቸዉን ወጣቶች በማባባል እና በማስገደድ ወደ ስልጠና ለማስገባት ሙከራ እያረገ ይገኛል ሲሉም ተደማጠዋል።

ከአመት በፊት ጀምሮ ሰራዊቱን እየለቀቁ የሚሄዱ አባላት ቁጥር  በተለይ ህዝባዊ ትግሉ ከተጀመረ በሁዋላ በመጨመሩ፤የህዋት መንግስት  በየክልሉ የመከላከያ  ሰራዊትነት ምዝገባን ለማካሄድ ከጥሩ የደሞዝ ክፍያ ጋር ጥሪ ቢያደርግም የሚመዘገብለት ማጣቱ በሌሎች አስገዳጅ መንገዶች ወጣቶችን በማታለል በግዳጅ ወደ መከላከያ ያስገባበት ሁኔታ መኖሩን ሲዘገብ መቆየቱ ይታወሳል።

Posted by https://eth-freedom.blogspot.com/ at 5:07 PM
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

No comments:

Post a Comment

Newer Post Older Post Home
Subscribe to: Post Comments (Atom)

Ethiopia flag

Ethiopia flag

victims 2005

victims 2005

Blog Archive

  • ►  2018 (5)
    • ►  September (2)
    • ►  March (1)
    • ►  February (2)
  • ►  2017 (17)
    • ►  December (1)
    • ►  November (1)
    • ►  October (1)
    • ►  August (2)
    • ►  July (5)
    • ►  June (1)
    • ►  April (4)
    • ►  February (1)
    • ►  January (1)
  • ▼  2016 (109)
    • ►  December (3)
    • ►  November (2)
    • ▼  October (10)
      • ኮንትራታቸውን የጨረሱ የወያኔ መከላከያ ሰራዊት አባላት አዲስ ኮንትራት እንዲፈ...
      • ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ያደረጉት ጥሪ በመከላከያ ሰራ...
      • የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊቶች ከታጣቂው ገበሬ ጋር ጥምረት ፈጥረው የወያኔን ...
      • የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት እየታደኑ መታሰር ጀመሩ
      • በኢትዮጵያ እስረኞች አጥንትን ቀስ በቀስ በሚያፈርስ መርዝ እየተጠቁ መሆኑን ታውቀ
      • German leader calls for Ethiopia to open up politi...
      • የትግራይ ተወላጆች በሙሉ ከቢሾፍቱ ተጭነው ተወሰዱ
      • ​አዲስ አበቤዎች ዛሬ ጡንቻዎቻቸውን ፈታትሸዋል፤ ይኽ ገና ፍተሻ ነው። ( ዶ/ር...
      • “አሁን ደም ተቃብተናል፤ ዕርቅ የለም፤ ሌላ ሳይከተል ልቀቁልን”፤ “ከህወሃት ጋ...
      • Ethiopia: many dead in anti-government protest at ...
    • ►  September (5)
    • ►  August (7)
    • ►  July (22)
    • ►  June (16)
    • ►  May (6)
    • ►  April (6)
    • ►  March (9)
    • ►  February (15)
    • ►  January (8)
  • ►  2015 (332)
    • ►  December (13)
    • ►  November (17)
    • ►  October (20)
    • ►  September (25)
    • ►  August (18)
    • ►  July (36)
    • ►  June (26)
    • ►  May (24)
    • ►  April (36)
    • ►  March (33)
    • ►  February (35)
    • ►  January (49)
  • ►  2014 (1343)
    • ►  December (51)
    • ►  November (60)
    • ►  October (88)
    • ►  September (84)
    • ►  August (96)
    • ►  July (125)
    • ►  June (104)
    • ►  May (121)
    • ►  April (125)
    • ►  March (135)
    • ►  February (146)
    • ►  January (208)
  • ►  2013 (865)
    • ►  December (185)
    • ►  November (65)
    • ►  October (69)
    • ►  September (68)
    • ►  August (99)
    • ►  July (97)
    • ►  June (46)
    • ►  May (44)
    • ►  April (69)
    • ►  March (84)
    • ►  February (33)
    • ►  January (6)
  • ►  2012 (30)
    • ►  December (30)

Popular Posts

  • “የአዲስ አበባ ፓሊስ” ለሉአላዊ ባለቤቱ ይመለስ!
  • Privatizing EFFORT and all Other EPRDF Controlled Companies to Build Abay Dam
  • የህወሃት የደህንነት ተቋም የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚን ስብሰባ መረጃዎችን “እያሾለከ” እያወጣ ነው።
  • ስለ ዳተኛ ምሁራንቸል አንበል
  • የአዲስጉዳይ ፎቶ ጋዜጠኛ አዚዛ መሐመድ ተጨማሪ የ5 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባት
  • 2nd Letter to H.E. Field Marshall Abdu Rabu Mansour Hadi President Republic of Yemen
  • ሚሊዮኖች ድምጽ -ሃብታሙ አያሌው ቶርቸር እየተደረገ ነው !
  • ይድረስ ለብአዴን አባላት
  • በቁም እስር ላይ ያሉት ብጹእ ኣቡነ ማቲያስ ከአሜሪካን መልስ በደህንነት ቢሮ ለ72 ሰአታት ታስረው ነበር::
  • ግን እስከ መቼ?

Popular Posts

  • “ሹገር ማሚዎች” የከተማችንን ጎረምሶች እያጠመዱ ነው Sugar Mommies trap young men in Addis Ababa
  • ወያኔ በባሕርይው ጅብና ውሻ ነው::
  • “የአዲስ አበባ ፓሊስ” ለሉአላዊ ባለቤቱ ይመለስ!
  • በምእራብ ኢትዮጵያ ለኩምሩክ ድንበር አቅራቢያ ጦርነት ተካሄደ።
  • ኢትዮጵያኖቹ በ ISIS ሲገደሉ በግድ እንዲያይ የተደረገው ታዳጊ ህፃን
  • የህወሃት የደህንነት ተቋም የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚን ስብሰባ መረጃዎችን “እያሾለከ” እያወጣ ነው።
  • የፍቅር ትርያንግል አዙሪት(Lovers Triangle)፤ ሼህ መሐመድ አላሙዲ-ከመንግስት ባለስልጣናት-ከልማታዊ አርቲስቶቻችን
  • የሰሜን ግንባር እየታመሰ ነው!
  • የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የግብረሰዶም አራማጆች “የመደራጀት መብታችን ይከበር” የሰጡት አስቂኝ ምላሽ
  • ሰው ለሰው እና አስናቀ ትንቅንቅ ውስጥ ገቡ።አስናቀ በቁጥጥር ስር
Simple theme. Theme images by gaffera. Powered by Blogger.