Tuesday, January 14, 2014

የመረጃ ነፃነት ?…

January 13/2014


ይድነቃቸው ከበደ
ማስታወሻ፡- ይህ ፁሁፍ በግል የቀረበ እንጂ በሰማያዊ ፓርቲ የህግ ጉዳይ ሃላፊነቴ አለመሆኑ ይታወቅልኝ በመሆኑም ስሜ ብቻ ይገልፅ ፁሁፉ ለእናተ በቂ መስሎ ከታያችሁ፡፡

ከከበረ ሠላምታ ጋር መልዕክቴ ይድረሳችሁ!!!!


‹‹ ሕዝቡ እኔ ማን እንደሆንሁ ይላል ? ›› በማለት እየሱስ ክርስቶስ መረጃ ይጠይቃል ፤ ደቀመዛምርቶችም ስለሱ የተባለውን አንድም ሳያስቀሩ ይነግሩታል፡፡ እሱም መልሱ እንዲህ ይላቸዋል ‹‹ እናንተስ እኔ ማን እንደሆንሁ ትላላችሁ ? ››አላቸው ፡፡ እነሱም መለሱለት፡፡ ሙሉ ታሪኩ ሉቃስ 9ቁ 18 ላይ ይገኛል ፡፡

መረጃ አይናቅም አይደነቅም ማለት እንዲህ ነው፡፡ በመሰረቱ ክርስቶስ ሰዎች ስለሱ ምን እንዳሉ ብቻ ሳይሆን ምን እያሰብ እንደነበር የሚያውቅ አምላክ ነው፡፡ ግን መጠየቅ እና መመለስ አሳብን መግለፅ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪ ነው፡፡ ለዚህም ነው ክርስቶ እንደሰው በምድር በተመላለሰበት ወቅት መረጃ ይጠይቅ የነበረው እሱም ስለራሱ መረጃ ይሰጥ የነበረው፡፡ እርግጥ ነው ክርስቶስ ይህን ሲጠይቅ የራሱ ምክንያት አለው፡፡

በመሆኑም ሃሳብ መግለፅ ተፍጥራዊ መብት ነው ወደሚለው ዓለም አቀፍ ስምምነት በመደረሱ የመናገር ሃሳብን የመግለፅ ነፃነት የዲሞክራሲ ዋና የድም ስር ነው የተባለው፡፡ ስለዚህም ተሰባስቦ መቃወም እንዲሁም መደገፍ ፣ አንድ ሰው የሚመስለውን ሃሳብ በፈለገው መንገድ መግለፅ፣ የመምረጥና የመመረጥ፣ መንግስትን የመተቸት፣ በራስ ፍቃድ የመናገረ እና ያለመናገር ፣ በዓልንና አይማኖትን መከተልና ማስፋፋት እንዲሁም ህግ ለሁሉም የሚሰራ ስለመሆኑ መረጋገጥ እና የመሳሰሉት ሁሉ ተግባራዊ የሚሆነው ተአቅቦ ያልተደረገበት የመናገርና የመረጃ መብት ልውውጥ ተግባሪዊ ሲሆን ብቻ ነው፡፡

ለመደርደሪያነት የዚህን ያኸል ከተባለ ወደ ዋናው ጉዳይ አስፈቅደን ሳይሆን ፈቅደን እንገባለን፡፡ ያነሳነው አሳብ ‹‹ መረጃ ›› እንደመሆኑ መጠን ያለማንም ጣልቃ ገብነት ተፍጥሯዊ መብታችን በፈለግነውና በፈቀድነው መንገድ እንገልፃለን፡፡ እኛ ስል ለመረጃ ነፃነት የቆምነው ሁላችንም ማለቴ ነው፡፡

ሰው በመናገሩ አና በመፃፉ ብቻ ለእስር እና ለስደት የሚዳረግበት አገር በዋነኝነት ከሚጠቀሱት ውስጥ ኢትዮጵያ አንዶ ናት፡፡ ነገር ግን ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የአመለካከት እና ሐሳብን በነፃ የመያዝና በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ የመግለፅ ነፃነት አለው፡፡የሚለው በኢትዮጵያ ህገመንግስቱ አንቀፅ 29 ተፅፎ ይገኛል፡፡ በእርግጥ ይህ መብት ገደብ ሊጣልበት እንደሚችል በህገ መንግስቱ ላይ ተገልፆ የተቀመጠ ሲሆን ገደብ ግን መሠረታዊ የሆነውን መረጃን የመስጠት እና የማግኘት እንዲሁም አስተሳሰብ ላይ ወይም አመለካከት ላይ ውጤት እንደማይኖረው በህገመንግስቱ ተገልፆ ይገኛል፡፡


ይሁን እንጂ አሳብን በነፃ ማሰብና ማንሸራሸር በአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ እጅግ አዳጋች ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ አልፎ ተርፎ በአስተሳሰብ ወይም በአመለካከት ላይ ተፅኖ እስከመፍጠር ተደርሶኦል ፡፡ ነገር ግን እንዲህ አይነቱ ሁኔታ ለህግም ሆነ ለሞራል ተቃራኒ እንደመሆኑ መጠን የፈጀውን ፈጅቶ ወደነበረበት መመለሱ የማይቀር ሃቅ ነው፡፡ ነፃ አሳብ የሚንሸራሸርባቸው ነፃ ጋዜጦችና መፅሔቶች ምን ያህል አሉ ? ያሉት ጋዜጦች እና መፅሔቶች እየደረሰባቸው ያለው ማስፈራሪያና ዛቻ ደረጃው ምን ያኸል ደርሶአል የሚለውን መመልከት ተገቢ ነው፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነው በቅርቡ በወጣው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ አክራሪነትና ፅፈኝነት የሚያበረታቱና የሚያሰራጩ በማለት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለህዝቡ ተገቢውን መረጃ እያስተላለፉ ያሉ የእትመት ውጤቶችን ከገቢያ ለማውጣትና ፈርጆ ለመክሰስ እየተደረገ ያለው ዝግጅት ሌላው ማሳያ ነው፡፡ጋዜጠኞችን በማሰቃየት፣በማሰር እና እንዲሰደዱ በማደረግ ኢትዮጵያ በዓለም ላይ በሁለተኝነት ደረጃ ላይ ትገኛለች ፡፡መንግስትን ተችቶ የፃፈና ፁሁፉ የወጣበት ጋዜጣ ወይም መፅሔት ጨምሮ ሁሉም ለእስር የሚዳረግበት ወይም አደገኛ ዛቻና መስጠንቀቂያ የሚሰጥበት ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡

በዲሞክራሳዊ ሥርዓተ ዜጎች የሚኖሩት ግልፅ በሆነ የሃሳብ ልውውጥ ነው፡፡ የትኛውም አይነት ሃሳብ ከማንም ሊመጣ ይችላል ቁም ነገሩ መሆን ያለበት የሚመጣው ሃሳብ የሚመከተው በምንድነው የሚለው ነው፡፡ ለነፃ ንግግር ችግር የተሻለው መንገድ የበለጠ ነፃ ንግግር ነው፤ በመናገር መብት ላይ የሚደረግ ማናቸውም ተፅእኖ ሲውል ሲያድር በእያንዳንዱ ግለሰብ የመናገር መብት ላይ ስጋት ሊያስከትል ይችላል፡፡ለዚህም ነው ወደነበረበት መመለሱ የማይቀር ነው ለማለት የሚያስደፍረው፡፡ምክንያቱ ደግሞ ማንም ሰው በስጋት ውስጥ መኖርን ስለማይፈልግ ነው፡፡

በመሆኑም በአገራችን እየከሰመ ያለው ሃሳብን በነፃ የመግልፅ እና መረጃ የማግኘት መብት በገዥው መንግስት መልካም ፍቃድ ላይ የተመሠረት ወደመሆን ደረጃ ተሸጋግሯል፡፡ለዚህም እንደማሳያ ከሰሞኑ የህዝብ ሳይሆን የገዥው መንግስት አንደበት በሆነው በኢቲቪ በተላለፈው የዘጋቢ ፊልም ግለሰቦችም ሆነ በአገር ውስጥ ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለይ ሰማያዊ እና አንድነት ፓርቲ ለኢሳት መረጃ ከመስጠት እንዲቆጠቡ ምክር መሰል ማስጠንቀቂያ ተላልፏል፡፡

ለዚህም እንደምክንያት የቀረበው ኢሳት የተባለው የመገናኛ ብዙሃን በሽብርተኛ ድርጅት የሚደገፍ ነው የሚል ምክንያት ነው፡፡ ኢቲቪ በኢህአዴግ እንደሚደገፍ ሁሉ ኢሳት በማንም ሊደገፍ ይችላል፤ ቁም ነገር ሆኖ መታየት ያለበት ኢቲቪ ሆነም ኢሳት የሚያስተላልፉት መልዕክት ምንድነው ፡፡ በተጨማሪ መልዕክቱ ለህግም ሆነ ለሞራል ምን ያኸል ተቃራኒ ነው የሚለውን ነው፡፡ በተጨማሪ ኢቲቪ እንዲሁም ኢሳት በህግ መደመጥ እንዲሁም መሰማት የተከለከሉ የመገናኛ ብዙሃን ናቸው ወይ ተብሎ መጠየቅና መልስ ሊሰጥባቸው የሚገባ አሳቦች ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ ወደ መልሱ ስናመራ ኢቲቪ እንዲሁም ኢሳት በህግ የተከለኩ አይደሉም ዋንኛው እና አስፈላጊው ነገር ይሄ ነው ሌላው የህጉ ደጋፊ ሃሳብ ነው፡፡

በመሆኑም ከዚህ በኋላ የህግ ጉዳይ ሳይሆን የፍላጎት ምርጫ ነው የሚሆነው፡፡ የፈለጉትን መስማት እና ማዳመጥ እንዲሁም በፈለጉት የመገናኛ ብዙሃን መንገድ ሃሳብን መግለፅ እና መረጃን ማግኘት ግለሰብ ከሆነ እንደግለሰቡ፣ ተቋም እንደተቋም እንዲሁም ፓርቲ እንደ ፓርቲ የመምረጥ የራስ መብት ነው፡፡ ይህ ደግሞ አንዱ የዲሞክራሲ መገለጫ ነው፡፡ በዚህም መሠረት ከኢቲቪ ኢሳት ከአዲስ ዘመን አዲስ አድማስ የዝወትር ፍላጎታቸው ለሆነ እንዲሁም በተመሳሳይ ከኢሳት ኢቲቪ ከአዲስ አድማስ አዲስ ዘመን ለመረጡ ምርጫቸውን ማክበረ ነው፡፡

ሌላው እና አሳሳቢ ሊሆን የሚገባው ሰው የመረጠውን መስማትና ማዳመጥ እንዲሁም ማንበብ መብቱ እንደጠጠበቀ ሆኖ ግለሰበ ወይም ተቋም ሃሳቡን እንዴት የመግለፅ መብት እና ግዴታ አለበት የሚለው ነው፡፡ ይህን በተመለከተ ተቋም ወይም ግለሰብ ሃሳብን ወይም መረጃን በማንኛውም መንገድ የመገልፅ ሙሉ መበት በህግ የተጠበቀ ነው ፡፡እንዲኹም የዚህ መብት ተቃራኒ የሆኑ ማናቸውም ነገሮች ተቀባይነት እንደሌላቸው በህገመንግስቱ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት በኢሳት ሆነ በማናቸውም የመገናኛ ብዙሃን ሃሳብን መግለፅ እና መረጃን መስጠጥ በራሱ ወንጀል ወይም ጥፋት አይደለም ይህ የሆነው ደግሞ መብት ከመሆኑ አንፃር ነው፡፡


ከዚህ ጋር ተያይዞ መታየት ያለበት ሃሳብን በመግለፅ እና መረጃን በመስጠት ዙሪያ ግዴታ ሊያመጣ የሚችለው ምንድነው የሚለው ነው፡፡ ግለሰቡ ወይንም ተቋሙ በግልፅ በህግ የተከለከለ መረጃ ወይም ሃሳብ የገለፀ እንደሆነ ግዴታው ተጠያቂነትን ስለሚያመጣ በህጉ መሠረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡ ይህ የህግ ተጠያቂነት አዱላዊነት የሌለበት ለሁሉም በሁሉም ቦታ እኩል የሚሰራ ነው፡፡ ይህም ማለት በህግ የሚያስጠይቅ ንግግር በኢሳትም ሆነ በኢቲቪ እንዲሁም በቢቢሲ ያደረግ በህግ ከመጠየቅ ንግግር ያደረገበት የብዙሃን መገኛኛ ሊታደገው አይችልም እንደማለት ነው፡፡
በመሆኑም በኢሳት ሃሳብን መግለፅ እንዲሁም መረጃ መስጠት አልፈልግም ማለት መብት ነው፡፡ ነገር ግን በኢሳት አሳባችሁን አትግለፁ መረጃም አትስጡ ማለት ከፍላጎት የመነጨ ሃሳብ ብቻ ሳይሆን የለየለት የእብሪት ተግባር ነው፡፡ እንዲህ አይነቱ አሰፋሪ ምኞት እና ተግባር የሕግና የዲሞክራሲያዊ መብት ካለማወቅ የሚመነጭ አስተሳሰብ ብቻ ሳይሆን ተምሮ ያለመለወጥ ልክፍትም ጭምር ነው! በተለይ በመንግስት ደረጃ ሲታሰብ እጅግ በጣም ያሳፍራል፡፡

 ዘ-ሐበሻ

የኢትዮጵያ የተቃውሞ የፖለቲካ መድረክ ግልፅ አቅጣጫ መያዝ የሚያስፈልግበት ደረጃ ላይ ደርሷል

January 13, 2014 

(ጌታቸው በቀለ - ከጉዳያችን ጡመራ)
Ethiopia map


በዚህ ፅሁፍ ውስጥ ከተካተቱት ንዑስ አርዕስቶች ውስጥ -
  • የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቀጣይ እርምጃ ምን መምሰል ይገባዋል?
  • የኢትዮጵያ የቅርብ ወቅታዊ ተግዳሮት ምንድን ነው?
  • የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች ህዝብን የሚንጥ እና ሚልዮኖችን ከጎናቸው የሚያሰልፍ የፖለቲካ ራዕይ ለሕዝቡ ማሳየት ለምን አልቻሉም?
እና ሌሎችም…
መግቢያ 
ኢትዮጵያን ውክፕድያ በድህረ ገፁ ላይ እንዲህ ይገልፃታል:-
”ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ የምትገኝ የረጅም ዘመን ታሪክ ያላት ሀገር ናት። በአፍሪካ ነፃነታቸውን ጠብቀው ለመኖር ከቻሉ ሁለት አገሮች አንዷ ነች። በህዝብ ብዛት ከአፍሪካ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ስትሆን፣ በቆዳ ስፋት ደግሞ አስረኛ ናት። ርዕሰ ከተማዋ አዲስ አበባ ናት።አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሀገሮች ዕድሜያቸው ከአንድ ምዕተ ዓመት የሚያንስ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ግን ከጥንት ጊዜ ጀምሮ በንጉሠ ነገሥታት እና ንግሥተ ነግሥታት የተመራች ሀገር ናት። የሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥት የአመጣጡን ዘር እስከ አስረኛው ዓመተ ዓለም ድረስ ይቆጥራል። ኢትዮጵያ የሰው ልጅ ከጥንት ጊዜ ጀምሮ የኖረባት ቦታ እንደሆነች ብዙ የሳይንሳዊ መረጃ ተግኝቷል። በበርሊን ጉባኤ በኩል የአውሮፓ ሀያላት ሀገሮች አፍሪካን ሲከፋፍሏት፣ ኢትዮጵያ ነፃነቷን ጠብቃለች። የሊግ ኦፍ ኔሽንስ አባል ከነበሩት ሶስት የአፍሪካ ሀገሮች አንዷ ነበረች። ከአጭር የኢጣልያ ወረራ ጊዜ በኋላም ከየተባበሩት መንግሥታት መሥራቾች አንዷ ናት። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ብዙ የአፍሪካ ሀገራት ነፃነታቸውን ሲያገኙ፣ ሰንደቅ አላማቸውን በኢትዮጵያ ቀለሞች ማለትም በአረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ላይ ነው የመሠረቱት። አዲስ አበባ ደግሞ ለየተለያዩ በአፍሪካ ላይ ላተኮሩ አለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ ሆነች።” ይላል
ወግ አጥባቂ የአረብ መንግሥታት እና ፍላጎታቸው
የዛሬ ሰላሳ ሰባት አመት በምዕራቡ አለም የተከፈተው የቀዝቃዛው ጦርነት እጅግ በተፋፋመበት፣ የኢትዮጵያ አብዮት ተጠምዞም ይሁን በጥቂት የወቅቱ ‘ልሂቃን’ ለደርግ በቀረበ ሃሳብ ወደ ሶሻሊዝም ስርዓት ሀገሪቱን ለማስገባት በሚውተረተርበት፣በደቡብ ምስራቅ የሀገራችን ክፍል በወቅቱ ከሶቭየት ህብረት ባገኘው የመሳርያ ድጋፍ የተመካው የሱማልያ-ዚያድባሬ መንግስት የኢትዮጵያን መሬት በኃይል የወረረበት ወቅት ነበር። በእዚህ ጊዜ ነበር የ’ፋይናንሻል ታይምስ’ ጋዜጣ የአፍሪካ ቀንድን ፖለቲካ ከቀዝቃዛው ጦርነት በዘለለ እይታ የሚያመላክት አንድ ፅሁፍ ይዞ የወጣው። ፅሁፉ እንዲህ የሚል ነበር:-
“በወግ አጥባቂ የአረብ መንግሥታት በሳውድ አረብያ ቀንደኛነት በግብፅ፣ ሱዳን እና ሶርያን ጨምሮ በቀይባሕር እና በአካባቢው ሃገራት የአረብ ወይንም የእስልምና መንግሥታት እንዲመሰርቱ የሚደረጉ ጥረቶች አሉ።’’
“the conservative Arab states, marshalled by Saudi Arabia and including Egypt, Sudan and Syria, want to create a band of Arab or Muslim states along the shores of the Red Sea and its approaches.” (Financial Times May 2, 1977)
የ ሶስት ሚልዮን ሕዝብ አናሳነት  በፖለቲካ ስሌት አንፃር 
ከሱማልያ ጎን ቆማ የቀዝቃዛውን ጦርነት ትዋጋ የነበረችው ሶቭየት ህብረት (የዛሬዋ ሩስያ) ከቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ መውረድ በኃላ ፊቷን ወደ ኢትዮጵያ ለማዞር አፍታም አልቆየችም። ለእዚህ ውሳኔ ካበቃት ጉዳይ አንዱ የኢትዮጵያ ስልታዊ ጠቀሜታ ዘለቄታዊ ጥቅሟን የሚያረጋግጥባቸውን ሁለት ዋና ዋና ጉዳዮችን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ነበር።እነኚህም ኢትዮጵያ በአካባቢው ያላት በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ መካከል እንደ ድልድይ የምትጠቅም ብቸኛ መሬት መሆኗ እና በሕዝብ ብዛትም ሆነ በተፈጥሮ ሃብቷ ከአካባቢው ሃገራት የምታማልል መሆኗ ነበር። በሕዝብ ብዛት አንፃር ካላት ጠቀሜታ አንፃር ሶቭየት ህብረት ኢትዮጵያን እንደምትመርጥ የገለፀችበትን ሰነድ የሚያመላክተው አሁንም ከዛሬ ሰላሳ ሰባት አመት በፊት እ ኤ አቆጣጠር ግንቦት 14/1977 ዓም በሱማልያ የሶቭየት ህብረት አምባሳደር የተናገሩትን  ’ዘ ኢኮኖሚስት’ መፅሄት እንዲህ ፅፎት ነበር:-
”መንግስቱ ኃይለማርያም ጥሩ ልጅ ነው። ሶሻሊዝም ኢትዮጵያ ውስጥ ካሸነፈ 30 ሚልዮን ወዳጆች በተጨማሪም የአሰብ እና ምፅዋ ወደብ ይኖሩናል። እናንተ ሱማሌዎች እኮ 3ሚልዮን ብቻ ናችሁ” ነበር ያሉት።
‘Mengistu Haile Mariam is a good boy. If socialism wins in Ethiopia we will have 30 million friends there plus the ports of Assab and Massawa. You Somalis are only 3 million.’ (The Economist, May 14 1977)
እዚህ ላይ የ 3 ሚልዮን ሕዝብ አናሳነት  በፖለቲካ ስሌት አንፃር ኢትዮጵያን ዛሬም ከአካባቢው ሀገሮች በበለጠ ባላት የህዝብ ብዛት እና የተፈጥሮ ሀብት በተለየ ተመራጭ ሀገር እንደሚያደርጋት አያጠራጥርም። እዚህ ላይ ይህንን ተመራችነቷን ለመጠበቅ እና እንደሀገር እንዳትቀጥል ከገዛ መንግስቷ የሚገዳደሯት ፈተናዎች የመኖራቸውን እውነታ ሳንዘነጋ ማለት ነው።
መንግስታዊ የጎሳ ፖለቲካ
ይህ ከሆነ ዛሬ ሰላሳ ሰባት አመታት ተቆጥረዋል። በእነኝህ ሰላሳ ሰባት አመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ሁኔታዎች ብቻ ሳይሆኑ አንድ ትውልድ አልፎ አዲስ ትውልድ ተተክቷል፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ከ 30 ሚልዮን  በሶስት እጥፍ ወደ 90 ሚልዮን ተተኩሷል፣ የባሕር በሯ ተዘግቷል፣ ወጥ የነበረው የመንግስት ስሪት በጎሳ እና ቋንቋ ላይ በተመሰረተ አስተዳደር ተቀይሯል፣ከተሞች በመጠን ሰፍተዋል። በከተማ የሚኖረው ሕዝብ ከገጠሩ ጋር ሲነፃፀር ግን በእነኝህ ሁሉ ከ ሶስት አስር አመታት በኃላም ከ 90 በመቶ ወደ 85 (83) በመቶ ነው ዝቅ ያለው። የህዝቡ የኑሮ ደረጃ እ አ አቆጣጠር በ 1970 ዎቹ ነፃነታቸውን ከተቀዳጁት የአፍሪካ ጥቁር ህዝቦች አንፃርም ገቢው ዝቅተኛ የሚባል እና ከእጅ ወደ አፍ ነው። ከላይ የተጠቀሱት ‘ፋይናንሻል ታይምስ’ እና ‘ዘ ኢኮኖሚስት’ ፅሁፎች ሲወጡ በአፍሪካ ቀንድ የነበረን አማላይነት በምድር ጦር፣ በአየር ኃይል እና በባህር ኃይል የነበረን የበላይነት የተገለፀ ሲሆን ዛሬ በሕዝብ ብዛት እና ዙርያችንን ያሉት የትናንሽ ደካማ ሃገራት መኮልኮል አጉልቶ ካሳየን የበላይነት ባለፈ መድረስ የሚገባንን ደረጃ አለመድረሳችንን ለማረጋገጥ ብዙ ማስረጃ ማቅረብ አያስፈልግም።
ባለፉት 37 አመታት ውስጥ ኢትዮጵያ የገጠማት ተግዳሮቶችን በሁለት መልክ ማስቀመጥ ይቻላል።እነርሱም የውስጥ ቁርሾ በአምባገነንነት መታገዝ እና የውጭ ግፊቶች ናቸው። የውስጥ ቁርሾው በተቻለ መጠን የሚቀልባቸው መንገዶች እንዳይኖሩ እልህ የተጋባው የአምባገነንነት እርምጃዎች በእሳት ላይ ቤንዚን የማርከፍከፍ ያክል ብዙዎች ሳያስቡት ቁርሾውን ለማባባስ ሰበብ እንዲሆኑ አደረጋቸው። ደርግ የእርስ በርስ ጦርነቶቹ በተቻለ መጠን ለማቅለል ከውስጥ የነበረበትን የህዝብ ድጋፍ ማጣት ስልጣንን ለሕዝብ በማስረከብ ሊያቀለው አልፈለገም። ይልቁንም ጦርነቶቹ የሰራዊቱን በሥራ መጠመድ ማምጣቱ የታያቸው ወገኖች እንደ መልካም እድልም ተመለከቱት። በዘመነ ኢህአዲግ/ወያኔ ደግሞ የውስጥ ቁርሾው በደርግ ዘመን ከነበረው የህዝብን ስልጣን ለሕዝብ ማስረከብ ብቻ ሳይሆን ”መንግስታዊ የጎሳ ፖለቲካ” በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ማኅበራዊ፣ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ግንኙነት ላይ አደገኛ ጥላ አጠላ። የጎሳ ግጭቱ ከክልሎች የመሬት ግጭት አልፎ እስከ መንደር የከብቶች መሰማርያ ሜዳ ድረስ ኢትዮጵያውያን ተጋጩ። በእነኝህ የጎሳ ግጭቶች የተነሱ ፀቦችን ለማስቆም ዋናው ችግር ”የመንግስታዊ የጎሳ ፖለቲካ” መሰረት ያደረገውን የፌድራል  ስርዓት በትክክለኛ የመሬት አቀማመጥ እና የህዝቦች ታሪካዊ አሰፋፈር መሰረት ያደረገ የፌድራል ስርዓት መቀየር መሆኑ እየታወቀ ኢህአዲግ/ወያኔ የተጋጩትን የጎሳ አባላት መዳኘትን እንደ ትልቅ ግብ እየቆጠረ በዜና እወጃው ላይ በስኬት ዜናነት ማውራቱን ቀጠለ።
የመንግስታዊ የጎሳ ፖለቲካ መዘዝ ለአፍሪካውያን እየተረፋቸው ነው
የመንግስታዊው የጎሳ ፖለቲካ ውጤት ከሀገር ውስጥ አልፎ ለጎረቤት ኬንያ የእራስ ምታት የሆነባቸው ብዙ ጊዜያት ነበሩ።ይህም ምን ያህል ኢህአዲግ/ወያኔ ”የፌድራ ስርዓቱ ለአፍሪካ ምሳሌ ሆነ”  እያለ የሚያሰራጨው ፕሮፓጋንዳ ባዶ መሆኑን ያረጋግጣል። መንግስታዊ የጎሳ ፖለቲካ ለቅርብ ኬንያ የየዕለት እራስ ምታት መሆኑ ፀሐይ የሞቀው ዜና ነው።ታህሳስ 27 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና ለእዚህ ጥሩ ማስረጃ ነው።ዜናው እንዲህ ይነበባል: -
“በደቡብ ኢትዮጵያ የተፈጠረው የጎሳ ግጭት ድንበር ተሻግሮ ኬንያ ውስጥ የሚገኙ ጎሳዎችንም እያተራመሰ ነው ተባለ በደቡብ ኢትዮጵያ በቦረናና በገርባ ጎሳዎች መካከል ከግጦሽ መሬትና ከውሀ ጋር በተያያዘ በተነሳው ግጭት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ተገድለዋል።
“ግጭቱ ወደ ኬንያም ተስፋፋቶ በአካባቢው የሚገኙ 17 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው ታወቋል።
“ከአካባቢው ርቀት አንጻር እስካሁን ድረስ የተጠናከረ መረጃ ባይቀርብም፣ በሞያሌ አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች እንደሚሉት በግጭቱ በርካታ ሰዎች ተገድለዋል፤ ብዙዎችም አካባቢውን እየለቀቁ ተሰደዋል።በኢትዮጵያ ሞያሌ ከተማ ደግሞ በሶማሊ እና በኦሮሞ ተወላጆች መካከል በቅርቡ የተፈጠረው ግጭት ፣ ዳግም ያገረሻል የሚል ፍርሀት መኖሩን የአካባቢው ነወራዎች ገልጠዋል። ሞያሌን የሶማሊ እና የኦሮሚያ ክልል ተወካዮች ከሁለት ከፍለው የሚያስተዳድሩዋት ሲሆን፣ በሁለቱ ብሄሮች ግጭት የከተማው ሰላም በተደጋጋሚ ሲደፈርስ ቆይቷል።
“በቅርቡ ከትምህርት ቤት ንብረት ጋር በተያያዘ የተነሳውን ግጭት ተከትሎ የፌደራል ፖሊሶች አሁንም አካባቢውን እንደተቆጣጠሩት ነው።’’ የዜናው መጨረሻ
በሌላ በኩል ከውጭ በኢትዮጵያ የውስጥ ፖለቲካ ጉዳይ ውስጥ ገብተው ወደሚፈልጉት አቅጣጫ የመዘወር ግፊት የሚሰሩት ኃይላት ፍላጎት ከቀዝቃዛው ጦርነት ጋብ ማለት በስተቀር ሌሎቹ ምክንያቶች ማለትም የአካባቢው እስልምና ተከታይ ሃገራት (ሳውዲ አረብያን ጨምሮ) በኢትዮጵያ ላይ የነበራቸው ግብም ሆነ ተግባራት ምንም ለውጥ አላመጡም። ከእዚህ በተለየ የአለም ሃያላን መንግሥታት በሽብርተኝነት ጉዳይ፣ በምጣኔ ሀብታቸው መዛባት እና ቻይና አዲስ አማራጭ ከመሆኗ ጋር በተያያዘ በታዳጊ ሃገራት ላይ ያላቸው የበላይነት የመርገብ አዝማምያ አሳይቷል። ይህ መርገብ ግን ምናልባትም ከያዝነው አመት ጀምሮ ባለበት ላይቆይ ይችላል። የአራቱ የዓለም ኃይላት ማለትም የአሜሪካ፣ የቻይና፣ የአውሮፓ እና የሩስያ በግልፅ በወጣ የመገፋፋት ሂደት አለመኖር እና በተሸፈነ ዲፕሎማሲ ነገሮችን ማቀዝቀዛቸው ደካማ ሃገራት በጥቅማቸው ጉዳይ ላይ ከአንዱ ጋር የመቦደን ግዴታ  ውስጥ እንዳይገቡ እረድቷቸዋል። ይህ ሁኔታ ግን እሰከመቼ ድረስ እንደሚዘልቅ የምናየው ይሆናል። በተለይ ከባድ የምጣኔ ሀብት ቀውስ መምጣት እና እጅግ በተሳሰረው የአለም ምጣኔ ሃብት አንፃር ከአራቱ ሃያላን አንዱ ወይንም ሁለቱ አልያም ሶስቱ ተነጥለው የመሄድ አዝማምያ ከመጣ የአለም የኃይል ቁርሾ ወደ 1970ዎቹ የማይወርድበት ምክንያት አይኖርም። ምናልባት ‘ሲ ኤን ኤን’  ”ቀዝቃዛው ጦርነት” የሚለውን የቀድሞ ፕሮግራሙን   ሰሞኑን እንደ አዲስ ልከልስልን የተነሳው በመጪው ላይ ያለው ስጋት አይሎበት ይሆን?
የኢትዮጵያ የቅርብ ወቅታዊ ተግዳሮት ምንድን ነው?
ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው ከሁለተኛው አለም ጦርነት አንስቶ  እስከ 1980ዎቹ እ አ አቆጣጠር ተጋግሎ የቆየው የቀዝቃዛው ጦርነት ኢትዮጵያ ወደራሷ የችግር ፈቺነት አቅም ሳያሸጋግር ”ለመንግስታዊ የጎሳ ፖለቲካ” አስረክቧት ቀዘቀዘ።ቀድሞ በምዕራባውያን ትምህርት የተዋከበው የእድገት ስልት ቀጥሎ በመጣው በደርግ ሶሽያልስታዊ አስተሳሰብ ተተራምሶ ከዛሬ 22 አመት ገደማ ደግሞ በ”መንግስታዊ የጎሳ ፖለቲካ” ቅርፁም ሆነ ይዘቱ ትውልድ አሻጋሪ እንዳይሆን ሆነ።
ዛሬ የምዕራባውያን ”ሌክቸር” መሰል አመራርም ሆነ የሶሻልስቱ አለም የማያላውስ ቀጭን ትዛዝ የኢትዮጵያ እራስ ምታቶች አይደሉም።የአካባቢ የአረብ መንግሥታት ግፊት ግን የቅርብ እና ከባድ የኢትዮጵያ ተግዳሮት ነው። ከኢህአዲግ/ወያኔ በፊት የነበሩት መንግሥታት በማዕከላዊነት ይዘውት የነበረውን የሀገር ጉዳይ በጎሳ ስለሸነሸነው ለአካባቢ ”ኢትዮጵያን አረብ ማድረግ አለብን” እንቅስቃሴዎች እጅግ አመቺ ሁኔታዎችን ፈጥሯል። ኢትዮጵያን አረባዊ የማድረጉ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ላይ ብቻ ሳይሆን በጥቁር ህዝቦች ላይም የተሞከረ እና የታቀደ ይልቁንም እስልምናን ከሃይማኖት ይልቅ ፖለቲካዊ ጥቅሙን ብቻ ነቅሶ የመንቀሳቀስ አላማ የያዘ ነው።
ኢትዮጵያን አረባዊ (እስላማዊ ሀገር ) በማድረግ ሂደት ላይ በጉልህ የተሳተፉ ውስጣዊ ኃይላት አሉ።እነርሱም-
  1. የኢህአዲግ/ወያኔ መንግስ እና ‘ፅፈኛ አጋር’ ተብዬ የጎሳ ድርጅቶቹ
  2. ኢህአዲግ/ወያኔን እንቃወማለን የሚሉ ግን የመገንጠል አላማ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ለምሳሌ የ ዑጋዴን ነፃነት ግንበር የመሳሰሰሉ ናቸው።
እነኝህ ኃይላት የተለያዩ ይምሰሉ እንጂ ያጣላቸው የበላይ ለመሆን የሚደረግ ግፍያ ካልሆነ በቀር የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው። ለምሳሌ ትግራይን የመገንጠል አላማ ይዞ በፕሮግራሙም አካቶ ይንቀሳቀስ የነበረው ህወሓት ዛሬም መንግስት ከሆነ በኃላም የቀድሞ የጎሳ ስሙን ካለመቀየሩም በላይ ለስልጣን ያበቃቸው አጋር ድርጅቶቹ ባብዛኛው በአንድም ሆነ በሌላ ኢትዮጵያን አረባዊ (እስላማዊ) ለማድረግ ከሚሹ ኃይላት በተገኘ የስልጠና፣ የቁሳቁስ እና የገንዘብ ድጋፍ የተመሰረቱ ናቸው። ይህ ድጋፍ ዛሬም ድረስ እያገኙ ነው።
እነኝህ ኃይላት አላማቸውን ለማስፈፀም የሚሞክሩት እና የሚተገብሩት በአፈሙዝ ነው። ይህ ማለት በሌላ አገላለፅ መጭውም  የፖለቲካ መድረክ የሚስተናገደው በአፈሙዝ ስልጣን ላይ የሚወጣ የሚደመጥበት ነው ማለት ነው። አሁንም ለሰላማዊ የስልጣን ሽግግር አልታደልንም ማለት ነው። በእነዚህ ሁሉ ውጥንቅት ውስጥ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በነበረው አካሂድ ምን መምሰል ይገባዋል?
የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቀጣይ እርምጃ ምን መምሰል ይገባዋል? 
የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዛሬ ያለው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግርም ሆነ ወደ ነፃነት እና ዲሞክራሲ የሚደረገው ጉዞ በሁለት ጉዳዮች የተወጠረ ነው። እነኝህ ሁለት ጉዳዮች ላይ የተቃዋሚ የፖለቲካ ኃይሎች ግልፅ እና ጥርት ያለ መስመር ማሳየት አለባቸው።ይህ መስመር ዛሬ ያለውን ጥቂቱን ወይም ብዙውን ያስከፋል ወይንም ያስደስታል ከሚል አንፃር ሳይሆን መሰመር ያለበት መጪውን ዘመን ያገናዘበ ብሎም አዋጪ እና አማራጭ መስመር ከመሆን አንፃር ብቻ  መታየት ይገባዋል። እነኝህ ሁለት ጉዳዮች:-
  1.  ባለፈ ታሪክነት ማንነት ላይ የጠራ አቋም ማሳየት
  2. ከባለፈ ታሪክ፣ባህል፣ማንነት፣ከአሁኑ እና ከመጪው ትውልድ ማንነት አንፃር ወደፊት ሊኖር ስለሚገባው የመንግስት ቅርፅ በግልፅ ማሳወቅ
1/ ባለፈ ታሪክነት ማንነት ላይ የጠራ አቋም ማሳየት
የኢትዮጵያን  ያለፈ ታሪክ በአንድ ገላጭ አረፍተ ነገር ሊጠቃለል ወይንም ይህንን ከማለት ውጭ ይህንን ማለት አይቻልም የሚል አስተሳሰብ የሚራመድበት ወቅት ላይ አይደለንም። በሌላ በኩል ደግሞ በድፍኑ የጋራ የሚያደርገንን ታሪክን እንደምናምን ቆጥሮ በዝምታ እና በብዥታ መቀጠልም ህዝብን ከሚመራ የፖለቲካ ኃይል የሚጠበቅ አይደለም። ይህ ያለንበት ወቅት የአንድን የፖለቲካ ድርጅት ባለፈ ታሪክ ላይ ያለው አመለካከት በራሱ የፖለቲካ ፓርቲውን የወደፊት ራዕይ የሚያመላክት ያክል እንደማሳያ እየሆነ ለመምጣቱ ብዙ ማሳይዎችን መጥቀስ ይቻላል።
እዚህ ላይ ትልቁ ጉዳይ ዛሬ ያለው ትውልድ ስለአለፈው በጎም ሆነ በጎ ያልሆነ ታሪክ ቅንጣት ታክል ተጠያቂ ሊሆን አይችልም። እርሱ የሚጠየቀው ዛሬ በሚሰራው እና ነገ ሊሰራ ስለሚያስበው ታሪክ ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ እና ታሪክን ተመርኩዘው ነገን በሚማትሩ የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆኑ ደጋፊዎቻቸው ዘንድ ሁለት አይነት ስሜቶች ይንፀባረቃሉ።
አስተሳሰብ አንድ – የባለፈው ታሪክን በዛሬ መነፀር የሚመለከት
የመጀመርያው ክፍል ባለፉት ዘመናት የተደረጉትን ታሪካዊ ሁኔታዎች ዛሬ 21ኛው ክ/ዘመን ላይ ሆኖ ለመገምገም የምፈልገው ነው። የዛሬ 600 አመት አፄ ዘርያቆብ ለምን እንዲህ አላሰቡም? እንዴት እንዲህ ይላሉ? እያለ በወቅቱ የነበረውን ስነ-ልቦና የማኅበረሰቡን ባህል፣ እምነት እና ወግ ሳያጠና እንዲሁ ለዛሬ የኢትዮጵያ እሷነት መነሻ ሰበብ ሲፈልግ ከድሮ ታሪክ ጋር እያዛመደ መማሰን ሙያ ተብሎ ተይዟል። ይህ ክፍል ትልቁ ግቡ ስልጣን ነው። ስልጣን ለመያዝ ደግሞ ዛሬም ሆነ ነገ እንቅፋት ይሆኑኛል የሚላቸው ሁለት ”ደንቃራዎች” ከፊቱ ይታዩታል። እነርሱም- በረጅም ዘመናት የተገነባው ያለፈው እና አሁን በሕዝቡ ልብ ውስጥ ያለው ኢትዮጵያዊነት ነው።ይህ ኢትዮጵያዊነት ደግሞ ባለፈ ማንነት፣ ታሪክ፣ ባህል እና እምነት ላይ የተመሰረተ ነው። ስለዚህ ዛሬ ሰበብ አስባብ ፈልጎ ያለፈ ማንነትን የሚንዱ ናቸው ያላቸውን የህዝብ ግጭቶችን፣በነበሩበት ጊዜ ጀግና ያስብሉ የነበሩ በ 21ኛው ክ/ዘመን ግን ክፉ ተግባራትን እና ፈፅመው የሌሉ ታሪኮችን በመፍጠር የኢትዮጵያዊነት መሰረቶች እንዲናዱ ይሞክራል።
ለምሳሌ የብሔር ብሔረሰቦች ጉዳይ እና ፌድራሊዝም አስተዳደሮች  በፅንሰ ሃሳብ ደረጃ ባልተፈጠሩበት ዘመን ለምን አልታወጁም ነበር? በሚል ውኃ ቀጠነ ንግግር ኢትዮጵያዊነትን ይሳደባል። ይልቁን ፌድራልዝም በአለም ሳይታወቅ እነ አባ ጅፋር የራሳቸውን ግዛት በራሳቸው ያስተዳድሩ እንደነበር ግን በጋራ ከማዕከላዊ መንግስት ጋር በሚያገናኛቸው ጉዳይ ላይ አብረው ይሰሩ እንደነበር አያስተውልም። በዚህ ክፍል ውስጥ የኢህአዲግ/ወያኔ መንግስትን ጨምሮ በፅንፈኛ የእስልምና እምነት የፖለቲካ አላማቸውን ለማሳካት እስከሚፈልጉት ኃይሎች ድረስ የባለፈውን ታርክ በዛሬ መነፀር እያዩ ህዝብን ማደናገር እና የዛሬውን ትውልድ በማያውቀው ጉዳይ አበሳውን ሲያሳዩት መመልከት የተለመደ ነው።
አሁን ባለንበት ዘመን በእዚህ አስተሳሰብ ሺዎች ተገለዋል፣ ሌሎች አያሌ ሺዎች ከመኖርያቸው ተፈናቅለዋል። ከእዚህ ሲዘል ደግሞ ማስረጃ ለሌለው ተረት ሁሉ ሃውልት ይሰራ ባይ ነው። የእዚህ አስተሳሰብ አራማጆች ዋና ግባቸው ”እኛ ስልጣን ላይ ከሌለን እና የምንፈልገውን ካልፈፅምን ጭር አይልም ባዮች ናቸው። ለእዚህ እኩይ ተግባር የምተባበራቸው ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይል ጋር ለመተባበር ዝግጁ ናቸው። ኢትዮጵያዊነት፣ አንድነት እና ህብረት ሲጠነክር ይደነግጣሉ። ምክንያት የእነርሱ አስተሳሰብ በጠንካራ ኢትዮጵያዊነት አስተሳሰብ ፊት ሞገስ እንደሌለው እና እነርሱንም ወደ ስልጣን ኮርቻ ላይ እንደማያፈናጥጣቸው ይረዳሉና።
አስተሳሰብ  ሁለት – የባለፈው በጎውን ይዘን ክፉውን ወቅሰን ያሁኑን ትውልድ ተጠያቂ ሳናደርግ ለወደፊቱ እናስብ
ሁለተኛው አስተሳሰብ የብዙ ኢትዮጵያውያን አስተሳሰብ ነው። ኢትዮጵያ በአንድ ምሽት በቤተ-ሙከራ ውስጥ የተሰራች ሀገር አይደለችም። የብዙ ዘመናት የህዝቦቿ አብሮ የመኖር፣የመተሳሰብ፣ የመሰደድ፣ የጦርነት፣ የሰላም ሁሉ ውጤት ነች። ባለፈው ታሪካችን ብዙ አንድ የሚያደርጉን ነገሮች አሉ። ብዙ የዛሬ ማንነታችን ላይ አሻራ ያላቸው ማንም በቀላሉ እንዲነቅላቸው የማይፈቀዱለት የጋራ ታሪክ አለን። በአንፃሩ ደግሞ የሚያሳዝኑ ታሪኮች ባለቤትም ነን። ዛሬ የሚያስፈልገን ያለፈው አንድ የሚያደርጉንን አጉልተን ባለፈው ለተሰሩት ስህተቶች ምንም ተጠያቂ ባንሆን ወደፊት እንዳይሰሩ አርመን መኖር ብቸኛ አማራጫችን ነው። ከእዚህ በዘለለ ባለፈ አሳዛኝ ታሪክ ሊሽር የሚችለው በዛሬው ትልውድ በጎ የታሪክ ተግባር ነው ብለው ያምናሉ።
አሁን በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ላይ የሚታዩት አስተሳሰቦች ከላይ ከተጠቀሱት ከሁለቱ አንዱ እንደሆኑ ይታወቃል። የኢትዮጵያ ሕዝብም የፖለቲካ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ያላቸውን ግልፅ አስተያየት እና ይህ እይታቸው የነገውን የሀገራችንን መፃኢ ዕድል ማሳያ እንደሆነ አመላካች ነው። ኢትዮጵያ ነገ እንዴት እንድትሆን እንደሚፈልጉ ሁሉ የባለፈው ዕይታቸውም በግልፅ መቀመጥ ያለበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።
ከባለፈ ታሪክ፣ ባህል፣ ማንነት፣ ከአሁኑ እና ከመጪው ትውልድ ማንነት አንፃር ወደፊት ሊኖር ስለሚገባው የመንግስት ቅርፅ በግልፅ ማሳወቅ
አሁን በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ፣ በሰላማዊ ትግልም ሆነ በትጥቅ ትግል ላይ እንደሆኑ የሚነገርላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች አንድ የጋር ነጥብ እና አሰልቺ ቋንቋ አለ። ይሄውም ”ዲሞክራሲያዊ የሆነ መንግስት” ይመሰረታል የሚል ነው። ደርግም ሆነ ኢህአዲግ/ወያኔ ”ዲሞክራሲያዊ” ያሉትን መንግስት ኢትዮጵያ እንዳጣጠመች ነግረውናል። ነገም ይህንኑ ተረኛው ስደግምልን መስማት ምንኛ ዘግናኝ ታሪክ መሆኑን ለአፍታም ማሰብ ይከብዳል።የብዙ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሰረታዊ ችግር እና ሚልዮኖችን በአጭር ጊዜ ማሰለፍ ያልቻሉት ነገ የሚመሰርቱት መንግስትን በደፈናው ”ዲሞክራሳዊ” ከማለት ባለለፈ መልክ አሁን ያለውንም ሆነ መጪውን ትውልድ የሚያማልል የኢትዮጵያን ታሪካዊ ዳራ ያገናዘበ ብሎም ነገ ተመንጥቃ የምታድግበትን አዲስ ሃሳብ ማፍለቅ አልቻለም። ኢህአዲግ/ወያኔ በትጥቅ ትግል ላይ ሳለም ይህንን ማድረግ አልቻለም ነበር። ግን ያስቀመጠው አንድ ሕዝቡን ያማለለ ጉዳይ ነበር ይሄውም ደርግ ይገረሰሳል የሚል ራዕይ ነበር።
ራዕይ ያሸፍታል፣ራዕይ ካላገኙት በቀር እረፍት ይነሳል፣ ራዕይ አያስበላም፣ አያስጠጣም፣ ዛሬን በጨለማ ያሳያል ነገን ግን በብሩህ ብርሃን አንቆጥቁጦ ያሳያል። የፖለቲካ ራዕዩን በትክክል የገለፀ እና ያ ራዕይ ደግሞ የሕዝብ ስስ ብልትን የነካ ሲሆን ሚልዮኖችን ያነቃንቃል፣ይፈነቅላል፣ሺ መትረጌስ ቢደገን ተራምዶት ይሄዳል። በትክክል የተቀመረ የፖለቲካ ራዕይ እንዲሁ ነው። ከእዚህ በተለየ ”ዲሞክራሲያዊ” መንግስት ይመጣል በሚል ንግግር የትም አይደረሰም። በ 1997 ምርጫ ቅንጅት የሰራው ተአምር ይህ ነው። የራሱ ጠንካራ ድርጅታዊ መዋቅር ሳይኖረው የህዝቡን ሥሥ ብልት የሚነካ ጉድለቱን የሚሞላ የፖለቲካ ፕሮግራም እና ራዕይ ብልጭ አደረገ በአንድ ቀን ሚያዝያ 30/1997 ዓም ሰልፍ ብቻ በአዲስ አበባ ከ አንድ ሚልዮን ሕዝብ በላይ ደግፎት ተሰለፈ።
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች ህዝብን የሚንጥ እና ሚልዮኖችን ከጎናቸው የሚያሰልፍ የፖለቲካ ራዕይ ለሕዝቡ ማሳየት ለምን አልቻሉም?
ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ሁለት መሰረታዊ ችግሮች በፖለቲካ ፓርቲዎቹ ላይ ይስተዋላል። አንደኛው የአመሰራረታቸው ሂደት ችግር ሲሆን ሁለተኛው የሕዝቡን ባህል፣እምነት እና ታሪክ ያገናዘበ ፕሮግራም ለማስተዋወቅ ድፍረት ማጣት ናቸው።
ሀ/ የአመሰራረታቸው ሂደት ችግር
የፖለቲካ ፓርቲዎቻችን በሰላማውም ሆነ በትጥቅ ትግል ላይ ያሉት መካከል ነገ ሊያመጡልን ይችላሉ በምንላቸው በጎ ነገሮች ላይ አንዳቸውን ካንዳቸው የምንለይበት ነጥብ ካጣን ቆይተናል። ብዙዎቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሲመሰረቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዋና እና ብቸኛ ችግር የዲሞክራሲ እጦት ችግር ብቻ ነው በሚል ትምህርት ቤት በተማሩት የምዕራቡ ፍልስፍና መግባብያነት ብቻ ይመሰረታሉ ወደ ትግል ይገባሉ። ኢትዮጵያን የሚያህል ከሶስት ሺህ አመታት በላይ የመንግስት ስሪት ያላት ሀገር ግን   ችግሯ የዲሞክራሲ ብቻ ሊሆን አይችልም። የማንነት መከበር፣በራስ ላይ ተመስርቶ የመፍጠር ክህሎት ማሳየት፣የራሷ የሆኑ የፖለቲካ ፍልስፍና እና ምጣኔ ሃብታዊ ተምኔቶች ማሳየት እነኝህ ሁሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች መንገዱን በተጠና እና ሊደረስበት በሚችል ራዕይ ለሕዝቡ እንዲያሳዩ ተደርገው አልተመሰረቱም። ለእያንዳንዱ ወቅታውም ሆነ የቆየ የሀገራችን ችግር ”የዲሞክራሲ እጦት” ነው ችግሩ እያሉ ህዝብን ማዘናጋት ለማንም አይበጅም።
ለ/  የሕዝቡን ባህል፣እምነት እና ታሪክ ያገናዘበ ፕሮግራም ለማስተዋወቅ ድፍረት ማጣት
ይህ ችግር ከመጀመርያው ከአመሰራረት እና ችግርን ከዲሞክራሲ ጋር ብቻ በማያይዝ ላይ በተመሰረተ የፖለቲካ ፓርቲ አንፃር የሚከሰት ይልቁንም ፕሮግራሙ እራሱ ይህኛውን ቡድን እዳያስከፋ፣ ያኛው እንዲደግፍ ወዘተ በሚል ፍርሃት የተሸበበ ማዕከላዊ መንገድ የያዘ ፕሮግራም ለመፈለግ የሚታታር አካህያድ ውጤት ነው። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የህዝቡን ባህል፣እምነት እና ታሪክ ያገናዘብ የፖለቲካ ፕሮግራም ማንንም ከፋው ወይንም ደስ አለው ሳይሉ በእውነታው ላይ ተመስርተው እንዳይቀርፁ የሚፈሯቸው ያለፉት 40 አመታት የሀገራችን የፖለቲካ መድረክ ክስተትን ነው። ኢትዮጵያ በመንግሥትነት የኖረችው አሁንም ልድገመው ላለፉት 40 አመታት አይደለም ለ ሶስት ሺህ አመታት ከዛም በላይ ነው።
የፖለቲካ ፓርቲ ፕሮግራሞች ሲቀረፁ ካለምንም ማጋነን መሰረት ያደረጉት ያለፉት 40 አመታት የአለማችንን እና የሀገራችንን የፖለቲካ የተደጋገመ እና አሰልቺ ቋንቋ ነው። የኢትዮጵያ ስነ-መንግስት ታሪክ ግን ሰፊ፣ ትልቅ እና ለቀሪው አለም ብዙ ቁም ነገሮችን ያበረከተ ነው።ለሙሴ አስተዳደርን ያስተማረ ኢትዮጵያዊው ዮቶርን የሚያስበው የለም። መገናኛ በሌለበት ዘመን የኢትዮጵያ የስነ-መንግስት ጥበብ መዋቅሩ ምን እንደነበር ሊመለከት የሚፈልግ የፖለቲካ ፓርቲ የለም። አውሮፓ እና አሜሪካ የተፃፉ መፃህፍትን ግን ለመጥቀስ የምያክለን የለም። ለአለም ልዩ ልዩ መንግሥታት ሕጎች የኢትዮጵያ ‘ፍትሃ ነገስት’ በምን መልክ ለግብአትነት አውሮፓውያን እንድተጠቀሙበት  ሊመረምር የሚፈልግ የለም። ኢትዮጵያ ሊኖራት የሚገባው መንግስት ሕዝብ ሊታገልለት እና ሊሞትለት የሚችለው ልዩ ጥበብ እኛው ጋር እንደተደበቀ ለሕዝቡ ገልፆ ካለፍርሃት ሊነገረው፣ ሊመራው እና ለእድገት ሊያበቃው የሚችል ጥበብ እንደሚያስፈልገው የፖለቲካ ፓርቲዎች ካላሰቡ ዛሬ የአስተሳሰብ ለውጥ የማመንጫ ሰዓት ላይ ይመስሉኛል። ከእዚህ በኃላ ኢትዮጵያውያን የምሸከሙት የመከራ ጫንቃም ሆነ የአስተሳሰብ ድግግሞሽ ጆሮ ያላቸው አይመስለኝም።
በአጠቃላይ
የኢትዮጵያ የመንግስት ስሪት ቅጥ ባጣ አምባገነኖች እጅ ከወደቀ አስርተ አመታት አስቆጠረ። ይብሱን ዛሬ ሀገራችን ሕልውናዋን በሚፈታተን ”መንግስታዊ የጎሳ ፖለቲካ” ውስጥ ተነክራ ህዝቧ ተስፋ በቆረጠ ስሜት ውስጥ ይገኛል። ታሪካዊ ጠላቶቿ የዛሬ 40 አመት የደገሱትን ድግስ ዛሬም አልቀየሩም። ኢትዮጵያን አረባዊ ለማድረግም ሆነ የፅንፈኛ እስልምና አላማ ያነገቡ ኃይሎችአንዴ  በኦሮሞ ሕዝብ ስም ሌላ ጊዜ ባለፈ ታሪክ ስም እያሉ የሚፈልጉትን ግብ ለማድረስ ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠሩ ነው። የኢህአዲግ/ወያኔ መንግስትም እንደ ማስፈራርያ ወጥ በብዙ መልኩ ድጋፉን ሲሰጣቸው እና ”ከእኔ ጋር ከልሆናችሁ አደገኛ ሁኔታ ይፈጠራል” እያለ ሲያስፈራራን ዘመናት አልፏል። አቦይ ስብሐት ይህንን ጉዳይ ደጋግመው  ለተለያዩ የዜና አውታሮች ገልፀውታል።
የህወሓት ፈጣሪው አቦይ ስብሐት አንድ ወቅት ለኢሳት በሰጡት ዘገባ ላይ ”ማንም በኃይል ስልጣን ሊይዝ አይችልም። ከሆነ ሌላው ክልል የራሱ ምክርቤት፣ በጀት ወዘተ አለው የራሱን አማራጭ ይወስዳል። ስልጣን የሚይዝ ኃይል አዲስ አበባን ብቻ ይዞ ይቀመጣል እንዴ?” በማለት ከኢህአዲግ በኃላ ኢትዮጵያ እንደምትበታተን ሁሉም የእራሱን መንግስት እንደሚያውጅ በተዘዋዋሪ ነግረውናል። አቦይ 22 አመት ቆይተው ሕዝቡን አለማወቃቸው አይደንቅም።
ቁም ነገሩ ግን ይህ አይደለም የአቦይ ንግግር የሚያመለክተው ኢህአዲግ/ወያኔ ኢትዮጵያን እየስራት ያለው ከእርሱ ውጭ እንዳትኖር ”እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” መርህ ላይ ተመስርቶ መሆኑን ነው። እዚህ ላይ ነው የተቃዋሚ የፖለቲካ ኃይሎች የህዝቡን ያለፈ ታሪክ፣ እምነት፣ ባህል እና ጥበብ ያገናዘበ አዲስ የፖለቲካ እና ምጣኔ ሃብታዊ  ራዕይ የሚያሳይ ፕሮግራም (”ዲሞክራሲ ዲሞክራሲ” ከሚል መዝሙር ባለፈ) ማሳየት ያለባቸው።
በመሆኑም የተቃዋሚ የፖለቲካ ኃይሎች እና ፓርቲዎች አዲስ እና ባለ ራዕይ ፕሮግራማቸውን በተናጥል ወይንም ግንባር በመፍጠር አዲስ መንፈስ በመፍጠር ማሳየት ይገባቸዋል። ይህ አዲሱ ሀሳባቸው ኢትዮጵያን በጎሳ እና በፅንፈኛ የእስልምና አስተሳሰብ ለመምራት የሚፈልጉትን ለማቀፍ አይድከም። እነኝህን ኃይሎች በሚቃረን መልኩ የህዝቡን የልብ ትርታ ባዳመጠ እና የማይረገጥ የመሰላቸውን በመርገጥ ለድል ይበቃሉ። ወደድንም ጠላንም የኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ በአንድነት ኃይሎች እና በበታኝ ኃይሎች ጎራ ተከፍሏል። ከአንድነት ኃይሎች ጎራ የዲሞክራሲ ጉዳይ ብቻ ሲለፈፍ ከበታኝ ኃይሎች በኩል ደግሞ የጎሰኝነት እና የፅንፈኛ እስልምና አስተሳሰቦች ይንፀባረቃሉ። አሁን ጥያቄው የአንድነት ኃይሎች ኢትዮጵያዊ ታሪክ፣እምነት እና ፍልስፍና የያዘ ጥበብ የተላበሰ ራዕይ ይዘው መውጣት እና ሕዝቡን ከአዙሪት ‘ዲሞክራሲ’ ከሚል ዲስኩር ማላቀቅ ነው።የኢትዮጵያ ሕዝብ ዛሬ ዲሞክራሲ አያስፈልገውም እያልኩ አይደለም። የህልውናው ጥያቄ ሲመጣ ግን ኢትዮጵያን በሁለት እግር የሚያቆም እና የሚያራምድ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ፍልስፍና በእጅጉ ተርቧል።ያን ጊዜ በኩራት እና በድፍረትይነሳል። በእዚህም አያቆምም  የበታኝ አስተሳሰብ የተጠናወታቸውን በምክርም በግሳፄም ያስተካክላል። የሩቅ ጠላቶቹን ያሳፍራል። የሚፈለገው ልማት እና እድገትም በራሱ ጊዜ መስመር ውስጥ ይስገባዋል። ከእዚያ በኃላ ማን ያቆመናል?
አበቃሁ።

Monday, January 13, 2014

የመከላከያ ሰራዊት የተለያዩ ወቅታዊ ጥያቄዎች እያቀረቡላቸው መሆኑ ታወቀ

January13/2014

ይህ በታህሳስ 23/2006 ኣ/ም የማእከላዊ እዝ የበላይ ኣመራሮች በተገኙበት ስብሰባ ላይ እንደ ኣንድ ትልቅ ኣጀንዳ ሆኖ የቀረበ። ኣብዛኛው የሰራዊቱ ኣባል ማግኘት የሚገባው ጥቅም ባለማግኘቱ በሰራዊቱ ውስጥ የመቀጠል ፍላጎቱ ያበቃና የሞተ በመሆኑ ምክንያት ክውትድርና ኣለም ተሰናብቶ የግል ሂወቱ መምራት እንደሚፈልግ ላቀረቡት ጥያቄ በስብሰባው ውስጥ የተካፈሉት የበላይ ኣመራሮች የቀረበው ጥያቄ ሰምተው እንዳልሰሙ በመምሰል ተገቢ መልስ ሳይሰጡበት እንዳለፉ ለማወቅ ተችለዋል::

መረጃው በማስከተል በስብሰባው ውስጥ የተገኙ የሃያሰዎስተኛ ክፍለጦር ኣዛዥ ብርጋዴል ጀነራል በላይ ስዩም፤ የሰላሳ ኣንደኛ ክፍለጦር ኣዛዥ ብርጋዴል ጀነራል ድሪባና፤ የሰላሳ ሰዎስተኛ ከፍለጦር ኣዛዥ ብርጋዴል ጀነራል ከበደ ፍቃዱ እኛ ኣዲስ ቶሻሚ በመሆናችን ብዙ ተቀባይነት የለንም ኣታስቸግሩን ብለው መልስ እንደሰጥዋቸው ለማወቅ ተችለዋል::

ይህ በንዲህ እንዳለ ከሰራዊቱ ውስጥ ለመኪና ሾፌርነት ስልጠና ተመልምለው ኣዲ ቡኽራይ ወደ ተባለው ቦታ የታላኩ ወተሃደሮች። ስልጠናውን በመተው ወደ ክፍላቸው ተመልሰው የ 7 ኣመት ኣገልግሎታችን ስለ ጨረስን ከሰረዊት የመሰናበት መብታችን ይረጋገጥልን ብልው ጥያቄ ማቅረባቸው ተገለጸ::

ወደ ስልጠናው ከተላኩ ቦሃላ ተመልሰው ወደ ክፍላቸው ከተመለሱ ምልምል ወተሃደሮች ስም ለመጥቀስ። ወ/ር ማእርግ ሰፍየ፤ ወ/ር ተሻለ ኣየነው፤ ወ/ር ክብሮም ኣስረስና ሌሎች ሲሆኑ። በተለይ ከ 1990 ኣ/ም ባሃላ የተቀጠሩ የሰራዊቱ ኣባላት የደሞዝ ይሁን የማእርግ እድገት መብታቸው እንዳላገኙና በላዩ ላይ ለኣባይ ግድብ፤ ለትምህርት ቤትና ሌሎች መሰረተ ልማቶች እየተባለ ደሞዛቸው እየተቆረጠ በመሆኑ ምክንያት ተማርረው ከሰራዊቱ ለመልቀቅ ስንብት እየጠየቁ መሆናቸው መረጃው ኣክሎ ኣስረድተዋል::

ዴ.ም.ህ.ት

“አጼ ምኒልክ መልካም መሪ አልነበሩም የሚሉ ካሉ መብታቸው ነው” – ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት

January13/2014

ከሕብር ራድዮ ጋር ቃል የተመላለሱት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ‘አጼ ምኒልክ መልካም መሪ አልነበሩም የሚሉ ካሉ መብታቸው ነው፤ እኛ አጼ ምኒልክን እየዘከርን ያለነው በሃገር ግምባታ ላይ ባደረጉት መልካም ነገር ነው” አሉ። ኢንጂነሩ “አጼ ምኒልክን መልአክ ናቸው ብለን ታቦት ባናስቀርጽም ለአፍሪካ ሕዝብ ነፃነት ተምሳሌት በመሆናቸው እንዘክራቸዋለን” ብለዋል። “ጡት ቆረጡ ብሎ በመናገር በሃያንደኛው ክፍለ ዘመን የፖለቲካ ጥቅም አገኛለሁ ብለው የሚያስቡ ካሉ ስህተት አለበት” ሲሉ የተናገሩበትን ይህን ቃለ ምልልስ ያድምጡት።

የህወሓት መፈክር፡ ‘የአማራ የበላይነት ይውደም!’ (በአብርሃ ደስታ)

January13/2014

ግርማይ ገብሩ የቀድሞ የህወሓት ታጋይና የአሁን የቪኦኤ (VOA) ዘጋቢና ደራሲ ነው። ዓላማዬ ስለ ግርማይ ገብሩ ለመፃፍ አይደለም፤ ግርማይ በፌስቡክ ገፁ ስላሰፈረው መረጃ ለመዋስ እንጂ። መረጃው ከዚህ በፊትም አውቀው ነበር። ግን ለማስረጃ ያህል ግርማይን ልጥቀስ: ምክንያቱም ግርማይ የህወሓት ታጋይ ነበርና።

ግርማይ በ1969 ዓም የህወሓት (ተሓህት) ሦስቱ መፈክሮች ሲጠቅስ የመጀመርያውና ዋነኛው አድርጎ የፃፈው “አፄነት፣ መስፍንነትና የአማራ የበላይነት ይወድማሉ” ይላል።

በትግርኛ “ካብ ጭርሖታት ህወሓት 1969 ዓም: ሃፀይነት፣ መስፍንነትን ናይ አምሓራ ዕብለላን ዓነውቲ እዮም!” ይላል። ግርማይ ገብሩ አልተሳሳተም። ከህወሓቶች ጋር የማልስማማበት ግን ነጥብ አለኝ።

እርግጥ ነው። እኔም አፄነትና መስፍንነትን እንደ ስርዓት አልቀበልም። ምክንያቱም አፄነትና መስፍንነት (እንደ ስርዓት) ላሁኗ ኢትዮጵያ አይመጥኑም። የአፄነትና መስፍንነት ስርዓት በኢትዮጵያ ታሪክ እዚ ግባ የሚባል ለውጥ አላመጣም። ስለዚህ እኛ የሚያስፈልገን ዘመናዊ (ከዘመኑ ንቃተ ህሊናችን ጋር አብሮ የሚሄድ) የህዝብ አስተዳደር (ዴሞክራሲ) እንጂ ንጉስነት (የሰው ገዢነት) አይደለም። የምንፈልገው የሕግ የበላይነት እንጂ የንጉስ የበላይነት አይደለም።

ግን አፄነትና መስፍንነት እንደ ስርዓት ባልቀበለውም የንጉሳውያን ቤተሰቦችና መሳፍንቶች መጥፋት አለባቸው ብዬ ግን አላምንም። እኔ ብሆን እነኚህ የንጉስ ቤተሰቦችና መሳፍንት ቁልፍ የመንግስት ስልጣን አልሰጣቸውም ነበር። በሀገራቸው በሰላም እንዲኖሩ ግን እፈቅድላቸው ነበር። ምክንያቱም እንደማንኛውም ሰው ዜጎች ናቸው፤ ለሀገራቸው በተቻላቸው መጠን አስትዋፅዖ አድርገዋል። ስለዚህ ንጉሳዊ ቤተሰብና መሳፍንት ስለሆኑ ብቻ መጥፋት አለባቸው ብዬ አልፈርድም። እንደ ጠላትም አላያቸውም፣ እንደ ዜጎች እንጂ።

ህወሓት ግን በመፈክር ደረጃ በጠላትነት ፈረጃቸው። በተግባርም አጠፋቸው፣ ገደላቸው። በንጉሳዊ ቤተሰብና መስፍንነት ዝንባሌዎች ሰበብ ብዙ የተምቤን፣ ዓጋመ፣ እንደርታ፣ ዓድዋ፣ ሽረ፣ አክሱም ወዘተ መሳፍንቶች እንዲጠፉ ተደረገ። ‘ትግራይ ከመሳፍንቶች ነፃ ወጣች’ ተባለ። እውነታው ግን ‘ትግራይ ተገደለች’ መባል ነበረበት። መሳፍንቶች ከስልጣን ማውረድ እየተቻለ መግደል ምን አመጣው (ህወሓቶች ከስልጣን ማውረድ እየተቻለ መግደል ለምን ያስፈልጋል)?

ባጠቃላይ መሳፍንቶቹ ሲወድሙ ትግራይ ወደመች። አሁን በትግራይ የተቃውሞ መንፈሱ የተዳከመው በመስፍንነት ሰበብ ብዙ ብቁ ሰው ስለተፈጀብን ነው የሚል እምነት አለኝ። በህወሓት የተገደሉብንን ያህን በሌላ ስርዓት አልተገደሉብንም። ስለዚህ መሳፍንቶች ከስልጣን በማውረድ (መሳፍንቶችን ሳይሆን መስፍናዊ ስርዓቱ) ከህወሓቶች ጋር እስማማለሁ። መስፍናዊ ስርዓቱ ለማጥፋት መሳፍንቶቹ ማጥፋት ከሚል የህወሓት መፈክር ወይ መርህ ግን አልስማማም።

ሌላውና መሰረታዊ የህወሓት ችግር “የአማራ የበላይነት ይውደም!” የሚል መፈክር ነው። እኔም ብሆን የማንም ሰው ወይ ብሄር ወይ ሌላ አካል የበላይነት አልቀበለም። የቴድሮስ ወይ ዮሃንስ ወይ ምኒሊክ ወይ ኃይለስላሴ ወይ መንግስቱ ወይ መለስ ወይ ኃይለማርያም ወይ አማራ ህዝብ ወይ ትግራይ ህዝብ ወይ ኦሮሞ ህዝብ ወይ ሌላ … የበላይነት አልቀበልም። እኔ የምቀበለው የበላይነት ‘የሕግ የበላይነት’ ብቻ ነው። የሌላ የማንም የበላይነት አልቀበልም።

እንደ ፖለቲካ ድርጅት አንድን ህዝብ ዒላማ አድርጎ መነሳት ግን ስህተት ብቻ ሳይሆን በሽታ ነው። ህወሓት (ተሓህት) የአማራን ህዝብ ዒላማ አድርጎ ሲነሳ፣ ሌሎች የህወሓት ተቃዋሚዎች ደግሞ በህወሓት ምክንያት የትግራይን ህዝብ ዒላማ ሲያደርጉ ዉጤቱ ምን ይሆናል? አንድን ህዝብ ከሌላ ህዝብ ጋር የማጣላት ስትራተጂ የፖለቲካ ዕብደት ነው። ህዝብና ገዢው መደብ አለመለያየት (አንድ እንደሆኑ አድርጎ ማሰብ) የፖለቲካ እውቀት ማነስ ዉጤት ነው። ስርዓቱ መቃወምና መታገል እየተቻለ ህዝብን ዒላማ አድርጎ በህዝቦች ላይ መተማመን እንዳይኖር መትጋትና በህዝቦች መካከል ጥላቻ እንዲነግስ መስራት ጠባብነት ነው።

አንድን ህዝብ የበላይነት ሊይዝ አይችልም። አንድን ቡድን ግን በአንድን ህዝብ ስም በመነገድ ሌሎችን ሊበድል ይችላል። የሰው የበላይነት (በህዝቦች ላይ) ሊተገብር ይችላል። ህዝብ እንደ ህዝብ ግን ሌላውን ህዝብ ሊበድል አይችልም። ህወሓት የትግራይን ህዝብ እንደሚወክል ይነግረናል። የትግራይን ህዝብ እወክላለሁ እያለ ሌሎች ህዝቦች (የትግራይን ጨምሮ) ይበድላል። ሌሎች ህዝቦች (የትግራይ ዉጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን) ደግሞ በህወሓት ስርዓት ሲበደሉ በትግራይ ህዝብ የተበደሉ አድርገው ያስባሉ። ግን ስህተት ነው። መታረም አለበት። የትግራይ ህዝብ ለራሱ በህወሓት አገዛዝ የሚበደል ነውና።

“የአማራ የበላይነት” የሚባለው የህወሓት በሽታ እስካሁን ፈውስ አላገኘም። በመርህ ደረጃ ህዝብን ዒላማ አድርጎ ህዝብን ለመታገል መነሳት ስህተት ነው ብያለሁ። በፖለቲካ ህዝብን ዒላማ አይደረግም። ምክንያቱም የፖለቲካ ዓላማ ህዝብን ማገልገል እንጂ ህዝብን መጨቆን አይደለም። ስለዚህ ህዝብን የመበደል ዓላማ መያዝም መተግበርም የህሊና ወንጀል ነው። ህወሓቶች ይህን በሽታ (“የአማራ የበላይነት” መፈክር) አልተዋቸውም። አሁንም “ፀረ አማራ” እንቅስቃሴዎች አሉ። የህወሓት የአሁኑ ስትራተጂ “እኛ ከስልጣን የምንወርድ ከሆነ ከአማራ ጋር አብረን አንቀጥልም” የሚል ገንጣይ አስተሳሰብ እያራመዱ ይገኛሉ። “እኔ ከሌለሁ ሠርዶ አይብቀል …” ዓይነት ስትራተጂ መሆኑ ነው። በጣም የሚገርመው ነገር ፀረ ብአዴንም መነሳታቸው ነው። ለነሱ ከስልጣን ከሚወርዱ ኢትዮጵያ ብትበታተንና ትግራይን አስገንጥለው ትግራይን እየጨቆኑ ቢገዙ ይመርጣሉ።

ግን ይህን “አማራ” የሚባል ህዝብ መቼ ይሆን የበላይነት ይዞ ሌሎች ህዝቦችን የበደለው? አንድን ህዝብ እንዴት ሌላውን ህዝብ ይበድላል? ህዝብ ህዝብን ሊበድል አይችልም። ምክንያቱም አንድን ህዝብ ሌላውን ህዝብ መበደል ከጀመረ (ከቻለ) ህዝብ መሆኑ ቀርቶ ገዢ መደብ (elite) ሁነዋል ማለት ነው። ገዢ መደብ ከሆነ ደግሞ ህዝብ አይደለም። ገዢ መደብ ስርዓት ነው። ህዝብና ስርዓት ደግሞ ይለያያሉ።

ምናልባት የህዝብ የበላይነት አለ የምንለው ህዝብን የሚያስተዳደር (የሚገዛ) ስርዓት ከህዝቡ የወጣ ሲሆን ይሆን? ይህም አሳማኝ አይደለም። ምክንያቱም ገዢ ሁሌ ከህዝቡ ነው የሚወጣው (የቅኝ ግዛት ካልሆነ በስተቀየር)፤ ገዢ ከህዝቡ እንጂ ከማርስ አይመጣም። የኢትዮጵያ መሪ ከኢትዮጵያ ህዝብ ይወጣል። በኢትዮጵያ ብዙ ብሄሮችና ብሄረሰቦች አሉ። ስርዓቱ ከሁሉም ህዝቦች ሰዎች ይኖሩታል። መሪ ግን አንድ ነው የሚሆነው። ያ አንድ ሰው (መሪው) ከአንድ ብሄር ሊሆን ይችላል። ያ አንድ ሰው ስልጣኑ ተጠቅሞ ሌሎች ህዝቦችን ሊበደል (ወይ ሊጠቅም) ይችላል። ሰውየው የፈጠረው ስርዓት ለህዝቡ ቢጎዳም ቢጠምም ከስርዓቱ ይገናኛል እንጂ መሪው ከመጣበት ብሄር ጋር አይገናኝም። ስለዚህ ገዢዎች የሚወክሉት የፈጠሩትን ስርዓት እንጂ የመጡበትን ብሄር አይደለም።

የደርግ ስርዓት ሲበድለን፣ “አማራ በድሎናል” ይሉናል። የኃይለስላሴ ስርዓት ሲበድለን “አማራ በድሎናል” ይሉናል። የምኒሊክ ስርዓት ሲበድለን “አማራ በድሎናል” አሉን። የህወሓት ስርዓት ሲበድለንስ ማን በደለን ሊሉን ነው? የትግራይ ህዝብ? አይሆንም። ምክንያቱም የትግራይ ህዝብ የትግራይን ህዝብ ይበድላል? አንድን ህዝብ ራሱን ይበድላል? በደል ሁሉ ወደ አማራ ህዝብ ለምን? ስርዓትና ህዝብ ማገናኘት የፖለቲካ ኪሳራ ያስከትላል።

ግን እስቲ ይሁን፤ መሪዎች የመጡበትን ብሄር ይወክላሉ እንበል (ስህተት ቢሆንም)። እነሱ (መሪዎቹ) ሲበድሉ የመጡበት ብሄር በበዳይነት ተፈርጆ እንደ ጠላት ይቆጠር እንበል። የአማራ ህዝብ መቼ ይሆን በመሪዎቹ አድርጎ ሌሎች ህዝቦችን የገዛ (የበደለ)? ያለፉ ጨቋኝ ስርዓቶች አማራ ነበሩ ያለው ማነው? አማርኛ የተናገረ ሁሉ አማራ አይደለም። እስቲ የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ መሪዎች እንመልከት።

ብዙ ግዜ የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ታሪክ የሚጀምረው ከአፄ ቴድሮስ ነው (ወይም ከዚሁ እንጀምር! ምክንያቱም ከአፄ ቴድሮስ በፊት ኢትዮጵያ በመሳፍንቶች ነበር የምትተዳደረው። በዘመነ መሳፍንት መሳፍንቶች የራሳቸውን ህዝብ (ብሄር) ይገዙና ይበድሉ ነበር)። “አማራ” ተብሎ ከተሰየመው አከባቢ የሚወለድ ገዢ ቴድሮስ ነው። አፄ ቴድሮስ ኢትዮጵያ አንድ ለማድረግ በዛን ግዜ የነበሩ መሳፍንቶች ተዋጉ። አፄ ቴድሮስ ዉግያው የጀመሩት በአማራ መሳፍንቶች (የጎጃም፣ ወሎና ጎንደር) ነበር። ቴድሮስ “ከአማራ ስለመጣሁ፣ አማራ ስለምወክል፣ የአማራ መሳፍንቶች ማጥፋት የለብኝም” አላሉም። (ህወሓት ለትግራይ መሳፍንቶች እንዳደረገው ሁሉ)። ስለዚህ አፄ ቴድሮስ አማራን ወክለው ሌላው ኢትዮጵያዊ አልበደሉም (ከበደሉም ለሁሉም ነው)። ስለዚህ “በአማራ ህዝብ ተገዛን” የሚለው ክስ “በአፄ ቴድሮስ ተገዛን” የሚል እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁ።

የአማራ ተወላጅ የሆነ የኢትዮጵያ ገዢ ቴድሮስ ብቻ ነው ብዬ አስባለሁ (ጉዳዩ ለታሪክ ተመራማሪዎች ልተወው እንዳልሳሳት፤ ከተሳሳትኩ እታረማለሁ)። ዮሃንስ አማራ አልነበረም፣ ምኒሊክ አማራ አልነበረም፣ ኃይለስላሴ አማራ አልነበረም፣ መንግስቱ አማራ አልነበረም፣ መለስ አማራ አልነበረም፣ ኃይለማርያም አማራ አይደለም። ማነው አማራ?

ምናልባት “የአማራ ገዢዎች” የምንለው ግለሰቦቹ (ንጉሶቹና መሪዎቹ) ሳይሆን ስርዓቱ ነው ካልን ያው ስርዓቱማ ከሁሉም ህዝቦች ተወካዮች አሉበት። አማራ ለብቻው ገዥ ነበር ማለት አንችልም። ምናልባት ገዢዎቹ አማርኛ ስለሚናገሩ ነው ካልን ደግሞ አማርኛ የተናገረ ሁሉ አማራ አይደለም። አቶ መለስም አማርኛ ይናገር ነበር። አፄ ዮሃንስም አማርኛ ይናገሩ ነበር (አማርኛ የኢትዮጵያ ኦፊሽየላዊ የስራ ቋንቋ እንዲሆን የወሰኑት አፄ ዮሃንስ ናቸው የሚል መረጃ አለኝ፤ ‘መረጃ’ እንጂ ‘ማስረጃ’ አላልኩም)።

የአማራ ህዝብ እንደ ማንኛው የኢትዮጵያ ህዝብ በኢትዮጵያ ገዢዎች ሲሰቃይ የነበረ ነው። ባልበላበት በልተሃል፣ ባልገዛበት ገዝተሃል ሲባል ይገርማል፤ ልክ እንደ ትግራይ ህዝብ። የትግራይ ህዝብ ሳይበላ በልተሃል፣ ሳይገዛ ገዝተሃል ይባላል፤ ህወሓት በበላው፣ ህወሓት በገዛው። ህወሓት ትግርኛ ተናጋሪ ስለሆነ ከትግራይ ህዝብ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም (በፖለቲካ መልኩ)። ያለፉ ገዢዎች አማርኛ ስለሚናገሩ ከአማራ ህዝብ ጋር የሚያገናኛቸው ነገር የለም። ህዝብ ሌላ ገዢ ሌላ።

ባጭሩ ፀረ ህዝብ አቋም መያዝ ተገቢ አይደለም (ለማንኛውም ህዝብ)። ሰው የፈለገውን የፖለቲካ አመለካከት መያዝ ይችላል። “የቀድሞ ስርዓት አባላት …” ምናምን እያልን አንፈርጅ። የህወሓት አባላት ለሌሎች ሰዎች የቀድሞ ስርዓት አባላት፣ ናፋቂዎች ወዘተ እያላቹ ስትፈርጁ እናንተም ራሳችሁ ከህወሓት ስርዓት በኋላ “የቀድሞ ስርዓት አባላት ..” ምናምን እየተባላቹ ስማቹ ይጠፋል፣ የፈለጋችሁን የፖለቲካ ፓርቲ አባል የመሆን መብታቹ ይገደባል። አሁን በሌሎች ላይ የምትፈፅሙትን ስም የማጥፋት ተግባር በናንተ (በራሳቹ) ይፈፀማል።

ስለዚህ እናስተውል። ከጥላቻ ፍቅር ይሻለናል። ጥላቻ ይውደም። አሜን!

It is so!!!

የህዝባዊ አንድነትና ሀይል የወያኔ ህወኃትማጥፊያ መዳኒት (ሮባ ጳዉሎስ)

January13/2014


unity



ካለመታደል  ሀገራችን ዛሬም ሰላም ፍትህና ዲሞክራሲ የሰፈነባት በልማትና በእድገት ጎዳና የምትራመድ ሀገር አልሆነችም። ለዚህም በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም እንደ ዓቢይ ምክንያት ተደርጎ የሚቀርበው የህዝብን ይሁንታን ያገኘ፡ ህዝብን በእኩልነት የሚዳኝ፡ ህዝባዊና ዲሞክራሲያዊ የሆነ መንግሥት አለመመስረቱ፡ አገርና ህዝብ የሚተዳደሩበት ዲሞክራሲያዊ ህገ መንግሥት አለመኖሩ ነው። እስከዛሬ በተጨባጭ እንደታየው በ ኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ የተፈራረቁበት ገዥዎቹ በየበኩላቸው አንዱ ከሌላው የሚለዩባቸው ባህርያት ቢኖራቸውም ሁሉንም ግን አንድ የሚያስመስሏቸው ባህርያትም አሏቸው። እነሱም ሁሉም በኃይል ሥልጣን መያዛቸው፡ አምባገነንነታቸው፡ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ማራመዳቸው፡ በህዝብ መካከል የጋራ መተማመንና ከበሬታን ለመፍጠር፡ ሁሉም ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን በሀገሪቱ ለማስፈን አለመቻላቸው ደግሞ ዛሬ ለሁሉም በግልጥ እየታየ ያለ ነው። በዚህም የተነሳ በሀገራችን ለብሔራዊ ክብርና ነፃነት፡ ለዲሞክራሲ፡ ለማህበራዊ ፍትህ፡ ለሰላምና ለእኩልነት የሚታገሉ ኃይሎች የሰላማዊ ለውጥ በሮች ስለተዘጉባቸው የአ መፅን ጎዳና እንዲከተሉ የሚጋብዝ በር ተቀዶ ይገኛል።
በሌላ በኩል ደግሞ በሀገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ መረጋጋት ንእዲፈጠር፡ ሕዝቡም አስተማማኝ ሰላምና ፀጥታ አግኝቶ ያለስጋት ለመኖር እንዲችል፡ የዳኝነት ተቋሞች ነፃ ሆነው የሚሠሩበት፡ የህግ የበላይነት የተረጋገጠበት ሁኔታ እንዲፈጠርና፡ ህዝቡም በህግና ሥርዓት መኖር ላይ እምነት እንዲያድርበት ለማድረግ እንዲቻል፡ ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊ ተቃዋሚ ኃይሎች በተናጠልም ሆነ በኅብረት በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል። ሆኖም እስከዛሬ የተደረጉት ጥረቶችን ሁሉ በማምከን ወያኔ የሰላምና የእርቅ መሰናከል ከመሆኑም ባሻገር በንፁሃን ዜጎች ደም ሰላምን አጠልሽቶታል። ወያኔ ስለ ሰላምና እርቅ ሊሰማም ሊነጋገርም እማይችልበት የደም ስካር ላይ ደርሷል።
ብአዴን ቢመጣ ኦህዴድ ቢመጣ ደህዴን ቢመጣ የሚለወጥ ነገር አይኖርም። ጠንከር ያለ ለለውጥ የተዘጋጀ – አስከ ሞት የቆረጠ -ጠቅላይ ሚኒስተር ስልጣን አገኘ ማለት የህወሃት የበላይነት እና ፈላጭ ቆራጭነት ፍላጎት ፈተና ይገጥመዋል ማለት ስለሆነ! ህወህት የበላይነቱን ለማሰጠበቅ የፈጠራቸው የመንግስት ስልጣን አደረጃጀት አና ተቋማት ዛሬም በሙሉ ሃይላቸው አሉ።  የህወሃት ፈላጭ ቆራጭነት ሳይዳከም ለውጥ አይመጣም። የህወሃት ፈላጭ ቆራጭነት መሰረቱ ደሞ ከምንም በላይ ወታደራዊ ሃይሉ ላይ የተመሰረተ አንደሆነ የአደባባይ ሚስጥር ነው። በደህነንት ቢሮ ያሉትን የህወሃት አመራሮች ከታች ያሉት ማዳክም የሚችሉበትን አጋጣሚ አና ሁኔታ ተጠቅመው አስካላዳከሙት ደረስ የህወሃት የስልጣን የበላይነት ትርጉም ባለው ሁኔታ እክል ሊገጥመው አይችልም።
ሌላ ሌላውን ትተን መሰረታዊ የሆነ ህገ-መንግስታዊ ማሻሻያ ያስፈልጋል፣ የፍትህ ስርዕቱ የፍትህ ስርእት መመስልም መሆንም አለበት፣ የነጻው ፕሬስና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ህዳሴ አንመራለን አየተባለ በመካከለኛው ዘመን አና ከዛ በፊት ከነበረው አንደነበረው በሰይፍ አና በሰደፍ መያዝ የለበትም። አነኚህ ወሳኝ ርምጃዎች በአዝጋሚ ለውጥ ይመጣሉ ብየ አላስብም። የአዝጋሚ ለውጥ ዲስኩር (ፍላጎት ካለ ፍላጎትም) ጭራሽ ወደማይቀልበስ የባርነት ዓለም አና ዘመን የመውሰጃ ከፓለቲካ ዘዴ ሊሆን ይችላል።  ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ ፓለቲካ መሪዎች ዘብጥያ ሲጣሉ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የፈጠሩትን ዓይነት ጫና መፍጠር ስላልተቻለ አንኳን መሰረታዊ የፕሬስ ነጻነት አና በነጻነት ያለገደብ የመደራጀት መብት የሚከበርበት ፍንጭ ሊገኝ ቀርቶ የታሰሩትን ጋዜጠኞች አና የፓለቲካ መሪዎች ማስፈታት አንኳን አልተቻለም። ጭራሽ መብታቸው ተረግጦ ያላግባብ አስር ቤት የተጣሉ ኢትዮጵያውያን ዛሬ ድረስ “አሸባሪ” አየተባሉ አየተፌዘባቸው ነው ያለው። አቶ ኃይለማርያምም ፌዙን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ አያስተጋቡት ነው።
ከበቀለበት የተጋጋበት አንዲሉ የ”በሳሉ መሪ ራዕይ” ዜማ ከህወሃት አባላት በእህት ድርጂቶች የፓለቲካ አላዋቂዎች አና መሪዎች ይበልጥ ተዜመ! በአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝም ተሰማ። ችግሩ የለውጥ ጥያቄ ማድበስበሻ ሆኖ ለረዢም ጊዜ ሊቆይ አይችልም። በውሽት ላይ የተመሰረተ ፐሮፓጋንዳ ስር ሊይዝ አይችልም።አንዴት ይሄን ማየት አቃታቸው?!የሕዝባችን መከራና ሰቆቃ እየከፋ ሄደ።  የተጨቆነዉ ሕዝብ ተነሳስቶ ለመብቱ ሲታገል ጨቋኝ መንግሥታት ለዉጥ እንዲያደርጉ ይገደዳሉ፤ ካለዚያ በተባበረዉ የሕዝብ ኃይል ተንኮታኩተዉ ይወድቃሉ። የታገለዉ ለዉጥ ያመጣል፤ ያልታገለዉ ቁጭ ብሎ በባርነት ሲገዛ ይኖራል፤ ቁጭም ባለበት ይሞታል ማለት ነው። የለዉጥ ባለቤት ሁሌ ሕዝብ መሆን አለበት። ህዝቡ ትግሉን በሚገባ እንዲያቀናጅ የትግል መሪ ይፈልጋል።
ስለዚህ የተቃዋሚ የፖሊቲካ መሪዎች ታላቅ ኃላፊነት ይጠበቅባቸዋል። ያገራችንን ጭብጥ ሁኔታ ስንመረምር ግን በሁለቱም በኩል ታላላቅና ተደጋጋሚ ድክመቶች ታይተዋል። አምባገነን መንግሥታት ለዘለዓለም ካልገዛን ሲሉ የተቃዋሚ ድርጅቶች ኅብረታቸዉን ማጠናከር ስላልቻሉ የጨቋኝ መንግሥታትን ዘመናት ሲያራዝሙ ቆይተዋል።ወያኔ/ኢሕአደግ ለዘለዓለም ሊገዛ አይችልም፤ ለሁሉም ጊዜ አለዉና።ትግሉ ይበልጥ መፋፋም፡ ይበልጥ መጨስ፡ መጋጋም፡ መንደድ ይጠበቅበታል። ትግሉን ለማፈንና አቅጣጫውን ለማሳት የወያኔ መንጋ እየተሯሯጠ ነው። በውጭ ያለውንም የሕዝብና የድርጅቶችን ተቃውሞ ቢቻለው ለማዳፈን፡ ካልሆነለት ደግሞ ለማዳከም፡ በአሁኑ ወቅት የወያኔ ከፋፋይ ቡድን በየቦታው በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ እያየን ነው። ይህ ቡድንም፡ ምሁር ነን፡ አስታራቂ ነን፡ ሽማግሌ ነን ወይም ታጋይ ነን በሚሉ መሰሪዎችም እየተደገፈ ነው። የሕዝብ ክንድ ይላላ፡ ይደክም ዘንድ፡ በከፋፋይ ሴራ የተሰማሩትን ነቅቶ መጠበቅ፡ ትግሉን መከላከል ብቻ ሳይሆን ወያኔ ለባሾችን፡ ሰላዮችን ሳንፈራ እየመነጠርን ማጋለጥ ይኖርብናል። ዘረኛው ቡድንና ጭፍሮቹ የሕዝቡን ትግል ለመከፋፈል ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እየጣሩ ናቸውና። ሕዝብ አንድነቱን ጠብቆ፡  የወያኔን ቡድን ለአንዴም ለሁሌም ለማስወገድ አስፈላጊውን መስዋእ ትነት እየከፈለ ባለበት ወቅት የፖለቲካ ድርጅቶችን እገዛና አመራር ይጠይቃል። የሕዝብ አሸናፊነት አጠራጣሪ ባይሆንም፡ አሸናፊ ለመሆን ግን መታገል መቅደም እንዳለበት ምን ጊዜም መረሳት የለበትም። ለዚህ መሠረቱ ግን ከራስ ጋር እየታረቁ፡ ከወገን ጋር እየተስማሙ በጋራ ዓላማና ብሔራዊ እጅንዳ ዙሪያ ተሰባስቦ በጋራ መታገል ብቻ ነው።
በዓለም ታላቅ ዝና ያተረፉት የግ/ቀ/ኃ/ሥና በአፍሪቃ አህጉር መሬትን ያንቀጠቀጠዉ የደርግ መንግሥት ቀናቸዉ ሲደርስ እንዴት እንደመነመኑና እንደከሰሙ መዘርዘር አይኖርብኝም፤ በታሪክ ፊት ተቀምጧልና። በሩቁም በእነ አሜሪካ ለረዥም ዓመታት ሲረዱና ሲደገፉ በነበሩት በእነ ሞቡቱ፤ የሻህ ንጉሥ፤ ሆስኒ ሙባረክ፤ ወዘተ ላይ በመጨረሻ የደረሰዉን ዉርደት መገንዘብ ያስፈልጋል። ተቃዋሚ የፖሊቲካ ድርጅቶች ነን የሚሉትና በተግባር ግን የጭቆናን ዘመን የሚያራዝሙ በሙሉ ካለፉት ስህተቶች ገና ሊማሩ አልቻሉም፤ ・ድር ቢያብር እንበሳ ያስር・ የተባለዉን ቅዱስ አሳብ ደጋግመዉ መናቃቸዉ ያስተዛዝባል። ቁርጥ ያለ አቋም ያስፈልጋል፤ ከዛፍ ዛፍ መዝለል ዬትም አያደርስም። ለጊዜያዊ ጥቅማ ጥቅሞች በርካሽ መገዛትና አገርን መሸጥ በሰማይም በምድርም ያስጠይቃል። ቀኑ ሲደርስ ራቆታችንን ወደምድር እነደመጣን ሁሉ ራቆታችንን ወደዚያዉ እነደምንመለስ አንርሳ!!!
ነገርግን በህብረት ለሀገር ታሪክ ሰርቶ ማለፍ ዘላለማዊ የትዉልድና የሀገር ክብር ነዉ!!!
ከጎልጉል የተወሰደ

‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ የጥላቻ ፖለቲካ ማብቃት አለበት››

January12/2014


‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ የጥላቻ ፖለቲካ ማብቃት አለበት››
ኢንጂነር ግዛቸው ሺፈራው፣  የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር
የምርጫ 97ን ቀውስ ተከትሎ ወደ እስር ቤት ከገቡት የቀድሞዎቹ የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ (ቅንጅት) አመራሮች መካከል አንዱ የነበሩት ኢንጂነር ግዛቸው ሺፈራው፣ በቅርቡ የአንድነት ለፍትሕና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡ ስለአዲሱ ሊቀመንበርነታቸው፣ ስለመጪው ዓመት ምርጫና ሌሎች ጉዳዮች ነአምን አሸናፊ አጋግሯቸዋል፡፡ 
ሪፖርተር፡- አንድነት የወጣቶች ፓርቲ ነው ይባላል፡፡ ነገር ግን አመራሩ ላይ ወጣቶች አይታዩም በማለት የሚተቹ አሉ፡፡ የእርስዎን ዳግም ሊቀመንበር ሆኖ መመረጥንም እንደ ምሳሌ ያነሱታል፡፡ ለምንድነው ወጣቶች ወደ አመራር የማይመጡት? 
ኢንጂነር ግዛቸው፡- ይህንን ጥያቄ መጠየቅ ያለባቸው መራጮች ናቸው፡፡ መራጮችንና የአንድነት አባላትን መጠየቅ ነው፡፡ በመሠረቱ አንድነት የወጣቶች ፓርቲ ነው፡፡ ባለፈው ሥራ አስፈጻሚም ሆነ በብሔራዊ ምክር ቤቱ የወጣቱ ተሳትፎ ከፍተኛ ነበር፡፡ በጠቅላላ ጉባዔው ሰባ በመቶ አካባቢ ወጣት ነው፡፡ የተወዳደርኳቸው ሰዎችም ወጣቶች ናቸው፡፡ ስለዚህ ይህ ነገር መጠየቅ ያለባቸው አባላትና ጉባዔው ናቸው፡፡ 
መጠየቅ ያለበት እኔ ፍላጎት ኖሮኝ ወጣቶችን ወደታች ገፍቼ ድርጅታዊ ሥራ ሠርቼ ብመጣ ኖሮ ነበር፡፡ ወጣቶችን ወደታች ተጭነሃል ማለት ይቻል ነበር፡፡ ዋናው ማየት ያለብን ጠቅላላ ጉባዔውና አጠቃላይ ሒደቱ ዲሞክራሲያዊ ነበር ወይስ አልነበረም ነው፡፡ በእኔ ግምት አንድነት ፓርቲ ለዲሞክራሲያዊ አሠራር ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ፓርቲዎች የሚበልጠው ያለ አይመስለኝም፡፡ ለዚህም የምገልጸው በምክር ቤታችንም በሕገ ደንባችን መሠረት የምንሰበሰበው በሦስት ወር አንዴ ነበር፡፡ ምክር ቤቱ ግን በዓመት እስከ 20 ጊዜ ይሰበስባል፡፡ ምክንያቱም የጀመርነውን አጀንዳ በምናደርገው ሰፊ ውይይት መጨረስ አንችልም፡፡ አጀንዳ ጨርሰን አናውቅም፡፡ አራት አጀንዳዎች ቀርበው እንደሆን ሁለቱን ጨርሰን ሁለቱን ደግሞ ለሚቀጥለው ጊዜ እናስተላልፋለን፡፡ ይህ ደግሞ የዲሞክራሲያዊ ውይይት ነፀብራቅ ነው፡፡ 
እኔ እንዲያውም ቅስቀሳ አላደረግኩም፡፡ የእኔ ተወዳዳሪዎች ቅስቀሳ አድርገዋል፡፡ ስለዚህ ምርጫው ዲሞክራሲያዊ ነው ወይም አይደለም? የሚለው ነው ጥያቄው፡፡ ዲሞክራሲያዊ ነበር፡፡ ለምን ወጣቶች አልመጡም ለሚለው የእነሱ ምርጫ ነው፡፡ እኔ በአብዛኛው የተመረጥኩት በወጣቶች ነው፡፡ ምናልባት ከዚህ በፊትም እንዳደረግኩት ወጣቶችን የማሳተፍ አመለካከትና ባህሪ አለኝ፡፡ እኔ አመራር በነበርኩበት ጊዜ በሕገ ደንቡ መሠረት በሥራ አስፈጻሚ 13 አባላት ነው የሚኖሩት፡፡ እኔ ግን ወጣቶች ወደፊት እንዲቆጠሩ ስድስት አባላት ድምፅ የመስጠት ሥልጣን ሳይኖራቸው አስገብቻለሁ፡፡ ደንቡ ስለማይፈቅድልኝ ነው እንጂ ባለድምፅ ሆነው መግባት ይችሉ ነበር፡፡ ደንቡ ግን አይፈቅድም፡፡ ስለዚህ ድምፅ አልባ ከመሆናቸው በስተቀር ሙሉ በሙሉ የአመራር አባል ነበሩ፡፡ 
አቶ ግርማ ሰይፉም የዚያ አባል ነበሩ፡፡ ሌላው ወጣቱን ለዚህ ቦታ ማንም አልከለከለውም፡፡ አንዳንድ ጊዜ የተሳሳተ አመለካከት አለ፡፡ ሜካኒካል ይሆናል፣ ኮታ ይሆናል፡፡ ወጣቶች መምጣት አለባቸው፡፡ የኮታ ጉዳይ አይደለም፡፡ ይህ የመብት ጉዳይ ነው እንጂ የሚሰጣቸው ስጦታ አይደለም፡፡ ስለዚህ በአንድነት ፓርቲ ለወጣቶችም ሜዳው ክፍት ነው፡፡ ነገ ጠዋት የላቀ ከመጣ ምክር ቤቱ በወጣት ሊተካ ይችላል፡፡ ከፖለቲካም አንፃር መታየት ያለበት ስብጥሩ ነው፡፡ ከወጣቶችም፣ ከጐልማሶችም፣ ከአዛውንትም ያ ስብጥር ነው መሆን ያለበት፡፡ ወጣትም ሆኖ ሽማግሌም ሆኖ የራሱ የሆነ ችግር አለበት፡፡ ያንን የሚያቻችለው መቀላቀሉ ነው፡፡ 
ሪፖርተር፡- በተቃዋሚውም ሆነ በገዥው ፓርቲ ውስጥ ያሉት የ60ዎቹ ትውልድ አባላት አመራርነት የሚያበቃውና ወጣቶች በሰፊው ወደ መሪነት የሚመጡት መቼ ነው? 
ኢንጂነር ግዛቸው፡- በእኔ በኩል በአመዛኙ በአንድነት ፓርቲ ውስጥ የ60ዎቹ ትውልድ ፖለቲካ የሚለው አይሠራም፡፡ ባለፈው አላየነውም አሁንም አይታይም፡፡ የአንድነት ዕድሜ ስድስት ዓመት ነው፡፡ በስድስት ዓመት ጊዜ ውስጥ አራት ፕሬዚዳንቶችን ለውጧል፡፡ የመጀመሪያዋ ብርቱካን ሚደቅሳ ነበረች፡፡ የወጣቶች ተወካይ ነበረች፣ የ60ዎቹ አይደለችም፡፡ ከዚያ እርሷ ስትታሰር እኔ ተጠባባቂ ሆኜ ኃላፊነቱን ተረከብኩ፡፡ ከዚያ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ሆነ፣ አሁን እኔ መጣሁ፡፡ ማንም ፓርቲ በስድስት ዓመት ውስጥ አራት ፕሬዚዳንት የቀየረ የለም፡፡ ይህ የሚያሳየው የአንድነትን ዲሞክራሲያዊነት ነው፡፡ በመሠረቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ብቃት ባለው ከ60ዎቹ በኋላ ባለው ትውልድ መተካት አለበት፡፡ ያ የእኔ እምነት ነው፡፡ የ60ዎቹ ፖለቲከኞች መጪውን ትውልድ አብቅተው መተካት እንዳለባቸው እምነቴ ነው፡፡ 
ሪፖርተር፡- አሁን አንድነትን እንደ ምሳሌ ከወሰድነው መጀመሪያ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ወጣት መሪ ነበሩ፡፡ ከዚያ እሳቸው ሲታሰሩ እርስዎ መሪ ሆኑ፡፡ ቀጥሎ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ አሁን ደግሞ ተመልሰው እርስዎ መጡ፡፡ በአንድነት ውስጥ ከወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ውጪ ያው የ60ዎቹ ትውልድ አባላት ስለሆናችሁ ከዚያ አንፃር ለማለት ፈልጌ ነው? 
ኢንጂነር ግዛቸው፡- ትክክል ያልሆነ ምዘና ነው፡፡ ምንድነው የ60ዎቹ ፖለቲከኞች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ቅድም እንዳልኩህ ስብጥሩን ነው ማየት ያለብን፡፡ ብርቱካን በነበረችበት ጊዜም ሆነ አሁን ሥራ አስፈጻሚ ውስጥ የነበሩ ግለሰቦች ጥቂት ናቸው፡፡ ምናልባት በጣት የሚቆጠሩ [እኔ፣ ነጋሶ፣ አስራት]፡፡ ነገር ግን ሥራ አስፈጻሚ ውስጥ የነበሩት አብላጫዎቹ ከ60ዎቹ በኋላ የመጡ ትውልዶች ናቸው፡፡ በአሁኑ ብሔራዊ ምክር ቤት ውስጥ ከ35 ዓመት ዕድሜ በታች ያሉት 72 በመቶ ናቸው፡፡ የ60ዎቹ አሉበት፡፡ ነገር ግን በአብላጫው ወጣቶች ናቸው፡፡ በእኔ ካቢኔ ውስጥ የ60ዎቹ ትውልድ ያለነው ሁለት ሰዎች ነን፡፡ ከ15 ሰዎች አንድ ሰው የ60ዎቹ ሆኖ ላይ ስለተቀመጠ የ60ዎቹ ተፅዕኖ አለ ለሚባለው ምዘናው ትክክል አይመስለኝም፡፡ መታየት ያለበት ይዘቱ ነው፡፡ የ60ዎቹ ትውልድ አባላት እንዲያውም የት እንዳሉ ግራ ይገባኛል፡፡ አንዳንድ ቦታ መሪ ስለሆነ ብቻ ነው፡፡ የፓርቲው መዋቅር መፈተሽ ካለበት የ60ዎቹ የፖለቲካ ተሳፊዎች ወጥተው ዳር የቆሙ ይመስለኛል፡፡ ደግሞም የተፈጥሮ ሒደት ነው፣ የፖለቲካም ሒደት ነው፣ የታሪክም ሒደት ነው፡፡ መታየት ያለበት የግለሰቦች የ60ዎቹ ትውልድ መሆን ሳይሆን ስብጥሩ ውስጥ ስንት አሉ የሚለው ነው፡፡ 
ሪፖርተር፡- አሁን እንደ አዲስ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ሆነው መጥተዋል፡፡ ለፓርቲው ምን አዲስ ነገር ይዘው መጡ? 
ኢንጂነር ግዛቸው፡- እኛ ፓርቲያችንን የምንመራው በሥርዓት ነው፡፡ ፓርቲው በ2002 ዓ.ም. የስትራቴጂ ዶክመንቱንና የአምስት ዓመት ዕቅዱን በመጽሐፍ መልክ አውጥቶታል፡፡ የአነድነት ፓርቲ መሠረታዊ ራዕይና ግብ በዚያ ውስጥ ነው የሚታየው፡፡ እዚያ ውስጥ ያለውን ሁኔታ ነው ሁላችንም በቀጣይነት እየገነባን የምንሄደው፡፡ ነገር ግን በ2002 እና በ2003 ዓ.ም. ያወጣነው የስትራቴጂ ግንባታ ከወቅቱ ሁኔታ ጋር መዛመድ አለበት፣ መቀነባበር አለበት፡፡ ስለዚህ በዚያ መንገድ አንዳንድ ለየት ያሉ ሙከራዎች አካሂዳለሁ፡፡ 
የመጀመሪያው ሙከራዬ አንድነት ምናልባት ካሉት ፓርቲዎች በጉልህ ጠንክሮ የሚታይና መዋቅሩ ታች ድረስ የወረደ ነው፡፡ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ እንዲያው እንደ ሌላው ጉልበት ወይም አቅም አለን ባንልም በቂ የመንቀሳቀስ ችሎታ አለን የሚል ግምት አለኝ፡፡    
ይህንን የአመራር መርህ ከአንድነት አቅምና ሕዝባዊ ገጽታ አንፃር የተለየ (Rebranding) እንዲሆን አደርጋለሁ፡፡ ለምሳሌ አንዱ ያደረግኩት ሥራ አስፈጻሚውን በአብዛኛው ወጣትና አዲስ ነው ያደረግኩት፡፡ በትምህርታቸው ብቁ የሆኑ ናቸው፡፡ በትምህርት ብትሄድ አሁን ከ15 ሰዎች ስድስቱ ሁለተኛ ዲግሪ አላቸው፡፡ ሰባቱ የመጀመርያ ዲግሪ አላቸው፡፡ ሁለቱ ደግሞ ዲፕሎማ አላቸው፡፡ አሁን ይኼ አዲስ ምልክት (New Branding) ነው፡፡ ሁለተኛ እነዚህን ሰዎች ስመድብ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ችሎታ እንዲኖራቸው አንዱ መሥፈርት ነበር፡፡ አሁን ዘመኑ ወደዚያው እያመራ ነው፡፡ ስለዚህ በኢንፎርሜሽን ግንኙነታችን ከውጭው መረጃ እኩል አንድነት መራመድ አለበት፡፡ 
ሌላው ትኩረት የምሰጠው ወጣቶችን የማብቃት ሥራ ነው፡፡ ወጣቶች በቅተው ፓርቲውን እንዲመሩ አደርጋለሁ፡፡ አሁን እኔ እዚህ ሆኜ ወጣቶችን ነው ወደፊት እንዲሮጡ የማደርገው፡፡ ይህን ካደረግኩ በኋላ በእኔ እምነት ክርክርም መካሄድ አለበት፡፡ እስካሁን የተካሄደው የተቃዋሚ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ውጤት አላስገኘም፡፡ ይኼ ምንም የምንክደው አይደለምና ይህ ለምንድን ነው የሚለው ብዙ ጊዜ ይረብሸኛል፡፡ ወይ ማቆም አለብን ወይ መሥራት አለብን፡፡ እስካሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የተበጣጠሱ ዘጠና ፓርቲዎች አሉ፡፡ ከዘጠናዎቹ ደግሞ ጉልህ የሆኑት አሥር አይሆኑም፡፡ አሥሩም አብረው መሥራት አልቻሉም፡፡ በጥምረትም በግንባርም አልተቻለም፡፡ ለምንድን ነው? ለአሥሩም ቢሆን አሥር መሪዎች አሉ፣ አሥር ፕሮግራሞች አሉ፡፡ አሥሩም እንግዲህ አሥር መሪ ኖሮዋቸው ፖለቲካ ይመራሉ የሚል እምነት የለኝም፡፡ ስለዚህ በብሔራዊ ምክር ቤትና በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውሳኔ አስገኛለሁ የሚል እምነት አለኝ፡፡ 
በእኔ እምነት እንግዲህ አንድነት ፓርቲ ግንባርና ጥምረት ውስጥ አይገባም፡፡ ወደ ውህደት አንድ አመራር አንድ ፕሮግራም ወዳለው እንቅስቃሴ እንገባለን የሚል እምነት አለኝ፡፡ ይህ የእኔ ሐሳብ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ስብሰባ ላይ ፈንጥቄያለሁ፡፡ ይህ መሆን አለበት፡፡ የተጀመሩት ውህደቶች በሚቀጥሉት ሦስት ወራት  ማለቅ አለባቸው ብሎ ጠቅላላ ጉባዔው ወስኗል፡፡ ወይ እንዋሀዳለን ወይ እንለያያለን፡፡ ስለዚህ በዚህ ሁኔታ አንድ የማየው እስከ 2007 ዓ.ም. ወይም በዚህ ዓመት ለእኔ የውህደት ዓመት ነው ብዬ የምገምተው፡፡ ወይ እንዋሀዳለን አለበለዚያ በሰላም ተለያይተን ሁላችንም ጉልበታችንን በየአካባቢው በትብብር እናጠናክር የሚል አመለካከት አለኝ፡፡ 
ይህን ካደረግኩ በኋላ ከኢሕአዴግ ጋር ገንቢ ግንኙነት (Constructive Engagement) እንዲኖረን እፈልጋለሁ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የጥላቻ ፖለቲካ ማብቃት አለበት፡፡ ኢሕአዴግ ተቃዋሚዎችን የሚያያቸው እንደ ጠላት ከዚያም አልፎ እንደ ሽብርተኛ ነው፡፡ ይኼንን ነገር ለሚያስብ ሰው እኮ በጣም ነው የሚያስደነግጠው፡፡ በእኛም በኩል ኢሕአዴግን የምናየው እንደ አውሬ ነው፡፡ ምናልባት የሠራውን ሥራ ሁሉ ዋጋ (Credit) ያለመስጠት አለ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ፖለቲካችን ኢሕአዴግን መቃወም ብቻ ሆኖአል፡፡ ያ መቆም አለበት፡፡ ትልቁ ኳስ ያለው ኢሕአዴግ ዘንድ ነው፡፡ እኔ በበኩሌ ወደፊት በማደርገው እንቅስቃሴ ገንቢ ግንኙነት አድርገን ያለውን የፖለቲካ ምኅዳር ለሁላችንም እኩል ማድረግ አለበት፡፡ ኢቴቪ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቴሌቪዥን ጣቢያ ነው፡፡ ለምንድነው የኢሕአዴግ ብቻ የሚሆነው? መብት እኮ አለን፡፡ ለኢቴቪ ደብዳቤ ጽፈናል፡፡ የጻፍነው ምንድነው የኢሕአዴግን ኮንፈረንስ ከባህር ዳርና የኢሕአዴግን ብሔራዊ ምክር ቤት በቀጥታ ስታስተላለፉ ነበር፡፡ የእኛን ግን አልዘገቡም፡፡ ለኢሕአዴግ 99 በመቶ ሰጥተው ለእኛ ግን አንድ በመቶ እንኳን አይሰጡንም፡፡ ይኼ ሁሉ ቁልጭ አድርጐ የሚያሳየው የኢሕአዴግን ድክመትና ስህተት ነው፡፡ 
ሪፖርተር፡- ለብዙ ፓርቲዎች የእንዋሀድ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ነገር ግን ከዚህ ቀደም እንደታየው ብዙ ውህደቶች ምርጫ ሲደርስ ከመሰባሰብ በዘለለ ብዙም ሲገፉበት አይስተዋልም፡፡ የ97ቱን ቅንጅት ማስታወስ ይቻላል፡፡ ከዚህ አንፃር አሁን እርስዎ የሚያቀርቡት ሐሳብ በምን ይለያል? ከዚህ ቀደም ተሞክረው እንደከሰሙት እንደማይሆንስ ማረጋገጫው ምንድነው? 
ኢንጂነር ግዛቸው፡- የቅንጅት ራሱን የቻለ ጉዳይ አለው፡፡ ቅንጅት አልተዋሀደም ነበር፡፡ ለዚህም ነው ቅንጅት ግንባር ደረጃ አልደረሰም የሚባለው፡፡ ለቅንጅት ከፍተኛውን ድቀት ያስከተሉት የኢሕአዴግና የቅንጅት መሪዎች ናቸው፡፡ በወቅቱ ኢሕአዴግ ያልጠበቀው የፖለቲካ አድማስ ነው የመጣበት፤ በ97 ምርጫ አልጠበቀውም ነበር፡፡ አራቱ ፓርቲዎች ማለትም መኢአድ፣ ኢዴፓ፣ ቀስተ ደመናና ኢዴሊ ሆነው ቅንጅት የተመሠረተው ኅዳር ላይ ነበር፡፡ ኅዳር ላይ ተመሥርተን ግንቦት ላይ ነው ከፍተኛ ዕርምጃ ያሳየነው፡፡ ያ ሁኔታ ኢሕአዴግ ያለውን ግምት በጣም ነው ያዛባው፡፡ ኢሕአዴግ አቅም አይፈጥሩም የሚል ግምት ነበረው፡፡ ገና ስንፈጠር በምርጫው አካባቢ አዲስ አበባን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጠርን፡፡ የምርጫው ዕለት ምሽት በአጠቃላይ የምርጫው ሒደት ተናጋ፡፡ በዚያ ምክንያት ቅንጅት ከፍተኛ ውድቀት ውስጥ ገባ፡፡ ኢሕአዴግ ትኩረት አደረገብን፡፡ 
በዚያ ምክንያት እኛም ወደ እስር ቤት ገብተን ከዚያ ደግሞ ወጣን፡፡ ያው ነገሩ ትክክል ስላልነበር መውጣት እንደነበረብን እኔ አምናለሁ፡፡ ከወጣን በኋላ ደግሞ እኛ አንድ መሆን አልቻልንም፡፡ በእስር ቤት ውስጥ ብሶት ተፈጠረ፡፡ እንደገና ቅንጅትን ለአቶ አየለ ጫሚሶ ሰጡት፡፡ በዚያ በዚያ በመካከላችን ችግሩን በሰከነ ሁኔታ ለማራመድ አልቻልንም፡፡ በዚህ በኩል የራሱ የኢሕአዴግም የእኛም ድክመት ነበር፡፡ ከዚያ በፊትም በተፈጠሩት ስብስቦች እንደዚሁ የመሪዎች ብዛት ነው ችግሩ፡፡ አሁን እኔ የምለው ውህደት ከሆነ አንድ መሪ ሊኖር ይችላል፡፡ ውህደቱም መፈጸም ያለበት በዲሞክራሲያዊ መርሆዎች መሆን አለበት፡፡ ውህደት ላይ ዲሞክራሲያዊ ባህል መፍጠር አለብን፡፡ አመራር አንድ መሆን አለበት፡፡ ሕግ፣ ሥነ ሥርዓትና ደንቡ መታየት አለበት፡፡ እናም ዲሲፕሊን ሊኖረን ይገባል፡፡ የባህሪ ለውጥም ያስፈልገናል፡፡ ከዚህ አንፃር አንደኛ እኛ አመራሮች የባህሪ ለውጥ ያስፈልገናል፡፡ ያ እስከሆነ ድረስ እኔ ውህደት ይወድቃል ብዬ አላስብም፡፡ አልተሞከረም፡፡ በተጨባጭ ብሔራዊ ዕይታ ያለው ውህደት እኮ እስካሁን አልተካሄደም፡፡ 
ሪፖርተር፡- ከዚህ ከውህደቱ ጋር በተያያዘ የርዕዮተ ዓለም ጉዳይስ እንዴት ነው የሚታየው? ብሔራዊ የሆነ ፓርቲ ይኖራል፤ ኅብረ ብሔራዊ የሆኑ ፓርቲዎችም ይኖራሉ፡፡ ይህስ ለውህደቱ እንቅፋት አይሆንም? 
ኢንጂነር ግዛቸው፡- እኔ ሁላችንም ወደ ብሔራዊ ምክክር መምጣት አለብን የሚል እምነት አለኝ፡፡ ለምሳሌ ብሔር ተኮር የሆነ ፓርቲ ከእኛ ጋር ሲዋሀድ ብሔራዊ ቅርፅ መያዝ አለበት፡፡ አለበለዚያ ብሔር ተኮርና ኅብረ ብሔር ሊዋሀዱ አይችሉም፡፡ ምንድነው ጠቃሚው ነገር? ዲሞክራሲ እስከሆነ ድረስ ለምሳሌ የእኛ ፕሮግራም የግለሰብንም የቡድንንም መብት ያከብራል፡፡ የብሔረሰብ ጉዳይ ከሆነ የቡድን ጉዳይ ነው፡፡ ያ እስከተጠበቀ ድረስ ማንኛውም የብሔር ፓርቲ እኛን ይቀላቀላል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ያ ነው ጠቃሚው ነገር፡፡ የፕሮግራሙ ዕይታ ብሔር ተኮር የሆኑትን ፓርቲዎች ፍላጐት ማሟላት አለበት፡፡ የብሔረሰቡ ቋንቋ፣ የብሔረሰቡ የመወሰን መብትና ባህል ማሟላት አለብን፡፡ ይኼ የኢትዮጵያ ነፀብራቅ ነው፡፡ አንዴ ወደ ላይ አንዴ ወደ ታች የምንልበት ጉዳይ አይደለም፡፡ እኩልነት እስካለ ድረስ የብሔረሰብ ጉዳይ አይነሳም ባይ ነኝ፡፡ ፍትሕ፣ እኩልነት፣ ነፃነትና ዲሞክራሲ እስካሉ ድረስ ችግር ያለ አይመስለኝም፡፡ 
ሪፖርተር፡- አንድነት አሳካዋለሁ ወይም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ አመጣዋለሁ የሚለው የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም ምንድነው? 
ኢንጂነር ግዛቸው፡- የእኛ ሊበራል ዲሞክራሲ ነው፡፡ ሊበራል ዲሞክራሲ ሆኖ የቡድንና የግለሰብ መብትን አንድ ላይ እናከብራለን፡፡ 
ሪፖርተር፡- በሊበራል ዲሞክራሲ የቡድንም የግልም መብት ይከበራል ብለዋል፡፡ ነገር ግን የፍላጐት መጋጨት አይኖርም? በቡድን መብትና በግለሰቦች መብት መካከል ማለት ነው? 
ኢንጂነር ግዛቸው፡- ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ነው የሚወሰነው፡፡ በዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ስንት ሰዎች ናቸው እንደዚህ የሚሉት? ሊኖርም ይችላል፡፡ ይህ ተፈጥሮአዊ ነው፡፡ አሥር ሰዎች ሁለቱን አባረው ማካሄድ አይችሉም የሚል ይኖራል፡፡ 90 በመቶ ከደገፈው የ90 በመቶ ይሆናል ለሚለው የዲሞክራሲ ውሳኔ ነው የሚጠይቀው፡፡ እኛም ተወያይተንበታልና የሚወሰነው በዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መሠረት ነው፡፡ 
ሪፖርተር፡- በሚቀጥለው ዓመት የሚካሄድ አገር አቀፍ ምርጫ አለ፡፡ አንድነት እንደ አንድ ተቃዋሚ ፓርቲ በምርጫው ለመሳተፍና ተጨባጭ ውጤት ለማስመዝገብ ምን ምን ሥራዎችን እየሠራ ነው?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- አንደኛ የራሳችንን አቅም እየገነባን ነው፡፡ ከጠቅላላ ጉባዔያችን ዕይታ አግኝተናል፡፡ በዚያ ዕይታ ለምሳሌ የውህደቱ አንዱ ዓላማ በምርጫ የማሸነፍ ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱም አንድነት ብቻውን ከሚሮጥ ሦስትና አራት ፓርቲ ሆነን ልክ እንደ ቅንጅት ብንሮጥ የተሻለ ውጤት እናገኛለን በማለት፣ በውህደቱ ለምርጫው አንድ የጐለበተ አቅም ለመፍጠር የምናደርገው ስትራቴጂ ነው፡፡ ሁለተኛው ፕሮግራማችንንና ርዕዮተ ዓለማችንን ልክ እንደ ሚሊዮኖች ንቅናቄ ወደታች እናወርደዋለን፡፡ አንድ የሕዝብን ዕይታ የሚስብ ከምርጫ 2007 ጋር የሚገናኝ ፕሮግራም እናወጣለን፡፡ ሕዝብን ለማንቀሳቀስ ከዚህ በተጨማሪ አንድነት የዲሞክራሲ ምርጫ ፓርቲ ነው፡፡ ለማንኛውም ሁልጊዜ ለምርጫ ይዘጋጃል፡፡ አሁን ስትራቴጂያችንን ከልሰን ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር አማራጭ ፖሊሲዎችን እንቀርፃለን፡፡ ከአማራጭ ፖሊሲዎች በመነሳት የምርጫ ማኒፌስቶ እናዘጋጃለን፡፡ በእኔ ዕይታ እስከ ሰኔ ድረስ ካለፈም እስከ ነሐሴ ድረስ አንዱና ትልቁ ሥራችን ይህንን የምርጫ ፖሊሲና ማኒፌስቶ ማዘጋጀት ነው፡፡ ከዚያ ብቁ የሆኑ ዕጩዎችን ከካቢኔያችን ውስጥ እንመለምላለን፡፡ ከየቦታው ብቁ የሆኑ ታዛቢዎችንም እንመርጣለን፡፡ ይህ ሒደት ነው፡፡ ሕዝባዊ ስብሰባ እናካሂዳለን፡፡ እንደዚሁም ሕዝባዊ ንቅናቄ ይኖረናል፡፡ እየሄድን ራሳችንን ወደ ሕዝብ የምናወርድበት፡፡ ይህን ሁሉ ለማድረግ ግን የምርጫ ፓርቲ ብንሆንም ምርጫ ውስጥ ጥልቅ ብለን አንገባም፡፡ ሜዳው ለሁላችን እኩል መሆኑን እናረጋግጣለን፡፡ ስለዚህ ከላይ እንዳልኩት ለዚህ ነው ገንቢ ግንኙነት (Constructive Engagement) ከገዥው ፓርቲ ጋር የምናደርገው፡፡ ይኼ ሜዳ ለሁላችንም እኩል እንዲሆን ነው የምንፈልገው፡፡ ኢትዮጵያ የጋራችን ነች፡፡ ኢሕአዴግ አንድ ፓርቲ ነው፡፡ እኛም አንድ ፓርቲ ነን፡፡ 
የምርጫው ሕግ በሕገ መንግሥቱና በምርጫ ቦርድ ሕግ መሠረት መካሄድ ስላለበት ያንን እንጠይቃለን፡፡ ምርጫ ቦርድ የኢሕአዴግ ከሆነ፣ ሚዲያው የኢሕአዴግ ከሆነ፣ የፍትሕ አካላቱ የኢሕአዴግ ከሆኑ እኛ ያን ጊዜ የምንወስነው ውሳኔ ይኖራል፡፡ ነገር ግን ከትዝብትም ጭምር እስካሁን ያሉት ተቋማት ለእኔ ዲሞክራሲያዊ አልነበሩም፡፡ የ2002 ምርጫ በጣም ያዘንኩበት ምርጫ ነበር፡፡ በ21ኛው ክፍለ ዘመን 99.6 በመቶ የሚያገኝ ፓርቲ የለም፡፡ በዓለም ላይ ዲሞክራሲያዊ በሆነና ውድድሩ በእኩል ሜዳ ላይ ተካሂዶ በእዚህ ውጤት ማሸነፍ አይቻልም፡፡ በዓለም ዙሪያ በአብዛኛው መንግሥት በቅንጅት እየተፈጠረ ነው፡፡ እንግሊዝን ውሰድ የኮንሰርቫቲቭና የሌበር ፓርቲ ቅንጅት ነው፡፡ ጀርመን፣ ጣሊያንና ኖርዌይም እንዲሁ ቅንጅት ነው፡፡ ምክንያቱ በዲሞክራሲያዊ ሥርዓቱ ውድድሩ ነፃ ነው፡፡ እናም ስለዚህ 99.6 በመቶ በጭራሽ ሊሆን አይችልም፡፡ እንኳን እንደ ኢትዮጵያ ያለ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችና የኅብረተሰብ ክፍል ባህሪ ባለበት አገር ይኼ አይቻልም፡፡ ይኼ ነገር መለወጥ አለበት፡፡ እናም ለምርጫ እንዘጋጃለን፡፡ ነገር ግን ሜዳው ሁላችንንም እኩል ማስተናገድ አለበት፡፡ 
ሪፖርተር፡- የመጫወቻ ሜዳው ለሁላችሁም እኩል መሆኑን እንዴት ማረጋገጥ ትችላላችሁ?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- ለምሳሌ በምርጫ 97 ሚዲያው ትንሽ ወደ ኢሕአዴግም ቢያደላ ተከፍቶ ነበር፡፡ እንዲያውም የእነሱ ሜዳ ከፍ የእኛ ሜዳ ዝቅ ቢልም፣ ነገር ግን የመወዳደርያ ቦታ ነበረው፡፡ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ክርክሮች ለሕዝብ የወጡት በ97 ምርጫ ነበር፡፡ በ2002 ምርጫ ሚዲያው ታፍኖ ነበር፡፡ ሚዲያው የሕዝብ ጥያቄ አላስተናገደም፡፡ ዝም ብሎ ለይስሙላ ቴሌቪዥን ጣቢያ ተሂዶ አንዳንድ ነገሮች መነጋገራችንን ሕዝብ ሊሰማው ይችላል፡፡ ነገር ግን በሆነ እጅ ቁጥጥር ሥር የወደቀ ነበር፡፡ ያ መሆን የለበትም፡፡ እናም ትልቁ ምሳሌ የ97 ምርጫ የሚዲያ ጉዳይ ነበር፡፡ ሚዲያው ያን ጊዜ ተከፍቶ ነበር፡፡ በእኩልነትም ባይካሄድም ያን ጊዜ እንደ እኩል ነው የወሰድነው፡፡ እንደዚያ መሆን አለበት፡፡ 
ሪፖርተር፡- ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ አንድነት የፀረ ሽብር ሕጉ ይሰረዝ የሚል አቋም ይዞ እየተከራከረ ነው፡፡ አሁን ደግሞ በመላው ዓለም ሽብርተኝነት ትልቅ ሥጋት ሆኗል፡፡ በእኛ አገር የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ አጠቃቀም ተቃዋሚዎችን ፀጥ ለማሰኘት ነው የሚለው እንዳለ ሆኖ፣ አንድነት እንደ ፓርቲ አማራጭ የፀረ ሽብር ሕግ አለው ወይ ይሰረዝ ሲል ምን ማለት ነው?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- መጀመርያ ሽብርተኝነትን መዋጋት የኢሕአዴግ ብቻ አይደለም፡፡ የማንኛውም ዜጋ ነው መሆን ያለበት፡፡ ይኼ ሽብርተኝነት ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴው አስከፊ፣ ከሰው ልጅ ባህሪ በተለየ የሰው ልጅን መንፈስ የሚሰብር፣ የሰው ልጅነትን የሚቀንስ ነው፡፡ አንድነትም ሆነ እኔ እንደ አንድነት አመራር እንደዚሁም እንደ ዜጋም እንዋጋለን፡፡ የእኛ ችግር የፖለቲካ መሣሪያ አይሁን ነው፡፡ የአንድነት አባላትና እኔ ከኢሕአዴግና ከገዥው ፓርቲ በምንም መልኩ አናንስም፡፡ ይህን ችግር ለመዋጋት፡፡ ይኼ የዜግነት ግዴታዬ ነው፡፡ ማንም ቢሆን ወገኑ እንደዚያ ሲጠፋበት ካልተዋጋ ከሰውነትም ከሰብዕናም መውጣት አለበት፡፡ ነገር ግን የእኛ አጽንኦት የፀረ ሽብር፣ የፕሬስና የመያዶች ሕግ የፖለቲካ መሣሪያ መሆን የለባቸውም ነው፡፡ የፖለቲካ መሣርያ ከሆኑ መሰረዝ አለባቸው ነው፡፡ የሕዝብ ተሳትፎ ያለበት ይሁን ነው፡፡ የሁላችንም የጋራ ሥጋት ነው፡፡ ሁላችንም መሳተፍ አለብን፡፡ የፀረ ሽብር አዋጅ ሲወጣ እኛ አልተሳተፍንበትም፡፡ ፓርላማውም እንደሰማሁት በጥልቀት አልተሳተፈበትም፡፡ ይህ አዋጅ የሕዝቡ አዋጅ መሆን አለበት፡፡ በኢትዮጵያ ማንም ከማንም ያነሰ የለም፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያ በሽብርተኝነት ስትጠቃ እኔ የመጀመርያው ተዋጊ ነኝ፡፡ 
ሪፖርተር፡- የፓርቲያችሁ ድረ ገጽ አብዛኛውን ጊዜ ቶሎ ቶሎ መረጃዎች ሲጫኑበት አይታዩም፡፡ በአብዛኛው የቆዩ መረጃዎች ናቸው ያሉበት፡፡ የእርስዎን ሊቀመንበር ሆኖ መመረጥ እንኳን በትኩሱ ይፋ አላደረገም፡፡ አሁን ደግሞ እንደዚህ ዓይነት የመረጃ ዘዴዎችን መጠቀም ወደ ሕዝብ ዘንድ ለመድረስ ዓይነተኛ ሚና ስለሚኖረው ድረ ገጻችሁ ለምንድነው መረጃዎችን ቶሎ ቶሎ ለሕዝብ የማያደርሰው?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- ያለፉትን መውቀስ አይሁንብኝና ድክመታችን ነው፡፡ እኔም አይቼዋለሁ፡፡ ዘገምተኛ ነው፡፡ አሁን ‹‹አክቲቭ›› እናደርገዋለን፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ተነጋግረንበታል፡፡ ጠንካራ የሆነ የሚዲያ ግሩፕ አለን፡፡ ነገር ግን እነርሱ ያንን ረስተው በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ነው ያሉት፡፡ ስለዚህ ጉዳይ አንስቼ ተነጋግረናል፡፡ የተነጋገርነውም አንደኛ ድረ ገጾችን ዘገምተኛና የነቃ አይደለም፡፡ ሰዎችን የሚስብ ባለመሆኑ ይህ ድረ ገጽ በሥነ ሥርዓት አሁን ለኢትዮጵያውያንም፣ ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡም አንድነት የሚሠራውን በየቀኑ ማንፀባረቅ አለበት፡፡ ድረ ገጹ ወቅታዊነት ይጐድለዋል፡፡ ሁኔታዎችን ብልጭ የሚያደርገው ጊዜው ካለፈ በኋላ ነው፡፡ በሚቀጥሉት ሦስት ወራት እንዲስተካከል የሕዝብ ግንኙነት ይሠራዋል፡፡
ሪፖርተር፡- ላለፉት ዓመታት ፖለቲካው ላይ ብዙም አይታዩም ነበር፡፡ አሁን ደግሞ እንደገና ተመረጡ ሲባል እሳቸው ፖለቲካ አልተውም እንዴ የሚል ጥያቄ ተነስቷል፡፡ እርስዎ ከፖለቲካ ወጥተው ነበር? 
ኢንጂነር ግዛቸው፡- አይደለም፡፡ አንደኛ ለአንድ ዓመት ያህል ተራ አባል ነበርኩ፡፡ ተራ አባል መሆንም አንዳንድ ጊዜ ወደ ላይም ወደታችም ያሳይሃል፡፡ ከዚያ ወደ ምክር ቤት አስገቡኝ፡፡ ብሔራዊ ምክር ቤት ከገባሁ አንድ ዓመቴ ነው፡፡ እዚያ በንቃት እሳተፍ ነበር፡፡ ነገር ግን ራሴን ከሚዲያ አግልዬ ነበር፡፡ እንዲሁ ዝም ብዬ የምናገረው ነገር የለኝም ብዬ ራሴን ከሚዲያው አውጥቼ ነበር፡፡ በመሠረቱ ወደዚህ መምጣትም መቶ በመቶ የእኔ ፍላጐት አልነበረም፡፡ የፓርቲ አባላት ፍላጐት ነው፡፡ የፓርቲ አባላት ፍላጐት በመሆኑ ምክር ቤትም እንደነበርኩ ይኼ ሐሳብ ተንሸራሽሮአል፡፡ ከዚያ በኋላ ያልጨረስከው ነገር ስላለ ግባና እስቲ ጨርሰው የሚል ነው፡፡ እኔ እንግዲህ ያመጣኝ ምርጫው ነው፡፡ 
ሪፖርተር፡- ፖለቲካ በቃኝ ብለው ነበር? 
ኢንጂነር ግዛቸው፡- ፖለቲካ በቃኝ አላልኩም፡፡ የፖለቲካ አመራርነት ግን ይበቃኛል ብዬ ነበር፡፡ ከፖለቲካ አልወጣሁም ነገር ግን ከፖለቲካ አመራርነት ወጥቼ ነበር፡፡ ይህንን እኔ የማምንበት ነው፡፡ ሌላ ለምን አናይም? አንዳንድ ጊዜ ጥላ አጥልተን መኖሩንም እኔ አልፈልገውም፡፡ አንዳንድ የፖለቲካ መሪዎች ጥላ ሁነው እነርሱ ብቻ ተሰይመው ታች ያለውን አጥልተውበት፣ ታች ያለው ዝም ብሏል፡፡ እንደዚያ መሆንም አልፈልግም፡፡ ያንን ጥላዬን ከአመራርነት አውጥቼ ልጆቹ ወደ ፀሐይ ወጣ ይበሉ ብዬ ነበር፡፡   

Sunday, January 12, 2014

በጅምላ ገድሎ በጅምላ መቅበር ወያኔ ተወልዶ ያደገበት ሙያዉ ነዉ (የግንቦት 7 መልዕክት)

January12/2014
በወያኔ ዘርኝነት፤ ጎጠኝነትና ወደር የለሽ ጭቆና ከሁለት አስርተ አመታት በላይ ጀርባዉ የጎበጠዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ባለፉት ሁለት ወራት ዉስጥ በሁለት እጅግ አስቀያሚና ዘግናኝ በሆኑ የታሪክ ምዕራፎች ዉስጥ አልፏል። ለወትሮዉ በወርሃ ህዳርና ታህሳስ፤ ህዳር ሚካኤልንና የገና በዐልን እያከበረ አጆቹን ወደ ፈጣሪዉ የሚዘረጋዉ የኢትዮጵያ ህዝብ፤ ዘንድሮ ከእነዚህ ሁለት የቆዩ ባህሎቹና ወጎቹ ፈቀቅ ብሎ በሁለት ክብሩን ባዋረዱና ማንነቱን ጥያቄ ዉስጥ በከተቱ ከስተቶች ልቡ ቆስሎ ከራሱ ጋር ሲነታረክ ሰንብቷል። የፈጠረዉን አምላክ መለምን እንጂ በፈጣሪዉ አማርሮ የማያዉቀዉ የኢትዮጵያ ህዝብ . . . የሚያስብልኝ መንግስት እንደለሌለኝ አዉቃለሁ፤ አምላኬ ግን በፍጹም አይረሳኝም። ምነዉ ቅዱስ ሚካኤል አንተና ሰይፍህ እያላችሁ እንዴት እንዲህ ይደረጋል አንዴ . . . እያለ በምድራዊዉም በሰማያዊዉም መንግስታት ላይ የመረረ ጩኸቱን አሰምቷል።
በህዳር 2006 ዓም የኢትዮጵያ ህዝብ አገራቸዉ ዉስጥ የስራ ዕድል ተነፍገዉ ስራ ፍለጋ ወደ ሳዑዲ የተሰደዱ ወገኖቹ በሳዑዲ ፖሊስና ህዝብ ከፍተኛ በደል ሲፈጸምባቸዉ ተመልክቶ በኃዘንና በቁጭት ልቡ በግኗል። በተለይ ወንዶች ልጆቹ ፈለጊ እንደሌለዉ እንስሳ በየአደባባዩ ሲረገጡና ሲደበደቡ፤ ሴቶች ልጆቹ ደግሞ በየማጀቱ ሲደፈሩ ተመልክቶ ለህዝብና ለአገር ለሚያስቡ አስተዋይና ጨዋ መሪዎች ባለመታደሉ በባዕድ አገር ዉስጥ በደረሰበት ዉርደትና መከራ በአለም አቀፍ ደረጃ ጩኸቱን አሰምቷል።በዚሁ በ2006 ዓም በታህሳሰ ወር አጋማሽ ላይ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይ ብርድ ልብስ ተጠቅልሎ የተጣለ የሰዉ ልጅ አጽም ቀርቶ በስመአብ ተብሎ የታረደ በሬ ስጋም ማየት በማይፈልግበት በገና ፆም ወቅት የገዛ ወገኖቹ አጽም በመንገድ ቆፋሪዎች ከመሬት ዉስጥ እየተጎተተ ሲወጣ አይቶ በቆሰለ ልብና በነደደ አንደበት “እባክህ ፈጠሪ ወይ ዉረድ ወይ ፍረድ” እያለ ከወያኔ ጋር ከመኖር የፈጣሪን ፍርዱን አለዚያም ዳግም ምጽአቱን ተመኝቷል።
ባለፉት ሁለት ወራት ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ በሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቻችን ላይ የደረሰዉ ግፍና መከራ ድፍን ህዳርንና ታህሳስን በአለም ዙሪያ በአራቱም ማዕዘን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንን ያሰባሰበ፤ ያነጋገረ፤ ያበሳጨ፤ ያስቆጨና አንጀት ያሳረረ ጉዳይ ነበር። አዎ የ2006 ህዳርና ታህሳስ አገር ዉስጥም ካገር ዉጭም ለምን መጡ የሚያሰኙ የቀን ጎደሎዎች ነበሩ። የወገኖቹ በባዕድ አገር አላግባብ መታሰር፤መደብደብና መገደል ያበሳጨዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ከዚህ ሀዘኑና ብስጭቱ ሳይላቀቅ ነበር ባለፈዉ ታህሳስ 18ትና 19 ቀን ሌላ አሳዛኝና አስደንጋጭ ዜና የጭንቅና የመከራ ጓዳ የሆነችዉን መዲናችን ከአዲስ አበባን አንደ ሐምሌ ጨለማ የከበባት። ደርግን አሸንፈዉ ስልጣን ሲይዙ ደርግ ገድሎ የቀበረዉን አስከሬን መቃብር እየቆፈሩ ያወጡት የወያኔ መሪዎች እነሱም በተራቸዉ በጅምላ ገድለዉ በብርድ ልብስ እየጠቀለሉ የቀበሯቸዉን ኢትዮጵያዉያን አስከሬን ዬት እንደቀበሩት እንኳን ሰለማያዉቁ እነሱ እራሳቸዉ እየቆፈሩ አዉጥተዉ ወንድሞቹና እህቶቹ እንደወጡ የቀሩበትን የኢትዮጵያን ህዝብ አንጀት እንደገና አቁስለዋል።
እዚህ ላይ አንድ እጅግ በጣም ሊያሳስበንና ሊያስጨንቀን የሚገባ ነገር ቢኖር ባለፈዉ ሳምንት ከስድት ኪሎ ወደ ፈረንሳይ ለጋሲዮን በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው የጃንሜዳ ጦር ካምፕ አካባቢ በብርድ ልብስ እንደተጠቀለለ የተገኘዉ የ6 ሰዎች አጽም ሊገኝ የቻለዉ ሆን ተብሎ የጅምላ መቃብር ለማግኘት በተደረገ ቁፋሮ ሳይሆን በአጋጣሚ ነዉ። ይህ የሚያሳየን አዲስ አበባን ጨምሮ በብዙ የአገራችን አካባቢዎች ዉስጥ መረጃ የተሰበሰባበቸዉንና የሚጠረጠሩ ቦታዎችን የኢትዮጵያ ህዝብ ከአለም አቀፉ ህብረተሰብ ጋር ተባብሮ እየቆፈረ መፈተሽ ቢጀምር ወያኔ ጭካኔዉን ሊያሳየን ከሞከረዉ ከደርግ ስርዐት ጋር ምንም የማይለያይ ጨካኝና አረመኔ ስርዐት ለመሆኑ ማንም ማስተባበል የማይችለዉ ተጨባጭ ማስረጃ ይገኛል ብለን እናምናለን።
የወያኔ ዘረኞች አዲስ አበባን በተቆጣጠሩ ማግስት ስራችን ብለዉ የጀመሩት ደርግ የሰለበዉን የኢትዮጵያን ህዝብ ሞራል ማደስ ወይም በሶሻሊዝም ስም የደቀቀዉን የአገራችንን ኤኮኖሚ መገንባት አልነበረም። የደርግ ሰርዐት አንደ ገለባ ሲበተን አብሮት የተበተነዉ የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያሰራዊትም ቢሆን እንደጠላት የሚመለከቱት ኃይል ስለነበር ይህ ለእናት አገሩ ዳር ድንበር መከበር ደሙን ያፈሰሰ ሰራዊት የሚበላና የሚቀመስ አጥቶ ወደ መንገድ ላይ ለማኝነት ሲቀየር ሌላ ቢቀር ጡረታዉን እንኳን ለማስከበር ያደረጉለት ምንም ነገር አልነበረም። ወያኔዎች ስልጣን እንደጨበጡ የደረጉት አቢይ ነገር ቢኖር ከክፍለ ሀገር ክፍለ ሀገረ እየዞሩ ደርግ በቀይ ሽብርና በሌላም ሌላ ግዜ ገድሎ የቀበራቸዉን ሰዎች መቃብር እየቆፈሩ አጽም መሰብሰብ ነበር። በወቅቱ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በተከታታይ እንደተመለከትነዉ የወያኔ ጉድጓድ ቆፋሪዎች የሰነበተ መቃብር እየከፈቱና አጽም እየሰበሰቡ ደርግ ምን አይነት ጨካኝ ነብሰ ገዳይ እንደሆነ ለአመታት የምናዉቀዉን እዉነት እንደገና እንድናዉቀዉ አድርገዉናል። በዚህ ከአንድ አመት ከመንፈቅ በላይ በዘለቀዉ የወያኔ መቃብር ቁፋሮ ወያኔ የቀድሞዉን ንጉስ የቀዳማዊ ኃ/ስላሤን ጨምሮ የብዙ ሰዎችን የመቃብር ቦታ እየቆፈረ እሱ ለፖለቲካ ፍጆታዉ የሚፈልጋቸዉንና በተለይ ደግሞ የኔ ናቸዉ የሚላቸዉን ሰዎች አጽም እየለቀመ አንደገና በክብር እንዲቀበሩ ሲያደርግ ሌሎቹን የደርግ ሰለባዎች ደግሞ ምሶ ያወጣዉን አፈር አንደገና መልሶባቸዋል። እንደዚህ አይነት ጉድ የተመለከትነዉ ከሃያ ሁለት አመታት በፊት ወያኔ ኢትየጵያን ሲቆጣጠር ነበር።
ባለፈዉ ሳምንት አዲስ አበባ ዉስጥ መንገድ የሚሰሩ ሰዎች ለራሳቸዉ ጉዳይ መሬት ሲቆፍሩ ከተጠቀለሉበት የደብረ ብርሀን ብርድ ልብስ ዉስጥ እየዘለሉ ወጥተዉ “የፍትህ ያለህ” እያሉ ሲጮኹ የሰማናቸዉ አጽሞች ወያኔ በእኔ ዘመነ መንግስት ሰዉ በሰዉነቱ ይከበራል እንጂ እየተጎተተ አየገደልም ብሎ ከማለ በኋላ በራሱ በወያኔ በግፍ እየተጎተቱ ተገድለዉ የተጣሉ ዜጎች አጽም ነዉ። ይህንን በታሪካችን ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ ጉድ በስፍራዉ ተገኝተዉ የተመለከቱ የአይን ምስክሮች እንደተናገሩት ቦታዉ ዘመናዊ የመቆፈሪያ ማሽኖች በመቆፈር ላይ እያለ በመጀመሪያ አራት አስከሬኖች በብርድልብስ እንደተጠቀለሉ ተንከባለዉ ወደላይ ሲወጡ የታዩ ሲሆን፤ በሁኔታዉ የተደናገጡት ቆፋሪዎች ስራቸዉን አቋርጠዉ ወደ ቤታቸዉ ከሄዱ በኋላ በነጋታው ረፋዱ ላይ በሌላ አቅጣጫ ሌላ ቁፋሮ ሲያደርጉ አሁንም እንደገና በተመሳሳይ ሁኔታ በብርድ ልብስ የተጠቀለሉ ስድስት አስከሬኖች አግኝተዋል።
አንድ አስከሬኖቹ በተገኙበት አካባቢ በብዛት ተገኝቶ ሁኔታዉን ይመለከት የነበረዉን ህዝብ ለማባረር ወታደሮቹን አስከትሎ የመጣ ከፍተኛ ወታደራዊ የጦር መኮንን “ይህ ግቢ ሶስት ስርዓቶችን ያገለገለ በመሆኑ የማናቸው እንደሆነ ለማወቅ አይቻልም፤ ሆኖም ሰዎች በመሆናቸው ክቡር ናቸውና አፈር አልብሷቸው” በማለት የዘረኞቹን የወያኔ መሪዎች አይን ያወጣ ወንጀል ለመደበቅ ሲሞክር ተደምጧል። ሆኖም ሁኔታዉን በቅርብ ሆኖ የተከታተለዉም ሆነ በርቀት ሆኖ በምስል የተመለከተ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ወንጀሉ የሌሎቹ መንግስታት ሳይሆን የወያኔ መሆኑን ለመገንዘብ ግዜ አልወሰደበትም። አስከሬኖቹ በጅምላ የተጠቀለሉበት የደብረ ብርሀን ብርድ ልብስም ቢሆን እንኳን መሬት ዉስጥ ተቀብሮ ምስጥ፤ እርጥበትና ዘመን ተፈራርቀዉበት፤ አልጋ ላይ ህያዉ ሰዉ ለብሶትም ቢሆን ሃያ አመት ቀርቶ አምስት አመትም የሚቆየዉ የዛሬዎቹ የወያኔ መሪዎች ለብሰዉት አንደመጡት ቁምጣ በመርፌ ከተጠቋቆመ ብቻ ነዉ። ባለፈዉ ሳምንት አርብና ቅዳሜ አስር አስከሬኖችን እንዳቀፈ ከመሬት ዉስጥ ሲወጣ ያየነነዉ ብርድል ልብስ የሚያሳየን ነገር ቢኖር ወያኔ በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ ኢትዮጵያዉያንን በሚስጢር እየገደለ እንደ ቆሻሻ ዕቃ ዬትም ቦታ መጣሉን እንዳማያቆም ነዉ።
የአገራችን የኢትዮጵያ ህዝብ ለሀይማኖት የሚሰጠዉ ቦታ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነዉ። በእስልምናዉ፤ በክርስትናዉም ሆነ በአይሁድ ሀይማኖቶች አስተምህሮ በሀይማኖት ዉስጥ ሁለቱ ዋና ዋና አካሎች እግዚአብሄርና ሰዉ ናቸዉ፤ ይህ የሚያሳየን ሰዉ ክቡር ፍጡር መሆኑን ነዉ። ወደዚህ አለም ሲመጣም ሆነ ይህችን አለም ሲለይ በከብር መጥቶ በክብር የሚሸኝ የሰዉ ልጅ ብቻ ነዉ። የኢትዮጵያ ክርስትና እምነት መሰረት ከሆነችዉ ከትግራይ ክልል የመጡት የዛሬዎቹ የኢትዮጵያ መሪዎች ግን ክርስትናዉን ብቻ ሳይሆን የራሳቸዉንም ሰዉ መሆን የረሱ ይመስላል። ሰዉን የመሰለ ክቡር ፍጡር በጅምላ ተገድሎ፤ በጅምላ ከተቀበረበት ቦታ በኮንስትራክሺን ሠራተኞች ከመሬት ዉስጥ እየተጎተተ መዉጣቱን የሰሙ የወያኔ መሪዎች ጉዳዩን አስመልክቶ አንድም ትንፍሽ ያሉት ቃል የለም። እነሱ ብቻ ሳይሆኑ በእነሱ ቁጥጥር ስር ያሉት የኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቪዥንም እነማን እንደሆኑ፤ መቼ እንደሞቱና ማን እንደገደላቸዉ የማይታወቅ ሰዎች አስከሬን በብርድልብስ ተጠቅልሎ ሲገኝ ያንን ለስድብና ህዝብን ለመኮነን ቀኑን ሙሉ የሚከፍቱትን አፋቹዉን መክፈት አልፈለጉም። የሚገርመዉ እንደ አለባሌ ነገር ከተጣሉበት ቦታ ተጎትተዉ የወጡት አስከሬኖች ሁኔታና የተጠቀለሉበት ብርድልብስ ሙሉ በሙሉ ወንጀሉን ወያኔ ላይ ስለሚያመለክት ነዉ እንጂ የእነሱ እጅ የሌለበት ወንጀል ቢሆን ኖሮ የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ሳምንት ሙሉ ሌላ ዜና አይሰማም ነበር።
አገር ዉስጥም ሆነ በዉጭ አገሮች የሚኖረዉ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ባለፈዉ ሳምንት እንደ ዋዛ ከመሬት ዉስጥ እየተጎተቱ የወጡ ወገኖቹን አስከሬን ጉዳይ በቀላሉ መመልከት የለበትም። ወያኔ ስልጣን እጁ ከገባ ጀምሮ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያንን እያፈነ በየማጎሪያ ቤቱ አጉሯቸዋል። ከሰሞኑ ጃንሜዳ አካባቢ ያየነዉ ዘግናኝ ክስተት ስለእነዚህ ወያኔ በየድብቅ አስር ቤቶች አስሮ አድራሻቸዉ ስለጠፋ ዜጎቻችን ብዙ የሚለዉ ነገር ያለ ይመስለናል። እኛ ነን አድራሻቸዉ የጠፋ ሰዎች እያልን የምንጨነቀዉ እንጂ እነዚህ ወያኔ አስሯቸዉ አድራሻቸዉ የጠፋ ሰዎች ዬት እንዳሉ ጃንሜዳ አፉን ከፍቶ ነግሮናል። አዲስ አበባና በየከተማዉ የሚኖረዉ ህዝብ ስለወያኔ የጅምላ ግድያ የሚያዉቀዉ ብዙ ሚስጢር ይኖራል፤ በጅምላ ተገድለዉ በጅምላ የሚቀበሩ ሰዎችንም ጉዳይ በተመለከተ ማንም ሰዉ ሳያየዉና ሳያዉቀዉ የሚፈጸም ነገር አይመስለንምና ከአሁን በኋላ ጥረታቻን ሁሉ የወያኔ የጅምላ ግድያዎች በብሄራዊና በአለም አቀፍ አካላት እንዲመረመሩና ወንጀለኞቹ ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ መሆን አለበት። በዚህ ጉዳይ ላይ መረጃ ያላቸዉ ዜጎች መረጃዎቻቸዉን ማሰባሰብ፤ማደራጀትና ለሚመለከተቸዉ አካላት መስጠት ይኖርባቸዋል። ዬት እንደደረሱ ሳናዉቅ ባለፈዉ ሳምንት ሳይተሳብ በደብረህርሃን ብርድ ልብስ እንደተጠቀለሉ ከመሬት ዉስጥ የወጡ ዜጎቻችን ፍትህ ሳያገኙ ማንም ኢትዮጵያዊ እንቅልፍ ሊወስደዉ አይገባም።

የኢትዮጵያና የግብፅ ድርድር - ውኃ ቅዳ ውኃ መልስ

January12/2014

የኢትዮጵያና የግብፅ ድርድር - ውኃ ቅዳ ውኃ መልስ






















በአሁኑ ወቅት 30 በመቶ ግንባታው የተጠናቀቀውና በሦስት ዓመታት ውስጥ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በተመለከተ፣ ‹‹ቴክኒካዊ›› በሆኑ ጉዳዮች ላይ ተከታታይ ድርድሮች እየተደረጉ ነው፡፡

በእያንዳንዱ ድርድር ከሚስተዋሉ አቋሞች ግን ለዘመናት የቆዩ ሴራዎች መልካቸውን ቀይረው እየመጡ ይመስላል፡፡

በታላቁ የዓባይ ግድብ ላይ የዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ቡድን ጥናት ውጤት የያዘው ሪፖርት አሁን እየተደረጉ ላሉት ድርድሮች መሠረት የሚጥል ነው፡፡ ሪፖርቱ እንደሚለው፣ የግድቡ ግንባታ እንዲቋረጥ ምንም መሠረታዊ ምክንያት ባለመኖሩ፣ በተቻለ መጠን በታችኛው የዓባይ ተፋሰስ አገሮች ላይ ሊያስከትለው የሚችለው የውኃ ፍሰት መጠን መቀነስና ቴክኒካዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሦስቱም አገሮች ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በጋራ ተቀራርበው መሥራት እንዳለባቸው ነው፡፡ በተረፈ የግድቡ ግንባታ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን ሪፖርቱ አጽንኦት ይሰጣል፡፡

የግብፅ ዥንጉርጉር አቋሞች

ኢትዮጵያና ሱዳን ሪፖርቱን በፀጋ የተቀበሉት በመሆናቸው ሚስጥርነቱ እንደተጠበቀ እንዲቆይም የሚቻላቸውን ጥረት አድርገዋል፡፡ በሌላ በኩል ግብፅ በሪፖርቱ ላይ የተዘበራረቀ አቋም እያንፀባረቀች በመሆንዋ ሪፖርቱ ይፋ በሆነበት ወቅት በተጠራው ብሔራዊ ምክክር፣ በተለይ የግብፅ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በኢትዮጵያ ላይ ጦር ኃይሉ እንዲዘምት ድምፃቸው ተሰምቷል፡፡ ግብፅ ባጋጠማት ቀውስ ምክንያት እየተደረጉ ያሉት የባለሥልጣናት መቀያየር የግብፅ መንግሥት አቋም ለትንተና የማይመች ቢሆንም፣ አንዱ የሌላውን ስህተት እየደገመ ይመስላል፡፡ አንዱ ከሌላው ስህተት እየተማረ አይመስልም፡፡ አሁን ሥልጣን ላይ ያለው የሽግግር መንግሥት ከአንድ ዓመት የሥልጣን ቆይታ ጊዜ በኋላ የተባረረውን የፕሬዚዳንት መሐመድ ሙርሲ መንግሥት በኢትዮጵያና በዓባይ ግድብ ላይ የተለሳለሰ አቋም መያዙ ለውድቀቱ ምክንያት መሆኑን እየተናገረ ነው፡፡

ሁለተኛ ከላይ ከተጠቀሰው ምክንያት ጋር ተያያዥነት ያለው ቢሆንም፣ ግብፅ በአንድ በኩል የባለሙያዎቹ ሪፖርትን አለመቀበልዋና በሌላ በኩል የቡድኑን ምክረ ሐሳብ ለመተግበር ድርድር እንዲደረግ መስማማቷ እርስ በርስ የሚጣረሱ አካሄዶች ናቸው፡፡

ሦስተኛ ሪፖርቱን በተመለከተ በሚስጥር ተይዞ መቀመጥ በነበረበት ጊዜ አንዳንድ ተፅዕኖ ያሳርፋሉ ተብለው ለሚገመቱ አገሮችና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተላልፎ እንዲሰጥ ማድረጓ ይነገራል፡፡ እንዲሁም ዋሽንግተን ፖስትን ጨምሮ አንዳንድ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችን በመጠቀም የሪፖርቱን ድምዳሜ በተሳሳተ መንገድ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ጥረት ተደርጓል፡፡ ይህ እንግዲህ በአገር ውስጥ የሚደረገውን አሉታዊ የሚዲያ ቅስቀሳን ጨምሮ ማለት ነው፡፡

ያም ሆነ ይህ ግብፅ የሪፖርቱን ውጤት መቀበሏን በግልጽ ባታሳውቅም፣ የባለሙያዎች የቡድንን ምክረ ሐሳብ ለመተግበር በቅርቡ ያለውጤት የተበተነውን ጨምሮ ሦስት ጊዜ ድርድር ተቀምጣ ነበር፡፡

ከኢትዮጵያ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ የባለሙያዎች ቡድን ያቀረበውን ምክረ ሐሳብ ተግባራዊ ለማድረግና ይህንን ተግባራዊ የሚያደርግ ኮሚቴ ለማቋቋም በሁለቱም የመጀመርያ ድርድሮች ግብፅ ተስማምታ ነበር፡፡

በኮሚቴው አወቃቀር ላይ አንዳንድ ውዝግቦች የነበሩ ቢሆንም፣ በመጨረሻ በኮሚቴው ውስጥ ሦስቱን አገሮች የሚወክሉ ዜጐች ብቻ እንዲካተቱ ስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር፡፡ ይህ የኢትዮጵያ አቋም ነበር፡፡ ኮሚቴውም ምክረ ሐሳቡን ተግባራዊ በማድረግ ረገድ የውጭ አማካሪ ድርጅትን የመቅጠርን ሥራ ጨምሮ አማካሪው የሚያቀርበውን ሐሳብ ይገመግማል ይላል፡፡

ባለፈው ሳምንት በካርቱም በተደረገው ሦስተኛው የድርድር ዙር ግን የግብፅ ተወካዮች ዓለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት እንዲቀጠር ይጠይቃሉ፡፡ የውኃ፣ የመስኖና የኢነርጂ ሚኒስቴር የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈቅ አህመድ ግብፆች እንዲቀጠር የፈለጉት የውጭ አማካሪ ድርጅት ቀደም ሲል ስምምነት ከተደረሰበት መንፈስ ውጪ የሚቋቋመውን ኮሚቴ በበላይነት የመቆጣጠር ኃላፊነት እንዲኖረው የሚል ድብቅ አጀንዳ የያዘ መሆኑን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ድርድሩ ያለውጤት ሲበተን በቀጣይነት ግን ለመነጋገር ቀጣሮ ተይዟል፡፡

የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን አባል የሆኑት በዓባይ ወንዝ ፖለቲካ ላይ ግንባር ቀደሙ ተመራማሪው ዶ/ር ያዕቆብ አርሳኖ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ በግብፅ የቀረበው የዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ቡድን እንዲመሠረት ብትቀበልም በሁለት ነገሮች አለመግባባት ተፈጥሯል፡፡ አንደኛው የባለሙያዎቹ ቡድን በሦስቱ አገሮች የጋራ መግባባት (ሙሉ በሙሉ) መመሥረት አለበት የሚል የኢትዮጵያ አቋምን ግብፅ መቀበል አለመቻሏ ነው፡፡

ሁለተኛው የባለሙያዎቹ ቡድን የሚመሠረተው ከሦስቱም አገሮች የተውጣጡ አባላትን ያቀፈው የምክረ ሐሳቡን አስፈጻሚ ኮሚቴ ባለሙያዎች ቀጥሮ ሥራውን ሲያስፈጽም ድንገት አለመግባባት ከተፈጠረ እንጂ፣ አሁን የሚመሠረትበት አመክንዮ የለም የሚለው የኢትዮጵያ አቋም ነው፡፡

ሌላው ስብሰባው ያለ ውጤት እንዲበተን ምክንያት የሆነው ሦስቱም አገሮች የጋራ መግባባት እንዲኖራቸው ግብፆች ሰባት መርሆች ይዘው መቅረባቸው ነበር፡፡ የመግባባት ሰነድ መፈራረም የዚሁ ስብሰባ አጀንዳ ካለመሆኑም ባሻገር፣ ቀደም ሲል በተለይ የውኃ አጠቃላይ የስምምነት ማዕቀፍ ላይ ሲፈራረሙ፣ ከአሥር ዓመት በላይ ከቆዩ በኋላ አሁን እንዲህ ዓይነት አጀንዳ ላይ መነጋገር ዋናውን ጉዳይ ወደ ጐን ለመግፋት ያለመ በመሆኑ ኢትዮጵያ ያልተቀበለች ምክንያት መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ እንደ ዶ/ር ያዕቆብ እምነት፣ ጥያቄው ሒደቱን ወደ ኋላ የሚመልስ ብቻ ሳይሆን ከዚህ በፊት የተደረገውን የሚቃረን መርህ ነው፡፡

ዴይሊ ኒውስ የተባለ ጋዜጣን ጨምሮ አብዛኞቹ የግብፅ ሚዲያዎች ግን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸውን ዋቢ አድርገው የዘገቡት ከዚህ በተቃራኒ ነው፡፡ ‹‹ከሦስቱም አገሮች የተውጣጣ አንድ ኮሚቴ እንዲቋቋም ግብፅ ያቀረበችው ሐሳብ በኢትዮጵያ ተቀባይነት አላገኘም፤›› በሚል፡፡

ምን ማለት ነው?

ዓለም አቀፍ የውኃ ኤክስፐርቶች ያሉበት ቡድን  ግድቡን አጥንቶ ሪፖርቱን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ፣ ያቀረበውን የምክረ ሐሳብ ለመተግበር ተደጋጋሚ ድርድር እየተደረገ ቆይቷል፡፡ አሁን ግን ድርድሩ እንከን እያጋጠመው ይመስላል፡፡

ዶ/ር ያዕቆብ፣ ‹‹ወደፊት ድርድሩ ምን የሚሆን ይመስልዎታል?›› በማለት ከሪፖርተር ለቀረብላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ ‹‹አሁን እየተሠራ ያለው ሥራ በባለሙያዎች ደረጃ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ጥናት እንዲደረግ ነው፡፡ በቁጥር ተለክቶ ተወስኖ የሚገለጽ ነገር ነው፡፡ ግብፆች ያንን ነገር መቀበል አይፈልጉም፤›› ብለዋል፡፡

እንደተደራዳሪም እንደ የፖለቲካል ሳይንስ ተመራማሪም የጀመሩትን ምላሽ በመቀጠል፣ ‹‹በቴክኒክ ደረጃ ያለውን ነገር ወደ ላይ ወደ መሪዎች ግብፆች ተመልሶ እንዲሄድና ፖለቲካዊ ይዘት እንዲኖረው ይፈልጋሉ፡፡ እስካሁን የተሠራውንና የተለፋበትን መና የሚያስቀር ነው፡፡ እንዳልተሠራ ሆኖ ወደ ኋላ የሚመለስ ከመሆኑም በላይ፣ በዚያውም ግብፆች የፖለቲካ ውዝግቡን ለሚዲያ ቀልብና ትችት ይዳርጋሉ፤›› ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ በኩል እያንዳንዷ እንቅስቃሴ በጥንቃቄ የምትታይ መሆኗን፣ ድርድሩ በዝርዝርና በቴክኒክ አፈጻጸም ጉዳዮች ላይ እንጂ ወደ ፖለቲካ ተመልሶ የሚሄድበት መንገድ በሩ ዝግ ነው ብለዋል፡፡

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህርና በዓባይ ውኃ ውዝግብ ላይ ጥናት ያካሄዱት አቶ ዘሪሁን አበበ በበኩላቸው፣ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ተደራዳሪውን ዶ/ር ያዕቆብ ሐሳብ ይደግፋሉ፡፡ ‹‹በግብፅ በኩል ለማድረግ የሚፈለገው አንድና አንድ ነው፡፡ የግድቡ ሥራ እንዲቋረጥ ወይም በጣም ትንሽ ሆኖ እንዲገነባ ነው፡፡ ያ እስካልተሳካላቸው ድረስ ጉዳዩ ሁሌም ፖለቲካዊ መልክ ይዞ በሚዲያ እንዲራገብና ኢትዮጵያን ለማስተቸት ይፈልጋሉ፤›› ብለዋል፡፡ ዞሮ ዞሮ ፍላጐታቸው ቀደም ሲል በብቸኝነት የተፈረመውን እ.ኤ.አ. የ1959 ‹‹ውል›› ማሽከርከር እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ እንደ አቶ ዘሪሁን ገለጻ፣ ግብፆች በአንድ በኩል የተፋሰሱን አገሮች የውኃ ትብብር ማዕቀፉን በጀርባ እየመጡበት ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት የያዘው መንገድ እንዳለ ሆኖ፣ በዓባይ ተፋሰስ አገሮች ሥራ ላይ የዋለውንና ሕግ ሆኖ የፀደቀውን የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት በፈራሚ አገሮች ፓርላማ እንዳይፀድቅ ጥረት ያደርጋሉ፡፡  

የተመናመነው የመደራደር አቅም

በዓባይ ግድብ ዙሪያ የሚደረጉ ድርድሮች በሦስት አገሮች መካከል ብቻ የሚደረጉ የሦስትዮሽ ድርድር ሆነዋል፡፡ ቀደም ሲል በግድቡ መገንባት ተቃውሞ ቢጤ አሰምታ የነበረችው ሱዳን ከተወሰነ ጊዜ በኋላ አቋሟን ለመከለስ ተገዳለች፡፡ በመሆኑም አሁን በጉዳዩ ላይ በሚደረጉ ድርድሮች ጐልተው እየወጡ ያሉት ጫፍ የረገጡ ውዝግቦች በሁለቱ አገሮች ማለትም በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል ሆነዋል፡፡ ይኼውም ከ80 በመቶ በላይ የዓባይን ውኃ ጥቅም ላይ በምታውለው ግብፅና ለዓባይ ውኃ 86 በመቶ አስተዋጽኦ በምታደርገው ኢትዮጵያ መካከል ነው፡፡ ውዝግቡ በተለያዩ መንገዶች የሚገለጽ ሲሆን፣ የሱዳን አቋም መለወጥ የግብፅን የመደራደር አቅም እየተመናመነ እንዲመጣ ምክንያት መሆኑን አንድ ሪፖርተር ያነጋገራቸው ስማቸው እንዲገለጽ የማይፈልጉ የውኃ ዲፕሎማሲ ተመራማሪ ተናግረዋል፡፡ እሳቸው እንደሚሉት፣ የግብፅ የመደራደር አቅም የተመናመነው ግብፅ ውስጥ ባለው ቀውስ ምክንያት ብቻም አይደለም፡፡ እንዲያውም ሚዲያዎቻቸው ከሚዘግቡት ማስተዋል እንደሚቻለው፣ የግብፅ ፖለቲከኞች አገራቸው ከገባችበት ቀውስ መውጣት የምትችለው አንድ ትልቅ ውጫዊ የሆነ አጀንዳ በመፍጠር መሆኑን የተስማሙ ይመስላሉ፡፡ እሱም የዓባይን ጉዳይ በማቀንቀን ሲሆን፣ ኢትዮጵያ የተባለችውን ‹‹ነባር ጠላት›› ማስቀደምና የውስጥ ጉዳያቸው በድርድር እንዲቆይ ማድረግ ነው፡፡ እንደ ዲፕሎማቱ እምነት ሱዳን በግድቡ ላይ የነበራት አቋም ሲለወጥ በግብፅ ላይ ከፍተኛ መደናገጥ ነበር የፈጠረው፡፡

የዓባይን ግድብ በተመለከተ የሱዳን አቋም መለወጥ ብቻ ሳይሆን፣ የግድቡን ተፅዕኖ ያጠኑት የውኃ ባለሙያዎች ቡድን ሪፖርት የግብፅ ፖለቲከኞች በኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠሩትን ሴራ አክሽፎባቸዋል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ግብፆች በኢትዮጵያ ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያደርጉት ጉትጐታ ተቀባይነት እንዳይኖረው አድርጐታል፡፡ በተቃራኒው የኢትዮጵያን አቋም በይፋ ሙሉ ለሙሉ ተሰሚነት አገኘ ባይባልም፣ አንዳንድ ትልልቅ መገናኛ ብዙኃን ሚዛኑን በጠበቀ አኳኋን መዘገብ ጀምረዋል፡፡ አሁን ቴክኒካዊ የሆነ ድርድር ወደ ፖለቲካ ደረጃ ከፍ ብሎ ውዝግብ እንዲፈጥር የሚፈለግበት ምክንያት ይኸው ነው፡፡

ቀደም ሲል ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ የምታራምደውን የማዳከም ስትራቴጂ የተገነዘበው የኢትዮጵያ መንግሥት ግድቡን ሙሉ ለሙሉ በራሱ ወጪ ለመገንባት ነበር ያቀደው፡፡ በመሆኑም በፕሮጀክቱ ተፈጥሮም ሆነ ፕሮጀክቱን በተመለከተ የወጣው ዓለም አቀፍ ሪፖርት ግብፅ በውጭው ዓለም ልታሳርፍ የነበረውን ተፅዕኖ በእጅጉ ቀንሶታል፡፡

‹‹በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ›› እንዲሉ፣ በቅርቡ ለግብፅ የውጭ ፖሊሲ ማስፈጸሚያ እንዳትውል ትሰጋ የነበረችው ሱዳን አቋም መለወጥ ብዙ ነገሮችን በግብፆች ላይ ያወሳሰባቸው ይመስላል፡፡ እዚህ ላይ ሁለት ነገሮች ማስታወስ ግድ ይላል፡፡

አንደኛው ከሁለት ዓመት በፊት የአሜሪካ አንድ የደኅንነት ድርጅት (Stratford) እና ዊኪሊክስ ይፋ እንዳደረጉት፣ ግብፅንና ሱዳን ኢትዮጵያንና ታላቁን ግድብ ለማጥቃት ሐሳብ ነበራቸው ተብሎ ነበር፡፡

ሁለተኛው ሱዳን ሥጋት በሚፈጥረው የሁለቱ አገሮች ጦርነት ውስጥ በቀጥታ ትሳተፋለች የሚል ግምት ያልነበረ ቢሆንም፣ ግብፅ ኢትዮጵያን ለማጥቃት የቅርብ ጐረቤት የሆነችው የሱዳንን ግዛት እንደ መንደርደርያ ልትጠቀምበት ትችላለች የሚል ግምት ነበር፡፡

ግብፅ የዓባይን ውኃ በብቸኝነት ለመጠቀም ታዋቂና በአብዛኛው የውኃው ባለቤት ከሆነችው ኢትዮጵያ ውጪ የተደረጉት እ.ኤ.አ. የ1929ና የ1959 አሮጌ ስምምነቶች በአዲሱ ሁለገብ የውኃ አጠቃቀም ማዕቀፍ (CFA) በስድስት አገሮች ፈራሚነት መተካታቸውና ሕግ ሆነው መፅደቃቸው ይታወሳል፡፡  

ሪፖርተር        

ለአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች የፀረ ሽብርተኝነት ሥልጠና ተሰጠ

January 12/2014


የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችን በፀረ ሽብርተኝነት ለማንቀሳቀስ ኢሕአዴግ አዲስ ዘመቻ ጀመረ፡፡ ኢሕአዴግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮችን ባለፈው ዓርብ ሰብስቦ በፀረ ሽብርተኝነት ወቅታዊ ክስተቶችና በፀረ ሽብር አዋጁ ላይ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡

ሥልጠናው በዚህ ሳምንት ቀጥሎ ለዝቅተኛና ለመካከለኛ አመራሮች፣ እንዲሁም ለተለያዩ ማኅበራትና ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ውስጥ ለሚሳተፉ አባላቶቹ ይሰጣል፡፡ ይህ ሥልጠና ለከተማው ነዋሪዎችም እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

ለአዲስ አበባ ከተማ አመራሮች በዋናነት ሥልጠናውን የሰጡት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕግ አማካሪና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ፣ የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተወልደ ገብረ ሚካኤልና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ ናቸው፡፡

‹‹የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ሽብርተኝነትን ከመከላከልና ሕገ መንግሥታዊ መብትን ከማስከበር አንፃር ያለው ገጽታ›› በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሑፍ ከመሠራጨቱም በላይ፣ አቶ አስመላሽና አቶ ተወልደ ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን የአመራር አባላት እንዴት መከላከል እንዳለባቸው ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

ከዚህ በኋላ ሁሉም የመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች እስከታችኛው የኅብረተሰብ ክፍል ድረስ ሽብርተኝነትን መከላከል እንዳለባቸው ተመልክቷል፡፡ በዚህ መሠረት በቀጣዮቹ ሳምንታት ሕዝቡን በፀረ ሽብርተኝነት ላይ አቋም ለማስያዝ ተከታታይ ሥራዎች እንደሚካሄዱ ተነግሯል፡፡

አሠልጣኞቹ የአስተዳደሩ መዋቅር አካላት መታወቂያ የሚሰጡትን ሰው ማንነትን በውል መረዳት እንዳለባቸው አስጠንቅቀዋል፡፡ የሃይማኖት አክራሪነትና የአሸባሪነት ዋናው ምንጭ ድህነትና ተስፋ መቁረጥ ነው ያሉት አሠልጣኞቹ፣ ተስፋ የቆረጡና ያልተሳካላቸው አካላት ወደ ሽብር ድርጊት እንደሚገቡ አመልክተዋል፡፡

መልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያሉ ችግሮች፣ እንዲሁም ሥራ አጥነት መቀረፍ እንዳለበት አሠልጣኞቹ ገልጸው፣ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል፡፡

ይህ ካልሆነ ግን የተከፉ ሰዎች ለሽብርተኞች እርሾ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጥርጥር እንደሌለው ተብራርቷል፡፡ አቶ አስመላሽ በሰጡት ማብራሪያ ከ1997 ዓ.ም. ምርጫ ጋር ተያይዞ የተነሳው ረብሻ ለዚህ ጥሩ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡ ምክንያቱም አዲስ አበባ ውስጥ በ54 ቦታዎች የተነሳው ረብሻ ለፀጥታ ኃይሎች አስቸግሮ እንደነበርና ይህም የሆነው ተገቢው ሥራ ባለመሠራቱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በመነሳት አመራሮቹ በተጀመሩ የቤቶች ልማት፣ በጥቃቅንና አነስተኛ፣ እንዲሁም በመልካም አስተዳደርና በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ መሠራት እንዳለበት በሥልጠናው ላይ ተገልጿል፡፡

ይህንን ችግር ለመፍታት በፍትሕና በመልካም አስተዳደር ዘርፍ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ማስወገድ፣ የሕግ የበላይነት፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት መስፈን እንዳለበትና የመልካም አስተዳደር እንቅፋት በመሆን ላይ ያለውን ሙስና እያንዳንዱ ተቋም ከሥራ ባህሪው አኳያ መታገል እንዳለበት ተገልጿል፡፡

አቶ ተወልደ በበኩላቸው፣ የፖሊስና የፀጥታ አካላት የማኅበረሰብ ፖሊስን በማስተባበር የሽብር አደጋዎችን ዜሮ ደረጃ ማድረስ እንደሚገባቸው ገልጸው፣ ኅብረተሰቡ ከእነዚህ አካላት ጋር እንዲታገል አመራሮች በዚህ ስሌት ሥራቸውን ማከናወን እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

አቶ አስመላሽ እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ባፀደቃቸው ሦስት አዋጆች የአገር ውስጥ ተቃዋሚዎችና በውጭ የሚገኙ አንዳንድ አካላት ዘመቻ ከፍተዋል፡፡ ሦስቱ አዋጆች የፀረ ሽብር አዋጅ፣ የበጎ አድራጎትና ማኅበራት አዋጅና የመገናኛ ብዙሃንና የመረጃ ነፃነት አዋጅ ናቸው፡፡

እነዚህ አዋጆች ከፍተኛ ጠቀሜታ ቢኖራቸውም፣ አዋጆቹን ለማስቀልበስ ተቃዋሚዎች ያልተገባ ዘመቻ ከመክፈታቸውም በተጨማሪ ፊርማ እያሰባሰቡ መሆኑ ተገልጿል፡፡ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ የፀረ ሽብር አዋጅ እንዲሰረዝ ፊርማ እያሰባሰበ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በወቅቱ በተሰራጨው ጥናታዊ ጽሑፍ እንደቀረበው ኢትዮጵያ የሽብርተኝነት ሥጋት የተደቀነባትና በርካታ ጥቃቶች የተፈጸሙባት አገር ናት፡፡ በዓለም አቀፍና በአገር ውስጥ በተደራጁ ሽብርተኞች የጥቃት ሰለባ ሆናለች፡፡ ከ1987 ዓ.ም. ጀምሮ ኦነግ ሰላማዊ ሰዎችን ዒላማ ያደረጉ ሕዝብ በሚዝናናባቸው ሆቴሎች፣ ባቡር ጣቢያዎች፣ ንግድ ቤቶች በፈጸመው የሽብር ጥቃቶች ለንፁኃን ዜጎች ሞት፣ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ማድረሱን የጥናት ጽሑፉ አትቷል፡፡ አቶ አስመላሽ ሲያብራሩም፣ ከ1987 እስከ 2000 ዓ.ም. ድረስ በኦነግ ላይ 106 ክሶች ቀርበዋል፡፡ ጥናታዊ መረጃው እንደሚያብራራውም ኦብነግ፣ አልኢታድ፣ አልሸባብ፣ ግንቦት 7 እና አልቃኢዳ በተለያዩ ወቅቶች የሽብር ጥቃት አድርሰዋል ይላል፡፡

አገሪቱን ከዚህ የሽብር ጥቃት ለመታደግ የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅን ማውጣት አስፈላጊ መሆኑን፣ አዋጁን ለማስፈጸም ኅብረተሰቡ ከመንግሥት ጐን እንዲቆም ጥሪ ቀርቧል፡፡
ሪፖርተር

More than 52 Ethiopian maids, 25 domestics arrested in Kuwait

         January12/2014
Network busted as 52 Ethiopian maids, 25 domestics arrested 
More 52 Ethiopian maids, 25 domestics arrested in KuwaitThe Jleeb Al- Shuyoukh police recently raided a residential building in the area and arrested 52 Ethiopian maids and 25 male servants - drivers and household help - on whom absconding reports had been filed by their sponsors at various police stations, reports Al-Anba daily.
According to security sources the building was being used by unidentified persons as safe haven for runaway people and then provided jobs in return for a certain fee. The daily added the transactions were made through Internet. All those arrested have been referred to the concerned authorities.
Meanwhile, Ahmadi securitymen arrested 24 individuals, issued two citations against traffic violations, seized two vehicles and confiscated 46 bottles of locally brewed liquor during the security campaigns that they launched from Dec 13, 2013 to Jan 4, 2014. Among the arrested individuals, 10 were involved in various cases while 14 did not have their Civil IDs. They were referred to the concerned authorities for necessary legal action against them. Ahmadi Security Directorate affirmed that they will continue to launch such security campaigns in all areas of Ahmadi Governorate to arrest the violators of law and traffic rules.

Source: ArabTimes


የሳዑዲ ጉዳይ፡ የአስከሬኑ ሽኝት – ከነብዩ ሲራክ

January 12/2014
እጣ ፈንታ …
(ፎቶ ፋይል)

(ፎቶ ፋይል)

ዘመኑ በፈቀደው የአረብ ሃገር ስደትን በኮንትራት ስራ የሳውዲን ምድረ በዳ የባለ ጸጎች ሃገር የረገጠከው ራስክን ደግፈህ ፣ ወላጅ ቤተሰብ፣ ዘመድ አዝማድ ወገኖችህን ለመደገፍ ነበር ። በሳውዲ ቆይታህ በትዕግስት ስታልፍ ያስብከውን ሁሉ ባይሳካም ጋብቻ መስርተህ ሌላዋን የኮንትራት ሰራተኛ ስደተኛ እህትክን ባንድ አቅፈህ ፣ ራስክን በሙያ አንጸህ የተረጋጋ ኑሮን በመኖርህ ላይ እንዳለህ ሳታስበው በውስጠ ደዌ በሽታ ተወጋህ ! ክፉውን ሁሉ የስደት ህይወት በትዕግስት ገፍተህ ደስተኛ ሆነህ ኑሮን ትገፋ እንደነበር አህትህና ባለቤትህ ቅሪት ገላህን ወደ ሃገር ለመሸኘት ለስንብት ስንጓዝ አጫውተውኛል። ፎቶህን አይቸ በህይወት ዘመንህ በአንድ አጋጣሚ አውቅህ እንደነበር ሳውቅ ደነገጥኩ ፣ ድንጋጤየን ዋጥኩት ! ነፍስህን ይማረው ወንደም አለም

ስንብት …
ወደ አልሰሜ እናትና ዘመድ አዝማድ የሚላከውን በድን አካልክን ለመሰናበት በሔድንበት አጋጣሚ በዚያው የሬሳ ማቆያ ጽህፈት ቤት ሃላፊውን ስንት የኢትዮጵያውያን ሬሳ አለ ብየ ጠየቅኩት ። የደስደስ ያለው አረብ ሲመልስ ” አሁን እንኳን ብዙ አይደሉም ፣ ከዚህ በፊት ብዙ ነበር ። እዚህ ማቆያ ውስጥ ፈላጊ ያልመጣላቸው ከአስር የማያንሱ የኢትዮጵያውያን ሬሳ ይገኛል!” ሲል ዘርዘር አድርጎ መለሰልኝ ። ጠያቂ ስለሌላቸው ፣ ስማቸው ስላማይገኝ ሬሳዎች እጣ ፈንታ ብቻ ሳይሆን የሬሳው ማንነት ታውቆ የሚያስቀብር ጠያቂ ከጠፋ በማዘጋጃ ቤትና በፖሊስ እንደሚቀበሩ ያጫወተኝ … ሊሰሙት የሚከብድ እውነት !

ከሬሳው ማስቀመጫ መስሪያ ቤት ሃላፊ ጋር ላፍታ ባደረግነው ቆይታ የሰማሁት አሳዛኝ ነባራዊ ሁኔታ ውስጤን አደማው ። ሬሳውን ወደ ምንቀበልበት የጓዳ በር ለየራሳችን ቆዛዝመን ደረስን: ( ታሞ ፣ እህት ሚስቱ አስታምመውት ፣ ማንነቱ ታውቆ እና ወደ ሃገር መላኪያ ገንዘብ ተገኝቶ ዛሬ ወደ ሃገር ለመሄድ ተዘጋጅቷል ፣ ከምሽቱ 9:45 … የብርቱ ወዳጀ አብሮ አደግ ከፈን ከተቀመጠበት ማቀዝቀዣ ወጣ … በተዘጋጀው የእንጨት ሳጥን ሆኖ ወደ አንቡላንስ ከመሸኘቱ በፊት በስትሬቸር እየተገፋ መጣና ለስንበት ፊቱ በአንድ የፊሊፒን የሬሳው ክፍል ሰራተኛ ተገለጠ … ያ ዘንካታ አይኑን ጨፍኖ ታጋድሟል …አንጀንታቸው የሚላወሰውን እህት ፣ ሚስት፣ ጓደኞች እና ጎረቤቶች ሃዘናቸውን እንደፈለጉ ጮኸው በማይገልጹበት ግቢ የወንድማቸውን በድን ተሰናበቱት … በሬሳው ክፍል ሃላፊ ባጫወተኝ አሳዛኝ ታሪክ ተጽናንቸ የነበርኩት እኔም እህት የወንድሟን ፣ ሚስት የባሏን ግንባር እየሳሙ በታመቀ የሃዘን ስሜት ድምጻቸውን አርቀው እያነቡ ሲሰናበቱት ሳይ ብርክ ያዘኝ !

ሽኝት …
በእርግጥም እኒህኞቹ ወገኖችም ሆኖ ታሞ አስታመውት የሞተው ወንደም እድለኛ ነው! ነገ የሃገሩን አፈር ፣ ታሞ እያለ እናቱን ናፍቆ ሁለቴ ለመሄድ ተነስቶ በተመለሰበት አውሮፕላን ዛሬ በድኑ በውድ ዋጋ ተጭኖ ይደርሳል ! እናት እና ልጅ ተነፋፍቀው አልተገናኙም: ( እናም አልሰሜ እናት አለም ነገ ሬሳ ለመቀበል በጠዋት መርዶ ይጠብቃታል !

ህይወት እንዲህ ነው የሞተውን ነፍስ ይማር ! እናት እና መላ ቤተሰብ ጽናቱን ይስጣችሁ ሌላ ምን ይባል?
ሌላ አሳዛኝ ታሪክ ትረካ በቪድዮ



ከዘ -ሐበሻ የተወሰደ 

ኢትዮጵያ ለምን ኋላ ቀረች?(ግርማ ሞገስ)

January12/2014

ኢትዮጵያ ከውጭ ወረራ ረጅም የነፃነት ዘመን እንዳላት የአገር ተወላጅ እና የውጭ አገር የታሪክ ተመራማሪዎች ያረጋግጣሉ። ይሁን እንጂ በስልጣኔ ግን ብዙም እንዳልገፋች ይኸው ዛሬ የእኛም ትውልድ ሳይቀር የሚያየው ሃቅ ነው። ይኽ እንዴት ሊሆን ቻለ? ረጅሙን የነፃነት ዘመን በስልጣኔ ወደፊት ለመራመድ ለምን አልተጠቀመችበትም ኢትዮጵያ? ምን ስትሰራ ነበር? የሚሉት የቁጭት ጥያቄዎች የሁላችንም አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጥያቄዎች ናቸው። በ19ኛው ክፍለ ዘመን በራሳቸው አነሳሽነት አውሮፓውያን ጎብኚዎችን እና ሚሲዮናውያንን እየተከተሉ ከአገራቸው ወጥተው የፖለቲካ ሳይንስ፣ የህክምና፣ የምህንድስና፣ የኢኮኖሚ፣ የመንገድ ስራ የመሳሰሉ ዘመናዊ (Secular) ትምህርት ቀስመው አገራቸውን ለመርዳት ወደ አገራቸው የተመለሱት የመጀመሪያዎቹ የኢትዮጵያ ምሁራን የእነ ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ (1886-1919) ሁሉ የቁጭት ጥያቄ ነበር። በጣት የሚቆጠረው የነገብረ ሕይወት ትውልድ የውጭ ትምህርት ቀስሞ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰው ባፄ ምኒልክ ዘመን ነበር። ይሁን እንጂ ለዘመናዊነት በር የተከፈተው ባፄ ኃይለ ስላሴ ዘመን እንደነበር፣ በኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት በ1942 ዓመተ ምህረት (እ.ኤ.አ. 1950) የአዲስ አበባ የተፈጥሮና የሶሻል ሳይንስ ኮሌጅ መከፈቱን፣ ኮሌጁ የተደራጀው በኢትዮጵያ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በመክፈት በንቃት ይሰሩ በነበሩ ካናዳውያን እየሱሳውያን (Jesuits) ሲሆን የተማሪዎቹ ቁጥር ከ100 በታች እንደነበር ክፍሉ ታደሰ (The Generation, p. 15-16) ያመለክታል። እሱም ቢሆን እጅግ ዘግይቶ የመጣ በውቅያኖስ ላይ ያረፈ ትንሽ ጠብታ ያህል ነበር። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)

የአሰብ ጉዳይ:- “ጦርነት ፈርተን ግን ሀገራችንን አሳልፈን አንሰጥም” – ከአብርሃ ደስታ

January12/2014

ገና በጠዋቱ “ዓሰብን ማስመለስ አለብን የምትለው እንዴት ነው? ወደ አላስፈላጊ ጦርነትና ደም ማፋሰስ ልታስገቡን ፈለጋቹ?” የሚል አስተያየት አዘል ጥያቄ አገኘሁ።





















መጀመርያ ወደ ጭንቅላታችን መምጣት ያለበት ጉዳይ ‘የዓሰብ ወደብ የማነው?’ የሚል ነው። ዓሰብ የኢትዮጵያ ልአላዊ ግዛት (ንብረት) ስለመሆኑ ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊና ሕጋዊ (በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት) ማረጋገጫዎች አሉን። ዓሰብ የኛ ስለመሆኑ የሚያጠራጥር ምንም ምክንያት የለም። ማስረጃዎቹ (ማረጋገጫዎቹ) እዚሁ ፌስቡክ ላይ ባልፅፋቸውም በወደቡ ባለቤትነታችን ጥርጣሬ አይግባቹ። ስለዚህ ጥያቂያችን ፍትሐብሄር ነው።
ሁለተኛ ጉዳይ ዓሰብ የኛ ቢሆንም አሁን ያለው ግን በኤርትራ ቁጥጥር ስር ነው። ንብረት ሃብታችን ተነጥቀናል ማለት ነው። ጥያቄው መሆን ያለበት ‘ዓሰብ ወደብ ለኢትዮጵያ ያስፈልጋል?’ የሚል ነው። መልሱ: ‘አዎ! ያስፈልጋታል’ ነው። የባህር በሯን የተነጠቀች ብቸኛዋ ትልቅ ሀገር ኢትዮጵያ ናት። በአሁኑ ግዜ የባህር በር የአንድ ሀገር የህልውና በር ነው። የህልውና በሩ መዘጋት የለበትም። ስለዚህ ኢትዮጵያ ንብረቷ (ወደቧ) የማስመለስ መብትም ታሪካዊ ግዴታም አለባት።

ሦስተኛ ‘እንዴት ነው ወደቡን ማስመለስ የምንችለው?’ የሚል ጥያቄ ማየት ተገቢ ነው። ምክንያቱም ዓሰብ የኢትዮጵያ ቢሆንም በመሪዎቻችን ሐላፊነት የጎደለው ዉሳኔ ምክንያት ለኤርትራ ተሰጥቶ ይገኛል። ‘ወደባችን አለ አግባብ ለኤርትራ በመሰጠቱ ምክንያት ዓሰብን የማስመለስ ጉዳይ ከባድ ሊያደርገው ይችላል’ የሚል ሐሳብ ቢነሳ አግባብነት አለው። ጦርነትም ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋት ሊቀቅ ይችላል።
ግን ማትኮር ያለብን ስለ ጦርነት አይደለም፤ ስለ ዓሰብ ንብረትነት እንጂ። ዓሰብ የኛ መሆኑ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ማረጋገጥ (ማሳመን) ይኖርብናል። በዓሰብ ጉዳይ ፅኑ አቋም ይዘን የኢትዮጵያም የኤርትራም ህዝብ እንዲገነዘበው መጣር አለብን። የዓለም ህዝብ ይሁን መንግስትታት ይደግፉናል። ምክንያቱም የባለቤትነት መከራከርያ ነጥባችን ጠንካራ ነው። የዓለም አቀፍ ሕግም ይደግፈናል። ዓሰብ የኢትዮጵያ ስለ መሆኑ የሚመሰክግሩ የተለያዩ ዓለም አቀፋዊ ስምምነቶችም አሉ።

አራተኛ ዓሰብ የኛ መሆኑ ቢናረጋግጥና ለዓለም መንግስታትና ማህበረሰብ ቢናሳውቅ እንኳ እንዴት ዓሰብን መመለስ እንችላለን? የኤርትራ መንግስትኮ ፍቃደኛ አይሆንም፣ ጦርነት ሊነሳ ይችላል … ወዘተ የሚሉ ጉዳዮች መነሳታቸው አይቀርም። ግን ችግር የለውም። ዓሰብ የኛ መሆኑ ካረጋገጥን ‘ንብረታችን መልስልን’ ብለን የመጠየቅ መብት አለን። የኤርትራ መንግስት ፍቃደኛ ላይሆን ይችላል። ጦርነትም ሊከፍት ይችላል።
እኛ ጦርነት አንፈልግም። ሕጋዊ ንብረታችን (ወደባችን) በሰለማዊ መንገድ እንዲሰጠን ነው የምንጠይቀው። አዎ! ጦርነት አንፈልግም። ጦርነት አንፈልግም ማለት ግን ጦርነት ከፍተን በሃይል የሌላ ሀገርና ህዝብ ንብረት አንወርም ማለት እንጂ ጦርነት ፈርተን ልአላዊ ግዛታችን (ሃብታችን) ለሌሎች ሃይሎች አሳልፈን እንሰጣለን ማለት አይደለም። ጦርነት አንፈልግም ማለት ጦርነት እንፈራለን ማለት አይደለም። አዎ! ጦርነት ስለማንፈልግ ሌሎች ህዝቦችን አንወርም። ጦርነት ፈርተን ግን እናት ሀገራችን አናስደፍርም።

ጦርነት ስለማንፈልግ ዓሰብን በሰለማዊ መንገድ የምንረከብበት መንገድ እናመቻቻለን። የኤርትራ መንግስት ጦርነት ሊከፍትብን ይችላል ብለን ግን ሃብት ንብረታችን ከመጠየቅ ወደኋላ አንልም። ጦርነት ተፈርቶኮ የሀገር ግዛት አሳልፎ አይሰጥም። ጦርነት ተፈርቶኮ ልአላዊ ግዛትን ከማስከበር ወደኋላ አይባልም። በባድመ ጉዳይ ጦርነት ዉስጥ የገባነው ጦርነት ስለምንፈልግ ሳይሆን ልአላዊ ግዛታችን የማስከበር፣ ሀገራችን ከወራሪዎች የመከላከል ሀገራዊ ግዴታ ስላለብን ነው። ጦርነት ፈርተን እጃችንና እግራችን አጣጥፈን የባድመን መሬት ለሻዕቢያ ወራሪዎች አሳልፈን አልሰጠንም።
(በኋላ በፖለቲካዊ ዉሳኔ፣ በመሪዎቻችን ግድየለሽነት ምክንያት ባድመን መስዋእት ከፍለን በደም አስመልሰን ሲናበቃ በእስክርቢቶ ለወራሪዎች ተላልፎ ተሰጠ እንጂ። በጦርነት የተመለሰ ንብረት በድርድር ሲከሽፍ በታሪክ ለመጀመርያ ግዜ ነው። የባድመ ጉዳይ …!)

ምንም እንኳ ጦርነት ባንፈልግም ሃብት ንብረታችን ግን አሳልፈን አንሰጥም። ጦርነት መስዋእት ይጠይቃል። ግን ለሀገራችን መስዋእት ብንከፍል ችግሩ ምንድነው? ለሀገራችንኮ መሞት አለብን። በምንክያት መስዋእት መሆን እንቻላለን። ደግሞኮ ኢህአዴጎች የዓሰብን ጉዳይ ስናነሳባቸው ‘ጦርነት ናፋቂዎች’ ይሉናል። እኔ ግን ለሀገር መስዋእት ብንከፍል ጉዳት የለውም ባይ ነኝ። እንኳንም ለሀገራችን ኢትዮጵያ ለሶማሊያም እየሞትን ነው። ይቅርታ ለሶማሊያም እየሞትን አይደለንም። ምክንያቱ ላልታወቀ ጉዳይ ነው በሶማሊያ እየሞትን ያለነው። ወታደሮቻችን በሀገረ ሶማሊያ እየሞቱ ያሉ ለምን ዓላማ ነው? ዜጎቻችን ዓላማው ለማይታወቅ ጉዳይ በሶማሊያ ከሚሞቱ ለሀገራችን ቢሞቱ አይሻልም ነበር? ኢህአዴጎች ‘ጦርነት ጥሩ አይደለም’ ይሉናል። ጦርነት ጥሩ አለመሆኑ ቢያውቁ ኑሮ ለምን በሶማሊያ ያሉ ወገኖቻችን ወደ ሀገራቸው አያስገቡም?
አዎ! ጦርነት ጥሩ አይደለም። በተቻለ መጠን ጦርነትን ማስወገድ አለብን። ጦርነት ፈርተን ግን ሀገራችንን አሳልፈን አንሰጥም።
አሜን!