January8/2014
በኢትዮጵያ መንግስት የሚታገዘው እና የበረከት ስምኦን ሁለተኛ ድምጽ እየተባለ የሚጠራው የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ስብስብ እስክንድር ነጋ አይፈታም ሲሉ ለመንግስት ጉዳዮች መምሪያ ገልጸዋል ከዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ተቋማትም እስክንድር ነጋ ሽብርተኝትን፣ ፋሺዝምንና ናዚዝምን በሚያበረታታ እንቅስቃሴና አስነዋሪ ተግባራት ውስጥ ሲሳተፍ የቆየ ከመሆኑ ሌላ በጋዜጠኝነት ሙያም በየትኛውም ሚዲያ እንደማይሠራ በመረጋገጡ ምንም ዓይነት ድጋፍና እገዛ እንደማያደርጉ ወስነዋል ሲሉ የሽብር ወሬአቸውን ሲነዙ የቆዩ እንደሆነ የሚያሳየው ይሄው ዘገባ የኢትዮጵያን ህዝብ እንዳስቆጣ አንዳንድ ህብረተሰቦች ለማለዳ ታይምስ በፌስቡክ ፔጅ ገልጸዋል ።
እንደማህበር እራሱን የሚጠራው እና የቀድሞው የጋዜጠኞች ማህበር ፈርሶአል እያለ ህብረተሰብን ግራ የሚያጋባው እና በአለም አቀፍ እውቅና የሌለው ይሄው በእነ አቶ ወንደሰን እና አንተነህ ፣ በአቶ በረከት ስምኦን እርዳታ በ1997 አመተ ምህረት የቀድሞውን የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች ማህበር ለማፍረስ ሲባል ያቋቋሙት ግለሰቦች የማህበሩን ማህተም እና ሌሎች ቁሳቁሶች ገንዘብ ጭምር በመዝረፍ እና በማሸሸ ፣በመንግስት ማህተሙ ተነጠቀ በማለት በመንግስት መገናኛ ብዙሃኖች ዜና በማወጅ እራሳቸውን የነጻው ፕሬስ መገናኛ ነን ሲሉ መግለጻቸውን ጠቁመው ከመንግስት ጎን ለጎን አብረው ጉዞአቸውን እንደቀጠሉ ይታወሳል ። በሌላም በኩል በአዲስ ዘመን ላይ አሁንም በነጻው ጋዜጠኖች ላይ ከፍተኛ የሆነ ጦርነት አውጀውባቸዋል ይሄውም በመጼሄቶች ላይ የሚታተመው ስራ በሙሉ የጽንፈኛ ፖለቲከኞችን የሚያንጸባርቅ ሃሳብ የሚያትሙ ናቸው ሲሉ አውግዘዋቸዋል ።መንግስት የነጻ መረጃ በማይሰጥበት አገር ላይ እንደገና ጋዜጠኖች ፈልፍለው የሚያወጡትን ወሬ አሸባሪ ነው እያለ መክሰስ ከጀመረ ረጂም ጊዜያትን እንዳስቆጠረ የሚታወስ ነው ።አዲስ ጉዳይ ፣ፋክት ፣ሎሚ ቆንጆ ጃኖ እንቁ እና ሊያ የተሰኞትን መጽሄቶች የተቃዋሚ ፓርቲ ልሳኖች ናቸው በማለት የፈረጇቸው ሲሆን የሁሉም አሉታዊ ተጽእኖ የሚያርፈው መረጃን አዛብቶ በማቅረብ እና ፖለቲከኞችን በመደገፍ ነው ሲሉ አትቶአል ። አሁንም በድጋሚ እንዲህ አይነቱ ክስ ሊፈጠር የሚችለው ሚዛናዊ የሆነ መረጃን በሃገሪቱ ማፍለቅ ሲችአል እና መንግስት ለነጻው ፕሬስ አስፈላጊውን መረጃ መስጠት ሲችል እና ለዚያ ምላሽ ከተቃዋሚዎቹም ወገኖች የሚቀርቡትን እኩል በማገናዘብ ማቅረብ ሲችሉ ሲሆን በሌላ ወገን ደግሞ መንግስት የሰጠውን አባሪ የህትመት ጽሁፍ ተዛብቶ ሲያገኘው ብቻ መሆኑን ለማወቅ ያልተረዱ የመንግስት መገናኛ ብዙሃኖች እና የመንግስት አካሎች እኛ ነጻ ነን ሊሉን ይሞክራሉ ። አጠቃላይ መረጃውን የማለዳ ታይምስ የደረሰው ሲሆን ይህንንም አያይዞ አቅርቦላችኋል ። የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ኅብረትና ዓለም አቀፍ ተቋማት የእስክንድር ነጋን የይፈታ ጥያቄ ውድቅ አደረጉት የቀድሞው የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ጋዜጠኞች ማኅበር ከአይ ኤፍ ኢ ኤክስ አባልነት ታገደ

በኢትዮጵያ ውስጥ በፈፀመው የሽብር ወንጀል ተፈርዶበት በእስር ላይ የሚገኘው እስክንድር ነጋ ጋዜጠኛ ነበር ብሎ ለመቀበል የማህበር ድጋፍና እገዛ ለማድረግ እንደሚቸገር የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ኅብረት ፕሬዚዳንትና የምሥራቅ አፍሪካ ጋዜጠኞች ማህበር ምክትል ፕሬዚዳንት ጋዜጠኛ አንተነህ አብርሃም ገለጹ፡፡
ምክትል ፕሬዚዳንቱ ጋዜጠኛ አንተነህ አብርሃም ከጋዜጣው ሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳሉት፤ ዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ተቋማትም እስክንድር ነጋ ሽብርተኝትን፣ ፋሺዝምንና ናዚዝምን በሚያበረታታ እንቅስቃሴና አስነዋሪ ተግባራት ውስጥ ሲሳተፍ የቆየ ከመሆኑ ሌላ በጋዜጠኝነት ሙያም በየትኛውም ሚዲያ እንደማይሠራ በመረጋገጡ ምንም ዓይነት ድጋፍና እገዛ እንደማያደርጉ ወስነዋል።
ከምርጫ 97 ጋር በተያያዘ በሚያቀርባቸው ጽሑፎቹ ምክንያት የጋዜጣ ድርጅቱ እንዲፈርስ በሕግ የተወሰነበት እስክንድር ነጋ፤ ከ1997 ዓ.ም ወዲህ በጋዜጠኝነት ላይ እንደተሰማራ ካለመታወቁም በላይ የመላ አማራ ድርጅት የተሰኘ ፓርቲ የቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ ኃላፊ እንደነበረም ፕሬዚዳንቱ ያስታውሳሉ። በእነዚህና ተያያዥ ምክንያቶች በማህበር ደረጃ እገዛ ለማድረግ የሚቻልበት ሁኔታ ዝግ እንደሆነበት አስረድተዋል፡፡
እርሳቸው ተካፋይ_ በሆኑበት የዓለም ጋዜጠኞች ፌዴሬሽን (አይ.አፍ.ጄ) ጠቅላላ ጉባዔ ላይ አንዱ መነጋገሪያ የእስክንድር ነጋ ጉዳይ እንደነበረም ጠቅሰው፤ «በወቅቱም ጉባዔው «እስክንድር ይፈታ» የተሰኘ ዘመቻ እንዲካሄድ የቀረበውን የሞሽን_ ሃሳብ በከፍተኛ ድምፅ ውድቅ አድርጎታል» ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታም በካምቦዲያ የዓለም ሃሳብን በነፃ የመግለጽና የፕሬስ ነፃነት ጉዳይ ላይ የሚሠሩ ሁሉም ተቋማት ባካሄዱት ጠቅላላ ጉባዔ፤ በቀድሞው የኢትዮጵያ ነፃ ጋዜጠኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ክፍሌ ሙላት የቀረበውና በሲፒጄ በኩል የተደገፈው_ የ«እስክንድር ይፈታ» ሞሽን_ አብዛኛዎቹ የእስክንድር ተሳታፊዎች ሽብርተኝነትን፣ ፋሺዝምንና ናዚዝምን የሚያበረታቱ ሥራዎች ላይ ነበረ በማለታቸው የቀረበውን የሞሽን ሃሳብ ውድቅ አድርገውታል ብለዋል፡፡እንደ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ገለጻ፤ የካምቦዲያው ጉባዔ የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ጋዜጠኞች ማህበር ህልውናው ያከተመ በመሆኑና በ IFEX አባልነት መቀጠል አለበት በሚል በሲፒጄ ተደግፎ የቀረበውን ጥያቄ በከፍተኛ ድምፅ ውድቅ በማድረግ በክፍሌ ሙላት የሚመራው ኢነጋማ ከአባልነት ተሰናብቷል፡፡ ቀደም ሲልም ሌሎች የዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች መብት ተሟጋቾች በክፍሌ ሙላት የሚመራውን ኢነጋማ ከአባልነት እንዳሰናበቱት አቶ አንተነህ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
በአሜሪካ የሚገኘውና የጋዜጠኞች ተከላካይ ኮሚቴ (Committee to Protect Journalists (CPJ)) በሚል ስያሜ የሚጠራው ቡድን ራሱን በኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚነት ያደራጀና በጋዜጠኝነት ሙያ አሳብቦ በኢትዮጵያ ውስጥ የሥርዓት ለውጥ ለማምጣት የሚተጋ አንድ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ አካል እንደሆነ ጋዜጠኛ አንተነህ አመልክተዋል።
ይሄው ድርጅት የማንም ውክልናና እውቅና ሳይኖረው የኢትዮጵያን ጋዜጠኞች የሚወክል በማስመሰል በሀገር ውስጥ ካለው እውነታ ተቃራኒ የሆኑ አፍራሽ ሥራዎችን ከማከናወን አልፎ ለኢትዮጵያ ጋዜጠኞች አንዳችም ድጋፍ አድርጎ እንደማያውቅ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጋዜጠኞች ኅብረት ኃላፊነት ከሚሰማውና ለአባላቱ ተጠሪ ከሆነው ዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች ፌዴሬሽን ጋር በቅርበት በሀገር ውስጥ ባከናወናቸው የውይይትና የድርድር ሥራዎች በርካታ ውጤቶችን አግኝቷል ያሉት አቶ አንተነህ፤ ሲፒጄ ግን ኒውዮርክ ላይ ሆኖ ከመንግሥት_ ጋር የጀመርናቸውን ድርድሮችና መልካም ሁኔታዎች የሚያበላሹ መግለጫዎችን በማውጣት የመንግሥትንና የጋዜጠኞችን ግንኙነት ለማበላሸት እየተሯሯጠ ይገኛል ሲሉ ወቅሰዋል፡፡
ሲፒጄ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ከሀገር እንዲኮበልሉ እያበረታታና ለስቃይ እየዳረጋቸው መሆኑን ጠቁመው፤ ኅብረቱ በቀጣይ ድርጅቱ የሚያካሂደውን አፍራሽ እንቅስቃሴ ካላቋረጠ አሠራሩን እየተከታተለ ለማውገዝ እንደሚገደድ ነው ያስገነዘቡት።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጋዜጠኞች ኅብረት በሀገር ውስጥ ምንም ዓይነት ጋዜጠኛ እንዳይታሰርና ሌሎች ጉዳቶች እንዳይደርሱበት በቅርበት እየተከታተለ እገዛ በማድረግና የሚፈጠሩ አለመግባባቶችም እንዲፈቱ ተቀራርቦ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በሰላም በመሥራት ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡
በሀገራችን በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞች ርእዮት ዓለሙና ውብሸት ታዬ መሆናቸውን ጠቁመው፤ ኅብረቱ እነዚህ ጋዜጠኞች በመንግሥት ላይ በሚፈጠር ጫናና ተጽዕኖ ሳይሆን ሕግ በሚፈቅደው አግባብ በይቅርታም ይሁን በምህረት እንዲለቀቁ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን ገልጸዋል።
እንደ ጋዜጠኛ አንተነህ ገለጻ፤ በተለያዩ መንገዶች የኢትዮጵያን መንግሥት ለማዳከምና የሥርዓት ለውጥ በኢትዮጵያ ለማምጣት በግልጽ እየሠራ ያለው ሲፒጄ፤ በተለያዩ መድረኮች በኢትዮጵያ ብሔራዊ የጋዜጠኞች ኅብረት ላይ አሉታዊ ጫና ለመፍጠር ይሞክራል፡፡ ይህም የሆነው መንግሥትን ከሥልጣን ለማባረር ኅብረቱ ሊተባበረው ባለመቻሉና በሙያ ጉዳዮች ላይ ብቻ አተኩሮ ከመሥራት ውጪ የፖለቲከኞች መሣሪያ ለመሆን ፈቃደኛ ባለመሆኑ እንደሆነም ጋዜጠኛ አንተነህ አስረድተዋል፡፡
«አሁን ሲፒጄ የያዛቸው አብዛኛዎቹ አፍራሽ እቅስቃሴዎች ተጋልጠዋል፤ ሌሎች ዴሞክራሲያዊ የሆኑ ዓለም አቀፍ ተቋማትም ሃሳቡን የማይጋሩ በመሆናቸው ሲፒጄ ብቻውን እንደ ውሃ ላይ ቄጤማ እየዋለለ ይገኛል»ብለዋል፡፡
ሲፒጄ በእውነት ለኢትዮጵያ ጋዜጠኞች የሚቆረቆር ከሆነ በሀገር ውስጥ ለምንገኘው ጋዜጠኞች ድጋፍ ማድረግ ይኖርበት ነበር ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ «ድርጅቱ በስማችንና በሙያችን ይነግድብናል እንጂ አንዳች የፈየደው ነገር የለም» በማለት ድርጊቱን ኮንነዋል፡፡