Thursday, June 5, 2014

የመቀሌ ጉራማይሌ (ግርማ ሰይፉ – የፓርላማ አባል)

June 5/2014
ጉብኝት አዋሳ ላንጋኖ ብቻ ነው ያለው ማነው? ያልን ሰዎች ትግራይ መቀሌ ለጉብኝት ጎራ ብለንለ ነበር፡፡ አንድ አንዶች ኤርትራ ሊሄዱ ነው ሲሉን ተመስገን ደሳለኝን ኤርፖርት ያዩት ሰዎች ደግሞ ተሰደደ ማለታቸውን ሰማን፡፡ አውሮፕላን ልትጠልፉ ነው ወይ ያሉንም ፌዘኞች ነበሩ፡፡ ስደትና ጠለፍ የትግላችን አካል አለመሆኑን የተረዱት ቢሆኑ ይህን ግምት ይተዉት ነበር፡፡ በቁጭት የተነጋገርንበት ግን አሰመራ የሰው ሀገር ሆኖ መሄድ ያለመቻላችን እንዲሁም ምፅዋ ከመሄድ ሞምባሳ መሄድ መቅለሉን ነው፡፡ ይህ የገዢዎች አጥር ፈርሶ አሰመራ ምፅዋ እንደምንሄድ ፅኑ እምነት አለኝ፡፡
Girma seifu
Girma seifu
በመቀሌ ባሰለፉክት ቆይታ የተረዳሁት ጥቂት ሰዎች በቁርጥና ውስኪ ቤት የሚገኙ ሲሆን፣ አብዛኛው ህዝብ ደግሞ የእለት ኑሮ ለመግፋት የሚውተረተር መሆኑን ነው፡፡ በሰራ ቀን፣ በቡና መጣጫ ሰፈሮች የሚገኘው ወጣት ብዛት የሚያሳዝን ነው፡፡ ከሁሉም የሚያሳዝነው ግን ከአንድ የወዳጃችን ዘመድ ጋር የነበረን ቆይታ ነው፡፡ ሌላው ካስፈለገ በሌላ ቀን እመለስበታለሁ፡፡
ለዚህ ፅሁፍ ሲባል ሰሙን ጥበቡ ብለነዋል፡፡ ጥበቡ በዚህ ጉዳይ ሰሙ እንዲነሳ ፈቃደኛ ሊሆን አይችልም፡፡ ጥበቡን ያገኘነው ከሰማዕታት ሀውልት ጉብኝት በኋላ 16 በሚባለው መዝናኛ ሰፈር ነው፡፡ ባንኮኒ ላይ ሆነን ስንጫወት ፈንጠር ብሎ ብቻውን ተቀምጦ ይተክዛል አብሮን ቢሆንም ልቡ ከእኛ ጋር አልነበረም፡፡ አንድ ሌላ ጓደኛውን ጠርቶት ሲቀላቀለን ከብቸኝነቱ ተገላገልን ብለን አርፈን እራት በልተን ሌላ ቤት ለማይት ጎራ አለን፡፡ ብቸኝነቱ ፍላጎት ስለመሰለን አላሰጨነቀንም፡፡ አብረውን ያሉት እነ አርሃያ እና ክብሮም በጫወታ ወጥረው ስለያዙን የጥበቡ ነገር ብዙም ልብ አላልነው፡፡(አርሃያና ክብሮም ትክክለኛ ሰማቸው ነው፡፡)
ግርማ ተመሰገን መቀሌ
ጥበቡና እኔ ጎን ለጎን ቁጭ ብለን በሙዚቃ መሃል አንድ አንድ ነገር እንጫወታለን፤ ከፊት ለፊታችን ተመስገን ደሳለኝ እና የጥበቡ ጓደኛ ቁጭ ብለዋል፡፡ ድንገት ከእኔ እና ጥበቡ ፊት ለፊት አንዲት ሴት በምሽት ዳንስ አለባበስ የሆነች እና አንድ የቪዲዮ ካሜራ የያዘ ወጣት ቁጭ አሉ፡፡ ጥበቡ እነዚህ ሰዎች እየቀረፁን ነው ወይ? ብሎ ሲጠይቀኝ አዎ አልኩት እንደቀልድ፡፡ ጥበቡ ከእኔ ጋር የነበረው ጫወታ ጠፋበት ይርበደበድ ጀመር፡፡ ሰዎቹ ተነስተው ወጡ፡፡ ቀስ ብሎ በጆሮዬ ግርማ አንተ ታወቂ ስለሆንክ ምንም አትሆንም እኔን ግን አያኖሩኝም አለ፡፡ ቀልዱን መስሎኝ ምን ያደርጉሃል? ሰለው ፍርሃት ያመጣለትን ሁሉ ነገረኝ፡፡ ፍርሃቱ ገባኝ፡፡ ሰቀልድ ነው እየቀረፁን አልነበረም፤ ካሜረው እኮ አልበራም ብዬ ለማረጋገት ሞከርኩ፡፡ እጁን ሰጥቶኝ መታሁለት እንድምልለት ጠይቆኝ ማልኩለት፡፡ እጁን ጭኔ ላይ አድርጎ ለመረጋጋት ሞከረ፡፡ እጁ ሲንቀጠቀጥ ይሰማኛል፡፡ “ግርማ ልብ አላልክም እንጂ ድሮም ከእናንተ ጋር መሆን አልፈለኩም፤ ለዚህ ነው ራቅ ብዬ ቁጭ ያልኩት” ብሎ የፍርሃቱን መጀመሪያ ነገረኝ፡፡
ሳቅም አዘንም ተሰማኝ፡፡ ቤት እንቀይር ብለን ስንወጣ ባለካሜራው ሰራውን እየሰራ ነው፡፡ አብራው የነበረችውን ልጅ ከምሽቱ ድባብ ጋር ይቀርፃታል፡፡ ሌሎችም ታዳሚዎችም አብረው አሉ፡፡ በግምት በፊልም ቀረፃ ላይ ናቸው፡፡ የጥበቡን ልብ ግን ሳያውቁ እሰኪጎን ድረስ በፍርሃት አርበደበዱት፡፡ ጥበቡን ጠርቼ “እመነኝ ይኽውልህ ሰዎቹ በሌላ ስራ ላይ ናቸው፤” ብዬ እንዲረጋጋ መከርኩት፡፡ የምታውቀው የደህንነት ሰው ቢኖር እንኳን እየጠበቁን ነው ብለህ አስብ፤ ግፋ ቢል ነገ ጠርተው ከእኛ ጋር ምን ምን እንዳደረክ ይጠይቁሃል በትክክል ያደረከውን ተናገር አልኩት፡፡ የተረጋጋ መስሎ ወደ ቀጣዩ ቤት እርሱ ባመጣልን ጓደኛው መሪነት ገባን፡፡ ጥበቡ ድንገት ተሰወረብን እምጥ ይግባ ስምጥ ማወቅ አቃተን ጓደኛው ደውሎ መሄዱን አረጋገጠ፣ ጥበቡም በማግሰቱ ጠዋት ደውሎ ይቅርታ ማታ ተረብሼ ስለረበሽኳቹ ብሎን በዝርዝር ፍርኃቱን ነገረን፡፡ ይህንን ፍርሃት ቀን ስንጎበኘው የነበረው የሰማዕታት ሀውልት ላይ ያየነው ተጋድሎ ያመጣው ሳይሆን በዚህ ትግል ጀርባ ለድል የበቁት እና በስልጣን ላይ ያሉት ሰዎች ዘርተውት መሆኑን መረዳት አያሰቸግርም፡፡ ስንት የትግራይ ልጆች በእንደዚህ ያለ ፍርሃት ስር እንደወደቁ ማሰብ አያሳቸግርም፡፡

Wednesday, June 4, 2014

በዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ወራሪው ማን ነው? ተወራሪዎቹስ?

June 4/2014
Ethiopian soldiers fighting against Somalian
በዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ታላቅ የሕዝብ ቅልቅል ተካሂዷል። ከእነዚህ ምክንያቶች መካከል፦ የአህመድ ግራኝ ወረራ፣ የኦሮሞ ወረራ፣ በዘመነ መሣፍንት የነበሩት የእርስ በእርስ ጦርነቶች፣ ፈፃሜ-ዘመነ መሣፍንትን ያበሠሩት የማዕከላዊ መንግሥትን እንደገና የማዋቀር ጦርነቶች እንዲሁም ሁለቱ የኢጣሊያ ወረራዎች የሚጠቀሱ ናቸው። እነዚያ ጦርነቶች እና የእርስ በእርስ ግጭቶች ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የሕዝብ ክፍል ሕይዎት እንዳሣጡ አይካድም። ያንንም ተከትሎ ከኑሮ አስገዳጅነት እና በአገዛዝ ኃይሎች የበላይነት የያዘው አካል በሚፈጥረው የፖለቲካ አሠላለፍ መለዋወጥ ምክንያት የአንዱ ጎሣ ወይም ነገድ አባሎች በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመጥፋት ጉዳት ደርሶባቸዋል። በዚህ ረገድ ከኢትዮጵያ ዋና ዋና ነገዶች እና ጎሣዎች መካከል፦ በምዕራብ ኢትዮጵያ ነዋሪ የነበሩት የጋፋት ነገድ በኦሮሞ ወረራ ሙሉ በሙሉ እንዲጠፉ ሆነዋል ወይም ማንነታቸውን ተገድደው ለውጠው «ኦሮሞዎች» ወይም «ዐማራዎች» ወይም በሌላ ነገድ ስም ይጠራሉ፤ የሜያ ነገድ ተወላጆች ደግሞ በግራኝ አህመድ እና በኋላም ተከትሎ በመጣው በኦሮሞዎች ወረራ ምክንያት ቁጥራቸው በእጅጉ ተመናምኖ ዛሬ በዝዋይ ኃይቅ ውስጥ በሚገኙ ደሴቶች እና አካባቢው ብቻ ተወስነው ይገኛሉ። ጥንት በባሊ (ባሌ) እና ፈጠጋር (አርሲ) ተስፋፍተው ይኖሩ የነበሩት ሐዲያዎች እና ከንባታዎች በኦሮሞዎች ወረራ ተጨፍልቀው «ኦሮሞዎች» ሲባሉ ቀሪ ወገኖቻቸው በደቡብ ምዕራብ ሸዋ በአንድ ጠባብ አካባቢ በተጨናነቀ ሁኔታ እንዲኖሩ ተገድደዋል። ከዚህ በተጨማሪም፦ አርጎባዎች፣ ቀቤናዎች፣ ወርጂዎች፣ አላባዎች፣ ሲዳማዎች፣ ወዘተርፈ በኦሮሞዎች ወረራ ምክንያት ማንነታቸውን እንዲቀይሩ ተገድደዋል፤ ከዚያም አልፎ በጅምላ ተጨፍጭፈዋል። በእናርያ ንጉሥ ግዛት ሥር የነበሩት ጃንጀሮዎች (የም) በኦሮሞ ቆሮዎች (በእነ አባ ጅፋር) በገፍ በባርነት ተፈንግለዋል። የዳውሮ እና የገሙ ሰዎች ደግሞ ግዛታቸውን በኦሮሞ ወራሪዎች ተነጥቀዋል። በመሆኑም የዘመናዊት ኢትዮጵያን የሕዝብ አሠፋፈር ጥንቅር ለውጥ ለመገንዘብ ከአህመድ ግራኝ ወረራ ጀምሮ ማዬቱ ለበለጠ ግንዛቤ ይረዳል።
ግራኝ አህመድ በኢትዮጵያ ላይ ወረራውን የጀመረው የንጉሡ የአፄ ልብነድንግል ሹም እና የደዋሮ (ምዕራብ ሐረርጌ) ገዢ ከነበረው ከአዛዥ ፋኑኤል ጋር በ፲፭፻፲፯ ዓ.ም. ባደረገው ውጊያ ነበር። ግራኝ አህመድ ዘንተራ (ደንቢያ፣ ሰሜን ጎንደር፣ ጣና ሐይቅ አጠገብ) በአፄ ገላውዲዎስ ሥር ሲዋጉ በነበሩት የፖርቱጋል ወታደሮች የጥይት አረር ተመትቶ በየካቲት ፳፯ ቀን ፲፭፻፴፭ ዓ.ም. እስኪገደል ድረስ ኢትዮጵያን ለ፲፱ ዓመታት ያህል በጦርነት አመሠቃቅሏታል፤ ዜጎቿን ኍልቆ-መሣፍርት ለሌለው ግፍ እና በደል ዳርጓቸዋል። የእርሱን የወረራ ፍፃሜ እግር በእግር ተከትለው የመጡት የኦሮሞ ወራሪዎች ደግሞ ከ፲፭፻፵ዎቹ ጀምረው ከደቡብ ከነጌሌ ቦረና አካባቢ ተነስተው ከፊታቸው የነበረውን የሌላውን ነገድ እና ጎሣ ሕዝብ ዕድሜ እና ፆታ ሣይለዩ በጅምላ እየፈጁ እስከ ትግራይ ድረስ ዘልቀዋል። ኦሮሞዎች አብዛኛውን የኢትዮጵያ ክፍል በተከታታይ ወረራዎች ለመያዝ የፈጀባቸው ጊዜ ከ፫፻ ዓመታት ይበልጣል። ስለዚህ ዛሬ ያለውን የኢትዮጵያን የሕዝብ አሠፋፈር በቅጡ ለመረዳት ያለፈውን የ፩፻፳ ያመታት ብቻ ታሪክ ሣይሆን አህመድ ግራኝ ኢትዮጵያን ከወረረበት ከ፲፭፻፲፯ ዓ.ም. ጀምሮ የነበረውን ሁኔታ መመርመር የግድ ያስፈልጋል። ሆኖም ባለፉት ፵ እና ፶ ዓመታት በኢትዮጵያ የፖለቲካ እንቅስቃሴ «መሪዎች ነን» ብለው የተነሱ ልሂቃን የኢትዮጵያን የረዥም ዘመን የታሪክ ጉዞ በ፻ ዓመታት ብቻ በመገደብ በጉንጭ አልፋ ውዝግብ ሕዝብን ሲያተራምሱ ይታያሉ። በተለይም ለዚህ ውዝግብ ቀዳሚዎቹ የትግሬ እና የኦሮሞ ልሂቃን ሲሆኑ እንደ ዋለልኝ መኮንን ዓይነቶቹ ጥራዝ ነጠቅ የዐማራ ልሂቃንም በዚህ ክበብ ውስጥ ይገኙበታል።
ታሪካቸውን በቅጡ ያልተረዱ ጥቂት፣ አክራሪ እና ዘረኛ የሆኑ የኦሮሞ ልሂቃን፣ ከጀርመናውያን የኃይማኖት ሠባኪዎቻቸው የተጋቱትን ለኢትዮጵያዊነት እና ለዐማራ ያላቸውን ጥላቻ እንደበቀቀን ደግመው፣ ደጋግመው ሲጮኹ ይሰማሉ። ለመሆኑ የዚህ አስተሣሰብ ምንጩ ከዬት ነው? በዘመነ ቅኝ አገዛዝ የአፍሪካ ቅርምት ወቅት፣ እንግሊዞች፥ «ግብፅን መቆጣጠር ማለት ቀይ ባሕርን መቆጣጠር ማለት ነው፤ ቀይ ባሕርን መቆጣጠር ማለት ደግሞ መላውን የመካከለኛውን ምሥራቅ መቆጣጠር ነው፤» ብለው በማመን ግብፅን «የገንዘብ ብድር ዕዳን» ሠበብ በማድረግ ከቱርኮች ነጥቀው ቅኝ ግዛታቸው አደረጓት። እንደዚያም ሁሉ፣ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሠባኪዎች «ቻይናን ስጡን እና እስያ የእኛ ትሆናለች» ብለው ሰላዮቻቸውን በኃይማኖት ሠባኪነት ሽፋን በቻይና አሠማሩ፥ ቻይናም ቀስ በቀስ በምዕራባውያን ተፅዕኖ ሥር ወደቀች። የኦነግ እና የኦሕዴድ የንስሃ አባታቸው የሆነው ጀርመናዊው ሰላይ ዩሓን ክራፍ በበኩሉ «ጋሎችን ስጡን እና መላው የመካከለኛው የአፍሪቃ ክፍል የኛ [የጀርመኖች] ይሆናል፤» በማለት ጀርመን የኦሮሞን ነገድ ተጠቅሞ ምሥራቅን እና መካከለኛውን የአፍሪቃ ክፍል በቅኝ ግዛቱ ሥር የሚያውልበትን መንገድ መጥረጉን እናያለን። ስለሆነም «የነፃ ኦሮሚያ» ዓላማ አራማጆችም «ኦሮሚያ» ከሚባለው አዲስ ወያኔ-ሠራሽ ግዛት ጀምሮ የሚያራግቡት ተግባር ሁሉ፣ በ፲፱ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ሠፊውን የኢትዮጵያ አካል ቆርሶ ለጀርመን የቅኝ ግዛት ለማድረግ የታቀደው ሤራ በዚህ በእኛ ዘመን ታድሶ መቅረቡን መገንዘብ ያስፈልጋል።
ከዚህ በተጨማሪ ዩሓን ክራፍ፣ ጀርመን በአውሮፓ ፖለቲካ እና ኢኮኖሚ የበላይነቱን እንድትይዝ ያለውን ፍላጎት እንደሚከተለው ገልጿል፥ «“ጋሎችን” መያዝ መካከለኛው አፍሪቃን ለመቆጣጠር ከማስቻሉም ሌላ፣ በቀይ ባሕር ዳርቻ የሚገኙትን አገሮችን መያዝ ከንግድ መቆጣጠሪያነት ባሻገር፣ ጀርመን በአውሮጳ ያላትን የበላይነት ማረጋገጥ እና የጀርመንን ሥልጣኔ በዐረቦች ምድር፣ በአበሻ እና በመላው ምሥራቅ አፍሪቃ ማስፋፋት ነው። የጀርመን በምሥራቅ አፍሪቃ መስፋፋት፣ የእስልምና ኃይማኖት በዐረብ ምድር እና በአፍሪቃ ጠረፎች የሚያደርገውን መስፋፋት የሚያዳክም፣ የዐረቦችን የባሪያ ንግድ የሚቀንስ፣ እንዲሁም የምሥራቅ አፍሪቃን ሕዝብ አረመኔነት በክርስትና ሥልጣኔ መዋጋት ነው። ከአበሻ በስተደቡብ ያሉት “ጋሎች” የሠፈሩበት ቦታ ለአውሮጳውያን ሠፋሪዎች ምቹ ቦታ ነው፤» በማለት ጀርመን የኦሮሞዎችን ልብ ከኢትዮጵያዊነት ስሜት በማውጣት ምሥራቅን እና መካከለኛውን አፍሪቃ እንዴት በቁጥጥሩ ሥር ማዋል እንደሚችል «ወንጌላዊው» ክራፍ ምክሩን ለግሷል፤ ምክሩም የመከነ አይመስልም፤ ኦነግን እና መሰል ድርጅቶችን አፍርቷል። ለአብነትም ያህል ለኦነግ መመሥረት እና መጎልበት የስካንዴኔቪያን አገሮች፣ ጀርመኖች እና ሌሎችም የቅኝ ገዢነት ቅዠታቸው ያልለቀቃቸው አውሮጳውያን የሚያደርጉትን ሁሉን-አቀፍ ድጋፍ ልብ ይሏል!
በማስከተልም ዩሓን ክራፍ፣ ከሸዋ በስተደቡብ የሚኖሩት “ጋሎች” ብዛት ያላቸው መሆኑን ገልጦ፣ የእስላሞችን የመሥፋፋት ወረራ ሊመክቱ እንደሚችሉ እና የአፍሪቃ ጀርመኖች ሊሆኑ እንደሚችሉ ዕምነቱን አስረድቷል። ዩሓን ክራፍ ምሥራቅ እና መካከለኛው አፍሪቃ በጀርመን ቁጥጥር ሥር እንዲውል የነደፈው አንዱ ሥልት፣ ሚሽነሪዎችን በወንጌል ማስፋፋት ስም በአካባቢው በማሠማራት፣ የየአገሮቹ ልዩ ልዩ ነገዶች እና ጎሣዎችን ሊለያዩበት እና ሊናቆሩበት የሚችሉበትን ዘዴ ማጥናት፣ እንዲሁም ያገኟቸውን የማናቆሪያ ቀዳዳዎች ማስፋት ነበር። ለዚህም ዩሓን ክራፍ ያቀረበው ኃሣብ፦ «በደቡብ እና በምዕራብ ኢትዮጵያ የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆችን ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ነገዶች በመለዬት፣ በተቃራኒው ተበታትነው ይኖሩ የነበሩትን የኦሮሞ ጎሣዎች አንድ የሚያደርግ አዲስ መጠሪያ ስም በመስጠት፣ በዚህ አዲስ ስም የሚታወቅ የአካባቢ ስም ፈጥሮ፣ ያን አካባቢ ከቀረው የኢትዮጵያ የሚገነጥል ብሔርተኛ ቡድን በጀርመን ሁለንተናዊ ርዳታ ማጠናከር፤» የሚለው ነበር። ለዚህም «“ጋላ” የሚለው ስም ሁሉንም የነገዱን አባሎች አጠቃሎ ለመጥራት አያስችልም» የሚል ምክንያት በመስጠት፣ «ኦርማኒያ» ከሚለው ስም «ኦሮሚያ» የሚል ቃል በማውጣት ጥንት “ጋላ” በመባል የሚታወቀው ነገድ በዚህ እርሱ ባወጣው አዲስ ስም እንዲጠራ እና «ኦሮሚያ» ለሚባል ክልል ነፃ መውጣት እንዲታገል በወንጌል ማስፋፋት ስም አስተማረ፣ ሰበከ። በዚህ መሠረት ዩሓን ክራፍ ራሱ «ኦሮሚያ» ብሎ የሰየመውን የኢትዮጵያ አካል መቆጣጠር  ማለት፣ ምሥራቅን እና መካከለኛውን አፍሪቃ መቆጣጠር እንደሆነ በማመን የጀርመን ተስፋፊዎች ዓይናቸውን ኢትዮጵያን በማፍረስ ላይ እንዲያነጣጥሩ ምክር ለገሠ።
የዩሓን ክራፍ እና የመሠሎቹ ምክር በጀርመን ቅኝ ገዢዎች ልብ ውስጥ መስረፁ ማስረጃው ጀርመን በአፍሪቃ አኅጉር ላይ ትከተል በነበረው የቅኝ ግዛት ፖሊሲ ላይ ጉልህ አሻራ አኑሯል። በዚህ ረገድ እስከ ፩ኛው የዓለም ጦርነት ድረስ ጀርመኖች ከምሥራቅ አፍሪቃ፥ ታንዛኒያን፣ ሩዋንዳን እና ብሩንዲን፤ ከምዕራብ አፍሪቃ ቶጎን፣ ከፊል ጋናን እና ካሜሩንን፤ ከደቡባዊ አፍሪቃ ደግሞ ናሚቢያን በቅኝ ግዛትነት በያዙበት ወቅት ከእንግሊዞች፣ ፈረንሣዮች እና ጣሊያኖች በከፋ ሁኔታ ያካሄዱት የከፋፍለህ-ግዛው የቅኝ አገዛዝ አካሄድ አይረሣም። ከሁሉም መዘንጋት የሌለበት አብይ ነጥብ፥ በ፲፱፻፹፮ ዓም በሩዋንዳ በሁቱዎች እና በቱትሲዎች መካከል የደረሠው የዘር ዕልቂት እና በብሩንዲም በየጊዜው በዘር ልዩነት ምክንያት የሚደረገው መተላለቅ ሠንኮፉ በጀርመን ቅኝ ገዢዎች የተተከለ እና በኋላም ጀርመኖቹን በተኩት ቤልጂጎች ዳብሮ በዘመናችን ደግሞ በፈረንሣዮች የተተበተበ የተንኮል ድር ድምር ውጤት መሆኑን ነው። በእኛም አገር በኢትዮጵያ፣ ላለፉት በርካታ ዓመታት በዩሓን ክራፍ መሠሎቹ አመለካከት ተኮትኩተው ያደጉ የኦሮሞ ልሂቃን የሚያቀነቅኑት አስተሣሰብ አለ። ይኼውም፥ የያዙትን የኢትዮጵያዊነት ማንነት ለማስጠበቅ ሣይሆን ለማጣት በሚያስገድድ መልክ በራሣቸው ላይ ዘመቻ ከፍተው፣ ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ቀርቶ ለራሳቸው ሊሰሙት የማይፈቅዱትን ጩኸት ሲያሰሙ ይደመጣሉ።
ለመሆኑ ጥቂት የኦሮሞ ልሂቃን ነገዳቸውን “ጋላ”፣ ቋንቋቸውን “ጋልኛ” የሚለውን ዐማሮች እንደሰጡዋቸው አድርገው የሚያቀርቡት ታሪካዊ መሠረት አለው? በመሠረቱ “ጋላ” እና “ጋልኛ” የሚሉትን ስሞች ዐማራው አላወጣቸውም። እንዲያውም የኦሮሞን ታሪክ በስፋት እና በጥልቀት ያጠኑ ሰዎች እንደሚያስገነዝቡት “ጋላ” ማለት እስላምም፣ ክርስቲያንም ያልሆነ ማለት እንደሆነ ያብራራሉ። የቃሉም ምንጭ ሶማሊኛ እንደሆነ ያስገነዝባሉ። በሌላ በኩል “ጋላ” ማለት ግመል ማለት ነው የሚሉም አሉ። ሌሎች ደግሞ “ጋላ” የሚለው ቃል «ገላ» ከሚለው የኦሮሚኛ ግሥ የወጣ መሆኑን እና ትርጉሙም «ወደ ቤታችን መሄድ ፈለግን፣ ወደ ቤታችን ሄድን ወይም ገባን» ማለት እንደሆነ ያስረዳሉ። ይህም ትርጉም ኦሮሞዎች በሶማሌና በባንቱ ጎሣዎች ተገፍተው፣ ከነበሩበት ከምሥራቅ አፍሪቃ የሕንድ ውቅያኖስ ዳርቻዎች ፈልሰው ወደ ደቡብምሥራቅ ኢትዮጵያ ግዛት፥ ወደ ባሌ፣ የተጠጉበትን ዘመን በማውሣት፣ በሰላም ተረጋግተው የሚኖሩበትን ሥፍራ ፈልገው ማግኘታቸውን የሚያመለክት ስያሜ እንደሆነ ብዙዎች በትርጉሙ ይማማሉ። ስለዚህ ጥቂት ዘረኛ የኦሮሞ ልሂቃን «“ጋላ” የሚለውን የስድብ ስያሜ የሰጠን ዐማራው ነው፤» የሚሉት የራሣቸው የማንነት ቀውስ ያስከተለባቸው ግራ መጋባት ከመሆን ውጭ ሌላ አሣማኝ ምክንያት የላቸውም። «ዐማራ ይህንን መጠሪያ ሰጠን» የሚሉትም ውንጀላ ፍፁም መሠረተ-ቢስ ሐሰት ነው። በአንፃሩ «ኦሮሞ» እና «ኦሮሚያ» ለሚሉት መጠሪያዎች የታወቀ ፈጣሪ አላቸው፦ እርሱም አፍቃሬ ቅኝ ገዢዎች የነበረው ጀርመናዊው ዩሓን ክራፍ ነው።
ዩሓን ክራፍ «ጋላ» የሚለውን ቃል ለመቀየር ያነሣሣውን ኃሣብ ሲያስተነትን፦ «ጋላ» የሚለውን ቃል ሲተረጉም «ስደተኛ» ማለት እንደሆነ እና ይህም መጠሪያ በዐረቦች እና በ«አበሾች» የተሰጠ እንደሆነ ይገልፃል። በአንጻሩ እርሱ የፈጠረው «ኦርማ» ወይም «ኦሮማ» ማለት ትርጉሙ «ጎበዝ» ማለት እንደሆነ ያምናል። በእርሱ አባባል «ጋሎች» ለራሣቸው እና ለሚኖሩበት አካባባቢ አጠቃላይ የወል መጠሪያ ስለሌላቸው «ኦርማኒያ» ተብለው እንዲጠሩ ኃሣብ አቅርቧል። ሆኖም ይህንን የዩሓን ክራፍን ኃሣብ የእርሱ-ቢጤ የሆኑ የዘመኑ ሚሽነሪዎች እና ተመራማሪዎች እንኳን አልተቀበሉትም። ለምሣሌም ያህል፦ ኢትዮጵያን ያጠኑ እንደ ዶክተር ቻርለስ ቴ ቢክ ያሉ የመልከዐምድር ተመራማሪዎች፣ ለኦሮሞዎች «ጋላ» የሚለውን ስም የሰጡዋቸው ዐረቦች እና «አበሾች» አለመሆናቸውን እና ስሙ ከራሣቸው ቋንቋ የተገኘ እንደሆነ ይሞግታሉ። ይሁን እንጂ፣ ዕውነቱን ትተው ውሸቱን፣ ሠፊውን ጠልተው ጠባቡን፣ የሚያኮራውን ንቀው የሚያቀልለውን፣ የሚያስከብረውን አውግዘው የሚያዋርደውን፣ የመረጡት ጥቂት «ተማርን ያሉ» የኦሮሞ ልሂቃን፣ የዩሓን ክራፍን ስብከት አምነው ተቀብለው፣ ዐማራን እና ኢትዮጵያን ከምድረ-ገፅ በማጥፋት፣ «ኦሮሚያ» የተባለ አዲስ አገር በመመሥረት እንቅስቃሴ ላይ ከተሠማሩ ከግማሽ ምዕተ-ዓመት በላይ አድርገዋል። ወራሪ የሆኑትን ኦሮሞዎችን እንደ ተወራሪ በመቁጠር፣ ወያኔም ዮሓን ክራፍ የሰጠውን የአካባቢ መጠሪያ በማፅደቅ፣ ዐማሮችን እና ሌሎችን ኢትዮጵያውያን ከአፅመ-ርስታቸው በማባረር፣ «ኦሮሚያ» የሚል አዲስ ግዛት ፈጥሮላቸዋል።
«እንግዳ ሲሰነብት፣ ባለቤት የሆነ ይመስለዋል፤» የሚሉት አባባል አለ። እንግዶቹ እና ወራሪዎቹ ኦሮሞዎች፣ የነባሮቹን የኢትዮጵያ ነገዶች እና ጎሣዎች ግዛቶች በወረራ ይዘው፣ የገደሉትን ገድለው፣ የሠለቡትን ሠልበው፣ ጡት ቆርጠው ሲያበቁ፣ ተበዳዮቹ «ይህ በደል ተፈፀመብን» ሣይሉ፣ እንዲያውም እነርሱ «ተበደልን» ብለው በወረራ የያዙትን አገር እንገንጥል ይላሉ፣ ነባሮቹን ኢትዮጵያዊ ነገዶች እና ጎሣዎች ያፈናቅላሉ። እነርሱው ነባር የአካባቢ ስሞችን ለውጠው እና በነገዳቸው ስም ቀይረው መያዛቸው እየታወቀ፣ «ዐማራው ስማችን እንድንቀይር አስገደደን፤ ቋንቋችንን፣ ባህላችንን እና የየአካባቢ ስሞችን ለወጠብን» እያሉ ስም ሲያጠፉ ይሰማሉ። ሃቁ ግን የአካባቢ ስሞችን በመለወጥና በራሱ ነገድ ስም በመጥራት የሚታወቀው የኦሮሞ ወራሪ ኃይል ነው። የታሪክ ሠነዶችን ማጣቀስ ካስፈለገም፥ በ፲፮፻ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያን ከጎበኙት እና በአገሪቱም ተቀምጠው የሕዝቡን የአኗኗር ልማድ እና ዘይቤ በቅርበት እያጠኑ የታሪክ መድበሎችን ካበረከቱልን የአውሮፓ ሊቃውንት መካከል ፔድሮ ደ-ኮቪልኻም፣ አባ ፍራንሴስኮ አልቫሬዝ እና ሌሎችም የፖርቱጋል ዜጎች አያሌ ጠቃሚ የታሪክ ማስረጃዎችን ትተውልን አልፈዋል። እንዲሁም አህመድ ግራኝን ተከትሎ የዘመተው፣ እርሱ ባደረጋቸው ወረራዎች ሁሉ የቅርብ ተሣታፊ የነበረው የመናዊው ሺሃብ አድ-ዲን አህመድ ቢን አብድልቃድር ቢን ሣሌም ቢን ዑትማን፣ «ፉቱህ አል-ሓበሻ» በተባለው የታሪክ ድርሣኑ የዚያን ዘመን የኢትዮጵያን የሕዝብ አሠፋፈር ቅጥ በዝርዝር መዝግቦት ይገኛል። በእነዚያ ጽሑፎች ውስጥ «ጋላ» ወይም ኦሮሞ የሚባል ነገድ ዛሬ «ኦሮሚያ» ተብሎ በተከለለው አብዛኛው የኢትዮጵያ ግዛት ስለመኖሩ በአንዱም ጭራሽ አልተጠቀሰም። ስለዚህ የዛሬው ዘመን የኦሮሞ ልሂቃን የጥንት አባቶቻቸው በወረራ የያዙትን ግዛት እንደ አፅመ-ርስት ቆጥረውት ሌላውን ኢትዮጵያዊ ሲያፈናቅሉ ሃግ ሊባሉ ይገባቸዋል። ከኦሮሞ ወረራ በፊት ዛሬ ወለጋ፣ አርሲ፣ ወሎ፣ ኢሉባቡር፣ ወረኢሉ፣ ወረሂመኖ፣ ወዘተርፈ በመባል የሚታወቁት የቦታ (የአካባቢ) ስሞች የሚታወቁት እና የሚጠሩት በሌሎች ስሞች ነበር። የሚከተለውን ሠንጠረዥ እንዲሁም አባሪ ካርታዎችን ፩ እና ፪ ልብ እንበል።
ተራ ቁጥርነባር ስምበኦሮሞዎች የተሰጠው ስምየትኞቹን አካባቢዎች እንደሚገልጽበአካባቢው ነዋሪ የነበሩ ነገድና ጎሳዎች
ቢዛሞቄለምምዕራብ ወለጋጋፋት፣ ዐማራ፣ ሽናሻ፣ ቤንሻንጉል፣ አንፊሎ፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
ዳሞትሌቃምሥራቅ ወለጋጋፋት፣ ዐማራ፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
እናርያኢሉ አባቦራኢሉባቦርዐማራ፣ ከፊቾ፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
ገሙጂማጂማየም (ጃንጀሮ)፣ ገሙ፣ ዳውሮ (ኩሎ)፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
ገንዝጅባት እና ሜጫምዕራብ ሸዋጋፋት፣ ዐማራ፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
ግራርያሰላሌሰሜን ሸዋጋፋት፣ ዐማራ፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
እንደጥናእንጦጦ፣ ጉለሌ፣ የካአዲስ አበባ ዙሪያሜያ፣ ዐማራ፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
ኦ(ወ)ይጃየረር እና ከረዩምሥራቅ ሸዋሜያ፣ ሐዲያ፣ ዐማራ፣ ከምባታ፣ ሲዳማ፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
ፈጠጋርአርሲአርሲሐዲያ፣ ከንባታ፣ ሜያ፣ ዐማራ፣ አዳል (አፋር)፣ ሲዳማ፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
ደዋሮጭሮምዕራብ ሐረርጌሐዲያ፣ ከምባታ፣ ዐማራ፤ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
ላኮመልዛወሎደቡብ ወሎዐማራ፤ አዳል (አፋር)፣ አገው፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
ቤተ-ጊዮርጊስወረኢሉወረኢሉዐማራ
ቤተ-ዐማራወረሂመኖወረሂመኖዐማራ
አንጎትራያሰሜን ወሎዐማራ፣ አገው፣ አዳል (አፋር)
ባሊባሌባሌሐዲያ፣ ከንባታ፣ ሜያ፣ ዐማራ፣ ሲዳማ፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች

ስለዚህ በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባን «ፊንፊኔ»፣ ናዝሬትን «አዳማ»፣ ደብረዘይትን «ቢሾፍቱ በሉ» እያሉ ለማስገደድ ለሚሞክሩት ዘመነኞች እኛም፥ ወለጋን ቢዛሞ እና ዳሞት፣ ኢሉባቡርን እናርያ፣ ወሎን ላኮመልዛ፣ አርሲን ፈጠጋር፣ ሐረርጌን ደዋሮ፣ ወዘተርፈ ብለን በጥንቱ ስማቸው የምንጠራ መሆናችንን እንዲያውቁት እንሻለን። ወደፊት ካላረፉም በእንግድነት ከኖሩበት አገር «ውጡ» የምንል መሆኑን ሊያውቁት ይገባል። የኦሮሞ ቀለም-ቀመስ ትውልድ ዐማራን በአውራ ጠላትነት ፈርጆ፣ ክንዱን አስተባብሮ ሊያጠፋው ሲነሣ፣ ዐማራው በተቃራኒው እጁን አጣጥፎ ተቀምጦ ይጠብቀናል ብለው ካሠቡ በእጅጉ ተሣስተዋል። በመሆኑም ለማንኛችንም የሚበጀው እኛ ኢትዮጵያውያን በጠቅላላ አንዳችን ለሌላችን ቀና መተሳሰቡ እንጂ፣ ፍጭው ፈንግጭው ከሆነ ዬትም አንደርስም። እንዲያውም ከኖረው መልካም ባህላችን ውስጥ የቀረንን አብሮ እና ተቻችሎ የመኖር መልካም ባህላችንን እንኳን ለማጣት እንገደዳለን። ስለሆነም ከዚህ ተነስተን «ወደፊት እንዴት እንጓዝ?» የሚለውን ጥያቄ አንስቶ በጋራ በሚደረስበት ውሣኔ የተሻለች ኢትዮጵያን በመገንባቱ ላይ ማተኮሩ ዐዋቂነት ብቻ ሣይሆን ብልኅነትም ነው። በየትኛውም መልኩ የትናንት ኢትዮጵያን ካነሣን፣ በዳዩ «ተበደልኩ» ባዩ፣ ወራሪውም «ተወረርኩ» የሚለው የኦሮሞው ልሂቅ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።
ሞረሽ ወገኔ በተለይ በአሁኑ ወቅት ራሱን በኢትዮጵያዊነት ጭንብል ውስጥ ሸፋፍኖ፣ ለጥፋቱ ሁሉ የሩቅ ተመልካች ሆኖ ለሚታዘበው የተማረው የዐማራ ተወላጅ የሚያስተላልፈው ግልፅ መልዕክት አለ፦ ወገናችን ከምድረ-ገፅ እየጠፋ ዝምታው እስከመቼ ነው? «ትውልድ ትውልድን ተክቶ ያልፋል፣ ታሪክም ይመዘገባል» ተብሏልና ዛሬ ለወገኖቻችን ካልደረስን ነገ እያንዳንዳችን የትውልድም፣ የታሪክም ተጠያቂ ከመሆን እንደማንድን መካድ አይቻልም። ስለዚህ በወገኖቻችን በዐማራው ነገድ ተወላጆች ላይ በትግሬ-ወያኔ እና በተባባሪዎቻቸው ላይ የሚደርሰው ሠቆቃ ከዚህ በላይ በዝምታ እና በቸልተኝነት ሊተው ከማይችልበት ምዕራፍ ላይ መድረሱን ተገንዝቦ ለወገን ጥሪ ተጨባጭ የተግባር ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል።
ዐማራን ከፈፅሞ ጥፋት እንታደግ!
ፈለገ-አሥራት የትውልዳችን ቃልኪዳን ነው!
ኢትዮጵያ በታማኝ ልጆቿ መስዋዕትነት እና ትግል ለዘለዓለም ፀንታ ትኖራለች!
ካርታ ፩፦ (ምንጭ፦Tellez, Balthazar, (1710). The Travels of the Jesuits in Ethiopia.)
ካርታ ፪፦ (ምንጭ፦ ፕሮፌሠር ጌታቸው ኃይሌ፣ ፲፱፻፺፭ ዓ.ም.። የአባ ባሕርይ ድርሰቶች፤ ኦሮሞችን ከሚመለከቱ ሌሎች ሰነዶች ጋራ። ገፅ ፲፪።)

አባ ዱላና ከንቲባ ድሪባ የቁም እስረኛ ሆኑ፣ ፓስፖርታቸው ተቀማ

May 4/2014
“የኢህአዴግ በርዕዮተዓለም መበላላት ይፋ እየሆነ ነው”
abadulla and deriba


አባ ዱላ ገመዳና የአዲስ አበባ ከንቲባ ድሪባ ኩማ ፓስፖርታቸውን ተነጥቀው የቁም እስረኞች መሆናቸው ከተለያዩ ምንጮች እየወጡ ያሉ መረጃዎች አመልከተዋል። የጎልጉል ምንጮች ግን ኦህዴድ ውስጥ በከፍተኛ አመራሮች ደረጃ እየተካሄደ ያለው ግምገማ ሲጠናቀቅ በርካታ ባለስልጣኖች ክስ እንደሚመሰርትባቸው ተናግረዋል።
በቀድሞው የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት አባ ዱላ ገመዳና በአቶ ድሪባ ላይ ይህ ውሳኔ የተላለፈው አገር ጥለው እንዳይወጡ በሚል ነው። ጎልጉል በቅርቡ ካገር መውጣት የማይችሉ ባለሥልጣኖች እንዳሉ ጠቅሶ መዘገቡ ይታወሳል። ውሳኔው የተላለፈው ሰሞኑን የአዲስ አበባን አዲስ ማስተር ፕላን ለመተግበር የኦሮሚያ ክልል ከተሞች መካተታቸው ይፋ መሆኑን ተከትሎ ከተነሳው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ነው። ከሁለቱ ባለስልጣናት በተጨማሪ ከፍተኛ የክልልና የዞን የኦህዴድ አመራሮችም በደህንነት ቅርብ ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑ ተሰምቷል። ካገር መውጣት የማይችሉም አሉ።
አባ ዱላ /ጃርሳው/
ሙክታር
ሙክታር
አባ ዱላ ኦሮሚያን ሲረከቡ በማክረር አካሄድ የሚታወቁት አቶ ጁነዲን ያዋቀሩትን ካቢኔ በመበተን ሥራቸውን አንድ ብለው ጀመሩ። አዲስ ካቢኔ ሲገነቡ የመረጡት አዲስ የዩኒቨርስቲ ተመራቂዎችንና በክልሉ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የተቀናቃኝ (የተቃዋሚ) ፓርቲ አባላትን በማስኮብለል ነበር። ህወሃት ለሁለት በተበረገደበት ወቅት ለአቶ መለስ ቡድን ድጋፍ በመስጠት ቅድሚያ የያዙት አባ ዱላ ባስቀመጡት ውለታ መሰረት ኦሮሚያ ላይ ያሻቸውን እንዲያደርጉ የሟቹ መለስ ድጋፍ ነበራቸው። በዚህም ድጋፍ ሳቢያ ኦሮሚያ ላይ የሚፈልጉትን ሲያደርጉ ከተባረሩት መካከል የአሁኑ ፕሬዚዳንት ሙክታር ከዲር ይገኙበታል።
“አትደግፉን ነገር ግን የክልሉን ልማት አታደናቅፉ” በማለት አዲስ የመለመሏቸው የተለያየ አመለካከት ያላቸው አዳዲስ የኦህአዴድ አባላት ኦሮሚያን ከአባ ዱላ እጅ ተረከቡ። አባ ዱላ ፍጹም ነጻነት ይሰጡ ስለነበር ካድሬው ወደዳቸው። ስማቸው ተቀይሮ መለያ ተሰጣቸው፤ “ብራንድ” ሆኑ – “ጃርሳው” ተባሉ። በካቢኔያቸውና በሳቸው መካከል የነበረው ፍቅር በነደደበት ወቅት አባ ዱላ ክልሉን እንደሚለቁ ተሰማ። ባለፈው ምርጫ አባ ዱላ ለፌዴራል እንጂ ለክልል እንደማይወዳደሩ ይፋ ሲደረግ ካድሬው ገነፈለ። “የኢህአዴግ ምክር ቤትን ውሳኔ አንቀበልም” በማለት ተቃወመ። ከአንዴም ሁለት ጊዜ ስብሰባ ቢካሄድም ከስምምነት ላይ ሊደረስ ባለመቻሉ ተበተነ። በመጨረሻም ራሳቸው አባ ዱላ በመሩት ስብሳባ ካድሬውን ተማጽነው ነገሩ ረገበ። ይሁን እንጂ ቅርሾ ግን ነበር። ይህንኑ አስመልክቶ “ኦህዴድ/ኢህአዴግ በመደብ ትግል መተላለቅ ጀመረ” በማለት ዘግበን ነበር።
አባ ዱላ ኦሮሚያን ሲመሩ ቆይተው ሲመሻሸ “ይህንን ቤት ይዤ ለመታገል አይመቸኝም” በማለት ቦሌ ያስገነቡትን አስገራሚ ህንጻ ለኦህዴድ አስረከቡ። በከፍተኛ ሙስና ይታሙ ስለነበር ተናዘውና ገብረው ታለፉ። ለፌዴራል ተወዳድረው አፈ ጉባኤ ለመሆን በቁ። በወቅቱ የወ/ሮ አዜብ ድጋፍ ቢኖራቸውም የሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲን የቀኝ እጅ የሆኑ ባለስልጣኖች ግን ጠምደዋቸው ነበር። ሙክታር አህመድ አንዱና ዋናው ነበሩ። ከላይ በረከት ስምዖንና አዲሱ ለገሰ አባ ዱላን ከሚቃወሙ መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚቀመጡ ናቸው።
በዚህ አጣብቂኝ ውስጥ አልፈው እዚህ የደረሱት አባ ዱላ ሰፊ ቁጥር ያላቸውን ተማሪዎች ህይወት የቀጠፈውን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን አስመልክቶ አምቦ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው ተማሪዎችን ከወ/ሮ አስቴር ማሞ ጋር በመሆን አነጋግረው ነበር። በወቅቱ የተማሪዎቹ ጥያቄ ፍትሃዊ እንደሆነ ሲመሰክሩ፣ ይህንኑ ምስክርነታቸውን ለተለያዩ የአገር ውስጥና የውጪ አገር ሚዲያዎች አሳውቀውም ነበር። አያይዘውም ነፍስ ያለ አግባብ ያጠፉ እንደሚጠየቁ ቃል ገቡ።abadulla
የጎልጉል ምንጮች እንዳሉት አባ ዱላ ይህንን ከተናገሩ በኋላ ከፍተኛ ወቀሳ ተሰንዝሮባቸዋል። “ረብሻውን ያስነሱት ራሳቸው የኦህዴድ ካድሬዎች ናቸው” ከሚል ድምዳሜ የደረሰው ኢህአዴግ ችግሩ ከተፈጠረ በኋላ ሰፊ የስለላ ስራ አከናውኗል። “ጥፋተኞቹን ለህግ እናቀርባለን” በማለት መግለጫ ያወጣው ኢህአዴግ በቀጣይ የሚያስራቸውና የሚከሳቸው ባለስልጣኖች አሉ። ምንጮቹ በተለይ አባዱላና የአዲስ አበባ ከንቲባ የሆኑት አቶ ድሪባ ኩማ ላይ ስለሚወሰደው ርምጃ ያሉት ነገር ግን የለም። ክስ ከተመሰረተባቸውና ምርመራው በሰንሰለት ታች ድረስ ከዘለቀ የኦህአዴድ የታችኛው መዋቅር ሊናጋ እንደሚችል ግን ግምታቸውን አኑረዋል። ለምሳሌ ያነሱት ሽፈራው ሽጉጤን ነው። ሽፈራው ሽጉጤ በሙስና እንዲከሰሱ ከተወሰነ በኋላ የታለፉት “የሲዳማ ብሔረሰብ ይነሳል” በሚል እንደሆነ ያወሱት ምንጮች “ክስ ተመስርቶ ምርመራው ቢካሄድባቸው ወ/ሮ አዜብም አሉበት ሲሉ አስቀድመው በምክር ቤት ይፋ በማድረጋቸው ዝምታ ተመርጧል”።
ኦህዴድን ወደ ታች ማዘዝ እንደ ቀድሞው አይቀልም
አዲስ አበባን የሚያሰፋው አዲሱ ማስተር ፕላን ተግባራዊ እንዲሆን ሀሳብ ሲቀርብ ድፍን የኦህዴድ ምክር ቤትና ካቢኔ ተቃውሞ አሰምቷል። በክልሉ ምክር ቤት ደረጃም የተያዘው አቋም ተመሳሳይ ነው። ይህንን እውነት የሚያነሱ ክፍሎች ኢህአዴግ/ህወሃት ስንቱን አስሮና ለፍርድ አቅርቦ ይችለዋል ሲሉ ጥያቄ ይሰነዝራሉ” ቀደም ሲል በምርኮኞች ስብስብ የተቋቋመው ኦህዴድና አሁን ያለው ኦህዴድ የተለያዩ መሆናቸውን ኢህዴግ ችግር ሊገጥመው እንደሚችልም ግምታቸውን ያስቀድማሉ።
አሁን ያለው ኦህአዴድ ከምርኮ አስተሳሰብ የተላቀቀ። አዲስ ትውልድ የተካተተበት፣ በጎሳ አስተሳሰብ የተቃኙ፣ ህወሃት በሚፈልገው መጠን ከመታዘዝ በላይ ወደ ራሳቸው ደምና ጎሳ የተሳቡ፣ ይህንኑ አስተሳሰብ እስከ ቀበሌ መዋቅር ድረስ የተከሉ በመሆናቸው የተወሰኑ የበላይ አመራሮችን በማሰር ችገሩ ሊፈታ እንደማይችል ሰፊ አስተያየት እየተሰጠ ነው። ለዚህም ይመስላል ኢህአዴግ በመደብ መተላላቅ መጀመሩ ይፋ እየሆነ የመጣው።
የመጨረሻው መጀመሪያ
ለጊዜው ይፋ ሆኑ መረጃዎች እንደሚያመክቱት አባዱላና አቶ ድሪባ ኩማ ካገር መውጣት አይችሉም። የተጀመረው ግምገማ ተጠናቆ የሚሆነው ሳይታወቅ በቅርብ ክትትል ስር ናቸው። የጎልጉል ምንጮች እንደጠቆሙት የዞንና ወረዳ መዋቅሮች ላይ ርምጃ ለመውሰድ  ስጋት አለ። ካድሬው ዘንድም መደናገጥ ተፈጥሯል። ህወሃት ውስጥም የአቋም መለያየት ተከስቷል፡፡ በአንድ ወገን ካድሬው እንዳይሸፍትና በቀጣዩ ምርጫ ኢህአዴግን አሳልፎ እንዳይሰጠው ርምጃው የተለሳለሰ መሆን አለበት እየተባለ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ግለ ሂስ በማካሄድ ነገሩን የማርገብና ምርጫውን የማለፍ ስልታዊ አካሄድ አለ። ይሁን እንጂ ኦህዴድ እየተለማመደ ያለው አካሄድ ሌሎችን ትምህርት በሚሰጥ መልኩ ካልታረመ ወደ ፊት ችግሩን ያገዝፈዋል የሚል አቋም የሚያራምዱ መኖራቸው ታውቋል። ህወሃት በዚህ ደረጃ አቋም ለመያዝ አለመቻሉና በርዕዮተ ዓለም መከፋፈል መጀመሩ ለዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ የዘራው መርዝ መልሶ ራሱን ሊያጠፋው አፉን መክፈቱ የሚጠቁም ነው፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ወቅት “ኢህአዴግ በርዕዮተ ዓለም መበላላት መጀመሩ ይፋ እየሆነ ነው” የሚለው ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚነሳ ዓቢይ ጉዳይ ሆኗል፡፡

Tuesday, June 3, 2014

Tigrean Opposition to the TPLF

June 3, 2014
by Messay Kebede
Despite the TPLF’s view of itself as the model of representation of ethnic interests and well-being, the growth of disenchantment is perceptible in Tigray. The proof is that non-violent Tigrean opposition to the TPLF is no longer negligible. Despite a tight control and continuous harassments, the movement known as ARENA is stepping up its criticisms of the regime and its attempt to organize and mobilize a credible popular opposition. Though the movement is ethnic-based, it is ideologically quite distinct from the TPLF, since its program includes not only the achievement of genuine democracy, but also the “restoration of Ethiopian Sovereignty.” The latter goal indicates a movement that counters the TPLF’s vision of Ethiopia as a mere collection of sovereign nations and nationalities.Tigray People's Democratic Movement (TPDM) is one of the strongest armed groups
Another countering movement is the TPDM (Tigray People’s Democratic Movement), considered by many observers as one of the strongest—if not the strongest—armed groups fighting to topple the EPRDF government. Even though I personally do not have any information about the actual strength of the movement other than what I read online, I note that their political program describes a vision of Ethiopia that it is antithetical to that of the TPLF. Indeed, the program denounces the TPLF system because it is “narrowly based on clan and family orientations.” It adds that the system “has endangered the collaborative culture and the historic unity of the people of Ethiopia . . . in the name of self-determination.” Unsurprisingly, the program says, the TPLF policy has created a barrier of “hatred” between the people of Tigray and the people of the rest of Ethiopia, a situation obviously fraught with ominous consequences for Tigreans as well as for Ethiopia.
The importance of these movements comes from the fact that they correct an anomaly, the very one that changed Tigray, the birthplace and the constant supplier of the guardians of Ethiopiawinet, into an initiator and proponent of ethnonationalism and secessionist movements. While the marginalization of Tigray under previous regimes by the hegemony of Amhara elite has understandably created resentment, the espousal of ethnonationalism and secessionism to the point of making Ethiopia landlocked directly contradicted the historic vocation of Tigray. The new path amounted to nothing less than the loss of its very soul. It is because many people were still counting on Tigray’s legacy of guardianship of Ethiopian unity that they welcomed the TPLF with open arms subsequent to the routing of the Derg’s army. The same reliance on Tigray’s traditional commitment to Ethiopian unity explains why the Derg was unable to convince people, despite repeated warnings, of the danger of a military victory of the TPLF.
We know when the turning point occurred: it was in the 60s and early 70s when a majority of Ethiopian educated elites turned against their own legacy and cultural identity through the instigation of the ideology of Marxism–Leninism. In one of my books, I describe the derailment as a “cultural dislocation,” one of its impacts being the measurement of revolutionary zeal by how far one is ready to deconstruct Ethiopia. When you add resentment against Amhara elite to the revolutionary zeal, you have a combination liable to produce estranged groups, the prototype of which is the late Meles Zenawi.
If people’s identity matters, then we should expect a retraction of the type that both renews and brings back the suppressed Tigrean commitment to Ethiopian unity. Is the opposition to the TPLF strong enough to change into a large movement of protest? It is hard to tell for the simple reason that many Tigreans, even though they are aware of TPLF’s derailment and its pernicious effects, are still apprehensive as to the future that awaits them if the TPLF is dislodged from power. The propaganda of the TPLF and its politics of fear have no doubt gotten into the head of many Tigrean elites, not to mention those supporting the TPLF out of greed or political ambition.
Still, the existence of an opposition, however small it may be, that is willing to confront the TPLF on the issue of Ethiopian sovereignty forebodes a change of heart that can further expand provided that favorable conditions upholds it. All the more reason for expecting the expansion of opposition is, as pointed out by Professor Mesfin in a recent article, the realization by ordinary Tigreans that the promise of rapid and all-out economic development of Tigray is far from being fulfilled. The realization contains the understanding that justice and freedom are indivisible, that you cannot have them in one place and not in others. If the system is just and democratic, it is so for everybody; if it excludes other ethnic groups, you can be damn sure that Tigreans too will become victims. Once you erect the wall of special privileges, you have a system that serves the few to the detriment of the many, regardless of ethnic groups.

U.S. Warns of Possible Terror Attack in Ethiopia

June2,2014

Addis Ababa — The US Embassy in Addis Ababa urged American citizens residing or traveling to Ethiopia to exercise caution over a possible attack by a Somali terrorist group.

The safety advisory the embassy said was issued due to threat from Al-Shabaab against Ethiopia and western interests in Ethiopia.

Citing to multiple and ongoing credible threats, the US embassy urged its citizens to take the highest precautions to maintain their personal safety and security.

“The Embassy continues to receive credible threat reports of Al-Shabaab’s intent and capability to attack Ethiopia and western interests in Ethiopia” it said in a statement Sudan Tribune received on Sunday.

The embassy said that there have been a number of incursions along the Ethiopian-Somali border in recent weeks urging its citizens to maintain a high level of vigilance and to take appropriate steps to enhance personal security.

“While there is no known specific information regarding the timing or location of an attack, we would like to remind U.S. citizens to be especially vigilant in areas where large numbers of US and western citizens congregate, including restaurants, hotels, bars, places of worship, supermarkets, and shopping malls” the statement said.
The embassy highly recommended for Americans living in Ethiopia and those travelling to Ethiopia to enrol in the Department of State’s Smart Traveler Enrollment Program (STEP).

“The STEP enrollment gives you the latest security updates, and makes it easier for the U.S. embassy or nearest U.S. consulate to contact you in an emergency. If you don’t have Internet access, enrol directly with the nearest U.S. embassy or consulate” it added.

Ethiopia, which is a regional security partner of the United States government, has a deployed forces in war torn Somalia to help the weak government battle the Al-Qaeda-allied Al-Shabaab group.

In the past Al-Shabaab has repeatedly warned to carryout massive attacks in Ethiopia in retaliation for its military intervention and Addis Ababa takes such threats seriously.

However government officials often disclose that the country’s defence force and intelligence are capable enough to thwart Shabaab’s terror plots and to defend the country from any external enemy.

Addis Ababa says it will remain determined to keep its troops in Somalia till order, peace and security is fully restored in Somalia.

However Ethiopian opposition politicians on the contrary call on government for immediate pull-out arguing keeping the troops longer will increase the risk of retaliation attacks against the horn of Africa’s nation.
Source: SudanTribune

የሕዳሴ አብዮት! (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ )

June 2/2014

የዛሬይቱ ኢትዮጵያችን ‹‹አብዮታዊ ሁኔታ›› ላይ ለመድረሷ በብዙሃን ዜጐች ዕይታም ሆነ፤ ሂደቱን በተከታተሉ ዓለም አቀፍ ተቋማትና ምሁራን ምልከታ የማይታበል ሐቅ ሊሆን መቃረቡ በዚህ ተጠየቅ ለማነሳው አጀንዳ ገፊ-ምክንያት ነው፡፡ በአናቱም ባለፈው ሳምንት ‹‹የ‹ቀለም› አብዮት ናፍቆት›› በሚለው መጣጥፍ ላይ ለማሳያነት የጠቀስኳቸው ፖለቲካዊ፣ ማሕበራዊ እና ነገረ-ንዋያዊ ችግሮች ተደማምረው፣ ሀገሪቷን በርቀት እንደታዘብናት ሶቪየት ሕብረት፣ አሊያም በቅርበት እንዳስተዋልናት ሶማሊያ በመጪዎቹ ጥቂት ጊዜያት የመፈራረሷን አይቀሬነት ማስረገጣቸውን ልብ እንላለን፡፡ ከዚህ ክፉ የታሪክ ዕጣ ለመታደግም ከሁለት አስርታት በላይ ያስቆጠረውን ይሄን አሮጌ ሥርዓት መቀየር ብቻውን ዘላቂ መፍትሔ ሊያመጣ እንደማይችል ዛሬ ግልፅ እውነታ ሆኗል፤ ምክንያቱ ደግሞ ለዘመናት በገዥነት የተንሰራፋው የፖለቲካ ባሕልም አብሮ ካልታደሰ ነገሩ-ሁሉ ‹‹ታጥቦ ጭቃ…›› ከመሆን አለመዝለሉ ነው፡፡

Temesgen Desalegn "Fact" Ethiopian Amharic newspaper editor
እናም ወደዚህ ከፍታ ለመሻገር ሶስተኛው አብዮት ብቸኛ መፍትሔ የመሆኑ ጉዳይ አከራካሪ አይደለም፤ ይህ ታላቅ ንቅናቄ ‹‹የሕዳሴ አብዮት›› በሚል ስያሜ ቢጠቃለል፣ ሂደቱ አንድም ኢህአዴግን ከክፉ ስራዎቹ ከመግታት ባለፈ፣ ኢትዮጵያን በሁለንተናዊ መልኩ የማደስና የተረጋጋ የፖለቲካ ማሕበረሰብ መፍጠርን የመሳሰሉ ተልዕኮዎችን በቀላሉ ወደ መሬት ለማውረድ ያስችላል፤ ሁለትም ከለውጡ ጋር የተያያዙ መሰረታዊ ጥያቄዎችን ከስያሜው አንድምታ አንፃር እየቃኙ በቀላል መንገድ ለመተንተን ጠቀሜታ ይኖረዋል ብዬ አምናለሁ፡፡ አምኜም በአዲስ መስመር የሕዳሴን ታሪካዊ ዳራ፣ አተገባበር እና ተያያዥ ጉዳዮችን እየጠቃቀስኩ ለማብራራት እሞክራለሁ፡፡
‹‹ህዳሴ›› ሲባል…
በ5ኛው ክፍለ ዘመን ከጀርመን የተነሱ ጎዝ፣ ቫንዳልና ቡርጉንዲያኖችን ጨምሮ ሰባት ጎሳዎች፣ በወቅቱ ከፊል አውሮፓን ያስተዳድር የነበረውን ልዕለ-ኃያል የምዕራብ ሮማ ኢምፓየር አንኮታኩተው ግብዓተ-ፍፃሜውን ዕውን አደረጉት፡፡ ይህም የኃያሉ አገዛዝ ፍፃሜ ፕላኔታችን በአዲስ የፖለቲካ ባሕል እንድትዋጅ ሌላ የታሪክ ምዕራፍ ከፈተ፡፡ የዚህ መነሾም አሸናፊዎቹ ጀርመናውያን ጎሳዎች የአስተዳዳሪነት ችሎታም ሆነ ልምዱ ስላልነበራቸው የተፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም የሮማ ቤተ-ክርስቲያን እና ፊውዳሎቹ ሥልጣኑን ሙሉ በሙሉ በመቀራመታቸው ነበር፡፡ መላ ግዛቱም ሥልጣኔ-ጠል (Barbarism) እየተባለ የሚጠራውንና እስከ 15ኛው ክፍለ ጊዜ ድረስ በዘለቀው ‹‹የጨለማው ዘመን›› ውስጥ ያልፍ ዘንድ ተገደደ፡፡ ይህን ተከትሎ ትምህርትም ሆነ መንግስታዊው አስተዳደር በኃይማኖታዊ ቀኖና እንዲበየን ተፈረደበት፡፡ በወቅቱ አብያተ-ክርስቲያናት በብዛት ከመታነፃቸው ባለፈ አይን የሚሞላ መሰረታዊ ልማት ባለመዘርጋቱ፣ ከተሞች እጅጉን ቆርቁዘው የገጠሩን ገፅታ እስከመላበስ ደርሰው ነበር፡፡ ከሁሉም የከፋው ደግሞ መመራመር፣ መጠየቅና አለማዊ እውቀትን መፈለግ ከደመ-ቀዝቃዛዎቹ ‹‹መንፈሳዊያን›› አስተዳዳሪዎች ዘንድ ምድራዊ ፍዳን ለመቀበል መዳረጉ ነበር፡፡
በዚህ መልኩ ክፍለ-አህጉሩ ሰባትና ስምንት መቶ የመከራ ዓመታት ካሳለፈ በኋላ፣ የጣሊያኖቹ ፍሎረንስ፣ ቬነስ እና ሮማ ከተሞች ከዘመኑ በተለየ እውቀት ፈላጊና አንሰላሳይ ልጆቻቸው መናጥ ጀመሩ፡፡ ይህንን የመነቃቃት መንፈስ በሥራዎቹ በማካተት የዘመኑ ዝነኛ ባለቅኔ ዳንቴ አሊጋሪ በቀዳሚነት ይታወሳል፡፡ በ15ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ አካባቢ ደግሞ መነቃቃቱ መላ ጣሊያንን በማዳረስ በምርምር ውጤት (በሳይንስ) መቃብር ላይ ተንሰራፍቶ የነበረውን ኃይማኖታዊ አስተዳደር ዳግም እንዳያንሰራራ አድርጎ አፈራረሰው፡፡ ይህ አይነቱ የለውጥ መንፈስ ከጣሊያን ባሻገር ከአልፕስ ተራሮች ጀርባ ባሉ የአውሮፓ ሀገራት ድረስ በመዛመቱም ታሪክ ይቀየር ዘንድ ግድ ሆነ፡፡ ለሁነቱም ዋናው ተዋናይ ሕዝባቸውን ከተዋጠበት የጨለማ ዳዋ ለማላቀቅ ሲሉ የጥንታዊያኑ ግሪክ እና ሮማ የተዘነጉ የአሰላሳዮችን የአእምሮ ውጤት መመርመር ቀዳሚ ስራዎቻቸው ያደረጉት የጊዜው ጠቢባን እንደነበሩ አይዘነጋም፡፡ ታሪክ፣ ፍልስፍና፣ ባህል፣ ስነ-ጽሁፍ፣ ሞራል እና መሰል ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ እውቀቶችን መልሶ በመመርመር ጠቃሜታውን ለይቶ ማሰራጨትን የቀን ተቀን ሥራ ማድረጋቸው የማታ ማታ ለስኬት አብቅቷቸዋል፡፡ እነሆም የታሪክ ምሁራን ‹‹ሕዳሴ›› (Renaissance) ብለው የሚጠሩት ይህንን ሁነት ነው፡፡
በርግጥም ሕዳሴ የታሪክ ሀዲድን ተከትሎ የኋሊት በመመለስ የማንፃት (የመታደስ) ተግባር የሚያከናውን የሳይንስ ዘርፍ ነው፡፡ ይህም ጥንታዊውን ዘመን ዛሬ ላይ እንዳለ ማንበር ሳይሆን፤ የቀደመውን ሥልጣኔ የወደቀበትን ህፀፅ መርምሮ ለዘመኑ የሚበጀውን አንጥሮ በማውጣት፣ ያረበበውን ማሕበራዊ ፍዝነት እና ኋላቀርነት አንገዋሎ በመጣል ላይ የሚያተኩር ፍልስፍና መሆኑ አፅንኦት ሊሰጠው ይገባል፡፡ ምዕራባውያን ለደረሱበት የሥልጣኔ ከፍታ ዋናው መሰረት የተጣለው በሕዳሴው ዘመን ስለመሆኑ ራሳቸው ይመሰክራሉ፡፡ ኮፖርኒከስ፣ ጋሊሊዮ፣ ቦይል፣ ሀአርቬይ፣ አይዛክ ኒውተን፣ ሊዎናርዶ ዳ ቪንቺ፣ ሚካኤል አንጀሎን የመሳሰሉ ጉምቱ ጠቢባን የሥራ ውጤትም አብርሆት (ኢንላይትመንት) የሚባለውን ዘመን ወልዷል፤ ይህም ወደ ኢንዱስትሪ አብዮት አሸጋግሮ ለዛሬው ዘመናዊነት መደላድልን ስለማመቻቸቱ የታሪክ ድርሳናት ያትታሉ፡፡
በወቅቱ የሕዳሴው መንገድ ቀያሽ ተደርጎ የሚጠቀሰው ገዥ-ሃሳብ፣ የሰውን ልጅ በቀዳሚነት በሚያጠናውና ሰዋዊነት (Humanism) ተብሎ በሚጠራው ዘርፍ ላይ የተመሰረተ ሲሆን፤ ይህ አስተሳሰብ በሀገረ-እንግሊዝ በተስፋፋበት በ16ኛው ክፍለ ዘመን የተነሳው ፀሐፌ-ተውኔት ዊሊያም ሼክስፒር፣ ኃይማኖታዊ ክብረ በዓላትን፣ ስሜት-ተኮር እንቅስቃሴዎችንና ሥነ-ምግባር ላይ ብቻ ያውጠነጥን የነበረውን የድራማ ዘውግ፣ ወደ አለማዊ ይዘትነት በመቀየር ለሀገራዊ ፍቅር መነቃቃት እና የአርበኝነት መንፈስን በማስረፅ ረገድ ወደር የማይገኝለት ሚና ለመጫወቱ ዘመን ተሻጋሪ ስራዎቹ ግንባር ቀደም ምስክሮች ናቸው፡፡ በጥቅሉ የ‹‹ሕዳሴ›› (Renaissance) ፅንሰ-ሀሳብ የግሪክና የላቲን ብሉይ መድብሎች ላይ ቆሞ ፍልስፍናን እና መሰል የእውቀት ዘርፎችን መተርጎምን የያዘ የብርሃን ንቅናቄ በመሆኑ፤ የግለሰብን አለማዊ ከፍታ ለማስረገጥ፤ የሰውን ልጅ ምክንያታዊነት፣ የምርምር ክሂልና የኪነ-ውበት ፈጠራ ማሳደግን ዋነኛ ማዕከሉ ያደረገ ብርቱ የለውጥ መንፈስ ነው ተብሎ ቢደመደም ማጋነን አይሆንም፡፡
የኢትዮጵያ ህዳሴ
በሚሊኒየሙ አከባበር ዋዜማ ይህንን ቃል በጥራዝ ነጠቅነት የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ መጠቀሙን ተከትሎ፣ ከክቡራን ሚንስትሮች እስከ የቀበሌ ካድሬዎች የንግግር መክፈቻና መዝጊያ ሆኖ ዛሬም ድረስ በማጭበርበሪያነት እያገለገለ ይገኛል፡፡ በአባይ ወንዝ ላይ እየተሰራ ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫንም «የሕዳሴ ግድብ›› ሲሉ ሰይመውታል፤ ምንም እንኳ የትኛውን ያለፈ ታሪካችንን እንደሚያድስ አፍታተው ባይነግሩንም፡፡ ሰሞኑን የተከበረውን የግንቦት ሃያ በዓል በማስመልከት በቴሌቪዥን መስኮት ቀርቦ በወሬ ደረጃ የሚያውቀውን ገድል እየተደነቃቀፈ የተረከልን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝም ቢሆን ‹‹የግንቦት ሃያ ድል ኢትዮጵያ ወደ ቀድሞ ገናናነቷ እንድትመለስ /እንድትታደስ/ የጠቀመ ነው›› ከሚል መታበይ አልፎ፣ የትኛውን የገናናነት ዘመናችንን ለመመለስ እንደተቻለ ለይቶ አላስቀመጠልንም፡፡ በርግጥ እርሱ እያወራ የነበረው የአክሱም ስልጣኔን በተመለከተ ከሆነ፣ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ታላቁ ስላቅ ተብሎ በታሪክ ማህደር ሊመዘገብ ይገባል፤ በተለይም የአቶ መለስ ዜናዊን ‹‹የአክሱም ሀውልት ለወላይታው ምኑ ነው?!›› ሽርደዳን ስናስታውስ፡፡ በተቀረ ‹‹ሕዳሴ›› ብሎ ለመሰየም በቅድሚያ መታደስ የሚገባው ጥንታዊ ሥልጣኔ ስለመኖሩ ማመን እንደሚጠይቅ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ፕሬዚዳንት ለነበረ ሰው ይጠፋዋል ብዬ አላስብም፡፡
በአናቱም ጀግናው ኢህአዴግ ከምንሊክ በፊት የነበረችዋን ኢትዮጵያ እንደማያውቃት ሲለፍፍ እና የኢትዮጵያ ታሪክን በ100 ዓመት ገድቦ፣ የቀደመው የሥልጣኔ አሻራ የአንድ ወይም የሁለት ቋንቋ ተናጋሪ ማሕበረሰብ ግንጥል ውበት እንደሆነ ለሃያ ሶስት አመት ሙሉ ሲሰብክ ኖሮ፣ ዛሬ ‹የጥንቱን ገናናነት እንመልሳለን› ማለቱ፤ ራሱ ካነበረው የሥርዓት አወቃቀር ጋር ፊት ለፊት እንደሚያላትመው የዘነጋው ይመስለኛል፡፡ ይህም ሆኖ ‹‹ስለሕዳሴ የማወራው ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ አይደለም!›› ካለን ደግሞ፣ የኢትዮጵያን የ3ሺህ ዘመን ቀደምት ታሪክ በይፋ አምኖ መቀበሉን ያወጀ ያህል አድርገን ልንወስደው እንችላለን፤ ግና፣ ይህ አይነቱ አቋም ድንገት በሞቅታ የሚለወጥ ሳይሆን፣ ብዙ ማብራሪያዎችን እና ደም ያፋሰሱ ጠማማ ታሪኮችን የማቃናት ከባድ ሥራ የሚጠይቅ ነው፡፡ በተረፈ የሕዳሴው ልፈፋ በታሪክ ብያኔው ያኮረፉትንና ‹ቅድሚያ ኢትዮጵያዊነት› የሚሉትን ስብስብ በሀሳዊ የፕሮፓጋንዳ ማግኔት ወደፓርቲው ለመጎተት የሚጠቀምበት ተራ የማጭበርበሪያ ስልት ከመሆን የሚዘል አይመስለኝም፡፡
የሆነው ሆኖ በዚህ አውድ መከረኛይቷን ኢትዮጵያ ከአደገኛው ማዕበል የሚታደጋት ቀጣዩ ሕዝባዊ ንቅናቄ ‹‹የሕዳሴ አብዮት›› በሚል ማዕቀፍ ስር ይወድቅ ዘንድ ገፊ-ምክንያቱ፣ የሥርዓት ለውጥ ብቻውን ለሀገሪቱ ትንሳኤ በቂ አለመሆኑን አፅንኦት ለመስጠት ነው፡፡ ስለምን? ቢሉ፣ በተለይም ከ1983ቱ የመንግስት ቅያሬ በኋላ የተከሰቱ አስጨናቂ ችግሮች መፍትሄ ያገኙ ዘንድ ዳግም የመታደስ (እንደገና የመወለድ) አስፈላጊነትን አማራጭ አልባ ምርጫ በማድረጋቸው ነው፡፡ በተለይም የብሔር ፖለቲካው የወለደው የጎሳ ክፍፍል፣ ከባህላዊ እሴቶች ማፈንገጥ፣ የትምህርት ጥራት ማሽቆልቆል፣ የኃይማኖት መቻቻል ወደ ታሪክነት መቀየር፣ የህሊና ታማኝነት መደብዘዝ እና ከሰው ልጅ ይልቅ ቁስ መከበሩ… ከሞላ ጎደል አብዮቱን በታሪክ ማንፃት መካከል የማለፍ ተልዕኮ እንዲያነግብ ገፍቶታል፡፡ በተጨማሪም የቀድሞ የታላቅነት መገለጫችን የሆነው የአክሱም ሥልጣኔ ክቡድ መንፈስ ለዚህ ዘመን መዋጀት የሚበቃ ሽራፊ ምስጢረ-ጥበብን ሸሽጎ ስለመያዙ ከቶም ቢሆን ቅንጣት ታህል የማንጠራጠር መሆናችን ሕዳሴን አጀንዳ እንድናደርገው ያስገድደናል፡፡
ከላይ እንዳየነው የአውሮፓን ሥልጣኔ በፅኑ መሰረት ላይ ያስረገጡት አሰላሳዮቻቸው እንደሆኑ ሁሉ፤ በእኛም አውድ ሀሳቦቻቸውን ወደ አደባባዩ ተዋስኦ አብዝተን ልናካትትላቸውና የሕዳሴያችን ምሁራን ሊሆኑ ይገባል ብዬ የማምንባቸው ሶስት መምህራን አሉ፡፡ መስፍን ወልደማርያም፣ መሳይ ከበደና ተከስተ ነጋሽ፡፡ አዛውንቱ ጠቢብ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በተለይም ‹‹መክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ›› በሚለው መጽሐፋቸው፣ የኋላው መዘንጋቱ የችግሮቻችን ምንጭ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው አሳስበዋል፡፡ በገፅ 12 ላይም እንዲህ በማለት በቁጭት ይጠይቃሉ፡-
‹‹ከአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዓመታት በፊት ሰረገላ ነበር፣ የመስኖ እርሻ ነበር፣ የግንብ ቤት ነበር፣ ሕዝብ የሚገበያየው በገንዘብ ነበር፤ ከአራት መቶ ዓመታት በፊት ጋሪ ነበር፣ ድልድይና የግንብ ቤቶች ተሰርተው ነበር፤ የዚህ ሁሉ የሥራ ጥበብ ለምን ከሸፈ? የአክሱም ሀውልቶችን የመስራት ጥበብ ለምን ከሽፎ ቀረ? የላሊበላን ከድንጋይ የተፈለፈሉ አብያተ ክርስቲያናት የመስራት ጥበብ ለምን ከሸፈ? የጎንደርን ቤተ-መንግስቶች የመስራት ጥበብ ምን አክሽፎ አስቀረው? እነዚህ ሁሉ የድንጋይ ስራ ጥበቦች በሚታዩበት አገር በደሳሳ ጎጆ ውስጥ መኖር ከትውልድ ወደትውልድ የሚተላለፍ ባሕል መሆኑ በምን ምክንያት ነው?››
ቀድሞ ግራ-ዘመም የነበሩት የፍልስፍና መምህር ፕ/ር መሳይ ከበደ ደግሞ ሌላኛው የሕዳሴው ምሁር ይሆናሉ ብዬ አስባለሁ፤ በተለይም ከ40ዎቹ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህራን ጋር በተባረሩ ማግስት ባሳተሟቸው መጻሓፍት፣ የቀደሙ ሀገር-በቀል የኢትዮጵያ ሊቃውንትን ሙግቶች በማብራራት ይታወቃሉ፡፡ ‹ወደ ምንጫችን የመመለስን› ጥሪ የሚያስተጋቡት ፕሮፌሰሩ፣ ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ማጥ ለመውጣትም ሆነ ወደፊት እንድትገፋ፣ ለረዥም ዘመን ካስተናገደቻቸው ዕሴቶች መካከል ረብ ያላቸውን መመለስ እንደሚገባት አብዝተው ተከራክረዋል፡፡
አስመራ የተወለዱት የታሪክ አጥኚው ፕ/ር ተከስተ ነጋሽም ሌላው ተጠቃሽ ናቸው፡፡ የትምህርት ስርዓቱ ላይ ባደረጉት አበርክቶ በዚህ አውድ የማነሳቸው እኚህ ምሁር፣ እንደ ፕ/ር መሳይ ሁሉ፣ ዘመናዊው የትምህርት ስርዓት አውሮፓ ተኮር እና ኢትዮጵያ-ጠል በመሆኑ ወደፊት መራመድ እንዳላስቻለን ደጋግመው ከመናገር ባለፈ፤ ቋንቋ የሚሸከመውን ሀገራዊ ማንነት ከመረዳት አኳያ አማርኛን እና ኦሮምኛን የስርዓተ-ትምህርቱ ቋንቋዎች ማድረግ ብቸኛው ከውድቀታችን መውጫ መንገድ መሆኑን ያምናሉ፡፡ …በጥቅሉ እነዚህ አንጋፋ ጠቢባን (ያልጠቀስኳቸው ሌሎችም እንደሚኖሩ ሳልዘነጋ) አውሮፓውያን ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት ከጨለማ የወጡበትን ብልሃት መመርመርን ይበልጥ አጠንክረው በመከተል፣ ሀገር የመታደግ ተልዕኮዎቻቸውን ከዳር ያደርሳሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ የኢትዮጵያ አምላክ ይሁናቸውና!
መጪው የሕዳሴ አብዮት በዋናነት የሚያተኩርበት ሌላው ጉዳይ፣ ከአራት አስርታት በፊት በያ ትውልድ ፈታኝ የትግል ጉዞ ላይ ትልቅ ተሳትፎ የነበራቸውን እንስቶች የተኳቸው የዛሬዎቹ የፆታ አቻዎቻቸው ለምን ከእንቅልፍ በከበደ አርምሞ ውስጥ ሰጠሙ? የሚለው ነው፡፡ ከአውሮፕላን ጠላፊዋ ማርታ መብራቱና ታደለች ኪዳነማርያም እስከ የመኢሶኗ ወሳኝ መሪ ንግስት አዳነ፤ እንዲሁም ከእልፎቹ የኢህአፓ ትንታግ ጓዲቶች እስከ ወያኔዎቹ አረጋሽ አዳነ እና ቀሺ ገብሩ ያሉ ተዘርዝረው የማያልቁ የዚያ ዘመን የአናብስት እንስቶች እንቅስቃሴ እንደዋዛ አክትሞ፣ በብርቱካን ሚደቅሳ፣ ርዕዮት አለሙና ፈቲያ መሀመድን በመሰሉ ጥቂት ጀግኖች ተገድቦ መታየቱ፣ በቀድሞው ታሪክ መታደስን አማራጭ የለሽ ያደርገዋል፡፡ በርግጥ የእንስቶቻችንን ፊኒክስነት ለመመለስ ከጥንቱ ይልቅ የትላንቱ የእናቶቻችን ጊዜ በተምሳሌነቱ ተስተካካይ የለውም፡፡ እነርሱ በያ ትውልድ ተጋድሎ የጊዜውን ጎታች የፆታ አመለካከት በመጋፋትና የወንዶችን ትምክህታዊ ዓለም በመነቅነቅ ታሪክ ለመስራት የታደሉ ፈርጦች እንደሆኑ አስመስክረዋል፡፡
የእኔ ዘመን አብዮተኛ ሴቶችም፣ በኮታ ሳይሆን በእውነተኛው እኩልነት እንዲገለጡ ግዴታቸውን ከወዲሁ መወጣት ይኖርባቸዋል፡፡ ከወቅታዊው የሀገሪቱ ሕዝብ ቁጥር እኩሌታውን የሚይዙት እንስቶቻችን በነቂስ ያልተሳተፉበት አብዮት በየትኛውም መስፈርት ውጤታማ ይሆናል ተብሎ አይታሰብም፡፡ በግልባጩ እነርሱን በዕኩልነት ማካተቱ ካልተሳካ ለውጡ ሊዘገይም ሆነ ክፉ ጠባሳ ሊኖረው ስለሚችል፣ ‹‹ያለሴቶች ተሳትፎ የኢትዮጵያ ሕዳሴ እውን አይሆንም!›› ከሚለው ዘመነኛ ኢህአዴጋዊ ቧልት እና ፕሮፓጋንዳ በተለየ መልኩ ተግባራዊ የሚሆን የንቃት ሕዳሴ ትኩረት ሊሰጠው ይገባዋል ብዬ አምናለሁ፡፡
ሌላው ጉዳይ ኢትዮጵያ በ66ቱ እና በ83ቱ የአብዮት ሀዲድ ላይ የመጣችበትን የማሕበረ-ፖለቲካ ታሪኳን ግድፈቶችና ስኬቶች በምክንያታዊነት መመርመር ለሁለንተናዊ ዳግም ልደት (ሕዳሴ) እንድንዘጋጅ መደላድል የመፍጠሩ እውነታ ነው፡፡ ይህ የዳግም ልደት አብዮታዊ ጉዞ ደግሞ በዋነኝነት የሁለት ማሕበረሰቦችን ቅሬታ የሚያቅፍ መሆን ይኖርበታል፡፡ ይኽን የምለው የሌሎቹን ዋጋ በመዘንጋት ሳይሆን፣ በቀዳሚነቱ ስለማምን ነው፡፡
የብሔር ጥያቄ የኢትዮጵያን ማዕከላዊ መንግስት ለመናድ ቅርብ የነበረባቸው ዘመኖችን ተመልክተናል፡፡ በዚህ መንገድ አልፈንም በዋናነት በአግባቡ መመለስ ካቃቱን ጥያቄዎች መካከል በኦሮሚኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች የሚነሳው ዋነኛው መሆኑ አያከራክርም፡፡ ይህ ጥያቄ ጠርዘኛ ልሂቃኑ በሚያቀርቡት ልክ ባይሆንም፤ መሬት የረገጡ ማንነታዊ ቅሬታዎችን ተንተርሶ መነሳቱ ግን መካድ የለበትም፡፡ እናም ኢትዮጵያችንን በማደስ ጉዞ፤ ኦሮሞነት ከሀገሪቱ ምንነት ብያኔ የተነጠለ ሆኖ የመጣበትን የታሪክ አጋጣሚ ሂደት በመግታት፣ የብሔሩን መለዮዎች የኢትዮጵያዊነት ብያኔ ገዢ መተርጎሚያና መዳረሻ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
ሌላኛው ጭብጥ ደግሞ የኢትዮጵያን እስልምና ነባራዊነት ማፅናት ነው፡፡ ኃይማኖቱም ሆነ ተከታዮቹ በአፄያዊዎቹ አፈና ውስጥ ለሺ ዓመታት የመቆየታቸውን እውነታ ተቀብለን፤ በኢትዮጵያዊነት ትእምርታዊ ገፆች ውስጥ ቀዳሚ አዋጭነታቸውን መቀበል የመታደሳችን ግብ ሊሆን ይገባል፡፡
ለነዚህና ለሌሎች መዘርዘር ለማይቻሉን የሀገሪቷ መከራዎች፣ መውጫው ኢትዮጵያን በማደስ የሚደመደም አብዮት ከሆነ ዘንዳ፣ የብሔራዊ ዕርቅ ጉዳይ ከዋነኛ የሽግግር ሂደቶች መካከል ከፊት የሚቆም እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ በእርግጥ ርዕሰ-ጉዳዩ በተነሳ ቁጥር፣ ‹ማን ከማን ጋር ነው የሚታረቀው?› እያለ የሚቀልድ ኢህአዴግ መራሹን መንግስት የመሰለ ቢኖርም፤ እየመጣ ካለው መዓት ሀገሪቷን ለማዳን፣ ብሔራዊ እርቅ ምቹ ድልድያችን መሆኑን ማመን ያስፈልጋል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ የኢትዮጵያን ፖለቲካ በበላይነት የሚዘውሩት ልሂቃንን በአንድ የጋራ መድረክ ላይ ማሰባሰብ፣ በቀጣይ እንድትኖረን በምንሻት ሀገር ምንነት ማዕቀፍ ውስጥ የሚያርፉ ተመጋጋቢ አመለካከቶችን ለመቅረፅ አይነተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡
የሆነው ሆኖ ይህን ተምኔት የመሰለ፣ ነገር ግን ሊከወን የሚችል የሕዳሴ አብዮት ያለእንቅፋት ለማሳለጥ፣ በቅድሚያ ገዥዎቻችን ‹በአንድ ክፉ አጋጣሚ ስልጣኑን ብናጣ ያበቃልናል› ከሚለው ነቢባዊም ሆነ ተጨባጭ ስጋት እንዲላቀቁ ዋስትና መስጠት ላይ መግባባት የግድ ይላል፡፡ በመገዳደል ከተበከለው የግራ-ቀኝ ፖለቲካ ለመንፃት፤ ከነነውረኝነታቸው ሀገሪቷ የእነርሱም እንደሆነች አምነው እንዲቀበሉ ማድረግ ብቸኛው መፍትሔ ነው፡፡ በመጪዋ ኢትዮጵያ አንዱ ልዩ ቀናዒ፣ ሌላኛው ደግሞ ተጠርጣሪ እንደማይሆንባት መተማመን፣ ለሕዳሴው የሚኖረንን ተስፋ ያጎለብታል የሚል ፅኑ እምነት አለኝ፡፡
(የሕዳሴው አብዮትን ማስፈፀሚያ ሃሳብን በተመለከተ ሳምንት እመለስበታለሁ)

[ከሱዳን ካርቱም የደረሰኝ መረጃ]በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያኖች ዘግናኝ ግፍ እየተፈጸመባቸው ነው


ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ ሌና
June 4/2014
በሱዳን በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸመው ግፍ ቀጥሏል:: በየጊዜው ለስራ ፍለካ ምክንያትና በኢትዮጵያ ባለው የፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት ሀገራቸውን እየለቀቁ ወደ ሱዳን የሚገቡ ኢትዮጵያኖችን ብዙ ሲሆን እነዚህ ኢትዮጵያኖች ወደ ሱዳን ከገቡ በኋላ ለተለያዩ ችግሮች እየተዳረጉ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል :: በተለይም   በሱዳን በሚኖሩ ኢትዮጵያን ዜጎቻችን ላይ ከመቼውም ጊዜ በተለየ ሁኔታ  ኢሰብዓዊ ድብደባ እየተፈጸመባቸውና  በሀገሪቱ ፖሊስ እና በሱዳን ማህበረሰብ ዘግናኝ ግፍና በደል እየደረሰባቸው  እንዳለ ለማወቅ ተችሏል :: በዛው በሱዳን ካርቱም ነዋሪ ከሆነ ግለሰበ እንዳገኘውት ምንጭ ከሆን በኢትዮጵያኖች ላይ ፖሊስ የተለያያ ድብደባና ጥቃት የሚያደርስባቸው ሲሆን በሀገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች ሴቶች በእነዚህ ፖሊሶች እና በወጣት ሱዳን ወንዶች  በግሩፕ በየቦታው እየተደፈሩ ሲሆን በፖሊሶችና በሱዳን ወጣት ወንዶች ወሲባዊ ጥቃት እየደረሰባቸው ያሉ  አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ሴቶች  የስነ ልቦና ቀውስ ውስጥ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል::

እነዚህ በሱዳን የሚኖሩኢትዮጵያውያኖች የድረሱን ጥሪ አያቀረቡ ሲሆን  ነገር ግን ማንም ሊደርስላቸው እንዳልቻለና በሱዳን ካርቱም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ችግሩን ለመፍታት ምንም አይነት ጥረት እያደረገላቸው አይደለም:: ኢምባሲው ወገኖቻችን ችግር ሲደርስባቸው ፈጥኖ ደርሶ የዜጓቹን ችግር ከመፍታት ይልቅ በሱዳን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ የማፍያዎች ስብስብ ሆኖል ስለ ዜጋ የሚቆረቆርና ሀላፊነት የሚሰማው አንድም ሰው የለም ካርቱም ኢትዮጵያ ኢምባሲ ሰራተኛ የሆኑ ለሕዝብ የሚያገለግሉና ሀላፊነት የሚሰማቸው ሰዎች እንዳይደሉ ::ነገር ግን እዛ ቁጭ ብለው ምንም ስራ እንደማይሰሩ በኢትዮጵያ ኢምባሲ ስም ብቻ በሙስና ሀብት ማካበት ብቻ እንደሆነ የደረሱኝ መረጃዎቹ ይጠቁማሉ ::

 በነዚህ ሁለት ወራት ውስጥ  በጣም አሳዛኝ ነገር ከመቼውም ጊዜ በተለየ ለየት ያለ ኢትዮጵያዊያንን የማጥቃት ዘመቻ  በካርቱም ተጦጥፎ ይገኛል:: ካርቱም ያሉ አራቱም ወህኒ ቤቶች ኩበር፣ሶባ፣ኦምዱራምሃ፣ሀል ሁዳ የተባሉ እስር ቤቱች በእስረኛ ተጨናንቀዋል በተለየ ኢትዮጵያኖች ከአስር እስከ ሃያ አመት ፍርደኛ ናቸው:: አንዲትም ቀን የኢትዮጵያ  ኢምባሲ ሂዶ ጠይቋቸውም አያውቅም በአሁኑ ሰአት ደግሞ ህገ ወጥ ስደተኛ ተብለው ከሶስት መቶ በላይ ኢትዮጵያዊ ስደተኞች በሆዳ እስር ቤት ይገኛሉ እንደዚሁ ህገ ወጥ ስደተኛ ተብለው ሆዳ እስር ቤት የታጎሩ ሰዎች ባለፈው 21/5/2014 ሶስት ኢትዮጵያውያን ሞተዋል:: ምክንያቱም ለሰባት ቀን ያህል በር ተዘግቶባቸው ያለ ምግብና ውሃ  በመቆየታቸው ሰውነታቸው ተዳክሞ ሲሆን ሌሎች 30 ሰዎች በወህኒ ቤቱ ግቢ ህክምና ተደርጎላቸው አስራ ሁለቱ  ከተወሰነ ሰአት በኋላ ሲመለሱ አስራ ስምንቱ በአንድ የፖሊስ ሆስፒታል በዝግ አይሱዚ መኪና ተወስደዋል:: በወቅቱ ጉዳዩን  መቀመጫው ካርቱም ኢትዮጵያ ኢምባሲ አማባሳደር አቶ አብዲ ዘሙ ተደውሎ ተነግሯቸው የነበረ ሲሆን እሳቸው ግን ችግሩን ችላ በማለት ጅብ ከሄድ ውሻ ጮኸ እንደሚባለው በነጋታው ሰው በማስላክ አይተዋቸዋል ::ከዛ እንደለመደው በመዋሸት ምንም የሞተ ሰው የለም በማለት አወራ::ምክንያቱም ጉዳዩን ካርቱም ያለ አብዛኛው አበሻ ስለሰማ  ለመሸፋፈን  ቢሆንም ነገር ግን ሆስፒታል የነበሩ የተቀሩት ሐበሾች ወዲያውኑ ከተመለሱ ጉዱ ስለሚገለጥ ፍርዳቸውን ሳይጨርሱ የት እንደሚወስዶቸው አልታወቀም ፈተው ወደ ሀገር ቤት እባረዋቸው ይሆን ወይም እነሱም የሶሰት ወንድሞቻቸው እጣ ፈንታ ደርሶቸው ይሆን ምንም የታወቀ ነገር የለም::

ሌላው በጣም የሚገርመው ነገር በዛው ካርቱም ኢትዮጵያ ኢምባሲ ባሉት አረመኔዎች እህቶቻችን ወሲባዊ ጥቃት ይፈጸምባቸዋል::አቶ መሀመድ ቱፋ የሚባል የኢምባሲው ሰራተኛ የሆነ ከኢትዮጵያ ጫት እያስመጣ የሚነግድ አደገኛ የጫት ነገዴ እንደሆ ነው የሚነገርለት::ሌላው ደግሞ ሌባ የኢምባሲው ሰራተኛ አቶ በላቸው ገብረ መስቀል ይባላል ከአሁን በፊት የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በካርቱም ብር ዘርፎ ሀገር ቤት ሄዶ ነበር ተመልሰው አምጥተውት ከፍ ያለ ስልጣን ተሰቶት ካርቱም በኢትዮጵያ ኢምባሲ እየሰራ ነው:: ካርቱም ኢትዮጵያ ኢምባሲ ባጠቃላይ የህገ ወጡች ስብስብ ሆኖል::


Monday, June 2, 2014

ግንቦት 20፡ የኢትዮጵያዊያን ጠላት መሆንን የመረጠ ጉጅሌ ለስልጣን የበቃበት ታሪካዊ ቀን፤

Jule 1/2014
በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ወርሃ ግንቦት የተለየ ሥፍራ አላት።ከወርሃ ግንቦት ግንቦት ሰባትንና ግንቦት ሃያን በተለይ አንረሳቸውም። ግንቦት ሃያ ጎጠኝነት፤ እኔ ብቻ ባይነት፤ አስመሳይነት ፤ስግብግብነት እና ሌብነት ተደምረው የወለዱት ቡድን ብሶት ወለደኝ ብሎ በትረ ስልጣኑን የተቆጣጠረበት ቀን። ብሶት ወለደኝ ብሎ ግንቦት 20 ዕለት በትረ ስልጣኑን የጨበጠው ቡድን ግንቦት ሰባት ዕለት ብዙ ህፃናትን፤ ብዙ ወጣት ሴትና ወንዶችን፤ ብዙ አረጋዊያንን ገድሎና በደም ሰክሮ የዴሞክራሲ ጥያቄዎችን ለማዳፈን የሞከረበት ቀን። አዎን ግንቦት ሃያ የኢትዮጵያ ጠላት መሆንን የመረጠ ጉጅሌ ለስልጣን የበቃበት ታሪካዊ ቀን።
ህወሃትን ስልጣን ይዞ አገርን ሊመራ እንደሚችል የፖለቲካ ተቀናቃኝ ድርጅት አድርጎ ማየት ከስህተት ይጥላል። ስህተቱ ደግሞ ለነፃነት፤ ለእኩልነት እና ለፍትህ የሚደረገውን የትግል አቅጣጫ ያዛባል። የትግሉ አቅጣጫ እንዳይዛባ ህወሃት የህዝብ ጠላት መሆንን የመረጠ ጉጅሌ መሆኑን አጥብቆ መያዝ ያስፈልጋል። ህወሃትን ከህዝብ ጠላትነት ዝቅ አድርጎ ማየት በማንኛውም መለኪያ ስህተት ነው።
በዚህ ወቅት ጉጅሌው ህወሃት የህዝብ ጠላት መሆኑን የሚጠራጠር ኢትዮጵያዊ እውነቱን ለመቀበል የማይፈልግ፤ ለነፃነት የሚከፈለውን ዋጋ ለመክፈል የማይፈልግ ሰነፍ አልባሌ ሰው ነው። እንዲህ ዓይነት ሰነፍ ሰዎች ጉጅሌዎቹ ሠላም ያመጣነው እኛ ነን ሲሉ ያምኗቸዋል። ልማትም ከመቼውም ግዜ በላይ ለኢትዮጵያ ያመጣንላት እኛ ነን ሲሉ እውነት ነው ይላሉ። እኛ ከሌለን ኢትዮጵያ ትበታተናለች ብለው ሲደነፉም ይደነግጣሉ።እንዲያውም ህወሃቶች ከሌሉ ማን አገሪቷን ሊመራት ይችላል ብለው ለመከራከር ይዳዳቸዋል።
ህወሃቶች በማንኛውም መስፈርት አገር ለመምራት ብቃት ያላቸው ቡድኖች አይደሉም። አገር የሚመራ ኃይል ኢትዮጵያዊ ብሄረተኝነትን ለማጥፋት ሳይታክት አይሠራም። ጉጅሌዎቹ ከተመሸጉባቸው የጎሳ ፖለቲካ ክበብ ውስጥ ሁነው ኢትዮጵያዊ ብሄረተኝነትን ለማጥፋት ያልፈነቀሉት ድንጋይ፤ያልቧጠጡት ዳገት የለም። ጉጅሌዎቹ የማያውቁት አንድ እውነት ግን ኢትዮጵያዊ ማንነት በፀና መሠረት ላይ የቆመ ተሸርሽሮ የማያልቅ ፅኑ ዓለት መሆኑን ነው። ግንቦት ሃያ ዕለት ስልጣኑን የጨበጠው ጎጠኛው ነፃ አውጪ ቡድን ከሃያ ዓመት በኋላም ሥሙን እንኳን ሳይቀይር “እኔ ካልገዛኋችሁ ኢትዮጵያ ትበታተናለች” እያለ ያሟርታል። ህወሃትን የህዝብና የአገር ጠላት የሚያሰኘው አንዱ አንጓም ይሄው ነው።”እኔ ያልኩት ካልሆነ አገሪቷን አፈርሳታለሁ፤ የጎሳ ግጭት ተነስቶ ህዝቡ እርስ በርሱ እንዲተላለቅ አደርጋለሁ” እያለ መዛቱ። እንግዲህ “እኔ ከሌለው አገሪቷን አፈርሳታለሁ” የሚል ቡድን በምን መሥፈርት አገርንና ህዝብን መርቶ ወደ ተሻለ ደረጃ ሊያደርሳት እንደሚችል “ህወሃቶች ከሌሉ አገሪቷን ማን ይመራታል” ብለው የሚጨነቁ ሰዎች መልሰው መልሰው ራሳቸውን እንዲጠይቁ እንመክራቸዋለን። ለማንኛውም ከግንቦት ሃያ መራራ ፍሬዎች መካከል አንዱ “እኔ ያልኩት ካልሆነ አገሪቷን እበትናታለሁ” የሚል ክፉና ጎጠኛ ጉጅሌ በአገራችን ጫንቃ ላይ መጫኑ ነው።
ጉጅሌዎቹ ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ ልማት አመጣንም እያሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ይጮኻሉ።የህወሃቶች ድንቁርና ልማትን ከሰው ልጅ ሠላምና ደስታ ይልቅ ዛሬ ታይቶ ነገ በሚጠፋ ግዑዝ ቁስ መለካታቸው ነው። ይህ ግዑዙ ቁስ ለሠው ልጆች ሠላም፤ ደስታና እፎይታ ካላስገኘ ልማት ሊባል አይቻልም። ጉጅሌዎቹ ልማትን የሚለኩት ከህዝቡ ደስታ፤ ሠላም እና የእለት ጉርሳቸውን ያለጭንቀት አግኝተው ማደር ከመቻላቸው አንፃር ሳይሆን ራሳቸው ዘርፈው ካካበቱት ሃብት አንፃር ነው። እነርሱ ዘርፈው ብዙ ሃብት ስላከማቹና ስም አጠራሩን እንኳ የማያውቁትን መጠጥ በብዙ ሺህ ብር ገዝተው መጠጣት ስለቻሉ አገሪቷ ያደገች ይመስላቸዋል። ጉጅሌዎቹ እንደሚሉት አገሪቷ በልማት ጎዳና ላይ እየተጓዘች ቢሆን ኑሮ ወጣቱ ትውልድ በአገሩ ተስፋ ቆርጦ የባእድ አሸከርና ገረድ ለመሆን ስደትን የሚመርጥ ባልሆነ ነበር።ጉጅሌዎቹ አገሪቷን ከተቆጣጠሩ ከግንቦት ሃያ 1983 ዓ.ም ጀምሮ ከኢትዮጵያ መሰደድን የማይመኝ ዜጋ አይገኝም። መንኩሴ፤ ሼኽ፤ ፓስተር፤ ገበሬ፤ ምሁር፤ ተማሪ ሁሉም የሚሰደድባት አገር ኢትዮጵያ ነች። ግንቦት ሃያ ካተረፈልን ፍሬዎች መካከል ሊጠቀስ የሚችለው የዜጎች ያለገደብ መሰደድ ነው። ልማታዊ ነን ብለው ራሳቸውን የሚጠሩት ጉጅሌዎቹ ዜጎች እጅግ አደገኛ በሆነ በርሃና ባህር ውስጥ አልፈው ከቀናቸው አሽከርና ገረድ መሆንን ለምን እንደሚመርጡ መልስ የላቸውም።
“የኢኮኖሚ ልማት … በሰው ልጅ ሁለንተናዊ እድገት፣ በዋና ዋና መሠረተ ልማት አቅርቦቶች፣ በአካባቢው ገበያ በሚኖር ተወዳዳሪነት፣ በምቹ የተፈጥሮ አካባቢ (ኢንቫይሮመንት)፣ በማኅበራዊ መስተጋብር፣ በጤና፣ በደህንነት፣ በትምህርት እና በመሳሰሉ ነገሮች እድገት ማምጣትን ያካትታል።ብለው ልማትን የሚተረጉሙ ሊሂቃን አሉ።”
የጉጅሌዎቹ ልማት በእነዚህ መሥፈርቶች ቢለካ ተስፋ በሚያስቆርጥ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አገራቸውን ጥለው የሚሰደዱ ዜጎች ብዛትና ዓይነት ደህና ምስክር ነው። የጉጅሌዎችን የህዝብ ጠላትነት ከሚያሳዩ እውነታዎች መካከል ሌላው ገፅ ይሄው ዜጎችን በሙሉ ተስፋ አስቆርጦ ለስደት የሚዳርግ ሥርዓት በአገሪቷ ውስጥ እንዲዘረጋ ማድረጋቸው ነው።
ህወሃቶች የህዝብ ጠላት መሆንን የመረጡ ጉጅሌዎች ናቸው ስንል ሌላው መገለጫቸው ህዝቡን ሠላም ማሳጣታቸው ነው። ጉጅሌዎቹ እኛ ከመጣን በኋላ አገሪቷ ሠላም ወረደላት፤ የህዝቡም አንድነት ከመቸውም ግዜ በላይ ተጠናከረ እያሉ ያላዝናሉ።
በእውኑ ኢትዮጵያችን ውስጥ ሠላም አለን? ህዝቦቿስ ከመቸውም ግዜ በላይ በኢትዮጵያዊነት ስሜት አብሮ የመኖር ዝንባሌ እያሳዩ ነውን ? መልሱ ግልፅ ነው። ሠላም የለም፤ ኢትዮጵያም የዜጎቿ አገር አልሆነችም።
ከግንቦት ሃያ መራራ ፍሬዎች መካከልም ዜጎች ለዘመናት ከኖሩበት እና እትብታቸው ከተቀበረበት መንደር ውጡና ወደ አገራችሁ ሂዱ ተብለው ከነ ቤተሰቦቻቸው ሜዳ ላይ ተበትነው ማየታችን ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ቁም ነገር ነው። ጉራፋርዳ አማራ ተብሎ ለሚጠራው ዘውጌ ማህበረሰብ አገሩ ካልሆነ የአማራ አገሩ የት ነው? ከቤንሻንጉል አማሮች ውጡ ሲባሉ ኢትዮጵያዊነት ከወደየት አለ? በአዲስ አበባ አካባቢ የሚኖሩ የኦሮሞ ገበሬዎች ተፈናቅለው የትም ተጥለው የጉጅሌው አባላት እና ደጋፊዎች መሬታቸውን ሲቀራመቱ ህግ የት ደረሰ? እነዚህ ሁሉ ፈተናዎች የግንቦት ሃያ ፍሬዎች መሆናቸውን መርሳት አይገባም።
እንግዲህ ጉጅሌዎቹ ነጋ ጠባ “ሰላማችን፤ ሰላማችን” እያሉ የሚያላዝኑት፤
  • ዘረኝነት የፓለቲካ ሥርዓቱ መታወቂያ ሆኖ እያለ፤
  • ኢፍትሃዊ የሀብትና የሥልጣን ክፍፍል እና ሙስና የሥርዓቱ መለያ ሆነው እያሉ፤
  • ፍትህ ተዋርዳ ፍርድ ቤቶች ገዢዎች የሰጡት ቅጣት ማሳወቂያ በሆኑበት፤
  • በዘርና በፓለቲካ ወገንተኝነት የተዋቀሩት የጦር ሠራዊት፣ የፓሊስና የስለላ ተቋማት ኢትዮጵያዊያንን ማጥቂያ ሆነው እያሉ፤
  • በፓለቲካ እምነታቸውና በሀይማኖቻቸው ምክንያት ታስረው ሰቆቃ እየተፈፀማቸው ያሉ ወገኖቻችን ብዛት በአስደጋጭ ፍጥነት እየጨመረ ባለበት ሁኔታ፤
  • ሚሊዮኖች ድሀ ገበሬዎች ከይዞታቸው እየተፈናቀሉ በገዛ አገራቸው ስደተኛ የሆኑበት ሁኔታ እየተባባሰ መምጣቱን እያየን፤
  • ኢትዮጵያዊያን ገበሬዎች ቤተሰቦቻቸውን የሚመግቡት ቁራጭ መሬት አጥተው እያለ ሰፋፊ ለም መሬቶች ለውጭ ባለሀብቶች በገፍ እየተሸጠ ባለበት ሁኔታ፤
  • የወያኔ ሹማምንት በሀብት ላይ ሀብት እየጨመሩ ከተሞችን በሕንፃዎች ሲያሽቆጠቆጡ ዛንጋባ እንኳን አጥተው በረንዳ ላይ የሚያድሩ ዜጎች ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ መሆኑን በገዛ ዓይኖቻችን እያየን፤
  • ከፍተኛ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ወጣቶች ለሚጠብቃቸው የሥራ እድል ባይማሩ ኖሮ ይበልጥ ተመራጭ ይሆኑ የነበረበት የመሆኑ አሳዛኝ ሐቅ እያየን፤
  • ወጣቶች በተስፋ እጦት ከአገር ሲሰደዱ በባህር ሰጥመው አሊያም በበረሃ ንዳድ ተቃጥለው እያለቁ ባሉበት በአሁኑ ሰዓት፤
  • አብዛኛው ሰው ቁርስ፣ ምሳና ራቱን ደርቦ “ቁምራ” እየበላ ስለ ተከታታይ ዓመታት 11.6 % ዓመታዊ የኢኮኖሚ እድገት መስማት ግዴታ የሆነበት የጉድ አገር ሆኖ እያለ፤
  • የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪቃና የአረብ አገራት እስር ቤቶች በኢትዮጵያዊያን ወንዶችና ሴቶች ተሞልተው እያለ፤ እና
  • ወያኔ የሚያደርሰው ግፍ ፅዋውን ሞልቶ በፈሰሰበት በአሁኑ ወቅት ነው “ሰላማችን፣ ሰላማችን” እያሉ የሚያደነቁሩን።
ይኸ ሁሉ ኢ-ፍትሃዊነት ባለበት ሊኖር የሚችለው ሰላም አሉታዊ ሰላም ያውም ተቃውሞን በጉልበት በመደፍጠጥ የሚገኘው አደገኛ አሉታዊ ሰላም ብቻ ነው።በጉልበት የሚመጣ አሉታዊ ሰላም ለአገራችን አይበጃትምና የወያኔን ሰላም መቃወም ተገቢ ነው። ከብዙ አገሮች ልምድ እንዳየነው አደገኛው አሉታዊ ሰላም ከመኖሩ አለመኖሩ ይሻላል። የወያኔ ሰላምም ለኢትዮጵያችን የሚበጅ አይደለም።
የግንቦት ሃያ መራራ ፍሬዎች ብዙ ናቸው።ግንቦት ሃያ የህዝብ ጠላት መሆንን የመረጠ ጉጅሌ የአገሪቷን ስልጣን የተቆጣጠረበት ቀን ነው።ከዚህ ቡድን የሚጠበቅ መልካም ፍሬ የለም። ግንቦት ሰባት የፍትህ፤ የነፃነት እና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ግንቦት ሃያ ቀን የአገሪቷን ስልጣን የተቆጣጠረው የጉጅሌው ቡድን ከህግ በታች እንዲውል ለማድረግ ትግላችንን አጠናክረን እየቀጠልን ነው። የትግላችን መዳራሻም የህዝብ ጠላት መሆንን የመረጠ ቡድን መሪዎች እጅ ተይዞ ለፍርድ እስከሚቀርብ ድረስ ይዘልቃል። ይሄም ያለምንም ጥርጥር ይሆናል።
እናሸንፋለን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !

Sunday, June 1, 2014

በትግራይ አለመረጋጋት አለ!

May1/2014
አብረሃ ደስታ

ጓዶች ህወሓቶች በጣም ደንግጠዋል። ባሁኑ ሰዓት በብዙ የሑመራ አከባቢዎች፣ ማይጨው (ሽኮማዮ)፣ ዓዲጎሹ (ተከዘ)፣ ሐውዜንና አፅቢ ህዝቡን ለመቆጣጠር ፖሊሶችና ምልሻዎች ተሰማርተዋል። ትናንት ማታ (ቅዳሜ ማታ) አቶ መሰለ ገብረሚካኤል (የዓረና ስራ አስፈፃሚ አባልና የምዕራባዊ ዞን የዓረና አስተባባሪ) ፊታቸው በሸፈኑ ታጣቂዎች ወደ ፖሊስ ጣብያ ተወስደው ምርመራ ተደርጎባቸዋል። ትናንት ቅዳሜ በእንዳ አብርሃ ወ አፅብሃ የዓረና ልሳን ለህዝብ ሲያድሉ የነበሩ የዓረና አመራር አባላት አቶ ዓምዶም ገብረስላሴ፣ አቶ ቴዎድሮስ ሞገስ ፣ አቶ ኃይለኪሮስ ታፈረና መምህር ይልማ ኩኖም በህወሓት አስተዳዳሪዎች ክፉኛ ተደብድበው ሆስፒታል ገብተዋል። አቶ ቴዎድሮስ ሞገስ ተደብድቦ በፖሊስ ታስረዋል። አቶ ገረችአል ግደይ (አባ ሐዊ) የተባለ ያከባቢው አስተዳዳሪ አቶ ቴዎድሮስን እንዲታሰር ስለወሰነ በሚል ምክንያት በዉቅሮ ከተማ ታስሮ ይገኛል። አሁን የእንዳ አብርሃ ወ አፅብሃ አከባቢ በፖሊሶች እየተጠበቀ ነው። ሁለትና ከሁለት በላይ ሁኖ መንቀሳቀስ ተከልክሏል። ከምሽቱ ሁለት ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ አይፈቀድም። በአፅቢ ወንበርታ ላለው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለመግታት የተቃውሞው መሓንዲስ የተባለውን አቶ ሕድሮም ሀይለስላሴን በሰበብ አስባቡ ለማሳሰር ዝግጅት መጀመሩ ከህወሓት ፅሕፈትቤት መረጃ ደርሶኛል። በሐውዜን ከተማ ዓረና ተብሎ የተጠረጠረ ሁሉ ድብደባ ተፈፅሞበታል። ከሐውዜን እንዲወጣም እየተደረገ ነው። አሁን እሁድ ግንቦት 24, 2006 ዓም ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ በእግሪሓሪባ መንደር ብዙ ቁጥር ያላቸው ፖሊሶች ተሰማርተዋል። አቶ ሙኡዝ ፀጋይ የተባለ ያከባቢው የዓረና አስተባባሪ ቤት ተከቧል። መንቀሳቀስ አይችልም። በያንዳንዱ የእግሪሓሪባ መኖርያቤት በር ሦስት ፖሊሶች ይገኛሉ። ዛሬ በህዝቡና አስተዳዳሪዎች አለመግባባት ተፈጥሮ ነበረ። ባጠቃላይ ባሁኑ ሰዓት በትግራይ አለመረጋጋት አለ። ይህን ሁሉ ችግር እየፈጠረ ያለ ግን ህወሓት ራሱ ነው። ከሰለማዊ ተቃውሞ ዉጭ ምንም ዓይነት ዓምፅ በሌለበት ህዝቡ ሊያምፅ ይችላል በሚል ስጋት ብቻ የፀጥታ ሃይሎች እያሰማራ ነው። ህዝቡም ተደናግጧል። እኛ ግን ብዕር እንጂ ጠመንጃ አልያዝንም።
በትግራይ አስቸኳይ መፍት ሄ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ተባራክተዋል። መነጋገር ይኖርብናል።
It is so !!!

ሦስተኛዋን ‹‹እሁድ›› – በአራዳ ምድብ ችሎት (ጽዮን ግርማ)

June1/2014
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ተጠርጣሪዎቹን እሁድ ለሚሰየም ተረኛ ችሎት መቅጠሩን የተለመደ አድርጎታል፡፡ ከቀናት በፊት በሦስቱ ብሎገሮች ላይ በተሰጠው የዐሥራ አራት ቀናት የጊዜ ቀጠሮ መሠረት የቀጠሮው ቀን ዛሬ ነበር፡፡ ዛሬ በዚህ ፍርድ ቤት ተገኝቼ የነበረውን ሁኔታ መከታተል ባልችልም ምንጮቼ የነገሩኝን ዝርዝር እንዲህ ጽፌዋለሁ፡፡

ጠዋት
የተጠርጣሪዎቹ ቤተሰቦች እንደተለመደው የአራዳውን ምድብ ችሎት የጓሮ በር እያለፉ ወደ አሮጌው ፍርድ ቤት ግቢ መግባት የጀመሩት ጠዋት ሦስት ሰዓት ከመሙላቱ አስቀድሞ ነበር፡፡ አብዛኞቹ ከፍርድ ቤቱ ከፍ ብሎ በሚገኘው ማዕከላዊ ለሚገኙት እስረኛ ልጆቻቸው ቁርስ የማድረሻ ሰዓት ስለኾነ ዛሬም ከቁርስ መልስ ሰብሰብ ብለው ነበር ወደ ፍርድ ቤት ግቢ የገቡት፡፡

ፍርድ ቤቱ ሲደርሱ ግቢው በጸጥታ የተሞላ ነበር፡፡አንድም የተከፈተ የችሎት በር አልነበረም፣ግቢውን ከሚጠብቀው አንድ ፖሊስ በስተቀር ሌላ ሰው የለም፡፡ ጠባቂው ፖሊስ ‹‹ዋናዎቹ›› ሲመጡ አንድ ላይ መሰብሰባቸው አይቀርም ብሎ ይመስላል የሚገባውን ሰው በሙሉ አንድ ላይ እንዲሰበሰብ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ ሰዓቱ ረፈድ እያለ ሲመጣና ጸሐዩ ሲበረታ ግን ግቢው ውስጥ የቆመው ሰው ተበታትኖም ቢሆን ጥላ ፈልጎ እንዲቀመጥ ፈቀደ፡፡ የቀጠሮው ሰዓት እስኪደርስ ድረስ ሁሉም አመጣጡ እንደገጠመለት እየተቧደነ ባገኘው ነገር ላይ ተቀምጦ ፖሊስ ሊጠይቅ ይችላል ያሉትንና ፍርደ ቤቱ ሊሰጠው ስለሚችለው ትእዛዝ ግምታዊ መላምቱን እያስቀመጠ ጭንቀቱን በተስፋ ለማራገፍ ውይይቱን ቀጥሏል፡፡
ችሎቱን ለመከታተል የመጡት ወጣቶች ከበፍቃዱ ኃይሉ ቤተሰቦች ጋራ እየተላቀሱ በጤና ጣቢያው በር በኩል ሲወጡ ፡፡
ችሎቱን ለመከታተል የመጡት ወጣቶች ከበፍቃዱ ኃይሉ ቤተሰቦች ጋራ እየተላቀሱ በጤና ጣቢያው በር በኩል ሲወጡ ፡፡

‹‹ተጨማሪ ዐስራ አራት ቀን ሊጠይቁባቸው ይችሉ ይኾን?›› አንዱ ይጠይቃል፡፡ ‹‹የሽብር ተግባሩን ጠቅሰው ሃያ ስምንት ቀን ይጠይቁባቸዋል›› ሌላኛው ሰው አስተያየቱን ይሰጣል፡፡ ከተሰበሰቡት ሰዎች መካከል በፍርድ ቤት ጉዳዮች በቂ ልምድ ያለው አንድ የሕግ ባለሞያ፤‹‹መዝገቡ በጊዜ ቀጠሮ ላይ የሚገኝ ቢኾንም ባለፈው ቀጠሮ ፍርድ ቤቱ የፖሊስን የሽብር ተግባርና የሃያ ስምንት ቀን የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ ውድቅ ስላደረገው ዛሬ መልሶ እሱን ማንሳት አይቻልም ፖሊስ ጥያቄውን እንደገና ማቅረብ ቢፈልግ እንኳን በይግባኝ እንጂ መልሶ በዚህ ችሎት የሚያቀርብበት ሥርዓት አይኖርም፡፡›› በማለት ሞያዊ አስተያየቱን ሰጠ፡፡ የሕግ ባለሞያው የተቀመጠበትን ዙሪያ ከበው የተቀመጡት ወዳጅ ቤተሰቦች አስተያየቱን ሰምተው ‹‹ቢበዛ ፖሊስ ሊጠይቅ የሚችለው ዐሥራ አራት ቀን ነው፤እሱንም ቢኾን የሽብር ተግባሩን ሳያካትት በማለት›› ተስፋን ለራሳቸው ሰነቁ፡፡
ከዚህ ቀደም በነበሩት ቀጠሮዎች ችሎቱ ሲሰየምበት ከነበረው ሰዓት እያለፈ ሲሄድ ሁሉም ሰው ግራ ተጋብቶ የነበረ ቢኾንም አምስት ሰዓት ሊመላ ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩት አንድ ዕድሜው ከሃያ አራት የማይዘለው ጎርመስ ያለ ወጣት ወደ ፍርድ ቤቱ ግቢ ገብቶ ተራኛ ኾኖ መመደቡንና ነገር ግን ችሎቱም አለመከፈቱን የጽፈት ቤት ኃላፊም አለማግኘቱን በመግለጽ የፍርድ ቤቱ ሠራተኛ የሚመስለውን አንድ ሰው ጠየቀ፡፡ ለችሎት ጸሐፊዋ ስልክ ተደወለላት፡፡ እርሷ እስክትመጣም አስቀድሞ ተጠርጣሪዎቹን ይዞ ሊቀርብ ከመጣው መርማሪ ፖሊስ ጋር ወደ ውስጥ ዘለቀ፡፡
ሠላሳ ያህል ደቂቃዎች እንደተቆጠሩ እስረኞቹን ይዘው የመጡት ቁጦ (ከሌላው ጊዜ እጅግ የተለዩ) የፌደራል ፖሊሶች ወደ ግቢው ገብተው ተበታትኖ የቆመውን ቤተሰብ እንደተለመደው ሰብስበው በአንድ መስመር አቆሙት፡፡ ከፍርድ ቤቱ ግቢ ጀርባ ባለው መኪና ማቆሚያ ቦታ ለረጅም ሰዓት ተቀምጠው የቆዩትን ተጠርጣሪዎቹንም ይዘዋቸው ወደ ግቢው ገቡ፡፡ የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች አቤል ዋበላና በፍቃዱ ኃይሉ እንደተለመደው በሰንሰለት ታስረው ገቡ፡፡ ማኅሌት ፋንታሁን እጆቿ በሰንሰለት ባይታሰሩም አንገቷን በሐዘን ቀብራ ነበር ወደ ግቢው የገባችው፡፡ አቤል የጠነከረ ቢመስልም የበፍቃዱ ዐይኖች መቅላት ለሊቱን በምርመራ ላይ ማደሩን ይጠቁማሉ፡፡
ችሎቱን ለመከታተል የመጡት ወጣቶች እና ቤተሰብ
ችሎቱን ለመከታተል የመጡት ወጣቶች እና ቤተሰብ

የእጆቻቸው ሰንሰለት ተፈቶ ችሎት ከገቡ በኋላ፤ከችሎት ውስጥ የሚወጣውን ምላሽ ለመጠበቅ ቤተሰብ ትንፋሹን ውጦ በቆመበት መጠባበቅ ጀመረ፡፡ እንደሌላው ጊዜ ቤተሰብ እንኳን እንዲገባ አልተፈቀደም ነበር፡፡ ዐሥር ደቂቃ እንኳን ሳይኾነው ለዘለፋ እና ለቁጣ የተዘጋጁ የሚመስሉ የፌደራል ፖሊሶች ወደ ተሰበሰበው ሰው ቀርበው ‹‹ግቢውን ለቃችሁ ውጡ እዚህ መቆም አይቻልም›› በማለት ማመናጨቅና መገፈታተር ጀመሩ፡፡ ‹‹ጠበቃው እስኪወጣ እንኳን እንጠብቅ የሚባለውን ከእርሱ ነው የምንሰማው›› ሲል ቤተሰብ ተማጸነ፡፡
አንዲት ሴት ፌደራል ፖሊስ እየተንደረደረች ወደ ተሰበሰበው ቀርባ ከፊት ያለውን ሰው መገፈታተር ጀመረች፡፡ ግፍተራው የደረሰባት የበፍቃዱ ኃይሉ እህት ግፍተራውን እየተከላከለች ፍርድ ቤት ግቢው ውስጥ ቆሞ የመጠበቅ መብት እንዳላት በመግለጽ ልታስረዳት ሞከረች፡፡ ፖሊሷ ተቆጣች እጅግም ተናደደች፤‹‹የምን መብት ነው ያለሽ፤ውጪ ብዬሻለሁ ውጪ፤አንተ ዱላውን አቀብለኝ›› የሥራ ባልደረባዋ ዱላውን እንዲያመጣላት ጠየቀች፡፡ ያሁሉ ሰው በተሰበሰበበት ዱላ ተቀብላ ለመማታት ተጋበዘች፡፡ የበፍቃዱ እናት ልጃቸውን ለመከላከል መሀል ገቡ ‹‹ዛሬ እናንተ ባለጊዜ ሆናችሁ ነው፤ፈጣሪ ፍርዱን ይሰጠናል›› እንባቸውን አረገፉት፡፡ ሌሎችም አገዟቸው፡፡ ቤተሰብ ተላቀሰ ፖሊሷ ግን ዱላዋን አቀባብላ ይበልጥ ተጠጋች ሰው ግቢውን ለቆ የማይወጣ ከኾነ ዱላው የማይቀርለት መኾኑን በሚገልጽ አኳኋን እያመናጨቀች አባረረች፡፡ ራሳቸውን ከፖሊሷ ዱላ መከላከል እንደማችሉ የገባቸው እናትና ልጅ እየተላቀሱ ተደጋግፈው ግቢውን ለቀው ወጡ ሌሎቹም ተከተሏቸው፡፡
ጠበቃው አቶ አመሐም ከችሎት ከወጣ በኋላ እንዳስረዱት ፖሊስ፤‹‹ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በወንጀል በሥነ ሥርዓት ሕጉ አንቀጽ 59/2 መሰረት የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ጠይቀን በምርመራ ላይ ነበሩ፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ተጠርጣሪዎች ሚስጥራዊ በኾነ መንገድ በሕቡዕ በመደራጀት በሕጋዊ መንገድ ሥልጣን የያዘውን መንግሥት በሕገ ወጥ መንገድ ከሥልጣን ለማውረድ በማሰብ፣ ይህንንም ሐሳብ በውጭ አገር ከሚገኙ አሸባሪ ድርጅቶች ጋራ በመስማማትና አገሪቱን ለማተራመስ ትእዛዝ በመቀበል፣ትእዛዙን ለማሳካት የሚያስችላቸውን ገንዘብ በመቀበል፣እንዲሁም ስልጠና በመውሰድ በአገሪቱ ላይ ብጥብጥ ለማነሳሳትና ብጥብጡንም ለመምራት በመንቀሳቀስ የሽብር ተግባር ፈፅመዋል፡፡ በመኾኑም ይህን የሽብር ተግባር ለማጣራት እንዲረዳን በፀረ ሽብር ዐዋጁ ቁጥር 652/2001 አንቀፅ 28 መሰረት ተጨማሪ 28 ቀናት የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠን እንጠይቃለን››የሚለውን ቀደም ሲል አቅርቦት የነበረውን ማመልከቻ መልሶ አቀረበ፡፡ እኛም ይህ ማመልከቻ ተቀባይነት ሊያገኝ የማይችልበትን ምክንያት በመጥቀስ መከራከሪያችንን አቀረብን ዳኛው ፖሊስ የጠየቀውን የጊዜ ቀጠሮ ፈቀደ ብለዋል፡፡
ከዐሥራ አራት ቀናት በፊት በነበረው ቀጠሮ ችሎቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ችሎቱን ለመታደም የመጣውን ሰው ፖሊስ ከግቢው ውጪ አቁሞት ነበር፡፡ ኾኖም ተጠርጣሪዎቹ በመኪና ተጭነው ሲወጡ ከበር ላይም ቢኾን እጁን እያውለበለበ፣ስማቸውን እየጠራና እያጨበጨበ ሸኝቷቸው ነበር፡፡ ዛሬ ግን ይህም አልነበረም ማንም ሰው የውጭው በር ላይ እንኳን እንዲቆም አልተፈቀደለትም፡፡
ምራቂ ወሬ
‹‹መዝገቡ በጊዜ ቀጠሮ ላይ የሚገኝ ቢኾንም ባለፈው ቀጠሮ ፍርድ ቤቱ የፖሊስን የሽብር ተግባርና የሃያ ስምንት ቀን የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ ውድቅ ስላደረገው ዛሬ መልሶ እሱን ማንሳት አይቻልም ፖሊስ ጥያቄውን እንደገና ማቅረብ ቢፈልግ እንኳን በይግባኝ እንጂ መልሶ በዚህ ችሎት የሚያቀርብበት ሥርዓት አይኖርም፡፡›› በማለት ሞያዊ አስተያየቱን ሰጠ፡፡ የሕግ ባለሞያው የተቀመጠበትን ዙሪያ ከበው የተቀመጡት ወዳጅ ቤተሰቦች አስተያየቱን ሰምተው ‹‹ቢበዛ ፖሊስ ሊጠይቅ የሚችለው ዐሥራ አራት ቀን ነው፤እሱንም ቢኾን የሽብር ተግባሩን ሳያካትት ነው ››በማለት ቀደም ሲል የሕግ አስተያየት ሰጥተው የነበሩት የሕግ ባለሞያ ችሎቱ ካለቀ በኋላ የፍርድ ቤቱን ትእዛዝ ሲሰሙ የፍርድ ቤቶቹ አሠራር ፊት ለፊት ከሕጉ ጋር እየተጣረሰ መሄድ ግራ ሲያጋባቸው ታይተዋል፡፡ ‹‹ከዚህ በኋላ የሕግ ባለሞያዎች ትንታኔ ዋጋ የሚያጡበት ጊዜ በጣም እየቀረበም ነው›› ብለዋል፡፡
tsiongir@gmail.com

የመከላከያ ሰራዊት መኮንኖች በአዛዦቻቸው ላይ ውጥረት ፈጥረዋል ጄኔራል አበባው ታደሰን እና የብኣዴን መኮንኖችን ያገለለ ስብሰባ መካሄዱ ጥያቄ አስነስቷል

June1/ 2014
mekelakeya
 በወያኔ የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ውጥረት መፈተሩን ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ተሰምቷል:: በወታደራዊ ጥቅማ ጥቅም እና በህገመንግሥቱ ዙሪያ ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥ አካል መጥፋቱ እና ዝም መባሉ ዉስጥ ውስጡን እየተብላላ ያለው የመኮንኖቹ ጥያቄ እንዳይፈነዳ የተሰጋ ሲሆን ከፈነዳ ሰራዊት ለሶስት ቦታ እንደሚከፈል ለምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮቹ ጠቁመዋል::

መኮንኖቹ በትምህርት በስራ እና በማእረግ እድገት በቤተሰብ እንክብካቤ በደሞዝ ጭማሪ እና በሕገመንግስታዊ የህዝብ መብቶች ዙሪያ ጥያቄ ያነሱ ሲሆን ወታደራዊ ጥቅማ ጥቅሞች ለአንድ ብሄር አባላት ብቻ ተመድበው እየተሰራባቸው ነው ከተማ ውስጥ ታጥቀው የመሸጉ እና ህዝብን እያጠቁ የሚገኙት የአንድ ብሄር አባላት ናቸው እንዱሁም ከሃገራዊ ጥቅም ይልቅ የፓርቲ ጥቅም እየተስተዋለ ነው: ወታደሩ የጦር ሳይንስን እና ዲሲፕሊን በጎደለው መልኩ እየተስተዳደረ ነው በሰራዊቱ እና በሃገሪቱ ሁሉ ወቅታዊ ጉዳዮችን ሽፋን እና ማዘናጊያ በማድረግ የሙስና እና የዘረፋ መስፋፋት መልስ ሊያገኝ ይገባዋል ጄኔራል መኮንኖች አላቸው የተባለው ንብረት ይጣራ በሃገሪቱ የፖለቲካዊ እና የኢኮኖሚ ጥያቄዎች ሊመለሱ ይገባል የሚሉ እና ተመሳሳይነት ያላቸውን ጥያቄዎች ማንሳታቸው ታውቋል::የመከላከያ አባላቱ በኑሮ ውድነት እና በተቃዋሚዎች ህገመንግስታዊ መብቶች ላይ ያነሱት ጥያቄ አዛዦቹን ያስደነገጠ ከመሆኑም በላይ በአንድ ብሄር ላይ የተመሰረተ አስተዳደር እስከመቼ የሚለውም ጥያቄ መመለስ አለበት በሚል የእግር እሳት እየሆነባቸው ነው::

ይህ ከዚህ ቀደም የተጀመረው እና አሁንም በሰሜን እዝ እና በምስራቅ እዝ የተከሰተው የሰራዊቱ ህገመንግስታዊ ጥያቄ እና የጥቅማ ጥቅም አቤቱታ በመላው ሃገሪቱ ተስፋፍቶ በሁሉም የሰራዊት እዞች ውስጥ ጥያቄው መነሳቱን ምንጮቹ አመልክተዋል:: በተለያዩ ጊዜያት እየተንከባለለ የመጣው ይህ የሰራዊቱ አቤቱታ እጅግ አደገኛ አዝማሚያ እያሳየ ሲሆን በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ አስተዳደር እንዲወገድ እና ህገመንግስታዊ መብቶች እንዲከበሩ ጥያቄዎች ገፍተው መምጣታቸው ሲታወቅ ከፍተኛ የሕወሓት ጄኔራሎች በየቀኑ ካለማቋረጥ ምስጢራዊ ስብሰባዎችን እያደረጉ ከመሆኑም በላይ ከየእዙ የሚመጣላቸው ሪፖርት መፍታት የሚቻልበትን ጉዳይ እየተወያየ መሆናቸውን ከዚህ ቀደም ምንጮቹ ገልጸው ነበር::

ሌ/ጄ ሳሞራ የኑስ ጡረታ ወቶ በምትኩ የብኣዴን ሜ/ጄ አበባው ይተካሉ ሲባል ወያኔ በድንገት የመለስ የቅርብ ሰው የነበሩትን እና በአንድ ወቅት የአማር ክልል አቶ አያሌው ጎበዜን ላንቻ አከባቢ በመኖሪያ ቤታቸው ለ3 ወር አግተው ሲያሰቃዩ የነበሩት ሌ/ጄ ዮሃንስ ገብረመስቀልን በማእረግ ሾሞ ሳሞራ የኑስን ለመተካት የሚያደርገውን ሩጫ የብኣዴን አባላት መቃወማቸውን ተከትሎ ጄኔራል አባባውን ጨምሮ የብኣዴን መኮንኖችን ያገለለ የሕወሃት አባላት የሆኑ ጄኔራሎች ብቻ የተሳተፉበት በትግሪኛ የተመራ ስብሰባ መደረጉን ውስጥ አዋቂ ምንጮቹ ተናግረዋል:: በስብሰባው ላይ ቀሪ ከፍተኛ ባለማእረግ መኮንኖች እና የመምሪያ ሃላፊዎች ለምን አልተሳተፉም የሚል ጥያቄ ከአንድ ስማቸው ካልተጠቀሰ ብርጋዴር ጄኔራል መነሳቱን ምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮቹ ጠቁመዋል::

ይህ ስብሰባ ዋና አትኩሮቱ የነበረው በብሄር አደና ላይ ሲሆን እንደ ምንጮቹ መረጃ በአማራ እና በኦሮሞ መኮንኖች እየተመራ ያለውን የለውጥ ጥያቄ በማክሸፉ ዙሪያ እንደነበር እና አሁንም በስፋት የሕወሓትን የፓርቲ አቋም የሚቀበሉ እና የጥቅም ተጋሪ የሆኑ ሰዎችን ለመሾም የታቀደ ሲሆን እንዲሁም ከፖለስ ሰራዊት በከፍተኛ የማእረግ ሹመት ወደ ጦር ሰራዊቱ ለማምጣት የታሰበ ሲሆን በወታደራዊ ደህንነት ዙሪያ ሌላ ተጨማሪ ሰልጣኞችን ከፖሊስ ወስዶ በማሰልጠን ወደ ሰራዊት ማዘዋወር የሚሉ ውይይቶች ተካሂደውበታል:: አሁንም ስብሰባው የቀጠለ ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎችን እንለቃለን::

ከማረሚያ ቤት ያመለጠው የሦስት ሕፃናት ወላጆች ገዳይ ተጠርጣሪ ተያዘ

June 1/2014

-የተያዘው የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጨዋታ ሲመለከት ነው

በወሰን ግጭት ምክንያት የሦስት ሕፃናትን ወላጆች በጥይት ደብድቦ በመግደል ወንጀል ታስሮ ከነበረበት የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ግንቦት 8 ቀን 2006 ዓ.ም.

አምልጦ የነበረው ተጠርጣሪ፣ ግንቦት 17 ቀን 2006 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ስታዲየም የኢትዮጵያንና የጋናን ብሔራዊ ቡድን ጨዋታ ሲከታተል መያዙን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

አቶ ዳንኤል ነጋሽና ወ/ሮ ምስለ ማሞ የተባሉ የሦስት ሕፃናት ወላጆችን፣ የካቲት 24 ቀን 2006 ዓ.ም. በንፋስ ስልክ ላፍቶ ከፍለ ከተማ ለቡ ማዞሪያ አካባቢ በጥይት ደብድቦ ገድሏል የተባለው ተጠርጣሪ መቶ አለቃ ጌትዬ አለሜ የተባለ ግለሰብ ሲሆን፣ እስከ 1999 ዓ.ም. ድረስ የመከላከያ ሠራዊት አባል እንደነበር በወቅቱ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ግለሰቡ የግድያ ወንጀሉን ፈጽሟል በሚል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር ውሎ በተመሠረተበት ክስ፣ ማረሚያ ቤት ሆኖ ክሱን እንዲከታተል በፍርድ ቤት በተሰጠው ብይን መሠረት ማረሚያ ቤት መውረዱን ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡

ማረሚያ ቤት ውስጥ መታመሙን በመግለጽ በማረሚያ ቤቱ ክሊኒክ በመታከም ላይ እያለ የላብራቶሪ ምርመራ ታዞለት ወደ መፀዳጀ ቤት ከገባ በኋላ፣ የመፀዳጃ ቤቱን መስኮት በመስበር ከግንቦት 8 እስከ 17 ቀን 2006 ዓ.ም. ድረስ ተሰውሮ መክረሙን ምንጮች አስረድተዋል፡፡

የተጠርጣሪውን ሙሉ መረጃ የወሰደው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ልዩ ክትትል ሲያደርግ ቆይቶ፣ ግንቦት 17 ቀን 2006 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር አውሎ ለማረሚያ ቤት ማስረከቡን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ግለሰቡ የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ አዳማ ላይ ልምምድ ሲያደርግ፣ በሥፍራው ተገኝቶ ‹‹ለቡድኑ የደኅንነት ሠራተኛ ልሁን›› ብሎ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ተቀባይነት በማግኘቱ፣ ከቡድኑ ጋር ናይጄሪያ መሄዱን፣ ለቻን ውድድርም ደቡብ አፍሪካ ደርሶ መመለሱንና ከቡድኑ ጋር ሽልማትም እንደተበረከተለት ምንጮች አክለዋል፡፡