Monday, May 12, 2014

ኦባማ ከትክክለኛው የ(ኢትዮጵያ)ታሪክ ምዕራፍ ጎን ተሰልፈዋልን?

May 12, 2014
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

የታሪክ ሸፍጥ
Obamas failed Africa policy
ፕሬዚዳንት ኦባማ “በትክክለኛው የታሪክ ምዕራፍ” መሰለፍ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦ ሰጥተው በመግለጽ እራስን በሚያወድስ መልኩ በተግባር ሳይሆን በንግግር ብቻ በማነብነብ እርሳቸው “በተሳሳተው የታሪክ ምዕራፍ” ተሰልፈዋል ብለው የፈረጇቸው ሰዎች አቋማቸውን እንዲያስተካክሉ በነገር ሸንቁጠዋቸዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2012 በተደረገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተቀናቃኛቸው ከነበሩት ከሚት ሮምኔይ ጋር ባደረጉት ክርክር ፕሬዚዳንት ኦባማ የእራሳቸውን ክብር ለመጠበቅ ሲሉ እንዲህ ብለው ነበር፣ “…ያሜ ሪካን መንግስትና ያሜሪካ ፕሬዝደንት በታሪክ ቀኝ ምዕራፍ ቆመዋል ብለው አስረዱ፡፡ “በብዙ አጋጣሚዎች ፕሬዚዳንት ኦባማ “በትክክለኛው የታሪክ ምዕራፍ” ላይ መሰለፍ የሞራል ልዕልናን የሚጠይቅ እንደሆነ በተደጋጋሚ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን በተለዬ መልኩ አሜሪካ በሰብአዊ መብት ጥበቃ መስክ ላይ ትኩረት ከማድረግ አንጻር ብቸኛዋ ልዕለ ኃያል እንደሆነች ተናግረዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2009 የኢራን ተቃዋሚዎች ወደ መንገዶች ሰልፍ ለማድረግ በወጡበት ጊዜ ኦባማ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ለፍትህ በጽናት የቆሙ ሁሉ በትክክለኛው የታሪክ ምዕራፍ ላይ የተሰለፉ ናቸው፡፡“ የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ከተካሄደ ጥቂት ዓመታት በኋላ ኦባማ ባደረጉት ንግግር እንዲህ የሚል ጥያቄ አቅርበው ነበር፣ “ማንኛችሁ ናችሁ በዚህ የስብሰባ አዳራሽ የተገኛችሁ ተሳታፊዎች መጭው ጊዜ ህዝቡን ነጻ ከሚያወጡት ይልቅ ሀሳብን ወይም ለውጥን የሚያፍኑ ይሆናል ብላችሁ የምትከራከሩ? ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በየትኛው የታሪክ ምዕራፍ ላይ እንደምትሆን አውቃለሁ፡፡“ በትክክለኛው የታሪክ ምዕራፍ ላይ ነውን?!

ፕሬዚዳንት ኦባማ በትክክለኛው የታሪክ ምዕራፍ ላይ ባልተሰለፉት ላይ ጩኸታቸውን አሰምተዋል፡፡ ቭላድሚር ፑቲን ክሪሚያን በመውረር እና የሶሪያን አምባገነን መሪ የሆኑትን ባሽር አላሳድን እየደገፉ ስለሆነ “በተሳሳተ የታሪክ ምዕራፍ ላይ ናቸው”፡፡ አላሳድ በእራሳቸው ህዝቦች ላይ አሰቃቂ የሆነ ግፍ እየፈጸሙ ስለሆነ በተሳሳተው የታሪክ ምዕራፍ ላይ ናቸው፡፡ በመካከለኛው ምስራቅ የአረብ አገሮች የሚገኙ ሁሉም አምባገነኖች ፕሬዚዳንት ኦባማ ወደ ትክክለኛው የታሪክ ምዕራፍ ላይ እንዲሰለፉ እስከሚነግሯቸው ድረስ ለአጭር ጊዜም ቢሆን በተሳሳተው የታሪክ ምዕራፍ ላይ ነበሩ፡፡ “ዩናይትድ ስቴትስ ከቀጥታው እና ከጠባቡ ትክክለኛው የታሪክ ምዕራፍ ላይ ያላትን አቋም በፍጹም አታለሳልስም፡፡ “በአሁኑ ጊዜ በሁሉም የመካከለኛው የአረብ አገሮች ላይ ያለን አቋም በትክክለኛው የታሪክ ምዕራፍ ላይ መሆናችንን ያመላክታል ምክንያቱም ንጹሀንን በአሰቃቂ እልቂት ከመታረድ እየጠበቅናቸው እና ለሁሉም ህዝቦች ሰብአዊ መብቶቻቸው እንዲጠበቁላቸው እምነት ይዘን አቋማችንን እያራመድን ስለሆነ ነው፡፡“ በማለት ፕሬዚዳንት ኦባማ ንግግር አድርገዋል፡፡ ተቃዋሚዎች ቀስ እያሉ በአረብ ከተሞች ወደ መንገዶች ለአመጽ በወጡ ጊዜ በብርሀን ፍጥነት ተገልብጠው የአረብ አገር አምባገነኖችን በመቀላቀል በተሳሳተው የታሪክ ምዕራፍ እረድፍ ላይ ሰልፋቸውን አስተካክለዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት ኦባማ ባለው ዓመት በግብጽ የተካሄደውን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ እርዳታ ላይ የዓመቱን ግማሽ እርዳታ በመልቀቅ “በዓለም ላይ በጣም ጠንካራ የሆኑ ተዋጊ ሄሊኮፕተሮችን“ በትዕዛዝ ማስተላለፍ እንዲቆም በከፊል ማዕቀብ ጣሉ፡፡ የኦባማ አስተዳደር ከግብጽ ጋር እንደ ቀድሞው ሁኔታ መሞዳሞዱን በቀጠለበት ጊዜ የግብጽ ወታደራዊ ጦር የሙስሊም ወንድማማቾችን ይደግፋሉ ብሎ የወነጀላቸውን 683 ዜጎች በይስሙላው ፍርድ ቤት የሞት ቅጣት እንዲበየንባቸው አድርጓል፡፡ ከዚህ አንጻር ሲገመገም በእርግጥ ኦባማ በትክክለኛው የታሪክ ምዕራፍ ነው ወይስ ደግሞ በተሳሳተው የታሪክ ምዕራፍ ላይ ነው የተሰለፉት?!
“ስለታሪክ” ማስመሰያነት እየተነገረ ያለው የተገላቢጦሽ ሁኔታ የሚያስገርም ነገር ነው፡፡ ማርክስ በማኒፌስቷቸው ላይ እንዲህ ብለው ነበር፣ “እስከ አሁን ድረስ ያለው የህብረተሰብ ትግል የመደብ ትግል ነው፡፡“ ሄግል የታሪክ ሂደት በፍጹም ሊገለበጥ አይችልለም ብለው ነበር፡፡ ማህተመ ጋንዲ በዚህ ጉዳይ ላይ የማይስማሙ መሆናቸውን በመግለጽ እንዲህ ብለው ነበር፣ “በጣም ውሱን የሆኑ ጽናት ያላቸው ያልተገደቡ መንፈሶች እና እምነቶች የታሪክን ሂደት ሊቀይሩ ይችላሉ፡፡“ ዱራንት “ከታሪክ ስህተቶች ትምህርት የማንቀስም ከሆነ እነርሱን ባሉበት ሁኔታ እንደግማቸዋለን“ ብለው ነበር፡፡ ናፖሊዮን “ታሪክ ምንም ነገር ሳይሆን ሰዎች በመግባባት የፈጠሩት አፈ ታሪክ ነው“ ብለው ነበር፡፡ ያም ሆነ ይህ ናፖሊዮን እና ከእርሳቸው በኋላ የመጡት ሌሎች ሁሉም አምባገነኖች ተጠራርገው በታሪክ የቆሻሻ ማስቀመጫ ውስጥ ለዘላለም ይኖራሉ፡፡

ኦባማ እና ኬሪ የአፍሪካን አምባገነኖች ተሸክመዋል፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ በትክክለኛው ወይስ በተሳሳተው የታሪከ ምዕራፍ ላይ ነው ተሰልፈው ያሉት?

እ.ኤ.አ በ2009 ፕሬዚዳንት ኦባማ በጋና አክራን ሲገበኙ ያሉት ታሪክ በጀግኖች አፍሪካውያን ላይ የሚኖር ነው፡፡ ለጀግና አፍሪካውያን/ት ያስተላለፉት መልዕክት የሚያበረታታ፣ በብሩህ ተስፋ የሚያስሞላ እና ጠንካራ ስሜትን የሚፈጥር ነበር… መሪዎቻችሁን ተጠያቂ እንዲሆኑ እና ህዝቡን ለማገልገል የሚያስችሉ ተቋማትን ለማቋቋም ስልጣን አላችሁ፡፡ በሽታን ልታሸንፉ ትችላላችሁ፣ የእርስ በእርስ ግጭቶችን ማቆም ትችላላችሁ፣ እናም ለውጥን ከታች ጀምሮ ማምጣት ትችላላችሁ፡፡ ይህንን ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ አዎ ትችላላችሁ፡፡ ምክንያቱም በአሁኑ ጊዜ ታሪክ በእንቅስቃሴ ላይ ነው፡፡ ኦባማ ቦቅቧቃዎቹን የአፍሪካ መሪዎች በአጽንኦ እስጠንቅቀዋቸዋል፡፡ “…ምንም ዓይነት ስህተት እንዳትሰሩ፣ ታሪክ በእነዚህ ጀገኖች አፍሪካውያን/ት ጎን ናት እናም መፈንቅለ መንግስት በሚያደርጉ ወይም በስልጣን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው ለመቆየት ሲሉ ህገመንግስትን በሚያሻሽሉ አምባገነኖች ጎን አይደለችም፡፡ አፍሪካ ጠንካራ ግልሰቦችን አትፈልግም፣ የምትፈልገው ጠንካራ ተቋማትን ነው…የዜጎቻቸወን ፍላጎት የሚያከብሩ መንግስታት የበለጸጉ የበለጠ የተረጋጉ እና የበለጠ ስኬታማ ናቸው…“

እ.ኤ.አ ጁን 2013 “የአፍሪካን አምባገነኖች መንከባከብ“ በሚል ርዕስ ትችት አቅርቤ ነበር፡፡ በዚህ ትችት ላይ የአሜሪካ “ዲፕሎአገዛዝ” እና “ዲፕሎቀውስ” (በእራሴ አባባል የአሜሪካንን መንታ ምላስ የሰብአዊ መብት አስመሳይ ዲፕሎማቶችን አመለካከቶች፣ ድርጊቶች እና ባህሪያት ለመግለጽ የተጠቀምኩበት) ነበር፡፡ በዚያ ትችቴ ላይ የአሜሪካው የመንግስት መምሪያ ጸሐፊ ኬሪ በጸሐፊነት ዘመናቸው ብዙም የማይጠቅሙ እና በደንብ ጎልተው የማይታዩ የሰብአዊ መበት አጠባበቅ በኢትዮጵያ እንዲሁም በመላው አፍሪካ የሚያራምዱ መሆናቸውን ለመተንበይ ሞክሬ ነበር፡፡ “የኬሪ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በአፍሪካ የሰብአዊ መብት ፖሊሲ“ ላይ በአስመሳይነት በባዶ ቃላት ታጅቦ የሚሽከረከር ምናባዊ እንጂ “ትርጉም ያለው የሰብአዊ መብት ፖሊሲ ሽግግር በኢትዮጵያ በማድረግ ላይ ያተኮረ አይደለም፡፡“ በኬሪ የዉጭ ጉዳይ አስተዳደር ዘመን ቀደም ሲል ከነበሩት ከሂላሪ ክሊንተን በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የተለየ ፖሊሲ እንደማያራምዱ እና ተመሳሳይ እንደሚሆን ለፖለቲካ መድረክ ትወና ምቹነት እና “በሽብርተኝነት ላይ ዓለም አቀፍ ጦርነት” ለማካሄድ በሚል ማካካሻ የተረሳ እንደሆነ ትንበያ ሰጥች ነበር፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ህልውናቸው በአምባገነኑ ገዥ አካል ሲሸበብ፣ በጠራራ ጸሐይ የህዝብ ድምጽ ሲዘረፍ፣ ሰላማዊ አመጸኞች መብቶቻቸው ሲደፈጠጡ፣ እና የተቃዋሚ ኃይሎች ሀሳቦቻቸውን እንዳይገልጹ ሲታፈኑ፣ የፕሬስ እና የኢንተርኔት ገደብ ሲጣል እንዲሁም ሙስና በኢትዮጵያ እንደ ካሰንሰር እየተስፋፋ የአገሪቱን ሀብት እያሽመደመደ ባለበት ሁኔታ የኦባማ አስተዳደር ለሁኔታዎች አይቶ እንዳላየ እያለፈ ነው፣ ለጉዳዩም ምንም ትኩረት ባለመስጠት ጆሮ ዳባ ልበስ ብሏል፣ ከንፈር ከመምጠጥ ያለፈ ተጨባጭነት ያለው ስራም አልሰራም፡፡ ቃል እና ተግባር ለየቅል ሆነዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የኦባማ የአፍሪካ ፖሊሲ የሰብአዊ መብት ጥበቃን አያካትትም፡፡

ኬሪ ባለፈው ሰኔ ኢትዮጵያን በጎበኙበት ጊዜ በሰቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ላይ እየተደረገ ያለውን የኃይል እርምጃ እዲቆም፣ ሁሉም የፖለቲካ አስረኞች እንዲፈቱ እንዲሁም ነጻውን የመገናኛ ብዙሀን መጨቆኑን እንዲያቆም፣ ነጻ ጋዜጠኞችን፣ ሰላማዊ አመጸኞችን እና የተቃዋሚ ፖለቲካ አመራሮችን ማሸማቀቁን እና ወደ እስር ቤት ማጋዙን እንዲያቆም ይማጸ ናሉ ወይም ደግሞ እንዲያቆም ያደደርጋሉ የሚል እምነት ነበረኝ፡፡ ይህንን ትንበያ በዘፈቀደ ወይም ደግሞ ከእውነታው በራቃ መልኩ ተምኔታዊ የሆነ አስተሳሰብም አልነበረም፡፡ ኬሪን እና ኦባማን በተናገሩት ቃላት ብቻ ነው እየመዘንኳቸው ያለሁት፡፡ እ.ኤ.አ በ2008 ዕጩ ተመራጮች የነበሩት ኦባማ እና ጆይ ቢደን የሚከተለውን ቃል ገብተው ነበር፣ “የታሰሩ ምሁራን፣ አክቲቪስቶች እና በግብጽ እንደ አይማን ኑር ያሉት የፖለቲካ የተቃዋሚ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ እንሰራለን፡፡” እ.ኤ.አ ጃንዋሪ 24/2013 በድምጽ ማሰባሰብ ሂደታቸው ላይ ኬሪ እንዲህ ብለው ነበር፣ “አንድ ወይም ሌላ አገር በምጎበኝበት ጊዜ ያለንን ቀዳሚ ዓላማ እና ይህም ተግባራዊ እንዲሆን በሚሉት ላይ አንዳንድ ጊዜ እጋፈጥ ነበር፣ ሆኖም ግን የሰብአዊ መብትን ጉዳይ በተለይም በእስር ቤት የሚገኙ ግለሰቦች እንዲለቀቁ ያላነሳሁበት ጊዜ አልነበረም፣ ይህንንም አቋሜን አጠናክሬ እቀጥልበታለሁ…“

ሴክሬታሪ ኬሪ እ.ኤ.አ በጁን 2013 ኢትዮጵያን በጎበኙበት ጊዜ በዲፕሎማክራሲያዊነት ጸጥ የማለት መብታቸውን ተጠቅመዋል፡፡ ኬሪ ለአምባገነኖቹ ስለሰብአዊ መብት ጥበቃ አንዲትም ቃል ትንፍሽ አላሉም፡፡ “የታሰሩ ምሁራን፣ አክቲቪስቶች እና የተቃዋሚ የፖለቲካ እስረኞች ማለትም እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ ውብሸት ታዬ፣ አንዷለም አራጌ፣ ኦልበና ሌሊሳ፣ በቀለ ገርባ፣ አቡባከር አህመድ፣ አህመዲን ጀበል፣ ካሚል ሸምሱ እና ሌሎችም በርካቶች እንዲፈቱ እንሰራለን፡፡” የሚለው ይቅር እና ስለሰብአዊ መብት ጥበቃ አንዲትም ቃል ትንፍሽ አላሉም፡፡

በኦባማ አስተዳደር የሰብአዊ መብት ዲፕሎክራሲ ይዞታ፣

ኬሪ ባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያን በጎበኙበት ጊዜ የእርሳቸው አስተናጋጆች አሸርጋጅ የገዥው አካል አዲስ በቁጥጥር ስር ያዋሏቸውን እና ወደ እስር ቤት የወረወሯቸውን የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን እና አባላትን፣ ነጻ ጋዜጠኞችን እና ጦማሪስቶችን እንዲሁም የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን በጥይት እየቆሉ የመቀበያ ስጦታ አድርገው ሰላምታ አቅርበውላቸዋል፡፡ ይኸ በእውነቱ ታላቅ ዘለፋ ነው፡፡ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያሉት ወሮበሎች በኦባማ የማስመሰያ አስተዳደር ላይ ምን ያህል መተማመን እንዳለባቸው የሚያመላክተው ተጫባጭ የግድያ እና የዘፈቀደ የእስራት ወንጀለኝነት መረጃ በመያዝ ኬሪ ከአውሮፕላን ሲወርዱ አቅርበውላቸዋል፡፡ “እህስ ኬሪ እንግዲህ ምን ይፈጠር!?“
ኬሪ “የደህንነት ጉዳዮችን” ለመወያየት ኢትዮጵያ ውስጥ ነበሩ፡፡ ሆኖም ግን በዘፈቀደ እየተጋዙ በእስር ቤት ስለሚማቅቁት እና የዘፈቀደ ግድያ ስለሚፈጸምባቸው የኢትዮጵያ ዜጎች ደህንነት ጉዳይ እልነበረም፡፡ ኬሪ ከእራሳቸው ፍላጎት ውጭ በተጽዕኖ ባለፈው ሳምንት በሸፍጥ ክስ ተመስርቶባቸው በእስር ቤት የሚገኙትን የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮቸን እና ደጋፊዎችን በማስመልከት የይስሙላ ንግግር አድርገዋል፡፡ የእስር ቤቱ ሰለባ ከሆኑት ከብዙዎቹ ጥቂቶች መርከቡ ኃይሌ፣ ሶሎሞን ፈጠነ፣ ዘሪሁን ተስፋዬ፣ አናኒያ ኢሳያስ፣ ፋሲካ ቦንገር፣ ጀሚል ሽኩር፣ ሰይፈ ጸጋየ፣ የሽዋስ አሰፋ፣ እመቤት ግርማ፣ ዮናስ ከድር፣ እየሩሳሌም ተስፋው፣ አበራ ኃይለማርያም፣ አበበ መከተ፣ ብሌን መስፍን፣ አስናቀ በቀለ፣ መስፍን፣ ተስፋዬ አሻግሬ፣ እዮብ ማሞ፣ ኩራባቸው፣ ተዋቸው ዳምጤ፣ ፍቅረማርያም አስማማው፣ እያስፔድ ተስፋዬ፣ ጋሻው መርሻ፣ ተስፋዬ መርኔ፣ ሀብታሜ ደመቀ፣ ጌታነህ ባልቻ፣ ንግስት ወንድይፍራው፣ ሜሮን አለማየሁ የሚባሉ ለሀገራቸው ብሩህ ራዕይ ያላቸው ወጣቶች ይገኙበታል፡፡

“ከውጭ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ጋር በመገናኘት እና የማህበራዊ መገናኛዎች ዘዴዎችን በመጠቀም በአገሪቱ ውስጥ አለመረጋጋትን ለመፍጠር“ በሚል ሰበብ ገዥው አካል በሸፍጥ ያሰራቸውን ጋዜጠኞች እና ጦማሪስቶች እንዲፈታ ኬሪ የተማጽዕኖ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከእነዚህ ከታሰሩት ውስጥ አስማማው ኃይለጊዮርጊስ፣ ተስፋለም ወልደየስ፣ ኤዶም ካሳዬ፣ አቤል ዋቤላ፣ አጥናፍ ብርሀኔ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ዘላለም ክብረት እና በፈቃዱ ኃይሉ ይገኙበታል፡፡

ስለአዲሶቹ ታሳሪዎች አዲስ ዜና ከአሜሪካ የመንግስት መምሪያ ምላሽ የሚጠበቅ ነበር፡፡ ኦህ እንዴት ያሰለቻል! የመንግስት ቃል አቀባይ የሆኑት ጄን ሳኪ በዲፕሎክራሲያዊ መልኩ እንዲህ በማለት ገልጸው ነበር፣ “የኢትዮጵያ መንግስት ለእስር የዳረጋቸውን እስረኞች ጉዳይ እንደገና እዲመረምር እና በአስቸኳይ እንዲፈታቸው እንጠይቃለን፡፡ ይህንን ጥያቄ በቀጥታ ለኢትዮጵያ መንግስት ያቀረብነው በተጨባጭ በመሬት ላይ ያለውን እውነታ ከግንዛቤ በማስገባት ካለን አሳሳቢ ሁኔታ በመነሳት ነው፡፡ እናም በእርግጥ እኛ ከረዥም ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ ስለፕሬስ ነጻነት እና ሀሳብን በነጻ መግለጽ መከልከል ያለንን ስጋት በተደጋጋሚ በመግለጽ የኢትዮጵያ መንግስት የእራሱን ህገመንግስት ሙሉ በሙሉ እንዲያከብር ተማጽዕኖ ስናደርግ ቆይተናል፡፡“

እ.ኤ.አ ጁን 2012 የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች በይስሙላው ፍርድ ቤት ክስ በተመሰረተባቸው እና የረዥም ጊዜ እስራት በተፈረደባቸው ጊዜ ቃል አቀባይ ቪክቶሪያ ኑላንድ እንደዚሁ ተመሳሳይ ንግግር በማድረግ እንዲህ ብለው ነበር፣ “የኢትዮጵያ መንግስት በበርካታ ጋዜጠኞች እና በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ላይ የጸረ ሽብር አዋጁን በመጠቀም የመሰረተው ክስ አሳስቦናል…የነጻ ጋዜጠኞች መታሰር በመገናኛ ብዙሀን እና ሀሳብን በነጻ በመግለጽ መብት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖረዋል፡፡ በኢትዮጵያ ስላለው የሰብአዊ መብት አያያዝ ሁኔታ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የውይይት መድረክ በመክፈት ሀሳብን በነጻ የመግለጽ እና የመገናኛ ብዙሀን ነጻ ማድረግ የዴሞክራሲያዊ ማህበረሰብ ግንባታ ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ መሆናቸውን በማስመልከት ሀሳባችንን ግልጽ አድርገናል፡፡“ እንግዲህ እንደዚህ ባለ የሰብአዊ መብት ሁኔታ ነው በኦማ አስተዳደር በተግባር እየተተረጎመ ያለው፡፡

ፕሬዚዳንት ኦባማ ከተሳሳተው የአሜሪካ ታሪክ ምዕራፍ የጎን ተሰልፈዋልን?

ኦባማ መጀመሪያ ፕሬዚደንት ሲሆኑ የስልጣን የመክፈቻ ንግግራቸው እንዲህ ብለው ነበር፣ “አሜሪካ በከፍተኛ የስልጣን እርከን ላይ ያሉ ባለስልጣኖች እውቀቱ ወይም ደግሞ ራዕይ ስላላቸው ብቻ አይደለም የምንተገብራቸው ሆኖም ግን የእኛ ህዝቦች የአያት ቅድመ አያቶቻችን መርሆዎች ታማኞች ሆነን ለመቀጠል ካለን ጽኑ ፍላጎት አንጻር ነው፡፡“ “ኦባማ ከአፍሪካ አምባገነኖነች ጎን በሚቆሙበት ጊዜ ከአያት ቅድመ አያቶቻችን መርሆች እና ከመመስረቻ ሰነዶች ተግባራዊ መሆን ጋር በጽናት ቆመዋልን?” የአሜሪካ ታላቁ የነጻነት አዋጅ የመመስረቻ ሰነድ የሚከተለውን ይላል፣

…መንግስታት ትክክለኛውን ስልጣን ከህዝቦች ፈቃድ በማግኘት የተዋቀሩ የሰዎች ስብስቦች ናቸው፡፡ የትኛውም ዓይነት መንግስት ለዓላማዎች ጎጅ ሆኖ ከተገኘ ይህንን መንግስት ለመለወጥ ወይም ደግሞ ለማስወገድ እና ደህንነታቸውን እና ደስታቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል በእነዚህ መርሆዎች ላይ በመመስረት የመንግስትን ኃይል ማዋቀር የሰዎች መብት ነው፡፡ ተከታታይ የሆኑ የመብት ረገጣዎች መፈጸም እና ከመብት ውጭ መሄድ እንዲሁም ባልተለያየ መልኩ አንድን ነገር በተግባር ማሳየት እራሳቸውን የለየላቸው አምባገነኖች በሚሆኑበት ጊዜ እንደዚህ ዓይነት መንግስታትን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው ለመጣል እና ለእነርሱ የሚስማሙ መንግስታትን ለወደፊቱ ደህንነታቸው ሲባል መመስረት የህዝቡ ስራ ነው…”

ኦባማ ስልጣንን ከጠብመንጃ አፈሙዝ በመያዝ ትክክለኛውን የህዝብ ይሁንታ ሳያገኙ በጉልበት ስልጣንን ጨብጠው ህዝብን በማሰቃየት ላይ ከሚገኙ የአፍሪካ ወሮበላ ገዥዎች እና አምባገነኖነች ጎን በሚቆሙበት ጊዜ ከነጻነት አዋጁ ጎን ቆመዋል ማለት ይቻላልን?

የአሜሪካን ነጻነት የሚያውጀው ታላቁ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ሰነድ የሚከተሉትን ኃላፊነቶች ይሰጣል፣
…ኃይማኖትን የማያከብር ወይም ደግሞ እምነትን ለማራማድ ክልከላ የሚጥል፣ በዚህም ሳቢያ ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብትን የሚሸብብ ወይም ደግሞ ነጻውን ፕሬስ የሚገድብ እና በነጻነት መሰብሰብን የሚከለክል እና ቅሬታን ለማቅረብ የሚከልክል መንግስት ህግ ሆኖ ሊወጣ አይችልም…ማንም ሰው ቢሆን ህይወትን፣ ነጻነትን ወይም ደግሞ ንብረትን ከህግ አግባብ ውጭ ሊያጠፋ ወይም ሊገድብ አይችልም፡፡

በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር የእራሳቸውን ዜጎች ለሚፈጁ የአፍሪካ አምባገነኖች (ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል 47 የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን መግደሉን መዘገቡን ልብ ይሏል)፣ ነጻ ጋዜጠኞችን በእስር ቤት ለሚያማቅቁ የእምነት ነጻነትን ለሚያፍኑ፣ ዜፈጎች ሀሳባቸውን በመግለጻቸው ምክንያት የሚሰቃዩበት፣ በነጻ የሚሰበሰቡ ዜጎችንን የሚያስፈራሩበት እና የሚያሸማቅቁበት ያለምንም ተጠያቂነት ዜጎቻቸውን በሙስና ከሚዘርፉ ሌቦች ጎን ነው ኦባማ በትክክለኛ ምዕራፍ ተሰለፍኩ የሚሉት?

አብርሀም ሊንከን በጌቲስበርግ ንግግራቸው ላይ እንዲህ ብለው ነበር፣ “በእግዚአብሄር ፈቃድ ይህች አገር አዲስ የውልደት ነጻነትን የሚያጎናጽፍ የህዝብ መንግስት፣ ለህዝብ የቆመ ከመሬት አይጠፋም“ ብለው ነበር፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ ይህንን ሲሉ በአፍሪካ እጃቸው በደም ከተጨማለቀ ወሮበላ መንታፊ ገዥዎች ለመንታፊዎች ከተቋቋሙት “አዲስ የውልደት ነጻነት” ጎን መሰለፋቸውን ያመላክታልን?

የታሪክ ክስና ዳኝነት በኦባማ ላይ፣

ታሪክ ትክክለኛ የሆነ፣ ትክክለኛ ያልሆነ እና ውጣውረድ የሞላበት ከሆነ ታሪክም መክሰስም መዳኘትም ይቻላለል፡፡ የታሪክ ዳኝነት ሊሆን የሚችለው ኦባማ በትክክለኛው የታሪክ ምዕራፍ ላይ አልተሰለፉም፣ እናም ታሪክ እራሱ ከኦባማ ጎን አይደለም፡፡ ኦባማ ሁልጊዜ ከትክክለኛው የታሪክ ምዕርፍ ጎን እንደሚሰለፉ ይናገራሉ፣ ሆኖም ግን እውነታው ሲመዘን በተሳሳተው የታሪክ ምዕራፍ ጎን ከተሰለፉት ጋር አብረው ተሰልፈው ይገኛሉ፡፡ ተግባር በተለይም የተሻለ ተግባር ከመናገር የበለጠ ይናገራል እናም በኦባማ ላይ የቀረበው ክስ በአፍሪካ ላይ በተሳሳተው የታሪክ ምዕራፍ ላይ በመሰለፋቸው የተመሰረተ ክስ ነው፡፡

በኦባማ ላይ የቀረበው ክስና ዳኝነት በአፍሪካ ከእርሳቸው በፊት ካገለገሉት ከጆርጅ ቡሽ ያነሱ ተግባራትን ነው ለአፍሪካ ያከናወኑት የሚል ነው፡፡ (ጆርጅ ቡሽን አልመርጣቸውም ወይም ደግሞ አልደግፋቸውም፡፡ ሆኖም ግን ስልጣን ለመስጠት ብቻ እውነታውን መናገር የለብኝም፡፡ በአሁኑ ጊዜ በስልጣን ላይ ሆነው ስልጣናቸውን እንዴት እየተጠቀሙበት እንዳሉ፣ የዜጎችን መብት በምን ዓይነት ሁኔታ እየደፈጠጡ እንዳሉ፣ ስልጣናቸውን ያለአግባብ እየተጠቀሙ እንዳሉ እና በአጭሩ ስልጣናቸውን ለበጎ ነገር መጠቀም ያለመቻላቸውን ያመላክታል፡፡) ቡሽ ገንዘባቸውን አፋቸው በተናገረው ቦታ ላይ ያስቀምጡ ነበር እናም በቢሊዮኖች የሚቀጠሩ ዶላሮች ኤች አይቪ ኤድስን ለመዋጋት እና በአፍሪካ የበሽታው ሰለባ የሆኑትን ወገኖች ለማገዝ ይጠቀሙበት ነበር፡፡ ኦባማ በግንባር ቀደምትነት ለዓለም አቀፍ የኤድስ ፕሮግም የሚውል በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ቅነሳ አድርገዋል፡፡ እንደ ዋሽንግተን ፖስት ዘገባ ከሆነ እ.ኤ.አ በ2012 በጠቅላላ 214 ሚሊዮን ዶላር ቅነሳ አድርገዋል፡፡ ይህም “በአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ይህንን ቀሳፊ የሆነውን እ.ኤ.አ በ1980ዎቹ በሬጋን አስተዳደር ጊዜ የተከሰተውን በሽታ ለማስወገድ አሜሪካ ተጨባጭነት ያለው ትግል ስታደርግ የቆየችበትን“ ኦባማ እ.ኤ.አ በ2014 ተጨማሪ 50 ሚሊዮን ዶላር ለመቀነስ ሀሳብ አቅርበው ነበር፡፡ የታሪክ ዳኝነት ሲመዘን ቡሽ በአፍሪካ የመጀመሪያ ገዳይ የነበረውን ወባን ከአፍሪካ ምድር ለማስወገድ አመርቂ የሆነ አስተዋኦ አድርገዋል፡፡ ቡሽ ለአፍሪካ ደኃ አገሮች የእዳ ቅነሳ አድርገዋል፡፡ ኦባማስ የፈየዱት ነገር ይኖር ይሆን?!? ካለስ እስቲ እንስማው፣ እንየው፡፡

ባለፈው ጁን ኦባማ አፍሪካን በጎበኙበት ጊዜ የጨለመውን የአፍሪካ አህጉር ለማብራት በሚል በርካታ የኤሌክትሪክ ፕሮጀክቶች ግንባታ ለማከናውን ተነሳሽነትን አሳይተዋል፡፡ “አፍሪካን በኃይል ለማጎልበት” በሚል መርህ ለሚቀጥሉት አምስት ተከታታይ ዓመታት በስራ ላይ የሚውል 7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንዲሁም ከዚሁ በተጨማሪ የግል ዘርፉን ለማጠናከር በሚል 9 ቢሊዮን ዶላር በተጨማሪነት ለመመደብ ቃል ገብተው ነበር፡፡ እስከ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ግን ኦባማ ያጠናከሩት የወታደራዊ እና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ የአፍሪካን ወሮበላ ገዥዎች ኃይል ማጠናከር ብቻ ነው፡፡ እነዚህ ቃል የተገባለቸው በቢሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮች በባዶ ተስፋ በጆንያ ታጭቀው ለጨለማው አፍሪካ ወሮበላ አምባገነኖች የሚደርሱ ከሆነ ለመንታፊ የአፍሪካ አምባገነኖች በውጭ አገር ለከፈቷቸው የሂሳብ አካውንቶቻቸው እንደ ገና ዛፍ መብራት ከመስጠት ያለፈ ለብዙሀኑ የአፍሪካ ህዝብ የሚፈይዱት አንዳች ነገር አይኖርም፡፡

የታሪክ ዳኝነት ሲመዘን ኦባማ ለአፍሪካ ባዶ የተስፋ ቃላትን እና በማነብነብ ላይ ያነጣጠረ ባዶ ተስፋ ሆኖ ይገኛል፡፡ ላለፉት የመከኑ ቃል ኪዳኖች እንደገና ሌላ አዲስ ቃል ኪዳኖችን ይገባሉ፡፡ “በሺዎች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን/ት ወደ ዩናይትድ ስቴትስ በመምጣት በምርጥ ዩኒቨርስቲዎቻችን በመግባት እውቀታችሁን ማበልጸግ የሚያስችል አዲስ ፕሮግራም ተመቻችቷል“ የሚል አዲስ ቃል ኪዳን ገብተዋል፡፡ በአፍሪካ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን/ት በወሮበላ አምባገነኖች ስቃያቸውን የሚያዩት ወጣቶች የወደፊተ ዕጣ ፈንታ ሲተን ምን ምን ማድረግ ይቻላል?
የታሪክ ዳኝነት ሲመዘን ኦባማ በአፍሪካ የሚኖሩ ህዝቦች በእርሳቸው ቃል ኪዳን “ተስፋ እና ለውጥ” የወደፊት ጥሩምባ ጥሪ እምነት ጥለው የነበሩት ተስፋቸው ሲሟጠጥ ማየት አሳዛኝ ሁኔታ ነው፡፡ የኦባማ “የተስፋ መጠናከር” ምንም ያለማድረግ ተስፋ እና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን/ት የባዶ ተስፈኛነት ምዕናባዊ ድርጊት ነው፡፡ የታሪክ ክሱ “ምንም የተደረገ ለውጥ እንደሌለ እናምናለን፡፡!“ በአፍሪካ ከወሮበላ አምባገነኖች እና ከእነርሱ ግብረበላ ሎሌዎቻቸው በስተቀር ማንም ቢሆን በኦባማ ላይ እምነት የለውም፡፡ የኦባማ “አዎ እንችላለን“ በተግባር ሲመነዘር “በአፍሪካ ውስጥ የሰብአዊ መብቶችን ሁኔታ ለማሻሻል ምንም ነገር ማድረግ አንችልም“ የሚል ግልባጭ ትርጉም ይዞ እናገኘዋለን፡፡

በአፍሪካ የተስፋ መጠናከር፣

ኦባማ እንዲመረጥ ሽንጤን ገትሬ ስታገል እና ሌሎችም ለኦባማ ደምጽ እንዲሰጡ ድጋፍ ሳሰባስብ ነበር፡፡ ይህንን ጉዳይ ግልጽ ላድርገው፡፡ ኦባማን በመደገፌ መቆርቆር ስሜት አይሰማኝም፡፡ አ..ኤ.አ በ2008 በተደረገው ምርጫ ኦባማ እንዲመረጡ ድጋፍ ባደረግሁ ጊዜ ያ ድርጊት ቆንጆ ሀሳብ ሆኖ ይታየኝ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ. በ2012 ምንም ምርጫ የሌለው ሆንኩ፡፡ ስለሚት ሮምነይ ምን ማለት እችላለሁ?! ጆን ሁንትስማን በሬፐብሊካን የምርጫ ዝርዝር ውስጥ አልነበረም፡፡ ምናልባትም እ.ኤ.አ በ2016 ሊሆን ይችላል፡፡

እ.ኤ.አ በ2008 ኦባማን ለመምረጥ የእኔ ውሳኔ የተመሰረተው ፍላጎታዊ እና የመጀመሪያው አፍሪካዊ አሜሪካ በመሆናቸው ብቻ አልነበረም፡፡ ኦባማ በህዝብ ላይ ያላቸውን አስተዋጽኦ ሪከርድ በማየት የተደረገ ጥንቃቄ የተሞላበት ምርጫ ነበር፡፡ ከዩናይትድ ስቴትስ ሴኔት የህግ አገልግሎት ፋይላቸውን አጥንቻቸዋለሁ፣ እዲሁም ኦባማ HR 2003ን (ኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እና ተጠያቂነት አዋጅ 2007) የሚያደንቁት እና ድጋፍም የሚያደርጉበት ስለነበር ነው፡፡ በኢሊኖይስ ህግ በደህንነት ፕሮግራሞች እና ዝቅተኝ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ድጎማ እንዲሰጣቸው እንዲሁም የቤተሰብ ሰራተኞች ከታክስ ነጻ እንዲደረጉ ሲያደርጉ የነበሩትን አስተዋጽኦ ከግንዛቤ በማስገባት ነበር ምርጫየን ያደረግሁት፡፡ በኢሊኖይስ ግዛት ሰራተኞች ከስራ እንዳይባረሩ እና ትላልቅ የምርት ተቋማትም እንዳይዘጉ ሲያደርጉት የነበረውን ጥረት አደንቃለሁ፡፡ እንዲሁም በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲያደርጓቸው የነበሩት መሳጭ እና ተያያዥ ንግግሮች እና በሚያቀርቧቸው በመረጃ ላይ በተመሰረቱ ጭብጦች እና የፖሊሲ መርሆዎች እገረም ነበር፡፡ “የአባታቸው ህልሞች” የሚለውን መጽሀፋቸውን በአንድ ቅምጥ በማንበብ፣ ሌሎችን መጣጥፎች እና ንግግሮቻቸውን በማዳመጥ እደሰት ነበር፡፡ በሀርቫርድ የህግ ትምህርት ቤት በነበራቸውን የአመራር ብቃት እና አካዳማያዊ ጥረት፣ በችካጎ የህግ ትምህርት ቤት በማስተማር ብቃታቸው ላይ ኩራት ይሰማኝ ነበር፡፡ እንደ መምህር እና የህገ መንግስት ባለሙያነቴ በሚያሳዩት አጋራዊ መንፈስ ኦባማ ጥሩ ብቃት ያላቸው ሰው አድርጌ እቆጥራቸው ነበር፡፡

ኦባማ የመጀመሪያው አፍሪካዊ አሜሪካ ፕሬዚዳንት መሆን በመቻላቸው ተጨማሪ እሴታቸው ነበር፣ ሆኖም ግን ይህ ለእኔ ወሳኙ ነገር አይደለም፡፡ እ.ኤ.አ በ1968 ሮበርት ኬኔዲ ያደረጓቸው ነብያዊ ንግግሮች ለእኔ እና ለሌሎቸ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ዜጎች አስገራሚዎች ነበሩ፡፡ እንዲህ ብለው ነበር፣ “እ.ኤ.አ በሜይ 1968 በሚቀጥሉት 40 ዓመታት ውስጥ እኔ የያዝኩትን ተመሳሳይ ስልጣን ጥቁር ሊይዘው ይችላል…“ “የኦባማ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጥ በዓለም ላይ በሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ሁሉ በተለይም በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ እና በአፍሪካውያን/ት “የተስፋን መጠናከር” በአሜሪካ በእራሷ በጉልህ እየታየ ስለሆነ የኦባማ ዕጩ ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጥ ተቀባይነትን አግኝቷል– በአሜሪካ የማይቻለው የሚቻል ሆኖ ታይቷል፡፡ የኦባማ አባት ግንድ ከኬንያ መሆን በብዙ ሚሊዮን ለሚቆጠሩ አፍሪካውያን/ት ተስፋ የሰጠ ክስተት ስለነበር ኦባማ አፍሪካን በዩናያትድ ስቴትስ የውጭ ፖሊሲ ማውጣት እና በሰብአዊ መብት አያያዝ ላይ ጠንካራ ሚና በመጫወት የአፍሪካን ቦታ ከፍ ያደርጋሉ የሚል ግምትን አሳርፎ ነበር፡፡ በእነዚህ ምክንያቶች በኦባማ ላይ እምነት የመጣል የተስፋ ጥንካሬ ነበረኝ፡፡

የተስፋ ውሸት፣

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ከኦባማ ያልተከበሩ ቃል ኪዳኖች እና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን/ት ባዶ ተስፋዎች ምክንያት ከተስፋ ውሸቶች ጋር ግብግብ ገጥሜ እገኛለሁ፡፡ ሴናተር ኦባማ “የተስፋ መጠናከር“ በሚለው መጽሀፋቸው ላይ የአሜሪካንን የውጭ ፖሊሲ በሰብአዊ መበቶች ጥበቃ ላይ የተመሰረተ መሆኑን በመግለጽ ጆን ኬኔዲን በመጥቀስ እንዲህ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፣

በመንደሮች እና በጎጆዎች ያላችሁ በዓለም ላይ ግማሹን የምትይዙት የብዙሀኑን የመሰቃየት ማሰሪያ ገመድ ለመበጠስ የምትታገሉ ያለንን መልካም አጋጣሚ ሁሉ በመጠቀም የፈለገውን ያህል ጊዜ ቢወስድም እንኳ እራሳቸውን እንዲያግዙ ለማስቻል እንደግፋቸዋለን፣ ይህንን የምናደርገው ኮሚኒስቶች ስለሚያደርጉት ሳይሆን ወይም ድግሞ ድምጻቸውን ለማግኘት አይደለም፣ ሆኖም ግን ፍትሀዊ እና ትክክለኛ ስለሆነ ብቻ ነው፡፡ ነጻ የሆነ ህብረተሰብ ሌሎችን ደኃ የሆኑ ዜጎችን መርዳት ካልቻል ጥቂት ሀብታም የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችንም ማገዝ አይችልም፡፡

ለለውጥ አስፋለጊነት በሚያወሳው ንግግራቸው ሴናተር ኦባማ እንዲህ የሚል ጽሁፍ አቅርበው ነበር፣ “ባለፈው ምዕተ ዓመት በተደረገው ከእንግሊዞች አገዛዝ ነጻ ለመውጣት ጋንዲ ባደረጉት ዘመቻ፣ በፖላንድ የተደረገው የጋራ እንቅስቃሴ፣ ከጸረ አፓርታይድ ጋር በደቡብ አፍሪካ የተደረገው የነጻነት ዘመቻ ስኬታማ ስራ ምክንያት ዴሞክራሲ የአካባቢ መነቃቃት ውጤት ነው፡፡ ሌሎች ሰዎች የእራሳቸውን ነጻነት ለመቀዳጀት እንዲችሉ ማደፋፈር እና ልናግዛቸው ይገባል…መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው መብታቸው የተረገጡትን በአካባቢ አመራሮች ስም ልንናገርላቸው እንችላለን፣ የእራሳቸውን ህዝቦች መብት በተደጋጋሚ በሚደፈጥጡ አምባገነኖች ላይ የኢኮኖሚ እና የዴፕሎማሲ ጫና መጣል ይኖርብናል…“

“መብቶቻቸውን በተነጠቁ ዜጎቻችን ስም እንዲናገሩላቸው እና ነጻነታቸውን እንዲያስመልሱ“ ፕሬዚዳንት ኦባማ ለሚከተሉት ጀግና ኢትዮጵያውያን/ት ጥቂት ቃላትን ሊናገሩላቸው ይገባል፡ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ ዉብሸት ታዬ፣ አንዷለም አራጌ፣ ኦልባና ሌሊሳ፣ በቀለ ገርባ፣ አቡባከር አህመድ፣ አህመዲን ጀበል፣ መርከቡ ኃይሌ፣ ሶሎሞን ፈጠነ፣ ዘሪሁን ተስፋየ፣ አናንያ ኢሳያስ፣ ፋሲካ ቦንገር፣ ጀሚል ሽኩር፣ ሰይፈ ጸጋየ፣ የሽዋስ አሰፋ፣እመቤት ግርማ፣ ዮናስ ከድር፣ እየሩሳሌም ተስፋው፣ አበራ ኃይለማርያም፣ አበበ መከተ፣ ብሌን መስፍን… አስማማው ኃይለጊዮርጊስ፣ ተስፋለም ወልደየስ፣ ኤዶም ካሳዬ፣ አቤል ዋቤላ፣ አጥናፍ ብርሀኔ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ዘላለም ክብረት እና በፈቃዱ ኃይሉ…? ከዚህ የተስፋ ጥንካሬ ማህጸን ውስጥ የወጣ የውሸት ተስፋ ነው! “ኦ በመጀመሪያ ጊዜ ማታለል በጀመረንበት ጊዜ ምን ዓይነት የተወሳሰበ ድር እያደራን ነው”

የተስፋ እጥረት፣

ኦባማ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ላሉ አምባገነኖች እያዩ ያላዩ ያሉ በመምሰል እየተመለከቱ ነው፡፡ ለዓመታት ፕሬዚዳንት ኦባማ ለፕሬዚዳንት ሮናልድ ሬጋን ከበሬታን ሰጥተዋል፡፡ ምናልባትም ከሮናልድ ሬጋን ታሪክ መማር ይችላሉ፡፡ “እያንዳንዱ መንግስት የራሱ የሆነ ልዩ ባህሪ አሉት እናም ያ ባህሪ ከጠፋ መንግስቱም ይወድቃል፡፡ አምባገነናዊነት በተንሰራፋበት ስርዓት ፍርሀት አንዱ ነው፡፡ ህዝቡ አምባገነኑን መፍራት ባቆመ ጊዜ አምባገነኑ ስልጣኑን ያጣል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አገር ወካይ መንግስት በተዋቀረበት አገር ትልቅ ክብር እና ሞገስ ነው፡፡ ክብር እና ሞገስ በሌለበት ጊዜ መንግስቱ ይወድቃል፡፡ የፖለቲካ ጥርጣሬ እና የሞራል ጥያቄ ያለባቸውን መንገዶች እንመርጣለን? ክብር እና ሞገስን በመተው በእውነታ ላይ ብቻ እንኖራለን?… ይህ ከሆነ ከምናውቀው በላይ ለታሪክ ቆሻሻ መጣያ እየቀረብን ነው፡፡“ የታሪክ መጨረሻው በምጻት ቀን እና በሰው ልጅ ክብር እና ሞገስ መካከል ስልጣንን አላግባብ መጠቀም ሊሆን ይችላልን?

የታሪክ ዳኝነት ፕሬዚዳንት ኦባማ ለሚመጣው ትውልድ የአፍሪካ ዋና አባካኝ ተብለው የሚታወቁበት ይሆናል፡፡ እኛ አፍሪካውያን/ት በኦባማ ላይ ያለንን ተስፋ አቁመናል፡፡ ከባርነት በማምለጥ የነጻነት ሻምፒዮን የሁኑትን ታላቁን አሜሪካዊ የፍሬድሪክ ዳጉላስን ወርቃማ ቃላት በመዋስ፣ ”ማንኛውም ሰው በዝግታ ለምን ግድየለሽ እንደሚሆን እስቲ ተመልከቱ፣ እናም በእነርሱ ላይ የሚጫኑትን የኢፍትሀዊነትን እና ስህተትን ትክክለኛ መለኪያ ታያላችሁ፣ እናም ይህ ጉዳይ በቃላት፣ ወይም በኃይል ወይም በሁለቱም እስካልተወገደ ድረስ ድርጊቱ ይቀጥላል፡፡ የአምባገነኖቹ ወሰን በተጨቆኑት የዝምታ ጽናት ደረጃ ይገለጻል፡፡“

የኢትዮጵያ ህዝብ ጽናት ወሰኑ እስከምን ድረስ ነው? የአፍሪካ ህዝብስ?

ኦባማ ለኢትዮጵያ ደንታ አላቸውን? ለአፍሪካስ? ኦባማ ለማናቸውም ደንታቸው የላቸውም!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ሚያዝያ 28 ቀን 2006 ዓ.ም

Sunday, May 11, 2014

የወያኔ ጥላቻ ፍሬ (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

May 11/2014

ወያኔ ለትግራይ ሕዝብ ሀብትንና ብልጽግናን አመጣ ብለው የሚያምኑ ሰዎች ብዙ ናቸው፤ ወያኔ የሥልጣን ወንበሩ ላይ በመውጣቱ ትግሬዎች ሁሉ አልፎላቸዋል ተብሎ ይታመናል፤ በተለይ በአውሮፓና በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዚህ ላይ የጠነከረ እምነት አላቸው፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ውጭ ብዙ ውይይትም ይሁን ንትርክ ይደረጋል፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ግን የተፈራ ርእስ ነው፤ ውስጥ-ውስጡን እንጂ አደባባይ አይወጣም፤ ይህንን ጉዳይ በኢትዮጵያ ውስጥ አደባባይ ለማውጣት ጊዜው የደረሰ ይመስለኛል፤ አረጋዊ በርሄ፣ ገብረ መድኅን አርአያ፣ አስገደ ገብረ ሥላሴ፣ አብርሃ ደስታ (አሥር ቢሞሉልኝ ደስ ይለኝ ነበር!) እየደጋገሙ ቢያነሡትም ሌሎች በቁም-ነገር የተቀበሉት አይመስልም፤ ሕዝቡ ግን በራሱ መንገድ እየተናገረና ምስክርነቱን እየሰጠ ነው፤ በመቀሌ የተሠራውን የመኳንንት መንደር ሕዝቡ አፓርቴይድ ብሎ ሲሰይመው፣ በአዲስ አበባ የተሠራውን መንደር መቀሌ ብሎ ሲሰይመው እየመሰከረ ነው፤ ‹‹የለሁበትም!›› እያለ ነው።

የትግራይ ሕዝብ መደህየቱ አልበቃ ብሎት ሲለምንም እየተሳቀቀ ነው፤ የሚለምነው ትግሬ ለብዙ ሰዎች ትግሬና ወያኔ አንድ መስሎ እንደሚታየው ያውቃል፤ አብዛኛው ሰው በወያኔ ላይ ያለውን ስሜት ያውቃል፤ ስለዚህም ሲለምን ሰዎች በወያኔ ላይ ያላቸውን ስሜት ስለሚያራግፉበት እየተሸማቀቀ ነው፤ አንድ የትግራይ ቄስ ከአርሲ ነኝ አሉኝና ለምን እውነቱን አይናገሩም ስላቸው እውነቱን ስናገር የማገኘው ስድብ ብቻ ነው አሉኝ፤ እኒህ ሰው ምን በወጣቸው የወያኔን ኃጢአት ተሸካሚ ይሆናሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በትግሬነቱ የተጠቀመ አለ፤ እኔ የማውቀው የደርግ ወታደር የነበረ ትግሬ ቆስሎ ከውትድርና ወጣና በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት የጥበቃ ሥራ ላይ ነበር፤ በጣም ይቸግረው ነበር፤ ሚስቱ ሕመምተኛ ነበረች፤ የቤት ኪራይ መክፈል ይቸገር ነበር፤ ዛሬ ግን የሚለብሰው ልብስ ሌላ ነው፤ ከኑሮውም ተርፎ ለሲጃራና ለጫት እያወጣ ነው፤ ወይም ሌሎች እያወጡለት ነው፤ ትግሬነታቸው ብቻ እንዲህ የደላቸው በጣም፣ በጣም ጥቂቶች ናቸው፤ ስለዚህም በወያኔ አገዛዝ ትግሬ ሁሉ ተጠቅሞአል ማለት ከጉልሁ እውነት ጋር የሚጋጭ ስሕተት ነው፤ አብርሃ ሰዎች ትግሬ ሁሉ ተጠቃሚ ሆኗል ሲሉ ‹‹ያመኛል›› ማለቱ ይገባኛል።

ወያኔ ትግሬ በመሆኑ ብቻ ትግሬ ሁሉ ዕዳ አለበት ማለት እንደወያኔ ማሰብ ነው፤ ወንጀል በዘር አይተላለፍም፤ እያንዳንዱ ሰው ለሠራው ሥራ ሁሉ ኃላፊነትን ይወስዳል፤ ጊዜው ሲደርስ ውጤቱንም ለመቀበል ይገደዳል፤ ይህ የሚሆነው ሰው ሁሉ በመንፈሳዊ ኃይል በጎ መንፈስ አድሮበት፣ አእምሮው በትምህርት ተገርቶ በትክክል ማሰብ ሲችል ነው፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁን በአለበት ሁኔታ በጎ መንፈስ የራቀው ይመስላል፤ አእምሮም ጭራሹኑ በእኩይ መንፈስና በጥላቻ እየዛገ ነው፤ ስለዚህ ያስፈራል፤ በደቡብ ሱዳን ሁለት መቶ ሰዎች በዘር ተለይተው ታረዱ ሲባል ያስፈራል፤ በናይጂርያ፣ በኮንጎ የሚካሄደውን የዘርና የሃይማኖት እልቂት ስንሰማ ያስፈራል፤ በ1997 ዓ.ም. መለስ ዜናዊና አዲሱ ለገሰ እንዳስታወሱን የሩዋንዳ የጎሣ እልቂት በብዙ ሰዎች አእምሮ ውስጥ አለ፤ የቅርብ ተኳሽ የሆነው የአግዓዚ ጦርም አድፍጦ መጠበቅ ያስፈራል፤ ሌላውም ይህንን አውቆ አድፍጦ መጠበቁ ያስፈራል፤ ሰማይ ጠቀስ የሠሩት፣ የሥልጣን ኃላፊነትን ችላ ብለው በሥልጣን የሚነግዱና የሚከብሩት፣ የማይኖሩበትን ሕንጻ የሚክቡት፣ ከሕዝብ ጋር ያላቸው የአይጥና የድመት ኑሮ ያስፈራል፤ አቶ አስገደ ወያኔ መደንገጡን ይነግረናል፤ መደንገጥ የማይቆጣጠሩት ፍርሃት ነውና አደጋ ያመጣል፤ አደጋው አደጋን ይጠራል፤ ይህም ያስፈራል።

በትግራይ ዙሪያ ያለው ምንድን ነው? የትግራይ ሕዝብ በየትኛው አቅጣጫ ነው አንደልቡ እየተዘዋወረ ለመሥራትና ለመኖር የሚችለው? ወያኔ የትግራይን ሕዝብ ከሰሜን ከወገኑ ከኤርትራ ሕዝብ ጋር ደም አቃብቶታል፤ በደቡብ-ምሥራቅ ከወሎ መሬት ቆርሶ የወሎን ሕዝብ ቂም አስቋጥሯል፤ በደቡብ-ምዕራብ ከጎንደር መሬት ቆርሶ የጎንደርን ሕዝብ ቂም አስቋጥሯል፤ የራስን ወገኖች አስቀይሞ ሱዳንን በመሬት ለመደለል የሚደረገው ጥረት ሁሉ ፋይዳ የለውም፤ ሱዳን ለራሱም ያልበጀ አገር መሆኑ እየታየ ነው፤ ወደፊት ደግሞ ይበልጥ ይታያል፤ በትግራይ ውስጥ ደግሞ ወያኔ የፈጠረው አፓርቴይድ የወያኔን የኑሮ ደረጃ ወደሰማይ ሲያስጠጋው፣ የቀረውን ወደአንጦርጦስ የደሀነት ገደል ውስጥ ከቶታል፤ በዚህም ምክንያት በአዲስ አበባ ከተማ ከነልጆቻቸው እየተዘዋወሩ የሚለምኑ ሞልተዋል፤ ይህ ልመናም ለወያኔ ለመገበር ነው፤ ብዙዎቹ እንደሚናገሩት የሚለምኑት የማዳበሪያ ዕዳቸውን ለወያኔ ለመክፈል ነው።

ወያኔ ከሀያ ዓመታት በላይ አፍንጫ እየያዘ ያስከፈለውን የሚመልስበት ጊዜ እየተቃረበ ነው፤ ጥያቄው ወያኔ እንዲመልስ የሚገደደው እንዴት ነው? የሚል ነው፤ጥላቻ ወደንዴት፣ ንዴት ወደቁጣ ተለውጦ ሲገነፍል ምጽዓት ደረሰ ማለት ነው፤ ሁሉምሰው ራቁቱን ይሆናል፤ አንደአውሬ ከጥፍሩና ከጥርሱ በቀር ሌላ መሣሪያ አይኖረውም፤ ሰው ሁሉ በክፋት ወደአውሬነት ይለወጣል፤ ጠመንጃና ቦምብ አያገለግሉም፤ ሕንጻው ምሽግ አይሆንም፤ መኪናው፣ ባቡሩ፣ ታንኩ ከቆመበት አይነቃነቅም፤ የትም አያደርስም፤ ጭፍራ ሁሉ በየራሱ ፍዳ ታንቆ እንኳን ለሌላ ሊተርፍ ለራሱም የማይበቃ ይሆናል፤ ለነገሩ ጌታና ሎሌም የለም፤ ሁሉም በአውሬ እኩልነት የተፋጠጠ ነው፤ ርኅራኄ ተሟጦ፣ መግል ያዘለ ልብ ፈርጦ፣ ውይይትና ክርክር አብቅቶ፣ ጥርሱን ያገጠጠና ጥፍሩን የሳለ መንጋ በደም የሚራጭበት ሁኔታ ነው።

ሌላ አገር እንዲህ አልሆነም፤ እዚያ አገር እንዲህ አልሆነም፤ የሚባል ነገር የለም፤ እኛ ዘንድ ሌላ ነው፤ የኢትዮጵያ ደሀዎች እንባ የእግዚአብሔርን ሰማይ አጨቀየው!

ክፋት እንደእሳት ይቃጠላል፤ ኵርንችቱንና እሾሁን ይበላል፤ ጭፍቅ የሆነውንም ዱር ያቃጥላል፤ ጢሱም ተትጐልጕሎ እንደዓምድ ይወጣል፤ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ቁጣ ምድር ተቃጥላለች፤ ሕዝቡም እሳት እንደሚበላው እንጨት ሆኖአል፤ ሰውም ለወንድሙ አይራራም፤ ሰው በቀኙ በኩል ይነቅላል፤ ይራብማል፤ በግራም በኩል ይበላል፤ አይጠግብምም፤ እያንዳንዱም የክንዱን ሥጋ ይበላል፤ ምናሴ ኤፍሬምን፣ ኤፍሬምም ምናሴን ይበላል፤… ኢሳይያስ 9/18-21

ትንቢተ ኢሳይያስ ለሩዋንዳውያን ብቻ አይደለም፤ ጥላቻና ክፋት በተዘራበት ቦታ ሁሉ ውጤቱ ጥፋት ነው፤ ምናሴ ኤፍሬምን በልቶ አይቀርም፤ ኤፍሬምም ምናሴን ይበላዋል።

በአዲስ አበባ ዙሪያ ገበሬዎች የሚፈናቀሉት ያለ በቂ ዝግጅት ነው ተባለ

May 11/2014
     
  ከግማሽ ሚሊዮን እስከ 2 ሚሊዮን ብር ካሣ የተከፈላቸው ገበሬዎች አሉ በተከፈላቸው ካሣ ንድግ ጀምረው የተሳካላቸው ጥቂቶች ናቸው
“ቦታው ለሪል እስቴትና ለልማት ይፈለጋል ተብለን የእርሻ መሬታችንና የመኖሪያ ቦታችን በመንግስት ከተወሰደብን አራት አመታት ሞላን” ይላሉ - በሰበታ አዋስ ወረዳ እያረሱ ይኖሩ እንደነበር የገለፁ አርሶአደሮች፡፡ ለእርሻ መሬት እንደየስፋቱ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ካሳ የተከፈላቸው ገበሬዎች መኖራቸው አይካድም፡፡ ለመኖሪያ ቤትም 24 ሺ ብር ድረስ ካሳ እንደተከፈላቸውና ቤት መስሪያ ቦታ እንደሚሰጥም ቃል ተገብቶላቸው እንደነበር የተፈናቀሉ ገበሬዎች ያስታውሳሉ፡፡ “ከዛሬ ነገ ቦታ ተሰጥቶን ባለችን ብር ጭቃ ቤት እንሰራለን ብለን ብንጠብቅም ቄሱም ዝም መፅሀፉም ዝም ሆነ” ብለዋል - ገበሬዎቹ፡፡ የአራት ልጆች አባት የሆኑት የሰበታ አካባቢ ገበሬ፤ መሬታቸው ከተወሰደባቸው በኋላ ስለገጠማቸው ህይወት ሲናገሩ፤ “ስድስት ቤተሰብ ይዤ ሰበታ ከተማ ሁለት ጠባብ ክፍሎችን ተከራይቼ በጭንቀት መኖር ጀመርኩ፡፡ ገንዘቡ ለቤት ኪራይ፣ ለቀለብ፣ ለልጆች ት/ቤት፣ ለትራንስፖርት ሲወጣ፣ በአጭር ጊዜ ተሟጦ ለችግር ተጋለጥኩ” ብለዋል፡፡ ከአካባቢው በርካታ አርሶ አደሮች አብረዋቸው እንደተፈናቀሉ የሚናገሩት አርሶአደሩ፤ አቅመ ደካማው ለረሀብና ለእርዛት ተጋልጦ፣ ለልመና እጁን ሲዘረጋ፣ ጉልበት ያለው የቀን ስራ እየሰራ ኑሮውን ሲገፋ፣ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እያቋረጡ ወደ ሰው ቤት ሰራተኝነትና ሴተኛ አዳሪነት ሲገቡ መመልከት ክፉኛ እንደሚያሳምም ተናግረዋል፡፡ ከአካባቢው በዚህ መልኩ የእርሻ መሬታቸውን ካጡ አርሶአደሮች መካከል ወደ ንግድ ገብተው የተሳካላቸው ሶስት ሰዎች ብቻ እንደሆኑ የጠቆሙት ተፈናቃዩ፤ የቀረው ግን በካሳ መልክ ያገኘውን ገንዘብ ለቤት ኪራይና ለቀለብ አውጥቶ በአካባቢው ብዙ ማህበራዊ ቀውስ መከሰቱንና እስካሁንም እልባት እንዳልተገኘለት በቁጭት ይናገራሉ፡፡ ሱሉልታ አካባቢ በግብርና ይተዳደሩ የነበሩ አንድ ሌላ አርሶአደር ደግሞ መሬታቸው ለልማት ሲወሰድ 19 ሺ 200 ብር ካሳ ማግኘታቸውን ይናገራሉ፡፡ ገንዘቡን ይዘው ወደ ከተማ በመምጣት፣ ቤት ተከራይተው ከሶስት ልጆቻቸውና ከሚስታቸው ጋር ለጥቂት ወራት ቢኖሩም፣ ኑሮው በዚያው መልክ መቀጠል አልቻለም ይላሉ፡፡ “ብሩ እየመነመነ ሲሄድ ትልቋን ልጄን ወንድሜ እንዲያስተምርልኝ ጫንቾ ልኬ፣ ሁለተኛዋ ልጄ ሰርታ ራሷን እንድትችል አዲስ አበባ ዘመድ ጋር አስጠግቼ፣ ቀን ቀን ዘመዶቼን እያገለገለች ማታ ማታ ትማራለች” ያሉት የቀድሞው አርሶ አደር፤ ትንሹን ወንድ ልጄንና ባለቤቴን ይዤ የቀን ስራ እየሰራሁ፣ ባለቤቴ ሰው ቤት እንጀራ እየጋገረችና ልብስ እያጠበች፣ በምናገኛት ገቢ ኑሮን እየገፋን ነው ብለዋል፡፡ “እህል ከጎተራ ዝቆ እንደልቡ ልጆቹን መግቦ መኖር የለመደ አርሶ አደር፤ ከለመደው ባህልና ወግ ውጭ ሲሆን ብስጭቱና ቁጭቱ ጤና ያሳጣዋል፤እኔም የዚህ ችግር ሰለባ ሆኜ ያለ እድሜዬ አርጅቻለሁ፤ ባለቤቴም ሁለት ሴት ልጆቿ ከጉያዋ እርቀው ሲበተኑ፣ ቀን ማታ እያለቀሰች ሌላ ራስ ምታት ሆናብኛለች” ያሉት አባወራው፤በአካባቢያችን የእኛ አይነት ችግር የደረሰባቸው በርካታ አርሶ አደሮችን ብታነጋግሩ፣ ከእኛ የበለጠ ችግር ውስጥ መሆናቸውን ትረዳላችሁ ሲሉ ሁኔታው የከፋ መሆኑን ጠቁመውናል፡፡ ከኦሮሚያ ልዩ ዞን አስተዳደር ወረዳዎች አንዷ በሆነችው ዱከም አካባቢ አርሶ አደር የነበሩት አቶ ደሜ ፈዬራ (ስማቸው ተለውጧል) ኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞንን ጨምሮ ለሌሎች የኢንዱስትሪ ልማቶች ከተወሰደባቸው የእርሻ መሬት ዳጎስ ያለ ካሳ ማግኘታቸውን ይገልፃሉ - የገንዘብ መጠኑን መጥቀስ ባይፈልጉም፡፡ ከ4 ዓመት በፊት ባገኙት በዚህ የካሳ ክፍያ፣ በዱከም ከተማ አንድ የሸቀጣ ሸቀጥ ንግድ መደብር እንዲሁም ባለ 5 ክፍሎች መኖሪያ ቤት እና ያገለገለ አይሱዙ መኪና ወደ 1 ሚሊዮን ብር ገደማ አውጥተው እንደገዙ ይናገራሉ፡፡ መኪናዋ የተገመተውን ያህል አገልግሎት መስጠት ባትችልም የንግድ ሱቁና የከተማ መኖሪያ ቤቱ ግን ለቤተሰቡ ሁነኛ የኑሮ ዋስትና ሆኗቸዋል፡፡ አቶ ደሜ፤ የእርሻ መሬታቸው ለልማት እንደሚፈለግ ከባለስልጣናት በሰሙ ጊዜ፣ ከሚወዱት የግብርና ሙያ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሊቆራረጡ እንደሆነ በማሰብ ከመጨነቅ ውጭ ቤተሰባቸውን በምን እንደሚያስተዳድሩ ግራ ገብቷቸው እንደነበር ያስታውሳሉ፡፡ ልጆቼ ፊደል የቆጠሩ መሆናቸው በጀኝ የሚሉት አባወራው፤ በልጆቻቸው ብርታት የተሰጣቸውን የካሣ ገንዘብ፣ ለቤተሰቡ ዋስትና በሚሆን ነገር ላይ ለማዋል እንደቻሉ ይናገራሉ፡፡ ከምወደው የግብርና ሙያ ብለያይም ፈጣሪ ይመስገን ሳልቸገር እኖራለሁ ብለዋል፡፡ እሳቸው የገንዘብ አጠቃቀሙን በማወቃቸው ለችግር ባይጋለጡም ከቅርብ ወዳጆቻቸው መካከል የተሰጣቸውን ገንዘብ ቁም ነገር ላይ ሳያውሉ በመቅረታቸው፣ ዛሬ ለከፋ ችግር የተጋለጡ እንዳሉ ይናገራሉ፡፡ አንድ ወዳጃቸው፣ መኖሪያ ቤት ገላን ከተማ ውስጥ ከገዙ በኋላ በቀሪው ሚኒባስ ታክሲ ቢገዙም፣ ኑሮን ማሸነፍ አቅቷቸው በችግር እየተንገላቱ መሆናቸውን ይጠቅሳሉ፡፡ የተሰጣቸውን ገንዘብ በየመጠጥ ቤቱ አራግፈው፣ የቀን ሰራተኛና በረንዳ አዳሪ የሆኑ በቅርብ የሚያውቋቸው ገበሬዎች እንዳሉም አቶ ደሜ ይናገራሉ፡፡ ሀገር ባደገና በዘመነ ቁጥር ከከተሜነት ጋር መተዋወቅና መለማመድ የግድ ነው የሚሉት ገበሬው፤ ነገር ግን መንግስት የእርሻ መሬትን ለኢንቨስትመንት ሲፈልገው፣ አስቀድሞ የገበሬውን መውደቂያ ሊያጤን ይገባል ይላሉ፡፡ ዝም ብሎ መሬቱ ለልማት ይፈለጋልና የካሳ ክፍያህን ተቀብለህ ተነስ ማለት ለገበሬው ከብርሃን ወደ ጨለማ የመጓዝ ያህል ነው የሚሉት አባወራው፤ መንግስት አስቀድሞ የስራ ፈጠራና የኑሮ ዘይቤዎችን የሚያመላክቱ ስልጠናዎችን መስጠትና ሁኔታውንም እስከመጨረሻው መከታተል አለበት ሲሉ በአፅንኦት ተናግረዋል፡፡ የኢንዱስትሪ መስፋፋት ገበሬውን ከይዞታው አያፈናቅልም፣ የእርሻ መሬቱንም አይነጠቅም የሚለው የመንግስት መከራከሪያ ተቀባይነት የለውም ያሉት አንድ የህግ ባለሙያ፤ ቤተሰቦቻቸው በኢንዱስትሪ መስፋፋት ምክንያት የእርሻ መሬታቸው ሙሉ ለሙሉ ተወስዶባቸው፣ወደ ከተማ መፍለሳቸውን ይናገራሉ - በርካታ የአካባቢው አርሶአደሮች በዚህ መልኩ ከምርት አቅራቢነት ወደ ሸማችነት መሸጋገራቸውን በመጠቆም፡፡ በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ውስጥ የሚገኙት ገላን እና ዱከም በተለይ በጤፍ አብቃይነታቸው የሚታወቁ ሲሆን ስንዴ፣ ሽምብራ፣ ጓያና ምስር የአካባቢው ገበሬዎች የሚታወቁባቸው ምርቶች እንደሆኑ የአካባቢው ተወላጅ የሆኑት የህግ ባለሙያው ይናገራሉ፡፡ አዲስ አበባና የዙሪያዋ ፊንፊኔ ልዩ ዞን ማስተር ፕላንን አስመልክቶ ለውይይት በቀረበው ሰነድ ላይም፣ በአጠቃላይ በልዩ ዞን ከ1.3 ሚሊዮን በላይ አርሶ አደሮች እንዳሉ መጠቀሱን አውስተዋል፡፡ የእነዚህ አርሶ አደሮች ምርት ዋነኛ የገበያ መዳረሻ ደግሞ አዲስ አበባ ነች፡፡ የገላን፣ የዱከም እንዲሁም በአዲስ አበባ አስተዳደር ስር የሚገኙት ገላን ጉራ፣ ቂሊንጦ፣ ኮዬና ፈጨ የሚባሉ የአርሶ አደር አካባቢዎች፣ ቀደም ሲል ለአዲስ አበባ ህዝብ እህል አቅራቢዎች እንደነበሩም ነጋዴዎች ይመሰክራሉ፡፡ በአቃቂና ሳሪስ ገበያ በእህል ነጋዴነታቸው የሚታወቁት አቶ ቶሎሳ ሁንዴ፤ በአቃቂና ገላን ከተሞች መካከል ባለው መንገድ ላይ በሳምንት ሁለት ቀን ማክሰኞ እና ቅዳሜ ሚዛናቸውን ሸክፈው እህል ለመገብየት የሚወጡ ሲሆን ማታ ላይ የሸመቱትን በአይሱዙ ጭነው አቃቂ ወደሚገኘው የእህል መጋዘናቸው ይሄዳሉ፡፡ ማክሰኞ በጅምላ የሸመቱትን ረቡዕ ለሳሪስ ገበያ ሲያቀርቡ፣ ቅዳሜ የሸመቱትን ማክሰኞ ለአቃቂ ገበያ እንደሚያቀርቡም ነጋዴው ይናገራሉ፡፡ አንዳንዴም በተለይ የደሞዝ ወቅት ሆኖ፣ የችርቻሮ ሸማች በርከት ሲል በሰራተኞቻቸው አማካኝነት እንደተፈላጊነቱ እያመላለሱ ይሸጣሉ፡፡ በአሁን ሰአት ግን እንደድሮው ከገበሬው ጤፍ እና ስንዴ እንደልብ ማግኘት አልተቻለም የሚሉት ነጋዴው፤በተለይ በክረምት ወቅት ገበሬዎቹ ራሳቸው ሸማቾች እንደሚሆኑ ይገልፃሉ፡፡ እህል ትሸምታላችሁ ሲባሉም “መሬታችን ተወስዶ በማለቁ ነው” የሚል መልስ እንደሚሰጡ ነጋዴው ተናግረዋል፡፡ የአካባቢው አርሶ አደር እንደ ነጋዴ እህል ቸርችሮ መሸጥን እምብዛም አለመደውም የሚሉት አቶ ቶሎሳ፤ አንዳንዶች ለእርሻ መሬታቸው ግምት ተሰጥቷቸው የግብርና ስራቸውን ካቆሙ በኋላ፣ ነጋዴ ለመሆን ይሞክሩና የስራውን ፀባይ ባለማወቅ ለኪሳራ ተዳርገው፣ ራሳቸውንም ቤተሰባቸውንም ለችግር ያጋልጣሉ ብለዋል፡፡ በርካታ ወዳጆቼን መጥቀስ እችላለሁ የሚሉት ነጋዴው፤ አንዳንድ አርሶ አደር አንዱ ያደረገው ለኔም አይቅርብኝ በሚል ገንዘቡን ዘላቂ ባልሆነ ጉዳይ ላይ አውሎ ባዶ እጁን ይቀራል በማለትም የአንድ ወዳጃቸውን ተመክሮ ይጠቅሳሉ፡፡ “የእርሻ መሬቱ ለልማት ተፈልጎ በመንግስት ሲወሰድ ወደ 750 ሺህ ብር ገደማ ካሳ ተከፈለው፤ ግማሹን መኖሪያ ቤት ሰራበትና ግማሹን ሚኒባስ ታክሲ ገዛበት፡፡ ለቤተሰቡ መተዳደርያ ተብላ የተገዛችው አሮጌ ሚኒባስ ግን የተገዛችበትን ዋጋ ሩብ ያህል እንኳ ሳትመልስ በዘጠኝ ወሯ ከአገልግሎት ውጪ ሆነች፡፡ ወዳጄ በመጦርያ እድሜው አካባቢው በሚገኝ አንድ የጠጠር ማምረቻ ድርጅት ውስጥ በጥበቃነት ተቀጥሮ በሚያገኛት 650 ብር ወርሃዊ ደሞዝ ቤተሰቡን ለማስተዳደር ቢታትርም የኑሮ ውድነቱን መቋቋም አልቻለም፡፡ ይሄኔ የቀረችውን ጥቂት ጥሪት አሟጦ፣ ሁለት ሴት ልጆቹን ከትምህርት ገበታቸው ላይ በማፈናቀል፣ ወደ አረብ ሃገር ሰደዳቸው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በአርሶ አደር አካባቢነታቸው የሚታወቁት ገላን ጉራ፣ ኮዬ፣ ፈጨ እና ቂሊንጦ የተባሉ አካባቢዎች ለጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ ለዩኒቨርሲቲና ለቢራ ፋብሪካ ግንባታዎች እንዲሁም ለተለያዩ የኢንዱስትሪ ልማቶች ይፈለጋሉ በሚል በርካታ አርሶ አደሮች ከእርሻ መሬታቸውና ከመኖሪያ አካባቢያቸው መፈናቀላቸውን ምንጮች ይናገራሉ፡፡ ሪፖርተሮቻችን በአካባቢው ተገኝተው እንደታዘቡት፣ በተለይ ለኮንዶሚኒየም እና ለቢራ ፋብሪካ ግንባታ ቁጥራቸው ከ50 የሚልቅ አርሶ አደሮች ከቀዬአቸው ተነስተው እዚያው አካባቢ በተሰጣቸው ተለዋጭ መሬት ሰፈረዋል፡፡ አብዛኞቹ ቦታዎችም የቤት እና የዩኒቨርሲቲ ግንባታ እየተከናወኑባቸው ነው፡፡ በርካታ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችም እየተካሄዱ ነው፡፡ በቅርቡ ከንቲባ ኩማ ድሪባ፤ ለ3 መቶ ሺህ ነዋሪዎች የሚሆን የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ በአካባቢው ላይ መጀመሩን መግለፃቸው የሚታወስ ሲሆን የአርሶ አደር አካባቢ የነበረው ሥፍራንም ወደፊት ዘመናዊ ከተማ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡ ካነጋገርናቸው የአካባቢው አርሶ አደሮች ስሜ አይጠቀስ ያሉን የ65 ዓመቱ አዛውንት፤ ከሁለት ዓመት በፊት ወደ 8 ሄክታር የእርሻ መሬታቸው ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ በሚል መወሰዱን ይናገራሉ፡፡ በወቅቱ ከወረዳው እና ከከተማ አስተዳደሩ የመጡ አመራሮች፤ የእርሻ መሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ሊሰጣቸው መሆኑን በመግለፅ በካሬ ሜትር መለካት እንደጀመሩ፣ ገበሬውም የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ይሰጠኛል በሚል ተስፋ ተባባሪ እንደሆነ አስታውሰው፤ ኋላ ላይ ግን ቦታው ለልማት ስለሚፈለግ ለመኖሪያ ቤታችሁ ምትክ ቦታና ግምት ይሰጣችኋል፤ ለእርሻ መሬታችሁም ከመሬቱ ላይ የሚገኘው የ10 ዓመት አላባ (ትርፍ) ተሰልቶ ካሳ ይከፈላችኋል እንደተባሉ ይገልፃሉ፡፡ ገበሬው ምንም አይነት ስነልቦናዊ ዝግጅት ሳያደርግ መተዳደሪያ መሬቱ እንደተወሰደበት የሚጠቅሱት አዛውንቱ ገበሬ፤ ለእርሻ መሬት በካ.ሜ 18ብር ከ50 ሳንቲም ተሰልቶ ክፍያ ሲፈፀም የመኖሪያ ቦታ ግምት 9 ብር ከ25 ሣንቲም ተሠልቶ ክፍያ መፈፀሙን ያስታውሣሉ፡፡ “ለእርሻ መሬቱ የ10 አመት አላባ ተሠልቶ ይከፈላችኋል የተባለው ግን እንዴት እንደተሰላ አላውቅም” የሚሉት ገበሬው፤ የእርሻ መሬት ካሣ፣ የመኖሪያ ቦታና ቤት ግምት እንዲሁም፣ የመፈናቀያ ካሣን ጨምሮ ከግማሽ ሚሊዮን እስከ 2 ሚሊዮን ብር ለእያንዳንዱ አርሶ አደር እንደተከፈለ ይጠቁማሉ፡፡ አብዛኛው አርሶ አደር በተሰጠው ምትክ ቦታ ላይ በተለምዶ አሞራ ክንፍ የሚባለውን የጭቃ ቤት እንደገነባና በተረፈው ገንዘብ ለወደፊት የኑሮ ዋስትና ይሆነኛል ያለውን ንብረት እንደገዛበት የጠቆሙት አዛውንቱ፤ ነቃ ያለው በከተማ የመኖሪያ ቤት ገዝቶ በማከራየት ኑሮውን ሲደጉም፣ ግንዛቤ የሌለው ደግሞ ስለተሽከርካሪ ምንነት በሚገባ ሳይረዳ ተሽከርካሪ በመግዛት፣ አጠቃቀሙን ባለማወቅ ለኪሣራ እየተዳረገ መሆኑን ይገልፃሉ፡፡ አንድም ገበሬ ከመኖሪያው የተፈናቀለ የለም የሚለው የመንግስት ባለስልጣናትን መግለጫ እንደማይቀበሉት የተናገሩት አዛውንቱ፤ ሩቅ ሳይሄዱ እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ የገበሬ አካባቢዎች ተዘዋውረው ቢመለከቱ፣ እውነታውን ይረዳሉ ብለዋል፡፡ አሁን በተሰጠን የመኖሪያ ቦታም ቢሆን ተረጋግተን ለመኖራችን ዋስትና የለንም የሚሉት እኚሁ አስተያየት ሰጪ፤ “ዙሪያውን ባለ ፎቅ መኖሪያ ቤቶች ተገንብተው፣ እኛ የጭቃ ቤታችንን ይዘን ማንም የሚያስቀምጠን የለም፤ ወደፊት ተነሺ ናችሁ የሚባሉ ወሬም እየተናፈሰ ነው” ይላሉ፡፡ አቶ ኤርሚያስ ሙሉጌታ በሙያቸው የማህበረሰብ ሰራተኛ (Social Worker) ናቸው፡፡ ላለፉት ሰባት ዓመታት በሙያው ማገልገላቸውን ይናገራሉ፡፡ አንድ ሰው ወይም ማህበረሰብ ከነበረበት አካባቢ ባህልና የአኗኗር ዘይቤ ሲፈናቀል ሊደርስበት ስለሚችለው ችግር ሲያስረዱ፡፡ “አንድ ማህበረሰብ ወይም ግለሰብ በምንም መልኩ ከኖረበት ባህል ወግና አካባቢ ባይለይ ጥሩ ነው፤ ግድ ሆኖ መልቀቅ ካለበት ግን ሊሟሉ የሚገቡ ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት አለባቸው” ብለዋል፡፡ አንዱና የመጀመሪያው ጉዳይ የስነ-ልቦና ዝግጅት እንደሆነ ጠቅሰው፤ ሁለተኛ ደግሞ በጉዳዩ ዙሪያ ወደፊት ስለሚያጋጥሙ ሁኔታዎች እና መሰል ጉዳዮች በቂ ግንዛቤ መፍጠር እንደሆነ ባለሙያው ይናገራሉ፡፡ ከትውልድ ቀዬ፣ ከለመዱት ሙያና የአኗኗር ዘይቤ መፈናቀልም ለከፍተኛ ምስቅልቅል እንደሚዳርግ የተናገሩት ባለሙያው፤ አንድ አርሶ አደርን ገንዘብ ሰጥተነው “ሂድ ነግድ” ብንለው አሊያም በንግድ ሥራ ጥርሱን የነቀለ አንድን ነጋዴ፣ ጥሩ ጥሩ በሬዎች አዘጋጅተን ሞፈርና ቀንበር አቀናጅተን “ሂድ እረስ” ብንለው የማይሆን ነገር ነው ይላሉ፤ አቶ ኤርሚያስ፡፡ “ይህ ማለት ግን ነጋዴውም ገበሬ፣ ገበሬውም ነጋዴ መሆን አይችሉም ማለት አይደለም” የሚሉት ባለሙያው፣ ነጋዴውን ጥሬ ገበሬ ለማድረግ የስነ ልቦና ዝግጅት፣ የሙያ ስልጠናና ምክር እንዲሁም በዘርፉ የሰለጠነ አማካሪና በቂ ጊዜ መስጠት እንደሚያስፈልግ ገልፀው፤ ገበሬውንም ጥሩ ነጋዴ ለማድረግ ተመሳሳይ ጉዳዮችን ማሟላት እንደሚስፈልግ ይናገራሉ፡፡ በዚህ በኩል የሚመለከተው አካል በተለይ መንግስት በጉዳዩ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ለተፈናቃዮች የስነ-ልቦና ዝግጅት ስልጠናና የምክር አገልግሎት እንዲያገኙ ካላደረገ፣ መዘዙ ለራሱ ለመንግስት በመሆኑ ጥንቃቄ ያስፈልጋል ሲሉ አስተያየታቸውን ቋጭተዋል፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በፊት የአዲስ አበባና ፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ማስተር ፕላንን የተቃወመው የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ፓርቲ አመራር አቶ ገብሩ ገብረማርያም፤ ኦሮሚያ ውስጥ ገበሬዎች እየተፈናቀሉ፣ በአጠቃላይ በሚሊዮን የሚቆጠር ሄክታር መሬት ለተለያዩ ፕሮጀክቶች እንደተሰጠ እናውቃለን ብለዋል፡፡ አብዛኛውም ለአበባ እርሻ ልማትና ለኢንዱስትሪ ዞን እየዋለ ነው ያሉት አመራሩ፤ በተለይ በዱከምና ቢሾፍቱ አካባቢ መንግስት ቁጥሩ በውል የማይታወቅ ገበሬ አፈናቅሎ፣ መሬት ለባለሀብት ሠጥቷል ብለዋል፡፡ ገበሬው ብዙ ቤተሰብ የማፍራት ልማድ እንዳለው የጠቀሱት አቶ ገብሩ፤ በመፈናቀሉ ራሱን ብቻ ሳይሆን ቤተሰቡም ተጐጂ ነው ይላሉ፡፡ ገበሬው ከመሬቱ እንዲለቅ ሲደረግም ተገቢው ካሣ ተሰጥቶት እንዳልሆነም ከተለያዩ አካባቢዎች የሚቀርቡ ቅሬታዎችን መነሻ አድርገው አቶ ገብሩ ይናገራሉ፡፡ ይህ በሆነበት ሁኔታ ህዝብ በሚገባ ሳይመከርበት በድንገት አዲስ ፕላን አውጥቶ ለመተግበር መሯሯጡ ቀውስ ማስከተሉ አይቀርም ብለዋል፡፡ በኦሮሚያ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች አዲሱን ማስተር ፕላን አስመልክቶ የተነሣውን ተቃውሞ ተከትሎ በማረጋጋት ስራ ላይ ከተጠመዱ የፌደራል መንግስት ባለስልጣናት መካከል አንዱ የሆኑት አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ፤ የጋራ ማስተር ፕላኑ አርሶ አደሩን ያፈናቅላል የተባለው አሉባልታ እንደሆነ ገልፀው፤ እቅዱ የአንድም አርሶ አደር መሬት እንደማይነካ ተናግረዋል፡፡

መድረክ በግጭቱ ከ45 በላይ ሰዎች ሞተዋል አለ

May 11/2014
ሰሞኑን ከጋራ ማስተር ፕላኑ ጋር በተገናኘ በተነሣው ሁከት በዩኒቨርሲቲዎች እና በኦሮሚያ ከተሞች የፀጥታ ሃይሎች በወሰዱት እርምጃ በአጠቃላይ ከ45 ሰዎች በላይ መሞታቸውንና በርካቶች መቁሰላቸውን እንዲሁም በመቶዎች የሚቆጠሩ መታሠራቸውን ምንጮች አረጋግጠውልኛል ሲል መድረክ አስታወቀ፡፡ በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት ሃዘኑን የገለፀው መድረክ፤ ክስተቱ ገዥው ፓርቲ ለጉዳዩ ወቅታዊ እና ህገ - መንግስታዊ መፍትሔ ለመስጠት ባለመቻሉ የተፈጠረ መሆኑን ጠቁሞ፤ ይሄም ኢህአዴግ ሀገሪቱን እየመራ ያለው በስሜታዊ የሃይል እርምጃ እንጂ በሠለጠነ አግባብ አለመሆኑን ያመለክታል ብሏል፡፡ የችግሩ መነሻ የጋራ ማስተር ፕላኑ ለየከተማዎቹ ነዋሪዎች ቀርቦ ግልፅ ውይይት ባለመካሄዱ የተፈጠረ የአረዳድ እና የትርጉም መዛባት ነው ያለው ፓርቲው፤ በቀጣይ ችግሩን በአስቸኳይ ለማስወገድና ሠላም እንዲሰፍን መንግስት ሊወስዳቸው የሚገቡ እርምጃዎች ያላቸውን ዘርዝሯል፡፡

የጋራ ልማት ሥራዎች በጋራ ውይይትና መግባባት የዜጐችንና የክልሎችን መብቶችና ጥቅሞች ባከበረ መልኩ እንዲካሄዱ ማድረግ፣ ዜጐች በሚያደርጉት የተቃውሞ ሠልፎች ላይ የሃይል እርምጃ ከመውሰድ መታቀብና ሙሰኛ ባለስልጣናትን በአግባቡ መቆጣጠር እንዲሁም ዜጐች ከመሬታቸው ሲፈናቀሉ፣ ተገቢውን ካሣ መክፈል …የሚሉት ይገኙበታል፡፡ “የብሔር ግጭት በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ የሠላማዊ ተማሪዎችን ህይወት አደጋ ላይ ጥሏል” ያለው ፓርቲው፤ የፀጥታ ሃይሎች ባሉበት ሁኔታ ግድያና ድብደባ መፈፀሙ አሣፋሪ ነው ብሏል፡፡ በድርጊቱ የተሳተፉ ደብዳቢዎችም ለፍርድ እንዲቀርቡ ፓርቲው ጠይቆ፤ የተበተኑ ተማሪዎች ተሰባስበው በሠላማዊ መንገድ ትምህርታቸውን የሚቀጥሉበት ሁኔታ ሊመቻችላቸው ይገባል ብሏል፡፡ ለዜጐች ህይወት መጥፋትና አካል መጉደል መንግስት ሃላፊነት ወስዶ እንዲክሣቸው፣ የታሠሩት ዜጐችም ሆኑ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል በመሆናቸው ብቻ የታሠሩ 35 የኦፌኮ (መድረክ) የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አመራሮች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ፓርቲው ጠይቋል፡፡

በነገው እለት ጥያቄውን በሠላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ አቅዶ የነበረው መድረክ፤ ከእውቅና ሠጪው አካል ጋር በቦታ መረጣ ላይ ባለመግባባቱ፣ የተቃውሞ ሰልፉ ለግንቦት 10 እንደተላለፈ የፓርቲው የስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ጥላሁን እንደሻው ገልፀዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰዎች ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ ተቃውሞን ለመግለፅ የሚደረገውን ሙከራ ያወገዘው ኢዴፓ፤ መንግስት ህግና ስርዓት እንዲከበር የማድረግ ሃላፊነትና ግዴታ ያለበት መሆኑን ጠቅሶ፤ በአመፅ መልክ በሚገለፁ ተቃውሞዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ጥንቃቄ የተሞላበትና በተቻለ መጠን በሰዎች አካልና ህይወት ላይ ጉዳት የማያስከትል መሆን እንደሚገባው ገልጿል፡፡ ፓርቲው በተጨማሪም ስለ ደረሰው የሰው ህይወት ጥፋትና ንብረት ውድመት ተጠያቂው በገለልተኛ አካል እንዲጣራና እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቋል፡፡

የችግሩ ምንጭ፣ ማንነትን መሠረት ያደረገው የፌደራል ስርአቱ ነው ያለው ፓርቲው፤ መፍትሔው የፌደራል አደረጃጀቱና ፖሊሲዎች ለአገር አንድነትና ለጋራ ልማት በሚበጅ መልኩ እንዲሻሻሉ ማድረግ እንደሆነ ጠቁሟል። መንግስት ባለፈው ሣምንት ባወጣው መግለጫ፤ በሁከቱ በድምሩ 11 ሰዎች መሞታቸውንና በርካቶች ቆስለው፣ ንብረትም እንደወደመ ማስታወቁ ይታወሳል። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ ታሳሪያዎቹን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ እስረኞቹ በምርመራ ወቅት ከህግ አግባብ ውጪ ድብደባና ስቃይ እየተፈፀመባቸው መሆኑ እንዲሁም ጉዳዩን አስመልክቶ ከመንግስት ይፋዊ መግለጫ አለመሰጠቱ እና ባለስልጣናት እርስ በእርሱ የሚጋጭ ምላሽ እየሰጡ መሆናቸው ያሳስበኛል ብሏል፡፡ ስለ ጋዜጠኞቹ እና ብሎገረቹ መንግስት የጠራ መረጃ እንዲሰጥ የጠየቀው ማህበሩ በእስር ቤት ያለው የአያያዝ ሁኔታም በእጅጉ እንደሚያሳስበው ገልጿል፡፡

የኦሕዴድ ከፍተኛ አመራሮች በማስተር ፕላኑ የተነሳውን ተቃውሞ ለማርገብ ተጠምደዋል

May 11/2014

የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ከፍተኛ አመራሮች በኦሮሞ ተወላጅ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተቀስቅሶ የተስፋፋውን ተቋውሞ ለማርገብ ያለፈውን ሳምንት በሥራ ተጠምደው አሳልፈዋል፡፡

የአዲስ አበባና የዙሪያዋ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን ለሕዝብ ውይይት ይፋ መሆኑን ተከትሎ ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ የኦሮሞ ተወላጆች የቀሰቀሱት ተቃውሞ፣ በተለይ በአምቦ ከተማና አካባቢው ተዛምቶ ሕይወት ማለፉና ንብረት መውደሙ ይታወሳል፡፡

በአሁኑ ወቅት ተቃውሞው የቀዘቀዘ ቢሆንም፣ በዩኒቨርሲቲዎቹ ሙሉ በሙሉ ትምህርት ማስቀጠል አለመቻሉን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ለመረዳት ተችሏል፡፡ በተለይ ችግሩ በተከሰተባቸው የአምቦና አካባቢው እንዲሁም በባሌና በወለጋ አካባቢ ከፍተኛ የኦሕዴድ አመራሮች የአካባቢውን የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ሰብስበው ሲያነጋገሩ ሰንብተዋል፡፡ ከፍተኛ ግጭትና ተቃውሞ በተስተዋለበት የአምቦ ከተማና አካባቢው በመገኘት ኅብረተሰቡን ለማወያየት የተጓዙት የኦሕዴድ ምክትል ሊቀመንበር ወ/ሮ አስቴር ማሞ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔና የኦሕዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ አባዱላ ገመዳ ናቸው፡፡

የኦሕዴድ መካከለኛ አመራር የሆኑ የዞን አመራሮች ደግሞ በሰበታ፣ በሆለታ፣ በቡራዩና በተለያዩ አካባቢዎች ተመሳሳይ ውይይቶችን ከኅብረተሰቡ ጋር ተገናኝተው ሲያካሂዱ ሰንብተዋል፡፡

በሁሉም ውይይቶች ላይ እየተነሳ ያለው ማስተር ፕላኑ በጭራሽ የኦሮሚያ ክልልን መሬት ቆርሶ ለአዲስ አበባ እንደማይሰጥ፣ ዓላማው በአዲስ አበባና በአካባቢዋ በሚገኙ የኦሮሚያ ከተሞች መካከል ተመጋጋቢ ልማትን ማምጣት የሚቻል መሆኑን የሚያስገነዝብ ቢሆንም፣ በይበልጥ ግን ትኩረት እየተሰጠ ያለው ብጥብጡን ያነሱት በኢትዮጵያ ውስጥ ሰላምን ማየት የማይፈልጉ ወገኖች ስለመሆናቸው የሚገልጽ እንደሆነ ሪፖርተር ያነጋገራቸው አንዳንድ የስብሰባው ተካፋዮች ገልጸዋል፡፡

በአምቦ፣ በጉደርና በአካባቢው የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ያነጋገሩት አፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳ ይህንኑ አስተሳሰብ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሲያንፀባርቁ ተስተውለዋል፡፡ በውጭ ኃይሎች የተጠመዘዘ ተቃውሞ መሆኑን የተናገሩት አቶ አባዱላ፣ የኦሮሞ ተወላጅ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም ሆኑ ነዋሪዎች በጉዳዩ ላይ ማንኛውንም ጥያቄ የማንሳትና ምላሽ የማግኘት መብት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

ማስተር ፕላኑ በሕዝብ ተቀባይነት ማግኘት ካልቻለ ተግባራዊ እንደማይደረግ ፍንጭ የሰጡት አቶ አባዱላ፣ ‹‹በሕዝብ ተቀባይነት ያላገኘ ጉዳይን አንፈጽምም፡፡ ይህንን ሕዝቡም ሆነ ኦሕዴድ ያውቁታል፡፡ ኦሕዴድ የሚመራው መንግሥትም ያውቀዋል፤›› ብለዋል፡፡

ባለፈው ሐሙስ ዕለት የአዲስ አበባ ጂቡቲ የባቡር መስመር ግንባታ የሐዲድ ዝርጋታን ለማስጀመር በድሬደዋ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝም፣ አጋጣሚውን በመጠቀም ከድሬዳዋ የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ጋር መክረዋል፡፡

ከኦሕዴድ አመራሮች ጋር ተመሳሳይ የሆነ ምክንያት ያስቀመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም፣ ‹‹አገሪቱን የመገነጣጠል ፍላጎት ያላቸው ወገኖች የቀሰቀሱት ብጥብጥ ነው፤›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

በማስተር ፕላኑ የተደናገሩ መኖራቸውን በመገንዘብ ‹‹ይችን አጋጣሚ እንጠቀም›› ያሉ የውጭ ኃይሎች ብጥብጡንና ተቃውሞውን እንደቀሰቀሱ አስረድተዋል፡፡

‹‹ተማሪዎችን በሚገባ እናስረዳለን፣ የጠላትን ሴል አንድ በአንድ ለይተን መልክ እናስይዛለን፤›› ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም አስታውቀዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልልና የፌዴራል መንግሥት ባደረጉት ጥረት በተለያዩ አካባቢዎች የተነሱት ብጥብጦች መርገባቸውን አንድ የኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣን ለሪፖርተር ገልጸው፣ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችና ከተማሪዎች ጋር በስፋት ውይይት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡ ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ሒደትም እንደሚጀምር አስታውቀዋል፡፡

በሁከቱ ምክንያት በሰው ሕይወት ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ የሚታወስ ሲሆን፣ መንግሥት 11 ሰዎች መሞታቸውን መግለጹ አይዘነጋም፡፡

ጠበቆች የታሰሩ ጋዜጠኞችንና ጦማሪያንን የማያገኙ ከሆነ ጥብቅና አንቆምም አሉ

May 11/2014
ሰበር ዜና፡- ፍርድ ቤቱ በተጠረጠሩት ጋዜጠኞችና ጦማሪያን ላይ የ10 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ፈቀደ
-ሁለት ጦማሪያን መደብደባቸውን ለፍርድ ቤት አስታወቁ
‹‹ግብረ አበሮቻቸውን መያዝና የምስክሮች ቃል መቀበል ይቀረናል›› የፌዴራል ፖሊስ መርማሪ ቡድን
‹‹ችሎቱ ጠባብ ስለሆነ እንጂ ጉዳዩ የሚታየው በግልጽ ችሎት ነው›› ፍርድ ቤት
በህቡዕ ተደራጅተው በአገር ውስጥና በውጭ አገር ካሉ አሸባሪዎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ ኅብረተሰቡንና መንግሥትን ለማተራመስ ሲንቀሳቀሱ ተገኝተዋል በሚል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞችና ጦማሪያን ጠበቆች፣
ተጠርጣሪዎቹን ማግኘትና ማነጋገር ካልቻሉ፣ ሁኔታውን ለፍርድ ቤት አስረድተው ጥብቅና መቆማቸውን እንደሚያቋርጡ ተናገሩ፡፡

ጠበቆቹ ጋዜጠኞቹና ጦማሪያኑ በቁጥጥር ሥር ከዋሉበት ከሚያዝያ 17 እና 18 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ፍርድ ቤት እስከቀረቡበት እስከ ሚያዝያ 29 ቀን 2006 ዓ.ም. ድረስ፣ ከቤተሰብም ሆነ ከሕግ አማካሪዎቻቸው ጋር አለመገናኘታቸውን ገልጸው ለፍርድ ቤት ጠበቆቹ በማመልከታቸው፣ በሦስት የምርመራ መዝገብ ተከፋፍለው ሚያዝያ 29 እና 30 ቀን 2006 ዓ.ም. በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ሲቀርቡ ፍርድ ቤት በቤተሰብና በሕግ አማካሪዎቻቸው እንዲጎበኙ አዞ እንደነበር ገልጸዋል፡፡

የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ተከትለው ግንቦት 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ጠበቆቹ አቶ አመሐ መኮንንና ዶ/ር ያሬድ ለገሰ በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማዕከል (ማዕከላዊ) ማልደው የተገኙ ቢሆንም፣ ‹‹ስብሰባ ላይ ስለሆንን በዚህ ሳምንት አናገናኝም፤›› በመባላቸው ሳያገኟቸው እንደተመለሱ ጠቁመዋል፡፡

በመሆኑም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ የማይከበርና ተጠርጣሪዎቹን ካላገኟቸው፣ ለመጨረሻ ጊዜ ግንቦት 6 ቀን 2006 ዓ.ም. ሄደው፣ የማያገናኟቸው ከሆነ፣ ሕገወጥ ሥራን መተባበር ስለሚሆን ለፍርድ ቤቱ አስታውቀው ጥብቅናቸውን እንደሚያቆሙ ተናግረዋል፡፡

ጋዜጠኞቹና ጦማሪያኑ ሚያዝያ 29 እና 30 ቀን 2006 ዓ.ም. ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ ሚያዝያ 29 ቀን የቀረቡት ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ፣ ጋዜጠኛ ኤዶም ካሣዬ፣ ጋዜጠኛ አስማማው ኃይለጊዮርጊስ፣ ጦማሪያን ናትናኤል ፈለቀ፣ ጦማሪያን አጥናፉ ብርሃኔ፣ ጦማሪያንና መምህር ዘለዓለም ክብረት ናቸው፡፡

ስድስቱም ተጠርጣሪዎች በአራዳ ምድብ ችሎት ቅጥር ግቢ ተሰብስበው ሲጠብቋቸው በነበሩት ቤተሰቦች፣ ጓደኞች፣ ዲፕሎማቶችና ጋዜጠኞች አጠገብ ሲያልፉ፣ ከኤዶም በስተቀር አምስቱም እጃቸው በካቴና ታስረውና ወደ መሬት እያዩ ስለነበሩ አንዳቸውም ማንንም ቀና ብለው አላዩም፡፡ ጋዜጠኞችና ከተለያዩ ኤምባሲዎች የተገኙ ዲፕሎማቶች ወደ ችሎት ለመግባት ሲጠጉ፣ አንድ የፍርድ ቤት ተላላኪ ‹‹ችሎቱ ጉዳዩን የሚያየው በዝግ ነው›› ሲል አጃቢ ፖሊሶችና የፌዴራል ፖሊስ አባላት በመከልከላቸው፣ ተጠርጣሪዎቹ የተናገሩትን ወይም መርማሪው ቡድን ያቀረበባቸውን የጥርጣሬ ክስ መስማት አልተቻለም፡፡

ፍርድ ቤቱ የመርማሪ ቡድኑንና የተጠርጣሪዎቹን ጠበቆች ክርክር ከጨረሰ በኋላ ፖሊስ የጠየቀባቸውን ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ፈቅዶ ሲጨርስ፣ በዕለቱ በችሎት ተገኝተው የነበሩት ጠበቃ አመሐ መኮንን ከችሎቱ ሲወጡ በቤተሰቦች፣ በጋዜጠኞች፣ በዲፕሎማቶችና በሌሎች ታዳሚዎች ተከበቡ፡፡ ‹‹ምን ተባሉ?›› ለሚለው የሁሉም ጥያቄ ማብራራት የጀመሩት ጠበቃ አመሐ፣ ‹‹እኛ ተጠርጣሪዎቹን አግኝተን ማነጋገር ባለመቻላችን፣ መከራከር አልቻልንም፡፡ አንዳንድ መከራከሪያ ሐሳብም የወሰድነው በደንብ ተደራጅቶና ተዘጋጅቶ የመጣው መርማሪ ፖሊስ ካቀረበው የምርመራ ውጤት ላይ ተነስተን ነው፤›› ካሉ በኋላ፣ መርማሪ ፖሊሱ ያቀረበውን የምርመራ ውጤትና የሚቀረውን አብራርተዋል፡፡

መርማሪ ፖሊሱ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ስላገኘው የምርመራ ውጤት ለፍርድ ቤቱ ያስረዳውን ነጥብ የገለጹት አቶ አመሐ፣ የ2007 አገራዊ ምርጫ ከመድረሱ በፊት ኅብረተሰቡን አነሳስተው በመንግሥት ላይ አመፅ ለመቀስቀስ፣ በህቡዕ ተደራጅተው በአገር ውስጥና በውጭ አገር ካሉ አሸባሪዎች ጋር ግንኙነት መፍጠራቸውን፣ ሥልጠና መውሰዳቸውንና ሌሎችን ለማሠልጠን ሲንቀሳቀሱ እንደተደረሰባቸው ማስረዳቱን ገልጸዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ሌሎችን ለማሠልጠንና ለመምራት ገንዘብ በመቀበል የመገናኛ መሣሪያዎችን፣ ላፕቶፖች፣ ኮምፒዩተሮችና ሌሎች ቁሳቁሶችን መግዛታቸውንም መርማሪው ማስረዳቱን አቶ አመሐ አክለዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በኬንያና በተለያዩ የአውሮፓ አገሮች ሄደው ሥልጠና መውሰዳቸውንና እነሱም ሌሎችን ለማሠልጠን እየተንቀሳቀሱ እንደነበርም መርማሪው ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ማስረዳቱን አቶ አመሐ ገልጸዋል፡፡

መርማሪ ፖሊስ ያልተያዙ ግብረ አብሮቻቸውን መያዝ እንደሚቀረው፣ የምስክሮች ቃል አለመቀበሉን፣ የያዛቸውን የተለያዩ ሰነዶች ለይቶ ማስተርጎምና  የቴክኒክ ምርመራም እንደሚቀረው በመግለጽ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን መጠየቁን ጠበቃው አስረድተዋል፡፡

በተጠርጣሪዎቹ የተገለጸላቸው ነገር ባይኖርም ከመርማሪ ፖሊሱ ሐሳብ በመነሳት፣ ጠበቃ አመሐና ጠበቃ ዶ/ር ያሬድ ባቀረቡት መቃወሚያ፣ የተጠርጣሪዎቹን ግብረ አበሮች ለመያዝ እነሱን ማሰር እንደማያስፈልግ፣ ምክንያቱም የሚያዙ ግብረ አበሮች ስላሉ በዋስ ቢለቀቁ ያስጠፉብናል ከተባለ እስካሁን ሊኖሩ እንደማይችሉ፣ ፖሊስ ሰነዶቹንም ስለወሰደና  በግሉ ሊያስተረጉም ስለሚችል ተጠርጣሪዎቹን ማሰር አስፈላጊ አለመሆኑን፣ ተጨማሪ የሚፈልገው ማስረጃ ካለም መጀመሪያውኑ ምርመራውን አጠናቆ መያዝ ይገባው እንደነበር በማስረዳት፣ ተጠርጣሪዎቹ በዋስ እንዲለቀቁ ማመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የተጠርጣሪዎቹ የዋስትና ጥያቄ የሚታለፍ ከሆነ ላለፉት 12 ቀናት የሕግ አማካሪዎችም ሆኑ ቤተሰቦቻቸው እንዳይጠይቋቸው መከልከል ሕገ መንግሥቱን መጣስ በመሆኑ፣ ተጠርጣሪዎቹ መጎብኘት እንዲችሉ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥ መጠየቃቸውን አክለዋል፡፡

ሚያዝያ 30 ቀን 2006 ዓ.ም. ፍርድ ቤት የቀረቡት ጦማሪያን በፍቃዱ ኃይሉ፣ አቤል ዋበላና ማሕሌት ፋንታሁን ናቸው፡፡ መርማሪ ፖሊስ በሌሎቹ ተጠርጣሪዎች ላይ ያቀረበው የምርመራ ውጤትና የሚቀረው የምርመራ ሒደት አንድ ዓይነት መሆኑን የገለጹት ጠበቃ አመሐ፣ ለየት ያለ ነገር የቀረበው ጦማሪያን ፍቃዱና አቤል በምርመራ ወቅት መገረፋቸውን ለፍርድ ቤት ማስረዳታቸው ነው፡፡ መርማሪዎች እንደገረፏቸው ያስረዱ ሲሆን፣ መርማሪ ፖሊስ ግን ተጠርጣሪዎቹ ያሉት ነገር ሊሆን እንደማይችል ተከራክሮ ሐሰት መሆኑን ለፍርድ ቤት በማስረዳት ድርጊቱን ማስተባበሉን ገልጸዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ድርጊቱ ተፈጽሞ ከሆነ አግባብ አለመሆኑን በመግለጽ፣ በሕግ ባለሙያዎችና በቤተሰቦቻቸው የመጎብኘት መብት እንዳላቸው በመግለጽ ማስጠንቀቁንና ትዕዛዝ መስጠቱን አስረድተዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ ሌላው ያነሳው የተጠርጣሪዎቹ ጉዳይ በግልጽ ችሎት እየታየ መሆኑን ሲሆን፣ የተከለከለው በዝግ ለማየት ሳይሆን ቦታው ጠባብ በመሆኑ እንደሆነ አስረድቶ፣ ሚያዝያ 30 የቀረቡት ተጠርጣሪዎች የቅርብ ቤተሰባቸውን ተናግረው እንዲያስገቡ ተጠይቀው፣ እንዲገቡ ማድረጋቸውን ጠበቃ አመሐ ገልጸዋል፡፡ ዲፕሎማቶችና ጋዜጠኞች ግን አልገቡም፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ወደ ችሎት ሲገቡ በፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ የነበሩ ታዳሚዎች ጩኸት በማሰማታቸው በሚቀጥለው ቀጠሮ ይህ የሚደገም ከሆነ፣ ፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ እንዳይገቡ እንደሚከለከል ፍርድ ቤቱ አስታውቋል፡፡

በተጠርጣሪዎቹ ላይ ፖሊስ የጠየቀው ጊዜ ተፈቅዶለት ለግንቦት 9 ቀን 2006 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Saturday, May 10, 2014

ብአዴን ማን ነው?

May 9/2014
[ጭንጋፍ ወይስ ልጅ? ምስክርነት!]
andm12


የአንድን ድርጅት ማንነቱን ከማቅረብ በፊት ቀደም ብሎ የተፈጸመውን ስህተት፣ ቀጥሎም ኢህአፓን ለማጥፋት በህወሓት እና በሻእቢያ የደረሰበትን ጥቃት አጠር ባለ መልኩ ማቅረብ አስፈላጊ ይሆናል።
የስትራተጂ ስህተት ለከባድ ወድቀት ይዳርጋል
ኢህአፓ ትግሉን የጀመረው ገና በ1960 መጀመሪያ ነበር። አብዮቱ እየተቀጣጠለ ሃገር አቀፍ ሆነ። ዘውዳዊ ስርዓት ወድቆ በማርክሲዝም ሌኒኒዝም ርእዮተ ዓለም የሚመራ ሶሻሊዝም የኢትዮጵያ ስርአት እንዲሆን ነበር። ይህ ግራ አክራሪ ስታሊኒዝም በቀ. ኃ. ሥ. ዩኒቨርሲቲ ይማሩ በነበሩ የተሰባሰበ ቡድን፣ የወቅቱ አብዮተኞች ተገቢውን መልክ የያዘ አደረጃጀት ያልነበረው፣ አብዮተኛ የሚል ስም በማግኘታቸው ብቻ “ዲሞክራሲያ” ተብሎ የሚታወቀውን የኢህአፓ ልሳን በየሳምንቱ በመበተን አሁን ኢትዮጵያ የደረሰባትና እየደረሰባት ያለው ከባድ ችግር የከፈተው እነ ዋለልኝ መኮንን እና የኢህአፓ ግብረአበሮቹ የስታሊን ደቀ መዛሙርት ኢትዮጵያን አደጋ ወስጥ ጣሏት። በዚህ ወቅት ሰፊውን ትኩረት የሰጡት፤
  1. በኤርትራ ጥቅያቄ ላይ ኢህአፓ ያለው አቋም ኤርትራ ከዚህ ቅኝ አገዛዝ ነፃ በመሆን ተገንጥላ ነፃ መንግሥት ማቋቋም ሙሉ መብቷ መሆኑን ያምናል፤
  2. ኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰቦች ወህኒ ቤት እንደመሆኗ የኢህአፓ አቋም በዚሁ ጥያቄ ላይ ርቱእና ግልጽ ሲሆን፣ ብሄር ብሄረሰቦች የራሳቸውን እድል በራሳቸው በመወሰን እስከ መገንጠል መብታቸው ያልተገደበ ነው ይላል።
ይህ ትንታኔ ማንም ኢትዮጵያዊ በተጨማሪ ለማረጋገጥ ክፈለገ “ዲሞክራሲያ” ቅጽ 8 ቁጥር 1፣ የካቲት 23 ቀን 1973 የታተመውን ሙሉ ሃሳቡን በድጋሚ ጽፎታል፣ የቃላት ለውጥ በትንሹ ቢኖርበትም። ይህንን ጽሑፍ ለማግኘት EPRP በሚለው ድረገጽ በመግባት የዲሞክራሲያን እትም ከ1961 እስከ ዛሬ የሚለውን ፈልጋችሁ አንብቡ። ይህ ጽሑፍ የሚያሳዝነው ኢህአፓ አሲምባ እንደገባ ታጋዮቹ በፈጠሩት ጫና በሻእቢያ 1ኛ ጉባኤ 1969 መጨረሻ የአቋም ለውጥ በማድረግ ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል ናት፤ የኤርትራ ጥያቄ የዲሞክራሲ ጥያቄ በመሆኑ ትግሉ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ትግል ስለሆነ ኤርትራም የዚሁ አካል እንጂ ቅኝ ተገዢ አይደለችም በማለት በጉባኤው የሰጠው ውሳኔ ቅጥረኛው ህወሓት ታህሳስ 1972 የኢህአፓ ተዋጊ ክንፍ ሰራዊት ከባድ መስዋእትነት ክፍሎ በወያኔ ተደመሰሰ። በውጭ ሃገር የሚኖሩ የኢህአፓ አመራር በየካቲ 1973 በዲሞክራሲያ ልሳን ያወጡት ጽሑፍ የኢህአፓው ተዋጊ ክንፍ ኢህአሠ ታጋይ ለናት ሃገሩ ኢትዮጵያ የከፈለውን መስዋእትነት ውድቅ ለማድረግ የታቀደ ነው፤ ለምን?
ከላይ የተጠቀሱት ሁለት ነጥቦች የኢህፓ አመራር በዲሞክራሲያ ልሳኑ ደጋግሞ በመዘርዘር ጠባቦችና ጸረ ኢትዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት ሃይሎች እንዲፈጠሩ አደረገ።
ጠባብና ዘረኛው ጸረ-ኢትዮጵያ ሉአላዊነት፣ ጸረ-ሕዝብና አንድነት ማገብት – ማህበር ገስገስቲ ብሄረ ትግራይ – ተሓህት የዛሬው ህወሓት ሊፈጠር ቻለ። ይህ የኢህአፓ ርእዮተ ዓለምና አቋም ኢትዮጵያና ሕዝቧን ለዛሬው ክፉ አደጋ ዳርጓት አልፏል።
የሻእብያው የበህር ልጅና በአምሳያው የተፈጠረው ህወሓት አረጋዊ በርሄ በዋና ፈላጭ ቆራጭነት እስክ 1977 መጨረሻ ሲመራው የነበረ ቡድን ተሰብስቦ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የኢትዮጵያን ሕዝብ በጎሳ፣ በቋንቋ እስከ መገንጠል ሃገርና ሕዝብን ለመበታተን ፕሮግራሙን አስተካክሎና ጽፎ በማዘጋጀት ደደቢት በረሃ ወረደ። ተሓህት፤ የዛሬው ህወሓት – ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ – ባረቀቀውና ባዘጋጀው ፕሮግራም እነሆ ዛሬ ኢትዮጵያ አሁን ላለችበት መከራና ችግር፤ ፈርሳ፤ ሕዝብ ተበታትኖ እየተገደለ ለስቃይና መከራ ተዳረገ። ኢትዮጵያን በህወሓት ፋሽስት ስርዓት ደም እያለቀሰች ትገኛለች። የወላድ መሃን። የኢትዮጵያ ሕዝብ ጽኑ ኢትዮጵያዊነቱን ህወሓት በሃይል ነጥቆ በጎሳህ እመን ብሎታል። የኢትዮጵያ ሕዝብ የህወሓትን ዓላማ አንቀበልም፣ በኢትዮጵያዊነታችን እናምናለን በማለት በግለጽ እየተናገረ ይገኛል።
የኢህአፓ አመራር በኢትዮጵያ ፈጥሮት ያለፈው ግዙፍ ስህተቶች በርካታ ስለሆኑ ከላይ የጠቀስኩት መሰረታዊ ስህተት ሆኖ በራሱም ላይ ድክመቶቹ ለጥቃት ሊዳርገው ቻለ። በወቅቱ የተሰባሰቡት አመራር ስለ ኢትዮጵያ ሁኔታ በቅጡ ያልተገነዙቡ ጭፍን በሆነ አመለካከትበማርክሲዝም ሌሊኒኒዝም አብዮተኝነት ደንዝዘው መጥፎውን እና ደጉን ማየት የተሳናቸው ነበሩ። ከስህተታቸው መሃከል ሁለቱን አስፈላጊ ነገሮች እንመልከት።
  1. ማእከላዊ አመራር (central leadership) የዚህ አይነት የአመራር ስርአት ለአንድ ድርጅት ወሳኝ ነው። በወቅቱ ኢህአፓ ሙሉ እንቅስቃሴው በከተማ ውስጥ ስለነበር በምስጢር ቦታ አባላቱን አሰባስቦ በኮንፈረንስ ደረጃ ጊዜያዊ ማእከላዊ  አመራር ለመስጠት ይችሉ ነበር። በዚሁ ጊዜ በአባላቱ የተመረጠው ማእከላዊ ኮሚቴም ተሰብስበው ድርጅቱን በሙሉ ሃላፊነት የሚመሩ ብቃት ያላቸው ሥራ አስፈዳሚ “ፖሊት ቢሮ” ይመርጣሉ። ከነዚህ ብቁ ናቸው የተባሉትን፣ የድርጅቱ ሊቀመንበርና ም/ሊቀመንበር፤ ካስፈለገም በሶስተኛ ዋና ጸሃፊ መርጠው የቀሩትም ማ/ኮሚቴ በሥራ አስፈፋሚው በየቦታው መድቦ ያሰራቸው ነበር። ግን በወቅሩ የነበሩት የኢህአፓ አመራር የዚህ አይነት የትግል ጉዞ አይፈልጉም፤ አልተቀበሉትም። ይህ ኢህአፓን ለውድቀት ዳረገው።
  2. የተመረጡት የሥራ አሰፈጻሚ አባላት የድርጅቱ መሰሶ የሆኑትን ክፍሎች ይቆጣጠራል፣ ይመራል። እነዚህም፤ ወታደራዊ፣ ፕሮፓጋንዳ ቢሮ፣ ኢኮኖሚ ቢሮ፣ የገጠር የሕዝብ ግንኙነት፣ የከተማ ግንኙነት፣ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ሲሆኑ፣ እነዚህን በበላይነት የሚመራው የሥራ አስፈጻሚው ነው። እንደ አስፈላጊነቱም ከማ/ኮምቴው ብቃት ያላቸው ታጋዮች በየዘርፉ ይመደባል። ትእዛዝ ከላይ ወደ ታች ሲተላለፍ ተግባራዊነቱን በመከታተል ከታች ወደ ላይ ይላካሉ። ይህ የድረጅቱ ጥንካሬና ብቃት ሆኖ ያድጋል። በጉባኤው ያልተመረጡት የኢህአፖ አመራር ይህን አይቀበሉትም። ይህን ባለመቀበሉ ኢህአፓ ለውድቀት ተዳረገ።
  3. ወታደራዊ እስትራተጂን በተመለከተ ሥራው ሁሉ የሚጠናቀቀው በሥራ አስፈጻሚው በኩል ነው። ወታደራዊ ተግባራት የሳይንስ ጥበብና እውቀት ይጠይቃል። በውስጡ ብዙ ዘርፎች በስትራተጂ ደራጃ፣ በታክቲክ ወይም ስልት ደራጃ ያቀፈ አሰራርና አጠቃቀሙ ብልህነትና አስተዋይነትን ይፈልጋል። ስለሆነም የአንድ ድርጅት እንቅስቃሴ ተግባራዊ ይሆናል። ይህን የማይቀበል ድርጅት ደግሞ በቀጥታ ለሞትና ለውድቀት አሳልፎ የሚሰጥ ነው። ይህን በወቅቱ የነበሩ የኢህአፓ አመራር ወታደራዊ ጥበብን በንቀት ይመለከቱት ስለነበር፣ የኢህአፓ ተዋጊ ክንፉ ኢህአሠ በቀላሉ በህወሓት እንዲጠቃ አደረገው። የኢህአፓ አመራር ከብቃት አነስተኛነት አልፎ በወታደራዊ ስትራቴጂ እምነቱ ዝቅተኛ ከመሆኑ የተነሳ ውድቀት አስከተለለት።
ሌላው ቀርቶ ኢህአፓ ከተማን ለቆ ለትጥቅ ትግል ኤርትራ በረሃ ገብቶ ከሻእቢያ እንደተጥጋ ጉባኤ ጠርቶ የነበሩትን ደካማ አመራር አሰወግዶ ብቃት ባላቸው ታግዮች መለወጥ ሲገባው አላደረገውም። በወቅቱ የነበሩ የኢህአፓ አመራር ጉባኤ መጥራትን አይፈልጉትም፣ የፈሩታል። ምክንያቱም፣
  1. የነበረው ደካማ አመራር ተወግዶ በብቁ ታጋዮች ስለሚተካ፣
  2. ኢህአፓ ሃብታም ድርጅት እንድመሆኑ እያላገጡ መብላትና መዝረፍ የለመዱ በመሆናቸው ጥቅማችው እንዳይነካ ስለፈለጉ ነው።
ኢህአፓ እንደ ዲሞክራሲ አብይ ጉዳይ የሚከተለው የክልል ነፃ አስተዳደር “Regional autonomy” ነበር። ይህ ደግሞ ማእከላዊ አመራርን የሚጻረር፣ ትእዛዝ ተቀባይ የሌለው፣ ደፈጣ ተዋጊ ሰራዊቱን ለክፉ አደጋ አሳልፎ የሚሰጥ አደገኛ መንገድ ነው። ድርጅቱም ስርዓት የለሽ “anarchy” እንቅስቃሴ በቀጥታ የሚዳርገው ነው።
ህወሓት፣ ኢህአፓን ለማጥቃት ሃይሉን ማጠናከር የጀመረበት ወቅት
 ኢህአፓ በትግሉ ወቅት ህወሓት ጠላቴ ነው ብሎ አልፈረጀውም። ይልቁንስ በአንድ ግንባር ተስልፈን ሃገራችን ኢትዮጵያን አሁን ካለው የደርግ ስርዓት ነፃ አውጥተን ሕዝባዊ መንግሥት እንድንመሰረት በአንድነት እንሰለፍ ከማለት በስተቀር። ደጋግም ኢህአፓ ለህወሓት አመራር በመቅረብ ቢጠይቅም በህወሓት አመራር የተሰጠው ምላሽ “ከአባይ ኢትዮጵያ” ተስፋፊዋ ኢትዮጵያ ታጋይ የሆንከው ኢህአፓ ግንባር አንፈጥርም በማለት ጥያቄውን ውድቅ አደረጉት። ትንሽ ቆየት ብሎም ኢህአፓ ትግራይን ለቆ እንዲወጣ በስብሃት ነጋ የተፈረመ ደብዳቤ ተላከለት። ኢህአፓም ትግራይ ኢትዮጵያ ስለሆነች አንወጣም፤ እናንተም ሸዋ፣ ጎጃም ወዘተ ቤታችሁ ነው፤ በምትፈልጉበት ቦታ ለመንቀሳቀስ መብታችሁ ነው የሚል መልስ ሰጠ። ይህ በኢህአፓ የተሰጠው ምላሽ ትክክል ነው።
ኢህአፓ በህወሓት ላይ ምንም የመተናኮስ ሥራ አልሠራም። የህወሓት አመራር ግን በኢህአፓ ላይ ብዙ መተናኮልና በተናጠል ግደያ ጀምረዋል። ቀስ በቀስም ኢህአፓን ለመደመሰስ ዝግጅቱ እየተጠናከረ መጣ። ይህ ሲሆን የኢህአፓ አመራር በተለያዩ መንገዶች መረጃ ሲደርሳቸው መደረግ የነበረበትን ሥራ አልሠሩም። አሲምባ የነበሩ አመራር በየቀኑ የሚደርሳቸውን መረጃ በንቀት ይሁን ወይም በትእቢት ግምት አይሰጡትም ነበር።
የኢህአፓ ተዋጊ ሰራዊት ኢህአሠ የከፈለው ከባድ መስዋእትነት
የኢህአፓ ተዋጊ ሰራዊት ኢህአሠ “የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮታዊ ሠራዊት” ተብሎ የሚታወቀው ነው። ኢህአሠ በተለያዩ የሃይል ምድብ ተመድቦ አንድ ሃይል ከ150 ታጋዮች በላይ እንደሆነም የህወሓት አመራር ሲናገሩ ነበር። ከ12-14 ሀይሎች ብዛት እንዳለውም ተናግረዋል። በወቅቱ የነበረው ትጥቁ  ዘመናዊ ክላሽንኮፍ የታጠቀ በአንድ ሃይል፤ ሶስት ዘመናዊ መትረየስም የታጠቀ በመሆኑ የህወሓት አመራር አረጋግጠው ተናግረዋል።
ኢህአፓ ከተለያዩ ግዛቶች የተሰባሰበ ኢትዮጵያዊ ሲሆን አብዛኛዎቹ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታችውን አጠናቅቀው በኢትዮጵያ ወስጥ በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በመማር ላይ የነበሩ ስለሆኑ ንቁና የተማረ ታጋይ ነበር። ብቁ የኢህአፓ አመራር ግን አላገኘም።
ህወሓት ኢህአፓን እና ተዋጊ ክንፉ ኢህአሠን ለማጥቃት ዝግጅቱ እንደተጠናቀቀ አሲምባ የነበሩ የኢህአፓ አመራር አስተማማኝ መረጃ ቢደርሳቸውም ተገቢውን ጥንቃቄ ባለመፈጸማቸው በታሪክና በሕግ የሚይስጠይቃቸው ስህተት ፈጽመዋል።
  1. ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሚያውቀው ኢህአፓ በማእከላዊ አመራር ያልተጀመረ፣ በወቅቱ የነበሩ አመራር በመሰላችው መንገድ የሚጓዙ፣ ስርዓት የለሽ ነበሩ። እያንዣበበ ያለውን አደጋ ለመከላከል አመራሩ ተሰብስቦ ጊዜያዊ አመራር መርጦ ቢሰይም ሁሉንም እየተቆጣጠረ ድርጅቱን እና ታጋዩን ከጥቃት ያድኑት ነበር። አልተደረገም።
  2. ጊዜያዊ ሥራ አስፈጻሚው ድርጀቱ በነፃ ክልል አስተዳደር የተበታተነው ታጋይ ነፃ ክልሉን አፍርሶ ሁሉንም የድርጅቱን እንቅስቃሴ በአንድ ማእከላዊ አመራር ይመራው ነበር።
ሀ. ኢትዮጵያ ሰፊ ሃገር እንደመሆኗ የድርጅቱን ሃብትና ንብረት ወደማይታወቅ ቦታ ወስዶ ከዘራፊውና ወንጀለኛው ህወሓት ይድን ነበር፤
ለ. ኢህአሠና ቀሪው የኢህአፓ ታጋይ ከሚከፍለው መስዋእትነት ለማዳን ጊዜያዊ አመራር፣ በጥናት የተመረኮዘ፣ ወደ ሚተማመንበት ቦታዎች በተለያየ አቅጣጫዎች ማፈግፈግ ይችል ነበር። ትግራይን ለቆ በመውጣት የታጋዩን ህይወት በማዳን እንደገና ተደራጅቶ በህወሓት ላይ ጥቃት የመሰንዘር ሰፊ እድል በመፍጠር ኢህአሠ ወያኔንም ሆነ ሻእቢያን ይደመስሳቸው ነበር። ምክንያቱም አሁን ስልታዊ ወታደራዊ ማፈግፈግ በሰፊዋ ኢትዮጵያ ስለሚንቀሳቀስ ብዙውን ወጣት ዜጋ ወደ ትግሉ ስለሚቀላቀሉ ሃይልና ግልበቱ ተጠናክሮ ስለሚወጣ ነው። ይህ መሆንና መደረግ ሲኖርበት፣ ደካማውና ብቃት አልባው የኢህአፓ አመራር    አላደረጉትም።
ሀወሓት የኢህአፓውን ተዋጊ ሰራዊት ኢህአሠን ሌሎች ታጋዮችን ለማጥቃት ቀናት እንደቀሩት አሲምባ ውስጥ የነበርው የኢህአፓ  አመራር ጓዛቸውን ተሸክመው ሶቦያ ወረዱ። መነኩሳይቶ ለነበሩ ጀብሃ – ተጋድሎ ሓርነት ኤርትራ – ጨለማን ተገን በማድረግ እጃቸውን ሰጡ። በነጋታው ደቀመሃሪ፣ ኤርትራ ወረዳ “ደርሆ ማይ” ወደ ተባለው ቦታ በሌሊት ወሰደው በመኪና ጭነው ሱዳን፣ ካርቱም አደረሷቸው።
የህወሓት አመራር የኢህአፓ ደካማ ጎኑን ለረጅም ጊዜ ያጠናው ስለነበር በተለያዩ የኢህአፓ ነፃ ክልል የተመደቡ ኢህአሠና ታጋዩ አመራሩ ቦታውን ለቆ ሌላውን መርዳት እንደማይፈቅድ ያውቃሉ።
የኢህአፓን ተዋጊ ክንፍ ኢህአሠን ለመደመሰስ የወጣው ፕላን
ጥቃቱ የተጀመረው ታህሳስ 1972 ሆኖ፣ የውጊያው ሁኔታ ከፋፍለው ያስቀመጡትን የህወሓት አመራር፣ ማለትም፣ አረጋዊ በርሄ ወታደራዊ አዛዥ፤ ስብሃት ነጋ የህወሓት ሊቀመንበር፤ መለስ ዜናዊ፤ አባይ ፀሃየ፤ ሥዩም መስፈን፤ አርከበ አቁባይ፤ አዋውአሎም ወልዱ፤ ጻድቃን ገብረተንሳይ፤ ስየ አብርሃ በዋናነት፤ ከህወሓት ተዋጊ አመራር፣ ሃየሎም አርአያ፣ ሳሞራ የኑስ ወዘተ ጋር በመሆን ጥቃቱ ተጀመረ።
የመጀመሪያው የጥቃት ኢላማ አጋሜ አውራጃ የሚንቀሳቀስ የኢህአሠ አሲምባ ሶቦያ አካባቢ በነበረው ላይ ጦርነቱ ተጀመረ። ረዳትና አስተባባሪ አመራር ሰጪ በማጣቱ፣ ለሶስት ቀን በመከላከልና በመልሶ ማጥቃት እንደቆየ ተጠቃ፣ ሊከፍለል የማይገባውን ከባድ የህይወት መስዋእትነት ከፈለ። ህወሓት የቆሰልውን ኢህአሠን ድገመው (አዳግመው) እያሉ ጨረሱት። የታጠቀውን ትጥቅ፣ ጥይት፣ ቦምብ፣ ራዲዎ መገናኛ የሞተውን እያገላበጡ ዘርፈው የኢህአሠን ትጥቅ ታጥቀው ፊታቸውን ወደ ሌላ ቦታ አዞሩ።TPLF-EPLF
ለቀጣዩ ጦርነት በፍጥነት ፊታቸውን ያዞሩት ወደ መሃል ትግራይ ወደነበረው ኢህአሠ ገሰገሱ። በድንገት ገብተው የጥቃት እርምጃ መውሰድ ሲጀምሩ እንዳሰቡት በቀላሉ የሚጠቃ ባለመሆኑ ኢህአሠ የመከላከል ጥቃቱን ከፋፍሎ በሃውዜን፣ በነበለት፣ በፈረሰማይ ወዘተ ስለነበር፤ የህአሠ ተዋጊ ቦታውን በሚገባ ስለሚያውቀውና ከአካባቢው ህዝብም ጥሩ መተበባር ስለነበረው አስቀድሞ የውጊያ ቦታውን በመያዝ እንዳለ የህወሓት ሃይሎች ጥቃት ቢከፍቱም በኢህአሠ አጸፋዊ ጥቃትና መልሶ ማጥቃት ወያኔዎች ሊቋቋሙት አልቻሉም። የህወሓት ታጋዮች ሙትና ቁስለኛ ሆነ። ውጊያውን ይመራ የነበርው አመራር ከአቅሙ በላይ ስለሆንበት ሌላ ተጨማሪ ሃይሎች በማስመጣት እንደ አዲስ ጥቃት ከፍቶ ኢህአሠን አዳከመው። በኢህአሠ በኩልም ወልቃይት ፀገዴ ያለው የኢህአፓ አመራር እዛ ያለው የኢህአሠ ሰራዊት ለእርዳታ እንዲመጣለት ሲጠይቅ የተሰጠው መልስ ክልላችንን ትተን እናንተን ለመርዳት አንመጣም የሚል ነበር። ጥቂት ታጋዮች በረሃው ወደመራቸው አፈግፍገው ህይወታቸውን አዳኑ። ኢህአሠ በዚሁ ውጊያ በጀግንነት ተዋግተው ከባድ መስዋእትነት ከፍለዋል። ህወሓት ኢህአሠን አጥፍቶ በዘረፈው ትጥቅና ጥይት ትምበሸበሸ፣ ሙሉ ሰራዊቱን ክላሺንኮፍ አስታጠቀ።
ቀጥሎም ፊቱን ያዞረው ወደ ወልቃይት ጸገዴ ነበር። በዛ ክልል የነበሩ አመራር አስቀድመው ደብዳቤ ወደ ህወሓት በመላክ እጃችንን እንሰጣለን፣ ተቀበሉን በማለት ገና ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት እጃቸውን ሰጡ። በአጠቃላይ ወደ 35 የሚሆኑ በቀጥታ በህወሓት ታጋዮች እየተመሩ ተምቤን ገቡ። ወያኔ ተቀበላቸው። የተቀበላቸው የድርጅቱ የስለላ ሃላፊ የነበረው ተክሉ ሃዋዝ ነበር። ሽሉም እምኒ በተባለችው ጎጥ እንዲያርፉ ተደረገ። በህወሓት ታጋዮች ጥብቅ ቁጥጥር እንደ ግዞተኛ ይጠበቁ ነበር።
eprp11ወልቃይት ጸገዴ አካባቢ የነበረው ኢህአሠ አምስት ሃይሎች ሲሆኑ ወያኔ ያለውን የሌለውን ሃይል ወየንቲ/ምልሻም/ ተጨምረው ጥቃት ጀመረ። ኢህአሠ አካባቢውን ስለሚያውቀው ካባድ መከላከል በማድረግ ቀላል የማይባል የህወሓት ታጋዮች ገድለዋል። ይህንን ጦርነት ሲመራው የነበረው ስብሃት ነጋ ለትንሽ ከእጃቸው አመለጣቸው። ብዙ የወያኔ ሃይል አመራር ተገድለዋል። ጦርነቱ ወያኔን ለከባድ ሽንፈት አድርሶት ነበር። ከአቅማቸው በላይ ስለሆነባቸው ሌላ ተጨማሪ ሃይል መጥቶ ውጊያው በክፉ መልኩ ቀጠለ። አርከበ እቁባይ የቀኝ እግሩ ቋንጃው ተመትቶ ስለቆሰለ በቃሬዛ ተሸክመውት ሸሹ። አሁንም ሌላ ተጨማሪ ሁለት ሃይሎች በበርሄ ሻእቢያና በታደሰ ወረደ የሚመሩ ተጨምረው ኢህአሠ የያዘው ጥይትና ቦምብ እያለቀ በመሄዱ ከባድ መስዋእትነት ከፍሎ በመጨረሻ ከአቅማቸው በላይ ስለሆነባቸው የተወሰኑት ታጋዮች ከጦርነቱ ጉዳት ደህና የነበሩ ኢህአሠ ተመከካረው ወደ መተማ አቅጣጫ አፈገፈጉ። የወሰዱት እርምጃ ትክክለኛ ነበር። ህዝቡም በየሄዱበት በመተባበር አስፈላጊውን እርዳታም በማቅረብ ወደሚፈልጉት ቦታ ሸኛቸው።
ባጭሩ ለኢህአፓ የተሰለፈው ተዋጊ ሰራዊት ኢህአሠ ኢትዮጵያዊ ራእይ ያለው፣ የነቃና ብቃት የነበረው ቢሆንም “የአሳ ግማቱ ከአናቱ” እንዲሉ የኢህአፓ አመራር ደካማና ብቃት የሌለው ስለነበር ሠራዊቱን እንደ ወያኔ ላለ ጸረ-ኢትዮጵያና ጸረ-ህዝብ ሃይል አጋልጦ ለውድቀት ዳርጎታል።
በኢትዮጵያ አርበኝነት ከሚወሱት የኢህአሠ ተዋጊዎች በተቃራኒ ደግሞ፣ ሰራዊቱ ሲፈርስ እጃቸውን ለወያኔ የሰጡትና ዛሬ እራሳቸውን ብአዴን ብለው የሚጠሩት ግንባር ቀደም የወያኔ ስርአት አስፈጻሚዎች፣ ዋናዎቹ የኢህአፓ ጥፋትና ወድቀት ማስታወሻዎች ሆነው ይገኛሉ።
ኢህአፓ ጠንካራ ጎኖችም የነበሩት መሆኑ የሚዘነጋ አይደለም። ዘውዳዊው ስርዓት ተንኮታኩቶ እንዲወድቅ ማድረጉና መሬት ላራሹ የመጀመሪያ መፈክሩ ተግባራዊ መሆኑና ሌሎችም አሉት።
የብአዴን አፈጣጠርና አመጣጥ!! መሪዎቹስ እነማን ከየትስ ናቸው?
ሽብርተኛው “terrorist” ቅጥረኛ “mercenary” ህወሓት፣ ኢህአሠን ካጠፋ በኋላ ፊቱን ያዞረው እጃቸውን የሰጡት ወዶ ገቦችን አስልጥነን በፕሮግራማቸው ብሄረ አማራ የመሰሉ ነገር ግን ፀረ-አማራ ሆነው ኢንዲቆሙ ማድረግ አለብን ተብሎ በወቅቱ የነበሩ የህወሓት አመራር፤ ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ፣ አረጋዊ በርሄ፣ አባይ ፀሃይ፣ ስዩም መስፍን፤ አውአሎም ወልዱ፤ አርከበ እቁባይ፣ ስየ አብርሃ፣ ገብሩ አስራት፣ ጻድቃን ገብረተንሳይ፣ ዘርአይ አስገዶም፣ አስፍሃ ሃጎስና የህወሓቱ ም/ሊቀመንበርና የድርጅቱ ዋና አስተዳዳሪ ግደይ ዘርአጽዮን በዚህ አርእስት ላይ አጀንዳ ቀርቦ ሲወያዩ ም/ሊቀመንበሩ ግደይ ዘርአጽዮን ይህንን ሃሳብ አልቀበልም በማለት ራሱን አገለለ። የተቀሩት ውይይቱን ቀጥለው ስምምነት ላይ ደረሱ። የግደይን ስም ለማጥፋት በዚህ ጉዳይ ላይ የታሰፉ አመራር፣ ግደይ የድርጅቱን ሃሳብ በመቃወም ችግር እየፈጠረብን ነው በማለት በደፈናው የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፈቱበት።
ከላይ ከተዘረዘሩት የመጀመሪያዎቹ 12ቱ የህወሓት አመራር ተሰባስበው፣ ተወያይተው ስምምነት የደረሱበት አማራ ጠላት እንደመሆኑ በራሳችን ትእዛዝና እንቅስቃሴ የሚታዘዝ ድርጅት ከፈጠርን አማራው ህልውናው የሚጠፋበት አማራጭ መንገድ ከዚህ የበለጠ ስለሌለን ፕሮግራሞቹን ጽፈን ሙሉ ቁጥጥር እያደረግን እነዚህን የኢህአፓ ወዶ ገቦች እናደራጅ ተብሎ ውሳኔ ተላለፈ።tamrat bereket meles
በዚህ ውሳኔ መሰረትም መለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየ ለሚመሰረተው የአማራ ድርጅት ፕሮግራምና የቅድመ ሁኔታ ውይይት እንዲያዘጋጁ ሃላፊነቱ ተሰጣቸው። እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት የህወሓት አመራር ያዘጋጁት ለህወሓት ፖሊት ቢሮ ስብሰባ ቀርቦ፣ እነ አረጋዊ በርሄና ስዩም መስፍን አንድ ላይ ሆነው የቀረበውን ጽሁፍ አንብበው ፕሮግራሙ ላይ ተስማሙበት። ይህም በዋናነት እጃቸውን የሰጡ የኢህአፓ አባላት ውይይቱን የሚመሩ ሶስት ሆነው ወዶ ገቦቹን አሳምነው መስራች ጉባኤ ተካሂዶ ፕሮግራሙን አምነው ተቀብለው በህወሓት እርዳታ የአማራ ብሄር ድርጅት ተመስርቶ እንዲቋቋም ተብሎ ተወሰነ።
በፕሮግራሙ መሰረት የመወያያ አርእስቶች
ውይይቱ የተጀመረው ግንቦት መጨረሻ 1972 ሲሆን፣ የውይይቱ መሪዎች መለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየ፤ ሲሆኑ ተጠባባቂ ረዳቶች ደግሞ አውአሎም ወልዱና አርከበ እቁባይ ሆኑ። የመወያያው ር ዕስ፣
  1. ነፃ ሃገር የነበረችው ኤርትራ ዛሬ በኢትዮጵያ ቅኝ አገዛዝ ስር ወድቃ ህዝብ ለመከራና ለችግር ተዳርጓል። ከህዝባዊ ሓርነት ኤርትራ ጋር በመተባባር ኤርትራን ነፃ እናወጣለን፣
  2. ነፃ ሃገር የነበረችው ትግራይ፤ የራሷ መንግሥትና መስተዳድር የነበራት ሃገር፣ ከአፄ ዮሐንስ ሞት በኋል በምኒልክ ተወራ በአማራው ቅኝ አገዛዝ ቀንበር መውደቋ፣
  3. የአሁኗ ኢትዮጵያ የታሪክ ድሃና ታሪክ የሌላት ሃገር፣ በአፄ ምኒልክ የተመሰረተችና ከ100 ዓመታት ያነሰ ታሪክ ያላት ሃገር መሆኗን አምኖ መቀበል፣
  4. ምኒልክ ግዛቱን ለማስፋፋት በመነሳት ሳይወድ በግድ ኢትዮጵያዊነትህን ተቀበል ተብሎ በአማራው የመንግሥት ስርዓት በስቃይና በችግር የሚገኙት ብሄር በሄረሰቦች የራስን እድል በራስ በመወሰን እስከ መገንጠል አምኖ መቀበል። በዚህም ላይ ኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰቦች ወህኒ ቤት መሆኗን አምኖ መቀበል፣
  5. አማራ የሚባለው ጨቋኝ ፀረ-ሕዝብ መሆኑን አምኖ መቀበል።
እነዚህ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱት ዋናውና የሚፈጠረው የአማራ ድርጅት የሚመራበት ፕሮግራም ሆነው ለውይይት ቀረቡ።
ABAYይህንን ውይይት የህወሓት አመራር አባይ ፀሃየ፣ ሊቀመንበር፣ መለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ ሆነው በመቅረብ ከሰኔ ወር መጀመሪያ 1972 እስከ ህዳር መጨረሻ 1973 ለ6 ወር ተከታታይ ውይይት ሲካሄድበት፣ በዚህ ጊዜም አዳዲስ የኢህአፓ አባላትም ሲቀላቀሉ ነበር። አብዛኛዎቹ ይህ ፕሮግራም ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ሉአላዊነትና ፀረ-ሕዝብ ነው ይሉ ነበር።
የኢትዮጵያ ህዝብ በብዙ ሺህ ዘመናት የዳበረ ወንድማማችነት፣ ኢትዮጵያዊነት፣ በጋብቻ፣ በባህል፣ በእምነት በአንድነት ሆኖ ሃገሩን ኢትዮጵያን ከባእዳን ወራሪዎች ተከላክሎ ለኛ አስረክቦናል። በህዝባችን ያልነበረና ያልታየ ፕሮግራም ተሸክመን አንታገልም ሲሉ፣ ከፈቀዳችሁ ፕሮግራሙን ራሳችን ጽፈን ለአንዲት ኢትዮጵያ፣ ለአንድ ህዝብ እንዲታገል ፍቀዱ። አማራ የህዝብ ጠላት ነው የምትሉት እኛም አማራ ነን፡፡ ኩሩውን አማራ የኢትዮጵያ የህዝብ ጠላት ነው ብላችሁ አትፈርጁት፣ በማለት እልህና ንዴት እንዲሁም ብስጭት በተቀላቀለበት ለወራት ከተወያዩ በኋላ ተሰብሳቢው በሶስት ተከፈለ።seyee
  1. በህወሓት ፖሊት ቢሮ ተረቆና ተዘጋጅቶ የቀረበውን ተቀብላችሁ ታገሉ የምትሉንን አንቀበለውም። በአማራው ህዝብ እውቅናም ውክልናም አልተሰጠንም። አማራውን ብቻ መነጠል ጠባብ አስተሳሰብነው፣ በዚህም ላይ አማራ ጠላት ነው እያላችሁን አማራውን ለክፉ ስቃይ አንዳርገውም። አማራ ኢትዮጵያዊ ነው፣ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር አብሮ ይታገል፣
  2. ጊዜ ስጡን፣ በረጋ መንፈስ አንብበን እና ተረድተን መልስ እንስጥበት የሚሉ፤
  3. በህወሓት የቀረበልን ፕሮግራም ለብዙ ወራት ገንቢ ውይይት ያካሄድንበት ትክክለኛ የአቋም ፕሮግራም መሆኑን ስለአመንበት ካለምንም ተቃውሞና ጥርጣሬ ተቀብለነዋል ያሉ ናቸው።
ከዚህ ተከትሎ ምን ተፈጠረ የሚለውን ባጭሩ እንመልከት። እንደሁኔታው ተራ ቁጥሩ ይለዋወጣል።
  1. ጊዜ ስጡን፣ በረጋ መንፈስ አንብበን መልስ እንሰጥበታለን ያሉት፣ ትንሽ ጊዜ ለማግኘትና ሕይወታቸውን ለማዳን የሚጠፉበትን እቅድ ማውጣት ላይ ተሰማሩ። ጋሻው ከበደ፤ አያሌው ከበደ፣ ምትኩ አሸብር ከማስታውሳቸውና ሌሎችንም ጨምሮ፣ የተወሰኑት ወደ ሱዳን፣ የተወሰኑት ደግሞ ለኢትዮጵያ መንግሥት እጃቸውን በመስጠት ሕይወታቸን አዳኑ። አሁንም በሕይወት አሉ።
  2. በህወሓት ፖሊት ቢሮ ተረቆ የተዘጋጀውን ፕሮግራም አንቀበልም ያሉት በህወሓት አመራር ላይ ጭንቀት ስለፈጠረበት የተወሰኑ አመራር ተሰብስበው፣ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየ፣ ስየ አብርሃ፣ መለስ ዜናዊ፣ አውአሎም ወልዱ፣ አርከበ አቁባይ፣ ጻድቃን ገ/ተንሳይና ስዩም መስፈን ተሰብስበው እነዚህን የህወሓት ሃሳብ ያልተቀበሉትን አፈንጋጭ በሞት እንዲቀጡ ውሳኔ ሰጡ። በውሳኔው መሰረት በስብሃት ነጋና አባይ ፀሃየ ሃላፊነት እንዲፈጸም ተወሰነ። በዚህ ጊዜ ሃለዋ ወያነ (06) በዙ እስረኞች ሞትን የሚጠባበቁ ስለነበሩ፣ የቦታው ርቀትን ጨምሮ ሃሳቡ ቀርቦ ከህዝብ ግንኙነት አባላትም ተጨምረው ግድያው እንዲፈጸም ተደረገ።
ግደያውን የሚያስፈጽሙት፣ ብስራት አማረና ሃሰን ሹፋ እንዲሆኑ ፖሊት ቢሮው ወሰነ።
1. ከወርዲ ሃለዋ ወያነ በአበበ ዘሚካኤልና ዘርአይ ይህደጎ የሚመሩ ተጨማሪ 5 ታጋዮች
2. ፃኢ ሃለዋ ወያነ በወልደሥላሴ ወልደሚካኤልና በተስፋየ መረሳ (ጡሩራ) የሚመሩ 5 ታጋዮች
3. ከህዝብ ግንኙነት
ለኡል በርሄ፣ አብያ ወልዱ፣ ሃይሉ በርሄ፤ ቢተው በላይና ወልደ ገብርኤል ሞደርን። ሁሉም ተሰብሰበው ተምቤን ውስጥ አምበራ መጡና ገቡ። ግደያውን የሚፈጽሙት ብስራት አማረና ሃሰን ሹፋም መጥተው ከእነ ታምራት ላይኔ ጋር ቆዩ። ስብሃት ነጋም መጣና ከነብስራት አማረ ጋር ተነጋገረ። እነታምራት ላይኔ፣ በረከት ስምኦን ወዘተ ከነበሩበት ቤት ራቅ ባለ ቦታ የመረሸኛ ጉድጓድ ተቆፍሮ ተዘጋጅቷል። እነዚህ በህወሓት የተረቀቀውን ፕሮግራም አንቀበለም ያሉት ቁጥራቸው በርካታ ነው። ስብሃት ነጋ ለልዩ ስብሰባ ብሎ በሃለዋ ወያነ አባላት ታጅበው ሄዱ። አባላቱ እጃቸውን በገመድ ጠፍረው በማሰር ወደ ተዘጋጀው መግደያ ጉድጓድ ወስደው በጥይት ደብድበው ገደሏቸው። ሁሉም አማራ ሲሆኑ፣ ሃይላይ የሚባል አንድ የትግራይ ልጅ ከነሱ ጋር ነበር።
seyoum mesfinይህ ፋሽስታዊ ተግባር እንደተፈጸመ በሶስተኛው ቀን በጣም አሳዛኝና አስደንጋጭ ወሬ በህወሓት ታጋይ ተናፈሰ። ወሬውን የበተኑት በግድያው የተሳተፉት የሃለዋ ወያነ አባላት እነ ሃሰን ሹፋ፣ አበበ ዘሚካኤል፣ ተስፈየ መረሳ ወዘተ ከህዝብ ግንኙነት ተመርጠው የመጡ ልኡል በርሄ፣ ቢተው በላይ በህወሓት ውስጥ ኦቦራ አስነሱ። የህወሓት ታጋይ ሁሉም ማለት ይቻላል፣ ተናደደ፣ አበደ። በዚህ ጊዜ መለስ ዜናዊና ስብሃት ነጋ ፈርተው ተደበቁ። እነብስራት አማረም ፈርተው ባኽላ ሄደው ተደበቁ።
በዚህ በተሰራጨው ወሬ ጠንከር ያሉ አመራር ስለነበሯቸው በተረጋገጠው ዜና የእንቅስቃሴው መሪዎች የነበሩ፣ ከልካይ ጎበና፣ አስራደው ዘውዴ፣ ዳኛቸው ታደሰና ሃይላይ፣ አክራሪ አማሮች፣ የነፍጠኛ ልጆች የተባሉ በነበሩበት ወቅት በፋሽስት ህወሓት አመራር ለህልፈት በቅተዋል።
በህወሓት የተረቀቀውን ፕሮግራም አምነን ተወያይተን ገምቢ ፖሊሲውን ተቀብለናል ያሉት እነዚህ ናቸው፣
  1. ሙሉአለም አበበ፣ አማራ                                    7. ህላዊ ዮሴፍ፣ ኤርትራ
  2. ሃይለ ጥላሁን፣ ትግራይ፣ እድገቱ ጎጃም            8. ተፈራ ዋልዋ፣ ሲዳማ
  3. ታምራት ላይኔ፣ ከንባታ                                     9. ታደሰ ካሳ፣ ትግራይ
  4. ዮሴፍ ረታ፣ ትግራይ፣ ኤርትራ                         10. መለሰ ጥላሁን፣ አማራ፣ ትግራይ
  5. በረከት ስምኦን፣ ኤርትራ                                   11. ሲሳይ አሰፋ፣ ትግራይ
  6. አዲሱ ለገሰ፣ ሂርና ሃረር                                      12. ኢያሱ በላቸው፣ ትግራይ፣ አማራ
ማሳሰቢያ፣ ከላይ የተጠቀሱትን ትወልድ ቦታቸውን ለማግኘት አስቸጋሪ ሆኖብኝ ለዓመታት ብቆይም፣ ዛሬ ግን ከሚያውቋቸው ሰዎች ጠይቄና አፈላልጌ ትክክለኛውን የትውልድ ቦታቸውን በማያያዝ ይህን ጽሑፍ አቅርቤአለሁ።
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ናቸው የአማራ ህዝብ ድርጅትን ለመመስረት ህወሓት ያዘጋጀው። ህዋሓት ሲፈጠር በሻእቢያ ነበር። ያደረገው ነገር ድርጅቱ በኤርትራውያን እና ከትግራይ የተፈጠሩ ባንዶች በማቀናጀት ህወሓትን ፈጠረ። ለምን ይህ ነገር ተደረገ የሚል ጥየቄ ከተነሳ፣ ሻእቢያ የትግራይና አማራውን ህዝብ ስለሚጠላ ህወሓት በህዝቡ ላይ ጥቃት ይፈጽማል በሚለው ፖሊሲ መሰረት ነው። ህወሓት በወቅቱ ተሓህት ገና ከመፈጠሪያ ትግሉ መነሻ ጀምሮ በትግራይና በአማራው ህዝብ ላይ የፈጸመው ግድያና እልቂት የአማራውን እና የትግራይ ህዝብ ያውቀዋል። ከዚህ በመነሳት ህወሓት የፈጸመውና እየፈጸመ ያለው የዘር ማጥፋት ወንጀል የዓለም ህዝብ ያወቀው እውነት ነው። አሁን ደግሞ ብአዴን በአማራው ላይ የሚፈጽመው ወንጀል አደባባይ የወጣ ሃቅ በተግባር እየታየ ነው።
ከዚህ ከአፈጣጠሩ ተነስተን ብአዴን ማን ነው? እውነትስ የአማራውን ህዝብ ይወክላል? ለሚሉት መልስ ለመስጠት እነማን ናቸው የአማራ መሪ ድርጅት ብለው የሰየሙት? ከየትስ መጡ? ብዙ ጥያቄ ሊነሳ ይገባል። ለዚህ ሁሉ መልስ ግን ይህ ጽሑፍ ሙሉ መልስ የሚሰጥ ነው። በእርጋታና በጥሞና አንብቡት። የአማራው ህዝብም ብአዴን አማራን አትወክልም፣ አናውቃትም በማለት እምቢ አልገዛም ማለቱ ትክክለኛ የትግል መስመር ነው። ቀሪው ኢትዮጵያዊም ትግራይ፣ ኦሮሞ፣ አፋር፣ ኦጋዴን፣ ደቡብ ህዝብ፣ የሁላችንም መልስ አንድ ነው። ህወሓት ዘረኛና ፋሽስት ነው፣ አጋር ድርጅቶችም የህወሓት ተግባር አስፈጻሚ ናቸው።
arkebeህወሓት ምን መብትና ሃላፊነት አለው ለአማራ፣ ለኦሮም፣ ለደቡብ፣ ለአፋር ወዘተ? ድርጅት የሚመሰርተውስ ህወሓት ራሱ ማን ነው? በቅጥረኝነት የተፈጠረ የባንዳ ስብስብ የተለያዩ ድርጅቶች መስርቶ ኢትዮጵያን ሊበትን የመጣ መብቱን ማን ሰጠው? ስለሆነም የኢትዮጵያ ህዝብ ከነዚህ የቀን ጅቦች የሚገላግለው ራሱ ነው።
ሐምሌ 1973 የህወሓት ፖሊት ቢሮ ያዘጋጀው የኢህዴንን ፕሮግራም በመያዝ ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ፣ አርከበ እቁባይ አምቦራ መጡ ልዩ ስሙ ሸሉም እምኒ ቁሽት በመሄድ ቀኑም የተቆረጠ ስለነበር ከኢህዴን አባላት ጋር ተገናኙ። በፕሮግራሙ ላይ ለአጭር ጊዜ ከተወያዩ በኋላ የብአዴን ፕሮግራም መሆኑን በድጋሚ ባማረጋገጥ ተቀበለው። የኢህዴን መስራች ጉባኤ እንዲመሰረት ተደረገ። በዚህ መስራች ጉባኤ አምስት ሰዎች ብቻ ስለሚፈለጉ በእቅዱ መሰረት ምርጫው ተካሄደ። በምርጫውም ታምራት ላይኔ፣ በረከት ስምኦን፣ አዲሱ ለገሰ፣ ህላዊ ዮሴፍና ተፈራ ዋለዋ ሲመረጡ፣ ሊቀመንበሩ ታምራት ላይኔ ሆነ።
መስራች ጉባኤ እየተባለም እስከ 1975 ቆየ። ለዚህ ምክንያት ካለ 12ቱ የኢህዴን ሰዎች ማንም ከትግሉ የሚቀላቀል አልተገኘም። ኢህዴን ወይም የኢትዮጵያ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ እየተባለ የመጣው ዋና ዓላማው የኢትዮጵያ ታጋይ እየተባለ ድጋፍና ታጋይ ወጣቶች ከአማራውና ከሌላውም ለማግኘት ህወሓት ያቀደው ዓላማ ነበር። ቢሆንም፣ አንድም አልተገኘም፣ ድጋፍም አላገኘም።
ህወሓት በኢህዴን ተስፋ በመቁረጥ ከራሱ 50 የህወሓት ታጋይ ጨመረለት። እነዚህ ደግሞ 12ቱን ግዞተኞች የሚከታተሉና የህወሓት ታጋዮች በሚሉት ስለሚመሩ መብት አልነበራቸውም።
የህወሓት አመራር የኢህዴን 1ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ የት ይደረግ የሚለው ሃሳብ ከተወያየ በኋላ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ሐምሌ 1975 ዋግ አካባቢ እንዲሆን ሲወሰን ህወሓት ደግሞ ሙሉውን የጉባኤ ወጪ ሸፍኖ እንዲዘጋጅ ተደረገ። በዚሁ ጉባኤ የህወሓት አመራር ትኩረት የሰጠው እነማን ጉባኤውን ይምሩት በሚለው ላይ ነበር። በህወሓት ውሳኔ መሰረት በሊቀመንበርነት ጉባኤውን የሚመሩ መለስ ዜናዊ፣ ሊቀመንበር፣ አባይ ፀሃየ፣ ከህወሃት፣ ህላዊ ዮሰፍ፣ ብአዴን ተብሎ ተወሰነ።
በፕሮግራሙ መሰረት በመለስ ዜናዊ ሊቀመንበርነት የኢህዴን ጉባኤ ተጀመረ። ለአንድ ቀን በተለያዩ ጉዳዮች ከተወያዩ  በኋላ በሁለተኛው ቀን 1ኛው የብአዴን አማራውን የሚወክል አርማና ባንዲራ ማጽደቅ፣ 2ኛ የብአዴን አመራር መምረጥ ሲሆን በአንደኝነት የተጠበቀው አልተዘጋጀም ተብሎ ለ2ኛ ጉባኤው ሲተላለፍ፣ መረጣው ግን ቀጠለ። ከዚህ በታች የሚታየው ስም ዝርዝር የአማራ ህዝብ አመራር ናቸው። ከአማራው ህዝብ አብራክ የተወለዱት አማሮች እንደመሆናቸው አማራውን ይመሩታል በማለት በህወሓት የማጭበርበር ዘዴ መለስና አባይ እየተቀባበሉ ተናግረው ምርጫው ቀጠለ።
ተ.ቁ
ስም ከነ አባት
የትውልድ ቦታ
ሃላፊነቱ
1ታምራት ላይኔ (ጌታቸው ማሞ)ከንባታየብአዴን ሊቀመንበር
2በረከት ስምኦንኤርትራም/ሊቀመንበር
3አዲሱ ለገሰሂርና፣ ሐራር
4ተፈራ ዋለዋሲዳማፕሮፓጋንዳ ቢሮ
5ዮሴፍ ረታኤርትራ
6መለሰ ጥላሁንአማራ፣ ትግሬ
7ህላዊ ዮሴፍኤርትራየህዝብ ግንኙነት ሃላፊ
ተ.ቁ
ተለዋጭ ማ/ኮሚቴ ስም ከነአባት
የትውልድ ቦታ
1ታደሰ ካሳትግራይ
2ሙሉአለም አበበአማራ
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት በጉባኤው ተመረጡ። ኢህዴን የሚለው ስም ተለውጦ ብአዴን (ብሄረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ) ተብሎ ተሰየመ። የአማራ መሪ ድርጅት ሆነ። ቀደም ብለው የተነሱ ጥያቄዎች ብአዴን ማን ነው? ከየትስ መጡ? እነማንስ ናቸው? ወዘተ ለሚሉትጥያቄዎች መልሱ ይህ ነው። እውነትስ ብአዴን የአማራውን ሕዝብ ይወክላል? መልሱ ፈጽሞ አማራውን የሚወክል ድርጅት አይደለም ነው።
ህወሓት ለራሱ ትግል የተነሳው ኤርትራን አስገንጥሎ የትግራይ መንግሥት እናቋቁማለን ብሎ ነው ፕሮግራሙን አዘጋጅቶ የካቲት 1967 ደደቢት በረሃ የወረደው። በምን መልኩ ነው ደመኛ ጠላቴ ለሚለው አማራ ድርጅት ብአዴንን ሊፈጠርለት የቻለው? ህወሓት ምን መብትና ሃላፊነት አለው? ማንስ ሰጠው? ህወሓት ይህን ሁሉ የፈጠረው የአማራውን ህዝብ ከዘር ማንዘሩ ሊያጠፋልኝ ይችላል ብሎ ነው የብአዴንን ቅጥረኞች “mercenary” የፈጠረው። ሌላውም ህወሓት ለአማራ ድርጅት መፈጠር ቅንጣት የምታክል መብት ፈጽሞ የለውም። ስለዚህ ብአዴን ፀረ- አማራ ቅጥረኛ ድርጅት ነው።
እነዚህ ወዶ ገቦች ብአዴን ከህወሓት እንደተቀላቀሉ በተግባር ያሳዩትን ግፍ ባይናችን አይተናል። የኢህአፓ አባላትና ደጋፊዎች እያሉ በወልቃይት፣ በፀገዴ፣ በጸለምት መሪ ሆነው ለህወሓት በመጠቆም ስላማዊ ዜጋውን አማራ አስጨርሰዋል። ንብረቱ በህወሓት እየተወረሰ ተገድሏል። ህፃን፣ ሽማግሌ፣ ሴት ሳይለይ እነበረከት ስምኦን በነስብሃት ነጋና አርከበ እቁባይ ትብብር ሙሉ ቤተሰቦች በሚኖሩበት የሳር ቤት እያስገቡ በላያቸው ላይ እሳት ለኩሰው አቃጥለው አስገድለዋል። በተመሳሳይ መንገድ ታምራት ላይኔ፣ ታደሰ ካሳ፣ መለሰ ጥላሁን እና ህላዊ ዮሴፍ ህዝቡን ቤት ውስጥ በማስገባት በእሳት በማቃጠል ጨርሰዋል። የወልቃይት ከሞት የተረፈው የፀገዴና ጸለምት ህዝብ ላይ የተፈጸመበትን ግፍ ይውጣና ራሱ ይመስክር። ምስክርነትህን ጮክ ብለህ አሰማ።
ብአዴን ከ1972 መጨረሻ ጀምሮ በአማራው ላይ አሰቃቂ ግፍ እየፈጸመ የመጣ ፀረ-አማራ የሆነ ቅጥረኛ “mercenary” ድርጅት ነው።
አዲሱ ለገሰ ወያኔ ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠረ በተወለድኩበት ለዘመናት የቆዩትን አማሮች ዘር እየለየ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አማራዎችን አልገድልክም? አፈናቅለህ አላባረርክም? በምን መልኩ ነው አንተ ወንጀለኛና ፋሽስት አማራውን የምትወክለው? ብአዴን ሁላችሁም ግፍ የፈጸማችሁና በደም የታጠባችሁ ናችሁ።
ብአዴን የአማራውን ህዝብ ባህልና ወግ የማያውቅ ስለሆነ የአማራ መሪ ድርጅት የመሆን መብትና ሕጋዊነት የለውም። በአንጻሩ ብአዴን ፀረ-አማራና አማራውን ለማጥፋት በህወሓት የተፈጠረ ነው።
የብአዴን 2ኛው ጉባኤ በ1981 ዋግ አውራጃ አውሰን ተብሎ በሚጠራው ቦታ ሲካሄድ፣ ብአዴን ያሳየው እድገት አልታየም። ሐምሌ 1975 የተመረጠው አመራር በድጋሚ ተመረጡ። አሁንም 12 ሰዎች ናቸው።
በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ ሀገራችን ወደ ጨለማ ጉዞ እያዘገመች ነበረች። ትናንትና ደህና የነበረው፣ ዛሬ አስደንጋጭ ሁኔታ ይዞ ብቅ ይላል። ደርግ ትግራይን ለቆ በመውጣቱ ህወሓት ትግራይን የመቆጣጠር እድል ስላገኘ፣ የአሜሪካ የስለላው ማእከል CIA ባለሥልጣናት መቀሌ ድረስ በመሄድ ቅድመ ሁኔታዎችን በማስተካከል ተባበሩት። ህወሓት ትግራይን ነፃ ለማውጣት በተላበሰው አልባሳት ላይ ሌላ ካባ ደረበበት። መስከረም 1982 እንደርታ አውራጃ ሰምረ ወረዳ ባኽላ ቁሽት ግዞተኛ የነበረው ብአዴን አመራሩ በሙሉ ተጠርተው መቀሌ ገቡ። የመጡበት ምክንያት ለስብሰባ መሆኑ ተነገራችው።arkebe meles
ስብሰባው ሁሉም የህወሓት የፖሊት ቢሮ አባላት፣ መለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየ፣ ሥዩም መስፍን፣ ስየ አብርሃ፣ ገብሩ አስራት፣ አለምሰገድ ገ/አምላክ፣ አበበ ተ/ሃይማኖት፣ አርከበ እቁባይ፣ አረጋሽ አዳነ፣ አውአሎም ወልዱ፣ ክንፈ ገ/መድህን እና ጻድቃን ገ/ተንሳይ ሲሆኑ፤ በብአዴን በኩል ታምራት ላይኔ፣ በረከት ስምኦን፣ አዲሱ ለገሰ፣ ተፈራ ዋለዋ፣ ዮሴፍ ረታ፣ መለሰ ጥላሁን፣ ህላዌ ዮሴፍና ተደሰ ካሳ ናቸው። በዋናው አጀንዳ ከተነጋገሩ በኋላ በመጨረሻ ብአዴን የህወሓት አጋር ደርጅት መሆኑ ተገለጸላቸው። በዚህ መሰረትም ህወሓትና ብአዴን በመሆን ኢህአዴግ (የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር) ተብለው እንደሚጠሩ ተወሰነ። የቀኑ ውሎ ሁኔታ እንደመግቢያ ተደርጎ “ድምፂ ወያነ” ልክ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በይፋ ታወጀ፣ በጽሑፍም ተበተነ።
እኔ የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ በወቅቱ የነበርኩት አዲስ አበባ ስለሆነ በጊዜው የነበረውን የኢትዮጵያ መንግሥት ህወሓት በትግራይ ውስጥ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በየሰዓቱ በሚስጥራዊ ሥራው ይከታተለው ስለነበር ከላይ ያስቀመጥኩት ሁሉ በተገኘው የስለላ መስመር ሁሉም በዝርዝር ተነገረኝ። ዛሬ ማታ በ12 ሰዓት በድምፂ ወያነ እንድከታተለው ተነገረኝ። ጠቅላላ የመረጃውን ጽሑፍ እንዳነበው ተሰጠኝ። አንብቤም አንዳንድ ነጥብ በማስታወሻ እንድጽፈው ፈቃድ ስጠይቅ ይቻላል፣ ምንም ችግር የለውም ተባልኩ። አስፈላጊውን ወሰድኩ። ቤቴ ሂጄ ልክ በ12 ሰዓት ድምፂ ወያነን ከፍቼ አዳመጥኩ። የደህንነቱ የመረጃ ክፍል ያነበብኩትና የነገሩኝ ሁሉ በትክክል ቃሉ ሳይዛነፍ ድምፂ ወያነ ሴኮ በሚባል ሰው አዋጁን አስነበበ።
የደርግ መንግሥት የደህንነትና የመረጃ ሥራ በጣም ረቂቅና የተደራጀ መሆኑን ያደነቅሁት በዚህ ጊዜ ነበር። ለነገሩ ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት የተማሩ ምሁራን መሆናቸውን አውቃለሁ።
የህወሓት ፋሽስት አመራር ኢትዮጵያን እና ህዝቧን ለማጥፋትና ለመበታተን በፕሮግራሙ ያስቀመጠው ኢህአዴግ በሚል ስም ግንቦት 20 ቀን 1983 ኢትዮጵያን በቅኝ አገዛዝ ስርዓቱ እንደተቆጣጠረ 12ቱም ብአዴን “ብሄረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ”ን  አጋር ድርጅት ብሎ የሰየመው ህወሓት አቅፎት አብረው አዲስ አበባ ሲገቡ፣ ህወሓት የኢትዮጵያን ህዝብ አደናግሮ ፋሽስትና ሽብርተኛ ስርዓቱን በመላ ሃገሪቷ ዘረጋ።
ፋሽስቱ ህወሓት በሽግግር መንግሥት ስም ስርዓቱን እንደ ዘረጋ፣ ቀዳሚ ትኩረቱ ያደረገው የአማራውን ህዝብ ዘሩን ለማጥፋት ተግባራዊ እርምጃ በቅጥረኛው “mercenary” ብአዴን ታምራት ላይኔ ጠ/ሚኒስትር ሆነ። የብአዴኑ መሪ የከንባታው ተወላጅ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ፀረ-አማራ ንግግር በተደጋጋሚ በመናገር ተስፋፊ፣ ትምክህተኛ፣ ነፍጠኛ አማራን ማጥፋት አለብን በማለት የዘር ማጥፋት ወንጀሉን ተግባራዊ ለማድረግ ተዘጋጀ።
በ1983 ከሰኔ ወር ጀምሮ በህወሓት ፋሽስቱ መሪና የህወሓት አመራር በሙሉ በሚያምኑበትና በተሰጠው ቀጭን መመሪያ በአማራውን ህዝብ በየአለበት በታምራት ላይኔ፣ በረከት ስምኦን፣ አዲሱ ለገሰ፣ በተፈራ ዋለዋ፣ በመለሰ ጥላሁን ወዘተ የብአዴን አመራር መሪነት የህወሓት የታጠቁ ሃይሎች በማሰለፍ በየቦታው ዘምተው በአማራ ህዝብ ላይ አሰቃቂ ግድያ በመፈጸም ዘሩን ለማጥፋት ዘግናኝ እርምጃ ወስደዋል። በአርባ ጉጉ፣ በደኖ፣ ቦረና፤ ጉጂ፤ ጋምቤላ ወዘተ የነበረውን አማራ ሙሉ በሙሉ ገድለው አጠፉት። ከሞት እንደ ምንም ብሎ የዳነውን፣ ውጣ አንተ ተስፋፊ፣ ትምክህተኛ ተብሎ በመፈናቀል በረሃ ላይ ወደቀ። ከህፃናት እስከ ሽማግሌ፣ ወንድና ሴት ሳይለይ፣ እርጉዝ ሴቶችን ጨምሮ በረሃ ተጥለው ለአራዊት ምግብ የተዳረገው፣ ለመጥፎና አሰቃቂ መከራ የተዳረገው፣ በህወሓትና ብአዴን የአማራው ህዝብ ነው።bereket s
በረከት ስምኦን ባደገበት ወሎ አካባቢ በሱ የሚመራው የህወሓት ታጣቂ ገዳዮች በመያዝ በአማራው ህዝብ ላይ ከፍተኛ ግድያ የፈጸመው የብአዴን መሪ ቅጥረኛ ኤርትራዊ ነው።
አዲሱ ለገሰ በተወለደበት አካባቢ ይኖሩ የነበሩትን አማሮች በአሰቃቂ ግደያ አጥፍቷቸዋል። ከንብረታቸው አፈናቅሎ ለመከራና ችግር የዳረጋቸው የብአዴን መሪ ነው።
መለሰ ጥላሁን ባደገበት የአማራው ቦታ በህወሓት የታጠቁ ሃይሎችን በመምራት በአማራው ላይ አሰቃቂ ግፍ የፈጸመaddisulegesse የብአዴን መሪ ነው። የብአዴን መሪዎች ሁሉም በአማራው ህዝብ ላይ ፋሽስታዊ ግፍ  ፈጽመዋል። ታድያ እነዚህ የብአዴን አምራር ፀረ-አማራ ሆነው ተፈጥረው አንተን በምርኮኛነት እየተቆጣጠሩህ የአማራ ህዝብ መሪዎች ናቸው? መልሱ፣ አይደለም ነው።
በኢሳት ሚዲያ የተሰራጨውን ዘገባ የሰማነው በትክክል ኤርትራዊው ቅጥረኛ በረከት ስምኦን የብአዴን ሥራ አስፈጻሚና መሪ የአማራ ሕዝብ ተነስ ስንለው ይነሳል፣ ተኛ ስንለው ይተኛል፣ አድርግ ስንለው ያደርጋል በማለት የተናገረው የአማራው ህዝብ ለ23 ዓመታት እንደ ባርያ እየገዙት፣ መብቱ እየተረገጠ፣ እንዴት በእነዚህ የብአዴን ቅጥረኞች ዘሩ እየጠፋ፣ ከየቦታው እየተፈናቀለ፣ እየተገደለ ሊኖር ነው? መልስ የሚሰጠው የነፃነት ግዴታው የሆነው ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው።
አለምነው መኮንን የተባለው ቅጥረኛ ባንዳ ህወሓት በአማራው ላይ የሚከተለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ፖሊሲ ፈጻሚና alemenew-mekonnenአስፈጻሚ በመሆን የሚሰራው የብአዴን መሪና ሥራ አስፈጻሚ በብአዴን የካድሬዎች ስብሰባ በአማራው ህዝብ ላይ ያወረደው አስጸያፊ ስደብ በጣም ያሚያሳዝን ነው። ሁሉም ኢትዮጵያዊ በኢሳት ሬዲዮና ቴሌቪዥን በሚገባ የተከታተልው ስለሆነ ይህንን ዘግናኝና አጸያፊ ስድብ እዚህ ባላነሳው ይሻላል። አለምነው መኮንን የተፋው ስድብ ለአማራ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ነው የሰደበው። ሲናገርም፣ ይህ የተናገርኩት ጉዳይ የድርጅቴ ብአዴን/ኢህአዴግ አቋምና እምነትም ነው፣ በማለት በድጋሚ አረጋግጦታል።
ደመቀ መኮንን የብአዴን ሥራ አስፈጻሚ መሪ ነው። ቅጥረኛው ባንዳ በጸረ አማራነቱ የተሰለፈ በመሆኑ በከፍተኛ ስልጣን ላይ የሚገኝ ነው። በአማራ የዘር ማጥፋት ወንጀል ከመነሻ ጀምሮ ከነበረከት ስምኦን፣ ህላዌ ዮሴፍ፣ ታደሰ ካሳ፣ አዲሱ ለገሰ፣ ተፈራ ዋለዋ፣ ታምራት ላይኔ ወዘተ በመተባበር አማራውን ከየቦታው በማፈናቀል ትምክህተኛ፣ ነፍጠኛ፣ ተስፋፊ በማለት ግፍ የፈጸመ ወንጀለኛ ሲሆን፣ በተጨማሪም ክህወሓቱ መሪ መለስ ዜናዊ ጎን በመቆም የሱዳን መንግሥት መሬቴን ባለፉት መንግሥታት የኢትዮጵያ መሪዎች ስለተቀማሁDemekeMመልሱልኝ በማለታቸው በአማራው ክልል ያለው የሱዳን መሬት ነው ብለህ ፈርም ተብሎ ካለምንም ማቅማማት ፈርሞ የሰጠ ፀረ-ኢትዮጵያ ሉአላዊነት ባንዳ ነው።
ብአዴን የህወሓት ተግባር ፈጻሚ ባንዳና ቅጥረኛ በመሆኑ በአማራው ላይ ያደረሰው ጥቃትና መፈናቀል ባጭሩ እንመልከት፤
  1. በቀጥታ በህወሓት የሚፈጸሙት ግድያዎች ዘር ማጥፋት ብአዴን በዋናነት በመሰማራት ግፍ የፈጸመ፣
  2. ከህፃናት ጀምሮ እስከ 45 ዓመት ክልል ወስጥ የሚገኙትን አማራዎች የዓይን ትራኮማ መድሃኒት ነው በማለትና ሽፋን በመስጠት የማምከኛ መርፌና ኪኒኒ  ለወንዱም ለሴቱም በመስጠት የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈጸሙና እያስፈጸሙ የሚገኙት የብአዴን አመራር በሙሉ ናቸው፣
  3. ከመሬቱ የተፈናቀለው አማራ ተፈናቅሎና ተበታትኖ በየቦታው እያለቀ፣ ረሃብና በሽታ በላዩ ላይ ወርዶ የሚፈጸምበት ያለ ህዝብ ነው። ይህንን ሁሉ በሰው ልጅ ላይ እየፈጸመ ያለው ቅጥረኛው ባንዳ ብአዴን ነው። ለምሳሌ ደመቀ መኮንን እና ግብረአበሮቹ እነ በረከት ስምኦን ሁሉ የብአዴን መሪዎች ከየአካባቢው ክልሎች አመራር ውስጥ ልወስጥ በምስጢር ተነጋግረው ከቤኒሻንጉል፣ ጉራ ፈርዳ፣ ወዘተ ትምክህተኛውና ተስፋፊው አማራን ከየክልላቸሁ ባሃይል አስወጡት በማለት የአማራው ህዝብ ተፈናቅሎ እንዲበታተን ያደረጉ፣ በአማራው ህዝብ ጉያ መሽጎ ያለው ብአዴን ነው። ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ሚና ተጫውተዋል። አማራው ለዚህ አስከፊ ሰቃይ የዳረገው የአማራ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ብአዴን ነው። ባነተ ስም ግን ይነግዳል፣ ይሾማል፣ የተንደላቀቀ ኑሮ ይኖራል። ይህንን የሰጠው ህወሓት አንተን ድርሻህን አጥፍቶ ለስደትና ለክፉ ሞት ስለዳረገህ ህወሓት ከመደሰቱ የተነሳ ነው። ታዲያስ አሁን በቃኝ ብለህ አትነሳም? ለማኝና ባሪያ ሆነህ እስከመቼ ትኖራለህ?
በአማራው እየደረሰ ያለው ሰቆቃ፣ ግድያና  ማፈናቀል በአማራ ብቻ አልተወሰነም። የህወሓት ፋሽስት ሰርዓት በሌሎች ኢትዮጵያውያንም ላይ እየፈጸመው ነው። የኦሮሞ ህዝብ በኦህዴድ፣ የደቡብ ህዝብ፣ በደህዴን፣ በትግራይ ወዘተ ከባድ ወንጀል እየተፈጸመበት ይገኛል። የዚህ ወጀል ፈጻሚዎች ቅጥረኛ ባንዳዎች ኦህዴድ፣ ደህዴን በሌላ ቦታዎች፣ ራሱ ህወሓት በቀጥታ በመግባት ግድያ፣ ዘር ማጥፋት፣ ማፈናቀል ከግብረአበሮቹ ጋር ሆኖ እየፈጸመው ይገኛል። ይህም የሚያበቃው ኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ የተባበረ ክንዱን ሲያሳርፍበት ብቻ ነው!! የኢትዮጵያ ህዝብ ተነሳ! ፍርሃትህን አስወግድ!!
1ኛ. የህወሓት ሽብርተኛው ስርዓት በምንም ተአምር በሰላማዊ መንገድ ከስልጣኑ አይወርድም። ይወርዳል የሚል ካለ በጭልምተኝነት ማእበል የሚንሳፈፍ ኢትዮጵያዊ ፍጡር ነው። ህዋሓት በዲሞክራሲያዊ መንገድ የመጣ ሳይሆን ወራሪና ቅኝ ገዢ ነው። ይህን አምባገነን ፋሽስት ቅጥረኛ የሚወርደው በህዝባዊ አመጽ በተባበረ ክንድ ተደምስሶ መቃብር ውስጥ ሲገባ ብቻ ነው። በዚህ ሁኔታ ብቻ የወያኔ ስርዓት ያከትማል።
2ኛ. አንድ አንባገነን ፋሽስት ስርዓት እውነተኛ ምርጫ የሚባል ነገር አያውቅም። ፀረ-ዲሞክራሲ ስርዓት ያለበት ሃገር ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ቦታ የለውም። ይህም በ1997፣ በ2002 ያየነው ነው። በህወሓት የተዘረፈው ምርጫ አስተምሮናል። በእነዚህ ሁለት ምርጫዎች የኢትዮጵያ ህዝብ አልመረጠውም። አሁንም የምርጫ ኮሚሽኑ ህወሓት፣ አስመራጭ ህወሓት፣ የምርጫ ሳጥን አቅራቢና ተቆጣጣሪ ህወሓት ነው። ተቃዋሚ ሃይሎች ከነተመራጮቻቸው በአካባቢው እንዳይደርሱ ተደርጎ እውነተኛ ምርጫ ሊከናወን አይችልም።
gedu
ጌዱ
ለሚመጣው 2007 ምርጫ ምን መተማመኛ አለን? በሚቀጥለው ምርጫ አንድነት ለፍትህና ዲሞክራሲ (አንድነት) አሸናፊ ሆኖ እንደሚወጣ ጥርጥር የለውም። ይህ ቢሆንም ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር የላቸውም። በተለይ ሰማያዊ ፓርቲ እየተከተለው ያለውን መንገድ፣ የፋኖ ጉዞውን፣ አቁሞ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር መተባበር አለበት። ካላደረገ የወያኔን እድሜ እያራዘመ ነው። በትግራይ አረና ሙሉ በሙሉ አሸናፊ ነው። የትግራይ ህዝብ ወያንኔ ህወሓትን አይመርጥም። ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳም ይመረጣሉ። ይህንን ድል ለመቀናጀት ግን ምን ዓይነት የምርጫ አካሄድና ዘዴ “Mechanism” ተዘጋጅቷል? ጥያቄው ይህ ሆኖ፣ ገለልተኛ ወይም ነፃ የምርጫ ኮሚሽን፣ ከውጭ የሚመጡ ገለልተኛ ታዛቢዎች፣ በኢትዮጵያ የሚገኙ የውጭ ሃገር ኤምባሲዎች ምርጫውን በታዛቢነት እንዲከታተሉ መገኘት፤ የወያኔም ሆነ የወያኔ አጋር ደርጅቶች ወይም ተለጣፊ የጎሳ ፓርቲዎች፣ ድህንነቶች፣ ፖሊሶች፣ የወያኔ ደጋፊዎች በምርጫ ቦታዎች እንዳይታዩ ማሳገድ ወዘተ የመሳሰሉትን ሁኔታዎች ለማቀነባበር ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ጊዜው አሁን ነው። ወያኔ ህወሓት ደግሞ ግርግር ፈጥሮ እንደማይቀበል የታወቀ ቢሆንም በስፋት ደግሞ እንደገና ይጋለጣ፣ እድሜው ግን ይራዘማል።
ለማጠቃለል፣ ይህ ጽሑፍ ትኩረት የሰጠው በአማራው ህዝብ ላይ ብአዴን “ብሄረ አማራ ዴሞራሲያዊ እንቅስቃሴ” ከመነሻውና ከአፈጣጠሩ ጀምሮ ፀረ-አማራ ሕዝብ ሆኖ የተፈጠረ፤ ትወልዳቸው ከአማራ ውጭ የሆኑ ብአዴን እና ህወሓት ሃገር እንደተቆጣጠሩ በገንዘብ የተገዙ ባንዳዎች ለመሆናቸው ምስክርነቴን ለመስጠት ነው። የብአዴን አመራር ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮቹና ባንዳዎቹ እነ ደመቀ መኮንን፣ አለምነው መኮንን፣ ጌዱ አንዳርጋቸው፣ አያሌው ጎበዜ፣ ተፈራ ደርቤ፣ ብናልፈው አንዱአለም፣ አህመድ አብተው፣ አምባቸው መኮንን ወዘተ ከነ በረከት ስምኦን፣ አዲሱ ለገሰ፣ ታደሰ ካሳ፣ ህላዌ ዮሴፍ፣ በህወሓት መሪነት በአማራው ላይ የከፋ ግፍና ሰቆቃ ፈጽመዋል። አማራው ከሌሎች ኢትዮጵያዊ ወገኖቹ ጋር ሆኖ፣ ለካስ እነዚህ ናቸው የኔ መሪዎች ብሎ በማሰብ፣ የገደሉትን፣ ዘሩን ያጠፉትን ሆዳሞች ሁሉ በጠንካራው ክንዱ ተባብሮ የማያዳግመውን ክንዱን እንዲዘረጋባቸው ነው። ድርጊቱ የተፈጸመው በአማራው ላይ ብቻ ሳይወሰን ኦሮሞ፣ አፋር፣ ኦጋዴን፣ ድቡብ ህዝቦችም ተመሳሳይ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል። ተገድለዋል፣ ዘራቸውን ለማጥፋት በየወህኒ ቤቱ ታስረው በውስር እየተገደሉ ናቸው። የኢትዮጵያ ህዝብ በግፍ እያለቀ ነው። ከመሬቱ ተሰዶ፣ ካደገበት ተፈናቅሎ ፋሽስታዊ ጭፍጨፋ እየደረሰበት ነው። ተባብሮ በመነሳት ህወሓት ወያኔን በህዝባዊ አመጽ ካልደመሰሰው ኢትዮጵያኝ ህዝቧ በህወሓት ሴራ ለክፉ አደጋ ይዳረጋሉ። በህዝብ ላይ የሚደርሰው ግፍና በደል በከፋ መንገድ ከመቀጠሉ በፊት በህዝባዊ አመጽ ህወሓትን ማንበርከኪያ ጊዜው አሁን ነው።
(ገብረመድህን አርአያ – አውስትራሊያ)