Friday, July 11, 2014

ትግል!!! ማንን? ለምን? ለማን? በማን? በምን? መቸና የት?

(ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)
struggle


ሀገራችን እድሜ ጠገብ፣ እድሜ እረጅም መሆኗን እናውቃለን፡፡ ከኖሕ ዘመን (ከጥፋት ውኃ) በኋላ ያለውን ብቻ እንኳን ብንይዝና ከመጀመሪያው ንጉሥ ከሰብታህ ጀምረን ብንቆጥር ከ4500 ዓመት በላይ ዕድሜ ያለው የመንግሥት መልክ የያዘ የአሥተዳደር ታሪክ ያላት ሀገር ናት፡፡ ይህች ሀገር ከዚህ ረጅም ታሪኳ ጋር እንደ ፀሐይ የሚያበራና አድማስ ተሻግሮ የሚሞቅ ብርቅዬ የነጻነት ታሪክ አላት፡፡ ሀገራችን ከ3 ሺህ ዓመታት በፊት ጀምሮ ይሄንን ዘውዷም ለመንጠቅ የሞከሩ እጅግ ከባባድ ፈተናዎችን አሳልፋለች፡፡ ፈተናው ያንን ያህል የከበደ ቢሆንም ያ ሕዝብ ከጠላቶቹ ከፈታኞቹ ከተገዳዳሪዎቹ ሁለንተናዊ አቅም የላቀ ጥንካሬ ብስለት ንቃት ወዘተ ስለነበረው ዘውዱን ሳያስነጥቅ ጠብቆ ለመቆየት ችሏል፡፡ ነገር ግን በመራር ጽናት ነጻነቱን ጠብቆ መቆየት ይቻል እንጅ ከጥንት ጀምሮ የነበረበት ፈተና ድምር ውጤት ይሁን ወይም ምድሪቱ አርጅታ አይታወቅም ከጥቂት ዐሥርት ዓመታት ወዲህ ያለውን ትውልድ ስናይ ከትውልዱ የሚበዛው ምርኮኛና ምንደኛ የሆነ ትውልድ አፍርታ ቁጭ ብላለች፡፡
እንዴት እንደምገልፀው አላውቅም አሳማኝ አይደለም ትንሽም እንኳን የሚመስል ምክንያት ሳይኖረው ለገዛ ማንነቱ፣ ታሪኩ፣ ሥልጣኔው ወዘተ. ከጠላቶቹ በላይ ጠላት የሆነን የትውልድ አካል እንደምን ባለ ቃል ሊገለጽ ይቻላል? ገና ሳስበው የሚያቅለሸልሸኝ ነገር ቢኖር ይህ ጉዳይ ብቻ ነው፡፡ ጨርሶ መልካምና ክፉውን መለየት አይችልም፡፡ ገደልም ይሁን ምን ማንም ቢሆን ና እያሉ መርተው ቢከቱት ዓይኑን ጨፍኖ የሚወረወር ሆኗል፡፡ እናት አባቶቹ ተነግሮ ሊያልቅ በማይችል መሥዋዕትነት ጠብቀው ያቆዩትን ነጻነት (ነጻነት ስል እንድታስቡት የሚፈልገው የግዛት ነጻነትን ብቻ ሳይሆን ከግዛት እስከ ሥነ-ልቡናዊ ያሉትን ዘርፈ ብዙ የነጻነት ዓይነቶችን ሁሉ ነው) እናም ይሄንን ነጻነቱን አውላላ ሜዳ ላይ ያለ ጠባቂ ቁጭ አድርጎ ለቀማኛ ለሌባ ለዘራፊ አጋልጦታል፡፡ ከፊሉን ሌቦች ወስደውታል ከፊሉን ደግሞ የአጋጣሚ ጉዳይ ሆኖ የሚወስድለት ቢያጣ አይሁድ በክርስቶስ መስቀል ላይ እንዳደረጉት ሁሉ የቆሻሻ ዓይነት እላዩ ላይ ሲደፋበት ሲደፋበት የቆሻሻው ክምር እንደ ተራራ ገዝፎ የነጻነት ዘውዱን ቀብሮታል፡፡ አውጥቶ የሚያከብረው ተቀዳጅቶ የሚያቀዳጅ እንደ እሌኒ ንግሥት ያለ አርበኛ ይፈልጋል፡፡
ከዚህ ትውልድ ራሱን ለጠላት ቀጥሮ የገዛ ማንነቱን በማውደም በማጥፋት ከተጠመደው አንሥቶ የእነኝህን ቅጥረኞች፣ ባንዶች የጥፋት ሥራ ልክና ቅጥ ባጣ እራስ ወዳድነት ፍርሐትና እንደ ዜጋ ሀገር የጣለችበትን ኃላፊነት ለመወጣት ቁርጠኝነትና ፍላጎት በማጣት እጁን አጣምሮ በዝምታ እስከ ሚመለከተው ድረስ ከትውልዱ የሚበዛው ቁጥር በእንደነዚህ ዓይነቶቹ ጃርቶች የተሞላ ሆኗል፡፡ “ምድር ሲያረጅ ጃርት ያበቅላል ወይም እሳት አመድን ወለደ” ይሏቹሀል እንዲህ ነው፡፡ እነዚህ እንከኖቻችን አንባገነን ገዥዎቻችንን ለመፍጠር ከመመቸቱም በላይ ለግፍ አገዛዛቸውም ምቹ መደላድል ሆኗቸዋል፡፡ በተለይም ከሁለት ዐሥርት ዓመታት ወዲህ ደግሞ በዓይነቱ አዲስ እንግዳና የተለየ ፍላጎት ጥቅምና ዓላማ የያዘ ገዥ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ለትውልዱ ከድጡ ወደማጡ ሆኖበት ወደከፋ የሰብእና ደረጃ ለመዝቀጥ ግዴታ ሆኖበታል፡፡ ከዚህ አገዛዝ አስቀድሞ በነበረው ትውልድ ዘንድ ይዘቱና ዓይነቱ ያነጋግር ካልሆነ በስተቀር የነበረው የሀገር ፍቅር ጨርሶ የሚያጠያይቅ አልነበረምና፡፡ አሁን ያለው ገዥ ሥልጣን ከያዘ ጊዜ ወዲህ ግን ሊያሠራኝ አይችልም ብሎ ያሰበውን ለዜጎች ለትውልዱ እንደ ጋሻና ጦር ሆኖ የማንነት ፈተናዎችን ለመቋቋም ለመከላከል ይረዳው የነበረውን የሀገር ፍቅር ስሜቱን በየሕሊናው ረሽኖ ከገደለበት ጊዜ ወዲህ ግን የዘቀጠ የሰብእና ደረጃ ላይ ለመገኘት ግዴታ ሆኖበታል፡፡
ገዝው ፓርቲ (ወያኔ) ይሄንን ካደረገ በኋላ የሥልጣን እስትንፋሱን ካራዘሙለትና እንዲያራዝሙለት ከተጠቀመባቸውና ከሚጠቀምባቸው ዘዴዎች ዋነኞቹ ሕዝቡን በፍርሐት ቆፈን ጠፍንጎ ማሰርና አስቀድሞ ፋሽስት ጣሊያን እንዳደረገው ሁሉ በዘር በሃይማኖት በመደብ ከፋፍሎ እንዳይተማመን ማድረግ ነው፡፡ ለምን ቢባል በፍርሐት ገመድ የታሰረና የማይተማመን ኅብረተሰብ ተባብሮ ሊሠራራና ሊተባበር ቀርቶ አይናገርም መናገር ቀርቶ አያስብም አይመክርምና ነው፡፡ ጭራሽም እርስ በእርሱ ይፈራራል፡፡ ከመሀከሉ አንዱ ወይም ጥቂቶቹ ለማፈንገጥ ሲሞክሩም አስፈራሪው እሱው ራሱ ኅብረተሰቡ ወይም ከቅርቡ ያሉት የገዛ ወገኖቹ ይሆናሉ፡፡ ለታሪኩ ለነጻነቱ ለማንነቱ ለመለያው ቀናኢ አይሆንም፡፡ ስለዚህም እንደተፈለገ መርገጥ መጫወቻ መቀለጃ ማድረግ ይቻላል፡፡ በእርግጥ ገዥው ፓርቲ ከሚናገራቸውና በይፋ ሳይናገራቸውም ነገር ግን ለማስፈራራት በካድሬዎቹ በአባሎቹ በኩል ሆን ብሎ እንዲወሩና ወደ ሕዝቡ እንዲደርሱ ከሚያደርጋቸው ወሬዎች ሁሉ “አይ ለማስፈራራት እንጅ አያደርገውም” የሚባል አንድም ነገር የለውም፡፡
ምንም ዓይነት ድርጊት ቢሆን ምርጫው ላይ ያላካተተው የለም፡፡ ለሀገር ሳይሆን ለቡድኑ ሕልውና ሲባል ሰዎች መሞት ካለባቸው ሰዎቹ የማይተኩና ለሀገርም ዓይን ቢሆኑም እንኳ የትንኝ ነፍስ ያህል ዋጋ አይሰጣቸውም፡፡ ከዚህም አልፎ ሀገር መፍረስ ካለባት ያለ አንዳች ማመንታት ትፈራርሳለች፡፡ በሕገ መንግሥታቸው ሳይቀር ለህልውናቸው ዋስትና አድርገውት ይሄንን ቀርጸው እያስፈራሩን እንደኖሩትና እንዳሉት ሁሉ፡፡ ነገር ግን ሕዝቡ ሊረዳውና ሊያውቀው ለራሱም ሊመልሰው የሚገባው ነገር ቢኖር፡-
1. እንዲህ ሰላሙንና ደኅንነቱን ከነሳው ዋስትና ካሳጣው ፍርሐትና ጭንቀት ነጻ ለመውጣትና የእፎይታ አየር ለመተንፈስ እንደ ሰው ኖሮ ለማለፍ የግድ ዋጋ መክፈል ያለበት መሆኑን፡፡
2. ከገዥው ፓርቲ ወጥመዶች ማለትም ከፍርሐት፣ እርስ በእርስ ከመጠራጠር፣ ካለመተማመን ወይም ከክፍፍል ሴራ ራሱን ማላቀቅ ናቸው፡፡
መቸም እንደ ሰው በተለይም እንደ ኢትዮጵያዊ ነጻነቱን አጥብቆ የማይሻ የማይፈልግ ይኖራል ብሎ ማለት የሚያስቸግር ይመስለኛል፡፡ ነገር ግን ይህ ትውልድ ያንን ነጻነት ማግኘት የሚችልበትን መንገድ ዐውቆ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረጉ ላይ ግን እስከ አሁን አልተረዳም አልገባውምም፡፡ ለዚህም ዐቢዩን ሚና የተጫወተው የሥርዓቱ የማስፈራሪያ ቱልቱላ በሕዝቡ ሥነ-ልቡና ላይ በከፍተኛ ደረጃ መነፋቱ ነው፡፡ ማስፈራሪያው ገዥውን ፓርቲ ጨርሶ የሌለውን አቅም እንዳለው አድርጎ አሳምኖለታል፡፡ ከሕዝቡ አቅም አንጻር ቢገልጡና ቢያዩት ግን ባዶና አቅመቢስ ሸንበቆና ቀሽማዳ የሆነውን በወሬ ብቻ ገዝፎ ያለውን የቆመውን አገዛዝ አግዝፎ እንዲያየውና ጨርሶ የማይገፋ የማይገረሰስ የማይቻል ጭራሽም ከአየሩና ከነፋሱ ጋር ያሉ ሁሉንም ነገር ማወቅ መቆጣጠር የሚችሉ መናፍስት እንደሆኑ አድርጎ እንዲያስበውና በተጨባጭ ግን ፈጽሞ ባልሆነውና በሌለው አቅም ጉልበት ሕዝቡን አንቀጥቅጦና ቀጥቅጦ ለመግዛት እንዲችል አብቅቶታል፡፡
ደርግን አስወግዶ ሥልጣን ለመቆናጠጥ ያበቃውም ይሄ ስልቱ ነው፡፡ በከፍተኛ ደረጃ በዘመናዊ ወታደራዊ ዲሲፕሊን (አደረጃጀት) የተደራጀውን የደርግ ሠራዊት ከአንድ ሁለቱ በስተቀር በየግንባሩ ገና ውጊያ ከመጀመሩ በፊት እንዲበተን ያደርገው የነበረው ባዕዳንንና የተገዙትን የራሱን የደርግን አመራሮች ጭምር በመጠቀም በተለያየ አቅጣጫ ወያኔ አስቀድሞ በሚነዛውና ለሠራዊቱ እንዲደርስ በሚያደርገው የማስፈራሪያ ወሬ የሠራዊቱ ልብ እንዲፍረከረክ ያደርግ ስለነበር ከዐሥሩ አንዱ ብቻ መሣሪያ በታጠቀው ዘጠኙ ጀሌ (ያልታጠቀ) በነበረው በወያኔ ሠራዊት ሊገረሰስ ቻለ፡፡ እውነቱና የወያኔ ሠራዊት አቋም ወይም አቅም ግን የታወቀው ነገሩ ካለቀለት በኋላ በመሆኑ የደርግ ወታደሮች ያተረፉት ነገር ቢኖር የማይጠቅም ጸጸት ብቻ ሆኖ ቀርቷል፡፡ የወያኔ ሠራዊት ስንቅና ትጥቅ በሙሉ ማለት ይቻላል ከደርግ የተወረሰ ነበርና፡፡ ነገሩ ግልጽ ተአምር ነው፡፡ እግዚአብሔር ኢአማኒውን ደርግ በቃህ ሊለው ስለወደደ ይሆናል ተብሎ የማይታሰብና የማይገመት ነገር እውን ሆኖ ቁጭ አለ፡፡ ይሄ ጉዳይ እጅግ አስገራሚና አስደናቂ በሆነ ሁኔታ የስለላን ሥራ አቅም እጅግ እጅግ ወሳኝነት በሚገባ የሚያሳይ ነው፡፡ “ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው” የሚባለውስ ለዚሁ አይደል?struggle1
እኔ ይህ ጉዳይ እጅግ ትኩረቴን ስለሳበኝ የወያኔን ሠራዊት “ጀግንነት” ለማየት ፈልጌ ነገሩን መርምሬው ነበር፡፡ ያገኘሁት ወይም የተረዳሁት ነገር ግን ያልጠበኩት ማለትም የወያኔን ሠራዊት ጀግንነት ሳይሆን የደርግን ሠራዊት ደካማነት ነው፡፡ የደርግ ሠራዊት በሕዝቡ ካለመወደዱ ከመጠላቱ ተቀባይነት ከማጣቱ ካለመደገፉ በተጨማሪ በተቀናጀ መልኩ ከውጭ (CIA) እና ከውስጥ በተሠራበት ሥራ ልክ ምስጥ እንደበላው እንጨት ላይ ላዩን ሲያዩት ደኅና መስሎ ነገር ግን በቀላሉ ሲነኩት ፍርክክ በሚልበት የነቀዘ አቋም ላይ የነበረ ሆኖ ነበር፡፡ በመሆኑም እንኳን የሚዋጋው እራሱን ያደረጀ ሠራዊት እያለ ቀርቶ በነፋስ ሽውታ ሁሉ ሊደረማመስ ይችል የነበረ ሠራዊት ነበር፡፡ ይህ ምቹ ሁኔታ ነው ወያኔን ለድል ያበቃው፡፡
ከዚህም የተነሣ ነው ከአቶ መለስ፣ ከጀኔራል ሳሞራ፣ ከአቶ ሥዩምና ከሌሎቹም አንደበት ግንቦት ሃያ በመጣ ቁጥር በተደጋጋሚ ሲሉት እንደሰማነው “ምንም እንኳ ስንሠራው የነበረው ሥራ ልክ ሥልጣንን ለመያዝ እንደሚችል ያለመ ያሰበ ያወቀ ቢያስመስለንም እስከ 1982(83) ዓ.ም. ድረስ ምንአልባት በትውልድ ይሆን ይሆናል እንጅ በእኛ እድሜ ደርግን ጥለን ሥልጣል እንይዛለን የሚል ሕልምና ተስፋ ለቅጽበት እንኳን ታስቦን የማያውቅና ጨርሶም ያልጠበቅነው ነበር እኛ በረሀ የገባነው እንቢ አሻፈረኝ አንገዛም ለማለት ነበረ እንጅ ለዚህ እንበቃለን ብለን አልነበረም” በማለት የሚናገሩት፡፡ ጀግንነትስ የሚታየው አሁን ነበር! ወያኔ ትግል ላይ እያለ ጀምሮ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የገባውን ቃል ሁሉ እንደማያደርገው ስለሚታወቅበት ሕዝቡም ይሄን በተረዳ ጊዜ ሊወስደው የሚችለውን እርምጃ ጠንቅቆ ስለሚገነዘብ ነው አስቀድሞ በታሪኩ እሱ ከሱዳንና ከሌሎችም ያገኘውን ሰፊ ድጋፍና ምቹ ሁኔታ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዳያገኝ የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅሞች ሁሉ አሳልፎ በመስጠት ጎረቤት ሀገሮችን ሁሉ በጠበቀ ወዳጅነት የያዛቸው፡፡ እሱ ከሱዳን አግኝቶት የነበረውን ሁለንተናዊ ድጋፍ ሩብ ያህል ይሄም ቀርቶ ተገን ብቻ እንኳን የሚሰጥ ጎረቤት ሀገር አሁን የኢትዮጵያ ሕዝብ ቢያገኝ እነሱ የፈጀባቸውን 17ና 30 ዓመታት  አይደለም አንድ ዓመት እንኳን ሳይፈጅ ድራቸውን እንደሚያጠፋቸው ያውቃሉና፡፡
የአንድን መንግሥት በይነ-ሕዝባዊነት (ዲሞክራሲያዊነት) ወይም አንባገነንነት የሚያረጋግጡት ሦስት ነገሮች ናቸው፡፡
1. የራሱ “መንግሥት” የተባለው አካል ሥራ ወይም ድርጊት
2. ስለ ሥርዓቱ ማንነት ሕዝቡ የሚገልጸው
3. የሦስተኛ አካላት ነጻና ትክክለኛ ምስክርነት ናቸው
እንጅ ራሱ “መንግሥት” ሊሆን አይችልም በራሱ ላይ የሚመሰክር የለምና፡፡ እንደዛማ ቢሆን ኖሮ ደርግም እኮ ዲሞክራሲያዊ መንግሥት ነበር፡፡ እስካሁንም እኔ አንባገነን መንግሥት ነኝ እንዲህ እንዲህ ዓይነት የመብት ጥሰቶችን፣ እረገጣዎችን፣ ሰቆቃዎችን፣ ወንጀሎችን በሕዝቤ ላይ እፈጽማለሁ ያለ መንግሥት በዓለም ላይ ኖሮ አያውቅም፡፡ በየትም ያለ መንግሥት በይነ ሕዝባዊ መንግሥት ሆኖ እያለ ሥራው ወይም ድርጊቱ የከፋ ሆኖ አያውቅም፣ በገዛ ሕዝቡ ላይ ሰቆቃ ወይም ግፍ አይፈጽምም፣ ሕዝቡም በሚፈጸምበት የከፋ የሰብአዊ መብት አያያዝ ወይም እረገጣ ለማማረር አይገደድም፣ ነጻ ሦስተኛ አካላትም በክስ የሚጠመዱበት ምክንያት አይኖርም፡፡
አንድ ሕዝብ በሰላማዊ ትግል ለውጥ የማምጣት ዕድል እያለው ሳይቸግረው የግድ ደም ተፋስሸ፣ ተቸግሬ ወጥቸ ወርጀ፣ አላስፈላጊ መሥዋዕትነት ከፍየ፣ ተዋግቸ ሊል የሚችልበት አንዳችም አመክንዮአዊ ማስረጃ የለም ኖሮም አያውቅም፡፡ ስለሆነም የሕዝቡ ትግል ምን ዓይነት መልክ ይኑረው የሚለውን ወሳኝ ጉዳይ የሚወስነው እራሱ ሥርዓቱ ማለትም የራሱ “የመንግሥት” አስተዳደራዊ ገጽታ ነው ማለት ነው፡፡
ብዙ ሰዎች ግፍና በደልን የመቃወም ለእውነትና ለፍትሕ የመቆም ሕይዎት የተለያዩ ተሞክሮዎችን አሳልፈዋል እኔን ጨምሮ፡፡ በዚህ የዜግነት ግዴታ በሆነው የሕዎት ተሞክሮ ብዙ ዓይነት አማራሪ ፈተና ይደርሳል ዋጋም ያስከፍላል በግሌ እያስከፈለኝም ይገኛል፡፡ ባለፉት ዘመናት ብዙ የተማረርኩባቸው ወቅቶች ቢኖሩም ግን አስቀድሜ ባደረኩትና ለዚህ የግፍ ቅጣት ባበቁኝ ነገሮች ሁሉ በአንዱም አልጸጸትም ለማንና ለምን እንዳደረኩት አውቃለሁና፡፡ ሥጋዬ ቢጎዳም የለመለመና የረሰረሰ ኅሊና እንጅ ወቃሽና ከሳሽ በጸጸት እሳት የሚለበልብ የሕሊና ጥያቄ ወይም ዕዳ የለብኝምና አልጸጸትም፡፡ ሆዴ ቢራብም ሕሊናዬ ግን የጠገበ ነው፡፡ ሰው ደግሞ ሰው እንጅ እንስሳ አይደለምና ክፉውና ጎጅው ረሀቡ የሕሊናው እንጅ የሆዱ አይደለም፡፡ በመሆኑም አልቆጭም፡፡ ከደረሱብኝ ፈተናዎች በወያኔ በቀጥታ ከደረሱብኝ ይልቅ በወያኔ ማስፈራሪያ ጭንቅላታቸው ከልክ በላይ በፍርሐት ከተሞላና ከተበከሉ ዜጎች የደረሰብኝ ይከፋል፡፡ በዚሁ ምክንያት ከ13 ዓመታት በላይ ከሠራሁበት ድርጅት ተሸኝቸ ያለምንም ሥራ ከመቅረት አንሥቶ ቅርቤ ናቸው ከምላቸው ሰዎች ዓይተው እንዳላዩ በመሆን የእግዚአብሔርን ሰላምታ እስከመነፈግ የደረሰ ፈተና፤ ከኔ ጋር በመቆማቸው ወያኔን ያስቆጣብናል ብለው በሚያስቡ ሁሉ ነገር ግን ደግሞ እንደማንኛውም ዜጋ የወያኔን ህልውና በማይፈልጉ ዜጎች ደርሶብኛል፡፡ የማደርገው ትግል ለእነሱ መሆኑን መገንዘብ ተስኗቸው ከዜጎች እንዲህ ዓይነት ፈተና ሲደርስ ምን ያህል ስሜትን የሚነካና ቅስም የሚሰብር ተስፋም አስቆራጭ እንደሆነ በቃላት ለመግለጽ እጅግ እቸገራለሁ፡፡
ለእንደነዚህ ዓይነት ዜጎች ባጠቃላይ ለሕዝቡ ማስገንዘብና በቅጡ እንዲያጤነው የምፈልገው ነገር ቢኖር ወያኔ በረሀ ትግል ላይ እያለ አሁንም ቢሆን በመላ ሀገሪቱ ያሉ ደጋፊዎቹ ወይም ወገኖቹ በያገባኛልና በባለቤትነት ስሜት በቁርጠኝነት በከፍተኛ ምሥጢራዊነት ይሆናል ተብሎ ሊገመት በማይቻል ድብቅነት ብልጠትና ብስለት የተሞላበት ሁለንተናዊ ድጋፍና እንቅስቃሴ ወያኔን ለሥልጣን እንዳበቁትና አሁንም በሥልጣን ላይ ለመዝለቅ ዋነኛ አቅሙ እነሱው መሆናቸውን እንዲያስብና ከዚህ ተሞክሮ ምን እንማራለን በማለት እራሱን እንዲጠይቅ ከራሱ ጋር እንዲመክር፤ የሚመኘውን ነጻነት ለማግኘትም እሰከ አሁን ባለው ሁኔታ እንደምናየው አማራጭና ተስፋ ስለሌለ በተሻለ ብቃት እራሱን በማዘጋጀት ነገሩን እንዲያውቅበት፤ ከሚጠላውም የግፍ አገዛዝ በተመኘው ፍጥነት ነጻ መውጣት እንዲችል እያንዳንዱ ዜጋ ባመቸው መንገድ እንዲታገል አበክሬ ማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡ ይህንን ለማድረግ ከላይ እንዳልኩት ብስለት ብልጠትና ቁርጠኝነት ይጠይቃል፡፡ ምናልባትም በአንድም በሌላም ምክንት የአንዳንዱ ዜጋ የዜግነት ግዴታ እንቅስቃሴ ቢደረስበትና እንደ ወንጀል ተቆጥሮ የሚጠየቅበት ሁኔታ ቢፈጠር የሚመጣውን ምንም ዓይነት ነገር በድፍረት ለመጋፈጥና ለሌላው አርዓያነት ባለው ጽናት ዋጋ ለመክፈል እራስን ማዘጋጀት ይጠይቃል፡፡
ምንጊዜም ቢሆን ታላቅ ድል ታላቅ ዋጋ ማስከፈሉ አይቀርምና፡፡ በዚህ ዓይነት ዝግጅትና አተገባበር መንቀሳቀስ ካልተቻለ የዘለዓለም ባርነት ውስጥ እንዳለ ይወቀው፡፡ መንቀሳቀስ ከቻለ ግን ሕዝቡ ትግሉን በጣም በአጭር ጊዜና በቀላሉ ለስኬት ማብቃት የሚችልበት በጣም ሰፊ ዕድልና አቅም አለው፡፡ አንድ ነገር ግልጽ ነው ሕዝቡ አገዛዙን እጅግ ተጸይፎታል ጠልቶታል እንዲወድቅለት እንዲወገድለትም በእጅጉ ይፈልጋል፤ ወገኔ እንግዲውስ ይሄ ከሆነ ፍላጎታችን ፍላጎታችንን ልናሳካ የምንችለው ቁርጠኝነት ድፍረት ብስለትና ብልጠት የተሞላበት ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ስናደርግ ጊዜ ብቻና ብቻ ነው፡፡ እንደ ጋንዲ ወይም እንደ ማንዴላ እንደ ቸጉቬራ አልላቹህም፡፡ ነገር ግን አገዛዙ እንደተወልን እንድናደርገው እንዳስገደደን አማራጭ ሁሉ እንጅ፡፡
struggle2የአንድ ለእናቱን የመይሳውን መንፈስ ግን ታጠቁ፡፡ ትልቁ ስንቃቹህ እሱ ይሁን፡፡ ባልተሰጠ ወይም በሌለ መንገድ ለመሄድ የሚፈልግ የሚሞክር ካለ ይሄ የሀገርና የትውልድ ኪሳራና ብክነት ነው፡፡ ከዚህ የባሰ ጅልነትም አለ ብየ አላስብም፡፡ ሰላማዊ የለውጥ አማራጭ መንገድ የሌለ ያልተሰጠ የተዘጋ ሆኖ እያለ ባለው አገዛዝ ሀገርና ሕዝብ እየጠፉ እየወደሙ እየፈራረሱ እየተሰቃዩ “አይ በቃ ከሰላማዊ አማራጭ ውጪ ሌላ አማራጭ ተገቢ አይደለም” ብሎ እጅና እግርን አጣምሮ የሀገርንና የሕዝብን ሞትና ጥፋት በዝምታ ለመመልከት መምረጥ ፍጹም ኃላፊነት የጎደለውና ያልበሰለ ኢትዮጵያዊም ያልሆነ አስተሳሰብ ነው፡፡ ሀገራችን በነጻነቷ ህልውናዋ ተጠብቆ ከእኛ የደረሰችው በዚህ ፈጽሞ ዋጋ ለመክፈል በማይፈልግ ሽባ አስተሳሰብ አይደለም፡፡ ይሄ የመከኑና ፈሪነታቸውን እራስ ወዳድነታቸውን በሰበብ መደበቅ የሚፈልጉ ዜጎች አገደኛ አስተሳሰብ ነው፡፡ ሀገርና ሕዝብ ሲጠፉ ዝም ብለን እንመልከት ማለት ታዲያ ምን የሚሉት ብስለት ነው ወገኔ?
ለ23 ዓመታት ያልተሰጠ ያልተፈቀደ ዕድል ከዚህ በኋላ ይሰጣል ይፈቀዳል ብላቹህ ታስባላቹህ? ነው ወይስ ለ23 ዓመታት ተታልላቹህ ተጃጅላቹህም አሁንም የማትነቁ ተላላና የዋሀን ናቹህ? በእነዚህ ሁሉ ዘመናት ለወያኔ የፕሮፖጋንዳ (የልፈፋ) ፍጆታ መጠቀሚያ ከመሆን የዘለለ ምን ትርፍ አስገኛቹህ? በዚህ ንቃት ነው አሁን ሀገር እንመራለን ብላቹህ የተሰለፋቹህ? በዚህ ወቅት ደግሞ የወያኔ ባለሥልጣናት በወንጀል በግፍና በሀገር ክህደት እስከ አፍንጫቸው የተነከሩበት ወቅት በመሆኑ ከመቸውም ጊዜ በላይ በሥልጣን መቆየታቸውን የሚፈልጉበት ወቅት ነው፡፡ ለ23 ዓመታት በእብሪትና በማናለብኝነት በሠሩት ሁሉ ለፍርድ እንደሚቀርቡ ጠንቅቀው ያውቁታልና፡፡ በመሆኑም በሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር መንገድ ከወያኔ ሥልጣንን መረከብ የሚቻልበት ዕድል ጨርሶ ዝግ ነው፡፡
እናም ሕዝቡ በዚሁ በተተወልን የትግል አማራጭ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ራሱን አነቃቅቶ ሥራውን ይሥራ፤ ነገ ሳሆን ዛሬ ከዛሬም ከአሁኑ ሰዓት ጀምሮ፡፡ ይሄንን ማድረግ በጀመረ ጊዜና በቁርጠኝነት በተንቀሳቀሰ ቁጥር የዛኑ ያህል ነጻነቱን ወደ ራሱ እያቀረባት እየሳባት መሆኑን ይወቅ፤ በዚህም ይደሰት ይጽናና፡፡ ይሄንን ባላደረገ ጊዜ ደግሞ ውጤቱ የዚህ ግልባጭና እጅግ የከፋ የማይወደውም መሆኑን ይወቅ፡፡ ነገር ግን ሕዝቡ ማድረግ ያለበትን ዐውቆ ትግሉን በቀጠለ ጊዜ እራሳቸውን ግልጽ ይፋ አውጥተው በተለያየ መንገድ ሥርዓቱን እየታገሉ ያሉ ዜጎች ከሚያገኙት ዘርፈ ብዙ ድጋፍ በበለጠ ዜጎች በዚያ የመነቃቃት ደረጃ መንቀሳቀሳቸው ከፍተኛ የሆነ ብርታት ጉልበትና ወኔ ይሰጣቸዋል፡፡ “ለማንና ለየትኛው ወገን ብየ ነው በከንቱ የምደክመው” የሚለው ቀቢጸ-ተስፋ አይፈታተናቸውም፡፡ ከፍተኛ መነቃቃት ያገኛሉ፡፡ በዓለማችን ታሪክ የትኛውም የትግል እንቅስቃሴ ከዚህ ውጭ በሆነ መንገድ ለስኬት በቅቶ አያውቅም፡፡ ምኞት ብቻ ከሆነ ግን ውጤቱም እንደምኞትነቱ ሁሉ ምናባዊ ወይም ቅዥት ብቻ ነው የሚሆነው፡፡ የሚጨበጥና በዓይን የሚታይ ነገር አይወጣውም፡፡ በመሆኑም ሕዝቡ ለራሱ ነጻነት ራሱ ካልተሳተፈ በስተቀር የዳር ተመልካች ሆኖ በጥቂቶች እንቅስቃሴ የሚመጣ ምንም ዓይነት ነጻነት ወይም ስኬት አይኖርም፡፡
ሕዝብ ያልተሳተፈበት ትግል ወይም እንቅስቃሴ በየትም ሀገር ለስኬት በቅቶ አያውቅምና፡፡ ይሄንን ከተረዳን የሚከፈለውና የግድ መከፈል ያለበት መሥዋዕትነት በተከፈለ ጊዜ የመጨረሻው ግብ ሀገርንና ሕዝብን ነጻ ማውጣቱ በጣም በተፋጠነና ቅርብ በሆነ ጊዜ እውን ይሆናል፡፡ የሀገራችን እጣ ፋንታ በዚህ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ይሄንን ማድረግና መላውን ሕዝብ በዘር በሃይማኖት በመደብ ሳይለያይ በማሳተፍ ሀገሪቱ እንድትጠቀም የሚፈቅድ በይነ-ሕዝባዊ (ዲሞክራሲያዊ) መንግሥት መመሥረት የቻልን ጊዜ ሀገራችን በዓለም ታይቶ በማይታወቅ እጅግ አስደናቂ ፍጥነት የማደግና ትንሣኤዋን የማረጋገጫ አቅም፣ ዘርፈ ብዙ የሆነ እጅግ ሰፋፊ ዕድሎችም አሏት የሕቧ ወኔ ትልቁ አቅሟ ነው ይህ ሕዝብ ሌሎች ሀገራት የያዙትን የመልካም አስተዳደርና በይነ ሕዝባዊ የመንግሥት ሥርዓት ቢያገኝ ባለው የሀገር ፍቅርና ወኔ የት ሊደርስ ይችል እንደነበር ሳስብ ቁጭት ያንገበግበኛል፡፡ ይሄ ሳይሆን ቀርቶ እንደ እስካሁኑ ሁሉ አገዛዙ በየጊዜው እንደፈለገ ማነቆውን ወይም ሸምቀቆውን እንዲያጠብቅብን ከፈቀድን ግን ማነቆው እየጠበቀ በሄደ ቁጥር እስትንፋሳችን ድንገት ታንቃ ለሕልፈት መዳረጋችን አይቀሬ ይሆናል፡፡ ሄንን የጥፋት ውጤት የሚፈልግ አንድም ዜጋ ይኖራል ብየ አልገምትም፡፡
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
እውነታው ይሄ ከሆነ ደግሞ እንዴት ነው ታዲያ ነቃ ነቃ ነቃ ነቃ ነዋ!! የምን መንገላጀጅ  የምን ማንቀላፋት ነው? ለመበላት??? እባካቹህ ከዶሮ እንኳን አንነስ፡፡ ዶሮ እግሩን ብታሥሩት የታሰረበትን ገመድ በአፉ እየነቆረ ለመፍታት ጥረት ከማድረግ አያርፍም፡፡ መብላትን ሁሉ ይረሳል፡፡ እንዴት ከዶሮ እንኳን እንነስ? ኧረ እባካቹህ እንፈር? ይሰማን? የመጨረሻ ወረድን እኮ! ምንም ቢያደርጉት የማይሰማው በድን እሬሳ ሆንን እኮ! እንደዚህ ሆነን እራሳችንን አመቻችተን ሰጥተን ምንም ቢያደርጉን በእነሱ ይፈረዳል እንዴ? ሰው እንዴት ለሆዱ ብሎ በዚህ ደረጃ ማንነቱን ያዋርዳል? ለሰው ልጅ እንደ ሰው ከሆዱና ከነጻነቱ ከክብሩ ከማንነቱ ማን ይበልጥበታል? ኧረ ሀፍረት ይሰማቹህ? እንዴ! ምንድን ነው የሆናቹህት? በተለይ የተማርን ነን የምትሉ ወገኖች ላልተማረው ወገናችን መጥፎ ምሳሌ ሆናቹህ እያሰናከላቹህብን ነው እባካቹህ? ነጻነታቹህን ክብራቹህን ማንነታቹህን አስቀድሙ ተባለ እንጅ አትብሉ መቸ ተባለ? እንደ እናት አባቶቻችን በነጻነታቹህ አትደራደሩ ተባለ እንጅ እያማረጣቹህም ቢሆን አትብሉ አትጠቱ ማን አለ?
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

Thursday, July 10, 2014

መንግስታዊ ሽብርተኝነትን የሚሸከም ትከሻ አይኖረንም!!!

July10/2014
image

















ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
ሀምሌ 3/2006ዓ/ም

የህወሓት/ኢህአዲግ አገዛዝ በኢትዮጵያ ስልጣን ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ዜጎችን በማፈንና በማሰቃየት ብሎም በመግደል የአፈና አገዛዙን ለረጅም ጊዜ ሲያራምድ መቆየቱ ዓለም የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡ በተለይም ባለፉት 10 ዓመታት የህዝብን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማፈን እስራትና ግድያውን ህጋዊ ለማስመሰል የተለያዩ አፋኝ አዋጆችን አውጥቷል፡፡ እነዚህን አዋጆችንም ተገን አድርጎ በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና አባለትን፣ ጋዜጠኞችንና ጦማርያንን፣ እንዲሁም የእምነት ተቋማት መሪዎችን እና በአገዛዙ ላይ ጥያቄ የሚያነሱ ዜጎችን ማሰሩን፣ ማሰቃየቱንና ግድያውን ተያይዞታል፡፡ በህገ መንግስቱ የተካተቱ የሰብዓዊ መብቶችንና ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን በሙሉ የሚጥሰውና የአምባገነንነት ስልጣኑን ለማራዘም ሲል ያፀደቀው የፀረ-ሽብር አዋጅ ከፀደቀበት እለት አንስቶ ኢህአዴግ ለስልጣኔ ያሰጉኛል የሚላቸውን ፍፁም ሰላማዊ ታጋዮችንና ህገ መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው በድፍረት የፃፉ ጋዜጠኞችን ብሎም የእምነት ነፃነታችን ይከበር ብለው የጠየቁ የሀይማኖት መሪዎችን በጠራራ ፀሃይ ያለምንም ወንጀል በዚሁ ህገ ወጥ አዋጅ ‹‹የፀረ ሽብር ግብረ ሀይል›› በሚባል ማንነቱ በማይታወቅ የጨለማ ቡድን ወደ እስር ቤት እያጋዘ ይገኛል፡፡

ይህን የሚያጋልጡ ሚዲያዎችንም ለማፈን እስር ቤቶችን ጨምሮ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር እያፈሰሰ የአየር ሞገድ ያውካል፤ በዚህ ሳያበቃ በሀገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን የሚያሰሙ ፖለቲከኞችን ለማሸማቀቅ እንደ ኢሳት ያሉ ሚዲያዎችን የአሸባሪ ልሳን ብሎ በመፈረጅ ሚዲያውን የሚጠቀሙትን ደግሞ ከአሸባሪዎች ጋር ንክኪ እንዳላቸው አድርጎ መወንጀሉን ቀጥሎበታል፡፡ እንደሰማያዊ እምነት ማንም አካል መልእክት የሚያስተላለፍበትን የሚዲያ ተቋም ሊመርጥለት እንደማይችል መንግስት እንዲገነዘበው ከዚህ በፊት በግልፅ ያሳወቀ ሲሆን አሁንም ፓርቲው በዚሁ የፀና አቋሙ እንደሚቀጥል በድጋሚ ይገልፃል፡፡

ባጠቃለይ የዚህን ገዢ አካል የእውር ድንብር ሀገር የማስተዳደር ጉዞ ለመታገል በርካቶች በሰላማዊ መንገድ እየተንቀሳቀሱ ቢሆንም በህወሓት/ኢህአዲግ ግፍና መከራ ተገፍተው ስርዓቱን በሃይል እናስወግዳለን ብለው ሀገር ጥለው የተሰደዱ ዜጎችም እንዳሉ ይታወቃል፡፡ የህወሓት/ኢህአዲግ ማናለብኝነትና የስልጣን ጥመኝነትም በግለሰቦች ላይ ከሚያስከትለው ማህበራዊ ቀውስ በላይ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ አለመረጋጋትን አስከትሏል፡፡ በአሁኑ ሰዓትም ይህ ገዢ ፓርቲ የፈጠረው ስርዓት የሀገሪቷን ሰላማዊ የፖለቲካ ምህዳር በማጥበብ ሀገራችንን ወደ አልተፈለገ አለመረጋጋትና ቀውስ እየመራት ይገኛል፡፡ፓርቲያችንም እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትና ሌሎችም በቅርቡ እየተፈፀሙ የሚገኙ ህገ ወጥ ድርጊቶች ስላሳሰበው ይህን መግለጫ ለማውጣት ተገዷል:-

1. ሰኔ 16 2006 ዓ.ም የየመን መንግስት የዓለም አቀፍ ስምምነቶችንና ድንጋጌዎችን በመጣስና በሰው ሀገር የውስጥ ጉዳይ በመግባት የአማፂ ቡድን ግንቦት ሰባት ዋና ፀሃፊ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን መያዟ ይታወሳል፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ ለህወሓት/ ኢህአዴግ ተላልፈው መሰጠታቸውን ከ16 ቀናት በኋላ መታወቁና ይህንንም ሁለቱ ሀይሎች ማመናቸው ተሰምቷል፡፡ ነፃነት በሌለበት ሀገር ዜጎች ሰብዓዊ ክብራቸውን ለማስጠበቅ የሚያደርጉት ጥረት የሌሎች ሀገር መንግስታት የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት በዓለም አቀፍ ስምምነቶችም ሆነ በተለይ በሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት ላይ ከፍተኛ ጥላ የሚያጠላ መሆኑን ግንዛቤ አለመወሰዱ እጅግ የሚያሳዝን ድርጊት ነው፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከተያዙ በኋላ ላለፉት 16 ቀናት በምን አይነት ሁናቴ እንደቆዩ ህዝብና ቤተሰቦቻቸው እንዲያውቁት አለመደረጉ፤ ስለ አያያዛቸው ሁኔታም በማህበረሰቡና በፓርቲያችን ውስጥ ከፍተኛ ጥርጣሬ እንዲኖር አድርጓል፡፡ሰማያዊ ፓርቲ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሰብዓዊ አያያዝ እያሳሰበው ህወሓት መራሹ የኢህአዴግ አገዛዝ አያያዛቸውን ግልፅ እንዲያደርግ ሰብዓዊ ክብራቸውም እንዲጠበቅ በጥብቅ ያሳስባል፡፡
2. በዚሁ ሳምንት ገዢው ፓርቲ ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ የአምባገነኑን መንግስት ህወሓት/ኢህአዲግን ሲታገሉ የነበሩ ፖለቲከኞችን በስመ አሸባሪ ከያሉበት እየለቀመ ህገ-ወጥ እስራት መፈፀሙ ይታወቃል፡፡ ህወሓት/ኢህአዲግ ይህ ግብታዊ ተግባሩ ምንም እንኳን አዲስ ባይሆንም በአሁኑ ወቅት ለውጥን ለማምጣት በቆራጥነት እየታገሉ ያሉ ሰላማዊ ታጋዮችን ማሰሩ በሀገር ውስጥ በህጋዊ መንገድ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ፓርቲዎችን ከአማፂ ቡድኖች ጋር ግንኙነት ያላቸው በማስመሰል ሰላማዊ ትግሉን ለማዳከምና መጪውን 2007 ዓ/ም ምርጫ ያለ ተቀናቃኝ ለማለፍ የሚደረግ ህገ ወጥ እንቅስቃሴ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ የፓርቲያችን ብ/ም/ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆነው አቶ የሺዋስ አሰፋ በሰላማዊ ትግሉ በቁርጠኝነት እየተሳተፈ ባለበት ሁኔታ ለእስር መዳረጉ፤ የአንድነት ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው፤ የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ምክትል ሀላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ከፍተኛ የህዝብ ንቅናቄን በመፍጠር ላይ ያለው የአረና /ትግራይ/ ፓርቲ አመራር አባል የሆኑትን አቶ አብረሃ ደስታ ለእስር መዳረጋቸው ህወኃት/ኢህአዴግ የመጨረሻው መጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱን ያረጋግጣል፡፡ በመሆኑም አገዛዙ እያካሄደ ያለውን መንግስታዊ ሽብር አቁሞ ለሀገርም ሆነ ለራሱ የሚበጀውን መንገድ እንዲከተል እያሳሰብን የታሰሩት የፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን፡፡

በመጨረሻም ፓርቲያችንን መንግስት እያደረገ ያለው ሽብርን የመንዛትና ህግን የመጣስ ተግባሩ መቼም ቢሆን ከሰላማዊ ትግሉ እንደማያቆመውና ሰላማዊ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል በአፅንኦት እየገለፀ እነዚህንና ከላይ የተጠቀሱትን የገዢውን ፓርቲ መርህ አልባነት፣ ህገ-ወጥነት እና የለየለት አምባገነንነትን አሁን ካለው ነባራዊ እውነታ ጋር አጣምሮ የትግል ስልቱን ደረጃ ከፍ ወዳለ ምዕራፍ ማሸጋገር እንዳለበት አምኗል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በኋላ ለምናደርጋቸው ሀገር አቀፍ ንቅናቄዎች መላው የሀገሪቱ ህብረተሰብ በንቃት ተዘጋጅቶ እንዲጠብቅ ጥሪውን እያስተላለፈ ለዚህም ቁርጠኛ አመራር ለመስጠት ዝግጁነቱን ለመግለፅ ይወዳል፡፡በዚህ አምባገነንነትን ለመታገል በሚደረገው ንቅናቄም በሀገር ውስጥ የሚገኙ ህጋዊና ሰላማዊ ፓርቲዎች፤አለም አቀፍ ተቋማት፤የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፤ሲቪክ ማህበራት፤መላው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከሰላማዊ ትግሉ ጎን በጋራ እንድንቆም እንጠይቃለን፡፡

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር
ሰማያዊ ፓርቲ
ሀምሌ 3/2006ዓ/ም

2nd Letter to H.E. Field Marshall Abdu Rabu Mansour Hadi President Republic of Yemen

July10/2014

July 7, 2014
H.E. Field Marshall Abdu Rabu Mansour Hadi
President Republic of Yemen Sana’a, Yemen
Re: Extradition of Andargachew Tsege, Secretary General of Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy from Yemen to Ethiopia
Your Excellency:
We are writing to you condemning in the strongest words possible the deplorable actions taken by your government to abduct and then extradite Andargachew Tsege, to the minority ethnic dictatorship in Ethiopia. On July 1, 2014, we had written a letter to you expressing our grave concern over the illegal abduction and detention of Andargachew Tsege while in transit at Sana’a International Airport on June 23, 2014.
In our letter dated July 1 that was hand delivered to your embassies around the world. it was made abundantly clear that Mr. Tsege a well-known pro-democracy icon and human rights advocate in his ancestral homeland, Ethiopia, presented no threat, what so ever, to Yemen or to the Yemeni authorities.
We had stated in the letter that the continued illegal detention of Mr. Tsege, a renowned critic of the Ethiopian government is politically motivated and against international law. We had also requested that you use the powers vested in your office to stop any illegal renditions the regime in Ethiopia may have requested.
It was explained in that letter that Mr. Tsege was imprisoned in Ethiopia for his political activities during the ill-fated national election of 2005 and had escaped recent assassination attempts by the tyrannical regime whose brutality, is well documented even by the United States State Department.
It is an affront to civilized society that Yemen has blatantly abrogated the doctrine of non-refoulement, now recognized as a norm of customary international law. Your government handed Mr. Tsege over to the security forces of the minority regime of the Tigrai People’s Liberation Front (TPLF) whose persecution of Ethiopian critics at home and in exile is well documented.
The brazen action of your government which defied International law, morality, and human decency, threatens to permanently impair the positive and historical relationship between the Ethiopian people and the Yemeni people. Nothing that Yemen can do will ever repair the damage that has already been done. Make no mistake that we will hold the government of Yemen responsible for the danger to the life and physical integrity of Andargachew Tsege.
Sincerely,
Berhanu Nega, Ph.D.
Chairman Ginbot 7 Movement for Justice Freedom and Democracy

ፋሽስታዊ ፕሮፖጋንዳው እና ምላሻችን!

July10/2014

ፋሽስታዊ ፕሮፖጋንዳው እና ምላሻችን!( pdf )

ሐምሌ 3 ቀን 2006 ዓ.ም.
ዘረኛውና ፋሽስታዊ ወያኔ፣ የኢትዮጵያዊያንን የትግል መንፈስ ለመስበር እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ለነፃነትና ለፍትህ የሚያደርገውን ትግል ወኔ ለመስለብ ያቀደበትን የመጀመሪያውን ፕሮፖጋንዳ ለቀቀ። የህግ ልጓም የማያውቀው ፋሽስት በግፍ የያዛቸውን ሰዎችን እይስሙላው ፍርድ ቤት እንኳን ከመቅረባቸው በፊት “ወንጀለኛ” እያለ እንዲህ ዓይነቱ ፕሮፖጋንዳ እንደሚነዛባቸው ተደጋግሞ የታየ በመሆኑ ይህ ፕሮፖጋንዳ የሚጠበቅ ነበር። ሆኖም ግን ፕሮፖጋንዳው ያዘጋጁ ሰዎች ተስፋ ያደረጉትን ውጤት ያመጣ አልሆነም። ወደፊት ደግሞ ሌሎች ሙከራዎች ይደረጉ ይሆናል፤ ውጤታቸው ግን ከዚህኛው የተለየ እንደማይሆን ይገመታል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ከኢቲቪ የእውነት ጥፍጣፊ እንኳን እንደማይገኝ ያውቃል።
በአሁኑ ተቆራርጦ በተለጣጠፈ ፊልም በታጀበው ፕሮፖጋንዳ ውስጥ፣ መሪያችን አንዳርጋቸው ጽጌ በምግብና ውሀ እጦት ብቻ ሳይሆን በተፈጸመበት የተለያዩ የማሰቃያ ወንጀሎች ብዛት አካሉ መዳከሙ ይታያል። ያም ሆኖ ግን ከእሱ ወጥተው እንድንሰማቸው የተደረጉት ቃላት የመንፈሱን ጥንካሬ ገላጮች ናቸው። እሱ ሥራውን መጨረሱንና በዚህም ምክንያት ህሊናው የተረጋጋ መሆኑን ነው የሰማናቸው ቃላት የነገሩን። በዚህ አጭር አጋጣሚ እሱ ግዴታውን ማጠናቀቁ፤ ሀገራችን ከወያኔ ፋስሽቶች ነፃ የማውጣት ኃላፊነቱ በእኛ ትከሻ ላይ መውደቁን ነገረን። ለዜናው ማጀቢያነት የገቡት ፎቶግራፎችም መሪያችን ፈታኝ በሆነ የተፈጥሮ አካባቢ የከፈለውን መስዋዕትነት የሚመሰክሩ ሆነው ተገኙ።
ጀግናው አንዳርጋቸው ጽጌን በተጎሳቆለ ሁኔታ ማየት ስሜትን የሚጎዳ ቢሆንም የመጀመሪያው ስሜት ካለፈ በኋላ ከፊልሙ በአዕምሮዓችን የሚቀረው ከላይ በአጭሩ የተገለፁት ጥንካሬውና ኃላፊነትን ወደ እኛ በይፋ ያስተላለፈበት አጋጣሚ መሆኑ ነው። በዚህም ምክንያት በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የተሠራው የመጀመሪያ በምስል የተደገፈ የወያኔ ፕሮፖጋንዳ ከታለበት ዓላማ በተፃራሪ የወያኔን ሹማምንት አውሬነትና የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ትልቅነት አሳይቷል።
ይሁን እንጂ ከላይ እንደተገለፀው ይህ የመጀመሪያ የፕሮፖጋንዳ ሥራ እንጂ የመጨረሻው አይደለም። የማስተዋል ችሎታ ያነሳቸው የወያኔ ፕሮፖጋንዲስቶችም ፊልማቸው ቁጣን ማባባሱ ሲያዩ ፈጥነውም ይሁን ዘግይተው ከዚህ በተለየ አቀራረብ መመለሳቸው አይቀርም። ስለሆነም የኢትዮጵያን ሕዝብ ከወያኔ የጅል ፕሮፖጋንዳ መንፈሱን እንዲጠብቅ ማሳሰብ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል። የወያኔ ፕሮፖጋንዲስቶች አሁን የደረሰባቸውን ኪሳራ ለማካካስ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ያላለውን አለ ይሉን ይሆናል፤ ቃላትን ፈጥረው እሱ የተናገራቸው ያስመስሉም ይሆናል። የቻይና ቴክኖሎጂ ከወያኔ ድድብና ጋር ሲደባለቅ ምን እንደሚያመጣ አስቀድሞ መገመት ያዳግታል። ኢቲቪ ለዘመናት የተካነበትን ውሸት የመፈብረክ ክህሎትን ወደ ላቀ ደረጃ የማሳደግያ አጋጣሚ አድርጎ ሊጠቀምበት ስለሚችል መንፈሳዊ ዝግጅት ማድረግ ተገቢ ነው።
ከዚህ በተረፈ የኢትዮጵያ ሕዝብ በጥብቅ ሊያስብበት የሚገባ ጉዳይ አለ።
ጀግናው፣ ብልሁና አስታራቂው አንዳርጋቸው ጽጌ ኢትዮጵያን በማጥፋት ዓላማ ባበሩ፤ ዘርፈውና በልተው በማይጠግቡ፤ የንፁሃንን ደም መጠጣት በለመዱ ዘረኞችና ፋሽስቶች መዳፍ ውስጥ ነው። ለዚህ ምላሻችን ምንድነው? ገና ከአሁኑ እንደታየው በሰላማዊ መንገድ ሥርዓቱን ለመገዳደር የደፈሩ ወጣቶችን ለማሰር አንዳርጋቸው ጽጌን ሰበብ ሲያደርግ የኛ ምላሽ ምንድነው? አገራችን ያፈራቻቸው ምርጥ ዜጎች በሙሉ ወይ ታስረው አልያም ተሰደው ሲያልቁ እያየን ምን እየሠራን ነው? ነፃነታችንና አገራችን ለህወሓት ዘረኞች አስረክበን እንቀመጣለን? በጭራሽ!
አንዳርጋቸው ጽጌ የተመቻቸ ኑሮዉንና ልጆቹን ጥሎ ለነፃነቱና ለሀገሩ የዘመተ ጀግና ነው። ከእኛም የሚፈለገው ይህንኑ ነው። ጀግናችንን ብቻ ሳይሆን አገራችንም ጭምር ከታሰረችበት ማስፈታት የምንችለው አንዳርጋቸው ጽጌ በተጓዘበት መንገድ ስንጓዝ ነው። ለዚህ የተዘጋጀ ሁሉ “አለሁ!” ይበል።
ማንም ዝርዝር መመሪያ በሬድዮ ወይም በቴሌቪዥን እንዲነገረው አይጠብቅ። የቆረጠና የመረረው ጀግኖች የሚገኙበት ድረስ ሄዶ ይቀላቀል። ከልቡ የቆረጠና ጥቂት ፍለጋ ያደረገ ሁሉ መንገዱን አያጣም።
  1. ቀደም ሲል ንቅናቄዓችን – ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ – ያወጣውን የመጀመሪያ እርከን የትግል ጥሪ ተግባሪዊ ለማድረግ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በቁርጠኝነት በተግባራዊ ትግልቶች ይመንዘሩት፤
  2. የተቆጣ፣ ጥቃት፤ ውርደት፤ ግፍ የመረረው ሁሉ፤ ለነፃነቱ ግድ ያለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ የስነ ልቦና ዝግጅት ያድርግ፤ ከወያኔ ሰላዮች ራሱን ተከላክሎ በያለበት በጥብቅ ከሚያምናቸው ጋር በመሆን በየአካባቢው በቡድን በቡድን ይደራጅ፤ በወያኔ ቀንደኛ ሹሞችና ወንጀለኞች ላይ ይሰልል፤ መረጃዎችን ለንቅናቄዓችን ይላክ።
  3. በየአካባቢያችን የወያኔን ፋሽስቶችን የሚያሸማቅቁ፣ በሁለተናዊ መልኩ (በስነልቦና፤ ማኅበራዊ ተጽዕኖ በመፍጠር፣ በኢኮኖሚ) ጉልበታቸውን የሚቦረቡሩ፣ የሚያድክማቸው፣ ውስጣቸውን የሚሸረሽራቸው ሥራዎችን በቁጭትና በእልህ ሳናሰልስ ተግባራዊ እናድርግ።
  4. በሕዝብ ጎራ ሳይሆን በጥቂቶቹ በወያኔ ፋሽስቶች ጎራ ፍርሃትና ብርክ የሚፈጥሩ የጀግንነት ሥራዎችን በቡድን በመደራጀት በመላው ዓለምና በኢትዮጵያ ውስጥ በብልሃት፣ በጥናትና በስልት በመተግበር ሕዝባዊ እምቢተኝነት እሁን እናድርግ፡፡
  5. ሁሉም ኢትዮጵያዊን የሚቻለውን ሁሉ ትንሿንም ጠጠር ብትሆን ወያኔና ጭፍሮቹ ላይ እንወርውር።
  6. በደጀን የተሰለፈው ኃይል ደግሞ የዘማቹን ስንቅ በማዘጋጀት በገንዘቡ፤ በጉልበቱ፤ በመረጃ ይተባበር።
የአገር ማዳን የክተት ዘመቻ ላይ ነንና በእያንዳንዱ ጉዳይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ሳንጠብቅ ቀበቶዓችንን አጠባብቀን እንነሳ። ድል እናደርጋለን!! አገራችን ከዘረኞችና ፋሽስቶች መንጋጋ መንጭቀን እናወጣታለን!!
ድል ለኢትጵያ ሕዝብ !!
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ

እንደ አመራር ከዚህ ስርአት እስር አይደለም ግድያዉንም የምንጠብቀዉ ነዉ፡፡

July 10/2014
ተክሌ በቀለ

ስንቱን ወጣት በቅርቡ ገድሎም የለ፡፡ጠላቶቼ ለሚለዉ ብቻ ሳይሆን ከራሱ የሚቃወሙትንና የሚያምኑቱንም ገዳይ ተፈጥሮ እንዳለዉ እድሜ ለእነ አስገደ ገ/ስላሴ አዉቀናል፡፡በቅርቡም ወጣቱ ዮናስ በላይ ያቅሙን አሳይቶናል( በዚህ አጋጣሚ በረታ ዮኒ)፡፡ለወንዙ ልጆችና ለጓዶቹም እንደማይሆን እናዉቃልን፡፡ዓረና እንደፓርቲ ከተቋቋመ ወዲህ ስንቱ ገበሬ በእስር እየተሰቃየ እንዳለ ፓረቲዉ እንደሌሎቹ እየጮኀ ሲሆን ባለጠመኔዉና እስክረቢቶዉ አብረሃ ደስታ በከፍተኛ አመራር ደረጃ ተጠቂ መሆኑ ነዉ፡፡ሃብታሙ አያሌዉና ዳንኤል ሽበሺ ፍጹም ሰላማዊ ታጋዮች ናቸዉ፤ሌሎችም፡፡እስሩ ቀጥሏል፤ሊቀጥል ይገባል፡፡ይህ ስርአት እስካለ ድረስ ማለቴ ነዉ፡፡ለዉጥ ፈላጊ ከሆነ ለመንም አይቀርለትም፡፡የአንድነትና መኢኣድ(ለግዜዉ ለያይቸ ልጥራቸዉ)፤የመድረክ፤የሰማያዊ፤የትብብርና ሌሎች ፓርቲዎች አመራርና አባላት (እባካችሁ እንወሃድ ወይእንተባበር!) ጠንክረን በመስራት የእስርን ፍርሃት እንደነ አንዷለም፤በቀለ፤ርእዮት፤እስክንድር….እንስበር!! ለመታሰር እንስራ
ልጆቻቸዉና ደጋፊዎቻቸዉ ይፈሩ፤በዉጭም ያላችሁም ኑና በሰላማዊ ትግል እየታሰርን ይህን ስርኣት እንለዉጥ፤እስክንድር እንዳለዉ ይሁን፤እስርበቱን እንሙላዉ፡፡ሃብታሙ አምነሃለሁ፤ህዉሓት/ኢህኣዴግ ይወድቃል! ለዉድቀት ስለሚሰራ!!!

Wednesday, July 9, 2014

ኢሕአዴጎች አብደዋል – አቶ ግርማ ሰይፉ በታሰሩ ወጣት ፖለቲከኞች ዙሪያ

July9/2014
የፓርላማ አባልና የአንድነት ከፍተኛ አመራር አባል አቶ ግርማ ሰይፉ የኢሕአዴግ መንግስት በሰላም የሚታገሉ ወጣት ፖለቲከኞችን የማሰሩን ጉዳይ እብድነት ብለዉታል።

«እነዚህ ሰዎች አብደው መሆን ይኖርበታል፡፡ ሀብታሙ አያሌውን ፖሊሶች ይዘውት እንደሄዱ ሰማው፡፡ ስልኩ ይጠራል ግን አይመልስም፡፡ የእነርሱን ሃሳብ የሚቃወም ሁሉ አሸባሪ እየመሰላቸው በሽብር እራሳቸውን እያናወዛቸው ያለ ይመሰለኛል፡፡ ሀብታሙን ሊያስሩት ይችላሉ በህዝብ ውስጥ ያለውን የነፃነት መንፈስ ግን ማስረ አይቻላቸውም፡፡ እልፍ አህላፍ የነፃነት ሰዎች ይፈጠራሉ፡፡ ለነገሩ የሚታሰሩ ንፁሃን ታሳሪዎች ሳይሆን አሳሪዎ በከፍተኛ የህሊና ስቃይ ውስጥ መሆናቸውን መረዳት አሰቸጋሪ አይደለም፡፡» ሲሉ ነበር አቶ ግርማ በፌስ ቡክ አስተያየታቸውን የሰጡት።
10528_100568456628045_5522392_a
«የዚህ ልጅ ነገር ሳያበሳጫቸው አይቀርም፡፡ ሰለማዊ ሰልፍ ላይ በባትሪ አንደሚሰራ ሳያርፍ ያጋልጣቸዋል፡፡ በየሳምንቱ ገበናቸውን በመፅኄት በጋዜጣ ያወጣል፡፡ በዓመት መጨረሻ ደግሞ ትምህርት ተምሮ በክብር በማዕረግ ይመረቃል፡፡ ኢዚህም እዚያም ያገኙታል ሁሉም ጋ ሲያወግዛቸው፤ በቃችሁ ሲላቸው ይሰማሉ፡፡ በቃቸው የሚላቸው ደግሞ እንደበቃቸው ስራቸው ሆኖ ያያቸው እርሱ መሆኑ ያበሳጫቸዋል፡፡ ሌላው በግምት አትችሉም ሲላቸው ሀብታሙ ግን አውቃችሀኋለሁ አትችሉም ይላቸዋል፡፡ በእውነት ነርቫቸውን ነው የነካው፡፡ የሚያጓጓው ግን ምን ብለው 28 ቀን የምርመራ ጊዜ ለመጠየቅ አሸባሪ እንደሚሉት ነው፡፡ ዛሬ ቄሱን አሸባሪ አሉ የሚለው ዜና አብርሃ ደሰታ ከመቀሌ ሹክ ብሎናል፡፡ ሀብታሙን ቢሉት አይገርምም፡፡ እንሰማለን፡፡ ተረኞች መዘጋጀት ነው፡፡» ብለው የጻፉት አቶ ግርማ የኢሕአዴግን የፖለቲክ ክስረትና የአቶ ሃብታሙን ታታሪነት የገለጹ ሲሆን፣ እርሳቸዉን ጨምሮ ሌሎች በሰላም የሚታገሉ ሁሉ፣ የሰላማዊ ትግል ለሚያስከፍለው እንዲዘጋጁ ጥሪ አቀርበዋል።
የሰላማዊ ትግል አልጋ በአልጋ እንደሆነ ለሚመስላቸውና በቀላሉ ተስፋ ለሚቆርጡ ወገኖች አቶ ግርማ ሰይፉን ጠንካራ ምክር ለግሰዋል። « ሰላማዊ ታጋዮች መንገላታት እና እስር አሰበውበት የገቡበት ነው፡፡ ምንም ጥርጥር የለውም ያማል ግን ይህን እመም ለመቻል ቁርጠኝነት ይጠይቃል፡፡ የሀብታሙ አያሌው ባለቤት ባለፈው ሳምንት አባቷን በድንገት በሞት ተነጥቃለች አሁን ደግሞ ባለቤቷ በግፍ ወህኒ ወርዶዋል ኮልታፋ ህፃን ልጅ ይዛ መከራዋን እንደምትገፋ ሀብታሙ ያውቀዋል፡፡ ሊያሞላቅቃቸው ቢፈልግ ግን ከኢህአዴ ደጅ ፍርፋሪ መልቀም የሚከለክለው አልነበረም፡፡ » ሲሉ ነበር በሰላምዊ ትግል ከአምባገነኖች ጋር ትንቅንቅ የየዙ ወገኖችን ጀግንነት ያስረዱት።
አቶ ግርማ ሲያጠቃልሉ « ውድ የትግል ጓዶች ከዞን ዘጠኝ ወደ ሌላ ዞን መሸጋገራችሁ ቢያሳዝነንም ፅናታችሁ ያበረታናል፡፡ ፅኑ፡፡ ለካ እነርሱ ይህን የማንበብ መብት የላቸው፡፡ በዞን ዘጠኝ የምትገኙ ሁሉ በርቱ ፅናቱን ይስጣችሁ ማለት የግድ ይላል» በማለት ትግሉን ከማፋፋም ዉጭ ሌላ አማራጭ እንደሌልም ለማሳየት ሞክረዋል።

Ethiopians voice their outrage after Yemen hands over political activist to Ethiopia

ESAT News
July 9, 2014

After Yemeni authorities have handed over Ethiopian-British rights activist and leader of the opposition Ginbot 7 Movement, Andargachew Tsige, to the “brutality and torture acclaimed” Ethiopian regime from its Sanaa airport two weeks ago, the angers and outrages of Ethiopians has been pouring. Those living in Ethiopia are calling to be shown the “the road to join the struggle for freedom” while Diaspora Ethiopians are organising and holding protests outside British and Yemeni Embassies.
ESAT has been receiving calls from inside and outside Ethiopia by angered fans, supporters and audiences since Andargachew’s arrest saying that they are ready to pay their souls as Andargachew did.
Most of them ask how they can join the struggle while others plead the Ginbot 7 leadership to inform them what kinds of measures they could take against the regime.
Last week Ginbot 7 stated that the struggle has grown to a new chapter called “We are all Andargachew Tsige”. The Movement said being Andargachew means “being humble and determined, being patient and bitter, being smart, wise and action orientated as him”.
Ginbot 7 said one of the main reasons that the regime focused on Andargachew is that he had been able to sterilise Woyane’s ethnic politics by forming action orientated cooperation with Oromo, Afar, Gambella, Ogaden and other ethnic organisations and movements.
It also stated that the main contributions in the efforts of removing this regime comes from people who have decided to give their lives, wrestle with them neck to neck and the actions of the people and forces; thus called on the youth to join the Movement.
Meanwhile, Ethiopians living in the U.S., U.K., Canada, Sweden, Switzerland, Germany and many other cities have protested outside Yemeni and British embassies. They have condemned Yemen for cooperating and handing over a sentenced human rights activist trespassing international law. The protesters also called on the U.K. government to press the Ethiopian regime to immediately release its citizen. Similar protests are scheduled to be held in other cities in Europe, Asia and the U.S.
There is an increasing call for opposition parties, groups and organisations to narrow their differences and stand together for change.

አንበሳውን በጅቦች ተከቦ አየሁት

July9/2014
ፋሲል የኔአለም
ኢቲቪ የአንዳርጋቸው ንግግር ነው ብሎ ያቀረበው ፊልም አስቂኝ ነው። እንደነ ቢቢሲ በኮርፖሬሽን ደረጃ ለመዋቀር በቃሁ የሚለው ድርጅት በሴኩርቲ ( በድብቅ )ካሜራ የተቀረጸ የደበዘዘና የተቆራረጠ ፊልም ሲያቀርብ ማፈር ነበረበት።
አንዳርጋቸው ከተያዘ 2 ሳምንታት አለፉ። ዛሬ በድብቅ ካሜራ ተቀርጾ የተላለፈው ፊልም በእለቱ ኢትዮጰያ ሲገባ የተቀረጸ ነው – አለማቀፍ ግፊት ቢበዛብን እናሳየዋለን ብለው ቀርጸው ያስቀመጡት ነው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ግን አንዳርጋቸው እያንዳንዷን ቀን በድብደባ እያሳለፈ ነው። ኢቲቪ ልብ ካለው አንዳርጋቸውን ላይቭ ያሳየን።
አንበሳው ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የሚውል አንድም ነገር አልሰጣቸውም። “እኔ ስራየን ጨርሼ ደክሞኛል፣ እረፍት እፈለግ ነበር” ነው ያለው፤ ይህንን ደግሞ ዶ/ር ብርሃኑ ና ንቅናቄው አስቀድመው ተናግረውታል- አንዳርጋቸው ስራውን በጊዜ አጠናቆና ሃላፊነቱን ለወጣት አመራሮች ሰጥቶ እሱ መጠነኛ የዲፕሎማሲ ስራ እየሰራ ነበር።
ህወሃቶች በደንፎ “የትግራይን ህዝብ ትጠላለህ?” ብለው ጠየቁት። “ለማንም ህዝብ ጥላቻ የለኝም” ብሎ መለሰላቸው። አንዳርጋቸው የትግራይን ህዝብ ከጉጅሌው እንለየው የሚል ጽኑ አቋም ነበረው፣ያንን ነው የደገመው።
የታዩትን ፎቶግራፎች ድሮም አውቃቸዋለሁ፤ ከላፕቶፑ የተወሰዱ ናቸው። በእዚህ እድሜው የአውሮፓ ህይወቱን ትቶ በዛ አይነት ህይወት ለመኖር መፍቀዱ የሚደነቅ ነው። የእኔንም ኮምፒዩተር በቫየረስ በከሉት እንጅ እነዚህና ሌሎች ፎቶዎችም ነበሩኝ።
ፈገግታና ደግነት ደግሞ ባህሪው ነው። ጠላቶቹን ሳይቀር በፈገግታው ይገላቸዋል።
ከሁለት ሳምንት ድብደባ በሁዋላ ለፕሮፓጋንዳ የሚሆን ነገር አለማግኘታቸው ሃረር ውስጥ በጅቦች ተከቦ አልበላም ብሎ ሲታገል የነበረውን አንበሳ አስታወሰኝ።
ኮራሁብህ ወንድሜ አንዲ።

ከልባቸው ደፋር የሆኑ የሀገሬን ልጆች ማየት በመጀመሬ ደስ አለኝ – ኤሊያስ ገብሩ

elias Gebru
ኤሊያስ ገብሩ
July9/2014
ፍኖተ ነፃነት
የሰሞኑ የኢትዮጵያችን ሁኔታ ሀዘን፣ ቁጣ፣ ንዴት፣ እልህ፣ ብሎም የደስታ ስሜትን የቀላቀለ ነበር፡፡ የእሰሩ ሁኔታ ቀጥሏል፡፡ ዛሬ እንኳን ከአንድነት ፓርቲ አቶ ሀብታሙ አያሌው እና ከሰማያዊ ፓርቲ አቶ የሺዋስ አሰፋ መታሰራቸውን ሰምተናል፣ አውቀናል፡፡ የዚህ መሰል አካሄድ ግን መዘዘን የሚስከትል ይመስለኛል፡፡
አሁን አሁን ሰዎች እንደጥጃ ከቤታቸው፣ ከየመንገዱ፣ ከሚሰሩባቸው ቦታዎች …እየተወሰዱ መታሰራቸው በሀገራችን እየተለመደ የመጣ አዲስ ክስተት ሆኗል፡፡ ሥልጣን በጨበጡ ኃይሎች ለነገሮች የሚሰጡት ምላሾች የእስር እርምጃ መሆናቸው ከቀጠለ ከትርፉ ይልቅ ኪሳራቸው ማመዘኑ አይቀሬ ነው፡፡ አይንም ጆሮም ያለው መንግሥት ይስማ!
‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ሰዎች ለምን ይፈራሉ?›› በማለት ራሴን ደጋግሜ የምጠይቅበት ጊዜ ነበር፡፡ አሁንም እጠይቅና የራሴን ምላሽ ለራሴ እሰጣለሁ፡፡ የምቀርባቸውን ሰዎች ጠይቄም ምክንያቱን ለመረዳት ጥረት አደርጋለሁ፡፡ ‹‹ፈሪ ለእናቱ›› የሚል መልስ አስተናግጄም አውቃለሁ፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ ግን ‹‹እመኑ እንጂ አትፍሩ›› ነው የሚለን፡፡
ግን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከልባቸው ደፋር የሆኑ ወንድ እና ሴት ኢትዮጵያዊ ወገኖቼን በድፍረት ብቅ ብቅ እያሉ ማየት በመቻሌ ደስ ብሎኛል፡፡
አሁን፣ ሕግን አክብሮ በድፍረት መንቀሳቀስ እንጂ ያለተፈጥሯችን መፍራት በብዙ ችግሮች ለተተበተበችው ሀገራችን አይጠቅማትም፡፡ ‹‹ፍትሕ አጥተናል››፣ ‹‹ተርበናል››፣ ‹‹ነጻነት አጥተናል››፣ ‹‹በኑሮ ተማርረናል››፣ … እያሉ የዳር ተመልካች መሆን መፍትሄ አይደለም፡፡ ‹‹ኢትዮጵኖች የጀግና ሕዝቦች ነን›› እንል የለ? ታዲያ ሕግን ተከትለን በተግባር እናሳየዋ!

ኢትዮጵያ ከዓለም ለምን ሁለተኛዋ ደሀ አገር ሆነች?

July 9/2014
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
መቀመጫውን በኢትዮጵያ ያደረገ አንድ ታዋቂ የአሜሪካ የዜና አውታር በቅርቡ ኮካኮላ በኢትዮጵያ እንዳይጠጣ በሚል ያሰራጨሁትን ጽሁፍ በማስመልከት የተሰማውን ቅሬታ አስመልክቶ አንድ የኢሜይል መልዕክት ላከልኝ፡፡ እንዲህ የሚል ጽሁፍ ጻፈ፣ “በድፍረት ልናገርና ሆኖም ግን ኮካኮላ እንዳይጠጣ ለማሳሰብ ስለተጻፈው ጽሁፍ ገቢራዊነት እምነት የለኝም፣ ይህንንም ጽሁፍ በማዘጋጀት በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ባለው ‘ሰይጣናዊ’ ገዥ አካል እና በ’ቅዱሳኑ በተባበሩት የተቃዋሚ ኃይሎች’ መካከል ባለው የፖለቲካ ውዝግብ በሚሊዮን ከሚቆጠሩ በጥቂቱ አንባቢዎችህን ሊያሳስት እንዲችል የታለመ ዓላማን ያዘለ ነው“ በማለት አስተያየቱን አጠቃሏል፡፡
ለዚህ አደናጋሪ የውጭ የዜና አውታር ቃል አቀባይ የሰጠሁት ምላሽ አጭር፣ ግልጽ፣ ፈጣን እና የማያወላዉል ነበር ፡፡ እንዲህ የሚል መልስ ሰጠሁት፣ “አዎ እውነት ነው፣ የራሰህ ጉዳይ ነው! በግልጽ ለመናገር እኔ በዚህ ጉዳይ አላዝንም፣ የገዥውን አካል ህሊና ቢስ አካሄድ በመከተል እንደ ገደል ማሚቶ ብትጮህ መብትህ ነው!!!“ በኢትዮጵያ የአንድ የጋዜጠኝነት የእውቅና እና የሙሉ ክብር ህልውና በመረጠው የቃላት አጠቃቀም እና እምነተቢስ የአዘጋገብ ዘይቤ ላይ የሚወሰን ከሆነ ድፍረት ማጣት እና አስመሳይነት እንደ እውነተኛ እና ገለልተኛ የጋዜጠኝነት ባህሪ የክብር መገለጫ ጸጋ ይሆናሉ፡፡
ይህ በድህነት ጥያቄ የቀረበው የትችት ጽሁፍ በኢትዮጵያ ያለውን ገዥ አካል፣ ተባባሪዎቹን፣ ደጋፊዎቹን እና የውስጥ እና የውጭ የፍልስፍናው ጠባቂ ተከራካሪዎቹን ሊያደናግር ሊያስከፋ ይችላል፡፡ እንዲህ ይሉም ይሆናል፣ “ይሄው ደግሞ የእዚህን ጭራቅ ገዥ አካል ስም ጥላሸት ለመቀባት ተነሳ፡፡ ለገዥው አካል ምክንያታዊነት ፍትህን አይሰጥም፣ እናም እስከ አሁን ድረስ ላከናወኑት ለማንኛውም ስራ በፍጹም እውቅና አይሰጥም፡፡“ “አገሪቱ ባለፉት አስርት ዓመታት አስመዘገበችው እየተባለ በየጊዜው ስለሚደሰኮርለት ተስፈንጣሪ የኢኮኖሚክ እድገት በማቀርበው የማስተባበያ አካሄድ የሆድ ቁርጠት ይይዛቸዋል፡፡“ ሁልጊዜ ሰኞ የማቀርባቸውን ትችቶቸ ለምን እንደማልረሳ እና አንድ ቀንም እንደማላሳልፍ ያላቸውን ቅሬታ ያሰማሉ፡፡
እውነታው ግን ምንም ይሁን ምን የፈለገው ነገር ይምጣ፡፡ እራሴን በሞራል ዝቅጠት ስር አለመደበቄ እና ለእራስ ጥቅም፣ ምቾት እና የሞራል ልዕልናን ባልተላበሰ መልኩ እያገለገለ ላለ ጋዜጠኛ የማላዝን በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል፡፡ ሰይጣንን አንደ መላዕክት ወደ ላይ ከፍ አድርጎ በማውጣት እና በማውረድ አላምንም፡፡ ያየሁትን እንደ አየሁት አድርጌ እናገራለሁ፡፡ ስልጣናቸውን ከህግ አግባብ ውጭ ለሚጠቀሙበት ለሌሎች ትክክለኛውን ንግግር ለማያቀርቡት እውነተኛ እና ቀጥተኛ የሆነውን ነገር እነገራለሁ፡፡
እንደዚሁም ሁሉ ትክክለኛ ያልሆኑ ነገሮችን ገለልተኛ በሆነ መልኩ አጋልጣለሁ፡፡ ለሰብአዊ መብቶች መጠበቅ፣ ለህግ የበላይነት መርሆዎች እና  ተግባራዊነት መቶ በመቶ ገለልተኛ ነኝ፡፡ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ገለልተኛ የሆነ አስተያየቴን እሰጣለሁ፡፡ በኢትዮጵያ ላይ የሚካሄዱ ነገሮችን ሁሉ በመጀመሪያ ጊዜ እንደ ህገመንግሰት የህግ ባለሙያ እና እንደ ፖለቲካ ሳይንቲስት የህገመንግስቱን መነጽር በማድረግ እመረምራቸዋለሁ፣ አገናዝባቸዋለሁም፡፡ በየጊዜው ወንዶቸም ሆኑ ሴቶች በሚያደርጓቸው አስደንጋጭ እና ሰይጣናዊ ስራዎች ሞራልን የሚመለከቱ ጉዳዮችን እመለከታለሁ፡፡ ድህነት የሁሉም ጭራቆች ሁሉ መሰረት እንደሆነ አምናለሁ፡፡ አሁን በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ለትውልድ የሚሸጋገር ጨለምተኝነትን፣ የሞራል የአካል ዝቅጠትን ትቶልን አልፏል፡፡ ሸክስፒር ጭራቃዊነትን በሚገባ በመገንዘብ በአንቶኒ በጁሊየስ ቄሳር በኩል እንዲህ በማለት ተናግሯል፣ “ሰይጣናዊ ስራ ሰሪዎቹ ሰዎች ካለፉ በኋላም ይኖራል፡፡ በጎው ነገር ከአጥንታቸው ጋር አብሮ ይቀበራል፡፡ ስለዚህ ከቄሳር ጋር ይሆናል፡፡ እንዲህ በማለትም በዚህ ላይ እጨምራለሁ፣ “ጭራቃዊነት በድል አድራጊነት ተንሰራፍቶ እንዲኖር የሚፈቅድለት ብቸኛው መንገድ ደጋግ ወንዶች እና ሴቶች ምንም ነገር አለማድረጋቸው እና አለመናገራቸው ነው፡፡ ስለሆነም ስለድህነት-ከድህነት ስለሚያተረርፉት እና ስለሚሰብኩት ሁሉ ድህነት በኢትዮጵያ ስላለው የሁሉም ጭራቃዊነቶች መሆኑን መናገር አለብኝ፡፡“
 ኢትዮጵያ  ከዓለም  ከመጨረሻዎቹ  ደሀ  አገሮች  ሁለተኛ  እንድትሆን  ያደረገሽንጡን  ገትሮ  የሚሰራ ጭራቃዊ  ኃይል 
ባለፈው ሳምንት የኦክስፎርድ የድህነት እና የሰብአዊ ልማት ተነሳሽነት ኦክስፎርድ/Human Development Initiative (OPHD) ዘርፈብዙ የድህነት መለኪያ (በቀድሞ ስሙ U.N.D.P Human Poverty Index) ለአራት ተከታታይ ዓመታት ባቀረበው ዘገባ መሰረት ኢትዮጵያ ከዓለም በድህነት ሁለተኛዋ አገር ሆናለች፡፡ ለዓመታት ሌሎች በርካታ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ደግሞ ከታች በድህነት አራንቋ ከተዘፈቁት አምስት የመጨረሻ አገሮች ውስጥ ኢትዮጵያ በድህነት ተተብትባ መያዟ ብቻ ሳይሆን በሰብአዊ መብት አያያዝ እና በሌሎች መለኪያዎችም ዝቅተኛውን ደረጃ ይዛ ትገኛለች፡፡ እ.ኤ.አ በ2010 OPHD ባቀረበው ዘገባ መሰረት “በአስከፊ ድህነት“ ውስጥ የነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት (በቀን ከአንድ ዶላር በታች ገቢ የሚያገኘው) 72.3 በመቶ ይሸፍን ነበር፡፡ ሆኖም ግን የ2014 የOPHD አሀዛዊ መረጃ ከዚህ የበለጠ አስደንጋጭ ነው፡፡ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የሚኖረው 82 በመቶ የሚሆነው ህዝብ በከተማ ከሚኖረው ከ18 በመቶው ህዝብ ጋር ሲነጻጻር የገጠሩ ህዝብ የበለጠ “በአስከፊ የድህነት“ ቀለበት ውስጥ ተተብትቦ ይገኛል፡፡ በ2014 በኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ በአስከፊ ድህነት ውስጥ ከሚገኘው ህዝብ ውስጥ አብዛኛው በሚከተሉት ክልሎች ይገኛል፡ ሶማሊ (93%)፣ ኦሮሚያ (91.2%)፣ አፋር (90.9%)፣ አማራ (90.1%)፣ እና ትግራይ (85.4%):: በOPHD የመለኪያ መስፈርት ውስጥ ድህነት ማለት በቀላል አገላለጽ የገንዘብ እጥረት ብቻ ማለት አይደለም፡፡ ይልቁንም ከዚህ በተለየ መልኩ አስከፊ የጤና፣ ትምህርት፣ ስነምግብ፣ የህጻናት ሞት እና ብልሹ የውኃ፣ የኤሌክትሪክ፣ የቤት እና የመጸዳጃ ቤት አቅርቦትም በጣም ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ በመጥፎ የድህነት ገጽታ ውስጥ ነው ያለችው፡፡ ለዚህም ነው ከዓለም አገሮች በድህነት ከመጨረሻዎቹ በሁለተኛነት ደረጃ ላይ ተሰልፋ የምትገኘው!
በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል ኢትዮጵያን በስልጣኔ ከፍ ወዳለ ደረጃ በማድረስ የተሀድሶ መሪ በመሆን ኢትዮጵያን ወደ ተምኔታዊ ኢትዮጵያ ለማሸጋገር ሌት ከቀን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል እየሰራ እንደሚገኝ ሁልጊዜ በብቸኝነት በያዛቸው የመገነኛ ዘዴዎች ይደሰኩራል፡፡ የይስሙላው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በመለስ የቀብር ስነስርዓት ላይ በመገኘት እንዲህ የሚል ንግግር አሰምተው ነበር፣ “ታላቁ መሪያችን አቶ መለስ ዜናዊ ላለፉት ስምንት ዓመታት ከሁለት አሃዝ በላይ እያስመዘገበ ላለው ኢኮኖሚያችን የሀገራችን ህዳሴ ቀያሽ መሀንዲስ ነበሩ“ በማለት ኩራትን በተላበሰ መልኩ ተናግረው ነበር፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በፊት አቶ ኃይለማርያም የአፍሪካን የኢኮኖሚ ዘገባ ባቀረቡበት ወቅት እንዲህ የሚል በኩራት የታጀበ ንግግር አሰምተው ነበር፣ “እያንዳንዱ ሰው ስለኢትዮጵያ ተሀድሶ ነው የሚያወራው“ (ይቀልዳል!?)
የወባ ትንኝ ተመራማሪው እና በብርሀን ፍጥነት ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት የተሸጋገረው እና በ2015 የይስሙላ ምርጫ ከአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በመረከብ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታውን የሚረከበው ቴዎድሮስ አድኃኖም ባለፈው መስከረም ወደ ኒዮርክ በመሄድ ስለኢትዮጵያ እና አፍሪካ ስኬት ገለጻ አድርጓል፡፡ እንዲህም ብሎ ነበር፣ “ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ፣ እና በፖለቲካው መስክ… ከበቂ በላይ ገስግሳለች:: በኢኮኖሚ እድገት ኢትዮጵያ ባለፉት አስር ዓመታት ከ10 በመቶ በላይ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግባለች…ኢትዮጵያ በእድገት ግስጋሴ ላይ ነች…”
ኢትዮጵያ “በህዳሴ እና በእድገት ግስጋሴ” ላይ ከሆነች በምን ዓይነት መለኪያ ነው ኢትዮጵያ ከዓለም/ፕላኔት በድህነት ከመጨረሻዎቹ አገሮች በሁለተኛነት ደረጃ ላይ የምትገኘው? ለምንድንስ ነው ኢትዮጵያ በህዳሴ እና በእድገት ግስጋሴ በመዝለቅ እራሷን ከድህነት ለማላቀቅ ያልቻለችው? ለምንድን ነው እ.ኤ.አ በ2014 82 በመቶ የሚሆነው በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የሚኖረው ህዝብ “በአስከፊ የድህነት” ባህር ውስጥ በመዋኘት ላይ የሚገኘው? በኢትዮጵያ ከ90 ወይም ከዚያ በላይ ከሚሆነው ህዝብ ውስጥ ወደ 60 በመቶ የሚሆነው ዜጋ ለምንድን ነው በቀን ከ1.25 ዶላር በታች የቀን ገቢ የሚያገኘው? ለምንድን ነው ወደ 60 በመቶ በላይ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በአስከፊ የምግብ ወይም በየጊዜው በሚከሰት ለምግብ ዋስትና እጦት የሚዳረገው?
እውነታው ግን ድህነት፣ በሽታ፣ ድንቁርና፣ ሙስና እና የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ብቻ ናቸው በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀቡ በመሄድ ላይ ያሉት፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለ ህዳሴ የሚኖር ካለ የሙስና ተሀድሶ ነው፣ አለ የሚባል ተሀድሶ ካለ የሰብአዊ መብቶች እጦቶች እና ጥሰቶች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ “በኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ መስኮች እድገት እና እመርታ” ማሳየት ሳይሆን እንዲያውም በአስደንጋጭ ሁኔታ ወደ ኋላ ተስፈንጥራ እየሄደች ነው፡፡ ሆኖም ግን በገዥው አካል “አብዮታዊ ዴሞክራሲ” እና “ልማታዊ መንግስት” (በተሻለ መልኩ ክህደታዊነት እየተባለ በሚጠራው) የገደል ማሚቶ ሰበካ ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ እና አጥጋቢ ነው፡፡ ከዚህ በተለየ መልኩ የሚያስብ እና የሚንቀሳቀስ እንዲሁም ስህተት ነው ብሎ የሚሞግት ከተገኘ ያ ግለሰብ የተሳሳተ ወይም ስንኩል እና ጤንነት የጎደለው አስተሳሰብ ነው ተብሎ ይፈረጃል፡፡
ሊሆን በማይችለው ከነባራዊ እውነታው ውጭ በሆነ ነገር ላይ እምነታቸውን የሚጥሉት የገዥው አካል አባላት ማስተባበል በማይቻል መልኩ በተዘጋጀ ማስረጃ የቀረበውን ሰው ሰራሽ የሆነውን ዓለም አቀፋዊ የአየር ንብረት የሙቀት መጠን እንደሚክዱት ዓይነት ቡድኖች እና ግለሰቦች ይሆናል፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል በሀገሪቱ ያለውን አስከፊ ድህነት ሙጥጥ አድርጎ በመካድ በዚህች አገር ለሚከሰተው ረሀብ በብቸኝነት ተጠያቂው እራሱ መሆኑን በመዘንጋት ተቃውሞውን ያሰማል፡፡ ይልቁንም ምናባዊ በሆነ መልኩ እራሳቸው ስለፈጠሩት ምናባዊ ህዳሴ ደጋግመው ይደሰኩራሉ!
እዉነታዎች በእራሳቸው ይናገራሉ፡፡ እ.ኤ.አ በ2011 ግሎባል ፋይናንሻል ኢንቴግሪቲ/Global Financial Integrity የተባለው ዓለም አቀፍ ድርጅት እንዲህ የሚል ዘገባ አቅርቦ ነበር፣ “የኢትዮጵያ ህዝቦች ደማቸው ተመጧል፣ ፍጹም ከሆነ እጦት እና ድህነት ለመውጣት የቱንም ያህል ጥረት ቢያደርጉም እንኳ በአሁኑ ጊዜ እየተደረገ ባለው የህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ባህር ውስጥ አገሪቱ ወደ ላይ በመስመጥ ላይ ትገኛለች“፡፡
እንደ ግሎባል ፋይናንሻል ኢንቴግሪቲ ዘገባ “ዓመታዊ የነፍስ ወከፍ ገቢዋ 365 የኤሜሪካ ዶላር የሆነችው ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ ከ2000 እስከ 2009 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ  11.7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በህግወጥ የገንዘብ ዝውውር ከሀገር ውስጥ ወጥቷል፡፡ እ.ኤ.አ በ2009 ህገወጥ የገንዘብ ዝውውሩ 3.26 የአሜሪካ ዶላር በመሆን ካለፉት ሁለት ዓመታት በእጥፍ ጨምሮ ታይቷል… እ.ኤ.አ በ2008 ኢትዮጵያ ከውጭ የተገኘ 829 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ሲሆን ይህም በህገወጥ የገንዘብ ዝውወር ምክንያት ባክኖ ቀርቷል፡፡“ የኢትዮጵያ የካፒታል ፍሰት ሁኔታ ሲታይ በግምት 3.26 የአሜሪካን ዶላር በአመዛኙ እ.ኤ.አ በ2009 ከተገኘው 2 ቢሊዮን የኤክሰፖርት ምርት ዋጋ በእጅጉ የበለጠ ነው፡፡
ኢትዮጵያ .. 2014 ከዓለም 2ኛዋ ደኃ አገር ለምን ሆነች?
በኢትዮጵያ ሰይጣናዊው ረሀብ ድልን ሊቀዳጅ የቻለበት ዋናው ምክንያት በገዥው አካል የእውቀት ማጣት፣ የችሎታ ማነስ፣ ድንቁርና፣ እብሪ እና ሙሰኝነት እንዲሁም አሁን በህይወት በሌለው በመለስ ዜናዊ ዋና መሀንዲስነት የአምባገነንነት ባህሪ ምክንያት ነው፡፡ መለስ ከሁሉም በላይ እራሱን እንደ የኢኮኖሚ ባለሙያ አድርጎ ይቆጥር ነበር፡፡ መለስ ግማሽ ብስል በነበረው የማርኪሲዝም የፖለቲካል ኢኮኖሚ በማመን ገና በወጣትነት እድሜው ወደ ጫካ በመግባት እራሱን በኢትዮጵያ “የአብዮታዊ ዴሞክራሲ” እና “የልማታዊ መንግስት” “ዋና መሀንዲስ” አድርጎ ሰየመ፡፡ ሆኖም ግን መለስም ሆነ የእርሱ አሻንጉሊት ተከታዮች የአብዮታዊ ዴሞክራሲ እና የልማታዊ መንግስት ህልዮትን እና ገቢራዊ አልሆኑም፡፡ ይልቁንም የልመና እጃቸዉን ለዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና ለዓለም ባንክ እየዘረጉ በሌላ በኩል ደግሞ “ኒዮሊበራልን” ለማውገዝ እና ለመርገም ድምጻቸዉን ከፍ አድርገው ይጮሃሉ፡፡ በአንድ ምሁራዊ የትችት መጽሄት ላይ የጸረ ኒዮሊቨራል አቀንቃኝ በሆነው በጆሴፍ ሰትልጊዝ እርማት መሰረት አቶ መለስ እንዲህ ብሎ ነበር፣ ”የኒዮሊቨራል አካሄድ የአፍሪካን ህዳሴ ያላመጣ የሞተ ነገር ነው፣ እናም የአፍሪካን ዓላማ ለማሳካት እና አፍሪካን ወደ ዘላቂ የሆነ መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡“
የመለስ መሰረታዊ ለውጥ የይስሙላ ዓላማ በአሁኑ ጊዜ እንደተረሳችው ራሽያ ማዕከላዊ የሆነ የአምስት ዓመት የኢኮኖሚ ዕቅድ ሳይሆን እንደ የእድገት እና ትራንስፎረሜሽን ዕቅድ ያለ ምዕናበዊ ዕቅድ ነው፡፡ ቀደም ሲል በተለያዩ አጋጣሚዎች እንዳየሁት ሁሉ መለስ የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የለውም፣ ይልቁንም ያለው ምዕናባዊ ሀሳባዊ የኢኮኖሚ እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ነው፡፡         
የመለስ ዜናዊ የዉሸት ምጣኔ  ሀብት ዘየቤ (The Fakeonomics of Meles Zenawi) በሚል ርዕስ ባቀረብኩት ትችት እንዲህ በማለት ለማሳየት ሞክሬ ነበር፣ “የዕድገት እና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ባዶ ሊስት ከመመዝገብ የበለጠ አይደለም፡፡“ ይህ ዕቅድ በረዥሙ ጉዞ ኢትዮጵያን የዴሞክራሲያዊ ህግ፣ መልካም አስተዳደር እና ማህበራዊ ፍትህ እንዲሰፍኑ ለማድረግ ነበር፡፡ ዘመናዊ እና ምርታማ የሆነ የግብርና ዘርፍ ከተሟላ ቴክኖሎጂ እና የኢንዱስትሪ ዘርፍ እንዲሁም የዜጎች ዓመታዊ የነፍስ ወከፍ ገቢ ለማሳደግ እና የመካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ጋር እኩል ለማድረግ የታለመ ነበር፡፡ ገዥው አካል የእድገት እና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በማሳካት ፈጣን እና ዘላቂ እንዲሁም ፍትሀዊ የኢኮኖሚ እድገት ለማምጣት ምሰሶ ስልቶችን በመጠቀም ግብርናን እንደ ዋና የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ሞተር በማድረግ ለኢንዱስትሪው መዳበር ጥሩ ከባቢ አየርን ይፈጥራል በማለት ጉራ ያደርጋል፡፡ ከዚህም ጎን ለጎን የመሰረተ ልማት እና የማህበራዊ ልማትን ማስፋፋት፣ የአቅም ግንባታ ስራዎችን ማካሄድ እና መልካም አስተዳደርን ማስፈን እንዲሁም ሴቶችን እና ወጣቶችን ማጠናከር እና የጋራ ተጠቃሚነትን ማጎልበት በሚል ሀሳብ ይመራል፡፡
በባዶ የኢኮኖሚ እድገት መፈክር ታጅቦ፣ በተደጋጋሚ እየተነገረ ባለ አሰልቺ አገላለጽ ታጅሎ፣ ፋሽንነትን በተላበሱ ቃላት እየተሽሞነሞነ እና በአንድ ታዋቂ ሰው ዲስኩር እየተምነሸነሸ የመለስ የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አደናጋሪና እና ከነባራዊ እውነታው ውጭ ሆኖ ቀርቷል፡፡
ከዚህ ቀደም “የመለስ ምዕናባዊ ኢኮኖሚከስ“ (The Voddo Economics of Meles Zenawi) በሚል ርዕስ ባቀረብኩት ትችት መለስ ግልጽ በሆነ መልኩ በፍብረካ ላይ በተመሰረተ ስታቲስቲካዊ አሀዝ በመጠቀም በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚክ እድገት ተመዝግቧል ይለው የነበረውን ተራ ማደናገሪያ የሆነ ውሸት በማጋለጥ አቅርቤ ነበር፡፡ ለበርካታ ዓመታት መለስ እና የእርሱ ገዥ አካል የማተለያ የህዝብ ግንኙነትን በመፍጠር እና በማታለል የዓለም የገንዘብ ድርጅትን ከፊት በማድረግ የእርሱን የሸፍጥ የኢኮኖሚ እድገት ዓለም አቀፉን ድርጅት ባስረጅነት ድጋፍ እንዲያደርግ አገሪቱ ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ እድገት እንዳስመዘገበች እና ውጤታማ እንደሆነች አድርገው የዓለምን ህዝብ በማደናገር ላይ ይገኛሉ፡፡
በኢትዮጵያ ያለውን ገዥ አካል የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ እውቀት አናሳነት፣ የብቃት የለሽ እና በሙስና ስርዓት በመዘርጋት የሀገሪቱን ሀብት እጠቀራመተ ያለ መሆኑን በማጋለጡ እረገድ እኔ የመጀመሪያው አይደለሁም፡፡ እ.ኤ.አ በሴፕቴምበር 7/2006 እትሙ የኢኮኖሚክ መጽሄቱ/Economic Magazine “የኢትዮጵያ መንግስት በአሁኑ ስልጣኔ በተስፋፋበት ዘመን አንዱ የኢኮኖሚክስ ማይም“ በማለት የሁኔታውን አሳሳቢነት  ገልጾት ነበር፡፡
እ.ኤ.አ ኖቬምበር 3/2007 የኢኮኖሚስት መጽሄት/the Economist Magazine እንዲህ የሚል ዘገባ አቅርቦ ነበር፣ “እውነታው ተግልጦ ሲታይ በእርዳታ የሚገኝ ገንዘብ እና ከቻይና የሚመጣ ብድር ቢኖርም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በፍጥነት ማደግም ሆነ በቂ የስራ እድል መፍጠር አልቻለም፡፡ የአበባ ምርት እየተባለ ብዙ በሚወራለት አዲስ የኢኮኖሚ ዘርፍ የተፈጠሩት አዲስ የስራ መስኮች በየዓመቱ በ2 ሚሊዮን እጨመረ ከመጣው የህዝብ እድገት በአፍሪካ ፈጣኑ የህዝብ እድገት ከመሆኑ አንጻር ሲታይ ብዙም አይደሉም… ገዥው አካል የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ2003-2004 በሚያስደምም ሁኔታ 10 በመቶ እድገት አሳይቶ ነበር፡፡ሆኖም ግን እውነተኛው እና ትክክለኛው የእድገት አሀዝ 5-6 በመቶ ማለትምከሰሀራ በታች ካሉ አገሮች አማካይ የእድገት ምጣኔ በላይ ይሆናል ተብሎይገመታል፡፡ እናም ያ መጠነኛ የተሻሻለ የእድገት ምጣኔ ለምሳሌም በአዲስ አበባ ከተማ እየተሰሩ ባሉ ጥቂት ህንጻዎች ሰበብ ኢኮኖሚው ከመጠን በላይ እየጋለ ሄዶ መንግስት በዚያው ዓመት እርምጃ ከመውሰዱ በፊት የዋጋ ንረቱ 19 በመቶ ደርሶ ነበር፡፡ ኢኮኖሚው ለምን  በእንደዚህ ያለ ሁኔታ እየዳኸ እንደሚሄድ ለማወቅ በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ነው፡፡ በአብዛኛው በውጭ እርዳታ የተንጠለጠለ ሆኖ ከመንግስት ትእዛዘዝ ውጭ – ለአፍሪካ ብቻ ልዩ የሆነ በእርግጠኝነት በንግድ ስራ ላይ የተሰማራ የንግድ ማህበረሰብ የለም፡፡ እ.ኤ.አ በ2009 ከፍተኛ የሆኑ የምእራቡ ዓለም ለጋሽ ድርጅቶች እና ፖሊሲ አውጭዎች በበርሊን ከተማ ባካሄዱት ጉባኤ አንድ የጀርመን ዲፕሎማት በመለስ ደካማ የኢኮኖሚክስ አረዳድ መሰረት የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ችግር በውል ሊታወቅ እና ሊደረስበት አይችልም“ ብለው ነበር፡፡
ጥቂቶችን ብቻ የማበልጸግ አባዜ የተጠናወተው የኢትዮጵያ ድህነት ገፊምክንያት፣ 
በኢትዮጵያ ለድህነት መሰረታዊ ምክንያቱ “ኒዮሊበራሊዝም” አይደለም፡፡ ይልቁንም ዋናው የድህነት መሰረቱ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ቀያሽ መሀንዲሶች እና በኢትዮጵያ ልማታዊ መንግስት እየተባለ ኢኮኖሚውን በብቸኝነት ይዘው ጥቂቶችን በማበልጸግ ሰፊውን ህዝብ የበይ ተመልካች የማድረግ አባዜ ነው፡፡ ጥቂቶችን የማበልጸግ ስስታዊ አካሄድ የኢኮኖሚ ተግባራትን እና የውጤታማነት መስፈርትን በማየት ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ በፖለቲካ ትስስር የሚከናወን የጥቂቶች የመዝረፊያ አካሄድ ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ በሀገሪቱ የአንበሳውን ድርሻ ለማግኘት ማንም ሰው ቢሆን በፖለቲካ እና በጎሳ ትስስር እና መስተጋብር አንድ በመሆን የኢኮኖሚ ጥቅም ያገኛሉ፡፡ በኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ሙያዊ የቃላት ድርደራ መሰረት እንደዚህ ያለው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ “ኪራይ ሰብሳቢነት“ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን የግል ወይም የቡድን ግምገማዎች ለግብር ጉዳይ መንግስትን መለማመጥ፣ የወጭ እና የቁጥጥር ፖሊሲዎችን በመንደፍ የገንዘብ ጥቅሞችን ወይም ደግሞ በሌሎች ግብር ከፋዮች ጉዳት ሌሎች ልዩ ጥቅሞችን የማግኘት ወይም ደግሞ የተጠቃሚዎች ወይም ሌሎች ቡድኖች ወይም ግለሰቦች ጋር ውድድር እንዲያደርጉ ይገዳዳሉ፡፡
የመለስ ጥቂቶችን ብቻ የማበልጸግ አባዜ የመለስ ደጋፊ እና የእርሱ ህወሀት ፓርቲ ሎሌዎች (የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር/ኢህአዴግ የጋራ መደጋገፍ ስርዓት በመዘርጋት የተለያዩ ጥቅሞችን የማሳደድ እንዲሁም ለእነርሱ የሚመች ከባቢያዊ ሁኔታ የመፍጠር እና የህዝብ ግዥ ሲፈጸም እና በመሳሰሉት ሁሉ ለጥቅመኛው ቡድን ተጠቃሚ እንዲሆን ይደረጋል፡፡ የውስጦቹ በውጮቹ ጉዳት መሰረት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ እናም እየንዳንዱ ለገንዘቡ ሲል ሎሌ ይሆናል፡፡ የኢንተርፕሪነር/ስራ ፈጣሪ ግለሰቦች እንኳ ለመኖር ሲሉ ለአዳኙ ግለሰብ/ቡድን ሎሌ መሆን ይፈልጋሉ፡፡
በመለስ ጥቂቶችን የማበልጸግ መርህ መሰረት መንግስት ኢኮኖሚውን በብቸኝነት ተቆጣጥሮ ለእርሱ ደጋፊዎች እና ሎሌዎች ትርፋማ የሆኑ የኢኮኖሚ ዘርፎችን ይይዛል፡፡ የመለስ ገዥ አካል በቁጥጥር፣ በግብር፣ በጠቅላላ ለወጭ እና ለኢኮኖሚያዊ ተግባራት እንቅስቃሴ በበላይነት ይዞ ይመራል፡፡ ታማኞቻቸውን እና ሎሌዎቻቸውን ለመጥቀም ሲሉ በልጓም የማይታዘዝ ስልጣን አላቸው፡፡ በውጤቱም ኢኮኖሚያዊው እንቅስቃሴ፣ የኢንተርፕሪነር ህልውና እና ሌሎችም የፖለቲካ ስልጣኑን በተቆጣጠረው ኃይል የሚወሰን ነው፡፡ እንግዲህ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ነው የሀብት ፈጠራ እና ባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግበን እያሉ ህዝቡን ጧት ማታ የሚያሰለቹት፡፡
በመለስ ጥቂቶችን የማበልጸግ ስራ በጣም ጥቂት የሚባሉ ነጻ የስራ ፈጣሪዎች ተሳክቶላቸዋል፡፡ ጥቂቶቹ የተሳካላቸውም ቢሆኑ በእርግጠኝነት በመለስ ሎሌዎች ተውጠው ይቀራሉ፡፡ የኢኮኖሚ ስኬታማነት በአመዛኙ የሚወሰነው በፖለቲካ እንቅስቃሴው እና ገዥውን አካል ከመደገፍ አንጻር ባለው አቋም ነው፡፡ ነጻ የሆኑ የስራ ፈጣሪዎች ህልውናቸው ተጠብቆ እንዲቆይ ከተፈለገ ድርጊቱን ቢጠሉትም እንኳ ጥቂቶችን በማበልጸግ ስራ ላይ መሳተፍ ይኖርባቸዋል፡፡ የመለስ ገዥ አካል የቁጥጥር ኃሉን፣ የግብር ስብሳቢ ባለስልጣኑን፣ እና ወጭዎችን እና ድጎማዎችን ለሚደግፉት ሲሰጥ በተቃራኒው ላሉት ግን አይሰጥም፡፡ ይህም በሚሆንበት ጊዜ ሁሉም ስራ ፈጣሪዎች የመንግስትን ልዩ አያያዝ ለማግኘት ሲባል እና እራሳቸውን ከህጎች፣ ወጭዎች እና እነርሱን ከውድድር ጉዳት ለሚከላከሉ ነገሮች አበርትተው ይሰራሉ፡፡
በመለስ ገዥ አካል ጥቂቶችን የማበልጸግ ስርዓት ውድድር የሌለበት እና በግልጽ ለተወሰነ ቡድን ተብሎ የተቀመጠ ነው፡፡ የሰብአዊ መብተ ቡድኖች፣ ተንታኞች እና ትችት እቅራቢዎች የመለስ ገዥው አካል በእርዳታ ስም ለህዝብ እንዲደርስ የሚላከውን እርዳታ ማለትም ምግብን፣ ማዳበሪያን፣ ስልጠናን፣ ወዘተ ጨምሮ ለፖለቲካ መጠቀሚያ በማድረግ ለሚታወቁ ተቃዋሚ ቡድኖች አብዛኛውን ጊዜ እንደሚከለክል ዘገባ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ በተደጋጋሚ በማወጣቸው ሳምንታዊ ትችቶቸ ላይ ሳቀርብ ቆይቻለሁ፡፡ እንደ ዓለም ባንክ ዘገባ የኢትዮጵያ ግማሽ አካባቢ የሚሆነው ብሄራዊ ኢኮኖሚ የተያዘው ለስርዓቱ ደጋፊ በሆኑ የንግድ ቡድኖች ማለትም በትግራይ ህዝብ መልሶ ማቋቋሚያፈንድ/Endowment Fund for the Rehabilitation of Tigray (EFFORT) በሚባሉ መንግስታዊ በሆኑ የንግድ ድርጅቶች ነው፡፡ የኢፈርት የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት፣ ኮንስትራክሽን፣ የመድሀኒት፣ እና የስሚንቶ የንግድ ተቋሞች ትርፋማ የሆኑ የውጭ የእርዳታ ስምምነቶችን እና ከመንግስት ባንኮች የብድር አገልግሎት ያለምንም ውጣውረድ እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡  እ.ኤ.አ በ2011 በተሟላ መልኩ በሳራህ ቫውግሀን እና መስፍን ገብረሚካኤል አማካይነት “Rethiniking business and politics in Ethiopia: The role of EFFORT, the Endowment Fund for the Rehabilitation of Tigray“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ዘገባ ገዥው አካል ከንግድ ድርጅቶች ጋር ቅርብ እና የጠበቀ ግንኙነት እንዳለው ከበቂ በላይ ማስረጃ እና ትንታኔ ይሰጣል፡፡ የዓለም ባንክ በ2012 “Diagnosing Corruption in Ethiopia“ በሚል ርዕስ  ባዘጋጀው ሰፊ ዘገባ እና በዚያ ዘገባ ውጤት ላይ እኔ እራሴ በመለየት በሰጠሁት ትችት ጥቂቶችን የማበልጸግ ወያኒያዊ ተውኔት ምን ያህል በፍትሀዊነት ላይ ድልን እንደተቀዳጀ የሚያሳይ እኩይ ኢመንግሰታዊ ምግባር መሆኑን መግለጼ የሚታወስ ነው፡፡(እነዚህ ትችቶች Al Mariam Commentaries በሚል የእራሴ ድረ ገጽ ላይ ይገኛሉ፡፡) በኢትዮጵያ ጥቂቶችን ማበልጸግ የሚለው ወያኒያዊ መርህ ምናልባትም በማዕድኑ ዘርፍ በይበልጥ ጎልቶ ይታያል፡፡ የዓለም ባንክ ጥናት የመለስን ጥቂቶችን የማበልጸግ መርህ በግልጽ አሳይቷል፡፡
የማዕድን ኩባንያ የማዕድን ፈቃድ ለማግኘት ብዙ ፕሪሚየም/ከተገቢው በላይ እንዲከፍል ይጠየቃል፡፡ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣኖች እና የማዕድን ኩባንያው ይህንን ክፍያ በሚስጥር እንዲያዝ ሊያደርጉ ይችላሉ፣ በቀጣይነትም ከአገር ውጭ ባሉ የባንክ ሂሳቦቻቸው ገንዘብ ገቢ እንዲያደርጉላቸው ያደርጋሉ፡፡
አንድ የማዕድን ኩባንያ የማዕድን ፈቃዱን በአስቸኳይ ለማግኘት የሚፈልግ ከሆነ ለበጎ ነገር እርዳታ በሚል ብዙ ገንዘብ እንዲሰጥ በመንግስት ባለስልጣኑ ሊጠየቅ ይችላል፡፡ የበጎ ነገር እርዳታው ለመልካም ነገር የታሰበ ቢሆንም ይህ ገንዘብ በትክክል ለፖለቲካ ፓርቲው ወይም ለባለስልጣኑ የግል ወይም ደግሞ ለቤተሰቡ መጠቀሚያ እንዲውል ሊደረግ ይችላል፡፡
ባለስልጣኖች ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ ከማዕድን ኩባንያው ጋር በመስማማት የተወሰነ ኮንትራት ለዘመዶቻቸው እንዲሰጥ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ የማዕድን ፈቃዱን የሚሰጠው ባለስልጣን ለማህበራዊ ልማት ዕቅድ በሚል ከሚጠየቀው ትክክለኛው የገንዘብ መጠን በተጨማሪ የመሰረተ ልማት ስራዎችን ኩባንያው በእራሱ ወጭ እንዲሰራ ሊጠየቅ ይችላል፡፡
የማዕድን ኩባንያው የማዕድን ፈቃድ ለመውሰድ ሲፈልግ የአካባቢ ስነምህዳር አያያዝ ዕቅድ እንዲያቀርብ ሊጠየቅ ይችላል፡፡ ይህም ጎጂ የሆኑ መርዛማ ኬሚካሎች ወደ ውኃ አካላት በመግባት ብክለትን እንዳያስከትሉ በሚል ምክንያት ነው፡፡ ትክክለኛ ቁጥጥር ከፍተኛ የሆነ ወጭን የሚጠይቅ ተግባር ነው፡፡ የማዕድን ኩባንያው የማዕድን ፈቃዱን ለማግኘት ሲል የሚፈጠሩ ድክመቶችን ለመሸፈን በሚል ተጨማሪ ከፍተኛ ገንዘብ እንዲከፍል እንዳይጠየቅ ፈቃዱን ለሚያጸድቀው ባለስልጣን ጉቦ ሊሰጥ ይችላል፡፡
ባለስጣኖች ከማዕድን ኩባንያው ትርፍ ድርሻ/share ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ የማዕድን ኩባንያ ከጥቅም ጋር በተያያዘ መልኩ ከማዕድን ትርፍ ለባለስልጣን ዘመድ ነጻ ድርሻ/share ሊሰጥ ይችላል፡፡
ባለስልጣኖች በድብቅ በእራሳቸው በተያዙት ኩባንያዎች የማዕድን ፈቃድ ይሰጣሉ፡፡
ባለስልጣኖች የፈቃድ ማመልከቻ የቀረበበትን መሬት በድብቅ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡
ባለስልጣን የማዕድን ስራው ይካሄድበታል ብሎ የሚያስበውን መሬት አስቀድሞ የማዕድን ፈቃዱ ከመሰጠቱ በፊት ሊያከራየው ይችላል፡፡ አንዴ ፈቃዱ ከተሰጠ የመሬቱ ጥሬ ዋጋ ሊጨምር ይችላል፡፡ ባለስልጣኑ ከውስጥ ባለው እውቀት መሰረት በመሸጥ ወይም ደግሞ ፈቃዱን በማከራየት ከኩባንያው ትርፍ ሊያገኝ ይችላል፡፡
ባለስልጣኖች የፈቃድ ምዝገባን ሊያዛቡ ይችላሉ፡፡
የማዕድን ፈቃድ መስጠት የሚችል በመምሪያ ደረጃ ያለ ባለስልጣን የማዕድን ኩባንያ የማዕድን ፈቃድ ለመጠየቅ የሚፈልግ መሆኑን ሊያውቅ ይችላል፡፡ ከዚህ አንጻር ባለስልጣኑ መረጃውን በመገንዘብ ሌላ ከዚህ ስራ ጋር ግንኙነት ያለውን ሰው አስቀድሞ እንዲያውቅ ሊያደርግ ይችላል፡፡ በዚህም መሰረት የንግድ ሰው በዚያው በአንድ ዓይነቱ መሬት ላይ ሊያመለክት ይችላል፡፡ ባለስልጣኑ ይህንን መሬት ለዚህ የንግድ ሰው ሊሰጠው ይችላል፡፡ ከዚያም የማዕድን ኩባንያው ይህንን ቀደም ሲል እራሱ እንዲሰጠው አመልክቶ የነበረበትን መሬት ከንግዱ ሰው እንዲገዛው ይደረግ እና የንግዱ ሰው ትርፉን ከባለስልጣኑ ጋር ይካፈላል፡፡
አንድ ማዕድን ፈላጊ ማዕድን ሊያገኝ ይችላል፣ ያገኘበትን አካባቢም ምልክት ሊያደርግበት ይችላል፡፡ በዚህም መሰረት የግኝት ሰርቲፊኬት እንዲሰጠው ጉዳዩን ለሚመለከተው የፈቃድ ሰጭ ባለስልጣን ሊያመለክት ይችላል፡፡ ሙስና የሚያካሂድ ባለስልጣን ግኝቱን ባገኘው ሰው ስም ላይመዘግበው ይችላል፣ ከዚህ ይልቅ የቢዝነስ ጓደኛውን እንዲያውቅ በማድረግ በጓደኛው ስም እንዲመዘገብ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ሙሰኛው ባለስልጣን ከዚህ በኋላ ማዕድኑ በመጀመሪያ የተገኘው በሌላው ሰው እንደሆነ ይነግረዋል፡፡
ኮንትራክተሮች እና አምራቾች በጨረታ፣ የባለቤትነት ጥያቄን በማቅረብ እና እንከን ያለባቸውን ስራዎች በመደበቅ ወይም በማጽደቅ ተግባር ላይ ሊሰማሩ ይችላሉ፡፡
የማዕድን ኩባንያዎች ስለ ማዕድናት ምንነት እና ጥራት የሀሰት መግለጫዎችን በመስጠት ወይም ደግሞ ፈቃድን  ለሚያጸድቁት ኃላፊዎች ጉቦ በመስጠት የሙስና ወንጀል ሊፈጽሙ ይችላሉ፡፡
ኢትዮጵያ ከዓለም ሁለተኛዋ ደኃ አገር ከሆነችበት የውርደት ቦታ የምትላቀቀውመቸ ነው? 
ከፖለቲካ ትስስር ጋር የተያያዙ ስራዎች ከስራ ፈጠራ ችሎታ እና ከተነሳሽነት የበለጠ ትኩረት እስከተሰጣቸው ድረስ ኢትዮጵያ ከዓለም ሁለተኛዋ ደኃ አገር ሆና ትቀጥላለች፡፡
በቁጥር ጥቂት የሆኑ ከላይ የተቀመጡ የተማሩ ዜጎች በህግ ስርዓቱ የተለየ ድጋፍ የሚደረግላቸው እስከሆነ ድረስ እና በጎሳ ዝርያቸው ምክንያት እና በጣም ምርታማ በሆነው የምጣኔ ሀብት ዘርፍ እየተሰማሩ እንዲበለጽጉ በማድረግ የመጀመሪያ ደረጃ ዜግነት እስከተሰጣቸው ድረስ ኢትዮጵያ ከዓለም ሁለተኛዋ ደኃ አገር ሆና ትቀጥላለች፡፡
ግለሰቦች እና ቡድኖች በስራ፣ በላብ እና በድካማቸው ከሚያገኙት አንጡራ ሀብታቸው ውጭ በፖለቲካ ትስስር ብቻ ያለፉበትን እና የላባቸው ዋጋ ያልሆነውን የሌሎችን ዜጎች አንጡራ ሀብት መዝረፍ እስካላቆሙ ድረስ ኢትዮጵያ ከዓለም ሁለተኛዋ ደኃ አገር ሆና ትቀጥላለች፡፡ 
ይህ ሰው አዳኝ መንግስት ደካማ እና ንጹሀን ዜጎችን እያሳደደ አቅማቸውን እያዳከመ ማደኑን እና የስራ ፈጠራ ክህሎታቸውን በማጥፋት እረፍትየለሾቹን ወጣቶች እንዳይሰሩ እና ለሀገሪቱ ዘለቄታዊ ለውጥ እንዲያመጡ እስካላደረገ ድረስ ኢትዮጵያ ከዓለም ሁለተኛዋ ደኃ አገር ሆና ትቀጥላለች፡፡
ድህነት በኢትዮጵያ ውስጥ ተንሰራፍተው ለሚገኙ ጭራቆች ሁሉ ዋና መሰረት ነው፡፡ ሆኖም ግን ማን (ምንድን) ነው በኢትዮጵያ ውስጥ የድህነት መሰረቱ?
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ሰኔ 27ቀን 2006 .

ኢህአዴግ በምርጫ ዋዜማ የጀመረው እስር የ2007ን ምርጫ ጠቅልሎ ለመውሰድ ያደረገው መጀመሪያው ርምጃ ነው!!! (አንድነት ፓርቲ )

July9/2014
የፓርቲያችን ከፍተኛ አመራሮች አቶ ሀብታሙ አያሌው እና አቶ ዳንኤል ሺበሺ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እናሳስባለን!!!

ከአንድነት ፓርቲ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

በቅርቡ ለህዝቡና ጋዜጠኞች ይፋ እንዳደረግነው ሕወሓት/ኢህአዴግ  ለአለፉት 23 ዓመታት ወደር የሌለው የዴሞክራሲያዊ መብት ገፈፋና የሰብአዊ መብት ረገጣ በዜጎች ላይ ሲፈጽም መቆየቱ ዓለም የሚያውቀው እውነ ታመሆኑን፤በአሁኑ ወቅት ይህ የሰብአዊ መብት ረገጣና ድፍጠጣበእጅጉተባብሶወደመንግሥታዊየውንብድናናጥቃትመቀየሩን፤ ዜጎችመንግሥትእንዳሰማራቸው የምንጠረጥራቸው የደህንነት ኃይሎች ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ በጅምላ መታሰራቸውን፣ መደብደባቸውንና በስውር እስር ቤቶችተወርውረውደብዛቸውእንዲጠፋመደረጉን ገልፀን ነበር፡፡ እንደዚህ አይነቱ ውንብድና ደግሞ ምርጫ ሲቃረብና የፖለቲካ ፓርቲዎች መሰባሰብ ብሎም መዋሃድ ሲገለፅ ተጠና ክሮ የሚቀጥል እንደሆነ ከዚህ በፊት በውዱ ታጋያችን አንዱአለም አራጌ እና ሌሎችም ያስተዋልነው የገዥው ፓቲ ድርጊት ነው፡፡

ለባለፉት 23 ዓመታት ሲያደርገው እንደነበረው ሁሉ ምርጫ ሲደርስ የሚጨነቀው ገዢ ፓርቲ አባሎቻችንን መደብደብና ማሳደዱ አልበቃ ብሎት በምርጫው ዋዜማ በተለመደውና አሰልቺ ፍረጃው ተደግፎ አመራሮቻችንን ማሰር ጀምሯል፡፡ ፓርቲያችን እንደሚረዳው ይሄው በዛሬው ዕለት እንደገና የተጀመረው የአንድነት የስራ አስፈፃሚ አባልና የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑትን አቶ ሀብታሙ አያሌውን እና የምክር ቤት አባልና የድርጅት ጉዳይ ምክትል ሃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሺን በማሰር እና በርካታ አባሎቻችን ላይ አፈና በማካሄድ የምርጫ ዘመቻውን ይፋ አድርጓል፡፡ ፀረ-ውህደት አቋሙን አንፀባርቋል፡፡

ይሄው እስር እንደተለመደው የተቀነባበረ የስርዓቱ ድራማ ከመሆኑም በተጨማሪ የ2007ን ሀገራቀፍ ምርጫ በተለመደው ማሸማቀቅና ማወናበድ ለመውሰድ የተጀመረ የመጀመሪያ ርምጃ ነው ብለን እናምናለን፡፡ የተቀነባበረ ድራማም በሚቆጣጠራቸው ስማቸው የህዝብ ተግባራቸው ግን የፓርቲ መገልገያ በሆኑ ሚዲያዎች ማቅረቡንም እንደሚቀጥልም እናውቃለን፡፡ ይህ ሁሉ ግፍና ድራማ የሚከናወነው ከአፍ ባለፈ መተግበር ያልቻለውን ዴሞክራሲያዊ ስርኣት ለማስመሰያነት ለመጠቀምና የቀጣዩን ዓመት ምርጫ በለመደው ሁኔታ ከቻለ አስሮና አደናግሮ ካልተጫለ ጉልበቱን ተጠቅሞ ለመጠቅለል ነው፡፡

ፓቲያችንአንድነት አባላትንና አመራሮቻችን በማሰቃየትና በማሸማቀቅ፣ በመደብደብ የአካል ማጉደል ጉዳት በማድረስ የሚያደርገውን አስነዋሪ ተግባር እያወገዘ የፓርቲያችን ከፍተኛ አመራሮች አቶ ሀብታሙ አያሌው፤ አቶ ዳንኤል ሺበሺና ሌሎችም በፖለቲካ አመለካከታቸውና እምነታቸው ብቻ ለእስር የተዳረጉ ፖለቲከኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እናሳስባለን፡፡ በተጨማሪም በተቃውሞ ጎራ የተሰለፉ ፓርቲዎችም ይህን ህገ ወጥ እስር በማውገዝ እንዲሁም ኢ-ፍትሀዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚደረገውን ሩጫ በመቃወም እጅ ለእጅ ተያይዘን እንድንቆም እየጠየቅን ይህንን ህገ-ወጥነት በህዝባዊ ንቅናቄ ለማሸነፍ በምናደርገው ትግል በጋራ እንድንሰራ ሀገራዊና ወቅታዊ ጥሪ እናቀርባለባለን፡፡ የሲቪክ ተቀቋማት፤ ነፃው ሚዲያና የሰብዓዊ መብት ድርጅቶችም በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን መንግስታዊ ግፍና በደል በዓለማቀፍ ደረጃ በማጋለጥ ግዴታችሁን እንድትወጡ እናሳስባለን፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብም ስለሰብዓዊ መብት መከበርና ዴሞክራሲ መረጋገጥ እየተደረገ ያለውን ተግል በመደገፍ የአምባገነኖችን ውድቀት እንዲያፋጥን ሀገራቀፍ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

                                              ትግላችን እስከ ነፃነት ይቀጥላል!!!  
                                            አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት)
                                                       ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም

የኢቲቪ የዛሬው የአቶ አንዳርጋቸውን ንግግር ያሳየበት ፊልም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሁለት መልዕክት አስተላልፏል

July9/2014

የኢቲቪ የዛሬው የአቶ አንዳርጋቸውን ንግግር ያሳየበት ፊልም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሁለት መልዕክት አስተላልፏል ዶ/ር ብርሃኑ ቀደም ብለው ስለ አቶ አንዳርጋቸው የተናገሩትን አቶ አንዳርጋቸው ሲያረጋግጡ እና ስለኢትዮጵያ ሕዝብ መብት እና ነፃነት በረሃ የወረዱ የሕዝብ ልጆች መኖራቸውን

Andargachew 1ዛሬ ሐምሌ 1/2006 ዓም ኢቲቪ አቶ አንዳርጋቸው የግንቦት 7 ንቅናቄ ፀሐፊን በድብቅ ካሜራ ያነሳውን ፊልም አሳይቷል።አቶ አንዳርጋቸው በተጎሳቆለ ሰውነት ሆነው የተናገሩት ዶ/ር ብርሃኑ ባለፈው ሳምንት ከተናገሩት ጋር ተመሳሳይ ነው።አቶ አንዳርጋቸውን ወያኔ በየመን ካስያዘ በኃላ ወደ ሀገር ቤት አምጥቶ ከፍተኛ ድብደባ እና ስቃይ እንዳደረሰባቸው ኢሳት ትናንት ከታማኝ ምንጮች ማግኘቱን ጠቁሟል።በዛሬው የኢቲቪ ፊልምም ይህንን መመልከት ይቻላል።
የኢቲቪ ፊልም ለኢትዮጵያ ሕዝብ መልዕክት አስተላልፏል።በባህር ማዶ ከ 30 ዓመት በላይ መኖር ሀገር አያስከዳም፣መማር ለሀገር በረሃ ለበረሃ መንከራተትን አይከለክልም።አቶ አንዳርጋቸው በሳር በተሰራ ጎጆ ፊት ሆነው፣አንዲት ምስኪን ኢትዮጵያዊት ሲያፅናኑ የሚያሳይ ፎቶም አሳይቷል።በወያኔ አስተሳሰብ አቶ አንዳርጋቸውን ያዋረደ እና ዝቅ አድርጎ ያቀረበ መስሎት ነው። ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግን መልክቱ ታላቅ ነው።በረሃ ስለመብትህ የሚታገሉ አሉ።እውነት ነው።የሚል መልዕክት አለው። 
በሌላ በኩል ኢቲቪ ያረጋገጠልን ነገር ዶ/ር ብርሃኑ ስለ አቶ አንዳርጋቸው ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የተናገሩትን ነው።ዶ/ር ብርሃኑ ያሉትን እና ዛሬ በኢቲቪ አቶ አንዳርጋቸው የተናገሩትን ተመልከቱ።ተመሳሳይ ነው።

ዶ/ር ብርሃኑ ስለ አቶ አንዳርጋቸው ባለፈው ሳምንት ያሉት እንዲህ ነበር -

‘እንደ አንዳርጋቸው ከራሱ ጋር የታረቀ ሰው አላየሁም”
”በእውነት በጣም እድለኛነት ነው እንዲህ ከውስጥ ከራስ ጋር መታረቅ”
” አንዳርጋቸው ሊገሉት ቢፈልጉ እየሳቀ ነው የሚሞተው የእነርሱን ከብትነት እያመነ ነው የሚሞተው”
”አንዳርጋቸው መስራት ያለበትን ጨርሶ ወጣቶችን ለመሪነት አብቅቶ አታስፈልገንም ሂድ ተብሎ እንግሊዝ ሀገር መኖር ጀምሯል”

አቶ አንዳርጋቸው ዛሬ በኢቲቪ ዜና እወጃ ላይ በድብቅ ካሜራ የተነሱት ፊልም ላይ ሲናገሩ የታየው -

”እኔ አሁን ከራሴ ጋር ታርቄ ሰላም አግኝቻለሁ”
”እውነቴን ነው የምልህ ተረጋግቼ ያለሁበት ሁኔታ ነው”
”ምንም አይነት ብስጭት የለኝም”
”ምንም አይነት መጥፎ ስሜት አይሰማኝም።የመጨረሻ እርጋታና እረፍት ውስጥ ነው ያለሁት”

ከአቶ አንዳርጋቸው ንግግር የምንረዳው ዶ/ር ብርሃኑ እንዳሉት ስራቸውን በሚገባ ጨርሰዋል።ለሚያምኑበት በመስራታቸውም ዛሬም በስቃይ መሃል ሆነው ህሊናቸው ተረጋግቷል።

የዶ/ር ብርሃኑን ንግግር ለመስማት ይህንን ይጫኑ።

ጉዳያችን 
ሐምሌ 1/2006 ዓም (ጁላይ 9/2014)