Friday, March 21, 2014

ህወሓቶች ሰግተዋል!

March 21/2014
"ህወሓት ካልተመረጠ የትግራይ ማንነት ይጠፋል"

ህወሓቶች በዓረና እንቅስቃሴና በትግራይ ህዝብ የተቃውሞ መንፈስ በጣም ደንግጠዋል። የዓረና ተከታታይ ህዝባዊ ስብሰባዎችን ተከትሎ ህወሓትም ተከታታይ ህዝባዊ ኮንፈረንስ ለማድረግ ወስኗል፤ ጀምሯልም። የህዝብ ተወካዮች ተብለው የተመረጡ የየአከባቢያቸው ህዝብ እንዲሰበስቡ መመርያ ተሰጥቷል። ይቅርታ የህዝብ ተወካዮች ሳይሆኑ የፓርቲ ተወካዮች መባል አለባቸው፤ ምክንያቱም የተመረጡት በህዝብ ሳይሆን በህወሓት ነው። የሚያገለግሉትም ለህዝብ ሳይሆን ለህወሓት ነው። ምክንያቱም በህዝብ ተመርጠው ተብለው የህዝብ ችግር ከመናገር ይልቅ የህወሓት አጀንዳ ደግፈው የሚያጨበጭቡ ናቸው። እስካሁን የመረጠውን ህዝብ ችግር የተናገረ የህዝብ ተወካይ የህወሓት አባል አላገኘሁም። በህወሓት የፖለቲካ ፍልስፍና የተማእከለ ዴሞክራሲ መሰረት አንድ አባል ከፓርቲው አስተሳሰብ ወጥቶ የፓርቲው ብልሹ አሰራሮች ባደባብይ ወይ በፓርላማ ማጋለጥ አይችልም። ካጋለጠ ከፓርቲው ይባረራል። ለዚህም ነው የህዝብ ተወካዮች ተብለው ፓርላማ ይገቡና የፓርቲው ተወካዮች ሁነው የሚቀሩ።
የህዝብ ወይም የህወሓት ተወካዮች ህዝብ ሲሰበስቡ ፈተና እያጋጠማቸው ነው። የሽረ ተወካይ ህዝቡ ሰድቦ አባሯታል። ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ በዓድዋ ህዝብ ተሰድባለች። የዓድዋ ህዝብ ለቅዱሳን “እናንተ ቤተሰቦቻቹ ለመርዳት እንጂ መቼ ለህዝብ ደህንነት ሰርታቹ ታውቃላቹ?” የሚል አስተያየት ሰጥቷል። በመቐለም አዲሳለም ባሌማ ህዝብ (ይቅርታ በመቐለ ህዝብ ተብለው የተሰበሰቡ ካድሬዎች ነበሩ) ሰብስቦ እርዱን ማለቱ ታውቋል። የመቐለ ዉሃ በ2007 ዓም ፕሮጀክት ቀርፀን እንፈተዋለን፤ ብቻ እኛን ምረጡ ብሎ ተማፅኗል። የመቐለ ነጋዴዎች ሰብስቦ ችግሮቻቹ ለመፍታት ተዘጋጅተናል ብሎዋል።
አጠቃላይ የህወሓት ስትራተጂ ህዝብን ለመሸወድ ያለመ ሲሆን የሚያጠነጥነውም “ህወሓት ካልተመረጠ የትግራይ ማንነት ይጠፋል” የሚል ነው። “ጠላቶቻችን እየመጡ ናቸው፤ ከህወሓት ጎን ተሰለፉ! ጦርነት ሊከፈትና ልጆቻችሁ አደጋ ላይ ሊወድቁ ይችላሉ” እያሉ ይገኛሉ።
ግን የትግራይ ማንነት በህወሓት ህልውና የተንጠለጠለ አይደለም። እንኳን የህዝብ ማንነት የአንድ ግለሰብ ማንነትም ሊጠፋ አይችልም። ምክንያቱም የህዝብ ማንነት ቀርቶ የአንድ ሰው ማንነት ከጠፋ የሰውየው መብትና ነፃነት ተጥሷል ማለት ነው። መብቱ ወይ ነፃነቱ ከተጣሰ ደግሞ አዲስ የመጣ ስርዓት ልክ እንደ ህወሓት አምባገነናዊ ስርዓት ነው ማለት ነው። የህውሓትን ያህል አምባገነን ስርዓት ከመሰረትን ደግሞ ህወሓት አልተቀየረም ማለት ነው። ህወሓት ካልተቀየረ የፖለቲካ ለውጥ አልመጣም ማለት ነው። የፖለቲካ ለውጥ ካልመጣ ደግሞ ትግላችን ይቀጥላል (ለውጥ እስኪመጣ ድረስ)። ስለዚህ እኛ የምንታገለው ከህወሓት የተሻለ ስርዓት ለመመስረት እንጂ ህወሓትን በሌላ አምባገነን ስርዓት ለመተካት አይደለም። ስለዚህ ላረጋግጥላቹ የምፈልገው ነገር ቢኖር የማንም ህዝብ ወይ ግለሰብ ማንነት ይከበራል እንጂ አይጠፋም።
“ጠላቶቻችን እየመጡ ነው” የሚለው ዉንጀላ ግዜው ያለፈበት ፕሮፓጋንዳ ነው። የህዝብ ጠላት ጨቋኝ ስርዓት ነው። ህዝብ ከጨቋኝ ስርዓት ዉጭ ሌላ ጠላት የለውም። ጨቋኝ ስርዓት የህዝብ ጠላት እስከሆነ ድረስ እንታገለዋለን። ጨቋኝ ስርዓት ምን ግዜም አንቀበልም። ጨቋኝ ስርዓት ስለማንቀበል ነው አሁን ህወሓትን የምንቃወመው። ስለዚህ ዓላማችን የስርዓት ለውጥ ማምጣት እስከሆነ ድረስ ለጨቋኞች ቦታ የለንም፤ ህወሓትም ሌሎችም። እኛ የምንቀበለው ዴሞክራሲያዊ የህዝብ መንግስት ብቻ ነው።
ህወሓቶች በዓረና አጀንዳዎች በመስጋታቸው ምክንያት የዓረና ሐሳቦችን ለመቀበል እየተገደዱ ነው። በቅርቡ በህዝብ ፊት እየቀረቡ የመሬት ይዞታ ጉዳይ በዓረና እየቀረበ ያለውን ሐሳብ እንደሚደግፉ እየገለፁ ነው። (የዓረና ሐሳብ እንደግፋለን እያሉ ሳይሆን የህዝብን ፍላጎት ለማሟላት እንሞክራለን በሚል ነው። የህዝቡ ፍላጎት ደግሞ የዓረና የመሬት ፖሊሲ ነው)። የዓሰብ ወደብም በሰለማዊ መንገድ ለማስመለስ እንሞክራለን በማለት እየተመፃደቁ ነው። ለነጋዴዎችም ግብር እንቀንሳለን በሚል ምክንያት ለመጀንጀን እየሞከሩ ነው።
አሁን ግራ ሲገባቸው ስራ የሌላቸው ወጣቶች ለውትድርና ለመመልመል እየሞከሩ ሲሆን ማንም ወጣት ፍቃደኛ ሊሆን አልቻለም። በወጣቶቹ ዉሳኔ የተደናገጡ ህወሓቶች የጎዳና ተዳዳሪ የነበሩ ህፃናት ልጆች አታለው (ስራ እንሰጣቸዋለን በሚል ምክንያት) ለዉትድርና መመልመላቸው ታውቋል። ለምሳሌ በመቐለ ከተማ የነበሩ ብዙ የጎዳና ተዳዳሪ ህፃናት ተወስደዋል (ማረጋገጥ ይቻላል፤ አሁን በመቐለ ከነበሩ ህፃናት አንድ የቀረ የለም)። ግን አብዛኞቹ ህፃናት ከ16 ዓመት በታች ናቸው። ከ16 ዓመት በታች ህፃናት ለውትድርና የሚመለምል የቸኛ ሕገወጥ መንግስት ኢህአዴግ መሆኑ አይቀርም። ምክንያቱም በማንኛውም ሕግ ከ16 ዓመት በታች ህፃናት ለውትድርና መመልመል ሕጋዊ ሊሆን አይችልም። ጉዳዩ የሚከታተለው ካገኘ በዓለም አቀፍ ሕግ ወንጀል ሊሆን ይችላል።
በዓዲግራት የፈፀሙብንን ድብደባ በጣም አክስሮባቸዋል። የትግራይ ህዝብ ሙሉበሙሉ እንዲጠላቸው ሁነዋል። እናም በጣም ሰግተዋል። በቅርቡ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ሊጀምሩ ይችላሉ። በወታድሩም ቢሆን ህወሓቶች ድጋፍ የላቸውም።
It is so!!!
አብረሃ ደስታ

በጋዜጠኞች ላይ ያለ ማስረጃ የሚሰነዘሩ ውንጀላዎች ባስቸኳይ እንዲቆሙ እንጠይቃለን!

March 21, 2014
ከኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ (ኢጋመ) የተሰጠ መግለጫ
ማህበራችን ጠቅላላ ጉባኤውን አካሂዶ የምዝገባ ሰርተፊኬት ለማግኘት የጀመረው እንቅስቀሴ በቅርቡ ከመንግስት አወንታዊ ምላሽ እንደሚያገኝ ተስፋ በማድረግ የተቋቋመለትን አላማ ለማሳካት እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን መብትና ጥቅም ከማስጠበቅና የመናገር ነፃነትን ከማበረታታት ባለፈም ከአህጉራችን አፍሪቃ ጋዜጠኞች ጋር በመተባበር የመላው አፍሪቃ ጋዜጠኞችን መብትና ጥቅም የሚያስጠብቅና የመናገር ነፃነትን የሚያበረታታ አህጉራዊ ተቋም ለመመስረት ተነሳሽነትን ወስዶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ በቅርቡም የምስራቅ አፍሪቃ ጋዜጠኞችን በማስተባበር አህጉር አቀፍ እንቅስቃሴያችንን ለማስጀመር ዝግጅት እያደረግን ነው፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተግባር ጋዜጠኛውን ሳይወክሉ የጋዜጠኛውን ስም የያዙት የኢጋማ፣ የኢነጋማና የኢብጋህ አመራሮች ነን የሚሉት ግለሰቦች በመቀናጀት በየሚዲያው እየቀረቡ ጋዜጠኞችንና የሚዲያ ተቋማትን ለማሸማቀቅ ያለመ ውንጀላና አሉባልታ የመንዛት ዘመቻ ጀምረዋል፡፡ ግለሰቦቹ በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ ቀርበው በጋዜጠኞች ላይ ከሽብር ፈጠራ እስከ ሀገር ማተራመስ የደረሰ የውንጀላ መዓት ቢደረድሩም አንዳችም ማስረጃ አላቀረቡም፡፡
ለምሳሌ የካቲት 22 ቀን 2006 ዓ.ም በታተመው አዲስ አድማስ ጋዜጣ (ቅጽ13 ቁጥር 737) ላይ ስማቸውን ደብቀው ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ጋዜጠኞች ሀገር ለማተራመስና ሽብር ለመፍጠር እየተዘጋጁ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ይሁን እንጂ “ምን ማስረጃ አላችሁ” ለሚለው የጋዜጠኛዋ ጥያቄ የመለሱት “እኛ እና እነሱ እንተዋወቃለን፡፡” የሚል አስገራሚ መልስ ነው፡፡ ይህ መሰረተ ቢስ ውንጀላ ጋዜጠኞችን ለማሸማቀቅ የተወረወረ በመሆኑ የኢጋማ፣ የኢነጋማና የኢብጋህ አመራሮች ነን የሚሉት ግለሰቦች ጋዜጠኞችን እና የሚዲያ ተቋማትን ያለ ማስረጃ መወንጀላዎች ባስቸኳይ እንዲያቆሙ ይጠይቀል፡፡
በመቀጠልም በሪፖርተር ጋዜጣ (የዕሁድ እትም ቅፅ 19 ቁጥር 1446) የካቲት 30 ቀን 2006 ዓ.ም “ኢጋማ በምስረታ ላይ ያለውን የጋዜጠኞች መድረክ አስጠነቀቀ” የሚል ዜና ተመልክተናል፡፡ ሆኖም በጋዜጠኞች ስም ተሰባስበው ጋዜጠኛውን የሚጠቅም አንዳች እንቅስቃሴ ሳያደርጉ ከመተኛታቸው ብዛት አልጋቸው ለረገበ ማህበራት ማስጠንቀቂያ ምላሽ በመስጠት ጊዜ በመሆኑም ምለሻችን በዝምታ መስራት ነው፡፡
የግለሰቦቹ የውንጀላ ንግግር የሚያስረዳው ከህግ፣ ከሞራል እና ከሙያዊ ስነምግባርም በላይ ራሳቸውን ለመሾም የሚፍጨረጨሩ መሆኑን ነው፡፡ ግለሰቦቹ በተለያዩ ጊዜያት መንግስት የፕሬስ ተቋማት ላይና ጋዜጠኞች ላይ የወሰዳቸውን ኢ-ህገመንግስታዊ እርምጃዎች እንደ ጋዜጠኛ ማህበር መሪ ከመኮነን ይልቅ የመንግስትን እርምጃ ሲያወድሱ ተስተውለዋል፡፡ በተጨማሪም በእስር ላይ ሆነው ህክምና በመከልከላቸው ለከፋ ስቃይ ስለተዳረጉ ጋዜጠኞችም ትንፍሽ ሲሉ አልታየም፡፡
እነዚህ የጋዜጠኛ ማህበራት መሪዎች ነን ያሉት ግለሰቦች እንደማህበር መሪ ሳይሆን እንደ ስለላ ተቋም ጋዜጠኞች እና አንዳንድ የሚዲያ ተቋማት ሃገር ለማተራመስና የሽብር ጥቃት ለመፈፀም እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ መረጃ እንዳላቸው በይፋ ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም
1ኛ. የሶስቱ ማህበራት መሪዎች አለን የሚሉትን መረጃ ለመንግስት በአፋጣኝ ሳይሰጡ መቆየታቸው በሀገራችን ህግ መሰረት ሊጠየቁው እንደሚገባ እንዲሁም
2ኛ. የሶስቱ ማህበራት መሪዎች በጋዜጠኞች እየተቀነባበረ ነው ካሉት የሽብርና ሀገር የማተራመስ እንቅስቃሴ ጀርባ እንዳሉ የጠቀሷቸውን ኤምባሲዎች በግልፅ ጠቅሰው ለመንግስት እና ለህዝብ እንዲያስታውቁ እንጠይቃለን፡፡
የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ (ኢጋመ)
መጋቢት 10 ቀን 2006 ዓ.ም

ለአልሙዲ “ማፅናኛ”(ከጋዜጠኛ ተስፋዬ ተሰማ)

March 20/2014

በቅርቡ ባህርዳር ላይ በተካሄደው የኢትዮጵያ ስፖርት በአል ሼኽ አልሙዲ በክብር እንግድነት ተጋብዘው ነበር። የበአሉን መክፈቻ በቲቪ ስከታተል አንድ ጥያቄ ወደ በአእምሮዬ መጣ። አልሙዲንን የክብር እንግዳ አድርጐ መጋበዙ ለምን አስፈለገ?..ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ። “የገዢው ፓርቲና የባለስልጣናቱ ታማኝ ወዳጅ ስለሆኑ፣ በባህርዳሩ ስታዲየም ግንባታ ድርጅታቸው ስለተሳተፈ ወይም ሼኹ ለስፖርት ያላቸውን ፍቅር በማየት..” የሚሉ ነገሮችን መደርደር ይቻላል።

በእኔ ግምት አልሙዲ በባህርዳሩ በአል በእንግድነት የተጋበዙት በሰሜን አሜሪካ ስፖርት በአል ላይ ስለተዋረዱ የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት የፈጠርዋት ማፅናኛ ትመስለኛለች። ባለፈው አመት እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በአንድ ሳምንት ሁለት የኢትዮጵያ ስፖርት በአል ተከበሮዋል። አንድኛው በሼኽ አልሙዲና የዳይስፖራውን ማንነትና ፍላጐት ባልተገነዘቡ ወዳጆቻቸው የተዘጋጀ ነበር። በነዚህ ወገኖች ግምት “ዳያስፖራው በተወሰኑ የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅት ካድሬዎች የሚሽከረከር የዋህ ህዝብ” አድርገው ይወስዱታል።

 አሜሪካ ሀገር ከኅይለስላሴ ጀምሮ በደርግ ጊዜ ከዛም በኋላ የመጣው አብዛኛው ኢትዮጵያዊ (በምንም መንገድ አሜሪካ ይምጣ) ለዘሩ፣ ለጐሳው ሳይሆን ለኢትዮጵያዊነቱ ጥልቅ የሆነ ፍቅርና ክብር አለው። በዚህ ምክንያት የኢህአዴግን የዘር ፖለቲካ አይደግፍም። ከደጋፊዎቹም ጋር የማይታረቅ ቅራኔ ውስጥ የገባው በዚህ አገር ወዳድ አቋሙ ነው። ይህ እውነት ያለገባቸው አልሙዲና ተከታዮቻቸው በስፖርቱ አስታከው ዳያስፖራውን እንቆጣጠራለን በማለት በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ቢከሰክሱም አልተሳካላቸውም። ባዶ ስታዲየም ታቅፈው ነው የቀሩት። ሁለተኛው ኢ.ኤስ.ኤፍ.ኤን የሚባለው ኢትዮጵያዊ ፌዴሬሽን የነሱን ያክል ገንዘብ ሳይኖረው በርካታ ህዝብ ከጎኖ ማሰለፍ ችሎዋል። እንዲያውም ስታዲየሙ ሞልቶ ሰው እስኪመለስ ድረስ። በዚህ በአል ከፍተኛ የሆነ የአንድነትና የአገር ፍቅር ስሜት የታየበት፣ የኢትዮጵያ ባንዲራ ከፍ ብሎ በብዛት የተውለበለበበትና ያሸበረቀበት፣ ሰዎች ከብሄራቸው ይልቅ ኢትዮጵያዊነታቸውን ያገነኑበት ትልቅ በአል ነበር።

ባዶ ስታድየም የታቀፉትና አፍረው በውርደት ለተመለሱት አልሙዲ የባህርዳሩ እድል በማፅናኛነት ተሰጣቸው። ኢትዮጵያዊያን በነፃነት በሚኖሩበት አሜሪካ ግን አልሙዲ በገንዘባቸው የህዝብን ድጋፍ መግዛት አይችሉም። በገንዘብ ምንም ማድረግ እንደማይችሉም ሊያውቁት ይገባል።

Land grabbing in Ethiopia – foreign investors and famine

March20/2014

Although one in 10 Ethiopians is going hungry, the government is leasing fertile land to foreign investors. Deutsche Welle spoke with Essayas Kebede from the Ethiopian government about so-called land grabbing.
farmers working land in EthiopiaFarmers cannot own land in Ethiopia, they must least it
Countries in Asia and the Gulf – such as China, India and Saudi Arabia – have rushed to foreign countries to buy farmland to grow crops for their own people. Food price inflation in recent years has highlighted the need for greater food security.
Africa has become a prime target, despite concerns about the impact on the world’s poorest people. Locals have nicknamed the practice “land grabbing.”
Essayas Kebede is the director of the Ethiopian government’s Agricultural Investment Agency and is responsible for the contractual agreements with foreign investors regarding Ethiopian farmland.
Deutsche Welle: Mr. Essayas, Ethiopia is experiencing a severe famine right now. Despite this, you have been tasked by the government to lease huge swaths of land to foreign companies. Critics have called this irresponsible. Are you acting in bad faith?
Essayas Kebede: Agriculture is the backbone of the Ethiopian economy. Fifteen million hectares of land are being worked by farmers and another 15 million are lying fallow. The Ethiopian government’s five-year development plan aims to increase the productivity of subsistence farmers, which is why we’ve turned our attention to commercial agriculture operations that can help our farmers increase their revenues.
The Gambella farm in EthiopiaThe Gambella farm is the size of Luxemburg 
Of the 15 million hectares of fallow land that I mentioned, we identified 3.6 million that are suitable for commercial farming. But for that we need investors. They can come from Ethiopia or from abroad, it doesn’t matter to us, but we urgently need capital and modern technology to increase our agricultural sector output. That way we can boost our foreign currency stocks and create jobs.
Are you saying that this policy can help solve Ethiopia’s hunger problems?
We have to increase productivity, but we also have to increase the buying power of our people. It’s the only way they are going to be able to afford food. The sale of goods produced on large farms will bring in desperately needed foreign currency, with which we can introduce modern production methods.
Ethiopian farmers are not allowed to own land, rather they lease it. Wouldn’t it be better to make life easier for them with microcredits, improved market access and roads than accommodating investors from India and China?
We are in the process now of regulating land ownership questions and have already granted the first land titles. Regarding infrastructure, the government has paved many kilometers of roads and built new ones. We have established government offices that support local farmers.
A full 85 percent of our population work as small farmers in rural areas and if we really want to stimulate the economy of our country, we have to improve the conditions our farmers live and work under. The foreign companies bring technology that helps our own farmers. Investors build bridges, schools and hospitals, and people here benefit from those.
Indian investors clearing Ethiopian landThe Indian investors clear Ethiopian land, but who profits?
There are rumors that the Indian Karuturi Global company has leased the Gambella farm in the west of the country, which has 300,000 hectares of land, in order to push up its stock price on the Mumbai stock exchange. However, most of the farm is still lying fallow. Where is the technology you were talking about, as well as the schools, hospitals and all the jobs?
We signed an agreement with Karuturi and they are working on it. Developing farmland doesn’t happen overnight. We want to help investors have successful relationships with us.
But the success doesn’t seem to be happening. You have already threatened to take back 200,000 hectares if there is no significant progress within two years. Something has obviously gone wrong. How much time does Karuturi have?
When the time comes, we will sit down together. The clearing of vegetation takes time and right now, we can’t really judge Karuturi’s performance. He has two years to cultivate the first 100,000 hectares and then one year for an additional 50,000.
Karuturi spokesman Birinder Singh Karuturi spokesman Birinder Singh call the land deal a “win-win” situation
To increase the food supply in the country, at least part of the harvest has to be sold on the local market. Was that a stipulation in the contracts with the big multinationals?
It’s not our task to take revenue away from investors. As I said, we want to increase the purchasing power of our people so that they can afford to buy corn from Karuturi. If the investors can get a good price here in this country, they will sell here.
Four decades after Ethiopia’s first famine, your country is suffering again. Has the government done enough to try to break this vicious circle of hunger and poverty?
There are 1.2 billion people suffering from hunger around the world. It’s a growing, global problem and we are part of a globalized world. If it rains less in Europe, we feel it here. You see, in the 70s we had a population of 25 million, today it’s 80 million. So hunger is not as widespread as it was then and today our food reserves are higher. In the 70s, the government didn’t have the situation under control. The current administration, however, knows what it’s doing. In fact, the chances are good that Ethiopia will be able to contribute to the global food supply in the future. We have enough land.
Interviewer: Ludger Schadomsky (jam)
Editor: Rob Mudge
Source: DW

በዘመነ ኢሕአዲግ ኑሮ ከድጡ ወደማጡ (ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ)

March20/2014
<<የኑሮ ውድነቱ እየተባባሰ መምጣት ሕዝቡ በመንግስት ላይ ያለውን ጥላቻ እንዲከር እያደረገው ነው>>
የኢህአዲግ ወያኔ መንግስት የስልጣን ወንበር በትሩን በሀይል ከተቆናጠጠበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ የአኖኖር ሁኔታ ከእለት ወደ እለት እያሽቆለቆለ እና እየወረደ በመምጣቱ ሕዝቡ ከምቼውም ጊዜ በበለጠ በአሁኑ ወቅት ኑሮን መቋቋም በማይችልበት አደገኛ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ እና በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የኑሮ ውድነት ተቋቁሞ መኖር ከባድ ፈተና እየሆነባቸው እንደሆነ የችግሩ ሰለባና ተጠቂ የሆኑት ሰዎች በየጊዜው ከሚያሰሙት ሮሮና ጩኸት መረዳት ይቻላል::ይህንንም እየተባባሰ እና እየጨመረ የመጣውን የኑሮ ውድነት ተከትሎ የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን ስራ አስፈፃሚ የተቃውሞ ሰልፍ ሊጠራ እንደሆነ ታውቋል:: የአንድነት ፓርቲ ሊጠራ ባሰበውና በታቀደው ሰላማዊ ሰልፉም ላይ በስርዓቱ እና በኑሮ ውድነቱ የተማረሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በነቂስ በመውጣት በምሬት የታመቀ የብሶት ድምጻቸውን በወያኔ ኢህአዲግ መንግስት ላይ እንደሚያሰሙ ይጠበቃል:: በአሁኑ ወቅት ጥቂት የስርአቱ ደጋፊዎች እና የወያኔ ካድሬዎች ካልሆኑ በስተቀር በኑሮ ውድነቱን የተነሳ ተጎጂ ያልሆነና ሕዝቡ ኑሮን መቋቋም በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ በመገኘቱ ስርዓቱን የማያማርር የህብረተሰብ ክፍል የለም ብል ማጋነን አይሆንብኝም ::
የወያኔ መንግስት የሚያራምደው ፖሊሲ የመላው ኢትዮጵያን ሕዝቡ ፍላጎት እና ጥቅም ማዕከል ያላደረገ ሲሆን የተወሰኑን የህብረተሰብ ክፍሎችን ብቻ ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል :: መላውን የኢትዮያ ህዝብ እና ክልል ተጠቃሚ ያላደረገው የመንግስት የልማት ስትራቴጂ ፖሊሲ እና በመላው ሀገሪቱ ላይ በስፋት ተንሰራፍቶ ያለው ሙሰኝነት ከእለት ወደ እለት የሕዝቡ የአኖኖር ሁኔታ እያሽቆለቆለ እና እየወረደ እንዲመጣ ካደረጉት ምክንያቶች ውስጥ ተጠቃሽ ሲሆኑ ለኑሮ ውድነቱ ግንባር ቀደም ተጠያቂው መሆን ያለበት ሀገሪቱን እየመራው እና የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እድገት በፍጥነት እያሳደገ እንዳለ የሚያወራው የወያኔ ኢህአዲግ መንግስት ነው:: በነገራችን ላይ የኢህአዲግ መንግስት በየጊዜው ስለ ሀገሪቷ ኢኮኖሚ እድገት የለመደውን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ይለፍልፍ እንጂ ይህን በፍጥነት እያደገ ነው ብሎ ወያኔ የሚያወራለትን የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገት በተመለከተ የተባለው እድገት ከወረቀት ኣልፎ መሬት ላይ የሚታይ ነገር የለም የሚሉ ሰዎች በብዛት የሚገኙ ሲሆን ይህም ሀሳብ እኔንም ጨምሮ ብዙዎች የሚስማሙበት ጉዳይ ነው::
ታስታውሱ እንደሆነ የወያኔ ቁንጮ የነበረው ሟቹ የቀደሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት በአሥር አመት ዉስጥ «ኢትዮጵያ በምግብ እራሷን ትችላለች። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በቀን ሶስቴ እንዲመገብ እናደርጋለን» ብለው ነበር ነገር ግን ይህ የአቶ መለስ ዜናዊ ንግግር የውሃ ላይ ሽታ ሆኖ ቀረ :: በአንጻሩ አቶ መለስ የኢትዮጵያን ሕዝብ በቀን ሶስቴ እንዲመገብ እናደርገዋለን ያሉለት ኢህአዲግ ኢትዮጵያን በብቸኝነት በሀይል መግዛት ከጀመረ ወደ 23 አመታት እየተጠጋ ሲሆን በእነዚህ አመታቶች ውስጥ ምንም የተለወጠ ነገር የለም:: የወያኔ መንግስት በተቆጣጠረው በመገናኛ ብዙሃን እንደሚለፈልፉት የኢትዮጵያ ኢኮነሚው ዕድገቱ በፍጥነት ሽቅብ እየገሰገሰ ሳይሆን ወደታች እያሽቆለቆለ ይገኛል:: ምናልባት የኢኮኖሚ እድገቱ በወረቀት ስሌት ላይ ኑሮ እጅግ መራራ ከመሆኑ የተነሳ የሰዉ የአኖኖር ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ ዉስጥ ዉስጡን የሚያልቁት ወገኖቻችን ብዛት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነዉ።በአሁኑ ሰአት ሕዝቡን የውሃ እጦት፣ የመብራት እጦት፣ የኔት ዎርክ ችግር፣ የትራንስፖርት እንደሚፈልገው አለማግኛት በአጠቃላይ ችግሩ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ በከፍተኛ ሁኔታ ተባብሶ ቀጥሏል:: በይበልጥ የአዲስ አበባን ነዋሪ ክፉኛ ምሪት ውስጥ አስገብቶታል::
በመላው አገሪቱ አዲስ አበባን ጨምሮ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው የውሃ፣የመብራትና የቴሌኮም አገልግሎት ጥራት መጓደልና የአገልግሎት መቋረጥ እንዲሁም በአገሪቷ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የዉጭ ምንዛሪ እጥረት እየታየ ሲሆን በሀገሪቱ ላይ በደረሰው በኢኮኖሚ ችግር የተነሳ ሕዝቡ ያለውን የኑሮ ውድነት መቋቋም በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ በመገኘቱ ነገሮች እየከረሩ በማንኛውም ጊዜና ሰሀት ግባታዊ ሕዝባዊ አመጽ ሊነሳና ትልቅ ችግር ሊፈጠር እንደሚችል የሚሰጉ ብዙዎች ናቸዉ።
በአሁኑ ሰአት እንደሚታየው እና መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥን ይፈልጋል ህዝቡ ሀገሪቱን እየመራ ባለው የወያኔ መንግስት ለመመራት ፍቃደኛ አይደለም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ሮሮ በማሰማት ላይ ይገኛል:: በአሁኑ ሰአት በኢትዮጵያ ውስጥ ከየቦታው የሚሰማው እና የሚታያው የሰበዓዊ መብት ረገጣው አፈናና ግድያው ከጊዜ ወደ ጊዜ ተባብሶ እየቀጠለ ባለበት ሁኔታ በየቀኑ እያሸቀበ የመጣው የኑሮው ውድነቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከወያኔ ኢህአዲግ መንግስት ጋር ሆድ እና ጀርባ ሆነው እንዲቀጥሉ እያደረጋቸው ሲሆን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ የሕዝቡ ንዴትና ቁጣ በከፍተኛ ሁኔታ በመፋፋም ላይ ይገኛል::
ከዚህም የተነሳ መንግስት በየቀበሌው፣በየመስሪያ ቤቱ በሚጠራቸው ማንኛውም ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ለመገኛት ሕዝቡ ፍቃደኛ እና ደስተኛ አይደለም:: ስለዚህም የሕዝቡ ከመንግስት ጋር ሆድና ጀርባ መሆን የወያኔን መንግስት ክፉኛ ጭንቀት ውስጥ የከተተው ጉዳይ ሲሆን በመሆኑም ለመጪው 2007 ለሚደረገው ምርጫ የሕዝቡ በመንግስት ላይ ያለው ጥላቻ እየጨመረ መምጣት እራሱን የቻለ አስተዋጽኦ ሊኖረው እንደሚችል በብዙዎች ዘንድ ይገመታል::
የወያኔ ኢህአዲግ መንግስት ባለስልጣኖች በሚቀጥለው አመት ምርጫ የሕዝቡን ድምጽ እንደማያገኙ በሚገባ ቢረዱትም ነገር ግን የለመዱትን የማጭበርበር እና የሌብነት ልምዳቸውን በመጠቀም ለቀጠይም አመታት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የበላይ በመሆን ሕዝብን እየጨቆኑና እየረገጡ ለመኖር የሚያስችላቸውን ስትራቲጂ በመንደፍ እነሱ እንደሚሉት የጀመሩትን የልማት ዕቅድ ለመተግበር ሳይሆን ኢትዮጵያን የማፈራረስና ኢትዮጵያውነትን የመጥፋት ዘመቻቸውን ለማስቀጠል የሚያረዳቸውን ማንኛውንም እርምጃ ሁሉ ከመውሰድ ወደ ኋላ አንደማይሉ የተረጋገጠ ነው::
እንደ እኔ አስተሳሰብ የወያኔ ኢሕአዲግ መንግስት በምንም ታአምር በምርጫ ተሸንፉ ስልጣኑን በቀላሉ ይለቃል ወይም ስልጣኑን ለተቃዋሚዎች ያጋራል የሚል እምነቱም የለኝም::በአሁኑ ሰአት እንደምናየው እንዲሁ በቀላሉ የኢሕአዲግ መንግስት ስልጣኑን ይለቃል ወይም ለተቃዋሚዎች ያጋራል ብሎ ማሰብ የዋህነትና የማይታሰብ ጉዳይ ቢሆንም ነገር ግን ወያኔና የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆድና ጀርባ እንደሆኑ ለብዙ ጊዜ እንደማይቀጥል በምሪት እና በህልእ የተሞላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጣ ገንፍሎ ወያኔ ዳግም እንዳያንሰራራ ወደ መቃብር ይወስደዋል ብዬ አምናለው:: ስለዚህ የወያኔ መሰሪ አካሂድ ተስፋ ሳያስቆርጠን የወያኔን መንግስት በተገኛው መንገድ ሁሉ በመታገል እና በመቃወም የኢትዮጵያን ሕዝብ ነጻነት ለማረጋገጥ ትግላችንን ማቀጣጣል ይጠበቅብናል::ኢትዮጵያ በቆራጥ ታጋይ ልጆቿ ከወያኔ አገዛዝ ነጻ ትወጣለች!!!
ድል ለሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ !!!
gezapower@gmail.com

በአዲስ አበባ “የእሪታ ቀን” በሚል ስያሜ በ1 ወር ጊዜ ውስጥ ሠላማዊ ሠልፍ ለማድረግ ወሰነ!! ከአዲስ አበባ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ!!

march 20/2014

ከአዲስ አበባ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ!
ኢህአዴግ አገር የመምራት ብቃት እንደሌለው አዲስ አበባ ማሳያ ናት!!

ሌሎች አገሮች ለዋና ከተሞቻቸው ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የየአገሮቻቸው ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ማሳያ በማድረግ አለም አቀፍ ተቋማትንና ጎብኝዎችን በመጋበዝ የከተሞቻቸውን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ያደርጋሉ፡፡
እንዳለመታደል ሆኖ ግን በብዙዎች የአፍሪካ አገራት የአህጉሪቱ መዲና ተደርጋ የምትጠቀሰው አዲስ አበበባችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ ኋላ አየተጎተተች ለኑሮ ምቹ ከሆኑ ከተሞች ምድብ መቀላቀለ ተስኗት ለነዋሪዎቿ የማትመች የፈተና ምድር ሆናለች፡፡
ኢህአዴግ ራሱን ልማታዊ መንግሥት በማድረግ ከሰየመበት ቅጽበት አንስቶ በልማት ሰበብ ዜጎች ከመኖሪያቸውና ቤተሰቦቻቸውን ከሚያስተዳድሩበት የንግድ ቦታ እንዲፈናቀሉ ተደርገዋል፡፡ በከተማይቱ እንዲነሱ የተደረጉት የንግድ ሱቆች በአብዛኛው በኪራይ ቤቶችና በቀበሌ ስም የተመዘገቡ በመሆናቸውም በሱቆቹ በመነገድ ይተዳደሩ የነበሩ ቤተሰቦች ባዶ አጃቸውን እንዲቀሩ ተደርገዋል፡፡
በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለውን የመንገድ ዝርጋታ የተነሳ የተጠና ሥራ ባለመሰራቱ ከፍተኛ የህዝብ ገንዘብ የወጣባቸው መንገዶች ለምረቃ በበቁ በጥቂት ቀናት ልዩነት እንዲፈርሱ ተደርገዋል፡፡ የከተማው ነዋሪ ለሚጠቀምባቸው የመጓጓዣ አውታሮች ተለዋጭ መንገድ ባለመዘጋጀቱም ለተጨማሪ ወጪ ተዳርጓል፡፡ ትራንስፖርት ማግኘት በሁሉም አካባቢዎች አስቸጋሪ በመሆኑ የከተማይቱ የሥራ እንቃስቃሴ ተዳክሟል፡፡ መንግሥት ‹‹የምትታለብ ላም›› በማለት የሚጠራው የኢትዮ ቴሌ ኮም አገልግሎት የለም የሚባልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ጭምር በኢትዮጵ ቴሌኮም የተንቀራፈፈ አገልግሎተ የተነሳ ባንኮችና የተለያዩ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ለደምበኞቻቸው ተገቢውን ግልጋሎተ ማበርከት አልቻሉም፡፡
የከተማይቱ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ችግር የተወሰኑ ሠራተኞች ችግር እንደሆነ ተጠቁሞ ሠራተኞች ለስንብት ቢዳረጉም የኤሌክትሪክ መቆራረጥና ለረጅም ግዜ መጥፋት የከተማይቱ ኢንዱስትሪዎች ፤ንግድ ተቋማትንና ነዋሪውን እያማረረና ህይወቱን እያመሰቃቀለ ከመሄድ ውጭ ምንም አይነት ለውጥ አልታየበትም፡፡ በከተማይቱ ውሃ ማግኘት እንደ ትልቅ እድል መቆጠር ጀምሯል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ የከተማይቱ 75% ነዋሪ ውሃ እንደሚያገኝ ቢናገሩም መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን በተቃራኒው ሆኗል፡፡ ጊዜያቸውን በትምሀርት ገበታቸው ላይ በመገኘት ማሳለፍ ይገባቸው የነበሩ ተማሪዎች ውሃ ለመቅዳት ረዥም መንገድ ለመጓዝ በመገደዳቸው የትምህርት ጊዜአቸው እየተበደለ ይገኛል፡፡
በአጠቃላይ ከተማይቱን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ የከተማይቱ ነዋሪ ለሚገፋው አስቸጋሪ ህይወት ተጠያቂ ነው፡፡ ድርጅቱ አገሪቱን የመምራት ብቃት እንደሌለውም የወቅቱ የአዲስ አበባ ሁኔታ አይነተኛ ማሳያ ነው፡፡
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ የአዲስ አበባ ምክር ቤት የከተማይቱ ነዋሪ እየገፋው የሚገኘውን ፈታኝ ህይወት በማጥናት ህዝቡን በተለይም የከተማውን እና የዙሪያ አካባቢዋን ነዋሪ በማደራጀት በቅርቡ ‹‹የእሪታ ቀን›› በማለት ሰይሞ በ1ወር ጊዜ ውስጥ ሠላማዊ ሠልፍ ለማድረግ የወሰንን መሆኑን እየገለፅን የአዲስ አበባና አካባቢዋ ነዋሪዎች ሰላማዊ ሰልፉ በሚደረግበት ቀን በነቂስ በመውጣት በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ለመግለፅ እንዲዘጋጁ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
ድል የህዝብ ነው
መጋቢት 11 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም
አዲስ አበባ1920578_827198673963262_1874916504_n

መኢአድ የቅድመ ውህደት ፊርማውን አደናቀፈ

March 20/2014

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)                                                     
  UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)
በመኢአድ በኩል የቀረበው ቅድመ ውህደት ያለመፈረም ሰበብ አሳዛኝና የሕዝቡን ጥያቄ ያኮሰሰ ነው!!
ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ  ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ለረዥም ዓመታት የሕዝብ ፍላጎትና  አንገብጋቢ የሆነውን ተቃዋሚዎች ‹‹ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ›› ጥያቄ   ለመመለስ በስትራቴጂና አምስት ዓመት ዕቅድ ውስጥ በማካተት መንቀሳቀስ ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ የውህደት ጉዳይ ለአንድነት ፓርቲ የአንድ ሰሞን ጥያቄ ሳይሆን ስትራቴጂክ ግብ ነው፡፡ የዚሁ አካል የሆነ እንቅስቃሴ በመኢአድና አንድነት ፓርቲዎች መሐከል መካሄድ ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ሂደቱን ለመቋጨት በርካታ ድርድሮችና የደብዳቤ ልውውጦችም  ቢከናወንም እነሆ አሁንም ተጨባጭ ውጤት በተግባር አለመታየቱ የሁለቱም ፓርቲ አባላት በእጅጉ እያሳዘነ ነው፡፡
በተለይ በቅርቡ እየተካሄደ ከነበረው ተግባር መካከል ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)    መጋቢት 1 ቀን 2ዐዐ6 ዓም የተፃፈልንን  ደብዳቤ መሠረት በማድረግ የሁለቱ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች እንዲገናኙ የተጠየቀውን ጥያቄ በደስታና በላቀ መንፈስ  ተቀብለነዋል፡፡ በዚሁ መሠረት      መጋቢት 4 ቀን 2ዐዐ6 ዓም  በሰጠነው የደብዳቤ መልስ ላይ እንደገለጽነው  በአንድነት ፓርቲ እይታ አመራሩ  የፊት ለፊት ውይይት የምንፈልገውና ወሳኝ ጉዳይ በመሆኑ  መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም በመኢአድ ጽ/ቤት በተጠራውና የሁለቱ ፓርቲዎች የብ/ም/ቤት አባላትና የላዕላይ ም/ቤት አባላት በተገኙበት ለታሪክ በተቀረፀ ወሳኝ ስብሰባ ሠፊ የኃሳብ ልውውጦች ተካሂደው የፓርቲዎቹ ከፍተኛ አመራሮች የሚከተሉትን አስገዳጅ የውሳኔ ሃሳብ አቅርበው ነበር፡፡
በዚሁም መሠረት፡-
  1. የሁለቱም ፓርቲዎች አባላት አላስፈላጊ ጥቃቅን ጉዳዮችን በማንሳት ውህደቱን አታጓቱ ውህደት የማትፈፅሙ ከሆነ እኛ አባላት በራሳችን ውህደት እንፈፅማለን የሚል ጥብቅ ተማፅኖና ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል፡፡
  2. በአጠቃላይ የሁለቱ ፓርቲዎች ፕሬዚደንቶችና አደራዳሪ ሽማግሌዎች በገቡት ቃል መሠረት ሐሙስ መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም ቅድመ ውህደት የመግባቢያ ሰነድ እንዲፈረም ከስምምነት ተደርሶ ነበር፡፡
  3. የሁለቱ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች የውህደት አስፈፃሚውን ጠቅላላ ጉባኤ ጠሪ ኮሚቴ አባላት የሚሆኑትን የስም ዝርዝር፣ የፊርማው ስነ ሥርዓት በሚከናወንበት እለት እንዲያመጡ ተስማምተን ነበር፡፡
በከፍተኛ አመራሮችና በሁለቱ ሥራ አስፈፃሚዎች ውሳኔ መሠረት የሁለቱ ፓርቲ ፕሬዝደንቶች ተስማምተው፣ የቅድመ ውህደት መግባቢያ ሰነድ በሁለቱ ፓርቲዎች የድርድር ኮሚቴ አባላት መካከል ተፈራርመን፤ ሆቴል ተከራይተንና ከአዲስ አበባ አስተዳደር የሕዝባዊ ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል  የዕውቅና  ሠነድ አግኝተን  የመጨረሻ የስነ-ስርዓቱን መርሃ-ግብር በመጠባበቅ ላይ እያለን  በድንገት በመኢአድ ፕሬዝደንት  በኩል  በቁጥር መ/ኢ/አ/ድ 278/06 መጋቢት 9 ቀን 2006 ዓ.ም በእለቱ የቅድመ ውህደት ፊርማውን መፈረም እንዳማይችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ ለፓርቲያችን  መድረሱ በእጅጉ አሳዝኖናል፡፡  ከደብዳቤው እንደተረዳነው  መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም የፓርቲዎቹ ከፍተኛ  አመራሮች ከበርካታ የሃሳብ ልውውጥ በኋላ የደረሱበትን ውሳኔ  የሚቀለብስ፣ የሁለቱ ፓርቲዎች ተደራዳሪዎች እየተስማሙ በቃለ ጉባኤ ያፀደቁትንና ከሁሉም በላይ የሁለቱ ፓርቲ  ተደራዳሪዎች ለቅድመ ውህደት ባዘጋጁትና ባፀደቁት የመግባቢያ ሰነዶች ላይ የሰፈሩ ነጥቦችን እንደ አዲስ  በማንሳትና በጥቃቅን ጉዳዮች በመጠመድ የቅድመ ውህደቱ እንዳይፈረም ተደርጓል፡፡ ለዚህ ታሪካዊና የሕዝብ ጥያቄ መደናቀፍ  ምክንያቱ የመኢአድ ፕሬዚንት ሲሆኑ  ይህን ሁኔታ   በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ለሚገኙ  ለሁለቱ ፓርቲዎች አባላት፣  ደጋፊዎች፣ በግል ተነሳሽነትና በሀገር ተቆርቋሪነት ስሜት ሁለቱን ፓርቲዎች ለማደራደር ሲደክሙ ለነበሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎችና ለሕዝቡ ጥሩ ዜና ባይሆንም ላለመፈረሙ   ኃላፊነቱን የሚወስዱት የመኢአድ አመራሮች በተለይም ፕሬዝደቱ  መሆናቸውን  ማሳወቅ እንወዳለን፡፡
በዚህ አጋጣሚ  ለውህደቱ መሳካት የመኢአድ አባላትና ከፊል አመራሩ  እያሳዩ ለሚገኘው ፍላጎትና ጥረት ፓርቲያችን መልካም አክብሮቱን መግለፅ ይወዳል፡፡
መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባ

Thursday, March 20, 2014

Extractive Industries: Transparency Group Rewards Repression

March 20/2014
Ethiopia: Stop Using Anti-Terror Law to Stifle Peaceful Dissent








Ethiopia Approved for Membership Contrary to Rules

Human Rights Watch
(Oslo) – A prominent international natural resource transparency group has damaged its credibility by approving membership for Ethiopia. On March 19, 2014, the governing board of the Extractive Industries Transparency Initiative (EITI), which promotes openness over oil, gas, and mining revenues, admitted Ethiopia as a candidate country despite harsh government repression that has crushed Ethiopia’s once vibrant independent organizations and its independent media.Ethiopia: Stop Using Anti-Terror Law to Stifle Peaceful Dissent
EITI rules call for candidate countries to make a commitment to meaningful participation of independent groups in public debate on natural resource management. Civil society representatives also sit on a national steering committee for EITI.
“The EITI’s decision to admit Ethiopia without insisting on reforms is an affront to the local activists who’ve been jailed or exiled for calling for a more transparent, accountable government,” said Lisa Misol, senior business and human rights researcher at Human Rights Watch. “With this decision, EITI has thrown its principles to the wind and damaged its reputation as a leading good governance group.”
The decision divided members of the EITI board, which includes representatives of governments, companies, and civil society organizations. It also reversed a 2010 decision by the board to defer membership until a draconian 2009 law, still in effect, that sharply limits the activities of independent groups, “is no longer in place.”
Several exiled Ethiopian and international rights advocates called for conditions to be imposed on Ethiopia’s membership bid, but the board did not reach a consensus on such measures.
Under EITI procedures, Ethiopia has three years to prove compliance with the organization’s standards on revenue transparency and other matters. The board can call for an early review based on poor or deteriorating civil society concerns but has never done so.
“EITI’s leadership had an opportunity to stand up for the core principle that civil society participation is a linchpin of good governance,” Misol said. “Instead, it sacrificed EITI’s credibility by allowing Ethiopia to join the ‘transparency’ club despite intense repression.”

በኑሮ ውድነቱ እየተባባሰ መምጣት ኢሕአዲግ እና ሕዝቡ ይበልጥኑ ሆድና ጀርባ ሆነዋል

March 20/2014

ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ

የኢህአዲግ ወያኔ መንግስት   የስልጣን ወንበር በትሩን በሀይል ከተቆናጠጠበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ የአኖኖር ሁኔታ ከእለት ወደ እለት እያሽቆለቆለ እና እየወረደ በመምጣቱ ሕዝቡ ከምቼውም ጊዜ በበለጠ በአሁኑ ወቅት  ኑሮን መቋቋም በማይችልበት አደገኛ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ እና በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የኑሮ ውድነት ተቋቁሞ መኖር ከባድ ፈተና እየሆነባቸው እንደሆነ የችግሩ ሰለባና ተጠቂ የሆኑት ሰዎች በየጊዜው ከሚያሰሙት ሮሮና ጩኸት መረዳት ይቻላል::ይህንንም እየተባባሰ እና እየጨመረ የመጣውን የኑሮ ውድነት ተከትሎ የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን ስራ አስፈፃሚ የተቃውሞ ሰልፍ ሊጠራ  እንደሆነ ታውቋል:: የአንድነት ፓርቲ ሊጠራ ባሰበውና በታቀደው ሰላማዊ ሰልፉም ላይ በስርዓቱ እና በኑሮ ውድነቱ የተማረሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በነቂስ በመውጣት  በምሬት የታመቀ የብሶት ድምጻቸውን  በወያኔ ኢህአዲግ መንግስት  ላይ እንደሚያሰሙ ይጠበቃል:: በአሁኑ ወቅት ጥቂት የስርአቱ  ደጋፊዎች እና የወያኔ ካድሬዎች ካልሆኑ በስተቀር በኑሮ ውድነቱን የተነሳ ተጎጂ ያልሆነና ሕዝቡ ኑሮን መቋቋም በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ በመገኘቱ ስርዓቱን የማያማርር  የህብረተሰብ ክፍል የለም ብል ማጋነን አይሆንብኝም ::

 የወያኔ መንግስት የሚያራምደው ፖሊሲ የመላው ኢትዮጵያን ሕዝቡ ፍላጎት እና ጥቅም ማዕከል ያላደረገ ሲሆን የተወሰኑን የህብረተሰብ ክፍሎችን ብቻ ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል :: መላውን የኢትዮያ ህዝብ እና ክልል ተጠቃሚ ያላደረገው የመንግስት የልማት ስትራቴጂ ፖሊሲ እና በመላው ሀገሪቱ ላይ በስፋት ተንሰራፍቶ ያለው ሙሰኝነት ከእለት ወደ እለት የሕዝቡ የአኖኖር ሁኔታ  እያሽቆለቆለ እና እየወረደ እንዲመጣ ካደረጉት ምክንያቶች ውስጥ ተጠቃሽ ሲሆኑ ለኑሮ ውድነቱ ግንባር ቀደም ተጠያቂው መሆን ያለበት ሀገሪቱን እየመራው እና የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እድገት በፍጥነት እያሳደገ እንዳለ የሚያወራው የወያኔ ኢህአዲግ መንግስት ነው::  በነገራችን ላይ የኢህአዲግ መንግስት በየጊዜው ስለ ሀገሪቷ ኢኮኖሚ እድገት የለመደውን  የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ይለፍልፍ እንጂ ይህን በፍጥነት እያደገ ነው ብሎ ወያኔ የሚያወራለትን የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገት በተመለከተ የተባለው እድገት ከወረቀት ኣልፎ መሬት ላይ የሚታይ ነገር የለም የሚሉ ሰዎች በብዛት የሚገኙ ሲሆን ይህም ሀሳብ እኔንም ጨምሮ ብዙዎች የሚስማሙበት ጉዳይ ነው::

ታስታውሱ እንደሆነ የወያኔ ቁንጮ የነበረው ሟቹ የቀደሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት  በአሥር አመት ዉስጥ «ኢትዮጵያ በምግብ እራሷን ትችላለች። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በቀን ሶስቴ እንዲመገብ እናደርጋለን» ብለው ነበር ነገር ግን ይህ የአቶ መለስ ዜናዊ ንግግር  የውሃ ላይ ሽታ ሆኖ ቀረ :: በአንጻሩ አቶ መለስ  የኢትዮጵያን ሕዝብ በቀን ሶስቴ እንዲመገብ እናደርገዋለን ያሉለት  ኢህአዲግ  ኢትዮጵያን በብቸኝነት በሀይል መግዛት ከጀመረ ወደ 23 አመታት እየተጠጋ ሲሆን በእነዚህ አመታቶች ውስጥ  ምንም የተለወጠ ነገር የለም:: የወያኔ መንግስት በተቆጣጠረው በመገናኛ ብዙሃን እንደሚለፈልፉት የኢትዮጵያ ኢኮነሚው ዕድገቱ በፍጥነት ሽቅብ እየገሰገሰ ሳይሆን ወደታች እያሽቆለቆለ ይገኛል:: ምናልባት የኢኮኖሚ እድገቱ በወረቀት ስሌት ላይ ኑሮ እጅግ መራራ ከመሆኑ የተነሳ የሰዉ የአኖኖር ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ ዉስጥ ዉስጡን የሚያልቁት ወገኖቻችን ብዛት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነዉ።በአሁኑ ሰአት ሕዝቡን የውሃ እጦት፣ የመብራት እጦት፣ የኔት ዎርክ ችግር፣ የትራንስፖርት እንደሚፈልገው አለማግኛት  በአጠቃላይ ችግሩ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ በከፍተኛ ሁኔታ ተባብሶ ቀጥሏል:: በይበልጥ የአዲስ አበባን ነዋሪ ክፉኛ ምሪት ውስጥ አስገብቶታል::

                                                 በአዲስ አበባ ታክሲ ለመያዝ በወረፋ ላይ
                                             
 በመላው አገሪቱ አዲስ አበባን ጨምሮ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው የውሃ፣የመብራትና የቴሌኮም አገልግሎት ጥራት መጓደልና የአገልግሎት መቋረጥ እንዲሁም በአገሪቷ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የዉጭ ምንዛሪ እጥረት እየታየ ሲሆን በሀገሪቱ ላይ በደረሰው በኢኮኖሚ ችግር  የተነሳ ሕዝቡ ያለውን የኑሮ ውድነት መቋቋም በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ በመገኘቱ ነገሮች እየከረሩ በማንኛውም ጊዜና ሰሀት ግባታዊ ሕዝባዊ አመጽ ሊነሳና ትልቅ ችግር ሊፈጠር እንደሚችል የሚሰጉ ብዙዎች ናቸዉ።

በአሁኑ ሰአት እንደሚታየው እና መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥን ይፈልጋል ህዝቡ ሀገሪቱን እየመራ ባለው የወያኔ መንግስት ለመመራት ፍቃደኛ አይደለም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ሮሮ በማሰማት ላይ ይገኛል:: በአሁኑ ሰአት በኢትዮጵያ ውስጥ ከየቦታው የሚሰማው እና የሚታያው የሰበዓዊ መብት ረገጣው አፈናና ግድያው ከጊዜ ወደ ጊዜ ተባብሶ እየቀጠለ ባለበት ሁኔታ በየቀኑ እያሸቀበ የመጣው የኑሮው ውድነቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ  ከወያኔ ኢህአዲግ መንግስት ጋር ሆድ እና ጀርባ ሆነው እንዲቀጥሉ እያደረጋቸው ሲሆን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ የሕዝቡ ንዴትና ቁጣ በከፍተኛ ሁኔታ በመፋፋም ላይ ይገኛል::

ከዚህም የተነሳ መንግስት በየቀበሌው፣በየመስሪያ ቤቱ በሚጠራቸው ማንኛውም ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ለመገኛት ሕዝቡ ፍቃደኛ እና ደስተኛ አይደለም:: ስለዚህም የሕዝቡ ከመንግስት ጋር  ሆድና ጀርባ መሆን የወያኔን መንግስት ክፉኛ ጭንቀት ውስጥ የከተተው ጉዳይ ሲሆን በመሆኑም ለመጪው 2007 ለሚደረገው ምርጫ የሕዝቡ በመንግስት ላይ ያለው ጥላቻ እየጨመረ መምጣት እራሱን የቻለ አስተዋጽኦ ሊኖረው እንደሚችል በብዙዎች ዘንድ ይገመታል::

                                               በአዲስ አበበ የውሃ ወረፋ

 የወያኔ ኢህአዲግ መንግስት ባለስልጣኖች በሚቀጥለው አመት ምርጫ የሕዝቡን ድምጽ እንደማያገኙ በሚገባ ቢረዱትም ነገር ግን የለመዱትን የማጭበርበር እና የሌብነት ልምዳቸውን በመጠቀም ለቀጠይም አመታት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የበላይ በመሆን ሕዝብን እየጨቆኑና እየረገጡ ለመኖር የሚያስችላቸውን ስትራቲጂ በመንደፍ እነሱ እንደሚሉት የጀመሩትን የልማት ዕቅድ ለመተግበር ሳይሆን ኢትዮጵያን የማፈራረስና ኢትዮጵያውነትን የመጥፋት ዘመቻቸውን ለማስቀጠል የሚያረዳቸውን ማንኛውንም እርምጃ ሁሉ ከመውሰድ ወደ ኋላ አንደማይሉ የተረጋገጠ ነው::

 እንደ እኔ አስተሳሰብ የወያኔ ኢሕአዲግ መንግስት በምንም ታአምር በምርጫ ተሸንፉ ስልጣኑን በቀላሉ ይለቃል ወይም ስልጣኑን ለተቃዋሚዎች ያጋራል የሚል እምነቱም የለኝም::በአሁኑ ሰአት እንደምናየው እንዲሁ በቀላሉ የኢሕአዲግ መንግስት ስልጣኑን ይለቃል ወይም ለተቃዋሚዎች ያጋራል ብሎ ማሰብ የዋህነትና የማይታሰብ ጉዳይ ቢሆንም ነገር ግን ወያኔና የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆድና ጀርባ እንደሆኑ ለብዙ ጊዜ እንደማይቀጥል በምሪት እና በህልእ የተሞላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጣ ገንፍሎ ወያኔ ዳግም እንዳያንሰራራ ወደ መቃብር ይወስደዋል ብዬ አምናለው:: ስለዚህ የወያኔ መሰሪ አካሂድ ተስፋ ሳያስቆርጠን የወያኔን መንግስት በተገኛው መንገድ ሁሉ በመታገል እና በመቃወም የኢትዮጵያን ሕዝብ ነጻነት ለማረጋገጥ ትግላችንን ማቀጣጣል ይጠበቅብናል::ኢትዮጵያ በቆራጥ ታጋይ ልጆቿ ከወያኔ አገዛዝ ነጻ ትወጣለች!!!

      ድል ለሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ !!!

      gezapower@gmail.com

የአዲስ አበባ የዉሃ ችግር

March 20/2014










የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግርን በተመለከተ የአባይን ልጅ ውሃ ጠማው እንዲሉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከተማዋ በርካታ አካባቢዎች ውሃ በፈረቃ የሚያገኙበት ያልታወጀ አሰራር እየተስተዋለ ነው። ብዙ አካባቢዎች ከ24 ሰዓታት በላይ የመጠጥ ውሃ በተደጋጋሚ በመጥፋቱ ነዋሪዎች መደበኛ ሥራዎቻቸውን ጭምር በመተው ጄሪካን ይዘው ውሃ ፍለጋ ከቦታ ቦታ የሚንከራተቱበት ትይዕንት አዲስነቱ እየቀረ የመጣ ይመስላል።

አቶ ድሪባ ኩማ ግን በያዝነው በጀት ኣመት ትኩረት ከተሰጣቸው ተግባራት አንዱ የውሃ ምርትን መጨመር መሆኑን ይናገራሉ። “በበጀት ዓመቱ በአቃቂ ዋልፊልድ የ19 ጥልቅ ጉድጓዶች ቁፋሮ እና ተያያዥ ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ። ከእነዚህ
ጉድጓዶች 70ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ ለማምረት ታቅዶ 80ሜትር ኪዩብ ማምረት ተችሎአል። በቅርቡ የውሃ ማሰባሰቢያ ሪዘርባየር ሥራው እንደተጠናቀቀ ምርቱ ወደ ሥርጭት ይገባል።
ከዚህም በተጨማሪ በለገዳዲ ዊልፊልድ የ11 ጉድጓዶች ሲጠናቀቅ እስከ 40ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ ማምረት ያስችለናል። እንዲሁም የለገዳዲ ማጣሪያ ጣቢያን በማስፋትና የድሬ ግድብን በማሻሻል የማጣሪያ ጣቢያውን የማምረት አቅም ወደ 195ሺ ለማሳደግ የሚያስችሉ ሥራዎች እየተሰራ ነው። የድሬ ግድብ ሲጠናቀቅ 30ሺ ሜትር ኪዩብ የውሃ ምርት የምናገኝበት ሲሆን ይህ የማስፋፊያ ግንባታ በ2007 ዓ.ም ክረምት ውሃ መያዝ ጀምሯል። እንዲሁም 70ሺ ሜትር ኪዩብ ማምረት የሚያስችል የ24 ጥልቅ ጉድጓዶች ቁፋሮና ተያያዥ የሲቪል ሥራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል። በዚህ ፕሮጀክት
እስካሁን ድረስ ከተጠናቀቁ 16 ጉድጓዶች ብቻ 94ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ ማግኘት ተችሏል።
ይህም ከፕሮጀክቱ ከሚጠበቀው 70ሺ ሜትር ኪዩብ በላይ ነው። ስለሆነም የተጀመሩ የሲቪልና መካኒካል ሥራዎች እንደተጠናቀቁ ምርቱ ወደሥርጭት ይገባል። በአጠቃላይ ወደ 260ሺ ሜትር ኪዩብ የሚጠጋ ውሃ ማምረት የሚያስችል ሥራ እተሰራ ነው። ይህ ማለት እስከአሁን በቀን በአማካኝ የውሃ ምርታችን 359ሺ ሜትር ኪዩብ ሲሆን አሁን ያገኘነው 260ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ ወደስርጭት ሲገባ የከተማዋ ውሃ አቅርቦት ችግር ይፈታል፤ የውሃ ምርታችንም ወደ610ሺ ሜትር ኪዩብ ያድጋል ብለዋል።
የውሃ አቅርቦት እጥረት ባለባቸው ዳገታማ አካባቢዎች ጊዜ የማይሰጡ አጣዳፊ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ እስከ30ሺ
ሜትር ኪዩብ ውሃ የሚይዙ 50 ትላልቅ የውሃ ታንከሮችና 20 ቦቴዎችን የማቅረብ ሥራ ተጀምሯል። በተጨማሪም በአንዳንድ አካባቢዎች የውሃ ጉድጓዶች በስፋት በመቆፈር ውሃን ማምረት እንዲቻል 5 ዘመናዊ ሪጎች ከኢትዮጵያ ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ የፌዴራል መንግስት ገዝተው ለከተማ አስተዳደር ድጋፍ አድርጓል።
ከረዥም ጊዜ አኳያ የውሃ አቅርቦት ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት የገርቢ ግድብ ጥናት ተጠናቆ ለግንባታ ሚሆን ፋይናንስ
እየተፈለገ ሲሆን በቅርቡ ወደግንባታ ይገባል። የአዲስ አበባ ውሃ አቅርቦትን ከ25-30 ዓመት ድረስ የሚቃለልበት ሌሎች ተጨማሪ ግድቦችን ለመሥራት ጥናቶች መጀመራቸውን ከንቲባው በመግለጽ መጪው ጊዜ ብሩህ መሆኑን
በንግግራቸው አመላክተዋል።

የኢትዮጵያ ተተኪ ሴቶች ትውልድ መነሳሳት! (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

March 20, 2014
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

“ከዚህ በኋላ ትዕግስታችን ተሟጧል!”

ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ እንደገና ወኔ የተሞላበት የትግል መንፈሱን በማደስ ጥንካሬውን አሳየ !
Semayawi party female youth activists released
እ.ኤ.አ ማርች 9/2014 የተከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች በዓል ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ከተማ ተዘጋጀቶ በነበረው የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሴቶችም ተሳትፎ አድርገው ነበር፡፡ ከዴሞክራሲያዊ ምርጫ ባፈነገጠ መልኩ በኃይል በስልጣን ኮርቻ ላይ ተፈናጥጠው ስልጣንን የሙጥኝ በማለት ከህግ አግባብ ውጭ በህዝብ ላይ ደባ በመፈጸም ላይ የሚገኙትን የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ዕኩይ ምግባር የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲገነዘበው በማሰብ ወጣት ሴቶቹ እውነታውን ያለምንም መሸፋፈን በማጋለጥ እምቢ አሻፈረኝ በማለት ተቃውሟቸውን ለዓለም በይፋ አሰምተዋል፡፡ እንዲህ በማለትም ተቃውሟቸውን አጠናክረዋል፣
“ከዚህ በኋላ ትዕግስታችን ተሟጧል! ተርበናል! ነጻነት እንፈልጋለን! ነጻነት እንፈልጋለነ! እስክንድር ይፈታ! አንዷለም ይፈታ! አቡባከር ይፈታ! ርዕዮት ትፈታ! የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ ይፈቱ! ፍትህ እንፈልጋለን! ነጻነት! ነጻነት! ነጻነት! አትከፋፍሉን! ኢትዮጵያ አንድ ነች! አንድ ኢትዮጵያ! ከዚህ በኋላ ትዕግስታችን ተሟጧል! ውኃ ናፈቀን! መብራት ናፈቀን! ተርበናል!…“
ለሰማያዊ ፓርቲ ሴት ወጣት አመራሮች ባርኔጣዬን ዝቅ በማድረግ ከወገቤ ጎንበስ በማለት ያለኝን አድናቆት ልገልጽላቸው እፈልጋለሁ፡፡ በእነርሱ እጅጉን ኮርቻለሁ፡፡ ባለፉት ጥቂት ወራት ሰማያዊ ፓርቲን ለምን እንደደገፍኩ እና በጽናትም ከፓርቲው ጎን ለምን እንደምቆምኩ በርካታ ሰዎች ጥያቄዎችን አቅርበውልኝ ነበር፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ቁጥር አንድ አድናቂ (አንደኛ ቲፎዞ) ለምን እንደሆንኩ ማንም ቢሆን ጥያቄዎች ካሉት/ካሏት ይህንን ቪዲዮ (እዚህ ይጫኑ) እንዲመለከቱት እጋብዛለሁ፣ እናም መልሱን ከእዚያው ያገኙታል፡፡
አረመኔው ገዥ አካል በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያን ወጣት ሴቶች እና ወንዶች በዱላ እየደበደበ እና እንደ እባብ እየቀጠቀጠ ሁሉንም የጭቆና ዓይነቶች በእነርሱ ላይ እየተገበረ ባለበት ሁኔታ ከዳር ቆሜ ለመመልከት ህሊናዬ ሊፈቅድልኝ አይችልም፡፡ የመናገር መብታቸውን ተጠቅመው ሀሳባቸውን ለመግለጽ በመሞካራቸው ምክንያት ብቻ የኢትዮጵያ ወጣቶች ሲታሰሩ፣ ሲደበደቡ፣ ሲሰቃዩ እና ግፍ ሲፈጸምባቸው በዝምታ አልመለከትም፡፡ በወጣቶቹ ላይ የሚፈጸመውን ግፍ እና ስቅይት የእነርሱ ድምጽ በመሆን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እናገራለሁ፡፡
ወጣት ሴቶቹ ተቃውሟቸውን የገለጹት በሰላማዊ መንገድ ነው፡፡ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን በማሰማታቸውም በጨካኙ የገዥ አካል ማሰቃየት ተፈጽሞባቸዋል፡፡ በሰላማዊ እና ከአመጽ በጸዳ መልኩ በአገሪቱ ውስጥ ለውጥ ለማምጣት ሲሉ ነው በአሁኑ ጊዜ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በመሰቃየት ላይ የሚገኙት፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ሴት ወጣት አመራሮች እና አባላት እንደማንኛውም ሰው ሁሉ የ5 ኪ/ሜ ሩጫውን ተቀላቀሉ፡፡ በሰላማዊ መንገድ እሮጡ እና ከማጠናቀቂያ ቦታው ደረሱ፡፡ ምንም ዓይነት ህግ አልጣሱም፡፡ አንድም ጠጠር አልወረወሩም፡፡ በማንም ላይ ጥቃት አልፈጸሙም፡፡ ምንም ዓይነት ሁከትን በሚያመጡ ተግባራት ላይ አልተሳተፉም፡፡ ከአንድ ሺህ በላይ ሯጮች በተሳተፉበት በዚያ ሩጫ ላይ የሰማያዊ ፓርቲ ሴት ወጣት አመራሮች እና አባላት በመሳተፋቸው (ወይም በሌላ ምክንያት) በአንድም ሰው ላይ ጉዳት አልደረሰም፡፡ ቅንጣት ያህል ንብረት ላይ ጉዳት አልተፈጸመም፡፡ አንድም ባለስልጣን ማስፈራሪያ አልደረሰበትም ወይም ደግሞ የጥቃት ሰለባ አልሆነም፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ሴቶች ምንም ዓይነት የዘለፋ ቃላት እንኳ አልተጠቀሙም፡፡ ሁሉምን ነገር በሰላማዊ መንገድ፣ ሞገስን በተላበሰበ መልኩ እና በሚያስደምም ሁኔታ ነው ያከናወኑት፡፡ እነዚያ ጀግና ወጣት ሴቶች የምርጥ ተደናቂነት ተምሳሌት ቀንዲል ናቸው! በእነዚህ ወጣቶች እጅግ ኮርቻለሁ እናም ባርኔጣዬን ዝቅ በማድረግ አድናቆቴን ልገልጽላቸው እፈልጋለሁ፡፡
በዕለቱ የተከበረውን በዓል ኃላፊነት በመውሰድ ያዘጋጀው የገዥው አካል የሴቶች፣ የህጻናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር ነበር፡፡ የገዥው አካል የዕለቱ መፈክር “የምርጥ ሴቶች የመጀመሪያው ዙር የ5 ኪ/ሜ ሩጫ“ የሚል ነበር (ምን ለማለት እንደተፈለገ ግልጽ ባይሆንም)፡፡ ገዥው አካል ዕለቱ ከ10,000 በላይ ሴቶችን እና ልጃገረዶችን ያሳትፋል በማለት ዲስኩር አድርጎ ነበር፡፡ ገዥው አካል በበዓሉ ዕለት ሴቶች እንዲሳተፉ በስፋት የጥሪ ማሳሰቢያ ሲያደርግ ጠንካራዎቹ የሰማያዊ ፓርቲ ሴት ወጣት አመራሮች ማሳሰቢያውን ሊሰሙት እንደሚችሉ እረስቶት ኖሯል፡፡ መንፈሰ ጠንካራዎቹ ወጣት ሴቶች ግን ማድረግ ያለባቸውን ነገር በሚያስደምም ሁኔታ አደረጉት፡፡ ወጣት ሴቶቹ ለገዥው አካል ፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሳይሆን ብጫ ካናቴራ በመልበስ ተልዕኳቸውን ሲፈጽሙ ታይተዋል፡፡ እዚያ የተገኙት ለመሮጥ ነበር፣ ለነጻነታቸው ለመሮጥ፣ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ለመሮጥ፣ የኢትዮጵያ እስረኞች እንዲፈቱ ለመሮጥ፣ በመሰቃየት ላይ ላለው እና ተስፋ ለራቀው ህዝብ ትኩረት በመሳብ  ለመሮጥ፡፡ ወጣቶቹ የሰማያዊ ፓርቲ ሴቶች አረመኒያዊ እና ጨካኝ እየተባለ በሚታወቀው ገዥው አካል ፊት ደፋርነታቸውን ማሳየት መቻላቸው ብቻ አይደለም አስደናቂ የሚሆነው ሆኖም ግን የእራሳቸውን የብልህነት ፈጠራ በመጠቀም የስርዓቱን ዕኩይ ምግባር በማጋለጣቸው ጭምር እንጅ፡፡
የአምስት ኪሎ ሜትሩ ሩጫ ከተጠናቀቀ በኋላ ሰባት የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሴቶች በቁጥጥር ስር ውለዋል፣ ተደብድበዋል እንዲሁም ለእስር ተዳርገዋል፡፡ የሰብአዊ መብት እረገጣው ሰለባ ከሆኑት ውስጥ፡ ሜሮን ዓለማየሁ፣ ምኞቴ መኮንን፣ መታሰቢያ ተክሌ፣ ወይኒ ንጉሴ፣ ንግስት ወንድይፍራው፣ ወይንሸት ሞላ፣ እና እመቤት ግርማ ይገኙበታል፡፡ በሰማያዊ ፓርቲ በከፍተኛ የስልጣን እርከን ላይ የሚገኙ  ጌታነህ ባልቻ (የድርጅተ ጉዳይ ኃላፊ)፣ ብርሀኑ ተክለያሬድ (የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ) እና አቤል ኤፍሬም (የህዝብ ግንኙነት ኮሚቴ አባል) የተባሉ ሌሎች ሶስት ወጣት ወንዶች ደግሞ እስረኛ ሴቶች ያሉበትን ሁኔታ ለመጠየቅ  በሄዱ ጊዜ በቁጥጥር ስር ውለው እነርሱም ለእስር ተዳርገዋል፡፡
የጣይቱ እና የምኒልክ ልጆች በይስሙላው/በዝንጀሮዎች (ካንጋሩ ኮርት) ፍርድ ቤት፣
በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል የይስሙላ ፍርድ ቤት ስርዓት በአገሪቷ ዘርግቶ በመተግበር ላይ ይገኛል በማለት ሁልጊዜ ስናገረው የቆየሁት ጉዳይ ነው፡፡ በሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ላይ የተመሰረቱት “ክሶች” የገዥው አካል የይስሙላ ፍርድ ቤቶች እንዴት ባለ ሁኔታ እየተካሄዱ እንዳሉ ከምንም ጥርጣሬ በላይ በግልጽ ያመላክታሉ፡፡ በሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ላይ የተመሰረቱት ክሶች በባዶው የትወና መድረክ ላይ ብቻ የሚከናወኑ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የይስሙላው ፍርድ ቤት  እ.ኤ.አ ማርች 14/2014 ያደረገው የሁለተኛው ቀን “የችሎት” ትወና በሳሙኤል በኬት፣ ኢጀን ኔስኮ፣ ጂን ገነት ወይም ካፍካ ላይ የተደረገ ያለቀለት የትያትር ትወና ይመስል ነበር፡፡ የህጋዊነት ትወናው በምግባር የለሾች፣ በስም የለሾች፣ የማስተዋል ብቃት በሌላቸው፣ በህሊና የለሾች፣ በሀሳብ የለሽ ደነዞች፣ታማኝነት በሌላቸው ፖለቲከኞች እና ዋናው ተግባራቸው ህዝቡን ማሰቃየትን እና መከራ ማሳየትን እንደመርሀ የሚከተሉ አስመሳዮች በግልጽ በማይታይ መልኩ የሚጦዝ የውሸት የህጋዊነት ሽፋንን ተላብሶ እየተተገበረ ያለ ኃላፊት የጎደለው እና የተዋረደ የመድረክ ተውኔት ነው፡፡ ፍትህ ፊት የሌላት እና ቅርጿ የተበላሸ የይስሙላ ስርዓት ዘርግታ ትገኛለች፡፡ ፍትህ በሚያስገርም ሁኔታ በመደምሰሷ ምክንያት አካል የላትም፡፡ በኢትዮጵያ የፍትህ ፊት እና አካል በይስሙላው ፍርድ ቤት በርቀት በቁጥጥር ስልት መጠቀሚያ መሳሪያ ተይዞ የሚመራ እና በጌቶቹ ትዕዛዝ እንዲያደርግ የተሰጠውን ብቻ ያለምንም ኃፍረት ተቀብሎ እንደበቀቀን የሚደግም የሮቦት ዳኛ (አንደየተሞላ አሻንጉሊት) የተሰማራበት ሆኗል፡፡ የፍትህ አካሉ በዘራፊዎች ቁጥጥር  ስር ዉሎአል፡፡
በ “ችሎቱ” ክፍል እንደ አንድ ተመልካች ዘገባ ከሆነ “የማታ” በሚል ስም የሚታወቅ “የፖሊስ መርማሪ” የሰማያዊ ፓርቲ ሴቶች የጣይቱ ልጆች ነን (የ19ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ንግስት የነበሩት) እና የእምዬ ምኒልክ ልጆች ነን (በ19ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ንጉስ እና የንግስት ጣይቱ ባለቤት የነበሩት) በማለት በአደባባይ በመጮህ በሽብር ተግባር ላይ ተዘፍቀው ታይተዋል በማለት የምስክርነት ቃሉን ሰጥቷል፡፡ “መርማሪው” በተጨማሪም ተከሳሾቹ እየተራቡ ያሉ መሆናቸውን እና የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ እንዲሁም በእስር ላይ የሚገኙት ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች ማለትም ርዕዮት፣ እስክንድር፣ አንዷለም እንዲሁም ሌሎች እንዲፈቱ” እያሉ በአደባባይ ጩኸት እያሰሙ ነበር ብሏል፡፡ እንግዲህ ይኸ ነው በሰማያዊ ፓርቲ ሴቶች ተፈጸመ የተባለው “የሽብር ተግባር” ይዘት፡፡
የችሎት ስነስርዓቱ ከታቀደለት በአንድ ሰዓት ዘግይቶ ነው የተጀመረው፣ ምክንያቱም የሰማያዊ ፓርቲ ሴቶች በሰልፉ ላይ ለብሰዋቸው የነበሩትን ካናቴራዎች ወደ ችሎቱ ሲቀርቡ እንዲቀይሯቸው ቢጠየቁም ለመቀየር ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ነበር፡፡ ፖሊሱ እስረኞቹን ከነካናቴራቸው ወደ ፍርድ ቤቱ እንዲቀርቡ መፍቀድ የፖለቲካ እምቢተኝነትን አምኖ እንደመቀበል ያስቆጥራል የሚል እምነት አደረበት፡፡ እንደ ዘገባው ከሆነ ሴቶቹ ወደ “ፍርድ ቤቱ” ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት የለበሷቸውን ካናቴራዎቻቸውን በማስገደድ እንዲቀይሩ ለማድረግ ፖሊ ሁከት ፈጥሮ እንደነበሩ ታውቋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሴቶች እስከሚወሰዱ ድረስ በተያዙበት ቦታ እንዲቆዩ ተደርገዋል፡፡ “የፍርድ ቤቱ” ክፍል በተመልካች ተጨናንቋል፣ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችም በሙሉ ተገኝተው ነበር፡፡
የፌዴራል አቃቤ ህግ ጉዳዩን ለመመርመር እና መረጃ ለማሰባሰብ ተጨማሪ የ14 ቀናት ጊዜ እንዲሰጠው ሴት እስረኞችም በእስር እንዲቆዩ ጠየቀ፡፡ (በቁጥጥር ስር የማዋል ልምድ እና ተጠርጣሪን በእስር ቤት አውሎ ለጥፋተኝነት መረጃዎችን ለመፈለግ መሞከር የገዥው አካል የይስሙላው ፍርድ ቤት አሰራር ዋናው መለያ ባህሪው ነው፡፡ አንድ ተጠርጣሪ ፍርድ ቤት ከመቅረቡ በፊት የሚደረገው አሳፋሪ ዘዴ በእያንዳንዱ ከፍተኛ የወንጀል ጉዳይ ከሁለት ደርዘን ወይም ከዚያ በላይ በሚሆኑ በቀድሞዎቹ ባለስልጣኖች እና ባለፈው ዓመት ደግሞ በንግዱ ማህበረሰብ አባላት ላይ ሙስና በሚል ሰበብ የተደረገው እስራት ሲታይ ገዥው አካል ካለፉት አስርት ዓመታት በላይ ሲፈጽመው የቆየ ተግባር መሆኑን ነው፡፡ አቃቤ ህጉ እስከ አሁንም ድረስ ለሙስናው መረጃ ፍለጋ በሚል ሰበብ ጊዜ እየነጎደ በሄደ ቁጥር እነርሱ በእስር ቤት ተረስተዋል፣ ገዥው አካል ጉዳዩን ለሁለት ዓመታት ያህል ምርመራ እየተካሄደበት ነው በማለት በይፋ የገለጸ ቢሆንም)፡፡
የይስሙላ አቃቤ ህጉ ለሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች የዋስትና መብት መሰጠት እንደሌለበት ተከራክሯል፣ ምክንያቱም “ዋስትናው ከተሰጠ አሁን በፖሊስ ቁጥጥር ስር ያሉት ታሳሪዎች መረጃዎችን ያጠፋሉ፣ እናም ምስክሮች የምስክርነት ቃላቸውን እንዳይሰጡ በማንገራገር እና በማስፈራራት እንዳይመሰክሩ ሊያደርጉ ይችላሉ” ብለዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ መከላከያ ጠበቃ አቶ ዓለሙ ጎቤቦ (በእስር ቤት የምትገኘው እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅናን ያተረፈችው ርዕዮት ዓለሙ አባት) ጉዳዩ የፖለቲካ ባህሪ ያለው ስለሆነ ልጆቹ የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ ከውጭ ሆነው እንዲከራከሩ እንዲደረግ በማለት የክርክር ጭብጣቸውን አቅርበዋል፡፡ ቀጥለውም እንደ ህጉ ከሆነ ደንበኞቼ የዋስትና መብት እንዲያገኙ ይፈቅዳል፣ እናም ይህንን ላለማድረግ እየተከናወነ ያለው የዳኞቹ ተቃውሞ ተጠርጣሪዎቹን በእስር ቤት ለማማቀቅ የተደረገ ደባ ነው ብለዋል፡፡ “ዳኛው” የዋስትና ጥያቄውን አልተቀበሉትም፣ እናም የዳኝነት ሂደቱን ቀጠሉ፡፡ (ባለፉት በርካታ ከፍተኛ የሆኑ የፍርድ ቤት ጉዳዮች የፍርድ ሂደት ላይ እ.ኤ.አ የ2006 የቅንጅት ፓርቲ አመራሮችን “የፍርድ ሂደት” ጉዳይ ጨምሮ ገዥው አካል ምስክሮችን በማስፈራራት፣ ጉቦ በመስጠት፣ በሙስና አማልሎ ተጽዕኖ በማሳደር እና ከህግ አግባብ ውጭ በሆነ መልኩ ቃለመሃላን በመጣስ የውሸት የምስክርነት ቃል እንዲሰጡ በማድረግ ዕኩይ ምግባር ላይ ተዘፍቆ ይገኛል)፡፡
እንደ ፍርድ ቤት ተመልካች ታዛቢዎች ከሆነ የሰማያዊ ፓርቲ ሴቶች በእስር ቤቱ ውስጥ በቁጥጥር ስር ሆነው እያለ ከህግ አግባብ ውጭ በፖሊስ እና በደህንነት ኃላፊዎች አካላዊ ጉዳት እንደደረሰባቸው እንዲሁም የማስፈራራት ሰለባ እንዲሆኑ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ለይስሙላው ፍርድ ቤት ተናግረዋል፡፡ በሌሎች የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ላይ ቅጥረኛ እና ሰላይ እንዲሆኑ ብዙ ገንዘብ ቀርቦላቸዋል፡፡ ከተከሳሾቹ መካከል ትዕግስት ወንድይፍራው የተባለችው ባለፈው እኩለ ሌሊት ላይ ሶስት ወንድ ፖሊሶች እርሷ ወደታሰረችበት ክፍል መጥተው እንድትወጣ ትዕዛዝ እንደሰጧት “ለፍርድ ቤቱ” ተናግራለች፡፡ ከኃላፊዎች መካከል አንደኛው ዱላ በማንሳት በማወዛወዝ ካልተባበረች በስተቀር እስክትሞት ድረስ እንደሚደበድቧት ማስፈራራታቸውን ገልጻለች፡፡ ሌሎችም ሴቶች ተመሳሳይ የማስፈራሪያ ዛቻ እንደተፈጸመባቸው ተናግረዋል፡፡ ፖሊስ ሴቶቹ በሰማያዊ ፓርቲ ላይ የሚያደርጉትን ንቁ የአባልነት ተሳትፎ እና ጓዳዊ የትግል መንፈስ እንዲተው እና ከድጊታቸው እንዲታቀቡ በመደብደብ እንዳዋረዳቸው እና እንዳስፈራራቸው ያላቸውን ምሬት ገልጸዋል፡፡ በተመልካቾች ዕይታ “ብቃት የለሽ” ተብሎ የተፈረጀው የዕለቱ የችሎት ዳኛ ፖሊስ ምርመራውን አጠናቅቆ እ.ኤ.አ ለመጋቢት 18/2014 እንዲቀርብ ትዕዛዝ በመስጠት አሰናብቷል፡፡
በይስሙላው ፍርድ ቤት ያለውን ኃይል መገዳደር፣
የሰማያዊ ፓርቲ ሴቶችን በቁጥጥር ስር የማዋል እና የፍርድ ሂደታቸው እንዲታይ ማድረግ እ.ኤ.አ በ2015 ይካሄዳል ተብሎ በሚታሰበው አገር አቀፋዊ ምርጫ ሰማያዊ ፓርቲ እንዳይሳተፍ እና ለመዝጋት በደጋኑ የተተኮሰ የመጀመሪያው ቀስት ነው፡፡ ገዥው አካል ለሰማያዊ ፓርቲ የሚያስተላልፈው መልዕክት ግልጽ እና ግድፈት ሊደረግበት የማይችል ሀቅ ነው፡፡ ይህም ሁኔታ በአንክሮ ሲታይ በቅርቡ ባረፉት በአቶ መለስ ዜናዊ የተጻፈው የባለ ሶስት ድርጊት የረዥም ጊዜ ተውኔት ተከታይ ነው፡፡ እነዚህ የተውኔት ድርጊቶችም እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡ ድርጊት አንድ፡ “ምርጫው” ከመድረሱ በፊት የሰማያዊ ፓርቲ, አመራሮችን እና አባላትን የይስሙላውን ፍርድ ቤቶች በመጠቀም ማሰቃየት፣ ማስፈራራት፣ ሽባ እና አቅመቢስ ማድረግ፡፡ በዚያ መንገድ ሌላ ተጨማሪ የኃይል እርምጃዎች ቢወሰዱ በህዝቡ ዘንድ የተለመደው አካሄድ እንጅ የበቀል እርምጃ አይደለም የሚል እንደምታ እንዲኖር ከመሻት የመነጨ ነው፡፡ ድርጊት ሁለት፡ ምርጫው ከመድረሱ ጥቂት ወራት በፊት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን እና አባላትን ሰብስቦ በእስር ቤት ማጎር፡፡  ይሄም የይስሙላውን ፍርድ ቤት አንደውነት የፍርድ ሸንጎ የሚሰራ ለማስመሰል ነው፡፡ ድርጊት ሶስት፡ ከምርጫ በኋላ እ.ኤ.አ በ2005  (1997 ምርጫ) የተደረገውን  ጭፍጨፋ ድርጊት መድገም ነው፡፡!
የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን እና አባላትን የህግ ሂደት እና ጥቃት በተመለከተ ሁለት አማራጮች አሉ፡፡ 1ኛ) በይስሙላው ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደት ላይ ተስፋ በመቁረጥ እራስን መነቅነቅ እና በመሰላቸት ጥሎ መሄድ 2ኛ) እንደ ኪልኬኔ አገር ድመቶች ከይስሙላው ፍርድ ቤት ጋር ጎሮሮ ለጉሮሮ መተናነቅ እና የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን እና አባላትን መብት ማስከበር፡፡
ገዥው አካል ኢትጵያውያን እና ሌሎች በይስሙላው ፍርድ ቤት የውሸት ማስመሰያ ምክንያት እራሳቸውን በመነቅነቅ ሁሉንም ነገር ይተውታል ወይም ደግሞ ትችት በመስጠት ብቻ ጥለው ይሄዳሉ የሚል እሳቤ ላይ የተንጠለጠለ ነው፡፡ ገዥው አካል በጊዜ ሂደት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችም እንደ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ አንዷለም አራጌ፣ አቡባከር አህመድ እና ሌሎችም  በእስር ቤት ታጉረው “ይረሳሉ” የሚል ስሌት አለው፡፡ ገዥው አካል የይስሙላው የፍርድ ቤት ማስፈራሪያ ዘመቻ በከፍተኛ ውጤታማነት እና ብቃት ላይ ተመስርቶ የሚቀጥል ላለመሆኑ ትንሽም እንኳ ቢሆን ጥርጣሬ የለዉም፡፡
የሰላማዊ ትግል ዋና ዓላማው የጨቋኙን አካል ተቋማት እና ህጎች በመጠቀም በጨቋኙ አካል ላይ ትግሉን በሰላማዊ መልኩ በማፋፋም መቀጠል ነው፡፡ በአጠቃላይ መልኩ ሲታይ ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ያለው ምንም ዓይነት የተፈጸመ ስህተት የለም፡፡ በገዥው አካል የይስሙላው ፍርድ ቤቶች ዘንድ የፍትህን ጥላ እንኳ ማግኘት እንደማይችል ማንም መገመት ይችላል፡፡ ማንም ቢሆን በውሸት እምነት ላይ በተመሰረተው የይስሙላው ፍርድ ቤት ፍትህ ሰበብ መሰቃየት የለበትም፡፡ ወደፊት ምን ሊከሰት እንደሚችል በእርግጠኝነት እናውቃለን፡፡ የክስ ሰነዱ ቀደም ሲል ተጽፎ ተዘጋጅቷል፣ በግልጽ ለመናገር ቀደም ሲል የነበረዉን የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ክስ ስማቸውን በመለወጥ፣ በማደስ እና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮችን በማካተት የክስ ሰነዶቹ እነዚህን ለመዳኘት በስራ ላይ ይውላሉ (በግልጽ አባባል ለማጥቂያነት ይውላሉ)፡፡
ያንን ትያትር ቀደም ሲል አይተነዋል፡፡ ክስ የቀረበባቸው የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት በየጥቂት ሳምንታት ልዩነት ከማጎሪያ እስር ቤቶች ወደ የይስሙላው ፍርድ ቤት እንዲመላለሱ ይደረጋል፡፡ የገዥው አካል አቃቤ ህግ ማስረጃ ለመፈለግ (የሩጫው ዕለት የተጠናቀቀ ስለሆነ እና ሌላ ተጨማሪ ማስረጃ ማግኘት የተሳሳተ እና ውኃ የሚቋጥር ባይሆንም) በሚል ስልት ብዙ የማዘግየት ስራዎችን በመስራት የተለመደውን የገዥውን አካል የበቀልተኝነት የሱስ ጥማት ለማርካት ጥረት ያደርጋል፡፡ የዋስትና መብት ጥያቄዎች ተከልክለዋል፣ ሺህ ጊዜ የሚጠየቁ ቢሆንም፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ሴቶች ይደበደባሉ፣ ህግወጥ አያያዝ ይፈጸምባቸዋል፣ እናም በእስር ቤት የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ይፈጸምባቸዋል፡፡ እርስ በእርሳቸው ላይ መተማመን እንዳይኖርም ጫና ይፈጸምባቸዋል፡፡ ህሊናቸውን እንዲሸጡ ገንዘብ እና ሌላ ሌላም ነገር ይሰጣቸዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲን ከፍተኛ አመራሮችን እንዲክዱ ላቅ ያለ ዋጋ የሚያወጡ ጌጣጌጦችን ይሰጧቸዋል፡፡ በጓደኞቻቸው፣ በፓርቲ አባላት እና አመራሮች እንዳይጎበኙ ክልከላ ሊጣል ይችላል፡፡ ለብቻ በአንድ ክፍል ውስጥ ሊታሰሩ ይችላሉ፡፡ የህክምና እርዳታ እንዳይደረግላቸው ክልከላ ሊደረግ ይችላል፡፡ በገዥው አካል በተቀጠረ ባለሙያ እንደተገለጸው እነዚህ እስረኞች  “በሚከረፋው እስር ቤት” የገሀነም ህይወት እንዲገፉ ሊደረግ ይችላል፡፡ ይህ ጉዳይ ለብዙ ጊዜ ማለትም እ.ኤ.አ በ2015 እስከሚደረገው አገር አቀፍ “ምርጫ” ድረስ ቀጣይነት ሊኖረው ይችላል፡፡ ዘዴው ቀላል ነው፡ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን ሃሳብ ማስቀየስ፣ ማሸማቀቅ፣ ማስፈራራት፣ ከመሰረታዊ ዓላማቸው እንዲርቁ ማድረግ እና በአጠቃላይ መልኩ ደግሞ ምርጫ እየተባለ ከሚጠራው የይስሙላ ምርጫ ተሳትፏቸውን ሽባ ማድረግ ነው፡፡
ገዥው አካል የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን ያለምንም ውይይት በፍጥነት ወደ እስር ቤት የመውሰዱን ሁኔታ በተመለከተ በእራሱ የይስሙላ ፍርድ ቤቶች ለምን ሊጠየቅ እና ሊሞገት እንደሚገባው አራት አሳማኝ ምክንያቶች አሉ፡፡ በመጀመሪያ የጅምላ ሰብአዊ መብት ረገጣው ተግባራዊ እንዲሆን የሚያግዙት የገዥው አካል ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች (በተለይም የምራብ መንግሥታት) እነርሱ በሚያደርጉት ልገሳ ድርጊት እየተደረገ ያለውን የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ በተጨባጭ እንዲያዩት ይገደዳሉ፡፡ ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እንዲስፋፋ እና ሰብአዊ መብት እንዲጠበቅ ደንታ አንደማይሰጣቸው የታወቀ ነው፡፡ ሁለተኛ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች የይስሙላ የፍርድ ሂደት በእራሱ በይስሙላው ፍርድ ቤት ላይ አንዲፈረጅበት ማድረግ ያስፈለጋል፡፡ ገዥው አካል እራሱ ለይስሙላው የፍርድ ቤት ሂደት መቅረብ አለበት፡፡ ሶስተኛ የይስሙላው ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደት ዛሬ በፍትህ ወንበር ላይ ተቀምጠው (እና ሌሎች ከመጋረጃ ጀርባ ተቀምጠው በዳኝት ወንበር ላይ የተሰየሙትን ዳኞች ጣቶች የሚጠመዝዙ) በእራሳቸው ዳኝነት ነገ እንደሚዳኙ በመገንዘብ ከፍተኛ ተቃውሞ መኖር አለበት፡፡ ዛሬ ከህግ አግባብ ውጭ ለመፍረድ በወንበር ላይ የተቀመጡት ሰዎች ከፍትህ ረዥም ክንድ ሊያመልጡ እንደማይችሉ የኑረምበርግ የፍርድ ሂደትን፣ የካምቦዲያ ፍርድ ቤት ልዩ የፍርድ ቤት ሂደትን፣ የሩዋንዳ የዓለም አቀፉን የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደትን፣ የደቡብ አፍሪካ የእውነት እና የዕርቅ ኮሚሽንን፣ የቻርለስ ቴለር የዓለም አቀፉን የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደትን እና የቦካሳን እና ሌሎች የአገር ውስጥ የፍርድ ሂደቶች ሊያስታውሱ ይገባል፡፡ ሁኔታዎች ሁልጊዜ ይገለባበጣሉ፡፡ ስለ ሁኔታዎች መገለባበጥ ጉዳይ እስቲ ደጋግማችሁ አስቡ፡፡ ሁልጊዜ ይገለባበጣሉ!
ከደቡብ አፍሪካ ታሪክ ብዙ ቁም ነገሮችን ልንማር እንችላለን፡፡ እ.ኤ.አ በ1964 የአፓርታይድ ገዥ አካል የአፍሪካ ኮንግረስ መሪዎችን እና ሌሎች የጸረ አፓርታይድ ተሟጋቾችን ኔልሰን ማንዴላን፣ ዋልተር ሲሱሉ፣ ጎቫን ኢምቤኪ፣ ራይሞንድ ሃላባ፣ አህመድ ካትራዳ፣ ኤሊያስ ሞሶሌዲ እና ቢሊ ኔይር ሰብስቦ በይስሙላው የአፓርታይድ የፍትህ ችሎት ፊት ገተራቸው፡፡ እነዚህ ሰባት አመራሮች እንደ “ጣይቱ ሰባት” የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ሁሉ በአፓርታይድ የይስሙላ ፍርድ ቤቶች ፍትህን እናገኛለን የሚል እምነት አልነበራቸውም፡፡ ሆኖም ግን መሰረተ ቢስ ክሱን አጥብቀው ተቃውመውታል፡፡ ይህንንም በማድረጋቸው  ለደቡብ አፍሪካ ብቻ ሳይሆን ለጠቅላላው ዓለም ታሪክ ሰርተዋል፡፡ የሰባቱ የጸረ አፓርታይድ መሪዎች የሪቮኒያ የፍርድ ሂደት ለዛሬዋ ደቡብ አፍሪካ ፍትህ መስፈን መሰረትን የጣለ ነው፡፡
አራተኛው እና ምናልባትም በጣም ጠቃሚው ነገር የይስሙላውን ፍርድ ቤት አጥብቀን መዋጋት አስፈላጊ ነው ምክንያቱም በህግ የበላይነት ለሚያምኑ ሁሉ ለህጉ ተገዥ ላልሆኑት ወንጀለኞች የህይወት እና የመተንፈስን ያህል ጠቃሚ መሆናቸውን ሊያስተምሩ የሚችሉበት ብቸኛው መንገድ ነው፡፡ በህግ የበላይነት ላይ እምነት ያላቸው ሰዎች ብቻ ናቸው ስለወንጀለኞች ማስተማር እና መጮህ ያለባቸው፡፡ እራሱ ያወጣቸውን እና ያጸደቃቸውን ህጎች የሚደፈጥጥ ወሮበላ መንግስት በእራሱ እና በህግ የበላይነት ላይ ንቀትን የሚፈለፍል ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ  የህግ የበላይነትን ለመያዝ እና ለመንከባከብ ከማንም የተሻለ መሆን አለበት፡፡
“የጣይቱ ሰባት የህግ ጥበቃ ፈንድን (ድጎማ/ዝክር)” እንደግፍ፣
ሁሉንም አንባቢዎቼን “ለጣይቱ ሰባት የህግ ጥበቃ ፈንድ (ድጎማ/ዝክር)” እንድታዋጡ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡ የሰኞ ትችት መጣጥፌን ለበርካታ ዓመታት ስታነቡ የቆያችሁ በርካታ ወገኖቼ እንዳላችሁ እገነዘባለሁ፡፡ የሰኞ ትችት መጣጥፌ አሁን ስምንተኛ ዓመቱ መሆኑ ነው፡፡ አንዳንዶች ከእኔ ጋር በሁሉም ነገር በሀሳብ የማይግባቡ እንዳሉ አውቃለሁ፡፡ እንደዚሁም በርካታ ለመቁጠር የሚያስቸግር ብዛት ያላቸው አንባቢዎቼ ደግሞ ቢያንስ በጥቂት ነገሮች ላይ ከእኔ ሀሳብ ጋር እንደሚስማሙ እገነዘባለሁ፡፡ የእኔ አቤቱታ የቀረበው ለእነዚህኛዎቹ ወገኖቼ ነው፡፡  በኢትዮጵያ በገዥው አካል የይስሙላው ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደት እየተሰቃዩ ያሉትን “የጣይቱ ሰባት” ጀግኖችን በመርዳቱ ጥረት እያንዳንዳቸው ማገዝ እንዲችሉ ያቀረብኩትን ሀሳብ በመደገፍ በተግባር እንዲያሳዩ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡ እርዳታ እንዲያደርጉም በአጽንኦ እማጸናለሁ፡፡ ምንም ትንሽም ቢሆንም እንኳን ስጋት አይደርባችሁ፣ ትልቅ ጋን በትንሽ ጠጠር ይደገፋል ነውና፡፡ ባለፉት ዓመታት ምን ለመስራት እንዳቀድኩ አድናቆታቸውን የገለጹልኝ በርካታ ኢትዮጵያዊያን/ት ወገኖቼን በተለያዩ ጊዚያት አግኝቸ ነበር፡፡ ምንም ይሁን ምን ለሰራሁት ሁሉ ምስጋናን አልሻም፣ በኢትዮጵያ ያለው የሰብአዊ መብት ያለመሻሻል ሁኔታን ስመለከት ካሁን የበለጠ ሺ አጥፍ መሆን የሆነ ስራ መስራት ነበረብኝ በማለት አራሴን ወቅሳለሁ፡፡
የዛሬ ሰባት ዓመት በዚሁ ወር “ትንሿ ወፍ እና የጫካው እሳት: የዲያስፖራው ማህበረሰብ የሞራል ትረካ” በሚል ርዕስ ስር በትችት መጣጥፌ ላይ ምን ለመስራት እንዳሰብኩ ለአንባቢዎቼ ተናግሬ ነበር፡፡ በዚህም መሰረት ማድረግ የምችለውን ሁሉ እያደረግሁ ነው፡፡ አሁን አንባቢዎቼን መጠየቅ የምፈልገው ማድረግ የሚችሉትን ሁሉ እንዲያደርጉ ነው፡፡ እስቲ በጥሞና አስቡት ወገኖቼ በመቶዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ትናንሽ ወፎች አንድ ላይ ተባብረው በመስራት የጫካን እሳት መግታት ይችላሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ የ”ጣይቱ ሰባት” ጀግኖች በአረመኔው ገዥ አካል የእሳት ማቀጣጠያ ጉድጓድ ውስጥ ናቸው፡፡ ሲቃጠሉ መመልከት አለብን ወይም ደግሞ ከእነርሱ ጎን በመቆም ታግለን ለድል መብቃት አለብን፡፡ “ለጣይቱ ሰባት የህግ ጥበቃ ፈንድ(ድጎማ/ዝክር)” እርዳታችሁን እንድታደርጉ እማጸናለሁ፡፡ ለወደፊቱ የኢትዮጵያ ወጣት ወንዶች እና ሴቶች ተቆርቋሪነታችሁን አሁኑኑ በተግባር አሳዩ፡፡
የሰማያዊ ፓርቲን ሴት ጠይቁ…
ከቀድሞዋ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ማጊ ታቼር ጋር በብዙ ነገሮች ላይ እንደማልስማማ አምናለሁ፡፡ ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትሯ በሴቶች የፖለቲካ አመለካከት ላይ በነበራቸው እምነት ምንም ዓይነት ያለመስማማት አዝማሚያ አልነበረኝም፡፡ “በፖለቲካው ዓለም የተነገረ ምንም ነገር በፈለጋችሁ ቁጥር ወንድን ጠይቁ፡፡ የተሰራ ምንም ነገር በፈለጋችሁ ጊዜ ግን ሴትን ጠይቁ“ ነበር ያሉት፡፡ ሰለሆነም ለእነዚህ ወጣት ሴት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት አንድ ነገር እናድርግ፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ሴቶች እሩጡ፣ እሩጡ…! ለነጻነት የምታደርጉትን ሩጫ በጽናት ቀጥሉበት…
በዚህ ድረ ገጽ የእርዳታ እጃችሁን ለምትዘረጉ:   http://www.semayawiusa.org/donate/
በባንክ ሐዋላ ለመርዳት ለምትፈልጉ
ለሰሜን አሜሪካ የሰማያዊ ድጋፍ የሚከፈል (የአሜሪካ ባንክ (Bank of America)
የሂሳብ ቁጥር፡   435031829977
የመላኪያ ቁጥር፡ 051000017
በቼክ ለመርዳት ለምትፈልጉ፡
ለሰሜን አሜሪካ የሰማያዊ ድጋፍ የሚከፈል
የ.ፖ ሳ.ቁ 75860
ዋሽንግተን ዲሲ. 20013

                                                                    ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
መጋቢት 9 ቀን 2006 ..

የአዳማ ከተማ የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ ወጣት ምርቱ ጉታ ታሰረ

march 20/2014

በአዳማ ከተማ የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ የሆነው ወጣት ምርቱ ጉታ ዛሬ መጋቢት 10 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ገደማ በተለምዶ ዠቅአለ ተብሎ በሚጠራው ገበያ አካባቢ መታሰሩን የከተማዋ የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወጣት ተስፋዬ ዋቅቶላ ለፍኖተ ነፃነት ገለፀ፡፡

የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው እንደገለፀው ዠቅአለ ተብሎ በሚጠራው ገበያ አካባቢ የሚገኙ አነስተኛ ነጋዴዎች የገበያ ስፍራው እንዲለቁ መጠየቃቸውን ተከትሎ ሲያሰሙ የነበረውን ብሶት እንደዜጋ ለማዳመጥ ከሞከሩ የአንድነት አባላት መካከል ወጣት ምርቱ ጉታን አስረውታል፡፡
ወጣት ምርቱ ጉታ በአሁኑ ሰዓት በአዳማከተማ ፖሊስ መንሪያ የወረዳ4 ፖሊስ ጽ/ቤት ውስጥ እንደሚገኝ የታወቀ ሲሆን በአዳማ ከተማ የአንድነት ጽ/ቤት ለማሰራጨት የተዘጋጀውን በራሪ ወረቀትና “ግጥም ለነፃነት” በሚል መሪቃል በአዳማ የአንድነት ጽ/ቤት በወሩ መጨረሻ ለሚዘጋጀው የኪነጥበብ ምሽት የተዘጋጀውን የፖስተር ንድፍ በእጁ ይዞ በመገኘቱ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑ ታውቋል፡፡

የአዳማ ከተማ የአንድነት ፓርቲ “ግጥም ለነፃነት” በሚል መሪ ቃል በጽ/ቤቱ በወሩ መጨረሻ የሚያደርገውን የኪነጥበብ ምሽት የከተማው ተወላጅ ለሆነችውና በህገወጥ እስር ለምትገኘው ለርዕዮት አለሙ መታሰቢያ እንደተሰየመ የከተማዋ የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወጣት ተስፋዬ ዋቅቶላ ለፍኖተ ነፃነት ጨምሮ ገልጧል፡

Photo: የአዳማ ከተማ የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ ወጣት ምርቱ ጉታ ታሰረ-------------------------------http://www.fnotenetsanet.com/?p=6438በአዳማ ከተማ የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ የሆነው ወጣት ምርቱ ጉታ ዛሬ መጋቢት 10 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ገደማ በተለምዶ ዠቅአለ ተብሎ በሚጠራው ገበያ አካባቢ መታሰሩን የከተማዋ የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወጣት ተስፋዬ ዋቅቶላ ለፍኖተ ነፃነት ገለፀ፡፡ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው እንደገለፀው ዠቅአለ ተብሎ በሚጠራው ገበያ አካባቢ የሚገኙ አነስተኛ ነጋዴዎች የገበያ ስፍራው እንዲለቁ መጠየቃቸውን ተከትሎ ሲያሰሙ የነበረውን ብሶት እንደዜጋ ለማዳመጥ ከሞከሩ የአንድነት አባላት መካከል ወጣት ምርቱ ጉታን አስረውታል፡፡ ወጣት ምርቱ ጉታ በአሁኑ ሰዓት በአዳማከተማ ፖሊስ መንሪያ የወረዳ4 ፖሊስ ጽ/ቤት ውስጥ እንደሚገኝ የታወቀ ሲሆን በአዳማ ከተማ የአንድነት ጽ/ቤት ለማሰራጨት የተዘጋጀውን በራሪ ወረቀትና “ግጥም ለነፃነት” በሚል መሪቃል በአዳማ የአንድነት ጽ/ቤት በወሩ መጨረሻ ለሚዘጋጀው የኪነጥበብ ምሽት የተዘጋጀውን የፖስተር ንድፍ በእጁ ይዞ በመገኘቱ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑ ታውቋል፡፡ የአዳማ ከተማ የአንድነት ፓርቲ “ግጥም ለነፃነት” በሚል መሪ ቃል  በጽ/ቤቱ በወሩ መጨረሻ የሚያደርገውን የኪነጥበብ ምሽት የከተማው ተወላጅ ለሆነችውና በህገወጥ እስር ለምትገኘው ለርዕዮት አለሙ መታሰቢያ እንደተሰየመ   የከተማዋ የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወጣት ተስፋዬ ዋቅቶላ ለፍኖተ ነፃነት ጨምሮ ገልጧል፡፡